***
ተጠርጣሪዋ ወንጀሉን የፈጸመችው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አያት ዞን1 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ነው፡፡ ተጠርጣሪዋ በደላላ አማካኝነት በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠረችበት መኖሪያ ቤት በሶስተኛው ቀን ቆይታዋ የግል ተበዳይ ወደ ስራ በሄዱበት ወቅት አጋጣሚውን በመጠቀም በቤቱ ውስጥ የተቀመጠውን የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች እንዲሁም የተለያዩ የወርቅ ጌጣጌጦችን ሰርቃ በመሰወሯ የግል ተበዳይ የተፈፀመባቸውን የወንጀል ድርጊት ለመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አመልክተዋል፡፡
ተጠርጣሪዋ የወንጀል ድርጊቱን ከፈፀመች በኋላ የግል ተበዳይ ጋር ከመቀጠሯ በፊት በክፍለ ከተማው ወረዳ 14 አባዶ አካባቢ ኮንዶሚኒየም ቤት ለሦስት ወራት ተከራይታ በነበረበት ቤት ተደብቃ በክትትል የፖሊስ አባላት ከሰረቀቻቸው የተለያዩ አልባሳት፣ የተለያዩ የሴትና የወንድ ጫማዎች፣ 18 ሺህ የአሜሪካ ዶላርና የህንድ ሩፒ፣ የተለያዩ የወርቅና ልዩ ልዩ ጌጣጌጦች ጋር በቁጥጥር ስር መዋሏን ከክ/ከተማው የተገኘው መረጃ ያስረዳል። በተጨማሪም በሁለት የተለያዩ ስሞች የነዋሪነት መታወቂያ እንደተገኘባትም ተገልጿል።
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመሪ ሉቄ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ኃላፊ ኢንስፔክተር ሰለሞን አበበ እንደገለፁት የግል ተበዳይ ተጠርጣሪዋን ለስራ ሲቀጥሯት ያቀረበችው የተያዥ ፎርም የራሷን ፎቶ በትክክል እንዳይለይ አድርጋ የለጠፈች ሲሆን የግል ተበዳይም ይህንን ሳያረጋግጡ በእምነት የቀጠሯት መሆኑን ገልፀው ህብረተሰቡ የቤት ሰራተኛ በአጋዥነት መቅጠሩ ተገቢ ቢሆንም በህጋዊ መንገድ በቂ ተያዥ በማስቀረብ የተያዣቸውን አድራሻና ማንነት በአግባቡ በማጤን መቅጠር እንደሚገባና ውድ የሆኑ ንብረቶችንና ገንዘቦችን ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ በማስቀመጥ በተገቢው ሊቆጣጠሩና ንብረታቸውን ከስርቆት ወንጀል ሊታደጉ እንደሚገባም ተናግረዋል። ዘጋቢ ፦ዋና ሳጅን አዳነ
*
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”