ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala @tariknwedehuala Channel on Telegram

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

@tariknwedehuala


የኢትዮጵያ ታሪኮች የሚቀርብበትና የሚዳሰስበት ቻናል

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala (Amharic)

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala በስልክ መሰናዶች ላይ የተገኘው ቻናል ነው። እንዴት እንዳለው ታሪኩን ለመመልከትና ማንበብ እንዴት እንደሚችሉ የሚረዳት መልእክት ለማድረግ ስብስቦን ይከተላቸዋል። ይህ ቻናል በኢትዮጵያ ታሪኩን በሚቀርብበትና የሚዳሰስበት፣ እና በሚስጥር አስራጭና ታማኝ ቻናሎችን ለማዘጋጀት እና ለማስታወቂያ ሊኖራቸው እንችላለን። በስልክ መሰናዶች እንቅስቃሴም ቻናሎች እንደሚፈታ እና እንደሚስራርም ቻናልን ስብስቡን ከእኛ እንደምንላክ ክፍል አለው።

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

10 Nov, 18:37


https://youtu.be/DNVFIh-P0aE?si=5FPIvcsBk1aVuGvx

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

10 Nov, 18:29


አንጋፋው ጋዜጠኛ ዜናነህ መኮንን

(1945 -- 2017)

https://youtu.be/DNVFIh-P0aE?si

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

10 Nov, 17:16


ባለወርቃማ ድምፁ ዜና አንባቢና ደራሲ ዜናነህ መኮንን በተወለደ በ 72 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

አንጋፋዎቹ መገናኛ ብዙሀን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን በ70ዎቹ እና 80ዎቹ ሲታወሱ ዛሬም ድረስ ስሙ በጉልህ ይነሳል። የታሪክ ተመራማሪ፣ የመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካ ተንታኝ የጀርመን ድምፅ ሬዲዮ ልዩ እና ተወዳጅ ዘጋቢ ነዉ፡፡

ዜናነህ መኮንን ከጋዜጠኛነቱ በተጨማሪ ደራሲ፣ ገጣሚና ሃያሲም ነው። ከግርማ ሞገሱ ጋር ግርማ ሞገስን የሚያላብስ ልብስ ለብሶ በኢትዮጲያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሸቱ ሁለት ላይ “ጤና ይስጥልኝ እንደምን አመሻችሁ ከሰዓቱ ዜና ጋር ዜናነህ መኮንን ነኝ” በማለት እጅ ሲነሳ የብዙዎች ትዝታ ሆኖ አልፏል።

በበርካታ የቲቪ እና የሬድዮ ተከታታዮች ዘንድም የሚወደድ ነው፡፡ የጀርመን ድምጽ (ዶቼ ዌሌ ሬዲዮ) የጣቢያው መክፈቻና መዝጊያ ድምፅ የዚሁ አንጋፋ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ይህ ሰዉ ኑሮውን በእየሩሳሌም ካደረገ ዘመናት ተቆጥረው ነበር።

ውልደት እና እድገት

ዜናነህ በ1945 ዓ.ም ጎንደር አዘዞ በምትባል ከተማ ውስጥ መስከረም ወር ላይ አደይ አበባና አዲስ አመቱን ተከትሎ ነበር ወደዚህች ምድር የመጣው። ውልደቱ አዘዞ ይሁን እንጂ በ ቤተሰቦቹ የሥራ ፀባይ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ የመጣው በልጅነቱ ነበር፡፡ በመቀጠልም ወደ ጂማ ሄዶ “ቆጪ” ሰፊር ይኖሩና ፃዲቁ ዮሀንስ (አሁን የመምህራን ማሠልጠኛ ተቋም ሆኗል) ይማር ነበር፡፡

ጂማ እስከ 3ተኛ ክፍል ድረስ ከተማረ በኋላ ወደ ጎንደር በመሄድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን ጨርሶ የሁለተኛውንም አጋምሷል።....

ሙሉውን ታሪክ
👇

https://www.facebook.com/share/p/1BFhVajoaY/

#ታሪክን_ወደኋላ

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

09 Nov, 10:36


የጅቡቲው ፕሬዝዳንት ሀሰን ጉሌድ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ወደ ኢትዮጵያ በመጡበት ወቅት ፕሬዚዳንት መንግስቱ ኃይለማርያም እና ባለቤታቸው ወ/ሮ ውብባንቺ ቢሻው አቀባበል ሲያርጉላቸው ፤

መጋቢት 9 ቀን 1973 ዓ.ም
አዲስ አበባ

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

09 Nov, 10:06


ጥቅምት 30 ቀን 1848 ዓ.ም

#በዛሬዋ_ዕለት

ከዛሬ 169 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የሸዋ ንጉሥ ሳህለሥላሴ ወሰንሰገድ እና የወይዘሮ በለጥሻቸው ወልዴ ልጅ የሆኑት ንጉስ ኃይለመለኮት ሳህለ ሥላሴ በድንገተኛ ኅመም ምክንያት አርፈው በደብረ በግዕ የተቀበሩበት ዕለት ነበር።

የሸዋው ንጉሥ ኃይለመለኮት በሰውነታቸው ግዝፈትና ጥንካሬ እንዲሁም በልባቸው ቀናነት በሸዋ ዘንድ የታወቁና የተወደዱ ንጉሥ ነበሩ። ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ የኢትዮጵያ ታሪክ በሚለው መጽሐፋቸው እንደሚነግሩን ንጉሥ ኃይለመለኮት ከጥንካሬያቸው የተነሳ ኢላማ ተኩስ በሚተኩሱ ጊዜ መሳሪያውን አጠንክረው በመያዛቸው ምክንያት ጥይቱ ሲወጣ ጠምንጃቸው ለሁለት ተሰብሮ እጃቸው ላይ ቀርቶ ያውቃል።

ንጉሥ ኃይለመለኮት ከአባታቸው ሞት በመቀጠል ወደንግሥናው ዙፋን ከወጡ በኋላ ሸዋን ለ 8 ዓመታት አስተዳድረዋል። በስልጣን ላይ ሳሉም ተቀናቃኝ ሊሆኑባቸው የሚችሉትን ወገኖቻቸውን በእስር ዞር እንዲያረጓቸው ከጓናቸው ያሉ ሰዎች ሲመክሯቸው "ተዉ ይሄን አላደርገውም እግዚአብሔር የወደደውን ነው የሚያስገዛው" የሚሉ ቀና እንደነበሩ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደሥላሴ በመጽሐፋቸው ይጠቅሳሉ።

በመጨረሻም አጼ ቴዎድሮስ በሀገሪቱ በየቦታው ያለውን የተከፋፈለ አገዛዝ ወደ አንድ በማምጣት በማእከላዊ መንግሥት ስር የምትተዳር አንዲት ሀገር ለመመስረት አስበው ከየመሳፍንቱ ጋር በሚዋጉ ጊዜ ወደ ሸዋም ሊመጡ ነው የሚል ወሬ ተሰምቶ ንገሥ ኃይለመለኮትም ለጦርነት ተዘጋጁ፤ ሆኖም ግን ገና ቀደም ብሎ ንጉሡ ኃይለመለኮት በጣም ታመው ነበርና እርሳቸው በጦርነቱ ሳይካፈሉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩት ንጉሥ ኃይለመለኮት ሳህለሥላሴ የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ አባት ናቸው።

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

08 Nov, 19:44


በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሴት ትራፊክ ፖሊስ በሥራ ውላለች ግን አንዳንድ ባለመኪኖች ማሽገጠጥ ጀምረዋል። ትናት ማታ ገደማ የሴት ፖሊስን ትዕዛዝ ባለመፈፀም ያሽገጥጣት የነበረው የጂፑ ሹፌር ነው.......

ታህሳስ 17 ቀን 1960 ዓ.ም
(አዲስ ዘመን)

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

08 Nov, 18:48


በሀገራችን የተደረገው 3ተኛው አጠቃላይ የምርጫ ሂደት ፤

ሐምሌ -- 1957 ዓ.ም

አዲስ አበባ

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

06 Nov, 20:07


ጀግናዋ አርበኛ ሸዋነሽ አብረሃ

ወይዘሮ ሸዋነሽ አብረሃ በጣሊያን ወረራ ዘመን ጠላትን በቆራጥነት የተዋጉ ሴት አርበኛ ናቸው። አባታቸው ደጃዝማች አብረሃ አርአያ የዘር ሀረጋቸው ከ አጼ ዮሐንስ አራተኛ ይመዘዛል። ባለቤታቸው ደጃዝማች ኃይሉ ከበደ በዋግ የታወቁ የአርበኛ መሪ ነበሩ።

በ1929 ዓ.ም ደጃዝማች ኃይሉ ሲሰው እና የዋግ አርመኞች ላይ ዘግናኝ የሆነ ፍጅት ሲፈጸም ወ/ሮ ሸዋነሽ በህይወት የተረፉትን አርበኞች አስተባብረው ወደ በጌምድር በመሻገር በልጆቻቸው ደጃዝማች ተፈራ ተሰማ እና ልጅ (ብኋላ ዋግሹም) ወሰን ኃይሉ እየታገዙ ትግሉን ቀጠሉበት።

ወይዘሮ ሸዋነሽ ትግላቸውን ለማጠናከር ከተለያዩ የአርበኛ መሪዎች ጋር ግንኙነት ይፈጥሩ ነበር። በዚህም መሰረት በበጌምድር ለታወቀው የአርበኛ መሪ ልጅ ዮሐንስ ኢያሱ (የልጅ ኢያሱ ልጅ) ልጃቸውን ዘውዲቱን በመዳር ዝምድናን ፈጥረዋል። ያም ሆኖ አልፎ አልፎ በአርበኛ መሪዎቹ መካከል የእኔ በልጥ እኔ በልጥ ግጭቶች እየተነሱ ትግሉን እንቅፋት ይፈጥሩበት ነበር።

ግርማዊ ቀዳማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ ጎጃም በደረሱ ጊዜ ወይዘሮ ሸዋነሽ አብረሃ ልጃቸው ወሰን ኃይሉ ንጉሡን እንዲያገኝ ልከው እሳቸው ወታደሮቻቸውን አስተባብረው ዋግን ነጻ ለማውጣት ዘመቱ። የዋግ አርበኞች በራስ ስዩም መንገሻ እየተመሩ ሚያዚያ 20 ቀን 1933 ዓ.ም ሰቆጣን ተቆጣጠሩ። የወወይዘሮ ሸዋነሽ ወታደሮች አምባላጌ ላይ በተደረገው ጦርነትም ተሳታፊ ነበር።

ከድል ብኋላ ለአርበኛ ሸዋነሽ አብረሃ ለፈጸሙት ጀግንነት የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳሊያዎች ተበርክተውላቸዋል።

ክብርና ሞገስ ለጀግናዋ አርበኛ ሸዋነሽ አብረሃ 🙏

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

06 Nov, 18:42


ጥቅምት 27 ቀን 1929 ዓ.ም

#በዛሬዋ_ዕለት

ከ 88 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በአድዋ ጦርነት ጀግንነታቸው ያስመሰከሩት እንዲሁም በ 2ተኛው የኢትዮ ኢጣሊያን ጦርነትም ወቅት በእርጅና ዕድሜያቸው ዳግም የዘመቱት ጀግናው አርበኛ ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ (አባ ነፍሶ) በተወለዱ በ 75 ዓመታቸው አቤቤ በተባለ ቦታ በኢጣሊያ ጦር ተመትተው ህይወታቸው ያለፈበት ዕለት ነበር።

*

ደጃዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ ነጻ በወጣው የመቀሌ ምሽግ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ስለመስቀላቸው እና የጣሊያን ሰራዊት ከመቀሌ ምሽጉ ስለመባረሩ

........እቴጌ ጣይቱም ሰራዊታቸውን እንዲህ ብለው አዘዙ፣

ከጉድባው ገብተን ካልተዋጋን ብላችሁ ብትመኙም ለብዙ ሰራዊት ትንሽ ጉድባ አይበቃውምና ከጣሊያን ሰራዊት ይልቅ እናንተው እርስ በርስ ተታኩሳችሁ ታልቃላችሁ፡፡ ከጉድባው ሄደን ካልተዋጋን የምትሉ ሰዎች ሜዳው ላይ ሆናችሁ ጣሊያን ውሃ እንዳይቀዳ ለማድረግ እንደማትፈሩ ተስፋ አደርጋለሁ።

ሙሉውን ታሪክ
👇

www.facebook.com/share/1293jsTUSoD/

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

06 Nov, 17:49


እጅግ የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜትር

አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

06 Nov, 17:29


የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ጓድ መንግሥቱ ኃይለማርያም (ሌ/ኮ) በሞስኮ ጉብኝት ሲያደርጉ ፤ ህዳር 7 ቀን 1971 ዓ.ም

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

06 Nov, 16:35


https://youtu.be/fZGXKcm3eHg?si=lCjlN042yPqeVcYL

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

05 Nov, 15:42


https://youtu.be/69UzW8NodMc?si=boUjHd_qwW80mr4U

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

03 Nov, 17:46


የመጨረሻው የወላይታ ንጉስ ካዎ ጦና ጋጋ የልጅ ልጆች:-

➺ ወይዘሮ አየለች አላየህ (በግራ)

➺ ወይዘሮ እልፍነሽ አላየህ (በቀኝ)

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

03 Nov, 17:16


የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዶክተር ምናሴ ኃይሌ በአዲስ አበባ የተደረገው የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ንግግር ሲያደርጉ ፤

ግንቦት 1964 ዓ.ም
አዲስ አበባ

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

02 Nov, 14:07


ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ

ሐረር ቤተመንግሥት ፤

1961 ዓ.ም

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

02 Nov, 10:25


ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም

#በዛሬዋ_ዕለት

ከ 94 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ልዑል አልጋ ወራሹ ንጉሥ ተፈሪ መኮንን በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የንጉሠ ነገሥትነት ዘውድ ጭነው ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የተባሉበት ዕለት ነበር።

ንግስተ ነገስት ዘውዲቱ መጋቢት 22 ቀን 1922 እንዳረፉ ፤ ስልጣኑን የተረከቡት ተፈሪ ከሰባት ወር በኋላ ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም ነበር የስርዓተ-ንግስ በዓላቸው በደማቅ ሁኔታ የተከናወነው፡፡

እነዚያ 7 ወራት በኢትዮጵያ ምድር ታይቶ የማይታወቅ የበዓል ማሸብረቂያ ዝግጅት የተካሄደባቸው ናቸው ፥ ንጉሠ ነገሥቱና እቴጌዋ የሚጓዙበት ሠረገላ ከጀርመን አገር መጣ ፥ ልብሱ ሁሉ በወርቅና በሐር የተሽቆጠቆጠ ነበር፡፡ የአዲስ አበባ ክርንክስ ቤቶች እንዲወገዱ ተደረገ ፥ መንገዱ አስፋልት ሆነ፡፡

ሙሉውን ታሪክ
👇
www.facebook.com/share/p/J1pYEP3ozdb4zXPL/

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

01 Nov, 18:38


ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም

#በዛሬዋ_ዕለት

ከ 94 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንግሥ በዓል ዋዜማ ፤ የንጉሠ ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለበዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ (ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ የተመረቀበት ዕለት ነበር።

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

01 Nov, 18:34


https://youtu.be/lor9HjgKY5A?si=pi8leBkwx0YrJh7X

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

31 Oct, 20:00


https://youtu.be/Qn4OFZcEKQ0?si=HHBtLTsgfpzkMVKN

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

31 Oct, 14:12


ራስ ብሩ ወልደገብርኤል

ራስ ብሩ ለአፄ ምኒልክ ስመጥር መኳንንት አንዱ ከሆኑት ደጃች ወ/ገብርኤል በ 1882 ዓ.ም ተወለዱ። ደጃ. ወ/ገብርኤል ከሚኒልክ ጋር በነበራቸው ልዩ ቀረቤታና ታማኝነት ሳቢያ እርሳቸው ሲሞቱ ልጃቸው ከልዑላን ጋራ በታላቁ ቤተ መንግስት ውስጥ አደጉ።

በዚህም ለምሳሌ ራስ ብሩ በልጅነታቸው በቤተመንግስት የግብር አመጋገብ ደረጃቸው ከልጅ ኢያሱ ሚካኤል፣ከራስ ተፈሪ (በኋላ አፄ ኃይለስላሴ) እና ከራስ ጌታቸው አባተ ቧያለው ጋር የተስተካከለ ነበር።

ራስ ብሩ የራስ ማዕረግ እስከሚያገኙ ድረስ በአገሪቱ ጦር ውስጥ ከፍተኛ ስም አትርፈዋል። በማይጨው ከባድ ተጋድሎ ያደረጉ ጀግና መሪም ነበሩ። የጦር ሚኒስትር ሆነውም አገልግለዋል።

ራስ ብሩ በአለባበሳቸው ሽቅርቅርና ስልጡን መስፍን ነበሩ። መኪና ትራንስፖርት ከመጣ በኋላ እርሳቸው በመኪና እየሄዱ በፈረስ ይታጀቡ ነበር።

ራስ ብሩ ሰፊ ሀብት የነበራቸው ቱጃር መስፍን ነበሩ። ሌላው የራስ ብሩ መለያ ለጋስነታቸው ነው። በዘመኑ የራስ ብሩን ያህል ግብር የሚያበላ መስፍን አልነበረም። 'ግብርስ እንደ ራስ ብሩ’ ይባልላቸውም ነበር።

የራስ ብሩ ወ/ገብረኤል መኖሪያ ቤታቸው ከመስቀል አደባባይ ከፍ ብሎ ኮረብታው ላይ ጎልቶ የወጣው ህንጻ ነው። ህንፃው የህንዶች የኪነ-ህንጻ አሻራ ያረፈበትና በ 1912 ዓ.ም ገዳማ የተሰራ ሲሆን የራስ ብሩን ዘመናዊ ቤት አሰራር የተመለከቱ በርካቶች መሳፍንትና መኳንንት የእርሳቸውን አርዓያነት በመከተል የውጭ አገር መሀንዲሶች እየከፈሉ ዘመን ተሻጋሪ ቤቶችን አስገንብተዋል። የመስቀል ደመራ በዓል ማክበሪያ ቦታም መጠሪያ ስሙ ራስ ብሩ ሜዳ ይባል ነበር።

➺ ከታች በምስሉ ላይ የሚታዩ ራስ ብሩ ፎቶ የተነሱት የደጃዝማች ማዕረግ በነበሩበት ወቅት ነበር።
#rare#photo

#ታሪክን_ወደኋላ

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

29 Oct, 19:43


የመጀመሪያዎቹ 7ቱ የግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የካቢኔ ሚኒስትር ተሿሚዎች ፤

ግንቦት 2 ቀን 1933 ዓ.ም

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

29 Oct, 17:05


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች

በ 1961 ዓ.ም

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

29 Oct, 15:34


በቀዳማዊ ኃይለሥሳሴ ዘመን እንግሊዝም ከኢትዮጵያ ምፅዋት ተቀብላ ነበር።

ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ በክረምቱ በዘነበው ኃይለኛ ዝናብ ምክንያት ጉዳት ለደረሰበት አገር ለእንግሊዝ እርዳታ ገንዘብ ልከው ነበር። ይህም እርዳታ በሌጋሲዮኑ በኩል ሲላክ ቀጥሎ ያለው ደብዳቤ አብሮ ተልኳል፡፡

ለክቡር ሚዬሪክናሺ ናልዲስትሬስ ሎንዶን:-

“ምንም እንኳን እኛም ራሳችን በሕዝባችን ላይ ያለ አግባብ በግፍ የደረሰበትን ጉዳት በማቃለል ሥራችን ላይ ብንሆንም ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቀው ኃይለኛና ጨካኝ በሆነው ክረምት ምክንያት ሁልጊዜ በምናስባት ለምለምና ውብ በሆነች አገርዎ ላይ ለደረሰው ጥፋት መጠነኛ የገንዘብ እርዳታ መጠየቅዎን ስለሰማን የገንዘቡ ቁጥር ምንም ከፍ ያለ ባይሆንም የኛንና የሕዝባችንን እርዳታ ለመግለፅ ያህል አንድ ሺህ ፓውንድ በሌጋሲዮናችን በኩል ልክንልዎታል።

(ብርሃንና ሰላም መጽሔት 1946 ዓ.ም)

በስምግባር የታነፀችና ሃይኖራት የምትቸር የትንሽ ትልቅ የሆነች ውድ እትዮጵያንን ውለታዋን እየረሱ በየታሪክ አጋጣሚው የታላላቅ አገሮች ወይም የእንግሊዝና ተፅዕኖ የማይለያት ለመሆኗ ባለፈው ወር የጣሉባትን ማዕቀብ ማስታወስ ይገባል።

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

29 Oct, 13:14


የመከላከያ ሚኒስትር ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህንፃዎች አጠቃላይ ዕይታ ፤

ነሐሴ -- 1960 ዓ.ም
አዲስ አበባ

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

29 Oct, 09:28


የኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩት ሌተናል ጄነራል መርዕድ መንገሻ ከባለቤታቸው ከወይዘሮ ገበያነሽ ኃይለ ሥላሴ ጋር ፤

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

©️ Solomon Zenah-bezu Messai

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

28 Oct, 19:33


ሰኔ 1987 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ላይ በተዘጋጀው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ የአፍሪካ መሪዎች ወደ ከተማዋ የመጡበት ወቅት ነበር። ከተገኙት መሪዎች መካከል አንዱ የግብፅ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ ናቸው።

ሆኖም በዕለቱ ያልታሰበ ከባድ ነገር በከተማዋ ላይ ተፈጠረ፤ ክስተቱም በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ፕሬዝዳንት ሆስኒ ከአዲስ አበባ አየር ማረፊያ ተነስተው ወደ ጉባኤው በሚሄዱበት ወቅት ከአውሮፕላን ማረፊያ በቅርብ ርቀት በሚገኘው የፍልስጤም ኤምባሲ አቅራቢያ 2 ተሽከርካሪዎች ወደ ዋናው መንገድ በመግባትና መንገዱን በመዝጋት ኤኬ-47 የተባለውን መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች ከተሽከርካሪዎቹ ወጥተው ፕሬዝዳንቱን ለመግደል ቶክስ የከፈቱበት ሙከራ ነበር።

ከዚያም የሙባረክ የፕሬዚዳንታዊ ጥበቃዎችና የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች በሽብርተኞቹ ላይ የመልስ ምት የተኩስ ጥቃት በወሰዱት እርምጃ 2 ወዲያውኑ ሲገደሉ 1ኛው በከባድ ቆስሏል።

በሁኔታው አስገራሚው ነገር የነበረው በወቅቱ ፕሬዝዳንቱ ላይ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው በህይወት መትረፋቸው ነው።

"በድንገት አንድ መኪና ከፊታችን መንገዱን ዘግቶ ቆመ! ከዚያም ከውስጡ አንድ ሰው ወጥቶ ወደ እኛ መተኮስ ጀመረ። የተኮሱብኝን በሚገባ አይቻቸዋለሁ" (ፕሬዝዳንቱ ስለተፈጠረው ሁኔታ የተናገሩት)

ከላይ በምስሉ ላይ በወቅቱ ፕሬዝዳንቱን ለመግደል የሞከሩት ታጣቂዎች የተጠቀሙበት ተሽከርካሪ መኪና፣ ለጥቃቱ አላማ ታስቦ ሊውል የነበረው የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና በኢትዮጵያ ፖሊስ በተያዘበት ወቅትና ስለጥቃቱ (The Ethiopian Herald) በሰኔ 20/ 1987 የፊት ገፁ ላይ ያወጣው እትም ምስል ናቸው።

#ታሪክን_ወደኋላ

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

28 Oct, 12:31


የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ቤተመንግሥት

በዘመኑ የነበረው ገፅታ ፤ 1909 ዓ.ም

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

28 Oct, 11:54


የጎንደር ገበያ በዘመኑ ፤

ግንቦት -- 1907 ዓ.ም

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

24 Oct, 20:41


ልዑል መኮንን ኃይለ ሥላሴ (መስፍነ ሐረር) ህይወታቸው ያለፈው ምክንያት በመኪና አደጋ ስለመሆኑ ምስክርነት ሲሰጡ ፤

(ግንቦት 24 ቀን 1949 ዓ.ም)

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

24 Oct, 20:36


ጥቅምት 14 ቀን 1900 ዓ.ም

#በዛሬዋ_ዕለት

ከዛሬ 117 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በሀገራችን የዘመናዊ የመንግስት አስተዳደር ስርዓት ካመጡት መሪዎች አንዱ የሆኑት ዳግማዊ አፄ ምኒልክ የሚኒስቴር መስሪያ ቤት በማቋቋም እና በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያዎቹ ለዘጠኙ ሚንስትሮቻቸው ሾሙት የሰጡበት ዕለት ነበር።

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

22 Oct, 18:44


ኢትዮጵያ የወገንና የቡድን መከፋፈል የሚያስፈልጋት አይደለችም፡፡ ዛሬ የምናገረው ፤ እንደ እያንዳንዳችሁ እንደ አንዱ ኢትዮጵያዊ ሆኜ ነው፡፡ አንድ ግብ ብቻ ነው ያለን - ኢትዮጵያ፡፡ አንድ መተባበሪያ ዓላማ ነው ያለን - ኢትዮጵያ፡፡ አንድ ፕሮግራም ብቻ ነው ያለን ኢትዮጵያ፡፡

ፀሐፊ ትዕዛዝ ክቡር አቶ አክሊሉ ሀብተወልድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በተሾሙበት ዕለት ያደረጉት ንግግር (ሚያዝያ -- 1958 ዓ.ም)

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

22 Oct, 16:59


በእጅግ የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የተሳለው የኢትዮጵያዊቷ ሴት (ወ/ሮ እሌኒ አብርሃም) ምስል ፤

የተሳለው በ 1947 ዓ.ም ፤ ሮም ከተማ

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

22 Oct, 16:26


ጥቅምት 12 ቀን 1923 ዓ.ም

#በዛሬዋ_ዕለት

ከ 94 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን አንጋፋው ደራሲ ፣ ጋዜጠኛ ፣ ተርጓሚና ገጣሚ አቶ ማሞ ውድነህ በቀድሞው የወሎ ክፍለሃገር በዋግ አውራጃ ዐምደ ወርቅ ከተማ ውስጥ የተወለዱበት ዕለት ነበር።

ደራሲና ጋዜጠኛ ማሞ ውድነህ ከአባታቸው ከአቶ ውድነህ ተፈሪ እና ከእናታቸው ወይዘሮ አበበች ወልደየስ በወርሃ ጥቅምት 12 ቀን 1923 ዓ.ም በዋግ አውራጃ ዐምደ ወርቅ ከተማ ተወለዱ።

ገና በልጅ እድሜያቸው ወላጆቻቸውን በአምስቱ አመት የጣሊያን ወረራ ጊዜ ነበር ያጡት። ማሞ ውድነህ 12ኛ ክፍልን ያጠናቀቁት ገና በ15 ዓመት እድሜያቸው መሆኑ በጊዜው ተደናቂ ወጣት አድርጓቸው ነበር።

👇 ሙሉውን ታሪክ

www.facebook.com/share/p/Pw9i8FE6rSRXBcqW/

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

22 Oct, 15:21


https://youtu.be/dFJD5v9S73w?si=O-kI7EtrgbDDwwLd

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

20 Oct, 20:11


108 መንገደኞችን አሳፍሮ የነበረውን የሶማሊያ አውሮፕላን የጠለፉት 5 ታጣቂዎች አዲስ አበባ አየር ማረፊያ የነበራቸው የድርድር ሂደት ፤
ህዳር - 1977 ዓ.ም
👇👇👇

https://youtu.be/5ubZL8aHaZY?si=OnxADULJOoWE_Mgt

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

20 Oct, 16:47


በመዲናዋ አዲስ አበባ የሚገኙ ተማሪዎች የፈንጣጣ በሽታ የመከላከያ ክትባት ለመከተብ በአዲስ አበባ ስታዲየም ውስጥ ተሰብስበው ይታያሉ ፤

ህዳር -- 1967 ዓ.ም

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

20 Oct, 09:35


ጥቅምት 10 ቀን 1961 ዓ.ም

#በዛሬዋ_ዕለት

ከ 56 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ጀግናወሰ ኢትዮጵያዊው አትሌት ሻምበል ማሞ ወልዴ በሜክሲኮ ኦሊምፒክ የማራቶን ውድድር ላይ 2:20:26 ሰዓት በመግባት ለሀገሩ 🥇የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘበት ዕለት ነበር።

አትሌት ሻምበል ማሞ ወልዴ በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ታሪክ በአንድ ኦሊምፒክ ሁለት ሜዳሊያ ያገኘ ቀዳሚው አትሌት ነው። ከማራቶን ድሉ አንድ ሳምንት በፊት በ 10 ሺሕ ሜትር በኬንያዊው ናፍታሊን ቴሙ በሽርፍራፊ ሴኮንዶች ተቀድሞ 2ኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ አግኝቶ ነበር።

በአንድ እሎምፒክ ታሪክም ረጅም ኪሎ ሜትሮችን ሸፍኖ የሮጠ ኢትዮጵያዊ በመሆን በብቸኝነት ስሙ ይጠቀሳል።

ክብርና ሞገስ ለጀግናው አትሌት ሻምበል ማሞ ወልዴ 🙏

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

18 Oct, 20:21


ዐፄ ኃይለሥላሴ ከአለማያ ሐይቅ ከመስመጥ የሞት አደጋ ስለተረፉ የተገጠመላቸው የሙገሳ ግጥም (1916 ዓ.ም)

👇
https://youtube.com/watch?v=YdJludYWmzs&si=5y_0tQcx8eW44tkX

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

18 Oct, 16:05


ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ በምዕራብ ጀርመን ለአራት ቀናት ያደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የተደረገላቸው አቀባበል ፤

አዲስ አበባ ፤ መስከረም -- 1966 ዓ.ም

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

18 Oct, 15:44


ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም ከባለቤታቸው

ከልዕልት አይዳ ደስታ ጋር ፤

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

16 Oct, 19:04


የበረሃዋ ንግስት ከተማ ድሬዳዋ ፤

የምድር ባቡሩ ጣቢያ እና የመንገደኞች ዕቃ በዘመኑ

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

16 Oct, 18:43


(Google) ጎግል ካምፓኒ ለጀግናው አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ የ 81ኛው ዓመት የልደት ቀኑን በማስመልከት እንኳን ተወለድክ በማለት በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ ሲወዳደር የመጨረሻውን መስመር ሲያልፍ የነበረውን የምስሉን ገፅታ በፊት (Search Engine) ገፁ ላይ አቅርቦት ነበር።

ነሐሴ 1 ቀን 2005 ዓ.ም

ዘላለማዊ ክብር ለጀግናው አቤ 🙏

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

16 Oct, 17:35


አዲስ አበባ ከተማ በዘመኗ ፤

ህዳር 1967 ዓ.ም

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

15 Oct, 18:25


አስካለ ነጋ ቦንገር

በ 1966ቱ አብዮት የወጣቶች ንቅናቄ ወቅት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳለች ኢትዮጵያ ዜጎቿ በእኩልነት የሚኖሩባት የተሻለች ሀገር ለማድረግ ህልም ቋጥራ መስዋእት የከፈለች የነፃነት ሰማእት ናት።

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች በኢሕአፓ ስር ተድራጅተው ከወንድ ጓዶቻቸው ጋር ጎን ለጎን በመቆም የደርግ ፋሺስታዊ አገዛዝን በመቃወም የስርአትን ለውጥ ለማምጣት ታግለዋል ፤ እራሳቸውንም አሳልፈው ለትግሉ ሰጥተዋል።

ከእነኝህ እንቁና ጀግና ወጣቶች አንዷ አስካለ ነጋ ናት። በ 1966 ዓ.ም አስካለ ነጋ በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በአራት ኪሎ ካምፓስ የሳይንስ ፋኩሊቲ ውስጥ በብዙ ጓደኞቿ "አስኩ" በመባል የምታወቀው አስካለ ነጋ ያኔ 2ተኛ አመትን ጨርሳ ወደ 3ተኛ አመት እየገባች ነበር።

የወ/ሮ አበበች ወ/ጊዮርጊስና የአቶ ነጋ ቦንገር ልጅ የሆነችው አስካለ በጓደኞቿ በጣም የምትወደድ፤ ተግባቢ በጣም ደግና እሩህሩህ እንደነበረች ብዙዎች ይናገራሉ።

በትምህርቷ በጣም ጎበዝ የነበረችው አስካለ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርቷን በአፄ ልብነድንግል የ 2ተኛ ደረጃ ትምህርቷን ደግሞ በመድሃኒዓለም ት/ቤት ካጠናቀቀች በኋላ በከፍተኛ ውጤት አልፋ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እጅ የወርቅ ቀለበት ተቀብላ ፤ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ገብታ ተከታትላለች።

አስካለ በኢሕአፓነት ስትታገል ቆይታ በ 1970 መጨረሻ አካባቢ በአንጃዎች ጥቆማ ተይዛ ለእስር ስትዳረግ የድርጅቷን ሚስጥር ላለማውጣትና ጓዶቿን ለፋሺስት ደርግ አሳልፋ ላለ መስጠት cyanide...(መርዝ) በመዋጥ እራሷን በማጥፋት በጀግንነት ተሰውታለች። አስካለ የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ታላቅ እህት ነበረች።

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

15 Oct, 17:37


የዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ሐውልት ታሪክ

ኢጣሊያኖች በመጀመሪያው የአድዋ ጦርነት ላይ በሽንፈት አንገታቸውን ደፍተው እና በውጊያ ተሸንፈው ተባረዋል።

ሆኖም በ 1928 ዓ.ም ለ 2ተኛ ጊዜ ሀገራችን በወረሩበት ጊዜ የመጀመሪያው የሽንፈታቸው ታሪክ እልህ አና ቁጭት ውስጣቸው ስለ ነበረ ሀምሌ 4 ቀን 1928 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚገኘው የዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ሀዉልት በምሽት ከቆመበት ስፍራ ነቅለው በምስጢር ቀበሩት።

ከዚያም በጀግኖች አርበኞች የኢትዮጵያ ህዝብ ተጋድሎ ጣሊያን በማሸነፍ ኢትዮጵያ ከፋሺስት ነፃ በሆነችበት ጊዜ ሀውልቱ ከተቀበረበት ወጥቶ በሚያዝያ 27 ቀን 1934 ዓ.ም ዳግመኛ በቦታው እንዲቆም ተደረገ።

ክብር ለኢትዮጵያውያን አርበኞቻችን !!!

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

13 Oct, 19:56


ከ 1952 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ -ክርስቲያን ፓትርያርክ ሆነው የተሾሙት ስድስቱ ፓትርያርኮች ፤

#ታሪክን_ወደኋላ
#TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

13 Oct, 12:46


ጥቅምት 3 ቀን 1957 ዓ.ም

#በዛሬዋ_ዕለት

ከ 60 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ገጣሚ ፣ ሰዓሊ፣ ቀራፂ ፣ ሙዚቀኛ ፣ ፖለቲከኛ ፣ የፎቶግራፍ ባለሙያ ፣ ነጋዴ ፣ ሹፌር እና ባለቅኔ.....የነበሩት ነጋድራስ ተሰማ እሸቴ በተወለዱ በ 88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩበት ዕለት ነበር፡፡

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

13 Oct, 10:41


https://youtu.be/sMwSO1wcWOA?si=eCZ4M0PK9FrXuLbw

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

11 Oct, 13:09


ግርማዊ ቀዳማዊ አጤ ኃይለሥላሴ ከ 3ቱ ወንድ ልጆቻቸው ጋር

➺ ልዑል ሳህለሥላሴ ኃይለሥላሴ
➺ ልዑል አልጋወራሽ አስፋወሰን ኃይለሥላሴ
➺ ልዑል መኮንን ኃይለሥላሴ

በቀድሞው ነገት ልዑል ቤተመንግሥት የአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፤

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11

ታሪክን ወደኋላ - Tarikn Wedehuala

09 Oct, 17:10


ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ

በድሬደዋ የምድር ባቡር ጣቢያ

በ 1925 ዓ.ም

#ታሪክን_ወደኋላ #TariknWedehuala

youtube.com/@tariknwedehuala11