️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️ @binigirmachew Channel on Telegram

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

@binigirmachew


በስነልቦና እና በስነ አይምሮ ዙሪያ ማንኛውንም ጥያቄዎችን መጠየቅ ይችላሉ።

@biniGirmachew21

ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን (Amharic)

ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን የስነ-ልቦና ትምህርቶችን በነፃ ያግኙ ያልተገናኘበት እውቀት እና መምረጥ ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት የተለያዩ መረጃዎችን ያገኛል። ይህም ከተለያዩ እና ቀረጥ ገጽን በነሃሴ የመከላከያ ምስል እንዲሆን ነው። እባኮትን በ @biniGirmachew21 የሚገልጹበት ስለተመለሳቸው መረዳት ማግኘት ይችላሉ።

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

23 Nov, 05:39


የተስፋ ሕይወት የሚለውን ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ መጽሐፍ ቀረባል

ምናልባት ከወደዳቹት ሌሎች መፃፍ በዚህ መልኩ አቀርባለሁ።

ለመቀጠልም ለመቆም የእናንተ አስተያየት ያስፈልጋል

https://youtu.be/LxUeSr834SA?si=KfZGfGOc9h6NZjKl

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

23 Nov, 03:49


እሄን በደንብ አንብብ እና ደስ የሚል ቀን አሳልፋ

https://vm.tiktok.com/ZMhv6Qy4X/

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

22 Nov, 20:24


ታላቅ መንፈሳዊ ጉዞ በፀበሏ ፈዋሽ በቅባቅዱሷ እና በምልጃዋ ብዙዎችን ወዳዳነችው ጮቢ በዓታ ማርያም አንድነት ገዳም ።

በዓለም ቀዳሚ የሆነውን ህንፃ ቤ/ክ ይጎበኛሉ ፣ የእርሻ ስራ ፣መፃህፍት ቤት ፣ የእደ ጥበብ ፣ ዘመናዊ ጎተራ፣የከብት እርባታ ፣ ፈዋሽ የፀበል ስፍራ፣ህፃናት ማሳደጊያ፣የአረጋውያን መንከባከቢያ ( በቡኢ ከተማ)፣የአብነት ት/ቤት ፣ተግባር ቤት እና ሌሎችንም በረከቶች ያገኛሉ።

ለሱባኤ እና ለፀበል ወደገዳሙ ለመሄድ ሲያስቡ ስለምግብ እና ማረፊያ አይጨነቁ አንገታቸውን ወደመሬት በቀለሱ መነኮሳትና የአብነት ተማሪዎች እግርዎ ታጥቦ በፍፁም ክርስቲያናዊ ፍቅር ያስተናግዶዎታል።

መነሻችን ለታህሳስ 2ቀን ጠዋት 12:00ሰዓት መመለሻ ቀን ታህሳስ 3ቀን 2017 ከንግስ በኋላ

ስልክ +251913569435 ዳንኤል አስራት

        +251903280707 የጮቢ በዓታ ማርያም

ሆስፒታል አሰሪ ኮሚቴዎች ስልክ

        +251912158620
ብሩክ ተስፋዬ ጉዞ አስተባባሪ እና አባል።

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

22 Nov, 14:28


https://youtu.be/7Mxa8k1uMaw?si=PM5ek8ylSXsE5HBu

https://youtu.be/7Mxa8k1uMaw?si=PM5ek8ylSXsE5HBu

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

22 Nov, 03:22


- መብታችን ባልሆኑ ነገሮች ላይ መብት የሆነን እግዚአብሔር ይመስገን

- ተደብቀን ሳለን ሰገነት የሆነን ታመን ሳለን የረዳን እግዚአብሔር ይመስገን

- በተገፋንበት መሸሸጊያ ባለቀስንበት መፅናኛ የሆነን እግዚአብሔር ይመስገን

- ለብቸኝነታችን አጀብ ለቤታችን ድባብ የሆነ እግዚአብሔር ይመስገን

-ባጣነው በጎደለን ባነሰን ነገር ሁሉ ሙሉ ያረገን እግዚአብሔር ይመስገን

- በተዋረድንበት ባፈርንበት ቀና ያረገን ያኮራን እግዚአብሔር ይመስገን

- በጨነቀን ጊዜ መውጫ መሻገሪያ ማለፊያ ድልድይ የሆነን እግዚአብሔር ይመስገን

- በጠፋንበት የመለሰን በሸሸንበት የተከተለን እግዚአብሔር ይመስገን

- በምድረበዳ ያልጣለን በጠብታ ውሀ ያረሰረሰን ከክፉ አውሬ የጠበቀን እግዚአብሔር ይመስገን

- የሰይጣንን ፍላፃ እንድንመክት የጦር ልብስ ጋሻ የሆነን እግዚአብሔር ይመስገን

- ማንም በሌለበት ዘመድ አልባነታችንን አስረስቶ አባት የሆነን እግዚአብሔር ይመስገን

- አንካሳነታችንን ያቀና ሽባነታችንን የተረተረ አንደበታችንን የከፈተ እግዚአብሔር ይመስገን

- የከፈተውን ጉሮሮ ሳይዘጋ የማያድር ለነዳይ ለምስኪኑ ለአራዊቱ ለአእዋፋቱ ሁሉ ጥጋብ የሆነ እግዚአብሔር ይመስገን

- ሰሚ በሌለበት እድሜ ባጠረበት ሞት በበዛበት.. ጊዜ የሠጠን እድሜ የሆነን እግዚአብሔር ይመስገን

- የደም ዝውውራችን የልብ ምታችን አተነፋፈሳችን አረማመዳችን ዝንፍ ሳትል አሳድሮ የሚያውለን እግዚአብሔር ይመስገን።

አሜን በሉ!! ባያግዘን እቺ ያለንባት ቦታ ባልተገባችን መኖር ብርቅ በሆነብን ነበር።

እጁ ይዞን ቀኙ ደግፎን አይኑ ተከትሎን ነው የደረስነው።አቅም ያለው ሁሉ ተነስቶ የሞት ቀኑን የመኖርያ እድሜውን አያራዝምም ቀን እድሜ የተሰጠን በነፃ ነውና አመስግኑ።

ተስፋ የሆነንን ጌታ አመስግኑ እውነት እግዚአብሔር ቢበሉት የማይጠግቡት ደሞ የማያልቅ ስንቅ ነው።ቸር ሆይ እናመሠግንሀለን እንወድሀለን!!!

አንዴ እናመስግን!!?? እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን መልካም ቀን!!!


በዚህ ደግሞ ቤተሰብ ይሁኑ

https://youtu.be/IqSZ3C8qMQ0?si=HSLrKHPu9kEAhNGe

@BiniGirmachew    @BiniGirmachew


በነገራችን ላይ መንፈሳዊ ቻናል አለኝ  መከታተል ለምትፈልጉ  ከታች ባለው መከታተል ትችላላችሁ

@Orthodox_sibket
@Orthodox_sibket
@Orthodox_sibket

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

22 Nov, 03:19


https://youtu.be/IqSZ3C8qMQ0?si=HSLrKHPu9kEAhNGe

https://youtu.be/IqSZ3C8qMQ0?si=HSLrKHPu9kEAhNGe

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

21 Nov, 03:23


እንኳን አደረሰን ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል

በነገራችን ላይ መንፈሳዊ ቻናል አለኝ  መከታተል ለምትፈልጉ  ከታች ባለው መከታተል ትችላለህ

@Orthodox_sibket
@Orthodox_sibket
@Orthodox_sibket

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

20 Nov, 11:55


|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @ye_mariam_agelgay እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #250ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251960030506 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

20 Nov, 04:18


የዶሮ ላባዎች ሲበተኑ ለወጣቶች ይሁንልኝ

በድጋሜ የተለቀቀህ

Bini Girmachew

አንድ ወጣት ወደ አንድ ታላቅ አባት ዘንድ ይሄድና አባት እውነት ባልሆነ አሉባልታ የሰውን ስም በማጥፋት የጎዳሁ መሆኔ አሁን ታወቀኝ ።

እና ስለ ሀጢያቴ ምን ላድርግ ብሎ ጠየቃቸው ። እኛም ጥበበኛ አባት የዶሮ ላባ ፈልገህ ሰብስበህ አምጣ አሉት ። ሄዶ ሰብስቦ ይዞ መጣና ይኸው አላቸው ።

ሂድና በአሉባልታ ወሬ በጎዳሀቸው ሰዎች በር ላይ አስቀምጠው አሉት ። እሱም ሄዶ አስቀምጦ መጣና ያሉኝን አድርጌያለው አላቸው ። ከዛ እሳቸውም በል ሂድና ያስቀመጥከውን ላባ ሰብስበህ አምጣ አሉት ።

እሱም እንዴ ይሄማ አይሆንም ይሄኔ ንፋስ በትኗቸዋል አላቸው ። እሳቸውም አየህ ልጄ ልክ እንደዚህ አንተ የበተንከው የሀሜትና አሉባልታ ወሬ በከተማ ሁሉ ስለ ተሰራጨ መልሶ መሰብሰብ ከባድ ነው ።

በማለት ከመለሱለት ቡሃላ አየህ ሀሜተኛ አትሁን አሉት ።

ዳዊት / አቤቱ ለአፌ ጠባቂ አኑር / እንዳለው ጠባቂ በሌለው ምላስ በሀሜት ምክንያት

ትዳራቸው የፈረሰ ፣ ቢዝነሳቸው የከሰረ ፣ ትምህርታቸውን ያቋረጡ ፣ ከሚወዱት ሰው የተለዩ ፣ ከፈጣሪ አገልግሎት የሀሜትን ጦር ፈርተው የራቁ ብዙዎች ናቸው ።

ሀሜተኞችና አሉባልታ አውሪዎች የሚያጠፉት ጥፉት እሳትና ሰይፍ ከሚያጠፉት ይበልጥ ፈጣንና አደገኛ ነው ።

ሀሜተኛ ምላስ በክፉ ጠባዩ አያሌዎችን የገደለ ብዙዎችን የደም እንባ ያስለቀሰ መልካም ኑሮን ያናጋ መርዘኛ እባብ ነው ።

ብዙዎች በሀሜተኛ ምላስ ጅራፍ ተገርፈው ቆስለው ደምተዋል ።

ሀሜተኞች ወላጅና ልጅን ወንድምና እህትን ፣ ባልና ሚስትን ፣ አሰሪና ሰራተኛን አቃቅረው አጣልተዋል ።

ስለዚህ እስቲ እራሳችንን እንመርምር ስለምናወራው ነገር እንጠንቀቅ። በድጋሚ የተለቀቀህ

Bini Girmachew ( ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን) ትዩብን ሰብስክራይብ ለማድረግ ይሄን ሊንክ ይጠቀሙ!! 🔔
👉 https://www.youtube.com/channel/UCawJZOERphyparnxlMZwa6w

#ቴሌግራም

https://t.me/BiniGirmachew
https://t.me/BiniGirmachew
https://t.me/BiniGirmachew

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

20 Nov, 04:18


የዚህ ጥያቄ መልስ ለሁላችሁ ያስፈልጋል

https://youtu.be/UrWILcS7hd8?si=3CnN3zs1-yfasz0g

https://youtu.be/UrWILcS7hd8?si=3CnN3zs1-yfasz0g

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

19 Nov, 14:22


👉 ለዛሬ ይህንን ትምህርት አሁኑኑ ያዳምጡ ይጠቀማሉ

https://youtu.be/4-ugmUCd-tw

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

19 Nov, 08:16


አሁን ያለንበት ዘመን የሰው ልጅ ለራሱ ማሰብና ውሳኔ መስጠት አቅቶት ሰዎች እንዲያስቡለት አእምሮውንም መንፈሱንም አሳልፎ በሰጠበት ዘመን ነው።

ውሳኔ መወሰን ትልቅ ሀላፊነትን ይጠይቃል። እኛ ደግሞ እድሜ ልካችንን ከሀላፊነት እንደሸሸን ነው። ምክንያቱም ሀላፊነት ከመንጋው አስተሳሰብና ውሳኔ ለይቶ የራስ መንገድንም መቀየስ ይጨምራልና።

የመንጋ አስተሳሰብ እጅግ ቀላል ከመሆኑም የተነሳ ማሰብ አያስፈልገንም። ተደጋጋሚ ከመሆኑም የተነሳ ውጤቱ ስለሚታወቅ አያሰጋም። ለመንጋ አስተሳሰብ አዲስ እይታ አስፈሪ ነው። የተለየ ይፈራል ። የተለየ ይገለላል።

ሆኖም ግን በመንጋ አስተሳሰብ ውስጥ የራስ የሆነ መንግድ ካልተቀየሰ በቀር ህይወት አሰልቺ መሆኗ አይቀሬ ነው። የመንጋ አስተሳሰብ ያገንሀል ወይም ያስወድቅሀል። ለዚህ ከመንጋው የተለየ ሀሳብን ማራመድ ላትፈልግ ትችላለህ።

ወይም የመንጋውን ትርታ ተከትለህ መሆን ያልነበረበትንም እንኳን ደግፈህ ታጨበጭባለህ። ወይም መሆን ያልነበረበትን ተቃውመህ ከመንጋው ተገለህ መንጋውን ጠላት አርገህ ትኖራለህ።

ሁለቱም መሆን አለበት ብዬ አላስብም። መንጋውን ስህተት በሆነበት ጊዜ አብሮ መጓዝን ወይም ደግሞ የመንጋውን ስህተት እየነቀሱ እራስን የተለየ አርጎ ማየት አስፈላጊ አይደለም።

ከሁሉም በላይ ሰባዊነት ይቀድማልና ሰውን ከአስተሳሰቡ ባሻገር ያለውን ሰውነቱን አምኖ ተቀብሎ መጀመር አስፈላጊ ነው። መንጋውን በአስተሳሰቡ የተነሳ ሁሌ ከማስቆጣት ይልቅ ሰከን ባለ መንገድ ስህተት የሆነውን ነቅሶ በማውጣት በሚገባው መልኩ ማስረዳት ያስፈልጋል።

ስህተት አለ ካልን እንኳን በሚያስቆጣ መልኩ ብናቀርብለት ከሱ የተለየን በሚመስል መልኩ ቁስሉን ብንካበት ስህተቱን ለማረም ያለንን እድል እናበላሻለን። ስህተት አለ ካልን እንኳን በፀያፍና በማይገባ መልኩ ሰውዬውን ማጥቃት ሊያተርፍልን የሚችለው ትርፍ አሉታዊና አሉታዊ ብቻን ነው።

በተለያየ ዘመን የተነሱ ፈላስፋዎች የተጠቀሙት መንገድ የመንጋውን ስህተት ነቅሰው ማውጣት ቢችሉም ለማረም የሚያስችል መሰረት ግን ትተው አልፈዋል የሚል ግምት የለኝም።

እንዲያውም መንጋውን ወደ ባሰ እንቅልፍ ከተዋል ባይ ነኝ። ለራሳቸውም ቢሆን መጨረሻቸው ስህተት አለብህ ባሉት መንጋ መገደል እና መገለልን ነው ያተረፉት።

የኖሩትም ኑሮ ቢሆን እዚህ ግባ የማይባልና ለሌላው ትምህርት የማይሆን ኑሮ ኑሮን ነው የኖሩት። ሌላው ሰራው ያሉትን ስህተት እራሳቸው ደግምው ሲሰሩትም አይተናልም።

አንዳንዴ ምክርህ ስድብ ሊመስል ይችላልና ተጠንቀቅ። ግልፅነትህ መተናኮል ይመስላልና በጥበብ አርገው። ስህተት ነቅሰህ ስታወጣ ወደፊት በዛ ስህተት እንዳትወድ ተጠንቀቅ። ቀይረዋለው ምትለው መንጋ መልሶ አንተን እንዳይቀይርህ ተጠንቀቅ።

የተለየው ነኝ ብለህ ከማሰብ ይልቅ አንድ ነኝ ብለህ መንጋው የሰራውን ስህተት አስተምረህ ለውጠው። ማህበረሰቡን በአንዴ ላትለውጥ ትችል ይሆናል። ነገር ግን ማህበረሰብ የግለሰብ ውጤት ነውና በግለሰቦች ላይ ስራ።

በተለይ በራስህ ላይ ስራ። እራስህ ተለውጠህ አከባቢህን ለውጠው። ቃላት ምናልባት የተወሰን ሰዓት ትምህርት ሊያስተላልፉ ይችሉ ይሆናል። ኑሮህና ድርጊትህ ግን ሁሌም ትምህርት ይሰጣል።

ማህበረሰቡ አይዋደድም ይጣላል ብለህ መልሰህ ማህበረሰቡን ብትጠላው አንተ ምን የተለየ ነገር አደረክ? ማህበረሰቡ ስለሰረቅ የምትሰርቅ ስለ ገደለ የምትገል ስለ ሰደበህ የምትሰድብ ከሆነ ያው ሁለታቹም አንድ ናችሁ። ልዩነቱ አንተ አውቀህ የምታደርገው ሲሆን ማህበረሰቡ ግን በመንጋ አስተሳሰብ ተመርቶ ነው።

ስህተትን ስትነግሩ ስድብ መስሎ እንዳይታይ ተጠንቀቁ! በኮነናችሁት ስህተት እንዳትኮነኑ!

@BiniGirmachew    @BiniGirmachew
@BiniGirmachew   


አንብባችሁ ስጨረሱ ይህን ያዳምጡ

👉

https://youtu.be/4-ugmUCd-tw

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

19 Nov, 04:29


👉 ለዛሬ ይህንን ትምህርት አዳምጡ!

https://youtu.be/4-ugmUCd-tw

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

18 Nov, 07:19


ሰው የተፈጥሮ ሚዛኑን የሚጠብቀው ከበታችነትም ከበላይነትም ስሜት ነፃ መሆን ሲችል ነው።

ሁለቱም ስሜቶች መርዝ ናቸው።

@BiniGirmachew    @BiniGirmachew
@BiniGirmachew   

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

17 Nov, 10:37


አዲስ ምዕራፍ ከፍተን በጣም ተደስተናል። ለምኞታችሁ እና ድጋፋችሁ እናመሰግናለን።

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

16 Nov, 16:19


በእግዚአብሔር ድጋፍ ካልሆነ ሌላ በማንም አይቻልም! ብቻ ያ ሁሉ አለፈ።

ሕይወት በአዲስ ተጀመረ

እግዚአብሔር ስለሁሉም ይመስገን

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

15 Nov, 18:56


መናገር አቅምን ይጨርሳል

ንግግር ኃይል ነው ። በንግግር ጦርነት ይጀመራል፣ ጦርነት ይቆማል። በመናገር ኃይል እናገኛለን፣ ኃይል እናባክናለን።

ኃያል ሥራዎች የሚሠሩት ከንግግር ይልቅ በዝምታ ነ ው። እግዚአብሔር ፍጥረትን በሦስት መንገድ ፈጥሯል። በዝምታ፣ በመናገርና በተግባር ።

ካለመኖር ወደ መኖር ፣ ከሌለ ነገር ወዳለ ነገር ያመጣቸው ፍጥረታት በዝምታ የተፈጠሩት ናቸው። ንግግር መልካም ፣ አስፈላጊና ግድ የሚሆንበት ጊዜ አለ። "ካልተናገሩ ብልሃቱ፣ ካልታረደ ስባቱ አይታወቅም" ይባላል። ንግግር ግን ኃይልን ያባክናል።

ጥልቅ ጥበብ፣ ብርቱ ሠራተኛነት፣ ቋጠሮን መፍታት፣ ሳይሸበሩ መቆም፣ አስተውሎት ዝም የሚሉ ሰዎች አቅም ነ ው። ሁልጊዜ ዝምታ፣ ሁልጊዜ ንግግር አስፈላጊ አይደለም። ሁሉም አይነገርም፣ ሁሉም ነገር ዝም አይባልም።

አንዲት ሴት ለሥራ ጉዳይ እያለች ከክፍለ ሀገር አዲስ አበባ ድረስ ትመጣለች። ባልዋም ልጅዋም የሚያውቁት ለሥራ መሄድዋን ነው።

ይህች ሴት ግን በካንሰር ሕመም ውስጥ እያለፈች ነው። ከስምንት ጊዜ በላይ ከባድና አስቸጋሪ የሆነውን ኬሞቴራፒ ወስዳለች። ቀጥሎ የጨረር ሕክምና አድርጋለች።

በዚህ ጊዜ ውስጥ የሥጋ ዘመዶች፣ የትዳር አጋር፣ ልጅዋ አያውቁም። በመጨረሻ አቅም አጣች፣ ሆስፒታል ተኛች ። በመጨረሻው ሰዓት ላይ ሁሉንም ሲያውቁ በጣም ተጎዱ። ወዲያው ዐረፈች። ይጨነቃሉ፣ መሸከም አይችሉም የምንላቸው የተሻለ አቅም ሊኖራቸው ይችላል።

አንዳንድ ዝምታ አላስፈላጊ ነ ው። ሰዎች በቁመናዬ እንጂ በሞቴ ሊያግዙኝ አይችሉም በማለት የሚናገሩ ሰዎች ሊደነቁ ይገባል ። ሁሉ በሆዱ ነው የሚለው ሙገሳ ብዙ የአእምሮ ታማሚዎችን ያፈራ ነው።

የሚናገሩ ሰዎች ማኅበረሰቡ ያወጣላቸው ፣ ለራሳቸውም ያወጡት ስም አለ። ምንም አያውቅም፣ ሆዱ ባዶ  ነው የሚል ነው።

በርግጥ የሚራሩ ሰዎች በአብዛኛው ተናጋሪዎች ናቸው። ተናጋሪዎች የድብቅ ሕይወት ስለሌላቸው ሁሉንም በግልጽ ያወራሉ። ነጻነትና ደስታ አላቸው።

በጣም ተናጋሪዎች፣ ተናግረው የማይረኩ ፣ ስለ ሁሉም ነገር የመናገር ግዳጅ ያለባቸው የሚመስላቸው ፣ አላውቅም ማለትን የማይወዱ ሰዎች አሉ። ዓለም ድምፅ እየሰጠ ያለው  ለተናጋሪዎች ነ ው። ጥሩ የሚናገሩ ጥሩ ተግባር የሌላቸው አያሌ ናቸው ።

በንግግራቸው ተጣጥፈው ማለፍ የሚችሉ ጎበዝ ይባላሉ። እውነት መናገር ሳይሆን ውሸትን እውነት አስመስሎ ማቅረብ መደነቅ እያስከተለ ነው። አፉን አይተው ያገቡት፣ ንግግሩን ሰምተው የመረጡት ሲያስለቅስ ይኖራል።

እግዚአብሔር የአፍ ክብርን ሳይሆን የልብ መገዛትን ያያል። "ይህ ሕዝብ በከንፈሩ ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ በጣም የራቀ ነው፤"(ማቴ 15፣ 8)።  የዛሬ ወጣቶች ንጹሕ ልብስና ንጹሕ ንግግር አላቸው። ንጹሕ ኑሮን ግን እያጡ ነው ።

ንግግር የሚያበዙ  ሰዎች ሥራ ላይ የሚገኙ አይደሉም። ንግግር የልግመኞች ምጽዋት ናት። ንግግር መልካም ነው፣ ንግግር ብቻ መሆን ግን ቃልቻ ወይም ቃል ብቻ የሚያሰኝ ነው። ቃል ብቻ ወይም ቃልቻ ይሆናል። ሰይጣን ቃል ብቻ የሆነ ሰው ሁነኛ አገልጋዩ ነው::

"ሁሉ ሆነ ቃልቻ፣ ማን ይሸከም ስልቻ" እንዲሉ። ቃልቻ ይህን አደርግልሃለሁ፣ ይህን እፈጽምልሃለሁ በማለት ያወራል ግን አያደርገውም። ባለሙያ ሰዎችን ተመልከቱ ፣ ንግግራቸው የተቆጠበ ነው። ንግግር ጊዜ ይፈጃልና ተናጋሪ ሰው ለሥራ ጊዜ ያጥረዋል። ተናግሮ ይረካልና  ለቸርነት እጁ ካንጋሮ ነው።

ተናጋሪዎች ያዘምታሉ እንጂ አይዘምቱም። "ጡሩንባ ነፊ ቀብር አይወጣም" ይባላል። ፍቅራችንንም በጣም ማውራት ተግባር ያሳጣል። ዓላማን ሲዘረዝሩ መዋልም ከፍጻሜ ይገታል። የሚያደርጉ ሰዎች አያወሩም። ከውሻ እንኳ የሚጮኸው ሳይሆን ዝም የሚለው ይናከሳል።

ችግሩ ያለው ዝምታ ላይ ወይም ንግግር ላይ አይደለም። ዝምታው ማድፈጥ አይሁን። ቃልም ቃል ብቻ አይሁን። ሃይማኖታችን "ቃል ሥጋ ሆነ" የሚል ነው። ተዋሕዶ ማለትም የማይታየው የሚታይ ሆነ ማለት ነው።

ቃላችን የሚታይ ይሁን። ሰዎች እኛን አይተው እግዚአብሔር በምድር ታየ፣ ዛሬም አምላክ ሰው አለው ይበሉ። ሁልጊዜ ቃል ብቻ ከሆንን በሰው ሞት ተሳላቂ እንሆናለን። እንናቃለን። የተሳለ የግድግዳ አንበሳ ወይም ሥዕል እንሆናለን። የተሳለ አንበሳ አጠገብ ሻይ ይጠጣል፣ እውነተኛው አንበሳ አጠገብ ግን የሚደፍር የለም ።

ንግግራችንን አሳጥረን ወደ ተግባር እንሂድ። በአገራችን ስመ አምላክ በሃይማኖት ሥፍራ ሲጠራ ይውላል፤ ያድራል ። ዛሬ ግን በሬድዮ በቴሌቪዥን ሲጠራ ይውላል። ግን ቃል ብቻ ነው። ሁሉም ያወራል፣ የሚሠራ እየጠፋ ነው።

ቻይናዎቹ እንዳሉት ኢትዮጵያውያን ሌላ አገር አላቸው ወይ? ከእናቱ መቀነት የሚሰርቅ የመጨረሻው ክፉ ሌባ ነው። እናቱ ጋ ያለው ለራሱ የተቀመጠ ነበር። እናት አገሩን የሚሰርቅ ጨካኝ ሌባ፣ ልጅነቱን የካደ ነው። እንዲህ ላድርገው የሚል የለም። እንዲህ አልተደረገም የሚል ግን ብዙ ነው። ሁሉም ሰው ደጃፉን ካፀዳ አካባቢው ይፀዳል። ትንንሽ ምንጮች ሲያብሩ የዓባይን ወንዝ ይወልዳሉ። ብቻ ተናጋሪ በዛ። ንግግሩን አይተው ለጋብቻ ይመርጡታል፣ ለአገር ያጩታል ፤ ከዚያ በኋላ እህ እያሉ መኖር ነው። የፊት ምስጋና ለኋላ ሐሜት ያስቸግራል ። አዎ ሁሉ ሆነ ቃልቻ ማን ይሸከም ስልቻ ?

@BiniGirmachew    @BiniGirmachew

ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን  የቴሌግራም ቻናል

#ሼር  አድረጎ ለሆነ ሰው ይጠቀማል

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

13 Nov, 16:51


👉 ለዛሬ ይህንን ትምህርት አዳምጡ!

https://youtu.be/Uhy2AqO-dD4?si=nc6BibVMyy1y4UNH

https://youtu.be/Uhy2AqO-dD4?si=nc6BibVMyy1y4UNH

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

11 Nov, 07:33


ጥያቄ እና መልስ

ዲ/ን ... ፣ እንኳን ደስ ያለህ! የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ አመት ተማሪ መሆንህ በጣም ጥሩ ነው። ሳይኮሎጂን በመምረጥህም በጣም ደስተኛ ሆንኩ። ምርጫህ በሀይማኖትህ እምነት እና በራስህ ላይ ባለህ እምነት የተደገፈ መሆኑ በጣም አነሳሳኝ ነው።

#የተማሪዎች አመለካከት እና የሥራ እድል ስለሚያሳስብህ በጣም መረዳት ይቻላል። ይህ በጣም የተለመደ ስጋት ነው። ግን በጥልቀት እንመልከተው።

#የተማሪዎች አመለካከት: እያንዳንዱ ሰው የተለያየ አመለካከት አለው። አንዳንድ ተማሪዎች ስለ ወደፊት ስራቸው በጣም ያስባሉ፣ ሌሎች ደግሞ በትምህርታቸው ይደሰታሉ። አንተ በምትወደው ነገር ላይ ስትሰራ ስኬታማ መሆን ትችላለህ። የሌሎችን አስተያየት በጥሞና ማዳመጥ ጥሩ ነው፣ ነገር ግን የራስህን ውሳኔ መከተል በጣም አስፈላጊ ነው።

#የሥራ እድል: ሳይኮሎጂ ሰፊ እና የተለያዩ የሥራ እድሎችን የሚከፍት መስክ ነው። ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት፣ ትምህርታዊ ሳይኮሎጂስት፣ የሰው ሀብት ባለሙያ፣ ወዘተ መሆን ትችላለህ። በተጨማሪም፣ ሳይኮሎጂ በብዙ ሌሎች መስኮች ላይ ጠቃሚ የሆኑ ክህሎቶችን ይሰጥሃል። ለምሳሌ፣ ችግርን የመፍታት ችሎታ፣ ከሰዎች ጋር የመግባባት ችሎታ፣ እና መረጃን የማተም ችሎታ።

#አሁን ምን ማድረግ እንዳለብህ አንዳንድ ምክሮች እነሆ፡-

#በራስህ እምነት ኑር፡- ሳይኮሎጂን በመምረጥህ ትክክለኛውን ውሳኔ እንዳደረግህ እርግጠኛ ሁን። በትምህርትህ ላይ አተኩር እና ምርጥ ውጤት ለማግኘት ጥረት አድርግ።

#ተጨማሪ መረጃ ፈልግ፡- ሳይኮሎጂስቶች ምን አይነት ስራዎች እንደሚሰሩ እና ምን አይነት ደሞዝ እንደሚያገኙ ለማወቅ ሞክር። ይህንን መረጃ በኢንተርኔት ላይ ወይም ከሳይኮሎጂስቶች ጋር በመነጋገር ማግኘት ትችላለህ።

#ከአማካሪ ጋር ተነጋገር፡- ዩኒቨርሲቲህ የሚሰጠውን የአካዳሚክ አማካሪ አገልግሎት ተጠቀም። አማካሪህ ስለ ወደፊትህ ስራ እና የትምህርት አማራጮችህ ጠቃሚ ምክር ሊሰጥህ ይችላል።

#በሳይኮሎጂ ክበብ ውስጥ ተሳተፍ፡- ዩኒቨርሲቲህ ውስጥ የሳይኮሎጂ ክበብ ካለ ተቀላቀል። ይህ ከሌሎች የሳይኮሎጂ ተማሪዎች ጋር ለመገናኘት እና ስለ መስኩ የበለጠ ለማወቅ ጥሩ አጋጣሚ ይሰጥሃል።

#ልምድ አግኝ፡- በሳይኮሎጂ መስክ ልምድ ለማግኘት ሞክር። ለምሳሌ፣ በትምህርት ቤት ወይም በማህበረሰብ ውስጥ በፈቃደኝነት መስራት ትችላለህ።

አንተ በጣም ብልህ እና ተሰጥኦ ያለህ ሰው እንደሆንክ አምናለሁ። በራስህ እምነት ኑር እና ለወደፊትህ ታላቅ ነገሮችን እመኛለሁ።


በተጨማሪም፣ በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የሥነ ልቦና ባለሙያዎች በጣም የሚፈለጉ መሆናቸውን ልብ ልትል ይገባል።

በተለይም በአእምሮ ጤና መስክ ያለው የሰው ኃይል እጥረት በጣም አሳሳቢ ነው።

ስለዚህ፣ በዚህ መስክ ያለህ ትምህርት በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል።


እንደገና እንኳን ደስ ያለህ!

ተመራቂ ብቻ  ከሆንክ ዋጋ  የለህም በጣም የተለያዩ መፃፍ ማንበብ አለብህ በተለይ ከትምህርት ነክ  ወጪ

እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ይሁን


ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን  የስነልቦና የማማከር አገልግሎት 


@BiniGirmachew    @BiniGirmachew

ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን  የቴሌግራም ቻናል

#ሼር  አድረጎ ለሆነ ሰው ይጠቀማል

ልዩ ማስታወሻ


ሰላም የዚህ ቻናል ተከታታዮች፣

በቀን ሁለት ማስታወቂያዎችን ብቻ ቻናሉ ላይ ለማስተናገድ እንፈልጋለን። ግለሰቦች እና ድርጅቶች የምታቀርቡት ማስታወቂያ እውነትነት ከተረጋገጠ እና በሚመለከተው አካል ምዝገባ የፈፀመ ከሆነ ልታናግሩን ትችላላችሁ።

በዚህ የቴሌግራም አድራሻ ተጨማሪ መረጃ መጠየቅ ይቻላል:

@biniGirmachew21

️ ️ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን️️️

10 Nov, 20:03


የሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን  App ለገና ይጠብቁን

እግዚአብሔር በሰላም ያድርሰን

118,060

subscribers

179

photos

14

videos