Feta Daily News @fetadaily Channel on Telegram

Feta Daily News

@fetadaily


Feta Daily News (English)

Feta Daily News is a Telegram channel dedicated to providing its subscribers with the latest news updates from around the world. The channel covers a wide range of topics including politics, technology, entertainment, sports, and more. With a team of experienced journalists and editors, Feta Daily News ensures that its followers are always informed about the most important events happening globally. Whether you are interested in breaking news, in-depth analysis, or trending stories, Feta Daily News has got you covered. Stay ahead of the curve and join the growing community of news enthusiasts on the Feta Daily Telegram channel today!

Feta Daily News

14 Feb, 14:41


በኢትዮጵያ ኮንዶምን የሚጠቀሙት ወንዶች 20 በመቶ ብቻ መሆናቸውን ጥናት አሳየ

ከኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ኮንዶምን የሚጠቀሙት ወንዶች 20 በመቶ ብቻ መሆናቸውንና የሴቶቹ ቁጥር 50 በመቶ እንደሚደርስ ጥናት አሳየ፡፡

ባለፈው 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የተከወነው የማህበረሰብ ጤና ጥናት ይህንን አሳይቷል፤ለዚህ ደግሞ የኮንዶም እጥረት እና የማህበረሰቡ ግንዛቤ ማነስ በምክንያትነት ይጠቀሳሉ፡፡

ይህ የተባለው በየዓመቱ የካቲት 6 የሚከበረው የዓለም የኮንዶም ቀን በፖሊስ ሆስፒታል በተከበረበት ወቅት ነው፡፡

Feta Daily News

14 Feb, 12:39


ኢትዮጵያ ለሱዳን 15 ሚሊየን ዶላር ለገሰች

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ለሱዳን ህዝብ ሰላምና መረጋጋት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
በሱዳን የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ላይ የሚመክር የመሪዎች ጉባኤ በኢትዮጵያ፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ በአፍሪካ ህብረትና ኢጋድ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን
ጉባኤው የሱዳንን ቀውስ ለማስቆም በተለይም በረመዳን የጾም ወቅት የተኩስ አቁም እንዲደረስ እና የሰብዓዊ ድጋፍ ለሱዳናውያን እንዲደርስ ለማስቻል የተደረገ ነው።

በጉባኤው የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያና ሱዳን ጎረቤት ሀገራት ብቻ ሳይሆኑ ጠንካራ ቁርኝት ያላቸው ሀገራት ናቸው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከሱዳን ህዝብ ጎን ትቆማለች፤ ባላት አቅምም የምታደረገውን የሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተናግረዋል።በዚህም ኢትዮጵያ ለሱዳን የሰብዓዊ ድጋፍ 15 ሚሊየን ዶላር ለግሳለች ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

Feta Daily News

14 Feb, 10:29


https://youtu.be/dt3GWrrdTa0?si=2StWlS2KAQ_xBvT2

Feta Daily News

14 Feb, 08:32


ዘለንስኪ የሰላም ስምምነቱን አልቀበልም አሉ


አሜሪካ እና ሩሲያ የሚያቀርቡትን ማንኛውም የሰላም ስምምነት አገራቸው ካልተሳተፈችበት እንደማይቀበሉ የዪክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ አስጠነቀቁ ።

ዘለንስኪ ይህንን ያሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጦርነቱን ለመቋጨት የሚያስችል ንግግር ለመጀመር ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ነው። "እንደ ነጻ አገር ይህንን ልንቀበል አንችልም" ሲሉ ዘለንስኪ ተናግረዋል።

Feta Daily News

14 Feb, 07:33


በሲዳማ ከአንድ ቤት ሦስት ህፃናት በቃጠሎ ህይወታቸው አለፈ

በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን በንሳ ወረዳ ሞኮንሳ ቀበሌ ውስጥ፣ በትናንትናው ዕለት በአንድ ቤት ላይ በተነሳ እሳት ሁለት መንታ እህትማማቾች እና አንድ ወንድማቸው ህይወታቸው ማለፉን፣ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የምርመራ ክፍል ሓላፊ ጠቅሶ ቪኦኤ ዘግቧል።

Feta Daily News

13 Feb, 15:02


ሀማስ የተኩስ አቁሙ ስምምነቱን አከብራለሁ አለ

ሀማስ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ታጋቹቹን እንደሚለቅና የተኩስ አቁምም ስምምነቱ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስታውቋል ።

ከቀናት በፊት ሐማስ እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሳለች በሚል ለጊዜው ታጋቾችን እንደማይለቅ ማሳወቁ የሚታወስ ነው፡፡

የሐማስ ታጣቂ ክንፍ ቃል አቀባይ ቡድኑ በቅርቡ ሊለቃቸው ያሰባቸውን ታጋቾችን ለጊዜው እንደማይለቅ ተናግረው ነበር፡፡

ይህንን ተከትሉም እስራኤል እና አሜሪካ የሐማስን ድርጊት “የተኩስ አቁም ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ የሚያፈርስ ነው” በማለት ጋዛ ላይ ዳግም ጦርነት እንደሚቀሰቀስ ሲያስጠነቅቁ ነበር።

Feta Daily News

13 Feb, 12:36


አህያ እየነዳ የተገኘው ግለሰብ 5ሺ ብር ተቀጣ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በኮሪደር ልማት በተሰራ መንገድ ላይ ሲጓዙ የነበሩ ሁለት አህዮች ከነባለቤታቸው በቀጠናው ደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ተይዘው የደንብ መተላለፍ ቅጣት እርምጃ መውሰዱን አሳወቀ።

የአህዮቹ ባለቤት ኮሪደር በማበላሸት የ5ዐዐዐ ብር የገንዘብ ቅጣት ተቀጥቶ ገንዘቡ ለፋይናንስ ገቢ መሆኑንና የደንብ ጥሰጥን አስመልክቶ ግንዛቤ የተሰጠው መሆኑን የወረዳ 03 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እስጢፋኖስ ጌታቸው ገልጸዋል።

Feta Daily News

13 Feb, 10:37


https://youtu.be/tC8B1cZn5IA?si=jFrfy3ikqGmJCZyz

Feta Daily News

13 Feb, 08:32


ትራምፕ እና ፑቲን ጦርነቱን ለማስቆም ድርድር እንዲጀመር ተስማሙ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያ ዩክሬን ያለውን ጦርነት ማስቆም የሚያስችል ድርድር በፍጥነት እንዲጀመር ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር መነጋገራቸውን ገለጹ። ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ÷”ቡድኖች ተዋቅረው በአስቸኳይ ድርድር እንዲጀምሩ ተስማምተናል፤ ለዩክሬኑን ፕሬዚዳንት ዘሌንስኪም ደውለን ስለ ውይይቱ እናሳውቀዋለን፤ ይህም እኔ የማደርገው ነገር ነው” ብለዋል።

Feta Daily News

13 Feb, 07:34


አመራሩ ከአዲስአበባ በቅርብ ርቀት በተከፈተባቸው ጥቃት ተገደሉ


በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሱሉልታ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ የሆኑት አበበ ወርቁ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው አማጺ ቡድን ዛሬ በደረሰባቸው ድንገተኛ ጥቃት መገደላቸው ተነግሯል።

ከአስተዳዳሪው ጋር የነበረ የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊም፣ በታጣቂ ቡድኑ ታፍኖ መወሰዱን ዋዜማ ራዲዮ በዘገባው አመልክቷል።

ሱሉልታ ወረዳ ከአዲስ አበባ በስተሰሜን በሃያ አምስት ኪሎሜትሮች እርቀት ላይ ትገኛለች።

Feta Daily News

12 Feb, 14:55


ዮርዳኖስ ፍልስጤማውያን ሕጻናትን ለመቀበል መስማማቷ ተሰማ


ዮርዳኖስ በአሜሪካ የቀረበላትን ጥያቄ ተከትሎ በጋዛ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ፍልስጤማውያን ሕጻናትን ለመቀበል መስማማቷ ተገልጿል፡፡

ዮርዳኖስ ፈቃድኝነቷን የገለጸችው የሀገሪቱ መሪ ንጉስ አብዱላህ 2ኛ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት ወቅት ነው፡፡

በዚህ ወቅት ንጉስ አብዱላህ 2ኛ አሜሪካ ያቀረበችውን ጥያቄ ተከትሎ 2 ሺህ በችግር ውስጥ የሚገኙ የጋዛ ህጻናትን ዮርዳኖስ በጊዜያዊነት እንደምትቀበል ተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በበኩላቸው÷ንጉስ አብዱላህ 2ኛ በችግር ላይ የሚገኙ 2 ሺህ የጋዛ ህጻናትን ለመቀበል ያሳዩትን ፈቃደኝነት አድንዋል፡፡

Feta Daily News

12 Feb, 12:27


''ያለፈቃድ ድሮን በሚያስነሱ አካላት እርምጃ እየተወሰደ ነው'' ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት

ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ፈቃድ ሳያገኙ በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ድሮን በሚያስነሱና በሚያበሩ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተገለጸ።

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የድሮንና ሌሎች በራሪ አካላት አጠቃቀምን በተመለከተ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ በአዲስ አበባና አካባቢዋ ማንኛውንም አይነት ድሮን ያለ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ፈቃድ ማስነሳትም ሆነ ማብረር እንደማይቻል በቅርቡ በመገናኛ ብዙኃን የተላለፈውን ማሳሰቢያ በማያከብሩ አካላት ላይ እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል፡፡

Feta Daily News

12 Feb, 10:32


https://youtu.be/tIdMw7OcSt8?si=UnK8JusSCq5y-2yK

Feta Daily News

12 Feb, 08:38


በአሜሪካ ስደተኞች ቤት ውስጥ ለመደበቅ መገደዳቸው ተሰማ


በአሜሪካ የሚገኙ ስደተኞች ዶናልድ ትራምፕ እየወሰዱ ያለውን ርምጃ በመፍራት ከቤት መውጣት አለመቻላቸውን ቢቢሲ ዘግቧል:: የትራምፕ አስተዳደር ወደስልጣን በመጣ ማግስት ከወሰዳቸው ርምጃዎች አንዱ የሕገ ወጥ ስደተኞች ጉዳይ ሲሆን፤ በዚህ ውሳኔም በርካቶች ወደሀገራቸው እየተመለሱ ይገኛሉ::

የአይስ አባላት ሰነድ አልባ ስደተኞችን ከትምህርት ቤት፣ ከሥራ ቦታ፣ ከእምነት ተቋማት፣ ከሆስፒታል እና ከመሰል ሊሸሸጉበት ይችላሉ ብሎ ካመነበት ስፍራ እያሳደደ ይገኛል:: በዚህ ስጋት የተነሳ ሥራ መሄድ እንዳቆሙና እና ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ እንዳልቻሉ ቃላቸውን ለቢቢሲ ከሰጡት ስደተኞች ማወቅ ተችሏል::

Feta Daily News

12 Feb, 07:31


"ከ250 በላይ አሽከርካሪዎች በሥራ ላይ እያሉ ተገድለዋል" ማኀበሩ

በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች የሚፈፀሙ እገታዎች እና ግድያዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ባለመወሰዱ አዳዲስ መስመሮችም የእገታ ተግባራት እየተፈፀመባቸው ነው ሲል ጣና የአሽከርካሪዎች ማህበር ገልጿል፡፡

በቅርቡም በጭልጋ እንዲሁም በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች መተሃራን ጨምሮ የሞቱ አሽከርካሪዎች ቁጥር በርካታ መሆኑን የማህበሩ ዋና ፀሐፊ አቶ ሰጡ ብርሃን ተናግረዋል፡፡

ከአዋሽ መተሃራ የተሸከርካሪዎች መቃጠልና የሚፈፀሙ እገታዎች ተበራክተው መቀጠላቸውን የሚናገሩት የማህበሩ ዋና ፀሐፊ፤ "በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ከዚህ ቀደም በስፋት እገታ ያልነበረባቸው እንደ ደባርቅ እና ከጎንደር መተማ ያሉ መንገዶች ላይ ተመሳሳይ ድርጊቶች እየተፈጸሙ ነው ማለታቸውን አሃዱ በዘገባው አመልክቷል።

Feta Daily News

11 Feb, 14:55


ዴንማርካውያን የአሜሪካዋን ካሊፎርኒያ ለመግዛት ዘመቻ ጀመሩ

ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች እስካሁን ፊርማቸውን ያኖሩበት ዘመቻ ውጤታማ እንዲሆን እያንዳንዱ ዴንማርካዊ 18 ሺህ ዶላር እንዲያዋጣ ተጠይቋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዴንማርክ ግዛት ስር ያለችውን ግሪንላንድ ለመግዛት ያቀረቡት ሃሳብን ተከትሎ ነው ዘመቻው የተጀመረው።

Feta Daily News

11 Feb, 12:39


የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች መቐለ ገቡ

የጀርመን፣ የአሜሪካ፣ የእንግሊዝ፣ የጣሊያን፣ ፣ የዴንማርክ፣ የፈረንሳይ እና የአውሮጳ ሕብረት አምባሳደሮች ቡድን በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ እና በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት አፈፃፀምን በተመለከተ ከክልሉ ባለሥልጣናት ጋር መቐለ ላይ እየመከሩ ነው።

አቶ ጌታቸው ረዳ የፕሪቶርያው የሰላም ውል በምሉእነት እንዲተገበር አምባሳደሮቹ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ መጠየቃቸው ተዘግቧል።

ከዚህ በተጨማሪ፤ በመቐለ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የጀርመን፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጣሊያን፣ የፈረንሳይ እና የአውሮጳ ሕብረት አምባሳደሮች ከህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ጋር ተገናኝተው እንደሚነጋገሩ፤ በኢትዮጵያ፤ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታዉቋል።

Feta Daily News

11 Feb, 10:25


https://youtu.be/QJZSxzFDmEw?si=b3XbUlif3IA52ja3

Feta Daily News

11 Feb, 08:35


እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሳለች ሲል የወቀሰው ሐማስ ለጊዜው ታጋቾችን እንደማይለቅ አስታወቀ

የሐማስ ታጣቂ ክንፍ ቃል አቀባይ ቡድኑ በቅርቡ ሊለቃቸው ያሰባቸውን ታጋቾችን ለጊዜው እንደማይለቅ ተናግረዋል።
በጋዛ የሚገኙ ሶስት ታጋቾች በሚቀጥለው ቅዳሜ ይለቀቃሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

እስራኤል ደግሞ ፍልስጤማዊያን እስረኞችን እንደምትለቅ ይጠበቃል።

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ የሐማስን ድርጊት "የተኩስ አቁም ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ የሚያፈርስ ነው" ብለውታል።

Feta Daily News

11 Feb, 07:31


''መንግሥት ቢከለክለኝም ሀገሬ እገባለሁ” ልደቱ

በአሜሪካ የነበሩት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው "ወደ ሀገሬ እንዳልገባ ተከልክያለሁ" ሲሉ ወደ ኢትዮጵያ መጓዝ እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

አቶ ልደቱ አያሌው ወደ አትላንታ አየር ማረፊያ ያቀኑት ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ነበር። ነገር ግን አየር ማረፊረያ ሲደርሱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቲኬታቸው "እንደታገደ" ተነገራቸው። አቶ ልደቱ ለቢቢሲ በሰጡት አስተያየት መንግሥት ቢከለክለኝም “ሀገሬ እገባለሁ” ብለዋል።

Feta Daily News

10 Feb, 14:41


ፑቲን እና ትራምፕ ጦርነቱን ለማስቆም መከሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲንን ጦርነት ማስቆም በሚቻሉባቸው ጉዳዮች ላይ በስልክ መምከራቸውን ተሰምቷል፡፡

ኒዮርክ ፖስትን ጠቅሶ ኣናዶሉ ኤጀንሲ እንደዘገበው፥ ሁለቱ መሪዎች በምን ጉዳይ ላይ እንደተስማሙ በውል ባይታወቅም ለዓመታት የቆየውን የዩክሬን እና ሩሲያን ጦርነት ያለመ የስልክ ልውውጥ ማድረጋቸውን ገልጿል፡፡

Feta Daily News

10 Feb, 12:31


እስራኤል የጋዛ ሰርጥን ለሁለት በመክፈል የጦር ቀጣና በማለት ከፈረጀችው ኮሪደር ጦሯን አስወጣች

ኔትዛሪም የተሰኘው ኮሪደር ሰሜናዊ ጋዛን ከቀሪው የጋዛ ሰርጥ የለየ እና ያቆራረጠ ኮሪደር ነው።

ጦሩ ከስፍራው መልቀቁን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን በመኪኖች እንዲሁም በጋሪዎች ፍራሻቸውን እና የቤት እቃዎቻቸውን ጭነው እስራኤል ወደ ፍርስራሽነት ወደቀየረችው ሰሜናዊ ጋዛ እየተመለሱ ይገኛሉ።

ጦሩ ከስፍራው የወጣው የጋዛው የመጀመሪያ ምዕራፍ የተኩስ አቁም ስምምነት እሁድ፣ ጥር 11/ 2017 ዓ.ም ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ ነው።

Feta Daily News

10 Feb, 10:40


https://youtu.be/wgF7aahD21Q?si=4eO7sHdCS_9x1BKn

Feta Daily News

10 Feb, 08:32


ከደመወዝ ላይ የፓርቲ መዋጮ እንዳይሰበሰቡ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ በምርጫ ቦርድ ተዘጋጀ

ይኸው አዲስ ረቂቅ አዋጅ የመንግሥት ተቋማት ከሠራተኞቻቸው ደመወዝ ላይ "በቀጥታ" የፓርቲ መዋጮ እየሰበሰቡ እንዳያስገቡ ይከለክላል ነው የተባለው፡፡

"የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ" የተባለው እና ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ ውይይት ሲደረግበት የቆየው ይኸው ረቂቅ አዋጅ በተጨማሪም በሁሉም አካባቢዎች በተመሳሳይ ጊዜ ጠቅላላ ምርጫ ማካሄድ በማይቻልበት ጊዜ ምርጫው "በተለያየ ጊዜ" ሊካሄድ እንደሚችልም ይደነግጋል ተብሏል፡፡

Feta Daily News

10 Feb, 07:32


''ትልቅ የቤት ሥራ አለብን'' የቀድሞዋ ፕሬዚዳንት

በአግራችን በተለያዩ ምክንያቶች ከትምህርት ቤት ውጭ ያሉ በሚልዮን የሚቆጠሩ ልጆች የመማር ዕድል እንዲያገኙ የማድረግ ትልቅ የቤት ሥራ አለብን ሲሉ የቀድሞዋ ፕሬዚዳንት ሳዕለወርቅ ዘውዴ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Feta Daily News

08 Feb, 15:15


ሃማስ ተጨማሪ እስራኤላዊያን ታጋቾችን ለቀቀ

ሃማስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ተከትሎ ታግተው የቆዩ ተጨማሪ ሶስት የእስራኤል ዜጎችን መልቀቁን አስታወቀ፡፡ ታጋቾቹ ወደ ቀይ መስቀል ከመተላለፋቸው በፊት በማዕከላዊ ጋዛ በሚገኘው እና ዴይር አል ባላህ በተሰኘው አካባቢ ለዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ይፋ መደረጋቸው ተገልጿል፡፡

Feta Daily News

08 Feb, 13:05


የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከደህንነት መረጃ ታገዱ

አሜሪካ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉ መሪዎች የሀገሪቱ ደህንነት መረጃዎች እንዲደርሳቸው የሚፈቅድ ህግ አላት።

ጆ ባይደን ወደ ስልጣን ሲመጡ ዶናልድ ትራምፕ የሚታመን ሰው አይደለም በሚል መረጃው እንዳይደርሳቸው አግደዋቸው የነበረ ቢሆንም አሁን በተራቸው ታግደዋል።

Feta Daily News

08 Feb, 10:28


https://youtu.be/MhcPsId1w3g?si=ot7ruqFKwXuEkN_N

Feta Daily News

08 Feb, 08:50


ታከለ ኡማ ይቅርታ ጠየቁ

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሲያነጋግር በቆየው እና ከማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ባነሱት ፎቶ ግራፍ ዙሪያ ይቅርታ ጠይቀዋል። "ለአፈር መዳበሪያ የጭነትና የማውረድ ሂደት ለማስረዳት የተጠቀምነው ፎቶ የቆየ በመሆኑ በተወሰነ መልኩ ግርታን ፈጥሯዋል ።" ያሉት ኢንጂነሩ፣ "ፎቶዎቹ የጭነት ሂደት ለማስረዳት የተጠቀምነው እንጂ የመዳበሪያውን አሁናዊ ሁኔታ የሚገልፅ አለመሆኑንና ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እጠይቃለሁ ብለዋል።

Feta Daily News

08 Feb, 07:33


ትራምፕ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ ጣሉ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት ላይ ማዕቀብ መጣላቸውን ከኋይት ሀውስ የወጣው መረጃ አመላክቷል። የቅርቤ በምላት እስራኤል ላይ እውነትነት የሌለው ረብ የለሽ ተግባር እየፈጸመ ነው ሲሉ በከሰሱት ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ላይ ትራምፕ የማዕቀብ ፊርማቸውን አኑረዋል።

Feta Daily News

07 Feb, 15:11


አስር ሺህ የዩኤስኤአይዲ ሰራተኞች ሊባረሩ እንደሚችሉ ተነገረ

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ከ9 ሺህ በላይ የአሜሪካ አለማቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ሰራተኞችን ለማሰናበት ማቀዱ ተሰምቷል።

ለእቅዱ ቅርበት ያላቸው አራት ምንጮች ነገሩኝ ብሎ ሬውተርስ እንዳስነበበው ድርጅቱ በመላው አለም ካሉት ከ10 ሺህ በላይ ሰራተኞች በስራ ገበታቸው የሚቀጥሉት 294ቱ ብቻ ናቸው።

ከድርጅቱ የአፍሪካ ቢሮዎች ውስጥ በስራቸው የሚቀጥሉት ስምንት ብቻ ናቸው፤ በእስያ ደግሞ ስምንት ይቀራሉ ብለዋል ምንጮቹ።

Feta Daily News

07 Feb, 12:42


በሰው ሰራሽ በተቀነባበረ አስር የቃጠሎ አደጋዎች መድረሳቸው ተሳማ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባለፉት 6 ወራት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የደረሱ 103 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ ምርመራ አጣርቼ አገኘሁ ያለውን ውጤት ይፋ አድርጓል ። በምርመራው በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰቱ 96 እንዲሁም በክልሎች ሰባት የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች መንስኤዎች ይፋ መደረጋቸው ተጠቁሟል፡፡

በዚህ መሰረትም በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር ምክንያት የደረሰ 50 ቃጠሎ፣ በመካኒካል ችግር ምክንያት የደረሰ 11 ቃጠሎ፣ ሆን ተብሎ በሰው አማካኝነት የደረሰ 10 ቃጠሎ፣ በቸልተኝነት የደረሰ 17 እና በሌሎች ምክንያቶች የደረሰ 15 ቃጠሎ መሆናቸው ተገልጿል።

Feta Daily News

07 Feb, 10:38


https://youtu.be/tAd0TsLKN2M?si=a7nO4jd1vvoyex0e

Feta Daily News

07 Feb, 08:39


የሀይማኖት አባቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ የሰላም ጥሪ እና መልእክት አስተላለፉ

በኢትዮጵያ የሲቪል እና የሙያ ማኅበራት ም/ቤት(ኮንግረስ) አዘጋጅነት ልዩ የጸሎት እና የሰላም ጥሪ አገራዊ ጉባኤ የተደረገ ሲሆን በየአቅጣጫው የሚታየው ግጭት እንዲቆም "ሰላም ለሀገራችን፤ ሰላም ለህዝባችን!!" ይሆን ዘንድ የየሃይማኖቱ አባቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ የሰላም ጥሪ እና መልእክት አስተላልፈዋል።

Feta Daily News

07 Feb, 07:34


አዲሱ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር የማያላውስ ነገር ካለ ወደ ግል ሥራዬ እመለሳለሁ አሉ


አዲሱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዋና ኮሚሽነር አቶ ብርሃኑ አዴሎ ሥራቸውን በጫና ምክንያት መፈፀም ካልቻሉ እንደሚለቁ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አቶ ብርሃኑ የቀድሞውን ዋና ኮሚሽነርን ጫማ ለመሙላት "እውቀቱ እና ልምዱ" አለኝ ብለዋል።

1995 ዓ.ም. ገደማ በንቃት ወደ ፖለቲካው ዓለም መግባታቸውን የሚናገሩት አቶ ብርሃኑ በ2007 ዓ.ም. "በፍላጎታቸው" ከፖለቲካ መውጣታቸውን ተናግረዋል።

Feta Daily News

06 Feb, 14:46


የእስራኤል ጦር ፍልስጥኤማዉያን በፈቃደኝነት እንዲለቁ የሚያስችል ዕቅድ እንዲነደፍ አዘዘ

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ ጦራቸዉ ጋዛ የሚኖሩ ፍልስጥኤማዉያን ግዛቲቱን በፈቃደኝነት እንዲለቁ የሚያችል ዕቅድ እንዲነድፍ አዘዘ።

የሚንስትሩ ትዕዛዝ የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጋዛ ሰርጥን ለመቆጣጠር እንደሚፈልጉ ካስታወቁ በኋላ ዓለማቀፍ ተቃዉሞ እየተሰማ ባለበት ወቅት ነው።

የመከላከያ ሚንስትሩ እስራኤል ካትዝ፣ ትራምፕ ከ2 ሚሊዮን በላይ ፍልስጥኤማዉያን የሚኖሩባትን ጋዛን ለመቆጣጠር ማቀዳቸውን አድንቀው «የፕሬዚደንቱን በድፍረት የተሞላ ዕቅድ በደስታ እንቀበላለን ፤ በየትኛውም ዓለም እንደሚሆነው የጋዛ ነዋሪዎች ከመኖሪያቸዉ በነጻነት መውጣት እና መሰደድ ሊፈቀድላቸው ይገባል ብለዋል።

Feta Daily News

06 Feb, 12:36


ተቃዋሚዎች ከስልጣን የተወገዱትን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤት አወደሙ

በባንግላዲሽ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ከስልጣን የተወገዱት የጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሃሲና የቀድሞ ቤተሰብ መኖሪያ ቤትን እና ሌሎች የፓርቲያቸውን አባላትን ቤት አወደሙ።
ብጥብጡ የተቀሰቀሰው ሃሲና ባለፈው አመት በተማሪዎች የተመራ ተቃውሞ ከስልጣን ከተባረሩበት ጊዜ አንስቶ በስደት ላይ ከነበሩበት ህንድ በማህበራዊ ድረ-ገጾች መልዕክት ማስተላለፋቸውን ተከትሎ ነው።

ባንግላዲሽን ለ20 ዓመታት የመሩት የ77 ዓመቷ ሃሲና መንግስታቸው ያለ ርህራሄ በተቃዋሚዎች ላይ ጨካኝ እንደነበረ ይነገራል ፡፡ለሀገሪው ሰውም ቢሆን ፈላጭ ቆራጭ ተደርገው ይታዩ ነበር።

ተቃዋሚዎች ትላንት ዕሮብ ምሽት ላይ፣ የባንግላዲሽ መስራች ፕሬዝዳንት የሆኑትን የሃሲናን አባት ሼክ ሙጂቡር ራህማንን ቤት በኤካቫተር አፈራረሰዋል ።

Feta Daily News

06 Feb, 10:31


https://youtu.be/8XL1dgrHmwo?si=jYDLYrGjFeoPSi5E

Feta Daily News

06 Feb, 08:36


በኤሌክትሮኒክ የነዳጅ ግዥ ስርአት ውስጥ ሁሉም ባንኮች ሊካተቱ መሆኑ ተገለጸ

በነዳጅ ሽያጭ እየተሳተፉ የሚገኙት ቴሌ ብር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አንድ የግል ባንክ ብቻ የነበሩ ሲሆን አሁን ግን መንግስት ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት መሳተፍ እንዲችሉ የወሰነ መሆኑ ታውቋል።

የነዳጅ ገበያውን ለማዘመን እና ህገወጥ አሰራርን ለማስቀረት በማሰብ መንግስት የነዳጅ ሽያጭ በሞባይል የክፍያ ስርአት ብቻ እንዲከናወን ወስኖ እየተተገበረ እንደሚገኝ ይታወሳል።

በዚህም ዘመናዊውን የግዥ መተግበሪያ/አፕ ያበለፀገው ኩባንያ ሌሎች ባንኮችን ለማካተት እየሰራ ሲሆን ባንኮቹ ግን ከመቼ ጀምሮ ወደ ስርአቱ ይገባሉ የሚለው አለመታወቁን ነው የተገለጸው ።

Feta Daily News

06 Feb, 07:41


መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ለኢትዮጵያ ሰላም እንዲጸለይ አወጀች

በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ባሉት ቀጣናዎች፣ ክልሎች እና አጥቢያዎች በሙሉ
የኢትዮጵያን ሰላም አስመልክቶ ከየካቲት 1 ጀምሮ እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በጌታ ፊት ጸሎት እንዲደረግ በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መሪዎች ጉባኤ ተወስኗል::

Feta Daily News

05 Feb, 14:46


የአሜሪካው የስለላ ድርጅት ሲአይኤ ሁሉንም ሰራተኞቹን ሊያሰናብት ነው

ሲአይኤ የስራ መልቀቂያ ለሚያስገቡ ሰራተኞቹ የስምንት ወራት ደመወዝ እከፍላለሁ ብሏል።

ሲአይኤ በአሜሪካ ህግን ተከትለው ከማይፈጸሙ ጥፋቶች ጀርባ እጁ አለበት የሚል ቅሬታ ቀርቦበታል።

Feta Daily News

05 Feb, 13:12


በስዊድን በመሳሪያ ጥቃት አስረ አንድ ሰዎች ተገደሉ

በስዊድን አንድ መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በፈጸመው ጥቃት እራሱን ጨምሮ 11 ሰዎች ተገደሉ። በጥቃቱ 5 ሰዎችም ክፉኛ ቆስለዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በስተምዕራብ በሚገኝ አንድ የወጣቶች ትምህርት ቤት ነው። ትምህርትቤቱ ለወጣት ስደተኞች የቴክኒክና ሙያ እንዲሁም የስዊድሽ ቋንቋ ትምህርቶች የሚሰጥበት ሲሆን የተገደሉትም ስደተኞች ሳይሆኑ እንዳልቀረ ታውቋል።

Feta Daily News

05 Feb, 10:31


https://youtu.be/FVvNukSwb2k?si=GWqzoIjxY9aFyfY4

Feta Daily News

05 Feb, 07:35


ትራምፕ አሜሪካ ጋዛን እንድታስተዳድር ያቀርቡትን ጥያቄ የሙስሊም ሀገራት መሪዎች አወገዙ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትላንትናው ዕለት ከእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ጋር በነበረው ውይይት አሜሪካ የፍልስጤም ግዛት የሆነቸውን ጋዛን እንድታስተዳድር ጠይቋል።

የሳዑዲ ቱርክ ጆርዳንና ግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ይህ ተግባር የፍልስጤምን ልዑላዊነት የሚጥስ በመሆኑ በፍፁም ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ሳዑዲ አረቢያ በይፋ ባወጣችው መግለጫ ፍልስጤማውያን በሀገራቸው ተከብረው እንዲኖሩ ሙሉ ድጋፍ እንደምታደርግ በመግለፅ ትራንፕ የተናገረው ሀሳብ በፅኑ እንደምታወግዝም ገልፃለች።

Feta Daily News

05 Feb, 07:32


የምስራቅ ወለጋ አባገዳዎች የሰላም ጥሪ አቀረቡ

የምሥራቅ ወለጋ ዞን የአባዳዎች ሕብረት ሰብሳቢ አባገዳ ደሳለኝ ፈይሳ ውስብስብ እየሆነ የመጣውን የሰላም እጦት ችግር ለመፍታት ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሸማቂዎችና መንግሥት የሕዝቡን የሰላም ጥያቄ በመቀበል ወደ እርቅ መምጣት እንደለባቸው አመልክተዋል።

ከዚህ ቀደም ተጀመሩ የተባሉ ድርድሮችም በተለያዩ ቦታዎች የተሟላ ሰላም ባለመኖሩ ለተፈጠሩ ለችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ያመጣል ተብሎ እምነት ተጥሎበት እንደነበር በማንሳት አሁንም ለሕዝቡ ሰላም ቅድሚያ በመስጠት ሁለቱም አካላት ድርድር በመቀመጥ ይሄን ችግር መፍታት አለባቸው ሲሉ መናገራቸውን ዶቼቬሌ ዘግቧል።

Feta Daily News

04 Feb, 14:37


ቻይና ለአሜሪካ ርምጃ የመልስ ምት ሰጠች

በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በምርቶቿ ላይ ታሪፍ የተጣለባት ቻይና የአጸፋ እርምጃ መውሰድ መጀመሯን አስታውቃለች።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር በቻይና ምርቶች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የ10 በመቶ ታሪፍ መጣሉን አስታቋል።

ይህንን ተከትሎም ቻይና ከአሜሪካ ወደ ሀገሯ የሚገቡ የኃይል ምርተች ላይ የ15 በመቶ ታሪፍ እንደምትጥል አስታውቃለች።

በተጨማሪም ቻይና በአሜሪካው ጎግል ኩባንያ ላይ በዛሬው እለት ተዓማኒነት ምርመራ እንደምትጀምርም አስታውቃለች።
የቻይና የንግድ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ በአሜሪካ የክሰል ድንጋይ እና ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ላይ የ15 በመቶ ታሪፍ እንደሚጣል አስታውቋል።

Feta Daily News

03 Feb, 12:23


ቢዮንሴ የመጀመሪያዋ ጥቁር ምርጥ የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበም አሸናፊ ሆነች

አሜሪካዊቷ አቀንቃኝ ቢዮንሴ ጂሴል ኖልስ በግራሚ ሽልማት የ21ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዋ ጥቁር ምርጥ የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበም አሸናፊ ሆናለች።

ቢዮንሴ በ67ኛው ግራሚ ሽልማት በምርጥ የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበም ዘርፍ አሸናፊ መሆን ችላለች።

በዚህም ከ1975 በኋላ በክፍለ ዘመኑ የመጀመሪያዋ ጥቁር የዘርፉ አሸናፊ ለመሆን በመብቃት ታሪክ ሰርታለች።

አቀንቃኟ “ካው ቦይ ካርተር“ በሚለው የሃገረሰብ ሙዚቃ አልበሟ ነው አሸናፊ መሆን የቻለችው።

Feta Daily News

03 Feb, 10:31


https://youtu.be/0Ku1tI_TvO4?si=DRkXaoLJVicuc8Hm

Feta Daily News

03 Feb, 08:38


ቻይና በትራምፕ የተጣለውን ታሪፍ አወገዘች


የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከካናዳ እና ከሜክሲኮ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ25% ታሪፍ መጣላቸው ይታወቃል።

የቻይና መንግስት በፕሬዝዳንት ትራምፕ የተጣለውን ታሪፍ በጽኑ ያወገዘ ሲሆን፤ ቤጂንግ ትራምፕ የሚያቀርቡትን ቤጂንግ ወደ አሜሪካ የሚፈሰውን ገዳይ የሆነውን ኦፒዮይድን መግታት ዙሪያ እና እየከፋ የንግድ ግጭት እንዳይፈጠር ለውይይት በሯን ከፍት መሆኑን አስታውቃለች።

 ቻይና ህጋዊ መብቷን እንዲሁም ጥቅሟን ለማስጠበቅ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚኖራትም አሳስባለች።

Feta Daily News

03 Feb, 07:36


በአፋር ክልል በደረሰው የድሮን ጥቃት የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፋን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ

በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አውሲ ረሲ ዞን፤ ኤሊዳር ወረዳ፣ ሲያራ ቀበሌ በጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 8 ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ ፖሊስ ለአሐዱ አስታውቋል።

የአፋር ክልል ፖሊስ የማህበረሰብ አቀፍ ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ዋና ሳጅን ዋሱ ናስር በጥቃቱ የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፋን የገለጹ ሲሆን፤ በተጨማሪም ሌሎች አራት ሰዎች መቁሰላቸውን ተናግረዋል።

የጂቡቲ መከላከያ ሚኒስቴር አካሄድኩት ባለው በዚህ የድሮን ጥቃት ስምንት አሸባሪዎች ገድያለሁ ብሏል። ይህ ጥቃት ሲፈጸም በጂቡቲ ንጹሐን ዜጎች ላይ አላስፈላጊ ጉዳት መድረሱን አምኖ ነገር ግን ጉዳቱ ምን እንደሆነ በዝርዝር አልገለጸም።

በጉዳዩ ዙሪያ በፌደራል መንግሥት በኩል እስከአሁን ምንም የተባለ ነገር የለም።

Feta Daily News

01 Feb, 14:44


የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በቀጣይ በሚያካሔደው የአመራር ምርጫ ሕዝበ ሙስሊሙ በንቃት እንዲሳተፍ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጥሪ አቀረበ

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ይህን ጥሪ ያቀረበው በዛሬው ዕለት ካከናወነው ሦስተኛ ዓመት አንደኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ በኋላ ባወጣው የአቋም መግለጫ ነው።

ዛሬ ቅዳሜ ጥር 24/2017 ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባው በገለልተኛ የባለሙያዎች ቡድን ተዘጋጅቷል ያለውን የምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያና የምርጫ ማስፈፀሚያ መመሪያ ሠነድን መርምሮ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁንም አሳውቋል።

Feta Daily News

01 Feb, 12:33


የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በመንግስት ስር ሆኖ እንደገና ሊደራጅ መሆኑ ተሰማ

ላለፉት አስርት ዓመታት ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ሆኖ ሲሰራ የቆየው ዩኤስኤይድ ነጻ ዓለም አቀፍ የረድኤት ድርጅት ነበር። የአሜሪካ መንግስት ለዩኤስኤይድ በዓመት ከ70 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደሚያደርግ ይታመናል።

Feta Daily News

01 Feb, 10:33


https://youtu.be/NrkXi9dCvvY?si=s2O_JMFqJRJe1wFL

Feta Daily News

01 Feb, 08:41


''እሁድ ጀምሮ በተካሄደው ውጊያ ቢያንስ 700 ሰዎች ተገድለዋል'' ተመድ

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ባለፈው እሁድ ጀምሮ በተካሄደው ውጊያ ቢያንስ 700 ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

ጦርነቱ በምስራቃዊ የአገሪቱ ክፍል በምትገኘው ትልቋ ከተማ ጎማ ተፋፍሟል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች እንደተናገሩት በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም23 አማጺያን የሰሜን ኪቩ ግዛት መዲና የሆነችውን ጎማን ለመቆጣጠር በተደረገው ፍልሚያ ከተገደሉት በተጨማሪ 2 ሺህ 800 ሰዎች ቆስለዋል።

ጎማን የተቆጠጠሩት አማጽያኑ ወደ ደቡባዊ ኪቩ መዲና ቡካቩ እየገሰገሱ መሆኑ ተነግሯል።

Feta Daily News

01 Feb, 07:33


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንትና ፖለቲካ ሲያንቦራጭቁ የነበሩ ሰዎች ለግጭቶች ተጠያቂ ናቸው አሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በትናንትናው የብልፅግና ፓርቲ መክፈቻ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር አባቶቻችን ሀገርኛ ሀሳብ አላፈለቁም። በተዋሱት ሃሳብ ሲጨቃጨቁ፣ ሲጋደሉ የኖሩ ስለሆነ፤ አሁንም ያንን ማስቀጠል ይፈልጋሉ ብለዋል።  

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን አባባላቸውን በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ካሉት ግጭቶች ጋር በማስተሳሰር፤ በኦሮሚያ ግጭት አለ። በአማራ ግጭት አለ። በትግራይ ግጭት አለ። በተለያዩ ቦታዎች ግጭት አለ። የእዚህ ግጭት ጠንሳሽ፣ ጨማቂዎች፤ ትላንትና ፖለቲካ ሲያንቦራጭቁ የነበሩ ሰዎች ናቸው ሲሉ አብይ ተናግረዋል።

Feta Daily News

31 Jan, 15:04


የሰላም ሚኒስትር የነበሩት ብናልፍ አንዱዓለም በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆኑ

ህዳር ወር 2017 ላይ ሹመት የተሰጣቸው አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም በዛሬው ዕለት ቃለመሐላ መፈፀማቸው ተነግሯል።

ይህን ተከትሎ ከፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሹመት ደብዳቤ እና የሥራ መመሪያ መቀበላቸው ለማወቅ ተችሏል።

Feta Daily News

31 Jan, 12:43


ትራምፕ በብሪክስ አባል ሐገራት ሸቀጦች ላይ 100% የግብር ጭማሪ እንደሚያደርጉ አስጠነቀቁ

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የብሪክስ  አባል ሐገራት የአሜሪካዉን ዶላር ትተዉ በሌላ ገንዘብ ለመገበያየት ከወሰኑ ለዩናይትድ ስቴትስ ገበያ በሚያቀርቡት ሸቀጦቻቸዉ ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ ለማድረግ አስጠንቅቀዋል።

ትራምፕ ትሩዝ ሶሻል በተባለዉ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴያቸዉ ባሠራጩት ማስጠንቀቂያ እንዳሉት የብሪክስ አባል ሐገራት ከዶላር ለማፈንገጥ ማሰባቸዉ «ማብቃት  አለበት።

ትራምፕ የብሪክስ አባል መንግሥታትን ለዩናይትድ ስቴትስ «የጠላትነት አዝማሚያ» የሚታይባቸዉ በማለት ወርፈዋቸዋልም።

Feta Daily News

31 Jan, 10:37


https://youtu.be/eiXK1L3aI3w?si=-VLkfHkefkknAJ91

Feta Daily News

31 Jan, 08:37


ኤም 23 ወደ ኪንሻሳ እንደሚገሰግስ አስታወቀ

ትላንት የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ ከተማ ጎማን በአብዛኛው የተቆጣጠሩትና በሩዋንዳ የሚደገፉት የኤም 23 አማጺያን፣ ወደ መዲናዋ ኪንሻሳ ግስጋሴያቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

“የነጻነት ግስጋሴያችንን እንቀጥላለን ነው” ያለው የአማጺያኑ መግለጫ፡፡

የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቺሰኬዲ በበኩላቸው ከበድ ያለ ወታደራዊ ምላሽ እንደሚሰጡ አስታውቀዋል።

Feta Daily News

31 Jan, 07:31


ደማቁ የአገው ፈረሰኞች በዓል በመከበር ላይ ነው

ደማቁ የአገው ፈረሰኞች በዓል በመከበር ላይ ነው።

85ኛ የአገው ፈረሰኞች ክብረ በዓል በእንጅባራ ከተማ መከበር በተለያዩ ስነስርአቶች እየተከበረ ይገኛል።

አሁን በአገው ምድር እንጅባራ ፈረሰኛው ስታዲየም ትርኢት በማሳየት ላይ ናቸው።

እንኳን አደረሳችሁ!!

Feta Daily News

30 Jan, 14:32


የቀድሞው የፓርላማ አባል አቶ ብርሃኑ አዴሎ የኢሰመኮ ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

በቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የስልጣን ዘመን ለስድስት ዓመት ገደማ የካቤኔ ጉዳዮች ኃላፊ ሆነው የሰሩት አቶ ብርሃኑ አዴሎ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን (ኢሰመኮ) እንዲመሩ በፓርላማ ተሾሙ። አቶ ብርሃኑ የብሔራዊው የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት፤ ተቋሙን ለአምስት ዓመታት የመሩትን ዶ/ር ዳንኤል በቀለን በመተካት ነው።

Feta Daily News

30 Jan, 12:32


ቀሲስ በላይ መኮንን በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እና በ10 ሺህ ብር ተቀጡ

ሐሰተኛ ሰነድ ተጠቅመው ከአፍሪካ ሕብረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ገንዘብ ለማውጣት ሞክረዋል በሚል የወንጀል ክስ የተመሠረተባቸው ቀሲስ በላይ በአምስት ዓመት እስራት እና በ10 ሺህ ብር እንዲቀጡ ተወስኗል።

Feta Daily News

30 Jan, 10:36


https://youtu.be/ap8Hv6qlqdE?si=QL-1kO1tzz0lKBjX

Feta Daily News

30 Jan, 08:26


ትራምፕ በመወለድ የሚገኝ የዜግነት መብት እንዲቀር ግፊት እያደረጉ መሆናቸው ተሰማ


ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ “በመወለድ የሚገኝ ዜግነት” በመባል የሚታወቀው የዜግነት መብት’ እንዲቀር ወይም እንዲቋረጥ የሚያደርግ ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ ፈርመዋል፡፡

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1868 የጸደቀው 14ኛው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ አንድ ሰው የወላጆቹ የዜግነት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በአሜሪካ ግዛቶች ውስጥ እስከተወለደ ድረስ የዜግነት መብቱን የሚያረጋግጥ ሲሆን የሲቪል መብቶች ዋና አካል ተደርጎ ይታያል፡፡

የፕሬዝደንት ትረምፕ ትዕዛዝ ታዲያ በአስፈጻሚው አካል ሥልጣን እና በሕገ መንግሥት ማሻሻያው ዙሪያ ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ ክርክሮች ቀስቅሷል።

Feta Daily News

30 Jan, 07:35


የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ተጨማሪ ብድር አጸደቀ

የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ)፣ ኹለተኛውን የኢትዮጵያ የተራዘመ ብድር ግምገማ በማጠናቀቅ ለአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብሩ ትናንት ተጨማሪ 248 ሚሊዮን ዶላር ብድር አጽድቋል።

ድርጅቱ ለኢትዮጵያ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ብድር ባለፈው ሐምሌ ካጸደቀ ወዲህ፣ እስከ ትናንት የለቀቀው ብድር 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።

መንግሥት ለማኅበራዊ ሴፍቲ ኔት መርሃ ግብሮች የሚሠጠው ድጎማ ከተጠበቀው በታች መኾኑን በግምገማ ሪፖርቱ የገለጠው ድርጅቱ፣ ለጉዳት ተጋላጭ ለኾኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሴፍቲ ኔት ድጋፎችን ማጎልበት ያስፈልጋል በማለት መክሯል።

ድርጅቱ፣ የነዳጅ ዋጋ የመንግሥትን ወጪ ሙሉ በሙሉ ሊመልስ በሚችል ደረጃ መስተካከል እንዳለበትም ምክረ ሃሳቡን ለግሷል።

Feta Daily News

18 Jan, 06:52


ለክርስትና እመነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለከተራ በዓል አደረሳችሁ!”


🙏💐ጥር 10 የከተራ በአል ነው እንኳን አደረሳችሁ አደረሳችሁ🙏

✍️ከተራ ማለት "ከተረ" ከምለው ከግዕዝ ግስ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ዙርያውን ከበበ፣ አጠረ፣ ገደበ ማለት ነው።

🥀ከተራ ማለት ከተረ፣ አጠረ፣ ሰበሰበ ማለት ሲሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስተምሮ ይኸውም ወራጁን ውሃ ሰብስቦ ወይም ገድበው በየሰበካው ተለይቶና ተከልሎ ለጥምቀት የመዘጋጃ ዕለት ነው።

Feta Daily News

17 Jan, 14:52


በአፋር ክልል የሴት ልጅ ግርዛት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ

በአፋር ክልል በሴቶች ላይ የሚፈፀመውን የሴት ልጅ ግርዛት ለመከላከል በርካታ ሥራዎች ቢሰሩም፤ በቂ ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን የክልሉ ሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ቢሮን ጠቅሶ አሐዱ ዘግቧል።

ጎጂ ባህላዊ ልማዶች እና ሃይማኖታዊ የሚመስሉ አካሄዶች የችግሩ ዋነኛ መንስኤ እንደሆኑ ነው የተገለጸው።

Feta Daily News

17 Jan, 12:51


እናት ፓርቲ የጣሪያ ግድግዳ ግብር ላይ የመሠረተው ክስ ተቀባይነት ማግኘቱን አስታወቀ

እናት ፓርቲ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣሪያ ግድግዳ (የንብረት ግብር) ብሎ ከከተማዋ ነዋሪ እየሰበበሰበ ባለው ግብር ላይ መስርቶ የነበረው ክስ ተቀባይነት ማግኘቱን ዛሬ ባወጣው መግለጫው አስታውቋል።

ፓርቲው ግብሩ "ሕገ ወጥ" መኾኑን በመግለጽ ክስ መስርቶ ነበር።

ክሱን የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አስተዳደር ችሎት በዛሬ እለት ባስቻለው ችሎት የንብረት ግብር ማሻሻያ ጥናት ተብሎ በሚያዝያ ወር 2015 ዓ/ም የወጣውና ለግብሩ መሰብሰብ መሠረት የሆነው መመሪያ "ተፈጻሚነት ሊኖረው አይገባም" ተብሎ መመሪያው እንዲሻር በሙሉ ድምጽ መወሰኑን እናት ፓርቲ አስታውቋል።

Feta Daily News

17 Jan, 10:35


https://youtu.be/Wf1I4CZoZuE?si=AzQw4DteUdaxye4F

Feta Daily News

17 Jan, 08:36


ታጋቾችን ለማስለቀቅ ከስምምነት መደረሱ ተሰማ

ታጋቾችን ለማስለቀቅ ከሐማስ ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ቢሮ አስታወቀ።

ኔታንያሁ ሐሙስ ዕለት ድምጽ እንደሚሰጥበት ሲጠበቅ የነበረውን የጋዛን የተኩስ አቁም ስምምነት 'ሐማስ በመጨረሻ ሰዓት ሃሳቡን ለመለወጥ እየፈለገ ነው' በማለት ስምምነቱን ለማፅደቅ የሚሰጠውን የምክር ቤት ድምፅ እንዲዘገይ አድርገው ነበር።

ሆኖም አርብ ጥዋት፣ ጥር 9/ 2017 ዓ.ም ተደራዳሪው ቡድን ስምምነት ላይ መደረሱን ለኔታንያሁ እንዳሳወቃቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ገልጿል።

Feta Daily News

17 Jan, 07:32


የጥምቀትን በዓል ያለምንም አደጋ ለማክበር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

የጥምቀት በዓልን ከአደጋ በፀዳ ሁኔታ ለማክበር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል፡፡

ለበዓሉ አከባበር የተለያዩ ዝግጅቶችን የሚያደርጉ ወጣቶች ማስጌጫዎችን ከመስቀላቸው በፊት የኤሌክትሪክ መስመሮችን በጥንቃቄ እንዲመለከቱ እና አስቀድመው ቅኝት እንዲያደርጉ ያሳሰቡት፤ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ናቸው።

ከዚህ ቀደም በነበረው የበዓሉ አከባበር የኤሌክትሪክ መስመሮችን ለበዓሉ ተብለው በሚተከሉ ድንኳኖች ውስጥ የሚያስገቡ ሰዎች እንዳጋጠሙ ያስታወሱት አቶ ንጋቱ፤ ከዚህ በፊት ለታቦታት መሸፈኛ የሚውሉ የብረት ሰረገላዎች ከኤሌትሪክ መስመር ጋር በመገናኘታቸው 4 ወጣቶች ሕይወታቸው ማለፉን አስታውሰው የጥንቃቄ መረጃዎች እንዲወሰዱ አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም ፀበል ለመረጨት ወደ ባህረ ጥምቀቱ የሚያመሩ አካላት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው፣ ነፍሰ-ጡሮች እና የታወቀ ሕመም ያለባቸው፣ አቅመ ደካሞችና ሕጻናት መገፋፋት ያለባቸው ቦታዎች እንዳይገቡ እንዲሁም ሁሉም የበዓሉ ታዳሚዎች የጥንቃቄ መመሪያዎችን እንዲያከብሩም መጠየቃቸውን አሃዱ በዘገባው አመልክቷል።

ለማንኛውም የአደጋ ጥቆማ 939 አጭር መስመር ላይ መደወል እንደሚቻል የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል፡፡

Feta Daily News

16 Jan, 14:43


የተኩስ አቁም ስምምነት በተደረሰባት ጋዛ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት 73 ፍልስጤማውያን መገደላቸው ተገለጸ

እስራኤል እና ሐማስ የደረሱበት የተኩስ አቁም ስምምነት በመጪው እሁድ፣ ጥር 11/ 2017 ዓ.ም ተግባራዊ መሆን ይጀምራል የተባለ ሲሆን እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ያለችው ጥቃት እንደቀጠለች ነው።

ሁለቱ ወገኖች የደረሱበት የተኩስ አቁም ስምምነት ከእስራኤል በኩል የምክር ቤቱን ይሁንታ ማግኘት አለበት ተብሏል።

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ረቡዕ፣ ጥር 9/ 2017 ዓ.ም ይፋ መሆኑን ተከትሎ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት 73 ፍልስጤማውያን በአንድ ምሽት መገደላቸውን በሐማስ የሚተዳደረው የሲቪል መከላከያ ኤጀንሲ አስታውቋል።

Feta Daily News

16 Jan, 12:23


“በወር ከ50 ሺህ በላይ ወጪ እያወጣን ነው” በትግራይ ክልል ያሉ የኩላሊት

በትግራይ ክልል ያሉ የኩላሊት ህመምተኞች ለመድኃኒት በወር ከ 50 ሺህ በላይ ወጪ እያወጣን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ የኩላሊት ሕሙማን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሃፍቶም አባዲ፣ ለአንዴ የኩላሊት እጥበት ለማድረግ መድኃኒት 4ሺ 500 ብር እየገዙ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ወጪያቸው በወር 50 ሺህ ብር እንደሚደረስ አመልክተዋል። በገንዘብ እጥረት ምክንያት የከፋ ችግር ላይ እንደሚገኙ ዋና ስራ አስኪያጁ ከአንድ የሀገር ውስጥ ዘጋቢ ጋር በነበራቸው ቆይታ አብራርተዋል።

Feta Daily News

16 Jan, 10:26


https://youtu.be/JdzMzg4uViY?si=NbIaVClW0xffwRrt

Feta Daily News

16 Jan, 08:43


የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት ግጭት ለመፍጠር የሚጥሩ አካላትን አሳሰበ

የአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፤ በጎዳናዎች ላይ ኃይማኖት በመስበክ ስም ተገቢ ያልሆኑ ተግባራትን በመፈጸም በኃይማኖቶች መካከል "ግጭት ለመፍጠር የሚጥሩ" አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

ምክር ቤቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወንዶቹን ጀለቢያና ሴቶችን ሂጃብ በማስለበስ በቡድን እምነትን የመስበክና በመሰጂዶች አካባቢ "ትንኮሳ" የመፈጸም ድርጊቶች እየተደጋገሙ እንደሆነ ገልጿል።

Feta Daily News

16 Jan, 07:54


እስራኤል እና ሃማስ የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማሙ

እስራኤል እና ሃማስ በጋዛ ሰርጥ ለ15 ወራት ሲያካሂዱት የቆየውን አውዳሚ ጦርነት በማቆም፤ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጣና ላይ ሰላም ለማስፈን መስማማታቸው ተገልጿል።

ስምምነቱ በመጀመሪያው ዙር የ6 ሳምንታት ቅድመ ተኩስ ማቆምን የያዘ ሲሆን፤ ይህም "ጦርነቱን በዘላቂነት ለማቆም እንዲሁም አሜሪካውያን ታጋቾችን ወደ አገራቸው ለማምጣት የሚያስችል ድርድርን ይፈቅዳል" ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስታውቀዋል።

የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ሦስት ደረጃዎች ያሉት ነውም ተብሏል። በዚህም የመጀመሪያው በጋዛ በሃማስ ታጣቂዎች የተያዙ ታጋቾችን እና በእስራኤል ውስጥ የሚገኙ የፍልስጤም እስረኞች እንዲለቀቁ የሚፈቅድ መሆኑ ተገልጿል።

Feta Daily News

15 Jan, 14:51


ከአራት መቶ በላይ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ ሠራተኞች ተባረሩ

የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት "በድልድል እና ምደባ" 400 የሚሆኑ ሠራተኞችን ከጥር ጀምሮ ከሥራ ማሰናበቱን ሠራተኞች እና ድርጅቱ ተናገሩ።

የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት የብቃት ፈተና እና ውድድር ያላለፉ ሠራተኞችን ከሥራ መቀነሱን በመግለፅ የሪፎርም ባሕሪ ነው ሲል ማብራሪያ መስጠቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

Feta Daily News

15 Jan, 12:24


የመሬት መንቀጥቀጡ ስጋት ሆኖ መቀጠሉ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ በፋንታሌ ተራራ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ መጣሉ ተነግሯል፡፡

የፈንታሌ ወረዳ ኮሙኒኬሽን እንዳለው የመሬት መንቀጥቀጡ እስካሁን ምንም አይነት ጉዳት ባያደርስም ነዋሪዎችን ስጋት ውስጥ በማስገባቱ የአካባቢው ነዋሪዎች በአደጋው ስጋት አካባቢውን ለቀው እየሸሹ መሆኑን ገልጿል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጡ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ ሲሆን በዛሬው ምሽትም በፈንታሌ አካባቢ ፍንዳታዎች ተከስተዋል ሲልም ቢሮው አስታውቋል፡፡

Feta Daily News

15 Jan, 10:22


https://youtu.be/pF8eWNhgfj4?si=RZrzKZcRj3pgy914

Feta Daily News

15 Jan, 08:32


ፕሬዝዳንቱ በቁጠጥር ሥር ዋሉ

የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ወታደራዊ አገዛዝን ካወጁ በኋላ አመጽ አነሳስተዋል የተባሉትን ፕሬዚዳንት ዮን ሱክ ዮልን ከጠባቂዎቻቸው ጋር ለሰዓታት ከቆየ አስገራሚ ፍጥጫ በኋላ በቁጥጥር ስር አዋሉ።

በዚህም በስልጣን ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር የዋሉ የመጀመሪያው የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ለመሆን በቅተዋል።

ዮን ወደ ሙስና ምርመራ ቢሮ መወሰዳቸው ታውቋል።

"ምርመራውን ህገወጥ" ሲሉ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ "ያልተፈለገ ደም መፋሰስን ለማስቀረት በሚል" ለምርመራው መስማማታቸውን ገልጸዋል።

Feta Daily News

15 Jan, 07:34


ኮሜዲያንና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ የነበረው አለባቸው ተካ ኅልፈት 20ኛ ዓመቱ ዛሬ እየታሰበ ነው

ኮሜዲያንና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ የነበረው አለባቸው ተካ ኅልፈት 20ኛ ዓመቱ ዛሬ እየታሰበ ነው። አድናቂዎቹ "አለቤ" ሲሉ የሚጠሩት ይህ ተወዳጅ ኮሜዲያን፣ ጥር 7 ቀን 1997 ዓ.ም ነበር ሕይወቱ በመኪና አደጋ ያለፈው።

በ1954 ዓ.ም በወሎ ውርጌሳ የተወለደው አለባቸው ተካ፣ በኢትዮጵያ የኮሜዲ ሥራ እንዲዘምንና እንዲተዋወቅ ካደረጉ አርቲስቶች መካከል ይጠቀሳል። ከባልደረባው ልመንህ ታደሰ ጋር በመሆን በሚያቀርባቸው የኮሜዲ ዝግጅትም ይታወቃል።

Feta Daily News

14 Jan, 14:32


ላሊበላን ለማደስ የሚደረገው ጥናት መቋረጡ ተገለጸ

በዓለም ቅርስ መዝገብ ላይ የሰፈረውን የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የቀድሞ ይዘታውን ሳይለቅ እድሳት ለማድረግ የተጀመረው ጥናት፤ በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት መቋረጡን የላሊበላ ከተማ አስተዳደር ባህል እና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ጠቅሶ አሐዱ ዘግቧል፡፡

Feta Daily News

11 Jan, 14:39


የትግራይ ፓርቲዎች 'ትግራይን የማዳን ቃል-ኪዳን' በሚል ሀሳብ ጥምረት መፍጠራቸውን አስታወቁ

ብሔራዊ ባይቶና አባይ ትግራይ፣ አረና ለዲሞክራሲ ለልዑዓላዊነት እና ውድብ ናፅነት ትግራይ የተሰኙ ሦስት በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች 'ትግራይን የማዳን ቃል-ኪዳን' በሚል ጥምረት መፍጠራቸውን ገልጸዋል፡፡

Feta Daily News

11 Jan, 12:45


ከአርባ በላይ ባቡሮች ውስጥ እየሠሩ ያሉት 16ቱ ብቻ መሆናቸውን ተገለጸ

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት ካሉት 41 ባቡሮች እየሠሩ ያሉት 16ቱ ብቻ እንደሆኑ አስታውቋል፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ብርሀን አበባው ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ወደ ሥራ ሲገባ 41 ባቡሮች የነበሩት ቢሆንም አሁን አገልግሎት እየተሰጡ ያሉት ባቡሮች ቁጥር 16 ብቻ ነው፡፡

ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ባቡሮች አገልግሎት የማይሰጡት በብልሽት ምክንያት መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

Feta Daily News

11 Jan, 10:34


https://youtu.be/60Vv4LW0DXg?si=FJvx0vv2UqqmZA-u

Feta Daily News

11 Jan, 09:33


የመሀሙድ አህመድ ህይወት ታሪክ እና ስራዎችን የያዘው መጽሐፍ ተመረቀ

የክቡር ዶክተር አርቲስት መሀሙድ አህመድ ካሁን ቀደም ያልተሰሙ የህይወቱን ገጽታዎች አካቶ የተሰናዳው መጽሀፉ ትላንት ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም በማሪዮት ሆቴል ለምረቃ በቅቷል።

ለዝግጀት 10 ዓምታትን የወሰደው መጽሐፉ፣ የክቡር ዶክተር አርቲስት መሀሙድ አህመድ ካሁን ቀደም ያልተሰሙ የህይወቱን ገጽታዎችን የያዘ ሆኖ የተሰናዳ ስለመሆኑ ደራሲው ወሰን ደበበ ማንደፍሮ ተናግሯል።

የክቡር ዶክተር አርቲስት መሀሙድ አህመድ ላለፉት 63 ዓመታት በሙዚቃው ዓለም ያሳለፋቸዉን ውጣ ውረዶች፣ የቤተሰብ የኋላ ታሪክና የወዳጅ ጓደኞቹን እንዲሁም የሙያ ባልደረባዎቹን ምስክርነት አካቶ የያዘው የሕይወት ታሪክ መፅሐፍ በጋዜጠኛና ደራሲ ወሰን ደበበ ማንደፍሮ ተዘጋጅቶ በንብ ኢንተርናሽናል ባንከ አማካኝነት ታትሞ ለንባብ ተዘጋጀቶዋል።

Feta Daily News

11 Jan, 08:08


ከአንድ ሺ በላይ ሠራተኞች ያለ ምንም ማስጠንቀቂያ እንዲለቁ መገደዳቸው ተሰማ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮሬ ዞን ኬሌ ከተማ በመንግሥት መስሪያ ቤት ውስጥ ይሰሩ የነበሩ ከ1 ሺሕ በላይ ሠራተኞች፤ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ከመስሪያ ቤታቸው መታገዳቸውን ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

በአካባቢው አዲስ የወረዳ አደረጃጀት መተግበሩን ተከትሎ፤ የተወሰኑት ሠራተኞች ከዚህ በፊት በሚሰሩበት ዞን ውስጥ 27 ኪሎ ሜትር ወደሚርቀው እና አዲስ ወደተዋቀረው ወረዳ እንዲሄዱ መታዘዛቸው ተጠቁሟል፡፡

"በዚህም እንዲዛወሩ ከታዘዙት ጥቂት የመንግሥት ሠራተኞች ውጭ ሌሎቻችን ሥራ አጥ እንድንሆን ተደርገናል" ሲሉ ቅሬታ ማቅረባቸውን አሃዱ ዘግቧል፡፡

Feta Daily News

10 Jan, 14:41


ትራምፕ እና ፑቲን ሊገኛኙ መሆኑ ተሰማ

ትራምፕ እና ፑቲን ለመገናኘት ቆርጠዋል። ትራምፕ ማራላጎ ከተሰኘው የተንጣለለ መኖሪያቸው ሆነው በሰጡት አስተያየት “ፑቲን እንድንገናኝ” ይፈልጋል ብለዋል።

Feta Daily News

10 Jan, 12:08


በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ የእሳት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 10 ደረሰ

በአሜሪካ በሎስ አንጀለስ በተከሰተው ሰደድ እሳት ሳቢያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 10 መድረሱ ተገለፀ። በሎስ አንጀለስ አካባቢ ከ10,000 በላይ ህንፃዎች፣ አብዛኞቹ ቤቶች፣ በእሳት ቃጠሎዉ መዉደማቸዉን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

በፓስፊክ ፓሊሳደስ ተራራማ አካባቢ ከ5,300 የሚበልጡ ሕንጻዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ አልያም ወድመዋል። በሎስ አንጀለስ ለቀናቶች በዘለቀዉ ሰደድ እሳት በከተማዋ ታሪክ እጅግ አውዳሚ እና የከፋ መሆኑን ባለስልጣናት በሚሰጡት መግለጫ እየገለፁ ነዉ።

Feta Daily News

10 Jan, 10:41


https://youtu.be/VMPLBKj8_7E?si=bPvuB_B1u8VQUUGD

Feta Daily News

10 Jan, 08:41


በሰሜን ወሎ የህፃናት እና እናቶች ህይወት አለፈ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ ከፍተኛ ምግብ እጥረት የእናቶች እና የህጻናት ሕይወት ማለፉ በዳሰሳ ጥናት ተረጋግጧል።

ካለፈው ወር ጀምሮ በወረዳው ከፍተኛ የምግብ እጥረት መከሰቱን ሲዘገብ የቆየ ሲሆን፤ ለዕይታ የሚረብሹ ምሥሎችም ይፋ ሆነዋል።

የአካባቢውን የምግብ እጥረት ለማረጋገጥ አጭር ዳሰሳ ያደረገው ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ቀውሱ ከተነገረው በላይ "ከባድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ" ብሏል።

የወረዳውን የምግብ እጥረት እና የጤና ሁኔታን የሚዳስሰው ጥናት ከወሊድ ጋር በተያያዘ ከተመዘገቡ ሞቶች ውጪ አምስት ህፃናት እና ሁለት እናቶች በምግብ እጥረት ሕይወታቸው ማለፉን ይገልጻል።

ሦስት ህፃናት በቆብ ቀበሌ (ክላስተር) ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ ብርቆ እና ቅዱስ ሀርቤ በተባሉ ቀበሌዎች ደግሞ ሁለት የህፃናት ሕይወት አልፏል። በወረዳው ዋና ከተማ አይና ደግሞ ሁለት እናቶች በምግብ እጥረት ሕይወታቸው ማለፉ ነው የተነገረው።

Feta Daily News

10 Jan, 07:41


ትናንት ምሽት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍሎች በሰማይ ላይ የታየው ክስተት

የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ በትናንትናው ዕለት ከምሽቱ 1፡30 ገደማ በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክፍሎች በሰማይ ላይ እየተቀጣጠሉ በከፍተኛ ፍጥነት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቁስ አካላት ስብስብ መታየታቸውን አስታውቋል።

ተቋሙ በታዩት ተንቀሳቃሽ ምስሎች ለመመልከት እንደቻለውም የእነዚህ አካላት ስብስብ የጠፈር ፍርስራሾች አሊያም የሚቲዮር አለቶች እንደሚመስሉ ይፋ አድርጓል።

ስብስቡ ወደ ደቡባዊ የሃገሪቱ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት በሰማይ ላይ ሲምዘገዘግ እንደነበረም ነው የተመላከተው።

የክስተቱን ተፈጥሮ በእርግጠኝነት ለማብራራት ያስችል ዘንድ ሁኔታውን በቅርበት እያጣራ እንደሚገኝ ተቋሙ ገልጿል።

Feta Daily News

09 Jan, 15:12


በርዕደ መሬቱ ከሰላሳ በላይ ትምህርት ቤቶች መጎዳታቸው ተሰማ

በአፋር ክልል ጋቢ ዞን እየተከሰተ ባለው ተከታታይ ርዕደ መሬት በሶስት ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ 37 ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

የቢሮው ሃላፊ አቶ አብዱ ሀሰን ያዮ ለሀገር ውስጥ ዘጋቢዎች በሰጡት ቃል፤ በጉዳቱ ሙሉ በሙሉ የወደሙ እና በከፊል ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡

Feta Daily News

09 Jan, 12:32


በአሜሪካ የተከሰተው እሳት ከባድ ውድመት ማስከተሉ ተሰማ

በአሜሪካ ደቡብ ካሊፎርኒያ ግዛት በምትገኘው ሎስ አንጀለስ የተከሰተው ሰደድ እሳት ከ52 እስከ 57 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ውድመት አድርሷል።

ሰደድ እሳቱ ከፍተኛ ነፋስ የቀላቀለ መሆኑን ተከትሎ አሁንም በፍጥነት እየተዛመተ ነው ተብሏል፡፡

Feta Daily News

09 Jan, 10:37


https://youtu.be/Qa9mZAJnvIE?si=qjaOCngYoL303cdL

Feta Daily News

09 Jan, 08:44


አሜሪካ ጄነራሉ ላይ ማዕቀብ መጣሏ ተሰማ

አሜሪካ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት አዛዥ ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ (ሄሚቲ)ና ቤተሰቦቻቸዉ አሜሪካ እንዳይገቡ አገደች። አሜሪካ ማዕቀቡን የጣለችዉ ሄሚቲ የሚያዙት ጦር ሱዳን ዉስጥ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሟል፣ ሴቶችና ልጃገረዶችን ደፍሯል በሚል ነዉ።

Feta Daily News

09 Jan, 07:35


የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ክስ መሰረተ

የትግራይ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት፣ በአክሱም ከተማ ትምህርት ቤቶች ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ እንዳይለብሱ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ የጣለውን እገዳ ለማስነሳት ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት መውሰዱን ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ችግሩን በመፍታት ረገድ ደብዳቤ ከመጻፍ ያለፈ ውጤታማ ሚና አልተጫወተም ያለው ምክር ቤቱ፣ በሂጃብ ምክንያት የ12ኛ ክፍል ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የመቀመጥ ዕድል ተነፍጓቸዋል በማለት ከሷል።

እገዳው የሙስሊም ተማሪዎችን መብት ብቻ ሳይኾን፣ ባጠቃላይ የሴቶችን ሰብዓዊ መብት የጣስ ድርጊት ነው በማለትም ምክር ቤቱ እገዳውን በድጋሚ አውግዞታል። የትምህርት ቢሮው ችግሩን በጥቂት ቀናት ውስጥ ካልፈታ፣ ቀጣይ ሕጋዊ ርምጃዎችን እንደሚወስድ ምክር ቤቱ ባለፈው ሳምንት አስጠንቅቆ ነበር።

Feta Daily News

08 Jan, 14:31


በአሜሪካ በሰደድ እሳት አስቸኳይ አዋጅ ታወጀ

የእሳት ሰደድ በከፍተኛ ሁኔታ የተዛመተባት የአሜሪካዋ ግዛት ሎስአንጀለስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀች።
እሳት ሰደዱ ከ10 ሄክታር ተነስቶ በሰዓታት ውስጥ ወደ 2 ሺህ 900 ሄክታር መዛመቱን ተከትሎ ነው ይሄ እርምጃ የተወሰደው።

የሰደዱ አደጋ የተጋረጠባቸው 30 ሺህ የሚሆኑ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ እንደተላለፈላቸው እና 13 ሺህ ህንጻዎች አደጋ ላይ መሆናቸውን የግዛቲቱ የእሳት አደጋ ኃላፊ ክርስቲን ክራውሌይ አስታውቀዋል።

በፓስፊክ ፓሊሴድስ አካባቢ ያሉ መኖሪያ ቤቶች በእሳት ተያይዘው እንዲሁም ነዋሪዎች መኪኖቻቸውን ትተው ሲሸሹ የሚያሳዪ ቪዲዮዎች ወጥተዋል።

Feta Daily News

08 Jan, 12:38


ሀሉት አርሶ አደሮች ተገደሉ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን በከሬዳ እና ጀሎ ቀበሌ፤ “ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ተሻግረው የመጡ ታጣቂዎች” ትናንት ታህሳስ 29/ 2017 ዓ/ም እና ከትላንት በስቲያ በፈጸሙት ጥቃት ሀሉት አርሶ አደሮች መገደላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች ጠቅሶ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።

“ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ” ተሻግረው በመጡ ታጣቂዎቹ በተፈጸመ ጥቃት አንታዮ ዞላና እና አድማሱ አሰፋ የተባሉ እርሶ አደሮች ተገድለዋል።

Feta Daily News

08 Jan, 10:29


https://youtu.be/s4i2ib7kckA?si=VPcDFXBYAQkxFWIb

Feta Daily News

08 Jan, 08:36


ለሊቱን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ በኢትዮጵያ አዋሽ አፋር አካባቢ በሬክተር መለኪያ 5.3 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መመዝገቡን አስታውቋል። የመሬት መንቀጥቀጡ ዛሬ ለሊት 9:53 ላይ በ10 ኪ.ሜ ጥልቀት ተከስቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡ ትክክለኛ መጠን እና ጥልቀት በሚቀጥሉት ጥቂት ሰዓታት ወይም ደቂቃዎች ውስጥ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመራማሪዎች መረጃውን ሲገመግሙ እና ስሌቶቻቸውን ሲያጠሩ ወይም ሌሎች ኤጀንሲዎች ሪፖርታቸውን ሲያወጡ ሊከለስ ይችላል።

Feta Daily News

08 Jan, 07:46


የአንድ ሊትር የቤንዚን ዋጋ 100 ብርን ተሻገረ

መንግስት በፔትሮሊየም ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ያደረገውን ማስተካከያ ተከትሎ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንድ ሊትር የነዳጅ ዋጋ ከ100 ብር በላይ ሆኗል።

ከትላንት ታህሳስ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ጭማሪ ቤንዚን በሊትር 101 ብር ከ47 ሳንቲም መድረሱ የተገለጸ ሲሆን የ11 ነጥብ 5 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።

እንዲሁም የናፍጣና ኬሮሲን ዋጋ በሊትር የ10 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።

Feta Daily News

04 Jan, 14:34


"ኑ በዓለ ልደትን በቅዱስ ላልይበላ እናክብር፤ የበረከቱ ተከፋይም እንሁን" ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል እና የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላልይበላ ገዳም የበላይ ጠባቂ የልደት በዓልን አስመልከቶ መልዕክት አሥተላልፈዋል።

ብፁዕነታቸው በመልዕክታቸውም "በመላው ዓለም የምትገኙ የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ" ሲሉ ገልጸው በደብራችን በቅዱስ ላልይበላ ቤተክርስቲያናችን መንፈሳውያን ልጆቿ ሲመጡ እግር በማጠብ ትቀበላለች ለዚህም እናንተን ለመቀበል ሁሉንም ሃይማኖታዊ ዝግጅት አከናውነናል ብለዋል።


ዘገባው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው፡፡

Feta Daily News

04 Jan, 12:24


በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች

ከቤት ውጭ ከሆኑ

በተለያየ ምክንያት ከቤት ውጭ ከሆኑ ከዛፎች፣ ከሕንጻዎች፣ ከኤሌክትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መሆን ይመከራል፡፡
በቤት ውስጥ ከሆኑ
የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት በቤት ውስጥ ያለ ሰው በበር መቃኖች፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ እንዲሁም ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች ፣ ከመስኮት አካባቢ መራቅ እና የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

ትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ


የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ያለ ሰው ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ ይመከራል።

መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ

በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት መኪና የሚያሽከረክር ሰው የኤሌክትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎች፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌክትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም እና መሰል የጥንቃቄ መንገዶችን መከተል እንደሚገባ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው መረጃ መክሯል።

Feta Daily News

04 Jan, 10:31


https://youtu.be/c58V_BAFZ-M?si=XI0pDUimeysVmoms

Feta Daily News

04 Jan, 08:29


የመቐለ ከንቲባ ሥራ መጀመራቸው ተሰማ

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተሾሙት ከንቲባ አቶ ብርሃነ ገብረየሱስ በጊዜያዊነት ወደ ቢሯቸው መግባታቸውን በሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የክልሉ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ጠቅሶ አሐዱ ዘግቧል፡፡

በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት በዋነኝነት በሚቆጣጠረው የመቐለ ከተማ ምክር ቤት፤ ዶክተር ረዳኢ በርሃ የመቀሌ ከተማ ከንቲባ ሆነው እንዲሰሩ ባለፈው ጥቅምት ወር አጽድቆ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ቅርጫፍ ጽህፈት ቤቱ በዚህ አንድ ወራት ግዜ ውስጥ ሕዝቡ የት መሄድ እንዳለበት ጭምር ግራ ከመጋባት በተጨማሪ አገልግሎት ለማግኘት መቸገሩንም የገለጹት የተቋሙ ኃላፊ አቶ ፀሐዬ አምባዬ ፤ በአሁን ሰዓት ግን ችግሩ ተፈቶ በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሾሙት ከንቲባ አቶ ብርሃነ ገብረየሱስ ወደ ቢሯቸዉ መግባታቸውን ተናግረዋል።

Feta Daily News

04 Jan, 07:52


ለሊቱን በሬክተር ስኬል 5.8 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ


ርዕደ መሬቱ ከለሊቱ 9:52 መድረሱን የአሜሪካ የጂኦሎጂካል ሰርቬይ መስሪያ ቤት አስታወቀ ሲሆን ሰሞኑን ሲከሰቱ ከነበሩት የመሬት መንቀጥቀጦች ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየውና ንዝረቱ አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የተሰም ሆኗል ።

Feta Daily News

03 Jan, 15:03


የጋዛ ህዝብ ቁጥር በ6 በመቶ ቀንሷል ተባለ

የጋዛ የህዝብ ቁጥር የቀነሰው የእስራኤል ሃማስ ጦርትን ተከትሎ ነው። የፍሊስጤም ስታተስቲክስ ቢሮ ከጦርቱ ወዲህ የጋዛ ህዝብ ቁጥር 160 ሺህ ገደማ ቅናሽ አሳይቷል ብሏል።

Feta Daily News

03 Jan, 12:26


የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎ የፈነዳው እስተ ጎመራ

ሰሞኑን የመሬት መንቀጥቀጥ ሲስተዋልባቸው ከነበሩት አካባቢዎች አንዱ በሆነው ዱለቻ ወረዳ ዶፋን ተራራ ላይ ዛሬ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ተከስቷል፡፡

Feta Daily News

03 Jan, 10:36


https://youtu.be/HgsfSka5J8w?si=9fSaNXXmK8lvYgeo

Feta Daily News

03 Jan, 08:36


በአሜሪካ አውሮፕላን ተጋጨ

በአሜሪካ፣ ካሊፎርኒያ ግዛት አንድ አነስተኛ አውሮፕላን ከንግድ ህንጻ ጋር ተጋጭቶ የሁለት ሰዎች ህይወት መቀጠፉን እና 18 ሰዎች መጎዳታቸውን ባለስልጣናቱ አስታወቁ።

Feta Daily News

03 Jan, 07:32


የትራፊክ ቅጣትን የሚያዘምን አሰራር ሥራ ሊጀምር ነው

የትራፊክ ቅጣትንና የፓርኪንግ ክፍያን የሚያዘመን እና መሰረታዊ የሆኑ ግብዓቶች የተሟሉት መተግበሪያ በልጽጎ ወደ ሥራ መግባቱን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል።

"ለአገልግሎቱ የሚውል የሰርቨር እና ታብሌቶች ግዢ ተፈጽሟል፣ መተግበሪያም በልጽጓል" ያለው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፤ ከኢንፍራ ቴክ ሶፍትዌር አበልጻጊ ድርጅት ጋር በመተባበር የተሰራውን መተግበሪያ ከቴሌብር እና ከባንኮች ጋር የማስተሳሰር ሥራው ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁን ገልጿል።

Feta Daily News

02 Jan, 14:58


የትራምፕ ሆቴል ፊት ለፊት በፈነዳ መኪና የሰው ህይወት አለፈ

የቴስላ ሳይበርትራክ መኪና ከመፈንዳቱ በፊት በነዳጅ እና በርችት የተሞላ ነበር ተብሏል። በፍንዳታው የአንድ ሰው ህይወት ሲያልፍ 7 ሰዎች ቆስለዋል።

በላስ ቬጋስ ትራምፕ ሆቴል መግቢያ በር በቴስላ ሳይበር መኪና ላይ የተከሰተው ፍንዳታ የሽብር ተግባር ሊሆን እንደሚችል የዓለም ቁጥር አንድ ቱጃሩ ታዋቂው ባለሃብት ኤሎን መስክ ገለጸ፡፡
ትናንት በፈረንጆቹ አዲስ አመት የመጀመሪያ ቀን የተመራጩ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ንብረት በሆነው ላስ ቬጋስ ትራምፕ ሆቴል መግቢያ በተከሰተ ፍንዳታ አንድ ሰው ሲሞት ሰባት ሰዎች ተጎድተዋል።

ይህንን ተከትሎ የቴስላ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኤሎን መስክ አደጋው በኒው ኦርሊያንስ የመኪና አደጋ እና በኒው ዮርክ ከተከሰው የጅምላ ተኩስ ጥቃትጋር የተያያዘ የሽብር ተግባር ሊሆን እንደሚችል ኤክስ ላይ ባሰፈረው መልእክት አስታውቋል።

Feta Daily News

02 Jan, 13:14


የመሬት መንቀጥቀጡ ዜጎችን እያፈናቀለ መሆኑ ተሰማ

በአዋሽ ፈንታሌ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ አጎራባች ስፍራዎች እየሸሹ መሆኑ ተገለጸ።

ካለፈው ወርሃ መስከረምና ጥቅምት ጀምሮ፤ እንዲሁም ከሰሞኑ በተደጋጋሚ እየከሰተ የሚገኘውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ፤ በአፋር ክልል አዋሽ ፈንታሌ አካባቢ የሚገኙ ዜጎች አካባቢያቸውን ለቀው ወደ አጎራባች ስፍራዎች እየሸሹ መሆኑ ተነግሯል።

በአካባቢው አስፓልት መንገዶችን ጨምሮ የተሰነጠቁ መሬቶች ከዕለት ወደ ዕለት እየሰፉ መምጣታቸው ነዋሪዎቹን ስጋት ውስጥ እንዳስገባቸው ተገልጿል።

በዚህም ስጋት የገባቸው ነዋሪዎቹ ቀያቸውን ለቀው ወደ አጎራባች ስፍራዎች መሸሽ መጀመራቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ።

Feta Daily News

02 Jan, 10:26


https://youtu.be/S_wHtwOlYXM?si=nSAGS8WVkES_VIiH

Feta Daily News

02 Jan, 08:35


በአዲስአበባ አደጋዎችን የመከላከል መስፈርት ያሟሉ ተቋማት ውስን መሆናቸው ተጠቆመ

በአዲስ አበባ ከሚገኙ 20 ሺህ ተቋማት መካከል አደጋዎችን የመከላከል መስፈርት ያሟሉት 42 ብቻ እንደሆኑ የአዲስ አበባ እሳት አደጋ እና ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ይከፈለው ወልደመስቀል ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ አብዛኞቹ ሆቴሎች፣ ፋብሪካዎች፣ ሕንጻዎች፣ የነዳጅ ማደያዎች፣ የገበያ ማዕከላት፣ መጋዘኖችና ሌሎችም ተቋማት የአደጋ ደኅንነት መስፈርትን የሚያሟሉ አይደሉም።

Feta Daily News

02 Jan, 07:35


የኔትዎርክ መቆራረጥ አሳሳቢ መሆኑ ተገለጸ


ኢትዮ ቴሌኮም በትናንትናው ዕለት ከሕዝብ ለተሰበሰቡ ጥያቄዎች በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመገኘት ምላሽ ሰጥቷል።

በዚህም የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ለቀረቡ ጥያቄዎች በምክር ቤቱ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፤ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ጨምሮ ሊሰሩ የታሰቡ የማስፋፋያ ሥራዎች በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።

የዋና ሥራ አስፈጻሚዋን ማብራሪያ ተከትሎም ከምክር ቤቱ አባላት በርካታ ጥያቄዎች ተነስተውላቸዋል።

ከጥያቄዎቹ መካከልም፤ አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች የኔትዎርክ መቆራረጥ እንዲሁም የኔትዎርክ ተደራሽነት የሌለባቸው ቀበሌዎች መኖራቸው ይገኝበታል።

Feta Daily News

01 Jan, 14:33


የዓለም ክብረወሰኖች የሰበረው የአረብ ኢምሬትሷ ራስ አል ካይማህ ደማቅ የአዲስ አመት አቀባበል

የኢምሬትሷ ራስ አል ካይማህ ለተከታታይ 6ኛ ዓመት ክብረወሰን የሰበረ የድሮንና ርችት ትርዒት አቅርባለች። የአል ካይማህን ሰማይ ያደመቀው ትዕይንትን በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችና ጎብኚዎች ተመልክተዋል።

Feta Daily News

01 Jan, 12:31


በመቐለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

በክልሉ ርዕሰ መዲና በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ መንግስትን ለማፍረስ የሚደረገው እንቅስቃሴ ይቁም’’፣ ‘ከፓርቲ በፊት መንግስት ይቀድማል’’ እና መሰል መፈክሮች ታይተዋል።

Feta Daily News

01 Jan, 10:32


https://youtu.be/pxutW5LvuGA?si=JIK06-gjgLgdjYL5

Feta Daily News

01 Jan, 08:31


ሩሲያ በዩክሬን በኩል ለአውሮፓ ሀገራት ነዳጅ መላክ ማቆሟን አስታወቀች

የሩሲያው ጋዝፕሮም እና የዩክሬኑ ናፍቶጋዝ የተፈራረሙት የአምስት አመት ስምምነት በመጠናቀቁ ነው ሞስኮ በዩክሬን በኩል ነዳጅ መላክ ያቋረጠችው።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜለንስኪ ሩሲያ "በእኛ ደም ቢሊየኖችን እንድታገኝ አንፈቅድም" በማለት ስምምነቱ እንደማይታደስ መናገራቸው ይታወሳል።

Feta Daily News

01 Jan, 07:43


በሲዳማ ክልል በደረሰው አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

በሲዳማ ክልል በምሥራቃዊ ሲዳማ ዞን በቦና ዙሪያ ወረዳ በገላና ወንዝ ድልድይ በደረሰው አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ወገኖች የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ትናንት በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው የተሰማቸውን ጥልቅ ኃዘን ገልፀዋል።

በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰብና ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል። የክልሉ መንግሥት ለሟቾቹ ቤተሰቦች አራት ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፤ ሁላችንም ለሟቾቹ ቤተሰቦች ድጋፋችንን አጠናክረን ልንቀጥልና ልናጽናናቸው ይገባልም ብለዋል።

Feta Daily News

31 Dec, 14:54


ቦርዱ ህወሓት በቀረው አጭር ጊዜ ውስጥ የጠቅላላ ጉባኤውን እንዲያደርግ በጥብቅ አሳሰበ

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በልዩ ሁኔታ ከተመዘገበበት ከነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ የሚገባው ወቅት ሊገባደድ ከሁለት ወር ያነሰ ጊዜ የቀረው በመሆኑ፤ በቀረው አጭር ጊዜ ውስጥ የጠቅላላ ጉባኤውን እንዲያደርግ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳስቧል፡፡

ህወሓት በኢትዮጵያ የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነምግባር አዋጅን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 1332/2016 መሠረት በልዩ ሁኔታ መመዝገቡ ይታወቃል።

ቦርዱ ለፓርቲው በታሕሳስ 17 ቀን 2017 በጻፈው ደብዳቤ፤ በአዋጅ ቁጥር 1332/2016 አንቀጽ 3 መሠረት በልዩ ሁኔታ የተመዘገበ ፓርቲ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ባሉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ የፓርቲውን ጠቅላላ ጉባኤ እንዲያደርግ እንደሚያዝ አስታውሷል።

Feta Daily News

31 Dec, 12:35


የአሜሪካ ግምጃ ቤት በቻይና የመረጃ መንታፊዎች መበርበሩን ገለጸ


በቤጂንግ የሚደገፍ የመረጃ ጠላፊ በታህሳስ ወር መጀመሪያ የሰራተኞች ኮምፒውተሮችና ሚስጢራዊ መረጃዎችን መመልከቱን ነው የአሜሪካ ባለስልጣናት የተናገሩት።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ "ትልቅ ክስተት" ነው ያለው ጥቃት ያስከተለውን ጉዳት ከአሜሪካ የወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) እና ሌሎች የደህንነት ተቋማት ጋር በመሆን እየመረመረ ነው።

Feta Daily News

31 Dec, 10:29


https://youtu.be/JEJN-Ns0YWA?si=tP1Q0EnJ-1K8wUOK

Feta Daily News

31 Dec, 08:29


አስገዳጅ የሚሊሻ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተሰማ

በኦሮምያ ክልል ሰንዳፋ ከተማ የባጃጅ ሹፌሮች እና የፈረስ ጋሪ አስጋሪዎች በአስገዳጅ ሁኔታ የሚሊሻ ስለጠና እንዲወስዱ በመደረጉ የባጃጅ እና የፈረስ ጋሪ እንቅስቃሴ መገደቡ ተገለጸ፤ የከተማዋ ነዋሪዎች በትራንስፖረት እጥረት ችግር ላይ መውደቃቸውን አስታውቀዋል።

በግዳጅ እንዲወስዱ እየተደረገ ያለው የሚሊሻ ስልጠናው የተጀመረው ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን እና እስከ ጥር ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚቀጥል ለአዲስ ስታንዳርድ የገለጹልን የከተማዋ ነዋሪ በስልጠናው ሳቢያ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ተኩል እስከ 3 ሰዓት ተኩል ትራንስፖርት እንዲገደብ ማድረጉን አስታውቀዋል።

Feta Daily News

31 Dec, 07:46


ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከ13 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች መመዝገቡ ተሰማ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከ13 በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች መመዝገባቸውን የአሜሪካ ጂኦሎጂካ ሰርቬይ መረጃ ያመለክል።

የመሬት መንቀጥቀጦቹ በሬትከተር ስኬል ከ4.4 እስከ 4.8 ማግኒትዩት መካከል መመዝገባቸውንም ነው ከማእከሉ ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው።

በአዋሽ እና መትሃራ አካባዎች ከትናንት ቀን ጅምሮ እስከ ሌሊት ድረስ ከ4.5 እስከ 4.7 ማግኒትዩት መካከል የተመዘገቡ ከስምንት በላይ የመሬት መንቀጥቀጦች መከሰታቸውን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ መረጃ ያመለክታል።

Feta Daily News

30 Dec, 14:52


አዲሱ የሶሪያ መሪና የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደማስቆ ውስጥ ተነጋገሩ

በይፋ ያልተሾመው አዲሱ የሶሪያ መሪ አህመድ አል ሻራ በዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪ ሲይቢሃ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ተቀብሎ ማነጋገሩን ሮይተርስ የሶሪያ ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ዘግቧል።

ኪቭ የበሽር አላሳድ አስተዳደርን ካስወገደው ቡድን ጋር ግንኙነቷን ለማጠናከር ጥረት እያደረገች ነው ተብሏል።

ስለንግግራቸው ዝርዝር ጉዳይ በሶሪያ በኩል የተገለጸ ነገር ለየም። የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሀገራቸው የሩሲያ አጋር ተደርጋ ስትታይ ለነበረችው ሶሪያ የመጨረሻውን ዙር እርዳታ ባለፈው አርብ እለት መላኳን ገልጸዋል። 

Feta Daily News

30 Dec, 12:28


በቀይ ባሕር ዳርቻ ጉብኝት ላይ የነበረ ግለሰብ በሻርክ ተገደለ

በግብፅ የቀይ ባሕር ዳርቻ አንድ ጎብኚ በሻርክ ጥቃት ሲገደል አንድ ሌላ ግለሰብ ጉዳት እንደደረሰበት የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

የሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር የተፈጥሮ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው እሑድ ዕለት አንድ ሻርክ ጎብኚዎች ላይ ሞት እና ጉዳት ያደረሰው ማርሳ አላም ተብላ በምትታወቀው ሥፍራ ነው።

ማርሳ አላም በውሀ ጠላቂዎች የምትወደድ የምስራቅ ግብፅ የባሕር ዳርቻ ከተማ ናት። የተፈጥሮ ሚኒስቴሩ አክሎ ጥቃቱ የተከሰተው "ሰዎች እንዲዋኙ ከተፈቀደላቸው ክልል ውጭ ጥልቁ ባሕር አካባቢ ነው" ብሏል።

ሚኒስቴሩ ሁለት ጎብኚዎች ሞት እና ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሎ ነገር ግን የጎብኚዎች ዜግነት ከመናገር ተቆጥቧል።

Feta Daily News

30 Dec, 10:27


https://youtu.be/sTvVNi3qImM?si=mV73yJ7fnJJgN6bu

Feta Daily News

30 Dec, 08:33


በትግራይ ክልል የምርመራ ዘገባ ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ከሰዓታት እስር በኃላ ተፈቱ

የትግራይ ክልል መንግስት ንብረት የሆነው ቴሌቭዥን ጣቢያ ጋዜጠኞች ቡድን አባላት ፣ ለእስር በተዳረጉበት ወቅት በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በሚገኝ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ላይ የምርመራ ዘገባ እየሰሩ እንደነበር ታውቋል።

Feta Daily News

30 Dec, 07:32


የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እንዲሁም በአወዛጋቢው የኢትዮጵያ ምርጫ 97 ወቅት የምርጫ ታዛቢ የነበሩት ጂሚ ካርተር በ100 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

Feta Daily News

29 Dec, 20:48


አሳዛኝ ዜና

ዛሬ በሲዳማ ክልል በቦና ዙሪያ ወረዳ በጋላና ወንዝ ድልድይ ላይ በደረሰው አደጋ 71 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ::


አደጋ የተከሰተው አንድ አይሱዙ መኪና 71 የሠርግ አጃቢዎች አሳፍሮ ወደ ዳዬ በንሳ መሥመር እየተጓዘ እያለ በጋላና ድልድይ ተምዘግዝጎ ወደ ወንዙ በመግባቱ እንደሆነ የዓይን እማኞች ገልፀዋል። በጋላና ድልድይ ተመሳሳይ የትራፊክ አደጋ ሲደርስ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን ይህ እጅግ የከፋ አደጋ ነው ብለዋል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል እንደሚችል ምንጮች ገልፀዋል።

Feta Daily News

27 Dec, 14:28


እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት ትራንስፖርት እንዲኖር ተወሰነ!

በአዲስ አበባ እስከ ምሽቱ አራት ሰዓት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ ተወሰነ።

የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ ውሳኔውን ማስተላለፉን ያስታወቀው የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ፤ አውቶቡሶች፣ ሚዲ ባስ እና ሚኒ ባሶች እስከ ምሽት አራት ሰዓት ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ አሳስቧል።

ተሽከርካሪዎች በመደበኛነት አገልግሎት በሚሰጡበት መስመርና በሚከፈለው ህጋዊ ታሪፍ አማካኝነት አገልግሎት እንዲሰጡም ቢሮው ጠይቋል።

የትራንስፖርት ቁጥጥር ሰራተኞችም የውሳኔውን ተግባራዊነት እንዲቆጣጠሩ ጥሪ ተላልፏል።

Feta Daily News

07 Dec, 14:22


የቡርኪናፋሶ ጁንታ የሀገሪቱን ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሊኒየር ጆቺም ኬለም ደ ታምቤላ ከስልጣናቸው አነሳ

የቡርኪናፋሶ ጁንታ የሀገሪቱን ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር አፖሊኒየር ጆቺም ኬለም ደ ታምቤላ ከስልጣናቸው አነሳ።
የኢብራሂም ትራወሬ ጽህፈት ቤት በመስከረም ወር 2022 የተሾሙት ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተባረሩበትን ምክንያት አልጠቀሰም።

ወታደራዊ ጁንታው የሀገሪቱን መንግስት መበተኑንም ነው ትናንት ባወጣው ድንጋጌ ያመላከተው። መንግስት ቢፈርስም ሚኒስትሮች አዲስ ካቢኔ እስኪሾም ድረስ በስራቸው ላይ ይቆያሉም ብሏል።

Feta Daily News

07 Dec, 12:27


የቲክቶክ ይግባኝ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ከአሜሪካ ሊታገድ ነው

ቲክቶክ ከ 2025 መጀመሪያ ጀምሮ በአሜሪካ ውስጥ እንዲታገድ አልያም እንዲሸጥ የሚለውን ሕግ እንዲቀለበስ ያቀረበው የይግባኝ አቤቱታ ውድቅ ተደረገ።

የማህበራዊ ሚዲያው ኩባንያው ለፌደራል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሕጉ ኢ ሕገመንግሥታዊ ነው፤ ምክንያቱም በ170 ሚሊዮን አሜሪካውያን ተጠቃሚዎቼ የመናገር ነፃነት ላይ የተጣለ "አስደንጋጭ" ተጽእኖ ነው በሚል ያቀረበው መከራከርያ ተቀባይነት ያገኛል ሲል ተስፋ አድርጎ ነበር ።

ነገር ግን ፍርድ ቤቱ "በኮንግረሱ እና በተከታታይ ፕሬዚዳንቶች የተደረገው ሰፊ የሁለትዮሽ እርምጃ መጨረሻ ነው" ያለውን ሕግ አጽንቷል።
ቲክ ቶክ ጉዳዩን አሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እወስዳለሁ ብሏል።

Feta Daily News

07 Dec, 08:37


የደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ይቅርታ ጠየቁ

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ወታደራዊ ህግ ያወጁት የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮል ለተግባራቸው ይቅርታ ጠየቁ። ፕሬዝዳንቱ አክለውም ሌላ እንደዚህ ዓይነት ድንጋጌ እንደማይኖር ቃል ገብተዋል።

Feta Daily News

07 Dec, 07:31


በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 700 የሚጠጉ የማዕድን አልሚዎች መኖራቸው ተገለጸ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ 700 የሚሆኑ የማዕድን አልሚዎች በሥራ ላይ እንደሚገኙ የክልሉ የማዕድን ሀብት ልማት ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ደርበው ዘንቶ ጠቅሶ አሐዱ ዘግቧል፡፡

ከእነዚህም ውስጥ በድንጋይ ከሰል ዘርፍ 450 ተቋማት ተሰማርተው በክልሉ በሥራ ላይ እንደሚገኙ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡

ቀሪዎቹ 250 ተቋማት ደግሞ በእምነበረድ ዘርፍ ፈቃድ ወስደው እየሰሩ መሆኑን የገለጹት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተሩ፤ 10 ግራናይት አምራች ተቋማትም በክልሉ መኖራቸን ተናግረዋል፡፡

Feta Daily News

06 Dec, 14:50


በዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ የጉንፋን ምልክቶች ባሉት አዲስ በሽታ ምክንያት በርካቶች ህይወታቸው አለፈ

በዲሞክራቲክ ኮንጎ ሪፐብሊክ የጉንፋን ምልክቶች ባሉት አዲስ በሽታ ምክንያት ቢያንስ 79 ሰዎች መሞታቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። የማዕከላዊ አፍሪካዊቷ ሀገር የጤና ሚኒስቴር እንዳለው ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 18 ያሉ ታዳጊዎች መሆናቸው ተገልጿል።

ትኩሳት፣ የራስ ምታት፣ ሳል፣ ለመተንፈስ መቸገር፣ ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ እና የደም ማነስ የበሽታው ምልክቶች ሲሆኑ፣ እስካሁን ከ300 በላይ ሰዎች እነዚህን ምልክቶች ማሳየታቸው ታውቋል። የሕክምና ባለሙያዎች በሽታው በስፋት ታይቶበታል ወደ ተባለው ክዋንጎ ግዛት አምርተው የበሽታውን ባህሪ እና ህመምተኞችን እየመረመሩ ይገኛሉ።

Feta Daily News

06 Dec, 12:38


የትግራይ ክልል ስደት አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ ተሰማ

ባለፉት ሶስት ወራት በህገወጥ መንገድ ለስደት ከተዳረጉ ከስድስት ሺ በላት ወጣቶች ውስጥ 294 የሚሆኑት ህይወታቸው ማለፉን የትግራይ ክልል የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።

ህገወጥ ስደት የበርካታ የክልሉን ወጣቶች ህይወት እየቀጠፈ ነው፣ የወጣቶች ህገወጥ ስደት የሁሉም ሰው አጀንዳ መሆን አለበት ሲሉ የቢሮው ሃላፊ አቶ ሓይሽ ስባጋድስ አሳስበዋል።

ይህ የተገለጸው የወጣቶች ህይወት በመቅጠፍ ላይ ያለውን ህገወጥ ስደት በጋራ መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር በመቐለ ከተማ ትላንት ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም በተዘጋጀው በመድረክ ላይ ነው።

Feta Daily News

06 Dec, 10:31


https://youtu.be/ZFVlf5JotFU?si=u8_GyVuJ_oSDh3VK

Feta Daily News

06 Dec, 08:35


ቻይና የአሜሪካ ወታደራዊ ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ ጣለች

ቻይና በ13 የአሜሪካ ወታደራዊ ቁሳቁስ አምራች ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ ጣለች። የቤጂንግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ቻይና ማዕቀቡን ለመጣል የወሰነችው አሜሪካ ለታይዋን የመሳርያ ቁሳቁሶች ሽያጭ መፍቀዷን ተከትሎ ነው።

በግዢው አሜሪካ ለታይዋን የ385 ሚሊየን ዶላር የኤፍ-15 ጀቶች መለዋወጫ እና ራዳሮች መፍቀዷን ቻይና በጽኑ ተቃውማለች። የሀገሪቱን ሉዓለዊነት ዝቅ የሚያደርግ ተግባርም ነው ብላለች።

Feta Daily News

06 Dec, 07:35


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህወሃት አመራሮች ጋር መከሩ

በትግራይ ክልል ያለውን አጠቃላይ የፓለቲካ የአስተዳደር እና የፀጥታ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ በክልሉ ያሉ የፓለቲካ እና የፀጥታ አመራሮች ከፌደራል መንግስት አመራሮች ጋር በትናንትናው ዕለት ሰፊ ውይይት ማድረጋቸው ተሰምቷል

በውይይቱም ላይ በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን እንዴት በጋራ መፍታት እንደሚገባ ምክክር ተደርጓል። በተደረገው ምክክርና ውይይት በተለያዩ አንኳር ጉዳዮች ላይ በተቀመጡ የጋራ አቅጣጫዎች መሠረት በጋራ ለመስራት እና የክልሉ ህዝብ የፀጥታ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ፍላጎት ለማሟላት አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር መግባባት ላይ ተደርሷል።

Feta Daily News

05 Dec, 14:31


ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ 97.6 በመቶ መጠናቀቁ ተገለጸ

ታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ 97.6 በመቶ መጠናቀቁን የፕሮጀክቱ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ለጣቢያች በላከው መግለጫ፣ በበጀት ዓመቱ አራት ወራት ውስጥ ለግድቡ ግንባታ ከ311 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን አስታውቋል።

የኮርቻ ግድቡ በ2010 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በአራት ተከታታይ ዙር ዓመታዊ ውኃ መያዝ መጀመሩን የገለፀው ጽ/ቤቱ፤ ሁለቱን ግድቦች የሚያገናኘው የድልድይ ስራ ሙሉ በሙሉ እየተጠናቀቀ ይገኛል ብሏል፡፡

የግድቡ የማስተንፈሻ በሮቹም እንዲሁ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸው ተመላክቷል፡፡ የዋናው ግድብ የሲቪል ስራዎች አፈፃፀም 99.6 በመቶ በላይ የተጠናቀቀ መሆኑን በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራዎች 87 በመቶ መድረሱም ተገልጿል፡፡

Feta Daily News

05 Dec, 11:57


አቶ ታዬ ደንደዓ ከእስር ተፈቱ

ትናንት አመሻሹን ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተለቀው ቤተሰቦቻቸውን ሳይቀላቀሉ ከማረሚያ ቤቱ በራፍ በጸጥታ ኃይሎች የተወሰዱት የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንደዓ፤ ዛሬ እኩለ ቀን ደግሞ ሜክሲኮ ከሚገኘው የወንጅል ምርመራ ማዕከል ተለቀው ቤታቸው መድረሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ ወ/ሮ ስንታየሁ እንዳሉት ጠዋት ቤተሰብ ሜክሲኮ ምግብ አድርሶላቸው ከተመለሰና ደህንነታው ከጤቀ በኋላ ዛሬ እኩለ ቀን ምሳ ሰዓት ከማቆያው እንዲወጡ ተወስኖ ሰባት ሰዓት ግድም መኖራቸው ቤት መድረሳቸውንም አክለው አብራርተዋል፡፡

Feta Daily News

05 Dec, 10:33


https://youtu.be/hIVjGbEhPfQ?si=K1EVxbQtvdLxYkMP

Feta Daily News

05 Dec, 08:46


የኤችአይቪ/ኤድስ መድሃኒት ስኬታማ በሆነ መንገድ መሞከሩ ተሰማ

ሌናካፓቪር፤ የተባለ አዲስ የኤችአይቪ/ኤድስ መድሃኒት ስኬታማ በሆነ መንገድ መሞከሩን ተመራማሪዎች ይፋ አድርገዋል። ጊሊድ በተባለ የአሜሪካ የመድሃኒት አምራች ኩባንያ የተሰራው ይህ መድሃኒት በመርፌ መልክ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚሰጥ ሲሆን፤100 ፐርሰንት ውጤታማ ነው ተብሏል።

Feta Daily News

05 Dec, 07:42


ቴሌግራም የተጠቃሚዎችን ደኅንነት በተመለከተ የአቋም ለውጥ ማድረጉ ተሰማ

ተጠቃሚያቸው እያደገ ከሚገኙት የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መተግበሪያዎች መካከል አንዱ የሆነው ቴሌግራም ሲወቀስበት የነበረውን የተጠቃሚዎች ደኅንነት ጥበቃን በተመለከተ የአቋም ለውጥ ማድረጉ ተገልጿል።

በዚህም ቴሌግራም ከዓለም አቀፍ ተቋም ጋር በመተባበር የሕጻናት የወሲብ ብዝበዛ ይዘቶች በገጹ ላይ እንዳይዘዋወሩ ለመገደብ መስማማቱ ቢቢሲ ዘግቧል።

ቴሌግራም ለሕጻናት ጥበቃ የሚያደርግ አሠራርን እንዲከተል ለዓመታት ጫና ሲደረግበት ቢቆይም፣ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ነበር።

ቴሌግራም አብሮት ለመሥራት የተስማማው ‘ዘ ኢንተርኔት ዋች ፋውንዴሽን’ ወይም አይደብሊውኤፍ ተቋም የበይነ መረብ አገልግሎት ሰጪዎች ለሕጻናት ጥበቃ የሚገለገሉበት ነው።

Feta Daily News

04 Dec, 14:33


አትሌቱ ተፈረደበት❗️

የሌላ አካል ይዞታን በሀሰተኛ ሰነድ በ700 ሚሊየን ብር ለመሸጥ በመደራደር የተከሰሰው አትሌት ድሪባ መርጋ በ3 ዓመት ከ4 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ወስኗል።

Feta Daily News

04 Dec, 12:33


እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ ወታደራዊ ሰፈሮችን እየገነባች መሆኑ ተሰማ

እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ ወታደራዊ ሰፈሮችን እየገነባች መሆኑንና ይህም በፍልስጤም ግዛት ውስጥ ያላትን ይዞታ ለማጠናከር የምታደርገዉን ጥረት እንደሚያሳይ ሪፖርቱ አስታዉቋል፡፡

ኒው ዮርክ ታይምስ የሳተላይት ምስሎችን እና የቪዲዮ ትንታኔዎችን መሰረት በማድረግ እንደዘገበው፤ የእስራኤል ሃይሎች በቅርብ ወራት ውስጥ ከ600 በላይ ህንፃዎችን በማፍረስ ቀጠና ፈጥረዋል ብሏል።

ኮሪደሩ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማዊያን ተፈናቃዮች ወደ ሰሜን ጋዛ እንዳይመለሱ ለማድረግ ጥቅም ላይ እንደዋለ ተገልጿል።

Feta Daily News

04 Dec, 10:50


https://youtu.be/870X3r5Df8M?si=Lfh2fTzkOd9KDIXA

Feta Daily News

04 Dec, 08:48


በኢትዮጵያ ከአስር ሴቶች መካከል አንዷ አካላዊ ጥቃት ይደርስባታል ሲል የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ

ኢትዮጵያ ውስጥ ከአስር ሴቶች መካከል አንዷ አካላዊ ጥቃት እንደሚደርስባት የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ አስታውቋል።

የፆታ ተኮር ጥቃት አድራሾች በብዛት የተጠቂዎች የቅርብ ሰዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም የትዳር አጋሮች በቀዳሚነት የጥቃቱ አድራሽ ሆነው ይታያሉ ብሏል።

የፆታ ጥቃት አካላዊ ብቻ አለመሆኑም ያመላከተም ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ውስጥ 13 ነጥብ 3 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ስነ-ልቦናዊ ጥቃቶች ደርሶባቸዋል ብሏል።

"ይህም ስድብ፣ ማስፈራራት እና አምባገነናዊ ተቆጣጣሪነትን ይጨምራል" ያለው ህብረቱ፤ በሰሃራ ዙሪያ ባሉ የአፍሪካ አካባቢዎች ደግሞ ወደ 29 ነጥብ 9 በመቶ ከፍ እንደሚል አስታውቋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ ከአስር ሴቶች አንዷ አካላዊ ጥቃት እንደሚደርስባት ያስታወቀ ሲሆን፤ በመላው አፍሪካ ደግሞ ቁጥሩ ወደ አንድ ሦስተኛ የቀረበ መሆኑን ገልጿል።

Feta Daily News

04 Dec, 07:45


የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ክስ እንዲመሰረትባቸው ተጠየቀ

የደቡብ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ ዮኤል ወታደራዊ የአስተዳደር ስርአት ህግን (ማርሻል ሎው) በማወጃቸው የተፈጠረውን ትርምስ ተከትሎ የሀገሪቱ ዜጎቸች ፕሬዘዳንቱ በወንጀል እንዲከሰሱ አየጠየቁ ነው።

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዝዳንት ትላንት ማምሻውን በየቴሌቭዥን በተላለፈ ንግግራቸው በዲሞክራሲያዊት ሀገር ውስጥ ወታደራዊ አስተዳደር ህግ ያወጁ ሲሆን እርምጃው ያስፈለገው ሀገሪቱን ከሰሜን ኮሪያ አካላት እና "ፀረ-መንግስት ሃይሎች" ለመጠበቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ይህንን ተከትሎ በሀገሪቱ ህጉን የሚቃወሙ በርካታ ዜጎች ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

Feta Daily News

03 Dec, 14:45


''ራሳችንን መከላከያችንን ተነጥቀናል'' የወለጋ ነዋሪዎች❗️

“ከፈጠሪ በታች ራሳችንን እንከላከልበት ዘንድ የታጠቅነውን መሣሪያ ከበባ አድርገው ገፈውናል፤ አኹን ለእርድ ተዘጋጅተን በመጠበቅ ላይ ነን ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

በኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ አንዶዴ ዲቾ፣ ደጋ ጂጊ ቀበሌዎች ትናንት ኅዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም መከላከያ ሠራዊት ነን ያሉ ኃይሎች ንጋት አሥራ አንድ ሰዓት እስከ ጠዋት ሦስት ሰዓት አዘናግተው ከበባ በማድረግ ራሳችንን እንጠብቅበታለን ብለን ከብቶቻችንን ሸጠን በመንግሥት እውቅና የገዛነውን መሣሪያ ገፈውናል ያሉት ነዋሪዎች አኹን ራሳችንን ለእርድ አዘጋጅቶ እንደመጠበቅ ነው የምንቆጥረው ማለታቸውን እናት ፓርቲ በይፋዊ የትስስር ገጹ ባጋራው መልዕክቱ አመልክቷል።

Feta Daily News

03 Dec, 12:31


በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ በተፈጸሙ የአየር ጥቃቶች ቢያንስ 25 ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

የሩስያ እና የአሳድ መንግሥት ተዋጊ ጄቶች በሰሜን ሶሪያ በአማፂያኑ ቁጥጥር ሥር በምትገኘው ኢድሊብ ከተማ በፈጸሙት ጥቃት 25 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል፡፡

ከዚህ በፊት የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ አማፂ ቡድኑን ለመደምሰስ ሃሳብ እንዳላቸው ሲገልጹ እንደነበር ተነግሯል፡፡

Feta Daily News

03 Dec, 10:26


https://youtu.be/XJUTJo5wAmM?si=UPcGnwO8WGnbRTju

Feta Daily News

03 Dec, 08:48


መንግስት የእግድ ውሳኔው እንዲቀለብስ ተጠየቀ❗️

በሲቪክ ድርጅቶቹ ላይ መንግስት ያስተላለፈውን የእግድ ውሳኔ እንዲያጤነው በመቅረብ ላይ ያሉ የአለም አቀፍ ተቋማት ጥሪዎች እንደቀጠሉ ነው፤ ሂዩማን ራይት ዎች ትላንት ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መንግስት ሶስት የሲቪክ ድርጅቶችን ማገዱን አስታውቆ የለምንም ቅድመ ሁኔታ ውሳኔውን ሊቀለብስ ይገባል ሲል አሳስቧል።

Feta Daily News

03 Dec, 08:00


አስር ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አደጉ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮችና የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና መካከል፤ 10ሩ ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ማደጋቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ፓርኮቹ ያሉበትን ደረጃ በመገምገም ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንነት ለማደግ 10ሩ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላታቸው፤ ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንነት እንዲያድጉ መወሰኑን ለኮርፖሬሽኑ በላከው ይፋዊ ደብዳቤ ገልጿል።

Feta Daily News

02 Dec, 14:32


አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሾሙ

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር የነበሩት አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል።

የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት አቶ ብናልፍ አንዱዓለም ከሕዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው መሾማቸውን አስታውቋል ሲል የኢዜአ ዘገባ አመላክቷል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

Feta Daily News

02 Dec, 12:32


ኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኛ ወድቆ ያገኘውን 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለባለቤቱ አስረከበ

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሴኪዩሪቲ ክፍል ባልደረባችን የሆኑት ፍሬዘር በቀለ ህዳር 16/2017 ከመንገደኛ ወድቆ ያገኙትን 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለባለቤቱ አስረክበዋል።

በአየር መንገዱ ሲቀጠሩ በገቡት ቃል መሰረት ተቋሙ የሚመራበትን መርህና ሥነ ምገባር እንዲሁም ሙያዊ ታማኝነታቸውን በብቃት በመወጣት ማስረከባቸውን የአየር መንገዱ መረጃ አመላክቷል።

Feta Daily News

02 Dec, 10:24


https://youtu.be/5q_Vb4WsS98?si=PMzOGgzbvZ622Qe5

Feta Daily News

02 Dec, 08:30


ታምራት ቶላ እና ሲምቦ አለማየሁ የአመቱ ምርጥ አትሌቶች ሽልማት አሸነፉ

አትሌት ታምራት ቶላ ከስታዲየም ውጪ በተደረገ የሩጫ ውድድር የዓመቱ ምርጥ አትሌት ሽልማትን አሸንፏል። አትሌት ሲምቦ አለማየሁ የዓመቱ ተስፋ የተጣለባት አትሌት ሽልማትን አሸንፋለች።

Feta Daily News

02 Dec, 07:24


የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ከጃል ሰኚ ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ሽመልስ አብዲሳ እና የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር የነበሩት ጃል ሰኚ ነጋሳ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ።

ጃል ሰኚ ነጋሳ መንግሥት ያቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል ነው ከአቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር የሰላም ስምምነቱን የፈረሙት፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት÷ የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ለመጡት ምስጋና አቅርበዋል።

Feta Daily News

30 Nov, 14:59


እስካሁን 140 የሚደርሱ ምዕመናን በግፍ ተገድለዋል ❗️

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሽርካ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ኦነግ ሸኔ በሚል መጠሪያ በሚታወቁ ታጣቂዎች 11 የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን ተገድለዋል፡፡

ከግድያው በእግዚአብሔር ፈቃድ ማምለጣቸውን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን የገለጹት መረጃ ሰጭው የ13 ዓመት አዳጊና የ80 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ 11 ሰዎች ከመኖሪያ አካባቢያቸው ተወስደው በጥምቀተ ባሕር ማክበሪያው ላይ መገደላቸውንና 6 ምእመናን ደግሞ ያሉበት አለመታወቁን ተናግረዋል፡፡

እየተገደሉ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን አርሰው የሚያድሩና ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎና ግንዛቤ የሌላቸው መሆናቸውን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪ የመንግሥት የጸጥታ አካላት የሞቱትን ከመቅበር ባለፈ የተሻለ መፍትሔ አላመጡልነም ሲሉ ገልጸዋል፡፡



ዘገባው የማኀበረ ቅዱሳን ቲቪ ነው

Feta Daily News

30 Nov, 12:25


ሰሜን ኮሪያ ሩሲያን መደገፍ እቀጥላለሁ አለች

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በዩክሬን ጦርነት ያለማቋረጥ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ቃል ገቡ፡፡ባለፈው ወር ሰሜን ኮሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ወደ ሩሲያ ከላከች በኋላ በሁለቱ ሀገራት ትብብር መጠናከር ላይ አለም አቀፍ ስጋት እየጨመረ ባለበት ወቅት በመከላከያ ሚኒስትር አንድሬ ቤሎሶቭ የሚመራ የሩሲያ ወታደራዊ ልዑክ በትላንትናው እለት ሰሜን ኮሪያ ገብቷል።
ኪም እና ቤሎሶቭ ስልታዊ አጋርነትን ለማሳደግ ፣ ሉዓላዊነት ፣የደህንነት ፍላጎቶችን እና ዓለም አቀፍ ፍትህን በመጠበቅ ላይ የጋራ መግባባት መድረሳቸውን የሰሜን ኮርያ ቴሌቪዥን ኬሲኤንኤ ዘግቧል፡፡

Feta Daily News

27 Nov, 12:15


በኮሬ ዞን በእሥር ላይ የነበሩ 66 መምህራን ተፈቱ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ በእሥር ላይ የነበሩ 66 መምህራን መፈታታቸውን የክልሉ መምህራን ማኅበርን ጠቅሶ ዶቼቬሌ ዘግቧል። የማኅበሩ ፕሬዝዳንት አማኑኤል ጳውሎስ ለዘገባው እንደገለጹት፦ መምህራኑ ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ ታስረው የነበረው «አለ አግባብ የተቆረጠብን ደሞዝ ይመለስልን» የሚል ጥያቄ በማንሳታቸው ነበር ።

Feta Daily News

27 Nov, 10:26


https://youtu.be/wpXu3S_IrYk?si=3AHrhsqXOlMAzU1m

Feta Daily News

27 Nov, 08:31


የእስራኤል እና ሄዝቦላህ የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ መደረግ ጀመረ

እስራኤል እና የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ትናንት ሕዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ባደረጉት የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት፤ ዛሬ ስምምነቱ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ተገልጿል፡፡

ለ13 ወራት የዘለቀውን ውጊያ ለመቋጨት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደረስ የእስራኤል የጸጥታ ካቢኔ ትናንት ባደረገው ምክክር ወስኗል፡፡

ይህንን ግጭት ለማቆም ስምምነት ላይ መደረሱን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ያረጋገጡ ሲሆን፤ የተኩስ አቁሙ ግጭትን በዘላቂነት ወደማቆም ስምምነት ለመምራት ያለመ መሆኑን መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ነገር ግን በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ በስምምነቱ ላይ የሰጠው መግለጫ የለም።

Feta Daily News

27 Nov, 07:58


የአቶ ታዬ ደንደአን ተጨማሪ የመከላከያ ምስክር ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

የቀድሞ የሰላም ሚኒስቴር ደ’ኤታ አቶ ታዬ ደንደአ መከላከያ ምስክሮች የመጥሪያ ትዕዛዝ ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው፣ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሕገ-መንግስትና ሕገ-መንግሥት ሥርዓት ችሎት፣ የተከሳሹን ቀሪ የመከላከያ ምስክሮችን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።

“የሰላም ሚኒስቴር ደ’ኤታ ኾነው ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ኀይሎች ጋራ በመተሳሰር ለጥፋት ተልእኮ በኅቡእ ተንቀሳቅሰዋል፤” በሚል ክስ የተመሠረተባቸው አቶ ታዬ ደንዳአ ቀሪ ምስክሮቻቸውን እንዲያቀርቡ መጥሪያ ለመጻፍ፣ ለትናንት ኅዳር 17፣ 2017 ዓ.ም. ቀጠሮ ተሰጥቶ የነበረ ሲኾን፣ ፍርድ ቤቱ ለምስክሮቹ መጥሪያ እንዲጻፍ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

Feta Daily News

26 Nov, 14:29


ከሶማሊያ ፌደራል መንግስት ጋር ውጥረት ውስጥ የገባችው ጁባላንድ አህመድ ማዶቤን ፕሬዝዳንት አድርጋ መረጠች


ውጤቱን የጁባላንድ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ ያደረገ ሲሆን
አህመድ መሀመድ እስላም (ማዶቤ)ሌሎች ሁለት እጩዎች በተሳተፉበት ምርጫ የጁባላንድ ፓርላማ አባላት ከሰጡት 75 ድምጽ 55 ድምጽ በማግኘት የጁባላንድን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሰኞ እለት በማግኝት አሸንፏል።

ከፕሬዚዳንት አህመድ ማዶቤ ጋር የተወዳደሩት ሁለቱ እጩዎች ፈይሰል አብዲ ማታን እና አቡበከር አብዲ ሀሰን ሽንፈታቸውን ተቀብለው ለሚቀጥሉት አምስት አመታት የጁባላንድ ግዛት ተመራጩ ፕሬዝዳንት የመልካም ምኞት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የሶማሊያ ፌድራል መንግስት የምርጫውን ሂደት ውድቅ አድርጎታል። ማዶቤ የሶማሌ ፌዴራል መንግስት አለመረጋጋትን በማቀነባበር እና የክልል አስተዳደርን እያናጋ ነው ሲሉ ተችተዋል። ጁባላንድ የሶማሊያ አካል እንጂ የኬንያ ወይም የኢትዮጵያ አካል አለመሆኑን አስረግጠው ተናግሯል።

አካሄድ እያስታወሰን ነው። ሀሰን ሼክን እላለሁ፣ ለውይይት ዝግጁ ነን እኔ ኬንያዊ አይደለሁም እኔ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም፣ ሶማሌ ነኝ” ሲሉ የሃሰን ሼክ መንግስት የሰላም ጥሪ አድርገዋል።

ማዶቤ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ጁባላንድን ለማተራመስ እና በአካባቢው የእርስ በርስ ጦርነት ለመቀስቀስ የወሰዱትን ወታደራዊ እርምጃ አውግዘዋል። የፌደራል መንግስት አልሸባብን ለመዋጋት የሚደረገውን ጥረት ለማደናቀፍ እየሞከረ ነው ሲሉም ከሰዋል።

Feta Daily News

26 Nov, 12:08


የፖሊስ አዛዥ በወርቅ ሥርቆት ተጠርጥረው ተያዙ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጌዴኦ ዞን ሦስት ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ በመሥረቅ የተጠረጠሩ የወረዳ ፖሊስ አዛዥ ታሠሩ ፡፡ በዞኑ የጮርሶ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ በቁጥጥር ሥር የዋሉት በኮትሮባንድ ሲዘዋወር ከተያዘው ሰባት ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ መካከል ሦስቱን ወደ ቤታቸው ይዘው በመሄዳቸው ነው ተብሏል ፡፡ አዛዡ ወርቁን ወደ ቤታቸው መውሰዳቸው ሊታወቅ የቻለው ወርቁን ሲያዘዋውሩ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሰዎች የተያዘብን ወርቅ ይሄ ብቻ አይደለም በሚል የሰጡትን ጥቆማ መሠረት በማድረግ በተካሄደ ምርመራ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዣ ኮማንደር ግርማ በየነ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል፡፡

Feta Daily News

26 Nov, 10:32


https://youtu.be/RxqLjEhi9Mc?si=BihkvqDDGQpAVuCO

Feta Daily News

26 Nov, 08:37


''በደል ተደጋግሟል'' ኦፌኮ

በኦሮሚያ ክልል ሰላሌ ዞን በደራ ወረዳ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለዉን ግድያና ማፈቀናል ተቃውሞ መግለጫ ያወጣው የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ)፤ “በታሪኩ ለመብቱና ነፃነቱ በእምቢ ባይነታቸዉ የሚታወቁ ታጋዮችን በአፈራዉ የሰላሌ ኦሮሞ ሕዝብ” ላይ በደል ተደጋግሟል  ነው ያለው፡፡ አከባቢው ላይ ተፈጸመ ያለውን በደል በስፍራው የሚንቀሳቀሱ አማጺያን እና መንግስት ማረጋገጣቸውን ያነሳው ኦፌኮ በአከባቢ በስፋት የሚከሰተውን ሰብዓዊ ቀውስ በተመለከተ ግን አንደኛው አካል በሌላኛው ወገን ላይ ያላክካል ሲል ተችቷል፡፡

Feta Daily News

26 Nov, 07:32


ኢራን በእስራኤል መሪዎች ላይ የሞት ቅጣት እንዲወሰን ጠየቀች

በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ እና በግብረአበሮቸው ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣት ብቻ ሳይሆን፤ የሞት ቅጣት እንዲወሰን ሲሉ የኢራን ጠቅላይ የሃይማኖት መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ጠይቀዋል።

አለም ዓቀፉ ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ባለፈነው ሳምንት ሐሙስ ዕለት በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚኒን ኔታንያሁ እንዲሁም፤ በቀድሞው መከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት የእስር ማዘዣ ማውጣቱ ይታወሳል።

Feta Daily News

25 Nov, 15:01


መስከረም አበራ ተፈረደባት❗️

ኢትዮ ንቃት” የተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ መሥራች እና ባለቤት መስከረም አበራ ከሦስት ሳምንት በፊት ጥፋተኛ በተባለችበት የኮምፒውተር ወንጀል ክስ የአንድ ዓመት ከአራት ወር እስራት ተፈረደባት።

የቅጣት ውሳኔው በፍርድ ቤት ሲገለጽ መስከረም አበራ ችሎት አለመገኘቷን ጠበቃዋ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በመስከረም አበራ ላይ የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀሎች ችሎት ነው።

Feta Daily News

25 Nov, 12:52


ፒያሳ የእሳት አደጋ ተከሰተ❗️

በተለምዶ ፒያሳ ደጃች ውቤ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ነው የእሳት አደጋው የተከሰተው።

የእሳት አደጋው የተከሰተበት ስፍራ ላይ ቻይኖች ሲሚንቶ እና ኮንክሪት የሚያዘጋጁበት ስፍራ ነው። በስፍራው ሲሚንቶና ኮንክሪት ለማዘጋጀት የሚጠቅሙ ኬሜካሎች እንዳሉ ነው የተነገረው።

እንደዚሁም ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅም በዚሁ ስፍራ እንዳለ ነው የተነገረው።

ለተለያዩ አገልግሎት የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎችም አደጋው በደረሰበት ቦታ መኖሩን ተመልክተናል።

እሳቱን ለማጥፋት የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታው ደርሰው እርብርብ እያደረጉ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ፖሊስም ባካባቢው ደርሶ ጥበቃ እያደረገ ነው የሚገኘው።

Feta Daily News

25 Nov, 10:32


https://youtu.be/qC1m2uXnCyc?si=wQS6cuX1i1FVqvXR

Feta Daily News

25 Nov, 08:32


የኤች አይቪ ስርጭት ከፍተኛ ስጋት መሆኑ ተገለጸ❗️

የጤና ሚኒስቴር በወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፕ፣ ተፈናቃዮች በሚኖሩበት አካባቢ እንዲሁም ለሱስ ተጋላጭ የሆኑ ግለሰቦች በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ላይ የኤች አይቪ ቫይረስ ስርጭት ከፍተኛ ስጋት ሆኗል ሲል ገልጿል፡፡

እነዚህ አካባቢዎች እና ግለሰቦች ለበሽታው ስርጭት ክፎኛ ተጋላጭ ስለሚሆኑ፤ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራበት መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ አንዳንድ ክልሎች የሚታዩ ግጭቶች፤ ለዜጎች የኤች አይቪ ምርመራ እና ክትትል ለማድረግ ተግዳሮት እየሆነበት መምጣቱን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

Feta Daily News

25 Nov, 07:35


በጋዛ ሰርጥ ከ1 ሺሕ በላይ ዶክተሮችና ነርሶች ተገድለዋል ተባለ

በእስራኤል ሐማስ ጦርነት ምክንያት ካለፈው ዓመት ጀምሮ በጋዛ ሰርጥ በደረሱት ጥቃቶች ከ1 ሺሕ በላይ ዶክተሮች እና ነርሶች መገደላቸውን የጋዛ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

ከ310 በላይ ሌሎች የህክምና ባለሙያዎች መታሰራቸው እና በእስር ቤቶች መገደላቸውንም ተናግረዋል።

የህክምና ቁሳቁሶች፣ የጤና ልዑካን ቡድን እና የቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ወደ ጋዛ እንዳይገቡ ሁኔታዎች አመቺ ሳይሆኑ መቀጠላቸውን አስረድተዋል ሲል አናዶሉ ዘግቧል።

በጦርነቱ ምክንያት የሟቾች ቁጥር እስካሁን ከ44 ሺሕ አልፏል።

Feta Daily News

23 Nov, 14:31


የቀድሞ ተዋጊዎችን ማሰልጠን ተጀመረ!

በትግራይ ክልል የሚገኙ የቀድሞ ተዋጊዎችን የማሰልጠን ስራ መጀመሩ ተገለጸ። የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ፥ በመጀመሪያው ዙር ወደ ማኅበረሰቡ የሚቀላቀሉ የቀድሞ ተዋጊዎችን፥ የመመዝገብና የማሰልጠን ስራ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

በ"ብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን" አዘጋጅነት በዛሬው ዕለት በመቐለ ከተማ የተጀመረው ስልጠና ለስድስት ቀናት የሚቆይ ስለመሆኑ ተገልጿል።

የስድስት ቀናቱን ስልጠና የሚያጠናቅቁ የቀድሞ ተዋጊዎች፥ ማኅበረሰቡ ውስጥ ሲገቡ ለመቋቋሚያ የሚሆናቸውን ገንዘብ በባንክ ሂሳባቸው ገቢ ይደረግላቸዋል ተብሏል።

በኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ እና የአፍሪካ ኅብረት ተወካዮች በዛሬው የመቐለ ከተማው የማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓት ላይ ስለመታደማቸው ተገልጿል።

Feta Daily News

23 Nov, 12:29


''አውሮፓ እና አሜሪካ ዜጎችን ሥራ ለማሰማራት ውክልና አልሰጠውም'' ሚኒስቴሩ

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር “ወደ አውሮፓ እና አሜሪካ ዜጎችን ሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና አለመኖሩን” አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ “ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፤ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎች እየተሰራጩ ነው” ሲል አሳስቧል።

ዜጎች በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ሲልም አስጠንቅቋል። 

Feta Daily News

19 Nov, 14:40


ፑቲን ፊርማቸውን አስቀመጡ❗️

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የተሻሻለው የሞስኮ የኑክሌር ጦር መሳሪያ አጠቃቀም ድንጋጌ ላይ ፊርማቸውን አስቀመጡ፡፡

የኑክሌር ጦር መሳሪያ አጠቃቀም ድንጋጌውን ፑቲን ያጸደቁት አሜሪካ ዩክሬን ረዥም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳዔሎችን(አርሚ ታክቲካል ባሊስቲክ ሚሳዔል ፤አታከምስ) ተጠቅማ ወደ ጥልቅ የሩሲያ ግዛት ጥቃት እንድትሰነዝር ፈቃዳለች በተባለ በማግስቱ ነው፡፡

ሰነዱ ማንኛውም ኑክሌር ያልታጠቀ አገር በኑክሌር ታጣቂ አገር ድጋፍ ሩሲያን እና አጋሮቿን ካጠቃ በትብብር እንደተመታን እንቆጥረዋለን የሚል ነው ፡፡

Feta Daily News

19 Nov, 12:23


''ወታደራዊ ኃይሉን እጠቀማለሁ'' ትራምፕ

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከህጋዊነት ውጪ ያሉ ስደተኞችን ለማባረር አስቸኳይ አዋጅ በማወጅ ወታደራዊ ሃይሉን እንደሚጠቀሙ ዛሬ አረጋግጠዋል::

Feta Daily News

19 Nov, 10:32


https://youtu.be/U2gs1PuLjrM?si=zELN-72oJqHVQzzm

Feta Daily News

19 Nov, 08:49


በትግራይ ክልል በየሳምንቱ 17 ሺህ ሰዎች በወባ እየተያዙ ነው

በትግራይ ክልል ባለፉት 3 ወራት በወባ በሽታ ምክንያት 13 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። የትግራይ ጤና ቢሮ በተለይም ወባን ለመካለከል እና ለመቆጣጠር ከፌደራል መንግስቱ የአቅርቦቶች ድጋፍ እንደሚሻ የሚገልፅ ሲሆን እስካሁን ግን የሚጠበቀው እንዳልተገኘ የክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ቡድን መሪ አቶ አረጋይ ገብረመድህን ጠቅሶ ዶቼቬሌ ዘግቧል።

Feta Daily News

19 Nov, 07:43


አብዲራህማን ሞሐመድ አብዱላሂ " ኢሮ " የሶማሌላድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫን አሸነፉ

የዋደኒ ፓርቲ እጩ ሆነው የቀረቡት አብዲራህማን ኢሮ ባለፈው ሳምንት የተካሄደውን የሶማሌላንድ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እንዳሸነፉ የምርጫ ኮሚሽኑ ዛሬ አሳውቋል።

በምርጫው ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ እንዲሁም ፋይሰል አሊ ዋርቤ ተሳታፊ የነበሩ ቢሆንም ድል ሳይቀናቸው ቀርቷል።

የኢሮ ፓርቲ ምርጫውን 63.92 በመቶ ድምፅ በማግኘት ነው ያሸነፈው። የተሰናባቹ ፕሬዜዳንት ሙሴ ቢሂ ፤ ኩልሚዬ ፓርቲ 34.81% ነው ያገኘው።

Feta Daily News

18 Nov, 14:29


የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ሽልማትና ዕውቅና አገኘ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው አፔክስ የመንገደኞች ምርጫ 2025 የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ደረጃ ሽልማትና ዕውቅና ማግኘቱን አስታውቋል።

የአለም አራት ኮኮብ አየር መንገድ ሽልማት ከአንድ ሚሊዮን በላይ ከተረጋገጡ ጉዞዎች ከበረራ በኋላ ከመንገደኞች በተሰጠ ድምፅ መሰረት የተበረከተና በአቪዬሽን ዘርፍ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው አለም አቀፍ ዕውቅና መሆኑ ተመላክቷል።

Feta Daily News

18 Nov, 12:33


ከአክሱም ከተማ ጠፍተው የነበሩትን የወርቅና የከበሩ ማዕድናት ፍለጋ መቀጠሉ ተገለጸ


በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ጦርነት እና አለመረጋጋት በነበረበት ወቅት 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች መጥፋታቸው እንደተረጋገጠ የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ማሳወቁ አይዘነጋም።

የአክሱም ከተማ ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊው አቶ ገ/መድህን ፍፁም ብርሀን የተዘረፉት እና የጠፉትን 23 የወርቅ እና የከበሩ ማዕድናት ሳንቲሞች ለማግኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ብለዋል።

የጠፉትን ቅርሶች ማን እንደወሰዳቸው ማወቅ እንዳልተቻለ የገለፁት ኃላፊው እነዚህን ቅርሶች የማስመለስ ስራ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

Feta Daily News

18 Nov, 10:29


https://youtu.be/cSldUA_c12I?si=r_dTIGmyL1vwdZKb

Feta Daily News

18 Nov, 08:49


በባህርዳር ሄሊኮፕተር ተከስክሷል የሚለው መረጃ ከእዉነት የራቀ ነዉ - መከላከያ ሚኒስቴር

ሄሊኮፕተር ተበላሸ፣ ተከሰከሰ በሚል በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ የተራገበዉ መረጃ ከእዉነት የራቀ ነዉ ሲል የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ካሉት "ቤዞች" አንደኛው ምድብ የሆነው ባህርዳር የሚገኘው የምዕራብ አየር ምድባችን ነው። ከትናንት በስተያ ቅዳሜ በነበረው የአየር ኃይል የምድብ ልምምድ ምክንያት መደበኛ የአየር መንገድ በረራ ለጥቂት ጊዜያት ተቋርጦ የነበር መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ማኒስቴር አስታውቋል።

ይሁን እንጅ የአየር መንገድ ተሳፍሪዎች የተወሰነ መጉላላትን አጋጣሚ በመጥቀስ ሄሊኮፕተር ተበላሸ፣ ተከሰከሰ በሚል የማደናገሪያ ሃሳብ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ እየተራገበ ይገኛል ያለዉ ሚኒስቴሩ

መደበኛ በረራ ለውስን ጊዜያት ተቋርጦ የነበረው በተገቢው መንገድ ስራ የጀመረ ሲሆን የምዕራብ አየር ምድብም ልምምዱን ስኬታማ በሆነ መንገድ አጠናቋል ብሏል።

Feta Daily News

18 Nov, 07:46


በመርካቶ ለሁለተኛ ጊዜ እሳት ቃጠሎ ተከሰተ

በአዲስ አበባ መርካቶ አከባቢ በተለምዶ "ድንች በረንዳ" እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ በተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ሰራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ትላንት ህዳር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ከ30 ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ መርካቶ ጃቡላኒ ህንፃ በተለምዶ "ድንች በረንዳ" እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ሲል ገልጿል።

ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ሸማ ተራ ተብሎ ከሚታወቅ ነባር ህንጻ አከባቢ በተነሳው ከባድ የእሳት አደጋ ከፍተኛ የንብረት ውድመት መከሰቱ ይታወሳል፡፡

Feta Daily News

16 Nov, 14:46


በእስራኤል ጥቃት 15 የነፍስ አድን ሰራተኞች መገደላቸው ተሰማ❗️

እስራኤል በሰሜን ምስራቅ ሊባኖስ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ማዕከል ላይ በፈጸመችው ጥቃት 15 የነፍስ አድን ሰራተኞች መገደላቸውን የአገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።

ከትናንት በስቲያ ሐሙስ፣ ኅዳር 6/ 2017 ዓ.ም በማዕከሉ ላይ የተፈጸመው ይህ ጥቃት በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ምላሽ እየሰጡ በነበሩ የነፍስ አድን ሰራተኞች ላይ የደረሰ የከፋ ጥቃት ተብሏል።

Feta Daily News

16 Nov, 12:43


በህንድ ሆስፒታል ውስጥ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ የ10 ጨቅላ ህጻናትን ህይወት ቀማ

ጠቅላይ ሚኒስትር ሞዲ “ልብን በሚሰብረው አደጋ ህጻናት ልጆቻቸውን ላጡ ወላጆች መጽናናትን እመኛለሁ" ብለዋል
በሰሜናዊ ህንድ በሚገኝ የመንግስት ሆስፒታል ውስጥ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ 10 አዲስ የተወለዱ ህጻናት ህይወት አለፈ። አርብ ምሽት በማሃራኒ ላክስሚ ባይ ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል የደረሰው የእሳት ቃጠሎ በኤሌክትሪክ ችግር የተከሰተ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

Feta Daily News

16 Nov, 10:26


https://youtu.be/YSxp7UzxPNs?si=BkRTVPX10g1IrX3i

Feta Daily News

16 Nov, 08:11


እርዳታ ካገኘን 2 ዓመት ሆነን” በሰሜኒ ጦርነት የተፈናቀሉ ወገኖች

በ2013 ዓም የሰሜኑ ጦርነት ወቅት ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማና አካባቢው የሚገኙ ተፈናቃዮች “እርዳታ ካገኘን 2 ዓመት ሆኖናል” አሉ፣ የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽ/ቤት በበኩሉ የእርዳታ አቅርቦት መዘግየት ቢኖርም “2 ዓመት የተባለው ግን የተጋነነ ስሞታ ነው” ማለቱን ዶቼ ቬለ ዘግቧል።

Feta Daily News

16 Nov, 07:22


ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን በጄክ ፖውል ተሸነፈ

የ58 ዓመቱ አሜሪካዊ የከባድ ሚዛን ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ከ27 ዓመቱ ጄክ ፖውል ጋር ባደረገው ግጥሚያ ተሸንፏል፡፡

ታይሰን ዛሬ ማለዳ ያደረገው ግጥሚያ ራሱን ከፕሮፌሽናል ውድድር ካገለለ ከ19 ዓመታት በኋላ የተከናወነ ነው፡፡

የግጥሚያውን ውጤት ተከትሎም ታይሰን 20 ሚሊየን እና ጄክ ፖውል 40 ሚሊየን ዶላር አግኝተዋል፡፡

Feta Daily News

15 Nov, 14:29


የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተሸለመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2024 የቢዝነስ ተጓዦች ሽልማት ውድድርን በማሸነፍ ‘ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ’ በመባል ተሸልሟል፡፡

ሽልማቱ በዘርፉ ለአምስተኛ ተከታታይ ዓመታት የተገኘ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡

ከሽልማቱ በኋላም አየር መንገዱ ደንበኞቹ ለሰጡት ድጋፍ ምሥጋና አቅርቧል፡፡

Feta Daily News

15 Nov, 12:20


ቶታል ሠፈረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ነገ ይመረቃል

ቅዳሜ እና እሁድ በ7 እና 8 ቀን 2017ዓም ይመረቃል።

አድራሻ ጦር ኃይሎች ወደ ቶታል በሚወስደው መንገድ ዱባይ ኤምባሲ ፊት ለፊት ይገኛል።

Feta Daily News

14 Nov, 14:59


የአርጀንቲና ልዑካን የኮፕ 29 ስብሰባን ለቀው ወጡ❗️

በአዘርባጃን ባኩ እየተካሄደ በሚገኘው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ በርካታ ሀገራት የተሳተፉ ሲሆን አርጀንቲናን ወክለው የሄዱት ልዑካን ግን ለሶስት ቀናት በኮንፈረንሱ ከተሳተፉ በኋላ ለቀው መውጣታቸው ነው የተገለጸው።

ታዳሽ ኃይል ላይ ትኩረቱን ባደረገው የባኩ ኮንፈረንስ ከሰማንያ በላይ የደቡብ አሜሪካ ሀገራት ተወካዮች የታደሙበት ነው።

የአርጀንቲና ፕሬዚደንት ዣቪዬር ማይሌ በበኩላቸው የአየር ንብረት ቀውስ ማለት ''የሶሻሊዝም ርዕዮት'' ውሸት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ልዑካኑ ለዘጋርዲያን እንደገለጹት “አዘርባጃንን ለቀን እንድንወጣ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኩል መመርያ ተሰጥቶናል'' ብለዋል።

አርጀንቲና የባኩን ጉባኤ ረግጣ መውጣቷ የሚወሰዱ የኮፕ 29 ውሳኔዎች በመኖራቸው ዋጋ ሊያስከፍላት ይችላል ሲሉ ተንታኞች ገልጸዋል።

Feta Daily News

14 Nov, 12:38


ሩሲያ እስራኤል በሶሪያ የምትፈጽመውን የአየር ላይ ጥቃቷን እንድታቆም ማስጠንቀቋ ተሰማ

የሞስኮ ማስጠንቀቂያ የተሰማው እስራኤል በሶሪያ የሩሲያ ጦር ማዘዣ በሚገኝበት ላታኪያ ወደብን መደብደቧን ተከትሎ ነው። እስራኤል ከሩሲያ ማስጠንቀቂያ በኋላ በወደቧ ላይ ድብደባዋን ቀንሳለች ተብሏል።

Feta Daily News

14 Nov, 10:31


https://youtu.be/XzXKtoFmIzM?si=ax9HdeLlJ_IUg396

Feta Daily News

14 Nov, 08:24


በምዕራብ ሸዋ ኦሮሚያ "ጦርነት ይቁም" በሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄዱ

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሰላምን ለማፅናት ያለመ ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል። ሕዝባዊ ስልፉ በምዕራብ ሸዋ፣ ምስራቅ ሸዋ፣ ቄለም ወለጋ እና የአርሲ ዞኖች እየተደረገ ሲሆን፤ በሕዝባዊ ሰልፉ ላይ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የሀይማኖት አባቶችና የተለያዩ ሕብረተሰብ ክፍሎች ታድመዋል።

Feta Daily News

14 Nov, 07:45


በሞቃዲሾ በተፈጸመ የቦንብ ጥቃት የ3 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ በመንገድ ዳር በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት ሁለት የጸጥታ አካላት እና አንድ ሰላማዊ ሰው መገደላቸው ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም በፍንዳታው ሌሎች ሦስት ሰዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ተነግሯል።

በሞቃዲሾ የደህንነት ባለስልጣን የሆኑት አሊ አህመድ፤ ፍንዳታውን በተመለከተ ፖሊስ እና የፀጥታ አካላት በአካባቢው በመገኘት ምርመራ መጀመራቸውን ለአናዶሉ ገልጸዋል፡፡

ለጥቃቱ እ.ኤ.አ ከ2007 ጀምሮ የሶማሊያ መንግሥትን እና የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪዎችን ሲዋጋ የቆየው አልሸባብ ሃላፊነቱን መውሰዱም ተነግሯል።

Feta Daily News

13 Nov, 14:45


ቱርክ ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች

ቱርክ ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በይፋ ማቋረጧን ፕሬዝዳንት ሬሲብ ጣይብ ኤርዶጋን አስታወቁ።

ፕሬዘዳንቱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከእስራኤል ጋር ያለንን ማንኛውንም የንግድ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋርጠናል፣ እስከመጨረሻው ከፍልስጤም ጎን በጽናት እንቆማለን ብለዋል።

ኤርዶጋን እስራኤል በጋዛ እና በሊባኖስ የምትፈጽመውን ‘የዘር ማጥፋት ወንጀል’ አውግዘው የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያሚን ኔታንያሁ ለፈጸሙት ድርጊት ተጠያቂ ለማድረግ የሚችሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ መግለፃቸውንም ሚድል ኢስት አይነት ዘግቧል፡፡

Feta Daily News

13 Nov, 12:23


የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች በአሜሪካ የጦር መርከብ ላይ ጥቃት አደረሱ

የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች በአሜሪካ የጦር መርከብ ላይ ጥቃት አድርሰዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው አሜሪካ ማዕከላዊ እዝ በሀውቲ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ላይ በተከታታይ የአየር ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነው።

Feta Daily News

13 Nov, 10:39


https://youtu.be/JY-tmXRfLJo?si=AZ_mEfK_pfz1A1aj

Feta Daily News

13 Nov, 08:50


በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ለተፈጸሙት አሰቃቂ ድርጊቶችና የጦር ወንጀሎች ተጠያቂነት እንዲኖር አሜሪካ ጠየቀች

በትናትናው ዕለት በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ግምገማ ላይ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ለተፈጸሙ አሰቃቂ ድርጊቶች፣ የጦር ወንጀሎች፣ በሰው ልጆች ላይ ለተፈጸሙ ሰብዓዊ እና የዘር ማጥፋትን ጨምሮ ተጠያቂነት እንዲኖር አሜሪካ ጠይቃለች፡፡

በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎችም አካባቢዎች የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና በመላ ሀገሪቱ የመሰረታዊ ነጻነቶች እገዳ በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን የአሜሪካ ተወካይዋ በግምገማው ገልጸዋል።

አክለውም፤ "ለኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰትን የሚከለክል እና ተጠያቂ የሆኑትን ግልጽነት ባለው፣ ተጎጂዎችን ያማከለ የፍትህ ሂደት ግምት ዉስጥ አስገብቶ ተጠያቂ እንዲሆኑ እናሳስባለን" ብለዋል።

Feta Daily News

13 Nov, 07:32


ኤለን መስክ ሹመት አገኘ

የተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ የጀርባ አጥንት የሆነው ቢሊየነሩ ኤለን መስክ የመንግሥትን ብቃት የሚገመግም አዲስ መስሪያ ቤት የኃላፊነት ሹመት ተሰጠው።

Feta Daily News

12 Nov, 14:41


በህወሃት ክፍፍል ፌድራል መንግስቱ ጣልቃ እንዲገባ ተጠየቀ

በህውሃት እና ጊዜዓዊ አስተዳደሩ መካከከል  በተፈጠረው አለመግባበት  የገፈቱ ቀማሽ  ህዘቡ በመሆኑ የፌድራል መንግሰት  ጣልቃ በመግባት ውሳኔ ይስጥበት ሲለ የትግራይ ዲሞክራሲዊ ፓርቲ (ትዴፓ)  ገልጿል::

የፓርቲው ማዓከላዊ ኮሚቴ አባል  አቶ ገ/ጊዮርጊስ ግደይ ለጣቢያችን  እንደተናገሩት  ከቅርብ ጊዜዓት ወዲህ የተፈጠረው የህውሃት እና የጊዜዓዊ አስተዳደሩ አለመግባባት መቋጫው “የፌድራል መንገስት ጣልቃ በመግባት ውሳኔ ማሳለፍ ብቻ ነው” ብለዋል፡፡

Feta Daily News

12 Nov, 12:07


ግብፅ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሱዳናውያን ስደተኞች መቀበሏ ተገለጸ

ግብፅ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን የሚደርሱ ሱዳናዊንን ስደተኞችን መቀበሏን አስታዉቃለች።

በግብፅ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ተወካይ ሃናን ሃምዳን፤ "ካይሮ ይህን ያህል ቁጥር ስደተኞችን ተሸክማ የመቆየት አቅም የላትም ሲሉ" ተናግረዋል።

"የግብፅ መንግሥት አለም አቀፍ ጥበቃን ለማድረግ ቁርጠኛ ቢሆንም፤ የቀውሱ መጠን ግን ከአቅሙ በላይ ሆኗል" ሲሉ ተወካዩ አስታዉቀዋል።

በተጨማሪ የአለም አቀፍ ሃገራት ድጋፍ እንዲያደርግ ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸውን ሱዳን ትሪብን ዘግቧል።

Feta Daily News

12 Nov, 10:13


https://youtu.be/gza32qjrbc8?si=TnKRGuCPqFor_ty2

Feta Daily News

12 Nov, 08:59


የሳኡዲ ልኡል አልጋወራሽ መሀመድ ቢን ሳልማን እስራኤል በጋዛ “የዘር ጭፍጨፋ” እየፈጸመች ነው ሲሉ አጥብቀው ተቃወሙ

ልኡል አልጋወራሹ የጋዛ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ ጠንከር ባለ ቃል ቴል አቪቭን ያወገዙት የሙስሊምና አረብ ሀገራት መሪዎች ጉባኤ በሪያድ ሲጀመር ባደረጉት ንግግር ነው።
እስራኤል በኢራን እና ሊባኖስ እየፈጸመች የምትገኘውን ጥቃትም የሳኡዲው ልኡል አልጋወራሽ ኮንነዋል።
የሪያድ እና ቴህራን ግንኙነት እየተሻሻለ መምጣቱን በሚያሳይ መልኩም እስራኤል በኢራን መሬት ላይ ጥቃት እንዳትፈጽም አሳስበዋል።

ሌሎች የጉባኤው ተሳታፊ ሀገራት መሪዎችም እስራኤል ከዌስትባንክ እና ጋዛ ሙሉ በሙሉ እንድትወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

Feta Daily News

12 Nov, 08:04


የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት አያያዝ በዛሬው ዕለት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሊገመገም ነው

ነኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ በአራተኛ ዙር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ሁሉን-አቀፍ ወቅታዊ ግምገማ (ዩ.ፒ.አር) መድረክ ላይ በዛሬው ዕለት ግምገማ እንደሚደረግበት ተገልጿል፡፡

የግምገማው ቡድኑ ስብሰባውን ዛሬ ሕዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም በጄኔቭ የሚካሄድ ሲሆን፤ ስብሰባው ከቀኑ 5፡00 ጀምሮ በቀጥታ በድህረ ገጽ (ዌብ ካስት) ይተላለፋል ተብሏል፡፡

በቡድኑ ከጥቅምት 25 እስከ ሕዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም በሚደረገው ስብሰባ ላይ፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ የ14 ሀገራት የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ እንደሚገመገም ምክር ቤቱ አመላክቷል፡፡

የግምገማው ቡድኑ 47 የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት አባል ሀገራትን ያቀፈ ሲሆን፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሀገራትም በግምገማው ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ተነግሯል፡፡

Feta Daily News

11 Nov, 14:52


በቦኮ ሃራም ጥቃት 17 የቻድ ወታደሮች እና 96 አማፂያን መገደላቸውን የሀገሪቱ ጦር አስታወቀ

የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ቅዳሜ እና እሁድ በወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ ላይ ባደረሱት ጥቃት 17 የቻድ ወታደሮች መግደላቸውን የቻድ ጦር አስታወቀ። በጥቃቱ ወቅት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ 96 የሚሆኑ አማፂያን መገደላቸውንም ጨምሮ ገልጿል።

የጦሩ ቃል አቀባይ ጀነራል ኢሳክ አቼክ እሁድ ምሽት በሀገሪቱ የቴሌቭዥን ጣቢያ በሰጡት መግለጫ በቻድ ሐይቅ ክልል ጥቃቱ የተፈፀመው ቅዳሜ ምሽት መሆኑን ተናግረዋል። የቻድ ሐይቅ አካባቢ በዚህ አመት ከቦኮ ሃራም እና የምዕራብ አፍሪካ እስላማዊ መንግስትን ጨምሮ በአማፂያን ተደጋጋሚ ጥቃቶች ደርሶበታል።

ባለፈው ወር በወታደራዊ ካምፕ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 40 ወታደሮች መገደላቸውን ተከትሎ፣ ፕሬዝዳንት ማሃማት ዴቢ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎችን ከቻድ ሐይቅ ለማትፋጥ ዘመቻ አካሂደው ነበር።

Feta Daily News

11 Nov, 13:05


ኳታር የሽምግልና ሚናዋን አቋረጠች


ኳታር በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የምታደርገውን የተኩስ አቁም እና ታጋቾችን የማስፈታት ሚናዋን አቋርጣለች ሲሉ ባለሥልጣናት ተናገሩ።

ሐማስ እና እስራኤል ለመደራደር "ፍቃደኛነታቸውን" ሲያሳዩ ሥራዋን እንደምትቀጥል ኳታር ተናግራለች።
አገሪቱ ከዚህ ውሳኔ የደረሰችው የፍልስጤሙ ቡድን በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የቀረበውን አዲስ ሃሳብ ውድቅ አድርጓል በማለት የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት የሐማስ ተወካዮች በኳታር መገኘታቸውን እንደማትቀበል መግለጻቸውን ተከትሎ ነው።

ኳታር ከድርድሩ ራሷን ማግለሏን የተናገረች ሲሆን በዶሃ የሚገኘው የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ "ዓላማውን አላስፈጸመም" መባሉን "የተሳሳተ ነው" ስትል ተናግራለች።

Feta Daily News

11 Nov, 10:19


https://youtu.be/TGZvezZHsRc?si=KcdiD3ofuQkpodpp

Feta Daily News

11 Nov, 08:53


የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት የሚወስን ደንብ ወጣ

በአዲስ አበባ ከተማ የሆቴል ባለሙያዎችን አለባበስ እና የመዋቢያ ጌጣጌጥ አጠቃቀም ሥርዓት የሚወስን ደንብ መውጣቱን የከተማ አስተዳደሩ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል።

ይህ ደንብ ቁጥር 178/2017 ሆኖ የወጣ ሲሆን በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ የአለባበስ፣ የጌጣጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ሥርዓት በመዘርጋት የሀገር ባህልና እሴት እንዲጠበቅ ለማድረግ የወጣ ደንብ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ከደንቡ የአለባበስ ሥርዓት ውስጥ ለአብነት ደረት ክፍልን ያልሸፈነ ወይም ከአንገት በታች ያለውን የሰውነት ክፍል የሚሸፍን ሸሚዝ ያለበሰ፣ የሴቶች ጉርድ ቀሚስ ቁመቱና ቅዱ ከጉልበት በላይ ከሆነ፣ ከጋብቻ ቀለበት ውጪ ጌጣጌጦችን በሚታዩ የሰውነት ክፍሎች ላይ ከተደረገ እንደሚያስቀጣ ማስቀመጡ ተገልጿል፡፡

Feta Daily News

11 Nov, 07:42


በላሊበላ ከተማ የማሕሌተ ጽጌ ፍፃሜ በደማቅ ሁኔታ ተከናወነ

በላሊበላ ከተማ ከሚከናወኑ ድንቅ ሀይማኖታዊ ሥርዓቶች አንዱ ማሕሌተ ጽጌ ነው። በትናንትናው ዕለት የማሕሌተ ጽጌ ፍፃሜ እጅግ በደማቅ ሁኔታ ተከናውኗል።

Feta Daily News

09 Nov, 15:28


''መድኃኒት ለመግዛት አቅም ካነስዎ'' ተከፍሏል

ይህ በአዲስ አበባ ሳርቤት አከባቢ መድኃኒት መግዣ ለሌላቸው ሰዎች በሃልተን ፋርማሲ የተከፈለባቸው መድሃኒቶች መገኛ በማህበራዊ የትስስር ገጾች አድናቆት ተችሮታል።

Feta Daily News

09 Nov, 12:41


የአትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ ቲሸርት ለጨረታ ሊቀርብ ነው

ከ23 አመታት በፊት በመጀመሪያው የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር ላይ የውድድሩ መስራች የሆነው አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የሮጠበት የሩጫ ቲሸርት በጨረታ ሊቀርብ እንደሆነ ተነግሯል።

ይህ ጨረታ የሚቀርበው የፊታችን ቅዳሜ ከታላቁ ሩጫ ቀን በፊት እንደሆነ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት መልካሙ ተገኝ ለሀገሬ ቴሌቪዥን ገለጿል።

Feta Daily News

09 Nov, 10:28


https://youtu.be/Bw25z_qzlD0?si=LtfjfHhwAipWBdeA

Feta Daily News

09 Nov, 08:28


''በጦርነት ወቅት ዋጋ የከፈሉና እስካሁን የት እንደደረሱ የማይታወቁ ተማሪዎች አሉ'' ርዕሰ መስተዳድሩ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ''በጦርነት ወቅት ዋጋ የከፈሉና እስካሁን የት እንደደረሱ የማይታወቁ ተማሪዎች መኖራቸውን'' ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይህን የተናገሩት የመቐለ ዩኒቨርስቲ ለሁለት ዓመታት የተካሄደው ደም አፋሳሹ የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በፕሪቶሪያ የዘላቂ ግጭት ማቆም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት 2ሺህ 729 ተማሪዎችን በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች በሀውልቲ ሰማዕታት አዳራሽ ባስመረቀበት ወቅት ነው።

Feta Daily News

09 Nov, 07:45


"የደመወዝ ማስተካከያው የጥቅምት ወር ክፍያን ታሳቢ በማድረግ ይከፈላል" ሲቪል ሰርቪስ

ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል የተባለው የመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ የጥቅምት ወር ክፍያን ታሳቢ በማድረግ እንደሚከፈል የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ኮሚሽነሩ በማህበራዊ ትስስት ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፤ "የተፈቀደው የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማስተካከያ ክፍያ ዘግይቷል፣ ቀርቷል የሚሉ ሃሳቦች እየተራመዱ ነው። በሲቪል ሰርቪስ በኩል የሚለቀቁ መረጃዎች ኦፊሴላዊና የሚተገበሩ መሆኑን መተማመን ጥሩ ነው።" ብለዋል፡፡

Feta Daily News

08 Nov, 14:28


በጋዛ ጦርነት ከሞቱት 70 ከመቶ የሚጠጉት ሴቶችና ህጻናት መሆናቸው ተነገረ

ባለፈው ዓመት በጋዛ ግጭት መሞታቸው ከተረጋገጠ ሰዎች መካከል 70% የሚጠጉት ሴቶች እና ህጻናት መሆናቸውን ዛሬ ዓርብ የወጣው የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ቢሮ ዘገባ አመልክቷል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ዘገባ “ይህ የዓለም ዓቀፍ የሰብአዊ ህግ መሰረታዊ መርሆችን ስልታዊ በሆነ መንገድ የጣሰ ነው” ሲልም ድርጊቱን አውግዟል፡፡

Feta Daily News

08 Nov, 12:10


የኢኳቶሪያል ጊኒው አነጋጋሪው ሰው ተባረረ❗️

ባለሥልጣኑ ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ቴዎዶር ኦቢያንግ ንጉዌማ ጋር ዝምድና ያለው ቢሆንም፣ የቪዲዮዎቹ ይፋ መሆንን ተከትሎ በፕሬዝዳንቱ በተፈረመ ደብዳቤ ከሥልጣኑ መባረሩ ተገልጿል።

Feta Daily News

08 Nov, 10:17


https://youtu.be/grwAIsMEQ1w?si=VmIlgGJB6Zuta4SH

Feta Daily News

08 Nov, 08:39


የእስራኤል ዜጎችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት ተሰነዘረ❗️

እስራኤል የዜጎቿን ህይወት ለመታደግ ወደ ኔዘርላንድ አውሮፕላኖች ልትልክ መሆኑን አስታወቀች። የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እንደገለጸው በደች እስራኤላውያንን ኢላማ ያደረገ ጥቃት ተፈጽሟል።

Feta Daily News

08 Nov, 07:37


ዩሪያ የጫነች የመጀመሪያዋ መርከብ ጂቡቲ ወደብ ደረሰች

በ2017/18 የምርት ዘመን ከውጭ ከሚገዛው 23 ሚሊየን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ፤ 472 ሺሕ 500 ኩንታል ዩሪያ የጫነች የመጀመሪያዋ ኤም ቪ አባይ ሁለት የተሰኘች የኢትዮጵያ መርከብ ጂቡቲ ወደብ መድረሷ ተገልጿል።

በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ጂቡቲ ወደብ እንደሚደርሱ እና ወደ ሀገር ውስጥ የማጓጓዝ ሥራውም በፍጥነት እንደሚጀመር የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም ለ2017/18 የምርት ዘመን ለሚውል 23 ሚሊየን ኩንታል ዩሪያ እና ዳፕ የአፈር ማዳበሪ ግዥ 1 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር በመንግሥት መፈቀዱ ይታወሳል።

Feta Daily News

07 Nov, 14:21


በሩሲያ የሰፈሩት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች የወሲብ ፊልሞችን በማየት መጠመዳቸው ተገለጸ❗️

የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ጦር ወይም ኔቶን ጨምሮ በርካታ ሀገራት 10 ሺህ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ወደ ሩሲያ መግባታቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል።

የወታደሮቹ ወደ ሩሲያ መምጣት ብዙ ትኩረት የሳበ ሲሆን ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ ዩክሬን እና አሜሪካ ወታደሮቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ሲጠይቁ ሰንብተዋል።
የዩክሬን ጦር በተቆጣጠራት የሩሲያዋ ኩርስክ ግዛት የሰፈሩት እነዚህ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ባሳለፍነው ሰኞ ዕለት ስራ ጀምረዋል ተብሏል።

ዘግይቶ በወጣ ዘገባ ደግሞ እነዚህ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች የኢንተርኔት አገልግሎት ሲያገኙ የወሲብ ፊልሞችን በማየት ተደምጠዋል ሲል ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል።

Feta Daily News

07 Nov, 12:00


''ግድቡን ማፈንዳት..'' ትራምፕ

ዶናልድ ትራምፕ ግድቡን በተመለከተ በአንድ ወቅት የተናገሩት ንግግር ምርጫውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ እንደ አዲስ እየተዘዋወረ ይገኛል። እንዴት ግድቡ ሲገነባ እያያችሁ ዝም ብላችሁ አሁን አስቁሙልን ትላላችሁ ያሉት ትራምፕ ግብፅ ግድቡን ማፈንዳት ሊኖርባት እንደሚችል ጠቁመዋል።

Feta Daily News

07 Nov, 10:30


https://youtu.be/UaBOIsZA_Ug?si=3S5b5WccJmO5dL9t

Feta Daily News

07 Nov, 08:31


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተወሰደብኝ ገንዘብ ያልተመለሰው 217 ሺሕ ብር ብቻ ነው አለ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሳይበር ድህንነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሳይበር ድህንነት ቀን እያከበረ ይገኛል።

በክብረ በዓሉ ላይ የተገኙት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ፤ ባለፈው ዓመት በራሳችን ስህተት በተፈጠረው የሲስተም ችግር ምክንያት ከተወሰደው ገንዘብ ሁሉም ተመልሶ የቀረው 217 ሺሕ ብር ብቻ ነው ብለዋል።

Feta Daily News

07 Nov, 07:42


የትራምፕን ድል ተከትሎ የኤለን መስክ ሀብት በ20 ቢሊየን ዶላር ጨመረ

የአለማችን ቁጥር አንድ ቢሊየነሩ ለትራምፕ የቅስቀሳ ቡድን ከ120 ሚሊየን ዶላር በላይ በማዋጣት በብዙው አትርፏል ተብሏል። የትራምፕን ድል ተከትሎ የኤለን መስክ ሀብት በ20 ቢሊየን ዶላር ጨምሯል።

Feta Daily News

06 Nov, 15:01


ኢኳቶሪያል ጊኒ በስራ ቦታ ወሲብ ሲፈፅሙ የተገኙ ከባድ ቅጣት አለው አለች

በሥራ ቦታቸው ወሲባዊ ግንኙነት ሲፈጽሙ የሚያዙ የመንግሥት ሠራተኞች “ከባድ እርምጃ” እንደሚጠብቃቸው የኢኳቶሪያል ጊኒ ምክትል ፕሬዝዳንት አስጠነቀቁ።

ይህ የምክትል ፕሬዝዳንቱ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው በመቶዎች የሚቆጠሩ የወሲብ ቪዲዮዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከተሰራጩ በኋላ ነው።

ቪዲዮዎቹ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣን የሆነውን ባልታዛር ኢባንግ ኢንጎንጋ የከፍተኛ ባለሥልጣናት ሚስቶችን ጨምሮ ከተለያዩ ሴቶች ጋር በቢሮው ውስጥ ወሲብ ሲፈጽም የሚያሳዩ ናቸው ተብሏል።

Feta Daily News

06 Nov, 11:02


https://youtu.be/CXeu47Fqvb0?si=Eagcj5U8rkmu8beF

Feta Daily News

05 Nov, 14:29


በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን አዲስ አበባ ገባ!


በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን አዲስአበባ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል ::

400 መቀመጫዎች ያሉት አውሮፕላኑ የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለትና ''ኢትዮጵያ ላንድ ኦፍ ኦሪጅንስ'' የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፣ የአየር መንገዱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲ ለሚክ፣ የኤር ባስ ኩባንያ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ተብሏል።

Feta Daily News

05 Nov, 12:22


ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን 738.2 ሚሊዮን ዶላር ብድር አፀደቀች

የኢትዮጵያ መንግሥት ለጎረቤት ደቡብ ሱዳን 738.2 ሚሊዮን ዶላር ብድር ለማቅረብ ያደረገውን ስምምት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፀደቀ።

ብድሩ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳንን በመንገድ ለማስተሳሰር የሚውል ሲሆን በዋናነትም ከኢትዮጵያ ድንበር አንስቶ ወደ ደቡብ ሱዳን እስከ 220 ኪሎ ሜትር የሚዘልቅ ነው።

Feta Daily News

05 Nov, 10:44


https://youtu.be/cGyJz5zlOVk?si=gc5Px6DG9aPUe93_

Feta Daily News

05 Nov, 08:42


ለንግድ ባንክ ዕዳ መክፈያ እና ካፒታል ማሳደጊያ የሚውል 900 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው ቦንድ ለሽያጭ ሊቀርብ ነው

የገንዘብ ሚኒስቴር 900 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው የመንግስት ዕዳ ሰነድ (ቦንድ) እንዲያወጣ የሚፈቅድ የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ። ገንዘቡ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልከፈሉትን ዕዳ ለመክፈል እና ለባንኩ ካፒታል ማሳደጊያ የሚውል ነው።

ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 26፤ 2017 በሚካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የቀረበው ይህ አዋጅ፤ “የመንግስት እዳ ሰነድ” የሚል ስያሜን የያዘ ነው። አዋጁን ማውጣት ያስፈለገው፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለበት “ከፍተኛ ዕዳ” በባንኩ የፋይናንስ ገጽታ ላይ “ከፍተኛ ተጽዕኖ ስላስከተለ” መሆኑ በረቂቅ ህጉ ላይ ተጠቅሷል።

Feta Daily News

05 Nov, 07:39


በአማራ ክልል ያለውን ችግር ለመፍታት መንግሥት ቁርጠኛ ሆኖ ተኩስ አቁም ማድረግ አለበት ሲሉ ፓርቲዎች ገለጹ

በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በየዕለቱ እየተከሰተ ያለዉን የሕጻናትና እናቶችን ሞት ለማስቆም፤ የፌደራሉ መንግሥት ቁርጠኛ በመሆን የተኩስ አቁም ሊያደርግ ይገባል ሲሉ ፓርቲዎች ተናግረዋል፡፡


የእናት ፓርቲ አባል አቶ ጌትነት ወርቁ "መንግሥት የተኩስ አቁም ማድረግ አለበት" ያሉ ሲሆን፤ 'ቁርጠኛ መሆን አለበት' ሲባልም "በሌላው ወገን ያሉትም ጦር በማዉረድ ወደ ሌላ አሸናፊ መንገድ ለመምጣት ቁርጠኛ መሆን አለባቸው" ብለዋል፡፡

"መንግሥት ለሰላም ቁርጠኛ ነኝ እያለ ይናገር እንጂ በእውነት መሬት ላይ የወረደ የተተገበረ ነገር ግን ማግኘት አይቻልም" ያሉት ደግሞ፤ የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ የአደረጃጀትና አቅም ግንባታ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙባረክ ረሽድ ናቸው፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማው 'እናንተም አግዙ' የሚል ጥሪ ስለማድረጋቸው በሚመለከት ሀሳባቸውን የሰጡት ፓርቲዎቹ፤ "ችግሩ ከእኛም ከመንግሥትም በላይ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል" ሲሉ መናገራቸውን አሃዱ ዘግቧል።

Feta Daily News

04 Nov, 12:21


በደቡብ ወሎ መምህራን ከ2 ወር በላይ ደምወዞ ስላልተከፈላቸው ለተለያየ ችግር እየተጋለጡ መሆኑን ገለጹ

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ወግዲ ወረዳ የመምህራን ደምወዝ ከ2 ወር በላይ ባለመከፈሉ ምክንያት፤ ለተለያዩ ችግሮች እየተጋለጡ መሆኑን የአካባቢው መምህራን ለአሐዱ ቅሬታቸዉን አሰምተዋል።

በአካባቢው ባለው የጸጥታዉ ችግር ምክንያት የተዘጉ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የገለጹት መምህራኑ፤ ከመስከረም ወር 2017 ጀምሮ ደምወዝ እየተከፈላቸዉ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

Feta Daily News

04 Nov, 10:20


https://youtu.be/3DBiy2Y0Rp8?si=k5DCWMk7k3Eu3gXE

Feta Daily News

04 Nov, 08:56


ካማላ ሐሪስ “የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ” አሉ

የዲሞክራቷ እጩ ካማላ ሐሪስ “የጋዛን ጦርነት ለማስቆም የተቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ” አሉ።
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 26/ 2015 ዓ.ም ከሚደረገው የአሜሪካ ምርጫ በፊት የመጨረሻ ቅስቀሳቸውን እያደረጉ ያሉት ካማላ ሃሪስ በሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርስቲ ተገኝተው ነው ይህንን ያሉት።

Feta Daily News

04 Nov, 07:35


በአማራ ክልል የ6 ዓመት ህጻንን ያገቱ ተያዙ❗️

እገታ አሁንም በአማራ ክልል ችግር መሆኑን ነዋሪዎች ገልጠዋል፣ ፖሊስ በበኩሉ ከህብረተሰቡ ጋር በተደረገ ውይይት የድርጊቱ ፈፃሚዎች በቁጥጥር ሥረ እየዋሉ ነው ብሏል። አንዳንድ ነዋሪዎችም ይህንኑ አረጋግጠዋል። ሰሞኑንም ደግሞ  አንድ የ6 ዓመት ህፃን አግተው ማስለቀቂያ ገንዘብ የጠየቁ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታውቋል።

ሰሞኑ አንድ ተጠርጣሪ ከሌላ ግብረ አበሩ ጋር በመሆን ቃፍታ ሁመራ “ባዕክር” በተባለ ቀበሌ በቀን ሠራተኛነት ተቀጥሮ የሚሰራበትን ቤተሰቦች የ6 ዓመት ህፃን አግቶ ተሰውሮ እንደነበርና ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተጠርጣሪዎቹ ጥቅም 21/2017 ዓም በጎንደር ከተማ ቀበሌ 16 “ብላጅግ” ከተባል ጫካ ውስጥ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊን ጠቅሶ ዶቼቬሌ ዘግቧል።

Feta Daily News

02 Nov, 14:10


የዶናልድ ትራምፕ ንብረት የሆነው ትሩዝ ሶሻል ዋጋ ወደ 10 ቢሊዮን ዶላር አሻቀበ

ትሩዝ ሶሻል አሁን ላይ የኢለን መስኩን ኤክስ (ትዊተር) በልጧል። ትሩዝ ሶሻል ዋጋው የጨመረው የዓለማችን ቁጥር አንድ ባለጸጋ የሆኑት ኢለን መስክ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊ መሆናቸውን ተከትሎ ነው።

Feta Daily News

02 Nov, 12:35


የኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማርያም አሁናዊ ገፅታ‼️
📷 ትዕግስት መንግሰቱ

Feta Daily News

02 Nov, 10:35


https://youtu.be/sCZ6B5dcATI?si=soEzVUoEWutcMcQk

Feta Daily News

02 Nov, 10:34


የቻይናው ቢዋዲ ኩባንያ የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ሻጭ ደረጃን ተቆናጠጠ

ለዓመታት የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ሻጭ የነበረው ቴስላ ኩባንያ በቢዋይዲ ተበልጧል። ቢዋይዲ ኩባንያ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ከ28 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሽያጭ አከናውኗል።

Feta Daily News

02 Nov, 07:29


በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በወባ ተጠቅተዋል ተባለ

በኢትዮጵያ ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ 7.3 ሚሊዮን ሰዎች በወባ መያዛቸውንና 1ሺሕ 157 በበሽታው መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

በኢትዮጵያ 75 ከመቶ የሚሆነው መሬት ለወባ ትንኝ ተጋላጭ በመሆኑ ለሃገሪቱ ከፍተኛ የጤና ተግዳሮት እንደደቀነም ድርጅቱ አስታውቋል። በእነዚህ አካባባዎች ከሚኖሩት ውስጥ 69 በመቶ የሚሆኑት በወባ የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ሲሆን፣ ከአምስት ዓመት በታች ሳሉ ከሚሞቱት ሕፃናት ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት ሕይወታቸው የሚያልፈው በወባ ምክንያት መሆኑንም ዓለም አቀፉ የጤና ተቋም አስታውቋል።

በተለይም ግጭት ባለባቸው ሥፍራዎች የጤና አገልግሎት ማዳረሡ አስቸጋሪ እንደሆነም የጤና ድርጅቱ ጠቁሟል። የሌሎች በሽታዎች መዛመትም ሁኔታውን ይበልጥ አስቸጋሪ እንዳደረገው ድርጅቱ አስታውቋል።

Feta Daily News

01 Nov, 14:32


"ባደረግነው የቤተመንግስት ዕድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገብተናል"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

Feta Daily News

01 Nov, 12:24


ከመደፈር ጥቃቱ በኋላ አዳጊዎቹ ወደ ትምሕርት ቤት አልተመለሱም

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ ውስጥ ሁለት ሴት አዳጊዎች ሲደፈሩና አሰቃቂ ጾታዊ ጥቃት ሲደርስባቸው የሚያሳው ቪዲዮ ከተለቀቀ ከኋላ፣ ተጎጂዎቹ ባጋጠማቸው ማሸማቀቅ ትምሕርት እስከማቋረጥ እንዳደረሳቸው ከተጎጂዎቹ አንዷ የኮነችው የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ገለጸች።

በጉልበት ሥራ የሚተዳደሩት የአንደኛዋ ተጎጂ እናት፣ በልጃቸው ላይ በደረሰው ጥቃት፣ ክፉኛ እንዳዘኑ ገልጸው፣ ፍትሕ ለማግኘት አቤት ማለታቸውን ተናግረዋል። ድርጊቱን ፈጽመዋል በተባሉ ግለሰቦች ላይ የፀጥታ አካላት ርምጃ መውሰዳቸውን፤ የነቀምቴ ከተማ ሴቶችና ሕፃናት ጽህፈት ቤት የሕግ ባለሞያ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

Feta Daily News

01 Nov, 10:33


https://youtu.be/QrKpazrgvIg?si=dmDtAf_imyx9dS1q

Feta Daily News

01 Nov, 08:33


ሩስያ ጎግል የምድር አጠቃላይ ገንዘብ ተሰብስቦ ሊሞላው በማይችለው 20 ዴሲሊየን ዶላር እንዲቀጣ ወሰነች

የሩሲያ ፍርድ ቤት ጎግል ከዩቲዩብ ላይ የሩሲያ መንግስት የቴሌቪዝን ጣብያዎችን ማገዱን ተከትሎ 20 ዲሲሊየን ዶላር እንዲቀጣ ወስኗል።

ሞስኮ የጠየቀችው ክፍያ ከትሪሊየን ቀጥሎ 7ተኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ የ34 ዜሮ ባለቤት ከፍተኛ ቁጥር ነው።

ጎግል ምንም እንኳን ከአለማችን ትርፋማ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ቢሆንም የድርጅቱ አጠቃላይ ዋጋ ከ2 ትሪሊየን ዶላር የሚሻገር አይደለም።

በዚህም የሩስያ ፍርድ ቤቶች የጣሉት ቅጣት 100 ተመሳሳይ ዋጋ ያላቸው ኩባንያዎች እንኳን ተደምረው ሊከፍሉት የሚችሉት አለመሆኑ ተገልጿል።

Feta Daily News

01 Nov, 07:44


የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የመኖሪያ ፈቃድ ሕግን ተላልፈው ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን የሰጠውን የምህረት አዋጅ ለሁለት ወራት አራዘመ

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግሥት የመኖሪያ ፈቃድ ሕግ ተላልፈው ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች የሰጠውን የምህረት አዋጅ ለቀጣይ ሁለት ወራት ማራዘሙን በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

ኤምባሲው ባለፉት ሁለት ወራት ከኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ማህበር ጋር ባደረገው ጥረት ከ10 ሺሕ የሚልቁ ኢትዮጵያውያን ወረቀት አልባ ዜጎች ያለምንም ቅጣት መኖሪያ ፈቃዳቸውን እንዲያስተካክሉ ወይም እገዳ ተነስቶላቸው አገሪቱን በሕጋዊ መንገድ ለቀው እንዲወጡ ድጋፍ ማድረግ መቻሉን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዑመር ሁሴን ገልጸዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ወራት በተለያዩ ምክንያቶች ከአዋጁ ተጠቃሚ መሆን ያልቻሉ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች ሳይዘናጉ እስከ ፈረንጆቹ ታሕሳስ 31 ቀን 2024 ድረስ ወረቀታቸውን እንዲያስተካክሉም አምባሳደር ዑመር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Feta Daily News

31 Oct, 14:41


ለመሬት መንቀጥቀጥ ለአደጋ ታጋላጭ የሆኑ 700 አባወራዎች መነሳታቸው ተገለጸ

በአፋል ክልል በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በተደጋጋሚ እየተከሰተ የሚገኘው የመሬት መንቀጥቀጥ በዜጎች ላይ አደጋ እንዳያስከትል 7 መቶ የሚሆኑ አባወራዎች ከስፍራው መነሳታቸው ተገልጿል፡፡

ከመስከረም አንድ ጀምሮ በአፋር ክልል በአዋሽ ፈንታሌ በተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ እንደሚገኝ እና ይህም ስጋት መፍጠሩ ነው የተገለጸው። ዘገባው የአሃዱ ነው።

Feta Daily News

31 Oct, 12:34


እስራኤል አዲስ ወታደር ለመመልመል ፈተና እንደገጠማት ተገለጸ❗️

ከአንድ ዓመት በፊት የፍልስጤሙ ሐማስ በእስራኤል ላይ ልተጠበቀ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የተጀመረው ጦርነት አድማሱን እያሰፋ ይገኛል፡፡

ከአንድ ወር በፊት በሊባኖሱ ሂዝቦላህ እና እስራኤል ጦር መካከል ይፋዊ ጦርነት የተጀመረ ሲሆን የእስራኤል ጦር ወደ ደቡባዊ ሊባኖስ ገብቶ ከሂዝቦላህ ተዋጊዎች ጋር እየተዋጋ ይገኛል፡፡

እስካሁን ባሉት ጊዜ ውስጥ እስራኤል 300 ተጠባባቂ ጦሯን የጠራች ሲሆን በጋዛ እና በሊባኖስ በተደረጉ ውጊዎች 367 ወታደሮቿ ተገድለውባታል፡፡

Feta Daily News

31 Oct, 10:13


https://youtu.be/gXn_jd-WV9A?si=SSiDHScoZXRQIKcl

Feta Daily News

31 Oct, 08:24


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽና ማብራሪያ የተወሰደ።
በተያዘው በጀት ዓመት፡-

¶ የኢንዱስትሪ ዘርፉ 12 ነጥብ 8 በመቶ እንደሚያድግ ይጠበቃል

¶ የሌማት ትሩፋት ምርቶች የ5 ነጥብ 4 በመቶ እድገት ያስመዘግባሉ

¶ በዓመቱ 12 ቢሊዮን ሊትር የወተት ምርት ይጠበቃል

¶ 8 ቢሊዮን የዶሮ እንቁላል ለማግኘት ታቅዷል

¶ 218 ሺሕ ቶን ስጋ እና 297 ሺሕ ቶን የማር ምርት ለማምረት እቅድ ተይዟል

¶ በዘንድሮው በጀት ዓመት 8 ነጥብ 4 በመቶ እድገት እንደሚመዘገብ ይጠበቃል

¶ 30 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማረስ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ኩንታል ምርት ይጠበቃል

¶ 72 ትልልቅ ፕሮጀክቶች ስራ ይጀምራሉ

¶ በኢንዱስትሪ ሴክተር 12 ነጥብ 8 በመቶ እድገት ይጠበቃል

¶ በማኑፋክቸሪንግ 12 በመቶ በኮንስትራክሽን ደግሞ 12 ነጥብ 3 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ ታቅዷል

Feta Daily News

31 Oct, 07:41


በስፔን የተከሰተ የተፈጥሮ አደጋ ከባድ ጥፋት አደረሰ

በምስራቃዊ የስፔን ከተማ ቫሌንሺያ በጣለው ከባድ ዝናብ፤ ቢያንስ 72 ሰዎች እንደሞቱ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

Feta Daily News

30 Oct, 14:59


በግጭቶች እና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት 5 ሺሕ 568 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ተገለጸ

በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ ክፍሎች በተከሰቱ እና በቀጠሉ ግጭቶች እንዲሁም በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት 5 ሺሕ 568 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ፡፡

ኮሚሽኑ ዛሬ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ.ም የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሁኔታ ላይ ያተኮረ ባለ 25 ገጽ ዓመታዊ ሪፖርት አውጥቷል።

በሪፖርቱም በትግራይ ክልል 105 ገደማ ትምህርት ቤቶች በጦርነት በመውደማቸውና የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ በመሆናቸው ምክንያት ተገቢውን አገልግሎት እየሰጡ አለመሆኑን ገልጿል።

Feta Daily News

30 Oct, 12:22


የቻድ መንግሥት የቦኮሐራም ታጣቂዎችን ለመደምሰስ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሩን ገለጸ

በመካከለኛዋ አፍሪካዊት ሀገር ቻድ ሐይቅ አካባቢ በሚገኝ የጦር ካምፕ ላይ በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ ዕለት በተፈጸመ ጥቃት 40 የሚጠጉ ወታደሮች መገደላቸው ተገልጿል።

ይህን ተከትሎም የቻድ ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቦኮ ሐራም ታጣቂዎችን ለመደምሰስ ወታደራዊ ዘመቻ ማስጀመራቸው የፕሬዚዳንቱ መግለጫ አስታውቋል።

ቦኮ ሐራም ካሜሩን፣ ናይጄሪያ፣ ኒዠር እና ቻድን በሚያዋስነው በቻድ ሐይቅ አካባቢ ድንገተኛ ጥቃት አድርሶ ብዛት ያላቸው የቻድ ወታደሮችን መግደሉ ነው የተገለጸው።

Feta Daily News

30 Oct, 10:30


https://youtu.be/010Umo8F9Ts?si=mAz4ytsCgldA_Fam

Feta Daily News

30 Oct, 08:26


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትርፍ ሰዓት ክፍያ ያልተከፈላቸው ባለሞያዎች ሥራ አቆሙ

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚገኘው አንጋጫ ሆስፒታል የጤና ባለሞያዎች ትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈላቸው፣ በክልሉ ካምባታ ዞን አንጋጫ ወረዳ የሚገኘውና በአካባቢው ለሚገኙ 2 መቶ ሺሕ ለሚኾኑ ነዋሪዎች አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት ተቋረጠ።

አገልግሎቱ የተቋረጠው ሃኪሞቹን ጨምሮ 80 የሚኾኑ፣ የጤና ባለሞያዎች ለስድስት ወራት የሠሩበት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈላቸው መኾኑን ተናግረዋል። የሆስፒታሉ አገልግሎት የተቋረጠው ካለፈው ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀመሮ ሲኾን ተገልጋይ የኅብረተሰብ ክፍሎች መቸገራቸውን ተናግረዋል።

Feta Daily News

30 Oct, 07:26


ሶማሊያ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት በ72 ሰአታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ በሶማሊያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ውስጥ በአማካሪነት ወይም በካውንስለርነት የሚሰሩት አሊ መሀመድ አደም የተባሉት ዲፕሎማት በ72 ሰአት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መታዛቸውን አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ዲፕሎማቱ ከሀገር እንዲወጡ የታዘዙት ከዲፕሎማሲ ስራዎች የሚጣረስ ተግባር ውስጥ ተሰማርተው በመገኘታቸው ነው ብሏል።

Feta Daily News

29 Oct, 14:28


በወሲባዊ ጥቃት ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች በመምህርነት እንዳይሰማሩ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ ቀረበ

በወሲባዊ ጥቃት ጥፋተኛ የተባሉ ግለሰቦች በመምህርነት እንዳይሰማሩ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቧል። “የአጠቃላይ የትምህርት አዋጅ” በሚል ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማክሰኞ ጥቅምት 19፤ 2017 ዓ.ም. የቀረበው ይህ ረቂቅ አዋጅ በመምህርነት ሥራ ተሰማርቶ የወሲባዊ ጥቃት ወንጀል መፈጸሙ የተረጋገጠበትን ሰውንም በመምህርነት ሥራ እንዳይሰማራ ይከለክላል።

ለምክር ቤቱ የቀረበው ይህ አዋጅ በወሲባዊ ጥቃት ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ሰዎች የግል ትምህርት ቤት እንዳያቋቁሙም ይከለክላል። በተጨማሪም ተማሪዎች ቢያንስ ሦስት ቋንቋዎች እንዲማሩ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ይደነግጋል። በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ስለሚደረግ ምደባ በሚደነገግገው የረቂቅ አዋጁ ክፍል ወሲባዊ ጥቃትን የሚመለከቱ ወንጀሎች መፈጸሙ ተረጋግጦ በፍርድ ቤት ጥፋተኛ መሆኑ የተረጋገጠበት ሰው በማንኛውም የአጠቃላይ ትምህርት ተቋም ውስጥ መምህር ሆኖ መቀጠርን ይከለክላል።

Feta Daily News

29 Oct, 12:13


የወፏ ቤት እንዳይፈርስ ተደረገ

በጀርመኗ ቲዩቢንገን ከተማ በሚገኝ የዩኒቨርሲቲ ክሊንክ ጣሪያ ላይ አንዲት ወፍ ጎጆዋን ቀልሳ መኖር ከጀመረች ከራርማለች። ይህች ወፍ እንደሌሎች ዝርያቸው በመጥፋት አደጋ ላይ ከሚገኙ የወፍ ዓይነቶች አንዷ ናት። የዩኒቨርሲቲ ክሊኒኩ የሕንጻ ማስፋፋት ሥራ ለማከናወን በተሰናዳበት አጋጣሚ በጣሪያው ጎጆዋን ቀልሳ የምትኖረውን ወፍ ይደርሱባታል።

ክሊኒኩም በማስፋፋት ፕሮጀክቱ መቀጠሉን ይገታል። 250 ሚሊየን ዩሮ የሚያወጣው ፕሮጀክትም ለዘጠኝ ዓመታት ባለበት ቆመ። በአካባቢው የሚገኘው ደን ጥበቃውም ቀጠለ፤ ወፏም ያለ ስጋት በጣሪያው ላይ ትኖር ጀመር። የወፎን ሁኔታ በቅርብ የሚከታተሉ ባለሙያዎች ታዲያ ድንገት ወፏ ትሰወርባቸዋለች።

ዘሯ ሊጠፋ ነው የተባለላት ወፍ አለመኖር ግን ወዲያው የታቀደውን የሕንጻ ማስፋፋት ፕሮጀክት መጀመር አላስቻለም። በጥንቃቄና በትዕግሥት ወፏ ወደ ቀለሰችው ጎጆዋ ትመለስ ይሆናል በሚል ተጠበቀች።

ጉዳዩ የግዛቷ ፖለቲከኞችና ምክር ቤት መነጋገሪያ ሆነ። ድመት በልቷት ይሁን ወይም አካባቢውን ለቃ ባልታወቀ ምክንያት የወፏ ከጎርጎሪዮሳዊው 2022 ጀምሮ አለመታየት በደስታ የማስፋፋት ሥራውን ለመጀመር አላጣደፈም። ይልቁንም የለመደችው አካባቢ ነውና ተመልሳ ብትመጣ ጎጆዋ ከፈረሰ የት ትገባለች የሚል ክርክር አስነሳ።

የከተማዋ ከንቲባ ወፏ አሁን እኛ ሳናባርራት ቦታውን ስለለቀች ሥራው መቀጠል ይችላል ቢሉም የጀርመን የተፈጥሮ ጥበቃ ሕግ ባለሙያዎች ግን አንቀጽ እየጠቀሱ ሞገቱ። የአእዋፍ ጥናት ባለሙያዎችም በዚህ እየተሳተፉ ነው። ይህች ወፍ ፈጣሪ አድሏት ጀርመን ሀገር በመኖሯ ጎጆዋ ሳይፈርስ የዩኒቨርሲቲ ክሊኒኩን የማስፋፊያ ፕሮጀክት አጓተተ። ዘገባው የዶቼቬሌ ነው።

Feta Daily News

29 Oct, 11:40


አመራሩ መታፈናቸው ተሰማ❗️

የኢሕአፓ የአዲስ አበባ ኮሚቴ አመራሩ ይስሃቅ ወልዳይ ማንነታቸው ባልታወቁ አካላት ‹‹ መታፈናቸውን ›› ፓርቲው ዋቢ በማድረግ አሻም ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) የአዲስ አበባ ኮሚቴ አመራር ይስሃቅ ወልዳይ ዛሬ ማክሰኞ በመዲናዋ ‹‹ 22 ጌትፋም ›› አካባቢ እስካሁን ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ‹‹ ታፍነው ›› መወሰዳቸውን የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አብርሃም ኃይማኖት ተናግረዋል ሲል ዘገባው አክሎ ገልጿል፡

Feta Daily News

22 Oct, 14:19


ተመድ የኬኒያ ውሳኔ አሳስቦኛል አለ❗️

የኬንያ መንግሥት በመዲናዋ ናይሮቢ ይኖሩ የነበሩ አራት ጥገኝነት ጠያቂ ቱርካውያንን በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል።

ይህ ድርጊትም ሰዎችን ነጻነታቸው እና ሕይወታቸው አደጋ ላይ የሚወድቅበት በመሆኑ ሁኔታው እንዳሳሰበው የመንግሥታቱ ድርጅት አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ከኬንያ ወደ ቱርክ የተመለሱት ስደተኞች ሁኔታ እንዳሳሰበው ገልጿል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ይህንን መግለጫ ያወጣው በኬንያ መዲና ናይሮቢ ባለፈው አርብ ጥቅምት 08/2017 ዓ.ም. በርከት ያሉ ውጭ አገር ዜጎች መታገታቸውን ተከትሎ ነው።

Feta Daily News

22 Oct, 12:32


ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት አዲስ ኮሚሽነር ተሾመ

የተቋሙ ኮሚሽነር የሆኑት ሃና አርዓያስላሴ የፍትህ ሚኒስትር ሆነዉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሾማቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን በምክትል ኮሚሽነርነት ሲመሩ የነበሩት ዘለቀ ተመስገን ( ዶ/ር) የኮሚሽነርነት ቦታን ተረክበዋል።

ዘለቀ ከጣልያን ቱሪን ዩኒቨርሲቲ በህዝብ አለምአቀፍ ሕግ የዶክትሬት ዲግሪ ማጠናቀቃቸው የተገለፀ ሲሆን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንን ከመቀላቀላቸዉ በፊት የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቢሮ ሃላፊ ሆነው አገልግለዋል።

በኢትዮጵያ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሆነው የሰሩት ዘለቀ ተመስገን ( ዶ/ር) የሀገሪቷን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብና ለማበረታታት የተቋቋመውን ተቋም በኃላፊነት እንዲመሩ ተሹመዋል።

Feta Daily News

22 Oct, 10:31


https://youtu.be/jBWO89Yqz8I?si=CTomJ0oBGxLWSiav

Feta Daily News

22 Oct, 08:34


የፊፋ ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ምሽት አዲስአበባ ገቡ

የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) ፕሬዝዳንት ጆያኒ ቪንቼንዞ ኢንፋንቲኖ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) 46ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚደንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) እና የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ(ዶ/ር) እንዲሁም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Feta Daily News

22 Oct, 07:42


በትግራይ ክልል ከጦርነቱ በፊት ለተሰጡ ብድሮች ፖለቲካዊ መፍትሔ ተጠየቀ❗️

በትግራይ ክልል ከተካሄደው ጦርነት በፊት ለንግዱ ማህበረሰብ ተሰጥተው መመለስ ያልቻሉ ብድሮች እና ወለድን በተመለከተ፤ የፌደራል መንግስት “ፖለቲካዊ መፍትሔ” እንዲሰጥ የሚጠይቅ የፊርማ ማሰባሰብ በክልሉ ባሉ 52 ከተሞች እየተካሄደ ነው።

አርብ የተጀመረው የፊርማ ማሰባሰብ በዛሬው ዕለት ተጠናቅቆ “ወደ ክልሉ ማዕከል ይላካል” ተብሎ እንደሚጠበቅ የትግራይ ክልል የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጠቅሶ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

Feta Daily News

21 Oct, 14:19


የቢትኮይን ዋጋ ከሶስት ወራት በኋላ ዳግም አሻቀበ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የብዙዎችን ትኩረት እየሳበ የመጣው የምናባዊ መገበያያ ገንዘቦች ጉዳይ ዋጋቸው ከፍ እና ዝቅ ሲል ቆይቷል።

በያዝነው የፈረንጆቹ 2024 ዓመት መጀመሪያ ወራት ላይ የምናባዊ መገበያያ ገንዘቦች ዋጋ በፍጥነት እየጨመረ ቢመጣም ላለፉት የተወሰኑ ወራት ደግሞ ዋጋቸው ዳግም አሽቆልቁሎ ነበር፡፡
ከነዚህ ምናባዊ መገበያያ ገንዘቦች መካከል አንዱ የሆነው ቢትኮይን ከሰሞኑ ከነበረበት የዋጋ ማሽቆልቆል ወደ መጨመር ተሸጋግሯል።

የቢትኮይን ዋጋ እየጨመረ የመጣው ከሁለት ሳምንት በኋላ በሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ዋነኛ እጩ የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ የማሸነፍ እድላቸው ጨምሯል ከተባለ በኋላ ነው፡፡

Feta Daily News

21 Oct, 12:27


የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል አሁንም ችግር ሆኖ መቀጠሉን ገለጸ

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል ብሎም እየተቆራረጠ በፐርሰንት መከፈል አሁንም ችግር መሆኑን አስታዉቋል፡፡ማህበሩ 37ኛ መደበኛ የምክር ቤት ስብሰባዉን አካሂዷል፡፡

በዚህ ስብሰባ ወቅትም የኑሮ ዉድነት መምህራንን እየተፈታተነ መሆኑን ገልጾ፤ በአንዳንድ ክልሎች የመምህራን ደሞዝ በጊዜ አለመከፈል አሁንም ችግር ሆኖብኛል ብሏል፡፡ያለመምህራን ዕውቅናና ፈቃድ በተለያዩ ምክንያቶች ደሞዝ እንደሚቆረጥ የተነሳ ሲሆን፤ ይሄንን የሚቃወሙ ደግሞ ማዋከብና ማንገላታት እንደሚደርስባቸዉ ተገልጿል፡፡

Feta Daily News

21 Oct, 10:20


https://youtu.be/M8lmD_ADJBU?si=Gof0_476AVzHAt_i

Feta Daily News

21 Oct, 08:34


የእስራኤልን የማጥቃት እቅድ የሚያሳይ ሚስጥራዊ ሰነድ ከአሜሪካ ደህንነት ሾልኮ መውጣቱ ተዘገበ

እስራኤል በኢራን ላይ የምትፈጽመውን የበቀል ጥቃት እቅድ ያሳያል የተባለ ጥብቅ ሚስጥራዊ ሰነድ ከአሜሪካ ደህንነት ሾልኮ ወጥቷል ተብሏል።

አሜሪካ፣ እስራኤል ልትፈጽመው የምትችለውን የማጥቃት እቅድ የሚዳስሰው ሚስጥራዊ ሰነድ እንዴት እንደወጣ ምርመራ እያካሄደች መሆኑን ኤፒ ሶስት የአሜሪካ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።

ኤፒ ያናገራቸው አራተኛው የአሜሪካ ባለስልጣን ሰነዱ ትክክለኛ ይመስላል ብለዋል።

ሰነዶቹ የወጡት ከአሜሪካ ጂኦስፓሺያል ኢንተሊጀንስ ኤጀንሲ ሲሆን እስራኤል ኢራን ባለፈው ጥቅምት አንድ ለፈጸመችባት የባለስቲክ ሚሳይል ጥቃት ምላሽ ለመስጠት መሳሪያዎቿን ጥቃት ለመፈጸም ወደሚያስቸል ቦታ ማንቀሳቀሷን ጠቅሷል።

Feta Daily News

21 Oct, 07:49


የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

8ኛው ዓመታዊ የአፍሪካ ሕብረት የተባበሩትና መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የትብብር ምክክር መድረክ በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በምክክሩ ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝን ጨምሮ የተቋማቱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱ የአፍሪካ ሕብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትብብር ማዕቀፎች አፈጻጸም እንደሚገመገም ኢዜአ በዘገባው አመላክቷል፡፡

ሁለቱ ተቋማት ሰላም እና ደህንነትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸው ትብብር ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ምክክሩን አስመልክቶ ከሰዓት በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ለማወቅ ተችሏል።

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በኢትዮጵያ የስራ ቆይታ ለማድረግ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወቃል። ዋና ፀሐፊው እድሳት የተደረገለትን የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ሕንጻን ይመርቃሉ ተብሎም ይጠበቃል።

Feta Daily News

19 Oct, 14:26


የኔታኒያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ❗️

የሊባኖሱ ሄዝቦላህ ቡድን በእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ተሰምቷል።

የድሮን ጥቃቱ በሰሜን ቴል-አቪቭ ኬሳሪያ አካባቢ የሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ መፈጸሙ ነው የተነገረው።

የእስራኤል ጦር ጥቃቱን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ፤ መነሻው ከሊባኖስ የሆን ድሮን በኬሳሪያ የሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስተር ኔታንያሆ መኖሪያ ቤት ላይ በቀጥታ ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጧል።

ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ እና ባለቤታቸው እንዲሁም ቤተሰቦቻው በቤቱ ውስጥ እንዳልነበሩ እና በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለም ነው የእስራኤል ጦር ያስታወቀው።

Feta Daily News

19 Oct, 12:41


ዘመን ባንክ ከሁለት ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉን ገለጸ

የባንክ ኢንዱስትሪውን ከተቀላቀለ 16 ዓመታትን ያስቆጠረው ዘመን ባንክ 2.39 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን እና ባለፈዉ ዓመት ካገኘዉ ትርፍ 579 ሚሊዮን ወይም 32 በመቶ ጭማሪ ማድረጉን ገልጿል።

የባንኩን እጠቃላይ ሀብት በ23.9 በመቶ በማሳደግ ወደ 59.2 ቢሊየን ብር ያደረሰዉ ባንኩ በተጠናቀቀው ሂሳብ ዓመት መጨረሻ ላይ የደንበኞች ተቀማጭ ገንዘብ 43.61 ቢሊየን ብር ደርሷል ብሏል።

የባንኩ 16ኛዉ የባለአክስዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንደተገለፀዉ የተከፈለ ካፒታሉን 7.5 ቢሊዮን ብር ማድረሱንና ከቀደመው በጀት ዓመት በ2.45 ቢሊዮን ብር ከፍ ያለ መሆኑ ተመላክቷል በአሁኑ ወቅት አጠቃላይ የባንኩ የተፈረመ ከፒታል 14.97 ቢሊየን ብር መሆኑን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

Feta Daily News

19 Oct, 10:33


https://youtu.be/mdTxaz2NaCo?si=he9sQdhvK9i4d6Y_

Feta Daily News

19 Oct, 08:36


በአማራ ክልል ከስልሳ በላይ ሰዎች በኮሌራ መሞታቸው ተሰማ❗️

ባለፉት ስምት ወራት በአማራ ክልል 66 ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ መሞታቸውን የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ከ4 ሺሕ በላይ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ መያዛቸውን ገልጿል።

በተቋሙ የበሽታዎች እና የጤና ሁኔታዎች ምላሽ አፈፃፀም ባለሞያ ሲስተር ሰፊ ድርብ፤ ካለፈው ዓመት መጋቢት ወር መጨረሻ ጀምሮ እስከ ትላንት ጥቅምት 7 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ በ41 ወረዳዎች በተከሰትው የኮሌራ ወረርሽኝ 66 ሰዎች ሲሞቱ ከ4 ሺ በላይ በወረርሽኙ መያዛቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

Feta Daily News

19 Oct, 07:31


የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ወደ ዩክሬን❗️

ሰሜን ኮሪያ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ወታደሮቿን በዩክሬን ምድር ለማስፈር መዘጋጅቷ ተገልጿል።

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቨሎዲሚር ዘለንስኪ በሰጡት ማብራሪያ ሰሜን ኮሪያ የጦር ሀይሏን ከሩሲያ ጦር ሀይል ጎን ለማሰለፍ የጦር ሀይሉም ብዛት ከአስር ሺ በላይ እንደሆነ አስታውቀዋል።

እንደዘለንስኪ ማብራሪያ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ገና እግራችው በሩሲያ በጊዜያዊነት በተያዘው የዩክሬን ምድር እንደረገጠ ነው የታወቀው።

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ/ ዋና ፀሃፊ ሩት በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በዩክሬን ጦርነት ስለመሳተፋቸው የተረጋገጠ መረጃ የለም ነው ያሉት ዘገባው የአይ ኒውስ ነው።