መዝሙር ግጥሞች ቤት @orthodoxss_tewahdo Channel on Telegram

መዝሙር ግጥሞች ቤት

@orthodoxss_tewahdo


ይህ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የምንማማርበት Channel ነው !
 ወደ ቻናላችን በመቀላቀል 👇
➲ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መፅሐፍትን በPDF
➲ስንክሳር ትምህርቶች
➲ መዝሙራትን በግጥሞች
➲ ኪነ-ጥበብ
➲ ጥያቄዎችን
በሐይማኖት ብትኖሩ እራሳችሁን መርምሩ"
  ( 2ኛቆሮ -13 ፥ 5)👇
Group ገጽ👇👇
https://t.me/Orthodoxs_Tewahdo_menfeswi_group

መዝሙር ግጥሞች ቤት (Amharic)

ይህ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የምንማማርበት Channel ነው! እንደምሳሌት እና ትምህርት እና ቀጣይ መዝሙርዎች እንኳን በቤቱ በተመረጠው በPDF ፋይል በሚሰጥ ለሃይማኖት ላይ በመዘገብ ተመልከቱ። ከግጥሞች ማለት የተበላሸብን የወላጆችን እና በርካታው የመዝሙራትን አስተባባሪ ይቀርባሉ። ለበርካታው ብትኖሩ እራሳችሁን መርምሩ! በስምህ በአያቶክስ ተወላጆችን መጫን በPDF ሽኖናውያንን ይበላሉ።

መዝሙር ግጥሞች ቤት

27 Dec, 19:07


📲ስልኩን ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ ስልኩን  ይጫኑ
/Start 👇👇
╭━━━━━━━╮
┃   ● ══        
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃███████┃
┃        🔘       ┃
╰━━━━━━━╯

መዝሙር ግጥሞች ቤት

27 Dec, 18:58


❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅

📜 የሀገራችን የኢትዮጵያ ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት እንሰጣለን። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
📜

መዝሙር ግጥሞች ቤት

27 Dec, 16:27


                          †                                     

[   † ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል   ]

🕊

" ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ። " [ ዳን.፱፥፳፩ ]

" ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ" [ዘፍ.፵፰፥፲፮]

💖                    🕊                      💖

† ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል :-

- ከ፯ [ 7 ] ቱ ሊቃናት አንዱ::
- በራማ አርባብ በሚባሉ ፲ [10] ነገደ መላእክት ላይ የተሾመ::
- በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን መላእክትን ያጸና::
- ቅዱሳንን ሁሉ የሚረዳ::
- ሠለስቱ ደቂቅን : ዳንኤልን : ሶስናን ከሞት የታደገ ታላቅ መልዐክ ነው::

ከምንም በላይ ግን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዱሱን መልዐክ "መጋቤ-ሐዲስ" ብላ ታከብረዋለች:: ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጉዋሜ "አምላክ ወሰብእ - እግዚእ ወገብር" ነውና ለሥነ ፍጥረት ሁሉ የሚሆን ሐዲስ ዜናን ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም አምጥቷል::

ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ያዳነበት ነው፡፡

                          †                           

[     የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት    ]

       
🕊  በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ  🕊
             
" የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ፥ ያድናቸውማል። " [መዝ.፴፬፥፯]

🕊

"ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ" [ዘፍ.፵፰፥፲፮]

† ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በክንፈ ረድኤቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን::


†                        †                         †
💖                    🕊                      💖

መዝሙር ግጥሞች ቤት

27 Dec, 15:02


                       †                       

[   🕊   † †   ዋዜማ   † †   🕊   ]


💖 የራማው ልዑል ቅዱስ ገብርኤል 💖

[  † እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

💖                    🕊                     💖

[ የአቡነ አብርሃም ደቀ መዝሙር በመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል ታህሳስ ፲፱ የተቀኙት ቅኔ ]


ገብርኤል አረጋዊ ይትዐጸፍ ምንተ ?
አመ ወርኃ ጥምቀት አልጸቀ
እስመ ነድ ልብሱ በሕጽበት ኀልቀ
ኅልቀተ ልብሱሰ ነድ ኢያስተኃዝኖ ጥዩቀ
አምጣነ እግዝእቱ ድንግል ትፈትል ወርቀ
ወእግዚኡ ያለብስ መብረቀ

ትርጉም  ፦

[ አረጋዊው ገብርኤል የጥምቀት ወር በደረሰ ጊዜ ምን ይለብስ ይሆን
እሳት የሆነ ልብሱ በመታጠብ አልቋልና
የልብሱ ማለቅ ግን ፈጽሞ አያሳዝነውም
ድንግል እመቤቱ ወርቅን ትፈትላለችና
ጌታውም መብረቅን የሚያለብስ ነውና ]

ምስጢር  ፦

[ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ታህሳስ ፲፱ ሠለስቱ ደቂቅን ከነደደው እሳት ሊያድናቸው ከአምላኩ ተልኮ ወደ እቶኑ ሲገባ "ለሠለስቱ ደቂቅ ዘአውረድከ ጠለ" ይለዋል እሳቱ ውኃ ሆነላቸው እርሱም በዚያ አብሯቸው ታይቷል ነገር ግን "ገብርኤል ነደ ወነበልባለ" እንዲለው እሳታዊ ልብሱ በውሃ ቢታጠብ አልቋልና [እሳት ውሃ ቢነካው እንዲጠፋ] ..... ይህስ የልብሱ ማለቅ "ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ...." ይባላልና ..... ምን ለብሼ እታያለሁ ብሎ አይጨንቀውም ከጥምቀቱ አስቀድሞ ታህሳስ ፳፪ ጽንሰት[ብሥራት] ይታሰባልና "ተፈስሒ" ብሎ ያበሰራት እመቤቱ ድንግል በእሳት ቢፈተን የሚነጥረውን ወርቅ ፈትላ ታለብሰዋለች

"አስተርአያ ገብርኤል ግብተ ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ" ይላል ..... ጌታውም ቢሆን "እለ ይትለአክዎ መባርቅት ወየአውድዎ ነጎድጓድ" የተባለለት መብረቅን ያለብሰዋል....መልአኩን "ልብሱ ዘመብረቅ" ይለዋልና ለተልእኮ እንደመብረቅ የሚፋጠን ስለሆነ አንድም ዜና ብስራቱ እንደመብረቅ ስለሚሰማ ..... ለዚያ ነው በዚህ ክብር ተገልጾ በትንሳኤው ያየነው፡፡

"እነሆም ፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ።" [ማቴ. ፳፰፥፪ ]

† † መልካም በዓል ይሁንላችሁ † †

[  ዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ ]

💖

[ የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጥበቃው አይለየን። ]


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

መዝሙር ግጥሞች ቤት

25 Dec, 03:54


ከ60 second በኋላ ሰለሚጠፋ አሁኑኑ 🆗በማድረግ የፈለጉትን የመጽሐፍ ስም 📕 በመንካት የመጽሐፉን pdf 📖 ያግኙ።

መዝሙር ግጥሞች ቤት

24 Dec, 23:35


የሕፃናት የአእላፋት ዝማሬ

የፊታችን ቅዳሜ እና እሑድ ፡ ታኅሣሥ 19 እና 20፡ከጠዋቱ 4፡00 - 12:00 በቦሌ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን

መዝሙር ግጥሞች ቤት

24 Dec, 21:35


🕊

[  ✞ እንኩዋን ለኃያል "መሥፍነ እሥራኤል ቅዱስ ጌዴዎን" እና "ማርያም እህተ ሙሴ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞  ]

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።  †

---------------------------------------------

🕊   †  ኃያል ጌዴዎን   †   🕊

- እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን: ፳፪ [22] ቱን ሥነ ፍጥረትን ፈጥሮ አዳምን ገዢ አደረገው:: አክሎም በነፍስ ሕያው አድርጐ: በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ: ነቢይና ካህን አድርጐ: ካንዲት ዕፀ በለስ በቀር በፍጥረት ሁሉ ላይ አሰለጠነው::

- አባታችን አዳም ግን ስሕተት አግኝቶት ከገነት ወጣ:: መከራና ፍዳም አገኘው:: በሁዋላም ለ፻ [100] ዓመት አልቅሶ ንስሃ ገባ:: ጌታም ንስሃውን ተቀብሎ "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ተስፋ ድህነትን ሰጠው::

- ስለዚህም ምክንያት ለ፭ ሺህ ፭ መቶ [5500] ዓመታት ትንቢት ሲነገር: ሱባኤ ወደ ታች ሲቆጠር: ምሳሌም ሲመሰል ኖረ:: ከደግ ፍጥረት አዳም እስከ ኖኅ ድረስ: የሴት ልጆች እግዚአብሔርን በንጽሕና ሁነው በደብር ቅዱስ አመለኩ::

- ትንሽ ቆይተው ግን ስለተቀላቀሉ ከቃየን ልጆች ጋር በማየ ድምሳሴ ጠፉ:: በጻድቅ ሰው ኖኅ የተጀመረው ትውልድም እግዚአብሔርን ለመዘንጋት ጊዜ አልፈጀበትም:: ነገር ግን ከሴም ዘር ቅንና ጻድቅ ሰው አብርሃም ተገኘ::

- ከእርሱም ይስሐቅ: ከዚያም ያዕቆብ [ደጋጉ] ተገኙ:: ያዕቆብም "እሥራኤል" ተብሎ: በልጆቹ "ሕዝበ እግዚአብሔር" የተባለ ነገድ ተመሠረተ:: በተስፋይቱ ምድር በከነዓን እንዳይኖሩም ረሃብ ምድረ ግብጽ አወረዳቸው::

- በዚያም ለ፪ መቶ ፲፭  [2015] ዓመታት በጭንቅ የባርነትን ሕይወትን አሳለፉ:: እግዚአብሔርም ስለ ወዳጁ አብርሃም ሲል እሥራኤልን አሰባቸው:: የዋሕና ጻድቅ ሰው ሙሴን አስነስቶ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አዳናቸው::

- ይኸውም በጸናች እጅ: በበረታችም ክንድ: በ፱ መቅሰፍት: በ፲ኛ ሞተ በኩር: በ፲፩ኛ ስጥመት ግብጻውያንን አጥፍቶ ነው:: በየመንገዱም ጠላቶቻቸውን እየተበቀለላቸው ነው:: ከዚህ ዘመን ጀምሮም እሥራኤል በመሳፍንትና በካህናት የሚተዳደሩ ሆኑ::

- አስቀድሞ ሙሴ በምስፍና: አሮን በክህነት መሯቸው:: ቀጥሎም በቅዱስ ሙሴ ኢያሱ: በአሮን አልዓዛር ተተኩ:: እንዲህ እንዲህ እያለም ከኃያል ሰው ጌዴዎን ደረሱ:: ይኸውም ከዓለም ፍጥረት ፬ ሺህ ፩ መቶ ፶፩ [4151] ዓመታት በሁዋላ መሆኑ ነው::

- በጊዜው እሥራኤል ጣዖትን እያመለኩ እግዚአብሕርን ስላሳዘኑት ለጠላቶቻቸው አሳልፎ ይሰጣቸው ነበር:: የአካባቢው መንግስታት እነ አሞን: አማሌቅ: ኢሎፍሊ ስንኩዋ ያኔ ዛሬም ቢሆን እንደምትመለከቱት ዶሮና ጥሬ ናቸው::

- ከክርስቶስ ልደት ፩ ሺህ ፫ መቶ ፵፱ [1349] ዓመታት በፊትም በእሥራኤል ላይ ምድያማውያን [ይህቺ ሃገር የኢትዮዽያ ግዛት ነበረች ይባላል] በጠላትነት ተነስተውባቸው ተጨነቁ::

- አምላካችን እግዚአብሔርም ሊያድናቸው ወዶ መልአኩን ወደ ጌዴዎን ላከው:: ቅዱስ መልአክም ወደ እርሱ ቀርቦ "ኃያል የእግአብሔር ሰው" ሲል ጠራው:: ጌዴዎን ግን "ባሮች ስንሆን ምን ኃይል አለን!" ሲል መለሰለት::

- መልአኩም "እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነውና ሒድ! እሥራኤልን ከምድያም እጅ አድናቸው" አለው:: ጌዴዎን ምልልሱን ቀጠለ:: "እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መሆኑን በምን አውቃለሁ?" ሲል ጠየቀው::

- ጌዴዎን ይህንን ያለው ፈጣሪውን ተጠራጥሮት አይደለም:: ይልቁኑ ጥበበ እግዚአብሔር ይገለጥ ዘንድና በሁዋለኛው ዘመን የሚፈጸመውን ምሥጢረ ሥጋዌ ሊያስረዳ እንጂ::

- መልአኩም መስፍኑ የሰዋውን መስዋዕት አሳረገለት:: ቀጥሎም ጌዴዎን "ጸምር [ብዝት ጨርቅ] ልዘርጋ:: ጠል [ዝናብ] በጸምሩ ላይ ይውረድ:: ዳር ዳሩ ግን ይቡስ [ደረቅ] ይሁን" አለ:: በጠዋትም እንዳለው ሆኖ አገኘው::

- በጸምሩ ላይ የወረደውን ጠል ጨምቆ በመንቀል ሞልቶ ቢጠጣው ሰማያዊ ኃይል ወረደለት:: ጥያቄውን አሁንም ቀጠለ:: "ጌታ ሆይ! እንደ ገናም ነገሩ ይቀየርልኝ:: ጠል በጸምሩ ላይ አይውረድ:: ዳር ዳሩ ግን ይውረድበት" አለ::

- እንዳለውም ሆነ:: ይህ ሁሉ ምሳሌ ነው:: ለጊዜው ጸምር የእሥራኤል: ጠል የረድኤት: ምድር የአህዛብ ምሳሌ ነው:: ጠል በጸምር እንጂ በምድር ላይ እንዳልወረደ ረድኤተ እግዚአብሔር ለእሥራኤል እንጂ ለአሕዛብ ያለ መደረጉ ምሳሌ ነው::

- አንድም ምሳሌውን ይለውጧል:: ጠል የሚለውን ብቻ እንቀይረውና ጠል የመቅሰፍት ምሳሌ: በ፪ኛው ጠል በምድር ላይ እንጂ በጸምር ላይ እንዳልወረደ: መቅሰፍቱም እሥራኤልን ትቶ በአሕዛብ ላይ ወርዷልና:: [ይህ ጊዜአዊ ምሥጢሩ ነው::]

- አማናዊ ምሥጢሩ ግን ወደ ሐዲስ ኪዳን ያመጣናል:: ጸምር የእመቤታችን: ጠል የጌታ ምሳሌ:: ጠል በጸምር እንጂ በምድር ላይ አለመውረዱ ጌታ ከድንግል ማርያም ብቻ መወለዱን ያሳያል::

- በ፪ኛው ምሳሌ ደግሞ ጠል የፍዳ: የመርገም ምሳሌ ይሆናል:: ጠል በምድር ላይ እንጂ በጸምር ላይ አለመውረዱ ድንግል ማርያም ፍዳ መርገም የሌለባት ንጽሕት መሆኗን ያሳያል::

- ይህ ሁሉ የተደረገለት ጌዴዎንም በወገኖቹ መካከል አዋጅ አስነግሮ ፴፪ [32] ሺ ሠራዊትን ሰበሰበ:: ግን እግዚአብሔር የእሥራኤላውያንን ክፋት [ማለትም በራሳችን ኃይል አሸነፍን] እንደሚሉ ያውቃልና "የፈራ ይመለስ በል" አለው::

- ፳፪ ሺ [22,000] ሠራዊት ፈርቶ ተመለሰ:: ምክንያቱም የምድያም ሠራዊት ከ፻ [100,000]  ሺ በላይ ነበርና:: አሁንም "፲ ሺው [10,000] ብዙ ነው:: ወደ ወንዝ አውርደህ ለያቸው" አለው:: ጌዴዎንም ወደ ወንዝ አውርዶ "ውሃ ጠጡ" አላቸው::

- ከ፲ ሺው ፫ [10,300] መቶው በእጃቸው እየጠለፉ ሲጠጡ ፱ ሺህ ፯ መቶ [9,700] ያህል ሰራዊት ግን ተጐንብሰው በአፋቸው ጠጡ:: በዚህም "ሌሎቹን [የተጐነበሱትን] አስመልሰህ በ፫ መቶው [300] ው ተዋጋ" ተባለ::

- እርሱም ፫ መቶ [300] ውን ተከታዮቹን ይዞ: መለከትና መብራት በሸክላ ይዞ በምድያም ሠራዊት አካባቢ አደረ:: በዚያች ሌሊትም ጌዴዎንና ሠራዊቱ በምድያም መካከል ገብተው እንስራቸውን ሰበሩ::

- መለከቱንም ነፉ:: እንደ አንበሳም "ኃይል ዘእግዚአብሔር: ኩዊናት ዘጌዴዎን - ኃይልን ከእግዚአብሔር: ጦርን ከጌዴዎን" እያሉ ገጠሙ::

- በድንጋጤ የተመቱት ምድያማውያንም እርስ በርሳቸው ተዋግተው በአንድ ሌሊት ብቻ መቶ ሁለት ሺህ [102,000] ሠራዊት አለቀባቸው:: ቀሪዎቹም ወገኖቻቸው አፈሩ:: እሥራኤል ግን በፈጣሪያቸው ኃይል ተፈሩ:: ጌዴዎንም ለ ፵ [40] ዓመታት እሥራኤልን አስተዳድሮ በዚህች ቀን ዐርፏል:: [መሣ.፮፥፩ - ፰፥፴፭] [6:1---8:35]


🕊  † ማርያም እህተ ሙሴ †   🕊

ይህች እናት የሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴና የሊቀ ካህናቱ ቅዱስ አሮን ትልቅ እህት ስትሆን ወላጆቿ እንበረምና ዮካብድ ይባላሉ:: እሥራኤል ከግብጽ ባርነት እንዲወጡ የእርሷን ያህል አስተዋጽኦ ያደረገች ሴት የለችም::

- ከመነሻውም ቅዱስ ሙሴን የጠበቀች: በሕግ በሥርዓት እንዲያድግ ከእናቱ ጋር ያገናኘች: ወገኖቿ ከግብጽ ሲወጡም ሴቶችን የመራች እናት ናት:: ወንድሞቿን ሙሴንና አሮንንም ታገለገላቸው ነበር:: በተለይ እግዚአብሔር ባሕረ ኤርትራን የብስ ሲያደርጋት ከበሮን አንስታ "ንሴብሖ ለእግዚአብሔር" ብላ ፈጣሪዋን አመስግናለች:: [ዘጸ.፲፭፥፳] [15:20]

መዝሙር ግጥሞች ቤት

24 Dec, 21:35


- አንድ ጊዜም "ኢትዮዽያዊቷን ሲፓራን ለምን አገባህ" በሚል ስለ ተናገረችው እግዚአብሔር ተቆጥቶ በለምጽ መቷታል:: [ዘኁ.፲፪፥፩] [12:1] ቆይቶም በቅዱሱ ምልጃ ምሯታል:: ማርያም በመንገድ ሳሉ: ወደ ርስት ሳይደርሱ ዐርፋ ተቀብራለች:: [ዘኁ.፳፥፩] [20:1]

አምላከ ኃያላን መንፈሳዊ ኃይልን ልኮ ጠላትን ያድክምልን:: ከወዳጆቹ በረከትም ይክፈለን::

🕊

[ † ታሕሳስ ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ጌዴዎን ኃያል
፪. ማርያም እህተ ሙሴ

[   † ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. ኪዳነ ምሕረት [የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም]
፪. ቅድስት ኤልሳቤጥ [የመጥምቁ ዮሐንስ እናት]
፫. ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
፭. ቅዱስ አኖሬዎስ ጻድቅ
፮. አባ ዳንኤል ገዳማዊ
፯. አባ አቡናፍር ገዳማዊ

" እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና:: እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅንም አደረጉ . . ." [ዕብ.፲፩፥፴፪]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

መዝሙር ግጥሞች ቤት

24 Dec, 20:35


የአእላፋት መዝሙር ጥናት ተጀመረ!!!

እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

አዲስ የአእላፋት መርሙራት ተለቀዋል!

መዝሙሮቹን በቴለግራም ለማጥናት JOIN በሉ!

@yeaelafat_zmare

መዝሙር ግጥሞች ቤት

24 Dec, 20:00


👉 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉 ግብረ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው በተክሊል ማግባት ይችላልን?
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ወደ ቦቱ ይግቡ 👇👇

መዝሙር ግጥሞች ቤት

24 Dec, 17:15


💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷   "  የ ኅ ሊ ና ዳ ኛ    !   "


💖  በቅዱስ ዮሐንስ-አፈወርቅ  💖 ] 

[                        🕊                        ]
-------------------------------------------------

❝ ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል። እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ ፥ ❞

[  ፩ጴጥ . ፬ ፥ ፯  ]


🕊                       💖                     🕊

መዝሙር ግጥሞች ቤት

24 Dec, 17:15


🌿🌿🌿መንፈሳዊ ጥያቄዎች 🍀🍀




1, ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው ?
2, ሰንበት በብሉይ ቅዳሜ, በሐዲስ እሁድ ለምን ሆነ?
3, አእማደ ሚሥጢራት ለምን ሚሥጢር ተባለ?
4, 10ሩን የቅድስና ማዕረጋት ዘርዝሩ?
5, ሚሥጢር ማለት ምን ማለት ነው ?
6, ሚሥጢረ ሥጋዌ ማለት ምን ማለት ነው?


መልስ ለማግኘት👇👇👇

መዝሙር ግጥሞች ቤት

24 Dec, 15:16


                        †                         

🕊  አስደናቂው የልደት ምስጢር  🕊 

💖

[  የአዳኛችንን በሥጋ መወለድ በተመለከተ በልደቱ ውስጥ ያለው አስደናቂ እና ጥልቅ መገለጥ  ]

💖                     🕊                     💖

❝ ጌታዬ ሆይ ዝናኽ አስፈሪ በመኾኑ እኔ ብቁ ያልኾንኁ እንዲኹም ኮልታፋ ነኝ። የውዳሴኽ ቅኔ ጥልቅ ነው፡፡ አንደበቴም መናኛ ነው ፥ በምን ብልኀት ልገነዘብኽ እችላለኁ ? ፍለጋኽ በእርጋታ የሚኾን ነው ፣ አእምሮዬ ግን ችኩል ነው እናም እንዴት ብቁ እኾናለኍ ?

ክብርኽ ያበራል ፤ አእምሮዬ ግን የጨለመ ነው ፤ ስለዚኽ እንዴት አይኻለኍ ? ዝምታን ልምረጥ ይኾን ? ግን ርሱ ደግሞ ስንፍና በመኾኑ ጉዳትን ይወልጻል።

ተነሥቼ ልናገር ይኾን ? ግን ርሱም የሚያስደነግጠኝ አስፈሪ ነገር ነው፡፡ በእነዚኽ በኹለቱ መኻከል አጣብቂኝ ውስጥ ነኝ ፣ እና የትኛውን ልያዝ ? ዝም ማለትንም ፈርቻለኍ ለመናገርም ፈርቻለኍ ፤ ስለዚኽ ምን ላድርግ ? የቃሎቼን በገና ላንተ አሳልፌ እየሰጠኍ ነኝ ፣ እናም ያንተን ጣቶች ልዋሳቸው ፣ እና በዚኽ ባንተው ዜማ ድምፅም ለክብርኽ በለኆሳስ ይናገር፡፡

አእምሮዬ በመንፈስ ግፊት ኾኖ ለምስጋናኽ ቅኔን ያምጣ ፤ እኔ ላንተ ልቀኝ ያልበቃኁ ነኝና እባክኽን አንተ በኔ ውስጥ ተናገር። ቃልኽ እስትንፋስ ታሪክኽም ድምፅ ሲኾን እኔ ግን ዋሽንት ነኝ ፤ እባክኽን አንተ ተቈጣጠረው እና ያንተ የኾነውን ነገር ተጠቅመን ባንተው መንገድ ላንተ እንዘምራለን [ እንቀኛለን ]፡፡ ❞

🕊 ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ  🕊 ]

💖

ድንግል ሆይ ቅድስት ሆይ ጌታን የወለድሽ ሆይ እኛን ለማዳን ድንቅ ምሥጢር [ ተዋሕዶ ] በአንቺ ቢደረግ ንጉሥን ወልደሽልናልና ፍጥረታትን በብዙ ድንቅ መልክ የፈጠረ የርሱን የግናንነቱን ነገርም ፈጽመን መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡ ❞ [ የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

መዝሙር ግጥሞች ቤት

24 Dec, 14:02


ምን አይነት መዝሙሮችን ይፈልጋሉ?👇👇👇

መዝሙር ግጥሞች ቤት

07 Dec, 19:34


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

መዝሙር ግጥሞች ቤት

07 Dec, 18:16


በግምት ከሌሊቱ 8 ሰአት ገደማ ነው ሶስት ጓደኛማቾች እንደ ለመደባቸው ቅዳሜን ወጥተው ክለብ ለክለብ እየተዝናኑ ሰአታትን አስቆጥረዋል እንደ አጋጣሚ ሆኖ እጃቸው ላይ ያለውን ብር የትራንስፖርት እንኳን ሳያስከሩ መጨረሳቸውን ያስተዋሉት ከረፈደ ነበር ያው የሁልጊዜ ቤታችን ስለሆነ ዱቤ ይሠጡናል ብለው አስተናጋጁን ይጠሩትና የተፈጠረውን ያስረዱታል እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሞባይል ባንኪንግ የማይጠቀሙበትን ተቀያሪ ስልካቸውን እንደያዙና እጃቸው ላይ በዚህ ሰአት ምንም ብር እንደሌላቸው ይነግሩታል እሱም ወደ ማናጀሩ መሄድ ሲጀምር.....see more

መዝሙር ግጥሞች ቤት

07 Dec, 17:30


🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ⁉️

📌 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
📌 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
📌 ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
📌 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
📌 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
📌 ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ

እና የሌሎችንም ...........

ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

መዝሙር ግጥሞች ቤት

07 Dec, 15:40


                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ]

🕊             
             
❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ፤ ነፍስን ይመልሳል ፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።

የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፥ ልብንም ደስ ያሰኛል ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ፥ ዓይንንም ያበራል። ❞

[ መዝ . ፲፱ ፥ ፯  ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞  ]

               [   ክፍል - ፴፱ -    ]

          💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                        👇

መዝሙር ግጥሞች ቤት

07 Dec, 15:25


📷 እርግጠኛ ነኝ ፕሮፍይሎን ለመቀየር ፈልገው ፕሮፍይል የሚያደርጉት ጠፍቶ  ተቸግረው ያውቃሉ።

የናንተን ችግር ለመፍታት በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ መንፈሳዊ ቻናል ይዘንላችሁ መተናል ከናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ join ማድረግ ብቻ ነው👇👇👇👇👇👇📷

https://t.me/addlist/gpX29GzfGs43MWE0

መዝሙር ግጥሞች ቤት

07 Dec, 08:10


💛

🕊     ቅ ዱ ስ አ ማ ኑ ኤ ል     🕊

❝ ሰላም ለአስተርእዮቱ በሥጋ
ዘአስተርአየ ገሃድ ከመ የሀበነ ጸጋ ❞

[  በግልጽ ጸጋን ያድለን ዘንድ በሥጋ የተገለጠ ለኾነ ለእርሱ አገላለጥ ሰላምታ ይገባል ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል ፤ እነሆ ፥ ድንግል ትፀንሳለች ፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች ፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ❞

[ ኢሳ.፯፥፲፬ ]

" Therefore the Lord himself shall give you a sign; Behold, a virgin shall conceive, and bear a son, and shall call his name Immanuel."

[ Isaiah 7:14 ]


🕊                        💖                     🕊
                             👇

መዝሙር ግጥሞች ቤት

06 Dec, 21:35


🕊  † ቅዱስ ሰረባሞን ሰማዕት †  🕊

ቅዱሱ ሰው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ሲሆን የቅዱሳን ሐዋርያት ዘመድ ነው:: እርሱ ተወልዶ ያደገው በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በኢየሩሳሌም ነው:: የዘር ሐረጉ ሲቆጠርም በቀጥታ ከሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስና ከስምዖን ቀለዮዻ ይደርሳል::

በልጅነቱ ያደገው በሥርዓተ ኦሪት ነው:: ወጣት በሆነ ጊዜ ግን ፈጣሪ በሰጠው ሕሊና ተመራምሮ በክርስትና ለመኖር ወሰነ:: የወቅቱን የኢየሩሳሌም ኤዺስ ቆዾስ ሒዶ "አጥምቀኝ" ቢለው "ልጄ! ደስ ይለኝ ነበር:: ግን ወገኖችህ አይሁድ ይገድሉኛል" ሲል መለሰለት::

አክሎም "ወደ ግብጽ ሒደህ ግን ብትመጠመቅ የተሻለ ነው" ስላለው ከኢየሩሳሌም ግብጽ ገባ:: ግብጽ ደርሶ: ከቅዱስ ቴዎናስ [፲፮ኛ ፓትርያርክ] ክርስትናን ተምሮ ተጠመቀ::ቀጥሎም ወደ ገዳም ገብቶ ከመጀመሪያዎቹ መነኮሳት አንዱ ሆነ:: ምናኔን ከአባ እንጦንስ ተምሮ ስም አጠራሩ ከፍ አለ::

በተጋድሎውና በንጽሕናው ስለ ወደዱትም የኒቅዮስ ዻዻስ አደረጉት:: በዘመነ ሲመቱም ጣዖት አምልኮን ከአካባቢው አጥፍቷል:: ስለዚህ ፈንታም በዲዮቅልጢያኖስ ተይዞ በዚህች ቀን ተገድሏል:: ሲገደልም ልክ እንደ ቅድመ አያቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ፊቱ ያበራ ነበር::

አምላከ አበው ቅዱሳን መዓዛ ቅድስናቸውን
ያሳድርብን::ከበረከታቸውም ይክፈለን::

 🕊

[ ኅዳር ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አባ ሊቃኖስ ጻድቅ [ከተስዓቱ ቅዱሳን]
፪. ቅዱስ ሰረባሞን ሰማዕት

[ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው /አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ/
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]

" ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘለዓለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::በእርምጃውም አይሰናከልም::" [መዝ.፴፮፥፳፱]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

መዝሙር ግጥሞች ቤት

06 Dec, 21:35


🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

†  እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "አባ ሊቃኖስ ወአባ ሰረባሞን ሰማዕት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †

" ኅዳር ፳፰ [ 28 ] "


🕊  †  አባ ሊቃኖስ ዘደብረ ቆናጽል  †   🕊

ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አባ ሊቃኖስ ከዘጠኙ [ተስዓቱ] ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::

ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር :-

፩. የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ
፪. ዓላማ [የእግዚአብሔር መንግስት] እና
፫. ገዳማዊ ሕይወት ነው::

አባ ሊቃኖስን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::

በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::

በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ፬ መቶ ፸ ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::

ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ ቤተ ቀጢን ትባላለች::

አባ ሊቃኖስና ፰ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር::

ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ ሊቃኖስ እንደ ገና አቀጣጠሉት::

ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት::የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ::

ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ ሊቃኖስ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማኅበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::

የነ አባ ሊቃኖስ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ::

- ዸንጠሌዎን በጾማዕት:
- ገሪማ በመደራ:
- አረጋዊ በዳሞ
- ጽሕማ በጸድያ
- አባ ይምዓታ በገርዓልታ
- ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::

ልክ እንደ ባልንጀሮቻቸው ፰ቱ ቅዱሳን አባ ሊቃኖስም ከጻድቅነታቸው ባሻገር ለሃገራችን ትልቅ ባለውለታ ናቸው::በነገራችን ላይ 'አባ ሊቃኖስ' የመጀመሪያ ስማቸው ሳይሆን በትምሕርታቸው [በእውቀታቸው] የተደመመ የአክሱም ሕዝብ ያወጣላቸው ስም ነው::

ሊቃኖስን 'ሊቁ አባት' ማለት ነው ብለው የተረጐሙልን አበው አሉና:: ይሕስ በምን ይታወቃል ቢሉ :- ፱ኙ ቅዱሳን የማኅበር አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደየ ራሳቸው ገዳማት ሲሔዱ አባ ዸንጠሌዎንና አባ ሊቃኖስ እዚያው አክሱም አካባቢ በመቅረታቸው ይሏል::

ምክንያቱም ሕዝቡና ንጉሡ ፪ቱን አበው "አትራቁን" ብለው ለምነዋቸው ነበርና:: በዚህም የተነሳ አባ ዸንጠሌዎን ከአክሱም ከተማ በላይ ባለች ጾማዕት [እንዳባ ዸንጠሌዎን] በሚሏት ተራራ ላይ ሲያርፉ: አባ ሊቃኖስ ደግሞ ከዚያው ከጾማዕት ፩ ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ደብረ ቆናጽል [የቀበሮዎችተራራ] ላይ ዐርፈዋል::

በመካከላቸው ደግሞ የቅድስት ማርያም መግደላዊት ቤተ ክርስቲያን ይገኛል:: አባ ሊቃኖስ በአታቸውን ካደራጁና ገዳም ካነጹ በኋላ ደቀ መዛሙርትን አፈሩ: አስተማሩ::

እጅግ ከበዛው ተጋድሏቸው ባልተናነሰ መንገድ ለ፳፩ ዓመታት ያህል ከተራራው እየተነሱ ወንጌልን ሰብከዋል:: መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች መጻሕፍትንም ከሱርስት [የሶርያ ልሳን] እና ከጽርዕ [የግሪክ ልሳን] ተርጉመዋል::

ሁልጊዜም ለአገልግሎት ሲወጡ በትረ ሙሴአቸውን አይለዩም ነበር:: ሲሰብኩም: ሲጸልዩም ተደግፈውባት ነበር:: ታዲያ ከዘመን ብዛት የእጃቸው መዳፍ መነደሉን አበው :-"ወበእሒዘ በትር ዘተሰቁረ ዕዱ" ሲሉ ይናገራሉ::

ዳግመኛ ማታ ማታ ለጸሎት እጆቻቸውን ሲያነሱ እንደ ፋና ቦግ ብለው ሲያበሩ ይታዩ ነበር:: ጻድቁ አባ ሊቃኖስ ሥሙር በሆነ ሕይወታቸው በእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን በነገሥታቱና በሕዝቡ ዘንድም ሞገስን አግኝተዋል:: ዛሬም ድረስ የአክሱም ሕዝብ ከልቡ ያከብራቸዋል::

አንድ ወቅትም ሳይገባን [በቸርነቱ] ሒደን ገዳማቸውን ተመልከተናል:: አበው እንደሚሉት በደብረ ቆናጽል ላይ ያለው ደን የብዙ ሥውራን መኖሪያ ነው:: ለ፩ ሺህ ፭ መቶ ዓመታት ተከብሮ ቢኖርም በ፲፱፻፳፰ቱ የጣልያን ወረራ ግን እንዳልነበረ ሆኖ ነበር::

ዛሬም በቀድሞ ገጽታው አይደለም:: በገዳሙም ያገኘነው አንድ አባትን ነው::

ዐይናችን ግን ብዙ ነገሮችን ተመልክቶ አድንቋል:: እንደ ሰማነውም ዛሬም መካነ ቅዱሳን በመሆኑ የጽዮን አገልጋዮችም ማረፊያ ነው:: ጻድቁ አባ ሊቃኖስ ያረፉት ሕዳር ፳፰ ቀን ነው::

መዝሙር ግጥሞች ቤት

06 Dec, 19:12


💁‍♂ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል።  ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
               ክፈት        ክፈት               
               ክፈት        ክፈት               
                                                   
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
                                                    
                                                   
                                                    
                                                    
                                                     
               ክፈት         ክፈት              
               ክፈት         ክፈት

መዝሙር ግጥሞች ቤት

06 Dec, 18:04


💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️

💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️

👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️

⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️

🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️

በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
                👇👇👇
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel



        
                     🔔
          🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
          ♦️ፊላታዎስ ሚዲያ♦️
                    👇🏽👇🏽
🧏መናፍቃን ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች⁉️
የጌታችን እናት የአዳም የውርስ ኃጢአት/ጥንተ አብሶ/አለባት⁉️
የጌታችን እናት አልተነሳችም⁉️
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
         👆👆👆
👉ለነዚህ ጥያቄዎች እና ለመሳሰሉት በቂምልሽ ተሰቶበታ ይቱብላይ ታገኙታላቹ።

መዝሙር ግጥሞች ቤት

06 Dec, 17:42


❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅

📜 የሀገራችን የኢትዮጵያ ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት እንሰጣለን። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
📜

መዝሙር ግጥሞች ቤት

06 Dec, 08:55


                           †                           

🕊  💖    ቀኑ አርብ ነው !    💖   🕊

🕊

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  ❝ የዕለተ ዓርቡን መከራህን አሳየኝ ! ❞ ]

💖

ሕሊናቸው የክርስቶስን ሕማም ከማሰብ አቁሞ የማያውቀው አባ መብዓ ጽዮን መድኃኔዓለምን ፦ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የዕለተ ዓርቡን መከራህን አሳየኝ፡፡ ስለ ራሴ ፈጽሞ አለቅስ ዘንድ " ሲሉ ለመኑት፡፡ ጌታም ፦ "መከራ መስቀሌን ለማየት ትፈቅዳለህን ? " ብሎ ጠየቃቸው። ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮንም ፦ "አዎ ! አይ ዘንድ እወዳለሁ" አሉት።

ያን ጊዜም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ እጆቹና እግሮቹ ተቸንክረው ታየ ፣ በራሱም ላይ የእሾህ አክሊል ደፍቶ ነበር፡፡ እንዲህ ሆኖ በሮም አደባባይ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንደታየው ታያቸው። ይህን የመድኃኔዓለም መከራ የተመለከቱ የጻድቁ ዓይኖችም ፈዝዘው እስኪጠፉ ድረስ ትኩስ እንባዎችን ሲያዘንቡ ኖረዋል

🕊

❝ ሰው ስለመሆኑ ፤ መከራ ስለመቀበሉ መድኅንን የሚከፍለው [ ሁለት የሚያደርገው ] ፤ እግዚአብሔር ነው ብሎ ስለመስገድ ፈንታ ዕሩቅ ብእሲ ነው የሚል ፤ የተሰቀለውንም ከመለኮት የተለየ ሰው ነው የሚል ፤ መለኮትንም ሥጋ ወደመሆን ተለወጠ የሚል ቢኖር እግዚአብሔር ሰው በመሆን ያደረገለትን ድኅነት አያገኝም። [መዝ.፲፪ (፲፩)፥፭  ፣ ፸፬(፸፫)፥፲፪ ፣ ፻፲፩(፻፲)፥፱] ❞ [ አቡሊዲስ ]

 
❝ ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ ❞  [ ኃይሌና መጠጊያዬ እርሱ ጌታዬ ነው ! ]

🕊

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


💖                    🕊                     💖

መዝሙር ግጥሞች ቤት

06 Dec, 08:27


🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ አምላክ ሰው ሆነ እንጂ .... !   ]

🕊

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❝ [ አምላካችን ] ሰውም በሆነ ጊዜ እንደ ዕሩቅ ብእሲ በዘር በሩካቤ አልተወለደም ፥ አምላክ ሰው ሆነ እንጂ ፤ እንደ ዕሩቅ ብእሲ በዘር በሩካቤ ተወልዶ ቢሆንስ ብዙ ሰዎች በተሳሳቱ ነበር ፥ አምላክ ሰው መሆኑንም ሐሰት በአደረጉት ነበር።

ዛሬ ግን ከድንግል ብቻ ተወለደ ፤ ድንግልናዋንም ባለመለወጥ አጸና ፤ ድንቅ የሚሆን መፅነስዋ የታመነ ይሆን ዘንድ ቅድመ ዓለም ከአብ እንደ ተወለደም ለማመን መሪ ይሆን ዘንድ።

የክብር ባለቤት ሲሆን ለሕፃናት እንደሚገባ በየጥቂቱ አደገ ፥ እርሱም ከአብ አንድነት ወደዚህ ዓለም መጥቼ ሰው ሆንኩ ወደ እግዚአብሔር እሔዳለሁ ፤ በእርሱ ፈቃድ ሰው ሆንኩ እንጂ በእኔ ፈቃድ ብቻ ሰው የሆንኩ አይደለም አለ። [ ዮሐ.፯፥፳፰ ። ፲፮፥፳፯—፳፱ ]

ይህም ከአብ ተወልዶ ሰው ለመሆን እንደመጣ ማርያም ለወለደችው አካል ምስክር ነው ፥ ወደ አብ የሔደውም ሌላ አይደለም ፥ በባሕርዩ አንድ የሚሆን እርሱ ነው እንጂ ፥ ከተወለደም በኋላ ሁለት አልሆነም ፤ ሁለት አካል ፤ ሁለት ባሕርይ አይደለም ፥ በሥራው ሁሉ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው እንጂ ፤ ሙት በማስነሣት ድውይ በመፈወስ ፤ መከራ በመቀበል አንድ ነው እንጂ

[ ማቴ.፬፥፳፫-፳፭ ። ፲፩፥፬—፮ ] ❞

[    ቅዱስ ጎርጎርዮስ  ዘእንዚናዙ    ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

መዝሙር ግጥሞች ቤት

06 Dec, 05:03


መዝሙር ግጥሞች ቤት pinned «ማስታወቂያ ሰላም ውድ የ መዝሙር ግጥሞች ቤት ቻናል ተከታታዮች ‼️ ✝️መንፈሳዊ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ቻናሉ ላይ መንፈሳዊ  ለማስተናገድ እንፈልጋለን ✝️ ✝️ የመንፈሳዊ #የጉዞ ማስታወቂያዎች ✝️ የመንፈሳዊ #ኮርስ ማስታወቂያዎች ✝️ለአዳዲስ #መዝሙሮች ✝️ የ መንፈሳዊ #መፅሃፍ ምረቃዎች 📱አንዲሁም ማንኛውንም ይዘት ያላቸው መንፈሳዊ ማስታወቂያዎች አንቀበላለን ✝️ 😀የምታቀርቡት ማስታወቂያ…»

መዝሙር ግጥሞች ቤት

06 Dec, 05:02


ማስታወቂያ

ሰላም ውድ የ መዝሙር ግጥሞች ቤት ቻናል ተከታታዮች ‼️

✝️መንፈሳዊ የሆኑ ማስታወቂያዎችን ቻናሉ ላይ መንፈሳዊ  ለማስተናገድ እንፈልጋለን ✝️

✝️ የመንፈሳዊ #የጉዞ ማስታወቂያዎች
✝️ የመንፈሳዊ #ኮርስ ማስታወቂያዎች
✝️ለአዳዲስ #መዝሙሮች
✝️ የ መንፈሳዊ #መፅሃፍ ምረቃዎች

📱አንዲሁም ማንኛውንም ይዘት ያላቸው መንፈሳዊ ማስታወቂያዎች አንቀበላለን ✝️

😀የምታቀርቡት ማስታወቂያ እውነትነት ከተረጋገጠ እና ሀይማኖታዊ ይዘት ያለው ከሆነ ልታናግሩን ትችላላችሁ

👉በዚህ አድራሻ ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ ይቻል
👉👆👇 @Orthodoxs_tewahedo_bot
@Orthodoxs_tewahedo_bot

👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ልብ የበሉ አገልግሎቱ ነጸ ነው ምንም አይነት ክፍያ የለውም አነግሩን

መዝሙር ግጥሞች ቤት

05 Dec, 20:37


🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

† ኅዳር ፳፯ [ 27 ] †


🕊 † ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ  †  🕊

ይህ ስም በቤተ ክርስቲያን እጅግ ዝነኛና ታዋቂ ነው:: ቅዱስ ያዕቆብ ቁጥሩ ከዓበይት ሰማዕታት ሲሆን የፋርስ ኮከብ በመባልም ይታወቃል:: ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ["ሙ" ጠብቆ ይነበብ] ተወልዶ ያደገው በ፬ኛው መቶ ክ/ዘ በምድረ ፋርስ [የአሁኗ ኢራን] ውስጥ ነው::

ያኔ ይህቺ ሃገር በአንድ ወገን ጠንካራ ክርስቲያኖች: በሌላ ወገን ደግሞ ጣዖትን የሚያመልኩ ጨካኝ ነገሥታት ነበሩባት:: ቅዱስ ያዕቆብም በክርስትና ትምሕርት አድጐ ሚስት አገባ::

በዘመኑ ከነበረው ንጉሥ ሠክራድ ጋር በጣም ይዋደዱ ነበርና በቤተ መንግስቱ ውስጥ ሹም አድርጐ አስቀመጠው:: በቤተ መንግስት ውስጥ ምቾት የበዛበት ቅዱስ ያዕቆብ የጾምና የጸሎት ሕይወቱ እየቀዘቀዘ መጣ:: በሒደትም ንጉሡ የሚለውን ሁሉ የሚፈጽም ሰው ሆነ::

አንድ ቀን ግን ሠክራድ ቅዱስ ያዕቆብን "ለእሳትና ለጸሐይ ስገድ: እነሱንም አምልካቸው" ሲል ጠየቀው:: ከመጀመሪያ የተሸረሸረ ነገር ስለ ነበረ "እሺ! ደስ ይበለው" ብሎ ለፀሐይ ሰገደ:: እርሷንም አመለከ::

ይህቺ ዜና በዘመኑ ክርስቲያኖች ዘንድ ስትሰማ ታላቅ ሐዘንን ፈጠረች:: ይልቁኑ ሚስቱ: እናቱና እህቱ ይህንን ሲሰሙ አንጀታቸው አረረ:: በዚህ ምክንያትም ፫ቱ ተሰብስበው አንድ ደብዳቤ ጽፈው: ተፈራርመው ላኩለት::

የደብዳቤው ይዘት እንዲህ ይላል:- "አንተ ክርስትናህን መካድህን ሰምተን አዘንን:: በዚህም ምክንያት ከዚህ በሁዋላ በአካባቢህ መኖርን አንፈልግም:: ለሞተልህ ለክርስቶስ ካልታመንሀ እኛ አንተን እንደ ልጅ: እንደ ወንድምና እንደ ባል ልናምንህ ይከብደናል::"

ይህንን ደብዳቤ ልከውለት እነርሱ አካባቢውን ለቀቁ:: ቅዱስ ያዕቆብ ደብዳቤውን ተቀብሎ: ወደ ቤቱ ገብቶ ሲያነበው ደነገጠ:: በዚህ ምድር ያሉት ዘመዶቹ ሚስቱ: እናቱና አንዲት እህቱ ብቻ ናቸውና ውስጡ ተሸበረ:: ተደፍቶም ምርር ብሎ አለቀሰ::

ሲመሽም በቤቱ ውስጥ ወደ ነበረው የቀድሞ የጸሎት ቦታ ሒዶ ተንበረከከ:: ከንጉሡ ጋር በነበረው ያልተገባ ቅርርብ የፈጸመው ስህተት ሁሉ ቁልጭ ብሎ ታየው::

በጌታችን ፊት ቁሞም "ጌታ ሆይ! በምድር ካሉ የሥጋ ዘመዶቼ መለየት እንዲህ ካሸበረኝ: ካንተ ፍቅር መለየትማ እንደ ምን ይጨንቅ ይሆን! በሰማያዊ ዙፋንህ ፊትስ እንዴት ብዬ እቆማለሁ!" ሲል አምርሮ አለቀሰ::

ሙሉውን ሌሊት በእንባና በጸሎት አድሮ በጠዋት ንስሃ ገባ:: ከዚያች ቀን ጀምሮም ፍጹም በክርስቶስ ፍቅር ተጠመደ:: ጾምና ጸሎትን ወዳጆቹ አድርጐ ከንጉሡ እልፍኝና አደባባይ ቀረ::

ይህንን ያወቀው ንጉሡ ሠክራድ ወደ እርሱ አስጠርቶ "ምን ሆነሃል? ስለ ምንስ በአምልኮ ከእኔ ተለየህ?" አለው:: ቅዱስ ያዕቆብም መልሶ "የፈጠረኝን ክርስቶስን ትቼ አንተን በባዕድ አምልኮ አስደስትህ ዘንድ የሚገባ አይደለም" ሲል ተናገረው::

ንጉሡ ቅዱሱን አስቀድሞ ሊያታልለው ሞከረ:: እንቢ ሲለው ግን ደሙ በመሬት ላይ እስኪንጠፈጠፍ ድረስ አስገረፈው:: አስደበደበው:: ጭንቅ መከራዎችንም አሳየው:: ቅዱስ ያዕቆብ ግን በፍቅረ ክርስቶስ ጸና::

በዚህ የተበሳጨው ንጉሡ እንዲቆራርጡት: ግን ቶሎ እንዳይገሉት አዘዘ:: ከዚያ ቀን በሁዋላ በቀን በቀን እየገቡ ከአካሉ ይቆርጡ ጀመር:: ከእጣቶቹ ተነስተው እጆቹን እስከ ክንዱ: እግሮቹን እስከ ታፋው ድረስ ቆረጡ:: መሐል አካሉ [ወገቡና ራሱ] ብቻ ቀረ::

ይህ ሄሉ ሲሆን እርሱ ጌታን ይቀድሰው: ይጸልይም ነበር:: "የወይን ግንድ ሆይ! እኔን ቅርንጫፍህ አድርገኝ" [ዮሐ.፲፭፥፭] ይለው ነበር:: ከአካሉ እየቆረጡ የጣሉትም ሲቆጠር ፵፪ ሆነ:: ፵፫ኛ ደግሞ የተረፈ አካሉ ነበር::

ያን ጊዜ ሊጸልይ ፈልጐ "ጌታ ሆይ!" ብሎ ጮኸ:: ይህንን አበው :-
"መንፈቀ አካሉ ጸለየ መዊቶ መንፈቁ" ብለው ገልጸውታል:: ግማሽ አካሉ ሙቶ በቀረው ይጸልይ ነበርና ንጉሡም ከጩኸቱ በሁዋላ አንገቱን በሰይፍ ሲያስመታው ጌታችን ወርዶ ታቅፎ ወደ ሰማይ አሳረገው::

እናቱ: እህቱ: ሚስቱ ይህንን ሲሰሙ እያለቀሱና እየዘመሩ አካሉን ሰብስበው ገንዘውታል:: ሽቱም አርከፍክፈውበታል:: የዚህ ቅዱስ ገዳም [ታቦት] በኢትዮዽያ: ታች አርማጭሆ በሚባለው በርሃ ውስጥ ይገኛል:: ድንቅ የሆነ የበረከት ቦታም ነው::


🕊  †  አባ ተክለ ሐዋርያት  †  🕊

ኢትዮዽያዊው ጻድቅ አቡነ ተክለ ሐዋርያት በ፲፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ከተነሱ ዐበይት ጻድቃን አንዱ ናቸው:: በተለይ በጻድቁ ንጉሥ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን በተባሕትዎም: በትሩፋትም እጅግ የተደነቁ አባት ነበሩ::

ጻድቁ ሲጠሩ "ዘደብረ ጽሙና": አንዳንዴም "ዘገበርማ" እየተባሉ ነው:: ምናልባትም በብዙ ቦታ ላይ ስለ ተጋደሉ በእነዚህ: ቦታዎችም ላይ ስለ ነበሩ ሊሆን ይችላል እንደዚህ ተብለው የተጠሩት::

በብዛት የሚታወቀው ደግሞ በምድረ ሸዋ: ጐጃምና በምድረ አፋር አካባቢ በመኖራቸው ነው:: እስኪ አንዳንድ ነገሮቻቸውን እናንሳ :-

- ጻድቁ ክርስቶስን በመከራው ይመስሉት ዘንድ ዘወትር ይተጉ ነበር::
- አንዴ ሥጋ ወደሙ የተቀበለ አንድ ሰው በመንገድ ላይ ሲያስመልሰው ተመልከተው ሁሉ ተጸይፎ ሲሸሽ እሳቸው ግን ደስ እያላቸው ተመግበውታል:: ምክንያቱም የእርሳቸው ዓይን የሚመለከተው የፈጣሪን ሥጋና ደም ነው:: በዚህ ጊዜም ጌታ ከሰማይ ወርዶ በግንባራቸው ላይ ፀሐይን ስሎባቸዋል:: በዚህ ምክንየትም ፊታቸው ያበራ ነበር::

- አንዴ ደግሞ በገዳማቸው አንድ ደሮ ለእንግዳ ሊያርዱት ሲሉ "በአባ ተክለ ሐዋርያት ተማጽኛቹሃለሁ!" በማለቱ ትተውታል::
- በአፋር በርሃ አካባቢ ለ፲፬ ዓመታት ኑረዋል::

በአንድ በአት ውስጥም ለ፵፩ ዓመታት ኑረዋል:: ጻድቁ አቡነ ተክለ ሐዋርያት እንዲህ ተመላልሰው በተወለዱ በ፸፩ ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈዋል::


🕊 †  ቅዱስ ፊልሞና ሐዋርያ  †  🕊

ቅዱስ ፊልሞና ከ፸፪ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን ብዙ ጊዜ "ጥዑመ-ቃል [አንደበቱ የሚጣፍጥ]" ተብሎ ይጠራል:: በዘመነ ሐዋርያት በጣም ልጅ በመሆኑ እየተሯሯጠ ለአበው ይታዘዝ ነበር::

ጌታን አምኖ ተከትሎ: ለ፫ ዓመት ከ፫ ወር ተምሮ: ከቅዱስ መንፈሱ ነስቶ: ከቅዱስ እንድርያስ ጋር ለስብከት ወጥቷል:: ሃገረ ስብከቱም ልዳ ነበረች:: እርሱ ሲያነብ [ሲያስተምር] ሰው ሁሉ በተመስጦ ይሰማው ነበር:: ሊገድሉት የመጡ ወታደሮች እንኩዋ በተደሞ መግደላቸውን ይረሱት ነበር::

መዝሙር ግጥሞች ቤት

05 Dec, 20:37


አንዳንድ ቀን ደግሞ ወፎችና ርግቦች ያደምጡት: ያዋሩትም ነበር:: ይህቺ ቀን ለቅዱስ ፊልሞና ዕለተ ዕረፍቱ ናት::

አምላከ ቅዱሳን ብርሃናቸውን ያብራልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

[  † ኅዳር ፳፯ [ 27 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
፪. አቡነ ተክለ ሐዋርያት ጻድቅ
፫. ቅዱስ ፊልሞና ሐዋርያ
፬. ቅዱስ ቀሌምንጦስ ሰማዕት
፭. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕት
፮. አባ ገብረ ዮሐንስ ጻድቅ

[    † ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
፪. አቡነ መብዓ ጽዮን ጻድቅ
፫. ቅዱስ መቃርስ [የመነኮሳት ሁሉ አለቃ]
፬. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፭. ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
፮. ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት

" ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? . . . እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና::" [፩ቆሮ.፲፥፲፬]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

መዝሙር ግጥሞች ቤት

05 Dec, 19:14


https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k

መዝሙር ግጥሞች ቤት

05 Dec, 19:01


👑  ስለ ንጉስ ቴዎድሮስ     🤴


🩸 ትንቢት የተነገረለትን ንጉስ የቴዎድሮስ የሚነሳበት አስደናቂና ምስጢራዊ ስፍራ

🩸 እውነት ትንቢት የተነገረለት ንጉስ ቴዎድሮስ ይመጣል ?

🩸 በፍካሬ ኢየሱስና በገድለ ፊቅጦር ስለ ትንቢታዊው ንጉስ ቴዎድሮስና ተጽፎ ይገኛል

🩸 የየረር ተራራ አስገራሚ ምስጢሮች

ለእነዚህ ጥያቂዎች መልስ ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

እዚህ ጋር ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN
➢ JOIN  ➢  JOIN  ➢ JOIN ➢JOIN

መዝሙር ግጥሞች ቤት

05 Dec, 17:08


💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊

▷ ❝ ለራስ የሚሰጥ ያልተገባ ክብር ! ❞


💖  አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ    ] 💖

[                        🕊                        ]
---------------------------------------------------

- ከንቱ ውዳሴን የሚያስወድድ ሰይጣን !

❝ እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ ፥ ግብዞች በሰው ዘንድ ሊከበሩ በምኩራብ በመንገድም እንደሚያደርጉ በፊትህ መለከት አታስነፋ ፤ እውነት እላችኋለሁ ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።

አንተ ግን ምጽዋት ስታደርግ ምጽዋትህ በስውር እንዲሆን ቀኝህ የምትሠራውን ግራህ አትወቅ ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።  ❞

[ ማቴ . ፮ ፥ ፪ ]


🕊                        💖                     🕊
                             👇

31,320

subscribers

5,755

photos

559

videos