አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት @addistiweled Channel on Telegram

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት

@addistiweled


ክለባችን በሶሻል ሚድያ አስተማማኝ በሆነ መልኩ በfb,YouTube,tiktok,instagram,twitter በመጠቀም ከፍተኛ ገቢ ሚያገኝበት መንገድ መፍጠር ነው


💥ሙሉ መረጃ
ትኩስ ዜናዎች
የጨዋታ ዘገባዎች
ታሪኮች

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት (Amharic)

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት ላይ በእንግሊዝ፣ አቤቴናው አፍሪጃ እና የቱርክ ቱዳዝ እናረጋግጥ እናደሳለን። የትኩስ ዜናዎችና የጨዋታ ዘገባዎች በመጠቀም በሶሻል ሚድያ አስተማማኝ በመጠቀም ከፍተኛ ገቢ እና መንገድን ከፍተኛ ቦታ ለመፍጠር እናወጣለን። ምንም ሰው እስከ ስድስት ቀናት ያሸንፍካል፣ ወይም የሚጣበቅበት ቀን ባለፈቁት አገር እና አዋጅ ሁኔታችንን ይከተላል። ሰላም፣ ዘርአይት እና በትክክለኛ እቅድ እንዲሁም ከእናቴ ቤተሰብ ሌሎች መረጃዎች ይደምሳሉ።

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት

24 Nov, 05:30


#የጨዋታ_ቀን

#Match_day

👉የኢትዮጵያ ፕሪሚየር _ሊግ  _8ኛ  ሳምንት  ጨዋታ
#Ethiopian_Premier_League

⚽️ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ #ሲዳማ_ቡና  ⚽️

📆 እሁድ  ህዳር 15/2017
🕗10:00
🏟  በድሬደዋ ስታዲየም

ድል ለአርበኛዉ ክለባችን ቅዱስ ጊዮርጊስ

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት

23 Nov, 09:41


ተስፋዉ ቡድናችን ትናንት በወዳጅነት ጨዋታ ከዲቪዚዮን ቡድኑ ሮሀ ጋ ተጫዉቶ 7-3 በሆነ ሰፊ ዉጤት አሸንፏል።
ያብፀጋ ⚽️⚽️⚽️
ከበር ⚽️⚽️
ያብስራ ⚽️
ሰለሞን ⚽️

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት

21 Nov, 08:37


👉ድሬዳዋ ተጉዤ፣ስታዲየም ተገኝቼ፣ ከክለቤ ጎን መቆም ባልችልም በአለሁበት ሆኜ እቅሜ በፈቀደው ልክ
ባለ 30፣50 እና 100 ብር ትኬት በመግዛት ኃላፊነቴን እወጣለሁ፡፡
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የሒሳብ ቁጥር 928 ወይም
በቴሌብር ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት

21 Nov, 06:46


👉የፈረሰኞቹን አዲሱ ማሊያ በፅህፈት ቤታችን በአሁን ሰዓት እየተሸጠ ይገኛል ።
💛ይህንን ውብ ማሊያ የግሎ ያድርጎ 💛
✌️አንድ ክለብ አንድ ቤተሰብ ✌️

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት

20 Nov, 12:38


👉ለስፖርት ማህበራችን አባላትና ደጋፊዎች አዲስ ማሊያ ያመጣን መሆኑን እየገለፅን ሽያጭ ነገ ህዳር 12/2017 ዓ.ም ይጀመራል፡፡
==============//=============
ሽያጭ የሚጀምርበት ሰዓት ነገ ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በቅሎ ቤት በሚነኘው የስፖርት ማህበራች መዝናኛ ማዕከል መሸጥ ይጀምራል ፡፡

👉የአንዱ ዋጋ 1000 (አንድ ሺ ብር ብቻ)

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት

20 Nov, 10:51


✌️ሳንጅዬን ያላችሁ✌️
✌️እስቲ እንያችሁ! ✌️

💛 ማሊያ ለመግዛት ዝግጁ? 💛


@goferesportswear

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት

19 Nov, 10:42


👉የፈረሰኞቹ ዋናው ቡድን በድጋሜ በዛሬው እለት የአቋም መፈተሻ ጨዋታውን ከ20 ዓመት በታች ቡድናችን ጋር ያደረገ ሲሆን 6 ለ 3በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ 6 - 3ቅዱስ ጊዮርጊስ U20
ፍፁም ጥላሁን ⚽️⚽️ ⚽️ፋይም ዘይኑ
መሀመድ ኮኔ ⚽️⚽️ ⚽️ሰለሞን ታደሰ
ቢኒያም ፍቅሩ ⚽️ ⚽️ክብር አክሊሉ
ፀጋ ከድር ⚽️

በተጨማሪ ከጉዳት ጋር በተያያዘ ኦጋንዳዊው ተጫዋች ከጊፍት ፍሪድ እና ከአሮን አንተር ውጪ ሁሉም ተጫዋቾቻችን በሙሉ ጤንነት ላይ ይገኛሉ።

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት

19 Nov, 05:37


በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ምክንያት ተቋርጦ የሚገኘው የሀገራችን ትልቁ ውድድር ቅዳሜ ህዳር 14 በአርባምንጭ እና ውልዋሎ ጨዋታ ይጀምራል። ክለባችንም ታላቁ ጊዮርጊስ ከሲዳማ ጋር እሁድ ህዳር 15 በ10:00 ሰአት ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል።

እናሸንፋለን💪❤️💛✌️

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት

18 Nov, 12:31


👉"ለዋናው ቡድን የሚመጥኑ ልጆችን ለማፍራት በቅንጅት እየሰራን እንገኛለን!!
ከ20 ዓመት በታች አሰልጣኝ ታደሰ ጥላሁን

የ2017 ዓ.ም ከ20 ዓመት በታች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ህዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ ውድድር ሲመለስ ያለፉትን ሁለት ዓመታት በርካታ ወጣትና ተስፋ ያላቸውን ወጣቶት ተጨዋቾች ወደ ዋናው ቡድን በማሳደግ ተተኪዎችን እያፈራ የሚገኘው ከ20 ዓመት በታች ቡድናችን ለአዲስ ምዕራፍ የዝግጅት ይረዳቸው ዘንድ ከዋናው ቡድን ጋር የወዳጅነት ጨዋታ በማድረግ እራሳቸውን እያጠናኩ ይገኛል፡፡

የባለፈውን ዓመት ከ17 ዓመት በታች ቡድናችን አሰልጣኝ የነበረው ታደሰ ጥላሁን አሁን ደግሞ ከ20 ዓመት በታች ቡድናችንን በመያዝ በርካታ ወጣቶችን በመመልመልና ከታች በማሳደግ ከነባር ልጆች ጋር እያዋሀደ ተተኪዎችን እያፈራ ይገኛል፡፡

ስለሆነም አሰልጣኝ ታደሰ ጥላሁን ስለ ወጣቶቹ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር አጠር ያለች ቆይታ አድርጓል ፡፡

መልካም ቆይታ ይሁንላችሁ፡፡

ጥያቄ :-ቡድኑን በተመለከተ

ታደሰ ጥላሁን፡- ያለው ሂደት ቡድን እየስራን ነው፣ ምርጫው በተወሰነ መልኩ አልቆ በአብዛኛው ምርጫ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ነው፣ እነሱን የማቀናጀት ስራ ነው እየስራን ያለነው፣ እስካሁን ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን አድርገናል፣ ነገም አንድ የወዳጅነት ጨዋታ አለን ከዋናው ቡድን ጋር የሚኖሩትን የወዳጅነት ጨዋታ ቅርፅ እያስያዝን የሚታዩ ክፍተቶችን እያስተካከልን እንሄዳለን፡፡ እንደ ቡድን ስናየው ቡድናችን ብዙ የሚቀረው ነገር አለ ፣ ሆኖም ግን አሁን ምርጫ ላይ ስለሆንን ልጆቹ በቦታቸው ያላቸውን ነገር የማስተማሩ ሂደት እስካሁን ብዙም አልሄድንበትም ምክንያቱም ገና ምልመላ ላይ ስለሆንን ፣ ባለው ነገር ላይ ነው እየስራን ያለነው፣ በጊዜ ሂደት ቡድኑን አጠናክረን የምንሰራ ይሆናል ።

👉በዘንድሮው ዓመት ስለተመለመሉ ልጆች

ታደሰ ጥላሁን፡- ከ20 ዓመት በታች ቡድን ውስጥ የነበሩ ልጆች አሉ፣ ከ17 ዓመት በታች ደግሞ 16 ልጆችን ይዘናል ፣ ነገር ግን 16 ልጆች ያድጋሉ ማለት ሳይሆን ተሸሎ የተገኘውን ተጫዋቾች ነው የምንይዘው፣ ይመጥናሉ በእንቅስቃሴ በስራ ይቀየራሉ ነገ ጥሩ ሊሆኑ ይችላሉ ብለን የምናስባቸውን ልጆች እንይዛለን፣ አሁን ለጊዜው ወደ 12 ልጆች አሉ፣ ከ17 ዓመት ወጥተው ወደ 20 ዓመት በታች የመጡ ናቸው፣ ከውጪ ያየናቸው ልጆች አሉ፣ የተሻለ ነገር ካላቸው ቅድሚያውን ለነሱ እንሰጣለን፣ የተሻለ ነገር የሌላቸው ከሆነ እኩል የመሆን ነገር ካለ ግን ለራሳችን ልጆች ቅድሚያ እድሉን እንሰጣለን፡፡

👉አዳዲስ ልጆችን ከነባሮቹ ጋር ስለማዋሃድ

ታደሰ ጥላሁን፡- አሁን ያለን የጊዜ ገደብ አጭር ነው፣ ህዳር 15 ይጀምራል ተብሎ የነበረው ወደ ህዳር 29 ከፍ ተደርጓል፣ ጊዜው መራዘሙ ለኛ ጥሩ ነው፣ የ20 ቀን ጊዜ ይኖረና፣ ለእኛ ጥሩ የመዋሀድ ነገር የምፈጥርበት ወቅት ይሆናል፣ በቂም ባይሆን የምፈልገውን ቡድን መስራት የምንችልበት ጊዜ ይኖረናል ብዬ አስባለሁ፡፡
የፊታችን ህዳር 19 ፌዴሬሽኑ የጠራው ስብሰባ አለ እዛ ስብሰባ ላይ የውድድሩ ቦታና የጨዋታው ድልድል ይወጣል ብዬ አስባለሁ፡፡

👉ከዋናው ቡድን አሰልጣኞች ጋር በቅንጅት ስለመስራት

ታደሰ ጥላሁን፡- በጣም ጥሩ ግንኙነት አለን፣ አዳዲስ ወጣትና ተስፋ ያላቸውን ልጆች በእረፍት ጊዜአቸው መጥተው ልምምድ ሜዳ ምልመላን በማየትና ሀሳብ በመስጠት ከ20 ዓመት በታች ያሉት ልጆች ምን ይመስላሉ የሚለውን ምን አይነት ስራ ብንሰራ ልጆች ጥሩ ይሆናሉ የሚለውን ነገር እስከ መወያየት ደርሰናል፡፡ ይሄንን ቅርርቦሽና ተግባቦት ከሌለ ለዋናው ቡድን የሚመጡትን ልጆች ማፍራት በራስ አመለካከትና በራስ ምርጫ ብቻ ነው የሚሆነው፣ ሌላው ደሞ ከዋናው ቡድን አሰልጣኞች ጋር በቅርበት ስንሰራ ሁሉንም ነገር የማየትና የመወያየት ነገር ጉልበትና አቅም ይኖረዋል፡፡ በጣም የሚገርመው እነሱ ደብረ ዘይት እኛ አዲስ አበባ ሆነን በስልክ የምናወራቸው ነግሮች አሉን፣ አሁን ለቅዱስ ጊዮርጊስ የሚመጥኑ ልጆች ለማፍራት በጋራ እየስራን ነው እና ጥሩ የሆነ ግኑኝነት ነው ያለን፡፡

👉ለነበረን አጭር ቆይታ ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
ታደሰ ጥላሁን፡- እኔም አመሰግናለሁ፡፡

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት

14 Nov, 16:10


"ጥሩ ቡድን ለመገንባት እየሰራን ነው!!
👉የእንስቶቹ አሰልጣኝ ሃና ተ/ወልድ
የክለባችን እንሰቶች ባለፈው ዓመት ወደ ታችኛው ሊግ መውረዳቸውን ተከትሎ በሃዋሳ በሚደረገው የ2017 ዓ.ም ብሔራዊ ሊግ ውድድር የተሻለ ውጤት በማስመዘገብ ወደ ፕሪሚየር ሊግ ለመመለስ በርካታ አዳዲስ ተጨዋቾች ከተለያዩ ክለቦች በማምጣት በአሰልጣኝ ሃና ተ/ወልድ ህዳር ወር ለሚጀምረው ውድድር ዝግጅት እያደረጉ ይገኛል፡፡
ስለሆነም አሰልጣኝ ሃና ተ/ወልድ ሰለ እንስቶቹ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ከዝግጅት ክፍላችን ጋር አጠር ያለች ቆይታ አድርጋለች፡፡
መልካም ቆይታ ይሁንላችሁ፡፡
👉ተጫዋቾቻችን በምን አይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?
ሀና ተ/ወልድ:-ተጫዋቾቻችን በሙሉ ጤንነት ላይ ናቸው፣ ተገቢውን ልምምድ አያደረግን እንገኛለን፡፡
👉ውድድሩ ህዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ይጀምራል፡፡

ሀና ተ/ወልድ፡- ለውድድሩስ እየተደረገ ያለው ዝግጅት ምን ይመስላል?
አሁን በምንወዳደርበት ሊግ ላይ ተወዳድረን አናውቅም፣ ግን ባለን አቅም እየተዘጋጀን እንገኛለን፡፡
አሁን የወዳጅነት ጨዋታዎችን እያደረግን ነው ጥሩ ቡድን እየሰራን ነው፡፡

👉ቡድናችንን የተቀላለቀሉት አዳዲስ ልጆች ናቸውና ከነባር ልጆች ጋር እንዴት እየተዋሀዱልሽ ነው?

ሀና ተ/ወልድ፡- ከነባር ስምንት የሚሆኑ ልጆች አሉን፣ ሌሎቹን በምልምላ ነው ያገኘናቸው፣ ከካምፖ አካዳሚና ከፕሮጀክት ላይ ነው ያመጣናቸው፣ እነሱን ከነባሮቹ ጋር ለማዋሀድ ትንሽ ጊዜ ያስፈልጋል፡፡
በአይምሮ ዝግጅትነት አንፃር ትንሽ ችግር ይኖራል፣ ያው ከነበርንበት ሊግ ወርደን ነው ዘንድሮ የምንጫወተውና ልጆቹ ላይ የሚፈጥረው ችግር ይኖራል፣ ግን እኛ ይሄን ነገር እንዳይፈጠር እየሰራን እንገኛለን ልጆቹም የተሻለ ነገር እንደሚሰሩ አምናለሁ፡፡
👉ለደጋፊው የምታስተላልፊው መልዕክት ካለሽ እድሉን ልስጥሽ
ሀና ተ/ወልድ :-ከዚህ በፊት በነበሩን ውድድሮች ላይ ክልሎች ላይ እንኳን ስናደርግ መጥተው የሚደግፉን የተወሰኑ ደጋፊዎች ነበሩ፣ አሁን የኛ ደጋፎዎች ትኩረት ሰጥተው ሴቶቹን ቡድን ሊያበረታቱ ይገባል፣ ልጆቹም ላይ መነሳሳትን ይፈጥራል፣ የተሻለ ውጤት እንድናመጣ በጣም ያግዘናልና፣ ከጎናችን ሁኑ ማለት እፈልጋሁ፡፡
👉ለነበረን አጭር ቆይታ ከልብ እናመሰግናለን፡፡
ሀና ተ/ወልድ :- እኔም አመሰግናለሁ፡፡

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት

14 Nov, 11:41


ከደጋፊዎች በተሰበሰብ ድምፅ የጥቅምት ወር ምርጥ ተጫዋች #አማኑኤል_ኤርቦ ⓬🔥🔥 ሆኗል።
አሙ⓬💪💪❤️💛

አዲስ ትውልድ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ጥምረት

12 Nov, 13:01


👉ክለባችን ከደጋፊዎች ጋር በመተባበር መንግስት ባቀረበው ተማሪዎችን የመመገብ መርሀግብር መሰረት ቢሾፍቱ አካዳሚያችን አጠገብ ለሚገኘው ማራናታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች ምገባ የሚሆን የሩዝ፤ የማካሮኒ እና የክለባችንን ማሊያ የሄረር ወረዳ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ምትኩ ዘለቀ ፤የሄረር ወረዳ የጥቃቅንና አነስተኛ ፅ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ትዝታ ዋቅቶላ፣
እርዕሰ መምህር አቶ ተሾመ ባይሳና መምህራን በተገኙበት የክለባችን የዋናው ቡድን የአሰልጣኞች ስጦታውን አበርክተዋል፡፡