ጃን ያሬድ | Jan Yared @jan_yared Channel on Telegram

ጃን ያሬድ | Jan Yared

@jan_yared


እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

ጃን ያሬድ | Jan Yared (Amharic)

ጃን ያሬድ | Jan Yared በእናንተ ለማከናወን ያስችላል! ይህ ቻናል ከአብዛኛው ሪዞን ጃን ያሬድ አይገኝምን? የተለያዩ ምርጥ ቪዲዮዎች እና በእጃችን አቃፍ ተነሳሸን ለባለቤትነት እንዲሰፍሩ የቀረቡት ሰዎች ምን ያላቸውን መረጃዎች እንዲጠቀሙ ለመውለድ ነው! የሰብላላ እና በተለያዩ ቀረጥ ቪዲዮዎችን ይሞክሩ ይከታተሉን! በባተረ የጃን ያሬድ ቻናል ለተጀመረው የአብዛኛው ብሄራዊ ሪዞን ጃን ያሬድ ላይ በእኛ መስለን እንችላለን! ከአንድ ሌላ የተዘረጉ ከሆነ መረጃዎችን ይመልሱ እና በመጀመር የዚህ ስልክ ላይ እንጠቀማለን።

ጃን ያሬድ | Jan Yared

17 Jan, 13:01


"ጃንደረባውም ደስ ብሎት መንገዱን ይሄድ ነበር"
ሐዋ. 8:39

ጃን ያሬድ | Jan Yared

16 Jan, 17:43


፨የአእላፋት ዝማሬ እንዲቀጥል እንፈልጋለን፨

አሁን በዶንኪ ቱዩብ ቀጥታ ስርጭት

https://www.youtube.com/watch?v=hwv5d5R2a3w

ጃን ያሬድ | Jan Yared

16 Jan, 13:01


የቀጥታ ስርጭቱ ሊጀመር ነው::
፨እንዲቀጥል እንፈልጋለን፨

ቀጥታ ስርጭት በዶንኪ ቲዩብ

https://www.youtube.com/watch?v=hwv5d5R2a3w

ጃን ያሬድ | Jan Yared

16 Jan, 12:02


1 ሰዓት ቀረው
፨እንዲቀጥል እንፈልጋለን፨ ቀጥታ ስርጭት በዶንኪ ቲዩብ

ጃን ያሬድ | Jan Yared

16 Jan, 11:00


2 ሰዓት ቀረው
፨እንዲቀጥል እንፈልጋለን፨ ቀጥታ ስርጭት በዶንኪ ቲዩብ

ጃን ያሬድ | Jan Yared

16 Jan, 10:00


3 ሰዓት ቀረው
፨እንዲቀጥል እንፈልጋለን፨ ቀጥታ ስርጭት በዶንኪ ቲዩብ

ጃን ያሬድ | Jan Yared

16 Jan, 09:07


4 ሰዓት ቀረው
፨እንዲቀጥል እንፈልጋለን፨ ቀጥታ ስርጭት በዶንኪ ቲዩብ

ጃን ያሬድ | Jan Yared

13 Jan, 15:38


አዲስ ዝማሬ | ይኼ ጃንደረባ | ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

የአእላፋት ዝማሬን በማስመልከት ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ከሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ በሥጦታ የተበረከተ:: ቪዲዮውን በጃንደረባው ሚዲያ የYouTube channel ላይ ያግኙ::

https://youtu.be/bPx2s6HqNac

ጃን ያሬድ | Jan Yared

12 Jan, 09:17


የቀን ለውጥ - ማክሰኞ ጥር 7/2016 ዓ.ም ቀጥታ ስርጭት በዶንኪ ቲዩብ

ጃን ያሬድ | Jan Yared

12 Jan, 05:56


እንዲቀጥል እንፈልጋለን።

ጃን ያሬድ | Jan Yared

11 Jan, 07:29


እንዲቀጥል እንፈልጋለን!
ቅዳሜ ጥር 4/ 2016 ዓ.ም በዶንኪ ቲዮብ ቀጥታ ስርጭት የአእላፋት ዝማሬ አንድ ሳምንት እናስታውሳለን።

ጃን ያሬድ | Jan Yared

07 Jan, 18:28


ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋራ፡አዩት፥ወድቀውም ሰገዱለት፥ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው፡በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሔዱ።

-የማቴዎስ ወንጌል 2:11-12

ጃን ያሬድ | Jan Yared

07 Jan, 15:26


የመጀመሪያው የአእላፋት ዝማሬ ተካሔደ

| ጃንደረባው ሚዲያ | ታኅሣሥ 27 2016 ዓ.ም.|
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ከመስከረም 2 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ይፋ የተደረገው የአእላፋት ዝማሬ ከሦስት ወራት የመዝሙር ጥናትና የማኅበራዊ ሚድያ ዘመቻ በኋላ አእላፋት በተገኙበት በእግዚአብሔር ቸርነት በድምቀት ተካሔደ::

ልክ 10:00 ሰዓት ላይ ሃያ አራት ዲያቆናትና አራት ቀሳውስት ባካሔዱት በመሐረነ አብ እና በምሕላ ጸሎት የተጀመረ ሲሆን በጸሎቱ ፍጻሜም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ጸሎተ ወንጌልና ኪዳን ደርሶአል::

በመምህር ጳውሎስ መልክዓ ሥላሴ የጉባኤ መሪነት የተካሔደው በአእላፋት ዝማሬው መክፈቻ ላይ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ፣ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ፣ ብፁዕ አቡነ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ፣ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ፣ ሊቀ ማዕምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ፣ ሊቀ ትጉኃን ታጋይ የአድባራትና የገዳማት አስተዳዳሪዎች ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣ ሰባኪያነ ወንጌል እንዲሁም አእላፋት ተገኝተዋል::

ቅዱስ ፓትርያርኩ ከጸሎት በኋላ "ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ" የሚለውን ቃል መነሻ አድርገው "ሰላም የሁሉ ነገር መሠረት ነው:: ሰላም ከሌለ ሁሉ ነገር የለም:: ሰላም የሦስት ፊደል ቃል ብትሆንም ዓለምን ትገዛለች:: በዛሬው ዕለት በታላቅ ጉባኤ ስለ ሰላም ጸሎት ማድረጋችሁ ደስ ያሰኛል:: ይህንን ተግባር እንድትቀጥሉበት ፣ እንድታበዙት ፣ እንድታሰፉት ፣ እንድትቀጥሉበት ቤተ ክርስቲያን ትጠይቃለች:: ምሕላችሁንና መዝሙራችሁን አስፉት ጨምሩበት" ብለዋል:: በመጨረሻም "የአእላፋት ዝማሬ በይፋ መከፈቱን እናበሥራለን" በማለት የአእላፋት ዝማሬን አስጀምረዋል::

"የአእላፋት ዝማሬ" ፕሮጀክትን ሃሳቡን በመስከረም ወር በጸሎተ ቡራኬ ያስጀመሩትና እስከ ፍጻሜውም ድረስ ብዙ ውጣ ውረዶችን ሲያልፍ በአባታዊ ሚናቸው የደከሙት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ "አትፍሩ ለዓለም ሁሉ ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁ" በሚል ርእስ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን "በልደትና በትንሣኤ ምክንያት ልጆቻችን በማይገባ ቦታ እያከበሩ ስለነበረ ልደቱን በቀድሞ የልደት ቦታችን ፣ በልደት ቤታችን እናክብር የሚለውን የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ጥሪ ተቀብላችሁ ስለመጣችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ" ብለው ዝማሬውን አስጀምረዋል::

ምእመናን 171 ካሬ ስክሪኖች በስምንት አቅጣጫ እየተመለከቱ አብረው የዘመሩ ሲሆን ፍጹም በተረጋጋ መንፈሳዊ ድባብ የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስን ልደት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን በአእላፋት ዝማሬ አክብረዋል:: የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ወጣቶች ለወራት በብዙ ጸሎትና ትጋት የደከሙበት ይህ የዝማሬ ማዕድ በእግዚአብሔር ጥበቃ ባማረ ሁኔታ ተከናውኖአል:: አእላፋት በዕንባና በተመሥጦ ሆነው እየዘመሩ የመድኃኒታቸውን ልደት በመንፈስ አክብረዋል::

ዝማሬውን ያሳረጉት ጸባቴ አባ ወልደ ማርያም "የአእላፋት ዝማሬ መሳካት ምሥጢሩ ለወራት ሲካሔድ የሰነበተው የመሐረነ አብ ጸሎት ነው:: ሊሳካ የሚችለው በስሜት ሳይሆን በጸሎት የተጀመረ ነገር ነው" ብለዋል:: የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ለአእላፋት ዝማሬ መሳካት ገንዘባቸውን ፣ ጉልበታቸውን ፣ ጊዜያቸውን ሥጦታ አድርገው ላቀረቡ ሁሉ የተወለደው ንጉሥ ከሰብአ ሰገል እጅ መንሻ ጋር ይደምርላችሁ በማለት ምስጋናውን ያቀርባል:: ከልዩ ልዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከሰሜን አሜሪካ ፣ ከአውሮፓ ፣ ከስዊድን ፣ ከኬንያ ለዚሁ የአእላፋት ዝማሬ ለመታደም የመጣችሁ ምእመናን የእረኞችና የሰብአ ሰገል በረከት ይድረሳችሁ እንላለን::

#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው
#የአእላፋት_ዝማሬ
#እንዳልዘምር_የሚክለክለኝ_ምንድን_ነው