የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations @hinokhailes_spiritual_teachings Channel on Telegram

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations

@hinokhailes_spiritual_teachings

"Welcome to Deacon Hinok Haila Educations!
This is henok haile official YouTube channel subscribe https://youtu.be/anPbn
For any advertisements click here https://telega.io/channels
F
http://www.facebook.com/profile.php?id=100064756446431&mibextid=ZbWKwL

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Education (Amharic)

ሄኖክ ኃይሌ በስልክ ተልእኮ የተለያዩ ትምህርቶች እና አስተዋይ መልእክቶች ከኢትዮጵያዊት አዲስ ልዩ መዋቅር በላይ ታማኝ ናቸው። ይሔንን ይበልጥ ሄኖክ ኃይሌ የተስማማችው ሎጅን አንድ ስህተት እና ሽማግሌን ሌላ ስህተት እንዲሆኑ ነው። አንድ በራስ መንግሥት እና ፍላጐ ወንዶች ተከታታይ በሆነ እዩም ፋሲልተር መዝጊያ ላይ ነበር። የሚለያዩ በመቆረጡበት አድራጊ እርሻዎችን መከላከያ፣ የትምህርቶችን ምስጋና እና መዝጊያ የሚገኘው እንጂ፣ የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች ፈቃደ እና እንዴት እንደሚከተለው ይከታንዋል።

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations

24 Nov, 10:15

"ዘመኑን መዋጀት ሲገባን ዘመኑ እኛን ዋጀን.."
.
.
.
"ያልተሰራ ምዕመን የተሰራን ቤተክርስቲያን ያፈርሳል።"
.
.
.
"አገልግሎት ማለት እየሰሩ መዋጋት ነው።"
.
.
.
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations

24 Nov, 04:29

+++ እራስን መግዛት!! +++

በውጭው ካሉት ይልቅ በአንተ ውስጥ የሚገኙት ፍትወታት ጠንካራ ጠላቶችህ ናቸው። ልክ ያልተሠራለት ምኞት ከባቢሎን እሳት ይልቅ ያቃጥላል። አልጠግብ ባይነትም ከጥፉት ውኃ ይልቅ ያሰጥማል። ያልተገራ ፍላጎት ማንነትን አስጥሎ የሰይጣን ባሪያ ያደርጋል። ራስን መግዛት የሰው ልጆች ጌጥ ነው። ዮሴፍ ግብጽን ከፈርዖን ሁለተኛ ሆኖ ከገዛበት ታላቅ ሥልጣን ይልቅ፣ በጌታው ሚስት ፊት ያሳየው ራስን መግዛት ይበልጥ ይደነቃል። ጠቢቡ "በመንፈሱ ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ (ከሚገዙ) ይበልጣል" እንዳለ።(ምሳ 16፥32)

ራስህን ነጻ ማውጣት ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ከውስጥህ ጀምር። ሁል ጊዜ ካልበላሁ የሚለው ሆድህ ስስት አስለምዶ በወንድምህ ላይ ጨካኝ እንዳያደርግህ ለሰውነትህ ጾም አስተምረው። "ነገ እሞታለሁና ልብላ ልጠጣ" የሚለውን የዐሣማ ፍልስፍናህን (Pig philosophy) ተውና አንተ በፈቃድህ እየተራብህ (እየጾምህ) ያለ ፈቃዱ የተራበው ወንድምህን በምጽዋት አጥግበው።

ጌታ ወደ ገሊላ የተመለሰው ሄሮድስ ከሞተ በኋላ ነበር።(ማቴ 2፥20) አንተ ውስጥ ያለውን ሄሮድስ የተባለ ክፉ ምኞት እንዲሞት ካላደረግኸው በቀር የተሰደደው ክርስቶስ ወደ አንተ ሊመለስ አይችልም። ይህ ክርስቶስን ከልብህ የሚያሳድድብህን ሄሮድስ እንዴት ልትገድለው ትችላለህ? እርሱንስ ወግተህ የምትጥልበት የብረት ካስማ ምን ይሆን? ለዚህስ ከጾም እና ከጸሎት የሚበረታ ምንም ዓይነት የጦር ዕቃ አታገኝም። በል እነዚህን ይዘህ ዝመትበት።የነቢያት ፆም/የገና ፆም ቤተክርስቲያን በአዋጅ ካሰፈረቻቸው አፅዋማት አንዱ ነው።ግማሹ ሰው ፆሞ ሌላው ሰው በፍስሃ የሚሆንበት አደለም።

እንደ ነብያት በሃጢያት ነደድን "ፅድቃችን እንደ መርገም ጨርቅ ተቆጠረብን" እያልን ሁለችንም ጌታ በልባችን ባለች የቅንነት ቤተልሔም ውስጥ እንዲወለድ በፆም በፀሎት የምንለምንበት ፆም ነው። ፆሙ ህዳር 15 በእለተ እሁድ ይያዘል እሁድ የገና ፆም ነው።

ሁላችንም የምንፈሳዊነት ህይወት አቅም ይሰጠን ዘንድ በቀናችው የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ያፀናን ዘንድ የእግዚአብሔር መልካም ፍቃድ ይሁንልን።

መልካም የነቢያት ጾም ይሁንልን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
አዲስ አበባ
2017ዓ.ም.
ቴሌግራም
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations

23 Nov, 09:24

የአእላፍት ዝማሬ መርሃ ግብር ዝግጅት በይፍ ተጀምሯል።👇
https://t.me/janderebaw_media

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations

22 Nov, 16:40

📚ርዕስ:- ታቦት በአዲስ ኪዳን
📝ደራሲ:-ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
📜ዘውግ፦ ሃይማኖታዊ
📖የገፅ ብዛት:- 140
📅ዓ.ም:-2001ዓ.ም.
ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ!
══════════════════
SHARE and JOIN🙏
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
👆👆👆JOIN👆👆👆
══════════════════
ለወዳጅ ዘመዶ ያጋሩ!
══════════════════

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations

22 Nov, 16:31

በአብዛኞቻቹ ምርጫ መሠረት ከአርብ እስከ አርብ የንባብ ቻሌንጅ ታቦት በአዲስ ኪዳን እናነባለን ማለት ነው። መፅሐፊ በHard ያላቹ በHard አንብቡ የሌላቹ ደሞ አሁን Pdf እናጋራቹሃለን።

በመቀጠል ለንባብ አዲስ የሆናቹ ሰዎች ያለምን ጭንቀት በቀን 20 ገፅ ብታነቡ የዛሬ ሳምንት አርብ 1 መፅሐፍን አንብበን ማጠናቀቅ እንችላለን ማለት ነው።

ከፍ ያለ የንባብ ክህሎት ያላቹ እንዴት እንደሚነበብ ለእናንተ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ይሆንብናል።

ስናነብ በምዕራፍ ለይተን ለመረዳት እንሞክራለን። መፅሐፉን Review እናደርጋለን።

መልካም ንባብ ይሁንልን!!

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations

22 Nov, 12:10

ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ብሔራዊ ቴአትር ጋር ያለውን ሐውልት እጅግ በውድ ዋጋ አሠርተው ነበር ይባላል:: ንጉሡ የአንበሳ ሐውልት ሊመርቁ ሲከፍቱ ግን ሐውልቱ አንበሳ አይመስልም:: የአንበሳና ቀጭኔ ድብልቅ መስሎ ጉብ ብሎአል:: ንጉሡ አንጀታቸው እያረረ ከመረቁ በኋላ ንግግር ሲያደርጉ "ይህ አንበሳ አንበሳ ባይመስልም የወጣበት ገንዘብ ግን አንበሳ ያደርገዋል" አሉ ይባላል::

የእኛም ሕይወት እንደዚያ ነው:: ስንታይ ምናችንም ክርስቶስን አይመስልም:: አንዳንዴም በክፋት ከሰውነት ተራ እንወርዳለን:: ሆኖም እንዲህ ብንበድልም "ክርስቶስ የሞተልን ነን"
ምንም እንኳን ክርስቲያን ባንመስል የተከፈለልን ደም  የክርስቶስ ያደርገናል:: ምንም እንኳን የከበረ ሕይወት ባይኖረንም የፈሰሰልን ክቡር ደም ክቡራን ያደርገናል::

"በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ"
                                                          
1ኛ ቆሮ.6:19

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations

22 Nov, 04:00

የእኔና የአንተ ዋጋ በወርቅ በብር የሚመዘን አይደለም:: ዋጋችን በመስቀል ላይ የፈሰሰው ክቡር ደም ነው::
ጌታ "መላእክቶቻቸው የአባቴን ፊት ያያሉና ማንንም እንዳትንቁ" ብሎ ነበር:: (ማቴ.18:10) ሰውን ስለ መልአኩ ብለን እንዳንንቅ ከተነገረን ስለፈሰሰለት ደምማ ምንኛ ልናከብረው ይገባን ይሆን?

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations

21 Nov, 16:22

ቅዱስ ሚካኤል ሲጨልም ከማብራት ፀሐይ ሲከርር ከማጥላላት በቀር ያልተናገረ ሲጠብቅ የማይታይ ውለታ ቁጠሩልኝ የማይል ቅዱስ ጠባቂ ነው።ይህንን ከእስራኤልም ታሪክ የመላአኩን ጥበቃ ከቀመስን ልጆቹም ታሪክ መረዳት ይቻላል።ሊቁ ቢቸግረው የመልአኩን በዝምታ የተሞላ ጠባቂነት ቢያይ "አንተኑ ሚካኤል መና ዘአውረድከ" "ሚካኤል ሆይ መናን ያወረድኸው አንተ ነህን?" ብሎ እየጠየቀ ያደንቃል።

https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations

21 Nov, 13:31

"ይቅርታ የሚለው ቃል ሁላችንንም ያስማማናል!!
በተናጥል ወደህይወታችን መጥቶ ይቅርታ መጠየቅም ሆነ ይቅርታ ማድረግ ግን ዳገት እንደመውጣት ይሆንብናል።"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations

21 Nov, 04:32

ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ችግረኛውን ለመርዳት ከልዑል ዘንድ የምትላክ አዳኝነትህ በማመን የለመነህን በክንፈ ረድኤትህ የምትሰውር ሚካኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን!!

https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations

20 Nov, 14:39

ስለሚካኤል ተግባራት ከብዙ በጥቂቱ ስንመለከት  
የመላእክት አለቃ ሚካኤል ከሥልጣኑ የወረደውን የቀድሞውን የመላእክት አለቃ ዲያቢሎስን አንድም ክፉ ቃል አልተናገረውም:: አንዱ ከሥልጣኑ ወድቆ ሌላው ሲሾም አዲሱ ተሿሚ ስለወደቀው ምን እንደሚል እናውቃለን:: አንደበቱ ስድብ በመናገር ያልረከሰው ቅዱስ ሚካኤል ግን ወድቆ በማያርፈው ዲያቢሎስ ላይ የስድብን ቃል አልተናገረም::

የይሁዳ መልክት 1፥9"ጌታ ይገስፅ። አለው"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
https://t.me/hinokhailes_spiritual_teachings

የዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ ትምህርቶች Deacon Henok Haile Educations

20 Nov, 04:21

"ሰርግን ከቤተክርስቲያን ውጪ ማድረግ 'ጌታ ሆይ በደስታዬ ቀን አትገኝ' እንደማለት ነው።"
ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
@hinokhailes_spiritual_teachings

11,761

subscribers

632

photos

15

videos