Voa Amharic @voa_amharic1 Channel on Telegram

Voa Amharic

@voa_amharic1


መረጃዎችን ለመላክ @Voa_News_Amharic_bot

Voa Amharic (Amharic)

በዚህ ውጤት እንዴት መናገር እና መልኩንን እንደሚከናወን አስቸጋሪ ግምት አድርገው እንደሚጠይቁ የVoa Amharic ቻንሎች እንደሚነሳዉ እንችላለን። ይህ ቻንላን በአማርኛ በተለያዩ ቀጥሎቻችን መረጃዎችን እንዴት ለመላክ ማንበብ እና አስተማማኝ እንድወንጀሉ ነው። Voa Amharic ቻንሎችን በመሳሪያ ማንበብ ብትገባን በአፍሪካል እና በተለያዩ በዓል ይከተሉ። እንደመጣጥነት ተጠቀምና ማማከር መገበየት እንዳሰጥነት ሊረስን ነው። ተጨማሪ መንገድ በመቅረብ ያሉ ነገሮችና መግለጫዎችን የሚሰጡ በሚሊኒን ቻንሎች ላይ ቅርብ አገልግሎቶች ይሰጣሉ።

Voa Amharic

09 Dec, 10:47


የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በተለያዩ ጊዜያት በእጣ እና በጨረታ ተላልፈው ነዋሪ ያልገባባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የቤት ባለቤቶቹ እንዲገቡባቸው የሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ዛሬ ህዳር 30/2017 ዓ/ም ያበቃል።

ኮርፖሬሽኑ በሰጠው የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የቤት ባለቤቶቹ ወደ ቤታቸው የማይገቡ ከሆነ በህግ አግባብ ውል የሚቋረጥ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።

ቀደም ብሎ የተሰጠው ገደብ ጥምቅት 30 የነበረ ቢሆንም ቤታቸውን አድሰው ለመግባት የጊዜ እጥረት ላጋጠማቸው የቤት ባለቤቶች ተብሎ እስከ ህዳር 30 ተራዝሞ ነበር።

ይህ ለመጨረሻ ጊዜ የተሰጠ የጊዜ ገደብ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ ገልጾ ነበር። ቀኑ ዛሬ ሰኞ ያበቃል። በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የማይገቡ ነዋሪዎች የሽያጭ ውላቸው የሚቋረጥ እና በቤታቸው ውስጥ ለሚፈጸም ማንኛውም ህገወጥ ድርጊት ተጠያቂ እንደሚሆኑ መግለጹ ይታወሳል።

የቤት ባለቤቶች ቢፈልጉ ቤታችሁን አድሰው ማከራየት መብታቸው እንደሆነ፤ የራሳቸው ቤት እስከሆነ ድረስ አድሰው እራሳቸው መግባት መብታቸው እንደሆነ፣ #ማከራት እንደሚችሉም ዞሮ ዞሮ ሰው በቤቱ ሊኖርበት እንደሚገባ ማብራራቱ ይታወሳል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

09 Dec, 10:47


ሶሪያን ሸሽተው ወደ ሞስኮ የተሰደዱት በሽር አል- አሳድ ጥገኝነት እንደሚሰጣቸው ሩሲያ አስታወቀች‼️

የሶሪያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ ደማስቆን ሸሽተው ሞስኮ ይገኛሉ ሲል የሩሲያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ሩሲያ የአሳድ መንግስት ቁልፍ አጋር የነበረች ሲሆን የቀድሞው ፕሬዝዳንት እና ቤተሰባቸው በሩሲያ ጥገኝነት ያገኛሉ ተብሏል። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ አማፂ ቡድኑ ኤችቲኤስ ዋና ከተማይቱን ዘልቆ በገባ ጊዜ አሳድ ሀገር ለቀው ተሰደዋል። የኤች ቲ ሲ መሪ አቡ መሐመድ አል ጃውላኒ በደማስቆ መስጊድ ውስጥ ለተሰበሰበው ሕዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሶሪያ ውስጥ ያሉ ተቃዋሚዎች የሽግግር ባለስልጣን እያቋቋሙ ይገኛል። ሩሲያ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በሶሪያ ሁኔታ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲደረግ ጠይቃለች። ይህም ስብሰባ ዛሬ ሰኞ ይካሄዳል። የሩስያ ባለስልጣናት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቁጥጥር ስር በሶሪያ ግጭት ላይ እልባት እንዲሰጥ የሚደረገው ድርድር መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። ሩሲያ ሁሉም ወገኖች ሰላማዊ የስልጣን ሽግግርን በፖለቲካዊ መንገድ እንዲቆጣጠሩ አሳስባለች። በአል አሳድ የግዛት ዘመን፣ ሶሪያ በመካከለኛው ምስራቅ የሩስያ ጠንካራ አጋር ነበረች።

አል-አሳድ ሩሲያ ለምትሰጣቸው የፖለቲካ እና ወታደራዊ ድጋፍ ምትክ ሩሲያ በታርቱስ የባህር ኃይል ጣቢያ እና በላታኪያ በሚገኘው በሂሚም የአየር ማረፊያ እንዲኖራት ፈቅዷል። ሞስኮ ቅጥረኞቿን ወደ አፍሪካ ሱዳን፣ ማሊ እና መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ለማዘዋወር በታርቱስ የሚገኘውን ጣቢያ ተጠቅማለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በሶሪያ በሚገኘው የሩስያ ጦር ሰፈር ውስጥ የሚገኙ ወታደራዊ ሰራተኞች በተጠንቀቅ ላይ ናቸው ነገር ግን ለደህንነታቸው ምንም አይነት ከባድ ስጋት የለም እና በጦር ሰፈራቸው የሚያሰጋ ነገር የለም ሲል አስታውቋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

09 Dec, 10:47


"መንግሰት ከታጣቂ ሃይሎች ጋር ያለውን ስምምነት ቅርፅ እና ይዘት ለህዝቡ ግልጽ ማድረግ አለበት"- ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ ፓርቲ (ኢዜማ ) ባወጣው መግለጫ በሰላም ስምምነቱ መሰረት እየገቡ ካሉ ታጣቂ ሀይሎች ጋር ያለውን ስምምነት ቅርፅ እና ይዘት መንግስት ለህዝቡ ግልጽ እንዲያደርግ ጠይቋል፡፡

ኢዜማ በመግለጫው አክሎም "ወደ ከተማም ሆነ ወደ ተሐድሶ ሥልጠና የሚገባ ታጣቂ ኃይል በሙሉ ትጥቁን ሙሉ ለሙሉ ለሚመለከተው የጸጥታ አካል አስረክቦ መሆን አለበት" ብሏል::

በመሆኑም በተለያዩ ቦታዎች ታጣቂዎች ወደ ከተማ ሲገቡ የጥይት ተኩስ ማድረጋቸው ንፁሀን ዜጎች ላይ ከፍተኛ ስጋት እና የስነ ልቦና ጫና የሚያሳድር፤ አግባብነት የሌለውም ተግባር መሆኑ ታውቆ በሁሉም ቦታዎች ላይ እንዲቆም አሳስቧል፡፡

ይህን ተከትሎም ትናንት ምሽት ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ የተሰማውን ተኩስ ተከትሎ ለዜጎች ድንጋጤ እና መረበሽ ይቅርታ ቢጠይቅም ታጣቂዎች ሲገቡ በተተኮሰ ጥይት የንጹሀን ዜጎች ህይወት ማለፉ እየተነገረ መሆኑን ፓርታው ጠቁሟል፡፡

"ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው ሕግና ሥርዓትን በማክበር መሆኑ መዘንጋት አይኖርበትም" ሲልም አሳስቧል::

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

09 Dec, 10:47


ኢትዮጵያ ከካርበን ሽያጭ አንድ ነጥብ ስምት ሚሊየን አግኝታለች፣ 388 ሺህ ዜጎቿንም ተጠቃሚ አድርጋለች - ዎርልድ ቪዥን

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ሁምቦና ሶዶ በተባሉ አካባቢዎች የተራቆቱ ተራራዎችን መልሶ በማልማትና አረንጓዴ በማልበስ ከካርቦን ሽያጭ አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱን፣ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ አስታወቀ፡፡ግዥውን የፈጸሙት የአሜሪካና አውሮፓ ውስጥ የሚገኙ ከካርቦን ልቀት ጋር በስፋት የሚሠሩ ትልልቅ ኩባንያዎች መሆናቸው ተገልጿል፤ በአጠቃላይ በፕሮጀክቱ 388 ሺህ ሰዎች ተጠቃሚ መደረጉም ተጠቁሟል።

በወላይታ ዞን በሚገኙ አምስት አካባቢዎች፣ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልልና በሌሎች አካባቢዎች የተራቆቱ ደኖችን መልሶ የማልማት ሥራዎችን በስፋት እየሠራ መሆኑንና እስካሁን ወደ ካርቦን ሽያጭ የገቡት ሶዶና ሁምቦ ብቻ መሆናቸውም ተገልጿል፡፡በዚህም በሶዶ 503 ሔክታር፣ እንዲሁም በሁምቦ 2ሺ 728 ሔክታር የለማ መሬት በየአመቱ ገቢ መገኘቱንና ለማኅበረሰቡ መከፋፈሉ ተጠቁሟል፡፡

የተራቆተ መሬትን መልሶ እንዲያገግም የሚያስችለው ፕሮጀክት በስምንት ክልሎች በሚገኙ 37 ወረዳዎች ላይ እየተተገበረ መሆኑን እና እስካሁን ከ268 ሺህ ሄክታር በላይ መሬትን መልሶ ማልማት መቻሉም ተገልጿል።ፕሮጀክቱ በዞኑ በሚገኙ አምስት አካባቢዎች፣ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልልና በሌሎች አካባቢዎች የተራቆቱ ደኖችን መልሶ የማልማት ሥራዎችን በስፋት እየሠራ መሆኑንና እስካሁን ወደ ካርቦን ሽያጭ የገቡት ሶዶና ሁምቦ ብቻ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ 4 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር የተራቆተ መልክዓ ምድርን መልሶ እንዲያገግም ታቅዶ እየተሠራ እንደሚገኝም መጠቆሙን ከኢፕድና ሪፖርተር ጋዜጣ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

09 Dec, 10:47


የ28 ሰዎች ህይዎት የቀጠፈ የሱዳን ቦምብ ጥቃት

በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በነዳጅ ማደያ ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት 28 ሰዎች ሲሞቱ 37 ሰዎች ቆስለዋል፡፡

የደቡብ ካርቱም የድንገተኛ አደጋ ክፍል በሰጠው መግለጫ፤ በነዳጅ ማደያው ላይ በተወረወረ ቦምብ ነው አደጋው የደረሰው፡፡

ይህም የ28 ሰዎችን ህይዎት በመቅጠፍ ከ37 በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ከማድረሱ ባለፈ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ማስከተሉ ተነግሯል፡፡

ለደረሰው ጥቃት ሃላፊነት የወሰደ አካል እንደሌለ የዥንዋ ዘገባ አመልክቷል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Dec, 18:15


"በየኬላው የሚጠየቀው የኮቴ ክፍያ ከፌደራል መንግሥት እውቅና ውጪ ነው" የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር
በሀገሪቱ የተለያዩ መስመሮች ከጅቡቲ ወደብ ምርቶችን ጭነው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች እና ባለንብረቶች የሚጠየቁት የኮቴ ክፍያ እንዳማረራቸው ሲገልጹ ይደመጣል።

የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፤ ይህ በየኬላው የሚጠየቀው ገንዘብ ከሚመሩት መስሪያ ቤትና ከመንግሥት እውቅና ውጪ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

"ይህ ተግባር የትራንስፖርት ዘርፉን ዋጋ የሚያንር ተገቢ ያልሆነ አሰራር ነው" ሲሉም ተችተዋል።

አሐዱ በተለያየ ጊዜ ያነጋገራቸው የአሽከርካሪ ባለንብረቶች እና ሹፌሮች፤ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኙ ኬላዎች ጭምር የሚጠየቁትን የኮቴ ክፍያ እና የሚደርስባቸውን ጥቃት ሲገልጹ ቆይተዋል።

ሚንስትሩ የክልል መንግሥታትም ጭምር የኮቴ ክፍያን በተመለከተ የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን ገልጸው፤ "የከተማ መስተዳደሮች ገቢያቸውን ለማሳደግ በሚል የሚያደርጉት ነው" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።

ይህንን ችግር ለመፍታት የክልል መንግሥታት አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን በመግለጽም፤ "እርምጃ የሚወሰድበት አሠራር ተዘርግቷል" ብለዋል።

አክለውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎችን እንደሚሠራ የገለጽ ሲሆን፤ የተቀመጠው መመሪያ ተግባራዊ የማይሆን ከሆነ ሌሎች ተጨማሪ ሥራዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ ይህንን ቢሉም የትራንስፖርት ማህበራቱና አሽከርካሪዎች ግን፤ ክፍያውን የሚጠይቁት ከመንግሥት አካል የተደራጁ ስለመሆናቸውና ሕጋዊ ክፍያ ክፈሉ እየተባሉ ስለመሆኑ ገልጸዋል፡፡
  
https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Dec, 18:15


በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ


በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰማው የጦር መሣሪያ ድምፅ የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ሥልጠና ማዕከላት በሚጓዙ የቀድሞ የኦነግ ታጣቂ ቡድን አባላት የተሰማ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

መንግሥት በሀገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች ታጥቀው ለሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ባቀረበው የሠላም ጥሪ መሠረት የኦነግ ታጣቂ ኃይል አባላት የሰላም ጥሪውን ተቀብለው በስፋት እየገቡ መሆኑ ይታወቃል።

የታጣቂ ቡድኑ አባላትን ወደ ተዘጋጀላቸው የተሃድሶ ስልጠና ማዕከላት የማጓጓዝ ስራ በስኬት እየተከናወነ ይገኛል።

በዚህ መሀል ታጣቂዎቹ አዲስ አበባ ከተማን አቋርጠው ወደ ስልጠና ማዕከላት በሚንቀሳቀሱበት ወቅት እየጨፈሩና የደስታ ስሜት እያሰሙ ሲንቀሳቀሱ የተኩስ ድምጽ በማሰማታቸው በከተማው ነዋሪ ህዝብ ላይ ድንጋጤና መረበሽ ሊፈጠር መቻሉን ፖሊስ ገልጿል።

ለተፈጠረው የዜጎች ድንጋጤና መረበሽ ይቅርታ የጠየቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ፤ በቀጣይ ተመሳሳይ ችግሮች እንዳይፈጠሩ ከፍተኛ ጥንቃቄና የማስተካከያ እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን አስታውቋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Dec, 18:15


የታጠቁ የባሕር ላይ ወንበዴዎች በሱማሊያ የባሕር ጠረፍ አካባቢ አንዲት የቻይና አሳ አጥማጅ መርከብ ከሐሙስ ጀምሮ እንዳገቱ መኾኑን ዓለማቀፍ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የባሕር ላይ ወንበዴዎቹ መርከቧን ያገቱት፣ በፑንትላንድ ግዛት የባሕር ጠረፍ አቅራቢያ እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

በመርከቧ ውስጥ ኹለት ጠባቂዎችን ጨምሮ 18 ሠራተኞች እንዳሉ መረጋገጡንና እስካኹን በመርከቧ ሠራተኞች ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

መርከቧን ለማስለቀቅ እየተደረገ ያለ ጥረት ስለመኖሩ ግን የተሰማ ነገር የለም።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Dec, 13:04


በቄለም ወለጋ ዞን የሸኔ ታጣቂዎች የሰላምን መንገድ መርጠው እየገቡ መሆኑ ተገለጸ‼️

በቄለም ወለጋ ዞን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሸኔ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል በደንቢ ዶሎ የሀገር ሽማግሌዎችና አባገዳዎች የዞኑ አመራሮች በተገኙበት ትጥቃቸውን ማስረከባቸው ተገለጸ።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Dec, 13:04


ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት የሚፎካከሩት ሦስት ዕጩዎች የምርጫ ክርክር ሊያደርጉ ነው።

ዓለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርነት የሚፎካከሩት ሦስት ዕጩዎች በቀጣዩ ሳምንት ታኅሳስ 4 በኅብረቱ አዳራሽ የምርጫ ክርክር እንደሚያደርጉ ኅብረቱ አስታውቋል።

የቀድሞው የኬንያ ጠቅላይ ሚንስትርና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዱንጋ፣ የጅቡቲው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሞሐሙድ ዓሊ የሱፍ እና የማዳጋስካሩ የቀድሞ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶ ናቸው የምረጡን ክርክር የሚያደርጉት።

እጩዎቹ ቀደም ሲል ወደየአባል ሃገራቱ እየዞሩ ድምፅ የማሰባስብ ተግባር እንደጀመሩ የሚታወቅ ነው።

የኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ፤ የሥልጣን ጊዜያቸውን በመጭው ጥር ወር በሚያጠናቅቁት ሙሳ ፋኪ ምትክ ቀጣዩን የኮሚሽኑን ሊቀመንበር የሚመርጠው በየካቲት ወር እንደሆነ ይታወቃል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Dec, 13:04


የሶርያው ፕሬዝዳንት በሽር አላሳድ ከስልጣን ተወግደው ከሀገር ኮበለሉ

በሶሪያ ዋና ከተማ የሚገኘውን የህዝብ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ህንፃን አማፂያኑ ተቆጣጥረዋል ። የህዝብ ራዲዮ እና ቲቪ ህንፃ በሶሪያ ውስጥ ጠቃሚ፣ ተምሳሌታዊ ቦታ ነው። ህንፃው በደማስቆ እምብርት ውስጥ ከመገኘቱ በተጨማሪ በሶሪያ በ 1950 ዎቹ እና 60 ዎቹ ተከታታይ መፈንቅለ መንግስት በነበረበት ጊዜ አዳዲስ መንግስታትን ስልጣን መያዛቸውን ለማወጅ ጥቅም ላይ ውሏል ።የአማፂው ቡድን ኤች ቲ ኤስ ወደ ሶሪያ ዋና ከተማ መግባት መጀመሩን ባሳወቀበት ወቅት የበሽር አላሳድ ከሀገር መኮብለል ዘገባዎች ወጥተዋል።

አማፅያኑ በሺዎች የሚቆጠሩ የተቃዋሚ ደጋፊዎቻቸው ተሰቃይተዋል እና ተገድለዋል ከተባለበት ከሳይድናያ እስር ቤት እስረኞችን ማስፈታታቸውን ተናግረዋል።የታጠቁት ተቃዋሚዎች "አዲሲቷ ሶሪያ" ሰላማዊ አብሮ የመኖር ቦታ ትሆናለች፣ ፍትህ የሚሰፍንበት እና የሁሉም የሶሪያውያን ክብር ይጠበቃል ሲሉ ተደምጠዋል። ያለፈውን ገጽ ቀይረን ለወደፊቱ አዲስ አድማስ እንከፍታለን ሲሉ አማፅያኑ ባወጡት መግለጫቸው ተናግረዋል።

የሮይተርስ የዜና ወኪል ምስክሮችን ጠቅሶ እንደዘገበው በሺዎች የሚቆጠሩ በመኪና እና በእግር የሚጓዙ ሰዎች በማዕከላዊ ደማስቆ “ነጻነት!” እያሉ በመሰብሰብ ላይ ናቸው። በኦንላይን የተለጠፉት ቪዲዮዎች በአልጀዚራ የተረጋገጠ በኡማያድ አደባባይ ላይ በርካታ ሰዎች በወታደራዊ ታንክ ላይ ቆመው በደስታ ሲዘፍኑ ያሳያሉ።

የሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ አውሮፕላን ተሳፍረው ወዳልታወቀ ቦታ ሄደዋል። ከሀገር መኮብለላቸውን የሚያውቁ ሁለት ስማቸው ያልተጠቀሰ ከፍተኛ የጦር መኮንኖችን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። ቅዳሜ ቀደም ብሎ አል አሳድ ደማስቆን ለቀው መጥተዋል መባሉን የሶርያ መንግስት አስተባብሏል። የሶርያ መንግስታዊ የዜና ወኪል በደማስቆ እንዳሉ እና ስራቸውን ከዋና ከተማዋ እያከናወነ መሆኑን ገልጾ ነበር። ሆኖም ፕሬዚዳንቱ የት እንዳሉ አይታወቅም እና ለቀናት እንዳልታዩ ተዘግቧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

07 Dec, 15:54


በሰሜን ወሎ ሲኖትራክ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በርካቶች መገደላቸውን የዓይን እማኞች እና የተጎጂ ቤተሰቦች ተናገሩ!

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ባለፈው ሳምንት 'ሲኖ ትራክ' በተባለ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 50 የሚሆኑ ሰዎች እንደተገደሉ የዓይን እማኞች እና የተጎጂ ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናገሩ።

ጥቃቱ የደረሰው ዞኑ ዳውንት ወረዳ ውስጥ ባለፈው ሐሙስ ኅዳር 19/2017 ዓ.ም. ቀትር 8፡00 አካባቢ መሆኑን የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች የጥቃቱ ሰለባዎች ከተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኩርባ ከተማ ሲመለሱ የነበሩ ሰዎች ናቸው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ስለ ጥቃቱ ጥቆማ እንደደረሰው እና መረጃ እያሰባሰበ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግሯል። ሐሙሲት የተባለ ገበያ ከሚውልበት ሾጋ አካባቢ ወጣ ብሎ ልዩ ስሙ ሰጎራ በተባለ አካባቢ ጥቃቱ መድረሱንም የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

በአካባቢው ባለው የትራንስፖርት ችግር ምክንያት በጭነት ተሽከርካሪዎች መጓዝ የተለመደ መሆኑን የተናገሩት ነዋሪዎች፤ ያለፈው ሳምንት ጥቃት አሸዋ እና ሰዎችን በጫነ 'ሲኖ ትራክ' በተባለው ተሽከርካሪ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። ገበያ ውለው ሲመለሱ የነበሩ ገበያተኞች፣ አርሶ አደሮች፣ ለሥራ ፍላጋ ከአጎራባች ዋድላ ወረዳ ሲመለሱ የነበሩ ወጣቶች እንዲሁም ከደላንታ ወረዳ ክርስትና ደርሰው ሲመለሱ የነበሩ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባዎች እንደሆኑ ተናግረዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

07 Dec, 15:54


የሰላም አማራጭን መቀበል አዋቂነት ነው- ጃል ሰኚ ነጋሳ

የሰላም አማራጭን መቀበል ብልህነትና አዋቂነት መሆኑን በመገንዘብ በጫካ የሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት የመንግሥትን ጥሪ እንዲቀበሉ የሠራዊቱ የቀድሞ ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ ጥሪ ማቅረባቸውን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል፡

የሀገሪቱን መካላከያ የክብር ልብስ ለብሰዉ መግለጫ መስጠታቸዉ ብዙዎችን ያነጋገረ ድርጊት ሆኖል ፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

07 Dec, 15:54


በመላው ሀገሪቱ የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ ነው - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

ዛሬ ማምሻውን በሲስተም አለመረጋጋት በተፈጠረ ችግር የተነሳ በመላው ሀገሪቱ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።

ችግሩን በመፍታት የተቋረጠውን ኃይል ወደነበረበት ለመመለስ በኃይል ማመንጫዎች እና በማከፋፈያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ ነው ብሏል።

የተፈጠረው ችግር እስኪፈታ ድረስ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቆ፤ ያሉትን መረጃዎች በፍጥነት የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

06 Dec, 19:31


ህወሓት በመቐለ ከተማ የጠራው ሰልፍ ፍቃድ ሳያገኝ ቀረ

የመቐለ ህወሓት ፅሕፈት ቤት "የጊዝያዊ አስተዳደሩን ህገ ወጥ" አሰራር በመቃወም በመቀለ ከተማ ሰላማዊ ሰለፍ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩን ፍቃድ መጠየቁ ይታወሳል።

ለዚሁ ጥያቂ መልስ የሰጠው የመቀለ ከተማ አስተዳደርም በአሁኑ ሰዓት በመቐለ ከተማ ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ አይቻልም ማለቱን VOAሰምቷል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

06 Dec, 19:31


ቱርክ፣ ኢራን እና ሩሲያ በሶሪያ ጉዳይ በዶሃ ሊወያዩ መሆኑ ተገለጸ።

የቱርክ፣ የኢራን እና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፈጣን በሆነው የሶሪያ አማጺያን ግስጋሴ ጉዳይ በነገው እለት በኳታር ዶሃ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ሮይተርስ ዘግቧል።

አማጺያኑ የሶሪያ የእርስበርስ ጦርነት ከተጀመረ ከ13 አመታት በኋላ በጦር ሜዳ ከፍተኛ ድል በመጎናጸፍ፣ በበሽር አላሳድ አገዛዝ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሰዋል።

ለበርካታ አመታት በሀገሪቱ ሰሜን ምዕራብ ክፍል ለበርካታ አመታት መሽገው የነበሩት አማጺያኑ በሀያት ታህሪር አል ሻም በተባለው ቡድን በመመራት ባለፈው ሳምንት የሶሪያን ትልቅ ከተማ አሌፖን ተቆጣጥረው፤ በደቡብ በኩል ወደ ሀማ ከተማ መግፋት ችለው ነበር።

አማጺያኑ በትናንትናው እለት ደግሞ ሁለተኛዋን ትልቅ ከተማ ሀማን ተቆጣጥረዋል።

ቱርክ፣ ሩሲያ እና ኢራን 'አስታና ፒስ ፕሮሰስ' በተባለ ማዕቀፍ በሶሪያ የወደፊት እጣፊንታ ላይ የሶስትዮሽ ምክክር ያደርጋሉ።

የኔቶ አባሏ ቱርክ ተቃዋሚዎችን የምትደግፍ ሲሆን ሩሲያ እና ኢራን ደግሞ የአሳድ አገዛዝን እንደሚደግፉ ይገለጻል።

ሮይተርስ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ሶስት ሚኒስትሮች ከዶሃ ፎረም ጎንለጎን በነገው እለት ይገናኛሉ።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

06 Dec, 19:31


የሶማሊያ መንግስት ወደ ጁባላንድ ኪስማዮ ምንም አይነት በረራ እንዳይደረግ መከልከሉ ተጠቆመ!

የሶማሊያ ፌደራል መንግስት ወደ ጁባላንድ አስተዳደር ዋና መቀመጫ ኪስማዮ ምንም አይነት በረራዎች እንዳይደረጉ መከልከሉ ተገለጸ።በሶማሊያ ፌደራል መንግስቱ እና በጁባላንድ አስተዳደር መካከል የተፈጠረው ልዩነት እጅግ መካረሩን ተከትሎ የፌደራል መንግስቱ ወደ ኪስማዮ የሚደረጉ በረራዎች መከልከሉን የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።

የፌደራል መንግስቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር ወደ ጁባላንድ አቅራቢያ እያሰፈረ መሆኑን የጠቀሙት ዘገባዎቹ የሶማሊያ መንግስት ለአየር መንገዶች በሰጠው ቀጥታ መመሪያ ወደ ኪስማዮ እንዳይበሩ ተዕዛዝ ማስተላለፉን አመላክተዋል።ከሶማሊያ መንግስት ቀደም ብሎ የጁባላንድ አስተዳደር በሶማሊያ የሚንቀሳቀሱ አየር መንገዶች ወደ ራስካምቦኒ ከተማ ምንም አይነት በረራ እንዳያደርጉ መከልከሉን ዘገባዎቹ አስታውሰዋል።

ውሳኔውን ተከትሎም ስትራቴጂክ ወደ ሆነችው የኪስማዮ ከተማ የሚደረጉ የትራንስፖርት አገልገሎቶች የደህንነት ስጋት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡የጁባላንድ ክልል ከፌደራል መንግስቱ እውቅና ውጭ ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደችው ምርጫ አህመድ ማዶቤን በድጋሚ ፕሬዘዳንት አድርጋ መምረጧን ያወሱት መገናኛ ብዙሃኑ የጁባላንድ ፕሬዝዳንት አህመድ ማዶቤ የሶማሊያ ፌደራል ጦር ከራስካምቦኒ ከተማ በ15 ቀናት ውስጥ የማይወጣ ከሆነ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስዱ ማስጠንቀቃቸውንም አስታውሰዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

06 Dec, 19:31


የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ለውጭ ውድድር ሊከፈት መሆኑ ተሰማ!

ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የባንክ ዘርፉን ለውጭ ውድድር ለመክፈት በዝግጅት ላይ ትገኛለች። ይህን ተከትሎ በአሁኑ ወቅት አዲስ ህግ በፓርላማ እየተገመገመ እና በሚቀጥለው ወር ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

ይህ ወሳኝ ውሳኔ በሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ገጽታ ላይ ከፍተኛ ለውጥን የሚያመለክት ሲሆን ይህም ውድድርን ለማሳደግ፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እና የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ያለመ ነዉ ተብሏል ።

ርምጃው በኢትዮጵያ መንግስት እና በብሄራዊ ባንክ የተጀመሩት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች አካል ሲሆን እነዚህ ማሻሻያዎች የተነደፉት የፋይናንስ ሴክተሩን ለማዘመን እና ለሀገር ውስጥ እና ለአለም አቀፍ ንግዶች የበለጠ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ጭምር ነዉ።

የውጭ ባንኮችን ወደ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ምኅዳር ማስገባቱ ፉክክር እንደሚያመጣ የሚጠበቅ ሲሆን ይህም ለተጠቃሚዎች የተሻሻሉ አገልግሎቶችን እና ምርቶችን ሊያመጣ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

06 Dec, 19:31


የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ተብሏል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

06 Dec, 12:28


“በሶስት ወራት ብቻ በህገወጥ መንገድ ለስደት ከተዳረጉ 6ሺ ወጣቶች 294ቱ ህይወታቸው አልፏል” - የትግራይ ክልል

ባለፉት ሶስት ወራት በህገወጥ መንገድ ለስደት ከተዳረጉ ከስድስት ሺ በላት ወጣቶች ውስጥ 294 የሚሆኑት ህይወታቸው ማለፉን የትግራይ ክልል የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ።ህገወጥ ስደት የበርካታ የክልሉን ወጣቶች ህይወት እየቀጠፈ ነው፣ የወጣቶች ህገወጥ ስደት የሁሉም ሰው አጀንዳ መሆን አለበት ሲሉ የቢሮው ሃላፊ አቶ ሓይሽ ስባጋድስ አሳስበዋል።

ይህ የተገለጸው የወጣቶች ህይወት በመቅጠፍ ላይ ያለውን ህገወጥ ስደት በጋራ መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር በመቀለ ከተማ ትላንት ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም በተዘጋጀው በመድረክ ላይ ነው።የቢሮው ሃላፊ አቶ ሓይሽ ስባጋድስ መንግስት እና ሁሉም አጋር አካላት ህገወጥ ስደትን የሚያባብሱ ተግባራትን በማስወገድ ሚናቸውን እንዲወጡ ጠይቀው በተለይም ዋነኛ ተዋናይ የሆኑትን የደላሎችን ሰንሰለት ለመበጣጣስ መስራት ይኖርበታል ሲሉ አሳስበዋል፤ መንግስት ለወጣቶች በቂ ድጋፍ ማድረግ ይገባዋል ሲሉም ጠይቀዋል።

በክልሉ እስከ ቀበሌ ድረስ ያለው የመንግስት አካል የጉዳዩ ክብደት በመረዳት እርብርብ ሊደረግ ይገባዋል ብለዋል፤ ቤተሰብ የልጆቹ ጉዳይ እንዲያሳስበው እየሰራን ነው ሲሉ ጠቁመዋል።በመድረኩ ላይ የተገኙት የመንግስታቱ ድርጅት ተወካይ ፀሃየ ወ/ጊዩርጊስ በኢትዮጵያ ከሚሰደዱ ወጣቶች መካከል 46 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ሲሉ መግለጻቸውን ከትግራይ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

06 Dec, 12:28


የደቡብ ኮሪያ ገዢው ፓርቲ መሪ የፕሬዝዳንት ዮን ስልጣን እንዲታገድ ጠየቀ

የደቡብ ኮሪያ ገዥ ፓርቲ መሪ የፕሬዚዳንት ዩን ሱክ-ዮል ስልጣን በፍጥነት እንዲታገድ የጠየቁ ሲሆን ፕሬዝዳንቱ የማርሻል ህግን ማወጃቸውን ተከትሎ የፖለቲካ መሪዎችን ለማሰር እንደፈለጉ "ተአማኒ ማስረጃ" አለ ብለዋል።

ቀደም ሲል ዮንን ለመክሰስ የሚደረገውን ጥረት እንደሚቃወሙ የገለፁት የፒፕል ፓወር ፓርቲ መሪ ሃን ዶንግ-ሁን “አዲስ እየወጡ ባሉ መረጃዎች ግን በፕሬዚዳንቱ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞን እያሳዩ ይገኛል። ፕሬዚዳንቱ የመከላከያ ኢንተለጀንስ አዛዥ ዋና ዋና የፖለቲካ መሪዎችን እንዲይዝ ፀረ-መንግስት ሃይሎች እንደሆኑ በመግለጽ እና የስለላ ተቋማትን በሂደቱ እንዲያንቀሳቅስ እንዳዘዙ ተረድቻለሁ ሲሉ ሃን ተናግረዋል። ሃን አክለውም “ይህች አገር ወደ ሌላ ትርምስ እንዳትገባ ለመከላከል፣ የክስ መቃወሚያ ሂደት እንዳይቋሩጥ ለማድረግ እሞክራለሁ ሲሉ ተናግረዋል። ደቡብ ኮሪያን እና ህዝቦቻችንን ለመጠበቅ ፕሬዝዳንት ዩን እንደ ፕሬዝደንት ስልጣናቸውን በፍጥነት እንዳይጠቀሙ ማስቆም አስፈላጊ ነው ብዬ አምናለሁ ብለዋል።

ሃን ፕሬዝዳንት ዩን የማርሻል ህግ መግለጫው ህገወጥ እና ስህተት መሆኑን አምነው መቀበል አልቻሉም ሲሉ አክለዋል። በስልጣን ላይ ከዚህ በላይ ከቆዩ እንደገና ተመሳሳይ ጽንፍ ያለው እርምጃ ሊወስዲ ይችላል የሚል ትልቅ ስጋት አለኝ ሲሉ አክለዋል።ደቡብ ኮሪያ ማክሰኞ ምሽት ላይ ለስድስት ሰአታት ያህል በማርሻል ወይም ወታደራዊ ህግ ስር ወድቃ የነበረች ሲሆን ፕሬዝዳንት ዮን እርምጃው መተግበሩን ለህዝቡ ያሳወቁት በድንገተኛ በቴሌቭዥን ላይ ቀርበው ነው።ለእርምጃው ምክንያት ሲሉ የገለፁት ከ"ፀረ-መንግስት ኃይሎች እና ከሰሜን ኮሪያ ደጋፊዎች የሚሰነዘሩ ዛቻዎችን ጠቅሰዋል። የብሄራዊ ምክር ቤቱ የዩኑን ትዕዛዝ በ190 ተቃውሞ ያለ አንዳች ድጋፉ በፍጥነት ውሳኔው እንዲሻር አድርገዋል።

ዩን በአሁኑ ወቅት ከስልጣን ከተነሱት የመከላከያ ሚኒስትር ኪም ዮንግ-ህዩን ፣የጦር ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል ፓርክ አንሱ እና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሊ ሳንግ ሚን ጋር በመሆን በሀገር ክህደት ወንጀል ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኝ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።የፍትህ ሚኒስትር የሆኑት እና በገዢው ፒ.ፒ.ፒ. ውስጥ የፕሬዝዳንት ዮን ከፍተኛ ተቀናቃኝ አንዱ የሆኑት ሃን ተቃውሞ ገዥው ፓርቲ ለችግሩ የሚሰጠውን ወሳኝ ምላሽ ለውጥ ያሳያል ተብሏል። ተቃዋሚው ዴሞክራቲክ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ዮንን ለመክሰስ ቅዳሜ ምሽት ድምጽ እንዲሰጥ ጠይቋል።

ነገር ግን 300 አባላት ባለው የብሄራዊ ምክር ቤት ውስጥ አስፈላጊውን ሁለት ሶስተኛ ደረጃ ላይ ለመድረስ ከገዥው ፓርቲ ቢያንስ ስምንት ድምጽ ያስፈልገዋል።አቤቱታው ከተሳካ፣የደቡብ ኮሪያ ሕገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ዮንን ከስልጣን እንዲወገዱ ውሳኔ ይሰጣል።እ.ኤ.አ. በ2016 የቀድሞ ፕሬዚደንት ፓርክ ጊዩን ሃይ ከስልጣን መነሳቷን ተከትሎ እንደተከሰችው አሁን ላይ ገዢው ፒፒፒ ፓርቲ የዮንን መከሰስ እንደሚቃወም አንዳንድ ተንታኞች ጠቁመዋል።ፓርክ ባምህረት ከመለቀቋ በፊት በሙስና ወንጀል የ20 አመት እስራት ተፈርዶባት እንደነበር ይታወሳል።ዩን ሳይጨምር፣ በ1980ዎቹ መገባደጃ ላይ ሀገሪቱ ወደ ዲሞክራሲ ከተሸጋገረችበት ጊዜ አንስቶ ከነበሩት ሰባት ፕሬዚዳንቶች አራቱ በሙስና ተከሰው ወይም በሙስና ተጠርጥረው ታስረዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

06 Dec, 12:28


ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጦር ወደ ሶማሊያ ልካለች ተባለ!

በፌደራሉ መንግስት እና በጁባላንድ ክልላዊ መንግስት መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ቁጥራቸው በውል ያልተገለጸ የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ በምትገኘው ዶሎው ከተማ ገብተዋል ሲል ካስሚዳ የተባለው የዜና ድረ-ገጽ ትናንት ዘግቧል።«የኢትዮጵያ መንግስት ትናንት በደርዘን የሚቆጠሩ ወታደራዊ  ተሽከርካሪዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ጭኖ በሶማሊያ ዶሎው ግዛት ጌዲኦ ወረዳ ገብቷል» ሲል ዘገባው አመልክቷል።

ዘገባው የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ በታችኛው ጁባ ክልል በደቡባዊ ራስ ካምቦኒ ከተማ ከሚያደርጉት  ጉብኝት ቀደም ብሎ ነው።የኢትዮጵያ ወታደሮች ወታደራዊ ድጋፍ ላደረጉት የጁባላንድ ክልል ፕሬዝዳንት አህመድ ማዶቤ በመንግስት ሃይሎች ላይ “ወታደራዊ ድጋፍ ሊሰጡ እንደሚችሉ” ቪዛ ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በሶማሊያ የሚገኙ አማፂ ቡድኖችን ትደግፋለች የሚለው ወቀሳ እና የሁለቱ መንግስታት ውዝግብ ተባብሶ የቀጠለው፤ ራሷን እንደ ሀገር ከምትቆጥረው  እና ሶማሊያ የግዛቴ አካል ከምትላት የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ ጋር   የመግባቢያ ሰነድ  መፈራረማቸውን ተከትሎ ነው።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

06 Dec, 12:28


በኦሮሚያ ክልል የ11 ዓመት ጨምሮ እድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህጻናት ለውትድርና ተመልምለዋል - ኢሰመኮ

በኦሮሚያ ክልል ከመከላከያ የምልመላ መስፈርት ውጪ ሕፃናትን በግዳጅ ለወታደርነት እየተመለመሉ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ትላንት ህዳር 26 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ተቸ።

ኢሰመኮ በመግለጫው ባደረኩት ክትትል እና ምርመራ የ11 አመት ህጻን ለወታደርነት ሞያ ተመልምሎ በማቆያ ቦታ አግኝቸዋለሁ ሲል ጠቁሟል፤ በተጨማሪም ዳቦ ለመግዛት ከቤት የወጣ የ15 ዓመት ጨምሮ እድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱ ህጻናት ተመልምለዋል ሲል ድርጊቱን ኮንኗል።

የተያዙትን ለመልቀቅ ቤተሰቦቻቸው ገንዘብ እንዲከፍሉ ስለመገደዳቸው መረጃዎች ደርሰውኛል ብሏል።ኢሰመኮ ክትትል እና ምርመራ ባደረገባቸው አንዳንድ አካባቢዎች ተይዘው የነበሩ ሕፃናትን እና የአእምሮ ሕሙማንን ጨምሮ በግዳጅ የተያዙ በርካታ ሰዎችን ለማስለቀቅ መቻሉን ጠቁሟል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Dec, 18:46


በትግራይ ክልል ባለው ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የአስተዳደርና የፀጥታ ሁኔታ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ውይይት ተካሄደ!

በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል ባለው አጠቃላይ የፖለቲካ፣ የአስተዳደር እና የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ ካሉ የፖለቲካ እና የፀጥታ አመራሮች ጋር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም ላይ በክልሉ የሚታዩ ችግሮችን እንዴት በጋራ መፍታት እንደሚገባ ምክክር ተደርጓል።በተደረገው ምክክርና ውይይት በተለዩ አንኳር ጉዳዮች ላይ በተቀመጡ የጋራ አቅጣጫዎች መሠረት በጋራ ለመስራት እና የክልሉን ህዝብ የፀጥታ፣ የመልካም አስተዳደር እና የልማት ፍላጎት ለማሟላት አስቻይ ሁኔታ ለመፍጠር መግባባት ላይ ተደርሷል።

በተለይም ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀዬአቸው እና የቀድሞ ታጣቂዎችን ደግሞ ወደ መደበኛ ሕይወት የመመለሱ ሂደት በትኩረት በሚሰራበት እና በሚሳለጥበት ሁኔታ ላይ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በተጨማሪም በክልሉ ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶች አጠቃቀም የህዝብን እና የሀገርን ጥቅም በሚያስጠብቅ ሕጋዊ አግባብ እንዲሆን፣ ለህዝብ የሚቀርቡ የመንግሥት አገልግሎቶች የህዝብን ፍላጎት በሚመጥን አግባብ በሚሻሻሉበት ሁኔታ ላይ ቀጣይነት ያለው ጠንካራ ስራ እንዲሰራ በውይይቱ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በመጨረሻም የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ክልላዊ ምርጫ እስኪያካሂድ ድረስ ያለበትን ኃላፊነት ለመወጣት በሚያስችለው አግባብ ላይም አቅጣጫ በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቅቋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Dec, 18:46


በሰሜን ወሎ ዞን ሌሊት ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት የ83 ዓመት እናት ተገደሉ

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ “ብልባላ” በተባለች መንደር ባለፈው ማክሰኞ ሌሊት በተፈፀመ የድሮን ጥቃት አንዲት የ83 ዓመት እናታቸው እንደተገደሉባችው የሟች ልጅ ተናገሩ።

ህዳር 24 ቀን 2017 ዓም ሌሊት 5፡30 አካባቢ በተፈጸመው ጥቃት ሌሎች ሁለት በግቢው ተከራይተው በሚኖሩ የጤና ባለሙያዎች ላይም የአካል ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

በግቢያቸው ከነበሩ ክፍሎች መካክል ሶስቱ እንዳልነበር ሆነው ሲፈርሱ በጥቃቱ ከተመቱ ክፍሎች በአንዱ የነበሩት እናታቸው ሰጋቸው ተበጣጠሶ ህይወታቸው አልፏል ሲሉ ልጃቸው ቀሲስ ይትባረክ አድማሱ ነግረውናል።

ቀብራቸው በወግ ባህል መስረት ፍትኃት ሳይደረግ መቀበራቸውን ያስታወቁት ልጃቸው ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ ተጨማሪ ጥቃት ይደርሳል ከሚል ሰጋት ህብረተሰቡ ተሰብስቦ ሥርዓቱን ማከናወን ባለመቻሉ መሆኑን እንደገለጹለት የጀርመን ድምጽ በዘገባው አስታውቋል።
በመኖሪያ ቤቱ አካባቢም ሆነ በግቢው ውስጥ ታጣቂዎች እንዳልነበሩ የገለፁልን ቀሲስ ይትባረክ፣ ግቢው ከዚህ በፊት የመኝታ አገልግሎት ይሰጥ እንደነበር ጠቅሰው ከሰሜኑ ጦርነት ወዲህ ግን ገበያው የተቀዛቀዘ በመሆኑ ከቤተሰብ የተረፉ ክፍሎችን ለመንግሥት ሠራተኞች ሲያከራዩ እንደነበር ተናግረዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Dec, 18:46


በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች አለመግባባት ምክንያት #የመቀለ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ታሽገ!

በሁለቱ የህወሓት ቡድኖች ከንቲባ የተሾመላት የትግራይ ክልል ርዕሰ መዲና መቀለ፣ የከንቲባ ጽሕፈት ቤቷ መታሸጉ ተገለጸ።በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነትና መከፋፈል እየተባባሰ በመምጣቱ፣ የመቐለ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ላለፉት ሦስት ቀናት "ታሽጓል" የሚል ጽሑፍ እንደተለጠፈበት ተጠቁሟል።

ሁለቱም ቡድኖች "የየራሳቸው ከንቲባ ሾመዋል" በሚል እርስ በእርስ እየተወቃቀሱ ሲሆን ሁለቱም ለከተማዋ ከንቲባ ሾመዋል።በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም ዶ/ር ረዳኢ በርኸን የከተማዋ ከንቲባ አድርጎ ያሾመ ሲሆን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንተ አቶ ጌታቸው ደግሞ ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም አቶ ብርሃነ ገ/እየሱስን ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

ከህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የከተማዋ የከንቲባ ጽሕፈት ቤቷ መታሸጉን መመልከቱን ቪኦኤ በዘገባው አስታውቋል፣ ሌሎች የከተማዋ አስተዳደር ቢሮዎች ግን አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ጠቁሟል።በደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት እና በጊዜያዊ አስተዳደሩ መካከል ያለው ልዩነት እየተካረረ ከመምጣቱ ባለፈ እውቅና እስከመነፋፈግ ደርሰዋል።

“ከፕሪቶሪያ ስምምነት አግባብ ውጭ በሆነ መንገድ ጊዚያዊ መስተዳድሩ በግለሰቦች እጅ ወድቋል” ሲሉ በዶ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው የህወሓት ቡድን ምክትል ሊቀ መንበር አቶ አማኑኤል አሰፋ ህዳር 18 ቀን 2017 ዓ.ም መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

በሌላ በኩል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መስከረም 27 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በክልሉ ስርአት አልበኝነት እንዲፈጠር እየሰራ ነው ባለው የእነ ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) “የህወሓት ቡድን ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እወስዳለሁ” ማስጠንቀቁን የተመለከተ ዘገባ ማቅረባችንም ይታወሳል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

20 Nov, 15:54


ሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውሳኔን አትቀበልም ሲሉ  ጀነራል አብደል ፈታህ አልቡርሃን ተናገሩ

የሉዓላዊው ምክር ቤት ፕሬዝደንትና የሱዳን ጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን፣ የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ በራሺያ ድምፅን በድሞፅ የመሻር መብት ተጠቅመው የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔን ውድቅ አድርገውታል።

በፖርት ሱዳን በተካሄደው የኤኮኖሚ ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ያደረጉት አል-ቡርሃን የውሳኔ ሃሳቡን ለፈጣን የድጋፍ ሰጪ ሃይሎች የጦር መሳሪያ በማቅረብ ረገድ የውጭ ተዋናዮችን ሚና ባለመቀበል ተችተዋል። አል-ቡርሃን ሱዳን ከጦርነቱ በኋላ ከዓለም አቀፍ ተዋናዮች ጋር የሚኖራት ግንኙነት በግጭቱ ወቅት ባላቸው አቋም እንደሚወሰን አጽንኦት ሰጥተዋል።

አርኤስኤፍ ቀደም ሲል በጅዳ የተካሄደውን የተኩስ አቁም ስምምነት እንደገና ለማስታጠቅ እና የከተሞችን ከበባ ለማጠናከር ውሏል ሲሉ ከሰዋል። ጦር አዛዡ በውስጥ በኩል መፍትሄ ለመፈለግ እና የውጭ ጣልቃ ገብነትን እንደሚቃወሙ ገልፀው ጦራቸው በሱዳን ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች ላይ ድል ለመጎናፀፍ መቃረቡን ተናግረዋል። አል-ቡርሃን የተኩስ አቁም ስምምነትን ለመቀበል ቅድመ ሁኔታዎችን ዘርዝረዋል።

የአርኤስኤፍ ኃይሎች ከተያዙ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ለቀው እንዲወጡ እና በተመረጡ ካንቶን ቦታዎች እንዲሰበሰቡ አሳስበዋል።  ይህም የሰሜን ዳርፉር ዋና ከተማ የሆነችውን ኤል ፋሸር ከበባ ለማንሳት እና የዜጎችን እና የዕርዳታ አቅርቦት ነጻ እንቅስቃሴን ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል። "ሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች ከገባችባቸው አካባቢዎች በሙሉ መውጣትን የማያካትት ማንኛውንም የተኩስ አቁም ወይም ጦርነት ማቆም አትቀበልም" ሲለ አል-ቡርሃን ተደምጠዋል።

መንገዶችን ለመክፈት እና ሰብአዊ ተደራሽነትን ለማሳለጥ አርኤስኤፍ በተለዩ ቦታዎች መሰብሰብ እንዳለበትም አሳስበዋል። የአል-ቡርሃን አስተያየት የሱዳን መንግስት ግጭቱን በራሱ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያጎላ ሲሆን ይህም የአለም አቀፍ ጣልቃ ገብነትን አለመቀበል እና በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች ላይ ወታደራዊ ድልን ለማምጣት ትኩረት የሰጠ ነው ተብሎ ታምኖበታል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

20 Nov, 15:54


የባይደን አስተዳደር የብሪታንያ የረዥም ርቀት ማዕበል ጥላ ሚሳኤሎችን ወደ ሩሲያ ገብተው ጥቃቶች እንዲፈፅሙ ፈቀደ።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

20 Nov, 13:17


በዩክሬን ያለው የአሜሪካ ኢምባሲ በሩሲያ ጥቃት ምክንያት ተዘጋ‼️

ወደ አዲስ ምዕራፍ የተሸጋገረው የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን በተለይም አሜሪካ ለዩክሬን የረጅም ርቀት ጦር መሳሪያ ሞስኮን እንድትመታ መፍቀዷን ተከትሎ ውጥረቱ ተባብሷል፡፡

ሁለቱም ሀገራት ከምድር ጦር ባለፈ የአየር ላይ ጥቃቶችን በስፋት እየተጠቀሙ ሲሆን በኪቭ ያለው የአሜሪካ ኢምባሲ ለአንድ ቀን እንደሚዘጋ አስታውቋል፡፡

ኢምባሲው ባወጣው ማስጠንቀቂያ መሰረት የኢምባሲው ሰራተኞች በያሉበት ሆነው ራሳቸውን ከአየር ላይ ጥቃቶች እንዲጠብቁም አሳስቧል፡፡

ሩሲያ በዛሬ ዕለት የአየር ላይ ጥቃት እንደምታደርስ መረጃ ደርሶኛል የሚለው ኢምባሲው አሜሪካዊያን የአደጋ ማስጠንቀቂያ ደወል ሲሰሙ ወደ ተሸለ ቦታ እንዲጠለሉ ብሏል፡፡

ሩሲያ በበኩሏ አሜሪካንን ጨምሮ የብሪታንያ እና ፈረንሳይ የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያዎችን ዩክሬን እንድትጠቀም መፍቀዳቸው ኔቶ በዚህ ጦርነት በቀጥታ እየተሳተፈ መሆኑን ማሳያ ነው ብላለች፡፡

 ዩክሬንም የረጅም ርቀት የጦር መሳሪያዎችን ተጠቅማ በሩሲያ ላይ ጥቃት የጀመረች ሲሆን ፕሬዝዳንት ፑቲን ምላሽ እንደሚሰጡ ዝተዋል፡፡


https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

20 Nov, 13:17


ኔታንያሁ ከጦርነቱ በኋላ ሀማስ ጋዛን አያስተዳድርም አሉ

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እስራኤል የሀማስን ወታደራዊ አቅም ለማውደም እያደረገች ያለው ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ ሀማስ ጋዛን አያስተዳድርም ብለዋል።

እስራኤል በጋዛ በህይወት አሉ ተብለው የሚገመቱት 101 ታጋቾች ያሉበትን ቦታ ለማግኘት ጥረት እያደረገች መሆኗን የገለጹት ኔታንያሁ አንድ ታጋች ለሚያስመልስ 5 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

"የታገቱ ዜጎቻችንን ለመጉዳት የሚደፍር ዋጋውን ያገኛል። አድነን እኒዘዋለን" ብለዋሌ ኔታንያሁ።
ኔታንያሁ ታጋቾችን ይዞ የሚመጣ ማንኛውም ሰው ከእነቤተሰቦቹ ከተከበበችው ጋዛ እንዲወጣ እንደሚመቻችለት ገልጸዋል።

"ምረጥ፤ ምርጫው ያንተ ነው። ነገርግን የኋላ ኋላ ታጋቾቹን ማግኘታችን አይቀርም።"
ኔታንያሁ ይህን የተናገሩት ከእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እና ጦር አዛዥ ጋር በጋዛ እየተካሄደ ያለውን ዘመቻ ለመገምገም በጋዛ በተገኙበት ወቅት ነው።
ባለፈው አመት ጥቅምት ወር ሀማስ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ 1200 ሰዎችን ሲገድል 250 የሚሆኑትን ደግሞ አግቶ ወስዷል። ይህን ተከትሎ እስራኤል በወሰደችው መጠነሰፊ የአየር እና የእግረኛ ጦር ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር ከ43ሺ በላይ አልፏል።
በኳታር አደራዳሪነት የተወሰኑ ታጋቾች በፍልስጤማውያን እስረኞች ተለውጠው የተለቀቁ ቢሆንም አብዛኞቹ እስካሁን በሀማስ እጅ እንዳሉ ይታመናል።
በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ኳታር፣ ግብጽ እና አሜሪካ ያደረጉት ጥረት አልተሳከም።
ሀማስ የእስራኤል ጦር ከጋዛ ጠቅልሎ እንዲወጣ መፈለጉ እና እስራኤል የጋዛን የጸጥታ ሁኔታ በዘላቂነት ለመቆጣጠር ያላት ፍለጎት ለድርድሩ አለመሳካት ዋነኛ ምክንያት ሆኗል።
https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

20 Nov, 13:17


ለቀጣይ 10 ቀናት አብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ደረቅ ፀሐያማና ነፋሻማ ይሆናሉ

በመደበኛ ሁኔታ በሚቀጥሉት 10 ቀናት በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ ፀሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ እንደሚኖር የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

ኢንስቲትዩቱ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት በሰሜን፣ ሰሜን ምሥራቅ፣ ምሥራቅ፣ መካከለኛው እና የደቡብ ደጋማ ቦታዎች ላይ የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ እንደሚዘወተር ገልጾ፤ አልፎ አልፎ የማስከተል ጥንካሬ እንደሚኖረውም ጠቁሟል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

20 Nov, 08:52


መረጃ ‼️

ዘመናቸውን የጨረሱ የምርጫ ቦርድ አመራሮች ከሃላፊነታቸው ሊነሱ ይገባል” ገዳ ቢሊሱማ ፓርቲ

ዘመናቸውን የጨረሱ የምርጫ ቦርድ አባላት ከሃላፊነት ሊነሱ ይገባል ሲል ከሰሞኑ ፍቃዱ የተሰረዘው ገዳ ቢሊሱማ ፓርቲ ከሷል፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን ፍቃድ በመሰረዝ የሰላማዊ ትግል በርን እየዘጋ ነው ያለው ፓርቲው፣ ይህ ደግሞ ሆን ብሎ የሚከናወን ነው ሲል አብራርቷል፡፡


https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

20 Nov, 08:52


መረጃ ‼️

አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ለኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር በመሆን በ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ተሹመዋል ፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

20 Nov, 08:52


አጸፋዊ ርምጃ እወስዳለው - ሩሲያ

ሩሲያ ዩክሬን በአሜሪካ ሰራሽ ረጅም ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤል በሞስኮ ላይ ለፈጸመችው ጥቃት አጸፋዊ ርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች፡፡

ዩክሬን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሰጡት ፍቃድ መሠረት አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤሎችን በትናንትናው ዕለት ወደ ሩሲያ ማስወንጨፏ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም ዘርፈ ብዙ ጉዳት እያደረሰ የሚገኘው የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ይበልጥ መባባሱ ነው የተነገረው፡፡

በዛሬው ዕለትም ሩሲያ ዩክሬን በአሜሪካ ሰራሽ ሚሳኤል ለፈጸመችው ጥቃት ተመጣጣኝ አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ አስታውቃለች፡፡

የረጅም ርቀት ሚሳኤል ጥቃቱንም የምዕራባውያን ሃላፊነት የጎደለው ተግባር ስትል ሩሲያ መወንጀሏን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ድርጊቱ ምዕራባውያን በሞስኮ ላይ የጀመሩት አዲስ የጦርነት ምዕራፍ መሆኑንና ለዚህም በየደረጃው ተመጣጣኝ ርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቃለች፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በምስራቃዊ ዩክሬን እየጨመረ የመጣውን የሩሲያ ወታደሮችን እንቅስቃሴ ለመገደብ የሚያስችል ጸረ-ሰው ፈንጂዎችን ለዩክሬን ለመስጠት መስማማታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

19 Nov, 18:53


ከደረሰኝ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ በመርካቶ የሚገኙ ሱቆች ከአንድ ሳምንት በላይ በመዘጋታቸው የበርካታ ሰዎች የዕለት ገቢ መቋረጡ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ከተማ ግዙፍ የንግድ ማዕከል በሆነው መርካቶ ከደረሰኝ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ የንግድ ሱቆች ከአንድ ሳምንት በላይ ዝግ በመደረጋቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች መስተጓጎል አስከትሏል።

ነጋዴዎች በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ የከተማ አስተዳደሩ ያጣው አስገዳጅ መመሪያን ተከትሎ በነጋዴዎች እና መነግስት መካከል አለመግባባት ያስከተለ ሲሆን በዚህም ምክንያት ሶቆች በመዘጋታቸው የዕለት እንጀራቸው መገደቡን አንዳንድ ነጋዴዎች እና በጫኝ- አውራጅ ሥራ የተሰማሩ ሠራተኞች ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

አዲስ ስታንዳርድ ትናንት ህዳር 9 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ የመርካቶ አከባቢዎች ተዘዋውሮ ባደረገው ምልከታ በተፈጠረው ስጋት የተነሳ በርካታ ሱቆች የተዘጉ መሆኑንና ክፍት በሆኑ መደብሮች ደግሞ  ምርቶች የሉም እየተባሉ መሆኑን ተገንዝቧል።

አጋጠሚውን ተከትሎ ከህጋዊ ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች “ገቢዎች ነን” የሚሉ ግን “በሙስና እና ዝርፊያ” የተሰማሩ አካላት መኖራቸውን ነጋዴዎች ገለጸዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

19 Nov, 18:53


የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ!

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል የመንግስት ሰራተኞች ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ።ምክር ቤቱ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል።

የምክር ቤቱ አባላትም የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅን ለማሻሻል የቀረበለትን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል።

በዚህም መሰረት የፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 10/64/2010 ተሻሽሎ አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 1353/2017 በምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ መጽደቁን ኢዜአ ዘግቧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

19 Nov, 18:53


በትግራይ ክልል የማዕከላዊ ዞን አስተዳዳሪ ‘ከግድያ ሙከራ መትረፋቸውን ተናገሩ!

በትግራይ ክልል የማዕከላዊ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን መዓሾ ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች በተፈጸመባቸው ‘የግድያ ሙከራ’ መትረፋቸውን ተናገሩ።አስተዳዳሪው እሁድ ኅዳር 8/2017 ዓ.ም. ከሰአት በኋላ በሥራ ምክንያት ከአክሱም ወደ መቀለ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ጥቃቱ እንደተፈጸመባቸው ለቢቢሲ ትግርኛ ገልጸዋል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የክልሉ ማዕከላዊ ዞን አስተዳዳሪ ሆነው የተሾሙት አቶ ሰለሞን ላይ የተፈጸመውን የግድያ ሙከራ በተመለከተ እስካሁን ድረስ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።ድርጊቱ በእርሳቸው ላይ ያነጣጠረ “የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ሊሆን እንደሚችል” የተናገሩት አቶ ሰለሞን በእርሳቸው ላይም ሆነ አብሯቸው በመኪናው ውስጥ የነበሩት የግል ጠባቂያቸው እና ሹፌራቸው ምንም ዓይነት ጉዳት ባይደርስባቸውም፣ መኪናቸው አራት ቦታ በጥይት እንደተመታ አረጋግጠዋል።

አቶ ሰለሞን በማዕከላዊ ዞን ያለውን የፀጥታ ሁኔታ በተመለከተም በአሁኑ ወቅት እጅግ አስቸጋሪ የፀጥታ ሁኔታ መኖሩን እና በበርካታ ሰዎች ላይ ጥቃት እና ግድያዎችም እንደሚፈጸሙ አመልክተዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

19 Nov, 18:53


ቱርክ የእስራኤል ፕሬዝዳንት አውሮፕላን በአየር ክልሏ እንዳያልፍ ከለከለች

ቱርክ የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት አይዛቅ ሄርዞግን አውሮፕላን በአየር ክልሏ ለማለፍ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አደረገች።

ፕሬዝዳንቱ በአዘርባጃኗ ባኩ ከተማ እየተካሄደ ባለው በ29ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ29) ላይ ለመሳተፍ በቱርክ አየር ክልል ለማለፍ ጥያቄ አቅርቦ ነበር ተብሏል።

ፕሬዝዳንቱ ባለፈው ቅዳሜ ወደ አዘርባጃን ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ በደህንነት ስጋት ምክንያት መሰረዛቸው ቲአርቲ ወርልድ ዘግቧል።

እስራኤል በጋዛ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከከፈተች ጀምሮ የሁለቱ አገራት ግንኙነት እየሻከረ መምጣቱ ተገልጿል።

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን የተባበሩት መንግስታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለፍልስጤማዊያን ምግብ፣ መድኃኒትና ሌሎችን አስፈላጊ ቁሳቁሶች በበቂ ሁኔታ እንዲገባላቸው በእስራኤል ላይ ጫና እንዲደረግ ተደጋጋሚ ጥሪ ሲያደርጉ ነበር።

ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ ቱርክ ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧን አስታውቃ እንደነበር ይታወሳል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

19 Nov, 13:37


ብሔራዊ ባንክ " የባንክ ኢንዱስትሪውን" ነፃ ከማድረጉ በፊት አሰራሩን ወደ ላቀ ደረጃ ያሻግራሉ የተባሉ አደረጃጀቶች ሊያደረግ ነዉ!

የፋይናንስ ዘርፉ ለውጭ ተዋንያን ቢከፈትም ቁጥጥር ማድረጌን እቀጥላለው ሲል ማእከላዊ ባንኩ ገልጿል።የፋይናንስ ስርዓቱ ወደ ሊበራላይዜሽን እየተሸጋገረ ባለበት ወቅት መረጋጋትን ለማረጋገጥ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ አዲሱን ማቋቋሚያ አዋጅ ይቀበላል ተብሎ የሚጠበቀው ብሔራዊ ባንክ አዳዲስ ክፍሎችን በማቋቋም ተቋማዊ ማሻሻያ እንደሚያደርግ አስታዉቋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በቅርቡ በፓርላማ ቀርበው የባንክ ኢንዱስትሪውን ነፃ ለማድረግና የብሔራዊ ባንክን አሠራር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በጉጉት የሚጠበቁትን ሁለት አዋጆችን ማንሳታቸው ታዉቋል።

ተቆጣጣሪ አካሉ ኢኮኖሚውን በዘመናዊ አሰራር ለመንዳት አካሄዱን በአዲስ መልክ እንደሚያደራጅና ይህም በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በተደረጉ ለውጦች የተመቻቸ መሆኑን ገልጸዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

19 Nov, 13:37


በትግራይ ክልል በየሳምንቱ 17 ሺህ ሰዎች በወባ እየተያዙ ነው

በትግራይ ክልል ባለፉት 3 ወራት በወባ በሽታ ምክንያት 13 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል። የትግራይ ጤና ቢሮ በተለይም ወባን ለመካለከል እና ለመቆጣጠር ከፌደራል መንግስቱ የአቅርቦቶች ድጋፍ እንደሚሻ የሚገልፅ ሲሆን እስካሁን ግን የሚጠበቀው እንዳልተገኘ የክልሉ ጤና ቢሮ የበሽታዎች መከላከል እና መቆጣጠር ቡድን መሪ አቶ አረጋይ ገብረመድህን ጠቅሶ ዶቼቬሌ ዘግቧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

19 Nov, 13:37


የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትር ጋር በአማራና ኦሮሚያ ባለው ግጭት እና በ ትግራይ ተዋጊዎችን በማቋቋም ዙሪያ መወያየታቸው ተገለጸ!

የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ የመከላከያ ሚኒስትሯ አይሻ መሀመድ ጋር በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች ያለውን ግጭት መፍታት በሚቻልበት ጉዳይ እና የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ መልሶ የማዋሐድና በምቋቋም ሂደትን በማጠናከር ዙሪያ በአዲስ አበባ መወያየታቸውን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል።

ትናንት በተካሄደው ውይይቱ የአሜሪካ-ኢትዮጵያ ግንኙነቶችን ለማጠናከር የሚያስችሉ መንገዶችም መዳሰሳቸው ተገልጿል።ውይይቱን ያካሄዱት የአሜሪካ አምባሳደር ኢርቪን ማሲንጋን ጨምሮ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ምክትል ረዳት ጸሃፊ የሆኑት ስፔራ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች የመከላከያ ረዳት ፀሃፊ የሆኑት ማውሪን ፋሬል እና ሌሎች የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴርን ያካተተ ልዑካን ቡድን እና የመከላከያ ሚንስትሯ አይሻ ሞሐመድ መሆናቸውን የኤባሲው መረጃ አመላክቷል።

የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ወታደራዊ ግንኙነት ለቀጣናዊ መረጋጋት፣ ለፀረ ሽብርተኝነት ትግልና ለሰላም ግንባታ ወሳኝ ሆኖ መቆየቱን ገልጸው ይህንን ለረጅም ጊዜ የቆየ ወታደራዊ ግንኙነት ኢትዮጵያ ዋጋ እንደምትሰጥና ግንኙነቱንም የበለጠ ለማጠናከር ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች የመከላከያ ረዳት ፀሃፊ ማውሪን ፋሬል በበኩላቸው አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር በተለይ በፀጥታና ሰላም ያላትን የቆየ ወታደራዊ ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልፀዋል፡፡

https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

19 Nov, 13:37


"በመርካቶ ሕጋዊ ግብይት እንዲደረግና ነጋዴው ደረሰኝ እንዲቆርጥ ቁጥጥር እያደረግን ነው" -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በመርካቶ ሕጋዊ ግብይት እንዲደረግና ለእያንዳንዱ ግብይት ነጋዴው ደረሰኝ እንዲቆርጥ ቁጥጥር እና ክትትል በመደረግ ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባ አዳነች ግብር እና ደረሰኝ ከመቁረጥ ጋር በተያያዘ ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።በምላሻቸውም "እንደ ሀገር ያለውን የግብይት ስርዓት በዘላቂነት ለማስተካከል የምናደርገውን ጥረት በጥናት ላይ ተመርኩዘን ክትትል ስናደርግ የቆየን ሲሆን፤ ያገኘነው ግኝት በርካታ ሕገ ወጥ የሆኑ አሰራሮች እንዳሉ ተመልክተናል" ብለዋል።

በዚህም "ግማሹ ግብር እየከፈለ ሌላው የማይከፍልበት አሰራር መኖሩን ከነጋዴዎች ጋር ባደረግነው ውይይት እና ክትትል ተገንዝበናል" ሲሉም አክለዋል።ግብር ለማስከፈል እና ደረሰኝ እንዲቆርጡ ለማድረግ በተደረገው ሂደት፤ በሀሰት ውዥንብር በመንዛትና መጋዘኖችን በመዝጋት በምሽት እቃዎች ሲጫኑ እንደነበርም ተናግረዋል።

"ይህ ፍፁም ስህተት ነው" ያሉት ከንቲባዋ፤ "በቀጣይ ሕጋዊ ስርዓት በመዘርጋት እና ለእያንዳንዱ ግብይት ደረሰኝ እንዲቆርጡ በማድረግ ግብርን በአግባቡ መሰብሰባችንን አጠናክረን እንቀጥላለን" ማለታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

19 Nov, 13:37


የአዲስ አበባ ምክር ቤት የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን፤ የአቶ ሰዒድ ዓሊ ከማል ያለመከሰስ መብትን አነሳ፡፡

ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳው የምክር ቤቱ አባል በሙስና መጠርጠራቸው ተነግሯል፡፡የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡

የምክር ቤቱ አባልና የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑትን የአቶ ሰዒድ ዓሊ ከማል ያለመከሰስ መብትን የተነሣው በፍትሕ ሚኒስቴር በቀረበ ጥያቄ መሠረት መሆኑን በምክር ቤቱ የሰላም፣ የፍትሕ እና መልካም አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ተናግሯል።

ቋሚ ኮሚቴው በሚኒስቴሩ የቀረበውን የሙስና ክስ በመመርመር የደረሰበትን ውጤት ለምክር ቤቱ ዝርዝር ሪፖርት አቅርቧል።ምክር ቤቱ የቀረበው ሪፖርትን በመመልከት፤ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል በሕግ እንዲጠየቁ ለማድረግ ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

19 Nov, 13:37


ኢትዮጵያ ለተመራጩ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፈች!

የኢትዮጵያ መንግስት የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ማስተላለፉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ፤ ሶማሊላንድ በቅርቡ ባካሄደችው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ በመመረጣቸው በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ስም የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፏል።

የተመረጡት ፕሬዚዳንት አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ እና ፕሬዚዳንት ሙሴ ቤሂ ላሳዩት ተምሳሌታዊነት ኢትዮጵያ አድናቆት እንዳላት የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ መጪው የሶማሊላንድ አስተዳደር ስኬታማ ጊዜ እንዲገጥመው ተመኝቷል።የሶማሊላንድ ምርጫ ኮሚሽን የዋዳኒ ፓርቲ እጩ አብዲራህማን መሀመድ አብዲላሂ 63 ነጥብ 92 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውን ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

19 Nov, 08:02


አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ!

አብዲራህማን ሞሃመድ አብዲላሂ ሕዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም. የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በማሸነፍ፤ የራስ ገዟ ሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት በመሆን መመረጣቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡በምርጫ የወቅቱ ገዥ ፓርቲ የሰላም፣ የአንድነትና የእድገት ፓርቲ (ኩልምዬ) በመወከል ፕሬዝዳንት ሙሴ ቤሂ፣ ተፎካካሪ ዋዳኒ ፓርቲን በመወከል አብዲራህማን ሞሀመድ እና የሰላምና ዊል ፌር ፓርቲን በመወከል ደግሞ ፈይሰል አሊ ፕሬዝዳንታዊ እጩ ሆነው መቅረባቸው ይታወቃል።

ይህንም ተከትሎ በተካሄደው ምርጫ የዋዳኒ ፓርቲ እጩ አብዲራህማን ሞሀመድ 63 ነጥብ 92 በመቶ ድምጽ በማግኘት ፤ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ኮሚሽኑ ይፋ አድርጓል፡፡የወቅቱ የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቤሂ 34 ነጥብ 81 በመቶ ድምጽ በማግኘት ድል ሳይቀናቸው መቅረቱንም አስታውቋል።ምርጫው በሶማሊላንድ ዲሞክራሲያዊ ጉዞ ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑን የገለጸው የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን፤ ሕዝቡ ላሳየው ተሳትፎ ምስጋና አቅርቧል።

በዚህም መሰረት አዲስ የተመረጡት ፕሬዚዳንት በሚቀጥሉት ቀናት ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች ያሳውቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ሙስታክባል ሚዲያ ዘግቧል፡፡በሶማሊላንድ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበው፤ በስድስት ክልሎች በተዘጋጁ 2 ሺሕ 648 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፃቸውን መስጠታቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

11 Nov, 18:30


ቀጣይ በሶማሊያ በሚሰፍረው የአፍሪካ ህብረት ጦር ውስጥ የኢትዮጵያ ሰራዊት አልካተተም ‼️

በሶማሊያ በሚሰፍረው የአፍሪካ ህብረት ጦር ውስጥ የኢትዮጵያ ሰራዊት እንደማይካተት የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዱልቃድር ሞሃመድ ኑር አስታወቁ።

የኢትዮጵያ ሰራዊት በቀጣይ የአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ጦር ላይ “በአባልነት እንዳይካተት የተደረገው ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት በመጣሷ ነው” ሲሉ ሚኒስትሩ ለሀገሪቱ የዜና አገልግሎት ሶና (SONNA) ገልጸዋል።

በቀጣይ በሶማሊያ በሚሰፍረው ጦር ላይ የትኞቹ ሀገራት ሰራዊት ያዋጡ በሚለው ጉዳይ "ሂደቱ እንደቀጠለ ነው” ሲሉ የገለጹት ሚኒስትሩ÷ በቀጣይ የትኞቹ ሀገራት ጦራቸውን እንዲያዋጡ እንደተፈቀደላቸው ይነገራል ብለዋል፡፡

“አሁን የሚታወቀው ኢትዮጵያ እንዳታሳትፍ መደረጓን ነው” ሲሉ አብራርተዋል።

ሶማሊያ በቀጣይ ከአፍሪካ ሀገራት ተወጣጥቶ ተልዕኮ ተሰጥቶት በግዛቴ በሚሰፍረው ጦር ዙሪያ የትኞቹ ሀገራትን ማዋጣት አለባቸው የሚለውን የምመረጠው እራሴ ነኝ ስትል መግለጿን መዘገቡ ይታወሳል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) ወታደር አዋጭ የሆኑ ሀገራት የመከላከያ ሚንስትሮች በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ጥረታቸውን በአዲሱ ተልዕኮ ለመቀጠል ያላቸውን “ፍላጎት እና ዝግጁነት” መግለጻቸው ይታወቃል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

11 Nov, 18:30


ሲጠበቅ የነበረዉ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ በዚህ ወር ስራዉን በይፋ እንደሚጀመር ተሰምቷል!

በኢትዮጵያ ገበያ ኢንዱስትሪ ታሪካዊ ጅማሮ ሆኖ የተገኘዉ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ በያዝነው ወር ላይ በይፋ ስራዉን እንደሚጀመር ታዉቋል።ጥቅምት 2016 ዓ.ም. የመንግሥትና የግል አጋርነትን መሰረት በማድረግ የተቋቋመዉ ገበያዉ ካፒታል በማሰባሰብ ሂደት ላይ ታይቶ ነበረዉ ከፍተኛ ፍላጎትና ርብርብ ኢትዮጵያ እያካሄደች ላለው የፋይናንስ ዘርፍ ልማትና የኢኮኖሚ ለውጥ አዲስ የስኬት ጉዞ መሆኑ ተገልፆ ነበር።

ኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ በመጋቢት ወር ላይ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከሀገር ውስጥና ከውጪ ባለሀብቶች 1. 5 ቢሊዮን ብር ካፒታል ማሰባሰቡን አሳዉቋል።የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል የካፒታል ማሰባሰቢያውን ማጠቃለያና የገበያውን ደንብ አስመልክተው በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት እንደተናገሩት፤ ገበያው ለመሰብሰብ ያቀደው 631 ሚሊዮን ብር ቢሆንም የተሰበሰበው ካፒታል 1.5 ቢሊዮን ብር ነው ማለታቸው ይታወሳል።

ይህም ከዕቅዱ በ240 በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልጸው 48 በፋይናንስና ከፋይናንስ ዘርፍ ውጪ ባሉ መስኮች የተሰማሩ የሀገር ውስጥና የውጪ ባለሀብቶች መሳተፋቸውን ተናግረዋል።ገበያው አዲስ የኢንቨስትመንት አማራጮችን የሚፈጥር፣ የሥራ ፈጣሪነትን የሚያበረታታና በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ዘላቂ ልማትን የማስፋት አላማን ይዞ መቋቋሙ ይታወቃል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

11 Nov, 18:30


በመርካቶ “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” በሚል የሚናፈሰው ወሬ ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል ነው
-አስተዳደሩ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ በመርካቶ አካባቢ አንዳንድ ነጋዴዎች “ንብረት ሊወረስ ነው፤ ሱቃችን ሊዘጋ ነው” የሚል መሰረት የሌለው ውዥንብር ውስጥ መግባታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ተመልክተናል ሲል አስታወቀ።ውዥንብሩ የመጣው “በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎች በዚህ ሂደት ውስጥ እንዲያልፉ በሚደረገው ሥራ” ነው ሲል የገለጸው አስተዳደሩ ይህ እንዲስተጓጎል ሆን ተብሎ የተነዛ አሉባልታ ነው ሲል ጠቁሟል።

“በደረሰኝ እንዲገበያዩ የሚጠበቅባቸው ነጋዴዎችን በመለየት በደረሰኝ ግብይት እንዲፈጽሙ የከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት ጥሪ ሲያቀርብ መቆየቱን” ያወሳው አስተዳደሩ “ይሁን እንጂ ይህንን ጥሪ ወደ ጎን በመተው እና ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተከናወነ ያለውን ሥራ ለማስተጓጎል የተሰራ ውዥንብር ነው” ብሏል።በውዥንብሮች እና የተሳሳቱ መረጃዎች ንብረት የሚያሸሹና ሱቅ የሚዘጉ ነጋዴዎች ተገቢነት ከሌለው ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሲል ያሳሰበው አስተዳደሩ “እንዲሁም አምራች፣ አከፋፋይና ቸርቻሪ ነጋዴዎች ያለደረሰኝ መገበያየት ህገወጥ ተግባር መሆኑን በአግባቡ በመረዳት ወደ ህጋዊ መስመር ሊገቡ ይገባል” ብሏል።

በመርካቶ እየተከናወነ የሚገኘው ሕጋዊ የንግድ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል የንግዱ ማኅበረሰብ ተባባሪ እንዲሆንም አስተዳደሩ ጠይቋል።ከዚህ በፊት ያለደረሰኝ የተገዙ ዕቃዎች ካሉ ሕጉ በሚያዘው መሠረት የማስመዝገብ ሥራ ማከናወን እንደሚጠበቅባቸው የአስተዳደሩ የከንቲባ ጽ/ቤት በፌስ ቡክ ገጹ ባጋራው መግለጫ አስታውቋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

11 Nov, 18:30


እናት ፓርቲ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ለ40 ዓመታት ቤተመንግስት ውስጥ ተቆልፎበት ያገኘነውን 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ አስረክበናል በማለት በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተናገሩት ንግግር ዙሪያ መንግሥት ለሕዝብ ግልጽ ማብራሪያ እንዲሰጥ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

ፓርቲው፣ ወርቁ የአገር ቅርስ የኾኑ ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚል እምነት እንዳለው ገልጧል። ወርቁ የድሮ ነገሥታት ያከማቿቸው ከወርቅ የተሠሩ መገልገያዎች ከኾኑ፣ በአገር ቅርስነት ተጠብቀው መቀመጥ እንዳለባቸው ፓርቲው አሳስቧል።

ከወርቅ በላይ የኾነ የአገር ቅርስ እንደኾነ የሚታመነው ወርቅ ከተሸጠ ብሔራዊ ባንክና የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን የጋራ ተጠያቂነት ይጠብቃቸዋል በማለት ያስጠነቀቀው ፓርቲው፣ ተቋማቱ ከዚህ ድርጊት እንዲታቀቡ ጥሪ አድርጓል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

11 Nov, 12:56


የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች መንግስት ለጠቅላይ ሚኒስተር አቢይ አስተዳደር  የመኪና ስጦታ አበረከተ

ባለፈዉ ሳምንት አንድ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ አዲስአበባ የገቡት የአቡዳቢዉ መሪ 30 ያህል ጥይት የማይመታቸዉ ዘመናዊ መኪኖች በስጦታ መልክ ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ማብርከታቸዉ ተሰምቶል ፡፡

ከዚህ በፊት የብልፅግና መንግስት ወደ መሪነት በመጣ ሰሞን የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች መንግስት ቁጥራቸዉ በርከት ያሉ  ኒሳን  V8  መኪኖችን ለጠቅላዩ መስጠታቸዉ የሚታወስ ነዉ ::

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

11 Nov, 12:56


ኢትዮ ቴሌኮም የስማርት ሲቲ (ስማርት ቢሾፍቱ) ፕሮጀክትን ዕውን ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ከከተማዋ አስተዳደር ጋር ተፈራረመ!

የስማርት ቢሾፍቱ ፕሮጀክት በምዕራፍ ከተማዋን ለማዘመን የሚያስችል የክላውድ፣ ጥሪ ማዕከል፣ ዳታ ሴንተር፣ እጅግ ከፍተኛ ፍጥነት እና ጥራት ያለው ኢንተርኔት፣ የኦፕቲካል ፋይበር እና ሌሎች የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ የመዘጋጃ አገልግሎቶችን ጨምሮ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና፣ ትራንስፖርት እና የግብር አሰባሰብ የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ለማዘመን እንዲሁም አስተማማኝ ደህንነት ያላት ከተማን ዕውን ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አጽንኦት ተሰጥቷል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

11 Nov, 12:56


አዲሱ "የሕንፃ ረቂቅ አዋጅ" እንዲካተቱ የተሰጡ ሐሳቦች አልተካተቱም በሚል ተቃውሞ ገጠመው!

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባ መርምሮ ለዝርዝር ዕይታ ለከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ የመራው የኢትዮጵያ የሕንፃ ረቂቅ አዋጅ ተቃውሞ ገጥሞታል።የሕንፃ ረቂቅ አዋጁ ተቃውሞ የገጠመው፤ በዛሬው ዕለት የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ቋሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ ላይ ነው።

በስብሰባው ተቃውሞ ካስነሱ ሐሳቦች መካከል፤ የግንባታ ፍቃድ አሰጣጥ ላይ ያሉ አሰራሮችን በተመለከተ ከቋሚ ኮሚቴው አባላት የተሰጡ ምክረ ሐሳቦችን አላካተተም የሚል ትችት ይገኝበታል።

ከዚህ ቀደም የሕንፃ አዋጅን በተመለከተ ከቋሚ ኮሚቴ አባላት ግብአትና አስተያየት ተሰጥቶበት የነበረ ቢሆንም፤ ለቋሚ ኮሚቴው በቀረበው ሪፖርት አብዛኞቹ አስተያየቶች አልተካተቱም ተብሏል።በተለይም ከከተማና መሰረተ ልማት ጋር ተያይዘው የሚነሱ በግንባታ ወቅት የሚደርሱ አደጋዎችን ጨምሮ ተያያዥ ጉዳዮች አዋጁ ላይ አልተሻሻሉም የሚል ቅሬታም ተሰምቷል።

እንዲሁም የሕግና መቀጮ በተመለከተ በፍትሐብሔርና በሕግ ጉዳዮች ማለቅ የሚችሉ ነገሮች በአዋጁ ላይ መስፈራቸው የሙያ ደሕንነትን የሚጋፋ መሆኑን ከተለያዩ የሙያ ማሕበራት የተወከሉ የቋሚ ኮሚቴው አባላት ገልጸዋል።በተጨማሪም የአንድ ሕንፃ ፕላን በሚወጣበት ጊዜ የተሳተፉበት ሙያተኞች የደረጃ ጥራታቸው ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑ በስብሰባው ላይ ተነስቷል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

11 Nov, 09:48


ኩላሊታችንን ግዙን እያሉ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚመጡ ሰዎች መኖራቸው ተገለጸ።

ብሔራዊ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ጸጋይ ብርሀነ ለአል ዐይን እንዳሉት ማዕከሉ ስራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በአጠቃላይ ለ187 ሰዎች የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና አገልግሎት አድርጓል ብለዋል።

አሁን ላይ ማዕከሉ በሳምንት እስከ ሶስት በዓመት ደግሞ እስከ 100 ሰዎች ድረስ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ህክምና የመስጠት አቅም እንዳለው የሚናገሩት ዶክተር ጸጋይ በግብዓት እጥረት ምክንያት በአቅሙ ልክ እየሰራ እንዳልሆነም ገልጸዋል።

የአካል ልገሳ ጉዳይ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ ነው የሚሉት ዶክተር ጸጋይ ኩላሊታችንን መሸጥ እንፈልጋለን፣ ኩላሊታችንን ግዙን የሚሉ ዜጎች ወደ ማዕከሉ እንደሚመጡም አክለዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

11 Nov, 09:48


በአዲስ አበባ የወንጀል ድርጊት በ37 በመቶ ቀንሷል ተባለ!

በአዲስ አበባ ከተማ ወንጀልን ቀድሞ ለመከላከልና ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተሰሩ ስራዎች የወንጀል ድርጊት በ37 በመቶ መቀነሱን የአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ተናገሩ::የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ስራዎችን እየገመገሙ ነው::

የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊድያ ግርማ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የከተማዋን ሰላም እና ፀጥታ ለማጽናት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል::በዚህም በአዲስ አበባ ከተማ የወንጀል ድርጊትን ቀድሞ ለመከላከልና ህብረተሰቡን በማሳተፍ በተሰሩ ስራዎች የወንጀል ድርጊት በ37 በመቶ ቀንሷል ብለዋል::በሩብ ዓመቱ በመዲናዋ የተከበሩ ሃይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ በዓላት እሴቶቻቸዉን ጠብቀዉ በድምቀት መከበራቸዉንም ኃላፊዋ ተናግረዋል፡፡

አዲስ አበባ በሩብ ዓመቱ በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ስብስባዎችም ማስተናገዷን አንስተዋል::የሰላም እና ፀጥታ ስራን ለማጠናከር በሩብ አምቱ 22 ሺህ የሰላም ሰራዊቶች ሰልጥነዉ ወደ ስራ መግባታቸውንም ገልጸዋል::ህገወጥ የመሬት ወረራ፣ ህገወጥ የመንገድ ላይ ንግድና ሌሎች የደምብ መተላለፍ ችግሮች መቀንሳቸዉንም ነው ኃላፊዋ የተናገሩት::

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

10 Nov, 17:23


የሩሲያ ጦር 300 ጦር ደምስሶ መላዉ የኔቶ አባል ሀገራት ድንኳን ጥለዉ ተቀምጧል

በዩክሬን ስም የሩሲያን ድንበር ገብቶ ሲዋጋ ከነበረዉ የምዕራባዊያን ቅጥረኛ ወታደሮች መካከል ከ30 ሺህ በላዩን ደምስሷል፡፡ በዚህ የተደናገጠችዉ አሜሪካ እኔ የለሁበትም እንደፍጥርጥራችሁ ብላ ምዕራባዊያኑን ሸምጥጣቸዋለች፡፡

በሬ ሆይ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ እንዳሉ አበዉ፤ክፍት በር አገኘዉ ያለዉ የኔቶ ቅጥረኛ ጦር የሩሲያ የድንበር ከተማ የሆነችዉን ኩርስክን ጥሶ ገብቶ ጉዳት ካደረሰ ቡሃላ በፑቲን ልዩ ኮማንዶ ጦር ተከቦ መዉጫዉ ጠፍቶት እየተቀጠቀጠ ነዉ፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት በዚህች ከተማ በተደረገ ዉጊያ ከ300 በላይ የዩክሬንና ኔቶ ወታደሮች ያለቁ ሲሆን፤ ወታደራዊ ተሽካርካሪዎች፤ ሞርታሮች እንዲሁም የኤልክትሮኒክስ መጥለፊያዎች መዉደማቸዉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሶ ታስ ዘግቧል፡፡

"በኩርስክ ግንባር አካባቢ በተካሄደው ውጊያ ከ30,800 በላይ የዩክሬን ወታደሮችን፣ 189 ታንኮችን፣ 123 እግረኛ ተዋጊ ተሽከርካሪዎችን፣ 107 ጋሻ ጃግሬዎችን፤ 1,095 የታጠቁ የጦር መኪኖች፣ 833 የሞተር ተሽከርካሪዎችን እና 262 መድፍ መሳሪያዎች መዉደማቸዉን የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

10 Nov, 17:23


ከሰሞኑ ወደ ኢትዮጵያ 'ስውር' በረራ ያደረጉ የውጭ ሀገራት ምዝገባ ያላቸው አውሮፕላኖች ጉዳይ

አንደኛው በረራ ሩስያ ስሪት በሆኑ ኢልዩሽን አውሮፕላኖች ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ወደ አዲስ አበባ የተደረጉ ተደጋጋሚ በረራዎች ናቸው።

እነዚህ ኢልዩሽን IL-76 አውሮፕላኖች ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ የራዳር ስማቸው በማጥፋት የተከናወኑ ሲሆን ወደ ኤምሬትስ ሲመለሱ ደግሞ ሌላ ስያሜ እንደተጠቀሙ ታውቋል።

አውሮፕላኖቹ ከኤምሬትስ ይነሱ እንጂ የተመዘገቡት ኪርጊዝታን መሆኑን ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል። አውሮፕላኖቹ ብዙ ግዜ የጦር መሳርያ በማመላለስ ይታወቃሉ።

ሌላኛው ስውር በረራ ደግሞ ባሳለፍነው ማክሰኞ የተከናወነ ሲሆን ፎኔክስ ኤር የተባለ የኪራይ የግል ጄት ከግሪክ ተነስቶ አዲስ አበባ ካረፈ በኋላ ከ90 ደቂቃ በኋላ ተመልሶ ወደመጣበት እንደሄደ ታውቋል።

ይህን አውሮፕላን ዘወትር የሚከራዩት የአሜሪካው CIA ሀላፊዎች ሲሆኑ በማክሰኞው በረራ ማንን ይዞ እንደነበር ግን አልታወቀም።

የሲአይኤው ሀላዊ ዊልያም በርንስ በቅርቡ በኬንያ እና ሱማልያ በመገኘት መሪዎችን ሲያናግሩ እንደነበር ይታወሳል።

ባለስልጣኑ ምናልባት በዚህኛው የአዲስ አበባ በረራ አዲስ አበባ ተገኝተው የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናትን በስውር አግኝተው ተመልሰው ሊሆን ይችላል ግምት እንዳለ ለሚድያችን የደረሰው ጥቆማ ያሳያል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

10 Nov, 17:23


አመራሩ ተገደሉ‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን የቆቦ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ የነበሩት ደርቤ በለጠ ዛሬ ረፋድ ላይ በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው ማለፉን የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

ነፍስ ይማር

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

10 Nov, 17:23


በእስራኤል-ሄዝቦላህ ጦርነት ምን አዳዲስ ክስተቶች አሉ እስካሁን የምናውቀው‼️

ሄዝቦላህ ጥቃቱን ማጠናከሩንና ትናንት ብቻ ከ20 በላይ የተሳኩ ዘመቻዎችን ፈጽሚያለሁ ብሏል
በእስራኤልና በሊባኖሱ ሄዝቦላህ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት በአየር ድብደባ እና በምድርጦር ተባብሶ እየተካሄደ ይገኛል።
እስራኤል በትናንትናው እለት በሊባኖስ በፈጸመችው የአየር ድብደባ ህጻናትን ጨምሮ 40 ሊባኖሳውያን መሞታቸውን የሊባኖስ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
የእስራኤል ጦር አዳሩን ድብደባ ከፈጸባቸው አካባቢዎች መካከልም የሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ደቡባዊ ክፍል አንዱ ነው ተብሏል።
ከሊባኖስ ወደ እስራኤል በተተኮሰ ሮኬት የአምስት ሰዎች ህይወት አለፈ
በታይሬ ከተማ አርብ ምሽት በእስራኤል በተፈጸመ የአየር ድብደባም ቢያንስ የ7 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
በታይሬ ከተማ አቅራቢያ በሚገኙ ስፍራዎች ላይ የአየር ድብደባው ትናንት ቅዳሜ በቀጠሉ የእስራኤል የአየር ድብደባዎች ቢያንስ 13 ሰዎች መሞታቸውን ነው የሊባኖስ ባለስልጣናት ያስታወቁት።
ትናንት ቅዳሜ በታሪካዊቷ ባልቤክ ከተማ ምስራቃዊ ክፍል በተደረገ የእስራኤል የአየር ድብደባዎች ቢያንስ 20 ሰዎች መሞታቸውንም ነው የሊባኖስ ጤና ሚኒስቴር የገለጸው።
የእስራኤል ጦር በታይሬ እና በባልቤክ ከሞች የሚገኙ የሄዝቦላህ መሰረተ ልማቶች እና ወታደሮች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ነው ያስታወቀው።
የሊባኖስ የጤና ሚኒስቴር የእስራኤል ጦር ባለፈው አንድ ዓመት በፈጸመው ጥቃቶች 3 ሺህ 136 ሰዎች መሞታውን እና 13 ሺህ 979 ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጾ፤ ከሟቾች መካከል 619 ሶቶች እና 194 ህጻት እንደሆኑም አስታውቋል።
የሊባሱ ሄዝቦላህ በእስራኤል ላይ የሮኬት ጥቃትን ጨምሮ የተለያዩ ጥቃቶችን እየሰነዘረ መሆኑን አስታውቋል።
ሄዝቦላህ በትናትናው እለት ብቻ በእስራኤል ላይ 20 የተሳኩ ኦፕሬሽኖችን መፈጸሙን ያስታወቀ ሲሆን፤ ከአንድ ቀን በፊትም በደቡባዊ ቴል አቪቭ የሚገኝ የእስራኤል ወታራዊ ፋሪካ ላይ ጥቃት በፈጸሙን ገልጿል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

10 Nov, 17:23


ቡድኑ “በይፋ መፈንቅለ መንግስትን ወደ መፈጸም ተሸጋግሯል” -የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

በልዩነት ውስጥ የሚገኘው የህወሓት ቡድን
በይፋ መፈንቅለ መንግስትን ወደ መፈጸም ተሸጋግሯል ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ።ወቅታዊ ሁኔታዎችን የተመለከተ መግለጫን ያወጣው ጊዜያዊ አስተዳደሩ ቡድኑ የመንግስት ስራዎችን ከማደናቀፍ አልፎ ይፋዊ የመፈንቅለ መንግስትን ወደ መፈፀምና ፍፁም ስርዓት አልበኝት ወደ ማስፋፋት ተሸጋግሯል ብሏል።

በህወሓት ከፍተኛ አመራር መካከል የተፈጠረው አለመግባባትና ከነሓሴ 2016 ጀምሮ በግልፅ እየታየ የመጣው ልዩነት የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ለሚደረገው ጥረት ከባድ እንቅፋት ፈጥሯል ያለው ጊዜያዊ አስተዳደሩ በአንድ በኩል ልዩነቱ ከጊዜ ወደጊዜ እየተካረረ እንዲሄድ በሌላ በኩል ደግሞ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ስራዎች በተደራጀ መንገድ እንዲደናቀፉ በማድረግ የመንግስት ስራዎችን የማሰናከል የተቀናጀ ስራ ሲከናወንም ቆይቷል፤ አሁንም እንደቀጠለ ነው ብሏል።

ይህ ዘመቻ ህጋዊ ያልሆነ ጉባኤ ባካሄደው ቡድን በበላይነት የሚመራና የሚገራ ነው ያለም ሲሆን “ህዝባችን ተስፋ እንዲቆርጥና በቀጣይ አዙሪት እንዲጠመድ ሆን ተብሎ የሚደረግ ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው” ሲል ገልጿል።ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ደግሞ “ቡድኑ የመንግስት ስራዎችን ከማደናቀፍ አልፎ ይፋዊ መፈንቅለ መንግስትን ወደ መፈፀምና ፍፁም ስርዓት አልበኝት ወደ ማስፋፋት ተሸጋግሯል”ም ነው ጊዜያዊ አስተዳደሩ በመግለጫው ያለው።

በመቐለ ከተማ፤ ሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች እየተደረጉ ያሉ እንቅስቃሴዎች የዚህ ተግባሩ ማረጋገጫ አብነቶች ናቸው ሲል ማሳያዎችንም ጠቅሷል።ካለፉት 2 ሳምንታት ወዲህ ደግሞ “ከትግራይ ሰራዊት አመራሮች ጋር ተረዳድተናል፤ ከላይ እስከ ታች የመንግስት መዋቅሩን ለመቆጣጠር ጨርሰናል” እያለ ሰፊ የማደናገር ተግባር ላይ ተጠምዷልም ነው ያለው።

ይህ አገላለፅ ራሱን በራሱን የሚያታልልበትና የሚያሞኝበት አጉል ተስፋ ከመሆን አልፎ ጠብ የሚል ሃቅ እንደሌለው መታወቅ አለበት ሲልም አጣጥሏል።ቡድን ከስልጣኑ ዉጭ ሊያስብና ሊያልም እንደማይችል በመግለጽም “በየእለቱ ስልጣን የሚይዝበትን ህልም በማለም፤ ለስልጣን ሲል ሁሉንም ዓይነት ጥፋት ከመፈፀም ወደ ኋላ እንደማይል በተደጋጋሚ እየታዬ መጥቷል” ብሏል።

“ከሰራዊቱ ጋር ተግባብተናል በሚል እያደረጋቸው ያሉ ተደጋጋሚ ማደናገሪያዎችም ቢሆኑ ለስልጣን ሲባል ለትግራይ ህዝብ ህልውና የቆመን ሰራዊት ጭምር ለጠባብ ፍላጎቱ ማሟያ ከመጠቀም ወደ ኋላ እንደማይል በሚገባ የሚያሳይ ድርጊት ነው” ሲልም ነው ያስቀመጠው በመግለጫው።በሰራዊት አመራሩም ሆነ በሃይማኖት አባቶች የተጀመሩ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ሂደቶችን ከልብ እንደማይቀበል በአደባባይ እየገለፀ መጥቷል ሲል ገልጿል።

የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ህወሓትን ለማዳን በሚደረግ ትግል የሚቻላችውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናችውን የገለጸው ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከማንኛውም አካል ጋር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገርም ዝግጁ ናቸውም ብሏል።ሆኖም መንግስታዊ ስልጣን ማን ይያዝ በሚል የስልጣን ክፍፍል ጉዳይ ላይ ግን በየትኛውም መመዘኛ ወደ ድርድር የማይቀርብ መሆኑን ግልፅ መሆን እንዳለበትም ነው ያስታወቀው።

በአመራሩ መካከል የተፈጠረውን ልዩነት በሂደት ሊኖር በሚችል ማንኛውም ዓይነት ዉይይት በሰላማዊ መንገድ ለማጥበብና ችግሮችን ለመፍታት እንጂ የስልጣን ክፍፍል ለማድረግ እንዳይደለም “አይታሰብምም” ሲል አስታውቋል።ጊዜያዊ አስተዳደሩ የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም በመጠበቅ የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄዎች ለመመለስ በሚያከናውነው የተወሳሰበ ትግል በሃገር ዉስጥና በውጭ የሚገኘው መላው ህዝብ ከጎናችን እንደሚሆን እምነታችን የፀና ነውም ብሏል በመግለጫው።

በክፍፍል ውስጥ የሚገኙት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች በኃይማኖት አባቶች በተደረገ ጥረት ተቀራርቦ ለመነጋገር ተስማምተዋል በሚል ከሰሞኑ መገለጹ ይታወሳል።የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከአሁን ቀደም ለመፈንቅለ ስልጣን እያሴረብኝ ነው ሲሉ በዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራውን የድርጅቱን ክንፍ መክሰሳቸው የሚታወስ ነው።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

10 Nov, 12:16


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር መስራች አባል ሆነ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሩሲያ፣ ህንድና ብራዚልን ጨምሮ ከብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመሆን በጣምራ የብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበርን በመመስረት የመጀመሪያው የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ዩኒቨርስቲ መሆኑን ዩኒቨርስቲው አስታውቋል።

አራቱ የብሪክስ ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች የመሰረቱት ማህበር በትምህርት በዲፕሎማሲ በጥናትና ምርምር እንዲሁም በፈጠራ ስራ በጋራ መሰራት የሚያስችላቸው መሆኑ ተመላክቷል።

ዩኒቨርስቲው በአዲሱ የራስ-ገዝ ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት አጋርነትና አለማቀፋዊነትን በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋልአስታውቋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

10 Nov, 12:16


ኳታር የሀማስ ሃላፊዎችን ከሀገሯ ለማስወጣት ተስማማች።

ኳታር በሀገሪቱ የሚኖሩ ከፍተኛ የሀማስ አመራሮችን ለማስወጣት ከአሜሪካ የቀረበላትን ጥያቄ መቀበሏ ተሰማ፡፡

ሀማስ በ2012 በሶርያ የእርስ በእርስ ግጭት መቀስቀሱን ተከትሎ ዋና ቢሮውን ከደማስቆ ወደ ዶሃ አዘዋውሯል፡፡

የጥቅምት ሰባቱን ጥቃት ተከትሎ አሜሪካ “ኳታር በተለመደው መንገድ ከቡድኑ ጋር ግንኙነቷን መቀጠል እንደማትችል” ስታስጠነቅቅ ሰንብታለች፡፡

ሀገሪቱ በዶሃ የሚገኘውን የቡድኑን ዋና ቢሮ እንድትዘጋ እና ለሀላፊዎቹ ጥገኝነት ከመስጠት እንድትቆጠብ ጫና ስታደርግ መቆየቷን ሲኤንኤን የአሜሪካ እና ኳታር ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ዘገባው ሀማስ ታጋቾችን ለመልቀቅ እና የሰላም ስምምነት ላይ ለመድረስ የቀረበለትን ተደጋጋሚ ጥያቅ ውድቅ ማድረጉን ተከትሎ፤ መሪዎቹ በማንኛውም የአሜሪካ አጋር ዋና ከተሞች ተቀባይነት ሊያገኙ አይገባም የሚል ሀሳብ በዋሽንግተን በኩል መንጸባረቁን ጠቅሷል፡፡

አሜሪካ ከሁለት ሳምንት በፊት ኳታር መሪዎቹን እንድታስወጣ በጠየቀችው መሰረት ኳታር ከሳምንት በፊት ባለስልጣናቱ ከሀገሪቷ ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ ሰጥታለች፡፡

በዚህም መሰረት የሀማስ ወቅታዊ መሪ ካሊድ ማሻልን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በቅርቡ ዶሀን ለቀው እንዲወጡ ሊደረግ ይችላል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

09 Nov, 17:13


የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ለክልሉ መምህራን እንዲከፈል ፌደራል መንግስት የፈቀደውን የአምስት ወር ደመወዝ ለሌላ አላማ አውሎታል በሚል ክስ ተመሰረተበት!

የትግራይ ክልል የመምህራን ማህበር በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና በፌደራል መንግስቱ ላይ የመሰረተው ክስ ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚታየ ተገለጸ።በነሀሴ ወር 2016 ዓ.ም ክሱን የመሰረተው ማህበሩ፣ ሁለቱም አካላት ለ17 ወራት ለክልሉ መምህራን መከፈል የነበረበትን ደመወዝ ባለመክፈላቸው መሆኑ ይታወቃል።የትግራይ መምህራን ማህበር ጠበቃ የሆኑት አቶ ዳዊት ገብረሚካኤል ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና በፌደራል መንግስት ላይ የቀረበው ክስ በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ እየታየ ነው።

"ክስ ከተመሰረተባቸው መካከል የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የክልሉ ትምህርት እና ፋይናንስ ቢሮዎች ይገኙበታል፣ ክሱም የፌደራል መንግስት ለመምህራን የላከውን የአምስት ወር ደሞዝ ለሌላ አገልግሎት በማዛወራቸው የተሰጣቸውን ስልጣን ያለአግባብ ተጠቅመዋል” የሚል ነው ሲሉ ገልጸዋል።በተጨማሪ የፌዴራል መንግስት ደግሞ “የ12 ወራት ደሞዝ ባለመልቀቁ ነው ክሱ የተመሰረተው" ሲሉ አቶ ዳዊት አስረድተዋል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

09 Nov, 17:08


በኦሮምያ ክልል ነዋሪዎች ለተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም እና ለሚሊሻዎች በሚል አስገዳጅ መዋጮ እየተጠየቁ መሆኑን አስታወቁ

የኦሮምያ ክልል ነዋሪዎች የአከባቢው ባለስልጣናት በግዳጅ ለተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም እና የአከባቢውን ሚሊሻዎች ለማጠናከር በሚል መዋጮ በተደጋጋሚ አንደሚጠየቁ አስታወቁ።

በተለያዩ መክንያቶች ባለስለጣናቱ አስገዳጅ መዋጮዎችን ስለሚያስከፍሏቸው ለከፍተኛ የገንዘብ ችግር እየተዳረጉ መሆኑን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፣ ለኑሮ ጫና ዳርጎናል ብለዋል።

ባለስልጣናቱ መዋጮ እንዲከፍሉ የሚያስገድዱት መንግስት ሰራተኞችን እና የየአከባቢዎቹን አርሶአደሮች ጨምሮ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል መሆኑን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

በምዕራብ አርሲ ዞን የቆፋሌ ወረዳ ነዋሪ የሆኑ እና ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ አርሶ አደር እንዳስታወቁት ከአምና 2016 ጥር ወር ጀምሮ ነዋሪዎች ለተማሪዎች ምግብ፣ ለሚሊሻ ዩኒፎርም እና ለምግብ አቅርቦት የሚሆን ገንዘብ እንዲያዋጡ እንደሚጠየቁ አስታውሰዋል።

በተመሳሳይ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የሆኑት ተስፋዬ ቶሎሳ (ስማቸው የተቀየረ) ከወርሃዊ ደመወዛቸው 6ሺ ብር ላይ ምክንያቱ ሳይገለጽላቸው እየተቀነሰባቸው መሆኑን ገልጸው እጅግ አሳስቦኛል ሲሉ አስታውቀዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

09 Nov, 17:08


የኢትዮጵያ አየር ሀይል ዋና አዛዥ የሆኑት ሌተናል ጄነራል ይልማ ከትዊተር (ኤክስ) መተግበርያ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደታገዱ ለማወቅ ችለናል።

እንዲህ አይነቱ ክስተት የሚፈጠረው የሀሰተኛ የጥላቻ ንግግሮችን በሚያሰራጩ ሰዎች ላይ ነው።
ጀነራሉ ወደፊትም በስማቸው የX አካውንት እንዳይከፍቱ ጭምር ነው እግዱ።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Nov, 18:30


ባለፈው ማክሰኞ በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ አርጌ በተባለች አነስተኛ ከተማ በድሮን ጥቃት ሕጻናትን ጨምሮ ከ40 በላይ ሰዎች እንደተገደሉና ከ60 በላይ ሰዎች እንደቆሰሉ ቢቢሲ ነዋሪዎችንና የዓይን እማኞች ጠቅሶ ዘግቧል።

ጥቃቱ ጧት ላይ በገበያ ቦታ አካባቢ፣ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤትና በጤና ጣቢያ ላይ ሦስት ጊዜ እንደተፈጸመ መስማቱን ዘገባው አመልክቷል። ከሟቾቹ መካከል በትምህርት ቤቱ ጊቢ ውስጥ ኳስ በመጫወት ላይ የነበሩ ከ13 በላይ ሕጻናት ጭምር እንደተገደሉ ዘገባው አመልክቷል።

በጤና ጣቢያው ላይ በተፈጸመው ጥቃት ደሞ፣ አምስት ነፍሰ ጡሮችና ኹለት አስታማሚዎች ተገድለው፣ ሦስት ሴት የጤና ባለሙያዎች ቆስለዋል ተብሏል።የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ስለ ጥቃቱ ጥቆማ ጥቆማ ደርሶት መረጃ እያሰባሰብኩ ነው ብሏል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Nov, 18:30


የገንዘብ ሚኒስቴር የፍራንኮ ቫሉታ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቅደው የነበሩ ምርቶች ፍቃድ መሰረዙን አስታወቀ!

የገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔውን ያሳለፈው መንግሥት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ተከትሎ የዋጋ ግሽበት እንዳይከሰት በሚል እንደነበር የገለጸ ሲሆን፤ አሁን ላይ ዋነኛውን ምእራፍ የታለፈ በመሆኑ ፍቃዱን አንስቻለሁ ብሏል።

ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ተፈቅደው የነበሩ የምግብና የፋብሪካ ግብአት የሚውሉ የውጭ ምርቶች መሆናቸውን አሐዱ በሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ ተፈርሞ የወጣ ደብዳቤ ላይ ተመልክቷል።የፍራንኮ ቫሉታ ፍቃዱን ከጥቅምት 29/2017 ዓም ጀምሮ ተግባራዊ የማይደረግ መሆኑን ለጉምሩክ ኮሚሽን አባሪ አድርጎ በላከው ደብዳቤ ላይ ተገልጿል።

መንግሥት የተሟላ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንና ወደ ከፍተኛ ምእራፍ እየተሸጋገረ በመሆኑን ገልጾ፤ ኢኮኖሚው መልካም ውጤቶች የታየበት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።የውጭ ምንዛሪ አቅርቦት በተመለከተ በኢትዮጵያ ያሉ ንግድ ባንኮች በቂ የሚባል የውጭ ምንዛሪ በበቂ ሁኔታ እየቀየረ ስለመሆነ ከእንግዲህ በኃላ ፍራንኮቫሉታ የሚባል ነገር እንደማይኖር የገንዘብ ሚኒስቴር በሚኒስቴሩ አሕመድ ሺዴ ተፈርሞ የወጣን ደብዳቤ ያሳወቀው።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Nov, 18:30


የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሮችን የዘረፉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ንብረት የሆኑ ሦስት የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሮችን ዘርፈው  ለመሸጥ በእንቅስቃሴ ላይ የነበሩ ግለሰቦችን ከነ ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ሥር  መዋላቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርፖሬት  ኮሙኒኬሽን  ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መላኩ ታየ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

የዋግኸምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደጀን ወዳጅ እንደገለፁት ካለፉት 3 ዓመታት ወዲህ በብሄረሰብ አስተዳደር ዞኑ የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ዘረፋ እየተበራከተ መምጣቱን ገልፀው ፤ጥቅምት 25/2017 ዓ.ም በማኅበረሰቡ ጥቆማ   ከነ ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር አውሎ የሰውና የሰነድ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ኮማንደሩ አክለውም ካሁን በፊትም አበርገሌና ሰቆጣ ወረዳ ወለህ አካባቢ ተመሣሣይ የትራንስፈርመር ሥርቆት የፈፀሙ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ለህግ አቅርቦ ውሳኔ መሠጠቱን ገልፀዋል።

በወንጀሉ የተጠረጠሩ  5 ዘራፊዎች ጋር በመቀናጀት ሦስት የኤሌክትሪክ ትራንስፈርመሮችን ዘርፈው ለመሸጥ በመዋዋል ላይ እያሉ መያዛቸውንም የብሄረሰብ አስተዳደር ዞኑ ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ደጀን ጨምረው አስረድተዋል።

ዘረፋና ሥርቆትን ለመከላከል ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ወልድያ ሪጅን ሰቆጣ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩም ተናግረዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Nov, 15:05


የግድያ ፣ የዘረፋ እና የሰው ማገት ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ 11 ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

ለራሳቸው የተለያዩ ስያሜዎችን በመስጠት ለ ሁለት አመታት የግድያ የዘረፋ እና የሰው ማገት ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ 11 ግለሰቦች በእስራት እንዲቀጡ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምዕራብ ኦሮሚያ ምድብ ችሎት ውሳኔ አሳልፏል።

በምስራቅ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በመዘዋወር ለራሳቸው ስያሜ በመስጠት ለሁለት አመታት የግድያ ፣የዘረፋ እና የሰው ማገት ተግባር ሲፈፅሙ የነበሩ 11 ሰዎች በእስራት እንዲቀጡ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምዕራብ ኦሮሚያ ምድብ ችሎት ውሳኔ የሠጠ መሆኑን የምስራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ገልፆል።

እንደ ምስራቅ ወለጋ ፖሊስ መምሪያ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት መግለጫ 11ዱ ግለሰቦች ከ 2014 ጀምሮ በምስራቅ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በመዘዋወር በተለይ በዋዩ ጡቃ፣ ሌቃ ዱለቻዝ ኩቱ ጊዳ በተባሉ ወረዳዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የግድያ ፣ የዘረፋ እና የእገታ ተግባር ሲፈፅሙ እንደነበረ ሙሉ በሙሉ በማስረጃ መረጋገጡን ፅህፈት ቤቱ ገልጿል።እነዚህ ግለሰቦች በሁለት ምድብ ተከፋፍለው የወንጀል ድርጊቱን ሲፈፅሙ እንደነበረ በአቃቤ ህግ ክስ ላይ ተጠቅሷል።

የፊት መሸፈኛ ጭንብሎችን በመጠቀም የተለያዩ ግለሰቦች ቤቶች በምሽት በማስከፈት በርካታ ገንዘብ እና የሞባይል ስልኮችን ዘርፈው እንደወሰዱ የተጠቀሰ ሲሆን በተጨማሪም የግድያ ወንጀል መፈፀማቸውን በአቃቤ ህግ ክስ ላይ ተመዝግቧል።

ግለሰቦቹ በምስራቅ ወለጋ የተለያዩ ወረዳዎች በመንቀሳቀስ የሚፈፅሙትን ወንጀል ድርጊት በመከታተል ፖሊስ እና ሌሎች የፀጥታ አካላት ባደረጉት ክትትል ሰኔ 27 ቀን 2015 ዓ.ም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልፆል። 11ዱ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ የምርመራ መዝገባቸው በፖሊስ ተጣርቶ ለአቃቤ ህግ ተልኳል።

አቃቤ ህግም ከፖሊስ የቀረበውን የክስ መዝገብ ተመልክቶ በከባድ የነፍስ ግድያ እና የውንብድና ተግባር ክስ መስርቷል። በአቃቤ ህግ የተመሠረተውን ክስ ለአመታት ሲከታተል የቆየው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የምዕራብ ኦሮሚያ ምድብ ችሎት ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በነቀምቴ ከተማ ባስቻለው ችሎት በሶስት ግለሰቦች ላይ የ 25 ዓመት እስራት፣ በ ሁለት ተከሳሾች ላይ የ11 አመት ከ ስድስት ወር እስራት ተወስኗል።

በሌሎች ስድስት ተከሳሾች ላይ ደግሞ ከ ሁለት አመት ከ ስድስት ወር እስከ አንድ አመት እስራት የተወሰነባቸው መሆኑን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ከምስራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ይህኛው መረጃ ያሳያል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Nov, 15:05


እስራኤላዊያን እግር ኳስ ደጋፊዎች ጥቃት ደረሰባቸው

ግጭቱ የተከሰተው የእስራኤሉ የማካቢ ቴላቪቭ ቡድን በአያክስ አምስተርዳም 5 ለ 0 ከተሸነፈበት ጨዋታ በኋላ ነው። ደጋፊዎች ከስታዲየም ከወጡ በኋላ ግጭቱ መቀስቀሱም ተገልጿል።

ግጭቱን ተከትሎ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ በፍጥነት ሁለት የህይወት አድን አውሮፕላኖች በኔዘርላንድስ የእስራኤላዊያንን ሕይወት ለመታደግ እንዲላኩ አዘዋል።

የእስራኤሉ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ጌዲዮን ሳር አስር ዜጎች ከሆቴላቸው እንዳይወጡ አሳስበዋል።

የእስራኤል መከላከያ የነፍስ አድን ልዑኩ በካርጎ አውሮፕላን የሚላክ መሆኑን እንዲሁም የጤና እና የሕይወት አድን ቡድኖችን የሚያጠቃልል መሆኑን አስታውቋል።

የሕይወት አድን ስራውም ከኔዘርላንድስ መንግስት ጋር በመተባበር እንደሚደረግ መግለጻቸውን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Nov, 15:05


የአትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም መቀሌ ቅርንጫፍ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ለስራው እንቅፋት አንደሆነበት ገለጸ።

“በክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ባለስልጣን ላይ ክስ መስርቻለሁ” ተቋሙ

የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በትግራይ ክልል በተለይም በመቀለ ተንቀሳቅሶ ስራ መስራት እንዳልቻለ አስታውቋል

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ጸሃዬ እምባዬ ለአዲስ ማለዳ አንደተናገሩት፣በመቀሌ ከተማ የሚገኙ አንዳንድ የመንግስት አመራሮች የተቋሙን ስራ ሆነብለው ያደናቅፋሉ ብለዋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የመቀሌ ከተማ የሀድነት ክፍለ ከተማ የመሬት አስተዳደር ሀላፊ አቶ ብርሃነ ነጋሽ ላይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ክስ መመስረቱን ገልጸዋል።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተገቢውን ምላሽ የማይሰጡ አስፈጻሚ አካላትን ጉዳይ ወደፍርድ ቤት መውሰዱን አንደሚቀጥልም አቶ ጸሃዬ አረጋግጠዋል።

በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ለክልሉ ወግናችሁ በጦርነቱ ተሳትፎ አላደረጋችሁም በሚል ከስራቸው የተሰናበቱ የክልሉ ፖሊስ አባላት ጉዳይ ላይ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ምላሽ አንዲሰጥ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዛሬ ጥቅምት 28/2017 ዓ/ም አንደሚጠናቀቅም ተናግረዋል።

ጉዳዩ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ በቀጣይ ቀናት ጊዜያዊ አስተዳደሩ ላይ ክስ አንደሚከፍቱ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሃላፊ አመልክተዋል።

ለተቋሙ ከሚደርሱ ቅሬታዎች ውስጥ ከፍተኛውን (46.8 በመቶ) ድርሻ የሚይዙት ከስራ ስንብትና ዝውውር ጋር የተያያዙ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Nov, 15:05


ገንዘብ ሚኒስቴር በፍራንኮ ቫሉታ የሚገቡ ምርቶች ላይ ክልከላ ጣለ

ዘይትን ጨምሮ ያለውጭ ምንዛሬ ፍቃድ በፍራንኮ ቫሉታ ይገቡ የነበሩ ምርቶች ላይ ሚኒስቴሩ ክልከላ እንዳደረገ ነው የገለጸው፡፡

በቅርቡ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሺያ ዘላቂ በሆነ መንገድ ውጤታማ እንዲሆን ከማስፈለጉ አንጻር ይህን ውሳኔ መወሰን የግድ ሆኖ መገኘቱም ነው የተገለጸው፡፡

በፍራንኮ ቫሉታ ግዢ የተፈጸመባቸው እቃዎችም ከዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ጀምሮ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ አስፈላጊውን የጉምሩክ መስፈርት በማሟላት እቃቸውን ማውጣት እንደሚገባቸው የገለጸው ገንዘብ ሚኒስቴር ይህን እንዲያስፈጽሙም ለጉምሩክ ኮሚሽንና ለብሄራዊ ባንክ ደብዳቤን ልኳል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተፈርሞ የወጣው ደብዳቤው በቀጣይ ዘይትን ጨምሮ በፍራንኮ ቫሉታ ይገቡ የነበሩ ምርቶች በምን አግባብ በአዲስ አሰራር ይቃኛሉ የሚለው ላይ ግን ግልጽ የሆነ ማብራሪያን አላስቀመጠም፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Nov, 09:08


ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ 163 ጋዜጠኞች ከሥራቸው ጋር በተያያዘ መገደላቸው ተገለጸ

በአንድ ዓመት ብቻ 163 ጋዜጠኞች ከስራቸው ጋር በተያያዘ ለህልፈት መዳረጋቸውን ዩኔስኮ ነው የገለጸው፡፡

ከተገደሉት ጋዜጠኞች በተጨማሪም ከሥራቸው ጋር በተያያዘ የሚታሰሩ ጋዜጠኞች ቁጥርም እምብዛም አለመቀነሱን አስታውቋል።

በዚህ መሰረት የዛሬ አስር ዓመት 95 በመቶ የነበረው የተገደሉ ጋዜጠኞች ፍትህ ያለማግኘ ሁኔታ ከአስር ዓመት በኋላም ቢሆን በ10 በመቶ ብቻ ቀንሶ 85 በመቶ ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

በጋዜጠኞች ላይ የሚደርሱ ግድያዎች፣ እስሮች እና መንገላታቶች ባለሙያዎችን ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸው ደህንነት ሲሉ ከሙያው እራሳቸውን እንዲያገሉ እያደረገ መሆኑን የገለጸው ተቋሙ በዚህም ምክንያት ሙያው አስጊ ከሚባሉ የስራ መስኮች በቀዳሚነት የሚመደብ እንደሆነ አስታውቋል።

ዩኔስኮ እነዚህን ነጥቦች ያነሳው በመዲናችን አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው ጋዜጠኞች በግጭት ቦታዎች ላይ እየገጠማቸው ያለውን የደህንነት ችግር ለመፍታት በሚመክረው 10ኛው ጉባዔው ላይ ነው፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Nov, 09:08


ፑቲን ትራምፕ ደፋር ነዉ አሉ‼️

የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ተመራጩን የአሜሪካ ቀጣይ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን እንኳን ደስ አልዎት ብለዋቸዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕም ለፑቲን እደዉላለሁ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በሶቺ ቫልዳይ ጉባዔ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ፑቲን ትራምፕ ደፋር ሰዉ ነዉ ብለዋል፡፡

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የተናገረዉን ሁሉ ማመን ባይቻልም ነገር ግን ከዩክሬን ቀዉስ ጋር ተያይዞ ያነሳዉን ሀሳብ ትኩረት መስጠት ይገባል ነዉ ያሉት ፑቲን፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ዶናልድ ትራም ደፋር ነዉ ያስገርመኛል ያሉት ፑቲን ከፖለቲካ ይልቅ የቢዝነስ ሰዉ በመሆኑ ብዙ ስህተቶችን ከዚህ ቀደም ይሰራ ነበር ሲሉም አንስተዋል፡፡

ሞስኮ ከዋሽንግተን ጋር ለመነጋገር በሯ ክፍት ስለመሆኑም ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል፡፡

ኔቶን አስመልከተዉ ሲናገሩም የጦር ጎራዉ ጊዜዉን የሳተ ስብስብ ሲሉ ወርፈዋቸዋል፡፡

የትራምፕን መመረጥ ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ የተቀመጡት የአዉሮፓ አገራት መሪዎቸ አደጋ ዉስጥ ነን እያሉ ነዉ፡፡

አውሮፓ ካማላ ወይም ትራምፕ ስለተመረጡ ሳይሆን የራሱን እጣፈንታ የሚወስንበትን አቅም ሊገነባ ይገባል ብለዋል፡፡

ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ከአውሮፓ ጋር ከሚኖረው የንግድ ጦርነት አንስቶ ከኔቶ ለመውጣት እና ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ጦርነት መሰረታዊ የሆነ የድጋፍ ለውጥ እንደሚያደርጉ ዝተዋል፡፡

ይህም በመላው አውሮፓ በሚገኙ ሀጋራት ላይ ከፍ ያለተጽዕኖ ሊያስከትል እንደሚችል ኤፒ ዘግቧል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

08 Nov, 09:08


የኢትዮጵያ እና ሩሲያ የትምህርት ተቋት በትብብር ለመስራት ተስማሙ

የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር እና የሩሲያ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፤ በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

እኩልነት፣ የጋራ ተጠቃሚነትና ውጤታማነት መርህ ላይ የተመሰረተ ነው የተባለው ይህ ስምምነት፤ ሁለቱ ሀገራት በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸው ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ በዚህ ወቅት፤ ሩሲያ የሰው ሃይል በማብቃት ዙርያ ድጋፏን አጠናክራ እንድትቀጥል ጠይቀዋል። ስምምነቱን ወደ ተግባር ለማስገባት፤ በሁለቱም ሀገራት በኩል የቴክኒክ ቡድን እንደሚቋቋም፤ የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ አስታውቋል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

07 Nov, 16:13


ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ ኢትዮጵያ በቀጣዩ ሰኔ ወር ይኖራታል ብሎ የሚገምተውን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ወደ 400 ሚሊዮን ዶላር ከፍ አድርጎታል።

ባለፈው ነሐሴ የአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት መጠን 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር የጠቀሰው ድርጅቱ፣ ይህም በእቅድ ተይዞ ከነበረው 630 ሚሊዮን ዶላር በእጥፍ የበለጠ ነበር ብሏል። የነሃሴ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከፍተኛ የነበረው፣ ብሄራዊ ባንክ ለጨረታ ያቀረበው የውጭ ምንዛሬ መጠን ከተጠበቀው በታች በመኾኑና የወርቅ ሽያጭ በመጨመሩ እንደኾነ ድርጅቱ ጠቅሷል።

ድርጅቱ አያይዞም፣ መንግሥት በ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮቦንድ ብድር ሽግሽግ ዙሪያ ከዩሮቦንድ ያዥ ዓለማቀፍ ኢንቨስተሮች ጋር ከስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት እያደረገ መኾኑን ገልጧል።

ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት፣ ኢትዮጵያ በቀጣዩ ሰኔ ወር ይኖራታል ብሎ የሚገምተውን የውጭ ምንዛሬ ክምችት ወደ 400 ሚሊዮን ዶላር ከፍ አድርጎታል።

ባለፈው ነሐሴ የአገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችት መጠን 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር የጠቀሰው ድርጅቱ፣ ይህም በእቅድ ተይዞ ከነበረው 630 ሚሊዮን ዶላር በእጥፍ የበለጠ ነበር ብሏል።

የነሃሴ የውጭ ምንዛሬ ክምችት ከፍተኛ የነበረው፣ ብሄራዊ ባንክ ለጨረታ ያቀረበው የውጭ ምንዛሬ መጠን ከተጠበቀው በታች በመኾኑና የወርቅ ሽያጭ በመጨመሩ እንደኾነ ድርጅቱ ጠቅሷል።

ድርጅቱ አያይዞም፣ መንግሥት በ1 ቢሊዮን ዶላር ዩሮቦንድ ብድር ሽግሽግ ዙሪያ ከዩሮቦንድ ያዥ ዓለማቀፍ ኢንቨስተሮች ጋር ከስምምነት ላይ ለመድረስ ጥረት እያደረገ መኾኑን ገልጧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

07 Nov, 16:13


ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ከ297 ሚሊዮን ብር በላይ እና 151 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ሃብት ታግዶ የወንጀል ምርመራ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የኦዲት ግኝት የባለድርሻ አካላት የትብብር ፎረም ገለጸ፡፡

የሦስት ዓመታት የኦዲት ግኝት የባለድርሻ አካላት የትብብር ፎረም የጋራ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ውይይት ትላንት ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተካሂዷል፡፡

ፎረሙ ባለፉት ሦስት ዓመታት ትግበራው፤ ከ297 ሚሊዮን ብር በላይ እና 150 ሚሊዮን 504ሺህ ዶላር ያህል ሃብት እግድ እንዲወጣ ማድረጉን በሪፖርቱ አመልክተዋል፡፡እንዲሁም 46 መኖሪያ ቤቶች እና አንድ ሕንጻ፣ 86 ተሽከርካሪዎች፣ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን የሚያወጣ የአክሲዮን ብር ዋጋ ያለው፣ 81 ሺህ ገደማ ካሬ የመሬት ይዞታዎች እግድ እንደወጣባቸው ተመልክቷል።

ፎረሙ ባካሄደው ግምገማ በፋይናንስ ሕጋዊነት ኦዲት በግኝት ከለያቸው መካከል የጥሬ ገንዘብ ጉድለት፣ ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከአንድ ወር ጀምሮ 10 ዓመትና ከዚያ በላይ የቆየ መሆኑ፣ የመንግሥትን ገቢ በወጡ ሕጎች መሠረት አለመሰብሰብ፣ ሕግን ያልተከተሉ ክፍያዎች መፈጸም ይገኙበታል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

07 Nov, 16:13


ባህር ዳር ከተማ በሰው ማገትና ዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ 121 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ!

በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር ከተማ በተቀናጀ መንገድ በተከናወነ የህግ ማስከበር ተግባር ተደራጅተው በሰው ማገትና ዘረፋ ወንጀል የተጠረጠሩ 121 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማ አስተዳደሩ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ አስታወቀ።የመምሪያው ኃላፊ አቶ ጌትነት አናጋው ዛሬ በሰጡት መግለጫ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች በማወክ ህብረተሰቡን ለስጋት ሲዳርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።

በተጨማሪም ለተለያዩ ባለሃብቶችና ግለሰቦች ስልክ በመደወልና በማፈን ገንዘብ ሲቀበሉና ህብረተሰቡን ለምሬት ሲዳርጉ የቆዩ መሆናቸውን አብራርተዋል። ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸው በህግ አግባብ የምርመራ ሂደት ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል።በተከናወነው ጠንካራ የህግ ማስክበር ስራም አሁን ላይ ችግሩ እየተቃለለ መምጣቱን ጠቅሰው፤ ህግ የማስከበሩ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቀዋል።

ይህም ሰላም ‘በዘላቂነት እንዲረጋገጥ’ እንዲሁም የከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሳለጡ ማድረግ መቻሉን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

07 Nov, 11:02


ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2017 ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ።

ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል)፣ አማኑኤል መውጫ፣ ናትናኤል ወንድወሰን፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት እና እሌኒ ክንፈ የተባሉ ስድስት ተከሳሾች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነትን አደጋ ላይ ለመጣል ተንቀሳቅሰዋል በሚል የቀረበባቸው ክስ ላይ የወንጀል ድርጊት እንዳልፈጸሙ ጠቅሰው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ዛሬ ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በተከሳሾቹ ላይ ከአንድ ወር በፊት አውሮፕላንን ያለአግባብ መያዝ ወንጀል፣ የመንግስት ሰራተኛ የስራ ግዴታውን እንዳይፈጽም መቃወምና አለመታዘዝ ወንጀል ክስ እንዲሁም በ1ኛ ተከሳሽ ብቻ ደግሞ የአየር መንገዱን መልካም ስም ለሚያጎድፍ በተንቀሳቃሽ ምስል በኮምፒውተር ስርዓት አማካኝነት ማሰራጨት ወንጀል የሚል ክስ ማቅረቡ ይታወሳል።

ከዚህም በኋላ ተከሳሾቹ በክሱ ዝርዝር የተገለጸውን የወንጀል ድርጊት ሰለመፈጸም አለመፈጸማቸው በፍርድ ቤቱ በቀረበላቸው ጥያቄ መሰረት "የወንጀል ድርጊቱን አልፈጸምንም " በማለት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ከሳሽ ዐቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም ያስረዱልኛል ያላቸው ምስክሮች ቃል እንዲሰማለት በጠየቀው ተለዋጭ ቀጠሮ መሰረት የምስክር ቃል ለመስማት ለሁለት ቀን ማለትም ለሕዳር 18 እና ለሕዳር 19 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

07 Nov, 11:02


ኢሰመጉ በአማራ ክልል በአዊ ብሄረሰብ ዞን አረጋዊያንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ገለጸ

”በወልቂጤ ከተማም ብሄርን መሰረት በማድረግ በርካታ ሰዎች ታስረዋል” ጉባዔው

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ባወጣው መግለጫ ጥቅምት 17/2017 በአማራ ክልል በአዊ ብሄረሰብ ዞን አዲስ ቅዳም ከተማ የፋኖ ደጋፊ ናችኹ በሚል አረጋዊያንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መግደላቸውን ገልጿል።

በክልሉ በቀጠለው ግጭት በመንግስትና በፋኖ ታጣቂዎች በሚተኮሱ ጥይቶች የንጹሀን ሰዎች ህይወት አያለፈ አንደሚገኝ በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ቦሩ ወረዳ እና ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ “በታጠቁ አካላት” በተፈጸመ ጥቃት በርካታ የንጹሀን ሰዎች እንደተገደሉ አስታውቋል።

በማእከላዊ ኢትዮጵያ አና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በርካታ ሰዎች ያለፍርድ ቤት ተእዛዝ በቁጥጥር ስር ውለው በተለያዩ ማቆያ ጣቢያዎች እንደድሚገኙ ኢሰመጉ አመልክቷል።

በተለይም በወልቂጤ ከተማ የሚታየው የዜጎች እስር ብሄርን መሰረት ያደረገ መሆኑን ጠቁሟል።

የፌደራል አና የሚመለከታቸው የክልል መንግስታት አነዚህን የመብት ጥሰቶች እንዲያስቆሙ ኢሰመጉ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

07 Nov, 11:02


🇪🇹ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ በትክክለኛ ጎዳና ላይ ነች ሲሉ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ ተገናሩ

ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባ በተካሄደው "ከረሃብ ነፃ ዓለም" ጉባዔ ተሳታፊ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ ሚኒስትሮችና የተቋማት ኃላፊዎች የእራት ግብዣ በተደረገበት ወቅት የተናገሩት ነው።

ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በግዜው ባደረጉት ንግግር፤ ረሃብ በርካታ የአፍሪካ ሀገራትን የፈተነና ችግር ፈቺ መፍትሔ የሚሻ የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ፤ ረሃብ የሚያስከትለውን ጉዳት በጽኑ ትገነዘባለችም ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚያስችል ትክክለኛ መንገድ ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል።

አክለውም፤ ኢትዮጵያ በስንዴ ራሷን ከመቻል ባለፈ ለውጭ ገበያ መላክ የሚያስችል አቅም መፍጠሯን ጠቅሰው፤ በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እያበረከቱት ያለውን የመሪነት ሚና አድንቀዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

07 Nov, 11:02


ብሔራዊ ባንክ ለሁሉም የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች የዲጂታል ክፍያ በQR ኮድ እንዲሆን ትዕዛዝ መስጠቱን ገለጸ!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለሁሉም የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች የዲጂታል ክፍያ በQR ኮድ ከህዳር 22 ቀን 2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንደያደርጉ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡አዲሱ መመሪያ ከጥሬ ገንዘብ ንክኪ ነጻ የሆነውን የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በኢትዮጵያ ለማጎልበት እየተሰራ ያለውን ስራ ለማጠናከር እንደሚያግዝ እና የዲጂታል ግብይትን እየለመደ ያለውን ማህበረሰብ በይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ይህ ኢት ኪውአር ኮድ (EthQR Code) የሚል ሥያሜ የሚኖረው አሠራር ዓለምአቀፍ የአሠራር ልምዶችን መሠረት ያደረገ፣ የክፍያም ሆነ የግብይት ተዋናያንን ሙሉ መረጃ የሚይዝ ነገር ግን ከተወሰኑ አስፈላጊ መረጃዎች በቀር ሌሎቹን በምሥጢር የሚጠብቅ ሥርዓት መሆኑ ተገልጿል።

ባንኩ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የዲጂታል ክፍያ አገልግሎትና ግብይት የጥሬ ገንዘብን ዝውውር የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ፣ ሕብረተሰቡ ለሥርቆት፣ በእጁ ያለው ገንዘቡም ለእርጅና እንዳይጋለጥ፤ ከባንክ ውጭ የሚዘዋወር የገንዘብ መጠን እንዲቀንስ፣ ብሎም በአገር አቀፍ ደረጃ ገንዘቡን ለማሳተም የሚወጣ ወጪን እንዳይጨምር ለማድረግ ይረዳል ብሏል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

07 Nov, 08:24


በየሳምንቱ በአማካይ ከ70 ሺሕ በላይ የወባ ሪፖርቶች እንደሚደርሰው የአማራ ክልል ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ!

የአማራ ክልልን ከ80 በመቶ በላይ የቆዳ ስፋት በሚሸፍኑት የምዕራብ አማራ፣ ጎንደር፣ ጎጃም እንዲሁም በምስራቅ አማራ ሰሜን ወሎ አከባቢዎች ከመስከረም ወር መግቢያ ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የወባ ወረርሽኝ መስፋፋቱ ተገልጿል፡፡በክልሉ በ40 ወረዳዎች በየሳምንቱ የሚደረገው የወባ ምርመራ ሪፖርት እንደሚደርሳቸው የገለጹት፤ የአማራ ክልል የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በላይ በዛብህ ናቸው፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም፤ በየሳምንቱ በአማካይ ከ70 ሺሕ በላይ የወባ ሪፖርቶች ለኢንስቲትዩቱ እንደሚደርሰው ተናግረዋል፡፡ከወባ ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የመድኃኒት እጥረት መኖሩን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ጉዳዩን በተደጋጋሚ ለጤና ሚኒስቴር ማቅረባቸውን ነግረውናል፡፡የጤና ሚኒስቴር ባሳለፍነው ሳምንት በቂ የወባ በሽታ መድኃኒት ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባቱን መግለጹ አይዘነጋም።

የወባ ወረርሽኝ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች በስፋት እየተስተዋል የሚገኝ ሲሆን፤በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማን ጨምሮ በሰባት ወረዳዎች እንዲሆም በወላይታና በሌሎች ከተሞች እና እካባቢዎች በአሳሳቢ ደረጃ እየተከሰተ መሆኑ እየተዘገበ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል የዓለም ጤና ድርጅት ከቀናት በፊት አዲስ ባወጣው ሪፖርት፤ በኢትዮጵያ ከታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ፤ ከ7 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን የገለጸ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል 1 ሺሕ 157 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል።በሪፖርቱ ወባ አሁንም አሳሳቢ የጤና ስጋት መሆኑን የገለጸ ሲሆን፤ 75 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ መሬት እና 69 በመቶ የሚሆነው በነዚህ አካባቢዎች የሚኖረው ሕዝብ በተለይም ሕጻናት ለከፍተኛ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸውንም ገልጿል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

07 Nov, 08:24


የ1997 የኮንዶምንየም ተመዝጋቢዎች የኛ እጣ ጉዳይ ምን ይሻላል በማለት ላይ ናቸው።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በአካውንቱ ውስጥ በቂ ብር ተቆጥቦ እያለ በቤቶችና በባንክ መካከል የመናበብ ችግር ምክንያት እጣው ሳይወጣ ቀርቶ እያለ ነገር ግን ችግሩ ምንድነው ብለን ወደ ቤቶች በማቅናት ስንጠይቅ ያገኘነው ምላሽ ግን ባንክ ያስገባችሁት ገንዘብ እነሱ ጋር 0 ቁጠባ እንደሚል እና ከባንክ በተመዝጋቢው ስም የኮንደሚንየም ቁጠባ የብር መጠኑን አጽፈን ደብዳቤ እንድናመጣ በታዘዝነው መሰረት አምጥተን ለቤቶች አስገብተን ደብዳቤውን ሲስተም ላይ ለማስገባት እያመለላለሱን 4ወር ሆኖናል በማለት በርካቶች ቅሬታቸው አቅርበዋል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ ሲናገሩም መንግስትን አምነን የቆጠብነውን ገንዘብ በራሱ በመንግስት መስርያ ቤት ሰራተኞች ስህተት ምክንያት 0 ብር ነው በማለት ማስቀመጣቸው ሳያንስ የእኛን ጉዳይ ምን ለማድረግ እንዳታሰበ እና ጉዳያችን ቸል ሊባል አይገባም የኛን ጉዳይ ሁሉም ይወቀው በማለት ላይ ናቸው።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

06 Nov, 07:03


ሰበር ዜና!!

ዶናልድ ጆን ትራምፕ 47ተኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን ፎክስ ዘግቧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

06 Nov, 06:01


#Update

ዶናልድ ትራምፕ ወላዋይ ከሚባሉት አንዱ የሆነውን ሰሜን ካራልዮናን አሸንፈዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

06 Nov, 06:01


#Update

ዶናልድ ትራምፕ ሌላኛውን ወላዋይ ግዛት ጂዮርጂያን ማሸነፋቸውን ሲቢኤስ ዘግቧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

06 Nov, 06:00


ኒውዮርክ ታይምስ ዶናልድ ትራምፕ ምርጫውን የማሸነፈቸው እድል ወደ 78% ከፍ ማለቱን እየዘገበ ይገኛል።ይሁን እንጂ ወላዋይ የሚባሉት ግዛቶች ውጤት ገና ይፋ አልተደረገም።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Nov, 17:47


በዚህ ወር ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ_ጭማሪ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

መንግሥት ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ያለው የመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ፣ በዚህ ወር ተግባራዊ አለመሆኑን ተሰምቷል።


በአአ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ መንግሥት ሠራተኞች በተወሰኑ ወረዳዎች ከሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን እና ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

ቢሮው፣ ለከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ሰራተኞች ጭማሪው የሚከፈልበት ጊዜ የተራዘመው የሰራተኞችን መረጃ ለማደራጀት ጊዜ ስለሚያስፈልግ ነው የሚል ምላሽ ሰጥቷል ።
ሆኖም ሰራተኞቹ ቢሮው እስካሁን ምን ያህል የመንግስት ሰራተኛ እንዳለ እና ሌሎች ከደሞዝ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን አያውቅም ወይ? የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ተሰምቷል ።

ሰራተኞቹ እስካሁን የተጨመረላቸውን ደሞዝ የሚገልጽ ይፋዊ ደብዳቤ አልደረሳቸውም።
በተጨማሪም ከተማ አስተዳደሩ አዲስ የመዋቅር ማሻሻያ አደረጃጀት ጥናት አድርገው የብቃት መመዘኛ ፈተና ለሰጡት ተቋማት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪው ይዘገያል መባሉንም ዋዜማ ተገንዝባለች። ጭማሪው የሚዘገየው ተቋማቱ የሰራተኞችን የሥራ ደረጃ ምደባ ገና ስላልጨረሱ ነው ተብሏል።
ከተማ አስተዳደሩ በመጀመሪያው ዙር የብቃት ምዘና ፈተና የተሰጠው ለቤቶች ልማት አስተዳደር ጽህፈት ቤት፣ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት፣ የሥራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ፅሕፈት ቤት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅሕፈት ቤት፣ ኅብረት ሥራ ፅሕፈት ቤት እና የመሬት ልማት አስተዳደር ፅሕፈት ቤት መሆኑ ይታወሳል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Nov, 17:47


በጆርጂያ በሐሰተኛ የቦምብ ዛቻዎች የተነሳ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ምርጫ ተቋረጠ!

በጆርጂያ አምስት ሐሰተኛ የቦምብ ዛቻዎች ነበሩ ሲል ሲቢኤስ ዘግቧል።የአካባቢው የምርጫ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት ናዳይን ዊሊያምስ በዛቻው የተነሳ በሁለት የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች በግምት ለ30 ደቂቃዎች ቦታውን ለቀው ወጥተው ነበር ብሏል።

አካባቢው አትላንታ ከተማን የሚያካትት ሲሆን፣ በሁለቱ ስጋቱ ተከስቶባቸው በነበሩ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ሰዓትን ለማራዘም የፍርድ ቤት ይሁንታን ለማግኘት እየተሞከረ እንደሆነ አስታውቋል።

በተመሳሳይ ዜና በፔንሴልቫንያ እንዲሁ በተፈጠረ የቴክኒክ ችግር ምክንያት መራጮች የምርጫ ወረቀታቸውን ስካን ማድረግ ባለመቻላቸው የተነሳ ለባከኑ ሰዓታት የምርጫ ሰዓቱን ለማራዘም ለፍርድ ቤት ጥያቄ መቅረቡ ተሰምቷል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Nov, 17:47


❗️መከላከያ ሰራዊቱ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከፍተኛ  አመራርን ገድያለሁ አለ

የኢፊዴሪ መከላከያ ሰራዊት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሸኔ  አመራርን  የነበሩትን   ጃል እንሰርሙ ከነግብረ አበሮቹ  ደምስሻለሁ ሲል ጃል ኦብሳ የተባለው ደግሞ በቁጥጥር ስር አዉያለሁ አለ ፡፡

ሰራዊቱ ይሄን ያለዉ የመከላከያ ሰራዊቱ 6ኛ ዕዝ ዋልታ ክፍለጦር በወረ ጃርሶ ወረዳ በአቡ ኬኮ ቀበሌ በኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ላይ ወሰድኩት ባለዉ ጥቃት ነዉ ፡፡

የማዕከላዊ ዕዝ ክፍለ ጦር በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና አሸባሪው የሚሉትን  የኦነግ ጦር  በማሳደድ የመደምሰስ ስራ እየሰራ መሆኑን  የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔሌ ደጀኔ ፈይሳ ተናግረዋል ፡፡

ኮሎኔሉ ይሄን ይበሉ እንጂ ኦነግ ሸኔ በቅርቡ ብዛት ያላቸዉን የመንግስት የስራ አመራሮች የፀጥታ ሀይሎች እንዲሁም ንፁሃን ገበሬዎችን ከአዲስ ቅርብ እርቀት መግደሉ አይዘነጋም ፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Nov, 17:47


በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ኤርባስ A350-1000 አውሮፕላን አዲስ አበባ ሲደርስ የተደረገ የአቀባበል መርሐ ግብር በምስል

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Nov, 08:29


የትግራይ ነጻነት ፓርቲ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን የትግራይ የጦርነት ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው እንደተመለሱና የተቋረጡ መሠረተ ልማቶች አገልግሎት እንደጀመሩ አድርገው የፕሪቶሪያውን ግጭት ማቆም ስምምነት ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት ሰሞኑን የሰጡትን አስተያየት ነቅፏል።

እንዲህ ያለው አስተያየት "አሳሳች ነው" ያለው ፓርቲው፣ የምዕራብ ትግራይ እንዲኹም አብዛኞቹ የምሥራቅ እና ደቡባዊ ትግራይ የጦርነት ተፈናቃዮች እስካኹን ወደ ቀያቸው እንዳልተመለሱ ገልጧል።

የብሊንከን አስተያየት፣ በትግራይ ባኹኑ ወቅት ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ የሚያጣጥልና አኹንም ተፈናቅለው የሚገኙ ዜጎችን አደጋ ላይ የሚጥል ነው በማለት ተችቷል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Nov, 08:29


የሱዳን ሉዓላዊ ምክርቤት ፕሬዝዳንት አል-ቡርሃን አዲስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሾሙ‼️

የሱዳን ጦር አዛዥ እና የሉዓላዊው ምክር ቤት ፕሬዝዴንቱ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን አዲስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ሌሎች ሶስት ሚኒስትሮችን እሁድ ዕለት መሾማቸውን አስታውቀዋል።

አምባሳደር አሊ የሱፍ አህመድ አል ሻሪፍ በአምባሳደር ሁሴን አዋድ ምትክ በመሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተደርገው ተሹመዋል።  አል-ቡርሃን ከ2021 መፈንቅለ መንግስት በኋላ የተሾሙትን አምባሳደር አሊ አል-ሳዲቅን ነው አሁን በአዋድን የተኩት።አሊ ዩሱፍ ጡረታ ከመውጣታቸው በፊት በሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ በበርካታ ቦታዎች ላይ ሠርተዋል።

የ2021 መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ የተፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት በሚጥር የሽማግሌዎች ኮሚቴ ውስጥ እና የአረብ-ቻይና ወዳጅነት ማህበራትን ይመሩ ነበር።የካቢኔ ሹም-ሽሩ ካሊድ አል አሲር ግርሃም አብደልቃድርን የባህል እና የማስታወቂያ ሚኒስትር አድርጓል። ኑሮራአቸውን ለንደን ያደረጉት አል አሲር የቡርሃን ሚዲያ እንቅስቃሴን በመደገፍ እና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ መንግስት ላይ የተካሄደውን መፈንቅለ መንግስት በማገዝ ይታወቃሉ።

ኦማር ባሂት መሀመድ አደም ደግሞ የሃይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል። ኦማር አህመድ መሃመድ አሊ ባንፊርም የንግድ እና አቅርቦት ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።እ.ኤ.አ. በጥር 2022 አል ቡርሃን የፈጣን የድጋፍ ሰጪ ኃይሎችን ይደግፋሉ ብለው ካሰናበቷቸው ሁለት ሰዎች በስተቀር የዳርፉር ታጤቂ ንቅናቄ እና የሱዳን ህዝቦች ነፃ አውጪ ንቅናቄ አባላት በነበሩበት የሚኒስተርነት ቦታ በማቆየት የበታች ፀሃፊዎችን በሚኒስትርነት ቦታ ሾመዋል።

የካቢኔ ለውጡ የተደረገው በሚያዝያ ወር በተቀሰቀሰው በሰራዊቱ እና በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሎች መካከል ያለው ደም አፋሳሽ ግጭት ተጠናክሮ በቀጠለበት በዚህ ወቅት ነው።አል ቡርሃን በጥቅምት 2021 በሲቪል የሚመራውን የሽግግር መንግስት ያስወገደው መፈንቅለ መንግስት በመምራት ሰፊ ተቃውሞዎችን እና አለም አቀፍ ውግዘቶችን አስተናግደው ነበር።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Nov, 08:29


❗️ደመወዝ

በዚህ ወር ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የመንግስት ሰራተኞች የደመወዝ_ጭማሪ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ
መንግሥት ከጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ያለው የመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ፣ በዚህ ወር ተግባራዊ አለመሆኑን ተሰምቷል።

በአአ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ መንግሥት ሠራተኞች በተወሰኑ ወረዳዎች ከሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን እና ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል።

ቢሮው፣ ለከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ሰራተኞች ጭማሪው የሚከፈልበት ጊዜ የተራዘመው የሰራተኞችን መረጃ ለማደራጀት ጊዜ ስለሚያስፈልግ ነው የሚል ምላሽ ሰጥቷል ።
ሆኖም ሰራተኞቹ ቢሮው እስካሁን ምን ያህል የመንግስት ሰራተኛ እንዳለ እና ሌሎች ከደሞዝ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን አያውቅም ወይ? የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ተሰምቷል ።

ሰራተኞቹ እስካሁን የተጨመረላቸውን ደሞዝ የሚገልጽ ይፋዊ ደብዳቤ አልደረሳቸውም።
በተጨማሪም ከተማ አስተዳደሩ አዲስ የመዋቅር ማሻሻያ አደረጃጀት ጥናት አድርገው የብቃት መመዘኛ ፈተና ለሰጡት ተቋማት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪው ይዘገያል መባሉንም ዋዜማ ተገንዝባለች። ጭማሪው የሚዘገየው ተቋማቱ የሰራተኞችን የሥራ ደረጃ ምደባ ገና ስላልጨረሱ ነው ተብሏል። 
ከተማ አስተዳደሩ በመጀመሪያው ዙር የብቃት ምዘና ፈተና የተሰጠው ለቤቶች ልማት አስተዳደር ጽህፈት ቤት፣ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽህፈት ቤት፣ የሥራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ፅሕፈት ቤት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ፅሕፈት ቤት፣ ኅብረት ሥራ ፅሕፈት ቤት እና የመሬት ልማት አስተዳደር ፅሕፈት ቤት መሆኑ ይታወሳል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Nov, 08:29


“በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት አሳስቦናል፣ በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያሉ የእርስ በርስ ግጭቶች እልባት እንዲያገኙ የፖለቲካ ውይይት ወሳኝነት አለው” - አንቶኒ ብሊንከን

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በስልክ ማውራታቸው ተገለጸ።“በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያሉ የእርስ በርስ ግጭቶች እልባት እንዲያገኙ የፖለቲካ ውይይት ወሳኝነት አለው” ሲሉ አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር አብይ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት ወቅት መናገራቸው የመስሪያ ቤታቸው መግለጫ አመላክቷል።

አሜሪካ “በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት ያሳስባታል” ሲሉ መናገራቸውን መግለጫው አካቷል።አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚኒስትር አብይ ጋር በስልክ ያወሩት በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ዙሪያ እንደነበር ጸ/ቤታቸው ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።አንቶኒ ብሊንከን “ኢትዮጵያ የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲደረግ ለምታደርገው ጥረት ሀገራቸው እገዛ ለማድረግ ዝግጁ ናት” ሲሉ መናገራቸውን መግለጫው ጠቁሟል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ጠ/ሚኒሰትር አብይ በአፍሪካ ቀንድ እየተካረረ በመጣው ውጥረት ዙሪያም መምከራቸውንም የመስሪያ ቤታቸው ቃል አቀባይ ቢሮ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Nov, 08:29


ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕዳ መክፈያ እና ካፒታል ማሳደጊያ የሚውል 900 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው ቦንድ ለሽያጭ ሊቀርብ ነው!

የገንዘብ ሚኒስቴር 900 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያለው የመንግስት ዕዳ ሰነድ (ቦንድ) እንዲያወጣ የሚፈቅድ የአዋጅ ረቂቅ ለፓርላማ ቀረበ። ገንዘቡ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልከፈሉትን ዕዳ ለመክፈል እና ለባንኩ ካፒታል ማሳደጊያ የሚውል ነው።ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 26፤ 2017 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ የቀረበው ይህ አዋጅ፤ “የመንግስት እዳ ሰነድ” የሚል ስያሜን የያዘ ነው።

አዋጁን ማውጣት ያስፈለገው፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለበት “ከፍተኛ ዕዳ” በባንኩ የፋይናንስ ገጽታ ላይ “ከፍተኛ ተጽዕኖ ስላስከተለ” መሆኑ በረቂቅ ህጉ ላይ ተጠቅሷል።የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመንግስት ለልማት ድርጅቶች ካበደረው ውስጥ እስካሁን ያልተሰበሰበው የገንዘብ መጠን፤ ከ846 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል። የልማት ድርጅቶቹ ብድሩን ከመንግስታዊው ባንክ የወሰዱት፤ ለተለያዩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ነው።

መንግስት የልማት ድርጅቶቹ ውስጥ ያልተከፈለ ከፍተኛ ብድር ያለበት፤ የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን ነው። ኮርፖሬሽኑ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መክፈል ይገባው የነበረው ብድር ከእነ ወለዱ 191.79 ቢሊዮን ብር እንደሆነ አዋጁን ለማብራራት በቀረበ ሰነድ ላይ ተጠቅሷል።ከመንግስት ተቋሟት መካከል ባልተከፈለ ከፍተኛ የብድር መጠን ሁለተኛውን ቦታ የያዘው፤ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ነው።

የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን በሁለት ዙር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተበደረው የገንዘብ መጠን ከእነ ወለዱ 110.68 ቢሊዮን ብር እንደሆነ በአዋጅ ማብራሪያው ላይ ሰፍሯል።እንደ ስኳር ኮርፖሬሽን ሁሉ በሁለት ዙሮች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ የተበደረው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፤ ባልተከፈለ የከፍተኛ ብድር መጠን ሶስተኛውን ቦታ ይዟል።የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተበደረው የገንዘብ መጠን ከእነ ወለዱ ሲሰላ 80.17 ቢሊዮን ብር ነው።

ከእነዚህ ሶስት የመንግስት ልማት ድርጅቶች በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩኘ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች የተባሉት የመንግስት ተቋማትም በቢሊዮኖች የሚቆጠር ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መበደራቸውን ለፓርላማ የቀረበው ሰነድ ዘርዝሯል።የልማት ድርጅቶቹ በዚህ መልክ የተበደሩትን ገንዘብ ለሜጋ ፕሮጀክቶች ቢያውሉትም፤ ፕሮጀክቶቹ “ከጥናት ጀምሮ በርካታ የተወሳሰበ ችግር ያለባቸው” መሆኑን የአዋጅ ማብራሪያ ሰነዱ አትቷል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Nov, 08:29


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን አውሮፕላን ተረከበ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤር ባስ A350-1000 አውሮፕላን በፈረንሳይ ቱሉዝ ከኤርባስ ኩባንያ መረከቡን አስታወቀ፡፡400 መቀመጫዎች ያሉት አውሮፕላኑ የላቀ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ቴክኖሎጂ የተገጠመለትና Ethiopia land of origins የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

በርክክብ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው፣ የአየር መንገዱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች፣ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር አሌክሲ ለሚክ፣ የኤር ባስ ኩባንያ ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ተብሏል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ አየር መንገዱ 124 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙን መናገራቸው ይታወሳል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

05 Nov, 08:29


ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የውጭ ብድር ሰጠች!

በአለም አዲስ አገር ለሆነችው ደቡብ ሱዳን የተሰጠው ብድር በሁለቱ አገራት መካከል አገናኝ ለሚሆን መንገድ ግንባታ የሚውል ነው።የአራት አመት እፎይታ ኖሮት በ10 አመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቀው ብድር ከ738 ሚሊየን ዶላር በላይ ነው።

በደቡብ ሱዳን ድንበር ውስጥ የሚገነባው 220 ኪሜ መንገድ በኢትዮጵያ ተቋራጮች እና አማካሪዎች እንዲከናወን በሁለቱ አገራት ከስምምነት መደረሱ ተገልጿል።የብድር አመላለሱም በካሽ እና በድፍድፍ ነዳጅ እንደሚሆን ነው የተጠቀሰው።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 18:54


መረጃ‼️

ግብጽ፣ የጦር መሳሪያ ድጋፍ በመርከብ ጭና ለሱማሊያ መላኳን የሱማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ጦር መሳሪያውን የጫነችው መርከብ ሞቃዲሾ የደረሰችው ዕሁድ'ለት እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የባሕር በር መግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች ወዲህ፣ ግብጽ የሱማሊያን ጦር ሠራዊት ለማጠናከር በሚል የጦር መሳሪያ ድጋፍ ስትልክ ያሁኑ ለሦስተኛ ጊዜ ነው።

ባሁኑ ዙር ግብጽ ለሱማሊያ የላከችው የጦር መሳሪያ ዓይነት ለጊዜው አልታወቀም።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 18:54


ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ ራሱን የቻለ ገለልተኛ ተቋም ሆኖ ሊቋቋም ይገባል ተባለ!

በኢትዮጵያ ያለውን የፍትህ ስርአት ሚዛናዊና ተቋማዊ እንዲሆን ካስፈለገ ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ ከፍትሕ ሚኒስቴር ተነጥሎ ራሱን መቻል አለበት ሲሉ የሕግ ባለሙያዎች ተናግረዋል።ባለሙያዎቹ ጠቅላይ "ዐቃቢ ሕግ ራሱን የቻለ ተቋም ሆኖ መቋቋም ባለመቻሉ የፍትሕ ስርዓቱ እንዳይፀናና ተአማኒ ተቋም እንዳይሆን እያረገው ይገኛል" ሲሉም ለአሐዱ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በዘርፉ ባለሙያዎች ዘንድ ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ ራሱን የቻለ ተቋም ሆኖ እንዲቋቋምና ከፓለቲካ ወገንተኝነት ነፃ በሆኑ ባለሙያዎች እንዲመራ ውትወታ ሲደረግ መቆየቱን ለአሐዱ ያስታወሱት፤ የሕግ ባለሙያው አቶ ታምራት ኪዳነማርያም ናቸው፡፡ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ ራሱን ችሎ መቆም ባለመቻሉና የፍትሕ ሚኒስቴር ጥገኛ እንዲሆን በመደረጉ ምክንያትም የፍትህ ስርአቱና የሕግ የበላይነት እንዲሸረሸር አድርጎታል ባይ ናቸው።

'የፍትህ ስርአቱ ገለልተኛ ነው' ማለት የሚቻለው፤ ጠቅላይ ዐቃቢ ሕግ ከፍትሕ ሚኒስቴር ተነጥሎ መውጣት ሲችልና ራሱን በራሱ ሲመራ ብቻ መሆኑንም አቶ ታምራት ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡በኢትዮጵያ እየተስተዋለ ያለው የፍትህ ስርአቱ መዛባት፤ የገለልተኝነት ጥያቄ ባለመፈታቱ ምክንያት የመጣ መሆኑንም አንስተዋል።

ሌላኛው በዚሁ ዙርያ ሐሳባቸውን እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የሕግ ባለሙያ ደበበ ወልደገብርኤል በበኩላቸው፤ "በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት እንዳይኖር ካደረጉ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ የፍትሕ ስርአቱ ከፓለቲካ ጣልቃ ገብነትና ጫና መላቀቅ አለመቻሉ ነው" ብለዋል፡፡ባለሙያው አክለውም፤ የፍትሕ ሚኒስቴር የፓለቲካ ተቋም እንደመሆኑ መጠን በፍትሕ ስርአቱ ላይ ገለልተኛ ነው ብሎ መውሰድ እንደማይቻል ነግረውናል።

"የፍትህ ሚኒስቴር በአገሪቱ ለፍትሕ መዛባትና በሕግ ላይ ተአማኒነት ማጣት ምክንያትም፤ ከሚኒስቴሩ እጅ ወጥተው በገለልተኛ ተቋም መተዳደር የነበረባቸው ጉዳዮች በመኖራቸው ነው" ሲሉም አክለዋል፡፡"በአገር ውስጥ ያለውን የፍትህ ስርአት የተስተካከለ እንዲሆን ከተፈለገ፤ የሚመለከታቸው አካላት ጉዳዩን በሚገባ ማጤን ይኖርባቸዋል" ሲሉም ባለሙያዎቹ ለአሐዱ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 18:54


ከ78 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ድምፃቸውን ሰጥተዋል!

የአሜሪካ ምርጫ ማክሰኞ ጥቅምት 26/2017 ይደረጋል። ከኦፊሴላዊው የድምፅ መስጫ ቀን በፊት ባሉት ጥቂት ቀናት ብቻ ከ78 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መምረጣቸው ተሰምቷል።በርካታ የአሜሪካ ግዛቶች ከዚህ ቀደም አይተውት በማያውቁት ሁኔታ በርካታ ሰዎች ከድምፅ መስጫው ቀን በፊት እየመረጡ እንደሆ አሳውቀዋል።ከሰባቱ ቁልፍ ግዛቶች አንዷ በሆነችው ኖርዝ ካሮላይና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ድምፃቸውን ሰጥተዋል።

አሪዞና፣ ጆርጂያ፣ ኔቫዳ፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ዊስኮንሲን፣ ፔንስሊቪኒያ እና ሚሸጋን የምርጫውን ውጤት ሊወስኑ የሚችሉ ቁልፍ ግዛቶች ናቸው።ከእነዚህ መካከል በሚሺጋን፣ ዊስኮንሲን እና ፔንሲልቬኒያ ከማክሰኞ በፊት ድምፅ የሚሰጡ ሰዎች ቁጥር ከቀደመው ጊዜ እጅግ ልቋል።

ታር ሒል ስቴት ተብላ በምትታወቀው ኖርዝ ካሮላይና ከ4.4 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን ድምፃቸውን ሰጥተዋል። በዚህች ግዛት በ2020 ምርጫ በተመሳሳይ ወቅት ከምርጫው በፊት ድምፃቸውን የሰጡ ሰዎች ቁጥር 3.6 ሚሊዮን ነበር።ምንም እንኳ በርካታ ሰዎች ከማክሰኞ በፊት ድምፃቸውን ቢሰጡም ካለፈው ምርጫ ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ ዝቅ ያለ ነው።

በአውሮፓውያኑ 2020 በተደረገው የአሜሪካ ምርጫ ከድምፅ መስጫው ቀን አስቀድሞ 101.5 ሚለዮን ሰዎች መርጠው ነበር። ነገር ግን ቁጥሩ እንዲህ ከፍ እንዲል ያደረገው ምርጫው የተካሄደው በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት በመሆኑ ሰዎች መጨናነቁን ፈርተው አስቀድመው በመምረጣቸው ነው።በ2016 የአሜሪካ ምርጫ 47 ሚሊዮን በ2012 ደግሞ 46 ሚሊዮን ሰዎች ነበሩ ከምርጫው ቀን በፊት ድምፃቸውን የሰጡት።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 18:54


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል‼️

ምክር ቤቱ በመደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

በሌላ በኩል የፌዴራል የፍትህ እና የሕግ ኢንስቲትዩትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት ሌላኛው የስብስባ አጀንዳ መሆኑም ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 18:54


የሩሲያ ጦር ደምስሶ ተቆጣጠረ

ሩሲያ ሁለት ተጨማሪ የዩክሬን መንደሮችን እንደተቆጣጠረች የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡የሩሲያ ወታደሮች በካርኪቭ ግዛት ፔርሾትራቭኒቭ እና በዶኔስክ ግዛት ኩራክሂቭካ የተሰኙ የዩክሬን መንደሮችን ነው የተቆጣጠሩት፡፡

በአካባቢው ሲደረግ በቆየው ፍልሚያ በርካታ የዩክሬን ጦር መሳሪያዎች መማረካቸውና መውደማቸውም ተገልጿል፡፡በዚህም በርካታ ተዋጊ አውሮፕላኖች፣ ሄሊኮፕተሮች፣ ድሮኖች፣ ታንኮች፣ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችና የሮኬት ማስወንጨፊያዎች መውደማቸው ተጠቁሟል፡፡

በአንጻሩ በጉዳዩ ላይ ከዩክሬን መንግስት በኩል የተባለ ነገር አለመኖሩን የቲ አር ቲ ዘገባ አመልክቷል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 18:54


ኢራን ኃይለኛ ጥቃት ለማድረስ እቅድ ይዛለች' - ሪፖርት ‼️

ቴህራን፣ ''ውስብስብ እና አዲስ''  ያለችውን ጥቃት ለማድረስ በዝግጅት ላይ መሆኗን ለተለያዩ አረብ ሀገራት በዲፕሎማቲክ ሚሲዮኖቿ በኩል ገልጻለች ሲል ዌል ስትሪት ጆርናል ያወጣው ሪፖርት ያሳያል፡፡      

ኢራን በእስራዔል ላይ 'አደርሰዋለሁ' ላለችው ጥቃት ካሁን በፊት ያልተጠቀመቻቸውን ከባባድ የጦር መሳሪያዎች በጥቅም ላይ እንደምታውልም ሪፖርቱ ያስረዳል።

ሪፖርቱ፣ "ኢራን ኃይለኛ ጥቃት ለማድረስ እቅድ ይዛለች" ይላል።

የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ካሚኒ፣ ሀገራቸው በእስራዔልና በአሜሪካ ላይ ጠንካራ ምላሽ እንደምትሰጥ ተናግረው ነበር፡፡

አሜሪካ በበኩሏ፣ እስራዔል የአጸፋ እርምጃ ከወሰደች በኋላ ኢራን ምላሽ እንዳትሰጥ ስታሳስብ ቆይታለች፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 14:06


ሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማን ጨምሮ በሰባት ወረዳዎች ላይ የወባ በሽታ መከሰቱ ተገለጸ!

በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማን ጨምሮ በሰባት ወረዳዎች ላይ የወባ በሽታ መከሰቱን የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቋል።የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዳመነ ደባልቄ (ዶ/ር) ለኢፕድ እንደገለጹት፤ የወባ በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ልየታ በማድረግ እና ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱ በማድረግ አስፈላጊውን ሕክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ነው።

የመከላከያ ኬሚካል በሀገር ውስጥ መመረት በመቆሙ ምክንያት እጥረት መኖሩን ገልጸው በአራት ወረዳዎች ላይ ርጭት ተደርጓል ብለዋል። ተጨማሪ ኬሚካል እና አጎበሮች እንዲላክ ለጤና ሚኒስቴር ጥያቄ መቅረቡን አክለው ገልጸዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት አዲስ ባወጣው ሪፖርት እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ከታህሳስ 23፣ 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ7.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን እና ከእነዚህም መካከል 1,157 ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል።

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ ወባ አሁንም አሳሳቢ የጤና ስጋት ሲሆን 75 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ መሬት እና 69 በመቶ የሚሆነው በነዚህ አከባቢዎች የሚኖረው ህዝብ በተለይም ህጻናት ለከፍተኛ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቁሟል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 14:06


የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን
Website: https://placement.ethernet.edu.et 
Telegram: https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 12:34


ሶማሊያ የኢትዮጵያን ኤምባሲ ከፕሬዝዳንቱ ቅጥር ግቢ ልታስወጣ መሆኑን ገለጸች!

በሶማሊያ ፕሬዝዳንት ቅጥር ግቢ (ቤተመንግስት) ውስጥ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቅርቡ ወደ ሌላ ቦታ ለማዘዋወር መታቀዱን የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሞአሊን ፊቂ አስታወቁ።ኤምባሲው ከዚህ ቀደም ወደ ነበረበት ቦታው እንዲመለስ ይደረጋል ሲሉ ሚኒስትሩ ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ለሀገሪቱ ጋዜጠኞች በሰጡተ መግለጫ መጠቆማቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ሚኒስትሩ በጋዜጣዊ መግለጫቸው “በፕሬዝዳንታቸው ቅጥር ግቢ ውስጥ የውጭ ሀገር ኤምባሲ መገኘቱ አግባብነት የለውም” የሚል ስሜት በበርካታ ሶማሊያውያን ዘንድ መኖሩን ጠቅሰው “ሶማሊያውን እያሰሙት ያለውን ቅሬታ መቀበል ተገቢ ነው” ሲሉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወደ ቀድሞ ቦታው እንዲመለስ የሚደረግበትን ምክንያት አስቀምጠዋል።“ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይገኝበት የነበረው አከባቢ በአሁኑ ሰአት ምንም አይነት ጥቅም እየሰጠ አይደለም፣ እሱን አድሰን ኤምባሲው ወደዚያው እንዲዛወር እናደርጋለን” ሲሉም አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ካልሆነ ግን በተመሳሳይ “በአዲሰ አበባ የሚገኘውን የሶማሊያ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ግቢ ውስጥ እንዲሆን የሚል ጥያቄ እናቀርባለን” ሲሉም ገልጸዋል።የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መግለጫ በሀገራቱ መካከል እየተካረረ የመጣውን ልዩነት የሚያንጸባርቅ ነው ሲሉ መገናኛ ብዙሃኑ በዘገባዎቻቸው አትተዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 12:34


በኮንታ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ካጡት መካከል የአምስት ሰዎች አስከከሬን ተገኝቷል
         
 👉 ማቾች በሙሉ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው


በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ጫሬ ዶቄ ቀበሌ በጣለው ከባድ ዝናብ የተነሳ የመሬት መንሸራተት አደጋ አጋጥሞ  በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል ። የመሬት መንሸራተት አደጋው በአካባቢው ከ70 በላይ በሚሆኑ ቦታዎች ማጋጠሙ ተገልጿል ።

በዚህ የተነሳ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ት ቤት ሃላፊ የሆኑት አ/ቶ አበበ ጎበና ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ። የቤተሰብ አባላቱ ተሰብስበው ቡና እየጠጡት ባለበት ሁኔታ አደጋው አጋጥሞ ህይወታቸው አልፏል ።

ህይወታቸው ካጡ ስድስት የቤተሰብ አባላት መካከል የአምስቱ አስከሬን ተገኝቶ ስርዓት ቀብር የተፈፀመ ሲሆን የአንድ ሰው አስክሬን እንዳልተገኘና እየተፈለገ መሆኑን አክለዋል ። በተጨማሪ የጉዳት መጠኑ በውል ያልታወቀ ባቄላ እና አተርን ጨምሮ የተለያዩ የሰብል ምርትች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል ።

አሁን ቢሆን ዝናብ የቀጠለ መሆኑን ያነሱት አ/ቶ አበበ ከፍተኛ የሆነ ስጋት እንዳለ ጠቁመዋል ። በተለይም አካባቢው ተዳፋት ወይም ዳገታማ በመሆኑ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው እንደሆነ ተገልጿል ። ስለሆነም ማህብረሰብ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል ።

አመራሮች ፣ የሰላምና ፀጥታ አካላትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች አደጋው በአጋጠመበት ቦታ በመገኝት የተጎጂ ቤተሰቦችን ማፅናናት እንደቻሉ ተነግሯል ። መሰል አደጋ በኮንታ ዞን አጎራባች አካባቢዎች ጭምር ማጋጠሙ ተሰምቷል ።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 12:34


"መንግስትም ሆነ ታጣቂ ቡድኖች እኛ ሰላም እንፈልጋለን ይላሉ ሰላምን ማጽናት የሚለው ግን ከባድ ጥያቄ ሆኗባቸዋል"- ዶ/ር ዳንኤል በቀለ

የቀድሞ የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ ታጣቂ ቡድኖች ሰላም እንደሚፈልጉና ተገደው ወደ ትጥቅ ግጭት እንደገቡ ደጋግመው እንደሚያነሱ ገልጸዋል፡፡

ትልቁ ጥያቄ መሆን ያለበት ሰላም እንዴት ይምጣ የሚለው ነው ያሉ ሲሆን መንግስትም ሲጠየቅ ሰላም እፈልጋለሁ፣ ሽማግሌ ልክያለሁ ሞክሬያለሁ፣ ሰላም አጥተናል ሰላም እንዲሆን እመኛለሁ ይላል  ታጣቂ ቡድኖችም ሲጠየቁ እኛም ሰላም እንፈልጋለን ተገደን ነው ወደዚህ ነገር ውስጥ የገባነው ማለታቸውን አንስተዋል።

በመሆኑም ሁለቱም ሰላምን እንፈልጋለን የሚሉ ወገኖች ናቸው ሰላምን እንዴት እናጸናለን የሚለው ግን ከባድ ጥያቄ ሆኖብናል ሲሉ ዶ/ር ዳንኤል ገልጸዋል።

በተጨማሪም ይሄ የሰላም ጥያቄ ለመንግሥት እና ለተፋላሚ ወገኖች ብቻ የሚተው መሆን የለበትም ተመሳሳይ የሆነ የግጭት ዓውድ ውስጥ ባለፉ ሃገሮች ልምድ መሰረት ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ የሚከተሏቸው ስልታዊ እና ተቋማዊ ሂደቶች አሉ እነዚህም የሃገራዊ ምክክር እና የሽግግር ፍትህ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

እነዚህ ሁለት መፍትሄዎች ቀደም ብለው ተጀምረው ተግባራዊ እየሆኑ መሆኑን ተናግረው የተዓማኒነት ጥያቄ ግን እየተነሳባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ሂደቱ በተቻለ መጠን ሁሉን አሳታፊና ተዓማኒ እንዲሆን ይፈለጋል፤ ነገር ግን በተዓማኒነታቸው ላይ ጥያቄ ምልክት ተነስቶባቸዋል። ይህ አይነቱ የተዓማኒነት ጥያቄ ግን በኢትዮጵያ ብቻ የተነሳ ጥያቄ አይደለም ተመሳሳይ ሂደት በተከተሉ ሃገሮች በሙሉ ጥያቄ ተነስቶባቸዋል ብለዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 12:34


አለምአቀፉ ኩባንያው ዩኒሊቨር ትርፋማነቱን ለመጨመር የተቋሙ ሰራተኞችን ሊቀንስ መሆኑ ተሰማ!

መቀመጫውን እንግሊዝ እያደረገዉ ዩኒሊቨር ትርፋማነትን ለማሳደግ በተያዘው ስትራቴጂ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ የሰው ሃይሉን ለመቀነስ ማቀዱን አስታውቋል።

በኢትዮጵያ ጨምሮ ከ 190 በላይ ሃገራት ላይ በተለያዩ የምርት ስም የሚታወቀው ዩኒሊቨር ቂጥራቸዉ ጥቂት የማይባል ሰራተኞቹን ከሚቀጥለው ወር በኃላ ሊቀንስ መሆኑ ተነግሯል።

አሁን ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ ከ 128 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉት ኩባንያው እያገኘ ያለዉ ትርፍ እና የሰራተኞች ቁጥር መመጣጠን አለመቻሉ እንዲሁም ትርፋማነቱን ለመጨመር በሚል ምክንያት ቅነሳ የሚያደርግ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 12:34


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ አነሳ።

ገደቡ የተነሳው ለጊዜው እንደሆነና ይህም ከባንክ ወደ ቴሌ ብር ለሚደርግ የገንዘብ ዝውውር ብቻ አንደሆነ ሸገር 102.1 ራዲዮ ከምንጮቹ ሰምቷል።የግል ባንኮችም ይህን እንዲያስፈፅሙ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዟል፡፡

መንግስት ወይም የኢትዮዽያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግዙፋን ኩባንያ ኢትዮ ቴሌኮምን 10 በመቶ ድርሻ ወደ ገበያ ማውጣቱ ይታወቃል።ይህን ተከትሎ ባንኮች ከአክስዮን ግዢ ጋር በተገናኘ በቀላሉ ገንዘብ እየለቀቁ እንዳልሆነ ተሰምቷል።የሞባይል ገንዘብ ግብይት ገደብ የተነሳውም ኢትዮ ቴሌኮም ለገበያ ያቀረበውን የአክሲዮን ሽያጭ ሂደቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ነው ተብሏል።

በተጨማሪም የግል ባንኮች ህዝብ የሚጠይቀው እንዲፈፀምለትና ለኢትዮ ቴሌኮም የአክሲዮን ግዥ ግብይቶች ከባንክ ወደ ቴሌብር ዝውውሮች ሲጠየቁ እንዲፈፅሙ ተጠይቀዋል።የኢትዮ ቴሌኮም 10% አክሲዮን ሽያጭ ተከትሎ 100 ሚሊዮን መደበኛ አክሲዮኖች እየተሸጠ ነው።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 08:09


ከትምህርት ቤት ስመለስ እግሬን በፍንዳታ አጣሁ” የትግራዩ ታዳጊ

በትግራይ ገጠራማ መንደር ነዋሪ የሆነው ብርሃነ ኃይሌ ከትምህርት ቤት ሲመለስ አንዲት ቅጽበት መላ ሕይወቱን ላይመለስ ቀየረችው።

የ16 ዓመቱ ታዳጊ የረገጠው መሳሪያ ፈንድቶ ግራ እግሩን መታው።
ስጋና አጥንቱ ተለያይቶ በደም አበላ ተጥለቀለቀ። ከፍተኛ ሕመም ሰቅዞ ያዘው።

“ፍንዳታው ወደ ኋላ አሽቀነጠረኝ። ስፍራው በደም ተጥለቀለቀ። የአካባቢው ነዋሪዎች ድምጹን ሰምተው እየተቻኮሉ መጡ” ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።

አባቱ እና ሌሎቹ የመንደር ነዋሪዎች ተሸክመው ወደ አድዋ ከተማ ለመሄድ ተራራማውን መንገድ ለሁለት ሰዓታት ያህል ሲጓዙም ብርሃነ ሕመሙን መቋቋም ነበረበት።

በመንደራቸው አቅራቢያ ያለው ሆስፒታል አድዋ በመሆኑም ነው ሕመምተኛ ተሸክመው ለሰዓታት በእግራቸው የተጓዙት።

ሆስፒታል ከደረሱም በኋላ የሕክምና ባለሙያዎቹ የታዳጊውን ሕይወት መታደግ ቢችሉም እግሩ መቆረጥ ነበረበት።

የተወሰነው የእጆቹ ክፍልም በፍንዳታው ተጎድቷል።

ለሁለት ዓመታት በዘለቀው ደም አፋሳሹ የትግራይ ጦርነት ፈንጂ መሬት ላይ ተዘርቷል። መሬት ላይ ተጥለው ወይም ተቀብረው ሳይፈነዱ በቀሩ የጦር መሳሪያዎች በብዛት ከሚገኙባት መካከል የእነ ብርሃነ ሳያቦ ተራራማ የገጠር መንደር አንዷ ናት።

በዚህች ገጠራማ መንደር በዋነኝነት የእጅ ቦምቦች፣ ተተኳሾች እንዲሁም ታጣቂዎች ሲሸሹ የተዋቸው የጦር መሳሪያዎች ይገኛሉ።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 08:09


በእግዚአብሔር እቅድ ላይ መገኘት አለብን ሲሉ ካማላ ሃሪስ የነብዩ ኤርሚያስን መልዕክት በመጥቀስ በቤተ ክርስቲያን ለተገኙ ደጋፊዎቻቸው ተናገሩ

ካማላ ሃሪስ በዲትሮይት ውስጥ ለ10 ደቂቃ ያህል ንግግር አድርጋለች። በንግግሯ፣ “ከባድ እውነት” የተናገረውን ከመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ነቢዩ ኤርምያስን ጠቅሳለች። "እግዚአብሔር ለእኛ እቅድ አለው" ነገር ግን እሱ ያዘጋጀልንን እቅዶች ተግባራዊ ማድረግ አለብን። በንግግሯ አጋማሽ ላይ “ጥላቻ እና መለያየትን” እንዲቆም ወደ ተለምዷዊ የዘመቻ መልእክቷ አምርታለች። "ልጆቻችን እና የልጅ ልጆቻችን እንዲኖሩ የምንፈልገው በምን አይነት ሀገር ነው?" በማለት የጠየቀች ሲሆን ይህንን ሀገር እንገነባለን ስትል ካማላ ሃሪስ መልዕክት አስተላልፋለች።

በሌላ በኩል በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በትራምፕ ዙሪያ የሚገኘ ሰዎች የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከሰባቱ ቁልፍ የምርጫ ግዛቶች ውስጥ ስድስቱን ያሸንፋሉ ብለው እንደሚያስቡ ተናግረዋል። ዶናልድ ትራምፕ ስደተኞች ለአሜሪካውያን አስጊ ናቸው በማለት መልእክቱን በተደጋጋሚ እየተናገሩ ይገኛል።የጥቃት ወንጀል ጉዳዮችን በመጥቀስ ካማላ ሃሪስን ለነዚያ ወንጀሎች ተጠያቂ አድርገዋል። ይህ ምንም እንኳን ጥናት ቢፈልግም ስደተኞች ከጠቅላላው የአሜሪካ ህዝብ የበለጠ ወንጀል እንደማይፈጽሙ ያሳያል። ትራምፕ ግን የአንድም አሜሪካዊ የደም ጠብታ እንዲፈስ አልፈቅድም ሲሉ ተናግረዋል። እና ማንኛውም “አሜሪካዊን የገደለ” ስደተኛ የሞት ቅጣት እንዲቀጣ ጠይቀዋል።

ካማላ ሃሪስ በበኩላቸው በምስራቃዊ ላንሲንግ በሚቺጋን ስቴት ዩኒቨርሲቲ በተካሄደው የምረጡኝ የድጋፍ ሰልፍ ላይ በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማስቆም የምችለውን ሁሉ አደርጋለሁ ብለዋል። ሃሪስ እንዳሉት ሚቺጋን በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከፍተኛው የአረብ-አሜሪካዊ ህዝብ መኖሪያ ነው በዚህ በመገኘቴ ተደስቻለሁ ብለዋል። ዶናልድ ትራምፕ አርብ እለት በትልቁ የአረብ አሜሪካውያን የመኖሪያ ከተማ ዲርቦርን የምረጡኝ ዘመቻ አካሂደዋል። በድጋፍ ሰልፉ የታደሙ ሰዎች በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ግጭት በዲሞክራቶች አያያዝ መስፋፍቱን እና ለእስራኤል የሚደረገውን የገንዘብ ድጋፍ ተችተዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

04 Nov, 08:09


ኢትዮጵያ ውስጥ፣ በጋራዦችና መለዋወጫዎች እጥረት ሳቢያ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ባለቤቶች ከፍተኛ ችግር እንደገጠማቸው መረዳቱን ጠቅሶ የፈረንሳይ ዜና ወኪል ዘግቧል።

አዲስ አበባ ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ መጠገን የሚችሉ ጋራዦች ከሦስት እንደማይበልጡ ዘገባው ጠቅሷል።

የትራንስፖርት ሚንስቴር ሃላፊዎች በበኩላቸው፣ መንግሥት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ባትሪ ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች እንዲቋቋሙ ገንዘብ እንደሚመድብ እንደነገሩት የዜና ምንጩ አመልክቷል።

ሃላፊዎቹ፣ መንግሥት የኤሌክትሪክ ባትሪዎችን የሚያመርት ፋብሪካ የማቋቋም ዕቅድ እንዳለውም ሃላፊዎቹ ተናግረዋል ተብሏል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

03 Nov, 16:10


የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ለሁለቱ የአገሪቱ ምክር ቤቶች ባደረጉት ንግግር በቅርቡ ከግብፅ እና ቱርክ ጋር የተፈራረሙትን የመከላከያ ትብብር ስምምነቶችን ከኢትዮጵያ ለሚመጣ ስጋት እንደሚጠቀሙባቸው ጠቁመዋል።

እነዚህ ስምምነቶች የአፍሪካ ቀንድ መረጋጋትን አያሳጡም፣ ነገር ግን ዓለም አቀፍ ህግን የሚቃረን የኢትዮጵያን ምኞት ያስቀራል ሲሉም አረጋግጠዋል።

የፕሬዝዳንቱ ንግግር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሰሞኑ ለፓርላማው ባደረጉት  ንግግር፣ ኢትዮጵያ በቀይ ባህር ላይ  መዳረሻ ለማግኘት ያላትን እና  የማይናወጥ ያሉትን ፍላጎት በድጋሚ ካረጋገጡ በኋላ የተሰማ ነው።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

03 Nov, 16:10


#የሀዘን_መግለጫ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ደራ ወረዳ፣ አድዓ መልኬ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኦነግ ሸኔ(ኦ.ነ.ሠ) ታግተው በግፍ ለተገደሉት የገንዳ አረቡ መስጅድ ኢማም ሼህ ሙሐመድ መኪን ሀጂ አረፉ ፓርቲያችን የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል።

ኢማሙ በአካባቢያቸው የተፈሩና የተከበሩ፣ የተጣላ አስታራቂ እንደነበሩና በመስጅድ ውስጥ ሳሉ ከሌሎች 12 የቅርብ ሰዎች ጋር ታግተው በቅድሚያ ለመልቀቅ መደራደሪያ  3ሚሊዮን ብር ተጠይቆ 1.4ሚሊዮን ሰጥተው መሣሪያ ጭምር ካላመጣችሁ በማለትና ቀሪውን ገንዘብ ሲፈልጉ በግፍ ኹሉንም እንደገደሏቸው ለማወቅ ችለናል። ኢማሙ የታገቱት ከወር በፊት እንደነበርና ለማስልቀቅም ከፍተኛ ርብርብ እንደነበር ሰምተናል። በሣምንት ልዩነት እንዲሁ አንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ 800ሺህ ብር ተጠይቆባቸው ብሩንም ከፍለው ከብዙ እንግልት በኋላ በአሰቃቂ ኹኔታ ገድለዋቸዋል። አካባቢው ከፍተኛ ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ የሚዘወተርበት በአንጻሩ ግፉ እንዳይነገር በሚዲያ በታገዘ ፕሮፓጋንዳ ጭምር የሚድበሰበስበት ነው።

ፓርቲያችን ደጋግሞ እንዳሳሰበው እንዲህ ከነባር ሃይማኖት ኢትዮጵያን ለማፋታትና ወደአዲሱ የዓለም ሥርዓት/New world order/ ለመውሰድ በሚደረገው ጥድፊያና ርብርብ መንግሥታዊ መዋቅር ጭምር ተከትሎ እየተሠራበት እንደሆነ ለዚህም በዋናነት የሃይማኖት ተቋማትን በቃልም በተግባርም መዳፈር፣ የሃይማኖት አባቶችን እያሳደዱ መግደል፣ ምዕመናንን ማሳሳት፣ ማፈናቀል፣ ዕምነት ተኮር ጭፍጨፋ የስልት ትግበራውና መንገድ ጠረጋው አካል ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን ደጋግመን ገልጸናል።

እንዲህ ያለው ተግባር በጥንቃቄ የሚፈጸም በመሆኑ ዛሬ ክርስቲያኑን ነገ ሙስሊሙን ቦታ እየቀያየረ የሚደረግ ነው። እንዲያውም በታሪክ፣ በባህል እንደምናውቀው አንዱ የሌላው መከታና ጠባቂ እንዳይሆን እርስ በእርስ ለማፈጀትም ሴራ ሲጠምቅ ይታያል። ውጤቱ ውሎ አድሮ ያለ ተው ባይና አስታራቂ፣ በጎውን መንገድ ከነውሩ ለይተውና አበጥረው በቃልም በጽሑፍም የሚያመላክቱንን ጠቋሚ አባቶች የሚያሳጣ አካሄድ መሆኑን በውል መረዳት ይገባል።

ፓርቲያችን እንዲህ ያለውን እኩይ ተግባር በጽኑ ያወግዛል፤ ባለ በሌለ ኃይሉም ይታገለዋል።
በድጋሚ በኢማሙ ግፍ ግድያ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጥን ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን።

እግዚአብሔር ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ጥቅምት ፳፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

03 Nov, 16:10


ካማላ ሀሪስ እና ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝደንት ለመሆን የትኞቹን ግዛቶች ማሸነፍ አለባቸው?

አሜሪካ 50 ግዛቶች አሏት። ሁለቱ አውራ የፖለቲካ ፓርቲዎች ማለትም ዲሞክራት እና ሪፐብሊካን እኒህን ግዛቶች ተቀራጭተዋቸዋል። ይህ ማለት የትኛው ግዛት ለየትኛው ፓርቲ ድምፁን እንደሚሰጥ ይታወቃል ማለት ነው።ነገር ግን ሰባት ግዛቶች ለየትኛው ፓርቲ ድምፃቸውን እንደሚሰጡ አይታወቅም። ለዚህ ነው ወላዋይ የሚባሉት።እኒህ ግዛቶች ኔቫዳ፣ አሪዞና፣ ኖርዝ ካሮላይና፣ ጆርጂያ፣ ዊስኮንሲን፣ ሚሺጋን እና ፔንሲልቬኒያ ናቸው።

በአሜሪካ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ዕጩዎች በርካታ ድምፅ ስላገኙ መንበረ-ሥልጣኑን ማግኘት ይችላሉ ማለት አይደለም።ሁለቱ ዕጩዎች የሚፎካከሩት በ50ዎቹ ግዛቶች የሚደረጉትን ምርጫዎች ለማሸነፍ ነው የሚታገሉት።

እያንዳንዱ ግዛት ኢሌክቶራል ኮሌጅ የሚባል ቁጥር አለው። ይህ የሚሆነው በሕዝብ ቁጥር ብዛት ላይ ተመስርቶ ነው። በአጠቃላይ 538 ኢሌክቶራል ኮሌጆች አሉ። ዕጩዎቹ ከእነዚህ መካከል 270 እና ከዚያ በላይ ማግኘት አለበባቸው።ይህ እንዲሆን ደግሞ ከሰባቱ ወሳኝ ግዛቶች ቢያንስ በሶስቱ ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል::

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

03 Nov, 09:35


ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የድሬዳዋ፣ የሀረረ፣ የጅግጅጋ ከተሞች እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት መቋረጡ ተገለጸ!

በሁርሶ ኃይል ማከፋፊያ ጣቢያ ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል በሚገኙ የድሬ ዳዋ፣ የሀረረ ፣ የጅግጅጋ ከተሞች እና አካባቢያቸው የኃይል አቅርቦት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡

በመሆኑም በአካባቢዎቹ የሚገኑ ደንበኞች በኃይል ማከፋፊያ ጣቢያው ላይ የተፈጠረው ችግር በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ተጠግኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

03 Nov, 09:35


በትግራይ ክልል ባለፈው ዓመት በኤች አይ ቪ ቫይረስ የ562 ሰዋች ህይወት ማለፉ ተነገረ

በትግራይ ክልል የኤች አይ ቪ ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ እንደሚገኝ ተጠቁሟል። ምርመራ ከተደረገላቸዉ 156 ሺህ ሰዎች ዉስጥ 1800 የሚሆኑት ላይ የኤች አይ ቪ ቫይረስ መገገኘቱ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ ዘርፈ ብዙ ምላሸ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክተር አቶ ፍስሃ ብርሃነ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡አያይዘውም ይህ የሆነበት ምክንያት ተጋላጭ በሚሆኑ ማህበረሰብ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ላይ በተፈጠረዉ ክፍተት ነዉ ሲሉ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

በትግራይ ክልል በተደረገ ጥናት ኤች አይ ቪ በብዛት ወጣቶች ላይ እንደሚገኝ እና በተለይ እድሜያቸዉ ከ15 እስከ 29 የሚሆኑ ወጣቶች ላይ እየተስፋፋ ይገኛል:: ሴቶች በይበልጥ የቫይረሱ ተጠቂዎች ናቸዉ ። ከጦርነቱ በፊት 46ሺህ የሚሆኑ መድሀኒት ተጠቃሚዎች የነበሩ ሲሆን በጦርነቱ አቁመው አሁን ላይ 37ሺህ የሚሆኑት ወደ ህክምና ተመልሰዋል፡፡ ከነዚህ መካከል 562 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ። ከጦርነቱ በፊት የኤችአይቪ ስርጭት 1.4 እንደነበር ገልፀው አሁን ላይ ምርመራ በተካሄደባቸው አካባቢዎች ላይ ስርጭቱ እንደጨመረ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በፊት ላይ መድኃኒት እየወሰዱ በመሀል ያቋረጡ የነበሩ ታካሚዎች መልሰው መድኃኒታቸውን በአግባቡ እንዲወስዱ እና ህክምናቸውን እንዲከታተሉ እንደተደረገ የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ ዘርፈ ብዙ ምላሸ መከላከልና መቆጣጠር ዳይርክተር አቶ ፍስሃ ብርሃነ ጨምረዉ ተናግረዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

03 Nov, 07:36


የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር፣ በፌደራል መንግሥቱ በኩል የፕሪቶሪያ ግጭት ማቆም ስምምነትን ሙሉ በሙሉ ለመተግበር ያለው ፍላጎት ዝቅተኛ ነው በማለት የስምምነቱን ኹለተኛ ዓመት አስመልክቶ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ተችቷል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ በርካታ የደቡብ ትግራይና ጸለምት አካባቢዎች እስካኹን ወደ ትግራይ እንዳልተመለሱና በምሥራቃዊ፣ መካከለኛውና ሰሜን ምዕራብ ትግራይ የሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ከኤርትራ ሠራዊት ነጻ እንዳልወጡ ገልጧል።

የሕወሓት አመራር የሕዝቡን ፍላጎት ወደ ጎን በማለት ፖለቲካዊ ንትርክ ውስጥ ገብቷል በማለት የወቀሰው ጊዜያዊ አስተዳደሩ፣ ፌዴራል መንግሥቱ፣ አፍሪካ ኅብረት፣ አውሮፓ ኅብረትና አሜሪካ በስምምነቱ ያልተመለሱ ጉዴዮችን ለመፍታት የሕግና የሞራል ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

03 Nov, 07:36


መረጃ‼️

የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት 120 የመንግስት ፀጥታ ሃይሎችን ደምሳሻለሁ ሲል  አስታወቀ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዉጫሌ በሚባል አካባቢ ላይ በሁለት አካባቢዎች የተሳካ ዘመቻ አድርጌ 120 የመንግስት የፀጥታ አካላትን ገድያለሁ ሲል ነዉ ኦነግ በመግለጫዉ ያስታወቀዉ ፡፡

ካራ በሚባል ወታደራዊ ካምፕ ላይ በፈፀመዉ ጥቃት 67 ወታደሮች መግደሉን ሲናገር በተመሳሳይ በደፈጣ እየተጎዙ ባሉ የሰራዊቱ አባላት ላይ ተኩስ በመክፈት 53 ወታደሮችን ገድያለሁ ብሎል ፡፡

ሰሞኑን በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ንፁሃን በአሰቃቂ መንገድ ሲገደሉ እንዲሁም የሀይማኖት አባት እስከ ቤተሰቦቻቸዉ ታግተዉ ተገድለዉ መገኘታቸዉ የሚታወስ ነዉ ፡፡

ፊልድ ማርሻሉን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮችን ኦነግ ሸኔ እየጠፋ ነዉ ቆሞ መዋጋት አይችልም ቢሉም ከ4ኪሎ 100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ኦነግ የሚፈልገዉን  እየገደለ የሚፈልገዉን እየዘረፈ ይገኛልል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

02 Nov, 11:53


የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለውጥ ማድረጉን አስታወቀ!

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአንዳንድ ተርሚናሎች ላይ የመጫኛና ማውረጃ ቦታ ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል በዚህም መሰረት መገናኛ ውስጥ ተርሚናል አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩት ከመገናኛ - ቃሊቲ ፣ ከመገናኛ - ሳሪስ ፣ ከመገናኛ - ጋርመንት መስመሮች ወደ መገናኛ ሙሉጌታ ህንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት መንገድ በጊዜያዊነት ተዛውሯል፡፡

ከቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ሲሰጥ የነበረው ከመገናኛ - ቱሉ ዲምቱ እና ኮዬ ፈቼ አገልግሎት ሲሰጥ የነበሩት መስመሮች ደግሞ አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ትንሽ ዝቅ ብሎ) ወዳለው ቦታ ተዛውሯል፡፡

ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ ይሰጡ የነበሩ መስመሮች ከመገናኛ - ገርጂ ፣ ከመገናኛ-ጎሮ ፣ ከመገናኛ - አያት እና ከመገናኛ - ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል ውስጥ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ቢሮው በመረጃው አስታውቋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

02 Nov, 11:53


የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ እና የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር የቀረቡባቸውን ክሶች እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ!

የማይገባ ጥቅም በመቀበል የሙስና ወንጀል በመፈጸም እና በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ በማቅረብ የተከሰሱት የቀድሞው የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጸጋዬ ቱኬ፤ በቀረቡባቸው ሁለት ክሶች ላይ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ። በቀድሞው ከንቲባ እና አብረዋቸው በተከሰሱ ሁለት ተከሳሾች ላይ ባለፈው ማክሰኞ ጥቅምት 19፣ 2017 ብይኑን የሰጠው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሀዋሳ ማዕከል ነው።

የሲዳማ ክልል ፍትህ ቢሮ፤ በአቶ ጸጋዬ እና ሁለት ተከሳሾች ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ የመሰረተው፤ ባለፈው ዓመት ግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ ነበር። በአንድ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ተከሳሾች መካከል፤ የሲዳማ ክልል የቀድሞ የፖሊስ ኮሚሽነር አቶ አበራ አሬራ ይገኙበታል።

የክልሉ ዐቃቤ ህግ በአቶ አበራ እና በአቶ ጸጋዬ ላይ የመሰረተው የመጀመሪያ ክስ፤ በሙስና ወንጀሎች አዋጅ የተቀመጠን ድንጋጌ በመተላለፍ “የማይገባ ጥቅም በመቀበል የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል” የሚል ነው። “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የተመለከተችው የመጀመሪያው ክስ፤ በሀዋሳ ከተማ ሳውዝ ስታር ኢንተርናሽናል ሆቴል ጎን የተወሰደ ቦታ ምትክ መሬት እንዲሰጥ ከቀረበ ጥያቄ ጋር የተያያዘ ነው።

የምትክ ቦታ ጥያቄ ቀርቦ የነበረው፤ ከአቶ ጸጋዬ አስቀድሞ በነበሩት የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የአመራር ጊዜ እንደነበር በክሱ ተመላክቷል። አቶ ጥራቱ የምትክ ቦታ እንዲሰጥ ውሳኔ ቢያስተላልፉም፤ የመሬት ርክክብ ከመፈጸሙ በፊት ከኃላፊነታቸው በመነሳታቸው ጉዳዩ ለተተኪያቸው ተላልፏል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

02 Nov, 11:53


ወላጆች ልጆቻቸውን ከመወለዳቸው በፊት በሚፈልጉት ጾታ፣ ቁመትና የማሰላሰል አቅም እንዲወስኑ የሚያደርግ አዲስ ፈጠራ ይፋ ሆነ
መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው አዲስ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ለማሰብ የሚከብዱ ፈጠራዎችን ለአገልግሎት አብቅቻለሁ ብሏል፡፡

ሄሊዮስፔክት ጄኖሚክስ የተሰኘው ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ልጆች ከመወለዳቸው በፊት ከፍተኛ የማሰላሰል አቅም ወይም አይኪው እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው ተብሏል፡፡ኩባንያው በሰውሰራሽ ቴክኖሎጂ ወይም በህክምና እገዛ በሚወለዱ ህጻናት ላይ በርካታ ሙከራዎችን ሲያደርግ መቆየቱን ዘ ጋርዲያን አስነብቧል፡፡

እንደ ዘገባው ከሆነ ቴክኖሎጂው ወላጆች ልጃቸው በሚፈልጉት ጾታ፣ ቁመት፣ የማሰላሰል አቅም መጠን እና ሌሎችም እንዲወለድ የሚያደርግ ነው፡፡ወላጆች ይህን አገልግሎት ለማግኘት እስከ 50 ሺህ ዶላር መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን አገልግሎቱን እያገኙ ያሉ ወላጆች እንዳሉም ተገልጿል፡፡

እስካሁን ለ12 ልጆችን በተፈጥሮ መንገድ መውለድ ላልቻሉ ነገር ግን በህክምና እገዛ ለወለዱ ወላጆች አገልግሎቱ ተሰጥቷቸዋል የተባለ ሲሆን ህጻናቱ በዚህ ቴክኖሎጂ የማሰላሰል አቅማቸው በተፈጥሯቸው ሊያገኙ ከሚችሉት ስድስት እጥፍ የተሻለ ነውም ተብሏል። ቴክኖሎጂው አይኪውን ከመጨመር በተጨማሪ ሊከሰቱ የሚችሉ እንደ የአዕምሮ ህመም፣ ከመጠን በላይ ውፍረትና ሌሎች ስጋቶች ህጻናቱን እንዳያጠቁ የሚያደርግ እንደሆነም ተገልጿል፡

ይህ ቴክኖሎጂ ለአገልግሎት መብቃቱን ተከትሎ አድናቆትና ትችቶችን ያስተናገደ ሲሆን ቴክኖሎጂው የማህበረሰብ ልዩነት እንዲፈጠር የሚያደርግና ተፈጥሮን የሚጋፋ ነው የሚል ትችት ቀርቦበታል፡፡ቴክኖሎጂውን ያበቃው ኩባንያ በበኩሉ አገልግሎቱ ገና በጅምር ላይ መሆኑንና በቀጣይ ለሁሉም እንዲቀርብ ሊደረግ እንደሚችል አስታውቋል::

https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

02 Nov, 11:53


በኢትዮጵያ የወባ በሽታ ትልቅ የጤና ስጋት መሆነን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቋል!

የዓለም ጤና ድርጅት አዲስ ባወጣው ሪፖርት እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ከታህሳስ 23 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ7.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መጠቃታቸውን እና ከእነዚህም መካከል 1,157 ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል።

እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ ወባ አሁንም አሳሳቢ የጤና ስጋት ሲሆን 75 በመቶ የሚሆነው የአገሪቱ መሬት እና 69 በመቶ የሚሆነው በነዚህ አከባቢዎች የሚኖረው ህዝብ በተለይም ህጻናት ለከፍተኛ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቁሟል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደ 'አኖፌሌስ ስቴፈንሲ' የተሰኘ የወባ ትንኝ መስፋፋት፣ ድርቅ፣ የምግብ ዋስትና እጦት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና በሃገሪቱ በቀጠሉት ግጭቶች የተነሳ በኢትዮጵያ ያለው የወባ በሽታ ስጋት ከባድ መሆኑን አመላክቷል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

01 Nov, 17:25


በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ውስጥ ባለው የታጣቂዎች ጥቃት ምክንያት በመንግሥት ፈቃድ የግል የጦር መሳሪያ የታጠቁ የአማራ ተወላጆች መሳሪያቸውን እንዲያስረክቡ በመጠየቃቸው በአካባቢው አዲስ ውጥረት ነግሷል

በዞኑ ጊዳ አያና ወረዳ የሚኖሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች “በመንግሥት ይሁንታ ታጠቅነዋል” የሚሉትን መሳሪያ አስረክቡ መባላቸውን ተክትሎ ስጋት ላይ መውደቃቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የአንዶዴ ዲቾ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ እና ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ነዋሪ በአካባቢው ተደጋጋሚ ጥቃቶች እንደሚፈጸሙ ጠቅሰው፤ በተለይ ከሦስት ዓመት በፊት ኅዳር 24/2014 ዓ.ም. በተፈጸመ ጥቃት “ጭፍጨፋ” መፈጸሙን ያስታውሳሉ።

የሰሜኑ ጦርነት መቀስቀቀሱን ተከትሎ በአካባቢው የነበረው መከላከያ ሠራዊት ቦታውን ለቆ ሲወጣ ራሳቸውን እንዲከላከሉ በመንግሥት እንደተነገራቸው የሚገልጹት ነዋሪዎች፤ በመንግሥት ተፈቅዶልን መሳሪያ ታጥቀናል ይላሉ።

“የሸኔ ታጣቂ በስፋት ከሚንቀሳቀስባቸው ቀጠናዎች ውስጥ አንዱ ምሥራቅ ወለጋ ነው። በዚያን ሰዓት [በሰሜኑ ጦርነት] እስከ መንግሥት መሥሪያ ቤት አቤቱታ ቀርቦጎ፤ መንግሥት ‘የሚደርስልህ አካል የለም፤ ገዝተህ ራስህን ተከላከል’ ብሎ በሰጠው ፈቃድ መሠረት [መሳሪያ] ገዝተን ቤተሳባችንን ስንከላከል ቆይተናል” ሲሉ ሌለ ነዋሪ ተናግረዋል።

“በየአካባቢው ሰላሙ ሲጠፋ ሕዝቡ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ መሳሪያ እየገዛ ታጠቀ” የሚሉት ሌላ ነዋሪ፤ “መሞታችን ካልቀረ እያለ ሰዉ በሬውን እየሸጠ፤ አንድ ለሁለት መሳሪያ እየገዛ፤ ራሱን መከላከል ጀመረ” ሲሉ የአካባቢው ማኅበረሰብ መሳሪያ እንዴት መታጠቅ እንደጀመረ ያብራራሉ።
በሰፈራቸው ታጣቂዎች ጥቃት ፈጽመው ሰው “ተገድሎ ቤቱ ሲቃጠል” በማየታቸው መሳሪያ ለመግዛት እንደወሰኑ የሚናገሩ ሌላ ነዋሪ ነዋሪ፤ በመንግሥት ይሁንታ ቤተሰባቸውን ለመጠበቅ ካላቸው የቁም እንስሳት መካከል የተወሰኑትን ሸጠው መግዛታቸውን ተናግረዋል።

በሬ እና ቀለባቸውን ሸጠው በ2013 ዓ.ም. “ራሳቸውን ለመከላከል” ‘ሙሉ ትጥቅ’ በ150 ሺህ ብር እንደታጠቁ የሚናገሩ ሌላ ነዋሪም፤ መሳሪያቸውን በአካባቢው ባለሥልጣናት “ተመዝግቦ፤ ሕጋዊ አድርገናል” ይላሉ።

“ይሄው ሦስት ዓመቱ ነው። ሕጋዊ አድርጎ ለመንግሥት እያገለገለ ነበር” የሚሉት ነዋሪ በበኩላቸው ከሰሞኑን በወረደው ትዕዛዝ ከመንግሥት ጋር ውጥረት ውስጥ መግባታቸውን ተናግረዋል።

“[መሳሪያውን] አስመዝግቦ እያገለገለበት፤ እየወጣ እየወረደ፤ ከወረዳ እስከ ክልል እየጠበቀ” ነበር ሲሉም ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት ፀጥታ የአካባቢያቸውን ሰላም ሲያስከብሩ እንደነገር ገልጸዋል።
ነዋሪዎች ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም. የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት በጠሩት ስብሰባ መሳሪያቸውን እንዲያስረክቡ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

ሆኖም ትዕዛዙ “ማንነትን የለየ ነው” ያሉት ነዋሪዎች በአካባቢው የሚኖሩ እና ታጠቁ “የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት ትጥቅ ፍቱ አልተባሉም” በማለት ትጥቅ ማስፈታቱ በእነሱ ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል።
“እነሱን ዛሬ [ትጥቅ] አውርዱ ያላቸው የለም። እነሱ ጠቅለው የመንግሥት ሚሊሻ ሆነዋል። ልብስም [የደንብ ልብስ] ለብሰዋል፤ መታወቂያም ተሰጥቷቸዋል። አሁን አውርዱ የሚባለው ብሔር የለየ ነው” በማለት ስጋት እንዳደረባቸው ተናግረዋል።

“ሽብሩ ከመጣ ዘንድሮ አራት ዓመቱ ነው” የሚሉት እና ዕድሜያቸው በመግፋቱ መሳሪያ እንዳልታጠቁ የሚናገሩ አንድ ነዋሪ፤ አማራጭ ማጣታቸውን ተናግረዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

01 Nov, 17:25


ከመደፈር ጥቃቱ በኋላ አዳጊዎቹ ወደ ትምሕርት ቤት አልተመለሱም

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምቴ ከተማ ውስጥ ሁለት ሴት አዳጊዎች ሲደፈሩና አሰቃቂ ጾታዊ ጥቃት ሲደርስባቸው የሚያሳው ቪዲዮ ከተለቀቀ ከኋላ፤ ወደ ትምሕርት ቤት እንዳልተመለሱ ተገልጿል፡፡

ተጎጂዎቹ ባጋጠማቸው መሸማቀቅ ትምሕርት እስከማቋረጥ እንዳደረሳቸው ከተጎጂዎቹ አንዷ የኮነችው የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ገልፃለች።

በጉልበት ሥራ የሚተዳደሩት የአንደኛዋ ተጎጂ እናት÷ በልጃቸው ላይ በደረሰው ጥቃት ክፉኛ እንዳዘኑ ገልጸው፤ ፍትሕ ለማግኘት አቤት ማለታቸውን ተናግረዋል።

ድርጊቱን ፈጽመዋል በተባሉ ግለሰቦች ላይ የፀጥታ አካላት ርምጃ መውሰዳቸውን፤ የነቀምቴ ከተማ ሴቶችና ሕፃናት ጽህፈት ቤት የሕግ ባለሞያ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

01 Nov, 17:25


በጋምቤላ ክልል የተከስተው ከፍተኛ የወባ ወረርሽኝ የመቀነስ አዝማሚያ ማሳየቱ ተገለጸ!

ከዚህ በፊት በጋምቤላ ከተማ በመንገሺ እና ጎሬ ወረዳዎች ከፍተኛ የሆነ የወባ ወረርሽኝ መከሰቱን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታዉቆ እንደነበር አይዘነጋም።ከሰሞኑ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍልች በተለይም በአማራ ትግራይ እና በአንድ አንድ የደቡብ ኢትዮጵያ ክፍሎች ከፍተኛ የሆነ የወባ ወረርሽኝ ተከስቶ እንደነበር መገለጹ ይታወሳል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም በጋምቤላ በሚገኙ መንገሺ እና ጎደሬ ወረዳዎች እንዲሁም በከተማው ተከሰቶ የነበረዉ ከፍተኛ የሆነ የወባ ወረርሽኝ አሁን ላይ መቀነስ ታይቶበታል ተብሏል፡፡ለዚህ ደግሞ እንደሀገር የወባ በሽታን ለመከላከል በተጀመረው ዘመቻ የአጎበር ስርጭት እና የኬሚካል ርጭት አስተዋፅኦ ማድረጉን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አቤል አሰፋ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የወባ ተጋላጭ በሆኑ የክልሉ ወረዳዎች የአካባቢ ጽዳትና ቁጥጥር ሥራዎችን በመስራት፤ የቅድመ መከላከልና ጥንቃቄ ሥራ መከናወኑን አስረድተዋል፡፡ኃላፊዉ አክለውም የወባ ወረርሽኙን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የማህበረሰቡን ተሳትፍ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዉ፤ "በሌሎች ወረዳዎችና አካባቢዎችም እንዳይስፋፋ ጥረት እየተደረገ ነዉ" ብለዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

01 Nov, 17:25


መረጃ‼️

#NewsAlert
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የወጫሌ ወረዳ አሥተዳዳሪ የሆኑት ንጉሤ ኮሩን ጨምሮ ከ ሃምሳ በላይ የሚሆኑ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ዛሬ ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም ማለዳ ላይ ራሱን ያኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ በሚጠራው አማጺ ቡድን በተከፈተባቸው ጥቃት መገደላቸውን ተሰምቷል፡፡

የወረዳው አሥተዳዳሪ፣ የዞን አመራሮች እንዲሁም በርካታ የመንግሥት ታጣቂዎች ታጣቂ ቡድኑ በስፋት ይንቀሳቀሳል ወደሚባልበት ካራ ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ ዛሬ ማለዳ 12 ላይ ለጸጥታ ስራ ተሰማርተው እንደነበር ነዉ የተነገረዉ።

በስፍራው እንደደረሱም ታጣቂ ቡድኑ በከፈተባቸው ድንገተኛ ጥቃት የወረዳ አሥተዳዳሪውን ጨምሮ ከሃምሳ በላይ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ወዲያው ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ የወረዳው የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊውን ጨምሮ በርካቶች ደግሞ ቆስለው ወደ ሙከጡሪ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የዐይን እማኞች አረጋግጠዋል።

በጥቃቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ከሙከጡሪ ሆስፒታል ሪፈር ተጽፎላቸው ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን የገለጹት ምንጮች፣ የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊያሻቅብ እንደሚችል ገልጸዋል።
ንጉሤ ኮሩ ከዚህ ቀደም በዞኑ የአለልቱ ወረዳ አሥተዳዳሪ በመሆን፣ በዞኑ ደግሞ በተለያዩ ኃላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፣ በቅርቡ ደግሞ የወጫሌ ወረዳ አሥተዳዳሪ ሆነው መሾማቸውን የሚታወስ ነዉ ፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

01 Nov, 11:36


ከ156 ዓመታት በኋላ የአጼ ቴዎድሮስ ጋሻ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ!

እኤአ 1868 በመቅደላ ጦርነት ወቅት የተወሰደው የአጼ ቴዎድሮስ ጋሻ ከ156 ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው (ረ/ፕ)፤ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፤ የአርበኞች የልጅ ልጆች፣ በተገኙበት ርክክብ ተደርጓል።

ጋሻውን ለማስመለስ ከአንድ ዓመት በላይ የፈጀ ጥረት ተደርጓል።ከአንድ ዓመት በፊት ቅርሱ በእንግሊዝ ለጨረታ ቀርቦ የነበረ ቢሆንም በተደረገው ጥረት ጨረታው እንዲነሳ ተደርጓል።ልዑል ኤርሜያስ ሣህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴና በኢትዮጵያ ንጉሳዊ በጎ አድራጎት ባለአደራ ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ተገልጿል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

01 Nov, 11:36


ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የሲሚንቶ ምርት ለገበያ ማቅረብ መጀመሩን አሰታወቀ!

በቅርቡ ሥራ የጀመረው ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ከትናንት ጀምሮ ምርቱን ለገበያ መቅረቡን አስታውቋል፡፡ፋብሪካው የማምረት ሥራውን በፍጥነት እንዲጀምር የተደረገው ምርቱን በቶሎ ወደ ገበያ በማቅረብ በሀገር ደረጃ ያለውን የሲሚንቶ ገበያ ለማረጋጋትና እንደሀገር የተጣለበትን ከፍተኛ ኃላፊነት ለመወጣት መሆኑ ተገልጿል፡፡


https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

01 Nov, 11:36


በኮንታ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ገለጸ

በቀበሌው ትናንት ምሽት የጣለው ከባድ ዝናብ ተከትሎ ዛሬ ጠዋት 2 ሠዓት ላይ የመሬት መንሸራተት መከሰቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ህይወታቸውን ያጡት ሰዎች የሁለት ቤተሰብ አባላት ሲሆን ከአንደኛው ቤተሰብ አራት እንዲሁም ከሌላኛው ቤተሰብ ሁለት ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ አስረድተዋል፡፡

በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋም ሁለት ቤት መውደሙን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት አረጋግጠዋል፡፡

የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸው፤ እስከ አሁን 1 አስከሬን ተገኝቷል ብለዋል፡፡

በአካባቢው አሁንም መሬቱ እየተናደ መሆኑ እና የውኃ ሙላት (ጎርፍ) መኖሩ የነፍስ አድን ሥራውን በሚፈለገው ልክ እንዳይሆን አድርጎታል ነው ያሉት፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

31 Oct, 09:44


#ይፈለጋል

በሓበን የማነ ግድያ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ለማዋል የህዝብ እገዛ እፈልጋለው ሲል የመቐለ ከተማ ሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አስታወቀ

የሓወልቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዛሬ ጥቅምት 21 እንደገለፀው ከሆነ በክፍለ ከተማው ዓዲ ሓ ተብሎ በሚታወቅ አከባቢ ሓበን የማነ የተባለች እንስት ግፍ በተሞላት መንገድ ግድያ እንደተፈፀመባት ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ግድያው በፍቅረኛዋ እንደተፈፀመ ለማወቅ ችያለዉ የሚለው ፖሊስ ግድያውን ፈፅሟል ተብሎ የተጠረጠረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር አለመዋሉ በመግለፅ ፖሊስ አረመኔያዊ ሲል የገለፀውን ግድያ የፈፀመው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ለማዋል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ሁሉ መረጃ ለፖሊስ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪውን አቅርቧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

31 Oct, 09:44


በበጀት አመቱ 72 ያህል ኘሮጀክቶች በኢንደስትሪዉ ዘርፍ ስራ ይጀምራሉ ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬዉ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ የኢንደስትሪ ዘርፍን ከነበረበት 59 በመቶ አቅም ወደ 67 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግብ ተናግረዋል።ከጠቀሳቸዉ አዳዲስ የኢንዱስትሪ አምራች ኘሮጀክቶች ዉስጥ በጨርቃጨርቅ 9 ኢንዱስትሪዎች በምግብ እና መጠጥ 41 ኢንዱስትሪ በኮንስትራክሽን እና ኬሚካል ግብአት አቅራቢ 4 ኢንደስትሪዎች ÷ በቴክኖሎጂ 15 ኢንደስትሪዎች እንዲሁም የወታደራዊ ግብአት ፋብሪካ 3 ወደ ስራ ይገባሉ ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የወርቅ ÷ የብረታብረት እና የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ ምርት እንደሚጠበቅባቸዉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉስጥ የሀገር ዉስጥ ባለሀብቶች ለማሳተፍ ተደርጓል በተባለዉ ስራ 50 በመቶ ያህሉ አሳታፊ ለማድረግ መቻሉ ተነግሯል።በዘንድሮዉ በጀት አመት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዉስጥ የኢንደስትሪዉ ዘርፍ 12.8 ድርሻ ይኖረዋል ተብሏል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

31 Oct, 09:44


አዲስ አየር መንገድ ለመገንባት ጥናት ተደርጎ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐብይ አህመድ አስታወቁ!

ሐሙስ ጥቅምት 21ቀን 2017 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት እያካሄደ ነዉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከምክር ቤት አባላት ለተነሳላቸዉ ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት ላይም ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ማብራሪያ ከሰጡባቸው ጉዳዮች ውስጥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 124 አዳዲስ አውሮፕላኖችን ማዘዙን እና በአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

በሌላ መልኩ ኢትዮጵያ 8 ነጥብ 1 በመቶ ዕድገት ማስመዝበቧን እና ባለፈው አመት 8 ነጥብ 4 የተመዘገበ ዕድገት መገኘቱን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስቴሩ፤ በዚህም ዓመት ከዓምናው የተሻለ ዕድገት እንደሚመዘገበ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት 180 ቢሊየን ብር ገቢ የተገኘ ሲሆን መቶ በመቶ እቅዱን ያሳካ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ይህም ገቢ የተደረገውን ሪፎርም ተንተርሶ የተገኘ ገቢ መሆኑን እና በ2014 ዓመት በሶስት ወራት ውስጥ የነበረው ገቢ 70 ቢሊዮን ብር እንደነበረ አስታውሰው በ2015 ዓመት ደግሞ በሶስት ወራት ውስጥ 93 ቢሊዮን ብር መግባቱን በመግለጽ የልዩነት ስፋቱን አመላክተዋል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

31 Oct, 09:44


አንዳንድ ኤምባሲዎች የኢትዮጵያን ሃብት በመዝረፍና በጥቁር ገበያ ሥራ ላይ መሰማራታቸውን ጠ/ሚ አብይ አህመድ ገለጹ!

የኢትዮጵያን ሃብት የመዝረፍና የውጭ ምንዛሬ ቢዝነስ መስራት ስራቸው የሆነ አንዳንድ ኤምባሲዎች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ገለጹ።ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ይህን የገለጹት እየተካሄደ ባለው 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበቅ ወቅት ነው።

“ነገር እንዳናበላሽ የታገስናቸው ስራቸው ግን ጥቁር ገበያ ማሯሯጥ የሆነ ኤምሲዎች አሉ” ያሉት አብይ አህመድ፤ “ጤናማ ዝምድና የማያደርግ ማንም ኤምባሲ እኛ አንፈልግም” ብለዋል።ስራቸው ይህ የሆነ ኤምባሲዎች ላይ ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግ እና የማይታረሙ ከሆነ እርምጃ እንደሚወሰድ በንግግራቸው አመላክተዋል።

በኩባንያ ስም፣ በፍራንኮ ቫሎታ ስም፣ በወርቅ ንግድ ስም የኢትዮጵያን ገበያ የሚያዛቡ ገለሰቦች መኖራቸውንም አክለው ተናግረዋል።የኢትዮጵያ የጥቁር ገበያ ዶላርና ወርቅ በባቡር እና በተሽከርካሪ ከአገር እንደሚወጣ የገለጹት ጠ/ሚንስትሩ ይህን ዘረፋ መከላከል ያስፈልጋል ሲሉ አክለዋል።አንዳንድ ሀገራት በዚህ መንገድ ኢትዮጵያን መዝረፍ መብት እንደሆነ እንደሚያስቡ ገልጸው ነገር ግን ኢትዮጵያ ከብሄራዊ ጥቅሟ አንጻር ጥያቄ ስታነሳ እንደ “ግስላ” ይሆናሉ ብለዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

31 Oct, 09:44


"አሁንም ለድርድር እና ምክክር ዝግጁ ነን" ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት 3ኛ መደበኛ ስብስባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን አባል የሆኑት አቶ አበባው ደሳለኝ ጥያቄ አቅርበው ነበር፡፡

በጥያቄያቸውም "በአማራ ክልል በሁለት ወራት ውስጥ የጸጥታውን ሁኔታ ለመቆጣጠር የታሰበ ቢሆንም፤ ከአንደ ዓመት በላይ ቆይቷል" ብለዋል፡፡አባሉ "መንግሥት የሰላምና የጸጥታ ችግሩን ለመፍታት እየሄደበት ያለው ርቀት ወታደራዊ ብቻ ነው ስለምን ፖለቲካዊ መፍትሄ ማምጣት አልተቻለም?" ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

ይህንን በተመለከተ ለምክር ቤት አባላት ምላሽ ለመስጠት በምክር ቤት የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሲመልሱ፤ "ሰው አመዛዛኝ ፍጡር ነው" ያሉ ሲሆን፤ "ለዲሞክራሲ ስርዓት መነጋገሩ የተሻለ ነው" ብለዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒሰትር ዐቢይ ጥያቄ ያቀረቡላቸውን የምክር ቤት አባል "እርሶ ካገዙን አሁንም ከድርድር እና ምክክር ዝግጁ ነን" ብለዋል፡፡

"ከዚህ ቀደም ሽማግሌዎች ልከን ነበር ግን በእንብርርክክ ሄደው የመጣው ውጤት የምትመለከቱት ነው በዚህ ምክንያት ሊሳካልን አልቻለም" ብለዋል፡፡"ሰላም እንፈልጋለን" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ ጦርነት በፍጹም መንግሥታቸው የሚፈልገው ጉዳይ እንዳልሆነ ለጥያቄው ምላሽ ሲሰጡ ተናግረዋል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

31 Oct, 07:55


ከመገናኛ ዐደባባይ ወደ ቦሌ እና ከቦሌ ወደ ወደ መገናኛ ዐደባባይ ያለው መስመር ለተሽከርካሪ ዝግ ሆኗል!

ከመገናኛ ዐደባባይ ወደ ቦሌ እና ከቦሌ ወደ መገናኛ ዐደባባይ በሁለቱም አቅጣጫ ላልተወሰነ ጊዜ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል፡፡በመገናኛ አካባቢ ያለውን ከፍተኛ የትራንስፖርት መጨናነቅ ለመፍታት የሚያግዝ የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላላፊያ መስመር ግንባታ መጀመሩንም ነው ባለስልጣኑ ያስታወቀው፡፡

ለዚሁ ሥራ ሲባልም ከመገናኛ ዐደባባይ ወደ ቦሌ እና ከቦሌ ወደ መገናኛ ዐደባባይ ያለው መንገድ በሁለቱም አቅጣጫ ለተሽከርካሪ ዝግ ሆኗል ብሏል::እግረኞችም መገናኛ በሚገኘው ሙሉጌታ ዘለቀ ሕንጻ በኩል ማለፍ እንደማይቻል አውቀው በቦሌ ክፍል ከተማ ከተማ አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት ባለው የእግረኛ መንገድ እንዲጓዙ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡አሽከርካሪዎችም ሌሎች አማራጭ መንገዶችን መጠቀም እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

31 Oct, 07:55


ኤርትራ የአየር ክልሏን ዘጋች

ኤርትራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኤርትራ የአየር ክልል ውስጥ እንዳይበር መከልከሏን የኤርትራ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

የኤርትራ ሲቪል አቬሽን የኢትዮጵያ አየር አየር መንገድ የተጓዦችን ሻንጣ ጥሎብናል በሚል ክስ መስርቻለሁ ማለቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ በረራ ማቆሙ ይታወሳል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

31 Oct, 07:55


በ6ኛው የህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት  4ኛ ዓመት 3 ኛ መደበኛ ስብሰባ  እየተካሄደ ይገኛል!!

ለጠቅላይ ሚኒስትር  ዶክተር ዓብይ አሀመድ ጥያቄዎች እየቀረቡላቸው ይገኛል ከነዚሀም መካከል ዶክተር አበባው ደሳለው ካነሱት ጥያቄ   በምክር ቤቱ  የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ አስካሁን  አልተስተካከለም የኑሮ ውድነቱ ግን የማይደፈር ሆኖ ምን እየተሰራ ነው የሚል ነው?

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

31 Oct, 07:55


ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት 8 ነጥብ 1 በመቶ እድገት አስመዝግባለች ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ተናገሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በህዘብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ በሰጡት ማብራሪያ በዚህ ዓመት ኢትዮጵያ ማንሰራራት የምትጀምርበት ዓመት እንደሆነ ተናግረዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት ስድሰት ዓመታት ገደማ ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበረው የፖለቲካ ኢኮኖሚ ስርዓት አንፃር ሪፎርም ስናካሂድ መቆየታችን ይታወቃል ብለዋል ።

ሪፎርም ያልነካው ሴክተር የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፎርሙ የሚቀረው ነገር እንዳለ ሆኖ የተለያዩ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው ብለዋል ። በዚህ ዓመት ኢትዮጵያ ማንሰራራት የምትጀምርበት ዓመት ነው ሲሉ አክለዋል ።

በዚህ ዓመት የሚጀመረው ማንሰራራት የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በሁሉም መስኮች ነው ብለዋል ። ባለፈው ዓመት ከእቅድ በላይ በሆነ መልኩ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት እድገት ጂዲፒ 8.1 በመቶ ተመዝግቧል ሲሉ ገልፀዋል ።

ይህ ውጤት በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እድገት እያመጡ ካሉ ሀገራት ተርታ የሚያሰልፈን ነው ብለዋል ። በዚህ ዓመት ደግሞ 8.4 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ እቅድ መያዙን ተናግረዋል ።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

30 Oct, 14:51


በስፔን በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ51 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በስፔን ቫሌንሺያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በትንሹ የ51 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

የአካባቢው ገዢ ካርሎስ ማዞን÷ የተከሰተውን አደጋ ተከትሎ 1ሺህ ወታደሮችና በርካታ የነፍስ አድን ሰራተኞች በስፍራው መሰማራታቸውን ተናግረዋል፡፡

በአደጋው እስካሁን የ51 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ጠቁመው÷የሟቶች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል አመልክተዋል፡፡

በአካባቢው በተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሳቢያም የባቡርና የአየር ትራንስፖርት መቋረጡን ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

30 Oct, 14:51


ሶማሊላንድ ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ ቢመጣ ከኢትዮጵያ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል ገለጸች!

ከየትኛውም ወገን ተቃውሞ እና ጫና ቢመጣ ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረመችውን ስምምነት ተግባራዊ ከማድረግ ወደ ኋላ እንደማትል የሶማሊላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ተናገሩ።“ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የደረሰችበት ስምምነት ምንም ነገር ሳይቀየር በነበረበት እንዳለ ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ አክለውም ሁሉም ወገን የተግባራዊነት ሰነዱ መቼ እንደሚፈረም በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የስምምነቱ ተግባራዊነት ሰፊ ጊዜን የሚጠይቅ እና ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ወደ ተግባር ለመቀየር በርካታ ዓመታትን የሚጠይቅ በመሆኑ መዘግየቱን ገልጸዋል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ “ ግብጽ በአባይ ወንዝ የተነሳ ከኢትዮጵያ ጋር ለገባችበት ውዝግብ ሶማሊያን እየተጠቀመችባት ወደ ጦርነት ልታስገባት ነው” ሲሉ ከሰዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

30 Oct, 14:51


‹‹በተወሰኑ ክልሎች ላይ የተከሰተው የወባ እና ኮሌራ ወረርሽኝ የጤና መብትን አሳሳቢ አድርጎታል›› ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው ሪፖርት የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ሁኔታን መዳሰሱን  አስታውቋል፡፡

ሪፖርቱ ከሰኔ 2015 እስከ ሰኔ 2016 ዓ.ም ያለውን ጊዜ የሸፈነ ሲሆን የጤና ፖሊሲው ሰብአዊ መብቶች ተኮር በሆነ መልኩ መቀረጹ፤ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ የተከራዮችን አቅም ባገናዘበና የመኖሪያ ቤት መብትን ለማረጋገጥ በሚያግዝ ሁኔታ ሥራ ላይ መዋሉ በሪፖርቱ ከተካተቱ ቁልፍ እመርታዎች መካከል መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ከነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል ከተከሰተው የትጥቅ ግጭት እና በሌሎች ክልሎችም ከቀጠለው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ መኖሪያ ቤትና የመተዳደሪያ ንብረቶችን ጨምሮ በመሠረተ ልማቶችና የአገልግሎት ተቋማት ላይ ውድመት የደረሰ ሲሆን በተለይም በምግብ፣ በጤና፣ በንብረት፣ በትምህርት፣ በሥራና ተያያዥ መብቶች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጻል።

በተጨማሪም አፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎችን ጨምሮ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተው ድርቅ ከግጭትና ከጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ከሚከሰት የምርት መቀዛቀዝ እንዲሁም የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ ንረት ጋር ተዳምሮ በርካታ ሰዎችን ለምግብ እጥረት መዳረጉም ተጠቁሟል።

በተመሳሳይ በተወሰኑ ክልሎች የተከሰተው የወባ፣ ኮሌራና ኩፍኝ ወረርሽኝ የጤና መብት ሁኔታን አሳሳቢ ማድረጉ እና አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች በርካታ የንግድና መኖሪያ ቤቶች ሕጋዊ ሂደትን ባልተከተለ መልኩ እንዲፈርሱ መደረጋቸው እና የሠራተኞች ደመወዝ በወቅቱና በአግባቡ ባለመከፈሉ ምክንያት ሠራተኞች ለተለያዩ ችግሮች መዳረጋቸው በሪፖርቱ የተነሱ ጉዳዮች ናቸው፡፡

በመሆኑም መንግስት በተነሱ አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ በማጤን እና ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮችን የሚመለከቱ ውሳኔዎችና እርምጃዎች ሕጋዊ ሁኔታን በተከተለ መልኩ ከባለመብቶች ጋር ተገቢው ውይይት ተደርጎ እንዲወስን ኢሰመኮ አሳስቧል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

30 Oct, 10:35


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የትርፍ ሰዓት ክፍያ ያልተከፈላቸው የጤና ባለሞያዎች ሥራ አቆሙ

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ የሚገኘው አንጋጫ ሆስፒታል የጤና ባለሞያዎች ትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈላቸው፣ በክልሉ ካምባታ ዞን አንጋጫ ወረዳ የሚገኘውና በአካባቢው ለሚገኙ 2 መቶ ሺሕ ለሚኾኑ ነዋሪዎች አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አገልግሎት ተቋረጠ።

አገልግሎቱ የተቋረጠው ሃኪሞቹን ጨምሮ 80 የሚኾኑ፣ የጤና ባለሞያዎች ለስድስት ወራት የሠሩበት የትርፍ ሰዓት ክፍያ ስላልተከፈላቸው መኾኑን ተናግረዋል። የሆስፒታሉ አገልግሎት የተቋረጠው ካለፈው ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀመሮ ሲኾን ተገልጋይ የኅብረተሰብ ክፍሎች መቸገራቸውን ተናግረዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

30 Oct, 10:35


በዎላይታ ዞን በከፍተኛ መጠን በጣለው ዝናብ በተከሰተው የመሬት ናዳ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ

በዚሁ በትላንትናው ዕለት ማታ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በካዎ ኮይሻ ወረዳ 01 ቀበሌ የአንድ ቤተሰብ አባለት በሙሉ እና ሌሎች ላይ አደጋ ደርሷል።

በዎላይታ ዞን በካዎ ኮይሻ ወረዳ በኮይሻ ላሾ ቀበሌ ሞግሳ ቀጠና በተከሰተው መሬት ናዳ 4 ሰውና በ01 ቀበሌ 3 ሰው አጠቃላይ የ7 ሰው ሕይወት አልፏል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

30 Oct, 10:35


የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ካለፈው ስምንት አጋማሽ ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ግንባሮች ከመንግሥት ኃይሎች ጋር በተካሄዱ ግጭቶች 102 የመንግሥት ወታደሮችንና በርካታ የጦር መሳሪያዎችን ማርኬያለኹ ሲል አዲስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

አማጺው ቡድን በመንግሥት ኃይሎች ላይ ወታደራዊ ድል ተቀዳጅቻለኹ ያለው፣ ድሬ ኢንጪኒ፣ ደራ፣ ወረ ጃርሶ፣ አመያ፣ ዩብዶ፣ ጉቴ፣ ቦጂ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሳሲጋ፣ አባይ ጮመን፣ ሀርጡማ ፉርሴ፣ ኤልዋዬ፣ ገላና፣ ሱሮ ቡርጉዳ፣ በቾ እና ቦራ በተባሉ የግጭት ግንባሮች ነው። ቡድኑ ግጭት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች፣ የግንኙነት መስመሮች እንደተቋረጡ መኾኑንም ጠቅሷል።

መከላከያ ሠራዊት በበኩሉ፣ በቡድኑ ላይ መጠነ ሰፊ የኃይል ርምጃ እየወሰደ መኾኑን ገልጧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

29 Oct, 17:36


❗️2 ወጣት ሴቶች በቡድን ሲደፈሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በቴሌግራም እየተዘዋወረ ነው፣ ድርጊቱን የፈፀሙት እየተፈለጉ ነው።

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወላጋ ዞን ነቀምቴ ውስጥ ሁለት ታዳጊ ልጆችን በቡድን በመሆን የደፈሩ ወጣቶች እስካሁን ድረስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር አለመዋላቸውን ፖሊስ እና የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናገሩ።

የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮሚሽነር ሻሎ ገለታ ወንጀሉ የተፈጸመው ነቀምቴ ከተማ ውስጥ ባለፈው መስከረም ወር ላይ መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ነገር ግን ወንጀሉን ከፈጸሙት መካከል “እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋለ የለም። ነገር ግን ሁለት ተጠርጣሪዎችን እየፈለግን ነው” ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

ሁለቱ ታዳጊ ልጆች በቡድን ሲደፈሩ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምሥል ባለፉት ቀናት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ከተሠራጨ በኋላ በርካቶች ቁጣቸውን እየገለፁ ነው።

ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋራው ተንቀሳቃሽ ምሥል ላይ ወንጀሉ የተፈጸመው ጊምቢ ከተማ ነው ቢባልም ነቀምቴ ከተማ መፈጸሙን ጥቃቱ ከደረሰባት ታዳጊ መካከል አንዷ ማረጋገጧን የፖሊስ ኃላፊው ተናግረዋል።

የከተማው የሴቶች እና ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ ወንጀሉ መፈጸሙን እንሚያውቅና ተጠርጣሪዎቹን ለፍርድ እንዲቀርቡ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል።

የቢሮው ኃላፊ የሆኑት መብራቴ ባጫ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋራውን ቪድዮ እንደተመለከቱ እና ምርመራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።

“መረጃው እንደደረሰን ማጣራት ጀምረናል። መጀመሪያ ወንጀሉ ጊምቢ ውስጥ መፈጸሙ ቢነገርም አሁን ግን እዚሁ ነቀምቴ ከተማ ውስጥ መፈፀሙን አረጋግጠናል” ብለዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

29 Oct, 17:36


❗️ናኢም ቃሲም የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድን መሪ ሆኖ ተመረጠ

ሂዝቦላህ የቡድኑ መሪ የነበረው ሃሰን ናስራላህ በቅርቡ በእስራኤል ጦር ጥቃት መገደሉን ተከትሎ ነው ናኢም ቃሲምን የቡድኑ መሪ አድርጎ የመረጠው፡፡

የ71 ዓመቱ ናኢም ቃሲም ከዚህ ቀደም በቡድኑ ውስጥ ለረጅም ዓመታት በተለያዩ የሃላፊነት ቦታዎች ላይ ማገልገሉን የሬውተርስ ዘገባ አመላክቷል፡፡

የሂዝቦላህ ታጣቂ ቡድንን ለረጅም ዓመታት ሲመሩ  የነበሩት ሃሰን ናስራላህ ከአንድ ወር በፊት እስራኤል በቤሩት በፈጸመችው የአየር ጥቃት መገደሉ ይታወሳል፡፡

በተመሳሳይ ናስረላህን ይተካል ተብሎ ሲታሰብ የነበረው ሃሺም ሴፊየዴን ከሳምንታት በፊት በእስራኤል ጥቃት መገደሉ ይታወቃል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

29 Oct, 17:36


የቲክቶክ መስራቹ የቻይና ቁጥር አንድ ሀብታም ሆነ

ቲክቶክን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው ባይተዳንስ ኩባንያ መስራች ዛንግ ይሚንግ በቻይና ሀብታሞች ዝርዝር አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠ።

በቻይና የሃብታሞች ደረጃ አውጭው ሁሩን እንዳስታወቀው ያንግ ይሚንግ በዓመታዊ የሀብታሞች ዝርዝር ሲወጣ በ49 ነጥብ 3 ቢሊዮን ዶላር ሃብት በማካበት ነው በቻይና ቁጥር አንድ ሀብታም ለመሆን የቻለው።

የ41 ዓመቱ ቱጃር እ.ኤ.አ በ2021 ከባይትዳንስ ዋና ስራ አስፈጻሚነት ስልጣኑ የለቀቀ ሲሆን የአንደኝነቱን ደረጃ የታሸገ ውሃ በማምረት ዘርፍ ከተሰማራው ዦንግ ሻንሻን ተቀብሏል።

ይህን ተከትሎ ሻንሻን በ47 ነጥብ 9 ቢሊዮን ዶላር ሀብት በማካበት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ምንም እንኳን ባይትዳንስ በአሜሪካና በአውሮፓ ክሶችና የእገዳ ማስፈራሪያዎች ቢበረክቱበትም የባለፈው ዓመት ዓመታዊ ገቢው በ110 ቢሊዮን ዶላር (30 በመቶ) እንዳደገለት ኢኮኖሚክ ታይምስ የተባለ ድረገፅ ዘግቧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

29 Oct, 17:36


❗️ዜናዎች

1፤ በአማራ ክልል በሚካሄደው ግጭት ምክንያት በርካታ የባንክ ቅርንጫፎች ፈተና እንደገጠማቸው ዋዜማ ሰምታለች። በሰሜን ጎጃም ዞን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፈረስቤትና ዓባይ ምንጭ ቅርንጫፎች በግጭት ምክንያት የተዘጉ ሲኾን፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ከተማና በምሥራቅ ጎጃም ዞን ጎዛምን ወረዳም ተዘግተው የከረሙ የባንኩ ቅርንጫፎች፣ በቅርቡ ሥራ መጀመራቸውን ዋዜማ ተረድታለች። በግጭቱ ሳቢያ በወረዳ ከተሞች የሚገኙ የተለያዩ ባንኮች ቅርንጫፎች ላንድ ቀን የሚያሳድሩት የገንዘብ መጠን ከ1.5 ሚሊዮን ብር እንዳይበልጥ እንደተደረገና፣ ይህም በባንኮቹ ላይ ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረ ታውቋል። ንግድ ባንክ የከፋ የጸጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ቅርንጫፎቹ ላንድ ቀን እንዲያሳድሩ የፈቀደላቸው የገንዘብ መጠን 500 ሺሕ ብር ነው ተብሏል።

2፤ ብሄራዊ ባንክ፣ የግል ባንኮች አገሪቱ ለምታስገባው ነዳጅ ከሚውለው የውጭ ምንዛሬ ከፍ ያለ ድርሻ እንዲሸፍኑ መመሪያ ማውረዱን ፎርቹን ዘግቧል። የግል ባንኮች ከኅዳር ጀምሮ ነዳጅ ለማስመጣት ሌተር ኦፍ ክሬዲት እንዲከፍቱ ባንኩ ማዘዙን ዘገባው ጠቅሷል። እስካሁን ባለው አሠራር፣ አገሪቱ ለምታስገባው ነዳጅ የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሬ የሚያቀርበው ብሄራዊ ባንክ ነው። ባንኩ አዲሱን መመሪያ ያወጣው፣ ከውጭ ምንዛሬ ፖሊሲ ለውጡ ወዲህ የግል ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ክምችት መሻሻል ማሳየቱን ተከትሎ ነው።

3፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ዛሬ በሚያካሂደው ስብሰባ በተሻሻለ የመገናኛ ብዙሃን ረቂቅ አዋጅ ላይ እንደሚወያይ አስታውቋል። ምክር ቤቱ፣ የከተማ መሬትን በሊዝ ለመያዝ እንዲሁም የከተማ መሬት ይዞታና መሬት ነክ ንብረቶችን ለመመዝገብ በቀረቡ ረቂቅ አዋጆች ላይ ጭምር ውይይት እንደሚያደርግም ገልጧል። የሊዝ ረቂቅ አዋጁ፣ የሊዝ መሬት በድርድር ማስተላለፍን እንደሚፈቅድ የአገር ውስጥ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። ምክር ቤቱ፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስን ጨምሮ ጠቅላይ ሚንስሩ በቅርቡ የሰጧቸውን የካቢኔ ሹመቶችም ያጸድቃል ተብሏል፡፡

4፤ የኤርትራ መንግሥት፣ ዘ ኢኮኖሚስት መጽሄት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች እንደሚገኙ አድርጎ ሰሞኑን የተሳሳተ ዘገባ አሠራጭቷል በማለት ከሷል። መጽሄቱ የጠቀሳቸው አካባቢዎች ዓለማቀፉ የድንበር ኮሚሽን "ለኤርትራ የከለላቸው ሉዓላዊ ግዛቶች" እንደኾኑ የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገ/መስቀል ገልጸዋል። የዓለማቀፉን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ በመቀበል ላይ የተመሠረተው የኤርትራና ኢትዮጵያ ግንኙነት ዳግም የታደሠበትን ዋና ምክንያትም መጽሄቱ አዛብቶ አቅርቦታል በማለት የማነ ወቅሰዋል።

5፤ የራስ ገዟ ፑንትላንድ አስተዳደር፣ በሱማሊያ የነዳጅ ፍለጋ መካሄዱን ፑንትላንድ ትቃወማለች በማለት ፌደራል መንግሥቱ ያሠራጨው ዘገባ "መሠረተ ቢስ ነው" በማለት ማስተባበሉን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የፑንትላንድ አስተዳደር፣ ፑንትላንድ በሱማሊያ ነዳጅ ፍለጋ እንዲካሄድ ቀዳሚዋ ደጋፊ ነበረች ብሏል። ሞቃዲሾ ውንጀላውን ያቀረበችው፣ ፌደራል መንግሥቱ "ውዝግብ ባለበት ቦታ ላይ" ቱርክ ነዳጅ ፍለጋ እንድታካሂድ ፍቃድ ሰጥቷል በማለት የራስ ገዟ ፕሬዝዳንት አብዱላሂ ደኒ መክሰሳቸውን ተከትሎ እንደኾነ ተገልጧል። ፑንትላንድ በነዳጅ የበለጸገች ግዛት እንደኾነች ይነገርላታል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

29 Oct, 17:36


❗️የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሩብ ዓመቱ ለጎረቤት አገራት ከሸጠው ኤሌክትሪክ ኃይል ከ31 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማግኘቱን እንደተናገረ የመንግሥት ዜና አውታሮች ዘግበዋል። ተቋሙ ለጅቡቲ ከሸጠው ከ169 ሺሕ 710 ሜጋ ዋት በላይ የሚኾን ኃይል፣ 10 ሚሊዮን 379 ዶላር እና ለኬንያ ከሸጠው ከ314 ሺሕ 931 ሜጋ ዋት በላይ የሚኾን ኃይል ከ20 ሚሊዮን 470 ሺሕ ዶላር ማግኘቱን እንደገለጠ ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል። በተመሳሳይ፣ ተቋሙ ለሱዳን ካቀረበው ከ13 ሺሕ 185 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል ከ659 ሺሕ በላይ ዶላር ያገኘ ሲኾን፣ በሱዳኑ ጦርነት ሳቢያ ተቋሙ በሩብ ዓመቱ ለአገሪቱ ለማቅረብ ካቀደው ኃይል ውስጥ ያቀረበው 15 በመቶውን ብቻ እንደኾነ ተገልጧል። ኢትዮጵያ ውስጥ በዲጂታል መረጃ ማቀነባበር ለተሠማሩ የውጭ ኩባንያዎች በሩብ ዓመቱ ውስጥ ከተሸጠው ኤሌክትሪክ ኃይል ደሞ፣ ከ27 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገኝቷል ተብሏል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

29 Oct, 13:55


የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች "ፋይዳ" መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ መሆኑን አስታወቀ

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በአዲስ አበባ በሚገኙት 16 ቅርንጫፎች ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ደንበኞች "ፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት ለማግኘት ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አስፈላጊ ስለመሆኑ ተቋሙ ባወጣው መረጃ አመላክቷል፡፡

በመሆኑም ከህዳር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙ ለሚሰጠው አገልግሎት ደንበኞች ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ወይም የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው ማሳሰቡን ከሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

29 Oct, 13:54


በነቀምቴ ከተማ ሁለት ታዳጊ ሴቶችን በቡድን የደፈሩ ወጣቶች እየተፈለጉ መሆኑን ፖሊስ ገለጸ!

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወላጋ ዞን ነቀምቴ ውስጥ ሁለት ታዳጊ ልጆችን በቡድን በመሆን የደፈሩ ወጣቶች እስካሁን ድረስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር አለመዋላቸውን ፖሊስ እና የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናገሩ።የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮሚሽነር ሻሎ ገለታ ወንጀሉ የተፈጸመው ነቀምቴ ከተማ ውስጥ ባለፈው መስከረም ወር ላይ መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ነገር ግን ወንጀሉን ከፈጸሙት መካከል “እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋለ የለም። ነገር ግን ሁለት ተጠርጣሪዎችን እየፈለግን ነው” ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።ሁለቱ ታዳጊ ልጆች በቡድን ሲደፈሩ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምሥል ባለፉት ቀናት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ከተሠራጨ በኋላ በርካቶች ቁጣቸውን እየገለፁ ነው።ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋራው ተንቀሳቃሽ ምሥል ላይ ወንጀሉ የተፈጸመው ጊምቢ ከተማ ነው ቢባልም ነቀምቴ ከተማ መፈጸሙን ጥቃቱ ከደረሰባት ታዳጊ መካከል አንዷ ማረጋገጧን የፖሊስ ኃላፊው ተናግረዋል።

የከተማው የሴቶች እና ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ ወንጀሉ መፈጸሙን እንሚያውቅና ተጠርጣሪዎቹን ለፍርድ እንዲቀርቡ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል።የቢሮው ኃላፊ የሆኑት መብራቴ ባጫ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋራውን ቪድዮ እንደተመለከቱ እና ምርመራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።

“መረጃው እንደደረሰን ማጣራት ጀምረናል። መጀመሪያ ወንጀሉ ጊምቢ ውስጥ መፈጸሙ ቢነገርም አሁን ግን እዚሁ ነቀምቴ ከተማ ውስጥ መፈፀሙን አረጋግጠናል” ብለዋል።በቪድዮው ላይ በቡድን ሲደፈሩ የሚታዩት ሁለቱ ታዳጊ ሴቶች ተማሪዎች መሆናቸውን እና ከታዳጊ ሴቶቹ በዕድሜ ተለቅ የሚሉ መሆናቸው የተነገረው ወንጀሉን የፈጸሙት ወንዶች ማንነት አልታወቀም።

ከዚህ የወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዘ ምንም አንኳ ፖሊስ ሁለት ተጠርጣሪዎችን ለይቶ ለመያዝ ጥረት እያደረገ እንደሆነ ቢገልጽም፣ የነቀምቴ ከተማ የሴቶች እና ሕጻናት ጉዳይ ኃላፊዋ ግን አራት ተጠርጣሪዎችን መለየታቸውን ይናገራሉ።“በቪድዮው ላይ የሚታዩ አራት ጥቃት አድራሾችን ለይተናል። የባጃጅ ሹፌሮች መሆናቸውንም ደርሰንበታል። አንዱ ባጃጁን ጥሎ የጠፋ ሲሆን የፀጥታ አካላት ክትትል አድርገው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተነጋግረናል” ብለዋል።

አክለውም ጥቃቱ የደረሰባቸውን ታዳጊዎች ቤተሰቦች ለማግኘት ጥረት ማድረጋቸውን እና አንዷ የሕክምና ድጋፍ እንድታገኝ መደረጉን ተናግረዋል።እንዲህ ዓይነት ወንጀሎች ሲፈጸሙ ተከታትሎ ጥቃት አድራሾችን ለፍትህ ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት የቢሮ ኃላፊዋ ሴቶች በነጻነት ወጥተው እንዲገቡ የሕግ የበላይነት መረጋገጡን እንከታተላለን ብለዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

29 Oct, 09:48


‹‹ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ብቁ አይደሉም›› ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

👉🏿‹‹ዶ/ር ጌዲዮንን በጥቅሉ ብቁ አይደሉም ብሎ መፈረጅ ተገቢ አይደለም›› ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ

በዛሬው እለት ሹመታቸው የጸደቀው የ5 ሚኒስትሮች የሹመት ሂደት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ዘንድ ቅሬታን አስነስቷል፡፡

የአካሄድ፤የስነስርአትና መሰል ህጋዊ አካሄዶች ተጥሰዋል በሚል በአንዳንድ የምክር ቤት አባላት ከተነሱ ቅሬታዎች ባላፈ የተሿሚዎች የግል አቅምን በማንሳት ተቋውሞ የቀረበበት ነበር፡፡

የአብን አባልና የፓርላማ እንደራሴ የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በተለይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስን በማንሳት ለቦታው ብቁ አይደሉም ሲሉ ሞግተዋል፡፡

ተቋማዊ ገለልተኝነትን አስጠብቆ ከመጓዝ አንጻር በፍትህ ሚኒስትር የሰሩት ስራ ጥያቄ የነበረበት ነበር ያሉት ዶ/ር ደሳለኝ አሁንም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ተሹመው ይህ ነው የሚባል ለውጥ ያመጣሉ ብዬ አላስብም ብለዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ እንዴት አዲስ የካቢኔ ሹመት ማግኘት አለባቸው የሚለው ሂደትም ተገቢ ግምገማ ሳይከናወንበት የተደረገ ነው የሚል እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

የመንግስት ተጠሪ ሚንስትር የሆኑት ዶ/ር ተስፋዬ በልጅጌ በበኩላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በተሸሙት ዶ/ር ጌዲዮን ላይ የተሰነዘረው አስተያየት ጥቅል ፍረጃ ያለበትና ተገቢው ምርመራ ያልተከናወነበት ነው ሲሉ ተከላክለዋል፡፡

ተሿሚን ብቁ አይደሉም በሚል የተሰጠው ጥቅል ፍረጃም ነባራዊውን ሁኔታ ያገናዘበ ነው ለማለት ይከብደኛል ሲሉም በዶ/ር ደሻለኝ ጫኔ የቀረበውን ቅሬታ አጣጥለውታል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

29 Oct, 09:48


የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሊከሰሱ ነው!

የአትዮጵያ ህዘብ እንባ ጠባቂ ተቋም መቀሌ ቅርንጫፍ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት "ከክልሉ ጎን ለምን ተሳትፎ አላደረጋቸህም" በሚል ከስራቸው ተሰናበተው ለሁለት አመታት የቆዩት የፖሊስ ሰራዊት አባለት ምላሽ ባለማግኘታቸው ጉዳዩን ወደ ህግ እንደሚወስደው አስታውቋል።

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ጸሃዬ እምባዬ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አንደተናገሩት በሚቀጥሉት "አምስት ቀናት" ከጊዜዓዊ አስተዳደሩ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ ጊዜያዊ አስተዳደሩን ፕሬዝዳንት እንደሚከሱ ተናግረዋል።

የአምስት ቀኑ ማስጠንቀቂያ ከጥቅምት 19 /02 /2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚቆጠር ነግረውናል፡፡አቶ ጸሃዬ ፕሬዝዳነቱን የምንከሰው "አሰራሩ ስለሚያስገድድ እና ያሉበት የስራ ሃላፊ እሳቸውን የሚመለከት ስለሆነ እንጂ" ሌላ አላማ ኖሮን አይደለም ብለዋል።

በአሰራሩ መሰረት ፕሬዝዳነቱ ለክስ የሚቀርቡት ለትግራይ ክልል አቃቢ ህግ ቢሆንም አቃቢ ህጉ ደግሞ በክልል ጊዜዊ አስተዳደር ስር በመሆኑ ምክንያት አቃቢ ህጉ ሀላፊውን ለመክሰስ ስለማይችሉ ክሱ ለፌድራሉ ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ቅርንጫ ጽ/ ቤቱ የፖሊስ ሰራዊት አባለቱ ወደ ስራ እንዲመለሱ ውሳኔያቸውን እንዳሳለፉ የነገሩን አቶ ጸሃዬ ውሳኔው ከተወሰነ 33 ቀናት ቢያስቆጥርም እስካሁን ደረስ ምላሽ ባላመገኘቱ ምክንያት "የአምስት ቀን ማስጠንቀቂያ ሰጥተን ነው ወደ ክስ ለመግባት ተገደናል" ነው ያሉት።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

29 Oct, 09:48


በጉራጌ ዞን “ከፋኖ ጋር በተያያዘ” ከ100 በላይ ሰዎች መታሰራቸው ተነገረ!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ከሰኔ 2016 ዓ.ም. ወዲህ ከ100 በላይ የአማራ ብሔር ተወላጆች “በሽብር” ተጠርጥረው ሲታሰሩ ስጋት ያደረባቸው ነዋሪዎች ደግሞ አካባቢውን ለቀው መሸሸታቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።በዞኑ አበሽጌ ወረዳ ከሰኔ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ‘ፋኖ ናችሁ፤ የፋኖ ክንፍ ናችሁ፤ ፋኖን በገንዘብ ትደግፋላችሁ’ በሚል የፀጥታ ኃይሎች ድብደባ እና እንግልትን ጨምሮ “ማንነትን የለየ” እስር እየፈጸሙ መሆናቸውን በመግለጽ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን አመልክተዋል።

የአካባቢው የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ በቁጥጥር ስር የሚገኙት ነዋሪዎች “በመሳሪያ ዝውውር እና እገታ” ወንጀሎች ተጠርጥረው የተያዙ ናቸው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።አብሸጌ ወረዳው ካሉት 30 ቀበሌዎች እና ማዘጋጃዎች 16ቱ በአብዛኛው የአማራ ብሔር ወላጆች እንደሚኖሩባቸው የተናገሩት ነዋሪዎች፤ ካለፈው ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ግን ከፋኖ ጋር በተያያዙ ክሶች ምክንያት “እየተሳደድን ነው” ይላሉ።

“ከባለሀብት እስከ ቀን ሠራተኛ፤ ከፖለቲከኛ እስከ ወጣት፤ ከባጃጅ ሹፌር እስከ ሞተረኛ ድረስ” የእስሩ ሰለባዎች እንደሆኑ አንድ አካባቢውን ለቀው የወጡ ነዋሪ ተናግረዋል።የመንግሥት ሠራተኛ የነበሩ አንድ ነዋሪ የታሰሩ ሰዎች ከ140 በላይ (በወልቂጤ 90 ሰዎች እና ዋልጋ ከ50 በላይ ሰዎች) እንደሚሆኑ ጠቁመው እስሩ አሁንም እንዳላቆመ ገልጸዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

29 Oct, 08:35


ብሔራዊ መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሠነድነት መጠቀም የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ!

ብሔራዊ መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሠነድነት መጠቀም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈረሙን የ ኢትዮጵያ አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ ለኢትዮጵያ) ናቸው፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት ሥርዓቶቻቸውን በማቀናጀት ብሔራዊ መታወቂያን ለሀገር ውስጥ በረራዎች በጉዞ ሠነድነት መጠቀም ያስችላል ተብሏል።በዚሁ መሠረት አየር መንገዱ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመሆን ምዝገባ ከመያዝ ጀምሮ እስከ መሳፈር ድረስ ያለውን የመንገደኞች አገልግሎት ባዮ ሜትሪክ መረጃን በመጠቀም ይበልጥ ለማቀላጠፍ ይሠራል ተብሏል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

29 Oct, 08:35


የአየር ክልሌ ለሌሎች ሀገራት ጥቃት እንዲውል አልፈቅድም- ኢራቅ

የኢራቅ መንግሥት በጻፈው የእስራኤልን ድርጊት የሚኮንን ደብዳቤ÷ “እስራኤል ከዓለም አቀፍ ሕግጋት አፈንግጣ የአየር ክልሌን ጥሳ በፈረንጆቹ ጥቅምት 26 ምሽት ላይ በኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈጽማለች” ብሏል፡፡

ኢራቅ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የጋራ ተጠቃሚነትን መሠረት ያደረገ ጥሩ ግንኙነት እንዳላት በደብዳቤው የተገለጸ ሲሆን÷ የአየር ክልሏ ወይም ግዛቷ ለሌሎች ሀገራት ጥቃት እንዲውል እንደማትፈቅድ ማሳሰቧን ስፑትኒክ ኢንተርናሽናል ዘግቧል፡፡

የኢራቅ ጠቅላይ ሚኒስትር መሐመድ ሺዓ አል-ሱዳኒ÷ የኢራቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሁለትዮሽ እና የስትራቴጂክ አጋርነት ማዕቀፍ ስምምነቶችን በተመለከተ ከአሜሪካ መንግሥት ጋር አፋጣኝ ውይይት እንዲያድርግ መመሪያ መስጠታቸውም ተመላክቷል፡፡

እስራኤል ከትናንት በስቲያ የኢራቅን የአየር ክልል ጥሳ በማለፍ ፈጽማዋለች በተባለው ጥቃት በኢራን፣ ኢራቅ እና ሶሪያ በሚገኙ ከ20 በላይ የኢራን ወታደራዊ ዒላማዎች ላይ ጉዳት ማድረሷን ዘገባው አስታውሷል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

29 Oct, 08:35


የኤርትራ መንግሥት ዘ ኢኮኖሚስት የተሰኘው መጽሄት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ አንዳንድ አካባቢዎች እንደሚገኙ አድርጎ ሰሞኑን የተሳሳተ ዘገባ አሰራጭቷል በማለት ከሷል።

መጽሄቱ የጠቀሳቸው አካባቢዎች ዓለማቀፉ የድንበር ኮሚሽን "ለኤርትራ የከለላቸው ሉዓላዊ ግዛቶች" እንደኾኑ የኤርትራ መንግሥት ቃል አቀባይ የማነ ገ/መስቀል ገልጸዋል።

የዓለማቀፉን የድንበር ኮሚሽን ውሳኔ በመቀበል ላይ የተመሠረተው የኤርትራና ኢትዮጵያ ግንኙነት ዳግም የታደሠበትን ዋና ምክንያትም መጽሄቱ አዛብቶ አቅርቦታል በማለት የማነ ወቅሰዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

28 Oct, 17:56


‹‹በዘፈቀደ የሚሰጡ ሹመቶች ከባድ ቅጣትን ያስከትላሉ›› የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር

ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፍቃድና እውቅና ውጪ የሚደረጉ ሹምሽሮች እስከ በጀት መገደብ የሚደርስ ቅጣት ሊጣል ይችላል ሲል በጌታቸው ረዳ የሚመራው ጊዚያዊ አስተዳደር አስጠንቅቋል፡፡

ጊዚያዊ አስተዳደሩ በአቶ ጌታቸው ረዳ ፊርማ ተፈርሞ ባሰራጨው መመሪያ ፤ " የጊዚያዊ አስተዳደሩን እቅዶች ማደናቀፍ እና በዘፈቀደ ህጋዊ ያልሆነ ሹመት መስጠትና መንሳት የበጀት ቅጣትና የህግ ተጠያቂነት ያስከትላል " ሲል ነው ማስጠንቀቂያ የሰጠው።

መንግስታዊ ስልጣን እና ሃላፊነት የሌለው ' ቡድን ' በማለት የተጠቀሰው በዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የሚመራው ህወሓት የሚሰጠው ሹመት የመሻርና ሹመት የመስጠት ተግባር ፍፁም ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

በመሆኑም ቡድኑ የሚያካሄዳቸውን ህጋዊ ያልሆኑ ተግባራት እንዲቆም ይህንን የጊዚያዊ መንግስቱ መመሪያ በመቀበል ፍርድ ቤት ጨምሮ የዞን እና የወረዳ የመንግስት መዋቅሮች ህጋዊ አሰራር እንዲከተሉና ህግ በሚጥስ ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንዲሁም በክልሉ በየመዋቅሩ ያሉ ምክር ቤቶች ጊዚያቸው ያለፈ እና ህጋዊ መሰረታቸው ያበቃ መሆኑን በመቀበል ሹመት ከመስጠትና ከመሻር እንዲቆጠቡ ሲል ነው ያሳሰበው፡፡

ላለፉት ወራት የዘለቀው የህወሃት አመራሮች ፍትጊያ አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን እኔ ብቻ ነኝ እውቅና ያለኝ የሚለው የሁለቱ ቡድኖች መካረርም ምንም አይነት መፍትሄ አላገኘም፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

28 Oct, 17:56


‹‹በምሥራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙት 996 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 86ቱ ብቻ ናቸው የተከፈቱት›› የዞኑ ትምህርት መምሪያ

በምስራቅ ጎጃም ዞን ውስጥ ከሚገኙ 996 ትምህርት ቤቶች ውስጥ 86ቱ ብቻ ትምህርት እየተሰተባቸው እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጌታሁን ፈንቴ በዘንድሮ ትምህርት ዘመን 710 ሺህ ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ታቅዶ መመዝገብ የቻሉት 70 ሺህ ብቻ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ተከፍተው ሥራ የጀመሩት ትምህርት ቤቶችም ከችግሮች የጸዱ አይደሉም ያሉት አቶ ጌታሁን ወደ ትምህርት ቤት የሚመጡ ሕጻናት በየመንገዱ “መጽሐፍና ደብተራቸው እየተቀደደባቸው እና እየተደበደቡ አልቅሰው ይመለሳሉ” ብለዋል።

ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት እንደላኩ የተሰማባቸው ወላጆችም እስከ “15 ሺህ ብር ቅጣት፣ ድብደባን ጨምሮ እስከ ግድያ የደረሰ ግፍም እንደተፈጸመባቸው” የትምህርት መምሪያ ኃላፊው ለአሚኮ ተናግረዋል።

አቶ ጌታሁን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ርቀው ቤት ሲውሉ በተለይም ሴት ልጆች “ያለዕድሜ ጋብቻ እየተፈጸመባቸው ነው” ሲሉ ገልጸው ወንዶቹም ቢኾኑ ዘመን በወለደው አጓጉል ቦታ እየዋሉ ለወላጆቻቸው የጭንቀት ምንጭ እየሆኑ ነው ብለዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

28 Oct, 17:56


የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው መጠለያዎች “የታጠቁ አካላት ሰርገው በመግባት” ጥቃት እንደሚፈጽሙ ኢሰመኮ አስታወቀ!

የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሚኖሩባቸው ጣቢያዎች “ተገቢ ጥበቃ ስለማይደረግላቸው”፤ የታጠቁ አካላት “ሰርገው በመግባት ጥቃት እንደሚፈጽሙ” የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ። በዚህ ሳቢያ ተፈናቃዮች “አስጊ በሆነ የደህንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ” ኮሚሽኑ ገልጿል።

➡️ ብሔራዊው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም ይህን ያስታወቀው፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን በተመለከተ ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 18፤ 2017 ባወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ነው።

➡️ ኮሚሽኑ ለሶስተኛ ጊዜ ያዘጋጀው ዓመታዊ ሪፖርት፤ ከሰኔ 2015 እስከ ሰኔ  2016 ዓ.ም. ድረስ ያለውን ጊዜ የሚሸፍን ነው። 

➡️ በስምንት ክልሎች የተፈናቃዮቹን ሰብአዊ መብቶች አያያዝን የተመለከተ ክትትል እና ምርመራ ማድረጉን በሪፖርቱ የገለጸው ኢሰመኮ፤ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የታጠቁ ቡድኖች በየጊዜው በሚያደርሱት ማንነትን መሰረት ባደረጉ ጥቃቶች ዜጎች እንደሚፈናቀሉ አመልክቷል። በመንግስት እና በታጠቁ ቡድኖች መካከል የሚደረጉ ግጭቶች ሌላኛው ምክንያት እንደሆነ ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

➡️ በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ያለው የጸጥታ ችግር፤ ዜጎችን እንዲፈናቀሉ ከማድረግ ባሻገር ለተፈናቃዮች ሊደረግ የሚገባውን ሰብአዊ ድጋፍ እና ጥበቃ “አስቸጋሪ” እንዳደረገው በኮሚሽኑ ሪፖርት ላይ ተገልጿል። 

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

28 Oct, 17:56


ከአፍሪካ ኅብረት ሒሳብ በሐሰተኛ የክፍያ ሠነድ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሊያወጡ ሲሉ ተይዘዋል ተብለው በከባድ ማታለል ሙስና ወንጀል የተከሰሱት እነ ቀሲስ በላይ መኮንን እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ!

ዛሬ ብይኑን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ ቄስ በላይ መኮንን፣ በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ የተሰማራው እያሱ እንዳለ፣ በኮሚሽን ስራ ላይ የተሰማራው በረከት ሙላቱ እና አለምገና ሳሙኤል እና የኒሞና ንግድ ስራ ኃላ/የተ/የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ አበራ መርጋ በተባሉ ተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ ቁጥር 32 ንዑስ ቁጥር 1(ሀ) እና የሙስና ወንጀሎች ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 2 እና ንዑስ ቁጥር 3 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ እና በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ ቁጥር 382 ንዑስ ቁጥር 1 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ከአፍሪካ ህብረት ምንም አይነት የክፍያ ትዕዛዝ ባልተሰጠበት ሁኔታ ላይ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ተራ ቁጥር ለተከሰሱ ተከሳሾች በተለያየ የዶላር መጠን ክፍያ እንዲፈጸምላቸው የሚል አጠቃላይ የ 6 ሚሊየን 50 ሺህ ዶላር ሐሰተኛ የክፍያ ሠነድ በአንደኛ ተከሳሽ መቅረቡ ተጠቅሶ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

በዚህ መልኩ የቀረበውን ክስ ከ1ኛ እስከ 3 ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ብቻ ችሎት የቀረቡና የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው የተደረገ ሲሆን÷ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በአድራሻቸው ባለመገኘታቸውና በተደጋጋሚ ቀጠሮ ባለመቅረባቸው ለጊዜው ክሳቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል።ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ክሱ እንዲሻሻልላቸው ያቀረቡት የመጀመሪያ ደረጃ ክስ መቃወሚያ ነጥቦችን ፍርድ ቤቱ መርምሮ ወደፊት በማስረጃ እንደሚጣራ ገልጾ መቃወሚያቸውን አልተቀበለውም።

በክሱ ላይ የተጠቀሰውን የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው ተከሳሾቹ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ህግ የአፍሪካ ኅብረት ቅርጫፍ የባንክ ባለሙያዎችን አጠቃላይ 3 ምስክሮችን አቅርቦ ምስክርነታቸውን አሰምቶ ነበር፡፡ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ህግ ያሰማቸውን የምስክሮችን ቃልና የሰነድ ማስረጃዎችን መርምሮ በአንደኛው ክስ እንዲከላከሉ በሙሉ ድምጽ ብይን ሰጥቷል።

ሁለተኛውን ክስ በሚመለከት በሐሰተኛ ሠነድ የተፈጸመ ድርጊት መሆኑ በአንደኛውን ክስ ላይ መገለጹን ተከትሎ በሰበር ሰሚ ችሎት ትርጉም የተሰጠባቸው በተደራራቢነት የቀረቡና ተጠቃልለው ሊያስቀጡ የሚችሉ ድንጋጌዎች መኖራቸውን ፍርድ ቤቱ አብራርቶ ሁለተኛውን ክስ ውድቅ በማድረግ በአንደኛው ክስ ብቻ በከባድ አታላይነት ሙስና ወንጀል እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል።ተከሳሾቹ የመከላከያ ማስረጃ ካላቸው ለመጠባበቅ ለሕዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

25 Oct, 17:15


እስራኤል በኢራን ላይ ለምትፈጽመው ጥቃት ምን አይነት መሳሪያ ትጠቀማለች

በኢራን ጥቃት የተሰነዘረባት እስራኤል የምትወስደው የአጸፋ እርምጃ እየተጠበቀ ነው
እስራኤል በኢራን ላይ ልትወስደው በምትችለው የአጸፋ እርምጃ ልትጠቀማቸው የምትችለውን መሳሪያ የሚያሳይ መረጃ አፈትልኮ ወጥቷል።
የእንግሊዙ ታይምስ መጽሄት ከአሜሪካ መከላከያ የደህንነት ተቋም ሾልኮ ወጣ በተባለ ሰነድ ላይ የተቀመጡ የመሳሪያ አይነቶችን ይፋ አድርጓል።
ከአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር እንደወጣ በሚያሳየው እና በቴሌግራም ላይ ተለቀቀው መረጃ እስራኤል እያደረገች ያለውን ዝግጅትና እንቅቀሴዎች የሳተላይት ምስሎች እና የደህንነት ምንጮችን ዋቢ ያደረገ ነው ተብሏል።
በዚህም ለየት ያለ ሚሳኤሎችን የታጠቁ የእስራኤል የጦር ጅቶች ቀለል ያሉ ልምምዶችን ሲያደርጉ ተመላክቷል።
የእስራኤል የደህንነት ምንጭ በጉዳዩ ላይ በሰጠው አስተያየት፣ መረጃው ከአሜሪካ እጅ አፈትልኮ መውጣቱ እስራኤል ጥቃት ለመፈጸም ያቀደችበትን ጊዜ እና ስትራቴጂ እንድትቀይር አስገድዷታል።
የእስራኤል ኢላማም ምን ነው?
ከአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ሾልኮ ወጣ በተባለው ሰንድ ላይ እስራኤል በኢራን ላይ በምትፈጽመው የአየየፋ እርምጃ የኢራን አብዮታዊ ዘብ እና ባሲጅ የተባለው ወታደራዊ ሃይል ዋነኛ ኢላማ ናቸው ተብሏል።
እስራኤል ምን አይነት መሳሪያ ትጠቀማለች?
ከአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ እስራኤል በኢራን ላይ በምትወስደው የአጸፋ እርምጃ ከምትጠቀማቸው የመሳሪያ አይነቶች ውስጥ የተወሰኑትን ይፋ አድርጓል።
ከእነዚህም ውስጥ ከተዋጊ ጄቶች ላይ የሚተኮሱ ከአየር ላይ የረጅም ርቀት ሚሳኤሎች ይገኙበታል የተባለ ሲሆን፣ ይህም የሌላ ሀገር የአየር ክልል መጠቀም ሳይያስፈልግ ጥቃት መሰንዘር የሚያስችል ነው።
ከሚሳኤሎቹ ውስጥም "ጎልደን ሆራይዘን" እና ሮክስ 2 የተባሉ ከአየር ላይ የሚተኮሱ ሚሳኤሎችን ያካተተ ነው።
"ሮክስ" የሚል መጠሪያ ያለው የባላስቲክ ሚሳዔል ከአየር ወደ ምድር የሚተኮስ ሲሆን፣ ከኤፍ 16 እና ኤፍ 35 የጦር ጄቶች ላይ መተኮስ የሚችል ነው።
"ጎልደን ሆራይዘን" የተባለው ሚሳኤል ከአየር ላይ የሚተኮስ ሲሆን: እስከ 2 ሺህ ኪሎ ሜትር ክልል ውስጥ ያለን ኢላማ መምታት የሚችል ነው ተብሏል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

25 Oct, 17:15


የኢትዮ ዛምቢያ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ

የዛምቢያ ባለ ሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ ሁኔታን በመጠቀም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትብብር እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀርባል

በአፍሪካ በማእድን ሀብት ከሚጠቀሱ ጥቂት ሀገራት መካከል የሪፓብሊክ ኦፍ ዛምቢያ ተጠቃሽ ናት፡፡

60ኛ አመት የነጻነት በአሏን በዚህ አመት በማክበር ላይ የምትገኘው ዛምቢያ ከኢትዮጵያ ጋር በንግድና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችላቸውን ውይይት በአዲስ አበባ አካሂደዋል፡፡

በአዲስ ቻምበር እና አዲስ አበባ በሚገኘው የዛምቢያ ኤምባሲ በትብብር የተዘጋጀው የኢትዮ ዛምቢያ የንግድና የኢንቨስትመንት ፎረም የሁለቱን ሀገራት ባለ ሀብቶች በአንድ መድረክ ያገናኘ ሲሆን ለመጀመርያ ጊዜ የተካሂደው የዛምቢያና የኢትዮጵያ የንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም በሁለቱ ሀገራት ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት እድሎች ፤ ማበረታቻዎች የፖሊሲ ማእቀፎችና አስቻይ ሁኔታዎች በዝርዝር የቀረቡበት መድረክ ነበር፡፡

በተለይም የዛምቢያ ባለ ሀብቶች በኢትዮጵያ ያለውን ፈጣን የኢንዱስትሪ ምቹ ሁኔታን እንዲሁም በመንግስት በኩል ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት የተወሰዱ የፖሊሲ ለውጦችን በመጠቀም ሙዋለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ቀርባል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

25 Oct, 17:15


እስራኤል ደጅ ኢራቅ የሚገኘው የአሜሪካ የጦር ከ እስላማዊው ሃይል IS ጋር ባደረገው የሞት ሽረት ፍልሚያ ሁለት የአሜሪካ ወታደሮች በሞት አፋፍ ላይ ሆነው ወደ አሜሪካ ለከፍተኛ ህክምና መላካቸውን የአሜሪካ ጦር ፔንታጎን አስታውቋል።

የፔንታጎን ምክትል ፕሬስ ፀሐፊ ሳብሪና ሲንግ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "ሁለቱም የአገልግሎት አባላት ከባድ ጉዳት ቢደርስባቸውም በተረጋጋ ሁኔታ ላይ ናቸው እናም በአሁኑ ነፍሳቸውን ለማትረፍ እና ለከፍተኛ ክትትል ወደ ዋልተር ሪድ የሕክምና ማእከል በመጓዝ ላይ ናቸው" ያሉት ሳብሪና ሲንግ “ነገር ግን በዚህ መሃል ከባድ ዜናም ልንሰማ የምንችልበት ሁኔታ እንዳለ ከህክምና ባለሙያዎች የተላከው የ TBI መረጃ ያስረዳል” ሲሉ ወታደሮቹ ሊሞቱ እንሰሚችሉ አመላክተዋል። 

ውጊያ የተካሄደው የአሜሪካ ጦር እንደተለመደው ድምጹን አጥፍቶ በሽብር የተፈረጀው IS መገኛ የሆነው ለመምታት በገቡበት ቅጽበት ከአየር ድብደባው የተረፉ የ IS አባላት በእግረኛው የአሜሪካ ጦር ላይ በከፈቱት የተኩስ ሩምታ የአሜሪካ ወታደሮች ተጎድተዋል።

የአሜሪካ ጦር ጥቃት የፈጸምኩት በ IS ይዚታዎች ላይ ነው ሲል የኢራቅ ጦር ግን ይሄን ማረጋገጥ አልቻለም።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

25 Oct, 17:15


ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት ወደ ውጭ ከላከቻቸው ምርቶች፤ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘቷ ተነገረ!

የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ የሶስት ወራት አፈጻጸም፤ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ83 በመቶ በመጨመሩ፤ 1.5 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።በአጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ ጭማሪ ቢታይም፤ ወደ ውጭ ከተላኩ የጫት እና የጥራጥሬ ምርቶች የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር መቀነሱን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ይህ የተገለጸው፤ የተለያዩ ምርቶችን ወደ ውጭ ሀገር ከሚልኩ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ትላንት ሐሙስ ጥቅምት 14፤ 2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ላይ ነው።በዚሁ ስብሰባ ላይ የዘንድሮ በጀት ዓመት የሶስት ወራት የወጪ ንግድ እቅድ አፈጻጸም ለተሰብሳቢዎች ቀርቧል። በአዲሱ የጥራጣሬ እና የቅባት እህሎች የቀጥታ ግዢ መመሪያ ላይም ውይይት ተደርጓል።

በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የወጪ ንግድ ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ አቶ በረከት መሰረት፤ በዘንድሮ በጀት ዓመት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ ሊገኝ ታቅዶ የነበረው አጠቃላይ ገቢ 1.12 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል።በሩብ ዓመቱ ሀገሪቱ ከዘርፉ ያገኘችው ገቢ በእቅድ ከታየዘው በ385 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ብልጫ ያለው እንደሆነም አመልክተዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

25 Oct, 17:15


በትራንስሚሽን መስመር ላይ ባጋጠመ ብልሽት ምክንያት የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል!

ከበደሌ - መቱ -ጋምቤላ የተዘረጋው ባለ 230 ኪቮ ትራንስሚሽን መስመር ከበደሌ 36 ኪሜ ላይ ብልሽት በመበላሸቱ በመቱ፣ ጋምቤል ክልል እንዲሁም ደምቢዶሎ ከተማ የሃይል አቅርቦቱ ተቋርጧል።

ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ብልሽቱ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ተጠግኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ተጠይቋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

25 Oct, 10:48


አቶ ታዲዮስ ታንቱ የ6 ዓመት ከ3ወር ጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት ተጣለባቸው!

የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና ግጭት መቀስቀስ ወንጀል የተከሰሱትን አቶ ታዲዮስ ታንቱ በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በገንዘብ ተቀጡ።የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የህገ-መንግስትና ህገ መንግስታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት አቶ ታዲዮስ ታንቱን በተከሰሱበትና ጥፋተኝነት በተባሉባቸው 3 ክሶች ነው የጽኑ እስራትና የገንዘብ ቅጣት የጣለባቸው።

አቶ ታዲዮስ ታንቱ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት እና የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በፍትህ ሚኒስቴር በተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ በኩል ተደራራቢ አራት ክሶች ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው አንደኛው ክስ ላይ እንዳመላክተው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/(1)ሀ እና አንቀጽ 257/ሀ ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ግንቦት 11 ቀን እና በመጋቢት 22 ቀን 2014 ዓ.ም እና በተለያዩ የዩቲዩብ ቻናሎች ህዝባዊ አመጽ መቀስቀስ ወንጀል የሚል ነው።

በ2ኛ ክስ በተመለከተ ደግሞ የጥላቻ ንግግርንና ሀሰተኛ መረጃን ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁ 1185/2012 አንቀጽ 4 እና 7/4 በመተላለፍ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም በአንድ የዩቲዩብ ቻናል ሀሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል የሚል ክስ በዐቃቤ ሕግ ክስ ቀርቦባቸው ነበር።

በ3ኛ ክስ ደግሞ የወንጀል ህግ ከንቀጽ 32 /1ሀ ና አንቀጽ 337 በመተላለፍ የመከላከያ ሰራዊትን እቅስቃሴን ለማሰናከልና የመከላከል አደጋ እንዲደርስ ለማድረግ በማሰብ ሀሰተኛ ወሬ በመንዛት ቅስቀሳ ማድረግ ወንጀል የተከሰሱ ሲሆን በ4ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል አዋጅ ቁ 958/2008 አንቀጽ 14 በመተላለፍ ህዝባዊ አመጽ እንዲፈጠር ቀስቃሽ መልዕክት በድምጽና በተቀሳቃሽ ምስል ተሰራጭቷል የሚል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱም የ6 ልጆች አባት መሆናቸውንና የ70 ዓመት አዛውንት መሆናቸውን ከግምት ውስጥ አስገብቶ ሁለት የቅጣት ማቅለያ በመያዝ በዕርከን 24 መሰረት በ6 ዓመት ከ3 ወራት ጽኑ እስራትና በ20 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

25 Oct, 10:48


የምክክር ኮሚሽኑ ጥቂት ወራት የቀሩት ቢሆንም “የስራ ጊዜው እንዲራዘም አልጠየቅንም፣ አልፈልግም” ሲሉ ዋና ኮሚሽነሩ አስታወቁ!

በየካቲት ወር አጋማሽ 2014 ዓ.ም 11 ኮሚሽነሮችን ይዞ ለሶስት አመታት የስራ ጊዜ የተቋቋመው የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ ዘመኑ ሊጠናቀቅ አምስት ወራት ቢቀሩትም “አሁን ባለው ሁኔታ የኮሚሽኑ ጊዜ እንዲራዘም አልፈልግም እንዲራዘምም አልጠየቅንም” ሲሉ ዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን ገለጹ።

ከሚሽኑ የስራ ጊዜው ሊጠናቀቅ ከአምስት ወራት ያነሱ ጊዜያት በቀሩበት ሁኔታ በትግራይ እና አማራ ክልል ያልጀመራቸውን ስራዎች ጨምሮ ሀላፊነቱን ሙሉ ለሙሉ ማጠናቀቅ ይችላል ወይ? ተብለው በአልአይን የተጠየቁት ዋና ኮሚሽነሩ አስቸጋሪ ይሆናል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

“የታጠቁ ሀይሎችን እስካሁን ገጽ ለገጽ ወይም በቀጥታ አግኝተን አነጋግረናቸው አናውቅም፤ ነገር ግን ለድህንታቸው ሙሉ ዋስትና እንደምንሰጥ ከዛም አልፎ በውጭ ሀገራት ተገናኝተን ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ፈቃደኛ መሆናችንን ገልጸናል” ብለዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

25 Oct, 10:48


የእንስሳት ክትባት የሚያመርቱ አራት የውጭ አገር ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ፋብሪካቸውን ሊተክሉ መሆኑን ተሰማ

በቅርቡ የእንስሳት ክትባት የሚያመርቱ አራት የውጭ አገር ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ፋብሪካቸውን ሊተክሉ መሆኑን የግብርና ባለስልጣን አስታውቋል።በኢትዮጵያ የሚስተዋለውን የእንስሳት ክትባት ችግር የተነሳ የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ላይ ክፍተት ሲስተዋል መቆየቱን ባለስልጣኑ ተናግሯል።

ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ክትባት ለማምረት የተስማሙት ኩባንያዎች፤ የችግሩን ስፋት ያጠቡታል የሚል እምነት እንዳለ በግብር ባለስልጣን የእንስሳት መድሀኒት ቁጥጥር ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ሰለሞን ከበደ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ደረጃ የእንስሳት ክትባት የሚያመርት ድርጅት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ጥበቃ ኢንሰቲትዩት ብቻ እንደነበር የገለጹት ኃላፊው፤ "የውጭ ኩባንያዎችን ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መፈቀዱ ክፍተቱን መድፈን ያስችላል" ብለዋል።

ወደ ሀገር ይገባሉ የተባሉት ክትባት አምራች ኩባንያዎች የማምረተ አቅምና የጥራት ደረጃቸውን በተመለከተ ሰፊ ግምገማ ሲደረግለት መቆየቱን ዶክተር ሰለሞን አስታውሰዋል።መንግሥት የያዘው የእንስሳት ጤና ጥበቃ እንቅስቃሴ አካል መሆኑን ኃላፊው ጨምረው ለአሐዱ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ በብቸኝነት የእንስሳት ክትባት በማምረት የሚታወቀው የመንግሥት የልማት ድርጅት የሆነው ብሔራዊ የእንሰሳት ጤና ጥበቃ ኢንሰቲትዩት ሲሆን፤ የተቋቋመው በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እንደነበር ይታወቃል።በርካታ የውጭ ምንዛሪ ከሚጠይቁ የግብርና ምርቶች መካከል አንዱ የእንስሳት ክትባት ተጠቃሽ መሆኑን በግብርና ባለስልጣን የእንስሳት መድኃኒት ቁጥጥር ኃላፊው ከዶክተር ሰለሞን ለማወቅና ችለናል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

25 Oct, 10:48


#ትምህርት ሚንስቴር


ከዚህ በፊት ለሪሚዲያል ተማሪዎች በተቋማት የሚሰጠው ውጤት 30% ሲሆን 70% ደግሞ የሚሰጠው ከት/ት ሚኒስቴር ነበር።

አሁን ግን ይህ አሠራር ተሻሽሎ 100% ከማዕከል(በትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጡ ምዘናዎች) በኩል እንዲሰጥ ተወስኗል።

ተማሪዎች በሚማሩት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጠው 30% የውጤት ምዘና  አሰጣጡ ወጥነት ስለሚጎድለው ይሄን ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አክሎ ገልጿል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

25 Oct, 08:23


ከታጣቂ ኃይሎች ጋር በውጭ ሀገራት ለመገናኘት ሀሳብ ማቅረቡን አገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ

የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እንዳሉት የታጠቁ ኃይሎች እና ራሳቸውን ከምክክሩ ያገለሉ ፓርቲዎችን እንዲሳተፉ ለማድረግ ጥረቶች እየተደረጉ ነው።

"የታጠቁ ሀይሎችን እስካሁን ገጽ ለገጽ ወይም በቀጥታ አግኝተን አነጋግረናቸው አናውቅም ያሉት ኮሚሽነሩ የፖለቲካ ጥያቄ አቅርበው በምክክሩ እንዲሳተፉ በተለያየ መንገድ ጥሪ አድርገናል፤ ለድህንታቸው ሙሉ ዋስትና እንደምንሰጥ ከዛም አልፎ በውጭ ሀገራት ተገናኝተን ሀሳባቸውን እንዲያቀርቡ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ፈቃደኛ መሆናችንን ገልጸናል ሲሉ ከዚህ በፊት የተደረገውን ጥረት አንስተዋል።

ከግጭት እና ጦርነት ያተረፍነው እንግልትና ስቃይ ነው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን እኛ የማደራደር ሀላፊነት ባይኖረንም ግጭቶች የሚፈቱበትን መንገድ የመቀየስ ስራ ግን እንሰራለን ብለዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

25 Oct, 08:23


ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ማሌዢያ ኳላላምፑር ገቡ

በብሪክስ ጉባኤ የነበራቸውን ቆይታ ያጠናቀቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ማሌዢያ ኳላላምፑር ገብተዋል።

የሚኒስትሮች ልዑካን ቡድንም አብሮ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመልክቷል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

24 Oct, 18:30


የብሪክሰ‍ ስብሰባዎች ስኬቶች:-

በሩሲያ ካዛን የተካሄደው የብሪክስ ስብሰባ ለአዳዲስ አባላት መስፈርቶችን ከማዘጋጀት አንስቶ የሕብረቱን አዲስ ልማት ባንክ ሥራ ለማስፋት ስምምነቶች፣ የዓለም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የብሪክስ የእህል ልውውጥን ማቋቋም እና ሌሎችም በርካታ ጠቃሚ ክንዋኔዎችን አስመዝግቧል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

24 Oct, 18:30


የአትሌት መዲና ኢሳ የ5 ሺህ ሜትር ውጤት ክብረ-ወሰን ሆኖ ፀደቀ
*

የዓለም አትሌቲ
ክስ የኢትዮጵያዊቷን አትሌት መዲና ኢሳ ከ20 ዓመት በታች የ5 ሺህ ሜትር ውጤት አዲስ የዓለም ክብረ-ወሰን በማድረግ አፅድቋል።

በቤልጂየም ብራስልስ በተካሄደው ሩጫ አትሌት መዲና ኢሳ 14 ደቂቃ ከ21 ሴኮንድ ከ89 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት ውድድሩን ማጠናቀቋ ይታወቃል፡፡ 

በአትሌት ገንዘቤ ዲባባ ከ20 ዓመት በፊት የተመዘገበው 14 ደቂቃ 30 ሴኮንድ 88 ማይክሮ ሴኮንድ የውድድሩ ክብረ-ወሰን እንደነበር የሚታወስ ነው።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

24 Oct, 09:35


ዜጎችን ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የወጣውን አለማቀፍ ስምምነት ኢትዮጵያ እንድታጸድቅ ኢሰመኮ ጥሪ አቀረበ!

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአዲስ አበባ ከተማ፣ እንዲሁም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የሚፈፀሙ የአስገድዶ መሰወር ሁኔታን ሊያቋቁሙ በሚችሉና ያሉበት ሳይገለጽ በተራዘመ እስር ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሁኔታና በተመለከተ መግለጫ አዉጥቷል።

ጉዳዩን በሚመለከት ጥብቅ ክትትል አድርጌያለሁ ያለዉ ኮሚሽኑ ከሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ተወስደው ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ የቆዩ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ከ50 በላይ ሰዎችን የተመለከቱ አቤቱታዎችን መመርመሩን አስታውቋል፡፡ኢሰመኮ አያይዞም "ይህ ሪፖርት እስከወጣበት ቀን ድረስ 44 ሰዎች ከ1 ወር እስከ 9 ወር በተለያዩ መደበኛ ባልሆኑ ቦታዎች ከቆዩ በኋላ መለቀቃቸውን አረጋግጫለሁ" ብሏል።

ሆኖም ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ በተራዘመ እስር፣ መደበኛ ባልሆኑ ማቆያ ቦታዎች፣ ብሎም በአስገድዶ መሰወር ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ ሆኖ መቀጠሉን ገልጿል፡፡በዚህም አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች መደበኛ ባልሆኑ ማቆያ ቦታዎች ሰዎችን የማቆየትና የማሰር ተግባር እንዲቆም ሁሉም የሚመለከታቸው የሕግ እና የጸጥታ አካላት ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ ኢሰመኮ ጠይቋል፡፡

አሁንም ያሉበት ቦታ በማይታወቅ፣ ብሎም የአስገድዶ መሰወርን ሊያቋቁም በሚችል ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሰዎችን የመንግሥት የጸጥታ አካላት አፋጣኝ ምላሽ ሊሰጡ ይገባልም ብሏል።ይህን መሰሉ የመብት ጥሰት እንዲቆም በአለማቀፍ ደረጃ ሁሉንም ሰዎች ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የወጣው ስምምነት ድርጊቱን ለመከላከል በመንግሥት ሊወሰዱ የሚችሉ እርምጃዎችንም የሚያካትት በመሆኑ ስምምነቱን ኢትዮጵያ ልታፀድቅ ይገባል ብሏል፡፡

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

24 Oct, 09:35


ነዳጅ

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የነዳጅ ማደያዎች እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠንን ከትላንት ጀምሮ ይፋ ማድረግ ጀምሯል።

አሁን ላይ በከተማዋ 123 ማደያዎች ግልጋሎት እየሰጡ ነው ተብሏል።

ቢሮው ፤ " በየዕለቱ የነዋጅ ማደያዎችን እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠን ይፋ ማድረግ የተጀመረው በአገልግሎቱ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም የተገልጋች እንግልት ለመቀነስ ነው " ብሏል።

ነዳጅ ማደያዎች የት ቦታ እንደሚገኙ እና በእለቱ የተራገፈው ነዳጅ መጠን እንዲሁም የጥቆማ ስርዓቱ ከላይ ተያይዟል።


https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

24 Oct, 09:35


በኮንሶ ዞን ሰገን ከተማ በተፈጸመ ጥቃት የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ተገለጸ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኮንሶ ዞን ሰገን ዙርያ ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ሰገን ከተማ ትናንት ጥቅሞት 12 ቀን 2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ወደ አካባቢው በመጡ ታጣቂዎች ተፈጽሟል በተባለ ጥቃት የሁለት ሰላማዊ ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰዎች መቁሰላቸው ተገልጿል።

ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የአካባቢው ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለፁት፣ ጥቃቱ የተፈጸመው ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡40 ሲሆን ከጉማይዴ አካባቢ በመጡ ታጣቂዎች መሆኑን ተናግረዋል።

በጥቃቱ ህይወታቸውን ያጡት በሹፍርና የሚተዳደሩት እሸቱ ጀማል እና ማዳቻ ኡዴሳ የተባሉ የሠገን ከተማ ነዋሪ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ደግሞ በፍቃዱ ማስረሻ እና አቶ ሀብታሙ ገነነ የተሰኙ ሲሆኑ፣ አቶ ሀብታሙ ጭንቅላታቸው ላይ ጉዳት ሲደርስባቸው አቶ በፍቃዱ ደግሞ እግራቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብሏል።

ሌላኛው ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ግለሰብ በበኩላቸው በጥቃቱ የሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን ገልጸው በፍቃዱ ማስረሻ እና አቶ ሀብታሙ ገነነ የተባሉት ግለሰቦች በደቡብ ክልል ሶዶ ከተማ ህክምና እየተደረገላቸው እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

ድንበር ዘለል ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መጥተዋል ያሉት ነዋሪው በሰገን ዙሪያ የቀጠለው አለመረጋጋት እና የጸጥታ ችግር አርሶ አደሩ መሬቱን በአግባቡ እንዳያርስ እንቅፋት እንደሆነበት ጠቁመዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

24 Oct, 09:35


"የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ መስፈሩ ይህ ነው የሚባል ለውጥ አላመጣም፣ እንዲያውም የአልሸባብ እንቅስቃሴ እንዲጨምር አድርጓል” -ሶማሊያ

ባለፉት ግዜያት የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ መስፈሩ ይህ ነው የሚባል ለውጥ አላመጣም እንዲያውም የአልሸባብ እንቅስቃሴ እንዲጨምር አድርጓል ሲል የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።ሶማሊያ በቀጣይ ከአፍሪካ ሀገራት ተወጣጥቶ ተልዕኮ ተሰጥቶት በግዛቴ በሚሰፍረው ጦር ዙሪያ የትኞቹ ሀገራትን ማዋጣት አለባቸው የሚለውን የምመረጠው እራሴ ነኝ ስትል ገለጸች።

ሶማሊያ ይህንን የገለጸችው የአፍሪካ ህብረት በሚያሰማራው ጦር ዙሪያ ኢትዮጵያ ስለሚኖራት ሚና እና ስለሶማሊያ ሉዓላዊነት በሚያትተው የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ላይ ነው።

“ኢትዮጵያ ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በተናጠል የምትወስዳቸው እርምጃዎች የሀገራችንን ሉዓላዊነት የጣሰ ነው፣ ይህም በሀገሪቱ ላይ ያለንን እምነት የሸረሸረ ነው” ሲል የገለጸው መግለጫው ከሶማሊላንድ ጋር የደረሰችውን ስምምነት በአብነት አስቀምጧል፤ “በሰላም ማስከበር ሂደት ላይ ወሳኝ እና አስፈላጊ የሆነውን መተማመን እንዳይፈጠር አድርጓል” ሲል ኮንናል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1

Voa Amharic

24 Oct, 09:35


ዩናይትድ ኪንግደም እና ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ወቅታዊ ጉዳይና በሽብርተኝነትና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዙሪያ ተወያዩ!

የዩናይትድ ኪንግደም ሴክሬት ኢንተለጀንስ ሰርቪስ እና የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት፣ በደኅንነትና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ የሚያከናውናቸውን የትብብር ሥራዎች ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ መስማማታቸውን አገልግሎቱ አስታወቀ።የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች፤ በተቋማት ደረጃ በሚከናወኑ የሁለትዮሽ ጉዳዮች እንዲሁም በቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ በስፋት በአዲስ አበባ ተወያይተዋል ተብሏል።

በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት መረጃ መሰረት፤ በውይይቱ ወቅትም ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ  ጉዳዮች በተለይም ደግሞ የቀይ ባሕር ወቅታዊ ጉዳይ፣ የደኅንነትና ሽብርተኝነት፣ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችንና ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን በቅንጅት ለመከላከል በቀጣይ የሚደረጉ የመረጃ ልውውጥ ስራዎችን ዳሰዋል።

https://t.me/voa_amharic1
https://t.me/voa_amharic1