ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ @zkretewahdo Channel on Telegram

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

@zkretewahdo


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

. #ዝክረ_ቅዱሳን
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ
፩.ግጻዌ
፪.የዘወትር፡ስንክሳር 📖
፫.መዝሙር
፬.ዜና ቤተክርስቲያን ፡ ምክር፡ለወዳጅ እና
የተለያዩ ፡መርሃ-ግብሮች፡ይቀርቡበታል

ማንኛውንም ሀሣብ፡ አስተያየት እንዲሁም ጥቆማ በ @zikrekdusannbot ላይ
ቢያስቀምጡልን ይደርሰና

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ (Amharic)

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ ማንኛውንም ሀሣብ፡ አስተያየት እንዲሁም ጥቆማ እንዳውጅ አስታውሱልን በየብዙ ስእላችሁ እስርቤት ይሰጣል። በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ይችላል፡

አልባሳቱ እና ላሁኑ ፡ ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ፡
፩.ግጻዌ
፪.የዘወትር፡ስንክሳር 📖
፫.መዝሙር
፬.ዜና ቤተክርስቲያን ፡ ምክር፡ለወዳጅ እና
የተለያዩ ፡መርሃ-ግብሮች፡ይቀርቡበታል ። ይህ ስራ ሁለቱንም ሚሊዮንን ብቻ ሲሆን አገልግሎታችንን በስተጀምሮ ዋናውን የበለጠ ጥሩ ትምህርትን እንቅስቃሴ። በዚህ ስእላችሁ ከዚህ ተወላጅሞአምሊሳችንን ዕቅድ ስለሚል ጠብቅቋችንን።

ለተጨማሪ መረጃችን እና መረጃ ለእናንተም ድረስ እንኳ ከእነሱ እኮ ነውና።

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

12 Feb, 04:00


† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን †

††† እንኩዋን ለአባታችን "አባ ብሶይ ዼጥሮስ" እና "ቅዱስ ዕብሎይ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

††† አክርጵዮስ †††

በዚች ቀን የእስክንድሪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት የከበረ አባት አክርጵዮስ አረፈ። እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አስረኛ ነው። ይህም አባት እግዚአብሄርን የሚፈራ ንፁህ ቅዱስ ነው ።

በእስክንድርያ አገርም ቄስ ሆኖ የሚያገለግል ነበር ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ ከላድያኖስ በአረፈ ጊዜ የእስክንድር አገር ህዝብና ኤጲስቆጶሳቱ መረጡት በወንጌላዊው ማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት።

ከዚህም በኃላ እንደ ሀዋሪያት መልካም ጉዞን ተጓዘ የእግዚአብሄርን ሀይማኖት ህይወት የሆነ ህጉንም እያስተማረ ቅዱሳት መፅህፍትንም እያነበበላቸውና እያስተማራቸው መንጋዎቹን ይጠብቃቸው ነበር ሁል ጊዜም ይመለከታቸዋል አንድ የብር አላድን ወይም አንድ የወርቅ ዲናርን ጥሪት አላኖረም ከእለት ምግቡ ከቁርና ከሀሩር ስጋውን ከሚሸፈንበት ልብስ በቀር ምንም አላከማቸም።

በዚህም ተጋድሎ አስራ ሁለት አመት ኑሮ ጌታችንንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።

+*" ቅዱስ ዕብሎይ "*+

=>አባ ዕብሎይ በቀደመ ሕይወቱ ለ40 ዓመታት በኀጢአት የኖረ: እግዚአብሔር ለንስሃ ሲጠራው "እሺ" ብሎ : ለ40 ዓመታት በንስሃ ሕይወት ተመላልሶ በበርሃ የተጋደለ: እንባው እንደጐርፍ ይፈስ የነበረ: አጋንንትንም ድል የነሳና ለፍሬ: ለትሩፋት የበቃ ቅዱስ አባት ነው:: እግዚአብሔርም ብዙ ቃል ኪዳን ገብቶለታል::

<< ባርያ ሆኖ ያለ ኀጢአት: ጌታ ሆኖ ያለ ምሕረት የለምና ይቅር በለን !! >> (የአባ ዕብሎይ የንስሃ ጸሎት)

+*" አባ ብሶይ (ዼጥሮስ) "*+

=>ብሶይ (ቢሾይ) በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የተለመደ
የቅዱሳን ስም ነው:: በተለይ በምድረ ግብ በዚህ ስም
ሰማዕታትም : ጻድቃንም ተጠርተውበታል:: ከእነዚህ
ቅዱሳን (ከገዳማውያኑ) አንዱ የሆነው አባ ብሶይም
(አንዳንዴ አባ ዼጥሮስም ይባላል) የዘመነ ጻድቃን ፍሬ
ነው::

+ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳን ቤት ናት:: ያ ማለት ራሳቸውን
ለክርስቶስ የለዩ ሰዎች ይኖሩባታል:: እነዚህ ሰዎች
ከተለያየ ጐዳና እና ማንነት ሊመጡ ይችላሉ:: ቢያንስ ግን
በንስሃ የታጠቡ መሆናቸው ወደ ተቀደሰው አንድነት
እንዲገቡ ትልቅ መሠረት ይሆናቸዋል::

+ቅዱሳንም አንዳንዶቹ ከእናታቸው ማኅጸን ሲመረጡ :
ሌሎቹ ደግሞ ከኃጢአት ሕይወት የተመለሱ ሆነው
ይታያሉ:: ደስ የሚለው ደግሞ በንስሃ ከታጠቡ በሁዋላ
በፍጹም ልባቸው በመጋደላቸው እነሆ በሰማያዊ አክሊል
ተከልለዋል::

+አባ ብሶይ ዼጥሮስም ከኃጢአት ተመልሰው ለቅድስና
ከበቁ ቀደምት አበው አንዱ ነው:: ቅዱሱ ተወልዶ
ባደገባት ምድረ ግብጽ የታወቀ ሽፍታ : ዝሙተኛና ክፋቱ
የተገለጠ ሰው ነበር:: ለብዙ ዘመናት በእንዲህ ካለ ግብሩ
መላቀቅ ባይችል እግዚአብሔር ጥሪውን ላከለት::

+የአምላካችን የጥሪ መንገዱ ብዙ ነውና ለእርሱ ደዌን
ላከለት:: መቼም ወደድንም ጠላንም በሽታ ወደ
እግዚአብሔር የሚያቀርብ ጥሩ ፈሊጥ (አጋጣሚ) ነው::
ዛሬም ቢሆን ዘለን : ዘለን ስንሰበርና የሐኪም መፍትሔ
ሲጠፋ የግዳችን ወደ እግዚአብሔር ቤት (ወደ ጸበሉ)
እንቀርባለንና:: አምላካችን ስለዚህ ጥበቡ ይክበር
ይመስገን::

+ቅዱስ አባት ብሶይም በሽፍትነትና በኃጢአት ኑሮ ሳለ
ለሞት የሚያበቃ ደዌ ደርሶበት የአልጋ ቁራኛ ሆነ::
ኃይሉም ደከመ:: በእንዲህ እያለም በራዕዩ ያየው ነገር
ፍጹም አስደነገጠው::

መላእክት ነፍሱን ወስደው መካነ ኩነኔን ካሳዩት በሁዋላ
አለቀሰ::

+ይልቁን ሌቦችና ዝሙተኞችን ከ4 ሲቆራርጣቸው ስላየ
ፈጽሞ አዘነ : ተጸጸተ:: ፈጣሪውንም ዕድሜ ለንስሃ
እንዲሰጠው ተማጸነ:: ጌታንም "አምላኬ ሆይ! ከበሽታየ
ብታድነኝ : ዳግመኛ አልበድልህም:: ዓለምን ሁሉም ንቄ
አገለግልሃለሁ" ሲል ተማጸነው::

+እግዚአብሔርም ሰምቶት ፈጥኖ ፈወሰው:: አባ ብሶይም
እንደ ቃሉ በፍጹም ልቡ ንስሃ ገብቶ መነነ:: በገዳመ
አስቄጥስ (ግብጽ) ለ38 ዓመታት ሲኖር የላመ የጣመ
በልቶ : ከሞቀ መኝታ ተኝቶ አያውቅም::

+ሰውነቱን ይቀጣት ዘንድም እስከ 30 ቀን ያለ እህል ውሃ
ይጾም ነበር:: በዘመኑ ሁሉም የሴት መልክን አላየም::
ንስሃን የሚወድ ጌታም ጸጋውን አብዝቶለት ብዙ ድርሳናትን
ጽፏል:: የሚገርመው ደግሞ ከትህትናውና ቅድስናው
የተነሳ የእያንዳንዱ ሰው ኃጢአት ተገልጦ ይታየው ነበር::

+ቅዱሱ አባታችን ብሶይ ዼጥሮስ በንስሃና በቅድስና
ሕይወት እንዲህ ተመላልሶ በዚህች ቀን ዐርፎ በገዳሙ
ተቀብሯል:: የድካሙን ዋጋም አድልዎ ከሌለበት :
ከእውነተኛው ፈራጅ ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
ተቀብሏል::

=>አምላከ ቅዱሳን ዕድሜ ለንስሃ : ዘመን ለፍስሐ
አይንሳን:: ከክብረ ቅዱሳንም ያካፍለን . . . አሜን !!

=>የካቲት 5 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አባ ዕብሎይ ገዳማዊ
2.ቅዱስ አባ ብሶይ ጻድቅ
3.አባ አክርዽዮስ
4."49" አረጋውያን ሰማዕታት (ፍልሠታቸው)
5.ቅዱስ አሞኒና ሚስቱ ቅድስት ሙስያ (የታላቁ ዕብሎይ ወላጆች)
6.አባ ኖብ ጻድቅ : መነሳንሱ ዘወርቅ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት
2.ቅዱስ ዻውሎስ ሐዋርያ
3.አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
4.ቅዱስ ዮሐኒ ኢትዮዽያዊ
5.ቅዱስ አሞኒ ዘናሒሶ

=>አምላክ በበረከታቸው ይባርከን::

=>+"+ መቶ በግ ያለው : ከእነርሱም አንዱ ቢጠፋ ዘጠና ዘጠኙን በበርሃ ትቶ የጠፋውን እስኪያገኘው ድረስ ሊፈልገው የማይሔድ ከእናንተ ማን ነው? ባገኘውም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ይሸከመዋል:: ወደ ቤትም በመጣ ጊዜ ወዳጆቹንና ጐረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ 'የጠፋውን በጌን አግኝቼዋለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ' ይላቸዋል:: እላችሁአለሁ: እንዲሁ ንስሃ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሃ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል:: +"+ (ሉቃ. 15:3-7)

†ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
†ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር አሜን †


© ዝክረ ቅዱሳን ማኀበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zikrekdusannbot

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

11 Feb, 18:19


❀✞ዘነነዌ ረብዕ።✞❀

የየካቲት ፭ #ግጻዌ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺

የዕለቱ ቅዳሴ ምንባባት

🌺📖ወደ ሮሜ ሰዎች ፭ ፥ ፩ - ፮
፩ እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤
፪ በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል፤ በእግዚአብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን።
፫-፬ ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤
፭ በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።
፮ ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና።

🌺📖የይሁዳ መልእክት ፩ ፥ ፳ - ፍጻሜው
፳ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
፳፩ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።
፳፪ አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥
፳፫ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።
፳፬ ሳትሰናከሉም እንዲጠብቃችሁ፥ በክብሩም ፊት በደስታ ነውር የሌላችሁ አድርጎ እንዲያቆማችሁ ለሚችለው
፳፭ ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኃይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።

🌺📖የሐዋርያት ሥራ ፲፬ ፥ ፳፩ - ፳፫
፳፩-፳፪ በዚያችም ከተማ ወንጌልን ሰብከው እጅግ ደቀ መዛሙርትን ካደረጉ በኋላ፥ የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና፦ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ፥ ወደ ልስጥራን ወደ ኢቆንዮንም ወደ አንጾኪያም ተመለሱ።
፳፫ በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው።

ምስባክ ዘቅዳሴ

‹‹ኵሉ ማዕበልከ ወሞገድከ እንተ ላዕሌየ ኃለፈ። መዓልተ ይኤዝዝ እግዚአብሔር ሣህሎ ወሌሊተ ይነግር። እምኀቤየ ብፅዐተ ሕይወትየ ለእግዚአብሔር።››

‹‹ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።
እግዚአብሔር በቀን ቸርነቱን ያዝዛል፥ በሌሊትም ዝማሬው በእኔ ዘንድ ይሆናል፤ የእኔ ስእለት ለሕይወቴ አምላክ ነው።››
🌺📖መዝሙር ፵፩ ፥ ፯ - ፰

ወንጌል ዘቅዳሴ

🌺📖የማቴዎስ ወንጌል ፲፮ ፥ ፩ - ፭
፩ ፈሪሳውያንና ሰዱቃውያንም ቀርበው ሲፈትኑት ከሰማይ ምልክት እንዲያሳያቸው ለመኑት።
፪ እርሱ ግን መልሶ እንዲህ አላቸው፦ በመሸ ጊዜ፦ ሰማዩ ቀልቶአልና ብራ ይሆናል ትላላችሁ፤
፫ ማለዳም፦ ሰማዩ ደምኖ ቀልቶአልና ዛሬ ይዘንባል ትላላችሁ። የሰማዩን ፊትማ መለየት ታውቃላችሁ፥ የዘመኑንስ ምልክት መለየት አትችሉምን?
፬ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። ትቶአቸውም ሄደ።
፭ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ማዶ በመጡ ጊዜ እንጀራ መያዝን ረሱ።

✝️✝️✝️ቅዳሴ፦ዘእግዚእነ

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

11 Feb, 17:55


🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ሥርዓተ ማኅሌት አመ ፭ ለየካቲት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐
የየካቲት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#ሥርዓተ_ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።


የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።


መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለሕፅንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ።


ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ፤ሃሌ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤አክሊለ ሰማዕት ሠያሜ ካህናት፤ወረደ እምሰማይ ዲበ ምድር፤በመስፈርተ ጥበቡ ለአቡሁ።


መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኆኅያቲሁ ቅሩጽ፤ኀበ ዓምደ ብርሃን ጽዱል ወአኮ ዘዕፅ፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኃያል ሠዋቄ ትንቱናን እምዳኅፅ፤ለዝክረ ስምከ ሠናየ ዜና ወድምፅ፤ትሴብሕ ኢትዮጵያ ወትዜምር ግብፅ።


ዚቅ
ለስሙ ይደሉ ስብሐት፤አኰቴት ወክብር፤ርቱዕ ሎቱ ይደሉ።


መልክአ ጴጥሮስ ወጳውሎስ
ውስተ ኵሉ ምድር ወጽአ ነገሮሙ፤ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ፤ጳውሎስ ወጴጥሮስ እለ ከዓዉ ደሞሙ፤ በሞቶሙ ወበሕይወቶሙ ኢተሌለዩ ቀዲሙ፤በድሮሙ ወስምዖሙ ኅቡረ ፈጸሙ።


ዚቅ
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ሰላም ለክሙ ሐዋርያቲሁ ለክርስቶስ፤እለ ተሰመይክሙ፤ወለለ ጽባሑ ዝክሩነ በጸሎትክሙ።


ዓዲ ዚቅ
ውስተ ኵሉ ምድር...በል አመ ፭ ለሐምሌ


መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለገጽከ ዘያበርህ ምስብዒተ፤እምብርሃነ ፀሐይ ዘይኴንን ወዘይመልክ መዓልተ፤ገብረ መንፈስ ቅዱሰ ባዕል እንተ ትዘሩ ምጽዋተ፤ምስሌከ እትቀበል መርዓዌ አመ ይመጽእ ሌሊተ፤እማኅቶትከ ሀበኒ ማኅቶተ።


ዚቅ
ረስየነ ድልዋነ፤ንትቀበልከ መርዓዌ፤በዘይተ ሃይማኖት ጥሉል በማኅቶተ ምግባር ጽዱል፤ከመ ሐምሰ ጠባባት ደናግል፤ወፈጺመነ ኵሎ ዘውስተ ወንጌል፤ንኩን ጸውዓነ ለበዓል።


መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካልዕ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ወለስእርተ ርእስከ ሠርጐ አባል፤ለርእስከ ሰላም ወለገጽከ ጽዱል፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ ርድአኒ ወአድኅነኒ እምኃጒል፤ ዝ ውእቱ ሰዓተ ተአምር ወገድል፤ወዝ ውእቱ ጊዜሁ ለሣሕል።


ዚቅ
ክፍለነ ምስለ ቅዱሳኒከ፤እለ ፃመዉ በእንቲአከ ወሠለጡ ገድሎሙ፤ወአተዉ ኀበ የዓርፉ ለዓለም፤ሀገረ ቅድስተ ሀገረ ሰላም፤በትፍሥሕት መነኑ፤ዓለመ ዘይበሊ፤ያስተፌሥሖሙ አምላኮሙ፤እስመ አድለዉ ሎቱ በሕይወቶሙ።


መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካልዕ
ሰላም ለመላትሒከ ወለተጸፍዖትከ አዕላፍ፤ወለአዕናፊከ ምውዝ ዘምስለ ከናፍር ወአፍ፤እንዘ እሰምዕ ቃለከ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፍ፤ኢሐፀብኩ እግረ እንግዳ ከመ አብርሃምትሩፍ፤ወከመ ጊዮርጊስ ኢይሙት ጐየይኩ እምሰይፍ።


ዚቅ
እንተ ታስተርኢ እምአርእስተ አድባር፤ወትትመረጐዝ በትእምርተ መስቀል።
/እንተ ታስተርኢ እምአርእስተ አድባር ርኁቅ፤ጻድቃን ኪያሃ አብደሩ እምወርቅ፤ሀገረ ክርስቶስ ሐዳስ ንድቅ፤ወበውስቴታ የሐድር ጽድቅ።


መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ካልዕ
ሰላም ለአስናኒከ ወለልሳንከ ቀዳሲ፤ምስለ ቃል ወእስትንፋስ ለብልየተ ጒርዔከ ተሐዳሲ፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸሊ ላዕለ ወልድከ አባሲ፤ምስሌከ ይቁም ለትጹን ድኅረ ጰልሞን ፈላሲ፤ለአድኅኖ ነፍሱ ቆመ ለኃጥእ ብእሲ።


ዚቅ
ጥዑመ ልሳን ምዑዝ ከመ ዕጣን፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ(ገብረ ሕይወት)መርሐ ዕውራን ዘበጽንፈ ልብስከ የሐይ ዱያን፤ስፋሕ እዴከ ዘየማን፤ትባርከነ ለጉቡዓን፤መምህር ዘበአማን።


ምልጣን
ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለተ ኃይል በብርሃኖሙ ለቅዱሳን ወልድ ፍጹም መድኃኔ ዓለም ወልዱ አንተ ወቃሉ ለአብ።


እስመ ለዓለም
ወበእንተዝ እትፌሣሕ ብክሙ እስመ ኅበርክሙ አሚነ ምስሌነ፤በክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር መድኃኒነ፤ዘተወልደ ወመጽአ እምዘርዓ ዳዊት ተአዛዜ ከዊኖ ለአቡሁ፤ያበርህ ላዕለ ጻድቃን።


እመሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕ(የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት)🙏🙏🙏

🌿  @zkretewahdo
🌿  @zkretewahdo
🌿  @zkretewahdo

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

11 Feb, 06:39


@Gozilla_bot

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

11 Feb, 03:44


፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

አርኬ

ሰላም ለአጋቦስ እምአርድእተ ክርስቶስ ዋሕድ ። አመ ወገርዎ በአዕባን ወቀተልዎ አይሁድ ። ተተክለ ብርሃን በአምሳለ ዓምድ ። መልዕልተ ሥጋሁ ቅድመ ጉቡአን በዓውድ ። እስከ አይሁዳዊት ተመይጠት ወአምነት በወልድ

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

11 Feb, 03:40


† እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ አጋቦስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ አጋቦስ ሐዋርያ †††

††† ከ72ቱ አርድዕት አንዱ የሆነው ቅዱሱ ሐዋርያ ሃብተ-ትንቢት የተሠጠውና በዘመነ ሐዋርያት (በቀላውዴዎስ ቄሳር ጊዜ) በዓለም ላይ ከባድ ረሃብ እንደሚሆን ትንቢት የተናገረና በርካታ ክርስቲያኖችን ከረሃብና ከሞት የታደገ ትልቅ ሐዋርያ ነው:: (ሐዋ. 11:27)

በቅዱስ ጳውሎስ ላይ የሚደርሰውን መከራ በመናገሩም "ሐዋርያ ትንቢት" ተብሏል:: በአገልግሎቱ ከአይሁድና ከአረማውያን ብዙዎችን ወደ ክርስትና በመሳቡ የተበሳጩ አይሁድም በዚህች ቀን ገድለውታል:: በተቀደሰ ሥጋው (መቃብሩ) ላይ ብርሃን ሲወርድ ያየች አይሁዳዊት ሴትም በክርስቶስ አምና ተሰውታለች::

††† የአባታችን በረከት ይደርብን::

የ††† ካቲት 4 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አጋቦስ ነቢይ: ሐዋርያና ሰማዕት
2.አባ ዘካርያስ ትሩፈ ምግባር

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ ወልደ ነጎድጓድ
2.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ
3.ቅድስት ሶፊያ ሰማዕት
4.ቅዱስ ዮሐንስ ዘሐራቅሊ

††† "በዚያም ወራት ነቢያት ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ወረዱ:: ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነስቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ:: ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ::
ደቀ መዛሙርትም እያንዳንዳቸው: እንደ ችሎታቸው መጠን አዋጥተው በይሁዳ ለሚኖሩት ወንድሞች እርዳታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ::
እንዲህም ደግሞ አደረጉ:: በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ሰደዱት::" †††
(ሐዋ. ፲፩፥፳፯)

††† "ስለ እኛ ትጸልዩ ዘንድ ይገባቹሃል: ለሁሉ መልካም ነገርን እንደምትወዱና እንደምትሹ እናምናለን::" †††
(ዕብ. ፲፫፥፲፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

© ዝክረ ቅዱሳን ማኀበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zikrekdusannbot

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

11 Feb, 03:36


❀✞ዘነነዌ ሠሉስ✞❀

የየካቲት ፬ #ግጻዌ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺

የዕለቱ ቅዳሴ ምንባባት

🌺📖ወደ ሮሜ ሰዎች ፭ ፥ ፩ - ፮
፩ እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤
፪ በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል፤ በእግዚአብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን።
፫-፬ ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን መከራ ትዕግሥትን እንዲያደርግ፥ ትዕግሥትም ፈተናን ፈተናም ተስፋን እንዲያደርግ እያወቅን፥ በመከራችን ደግሞ እንመካለን፤
፭ በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም።
፮ ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና።

🌺📖፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ፩ ፥ ፲ - ፲፫
፲ ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤
፲፩ በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።
፲፪ ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።
፲፫ ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኖራችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ።

🌺📖የሐዋርያት ሥራ ፰ ፥፲፰ - ፳፭
፲፰ ሲሞንም በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጥ ባየ ጊዜ፥ ገንዘብ አመጣላቸውና።
፲፰ እጄን የምጭንበት ሁሉ መንፈስ ቅዱስን ይቀበል ዘንድ ለእኔ ደግሞ ይህን ሥልጣን ስጡኝ አለ።
፳ ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው፦ የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ።
፳፩ ልብህ በእግዚአብሔር ፊት የቀና አይደለምና ከዚህ ነገር ዕድል ወይም ፈንታ የለህም።
፳፪ እንግዲህ ስለዚህ ክፋትህ ንሰሐ ግባ፥ ምናልባትም የልብህን አሳብ ይቅር ይልህ እንደ ሆነ ወደ እግዚአብሔር ለምን፤
፳፫ በመራራ መርዝና በዓመፅ እስራት እንዳለህ አይሃለሁና።
፳፬ ሲሞንም መልሶ፦ ካላችሁት አንዳች እንዳይደርስብኝ እናንተው ወደ ጌታ ለምኑልኝ አላቸው።
፳፭ እነርሱም ከመሰከሩና የጌታን ቃል ከተናገሩ በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ በሳምራውያን በብዙ መንደሮችም ወንጌልን ሰበኩ።

ምስባክ ዘቅዳሴ

‹‹ወፈርሃ ኵሉ ሰብእ። ወነገሩ ግብረ እግዚአብሔር። ወአዕመሩ ምግባሮ››

‹‹ ሰዎች ሁሉ ፈሩ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ ተናገሩ፥ ሥራውንም አስተዋሉ።››
🌺📖መዝሙር ፷፫ ፥ ፱

ወንጌል ዘቅዳሴ

🌺📖የሉቃስ ወንጌል ፲፩ ፥ ፳፱ - ፴፪
፳፱ ብዙ ሕዝብም በተሰበሰቡ ጊዜ እንዲህ ይል ጀመር፦ ይህ ትውልድ ክፉ ነው፤ ምልክት ይፈልጋል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።
፴ ዮናስ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደ ሆናቸው፥ እንዲሁ ደግሞ የሰው ልጅ ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል።
፴፩ ንግሥተ አዜብ በፍርድ ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነሥታ ትፈርድባቸዋለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳር መጥታለችና፥ እነሆም፥ ከሰሎሞን የሚበልጥ ከዚህ አለ።
፴፪ የነነዌ ሰዎች በፍርድ ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገብተዋልና፥ እነሆም፥ ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ።


✝️✝️✝️ቅዳሴ፦ዘእግዚእነ

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

09 Feb, 03:23


††† እንኳን ለታላቁ ገዳማዊ አባ ጳውሊ እና ለጻድቁ አባ ለንጊኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ታላቁ ቅዱስ ጳውሊ †††

††† በቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ "ታላቁ /ዐቢይ/ THE GREAT" የሚል ስም የሚሰጣቸው አባቶች የተለዩ ናቸው። አንድም እጅግ ብዙ ትሩፋቶችን የሠሩ ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ በተመሳሳይ ስም ከሚጠሩ ሌሎች ቅዱሳን እንለይበታለን።

ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው። በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል። ሕይወቱ በጐላ በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው።

ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል። በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል።

ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለአርባ ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል፤ አስተምሯል። በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት።

ከጌታ ዕርገት በኋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ። አኗኗራቸውም በቡድንም በነጠላም ሊሆን ይችላል። ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው። ይህም ሲያያዝ እስከ ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ደረሰ። በዚህ ዘመን ግን አባ ጳውሊ የሚባል ንጹሕ ክርስቲያን ይህንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው። ለሰማንያ ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ። ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ።

ይህ ከሆነ ከሃያ ዓመታት በኋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት። በቅዱስ ሚካኤል አመንኳሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ። ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ።

እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል። ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል።

አንድ ቀን ቅዱስ እንጦንስ (የመነኮሳት ሁሉ አባት) እንዲህ ሲል አሰበ። "በውኑ በበርሃ ለበርካታ ዘመናት በመኖር ከእኔ የሚቀድም (የሚበልጥ) ሰው ይኖር ይሆን?"
ይህንን ሃሳቡን ገና ሳይጨርሰው ቅዱስ ሚካኤል ወደ እርሱ ዘንድ ደረሰ።

"እንጦንስ ሆይ! ከእኔ የሚቀድም የበርሃ ሰው ይኖር ይሆን ብለህ አስበሃል። በእርግጥም ከአንተ ሃያ ዓመታትን ቀድሞ ወደ በርሃ የገባ፣ በቅድስናው ፈጣሪውን ያስደሰተ፣ ዓለም ከነ ክብሯ የእግሩን መረገጫ ያህል እንኳ የማትመጥነው በጸሎቱና በምልጇው ዓለም የምትጠበቅለት ሞገስን የተሞላ አንድ ሰው በበርሃ ስላለ ሒድና ተመልከተው።" ብሎት ተሠወረው።

ቅዱስ እንጦንስም ከሰማው ነገር የተነሳ እየተደነቀ ተነሳ። እርሱ ካለበት በርሃ በራቀ መንገድም ለቀናት ተጉዞ አንድ በዓት (ዋሻ) በር ላይ ደረሰ። በበሩ አካባቢ የሰውና የአራዊት ኮቴ ተመልክቶ በሩን ጸፋ (ቆፈቆፈ)። በውስጥ ያለው አረጋዊ ሰው ግን ትልቅ ድንጋይ ገልብጦ በሩን አጠበቀው። ለሰማንያ ዓመታት ሰውን አይቶ አያውቅምና ሰይጣን ሊያታልለኝ መጥቷል ብሎ አስቧል። ቅዱስ እንጦንስ ግን "ኃሠሥኩ እርከብ ጐድጐድኩ ይትረኃው ሊተ - ሽቻለሁና ላግኝ፤ ደጅ መትቻለሁና ይከፈትልኝ።" ሲል አሰምቶ ተናገረ።

ቅዱሱ ገዳማዊም ሰው መሆኑን ሲያውቅ በሩን ከፈተለትና ወደ ዋሻው አስገባው። መንፈሳዊ ሰላምታንም ተለዋወጡ። ሲመሽም ቅዱስ እንጦንስ ሽማግሌውን ገዳማዊ "ስምህ ማን ነው?" ቢለው "ስሜን ካላወክ ለምን መጣህ?" ሲል መለሰለት።

ያን ጊዜ ቅዱስ እንጦንስ ቀና ብሎ ሰማይን ሲመለከት ምሥጢር ተገለጠለትና "ቅዱስ ጳውሊ ሆይ! ከአንተ ጋር ያገናኘኝ ፈጣሪ ይክበር፤ ይመስገን።" ሲል ፈጣሪውን ባረከ። ቅዱስ ጳውሊም መልሶ (በጸጋ አውቆት) "አባ እንጦንስ ሆይ! እንኳን ደህና መጣህ።" አለው። ሁለቱም ደስ ብሏቸው ፈጣሪያቸውን እያመሰገኑ ተጨዋወቱ።

ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ዓይነት የቅድስና ሕይወት የመጀመሪያ የምትላቸው አላት። ለምሳሌ፦
የመጀመሪያው ሐዋርያ ቅዱስ እንድርያስ፣
የመጀመሪያው ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ፣
የመጀመሪያው ባሕታዊ (ገዳማዊ) ቅዱስ ጳውሊ እና የመጀመሪያው መነኮስ ቅዱስ እንጦንስን ማንሳት እንችላለን።

ቅዱስ ጳውሊ የተወለደው በሰሜናዊ ግብጽ በእስክንድርያ ከተማ ሲሆን ዘመኑም ሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ነው። ወላጆቹ ባለጸጐች ነበሩ። ቅዱሱንና ታላቅ ወንድሙን አባ ጴጥሮስን ወልደዋል። ሁለቱ ክርስቲያን ወንድማማቾች ገና ወጣት ሳሉ ወላጆቻቸው ሞቱባቸው። ሃዘናቸውን ፈጽመው ሃብት ሲካፈሉ ግን መስማማት አልቻሉም።

ምክንያቱ ደግሞ ትልቁ ጴጥሮስ ደህና ደህናውን እቃ ወስዶ መናኛ መናኛውን ለትንሹ ለጳውሎስ (ጳውሊ) መስጠቱ ነበር። ስለዚህ ነገር ተካሰው ወደ ፍርድ ቤት ሲሔዱ ግን መንገድ ላይ አንድ ባለጸጋ ሙቶ ደረሱ።

ቆመው ሳሉም ቅዱስ መልአክ ሰው መስሎ ጳውሊን "ይህ ሰው ባለጸጋ ነው። በገንዘቡ የሰጠውን ፈጣሪ ሲበድልበት ኑሮ እነሆ ተሸኘ። በሰማይም አስጨናቂ ፍርድ ይጠብቀዋል።" ሲል ነገረው።

በዚያች ቅጽበት የወጣቱ ጳውሊ ሐሳብ ተለወጠ። ወደ ወንድሙ ተመልሶ "ወንድሜ ሆይ! ሁሉ ንብረት ያንተ ይሁን።" ብሎት ከአካባቢው ጠፋ። በመቃብር ሥፍራ ለሦስት ቀናት ያለ ምግብ ጸልዮ የእግዚአብሔር መልአክ ሰው ወደ ማይደርስበት በርሃ ወሰደው።

በዚያም ምንጭ ፈለቀችለት። እየጾመ ይጸልይ ይሰግድ ገባ። ሁሌ ማታ ግማሽ ሕብስት ከሰማይ እየወረደለት ቅዳሜና እሑድ መላእክት እያቆረቡት ለሰማንያ ዓመታት ኖረ። (አንዳንድ ምንጮች ግን ለዘጠና ዓመታት ይላሉ።) ከቅዱስ እንጦንስ ጋር የተገናኙትም ከዚህ በኋላ ነው።

ከቅዱስ እንጦንስ ጋር በነበራቸው የሁለት ቀናት ቆይታም ቅዱስ ጳውሊ ብዙ ትንቢቶችን ተናግሯል። በዚህች ቀን ሲያርፍም መቃብሩን አናብስቱ ቆፍረዋል። ቅዱስ እንጦንስም በክብር ቀብሮታል። ለሰማንያ ዓመታት የለበሳት የዘንባባ ልብሱም ሙት አስነስታለች።

††† ጻድቅ፣ ቡሩክ፣ ቀዳሚው ገዳማዊ፣ መላእክትን የመሰለና የባሕታውያን ሁሉ አባት ለተባለ ለቅዱስ ጳውሊ ክብር ይገባል!

††† አባ ለንጊኖስ †††

††† ጻድቁ ከኪልቅያ እስከ ሶርያ ከሶርያ እስከ ግብጽ ድረስ በተጋድሎ የተጓዙ አባት ናቸው። በአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽም የደብረ ዝጋግ (ግብጽ፤ እስክንድርያ) አበ ምኔት ሆነው አገልግለዋል።

ሙታንን አስነስተው ሃይማኖታቸውን ጠብቀው ብዙ ተአምራትን ሠርተው በዚህች ቀን ዐርፈዋል። ከድንቅ ነገራቸው ሰይጣን የእርሳቸውን የምንኩስና ቆብ ዐይቶ ደንግጦ መሸሹን እንጠቅሳለን።
"ኀበ ኢኀሎከ ሶበ ቆብዓከ ርዕየ
ሰይጣን ተኃፊሮ እፎኑመ ጐየ።" እንዲል።
(አርኬ)

††† አምላክ በበረከታቸው ይባርከን።

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

09 Feb, 03:23


የካቲት ፪ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ (የባሕታውያን ሁሉ አባት)
፪.ቅዱስ አባ ለንጊኖስ ሊቀ ምኔት (ደብረ ዝጋግ)
፫.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
††† ወርኀዊ በዓላት
፩.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፪.ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ
፫.ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ (የሃይማኖት
ጠበቃ)
፬.ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ
፭.ቅዱስ አቤል ጻድቅ
፮.አባ ሕርያቆስ ዘሐገረ ብሕንሳ

††† "የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ። ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ። በድንጋይ ተወግረው ሞቱ። ተፈተኑ፤ በመጋዝ ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ። ሁሉን እያጡ፣ መከራን እየተቀበሉ፣ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ። ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ።" †††
(ዕብ ፲፩፥፴፭-፴፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

© ዝክረ ቅዱሳን ማኀበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zikrekdusannbot

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

08 Feb, 18:54


❀✞፰ተኛ መዝሙር ኢየሩሳሌም ትቤ።✞❀

የየካቲት ፪ #ግጻዌ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺

የዕለቱ ቅዳሴ ምንባባት

🌺📖ወደ ገላትያ ሰዎች ፬ ፥ ፳፩ - ፍጻሜው
፳፩ እናንተ ከሕግ በታች ልትኖሩ የምትወዱ፥ ሕጉን አትሰሙምን? እስኪ ንገሩኝ።
፳፪ አንዱ ከባሪያይቱ አንዱም ከጨዋይቱ የሆኑ ሁለት ልጆች ለአብርሃም እንደ ነበሩት ተጽፎአልና።
፳፫ ነገር ግን የባሪያይቱ ልጅ እንደ ሥጋ ተወልዶአል፥ የጨዋይቱ ግን በተስፋው ቃል ተወልዶአል።
፳፬ ይህም ነገር ምሳሌ ነው፤ እነዚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና። ከደብረ ሲና የሆነችው አንዲቱ ለባርነት ልጆችን ትወልዳለች፥ እርስዋም አጋር ናት።
፳፭ ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረ ሲና ናት፤ አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፥ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና።
፳፮ ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት የምትኖር ናት እርስዋም እናታችን ናት።
፳፯ አንቺ የማትወልጅ መካን፥ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፥ እልል በዪና ጩኺ፤ ባል ካላቱ ይልቅ የብቸኛይቱ ልጆች በዝተዋልና ተብሎ ተጽፎአል።
፳፰ እኛም፥ ወንድሞች ሆይ፥ እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ነን።
፳፱ ነገር ግን እንደ ሥጋ የተወለደው እንደ መንፈስ የተወለደውን በዚያን ጊዜ እንዳሳደደው ዛሬም እንዲሁ ነው።
፴ ነገር ግን መጽሐፍ ምን ይላል? የባሪያይቱ ልጅ ከጨዋይቱ ልጅ ጋር አይወርስምና ባሪያይቱን ከልጅዋ ጋር አውጣት።
፴፩ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለንም።

🌺📖፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ፪ ፥ ፩ - ፱
፩ እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥
፪-፫ ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።
፬ በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥
፭ እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
፮ በመጽሐፍ፦ እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና።
፯ እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤
፰ የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።
፱ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤

🌺📖የሐዋርያት ሥራ ፭ ፥ ፲፯ - ፳፱
፲፯ ሊቀ ካህናቱ ግን የሰዱቃውያን ወገን ሆነውም ከእርሱ ጋር የነበሩት ሁሉ ተነሡ ቅንዓትም ሞላባቸው።
፲፰ በሐዋርያትም ላይ እጃቸውን ጭነው በሕዝቡ ወኅኒ ውስጥ አኖሩአቸው።
፲፱ የጌታ መልአክ ግን በሌሊት የወኅኒውን ደጅ ከፍቶ አወጣቸውና፦
፳ ሂዱና ቆማችሁ የዚህን ሕይወት ቃል ሁሉ ለሕዝብ በመቅደስ ንገሩ አላቸው።
፳፩ በሰሙም ጊዜ ማልደው ወደ መቅደስ ገብተው አስተማሩ። ግን ሊቀ ካህናቱና ከእርሱ ጋር የነበሩት መጥተው ሸንጎውንና የእስራኤልን ልጆች ሽማግሌዎች ሁሉ በአንድነት ጠሩ፥ ያመጡአቸውም ዘንድ ወደ ወኅኒ ላኩ።
፳፪-፳፫ ሎሌዎችም መጥተው በወኅኒው አላገኙአቸውም፤ ተመልሰውም፦ ወኅኒው በጣም በጥንቃቄ ተዘግቶ ጠባቂዎችም በደጁ ፊት ቆመው አገኘን፥ በከፈትን ጊዜ ግን በውስጡ አንድ ስንኳ አላገኘንም አሉአቸው።
፳፬ የመቅደስ አዛዥና የካህናት አለቆችም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ፦ እንጃ ይህ ምን ይሆን? እያሉ ስለ እነርሱ አመነቱ።
፳፭ አንድ ሰውም መጥቶ፦ እነሆ፥ በወኅኒ ያኖራችኋቸው ሰዎች እየቆሙ ሕዝቡንም እያስተማሩ በመቅደስ ናቸው ብሎ አወራላቸው።
፳፮ በዚያን ጊዜ አዛዡ ከሎሌዎች ጋር ሄዶ አመጣቸው፥ በኃይል ግን አይደለም፤ ሕዝቡ እንዳይወግሩአቸው ይፈሩ ነበርና።
፳፯ አምጥተውም በሸንጎ አቆሙአቸው።
፳፰ ሊቀ ካህናቱም፦ በዚህ ስም እንዳታስተምሩ አጥብቀን አላዘዝናችሁምን? እነሆም፥ ኢየሩሳሌምን በትምህርታችሁ ሞልታችኋል፤ የዚያንም ሰው ደም በእኛ ታመጡብን ዘንድ ታስባላችሁ ብሎ ጠየቃቸው።
፳፱ ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ፦ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።

ምስባክ ዘቅዳሴ

‹‹ትሴብሖ ኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር። ወሰብሒዮ ለአምላክኪ ጽዮን። እስመ አጽንዐ መናስግተ ኖኃትኪ። ››

‹‹ኢየሩሳሌም ሆይ እግዚአብሔርን አመስግኚ፥ ጽዮንም ሆይ፥ ለአምላክሽ እልል በዪ፤ የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቷልና፥››
🌺📖መዝሙር ፻፵፮ ፥ ፩-፪

ወንጌል ዘቅዳሴ

🌺📖የሉቃስ ወንጌል ፪ ፥ ፵፪ - ፍጻሜው
፵፪ የአሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በሆነ ጊዜ፥ እንደ በዓሉ ሥርዓት ወደ ኢየሩሳሌም ወጡ፤
፵፫ ቀኖቹንም ከፈጸሙ በኋላ፥ ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፥ ዮሴፍም እናቱም አላወቁም ነበር።
፵፬ ከመንገደኞች ጋር የነበረ ስለ መሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፥ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት፤
፵፭ ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
፵፮ ከሦስት ቀንም በኋላ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲሰማቸውም ሲጠይቃቸውም በመቅደስ አገኙት፤
፵፯ የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ።
፵፰ ባዩትም ጊዜ ተገረሙ፥ እናቱም፦ ልጄ ሆይ፥ ለምን እንዲህ አደረግህብን? እነሆ፥ አባትህና እኔ እየተጨነቅን ስንፈልግህ ነበርን አለችው።
፵፱ እርሱም፦ ስለ ምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት እሆን ዘንድ እንዲገባኝ አላወቃችሁምን? አላቸው።
፶ እነርሱም የተናገራቸውን ነገር አላስተዋሉም።
፶፩ ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።
፶፪ ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።


✝️✝️✝️ቅዳሴ፦ዘዲዮስቆሮስ

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Feb, 18:22


††† እንኳን ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ዼጥሮስ እና ለ150ው ቅዱሳን ሊቃውንት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ዼጥሮስ ሰማዕት †††

††† የቅዱሳን ሰማዕታት መነሻቸው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲሆን ፍጻሜአቸው ደግሞ ቅዱስ ዼጥሮስ ሊቀ ዻዻሳት ነው::

ይህ ቅዱስ የሚታወቀው "ተፍጻሜተ ሰማዕት (የሰማዕታት መጨረሻ)" በሚለው ስሙ ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
የቅዱሱ ሃገረ ሙላዱ ግብጽ ናት:: ዘመኑም 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ወላጆቹ ካህን ቴዎድሮስና ቡርክት ሶፍያ ልጅ አጥተው ሐምሌ 5 ቀን ወደ ፈጣሪ ቢማጸኑ በራዕይ ዼጥሮስ ወዻውሎስ ተገልጠው ብሥራትን ለሶፍያ ነገሯት:: በወለደችው ጊዜም በራዕዩ መሠረት "ዼጥሮስ" አለችው::

ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜም ለቤተ እግዚአብሔር ሰጥተው በሊቀ ዻዻሳቱ ቅዱስ ቴዎናስ እጅ አደገና በወጣትነቱ ሊቅ: ጥዑመ ቃልና በጐ ሰው ሆነ:: ዲቁናና ቅስናን ተሹሞ ሲያገለግል ቅዱስ ቴዎናስ በማረፉ ቅዱስ ዼጥሮስን የግብጽ 17ኛ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት::

ዘመኑ ደግሞ እጅግ ጭንቅ ነበር:: ክርስቲያኖች በተገኙበት ስለሚገደሉ: አብያተ ክርስቲያናትም ስለ ተቃጠሉ የቅዱሱ መከራ የበዛ ነበር:: ለ14 ዓመታት በፍጹም ትጋት ከመንጋው ጋር ተጨነቀ::

አርዮስን (ተማሪው ነበር) አውግዞ ለየው:: ከጌታ ጋርም ብዙ ጊዜ ተነጋገረ:: ብዙ ተአምራትንም ሠራ:: በዚህ ሁሉ ጊዜ አንድም ቀን በመንበረ ዽዽስናው ላይ አልተቀመጠም:: በሁዋላ ግን ጨካኙ ንጉሥ እንዲገደል አዘዘ::

ሕዝቡ "ከእሱ በፊት እኛን ግደሉን" በማለታቸው ሁከት እንዳይነሳ ቅዱስ ዼጥሮስ ተደብቆ ሔደና በፈቃዱ ለወታደሮች ተሰጠ:: በዚያች ሌሊትም የእርሱ ደም የግፍ ማብቂያ እንዲሆን እያለቀሰ ጮኸ:: ከሰማይም "አሜን! ይሁን!" የሚል ቃል መጣ:: ያን ጊዜ የእርሱ አንገት ተሰየፈ:: ዘመነ ሰማዕታትም አለፈ::

††† የቅዱሳንን ዝክር ከማንበብ ባለፈ በስማቸው መጸለይ (ዘፀ. 32:13): በምጽዋትም ማሰብ (ማቴ. 10:41) ይገባል::

††† ወርኀ የካቲትን ይባርክልን!

††† የካቲት 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1."150"ቅዱሳን ሊቃውንት ዻዻሳት (በቁስጥንጥንያ ተሠብሥበው መናፍቃንን ያወገዙበት: ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን ያፀኑበት /ጉባዔ ቁስጥንጥንያ/ በ381 ዓ/ም::
ከወቅቱ ቅዱሳን ሊቃውንት እነዚህ ይጠቀሳሉ:-
*ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ
*ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘእንዚናዙ
*ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት
*ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም)
2.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
3.ታላቁ ቴዎዶስዮስ ጻድቅ (ንጉሠ ቁስጥንጥንያ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ልደታ ለቅድስት ድንግል ማርያም እግዝእትነ
2.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3.ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ
4.ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
5.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና

††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ዻዻሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በሁዋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ 3 ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቁዋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" †††
(ሐዋ. 20:28)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††


© ዝክረ ቅዱሳን ማኀበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zikrekdusannbot

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Feb, 16:39


❀✞ ጉባኤ ኤጲስ ቆጶሳት ፻ወ፶ በቊስጥንጥንያ በእንተ መቅዶንዮስ ዘይቤ መንፈስ ቅዱስ ሕፁፅ ወበእንተ ሰባልዮስ ዘይቤ ፩ ገጽ ወበእንተ አቡሊናርዮስ፣ ወቅዳሴ ቤቱ ለጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት ወዕረፍቶሙ ለአስከናፍር ወብእሲቱ።✞❀

የየካቲት ፩ #ግጻዌ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺

ዘነግህ ምስባክ

‹‹ወኀለፈ እምትዕቢተ ልቦሙ። ሐለዩ ወነበብ ከንቶ። ወነበቡ ዐመፃ ውስተ አርያም።››

‹‹ስለዚህ ትዕቢት ያዛቸው፤ ኃጢአትንና በደልን ተጐናጸፉአት።ዓይናቸው ስብ ስለ ሆነ ወጣ፤ ልባቸውም ከምኞታቸው ይልቅ አገኘ።አስበው ክፉ ነገርን ተናገሩ፤ ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ።››
🌺📖መዝሙር ፸፪፡፯

ወንጌል  ዘነግህ

🌺📖 የማቴዎስ ወንጌል ፲፪፡፴፩-፴፰
፴፩ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም።
፴፪ በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።
፴፫ ዛፍ ከፍሬዋ ትታወቃለችና ዛፍዋን መልካም፥ ፍሬዋንም መልካም አድርጉ፥ ወይም ዛፍዋን ክፉ ፍሬዋንም ክፉ አድርጉ።
፴፬ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።
፴፭ መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።
፴፮ እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤
፴፯ ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ።
፴፰ በዚያን ጊዜ ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ መለሱና፦ መምህር ሆይ፥ ከአንተ ምልክት እንድናይ እንወዳለን አሉ።

የእለቱ የቅዳሴ ምንባባት

🌺📖ወደ ኤፌሶን ሰዎች ፬፡፲፯-ፍጻሜው
፲፯ እንግዲህ አሕዛብ ደግሞ በአእምሮአቸው ከንቱነት እንደሚመላለሱ ከእንግዲህ ወዲህ እንዳትመላለሱ እላለሁ በጌታም ሆኜ እመሰክራለሁ።
፲፰ እነርሱ ባለማወቃቸው ጠንቅ በልባቸውም ደንዳንነት ጠንቅ ልቡናቸው ጨለመ፥ ከእግዚአብሔርም ሕይወት ራቁ፤
፲፱ ደንዝዘውም በመመኘት ርኵሰትን ሁሉ ለማድረግ ራሳቸውን ወደ ሴሰኝነት አሳልፈው ሰጡ።
፳ እናንተ ግን ክርስቶስን እንደዚህ አልተማራችሁም፤
፳፩ በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤
፳፪ ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥
፳፫ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥
፳፬ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።
፳፭ ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።
፳፮ ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤
፳፯ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት።
፳፰ የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።
፳፱ ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።
፴ ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።
፴፩ መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።
፴፪ እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ።

🌺📖የይሁዳ መልእክት ፩፡፲፯-፳፫
፲፯ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያት ቀድሞ የተነገረውን ቃል አስቡ፤
፲፰ እነርሱ፦ በመጨረሻው ዘመን በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ ብለዋችኋልና።
፲፱ እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸው።
፳ እናንተ ግን፥ ወዳጆች ሆይ፥ ከሁሉ ይልቅ በተቀደሰ ሃይማኖታችሁ ራሳችሁን ለማነጽ እየተጋችሁ በመንፈስ ቅዱስም እየጸለያችሁ፥
፳፩ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ።
፳፪ አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ፥
፳፫ አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።

🌺📖የሐዋርያት ስራ ፳፡፳፰-፴፩
፳፰ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።
፳፱-፴ ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።
፴፩ ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ።

ምስባክ ዘቅዳሴ

‹‹ሣህሉ ለእግዚአብሔር መልዐ ምድረ። ወበቃለ እግዚአብሔር ጸንዐ ሰማያት ወእምእስትንፋስ አፉሁ ኵሉ ኃይሎሙ።››

‹‹ የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች። በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ››
🌺📖መዝሙር ፴፪፡፭

ወንጌል  ዘቅዳሴ

🌺📖 የዮሐንስ ወንጌል ፲፭፡፳፮-፳፯
፳፮ ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤
፳፯ እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋር ኖራችኋልና ትመሰክራላችሁ።

✥✥✥ቅዳሴ፦ዘሰለስቱ ምዕት (ግሩም)

🌿  @zkretewahdo
🌿  @zkretewahdo
🌿  @zkretewahdo

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Feb, 04:08


የጥር ፴ (30) የነግህ እና የቅዳሴ ምስባክ ዜማ

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Feb, 03:37


++"++ ቅድስት ሶፍያና 3ቱ ሰማዕታት ልጆቿ (ዺስጢስ አላዺስና አጋዺስ) ++"++

=>+"+ ለእናንተም ጠጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጐናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ:: ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ:: +"+ (1ዼጥ. 3:3)

   <ወስብሐት ለእግዚአብሔር>

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Feb, 03:35


ገሃነመ እሳትን ስናስብ፦

"እመትለድ እምየ፥ ኪያየ ጸኒሳ፤
ተአጽዎ ማኅጸን እምሔሳ፤
ወከዊነ ጾም እምከርሣ፤
መንገለ ቤትክሙ ጻድቃን፥ ፍዳ አእጋርየ ጌሣ፤
ስረዩ ኃጢአትየ፥ ወዘገበርኩ አበሳ፤
እስመ እምኔየ ይሔይስ እንስሳ!" (መልክአ ጻድቃን ዘዴጌ)

ትርጉም፦
እናቴ ጸንሳ፥ እኔን ከምትወልድስ፥ ማኅጸንዋ ጾመኛ በሆነ፥ በተዘጋም በተሻለ ነበር!
ግን፦
የዴጌ ጻድቃን እግሮቼ ወደ መቅደሳችሁ ለሔደበት ፈንታ፤
ኃጢአቴንና በደሌን ይቅር በሉኝ፤
ከእኔ እንስሳ ይሻላልና!

እንኳን አደረሰን!

(ናርጋ ቅድስት ሥላሴ - ጣና)

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

31 Jan, 05:06


@Gozilla_bot

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

31 Jan, 03:01


† እንኳን ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ: እና ጻድቅ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ †††

††† ይህ ቅዱስ ሐዋርያ አንድ የቤተ ክርስቲያናችን መብራት ነው:: ወደ ክርስትና የመጣው በ40ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ሲሆን አሳምኖ ለቅድስና ያበቃው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ዻውሎስ ነው::

በጊዜውም በነበረው ትጋትና ተጋድሎ ፍሬ አፍርቷል:: ሆዱንም እጅግ ያመው ነበር:: ቅዱስ ዻውሎስ ሲጠራው "የምወድህ ልጄ" እያለ ነበር:: በኤፌሶንም ዽዽስናን ሹሞ 2 መልዕክታትን ልኮለታል:: ቅዱስ ጢሞቴዎስ ቤተ ክርስቲያንን ለብዙ ዘመናት አገልግሎ በሰማዕትነት ዐርፏል::

ከሐዋርያው ቅዱስ ጢሞቴዎስ በረከትን እንሳተፍ ዘንድ ጊዜ ካለን ቅዱስ ዻውሎስ ለልጁ ጢሞቴዎስ ከላካቸው መልዕክቶች ጥቂት እናንብብ::

††† ቴዎዶስዮስ †††

††† በዚህ ስም የሚጠሩ ብዙ አበው አሉ:: ሰማዕታትም: ጻድቃንም: ሊቃውንትም: ነገሥታትም ተጠርተውበታልና:: ዛሬ የምናከብረውም ቴዎዶስዮስ ዘየዓቢ (ታላቁ) የሚባል ሲሆን ይህን የምንለው ከትንሹ ቴዎዶስዮስ (የልጅ ልጁ ነው) ለመለየት ነው::

ታላቁ ቴዎዶስዮስ በሮም የነገሠው በ370 ዓ/ም አካባቢ ሲሆን ከነ ቤተሰቡ ክርስቲያን ነበር:: እነዚህ ነገሮቹ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን እንዲታሰብ አድርጐታል:-
1.በዓለም ታሪክ ክርስትና በሮም ግዛት ሁሉ ብሔራዊ ሃይማኖት እንዲሆን አውጇል::
2.የቤተክርስቲያንን ትልቁን 2ኛ ጉባኤ ቁስጥንጥንያን በ381 (373) ዓ/ም አሰናድቷል::
3.ከበጐነቱ የተነሳ የተቀደሱ ልጆችን አፍርቷል:: ሙሽራው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ: ቅዱስ አኖሬዎስ: ቅዱስ አርቃዴዎስ እና ቅድሰት ታኦድራ ልጆቹ ሲሆኑ አቡነ ኪሮስ ትንሽ ወንድሙ ናቸው::

ጻድቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ በ390 ዓ/ም አካባቢ ዐርፏል::

††† አምላከ ቅዱሳን ስለ አባቶቻችን ሲል ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

††† ጥር 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ጢሞቴዎስ (ሐዋርያና ሰማዕት-የቅዱስ ዻውሎስ ደቀ መዝሙር)
2.ቅዱስ ጌርሎስ ሰማዕት
3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሰማዕት
4.ጻድቅ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ (ዘቁስጥንጥንያ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ቅዱስ ሰሎሞን ንጉሠ እሥራኤል
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.አባ ሳሙኤል
6.አባ ስምዖን
7.አባ ገብርኤል

††† "መድኃኒታችን እግዚአብሔር: ተስፋችንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳዘዘው ትእዛዝ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ዻውሎስ: በእምነት እውነተኛ ልጄ ለሆነ ለጢሞቴዎስ::
ከእግዚአብሔር ከአባታችን: ከክርስቶስ ኢየሱስም ከጌታችን: ጸጋና ምሕረት: ሰላምም ይሁን . . ." †††
(1ጢሞ. 1:1)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

© ዝክረ ቅዱሳን ማኀበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zikrekdusannb

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

30 Jan, 17:56


❀✞ ጢሞቴዎስ ሰማዕት ወለሐዊኖስ ወቴዎዶስዮስ ንጉሥ።✞❀

      የጥር ፳፫ #ግጻዌ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺

ዘነግህ ምስባክ

‹‹እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ። ወብዙኃ ይትሐሠይ በአድኀኖትከ። ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ።››

‹‹አቤቱ፥ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፤ በማዳንህ እጅግ ሐሤትን ያደርጋል። የልቡን ፈቃድ ሰጠኽው፥››
🌺📖መዝሙር ፳፩፡፲

ወንጌል ዘነግህ

🌺📖 የሉቃስ ወንጌል ፲፡፲፯-፳፭
፲፯ ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው፦ ጌታ ሆይ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት።
፲፰ እንዲህም አላቸው፦ ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ።
፲፱ እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም።
፳ ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።
፳፩ በዚያን ሰዓት ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሐሤት አደረገና፦ የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግናለሁ፤ አዎን አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና።
፳፪ ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፥ ወልድንም ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፥ አብንም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር ወልድም ሊገልጥለት ከሚፈቅድ በቀር የሚያውቅ የለም አለ።
፳፫ ወደ ደቀ መዛሙርቱም ዘወር ብሎ ለብቻቸው፦ የምታዩትን የሚያዩ ዓይኖች ብፁዓን ናቸው።
፳፬ እላችኋለሁና፥ እናንተ የምታዩትን ብዙዎች ነቢያትና ነገሥታት ሊያዩ ወደዱ አላዩምም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ወድደው አልሰሙም አለ።
፳፭ እነሆም፥ አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው ተነሥቶ፦ መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? አለው።

የእለቱ ቅዳሴ ምንባባት

🌺📖፪ኛ ወደ ጢሞቴዎስ ሰዎች ፩፡፩-፲
፩ በክርስቶስ ኢየሱስ እንደሚሆን የሕይወት ተስፋ፥ በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥
፪ ለተወደደው ልጄ ለጢሞቴዎስ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከጌታችንም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።
፫ ሌትና ቀን በልመናዬ ሳላቋርጥ ስለማስብህ እንደ አባቶቼ አድርጌ በንጹሕ ሕሊና የማመልከውን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤
፬ እንባህን እያሰብሁ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ።
፭ በአንተ ያለውን ግብዝነት የሌለበትን እምነትህን አስባለሁ፤ ይህም እምነት ቀድሞ በአያትህ በሎይድ በእናትህም በኤውንቄ ነበረባቸው፥ በአንተም ደግሞ እንዳለ ተረድቼአለሁ።
፮ ስለዚህ ምክንያት፥ እሳት እንደሚያቀጣጥል ሰው፥ እጆቼን በመጫኔ በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሣሣ አሳስብሃለሁ።
፯ እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።
፰ እንግዲህ በጌታችን ምስክርነት ወይም በእስረኛው በእኔ አትፈር፥ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል፤
፱ ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፥
፲-፲፩ አሁን ግን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ታይቶአል። እርሱ ሞትን ሽሮአልና እኔ ሰባኪና ሐዋርያ አሕዛብንም አስተማሪ እንድሆን በተሾምሁበት በወንጌል ሕይወትንና አለመጥፋትን ወደ ብርሃን አውጥቶአል።

🌺📖፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ፫፡፲፫-፲፰
፲፫ በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው?
፲፬ ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራን ብትቀበሉ ብፁዓን ናችሁ። ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ አትናወጡም፥
፲፭ ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስ በልባችሁ ቀድሱት። በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቁአችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ፥ ነገር ግን በየዋህነትና በፍርሃት ይሁን።
፲፮ በክርስቶስ ያለውን መልካሙን ኑሮአችሁን የሚሳደቡ ሰዎች ክፉን እንደምታደርጉ በሚያሙበት ነገር እንዲያፍሩ በጎ ሕሊና ይኑራችሁ።
፲፯ የእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲህ ቢሆን፥ ክፉ ስለ ማድረግ ሳይሆን በጎ ስለ ማድረግ መከራን ብትቀበሉ ይሻላችኋልና።
፲፰ ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፥

🌺📖 የሐዋርያት ሥራ ፲፮፡፩-፲፫
፩ ወደ ደርቤንና ወደ ልስጥራንም ደረሰ። እነሆም፥ በዚያ የአንዲት ያመነች አይሁዳዊት ልጅ ጢሞቴዎስ የሚባል አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ፤ አባቱ ግን የግሪክ ሰው ነበረ።
፪ ለእርሱም በልስጥራንና በኢቆንዮን ያሉ ወንድሞች መሰከሩለት።
፫ ጳውሎስ ይህ ከእርሱ ጋር ይወጣ ዘንድ ወደደ፥ በእነዚያም ስፍራዎች ስለ ነበሩ አይሁድ ይዞ ገረዘው፤ አባቱ የግሪክ ሰው እንደ ሆነ ሁሉ ያውቁ ነበርና።
፬ በከተማዎችም ሲዞሩ በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያትና ሽማግሌዎች የቈረጡትን ሥርዓት ይጠብቁ ዘንድ ሰጡአቸው።
፭ አብያተ ክርስቲያናትም በሃይማኖት ይበረቱ ነበር፥ በቍጥርም ዕለት ዕለት ይበዙ ነበር።
፮ በእስያም ቃሉን እንዳይናገሩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አገር አለፉ፤
፯ በሚስያም አንጻር በደረሱ ጊዜ ወደ ቢታንያ ይሄዱ ዘድን ሞከሩ፥ የኢየሱስ መንፈስም አልፈቀደላቸውም፤
፰ በሚስያም አጠገብ አልፈው ወደ ጢሮአዳ ወረዱ።
፱ ራእይም ለጳውሎስ በሌሊት ታየው፤ አንድ የመቄዶንያ ሰው፦ ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን እያለ ቆሞ ሲለምነው ነበር።
፲ ራእዩንም ካየ በኋላ ወዲያው ወደ መቄዶንያ ልንወጣ ፈለግን፥ ወንጌልን እንሰብክላቸው ዘንድ እግዚአብሔር እንደ ጠራን መስሎናልና።
፲፩ ከጢሮአዳም ተነሥተን በቀጥታ ወደ ሳሞትራቄ በነገውም ወደ ናጱሌ በመርከብ ሄድን፤
፲፪ ከዚያም ወደ ፊልጵስዩስ ደረስን፤ እርስዋም የመቄዶንያ ከተማ ሆና የወረዳ ዋና ከተማና ቅኝ አገር ናት፤ በዚህችም ከተማ አንዳንድ ቀን እንቀመጥ ነበር።
፲፫ በሰንበት ቀንም ከከተማው በር ውጭ የጸሎት ስፍራ በዚያ መሆኑን ስላሰብን ወደ ወንዝ አጠገብ ወጣን፤ ተቀምጠንም ለተሰበሰቡት ሴቶች ተናገርን።

ምስባክ ዘቅዳሴ

‹‹ወበመንፈስ አዚዝ አጽንዐኒ። ከመ እምሀሮሙ ለኃጥኣን ፍኖተከ ወረሲዓን ይትመየጡ ኀቤከ።››

‹‹በእሽታ መንፈስም ደግፈኝ።ለሕግ ተላላፎች መንገድህን አስተምራለሁ፥ ኃጢአተኞችም ወደ አንተ ይመለሳሉ።››
🌺📖መዝሙር ፶፡፲፪

ወንጌል ዘቅዳሴ

🌺📖 የማቴዎስ ወንጌል ፲፪፡፲፯-፴፭
፲፮-፲፯ በነቢዩ በኢሳይያስ የተባለው ይፈጸም ዘንድ እንዲህ ሲል፦
፲፰ እነሆ የመረጥሁት ብላቴናዬ፥ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ወዳጄ፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አኖራለሁ፥ ፍርድንም ለአሕዛብ ያወራል።
፲፱ አይከራከርም አይጮህምም፥ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም።
፳ ፍርድን ድል ለመንሣት እስኪያወጣ፥ የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም የሚጤስን የጥዋፍ ክርም አያጠፋም።

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

30 Jan, 17:56


፳፩ አሕዛብም በስሙ ተስፋ ያደርጋሉ።
፳፪ ከዚህም በኋላ ጋኔን ያደረበትን ዕውር ዲዳም ወደ እርሱ አመጡ፤ ዕውሩም ዲዳውም እስኪያይና እስኪናገር ድረስ ፈወሰው።
፳፫ ሕዝቡም ሁሉ ተገረሙና፦ እንጃ ይህ ሰው የዳዊት ልጅ ይሆንን? አሉ።
፳፬ ፈሪሳውያን ግን ሰምተው፦ ይህ በብዔል ዜቡል በአጋንንት አለቃ ካልሆነ በቀር አጋንንትን አያወጣም አሉ።
፳፭ ኢየሱስ ግን አሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፥ እርስ በርሱ የሚለያይ ከተማም ሁሉ ወይም ቤት አይቆምም።
፳፮ ሰይጣንም ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፥ እርስ በርሱ ተለያየ፥ እንግዲህ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች?
፳፯ እኔስ በብዔል ዜቡል አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ ልጆቻችሁ በማን ያወጡአቸዋል? ስለዚህ እነርሱ ፈራጆች ይሆኑባችኋል።
፳፰ እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።
፳፱ ወይስ ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቀው እንዴት ይችላል? ከዚያም ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል።
፴ ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፥ ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል።
፴፩ ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ኃጢአትና ስድብ ሁሉ ለሰዎች ይሰረይላቸዋል፥ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ለሰደበ አይሰረይለትም።
፴፪ በሰው ልጅ ላይ ቃል የሚናገር ሁሉ ይሰረይለታል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ ግን የሚናገር ሁሉ በዚህ ዓለም ቢሆን ወይም በሚመጣው አይሰረይለትም።
፴፫ ዛፍ ከፍሬዋ ትታወቃለችና ዛፍዋን መልካም፥ ፍሬዋንም መልካም አድርጉ፥ ወይም ዛፍዋን ክፉ ፍሬዋንም ክፉ አድርጉ።
፴፬ እናንተ የእፉኝት ልጆች፥ ክፉዎች ስትሆኑ መልካም ለመናገር እንዴት ትችላላችሁ? በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና።
፴፭ መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።

✥✥✥ቅዳሴ፦ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ)

🌿  @zkretewahdo
🌿  @zkretewahdo
🌿  @zkretewahdo

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

30 Jan, 17:55


🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ሥርዓተ ማኅሌት ዘቅዱስ ጊዮርጊስ "ጥር ፳፫"
💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐💐

የጥር ጊዮርጊስ
#ሥርዓተ_ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።


የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።


መልክአ ሥላሴ፦
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ፤ ትሩፋተ ገድል ኲኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤ ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤ ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤ ወተክለ ሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዓፅሙ።


#ዚቅ፦
አባ ጊዮርጊስ ጸለየ ወሰአለ፤እንዘ ይብል ማኅቶተ ብርሃን ዘኢትጠፍዕ፤አመጽካ ለምድር በሥላሴከ።


#ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።


#ዚቅ
ነያ ሠናይት ወነያ አዳም ጽርሕ ንጽሕት አግዓዚት እሞሙ ይእቲ ለሰማዕት፤ወእኅቶሙ ለመላእክት ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን ደብተራ ፍጽምት እንተ ኢገብራ እደ ሰብእ።

#ዓዲ_ዚቅ፦
አዳም ይእቲ ወሠናይት፤እሞሙ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን፤ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን።


መልክአ ጊዮርጊስ፦
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘሰሌዳ ሞገስ መጽሐፉ፤ ዘያሜኒ ኲሎ ወዘያስተሴፉ፤ ጥዑመ ዜና ጊዮርጊስ ለሀሊበ ዕጎልት ሱታፉ፤ ሰላምከ ወረድኤትከ በላዕሌየ ያዕርፉ፤ አኮ ለምዕር ዳዕሙ ለዝላፉ።


#ዚቅ፦
ሰላም ለከ ጊዮርጊስ እግዚእየ፤ሰላም ለከ ፍቊርየ፤ዘሠምረት ነፍስየ በሰላመ እግዚአብሔር።(ይህ የአበራ ጊዮርጊስ ነዉ)


መልክአ ጊዮርጊስ
ሰላም ለድማኅከ በቅብዐ ደመ ስምዕ ዘተሤረየ፤አመ ተወክፈ ርእስከ ዘሰፌልያ ሥቃየ፤ጊዮርጊስ ልዳዊ ቃውመ ነፍስየ፤እንበለ ይፈጽማ ከናፍርየ ስመ ዚአከ ስምየ፤በጊዜ ምንዳቤ በለኒ ሀለወኩከ ዝየ።


#ዚቅ
ገጹ ብሩህ ከመ ፀሐይ፤ወእምኵሉ ስነ ሠርጐ ሰማይ፤ለጊዮርጊስ ኅሩይ ዘተወልደ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ፤አልባሲሁ በደመ በግዕ ዘሐፀበ፤ወእምሠረቅት መርዔቶ ዓቀበ።


መልክአ ጊዮርጊስ
ሰላም ለአስናኒከ ቈዓ አጣዕዎ ዘኢሔካ፤ኮከበ ልዳ ጊዮርጊስ መዓድመ ዋካ፤ለቤሩታዊት ወለት እምአፈ ደራጎን አመ ቤዘውካ፤ለነፍሰ ዚአየ እምእደ ፀራዊ መሐካ፤እስመ ትንብልናከ ዘልፈ ረስየት ምስማካ።


#ዚቅ
ነጽር ላዕሌነ፤ዘነጸርከ ላዕለ ፈላስያን፤አድኅነኒ ዘአድኃንካ ለወለት እምአፈ ደራጎን።


መልክአ ጊዮርጊስ
ሰላም ለገቦከ በመኃትወ ጽጒ ዘሐለለ፤ወበተሰትሮ ዘቆስለ፤ጊዮርጊስ ኀቤከ እስመ ልብየ ተሰቅለ፤መርዓዊ ሰማያዊ አመ ይገብር በዓለ፤በጥቃ ገቦከ ለእኩን ውዑለ።


#ዚቅ
ሰአል ለነ ጊዮርጊስ ይክሥት ለነ መንግስቶ፤አመ ምጽአቱ ዳግመ ያቊመነ ቅድሜሁ፤ያስተሳትፈነ ምስሌሁ፤እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ።


ምልጣን
ዝንቱሰ ብእሲ ኮከበ ክብር፤ዘዓቢየ ኃይለ ይገብር፤ጊዮርጊስ ኃያል መስተጋድል ስምዓ ጽድቆሙ ለቅዱስ፤አማን ብርሃን ስምዓ ብርሃን።


እስመ ለዓለም
ዘኅቡዕ እምኅቡዓን ክብረ ቅዱሳን አስተርአየ፤ነገሥተ ተርሤሥ ወደሰያት አምኃ ያበዉዑ፤አንሶሰወ ወአስተርአየ እንዘ አምላክ ዉእቱ፤ወተወልደ እምቅድስት ድንግል፤እስመ መለኮቶ ኢማሰነ።


#ወረብ
ዘኅቡዕ እምኅቡዓን ክብረ ቅዱሳን ዘኅቡዕ እምኅቡዓን ክብረ ቅዱሳን
"ነገሥተ ተርሤሥ ወደሰያት አምኃ ያበዉዑ"/2/


ሰላም
ሰዓል ለነ ጊዮርጊስ ኀበ እግዚአብሔር ወጸሊ በእንቲአነ ሐረድዎ ወገመድዎ ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ሐመድ ወወሰድዎ ኀበ ሰብአ ፸ ነገሥት ረገፀ  ምድረ  አባ ጊዮርጊስ አንሥአ ሙታነ በሰላም አደወ መንግሥተ ክብር ወረሰ።(የአቋቋም አንሥአ ሙታነ አባ ጊዮርጊስ በሰላም አደወ መንግሥተ ክብር ወረሰ።)


እመሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕ(የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት)🙏🙏🙏


🌿  @zkretewahdo
🌿  @zkretewahdo
🌿  @zkretewahdo

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

30 Jan, 04:08


የጥር 22 የቅዳሴ ምስባክ ዜማ

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

30 Jan, 04:04


የጥር 22 የነግህ ምስባክ ዜማ

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

30 Jan, 02:59


#የአባ_እንጦንስ_ምክሮች

✞ ከዕለታት በአንድ ቀን አባ ፓምቦ አባ እንጦስን "ማድረግ ያለብኝ ነገር ምንድን ነው?" ብሎ ይጠይቃል።አባ እንጦስም እንዲህ ሲል መለሰለት "በራስህ ጽድቅ አትታመን፤ላለፈው አትጨነቅ፤ይልቁኑ አንደበትህንና ሆድህን ግዛ።"

✞ አባ እንጦስ በአንድ ወቅት እንዲህ አለ፦ "በዚች ምድር ላይ ስንኖር ህይወታችንንም ሆነ ሞታችን ከባልጀራችን ጋር ነው። ወንድማችንን ገንዘብ ካደረግነው እግዚአብሔርን ገንዘብ እናደርጋለን፤ ወንድማችንን ካስቀየምነው ግን በክርስቶስ ላይ ኃጢአትን እናመጣለን።"

✞ በአንድ ወቅት አንድ ወንድም አባ እንጦስን "ጸልይልኝ" በማለት ይጠይቃል። እንጦስም "አንተ ራስህ ጥረት የማታደርግና ወደ እግዚአብሔር የማትጸልይ ከሆነ እኔም ሆንሁ እግዚአብሔር ምህረት ልናደርግልህ አንችም" አለው።

✞ እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው  ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።

✞ ኃጢአታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል፤ ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።

✞ ብዙ ጊዜ ሰዎች ብልህ ነን እያሉ ይሳሳታሉ። ነገር ግን ብልህ የሚባሉት ብዙ የተማሩና ብዙ ያነበቡ ብዙ የሚናገሩ ብቻ አይደሉም። ይልቁንም ጠቢባን የሚባሉት ጥብብት መጥበቢት ብልህ ነፍስ ያላቸው፤ የእግዚአብሔርንና የሰይጣንን ለይተው ለእግዚአብሔር ሆነው የሚኖሩ ናቸው። ፍጹም ምልዓተ ኃጢአትንና ከጦር ይልቅ የሚወጉ የኃጢአት እሾሀቸውን የነቀሉ ናቸው ጠቢባን።

✞ ጠቢባንስ እግዚአብሔርን ያለጥርጥር በሙሉ ልብ የሚያምኑት፤ አምነውም እንደ ፈቃዱ የተከተሉት፤ በክንፈ ጸጋ ተመስጠው ከልብ በሚወጣ ውዳሴ ከእርሱ ጋር ተዋሕደው የሚኖሩ ናቸው። የነፍሳቸውን ረብሕ ጥቅም አውቀው ዕለት ዕለት ያንን የሚለማመዱ በእውነት ጠቢባን እነዚህ ናቸው።

✞ የጋለ ብረትን ለመቀጥቀጥ የሚነሣ ሰው አስቀድሞ በብረቱ ምን ለመሥራት እንዳሰበ መወሰን አለበት፤ መጥረቢያ፥ ሰይፍ፥ ወይስ ማጭድ? እኛም በምን ዓይነት የሕይወት መስመር ፍሬ ለማፍራት እንዳሰብን አስቀድመን ልቡናችንን ማዘጋጀት አለብን፡፡

✞ ዘወትር በዐይንህ ፊት ፈሪሃ እግዚአብሔር ይኑር፤ ሕይወትና ሞት የሚሰጠውን አዘክረው፡፡ ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ጥላው፤ ከሥጋ የሚመጣውን ደስታና ሰላም አትሻ፤ ለዚህኛው ኑሮ ሙትና ለእግዚአብሔር ሕያው ሁን፤ ለእግዚአብሔር ቃል የገባኸውን አትርሳ፤ ያም በፍርድ ቀን ካንተ ይፈለግብሃል፡፡ ረኀብን በጸጋ ተቀበለው፤ ተጠማ፥ ተራቆት፥ ንቁና በሐዘን የምትኖር ሁን፡፡ በልቡናህ አልቅስና ጩኽ፤ ለእግዚአብሔር የምትመች መሆን አለመሆንህን ፈትን፤ ሥጋህን ቀጥተህ ነፍስህን ታድናት ዘንድ፡፡

✞ የቱንም ያህል በመከራ ቢወድቅብህ የቱንም ያህል በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ብታልፍ ይህንን ለጌታዬ ለመድኃኒቴ ለኢየሱስ ክርስቶስ ስል እቀበላለሁ በል። ቀላል ይሆንልሀል። የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ኃይል ነውና። በእርሱ ማእበሉ ፀጥ ይላል ሰይጣንም ይሸሻል።

✞ ለተወሰን ጊዜ ለሀይማኖት መከራከር፤ ጠበቃ መሆን፤ መዋጋት ብሎም መሞት አይከፋም ሁልጊዜ ለሀይማኖት መኖር ግን ከሁሉ የበለጠ መስዋእትና ክብር ያለው ህይወት ነው፡፡

(#ከተለያዩ_ጽሑፎች_የተሰበሰቡ)

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

22 Jan, 06:43


ገድለ አቡነ አረጋዊ ዘወርሃ ዘጥር

እመሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕ(የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት)🙏🙏🙏

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

22 Jan, 06:23


ስንክሳር ዘወርሃ ጥር አሥራ አራት(፲፬)
ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ:

እመሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕ(የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት)🙏🙏🙏

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

22 Jan, 06:22


የጥር ፲፬ የቅዳሴ ምስባክ ዜማ

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

21 Jan, 13:14


††† እንኳን ለጻድቃን ቅዱሳን አቡነ አረጋዊ እና አባ አርከሌድስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ †††

††† ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አቡነ አረጋዊ ከዘጠኙ (ተስዓቱ) ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::

ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር:-
1.የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ:
2.ዓላማ (የእግዚአብሔር መንግስት) እና
3.ገዳማዊ ሕይወት ነው::

አቡነ አረጋዊን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::

በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት 5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::

በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ470ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::

ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ ቤተ ቀጢን ትባላለች:: አቡነ አረጋዊና 8ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር::

ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አቡነ አረጋዊ እንደገና አቀጣጠሉት::

ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት:: የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ::

ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አቡነ አረጋዊ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማሕበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::

የነ አቡነ አረጋዊ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ::

*ዸንጠሌዎን በጾማዕት:
*ገሪማ በመደራ:
*ሊቃኖስ በቆናጽል:
*አባ ይምዓታ በገርዓልታ:
*ጽሕማ በጸድያ:
*ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::
*አባ አረጋዊ ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ምርጫቸው ዳሞ (እዛው ትግራይ) ሆነ::

በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው:: ጻድቁ የተወለዱት በ5ኛው መቶ ክ/ዘ አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅና ቅድስት እድና ይባላሉ:: የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው::

ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው:: ወላጆቻቸው "ዘሚካኤል" ሲሏቸው በበርሃ "ገብረ አምላክ" ተብለዋል:: በኢትዮዽያ ደግሞ "አረጋዊ" ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ::

በዚያም በገዳመ ዳውናስ (ግብጽ) የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል:: ከመነኮሱ ከዓመታት በሁዋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር 7 ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል::

"የት ልሒድ" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው:: ተመልሰውም ለ8 ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከ8ቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ::

በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ:: ወደ ሃገራችን የመጡ በ470ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል:: በቤተ ቀጢን (አክሱም) ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ: ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል::

ለሥራ በተለያዩ ጊዜም አቡነ አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል:: በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን (ደብረ ሃሌ ሉያን) አይተው ወደዷት:: የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ 60 ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል::

እንደ ወጡም "ሃሌ ሉያ ለአብ: ሃሌ ሉያ ለወልድ: ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል:: በዚህም ቦታዋ "ደብረ ሃሌ ሉያ" ተብላለች:: ጻድቁ ቦታውን ከገደሙ በሁዋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው 6ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል::

ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም "አቡሆሙ ለመነኮሳት ዘኢትዮዽያ - የኢትዮዽያ መነኮሳት አባት" ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል::

ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ:: በተራራው ግርጌ ያለችውን ኪዳነ ምሕረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች::

ጻድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ99 ዓመታቸው በገዳሙ በስተ ምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል:: ጌታም 15 ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል:: ዛሬ ጻድቁ የተወለዱበት ቀን ነው::

††† አባ አርከሌድስ †††

††† በዚህ ስም የሚጠሩ ቅዱሳን በግብጽም በሃገራችንም አሉ:: ዋናውና በብዙ መጻሕፍት ዜናቸው የተጻፈላቸው ግን ዛሬ የምናከብራቸው ናቸው:: አባ አርከሌድስ የነበሩት በዘመነ ጻድቃን ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው ሮም ናት::

ወላጆቻቸው ክርስቲያን: በዚያውም ላይ ባለ ጠጐች ነበሩ:: አባታቸው ደግሞ መስፍነ ሃገር ነበር:: ቅዱሱን ወልደው: በሕግ በሥርዓት አሳድገዋል:: ለአካለ መጠን አባ አርከሌድስ ሲደርሱ ግን አባታቸው ሞተ::

መዋዕለ ሐዘናቸው ከተፈጸመ በሁዋላም እናት አባ አርከሌድስን ጠርታ:- "ልጄ! ሒድና የአባትህን ሹመት እጅ አድርግ" አለችው:: ለመንገድ የሚያስፈልገውን ሁሉ አሰናድታ: አገልጋዮችንና ብዙ ወርቅ (ለሿሚው አካል የሚሰጥ) ጨምራም ልጇን ሸኘች::

ቅዱስ አርከሌድስም ከእናታቸው ተለይተው በአገልጋዮች ተከበው ወደ መርከብ ገቡ:: በባሕር መካከል ሳሉ ግን ታላቅ ማዕበል ተነስቶ መርከቡን በታተነው:: በመርከቡ የነበረው ሰው ሁሉ ሲያልቅ አባ አርከሌድስ ግን በስባሪ ላይ ተንጠልጥለው ተረፉ::

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

21 Jan, 13:14


ዋኝተው ወጥተው ወደ ዳርቻ ሲደርሱም ማዕበል የተፋው አንድ በድን ወድቆ ተመልክተው ፈጸመው አለቀሱ:: ወዲያውም በልባቸው የዚህን ዓለም ኃላፊነት አሰቡ:: ሹመት ፍለጋ መሔዳቸውን ትተው ወደ ገዳም ሔዱ::ወደ ምድረ ሶርያ ደርሰው በታላቁ ደብረ ሮማኖስ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበሉ:: በእጃቸው የነበረውን 200 ዲናር ወርቅም ለገዳሙ አበረከቱ:: ለጥቂት ጊዜ በገዳሙ ካገለገሉ በሁዋላም ጾማዕት (በዓት) ተሰጣቸው::

በዚህ ጊዜም "እንግዲህ ወደ ዓለም አልወጣም:: የሴቶችን መልክም አልመለከትም" ሲሉ ቃል ገቡ:: በተጋድሏቸውም በጾምና በጸሎት: በትጋሃ ሌሊት ለ12 ዓመታት ቀጠሉ:: ጾማቸውም 7 ቀን ነበር:: አምላክ ጸጋውን ስላበዛላቸውም ብዙ ድውያንን ፈወሱ::

ዜናቸውም እስከ ምድረ ሮሜ ተሰማ:: እናታቸው (ሰንደሊቃ) የመርከቡን ዜና ከሰማች በሁዋላ የሞቱ መስሏት አልቅሳ ቤቷን የእንግዳ ቤት አድርጋ: በበጎ ምግባር ትኖር ነበርና አንድ ቀን የልጇን ዜና ሕይወት ሰማች::

ከደስታዋ የተነሳ ፈጥና ወደ ደብረ ሮማኖስ ደርሳ "ልጄን ልይ" አለች:: ግን "ሴትን አላይም" ብለው አባ አርከሌድስ ቃል ገብተዋልና ምን ይሁን! ሰንደሊቃም "አራዊት ይብሉኝ እንጂ ልጄን ሳላይ አልሔድም" አለች:: ወዲያው ግን "አባ አርከሌድስ ፈቅደዋልና ግቢ" የሚል መልእክት መጥቶላት ገባች::

ግን ያገኘችው የጻድቁን ልጇን ሥጋ ነበር:: ምክንያቱም የፈጣሪንም: የእናታቸውንም ልብ ላለማሳዘን እንዲወስዳቸው ለምነውት ዐርፈው ነበር:: እናትም በልጇ ሥጋ ላይ እያለቀሰች እዚያው ዐረፈች:: "አብራችሁ ቅበሩን" የሚል ቃል ከቅዱሱ ሥጋ ስለ ተሰማም አብረው ቀብረዋቸዋል::

††† አምላከ ቅዱሳን ለእነርሱ ካደለው ፍቅራቸው ለእኛም አይንሳን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

††† ጥር 14 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ አረጋዊ (ዘሚካኤል)
2.ቅዱስ አባ መክሲሞስ
3.ቅዱስ አባ አርከሌድስ
4.ቅድስት እምራይስ
5.ቅድስት ምሕራኤል
6."4034"ሰማዕታት (ማሕበራነ ቅዱስ ቂርቆስ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.አባ ስምዖን
2.አባ ዮሐንስ
3.ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ (ሙሽራው)
4.ቅዱስ ሙሴ
5.ቅዱስ ፊልዾስ (ከ72 አርድዕት)
6.ቅድስት ነሣሒት

††† "እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና::
ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና::
ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . .
ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ::
በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ::
የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም::" †††
(መዝ. 36:28)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

© ዝክረ ቅዱሳን ማኀበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zikrekdusannbot

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

21 Jan, 13:07


❀✞ምኀራኤል ወእኊሁ ፵፻፴ ወ፬ ሐራ ማኀበራነ ቅዱስ ቂርቆስ ወአርከሌዲስ ዘተናገረ በድኑ ወእመራዶስ ወመኪሞስ እኀወ ዱማቲዎስ።✞❀

የጥር ፲፬ #ግጻዌ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺

ዘነግህ ምስባክ

‹‹ፍኖተ ጽድቅከ አብደርኩ። ወኵነኔከሰ ኢረሳዕኩ። ተለውኩ ስምዐከ እግዚኦ ኢታስተኀፍረኒ።››

‹‹የእውነትህን መንገድ መረጥሁ፥ ፍርድህንም አልረሳሁም።አቤቱ፥ ምስክርህን ተጠጋሁ፤ አታሳፍረኝ።››
🌺📖መዝሙር ፻፲፰፡፴

ወንጌል ዘነግህ

🌺📖የማቴዎስ ወንጌል ፲፡፳፰-፴፪
፳፰ ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።
፳፱ ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም።
፴ የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል።
፴፩ እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ።
፴፪ ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤

የዕለቱ ቅዳሴ ምንባባት

🌺📖ወደ ገላትያ ሰዎች ፩፡፲፭-ፍጻሜው
፲፭-፲፮ ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥
፲፯ ከእኔም በፊት ሐዋርያት ወደ ነበሩት ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፥ ነገር ግን ወደ ዓረብ አገር ሄድሁ እንደ ገናም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ።
፲፰ ከዚህ ወዲያ ከሦስት ዓመት በኋላ ኬፋን ልጠይቅ ወደ ኢየሩሳሌም ወጥቼ ከእርሱ ጋር አሥራ አምስት ቀን ሰነበትሁ፤
፲፱ ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በቀር ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም።
፳ ስለምፅፍላችሁም ነገር፥ እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት ሐሰት አልናገርም።
፳፩ ከዚያ ወዲያ ወደ ሶርያና ወደ ኪልቅያ አገር መጣሁ።
፳፪ በክርስቶስም ያሉት የይሁዳ ማኅበሮች ፊቴን አያውቁም ነበር፤
፳፫ ነገር ግን፦ ቀድሞ እኛን ያሳድድ የነበረ፥ እርሱ በፊት ያጠፋው የነበረውን ሃይማኖት አሁን ይሰብካል ተብሎ ሲነገር ይሰሙ ነበር፤
፳፬ ስለ እኔም እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበር።

🌺📖፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ፭፡፲፰-ፍጻሜው
፲፰ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።
፲፱ ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።
፳ የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።
፳፩ ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።

🌺📖የሐዋርያት ሥራ ፳፪፡፲፬-፳፪
፲፬ እርሱም አለኝ፦ የአባቶቻችን አምላክ ፈቃዱን ታውቅ ዘንድና ጻድቁን ታይ ዘንድ ከአፉም ድምፅን ትሰማ ዘንድ አስቀድሞ መርጦሃል
፲፭ ባየኸውና በሰማኸው በሰው ሁሉ ፊት ምስክር ትሆንለታለህና።
፲፮ አሁንስ ለምን ትዘገያለህ? ተነሣና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ ከኃጢአትህም ታጠብ።
፲፯ ወደ ኢየሩሳሌምም ከተመለሱ በኋላ በመቅደስ ስጸልይ ተመስጦ መጣብኝ፥
፲፰ እርሱም፦ ፍጠን ከኢየሩሳሌምም ቶሎ ውጣ፥ ስለ እኔ የምትመሰክረውን አይቀበሉህምና ሲለኝ አየሁት።
፲፱ እኔም፦ ጌታ ሆይ፥ በአንተ የሚያምኑትን በምኵራብ ሁሉ እኔ በወኅኒ አገባና እደበድብ እንደ ነበርሁ እነርሱ ያውቃሉ፤
፳ የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር አልሁ።
፳፩ እርሱም፦ ሂድ፥ እኔ ወደ አሕዛብ ከዚህ ወደ ሩቅ እልክሃለሁና አለኝ።
፳፪ እስከዚህም ቃል ድረስ ይሰሙት ነበር፥ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው፦ እንደዚህ ያለውን ሰው ከምድር አስወግደው፥ በሕይወት ይኖር ዘንድ አይገባውምና አሉ።

ምስባክ ዘቅዳሴ

‹‹ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕዎ ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን።››

‹‹ የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ። የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤››
🌺📖መዝሙር ፸፰ ፥ ፲-፲፩

ወንጌል ዘቅዳሴ

🌺📖የማርቆስ ወንጌል ፲፡፳፱-፴፩
፳፱ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ፥
፴ አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን ወንድሞችንና እኅቶችንም እናቶችንም ልጆችንም እርሻንም መቶ እጥፍ፥ በሚመጣውም ዓለም የዘላለም ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም።
፴፩ ግን ብዙ ፊተኞች ኋለኞች ኋለኞችም ፊተኞች ይሆናሉ።


🌺📖የዮሐንስ ወንጌል ፫፡፳፪-ፍጻሜው
፳፪ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ፥ በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር።
፳፫ ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን በዚያ ብዙ ውኃ ነበርና ያጠምቅ ነበር፥
፳፬ እየመጡም ይጠመቁ ነበር ዮሐንስ ገና ወደ ወኅኒ አልተጨመረም ነበርና።
፳፭ ስለዚህም በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከል ስለ ማንጻት ክርክር ሆነ።
፳፮ ወደ ዮሐንስም መጥተው፦ መምህር ሆይ፥ በዮርዳኖስ ማዶ ከአንተ ጋር የነበረው አንተም የመሰከርህለት፥ እነሆ፥ እርሱ ያጠምቃል ሁሉም ወደ እርሱ ይመጣሉ አሉት።
፳፯ ዮሐንስ መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ ከሰማይ ካልተሰጠው ሰው እንዳች ሊቀበል አይችልም።
፳፰ እናንተ፦ እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፥ ነገር ግን፦ ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ እንዳልሁ ራሳችሁ ትመሰክሩልኛላችሁ።
፳፱ ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ።
፴ እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።
፴፩ ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው።
፴፪ ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ ምስክሩንም የሚቀበለው የለም።
፴፫ ምስክሩን የተቀበለ እግዚአብሔር እውነተኛ እንደ ሆነ አተመ።
፴፬ እግዚአብሔር የላከው የእግዚአብሔርን ቃል ይናገራልና፤ እግዚአብሔር መንፈሱን ሰፍሮ አይሰጥምና።
፴፭ አባት ልጁን ይወዳል ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል።
፴፮ በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።


✥✥✥ ️ቅዳሴ፦ ዘኤጲፋንዮስ (ዐቢይ)

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

21 Jan, 04:21


እመሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕ(የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት)🙏🙏🙏

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

21 Jan, 04:20


ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ:
ዝክረ ቅዱሳን ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት - ዘብሔረ ጎንደር (ዲ/ዮርዳኖስ አበበ):
እንኩዋን ለጻድቃን ቅዱሳን አቡነ ዘርዓ ቡሩክ እና 7ቱ ደቂቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

አቡነ ዘርዓ ቡሩክ

=>ሃገራችን ኢትዮዽያ:-
*ብሉይ ከሐዲስ ያልጐደለባት
*በክርስቶስና በድንግል እናቱ ኪደተ እግር የተቀደሰች
*የቅዱሳን መጠጊያ እና
*ብዙ ቅዱሳንን ከእቅፏ ያፈራች ስለ ሆነች የተባረከች ሃገር ትባላለች::

+ሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ቅዱሳንን አፍርተዋል:: በምሥራቅም: በምዕራብም: በሰሜንም: በደቡብም ያሉ አካባቢዎች ሁሉ የቅዱሳን ቤቶች ናቸው:: ቅዱሳንን በብዛት ካፈሩ አካባቢዎች አንዱ ደግሞ ምድረ ጐጃም ነው::

+በጐጃም አካባቢ ከተነሱ ቅዱሳን ደግሞ አንዱና ስመ ጥሩ ጻድቅ አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ናቸው:: አቡነ ዘርዓ ቡሩክ በብዙ ጐዳና የተለዩ አባት ናቸው:: ለመጥቀስ ያህል እንኩዋ:-

1.በታሪክ ዓለምን ከበው የያዙ 2ቱ ግሩማን አራዊት (ብሔሞትና ሌዋታንን) ጥርስ ቆጥረው: ብዙ ምሥጢራትንም ተመልክተው ተመልሰዋል:: (በነገራችሁ ላይ ይህ ጉዳይ ዛሬም ድረስ ሳይንሱ በብዙ ድካም ያልደረሰበት ነው)
2.ጻድቁ በልደታቸው ጊዜ ዓይነ ስውራንን አብርተዋል:: ለራሳቸው ግን ይህን የግፍ ዓለም ላለማየት ጸልየው ዓይናቸው እንዲጠፋ አድርገዋል::
3.መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል ቅዱስ ኢያሱ በገባኦን ፀሐይን አቁሟል:: ዘርዓ ቡሩክ ግን በጥበበ እግዚአብሔር ፀሐይን ለ5 ዓመት አቁመዋል::
4.ጻድቁ ከንጽሕናቸው ብዛት 12 ክንፍ (መንፈሳዊ ክንፍ) ተሰጥቷቸው ነበር:: ከዚህ በተረፈም በጾም: በጸሎት: በትርምትና በስብከተ ወንጌል ፍጹም ጽሙድ ነበሩ::

+ጻድቁ የተወለዱት በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን እዚያው ጐጃም ውስጥ ሲሆን አባታቸው ደመ ክርስቶስ: እናታቸው ደግሞ ማርያም ሞገሳ ይባላሉ:: ወላጆች በልጅ እጦት ተማለው ይህን የተቀደሰ ፍሬ አገኙ:: "ጸጋ ኢየሱስ" ብለውታል:: ከኢየሱስ ክርስቶስ ተሰጥቷቸዋልና::

+ቀጥሎ የወለዱትንም "ተስፋ ኢየሱስ" ብለውታል:: ይህም የጻድቁ ታናሽ ወንድም ነው:: በሒደት ግን የጸጋ ኢየሱስ ስም በፈቃደ እግዚአብሔር ወደ ዘርዓ ቡሩክነት ተቀይሯል:: ጻድቁን ስመ ጥር ካደረጉዋቸው ሥራዎቻቸው መካከል በአፄ ሱስንዮስ ዘመን የሠሩት ቅድሚያውን ይወስዳል::

+ነገሩ እንዲህ ነው:: በ1598 ዓ/ም በኢትዮዽያ ላይ የነገሡት አፄ ሱስንዮስ ዼጥሮስ ፓኤዝ (ፔድሮ ፓኤዝ) ከሚባል ፈረንጅ መናፍቅ ጋር በፈጠሩት ወዳጅነት ሃይማኖታቸውን ለወጡ:: ካቶሊክ (ሮማዊ)ም ሆኑ::

+በሁዋላም አልፎንሱ ሜንዴዝ የሚሉት እሾህ መጥቶ ሁሉም የኢትዮዽያ ሕዝብ መናፍቅ እንዲሆን ከንጉሡ ጋር መከረ:: ለጊዜው በቤተ መንግስቱ አካባቢ የነበሩ መሣፍንት ተቀላቀሉ:: እየቆየ ግን ዜናው በመላ ሃገሪቱ ተሰማ::

+በተለይ በ1611 በተዋሕዶ አማኞችና በመናፍቁ ንጉሥ መካከል ነገሩ ተካሮ ዻዻሱ አቡነ ስምዖን ጠዳ ላይ መገደላቸው ተሰማ:: በዚህ ጊዜ ገበሬው ከእርሻው: ሴቷ ከማዕድ ቤት: ካህኑ ከመቅደሱ: ነጋዴው ከገበያው እየወጡ ስለ ቀናችው ሃይማኖት ደማቸውን አፈሰሱ::

+በበዓት የተወሰኑ በሺህ የሚቆጠሩ ቅዱሳንም ወጥተው ተሰየፉ:: በዚህ ጊዜም የግሺው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ዳዊታቸውን አንግበው ለሰማዕትነት ሔዱ:: ዓባይ ወንዝ ላይ ሲደርሱ ዳዊታቸውን ወደ ወንዙ ውስጥ ጣሉት::

+ተሻግረውም ከንጉሡ አደባባይ ደንቀዝ ደረሱ:: በጊዜውም ልክ እንደነ ፍቅርተ ክርስቶስና ወለተ ዼጥሮስ እርሳቸውም መከራ ደረሰባቸው:: ንጉሡም ሳይገደሉ እንዲታሠሩ አደረገ:: በጨለማ እስር ቤትም 5 ዓመታትን ሲያሳልፉ ትኩስ ምግብን ያመጡላቸው ነበር::

+እርሳቸው ግን ምግባቸው ሰማያዊ ነበርና አልነኩትም:: ከ5 ዓመት በሁዋላም ያ ሁሉ ምግብ በተአምራት በትኩስነቱ እየጨሰ ተገኝቷል:: ዘርዓ ቡሩክም ከእሥር ተፈትተዋል::
+እግዚአብሔርም በከሐዲው ንጉሥ ላይ ፈርዶ ፋሲል ነግሷል: ሃይማኖት ተመልሷል:: ጻድቁም በዓባይ ወንዝ ላይ የጣሉት ዳዊታቸውን ሳይርስ አግኝተውታል::

+ጐጃም ሲደርሱም ሰይጣን እርሳቸውን መስሎ ሲያስት ስላገኙት ወደ ጥልቁ አስጥመውታል:: በተረፈ ዘመናቸው አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ብዙ ተጋድለው ጥር 13 ቀን ዐርፈዋል:: ታኅሳስ 13 ቀን ልደታቸው ነው::

<< ድንቅ ሠሪ አባት ናቸውና ዛሬም በግሺ ብዙ ተአምራት ይደረጋሉ >>

+" ቅዱሳን 7ቱ ደቂቅ "+

=>እነዚህ 7 ቅዱሳን ከዘመነ ሰማዕታት እስከ ዘመነ ጻድቃን የተዘረጋ ታሪክ አላቸው:: 7ቱም ባልንጀሮች ሲሆኑ በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን በኤፌሶን ተወልደው አድገዋል:: ክርስትናን ተምረውም በወጣትነታቸው የንጉሥ ጭፍሮች ሁነዋል:: የተቀጠሩትም የቤተ መንግስቱን ግምጃ ቤት ለመጠበቅ ነው::

+በሥራቸውም ሆነ በጠባያቸው ደጐች ነበሩና ንጉሡ ዳኬዎስም: ሕዝቡም ይወዷቸው ነበር:: እነርሱ ግን በጉብዝና ወራት ፈጣሪን ማሰብን መርጠው በፍቅር: በጸሎትና በምጽዋት ይተጉ ነበር:: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ ግን ጭንቅ መከራ መጣ::

+ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስትናውን ትቶ ጣዖት አምላኪ ሆነ:: አዋጅም አስነገረ:: አዋጁም "ክርስቶስን ያልካደ: ለጣዖትም ያልሰገደ: ሃብት ንብረቱ ለዘረፋ: እጅ እግሩ ለእስር: ደረቱ ለጦር: አንገቱ ለሰይፍ: ቤቱም ለእሳት ይሰጣል" የሚል ነበር:: በዚህ ምክንያት ብዙ ክርስቲያኖች ተሰደዱ::

+የበርካቶቹም ደማቸው ፈሰሰ:: ኤፌሶን የግፍና የአመጻ ከተማ ሆነች:: የመከራ ጽዋው ጊዜውን ጠብቆ ወደ 7ቱ ወጣቶች ዘንድ ደረሰ:: ንጉሡ እነሱንም አስጠርቶ "ለጣዖት ስገዱ" አላቸው:: እነርሱ ግን የአምላካቸውን ፍቅር በዋዛ የሚቀይሩ አልነበሩምና "እንቢ" አሉት::

+ንጉሡ ምንም ክፉና አውሬ ቢሆንም ይወዳቸዋል:: ሊገድላቸው አልፈለገምና አሳሰራቸው:: ከቀናት በሁዋላ አስጠርቶ ሊያታልላቸው ሞከረ:: ግን አልተሳካለትም:: በዚያ ወራት ጦርነት ይበዛ ነበርና ግዛት ለማስፋትም ቢሉ ለማስገበር ዳኬዎስ ወጣ::

+ከመውጣቱ በፊት ግን 7ቱን አስጠርቶ "አሁን ከእስር ፈትቻቹሃለሁ:: ከጦርነት እስክመለስ ከልባችሁ ጋር ምከሩ:: ካልሆነ ሞት ይጠብቃቹሃል" ብሏቸው ነበር የወጣው:: ቅዱሳኑ ንጉሡ እንደ ወጣ ተቀምጠው መከሩ:: ውሳኔንም አስተላለፉ::

+ዓለምን ንቀው: ሃብት ንብረታቸውን መጽውተው: ትንሽ ሳንቲም ብቻም ይዘው በድብቅ ወጡ:: አንድ ወታደር (በጐች አሉት) ይከተላቸው ነበርና የት እንደ ገቡ ተመለከተ:: ቅዱሳኑ ዘወትር በመዓልትና በሌሊት በበዓታቸው ውስጥ ይተጉ ነበር:: ከእነሱም አንዱ በተራ እየወጣ ቂጣ ይገዛ ነበር::

+አንድ ቀን ግን ከእነሱ አንዱ ራት ሊገዛ ሲወጣ ንጉሡ መመለሱን ሰማ:: ወደ በዓቱ ተመልሶ ለወንድሞቹ ነገራቸው:: ከዚያች ቀን በሁዋላ 7ቱም አልወጡም:: በዓታቸውን ዘግተው ሲጸልዩ ደክሟቸው ተኙ:: ከዚያች ቀን በሁዋላ ግን አልነቁም::

+ያ የበጐች ባለቤት (ወታደር) ለብዙ ቀናት አለመውጣታቸውን ሲመለከት "ሙተዋል" ብሎ አዘነ:: በድብቅ ክርስቶስን ያመልከው ነበርና:: እርሱ የቅዱሳኑን ተጋድሎ በድንጋይ ሰሌዳ ላይ ጽፎ ወደ በዓታቸው ውስጥ ጣለው::

+ትልቅ ድንጋይም አምጥቶ ገጠመው:: እነዚህ ቅዱሳን ተኝተዋልና አልነቁም:: ቀናት: ወራት: ዓመታት ተዋልደው ለ372 ዓመት ተኙ:: አንድ ቀን አንድ እረኛ ለሥራ ፈልጐት ድንጋዩን ፈነቀለው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳኑ ነቁ::

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

21 Jan, 04:20


+በወቅቱ መልካቸው የወጣት ነው:: እድሜአቸው ግን 400 ሊሞላ ትንሽ ቀርቶት ነበር:: ልክ እንደ አቤሜሌክ ብዙ መተኛታቸው አልታወቃቸውምና ከመካከላቸው አንዱ የራት ዳቦ ሊገዛ ቢወጣ ግራ ተጋባ:: ኤፌሶን የማያውቃት ሌላ ሃገር ሆነችበት:: ከተማዋ ዘምናለች::+በየቦታው አብያተ ክርስቲያናት: ቅዱስ መስቀልም በየአደባባዩ ተተክለዋል:: ነገሩ ግር ቢለው አንዱን ከመንገድ ጠርቶ "ወንድሜ! ይህቺ ከተማ ኤፌሶን አይደለችምን?" አለው:: እርሱም "አዎ ናት" ብሎት አለፈ::

+ችግሩ ግን "ራት ልግዛ" ብሎ ወደ ገበያ ሲሔድ: እርሱ የያዘው ገንዘብ የዳኬዎስ ስም የተጻፈበት መሆኑ የፈጠረው ነበር:: በነጋዴዎቹ "የተደበቀ የጥንት ገንዘብ አግኝተሃል" በሚል ተከሶም ወደ ንጉሡ ቴዎዶስዮስ ዘንድ ቀረበ:: (ትንሹ ቴዎዶስዮስ ነው:: የነገሠውም በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው)

+በክርክሩ መካከል ቅዱሱ የእሱንና የወንድሞቹን ነገር ሲናገር ንጉሡም: ሊቀ ዻዻሱም (አባ ቴዎድሮስ ይባላል) ተገረሙ:: አብረው ከከተማ ወጥተው ሔደው: 7ቱንም ሲጸልዩ አገኟቸው:: ፊታቸውም እንደ እግረ ፀሐይ ያበራ ነበር:: 7ቱም ለ7 ቀናት በኤፌሶን ድውያንን እየፈወሱ: ሰውን ሁሉ እየባረኩ ቆዩ::

+ይህ ሁሉ የተደረገው በወቅቱ "ትንሳኤ ሙታን የለም" የሚሉ መናፍቃን ተነስተው ብዙ ሰው ክዶ ነበርና ለእነሱ ምሥክር ሊሆንባቸው ነው:: በርካቶችም በዚህ ድንቅ ተስበው ወደ ሃየማኖት ተመልሰዋል:: 7ቱ ቅዱሳን ግን በ7ኛው ቀን በክብር ዐርፈዋል:: ንጉሡ 7 የወርቅ ሣጥኖች ቀብሯቸዋል::

=>አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለን::
ጥር 13 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አቡነ ዘርዓ ቡሩክ ኢትዮዽያዊ (እረፍታቸው)
2.ሰባቱ ደቂቅ ቅዱሳን (ከኤፌሶን)
3.ቅዱስ አባ ነካሮ
4.ቅዱስ ቃሮስ

=>ወርሐዊ በዓላት
1.እግዚአብሔር አብ
2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
3.ቅዱስ አስከናፍር
4."13 ግኁሳን ጻድቃን"
5.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ
6.ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት

=>+"+ በተቀደሰ አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ:: ቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላቹሃል:: የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: +"+ (2ቆሮ. 13:12)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

21 Jan, 04:20


፭ እናቱም ለአገልጋዮቹ፦ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ አለቻቸው።
፮ አይሁድም እንደሚያደርጉት የማንጻት ልማድ ስድስት የድንጋይ ጋኖች በዚያ ተቀምጠው ነበር፥ እያንዳንዳቸውም ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር።
፯ ኢየሱስም፦ ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸው። እስከ አፋቸውም ሞሉአቸው።
፰ አሁን ቀድታችሁ ለአሳዳሪው ስጡት አላቸው፤ ሰጡትም።
፱ አሳዳሪውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴት እንደ መጣ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱት አገልጋዮች ግን ያውቁ ነበር፤ አሳዳሪው ሙሽራውን ጠርቶ፦
፲ ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል፥ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተስ መልካሙን የወይን ጠጅ እስከ አሁን አቆይተሃል አለው።
፲፩ ኢየሱስ ይህን የምልክቶች መጀመሪያ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክብሩንም ገለጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አመኑ።
፲፪ ከዚህ በኋላ ከእናቱና ከወንድሞቹ ከደቀ መዛሙርቱም ጋር ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፥ በዚያም ጥቂት ቀን ኖሩ።

✥✥✥ቅዳሴ፦ ዘሰለስቱ ምዕት (ግሩም)

🌿  @zkretewahdo
🌿  @zkretewahdo
🌿  @zkretewahdo

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

08 Jan, 03:44


ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሠላሳ(፴)
https://t.me/SinkisarZekidusan2

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

08 Jan, 03:43


የታህሳስ 30(፴) የነግህ እና የቅዳሴ ምስባክ

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

08 Jan, 03:36


እንኩዋን ለቅዱሳን ጻድቃን ወገዳማውያን "አባ ዮሐንስ" : "አባ ዘካርያስ ወአባ ዮሐንስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" አባ ዮሐንስ ዘአስቄጥስ "*+

=>ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::

+ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም (በበርሃ) ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::

+ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ40 ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ (ኤሌዎን ዋሻ) በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::

+ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::

+ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ 3ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ80 ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::

+ይህ ከሆነ ከ20 ዓመታት በሁዋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኩዋሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::

+እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::

+አባ እንጦንስ አባ መቃርስን: አባ መቃርስ አባ ዮሐንስን ወልደዋል:: አባ ዮሐንስም የታላቁ ገዳመ አስቄጥስ አበ ምኔት ሆነው በጸጋ አገልግለዋል:: አስቄጥስ በምድረ ግብጽ የሚገኝ: በስፋቱና ብዙ ቅዱሳንን በማፍራቱ ተወዳዳሪ የሌለው የዓለማችን ቁጥር አንድ ገዳም ነው::

+ሕይወተ ምንኩሰናም ወደ መላው ዓለም የተስፋፋ በዚህ ገዳም መናንያን አማካኝነት ነው:: በዚህ ገዳም ላይ የሚሾሙ አበው ደግሞ በብዛት መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸውና አባታቸውን ቅዱስ መቃርስ ታላቁን የመሰሉ ናቸውና ኃላፊነቱ እጅግ ከባድ ነው::

+በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ተወልደው ያደጉት አባ ዮሐንስ ከመነኑባት ዕለት ጀምረው በፍጹም ተጸምዶና ተጋድሎ ለፈጣሪያቸው ስለ ተገዙ የታላቁ ገዳም አበ ምኔት ሊሆኑ ተገባቸው::

+በአበ ምኔትነት ዘመናቸውም መንጋውን ይጠብቁ ዘንድ ብዙ ደከሙ:: በተለይ ቅዱስ ቃሉን ያስተምሩ ዘንድ ተጉ:: ሕይወተ መላእክትንም ያሳዩ ዘንድ በቃል ብቻ ያይደለ በተግባር ሆነው ከመንፈሳዊ አብራካቸው ብዙ ቅዱሳንን ወለዱ::

+ከዋክብቱ አባ ገዐርጊ: አባ አብርሃም: አባ ሚናስ: አባ ዘካርያስ . . . የአባ ዮሐንስ ፍሬዎች ናቸውና:: ጻድቁ በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: ከዕረፍታቸው በሁዋላ እንኩዋ መግነዛቸውና የልብሳቸው እራፊ ብዙ ድውያንን ፈውሷል::

+አንድ ጊዜም ለልጆቻቸው መነኮሳት ቤዛ ሆነው በበርበር (አረማውያን) ተማርከዋል:: በዚያም ክፉዎች ባሪያ ቢያደርጉዋቸው እግዚአብሔር ድንቅን ሠርቶ ወደ ገዳማቸው መልሷቸዋል:: ከብዙ ተጋድሎ በሁዋላም በ90 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈው በበዓታቸው ተቀብረዋል::

+"+ አባ ዘካርያስ ገዳማዊ +"+

=>ይሕም ቅዱስ የተነሳው በዚያው በዘመነ ጻድቃን ነው:: ምንም ክርስቲያን ቢሆንም በቀደመ ሕይወቱ ገንዘብ የሚጥመው ነጋዴ ነበር:: በንግድ ሥራውም ሃብታም መሆን ችሎ እንደ ነበር ዜና ሕይወቱ ይናገራል::

+እግዚአብሔር ሁሉም የሰው ልጆች ወደ መንግስተ ሰማያት ቢገቡ መልካም ፈቃዱ ነው:: ያ ብቻ አይደለም:: ለእያንዳንዱ ሰው የድኅነት ጥሪን በተለያየ መንገድ ያቀርብለታል:: ድምጹን ለሰማ ወደ ወንጌል ወደብ ያደርሰዋል::

+አንዳንዴ "እንቢ" ስንለው እንደ በጐ አባትነቱ በተግሣጹ ሊጠራንም ይችላል:: ተግሣጹም በደዌ: በአደጋና በመሰል መንገዶች ሊሆን ይችላል:: ዋናው ቁም ነገር ግን ጊዜው ሳያልፍብን: ቀኑም ሳይመሽብን ድምጹን መስማት: ለቃሉ መታዘዝ: ጥሪውንና ተግሣጹን አለማቃለል ነው::

+አባ ዘካርያስም የቅድስና ሕይወት ጥሪ የደረሰው ለሥጋ ገበያ ሲታትር ነበር:: አንድ ቀን ንብረቱን ይዞ ለንግድ መንገድ ላይ ሳለ ሽፍቶች ያዙት:: ሊያርዱት አጋድመውት ሳለ ግን የገዳመ ዻኩሚስ አበ ምኔት በሥፍራው ነበርና ጮኸባቸው::

+ቅዱሱ አበ ምኔት አካሉ በገድል ያለቀ ቢሆንም ድምጹ እንደ ነጐድጉዋድ ሲመጣ ገዳዮቹ ደንግጠው በረገጉ:: ዘካርያስም ከሞት ተረፈ:: እንደ ገና ሃብቱን ይዞ ወደ ከተማ ሲገባ በሃገረ ገዢው ተይዞ ሞት ተፈረደበት:: ከገንዘቡ መብዛት የተነሳ ዘራፊ መስሏቸው ነበርና:: በዚህ ጊዜም እግዚአብሔር በመኮንኑ ልብ ርሕራሔን ጨምሮ አዳነው::

+በዚያች ሌሊት ግን ነገሮችን ያስተዋለው ዘካርያስ የተፈጠሩት አጋጣሚወች የፈጣሪው ጥሪ እንደ ሆኑ አስተዋለ:: ወዲያውም ለዓይነ ሥጋ የሚያሳሳውን ያን ሁሉ ንብረቱን መጽውቶ በርሃ ገባ:: በደብረ አባ ዻኩሚስም መንኩሶ በዓት ወሰነ::

+ከዚያች ቀን ጀምሮም በፍጹም አምልኮ: በጾምና በጸሎት እግዚአብሔርን እያገለገለ ከርኩሳን መናፍስት ጋር ታገለ:: በእግሩም ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዞ ቅዱሳት መካናትን ተሳለመ:: አንድ ጊዜም ሰይጣን ሰው መስሎ "አባትህ ሳልሞት ልየው እያለህ ነው" አለው:: ውስጡ ግን ፈቃደ ሥላሴ ነበረበትና "እሺ" ብሎ ሒዶ: አባቱን ቀብሮ ተመልሷል::

+ቅዱስ አባ ዘካርያስ ከብቃቱ የተነሳ የሚኖረው ከግሩማን አራዊት ጋር ነበር:: ሁሉንም አራዊትም ይመግባቸው ነበር:: በተለይ ደግሞ ዘንዶዎች ሰውን እንዳይጐዱ አዝዞ እርሱ ይመግባቸው ነበር:: የተጋድሎ ዘመኖቹን ከፈጸመ በሁዋላም በዚህች ቀን በክብር ዐርፏል::

+"+ አባ ዮሐንስ ብጹዕ +"+

=>ይህም ቅዱስ በተመሳሳይ የዘመነ ጻድቃን ቅዱሳን ፍሬ ነው:: "ኢትርአይ ገጻ : ወኢትስማዕ ድምጻ" በሚለው ሕገ ተባሕትዎ ለ40 ዓመታት ተወስኖ ኑሯል::

+ይህም ማለት አንድ ወንድ ከመነነ በሁዋላ ሴቶችን እንዲያይና ከእነርሱም ጋር እንዲያወራ አይፈቀድለትም:: ሴትም ብትመንን ሕጉ ያው ነው:: (ዛሬ እየተደረገ ያለውን ግን ፈጣሪ ይመርምረው)

+አባ ዮሐንስ ብጹዕም እንዲህ ባለ ፈሊጥ: ማለትም በጾምና በጸሎት: ከዓለም ተለይቶ: ከሴት ርቆ: ንጽሕ ጠብቆ ሲኖር አረጀ:: በጊዜው በከተማ የሚኖር አንድ መስፍን ወዳጅ ነበረው:: ይህ መስፍን ዘወትር ወደ ጻድቁ እየመጣ ይባረካል::

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

08 Jan, 03:36


+ሚስቱ ግን በረከቱን ሽታ ልታየው ብትሞክርም አልተሳካም:: ሕገ ምናኔ አይፈቅድምና:: በዚህ ነገር ፈጽማ ማዘኗን በጸጋ ያወቀው አባ ዮሐንስ ግን በራዕይ ወደ እርሷ መጣ::+"ሚ ሊተ ወለኪ ብእሲቶ - አንቺ ሆይ! ለምን ካላየሁህ እያልሽ ትዘበዝቢኛለሽ? እኔ ነቢይ ወይ ጻድቅ አይደለሁ" ብሏት ባርኯ ተሠወራት:: እርሷም ደስ ብሏት ለባሏ ነገረችው:: ባሏ ወደ ጻድቁ ሲሔድም ገና ሳይነጋገሩአባ ዮሐንስ ሳቅ ብሎ "ሚስትህ ደስ አላት አይደል?" ብሎታል:: ጻድቁ በ90 ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፎ ተቀብሯል::

=>አምላከ ጻድቃን ቅዱሳን ስለ ወዳጆቹ በጐ ምኞታችንን ይፈጽምልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

=>ታሕሳስ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.አባ ዮሐንስ አበ ምኔት
2.አባ ዘካርያስ ገዳማዊ
3.አባ ዮሐንስ ብጹዕ
4."144 ሺ" ሕጻናት (ሔሮድስ የገደላቸው)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
2.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
5.አባ ሣሉሲ ክቡር ጻድቅ

=>+"+ ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኑራችሁ: ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ:: እንደሚታዘዙ ልጆች ባለ ማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ:: ዳሩ ግን 'እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ' ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ:: +"+ (1ዼጥ. 1:13)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>


© ዝክረ ቅዱሳን ማኀበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zikrekdusannbot

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

08 Jan, 03:29


❀✞ተዝካረ ሕፃናት ወአባ ዮሐንስ ክቡር ወክርዮን ወፊልሞን ወ፵ሐራ ሰማይ ወዮሐንስ ወአባ ዘካርያስ።✞❀

የታህሳስ ፴
🌺🌺🌺🌺🌺🌺

ዘነግህ ምስባክ

‹‹የሐዩ ወይሁብዎ እምወርቀ ዓረብ፣ ወዘልፈ ይጼልዩ በእንቲአሁ። ወኵሎ አሚረ ይድርኀዎ››

‹‹ርሱ ይኖራል ከዐረብም ወርቅ ይሰጡታል፤ ኹልጊዜም ወደርሱ ይጸልያሉ፥ ዘወትርም ይባርኩታል።››
🌺📖መዝሙር ፸፩ ፥ጰ፲፭

ወንጌል ዘነግህ

🌺📖የሉቃስ ወንጌል ፪ ፥ ፩-፳፩
፩ በዚያም ወራት ዓለሙ ሁሉ እንዲጻፍ ከአውግስጦስ ቄሣር ትእዛዝ ወጣች።
፪ ቄሬኔዎስ በሶርያ አገር ገዥ በነበረ ጊዜ ይህ የመጀመሪያ ጽሕፈት ሆነ።
፫ ሁሉም እያንዳንዱ ይጻፍ ዘንድ ወደ ከተማው ሄደ።
፬-፭ ዮሴፍም ደግሞ ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ ከገሊላ ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ ቤተ ልሔም ወደምትባል ወደ ዳዊት ከተማ ወደ ይሁዳ፥ ፀንሳ ከነበረች ከእጮኛው ከማርያም ጋር ይጻፍ ዘንድ ወጣ።
፮ በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፥
፯ የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው።
፰ በዚያም ምድር መንጋቸውን በሌሊት ሲጠብቁ በሜዳ ያደሩ እረኞች ነበሩ።
፱ እነሆም፥ የጌታ መልአክ ወደ እነርሱ ቀረበ የጌታ ክብርም በዙሪያቸው አበራ፥ ታላቅ ፍርሃትም ፈሩ።
፲ መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
፲፩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
፲፪ ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ።
፲፫ ድንገትም ብዙ የሰማይ ሠራዊት ከመልአኩ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፦
፲፬ ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ አሉ።
፲፭ መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ፥ እረኞቹ እርስ በርሳቸው፦ እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ ተባባሉ።
፲፮ ፈጥነውም መጡ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ።
፲፯ አይተውም ስለዚህ ሕፃን የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ።
፲፰ የሰሙትን ሁሉ እረኞቹ በነገሩአቸው ነገር አደነቁ፤
፲፱ ማርያም ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር።
፳ እረኞችም እንደ ተባለላቸው ስለ ሰሙትና ስላዩት ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ ተመለሱ።
፳፩ ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ፥ በማኅፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደ ተባለ፥ ስሙ ኢየሱስ ተብሎ ተጠራ።

የዕለቱ ቅዳሴ ምንባባት

🌺📖ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ፫፡፲፭-ፍጻሜው
፲፭ እንግዲህ ፍጹማን የሆንን ሁላችን ይህን እናስብ፤ በአንዳች ነገርም ልዩ አሳብ ቢኖራችሁ፥ እግዚአብሔር ይህን ደግሞ ይገልጥላችኋል፤
፲፮ ሆኖም በደረስንበት በዚያ እንመላለስ።
፲፯ ወንድሞች ሆይ፥ እኔን የምትመስሉ ሁኑ፥ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ፥ እንዲሁ የሚመላለሱትን ተመልከቱ።
፲፰ ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ።
፲፱ መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።
፳ እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤
፳፩ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።

🌺📖፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ፪፡፲፪-፳፩
፲፪ ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።
፲፫ ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤
፲፬ ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ።
፲፭ በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤
፲፮ አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።
፲፯ ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ንጉሥን አክብሩ።
፲፰ ሎሌዎች ሆይ፥ ለበጎዎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሃት ሁሉ ተገዙ።
፲፱ በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባዋልና።
፳ ኃጢአት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሡ፥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሡ፥ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል።
፳፩ የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።

🌺📖የሐዋርያት ሥራ ፲፱፡፰-፳፩
፰ ወደ ምኵራብም ገብቶ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየተነጋገረና እያስረዳቸው ሦስት ወር ያህል በግልጥ ይናገር ነበር።
፱ አንዳንዶች ግን እልከኞች ሆነው በሕዝብ ፊት መንገዱን እየሰደቡ ባላመኑ ጊዜ፥ ከእነርሱ ርቆ ደቀ መዛሙርትን ለየ፥ ጢራኖስም በሚሉት በትምህርት ቤት ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር።
፲ በእስያም የኖሩት ሁሉ አይሁድም የግሪክ ሰዎችም የጌታን ቃል እስኪሰሙ ድረስ ሁለት ዓመት ያህል እንዲህ ሆነ።
፲፩ እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥
፲፪ ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር።
፲፫ አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች፦ ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ።
፲፬ የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት።
፲፭ ክፉው መንፈስ ግን መልሶ፦ ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው።
፲፮ ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም።
፲፯ ይህም በኤፌሶን በሚኖሩት ሁሉ በአይሁድና በግሪክ ሰዎች ዘንድ የታወቀ ሆነ፥ በሁላቸውም ላይ ፍርሃት ወደቀባቸው፥ የጌታም የኢየሱስ ስም ተከበረ፤
፲፰ አምነውም ከነበሩት እጅግ ሰዎች ያደረጉትን እየተናዘዙና እየተናገሩ ይመጡ ነበር።
፲፱ ከአስማተኞችም ብዙዎቹ መጽሐፋቸውን ሰብስበው በሰው ሁሉ ፊት አቃጠሉት፤ ዋጋውም ቢታሰብ አምሳ ሺህ ብር ሆኖ ተገኘ።
፳ እንዲህም የጌታ ቃል በኃይል ያድግና ያሸንፍ ነበር።
፳፩ ይህም በተፈጸመ ጊዜ ጳውሎስ፦ ወደዚያ ደርሼ ሮሜን ደግሞ አይ ዘንድ ይገባኛል ብሎ በመቄዶንያና በአካይያ አልፎ ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄድ በመንፈስ አሰበ።

ምስባክ ዘቅዳሴ

‹‹ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕዎ ይባዕ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሓን።››

‹‹ የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ። የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤››
🌺📖መዝሙር ፸፰ ፥ ፲-፲፩

ወንጌል ዘቅዳሴ

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

08 Jan, 03:29


🌺📖የማቴዎስ ወንጌል ፪፡፩-፲፫
፩-፪ ኢየሱስም በይሁዳ ቤተ ልሔም በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰብአ ሰገል፦ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? ኮከቡን በምሥራቅ አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና እያሉ ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ።
፫ ንጉሡ ሄሮድስም ሰምቶ ደነገጠ፥ ኢየሩሳሌምም ሁሉ ከእርሱ ጋር፤
፬ የካህናትንም አለቆች የሕዝቡንም ጻፎች ሁሉ ሰብስቦ ክርስቶስ ወዴት እንዲወለድ ጠየቃቸው።
፭-፮ እነርሱም፦ አንቺ ቤተ ልሔም፥ የይሁዳ ምድር፥ ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሽም፤ ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፎአልና በይሁዳ ቤተ ልሔም ነው አሉት።
፯ ከዚህ በኋላ ሄሮድስ ሰብአ ሰገልን በስውር ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ዘመን ከእነርሱ በጥንቃቄ ተረዳ፥
፰ ወደ ቤተ ልሔምም እነርሱን ሰድዶ፦ ሂዱ፥ ስለ ሕፃኑ በጥንቃቄ መርምሩ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔ ደግሞ መጥቼ እንድሰግድለት ንገሩኝ አላቸው።
፱ እነርሱም ንጉሡን ሰምተው ሄዱ፤ እነሆም፥ በምሥራቅ ያዩት ኮከብ ሕፃኑ ባለበት ላይ መጥቶ እስኪቆም ድረስ ይመራቸው ነበር።
፲ ኮከቡንም ባዩ ጊዜ በታላቅ ደስታ እጅግ ደስ አላቸው።
፲፩ ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
፲፪ ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሄዱ።
፲፫ እነርሱም ከሄዱ በኋላ እነሆ፥ የጌታ መልአክ በሕልም ለዮሴፍ ታይቶ፦ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፥ እስክነግርህም ድረስ በዚያ ተቀመጥ አለው።

✥✥✥ቅዳሴ፦ ዘእግዝአትነ (ጎሥዓ)

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

07 Jan, 22:19


+++"ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት ወድቀውም ሰገዱለት ሳጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት" ተብሎ እንደተጻፈ ማቴ 2:11

እንኳን ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ በዓለ ልደት አደረስን/ እደረሳችሁ።
ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሃያ ዘጠኝ(፳፱)
https://t.me/SinkisarZekidusan2

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

06 Jan, 19:59


ጌታችን ስለተወለደባት ምሽት ቅዱስ ኤፍሬም አንዲህ አለ....
.
‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡ ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!

ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም! ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡ ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን! ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው እንዳይታበይባት! ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን አንበቀልባት! የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት! የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!

ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው! ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡ ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!

የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት! ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!››

እንኳን ለአምላካችን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

03 Jan, 03:14


ስንክሳር ዘወርሃ ታህሣሥ ሃያ አምስት(፳፭)
https://t.me/SinkisarZekidusan2

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

03 Jan, 03:14


የታህሳስ ፳፭ የነግህ እና የቅዳሴ ምስባክ ዜማ

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

02 Jan, 18:21


እንኩዋን ለ5ቱ "ቅዱሳን መቃብያን" እና "ቅዱስ ዮሐንስ ከማ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

+*" 5ቱ መቃብያን "*+

=>እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን: 22ቱን ሥነ ፍጥረትን ፈጥሮ አዳምን ገዢ አደረገው:: አክሎም በነፍስ ሕያው አድርጐ: በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ: ነቢይና ካህን አድርጐ: ካንዲት ዕፀ በለስ በቀር በፍጥረት ሁሉ ላይ አሰለጠነው::

+አባታችን አዳም ግን ስሕተት አግኝቶት ከገነት ወጣ:: መከራና ፍዳም አገኘው:: በሁዋላም ለ100 ዓመት አልቅሶ ንስሃ ገባ:: ጌታም ንስሃውን ተቀብሎ "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ተስፋ ድህነትን ሰጠው::

+ስለዚህም ምክንያት ለ5,500 ዓመታት ትንቢት ሲነገር: ሱባኤ ወደ ታች ሲቆጠር: ምሳሌም ሲመሰል ኖረ:: ከደግ ፍጥረት አዳም እስከ ኖኅ ድረስ: የሴት ልጆች እግዚአብሔርን በንጽሕና ሁነው በደብር ቅዱስ አመለኩ::

+ትንሽ ቆይተው ግን ስለተቀላቀሉ ከቃየን ልጆች ጋር በማየ ድምሳሴ ጠፉ:: በጻድቅ ሰው ኖኅ የተጀመረው ትውልድም እግዚአብሔርን ለመዘንጋት ጊዜ አልፈጀበትም:: ነገር ግን ከሴም ዘር ቅንና ጻድቅ ሰው አብርሃም ተገኘ::

+ከእርሱም ይስሐቅ: ከዚያም ያዕቆብ ደጋጉ ተገኙ:: ያዕቆብም "እሥራኤል" ተብሎ በልጆቹ "ሕዝበ እግዚአብሔር" የተባለ ነገድ ተመሠረተ:: በተስፋይቱ ምድር በከነዓን እንዳይኖሩም ረሃብ ምድረ ግብጽ አወረዳቸው::

+በዚያም ለ215 ዓመታት በጭንቅ የባርነትን ሕይወትን አሳለፉ:: እግዚአብሔርም ስለ ወዳጁ አብርሃም ሲል እሥራኤልን አሰባቸው:: የዋሕና ጻድቅ ሰው ሙሴን አስነስቶ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አዳናቸው::

+ይኸውም በጸናች እጅ: በበረታችም ክንድ: በ9 መቅሰፍት: በ10ኛ ሞተ በኩር: በ11ኛ ስጥመት ግብጻውያንን አጥፍቶ ነው:: በየመንገዱም ጠላቶቻቸውን እየተበቀለላቸው ነው:: ከዚህ ዘመን ጀምሮም እሥራኤል በመሳፍንትና በካህናት የሚተዳደሩ ሆኑ::

+አስቀድሞ ሙሴ በምስፍና: አሮን በክህነት መሯቸው:: ቀጥሎም በቅዱስ ሙሴ ኢያሱ: በአሮን አልዓዛር ተተኩ::

+ከዚህ በሁዋላ ለ300 ዓመታት ያህል መሣፍንት እየተቀያየሩ አስተዳደሩዋቸው:: ሲበድሉ ጠላት እየገዛቸው: ሲጸጸቱ በጐ መሥፍን እየመጣላቸው ከነቢዩ ሳሙኤል ደረሱ::

+በዚህ ጊዜም ሕዝቡ እንደ አሕዛብ ሥርዓት ንጉሥ በመፈለጋቸው ክፉው ሳዖል ለ40 ዓመት ገዛቸው:: ቀጥሎ ግን እንደ አምላክ ልብ የሆነ ቅዱስ ሰው ዳዊት ነግሦላቸው እሥራኤል ከፍ ከፍ አሉ:: ከቅዱስ ዳዊት እስከ ሮብዓም ቆይተው ግን እሥራኤል ከ2 ተከፈሉ::

+10ሩ ነገድ በሰማርያ ሲኖሩ ግፍን ስላበዙ ስልምናሶር ማርኮ አሦር አወረዳቸው:: ባሮችም አደረጋቸው:: 2ቱ ነገድ ደግሞ ከብረው: ገነው በኢየሩሳሌም ቢኖሩም እነርሱም አመጸኞች ነበሩና ናቡከደነጾር ወስዶ የባቢሎን ባሪያ አደረጋቸው::

+እግዚአብሔር ግን እንደ ነቢያቱ ቃል 70ው ዘመን ሲፈጸም በኃይል ወደ ርስታቸው መለሳቸው:: በዚያም ዘሩባቤል የሚባል ደግ ንጉሥ ነግሦላቸው: ቤተ መቅደስ ታንጾላቸው ኖሩ:: ክፋታቸው ግን ማብቂያ አልነበረውምና ከዘሩባቤል በሁዋላ ቅን ንጉሥን ማግኘት አልቻሉም::

+እግዚአብሔር ግን ምሕረቱንና መግቦቱን አይተውምና አልዓዛርን የመሰሉ ደጋግ ካህናትን እያስነሳ ሰው እስከሚሆንባት ቀን ድረስ አቆይቷቸዋል:: በዚህም ምክንያት ይህ ዘመን "ዘመነ ካህናት" ተብሏል::

+በዚህ በዘመነ ካህናት ውስጥ ደግሞ በጐነታቸው የታወቀላቸው: ግን ደግሞ መከራው የበዛባቸው እሥራኤላውያን ነበሩ:: ብዙ ጊዜ የሚጠሩት "መቃብያን" በሚል ስም ነው::

+በያዕቆብ እሥራኤል: በዔቦር ዕብራውያን: በይሁዳ አይሁድ: በፋሬስ ፈሪሳውያን: በሳዶቅ ሰዱቃውያን እንደተባሉት ሁሉ እነዚህም በአባታቸው በመቃቢስ ምክንያት መቃብያን ተብለዋል:: ታሪካቸው ሰፊና በመጽሐፈ መቃብያን የተጻፈ ሲሆን እኛ ግን በአጭሩ አንዷን የታሪክ ዘለላ ብቻ እንመለከታለን::

+በዘመኑ መቃቢስ የሚባል ደግ ሰው 5 (3) ወንዶች ልጆችን (መቃብያንን) ወልዶ ነበር:: እነዚህም በመልክ ይህ ቀራችሁ የማይባሉ: በጠባይ እጅግ የተመሰገኑ: በኃይላቸው ጽናትም የተፈሩ ነበሩ::

+በተለይ 3ቱ ከግሩማን አራዊት አንበሳና ድብ ታግለው ያሸነፉ: በጦርነትም ጠላትን ያንበረከኩ ነበሩ:: ታዲያ ይህ ሁሉ የተሰጣቸው ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ያውቁ ነበርና ፈጣሪያቸውን በንጹሕ ልብ ያመልኩት ነበር::

+በዘመኑ ደግሞ ሞዐባውያንና ሜዶናውያን አካባቢውን ያስገብሩ ነበር:: በተለይ የሞዐቡ ንጉሥ ጺሩጻይዳን ከክፋቱ ብዛት 70 ጣዖታት በወንድና በሴት ምሳሌ አስቀርጾ ያመልክ ነበር:: ከዚያም አልፎ ሕዝቡን "አምልኩ" እያለ ያውክ: ይቀጣ: ይገድልም ነበር::

+ቅዱሳን መቃብያን ይህንን ሲሰሙ ወደ እርሱ ገሰገሱ:: ምንም እንኩዋ ሊያጠፉት ኃይል ቢኖራቸውም አላደረጉትም:: ይልቁኑ ቀርበው ዘለፉት እንጂ::

+እርሱም "ጣዖትን አናመልክም" ስላሉ ለአንበሳ ጣላቸው:: አንበሶቹም ለቅዱሳኑ ሰግደው የንጉሡን ወታደሮች ፈጇቸው:: እርሱም 3ቱን ወደ እሥር ቤት ጣላቸው:: በዚህ ጊዜ 2ቱ ወንድሞቻቸው መጥተው ተቀላቀሉ::

+ቀጥሎም 5ቱንም አስወጥቶ በሰይፍ አስመታቸው:: ከተገደሉ በሁዋላም ወደ ውሃ ጥሏቸው: በእሳት አቃጥሏቸው ነበር:: ባይሳካለት ስለ ተቆጣ ሳይቀበሩ እንዲጣሉ አዘዘ:: ከ14 ቀናት በሁዋላም የቅዱሳኑ አካል እንደ መብረቅ እያብለጨለጨ ተገኝቶ በክብር እንዲቀበር ሆኗል::

<< ቀሪው ታሪካቸው በመጽሐፈ መቃብያን የተጻፈ አይደለምን !! >>

+*" አባ ዮሐንስ ከማ "*+

=>ቅዱስ ዮሐንስ ከማ በዘመነ ጻድቃን (በተለይም በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን) ከተነሱ አበው አንዱ ነው:: ቅዱሱ ድንቅ ሕይወት ስለ ነበረው በዜና አበው በስፋት ተጠቅሷል:: መጽሐፈ ስንክሳር "ከማ" የሚለውን ቃል "ከማ ብሒል ካም - 'ከማ' ማለት 'ካም' ማለት ነው" ይላል::

+"ካም" የሚለው ቃል ደግሞ ብዙ ጊዜ መልካቸው ጠቆር ላሉ ሰዎች የሚሰጥ ስም ነው:: ምናልባት የድሮ የኢትዮዽያ ግዛት በነበረው ደቡብ ግብጽ የነበረ አባት እንደ መሆኑ የዘር ሐረጉ ከኢትዮዽያ የተመዘዘ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል::

+ቅዱሱ በስፋት የሚታወቀው በድንግልና ሕይወቱ ነው:: መልካም ቤተሰቦቹ በሥርዓት አሳድገው "እንዳርህ" አሉት:: እንቢ ቢላቸው ብቸኛ ልጃቸው ነውና ፈጽሞ ሊያዝኑበት ነው:: ደስታውን ለቤተሰቦቹ ሰውቶ በተክሊል ተዳረ::

+እርሱ የሚሻው በድንግልና መኖርን ነውና ጥበበኛ እግዚአብሔር ሚስቱ የተቀደሰች እንድትሆን አደረጋት:: በሠርጋቸው ምሽት ቅዱስ ዮሐንስ ከማ መልከ መልካሟን ሙሽራ በድንግልና ይኖሩ ዘንድ ቢጠይቃት በደስታ አነባች::

+ምክንያቱም እርሷም ያገባችው ቤተሰብን ለማስደሰት እንጂ ፈቃዷ በድንግልና መኖር ነበርና:: 2ቱም ስላደረገላቸው ፈጣሪን እያከበሩ የድንግልና ሕይወት ተጋድሎን ቀጠሉ:: ቅዱሳኑ በአንድ አልጋ ላይ እየተኙ: አንዲት ምንጣፍን እያነጠፉ: አንድ ልብስንም በጋራ ለብሰው እያደሩ ድንግልናቸውን ጠበቁ::

+አምላከ ድሜጥሮስም ቅዱስ መልአኩን ልኮላቸው በመካከላቸው ያድር: ክንፉንም ያለብሳቸው ነበር:: ክብራቸውን ይገልጥ ዘንድም በቤታቸው መካከል ታላቅ ዛፍን ያለ ማንም ተካይነት አበቀለ::

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

02 Jan, 18:21


+በዚህ ጊዜ ግን ቅዱስ ዮሐንስ ከማ ድንግሊቱን ሚስቱን "የከተማ ኑሮ ይብቃን: ወደ በርሃ እንሒድ" አላት:: እርሷም "ፈቃድህ ፈቃዴ ነው" ስላለችው እርሷን ወደ ደናግል ገዳም አስገብቶ እርሱ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ተጉዋዘ::+ቅድስቲቱ አስቀድማ ጸጋው በዝቶላት ነበርና ድውያንን ትፈውስ ነበር:: የገዳሙ እመ ምኔት ሆና መርታ በክብር አረፈች:: ቅዱስ ዮሐንስ ከማም በቅዱስ መልአክ መሪነት መጀመሪያ ወደ አባ ዳሩዲ ሔዶ መነኮሰ::

+በመጨረሻም በቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ገዳም ጐን ማደሪያን አነጸ:: በዚያም በመቶ የሚቆጠሩ ደቀ መዛሙርትን አፍርቶ በአበ ምኔትነት አገለገለ:: ለእመቤታችንና ለቅዱስ አትናቴዎስ ልዩ ፍቅር የነበረው ቅዱሱ ከበርካታ የቅድስና ዘመናት በሁዋላ በዚህች ቀን በክብር ዐርፎ ተቀብሯል::

=>አምላከ ቅዱሳን ይራዳን: ይባርከን: ይቀድሰን:: ከወዳጆቹ በረከትም ያሳትፈን::

=>ታሕሳስ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱሳን 5ቱ መቃብያን
2.ቅዱስ ዮሐንስ ከማ (እና የተቀደሰች ሚስቱ)
3.ቅዱስ ዳንኤል መነኮስ
4.ቅዱስ ኒቆላዎስ መኮንን

=>ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
7.ታላቁ አባ ቢጻርዮን ገዳማዊ

=>+"+ ቃሌን የሚጠብቅ: በትዕዛዜም ጸንቶ የሚኖር: በረከቴን የሚያገኝ: በእኔ ዘንድ የሚከብር እርሱ ነው::
ቃሌን የሚጠብቅ: በትዕዛዜም ጸንቶ የሚኖር ሰው ሁሉ ከምድር የተገኘውን ድልብ ይበላል:: ቅን ልቡና ያላቸው ደጋጎች ነገሥታት ወደ ገቡበት ወደ ገነትም ገብቶ ይኖራል:: +"+ (መቃ. 12:43)

   <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

© ዝክረ ቅዱሳን ማኀበረ ቅዱስ ዳዊት ጉባኤ ዘጎንደር

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zikrekdusannbot

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

02 Jan, 17:11


❀✞ዮሐንስ ከማ ወመቃብያን ፫ ኒቆላ ወብእሲቱ ወአባ ዳንኤል። ✞❀

የታኅሣሥ ፳፭ #ግጻዌ
🌺🌺🌺🌺🌺🌺

ዘነግህ ምስባክ

‹‹ጻድቅ እግዚአብሔር በኵሉ ፍናዊሁ ውኄር በኵሉ ምግባሩ። ቅሩብ እግዚአብሔር ለኵሎሙ እለ ይጼውዕዎ ››

‹‹እግዚአብሔር በመንገዱ ኹሉ ጻድቅ ነው በሥራውም ዅሉ ቸር ነው። እግዚአብሔር ለሚጠሩት ዅሉ፥ በእውነት ለሚጠሩት ዅሉ ቅርብ ነው››
🌺📖መዝሙር ፻፵፬፡፲፯

ወንጌል ዘነግህ

🌺📖የዮሐንስ ወንጌል ፮፡፳፮-፴
፳፮ ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የምትፈልጉኝ እንጀራን ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ምልክቶችን ስላያችሁ አይደለም።
፳፯ ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።
፳፰ እንግዲህ፦ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድንሠራ ምን እናድርግ? አሉት።
፳፱ ኢየሱስ መልሶ፦ ይህ የእግዚአብሔር ሥራ እርሱ
በላከው እንድታምኑ ነው አላቸው።
፴ እንግዲህ፦ እንኪያ አይተን እንድናምንህ አንተ ምን
ምልክት ታደርጋለህ? ምንስ ትሠራለህ?

የዕለቱ ቅዳሴ ምንባባት

🌺📖ወደ ቲቶ ፪፡፲፫- ፍጻሜው
፲፪-፲፫ ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤
፲፬ መድኃኒታችንም ከዓመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።
፲፭ ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።

🌺📖፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ፪፡፲፪-፲፰
፲፪ ልጆች ሆይ፥ ኃጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና እጽፍላችኋለሁ።
፲፫ አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጎበዞች ሆይ፥ ክፉውን አሸንፋችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ልጆች ሆይ፥ አብን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ።
፲፬ አባቶች ሆይ፥ ከመጀመሪያ የነበረውን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ። ጐበዞች ሆይ፥ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም ቃል በእናንተ ስለሚኖር ክፉውንም ስለ አሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ።
፲፭-፲፮ ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ፤ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የሥጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለ ገንዘብም መመካት ከዓለም ስለ ሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ፥ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም።
፲፯ ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘላለም ይኖራል።
፲፰ ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።

🌺📖የሐዋርያት ሥራ ፬፡፴፩-ፍጻሜው
፴፩ ከጸለዩም በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ።
፴፪ ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፥ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደ ሆነ ማንም አልተናገረም።
፴፫ ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው።
፴፬ በመካከላቸው አንድ ስንኳ ችግረኛ አልነበረምና፤ መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ የተሸጠውን ዋጋ ያመጡ ነበርና፥
፴፭ በሐዋርያትም እግር አጠገብ ያኖሩ ነበር፤ ማናቸውም እንደሚፈልግ መጠን ለእያንዳንዱ ያካፍሉት ነበር።
፴፮ ትውልዱም የቆጵሮስ ሰው የነበረ አንድ ሌዋዊ ዮሴፍ የሚሉት ነበረ፥ እርሱም በሐዋርያት በርናባስ ተባለ ትርጓሜውም የመጽናናት ልጅ ነው፤
፴፯ እርሻም ነበረውና ሽጦ ገንዘቡን አምጥቶ ከሐዋርያት እግር አጠገብ አኖረው።

ምስባክ ዘቅዳሴ

‹‹ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም ከዐው ደሞሙ ከመ ማይ ዐውዳ ለኢየሩሳሌም። ወኀጥኡ ዘይቀብሮሙ።››

‹‹የባሪያዎችኽንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ ፥ የጻድቃንኽንም ሥራ ለምድር አራዊት፤ ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውሃ አፈሰሱ፥የሚቀብራቸውም አጡ።››
🌺📖መዝሙር ፸፰፡፪

ወንጌል ዘቅዳሴ

🌺📖የማቴዎስ ወንጌል ፲፫፡፴፮-፵፬
፴፮ በዚያን ጊዜ ሕዝቡን ትቶ ወደ ቤት ገባ። ደቀ መዛሙርቱም ወደ እርሱ ቀርበው። የእርሻውን እንክርዳድ ምሳሌ ተርጕምልን አሉት።
፴፯ እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ መልካምን ዘር የዘራው የሰው ልጅ ነው፤ እርሻውም ዓለም ነው፤
፴፰ መልካሙም ዘር የመንግሥት ልጆች ናቸው፤
፴፱ እንክርዳዱም የክፉው ልጆች ናቸው፥ የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፥ አጫጆችም መላእክት ናቸው።
፵ እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፥ በዓለም መጨረሻ እንዲሁ ይሆናል።
፵፩ የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፥ ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን ይለቅማሉ፥
፵፪ ወደ እቶነ እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።
፵፫ በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።
፵፬ ደግሞ መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ የተሰወረውን መዝገብ ትመስላለች፤ ሰውም አግኝቶ ሰወረው፥ ከደስታውም የተነሣ ሄዶ ያለውን ሁሉ ሸጠና ያን እርሻ ገዛ።


✥✥✥ቅዳሴ፦ዘሰለስቱ ምዕት (ግሩም)


🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

02 Jan, 05:32


ገድለ አቡነ ተክለሃይማኖት
@SinkisarZeKidusan

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

02 Jan, 05:31


የታህሳስ ፳፬ የነግህ እና የቅዳሴ ምስባክ ዜማ

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

01 Jan, 18:38


፭.ለገጽከ

ተክለ ሃይማኖት ሆይ፤ ከፀሐይና ከጨረቃ ሥነ ፀዳል ይልቅ በክርስቶስ የምስጋና ሥነ ጸዳል ለተዋበው ፊትህ ሰላም እላለሁ።

ቅዱሱ አባት ሆይ፥ ትምህርትህ የተስፋፋ ትሩፋትህ የተትረፈረፈ ዮሐንስ የተባለክ አንተ ተክለ ሃይማኖት ነህ እኮን። ስለዚህ  የዓለም ሥራው ብዙ ስለሆነ ንጹሑ የትዕዛዝህ ቃል ከድካም ያሳርፈኝ ከማዕሰረ ኃጢአት ይፍታኝ።

📖መልክአ ተክለ ሃይማኖት

የቅዱሱ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በረከታቸው ይደርብን!!
      🤲አሜን🤲

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

01 Jan, 18:19


፩፤ ለፅንሰትከ፡፡
ተክለ ሃይማኖት ሆይ፤ አስቀድሞ በማኅፀን ለተፀንስከው ፅንሰትህና በታኃሣሥ ሃያ ዐራት ቀን ለተወለድከው መወለድም ሰላም እላለሁ፡፡

ቅዱሱ አባት ሆይ፤ ሁሉ በሁሉ የተመሰገንህ ነህና እኔም በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብዬ እነሆ አዲሱን ምስጋናህን እጀምራለሁ፡፡

፪፤ ለዝክረ ስምከ፡፡
ተክለ ሃይማኖት ሆይ፤ የስምህ የመነሻ ፊደሉ ትእምርተ መስቀል ለሆነው ስም አጠራርህ ሰላም እላለሁ፡፡ እሱም ገናናና የከበረ ስም ነው፡፡

ቅዱሱ አባት ሆይ፤ የወንጌል ተቀዳሚ ስም ማቴዎስ የተባልክ አንተ ተክለ ሃይማኖት ነህ እኮን፤ ስለዚህም በችሎታዬ መጠን እንዳመሰግንህ አንደበቴን ትፈታልኝ ዘንድ ድንግል ማርያምን እማልዳለሁ፡፡

📖መልክአ ተክለ ሃይማኖት

https://t.me/+9wbcPYMusgQ1NGU0

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

01 Jan, 18:19


፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

አርኬ

ሰላም ለልደትከ ድኅረ ነበረት መካነ ። ለእምከ ልባ ከመ ቃለ መልአክ ተአምነ ። ተክለ ሃይማኖት በርትዕ እንተ ቀነይከ አዝማነ ። መልአ ምድረ ትምህርትከ እምወሰን ወሰነ ወሰማያተ ጽድቅከ ከደነ ።

፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

01 Jan, 18:19


✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ነሐሴ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

✞✞✞ እንኩዋን ለቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት: ቅዱስ አግናጥዮስ እና ቅድስት አስቴር ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+*" ቅዱስ #‎ተክለ_ሃይማኖት ሐዋርያዊ "*+

*ልደት*

=>መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ያፈራልና ተክለ ሃይማኖትን የወለዱት ደጋጉ: #‎ጸጋ_ዘአብ ካህኑና #‎እግዚእ_ኃረያ ናቸው:: እርሱ በክህነቱ: እርሷ በደግነቷ: በምጽዋቷ ጸንተው ቢኖሩ እግዚአብሔር ጣፋጭ ፍሬን ሰጥቷቸዋል::

+በዳሞቱ ገዢ በሞተለሚ አደጋ ቢደርስባቸው #‎ቅዱስ_ሚካኤል : ጸጋ ዘአብን ከሞት: እግዚእ ኃረያን ከትድምርተ አረሚ (ከአረማዊ ጋብቻ) አድኗቸዋል:: በኋላም የቅዱሱን መወለድ አብስሯቸዋል::

+አቡነ ተክለ ሃይማኖት የጸነሱት መጋቢት 24, በ1206 (1196) ሲሆን የተወለዱት ታሕሳስ 24, በ1207 (1197) ዓ/ም ነው:: በተወለዱበት ቀንም ብዙ ተአምራት ተገልጸዋል:: ቤታቸውም በበረከት ሞልቷል::

*ዕድገት*

=>የጻድቁ የመጀመሪያ ስማቸው " #‎ፍሥሃ_ጽዮን " ይሰኛል:: ይሕንን ስም ይዘው: አባታቸው ጸጋ ዘአብን ተከትለው አድገዋል:: በተለይ ቅዱሳት መጻሕፍትን (ብሉያት: ሐዲሳትን) ተምረዋል:: በሥጋዊው ጐዳናም ብርቱ አዳኝ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ዲቁና ከወቅቱ ዻዻስ #‎አባ_ጌርሎስ ተቀብለዋል::

*መጠራት*

=>አንድ ቀን ፍሥሃ ጽዮን ለአደን ወጥቶ ሲያነጣጥር ድንገት ከሰማይ አስደንጋጭ ድምጽ ተሰማ:: የክብር ባለቤት #‎ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ አእላፍ መላእክት እያመሰገኑ በሚካኤል ክንፍ ተቀምጦ ወረደ::

+የወጣቱን አዳኝ ፍርሃቱን አርቆ ጌታችን ተናገረ:

"ከዛሬ ጀምሮ ስምህ ተክለ ሃይማኖት (ተክለ ሥላሴ) ይሁን:: አራዊትን ሳይሆን ነፍሳትን ታድናለህ:: ዘወትር ካንተ ጋር ነኝ" ብሎ በግርማ ዐረገ:: ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዚህ ጊዜ በኋላሰዓትን አላጠፉም:: ንብረታቸውን ለነዳያን በትነው በትር ብቻ ይዘው ቤታቸው እንደ ተከፈተ ወደ ምናኔ ወጡ::

*አገልግሎት*

=>ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከዻዻሱ ቅስና ተቀብለው የወንጌል አገልግሎትን ጀመሩ:: በመጀመሪያ ስብከታቸው እዚያው ሽዋ ( #‎ጽላልሽ ) አካባቢ ብቻ በ10ሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን አሳምነው አጠመቁ:: ያንጊዜ #‎ኢትዮዽያ 2 መልክ ነበራት::

1.ዮዲት (ጉዲት) በፈጠረችው ጣጣና በእስላሞች ተጽዕኖ ወደ ደቡብ አካባቢ ያለው ነዋሪ አንድም ሃይማኖቱን ክዷል: ወይም በባዕድ አምልኮ ተጠምዷል::

2.ደግሞ በዛግዌ ነገሥታት ጥረት ክርስትናና ምናኔ ተነቃቅቶ ነበር::

+ግማሹ ሃገር በጨለመበት ወቅት የደረሱት #‎ሐዲስ_ሐዋርያ አባ ተክለ ሃይማኖት በወጣት ጉልበታቸውና በኃይለ መንፈስ ቅዱስ ብዙ ቦታዎችን አደረሱ:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን ወደ ሃይማኖት መልሰው: ማርያኖችን (ጠንቁዋዮችን) አጥፍተዋል::

*ገዳማዊ ሕይወት*

=>ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት በወንጌል ብርሃን ኢትዮዽያን ከማብራታቸው ባለፈ ገዳማዊ ሕይወትንም አስፋፍተዋል:: እርሳቸው ከሁሉ የተሻሉ ሳሉም በ3 ገዳማት በረድዕነት አገልግለዋል::

+እነዚህም በአቡነ #‎በጸሎተ_ሚካኤል ገዳም ለ12 ዓመታት: በአቡነ #‎ኢየሱስ_ሞዐ_ዘሐይቅ ገዳም ለ7 ዓመታት: በደብረ ዳሞ ከአቡነ #‎ዮሐኒ ጋር ለ7 ዓመታት: በአጠቃላይ ለ26 ዓመታት አገልግለዋል::

+በአቡነ ኢየሱስ ሞዐ ከመነኮሱ በኋላም ወደ ምድረ ሽዋ #‎ዞረሬ ተመልሰው በአንዲት በዓት ውስጥ ለ22 ዓመታት ቆመው ጸልየዋል:: በተሰበረ እግራቸውም 6 ጦሮችን በግራና በቀኝ ተክለው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል::

*ስድስት ክንፍ*

=>ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል:: ጻድቁ ምድረ #‎እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር::

+የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት #‎አባ_ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል:: ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በኋላ ነው:: ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር::

+ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
¤በቤተ መቅደስ ብስራቱን
¤በቤተ ልሔም ልደቱን
¤በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
¤በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
¤በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::

+የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደሆነው #‎ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ #‎እመቤታችን_ድንግል_ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደሰማይ አሳረገቻቸው::

+በዚያም:-
¤የብርሃን ዐይን ተቀብለው
¤6 ክንፍ አብቅለው
¤የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
¤ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
¤ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
¤ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
¤"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::

*ተአምራት*

=>የተክልየ ተአምራት እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ነው::
*ሙት አንስተዋል
*ድውያንን ፈውሰዋል
*አጋንንትን አሳደዋል
*እሳትን ጨብጠዋል
*በክንፍ በረዋል
*ደመናን ዙፋን አድርገዋል::

+ብዙ ደቀ መዛሙርትን አፍርተው ደብረ ሊባኖስን መሥርተዋል:: በዚያም ሴትና ወንድ መነኮሳት እንደ ሕጻናት አብረው ኑረዋል:: በዘመናቸው ሰይጣን ታሥሯልና::

*ዕረፍት*

=>ጻድቅ: ሰማዕትና ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ብርሃን ሆነው መከራን በብዙ ተቀብለው: አእላፍ ፍሬን አፍርተው: በተወለዱ በ99 ዓመት: ከ8 ወር: ከ1 ቀናቸው ነሐሴ 24, በ1306 (1296) ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታ: ድንግል ማርያምና ቅዱሳን ከሰማይ ወርደው ተቀብለዋቸዋል:: 10 ትውልድ የሚያስምር ቃል ኪዳንም ተቀብለዋል::

=>የጻድቁ አባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የቅድስናና የክብር ስሞች :-

1.ተክለ አብ: ተክለ ወልድ: ተክለ መንፈስ ቅዱስ
2.ፍስሐ ፅዮን
3.ሐዲስ ሐዋርያ
4.መምሕረ ትሩፋት
5.ካህነ ሠማይ
6.ምድራዊ መልዐክ
7.እለ ስድስቱ ክነፊሁ (ባለስድስት ክንፍ)
8.ጻድቅ ገዳማዊ
9.ትሩፈ ምግባር
10.ሰማዕት
11.የኢትዮዽያ መነኮሳት አለቃ
12.ፀሐይ ዘበፀጋ
13.የኢትዮዽያ ብርሃኑዋ
14.ብእሴ እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ሰው)
15.መናኒ
16.ኤዺስ ቆዾስ (እጨጌ)

=>እነዚህ የአባታችን ስሞች እንደዘመኑ ሰው ለመሞጋገስ የወጡ ሳይሆኑ ሁሉም በትክክል ሥራዎቹንና ለቤተ ክርስቲያን የሆነላትን የሚያዘክሩ ናቸው:

+" ቅዱስ አግናጥዮስ "+

=>ይህ ቅዱስ ሰው ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠገበ በመሆኑ በመላው ዓለም ዝነኛ ነው:: እርሱ:-
*በክርስቶስ እጅ ተባርኩዋል
*ፈጣሪውን ፊት ለፊት አይቷል
*ሐዋርያትን አገልግሏል
*ከምሥጢር አባት ከዮሐንስ ወንጌላዊ እግር ተምሯል
*ስለ ክርስትና ለአንበሶች ተጥሎ በመገደሉ "ምጥው ለአንበሳ" ይባላል::

+ቅዱስ አግናጥዮስ የተወለደው በክርስቶስ አምላካችን መዋዕለ ስብከት (በ30 ዓ/ም አካባቢ) እንደ ሆነ ይታመናል:: በትውፊትም በማቴ. 18:1 ላይ ያለው ሕጻን እርሱ ነው ይባላል::

ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

01 Jan, 18:19


+ሐዋርያት ከመካከላቸው ማን እንደሚበልጥ ሲጠይቁት አንድ ሕጻንን (አግናጥዮስን) ከመሃል አቁሞ "ካልተመለሳችሁ: እንደዚህም ሕጻንካልሆናችሁ ከቶውንም ወደ እግዚአብሔር መንግስት አትገቡም" ብሏቸዋል::

+ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ሐዋርያት ለወንጌል ሲፋጠኑ ሕጻኑ ቅዱስ አግናጥዮስ እየተከተለ አገልግሏል: ተምሯል:: ኢየሩሳሌም በጥጦስ አስባስያኖስ ቄሣር በጠፋችበት ዓመት (በ70 ዓ/ም) ቅዱሱ የአንጾኪያ ሊቀ ዻዻሳት ሆኖ ተሹሟል::

+ከዚህ በሁዋላም ለ2 እና 3 አሠርት ዓመታት ከወንጌላዊ ዮሐንስ ጋር አብሮ ወንጌልን ሰብኩዋል:: የዚህ ቅዱስ ተጋድሎ ጫፍ የደረሰው ከ100 ዓ/ም በሁዋላ ሁሉም ሐዋርያት ሰማዕት በመሆናቸውና ትልቁን ኃላፊነት እርሱ በመሸከሙ ነው:: የወቅቷን ቤተ ክርስቲያን ከቅዱሳኑ ቀሌምንጦስ ዘሮምና ፖሊካርፐስ ዘሰርምኔስ ጋር ሆኖ እስከ ደም ጠብታ ጠብቁዋል::

+ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ አግናጥዮስ ለዘመናት ወንጌልን እየሰበከ በሕይወቱና በትምሕርቱ አስተማረ:: ብዙ መልእክቶችን (ድርሳናትንም) ጻፈ:: በመጨረሻው ግን በጠራብሎስ ቄሣር ተይዞ: በብረት ሰንሰለት ታስሮ: ከአንጾኪያ (ሶርያ) ወደ ሮም (ጣልያን) ተወሰደ::

+ደሙ እስኪፈስም ገረፉት:: ዛሬ በሮም ከተማ ግማሽ አካሉ ፈርሶ በሚታየው ስታዲየም (በአባቶቻችን አጠራር ተያጥሮን) እንዲገደል ተወሰነበት:: በወቅቱ ባደረገው ንግግርም ቄሣሩና ሕዝቡ ድፍረቱን አደነቁ:: በመጨረሻም ለአንበሳ እንዲሰጥ ተደርጐ በዚህች ቀን ሰማዕት ሆነ::

+" ቅድስት አስቴር "+

=>ይህቺ ቅድስት እናት:-
*እሥራኤል በባቢሎን ምርኮ ሳሉ የነበረች
*አባቷ አሚናዳብ ባለ መኖሩ በአጐቷ መርዶክዮስ እጅ ያደገች
*እጅግ ውብ በመሆኗ የአርጤክስስ ሚስት (ንግሥት) ለመሆን የበቃች
*ራሷን መስዋዕት አድርጋ ወገኖቿን አይሁድን ከሞት ያተረፈች
*ለመርዶክዮስ ክብርን: ለአማሌቃዊው ሐማ ደግሞ ስቅላትን ያስፈረደች እና
*እግዚአብሔር ሞገስ የሆናት እናት ናት::
*ዛሬ ዕረፍቷ ነው::

=>አምላከ ቅዱሳን ወዳጆቹን ባጸናበት ቅዱስ መንፈሱ እኛንም ያጽናን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

=>ታሕሳስ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱሳን ጸጋ ዘአብና እግዚእ ኃረያ
3.ቅዱስ አግናጥዮስ ሐዋርያ
4.ቅድስት አስቴር
5.አባ ፊሎንጐስ ሊቀ ዻዻሳት
6.አባ ዻውሊ ጻድቅ
7.ጻድቃን ቅዱሳን ዘከዲህ

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
2.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን
3.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
4.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
5."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
6.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮዽያዊ)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ

=>+"+ ንግሥቲቱም አስቴር መልሳ:- 'ንጉሥ ሆይ! በአንተ ዘንድ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ: ንጉሡንም ደስ ቢያሰኘው: ሕይወቴ በልመናዬ: ሕዝቤም በመሻቴ ይሰጠኝ:: እኔና ሕዝቤ ለመጥፋትና ለመገደል: ለመደምሰስም ተሸጠናልና:: +"+ (አስቴር. 7:3)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

🌿 @zkretewahdo
🌿 @zkretewahdo
🌿 @zikrekdusannb

4,146

subscribers

5,397

photos

18

videos