Kokebe Tsibah General Secondary School @kok1924 Channel on Telegram

Kokebe Tsibah General Secondary School

@kok1924


Since 1924

Kokebe Tsibah General Secondary School (English)

Are you looking for a reputable and long-standing secondary school for your child in Ethiopia? Look no further than Kokebe Tsibah General Secondary School, also known as @kok1924 on Telegram. Established in 1924, Kokebe Tsibah General Secondary School has been a pillar of education in the region for nearly a century. With a rich history and a commitment to academic excellence, this school is the perfect choice for students seeking a quality education. nnKokebe Tsibah General Secondary School offers a wide range of academic and extracurricular programs to meet the diverse needs of its students. From science and math to arts and humanities, there is something for everyone at this esteemed institution. The dedicated staff and faculty at Kokebe Tsibah General Secondary School are passionate about helping students reach their full potential, both academically and personally.nnWhat sets Kokebe Tsibah General Secondary School apart from other schools is its focus on holistic education. In addition to rigorous academic programs, the school places a strong emphasis on character development, leadership skills, and community service. Students at Kokebe Tsibah General Secondary School not only excel in the classroom but also become well-rounded individuals who are prepared to succeed in a rapidly changing world.nnWhether your child is interested in pursuing a career in STEM fields, humanities, or the arts, Kokebe Tsibah General Secondary School provides the resources and support needed to help them achieve their goals. With a proud history dating back to 1924, this school has a proven track record of success and continues to be a leader in education in Ethiopia.nnIf you are looking for a school that combines tradition with innovation, look no further than Kokebe Tsibah General Secondary School. Join @kok1924 on Telegram today to learn more about the admissions process, upcoming events, and how your child can become a part of this prestigious institution. Enroll your child at Kokebe Tsibah General Secondary School and help them embark on a journey of academic excellence and personal growth like no other!

Kokebe Tsibah General Secondary School

11 Nov, 12:46


Kokebe Tsibah Secondary School
To day's knowledge Sharing PPT.

Kokebe Tsibah General Secondary School

11 Nov, 08:54


የህዳር 2/2017 ዓ.ም የማለዳ የእውቀት ሽግግር መርሐ-ግብር ተካሂዷል
👉 የዕለቱ ርዕሠ ጉዳይ በጥሩ ሁኔታ የሒሳብ ትምህርት ክፍል ባልደረባ በሆኑት በመ/ መስጦፋ ከድር ቀርቧል።
👉 በመርሐ -ግብሩ 66 መምህራን ተሳትፈዋል

Kokebe Tsibah General Secondary School

09 Nov, 11:47


በየካ /ከተማ ትምህርት /ቤት የኮከበ ፅባህ 2ኛ ደረጃ /ቤት ዛሬ ቅዳሜ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም የተለያዩ ፕሮግራሞች አከናውኗልክንውኖቹም:-
👉ለእንግሊዝኛ እና ሒሳብ መምህራን ስትራቴጅውን መተግበር የሚያስችል ስልጠና ከኮተቤ ትምህርት ዩንቨርሲቲ በመጡ አሰልጣኞች ተሰጥቷል።
👉 ከንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር እና ከአዲስአበባ ንግድ ቢሮ ጋር በመተባበር ለት/ቤቱ ሸማቾች መብት ክበብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በራሳቸው ወጭውን ሸፍነው ለ50 መምህራን እና ተማሪዎች ሰጥተዋል።
👉 የ12ኛ ክፍል የቅዳሜ የማጠናከሪያ ትምህርት ለአራተኛ ሳምንት ተሰጥቷል።

Kokebe Tsibah General Secondary School

08 Nov, 15:12


🌟🌟ለ ኮከበ ፅባህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችና ወላጆች 🌟🌟

👉 በ 2017 የ 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ዉጤት ለማምጣት ከወላጆች ጋር በተነጋገርነው መሰረት የተለያዩ ስራዎች እየሰራን እንገኛል::

👉 እየሰራን ካለነው ስራ አንዱ የቅዳሜ የማጠናከሪያ ትምህርት አንዱ ነው::

👉 ይህንን የማጠናከሪያ ትምህርት ዉጤታማ ለማድረግ ወላጆች ልጆቻችሁን ቅዳሜ ማለትም ነገ 30/02/2017 ዓ.ም ጥዋት እንድትልኩ እናሳስባለን::

👉 ተማሪዎችም ነገ በሰዓት በመገኘት የማጠናከሪያ ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ እንጠይቃለን::

👉ማጠናከሪያ ትምህርቱ 2:30 ላይ የሚጀምር መሆኑን እንገልፃለን::

ትምህርት ቤቱ

Kokebe Tsibah General Secondary School

08 Nov, 13:59


ቀን 29/2/2017 ዓ.ም
ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ
ጉዳዩ:- የኳስ ሜዳ አጠቃቀም ፕሮግራም ስለማሳወቅ
1ኛ,ማክሰኞ እና ዓርብ ከ9:00 ሰዓት በሗላ የት/ቤቱ መምህራን :አስተዳደር ሰራተኞች እና ቀበና ናዳ ስፓርት ማህበር
2ኛ, እሮብ የ08 አዳራሽ ወጣቶች የስፓርት ማህበር
3ኛ, ሐሙስ እና እሁድ እስከ ጠዋቱ 3:30 ሰዓት ፍቅር ወንድማማቾች የጤና ስፓርት ማህበር
4ኛ,ሰኞ እና ቅዳሜ አስከ 4:00ሰዓት ቅዱስ የታዳጊዎች ስፓርት ክለብ/የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የስፓርት ሳይንስ ት/ት ክፍል ባልደረባ የሆኑት ኢንስትራክተር የሚያሰሩት/
5ኛ,ቅዳሜ 7:00-10:30 ሰዓት እና እሁድ 3:30-6:30 ሰዓት ዳግላስ የታዳጊዎች አሰልጣኝ የተከራዩ መሆኑን እናሳውቃለን።
ከዚህ ውጭ የትምህርት ቤቱን የስፓርት ሜዳ ያለ ፕሮግራም መጠቀም የማይቻል መሆኑን እንገልፃለን።
ማሳሰቢያ:-
👉 የት/ቤቱ ተረኛ ጥበቃዎች ይህን የማስፈፀም ስራ ይሰራሉ።
👉ሜዳ ተከራዮችም የከፈላችሁበትን የባንክ ስሊፕ ተራኛ ጥበቃዎች ሲጠይቁ የማሳየት ግዴታ አለባቸው።
👉 የሜዳ ኪራይ ክፍያ ቅድሚያ በዉሉ መሠረት ይፈፀማል።
👉 ከተራ ቁጥር 1-5 ከተዘረዘሩት ድልድል ውጭ ፍቃድ ሳያገኝ በራሱ በሌላ ቡድን ፕሮግራም ቀን ሜዳውን የሚጠቀም የትምህርት ቤቱ መምህራን:አስተዳደር ሰራተኛ እና ሌላ የውጭ አካል ተጠያቂ ይሆናል።

ትምህርት ቤቱ

Kokebe Tsibah General Secondary School

08 Nov, 02:32


ቀን 29/2/2017 ዓ.ም
  ለመምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ
የሰኞ ህዳር 2/2017 ዓ.ም የማለዳ የእዉቀት ሽግግር አቅራቢ እና የሚቀርበዉን ርዕሰ ጉዳይ ስለማሳወቅ
👉 አቅራቢ:- / መስጦፋ ከድር
👉 ርዕስ:- 21 century core skills in teaching and learning.
👉ሰዓት:- ከጠዓቱ 1:30-2:10 ሰዓት
👉 ቦታ:- በት/ቤቱ ትንሿ አዳራሽ
👌 ሁላችንም በተጠቀሰዉ ቀን እና  ሰዓት በሰዓቱ እንገናኝ::
                            /ቤቱ

Kokebe Tsibah General Secondary School

07 Nov, 03:53


ቀን 28/2/2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለሁሉም ተማሪዎች እና ወላጆች/አሳዳጊዎች
👌 የ2017 ዓ.ም ትኩረታችን :-
1ኛ, የክፍል ውስጥ የመማር ማስተማር ሒደትን እና የምዘና ስርዓታችን ጥራት ያለው እንዲሆን በማድረግ የተማሪዎች ከክፍል ክፍል ዝውውር እና የሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ማሻሻል :
2ኛ,የእንግሊዝኛ እና ሒሳብ ትምህርት ውጤት እንዲሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጂት መስራት:
3, ተከታታይ እና ወጥነት ያለው ስራ በመስራት የተማሪዎችን ስነ-ምግባር ማሻሻል :
በመሆኑም እነዚህን ከላይ የተገለፁ ወሳኝ ግቦችን ለማሳካት ከምንከተላቸው የአሰራር ስልቶች አንዱ ዜሮ የአርፋጂ ፓሊሲ መተግበር ነው። ሁሉም የት/ቤቱ ማህበረሰብ በትብብር በሰራው ስራ በመስከረም እና በጥቅምት ወራት የአርፋጂ ተማሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል። ነገር ግን ዜሮ ማድረግ አልተቻለም።
ስለሆነም ዜሮ አርፋጂ ፓሊሲ ሰኞ ህዳር 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ ስለሚተገበር ማንኛውም ተማሪ እስከ 2:20 ሰዓት ብቻ ወደ /ቤት ገብቶ የሰንደቅ ዓላማ ስነ-ስርዓት አክብሮ 2:30 ሰዓት አንደኛ /ጊዜ ይጀመራል
ማሳሰቢያ:-, ከ2:20-2:27 ሰዓት በሗላ የሚመጣ ተማሪ መታወቂያውን ለዩኒት መሪ መምህራን ሰጥቶ ወደ ክፍል መግባት ይችላል። ከ2:28 ሰዓት ጀምሮ የሚመጣ ተማሪ መታወቂያውም ተይዞ አንድ ክ/ጊዜም ተቀጥቶ 2ኛ ክ/ጊዜ ወደ ክፍል ይገባል።
👉 ለመማር ከተመዘገባችሁ በሗላ ቤተሰብ የመኖሪያ አድራሻ በመቀየሩ ምክንያት ሸኝ አንወስድም ከዚሁ ነው መማር ያለብን ብላችሁ ከርቀት የምትመጡ ተማሪዎች ያስመዘገባችሁን ትክክለኛ ወላጂ/አሳዳጊ ቢሮ ቁጥር 04 ይዞ በመምጣት ልዩ የመግቢያ መታወቂያ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ትምህርት ቤቱ

Kokebe Tsibah General Secondary School

04 Nov, 10:58


ቀን 25/02/2017ዓ.ም
ማስታወቂያ
በ2017ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተግባራዊ የጥናት ና ምርምር  ርዕስ የፀደቀላችሁ የሁሉም የትምህርት ክፍል propozal ሠርታችሁ እስከ ህዳር 5/03/2017ዓ.ም 9:00 ድረስ ቢሮ ቁጥር 03 ገቢ እንድታደርጉ እናሳውቃለን።



ት/ቤቱ

Kokebe Tsibah General Secondary School

04 Nov, 07:44


ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም የእውቀት :የልምድ እና የተሞክሮ ልዉዉጥ መድረክ በአንጋፋ መምህራን አቅራቢነት ተካሂዷል::
👉 የፕሮግራሙ ይዘት እና አቀራረብ የመምህራንን የጋራ ግንዛቤ በማሳደግ የተማሪዎችን ዉጤት ለማሻሻል በሚረዳ መልኩ እተካሄደ ይገኛል

Kokebe Tsibah General Secondary School

02 Nov, 13:23


Good news!
There will be question and answer competition among grade 11 students in English subject.

Participants are:
@ Firdows Yimam
@ Fuad Abrar
@ Amanda Kahsay
@ Firezer Kassahun
@ Abenezer Wendwossen
@ Edlawit Desalegn

The competition is going to be held on Monday at 2:05 local time.

Be member of the English Language Club!
https://t.me/KTGSSELC

Kokebe Tsibah General Secondary School

02 Nov, 10:39


ቅዳሜ ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም ከየካ ፓሊስ መምሪያ እና ከላምበረት እና አካባቢዉ ፓሊስ ጣቢያ ማህበረሰብ አቀፍ ፓሊስ አመራሮች ጋር በመቀናጀት ከወላጆች /አሳዳጊዎች ጋር በሰላማዊ መማር ማስተማር ላይ ያተኮረ ዉይይት አድርገናል
👉 ከህዳር 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች ወደ ት/ቤት የመግቢያ ሰዓት አስከ 2:20 ሰዓት ብቻ እንዲሆን ከ2:20 ሰዓት በሗላ የሚመጣ ተማሪ እስከ 2:30 ሰዓት መታወቂያ ለዩኒት መሪ መምህራን ሰጥቶ መታወቂያዉ ተበስቶ እንደሚመለስ ተማሪዉ ግን ወደ ክፍል መግባት እንደሚችል ቀርቦ የተገኙ ወላጆች/አሳዳጊዎች ሃሳቡን ሙሉ በሙሉ ተቀብለዉ ወስነዋል።
👉 በተጨማሪም የ12ኛ ክፍል የዉጤት ትንተና እና የእንግሊዝኛ እና ሒሳብ ትምህርት የዉጤት ማሻሻያ ስትራቴጂክ ዕቅድ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል።
👌 በዉይይቱ ለተገኛችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች እና ጥሪዉን በአግባቡ ለወላጂ/አሳዳጊ ላደረሳችሁ ተማሪዎች ላቅ ያለ ምስጋና እናቀርባለን

/ቤቱ

Kokebe Tsibah General Secondary School

01 Nov, 14:01


🌟🌟ለ ኮከበ ፅባህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችና ወላጆች 🌟🌟

👉 በ 2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ዉጤት ለማምጣት ከወላጆች ጋር በተነጋገርነው መሰረት የተለያዩ ስራዎች እየሰራን እንገኛል::

👉 እየሰራን ካለነው ስራ አንዱ የቅዳሜ የማጠናከሪያ ትምህርት አንዱ ነው::

👉 ይህንን የማጠናከሪያ ትምህርት ዉጤታማ ለማድረግ ወላጆች ልጆቻችሁን ቅዳሜ ማለትም ነገ 23/02/2017 ዓ.ም እንድትልኩ እናሳስባለን::

👉 ተማሪዎችም ነገ በሰዓት በመገኘት የማጠናከሪያ ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ እንጠይቃለን።
ማሳሰቢያ:- የነገ ቅዳሜ 23/2017 ዓ.ም የወላጆች/አሳዳጊዎች 2:30 ሰዓት ስብሰባ እንደተጠበቀ ነዉ። ተማሪዎች መጥሪያ ማድረሳቸዉን ወላጆች/አሳዳጊዎች ተከታተሉ።


ትምህርት ቤቱ

Kokebe Tsibah General Secondary School

01 Nov, 13:37


ቀን 22/02/2017 ዓ.ም
ለመምህራን እና አስተዳደር ሠራተኞች
የእዉቀት :የልምድ እና የተሞክሮ ልዉዉጥ ፕሮግራም ስለማሳወቅ
👉ሰኞ ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም የሚደረገዉ ፕሮግራም አቅራቢዎች
1,መ/ር በላይነህ አሰፋ
2,መ/ር ዮሗንስ ያየህራድ
3,መ/ር አለማየሁ አሸብር
4,መ/ርት አስቴር አባይነህ
5,መ/ር አለማየሁ ወ/ስላሴ
👉ርዕስ:- How to creat table of specification for an exam?
ሰዓት:-ከጠዋቱ 1:30-2:10 ሰዓት
👌ከዚህ በፊት ባንድ አቅራቢ ይቀርብ የነበረን የአቀራረብ ስልት በቀጣይ በአንድ ርዕሠ ጉዳይ 5 አንጋፋ መምህራን ይናገራሉ።
በሰዓቱ በመገኘት የፕሮግራሙ ተካፋይ እንሁን።
/ቤቱ

Kokebe Tsibah General Secondary School

30 Oct, 17:47


Kokebe Tsibah General Secondary School pinned «ለትምህርት ቤታችን ተማሪዎች በነገው እለት ማለትም 21/02/2017 ዓ. ም 5 ሚሊዮን ኮደር ተሳታፊዎች በሚሳተፉት የ5 ሚሊዮን ኮደሮች ላይ ተሳታፊ የሆናችሁ የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች ነገ ከ 2:30 - 3:30 የቪዲዮ ኮንፍራንስ ስላለ ተሳታፊ እንድትሆኑ ትምህርት ቤታችን ጥሪ ያቀርብላችሁአል:: ኮንፍራንሱ በ አይ ቲ ላብ ይከናወናል:: ት/ቤቱ»

Kokebe Tsibah General Secondary School

30 Oct, 17:45


ለትምህርት ቤታችን ተማሪዎች

በነገው እለት ማለትም 21/02/2017 ዓ. ም 5 ሚሊዮን ኮደር ተሳታፊዎች በሚሳተፉት የ5 ሚሊዮን ኮደሮች ላይ ተሳታፊ የሆናችሁ የትምህርት ቤታችን ተማሪዎች ነገ ከ 2:30 - 3:30 የቪዲዮ ኮንፍራንስ ስላለ ተሳታፊ እንድትሆኑ ትምህርት ቤታችን ጥሪ ያቀርብላችሁአል:: ኮንፍራንሱ በ አይ ቲ ላብ ይከናወናል::

ት/ቤቱ

Kokebe Tsibah General Secondary School

30 Oct, 17:35


ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ

የብሔራዊ ፈተና ዉጤት ሰርተፊኬት ስለመጣ ከነገ 9:00 ጀምሮ መዉሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን :: ከተጠቀሰዉ ሰዓት ዉጭ የሚመጣን የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን::

👉👉
t.me/kokebetsibahexam 👈👈

ት/ቤቱ

Kokebe Tsibah General Secondary School

30 Oct, 10:23


👉👉👉የተማሪዎች መብት👈👈👈
ተማሪዎች የሚከተለት መብቶች ይኖራቸዋል፡-

1. የመማር፣ ጠይቆ የመረዳትና የማወቅ፤
2. ተማሪዎች ከማንኛውም ዓይነት የአካልና ሥነልቦና ጥቃቶች የመጠበቅ፤
3. በትምህርት ቤቱ የትምህርት ግብዓቶች የመጠቀም ወይም አገልግሎት የማግኘት፤
4. የትምህርት ውጤትና የምስክር ወረቀት በወቅቱ የማግኘት፤
5. ስርአትና ደህንነቱ በተጠበቀ ክፍል እና ትምህርት ቤት የመማር፤
6. ሃሳባቸውን የመግለፅና የመደመጥ መብት፤
7. የግል ሚስጢራዊ ጉዲዮች የመጠበቅ፤
8. ፆታን መሰረት ካደረገ ጥቃት የመጠበቅ፤
9. የትምህርት ቤቱን ደንብና መመሪያ የማወቅና የማግኘት፤
10.ከመምህራን ድጋፍና ና እርዳታ የማግኘት፤
11የሚደርስባቸዉን በደልና ቅሬታ በየደረጃዉ ላለ የትምህርት ቤቱ አካላት የማቅረብ፤
12. የመምህራን የማስተማር ክህልት በሚዛናዊነት የመገምገም፤ አስተያየት ሲጠየቁ የመስጠት፤
13.ከመማሪያ ክፍል ውጭ የሚከናወኑ የተጓዳኝ ትምህርት ፕሮግራሞች ላይ የመሳተፈ፤
14. ለተማሪዎች ከሚሰጠው ልዩ ልዩ የኃላፊነት ቦታዎች የመምረጥና የመመረጥ፤
15.ከት/ቤት ወይም በቅርብ ከሚገኝ የጤና ማዕከል የመጀመሪያ የጤና ዕርዳታ የማገኘት፣
16. ልዩ ልዩ ፍላጎታቸውን መሰረት ያደረገ አገልግሎት የማግኘት እና ከጥቃት የመጠበቅ መብት፣
17.በት/ቤት የዕቅድ ዝግጅትና የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ በተወካዮቻቸው አማካኝነት የመሳተፍ መብት አላቸው፡፡

ት/ቤ

Kokebe Tsibah General Secondary School

29 Oct, 16:40


ዛሬ ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም ለክፍል ሃላፊ መምህራን በሚኖራቸዉ ተግባር እና ሃላፊነት ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥቷል::
👉 የክፍል ሃላፊ መምህራን በክፍል ሃላፊነት ቆጥረዉ የተረከቧቸዉን ተማሪዎች በአግባቡ በማወቅ አስፈላጊዉን ክትትል:ድጋፍ እና ቁጥጥር ካደረጉ የተማሪዎች ዉጤት እና ስነ-ምግባር በላቀ ደረጃ ይሻሻላል::
👉 ዓላማችን በክፍል ዉስጥ የክፍል ሃላፊ መምህራን የአመራርነት ሚና/assuring teacher leadership in the class room/ እንዲጫዎቱ ማድረግ ነዉ::
👉 ይህ ከሆነ የአርፋጂ ተማሪ ቁጥር ዜሮ ይሆናል: ለቤተሰብ/አሳዳጊ /ቤት ሄድኩ ብሎ የሚቀር/የሚፎርፍ/ ተማሪ አይኖርም: አርፍዶ በር ሳይዘጋበት ተዘጋ ብሎ መታወቂያ እንዳይበሳበት /ቤት ሳይገባ ሚመለስ ተማሪ አይኖርም: ያለክፍሉ ሌላ ክፍል የሚገኝ ተማሪ አይኖርም : የት/ቤት እና የሌላ ተማሪ ንብረት የሚነካ/የሚወስድ ተማሪ አይኖርም: ተማሪዉ የትምህርት ግብዓትን አሟልቶ ይይዛል :ከቤተሰብ/አሳዳጊ ጋር የሚኖር ግንኙነት ይጠናከራል......::
👌 በመሆኑም በትምህርት ቤት ዉስጥ ጤናማ የመማር ማስተማር ሒደት እንዲኖር በማድረግ ሒደት የክፍል ሃላፊ ሚና/ድርሻ የማይተካ ነዉ::

Kokebe Tsibah General Secondary School

25 Oct, 13:25


🌟🌟ለ ኮከበ ፅባህ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችና ወላጆች 🌟🌟

👉 በ 2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተሻለ ዉጤት ለማምጣት ከወላጆች ጋር በተነጋገርነው መሰረት የተለያዩ ስራዎች እየሰራን እንገኛል::

👉 እየሰራን ካለነው ስራ አንዱ የቅዳሜ የማጠናከሪያ ትምህርት አንዱ ነው::

👉 ይህንን የማጠናከሪያ ትምህርት ዉጤታማ ለማድረግ ወላጆች ልጆቻችሁን ቅዳሜ ማለትም ነገ 16/02/2017 ዓ.ም እንድትልኩ እናሳስባለን::

👉 ተማሪዎችም ነገ በሰዓት በመገኘት የማጠናከሪያ ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ እንጠይቃለን

ትምህርት ቤቱ

Kokebe Tsibah General Secondary School

24 Oct, 15:06


ቀን 14/2/2017 ዓ.ም
ለመምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ሠራተኞች በሙሉ
የሰኞ ጥቅምት 18//2017 ዓ.ም የእዉቀት ሽግግር አቅራቢ እና የሚቀርበዉን ርዕሰ ጉዳይ ስለማሳወቅ
👉 አቅራቢ:- / ካሳሁን ደምሴ
👉 ርዕስ:- አቴንዳንስ ፓሊሲ
👉ሰዓት:- ከጠዓቱ 1:30-2:10 ሰዓት
👉 ቦታ:- በት/ቤቱ ትንሿ አዳራሽ
👌 ሁላችንም በተጠቀሰዉ ቀን እና ሰዓት በሰዓቱ እንገናኝ::
/ቤቱ

Kokebe Tsibah General Secondary School

24 Oct, 01:48


"ሥነ-ምግባር!"🙏👇
ከምንም በላይ ለሠው ልጅ ሥነ ምግባር ቁልፍ ጉዳይ ነው።
👉ሥነ-ምግባር ምንድን ነው?
ሥነ-ምግባር ማለት የሁለት ቃላት ጥምር ውጤት ነው፡፡ “ሥነ” የሚለው
ቃል “ሠነየ” ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን፤ ያማረ፣ መልካም የሆነ፣ ደስ የሚያሰኝ፣ በለጠ፣ ተሻለ ማለት ነው፡፡ ምግባር የሚለው ደግሞ “ገብረ”
ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሥራ፣ ፈጠራ፣ ድርጊት፣ ክንውን ማለት ነው፡፡
👉 በአጠቃላይ ሥነ-ምግባር ማለት መልካም፣ የተገነባ፣ የተፈቀደ፣ የተወደደ፣ ያማረ ሥራ ወይም ድርጊትን የሚያጠና የፍልስፍና ዘርፍ ሲሆን አንድን ነገር ትክክል ነው ወይም አይደለም ብለን እንድንጠራ የሚያደርገን እሴት ነው፡፡

👉 በዚህ መልኩ ጠለቅ ብሎ የተነተነው ሥነ-ምግባርም በህይወታችን ዋጋ ልንሰጣቸው ከሚገቡን ነገሮች አንዱ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ እያንዳንዳችን የምንፈፅመው ተግባር ደግ ወይም መጥፎ መሆኑ የሚታወቀው በውጤቱ ነው፡፡ ውጤቱም ያማረ እና የተዋበ የሚሆነው በመልካም ሥነ-ምግባር ላይ ተመርኩዞ ከተሠራ ብቻ ነው፡፡ ይሄንን ውጤቱ ያማረ ተግባር ለመፈፀም ደግሞ መልካም የሆነ የሙያ ሥነ-ምግባር ያስፈልጋል፡፡
ሆኖም ሁሉም ዜጋ ለሚሰራው ስራ የስነ-ምግባር መርሆችንና እሴቶችን
በመከተል ሀገራዊ፣ ቤተሰባዊና ግላዊ ግዴታዎቹን በመልካም ሥነ-ምግባር
ለሀገር ልማትና ዕድገት አስተዋፆውን ማበርከት ይገባል፡፡

👏 የሙያ ስነ-ስነምግባር!
👉 በመጀመሪያ ስለሙያ ሥነ-ምግባር ከመነጋገራችን በፊት ሙያ ምንድነው?
የሚለውን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ ሙያ በስልጠና የሚገኝ ንድፈ ሀሳባዊ እውቀት ችሎታና ክህሎት መሰረት ያደረገ የዳበረ ልምድና የጠለቀ ግንዛቤ የሚጠይቅና ለህብረተሰቡ ተጨባጭ ጠቀሜታ የሚሰጥ ስራ ነው፡፡
ብዙዎች ሙያ አራት መሰረታዊ ባህርያት እንዳሉት ይገልጻሉ፡፡ እነርሱም፡-
ልዩ የሆነ እውቀት የሚጠይቅ፣
ወደሙያው ለመግባት የተወሰነ የመግቢያ መስፈርት ያለው፣
ማህበራዊ እሴት ያለውና ለሌሎች ጥቅም የሚሰራ ወይም አገልግሎት
የሚሰጥ፣ ስራውን በሚመራና በሚቆጣጠር የሥነ-ምግባር ደንብ የሚመራ መሆኑ ናቸው፡፡
👉 የሙያ ሥነ-ምግባር ምንነት የሚል ፅሑፍ ላይ እንደተገለፀው ሙያተኛ
በተወሰነ የስራ መስክ ላይ በከፍተኛ ስልጠና ወይም ትምህርት የተገኘ ልዩ
እውቀት፣ ክህሎትና ልምድ ያላቸው እውቀታቸውንና ልምዳቸውን ለህብረተሰቡ ጠቀሜታ ለማዋል፣ ሌሎችን ለመምራትና ለማሰልጠን እምቅ አቅም ያላቸው ሰዎች መለያ ነው በማለት ያብራራል፡፡
ሆኖም ህብረተሰቡ በተለያየ ደረጃ የሚገጥሙትን ችግሮች ለመፍታት በየዘርፉ የተለየ እውቀትና ችሎታ ያላቸውን ሙያተኞች ይሻል፡፡ ይህ እውቀት በአግባቡ ከተጠቀሙበት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን፣ በአግባቡ ካልተጠቀሙበት ደግሞ አገርህንና አንተነትህን ባጭሩ ይቀጫልና አዕምሮህ ለመልካም ነገር እና ለሀገር ግንባታ ተጠቀምበት!!

መልካም ቀን
WoldeyohWoldeyohanis Worku Gami

Kokebe Tsibah General Secondary School

22 Oct, 16:59


ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም ከ12ኛ ክፍል የደረጃ ተማሪዎች ጋር በመማር ማስተማሩ ሂደት ዙሪያ ዉይይት አድርገናል::
👉 ተማሪዎች መሻሻል አለባቸዉ ብለዉ ያነሷቸዉን ጥያቄዎች ይዘን በአፋጣኝ ለማሻሻል የምንሰራ ይሆናል::
ማሳሰቢያ:- ከነገ ጥቅምት 13/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ት/ቤት የመግበያ ሰዓት 2:25 ሰዓት ይሆናል:: ከተጠቀሰዉ ሰዓት ዉጭ የሚመጣ ተማሪ መታወቂያዉ ተበስቶ እና አንድ ክፍለ ጊዜ ተቀጥቶ 2ኛ ክ/ጊዜ ወደ ክፍል የሚገባ ይሆናል::
/ቤቱ

Kokebe Tsibah General Secondary School

21 Oct, 08:23


ዛሬ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም የጠዋት የእዉቀት:የልምድ እና የተሞክሮ ልዉዉጥ መድረክ አካሂደናል::
ዛሬ የተካሄደዉን ጨምሮ የ5ቱ ቀናት አካሄዳችን ምን እንደሚመስል ተሳታፊዎች አስተያየት እንዲሰጡ ተጠይቀዉ ተጠናክሮ ይቀጥል ጥሩ ነዉ በሚል ሃሳብ ሰጥተዋል::
👉 በቀጣይ ቀደም ብሎ ማን እና በምን ርዕሠ ጉዳይ እንደሚያቀርብ ይታወቅ በሚል የተነሳዉ እና ሌሎችም መሻሻል አለባቸዉ የተባሉትን አሻሽለን በቀጣይ ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም በሚኖረን ፕሮግራም ተግባራዊ ይደረጋል::
/ቤቱ

3,370

subscribers

2,187

photos

15

videos