ማራናታ 🙏🤲 @yleybgal19 Channel on Telegram

ማራናታ 🙏🤲

@yleybgal19


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው ;ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሳጽን ይንቃሉ " ምሳሌ 1:7
👉 የቻናሉ አላማ
✔️💠 የአባቶች ምክር
✔️💠መንፈሳዊ መዝሙሮች
✔️💠ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን መረጃ ያገኙበታል

ለማንኛውም ሀሳብ @merii19✣✣

ማራናታ 🙏🤲 (Amharic)

ማራናታ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አለ። የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው። ወሮች የጥበብንና ተግሳጽን ይከታተሉ። የቻናሉ አላማ፣ የአባቶች ምክር፣ መንፈሳዊ መዝሙሮችና ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን መረጃ ያገኙበታል። ማራናታ ለማንኛውም ሀሳብ @merii19✣✣ መረጃዎን የምንገባውን መልኩን እንደሚያገኙ፣ እንደማይረዳት ለማረጋገጥ ከተወሰነ መረጃ ለመረጃ እንደገና ይሆናል። ለዚህ ቅናሽን መንገድ ተደጋግሞ ይሁኑ።

ማራናታ 🙏🤲

23 Nov, 19:50


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

ማራናታ 🙏🤲

23 Nov, 19:10


በግምት ከሌሊቱ 8 ሰአት ገደማ ነው ሶስት ጓደኛማቾች እንደ ለመደባቸው ቅዳሜን ወጥተው ክለብ ለክለብ እየተዝናኑ ሰአታትን አስቆጥረዋል እንደ አጋጣሚ ሆኖ እጃቸው ላይ ያለውን ብር የትራንስፖርት እንኳን ሳያስከሩ መጨረሳቸውን ያስተዋሉት ከረፈደ ነበር ያው የሁልጊዜ ቤታችን ስለሆነ ዱቤ ይሠጡናል ብለው አስተናጋጁን ይጠሩትና የተፈጠረውን ያስረዱታል እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሞባይል ባንኪንግ የማይጠቀሙበትን ተቀያሪ ስልካቸውን እንደያዙና እጃቸው ላይ በዚህ ሰአት ምንም ብር እንደሌላቸው ይነግሩታል እሱም ወደ ማናጀሩ መሄድ ሲጀምር.....see more

ማራናታ 🙏🤲

20 Nov, 20:42


ያለ አንተ ማን አስቦኛል
ከአንተ በቀር ማን ረድቶኛል
ክብሬ ኢየሱስ ላመስግንህ
ለዘላለም መጠጊያዬ ነህ

ሰው ለመዳን ሲሽቀዳደም
ሁሉም ሲያልፍኝ አጥቼ አቅም
ሰው የለኝም ስል ስትሰማ
ጌታ ክንድህ ሆነኝ ግርማ
ቤተ ሳይዳ ቤቴ አይደለች
ነፍሴ ጣትህን ተማመነች
በአንተ አልጋዬን ተሸክሜ
አሳረፍከኝ ከህመሜ

አስታዋሽ ነህ ለተረሳው
አጉራሹ ነህ ለተራበው
ከደጃፌ ስትመጣ
የዘንዶው ቃል ጉልበት አጣ
ስንት ጊዜ አወጣኸኝ
የአይኔን እንባ አበስክልኝ
አቤት ፍቅር አቤት ምህረት
ቋንቋ ቃላት የማይገልጹት

የተተወ በወገኑ
ምን ቢያነባ በዘመኑ
ወዳጅ ያሉት ሲሄድ ሸሽቶ
ስትዳስሠው ቆመ ጸንቶ
ጥልቁ ኑሮ ተሸበረ
የሞት ዘንጉ ተሰበረ
ማርዳዬ ነህ ጌጥ ለአንገቴ
ታየሁብህ ሰገነቴ

በህሊና ታላቅ ስደት
የተመታ ያሰረው ሞት
ያየኸው ዕለት ተፈወሰ
በደስታ ተመለሰ
የነጠቅኸው ከሞት መንደር
የሰጠኸው ታላቅ ክብር
ሌላ አይደለም ይህ ልቤ ነው
ንገስበት ዙፋንህ ነው

ዘማሪት ዕንቁሥላሴ ጎሳ

21 መዝሙር
ተጨማሪ ለማግኘት Join ያድርጉ
➪@yleybgal19
➪@yleybgal19

ማራናታ 🙏🤲

20 Nov, 20:28


የልቤን ሁሉ
ዘማሪት ፋንቱ
========
የልቤን ሁሉ ለማን ላማክር
እመቤቴ ሆይ ከአንቺ በቀር
የደካማው ሰው መጠጊያ እኮነሽ
ሃዘን ጭንቀቴን የምረሳብሽ
አዝ---------------//
ቅዱሳን አበው አንቺን መረጡ /2/
ከሲኦል ዓለም ስላመለጡ
ፃድቅ በስራው ያኔ ሲድን/2/
እጠራሻለሁ ድንግል አንቺን
አዝ---------------//
የጭንቄ ደራሽ አክኪሌ ነሽ/2/
ቂም በቀል አያውቅ የዋህ ልብሽ
ልቤ ለፍቅርሽ ሰፊ ስፍራ አለው /2/
በአዘ ንኩኝ ሠዓት እጠራሻለው
አዝ---------------//
ዋሴ ነሽ ለእኔ ድንግል እናቴ/2/
ስምሽ ጠበቀኝ ከልጅነቴ
ሁልጊዜ ለእኔ በጎ ያረግሽልኝ /2/
ምን ልበል ለአንቺ ቃላት የለኝ
አዝ---------------//
ለአዘንኩኝ ለእኔ ደስታዬ ነሽ/2/
ያረጋጋሽኝ ፈጥነሽ ደርሰሽ
ስምሽ ሃጥአንን የሚቀድስ/
ከሞት ወደ ህይወት የሚመልስ


ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
               
ተጨማሪ ለማግኘት ይቀላቀላሉ
ለመቀላቀል▻ @yleybgal19
                ▻ @yleybgal19

ማራናታ 🙏🤲

16 Nov, 16:07


#ቅዱስ_ጊዮርጊስ_ሊቀ_ሰማዕታት

ሕዳር 7 እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ አመታዊ
#የቅዳሴ_ቤቱ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።🙏🙏🙏

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሀያል ሰማዕት ፣
መክብብ ሰማዕት
#የሰማዕታት_አለቃ ይባላል #ሰማዕት ማለት ምስክር ማለት ነው ። ይህን ስም ሊያገኝ የቻለው ከተጋድሎው ጽናት ነው
#ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሦስት ጊዜ ሞቶ ሦስት ጊዜ ተነስቷል። #አንደኛው ፦ ከዛፍ ግንድ ጋር አጣብቀው አስረውት አቃጠሉት ከዛም አመዱን በይድራስ ተራራ ላይ በተኑት ። ጌታ ግን በተአምር ከሞት አስነስቶ እንዲያስተምር አደረገው። ጠላቶቹ ተደንቀው ቢጠይቁት ''አይዟችሁ #አመዱን_ሰው የሚያደርግ #አምላክ_አለኝ" አላቸው።
በፃድቃን ላይ አድሮ ሁሉን የሚያደርግ
#እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን🙏🙏

#ሰማዕቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ
ሀገራችንና ህዝባችንን ይጠብቅልን🙏🙏🙏

#መልካም___ቀን🙏

አጫጭር ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇

@Enatachn_mareyam  
@Enatachn_mareyam

ማራናታ 🙏🤲

16 Nov, 07:58


https://vm.tiktok.com/ZMhGuWn4F/
Download TikTok to enjoy more posts. This post is shared via TikTok: https://vm.tiktok.com/ZMhGuKLhY/

ማራናታ 🙏🤲

16 Nov, 07:26


አዲስ የአእላፋት መርሙር ተለቀዋል!

መዝሙሮቹን በቴለግራም ለማጥናት JOIN በሉ!

@janyared

ማራናታ 🙏🤲

16 Nov, 05:09


https://www.youtube.com/live/HYiTwAUj328?si=6ZLcyl8bM5_4EZEP

ማራናታ 🙏🤲

11 Nov, 18:27


ልጆቼ! በድህነቴ ላይ ቸርነትን አድርጉልኝ፡፡ በዚህስ አልችልም ካላችሁ እሺ በቁስሌ ላይ ዘይትን አፍስሱልኝ፡፡ አሁንም ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ ወደ እኔ ጠጋ በሉና አናግሩኝ፡፡ እናንተን ማየት፣ ከእናንተ ጋር መጨዋወት ይናፍቀኛልና፡፡

በገዛ ደሜ የገዛኋችሁ ልጆቼ! ከባድ ነገር እኮ አልለመንኳችሁም፡፡ እኔ የምፈልገው ትንሽ ዳቦ፣ ጊዜአዊ ማደርያ፣ እንዲሁም የሚያጽናኑ ቃላትን ብቻ ነው፡፡ “ይህ ሁሉ ማድረጌ ምን ይጠቅመኛል?” ካላችሁ ስለ ምሰጣችሁን ርስት መንግሥተ ሰማያት ብላችሁ አድርጉት፡፡ አሁንም ልባችሁ አልተነካምን? ስለ መንግሥተ ሰማያት አታድርጉት፤ ግን ደግሞ ስለ ሰብአዊ ርኅራኄ ይህን አድርጉልኝ፡፡ የእኔን መራቆት የሚያሳዝናችሁ በቀራንዮ አደባባይ ስለ እናንተ ብዬ የተራቆትኩት ብቻ ነውን? ታድያ አሁንም ‘ኮ በደጃችሁ ላይ ተጥዬ ዕራቆቴን ነኝ፡፡ ለምን አላዘናችሁልኝም? የታሰርኩት በቀራንዮ ብቻ ነውን? አይደለም፡፡ ታድያ እንደምን አታዝኑልኝም?

የማፈቅራችሁ ልጆቼ! በመስቀል ላይ ተሰቅዬ ሳለሁ “ተጠማሁ” እንዳልኩ ዛሬስ ስለ እናንተ ብዬ ደጋግሜ ይህን ቃል አልተናገርኩምን? ጕሮሮዬ ደርቆ ስለምን ትንሽ እንኳ አላሳዝናችሁም? ስለምንስ ይህ ሁሉ ፍቅር ስለ እናንተ መሆኑን ትዘነጉብኛላችሁ? የምለምናችሁ እናንተን ባለጸጋ ለማድረግ አይደለምን? ይህችን ትንሽ ቸርነት ስላደረጋችሁልኝ በዐይን ያልታየች፣ በጀሮ ያልተሰማች፣ በሰውም አእምሮ ያልታሰበች ርስት መንግሥተ ሰማያት እንድታገኙ ብዬ አይደለምን? ስለ እናንተ ብዬ ደሀ የሆንኩት ያኔ በመዋዕለ ሥጋዌዬ ብቻ እንደሆነ አታስቡ ልጆቼ! ዛሬም ቢሆን በደጃችሁ የተጣልኩት ስለ እናንተ ጥቅም እንደሆነ ተረዱልኝ፡፡

ከባድ ነገር ‘ኮ አልለመንኳችሁም፡፡ እስር ቤት መጥታችሁ ጠይቁኝ እንጂ አስፈቱኝ አላልኳችሁም፡፡ ታምሜ ጠይቁኝ እንጂ ፈውሱኝ አላልኳችሁም፡፡ ከጠየቃችሁኝ ብቻ በቂዬ ነው፡፡ እስኪ ልጠይቃችሁና እናንተም መልሱልኝ! በዚያ በአስፈሪው ቀን ስመጣ “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን” የሚለውን ቃለ ሕይወት መስማት አትፈልጉምን? ዛሬ የሰጣችሁኝ ሁሉ የምረሳ ይመስላችኋልን? ያኔ በክብር ስመጣ ከእልፍ ወለዱ ጋር እንድሰጣችሁ አትሹምን? የማፈቅራችሁ ልጆቼ! ከደጃችሁ ተጥዬ የምለምናችሁ፣ ከበራችሁ ላይ ቆሜ ማደርያን የምጠይቃችሁ፣ እጄን ዘርግቼ እናንተን እናንተን የማየው ያኔ ትሉ ወደማይጠፋው እሳቱ ወደማያንቀላፋው እሳት እንዳትሄዱብኝ ብዬ ነው፡፡ ታድያ ይህን ለምን አትረዱልኝ ልጆቼ? ስለምን እንዳስቸገርኳችሁ ታስባላችሁ? ለእናንተ ጥቅም እንደሆነ እንዳትረዱ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? ከእናንተ ጋር ቁጭ ብዬ ልብላ ስላችሁ ስለምን ትገፈትሩኛለችሁ? ይህን ያህል ቸርነት አድርጌላችሁ ሳለሁስ ስለምን በግልምጫ አያችሁኝ? ይህን ያህል መውደድ ወድጃችሁ ሳለሁ ስለምን በቅጡ ልታነጋገግሩኝ አልወደዳችሁም? ከአዳም ጀምሮ ዓለም እስኪያልፍ ድረስ ያለው ሕዝብ ሁሉ በአንድ አደባባይ ላይ ቆሞ፣ እልፍ አእላፍ መላእክት በዙርያዬ ረበው “ይህ/ ይህቺ ልጅ ወዳጄ ነው/ ናት፤ በመሆኑም በታላቅ ክብርና ዕልልታ አጅባችሁ ወደ ዘለዓለም ደስታዋ አግቡት/ አግቧት” የሚለውን ፍርዴ አትናፍቁምን?

ልጆቼ! እኔን ላለማየት ስለምን ፊታችሁን ትሸፍናላችሁ? ስለምን፡ታፍራላችሁ? እኔ ሳላፍርባችሁ ስለምን እናንተ አፈራችሁ?

ልጆቼ! ልባችሁ እንደተነካ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ስሜት ብቻ አይሁን፡፡ ከንፈራችሁን ብቻ አትምጠጡብኝ፡፡ ከእናንተ የምፈልገው አንዲት ነገር ብቻ ነው፡፡ ከላይ የጠየቅኳችሁን ነገሮች ወደ ተግባር ቀይሯቸው፡፡ ለማይጠቅማችሁ ነገር አብዝታችሁ እየሮጣችሁ ለሚጠቅማችሁ ነገር አትስነፉ፡፡ “እኔኮ ሥጋ ለባሽ ነኝ፤ ይህን እንደምን እችላለሁ?” አትበሉኝ፡፡ አውቃለሁ! ነገር ግን ፈቃዳችሁን ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ራሴ አደርግላችኋለሁ፡፡ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብዬ.ያስተማርኳችሁን ቃል ረሳችሁትን? /ዮሐ.15፡5/፡፡ እንግዲያውስ ከእናንተ የምፈልገው ፈቃዳችሁን ነው፡፡ አሁን ካላችሁበት ቦታ ተንቀሳቅሳችሁ ወጣ ስትሉ ታገኙኛላችሁ፡፡ አናግሩኝ! አፍቃሪያችሁ መድኃኔዓለም ነኝ፡፡

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
     🔸 @yleybgal19
🔸🔹🔸 @yleybgal19
     🔸 @yleybgal19

ማራናታ 🙏🤲

08 Nov, 04:15


ስጦታዎች ማዘዝ ከፈለጉ

እንደምርጫዎ በትዕዛዞ መሰረት እናዘጋጃለን

     
             👉@merii19
@merii19