#Ethiopia | በአፋር ክልል፣ ዱለሳ ወረዳ በተከሰት የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ፍል ውሃዎች እየተፈጠሩ ይገኛሉ።
በወረዳው በሳጋንቶ ቀበሌ የደረሰውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በስፍራው በአካል በመገኘት የመስክ ምልከታ ያደረገ የኢቢሲ ሪፖርተር በቀበሌው በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ፍል ውሃዎች እየወጡ መሆኑን መታዘቡን ገልጿል።
በቀበሌው በተለይ በዶፈን ተራራ ላይ የመሬት መንቀጥቀጡ በመጠኑም በድግግሞሹም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን በዚህም ሳቢያ ተራራው እየተናደ እንደሆነ ገልጿል።
የመሬት መንቀጥቀጡ በፈጠረው ግፊት በቀበሌው እንፋሎት አዘል ፍል ውሃ እና ቅባት አዘል ጥቁር ውሃ ከመሬት እየፈለቀ መሆኑንም ጠቅሷልል።
በቀበሌው የሚኖረው አርብቶ አደር ማህበረሰብ ከሥፍራው ተነስቶ በሌሎች አካባቢዎች እንዲሰፍር እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።
በመሬት መንቀጥቀጡ ሳቢያ በፈንታሌ እና በዶፈን ተራራ መካከል የተፈጠረው የመሬት ስንጥቅ ክፍተቱ እየጨመረ መሆኑንም አክሏል።