ቅዳሴ ተሰጥሖ @betekidase Channel on Telegram

ቅዳሴ ተሰጥሖ

@betekidase


ለሁሉም ኦርቶዶክሳዊያን ስለ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን እና ስለ ሥርዓተ ቅዳሴ ለመማር እንዲሁም ለማወቅ የተዘጋጀ ቻናል ነው ሼር እያደረጉ ሃይማኖታዊ ድርሻዎን ይወጡ።https://t.me/kidasee

ቅዳሴ ተሰጥሖ (Amharic)

ከዚህ በኋላ ቅዳሴ ተሰጥሖ በትምህርት አቅቦና ምርቶችን ብትመረብና የምንደርስ ንግድ እንደሆነ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊያንን በሥርዓት አገኘቸው። እናንተ እናላችሁ ስለ ሥርዓተ ቅዳሴና ስለ መማር ማወቅ የተዘጋጀ ሃይማኖታዊ ድርሻዎን ይጠብቁ። በትምህርት አቅቦ እንዲሁም ባለው ቻናሉ የትከሥለውን መሳሪያ ሚኒስቴር ከዚሁ ሼር ጋር ከዚህ በታች ሃይማኖታዊ ድርሻዎን እያደረጉ እንደሚረዳ ይሆናል።

ቅዳሴ ተሰጥሖ

14 Jan, 17:20


ይደመጥ ‼️‼️

ቅዳሴ ተሰጥሖ

14 Jan, 11:56


#ቃለ_ወንጌል

6/05/2017
ሉቃስ 4:24-33


እንዲህም አላቸው፥ “እውነት እላችኋለሁ፤ ነቢይ በሀገሩ አይከብርም። "እውነት እላችኋለሁ፤ በነቢዩ በኤልያስ ዘመን በምድር ሁሉ ብርቱ ረኃብ እስኪሆን ድረስ ሰማይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር በተዘጋበት ጊዜ ብዙ መበለቶች በእስራኤል ውስጥ ነበሩ። ወዷልያስ የሲዶና ክፍል በምትሆን በስራጵታ ወደምትኖር ወደ አንዲት መበለት ሴት እንጂ ዚዩነዚህ ወደ እንዲቱ እንኳን አልተላከም። በነ ቢዩ በኤልሳዕ ዘመንም ብዙ ለምጻሞች በእስራኤል ውስጥ ነበሩ፥ ነገር ግን ከሶርያዊው ከንዕማን በቀር ከእነዚያ አንድ እንኳን አልነጻም።”በምኵራብም የነበሩት ሁሉ ይህን ሰምተው ተቈጡ። ያንጊዜም ተነሥተው ከከተማ ወደ ግሞ አወጡት ገፍተውም ይጥ ሉት ዘንድ ከተማቸው ተሠርታባት ወደ ነበ ረች ተራራ ጫፍ ወሰዱት። “እርሱ ግን በመ ካከላቸው አልፎ ሄደ።

ወደ ገሊላ ከተማም ወደ ቅፍርናሆም ወረደ በሰንበትም ያስተምራቸው ነበር። አነጋገሩም በትእዛዝ ነበርና ትምህርቱን ያደንቁ ነበር።

ቅዳሴ ተሰጥሖ

14 Jan, 10:55


✧°༺༻°✧ የጥር 6 ግዝረትና በዓላት ✧°༺༻°✧

ግዝረት ከጌታችን ከመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት አንዱ ነው፡፡ በተጨማሪም ይህ ቀን ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ዕረገተ ኤልያስ፤ ዕረፍተ ኖኅ፤ ልደተ ቅድስት አርሴማ፤ ዕረፍተ ዐቢይ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ፤ አቡነ ኖኅ አባ ሙሴ ገዳማዊ፤ አባ ወርክያኖስ እና ወአባ ሙሴን በዓላት ታከብራለች፡፡

ከእናቱና ከደቀመዛሙርቱ ጋር በሰርግ ቤት የተገኙበት ቃና ዘገሊላ፣ በአርባ ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ የገባበትና አረጋዊ ስምዖንን የሰላሳ ዓመት ጎልማሳ የሆነበት “ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ ዐይኖቼ ማዳንህን አይተዋልና” በማለት የተናገረበት ልደተ ስምዖን ከንዑሳን በዓላት ይመደባሉ፡፡ ክብር ምስጋና ይድረሰውና የጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ግዝረት በየዓመቱ ጥር ፮ ቀን ይውላል።

ልሳነ ዕፍረት ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ፡፡ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ፤›› በማለት እንደ ተናገረው [ሮሜ.፲፭፥፰]፣ የክብር ባለቤት መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጽሟል፡፡ በቅዱስ ወንጌል እንደ ተጻፈ በስምንተኛው ቀን እንደ ኦሪቱ ሥርዓት ግዝረት ይፈጸምለት ዘንድ ሕፃኑ ጌታችንን ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዱት፡፡ ስሙም ገና በሥጋ ሳይፀነስ የእግዚአብሔር መልአክ ባወጣለት ስም ‹‹ኢየሱስ›› ተብሎ ተጠራ [ሉቃ.፪፥፳፩-፳፬]፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ሲገረዝ የሊቀ ካህን ልጅ ነው ብለው ሊገርዙት ወደ እርሱ መጡ፡፡ ጌታችን ግን ወደ ምድር የመጣው ለትሕትና ነው እንጂ ለልዕልና አይደለምና ወሰዱት አለ [ትርጓሜ ወንጌለ ሉቃስ]፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም አረጋዊው ዮሴፍን ‹‹እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙንም እንድንሰይመው ብልህ የኾነ ገራዥ ሰው አምጣልኝ፤›› አለችው፡፡ ጻድቁ ዮሴፍም እንዳዘዘችው የሚገርዝ ባለሙያ ይዞ መጣ፡፡ ባለሙያውም በእናቱ በንጽሕት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ ሕፃኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ባየው ጊዜ ‹‹እንድገርዘው በጥንቃቄ ያዙት›› አላቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስም ‹‹ባለሙያ ገራዥ ሆይ! ደሜ ሳይፈስ ልትገርዘኝ ትችላለህን? በዕለተ ዓርብ በመስቀል ስሰቀል ካልኾነ በስተቀር ደሜ አይፈስምና፡፡ ጐኔን በጦር ሲወጉኝ ያን ጊዜ ውኀና ደም ይፈሳል፡፡ ይኸውም ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆቹ መድኀኒት ይኾናል፤›› አለው፡፡

የክብር ባለቤት ጌታችን የተናገረውን ይህን ቃል ባለሙያው በሰማ ጊዜም አደነቀ፡፡ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሣና ከጌታችን እግር በታች ወድቆ ሰገደ፡፡ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጁ ላይ እንዳሉ እንደ ውኀ ቀለጡ፡፡ ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም ‹‹ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ፡፡ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡ ይህ ልጅሽ ስለ እርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው፤›› አላት፡፡

ጌታችንም ባለሙያውን ‹‹እኔ ነኝ! ትገዝረኛለህን ወይስ ተውክ? ወይስ የአባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ ላድርግ?›› አለው፡፡ ባለሙያውም መልሶ ‹‹የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ጌታችንም አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ የሕዝቡ ዅሉ አባት እንደ ኾኑ ካስገነዘበው በኋላ ‹‹ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው›› በማለት የግዝረትን ሕግ አስረዳው፡፡ ባለሙያውም ይህን ምሥጢር ሲሰማ ‹‹እኔ ከአንተ ጋር እነጋገር ዘንድ አልችልም፡፡ በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና፤›› ብሎ የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት መሰከረ፡፡

በዚህ ጊዜ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ ‹‹አባት ሆይ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው፤ ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ›› አለ፡፡ ያንጊዜም ያለ ሰው እጅ በጌታችን ላይ ግዝረት ተገለጠ (የግዝረት ምልክት ታየ)፡፡ ከዚህ ላይ ጌታችን ወደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር አብ ልመና ማድረሱ የለበሰው ሥጋ የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የያዕቆብ መኾኑንና ጸሎት ማቅረብ የሚስማማው ሥጋን መልበሱን ለማጠየቅ ነው እንጂ በእርሱና በአብ መካከል ልዩነት ኖሮ አይደለም፡፡

ጌታችን ድንግልናዋን ሳያጠፋ ከድንግል ማኅፀን እንደ መውጣቱ ግዝረቱም አይመረመርም፡፡ በተዘጋ ቤት ወደ ሐዋርያት እንደ ገባና እንደ ወጣ ዅሉ እርሱ በሚያውቀው ረቂቅ ጥበብ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቈረጥ፣ ምንም ደም ሳይፈሰው መገረዙ ተገለጠ፡፡

ገራዡም የጌታችንን ቃል ከመስማቱ ባሻገር በሥጋው ላይ የተደረገውን ተአምር ባየ ጊዜ እጅግ አደነቀ፡፡ ከክብር ባለቤት ከጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር በታች ወድቆም ሦስት ጊዜ ሰገደና ‹‹በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ!›› በማለት በክርስቶስ አምላክነት አመነ፡፡ ከዚህ በኋላ ያየውንና የሰማውን ዅሉ እየመሰከረ ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡

በዚህች ዕለት ‹‹መሲሑን ሳታይ አትሞትም›› ተብሎ የተነገረለት፤ በንጉሥ በጥሊሞስ መራጭነት መጻሕፍተ ብሉያትን ከዕብራይስጥ ወደ ጽርዕ(ግሪክ) ቋንቋ ከመለሱ ሰባው ሊቃናት አንዱ የኾነውና ትንቢተ ኢሳይያስን ወደ ጽርዕ ቋንቋ የመለሰው ነቢዩ ስምዖን ጌታችንን በታቀፈው ጊዜ ከሽምግልናው ታድሷል፤ የእግዚአብሔርን ማዳን በማየቱና በተደረገለት ድንቅ ተአምር በመደሰቱም ‹‹አቤቱ ባሪያህን ዛሬ አሰናብተው›› እያለ እግዚአብሔርን ተማጽኗል፡፡

በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶም የክርስቶስን የዓለም ቤዛነትና ክርስቶስ በሥጋው በሚቀበለው መከራ እመቤታችን መራራ ኀዘን እንደሚደርስባት፤ እንደዚሁም ጌታችን ለሚያምኑበት ድኅነትን፣ ለሚክዱት ደግሞ ሞትን የሚያመጣ አምላክ እንደ ኾነ የሚያስገነዝብ ትንቢት ተናግሯል [ሉቃ.፪፥፳፭-፴፭]፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ነቢዪት ሐናም በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝታ የክርስቶስን ሥራ እያደነቀች ቸርነቱን ለሕዝቡ ዅሉ መስክራለች [ሉቃ.፪፥፴፮-፴፱]፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

ቅዳሴ ተሰጥሖ

13 Jan, 05:56


"ድንግል ሆይ አንቺን የሰደበ ሰው እንዴት ይኖራል " አይኖርም እንጂ ምክንያቱም በልጅሽ የፍርድ መፅሐፍ ላይ እናት አባቱን የሰደበ ሰው ይሙት ይላል የጌታን እናት ሰድቦ እንዴት ይኖራል።

#አባ ፅጌ ድንግል

ለመቀላቀል 👉 @betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

13 Jan, 05:48


#ቃለ_ወንጌል

05/05/2017
ዮሐንስ 18:23-28


ጲላጦስም እንደገና ወደ ፍርድ አደባባይ ገብቶ ጌታችን ኢየሱስን ጠራና፥ “የአይሁድ ንጉሥ አንተ ነህን?” አለው። ጌታችን ኢየሱስም፥ “ይህን የምትናገር ከራስህ ነውን? ወይስ ስለ እኔ የነገረህ ሌላ አለን?” ብሎ መለሰለት። ጲላጦስም መልሶ፥ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ለእኔ አሳልፈው የሰጡህ ወገኖችህና ሊቃነ ካህናት አይደሉምን? ኧረ ምን አድርገሃል?” አለው።

ጌታችን ኢየሱስም፥ “የእኔ መንግሥት ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴስ በዚህ ዓለም ብትሆን ኖሮ ለአይሁድ እንዳልሰጥ አሽከሮቼ በተዋጉልኝ ነበር፤ አሁንም መንግሥቴ ከዚህ አይደለችም” ብሎ መለሰለት። ጲላጦስም፥ “እንግዲያ አንተ ንጉሥ ነህን?” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ራስህ ትላለህ፤ እኔ ስለዚህ ተወለድሁ፤ ስለዚህም ለእውነት ልመሰክር ወደ ዓለም መጣሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰማኛል” አለው።

ምስባክ
                    መዝሙር 83:6

እስመ መምህረ ህግ ይሁብ በረከተ

ወየኃውር እምኃይል ውስተ ኃይል

ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን

               ትርጉም

የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና

ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ

የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል

ቅዳሴ ተሰጥሖ

12 Jan, 17:21


ለ 2017 ዓ.ም የ ጥምቀት በዓል የ አቃቂ ቃሊቲ መጠመቂያ ገንዳ በ ማፅዳት ላይ 🥰🥰🥰🥰

ቅዳሴ ተሰጥሖ

12 Jan, 08:21


#ቃለ_ወንጌል
ማቴዎስ 2:1-13


በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በይሁዳ ክፍል በቤተ ልሔም ጌታችን ኢየሱስ በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። ፤እንዲህ ሲሉ፥ “ኮከቡን በምሥራቅ አይተን እንሰግድለት ዘንድ መጥተናልና፥ የተወ ለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?” ፤ንጉሥ ሄሮድስም በሰማ ጊዜ ደነገጠ፤ ኢየሩሳሌምም በመላዋ ከእርሱ ጋር ደነገጠች። ፤የካህናት አለ ቆችንና የሕዝቡን ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ “ክርስቶስ በየት ይወለዳል?” ብሎ ጠየቃቸው። እንዲህም አሉት፤ “በይሁዳ ክፍል በቤተ ልሔም ነው፤ በነቢይ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአ ልና። የይሁዳ ምድር አንቺ ቤተ ልሔም ከይ ሁዳ አለቆች፤ ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራ ኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና።”

ከዚህም በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠራቸው፤ ኮከቡ የታየበትንም ዘመን ከእነርሱ ተረዳ። “ሂዳችሁ የዚያን ሕፃን ነገር ርግ ጡን መርምሩ፤ ያገኛችሁትም እንደ ሆነ እኔም መጥቼ እሰግድለት ዘንድ በእኔ በኩል ተመልሳችሁ ንገሩኝ” ብሎ ወደ ቤተ ልሔም ሰደዳቸው። እነርሱም ከንጉሡ ሰምተው ሄዱ፤ እነሆ፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ በአለበት ቦታ ላይ ደርሶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር። ፤ኮከቡንም አይተው ታላቅ ደስታ ደስ አላቸው።ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አገኙት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው ወርቅና ዕጣን፥ ከርቤም፥ እጅ መንሻ አቀረቡለት። ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ነገራ ቸው፤ በሌላ መንገድም ወደ ሀገራቸው ሄዱ።


ምስባክ
መዝሙር 88:27-28

ወአነሂ በኵርየ እሬስዮ

ወልዑል ውእቱ እምነገሥተ ምድር

ወለዓለም አዐቀብ ሎቱ ሣህልየ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

11 Jan, 22:31


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
              🕯 #ዮሐንስ_ወልደ_ነጐድጓድ
   ዮሐንስ ማለት ፍሥሐ ወሐሴት፣ ርኅራኄ ወሣህል ማለት ነው፡፡ ቁጥሩ ከ12ቱ ሐዋርያት መካከል የሆነው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ አባቱ ዘብዴዎስ እናቱ ማርያም ባውፍልያ (ሰሎሜ) ይባላሉ፡፡ ለአገልግሎት የተጠራው ከአባቱና ከወንድሙ ያዕቆብ ጋራ በገሊላ ባሕር ዓሣ ሲያጠምዱ እንደሆነ ወንጌላዊው ማቴዎስ ገልጾታል፤ (ማቴ 4÷21-22)፡፡
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የሚጠራባቸው ሌሎች ስሞች፦
#ፍቁረ_እግዚእ፦ ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ያዕቆብ ፣ ዮሐንስና ጴጥሮስ) ቀዳሚው ነው፤ በኑሮው ጌታን ለመምሰል ይጥር ነበርና ጌታ የሚወደው (ፍቁረ እግዚእ) ተባለ፤ (ዮሐ 20÷2 ፣ ዮሐ 13÷23)፡፡ በዚህም ምክንያት ምሥጢረ መንግሥትን በታቦር ተራራ፣  ምሥጢረ ጸሎት በጌቴሴማኒ፣ ምሥጢረ ቁርባንን በምሴተ ሐሙስ ከጌታ ጎን ተቀምጦ አይቷል፡፡ በተጨማሪም ጌታችን በጸሎተ ሐሙስ ለደቀ መዛሙርቱ ትህትናን ሊያስተምር እግራቸውን ሲያጥብ በድር የተሠራች የወገብ መታጠቂያ አድርጎ ነበር፤(ዮሐ 13፥4-5)፡፡ ይህችንም የወገብ መታጠቂያ ለቅዱስ ዮሐንስ ሰጥቶታል፡፡ እርሱም ጌታ በታጠቀበት መታጠቂያ ቢታጠቅ ሕገ ሥጋ ጠፍቶለታል፤ ይህም ፍቁረ እግዚእ አሰኝቶታል፡፡
#ቦአኔርጌስ፦ ቅዱስ ዮሐንስ እና ታላቅ ወንድሙ ያዕቆብ ከቤተ ክህነትና ከቤተ መንግሥት (በአባታቸው ከነገደ ይሁዳ በእናታቸው ከነገደ ሌዊ) ተወልደዋል፤ እነዚህ ሁለቱ ወንድማማቾች የሰማርያ ሰዎች በእሳት እንዲጠፉ ተመኝተው ነበርና በዚህ የችኩልነት ስሜታቸው ጌታ ‹‹ቦአኔርጌስ›› (የነጎድጓድ ልጆች) ብሏቸዋል፤ (ማር 3÷17 ፣ ሉቃ 9÷54 ፣ 2ነገ 1፥10-12)፡፡
#ታኦጎሎስ (ነባቤ መለኮት)፦ ቅዱስ ዮሐንስ ንጽሐ ሥጋ፣ ንጽሐ ነፍስ፣ ንጽሐ ልቡና ተሰጥቶት በትምህርቱ ጥልቀትና ኃይል የኢየሱስን አምላክነት በመግለጡ ከሌሎች አልቆና አምጥቆ ምሥጢረ ሥላሴን የቃልን ቀዳማዊነትና አምላክነት ‹‹በመጀመሪያ ቃል ነበረ፤ ያም ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ›› እያለ በማመሥጠሩ ነባቤ መለኮት (ታኦጎሎስ) ተብሎ ተጠርቷል፤ (ዮሐ 1÷1-2)፡፡
#አቡቀለምሲስ፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ትርጓሜውም ባለራእይ ማለት ነው፤ በፍጥሞ ደሴት ራእይን አይቷልና (የራእይ መጽሐፍን ጽፏልና) አቡቀለምሲስ ተባለ፡፡
#ቁጽረ_ገጽ፦ ከሌሎች ሐዋርያት ተለይቶ በዕለተ ዐርብ ከመስቀል ሥር የዋለ ብቸኛ ሐዋርያ በመሆኑ የጌታን መከራ መስቀል በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ያማረ ሳይለብስ ፊቱ በሐዘን እንደተቋጠረ ስለ ኖረ ቁጽረ ገጽ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ በመስቀል ሥር በመገኘቱም የመስቀል ሥር ስጦታችንን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን እናት አድርጎ ሰጥቶታል፤ (ዮሐ 19÷25-27)፤ እመቤታችንም በዮሐንስ ቤት ለ15 ዓመት ኖራለች፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ቅዱስ ዮሐንስን አዕማድ ብሎ ይጠራዋል፤ (ገላ 2÷9)፡፡
   በቅድስት ሥላሴ ሥዕል ላይ ካሉት አራቱ እንስሳት አንዱ ንስር ነው፤ ንስር በእግሩ ይሽከረከራል በክንፉ ይበራል፡፡ ንስር በእግሩ እንደሚሽከረከር ቅዱስ ዮሐንስም የክርስቶስን ምድራዊ ታሪኩን ጽፏል፡፡ ንስር በክንፉ መጥቆ እንደሚበር ቅዱስ ዮሐንስም ከሌሎቹ ወንጌላውያን ለየት ብሎ የመለኮትን ሰማያዊ አኗኗር ጽፏልና በንስር ተመስሏል፡፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ አምስት ቅዱሳት መጽሐፍትን የጻፈ ሲሆን እነዚህም ወንጌለ ዮሐንስ፣ ሦስት መልእክታት እና ራእይ ናቸው፡፡ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤  ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፤ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ብሎ መጻፍ ሲጀምር መልአኩ ከትልቅ ሐይቅ ዳር ቁጭ ብሎ የሐይቁን ውኃ በእንቁላል ቅርፊት እየጨለፈ ወደ መሬት ሲያፈስ አየው፤ ቅዱስ ዮሐንስ ምን እየሰራህ ነው ብሎ ሲጠይቀው የሐይቁን ውኃ ወደ መሬት አፍስሼ ለመጨረስ ነው ይለዋል፡፡ ዮሐንስም በእንቁላል ቅርፊት ይህ እንዴት ይሆናል አለው፤ ያም መልአክ ይህ ሐይቅ ፍጡር ነው ከረጅም ዘመን በኋላ ያልቃል አንተ ግን ቢቀዱት የማያልቀውን ቢጀምሩት የማይጨርሱትን የመለኮት ነገር የምትመራመር አለው፡፡ በዚህ ጊዜ የጀመረውን አቁሞ ‹‹ከእግዚአብሔር የተላከ ስሙ ዮሐንስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ›› በማለት ስለ መጥምቁ ዮሐንስ መጻፍ ጀመረ፤ ከዚያ ቃልም ሥጋ ሆነ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ አደረ ብሎ ወደ ምሥጢረ ሥጋዌ ገባ፡፡
   ወንጌላዊው ዮሐንስ መልኩ ጌታችንን ስለሚመስል ይሁዳ ጌታን በመሳም ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠው መልካቸው ስለሚመሳሰል ተሳስተው ዮሐንስን እንዳይዙት ነው፡፡
   የቅዱስ ዮሐንስ ሀገረ ስብከቱ እስያ ሲሆን በዚያ እየተዘዋወረ ለብዙዎች የክርስቶስን ወንጌል እየሰበከ ፣ ድውያንን እየፈወሰ፣ ሙታንን እያስነሳ ብዙ ገቢረ ተአምራትን እያደረገ በክርስቶስ እንዲያምኑ አድርጓቸዋል፡፡
   ሞትን ያልቀመሰ በሕይወተ ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ፣ እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ ነው፤ ጌታችን ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ?›› (ዮሐ 21፥20-23)፤ ይህ የሚያሳየው እስከ ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነው፡፡ ‹‹እውነት እላችኋለሁ የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ አስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ›› (ማቴ 16፥28) ተብሎ የተጠቀሰው ቃል ለቅዱስ ዮሐንስ እና መሰሎቹ የተነገረ ነው፡፡ በፍጥሞ ደሴት የተሰወረበት መታሰቢያ ጥር 4 ቀን ይከበራል፡፡ ከወንጌላዊው በረከት ያሳትፈን አሜን!
            ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ፣ መድበለ ታሪክ ፣ ስንክሳር ዘጥር 4

ቅዳሴ ተሰጥሖ

11 Jan, 19:24


ይህንን ያውቃሉ?

    ቅዳሴ ማለት አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እለተ አርብ የቆረሰው ስጋውና ደሙ አማናዊ(የራሱም ስጋና ደም) ወደመሆን ሚቀየርበት ድንቅ ስርዓት ነው።

ያ' ማለት ቅዳሴ ተገኝተን በምናስቀድስበት ጊዜ የቆምነው እውነተኛ ከሆነው ስጋና ደሙ ከክርስቶስ አጠገብ መቆም ነውና በማስቀደስ ክርስቶስን እንጠጋ።

       🌼ልዕልት ሰንበትን በቅዳሴ🌼

ቅዳሴ ተሰጥሖ

11 Jan, 08:23


ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣

ያኔ ማህሌቱ አቋቋሙ ሳይበረዝ መፈንጫ ከመሆኑ በፊት የዛሬ 40 ዓመት ጥንታዊ አባቶቻችን በማህሌቱ መዳኒህ ዓለም ክርስቶስን ሲያመሰግኑት።

https://t.me/betekidase

https://t.me/betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

11 Jan, 05:06


" በትግራይ ክልል የምትገኙ የሃይማኖት አባቶች መበደላችሁን እናውቃለን ፣ በኀዘናችሁ ሰዓት አብረን መቆም ባለመቻላችን ማዘናችሁም እርግጥና ተገቢ ነው። ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚካሰው በእርቅ ሲሆን እኛ የገፋነውን እርቅ ዓለም ሊቀበለው ስለማይችል፤ በእጃችንም የያዝነው መስቀለ ክርስቶስ የሰላም ዓርማ ነውና ልባችሁን ለሰላም፣ ለአንድነት እንድታዘጋጁ እንጠይቃለን " -  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ቅዳሴ ተሰጥሖ

11 Jan, 05:06


" ልጆቻችን በሰላም መኖር እንዲችሉ፣ በጦርነት እየተሰቃዩ የሕመማቸውን ልክ መናገር የማይቻለን የኦሮሚያና የአማራ ክልል ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ ጥሪ እናስተላልፋለን " - ቅዱስነታቸው

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክተው አባታዊ የሰላም ጥሪ አስተላለፉ።

ቅዱስነታቸው ፤ በሀገራችን በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶች እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

" ልጆቻችን በሰላም መኖር እንዲችሉ፣ በጦርነት እየተሰቃዩ የሕመማቸውን ልክ መናገር የማይቻለን የኦሮሚያና የአማራ ክልል ነዋሪዎች ሰላምን እንዲያገኙ አባታዊ ጥሪ በድጋሚ እናስተላልፋለን " ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ፤ በትግራይ ክልል ያለው የአስተዳዳሪዎች አለመግባባት በሕዝቡ ላይ ተጨማሪ ችግርና ጭንቀት እያመጣ መሆኑን ጠቁመዋል።

" በትሕትና መንፈስ እርስ በርስ መገናዘብ ተፈጥሮ ዕረፍት ያጣው ሕዝብ መረጋጋት እንዲችል ታደርጉ ዘንድ አደራችን የጠበቀ ነው " ብለዋል።

በተጨማሪም ቅዱስነታቸው በትግራይ ክልል ስለሚገኙ የሃይማኖት አባቶች ጉዳይ በአባታዊ የሰላም ጥሪ መልዕክታቸው አንስተዋል።

" መበደላችሁን እናውቃለን ፣ በኀዘናችሁ ሰዓት አብረን መቆም ባለመቻላችን ማዘናችሁም እርግጥና ተገቢ ነው " ያሉት ቅዱስነታቸው " ነገር ግን ሁሉም ነገር የሚካሰው በእርቅ ሲሆን እኛ የገፋነውን እርቅ ዓለም ሊቀበለው ስለማይችል፤ በእጃችንም የያዝነው መስቀለ ክርስቶስ የሰላም ዓርማ ነውና ልባችሁን ለሰላም፣ ለአንድነት እንድታዘጋጁ እንጠይቃለን " ብለዋል።

በሌላ በኩል ቅዱስነታቸው በመሬት መንቀጥቀጥ እየተጨነቁ ላሉ እና ስለተጎዱ ልጆቻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

" የመሬት መንቀጥቀጥ ባለበት አካባቢ እየተጨነቃችሁ ያላችሁ ልጆቻችን ረድኤተ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዲሆን ቤተ ክርስቲያን በጸሎት የምታስባችሁ መሆኑን እየገለጽን መላው ኢትዮጵያውያን ለጉዳቱ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ለሚኖሩት ወገኖቻቸው አቅማቸው በፈቀደው መጠን ድጋፍ ያደርጉ ዘንድ አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን " ብለዋል።

(የቅዱስነታቸው ሙሉ መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia

ቅዳሴ ተሰጥሖ

11 Jan, 04:39


#ቃለ_ወንጌል

03/05/2017
ማቴዎስ 2:13-ፍጻሜ


እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ፥ “ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይሻዋልና ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ምድረ ግብፅ ሽሽ፤ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ኑር” አለው፤ "እርሱም በሌሊት ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ ግብፅ ሄደ። ።ከእግዚአብሔር ዘንድ “ልጄን ከግብፅ ጠራሁት” ተብሎ በነቢይ የተ ነገረው ይፈጸም ዘንድ፣ ሄሮድስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ።

ከዚህም በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገል እንደ ተዘባበቱበት ባየ ጊዜ እጅግ ተቈጣና ጭፍራዎቹን ልኮ ከሰብአ ሰገል እንደ ተረዳው ዘመን ልክ ሁለት ዓመት የሆናቸውን፥ ከዚያም የሚያንሱትን፥ በቤተ ልሔምና በአውራጃዎችዋ ሁሉ የነበሩትን ሕፃናት አስገደለ። "ያንጊዜ፥ በነቢዩ በኤርምያስ የተነገረው ተፈጸመ፤ እንዲህ ሲል፦ “ራሔል ስለ ልጆችዋ ስታለቅስ ብዙ ልቅሶና ዋይታ በራማ ተሰማ፣ መጽናናትንም እንቢ አለች፤ ልጆችዋ የሉምና።”

“ሄሮድስም በሞተ ጊዜ እነሆ፥ የእግዚእ ብሔር መልአክ በግብፅ ሀገር ለዮሴፍ በሕ ልም ታየው። እንዲህ ሲል፡ “የሕፃኑን ነፍስ የሚሹ ሙተዋልና፥ ተነሥተህ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ሀገር ሂድ።” እርሱም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ ወደ እስራኤል ምድር ገባ። “አርኬላኦስም በአባቱ በሄሮድስ ፋንታ በይሁዳ እንደ ነገሠ በሰማ ጊዜ፥ ወደዚያ ለመሄድ ፈራ፤ በሕልምም ተገልጦለት ወደ ገሊላ አውራጃ ሄደ። በነቢያት “ልጄ ናዝራዊ ይባላል” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ናዝሬት ወደ ምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።
 
                                    ምስባክ
                            መዝሙር 43:22-23

እስመ በእንቲአሁ ይቀትሉነ ኩሎ አሚረ

ወኮነ ከመ አባግዕ ዘይጠብሑ

ንቃዕ እግዚኦ ለምንት ትነው

ቅዳሴ ተሰጥሖ

10 Jan, 12:50


+ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር+

የመጀመሪያው ሰማዕት ዲያቆን እስጢፋኖስን በግፍ ከቤተ ሳይዳ መግቢያ ከአንበሳ በር አውጥተው በድንጋይ ወግረው በግፍ እንዴት እንደገደሉት ዝርዝር ታሪኩ በሐዋርያት ሥራ ላይ ተጽፎአል:: የታሪኩ ማብቂያ ላይ ያለው ዐረፍተ ነገር እስጢፋኖስን በጭካኔ በድንጋይ ከቀጠቀጡት ሰዎች ጋር አብሮ ባይቀጠቅጠውም የሌላ አንድ ተሳታፊ ስም ተጠቅሶአል::  "ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር" (ሐዋ. 7:60)

በዚያች የምታሳዝን ዕለት ራሳቸው ከሳሽ ራሳቸው ፈራጅ የነበሩት ጸሐፍት በጭካኔ ታውረው ሆ ብለው በእስጢፋኖስ ላይ ተነሥተውበት ነበር:: በዚያ ባለ ብዙ ተስፋ ወጣት ላይ የድንጋይ ዶፍ ሲያወርዱ ትንሽ እንኳን አልዘገነናቸውም:: ይቅር በላቸው ከማለት ውጪ ክፉ ያልወጣውን ምስኪን ክርስቲያን ወጣት ያለ ርኅራኄ ቀጥቅጠው ገደሉት::

በዚያች ዕለት ሳውል ተሳትፎው ምን ነበር? እርግጥ ነው በእጁ ድንጋይ አልያዘም:: በእስጢፋኖስ ጭንቅላት ላይ ጉዳት ለማድረስ እጆቹን አላስወነጨፈም::  ነገር ግን አንድ እውነታ መካድ አይቻልም:: ሳውል በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ስለነበር በቀጥታም ባይሆን በተዘዋዋሪ ከእስጢፋኖስ ሞት ጋር ስሙ አብሮ ተነሥቶአል::

የሰው ልጅ ሁኔታዎች ከተመቻቹለት ፍጹም አዛኝ መልአክ መሆን እንደሚችል ሁሉ ሁኔታው ከተመቻቸለት ፍጹም አውሬ የመሆን እምቅ ችሎታ ያለው ፍጡር ነው:: ጭካኔም ሆነ ርኅራኄ ከየትኛውም ዘር ብትወለድ ሊኖርህ የሚችል ነገር ሲሆን  በሕግ በሃይማኖትና በሰብአዊነት መርሆች  ካልተገታ በስተቀር የሰው ልጅ የማያደርገው ክፉ ነገር እንደሌለ የዓለም ታሪክ ያስረዳል::

በዘመናችን የምናየው የንጹሐን ግድያ ላይ በቀጥታ የሚሳተፉና ብዙ እስጢፋኖሶችን በግፍ የሚገድሉ ጨካኞች አሉ:: በሕግ የሚጠየቁትም የሚቀጡትም እንደዚህ ያሉት ቀጥተኛ ተሳታፊዎች ናቸው::

ሆኖም በእኛ ሀገር በቁጥር እጅግ የሚበዙት እስጢፋኖስ ላይ ድንጋይ ከወረወሩት አይሁድ ይልቅ በእስጢፋኖስ መገደል የተስማሙት ሰዎች ናቸው:: ከሩቅ ሆኖ "ተነሣ በለው" ማለት ያም ባይሆን "እዚህ ሰፈር ሰው ተገደለ" ሲባል "እዚያ ሰፈርስ ሞቶ የለ ወይ?" እያሉ ለማካካስ መሞከር : ይበለው ይበላት ብሎ መናገርም በእስጢፋኖስ መገደል መስማማት ነው::

ወዳጄ በክፋት ውስጥ በቀጥታ መሳተፍም : ከሩቅ ሆኖ ቃላት መወራወርም : ጥላቻን መዝራትም : ሌላውን እየናቁ ራስን መኮፈስም ዞሮ ዞሮ በፈጣሪ ፊት ስለ ንጹሐን ደም ማስጠየቁ አይቀርም::

እስጢፋኖስን የመሰሉ በግፍ የተገደሉ ሁሉም ሰማዕታት በፈጣሪ ዙፋን ፊት ቆመው "እስከመቼ አትፈርድም?" ማለታቸው ስለማይቀር ሳናውቀው ዕዳ በራሳችን ላይ እንዳናከማች ከየትኛውም የጥላቻ ንትርክ ራሳችንን እናውጣ::

እስጢፋኖስ ሲገደል ሳውል የተስማማ ቢሆንም በመጨረሻ ግን "ይቅር በላቸው" በሚለው የእስጢፋኖስ ጸሎት ምክንያት በክርስቲያኖች መገደል ከመስማማት ወጥቶ በክርስትናው መከራ የተቀበለ ሐዋርያ ሆነ::
በጣም የሚደንቀው የእስጢፋኖስን ቤተሰቦችም ያጠመቀው በልጃቸው መገደል ተስማምቶ የነበረው ሳውል (ጳውሎስ) ነበረ:: የልጃችን ደም አለበት ሳይሉ ይቅር ብለው የተጠመቁት ጥፋትን በጥፋት ማረም እንደማይቻል ተረድተው ነበር:: ክርስትና ዘር ቆጥሮ የእኔን ወገን እንዲህ አድርገሃል ብሎ የመበቀል ሕይወት ሳይሆን
ባለፈ የጥላቻ ቁስል ማነከስን ትቶ በይቅርታ ዛሬና ነገን መኖር ነው:: ለትውልድ ቂም ማውረስ ለልጅ መርዝ ከማጠጣት አይተናነስም : ይቅርታን ማስተማር ግን ለልጅ በሰማይም በምድርም ርስት እንዲያገኝ ማድረግ ነው::

ኢትዮጵያ እግር አውጥታ ከእኛ እንዳትሸሽ እነዚህ ሦስት ነገሮች ከእንግዲህ በሀገራችን አይኑሩ

- በግፍ የሚገደል እስጢፋኖስ
- በግፍ የሚገድሉ ፈሪሳውያን
- በእስጢፋኖስ መገደል የሚስማሙ ሳውሎች

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሐምሌ 9 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

04 Jan, 09:14


🗣 የበግ ቆዳ ያለው?

ለገና በዓል በቤትዎ ወይም በአካባቢዎ ከሚከናወኑ እርዶች የበግ እና የፍየል ቆዳን ለሐመረ ብርሃን በመስጠት የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ፣ ትውፊት እና ታሪክ ያስቀጥሉ።

የመቀበያ ቦታዎች ፦

📍ፒያሳ አሮጌው ፖስታ ቤት
📍ሰአሊተ ምሕረት
📍አየር ጤና ኪዳነ ምሕረት
📍መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል
📍ጀሞ መድኃኔዓለም
📍ገላን ልደታ ለማርያም


ለበለጠ መረጃ፦

09 66 76 76 76
09 44 24 00 00
09 09 44 44 55
09 44 17 61 26

https://t.me/Hamerebirhan

ቅዳሴ ተሰጥሖ

04 Jan, 09:09


፨የጌታን ልደት በዝማሬ፨
የአእላፋት ዝማሬ 2 ቀን ቀረው::

#አእላፋት_ዝማሬ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

04 Jan, 06:06


#ቃለ_ወንጌል

26/04/2017
               ማቴዎስ 25:1-14


       ያንጊዜም መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ለመቀበል የወጡ ዐሥሩን ደናግል ትመስላለች። ከእነርሱም ውስጥ አምስቱ ሰነፎች፥ አምስቱም ልባሞች ነበሩ። ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ዘይት አልያዙም ነበር። ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮቻቸው ዘይት ይዘው ነበር። ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉም አንቀላፉና ተኙ። መንፈቀ ሌሊት በሆነም ጊዜ “እነሆ ሙሽራ መጣ፤ ልትቀበሉት ውጡ” የሚል ጩኸት ሆነ። ያንጊዜ እነዚያ ደናግል ሁሉ ነቁና መብራታቸውን አዘጋጁ። እነዚያ ሰነፎችም ልባሞችን፦ መብራታችን ሊጠፋብን ነውና ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው። ልባሞ ችም፦ ለእኛና ለእናንተ የሚበቃ የለም፤ ነገር ግን ወደሚሸጡ ሂዱና ለራሳችሁ ግዙ ብለው መለሱላቸው። ሊገዙም እንደ ሄዱ ሙሽራው መጣ፤ እነዚያም የተዘጋጁት ከእርሱ ጋር ወደ ሰርጉ ገቡ፤ ደጁም ተዘጋ። በኋላም እነዚያ ደናግል መጥተው፦ አቤቱ አቤቱ ክፈትልን አሉ። እርሱ ግን መልሶ፦ እውነት እላች ጓለሁ፤ አላውቃችሁም አላቸው። "እንግዲህ ትጉ፤ የሰው ልጅ የሚመጣባትን ቀኒቱንና ሰዓ ቲቱን አታውቁምና
::

                ምስባክ
            መዝሙር 44:9-10

አዋልደ ንግሥት ለክብርከ

ወትቀውም ንግሥት በየማንከ

በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት

              ትርጉም

የንጉሦች ሴት ልጆች ለክብርህ ናቸው

በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና፡

ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።

ቅዳሴ ተሰጥሖ

03 Jan, 08:31


#ቃለ_ወንጌል

25/04/2017
ማቴዎስ 13:36-44


ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ፤ ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው “የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጒምልን” አሉት። እርሱም መልሶ አላቸው፤ “መልካም ዘርን የዘራ የሰው ልጅ ነው። እርሻውም ዓለም ነው፤ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው። የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም ፍጻሜ ነው፤ አጫጆ ቹም መላእክት ናቸው። “እንግዲህ አስቀድሞ እንክርዳዱን እንደሚለቅሙት፥ በእሳትም እንደሚያቃጥሉት በዚህ ዓለም ፍጻሜም እንዲሁ ይሆናል። የሰው ልጅም መላእክቱን ይልካል፤ ከመንግሥቱም ዐላውያንንና በደልን የሚያደርጉትን ሁሉ ይሰበስባሉ። ወደ እሳት ጒድጓድም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል። ያንጊዜም ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ፤ ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ
::"

ምስባክ
መዝሙር 78:2-3

ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም

ወከዐዉ ደሞሙ ከመ ማይ ዐውዳ ለኢየሩሳሌም

ወኀጥኡ ዘይቀብሮሙ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

03 Jan, 04:41


ከሁለቱ የጽድቅ እንቅፋቶች እናስተውል!

       ፩.ጸድቄአለሁና
       ፪. አልጸድቅም


ጸላኤ ሠናያት ሰውን የሚጎዳበት ሁለት ወጥመዶች  አሉት። አንዱ ጸድቂያለሁ ማሰኘት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አልጸድቅም ማሰኘት ነው። በሁለቱም ምክንያቶች ጽድቅ መሥራት አይቻልም። ጸድቄያለሁ የሚያሰኛቸው መናፍቃንን ነው። ለምን ሲባሉ ጌታን እወደዋለሁና ይላሉ። አምናለሁና ይላሉ።

ጌታን ስለምወደው ጸድቄያለሁና ጽድቅ አልሠራም የምትል ከሆነ የምትድን አይምሰልህ። ለምን ትለኝ እንደሆነ ጌታ ራሱ በመውደድ ብቻ አላዳነንምና። እወዳችሁአለሁና ዳኑ ብሎ በዙፋኑ ተቀምጦ ትእዛዝ ሰጥቶ አልቀረም።
ወዶ ምን አደረገ ትለኝ እንደሆነ፦

ምሉዕ ስፉሕ  ጌታ በጠባብ ደረት በአጭር ተወሰነ። ሰማይን በደመና የሚሸፍነው በጨርቅ ተጠቀለለ።
ከነደ እሳትነቱ የተነሳ ኪሩቤል የሚንቀጠቀጡለት በብላቴናዋ በድንግል ማኅፀን ተወሰነ። ምድርና ሰማይን የሚያቀልጠቸው የክብር መብረቅ በክንደቿ ታቀፈችው። በፊቱ የእሳት ጎርፍ የሚንቀረቆርለትን በከንፈሮቿ ሳመችው። አገልጋዮቹን የእሳት ነበልባል የሚያደርገውን  እንዳይበርደው እንስሶች አሟሟቁት። አዳራሹን በመብረቅ የሠራው በበረት ተኛ። ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን የተሠወረው ቅጠል ለበሰ። የስደተኞች ተስፋ ተሰደደ። የሰማይና የምድር አባት በየጥቂቱ አደገ። ምድርን በደሙ የሚያነጻት ማይን ያነጻት ዘንድ ተጠመቀ። የዓለማት ዓለም ማደሪያ አጥቶ ቀን በምኩራብ ሌሊት በተራራ ተንከራተተ። የመምህራን አምላክ ለማይሰማ ሕዝብ በሰው ቃል ዝቅ ብሎ አስተመረ። ለመምህራን  በሞገስ መከበርን የሰጠ እየተደበ አስተማረ። መላእክት እያመሠገኑ ለማመስገን የሚሳሡለት የአይሁድን ጽርፈት ሰማ። ለተበደሉት የሚፈርድላቸው በፍርድ አደባባይ ቆመ። ከፍርድ የሚያድነው ተፈረደበት። እስረኞችን የሚፈታ ታሰረ። ሰውን ወደ ሰማይ በልዕልና ስቦ የሚያሳርገውን ጎተቱት። መንሥኤ ሙታኑን ጣሉት። ቁስለኞችን የሚፈውሰውን ቸንክረው አቆሰሉት። ራሱን ሊያለብስ የመጣውን አራቆቱት። ርኩሳኑን በደሙ ያጠበውን ርኩስ ምራቅ ተፉበት።የኃጢአትን እሾህ የሚነቅለውን የእሾህ አክሊል ደፉበት። የሕይወትን ውኃ መራራ አጡጡት። ዲያብሎስን በመስቀሉ የቸነከረውንበጦር ወጉት። ሕይዎት እርሱን ሰቅለው ገደሉት። የምድር መሠረት የሰማይን ጽንዓት በምድር ውስጥ ተቀበረ። ትንሣኤና ሕይወት ነውና ሞትን በሞቱ ደምስሶ ተነሣ!

ወደጄ ሆይ ጌታን ስለምወደው ስለማምነው ጸድቄያለሁ የምትል ከሆነ እንዲህ ብሎ ሲጠይቅህ ምን ትመልስለታለህ? ልጄ ሆይ እኔ አንተን ወድጄ ተሰቀልኩልህ።አንተ እኔን ወደህ ምን ሆንህልኝ?በዚህ ጊዜ ስለምወድህ ትጋት ትቼ ሰነፍሁልህ ልትለው ነው? ሁሉን የሚችል አምላክ በቃሉ ብቻ ማዳን እየቻለ ነገር ግን ፍቅሩን በመከራ ገልጦ ካዳነ ሰው ለአምላኩ ቃል ብቻ እንዴት ይበቃዋል
?

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወረቅ እንዲህ ሲለን እንስማ!         
"ኢትበል እፈቅድ ባሕቲቱ=ወዳጄ እወዳለሁ ብቻ አትበል"ዋናተኛ ዋና እወዳለሁ በማለት ወንዝ ይሻገራልን?ሐናጺ መሆን የሚሻ ቤት መስራት በመፈለግ ብቻ ሙያውን ሳይለምድ ቤት መስራት ይችላልን? መርከበኛ መሆን የሚሻ መርከብ መቅዘፍን ሳይለምድ ሊቀ ሐመር መሆን ይችላልን?ጸሐፊስ መጻፍ በመፈለግ ብቻ ፊደል ሳያውቅ መጻፍ ይችላልን? መንጻት የሚፈልግስ ሳይታጠብ በመፈለግ ብቻ ይነጻልን? የተራበስ ስለ ምግብ በማሰብ ብቻ ይጠግባልን? ጽድቅንስ በመሥራት እንጅ በመውደድ ብቻ መዳን ይቻላልን?

ሁለተኛው ደግሞ  አልጸድቅም ማለት ነው።
እንደዚህ የሚያሰኛቸው ደግሞ ምእመናንን ነው። መጀመሪያ ጥቂት ጥቂት እያለ ከጽድቅ ስራ ያወጣቸዋል። ከዚያ እግዚአብሔር መሐሪ ነው እያሰኘ ኃጢአት እንዲጨምሩ ያደርጋቸዋል። ከዚያ ወዲያ ፍጹም ኃጢአተኛ ሲሆኑ በኋላ እንዳይመለሱ መቼም አልጸድቅ ያስብላቸዋል።

የእመቤ ታችን ልጆች ንቁበት። ላልጸድቅ ሲያሰኛችሁ ክርስቶስ የውበት ባሕር ነው ብላችሁ መልሱለት። በአንዲት ውኃ ብዙ ሰዎች ቢታጠቡ ትደፈርሳለች። ክርስቶስ ግን የጎሰቆሉ ሁሉ ወደ እርሱ ገብትው ሲነጹ የእነርሱ ጉስቁልና እርሱን የማይለውጠው የምሕረት ባሕር ነውና እየገባን እንንጻ! በጭቃ የተለወሰውን ወርቅ ወልውለው አጥርተው ለአክሊልነት ያበቁታል። በእግር ከሚረገጥ ጭቃ በታች የነበረውን አጥርተው ከራስ በላይ ያውሉታል። ከምእመንነት በታች ወርዶ ጌታውን የካደውን ቅዱስ ጴጥሮስን በንስሐ ጠርቶ ርእሰ ሐዋርያት እንዳደረገው  አትዘንጋ! እጎዚአብሔር ቸር ነው ብሎ ኃጢአት መስራት ነው እንጅ ክፉ
እግዚአብሔር ቸር ነው እያሉ መመለስ ያድናል።


አሁንም ተስፋ ቆርጠን አንዘግይ! ለመመለስ ያብቃን! ደግሞ ማንንም የማትጸየፍ እናት አለችን። ምን ብንገዳገድ እርሷን እየተመረኮዝን እንነሳ!( በትረ ሃይማኖት ድንግል ማርያም)

#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን

ቅዳሴ ተሰጥሖ

03 Jan, 04:38


ታህሳስ 25/2017 #ሰማእቱ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ሰማእቱ #ቅዱስ_መርቆሬዎስን በምልጃ ፀሎቱ እንዲያስበን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአሉ እንኳን አደረሰን

👉ሰማዕታት የዚችን ዓለም ጣዕም በእውነት ናቁ ደማቸውንም ስለ #እግዚአብሔር አፈሰሱ ስለ መንግስተ ሰማያትም መራራ ሞትን ታገሱ፤ዉዳሴ ማርያም ዘሐሙስ ቁ.7

👉 #ቅዱስ_መርቆሬዎስ አገሩ ሮም አስሌጥስ ነው አባት እናቱ አረማውያን ነበሩ ቅዱስ መርቆሬዎስ ከተወለደ በኋላ መልአኩ የተናገረው ቃል ሁሉ እንደተፈፀመ ሲያውቅ አባቱ ከነ ቤተሰቡ አምነው ተጠምቀዋል #የመርቆሬዎስ ስመ ጥምቀቱ ፕሉፓዴር ነው ገብረ እግዚአብሔር ማለት ነው በጥበብ በፈሪሀ #እግዚአብሔር አድጎ አባቱ ሲሞት የአባቱን ሹመት ወረሰ

👉ንጉሱ ዳኬዎስ ይባላል መምለኬ ጣዖት ነበር በርበሮች በጠላትነት ተነስተውበት እንደምን ላድርግ ብሎ የምክር ቃል ሲልክበት መልአኩ በአምሳለ ወሬዛ ቀይህ በሊህ ሰይፍ ይዞ በዚህ ጠላቶችህን ድል ትነሳለህ ደስ ብሎህ በተመለስክ ጊዜ ግን ጌታህ #እግዚአብሔርን አስበው ሲለው ታይቶት ነበርና

👉አትፍራ ጌታ ጠላቶቻችንን አሳልፎ ይሰጠናል ብሎት አፅናንቶት ዘመቱ #መርቆሬዎስም ኃይል ተሰጥቶት ጠላቱን ድል ነስቶ ሲመለስ ከሃዲው ንጉስ ኡልያኖስ ወዲያው ኃይል ለሰጡን ለረዱን ለዓማልክቶቼ በዓል አድርጌአለሁና ፈጥነህ ና ብሎ ላከበት ሄዶ ሹመት ሽልማትህ ላንተ ይሁን

👉ላቆመው ጣኦት አልሰግድም በማለቱ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ በመጨረሻም ህዳር 25 ቀን አንገቱን ቆርጠው ገደሉት ደም ውኃና ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ #መርቆሬዎስ ከዕረፍቱም በኋላ ብዙ ተአምራትን አድርጓል

👉ፈረሱ ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል በኋላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል እንዴት ብሎ የሚገረም የበልአምን አህያ ይጠይቃት ዘኁልቁ.22፥28 #ለእግዚአብሔር የሚሣነዉ ነገረ ስለሌለ

👉 #የቅዱስ_መርቆሬዎስ ስዕልም በአዎንታ አንገቱን ዘንበል አድርጎ ምስክርነት ሰጥቷል ይህም ሊታወቅ ዛሬ በሀገራችን በምድረ ተጉለት በስሙ ከታነፀ ቤተ ክርስቲያን ካህናት ደነነ ስዕሉ እያሉ ሲዘምሩ ጎንበስ ቀና ሲል እንደሚታይ ይነገራል የሰማዕቱ #የቅዱስ_መርቆሬዎስ ረድኤቱ በረከቱ አማላጅነቱ ቃል ኪዳኑ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን እኔን የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ ዕለት ዕለት ይከተለኝ ማቴ.10፥38-40

👉እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን የእምነታችንንም ራስና ፈፃሚውን ኢየሱስን ተመልክተን በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ #በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና ዕብ.12፥1-2

👉የሰማእቱ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ምልጃና ፀሎቱ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን በዚህ እለት የሚታወሱ ቅዱሳን ቃል ኪዳናቸዉ ከኛ ጋር ይሁን "አሜን"✝️💒✝️

ቅዳሴ ተሰጥሖ

02 Jan, 20:00


ክብር አባታችን የንታ መንክር ከ screen record 🥰🥰🥰🥰

ቅዳሴ ተሰጥሖ

02 Jan, 20:00


ሥርዓተ ቅዳሴ፣
ዘሥልጣኑ ዲበ መትከፍቱ ሎቱ ስብሐት ወአኮቴት ዕበይ ወባርኮት ውዳሴ ወማህሌት ይዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም።

ቅዳሴ ተሰጥሖ

02 Jan, 18:24


ሰላም ቤተሰብ በ መልካ ሕማማት ዜማ የምናቃቸው ባለ ድምፀ ግርማው የ የንታ መንክር የ ቴሌግራም ቻናልን ይቀላቀሉ በተጨማሪም በ TikTok live እየገባቹ ተከታትሉ ፤

Join የምትለውን በመንካት ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

የንታመንክር join


ሼርር ሼርርር

ቅዳሴ ተሰጥሖ

02 Jan, 04:47


፨የጌታን ልደት በዝማሬ፨
የአእላፋት ዝማሬ 4ቀን ቀረው::

#አእላፋት_ዝማሬ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

02 Jan, 04:45


'በከመ ዜነዎ'/፪/ መንፈሳዊ ለጸጋ ዘአብ/፪/
ተወልደ ተክለ ሃይማኖት ዓርኩ ለመርዓዊ/፪/

ቅዳሴ ተሰጥሖ

02 Jan, 04:38


ታህሳስ 24

በዚህች ቀን ታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክልሃይማኖት የተወለዱበት ቀን ነው። የትውልድ ቦታቸው ሸዋ ጽላልሽ አወራጃ ዞረሬ ነው፤ የአባታቸው ስም ጸጋ ዘአብ የእናታቸው ስም እግዚ ሐርያ ይባላል መካን ነበሩ ልጅ እንዲሰጣቸው ወደ እግዚያብሔር ዘወትር ይጸልዩ ነበር፤ መጋቢት 12 ቀን እንዲህ ሆነ።

ሞተሎሜ የተባለ ጣኦት አምላኪ ንጉስ አገራቸውን ወረረ መንደሩንም አጠፋ ጸጋ ዘአብ ወንዝ ውስጥ ገብቶ አመለጠ እግዚ ሐርያ ግን ተማርካ ሄደች፤ በጣም መልከ መልካም ስለነበረች ሞቶሎሜ ሊያገባት አሰበ ታላቅ ድግስም ደገሰ አገር ምድሩ ተሰብስቦ ሲዘፍን ሲጨፍር ሳለ ቅዱስ ሚካኤል ታላቅ መብረቅ ነጎድጓድ አሰማ ብዙዎች ሞቱ እግዚሐርያን በክንፎ ተሸክሞ ዞረሬ ከቤተክርስቲያን ውስጥ አስቀመጣት ከባለቤቷ ጸጋ ዘአብ ጋር ተገናኙ ተቃቅፈው ተላቀሱ፤ከሁለት ቀን በኃላ መጋቢት 24 ቀን ተክለሃይማኖት ተጸነሱ።

በዛሬዋ ቀን 1167 ዓ/ም ተወለዱ ቀኑ አርብ ነበር፤ በተወለዱ በ3ኛ ቀናቸው እሁድ በ 3 ሰዓት “አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ” ብለው ሥላሴን አመሰገኑ፤ ሁለተኛ ተአምር ከዚህ በታች ያለው ስዕል ተክልዬ የአንድ ዓመት ከመንፈቅ ህጻን እያሉ ነው፤ በድፍን ሸዋ ርሃብ ተከስቶ ነበር በተለይም በዞረሬ እግዚሐርያ አዘነች አለቀሰች ምነው እርቧት ነው ጠምቷት ነው ቢሉ የለም እርቧትስ ጠምቷትስ አይደለም የቅዱስ ሚካኤል ዝክሩ ታጎለቢኝ ብላ እንጂ።

ህጻኑ ተክለሃይማኖት ከእናቱ ጭን ወርዶ እየዳኸ ወደ ጓዳ ሄደ አንስታ አቀፈችው እርሱ ግን አለቀሰ ዱቄት የተቀመጠበትን እንቅብ እንድትሰጠው በእጁ ጠቆማት ሊጫወትበት መስሏት ሰጠችው በትንንሽ እጆቹ እንቅቡ ላይ አማተበ ዱቄቱ ሞልቱ ፈሰሰ ዳግመኛ የቅቤ የዘይት ማስቀመጫ ማድጋዎች ላይ በተመሳሳይ አማተበ ሞልቶ ፈሰሰ ቤቱ በበረከት ተትረፈረፈ፤ የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን አዘከረች አገሬውን ጠርታ መገበች፤ ለተቸገሩትም አብዝታ ሰጠች፤ ይህ በረከት ሁለቱም እስኪሞቱ ድረስ አላለቀም ይላል ገድላቸው።

ተክለ ሃይማኖት በ 99 ዓመት ከ8 ወር ከ5 ቀን በዚህ ምድር ኖረው ነሐሴ 24 ቀን አርፈዋል። በደብረሊባኖስ ገዳማቸው የንፍሮ ውኃ አይነስውር ያበራል ድውይ ይፈውሳል ገድላቸው ሊነበብ ሲወጣ አጋንንት ተቃጠልን ይላሉ ሲገርም ምን ያህል ባለጸጎች ነን። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን።

#ሼር

ቅዳሴ ተሰጥሖ

02 Jan, 04:37


#ቃለ_ወንጌል

24/04/2017
ማቴዎስ 18:1-12


      በዚያች ሰዓት ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ ማን ይሆን? አሉት። ሕፃንም ጠርቶ በመካከላቸው አቆመ፡ እንዲህም አለ እውነት እላችኋለሁ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም። እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፥ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው። እንደዚህም ያለውን አንድ ሕፃን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር።

ወዮ ለዓለም ስለ ማሰናከያ፤ ማሰናከያ ሳይመጣ አይቀርምና፥ ነገር ግን በእርሱ ጠንቅ ማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት። እጅህ ወይም እግርህ ብታሰናክልህ፥ ቈርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት እጅ ወይም ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል ይልቅ አንካሳ ወይም ጉንድሽ ሆነህ ወደ ህይወት መግባት ይሻልሀል። ዓይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት ዓይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል ይልቅ አንዲት ዓይን ኖራህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል። ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና። የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቶአል
::

ምስባክ
መዝሙር 8:2-3

እም አፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ

በእንተ ጸላኢ

ከመትንስቶ ለጸላኢ ወለገፋኢ

          

ቅዳሴ ተሰጥሖ

02 Jan, 04:08


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ታኅሣሥ ሃያ አራት በዚህች ዕለት ጌታ ሐዲስ ሐዋርያ ብሎ የሾማቸው የኢትዮጵያ ብርሃኗ የሆኑ የደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ልደታቸው ነው ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

ቅዳሴ ተሰጥሖ

01 Jan, 19:01


እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአሳዳግያችን ለአማላጃችን ለኢትዮጵያዊው መናኝ የወንጌል ገበሬ የወንጌል አርበኛ ለባለስድስት ክንፉ ለሩሩሁ አባት አቡነ ተክለሃይማኖት የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን አሜን! መልካም በዓል ❤️🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

ቅዳሴ ተሰጥሖ

26 Dec, 20:03


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱

ቅዳሴ ተሰጥሖ

26 Dec, 19:48


🙋‍♂አንድጥያቄ

✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ⁉️

         

ቅዳሴ ተሰጥሖ

26 Dec, 17:07


#ከእግዚአብሔር_ምን_ትሻለህ?

#ሰሎሞን በምሳሌ 30 ÷7-9 ለአምላኩ እንዲህ በማለት ጠየቀ :-
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
"⁷ ሁለትን ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ሳልሞትም አትከልክለኝ፤
⁸ ከንቱነትንና ሐሰተኛነትን ከእኔ አርቃቸው፤ ድህነትንና ባለጠግነትን አትስጠኝ፤ ነገር ግን የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ፥
⁹ እንዳልጠግብ እንዳልክድህም፦ እግዚአብሔርስ ማን ነው? እንዳልል፤ ድሀም እንዳልሆን እንዳልሰርቅም፥ በአምላኬም ስም በሐሰት እንዳልምል።"


#ዳዊትም በመዝሙሩ እንዲህ አለ :-
  መዝ 26/27 ÷4-5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
"⁴ እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
⁵ በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥ በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።"


አንተ ከእግዚአብሔር ምን ትሻለህ?

ቅዳሴ ተሰጥሖ

26 Dec, 10:28


የጥበብ ወዳጇ ማን እንደሆነች ታውቃለህ? ትዕግስት ናት! ትዕግስት በጽናቷና እርጋታዋ ምክንያት የጥበብ እውነተኛ ወዳጅ ናት!

ቅዳሴ ተሰጥሖ

26 Dec, 10:26


#ቃለ_ወንጌል

17/04/2017
                 ሉቃስ 11:1-14

      እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፥ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንጸልይ ዘንድ አስተምረን አለው። አላቸውም ስትጸልዩ እንዲህ በሉ፦ በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፤ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤የዕለት እንጀራችንን ዕለት ዕለት ስጠን፤ ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፥ እኛ ደግሞ የበደሉንን ሁሉ ይቅር ብለናልና፤ ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን። እንዲህም አላቸው ከእናንተ ማናቸውም ወዳጅ ያለው፥ በእኩል ሌሊትስ ወደ እርሱ ሄዶ ወዳጄ ሆይ፥ ሦስት እንጀራ አበድረኝ፥ አንድ ወዳጄ ከመንገድ ወደ እኔ መጥቶ የማቀርብለት የለኝምና ይላልን? ያም ከውስጥ መልሶ አታድክመኝ፤ አሁን ደጁ ተቈልፎአል ልጆቼም ከእኔ ጋር በአልጋ ላይ አሉ፤ ተነሥቼ ልሰጥህ አልችልም ይላልን? እላችኋለሁ፥ ወዳጅ ስለ ሆነ ተነሥቶ ባይሰጠው እንኳ፥ ስለ ንዝነዛው ተነስቶ የሚፈልገውን ሁሉ ይሰጠዋል። እኔም እላችኋለሁ፦ ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፍትላችሁማል። የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልግም ያገኛል፥ መዝጊያውንም ለሚያንኳኳው ይከፈትለታል። አባት ከሆናችሁ ከእናንተ ከማንኛችሁም ልጁ እንጀራ ቢለምነው፥ እርሱም ድንጋይ ይሰጠዋልን? ዓሣ ደግሞ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ ይሰጠዋልን? ወይስ እንቍላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋልን? እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆኑ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ ያለው አባት ለሚለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው?

                            
ምስባክ
መዝሙር 2:11-12


ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሃት

ወተሐሠዩ ሎቱ በረዓድ


አጽንዕዋ ለጥበብ ከመ ኢይትመዐዕ እግዚአብሔር

ቅዳሴ ተሰጥሖ

25 Dec, 15:21


ቅ/ገብርኤል አጥቢያ ወጣቶች ህብረት ማህበር 🥰🥰

ቅዳሴ ተሰጥሖ

25 Dec, 15:02


#ኢየሱስ ጌታ ነው !

ሮማውያን ቄሳርን ጌታ ከማሰኘት አልፈው ክብር ይግባውና <ኢየሱስ ርጉም ይሁን>(Anathema Iesus)  በሉ ብለው ክርስቲያኖችን ያሰቃዩቸው ነበር ። ቅዱስ ፓሊካርፐስ
<<ንጉሤን እንዴት እረግመዋለሁ?>> ብሎ ሰማዕት የሆነውም በዚህ ምክንያት ተበረ።

በዚያ ዘመን <ቄሳር ጌታ ነው> በሉ ሲባሉ እሳት ስለቱን ሳይፈሩ በአጸፋው <ኢየሱስ ጌታ ነው> (Kuios Iesus) ብለው በጣዖት አምላኪዎች ፊት መስክረው በሰማዕትነት የሞቱ ምእመናን ብዙ ናቸው ።

ይህንን ቄሣርን ለሚያመልኩ ጣዖት አምላኪዎች የሚሰጥ <
ኢየሱስ ጌታ ነው> የሚል የምስክርነት ቃል በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አምኖ ሳያማትብና ሳይጸልይ ከቤቱ ለማይወጣ ኦርቶዶክሳዊ ምእመን እንደ አዲስ ሊነግሩትና በፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት አገላለጽ የወነገለውን ለማወንገል (evangelizing the evaangalized) የሚሞክሩ ሰዎች ምን ያህል እንደተሳሳቱ በዚህ መረዳት ይቻላል።

አንዳንድ ኦርቶዶክሳዊውያን <ኢየሱስ ጌታ ነው> ሲሏቸው <ታዲያ እኛ ምንድን ነው አልን ?> የሚሉት እንዲህ ታሪካዊ እውነታን ያዘለ ነው። <ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ > ብለው ለሚጥሩ ሰዎች ይህ ምስክርነት አይሠጥም ።



ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ :- ገፅ 112-113
ዲን. ሄኖክ ኃይሌ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

25 Dec, 15:02


የ እረፍት እናት 🥰

ቅዳሴ ተሰጥሖ

24 Dec, 16:45


ይህ ሳምንት የብርሃን ሳምንት ነው::

ከእነዚህ ብርሃናዊ ጥቅሶች አንዱን ገልጠው ያብሩና ይጻፉልን::

#ዓይን_የተፈጠረው_ለመጽሐፍ_ቅዱስ_ነው
#ዓይንዎ_ላይ_ያረፈውን_ቃል_ይጻፉልን
#ቀንዎን_በመጽሐፍ_ቅዱስ_ይጀምሩ
#መጽሐፍ_ቅዱስ_ሳላነብ_አልውልም
#እንደጃንደረባው_መጽሐፍ_ቅዱስን_እናንብብ
#ወደዚህ_ሠረገላ_ቅረብ
#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው

ቅዳሴ ተሰጥሖ

24 Dec, 16:42


ቅዱሳን ነቢያት

ቅዳሴ ተሰጥሖ

24 Dec, 14:18


አትፍረድ! ያ ሰው በምን አይነት መከራና ስቃይ ውስጥ እያለፈ እንደሆነ አታውቅምና ፈጽሞ ፈራጅ አትሁን።

ቅዳሴ ተሰጥሖ

24 Dec, 14:18


እረፉ !

ቅዳሴ ተሰጥሖ

05 Dec, 09:31


#ቃለ_ወንጌል

26/03/2017
                 
   ሉቃስ 21:12-21

       ከዚህም ሁሉ በፊት እጃቸውን በላያችሁ ይጭናሉ ያሳድዱአችሁማል፤ ስለ ስሜም ወደ ምኵራብና ወደ ወኅኒ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ወደ ነገሥታትና ወደ ገዥዎችም ይወስዱአችኋል፤ ይህም ለምስክርነት ይሆንላችኋል። ሰለዚህ እንዴት እንድትመልሱ አስቀድማችሁ እንዳታስቡ በልባችሁ አኑሩት፤ ወደረኞቻችሁ ሁሉ ሊቃወሙና ሊከራከሩ የማይችሉትን አፍና ጥበብ እሰጣችኋለሁና። ወላጆችም ስንኳ ወንድሞችም ዘመዶችም ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ፤ በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ። ከራሳችሁም አንዲት ጠጉር ስንኳ አትጠፋም፤ በመታገሣችሁም ነፍሳችሁን ታገኛላችሁ። ኢየሩሳሌም ግን በጭፍራ ተከባ ስታዩ በዚያን ጊዜ ጥፋትዋ እንደ ቀረበ እወቁ
       
                                 ምስባክ
                         መዝሙር 9:12-13

እስመ ተዘከረ ዘይትኀሠሥ ደሞሙ

ወኢረሥዐ ዐውያቶሙ ለነዳያን

ተሣሃለኒ እግዚኦ ወርኢ ዘከመ የሐሙኒ ጸላእትየ

                           ትርጉም

ደማቸውን የሚመራመር እርሱ አስቦአልና

የድሆችንም ጩኸት አልረሳምና

አቤቱ እዘንልኝ ጠላቶቼም የሚያመጡብኝን መከራ እይ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

05 Dec, 09:30


አንድ ሰው መጥቶ ለአንድ ቅዱስ አባት ጥያቄ አቀረበለት "ተአምር መሥራት እፈልጋለሁ፣ እንዴት ላድርግ?" ቅዱሱ አባት መለሰለት፦
"አንድን ሰው ወንጌል እንዲያነብ ካስተማርከው ዓይን አበራህ ማለት ነው፤  ድሆችን እንዲረዳ ካስተማርከው ሽባውን አዳንክ ማለት ነው፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሔድ እንዲችል ካደረግህ አንካሳውን ፈውሰሃል፤ ሙት ማንሣት ከፈለግህ ደግሞ ንስሓ እንዲገባ አድርገው ያኔ የሞተ ሰውን አስነሥተሃል ማለት ነው።  በል ሒድና ተአምር ሥራ!"

ይቀላቀሉ...
@betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

04 Dec, 05:52


#ቃለ_ወንጌል

25/03/2017
                    ማቴ፲÷፲፮ -

      እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ። አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና።

ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ ይገድሉአቸውማል። በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም። ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፥ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም። ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው እንግዲህ አትፍሩአቸው፤

የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና። በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ። ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።

ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል። እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ

                           ምስባክ
                   መዝሙር 67:23-24

ልሳነ ከለባቲከ ላዕለ ጸላዕቱ

አስተርአየ ፍናዊከ እግዚኦ

ፍናዊሁ ለአምላክነ ለንጉሥ ዘውስተ መቅደስ

                           ትርጉም

የውሾችህ ምላስ በጠላቶች ላይ ይሆን ዘንድ

የአምላኬ የንጉሥ መንገድ በመቅደሱ

አቤቱ መንገድህ ተገለጠ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

03 Dec, 13:55


ምን አይነት መዝሙሮችን ይፈልጋሉ?👇👇👇

ቅዳሴ ተሰጥሖ

03 Dec, 06:05


#ቃለ_ወንጌል

24/03/2017
                              ማቴዎስ ፲፫÷፴፮-
፵፫

      በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበውየእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት። እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።

እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል። የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል


                                 ምስባክ
                        መዝሙር 102:20-22


ባርክዎ ለእግዚአብሔር ኵልክሙ መላእክቲሁ

ጽኑዓን ወኃያላን እለ ትገብሩ ቃሎ

ወእለ ትሰምዑ ቃለ ነገሩ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

02 Dec, 18:04



ቅዳሴ ተሰጥሖ

02 Dec, 12:01


ቤቴ የፀሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተጽፏል እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አረጋቹት፤😔

ቅዳሴ ተሰጥሖ

02 Dec, 03:58


#ቃለ_ወንጌል

04/03/2017
                      ማቴ 10:32-ፍጻሜ


     ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ። በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም።

ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤ ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል። ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።

ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል። እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም

                                    ምስባክ
                            መዝሙር 43:22-23


ወበኀቤየሰ ፈድፋደ ክቡራን አዕርክቲከ እግዚኦ

ወፈድፋደ ጸንዑ እምቀደምቶሙ

እኌልቆሙ ወእምኆፃ ይበዝኁ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

01 Dec, 18:33


https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=0Go7sSnRgmJ6VFe7

ቅዳሴ ተሰጥሖ

01 Dec, 18:29


አንቀፀ ብርሃን ማርያም

ቅዳሴ ተሰጥሖ

01 Dec, 15:11


ልቡ ደም መርጨት
                          ሳንባው መተንፈስ
~ ያቆመ ምን ይሆናል?
*** መልስ፦ ይሞታላ!

     እንግዲያውስ የማይቆርብ ክርስቲያንና የማይጸልይ ክርስቲያን የሞተ ነው። ሕይወት የሌለው በድን መናፍቃንን ይራከራልን? ኧረ  በየት አልፎ!

እንግዲያውስ በሕይወት ለመኖር እንፍጠን።  ያለዚያ ከጸሎትና ከምስጢራት ተለይተን ስለ ቤተ ክርስቲያን ችግር ብንደራጅ ለእሳት እንደ ተከማቸ የገለባ ክምር መሆን ነው።

"እስመ ዘእንበሌየሰ ኢትክሉ ገቢረ ወኢምንተኒ -ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም" ብሏልና ባለቤቱ።

#ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን_ግርማ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

30 Nov, 16:29


የአክሱም ፅዮን በዓል !

" አክሱም ፍፁም ሰላም ናት ፤ ለአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች የሚያውክ የፀጥታ ስጋት የለም " - የአክሱም ከተማ ከንቲባ አበበ ብርሃነ

ዓመታዊው የአክሱም ህዳር ፅዮን 2017 ዓ.ም በዓል በልዩ ድምቀት መከበሩን አክሱም የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል አሳውቆናል።

በዓሉ ለመታደም ከቅርብ እና ከሩቅ የመጡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምእመናን ምእመናትና ጉብኚዎች ተገኝተው ነበር።

በዓሉ በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁም ታውቋል።

አክሱም ከተማ እጅግ ደምቃለች።

ከበዓሉ ጋር በተያያዘ ግን ወደ አክሱም የሚደረግ የአውሮፕላን ትኬት ዋጋ ልክ በዓሉ ሲቃረብ መጨመሩ በርካቶችን እንዳስከፋ ከበዓሉ ታዳሚዎች ለመረዳት ችለናል።

የዋጋ ጭማሪው ከተጓዦች ባለፈ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔዎች መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን በጉዳዩ ላይ እንደሚነጋገሩበት ለመረዳት ተችሏል።

በሌላ በኩል ፤ ካለፉት የአከባበራ ዓመታት በተለየ መልኩ ዘንድሮ በበዓሉ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጨምሮ የተገኘ ከፍተኛ የመንግስትም ሆነ የፓለቲካ ፓርቲ አመራር  የለም።

በአክሱም የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከበዓሉ አዘጋጆች ጠይቆ ባገኘው መረጃ ፤ ለሁለት የተከፈሉት የህወሓት አመራሮች በበዓሉ መልእክት እንዳያስተላልፉ መከልከላቸውን አረጋግጠዋል።  

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ በ X ገፃቸው ፤ የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በፌስኩክ ገፃቸው " የእንኳን አደረሳችሁ !! " መልእክት አስተላልፈዋል።  

ዛሬ በተከናወነው ደማው የበዓል ስነስርዓት የአክሱም ከተማ ከንቲባ አበበ ብርሃነ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

" ስጋት ያንዣበበባቸው የአክሱም ሀውልቶች የመጠገን ስራ ተጀምረዋል " ያሉ ሲሆን ጅምሩ ከጫፍ እንዲደርስ የፌደራል መንግስትና የዓለም አቀፍ የቅርሶች ተቆርቋሪ ተቋማት ድጋፋቸው እንዲቸሩ ጠይቋል።

" አክሱም ፍፁም ሰላም ናት፣ ለአገር ውስጥ እና የውጭ ቱሪስቶች የሚያውክ የፀጥታ ስጋት የለም " ያሉት ከንቲባው " በትግራይ የፀጥታ ሃይሎች ላይ የሚደረገው ስም የማጥፋት ዘመቻ በመከላከል ህዝቡ የበኩሉ እንዲወጣ " ሲሉ አደራ ብለዋል።

በዋዜማ እና በዋናው የበዓሉ ዕለት በ14 ቤተ መቅደሶች በአበው ጳጳሳት የተመሩ የቅዳሴ ፣ የስብከት እና የመዝሙር ስነ-ሰርዓቶች ተከናውነዋል።

ከታሪካዊቷ ዓድዋ በ25 ኪ/ሜ ፣ ከእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ በ60 ኪ/ሜ ርቀት የምትገኘው ቅድስት እና ታሪካዊትዋ የአክሱም ከተማ በውስጥዋ እና በዙሪያዋ በቱሪስት መስህቦች የበለፀገች ናት።
- የታቦተ ፅዮን ማድሪያ
- የበርካታ ሀውልቶች መገኛ 
- የማህሌታይ ያሬድ የሙዚቃ ኖታ እና የፈላስፋ ዘርዓያዕቆብ ማህደር
- የኢትዮጵያ ፊደላት ፣ ቁጥር ፣ የግእዝ ቋንቋና  የዘመን አቆጣጠር ያበቀለች
- የኢትዮጵያ የኪነ-ህንፃና ስነ-ፅሁፍ መፍለቂያ
- የነገስታት መቃብር
- የተለያዩ የእጅ ጥበብ ውጤቶች
- ጥንታዊ ሙዝየሞችና ሌሎች መገኛ ናት አክሱም። 

እንዲሁም በአርኪሎጂስቶች ግኝት መሰረት ከአክሱም ከተማ ቀድሞ መመስረቱ የሚነገርለት በእንዳስላሰ-ሽረ ከተማ አጠገብ የማይ አድራሻ ጥንታዊ ከተማ ፤ ነጮች የተሸነፉበት የዓድዋ እና የተምቤን ወርቃኣምባ ታሪካዊ ተራራዎች ከአክሱም ከተማ በቅርብ ርቀት ይገኛሉ።

#TikvahEthiopiaFamilyAxum

ፎቶ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia            

ቅዳሴ ተሰጥሖ

29 Nov, 21:45


እመቤታችን ሆይ፣ የቅዱሳንና የምእመናንን ኹሉ ጸሎት በማዕጠንታቸው ከምድር ወደ ሰማይ በሚያሳርጉ በሰማያውያን የካህናት አለቆች አጆች ውስጥ ባለ የወርቅ ማዕጠንት እንመስልሻለን። እንዲኹም ስምሽን በመጥራት የሰው ልጆችን ልመና ወደ ልዩ ሦስትነት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ያሳርጋሉ። የወገኖችሽንም ኅጢአት ታስተሠርዪ ዘንድ ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ተፈቅዶልሻልና። ለሰዎች ልጆች የዘለዓለም ሕይወት ድልድይ ትሆኝ ዘንድ የዓለም ኹሉ መድኃኒት ሆይ፣ ለምእመናን ወገኖችሽ መድኃኒታቸው ልትባይ ይገባል። ቅድስት ሆይ ልጅሽ ይቅርታውን ያድለን ዘንድ ለምኝልን።

አንቀጸ ብርሃን

ቅዳሴ ተሰጥሖ

29 Nov, 19:17


#አንቺ ጽዮን ማርያም አክሱም ላይ ያለሽው
ፅላተ ሙሴን በጉያሽ የያዝሽው
በህዳር 21 ለክብርሽ ስትወጪ
ለኢትዮጵያ ሀገሬ መፍትሄሽን አምጪ።
💦እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን💚💛

ቅዳሴ ተሰጥሖ

29 Nov, 14:44


"ጽዮንን ክበቧት"  መዝ.፵፯፥፲፪

መጽሐፈ ኦሪት ዘፀአት የታቦተ ጽዮንን ነገር እንዲህ ይተርከዋል። ሙሴ እስራኤልን ከካራን ወደ ከነዓን ይዞ ሲወጣ በሲና ተራራ  ፵ መዓልትና ሌሊት ከዘረጋ ሳያጥፍ ከቆመበት ሳይቀመጥ በፍጹም ጽሙና ሁኖ በጾምና ጸሎት እግዚአብሔርን ጠየቀው። የለመኑትን የማይነሣ የጠየቁትን የማይረሳ እግዚአብሔርም ዐሥርቱ ትእዛዛት የተጻፈበትን ሁለት ጽላት ለሙሴ ሰጠው። ሙሴም ወደ ሕዝበ እስራኤል ይዞ ወረደ። እስራኤል አሮንን አስገድደው፤ በጌጦቻቸው የጥጃ ምስል ያለው ጣዖት ሠርተው እያመለኩ ቢጠብቁት ሙሴ ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ታቦት ሰበረ። ዳግመኛም እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ቀድሞዎቹ አድረገህ ቅረጻቸው ብሎ ጽላትን እንዲያዘጋጅ አስተማረው። ሙሴም እንደታዘዘው አድርጎ ሠራ። (ዘፀ.፳፬ እና ፳፭) ‹‹ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን›› እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ ሙሴ ጽላቶቹን ባይሰብር ጽላትን መሥራት እንዴት ይቻል ነበር? (ሮሜ ፰፥፳፰)

ለ፭፻ ዓመታት ገደማ በእስራኤል ብዙ ገቢረ ተአምራትን ስታደርግ የነበረችዋ ይህች በሙሴ የተቀረጸች ታቦት በቀዳማዊ ምኒልክ በኩል ለኢትዮጵያ ተሰጠች። (መጽሐፈ ክብረ ነገሥትን ሙሉውን ያንብቡ) የቤተ ክርስቲያን መረጃዎች ስለ አመጣጧ እንዲህ ያስነብበናል፤   ‹‹በማእከላዊ ትግራይ አክሱም ሀገረ ስብከት አክሱም ከተማ የምትገኘው ታቦተ ጽዮን በቀዳማዊ ምኒልክ ከኢየሩሳሌም መጥታ በምኩራብ ትኖር ነበር። ይህም ከጌታ ልደት በፊት ፱፻ ዓመት ገደማ ነው።›› (የቤተ ክርስቲያን መረጃዎች፣ በሙሐዘ ጥበባት ዳንኤል ክብረት፣ ገጽ ፪፻፭)

በምኩራብ ብትቆይም አብርሃ እና አጽብሐ የተባሉት ነገሥታት ፲፪ መቅደስ ፸፪ አዕማድ ያላት የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን አሠርተውላታል። ቀጣዩ ቤተ መቅደስ በዐፄ አንበሳ ውድም ተሠርቷል፤ ይህን ደግሞ ግራኝ አቃጠለው፤ መልሰውም ዐፄ ፋሲል አሠርተውታል፤ አሁን ያለውን ደግሞ በዘመናዊ መንገድ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ አሠርተዋል፤ ይህን ተከትሎም የጽዮን በዓል በታላቅ ድምቀት ኅዳር ፳፩ ይከበራል።

ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር ናት ከምትባልባቸው ምክንያቶች አንዱ ይህ የጽላተ ሙሴ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ኅዳር ፳፩ ቀን በታላቅ ክብር ታከብረዋለች፡፡ በዚሁ ዕለት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወዳጆች ምእመናን በዓሉን ለማክበርና ለመሳለም ወደ አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን በብዛት ይገሠግሳሉ፡፡ ዕጣን፣ ጧፍ፣ ዘቢብና መባ ይሰጣሉ፡፡ ካህናቱም ከዋዜማው ጀምረው በከበሮና በጸናጽል ስብሐተ እግዚአብሔር ያደርሳሉ፡፡ በድርሳነ ጽዮን መጽሐፍ እንደተገለጠው በጽዮን ፊት እንደ የመዓርጋቸው ቆመው ‹‹ዕግትዋ ለጽዮን ወህቀፍዋ፤ ጽዮንን ክበቧት፥ በዙሪያዋም ተመላለሱ›› የሚለውን መዝሙር ከዳዊት እያወጣጡ ይጸልያሉ፤ ይዘምራሉ፡፡ ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ የታቦተ ጽዮንን ተራዳኢነት በምእመናን ፊት ይመሰክራሉ፡፡ (መዝ. ፵፯፥፲፪)

ታቦት የአመቤታችን ምሳሌ ነውናም ነቢያት ስለ ክርስቶስ በተለያየ ኅብረት፣ ትንቢትና አምሳል እንደ ተናገሩ ሁሉ ክርስቶስ ስለሚገኝባት አማናዊት ድንግል ማርያምም ተናግረዋል፤ እግዚአብሔር ወልድ ወደዚህ ዓለም በሥጋ ማርያም ከመገለጡ በፊት ከእግዚአብሔር ተልከው ሕዝቡን ከአምልኮተ ጣዖትና ከገቢረ ኃጢአት እንዲጠበቅ የሚመክሩ፣ የሚያስተምሩና የሚያጽናኑ ነበሩ፡፡ (ሉቃ.፲፮፥፲፯፣ኢሳ.፵፥፩፣ኢሳ.፵፬፥፩-፲፩) የነቢያት ትንቢት ዋናው ዓላማም እግዚአብሔር አምላክ ሕዝቡን እንደተዋቸው እንደማይቀር፣ ወደዚህ ዓለም መጥቶ. ሰው ሆኖ ተገልጦ. ወንጌልን አስተምሮና ስለ እኛ መከራን ተቀብሎ እንደሚያድነን መግለጥ ነበር፡፡ በዚህም ስለ እግዚአብሔር ማደረያ እመቤታችን ትንቢት ተናግረዋል፡፡ (ኢሳ.፯፥፬፣ማቴ.፩፥፳፫፣ሚክ. ፭፥፪)

በታቦት ሰሌዳ ላይ ‹አልፋ ወዖ› የሚለው ስመ እግዚአብሔር እንደተቀረጸ ሁሉ በአማናዊቷ ታቦት በእመቤታችን ማሕፀንም ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀርጿል። በዚህ ዕለት በኢትዮጵያ የሚከበረው ታቦተ ጽዮን ባለችባት አክሱም ብቻ አይደለም። በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በተለያዩ ቦታዎች ይከበራል።

ስለዚህም ተወዳጆች ሆይ! ጽዮንን እንክበባት! በእርሷ ምልጃና ጸሎት እንዲሁም ተራዳኢነት አምላካችን እግዚአብሔር ምሕረቱን ያወርድልን፣ ሰላምና ፍቅር ይሰጠን ዘንድ!

የአምላካችን የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የቅድስት ድንግል ማርያም አምላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ አሜን!

ቅዳሴ ተሰጥሖ

29 Nov, 12:40


ታላቅ በዓለ ንግስ በደብራችን በቃሊቲ አንቀጸ ብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ካቴድራል

ቅዳሴ ተሰጥሖ

29 Nov, 05:31


#ቃለ_ወንጌል

20/03/2017
                     ዮሐ ፲÷፩-፳፪


       እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው፤ በበሩ የሚገባ ግን የበጎች እረኛ ነው። ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል፥ የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል። የራሱንም ሁሉ ካወጣቸው በኋላ በፊታቸው ይሄዳል፥ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል፤ ከሌላው ግን ይሸሻሉ እንጂ አይከተሉትም፥ የሌሎችን ድምፅ አያውቁምና። ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ምን እንደ ሆነ አላስተዋሉም።

ኢየሱስም ደግሞ አላቸው፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እኔ የበጎች በር ነኝ። ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦችና ወንበዴዎች ናቸው፤ ዳሩ ግን በጎቹ አልሰሙአቸውም። በሩ እኔ ነኝ፤ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል፥ ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል።

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ። መልካም እረኛ እኔ ነኝ። መልካም እረኛ ነፍሱን ስለ በጎቹ ያኖራል። እረኛ ያልሆነው በጎቹም የእርሱ ያልሆኑ ሞያተኛ ግን ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፤ ተኵላም ይነጥቃቸዋል በጎቹንም ይበትናቸዋል። ሞያተኛ ስለ ሆነ ለበጎቹም ስለማይገደው ሞያተኛው ይሸሻል።

መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ። ከዚህም በረት ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱን ደግሞ ላመጣ ይገባኛል ድምፄንም ይሰማሉ፥ አንድም መንጋ ይሆናሉ እረኛውም አንድ። ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል። እኔ በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ ይህችን ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።

እንግዲህ ከዚህ ቃል የተነሣ በአይሁድ መካከል እንደ ገና መለያየት ሆነ። ከእነርሱም ብዙዎች፦ ጋኔን አለበት፡ አብዶአልም፤ ስለ ምንስ ትሰሙታላችሁ? አሉ። ሌሎችም ይህ ጋኔን ያለበት ሰው ቃል አይደለም፤ ጋኔን የዕውሮችን ዓይኖች ሊከፍት ይችላልን?
አሉ።
                   

ምስባክ
                    መዝሙር 83:6

እስመ መምህረ ህግ ይሁብ በረከተ

ወየኃውር እምኃይል ውስተ ኃይል

ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን

              

ቅዳሴ ተሰጥሖ

28 Nov, 11:46


🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣🗣
ገበሬው በጣም የሚወደው ፈረሱ ይታመምበትና ሀኪም አስጠርቶ ያስመረምረዋል ። ሀኪሙም ፈረሱ አርእጅቷል መድኃኒት እንስጠውና ከ3 ቀን በፊት ካልተሻለው ላንተም ሸክም ከሚሆን እንገለዋለን ብሎት ሄደ ።
ይህን ሲያወሩ ፍየል ሰምታ ኖሮ ለፈረሱ ያወረቱን ሁሉ እያዘነች ነገረችው ። በ3ተኛው ቀን ሀኪሙ መጣ ፈረሱም ለውጥ አላሳየም ይህን ጊዜ ሊገሉት ወሰኑ ጓደኛዬ አንተን ማጣት አልፈልግም ። ሳይገሉህ በፊት ሸክም አለመሆንህን ተነስተህ አሳያቸው ብላ እያለቀሰች ለመነችው በፍየሏ ግፊት እንደ ምንም ተነስቶ መሮጥ ጀመረ ። ገበሬው በፈረሱ መዳን ተደስቶ ፍየሏን አርዶ በላት ።

ይህ የአለም መራር እውነት ነው ። መልካም ስራ ሰርታችሁ በምስጋና ፈንታ ውርደትን ትሸለማላችሁ ። ያም ቢሆን ግን ቅን ሰው ከመሆን አትቦዝኑ ።

@betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

28 Nov, 07:35


በሠራዊት ሁሉ ላይ የተሾመ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው። [ሄኖ.10:14]
ሰላም ለሰኰናከ
ገብርኤል ሆይ፥ በዚያ ድብቅልቅና ሽብር በሆነበት ዕለት ከጌታ እግረ መስቀል ሥር ለቆሙት ተረከዞችህና ጫማዎችህ ሰላም እላለሁ፤ ገብርኤል ሆይ የጌታን ትዕግሥት የአይሁድን ግፍ ተመልክተህ በታላቅ ዐደባባይ ላይ ሰይፈ ቁጣህን አምዘገዘግኸው ቅዱሳት አንስት ግን ክርስቶስ ተነሥቷል ስላልካቸው የትንሣኤውን ምሥራች ይነግሩ ዘንድ ወደ ሐዋርያት ሄዱ።

ቅዳሴ ተሰጥሖ

22 Nov, 18:58


☆•• ☆ #ቅዳሴ ☆•• ☆
ቅዳሴ በሥርዓተ ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት በኅብረት የሚጸለይ የኅብረት ጸሎት ነው፡፡ ከፀሎቶች ሁሉ የላቀ የፀሎት ክፍል ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ፭ቱ ምሥዋዕቶች ተሞልተው ይገኙበታል እዚህንም ፭ቱን መሥዋዕቶች ማንኛውም ክርስተያን ለፈጣሪው የሚያቀርበው ነው፡፡
፩. የቁርባን መስዋዕት፡-
+
በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ውስጥ ኅብስቱ ተለውጦ ሥጋ መለኮት ወይኑ ተለውጦ ደመ መለኮት የሚሆነው በቅዳሴው ፀሎት ነው ሳናስቀድስ አንቆርብምና የቁርባን መስዋዕት የሚፈጸመው በሥርዓተ ቅዳሴ ብቻ ነው፡፡ መስዋዕቱም በቤተልሔም ይዘጋጃል በቤተክርስቲያን ውስጥ በቤተ-መቅደስ ውስጥ ደግሞ ይቀርባል ወይም ይታደላል፡፡ ጌታችን ሲወለደ በቤተልሔም ተወልዶ ቀራንዮ ለዓለም ሁሉ መስዋዕት ሆኗልና ቀራንዮ በተባለች በቤተክርስቲያን ቅዱሱ መስዋዕት ለሕዝብ ይታደላል፡፡..........

ቅዳሴ ተሰጥሖ

22 Nov, 18:09


☆•• ☆ #ቅዳሴ ☆•• ☆
በቅዳሴ ጊዜ 5ቱ ምሥዋዕቶች ምን ምን ናቸው?
14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት እነማን ይሆኑ?
ካህናት በቅዳሴ ወቅት 2: 3: 4: 5: 7: 12: ወይም 24: ሆነው ከቀደሱ ምሳሌነቱ ምን ምን ይሆን?
እኛ ክርስቲያኖች ቅዳሴን ባስቀደስን ቁጥር 4 ነገሮች እናገኛለን ምን ይሆኑ?
አምስቱ የስሜት ሕዋሳት በፀሎተ ቅዳሴ ጊዜ ያስቀድሳሉ እንዴት?

የሚሉትን ከ እግዚአብሔር ፍቃድ ጋር የምናይ ይሆናል

ቅዳሴ ተሰጥሖ

22 Nov, 18:04


14ቱ የቅዳሴ ዓይነቶች(በቅደም ተከተል)
1. ❖ ቅዳሴ ሐዋርያት(የሐዋርያት ቅዳሴ)
2. ❖ ቅዳሴ እግዚእ (የጌታ ቅዳሴ)
3. ❖ ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደነ-ነጎድጎድ
(የዮሐንስ ወልደነ-ነጎድጎድ ቅዳሴ)
4. ❖ ቅዳሴ ማርያም (የማርያም ቅዳሴ)
5. ❖ ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት
(የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ)
6. ❖ ቅዳሴ አትናቴዎስ (የአትናቴዎስ ቅዳሴ)
7. ❖ ቅዳሴ ባስልዮስ (የባስልዮስ ቅዳሴ)
8. ❖ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ (የጎርጎርዮስ ቅዳሴ)
9. ❖ ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ (የኤጲፋንዮስ ቅዳሴ)
10. ❖ ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ
(የዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ)
11. ❖ ቅዳሴ ቄርሎስ (የቄርሎስ ቅዳሴ)
12. ❖ ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ
(የያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዳሴ)
13. ❖ ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ
(የዲዮስቆሮስ ቅዳሴ)
14. ❖ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልዕ
(የጎርጎርዮስ ሁለተኛ ቅዳሴ)

ቅዳሴ ተሰጥሖ

22 Nov, 18:04


🟣ፊላታዎስ ሚዲያ🟣

⛪️የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ስረዓቱን እና ደምቡን ጠብቀው የተዘጋጁ ዝማሬዎች እንዲሁም የተለያዩ ትምህርቶችን መንፈሳዊ የቅዱሳን አባቶች ታሪኮችን የሚያገኙበት ፊላታዎስ ሚዲያ
በዚህ ሚዲያ እግዚአብሔር በረዳን መጠን
👉 የተለያዩ የአውደምህረት ስብከት ዝማሬ
👉  አዳዲስ ዝማሬ የሚያገኙበት
👉 የቅዱሳን አባቶች ታሪክ የሚያገኙበት ሚዲያ ነው‼️

የተዋህዶ ልጆች  ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ አገልግሎቱንም ያበረታቱ
              👇🏽👇🏽
https://youtu.be/qE-CX-_SDY4

ቅዳሴ ተሰጥሖ

22 Nov, 17:35


⛪️📚🙏
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ

📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

    
                      ይቀላቀሉን                   

ቅዳሴ ተሰጥሖ

22 Nov, 14:07


#ሥርዓተ_ቤተ_ክርስቲያን

በ ቅዳሴ ግዜ መለበስ ስለሌለባቸው ልብሶች.......


ምእራፍ ቅዳሴ ፡- እግዚአብሔር ያያል

ቅዳሴ ተሰጥሖ

22 Nov, 07:39


 🕊  ጾመ ነቢያት   🕊    

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

የጾመ ነብያት ምስጢር ምንድነው ?


    

ጾመ ነቢያት [ የገና ጾም ] ከልደት አስቀድሞ የሚጾም ጾም ነው፡፡ ከህዳር ፲፭ [ 15 ] ጀምሮ ለ ፵፫ [43] ቀናት የሚጾም ሲሆን ፋሲካው [ ፍቺው ] በልደት በዓል ነው፡፡ ይህም ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳንና ምዕመናን ጾመውታል፡፡

ጾመ ነብያት ስያሜውን ያገኘው ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለተፈጸመበት ነው፡፡ በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምስጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ ፣ የረቀቀው ገዝፎ ጎልቶ እየተመለከቱ ትንቢት ተናገሩ ፤ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ጾሙ ጸለዩ፡፡

ነቢያት ከእመቤታችን ስለ መወለዱ ፥ ወደ ግብፅ ስለ መሰደዱ ፥ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ ፥ ብርሃን በሆነው ትምህርተ ወንጌል ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ ፥ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ ስለመቀበሉና ስለ መሰቀሉ ፥ ስለ ትንሣኤው ፥ ስለ ዕርገቱና ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፡፡

ለአዳም የተሠጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑትም እንጂ፡፡ በየዘመናቸው ፦ "አንሥእ ኃይልከ ፣ ፈኑ እዴከ" እያሉ ጮኹ፡፡ በጾምና በጸሎት ተወስነውም እግዚአብሔር ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት ፣ በሳምንታት ፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ኤርምያስ ስለ ሥጋዌው ትንቢት በተናገረ በ፬፵፮ ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል፡፡

ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር ፦ "አያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር" ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ፡፡ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩ እነ ነቢዩ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም፡፡ [ኢሳ.፶፰፥፩]፡፡ በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለተፈጸመበት ይህ ጾም "የነቢያት ጾም" ይባላል፡፡ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ስለሆነም "ጾመ ስብከት" ይባላል፡፡

ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፦

† ፩. [    ጾመ አዳም   ]

አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገነት ከተባረረ በኋላ በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ ፤ አለቀሰ [እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ] ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ "ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ፣ በደጅህ ድኼ ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡" የሚል ነው፡፡ [ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ] ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት "ጾመ አዳም" ይባላል፡፡

† ፪. [   ጾመ ነቢያት   ]

ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው ፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች : ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም : ቅዱስ ሙሴ : ቅዱስ ኤልያስ ፣ ቅዱስ ዳንኤልና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: [ዘዳ.፱፥፲፱ ፣ ነገ.፲፱፥፰ ፣ ዳን.፱፥፫ መዝ.፷፰፥፲ ፻፰፥፳፬] ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል::

† ፫.  [   ጾመ ሐዋርያት  ]

ሐዋርያት "ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን ፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?" ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡

† ፬.  [   ጾመ ማርያም   ]

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና "ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?" ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና "ጾመ ማርያም" ይባላል፡፡

† ፭.  [   ጾመ ፊልጶስ   ]

ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት ፤ አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ ፤ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል፤ ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡

† ፮.  [   ጾመ ስብከት  ]

የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት ፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡

† ፯.  [   ጾመ ልደት   ]

የጾሙ መጨረሻ [ መፍቻ ] በዓለ ልደት ስለሆነ "ጾመ ልደት" ይባላል፡፡

በጾማችን በጸሎታችን - ስለ ቤተክርስቲያን ፥ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝብ በማሰብ በእንባ እራሳችንን ዝቅ በማድረግ እንጾም ዘንድ ይገባል፡፡


ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፡ ወለወላዲቱ ድንግል ፡ ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

ቅዳሴ ተሰጥሖ

22 Nov, 06:20


#ቃለ_ወንጌል

13/03/2017

ማቴዎስ 25:31-ፍጻሜ


የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል፤ አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል፥ በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል።

ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።

ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።

ጻድቃንም መልሰው ይሉታል ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ? እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ? ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን? ንጉሡም መልሶ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።

በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።

እነርሱ ደግሞ ይመልሱና ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።

ያን ጊዜ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል። እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ::

ምስባክ
መዝሙር 102:20-22

👉ባርክዎ ለእግዚአብሔር ኵልክሙ መላእክቲሁ

ጽኑዓን ወኃያላን እለ ትገብሩ ቃሎ

ወእለ ትሰምዑ ቃለ ነገሩ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

21 Nov, 15:58


💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

ቅዳሴ ተሰጥሖ

21 Nov, 07:35


✥••┈••●◉ ቅዱስ ሚካኤል ◉●••┈••✥
ሚካኤል (በዕብራይስጥ: מִיכָאֵל‎, ሲነበብ፡ ሚካኤል, ሲተረጎም፡ 'ማንነው እንደ እግዚአብሔር?'; በግሪክ: Μιχαήλ, ሲነበብ፡ Mikhaḗl; በላቲን: Michahel-ሲነበብ፡ ሚካኤል; በአረቢኛ: ميخائيل‎, ሲነበብ፡ ሚካኤል) በክርስትና በአይሁድ በእስልምና እንዲሁም በመላዕክት አማላጅነት በሚያምኑ ሃይማኖቶች የመላዕክት ሁሉ አለቃ ሊቀ መላዕክት ተብሎ ይጠራል።

በኅዳር ወር በዐሥራ ኹለተኛው ቀን ቤተ ክርስቲያናችን የታላቁ መልአክ የቅዱስ ሚካኤልን በዓለ ሲመት በታላቅ ድምቀት ታከብረዋለች፡፡ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን አስተምህሮ ኅዳር 12 ቀን ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በዐሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ ተሹሟል፡፡ (ይህን ኹለተኛውን ሹመት ያገኘው በሚያዚያ 2 እንደሆነ አክሲማሮስ በሚባለው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡)

መላእክት ቊጥራቸው እጅግ ብዙ ቢሆንም በ 99ኙ ነገደ መላእክት የተከፈሉና አለቆችም ያሏቸው ናቸው፡፡ የእነዚህ ሁሉ መላእክት አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ በትህትናው ልዕልናን ያገኘው ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ክብር ከማንኛውም መልአክ የበለጠ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡

በተጨማሪም ስለ መላእክት ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመረዳት እነዚህን ጥቅሶች ይመለከቱ:-

• ሰውን ይረዳሉ [ዘፍ.16፡7፤ ዘፍ.18፡15፤ ዘጸ.23፡20፤ መሳ6፡11፤ 1ኛነገ.19፡5፤ 2ኛነገ 6፡15፤ ዳን.8፡15-19፤ ዳን.3፡17፤ ት.ዘካ.1፡12፤ ማቴ.18፡10፤ሉቃ. 1፡26፤ ሉቃ.13፡6፤ ዩሐ.20፡11፤ ሐዋ.12፡6፤ ራዕይ 12፡7፤]

• ስግደት ይገባቸዋል [ዘፍ.19፡1-2፤ ዘኁ.22፡31፤ ኢያሱ 5፡12፤ መሳ.13፡2፤ 1ኛ ዜና 21፡1-7፤ ዳን.8፡15]

የቅዱስ ሚካኤል ስሞች
ሚካኤል ማለት "መኑ ከመ አምላክ (እግዚአብሔር) እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው" ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ የሚያመለክት ነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ንጹሕ ርህሩህ ኃይል ረቂቅ ማነው መልሱ የለም ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ዘርፍ ሆነው የሚጨመሩ መጠሪያዎች አሉት እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነት ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ ይኸውም መልአከ ኃይል፣ መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ፣…ናቸው፡፡
መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸ - ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡
መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡
መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታል በሱም አማካኝነት ይሠራል።

ሰላም ለርእስከ
ሚካኤል ሆይ፣ መብረቅን ለተጎናጸፈ መልአካዊ ረቂቅ ርእስህ ሰላም እላለሁ።
ተፈጥሮአቸው ከእሳት የሆነ የሰማያውያን የመላእክት ሠራዊት አለቃቸው የምትሆን ሚካኤል ሆይ፣ በኃጢአት ተሰናክዬ ወድቄ እንዳልፍገመገም አንተን ድጋፌ አድርጌአለሁና ፍጹም የማዳንህን ትድግና በኔ ላይ ትገልጽ ዘንድ በስተቀኜ ቁመህ አለሁልህ በለኝ እንጂ በሩቅ ሆነህ አትመልከተኝ። [መልክአ ሚካኤል አንቀጽ ፫]
መልካም በዓል ይሁንላችኹ።

✥••┈••●◉ ይቆየን ◉●••┈••✥

ቅዳሴ ተሰጥሖ

20 Nov, 20:09


መና ዘአውረድከ ሚካኤል /፪/
ሚካኤል መና ዘአውረድከ/፪/
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰

ቅዳሴ ተሰጥሖ

20 Nov, 17:58


ኦ ሚካኤል ኦ ሚካኤል ኦ መተንብል
ካህነ አርያም ትሰመይ ቢጸ ሱራፌል
ዘእምርኡሳን ረሑስ ወዘእምልዑላን ልዑል
ጊዜ ጸዋእኩከ ቅረበነ በምህረት ወሳህል።

◈◈◈◈◈◈◈
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

20 Nov, 10:15


ሃና ዘመዴ🥰🥰🥰🥰

ቅዳሴ ተሰጥሖ

20 Nov, 05:13


ወር በገባ ህዳር 11ቀን የሚከበሩ
ዓመታዊ
የቅዱሳን በዓላት

1.ቅድስት ሐና ቡርክት
2.ቅዱስ አርኬላዎስ ሰማዕት
3.አባ ኤልሳዕ አባ ምኔት
4.አባ ጳኩሚስ መነኮስ
5.ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
6.ቅድስት አውራኒያ (የሰማዕቱ እናት)

ወርኀዊ በዓላት
7.ቅዱስ ያሬድ ካህን
8.ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
9.ቅዱስ ፍሲለደስ ሰማዕት
10.አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ

🌷እንኳን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለወለደችልን ለቅድስት ሐና ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ።🙏❤️

ቅዳሴ ተሰጥሖ

20 Nov, 04:18


#ቃለ_ወንጌል

11/03/2017
                     ሉቃስ 18:1-9


ሳይታክቱም ዘወትር ሊጸልዩ እንዲገባቸው የሚል ምሳሌን ነገራቸው፥ እንዲህ ሲል በአንዲት ከተማ እግዚአብሔርን የማይፈራ ሰውንም የማያፍር አንድ ዳኛ ነበረ። በዚያችም ከተማ አንዲት መበለት ነበረች፥ ወደ እርሱም እየመጣች ከባላጋራዬ ፍረድልኝ ትለው ነበር። አያሌ ቀንም አልወደደም፤ ከዚህ በኋላ ግን በልቡ ምንም እግዚአብሔርን ባልፈራ ሰውንም ባላፍር፥ ይህች መበለት ስለምታደክመኝ ሁልጊዜም እየመጣች እንዳታውከኝ እፈርድላታለሁ አለ። ጌታም አለዓመፀኛው ዳኛ ያለውን ስሙ።

እግዚአብሔር እንኪያስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? እላችኋለሁ፥ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?

ምስባክ
                   መዝሙር 44:9-10

አዋልደ ንግሥት ለክብርከ

ወትቀውም ንግሥት በየማንከ

በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት

ቅዳሴ ተሰጥሖ

19 Nov, 15:39


https://www.youtube.com/live/aC9FUtVHFqs?si=wBUNYf59d2i_cuD4

ቅዳሴ ተሰጥሖ

19 Nov, 13:44


🔊🔊🔊አፋልጉኝ
እኚህ አዛውንት ወ/ሮ እታለማሁ ስሜነህ ይባላሉ ትናንት እሁድ 8/3/2017 ከ አለምባንክ ገብርኤል 4:00 አካባቢ ወጥተው አልተመለሱም። ሴትዮዋ በሰማያዊ ጥለትየሀበሻ ቀሚስ እና ቀይሹራብ ለብሰዋል።ሴትዮዋን ያየ ወይም ያሉበትን የሚያውቅ በ#0915577048 ደውሎ እንዲያሳውቀን እንዲሁም ሼር በማድረግ ለብዙ ሠው እንዲደርስ እንዲያረጉልን በእ/ር ስም እንማፀናለን።ፈላጊቤተሰቦቻቸው።

ቅዳሴ ተሰጥሖ

19 Nov, 11:43


ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ጋብቻና ልማዶቻችን ድንቅ ትምህርት ሙሉውን በ ቀንዲል ሚዲያ YouTube ያገኙታል ይጠብቁ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

19 Nov, 05:09


በዚህ ሳምንት የ ቅዳሴ ትምህርታችንን እንጀምራለን እስከዛው ለ ጓደኞቻቹ እዲሁም ለወንድሞቻቹ ሼር በማድረግ ያስተላልፉ

የ እግዚአብሔር ፍቃዱ ይሁንልን አሜን

@betekidase @betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

19 Nov, 04:52


#ቃለ_ወንጌል

10/03/2017
ማቴዎስ 25:1-14

በዚያን ጊዜ መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ የወጡ አሥር ቆነጃጅትን ትመስላለች። ከእነርሱም አምስቱ ሰነፎች አምስቱም ልባሞች ነበሩ። ሰነፎቹ መብራታቸውን ይዘው ከእነርሱ ጋር ዘይት አልያዙምና፤ ልባሞቹ ግን ከመብራታቸው ጋር በማሰሮአቸው ዘይት ያዙ። ሙሽራውም በዘገየ ጊዜ ሁሉ እንቅልፍ እንቅልፍ አላቸውና ተኙ።

እኩል ሌሊትም ሲሆን፦ እነሆ፥ ሙሽራው ይመጣል፥ ትቀበሉት ዘንድ ውጡ የሚል ውካታ ሆነ። በዚያን ጊዜ እነዚያ ቆነጃጅት ሁሉ ተነሡና መብራታቸውን አዘጋጁ። ሰነፎቹም ልባሞቹን መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው።ልባሞቹ ግን መልሰው ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው።

ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ፥ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ፥ ደጁም ተዘጋ። በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ክፈትልን አሉ። እርሱ ግን መልሶ

እውነት እላችኋለሁ፥ አላውቃችሁም አለ ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ::

ምስባክ
መዝሙር 68:10-11

👉ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ

ወኮነኒ ጽእለተ

ለበስኩ ሠቀ ወኮንክዎሙ ነገረ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

18 Nov, 14:21


ሰይጣን የኢዮብን ሀብት ሲያወድምበት ፣ ዐሥር ልጆቹን ሲገድልበት ፣ ጤናውን ሲወስድበት አንድ ነገር ግን አልነካበትም::

ሚስቱን::

ለምን?

ሚስቱን ያልነካው ምናልባት ነገረኛ ቢጤ ስለሆነች ከኢዮብ መከራ ውስጥ ተቆጥራ ይሆን?  ሰይጣን ሚስቱን ያልነጠቀው " ታንገብግበው" ብሎ ይሆን?  

ጠቢቡ "በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው" ይላል:: ምሳ.27:15 ምናልባት በሰይጣን እይታ ኢዮብን ለማማረር ሚስቱ መቆየት ነበረባት ይሆን?

በእርግጥ የኢዮብ ሚስት "ፈጣሪን ሰድበህ ሙት" የምትል መሆንዋን ስናይ ለኢዮብ ፈተና እንድትሆን ይሆናል ሳንል አንቀርም:: ሰይጣንም እንዲህ ብናስብ አይጠላም::

ነገሩ ግን ወዲህ ነው:: ሰይጣን የኢዮብን ሚስት እንዳይነካት ያደረገው የራሱ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነበር::

"ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ እርሱ በእጅህ ነው" ብሎ እግዚአብሔር ለሰይጣን አስጠንቅቆት ነበር:: ሕይወቱን አትንካ የተባለው ሰይጣን ሌላውን ሁሉ ሲያጠፋ ሚስቱን ግን ያልነካው ሚስት ሕይወት ስለሆነች ነው:: ሚስቱን መንካትም ራሱን ኢዮብን መንካት ነበር:: አዎ ሚስት ሕይወት ናት:: እንደ ኢዮብ ሚስት ብትከፋም እንደ ምሳ. 31ዋ ሚስት መልካም ብትሆንም ሕይወት ናት:: ሕይወት ደስታም ኀዘንም አለበት::  "ሕይወት እንዲህ ናት" c'est la vie እንዲል ፈረንሳይ:: ራሱ ኢዮብም "በምድር ላይ የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ አይደለምን?" ብሎአል:: ኢዮ. 7:1

አዳምም አለ :-

"ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት"

"አዳምም ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ይላት ነበር"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

18 Nov, 14:19


ኅዳር ፱ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩.ቅዱሳን ፫፲፰ቱ ሊቃውንት

፪.ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ

፫.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ

፬.አባ ይስሐቅ ሊቀ ዻዻሳት

፭.ሊቁ አካለ ወልድ

ወርኀዊ በዓላት

፩.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት)

፪.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ

፫.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን

፬.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ

፭.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ

እውነት እላቹሃለሁ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል ። በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል ። ደግሞ እላቹሃለሁ ከእናንተ ሁለቱ በምድር በማናቸውም በሚለምኑት ነገር ሁሉ ቢስማሙ በሰማያት ካለው ከአባቴ ዘንድ ይደረግላቸዋል ። ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና ። (ማቴ. ፲፰፥፲፰)

ቅዳሴ ተሰጥሖ

18 Nov, 08:31


#እናስተውል_እንመልከት

በአሁኑ ጊዜ በስርዓተ ቅዳሴ ላይ የሚገኙት አረጋውያን አባቶች እና እናቶች ብሎም ህፃናት እየሆኑ መጥተዋል ። እነዚህ ሰዎች አስቀድሰው ሚመለሱት ከሰዎች ጋር ብቻ አይደለም ከመላዕክት ጋር ጭምር ነውና ባለማስቀደስህ ይህ ትልቅ ክብር እያመለጠህ ነውና አስተውል።

በቅርብ ትምህርታችንን እንጀምራለን
          እንድናስቀድስ የ እግዚአብሔር ፍቃዱ ይሁንልን 🙏

@betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

18 Nov, 08:26


:ሊቀ ልሳናት ቀሲስ ሳሙኤል

ቅዳሴ ተሰጥሖ

18 Nov, 04:22


ማኅሌተ ጽጌን የደረሱት አባት ማን ናቸው?

ቅዳሴ ተሰጥሖ

18 Nov, 04:15


#በርን_መዝጋት

#ርእሰ_ሊቃውንት #አባገብረኪዳን ካስተማሩት


🔻ኁር ሕዝብየ ወባእ ቤተከ ወእጹ ኆኅተከ
ህዝቤ ሆይ ወደቤትህ ግባ፤ ደጅህንም ዝጋ
ይላል ኢሳይያስ 26


🔻ቤት ያለው ልብን ነው።
ወደቤትህ ግባ ያለው፦
ወደ ልብህ ግባ ህዋሳቶችህን ሰብስባቸው ማለት ነው።

ደጅን መዝጋት ማለት የማይረቡ ወሬወች ወደኛ እንዳይገቡብን ማድረግ ነው።ልብን የሚያረክሱ ነገሮችን ከመስማት መጠንቀቅ።


🔻አይንን መጠበቅ። ሚጦን ለአእይንትየ ከመ ኢይርአያ ከንቶ
አይኖቼ ከንቱ/ክፉ ነገሮችን እንዳያዩ መልሳቸው ብሏል ቅ/ዳዊት
በአይን የሚገባው ልብን ያረክሰዋል።

በጆሮ የሚገባው ልብን ያረክሰዋል። ልብን እንዳያሰናክለው አይንን፤ ጆሮን መጠበቅ ።



🔴 አባቶች ይሄን በ2 በምሳሌ ያስረዱታል።

🔶1ኛ
አንድ እብድ ድንጋይ እያነሳ ወደ ቤትህ ይወረውራል። ድንጋዩም መጠራቀም ይጀምራል። በውጭ ቆመህ ዝም ብለህ ብታየው ምን ይሆናል? 1ቀን ሲወረውርበት ዋለ፣ ሁለት ቀን ፣ ሶስት ቀን እያለ ቢደጋገም... ድንጋዩ ቤትህን ይሞላና እብዱ ከቤትህ ያስወጣኀል።


🔶እብድ የተባለ ማን ነው?
ሰይጣንና የሰይጣን ሰዎች የሚወረውሯቸው ቃላት ናቸው። እነዚያን ወደ ጆሮህ ሲገቡ ዝም ብለህ የምታዳምጥ ከሆነ ከልብህ ትወጣለህ ነው።

ቤቱን ድንጋይ ሞላው ማለት ልብህ ውስጥ የማይረቡ ነገሮች ሞሉበት ማለት ነው።


🔹ስለዚህ ድንጋዩን መጀመሪያ ሲወረውር አውጣው ማለት መጀመሪያ እንደሰማህ ሀሳብን አውጥተህ ጣል ነው።

ወይ አትስማ አሊያም ነገሩን እንደሰማህ ወዲያው እንደከንቱ ተወው። መልሰህ አታንሰላስለው ነው።


🔶2ኛ
ያየኸውንና የሰማኸውን ነገር እንደ እሳት አድርገው ይላሉ። ያየነው የሰማነው ነገር ወደ ምኞት ይቀየራል። ምኞት ወደ ተግባር ይለወጣል።


🔹እሳት ድንገት ብትይዝ (ድንገት እጅህ ላይ ቢያርፍ) ምን ታደርገዋለህ? ወርውረው ነው። ብትይዘው ምን ያደርግኀል? ሳያቃጥል አይለቅህም። ክፉ ሀሳብም ወዲያው እንዳየህና እንደሰማህ ካላስወገድከው ከዋለ ካደረ ነብስህን ሳያቃጥላት አይለቅህም።

ስለዚህ እሳት ነውና አይተህ ሰምተህ ወደልብህ የገባውን ነገር ወዲያው አውጥተህ ጣል። ሽሸው ሀሳቡን።


🔹ለዚህ ነው ማር.ይስሃቅ በቀዳሚ ጉየይ ወበካልእ ጉየይ ወበሳድስ ተንስእ ወተቃተል ያለው። ይሄንን ሀሳብ ሽሸው። ስለዚህ በርን መዝጋት።


🔻ከቤት መውጣት
ዲና የምትባል ነበረች ኦ.ዘጸአት ም34 ላይ ያለችው። የያእቆብ ልጅ ናት። እና እሷ ሳይቸግራት ከሰፈር ወጣ አለችና በሴኬም ያሉ ሰዎች ሁሉ አገኟት።

ከወጣቶች ጋር ተሰብስቦ ያለ አንድ ወጣት ጠለፈና አስነወራት። ክብሯን አጣች። በዚህም ምክንያት ደግሞ ወንድሞቿ ሄደው ህዝብ አጠፉ። ገደሉ። 


🔻ይቺ ዲና የምትባለው ነብስ ከልቧ ወጥታ የምትኮበልል ናት።
ሁሉን ማየት ደስ የሚያሰኛት ፣ የምትቅበዘበዝ፣ ሁሉን መስማት፣ ሁሉን መነካካት ደስ የሚያሰኛት፣ ከሁሉ የምትሆን፣ ከሁሉ የምትደርስ፣ ይቺ ነብስ ናት ዲና።

እራሷም ክብሯን አጣች ወንድሞቿም ነብስ ገደሉ። በዚህ ምክንያት አባቷ ያእቆብ ድንኳን ነቅሎ ተሰደደ።


🔹በእኛ ምክንያት መከራ የሚመጣው ሁሉን ልየው ፣ ሁሉን ልስማው በማለታችን ምክንያት ነው።

🔹እንሞክረው ተብሎ የተጀመረ ነገር ነው መከራ ሁኖ ከሰዎች ልብ አልወጣ ያለው። እንደቀላል የተጀመረ ነገር። ስለዚህ ሁሉን ከማየትና ሁሉን ከመስማት መቆጠብ።

የማይረባንን ነገር። ሁሉ ትምህርት ቤታችን አይደለም። ሁሉ መምህራችን አይደለም። መውጣት አለብን ከዚያ የማይረባን ከመስማት ፣ መውጣት አለብን።




🔊ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ

(በርእሰ አድባራት ወገዳማት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም የ፬ቱ ጉባኤያት ምስክር መምህር)

ቅዳሴ ተሰጥሖ

18 Nov, 04:02


#ቃለ_ወንጌል

09/03/2017

     ዮሐንስ 10:25-ፍጻሜ


   ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል ነገርኋችሁ፡ አታምኑምም፡ እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ይህ ስለ እኔ ይመሰክራል፤ እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም። በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።

የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም። እኔና አብ አንድ ነን።

አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ። ኢየሱስ ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው።አይሁድም ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት።

ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው እኔ አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን? መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ፡ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን ትሳደባለህ ትሉታላችሁን? እኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ፤ ባደርገው ግን፥ እኔን ስንኳ ባታምኑ አብ በእኔ እንደ ሆነ እኔም በአብ እንደ ሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።

እንግዲህ ደግመው ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም ወጣ። ዮሐንስም በመጀመሪያ ያጠምቅበት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ እንደ ገና ሄደ በዚያም ኖረ። ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ መጥተው ዮሐንስ አንድ ምልክት ስንኳ አላደረገም፥ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነበረ፡ አሉ። በዚያም ብዙዎች በእርሱ አመኑ::


                              ምስባክ
                        መዝሙር 72:8-9


👉ወነበቡ ዓመፃ ውስተ ዓርያም

     ወአንበሩ ውስተ ሰማይ አፉሆሙ

     ወአንሶሰወ ውስተ ምድር ልሳኖሙ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

17 Nov, 13:31


የእግዚአብሔር ልጆች እንደምን ዋላችሁ?


# አስደሳች ዜና
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ከእዚህ ሳምንት ጀምሮ የአብዛዠኞቻችንን ጥያቄ የሚመልስ 2ተኛ ዙር መርሐግብር እንጀምራለን

መርሐግብሩም #ብዙዎቻችን ቅዳሴ ተሰጥኦ መመለስ እንፈልጋለን ነገር ግን አልተማርንም

ስለዚህ እኛ አሁን ለእናንተ በድምጽ ቅጂ የቅዳሴ ተሰጥሖውን ለእናንተ እንልካለን

እናንተም ድምጹን እያዳመጣችሁ ከተማራችሁ በትንሽ ጊዜ ውስጥ እንደማንኛውም ክርስቲያን ተሰጥዖውን መመለስ እንችላለን።



ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።

@betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

17 Nov, 08:40


🔥 ✣ #_አርባዕቱ_እንስሳ  ✢
#ህዳር_8 በዓላቸው
      መንፈሳውያን አመስጋኞችና መዘምራን የምትሆኑ
               አራቱ እንስሳት ስለ አኛ ለምኑ
 
🍂አርባዕቱ እንስሳ መንፈሳውያን ሰባሕያን ወመዘምራን

                      ሰዐሉ በእንቲአነ
      ( አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ሰዓታት )  

                    #_ኪሩቤል
                          🔥 ገጸ ሰብዕ
                          🔥  ገጸ አንበሳ
     #_ሱራፌል
          💥 ገጸ ላህም
          💥  ገጸ ንስር

👉 ገጸ ሰብዕ ፦ ስለ ሰው ልጆች ይለምናል
      ገጸ አንበሳ ፦ ስለ አራዊት ይለምናል
      ገጸ ላህም ፦ ስለ እንስሳት ይለምናል
      ገጸ ንሥር ፦ ስለ አዕዋፍ ይለምናል
( ሥንክሳር ኅዳር 8 ፥ ቁጥር 17 )

🔥 ቅዱስ ጄሮም እንዲህ አለ ፦
     አርባዕቱ እንስሳት የድኅነታችን ምሥጢር የሆኑትን አራት ደረጀዋች ያስረዳሉ ።

     ገጸ ሰብእ ፦ ሥጋዌውን ( ቃል ስጋ መሆኑን )
         ገጸ አንበሳ ፦ ትንሣኤውን
        ገጸ ላህም ፦ ንጹሕ መሥዋዕት ( ቤዛ ) መሆኑን
        ገጸ ንሥር ፦ ዕርገቱን

🔥  አርባዕቱ አንስሳት
                 የጳጳሳት
                 የቀሳውስት
                 የዲያቆናት
                የምዕመናን
   ( የቤተ ክርስቲያን አምድ እኚህ ናቸውና )

   🔥 የእግዚአብሔርን ባሕርያት ያመለክታሉ።

            ገጸ ሰብእ ፦ ጥበቡንና ዕውቀቱን
                  ገጸ አንበሳ ፦ ግርማውንና ኃይሉን
                   ገጸ ላህም ፦ ትዕግስቱን ፈታሒነቱን
                    ገጸ ንሥር ፦ ክብሩን ልዕልናውን

🔥አንድም አርባዕቱ እንስሳት
በአራቱ ወንጌላውያን ይመሰላሉ።
    
🔥 “አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፥ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዓይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ እያሉ ቀንና ሌሊት አያርፉም።”
   ( ራእይ 4፥8 )

  🔥 #አርባዕቱ_እንስሳት
     #በእመቤታችን_ድንግል_ማርያም_ይመሰላሉ።
   እነሱ መንበሩን ለመሸከም እንደተመረጡ ፤  ሰማይና ምድር የማይችሉትን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ ተሸክማዋለችና ።  

ወርኃዊ መታሰቢያ በዓላቸው  በ 8 ነው.

🙏 በረከት ረድኤታቸው አይለየን 🙏

ቅዳሴ ተሰጥሖ

17 Nov, 08:37


ዛሬ ቅደሴ ላይ ከተነበበው የቅዱስ ወንግል ክፍል..

“ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ፥ እሾህም ወጣና አነቀው።”
[ማቴዎስ 13: 7]

ጌታ ቃሉን ወደ ልባችን ሲልክ ፍሬን እንድናፈራና ይበልጥ ወደ እርሱ እንድንቀርብ የሚያደርገን ነው.. ታድያ ግን በልባችን ውስጥ የዓለም የሆነው ምድራዊ አሳብ ሲነግስብን እርሱ እንደ እሾህ ይሆንና ወደ ልባችን የሚመጣውን የጌታን ቃል እንዳያፈራ ያደርገዋል.. ስለዚህም እንዲህ ያለው እሾህ ሊቆረጥ ይገባዋል..

እግዚአብሔር አምላካችን ፍሬን እናፈራ ዘንድ በጸጋው መልካም መሬት ያድርገን

መልካም የጌታ ቀን

ቅዳሴ ተሰጥሖ

16 Nov, 16:33


"በጎን የሚያደርግ ሰንበትን የሚያከብር ሁሉ ጻድቅ ነው፤ ወደ እግዚአብሔር አምልኮ የገባ መጻተኛ ከሕዝቡ ይለየኝ ይሆን? አይበል ፤ በጎ ያደረገ ሰንበትን የሚያከብር ሁሉ ጻድቅ ነው።"
   
       በጎ ሽልማት የምታስገኝ ሰንበትን
           በቅዳሴ እናክብራት🤍

ቅዳሴ ተሰጥሖ

16 Nov, 08:24


ለ ሥላሴ ኩሉ ይሰግዱ ፣

ቅዳሴ ተሰጥሖ

16 Nov, 07:43


#ንግስ_ክብረ_በዓል

በ ቃሊቲ አረጋዊያን ክብካቤ መካነስ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ወ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን 4ኛ ዓመት ክብረ በዓል በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ነው ፣

ቅዳሴ ተሰጥሖ

16 Nov, 05:09


https://www.youtube.com/live/HYiTwAUj328?si=6ZLcyl8bM5_4EZEP

ቅዳሴ ተሰጥሖ

16 Nov, 04:36


#ቃለ_ወንጌል

07/03/2017
ማቴዎስ 10:16-ፍጻሜ


እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ። አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና።

ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ ይገድሉአቸውማል። በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም። ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፥ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም። ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው! እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና። በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ። ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።

ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል። እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ። ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ። በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤ ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል። ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።

ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል። እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም::

ምስባክ
                                 መዝሙር 78:10-11

ወይርአዪ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ

በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ

ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን

ቅዳሴ ተሰጥሖ

15 Nov, 07:51


https://www.youtube.com/live/7lsqNeFUkuM?si=TL9FYOs2TltZRCqC

ቅዳሴ ተሰጥሖ

15 Nov, 04:25


ህዳር 6
በዓለ ደብረ ቁስቋም

🌷የአርያም ንግሥት፣ የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ አምላክ ልጇን አዝላ ወደ ምድረ ግብጽ ወርዳለች። በወንጌል ላይ (ማቴ. ፪፥፩-፲፰) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በሁለት ዓመቱ የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት ወርቅ፣ እጣን፣ ከርቤውን ገበሩ፤ አገቡለት።
🌷ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሄሮድስ መቶ አርባ አራት ሺህ ሕፃናትን ሲፈጅ በቅዱስ ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አንድ አምላክ ልጇን አዝላ በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቋጥራ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት ወጣች።
🌷ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ፣ በመከራ፣ በረሃብና በጥም፣ በሐዘንና በድካም፣ በላበትና በእንባ ተጉዛ ምድረ ግብጽ ገብታለች።

•የአምላክ እናቱ እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች።

•ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች።

•የሕይወትን ውኃ ተሸክማ ተጠማች።

•የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች።

•የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች።
እመ አምላክ

•ተራበች፣

•ተጠማች፣

•ታረዘች፣

•ደከመች፣

•አዘነች፣

•አለቀሰች፣

•እግሯ ደማ፣

•ተንገላታች።

🌷•ለሚገባው ይህ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው። በእውነት ይህንን እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው። አራዊት፣ ዕፅዋትና ድንጋዮች እንኳ ለአምላክ እናት ክብር ይሰጣሉ።
አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅድስት ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል። ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን መርጠዋልና።
"መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ?

•ለምን ስደቱን ወደ ግብጽና ኢትዮጵያ አደረገ?"

፩.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ። በፈጣን ደመና ወደ ግብጽ እንደሚወርድ ተነግሯልና።

(ኢሳ. ፲፱፥፩ ፣ ዕን. ፫፥፯)

፪.ምሳሌውን ለመፈጸም። የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም፣ ያዕቆብ (እሥራኤል)፣ ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና።

፫.ከግብጽ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ።

(ኢሳ. ፲፱፥፩)

፬.የግብጽና የኢትዮጵያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ።

፭.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ። (ሰው ባይሆን ኑሮ አይሰደድም ነበር። ሄሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም። ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዓርብ ደሙ አይፈስምና።)

፮.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት እና

፯.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው።
እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ለሦስት ዓመት ከስድስት ወር (ለአርባ ሁለት ወራት) በስደት የቆየችባቸው ቦታዎች አሉ። ድንግል ማርያም ከርጉም ሄሮድስ ስትሸሽግ  መጀመሪያ የሔደችው ሶርያ ድንበር (ደብረ ሊባኖስ) ነው ።
በዚህ የሸሸጋት ቅዱስ ጊጋር መስፍኑ በሄሮድስ ሲገደል ወደ ምድረ ግብፅ ወረደች። በግብፅ ብዙ ጊዜ ከአንዱ ወደ ሌላው ስትሸሽ ቆየች።

•"እንዘ ከበ በግዕት ግድፍት አመ ሳኮይኪ ውስተ ምድረ በዳ "እንዲል።

(እሴብሕ ፀጌኪ)
ቀጥላም በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ገብታ ደብረ ቢዘን ላይ(አሁን ኤርትራ ውስጥ ነው።)አረፈች። በደብረ ቢዘን ከደብረ ዳሞ፣አክሱም፣ደብር ዓባይ፣ዋልድባ እየባረከች ጣና ደርሳለች። በጣና ገዳማትም በተለይ በጣና ቂርቆስ ለመቶ ቀናት ቆይታ ቀጥታ በጎጃም ወደ ሸዋ ሂዳ ደብረ ሊባኖስን ቀድሳለች።
ቀጥላም እስከ ደብረ ወገግና ደብረ ሐዘሎ ደርሳለች። በእግሯ ያልደረሰችባቸውም የሃገራችን ክፍሎች በደመና ተጭና አይታ ባርካቸዋለት።

🌷ከልጃም በአስራትነት ተቀብላለች።
ሄሮድስ መሞቱን መልአክ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል የነገራትም እዚው ኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑን ትውፊት ያሳያል።
🌷እመ ብርሃንም ከሃገራችን ሰዎች(ከሰብአ ኦፌር) የተቀበለችውን ስንቅና ስጦታ በአምስት ግመሎች ጭና ከቅዱሳኑ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በዚእች ቀን የግብጿ ደብረ ቁስቋም ታንጻ ተቀድሳለች። የቅዱሳን ማደርያም ሁናለች።

∆ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

🌷ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ፫፻፺ዎቹ አካባቢ ድንግል እናቱን፣ ቅዱሳን ሐዋርያትን፣ አእላፍ መላእክትን፣ ጻድቃንና ሰማዕታትን አስከትሎ ወረደ።
የወቅቱ የግብፅ ፓትርያሪክ ቅዱስ ቴዎፍሎስና ሊቁ ቅዱስ ቄርሎስ ቤተክርስቲያኑን አንፀው ሕዝቡን ሰብስበው ይጠብቁት ነበረና ወርዶ ቀድሶላቸው ታላቅ ደስታ ሆኗል።
ስደቷን መሳተፍን ሽተው አበው:-

"እመ ኅሎኩ በጐይየቱ ውእተ መዋዕለ

•እምተመነይኩ ኪያሁ በዘባንየ ሐዚለ

•በበልሳንየ እልሐስ ዘአእጋሪሁ ፀበለ

•ወከመ አዕርፍ ምስሌሁ በትረ ዮሴፍ ኅበ ተተክለ

•ለወልደ ማርያም በሐጸ ፍቅሩ ልቡናዬ ቆስ።"እንዳሉ።

(ሰቆቃወ ድንግል)

🌷እኛም እመ ብርሃንን ልንሻት ያስፈልገናል። ይህ ቀን ለእኛ ለክርስቲያኖች ሁሉ እጅግ የደስታ ቀን ነውና ሐሴትን እናድርግ።
የሰማይና የምድር ጌታ ለእኛ ሲል ካደረገው ስደቱ በእዚች ቀን ተመልሷልና። ስደቷን አስበን ካዘንን፣ መመለሷን አስበን ደስ ልንሰኝ ይገባናል።

"አብርሒ አብርሒ ናዝሬት ሃገሩ

🌷ንጉስኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መጾሩ።" ልንልም ይገባል።

✟••ወስብሐት ለእግዚአብሔር••✟

@betekidase
@betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

14 Nov, 19:20


በእጃችሁ...👏

ቅዳሴ ተሰጥሖ

14 Nov, 18:56


https://youtu.be/qE-CX-_SDY4

https://youtu.be/PYhgHxupzLI?si=pQaqogjyj_DUcNXW

ቅዳሴ ተሰጥሖ

14 Nov, 18:37


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

ቅዳሴ ተሰጥሖ

14 Nov, 17:24


‹‹እስከማእዜኑ ትነብሪ ከመ ፈላሲ ወነግድ
ውስተ ርስትኪ ግብኢ እምብሔረ ባዕድ
ብሥራትኪ ድንግል ክብርተ ዘመድ
እስመ ጠፍአ ናሁ ቀታሌ ሕፃናት ብድብድ
በቤተልሔም አልቦ ዓመፃ ወሀይድ፡፡

እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሄልዊ
ሀገረኪናሁ ገሊላ እትዊ
ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ
ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ዖዝያን ዜናዊ
እምግብፅ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ፡፡››

ትርጉም፡-
በዘመድ የከበርሽ ድንግል ሆይ! ሕፃናትን የሚገድል ድንገተኛ በሽታ ሄሮድስ ስለሞተ በቤተልሔም ቅሚያና በደል የለምና እንግዳ ሆኖ እንደሚኖር ምርኮኛ በባዕድ አገር እስከ መቼ ትኖሪያለሽ? ከስደት የመመለስሽ ብሥራት በነቢያት እንደተነገረልሽ (ሆሴ11÷1፣ ማቴ2፡19÷22) ወደ ርስትሽ ቤተልሔም ተመለሺ፡፡

እመቤቴ ማርያም ሆይ! ስሙ ናዝራዊ የሚባል ልጅሽን ለአዳምና ለሔዋን ክብር የባሕርይ አባቱ አብ ከግብጽ ይጠራዋል፣ማለት በግብጽ ስደት አይሞትም ኋላ በቀራንዮ ተሰቅሎ ዓለምን ያድናል ብሎ ነቢዩ ዖዝያን (ሆሴዕ) ትንቢት እንደተናገረ እስከ መቼ በባይድ አገር ትኖሪያለሽ? እነሆ ወደ አገርሽ ናዝሬት ተመለሽ፡፡

(ሰቆቃወ ድንግል)

@betekidase
@betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

14 Nov, 16:59


ዛሬን በማህሌት ለምታገለግሉ ሁሉ መልካም አገልግሎት

ቅዳሴ ተሰጥሖ

14 Nov, 16:59


🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
አመ ፮ ለኅዳር ቁስቋም ስረዓተ ማኅሌት
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ
ስብሐት ለኪ ኦ ወላዲተ እግዚአ ኲሉ አኮቴት ወክብር ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰዓሊ ለነ ቅድስት።


ነግስ/ለልሳንከ/

ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤
ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤
ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤ አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል፤
እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።

ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል ወብሥራት ለገብርኤል ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።


ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ንዒ ርግብየ ኲለንታኪ ሠናይት ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት መሶበ ወርቅ እንተ መና በትረ አሮን እንተ ሠረፀት።

ወረብ፦
ፀምር ፀዓዳ መሶበ ወርቅ እንተ መና መሶበ ወርቅ/2/
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት እንተ ሠረፀት መሶበ ወርቅ/2/


ሰቆቃወ ድንግል

በስመ እግዚአብሔር

በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ ህፀተ ግፃዌ ዘአልቦ፤
ሰቆቃወ ድንግል እጽህፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ፤
ወይሌ ወላህ ለይበል ዘአንበቦ፤
ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ሶበ በኲለሄ ረከቦ፤
ርእዮ ለይብኪ አይነ ልብ ዘቦ።

ወረብ
ከማሃ ኃዘን ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ኃዘን/2/
ሶበ በኲለሄ ረከቦ ከማሃ ኃዘን/2/

ዚቅ
አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዓ ምንዳቤ ወኃዘነ ወኲሎ ዓፀባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ።

ወረብ
ረኃበ ወጽምዓ አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዓ/2/
ምንዳቤ ወኃዘን አዘክሪ ድንግል/2/

ምዕረ በዘባንኪ

ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ፤
ማርያም ብዙኃ በሐዚለ ሕፃን ደከምኪ፤
ሶበኒ የሐውር በእግሩ ከመ ትፁሪዮ ይበኪ፤
አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ፤
ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ።

ወረብ
አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ/2/
ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ/2/

ዚቅ
ሐዊረ ፍኖት በእግሩ ሶበ ይስዕን ሕፃንኪ ያንቀዓዱ ኀቤኪ ወይበኪ እኂዞ ጽንፈ ልብስኪ እስከ ትፀውሪዮ በገቦኪ ወትስዕሚዮ በአፉኪ።

አብርሂ አብርሂ

አብርሂ አብርሂ ናዝሬት ሀገሩ፤
ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መፆሩ፤
ጣዖታተ ግብፅ ኲሎ ቀጥቂጦ በበትሩ፤
ይጒየዩ ወይትኃፈሩ ሠራዊተ ሄሮድስ ፀሩ፤
ዘበላዕሌሁ እኩየ መከሩ።

ዚቅ
አብርሂ አብርሂ ኢየሩሳሌም በጽሐ ብርሃንኪ ወስብሐተ እግዚአብሔር ወብርሃኑ ሠረቀ ላዕሌኪ አብርሂ ጽዮን በጽሐ ብርሃንኪ ተጽዒኖ ዲበ ዕዋል በሰላም ቦአ ኀቤኪ።

ወረብ
አብርሂ አብርሂ ኢየሩሳሌም/2/
በጽሐ ብርሃንኪ ኢየሩሳሌም (ደብረ ... እከሌ)/2/


ምልጣን
ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም፤ወላዕለ ወልዳ ክርስቶስ በደብረ ቊስቋም፤ እንዘ ይብሉ ስብሐት በአርያም፤ አማን፤ ወበምድር ሰላም።


እስመ ለዓለም፦
ይቤ ቴዎፍሎስ ሊቀ ጳጳሳት፤ ሶበ ዕኩ ውስተ ዝ ንቱ ቤት፤ አዕረፈት ነፍስየ እምፃማ ዘረከበኒ በፍኖ ት፤ ኀበ ኀደረት ቅድስት ድንግል፤ ምስለ ፍቁር ወ ልዳ ኢየሱስ ክርስቶስ።

እስመ ለዓለም ዓዲ (ወይም)፦
መንግሥቱ ሰፋኒት ዘእምቅድመ ዓለም፤ ወልደ ቅ ድስት ማርያም፤ ኃሠሠ ምዕራፈ ከመ ድኩም ንጉ ሥ ዘለዓለም፤ ግሩም እምግሩማን፤ ብርሃነ ሕይ ወት ዘኢይጸልም ኃደረ ደብረ ቍስቋም፤ ኃይል ወጽንዕ ዘእምአርያም።

ቅዳሴ ተሰጥሖ

14 Nov, 09:38


አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዓ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

14 Nov, 05:50


ቅዳሴ ተሰጥሖ pinned «🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 አመ ፮ ለኅዳር ቁስቋም ስረዓተ ማኅሌት 🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀 መልክአ ሥላሴ ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል። ዚቅ ስብሐት ለኪ ኦ ወላዲተ እግዚአ ኲሉ አኮቴት ወክብር ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ…»

ቅዳሴ ተሰጥሖ

14 Nov, 04:07


#ቃለ_ወንጌል

05/03/2017
                ዮሐንስ 19:31-ፍጻሜ


      አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ሆነ ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት። ጭፍሮችም መጥተው የፊተኛውን ጭን ከእርሱም ጋር የተሰቀለውን የሌላውን ጭን ሰበሩ፤ ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፤ ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ወጣ።

ያየውም መስክሮአል፤ ምስክሩም እውነት ነው፤ እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል። ይህ የሆነ ከእርሱ አጥንት አይሰበርም የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው። ደግሞም ሌላው መጽሐፍ የወጉትን ያዩታል ይላል። ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት።

ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ። ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ። የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት። በተሰቀለበትም ስፍራ አትክልት ነበረ፥ በአትክልቱም ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ። ስለዚህ መቃብሩ ቅርብ ነበረና ስለ አይሁድ ማዘጋጀት ቀን ኢየሱስን በዚያ አኖሩት::

                                          ምስባክ
                                    መዝሙር 24:7-8

ኃጢአትየ ዘበንዕስየ ወዕበድየ ኢትዝክር ሊተ

ወበከመ ሣህልከ ተዘከረኒ

በእንተ ምሕረትከ እግዚኦ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

13 Nov, 20:39


እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ - #መንፈሳዊው_መንገድ መጽሐፍ #አያሌው_ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)

ቅዳሴ ተሰጥሖ

13 Nov, 17:38


🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
አመ ፮ ለኅዳር ቁስቋም ስረዓተ ማኅሌት
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

ዚቅ
ስብሐት ለኪ ኦ ወላዲተ እግዚአ ኲሉ አኮቴት ወክብር ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰዓሊ ለነ ቅድስት።


ነግስ/ለልሳንከ/

ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤
ወለድምፀ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤
ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤ አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሳሕል፤
እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል።

ዚቅ
ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል ወብሥራት ለገብርኤል ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።


ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
ንዒ ርግብየ ኲለንታኪ ሠናይት ፀምር ፀዓዳ እንተ አልባቲ ርስሐት መሶበ ወርቅ እንተ መና በትረ አሮን እንተ ሠረፀት።

ወረብ፦
ፀምር ፀዓዳ መሶበ ወርቅ እንተ መና መሶበ ወርቅ/2/
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት እንተ ሠረፀት መሶበ ወርቅ/2/


ሰቆቃወ ድንግል

በስመ እግዚአብሔር

በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ ህፀተ ግፃዌ ዘአልቦ፤
ሰቆቃወ ድንግል እጽህፍ በቀለመ አንብዕ ወአንጠብጥቦ፤
ወይሌ ወላህ ለይበል ዘአንበቦ፤
ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ሶበ በኲለሄ ረከቦ፤
ርእዮ ለይብኪ አይነ ልብ ዘቦ።

ወረብ
ከማሃ ኃዘን ከማሃ ኃዘን ወተሰዶ ኃዘን/2/
ሶበ በኲለሄ ረከቦ ከማሃ ኃዘን/2/

ዚቅ
አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዓ ምንዳቤ ወኃዘነ ወኲሎ ዓፀባ ዘበጽሐኪ ምስሌሁ።

ወረብ
ረኃበ ወጽምዓ አዘክሪ ድንግል ረኃበ ወጽምዓ/2/
ምንዳቤ ወኃዘን አዘክሪ ድንግል/2/

ምዕረ በዘባንኪ

ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ፤
ማርያም ብዙኃ በሐዚለ ሕፃን ደከምኪ፤
ሶበኒ የሐውር በእግሩ ከመ ትፁሪዮ ይበኪ፤
አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ፤
ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ።

ወረብ
አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ/2/
ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ/2/

ዚቅ
ሐዊረ ፍኖት በእግሩ ሶበ ይስዕን ሕፃንኪ ያንቀዓዱ ኀቤኪ ወይበኪ እኂዞ ጽንፈ ልብስኪ እስከ ትፀውሪዮ በገቦኪ ወትስዕሚዮ በአፉኪ።

አብርሂ አብርሂ

አብርሂ አብርሂ ናዝሬት ሀገሩ፤
ንጉሥኪ በጽሐ ዘምስለ ማርያም መፆሩ፤
ጣዖታተ ግብፅ ኲሎ ቀጥቂጦ በበትሩ፤
ይጒየዩ ወይትኃፈሩ ሠራዊተ ሄሮድስ ፀሩ፤
ዘበላዕሌሁ እኩየ መከሩ።

ዚቅ
አብርሂ አብርሂ ኢየሩሳሌም በጽሐ ብርሃንኪ ወስብሐተ እግዚአብሔር ወብርሃኑ ሠረቀ ላዕሌኪ አብርሂ ጽዮን በጽሐ ብርሃንኪ ተጽዒኖ ዲበ ዕዋል በሰላም ቦአ ኀቤኪ።

ወረብ
አብርሂ አብርሂ ኢየሩሳሌም/2/
በጽሐ ብርሃንኪ ኢየሩሳሌም (ደብረ ... እከሌ)/2/


ምልጣን
ዮም ጸለሉ መላእክት ላዕለ ማርያም፤ወላዕለ ወልዳ ክርስቶስ በደብረ ቊስቋም፤ እንዘ ይብሉ ስብሐት በአርያም፤ አማን፤ ወበምድር ሰላም።


እስመ ለዓለም፦
ይቤ ቴዎፍሎስ ሊቀ ጳጳሳት፤ ሶበ ዕኩ ውስተ ዝ ንቱ ቤት፤ አዕረፈት ነፍስየ እምፃማ ዘረከበኒ በፍኖ ት፤ ኀበ ኀደረት ቅድስት ድንግል፤ ምስለ ፍቁር ወ ልዳ ኢየሱስ ክርስቶስ።

እስመ ለዓለም ዓዲ (ወይም)፦
መንግሥቱ ሰፋኒት ዘእምቅድመ ዓለም፤ ወልደ ቅ ድስት ማርያም፤ ኃሠሠ ምዕራፈ ከመ ድኩም ንጉ ሥ ዘለዓለም፤ ግሩም እምግሩማን፤ ብርሃነ ሕይ ወት ዘኢይጸልም ኃደረ ደብረ ቍስቋም፤ ኃይል ወጽንዕ ዘእምአርያም።

ቅዳሴ ተሰጥሖ

13 Nov, 17:23


የቀጠለ 🥰🥰

ቅዳሴ ተሰጥሖ

13 Nov, 15:04


አምና ህዳር 6 2016 በ ቃሊቲ ድንኳኖ ቁስቋም ማርያም ማህሌት ምስጋና 🥰🥰🥰

ለትውስታ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

13 Nov, 13:50


The Time መጽሔት በልዮ እትሙ "የአእላፋት ዝማሬን" ምስል የፊት ገፅ አድርጐ ይዞ መውጣቱን ተከትሎ
| ጃንደረባው ሚዲያ |...........ኅዳር 2017

ቅዳሴ ተሰጥሖ

13 Nov, 11:42


ድንግል እመቤቴ ሆይ
አንቺ የብርሃን ደጃፍ ነሽ እኮን
አንቺ ከመወለድሽ አስቀድሞ ባለው ዘመን ሁሉ ሠልጥኖ የነበረ ሰይጣን እነሆ በልደትሽ ፊት አፈረ።

@betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

13 Nov, 10:49


አንዳንድ ጊዜ ኃጢአት የሠሩ፣ ነገር ግን ንስሐ ያልገቡ፣ እና ሌሎች ኃጢአት የሠሩ እና ንስሐ የገቡ ሰዎችን እናገኛለን…

ላልሠሩት ኃጢአት ንስሐ የገቡ ሰዎች እና ሌሎች ስህተታቸውን በሌሎች ላይ ያደረጉ...

ምንም ኃጢአትን ላለማድረግ የታገሉ ሰዎች አሉ፤ ሌሎችም ኃጢአትን ለመሥራት የጸኑ አሉ።…

ስለሌሎች ኃጢአት የሚያስብ አለ፥ ስለ ራሱም ኃጢአት የሚጨነቅ...

ለኃጢአተኞች ንስሐ እንዲገቡ የሚጸልይ ሰው አለ፣ ሌሎችም የሚኮንኑአቸው...

እና “በኹለት ሀሳብ መካከል የሚንኮታኮት ሰው አለ” [1ኛ ነገ 18፡21] በትሩን ከመካከላቸው ሊይዙት ይፈልጋሉ፣ እሱ ንስሃ የገባ ወይም ኃጢአተኛ አይደለም፣ ከእግዚአብሔር ጋር ወይም ከዲያብሎስ ጋር…

እናም በንስሃ ህይወት የኖሩ ሰዎች አሉ እናም የመጽናኛ ስርአተ ትምህርት ሆነ በእርሱም የዘላለምን ሕይወት አሸንፈዋል…

ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱ እርስዎን የሚመለከት የግል ልምምድ ያድርጉት…

ቅዳሴ ተሰጥሖ

01 Nov, 11:18


⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
ማህሌተ ጽጌ ዘሐምሳይ ሣምንት በዓለ ተክለሃይማኖት
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ስርዓተ ነግሥ፦
ለማንኛውም ወርኃዊ እና አመታዊ ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
.....................................................
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።


ገባሬ ኩሉ-
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።

ዚቅ
ዛቲ ይእቲ እኅተ ትጉሃን መላእክት፤ ወለተ ኄራን ነቢያት፤ እሞሙ ለሐዋርያት፤ ሞገሶሙ ለጻድቃን ወሰማዕት።

ወቦ መልክዓ ሥላሴ(ሌላ)

ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ
ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤ወተክለ ሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዐጽሙ፡፡

ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ ንዕዱ ማዕዶተ ንትካፈል ርስተ ኀበ ጽጌ ዘሠምረ ኀበ አስተዳለወ ዓለመ ክቡረ ምስለ ተክለሃይማኖት ንትፈሳሕ ሀገረ


ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ

ወረብ፦
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሠናይትየ  ምስለ ገብርኤል ገብርኤል ፍሡሕ ሊቀ መላእክት/፪/

ዚቅ፦
በሰላም ንዒ ማርያም፤ትናዝዝኒ ኃዘነ ልብየ፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሚካኤል ወገብርኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ሱራፌል ወኪሩቤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ኲሎሙ ቅዱሳን፤በሰላም ንዒ ማርያም ምስለ ወልድኪ አማኑኤል፤በሰላም ንዒ ማርያም ለናዝዞ ኩሉ ዓለም።


ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘይኀቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/

ዚቅ፦
ሰአሊ ለነ ማርያም አክሊለ ንጹሐን ብርሃን  ቅዱሳን።

ዓዲ ዚቅ፦
አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት ሠያሚሆሙ ለካህናት፤ነያ ጽዮን መድኃኒት

ማኅሌተ ጽጌ፦
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማህበረ ጻድቃን ተወደሰ፤ ወፈድፋድሰ በላዕለ ኃጥአን ነግሠ፤ እስመ አንሥአ ሙታነ ወሕሙማነ ፈውሰ፤ ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ፤ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ

ወረብ፦
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማህበረ ጻድቃን ተወደሰ ተአምረ ፍቅርኪ/፪/
ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ/፪/

ዚቅ፦
ይዌድስዋ ኵሎሙ ወይብልዋ እኅትነ ነያ ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ በሰማያት ኵሎሙ መላእክት

ማኅሌተ ጽጌ፦
ለምንት ሊተ ኢትበሊ እምአፈ ኃጥእ ውዳሴ፤ ይበቁዓኒ ዘብየ እምአፈ ጻድቃን ቅዳሴ፤ጽጌ መድኃኒት ማርያም ዘሠረፅኪ እምሥርወ እሴ፤ እመ ተወከፍኪ ኪያየ አባሴ፤ተአምረኪ የአኵት ብናሴ

ወረብ-
ለምንት ሊተ ኢትበሊ ድንግል ውዳሴ እምአፈ ኃጥእ/፪/
ይበቁዓኒ ዘብየ ቅዳሴ እምአፈ ጻድቃን/፪/

ዚቅ፦
አዘክሪ ለኃጥአን ወአኮ ለጻድቃን አዘክሪ ለርሱሐን ወአኮ ለንጹሐን


ሰቆቃወ ድንግል
እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሔልዊ፤ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤ለክብረ ቅዱሳን በከመይቤ ኦዝያን ዜናዊ፤እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።

ወረብ
በከመ ይቤ ኦዝያን ኦዝያን ክብረ ቅዱሳን/፪/
እምግብጽ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡ/፪/

ዚቅ
ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን ጸዋዕክዎ


መዝሙር በ5-
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን፤ወፈረዩ ኩሉ ዕጽወ ገዳም ቀንሞስ ዕቁረ ማየ ልብን፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ጸገዩ ደንጎላት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በስነ ጽጌያት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ምሕረት፤ማ፦ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ።


አመላለስ፦
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ወለመድኃኒት/፬/

ቅዳሴ ተሰጥሖ

31 Oct, 19:16


#ቅዱስሲኖዶስ

" በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለም !! ... ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን የሰላም ጥሪ እናቀርባለን " - ቅዱስ ሲኖዶስ

የጥቅምት 2017 ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ስብሰባ ተጠናቋል።

ምልዓተ ጉባኤው ከጥቅምት 11 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ መደበኛ ስብሰባውን ሲካሄድ ሰንብቷል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈሳዊ፣ በማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉ ተገልጿል።

የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ተሰጥቷል።

ከመግለጫው የተወሰደ ፦

" በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች እየተከሰተ ባለው የሰላም እጦት፣ የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወት እየተቀጠፈ፣ አካል እየጎደለ፣ ማኅበራዊ ትሥሥር እየተናደ፣ ሰብአዊ ክብር እየተጎዳ፣ መብት እየተጣሰ፣ በዜጎች ላይ ሥጋትና አለመረጋጋት እየበዛ ሀብትና ንብረት እየወደመ ስለሆነ ጉዳዩ አስቸኳይ መፍትሔ የሚያስፈልገው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ 

ስለሆነም በጦርነትና በግጭት የመጣ ሰላም፣ የተገነባ ሀገር የለምና በሀገራችን እያጋጠመ ያለውን ችግር ለመፍታት ካለፈው በመማር በጥበብ፣ በማስተዋልና በሰለጠነ አካሄድ በሰላማዊ መንገድ በመወያየት ችግሩ በእርቅ እንዲፈታ ለሁሉም ወገኖቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪውን በአጽንኦት ያቀርባል፡፡ "


(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት)

/ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል /

ቅዳሴ ተሰጥሖ

31 Oct, 19:04


💁‍♂እቤቶ ቁጭ ብለው ገንዘብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?

ቅዳሴ ተሰጥሖ

31 Oct, 18:47


💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

ቅዳሴ ተሰጥሖ

30 Oct, 12:07


"ሰው እና ግብሩ "  //

"ሰው ለመግባባት 1 ሺህ ምክንያት ኖሮት
ለመለያየት አንድ እንከን ይፈልጋል። እግዚብሔርን ደግሞ ከሱ ጋ የሚያጣላን አንድ ሺህ ምክንያት እያለ ከሱ ጋር የሚያስታርቀን አንድ በጎ ነገር ብቻ  ካገኘ ይቅር ይለናል ።

እማምላክን....የእግዚአብሔር ምህረቱ እኮ ልዩ ነው።"


#በርእሰ ሊቃዉንት አባ ገብረኪዳን ግርማ


💖

ቅዳሴ ተሰጥሖ

29 Oct, 19:42


አበው ስለ እመቤታችን እንዲህ አሉ

"አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

"ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻላት መጠን አድርገህላት ነው ፣ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማህ ያልተቃጠለችው ኃይልን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው " 
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

"ይህ ዓለም የእግዚአብሔርን ልጅ በቀጥታ ከእግዚአብሔር አብ እጅ ለመቀበል የተገባ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ዓለም ከእርስዋ ይቀበል ዘንድ አንድያ ልጁን ለድንግል ማርያም እናት ትሆነው ዘንድ ሠጣት"
ቅዱስ አውግስጢኖስ

"ሔሮድስ የማይያዘውን ይይዝ ዘንድ ተነሣ ፣ ዓውሎ ነፋስንም በቤቱ አስገብቶ ሊዘጋ ታገለ"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??"
ቅዱስ ኤፍሬም,
@betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

29 Oct, 16:53


💰ONLINE ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ

አዋ ከሆነ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
                 👇👇

ቅዳሴ ተሰጥሖ

29 Oct, 16:35


💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

ቅዳሴ ተሰጥሖ

28 Oct, 11:02


ስርዓተ ቅዳሴ ላይ.............
ልብ ብላችሁ አዳምጡት👂 ታተርፋላችሁ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

28 Oct, 07:25


#ሺ_ዓመት_አይኖር

ብዙ ጊዜ ለስንፍናችን ምክንያት ወይም ተስፋ ለመቁረጥ ሰበብ ከሚሆኑን ነገሮች አንዱ "ሺ ዓመት አይኖር" የሚለው አባባል ነው በእርግጥ በምድር ሺ ዓመት መኖር የቻለ የለም ረጅም ዓመት እንደኖረ የሚነገርለት ማቱሳላ እንኳን ሺ ዓመት አልኖረም ወዳጆቼ በተለይ እኛ ባለንበት በዚህ ዘመን ደግሞ እንኳን ሺ ዓመት ሊኖር ቀርቶ መቶ የሞላ እንኳን ቢገኝ የሚድያ የአንድ ወቅት የዜና ሽፋን መሆኑ የማይቀር ነው ስለዚህ ወደ ዘመናችን አባባሉን ማምጣት ከፈለግን "መቶ ዓመት አይኖር" በሚል ልንቀይረው ያስፈልጋል።

የሚያሳዝነው ሺ ዓመት አይኖር የምንለው ለመዝናናት ለመጨፈር ራስን ለመርሳት ፈቃደ ሥጋን እንደ ልብ ለመፈፀም ብቻ እንጂ ለመንፈሳዊ ሕይወት ለመሰናዳት አይደለም "አንቂ የሚባሉ አካላት የእድሜህን አጭርነት የሚነግሩህ ከሞት በኋላ ላለው ረጅሙ ዕድሜ በዚህች በአጭሯ የምድር ዕድሜህ በጎ ሰርተህ እንድታልፍ ሳይሆን እንዳትጨናነቅ ፈታ ብለህ (በእነርሱ አማርኛ እንድትኖር ለማስታወስ ብቻ ነው።

ወዳጆቼ ልበ አምላክ ዳዊት ግን በምድር ስለምንኖርበት ዕድሜ ሲነግረን ቢበዛ (ቢበረታ) ሰማንያ ይለናል። ስለዚህ ሰዎች ሺ ዓመት አይኖር ሲሉህ ቢበዛ ሰማንያ እርሱም በተገኘ በላቸው ታዲያ በምድር የምትኖርበት ዕድሜህ ጥቂት ከሆነ ከዚህ በኋላ በሞት ይህን ምድር ከተሰናበትክ ከሞት በኋላ የት ትሄድ ይሆን? የዚህ ምድር ኑሮህ በሞት ከተቋጨ በኋላ ሞተህ የምትቀር መሰሎህ እንዳይሰማህ። ከሞት በኋላ ሕይወት አለህ። ያውም እንደ ሰው ኖረህ ከሞትክ የምትነሳው እንደ ሰው ሆነህ የምትኖረውን ሕይወት ለመድገም እንዳይመስልህ።

ከትንሣኤ በኋላ የምትኖረው እንደ መላእክት ነው "በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ" /ማቴ 22÷30/ እንዲል። ስለዚህ አስታውስ የምድር ኑሮህ ቢበዛ #ሰማንያ ነው ያ ማለት ጥቂት ነው መፅሐፍ እንደሚነግርህ። "ሕይወታችሁ ምንድን ነው ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና" /ያዕ 4÷14/

አምላከ ቅዱሳን ለንስሐ የተዘጋጄ ልብ ያድለን ለንስሐ ሞት ያብቃን። አሜን !

@betekidase
# ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

28 Oct, 06:10


ድስትና ሰሐን
እሳቱን ግር አድርገው አንድደው ይለበልቡታል፡፡ ዕዳው የጀመረው ‹ትንሽ እሳት ይስማው› ብለው የጣዱት ጊዜ ነው፡፡ እሳቱ ሞቅ ሲያደርገው ሽንኩርቱን አቀመሱት፡፡ ሽንኩርቱ ብቻውን አልመጣም፡፡ ወደል ማማሰያ ይዞ እንጂ፡፡ ባልተወለደ አንጀቱ ሆዱን ያተራምስለት ገባ፡፡ አንዴ እያማሰለ፤ አንዴም ሆዱን እየፋቀ የክብደት አንሽ እግር የሚያህለው ማማሰያ  ድስቱን ይፈቀፍቀዋል፡፡ ሽንኩርቱ አጋም ሲመስል ደግሞ ውኃውን ቸለስ አደረጉበት፡፡ እፎይ አለ ድስቱ፡፡ ግን ምን ዋጋ አለው እፎይታው የዘለቀው እስኪንፈቀፈቅ ድረስ ብቻ ነው፡፡
የድስቱ ዙሪያ መጀመሪያ ጠቆረ፣ ቀጥሎም ጥላሸት ተቀባ፡፡ በመጨረሻም ራሱ ከሰለ፡፡ ሁለቱ ጆሮዎቹ ከሥሩ የሚነደውን ገሞራ እያዩ ‹ማርያም ማርያም› ይላሉ፡፡ ሥጋው ከገባበት በኋላማ ከሥሩ ማገዶውን፣ ከሆዱ ማማሰሉን እያከታተሉ ስቃዩን አበዙት፡፡ ደግሞ የጉልቻው መከራ፡፡ ይቆረቁራል፡፡ ‹‹የእናት ሞትና የድንጋይ መቀመጫ እየቆዩ ይቆረቁራል›› እንዲሉ በአንድ በኩል የድንጋዩ ጉብጠት፣ በሌላ በኩል የድንጋዩ ትኩሳት፣ እንኳን ለመቀመጫነት ለሲኦልነት እንኳን ሲበዛበት ነው፡፡
ለአራት ሰዓታት ያህል በውስጥ በአፍኣ አሳሩን ሲበላ ቆይቶ እዚያው ምድጃው ላይ ተዉት፡፡ እርሱም ተንፈቅፍቆ - ተንፈቅፍቆ፣ በመጨረሻ በክዳኑ በኩል ትንፋሹ እያወጣ ያንኮራፋ ጀመር፡፡ እሳቱም እየደከመውና ዓይኑ እየተስለመለመ ሄዶ አሸለበ፡፡ አልፎ አልፎ ብቻ ቆይተን የዚህን ድስት መጨረሻ እናያለን ያሉ ጉማጆች የዐመድ ሻሽ ለብሰው፣ ዓይናቸውን ከፈት ከደን እያደረጉ ሙቀቱ ጨርሶ እንዳይጠፋ አድርገውታል፡፡ ጉልቻውም ዋናው እሳት የተወውን እኔ ‹ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ› አልሆንም ብሎ መቀዝቀዝ ጀምሯል፡፡

ድስቱ ግን ዕንቅልፍ ሊወስደው አልቻለም፡፡ ኳ - ኳኳ - ቂው - ቂው ቂው - ቻ - ቻቻ - የሚል ድምጽ ማዕድ ቤቱን ሞላው፡፡ እዚህና እዚያ የሚጣደፉ ሰዎች ይታያሉ፡፡ ይወጣሉ፤ ይገባሉ፡፡ ይከራከራሉ፤ ይነታረካሉ፡፡ ድስቱን ረበሸው፡፡ እንዲያም ሆኖ ድካሙ ስለበረታበት ክዳኑን አናቱ ላይ ጣል አድርጎ ሸለብ ማድረግ ሲጀምር - ኳ - የሚል የቅርብ ድምጽ ሰማ፡፡ ይበልጥ ያነቃው ደግሞ - ኳ - የሚለው ድምጽ እዚያው ድስቱ አካባቢ የተሰማ መሆኑ ነው፡፡
የድስቱ ክዳን ተነሣ፡፡ ‹እባብ ያየ በልጥ ይደነግጣል› እንዲሉ ለአራት ሰዓታት ያህል ያሰቃየው እሳት ደግሞ ሊመለስ ነው ብሎ ሰቀጠጠው፡፡ ግድንግዱ ማማሰያ መጥቶ ሊወቅጠኝ ነው ብሎ ሲጠብቅ አንዲት አንገቷ የሰለለ፣ አናቷ የሞለለ ጭልፋ ቀጫ ቀንቧ እያለች ስትመጣ ታየች፡፡ ‹ይቺ ደግሞ ምንድን ናት?› አለ ድስቱ፡፡ የሚገርመው ነገር ብቻዋን አልነበረችም፡፡ ሁለት ድንቡሽ ያሉ ወጣት ሴቶች አንዲት እንደነርሱ ድንቡሽ ያለች ሰሐን ይዘዋል፡፡ ዙሪያዋን በአበባ ምስል ተጊጣለች፡፡ ሁለመናዋ ነጭ ነው፡፡ አንድም የቆሸሸ ነገር አይታይባትም፡፡ እንዲያውም ከሁለቱ ወጣት ሴቶች ጀርባ ፎጣ ይዛ አንዲት ልጅ ትከተል ነበር፡፡  ያቺ ሰሐን አንዳች ነገር ጠብ ሲልባት ፈጠን ብላ ጠረግ ታደርግላታለች፡፡

ጭልፋዋ ወደ ወጡ ጎንበስ ስትል ድንገት አንዲት ፍንጣቂ ዘልላ ሰሐኗ ላይ ዐረፈች፡፡ ያቺ እንደ ደንገጡር ከኋላ የምትከተል ወጣት እንደ ጀት ፈጥና በያዘችው ፎጣ ጥርግ አደረገችላት፡፡ ድስቱ ተገረመ፡፡ አራት ሰዓት ሙሉ ሲንፈቀፈቅ፣ ከታች የሚመጣ እሳት፣ ከውስጥ የሚፈነጥቅ ወጥ እንዲያ ጥቁርና ቀይ ሲያደርገው ዘወር ብሎ ያየው የለም፡፡ ጠቁሮ - ጠልሽቶ -ከስሎ -  እንኳን ሌላ ራሱ ድስቱ ራሱን እስኪረሳው ድረስ - ካሉት በታች ከሞቱት በላይ ሆነ፡፡ ያን ጊዜ ቀርቶ ወጡ በስሎ ሲያልቅ እንኳን ልጥረግህ፣ ልወልውልህ ያለው የለም - አየ ድስት መሆን፡፡
‹ደግሞ አንቺ ማነሽ?› አላት ድስት በሁለት ቆነጃጅት እጆች የተያዘችውን ሰሐን፡፡
‹የወጥ ማቅረቢያ ሰሐን ነኝ› አለችው ፈገግ እያለች፡፡
‹ምን ልታደርጊ መጣሽ?› አለ ከዚህ በፊት እዚያ አካባቢ አይቷት አያውቅም፡፡
‹ለእንግዶቹ ወጥ ልወስድ ነው› አለች የወጡ ፍንጣቂ እንዳይነካት ፈንጠር እያለች፡፡
‹ማን የሠራውን ማን ያቀርበዋል?› አለ ድስት እንደመፎከር ብሎ፡፡
‹ድስቶች ለፍተው የሠሩትን ሰሐኖች ተዉበው ያቀርቡታል› አለችውና ፍልቅ ብላ ሳቀች፡፡
‹የት ነበርሽ አንቺ ለመሆኑ? እሳት ከሥር፣ ማማሰያ ከላይ ሲኦል እንደገባ ኃጥእ ሲያሰቃዩኝ? ለመሆኑ ሽኩርቱ ሲቁላላ፣ ቅመሙ ሲዋሐድ፣ ሥጋው ሲወጠወጥ፣ ጨው ጣል ሲደረግ፣ ማማሰያው ሆዴን ሲያተራምሰው - ለመሆኑ አንቺ የት ነበርሽ? የመሥዋዕቱ ጊዜ የት ነበርሽ፣ የመከራው ጊዜ የት ነበርሽ፣ የችግሩ ጊዜ የት ነበርሽ፣ ሽንኩርቱ፣ ቅመሙ፣ ቅቤው፣ ሥጋው መልክና ስማቸውን ቀይረው ‹ወጥ› እስኪባሉ ድረስ የት ነበርሽ? አሁን ወጥ ሆኑ ሲባል ነው የምትመጭው› አላት ድስቱ ከጉልቻው ላይ እየተወዛወዘ፡፡
‹ስማ ድስቱ› አለችው ሰሐኗ፡፡ ‹ዋናው መሥዋዕትነቱ አይደለም፡፡ አቀራረቡ ነው፡፡ ሰውኮ ድስቱን ሳይሆን ወጡን ነው የሚፈልገው፡፡ ወጡ ደግሞ በእኛ በኩል ነው የሚቀርበው፡፡ በድስት ይሠራ፣ በበርሜል ይሠራ፣ በገንዳ ይሠራ፣ በጉድጓድ ይሠራ ማን ያይልሃል፡፡ ተጋባዦቹምኮ አዳራሹን እንጂ ማዕድ ቤቱን አያዩትም፡፡ ለመሆኑ ምግብ ቤት ገብቶ ‹አስተናጋጇ በደንብ አላስተናገደችኝም› የሚል እንጂ ‹ወጥ ሠሪዋ በሚገባ ለብሳ፣ ጤናዋን ጠብቃ፣ ከአደጋ የሚከላከል ልብስ አጥልቃ፣ አካባቢዋን አጽድታ አልሠራችውም› ብሎ የሚያማርር ተስተናጋጅ ሰምተህ ታውቃለህ? ወዳጄ ዘመኑ ለድስቶች ሳይሆን ለሰሐኖች ነው ዋጋ የሚሰጠው›› አለችው፡፡
ድስቱ አልተዋጠለትም፡፡ በተለይ ደግሞ አራት ሰዓት ሙሉ ከሥር ከላይ የከፈለውን መሥዋዕትነት ሲያስበው - እንኳን ሊዋጥለት፣ ሊጎረስለት አልቻለም፡፡

👇 ቀጣዩን ያንብቡ 👇

ቅዳሴ ተሰጥሖ

28 Oct, 06:10


👆 የቀጠለ 👆

የለፋነው እኛ፣ የነደድነው እኛ፣ የተማሰልነው እኛ፤ መከራውን የቀመስነው እኛ - ለመሆኑ ከየት የመጣ ወጥ ነው ብሎ ነው ተጋባዡ የሚያስበው? ለመሆኑ ያለ አኛ እናንተ መኖር ትችሉ ነበር? ያንቺ ውበት የኔ መቃጠል ውጤት አይደለም? አንቺ በሁለት እልፍኝ አስከልካዮችና በአንዲት ደንገጡር እንድትከበቢ ያደረግንሽ እኛ አይደለንም? እኔና የወጥ ማማሰያ የከፈልነው መሥዋዕትነት እንዴት ቢረሳ ነው አንቺና ጭልፋ በመጨረሻ መጥታችሁ የምትሽረቀሩት››
ሁለቱ ሴቶች ወጡን እያወጡ ወደ ሰሐኗ ሲጨምሩ - ‹ስማ› አለቺው ሰሐኗ ‹አንተ የተናገርከው እውነቱን ነው፡፡ እኔ የምነግርህ የሚያዋጣውን ነው፡፡በዚህ ዘመን በሚፈለገውና በሚያስፈልገው መካከል ልዩነት መፈጠሩን አልሰማህም መሰል፡፡ በዚህ ዘመን ማራቶኑን የምትፈልገው ለጤና ከሆነ ዐርባ ሁለቱን ኪሎ ሜትር ሩጥ፤ ማራቶኑን የምትፈልገው ለሽልማቱ ከሆነ ግን ዐርባውን ሌሎች ይሩጡልህ፣ አንተ ግን ሁለት ኪሎ ሜትር ሲቀር ገብተህ ቅደም፡፡ ያን ጊዜ ልፋቱን ሌላው ይለፋል -ሽልማቱን አንተ ትወስዳለህ፡፡ እስኪ ለሀገራቸው ዋጋ የከፈሉትን፣ የተሠዉትን፣ የሞቱትን፣ የደከሙትንና ሀገሪቱን ሀገር ያደረጉትን አስባቸው፡፡ ምን አገኙ? እነርሱ እንዳንተ ማዕድ ቤት ውስጥ ተረስተው  ቀርተዋል፡፡ ስለ እነርሱ የሚደሰኩረውና የሚተርከው ግን ዛሬ የት ነው ያለው? ዘመኑ የዐርበኞች ሳይሆን የድል አጥቢያ ዐርበኞች ነው፡፡››
ይህንን ስትነግረው ወጡ ተጠቃልሎ ወጥቶ ደንገጡሯ የተፈናጠቀውን እየጠረገች ነበር፡፡ በድስቱ ክዳን አናት ላይ ባለችው ቀዳዳ አበባ ተደረገባት፡፡ ሰሐንዋን የያዘችው ወጣት ለሌላዋ ወጣት ስትሰጣት እንደ አራስ ልጅ በባለ አበባ ጨርቅ አደግድጋ ተቀበለቻት፡፡ ጭልፋ የያዘችው ወጣት ከፊት እንደ እልፍኝ አስከልካይ እየመራች፣ ፎጣ የያዘችው ወጣት እንደ ደንገጡር እየተከተለች አጅባት ሄደች፡፡ ድስቱም ‹እዚህ ሀገር እንደ ጠረጲዛ አበባ ፊት  ሆኖ የሚታየውን እንጂ፣ እንደ ጄነሬተር ከኋላ ሆኖ የሚሠራውን የሚያየውና የሚያከብረው የለም ማለት ነው?›› አለ፡፡ ይህን ሲናገር ሁለት ወጠምሻ ጎረምሶች መጥተው ከጉልቻው አውጥተው ድስቱን ዐመድ ላይ ጣሉት፡፡

ቅዳሴ ተሰጥሖ

27 Oct, 05:30


፣ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን፣
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ቅዳሴ ተሰጥሖ

26 Oct, 21:54


ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ወቀዳሜ ሰማዕት
ክርስትናን በሰማዕትነት በማሳደግ የመጀመሪያ ምሳሌ የሆነ ሊቀ መምህር

እስጢፋኖስ (በግሪክ: Στέφανος ሲነበብ ፡ Stéphanos ስቴፋኖስ፤ በዕብራይስጥ ፡ הקדוש סטפנוס ፤ በእንግሊዘኛ ፡ Stephen ሲነበብ ፡ ስቴፈን) በሕገ ወንጌል (በክርስትና) የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው።

የተወለደው በ፩ኛው ክፍለ ዘመን፤ የትውልድ ቦታ ኢየሩሳሌም፤ የእናት ስም ማርያም፤ የአባት ስም ስምዖን፤ የሚከበረው በመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ሥንክሳር፤ በዓለ ንግሥ ሲመቱ ጥቅምት ፲፯ ቀን፣ ዕረፍቱ ጥር ፩ ቀን ፍልሰቱ መስከረም ፲፯ ቀን
በግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን ቶቢ ፩ ቀን በምዕራባውያን ዲሴምበር ፳፮ ቀን፤ ያረፈበት ቀን ጥር ፩ ቀን በመናፍቃን በድንጋይ ተወግሮ

ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር። ይህም በወጣትነት ያለፈችው ሕይወቱ ስትሠራ የነበረው ታላቅ መንፈሳዊ ሥራ ይመሠክራል።

የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ። (ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ) ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ። የወቅቱ ታላቅ መምህር ገማልያል ይባል ነበር። ይህ ሰው [በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፭፥፴፫] ላይ ተጠቅሷል። በትውፊት ትምህርት ደግሞ ይህ ደግ (ትልቅ) ሰው በርካታ ቅዱሳንን (እስጢፋኖስን፣ ጳውሎስን፣ ናትናኤልን፣ ኒቆዲሞስን...) አስተምሯል። በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር ፤ በፍጻሜውም አምኗል ። ቅዱስ እስጢፋኖስም ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ። ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር።

ከቅዱስ ዮሐንስ መጥምቁ ጋር
በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሐ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ። ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ። ለስድስት ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ። ለስድስት ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በኋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠመቀ። በወቅቱ የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ መምህሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው። "ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው።" በሚል ላከው። ቅዱሱም ከጌታ ዘንድ ሔዶ እጅ ነስቶ ተማረ። [ሉቃ. ፯፥፲፰] በዚያውም የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ።

ወንጌል ስለማጥናቱ
ጌታም ከሰባ ኹለቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው፤ አጋንንትም ተገዙለት። [ሉቃ. ፲፥፲፯] ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ፤ ምስጢር አስተረጐመ። ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ ከተነሳ በኋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ባርኳል። በዚህ ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን (ጵጵስናን) ተሹሟል። በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከሰባ ኹለቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት፣ ምሥጢርን የተገለጠለት የለም። በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን ይሰብክ ገባ።

በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ ሰባቱ ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር። አልፎም የስድስቱ ዲያቆናት አለቃ እና የስምንት ሺው ማኅበር መሪ(አስተዳዳሪ) ሆኑዋል። ስምንት ሺህ ሰውን ከአጋንንት መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ አባቶቻችን መጠየቅ ነው። አንድን ሰው ተቆጣጥሮ ለደኅንነት ማብቃት እንኳን እጅግ ፈተና ነው። መጸሐፍ እንደሚል ግን መንፈስ ቅዱስ የሞላበት ማኅደር እግዚአብሔር ነውና ለርሱ ተቻለው። [ሐዋር፣ሥ፡፮ ቁ፡፭] አንዳንዶቻችን ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ሲባል እንደዘመኑ ይመስለን ይሆናል። እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው። ዲቁና ለእርሱ " በራት ላይ ዳርጎት" እንጂ እንዲሁ ድቁና አይደለም።

ከጌታችን ዕርገት በኋላ
ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በኋላ ለአንድ ዓመት ያህል ስምንት ሺውን ማኅበር እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት "እጠፋ እጠፋ" አለች። በዚህ ጊዜ "ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው  ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው " ብለው አይሁድ በማመናቸው አልቀረም ገደሉት። እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው። በመጨረሻውም ስለ እነሱ ምሕረትን እየለመነ በድንጋይ ወገሩት። ደቀ መዝሙርቱም ታላቅ ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት።

ከአረፈ በኋላ 
ቅዱስ እስጢፋኖስ ከአረፈ ከሦስት መቶ ዓመት በኋላ በኢየሩሳሌም የሚኖር አንድ ደግ ሰው ነበረ ስሙም ሉኪያኖስ ይባላል። በተደጋጋሚ በራዕዪ ቅዱሱ እየተገለጠለት "ሥጋዬን አውጣ" ይለው ነበርና ሒዶ ለጳጳሱ ነገረው። ጳጳሱም ደስ ብሎት ካህናትና ምዕመናንን ሰብስቦ ወደ አፀደ ገማልያል ማለት ወደ መምህሩ ሄደ። ቦታውንም በቆፈሩ ጊዜ ታላቅ መነዋወጥ ሆነ። መላዕክት ሲያጥኑም በጎ መዓዛ ሸተተ። ዝማሬ መላዕክትም ተሰማ። ሕዝቡና ጳጳሱም በቅዱስ እስጢፋኖስ ፊት ሰግደው በታላቅ ዝማሬና በሐሴት ዐፅሙን ከዚያ አውጥተው በጽርሐ ጽዮን (በተቀደሰችው ቤት) አኖሩት። እለ እስክንድሮስ የተባለ ደግ ሰውም ቤተክርስቲያን አነጸለት ወደዚያ  አገቡት።
ከአምስት ዓመታት በኋላም እስክንድሮስ ሲያርፍ በሳጥን አድርገው በቅዱሱ ጎን አኖሩት። የእስክንድሮስ ባለቤት ግን ወደ ሀገሩዋ ቁስጥንጥኒያ ስትመለስ የባሏ ሥጋ መስሉዋት የእስጢፋኖስን ቅዱስ ሥጋ በመርከብ ጭና ወሰደችው። መንገድላይም ከሳጥኑ ውስጥ ዝማሬ ሰምታ ብታየው ያመጣችው የቅዱሱን ሥጋ ነው። እጅግም ደስ አላት አምላክ ለዚህ አድሉዋታልና። እርሷም ወስዳ ለታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጥንጢኖስ አስረከበችው። በከተማው ታላቅ ሐሴት ተደረገ። ሥጋውን ሊያኖሩት በበቅሎ ጭነው ሲወስዱትም በቅሎዋ በሰው ልሳን ተናግራ ማረፊያውን አሳወቀች። በዚያም ላይ ትልቅ ቤተክርስቲያን ታንጾለታል።[1]

ማጣቀሻ
* ሲመቱ ጥቅምት ፲፯ ቀን፤ ዕረፍቱ ጥር ፩ ቀን ፍልሰቱ መስከረም ፲፭ ቀን ነው ።
^ ከስንክሳር የተገኘ መረጃ
* መጽሐፍ ቅዱስ (የሐዋርያት ሥራ አንድምታ)
* መዝገበ ቅዱሳን

ቅዳሴ ተሰጥሖ

26 Oct, 17:12


ዛሬን በማኅሌተ ጽጌ ለምታገለግሉ ሁሉ መልካም ቁመት 🙏

ቅዳሴ ተሰጥሖ

26 Oct, 07:19


⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️
ማህሌተ ጽጌ ዘራብዓይ ሣምንት
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ስርዓተ ነግሥ፦
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።


መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕፆሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋሕዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢ ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣዖት ግሉፍ አሐዱ ድርህም።

ዚቅ፦
መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ጽጌ ደንጐላት ወከመ ሮማን ዘውስተ ገነት ይትፌሥሑ ጻድቃን የውሃን ውሉደ ብርሃን በትፍሥሕት ዔሉ ውስተ አድባር

ማኅሌተ ጽጌ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እንዘ ተሐቅፊዮ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ/፪/
ንዒ ርግብየ  ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/

ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ አግዓዚት ከመ ጎሕ ሠናይት ታቦተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጣስ ደብተራ ፍጽምት ማኅደረ መለኮት

ማኅሌተ ጽጌ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ ዘይኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ  ማርያም  ቀጸላ  መንግሥቱ ለጊዮርጊስ።

ዚቅ፦
ሰአሊ ለነ ማርያም አክሊለ ንጹሐን ብርሃን  ቅዱሳን።

ማኅሌተ ጽጌ፦
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማህበረ ጻድቃን ተወደሰ፤ ወፈድፋድሰ በላዕለ ኃጥአን ነግሠ፤ እስመ አንሥአ ሙታነ ወሕሙማነ ፈውሰ፤ ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ፤ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ወረብ፦
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማህበረ ጻድቃን ተወደሰ ተአምረ ፍቅርኪ/፪/
ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ/፪/

ዚቅ፦
ይዌድስዋ ኵሎሙ ወይብልዋ እኅትነ ነያ ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ በሰማያት ኵሎሙ መላእክት

ማኅሌተ ጽጌ፦
ለምንት ሊተ ኢትበሊ እምአፈ ኃጥእ ውዳሴ፤ ይበቁዓኒ ዘብየ እምአፈ ጻድቃን ቅዳሴ፤ጽጌ መድኃኒት ማርያም ዘሠረፅኪ እምሥርወ እሴ፤ እመ ተወከፍኪ ኪያየ አባሴ፤ተአምረኪ የአኵት ብናሴ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ወረብ-
ለምንት ሊተ ኢትበሊ ድንግል ውዳሴ እምአፈ ኃጥእ/፪/
ይበቁዓኒ ዘብየ ቅዳሴ እምአፈ ጻድቃን/፪/

ዚቅ፦
አዘክሪ ለኃጥአን ወአኮ ለጻድቃን አዘክሪ ለርሱሐን ወአኮ ለንጹሐን

ሰቆቃወ ድንግል
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ወረብ፦
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም/፪/
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል/፪/

ዚቅ
አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤ አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም ያንጸፈጽፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ።
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ወረብ፦
አመ አመ አጒየይኪ ዕጓለኪ በሐቂፍ/፪/
እንዘ ከመ ዝናም ያንጸፈጽፍ እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ/፪/

መዝሙር በ6፦
በጊዜሁ ኀለፈ ክረምት፤ ቆመ በረከት ናሁ ጸገዩ ጽጌያት፤ናርዶስ ፈረየ በውስተ ገነት፤ቀንሞስ ቀናንሞስ ከርካዕ ምስለ ዕንጎታት ማ፦ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበተ፤ነአኩቶ ለዘጸገወነ ሠናይቶ።



ቅዳሴ ተሰጥሖ

25 Oct, 20:20


ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ
(ዲ/ን ሕሊና በለጠ)

በማኅሌተ ጽጌ
"አክሊለ ጽጌ ማርያም
ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ
ክበበ ጌራ ወርቅ" እያልን እንዘምራለን። ግን ለምን እንዲህ እንላለን?
በቅድሚያ ሙሉ የማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱን ከነ ትርጉሙ ላስቀምጥ:-
"ክበበ-ጌራ-ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኀቱ፣
ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፣
አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፣
አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፣
ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።"
#ትርጉም:-
"ባሕርይ ከሚባል ከሚያበራ ዕንቁ ይልቅ የጠራ የወርቅ ጌጥ የኾንሽለት፣
(የጊዮርጊስ) የስሙ ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የተጻፈብሽ፣
ለጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ የሆንሽ የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ፣
አንቺ ለእርሱ ኹሉን ታሰግጂለታለሽ፣
እርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል።"

ቅዱስ ጊዮርጊስ የ7 ዓመታት ተጋድሎውን የጀመረው በ20 ዓመቱ ነበር። ለሰባት ዓመታት ያክል እየሞተ እየተነሣ ተጋድሎውን ፈጽሞ በ27 ዓመቱ፣ በሚያዝያ 23፣ በ304 ዓ.ም. ዐረፈ። እስከዚያው ጌታችን ቃል እንደ ገባለት 3 ጊዜ ሞቶ 3 ጊዜ ተነሥቷል። በዐራተኛው ሞቱ ፈጽሞ ዐረፈ። ያረፈውም በዕለተ ዓርብ በ9 ሰዓት ነበር።
ቅዱስ ጊዮርጊስ 4 ጊዜ መሞቱን "ማርያም" ከሚለው ባለ 4 ፊደል ቃል ጋር ያመሣጠረው ደራሲው "ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ - የስሙ ምልክትና የሞቱ መታሰቢያ የተጻፈብሽ" ሲል እመቤታችንን በማኅሌተ ጽጌ አመሰገናት።
ቅዱስ ጊዮርጊስን ያንገላታ የነበረው ንጉሥ ዱድያኖስ ንግሥት እለስክንድርያ የምትባል ሚስት ነበረችው። መሳፍንቱና መኳንንቱ ኹሉ ለእርሷ ይሰግዱ ነበር። በሰማዕቱ ትምህርት አምና ለቅዱስ ጊዮርጊስ የፀጋ ስግደትን ሰገደችለት። በዚህም ምክንያት በሚያዝያ 15 አንገቷን በሰይፍ እንድትቆረጥ ተደርጋለች።
ያቺ ሣር ቅጠሉ ኹሉ ይሰግድላት የነበረች ንግሥት ለቅዱስ ጊዮርጊስ መስገዷን ያስተዋለው ሊቁ ግን በማኅሌተ ጽጌው "አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ - አንቺ ለእርሱ ኹሉን ታሰግጂለታለሽ" ሲል በእመቤታችንና በሰማዕቱ ምስጋና ላይ ዘከራት። ቅዱስ ጊዮርጊስ ፍጥረት ኹሉ "ብፅዕት" ለሚላት ለድንግል እንደሚሰግድም "ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ - እርሱ ግን ላንቺ ይሰግዳል" ሲል ገልጾአል።
"የደናግል መመኪያ፣ የሰማዕታት አክሊል፣ ..." የምትባለው እመቤታችን: ቀደም ሲል ባነሣናቸው ምክንያቶች የተነሣ: ይልቁንስ ለሊቀ ሰማዕታት ለቅዱስ ጊዮርጊስ የከበረች አክሊሉና ዘውዱ መኾኗን ሲገልጽም "ክበበ-ጌራ-ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኀቱ... አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ - ባሕርይ ከሚባል ከሚያበራ ዕንቁ ይልቅ የጠራ የወርቅ ጌጥ የኾንሽለት... ለጊዮርጊስ የመንግሥቱ ዘውድ የሆንሽ የአበባ አክሊል ማርያም ሆይ" ብሏል።
እኛም እንደ አባ ጽጌ ድንግልና እንደ አባቶቻችን በማኅሌተ ጽጌ "ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ" እያልን እመቤታችንንና ሰማዕቱን እንዘክራለን።

ቅዳሴ ተሰጥሖ

25 Oct, 20:15


ከ15 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

10+10×0+10=???

ቅዳሴ ተሰጥሖ

25 Oct, 19:50


🫃👉መንታ ወንድና ሴት ቢወለዱ ክርስትና እንዴት  ይነሳሉ⁉️
👉ሴት በወር አበባ ጊዜስ⁉️
👉 ወንድ ህልመ ሌሊት ቢያጋጥመው ለስንት ቀን ይረክሳል ⁉️
👉 ሰባቱ አጽዋማት እነማን ናቸው⁉️
👉 አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ማን ናቸው⁉️
👉 ከአስርቱ ትዕዛዛት ውጪ ያለው ትዕዛዝ ምነው⁉️

⛪️ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንፃር መልሱን ይመልከቱ⛪️
                    👇👇👇👇

ቅዳሴ ተሰጥሖ

25 Oct, 05:24


✝️ቅንነትንጉሥ ሰሎሞንን ለማየት ዉጡ



በርእሰ ሊቃዉንት አባ ገብረኪዳን ግርማ ❤️🙏


ሠናይ ቀን ቤተሰብ 💖

ቅዳሴ ተሰጥሖ

24 Oct, 13:16


እግዚአብሔር ለምን ይቆጣናል?

እግዚአብሔር የሚቆጣን ስለ ራሱ ክብር ብሎ አይደለም፡፡ ብንሰድበውም ብንክደውም እንኳን የሚቆጣን ስለ ሰደብነው ወይም ስለ ካድነው አይደለም፡፡ ምክንያቱም እኛ ስለ ካድነው እግዚአብሔር ምንም አይጎድልበትም፡፡ እኛ ስለ ሰደብነው እግዚአብሔር ምንም አይጎድልበትም፡፡ ይልቁንም እንዲህ በማድረጋችን የምንጎዳው እኛው ነን፡፡ በመኾኑም የሚቀጣን ለእኛ ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሣ ነው፡፡ የሚቆነጥጠን ለእኛ ካለው ወደርየለሽ ጠብቆቱ የተነሣ ነው፡፡ እርሱን እየናቅነውና እየራቅነው ስንሔድ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን ስንሔድ እንዳንጎዳ ሽቶ ነው፡፡

ብርሃንን የሚጠላ ሰው ብርሃኑን ሊጎዳው አይችልም፤ በጨለማ ውስጥ በመቀመጡ ራሱን ይጎዳል እንጂ፤ በራሱ ላይ የጉዳት ዓይነትን ይከምራል እንጂ፡፡ እኛም እግዚአብሔርን ብንጠላው በእግዚአብሔር ባሕርይ ላይ ምንም ነገር አናጎድልም፤ ምረረ ገሃነምን በራሳችን ላይ እንፈርዳለን እንጂ፡፡

እግዚአብሔር በእኛ እይታ እጅግ ክፉ የሚመስሉ ነገሮች በእኛ ላይ ሲያመጣ እኛን ከመበቀል አንጻር አይደለም፤ ይበልጥ ወደ እርሱ እንድንቀርብ እንጂ፡፡ ሐኪሞች አእምሮአቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡዋቸው አይከፋቸውም፡፡ በዚህ አኩርፈውም መድኃኒት ማድረጋቸውን አያቆሙም፡፡ ሕሙማኑ ለዚህ በሽታ የዳረጋቸውን በሽታ ይፈውሱላቸው ዘንድ ይተጋሉ እንጂ፡፡ የሕሙማኑን ችግር እንጂ የእነርሱ መሰደብ አያሳስባቸውም፡፡ እግዚአብሔር አምላካችንም የሚቆነጥጠን ስለ ሠራነው ኃጢአት አይደለም፤ ኃጢአት ሕመም ነውና ከሕመማችን እንድንፈወስ ሽቶ እንጂ፡፡

ቸር አባት ሆይ! ይህ ከአእምሮ የሚያልፍና የዚህ ዓለም ቋንቋ ሊገልፀው የማይችለው ፍቅርህና ጠብቆትህ ዘወትር እናስበው ዘንድ፣ አስበንም በተግባር እንኖረው ዘንድ አእምሮን ለብዎን ስጠን፡፡ ለዚህ ግሩም ፍቅርህ ያልተገባንና የዕውቀት ግምጃ ቤት ብቻ ኾነን እንዳንገኝ ብርታቱን አድለን፡፡ አሜን!

Add እያረጋችሁ ቤተሰብ 🙏
@betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

24 Oct, 12:26


⛪️📚🙏
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ

📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖

    
                      ይቀላቀሉን                   

ቅዳሴ ተሰጥሖ

24 Oct, 11:58


ዋዜማ ማለት በዓለ ንግስ ከ1 ቀን በፊት የሚደርስ ስርዓት ነው። ቅዱስ ብሎ ኪዳንን በዜማ በማድረስ ይጀመራል። ከዛ መሀትው ሚባለው በዜማ ይደረሳል። የራሱ መሀትው ከሌለው ዋዜማውን ሀሌታውን በማውጣት ይባላል።

  ዋዜማ፦
በሁሉም ቦታ ቋሚ የሆነ ሲሆን ሀሌታ ያለውና በምልጣን መልኩ ይደርሳል። የራሱ የሆነ ማንሻና አመላለስ አለው።መሪ ና ተመሪ ካደረሱት በኃላ በዝማሜ ተብሎ ከከበሮ ጋር ይቀርባል።

ዋዜማው እንዳለቀ መስተበቁዕ በዜማ ይደረሳል። ቄሱ ወካዕበ ናስተበቁዕ እያለ ያደርሳል።

ከዛ መስተበቁዕ በዜማ ከተባለ በኃላ ሚደረስ ስርአት አሉ። ከመዝሙረ ዳዊት የተወጣጡ ናቸው።
1. ለእግዚአብሔር ምድር በምላ፦
መዝሙር 23 ላይ ያለ ነው። አንድ ቅኔ ከዝክረ ቃል ይጨምራል። አባባሉም የመጋቢት 5፦

መሪ፦ለእግዚአብሔር ምድር በምልዐ
ተመሪ፦ለእግዚአብሔር ምድር በምልዐ
መሪ፦አባ ጸሊ በእንቲአነ
ተመሪ፦አባ ጸሊ በእንቲአነ
መሪ፦አለምኒ ወኩሎሙ
ተመሪ፦አለምኒ ወኩሎሙ
መሪ፦እለ ይነብሩ ውስቴታ
ተመሪ፦እለ ይነብሩ ውስቴታ
መሪ፦አባ ጸሊ በእንቲአነ
ተመሪ፦አባ ጸሊ በእንቲአነ

ከዛ ማንሻውን ተከትለው ሊቃውንቱ ለ2 ቡድን በመሆን ያደርሱታል።

2.እግዚአብሔር ነግሰ፦መዝሙር 92 ሲሆን አባባሉ

መሪ፦እግዚአብሔር ነግሰ
ተመሪ፦ እግዚአብሔር ነግሰ
መሪ፦ስብሀቲሁ ለብሰ
ተመሪ፦ስብሀቲሁ ለብሰ
መሪ፦ሃሌሉያ ሃሌ ሉያ
ተመሪ፦ሃሌሉያ ሃሌ ሉያ
መሪ፦ለብሰ
ተመሪ፦ለብሰ
መሪ፦እግዚአብሔር
ተመሪ፦እግዚአብሔር
መሪ፦ኃይሎ ወቀነተ
ተመሪ፦ኃይሎ ወቀነተ
መሪ፦ሃሌሉያ ሃሌ ሉያ
ተመሪ፦ ሃሌሉያ ሃሌ ሉያ
መሪ፦ወአጽንዓ ለዓለም ከመ ኢታንቀልቅል
ተመሪ፦ ወአጽንዓ ለዓለም ከመ ኢታንቀልቅል

ቻናል ላይ ምንለቀው እዚህ ጋር በዜማ ይባላል።

ማህሌታውያን በተለይ ዋዜማ ከበሮ ምትመቱ ወንዶች መዝሙር 23 እና መዝሙር 92ን በቃል መያዝ አለባችሁ። ዳዊት የዘለቃችሁ(የተማራችሁ) ጥሩ በርቱ ግን ካልተማራችሁ ቢያንስ መዝሙር 23 እና መዝሙር 92ን በቃል ያዙ፤ ዜማው ቀላል ነው።

3.ይትባረክ፦
ጸሎተ ሠለስቱ ደቂቅ ፱ ላይ አለ።

እነዚህ እየተባለሉ በየመሀሉ ባለ 5 መስመር ቅኔ ከሊቃውንቱ ይቀርባል። 6 ቢሆንም የመጀመሪያው መስመር ላይ ይደረባል። ዝማሜና አንዳንድ ጊዜም አመላለስ ይኖረዋል። የከበሮ አመታቱም ለየት ያለና ደስ የሚያሰኝ ነው።

  ሰላም፦
የዋዜማው መጨረሻ ነው። ሀሌታ ያለው ሲሆን መጨረሻ ላይም አመላለስ ይኖረዋል። አብዛኛውን ቦታ እዚጋ በጸሎት ቢዘጉም አንዳንድ ደብር ደግሞ ኢትግድፈነ ወኢይትመንነነ ና እግዝእትነ ነፅሪ ሐቤነ እያሉ ያመሰግናሉ።

@betekidase
Share share
@betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

24 Oct, 07:35


በዓለ ልደቱ ለአቡነ አረጋዊ

የጻድቁ የአቡነ አረጋዊ አባት ይስሐቅ እናቱም እድና ይባላሉ፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ነበሩ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የተባረከውን ልጅ ሰጣቸው፤ይህም የሆነው በጥር ፲፬ ቀን ነው፡፡ እግዚአብሔርን መፍራት፣ ሕገ ኦሪትን ትምህርተ ነቢያትንና ቅዱሳት መፃሕፍትን እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ እርሱም በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እየጸና እየበረታ አደገ፡፡ ሚስት ያገባ ዘንድ አጩለት፡፡ ጻድቁ አባታችን አቡነ ዘሚካኤል(አረጋዊ) ፈጽሞ እምቢ አለ፡፡ ከብዙ ዘመን በኋላ ከሮም ወደ ግሪክ ሀገር አባ ጳኩሚስ የሚኖርበት ደውናስ ወደምትባል ገዳም የምንኩስናን ልብስ ይለብስ ዘንድ ሄደ፡፡ አባ ጳኩሚስንም አገኘው፡፡ አባ ጳኩሚስም ‹‹ልጄ ሆይ፥  አንተ የንጉሥ ልጅ እንደ መሆንህ መጠን የመንግሥቱ ወራሽ ነህና መንኰሰህ ለመኖር ይቻልሃልን?›› አለው፡፡ ብፁዕ አባታችንም ‹‹አባቴ ሆይ፥ የምድር መንግሥት ኃላፊ ጠፊ ነው፤ ነገር ግን የማታልፈውን የማትጠፋውን ዘለዓለማዊት መንግሥት እወርስ ዘንድ እፈልጋለሁ›› አለው፡፡ በፈተናም ከጸና በኋላ በዐሥራ ዐራት ዓመቱ በአባ ጳኩሚስ እጅ የምንኩስናውን ልብስ ለበሰ፡፡ ከአመነኮሰውም በኋላ ስሙን ዘሚካኤል ብሎ ሰየመው፡፡

ከአባ እንጦንስ ዐራተኛው የቆብ ልጅ ሲሆን እርሱን በቆብ የሚወልደው ደገኛውን የገዳም ሥርዓትን ከሠሩልን አበው አንዱ የሆነው ታላቁ ቅዱስ ጳኲሚስ ነው። ቀድሞም በአባ ጳኲሚስ ዘንድ መንኲሶ ለመኖር ሲመጣ የመጣው ከንጉሥ ቤት ነበርና አባ ጳኲሚስ ከማመንኰሱ በፊት ብዙ ፈትኖታል። በኋላም ገና ልጅ ሳለ በዐሥራ ዐራት ዓመቱ አመነኰሰው። የምንኲስና ስሙንም አባ ዘሚካኤል ብሎ ሰየመው። አረጋዊ የተባለው ገና ወጣ ሁኖ ሳለ ልባዌውና ግብሩ ሁሉ እንደሚያስተውል አረጋዊ ነውና ‹‹አንተስ አባታችን አረጋዊ ነህ›› ብለው ጠሩት።
በገድልም ተጸምዶ የሚኖር ሆነ። በኋላም ከሁለት ደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ከተመለከታት በኋላ ወደ ሮም ተመልሶ ለወንድሞቹ ለስምንቱ ቅዱሳን ነገራቸውና እየመራ አብረው መጥተው በኢትዮጵያ መኖር ጀመሩ። በኋላ እነርሱ በአንድነት መኖራቸው ለወንጌልና ለምንኲስና መስፋት አይሆንም ነበርና ሀገሪቱን ተከፋፈሏት። በዚህም አባታችን አቡነ አረጋዊ ወደ ትግራይ በተለይም ወደ ደብረ ዳሞ መጦና በዚያ በዓታቸው ወሰኑ። በእሊህ ዘጠኝ ቅዱሳን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት እጅግ ብዙ የሐዋርያዊ አገልግሎት እንዲሰፋ ሆኗል።፣

አባ አረጋዊም ወደ ደብረ ዳሞ ለመውጣት በአደዱ ጊዜ የታዘዘ ዘንዶ ከወገባቸው ይዞ አውጥቷቸዋል። በዚያም ሲጋደሉ ከኖሩ በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያንን ሠሩና መወጣጫውን ‹‹ዳህምሞ-አፍርሰው›› ብለው አስፈረሱት። በዚህም ዳሞ ተብላ እንደተጠራች ይነገራል። እርሳቸውም በገድል ተጸምደው ከኖሩ በኋላ በዚያችው ገዳማቸው ሳሉ ወደ ብሔረ ሕያዋን ተሠውረው ሄደዋል። እኒህ ደግ ጻድቅ ከቅዱስ ያሬድም ጋር የሚነገርላቸው ግሩም ዜና አላቸው።
የጻድቁ በረከት በሁላችንም ይደርብን። እግዚአብሔርም በጸሎታቸው ይማረን፤ ለዘላለሙ አሜን።
ምንጭ፥ ስንክሣር ዘወርኃ ጥቅምት፣ ገድለ አቡነ አረጋዊ

ቅዳሴ ተሰጥሖ

23 Oct, 12:23


ስለ ትዕግስት እንዲህ መባሉን ሰምተዋል?
ጠቢቡ ሰለሞን ትዕግስተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል ብሏል። ምሳ 16፥3
አባባሉ ከባድና የየማይታመን መስሎ ይታየን ይሆን? ለምን ሞክረን አናረጋግጠውም፡፡ ኃያል ለመባል ብዙ ነገሮች ሊጎድሉንና ላይሳካልን ይችላል። ትዕግስተኛ ስንሆን ካልቻልነው ከኃያል ሰው መብለጥ እንችላለን፥፥ ትዕግስተኛ ስንሆን ካልቻልነው ከኃያል ሰው መብለጥ እንችላለን ማለት ነው። ትዕግስተኛ ከሆንን የማናሳካውና የማናሸንፈው ነገር አይኖርም ካሰብነውም የማንደርስበት ምንም ምክንያት የለም።
ትዕግስት ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው ከነሱ መካከል እንደሚከተሉት ናቸው፥
፩ ትዕግስት የመብሰል ምልክት ነው።
፪ ትዕግስት ግልፍተኛ እንዳንሆን ያደርገናል።
፫ የደቂቃዎች ትዕግስት ከፍፃሜ ልክ ፀፀት ታድናለች።
፬ ትዕግስት ቀዝቃዛ ውሃ ነው የጋለውን ያበርዳል።
፭ ትዕግስት እርጋታንና ማስተዋል ያላብሳል።
፮ ትዕግስት ግንዛቤን ያሰፋል።
፯ ትዕግስት እውቀትን ይጨምራል።
፰ ትዕግስት የምንፈልገውን ለማግኘት የምንገብረው ምስዋዕት ነው።
፱ የትዕግስት የመጨረሻ ውጤት ከመከራ በኋላ የሚመጣ እውነተኛ ደስታ ነው።
እንግዲህ ልብ እናድርግ መታገስ ማለት መቻል፣ መቻል ማለት እስከ መጨረሻው መቻል ማለት ነው። ታገስ ማለት መጥፎ ሁኔታ የሚያስከትሉትን ነገሮች ንቆ መተው ማለት ነው።
ከወደዱት ሼር ያርጉት
ሼር @betekidase
ቻናሉን ለመቀላቀል @betekidase

ቅዳሴ ተሰጥሖ

22 Oct, 12:30


፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ፣

ቅዳሴ ተሰጥሖ

22 Oct, 07:01


ቅዱስ ሚካኤል

ቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ ነህ ለሁሉ
ዛሬም ቆመሀል በኪዳንህ ላሉ
አዝ።።።።።
ክንፍህን ዘርጋ ሚካኤል ቅደም ከፊቴ
ምራኝ መንገዱን እንዳይመሽ ልድረስ ከአባቴ
እንዴት ይገፋል ጎዳናው ያላንተ እርዳታ
ጥሜን ቁረጠው በትርህ ጭንጫውን ምታ
አዝ።።።።
ተጠመጠመ ጠላቴ በእሳት ሰንሰለት
የጌታ መልአክ ሚካኤል በሰይፍ ወድቆበት
የለም በቦታው ስመለስ አጥቼዋለሁ
የሚረዳኝን ተሹሞ አይቼዋለሁ
አዝ።።።።
ከመቃብሩ ድንጋዩን አንከባለሃል
ስለረዳኸው ዳንኤል እጅግ ወዶሃል
ይነዋወጻል ባሕሩም አንተ ስትመጣ
እግዚአብሔር ይንገስ ዲያብሎስ መድረሻ ይጣ
አዝ።።።።።።
አለኝ ትዝታ በቤትህ ከልጅነቴ
ስትሳሳልኝ እያየሁ ፀንቷል ጉልበቴ
ልዘምር እንጂ ላመስግን ታላቁን ጌታ
አንተን የሰጠኝ ጠባቂ በቀን በማታ

ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን

ቅዳሴ ተሰጥሖ

22 Oct, 07:01


መንፈሳዊነት ምንድን ነው ?


፩. መንፈሳዊነት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር ያለ ኅብረትና አንድነት ነው፡፡

፪. መንፈሳዊነት ስሜትን፣አእምሮንና መንፈስን ሲገዛ ነው፡፡

፫. መንፈሳዊነት ጥረት፣ተጋድሎ፣ ውጣ ውረድ ነው

፬. መንፈሳዊነት ጊዜና ቦታ የማይወስነው ነው፡፡

፭. መንፈሳዊነት የኑሮ ሁኔታ የማይወስነው ነው፡፡

በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
በእዉነት መምህራችን እግዚአብሔር በዕድሜ በጤና ይጠብቅልን!!❤️

ቅዳሴ ተሰጥሖ

22 Oct, 06:34


የ4ተኛ ሳምንት ጽጌ በኃላ ተጽፎ ሲያልቅ ይላካል...

ቅዳሴ ተሰጥሖ

20 Oct, 09:47


ዛሬ ቅዳሴ ላይ ከተነበበው የወንጌል ክፍል:

“ስምዖን ጴጥሮስ ግን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጕልበት ላይ ወድቆ፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከኔ ተለይ፡ አለው።”
[ሉቃስ 5: 8]

ቅዱስ ጴጥሮስ ይህንን ያለው አንድ ተአምርን ከጌታችን አይቶ ነው.. አሣ ለመያዝ መረብን ጥለው ነበር ነገር ግን ሌሊቱን ሁሉ ቢፈጉም ምንም ሊያገኙ አልቻሉም ነበር

ነገር ግን ጌታችን ወደ ጥልቁ ፈቀቅ ብለው መረቦቻቸውን ለማጥመድ እንዲጥሉ ይነግራቸዋል.. እናም ጴጥሮስም “ሌሊቱን ሁሉ ደክመን ምንም አልያዝንም ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ” አለው.. እናም ጣለ መረቡም እስኪቀደድ ድረስ ብዙ አሣዎችን ያዘ..

አያችሁ የኔ ተወዳጆች ብዙ ያደከሙን ነገሮች ጌታ ሲገባበት ቀላል ይሆናል.. በሕይወታችን ፍሬን ማፍራት ቢከብደን በክርስቶስ ግን እናፈራለን.. ያለ እርሱ ምንም ልናደርግ አንችልም.. ጌታችንም “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብሎናል..

የጌታን እርዳታ ለማግኘት ደግሞ እኛ በራሳችን ደካማና ኃጢአተኞች መሆናችንን ማወቅ አለብን.. ቅዱስ ጴጥሮስ በጌታው ጉልበት ላይ ወድቆ እኔ ጌታ ሆይ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከኔ ተለይ አለው.. ራሱን በእንደዚህ ዓይነት ቦታ ሲያስቀምጥ ጌታም ደግሞ መለስ አድርጎ “አትፍራ ከእንግዲህስ ወዲህ ሰውን የምታጠምድ ትሆናለህ” አለው..

ከክርስቶስ የተነሣ ፍሬን የምናፈራ እንሁን

መልካም የጌታ ቀን

ቅዳሴ ተሰጥሖ

19 Oct, 17:46


"በጎን የሚያደርግ ሰንበትን የሚያከብር ሁሉ ጻድቅ ነው፤ ወደ እግዚአብሔር አምልኮ የገባ መጻተኛ ከሕዝቡ ይለየኝ ይሆን? አይበል ፤ በጎ ያደረገ ሰንበትን የሚያከብር ሁሉ ጻድቅ ነው።"
   
       በጎ ሽልማት የምታስገኝ ሰንበትን
           በቅዳሴ እናክብራት🤍

ቅዳሴ ተሰጥሖ

19 Oct, 17:28


ዛሬን በማኅሌተ ጽጌ ለምታገለግሉ ሁሉ መልካም ቁመት 🙏

ቅዳሴ ተሰጥሖ

19 Oct, 17:28


🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ስርዓተ ማሕሌት ዘሣልሳይ ጽጌ በዓለ መስቀል
💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠
ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክዓ ሥላሴ
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል፡፡

ዚቅ
ዝኬ ዘተዘርዓ ቃለ ጽድቅ በትውክልተ መስቀል፤ ወፍሬሁኒ ኮነ መንፈሰ ህይወት፤ ተስፋሆሙ ለእለ ድኅኑ፤ ወበጽጌሁ አርዓየ ገሃደ አምሳለ ልብሰተ መለኮት፤ ዕቊረ ማየ ልብን፤ ጽጌ ወይን ተስፋሆሙ ለጻድቃን።


ማኅሌተ ጽጌ
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል፤ ወጸገይኪ ጽጌ በኢተሰቅዮ ማይ ወጠል፤ ወበእንተዝ ያሬድ መዓርዒረ ቃል፤ ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ወይብል፤ ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል።
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ወረብ፦
በትረ አሮን ማርያም ዘሠረጽኪ እንበለ ተክል/፪/
ምስለ ሱራፌል ይዌድሰኪ ያሬድ ወይብል ሐጹር የዓውዳ ወጽጌረዳ በትእምርተ መስቀል/፪/

ዚቅ፦
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት ወባቲ ይገብሩ ተአምረ በውስተ አህዛብ እስመ አርአያ መስቀል ይዕቲ


ማኅሌተ ጽጌ
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ፤ዘወለደት ጽጌ ወፀሐየ ዓለም ብርህተ፤ካዕበ (ወካዕበ) ትመስል ሳብዕተ ዕለተ፤እስመ ፈረየት ኪያኪ ተአምረ ግዕዛን ሰንበተ፤ ለእለ በሰማይ ወምድር ዘኮንኪ ዕረፍተ።
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ወረብ፦
ትመስል እምኪ ማርያም ዕለተ ሣልስተ ወራብዕተ ትመስል እም/፪/
ዘወለደት ጽጌ ጽጌ ጽጌ ወፀሐየ ዓለም/፪/

 
ዚቅ
እምኲሉ ዕለት ሰንበተ አክበረ ወእምኲሎን አንስት ማርያምሃ አፍቀረ ከመ ትኩኖ ማኅደረ ለመንፈስ ቅዱስ ወምስጋድ ለኲሉ ዓለመ።

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ  ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ ፣አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፣ንዒ  ርግብየ  ትናዝዝኒ  እምላህ፣ወንዒ  ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፣ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ወረብ፦
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ/፪/
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/

ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ ሰላማዊት፤ ተመየጢ ወንርአይ ብኪ ሰላመ፤ በአምሳለ ወርቅ ይግበሩ ለኪ ኮሰኮሰ ዘብሩር፤ አመ ወለደቶ አርአያ ወሰደቶ፤ በትእምርተ መስቀል፤ ትፍሥሕትኪ ውእቱ፤ ብርሃንኪ ውእቱ ሰላምኪ።

ዓዲ ዚቅ
ወይቤላ ንዒ ንሑር፤ኀበ ደብረ ከርቤ ውስተ አውግረ ስኂን፤ እኅትየ መርዓት ርግብየ ሠናይት


ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ  ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ  ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም  ለጊዮርጊስ ቀጸላ  መንግሥቱ፤አንቲ  ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ወረብ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘየሐቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/

ዚቅ
ነያ ሠናይት ወነያ አዳም፤ አግዓዚት ማርያም ጽርሕ ንጽሕት፤ በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤  ወዲበ ርእሳኒ አክሊል፤ ፅሑፍ በትምህርተ መስቀል

ዓዲ ዚቅ፦
በወርቅ ወበዕንቍ ወበከርከዴን፤ሥርጉት ሥርጉት በስብሐት፤ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ፤ትርሢተ መንግሥቱ አንቲ መድኃኒቶሙ ለነገሥት

ሰቆቃወ ድንግል
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ወረብ፦
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም/፪/
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል/፪/

ዚቅ
አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤ አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ወረብ፦
አመ አመ አጒየይኪ ዕጓለኪ በሐቂፍ/2/
እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ/2/


ሰቆቋወ ድንግል(ሌላ)
ኀበ አዕረፍኪ እግዝዕትየ ማርያም ታሕተ ጽላሎተ ዕፅ እምፃማ፤ፈያት ክልኤቱ ሶበ በጽሑኪ በግርማ፤እምትሕዝብተ ሞቱ ማሕየዊ ለወልድኪ ንጉሠ ራማ፤እፎኑ አዕይንትኪ ማያተ አንብዕ አዝንማ፤አዕይትየ ለገብርኪ ክልኤሆን ይጽለማ

ዚቅ
ሐፃቤ ርስሐትየ ይኩን አንብዕኪ ዘአንፀፍፀፈ ዲበ ምድር አመ ወልድኪ ይፄዓር በመልዕልተ

መዝሙር፦
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፣ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘዓቀምከ፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ ፤ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወከመ ወሬዛ ኀይል መላትሒሁ፤ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ሰማይ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ  በከዋክብት ሠማይ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤  ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኩሉ ዕለት፤ማ፦ ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፥ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ።

አመላለስ

ወመኑ መሐሪ ዘከማከ/፪/
ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ ወኩሉ ይሴፎ ኪያከ/፪/
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ቅዳሴ ተሰጥሖ

18 Oct, 13:43


ዘመነ ጽጌ ካለፈው የቀጠለ

በጊዜ እንደመወሰን ⇛ ፈጣሪያችን ቅድመ ዘመናት ሰው በማይቆጥረው ፍጥረት በማይሰፍረው በራሱ ዘመን የነበረና ሁሉ ሲቋጭና ሲያበቃ የእርሱ  ዓመታት ግን ሳያልቅ ድኅረ ዘመናት የሚኖር ነውና እርሱ ብቻውን ሳይለወጥ ሌላውን የሚለውጥ ሆኖ ይጸናል። " አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጡማል ::  አንተ ግን ያው አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም።" [መዝ101:26] በኢየሩሳሌም የነገሠው ሰባኪው የዳዊትም ልጅ እንዲህ ይላል "ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። " [መክ. 3:1]

አበባ በዘመነ ጽጌ ወቅትን ጠብቆ የሚተርፍ ጊዜው ሲያልፍ የሚረግፍ  ዘር ለፍሬ መብቃቱን እንደምልክት የሚያስረዳ ለኑሮውም የወራት እድሜ ብቻ የተቸረው ነው ፍጥረት ነው:: " ጽጌ ገዳምኒ በጊዜሁ የኃልፍ ኩሉ በጊዜሁ የሐልፍ ወዘኢየሐልፍ አልቦ ዘይመጽእ ... የምድረበዳ አበባ በጊዜው ያልፋል ሁሉም በጊዜው ያልፋል ላያልፍ የሚመጣ አንዳች የለም " ይለናል ቅዱስ ያሬድ።

እንግዲህ ይህን ወደኛ ሕይወት ስናዞረው  ቅዱስ ዳዊት
" ዘመናችን ሁሉ አልፎአልና፥ እኛም በመዓትህ አልቀናልና ዘመኖቻችንም እንደ ሸረሪት ድር ይሆናሉ። የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት፥ ቢበረታም ሰማንያ ዓመት ነው ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው ከእኛ ቶሎ ያልፋልና፥ " አለ  መልሶም " ሰውከንቱን ነገር ይመስላል ዘመኑ እንደ ጥላ ያልፋል። " [መዝ .89:10,143:4] ይለናል:: 

ማጠቃለያ 
በሚያልፍ ዘመኑ የማያልፍ ሥራ የሚሰራ በተወሰነለት መዋዕሉ ፈቃደ ሥጋውን ወስኖ ለነፍሱ ሥምረት ያደረ የሰማይ አእዋፋትን ያጠገበ የምድር አበቦችን ያደመቀ ያስሸበረቀ ፈጣሪ " እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን ?" ሲለን በቅዱስ መጽሐፍ እናነባለን 

"የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ"  የሚለውን የጌታችንን ቃል ይዘን ጊዜው ዘመነ ጽጌ ከምድር አበቦችየምንማርበት ወቅት ነው አበባ ለአንክሮ ለተዘክሮ ተፈጥሯልና [ማቴ .6:28]:: 

ሰው ራሱ  የእግዚአብሔር አበባ ነው! ጽጌ ባለ ብዙ መዓዛና መልክእ ነው፤ ከአቃፊው ወጥቶ ለዓይን የሚማርከው እምቡጥ አበባ ሲፈነዳም ለአፍንጫ የሚያውደው መልካም መአዛ ለዓይን የሚስበው የቀለም ለዛ በሰው ልጆች ዘንድ ያለው ቦታ ልዩ ነው! የአበባ መዓዛና ቀለም መለያየቱና መብዛቱ እኛ ባለ ልሳነ ብዙኅ ፣ ባለ ኅብረ መልክእ መሆናችንን የሚያሳይ ነው! 

ምን አበባ በህጹጽ መገለጫው በጊዜ የሚወሰንእና ፈጥኖ የሚጠወልግ ሆኖ ለደካማው የሰው ልጅ የሥጋ ጠባይ መገለጫ ሆኖ ትምህርት ቢሰጥ ይህን እያየን በነፍስ ደርቀን ወደማንጠወልግበት ተቀብረን ወደማንቀርበት ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት ለመሻገር የሚሰራው ሁሉ ለሚከናወንለት ምሳሌ የተገለጸውን ዕለት ዕለት በደጁ እየተጋ ከህይወት ምንጭ ቅዱስ ቃሉ እየጠጣ አበባነቱ ሲያልፍ የሃይማኖት ቅጠሉ ሳይረግፍ የምግባር ፍሬን እየሰጠ በዘመናት ሳያፍ ዘመናትን የሚያሳልፍ መልካሙን ዕፅ መስሎ መኖር ይገባል "... ከመ ዕፅ እንተ ትክልት ሀበ ሙኃዘ ማይ እንተ ትሁብ ፍሬሃ በበጊዜሃ ወቆጽላኒ ኢይትነገፍ ወኩሎ ዘገብረ ይፌጽም = ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ ቅጠሏም እንደማይረግፍ በፈሳሽ ውኃ ዳር እንደ ተከለች ዛፍ የሚሰራው ሁሉ ይከናወንለታል " [መዝ1:3]፡፡ በቸርነቱ የምናስብ የምንናገረውን የምንሠራውን ሁሉ የሠመረ የተከናወነ ያድርግልን!
ይቆየን...

ቅዳሴ ተሰጥሖ

18 Oct, 08:19


“አፈወ ሮማን ማርያም ጽጌ ቀናንሞ ወአበሜ፣ እስከ ተጸምሐየየ በጾም ዘመልክዕኪ ጊዜ ድክታሜ፣ እምተመነይኩ ተሳትፎ ከመ አኅትኪ ሰሎሜ፣ ወፍሥሓኪ ዘአልቦ ፍጻሜ”፡፡

የሮማን ሽቱ የቀናንሞ አበባ የምትሆኚ ማርያም ሆይ፣ በርሃብ በጾም አበባ የመሰለ የመልክሽ ደም ግባት እስኪጠወልግ ድረስ በስደትና በልቅሶ የደረሰብሽን ችግርና ድካም መከራሽንም ሁሉ እንደ እኅትሽ እንደ ሰሎሜ አብሬሽ ብቀበል ምኞቴ ነበር፤ በዚህ ፍጻሜ የሌለውን ደስታሽን እሳተፍ ነበር፡፡

#አባ_ጽጌ_ድንግል

ቅዳሴ ተሰጥሖ

18 Oct, 06:01


"ሰማዕትነት ስር ነው፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ከዚኽ ስር የሚያቆጠቁጡ ምርጥ ዘሮች ናቸው፡፡ ብዙ ዛፍ የሚያቆጠቁጥበት ስር በለም አፈር ስለሚሸፈን አይታይም፡፡ ከዚያ በሚያቆጠቁጡ ዛፎች ግን ስሩ እንዴት እንደተመቸው ይታወቃል፡፡ ሰማዕታትም በግዙፉ ዓይናችን እንደምን ያለ አክሊል ሽልማት እንደተቀበሉ አይታየንም፡፡ ፍሬያቸው ግን እነርሱን መስለው እነርሱን አኽለው በሚጋደሉ ምርጥ ዘሮች ይታወቃል፡፡

ሰማዕታት አክብሩን ብለው አይናገሩም፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ልብ የሚዘሩት ፍሬ ምእመናንን በፍቅር ያስገድዳል፡፡ እነርሱን እንዲመስሉ ያሳስባል፡፡

ሰማዕታት እንደ ፍቅረኛ ናቸው፡፡ አንድ ሰው የፍቅረኛውን ስም በየአጋጣሚው ያነሣል፡፡ በዓይነ ሕሊናው ያስባል፡፡ በተለያየ መልኩ ያያል፡፡ ሰማዕታትም ለክርስቲያኖች እንደዚያ ናቸው፡፡ እጅግ የተወደዱና በፍጹም ከሕሊና የማይጠፉ ተወዳጆች ናቸው፡፡ የልጆቻችንን ስም በነርሱ ስም የምንሰይመው፣ ሥዕላቸውን ሥለን የምንተሻሸው የምንስመው ለሰማዕታቱ ያለንን ጥልቅ ፍቅር የምንገልጽበት መንገድ ስለኾነ ነው፡፡"

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

ቅዳሴ ተሰጥሖ

17 Oct, 15:57


ዘመነ ጽጌ ካለፈው የቀጠለ.  …†… ስለ ነገረ ክርስቶስ …†…
ሊቃውንቱ " ቡሩክ እጽ ዘሰናየ ይፈሪ ወኃጢዓተ ይሰሪ " እያሉ መልካም ፍሬን የሚያፈራ ኃጢዓትን የሚደመስስ ቡሩክ እጽ ( የበረከት ተክል/እንጨት ) ክርስቶስ መሆኑን ከሊቁ የማኅሌት ምንጭ ቅዱስ ያሬድ ድጓ ጠቅሰው ይመሰክራሉ።
መልሰውም ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ " ትወጽእ በትር እምስርወ እሴይ ወየአርግ ጽጌ " [ኢሳ.11:1] ያለውን ምስጢራዊ የትንቢት ፍጻሜይዘው እንዲህ ይላሉ " ይእቲ በትር አምሳለ ማርያም ቅድስት ወጽጌ ዘወጽአ እምኔሃ አምሳሉ ለወልድ = ይህችውም በትር የቅድስት እናቱ የድንግል ማርያም ምሳሌ ናት ከእርሷ የተገኘው አበባም የወልድ አምሳል ነው ":: 
በዚህም ላይ የድንግል አበባ ክርስቶስ "የእግዚአብሔር ጸጋ ለማንም እንዳይጎድለው፥ ብዙዎቹም የሚረክሱበት አንድ መራራ ሥር ወደ ላይ በቅሎ እንዳያስጨንቅ " በበጎ መአዛው የመላውን ዓለም ክፉ ጠረን ለውጦ በመልካም ጣዕም ከህዝብና ከአህዛብ መራራነትን አጥፍቶ ህዝቡን ሁሉ ስለማዳኑ ይነገራል [ዕብ 12:15]:: 
በጥልቀትም ናዝራዊ የነበረው ብርቱ ሰው ሶምሶን "ምአፈ በላኢ ተረክበ መብልዕ ወእምአፈ ህሱም ተረክበ ጥዑም" ብሎ ለጠየቀው እንቆቅልሽ ፍቺ በፍፃሜው ከበላተኛ የተገኘ ምግብ ከመራራው የሰው ልጅ ግንድ የተገኘ ጣፋጭ ፍሬ ክርስቶስ ሁሉን አጽንቶ ለአበባና ለፍሬ እንዳበቃ ምስክርነት ይሰጣል [መሳ . 14:14]:: 

ስለ ነገረ ማርያም 
" መዝገቡ ለቃል ጽጌ እንተ ኢትትነገፍ " ይህችን ለቅዱሳን አበው የህሊናቸው እረፍት ..... ለፍሬ ሕይወት ክርስቶስ የማረፊያው ሙዳይ የሆነች አበባ ድንግል ማርያምን " የቃል ማደርያ የሆነች የማትረግፍ አበባ " እያለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ያወድሳታል ሊቃውንቱም በምስጋናው ይተባበሩታል :: 

ይልቁንም ዘመኑ ዘመነ ጽጌ የሌሊቱ ምስጋና ማኅሌተ ጽጌ የምስጋናውም ደራሲ አባ ጽጌድንግል እየተባለ ድንግል የተወደደ ልጇንይዛ ወደ ግብጽ በረሃ መሰደድዋን በማሰብ መፍቀሬ ጥበብ ሰሎሞን " በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ፥ እንዲሁ ወዳጄ በቈነጃጅት መካከል ናት።" ያለውን ምስጢራዊ ፍቺ እሾህ ከሆኑ አይሁድ መካከል ተገኝታ በሃይማኖት አብባ ፍሬ ትሩፋት ሰርታ የተገኘች የቆላ የሱፍ አበባ ድንግል ማርያም መሆኗን እየገለጡ  " ሌቱን" የንጋትዋን ምስራቅ ፣ የማለዳዋን ፀሐይ መውጫ ፣ አጥቢያ ኮከቡን መገኛ ሲያመስግኗት ያድራሉ :: [መኃ 2:2]

ስለ ነገረ መስቀል 
ቀድሞ በዘመነ መስቀል [ከመስከረም 17 እስከ መስከረም 25] ለዘጠኝ ቀናት ሲነገር የቆየው ምስጢር መስቀል አበባ ተብሎ እየተዘመረ ከዚህም ይሻገራል :: ልብ በሉ አዳም ወደ ሞት እንጨት ( እጸ በለስ )እጆቹን ዘርግቶ ሞቱን ቢያቀብለን ከማዕረጋችን ተዋርደን ወደ ምድርም ወረድን ክርስቶስ ግን ወደ ሕይወትእንጨት ( እጸ መስቀል ) እጆቹን ዘርግቶ ሕይወቱን ቢያቀብለን ወደ ቀደመ ክብራችን ተሻገርን :: ምንም እንኳ ጢቢቡ በማኅሌቱ "እነሆ፥ ክረምት አለፈ፥ ዝናቡም አልፎሄደ። አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ "( መኃ2:11) እንዳለው ዘመነ ክረምቱም ቢያልፍ ዘመነ መጸው ቢተርፍ ዜና መስቀሉ ግን ዓመቱን ሁሉ ይሰበካል :: ለዚህም የመንፈሳዊው ዜማ አባት ቅዱስ ያሬድ " በከመ ይቤ ሰሎሞን በእንተ ማርያም ንዑ ንትፈጋዕ ወኢይኅልፈነ ጽጌ ደመና መስቀል ዘዮም አብርሃ በስነ ማርያም = ሰሎሞን ስለማርያም እንደተናገረው ኑ ደስ ይበለን የበረከቱ አበባ አይለፈን ይኸውም ዛሬ በማርያም ውበት ( በድንግል ባህሪ በክርስቶስ ሥጋ ) መስቀሉ አብርቷልና " (ድጓ ዘዘመነ ጽጌ ) 

ስለ ነገረ ቤተ ክርስቲያን 
ሥሯ በምድር ላይ ቅርንጫፎቿ በሰማይ ያለውን ኆኅተ ሰማይ ቤተክርስቲያንን ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ አስቀድሞ ስለ አማናዊቷ የክርስቶስ መርዓት ስለቅድስት ቤተክርስቲያን ይኽን ይናገራል  "እነሆ፥ ድንጋዮችሽን ሸላልሜ እገነባለሁ፥ በሰንፔርም እመሠርትሻለሁ። የግንብሽንም ጕልላት በቀይ ዕንቍ፥ በሮችሽንም በሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ዳርቻሽንም ሁሉ በከበሩ ድንጋዮች እሠራለሁ። ልጆችሽም ሁሉ ከእግዚአብሔር የተማሩ ይሆናሉ፥ የልጆችሽም ሰላም ብዙ ይሆናል። ... በአንቺ ላይ የተሠራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም በፍርድም በሚነሣብሽ ምላስ ሁሉ ትፈርጂበታለሽ። የእግዚአብሔር ባሪያዎች ርስት ይህ ነው፥ " [ኢሳ 54:11] ሊቁም ከዚህ አያይዞ የቤተ ክርስቲያንን ውበት እንዲህ እያለ ያደንቃል " በከመ አሰርገዎሙ ለሰማይ በከዋክብት ወለምድርኒ በሥነ ጽጌያት ከማሁ አሰርገዋ ለቤተ ክርስቲያን በደመ ሰማዕታት = ሰማያትን በከዋክብት ያስጌጠ ምድርንም በአበባ የሸለመ ቤተክርስቲያንንም በሰማዕታቱ ደም አሸበረቃት" 

መሠረተ ዜማ ቅዱስ ያሬድም ጨምሮ በዚህ መንገድ ለቤተክርስቲያን የመወደድ ጌጧ የሰማዕታት ገድል መሆኑን እንዲህ እያለ አስረድቷል "ሰማዕትኒ ያሰረግዋ ለቤተ ክርስቲያን በገድሎሙ " / ድጓ ዘቴዎቅርጦስ / 

ጽጌን ( አበባን ) በጠንካራ ጎንና መልካም ምሳሌው ከላይ ያየነውን ጥልቅ የነገረ ሃይማኖት ማብራርያ ከዚህ እናቆየውና ወደኛ ከሚሻገረው የክርስቲያናዊ ሕይወት ምክር እንፃር ደግሞ ለሰው ደካማ ባህሪያት አብነት የሚሆኑ የጽጌን ደካማ ባህሪ የሚመለከቱ ጥቂት ነጥቦችን እንደ ማጠቃለያ ለመመልከት እንሞክር :: 

ሁላችን እንደምናውቀው  ከአቃፊው ወጥቶ ለዓይን የሚማርከው እምቡጥ አበባ ሲፈነዳም ለአፍንጫ የሚያውደው መልካም መአዛ ዘላቂ ሳይሆን አላቂ ቋሚም ሳይሆን ጊዜአዊ ነው :: 

ልብ እናድርግ ለአበባ ህጹጽነቱ ፈጥኖ መጠውለጉና በጊዜ መወሰኑ ነው እኛም ሥጋ ለባሾቹ የሰው ልጆች በምድር ላለን ቆይታ ህያው ሆኖ ነዋሪ በምድር ላይ ሞትን ሳያይ ቀሪ ማንም የለምና እንደዚሁ ነን :: 

★ ፈጥኖ እንደ መጠውለግ ⇛  ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል
" ሰውስ ዘመኑ እንደ ሣር ነው እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋልና፥ ስፍራውንም ደግሞ አያውቀውምና። "( መዝ. 102:15)
ቅዱስ ያሬድም በዘመነ ጽጌ ድጓው እንዲህ ሲል ከነቢዩን ቃል እያጣቀሰ ነገሩን ያጸናዋል " ተዘከር እግዚኦ ከመ መሬት ንህነ ዘለሐኮ በእዴከ ኢታማስን ህዝበከ ከመጽጌ ገዳም ዘይፀመሂ ፍጡነ ከማሁ መዋዕሊነ .... አቤቱ እኛ እኛ እንደ አፈር መሆናችንን አስብ የምድረ በዳ አበባ ፈጥኖ እንደሚጠወልገው የእኛም ዘመን እንደዚያው ነውና በእጅህ ያበጀኸውን ህዝብህን አታጥፋ ":: 
እንግዲህ በአምላኩ ፊት ሰው ምን ያህል ደካማ እንደሆነ እናስተውል ::  
ታዲያ ስለምነው በሚያልፍ እውቀቱ የሚታበይ ?  
  በሚጠፋ ጉልበቱ  የሚመካ? 
በሚረግፍ ውበቱ የሚመጻደቅ? 
በሚያልቅ ሀብቱ ሲተማመን የሚኖር ? 
ቅዱስ ያሬድ ግን እንዲህ እያለ ይዘልፈናል "ብዕሉሰ ለሰብዕ ከመጽጌ ገዳም ወኃይሉሰ ለሰብዕ ከመ ሳዕር ድኩም ... የሰው ንብረቱ እንደምድረ በዳ አበባ ኃይሉም እንደ ደረቅ ሳር ነው " አዎ የምንመካበት ክብራችን ታይቶ ጠፊ ፈጥኖ አላፊ ነው :: ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስም " ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው። " ሲል የተናገረው መልእክት የተነሳንበትን ፍሬ ሃሳብ የሚያጠናክር ነው [ኢሳ . 40:6]:: 
ይቆየን...

ቅዳሴ ተሰጥሖ

16 Oct, 20:00


 …†… ዘመነ ጽጌ  …†…
ከላይኛው መንበር ከሰማይ በላይ ካለው ሰማይ በምድር ወዳለችው ዙፋን ዳግሚት አርያም ወርዶ፣ መለኮታዊ እሳትነቱን በደመ ድንግልናዋ አብርዶ፣ ደካማውን የሰውነት ባህሪ ከመለኮትነቱ ጋር አዋሕዶ  … የሕይወት ፍሬ መገኛ አበባ እናቱን ድል ከምንነሳበት ከመስቀሉ ሥር ዋጋ ከሚገኝበት መከራ ጋር   የሰጠን አምላካችን የተመሰገነ ይሁን። 

ክኅሎቱ ከፍጡራን ኅሊና በላይ የሆነ የቅዱሳን አምላክ የመላው ዓለም ፈጣሪ "ይህን " የሚታየውንና " ያን " የማይታየውን ሁሉ መልካም አድርጎ ፈጥሮታል። በዚህም ሁሉ ውስጥ ፍጥረታቱን በሦስት መንገዶች ለሦስት ዓላማ መሆኑን የሥነ ፍጥረት መጻሕፍትና ሊቃውንት ያስረዳሉ። 

ከአፈጣጠር መንገዶቹም
በኃልዮ (በማሰብ) የተፈጠሩ አሉ እንደመላእክት ያሉት ለዚህ ምሳሌ ሆነው ይቀርባሉ።
  ደግሞም በነቢብ (በመናገር ) የተፈጠሩ አሉ እንደ ብርሃን ያሉትን ለአብነት መጥቀስ የሚቻል ሲሆን። 
በሦስተኛው መንገድ በገቢር ( በመሥራት ) የተፈጠረ አለ። በዚህ መንገድ  የሰውን ልጅ ብቻ ፈጥሮታል።

ፍጥረታቱ ከተፈጠሩበት ዓላማ አንጻር ደግሞ 

ለአንክሮና ለተዘክሮ (ለመደነቅና ለማስታወስ ለማሰብ)  የተፈጠረ አለ :- ይህ ለመጠቀሚያ ነው። የዚህ ዓይነት ፍጡር መኖሩ ለፈጣሪ ሃለዎት ማስረጃነት እርባና (ጥቅም) ያለው ነው። ቅዱስ መጽሐፍ ይህን ሲያስረዳን 
☞  " የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና" ፣ 
“ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።”
  " ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን ?" 

[ሮሜ .1:20,  መዝ 19፥1, 1ኛ. ቆሮ. 11:15] 

ለምግብነት የተፈጠሩም አሉ :- እነዚህ ጉልበትን ያጠነክራሉ የኑሮ መሰረትይሆናሉ " እክል ያጸንዕ ኃይለ ሰብዕ ....እህልም የሰውን ጕልበት ያጠነክራል።"~~" የኑሮህ መጀመርያ የምትበላው እህል... ነው " [መዝ .103:15, ሲራ 29:21] ይላልና :: 

ሦስተኛው ወገን መላእክትንና የሰው ልጆችን የያዘ ሲሆን እነዚህም ጥንቱን ፈጣሪያቸውን አመስግነውት ክብሩን ለሚወርሱበት ዓላማ የተፈጠሩ ናቸው ::

በዚህ የሥነ ፍጥረት ጥልቅ ፍልስፍና ውስጥ ሊቃውንቱ የመጀመርያው ፍጥረትጊዜ ነው ይላሉ። ሊቀ ነቢያት ሙሴ የዘልደት መጀመርያ ባደረገው መነሻ እንዲህ ይለናል 
" በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ " [ዘፍ 1:1] «በመጀመርያ» ብሎ ጊዜ ቀዳሚ ግኝት የግኝቶችም ልኬት ቀመር መሆኑን ይጠቁመናል :: የአልዓዛር ልጅ ሲራክ የተባለ ኢያሱ በመጽሐፉ እግዚአብሔር ከምድር በአርአያውና በአምሳሉ ለፈጠራቸው ለሰው ልጆች ከሰጠው ገጸ - በረከት ቀዳሚው ጊዜ ነው ይለናል።
"(ለሰው ልጆች) ዘመንን ቀንን በቍጥር ሰጣቸው "[ሲራ 17:2] በዚህ የጊዜ ምህዋር ውስጥ ደግሞ የአዝማናትን ኡደት የወቅቶችን መፈራረቅ የሚቆጣጠር ምድርን በዳርቻው የሚያጸናው እርሱ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ነው። ነቢዩ ዳዊት " አንተ የምድርን ዳርቻሁሉ ሠራህ በጋንም ክረምትንም አንተአደረግህ። "  ይለዋል። [መዝ . 75:17]:: 

በጊዜአቱ ቀመር ውስጥ አንድ ዓመት በአራት ወቅቶች (አዝማናት ) የተከፋፈለ ነው :: እነዚህም፡-
  ዘመነ መጸው
  ዘመነ ሐጋይ
  ዘመነ ጸደይና
  ዘመነ ክረምት ይባላሉ ::  (የዘጠኝ ወር በጋ
የዐሥራ ሦሥት ወር ጸጋ የሚል ብኂል በማኅበረሰባችን ዘንድ መገኘቱ ከወቅቱ ርቦው  (አንድ አራተኛ) ውጪ ሌላው በጋ መሆኑን ያሳያል) አሁን ያለነው ከመስከረም 26 እስከ ታኅሣሥ 25 ድረስ ለ 90 ዕለታት በሚታሰበው ዘመነ መጸው ወርኃ ነፋስ ውስጥ ነው። በሥሩም አምስት ንዑሳን ክፍላት ያካትታል ዘመነ ጽጌ : ዘመነ አስተምሕሮ : ዘመነ ስብከት : ዘመነ ብርሃንና ዘመነ ኖላዊ የሚባሉትን ::
ለዚህም እንዲህ የሚል አብነት ይገኛል " ወለእመ ፈቀድከ ታእምር ክፍለ ዘመኑ ለመጸው ትዌጥን እምዕሥራ ወሰዱሱ ለመስከረም ወትፌጽም እምዕሥራ ወሐሙሱ ለታህሳስ ወኁልቆ ዕለቱ ተስአ ውእቱ ወእምዝ ኢታህፅፅ ወኢትወስክ :: በውስቴቱ ሐለዉ ሐምስቱ ንዑሳት ክፍላት ዘውእቶሙ ዘመነ ጽጌ : ዘመነ አስተምሕሮ : ዘመነ ስብከት :ዘመነብርሃን ዘመና ኖላዊ " 

በዚሁ ዘመን ሥር የመጀመርያው ንዑስ ክፍል ዘመነ ጽጌ ( የአበባ ጊዜ) ከመስከረም 26 እስከ ህዳር 5 ያለውን 40 ዕለታት አካቶ የያዘው ነው። በጊዜውም ለምዕመናን የነፍስ ቀለብ የሰማይ ፍኖት ስንቅ በዜማ ቢሉ በንባብ በብዙ ህብረ አምሳል ስለ አበባ በቤተክርስቲያናችን ወንጌል ይሰበካል በነገረ ሃይማኖትና በክርስቲያናዊ ሕይወት ዙርያ ሰፊ ትምህርት ይሰጣል።

እስኪ በጣም በጥቂቱ በአበባው ወቅት  በቤተ ክርስቲያናችን ዘመነ ጽጌ ለነገረ ሃይማኖት አስተምሮ  እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል እንመልከት።
ይቆየን.. .

ቅዳሴ ተሰጥሖ

16 Oct, 20:00


ክርስቶስን አንዘንጋ ፤🙏 የሚገባውን ስጦታ ከሱ አናስቀርበት።

ቅዳሴ ተሰጥሖ

16 Oct, 04:27


ማንም እንዳይቀር የማይቀርበት ጉባኤ ነው።

ቅዳሴ ተሰጥሖ

15 Oct, 16:27


ቅዳሴ ተሰጥሖ pinned «🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 ስርዓተ ማሕሌት ዘሣልሳይ ጽጌ በዓለ መስቀል 💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠 ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም…»