ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ @hu_main_campus_gibi_gubae Channel on Telegram

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

@hu_main_campus_gibi_gubae


በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክርስቲያን ማህበረ ቅዱሳን ሀዋሳ ማዕከል የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ግቢ ጉባኤ መደበኛ ቻናል
በዚህ ቻናል
👉 ትምህርታዊ ጽሑፎች
👉 የግቢ ጉባኤ መልዕክት
👉 የክፍላት ማስታወቂያ ይተላለፍበታል።
ማንኛውንም ሀሳብ አስተያየት ከታች ባለው አድራሻ ይላኩልን
👇👇👇
@ZHawassa_GGbot

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ (Amharic)

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ግቢ ጉባኤ መደበኛ ቻናል ለክርስቲያን ማህበረ ቅዱሳን ሀዋሳ ማዕከል እና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የግቢ ጉባኤ ፣ እና ሱስ ስለሚሉ በሚከተለው ቻናል፡፡ በቻናል ይተላለፋሉ በምግባሩ ይጠቀሙ። እስከሚለያየም ሀሳብ ከሚከተለው አድራሻ እና ትልቁ መረጃ ይላኩልን። ለግቢ ጉባኤ መልዕክት እና ስለ ግቢ ጉባኤ ከዚህ ቻናል የሰራውን መረጃን በማስመዝገብ እና በቀጣይ ትክክለኛ ስብስብ በመረጃ ጊዜ አድራሻውን ከዚህ ማስይበት እንዴት እንችላለን፡፡

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

25 Jan, 08:38


  ታላቅ የንግስ በዓል ጥሪ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

24 Jan, 06:04


“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ኹሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።”
  ፊልጵስዩስ 4፥6

          ሳምንታዊው የአንድነት ጸሎት ዛሬ አርብ ሰርክ ሰዓት (11:45) ላይ ስለሚቀጥል ሁላችንም ተቀሳቅሰን በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን ።

👉ውዳሴ ማርያም
👉መዝሙረ ዳዊት
👉መሐረነ አብ ጸሎት
👉ስንክሳር
📍ቦታ ማርያም ቤተክርስቲያን አዳራሽ ላይ።

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

23 Jan, 18:14


የግቢ - ጉባኤያችን የመዝሙር ክፍል ከማዕከል ጋር በመሆን የጥምቀት በዓልን  እንደዚህ ደስ በሚል መልኩ አሳልፈዋል።

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

21 Jan, 10:07


ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ pinned «"ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።"      መዝሙር 18፥35 የባች ኮርስ መርሐግብር          👉 ዛሬ በ13/5/17ዓ.ም የአንደኛ ዓመት የሜን ተማሪዎች (fresh) የባች ኮርስ የትምህርት መርሐ-ግብር ስለሚቀጥል በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ በሰዓቱ እንድትገኙ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። 👉የቴክኖ ተማሪዎች ኮርሱን…»

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

21 Jan, 05:23


"ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።"
     መዝሙር 18፥35

የባች ኮርስ መርሐግብር

         👉 ዛሬ በ13/5/17ዓ.ም የአንደኛ ዓመት የሜን ተማሪዎች (fresh) የባች ኮርስ የትምህርት መርሐ-ግብር ስለሚቀጥል በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ በሰዓቱ እንድትገኙ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

👉የቴክኖ ተማሪዎች ኮርሱን ስለጨረሳችሁ ለዛሬ አይኖራችሁም የፈተና ቀን እስኪነገር ድረስ የተማራችሁትን እያነበባችሁ እንድትጠብቁ።

⛪️ቦታ፦
👉 ቅድስትሥላሴ ቤተክርስቲያን


ሰዓት፦11:45

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

20 Jan, 16:00


ዋራ እየሱስ ቤተክርስቲያን

የጥምቀትን በዓል የካህናት እና የምዕመን እጥረት ካለበት ቤተክርስቲያን አንዱ በሆነው በዋራ እየሱስ ቤተክርስቲያን እንደ ግቢ - ጉባኤ እንደዚህ ደስ በሚል ሁኔታ አብረናቸው አሳልፈናል።

ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይመስገን።

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

20 Jan, 06:09


“በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥”
         ራእይ 12፥7

       እንኳን ለሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

       👉ሁልጊዜም በየወሩ በግቢ ጉባኤአችን የሚዘጋጀው ወርሃዊ የቅዱስ ሚካኤል የጸበለ ጸዲቅ መርሐ-ግብር በዛሬዋ ዕለት ማለትም በ12/05/17ዓ.ም ስላለ ሁላችንም ከእኅት ወንድሞቻችን ጋር በመሆን በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
           (ትልቁ አዳራሽ)
ሰዓት፦11:45

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

14 Jan, 17:41


“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ኹሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።”
  ፊልጵስዩስ 4፥6

          ወርኃዊው የ3 ቀን የአንድነት ጸሎታችን ነገ ረቡዕ ጠዋት 12:00 ላይ ስለሚጀምር ሁላችንም ተቀሳቅሰን በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን ።
📍ቦታ ማርያም ቤተክርስቲያን አዳራሽ ላይ።

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

14 Jan, 07:01


"ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።"
     መዝሙር 18፥35

የባች ኮርስ መርሐግብር

         👉 ዛሬ በ6/5/17ዓ.ም የአንደኛ ዓመት የቴክኖ ተማሪዎች (fresh) የባች ኮርስ የትምህርት መርሐ-ግብር ስለሚቀጥል በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ በሰዓቱ እንድትገኙ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

የ1ኛ አመት የሜን ተማሪወች ለዚህ ሳምንት ሀሙስ ነው የኮርስ መርሐግብር

⛪️ቦታ፦
👉ለቴክኖ ተማሪዎች ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን


ሰዓት፦11:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

14 Jan, 05:44


ጥር ፮ /6/

በዚች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጸመ።

የከበረ ወንጌል ስምንተኛው ቀን በተፈጸመ ጊዜም ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት  ያ ባለሙያም ሕፃኑን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በእናቱ በንጽሕት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ አየው እንድገርዘው ሕፃኑን በጥንቃቄ ያዙት አላቸው።

ሕፃን ጌታ ኢየሱስም ባለሙያውን ደሜ ሳይፈስ ትገርዘኝ ዘንድ ትችላለህን በዕለተ ዓርብ ካልሆነ በቀር ደሜ አይፈስምና አለው።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ያ ባለሙያ በሰማ ጊዜ አደነቀ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሥቶ ከሕፃኑ ጌታ እግር በታች ሰገደ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጆቹ ላይ ቀልጠው እንደ ውኃ ሆኑ የከበረች ድንግል እመቤታችንን ማርያምን ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ የማሕፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው ይህ ልጅሽ ስለርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው አላት።

ሕፃኑ ኢየሱስም እኔ ነኝ ትገዝረኛለህን ወይስ ተውከኝ ወይም ያባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ እኔ ላድርግ አለው። ያም ባለሙያ የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው አለው ሕፃን ጌታችንም አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብ የሕዝቡ ሁሉ አባቶች የሆኑ ናቸው ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው ባለሙያውም እኔ ከአንተ ጋር እናገር ዘንድ አልችልም በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና አለው።

በዚያንም ጊዜ ሕፃኑ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ አባት ሆይ ለአብርሃም ለይስሐቅ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ አለ። ያን ጊዜ ያለ ሰው እጅ በሕፃኑ ሥጋ ላይ ግዝረት ተገለጠች።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

13 Jan, 15:50


የጥምቀት መዝሙር ጥናት

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

13 Jan, 13:43


1386  አዳዲስ አማንያን የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን አገኙ።

ጥር ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም

በደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ዳሰነች ወረዳ 1386  አዳዲስ አማንያን በማኅበረ ቅዱሳን የሐዋርያዊ ተልእኮ አስተባባሪነት የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን አግኝተዋል።

ተጠማቂያኑ ባለፉት ወራት መሠረታዊ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መሠረተ እምነት ሲማሩ  ከነበሩ ወገኖች መካከል  ሲሆኑ ሥርዓተ ጥምቀታቸው በኦሞ ብሔረ ብፁዓን አቡነ ዜና ማርቆስ ወአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ  አንድነት ገዳም ዛሬ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ተፈጽሟል።

በዕለቱ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተገኝተው ሥርዓቱን ፈጽመዋል።

ቅድመ ጥምቀት ሐዋርያዊ ተልእኮ ማስፋፊያ እና ሥርዓተ ጥምቀት ማስፈጸሚያ ተግባራት ሙሉ ወጪ በማኅበረ ቅዱሳን ተሸፍኗዋል፡፡

የማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት በተለያዩ አካባቢዎች  ባለፉት ወራት ባከናወናቸው የሐዋርያዊ ተልእኮ ማስፋፊያ ተግባራት 8547 አዳዲስ አማንያን ተምረው አምነው በመጠመቅ የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን እንዲያገኙ  ማድረጉ ተገልጿል፡፡

ይህንን ሐዋርያዊ አገልግሎት ለመፈጸም የሚመለከተው ሁሉ በመሳተፍ ኦርቶዶክሳዊ ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

13 Jan, 11:32


የጥምቀት መዝሙር ጥናት

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

13 Jan, 11:01


የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ተዘጋጅቶ የነበረውን የእጣ መርሐግብር እጣ ለወጣላቸው ተማሪወች አድርሰናል።

እንኳን ደስ አላችሁ በድጋሚ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

12 Jan, 14:43


የሲኒየር ተማሪወች ፈተና እስኪያልቅ ድረስ የዝክረ ሰንበት የአንድነት መርሐግብር አይኖረንም።
👉አንደኛ አመቶች የባች ኮርስ መርሐግብር የሚቀጥል ይሆናል
👉ለዚህ ሳምንት የአንደኛ አመት ባች ኮርስ
ለቴክኖ ተማሪወች ማክሰኞ ሰርክ ሰዓት በማርያም ቤተክርስቲያን
ለሜን ተማሪወች ሀሙስ ሰርክ ሰዓት በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን የሚካሄድ ይሆናል

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

12 Jan, 12:17


በማይነገር ፍቅሩ ከዙፋኑ ወርዶ የዘላለም ልጅነትን የሰጠን አምላከ አበው በፈተናችሁ ይርዳችሁ በሁሉ ይከተላችሁ።

መልካም ፈተና!!

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

12 Jan, 08:48


ጥር ፬ /4/

የተመሰገነ ዮሐንስም ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ሰዓት እንደ ቀረበ በአወቀ ጊዜ ሕዝቡን ጠራቸው ጸሎትንም ጸለየና ኅብስቱን ባርኮ ቆረሰ ይህም የጌታችን ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ባረካቸው አጽናናቸውም ።

ከዚህም በኋላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ ። ከኤፌሶንም ከተማ ውጭ ወጣ ጕድጓድ እንዲቆፍሩም አዘዘ ከውስጥዋም ወርዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ ከአንድ የበፍታ ቀሚስ በቀር አላስቀረም ። እጆቹንም አንሥቶ ጸለየና ወደ ከተማ ይመለሱ ዘንድ አሰናበታቸው በክርስቶስም ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝቡ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዛቸው በጎ ሥራዎችንም ይሠሩ ዘንድ ጌታችን ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፈለው ዘንድ አለውና ።

ይህንንም በተናገረ ጊዜ አለቀሱ እጆቹንና እግሮቹን ስመው በጒድጓዱ ውስጥ ትተውት ወደ መንገድ ተመለሱና የሆነውን ሁሉ ለሰዎች ነገሩዋቸው ሁሉም ደንግጠው መጡ ግን ልብስና ጫማ እንጂ መቃብሩን አላገኙም እጅግም አደነቁ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን በዚህ በጎ ዕረፍት ያሳረፈው እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

12 Jan, 03:01


የጥምቀት መዝሙር ጥናት

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

11 Jan, 18:03


የጥምቀት መዝሙር ጥናት

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

11 Jan, 15:28


ከነገው የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ዓመታዊ ክብረ በዓል ላይ ማስተባበር የምትፈልጉ ተማሪወች @yitbba24 በመመዝገብ በዕለቱ በማስተባበር የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን።

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

11 Jan, 14:46


የጥምቀት መዝሙር ጥናት

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

10 Jan, 12:16


1ኛ አመቶች የባች ኮርስ ትምህርት
2ተኛ አመቶች የባች የኮርስ ፈተና

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

10 Jan, 05:41


"ለምኑ ይሰጣችኹማል ፤ ፈልጉ ታገኙማላችኹ ። መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችኹማል። የሚለምነው ኹሉ ይቀበላልና የሚፈልገውም ያገኛል መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።"
ማቴ7፥7

          ሳምንታዊው የአንድነት የጸሎት መርሐ-ግብር ዛሬ አርብ በ02/05/17ዓ.ም ስለሚቀጥል ሁላችንም ላልሰሙት እኅት እና ወንድሞቻችን በማስታወስ በሕብረት በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

👉ውዳሴ ማርያም
👉 መዝሙረ ዳዊት
👉መሐረነ አብ
👉ስንክሳር እና ተአምረ ማርያም

⛪️ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
ሰርክ ሰዓት (11:45) ጀምሮ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

09 Jan, 17:35


በእናት ግቢ ጉባኤ የተዘጋጀው የ ገና በዓል መርኃ ግብር በዚ መልኩ ተከብሮ አልፍዋል።

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

08 Jan, 10:09


እጣ የወጣላቸው ተማሪወች

1 ቢጫ 34  ኢየሩሳሌም090995..82 (መፅሐፍ ቅዱስ)
2 ቢጫ 38  ወልደሚካኤል 092387..25 (አሐቲ ድንግል መፅሐፍ )
3 ቀይ 92    093086..18 (ስዕለ አድኅኖ)
4 ሰማያዊ 99  መሠረት 093972..58 (ቲሸርት )

👉0923990108(derba)
0703044969

በዚህ ስልክ ደውላችሁ መውሰድ ትችላላችሁ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

07 Jan, 07:13


Jaallatamtoota maatiiwwaan Waaqayyo ijoollee Dubree Maariyaam baga guyyaa yaadannoo dhalachuu Gooftaa keenya, Fayyisaa keenya Iyyesuus Kiristoosiin nagaan isin ga'e.
Ayyaanichi kan nagaa, gammachuu, eebbaa, jaalalaa, fi kan milkii isiniif hata'u.
👉Sahatii 8:00 irraa kaase sagantaan waan jiruuf mana amantaa qulqulleetti sillaseetti irratti argamaa.
Faaruu
Walaloo fi
Barnoota afaan lamaan waan jiruuf.
AYYAANA GAARII !!!!

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

07 Jan, 07:08


ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና፡ እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። ማቴ 2÷ 1 -2

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

የልደት በዓል መርኃግብራችን ዛሬ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች እና ልዩ ልዩ መርሐግብራት ይካሄዳል።

በዕለቱም
👉ወረብ
👉ትምህርተ ወንጌል
👉መዝሙር
👉ግጥም
👉ቅኔ
👉የኪነ ጥበብ ስራዎች
👉መንፈሳዊ ጨዋታ
👉የአንድነት ዝማሬ
👉 የእራት መርሐግብር ይኖረናል

📅ቀን 29/4/2017
🕑ሰዓት 8:00
📍ቦታ - ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

07 Jan, 05:50


✨️️️️️️✨️️️️️️✨️️️️️️ 👑👑👑✨️️️️️️✨️️️️️️✨️️️️️️ 👑👑👑✨️️️️️️✨️️️️️️✨️️️️️️

እንኳን ለክብር ባለቤት ለአምላካችን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ️️️️ለብርሃነ ልደቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። ✨️️️️️️✨️️️️️️✨️️️️️️
ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ
✨️️️️️️✨️️️️️️✨️️️️️️ 👑👑👑✨️️️️️️✨️️️️️️✨️️️️️️ 👑👑👑✨️️️️️️✨️️️️️️✨️️️️️️

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

07 Jan, 05:43


  “ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
  — ሉቃስ 2፥11

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ  በሰላም አደረሳችሁ
ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

06 Jan, 09:01


“ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።”
— ማቴዎስ 2፥1-2

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የአደራ ልጆች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርሰቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

የጌታችን ልደት በአንድነት ለማክበር ትኬት የገዛን እኅት ወንድሞች ዛሬ በ28/04/17 ዓ.ም ከእራት በኋላ ከ11:30-12:00 ሰዓት ድረስ ሁላችንም ዋናው ግቢ(main campus) በር ላይ ተሰብስበን እየዘመርን በአንድ ላይ ወደ ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ስለምንሄድ ሁላችንም ሳናረፍድ በቦታው እንድንገኝ ይሁን።

👉የአዳር መርሐ-ግብሩ ቅድስት ሥላሴ ነው።
👉 ሥርዓተ ማህሌት መሳተፍ የምንችል እነሳተፋለን የማንችል ደግሞ በስራ እኅት ወንዶሞቻችንን እናግዛለን።
👉ሌሊት 9:00 ሰዓት (ከቅዳሴ በኋላ)በትልቁ አዳራሽ ተማሪዎችን የማስፈሰክ መርሐ-ግብሩ ይጀምራል።

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

05 Jan, 23:01


የልደት በዓል ትኬት ያልገዛን ልጆች እስከ ነገ 6:00 ሰዓት ድረስ ደውላችሁ መቁረጥ ትችላላችሁ ።
👉ትኬት የመቁረጥ አቅም የለለን ልጆች @aamkbf ላይ እንመዝገብ ።
👉የልደት በዓል ሙሉ መርሐግብር ነገ ስለምንለቅ በዚሁ ተከታተሉን።
📌የትኬት ዋጋ 150 ብር ነው

ለበለጠ መረጃ
አብርሐም 0946146377
ኤልቤቴል     0920865903
ባምላክ 0901338863

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

05 Jan, 16:47


ኑ ልደትን ከባለ ልደቱ ጋር እናክብር
2 ቀን ቀረ
እንደሚታወቀው እናት ግቢ- ጉባኤያች ሁልጊዜም የገናን ፆም ታስፈስከናለች።

👉ትኬት ያልገዛን ተማሪወች ትኬት መሸጥ የሚያልቀው ዛሬ  ስለሆነ ደውለን እንድንቆርጥ ይሁን ።
👉የትኬት ብር የለለን ተማሪወች ካለ @aamkbf ላይ ስም,ዲፓርትመንት እና ስልክ ቁጥር በመላክ እንመዝገብ።
👉በዓልን ከቤተሰቦቻችሁ ሂዳችሁ የምታሳልፉ የቻላችሁትን ያህል ለግቢ - ጉባኤ መስጠት ትችላላችሁ።

📌የትኬት ዋጋ 150 ብር ነው

ለበለጠ መረጃ
ዲ/ን አብርሐም 0984493404
ኤልቤቴል     0920865903
ይትባረክ      0965310936

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

04 Jan, 05:31


ኑ ልደትን ከባለ ልደቱ ጋር እናክብር

እንደሚታወቀው እናት ግቢ- ጉባኤያች ሁልጊዜም የገናን ፆም ታስፈስከናለች።

👉ትኬት ያልገዛን ተማሪወች ትኬት መሸጥ የሚያልቀው ዛሬ ስለሆነ ደውለን እንድንቆርጥ ይሁን ።
👉የትኬት ብር የለለን ተማሪወች ካለን @aamklb ላይ ስም,ዲፓርትመንት እና ስልክ ቁጥር በመላክ እንመዝገብ።
👉በዓልን ከቤተሰቦቻችሁ ሂዳችሁ የምታሳልፉ የቻላችሁትን ያህል ለግቢ - ጉባኤ መስጠት ትችላላችሁ።

📌የትኬት ዋጋ 150 ብር ነው

ለበለጠ መረጃ
ዲ/ን አብርሐም 0984493404
ኤልቤቴል 0920865903
ይትባረክ 0965310936

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

03 Jan, 16:03


“ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥”
— ማቴዎስ 25፥35

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የአስራት የአደራ ልጆች እንደምን ሰነበታቹ? አሜን የእግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነና ከፍ ከፍ ያለ ይሁን።

እንደሚታወቀው በግቢ ጉባኤአችን በየዓመቱ በዓላትን ምክንያት በማድረግ የተቸገሩ ወገኖቻችንን እናስባለን።
👉ስለዚህም ነገ በ26/04/2017ዓ.ም ለነድያንና ማረሚያ ቤት ላሉ እህት ወንድሞቻችንን ለፆም ማስፈሰክያ የሚውል ብርና ቁሳቁሶች ዲያስፖራ ሰፈር ከሚኖሩ ምዕመናን እየጠየቅን ስለምንሰበስብ ሁላችሁም የበረከቱ ተሳታፊ ትሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን

የምንገናኝበት ቦታ: ሰዓሊተ ምህረት ማርያም ቤ/ክ በር ላይ
ሰዓት: ጠዋት2:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

03 Jan, 06:46


ኑ ልደትን ከባለ ልደቱ ጋር እናክብር

እንደሚታወቀው እናት ግቢ- ጉባኤያች ሁልጊዜም የገናን ፆም ታስፈስከናለች።

👉ትኬት ያልገዛን ተማሪወች ትኬት መሸጥ የሚያልቀው ዛሬ ስለሆነ ደውለን እንድንቆርጥ ይሁን ።
👉የትኬት ብር የለለን ተማሪወች ካለን @aamklb ላይ ስም,ዲፓርትመንት እና ስልክ ቁጥር በመላክ እንመዝገብ።
👉በዓልን ከቤተሰቦቻችሁ ሂዳችሁ የምታሳልፉ የቻላችሁትን ያህል ለግቢ - ጉባኤ መስጠት ትችላላችሁ።

📌የትኬት ዋጋ 150 ብር ነው

ለበለጠ መረጃ
ዲ/ን አብርሐም 0984493404
ኤልቤቴል 0920865903
ይትባረክ 0965310936

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

03 Jan, 04:54


"ለምኑ ይሰጣችኹማል ፤ ፈልጉ ታገኙማላችኹ ። መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችኹማል። የሚለምነው ኹሉ ይቀበላልና የሚፈልገውም ያገኛል መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።"
ማቴ7፥7

          ሳምንታዊው የአንድነት የጸሎት መርሐ-ግብር ዛሬ አርብ በ25/04/17ዓ.ም ስለሚቀጥል ሁላችንም ላልሰሙት እኅት እና ወንድሞቻችን በማስታወስ በሕብረት በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

👉ውዳሴ ማርያም
👉 መዝሙረ ዳዊት
👉መሐረነ አብ
👉ስንክሳር እና ተአምረ ማርያም

⛪️ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
ሰርክ ሰዓት (11:45) ጀምሮ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

02 Jan, 09:06


ኑ ልደትን ከባለ ልደቱ ጋር እናክብር

እንደሚታወቀው እናት ግቢ- ጉባኤያች ሁልጊዜም የገናን ፆም ታስፈስከናለች።

ትኬት ያልገዛን ተማሪወች ትኬቱ ሳያልቅ በክላስ አስተባባሪወች ትኬቱን እንድትወስዱ ይሁን ።
በዓልን ከቤተሰቦቻችሁ ሂዳችሁ የምታሳልፉ የቻላችሁትን ያህል ለግቢ - ጉባኤ መስጠት ትችላላችሁ።

📌የትኬት ዋጋ 150 ብር ነው

ለበለጠ መረጃ
ዲ/ን አብርሐም 0984493404
ኤልቤቴል 0920865903
ይትባረክ 0965310936

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

02 Jan, 06:22


🌟🌟🌟በገና አባት የተሸፈነ ቅዱስ አባት🌟🌟🌟
+++ቅዱስ ኒቆላዎስ ገባሬ መንክራት (St.Nicholas the wonder worker)+++

ምንጭ:– -መጽሐፈ ስንክሳር
-Coptic synaxarium

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

01 Jan, 09:06


ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ pinned «"ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።"      መዝሙር 18፥35          👉 የ2ኛ እና 3ኛ  ዓመት የሆናችሁ ሁላችሁም የግቢ ጉባኤአችን ተማሪዎች በእመቤታችን በድንግል ማርያም ወርሃዊ በዓል ምክንያት ሰኞ ዕለት ቀርቶ ነገ ረቡዕ በ23/04/2017ዓ.ም ለሚኖረን የባች ኮርስ የትምህርት መርሐ-ግብር የማጠቃለያ ፈተና ሁላችንም…»

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

31 Dec, 18:23


"ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።"
     መዝሙር 18፥35

         👉 የ2ኛ እና 3ኛ  ዓመት የሆናችሁ ሁላችሁም የግቢ ጉባኤአችን ተማሪዎች በእመቤታችን በድንግል ማርያም ወርሃዊ በዓል ምክንያት ሰኞ ዕለት ቀርቶ ነገ ረቡዕ በ23/04/2017ዓ.ም ለሚኖረን የባች ኮርስ የትምህርት መርሐ-ግብር የማጠቃለያ ፈተና ሁላችንም በተማርነው መሰረት እንዲሁም እግዚአብሔር አምላክ በፈቀደልን መጠን ተዘጋጅተን እንድንመጣ።

👉እንዲሁም ላልሰሙት እኅት ወንድሞች በመናገር በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ምርያም ቤ/ክ
👉2ኛ ዓመት:-(በትልቁ አዳራሽ )
👉3ኛ ዓመት:-(በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ)
ሰዓት11:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

31 Dec, 16:01


ትኬት መግዛት የምትፈልጉ የእጣ ትኬቱ ሳያልቅ አሁኑኑ ይደውሉ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

31 Dec, 10:25


ኑ ልደትን ከባለ ልደቱ ጋር እናክብር

እንደሚታወቀው እናት ግቢ- ጉባኤያች ሁልጊዜም የገናን ፆም ታስፈስከናለች።

ትኬት ያልገዛን ተማሪወች ትኬቱ ሳያልቅ በክላስ አስተባባሪወች ትኬቱን እንድትወስዱ ይሁን ።
በዓልን ከቤተሰቦቻችሁ ሂዳችሁ የምታሳልፉ የቻላችሁትን ያህል ለግቢ - ጉባኤ መስጠት ትችላላችሁ።

📌የትኬት ዋጋ 150 ብር ነው

ለበለጠ መረጃ
ዲ/ን አብርሐም 0984493404
ኤልቤቴል 0920865903
ይትባረክ 0965310936

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

03 Dec, 06:07


"ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።"
     መዝሙር 18፥35

         👉 ዛሬ የአንደኛ አመት ተማሪወች (fresh) የባች ኮርስ ትምህርት መርሐግብር ስለሚጀምር በተጠቀሰው ሰዓት እና ቦታ በሰዓቱ እንድትገኙ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

⛪️ቦታ፦
👉ለሜን ተማሪወች ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያ
👉ለቴክኖ ተማሪወች ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን


ሰዓት፦11:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

02 Dec, 13:18


የሕይወት ልቃቂት

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

02 Dec, 05:11


"ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።"
     መዝሙር 18፥35

         👉 የ2ኛ3ኛ እንዲሁም 4ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ሁላችሁም የግቢ ጉባኤአችን ተማሪዎች ዛሬ ሰኞ በ23/03/17ዓ.ም የባች ኮርስ መርሐ ግብራችን ስለሚቀጥል ሁላችንም ላልሰሙት እኅት ወንድሞች  በመናገር በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ምርያም ቤ/ክ
👉2ኛ ዓመት:-(በትልቁ አዳራሽ )
👉3ኛ ዓመት:-(በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ)
👉4ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ:-(የአብነት ት/ት መማሪያ አዳራሽ)

ሰዓት፦11:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

01 Dec, 11:13


የእመቤታችን ልዩ ጉባኤ ዛሬም ስለሚቀጥል የዝክረ ሰንበት መርኃግብር ለዚህ ሳምንት አይኖረንም።
👉አውደ ምህረት ላይ የእመቤታችንን ልዩ ጉባኤ በሰዓቱ ተገኝተን እንድንከታተል ይሁን።

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

30 Nov, 04:02


እንኳን ለጽዮን ማርያም ማሕደረ አምላክ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ::

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

29 Nov, 13:43


የእመቤታችን ልዩ ጉባኤ ዛሬ ከ11:00 ጀምሮ ስለሚጀምር እራት ተሎ በልተን በሰዓቱ እንድንገኝ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

27 Nov, 09:41


የግቢ ጉባኤያችን ቢዝነስ ሴንተር ስለሆነው ስለ ናትና ምን ያህል እናውቃለን ?

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

26 Nov, 19:19


“እኔም ወንጌልን ማድረስ እችላለሁ” የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ሰብስክሪብሽን ዘመቻ ተቀላቀሉ።

Subscribe and share

https://youtube.com/@eotcmk?si=_we8ZKBkbmex6PJ3


የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመቻ!

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

26 Nov, 04:42


ሰላም ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች
ወደ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ከጠዋቱ 12:00 በፊትም ሆነ ከምሽቱ 12:30 በኋላ በመንገዱ ላይ አደጋ በማድረስ ስልክ እና ሌሎች ንብረቶችን የሚቀሙ ሌቦች ስላሉ
👉በርከት ካላላችሁ በስተቀር ብቻችሁን ባለመሄድ
👉ስልክ ባለመያዝ
እራሳችሁን ትጠብቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን ።


https://t.me/HU_main_campus_gibi_gubae

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

25 Nov, 10:58


ለእንቅልፋሞች መልካም ዜና
የመጨረሻ ክፍል

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

25 Nov, 09:58


የእንኳን ደኅና መጣችሁ መርኃ ግብር

የተወደዳችሁ ቤተሰቦቻችን የ2ተኛ ቀን የእንኳን ደህና መጣችሁ መርኃግብር በደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እንዲህ ባለመልኩ ተካሔዷል። 
@HU_main_campus_gibi_gubae                                                                                                                                            
ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

25 Nov, 07:14


"ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።"
     መዝሙር 18፥35

         👉 የ2ኛ3ኛ እንዲሁም 4ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ሁላችሁም የግቢ ጉባኤአችን ተማሪዎች ዛሬ ሰኞ በ16/03/17ዓ.ም የባች ኮርስ መርሐ ግብራችን ስለሚቀጥል ሁላችንም ላልሰሙት እኅት ወንድሞች  በመናገር በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ምርያም ቤ/ክ
👉2ኛ ዓመት:-(በትልቁ አዳራሽ )
👉3ኛ ዓመት:-(በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ)
👉4ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ:-(የአብነት ት/ት መማሪያ አዳራሽ)

ሰዓት፦11:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

24 Nov, 12:07


ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ pinned «“የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።”        ዘጸአት 20፥8     📌 በግቢ ጉባኤአችን በየሳምንቱ የሚካሄደው ዝክረ ሰንበት የተሰኘ መርሐ-ግብር ዛሬ በዕለተ እሑድ በ15/03/17ዓ.ም ስለሚቀጥል  ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን ከእኅት ወንድሞቻችን ጋር በጋራ እንድንገኝ ይሁን። በዕለቱም የሚኖሩን መርሐ-ግብሮች 👉ትምሕርተ ወንጌል 👉የኪነ-ጥበብ ስራዎች 👉ዝክረ ቅዱሳን 👉ዝማሬ ⛪️ቦታ:-ሰአሊተ ምሕረት…»

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

24 Nov, 05:02


“የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።”
       ዘጸአት 20፥8

    📌 በግቢ ጉባኤአችን በየሳምንቱ የሚካሄደው ዝክረ ሰንበት የተሰኘ መርሐ-ግብር ዛሬ በዕለተ እሑድ በ15/03/17ዓ.ም ስለሚቀጥል  ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን ከእኅት ወንድሞቻችን ጋር በጋራ እንድንገኝ ይሁን።

በዕለቱም የሚኖሩን መርሐ-ግብሮች
👉ትምሕርተ ወንጌል
👉የኪነ-ጥበብ ስራዎች
👉ዝክረ ቅዱሳን
👉ዝማሬ

⛪️ቦታ:-ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
(ትልቁ አዳራሽ ላይ)

ሰዓት:- 11:45

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

23 Nov, 12:41


የጸሎት ማስተካከያዎች

1, ጸሎተ ሃይማኖት ላይ

ከአብ ጋር የሚስተካከል
ከአብ ጋር የሚካከል ✔️ ( እኩል መሆንን ያሳያል)

2, የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም ላይ
ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ የውዳሴ ማርያም ደራሲ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በሰባቱ ዕለታት እየተገለጠችለት በሰባቱ ዕለታት ከፋፍሎ ምስጋናዋን አዘጋጅቷል። ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በዕለት በዕለት ብቻ የተከፈለውን ውዳሴ ማርያም ሰአሊ ለነ ቅድስት (ቅድስት ሆይ ለምኝልን) በማለት በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእድሜ ዘመን በ64 ከፍሎታል። የእያንዳንዱ ቀን ውዳሴ ማርያም ቆጥረው ቢደምሩት 64 ይሆናል። ይኸውም የሰኞ 9 ፣ የማግሰኞ 15 ፣ የረቡዕ 8 ፣ የሐሙስ 7 ፣ የዓርብ 6 ፣ የቅዳሜ 10 ፣ የእሑድ 9 ነው።

በአንዳንድ የአማርኛ ውዳሴ ማርያም መጻሕፍት ላይ ይኽ ተዛብቷል። በቅዳሜ ውዳሴ ማርያም ላይ ለብቻቸው በቅድስት ሆይ ተከፍለው መቀመጥ የነበረባቸውን የመጀመሪያዎቹን ሁለቱን ክፍሎች በአንድ አስቀምጠዋቸዋል  (በአንድ ቅድስት ሆይ ለምኝልን) ፤ እንዲህ በመኾኑ ብዛቱ 63 ይሆናል

ትክክለኛ መሆን ያለበት ግን
'' ንጽሕት ነሽ ብርህትም ነሽ ጌታን በመኻል እጅሽ የያዝሽው ሆይ በሁሉ የተቀደስሽ ነሽ ፤ ፍጥረት ሁሉ ቅድስት ሆይ ለምኝልን ብለው እየጮኹ ከአንቺ ጋር ደስ ይላቸዋል ''
ካለ በኋላ '' ቅድስት ሆይ ለምኝልን'' መግባት አለበት።

'' ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ( ብሎ ጀምሮ )..... ወደ አባቱ ወደ እግዚአብሔርም አቀረበን ፤ ቅድስት ሆይ ለምኝልን ''

ሁለቱም ጋር ቅድስት ሆይ ለምኝልን በማስገባት እናስተካክል።

3,  ይዌድስዋ ላይ

እንዴት ከድሀ ቤት አደረ እንደ ምስኪን የሚለውን አንድ ላይ እናንብብ። ከሰማያት ወርዶ የሚለውን ለብቻው እናንብብ ፤ከሰማይ የወረደ ምስኪን የለምና

4, ይዌድስዋ ላይ

ይህ እንዴት ይሆንልኛል ካለ በኋላ ወንድ አላውቅም (ወንድ ስለማላውቅ) የሚለውን በግዕዝ ቃል ተጠቅሞ '' እንዘ ኢየአምር ብእሴ'' ይላሴ መጽሐፉ ፤  አላውቅም ለማለት '' ኢ '' አፍራሽ ስለሆነች  እንዘ የአምር ሳይሆን ኢየአምር ብለን እናስተካክል።

እንዘ የአምር ብእሴ
እንዘ ኢየአምር ብእሴ ✔️

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

22 Nov, 16:37


ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ pinned «»

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

22 Nov, 04:45


"ለምኑ ይሰጣችኹማል ፤ ፈልጉ ታገኙማላችኹ ። መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችኹማል። የሚለምነው ኹሉ ይቀበላልና የሚፈልገውም ያገኛል መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።"
ማቴ7፥7

          ሳምንታዊው የአንድነት የጸሎት መርሐ-ግብር ዛሬ አርብ በ13/03/17ዓ.ም ስለሚቀጥል ሁላችንም ላልሰሙት እኅት እና ወንድሞቻችን በማስታወስ በሕብረት በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

👉ውዳሴ ማርያም
👉 መዝሙረ ዳዊት
👉መሐረነ አብ
👉ስንክሳር እና ተአምረ ማርያም

⛪️ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
ሰርክ ሰዓት (11:45) ጀምሮ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

18 Nov, 13:31


ለእንቅልፋሞች መልካም ዜና
ክፍል 1

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

17 Nov, 18:16


"ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።"
     መዝሙር 18፥35

         👉 የ2ኛ3ኛ እንዲሁም 4ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ሁላችሁም የግቢ ጉባኤአችን ተማሪዎች ነገ ሰኞ በ09/03/17ዓ.ም የባች ኮርስ መርሐ ግብራችን ስለሚቀጥል ሁላችንም ላልሰሙት እኅት ወንድሞች  በመናገር በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ምርያም ቤ/ክ
👉2ኛ ዓመት:-(በትልቁ አዳራሽ )
👉3ኛ ዓመት:-(በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ)
👉4ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ:-(የአብነት ት/ት መማሪያ አዳራሽ)

ሰዓት፦11:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

17 Nov, 11:00


ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ pinned «“የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።”        ዘጸአት 20፥8     📌 በግቢ ጉባኤአችን በየሳምንቱ የሚካሄደው ዝክረ ሰንበት የተሰኘዉ መርሐ-ግብር ነገ በዕለተ እሑድ በ08/03/17ዓ.ም ስለሚቀጥል  ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን ከእኅት ወንድሞቻችን ጋር በጋራ እንድንገኝ ይሁን። በዕለቱም የሚኖሩን መርሐ-ግብሮች 👉ትምሕርተ ወንጌል 👉የኪነ-ጥበብ ስራዎች 👉ዝክረ ቅዱሳን 👉ዝማሬ ⛪️ቦታ:-ሰአሊተ…»

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

16 Nov, 19:18


“የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።”
       ዘጸአት 20፥8

    📌 በግቢ ጉባኤአችን በየሳምንቱ የሚካሄደው ዝክረ ሰንበት የተሰኘዉ መርሐ-ግብር ነገ በዕለተ እሑድ በ08/03/17ዓ.ም ስለሚቀጥል  ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን ከእኅት ወንድሞቻችን ጋር በጋራ እንድንገኝ ይሁን።

በዕለቱም የሚኖሩን መርሐ-ግብሮች
👉ትምሕርተ ወንጌል
👉የኪነ-ጥበብ ስራዎች
👉ዝክረ ቅዱሳን
👉ዝማሬ

⛪️ቦታ:-ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ

ሰዓት:- 11:45

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

16 Nov, 06:00


በዚች ቀን የእስክንድርያ አገር የሆነ ቅዱስ ጊዮርጊስ በሰማዕትነት አረፈ።

የዚህም ቅዱስ አባቱ ልጅም አልነበረውም የልዳዊው ቅዱስ ጊዮርጊስም ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት የበዓልዋ መታሰቢያ ኅዳር ሰባት በደረሰ ጊዜ ልጅን ይሰጠው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲማልድለት ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመነው ጌታችንም ልመናውን ተቀብሎ ይህን ልጅ ሰጠው ስሙንም በታላቁ ሰማዕት ስም ጊዮርጊስ ብሎ ስም አወጣለት።

የዚህም ልጅ እናትና አባቱ አረፉ እርሱም ከእናቱ ወንድም ዘንድ ተቀመጠ ሃያ አምስት ዓመትም በሆነው ጊዜ በጎ ሥራ የሚሠራ ሆነ ድኆችን እጅግ ይረዳቸው ይወዳቸውም ነበረ የሚራራና የሚመጸውት ሆነ ወደ ቤተክርስቲያን መገሥገሥንም ይወዳል። ለመኰንን አርማንዮስም ሴት ልጅ አለችው ቦታዎችንም በመጐብኘት ደስ ይላት ዘንድ ከባልንጀሮቿ ጋር ወጣች ወደ ደብረ ቊስቋምም ስትደርስ ጣዕም ባለው ድምጽ በመዘመር ሲያመሰግኑ የተሰበሰቡ መነኰሳትን አገኘቻቸው ምስጋናቸውና መዝሙራቸውም ወደ ልቡዋ ገብቶ ተቀረጸ።

ጊዮርጊስንም መነኰሳቱ ስለሚዘምሩት ያስረዳት ዘንድ ጠየቀችው እርሱም ወደማይጠፋ ዕረፍትና ተድላ እንደሚያደርሳቸው ነገራት ወደ አባቷም በተመለሰች ጊዜ በፊቱ ቁማ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመነች አባቷም ሊሸነግላት ጀመረ ልጄ ሆይ ይህን አታድርጊ አላት ነገሩን ባልተቀበለች ጊዜ ራሷን በሰይፍ አስቆረጠ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለች ከዚህም በኋላ ልጅህን ያሳታት ጊዮርጊስ ነው ብለው ለመኰንኑ ነገሩት እርሱም ቅዱስ ጊዮርጊስን ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው ጭካኔውንም አይቶ ወደ ሀገረ እንጽና ሰደደው በዚያም የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበለ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ :- መጽሐፈ  ስንክሳር

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

15 Nov, 18:05


ሰላም ውድ ወንድሞችና እህቶች እንደምን ቆያችሁ።
አሜን የአምላካችን ስሙ ለዘለአለም የተመሰገነ ይሁን።

📌ነገ ቅዳሜ በ7/3/2017 ዓ.ም መዝሙር ክፍል ከማዕከል ጋር በመሆን  ስለ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር አጭር ስልጠና አዘጋጅቷል።


📌ስልጠናው ለሁሉም  የግቢ ጉባኤ አባላት የተዘጋጀ ስለሆነ በእለቱ ተገኝታችሁ ስልጠናውን እንድትወስዱ ስንል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።


📍ቦታ=ሰ/ም/ቅ/ማርያም ቤ/ክ
🕑ሰዓት=ጠዋት 2:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

15 Nov, 09:43


📌ትኬት የቆረጥን ተማሪወች ባሱ 8:45 ላይ ቴክኖ ግቢ በር ላይ ስለሚመጣ በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

👉ለበለጠ መረጃ +251974651456
                            +251965310936

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

15 Nov, 07:24


ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከስደት በሚመለሱ ጊዜ ወደ  ደብረ ቊስቋም ገብተው በመንገድ ጒዞ ካገኛቸውም ድካም ላአረፉበት ዓመታዊ መታሰቢያ ለበዓለ ቍስቋም እንኳን  አደረሳችሁ!

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

13 Nov, 12:53


ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ pinned «“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።”         ዕብራውያን 13፥7 👉4ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኦርቶዶክሳውያን የባች ኮርስ መርሃ-ግብራችን ዛሬ ረቡዕ ስለሚቀጥል በሰዓቱ እድንገኝ ይሁን። ⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ ሰዓት፦11:30»

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

13 Nov, 05:16


“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።”
        ዕብራውያን 13፥7

👉4ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኦርቶዶክሳውያን የባች ኮርስ መርሃ-ግብራችን ዛሬ ረቡዕ ስለሚቀጥል በሰዓቱ እድንገኝ ይሁን።

⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ


ሰዓት፦11:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

12 Nov, 16:08


“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ኹሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።”
  ፊልጵስዩስ 4፥6

          ወር በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ከረቡዕ እስከ አርብ የሚደረገው የጸሎት መርሐ-ግብር ከነገ ስለሚጀምር ሁላችንም ላልሰሙት እኅት እና ወንድሞቻችን በማስታወስ በሕብረት በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

👉ውዳሴ ማርያም
👉 መዝሙረ ዳዊት
👉መሐረነ አብ
👉ስንክሳር እና ተአምረ ማርያም

⛪️ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

09 Nov, 15:24


የዓለም ሁሉ መድኃኒት የምትሆን ብላቴና እግሯ የተመላለሰበቱን ምድር እስም ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡ ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡የብርሃን ልጅ ወደ ሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን በከፈለኝ የእግሯንም ጫማ እሸከም ዘንድ ማን በከፈለኝ፡፡

🌹
አሁንም ያን ጊዜ በዕብራይስጥ ማሪሃም ከተባለች ከተመረጠች ድንግል ማርያም ጋራ ያን ጊዜ ካሉት አላንስም ሀሳቤን ከዚያ እንዳለሁ አድርጌ አለሁና፡፡ በስጋ አልነበርሁም በመንፈስ ግን አለሁ፡፡ ባነዋወር አልነበርሁም በሃይማኖት ግን አለሁ በገጽ አልነበርሁም በማመን ግን አለሁ፡፡ ሳልኖር እራሴን እንዳለሁ ያረደረግሁ እኔ የተመሰገንሁ ነኝ ጌታችን በወንጌል እንደተናገረ እንዲህ ሲል ሳያዩኝ የሚያምኑብኝ ግን የተመሰገኑ ናቸው፡፡

እኔ ባሪያህ ስለሃይማኖቴ የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ ስለ ዕውነቴ አይደለም ስለ መረዳቴም የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ ስለ ንጽህናዬም አይደለም በእግዚአብሔር ስም ስለ አመንኩ የተመሰገንሁ ነኝ፡፡ በናቱም ጸሎት ስለ አመንሁ ንዑድ ክቡር ነኝ፡፡


(አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በአርጋኖን)

🌹🌹🌹🌹🌹

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

09 Nov, 15:01


“የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።”
       ዘጸአት 20፥8

    📌 በግቢ ጉባኤአችን በየሳምንቱ የሚካሄደው ዝክረ ሰንበት የተሰኘ መርሐ-ግብር ነገ በዕለተ እሑድ በ01/03/17ዓ.ም ስለሚቀጥል  ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን ከእኅት ወንድሞቻችን ጋር በጋራ እንድንገኝ ይሁን።


⛪️ቦታ:-ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ

ሰዓት:- 11:45

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

07 Nov, 18:39


"ለምኑ ይሰጣችኹማል ፤ ፈልጉ ታገኙማላችኹ ። መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችኹማል። የሚለምነው ኹሉ ይቀበላልና የሚፈልገውም ያገኛል መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል።"
ማቴ7፥7

          ሳምንታዊው የአንድነት የጸሎት መርሐ-ግብር ነገ አርብ በ29/02/17ዓ.ም ስለሚቀጥል ሁላችንም ላልሰሙት እኅት እና ወንድሞቻችን በማስታወስ በሕብረት በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

👉ውዳሴ ማርያም
👉 መዝሙረ ዳዊት
👉መሐረነ አብ
👉ስንክሳር እና ተአምረ ማርያም

⛪️ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
ሰርክ ሰዓት (11:45) ጀምሮ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

05 Nov, 16:52


“እኛም አይተናል አባትም ልጁን የዓለም መድኃኒት ሊሆን እንደ ላከው እንመሰክራለን።”
1ኛ ዮሐንስ 4፥14

📌 በነገዋ ዕለት የአባታችን የቸሩ መድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል ነውና ሁልጊዜም በየወሩ በግቢ ጉባኤአችን የሚዘጋጀው ወርሃዊ የመድኃኔዓለም ጸበለ ጸዲቅ መርሐ-ግብር ስላለ ሁላችንም ከእኅት ወንድሞቻችን ጋር በመሆን በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።


⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
           (ትልቁ አዳራሽ)
ሰዓት፦11:00

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

05 Nov, 05:03


"ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።"
     መዝሙር 18፥35

👉4ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኦርቶዶክሳውያን የባች ኮርስ መርሃ-ግብራችን ዛሬ ማክሰኞ ስለሚቀጥል በሰዓቱ እድንገኝ ይሁን።

⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
(በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ)
ሰዓት፦11:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

04 Nov, 11:30


የዘኬዎስ ዛፍ ክፍል 1

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

04 Nov, 06:06


"ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።"
መዝሙር 18፥35

👉 የ2ኛ እና 3ኛ ዓመት ተማሪዎች ዛሬ ሰኞ በ25/02/17ዓ.ም ስለሚቀጥል ሁላችንም ላልሰሙት እኅት ወንድሞች በመናገር በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ምርያም ቤ/ክ
2ኛ ዓመት:-(በትልቁ አዳራሽ )
3ኛ ዓመት:-(በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ)

ሰዓት፦11:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

03 Nov, 12:15


ልዩ ሳምንታዊ ጉባኤያችን ሊጀምር ሰዓታቶች ብቻ ይቀራሉ። 11:45 ሲል በማርያም ቤ/ክ አዳራሽ ላይ በሰዓት እንድንገኝ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

02 Nov, 15:01


“የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።”
       ዘጸአት 20፥8

    📌 በግቢ ጉባኤአችን በየሳምንቱ የሚካሄደው ዝክረ ሰንበት የተሰኘ መርሐ-ግብር ነገ በዕለተ እሑድ በ24/02/17ዓ.ም ስለሚቀጥል  ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን ከእኅት ወንድሞቻችን ጋር በጋራ እንድንገኝ ይሁን።


⛪️ቦታ:-ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ

ሰዓት:- 11:45

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

31 Oct, 15:53


“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ኹሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።”
  ፊልጵስዩስ 4፥6

          ሳምንታዊው የአንድነት የጸሎት መርሐ-ግብር ነገ አርብ በ22/02/17ዓ.ም ስለሚቀጥል ሁላችንም ላልሰሙት እኅት እና ወንድሞቻችን በማስታወስ በሕብረት በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

👉ውዳሴ ማርያም
👉 መዝሙረ ዳዊት
👉መሐረነ አብ
👉ስንክሳር እና ተአምረ ማርያም

⛪️ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
ሰርክ ሰዓት (11:45) ጀምሮ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

28 Oct, 19:40


“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።”
ዕብራውያን 13፥7

👉4ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኦርቶዶክሳውያን የባች ኮርስ መርሃ-ግብራችን ነገ ማክሰኞ ስለሚቀጥል በሰዓቱ እድንገኝ ይሁን።

⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
(በሰንበት ት/ቤቱ አዳራሽ)

ሰዓት፦11:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

28 Oct, 13:59


ማርያማዊ ደስታ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

28 Oct, 04:03


“የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤”
      መክብብ 12፥1

         👉 የ2ኛ እና 3ኛ ዓመት ተማሪዎች ባች ኮርስ ዛሬ ሰኞ በ18/02/17ዓ.ም ስለሚቀጥል ሁላችንም ላልሰሙት እኅት ወንድሞች  በመናገር በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ምርያም ቤ/ክ
👉ለ2ኛ አመት ትልቁ አዳራሽ
👉ለ3ኛ አመት ሰንበት ት/ት አዳራሽ

ሰዓት፦11:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

27 Oct, 13:08


ልዩ ሳምንታዊ ጉባኤያችን ሊጀመር ሰዓታቶች ብቻ ይቀራሉ ።
ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር መርኃግብሩ ላይ እንዲሳተፉ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
👉11:45 ላይ በሰአሊተ  ምህረት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን

https://t.me/HU_main_campus_gibi_gubae

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

26 Oct, 17:45


“የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።”
ዘጸአት 20፥8

📌 በግቢ ጉባኤአችን በየሳምንቱ የሚካሄደው ዝክረ ሰንበት የተሰኘ መርሐ-ግብር ነገ በዕለተ እሑድ በ17/02/17ዓ.ም ስለሚጀምር ሁላችንም ኦርቶዶክሳውያን ከእኅት ወንድሞቻችን ጋር በጋራ እንድንገኝ ይሁን።
👉በዕለቱም አስተማሪ እና ቁምነገር አዘል መርሐ-ግብራት ስለተዘጋጁ በሰዓቱ ተገኝተን የበረከቱ ተካፋይ እንሁን።

⛪️ቦታ:-ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ

ሰዓት:- 11:45

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

25 Oct, 19:00


“እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤”
       1ኛ ጴጥሮስ 2፥9

       👉በዕለተ ቅዳሜ በ16/02/17ዓ.ም ክብረ ክህነት በሚል ርዕስ ለዲያቆናት ብቻ የተዘጋጀ መርሐ-ግብር ስላለ በሰዓቱ እና በቦታው ከወንድሞቻችን ጋር እንድንገኝ።

⛪️ቦታ:-ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ

ሰዓት:- ከሰዓት 8:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

25 Oct, 14:49


“ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል? ዋጋዋ ከቀይ ዕንቍ እጅግ ይበልጣል።”
ምሳሌ 31፥10

📌በግቢ ጉባኤአችን በወር አንድ ጊዜ የሚዘጋጀው የጉባኤ አንስት(የእኅቶች) መርሐ-ግብር ነገ ቅዳሜ በ16/02/17ዓ.ም ስለሚጀመር ሁላችሁም እኅቶች ከመንፈሳዊ እኅቶቻችሁ ጋር በሕብረት እንድትገኙ እናሳስባለን።

⛪️ቦታ:- ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ
(ለቴክኖ ተማሪዎች ትራንስፖርት አለ)

ሰዓት:- ጠዋት 2:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

24 Oct, 19:13


“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ኹሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።”
  ፊልጵስዩስ 4፥6

          ሳምንታዊው የአንድነት የጸሎት መርሐ-ግብር ነገ ስለሚቀጥል ሁላችንም ላልሰሙት እኅት እና ወንድሞቻችን በማስታወስ በሕብረት በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

👉ውዳሴ ማርያም
👉 መዝሙረ ዳዊት
👉መሐረነ አብ
👉ስንክሳር እና ተአምረ ማርያም

⛪️ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
ሰርክ ሰዓት (11:45) ጀምሮ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

24 Oct, 05:09


​​እንኳን ለአባታችን አቡነ አረጋዊ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን! ጥቅምት 14

አባታችን አቡነ አረጋዊ ከዘጠኙ ቅዱሳን አባቶች አንዱ ናቸው። ትውልዳቸውም ከሮም ነገሥታት ወገን ሲሆን አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉሥ ነበር፤ እናታቸው እድና ትባላለች፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩ ነበሩ፡፡ የተባረከ ልጅም ወለዱ፤ በሕገ እግዚአብሔርና ቅዱሳት መጻሕፍትን እያነበቡ አደጉ፡፡ ለአቅመ አዳም ሲደርሱ ሚስት ቢታጭላቸውም ከነበራቸው የክርስቶስ ፍቅር የተነሳ ትዳር መመሥረትን ትተው  ደውናስ ወደ ምትባል ገዳም ሔዱ፤ በዚያም አባ ጳኩሚስ ይኖሩ ነበር።
በረከታቸው ይደርብን !!!!

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

23 Oct, 16:21


ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶችን፣ ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎችን እና  ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ሃይማኖትን  እና ያሬዳዊ ዜማን የጠበቁ መዝሙራት ለማዳመጥ፤ እነዚህን ማኅበራዊ ሚዲያዎች ይጠቀሙ።
"ዜማ ወጥበብ ዘማኅበረ ቅዱሳን" ዩቲዩብ ቻናልን ይከታተሉ።
ማስፈንጠሪያ
-https://youtube.com/@-zemawetibebzmk7905?si=4jFEU4PUj6YvA9HX

የማኅበረ ቅዱሳን ዩቲዩብ ቻናልን
ማስፈንጠሪያ -https://youtube.com/@eotcmk?si=Yk-a-78rKJk6d-7r
ቴሌግራም- https://t.me/eotcmk

የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድ ካስት አገልግሎት የፌስ ቡክ ገጽ
ማስፈንጠርያ-https://www.facebook.com/eotcmkidusan?mibextid=LQQJ4d

የማኅበረ ቅዱሳን መካነ ድር[website]
https://eotcmk.org/a/

የግቢ ጉባኤያት ማስተባበርያ መካነ ድር[website]
https://eotcmk.org/gibi-a/

ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ Subscribe ,Like ,Follow and Share ያድርጉ።

ለግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ይዳረስ ዘንድ በየ ግቢ ጉባኤያችሁ ቴሌግራም ላይ ይለጠፍ!

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

22 Oct, 03:00


“በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥”
ራእይ 12፥7

📌 በዛሬዋ ዕለት ሁልጊዜም በየወሩ በግቢ ጉባኤአችን የሚዘጋጀው ወርሃዊ የቅዱስ ሚካኤል የጸበለ ጸዲቅ መርሐ-ግብር ስላለ ሁላችንም ከእኅት ወንድሞቻችን ጋር በመሆን በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
(ትልቁ አዳራሽ)
ሰዓት፦11:00

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

21 Oct, 18:28


“የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።”
ዕብራውያን 13፥7

👉4ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኦርቶዶክሳውያን የባች ኮርስ መርሃ-ግብራችን ነገ ማክሰኞ ስለሚቀጥል በሰዓቱ እድንገኝ ይሁን።

⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ
👉ሰንበት ት/ት ቤት አዳራሽ

ሰዓት፦11:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

20 Oct, 14:10


“የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤”
መክብብ 12፥1

👉 የ2ኛ እና 3ኛ ዓመት ተማሪዎች ባች ኮርስ ነገ ሰኞ በ11/02/17ዓ.ም ስለሚቀጥል ሁላችንም ላልሰሙት እኅት ወንድሞች በመናገር በሰዓቱ እንድንገኝ ይሁን።

⛪️ቦታ፦ሰአሊተ ምሕረት ምርያም ቤ/ክ
👉ለ2ኛ አመት ትልቁ አዳራሽ
👉ለ3ኛ አመት ሰንበት ት/ት አዳራሽ

ሰዓት፦11:30

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

19 Oct, 09:33


“ወንድሞች ሆይ፥ እኔን የምትመስሉ ሁኑ፥ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ፥ እንዲሁ የሚመላለሱትን ተመልከቱ።”
ፊልጵስዩስ 3፥17

👉የአብነት ት/ት መርሐ-ግብር በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ዘወትር ከሰኞ-አርብ ጠዋትና ማታ እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋትና እሁድ በሰርክ ሰዓት

👉ለበለጠ መረጃ፦ ዲ/ን ምሕረቱ
👉ስልክ፦+251928394981

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

18 Oct, 13:44


👉የሙያ እና በጎ አድራጎት ስራ ነገ ቅዳሜ በ09/02/2017 ዓ.ም ጠዋት ይጀምራል።

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

17 Oct, 18:13


ማስታወቂያ‼️

የአንድነት ጸሎት መርሐ-ግብራችን ነገ ማለትም አርብ 08/02/17 ዓ.ም ይቀጥላል ሁላችንም ከእኅት ወንድሞቻችን ጋር በሕብረት በሰዓቱ እድንገኝ ይሁን።


⛪️ሰአሊተ ምሕረት ማርያም ቤ/ክ

ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

17 Oct, 17:27


ውድ ወንድሞች እና እህቶች እንደምን ቆያችሁ። በቅድሚያ በየክፍላችሁ (2ኛ ዓመቶች) ለተካሄደው የክርስቲያን ተማሪዎች ምዝገባ ላደረጋችሁልን ትብብር በእግዚአብሔር ስም እያመሰገንን በመሃል ሳትመዘገቡ ለቀራችሁ ወንድሞች እና እህቶች ከዚህ ቀጥሎ በተቀመጡት አድራሻዎች ( ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት,ስልክ ቁጥር እና ከዚህ በፊት በተለያየ በአገልሎት ወይም በድቁና ከቆያችሁ የሚለውን) እንድትልኩልን ለማሳሰብ እንወዳለን።

@Ehagiz  (0927549047)
@BISRE_12  (0976555989)

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።

ሀዋሳ ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉባኤ

17 Oct, 04:09


📌የመዝሙር ጥናት እሁድ 3:30 ጀምሮ የሚጀምር ይሆናል።