🕯በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት የነበሩ፡፡ የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ አላፊ ጠፊ ሆነው እናስተውላቸዋለን፡፡ ሌላው ይቅርና በሽታ እንኳን ሩቅህ አይደለም፣ የተዘረጋው እጅ አሁን በቅፅበት ማጠፍ ሊቸግርህ ይችላል። በሃብታችን በእውቀታችን በዝናችን .... አለን ባልነው ነገር ሁሉ መማፃደቁ ከንቱ ነው .... ሌላው ቢቀር የዘረጋነውን የምናጥፈው በፈጣሪ ቸርነት ነው።
💡ታላቁ እስክንድር ወደ ሞት አፋፍ መቃረቡን ሲያውቅ፤ ወዳጆቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው "ስትቀብሩኝ፤ እጄን ወደ ላይ አርጋችሁ ቅበሩኝ" አለ። ሰዎቹም ግራ ገብቷቸው ለምን እንደሆነ ጠየቁት፤ እሱም መልሶ ፤ "እጄን ወደላይ አድርጋችሁ ቅበሩኝ ያልኩት፤ ስሞት ከምድር ምንም ነገር ይዤ እንዳልሄድኩኝ ሰዎች እንዲያዩ ነው " አለ። ይህንን ያለው እንግዲህ በጊዜው አለምን ያስገበረው ታላቁ እስክንድር ነው።
🔷ብርሌ በመሰለ ዓለም ፡ መጥፊያው ሰፊ መልሚያው ጠባብ በሆነ ኑሮ፣ በዙፋን ላይ ካለ ንጉስ በፈጣሪው የታቀፈ አማኝ ይበልጣል!! Impermanenceን በቅጡ የተረዳነው ያህል ሆኖ ያታልለናል። በሕይወት መንገድ ስለ ጤዛነት ብዙ እያየንም አልማር ብሎ የፈተነን አንጎላችን ብዙ ያነበብነና ያወቀ ይመስለዋል።
ማጠቃለያው፣
📍ህይወትን ቀለል አርገህ ኑር፡፡ ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ እንደ ትልቅ ሀብት የምናያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡
ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መከባበርን እናስቀድም፣ከጀርባ መወጋጋት፣ መጠላለፍ አክሳሪ ነው፡፡ ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡ የሰው ሕይወት በምድር ላይ በጣም አጭር ናት። ኑሮ ማለት ደግሞ በውልደት እና በሞት መካከል ያለ የመሸጋገሪያ ጊዜ ነው። በድንገት ተጀምሮ በድንገት የሚቆም የመሸጋገሪያ ጊዜ.......
💡ቃሉም እንደሚለው "ሕይወታችሁ ምንድን ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁና።ያዕ 4፡14
💡ሀዲሱም እንዲል "ምድር ላይ ስትኖር እንደ እንግዳ እንደ መንገደኛ እንደ አልፎ ሂያጅ ሆነህ ኑር" (ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ )
🔑 በዚህ ዓለም ላይ ምንም ቋሚ የሚባል ነገር የለም እንኩዋን ሰውና ግዑዝ ነገር ሁሉ አላፊ ነው . . . እንደ አልፎ ሂያጅ አልሆንም ብንልም ማለፋችን አይቀርምና መልካም ስራን ለነፍሳችን እናስቀድም ዘንድ ፈጣሪ ያግዘን።
ውብ አሁን❤️
@Ethiohumanity
@EthioHumanity
✍ @EthioHumanitybot