አትሮኖስ @atronosee Channel on Telegram

አትሮኖስ

@atronosee


╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳

አትሮኖስ (Amharic)

አትሮኖስ በታሪኮችና ፅሁፎች ላይ የተወሰነ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF በትክክል እንዲሁም ግጥሞችን በትክክል ያገኙበታል። የእርስዎ የታሪኮችን ደምበማል፣ አንዳንድ እርስዎን የተማርከበትን ለማንበብ ቫይረስ በመጠቀም እናስተንግናለን። ከዚህ በላይ፣ በዚህ በእርስዎ መረጃና እንዚያ ርዝመት ከማረጋገጥ ይውጡ። አትሮኖስ በ Telegram በ @atronosee ሞባይል አዳብ እናፈልጋለን። የታሪኮችን መፅሐፍትን ለመማርከት እና ለመጽሐፍ እባኮት በ @atronosebot ተጠቀሙ። እና ለማለፊያ ላይ ታሪኮችን እንደገለጹ ይሞክሩ። እንዚህ ላይ እንክብካቤ በሚጠቀሙበት አገልግሎት እና መረጃ ይጠቀሙ። አትሮኖስ ከእርስዎ መረጃ እና የሚጠቀሙ አማካኝ ተጠቃሚዎች ለተዘጋጀው በተጨማሪም የግጥሞች መረጃዎችን ለመገንባት እና በግጥሞች ላይ ለመኖር እናስተንግናለን። ግጥሞችን ይመልከቱ ፡፡

አትሮኖስ

11 Jan, 21:53


🔵 ቤቲንግ ለምትመድቡ ሁሉ ይህን ምርጥ ቻናል እናስተዋውቃቹ  🤑

🔥 ብዙ ዓመት ልምድ ባላቸው ቀማሪዎች የተከፈተ ብችኛ ታማኝ ቻናል ነው ከኛጋ በመሆን ከሳምንት እስከ ሳምንት አሸናፊ ለመሆን ቻናሉን JOIN ያድርጉ 👇

አትሮኖስ

11 Jan, 21:45


ከነዚህ ዉስጥ የማን ደጋፊ ኖት?

አትሮኖስ

11 Jan, 21:29


🌹♥️🌹የሴት ጓደኛ ለመያዝ አስበህ ታውቃለህ ምን ልበላት ብለህ ቃላትስ አተህ ታውቃለህ🌹🌹 እንግዲያውስ የፍቅር ቃላት ፍለጋ አበቃ በቀላሉ ማግኘት ትችላለህ🥰🌹👇🌹👇🌹

አትሮኖስ

11 Jan, 15:00


የታመመ ሰው ልናመጣ ነው የምንሄደው ሲለው ሆዱ እንደመራራት አለ ሹፌሩ፡፡

እሽ አሁን "ፍጠኑና ውጡ አላቸው፡፡

እረፍዶባቸውም ቢሆን አዳማ ደረሱ፡፡ ከመኪናው ወርደው እየተቻኮሉ ወደ አቶ ላንቻ ቡቲክ አመሩ፡፡ ቡቲኩ አልተከፈተም፡፡ ያሬድ በተዘጋው ቡቲክ ላይ ሁለት አይኖቹን ተክሎ ሳይነቅል ቆየ፡፡ መብረቅ እንደመታው እንጨት ክው ብሎ ቀረ፡፡

ተመስገን አልመጡ ይሆን ወይስ መጥተው ተመልሰው ሄደው ይሆን? አለ፡፡

"እስካሁን መቼ ይቆያሉ፡፡ ስንቀርባቸው ጠብቀውን ሄደው ይሆናል አለ፡፡ ራሱን እየነቀነቀ፡፡

"ለማንኛውም ደንበኛቸውን እንጠይቀው ተባብለው ወደ ቢያድግልኝ የጅምላ ማከፋፈያ ሱቅ ተጠጉ፡፡

ከቢያድግልኝ ጋር የእግዚአብሔር ሰላምታ ተለዋውጠው "አቶ ላንቻ ዛሬ አልመጡም እንዴ"? አለ
"እስከ አሁን አልመጡም፡፡ እቃ አምጡልኝ ብየ እየጠበኳቸው ነበር፡፡ ምን ነክቷቸው እንደሆነ ዛሬ አርፍደዋል፡፡ እንደው ደህና ባይሆኑ ነው እንጅ ፤ ደህና ቢሆኑ እስካሁን አይቆዩም ነበር አለ ቢያድግልኝ፡፡

ያሬድ ግራ ተጋባ፡፡ የሚሆነው ጠፋበት፡፡ "እና አሁን ምን ይሻለኛል"?

"ምን ታደርጋለህ ፤ትንሽ ጠብቃቸው፡፡ ካልመጡ ወደ ድሬ መሄድ ነው፡፡ ወይም ወደ ቤትህ ተመልሰህ በሌላ ጊዜ መምጣት ነው የሚሻለው፡፡ ለማንኛውም የአንተ አማራጭ ነው አለ ቢያድግልኝ፡፡

"እሱማ ልክ ነህ፡፡ አሁን ወደ ቤት ብመለስ መቼ እንደሚመጡ አውቃለሁ፡፡ ትንሽ ጠብቀን ፤ ካልመጡ አድረን ነገ ሄደን ምን ሆነው እንደቀሩ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ ብሎ ከቢያድግልኝ ጋር ተሰነባብተው ወደ አንድ ካፌ ጎራ አሉ፡፡

በጥዋት የለከፋቸውን ጋኔል ፤ ረፋድም ሳይፋታቸው ፤ አቶ ላንቻ ሳይመጡ ቀሩ፡፡ ተመስገንና ያሬድ አዳማ አድረው በጥዋት የሚወጣውን የድሬ መኪና
ተሳፍረው ጉዟቸውን ወደ ድሬ መጓዝ የግድ ሆነባቸው፡፡

ተመስገን ገና ከቤት ተነስተው ሲወጡ የገጠማቸውን አንድ ጥቁር ሰው እንደማይቀናቸው ሆዱ ጠርጥሮ ነበር፡፡

ታዲያ ሁለት ቀን ሙሉ እንቅልፍ አጥቶ ማደሩም ፤ ጭንቀቱን አባብሶታል፡፡ ወደ ድሬ ለመሄድም ደስተኛ አልነበረም፡፡ አይናገር ፣ አይጋገር እንደማር ቆራጭ ፎጣውን ተከናንቦ በዝምታ ተውጧል፡፡

"ምን ሆነህ ነው ዝም ያልከው? አለ ያሬድ፡፡

ተመስገን ውስጡ ተረብሿል ፡፡ ለመናገር አልፈለገም፡፡ "አይ! ምንም አልሆንኩም ብርድ ብርድ ስላለኝ ነው፡፡

"አየሩ ሲቀያየርብህ ይሆናል ፤ ብርድ ብርድ ያለህ፡፡ ለማንኛውም አሁን እየደረስን ነው ብሎ...ድንገት የተሳፈሩበት መኪና ከመኪና ተጋጨ፡፡

በአደጋው ስድስት ተሳፋሪዎች ላይ ቀላል የመቁሰል አደጋ ደረሰባቸው፡፡ የተቀሩት ተሳፋሪዎች ያሬድንና
ተመስገንን ጨምሮ ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው ተረፉ፡፡

ራሱን የመሳት ያህል ደነገጠ፡፡ እውነት ነው እንዴ? ገና ከትላንትና ጥዋት የለከፈን አክላፋ ምን አይነት ነው አለ ያሬድ፡፡

"እንኳን ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ" እንደሚባለው ተመስገን ድሮም ወደ ድሬ እየፈራ መጓዙ አልቀረም ነበር፡፡ ታዲያ የፈራው አልቀረም፡፡

በፍራት ላይ ፍራት ሆኖበት ዝናብ ደብድቦት እንደሚንቀጠቀጥ ሰው ተንዘፈዘፈ፡፡ አይኖቹ እርግብ እርግብ አሉ፡፡

ያሬድ ተጨነቀ ፡፡ ምነው ይዠው ባልመጣሁ ኖሮ ፤ አሁን እግዚአብሔር አትርፎናል፡፡ ከዚህ የባሰ ባልመጣ ብቻ ፤ አንዴ እቤት መልሸው እስከምገባ አለ፡፡ እየለመነና ለምን ይዞት እንደመጣ እራሱን እየወቀሰ፡፡ ሌላ መኪና መጥቶ ወሰዳቸው፡፡

ድሬ አምሽተው ሶስት ሰዓት አካባቢ ደረሱ፡፡ ወደ አቶ ላንቻ ቤት ለመሄድ ቀኑ መሽቷል፡፡ ለአልባሳት መግዣ የያዙትን ገንዘብ ሌባ እንዳይዘርፋቸው ለመንቀሳቀስ አልፈለጉም፡፡ አልጋ ለመያዝ አሰቡ፡፡ ከመነሃሪያ ላለመራቅ ፊት ለፊት ወደ ሚገኝ አንድ ሆቴል አምርተው አልጋ ጠየቁ፡፡ ከቤታቸው ሲነሱ የገጠማቸውን ሰው የሚመስል ከሆቴሉ ወጥቶ አልጋ አልቋል አላቸው፡፡

ያሬድ "ወይ! የዛሬና የትላንት ቀን የምን ምቀኛ ነው፡፡ ከወጣን አንስቶ አንዴም ሳይቀናን እያለ አልፎ የሚቀጥለውን አልጋ ቤት ጠየቀ፡፡ ተመሳሳይ መልስ ሰጧቸው፡፡ ለነገሩ መነሃሪያ አካባቢ ስለሆነ በጊዜ ስለሚያዝ እዚህ አናገኝም፡፡ ወደ ታች ዝቅ እንበልና እንጠይቅ ብለው ትንሽ ዝቅ አሉ፡፡

አንድ ከአካባቢው ለየት የሚል ሆቴል አገኙ፡፡ አንድ አጠር ያለች የወንድ ሱሪ የለበሰች ወጣት ሴት ከሆቴሉ ወጥታ አለ አለች፡፡

"እስኪ አሳይን ብሏት ተከታትለው ገቡ፡፡

አንድ ነው ሁለት የምትፈልጉት አለች አከራይዋ፡፡

ኧረ ! አንድ ይበቃናል አለ ያሬድ፡፡

"እሽ የቀረውም ሁለት አልጋ ስለሆነ ከሁለት አንዱ ምረጡና ያዙ አለች፡፡ የሚሻለውን አልጋ መረጡ፡፡

"ምግብ ነገር ይኖራል እንዴ ? አላት ያሬድ፡፡

"አዎ፤ አለ" አለች፡፡

"እሽ እንመጣለን፡፡ ብሏት የአልጋ ሒሳብ አስር ብር ሰጥቷት ሄደች፡፡

ተመስገን በድንጋጤ የተነሳ ሰውነቱ የሚንቀጠቀጥበት አለቀቀውም፡፡ ምነው አምላኬ አሁን ደግሞ መሽቷል፡፡ ምን ልታሳየኝ ይሆን? ከሞት አፋፍ ላይ የመለስከኝ አይበቃም እንዴ ? እያለ ፈጣሪውን በውስጡ ይማፀናል፡፡

"ምነው ድንጋጤው አልለቀቀህም እንዴ? አለው ያሬድ::

"ኧረ ! አለቀቀኝም፡፡ የባሰ ከቅድሙ አሁን የባሰብኝ መሰለኝ፡፡

"በቃ! እንግዴህ አትጨነቅ እግዚአብሔር እንኳን ከሞት አፋፍ መለሰን እንጅ፡፡ አሁን እንግዴህ ይህንን ቀፎ ቆራጭ ያስመሰለህን ፎጣ አውርደውና ከተሜም ባንመስል ነቃ ያልን ባላገር እንምሰልና ወደ ሆቴሉ እንግባ ፡፡ እራታችንን በልተን አንዳንድ ቢራ ስንለቅበት ጭንቀቱና ድብርቱ ለቆን ይጠፋል፡፡......

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose



ZOO አዲሱ  ፕሮጀክት... 20 ቀን ብቻ ቀርቶታል ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

አትሮኖስ

11 Jan, 15:00


#የጣት_ቁስል


#ክፍል_ስምንት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ


እጅግ በጣም ይቅርታ ስልኬ ስለጠፋ እረጅም ጊዜ ታሪኩን ሳለቅ ቀረሁ ወደኋላ መለስ ብለቹ ታሪኩን በማስታወስ ቀጥሉ እንደእግዚአብሔር ፍቃድ ከነገ ጀምሮ ሁለት ክፍል እለቃለሁ እንዲሁም ነገ ማታ ሁለት ሰአት ላይ ሌላ አዲስ ታሪክ እንጀምራለን የተከፋችሁብኝ አሁንም በድጋሚ ይቅርታ እጠይቃለሁ🙏

ያሬድ

ከገበያ መጥቶ ደክሞታል፡፡ ገና ሳይመሽ ከመኝታው ላይ ጋደም እንደማለት ብሏል፡፡

"ተመስገንን አብረን እንሄዳለን ብለኸው ነበር እንዴ"? አለች ፤ ባለቤቱ አበበች፡፡

"አዎ ፤ ብዬው ነበር፡፡ ገንዘብ እንዳዘጋጀ ነገረሽ እንዴ"?

"ትላንት አንተን ፈልጎ መጥቶ ነበር፡፡ ሳያገኝህ ሲቀር ለእኔ አጫውቶኛል፡፡ እንሂድ እስከምትለው ነው የሚጠብቀው" ፡፡

"ታዲያ ምን ችግር አለ፡፡ የመነገድ ፍላጎት ካለው አሁን ደግሞ ውሎ ገባ ስለሆነ የምንመጣው ቀን እንኳን ቢመሽም ሁለት መሆኑ አይከፋም፡፡ ከነገ ወዲያ ይዠው እሄዳለሁ"፡፡

ገና በደንብ አልነጋም፡፡ ያሬድም ከመኝታው አልተነሳም፡፡ አበበች አለ ፡፡ ሳይደጋግም በአንዴ የሚሰማ መስሎት፡፡ ነገር ግን የሚሰማው አላገኘም፡፡ አቤት የሚለው አጣ፡፡ ደግሞ ተጣራ፡፡ ያሬድ…..ያሬድ አለ፡፡ አቤት አለች አበበች፡፡ ብቅበይ አለ፡፡ በጥዋት ወደ ያሬድ ጋር የመጣው ተመስገን፡፡

ማነው በጥዋት ብቅበይ የሚለው ብላ ብቅ አለች፡፡

"ደህና አደርሽ አበበች ? አለ" ተመስገን፡፡

"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አደርህ ተመስገን፡፡ አትገባም እንዴ ከብርድ ላይ ፡፡

"ይሁን አልገባም፡፡ ያሬድ የለም እንዴ ? ፡፡

"አለ ፤ ከመኝታውም አልተነሳም፡፡ ምነው ደህና አይደለህም እንዴ ?

"ኧረ ደህናነኝ፡፡ ለዛ ላጫወትኩሽ ጉዳይ ነበር የመጣሁት ፡፡

"አይ! እሱንማ ከሆነ እኔም ማታ አጫውቸዋለሁ፡፡ ለመነገድ ፍላጎት ካለው ይዠው እሄዳለሁ ብሏል፡፡ ለማንኛውም ግባና አነጋግረው ፡፡

ተመስገን የመጣበትን ጉዳይ እንደተሳካለት አሰበ፡፡ ያሬድን ለማነጋገር ወደ ቤት ገባ፡፡

"ደህና አደርህ ያሬድ? ፣ ደሞ ዛሬ በጥዋት አልተነሳህም፡፡ እንቅልፍ ነው ወይስ ድካም ነው?፡፡ ያስተኛህ ፡፡

"ሰላም አደርህ ተመስገን፡፡ ምን የትናንት ገበያ ውልቅልቅ አድርጎኛል፡፡ አሁን በደንብ ነግቷል ማለት ነው እንዴ? አለ፡፡ ከተኛበት መኝታ ተነስቶ እየተንጠራራ፡፡

"ስድስት ሰዓት ሆኖ ነግቷል ትላለህ እንዴ ፤ ለነገሩ ከተማ ለከተማ ስትመላለስ የከተማ ሰው ሆነሃል፡፡ እነኝህ ከተመኞች ሰዓት አስረው ቢይዙም ፤ የሚቆጥሩ መሆናቸውን እንጃ ፤ በየሰዓቱ ነው የሚበሉ

አለ፡፡ ተመስገን እንደማሾፍ ብሎ፡፡

"አይ! ተመስገን እነሱማ በሰዓት የማይበሉበት ጊዜ ስለሌላቸው ነው፡፡ ያለመቁጠር አይደለም፡፡ እንዲያውም እኛ ነን አንዴ ቁርስሠ ፣ አንዴ ምሳ ሰዓት ፣ ደረሰ እያልን ሰዓት የሚቃወመን ይመስል በቀን ሶስቴ ሳይበቃን አራተኛ መክሰስ እያልን የምንመገበው፡

"አይ! መልካም ነው" ብሎ "ለባለፈው ጉዳይ ነበር የመጣሁት" አለ ተመስገን ፡፡

"አበበች ማታ በጨዋታ አንስተን ነግራኛለች፡፡ እና ለመነገድ ፈልገሃል ማለት ነው?፡፡

"የመነገድ ፍላጎት እንኳን ብዙም የለኝም፡፡ እንዴው የዛችን የእህቴ ነገር አንጄቴ አልቆርጥ ብሎኝ ነው፡፡ መቼም እቤት ከመቀመጥ አካባቢንና አገርን ማወቅ አይከፋም፡፡ የእግዚአብሔር ስራም አይታወቅም፡፡ በዛውም እናገኛት ይሆናል"፡፡

"ጥሩ ነው ለማንኛውም ሃሳብህ አይከፋም፡፡ ነገ አብረን ማለድ ብለህ በጥዋት ና፡፡ ውሎ ገባ ስለምንመለስ እንዳይረፍድብን"፡፡

"እሽ በጥዋት እመጣለሁ፡፡ ብሎት ተሰነባብተው ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡

"በነጋታው በጥዋት ቡና ፈልቶ ተመስገን እየተጠበቀ ነው፡፡ ግን ቶሎ ሊመጣ አልቻለም፡፡ በቃ ቀርቶ ነው ብላ አበበች ቁርስ ልታቀርብ ስትል ተመስገን መጣ፡፡ ሰላምታ ተለዋውጠው ተቀመጠ፡፡

"ምነው አረፈድህ" አለው ያሬድ
"ምን ሌሊቱን እንቅልፍ ሳይወሰደኝ አድሮ ሊነጋጋ አካባቢ ሸለብ አላደረገኝ መሰለህ ፡፡

"አይ! አንተ ሌሊቱን ሙሉ በሃሳብ ስትሄድ አድረህ ነዋ፡፡ ጥዋት በመነሻህ ሰዓት እንቅልፍ የጣለህ፡፡ በል አሁን የቡና ቁርሱን ያዝና ቡናውን ጠጥተን ቶሎ እንውጣ፡፡ የባልጪ መኪና ሳያመልጠን እንድረስበት፡፡ አንዴ ካመለጠን መመለስ ካልሆነ ሌላ መኪና አናገኝም፡፡

ባለቤቱን በይ እንግዴህ ከብት ሳይበዛ ከብቶቹን ውሃ አጠጫቸው ብሏት ተነስተው ከተመስገን ጋር ጉዞዋቸውን ወደ አዳማ ቀጠሉ፡፡

መኪና እንዳያመልጣቸው እየተጣደፉ ነው፡፡ ከመንገድ ላይ አንድ ጥቁር ሰው ከፊት ለፊታቸው ገጠማቸው፡፡

"ዛሬ ላይቀናን ነው መሰለኝ አለ ተመስገን፡፡ ውስጡ እንደመረበሽ እያለበት፡፡

"ምነው ምን አየህ አለው? ያሬድ፡፡

"ተመስገን የፍጥነት እርምጃውን ገታ አድርጎ ፤ መንገድ ስትሄድ አንድ ሰው ከገጠመህ የምትሄድበት አይቀናህም፡፡ አባቴ ሲናገር ሰምቻለሁ፡፡ አሁንም እኛ አንድ ሰው ሰለገጠመን ብዬ ነው፡፡

ባያምንበትም ግን ሆዱ እንደመፍራት ብሏል፡፡ "ተው! እባክ ይህ የአንዳንድ ሰው አባባል ነው፡፡ አንተ ደግሞ ያባትህን አትከተል እግዚአብሔር እንደፈቀደ ያድርገን እንግዴህ አለ፡፡ በፍራቻ ንግግርም ቢሆን፡፡

"እሱማ እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው፡፡ እንዴው የሚባለውንና ነው እንጅ ያልኩህ፡፡

ያሬድ ነገሩን ተወት አድርጎ ፤ አሁን ቶሎ ቶሎ ራመድ ራመድ በል፡፡ ያ አቶ ላንቻ ብቻ ሳይቀድመን እንድንደርስበት፡፡

"የማነው አቶ ላንቻ? አለ ተመስገን፡፡

"ለእኔ ከድሬ አዳማ ድረስ አልባሳ የሚያመጡልኝ ናቸው፡፡ መቼም ብታያቸው የተባረኩ እና ደግ ሰው ናቸው፡፡

አሁንም ከሳቸው ተረክበን ነው፡፡ የምንመለሰው ከቀናን"፡፡

"እኔ እኮ ውሎ ገባ ስትመጣ በአየር መምጣት ጀመረ እንዴ ብየ ነበር፡፡ ለካስ አንተ አዳማ ድረስ የሚያመጣልህ ደንበኛ አግኝተህ ኖሯል፡፡እየከነፍህ የምትመጣው"፡፡

"መኪናው ሞልቶ አንድ ሰው ብቻ ቀርቶት ይጠባበቃል፡፡ እየተጣደፉ ደረሱ፡፡ ግን እረዳቱ ከአንድ ሰው ውጭ አልጭንም አላቸው፡፡ ጫነን አልጭንም ፤ ሲከራከሩ አንድ ረፍዶበት የነበር ሰው ረዳቱንም ሳይጠይቅ አልፎ መኪናው ውስጥ ገባ፡፡ ያሬድ ቢለምንም ፣ ቢማፀንም ሳያሳፍራቸው ጥሏቸው ሄደ፡፡

አላልኩህም፡፡ አንድ ሰው ጥሩ አይደለም ብየህ ነበር አለው ተመስገን፡፡

ጸያሬድ ተመስገን ያለውን የሰማው አይመስልም፡፡ ልቡ ያለው አቶ ላንቻ ጋር ነው፡፡ አንድ የጭነት መኪና ወደ አዳማ ልትወጣ ከመንገድ ላይ ቆማለች፡፡

"ይችን መኪና እንጠይቃት እስቲ ፤ ትጭነን እንደ ሆነ አለ ተመስገን፡፡

"እህል ጭና እያየሃት እንዴት እሽ ብለው ይጭኑናል፡፡ ያጠፋነው እኛ ነን፡፡ በጥዋት መምጣት ሲገባን አርፍደን፡፡ አሁን ያለን አማራጭ ወደ ቤት መመለስ ነው፡፡ ነገ ተመልሰን እንመጣለን፡፡ እንደው
የሚያነድደኝ እምነት ማጉደሌ ነው፡፡ መቼም መኪና አጥቶ ቀረ አይሉኝም፡፡ ሆነ ብሎ ነው እንጅ የሚሉኝ፡፡ እህል ወደ ጫነችው አይሱዚ ተጠጉ፡፡

ፈራ ተባ እያለ ማነህ ወንድም ወደ አዳማ እንደሆነ የምትሄደው መኪና ጥሎን ስለሄደ ነው፡፡ እባክህ ተባበረን ብሎ ሹፌሩን ጠየቀው ያሬድ፡፡

የመኪናው ሹፌር አላመነታም፡፡ "ስንት ናችሁ"? አለ፡፡

"ሁለት ነን አለ፤ ያሬድ፡፡

"ሁለት ሰው ከሆነ አልጭንም"፡፡ አንድ ሰው ከሆነ ጋቢና ግባ አለ፡፡ ባጭር ቃል ሹፌሩ፡፡

"እባክህን ወንድም ተባበረን ስለማንነጣጠል ነው፡፡ የምንሔደውም የታመመ ሰው ለማምጣት ነው፡፡

እንደምንም ተቸገርልን፡፡ ከላይም ቢሆን ተጭነን እንሄዳለን እያለ ሹፌሩን ተማፀነው፡፡

አትሮኖስ

09 Jan, 19:51


5+5×5-5 = ?

አትሮኖስ

09 Jan, 19:40


🙏🙏ወላሂ ለአዚም አላህ ሻሂዴ ነው  ይሄን ቻናል ተቀላቅዬ ከድህነት ወጥቻለው እናንተም ተጠቀሙበት betting ምትጫወቱ  الوالد لأخيم الله شهيد ، انضممت إلى هذه القناة وخرجت من الفقر واستخدمته
https://t.me/+wiQ0pgVU6vI1YWI0
https://t.me/+wiQ0pgVU6vI1YWI0
https://t.me/+wiQ0pgVU6vI1YWI0

አትሮኖስ

09 Jan, 19:27


◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇

አትሮኖስ

04 Jan, 21:36


🔴 ሰበር ዜና ዛሬ ትምህርት ሚኒሰትር ያወጣው አዲስ ያልተጠበቀ መግለጫ   ‼️

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ ከስር open ሚለውን ይጫኑ 👇👇

አትሮኖስ

04 Jan, 21:29


🙏🙏ወላሂ ለአዚም አላህ ሻሂዴ ነው  ይሄን ቻናል ተቀላቅዬ ከድህነት ወጥቻለው እናንተም ተጠቀሙበት betting ምትጫወቱ  الوالد لأخيم الله شهيد ، انضممت إلى هذه القناة وخرجت من الفقر واستخدمته
https://t.me/+Ko1toim86Y43NGE8
https://t.me/+Ko1toim86Y43NGE8
https://t.me/+Ko1toim86Y43NGE8

አትሮኖስ

04 Jan, 21:18


🌹♥️🌹የሴት ጓደኛ ለመያዝ አስበህ ታውቃለህ ምን ልበላት ብለህ ቃላትስ አተህ ታውቃለህ🌹🌹 እንግዲያውስ የፍቅር ቃላት ፍለጋ አበቃ በቀላሉ ማግኘት ትችላለህ🥰🌹👇🌹👇🌹

አትሮኖስ

02 Jan, 22:03


Free ተለቋል።
ቤቲንግ ለጠመመባቹ ብቻ።

ከኛ ጋር የማይቻል ይቻላል
ድንቅ አዲስ ቻናል፣ ምን ትጠብቃላቹ፣ ተቀላቀሉ እና የድሉ ተካፋይ ሁኑ

አትሮኖስ

02 Jan, 21:34


ከ17 ደቂቃ በኃላ ይጠፋል


የ200 ብር ካርድ የሚያሸንፍ  ጥያቄ !!

በኢትዮጽያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ ረሀብ መቼ አመተ ምህረት ነዉ

አትሮኖስ

30 Dec, 17:28


አትሮኖስ pinned «#የጣት_ቁስል ፡ ፡ #ክፍል_ሰባት ፡ ፡ #ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ እድላዊት "የባሰ አለና አገርህን አትልቅ" እንደሚባለው እድላዊት ከወ/ ሮ በሰልፏ ሞት ጋር የተቃጠረች ይመስላል፡፡ ሳይሞቱ ቀድሜ ልውጣ ማለቷ በአካል ባትነሳም በመንፈስ ተነስታ ጉዞዋን ማሰቧ ፤ አፈር ሳታለብሽኝ ፤ ጥለሽኝ ልትሄጅ ነው? ያሏት፡፡ ወ/ሮ በሰልፏ ፤ ከህሊና የማይወጣ ጥያቄ አሳደረባት፡፡ እድላዊት ግን አፈር ሳታለብሳቸው…»

አትሮኖስ

30 Dec, 17:00


የትውልድ ቀየዋን የረሳች ይመስላል፡፡ ለስምንት ዓመት የቆየችበትን የነ አቶ አርምዴን አካባቢ መናገሯ፡፡
ታዲያ እድላዊት የተጠየቀችውንም ፣ ያልተጠየቀችውንም ተናግራ እናትና አባቷ ይሙቱ ይኑሩ ሳታውቅ በውሸት ገድላ ለወ/ሮ ዘነቡ ስትናገር ቅር እንኳን ያላት አትመስልም ነበር፡፡

ወ/ሮ ዘነቡ በሰሙት ነገር በጣም አዘኑ፡፡ አይዞሽ አሉ፡፡ አቅፈዋት የአይኖቿን እንባ በእጃቸው መዳፍ ጠራረጉላት፡፡

ወ/ሮ ዘነቡ በድሬደዋ ከተማ ተወልደው ያደጉ ናቸው፡፡ ኑሮአቸው በንግድ ስራ ላይ የተመሰረተ ሆኖ በድሬ ከተማ ውስጥ የናሆም ሆቴል ባለቤት ናቸው፡፡

ሰራተኛ እየፈለጉ ባሉበት ሰዓት በአጋጣሚ በተሳፈሩበት መኪና ላይ ማረፊያዋንና መድረሻዋን የማታውቅ የገጠር መልከ መልካም የጠይም ቆንጆ የሆነች ልጅ በማግኘታቸው ወደር የሌለው ደስታ ፈጥሮላቸዋል፡፡ እድላዊትን የሰጣቸውን አምላክ እያመሰገኑ ወደ ቤታቸው ይዘዋት ገቡ፡፡ የሆቴላቸው አልጋ ልብስ አጣቢ አድርገውም ቀጠሯት፡፡

እድላዊት ስራ በማግኘቷ ተደስታለች፡፡ መድረሻየንና መጠጊያዬን ፈልግልኝ ብላ እያለቀሰች እንደተማፀነችው ፈጣሪዋም ልመናዋን ሳያሳፍራት ሰቷታል፡፡

የተሰጣትን ስራ በትጋት እያከናወነች ሰነባበተች፡፡ በሳምንታት ውስጥ በእናት አባቷ ቤት እያለች የነበረው መልክና ወዘናዋ ተመለሰ፡፡ እያማረባት ከገጠር ልጅ ወደ ከተማ ልጅ ተቀየረች፡፡

ቤተሰቦቿን ሁሉ እረስታ የተደላደለ ሂወት መኖር ባትችልም ከነበራት የተጎሰቋቆለ ህይወት ተላቃ መኖር ጀምራለች፡፡

ወ/ሮ ዘነቡ በእድላዊት እሩህሩህነት ፣ ታማኝነትና ታዛዥነት እንዲሁም ፤ በስራዋ ላይ ባላት ቅልጥፍና ኮሩባት፡፡ ከልጆቻቸው በላይ አስበልጠው ያምኗት ጀመር፡፡ ቤታቸውንም አደራ ሰተዋት ወደ ፈለጉበት ቦታ ደርሰው ይመለሳሉ፡፡

ታዲያ ሲያገኟት በመከራና በስቃይ ተጎሰቋቁላ የተማረች አይደለም ትምህርት ቤት ያየችም አልመሰለቻቸውም ነበር፡፡

አንድ ቀን በጨዋታ የተነሳ "ለምን ትምህርት አላስተምርሽም አሉዋት?፡፡

"አይ! እትዬ የትምህርት ጉዳይማ አልጨረስኩም እንጅ እስከ ሰባተኛ ተምሬ ነበር አለች፡፡

ወ/ሮ ዘነቡ ተገርመው እና "እስካሁን ለምን ዝም አልሽኝ ? ካሻሪ አጥቼ የምከራተተው አንችን ከቤት አስቀምጨ ነው ?

በይ....


ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...32 ቀን ብቻ ነው የቀረው አዋጭ ነው ጀምሩት

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

አትሮኖስ

30 Dec, 17:00


#የጣት_ቁስል


#ክፍል_ሰባት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

እድላዊት

"የባሰ አለና አገርህን አትልቅ" እንደሚባለው እድላዊት ከወ/ ሮ በሰልፏ ሞት ጋር የተቃጠረች ይመስላል፡፡

ሳይሞቱ ቀድሜ ልውጣ ማለቷ በአካል ባትነሳም በመንፈስ ተነስታ ጉዞዋን ማሰቧ ፤ አፈር ሳታለብሽኝ ፤ ጥለሽኝ ልትሄጅ ነው? ያሏት፡፡ ወ/ሮ በሰልፏ ፤ ከህሊና የማይወጣ ጥያቄ አሳደረባት፡፡

እድላዊት ግን አፈር ሳታለብሳቸው አልሄደችም ነበር፡፡ አንዴ ያደላትን የስቃይና የመከራ ፅዋ ተቀብላ የወ/ሮ በሰልፏን ተስካር አወጣች፡፡ ሁሉን ነገር ምላድ ምላድ አሰያዘች፡፡ ልብሶቿን አጣጥባ ተነሳች፡፡

"አሁን ባዶሽን አትሄጅም"፡፡ ስንቅ አሰናድተሽ ነገ እሸኝሻለሁ ብሎ አስቀራት፡፡ እሸ ብላ ቀረች፡፡

ስንቅ ለማሰናዳት አልፈለገችም፡፡ ግን ደግሞ ፀበል አለመሔዷን እንዲነቃባት አትፈልግም፡፡ ትንሽ ዳቦ ቆሎ መሳይ አዘጋጀች፡፡ በነጋታው ጠዋት ከአቶ አርምዴ ጋር ተነሳች፡፡

አንዳንዴ እየተነጋገሩ ፤ አንዳንዴ የመለያየታቸው ነገር እያሳሰባቸው ፤ ለየብቻቸው ፣ በየራሳቸው ሃሳብ እየነጎዱ ሳይታወቃቸው ሸንኮራ ዮሐንስ ደረሱ፡፡

የሸንኮራ ዮሃንስ ፀበል ከመዲናችን አዲስ አበባ በ144 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ሚያዝያ 15/1654 ዓ/ም ገደማ ፀበሉ ለአባ ካሳ እንደተገለፀላቸው ይነገራል፡፡

ይህ ፀበል አይነ ስውር የሚያበራ ፤ ለምፅን የሚያነፃ ፤ ኤች አይቪን የሚፈውስ ፤ የአጥንት ካንሰርን ነቅሎ የሚጥል ፤ በአጠቃላይ ሰው ሰራሽ ይሁን ተፈጥሯዊ በሽታዎችን የሚፈውስ ለመሆኑ ብዙዎች ድነዋል፡፡ ተፈውሰዋል ፣ ምስክርነታቸውንም ተናግረዋል ፡፡

"የት አካባቢ ይሻልሻል"? አላት፡፡ ቤት ሊያሲዛት ፈልጎ ፤ አቶ አርምዴ፡፡

እድላዊት ሸንኮራን አልፋ ለመሄድ እንጅ ቤት ለመያዝ አልፈለገችም፡፡

"አሁን ቤት አልይዝም ወደ ፀበሉ ልሂድና ስመለስ እይዛለሁ፡፡አይታወቅም ወይም የማቀው ሰው ላገኝ እችላለሁ፡፡ ለእኔ ምንም አታስብ ፤ በቃ አንተም ተመለስ፡፡ ስራህን ትተህ ነው የመጣኸው፡፡ ላደርክልኝ ውለታና እገዛ እግዚአብሔር ሁሉንም እሱ ይክፈልልኝ አመሰግናለሁ" አለች፡፡ የሃዘን ስሜት በውስጧ እየተሰማት፡፡

አይ! እድል እኔ ምን አላደረግሁልሽም፡፡ ትንሽ ስንዴ ነገር ሸጥ እንኳን አድርጌ ፤ እንዳላዘጋጅልሽ ለመሄድ ቸኮልሽ፡፡

ለስምንት ዓመት አብራው የኖረችው የሟች እህቶቹ ምትክ እድላዊት ልትለየው በመወሰኗ ፤ የወንድ አንጀቱ እንደወላድ ተላወሰ፡፡ በአይኖቹ እንባው ግጥም አለበት፡፡

እድላዊት ከሞት አፋፍ ላይ ያተረፋትን አርምዴን መለየት አቃታት፡፡ ሆድ ባሳት፤ አለቀሰች፡፡ አርምዴ ያወራውን የሰማች አትመስልም፡፡

በፊቱ ላይ የወረደውን እንባ ጠራረገ፡፡ እድል ይበቃል አስካሁን ስታለቅሽ የኖርሽው፡፡ በትንሹም ፣ በትልቁም ማልቀስ ጥሩ አይደለም፡፡ የባሰ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ለማፅናናት ሞከረ፡፡

እዚህ ከቆየሽ ተመልሸ አይሻለሁ፡፡ ሰባት መቶ ብር ለአንድ ነገር ይሆንሻል ብሎ ሰጣት፡፡ እግዚአብሔር ከአንች ጋር ይሁን፡፡ ብሏት ተሰነባብተው አቋርጦት ወደ ነበረው ስራው ተመለሰ፡፡

ከተሰነባበቱ በኋላ፤ አቶ አርምዴ ከአካባቢው ዞር እስከሚልላት ድረስ ፀበልተኛ መሰለች፡፡ ከአካባቢው እስኪሰወር ጠብቃ ወደ ሸንኮራ ባልጭ የሚወስደውን የፈረስ ጋሪ ተሳፈረች፡፡

ሰው እያባረረ የሚከተላት መሰላት፡፡ ከፈረስ ጋሪ እንደወረደች ከባልጭ ሞጆ የሚያደርሳትን ያዘች፡፡

እድላዊት አሁንም መነሻዋን እንጅ መድረሻዋን አታውቅም፡፡ ሞጆ መነሃሪያ ደረሰች፡፡ ከተሳፈረችበት ባስ ወርዳ ልብስ የያዘችበትን ፌስታል አንጠልጥላ ስራ ፈላጊዎች ወደ ሚቀመጡበት አካባቢ አመራች፡፡

አዳማ ናዝሬት አዳማ ….እያለ ይለፈልፋል፡፡ ጆሯዋ ጥልቅ አለ፡፡ ሃሳቧን ሰርዛ አዳማ ናዝሬት የሚለውን ሚኒባስ ተሳፍራ ጉዞዋን ወደ አዳማ ናዝሬት አደረገች፡፡

እረዳቱ ውረዱ አለ፡፡ መነሃሪያ ደርሰው፡፡ እድላዊት ሞጆና አዳማ የሚራራቁ መስሏት ውረዱ ሲባል አላመነችም ነበር፡፡

ከሞጆ እስሯ ተቀምጦ የመጣ አንድ መልከ መልካም ፍሪዛም ወጣት ሲወርድ ለመጠየቅ እየፈራች አንተ አንተ…..ብላ ሳትጨርስ ሳይሰማት ጥሏት ወረደ፡፡

እድላዊት ያላት አማራጭ ወርዳ መጠየቅ ሆነ፡፡ ፌስታሏን አንጠልጥላ ወረደች፡፡

የአዳማ መነሃሪያ ደላሎች እንደተገለበጠ የንብ ቀፎ ከበቧት፡፡ እያዋከቡ አንዱ ደላላ የትነሽ ? ድሬ ከሆንሽ አንድ ሰው የቀረው ነው፡፡ አሁን ልንወጣ ነው ነይ፡፡ ያንጠለጠለችውን ፌስታል የመዝረፍ ያህል ነጥቋት ሄደ፡፡

ሁለተኛው ደላላ ደግሞ የት ነሽ ? አሰላ ከሆንሽ ባይሞላም አሁን ይወጣል፡፡ ነይ እያለ እጇን እየጎተተ ወደ አሰላ በሚሄደው አውቶቢስ ውስጥ አስገባት፡፡ የአውቶቢሱን በር ዘግቶባት ወረደ፡፡

እድላዊት ወዲያና ወዲህ ሲያዋክቧት ቀልቧ ተገፏል፡፡ አፏን በፕላስተር የታሸገች መስላለች፡፡ ይህ ሁሉ ትእሪት ሲካሄድ የምትሄድበትን አልተናገረችም ነበር፡፡

"አንች እዚህ ምን ትሰሪያለሽ ? ያልሞላ መኪና ውስጥ እቃሽ እኮ ተጭኗል፡፡ አሁን ልንወጣ ነው ነይ፡፡

የዘጋባትን በር ከፍቶ ይዟት ሄደ፡፡ ፌስታሏን ወስዶ የጫነባት ደላላ፡፡ እኔ ነኝ ፣ እኔ ነኝ የምጭነው፡፡ ግብግብ ተፈጠረ፡፡ ከአሰላው ደላላ ጋር፡፡

የድሬው አሸንፎ መኪናው ውስጥ ጎትቶ አስገባት፡፡ ገና መቀመጫ ሳይሰጣት የአውቶቢሱን በር ዘግቶ ተንቀሳቀሰ፡፡ እድላዊት እኔ አልሔድም ፣ እቃየን ስጠኝ፡፡ አውርደኝ ብትልም የሚሰማት አላገኘችም፡፡

"ሂጅ እዛጋ ክፍት ወንበር አለ፡፡ ተቀመጭ" አላት እረዳቱ፡፡

ግራ የገባት ከርታታዋ እድላዊት ተቀመጭ ከተባለችበት ወንበር ላይ ተቀመጠች፡፡ ከአንገቷ አቀርቅራ መኪናው ወንበር ላይ ተደገፈች፡፡ ለተሳፋሪ እንቅልፍ የወሰዳት መሰለች፡፡ የመውደቂያዋ ቦታ አሳስቧታል፡፡ ተጨንቃለች ፣ ሆዷ ተርፏ ተርፏ ይላል፡፡

አይኖቿ እንባ አቅረዋል፡፡ ምነው አምላኬ የት ልታደርሰኝ ነው?፡፡ መድረሻየን አላውቀውም፡፡

አንተን አምኘ ነው፡፡ እንግዴህ እንደፍቃድህ አድርገኝ እያለች ፈጣሪዋን እያለቀሰች ተማፀነችው፡፡

የራሳቸውን ሃሳብ እያወጡ እያወረዱ ስለስራ ያስባሉ፡፡ ከስሯ የተቀመጡት ወ/ሮ ዘነቡ፡፡ እድላዊት ለምን አቀርቅራ እንደምታለቅስ ግራ ገብቷቸዋል፡፡

"ምነው ልጄ ምን ሆነሽ ነው የምታለቅሽው ? አሏት፡፡

"አይ! ምንም አልሆንኩም፡፡ አይኔን አሞኝ ነው አለች፡፡ ለራሷ ማልቀሷ ቢታወቃትም ፤ ስታለቅስ ግን ሰው የሰማት አልመሰላትም ነበር፡፡

"እና ማልቀሱ ጥሩ እኮ አይደለም፡፡ የባሰ ያምሻል አሉ፡፡ የእውነት አይኗን የታመመች መስሏቸው፡፡

ወ/ሮ ዘነቡ እድላዊትን በአለባበሷና በአነጋግሯ የገጠር ልጅ ለመሆኗ አልተጠራጠሩም ነበር፡፡

"እና አሁን የት ነው የምትሄጅው? አሏት ወ/ሮ ዘነቡ፡፡

እድላዊት የምትሄድበትን ቦታ አታውቅም፡፡ መጠጊያና ማረፊያ ለማግኘት ግን ሁሉንም አፍረጥርጣ መናገር የግድ ሆነባት፡፡

"የምሄድበትና መውደቂያዬን ባውቅማ ምን ያስለቅሰኝ ነበር፡፡ ያለማወቄ ነው እንጅ አለች፡፡ እንባዋ ሳያቋርጥ ግራና ቀኝ ጉልበቶቿ ላይ እየተንጠባጠበ፡፡

ከቤተሰቦቿ ጠፍታ መሆን አለበት ብለው ጠርጥረዋል ወ/ሮ ዘነቡ፡፡ ደግመው "ከየት ነው የመጣሽው? ታዲያ አሏት፡፡

"ከሸንኮራ ጅማ ነው የመጣሁት፡፡ ቤተሰቦቼን በህፃንነቴ ሞተውብኛል፡፡ ከዘመዶቼ ጋር አልስማማ ብዬ ጠፍቼ ነው፡፡

አትሮኖስ

29 Dec, 08:19


#የጣት_ቁስል


#ክፍል_ስድስት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

ደላላው

ያዋጣኝ ይሆን ? ወይስ ያከስረኝ ? ይሆን ? ተጠራጠረ ፤ የአልባሳት ንግዱ ግን ውጤታማ አድርጎታል፡፡ እየተመላለሰ መነገዱን ቀጥሏል፡፡

የባልጪ መኪና ቶሎ ያሬድ ወደ ድሬድዋ ሊሄድ ረፍዶበት ተቻኩሏል፡፡ መኪናው ግን ሳይሞላ መውጣት አልቻም፡፡ አዳማ አርፍዶ ደረሰ፡፡ ወደ ድሬደዋ በጥዋት የሚወጣው መኪና አምልጦታል፡፡

ተናደደ ፣ ተበሳጨ፡፡ ምነው ዛሬ ባልመጣሁ ኖሯል፡፡ እንደሚረፍድብኝ እያወቅሁ፡፡ ከባልጪ መመለስ ሲኖርብኝ፡፡ ወደ አዳማ መንከርፈፍ ምን ይሉታል? ራሱን እየወቀሰ ከአሰላ መውጫ መነሃሪያ ወጥቶ በስተቀኝ በኩል ወደ ምትገኝ አንድ ሻይ ቤት አመራ፡፡

አንድን ጠቆር ያለ ወጣት ነው፡፡ ቁመተ አጭር ዳክየ፡፡ የተከረከመ ጉቶ ይመስላል፡፡ ፀጉሩ በአቧራ የተለወሰ ፣ የተንጨበረረ ፣ ቁጥርጥር ፀጉራም፡፡

ከመነሃሪያ ውጭ ቆሞ አላፊ አግዳሚውን ድሬ ፣ ድሬ አንድ ሰው የቀረው እያለ ይለፈልፋል፡፡
ቀኝ እግሩን አንስቶ ግራ እግሩን አልደገመም፡፡ ድሬ አንድ ሰው የሚል ድምፅ ሰማ፡፡ ወደ ፊት መራመዱን ትቶ ወደ ኋላ ተመለሰ፡፡ ብስጭትና ንዴቱ ለቀቀው፡፡ እየተጣደፈ ድሬ ፣ ድሬ አንድ ሰው እያለ ወደ ሚለፈልፈው ደላላ ተጠጋ፡፡ እኔ አለሁ ድሬ አለ፡፡

"ኧረ! ድሬ ነህ ና ተከተለኝ፡፡ አሁን ልንወጣ ነው"፡፡ ብሎት ወደ መኪናው ወሰደው፡፡ ሂሳብ ክፈልና እዚህኛው መኪና ግባ አለው፡፡

ለመሳፈሪያ ብሎ ለይቶ ካስቀመጠው የሱሪ ኪሱ አውጥቶ ከፈለ፡፡ ደረሰኝ ግን አልተቀበለም፡፡ ደላላው ገንዘቡን ተቀብሎት ታጠፈ፡፡

ያሬድ ግባ ወደ ተባለበት አውቶቢስ ገባ፡፡ እውነትም አንድ ሰው ብቻ ነበር የቀረው፡፡ አንድ ተሳፋሪ ቀርቷት የነበረች ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡

እረዳቱ የአውቶቢሱን በር ዘጋ፡፡ ሹፌሩ መኪናውን አስነሳ፡፡ ጉዞው ከአዳማ ወደ ድሬደዋ ተጀመረ፡፡

"ምዕመናን ሂሳብ ወጣ! ወጣ! አድርጉ አለ እረዳቱ፡፡ እየተቀበለ ያሬድ ጋር ደረሰ፡፡

"ለእኔ ደረሰኝ ብቻ ስጠኝ ገንዘቡን ከፍያለሁ አለ ያሬድ፡፡

"ለማነው የከፈልከው አለ እረዳቱ?፡፡

"ሊያሳፍረኝ ይዞኝ ለመጣው ሰውየ ፡፡

"አባት የከፈሉት ሂሳብ ለእኔ አልደረሰኝም፡፡ አሁን ለእኔ ይክፈሉኝ አለ፡፡ ትህትና በተሞላበት ንግግር፡፡

"አልከፍልም" አለ ያሬድ፡፡

"እባክዎት ይክፈሉኝ" አባት ቢልም ፤ ምንም ቢል ያሬድ ሊሰማ አልቻለም፡፡ ክፈል ፣ ጭቅጭቅና ንትርኩ ተባባሰ፡፡ ሹፌር መኪናውን መንዳቱን አቆመ፡፡ በረዳቱና በያሬድ መሃል ጣልቃ ገባ

"ለምንድ ነው የማከፍለው? በነፃ ተሳፍረህ የምትሄደው የአባትህ ፈረስ አደረግከው አለ ሹፌሩ፡፡ በፊቱ ላይ የደም ስሮቹ ተወጣጠሩ፡፡

"የአባቴ ፈረስ ባይሆንም ገንዘብ ከፍየ ነው የተሳፈርኩት፡፡ ያጭበረበራችሁኝ እናንተ ናችሁ፡፡ በማስፈራራት ደግማችሁ ልታስከፍሉኝ ነው? አልከፍልም፡፡ ወደ ህግ እንሄዳለን እንጅ አለ ያሬድ፡፡

ከመኪናው ውስጥ ጎትተው አወጡት፡፡ ሊደበድቡት ተጋበዙ፡፡ ተሳፋሪዎቹ ገላገሏቸው፡፡ ክርክሩና ንትርኩ አላቋረጠም፡፡

አቶ ላንቻ ባልቻ የሚባሉ ከያሬድ ጋር አንድ ወንበር ላይ አብረው ተቀምጠዋል፡፡ ጭቅጭቁ አበሳጭቷቸዋል፡፡ ቶሎ ለመድረስ ያሰቡበት ቦታ እየረፈደባቸው ነው፡፡

"ለረዳቱ በቃ! ተወው እኔ እከፍለዋለሁ፡፡ ንትርኩን ተውና ቶሎ ቶሎ ንዳ፡፡ እውነት ይሄ ሰውዬ ሳይከፍልም የተከራከረ አይመስለኝም፡፡ የአዳማ ሞጭላፋ ጩልሌዎች ጨልፈውት ይሆናል፡፡ እንኳን የክፍለ ሃገር ሰው አግኝተው አይደለም ወፍ ከሰማይ ያወርዳሉ፡፡ ይዞት የመጣው ደላላ የሻይ ሲጠይቀው የመሳፈሪያውን ሂሳብ ተቀብሎት ላፍ ብሎ ይሆናል፡፡ ብለው የሚያጨቃጭቀውን የያሬድን ሂሳብ ከደረት ሸሚዝ ኪሳቸው አውጥተው ከፈሉለት፡፡

"አጭበርብረውኝ ነው፡፡ እንጅ እኔ እኮ ገንዘቡን ከፍያቸዋለሁ አባት አለ፡፡ እንደ መፀፀት ብሎ፡፡

"ያጭበረበሩህ ባለ መኪናዎቹ አይደሉም፡፡ ዱርዬዎች ናቸው፡፡ አንተም መኪና ውስጥ ሳትገባ መክፈል አልነበረብህም፡፡ ወይም ስትከፍል ደረሰኝ መቀበል ነበረብህ::

"እኔ መቼ አወኩ፡፡ እንደዚህ መሆኑን የት አውቄ፡፡ የእነሱ አጋዥ መስሎኝ ነው፡፡ የከፈልኩት፡፡ መቼ ሰባራ ሳንቲም አቀምሰው ነበር፡፡ ብሎ ስህተቱ የራሱ መሆኑን አውቆ የከፈሉለትን ገንዘብ ሊከፍል ከኪሱ አወጣ፡፡
አባት አመሰግናለሁ ገንዘቡን እንኩ አለ፡፡ በፊቱ ላይ የይቅርታ ምልክት እያሳየ፡፡

ገንዘቡን ለመቀበል አልፈለጉም፡፡ ተወው ችግር የለውም፡፡ አንተም ተወስዶብህ ነው፡፡ እንጅ አውቀህ አይደለም፡፡ አሁን ያወጣኸውን ገንዘብ መልሰህ ወደ ኪስህ አስገባ እኔ አልቀበልም አሉ አቶ ላንቻ፡፡

አቶ ላንቻ ከድሬደዋ አዳማ እየተመላለሱ የሚነግዱ የታወቁ ቱጃር አልባሳ ነጋዴ ናቸው፡፡ ጨዋታቸው እየሞቀ ሄደ፡፡ አቶ ላንቻ ከተደገፉበት ወንበር ቀና አሉ፡፡

"ስምህን ማን አልከኝ"? አሉት፡፡ መጀመሪያ ነግሯቸው በጭዋታ የተነሳ ዘንግተውት ይሁን ተመስሎባቸው ደግመው መጠየቃቸው፡፡

"ያሬድ እባላለሁ አለ፡፡ ፊቱን ወደ አቶ ላንቻ መለስ አድርጎ፡፡

"አሁን ወዴት ነው የምትሄደው"? ፡፡

"ወደ ድሬ የምሄደው"፡፡

"እዛው ነዋሪ ነህ ወይስ ለስራ ነው የምትሄደው?፡፡

"አይ! ለስራ ነው፡፡ ነገ እመለሳለሁ፡፡ እቤት ከመቀመጥ ብዬ ትንሽ ሳልባጅ ቢጤ ጀምሬ ነበር፡፡ ሞልቶ ለማይሞላ ነገር ስንት ገዛኸው ዘጠኝ ፤ ስንት ሸጥከው ዘጠኝ ፤ ትርፉስ ምንድነው? ዘጥ ዘጥ እንደሚባለው የበሰለውን ከማጥፋት ውጭ ድካም ነው፡፡ ውጤት የለውም አላቸው፡፡ ንግግሩ የሚያስቅ ስለነበር ፈገግ አደረጋቸው፡፡

አቶ ላንቻ አለመተዋወቅ እንጅ አልባሳት ከሆነ የምትነግደው እኔ አዳማ ድረስ አመጣልህ ነበር አሉ፡፡

"አልባሳት ይነግዳሉ እንዴ? አለ ያሬድ፡፡

"አዎ፤ ነጋዴ ነኝ፡፡ አሁንም አራግፌ እየተመለስኩ ነው፡፡

"ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ እንዴው የሰው መተዋወቂያው መንገዱ ብዙ ነው አለ ያሬድ፡፡ ያገናኛቸው አጋጣሚ እያስገረመው፡፡

"ድሬ ደንበኛ አለህ የምትረከብበት"? ፡፡

"ደንበኛ እንኳን የለኝም፡፡ የጀመርኩት ቅርብ ጊዜ ስለሆነ ደንበኛ አላበጀሁም፡፡ ከአሸዋ ሜዳ ነው የምገዛው ፡፡

የዛሬ መገናኘታችን ጥሩ አጋጣሚ ነው፡፡ አሁን እየደረስን ስለሆነ መነሃርያ ሳንገባ ወርደን አረፍ ብለን እንነጋገራለን" አሉ ፤ አቶ ላንቻ፡፡

ከመኪና ወርደው ወደ አንድ ሪስቶራንት አመሩ፡፡ አረፍ ብለው የሚጠጣ ለስላሳ አዘዙ፡፡ በመኪና ላይ የጀመሩትን ጭውውታቸውን እንደቀጠሉ ናቸው፡፡

"አዳማ ውስጥ የራስዎ ቡቲክ አሎት እንዴ? አለ ያሬድ፡፡

"የራሴ እንኳን ቡቲክ የለኝም፡፡ አዳማ መነሃሪያ አካባቢ ቢያድግልኝ የሚባል የጅምላ አከፋፋይ ሱቅ አጠገብ የተከራየሁት ቡቲክ አለኝ፡፡ እዛ ነው የምሸጠው፡፡ ቦታውን ነገ አብረን ስንሄድ አሳይሃለሁ፡፡ አሁን እንሂድና እዚህ ድሬ ውስጥ ያለኝን ቡቲክ ላሳይህ፡፡ የሚያስፈልግህንም ገዝተህ እኔ በምጭንበት መኪና ጭነህ ነገ አብረን አንሄዳለን፡፡

ያሬድ ያገናኘውን አጋጣሚ እየመረቀ እንዴው ምን ዓይነት ደግ ሰው ነው፡፡ ያጋጠመኝ የእግዚአብሔር ሰው ናቸው፡፡ እያለ "አይደህና ነው፡፡ ለእኔም እዚህ ድረስ ከምለፋ ጥሩና መልካም ነው፡፡ እንዴው ውለታዎን ለመክፈል ያብቃኝ" አለ፡፡ ቀለስለስ እያለ፡፡

"አይ! ምንም ማለት አይደለም፡፡ የራሴም ስራ ነው፡፡ አሁን ከአንተ የምጠብቀው ታማኝ ሆኖ መገኘት ብቻ ነው"፡፡ ብለውት ሊያሳድሩት ወደ ቤታቸው ወሰዱት፡፡

በነጋታው በጥዋት ተነሱ፡፡ በተነጋገሩት መሰረት የሚያስፈልገውን ልብሶች ገዝቶ አብረው ወደ አዳማ ተጓዙ፡፡

አትሮኖስ

29 Dec, 08:19


አቶ ላንቻ ቡቲካቸው ደረሱ፡፡ ከደንበኛቸው ከቢያድግልኝ ጋርም ያሬድን አስተዋወቁት፡፡ ለቀጣይ የሚያስፈልገውን አልባሳት እንደሚያመጡለት ተነጋግረው ያሬድ ወደ ቤቱ ተመለሰ፡፡

ለአይን ያዝ ሲያደርግ እቤቱ ደረሰ፡፡ እግሩን ተጣጥቦ የበጉን ድብዳብ ነጠል አድርጎ ወገቡን በመደብ ላይ ደገፍ አደረገ፡፡
ባለቤቱ አበበች ወጥ እስከ ምትሰራ ድረስ ከስንዴና ከሽንብራ የተቀላቀለ ቆሎ አቀረበችለት፡፡ ከውሃ ሻል የሚል ሰንበትበት ያለም ቅራሬ ሰጠችው፡፡ ከጥሬው ቀጭ ፣ ቀጭ እያደረገ ከቅራሬውም ጎንጨት እያለ ፤ አዳማ ላይ የገጠመውን ሁሉ እያስታወሰ በውስጡ ይገረማል፡፡

"ምነው ዛሬ ደግሞ የደከመህ ትመስላለህ ? የሄድክበት አልቀናህም እንዴ ? አለች አበበች፡፡ የወጥ መስሪያ ሽንኩርት እየላጠች፡፡

በውስጡ የሚያብሰለስለውን የገጠመኝ ሃሳብ ተወት አደረገ፡፡

ገበያውስ ቀንቶኛል፡፡ እንዴው የገጠመኝ ነገር እየገረመኝ ነው አላት፡፡

"ደግሞ ምን ገጠመህ"?፡፡

"ባልጪ መኪና ሳይሞላ ቀርቶ ፤ አዳማ ስደርስ ረፍዶ ወደ ድሬ በጥዋት የሚወጣው መኪና አምልጦኝ ተናድጄ ነበር፡፡ በኋላ፤ አርፍዶ መኪና ኖሯል እሱን አግኝቼ እየተጣደፍኩ ልሳፈር ስል ረዳቱ የመሳፈሪያ ገንዘብ አምጣ
ሲለኝ የመኪናው ባለቤት ነው ብየ ከፈልኩት፡፡ ለካስ ገንዘቡን የተቀበለኝ ዱርየ ኖሯል፡፡ ከዛ ባለመኪናዎቹ ክፈል ፣ አልከፍልም፡፡ ስከራከር አንድ ተሳፋሪ ያጭበረበረኝን አውቀውት ኖሯል፡፡ ተወው ብለው ከፈሉልኝ ፡፡

"አንተ አዲስ አይደለህ ፤ ብትቼኩልስ ለምትከፍለው ሰው አታውቅም እንዴ፡፡ ሆሆይ እግዚአብሔር ደግ ሰው ጥሎልሃል፡፡ እንዴው ሰውዬው ምን አይነት ሰው ናቸው? አለች፡፡

"ሰውዬውስ የተባረኩና ደግ ሰው ከመሆናቸውም የናጠጡ ቱጃር አልባሳት ነጋዴ ናቸው፡፡

"ባለ ሃብት ሆነው ነዋ የከፈሉልህ ፡፡ እኔ እኮ ምን አይነት ሰው ከፈለልህ እያልኩ ነበር፡፡ "

ባለ ሃብት የሆነ እንደሆነ ለማያውቀው ሰው ገንዘቡን ይከፍላል እንዴ"? እንዲያውም እሳቸው ደግና የእግዚአብሔር ሰው በመሆናቸው ነው እንጅ የከፈሉልኝ፡፡ ከአሁን በኋላ ደግሞ ድሬ ድረስ አልሄድም ፡፡

"የትድረስ ነው አምጥተው የሚሸጡት?"፡፡

"አዳማ ድረስ ነው"፡፡ ለእኔም እንደሚያመጡልኝ ተነጋግረን ነው የመጣሁት፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...33 ቀን ብቻ ነው የቀረው አዋጭ ነው ጀምሩት

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

አትሮኖስ

28 Dec, 17:40


አትሮኖስ pinned «#የጣት_ቁስል ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ #ያሬድ ሁሉም ተሳካለት፡፡ ከዚያው አካባቢ አበበች የምትባል ልጅ አገባ፡፡ ኑሮውን ለማሻሻል ከግብርና ስራው በተጨማሪ የንግድ ስራ ለመስራት አቀደ፡፡ ለባለቤቱ ማማከር እንዳለበት ወሰነ፡፡ አንድ ቀን ከባለቤቱ ጋር እራት እየበሉ ነው፡፡ "እንዴው ይሔ የግብርና ስራ ከእጅ ወደ አፍ ብቻ ሆነ፡፡ በትርፍ ሰዓቴ እንኳን ንግድ ብሞክር ፤ ሳይሻል…»

አትሮኖስ

28 Dec, 17:38


#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አምስት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

#ያሬድ

ሁሉም ተሳካለት፡፡ ከዚያው አካባቢ አበበች የምትባል ልጅ አገባ፡፡ ኑሮውን ለማሻሻል ከግብርና ስራው በተጨማሪ የንግድ ስራ ለመስራት አቀደ፡፡ ለባለቤቱ ማማከር እንዳለበት ወሰነ፡፡

አንድ ቀን ከባለቤቱ ጋር እራት እየበሉ ነው፡፡ "እንዴው ይሔ የግብርና ስራ ከእጅ ወደ አፍ ብቻ ሆነ፡፡ በትርፍ ሰዓቴ እንኳን ንግድ ብሞክር ፤ ሳይሻል አይቀርም" አላት ያሬድ ለባለቤቱ አበበች፡፡ በእጁ የተቀለለውን እንጀራ እየጎረሰ፡፡

"ሃሳብህ ጥሩ ነው፡፡ ግን ምን ዓይነት ንግድ ነው የምነግደው? አለች አበበች፡፡

ጥያቄን በጥያቄ እንዲሉ መልሶ "ቡና ይሻላል ወይስ አልባሳት?'' አላት፡፡

ሁለቱም አማራጮች ጥሩ ናቸው፡፡ ግን ከየት አምጥተህ ነው የምትነግደው ?፡፡

ያሬድ ተጨማሪ የንግድ ስራ ለመስራት እንጅ ከየት አምቶ እና ምን እንደሚነግድ እንኳን በደንብ አላሰበበትም፡፡

አልባሳት በቅርብ ባይገኝም ወደ ድሬደዋ በመሔድ ማግኘት እንደሚቻል ግን ያውቃል፡፡

"ድሬደዋ በውሎ ገባ መድረስ ይቻላል እንዴ"? አለችው፡፡

ያሬድ ድሬደዋ ሔዶባት አያውቅም፡፡ "ሰዎች ሲያወሩ ሰምቻለሁ፡፡ ውሎ ገባ አይደረስም፡፡ መኪና ከተገኘ ሁለት ቀን ቢወስድ ነው"፡፡

ያሬድ ከባለቤቱ ተስማምቶ ፤ ማምጫ ገንዘብ ለሰው አበድሮት የነበረውን ሰበሰበ፡፡ ከቤትም ትንሽ ስንዴ ሸጦ ለመነገጃ የሚሆን ገንዘብ አጠራቀመ፡፡

ታዲያ ወደ ድሬደዋ ሲሔድ ቤቱን ፣ ከብቶቹንና ባለቤቱን ብቻዋን ጥሏት እንዳይሄድ ስጋት አደረበት፡፡

ተመስገን ለቤተሰቦቹ ውሃ ሊቀዳ አህያ ላይ ጀሪካን እየጫነ ነው፡፡

"ደህና አደርህ ተመስገን" አለ፡፡ ቤቱን እና ከብቶቹን እስከሚመለስ እንዲያይለት ሊጠይቀው በጥዋት የመጣው

"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አደርህ ያሬድ" አለ፡፡ ጀርካን መጫኑን ተወት አድርጎ ወደ ያሬድ እየተጠጋ፡፡ የእጅ ሰላምታ ሰጥቶት ወደ ቤት ግባ አለው ተመስገን፡

"አልገባም ይሁን" ብሎ "አንተጋር ነበር የመጣሁት" አለ

"ምነው በሰላም" ?

"አይ! በሰላም ነው፡፡ አንድ ነገር ላስቸግርህ ብየ ነው የመጣሁት"፡፡

"ምን ችግር አለው የምችል ከሆነ"፡፡

"አይ! ቀላል ነው"፡፡ እኔ ወደ ድሬደዋ ለመሄድ ስለፈለግሁ ቤቴን እንድትከታተልልኝ ፈልጌ ነበር፡፡

"ምነው በሰላም ነው፡፡ ወደ ድሬደዋ የምትሄደው ?

"ለራሴ ጉዳይ ነው፡፡ ትንሽ አልባሳት ለመነገድ ስላሰብኩ ለማምጣት ነው የምሔደው ፡፡

"አይ! ደህና ነው፡፡ እከታተልልሃለሁ ግን ለምን አብረን ብቻህን እዛ ድረስ ከምትሄድ ለኔም ታስተዋውቀኝ ነበር አለ ተመስገን፡፡

"ሐሳብህ ጥሩ ነው፡፡ ግን እኔም ገና አዲስ ስለሆንኩ መጀመሪያ ልየውና የሚያዋጣ ከሆነ አብረን እንሔዳልን እስከዛ ገንዘብ አጠራቅም፡፡ ብሎት ተሰነባብተው ተለያያዩ።

እድላዊት

ሲሻለኝ ውለታቸውን በጉልበቴም ቢሆን አግዠ እከፍላቸዋለሁ ብላ አሰበች፡፡ ግን ያሰበችው ቶሎ አልሆነም፡፡

ከህመሟ ሳይሻላት እየባሰባትና እየጠናባት ሄደ፡፡ ሁለት ወር ከ18 ቀን የአልጋ ቁራኛ ሆና አሳለፈች፡፡ ምነው እዛው ጫካ ሞቼ በቀረሁ ኖሮ፡፡ እንደዚህ የአልጋ ቁራኛ ሆኘ ሰው ከማስቸገር ምን አለ ፈጣሪየ መከራና ስቃየን ከምታበዛብኝ ብትገላግለኝ?፡፡ ፈጣሪዋን እየተማፀነች እና እያማረረች ውላ በተራው ጨለማውን ተገን አድርጎ ሌሊቱ ይተካል፡፡

እድላዊት ሌሊትም ሆነ ቀን የምትተኛበት የእንቅልፍ ሰዓት በሃሳብና በጭንቀት ሳይታወቃት ቀን መሽቶ ይነጋል፡፡ በብርድልብስ ውስጥ ተሸፍና የምታለቅሰው እንባ ቢጠራቀም ዘመዶቿንና ቤተሰቦቿን ይቀብርላት ነበር፡፡

አንዳንዴ ሲጨንቃት የተሻላት ይመስላታል፡፡ ለመሄድ አስባ ትነሳለች፡፡ አሁን ልሂድ በቃ ተሸሎኛል፡፡ እናንተንም
አስቸገርኳችሁ፡፡ ተነስታ ለመሄድ ስታስብ አቅም ያንሳታል ፤ እራሷን ያዞራታል፡፡ ተመልሳ መቀመጥ አትችልም፡፡

የእድላዊት ቶሎ አለመዳንና የአልጋ ቁራኛ መሆኗ አሳስቧቸዋል ፤ ወ/ሮ በሰልፏ፡፡ ምነው ፈጣሪዬ ይህችን አንድ ፍሬ ህፃን የአልጋ ቁራኛ ከምታደርግብኝ ለኔ ብሰጠኝ፡፡ እያሉ ፈጣሪያቸውን እየተማፀኑ ውለው ማደራቸው ሳያንሳቸው እድላዊት ደግሞ በሽታዋን ሳታስብ አስቸገርኳችሁ ስትላቸው የባሰ ያስጨንቃቸዋል፡፡

እባክሽን ልጄ ተለመኝኝ ; እባክሽ ስለፈጠረሽ አምላክ ; በደንብ ሲሻልሽ ትሔጃለሽ፡፡ ልጄ እባክሽ ለኔ ምንም አታስቢ፡፡ አንቺ ብቻ ዳኝልኝ፡፡ ለሁሉም ይደረሳል፡፡ ብለው ምንም እንዳታስብና እንዳትጨነቅ ይማፀኗታል ፡፡

እድላዊት በትንሹም ቢሆን እየተሸላት መጣ፡፡ መጀመሪያ ውለታቸውን ከፍየ እሄዳለሁ ብላ ያሰበችውን አረሳችም፡፡

ገና በደንብ ሳይሻላት ለመርዳት ተቻኮለች፡፡ ቡና ሲያፈሉ እኔ አፈላለሁ እያለች ወ/ሮ በሰልፏን ታስቸግራቸውም ጀመር፡፡ ቆይ በደንብ አልተሻለሽም፡፡ በደንብ ሲሻልሽ ታፈያለሽ፡፡ ቢከለክሏትም እሽ አትላቸውም ነበር፡፡

እድላዊት በቤቱ ውስጥ ያለውን ስራ በመስራት መርዳትና ማገዝ ጀመረች፡፡ ትንሽ ሲሻለኝ እሄዳለሁ ያለችውን ሰረዘች፡፡ ውለታቸውን በደንብ ለመክፈል ህሊናዋ አስገደዳት፡፡

የተባረከች ልጅ የእግዚአብሔር ቸርነት ያደረባት፡፡ የትንሽ አዋቂ በማለት ያመሰግኗትም ነበር ፤ ወሮ በሰልፏ፡፡

ከባለቤታቸው አንድ ወንድ ልጅና ሁለት ሴት ልጆችን ወልደዋል፡፡ያለመታደል ሆኖ ግን ሁለቱን ሴት ልጆቻቸውን በአንድ ወቅት በተከሰተው የኩፍኝ ወረርሽኝ በሞት ተነጥቀዋል፡፡

የሴትን ልጅ ጥቅም በደንብ ያወቁት በእድላዊት እንጅ በልጆቻቸውም አልነበረም፡፡ እርጅናቸው ገፋ ባይባልም በባለቤታቸውና በልጆቻቸው ሞት በመከራ ላይ መከራ አሳልፈዋል፡፡ አቅማቸው እየደከመ ፤ ጤንነታቸው ከቀን ቀን እየባሰባቸው ሄደ፡፡ የጤና ማጣታቸው ታዲያ አልጋ እንዲይዙ አስገድዷቸዋል፡፡

እድላዊት ከቤተሰቦቿ የተፈጠረችበትን ቀን ስታስታውስ አምርራ ትረግማለች፡፡ ቤተሰቦቿ እንደ ወ/ሮ በሰልፏ ቅን ፤ የሰውን ሃሳብ የሚረዱ ቢሆኑ ኖሮ ዛሬ ትምህርቷን ጨርሳ እሩቅ የመድረስ ፤ አላማዋና ተስፋዋ በተሳካላት ነበር፡፡

አንዴ ለመከራ የታደለች አድርጎ የፈጠራት እድላዊት፡፡ ከአልጋ ቁራኛ ተነስታ ውለታቸውን በጥቂቱም ቢሆን በጉልበቷ ከፍላ ለመሔድ ተነሳች፡፡ ግን አልተሳካላትም፡፡ ያስታመሟት ወሮ በሰልፏ ተረኛ የአልጋ ቁራኛ ሆኑባት፡፡

ጥላቸው እንዳትሄድ በእጃቸው በልታ ፣ ጠጥታ ያደረጉላት ውለታ ፤ መቼም የማይረሳ ሆነባት፡፡ ብትሔድ እንኳን  የማይቀናትና የማይሳካላት መስሎ ታያት፡፡ ከስራቸው ሆና ለማስታመም ተገደደች፡፡

ወላጅ እናቷን እንደምጠራው እማዬ ምን ላምጣሎት ? ምን ላድርግሎት ? ምን ይሻላል ? እያለች አቅሟ የፈቀደውን ሁሉ እያደረገች አስታመቻቸው፡፡

ታዲያ ስትወጣና ስትገባ አይን አይናቸውን ስትመለከት ህመማቸው ፤ ህመሟ ይሆንባታል፡፡ ሁለት ወር ከ18 ቀን የአልጋ ቁራኛ እያለች

ያደረጉላት ሁሉ በሃሳቧ ይመጣ፡፡

አይኖቿ በእንባ ይሞላሉ፡፡ ስታለቅስ እንዳያዩዋት ወደ ውጭ ወጥታ ልውጣ ልውጣ እያለ በሃይል የሚያስቸግራትን ፤ የእንባ ጎርፍ ፊቷንና አይኖቿ እስከሚቀሉ ድረስ ታዘንበዋለች፡፡

ወ/ሮ በሰልፏ የራሳቸው በሽታና ስቃይ ሳያንሳቸው በእድላዊት ማሰብና መጨነቅ አንጀታቸው አልችል አለ፡፡

አትሮኖስ

28 Dec, 17:38


በደከመ አቅማቸው ምነው? ይበቃ ነበር፡፡ የኔ መሰቃየት ልጄን ከምታሰቃይብኝ ምነው ፈጣሪዬ የእለት ሞቴን ብሰጠኝ ? እባክህን ይህችን አንድ ፍሬ ህፃን ስታለቅስ
ከምታሳየኝ ውሰደኝ፡፡ ፈጣሪያቸውን እየተማፀኑ ልማደኛውና ማለቂያ የሌለው እስኪመስል ድረስ ድምፁን ሳያሰማ ስቃይና በሽታ ያስታግስ ይመስል የአይናቸው እንባ ግራና ቀኝ በጉንጫቸው ላይ ኮለል እያለ ፤ የለበሱትን ሸማ እስከሚያርስ ድረስ መውረዱን ይያያዘዋል፡፡

እድላዊት ከቤተሰቦቿና ከተወለደችበት ቀዬ ተለይታ ፤ በሸንኮራ ጅማ አካባቢ ከወ/ሮ በሰልፏ ቤት በደስታና በምቾት ሳይሆን ፤ በመከራና በስቃይ ፤ ማይክሮ ሰከንድ ወደ ሰከንዶች ፣ ሰከንዶች ወደ ደቂቃ ፣ ደቂቃዎች ወደ ሰዓታትት ፣ ሰዓታቶች ወደ ቀናት ፣ ቀናቶች ወደ ሳምንታት ፣ ሳምንታቶች ወደ ወራት ፣ ወራቶች ወደ ዓመትት ተቆጥረው ለስምንት ዓመታት አሳለፈች፡፡

ታዲያ ወ/ሮ በሰልፏን በአልጋ ላይ ተኝተው ከቤት ውስጥ ያለውን የቤት ስራ እየሰራች ከውጭም ውሃ እየቀዳች ፤ ወፍጮም እየሄደች ፤ በማገልገል ለስምንት ዓመት አስታመመቻቸው፡፡

ወ/ሮ በሰልፏ እየተሸላቸው መጣ፡፡ እድላዊትም ከዛሬ ስምንት ዓመት በፊት ያሰበችውን ሐሳብ ሳትቀይር ወደ ሸንኮራ ዮሃንስ ፀበል ለመሄድ ተነሳች፡፡

"እኔም ወደ ፀበል ልሂድ፡፡ ይሔኔ ቤተሰቦቸም ፀበል ቦታ መተው ፈልገው ሲያጡኝ ሞታለች ብለው እርማቸውን አውተው ይሆናል፡፡ አሁን ሸንኮራ ዮሃንስ ፀበል ትንሽ ተቀምጨ ወደ ቤተሰቦቼ እመለሳለሁ አለች፡፡

እድላዊት ውሸት ቀላቅላ በመናገሯ ተፀፀተች፡፡ አንገቷን ወደ መሬት አስደፋት፡፡

ወ/ሮ በሰልፏ ከበፊቱ ትንሽ ተሸሏቸዋል፡፡ አልጋ ላይ ቁጭ ብለው ማነጋገርና ትንሽ እህል መቅመስ ከጀመሩ አንድ ወር አድርገዋል፡፡ ልጃቸው እድላዊት ለመሔድ በመነሳሳቷ ውስጣቸው ተረበሸ፡፡ ሰውነታቸው እንደእስስት ተለዋወጠ፡፡

"ልጄ እስካሁን አስታምመሽኝ አፈር ሳታለብሽኝ ጥለሽኝ ልትሔጅ ነው? አሏት፡፡ ወ/ሮ በሰልፏ የእድላዊትን ሃሳብ ቢረዱ ኖሮ እንዲህ ባልተናገሯት ነበር፡፡

እድላዊት መለየትን ወዳ ሳይሆን የሰው ቤት ተቀምጣና የመጨረሻ መውደቂያዋን ባለማወቋ እንጅ እያስታመመች ከስራቸው ብትሆን በተደሰተች ነበር፡፡

የወ/ሮ በሰልፏ መረበሽ ለእሷም የባሰ ጨለማ ሆነባት፡፡ ያልጠበቀችውን ነገር በመስማቷ ሆዷ እንዲረበሽ እና እንድትጨነቅ አደረጋት፡፡

"ምነው ፈጣሪዬ? አይበቃኝም መከራና ስቃይ? አንተን ለሚያምኑ ሁሉ ታማኝ ነህ፡፡ በችግር ጊዜ ለሚጠሩህ ሁሉ ደራሽ ነህ፡፡ ለሚለምኑህ ሁሉ ሰሚነህ፡፡ ምነው ታዲያ በእኔ ጨከንህ ?፡፡ እያለች ፈጣሪዋን እያለቀሰች ለመነችው፡፡

በዛው መኝታዋ ላይ ጋደም አለች፡፡ እንቅልፍ ግን ሊወስዳት አልቻለም፡፡ በአይኗ ሳያልፍ ለሊቱ ተገባደደ፡፡

ወ/ሮ በሰልፏ በልጃቸው ለመሔድ መነሳሳት በሽታቸው እንደገና አገርሽቶባቸዋል፡፡ ትንፋሻቸው ቁርጥ ፣ ቁርጥ ፤ ሰውነታቸው ድካም ድካም ተሰማቸው፡፡ እኩለ ሌሊት ሆኗል፡፡ እድላዊትን ውሃ ስጭኝ አሉ፡፡እድላዊት በድንጋጤ ተነሳች፡፡ ውሃ ቀድታ ሰጠቻቸው፡፡ ትንሽ ከአንገቴ ቀና አድርጊኝ፡፡ በእጅሽም ደግፊኝ ልጄ ፤ አቃተኝ ምነው?፡፡ አንችንም አስቸገርኩሽ እስካሁን አስታመምሽኝ እግዚአብሔር ይስጥሽ፡፡ ውለታሽን እሱ ይክፈልሽ ፡፡ በሄድሽበት ቦታ ሁሉ ክፉ አይንካሽ፡፡ እያሉ በእድላዊትን ክንድ ላይ እንቅልፍ ሸለብ አድርጓቸው፡፡

ታዲያ ከእንቅልፋቸው ሳይነቁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይችን አለም ተሰናበቷት፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...34 ቀን ብቻ ነው የቀረው አዋጭ ነው ጀምሩት

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

አትሮኖስ

28 Dec, 13:00


አቶ አርምዴ እድላዊት ወደ ተኛችበት ፍራሽ ተጠጋ፡፡ ትንፏሿን ለማዳመጥ በርጩማ ላይ ተቀምጦ ከአንገቱ አቀረቀረ፡፡ በቤቱ ወለል ላይ አይኖቹን ተከላቸው፡፡ እድላዊት ከተኛችበት ፍራሽ ላይ ገልበጥ አለች፡፡

"እንዴት አደርሽ ? ተሻለሽ ? አለ፡፡ ጥድፍ ጥድፍ እያለ ስሟን እንኳን ሳይጠራ፡፡

እድላዊት ከተኛችበት እንደመባነን አለች፡፡ የሰማችውን ድምፅ እያስታወሰች፡፡ ትናንት ከአንበሳ ጉሮሮ ውስጥ ነጥቆ ያወጣት የእግዚአብሔር መላዕክተኛው አቶ አርምዴ መሆኑን በድምፁ
ለመለየት አልተቸገረችም፡፡

ተሽሎኛል የሚለውን ቃል ለመናገር ጉሮሮዋ በቶንሲሏ ምክንያትና የጮኸችበት በተራው ተዘግቶ የወንድ ድምፅ ይሁን የሴት ድምፅ በማይለይ ተክሎኛል አለች፡፡

አቶ አርምዴ በሚያደናግር እና በተኮላተፈ አማርኛ የተናገረችው ተሸሎኛል የሚል እንደሆነ ተረድቷል፡፡ በልቡ ላይ ያደረበት ስጋት እና ፍርሃት ለቀቅ አድርጎት በተራው የደስታና የፈገግታ ምንጭ አደረበት፡፡

ወ/ሮ በሰልፏ "አናገረችህ? ተሽሎኛል አለችህ ? ልጄ አሉ፡፡ የደስታውን ምንጭ ለመስማት እየተጣደፉ፡፡

እናቱ መጣደፋቸው ለምን እንደሆነ ተረድቷቸዋል፡፡ "አዎ፤ በደንብ ባይሻላትም ከትላንቱ ትንሽ የተሻላት ይመስላል አለ፡፡

"እሰይ ደግ ትንሽ መናገር ከጀመረች ቶንሲሏ ተመልሶላታል ማለት ነው፡፡

፡"አሁን ከምንቀሰቅሳት ትንሽ ትተኛና ሞቅ ሲል ብትነሳ ይሻላል? ለቀቅ ያድርግ እኔም ለከብቶቹ የሚበላ ሰጥቼ ተመልሸ እመጣለሁ፡፡ አንችም የሚበላ ትናንት ካሰናዳሽላትም ቢሆን አዘጋጅላት፡፡ እንዴው ሳትበላ ጦሟን አደረች፡፡ እኔም እነ ፈጠነ ጋር በዛው ሔጄ ላሟ አላስጣለች እንደሆን ወተት ይዠላት እመጣለሁ፡፡ በባለፈው አጨዳ ለምኖኝ የሄድኩ ቀን ሲያልቡ አይቸ ነበር፡፡ ብሎ ተመልሶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡

ወ/ሮ በሰልፏ ቤታቸውን ቀጥፈው ባመጡት ቅጠል ጠራርገው ማገዶ የሚያመጣላቸው ስለሌለ አብዛኛውን ጊዜ የሚጠቀሙት በደከመ አቅማቸው ከዶሮ ተሻምተው በሚጠፈጥፉት የማገዶ ኩበት ነው፡፡

ኩበታቸውን ከተከመረበት መዘው እሳት አቀጣጠሉ፡፡ ውሃ አሙቀው ለእድላዊት ትላንት ካስተረፉት የስንዴ ዱቄት ትንሽ እንኳን ብትቀምስ ብለው ገንፎውን አገነፉላት፡፡ ልጃቸው እስከሚመጣ ቡና እያፈሉ እና ለእድላዊት መታጠቢያ ውሃ አሙቀው እንዳይፈጃት በቀዝቃዛ ውሃ ትንሽ በረዝ አደረጉት፡፡

"ልጄ ደህና አደርሽ ? እንዴት ነሽ ? ቶንሲልሽን ተሻለሽ ? አሉ፡፡ ወደ ተኛችበት እየተጠጉ፡፡

እድላዊት አቶ አርምዴን ካነጋገረችበት ሰዓት አንስቶ እመኝታ ላይ ትተኛ እንጅ እንቅልፍ አልወሰዳትም፡፡ የደረሰባትን ስቃይ እና መከራ በሃሳቧ እያወጣችና እያወረደች ለዚህ ሁሉ ስቃይና መከራ የዳረጓትን ቤተሰቦቿን እየረገመች በአንድ ፊት ደግሞ አቶ አርምዴን የእግዚአብሔር መላክተኛ ሆኖ እንዳዳናት እያመሰገነች ደህና አደርሽ ልጄ የሚል ድምፅ ሰማች፡፡

ከሄደችበት የሃሳብ ሰመመን ተመለሰች፡፡ "እግዚአብሔር ይመስገን ተሸሎኛል" አለች፡፡ አሁንም የሴት ይሁን የወንድ በማይለየው ድምፃዋ፡፡

ወ/ሮ በሰልፏ እስኪ ትንሽ ቀና በይ ሰውነትሽን ለቀቅ እንዲያደርግሽ፡፡ ፊትሽንና እጅሽን ታጠቢ ፤ እህልም አፍሽ አድርጊ፡፡ እዴው ምንም ሳትቀምሽ ጦምሽን አደርሽ፡፡ ብለው ስለደረሰባት ስቃይና መከራ ሲያስቡ አንጀታቸው አልችል አለ፡፡

እምባቸው በአይኗቻቸው ሞላ፡፡ እድላዊት እንባቸውን እንዳታይባቸው ፊታቸውን ዞር አደረጉ፡፡ በውስጥ ቀሚሳቸው ጠራርገው ፊታቸውን መለስ አድርገው "ተነሽ ልጄ" አሉ፡፡

እድላዊት እረኞቹ መሬት ለመሬት የጎተቷት ሰውነቷ ቆስሏል፡፡ ወገቧ ቀና ለማለት አልቻለም፡፡ እንደምንም ብላ ቀና አለች፡፡ ግን ወደ ውጭ መውጣት አልቻለችም፡፡ በተኛችበት መኝታ ላይ ቁጭ ለማለት ሞከረች፡፡

ወ/ሮ በሰልፏ እጇን አስታጠቧት፡፡ "ፊትሽን ቢያምሽም እንደምንም ብለሽ ታጠቢው ያበጠው እንዲለቅሽ ፤ አይዞሽ አሁን ይሻልሻል አሏት፡፡

እድላዊት ያሏትን እያመማት እጇ አልታጠፍ ቢላትም እንደምን ብላ ፊቷን ታጠበች፡፡

በደካማ አቅማቸው የሰሩላትን ገንፎ ብይ እስቲ ፣ አፍሽ አድርጊ ፣ አትፍሪ ሲሏት ሆድ ባሳት፡፡ የቀረበላትን ገንፎ ገና ሳትቀምሰው ሳይታወቃት አይኖቿ የእንባ ዘለላዎችን መፈንጠቅ ጀመሩ፡፡

ወ/ሮ በሰልፏ ለማፅናናት አልቻሉም፡፡ ከእድላዊት ብሰው እራሳቸው የእንባ ጎርፍ አዘነቡት፡፡ አሁንም በውስጥ ቀሚሳቸው እየጠራረጉ "አንችን አይዞሽ ማለቱን ትቼ እኔው አባባስኩሽ? እባክሽ እባክሽ ልጄ አፈር ስሆንልሽ አታልቅሽ እያሉ እድላዊትን ተማፀኗት፡፡

እድላዊት የወ/ሮ በሰልፏ ልመናና መንሰፍሰፍ ማልቀሷን አባባሰው፡፡ እንደምንም ለመቋቋም ሞከረች፡፡ እናንተንም አስቸገርኳችሁ ብላ ሌላም ሳትናገር አሁንም እንባዋ በአይኖቿ ግጥም አሉ፡፡

"እባክሽ ስለ ፈጠረሽ አምላክ ፤ በፈጠረሽ አታልቅሽ፡፡ ምንም አላስቸገርሽንም፡፡ ስለኛ ምንም አታስቢ፡፡ እግዚአብሔር እንኳን ነብስሽን አተረፈሽ፡፡ ብለው እድላዊትን ትንሽ ለማረጋጋት ሞክረው "እንዴው ከየት ነው አመጣጥሽ" ? አሉ፡፡

እድላዊት የመጣችበትን ለመናገር አልፈለገችም፡፡ ምን ማለት እንዳለባት አሰበች፡፡ ከሸንኮራ ዮሃንስ ፀበል ወደ ቤቴ ስመለስ ነው አለች፡፡

"እንዴው አብሮሽ የሚሔድ ሰው አልነበረም ? ቤተሰቦችሽስ ወዴት ናቸው ?

"ተሸሎኝ ስለነበር ሰው አያስፈልገኝም ብዬ ብቻዬን ነው የተነሳሁት፡፡ ቤተሰቦቼ ጉራንባ ውስጥ ናቸው" አለች፡፡

እድላዊት ትንሽ ተሸሏት ስታነጋግራቸው ከየት እንደመጣችና ወዴት እንደምትሄድ ጠይቀው ለማወቅ ቻሉ፡፡

"ገንፎውም ቀዘቀዘ እስኪ ትንሽ እንኳን ቅመሽ እባክሽ፡፡ እኔም እንዴው በወሬ ያዝኩሽ አይ! የኔ ነገር ብለው የጣዱትን ቡና ለማፍላት ሲመለሱ ልጃቸው ከቤቱ ተመልሶ የውጭውን በር ከፍቶ ገባ፡፡

"መጣህ ልጄ ቡናው ሲፈላ ደረስክ፡፡

አቶ አርምዴ እቤት እንደ ገባ እድላዊትን ከመኝታዋ ባትነሳም በመኝታዋ ላይ ተቀምጣ አያት፡፡ ደስ አለው፡፡

እንዴት ነሽ ? ተሻለሽ ? አላት፡፡ በጥዋት መጥቶ እንደጠየቃት ታስታውሳለች፡፡ "ከጥዋቱ አሁን ተሸሎኛል ደህናነኝ" አለችው፡፡

አቶ አርምዴ ለእድላዊት ብዙ ጥያቄ ሳያበዛባት ለእናቱ እንዴው ትንሽ ተሸሏት አነጋገረችሽ ? ከየት እንደመጣችስ ነገረችሽ ? አለ፡፡

"አዎ ፤ ትንሽ አነጋግራኛለች፡፡ ከሸንኮራ ዮሃንስ ፀበል እንደምትመጣና ወደ ቤተሰቦቿ እንደምትሔድ፡፡ ቤተሰቦቿም ጉራንባ ውስጥ እንደሚኖሩ ነጋራኛለች" አሉ፡፡ የቡና ቁርሱን እየሰጡት፡፡

አርምዴ ለእድላዊ አይዞሽ ሲሻልሽ እሸኝሻለሁ፡፡ ምንም አታስቢ፡፡ ይችም እናቴ ናት፡፡ የሚያስፈልግሽን ጠይቂያት ትሰጥሻለች፡፡ ብሏት ስራ ለመሔድ ስለቸኮለ እድላዊትን ለእናቱ አደራ ብሎ ተነስቶ ሔደ፡፡

እድላዊት አርምዴ ሲጨነቅላትና ሲያስብላት ትህትናው ልክ እንደወንድሟ እንደተመስገን ሆነባት፡፡...

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...34 ቀን ብቻ ነው የቀረው አዋጭ ነው ጀምሩት

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

አትሮኖስ

28 Dec, 13:00


#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አራት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ


ተመስገን

ከጠፋች በኋላ፤ ብቻ ሳይሆን ከእድላዊት ጋርም ከትምህርት ቤት መጥተው ምሳቸውን ከበሉበት ቀን አንስቶ ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ አይደለም አስቦትም አያውቅም፡፡

ወደ ትምህርት ቤትም አልሄደም፡፡ ትዳር የሚባል ሳያስብ እናት አባቱን እየረዳ የግብርና ስራውን ሌት ከቀን እየተጋ መዋሉን ተያይዞታል፡፡

ከሚወዳት እህቱ እድላዊት ውጪ የቅርብ ጓደኛዬ የሚለው ሴትም ይሁን ወንድ ለግዜው አልነበረውም፡፡ አንድ ቀን በስራ ምክንያት ከሰፈሩ ልጅ ያሬድ ጋር ይገናኛል፡፡ ታዲያ ተመስገንና ያሬድ ከዚህ በፊት ከእግዚአብሔር ሰላምታ በስተቀር የጠበቀ ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡

ያሬድ ተመስገንንም ይሁን ቤተሰቦቹን በደንብ ጠንቅቆ ያውቃቸዋል፡፡ በጥሩ ቤተሰብ ያደገና ከቤተሰቦቹ ጋር የሚኖር ገና ታዳጊ ወጣት ሆኖ በራሱ ፈቃድ
ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ግብርናው ከተሰማራ ሰንበትበት ብሏል፡፡

ከተመስገን ጋር ግንኙነታቸው ከእግዚአብሔር ሰላምታ አልፎ ወደ መቀራረብ ደረሰ ፤ አልፎ አልፎም ስራ በመተጋገዝ መረዳዳት ጀምረዋል፡፡

ተመስገን እንደ እህቱ የሚሆንለት ባያገኝም ለእሱ የሚሆንና የሚያበረታታው የቅርብ ጓደኛ በማግኘቱ ደስተኛ አድርጎታል፡፡

ከእለታት አንድ ቀን እነያሬድ ቤት የሽንብራ ቆሎ እየፈጩ ፤ ከስንዴው ጠላ ጎንጨት እያሉ የወደፊት ምኞታቸውና አላማቸውን ይጫወታሉ፡፡

"ለወደፊት ምን ለመስራት አስበሃል?" ብሎ ጠየቀው ተመስገን፡፡

"እኔ ለቀጣይ ያስብኩት አሁን የጀመርኩትን ቤት ስጨርስ ቤተሰቦቼ ትምህርትህን ከተወህ ማግባት አለብህ እያሉኝ ስለሆነ ለማግባት አቅጃለሁ፡፡ ብሎት አንተስ ምን አስበሃል? አለው ያሬድ፡፡

ተመስገን የወደፊት ምኞትና እቅዱ ከጓደኛው ያሬድ የተለየና ተቃራኒ ነው፡፡ "እኔ እንኳን እህቴን እስከማገኝ ድረስ ትዳር የመያዝ ሃሳብና ፍላጎት የለኝም"፡፡

ቤተሰቦቸን እየረዳሁ ለራሴም ትንሽ እያጠራቀምኩ ለመኖር ነው የማስበው አለ፡፡

ያሬድ የተመስገንን እቅድ ሲሰማ እህቱን በፊትም እደሚወዳት ስለሚያቅ ለምን አታገባም ብሎም አልጠይቀውም..፡፡

አርምዴ

ባለቤታቸው ከሞተ በኋላ፤ ሌላ ባል አላገቡም፡፡ ወደ ውጭ ወጥተው ጎንበስ ቀና ብለው መስራት አይችሉም፡፡

ልጃቸው ሰርቶ የሚሰጣቸውን እህል አብስለው ለመብላት ያልተቸገሩ የስልሳ ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ናቸው፡፡ የአርምዴ እናት ወ/ሮ በሰልፏ፡፡

ቀኑ እንደመምሸት ብሎ ለዓይን ያዝ አድርጓል፡፡ ኩራዝ ለመለኮስ ከምድጃቸው እሳት ለማቀጣጠል ይታገላሉ፡፡

አይናቸው ተርገበገበባቸው፡፡ ዛሬ ደግሞ በምሽት ምን ሊያሳየኝ ነው ፡፡ አይኔ የሚርገበገበው እያሉ የውጭ በር ተንኳኳ

እሳት ማቀጣጠሉን ተወት አርገው ወደ ውጭ ወጡ፡፡ ልጃቸው አርምዴ እድላዊትን አዝሎ ገባ፡፡ ደነገጡ፡፡

"ውይ! በሞትኩት ልጄ ምን ሆና ነው? ብለው ጠየቁት፡፡

እረኞች ጫካ ውስጥ መሬት ለመሬት ጎትተዋት ነው፡፡

"እና በጣም ጎድተዋታል" ?

"አዎ! ይዣትም ስመጣ ለማናገር ብሞክርም ማናገር አልቻለችም"፡፡

"ታዲያ ከየት እንደመጣችም አልነገረችህም"?

"አልነገረችኝም ፡፡ ጩኸት ሰምቼ እየሮጥሁ ሲሄድ ጥለዋት ተበታተኑ፡፡ እሷም ተጎድታ ስለነበር አላናገረችኝም፡፡ እንዴው እግዚአብሔር ድረስላት ሲለኝ ነው እንጂ ዛሬ አደን የሔድኩት ይገሏት ነበር፡፡

"አሁን ምን እንስጣት? ነው ትንሽ ትተኛ? ድካሟ እስከ ሚያልፍላት አሉ ወ/ሮ በሰልፏ፡፡

ወደ አስተኛት ፍራሽ ላይ ተጠጋ፡፡ እድላዊት አይኖቿን አንከራተተች፡፡ ግራና ቀኝ ተቁለጨለጨች፡፡

አርምዴ የእድላዊትን አይኖች መንከራተትና በእንባ መሞላት አየ፡፡ እሱም ከየት መጣ ሳይባል አይኖቹ በእንባ ተሞሉ፡፡

እድላዊት አርምዴን የምትመለከተው ውሃ ስጠኝ ለማለት ነበር፡፡ ግን መናገር አቅቷታል፡፡

አቶ አርምዴ ውሃ መፈለጓን የተረዳት አይመስልም፡፡ አንጀቱ እንደነብሰጡር ተላወሰ፡፡ እንባ እየተናነቀው "ምን ልስጥሽ " አላት፡፡

እድላዊት መናገር አልቻለችም፡፡ በእጇ ውሃ እንደ ጠማት አመለከተችው፡፡

አቶ አርምዴ በምልክት የገለፀችውን ሳያደናግረው ተረዳት፡፡ ውሃ ቀድቶ ሰጣት፡፡

ውሃው ወደ ውስጥ መግባቱን ትቶ ግራና ቀኝ በአፏ ወደ ውጭ ፈሰሰ፡፡

እድላዊት በውሃ ጥም የተነሳ ቶንሲሏ ወርዷል፡፡ አቶ አርምዴ የባሰ ተጨነቀ

"ውይ በሞትኩት ልጄን ውሃ አልወርድላት አለ ? ቶንሲሏ ወርዶ ይሆናል አሉ፤ ወ/ሮ በሰልፏ፡፡

"እና ምን ይሻላል? መድሃኒት በቅርብ አይገኝም? አለ ፤ አቶ አርምዴ፡፡

ወ/ሮ በሰልፏ የሃበሻ መድሃኒት ሊያቀምሷት መድሃኒቱን እንዲያመጣላቸው ልጃቸውን እንዳይልኩት መድሃኒቱ ሲቆረጥ ስሙ መጠራት የለበትም፡፡ እራሳቸው ለመቁረጥ ቆይ እስቲ መጣሁ ብለው ወደ ጓሮ ሄዱ፡፡

ለቶንሲል መድሃኒት የሚሆነውን ሰባት የጌሾ ቀንበጥ ቆርጠው አመጡ፡፡ ለእድላዊት እንድታኝከው ሰጧት፡፡

እድላዊት መናገር ቢያቅታትም መስማት ትችላለች፡፡ የተሰጠችውን የቶንሲል መድሃኒት አኝኪው ስለተባለች ብቻ

እየመረራት ቢሆንም ጨክና አኘከችው፡፡

በውሃ ጥም ምራቋ ደርቋል፡፡ ከንፈሮቿም ኩበት መስለዋል፡፡ ምላሷ ብቻ ብቅ ጥልቅ ይላል፡፡ ነብሷ ልትወጣ ደረሰች፡፡ ሰውነቷ በላብ ተዘፈቀ፡፡ ልቧ ተጨነቀች፡፡ በጀመረችው የምልክት ቋንቋ ውሃ ስጡኝ ብላ በእጇ አመለከተች፡፡

አቶ አርምዴ የእድላዊት ነገር አሁንም ግራ ገባው፡፡ ከሸንበቆ ላይ ቀጭን ሸንበቆ ተከርክሞ እድላዊት በሸንበቆው አማካኝነት ውሃ እንድትቀምስ ተደረገ፡፡

ለእድላዊት እንጀራ እንዳይሰጧት ችላ አትበላም፡፡ ምን እንደሚሰጧት ጨነቃቸው፡፡ የእድላዊት ነገር አንጀታቸውን በላው፡፡

በደከመ አቅማቸውም ቢሆን ትንሽ ገንፎ አገንፍተው እንድትቀምስ አደረጉ ወ/ሮ በሰልፏ፡፡

እድላዊት የተሰራላትን ገንፎ ለመድሃኒት ያህል ቀመሰች፡፡ ወ/ሮ በሰልፏ ለቶንሲሏ ሌላ መዳኒት ዝንጅብል እንድታኝክበት ሰጧት፡፡

"ለቶንሲል ጥሩ ነው፡፡ ለነገ በደንብ ይሻልሻል፡፡ አይዞሽ እያሉ ልጃቸው ያሰረላትን ጨርቅ ከቁስሏ ላይ ፈቱላት፡፡ ለብ ባለ ውሃ አጠቡላት፡፡ ያበጠውን እግርና እጇንም በቅባት አሹላት፡፡ የተላላጠውን ቁስሏንም በነጠላ ጨርቅ ተኩሰው መኝታ ላይ ጋደም እንድትል አደረጉ፡፡

አቶ አርምዴ የሚደረግላትን ካደረገ በኋላ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ አድሮ በነጋታው ጥዋት እድላዊት እንዴት እንዳደረች ለመጠየቅ ከመኝታው ተነስቶ ሲመጣ እናቱ የቤቱን በር ከፍተው ሲወጡ ደረሰ፡፡

የእግዚአብሔር ሰላምታ ተለዋውጠው "ደግሞ ማታ እመለሳለሁ ብለህ ሳትመጣ ቀረህ በሰላም ነው ያልተመለስከው? አሉት ወ/ሮ በሰልፏ፡፡

"ለመምጣት አስቤ ነበር፡፡ ግን ቤቱንና ከብቶቹን ትቼ እንዳልመጣ አውሬ እንኳን ቢገባ የሚሰማ ስላልነበረ ቀረሁ"፡፡ እንዴት አደረች ልጅቷ?ተሸሏት አላደረችም? አለ፡፡

የእድላዊት ስቃይና መከራ ከአንጀቱ ገብቶ ሳይወጣ አንጀቱ እያለቀሰላት እህል እንኳን አልወርድ ብሎት ለአደን ሲሄድ በቀመሰው ቁራሽ እንጀራ ነበር፡፡ እራት ሳይቀምስ ያደረው፡፡

ከአሁን አሁን ያማት ይሆን ? እያሉ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ ሳይወስዳቸው አይደለም በዓይናቸው ሳይዞር ነበር ያደሩት ወ/ሮ በሰልፏም፡፡

"ሰላም አድራለች፡፡ ብቻ ሌሊቱን ሲያቃዧት ነው ያደረው፡፡ አሟት ይሆን ብየ ሌሊት ተነስቼ ሳያት ከቅዠት በስተቀር ምንም አላየሁባትም፡፡ ከነጋም አልቀሰቀስኳትም፡፡ ቅዝቃዜ ስላለ ትንሽ ትተኛ ብየ ነው፡፡ እስኪ አሁን አንተ ከመጣህ ቀስቅሳትና እንዴት እንዳደረች ጠይቃት አሉ፡፡ ቤታቸውን ለመጥረግ የቤት መጥረጊያ ቅጠል ለማምጣት ወደ ውጭ እየወጡ፡፡

አትሮኖስ

26 Dec, 20:55


🔴 ሰበር ዜና ዛሬ ትምህርት ሚኒሰትር ያወጣው አዲስ ያልተጠበቀ መግለጫ   ‼️

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ ከስር open ሚለውን ይጫኑ 👇👇

አትሮኖስ

26 Dec, 20:45


🙏🙏ወላሂ ለአዚም አላህ ሻሂዴ ነው  ይሄን ቻናል ተቀላቅዬ ከድህነት ወጥቻለው እናንተም ተጠቀሙበት betting ምትጫወቱ  الوالد لأخيم الله شهيد ، انضممت إلى هذه القناة وخرجت من الفقر واستخدمته
https://t.me/+79_X7c3c-fU3YzU0
https://t.me/+79_X7c3c-fU3YzU0
https://t.me/+79_X7c3c-fU3YzU0

አትሮኖስ

26 Dec, 20:38


ፍቅር እስከ መቃብር

ዴርቶ ጋዳ

ዣንቶዣራ

ዝጓራ አንዲሁም የተለያዩ  pdfochen ይፈልጋሉ እንግዲያዉስ የፈለጉትን አማርጠዉ ያንብቡ📝📝📝📝📝

https://t.me/addlist/bQTU4Dm8CEBjYTE0

አትሮኖስ

22 Dec, 19:48


አትሮኖስ pinned «#የጣት_ቁስል ፡ ፡ #ክፍል_ሶስት ፡ ፡ #ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ እድላዊት ከወሰዳት የንቅልፍ ሸለብታ ነቃች፡፡ መኝታዋን ሳታነጥፍ ለምን እንደተኛች ግራ ተጋባች፡፡ የሆነውን እና የተፈጠረውን ነገር ሁሉ ለማስታወስ አንድ በአንድ ወደ ኋላ ተመልሳ በሃሳብ ነጎደች፡፡ የተነሳችበት ሰዓት ሳይነጋ እኩለ ለሊት ላይ ነው፡፡ ወዴት እንደምትሔድ ጨነቃት፡፡ ልቧ ሸፍቶ ጥፊ እያለ አስቸግሯታል፡፡ ለመጥፋት ወሰነች፡፡…»

አትሮኖስ

22 Dec, 17:00


እረኞቹ እድላዊትን ለቀው እግሬ አውጭኝ እያሉ ተበታተኑ፡፡ አቶ አርምዴ እረኞቹን ትቶ በደምና በአቧራ ተለውሳ ወደ ወደቀችው እድላዊት ተጠጋ፡፡ ጥልቅ ሃዘን ተሰማው፡፡ አይኖቹ እንባ ቋጠሩ፡፡
ከወደቀችበት አነሳት፡፡ አይዞሽ አይዞሽ አላት፡፡ ደፈሩሽ እንዴ ብሎ ጠየቃት፡፡ እድላዊት የዋለባት ውሃ ጥም ሳያንሳት ተጨማሪ በደረሰባት ጉዳት የድረሱልኝ ጩኸት ስትጮህበት የቆየችው ድምጿ ለመናገር ተሳነው፡፡ የሞት ሞቷን አልደፈሩኝም አለች፡፡

"ደብድበውሻል እንዴ" አላት፡፡ እድላዊት ግን መናገር አቃታት፡፡ መልስ አልሰጠችውም፡፡
እሱም ከእድላዊት መልስ አልጠበቀም፡፡ እረኞቹ ሲጎትቷት ደምቶ የነበረው ጉልበቷን የለበሰውን ሸሚዝ ቀዶ ደሟን ጠራርጎላት፡፡ በቀረው ጨርቅ ቁስሏን አሰረላት፡፡ እድላዊት እራሷን ችላ መሄድ አልቻለችም፡፡ የያዘውን መሳሪያ በፊት ደረቱ አንግቶ…..

ተመስገን

ከጠፋች በኋላ፤ ብቻ ሳይሆን ከእድላዊት ጋርም ከትምህርት ቤት መጥተው ምሳቸውን ከበሉበት ቀን አንስቶ ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ አይደለም አስቦትም አያውቅም፡፡

ወደ ትምህርት ቤትም አልሄደም፡፡ ትዳር የሚባል ሳያስብ እናት አባቱን እየረዳ የግብርና ስራውን ሌት ከቀን እየተጋ መዋሉን ተያይዞታል፡፡

ከሚወዳት እህቱ እድላዊት ውጪ የቅርብ ጓደኛዬ የሚለው ሴትም ይሁን ወንድ ለግዜው አልነበረውም፡፡ አንድ ቀን በስራ ምክንያት ከሰፈሩ ልጅ ያሬድ ጋር ይገናኛል፡፡ ታዲያ ተመስገንና ያሬድ ከዚህ በፊት ከእግዚአብሔር ሰላምታ በስተቀር የጠበቀ ግንኙነት አልነበራቸውም፡፡

ያሬድ ተመስገንንም ይሁን ቤተሰቦቹን በደንብ ጠንቅቆ ያውቃቸዋል፡፡ በጥሩ ቤተሰብ ያደገና ከቤተሰቦቹ ጋር የሚኖር ገና ታዳጊ ወጣት ሆኖ በራሱ ፈቃድ
ትምህርቱን አቋርጦ ወደ ግብርናው ከተሰማራ ሰንበትበት ብሏል፡፡

ከተመስገን ጋር ግንኙነታቸው ከእግዚአብሔር ሰላምታ አልፎ ወደ መቀራረብ ደረሰ ፤ አልፎ አልፎም ስራ በመተጋገዝ መረዳዳት ጀምረዋል፡፡

ተመስገን እንደ እህቱ የሚሆንለት ባያገኝም ለእሱ የሚሆንና የሚያበረታታው የቅርብ ጓደኛ በማግኘቱ ደስተኛ አድርጎታል፡፡

ከእለታት አንድ ቀን እነያሬድ ቤት የሽንብራ ቆሎ እየፈጩ ፤ ከስንዴው ጠላ ጎንጨት እያሉ የወደፊት ምኞታቸውና አላማቸውን ይጫወታሉ፡፡

"ለወደፊት ምን ለመስራት አስበሃል?" ብሎ ጠየቀው ተመስገን፡፡

"እኔ ለቀጣይ ያስብኩት አሁን የጀመርኩትን ቤት ስጨርስ ቤተሰቦቼ ትምህርትህን ከተወህ ማግባት አለብህ እያሉኝ ስለሆነ ለማግባት አቅጃለሁ፡፡ ብሎት አንተስ ምን አስበሃል? አለው ያሬድ፡፡

ተመስገን የወደፊት ምኞትና እቅዱ ከጓደኛው ያሬድ የተለየና ተቃራኒ ነው፡፡ "እኔ እንኳን እህቴን እስከማገኝ ድረስ ትዳር የመያዝ ሃሳብና ፍላጎት የለኝም"፡፡

ቤተሰቦቸን እየረዳሁ ለራሴም ትንሽ እያጠራቀምኩ ለመኖር ነው የማስበው አለ፡፡

ያሬድ የተመስገንን እቅድ ሲሰማ እህቱን በፊትም እደሚወዳት ስለሚያቅ ለምን አታገባም ብሎም አልጠይቀውም..፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...
ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

አትሮኖስ

22 Dec, 17:00


#የጣት_ቁስል


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

እድላዊት

ከወሰዳት የንቅልፍ ሸለብታ ነቃች፡፡ መኝታዋን ሳታነጥፍ ለምን እንደተኛች ግራ ተጋባች፡፡ የሆነውን እና የተፈጠረውን ነገር ሁሉ ለማስታወስ አንድ በአንድ ወደ ኋላ ተመልሳ በሃሳብ ነጎደች፡፡

የተነሳችበት ሰዓት ሳይነጋ እኩለ ለሊት ላይ ነው፡፡ ወዴት እንደምትሔድ ጨነቃት፡፡ ልቧ ሸፍቶ ጥፊ እያለ አስቸግሯታል፡፡ ለመጥፋት ወሰነች፡፡

መተኛቷን ትታ ቁጭ አለች፡፡ ወዴት እንደምትጠፋ እና ወዴት እንደምትሔድ አሰበች፡፡ ምን ይገጥመኝ ይሆን ? እንደገና ደግሞ ሃሳቧ እየተቀያየረባት ከምጠፋ ታንቄ ብሞት አይሻልም ? ሰርጌን ለመብላት ሲያደገድጉ በአቋራጭ ተስካሬን ይበሉ ነበር፡፡

ሃሳቧን እየቀያየረች ስታወጣና ስታወረድ ቆየች፡፡ አልሸነፍም ፤ አልረታም ፤ ለሞት እጄን አልሰጥም ብሎ የመጥፋት መንገድን የመረጠው ልቧ ሳይመለስ ቀረ፡፡ ሲገፋፋት ቆየ፡፡ ልቧ የመጥፋት መንገድን ማሸነፍ አልቻለም፡፡
ከሔደችበት የሃሳብ ሰመመን ተመለሰች፡፡ ሌሊቱ እየነጋጋ ነው፡፡ የታጠበውንም ፣ ያልታጠበውንም ልብሷን በፌስታል ሸከፈች፡፡ ቤተሰቦቿ ሳይሰሟት መውጣት እንዳለባት ወሰነች፡፡

መጥፋትን የወሰነችው እድላዊት መነሻዋን እንጅ መድረሻዋን አታውቅም፡፡ ጓዟን ጠቅልላ የእናት አባቷን ቤት እና የተወለደችበትን ቀዬ ለቃ ለመሄድ ተነሳች፡፡በሮቹን ድምፅ ሳታሰማ እና የተከፈቱ ሳታስመስል ግቢውን ለቃ ጨለማ በተቀላቀለበት ሌሊት ጉዞዋን አሃዱ አለች፡፡
ትንሽ እንደተጓዘች ጨለማው እየለቀቀና እየነጋጋ ሄደ፡፡ እለቱ እሁድ በመሆኑ በሩቅ ርቀት ላይ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲሔዱ ተመለከተች፡፡ የምትጓዝበትን መንገድ ትታ ሰው ሳያያት ለመሔድ ፈለገች፡፡ አማራጭ መንገድ በጫካ ውስጥ መረጠች፡፡ የአካባቢው ሰው እንዳያያት የጫካውን መንገድ ይዛ መጓዝ የግድ ሆነባት፡፡

እድላዊት ከቤት ስትወጣ ከልብሷ በስተቀር የሚበላ ስንቅ አልያዘችም፡፡ በጉዞው አድካሚነትና አሰልችነት የተነሳ እራባት፡፡ ውሃም እየጠማት መጣ፡፡ ምግብ የበላችበትን ሰዓት አስታወሰች፡፡ ከትምህርት ቤት  ከወንድሟ ጋር ስትመጣ የቀመሰች ነው፡፡ እራትም ሳትበላ ነበር ያደረችው፡፡

ድካሟ እየባሰባት መጣ፡፡ አረፍ ለማለት በምትጓዝበት ጫካ ውስጥ ወደ ሚገኝ አንድ ትልቅ ዛፍ ስር ተቀመጠች፡፡ ውሃ ጥሙ ግን እየባሰባት ሄደ፡፡ ካረፈችበት ዛፍ ስር ተነሳች፡፡እየተጓዘች በአይኖቿ መንደር እና ውሃ በአካባቢው እያፈላለገች ፣ እየቃኘች ስትሔድ ጫካ ከመሆኑ አንፃር ውሃና መንደር የሚባል በቅርብ ልታገኝ አልቻለችም፡፡ ታዲያ ማፈላለጓን አላቋረጠችም፡፡ ከምትሄድበት መንገድ ባሻገር ከብቶች ሲሔዱ ተመለከተች፡፡

ከብቶቹ ወደ ውሃ እንደሚሄዱ ገመተች፡፡ የያዘችውን መንገድ ለቃ ከብቶቹ የሚጓዙበትን መንገድ በመያዝ ተከተለች፡፡

እውነትም የገመተችው ትክክል በመሆኑ ከብቶቹ ውሃ ሲጠጡ አገኘቻቸው፡፡

እድላዊት የጠማትን ውሃ ለመጠጣት ከብቶቹ ከሚጠጡበት ከፍ ብላ ልትጠጣ ተቀመጠች፡፡ የሚያንጎራጉር እና የፉጨት ድምፅ ሰማች፡፡ውሃውን ሳትጠጣ የሚያንጎራጉረውን የሰው ድምፅ ከየት አቅጣጫ እንደሆነ ለመለየት በአይኖቿ አማተረች፡፡
የእንጉርጉሮው ድምፅ እየቀረባት መጣ፡፡ ፍራት ፍራት ተሰማት፡፡ የዛሬን አውጣኝ ከዚህ ጫካ እያለች ፈጣሪዋን እየተማፀነች ፤ እየተርበተበተች አብዝታ ለመነች፡፡
የሚያንጎራጉረው የእንጉርጉሮው ድምፅ ከብቶች የሚያጠጡ እረኞች ነበሩ፡፡

እድላዊት እረኞቹን ፈራች፡፡ የመውጫዋን እና የማምለጫ መንገዷን ፈለገች፡፡

ከብቶቹን ከሚያጠጡት ሁለት እረኞች መካከል አንዱ ከበደ የሚባለው እረኛ እያንጎራጎረ ወደ ወንዙ ቀና አለ፡፡ አንድ የተቀመጠ ሰው ተመለከተ፡፡
ለጓደኛው ደበበ ያየውን ሰው ያ ማነው ? እዛ ላይ የተቀመጠው? አለ፡፡ ደበበ ጓደኛው እንዳለው ወደ ላይ ቀና ብሎ አየ፡፡ ቁጭ ያለ ሰው ተመለከተ፡፡

"ውሃ የሚጠጣ ሰው ይሆናል" አለው ለጓደኛው፡፡

እድላዊት እረኞች በእጃቸው እየተጠቋቆሙ ሲመለከቷት የባሰ ፈራች፡፡ በድንጋጤ እንደጠማት ልትጠጣ በእጇ የጨለፈችውን ውሃ እንኳን ሳትጠጣ ተነሳች፡፡ ቁጭ ብላ ከእረኞቹ ማምለጫ ስታማትር ወደ አገኘችው መውጫ መንገድ ተነስታ ለማምለጥ ሞከረች፡፡
እረኞቹ እድላዊትን ወንዝ ላይ ተቀምጣ ሰው ከመሆኗ ውጪ ወንድ ይሁን ሴት ትሁን አላወቋትም ነበር፡፡

እድላዊት ውሃ ለመጠጣት ከተቀመጠችበት ተነስታ ስትሮጥ ተመልክተው ሴት መሆኗን ለይዋት ፤ ከብቶቻቸውን ማጠጣታቸውን ትተው በእድላዊት መልክና ውበት እየተገረሙ በአይናቸው ተከትለው ሸኟት፡፡

አይን ለአይን እየተያዩ፡፡ የማነች ቀሽት ባክህ! ስታምር ፤ ከየት ይሆን የምትመጣው?

እውነትም ቀሽት ናት፡፡ ደግሞ እየፈራች ነው ፣ የምትሔደው፡፡ ምን ያገላምጣታል;

እረኞቹ እድላዊት ስትርበተበት አይተዋት ፤ ብቻዋንና የተከተላት ሰው አለመኖሩን ነቅተውባታል፡፡ይች ቀሽት ሳታመልጠን እንከተላት ተባባሉ፡፡ መጀመሪያ በአይናቸው ሸኝተዋት ቢመለሱም ልባቸው ግን ተከትሏት ነበር፡፡ እየተጣደፉ
እንዳታመልጣቸው በሔደችበት መንገድ ተከተሏት፡፡ እድላዊት የልቧ ትርታ ጨመረ፡፡ ሰውነቷ ሁሉ እየተንቀጠቀጠ፡፡ ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ አለ፡፡ ይከተሉኝ ይሆን ብላ ተጠራጠረች፡፡ እንዴው አምላኬ
የዛሬን አውጣኝ፡፡ ከዚህ ከጨለማ፡፡ እያለች እንዳይደርሱባት በደከመ አቅሟ ለመሮጥ ሞከረች፡፡ ለእሷ የሮጠች መሰላት፡፡ ዳገቱ ግን ሊገፋላት አልቻለም፡፡ መልሶ ወደ መጣችበች ይገፈትራት ነበር፡፡ በአይኖቿ ወደ ኋላ፤ እየተመለሰች ብትገላመጥም የጠረጠረችው እና የፈራችው አልቀረም ፡፡ ባልጠበቀችው አቅጣጫ ሁለቱም እረኞች ከላይ እንደመጣ የመብረቅ ነበልባል ሆነው ደረሱባት፡፡

እድላዊት መሬት ተከፍታ ብትውጣት እንዴት በተደሰተች ነገር፡፡ ግን መሬት ተከፍታ ልትውጣት አልቻለችም፡፡ በድንጋጤ ሰውነቷ ተርበተበተ፡፡ ላብ በላብ ሆነች፡፡ እረኞቹ ግን የሚተዋትና የሚያዝኑላት አይመስሉም፡፡

ገና ሳይዟት ከነ ነብሷ የሚውጧት ነበር የሚመስሉት፡፡ አንበሳ አፍ ውስጥ እንደገባ ስጋ እንደሆነች ታወቃት፡፡

እረኞቹ ከመንገድ ላይ እጆቿን ይዘው ወደ ጫካ ጎተቷት፡፡ ማምለጥ አልቻለችም፡፡ ነብስ ዝም ብላ ከስጋ እስከ ምትለይ መፈራገጧን አተውም እና እድላዊትም እየጮኸች ባላት አቅም እየተፈራገጠች ጩኸቷን አባረቀችው፡፡

ዘመድና ወገን እንደሌላት መሬት ለመሬት ነብሱ እንደወጣ የአህያ እሬሳ ጎተቷት፡፡ ያ የሚያምረው ለግላጋና ማራኪ ውበቷ በደምና በአቧራ ተለወሰ፡፡
ከሴት ልጅ እንዳልተፈጠሩ እናትና ሴት እህት እንደሌለው ሰው ጭካኔ በተሞላበት አረመኔያዊ ድርጊት ለወሷት፡፡ መንገዱን አስለቅቀው ጫካው ውስጥም አስገቧት፡፡

እግዚአብሔር የእድላዊትን ስቃይና መከራዋን አይቶ ፤ የመማፀኒያ ልመናዋን ሰምቶ ፤ መላክተኛውን የሚካኤል አምሳያ ላከላት፡፡

አደን እንኳን ወጥቶ አያውቅም፡፡ አቶ አርምዴ የሚባል ሚንሻ፡፡ እድላዊት በአረመኔዎቹ እረኞች ተይዛ በምጮህበት በረሃ አካባቢ ነበር፡፡ አንድ አሳቻ ቦታ ተቀምጦ የሚያድነውን አውሬ እየፈለገ፡፡ በጫካው ውስጥ የሴት ልጅ ጩኸት ሰማ፡፡ ተነስቶ ወደ ጩኸቱ እሮጠ፡፡ ሁለት ልጆች እድላዊትን መሬት ለመሬት እየጎተቷት ደረሰ፡፡

አትሮኖስ

21 Dec, 18:41


አትሮኖስ pinned «#የጣት_ቁስል ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ #ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ ቄስ አሻግሬ ሔደውልኝ ይሆን? ዛሬ ደግሞ ማርያም ናት፡፡ ቅዳሴ ይኖርባቸው ይሆን? ለነገሩ ቅዳሴ እንኳን ከሰዓት ነው፡፡ ቀኑ ዕሮብ አይደለም ምናልባት ጠዋት ሄደውልኝ ይሆናል፡፡ ለማንኛውም እኔም ማህበር ስላለኝ እዛው ቤተ ክርስቲያን አገኛቸዋለሁ፡፡ ከማህበር ስንወጣ እጠይቃቸዋለሁ፡፡ ብሎ ከሰው ጋር ባይይሆንም ከራሱ ሃሳብ ጋር የተናገረው…»

አትሮኖስ

21 Dec, 18:06


#የጣት_ቁስል


#ክፍል_ሁለት


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

ቄስ አሻግሬ

ሔደውልኝ ይሆን? ዛሬ ደግሞ ማርያም ናት፡፡ ቅዳሴ ይኖርባቸው ይሆን? ለነገሩ ቅዳሴ እንኳን ከሰዓት ነው፡፡ ቀኑ ዕሮብ አይደለም ምናልባት ጠዋት ሄደውልኝ ይሆናል፡፡ ለማንኛውም እኔም ማህበር ስላለኝ እዛው ቤተ ክርስቲያን አገኛቸዋለሁ፡፡ ከማህበር ስንወጣ እጠይቃቸዋለሁ፡፡ ብሎ ከሰው ጋር ባይይሆንም ከራሱ ሃሳብ ጋር የተናገረው ነበር፡፡ አቶ ለማ ሽፈራው፡፡

ከቅዳሴ የመውጫ ሰዓት ስለደረሰ ጋቢውን ለባብሶ ተነሳ፡፡ ወደ ጉራንባ ማርያም ቤተክርስቲያን ጉዞውን ቀጠለ፡፡

ቄስ አሻግሬ አማላጅነቱ ሙሉ በሙሉ ተሳክቷል ባይባልም በተወሰነ መልኩ ተስፋ የሚሰጥ መልስ በማግኘታቸው ተደስተዋል፡፡ ወደ ቤታቸው ከተመለሱ በኋላ ከሰዓት ቅዳሴ ስለነበረባቸው ብዙም ሳይቆዩ ተነስተው ወደ ጉራንባ ማርያም ቤተክርስቲያን ጉዞዋቸውን አቀኑ፡፡

አቶ ለማ ከቅዳሴ ሲወጡ ደረሰ፡፡ ቄስ አሻግሬን ለማናገር ከማህበር በኋላ ሊመሽ ስለሚችል ዛቲ እንደቀመሱ ማናገር እንዳለበት አሰበ፡፡ ከዛቲ እንደተበተኑ ካህናት ከቅዳሴ ወጥተው ወደ ተቀመጡበት ቦታ ሔደ፡፡

"ሰላም ዋሉ ቄስ አሻግሬ” ፡፡

"እግዚአብሔር ይመስገን ሰላም ዋልህ?፡፡ ለማ" ብለው አጠፌታ መልስ ሰጥተውት መስቀል አሳለሙት፡፡ "ዛሬ ማርያም መጥተህ ኖሯል፡፡ መሃበር አለህ ለካስ" አሉ፡፡

"አዎ፤ ማህበር አለኝ"፡፡ ብሎ በቀጥታ ለማናገር ወደ ፈለገው ጉዳይ ገባ፡፡ "እንዴው እዛ ጉዳይ ጋር ሔደውልኝ ነበር ?"፡፡

"አዎ፤ ሔጀ ነበር፡፡ ያው! መቼም በአንዴ እሽ እንደማይባል አንተም ታውቃለህ፡፡ ለማንኛውም ለዛሬ አስራ አምስት ቀን ቀጥረውኛል፡፡ ቁርጡ ያኔ ይታወቃል" ::

"ቀጠሮ መስጠታቸውም ጥሩ ተስፋ ነው፡፡ እና እርሶንም በጣም አመሰግናለሁ"፡፡ ብሎ የማህበር ሰዓት ስለደረሰባቸው ወደየ ማህበራቸው ገቡ፡፡

አቶ ለማ ከማህበሩ እንደወጣ ወደ ቤቱ እየሔደ ፤ እንዴው እሽ ባለኝ፡፡ ልጅቷ ጎበዝ ተማሪ እና ጨዋ እንደሆነች መቼም አገር ነው የሚያወራላት፡፡ ፀባይዋም ቢሆን ምንም አይወጣላትም ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ እንዴው በተሳካልኝ፡፡ ሰዎች ስለእድላዊት መልካምነት ሲያወሩ የሰማውን ሁሉ በሃሳቡ እየደጋገመ እና እያወራ ሳይታወቀው እቤቱ ደረሰ፡፡

"ምነው ዛሬ ደግሞ አመሸህ? ማህበሩ ቶሎ አላለቀም እንዴ?" አለ አበበ ላባቱ፡፡

"አዎ፤ ዛሬ ደግሞ ቶሎ ወደ ማህበር አልገቡም ነበር፡፡ ማህበረተኛውም የት እንደ ሄደ እንጃ ፤ጠላውም አላልቅ ብሎን እኔም ይመሽብኛል ብየነው ፤ ሳያልቅ ትቸው ነው የመጣሁት"፡፡

ከዛቲ መልስ ቄስ አሻግሬንም አግኝቻቸው ነበር፡፡ እቄስ መልካሙ ጋር እንደ ሔዱልኝ እና የድጋሜ ቀጠሮውም ለዛሬ አስራ አምስት ቀን እንደቀጠሯቸው ነገሩኝ" አለው፡፡

አበበ ለእድላዊት አማላጅ እንደላከለት ሲነግረው በጣም ወደር የሌለው ደስታ ተሰማው፡፡ ለማግባት የሚያስፈልገውን ነገር ማሟላት እንዳለበት በመወሰን የጀመረውን የቤት ስራ ለመጨረስ እየተጣደፈ ነው፡፡

እድላዊት ግን እሽ ትበለውም አትበለውም ባያውቅም ማድረግ የሚችለውን ሁሉ እያደረገ ባለበት ሰዓት በህሊናው አንድ ሃሳብ ያቃጭልበታል ?

ተመስገን

ሊነጋጋ ሲል የወሰደው እንቅልፍ ተጫጭኖት ቶሎ አልተነሳም፡፡ ለትምህርት ከሚነሳበት ሰዓት አርፍዶ ነው የተነሳው፡፡ የእድላዊት ባል ማግባት እና ከትምህርት መቅረት እውነት ሆኖ ቀረ ማለት ነው?፡፡ እውነት ባይሆንማ ኖሮ ሳትቀሰቅሰኝ ባልቀረች ነበር፡፡ ከራሱ ጋር እያወራ ከመኝታው ተነሳ፡፡ ሽንት ቤት ተፀዳድቶ ተመለሰ፡፡

እናቱን ከቤት ሲወጡ እበር ላይ አገኛቸው፡፡ እንደማይተዋወቅ ሰው የእግዚአብሔር ሰላምታ ሳይለዋወጡ ተላለፉ፡፡ የቤተሰቦቹ ድርጊት እና እርህራሔ የሌለው ውሳኔ ያስከፋው ተመስገን ለማነጋገር አይደለም የሚጨክን አንጀት እና አቅም ቢኖረው ቤተሰቦቹን በደበደባቸው ነበር፡፡

ወደ እድላዊት መኝታ ቤት አመራ፡፡ የቤቱ በር ከውስጥ የተዘጋ መስሎ ገርበብ ብሏል፡፡ እስካሁን ያልተነሳችው አሟት ቢሆን ነው፡፡ የቤቱን በር አንኳኳው፡፡ መልስ የሚሰጥ አላገኘም፡፡ ደጋግሞ በሩን ተመለከተ፡፡ ከነጋ የተከፈተ አይመስልም፡፡
ደግሞ ለማንኳኳት ሰውነቱን ከነከነው፡፡ ውስጡ ፍራት ፍራት ተሰማው፡፡ እጆቹም ተንቀጠቀጡ፡፡ የሚሆነው ሁሉ ጠፋበት፡፡ ከውስጥ አልተዘጋ ይሆን እንዴ? ተጠራጠረ፡፡ በሩን ማንኳኳቱን ትቶ የሞት ሞቱን ገፋው፡፡ መዝጊያው ከውስጥ ምንም የያዘው ነገር ባለመኖሩ ተከፈተ፡፡ በፍርሃት ወደ ውስጥ ገባ፡፡

ከአልጋ በስተቀር እድላዊት አይደለችም ፤ የእድላዊት ልብስ እንኳን አላገኘም ነበር፡፡ የህሊና ፀሎት እንደሚያደርስ ሰው ቆሞ የስልክ እንጨት መሰለ፡፡ ደቂቃዎች አልፈው ከወሰደው የድንጋጤ ሰመመን ባነነ፡፡ በቀጥታ ወደ እናት አባቱ ቤት ሄደ፡፡ እድላዊትን የት ሄደች ? ብሎ እናቱን ጠየቀ፡፡

ወ/ሮ አሰገደች የሚናገሩት ፣ የሚያነሱት ፣ የሚቧጥጡት አጡ፡፡ የት ሔደች? የለችም መኝታዋ ላይ ፤ እንደፎከረችው አደረገችው ማለት ነው፡፡ ወይ ጉዴ! እያሉ ከተመስገን መልስ ሳይጠብቁ ኡኡታቸውን አቀለጡት፡፡

የአካባቢው ሰውና ጎረቤቱ ምን ደረሰባቸው? ምን አጋጥሟቸው ይሆን?፡፡ እየተሯሯጡ ግቢው ሰው በሰው አጥለቀለቁት፡፡ታዲያ የሰው መዓት ቢሰበሰብ እና እሪ እየተባለ ቢጮህም እድላዊት ልትገኝ አልቻለችም፡፡ ኡኡታ
ሰምተው ከመጡት ሰዎች መካከል ወ/ሮ ስንዱ "የት ትሔዳለች ፤ ከዚህ በፊት ከቤት ወጥታ አታውቅም፡፡

ወደ ዘመዶቿ ሔዳ ይሆናል፡፡ ሰው ልኮ ማጠያየቅ ነው" አሉ፡፡

ወ/ሮ አሰገደችን ለማረጋጋት ቢሞክሩም ወ/ሮ አሰገደች ግን የሚረጋጉ አይደለም፤ ጨርቃቸውን ጥለው የሚያብዱ ነበር የሚመስሉት፡፡

ቄስ መልካሙ በድንጋጤ የተነሳ የሚጮኸውን ጩኸት የራሳቸው ችግር አይደለም፤ ለተመለከታቸው ሰው ከነጭራሹም ጩኸቱን የሰሙት አይመስልም ነበር፡፡

ጎረቤት የሆኑት አቶ ማን ችሎት ማን ያዝልሃል፡፡ ቄስ መልካሙን ለማነጋገር እና የተፈጠረውን ለመጠየቅ ቢሞክሩም ቄስ መልካሙ አይናቸውን ከማቁለጭለጭ ውጭ መልስ የሚባል ለመመለስ አይደለም ከነጭራሹም ለመናገር አቅቷቸው ነበር፡፡ ተመስገን ከእናት አባቱ የተሻለ ቢሆንም ሰው የሚጠይቀውን ጥያቄ ግን እሱም መመለስ አልቻለም፡፡

የተሰባሰቡት ሰዎች ሁሉ የሚያደርጉት ጠፋቸው፡፡ ከመካከላቸው አንድ ሰው መኮንን ሃይሌ የሚባል ተነሳ

"አሁን ሁላችንም አብሮ ማጃበሩን እና ማልቀሱ ዋጋ ያለው አይመስለኝም፡፡ እነሱን አረጋግተን መላ ብንፈልግ የሚሻል ይመስለኛል፡፡ ብሎ ሃሳብ ሰነዘረ፡፡ የተሰበሰበው ሰው በሃሳቡ ተስማምቶ ወሮ አሰገደችንና ባለቤታቸውን አረጋግተው እድላዊትን ፍለጋ በየ አቅጣጫው ሁሉም ሰው ተበታተነ፡፡

እድላዊት ግን በዘመዶቿ ቤት አይደለም በዱር በገደሉም ልትገኝ አልቻለችም፡፡ ከጠፋችበት ቀን አንስቶ አየናት፡፡ በዚህ አልፋለች የሚል አይደለም የበላት ጅብ እንኳን ሊጮህ አልቻለም፡፡

ቄስ መልካሙ በልጃቸው መጥፋት ጥልቅ ሃዘን ተሰማቸው፡፡ እድላዊት ትሙት ትኑር ሳያውቁ "አይ! አንተ ሰማይ እና ምድርን የፈጠርህ ጌታ እንደዚህ በቁሜ እንዳዋረደችኝ እና እንዳሰቃየችኝ በቁሟ የሚያዋርድ ይስጣት፡፡ የፈጠሯትን ልጅ አምርረው ረገሟት፡፡

አትሮኖስ

21 Dec, 18:06


ተመስገን እህቱን ፍለጋ እንደወጣ ቶሎ አልተመለሰም፡፡ እየተንከራተተ አንዴ እራራቲ ፤ አንዴ ዶፋ ፤ አንዴ ብቻሽ እና በየቤተክርስቲያኑ እየዞረ ቢጠይቅም ቢያጠያይቅም ፤ ቢያስስም ፣ ቢያሳስስም እድላዊትን ግን ሊያገኛት አልቻለም ነበር፡፡ ተንከራቶ እህቱን ባለማግኘቱ በጣም አዘነ፡፡ የተፈጠረበት ቀን እስከ ሚያስጠላው ድረስ አምርሮ ረገመ፡፡ እያለቀሰ ቢውልና ቢያድርም የሱን እንባ እድላዊት ልትሰማለት አልቻለችም፡፡

እድላዊት እና ተመስገን ትምህርት ቤት እንኳን ሲሔዱ አንድ ቀንም ተለያይተው አያውቁም ነበር፡፡ በጣም ሲዋደዱ እና ፍቅራቸውን ላየ የሚያስቀኑም ልጆች ነበሩ፡፡

ተመስገን እህቱን ፍለጋ ሲወጣ በቅርብ የሚመለስ መስሎት ስንቅ እንኳን አልያዘም፡፡ እርሃብ ሲብስበት እና ሲጠናበት ከሰው ቤት እዳይለምን እፍረት እየያዘው ሳይጠይቅ ሲርበው ውሎ ሲርበው ያድራል፡፡ ለማደር ሲፈልግ ፀበለተኛ መስሎ ሲመሽበት ወደ አገኘው ቤተክርስቲያን ይሄዳል፡፡ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና ፀበለተኞች ከያዙት ስንቅ አካፍለውት በልቶ ሳይሆን ቀምሶ ያድር ነበር፡፡

ታዲያ የሚያውቀውንም ፣ የማያውቀውንም ፣ አገር አካሎ ከመድከም ውጭ ምንም ባለ ማግኘቱ ሲንከራተት ከርሞ ወደ ቤቱ ለመመለስ ሲያስብ የእናት አባቱን አይን ለማየት አስጠልቶት እኔም እንደ እድላዊት ብን ብየ በዚሁ ልጥፋ ወይስ ገደል እና ውሃ ውስጥ ገብቼ ብሞት ይሻላል፡፡ በውስጡ የተሰማውን ተናግሮ ሳይጨርስ ልቡ በሌላ ሃሳብ ይቀየርበታል፡፡ እህቴን ሳላያት ከምሞት ከቤት ከወጣሁ ቆይቻለሁ፡፡ ምን አልባት ተመልሳ እቤት መጥታ ሊሆን ይችላል፡፡ ብሎ በማሰብ ከራሱ ሃሳብ ጋር ሲሟገት እና ሲከራከር ቆይቶ ወደ ቤቱ ለመሔድ ወሰነ ።

ተመስገን ጉዞ ላይም እያለ በሃሳቡ ስለ እህቱ ማብሰልሰሉን ይሁን መጨነቁን አላቋረጠም፡፡ ምነው ያን እለት ማታ ባናግራት፡የምትሔድበትን እንኳን ትነግረኝ ነበር፡፡ ለእኔ አትደብቀኝም ነበር፡፡ ይሔ ሁሉ ስቃይና መንከራተትም አይደርስብኝም ነበር፡፡ ያለፈው እያናደደው ሲጓዝ መድረስ አይቀርም እቤቱ ደረሰ፡፡

እናት እና ልጅ ለብዙ ቀን ተለያይተው እንዳልቆዩ አብረው እንደከረሙ እና አብረው እንዳደሩ ሰላም እንኳን አልተባባሉም፡፡ በቀጥታ እድላዊት አልመጣችም እንዴ?" አላቸው፡፡ እልህ እና ንዴት በተቀላቀለበት አንደበት፡፡

"አይ! ልጄ ከየት ትመጣለች፡፡ እሳት የገባ ቅቤ ይታፈሳል እንዴ? እግዚአብሔር ባያድለኝ ነው እንጅ፡፡ ምነው እንዳሁኑስ የነገርኳት እለት ሞቴን ቢያደርግልኝ ይሻል ነበር"፡፡ እስካሁን በሔድህበት ቦታ እና አካባቢ ምንም ወሬዋን አልሰማህም ? አየኋት ፣ አልፋለች የሚል ሰው ጠፋ ልጄ? "አሉት፡፡ የአይናቸውን እንባ እየጠራረጉ ፡፡

ተመስገን ከእናቱ የሰማው መልስ ተስፋ አስቆረጠው፡፡ እድላዊት ወደ ቤት መታ እቤት አገኛታለሁ ያለው ሃሳብ አልተሳካለትም፡፡ መጓጓቱ እና ማሰቡ ከንቱ ሆነ፡፡ እንዳትገኝ አድርጋችሁ ከሸኛችኋት በኋላ፤ ማንስ አየሁ ይለኛል ? የትስ አገኛታለሁ?"፡፡

ወደ ቤት ሲመጣ እመንገድ ላይ እህል አምጣ እያለ እንደ አዲስ መሬት ያስቸገረው ሆዱ እቤት ሲገባ እድላዊትን ባለማግኝቱ በንዴት እና በብስጭት የራበው ሁሉ ጠፋ፡፡

ወ/ሮ አሰገደች የልጃቸው ብሶትና ብስጭት ተሰማቸው፡፡ ሳይታወቃቸው በግራና በቀኝ ጉንጫቸው ላይ እንባቸው እንደ ሃምሌ ዝናብ መውረዱን ተያያዘው፡፡ ታዲያ እንባቸው ሲወርድ ላየው ሰው ወላድ መሆን አይደለም ሰው መሆንም ያስጠላ ነበር፡፡ ደግመው ለመናገር እንባ ተናነቃቸው፡፡ መናገር አልቻሉም፡፡ አንደበታቸው ተሳሰረ፡፡ ከተቀመጡበት ተነሱ፡፡ እንባቸውን በቀሚሳቸው እየጠራረጉ ወደ ጓዳ ሊገቡ ሲሉ ራሳቸውን አዞራቸው ፤ ከቤቱ ግድግዳ ጋር ተላተሙ፡፡

ተመስገን እናቱ በልጇ መጥፋት ሆድ እንደባሳቸውና በሃዘን እንደ ተጎዱ ታወቀው የእድላዊት መጥፋት ሳያንሰው የእናቱ እንደዚህ መሆን የባሰ ስቅስቅ አድርጎ አስለቀሰው፡፡

ከተላተሙበት የቤት ግድግዳ ተመለሱ፡፡ እንደገና አዙሯቸው የቤቱ ወለል ላይ ወደቁ፡፡ ከወደቁበት ሳይነሱ

ጆሮ ግንዳቸውን በቀኝ እጃቸው ደግፈው አቀረቀሩ፡፡ ምን ነክቷቸው ከግድግዳ እንደተላተሙ ለማስታወስ እየሞከሩ ፤ ካቀረቀሩበት ቀና ሲሉ ልጃቸው እያለቀሰ አዩት፡፡ ማፅናናታቸውን ትተው ያቋረጡት ለቅሶ ተያያዙት፡፡

ቄስ መልካሙ ከስራ ቆይተው ሲመለሱ ቤቱ በሃዘን እና በለቅሶ ተሞልቷል፡፡ "ምንድነው ለቅሶው ; ልጄ መሞቷ ተሰማ እንዴ ? ምን ተፈጥሮ ነው "አሉ፡፡ አይኖቻቸው ላይ የእንባ ብዥታ እየታየባቸው፡፡

"የልጄን መሞት እማ ብሰማ አንዴ አልቅሼ እና እርሜን አውጥቸ አርፍ ነበር"፡፡ የገባችበትን እና የበላትን ጅብ አለመጮሁ ነው እንጅ ፤ የሚያስለቅሰኝ" አሉ ፤ ወ/ሮ አሰገደች፡፡

ተመስገን አባቱ ሲመጡ ማልቀሱን ባያቋርጥም እያለቀሰ በአባቱ ፊት መቆየት አልፈለገም፡፡ እረስቷት ወደ ሰነበተው የመኝታ ቤቱ ተነስቶ ሄደ፡፡

"ተመስገን ምን አለሽ ? እንዴው ወሬዋን እንኳን የሰማ ሰው አላገኘም ? አሉ ፤ ቄስ መልካሙ ለባለቤታቸው ፡፡

"ያየ አይደለም ሰማሁ የሚልም አላገኘም፡፡ እሱም እንዴው ሲንከራተት ከርሞ ይሔው ሰውነቱ አልቆ መጣ፡፡ እኔ ደግሞ ሲሰነብት ጊዜ በዛው ሔደ ብየ ፈርቼ ነበር፡፡ እግዚአብሔር እንኳን ፊቱን ወደ ቤት መለሰልኝ" እንጅ ፡፡ቄስ መልካሙ ልውጣ ልውጣ እያለ ሲተናነቃቸው የነበረውን እንባ በጋቢያቸው ጠራርገው መለሱት፡፡

"ምን እናደርጋለን ታዲያ እንግዴህ አንዴ ሲፈጥረን ተሰቃዩ ብሎን የለ፡፡ የእኔ መሞቻ የቀረው እናት አባቴን ያጣሁ ዕለት ነበር"፡፡ ምነው ያኔ ከነሱ ጋር ሞቴን ብታደርግልኝ፡፡ ምን አለ ፈጣሪየ ፣ ምን በደልኩህ ; ምንስ አልኩህ ? የአንተ አገልጋይ እንኳን ነበርኩ፡፡ ስቃየን እነደዚህ ባታበዛብኝ ምን ? አለ"፡፡

መጀመሪያ ልውጣ ልውጣ እያለ ሲተናነቃቸው የነበረውን እንባ በጋቢያቸው ጠርገው ቢመልሱትም አሁን ግን ገፍቶ መጥቷል፡፡ ሊመልሱት አልቻሉም፡፡ የተናነቃቸውን እንባ ዘረገፉት፡፡

ቄስ መልካሙ በምንጃር አውራጃ ውስጥ ጉራንባ ማርያም በሚባል ጎጥ ተወልደው ባደጉበት አካባቢ የድቁና ትምህርታቸውን በጉራንባ ማርያም ቤተክርስቲያን እየተከታተሉ ባሉበት ሰዓት ነበር፡፡ እናት አባታቸውን በመብረቅ አደጋ በሞት የተነጠቁት፡፡ ለእናት አባታቸው አንድ ልጅ ብቻ ነበሩ፡፡ እናት አባታቸው ከሞቱባቸው በኋላ ፤ ያላሳዳጊ ብቻቸውን በባዶ ቤት ሲሰቃዩ ቆይተው ከአራት አመት እንግልት በኋላ፤ ነበር፡፡ ወ/ሮ አሰገደችን አግብተው ተመስገንን እና እድላዊትን ማፍራት የቻሉት፡፡

ታዲያ ተመስገን የመጀመሪያ ልጃቸው ሲሆን እድላዊት ሁለተኛ ልጃቸውም ነበረች፡፡

"በቃህ! አይበቃህም ወይ! ለቅሶ አልነው ፤ አልነው፡፡ እድላዊት በለቅሶ የምትመጣ ቢሆን እስካሁን ባልቆየች ነበር፡፡ የባሰ ስታለቅስ አይንህን እንዳታጣና በንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዳይሆን፡፡ እንግዴህ እግዚአብሔር ከፈቀደ ልቧን አራርቶት ተመልሳ ልትመጣ ትችላለች፡፡ አይታወቅም፡፡ ሰጭውም ነሽውም እሱ አንድ አምላክ እስከሆነ ድረስ አደራውን ለሱ መስጠት ነው አሉ ፤ ወ/ ሮ አሰገደች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose



ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...
ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

አትሮኖስ

20 Dec, 17:29


አትሮኖስ pinned «#የጣት_ቁስል ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ አማላጅ ከራሳቸው ሃሳብ ጋር ሙግት ገጥመዋል ፡፡ እሽ ይሉኝ ይሆን ? ወይስ እንቢ ? እንደገና ደግሞ በአንዴማ እንቢም ፤ እሽም   አይሉኝም ፡፡ እያሉ ሳይታወቃቸው ቄስ መልካሙ ቤት ደረሱ፡፡ ለመጣራት ወደ አጥሩ ተጠጉ ፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ቄስ መልካሙን ግቢያቸው ውስጥ መፅኃፍ እያነበቡ ተመለከቷቸው ፡፡ መጣራታቸውን ትተው "ደህና…»

አትሮኖስ

20 Dec, 17:00


"እንጃ ውስጤ ሰላም አይሰማኝም፡፡ ዛሬ ደግሞ ሲያቃዠኝ ነው ያደረው"፡፡

ተመስገን ቅዠት ይሁን ህልም መፍታት ባይችልም ፤ ለመስማት ስለፈለገ ብቻ "ምንድ ነው ያቃዠሽ ንገሪኝ" አላት፡፡

"ቅዠት ይሁን ህልም ባላቀውም የሆነ ሰው ይመስለኛል ፤ ሲያባርረኝ እየሮጥሁ ከእሱ ለማምለጥ ስል ገደል ገባሁ፡፡ ከዚያ ብንን ስል ያለሁት መኝታየ ላይ ነው" አለች፡፡ አሁንም የፍራትና የጭንቀት ምልክት እየተሰማት፡፡

ተመስገን በግምትም ቢሆን ገደል መግባቷ መጥፎ ህልም ሳይሆን አይቀርም ብሎ በውስጡ አሰበ፡፡

እድላዊት የነገረችውን ህልም ከአሁን አሁን ፈቶ ይነግረኛል ብላ ብትጠብቅም ሳይፈታላትና ሳይመልስላት ትምህርት ቤት ደረሱ፡፡

"ታመመሽ አስፈቅደን እንመለሳለን" አላትና ሁለቱም የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ቢሆኑም ክላሳቸው ስለሚለያይ ተጨባብጠው ወደዬ ክላሳቸው ገቡ፡፡

እድላዊት ለትምህርት ያላት ፍላጎት ወደር የለውም ነበር፡፡ ዛሬ ግን በተፈጠረባት የጭንቀት ስሜት የምትወደው ትምህርት አስጠልቷታል፡፡ እንደ ነብር ዘሎ የሚውጣት መስሎም ታይቷታል፡፡

መድረስ አይቀርም ሰዓት ደርሶ ተማሪ ተለቀቀ፡፡ እድላዊት ትምህርት ቤት ይሁን የፀሎት ቦታ ያለችበት ተዘንግቷታል፡፡ የመለቀቂያ ሰዓት ደርሶ ውጡ ሲባል እንኳን አላመነችም ነበር፡፡ ከተማሪዎች ቀድማ ወጣች፡፡ ወንድሟን መንገድ ላይ ስትጠብቅ ቆይታ ሲመጣ አብረው ጉዟቸውን ወደ ቤት ቀጠሉ፡፡

"አሁንም አልተሻለሽም እንዴ? ብሎ እጇን ጨበጥ አደረጋት፡፡

"ከጥዋቱ አሁን ተሸሎኛል" አለች፡፡ የሆዷ መረበሽና ጭንቀት እየባሰባት ቢመጣም ወንድሟ ላለማስጨነቅ ብላ፡፡

ተመስገንም አይዞሽ፡፡ እያለ እያፅናናት እቤት ደረሱ፡፡

እናታቸው ወ/ሮ አሰገደች "መጣችሁ አሉ፡፡

"አዎ ፤ መጥተናል" አለች እድላዊት፡፡

በይ! ምሳችሁን ብሉና ተመስገን ከብቶቹን ውሃ ያጠጣ፡፡ አንች ስራ ትረጅኛለሽ ብለው ወደ ማድቤት ገቡ፡፡ እንጀራ ለመጋገር የገለባ ማገዷቸውን ማቀጣጠል ጀመሩ፡፡

እድላዊት ምሳዋን ተመግባ እንደደበራት እናቷን ለማገዝ ወደ ማድቤት ገባች፡፡ "ምን ልርዳሽ ? አለች፡፡ ወደ እናቷ እየተጠጋች፡፡

"አንች ወጡን ስሪ ፤ እኔ እንጀራውን ቶሎ ቶሎ ልጋግር፡፡ አባትሽም ከቤተክርስቲያን መምጫው ሰዓት ደርሷል"አሏት፡፡

እሽ ብላ መስራት ጀመረች፡፡ እናትና ልጅ የተኮራረፉ ይመስላል፡፡ ሁለቱም በዝምታ ተውጠው ስራ ስራቸውን ይላሉ፡፡

ወ/ሮ አሰገደች የእድላዊት ዝምታ ከምን የመጣ እንደሆነ ግራ ገብቷቸዋል፡፡ ዝም በማለቷ ተጠራጠሩ ፤ ሰምታ ይሆን እንዴ? ባል እንደመጣላት ; ማንስ ይነግራታል? ለነገሩ የዛሬ ወሬ አይደበቅም፡፡ ንፋስ የሚያወራው ይመስል ውሎ ሳያድር አገሩን ያዳርሰዋል፡፡ ከራሳቸው ሃሳብ ጋር ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ፤ "ምን ሆነሽ ነው ዛሬ ያለወትሮሽ ዝም ያልሽው?

አሞሻል እንዴ? አሉ፡፡ ቁጣ የተቀላቀለበት በሚመስል ንግግር፡፡

"አላመመኝም" አለች እድላዊት፡፡

"እና ምን ሆነሽ ነው? አሏት፡፡ አሁንም ቁጣ ቁጣ በሚል ንግግራቸው፡፡

እድላዊት የእናቷ ቁጣ የተቀላቀለበት ንግግር አልገባትም፡፡ "ከትምህርት ስለመጣሁ ደከሞኝ ይሆናል፡፡ ሌላ ምንም አልሆንኩም" አለች፡፡ አቀርቅራ የወጥ መስሪያ ሽንኩርቷን እየላጠች፡፡

አይ! ድካም ከሆነ ምንም ማለት አይደለም፡፡ የሰማሽው ወሬ እንዳለ ብየ ነው አሉ፡፡ የልጃቸው መልስ ባይዋጥላቸውም፡፡

እድላዊት ግን የሆነችውንና የተሰማትን ለመናገር አልፈለገችም፡፡ ካቀረቀረችበት ቀና ብላ "የምን ወሬ ነው የምሰማው? አለች እንደ መደንገጥ ብላ፡፡

ወ/ሮ አሰገደች ገና ሳይነግሯት የልብ ትርታቸው ጨመረ፡፡ እየፈሩ ብነግራት ምን ትል ይሆን? ብትደነግጥስ ምን ትሆናለች? በማለት እራሳቸውን አፅናኑ፡፡ ለመናገር ወሰኑ፡፡ ስልታዊ አነጋገር እንኳን አልተጠቀሙም፡፡ በቀጥታ "ካልሰማሽማ እኔው ልንገርሽ ባል መቶልሻል፡፡ ከነገ ጀምረሽ ትምህርት ቤት አትሔጅም፡፡ ትምህርቱን ትተሸ የቤት ውስጥ ሙያ ትለምጃለሽ አሏት፡፡

ታዲያ ወ/ሮ አሰገደች ልውጣ ልውጣ እያለ ሲተናነቃቸው የነበረው በመናገራቸው ለራሳቸው ቢቀላቸውም ለልጃቸው ግን ከሰማይ የመጣ ዱብዳ ሆኖባታል፡፡

እድላዊት በሰማችው ነገር ደነገጠች፡፡ በተቀመጠችበት ጉጉት ሆና ቀረች፡፡ አትናገር አትጋገር ፍጥጥ ብላ
እናቷን ታያለች፡፡

‹‹የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽ ሆነና ነገሩ›› ወ/ሮ አሰገደች በልጃቸው ሁኔታ ተደናግጠው ምነው ባልነገርኳት፡፡ እያወኩ ፣ ሆዴ እየፈራ ፣ እየተርበተበቱ ራሳቸውን መውቀስ ጀመሩ፡፡

እድላዊት እናቷ የተናገሯትን ማመን አቃታት፡፡ መልስም አልሰጠችም፡፡ ቀኑ ሁሉ ሲጨንቃት የነበረውና ሲያምሳት የዋለው ይሔ የወደፊት አላማዋንና ሃሳቧን ከግብ አይደለም ከማሃል እንኳን ሳይደርስ ወሽመጧን የሚቆርጥ መርዶ ሊያሰማት መሆኑን አላወቀችም ነበር፡፡ ከሔደችበት የሀሳብ ሰመመን አልተመለሰችም፡፡ ባል! ባል! ባል! እኮ ባል መጥቶልሻል ታገቢያለሽ አለች እናቴ፡፡ በቃ ወስነዋል ማለት ነው?፡፡ የእኔ መጨረሻ ይሔ ሆነ?፡፡ በውስጧ እልህና ቁጭት አደረባት፡፡ ከወሰዳት የድንጋጤ መንፈስ መለስ አለች፡፡ ከየት መጣ ሳይባል እንባዋ ግራና ቀኝ በጉንጮቿ ላይ መውረዱን ተያያዙት፡፡

ቄስ መልካሙ ከቤተክርስቲያን ተመልሰው መጡ፡፡ እድላዊት እያለቀሰች ደረሱ፡፡ ምን ሆና ነው የምታለቅሰው ነገርሻት እንዴ? ባል እንደመጣላት" አሉ ለባቤታቸው፡፡

አዎ"ነግሬያት ነበር፡፡

"እና እሷስ ምንም አላለችሽም"?፡

"ምንም አላለችም፡፡ ይኸው እንደምታያት ዝም ብላ ትነፋረቃለች፡፡ እስኪ አንተን የምሰማህ ከሆነ ዝም እንድትል አድርጋት''

የባለቤታቸው መርበትበትና መረበሽን የተካፈሉት ይመስላል፡፡ እድላዊትን ለማናገር ሆዳቸው ፈራ ተባ አለ፡፡ "ምን ሆነሽ ነው? የምትነፋረቂው" አሏት፡፡ በፊታቸው ላይ የቁጣ ምልክት በማሳየት፡፡

እድላዊት የባሰ አባቷን ስታይ እንባዋን መቆጣጠር አቃታት፡፡ መልስ ለመስጠት ተርበተበተች፡፡ እልህ ተናነቃት፡፡ "ምን ሆነሽ ነው ትለኛለህ ? ስራህን ሰርተህ ከጨረስህ በኋላ!፡፡ ግን የማገባ ይመስልሃል ትምህርቴን ሳልጨርስ አላገባም፡፡ ቆሜ እቀራለሁ እንጅ ብላ እልህና ንዴት በተቀላቀለበት ንግግር አባቷን ከአሁን በፊት ደፍራ ተናግራቸው የማታውቀውን ተናገረቻቸው፡፡

ቄስ መልካሙ ከልጃቸው የሰሙት ንዴት የተቀላቀለበት ንግግር አስከፊና መመለሻ የሌለው መስሎ ታያቸው፡፡ ልጃቸውን ተቆጥተውና አስፈራርተው መናገር ስላለባቸው "ታገቢያለሽ"፡፡ ስለ ማግባትሽ ደግሞ አንች ሳትሆኝ የምትወስኝው እኔ አባትሽ ነኝ፡፡ አሁን ተነስተሸ ወደ ቤት ግቢ መነፋረቁን ትተሸ" አሉ፡፡ በዱላ የመምታት ያህል በሚሰማ ንግግራቸው፡፡

እድላዊት በአባቷ ቁጣ ብትደነግጥም እንባዋ ግን መውረዱን ቀጥሏል፡፡ እንባዋን ሳያቋርጥ እያለቀሰች ተነስታ ወደ መኝታ ቤቷ ገባች፡፡ እራሷን አሟት ስለነበር መኝታዋን ሳታነጥፍ ጋደም እንዳለች እንቅልፍ ሸለብ አደረጋት፡፡

ተመስገን እቤት ሲገባ የሰማውንና ያየውን ትርኢት ማመን አቃተው፡፡ በሰማው ነገር ግራ ተጋባ፡፡ ሃዘንም ተሰማው፡፡ ሆዱ ተረበሸ፡፡ አይኖቹ በእንባ ተሞሉ፡፡ በማይል የማይለካ እሩቅ የመድረስ አላማና ተስፋው ፍሬ ሳያፈራ አይደለም እንቡጥ እንኳን ሳይዝ መቀጨቱ ታወቀው፡፡ የእህቴ ምኞትና ተስፋ የእኔም ነበር፡፡ አሁን ግን አበቃለት ፤ አከተመለት፡፡ በሃዘን በተሞላ እና እንባ በተናነቀው አንደበቱ ሰው ሳይሰማው ለራሱ እየተጨናነቀና እያማረረ የተናገረው ነበር፡፡

አትሮኖስ

20 Dec, 17:00


ቤተሰቦቹንም ሆነ እህቱን ሳያነጋግር ወደ መኝታው ሄደ፡፡ ጭንቀቱና መረበሹ የሚቀልለት መስሎት እራት እንኳን ሳይበላ መኝታው ላይ ጋደም አለ፡፡ መረበሹና ጭንቀቱን ሊያስታግስለት ግን አልቻለም፡፡ እንቅልፍ የሚባል አልወስድ ብሎታል፡፡ መኝታው የቆረቆረው ይመስል እየተገላበጠ ሌሊቱን ሁሉ አሳልፎ
ሳይወስደው ያደረው እንቅልፍ ሊነጋጋ አካባቢ መጥቶ ሸለብ አደረገው፡፡

ቄስ መልካሙ የተፈጠረው ነገር ሁሉ አሳስቧቸዋል፡፡ እድላዊትን በመቆጣታቸው እና በማስፈራራታቸው ተፀፅተዋል፡፡ ምነው? ባልተቆጣኋት፤ ቀስ ብየ ብመክራት ይሻል ነበር፡፡ አሁን ከሆነ ወዲያ ምን አደርጋለሁ፡፡ እንግዲህ ነገ የተሻላት እንደሆነ ቀስብየ እመክራታለሁ፡፡ በስጋ ከባለቤታቸው ጋር ቢሆኑም በመንፈስ ግን የት እንደደረሱ ባይታወቃቸውም እራሳቸውን ለማረጋጋት ያወሩት ነበር፡፡

ወ/ሮ አሰገደች እንደ ባለቤታቸው በሃሳብ ፈረስ ነጉደው ሲመለሱ "የተመስገን ደግሞ ተደርቦ ማኩረፍ ምን ይሉታል?" አሉ ፤ ከባለቤታቸው መልስ የሚያገኙ መስሏቸው፡፡

ተመስገንና እድላዊት በተፈጠረው ነገር ከእናት አባታቸው ጋር አለማምሽታቸው ቤቱን በሃዘን የተዋጠ አስመስሎታል፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose



ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...
ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት አጭር ግዜ ነው የቀረው..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

አትሮኖስ

20 Dec, 17:00


#የጣት_ቁስል


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_በአብርሃም_ቃሉ

አማላጅ

ከራሳቸው ሃሳብ ጋር ሙግት ገጥመዋል ፡፡ እሽ ይሉኝ ይሆን ? ወይስ እንቢ ? እንደገና ደግሞ በአንዴማ እንቢም ፤ እሽም   አይሉኝም ፡፡ እያሉ ሳይታወቃቸው ቄስ መልካሙ ቤት ደረሱ፡፡ ለመጣራት ወደ አጥሩ ተጠጉ ፡፡ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ቄስ መልካሙን ግቢያቸው ውስጥ መፅኃፍ እያነበቡ ተመለከቷቸው ፡፡

መጣራታቸውን ትተው "ደህና አደራችሁ መልካሙ" ? አሉ፡፡ ቄስ አሻግሬ ፤

አቀርቅረው ከሚያነቡት መፅሃፍ ላይ አንገታቸውን ቀና አድርገው "እግዚአብሔር ይመስገን ሰላም አደሩ" ? አሉ ፡፡ ቄስ መልካሙ፡፡ ንስሃ አባታቸው ያለወትሯቸው በጥዋት በመምጣታቸው የመደናገጥ ምልክት እየታየባቸው ፡፡ ፀበል ሊረጩን ይሆን ? ሳንነግራቸውና ሳንዘጋጅ ፤ እነሱም ሳይነግሩን ፤ በሰላም ይሆን የመጡት? ከራሳቸው ሃሳብ ሳይወጡ የተናገሩት ነበር

"አንተን ፈልጌ ነበር የመጣሁት"፡፡ እደጅ ላግኝህ አሉ ቄስ አሻግሬ ፡፡ ለስለስ ባለ አነጋገር ፡፡

"ለምን እንደተፈለጉ ባያውቁም "ምነው ደህና አይደሉም እንዴ"?

አይ ደህና ነኝ ፡፡ ለጉዳይ ፈልጌህ ነበር አሉ
ከየት መጀመር እንዳለባቸው ግራ ቢገባቸውም "አቶ ለማ ልጅህን ለልጄ እንዲሰጡኝ አማላጅ ሂድልኝ ብሎኝ ነው የመጣሁት"፡፡ ብለው ሃሳባቸውን ሳያቋርጡ በመቀጠል አቶ ለማ ሽፈራው ጥሩ ሰው ናቸው፡፡ ዘራቸውም ቢሆንም ምንም አይወጣለትም ፡፡ ልጁም የተባረከ ፤ የተመሰገነ ፤ ጨዋ ፤ ድምፁም የማይሰማ ማለፊያ ገበሬ ነው" አሉ፡፡

ቄስ መልካሙ ያልጠበቁትና ያላሰቡት ነገር ሆነባቸው፡፡ ለጊዜው ምን ማለት እንዳለባቸው አብሰለሰሉ፡፡ የማይሆን ነገር ነው፡፡ አሁን እድላዊትን አግቢ ብላት ትምህርቷን ትታ የምታገባ አይመስለኝም፡፡ ከራሳቸው ሃሳብ ጋር እየተሟገቱ ከቆዩ በኋላ "እንግዲህ
ከቤተሰብና ዘመድ ጋር መክረን መልስ ብንሰጥ ይሻላል፡፡ አሁን እኔ ለብቻየ የምወስነው ነገር የለም" አሉ፡፡ ሆዳቸው እንደመባባት እያለም ቢሆን፡፡

"ታዲያ ቀነ ቀጠሮው ለመቼ ይሁን" ? አሉ፡፡ መቼም በአንዴ እሽ እንደማይባል የአገሩ ባህልና የተለመደ መሆኑን ስለሚያውቁ ፡ተመልሰው የሚመጡበትን ቀን በጉጉት ለመስማት እየጠበቁ ፡፡

"ዛሬ ቀኑ ሮዕብ አይደለም፡፡ የዛሬ አስራ አምስት ቀን ይመለሱ፡፡ እኛም እስከዛ ብንመካከርበት ይሻላል" በማለት መልስ ሰጧቸው፡፡

ይሁን መልካም ነው፡፡ ብለው የተሰጣቸውን ቀነ ቀጠሮ ተቀብለው ከቄስ መልካሙ ጋር ተሰነባብተው ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡

ንሰሃ አባታቸውን ከሸኙ በኋላ ፤ ወደ ቤታቸው ገቡ፡፡ በመጨጊያቸው ላይ ተቀመጡ፡፡ አገጫቸውን በቀኝ እጃቸው ደገፍ አደረጉ፡፡ ትክዝ ባለ አንደበት ስለልጃቸው እድላዊት በውስጣቸው ማብሰልሰል ተያያዙት፡፡

ወ/ሮ አሰገደች ከማድቤት ወጥተው ወደ መኖሪያ ቤት እየሄዱ ባለቤታቸው ከወትሯቸው በተለየ ተክዘው ተመለከቷቸው፡፡ እርምጃቸውን ገታ አድርገው "ምነው ቄስ አሻግሬ አመጣጣቸው በደህና አይደለም እንዴ"? አሉ ፤ ለባለቤታቸው ፡፡

"አይ ደህና" ናቸው ፤ አሉ፡፡ ሃዘን ይሁን ትካዜ በተቀላቀለበት ንግግር፡፡

ወ/ሮ አሰገደች የንሰሃ አባታቸው ዛሬ በጥዋት አመጣጣቸው ለምን እንደሆነ ባያውቁም የባለቤታቸው መተከዝ አስጨንቋቸዋል፡፡ "በሰላምማ አልመሰለኝም" አሉ፡፡ ወደ ባለቤታቸው እየተጠጉ፡፡

"የመጡትስ በሰላም ቢሆንም አቶ ለማ ሽፈራው አማላጅ ልከዋቸው ነው የመጡት" አሉ፡፡ የባለቤታቸውን ሁኔታ እየተመለከቱ፡፡

"የምን አማላጅ ነው?" አሉ፡፡ ሆዳቸው እንደመርበትበት እያለ፡፡ የምን አማላጅነት እንደሆነ ለመስማት በመቸኮል፡፡

የአቶ ለማን ልጅ ታውቂዋለሽ ?"፡፡

"ትንሹን ነው ትልቁን?፡፡

"አይ! ትንሹን ይሁን ትልቁን አለየሁትም፡፡ አበበ የሚባለውን፡፡

ምን እንደሆነ ሳያውቁ "በሞትኩት ምን ነካው ያምስኪን ልጅ ከሰው ተጣላ" እንዴ ?፡፡

"እሱስ አልተጣላም፡፡ አቶ ለማ ሽፈራው እድላዊትን ለአበበ ስጡኝ ብሎ ነው፡፡ ቄስ አሻግሬን አማላጅ ተልከው የመጡት"፡፡

ወ/ሮ አሰገደች ለመስማት የጓጉትና ልባቸው ተንጠልጥሎ ሲጠብቁት የነበረው ምን እንደ ሆነ ባያውቁም ከባለቤታቸው የሰሙት ያልጠበቁትና ያላሰቡት ሆነባቸው፡፡ ለጊዜው መርዶ እንደ ተነገራቸው ያህል በዝምታ ተዋጡ፡፡ በሃሳባቸው ልጄን እማ አልሰጥም አስተምራለሁ፡፡ ትምህርቷን ሳትጨርስ አልድራትም፡፡ እሷም እሽ አትልም በዛ ላይ ጎበዝ ተማሪ እየተባለች አገር የመሰከረላት ነች ፡፡ የልጃቸውን ሃሳብ እያወጡና እያወረዱ ከሔዱበት የሃሳብ ሰመመን ሳይመለሱ..

እና "አሁን ምን ይሻላል ትያለሽ? አሉ ፤ ቄስ መልካሙ፡፡ ከነጎዱበት የሃሳብ ሰመመን መለስ ብለው "እኔ ምን እላለሁ አንተ ምን አልካቸው?፡፡

"እኔማ ለዛሬ አስራምስት ቀን ተመልሰው እንዲመጡ ቀጥሪያቸዋለሁ፡፡ እኛም መመካከርና የእድላዊትን ፈቃድ ማወቅ ስላለብን ብየ ነው፡፡ ቀኑን ያስረዘምኩት፡፡ ለመሆኑ የሚሳካ ይመስልሻል ?፡፡

"እኔ እድላዊት ለማግባት እሽ የምትል አይመስለኝም፡፡በዛ ላይ ለትምህርቷ ያላት ፍላጎት ጎበዝ ተማሪ እንደሆነች ማንም ያውቃታል፡፡ እንደ እኔ ሃሳብ ትምህርቷን ከጨረሰች በኋላ፤ ብታገባ ይሻላል፡፡ ትዳር ይደረሳል፡፡ የት እንዳትሔድ ነው፡፡ ብለው አሁን አንተ ምን ወሰንክ አሉ?፡፡

"ማድረግ ያለብንማ ሁለታችንም ተመካክረን መወሰን ነው፡፡ እንደ እኔ እድላዊት እሷ እንኳን ባትፈቅድም ማግባት አለባት፡፡ ለትዳር ደርሳለች፡፡ ትምህርቷም ይበቃታል፡፡ ከአሁን በኋላ፤ ከትምህርቷ ቀርታ የቤት ሙያ መልመድ አለባት" አሉ፡፡

እድላዊት እንደ እናቷ የጠይም ቆንጆ ሰለክለክ ያለች ፤ ቁመናዋ እና ጥርሶቿ ልክ እንደ አባቷ ከሩቅ የሚያማልል ነው፡፡ ታዲያ የጠይም መልከመልካሟን ቆንጆ እንድላዊትን የሚያያት ሁሉ ሳይጎመዣት
አያልፍም ነበር ፡፡

አበበ ለማ እድላዊትን ሊያገባት አማላጅ የላከው በአጋጣሚ ከወንድሟ ከተመስገን ጋር ወደ ትምህርት ቤት ስትሄድ ባያት ማግስት ነበር፡፡ለቤተሰቦቹ ነግሮ አማላጅ እንዲላክለት ያደረገው፡፡

ወ/ሮ አሰገደች እድላዊትን አልድርም ፤ አስተምራለሁ ፤ እያሉ በሃሳባቸውም ሲፎክሩ የነበሩት በባለቤታቸው ቁጣ ያዘለ ንግግር ተቀየሩ፡፡

አንተ ከወሰንህ ታዲያ ምን አደርጋለሁ፡፡ እኔም ማግባት አለባት ባይ ነኝ፡፡ ማግባቷ ለእኔም ትጠቅመኛለች፡፡ ብታመም እንኳን ጠያቂ ዘመድ በቅርብ የለኝ፡፡ የምታገባበት ቦታ ቅርብም በመሆኑ እየመጣች ትጠይቀኛለች፡፡ በፍራትም ቢሆን ከባለቤታቸው ሃሳብ ላለመውጣት የተናገሩት ነበር፡፡

ቄስ መልካሙ የባለቤታቸውን ሃሳብና የራሳቸውን ሃሳብ አንድ ላይ ካሰባሰቡ በኋላ፤ እድላዊትን አሁን የተባባልነውን ሁሉ ከትምህርቷ ስትመጣ ንገሪያትና ከትምህርት ቀርታ የቤት ውስጥ ስራ እንድትለምድ አድርጊያት አሉ፡፡ ቁርጥና ኮስተር ባለ ንግግር፡፡

"እሽ ነግሬያት እንድትቀር አደርጋለሁ ፡፡

እድላዊትና ተመስገን

የጥዋት ተማሪ ናቸው፡፡ ወደ ትምህርት ቤት እየሔዱ እድላዊት ከወትሮው በተለየ ምክንያቱ በምን እንደሆነ አላወቀችውም፡፡ ግራ ተጋብታለች ፤ ሰውነቷ ይርበተበታል፡፡ ወደ ፊት መሔዷን ተወት አድርጋ አንዳንዴ ቆም በማለት ራሷን ለማረጋጋት ትሞክራለች፡፡

ተመስገንም በእህቱ መለዋወጥና ዝምታ ግራ ገብቶታል፡፡ ከአሁን አሁን ትነግረኛለች ብሎ ቢያስብም እድላዊት ግን የሆነችውን ለራሷ አላወቀችም፡፡ ምን እንደሆነችም ልትነግረው አልቻለችም ነበር፡፡

"ምን ሆነሽ ነው አሞሻል እንዴ?፡፡

"አላመመኝም ውስጤን ግን ፍራት ፍራት ይለኛል፡፡

"ምነው በሰላም ?፡፡

አትሮኖስ

19 Dec, 17:04


#ወይ_አጋጣሚ(አጭር ልብወለድ)


#ክፍል_ሶስት


#ድርሰት_በዘሪሁን

====================
‹‹ካሰብሽበት አሁንም ቀን ነው፡፡››
‹‹አንተ ቤተሰብ ያለኝ ሰው እኮ ነኝ፡፡››
‹‹አንቺ እሺ ይኑርሽ.. ያደነዘዘኝን ቂጥሽን ግን ላኪልኝ፡፡››መቼስ የምላሴ ፍሬኔ ብጥስጥስ ብሎብኛል፡፡
‹‹ናና ውሰደዋ፡፡››
‹‹በቃ መጣሁ፡፡››
‹‹እውነትህን ነው?››
‹‹አዎ እውነቴን ነው..ትናንት የተለያየንበት ቦታ ስደርስ ደውልልሻለሁ››
‹‹ያ እኮ ሰፈሬ አይደለም ብላ …የእሷን ትክክለኛ ሰፈር በምልክት ነገረችኝ.. ሂሳብ እንዴት እንደከፈልኩ.. እንዴት ተንደርድሬ ሰፈሯ እንደደረስኩ አላውቅም..ግን ስደውልላት ባሏ ተከትሏት ቢወጣስ..?የራሱ ጉዳይ ‹‹የቆመበት የቆመ ነገር አያይም››ይባል የለ፡፡ ደወልኩላት… ከአምስት ደቂቃ በኃላ መጣች፡፡ጨለማ ውስጥ ሆኜ ያለሁበትን ቦታ በእጅ ምልክት ጠቆምኳት..መጣች፡፡
‹‹አንተ ጉደኛ!!!››
በቃላት መልስ ከመመለሴ በፊት ጐተትኩና ከሰውነቴ አጣብቄያት ከንፈሯን ገመጥኳት ፡፡የሀይሚን እልክ በእሷ እየተወጣሁ ያለው መሰለኝ፤ በግድ ነው ያስለቀቀቺኝ‹‹አንተ ሰፈሬ እኮ ነው ያለሁት…ሰው ቢያየኝስ?››አለችኝ፡፡ ንግግሯ ደስ አሰኘኝ…ሰፈሯ ባይሆን ኖሮ በመሳሟ ደስተኛ ነች ማለት ነው፡፡
‹‹ባክሽ ጭለማ ውስጥ ነው ያለነው..ማንም አያይሽም፡፡››
‹‹ወይኔ ጉዴ!!!››አለች ድንገት ራሷን ይዛ እየተርበተበተች፡፡
‹‹ምነው….?ምን ሆንሽ…?›.
‹‹ባሌ መጣ …ባሌ፡፡››
በድንጋጤ ተሸቀንጥሬ ጨለማ ውስጥ ተሸገጥኩ፤እሷ በቆመችበት ሆና በሳቅ ፍርስ አለች‹‹ሲያዩህ ጀግና ትመስላለህ››
ከተወሸቅኩበት ወጣሁና ወደ እሷ በእርጋታ እየቀረብኩ ‹‹ጀግናማ ጀግና ነኝ ላንቺ ደህንነት አስቤ አስጂ..፡፡››
‹‹እሱን እንኳን ተወው..ጀግና አናውቅም እንዴ?››
‹‹ግን ባልሽ እቤት ነው?››
‹‹ባሌ እቤት ቢኖር..እንዲህ አጥር ስር አስደግፌህ አዋራሀለው፡፡››
‹‹ጥሩ አጋጣሚ ነው ፊልድ ሄዶል ማለት ነው››..አንገቷን ወደ መሬት ደፍታ ዝም አለች፡፡ግራ ገባኝ‹‹ምነው ያልኩሽን ሰምተሸል?››
‹‹አዎ ባሌ የሞተብኝ በቅርብ ነው፡፡ ሰሞኑን ነው ጥቁሩን የሀዘን ልብሴን ያወለቅኩት ››ደነገጥኩ፡፡የተደፈነ ልብ ሸሽቼ ስመጣ የተሸነቆረ ልብ ገጠመኝ እንዴ..?
‹‹ይቅርታ›› ብዬ ዳግመኛ ወደ ሰውነቴ አጣበቅኳትና ከንፈሯ ላይ ተጣበቅኩ፡፡እጄ ትናንትና ያደነዘዘኝ ቂጦ ላይ አርፎል… ቃተተች፡፡ እንደምንም ተላቀቀቺኝና ‹‹እዚሁ ብትንትኔን አወጣኸው እኮ..በዛ ላይ ረሀብተኛ ነኝ፡፡››
‹‹እኔም ጠኔ ሊጥለኝ ትንሽ ነው የቀረኝ፡፡በቃ ይዘሺኝ ወደ ቤት ግቢያ..››
‹‹ወዴት?››
‹‹ወዳንቺ ቤት ነዋ፡፡››
‹‹እንዴ ልጄ እኮ አለች..በዛ ላይ ሰራተኛዋም….››
‹‹እሺ የሆነ ሰበብ ፍጠሪና ወደ እኔ ቤት ወይም ወደፈለግሽበት ሌላ  ቦታ ይዤሽ ልሂድ፡፡››
‹‹እሱማ አይቻልም..ውጭ ለማደር ምንም የምሰጠው ምክንያት የለኝም..ይልቅ ደፋር ከሆንክ አንድ ሀሳብ አለኝ፡፡››
‹‹ኸረ አፄ ቴዎድሮስ አጐቴ ነው… ጀግንነቱ ከደማችን ነው ሚንጠባጠበው፡፡››
‹‹ከ3-4 ሰዓት ባለው ጊዜ ይተኛሉ ..መኝታ ቤቴ ለብቻዬ ስለሆነ ስደውልልህ ትመጣና ትገባለህ..ታዲያ ለሊት 11 ሰዓት ወጥተህ ለመሄድ ከተስማማህ ነው ?››
ጥብቅ ብዬባት ሳምኳት እና ‹‹ቂጥሽ ብቻ ሳይሆን ልብሽም ቀይ ነው..ተስማምቼያለሁ፡፡››
‹‹ታዲያ እስከዛ የት ትቆያለህ?››
‹‹ችግር የለውም..ወደኃላ ተመልሼ በቅርብ የሚገኝ አንዱ ቡና ቤት አመሻለሁ… ስለ እሱ አታስቢ አንቺ ብቻ እንዳልሺው አድርጊ፡፡››
‹‹ችግር የለውም …አሁን ግን ሱቅ ዕቃ ልግዛ ብዬ ስለወጣሁ  መመለስ አለብኝ፡፡››
‹‹ታዲያ የገዛሽው ዕቃ የታል?››
‹‹አጣኋ…ባለሱቆቹ የለንም ጨርሰናል አሉኝ፡፡›› ብላ ጉንጬን በስሱ ስማኝ እየፈገገች ወደ ግቢዋ ተመልሳ ገባች፡፡››
አቤት የሰው ልጅ ልዩነት ድሮም ከህፃን ጋር መከራዬን ሳይ መኖሬ እንዲህ ትናንት ተዋውቆ ለዛሬ ብን ማለት እያለ ስድስት ወር ሙሉ  ስዳክር መኖሬ..አምኜ ወደ ኃላ ልመለስ አልቻልኩም፡፡እንዴ የሆነ ነገር ቢያጋጥመኝስ..? ድንገት ሳልሰማ ጉልበተኛው መንግስታችን ሰዓት እላፊ አውጆ ቢሆንስ…?ድንገት ዘራፊዎች ሞባይሌን ቢመነትፉኝስ በምን ደውዬ አገኛታለሁ…?ኸረ የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እንጂ በእንደዚህ አይነቱ ቀን ድንገት የሚፈጠር ስንት አደናቃፊ ነገር አለ መሰላችሁ፡፡ለሀይሚ ተብዬዋ እንኳን ያን ሁሉ ሰዓት በባዷ አባክኜ የለ…ያደረግኩት አንድ ነገር ቢኖር እዛው ፊት ለፊቴ ካለች አንድ ትንሽ ኪወክስ ሄጄ ጭንብል መሸመት ነው፡፡ሶስት እሽግ ህይወት ትርስት..ሶስት እሽግ ሰንሴሽን ሸመትኩና በእያንዳንዱ ኪሴ ሁለት ሁለት በታትኜ ከተትኩ፡፡
አንድ ወንዳ ወንድ የሆነች የሱቁ ሻጭ‹‹ምነው የወር ቀለብ ነው እንዴ?›› አለቺኝ፡፡
‹‹ምነው ችግር አለው?››
‹‹ለምን ችግር የለውም ፡፡ ሆነ ብለህ ምርትን ከተገቢው በላይ በማከማቸት የዋጋ ንረት ለመፍጠር አስበህ ቢሆንስ?››
‹‹አይዞሽ አትስጊ ከተረፈኝ ጥዋት መልስልሻለው ›› አልኳት እና መልሼ ጨለማዬ ውስጥ ተወሸቅኩ፡፡3፤15 ሲሆን ተደወለ.. ባለቂጧ መስላኝ ተንደርድሬ አፈፍ አድርጌ አነሳሁና‹‹እሺ ተኙልሽ››
‹‹አዎ ልተኛ ነው››አለችኝ፡፡አቤት የደነገጥኩት ድንጋጤ.. ከራማዬ ነው ቡን ያለው፡፡ ሀይሚ ነበረች ደዋዮ፡፡አሁን በዚህ አሳሳች ሰዓት  ማን ደውይ አላት?
‹‹ሄሎ ምነው ዝም አልከኝ፤አኩርፈኸል እንዴ?››
‹‹አይ ለምን አኮርፍሻለሁ?››
‹‹ደግሞ ውጭ ነው እንዴ ያለኸው...፡፡ንፋስ ነገር ይሰማኛል›› ብላኝ ቁጭ፡፡ሁሉም ሴቶች ከጥንቆላ መንፈስ የተገነባ ስድስተኛ የስሜት ህዋሳት አላቸው…፡፡ይሄ ጉዳይ ሁሌ ይገርመኛል፡፡ከሆነች ሴት ጋር አፍ ለአፍ ገጥመህ ስታወራ…ወይንም የሆነች ሴት ልትስም አፍህን አሞጥሙጠህ ወደ ፊት መጓዝ ስትጀምር..ወይ ለአንዴ ልስረቅ ብለህ ሱሪህን በማውለቅ ላይ ሳለህ…ስልካቸው ጭርርርርርር ይልብህና ያሳቅቅሀል፡፡
‹‹ባክሽ ደብሮኝ እቤቴ በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ ከዋክብት እየቆጠርኩ ነው››
‹‹አውቄያለሁ ደብሮሀል ማለት ነው..?ግን ለቀኑ ነገር ተረድተኸኛል አይደል…?››ለዚህ ጥያቄዋ መልስ ከመመለሴ በፊት ሌላ ስልክ ዌይቲንግ ገባብኝ..ቂጣሟ ነች፡፡
‹‹በጣም ነው የተረዳሁሽ የእኔ ፍቅር፡፡አሁን ግን ሀለቃዬ እየደወለልኝ ነው..ላናግረውና መልሼ ደውልልሻለሁ፡፡››
‹‹አይ አያስፈልግም ፍቅር ..ልተኛ ስለሆነ ደህና እደር… ነገ ትደውልልኛለህ..ደግሞ አፈቅርሀለው እሺ፡፡››አለችኘ፡፡
‹‹እኔም አፈቅርሻለሁ፡፡›› አልኩና ዘጋሁት ..አያችሁልኝ አይደል፡፡‹‹አፈቅርሀለሁ፡፡››ብላኝ እኮ አታውቅም፡፡ሁልጊዜ ከስልክ ልውጥ  በኃላ ‹‹አፈቅርሻለሁ›› ስላት ‹‹እኔም›› ብላ ነው ምታሳርገው፡፡ ዛሬ ግን እኔን ለማሳቀቅ እና በአእምሮዬ ፀፀት ለመርጨት ሆነ ብላ አቅዳ እና አልማ ‹‹አፈቅርሀለሁ›› አለችኝ፡፡..ሞኟን ትፈልግ …በዚህ ሰዓት ለእሷ ንግግርም ሆነ ለአዕምሮዬ ፊት አልሰጣቸውም፡፡….
የቂጣሟን ስልክ አነሳውት…..‹‹ሄሎ››
‹‹ና በቃ … በራፍ ላይ ስትደርስ ደውልልኝ››
‹‹በመጀመሪያውስ ከበራፍሽ መች ተንቀሳቀስኩ››
‹‹እስከአሁን እዛው ነኝ እንዳትለኝ?››
‹‹አልኩሽ..ከስልክ እንጨቱ ጋር ተጣብቄልሻለሁ፡፡››
‹‹እውነትም ቀንዝሮብሀል..እሺ መጣሁ ››ብላ ስልኩን ዘጋች፡፡የውጩ በራፍ ተከፈተ፤ ጐትታ ወደ ውስጥ አስገባችና መልሳ ዘጋችው፡፡በግቢው ሆነ በቤታቸው ምንም አይነት መብራት አይታይም፡፡‹‹ምነው መብራ ተቆርጦባችሁ ነው?››በሹክሹክታ ጠየቅኳት፡፡

አትሮኖስ

19 Dec, 17:04


‹‹አንተን ለማስገባት እራሴው ነኝ የቆረጥኩት…እቤቱ ጋ እንደተጠጋሁ ወደ ሳሎኑ በረንዳ ሳቀና..‹‹ኸረ ባክህ እንደ አባወራ በፊት ለፊት በር መግባት ያምርሀል? ››ብላ በመጐተት ወደ ጓሮ ይዛኝ ሄደችና አንድ መስኮት ጋር ስንደርስ ቆመች ፡፡መስኮቱ በቁመት ከፍ ያለ ነው፤ግን ዘዴኛ ነች መሰላል አገድማበታለች፡፡ትከሻዬን ተደግፋ በመሰላሉ እየተራመደች ቀድማኝ ገባች፤ ተከተልኳት.. መስኮቱን ዘጋችው፡፡
‹‹ አልጋው ላይ ተቀመጥ፡፡›› አለችኝ..ባትለኝስ እኔ ሀይሚን አይደለው ኩርሲ ላይ የምቀመጥ ፡፡ፍልስስ ብዬ አልጋው ላይ ተቀመጥኩ፡፡ክፍሉ በሻማ ብርሀን ደምቋል
‹‹መብራቱ የእውነት የለም?››
‹‹ባክህ ከቆጣሪው አጥፍቼው ነው..ምን ይታወቃል የሆነ ነገር ፈልጋ ልጄ ወደ መኝታ ክፍሌ ብትመጣ እንኳን አንተን መደበቅ እንድችል  ብዬ ነው፡፡››
‹‹አንድ ልጅ ነው ያልሺኝ?››
‹‹አዎ በልጅነቴ የወለድኳት ልጄም ጓደኛዬም ነች፡፡››
‹‹ትልቅ ነቻ?››
‹‹አስራ ስምንት እየተጠጋት ነው፡፡››
‹‹አስራ ስምንት?››
‹‹አዎ-ምነው?››

‹‹አይ 18 ዓመት ልጅ ያለሽ ሳይሆን አንቺ እራስሽ የአስራ ስምንት ዓመት ልጃገረድ ነው የምትመስይው፡፡››
‹‹ፎገርከኝ ማለት ነው…?አይዞህ አግባኝ አልልህም.. ቂጤን ደግመህ ለማየት እንጂ የትዳር ጥያቄ ልታቀርብልኝ እንዳልመጣህ አውቃለሁ?››
‹‹ከተመቸሺኝ የት ይቀራል..ግን ብዙ ዓመት በትዳር አሳልፈሻል ማለት ነው?››
‹‹አይ 6 ዓመት ብቻ ነው፡፡››
‹‹ገባኝ ከመጋባታችሁ በፊት ነው የወለዳችሁት ማለት ነው?››
‹‹አይደለም ለሟቹ መውለድ አልቻልኩም…›› ይሄንን ስትናገር ልብሷን አውልቃ ዕርቃኗን ቆማ ነበር..፡፡ በደብዛዛው ብርሀን ተያየን፡፡ ተንደርድሬ ከአልጋው ላይ በመነሳት ተለጠፍኩባት ፡፡ከዛ በኃላ ምን ልበላችሁ ሁለት ረሀብተኞች ተገናኝተው የሚፈጠረውን መገመት አይከብዳችሁም፡፡ሀይሚ ይብላኝልሽ ላንቺ እንጂ እኔስ የቅንዝር አምላክ በነፍስ ደረሰልኝ፡፡ስንት ሰዓት ፍትጊያው ተጠናቆ እንቅልፍ እንደወሰደን ትዝ አይለኝም፡፡ሁለታችንም በሌላ ቀን ተገናኝተን ስለመድገማችን እርግጠኞች ስላልነበርን ይመስለኛል ውልቅልቃችን እስኪወጣ ነው ስንጋልብ ያደርነው ፤የባነነው በራሳችን ጊዜ ነቅተን ሳይሆን በበር መንኳኳት ነበር
‹‹እማ..እማ ረፈደብኝ …ትምህርት ቤት ሄጄያለሁ›› በሰመመን ነው የሰማሁት፡፡ ብቻ ሁለታችንም በርግገን በድንጋጤ ከተኛንበት በመፈናጠር ወዲህ ማዶ እና ወዲያ ማዶ ካልጋው ወርደን ቆምን፡፡..እርቃናችንን ነን..ሁሉ ነገሯን እስክጠግብ በግልፅ አየኋት፡፡
‹‹አንተ ወይኔ ቅሌቴ!!! ››እያለች ወለሉ ላይ የተጣለውን ፓንቷን ከወደቀበት አንስታ ወደ ቁም ሳጥኑ ሄደች፡፡..ያ አደንዛዥ ቂጧ ሰንበር በሰንበር ሆኗል፡፡ጥፍሮቼን አየኋቸው…  አድገዋል፡፡እኔም  ከወለሉ ላይ ልብሶቼን ተራ በተራ በመለቃቀምና በማራገፍ መልበስ ጀመርኩ፡፡ ሁለታችንም እኩል ጨረስን፡፡
‹‹በይ ቸው መስኮቱን ክፈቺልኝ ››አልኳት፡፡
‹‹እሱማ ጊዜው አለፈ ..አሁን አይሆንም፡፡››
‹‹ታዲያ ታግቼ መዋሌ ነዋ?››
‹‹እዚሁ ቆየኝ… ሰራተኛዋን ሱቅ ልኬያት ልምጣና በፊት ለፊት በር ትወጣለህ፡፡››ብላኝ የመኝታ ቤቱን በራፍ ከፍታ ወጣችና በላዬ ላይ ጠርቅማብኝ ሄደች፡፡ እኔም አልጋው ጠርዝ ላይ አረፍ ብዬ ማሰብ ጀመርኩ‹‹አቤት ይህቺን ሴትማ መደጋገም አለብኝ..እርግጥ አሁንም ስሜቴ ያለው እዛችው ግትሯ ሀይሚ ጋር ነው… ቢሆንም ግን…፡፡››
በራፉ ተከፈተ‹‹ያው ውጣ››አለችኝ ፡፡ወጣሁ.. ተከትያት ሳሎን ገባሁ…. ወደ መውጫው በር ሳመራ‹‹ቁጭ በል እንጂ …ያልጋ መውረጃ ቁርስ በልተህ ትሄዳለህ፡፡››
‹‹ሰራተኛሽ ተመልሳ ብትመጣብኝስ?››
‹‹ትምጣ..አሁን ነው የመጣሀው..የሟች ባሌ ጓደኛ የነበርክ…አሁን ልትጠይቀኝ የመጣህ እንግዳ ነህ..በቃ ምን ችግር አለው?››
‹‹እሱስ ችግር የለውም፡፡››
ወደ ጓዲያ ሄደች..ቁጭ አልኩ፡፡ ሳሎናቸው ሰፊ ነው የሟች ባሏ ፎቶ ፊት ለፊት ግድግዳ ላይ ተንጠልጥሏል፡፡ የሚያምር ደልዳላ ሰው ነበር፡፡ኸረ ሌላም ፎቶ አየሁ ተስፈንጥሬ ከመቀመጫዬ ተነሳሁና ተጠጋሁት ፡፡ባየው ባየው ያልገባኝ ፎቶ ‹‹ምነው?››አለችኝ በአንድ እጇ ትኩስ እንቁላል ፍርፍራ በሌላው ሁለት ብርጭቆ ሻይ በሰርቢስ ይዛ‹‹ይህቺ ልጅ….?››
‹‹አዎ ልጄ ነች፡፡››
‹‹ሀይማኖት ልጅሽ ነች?››
‹‹ሀይማኖት…!!! ታውቃታለህ?››ቀይ የነበረችው ሴትዬ በሽርፍራፊ    ሰከንድ ጭላሼት ለበሰች፡፡
‹‹እኔ እንጃ፡፡››
‹‹እንዴት እኔ እንጃ?››
‹‹የእሷ ጓደኛ የጓደኛዬ እህት ነች ….እዛ ቤት አብረው ሲመጡ        አውቃታለሁ፡፡››
‹‹ሁፍፍፍ..እንዴት አስደነገጥከኝ መሰለህ፡፡››
‹‹ለምን ደነገጥሽ?››
‹‹እንዴ ምን ይታወቃል…የዛሬ ልጆች እኮ የት እና ከማን ጋር          እንደሚውሉ መገመት ከባድ ነው…፡፡››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው.. እኔም ጉድ ሆኜያለሁ፡፡››
‹‹እንዴት ?››
‹‹ያንቺን  ቂጥ  አፍቅሬ  ነዋ፡፡››በማለት  አስቀየስኩ፤ 
‹‹የአንቺን  ልጅ አፍቅሬ፡፡›› ለማለት ነበር የፈለግኩት፡፡
ቁርሴን በላሁና ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ ፤ ቀጥታ ወደቤት ነው የሄድኩት፡፡ ሰውነቴ ድክምክም ውስጤም እርብሽብሽ ብሎብኛል፡፡አሁን እንዴት ነው የማደርገው..? የእኔ እና የሀይሚ ጉዳይ አበቃለት ማለት ነው ? ልብሴን ማወላለቅ ጀመርኩ … ኪሱ ቆረቆረኝ … እጄን ስሰድ ያልተከፈት ሁለት እሽግ ኮንደም፡፡ልቤ ትርትር አለ፡፡ሌላኛው ኪሴ ገባሁ፡፡ አዛም እንደታሸገ፡፡ ማታ ማሰቢያ ጭንቅላቴን እቤት ነበር እንዴ ረስቼው የሄድኩት….? እንዴት ኮንደም በኪሴ እንዳለና መጠቀም እንዳለብኝ ለማስታወስ ሚሆን ሜሞሪ አጣለሁ.... ? ወይ ንዴት!!!ወይ ስካር!!! ወይ መስገብገብ!!! ውጤቱ እንዲህ ይሁን?
ወይ እኔ…!!!ወይ ሀይሚ..!!!ወይ ቂጣሟ…!!!

ተጠናቀቀ

ነገ በአዲስ ታሪክ እንገናኛለን

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...
ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

አትሮኖስ

18 Dec, 17:00


‹‹ጐሽ ስለዚህ ትጠብቀኛለህ ማለት ነው…?›› ብላ ከመቀመጫዋ ተነስታ በስሱ እና በስስት ከንፈሬን ስማ እንድሸኛት ጠየቀችኝ፡፡እኔም እንዳለቺኝ አደረግኩ፡፡በቃ ተመለስ እስክትለኝ ድረስ ሸኘኋት…፡፡ተመለስኩና የቀረውን ወይን በንዴት መጠጥኩት..ምጥጥ አድርጌ ሳጠናቅቅ 12 ሰዓት ሆኖ ነበር፡፡አልጠገብኩም… ፡፡ቤቴን ዘግቼ ወጣሁና ሰፈራችን ከሚገኘው ግሮሰሪው ተሰየምኩ፡፡ቢራ አዘዝኩ ፡፡ሁለት ሰዓት ሲሆን ጥግብ አልኩ..ጥግብ አልኩና ስልኬን በማውጣት ደወልኩ.. ባለቀይ ቂጥ   ባለቤቷ ጋር፡፡

‹‹ሄሎ፡፡››

‹‹ሄሎ ማን ልበል?››

‹‹የምን ማን ልበል ነው… ? ምንድነው ምትረብሺኝ፡፡››አንቧረቅኩባት፡፡

‹‹ይቅርታ የተሳሳትክ መሰለኝ፡፡››

‹‹አልተሳሳትኩም ባክሽ፡፡››

‹‹እና አላወቅኩህማ፡፡››

‹‹እኔም እኮ አላውቅሽም..ቂጥሽን ግን… ወይ ቂጥ›› 

ሳቋን አንጣረረችው‹‹አንተ ጉደኛ..አንተው ነህ?››

‹‹አዎ እኔው ነኝ..ፈፅሞ ልረሳው እኮ አልቻልኩም፡፡››

‹‹እሱማ እኔም ደግመህ እያየኸኝ እየመሰለኝ አስሬ እየተገላመጥኩ  ኃላ ኃላዬን ሳይ ነው የዋልኩት.. አሳቀቅከኝ፡፡››
‹‹አትይኝም..ታዲያ ደግመሽ ለምን አታሳይኝም?››

‹‹ኸረ ባክህ!!! ደግመህ ማየትም ያምርሀል..?በትክክል ድጋሚ ማየት ፈልገህ ቢሆን ኖሮማ ቀን ትደውልልኝ ነበር፡፡›› አለችኝ፡፡ ምን ታድርግ… ቀኑን በእንዴት አይነት መከራ ውስጥ እንዳሳለፍኩ አታውቅም….ሀይሚን በእጄ ይዤ እንዴት እሷ ጋር ልደውል አቅም ይኖረኝል፡፡ አሁንም ሀይሚ የጋተችኝ ንዴት እና በገዛ እጄ የተጋትኩት መጠጥ ናቸው ተባብረው ድፍረቱን የሰጡኝ፡፡ አይገርምም ግን ሀይሚና ይህቺ ባለቀይ ቂጧ ያላቸው  ልዩነት..ፍጹም ተቃራኒ ናቸው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose



ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...
ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

አትሮኖስ

18 Dec, 17:00


#ወይ_አጋጣሚ(አጭር ልብወለድ)


#ክፍል_ሁለት


#ድርስት_በዘሪሁን
==========================
ቢሆንም ቅንዝሬ ያው ቅንዝር ነውና ጆሮው የተደፈነ ነው፤የእኔ እና የእሷን ምክንያት አያዳምጥም ፡፡ስለዚህ እመክረው እመክረውና…ከዛም ደግሞ እለምነው እለምነው እና በቃ ከአቅሜ በላይ ሲሆን  እንደነርኳችሁ በወር አንዴ በደሞዝ ሰሞን ወደ አብረቅራቂ መብራት ወደሚንቦገባግባቸው የለሊት ቤቶች ጐራ እላለሁ ፡፡ እንደዛም ሆኖ ግን ልቤ ለሀይሚ እንዳላዘነ ነው፡፡ዛሬ ግን እፎይ ልገላገል ነው ፡፡ሀይሚ እቤት ለመምጣት ከስድስት አታካች ወራቶች ጭቅጭቅ በኋላ ተስማምታለች፡፡ከቀኑ 8 ሰዓት ነው የምትመጣው፡፡እኔ ግን ከእንቅልፍ የባነንኩት ከለሊቱ 8 ሰዓት ነው፡፡ለዝግጅት፡፡እውነቴን ነው እኮ ፡፡ገና እቤት ማዘጋጀት አለ፣ዕቃ ማጣጠብ አለ፣አልጋ በስርአት ማንጠፍ አለ፣ለፍቅራችን ማጀቢያ ሙዚቃ መምረጥ አለ፣ደግሞ እኔም እንድደፍራት እሷም እንድትደፈርልኝ የሚያግዝ መጠጥ ማዘጋጀት አለ፣አረ ስንቱ….፡፡

ደግሞ አይገርማችሁም ዛሬ ሀይሚ ቤት ልትመጣ ትናንትና ቂጣሟን ማግኘቴ….፡፡ ማግኘቴ ብቻ ሳይሆን እቤቷ ድረስ መከተሌ..ከዛም አልፎ ስልክ ቁጥሯን መቀበሌ..፡፡አሁን ልደውልላት እንዴ….? የሚል ሀሳብ መጣብኝ ፡፡መልሼ ሀሳቤን ውድቅ አደረግኩት ::ለሀይሚ ያለኝን ታማኝነት ዝቅ ማድረግ ነው:: አይደለም መደወል …ቢቻል በምናቤ ተንጠልጥሎ አልወርድ ያለኝን የቂጧን ምስል አሽቀንጥሬ መጣል ብችል ደስ ይለኝ ነበር፡፡እንደቀጠሯችን ምንም ሳታረፍድ ከቀኑ 9 ሰዓት ሀይሚ መጣች..ያው አንድ ሰዓት ዘገየች ማለት አረፈደች ተብሎ መደምደም የለባትም ብዬ ነው፡፡ አለባበሷን ልግለጽላችሁ፣ቡትስ ጫማ፣ጥብቅ ያለ ጅንስ ሱሪ፣በሱሪው ላይ ቁርጭምጭሚቷ ጋር የሚጠጋ ቀሚስ፣በቀሚሱ ውስጥ ደግሞ ሱሪዋ በቀበቶ የተጠፈረ መሆኑን በሚታየው የቀበቶ ቅርፅ ማወቅ ይቻላል፣ከላይ ደግሞ ግብዳ ሹራብ ደርባለች፡፡
ጉንጯን እያገላበጥኩ እየሳምኩ ቢሆንም አይኖቼን ግን ሰማዩ ላይ አንጋጥጬ እያንከራተትኩ ነው፡፡ሀሞቴ ፍስስ ነው ያለው፡፡አሁን እሺ ብላ እንድናደርግ ፍቃዱን ብትሰጠኝ ..ይሄን ጫማዋን ፈትቼ እስካወልቅ አንድ ሰዓት፣ሱሪዋን እስካወልቅ ሌላ አንድ ሰዓት፣ምን አልባት ከሱሪዋ ስር ታይት፣ከታይቱ ስር ደግሞ ሁለት ወይም ሶስት ፓንት ታጥቃ ሊሆን ይችላል..? ታዲያ መሽቶ ነጋ ማለት አይደል?፡፡

ወደ ቤት ዘልቃ ቁጭ አለች፡፡ቁጭ አባባሏ እራሱ ሲያበሳጭ፡፡ ከጓዲያ ወጥቶ ማጅራቷን አንቆ የሚውጣት ዳይኖሰር ያለ ይመስል በራፉ ጥግ የሚገኝ ኩርሲ ላይ ተቀመጠች፡፡ፈርጥጣ ለመውጣት እንዲያመቻት ይመስለኛል፡፡ ደግሞ እሷ ብቻ ሳትሆን እኔም አበሳጫለሁ ፤ ምን አለበት ከመምጣቷ በፊት እቤቴ ያሉትን መቀመጫቸው ሁሉ ሰብስቤ ጓዲያ አስገብቼ ቢሆን ኖሮ ምርጫ ስታጣ አልጋ ላይ መቀመጧ አይቀርም ነበር፡፡

‹‹ሀይሚ ..ምነው በራፍ ላይ….. ?አልጋው አይሻልሽም…?››

‹‹አይ መጣለሁ  ብዬህ እንዳልቀር ነው እንጂ …እሄዳለሁ፡፡››

‹‹ወዴት?››

‹‹ወደቤት ነዋ…እናቴ ስራ አዛኝ ነበር ….ተደብቄ ነው የመጣሁት››ብላኝ እርፍ፡፡

ይታያችሁ ሰው አሁን ይህቺን ያፈቅራል...?ከለሊቱ 8 ሰዓት እስከ ቀኑ 9 ሰዓት ፍዳዬን ስበላ ቆይቼ እሷ ግን ገና መጥታ ሳትጨርስ ልሄድ ነው ትላለች፡፡ቀኑን ሙሉ እሷን እያሰበ ሲወጣጠር የዋለውን እንትኔ ወዲያው ልፍስፍስ ብሎ ሲሸበለል ይታወቀኛል፡፡ችላ አልኳት እና ወደ ጓዲያ ገብቼ የሰራሁትን ምግብ በማምጣት ጠረጴዛ ላይ ደረደርኩት፡፡ ወይኑንም አወጣሁ..አሁን የምግብ ጠረጰዛው አልጋውን ተጠግቶ ስለሚገኝ ምርጫ የላትም መጥታ አልጋው ላይ ከጐኔ መቀመጧ አይቀርም ፡፡

‹‹ሀይሚ ነይ ምሳ እንብላ ፣እርቦኛል..እስከአሁን እኮ አንቺን ስጠብቅ አልበላሁም፡፡››

‹‹እኔ እኮ በልቼያለሁ፡፡››አቤት ወሽመጥ ስትቆርጥ፡፡

‹‹ባክሽ አታበሳጪኝ..በስንት ጣጣ  መጥተሸ ደግሞ..?›› ተኮሳተርኩ፡፡ እንደመደንገጥ አለችና መጣች፡፡ እንዴት መጣች አትሉኝም…? ኩርሲዋን ይዛ በመምጣት ከአልጋው ራቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ ምርጫ አልነበረኝም፤ እጇን አስታጠብኳት ፤ወይኑን ስቀዳ‹‹ለእኔ እንዳትቀዳልኝ››አለችኝ እየተንዘረዘረች፡፡ መርዝ ልቀዳላት የተዘጋጀው አስመሰለችው፡፡

‹‹አንድ ብርጭቆ ብቻ››ተለማመጥኳት፡፡
‹‹አንድ መለኪያም አልጠጣም..እንድበላ ከፈለክ በውሃ ቀይርልኝ…›› ለወራት ተጨንቆ የቀየሰው የጦርነት እስትራቴጂ ፍርክስክሱ እንደወጣበት የጦር ጄኔራል ሞራሌ ድቅቅ አለበኝ፡፡ለንቦጬን ጣልኩ …ያለችውን አደርግኩ፡፡

እየተጐራረስን በፀጥታ በልተን ጨረስን፡፡እኔ የእሷንም ፋንታ የምጠጣ ይመስል እንደውሃ እጋተው ጀመር ፡፡ እንደጨረስን የተበላበትን ዕቃ አነሳሳሁ..እጇን አስታጠብኳት እና እኔም ታጥቤ  ወደ ቦታዬ ተመለስኩ፡፡

ልክ ምሳዋን ለመብላት የመጣች ይመስል…‹‹ልሂድ በቃ፡፡›› አለችኝ፡፡

‹‹ቆይ ማውራት አለብን፡፡››

‹‹ምንድነው የምናወራው?››

‹‹ስለፍቅራችን ነዋ፡፡ ››

እንደመደንገጥ ብላ‹‹ፍቅራችን ምን ሆነ ?››አለችኝ፡፡

‹‹እስከአሁን ምንም አልሆነ …ካላወራንበት እና መፍትሄ ካላበጀንለት ግን መሆኑ አይቀርም.››ወይኑን በደረቁ እየለጋሁት ስለሆነ በድፍረት የመናገር ወኔዬ ሙሉ ነው፡፡

‹‹እሺ ፈጠን በልና እናውራበት››

‹‹ታፈቅሪኛለሽ?››

ግራ በመጋባት‹‹ምን ማለት ነው?››

‹‹ታፈቅሪኛለሽ ወይ?››ደግሜ ጠየቅኳት፡፡  

‹‹በጣም አፈቅርሀለሁ፡፡››
  ‹‹ካፈቀርሺኝ …ዛሬ ፍቅር እንድንሰራ እፈልጋለሁ፡፡››

‹‹ፍቅር እየሰራን አይደል እንዴ?››

‹‹እንደ እሱ አይደለም..ልብስሽን አወላልቀሽ..እኔም ልብሴን አውልቄ… እዚህ አልጋ ላይ ወጥተን ምናምን ማለቴ ነው… በጣም አምሮኛል…ስንት ወር ነው የምሰቃየው…?››ብሶቴን ተረተርኩት፡፡

‹‹እሱማ አይሆንም፡፡››

‹‹ለምን አይሆንም?››

‹‹አፈቅርሀለሁ… ግን ጊዜው አሁን አይደለም…ገና 18 ዓመት እኮ አልሞላኝም፡፡ በዛ ላይ የሃይእስኩል ትምህርቴንም አልጨረስኩም፡፡››

‹‹ስንት ዓመትሽ ነው?››

‹‹17 ዓመት ከ11 ወር…››

‹‹እና ታዲያ ሰው ለሚወደው እንኳን አንድ ወር ይቅርና አንድ ዓመትስ ቢያጭበረብር ምን አለበት?››

‹‹እንደ እናቴ መሆን አልፈልግም፡፡››

‹‹እንዴት እንደ እናትሽ?››

‹‹እሷም 10ኛ ክፍል እያለች ነው እኔን ያረገዘችው፡፡በዛ የተነሳ ትምህርቷን አቋርጣ ብዙ ስቃይ ተሰቃይታለች፡፡ ብዙ ብዙ መከራ ካሳለፍን በኋላ ነው በቅርቡ ህይወታችን የተስተካከለው፡፡››

‹‹እኔ እኮ ብታረግዢም አፈቅርሻለሁ..ማለቴ አገባሻለሁ፡፡››

‹‹አባቴም እሷን እንደዛ ነበር የሚላት…፡፡የእውነት እንዳረገዘች ስትነግረው ግን የራስሽ ጉዳይ ነበር ያላት፡፡››

‹‹እሺ በቃ በኮንዶም እንጠቀም..ህይወት ትረስት፣ሴንሴሽን፣ሜምበርስ ኦንሊ… የፈለግሽው አይነት አለ፡፡››

‹‹እንዴ ዲኬት ነው እንዴ የምትሰራው…? ይሄ ሁሉ ኮንደም ምን ልታደርግ ሰበሰብከው…?››ያላሰብኩትን መስቀለኛ ጥያቄ ጠየቀችኝ፡፡

‹‹ባክሽ አንድ ዲኬት የሚሰራ ጓደኛዬ ነው አምጥቶ ለማንኛውም እያለ ቤቴ የሚያስቀምጠው፡፡››

‹‹ጥሩ…. ግን ድንግል ነኝ… ድንግልናዬን ደግሞ በኮንደም አላስወስደውም፡፡››

‹‹እኔ እኮ ድንግልናውን አልፈልገውም..፡፡››
‹‹……እና አውልቄ ላስቀምጠውና ተጠቅመህ ከጨረስክ በኃላ መልሼ ላጥልቀው?››ንግግሯ ከማበሳጨትም አልፎ አሳቀኝ፡፡

‹‹እና ምንድነው መፍትሄው?››

‹‹ምታፈቅርኝ ከሆነ ጠብቀኝ?››
‹‹እሱማ አፈቅርሻለሁ፡፡››

አትሮኖስ

17 Dec, 17:40


#ወይ_አጋጣሚ(አጭር ልብወለድ)


#ክፍል_አንድ


#ድርሰት_በዘሪሁን
==========================
ዛሬ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ድክምክም ብሎኛል፡፡ብዙ ስራ እየሰራሁ ስለዋልኩ አይደለም..እንደውም በተቃራኒው ስቀመጥ ስለዋኩ ይመስለኛል ዛል እስክል የደከመኝ፡፡ ‹‹መቀመጥ መቆመጥ ነው››ትል ነበር አንድ ኑሮዋ ጠቅላላ ተረት በተረት የሆነባት ተራች አክስቴ፡፡ ሰዓቱ 12፡35….ሆኗል ፡፡ምሽቱ ደረስኩ እያለ ነው፡፡ስቀመጥ ከዋልኩበት ቢሮዬ ለሊቱን ስተኛ ወደማሳልፍበት ቤቴ ቀጥታ ማምራት ስላልፈለግኩ ለምን ትንሽ ወክ አላደርግም አልኩና ወደ ቤቴ አቅጣጫ በጣም በዝግታ ማዝገም ጀመርኩ፡፡እርምጃዬ ጽሞና የታከለበት እንዲሆን ስለፈለኩ ዋናውን የአስፓልት መንገድ ለቀቅኩና በሁለተኛው መንገድ መጓዝ ጀመርኩ.፡፡እሱም በባጃጅና በመንገደኛ ሰዎች ስለተሞላ አልተመቸኝም ወደ 3ተኛው መንገድ ተሸጋገርኩ፡፡አዎ ይሄ ይሻላል.. እሬሳን ወደ የዘላለም ማረፊያው ወደ ሆነው ቀብሩ እንደሚሸኝ ሰው ወይም በመንግስት ወታደሮች እጅ ወድቆ እጁ በሰንሰለት ወደኃላ እንደተጠፈረ አሸባሪ ተብዬ እጆቼን ወደኃላ አጣምሬ በዝግታና በፀጥታ እጓዛለሁ፡፡አካባቢው ፀጥ ያለ ነው፡፡አዕምሮዬ ግን በጫጫታ የተሞላ ነው፡፡ዝም ብሎ ህልሙንም እውኑንም ይፈተፍታል፡፡

ድንገት ከአንዱ መንገድ ተጠምዝዤ ወደ አንዱ ስገባ ዓይኔ አየ.. ምን ዓየ …..?አትሉኝም፡፡ልክ ለዘመናት እንደተራብኩት የእናቴ ጡት ዓይነት ነገር፣ልክ በፀሎት እና በእምነት አማኞች እንደሚናፍቆት ገነት ዓይነት ፣ልክ ፖለቲከኞች ለዘመናት ይመኙት እንደነበረው የቤተ መንግስት ወንበር ዓይነት… አይገርምም…፡፡ ያየሁት እኮ አሁን እንደጠቀስኩላችሁ ዓይነት ነገር ሆኖ አይደለም..እኔን ግን ውስጤን የተሰማኝ…በወቅቱ አደነዛዘዜ ፤ አደነጋገጤ እንደዛ ነው ያስመሰለብኝ፡፡ …ወፈር ደልደል ያለ ቀይ ቂጥ ነው ያየሁት..….ያየሁት ከገባሁበት መንገድ በግራ ጠርዝ በኩል በግምት 100ሜትር ርቀት ላይ የቀበሌውን ጽ/ቤት አጥር ተጠግቶ ነው፡፡እኔ ያልኳችሁ ፍም ቂጥ ብቻ አየሁ አይደል..?ግን የዘነጋሁት ወይም ያልነገርኳችሁ አንድ ነገር የቂጡንም ባለቤት ማየቴን ነው፡፡ግራ ቀኝ ስታማትር እሷም እኔን አይታኛለች፡፡ግራ የተጋባች ይመስላል፡፡የለበሰችውን ቡኒ ጅንስ ሱሪ አውልቃ ጉልበቷ ጋር አድርሳዋላች ፣በእርቃን ቂጧ እና ወልቆ ጉልበቷ ጋር በደረሰው ሱሪዋ መሀከል ሆኖ የሚዋልል ሌላ ቀይ ነገር ይታየኛል..አዎ ፓንቷ ነው ፡፡ ግራ ገብቷት ወይም የራሱ ጉዳይ ብላ መሰለኝ ችላ አለቺኝና ቁጢጥ አለች፡፡
እኔም የእራሴው እርቃን በአደባባይ እየታየብኝ ያለ ይመስል ሽምቅቅ ብዬ የ100 ሜትሩን ርቀት ወደ 70 ሜትር ካጠበብኩት በኃላ ቆምኩ፡፡..በቃ  ዝም  ብዬ  ቆምኩ፡፡ ቆሜም  ማሰላሰል  ጀመርኩ፡፡ እሷም አንዴ ወደ መሬት አንዴ ወደ እኔ እያች የኩላሊቷን ጥዝጣዜ ና የፊኛዋን ውጥረት ማስተንፈስ ቀጠለች….‹‹ሾሾ… ሾ… ዋዋ›› የሚል የሽንት ድምፅ ተሰማኝ..፡፡እርግጠኛ ግን አይደለሁም፡፡ ብቻ የሰማሁ መስሎኛል፡፡
ግን በፊት ቅምቅም አያቶቻችን ለወንድ ሱሪ ለሴት ቀሚስ የሚባል ልብስ ለምን እንዲኖር እንዳደረጉ ዛሬ ነው ፍንትው ብሎ የገባኝ.፡፡ይሄኔ እኮ ይህቺ ሚስኪን ሴት ቀሚስ ለብሳ ቢሆን ኖሮ እሷም አትጋለጥም.. እኔም አልደነግጥም ነበር፡፡ቁጭ ብላ ቀሚሷን ገለብ ታደርግና ‹ሾዋ..ዋ…ዋ› በማድርግ ከተነፈሰች በኃላ ምንም እንዳልተፈጠረ ተነስታ ትሄድ ነበር፡፡
ወይ..ሀሳቤን ሳልጨርስ ጨርሳ ቆመች፡፡ፊቷን ከእኔ በተቃራኒው  አዞረችና መጀመሪያ ቀዩን  ፓንቷን ወደ ላይ ስባ  ቀዩን ቂጧን ሸፈነችው፤  አቤት  በፓንትም  ሲታጠር  ያምራል፣ምራቄን  ገርገጭ አደረግኩ፡፡ ከዛ ሱሪዋን ወደ ላይ እየጎተተች ለበሰች፡፡ከጨረሰች በኃላ ቀጥታ ወደ እኔ አቅጣጫ መጣች፡፡ግራ ገባኝ፡፡ ወደ ኃላ ልመለስ ወይስ ወደ ፊት ልቀጥል…?፡፡ከሁለቱ እግሮቼ የትኛውን ላስቀድም?፡፡ እያልኩ በሀሳብ እየተጨነቅኩ ስዋልል እሷ ቀድማኝ ስሬ ደረሰች፡፡አትኩሬ አየኋት… ቂጧም ብቻ ሳይሆን መልኳም ቀይ ነው፡፡የሆነ ክልስ ነገር ሳትሆን አትቀርም…፡፡ፈርዶብኝ ቀይ ሴቶች ልቤን በቀላሉ ብትንትን ያደርጉታል ፡፡ፍቅረኛዬ ሀይሚም እንደዚህችው ነች፡፡ ዓይኖቾ ጐላ ጐላ ያሉ ባለ ሉጫ ፀጉር ነች..፡፡አደንዛዥ ፈገግታ መግባኝ ታካኝ አልፋኝ ሄደች፡፡ እኔም ቀኝ ኃላ ዞሬ ተከተልኳት፡፡ ውሳኔዬ እሷን መከተል እንዲሆን ያስገደደኝ የቂጧ ቀይነት ይሁን የፈገግታዋ ጉዳይ አልገባኝም፡፡ደረስኩባት እና ዝም ብዬ ከጎኗ መራመድ ጀመርኩ፡፡
ግራ ገባቷት‹‹እንተዋወቃለን?››አለቺኝ፡፡

‹‹አሁን ተዋወቅን አይደል እንዴ?››መለስኩላት፡፡

‹‹አሁን የት ?››

‹‹እዛ ነዋ.. እኔ ፈዝዤ ተገትሬ አንቺ ቁጢጥ ብለሽ፡፡››

ከት ብላ ሳቀች… ሳቋ ያምራል‹‹…ጉደኛ ነህ!!! ትንሽ እንኳን አታፍርም እንዴ..?እኔስ ተጨንቄ ነው አንተ ምን አለ ዞር ብትልልኝ  ኖሮ?››

‹‹ወዴት ዞር ልበል..?ከተጠጋሁሽ እኮ ይበልጥ አይሻለሁ ብዬ ነው  የቆምኩት፡፡››

‹‹ዞረህ በሌላ መንገድ አትሄድም እንዴ?››

‹‹አኸ እንደዛም ይቻል ነበር ለካ..?እሱ እንኳን ትዝ አላለኝም፡፡››

‹‹ደንዝዘህ እንዴት ትዝ ይልሀል..?ወይ ወንዶች ስትባሉ!!!›› አለችኝ፡፡ይህቺን‹ ወይ ወንዶች ስትባሉ!!! › ቢያንስ ከ100 ሴቶች ሰምቼያታለሁ ፡፡ግን ወንዶች ስንባል እንዴት ነን..? ያው እንደዛ የሚሉን ሴቶች እራሳቸው ይመልሱት ፡፡

‹‹ግን ያምራል›› አልኳት፡፡

የድንጋጤም የእፍረትም ሳቅ እየሳቀች‹‹ምኑ?›› አለችኝ፡፡

‹‹ያየሁት ››አልኳት… አኔም በተራዬ እንደማፈር ብዬ፡፡

‹‹የትኛውን አይተህ የትኛውን እንደዘለልክ በምን አውቃለሁ?›››

‹‹ከወርቃማዋ ሸለቆሽ በስተቀር ሁሉንም አይቼያለሁ››

አቤት የሳቀችው ሳቅ… እንባዋ እስኪንጠባጠብ ነው ተንፈራፍራ የሳቀችልኝ፤ሴት  ልጅ  እንደዚህ  ስትስቅልኝ  ለመጀመሪያ  ጊዜ ይመስለኛል፡፡ ባይገርማችሁ ከቤቴ መንገድ በተቃራኒው ይህቺን ባለ ቀይ ቂጥ ሴትዬ ተከትዬ ለ24 ደቂቃ ተጉዤያለሁ፡፡

‹‹ምትገርም ልጅ ነህ ..ለማንኛውም የምሄድበት ቦታ ደርሼያለሁ በዚህ ነው የምጠመዘዘው፡፡ ››

‹‹እንዴ!!! እኔስ?›› አልኳት ደንግጬ፡፡

‹‹አንተ ምን..?ወደምትሄድበት ሂዳ፡፡››

‹‹የምሄደውማ ወደ ቤቴ ነበር …ቅድም እሄድበት በነበረው አቅጣጫ፡፡››

‹‹በል እንግዲህ የቂጥ አምላክን እየረገምክ ቀኝ ኃላ ዙርና ንካው›› አለችኝ፡፡

‹‹ስልክ ቁጥርሽን ስጪኛ?››

‹‹ምን ልታደርገው?››

‹‹በቃ እንዲሁ፡፡››

‹‹ባለትዳር ብሆንስ?››የማልመልሰውን ጥያቄ ጠየቀችኝ፡፡

‹‹ሁኚያ..እኔ እንዲሁ ነው የፈለኩት አልኩሽ እኮ፡፡›› እንዲሁ መፈለግ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ብትጠይቀኝ ግን መልስ አልነበረኝም፡፡

‹‹ሁላችሁም ወንዶች በመጀመሪያ እንዲሁ ነው የምትፈልጉት በኃላ እንጂ ነገር የምታመጡት፡፡››

‹‹ኸረ እንዲሁ ነው ስጪኝ፡፡››በአሳዛኝ ሁኔታ ተለማመጥኳት፡፡

እያጉረመረመች ሰጠችኝ፡፡ተሰናበተኳትና እንዳለቺኝ ቀኝ ኃላ ዞሬ ወደቤቴ ነካሁት፡፡
ለሊቱን ሙሉ የቂጧ ምስል በህልሜ ሲመላለስ እና ሲያሰቃየኝ አደረ፡፡ ምን ነካኝ ግን ?ፍቅር ሊይዘኝ ይሆን እንዴ? ኸረ አይደረግም…፡፡ ቢያንስ በ10 ዓመት እኮ ትበልጠኛለች፡፡ ግን ይሄ ምን ችግር አለው? ከስድስት ወር በፊት የጠበስኳት ቀሚ ፍቅረኛዬ የሆነችውን ሀይሚን በ10 ዓመት እበልጣት የለ?አንዷን እበልጣታለሁ አንዷ ደግሞ ትበልጠኛለች..በቃ ማቻቻል ማለት እንዲህ ነው፡፡

አትሮኖስ

17 Dec, 17:40


ደግነቱ በማግስቱ ቅዳሜ ነው፡፡ ቅዳሜ ደግሞ ሀይሚ እቤቴ እንደምትመጣ ቃል ገብታልኛለች፡፡መቼስ እንዲህ ስላችሁ ታድለህ ሁል ጊዜ በሳምንቱ መጨረሻ የረፍት ቀንህን እየጠበቀች ፍቅረኛህ እቤትህ ስለምትመጣልህ በደስታ አለምህን ትቀጫለህ ብላችሁ አስባችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ ግን በጣም..በጣም ተሳስታችኋል ፡፡ አይደለም በሳምንት ልትመጣ በስድስት ወር የፍቅረኝነት ጉዞችን ካፌ እንኳን አስቀምጬ ለመጋበዝ ከእሷ ፍቃድ ያገኘሁት ከ3 ቀን   ለማይበልጡ ቃናቶች ብቻ ነው፡፡… በቃ ፍቅራችን በአብዛኛው በስልክ ነው…. በሚሴጅ እና በቻት….ቀላል ሞዛዛ መሰለቻችሁ..፡፡

..ይሄ የእሷ ባህሪ ግን አንድ ወሳኝ ጥቅም አለው መሰለኝ፡፡ ወጪ በመቆጠብ… ፡፡የእኔ ጓደኞች በሳምንት አንድ ቀን ፍቅረኛቻቸውን ለመጋበዝ በሳምንት 3 ቀን ምሳ እንደሚዘሉ አውቃለሁ፡፡ ካለ በለዚያማ ያቺ ሚጢጢዬ ከመንግስት ሚወረውርላቸው ደሞዝ ተብዬ ክፍያ እንዴት ትበቃቸዋለች..?ውይ እረስቼው፡፡እኔም ለካ ሀይሚን በመጋበዝ ምንም የማወጣው ወጪ ባይኖርብኝም በወር አንድ ቀን ደሞዝ በምቀበልበት ሰሞን እንትን ስለሚያምረኝ..ሀይሚም እሺ ብላ ስለማትሰጠኝ ግዢ ወጣለው፡፡
የዛን ቀን ታዲያ የደሞዜን ግማሽ አስረክቤ እመለሳለው፡፡ ይሄኔ አመንዝራ..ባለጌ …ፍቅረኛ እያለህ.. ኃጥያት አይደለም? ብላችሁ በሆዳችሁ አምታችሁኝ ይሆናል? ታዲያ ምን እንዳደርግ ትጠብቃላችሁ ?ፍቅረኛ ቢኖረኝ እምቢኝ ካለችኝ በግድ አልደፍራት፡፡ሀይሚ እኮ ማለት ምግብ ቤት ግድግዳ ላይ ተለጥፎ የሚታይ የፍራፍሬ ፖስተር ማለት ነች፡፡ለማስጐምዠት አገልግሎት ብቻ የተፈጠረች፡፡ አስገድጄ …ብፈልግስ የት አግኝቼት… ?መንገድ ላይ አላደርገው፡፡ እሷ እንደሆነ ከእኔ ጋር በባዶ ቤት ላለመገናኘት የምታደርገው ጥረት ልነግራችሁ አልችልም፡፡ጥሩነቱ የእሷም ሰበብ እንደአለማለቁ የእኔም ትዕግስት አያልቅም.፡፡.እወዳታለሁ…፡፡ በጣም ነው የማፈቅራት፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


የጣት ቁስልድርሰት #በአብርሃም_ቃሉ በቀጣይ የማቀርበው ድርሰት ይሄ አሁን የጀመርነው አጭር ታሪክ ሲያልቅ መልካም ምሽት



ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...
ቢያንስ ገባ ብላችሁ እዩት..ይመቻቹ

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

አትሮኖስ

16 Dec, 09:55


ZOO አዲሱ የX-Empire ፕሮጀክት...

🦧| ምትሰበስቡት ነጥብ ቀጥታ ወደ ቶክን ይቀየራል
🦓| ፕሮጀክቱ ለጥቂት ግዜ የሚቆይ ስለሆነ አያሰላቻም
🐊| አጨዋወቱ እንስሶችን በተሰጣችሁ Feed መመገብና Upgrade ማድረግ ነው
🦜| ብዙ ሰው ስላልበዛበት በግዜ ብትጀምሩ ይመረጣል

ለመጀመር 🦒👇
t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref405867113

አትሮኖስ

06 Dec, 21:19


Betty እባላለሁ እድሜ  23 ነው በጣም ቆንጆ  እና ለ kiss የሚገፋፋ ከንፈር አለኝ ስራዬ የ ሆቴል  አስተናጋጅ ነኝ
በምሰራበት ሆቴል በጣም ብዙ ደምበኞች ነበሩኝ  ቀኑን ባላስታውስም ወደ 2:30 አካባቢ ይሆናል ከደንበኞቼ አንዱ መኝታ ቤቱ ድረስ ቢራ እንዳመጣለት ይጠይቀኛል እኔም ቢራዉን ወሰድኩለት ክፍሉ ስገባ ግን ያልጠበኩት
see more....

አትሮኖስ

06 Dec, 21:06


ሴት ልጅ አንተን እንዳፈቀረችክ የምታቅበት 10 ምልክቶች ከታች #JOIN ብለክ ተተቀምበት እና ህዝቤ ሆይ ምን ትተብቂያለሽ ገብተህ አንበዋ😋😋😋😋
👇👇👇👇👇👇👇

አትሮኖስ

02 Dec, 21:18


ቤቲንግ ይጫወታሉ መበላትስ ሰልችቶታል እንግዲያውንሱ በነፃ ያለምንም ክፍያ በቀን ከ 50-150 odd የሚለቀቅበት ቻናል ልጠቁማቹ ይጠቀሙበታል ቻናሉን ከስር ያሉትን በመንካት ቶሎ ይቀላቀላሉ

አትሮኖስ

02 Dec, 21:07


Wallpaper ወይስ Profile ይፈልጋሉ? 😍

አትሮኖስ

02 Dec, 15:00


#መራራቅ
:
:
ቅዠታም አዳሩን ጨፍጋጋ ዉሎዉን
ዝብርቅርቅ ተስፋዉን ደረቅ ትዝታዉን
በይሉኝታ ከፈን እየጠቀለለ ከጥርሱ ሲጥለዉ
ተቀባይ ይሻማል ሳቅ እየመሰለዉ።

🔘በረከት በላይነህ🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

02 Dec, 09:00


#ትርጉም !
..
"አስቀያሚ፣
አሰጠሊታ ፣
መልከ  ጥፉ፤
እንደ ደሀ  ቀዬ መስቦችህ የረገፉ!

የማትባል  እዚህ ግባ ፣
የሰው ፍራሽ  ፣ ማማር አልባ!

ፊተ መአት ፣ ያመድ ክምር!
የጭራቅ ሳቅ  ያይጥ ፞ ድምር
              ባትታይም የማታምር! !!"

እረ !  ሌላም፣ ሌላም፣
ትልሀለች ብለው የነገሩኝ ለታ ፤
አቤት ሀሴት ፣ አቤት ደስታ!

ለምን ብትይ?

መልኬ ከሸለመሽ  የማይሽር ጥላቻ ፤
ደስታ  አሰከረኝ 'ስላየሺኝ' ብቻ

🔘በረከት በላይነህ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

02 Dec, 05:36


#እንደነገርኩሽ_ነው 
         
        አፍሽም ለብቻው - ስሙን እያወጣ ፣
        ጆሮሽም ለብቻው - ስሙን እያወጣ ፣
        ወየው ! ወየው ! እንጂ … ወዬ ! የሚል ታጣ

እግዜሩም! እንደ ሰው!
         ባለመስጠት ሞላ ፣ ከመስጠት ጎደለ ፤
         ብጠራው? ብጠራው? 'አቤት' አልል አለ ።
ማለትሽን ሰምቼ
… እኔ ምልሽ...
ምስኪን እግዜርሽን!
         ካመልሽ አዛምደሽ ፣ ከምትጠረጥሪው ፣
         እስቲ ቅፅሉን ተይና  በዋና ስም ጥሪው ።

ሰሚን ሲደልሉ !
ጠሪን ሲበድሉ !
ለግዜሩም! 'ቅፅል-ስም' አወጡለት አሉ ።

እናልሽ  . . .
በልጥፍጥፍ መአት ዋናው ገጽ ፈረሰ ፤
ስም አውጪው ቢበዛ አቤት ባይ አነሰ ።

ደግሞ . . .
አመሌን ! አመልሽን ! ለማያውቁ ሁሉ ፣
"ጠርቼው አልመጣም" ትይኛለሽ አሉ ።

         እሷ የስም ሀብታም !
         ትጠራው አታጣ ! ትሸኘው አታጣ !
እኔ ባለ አንድ ስም ― ምን ሰምቼ ልምጣ ?

         እሷ የስም ሀብታም !
         ስትገዛ በደርዘን ! ስትሸጥ በደርዘን !
ይኸው ከስረን ቀረን ― አንድ አንድ ስም ይዘን።

         ሰሚን ሲያጣጥሉ ― ጠሪን ሲያቃልሉ ፤
         ስም አምራቾች ሞሉት ― ጉራንጉሩን ሁሉ ።

      ]  የላክሽው ፎቶ አንሺ  [
በጥላሽ ከልሎ ፣ ባንቺ ብርሃን ኩሎ ፤
ፎቶ ነስቶኝ ሄደ ― ፎቶ አነሳሁ ብሎ ።

        ፓ!  ፓ¡  ፓ!  ካሜራ ¿  ...  ኧረረ ! !  ካሜራ ¡ ¡
                     በሌሉበት ሁሉ ማንሳት የማይራራ ¡
                     ሊያውም በክት ልብስ ጥለት አዛንቄ …
                     ሊያውም በጀግና ልብስ በኒሻን ደምቄ …

             ... … እያገላበጠ … …

     'ተዟዟርር' እያለ ― ሲያነሳኝ ሰንብቶ ፣
              በትኖልኝ ሄደ ― ልብስ የሌለው ፎቶ ።
                      ካሜራሽ ስልጡኑ ¡ ካንቺ እኩል ያወቀ ¡
                                  ፎቶ ያጥባል ! አሉኝ … ልብስ እያወለቀ ።

እንደነገርኩሽ ነው ።

              የማንም ያልሆነን ― ያንተ ነው ተብዬ ፣
              በምስልሽ ፈንታ ― ፍሬምሽን ሰቅዬ …
                       … ግራ የገባው ዓይኔ …
               በከልካይ መነፅር ከቧልት ይፋጠጣል!
                       … ካሽሙር ይፋጠጣል …
                   የጀግና ፎቶዬ ከሱቅሽ ይሸጣል ።
.
                 አንቺ የመልክ ሀብታም ፤ ቀለም የተረፈሽ ፣
                 አንቺ የመልክ ሀብታም ፤ መስመር የተረፈሽ ፣
                 የተኩላዎች ክፋት ― በበጎች ስም ፅፈሽ ፤
                 መጥቀሻል ይሉኛል ― በምኞት መሠላል ።
       … ግድየለም ምጠቂ …
                 ቅዠት ሲደጋገም ― ከህልም ይመሳሰላል ።

እንደነገርኩሽ ነው
      ቧልተኛው ዶክተርሽ በስላቁ ፈዞ ፣
             'አከምኩህ' ይለኛል ¡¿
      የራሱን መዳኒት ለመምተኛው አዞ ።

የመምተኛሽ ደግሞ …
       ካኪምሽም ብሶ ሁለቴ ገደለኝ ፤
               ተመረመርኩልህ ይቺን ዋጣት አለኝ።
                       በታመመ ልኩ ― ጤና ሲሰፍርልኝ …
                                በሽተኛ ልጅሽ ― ተመረመረልኝ ።
.
መድሃኒት ከሰረ
      ጤና ተቃወሰ በሽታ ተስፋፋ
              ግብረ ገብ ጎደለ ስነ ምግባር ጠፋ
                             ወዘተ . . . ወዘተ . . .
                  ጉባኤ ሰብስበው ሰበብ ሲያዳምቁ
                              እኔን የገደለኝ ከበሽታው ይልቅ
                                        በሽተኛው በውል አለመታወቁ ።

ያንቺማ ዓይነቱ
ማድማቱን ደብቆ ፣ መድማቱን ለብቻ እያስመረመረ ፤
             ፈውስ በስም ብቻ ተድበስብሶ ቀረ ።

በኔ"ና አንቺ ዓለም … ከማዘን ! ― ማሳዘን !
       ከመሳት ! ማሳሳት ! ― ከደም ማነስ ! ደም ማሳነስ !
               ከመርሳት ! ማስረሳት ! በእጥፍ ይቀድማል ፤
                       ከበሽታው ይልቅ … በሽተኛው ያማል ።
.
ኧረ ያንቺስ ሞያ
       ትንሽ እየሰፋ ― ብዙ መቅደድ ያውቃል ፤
       ክርሽ ስራ ፈትቶ ― መርፌሽ ብቻ ያልቃል ።
ኧረ ያንቺስ አራጅ ቅርጫሽን ሳንበላው …
" ያልቅብሻል " አሉ! ሞረድ እና ቢላው ።
.
... እንደነገርኩሽ ነው …

                        ጎዳናው ሳይጠበን አመል እያጋፋን !
                        እንኳን አካሄዱ ― አቋቋሙ ጠፋን ።

🔘በረከት በላይነህ🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

29 Nov, 16:00


#ሳትመጪ_ነይ

የጀመርሽው መንገድ ፥ ጉዞሽ እንዲቃና
በስሌት ተራመጅ ፥ ስሜቱን ተይና፣
ከልካይ የለም ብለሽ ፥ አቲጅ በመደዳው
ፈንጂ ወረዳ ነው ፥ የጨዋታ ሜዳው፣
ይልቅ ኳሷን ላኪያት ፥ ትሂድ ቃልሽን ሰምታ
ገላሽ ሳይሸራረፍ ፥ ህልምሽ ግቡን ይምታ።

🔘በርናባስ ከበደ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

29 Nov, 14:39


#ምኑ_ነው_ስህተቴ'

ተሳሳትሽ አትበለኝ የቱ ነው ስህተቴ፤
ጥበብ ነው ማርከሻ የብዕር ጥይቴ።
አዎ መንጋማ አለ ከጥንት መሰረቱ፤
እየሱስን አስረው በርባንን ሲያስፈቱ።

ዛሬም በኔ ዘመን
የመንጋ ፍርድ ነው ሀገሬን የፈታት፤
አዋቂ ዝም ብሎ መንጋ እየፈተታት።
በድንጋይ በርሚል ውስጥ ሽ ድንጋይ ቢቀቀል፤
ሽ ዘመን ተጥዶ እልፍ አመት አይበስል።

አገር ተረክቦ በሰፈረ የኮራ፤
የመንጋ ፍርድ አይደል ያበቃን ለተራ።
የቱ ጋ ነው የሳትኩ አርመኝ መምህሩ፤
ምላስክን አጥፈኽው ሞክር በብዕሩ።
ዘመን የሰጠው ቅል ድንጋይ ቢሰብር ጣሪያ፤
ማዕዘን ተደርጎ አይሆን ለቤት መስሪያ።
ሰውነት ነው ልኩ የሰው ሚዛን ፍርዱ፣
አዋቂ እንዲበይን መንጋዎች ይውረዱ።

አሁንም እላለው
በመንጋ ተፈጭቶ በመንጋ ተጋግሮ፤
እልፍ ጾም አዳሪ ወና ነው ጉረሮ።
ቤት መምታት ቤት መድፋት ስንኝ መቋጠሩ
ጥበቡ ቢያቅተው፤
ቤት እያፈረሰ ህዝብ እያስደደ
አገሩን አመሰው።
እኔ ይሄንን ሰው፣
ሌላ ምን ልበለው፣
መንጋነትም ሲያንሰው።

በባዶነት ሙሌት በዘር እብሪት ታስሮ፣
ከጥበብ ጓዳ ውስጥ ከሰውነት አጥሮ።
አበውን ሲያሰደድ ሲያርድ ሲያጎሳቁል፣
አንተም መንጋ ካልሆንክ መቼም ሰው ነው አትል።

እና ምኑ ላይ ነው ብዕሬ የሳተች፣
ብሔር የነቀፈች ህዝብን ያዋረደች።
"ንገረኝ በሞቴ የመንጋው ጠበቃ
አንተም ሰው ሁንና መንጋነትህ ይብቃ"

🔘ገጣሚ ህሊና ደሳለኝ🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

28 Nov, 16:27


በዚህ በተጧጧፈ ነቆራ እንደ የትሮል ቻናል ያልተቀላቀለ ሰው የተበደለ የለም👌

ምን ትጠብቃለህ ሊንክ ነክተህ ተቀላቀል😁👇👇👇

https://t.me/+j3su9dwjQ_w3Yzc8

አትሮኖስ

28 Nov, 16:15


🥰ለፕሮፋይል የሚሆኑ ገራሚ ገራሚ ፎቶዎችን ለማግኘት ከስር ጆይን ያድርጉ የፈለጉትን አይነት ያገኛሉ ይ🀄️🀄️ሉን!👇

https://t.me/+UqU8zCoHqyw2NzQ0

አትሮኖስ

28 Nov, 16:05


◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇

አትሮኖስ

26 Nov, 12:00


#ምን_እየሆንኩ_ልጠብቅሽ?

ቅድ ሰማይ እየሰፋሁ
ራስ ዳሽን እየገፋሁ
ወይስ
እየሰራሁ የኖኅ መርከብ
ሳፈላልግ የሰው ኮከብ..
ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ?

እየዘመርኩ?
እየዘፈንኩ?
እያረመምኩ?
ግራ ገባኝ እኮ
ያልለየት ድል ነው ያልለየት ምርኮ።

ምን ስሆን ልጠብቅሽ?
አባይን ስጠልቀው
ኤርታሌን ስሞቀው
ቆዳዬን እንደጨርቅ ችሎ ቢተኩሰው
ተዋነይ ጋር ልሂድ ዕፁን እንዲምሰው።

ማን ጋር ልጠብቅሽ?
ከጌታዬ ግራ ከጌታዬ ቀኙ
በየት ትመጫለሽ ወይ አፍቃሪ ሞኙ።
ካብርሃም ቤት  አጋር
ወይስ
ባቢሎን ግንብ ጋር።

የት ጋር ትመጫለሽ?

በዘመን የት ዘመን?
በቦታ የት ቦታ?

ከንጉሥ የት ንጉሥ?
ከባህር ምን ባህር?

ከጫካ የት ጫካ?
ከደብር የት ደብር?
           :
ከሶላት ምን ሰዓት?

ምን እያረግኩኝ ልጠብቅሽ?
ከመላእክት ጋር ስገለፍጥ
የዛፍ ቆዳ ስልጥ...

ግዙፍ ሆኜ ወይ ረቂቅ
ንፋስ ሆኜ ወይስ ደቂቅ....

ወንዝ ሆኜ ወይስ አምባ
ደስታ ሆኜ ወይስ ዕምባ...

ፀሀይ ግርጌ ወይ ጨረቃ
ግጥም ሆኜ ወይ ሙዚቃ...

ምን እየሆንኩ ልጠብቅሽ?

🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

26 Nov, 09:00


አንድ በይ

አልቸኩልም ገላ አውቃለሁ
                :
አልስምሽም ከንፈር ያው ነው::
               
ደክሜያለሁ በብዙ ሴት
ግና የለም አዲስ ሀሴት።


ሁለት በይ

ስንቱን ጣለ ወገብ ዳሌ
              :
ወንድ ይቀልጣል እንዳሞሌ።
                
በቃኝ አይሉት ደስታ ባለም
ስሜት አውሬ ጠገብኩ የለም።

ያጠምደዋል ስሜት መረብ
ለመለያየት ነው ያንዳዱ አቀራረብ።

በመጨረሻም

አንቺን ግና
እስክትስሚኝ እንዲጨንቀኝ
ተረት አውሪኝ ሴት ይናፍቀኝ።
ፍቅራችንን ነፍስ ዘርቶ እንድናየው
ደስታችንን እናቆየው።

በትንሽ እንኑር
ቶሎ አይፈጸም የጎዟችን ሜዳው
ደስታን ሲያሳድድ ነው ፍቅር የተጎዳው።


🔘ኤልያስ ሽታኹን🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

26 Nov, 06:00


"ሁሌ ባገኝህ አይሰለቸኝም" አለችው

"እውነትሽ ነው"

"አዎ ገና መተዋወቃችን ቢሆንም ደጋግሜ ላገኝህ እፈልጋለሁ"

ዝም ተባባሉ ረጅም ሰዓት።

"እኔ ምልህ ህይወት ላንተ  ምንድነው አለችው?"

"ቀይሮ መድገም ነው" አላት

"ማለት"

"አሁን የሆነች ተራ ካፌ ቡና ትጠጪያለሽ ሲኖርሽ ሸራተን ነው ራሱን ቡና

አሁን  አንድ ክፍል ቤትሽ ውሰጥ ትተኛለሽ
ሲኖርሽ አስር ክፍል ያለው ግን አንዱ ክፍል ብቻ ራሱን እንቅልፍ ትተኛለሽ

ደሀ ሆነሽ አረቄ ነው
ሀብታም ስትሆኚ ውስኪ ነው ቀይሮ መድገም

ሰው ለምን ይመስለሻል አንድ ደብር ደጋግሞ ከመሳለም ደብር የሚቀያይረው ቦታ ቀይሮ ጸሎት ለመድገም ነው።

በፊት የሆነ ልጅ ትወጃለሽ ስትለያይ
ልጅ የሆነ ትወጃለሽ 
ያንኑ መውደድ ቀይሮ ነው መድገም ነው

የሆነ ዘፈን በሌላ ዘፈን ዘፋኝ ቀይሮ መድገም

የምታውቂውን ስብከት በሌላ ሰባኪ ወይም ቄስ ቀይሮ መድገም 

በኢኮኖሚ ክላስ መሄድ ዝነኛ ስትሆኚ እዛው ፕሌን ውስጥ ቢዝነስ ክላስ ሆኖ ወንበር ቀይሮ በረራ መድገም

ሰው ሁሉ ገንዘብ የሚፈልገው የነበረውን ነገር ቀይሮ ለመድገም ነው።"

የሆነ ነገሯ ተዛባባት።

"በቃ የዘመኑን ከቨር ሙዚቃ ታውቂያለሽ?"

"አዎ" አለችው

"የኛ ሰው ህይወት እንደዛ ነው
የህይወት ከቨር በይው።
የሆነ የሆነ ነገር ቀንጭጮቦ መምጣት ቀጣጥሎ ማዜም
ቀያይሮ መድገም..."


"የሚቀጥለው አመት እደውልልሀለሁ" አለችው


🔘ኤልያስ ሽታሁን🔘


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

25 Nov, 17:00


​አብራን በሌለችው በበሬዱና አጠገባችን ባለችው በፀሎት ነው፡፡የእኔ ልጅ ዛሬ በህይወት ያለችው ከበሬዱ በተሰጣት ልብ ነው፡፡እዚህ እነአቶ ለሜቻ ቤት ለሟች ልጃቸው የሙት አመት መታሰቢያ ሲከበር በእኛ ቤት ግን ለልጃችን ንቅለ-ተከላ ተደርጎላት ዳግም የመኖር እድል ስላገኘች ድል ያለ የምስጋና ድግስ እናዘጋጅ ነበር ..ዘንድሮ ግን በፀሎት ውሳኔ እንደዛ ማድረግ አልቻልንም…እዚህ ግቢ አንድ ላይ መታሰቢያውንም ምስጋናውንም አብረን እንድናከብር ወስነናል..አሁን ሁላችንም ወርደን የተዘጋጀውን ዝግጅት እንታደም፡፡››የሚል ንግግር ካሰሙ በኃላ በራፉ ተከፈተ …
ዛሬ እየሆነ ያለው ነገር በጠቅላላ ምንም ያልገባቸው አቶ ለሜቻና ወ.ሮ እልፍነሽ አቶ ኃይለልኡልንና ባለቤታቸውን ተከትለው ከባስ ወረዱ፡፡ይሄንን ሰፈራ የሚገኘው በገዛ ቀበሌያቸውና በሰፈራቸው ስለሆነ በደንብ ያውቁታል፡፡ግቢው ንብረትነቱ የቀበሌው ሲሆን  ባለ5 ሺ ካሬ ግዙፍ ጊቢ ነው…ከመኪና ወርደው ሲመለከቱ ግቢው በሰዎች ታጭቆል ፡፡ ሰዎቹ ደግሞ አብዛኛው ጎዳና ተዳዳሪዎች፤የኔ ቢጤዎች የደከሙና የተጎዱ አቅመ ደካሞች…..ለአይን እንኳን ተቆጥሮ የማያልቅ የእንጀራ ክምር ..በበርሜል የተደረደረ ልዩ ልዩ የወጥ አይነት…ራቅ ብሎ ደግሞ በተንጠልጣይ ብረት ላይ የተደረደረ ጥሬ ስጋ እንደተራራ የተቆለለ የታሸገ ውሀ……

በሌላ ጎን ከአዳራሹ ፊት ለፊት ግዙፍ ፖስተር ይታያል…በፖስተሩ ላይ በቀኝ የበሬዱ ፎቶ በስተግራ ደግሞ የበፀሎት ፎቶ መሀከል ላይ የበሬዱ በፀሎት የምገባ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ይላል፡፡ብዛት ያላቸው ጋዜጠኛች ከወዲህ ወዲያ እየተዘዋወሩ ፎቶ ያነሳሉ ኢንተርቪው ያደርጋሉ፡፡
ማታ በሁለት ሰዓት ዜና ላይ በኢትዮጴያ ቴሌቭዝን የቀረበው ዜና የሚከተለው ነበር….
‹‹የታዋቂ የቢዝነስ ማን አቶ ሃይለልኡል ብቸኛ ልጅ ከጠፋችበት መገኘቷ ታወቀ…በፀሎት ከሶስት አመት በፊት ልቧ መስራት አቁሞ የነበረ ሲሆን በዛን ወቅት የመኪና አደጋ ደርሶባት አብራት ለህክምና ወደ ታይላንድ የሄደችው በሬዱ ለሜቻ ህይወቷ በማለፉ አባትዬው በሰጡት ፍቃድ መሰረት ልቧን ለበፀሎት በመለገሷ የልብ ንቅለ-ተከላ ሊደረግላትና ድና ወደሀገር ልትመለስ ችላለች…ባለፈው ወር የጠፋችው በፀሎት ኃይለልኡል የተገኘችው በእነዚሁ በአቃቂ ክፍለከተማ በሚኖሩት ልብ በለገሰቻት ልጅ ቤተሰቦች ቤት መሆኑ በጣም አነጋጋሪና አስደማሚ ታሪክ ሆነዋል፡፡
በዛሬው እለት የበሬዱ የሶስተኛ አመት የሙት አመት መታሰቢያ የነበረ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ባለፉት ሁለት አመት እንደተደረገው በአቶ ኃይለልኡል ቤት የምስጋና ድግስ ሲደገስ የቆየ ቢሆንም..ዛሬ ግን ይሄ ቀርቶ አቶ ኃይለልኡልና ቤተሰባቸው በቤታቸው የደገሱትን ድግስ ሙሉ በሙሉ ሰርዘው በሞች በሬዱ ለሜቻ የትውልድ አካባቢ ለስሟ መታሰቢነት እንዲሆን ከዛሬ ጀምሮ በአካባቢው አቅም የሌላቸውና ችግረኞችን በቀን ሁለት ጊዜ የሚመግብ በሬዱ በፀሎት ምገባ ተቋምን ከፍተው ያስመረቁና በቦታውም ከ500 በላይ ሰዎችን በመመገብ ማስጀመራቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡
በዚህም የሞች አባት የሆኑት አቶ ለሜቻ ስለሁኔታው ሲናገሩ‹‹በእውነት ልጄ ዛሬ ሞትን ድል ነስታ እንደተነሳች ነው የምቆጥረው..ልጄ በህይወት እያለች ለተቸገረ ሁሉ የምታዝን የዋህ ነበረች..አሁንም ከሞተች በኃላ ይሄው በስሟ ብዙዎች ጠግበው እንዲያድሩ ምክንያት ስለሆነች ኮርቼለሁ….ይሄንን እውን ያደረጉትን አቶ ኃይለልኡል እና ባለቤታቸውን አመሰግናለሁ….የእነሱ ልጅ የሆነችው በፀሎት ለእኔም ልጄ ነች….ከአሁን በኃላ በሬዱ ሞተች ብዬ አላዝንም…. ስትናፍቀኝ በፀሎትን አቅፌ አፅናናለሁ…ደግሞ እዚህ ስፍራ መጥቼ በስሟ ሰዎች ምግብ ቀምሰው ሲያድሩ ተመልክቼ ረካለው››በመላት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል…የሚል ነበር፡፡

ከድግሱ በኃላ አቶ ኃይለልኡልና ወ.ሮ ስንዱ ወደቤታቸው ሲሄዱ በፀሎት ግን ለሊሴን ተከትላ ወደእነሱ ቤት ነበር የሄደችው…በማግስቱ ግን ቤተሰቡ በአጠቃላይ ተሰብስበው ወደቦሌ ሄዱ ፡፡ሲደርሱ ሰለሞንም ነበር….ይህ ዝግጅትና ግንኙነት ለሁለቱም ቤተሰብ ልክ እንደቅልቅል ነው፡፡በዚህ ደግሞ ቁጥር አንድ የፈነጠዘችው በፀሎት ነች፡፡የእሷን ደስታና ፈንጠዝያ ሲከታተል የነበረው ሰለሞን ‹‹እሺ ይህቺን ልጅ ለማግባት ልጃችሁን ስጡኝ ብዬ ሽማግሌ ምልከው ለየትኛው ቤተሰብ ነው፡፡ብሎ እራሱን ጠየቀና ፈገግ አለ፡፡‹‹ግድ የለም እሷ ትስማማ እንጂ እኔስ ሁለት የሽማግሌ ቡድን ማቋቋም አያቅተኝም፡፡›› ሲል ለራሱ መልስ ሰጠ፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ ፊራኦልም ከሰለሞን ጎን ተቀምጦ ፊት ለፊቱ በፀሎትን እየተመለከተ በውስጡ ‹‹እሺ አሁን የእህቴን ልብ ተሸክማ እህቴ ስለሆነች ልደሰት ወይስ. ፍቅሬን ተቀብላ ፍቅረኛዬ መሆን ስለማትችል ልከፋ?››በውስጡ የሚያመነዥገው ጥያቄ ነበር፡፡‹‹ፍቅሯ በዚሁ ቀጥሎ ከባሰብኝ ምንድነው የማደርገው?››በጣም ተጨነቀ፡፡

ተፈፀመ

በሌላ ስራ እስክንገናኝ ደህና ሁኑልኝ።


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

25 Nov, 17:00


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ድክምክም ብሎታል፡፡ግን ደግሞ አልጋው ላይ ተኝቷ በሀሳብ እየተንገላታ ነው፡፡ ሰለሞን በሁለት በኩል ስለት ባለው ሰይፍ የሚጫወት ህፃን አይነት ሰው እንደሆነ እየተሰማው ነው፡፡ሞያውን በተመለከተ ለሶስት አመት በከፍተኛ የፕሮፌሽናል ደረጃ በምድረ-አሜሪካ ሲሰራ አንድም ጊዜ እንደዚህ አይነት ክፍተት ተከስቶበት አያውቅም..በዛም በራሱ ሲመካና ሲኮራ ኖሮ ነበር፡፡አሁን ግን ወደሀገሩ ተመልሶ ባጋጠሙት የመጀመሪያ ደንበኞቹ ከፍተኛ የሚባል ሽንቁር ተከስቶበታል፡፡አንድ ባለሞያ የሞያውን ስነምግባር አክብሮ ስራውን መስራት የሚገደደው ለደንበኞች ደህንነትንና ጥቅም ሲባል ብቻ አይደለም…ለራሱ ለሞያው ክብርና ተቀባይነትም እያንዳንዱ ባለሞያ የስራ-አፈፃፀም ሁኔታ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡በሙስናና በጥቅማጥቅም የሚታለሉ ዳኞችና አቃቢ-ህጎች በሞሉበት ሀገር ፍርድቤት ሊከበርና ሊታመን አይችልም፡፡ሌላውም ሞያ እንደዛው ነው፡፡ ይህን ስራ ከጀመረ ያጋጠመችው ትልቋ ደንበኛው በፀሎት ነች፡፡እርግጥ ቀጥታ ደንበኛው እሷ ሳትሆን ወላጆቾ ናቸው፡፡ከእነሱ ጋር እየሰራ ያለውን ስራ የሞያው ስነምግባር በሚፈቅደው መንገድ ጥርትና ጥልል አድርጎ እየሰራ ነው፡፡ቢሆንም ቀጥታ ቀጣሪው ልጃቸው በፀሎት ነች፡፡እሷ ፍላጎቱን ተረድታ አፈቅርሀለው ብትለው እንኳን ፍቅሯ እሱ ለወላጆቾ በሚያደርገው የሞያ ድጋፍ ተፅዕኖ ስር የወደቀ ወይንም በይሉኝታ ስሜት የተቀነበበ ሊሆን ይችላል…ይሄንን ማንም በእርግጠኝነት ማወቅ አይችልም…በዚህም ምክንያት ከእሷ ጋር ደግሞ ያለው ግንኙነት እየሄደ ያለበት መንገድ ትክክል እንዳልሆነ ያውቃል፡፡ከሞያ ስነምግባር ውጭም እንደሆነ ያምናል፡፡ይሄ ጉዳይ ነው በጣም እያስጨነቀው ያለው፡፡ ከበፀሎት ጋር የፍቅር ስሜት በተሰማበት ቅፅበት ሁለት ምርጫ ነበረው፡፡አንድም በእሷ ቀጣሪነት ወላጆቾን ለማከም የተዋዋለውን የስራ ውል አፍርሶ ነፃ መውጣትና.. ከልሆነም ልቡን ገስፆ እና ፍቅሩን በውስጡ አክስሞ ስራው ላይ ብቻ አትኩሮ መቀጠል፡፡ቢያንስ ስራውን በተዋዋለው መሰረት ሙሉ በሙሉ አጠናቆ እስኪጨርስ ድረስ እንደዛ ነበር ማድረግ ያለበት፡፡ግን ይሄው ሁለቱንም ማድረግ አልቻለም፡፡ ‹‹ግን እኮ ይሄ በስራ አለም ቆይታዬ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈፀምኩት የሞያ ስነምግባር ጥሰት ነው››ሲል እራሱን ለማፅናናት ሞከረ…..፡፡ንግግሩ ግን እራሱንም ሊያሳምነው አልቻለም፡፡ ‹‹ስህተት የመጀመሪያም ሆነ የመጨረሻ ያው ስህተት ነው››የገዛ አእምሮ መልሶ የነገረው ነበር፡፡ ‹‹አሁን ወደኃላ መመለስ አልችልም…ይሄንን ጉዳይ ከዳር ላድርስና ..ከእሷ ጋር ያለኝ የፍቅር ግንኙነት የሚደርስበትን ከፍታ አይቼ ውጤታማ የሚሆን ከሆነ ምን አልባት ሞያውን በክብር ብለቅና ወደሌላ ዘርፍ ብሸጋገር እንኳን ያዋጣኛል››ሲል ለጊዜው የታየውን መፍትሄ አስቀመጠ…የገዛ አእምሮው ግን ወዲያው ነበር አፍራሽ የሆነ ሀሳብ የሰጠው‹‹ሰውዬ ምን ነካህ..?ይሄንን ሞያ ለቀህ…ነጋዴም ብትሆን …ወይም ደራሲ… ሁሉም ሞያ አይነቱ እና ተጋላጭነቱ በመጠኑ ይለያይ እንደሆን እንጂ የራሱ ህጋዊም ሆኑ ሞራላዊ የስነምግባር ገደቦች አሉበት…በተለይ ፍቅርን በተመለከተ ሁሉም ሞያ ይፈተናል…አስተማሪ ብትሆን ተማሪህ ላይ አይንህን መጣል የለብህም…ማናጀር ሆነህ ፀሀፊህን መጎነታተል ስህተት ነው፡፡ሞያህን ሳይሆን አመለካከትህን ነው መቀየር ያለብህ… ራስህን አታሞኝ፡፡››አለው…. ለጊዜው በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ በላይ ማሰብ አልፈለገም….ጉዳዩን ለጊዜ አሳልፎ ሰጠና ብድርብሱን ተከናንቦ እራሱን ለእንቅልፉን አሳልፎ ሰጠ ....ወዲያው ነበር ያሸለበው…የሚገርመው ደግሞ አይኖቹ በተከደኑ ከሁለት ደቂቃ በኃላ ነበር በፀሎት ነጭ ቬሎ ለብሳ ጭንቅላቷ ላይ የሚያብረቀርቅ የወርቅ አክሊል አጥልቃ ግራና ቀኝ ጎኗ ላይ የበቀሉ ውብ ክንፏቾን እያማታች ከሰማዩ ላይ ሰንጥቃ መጥታ እቅፉ ውስጥ ስትገባ በህልሙ ያየው፡፡
///
በፀሎትና ለሊሴ ከወንጪ ከተመለሱ ሁለት ቀን ሆኗቸዋል፡፡መሽተዋል…አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ነው…በፀሎት እና ፊራኦል ግቢው ውስጥ ካለ ግዙፍ የመንጎ ዛፍ ስር ጎን ለጎን ቁጭ ብለው እያወሩ ነው፡፡
‹‹እንዴት ነበር ወንጪ?››
‹‹ውይ ሲዊዘርላድ በለው፡፡››
‹‹እኔ ወንጪን እንጂ ሲዊዘርላንድን አላውቃትም፡፡››
‹‹አኔ ደግሞ አውቃታለዋ ለዛ ነው ያነፃፀርኩልህ..ደግሞ ዘመዶቻችን እንዴት ደግና ቀሽት መሰሉህ?፡፡››
‹‹የእኔም ዘመዶች እኮ ናቸው አውቃቸዋለው››
‹‹አይ ቢሆንም ..አንተ ምንአልባት ከልጅነትህ ጀምሮ ስለምታውቃቸው …ብዙም ጣእም ላይሰጥህ ይችላል..ማለት ሁለም ሰው እንደእነሱ አይነት ዘመድ ያለው ስለሚመስልህ ተራ ነገር አድርገህ ልትቆጥረው ትችላለህ….እንደእኔ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደዛ አይነት ዘመድ ሲኖርህ ግን በቃ ..ከአሁኑ እንዴት እንደናፈቁኝ ብታውቅ››
‹‹ገና በሁለት ቀን››
‹‹አዎ በሁለት ቀን››
‹‹አሁን ከእኛ ስትለይና ወደቤትሽ ስትሄጂ እንናፍቅሻለን ..?ማለት እኔ ናፍቅሻለሁ?››ለቀናት በውስጡ ሲያብሰለስለው የነበረውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
‹‹ምን ማለት ነው….?ወደየትኛው ቤቴ ነው የምሄደው?››
‹‹ወደቦሌው ቤትሽ››

‹‹ምን….ለሊሴ ነገረችህ››
‹‹እሷ ታውቃለች እንዴ?››
‹‹እሷ ካልነገረችሽ ታዲያ ማን ነገረህ?››
‹‹እራሴ ነኝ የደሰረስኩበት ..ወደ ወንጪ ከመሄዳችሁ በፊት ነው ያወቅኩት››
‹‹እኮ እንዴት ልታውቅ ቻልክ?››
‹‹ያው እንዳልኩሽ የእህቴን ልብ ከተቀበልሽ በኃላ በሩቅ ሆኜ ለረጅም ጊዜ ስከታተልሽ ነበር..ስለዚህ በደንብ አውቅሻለው…እዚህ ቤት ከመጣሽ ከሳምንት በኃላ ጀምሮ ከፍተኛ ጥርጣሬ አድሮብኝ ነበር..ከዛ ምን አደረኩ አንድ ቀን ስትተኚ ሻርፕሽን ሙሉ በሙሉ ከፊትሽ ላይ ገፍፌ ተመለከትኩሽ…እና ኦርጅናለዋ በፀሎት መሆንሽን አረጋገጥኩ፡፡
‹‹ትገርማለህ..ከዛ ፀጥ አልክ?››
‹‹ምን ላድርግ…ምንም ማለትና ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላወቅኩም ነበር፡፡››
‹‹አሁንስ አወቅክ?››
‹‹አይ….አንቺ ንገርኝ እስኪ …ምን ልታደርጊ ነው…?እስከመቼ ነው ከወላጆችሽ ምትደበቂው?››
‹‹ወላጆቼን በቀደም አግኝቼቸዋለው..እዚህ መሆኔን ያውቃሉ››ብላ ያልጠበቀውን ዜና ነገረችው፡፡
‹‹ጥሩ..እሺ እነአባዬን እንዴት ልታደርጊ ነው….?እንደዋሸሻቸው ሲያውቅ በጣም ነው የሚያዝኑብሽ…በአንቺ ብቻ ሳይሆን እኛም አውቀን ከነሱ ደብቀን ዝም በማለታችን ምን እንደሚወጥን አላውቅም? በጣም ጨንቆኛል›ብሎ እውነተኛ ስሜቱን ነገራት፡፡
‹‹ይቅርታ ፊራኦል..እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ ስላስገባዋችሁ በጣም አዝናልው…ግን በዚህ ሁለት ሶስት ቀን ውስጥ እፈተዋለው…ማለት እናንተ ቀድማችሁ እንደምታውቁ ሳላሳውቅ እፈተዋለው››
‹‹እስኪ እናያለን…››

‹‹እኔ የእህትህን ልብ የተሸክምኩ በፀሎት መሆኔን እርግጠኛ ስትሆን ምን ተሰማህ?››
‹‹ግማሽ ሀዘን ግማሽ ደስታ››
‹‹አልገባኝም››
‹‹ለረጂም ጊዜ ላናግርሽና ቀርቤ ላወራሽ የምመኝሽ የእህቴን ከፊል አካል የተሸከምሽው በፀሎት የገዛ ቤቴ መጥተሸ ከእኔ ጋር አንድ መአድ እየቆረሽ መሆንሽን ሳውቅ ፍጽም ድስታ ነው የተሰማኝ…በሌላ ጎኑ ደግሞ ያችኛዋን በፀሎት አፍቅሬት ስለነበር….ሌላ በፀሎት እንዳልሆንሽ ሳውቅ ቅር ብሎኛል››
‹‹ከመቀመጫዋ ተነሳችና እላዩ ላይ ተጠምጥማ ጉንጩን እየሳመችው‹‹….የእኔ ወንድም

አትሮኖስ

25 Nov, 17:00


…..በጣም ነው የምወድህ……››አለችው
‹‹እኔም እህቴ በጣም ወድሻለው…አሁን እራት እየቀረበ ነው መሰለኝ ወደቤት እንግባ…››
‹‹እሺ እንግባ››ተባባሉና ተያይዘው ወደቤት በመግባት ከቀረው ቤተሰቡ ጋር ተቀላቀሉ፡፡
//
አቶ ለሜቻና ቤተሰባቸው በአጠቃላይ ሙሉ ትኩረቱ የበሬዱ የሶስተኛ አመት የሙት አመት መታሰቢያ ላይ ነው፡፡ይሄ ባለፈው ሁለት አመት በተመሳሳይ የመታሰቢያ ድግስ የተደገሰ ቢሆንም የዘንድሮ ግን በተለየ ሁኔታ ትኩረት ተሰጥቶታል ፡፡የዚህም ምክንያት በቤተሰቡ ውስጥ ተአምራዊ በሆነ መንገድ በፀሎት የምትባል ልጅ ስለተጨመረችና ከዛም ተያይዞ ከሞላ ጎደል የቤተሰቡ የገንዘብ ችግር ስለተሻሻለ፤ ከዚህ በፊት ከነበረው ከፍ ባለ ሁኔታ ለመደገስና በሟቾ ስም በርከት ያሉ ችግረኞችን በማብላት ነፍስ ይማር በማሰኘት የተወሰነ የመንፈስ እረካታና የአእምሮ መረጋጋት ለማግኘት ጠንክረው በጥሩ ሞራል እየደገሱ ነው፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ አቶ ኃይለልኡል ቤት በአይነቱ ለየት ያለ ድብልልቅ ያለ ድግስ እየተደገሰ ነው፡፡የእነሱ ምክንያት ደግሞ ሚያዚያ 20 ቀን የልጃቸው በፀሎት የልብ ንቅለተከላ ያደረገችበትና ሁለተኛ የመኖር እድል ያገኘችበት ስለሆነ ያንን ቀን በፌሽታና በምስጋና የማሳለፍ አላማ ያለው ነው፡፡ይሄንን ድግስ ያለፉትን ሁለት አመታት አድርገውታል፡፡ የዘንድሮው ግን በአይነትም ሆነ በመጠን ከፍ ያለ ነው፡፡ይሄም ዘንድሮ ሁኔታዎች የተለዩ

ስለሆኑ ነው፡፡ከቤታቸውም ከፊታቸውም የተሰወረችው የልጃቸው በፀሎት ከወር በኃላ ወደቤቷ ምትመለስበት ቀን ይሆናል የሚል ጉጉት ስላላቸው ልጃቸውን እጥፍ ድርብ በሆነ ፌሽታ ለመቀበል ያደረጉት ነው፡፡ከዚህም በተጨማሪ ሌላ የተለየ ምክንያት አላቸው ፡፡ባልና ሚስቶቹ ለአመታት ከገቡበት አስጠሊታ ግንኙነት እና የእርስ በርስ ጥላቻ ተገላግለው. ቀሪ ህይወታቸውን በመከባበር እና በፍቅር ለማሳለፍ ወስነውና ተስማምተው ቀሪ እንደአዲስ ለመጀመር የወሰኑበት ወቅት ስለሆነ ለእነሱም እንደ ዳግማዊ ሰርግ ነው…ለዛ ነው የተለየና እንከን አልባ ድግስ እንዲሆን እየጣሩ ያሉት…ያው እንደተለመደው የድግሱን ቅንጅት በሀላፊነት የወሰዱት ፕሮፌሽናል ባለሞያዎች ናቸው፡፡
የጭንቁ ቀን ደርሶል ፡፡አቶ ለሜቻና ወይዘሮ እልፌ ከሌሎች ጎረቤቶች ጋር በለሊት ነው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው ቅዳሴ የገቡት…በጸሎትን ጨምሮ ሌሎቹ ልጆች ግን ወደ ቤተክርስቲያን የሚወሰደውን ምግብና መጠጥ ሲያዘጋጁ ከቆዩ በኃላ አንድ ሰዓት ተኩል ሲል ዳቦ፤ እንጃራና ጠላውን በፒካፕ መኪና እስጭነው ቤተክርስቲያን በመውሰድ ለቄሶቹ የተዘጋጀውን ወደሰንበቴ ቤት አስገብተው ሌላውን ውጭ አስቀምጠው ቅዳሴው እስኪገባደድ መጠበቅ ጀመሩ ፡፡ልክ ቅዳሴው ተጠናቆ ሁሉም እንደወጣ አቶ ለሜቻና ወይዘሮ እልፌ ከቄሶቹ ጋር ወደሰንበቴ ቤት ቄሶቹንና ሌሎች ምዕመናንን ለማሰተናገድ ሲገቡ፡፡ በፀሎትና እና ለሊሴ ደግሞ ከሌሎች የሰፈር ወጣቶች ጋር በመሆን ቤተክርስቲያኑ የውጭ አጥር ጋር ተኮልኩለው ለሚገኙ የእኔ ቢጤዎችና፤ ምፅዋት ጠያቂዎች አንድ እንጀራ በወጥ ፤አንድ ጉማጅ ዳቦና አንድ ሀይ ላንድ ጠላ ለእያንዳንዱ እያደሉና ነፍስ ይማር እያስባሉ ካጠናቀቁ በኃላ ዕቃቸውን ሰብስበው እነአቶ ለሜቻ ከሰንበቴ ቤት እስኪወጡ መጠበቅ ጀመሩ…ሁሉ ነገር ከተጠናቀቀ በኃላ ቤተሰቡ ወደቤታቸው ከመመለሳቸው በፊት ቀጥታ ተያይዘው ወደበሬዱ መቃብር ነው የሄዱት፡፡የእሷ ምስል ያለበት ጥቁር ቲሸርት የለበሱት አስራ ምናምን ሰዎች የሀውልቱን ዙሪያ ገባ ከበው በዝምታ ሲፀልዩና አንዳንዱም ሲያነባ ከቀዩ በኃላ ሁሉም ቀስ በቀስ ስፍራውን እየለቀቁ ሄዱ…በመጨረሻ የቀሩት በፀሎት አቶ ለሜቻና ወ.ሮ እልፍነሽ ነበሩ፡፡
በፀሎት ይሄንን የልጅቷን ሀውልት ስታይ በጣም ትልቅ የሆነ ሀዘን ነው የተሰማት…‹‹በእሷ ምትክ..እኔ ነበርኩ እዚህ ስፍራ ከዚህ ሀውልት ስር መተኛት የሚገባኝ››ብላ ስታስበው እራሱ ዝግንን አላት…ልክ እንደሁል ጊዜውም የሌላን ሰው ህይወት ሰርቃ እየኖረች እንዳለች አይነት ስሜት ነው እተሰማት ያለው….የሚቀፍ አይነት ስሜት…›

አቶ ለሜቻ በዝምታ ሲያስተውሏት ስለቆዩ ያመማት መሰላቸው…‹‹ለማታውቃት ልጅ ይሄን ያህል ሀዘን ከየት የመጣ ነው?››በውስጣቸው ያብሰሰሉት ሀሳብ ነበር፡፡ በዝምታ ወደእሷ መጥተው ትከሻዋን በመያዝ…‹‹ልጄ በቃ እንሂድ ይበቃል››ሲሏት ከገባችበት ጥልቅ የመደንዘዝ ስሜት ባነነችና ቀና ብላ አየቻቸው…ትከሻዋን አቅፈው በፍቅር እየተመለከቷት ነው፡፡በሶስት ሜትር ርቀት ፈንጠር ብለው ወ.ሮ እልፍነሽ እያነቡ ይታዬታል…የአቶ ለሜቻን እጅ ያዘችና ‹‹አባዬ ና..››ብላ ወስዳ ከባለቤታቸው ጎን አቆመቻቸውና…ሁለቱም እግር ስር ድፍት ብላ አንድ አንድ እግራቸውን በመያዝ…‹‹አባዬ እማዬ እኔን ይቅር በሉኝ….በበሬዱ ይዣችኃለው ይቅር በሉኝ….ይቅር ካላላችሁኝ መኖር አልችልም….የእውነቴን ነው የምላችሁ ይቅርታችሁን ካላገኘው ሞታለው፡፡››ስትል ሁለቱም በድንጋጤ እርስ በርስ ተያዩ…ምንም እየገባቸው አይደለም….‹‹ምን አጥፍታ ነው…?ምንስ ብታጠፋ ይቅርታ መጠየቂያው ቦታና ጊዜው ትክክል ነው?፡፡››በውስጣቸው የተፈጠረ ጥያቄ ነበር…ሁለቱም ግራና ቀኝ ትከሻዋን ይዘዘው ቀና ሊያደርጎት ሞከሩ ..ግን እልቻሉም፡፡
‹‹ይቅርታ ካላደረጋችሁልኝ አልነሳም››
‹‹ምን አጥፍተሸ ነው? ምንም አልገባንም እኮ››አቶ ለሜቻ ጠየቋት፡፡
‹‹አጭበርብሬችኃለው ..ዋሽቼያችኃለው..እኔ እናንተ ጋር የመጣሁት ከእንጀራ አባቴ ጠፍቼ አይደለም….››
‹‹እና ምን ሆነሽ ነው?፡፡››ወ.ሮ እልፍነሽ ጠየቁ፡፡
‹‹እኔ ማለት …የልጃችሁን ልብ በውስጤ ተሸክሜ የምዞር..በእሷ ምክንያት እየተነፈስኩ ያለው ልጅ ነኝ…..፡፡››
ሁለቱም የሚሰሙትን ለማመን አልቻሉም ..አቶ ለሜቻ ቀስ ብለው ትከሻዋን ይዘው አስነሷት…ፊቷን የተሻፋፈነችበትን ሻርፕ ቀስ ብለው ከላዮ ገፈፉና ጣሉት.. ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ፊቷን ተመለከቱት‹‹አዎ እራሷ ነች››ትከሻዋን ያዙና ደረታቸው ላይ ለጠፏት…ግንባሯን፤ ጉንጮን፤ ፀጉሯን እየደጋገሙ ሳሟት‹‹….ልጄ አዎ አውቄው ነበር..አንቺ ወደቤቴ ያለምክንያት እንዳልመጣሽ ታውቆኝ ነበር….ከዛሬ ነገ ጥላኝ ትሄዳለች በሚል ስጋት ስሳቀቅ ነበር..አሁን ግን የራሴው ልጅ ነሽ የትም አትሄጂም..አዎ የራሴው ልጅ ነሽ››ተንሰፈሰፉላት….ፍፁም ያልጠበቀችውን ምላሽ ነው ያገኘችው፡፡

‹‹አዎ አባዬ ያንተው ልጅ ነኝ…ዘላለም ካአንተ መለየት አልችልም…እማዬ እኔ ልጅሽ ነኝ››ሶስቱም አንድ ላይ አርስ በርስ ተቃቅፈው ለበርካታ ደቂቃ ተላቀሱ ..በመከራ ነበር አካባቢውን የለቀቁት…ሁሉም የቤተክርስቲያኑ በራፍ ላይ ተሰብስበው እየጠበቋቸው ነበር….ግን በፊት ከነበሩት በተጨማሪ የበፀሎት እናትና አባት ልዩ አይነት ባስ መኪና አጠገብ ቆመው በራፍ ላይ ሲጠብቋቸው ነበር..ይሄ ደግሞ እነአቶ ለሜቻን ብቻ ሳይሆን በፀሎትንም ጭምር ነበር ያስደነቃት…እርስ በርስ ተቀራርበው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ሁሉም በመኪና ውስጥ እንዲገቡ ተደረገ…በመኪና ውስጥ ጠቅላላ 25 የሚሆኑ ሰዎች ገቡ…ሹፌሩ መኪናውን ወደእነ አቶ ለሜቻ ቤት አቅጣጫ መንዳት ጀመረ…ቤታቸው ለመድረስ ግማሽ ኪሎ ሜትር ያህል ሲቀረው ግን ወደግራ ተጠመዘዘና አንድ ግቢው ውስጥ ገባ..ሁሉም ግራ ተጋባ….አቶ ኃይለልኡል መኪናው እንደቆመ በራፈ ከመከፈቱ በፊት ከተቀመጡበት ተነሱና መናገር ጀመሩ‹‹ ..ይቅርታ የማታውቁኝ ካላችሁ ኃይለልኡል እባላለሁ…የበፀሎት አባት ነኝ…በዛሬው ቀን በደም የተጣመሩ ሁለት ቤተሰቦች እዚህ ይገኛሉ ..የእኛና የአቶ ለሜቻ ቤተሰብ፡፡ይሄ ሁለት ቤተሰብ የተሳሰረው ዛሬ

አትሮኖስ

23 Nov, 17:16


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሰባት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ጨጓራው ሲለበልበው ይታወቀዋል…በቃ ውስጡ እየነደደ ነው…አሁን ምንም የማያውቀውን አዲስ ነገር አልነገረችውም…ምን እንዳበሳጨው ለራሱም አልገባውም….ሌላ ቢራ ከፈተና አንደቀደቀው…ስልኩን ደግመኛ አነሳና ደወለ… ‹‹ሄሎ ሶል ምነው?›› ‹‹እባክሽ…»

አትሮኖስ

23 Nov, 17:15


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ጨጓራው ሲለበልበው ይታወቀዋል…በቃ ውስጡ እየነደደ ነው…አሁን ምንም የማያውቀውን አዲስ ነገር አልነገረችውም…ምን እንዳበሳጨው ለራሱም አልገባውም….ሌላ ቢራ ከፈተና አንደቀደቀው…ስልኩን ደግመኛ አነሳና ደወለ…

‹‹ሄሎ ሶል ምነው?››

‹‹እባክሽ ስለሆነ ነገር ላማክርሽ ነበር… እኔ ክፍል ድረስ መምጣት ትችያለሽ?››

‹‹መቼ አሁን?››በመገረም ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ አሁን››

‹‹እሺ በቃ መጣሁ››

‹‹ስልኩን ዘጋና ከተቀመጠበት ተነሳ…መልሶ ቁጭ አለ‹‹ሰለሞን ምን እያደረክ ነው…?በዚህ ሰአት ስለምን ጉዳይነው የምታወራት.?›እራሱን በብስጭት ጠየቀ፡‹‹፡መልሼ ደውዬ በቃ ተይው ነገ ይደርሳል ማለት አለብኝ..››ወሰነና ስልኩን አነሳ….ቁጥሩን ከመጫኑ በፊት የመኝታ ቤቱ በራፍ ተቆረቆረ…..

ስልኩን ወደ አልጋው ወረወረና ተንደርድሮ ሄዶ ከፈተላት…በፀሎት ሮዝ ቀለም ያለው ስስና ልስልስ ቢጃማ ቀሚስ ለብሳለች… ፀጉሯን ወደላይ ጠቅልላ በሻሽ አንድ ላይ ጠፍራ አስራዋለች…ውብና መራኪ ሆና ነው እየመጣችው …ወደውስጥ ዘልቃ ገባች‹‹….ምነው በሰላም ነው…?አስደነገጥከኝ እኮ››

ፊት ለፊቷ ተገትሮ ቆመ….ግራ ገባት
‹‹ሶል ምን ሆነሀል…?.ምንድነው የምትነግረኝ?››ጉጉትና ፍራቻ በተቀየጠበት ስሜት ጠየቀችው፡፡

ተንደረደረና በሁለት እጆቹ አገጯን ግራና ቀኝ ክንዶን ይዞ ወደእሱ አስጠጋት… ከንፈሯ ላይ ተጣበቀ….በቀላሉ አለቀቃትም…ምን ይህል ደቂቃ እንደተሳሳሙ ሁለቱም አያቁም …ምን አልባት አንድ ደቂቃ ሊሆን ይችላል …ምን አልባትም ዘላለምም ሊሆን ይችላል….ግን የሁለቱም ልብ በየውስጣቸው ሲንፈራፈር ታውቋቸዋል…ሁለቱም በአየር ላይ የሚንሳፈፉበት ክንፍ እንዳበቀሉ አይነት ስሜት ተሰምቷቸዋል….ለሁለቱም ያልተጠበቀና ልዩ ክስተት ነበር….ሁለቱም ደግሞ ከገዛ ራሳቸው ጋር እንኳን ተነጋግረው ሳይወስኑ በነገሩ መሆን ተስማምተው በደስታ ፈንጥዘዋል፡፡በፀሎት አራት ተኩል ላይ ሰለሞን ክፍል የሄደች ስድስት ሰዓት ሲሆን ነበር ወደክፍሏ የተመለሰችው፡፡እሱንም ለሊሴ ምን ትለኛለች የሚል ይሉኝታ ቀፍድዷት እንጂ እዛው እቅፉ ውስጥ ሟሙታ እየቀለጠች ቢነጋ ደስ ይላት ነበር፡፡እሱም እንደዛው፡፡
በማግስቱ እስከአራት ሰዓት ከአልጋቸው መውረድ አልቻሉም ነበር፡፡

‹‹ልጁ ምን ይለናል ብዬ ነው እንጂ ቀኑን ሙሉ ከዚህ አልጋ ባልወርድ ደስ ይለኝ ነበር››ወ.ሮ ስንዱ ተናገሩ
‹‹ከአልጋው መውረድ ነው ወይስ ከእኔ እቅፍ መውጣት ነው ያስጠላሽ?››

‹‹አንተ ደግሞ…ለምን ታሳፍራኛለህ?››
‹‹ይሄውልሽ ነገ ወደአዲስአበባ እንመለስ የለ ..የልጃችንን የንቅለተከላ የተደረገላትን አመታዊ የመታሰቢያ በአል ድል አድርገን ከደገስን እና አንዳንድ ነገሮችን ካስተካከልን በኃላ..ለአንድ ወር ሲዊዘርላንድ እንሄዳለን፡፡›

‹ማ እና ማ?››

‹‹እኔ እና አንቺ..፡፡ያው አሁን ዳግመኛ እንደተጋባን እና ጉዞውንም ልክ እንደጫጉላ ሽርሽር ቁጠሪው››

‹‹በጣም አጓጓኸኝ ..ግን እኮ ይሄ ያለንበትም ስፍራ ከሲዊዘርላንድ አይተናነስም››

‹‹ገባኝ… ግን ራቅ ብዬ ካንቺ ጋር መጥፋት ነው የምፈልገው…››

‹‹ውይ የፍቅር ግርሻ እኮ መጥፎ ነገር ነው…ግን እንደምታየው ከልጄ ጋር ላለፈው አንድ ወር አልተገናኘሁም…እኔ ለሌላ አንድ ወር ከእሷ ውጭ ማሳለፍ አልችልም››

‹‹አንቺ ደግ…በቃ ይዘናት እንሄዳለን…ሶስታችን እንደቤተሰብ ከእንደገና አብርን በፍቅር እንቆማለት….›

‹‹እሱ ያስማማኛል፡፡››አሉና ከአልጋቸው ላይ ወረዱ…ተጣጥበውና ተዘጋጅተው ከክፍላቸው ሲወጡ አምስት  ሠዓት ሆኖ ነበር፡፡የሰለሞንን ክፍል ሲያንኳኩ አልነበረም…ደወሉለት

..በደቂቃዎች መጣላቸው፡፡

‹‹እንዴት ነበር አዳር?››

‹‹ዕድሜ ላንተ ሁሉ ነገር ውብና ማራኪ ነበር››አቶ ኃይለልኡል መለሱ፡፡

‹‹ጥሩ …አሁን እርግጠኛ ነኝ እርቦችኃላ?››

‹‹አዎ …የራበን ይመስለኛል›››

‹‹በሉ ተከተሉኝ …ቆንጆ ቁርስና ምሳ አንድ ላይ እንዲዘጋጅላችሁ አድርጌለው…››ብሎ ይዟቸው ሄደ..፡፡

በቀይ መንጣፍ ያሸበረቀ ግዙፍ የሞጃ ሳሎን የመሰለ ክፍል ውስጥ ነው ይዞቸው የገባው….ልክ አዲስ ሙሽሮች እንደሚስተናገዱበት አዳራሽ ውብና ልዩ ተደርጎ ዲኮር ተደርጓል….ግዙፉ ጠረጴዛና ጠረጴዛውን የከበቡት ወንበሮች ከቆዳ የተለበጡ ውብና ልዩ ናቸው…ልዩ ልዩ ባህላዊ ቅርሶች ግድግዳው ሞልተውታል፡፡እየመራ ወሰደና ወንበሩን እየሳበ ሁለቱንም አስቀመጣቸውና ..ከፊት ለፊታቸው ዞሮ ቆመ….
‹‹አቶ ኃይለልኡልና ወ.ሮ ስንዱ…ዛሬ የመጨረሻ ቀናችን ነው፡፡ማለቴ ከአሁን በኃላ ያለውን ቤታችሁ ተመልሳችሁ መደበኛ ስራችሁን እየሰራችሁ የምናከናውነው ይሆናል፡፡እስከአሁን ላለው ግን በእውነት እናንተ ለእኔ ትልቅ ውለታ ስለዋላችሁልኝ ላመሰግናችሁ እወዳለው..ይሄንን ስራ ከልጃችሁ ከበፀሎት ስቀበል በከፍተኛ ፍራቻና በወረደ የራስ መተማመን ነበር…እናንተ ግን ለልጃችሁ ስትሉ ጠንክራችሁ አጠነከራችሁኝ….በሶስት ወርና በአራት ወር እፈተዋላው ያላልኩትን በመሀከላችሁ ያለውን ውስብስብ ችግር በአንድ ወር አዚህ ደረጃ እንዲደርስ አድርጋችሁ አስደመማችሁኝ..ይህ አንድ ወር ለእኔ ታላቅ ትምህርት

ያገኘሁበት ነው..በሀገራችን የማህበራዊ ስሪትና ባህል የጋብቻ አማካሪ ብሎ ዘመናዊ አሰራር ተግባራዊ ማድረግ ውጤታማ አይሆንም ተጠቃሚም አይኖርም ብዬ ተስፋ ቆርጬ ድርጅቴን ልዘጋ እያሰብኩ ባለሁበት ወቅት ነው የእናንተን ስራ ያገኘሁት…አሁን ግን ዘመናዊውን ሳይንስ በሀገራችን ተጫባች ሁኔታ አንፃር ቃኝተን በጥበብ ከተጠቀምነው የብዙ ውስብስብ ጋብቻዎችን ችግር ለመቅረፍ እንደሚቻልና ስራዬም ለማህበረሰቡ ጠቃሚ እንደሆነ እንድረዳ አድርጋችሁኛልና አመሰግናለው….በአጭር ቀናት ውስጥ ባሳያችሁት ውጤት ልጃችሁ ብቻ ሳትሆን እኔም ደስተኛ ነኝ፡፡
‹‹ልጄ ..አንተም እንደምትረዳው ወደእዚህ ጉዳይ ስንገባ ..አንተ ስለምትለው በእኔና ስንዱ መሀከል ስላለው ግንኙነት ማሻሻል ምንም አይነት ፍላጎትም ሆነ እምነት የለኝም ነበር…ልጄን ለማግኘት ስል ነበር ሳልወድ በግዴ የተስማማሁት…እያደረ ግን ሀሳቤን ሙሉ በሙሉ እንድቀይር አድርገሐኛል…ጋብቻዬ ጥሩ ባለመሆኑ ሕይወቴም ምን ያህል የተዛባ እና በጭንቀትና በሀዘን የተሞላ እንደሆነ እንዳስተውል አድርገሐኛል…እኔ ምን የህል አጥቼ ቤተሰቦቼንም ምን ያህል እንዳሳጣኋቸው እንዳስብና ወደቀልቤ እንድመለስ አድርገኀኛል..እኔ ነኝ አንተንም ሆነ ስንዱን ማመስገን አያለብኝ…በእውነት የእድሜ ልክ ባለውለታዬ ነህ…አንተ ከአሁን ወዲያ ልክ እንደልጄ ነህ….በማንኛውም ህይወት ጉዞህ እኔም ሆንኩ ቤተሰቦቼ ከጎንህ እንደሆን ልታውቅ ይገባል፡፡እርግጠኛ ነኝ ነገ ተነጋ ወዲያ አዲስአበባ እንደተመለስን ልጃችንም ወደቤቷ ትመለሰላች ብዬ ተስፋ አደርጋለው…እሷ ስትመለስ የተቀረውን ነገር እናወራለን፡፡››

ሰለሞን‹‹እሺ ጥሩ አሁን ስለራባችሁ …ከዚህ በላይ በወሬ አልያዛችው ››እጁን ሲያጨበጭብ ነጭ ዩኒፎርም የለበሰ አስተናጋጅ መጣ…..‹‹ምግብ ይቅረብ…መጀመሪያ የእጅ ውሀ አምጡ በላቸው››ሲል አዘዘው…ልጁ በቆመበት በራፍ ላይ ላሉት ልጆች ምልክት ሰጠው፡፡ውብ የሆነ ባህላዊ ነጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ወጣት ሴቶች ውብ የሆነ ወርቅ ቅብ ማስታጠቢያ በእጃቸው ይዘው መጡና….አንደኛዋ አቶ ኃይለልኡልን ሌለኛዋ ወ.ሮ ስንደን ለማስታጠብ ጎንበስ አሉ…ሁለቱም ታጥበው..ቀና ሲሉ በተመሳሳይ ቅፅበት ነው የአንደኛዋ ፊት

አትሮኖስ

23 Nov, 17:15


ላይ አይናቸው ያረፈው….ከዛ በኃላ ያለው ነገር ለመግለፅ ሚያስቸግር ነበር..ምግብ አዳራሹ በወ.ሮ ስንዱ እልልታና ጩኸት ተናጋ…አቶ ኃይለ ልኡል ከተቀመጡበት ተነስተው ልጃቸውን በማቀፍ ልክ እንደባሌት ዳንስ በአየር ላይ ነው ያሽከረከሯት…..ለሊሴ እና ሰሎሞን ትዕይንቱን በተመስጦ እየተከታተሉ ነው፡፡

ይሄንን ትዕይንት ለሚከታተል ሰው ልጃቸው ለአለፈው አንድ ወር ብቻ ተለይታቸው የቆየች ሳይሆን በአራስነቷ ተሰርቃባቸው ከሀያ አመት በኃላ በተአምር የተገኘች አይነት ነው የሚመስለው፡፡
በነጋታው አምስቱም በቻርተር አውሮፕላን ተጭነው ወደአዲስ አበባ ተመሱ፡፡በፀሎት ግን ቀጥታ ወደቤቷ ሳይሆን ወደ ለሊሴ ቤት ነው መሄድ የፈለገችው..ውሳኔዋን ስትነግራቸው ሁለቱም ወላጆቾ ክፉኛ ተቃውመው ነበር፡፡
‹‹አባዬ እማዬ.ስሙኝ…እኔን ወደቤት ለመመለስ ባደረጋችሁት ነገር በጣም ኮርቼባችኃላው በጣም እንደምትወዱኝም አውቄለው…ግን አሁን መጀመሪያ ያበላሸሁትን ነገር ማስተካከል አለብኝ…ከአሁን ወዲህ እንድታውቁት ምፍልገው እናንተ ብቻ ሳትሆኑ እነሱም ወላጆቼ ናቸው….ከአሁን ወዲያ ብቸኛ ሳልሆን ወንድምና እህት አለኝ…ቦሌ ያለው የተንጣለለ ቪላ ብቻ ሳይሆን አቃቂ ያለውም ደሳሳ ቤት ቤቴ ነው፡፡እና የግድ አሁን ከለሊሴ ጋር ወደቤት መሄድ አለብኝ…ከዛ እስከአሁን የዋሸዋቸውን ናግሬ ይቅርታ ካገኘሁ በኃላ እመጣለሁ››
‹‹እንዴት አድርገሽ ነው የምትነግሪያቸው…?.››
‹‹አላውቅም… ብቻ የሆነ መንገድ ፈልጋለው››
‹‹ካልሽ እሺ ልጄ….ግን ታውቂያላሽ ከአምስት ቀን በኃላ ቤት ድግስ አለ…ንቅለ ተከላ የተደረገልሽ ቀን ነው..ያው እንደተለመደው ዘንድሮም እየተደገሰ ነው፡፡
‹‹አዎ አውቃለው…..የሚገርመው እነዛኞቹም ቤተሰቦቼ ጋር ድግስ አለ….በዛው በተመሳሳይ ቀን የሙት አመት መታሰቢያ ድግስ አለባቸው…የማ ለእኔ ልቧዋን የሰጠችኝ የበሬዱ የሙት መታሰቢያ….››ስትናገር የሚረግፈውን እንባዋን መገደብ አልቻለችም….እናትና አባቷም በሰሙት ነገር ሽምቅቅ ነው ያሉት….፡፡
‹‹እና በእለቱ የትኛውን ድግስ እንዳምሳተፍ ግራ ገብቶኛል..ግን አታስቡ ጥዋት እዚህ ቆይና ከሰዓት እናንተ ጋር መጥቼ የእኔን የምስጋና በአል አከብራለው….አዎ እንደዛ አደርጋለው››
በቃ የእኔ ቆንጆ …እንደሚሆን እንደርጋለን..አንቺ ምንም አትጨነቂ…አሁን ሹፌሩ እናንተን ቤታቸው ያድርሳችሁ እኛ ከሰለሞን ጋር በራይድ እንሄዳለን፡፡››አሉ አቶ ኃይልኡል

‹‹አረ አባዬ ግድ የለም እኛ በራይድ ብንሄድ ይሻላል፡፡››ለሊሴና በሬዱ ፈጠን ብለው አካባቢው ወደአለ ራይዱ ሄዱና .ውስጥ ገብተው ወደአቃቂ ሲያመሩ ሰለሞን እና ባልና ሚስቶቹን ሊቀበላቸው በመጣ መኪና ቦሌ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ሄዱ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

22 Nov, 17:27


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ የባልና ሚስቶቹ የምክር አገልግሎት እንደቀጠለ ነው…ዛሬ ወንጪ ከከተሙ አስራአራተኛው ቀን ላይ ሲሆኑ በዚህ የ14 ቀን ጉዞቸው ከፍተኛ ለውጥ ላይ ደርሰዋል… አሁን በዚህ ሰአት ከሁለቱም ፊት ለፊት ተቀምጦ ተራ በተራ እያያቸው እያተናገረ ነው.. ‹‹ሰው…»

አትሮኖስ

22 Nov, 17:04


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

የባልና ሚስቶቹ የምክር አገልግሎት እንደቀጠለ ነው…ዛሬ ወንጪ ከከተሙ አስራአራተኛው ቀን ላይ ሲሆኑ በዚህ የ14 ቀን ጉዞቸው ከፍተኛ ለውጥ ላይ ደርሰዋል…
አሁን በዚህ ሰአት ከሁለቱም ፊት ለፊት ተቀምጦ ተራ በተራ እያያቸው እያተናገረ ነው..
‹‹ሰው ምን ጊዜም ከስህተት ጋር ሚኖር ፍጡር ነው፡፡ከሰው ጋር ስንኖር ስህተት ፈላጊ ከሆን በማንኛውም ሰው ላይ ከመጠን ያለፈ ስህተቶችን በቀላሉ ማግኘት እንችላለን…..ያ ደግሞ ከሰው ጋር አያኖረንም…አንዳችን የሌላችንን ክፍተት ለመድፈን መፈጠራችንን እስካላሰብን

ድረስ ምንም ነገር ሰላም ሊሆን አይችልም፡፡ደግሞ አስቡት የጋብቻ ዋናው አስፈላጊነትም ይህ ነው ፡፡ወንድ ልጅ በራሱ ፍፅም ወንድ ብቻ አይደለም..75 ፐርሰንት የወንድነት ሆርሞን ሲኖረው 25 ፐርሰንት ግን የሴት ሆርሞን በውስጡ ይዞል..ሴቷም በተመሳሳይ 75 ፐርሰንት የሴት ሆርሞን ሲኖራት 25 ፐርሰንት የወንድ ሆርሞን ይዛለች…አያችሁ የተፈጥሮን ረቅቂነት ..ሁለቱ ሲጣመሩ ...አንድ ሙሉ ወንድና አንድ ሙሉ ሴት ይገኛል ማለት ነው፡፡ለመዋሀድ ደግሞ ፍቅር ዋናው አገኛኝ መሰላል ነው፡፡››
‹‹ግልፅ ነኝ አይደል?››
‹‹አዎ .. ቀጥል››ሲሉ የተናገሩት አቶ ኃይለ ልኡል ናቸው
ሰለሞን ንግሩን ቀጠለ‹‹በአንድ መንደር ውስጥ ትኖር የነበረች ሴት ሶስት ሽማግሌዎች ከቤቷ አካባቢ ከውጭ በፀጥታ ተቀምጠው ተመለከተች። ሴትዬዎም ከቤቷ ወጣችና ወደሽማግሌዎቹ ቀርባ" እናንተን ከዚህ በፊት አይቼያችሁ አላውቅም።ግን እዚህ በደጃፌ ለረጅም ጊዜ ተቀምጣችኋል። እርግጠኛ ነኝ እርቦችኋል። እባካችሁ ወደቤቴ ዘልቃችሁ ግብና ቤት ያፈራውን ቅመሱ››አለቻቸው።
ከመካከላቸው አንደኛው ሽማግሌ‹‹የቤቱ አባወራ በቤት አለ?››ሲሉ ጠየቋት። እሷም መለሰች‹‹አይ የለም››ስትል መለሰች።
ሽማግሌውም"ስለዚህ ወደቤት መግባት አንችልም።"ሲሉ መለሱላት።
ሴትዬዋም ወደውስጥ ተመልሳ ገባች ።መሸቶ ባሏ እንደመጣ ስለሰዎቹ ነገረችው። ባሏም
‹‹በይ አሁን ሂጂና ወደውስጥ እንዲገብ ጋብዢያቸው››አላት።
እሷም ወጣችና ወደውስጥ እንዲገብ በድጋሚ ጠየቀቻቸው‹‹ባለቤቴ ቤት ነው ያለው..ወደውስጥ እንድትገብም ጋብዛችኋል...እባካችሁ ወደ ውስጥ ዝለቁና የሆነ ነገር ቅመሱ››
‹‹እኛ በአንድ ላይ ወደውስጥ መግባት አንችልም››አሏት
‹‹ለምን ?››ግራ ገብቷት ጠየቀች።

ከሽማግሌዎቹ አንድ መመለስ ጀመረ "ይሄውልሽ ..."ወደአንደኛው ጓደኛው በጣቱ እየጠቆመ "..እሱ አቶ ሀብት ነው ወደቤትሽ ከገባ ቤትሽ በሀብት ለዘላለም እንደተሞላ ይዘልቃል።...ይሄኛው ደግሞ አቶ ስኬት ነው ከአንቺ ጋር ተከትሎ ወደውስጥ የሚገባው እሱ ከሆነ ቤትሽ በስኬት ይሞላል።እኔ ደግሞ አያ ፍቅር እባላለሁ። እኔ ከገባሁ ደግሞ በዘመንሽ ሁሉ በቤትሽ ፍቅር ሞልቶ ይፈሳል።ክፍቱ ግን አስቀድመን እንደነገርንሽ ሶስታችንም በአንድ ላይ ወደውስጥ መግባት አንችልም። ስለዚህ ወደቤትሽ ተመለሺና ከባልሽ ጋር በመማከር ከሶስታችን ማንኛችንን ወደውስጥ እንደምታስገብ ወስኑ "በማለት አብራሩላት።
እሷም እንደተባለችው ወደውስጥ ተመልሳ የሰማችውን ሁሉ ለባሏ አስረዳችው። ባሏ በሰማው ነገር ፈነጠዘ‹‹አቶ ሀብትን እንጋብዘው ፤ይግባና ቤታችን በሀብት ይሙላው፤ከእሱ የሚበልጥ ምን አለ?።››አላት።
ሚስትዬው ግን ውሳኔውን ተቃወመች"ለምን ስኬትን አንጋብዘውም፤ከሀብት ይልቅ ስኬት ነው የሚጠቅመን"አለች። እቤት ውስጥ የነበረች የልጃቸው ሚስት ወሬቸውን ስታዳምጥ ስለነበረ ወደእነሱ ቀረበችና‹‹ለምን ፍቅርን አንጋብዘውም..ከሁሉም በላይ በቤታችን ፍቅር ቢሞላ ይሻላል››የሚል ሀሳብ አቀረበች።
ጥቂት ካሠላሠሉ እና ከተከራከሩ በኃላ ባልና ሚስቶቹም በሀሳቧ ተስማሙ ፤ሚስትም ተመልሳ ወጣችና ወደእንግዶቹ ሄደች። ‹‹ከመካከላችው ፍቅርን ለመጋበዝ ወስነናል፤አያ ፍቅር እባክህ ተነስና ወደቤታችን ዘልቀህ ግባ...የተዘጋጀውን መአድም አብረኸን ተቋደስ..ሌሎቻችሁ ስላልመረጥናችሁ ይቅርታ "ስትል ተናገረች።
ፍቅር ተነሳና ወደቤት ለመግባት መንቀሳቀስ ሲጀምር ስኬትና ሀብትም ከተቀመጡበት ተነስተው ከኃላው ተከተሉት። ሴትዬዋ ግራ ገባት ‹‹አብረን መግባት አንችልም.. ከመሀላችን አንዳችንን ምረጪ አላላችሁኝም ነበር እንዴ?"ስትል ጠየቀች።
ከመሀከላቸው አንደኛው ማስረዳት ጀመረ‹‹ልጄ ስትመርጪ ስኬትን ወይም ሀብትን መርጠሽ ቢሆን ኖሮ አንዳችን ብቻ ነበር ወደቤትሽ የምንገባው።አሁን ግን የመረጥሽው ፍቅርን ነው። እኛ ደግሞ ፍቅር በገባበት ሁሉ ተከትለን መግባት ግዴታችን ነው።እኛም እራሳችን የፍቅር ምርኮኞች ነን።በዚህ ምክንያት ሶስታችንም የግድ ወደቤትሽ እንገባለን። ካዘጋጀሽውም መአድ እንቋደሳለን።ቤትሽንም ዘላለም በሚትረፈረፍ ሀብት ፤ስኬትና ፍቅር እንሞላዋለን።"አሏት። እሷም በደስታ እየፈነጠዘች ወደቤቷ ይዛቸው ገባች።

አያችሁ እናነት ሀብታም ናችሁ ስኬታማም ናችሁ…አሁን እየጣርን ያለነው ከመሀከሏችሁ ሾልኮ ተሰዶ ነበረውን ዋናውን ፍቅር ለመመለስ ነው..ፍቅር ከተመለሰ ሁሉ ነገር ሙሉ ይሆናል››
ዛሬ በዚህ በሰጠኋችሁ ምሳሌ በመሀከላችሁ፤በቤታችሁና በአካባቢያችሁ ፍቅር ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እያሰላሰላችሁ እንድታድሩ እፈልጋለው…ነገ እዚህ የምናሳልፍበት የመጨረሻ ቀናችን ነው…ተነገ ወዲያ ወደአዲስ አበባ እንመለሳለን….አሁን ዋናውን ነገር አጠናቀናል…በቀጣይ ቤታችሁ ሆናችሁ ልጃችሁም ተመልሳ ስራችሁን እየሰራች የምናደርገው ይሆናል…››በማለት የእለቱን ፕሮግራም አገባደደ
ባልና ሚስቶቹ ክፍላቸው ተያይዘው ሲገቡ የጠበቃቸው የተለየ ነገር ነበር፡፡የመኝታ ክፍላቸውን ግራና ቀኝ ግድግዳ ታኮ የነበረው ሁለት አልጋ ሁለቱም ወደመሀል ተስቦና አንድ ላይ እንዲገጥም ተደርጎ አንድ አልጋ ሆኗል….ግዙፉ የተዋሀደው አልጋ በነጭ ውብ አልጋ ልብስ ተሸፍኗል.. አልጋ ልብሱ መሀል ላይ በልዩ ዲዛይን የተሰራ ባለቀይ ቀለም የልብ ቅርፅ ይታያል..ሙሉ ወለሉ በቀይ ፅጌረዳ አበባ ከመሞላቱም በተጫማሪ ባለቆርቆሮ ልዩ ሻማ በመሀከል መሀከል ጣልቃ በማስገባት የተለያ ቀለም ያው ብርሀን እየረጩ ነው፡፡አደኛውን ግድግዳ ተጠግቶ በሚታይ ጠረጴዛ ላይ ሻማፓኝ መጠጥ ከውብ ብርጭቆዎች ጋር ይታያል…በሚገፋ ተሸከርካሪ ጠረጴዛ ላይ አስጎምዢ ምግቦች ተደርድረዋል…
ሁለቱም ባልና ሚስት በመጀመሪያ የተሳሳተ ክፍል የገቡ ነበር የመሰላቸው….የገዛ ሻንጣቸውንና ሌሎች የግል እቃዎችን ሲያዩ ተረጋጉና ወደውስጥ ዘልቀው በራፉን ዘጉት፡፡
‹‹ስንድ ይሄ ጉደኛ ልጅ የ20 አመት ጎረምሳ አደረገን እኮ..››
ወ.ሮ ስንዱ እንባቸው እየረገፈ ተናገሩ‹‹ያበቃልኝ መስሎኝ ነበር….እድሜ ለልጄ ይሄው ዳግመኛ ልጃገረድ ሆንኩ››
‹‹እንዴ ስንድ ዛሬ ሳቅና ፈንጠዝያ ነው እንጂ የምን ለቅሶ?››አሉን እጃቸውን ወደባለቤታቸው ጉንጮች በመላክ እንባቸውን ጠረጉላቸውና አቅፈው ሳሞቸው….‹‹በይ ዛሬ ምሽቱ የእኛ መሰለኝ..እንቀመጥ››
‹‹መጀመሪያ ልብሴን ልቀይርና ቀለል ያለ ልብስ ልልበስ…እስከዛ እንተ ቁጭ በል››

አትሮኖስ

22 Nov, 17:04


‹‹ጥሩ ..እኔም ቢጃማ ነገር ብለብስ ደስ ይለኛል…››አሉና ሁለቱም ወደ የሻንጣቸው ሄዱ…ከ10 ደቂቃ በኃላ ሁለቱም በለሊት ልብሳቸው ለበሱና እጃቸውን ታጥበው የምግብ ጠረጴዛው ፊት ለፊት ተቀመጡ…ከአመታት በኃለ አንደኛው በሌለኛው እጅ በፍቅርና በሳቅ ታጅበው ራታቸውን በሉና ሻምፓኛቸውን ከፈቱ..ሁሉ ነገር ውብ ነበር…ልክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተያዩ ነው የሆነው…የሁለቱም ልብ ምት እንደወጣት ልብ ነው ከቁጥጥር ውጭ የሆነው…ከአመታት በኃላ ነው የአንዳቸው ገላ ለሌለኛቸው ምላሽ በመስጠት እንደ እሳት ጎመራ መንቀልቀል የጀመረው….ከአስራ ምናምን አመት በኃላ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ የአንደኛቸው ከንፈር ሌላኛቸው ላይ ያረፈው….የአንዳቸው እጅ የሌለኛቸውን ፓንት ወደታች አንሸራቶ ያወለቀው፡፡
///
በፀሎት እና ለሊሴ ዛሬ የመጨረሻ ቀን የወንጪ ቆይታቸው ነው፡፡በዚህም የተነሳ ቀኑን ሙሉ ላለፉት 15 ቀን ሲያስተናግዶቸው የነበሩትን ዘመዶቻቸውን በጠቅላላ እየዞሩ ተሰናብተው ጨለምለም ሲል ቀጥታ ሻንጣቸውን አንጠልጥለው የመጨረሻ አዳራቸውን በፓርክ ውስጥ ለማድረግ  እነአቶ ኃይለልኡል እንዳያዮቸው እየተጠነቀቁ ቀጥታ ሰለሞን ወደ ያዘላቸው ሎጅ ነው ያመሩት፡፡ክፍላቸው ከሰለሞን ክፍል ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን በለሁለት አልጋ ክፍልነው፡፡
ሰለሞን አቶ ኃይለልኡልና ባለቤታውን ራት ካበላና ወደ መኝታ ቤታቸው ካስገባቸው በኃላ ሌሊሴንና በፀሎትን እራት ለመጋበዝና ውቡን የመጨረሻውን ምሽት አብሮቸው ለማሳለፍ ይዞቸው ወጣ፡፡
ከሎጃቸው ፊትላፊት ባለው ጉብታ ላይ ቁጭ ብለው ሀይቁን ቁልቁል እያዩ እያወሩ ነው፡፡
‹‹በእውነት በሕይወቴ እንደዘንድሮ አስደማሚና አስደናቂ ነገር ገጥሞኝ አያውቅም›› በማለት የጫወታውን ርዕስ የመረጠው ሰለሞን ነበር፡፡
‹‹እንዴት ማለት?››አለችው ለሊሴ፡፡
‹‹እንዴ ..ይታይሽ አንድ ሴት ዝም ብላ በስልኬ በመደውል ስራ ልቀጥርህ እፈልጋለው
…አሁን  መቶ ሺብር  ልላክልህ  ፣  ስራውን  ስትጨርስ  5  ሚሊዬን  ብር  እንድታገኝ

አደርጋለው››ስትለኝ መጀመሪያ ቀልድ ነበር የመሰለኝ…ይገርምሻል የባንክ ቁጥሬን አንኳን ስልክላት ቆይ እስኪ ጉዷን አያለው ብዬ ነበር…እሷ ግን ብሩን ልካ አስደመመችኝ፡፡ወዲያው ከወላጆቾ ስር ጠፍታ በሀገር አቀፍ ደረጃ የምትፈለግ ልጅ ሆና አገኘኋት..በእውነት ያንን ሳውቅ በጣም ፈርቼ ነበር፣በዛ ተገርሜ ሳልጨርስ እንቺ ለማሪያም ድግስ በጠራሽኝ ጊዜ እናንተ ቤት ቁጭ ብላ አገኘኋት….ከዛ የሁሉ ነገር መነሻ አንቺ እንደሆንሽ ተረዳሁ…ምክንያቱም ስለእኔ ከአንቺ ባትሰማና ስልኬንም ካንቺ ዘንድ ባታገኝ ይሄን ሁሉ ታሪክ አምልጦኝ ነበር…ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ደግሞ አሁን የምሰማው ነገር ነው…የአንቺ እህት ለእሷ ልቧን መለገሷ……ይገርምችኋላ ለቀናት እንዴት ያንን ቤት መረጠች …?ብዬ ስብሰለሰል ነበር..ለካ ከዛ ቤተሰብ ጋር ያላታ ትስስር ጥልቅና በደም የተገመደ ነበር›››
‹‹ታድዬ ደግሜ ደጋግሜ ነው ያስደመምኩህ ማለት ነው››አለችው በፀሎት
‹‹በጣም..እንጂ››
‹‹ምን እሱን ብቻ እኔንም ነው ስታስደምሚኝ የከረምሽው…በተለይ በቀደም ማንነትሽን ስትነግሪኝ….አብጄ እየቃዠው ነበር የመሰለኝ››አለች ለሊሴ፡፡
ለተወሰነ ጊዜ ዝም ተባባሉና በለሊሴ ጥያቄ ሌላ ርዕስ ተከፈተ
‹‹ሶል አሁን ቤተሰቦቾን የምታገኘው ከዚህ እንደተመለስን ነው እንዴ?››ስትል ያሳሰባትን ጥያቄ የጠየቀችው፡፡
‹‹ምነው ጠየቅሽኝ?››
‹‹እኔ እንጃ የእኛ ቤተሰብ በፀሎትን እንዲህ በቀላሉ ለማጣት ዝግጁ የሚሆኑ አይመስለኝም…በተለይ ስለማንናቷ እነ አባዬ ሲያውቁ በጣም ነው የሚከብዳቸው..››
‹‹በፀሎት ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደለሊሴ ተጠጋችና አቅፋ እየወዘወዘቻት‹‹‹እህቴ ስለምን ማጣት ነው የምታወሪው…?ከአሁን ወዲህ እኔ ሁለት ቤተሰብ ነው ያለኝ…አንድ ቀን እዚህ ቤት ካደርኩ በሚቀጥለው ቀን እዛ አድርለሁ….ከተቻለ እና ሁሉም ከተሳማማ ደግሞ ሁላችንም ተሰብስበን አንድ ቤት ውስጥ እንድንኖር ነው የምፈልገው…እርግጥ ይሄ በአንዴ አይሆንም አውቃለው…ግን ሁለቱም ቤተሰቦቼ ቀስ በቀስ በደንብ እንዲተዋወቁና እንዲግባቡ ካደረግኩ በኃላ አንድ ላይ ሰበስባቸዋለው…የቦሌው ቤታችን እኮ አርባ ምናምን

ክፍል ነው ያለው…ከዛ ውስጥ አስሩን አንኳን አንጠቀምበትም…..እና እህቴ ስለመለያየትና ስለማጣት ምንም አታስቢ››
ለሊሴም‹‹እህቴ  በጣም  ነው  የምወድሽ….ከእህቴ  ሀዘን  እንድፅናና  ስላደረግሺኝ አመሰግናለው፡፡››ብላ እሷም በተራዋ አቅፋ ጉንጮን ሳመቻት፡፡
‹‹በቃ በቃ…መላቀሱ ይብቃችሁ…ለማንኛውም በፀሎት ቤተሰቦችሽን የምታገኝው እንዴት እና መቼ እንደሆነ ነገ ጥዋት ቁርስ እየበላን እናወራለን፡፡››
‹‹ለምን አሁን አናወራም… ?››መለሰችለት
‹‹አይ አሁን መሽቷል…ተነሱ እናንተም ወደክፍላችሁ ግቡ››ብሎ ቀድሞ ተነሳ..ለሊሴና በፀሎትም ተከትለውት ተነሱ
ሰለሞን እነሱን ወደክፍላቸው አስገብቶ ወደገዛ ክፍሉ ገባና ቢጃማውን ቀይሮ ቀድሞ ያዘጋጀውን ቢራ ከፈፍቶ መጠጣት ጀመረ…ሁለት ጠርሙስ ካገባደደ በኃላ አስቴር ትዝ አለችው፡፡ ሞባይሉን አነሳና ሰዓቱን ተመለከተ፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት አልፏል…ደወለ….ከበርካታ ጥሪዎች በኃላ ተነሳ፡፡
‹‹ሄሎ ኪያ ተኝታሻል እንዴ ?ቀሰቀስኩሽ?››
አስቴር መለሰችለት‹‹አይ ወንድሜ ገና ለመተኛት እየተዘገጃጀው ነበር፡፡››
‹‹ደህና ነሽ?››
‹‹ደህና ነኝ…ምነው ቆየህ እኮ !አልጨረስክም አትመጣም እንዴ?››
‹‹ነገ ከሰዓት የምመጣ ይመስለኛል፡፡››
‹‹ጥሩ ነው…ልደውልልህ ነበር…››
‹‹ምነው በሰለም…፡፡››
‹‹አይ የፊታችን እሁድ የመስፍኔ ልደት ስለሆነ ሰርፕራይዝ ላደርገው አስቤላው…አንተም እንድትገኝ እፈልጋለሁ››
‹‹እንዴ እስከአሁን ወደመጣበት አልሄደም እንዴ?››

‹‹አይ ቀረ እኮ ….በፊትም ጥዬሽ የሄድኩት እየቆጨኝ ነው….ትዳሬን አክብሬ እዚሁ እየሰራሁ ከአንቺ ጋር ልጄን አሳድጋለው አለኝ››
‹‹እና መፋታቱን ሙሉ በሙሉ ተዋችሁት ማለት ነው?››
‹‹አንተ ደግሞ ስለምን መፋታት ነው የምታወራው….?በቃ ደህና እደር በሰላም ተመለስልኝ…መስፍኔ ከመኝታ ቤት እየጠራኝ ነው…››ብላ ስልኩን ዘጋችው፡፡
ጨጓራው ሲለበልበው ይታወቀዋል…በቃ ውስጡ እየነደደ ነው…አሁን ምንም የማያውቀውን አዲስ ነገር አልነገረችውም…ምን እንዳበሳጨው ለራሱም አልገባውም….ሌላ ቢራ ከፈተና አንደቀደቀው…ስልኩን ደግመኛ አነሳና ደወለ…

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

22 Nov, 12:00


#አልፎ_አልፎ_መሞት

ሰው
አንድም - በእግዜር፡
አንድም - በመውዜር፡
እያዋሀደ የዕድሜውን አመል፡
ማታ በውስኪ ጠዋት በጠበል።

ሰው ቢያጣ መንገድ  ሰው ቢያጣ ምርጫ፡
ተከፋፍለው ተስፋን ለቅርጫ።

ተመዳደቡብኝ የመኖሬን ኮታ፡
አንድ ላይ ለበሱት ነፍሴን እንደኩታ።

እኔ ግን፡
ይጥቀማቸው ብዬ አልተወው መኖሬን፡
ብረግፍም አለሁኝ እድሜ ይስጠው ስሬን።

ሰው
ይመስለዋል እንጂ መተንፈስ አክራሞት፡
ስንቱን ያሻግራል አልፎ አልፎ መሞት።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

22 Nov, 09:00


#አዎ !
ለጊዜውም ቢሆን፤ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ ፤ ወደፊት ይጓዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ ፤ ሚስቱን ያስረግዛል

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

22 Nov, 06:15


#እንደምትወዳት_ንገራት

ሕይወት የብድር በሬ፥መቼ ሁሌ ይጠመዳል
ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል::

ቀለበት፥ አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም
-ቀናት ሳምንታት ወራት
ዛሬውኑ ፥አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት::

አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ
ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ
ያጸድ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ፥ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ሕይወት የላምባ መብራት
አሁንኑ ዛሬውኑ ፥እንደምትወዳት ንገራት፤

ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደማትቀባው አመድ
ወደማትስበው አየር
ሳትቀየር
አንትም አንደበት ሳለህ፥ እሷም ጆሮ ሳያጥራት
ዛሬውኑ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት።

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

21 Nov, 18:15


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አራት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ከላይ የተለቀቀው ክፍል 24 ሳይለቀቅ 25  ተለቆ ነበር ክፍል 24 አሁን ተለቋል ለነበረው መዛባት ይቅርታ  እጠይቃለው🙏 ቤተሰቦች ለሊሴና በፀሎት በእቅዳቸው መሰረት በአንቦ በኩል አድርገው ወንጪ በመድረስ የለሊሴ አጎት ቤት ከደረሱ ሁለት…»

አትሮኖስ

21 Nov, 18:00


​‹‹እሱማ ምን ጥርጥር አለው….ግን እንደው ትረዳዋለች ወይ የሚለው ጥርጣሬ አድሮብኝ ነው..እሷን ለማታለል ለማስመሰል ያደረግነው መስሎ እንዳይሰማት››ወ.ሮ ስንዱ ጥርጣሬያቸውን አሰሙ፡፡
‹‹እሷ የምታውቀንን ያህል እኛ እኮ ልጃችንን አናውቃትም …..››ሃይለልኡል የሚስታቸው ሀዘንና ጥርጣሬ ውደውስጣቸው እንዳይገባ እየታገሉ መለሱ፡፡
‹‹እሱስ እውነትህን ነው….የልጃችን ትልቅ ውለታ አለብን››
‹‹አዎ .አሁን ልጃችን በጣም በስላለች…ምን አስቤለው መሰለሽ….ካምፓኒው ውስጥ የሆነ ቦታ ይዛ ስራ መጀመር አለባት…እኔ በቅርቡ ጡረታ ወጥቼ ከአንቺ ጋር አለምን እየዞርኩ ዘና

ማለት ነው የምፈልገው…ከአሁን በኃላ በተጨናነቀው የቢዝነስ አለም ውስጥ ቀሪ ህይወቴን ማባከን አልፍልግም››
‹‹እና ስራውን ሙሉ በሙሉ እንድትረከብህ ነው የምትፈልገው?፡፡››
‹‹አዎ ከእኔ ጋር ሆና አንድ ሁለት አመት ከሰራች በቃ ከእኔ በተሻለ ውጤታማ እንደምትሆን እርግጠኛ ነኝ..እይ እስኪ እኔና አንቺን ወደስምምነት ለማምጣት የተጠቀመችበት የረቀቀ ውጤታማ ዘዴ….እንዴት እንዳቀናጀችው…ያን የመሰለ ባለሞያ እንዴት እንደመለመለች
…በእውነት ይህቺ የእኛ ልጅ ነች ብዬ እስክደነቅ ድረስ ነው ያስደመመችኝ፡፡››በንግግራቸው ኩራታቸውን ሲግልፁ ፊታቸውም በደስታ እያበራ ነበር፡፡

…በሶስተኛው ቀን
ሰለሞንና በፀሎት ቢያንስ በቀን አንድና ሁለት ጊዜ እየተደዋወሉ ለረጅም ሰዓት ማውራትና የተለያዩ ርዕሶች እያነሱ መወያየት ልምድ አድርገውታል..ይሄ ደግሞ እርስ በርስ የበለጠ እንዲተዋወቁና በደንበኝነት መልክ ሳይሆን ልክ እንደአንድ የልብ ጓደኛ ወጣ ባለ ርዕሶች ላይም ረጅም ሰዓት ማውራት ጀምረዋል፡፡፡ይሄ ጉዳይ ለሁለቱም በጣም ተመችቷቸዋል፡፡አሁንም ተደዋውለው እያወሩ ነው፡፡
በፀሎት‹‹አንድ ሰው እንዳፈቀረን እንዴት ማወቅ እንችላለን…?ለምሳሌ እኔ አንድ አብሮኝ ያለ ወንድ የእውነት እንደሚያፈቅረኝና በምን ማረጋገጥ እችላለው፡፡››ስትል ያስደነቀውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹ሴት ልጅ ካለገመች በስተቀር አንድ ወንድ እንደሚያፈቅራትና እንደማያፈቅራት በቀላሉ መለየት ትችላለች…አንዳንድ ጊዜ ግን ምን ይሆናል ?እሷ በጣም ካፈቀረችው እሱ እንደማያፈቅራት ብታውቅ እንኳን ሽንፈትን ላለመቀበል ብላ እንደሚያፈቅራት እራሷን ለማሳመን ትጣጣራለች..የዛን ጊዜ የምታያቸውን ምልክቶች ሁሉ በተቃራኒው ተርጉማ ለመረዳት ትሞክራለች››
‹‹እና ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?››

‹‹ለምሳሌ ድምፅሽን ለመስማት ብቻ ይጠራሻል።ስትስቂ ስቆ ስታለቅሺም ያለቅሳል። ከመተኛቱ በፊት በመጨረሻዋ ደቂቃና ከእንቅልፍ በነቃ በመጀመሪያው ደቂቃ ስለአንቺ ነው የሚያስበው።ያለምክንያት ሊያቅፍሽ እና ከሰውነቱ ሊለጥፍሽ ይፈልጋል።አንቺን ከነማንነትሽ ለመቀበል ፍቃደኛ ሆኖ ይገኛል።አንቺን በሌላ ለመቀየር ፍፅም ፍቃደኛ አይደለም።ስህተት ሲሰራ አንቺ እንዲያስተካክል ከመጠየቅሽ በፊት ቀድሞ ለማስተካከል ጥረት ሲያደርግ ታገኚዋለሽ፤ሁል ጊዜ ሊረዳሽ ጥረት ያደርጋል።እንቅልፍ አሸልቦሽ ሊመለከትሽ ነቅቶ ይጠብቃል።ግንባርሽን በስስት ይስማል።መክሳትሽም ሆነ ክብደት መጨመርሽ ከውበትሽ አንፃር ብዙም አያስጨንቀውም፡፡በጓደኞቹ መካከል እጆችሽን ይይዛል።ወይም አቅፎ ጉያው ይሸጉጥሻል።ወዘተ…እንግዲህ እኚንና መሰል ምልክቶችን በማየትና በማመዛዘን አንድ ሰው አፍቅሮሽ ይሁን ወይስ አይሁን መለየት ትችያለሽ››
‹‹እሺ ወሲብስ ምንድነው..?በፍቅር ውስጥ ያለው ድርሻስ?››
‹‹ወሲብን የፍቅር ተጣማሪሽ ጋር ያለሽን ግንኙነት ለማጠንከር እና ለማዋሀድ እንደ ሲሚንቶ የሚያገለግል ተፈጥሯዊ ቅመም ነው፡፡ወሲብ በአግባቡ ከተጠቀምሽበት ፍቅርን በማሳደግና በማጎልበት ትልቅ የሆነ ድርሻ አለው፡፡አይደለም ወሲብ መተሻሸትና መሳሳም እራሱ የፍቅር ግለትን ጠብቆ ለማስቀጠል ትልቅ ጥቅም አለው፡፡››
‹‹እና ከፍቅረኛሽ ጋር ተሳሳሚ እያልከኝ ነው››
‹‹ፍቅረኛው ካለ አዎ በደንብ..ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሚስቶች በጋብቻ ውስጥ ከከራረሙ በኃላ ለመሳሳም ያላቸው ፍላጎትና ትኩረት በጣም ይቀንሳል ወይም እስከወዲያኛው ይጠፋል።ላጤዎች ደግሞ ብዙውን ጊዜ በዚህ ረገድ ትኩስና ያልተገደበ ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡ይሄ ግን አግባብ አይደለም ።ባልዬው ድንገት ውጭ ሌላ ላጤ ሴት ቢያጋጥመው ከኤክስፐርት ጋር ነው የሚላተመው...ልዩነቱ ሰፊ ስለሚሆንበት ይከብደዋል።ቶሎ ስህተቱን ለማረም እንዳይችል ይፈተናል።››
‹‹እኔ ግን ሳገባ እንደዛ አላደርግም…ለባሌ በጣም የምመቸው ይመስለኛል›››
‹‹እያስጎመዠሺኝ ነው››
‹‹ምን ያስጎመዠሀል ..አንተን አላገባ?››

‹‹ምን ይታወቃል….ካፈቀርሺኝ ለምን አታገቢኝም?››
‹‹ሳላውቅህ እንዴት ላፈቅርህ እችላለው?››
‹‹ከዚህ በላይ እንዴት ታውቂኛለሽ..ለወራት ድምፄን በስልክ ስትሰሚ ነበር…በቀደም ደግሞ በአካል አይተሸኛል…ምነው አላምርም እንዴ?››
‹‹አረ ቆንጆ ነህ…ግን ቁንጅና ብቻ በቂ አይደለም››
‹‹እስኪ እናያለን››
‹‹ለማንኛውም ለባልሽ መዋብ የምትጀምሪው ከእርቃን ገላሽ ጀምሮ መሆን አለበት...ፓንትሽንና ጡት ማሲያዛሽን የሚያየው ባልሽ ነው።...ለእነሱ ትኩረት መስጠት መቻል በባልሽ እና በአንቺ የፍቅር ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይፈጥራል።ከላይ ያሉ ልብሶችሽን፣ ፀጉርሽን ፣ጌጣ ጌጦችሽን ለሁሉም ሰው በጋራ የምታደርጊያቸው መዋቢያዎች ናቸው።የውስጥ ልብሶችሽ ጥራት ግን የባልሽ ስሜት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንደሚኖራቸው ግንዛቤ ሊኖርሽ ይገባል፡፡››
‹‹ገባኝ››

‹‹አይ ስለአንቺ እኮ አይደለም ያወራውት አጠቃላይ ስለፍቅር እና ፍቅረኛሞች ለማውራት ፈልጌ ነው…ባልሽ በአጋጣሚ የሚያገኛቸው እንግዳ ሴቶች ድንገት ፊቱ ልብሳቸውን የማውለቅ እድል ካገኙ እመኚኝ የውስጥ ልብሶቻቸው ብቻ አይደሉም ውብና አማላይ የሚሆነው.. ለሊቱንም ውብና አማላይ እና ያልተለመደ አይነት ያደርጉለታል።አንቺ ሚስቱ ነሽና ብዙ ኃላፊነትና የህይወት ውጣ ውረዶች ስላለብሽ የአመቱን ቀናቶች ሁሉ ውብና አማላይ ልታደርጊለት አትቺይም ግን በሳምንት አንድ ቀን ካልሆነም በወር አንድ ቀን መቼም ሊረሳው የማይችል እንደዛ አይነት ውብ ለሊቶችን በገፀ-በረከትነት ልታቀርቢለት ይገባል።የዛኔ ከውጭ፣በአጋጣሚ የሚፈቱኑትን በልበ ሙሉነት ሊያልፋቸው አቅም ይኖረዋል።››
‹‹ይገርማል …ምንም ሳልከፍልህ በነፃ የቅድመ ጋብቻ ስልጠና እየሰጠኸኝ ነው፡፡››
‹‹ያው ማወቅሽ ዞሮ ዞሮ ጥቅሙ ለእኔው ነው ብዬ ነው››
‹‹እንዴት ማለት?››
‹‹ነገርኩሽ እኮ…ምን አልባት እድለኛው ባልተቤትሽ እኔው ልሆን እችላለሁ››

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

21 Nov, 11:44


⚡️ፊልም በነፃ ለማግኘት⚡️ ሶደሬ Tube 😍
ዝምብላቹ #Download ለማረግ 😍

Join😀 👇

አትሮኖስ

21 Nov, 11:38


ት/ት ሚኒስቴር ድንገተኛ መግለጫ አወጣ ‼️
በመግለጫውም ስለ ዘንድሮ remedial እና 12ኛ ክፍሎች አዲስ መረጃ.....  Continue

አትሮኖስ

20 Nov, 18:00


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በማግስቱ የናፈቀው ቢሮ የገባው አራት ሰዓት አካባቢ ነበር….የማታው ስካር አንጎበሩ ሙሉ በሙሉ አለቀቀውም…አሁንም ጭንቅላቱን እየወቀረው ነው፡፡ለፀሀፊው መምጣቱን
ስላልነገራት አልገባችም…ከፍቶ ገባና ቁጭ አለ ..የሚሰራው ስራ ስላልነበረ የሚያደርገው ነገር ግራ ገባው..ስልክ አውጥቶ ደወለ፡፡
‹‹እንዴት ነሽ…ለሊሴ?››
‹‹ደህና ነኝ ሰለሞን…እንዴት ነው ስራ?››
‹‹አሪፍ ነው..አሁን ተመልሼለሁ…ቢሮ ነው ያለሁት››
‹‹ውይ ለምን ሳትነግረኝ..ቀድሜ ገብቼ አፀዳድቼ ጠብቅህ ነበረ እኮ››
‹‹አይ ችግር የለውም..ቢሮው አሁንም ንፅና የተስተካከለ ነው››
‹‹አዎ እሱማ በሶስት ቀን አንዴ ከፍቼ አናፍሰዋለው….እና ስራህን ጨረስክ ማለት ነው?››
‹‹አይ አልጨረስኩም…በመሀል የሶስት ቀን እረፍት ስላለኝ ነው የመጣሁት…ለመሆኑ ያንቺ ነገር እንዴት ሆነ?››
‹‹የቱ?››
‹‹የሁለቱ ፍቅረኞችሽ ነገር?››
ለሊሴ ሰለሞን ባቀረበላት ሀሳብ መሰረት ከሁለት ፍቅረኞቾ መካከል አንዱን ለባልነት ለመምረጥ ምታደርገውን ጥረት ወዲያው ነበር የጀመረችው ….መጀመሪያ ነጋዴውን ለአንድ ወር ላታገኘው እንደማትችል ነግራ ከመንግስት ሰራተኛው ጋር ነበር የቀጠለችው..ሲደውልላት ትሄዳለች..ዝም ሲላት ትደውልለታልች….ከስራ መልስ ሳታገኘው ወደቤት አትገባም…እሁድ ቢያንስ ግማሹን ሰዓት ከእሱ ጋር ነች፡፡ይበልጥ ትኩረቷን ሰብስባ ከእሱ ጋር ባሳለፈች መጠን በፊት ከምታውቀው በላይ እያወቀችው …በፊት ከምታዳምጠው በላይ እያዳመጠችው መጣች፡፡አሁን ያለበትን የኑሮ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ..

የወደፊት እቅዶቹንና እነዛን እቅዶች ለማሳካት እያደረገ ያለውን ተጋድሎም እየተረዳችና እየተገነዘበች መጣች…..እሱ ላይ ያላት ቅሬታ ባገባው እኔን አኑሮ ቤተሰቦቼንም እንድረዳ የሚያበቃኝ ህይወት ሊሰጠኝ አይችልም የሚል ነበር…አሁን ስታስበው ግን ያንን ከእሱ ብቻ መጠበቅ እንደሌለባት ነው የገባት…እሱ ባለው ቁርጠኝነት ላይ እሷ ተጨምራበት ካገዘችውና ከጎኑ ሆና አብራው ከታገለች ጎዶሎው ሊሞላ የሚችል አይነት እንደሆነ ተረድታለች…ግን ውሳኔ ላይ ከመድረሷ በፊት ለእሱ የመደበችለት ወር ተገባደደ እና ለዛኛው የሰጠችውን ተመሳሳይ ምክንያት ሰጥታ ..ለአንድ ወር ያህል ልትደውልለትም ሆነ ልታገኘው እንደማትችል ነገራ ወደነጋዴው ሄደች፡፡
በእውነት ነገዴው ጋር ልክ እንደወትሮ ሁሉ ነገር ተሰርቶ ያለቀ ሆኖ ነው የጠበቃት…ቤቱ የተዘጋጀ..እቃዎቹ የተደራጁ ናቸው…አዎ እያንዳንዱን ሀብቱንና አኗኗሩን ተራ በተራ አሳያት፣ቀጥታ እንዳገባችው ሕይወቷን ወደመስራት ሳይሆን የተሰራ ህይወት ውስጥ ገብቶ ለመኖር መሞከር ብቻ እንደሚጠበቅባት ተረዳች ፣ግን ለምን ልቧ ወደኃላ እንደሚጎትታት ግልፅ ሊሆንላት አልቻለም‹‹…ታግዬ ያላሸነፉኩት በሌላ እጅ የተሰራ ህይወት ምን ትርጉም ይኖረዋል?››እራሷን ጠየቀች… መልሱ ቀላል አልነበረም….፡፡
ሁሉንም ሂደት አንድ በአንድ ዘርዝራ አስረዳችው፡፡ ሰለሞንም‹‹እና ምን ተሰማሽ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አሁንም እንደተወዛገብኩ ነው…ግን በአእምሮዬ ውስጥ የሚመላለሱ ጥያቄዎች በፊት ከሚመላለሱት የተለዩ ናቸው…እንግዲህ እኔ በህይወቴ ጠንከር ያሉ ውሳኔዎችን የማስተላለፍ ከፍተኛ ድክመት እንደለብኝ ነው የተረዳሁት፡፡››
‹‹አይ እንደዛ አይመስለኝም …አንቺ ቀሪ ህይወትሽን አብሮሽ በደስታ የሚዘልቅና ከቤተሰቦችሽም ጋ ተሰስማምቶ የሚያኮራሽ ለፍፅምነት የተጠጋ ባል እየፈለግሽ ነው….በዚህ ምድር ላይ ደግሞ ለፍጽምና የተጠጋ ነገር መምረጥ ቀላል ነገር አይደለም፡፡አንድ ታሪክ ልንገርሽ..
‹‹ደስ ይለኛል››
ደቀ መዝሙሩ  መምህሩን ‹‹ፍፁምና በህይወታችን እንዴት አድርገን ነው ፍፅማዊ የሆነ ነገር መጎናፀፍ የምንችለው? ሲል ጠየቀው ፡፡ መምህሩም አሰብ አደረገና ‹‹የዚህን መልስ

እንድነግርህ ከፈለክ በፊት ለፊት በር ወደ ግቢው የአትክልት ስፍራ ቀጥ ብለህ ግባ ።በመንገድህ ከምታገኛቸው አበቦች መካከል በጣም የሚያምረውንና ደስ ያሰኘህን ቀንጥስና በጎሮ በር ውጣ …አንዴ ያለፍከውን አበባ ከእንደገና ወደኃላ ተመልሰህ መቅጠፍ አትችልም አሉት።›› አለው ።እሱም ትዕዛዙን አክብሮ እንዳተባለው ወደ አትክልቱ ስፍራ ገባና እስከመጨረሻው ጥግ ከተጓዘ በኃላ ባዶ እጅን በጓሮ በር ወጣ።
መምህሩ ‹‹ለምንድነው አንድ ቀንበጥ አበባ እንኳን ይዘህ መውጣት ያልቻልከው?››ሲሉ ጠየቁት፡፡
‹‹ምርጥ የተባለውን አበባ ወዲያው እንደገባሁ ነበረ ያገኘሁት... ግን የተሻለ አገኛለሁ ብዬ በማሰብ ሳልቀነጥስ ወደፊት ቀጠልኩ .. መጨረሻው ላይም ደረስኩ.. ወደኃላ የመመለስ እድል ስለሌለኝ ባዶዬን ለመውጣት ተገደድኩ›› ሲል መለሰ።
መምህሩ መልሱን ሲሰሙ ፈገግ አሉና ‹‹አዎ! ትክክል ነህ ፤ህይወት እንደዛ ነው ።ፍፁምናን ለማግኘት ይበልጥ በዳከርን ቁጥር ብኩን እየሆንክ ትሄዳለህ።እውነተኛ ፍፁምናን መቼም የትም አታገኝም።››ሲሉ መለሱለት። ‹‹ገባሽ አይደል?››
‹‹አዎ ገብቶኛል››
‹‹እንግዲያው ፍፅም በምናብ አለም ካስቀመጥሽው ወንድ ጋር የሚስማማ ባል እንደማታገኚ አውቀሽ ለሚማጡት 10 ቀናት ሁለቱንም ሳታገኚ አስቢበት..ከዛ ማንኛቸው ናቸው የበለጠ የሚናፍቁሽ..የትኛው ቢያቅፍሽ ትፈልጊያለሽ ….?ማንኛቸው የልጆችሽ አባት ቢሆኑ ይሻላል..?በህልምሽ እየደጋገመ የሚመጣው የትኛው ነው?፡፡ለ10 ቀን አስቢበት፡፡››
‹‹እሺ እንደዛ አደርገላው..ግን አሁን አሁን እየገባኝ ያለው እኔ ከባሌ ምን እጠብቃለው ብቻ ሳይሆን ለባሌስ ምን ይዤለት ሄዳለው…?የሚለውን በጥልቀት ማሰብና መዘጋጀት እንዳለብኝ ነው፡፡ ››
‹‹ጎበዝ ነሽ…ይሄ ትልቅ መረዳት ነው..በይ ደህና እደሪ››
‹‹ውይ …ከመዝጋትህ በፊት…ድፍረት አይሁንብኝና ዛሬ ቤት ለምን አትመጣም››
‹‹ለምን?››
‹‹እማዬ የማሪያም ድግስ አለባት….ማህበርተኞቹ እስከ10 ሰዓት ነው የሚቆዩት 11 ሰዓት ብትመጣ በጣም ደስ ይለኝ ነበር…››
‹‹አረ ተይ››
‹‹ምን አለበት…ቤተሰቦቼ በጣም ነው ደስ የሚላቸው››
‹‹11 ሰዓት ነው ያልሽኝ?፡፡››
‹‹አዎ 11 ሰዓት››
ብቻውን ሆኖ ስለአስቴር እያሰበ ከሚሰቃይ ከሰው ጋር ተቀላቅሎ የባጥ የቆጡን እያወራ ሊረሳት ቢሞክር እንደሚሻለው አሰበእና ‹‹በቃ እሺ መጣለሁ››አላት፡፡
‹‹በቃ አቃቂ ፖሊስ ጣቢያው ጋር ስትደርስ ደውልልኝ..ወጥቼ እቀበልሀለው››
‹‹እሺ ደውላለው››
ስልኩን ዘጋው፡፡ እሺ ማለቱን ፍጽም አላመነም….ጠበል ለመቅመስ ከሜክሲኮ
አቃቂ….ለመሆኑ በህይወቱ ጠበል የተጠራውና ጥሪውን አክብሮ የሄደው መቼ ነው..?ፍጽም አያስታውስም….
እንዳለችው …..እንደደወለላት ደቂቃ ሳታባክን ነው ወጥታ የተቀበለችው….መኪናውን
እዛው አስፓልት ዳር ፓርክ አደረገና ተከትሏት ይዛው ሄደችው.. ግን ወደሚያስደነግጥ ቦታ ነው ይዛው የሄደችው…ይሄንን ግቢ ትናንትና በዚህን ሰዓት መኪና ውስጥ ሆኖ ከአሰሪዎቹ ጋር በመሆን ሲሰልለው ነበር …‹‹ምን አይነት መገጣጠም ነው?››ለለሊሴ ምንም አይነት የመደነቅና የመገረም ስሜት ሳያሳያት ተከተላት፡፡አሁን ነገሮችን ገጣጥሞ ሲያስብ በፀሎት እሱን እንዴት እንዳገኘችውና ስልኩን ከማን እንደወሰደች ተገለፀለት፡፡

አትሮኖስ

20 Nov, 18:00


ለሊሴ ግቢው ውስጥ ይዛው ገባችና መጀመሪያ ከአባቷ ጋር ከዛ ከወንድሞ ጋር አስተዋወቀችውና ይዛው ወደ ሌላ ክፍል ውስጥ ይዛው ገባች…ክፍሉ አዲስ የተሰራ መሆኑን ያስታውቃል….ጥግ ላይ በስርአት የተነጠፈ አንድ አልጋ ..ከዛ ሁለት ወንበር እና አነስተኛ ጠረጴዛ ይታያል..ጠረጴዛ ላይ ሁለት ነጭ ሻማ ተለኩሶ እየበራ ነው…የቤቱ ወለል ሙሉ በሙሉ ቄጤማ ተጎዝጉዞ አውዳአመት መስሏል…አልጋው ጠርዝ ላይ አንድ ወጣት ተቀምጣለች …ከዛ ውጭ ቤቱ ባዶ ነው፡፡
በፀሎት‹‹ግባ ዝለቅ…. ››የሚል ድምጽ ስትሰማ ካቀረቀረችበት ቀና አለችና ግባ እየተባለ ያለው ሰው ላይ አፈጠጠች…ጠይም ነው…ባለደማቅ ጥቁር ፀጉር…ቆንጆ ወንዳወንድ
ነው…ልክ እንደባንክ ቤት ስራአስኪያጅ ሽክ ብሎ ሰማያዊ ሱፍ ለብሶል..ሰማያዊ ሱፍ በነጭ ሸሚዝ…ከረባት አላሰረም….በቅፅበት ውስጥ ነው ሙሉ ቁመናው ውስጧ ስምጥ ብሎ የገባው፡፡ስሯ ደርሶ ሲቆም ከተቀመጠችበት ተነሳች…..‹‹ተዋወቂው ሀለቃዬ ነው….እሷ ደግሞ እህቴ ነች››
‹‹ሰለሞን እባላለሁ››ብሎ እጁን በትህትና ዘረጋላት፡፡
በደመነፍስ እጇን ዘረጋችለት..ጨበጣትና እየወዘወዛት ስሟን እስክትነግረው ይጠብቅ ጀመር…..ምን ብላ ትንገረው….ለእሷ በዛሬው ቀን ይሄ ሰው ያለችበት ቦታ ድረስ መጥቶ እጇን መጨበጥ የማታሰብ ነገር ነው….፡፡
‹‹ስምሽን ንገሪው እንጂ …?.›››
‹‹ስሜን የማን የእኔ..ማለቴ..››ተርበተበተች፡፡
‹‹ተዋትና ተቀመጥ ልጄ…..››እጇን ለቀቀና ወደመቀመጫው ሄዶ ተቀመጠ… ፡፡ ለሊሴ‹‹ተጫወቱ መጣው..››ብላ ወደ ዋናው ቤት ሄደች፡፡
‹‹ምነው ስምሽ ያስጠላል እንዴ?››ሲሌ ጠየቃት፡፡
‹‹እኔ እንጃ….ሰናይት እባላለሁ››
‹‹እና ሰናይት የሚለውን ስም ለመናገር ነው የተናነቀሽ?››
‹‹አይ …ሱፍ ለባሽ ክፍላችን ሰተት ብሎ ይገባል ብዬ ስላልጠበቅኩ ነው፡፡››
‹‹ቱታ ለብሼ መምጣት ነበረብኝ…?››
‹‹ለካ እንዲህ ነገረኛ ና አሽሟጣጭ ሰው ነው እንዴ? ››ስትል በውስጧ አሰበች…ዝም አለችው….. ወዲያው ለሊሴ እና እናቷ እንጀራና ወጡን ይዘው መጡ…እዛው የእጅ ውሀ አስታጠቡትና የሚበላ ቀረበለት…እንጀራውን ሲነሳ ደቦና ቆሎ ቀረበለት..ለእሱ ተብሎ የተገዛ ቢራ ተከፈተለት…..
‹‹እንዴ ቢራ እኔ ብቻ ነኝ እንዴ ምጠጣው…?››

‹‹ለጊዜው አዎ…አባዬ ትንሽ ቆይቶ መጥቶ ይቀላቀልሀል….እንግዶች ስለመጡ እማዬን ባግዛት ቅር ይልሀል..አልቆይም፡፡ ››
‹‹ሂጂ ችግር የለውም ..እህትሽ ታጫውተኛለች›› ለሊሴ‹‹ጥሩ ..በቃ መጣሁ››ብላ ወጣች
ሰለሞን ወደ በፀሎት ዞረና ‹‹አሁን ብቻችንን ቀርተናል….››አላት፡፡ ደንግጣ‹‹ ማለት?››
‹‹አትደንግጪ ሰኒ…ምን አስደነገጠሸ?››
‹‹አይ እሱማ ምን ያስደነግጠኛል…?አልደነገጥኩም…››እውነቱን ለመናገር ከመደንገጥም አልፋ ሰውነቷ በላብ እየተዘፈቀ ነው፡፡
‹‹አህቴ ስለአንተ ብዙ ነገር ነግራኛለች….››
‹‹እህትሽ ብቻ… እኔስ ብዙ ነገር ነግሬሽ የለ እንዴ?››
‹‹መቼ ..?የት ተገናኝተን….?››
መልስ ይመልስልኛል ብላ ስትጠብቅ ስልኩን አወጣና እያየችው ደወለ…ኪሷ ያለው ስልክ ተንጣረረ…አወጣችና አየችው…ምን እንደምትል እንዴት እደምታደርግ ግራ ገብቶት
አፍጥጣ እስክሪኑን እያየች ባለችበት ሰዓት ለሊሴ ከውጭ ገባች….ሰለሞን ስልኩን ዘጋው..የሚያንጣርረው የበፀሎት ስልክም ተቋረጠ…፡፡
‹‹በፀሎት ሀለቃዬን እንዳታስደብሪው››
‹‹አረ …የምን መደበር አመጣሽብኝ….እህትሽ ካንቺ በላይ ተጫዋች አይደለች እንዴ?››
‹‹እንግዲያው ጥሩ ..ቢራውን ጨምሪለት››ብለ ተመልሳ ወጥታ ሄደች፡፡
‹‹እሺ ጨምርለታለው››
መሄዷን ከረጋገጠች በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀና ብላ በትኩረት አየችው‹‹ምነው ቆንጆ ነኝ?››

‹‹በጣጣጣ…..ም››
‹‹አንቺም ልክ እንደጠበኩሽ ነሽ…ግን እንዳትታወቂ ነው የተሸፋፈንሽው….››
ቀስ ብላ ሻርፕን ከፊቷ አነሳችና አሳየችው…..ደነገጠ….ወዲያው በፍጥነት መልሳ አሰረችው፡፡
‹‹ምን ተፈጥሮ ነው?››
‹‹የጠፋው ቀን በሞተር ነበር ከቤት የወጣሁት..እና ይዚህን ጊቢ አጥር ጥሼ ከበሩ ጋር ተላትሜ ነው የቆምኩት….እግሬ ሁሉ ተሰብሮ ነበር…አሁን ግን ድኛለሁ››
‹‹ይሄንን እንዴት እስከዛሬ ሳትነግሪኝ?››
‹‹ለምን ነግርሀለው..?ምን እንድታደርግልኝ?››
‹‹ምን ባላደርግልሽስ….እኔ ላንቺ አንደዚህ ነኝ?››
‹‹እንዴት ነህ?››
‹‹ትናት ማታ እንደዛ ዳባሪ ስሜት ላይ ሆኜ ለማን ደወልኩ ?ላንቺ አይደል?››
‹‹በነገራችን ላይ በጣም ስታሳስበኝ ነበር…ለሊቱን ሙሉ ስላአንተ እየተጨነኩነው ያሳለፍኩት…..እንደማይህ ግን እንደማንኛውም ወንድ ወዲያው ማገገምና ወደተመደ እንቅስቃሴ መግባት ችልሀል፡፡››
‹‹ምን ጠብቀሽ ነበር…?ዛሬም አልጋዬ ላይ ተኮራምቼ እንዳለቅስ?››
‹‹አዎ.. እኛ ሴቶች ብንሆን እንደዛ ነው የምናደርገው››
‹‹ይሁን…አሁን እንደተመለስኩ እንዳልሺኝ አደርጋለው….በነገራችን ላይ ይሄንን የመቁሰልሽን ዜና ወላጆችሽ ቢሰሙ በቃ ቁም ስቅሌና ነበር የሚያሳዩኝ…››
‹‹ቆይ እንዴት እኔ መሆኔን አወቅክ…..ማለት እንዳየሁህ እኮ ስሜን ቀይሬ የነገርኩህ ማንነቴን የምትለይበት ምንም መንገድ እንደሌለ እርግጣኛ ሆኜ ነበር፡፡››
‹‹እንግዲህ ይሄን ያህል ነው የማውቅሽ….››
‹‹በጣም ነው ያስገረምከኝ››

‹‹ያው ሰውን ማስገረሙን ካንቺው ነው የኮረጅኩት››
‹‹እሺ..በመሀከላችን ስላለው ነገር ለሊሴ ምንም ማወቅ የለባትም››
‹‹እንዴ በመሀከላችን የሆነ ነገር አለ እንዴ?››
‹‹አትቀልድ››
‹‹እሺ እንዳልሽ››
‹‹በነገራችን ላይ ከለሊሴ ጋር ከነገ ወዲያ ወደወንጪ ልንሄድ ነው…የጋሼ ዘመዶች እዛ አሉ….እንዝናናለን፡፡››
‹‹ደስ ይላል..ያው እኔም ከተውሻቸው ወላጆችሽ ጋር የሆነ ቦታ ሄጄ ዘና እላለው…ሳስበው አንቺ እዚህ ስለተመቸሽ አነሱን ለእኔ ብትሰጪኝ ደስ ይለኛል፡፡;;
‹‹ውሰዳቸው››
‹‹ተይ በኃላ..እንደድሮ እንዳይመስሉሽ…ፍቅር ሲያገረሽ አደገኛ መሆኑን ያየሁት በእነሱ ነው…ጎረምሳ በያቸው››
ለሊሴ አባቷን አስከትላ መምጣቷን ጫወታቸውን እንዲያቆርጡ አደረጋቸው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

20 Nov, 17:52


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሁለት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ _ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ባልና ሚስቶቹን ቤታቸው ወስዶ እንደጣላቸው ቀጥታ የመኪናውን መሪ ወደአስቴር ቢሮ ነው የጠመዘዘው…ገብቶ ምሳ እንዲበላ ቢለምኑት እንኳን እሺ አላለቸውም፡፡እንደሚመጣ አልነገራትም ቀጥታ ከቢሮዋ ፊት ለፊት አቆመና ደወለ ‹‹ሄሎ ወንድሜ….እንዴት ነው ቢሾፍቱ…»

አትሮኖስ

20 Nov, 17:29


‹‹አይ..ያ እውነት አይደለም…ቤተሰቦቼን ምን ያህል እንዳገዝካቸው እኔ ነኝ ማውቀው..አረ የእነሱን ተወውና እኔን እራሱ በስልክ ብቻ በምታወራኝ ምን ያህል ጥንካሬና ብርታት እንደምትሰጠኝ አታውቅም..ፈፅሞ በምንም ምክንያት ተስፋ መቁረጥ የለብህም..ደግሞ አንድ ግንኙነት አልተሳካምና ጠቅላላ ያንተ ህይወት አበቃለት ማለት አይደለም…አንዳንዱ ግንኙነቶች ምንም ቢለፋባቸውና ፍሬ አያፈሩም…ያንተም እንደዛ ሆኖ ይሆናል››
‹‹ይገርማል››
‹‹ምኑ ነው የሚገርመው?››
‹‹እኔ ሳልሆን አንቺ ነሽ የፍቅር አማካሪ መሆን የነበረብሽ››
‹‹እንግዲህ በችሎታዬ ከተማመንክ ስልጠና ሰጥተህ ወደፊት በረዳትነት ልትቀጥረኝ ትችላለህ››
‹‹ደስ ይለኝ ነበር…ደሞዝሽ ይከብደኛል እንጂ››
‹‹አይዞህ..አትፍራኝ …አንደራደራለን››
‹‹አመሰግናለሁ…አንቺ ጋር መደወሌ ምክንያታዊ ባይሆንም ..ግን ሰርቷል አግዘሺኛል፣አሁን ትንሽ ቀለል አለኝ፡፡››
‹‹አሁን መጠጣቱ ይብቃህ…ሻወር ወሰድና ተኛ…ጥዋት ስትነሳ ሁሉ ነገር ቀለል ብሎህ ታድራለህ››
‹‹እሺ….እንዳልሺኝ አደርጋለው….ደህና እደሪ››

‹‹ደህና እደር››ብላ ስልኩን ዘጋችው ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

20 Nov, 17:29


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ _ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧
ባልና ሚስቶቹን ቤታቸው ወስዶ እንደጣላቸው ቀጥታ የመኪናውን መሪ ወደአስቴር ቢሮ ነው የጠመዘዘው…ገብቶ ምሳ እንዲበላ ቢለምኑት እንኳን እሺ አላለቸውም፡፡እንደሚመጣ አልነገራትም ቀጥታ ከቢሮዋ ፊት ለፊት አቆመና ደወለ
‹‹ሄሎ ወንድሜ….እንዴት ነው ቢሾፍቱ በጣም ተመችታሀለች መሰለኝ?፡፡››
‹‹መጥቻለው….ምሳ አትጋብዢኝም?፡፡››
‹‹የእውነት መጣህ?››
‹‹አዎ ቢሮሽ ፊት ፊት መኪናዬን አቁሜያለው፡፡››
‹‹በቃ መጣሁ››ብላ ስልኩን ዘጋች….5 ደቂቃ ነው ያስጠበቀችው፡፡ገና የቢሮዋን የህንፃ ደረጃ ስትወርድ ጀምሮ ነው አይኑ ውስጥ የገባችው…ሙሉ ሮዝ ቀለም ያለው ጉረድ ቀሚስና ኮት ለብሳለች…ፀጉሯ ወደኃላዋ ትከሻዋ ላይ እንዲተኛ ተደርጎል…ውብ ሆናለች….መኪናዋን ስለምታውቃት ብዙም ሳትደነጋገር ቀጥታ ወደእሱ ነው ያመራችው…ይህቺ ሴት እህቱ እንድትሆን አይደለም የሚፈልገው…ጓደኛም እንድትሆነው አይደለም…የፍቅር አጋሩ ሚስቱ ሊያደርጋት ነው ምኞቱ..ይሄ ምኞቱ ደግሞ አሁን በቅርብ በውስጡ የበቀለ ስላልሆነ ህመሙ ቀላል አይደለም…ገና አፍ ፈቶ በኮልታፋ አንደበት መንተባተብ በጀመረበት በጮርቃነት እድሜው ጀመሮ እሷ ሚስቱ እንደሆነች ያስብ ነበር፣እርግጥ በዛን እድሜ ሚስት ማለት እራሱ ትርጉሙ ምን ማለት አንደሆነ አያውቅም ነበር፣ቢሆንም ጭላንጭል የሆነ ግንዛቤ ነበረው…ሚስት ማለት አንድ ክፍል ውስጥ አንድ አልጋ ላይ ሁሌ አብራ

የምትተኛ ሴት እንደሆነች ከአባትና ከእናቱ ግንኙነት መረዳት በቻለበት ጊዜ ነው፣ከእሱ ጋር ለዘላለም መተኛት ያለባት ሴት አስቴር እንደሆነች ወስኖ የነበረው፣በዛን የልጅነት ጊዜ እናቷ የቤታቸውን እንጀራ ልትጋግር ስትመጣ አስከትላት ስትመጣ ጀምሮ እዛው እሷን ማስቀረት ምኞቱ ነበር…እና ያ ምኞት ግለቱን ጠብቆ እየፋመ ነበር የቀጠለው…
ጊዜው ሲደርስ ግን ነገሮች ቀደም ብሎ እንዳሰባቸው ቀላል አልነበሩም…ገቢናውን ከፈተላት ገባች.. ጉንጩን አገላብጣ ሳመችው…ሁል ጊዜ የእሷ መሳም ከሌላው መሳም በጣም ይለይበታል…ወፈር ብሎ ወደፊት ግልብጥ ያለው ፍም ከንፈሯ ሰውነቱ ላይ ሲርፍ የተለየ ሙቀት ነው ሰውነቱ የሚያመነጨው…ልክ የጋለ ቢላዋ አካል ላይ ሲያርፍ የሚሰማው አይነት ትሽሽሽ..የሚል የማቃጠል የመለብለብና የመላጠ ስሜት……
‹‹አንተ ወፍረህ ነው የመጣሀው….ስራ ላይ ነበርክ ወይስ ጫጉላ ሽርሽር ላይ?››
‹‹በይው…አንቺም ተመችቶሻል…ምሳ የት አንብላ?››
‹‹ወደ እኔ ቤት ንዳው››
‹‹ምነው ከሰዓት ስራ የለሽም እንዴ?››
‹‹ዛሬ ቅዳሜ እኮ ነው…ግማሽ ቀን ነው የምንሰራው››
‹‹እና አራበሽም ..በልተን ብንሄድ አይሻልም?››
‹‹አይ ሰራተኛዬ አዘጋጅታ እየጠበቀችን ነው…ዘና ብለን ቤታችን ብንበላ ይሻላል….ወንድሜ ስለመጣህ ደስ ብሎኛል››
‹‹እኔም ከሰዓት ስራ ስለሌለሽ ደስ ብሎኛል››ብሎ መኪናዋን ወደ አስፓልት መሀል አስገባና ነዳት….የእውነትም ከሰዓት ስራ የለኝም ብላ ወደቤቷ ይዛው እየሄደች በመሆኑ ከፍተኛ ደስታ ተስምቶታል…ከአመታት በኃላ መልሶ ዛሬ እድሉን ይሞክራል፡፡አዎ በስደት ከሄደበት ባእድ ሀገር ተመልሶ የመጣውም ለዚሁ ነው፡፡ከባሎ እንደተለያየችና እሱም በዛ ንዴት ከሀገር ውጭ መሰደዱን ሲሰማ ነው ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ የመጣው…አንሆ ተመልሶ በመጣበት ባለፉት ስድስት ወሮች እሷን ከገባችበት ድባቴ እንድትወጣና ያልተሳካ ትዳሯ ከፈጠረባትን የስነልቦና መሰበር እንድታገግም እንደወንድም እንደ ጓደኛም ከዛም አልፎ እንደባለሞያም  ከጎኗ  ሆኖ  ሲያግዛትና  ሲደግፋት  ነበር…አሁን  ግን  ልቧ  ሌላ  ፍቅር

ለማስተናገድ ዝግጁ ነው ብሎ ያስባል..በዛ ላይ የእሱ እና የእሷ ፍቅር አዲስ ዛሬ የበቀላ ሳይሆን ድሮ በየሁለቱም ልብ ተዳፍኖ ያለ ነው…አሁን ያንን መቆስቆስና መልሶ እንዲቀጣጠል ትንሽ የፍቅር ቤንዚል ማርከፍከፍ ነው…ለዚህ ድርጊት ያበረታታው ሰሞኑን ያየው በአቶ ሃይለልኡል እና በወ.ሮ ስንዱ መካከል የተከሰተው የፍቅር ግርሻ ነው፡፡
‹‹አዎ…አስቴርን አገባታለሁ…ከበፊት ባሏ የወለደችውን አንድ ልጅም እንደልጄ አድርጌ አሳድገዋለው››በውስጡ አልጎመጎመ…‹‹እና በቅርብ ቀን እሷም ወንድሜ የምትለውን ጥሪ ትተውና ባሌ ብላ ትጠራኛለች…ልጇም አጎቴ ብሎ የሚጠራውን አቁሞ አባቴ እንዲለኝ
አደርጋለው››ይሄንን ስላሰበ ብቻ ውስጡ በደስታ ተፍነከነከ..ቤት ሲደርሱ እውነትም እንዳለችው ቆንጆ ምሳ ተዘጋጅቶ ነበር የጠበቃቸው፡፡እየተጎራረሱ በሉ፡፡ከምግብ በኃላ ብና ተፈላላቸው..እሷ ሁለት ሲኒ እሱ አንድ ሲና ጠጡና ተጠናቀቀ፡፡
‹‹እዚሁ ልንገራት ወይስ ይዣት ወጣ ልበልና ዘና ያለ ቦታ ወስጄ ዘና ባለ ስሜት ላይ ከሆነች በኃላ ልንገራት ››እያለ ሲወዛገብ ቆየና‹‹እ…ፕሮግራማችን እንዴት ነው….?ወጣ እንበል ወይስ እዚሁ ነው የምንቆየው?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹አይ…ወጣ እንላለን..ሱፐርማርኬት ወጥቼ መሸማመት አለብኝ..መጠነኛ ድግስ ደግሳለው፣ማታ እንግዳ አለብኝ››
ንግግሯ ግራ አጋባውም.. ደነገጠም፡፡
‹‹የማታ እንግዳ ምን አይነት ነው?›› our
‹‹አንተም አለህበት…ዛሬ እዚህ ነው አይደል የምታድረው?››
እሷ ጋር እንዲያድር ስለጠየቀችው ደስ ብሏታል ..ግን እንግዳውስ…?ለመሆኑ ማን ነው
…?ሴት ነው ወንድ?፡፡‹‹እሺ ..እዚህ ነው የማድረው…ግን እንግዳውስ?››
‹‹እንግዲህ እሱን ከመጣ በኃላ ነው የምናውቀው…ልደር ካለ ግን እምቢ ማደር አትችልም የምለው አይነት ሰው አይደለም››በማለት ግራ አጋቢ መልስ ሰጠችው፡፡መልሷ ይብልጥ ቁርጠት ለቀቀበት…ይሄኔ ከመስሪያ ቤቷ ባለደረቦች አንዱ ነው….ሀለቃዋ ይሆን እንዴ…?ቢሆንስ ልደር ስላለ እንዴት እሺ ልትለው ትችላለች..?››ወይ ሴቶች ምን አይነት ቅኔ የሆኑ ፍጡሮች እንደሆኑ ሁሌ እንደደነቀው ነው፡፡ወንድም ሴትም በአንድ ላይ ሰው ተብሎ

መፈረጁ  አግባብ  አይደለም….አስተሳሰባችን  እምነትና  ፍላጎታችን  ምኑም  እኮ አይገናኝም››ሲል በውስጡ አብሰለሰለና..ነገሮች እስኪደርሱ ጠብቆ ለማየት ወሰነ…
‹‹ከዛ በፊ የተመቻቸ ጊዜ ካገኘው ነግራታለሁ…እንደውም ከማታው ፕሮግራሞ በፊት የእኔን ሀሳብ መስማት አለባት››የሚል ድምዳሜ ላይ ደረሰ‹‹በቃ እንሂዳ››አላት፡፡
‹‹እሺ፣ተነስ ብላ ቦርሳዋን አንጠለጠለችና ተነሳች..ተያይዘው ወጡ ..ያለችው ሱፐር ማርኬት ይዛው ከገባች በኃላ ምትፈልገውን ነገሮች ሁሉ ተገዝተው በመኪናው ከተጫኑ በኃላ.. ማኪያቶ እንጠጣ ብሎ አንድ ፀጥተኛ ካፌ ይዞት ገባና..ፊት ለፊት እንደተቀመጡ እንደምንም እራሱን አጠንክሮ ወደነጥብ መንደርደር ጀመረ
‹‹ለምን ወደውጭ እንደሄድኩ ታውቂያለሽ አይደል?››
‹‹ሁለተኛ ዲግሪህን ለመማር ነዋ››
‹‹አይ ያማ ሽፋን ነው….እውነተኛ ምክንያቴን አንቺም በደንብ ታውቂዋለሽ..ወደውጭ የሄድኩት ባንቺ ተበሳጭቼ ነው፡፡››
‹‹አንተን ለማበሳጨት ብዬ ግን ምንም ያደረኩት ነገር የለም››
‹‹እሱን ማግባት አልነበረብሽም››
‹‹ለምን …ታዲያ አንተን ወንድሜን ማግባት ነበረብኝ?››
‹‹ምን ችግር አለው?እርግጥ እንደወንድምና እህት አንድቤት አድገናል..ግን የስጋ ትስስር አልነበረንም››

አትሮኖስ

20 Nov, 17:29


‹‹‹አይ ይሄ ለነገሮች ያለን ትርጉም ልዩነት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡እኔ ወላጅ አልባ ብቻ ሳልሆን ዘመድ አልባ በሆንኩበት በዛ ጨለማ ጊዜ እናትና አባትህ ያለምንም ማቅማማት ወደቤታቸው ወስደው ከዛሬ ጀመሮ አንቺም ሌለኛዋ ልጃችን ነሽ አሉኝ፡፡እውነትም እንዳሉት ለእህትህ ስህን የሚደረገው ሁሉ ለእኔም ይደረግልኝ ነበር..ለእሷ ቀሚስ ሲገዛ ለእኔም ዘለውኝ አያውቁም.. ከፓንት አቅም ለእሷ የተገዛው አይነት ለእኔም ይገዛልኝ ነበር… የእውነት ልጃቸው ነበርኩ..ዩኒቨርሲቲ ገብቼ አንድም ወር የኪስ ገንዘብ ለእኔ ከመላክ እረስተውና ዘለውኝ አያውቁም…እና ሁለቱም ሲሞቱ ከእናንተ እኩል ነው ያጣዋቸው…..አንተ የምትወዳቸውን ያህል እኔም ወዳቸዋለው…አሁን የሚናፍቁህን ያህል

እኔንም ይናፍቁኛል..እና እኔ የእውነትም አንተም ወንድሜ እነሱም ወላጆቼ እንደሆኑ ነው የማምነው..ይሄንን እምነቴን ማንም በየትኛውም ሎጂክ ተከራክሮ ሊያስቀይረኝ አይችልም…እምነት ያው ከቃሉም እንደምትረዳው ዝምብለህ ነገሩን በቀና ልብ መቀበል አይደል..እኔም እንደዛው ተቀብዬዋለው…፡፡አሁን እንተ የደም ትስስር የለንም ምናምን ብትለኝ.በአንዱ ጆሮዬ ገብቶ በአንድ ይፈሳል እንጂ በእኔ ስሜት ላይ ምንም የሚያመጣው ለውጥ የለም…አንተ እንደፈለከው ማመን ትችላለህ…እህቴ አይደለሽም ልትለኝም ትችላለህ…በግድ ላሳምንህ አልችልም..፡፡››
‹‹ይገርማል… ልጅ እያለንም ጭምር እንዲህ ነገሮችን ውስብስብ ማድረግ ትወጂ ነበር…እሺ አሁን ለምን ተመልሼ እንደመጣሁ ታውቂያለሽ?››
‹‹ያው የሰው ሀገር አይደል ..ደብሮህ ነዋ››
‹‹አይ አይደለም….ከመስፍን ጋር እንደተፋታችሁ ስሰማና ፣አገር ለቆ እንደሄደ ሳረጋግጥ…ዳግመኛ እድሌን ለመመከር ነው..ምን አልባት አሁን እነአባዬና እማዬ በህይወት ስለሌሉ እሺ ብለሽ ፍቅሬን ትቀበይዋለሽ..እኔንም ከቁም ሞት ቀስቅሰሽ ታድኚኛለሽ..ባል አድርገሽ ታገቢኛለሽ ብዬ ነው››
ዝም ብላ በፍዘት ታየው ጀመር…ቡዝዝ ባሉት አይኖቾ እንባ ሞላባቸው…
‹‹ወንድሜ እኔ በጣም ነው የምወድህ..ያንተ ከጎኔ መሆን የሚፈጥርልኝ ጥንካሬና የመንፈስ ከፍታ ልትገምተው አትችልም…አንተ የራስህን ሰው አግኝተህ አፍቅረህና አግብተህ እዚሁ
አጠገቤ አዲስአበባ እንድትኖር ነው የምፈልገው…እባክህ ወንድሜ መልሰህ ጥለሀኝ አትሂድ
..ዳግመኛ እሰደዳለሁ ካልከኝ..በጣም ነው የማዝነው..እራሴንም መቼም ይቅር አልለውም››
‹‹የምታወራው ምንም ሊገባው አልቻለም..እሱ የሚያወራው እሷን ስለማግባት እና አብሮ አንድ ቤት ስለመኖር…እሷ የምታወራው ስለእሱ ዳግመኛ መሰደድ…‹‹ድንገት ሳላውቅ ተመልሼ ሄዳለው ብያት ይሆን እንዴ ?››ሲል እራሱን ተጠራጠረ፡፡
‹‹ኪያ ምን ነካሽ…?ተመልሼ ሔዳለው ብዬሻለው…እንዴ..?››
‹‹አላልከኝም…ግን ወንድሜ በወላጆቻችን አጥንት ይዤሀለው፣ምንም ቢፈጠር ምንም ጥለኸኝ እንደማትሄድ ቃል ግባልኝ››

‹‹እሺ..እንዳልሽ ቃል ገባልሻለው…ምንም ቢፈጠር ምንም ተመልሼ በድጋሚ አልሰደድም፡፡››
‹‹ጥሩ….ማታ የምቀበለው እንግዳ መስፍን ነው››
የቤተሰቦቹን ሞት የሰማ ቀን እንኳን እንዲህ አልደነገጠም‹‹ምን ..?መስፍን….?ከየት…ወጭ አይደል እንዴ?››
‹‹አዎ..ለአለፉት ሁለት ሶስት ወራት ስንደዋወል ነበር..ችግሮቻችን ተነጋገርን ለመፍታት እና የተበላሸውን ግንኙነታንን ለማስተካከል ወስነን አሁን እየመጣ ነው…ዛሬ ሁለት ሰዓት ነው የሚገባው..ቀጥታ ከቦሌ እኔ ነኝ የምቀበለው..እየመጣ መሆኑን ቤተሰቦቹም አያውቁ..ማለቴ ከቦሌ ቀጥታ ወደቤት ነው ይዤው የምመጣው..ልጅንም በጣም ናፍቆል..እና ተነጋግረን ችግሮቻችንን መቅረፍ ከቻልን ነገሮች ወደድሮ ቦታቸው ይመለሳሉ ማለት ነው..ያው ታውቃለህ የፍቺው ጉዳይ ገና ፕሮሰስ ላይ ነው…ያ ማለት አሁንም በህግ ፊት ባልና ሚስቶች ነን››
ድንዝዝ ባለ ስሜት ንግግሯን እስክትጨርስ ዝም ብሎ አዳመጣት…በፍጽም ፀጥታ ነው የተቀመጠው…ሰውነቱ አይንቀሳቀስም…የአይኖቹ ቅንድቦች እንኳን መንቀሳቀስ አቁመው ነበር፣ትንፋሹ መተንፈስም እንዳቆመ አይነት የመታፈን ስሜት እየተሰማው ነው…ንግግሯን ካጠናቀቀች በኃላም እሱ በዝምታው እንደቀጠለ ነው፡፡
ግራ ገባት…የሆነ ነገር እንዲል እየጠበቀችው ነው…እንዲወቅሳት..እንዲረግማት….በእሷ እንዲያማርር እየጠበቀች ነው..እሱ ግን እንደዛ እያደረገ አይደለም…አስፈሪ ዝምታ ላይ ነው፡፡
‹‹ወንድ….ሜ››
‹‹ሂሳብ ክፈይና እንሂድ››ብሎ መኪናውን ቁልፍ ከጠረጴዛ ላይ አነሳና ቀመ ..ወደመኪናው መራመድ ጀመረ…ከቦርሳዋ ብር አውጥታ ጠረጴዛ ላይ ወረወረችና ፈጠን ብላ ከኃላው ተከተለችው፡፡በህይወቱ እደዛሬው ባዶነትና ተስፋ ቢስነት ተሰምቶት አያውቅም..ፍፅም ተስፋ መቁረጥ ማለት ምን ማለት እንደሆነ የገባውም ዛሬ ነው..በቃ መቼም ይህቺን ሴት ማግባት እንደማይችል አምኖ ተቀበለ…ባያገባትም ግን መቼም ደግሞ ማፍቀሩን እንደማያቆም ያውቃል፡፡

እቤት አድርሷት ብዙም ሳይቆይ ነው ወደቤቱ ያመራው፡፡የሚኖረው ወላጀቹ ቤት ነው ሁሉም ወንድሞቹ የራሳቸውን ህይወት መስርተውና የገዛ ቤታቸውን ሰርተው ቤቱን የለቀቁት ገና ወላጆቹ በህይወት እያሉ ነው፡፡እህቱም ሀገር ውስጥ አትኖርም አሁን በብቸኝነት እየኖረበት ያለው እሱ ነው፡፡ወደቤት ሲገባ ሙሉ ጠርሙስ ጎርደን ጅን ይዞ ነበር የገባው….ገና በቀኑ ነው መኝታ ቤቱን ዘግቶ መጠጣት የጀመረው…
ማታ አንድ ሰዓት ሲሆን ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ ነበር‹‹ይሄን ያንን ጉረኛ ልትቀበለው ቦሌ አየር ማረፊያ ቆማ ብርድ እያንቀጠቀጣት ነው››አለ..አሳዘነችው…‹‹ለእሷ የምገባት እኔ ነበርኩ….››ማልቀስ አማረው..እዬዬ ብሎ ማልቀስ አማርው..ግን ማድረግ አልቻለም፡፡ስልኩን ከኪሱ አወጣና ‹‹ማውራት ከቻልሽ ደውይልኝ ››ብሎ ፃፈና ለከ..
ከ5 ደቂቃ በኃላ ተደወለለት‹‹ወይ እግዜር ይስጥሽ…አትደውይልኝም ብዬ ፈርቼ ነበር››
‹‹ምነው? ችግር አለ እንዴ…?ወላጆቼ ምን ሆኑ?››
‹‹‹እነሱ ሰላም ናቸው..በጣም ሰላም ናቸው…ዛሬ አዲስ አበባ ተመልሰናል..እነሱም እቤታቸው ናቸው….እኔ ግን…››ሲያወራ አፉ ይኮለታተፋል..
‹‹ምነው ?አንተ ምን ሆንክ?››
‹‹ተሰብሬለሁ…ሌላ ማወራው ሰው ስለሌለን ነው አንቺ ጋር የደወልኩት…አይገርምም ደህና ጓደኛ እንኳን የለኝም….ቢኖረኝም እንዲህ አይነት ነገር የምነግራቸው አይደሉም››
‹‹ወይኔ በፈጣሪ..እስኪ የሆንከውን ንገረኝ…?.››
‹‹በፀሎት…››
‹‹ወዬ››
‹‹አሁን ካለሽበት መጥተሸ አጠገቤ ብትሆኚና ብታጣጪኝ ደስ ይለኝ ነበር››
‹‹እኔም ደስ ይለኝ ነበር…እይዞህ አንተ ብዙ ነገር የምታውቅ ሰው አይደለህ..?››
‹‹ማወቅ ምን ይሰራል…በፍቅር ስትንኮታኮቺ እኮ ያንቺ ማወቅ እርባነ ቢስ ነው፡፡እኔ እንደውም ይሄንን የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ የሚባለውን ጫወታ መተው አለብኝ..አዎ ፍቃዴን መልሼ ቢሮዬን ዘጋለሁ…››

‹‹ለምን ..ያ ደግሞ ምን ማለት ነው?››
‹‹አይታይሽም እንዴ…ከልጅነቴ ጀምሮ ሳፈቅራት የኖርኳትን ሴት የሆነ ዘዴ ተጠቅሜ እንድታፈቅረኝና እሺ ብላኝ እንድታገባኝ ማድረግ ካልቻልኩ እንዴት ነው ሌላ ሰውን ማገዝ የምችለው…ይሄው ለሁለተኛ ጊዜ አጣኋት …ያሁን ማጣት ደግሞ ይግባኝ የሌለው ነው…እራሴንም ሰዎችንም እያጭበረበርኩ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ፡፡››

አትሮኖስ

18 Nov, 03:40


💰💵 በቤቲንግ መበላት ሰልችቷችኋል

እንግዲያውስ ይሄን ቻናል ተቀላቅላችሁ ትርፋማ ሁኑ ማየት ማመን ነው 🏆

አትሮኖስ

18 Nov, 03:33


የየትኛው ክለብ ደጋፊ ናችሁ የክለባቹሁን ቻናል በመምረጥ ተቀላቀሉ ⁉️

አትሮኖስ

17 Nov, 17:21


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) : : #ክፍል_ሀያ_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ተካ አቶ ኃይለልኡል ባዘዙት መሰረት ሽጉጡን ሙሉ ጥይት ሞልቶ ወገቡ ላይ ከሸጎጠ በኃላ አጉሊ መሳሪያ ያዘና  ማንን ሳያስከትል ቀጥታ መኪና ውስጥ ገብቶ ወደ ቃሊቲ ነዳው….የሰውዬውን ጥርጣሬ ምንም አልተዋጠለትም…‹‹ልጅቷ ስንት አማራጭ እያላት እንዴት እዛ…»

አትሮኖስ

17 Nov, 17:00


በድንጋጤ እርስ በርስ ተያዩ‹‹በእውነት እምቢ ብትለን ምንድነው የምናደርገው?›ወ.ሮ ስንዱ በተሰበረ ድምፅ ባላቸውን ጠየቁ፡፡
አቶ ኃይለልኡልም እጅ በሰጠ ድምፅ‹‹አንተ ምን ብናደርግ ትመክረናለህ?››ሲሉ እሱኑ መልሰው ጠየቁት፡፡
‹‹ይሄውላችሁ እንደእኔ እንደእኔ በፀሎት ወደቤት መመለስ ያለባት በእናንተ ላይ የነበራት ቅሬታ ሙሉ በሙሉ ተቀርፎ…ሁሉን ነገር በራሷ መንገድ አረጋግጣና ፈቅዳ…ደስ ብሎት ነው
…ይሄውላችሁ አሁን አብዛኛውን አስቸጋሪ የነበረውን መንገድ ተጉዛችኃላ …እስኪ አስቡት ከአስራአምስተ ቀን በፊት ወደቢሾፍቱ ስንሄድ አንድ መኪና ውስጥ መቀመጥ እራሱ የሚቀፋችሁ ሰዎች ነበራችሁ፣ትዝ ይላችኃላ ጋሼ ገቢና ነበር የተቀመጥከው…አሁንስ ይሄው በደስታ ጎን ለጎን በራሳችሁ ፍቃድ ተቀምጣችሁ እርስ በርስ ተጣብቃችሁ የደስታ ወሬ እያወራችሁ ትሳሳቃላችሁ..ከባዱ ነገር እናንተን እዚህ ስሜት ላይ ማድረስ ነበር…ከአሁን ወዲህ ያለው ይሄንን ግንኙነት መሰረት እንዲይዝና ስር እንዲሰድ ማድረግ ብቻ ነው… ያ ደግሞ ቀላል ነው…ቢያንስ 15 ቀን መታገስ ያቅታችኃላ….?፡፡››
‹‹እና ባለችበት ትቀመጥ እያልክ ነው…?ያለችበት ሁኔታ… እቤቱ የሰዎቹ ኑሮ ምኑም አይመቻትም እኮ…››
ከቀናት በፊት ስላለችበት ቤት ሲጠይቃት ያለችው ነገር ትዝ አለውና ፈገግ አለ፡፡

‹‹እውነቴን ነው..እርግጥ ሽማግሌው በጣም ጥሩና ደግ ሰው ናቸው….ቢሆንም ኑሮቸው ከእጅ ወደአፍ ነው..ልጄ ከቤት ስትወጣም ደህና ብር እንኳን ይዛ አልወጣችም››
‹‹አይዞችሁ እስከዛሬ ድምጻን አጥፍታ ኖረች ማለት በጣም ቢመቻት ነው….ደግሞ እንዳላችሁ ባይመቻትም ለ15 ቀን ምንም አትሆንም፡፡አለመመቸትን ማጣጣም በቀጣይ ለሚመጣ መመቸት መደላደል መፍጠር ነው፡፡››
‹‹እሺ ቢያንስ እንሄድና ከሩቅም ቢሆንም እንያት››
‹‹እንደእሱ ይቻላል››አላና ያጠፋውን የመኪና ሞተር አስነሳው፡፡
ሰለሞን መኪናውን ነዳና  ከተካ መኪናው ፊት ለፊት አቆመ….ተካ መኪናውን ከፊቷ ወጣን ወደእነሱ መጣ ..ሰለሞን የገቢናው በራፍ ከፈተለት ……ገባና ቁጭ አለ››
ወደኃላ ዞረና…..‹‹አሁንም ውስጥ ነች…እንዴት ነው ምናደረገው? ››
‹‹ቆይ እስኪ ተረጋጋ ስትወጣ እንያት….››ሁሉም አይናቸውን የግቢው መውጫ መግቢያ ላይ ተከሉ….በርከት ያሉ ሴቶች ሲወጡ ሲገቡ ይታያል፣››
‹‹ምንድነው ብዙ ሰዎች ይታያሉ… ችግር አለ እንዴ?››አቶ ኃይለ ልኡል ጠየቁ፡፡
‹‹አይ ጌታዬ ችግር የለም… እኔም በመጀመሪያ ግራ ገብቶኝ ነበር…ስጠይቅ ግን ፣ሰዎቹ ነገ የማሪያም ፅዋ ማህበር አለባቸው ..የድግሱ ስራ ለማገዝ የመጡ ጎራቤቶች ናቸው››
‹‹እ …እንደዛ ነው….››በፀሎት ወጥታ ከሩቅ ለማየት ከአንድ ሰዓት በላይ በትዕግስት መጠበቅ ነበረባቸው….ግቢ ውስጥ ካለ የማንጎ ዛፍ ስር ቆማ ከአቶ ለሜቻ ጋር እየተሳሳቀች ስታወራ ነበር የተመለከቱት…ሁለቱም ወላጆች ሄደው ልጃቸው ላይ ለመጠምጠም የሚተናነቃቸውን ስሜት በመከራ ነበር የተቆጠጠሩት፡፡ሁለቱም ስሜታዊ ሆነው እንባ አውጥተው እስከማልቀስ ደርሰው ነበር፡፡
‹‹አሁን በቃ ይበቃናል…ከዚህ በላይ እዚህ ከቆየን  ራሳችንን ማጋለጥ ይሆናል…ድንገት እዚህ እንዳለች እንደደረስንባት ካወቀች….ቦታ ለመቀየር ታስብና ዳግመኛ አድራሻዋን ትሰውርብን ይሆናል፡፡››ሰለሞን ነው የተናገረው፡፡
‹‹አዎ ትክክለ ነህ….እንዴት ነው ምናደርገው ታዲያ? እሱ እዚሁ ይጠብቃት አይደል…?››.

‹‹አይ ምንም ጠባቂ አያስፈልግም…ባይሆን በየቀኑ እየመጣ ለተወሰነ ደቂቃ ሰላም መሆኗን ብቻ ካረጋገጠ ይበቃል፣አሁን ሁላችንም ነን አካባቢውን መልቀቅ ያለብን፡፡››ሰለሞን ቁርጥ ያለ ውሳኔውን አስተላለፈ…የተቃወመው ወይም የተከራከረው አልነበረም፡፡
‹‹እሺ ይሁን …..በቃ ተካ አንተም ወደቤትህ ሄደህ እረፍ …ነገ ደውልልሀለው››ብለው አሰናበቱት…‹‹እሺ ጌታዬ እንዳሉ››ብሎ ገቢናውን ለቆ ወረደና ወደአቆማት መኪና ተንቀሳቀሰ…..ሰለሞንም ባልና ሚስቱን ይዞ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተፈተለከ…..

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

17 Nov, 17:00


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)
:
:
#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ተካ አቶ ኃይለልኡል ባዘዙት መሰረት ሽጉጡን ሙሉ ጥይት ሞልቶ ወገቡ ላይ ከሸጎጠ በኃላ አጉሊ መሳሪያ ያዘና  ማንን ሳያስከትል ቀጥታ መኪና ውስጥ ገብቶ ወደ ቃሊቲ ነዳው….የሰውዬውን ጥርጣሬ ምንም አልተዋጠለትም…‹‹ልጅቷ ስንት አማራጭ እያላት እንዴት እዛ ጭንቁርቁስ ቤት ከጭርቁስቁስ ሰዎች ጋር ለመቆየት ታስባለች? ››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡ ሊዋጥለት አልቻም…፡፡

በፀሎት ከጠፋችበት ቀን አንስቶ በመላ ሀገሪቱ ፍላጋ የተሰማሩትን በመቶ የሚቆጠሩ ግለሰቦችን የሚመራው ..መረጃ የሚቀበለው አዲስ ቦታ ስምሪት የሚሰጠው እሱ ነው፡፡እና የእሱ እቅድ የሆነ ቦታ መኖሯን በሆነ መንገድ ቀድሞ ቢደርስበት እንደምንም ብሎ የራሱ ሰው በሚስጥር እንዲያገኛት አድርጎ በእጅ አዙር 5 ሚሊዬኑን የሽልማት ገንዘብ ለመቀባበል አቅዶ ከልቡ እየሰራ ነበር...እርግጥ እንደዚህ እያደረገ መሆኑን ቀድመው ቢደርሱበት ያለምንም ማቅማማት ግንባሩን በጥይት እንደሚነድሉት እርግጠኛ ነው…ግን በህይወት የተሻለ ነገር ማግኘት ሪስክ መውሰድ የግድ እንደሆነ የሚያምን ስለሆነ ነገሩን ልክ እንደቁማር ነው ያየው..‹‹ወይ በላለሁ..ወይ ደግሞ እበላለው››ብሎ ነበር ውሳኔ ላይ ደርሶ በተግባር ሲንቀሳቀስ የከረመው፡፡…አሁን ሰውዬው እንደሚሉት ልጅቷ የገመቱት ቦታ የምትገኝ ከሆነ ያ ሁ እቅዱ ውሀ በላው ማለት ነው፡፡ቦታውን ራሳቸው ቀድመው አውቀው ስለነገሩት ሽልማት የሚሰጡበት ምንም ምክንያት የለም….መኪናውን ወደእዛ ሲያሽከረክር በውስጡ በፀሎት የተባለው ቤት በፍፅም እንዳትገኝ እየፀለየ ነበር፡፡እንደደረሰ ከመንገድ ማዶ አስፓልት ጠርዝ ላይ መኪናውን ፓርክ አደረገና የመኪናው መስኮት በከፊል ከፍቶ ማጊሊያ መነፅሩን ወደእነ አቶ ለሜቻ ግቢ አነጣጠረና ገቢ ወጪውን መመልከትና በመሀከልም የተለየ ነገር ያገኘ ሲመስለው በሞባይሉ ፎቶ ማንሳት ጀመረ…
ስራ የጀመረው ከጥዋቱ 5 ሰዓት አካባቢ ቢሆንም እሰከ 10 ሰዓት ሁለት ሶስት ጊዜ አሮጊት ሴት ስትወጣ ስትገባ ከማየት ውጭ በግቢው ውስጥ አይን የሚስብ ምንም አይነት እንቅስቃሴ አልነበረም…ሰዓቱ እየረዘመ ሲሄድ ተስፋ እየቆረጠና እየተሰላቸ መጣ…ለዛሬ ይበቃኛል ብሎ 11 ሰዓት ላይ አካባቢውን ለቆ ወደቤቱ ሄደ ..
በማግስቱ በጥዋት ማለዳ አንድ ሰዓት ላይ ነበር የመጣው፣እና ሁለት ሰዓት ላይ የሚፈልገውን አገኘ ..ደጋግሞ ፎቶ አነሳው…በቤቱ አንድ ሴት ልጅ ብቻ እንዳላቸው አጣርቷል ..አሁን እየገቡ እየወጡ ያሉት ግን በተቀራራቢ እድሜ ላይ የሚገኙ ሁለት ወጣቶች ናቸው፡፡አንደኛዋ የቤቱ ልጅ እንደሆነች እርግጠኛ ነው…ሁለተኛዋ ግን የሚፈልጋት የባለፀጋው ቅምጥል ልጅ ትሁን አትሁን መለየት አልቻለም…የለበሰችው ልብስ የተለመደ አይነት ነው..በዛ ላይ ፊቷን ጭንቅላቷን ጭምር በሻርፕ ሸፍናለች…ዝም ብሎ ከመኪናው በመውረድና በእግሩ ወደ አጥሩ በመጠጋት ከቅርብ ርቀት በርከት ያለ ፎቶ አነሳና ለአቶ ኃይለ ልኡል ላከላቸው፡፡

አቶ ኃይለልኡል በዚህ ጊዜ ከባለቤታቸው ጋር በሰለሞን በሚሾፈር መኪና ከቢሾፍቱ ወደአዲስ አበባ እየተመለሱ ነበር፡፡ስልካቸው ድምፅ ሲያሰማ ከኪሳቸው አወጡና ተመለከቱት..መልዕክት መሆኑን ሲያዩ ከፈቱት…አይናቸው ተጉረጠረጠ….
‹‹እራሷ ነች ..ልጄ እራሷ ነች….ከጎናቸው ያለችው ሚሳታቸው ላይ ተጠመጠሙና ጉንጮቾን አገላብጠው ይስሙ ጀመር››
‹‹እንዴ ኃይሌ ምን ተፈጠረ..?ምን ተገኘ..አረ ንገረኝ?››
‹‹ይሄውልሽ..እንቺ እይው..ፊቷን ብትሸፋፈንም እራሷ ነች፡፡››ወይዘሮ ስንዱ ስልኩን ከባላቸው እጅ ተቀበሉና አፍጥጠው ተመለከቱ…..ከባላቸው በበለጠ በመደነቅ ኡኡ.አሉ…መኪናዋን በእልልታ አደባላለቁት…ሰለሞን የነገሩ ውል ስላልገባው መሪውን ጠመዘዘና የመንገዱን ዳር አስይዞ መኪናዋን አቆማት…በራፉን ከፍተው ወረዱ….እሱም ተከትሏቸው ወረደ‹‹አረ ለእኔም ንገሩኝ ምንድነው? እንዲህ የሚያስፈነጥዝ ደስታ፡፡››
‹‹ልጃችን የት እንዳለች አወቅን..እያት ተመልከት››ስልኩን ከሚስታቸው ተቀበሉና ለሰለሞን አቀበሉት..አንድ ፊቷ በቅጡ የማይታይ ወጣት ፎቶ ነው…ግን በፀሎት እንደሆነች ወዲያው ነው ያወቃት..ሙሉ ፊቷን ሳያይ እሷ እንደሆነች አንዴት እንዳወቀ አልገባውም…››
‹‹አየህ …ልጃችን እራሷ ነች…ሰው እንዳይለያት ነው ፊቷን የሸፋፈነችው……››
‹‹ለመሆኑ የት ነው ያለችው?››ጠየቀ ሰሎሞን፡፡
‹‹የት እዳለች ቆይ ነግራችኃላው››ብለው ስልኩን ተቀበሉና ደወሉ
‹‹ሄሎ….ፎቶው ደርሶኛል፡፡››
‹‹አዎ ሳስበው እሷ ትመስለኛለች››
‹‹አዎ እሷ እራሷነች…ከቦታው እንዳትንቀሳቀስ..እዛው ጠብቀን…ከቢሾፍቱ እየተመለስን ስለሆነ ከ15 ደቂቃ በኃላ ያለህበት እንደርሳለን››
‹‹ወጥታ ከሄደችስ…?ላስቁማት››
‹‹አይ..ልጄን ቀጥታ እኔው ነኝ የማገኛት..እንዳታስቆማት ትደነግጥብኛለች…ከቤት ከወጣች ዝም ብለህ በርቀት እየተከታተልክ ያለችበትን ታሳውቀኛለህ፡››

‹‹እሺ..ጌታዬ እንዳሉት አደርጋለው››
‹‹ጎበዝ ..እንዳስደሰትከኝ አስደስትሀለው…ቆንጆ ጉርሻ ይጠብቅሀል ››
‹‹እሺ ጌታዬ››ስልኩን ዘጉና‹‹በሉ ጊዜ አናባክን ..ግቡና እንሂድ››
‹‹እንዴ የት አንዳለች ንገረን እንጂ……?››ወ.ሮ ስንዱ ጠየቁ
‹‹ስንድ ልጃችን ሰዎቹ ጋር ነው ያለችው….››
‹‹የትኞቹ ሰዎች››
‹‹እነአቶ ለሜቻ ጋር..ማለቴ የልብ ለጋሾ ቤተሰብ ጋር ነው ያለችው››
‹‹ወይ ጉዴ….አሁን ምንድነው የምናደርገው?››እያሉ ወደመኪናው ገቡ፡፡ አቶ ኃይለልኡልም ተከትለዋቸው ገቡ….ሰለሞን በሰማው ያልተጠበቀ ነገር ግራ እንደተጋባና ምን ማድረግ እንዳለበት እያሰላሰለ ገቢና ገባ፡፡ መኪናውን አንቀሳቀሳት…ባልና ሚስቶቹ በደስታ ሰክረው እሱን ከቁብ ሳይቆጥሩት እርስ በርስ በፈንጠዝያ ሲጎሻሸምና ሲሳሳሙ እሱ ምን ማድረግ እንዳለበትና ይሄንን ያለጊዜው ያጋጠመውን ነገር እንዴት እንደሚፈታ እያሰላሰለ ነበር የሚነዳው….
አቃቂ አቶ ለሜቻ ቤት ለመድረስ 500 ሜትር ያህል ሲቀራቸው የመኪናውን መሪ ወደግራ ጠመዘዘና ፊት ለፊት ከሚታየው ሆቴል ይዞቸው ገባ..ባልና ሚስቶቹ በድንጋጤ እርስ በርስ ተያዩ
‹‹ሰለሞን…ምን እያደረክ ነው?››አቶ ኃይለልኡል ጠየቁ፡፡
‹መነጋገር አለብን››
‹‹ስለምን?››
‹‹አሁን ልጃቹህ ጋር ከመሄዳችሁ በፊት አረፍ ብለን መነጋገር አለብን››
‹‹ምን መነጋገር ያስፈልጋል…?በቃ እኔና እናቷ ሄደን ልጃችንን ወደቤት ይዘን እንሄዳለን….እንደምታየው  አሁን  ሁሉ  ነገር  ውብ  እና  የተስተካለከለ  ነው..አይዞህ

አታስብ…ከንተጋር  ያለንን  ነገር  እንቀጥላለን..ከሶስት  ቀን  በኃላም  ወደአልከው  ቦታ ትወስደናለህ››
መኪናውን  አቆመና  ሞተሩን  አጥፍቶ  ወደኃላ  ዞረ..ፊት  ለፊት  እያያቸው‹‹ይሄ  ነገር እንደምታስብት ቀላል ይመስላችኃላ?››
‹‹ማለት?››
‹‹አሁን ያለችበት ቤት ሄደችሁ በማንኳኳት..ነይ ልጄ በቃ አግኝተንሻል አሁን ወደቤትሽ ተመለሺ ብትሏት ..እሺ ብላ በደስታ ዘላ የምትጠመጠምባችሁ ይመስላችኃላ…እምቢ መሄድ አልፈልግም ብትል ምን ታደርጋላችሁ ?በግድ በጎረምሳ አሳዝላችሁ መኪና ውስጥ በመክተት ወደቤት ትወስዷታላችሁ….?ከዛስ..?አንድ ክፍል ውስጥ ቆልፋችሁባት በራፍ ላይ ሁለት ጠብደል ጠባቂ ታቆማላችሁ?እስኪ ንገሩኝ ምንድነው የምደርጉት?››

አትሮኖስ

16 Nov, 02:02


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ‹‹አግብተሀል እንዴ?›› ድንገት ከርዕሳቸው ውጭ የሆነ ጥያቄ ስለጠየቁት ድንግርግር አለው፡፡ ‹‹ለምን መሰለህ የጠየቅኩህ..?እንዲሁ ሳስበው አንተን ያገባች ሴት በጣም እድለኛ ትመስለኛለች….፡፡›› ‹‹ምን አልባት ልትሆን ትችላለች ..እስከአሁን ግን አለገባሁምም…»

አትሮኖስ

16 Nov, 02:01


ጥቅም አልባ ነው። ለፍቅረኛ ወይም ለትዳር አጋር የሚኖር አክብሮት ጥልቅና ሩቅ መሆን አለበት። ከልብ የመነጨ ብቻ ሳይሆን ከነፍስም የተጨለፈ መሆን አለበት።ሚስት ለባሏ ሚስት ብቻ አይደለችም..የሴት ጓደኛ…የእናት ምትክ ዘመድ ጭምር መሆን አለባት..ባልም ለሚስቱ ወንድ ጓደኛ..ከዛም አልፎ የአባት ምትክ ዘመድ መሆን አለበት፡፡የማወራው ግልፅ ነው አይደል?››
‹‹አዎ ..በጣም ግልፅ ነው..ቀጥል››

ትንፋሽ ወስዶ ከንፈሩን በምራቁ አረጠበና ንግግሩን ካቆመበት ቀጠለ‹‹…ከቤት ወጥታችሁ ስትለያዩ የሚኖር ሽኝት እና ከውጭ ውላችሁ ስትመለሱ እርስ በርስ የሚኖር የሞቀ አቀበል በጣም ወሳኝ ኩነት ነው።ተሳሳሞ ደህና ዋል..ደህና ዋይ ተባብሎ መለያየት እና ሲገናኙ እንዴት ዋልሽ…?እንዴት ዋልክ? ተባብሎ በናፍቆት መሳሳም በመሀከል ያለን ግንኙነት ያደረጃል ፍቅርም ግለቱን ጠብቆ እንዲጓዝ ያግዛል።በመጨረሻው ሚቻላችሁ ከሆነ እቤት ከገባችሁ  በኃላ  ለተወሰነ  ሰዓት  ስልክ  የሚጠፋበት  እና  ቲቨ  የሚዘጋበት  ልዩ የሆነ የቤተሠብ የጋራ የመጫወቻና የመወያያ ሰአት ቢኖር እንደቤተሠብ ለሚኖር መስተጋብር ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋል።
‹እና ሌላው ልጃችሁ ላይ ያላችሁ አቋም ትልቅ ማስተካከያ ሊደረግበት ይገባል፡፡››
‹‹ማለት?››
‹‹በፀሎት ነገሮች ተስተካክለው ወደቤት ስትመለስ..ለምሳሌ ስትወጣ ስትገባ በጋርድ እንድትጠበቅና እንድታጀብ ማድረግ አይገባችሁም..እንደማንኛውም ሰው በነፃነት ከፈለገችው ሰው ጋር ወጥታ ከፈለገችው ጋር የመመለስ መብት ሊኖራት ይገባል፡፡››
‹‹ሰለሞን እዚህ ላይ አንድ ያልገባህ ነገር አለ…እኔ እኮ ልጄን በጋርድ ማስጠብቀው ወድጄ አይደለም…..ልጄ ልብ በሽተኛ ነኝ..የልብ ንቅለ ተከላ ተደርጎላታል …በጣም ጥንቃቄ የምትፈልግ ልጅ ነች..ድንገት መንገድ ላይ ወድቃ አጉል እንዳትሆንብኝ ስለምሰጋ ነው ዘወትር ሰዎች በዙሪያዋ እንዲሆኑ የማደርገው፡፡››ሲሉ ተቃውሞቸውን ያሰሙት አቶ ኃይለልኡል ናቸው

‹‹ቢሆንም ለዛ መፍትሄው ያ አይደለም….ይሄ የልጅቷን ነፃነት ከመንፈጉም በላይ በራስ የመተማመን ችሎታዋን በጣም ይጎዳዋል…በየሄደችበት በሰው መጠበቅ የመታፈን ስሜት እንዲሰማት ነው የሚያደርጋት፣እና የእዛ ውጤት ደግሞ እንዲህ አሁን እንዳደረገችው ራሷን ነፃ ለማውጣት አላስፈላጊ ጣጣ ውስጥ እንድትገባ ትገደዳለች››
‹‹ትክክል ልትሆን ትችላለህ …ግን ያው ነፃ ትሁን… ብቻዋን ትንቀሳቀስ ብዬ ከፈቀድኩላት አንዳንድ አላስፈላጊ ቦታዎች ትሄድና የማይሆን ነገር ትሰራለች፡፡››
‹‹ለምሳሌ የት?››
‹‹ይሄውልህ የልብ ንቅለ ተከላ ሲደረግላት ልብ የሰጠቻት ልጅ ቤተሰቦች እዚሁ አዲስ አበባ አቃቂ አካባቢ ነው የሚኖሩት ..ልጄ አሁን አሁን ተወች እንጂ በፊት ሰሞን ቀንና ሌት እዛ ካልወሰድከኝ እያለች ታስቸግረኝ ነበር፣..እኛ ደግሞ ከልጅቷ አባት ጋር ስንስማማ በምንም አይነት ከእኛ በአካል መገናኘት እንደማይፈልጉ ነው ያነገሩን..እሷ ቤታቸው ሄዳ ቢያገኟት ልጃቸውን ስልምታስታውሳቸው ሀዘናቸውን ክፉኛ ትቀሰቅሳባቸዋለች.. እንደዛ አይነት ውለታ የዋሉልኝን ሰውዬ ደግሞ የማይፈልጉትን ነገር ማድረግ ላሳዝናቸው አልፈልግም..አንድ ለዛ ነው የማስጠብቃት››ንግግራቸውን እየተናገሩ ሳለ የሆነ እስከዛሬ ያላሰብት ገራሚ ሀሳብ በአእምሯቸው ብልጭ አለ….እንዴት እሰከዛሬ ትዝ ሊላቸው እንዳልቻለ ግራ ገባቸው‹‹ልጄ እነሱ ጋር ሄዳ ቢሆንስ?››ሀሳቡን በውስጣቸው አፍነው ያዙት፡፡
‹‹የልጃችሁን ደስተኝነትና ሳቅ የምትፈልጉ ከሆነ ለችግሮች ሁሉ ሌላ መፍትሄ አበጁላቸው..ደግሞ ለበፀሎት በግልፅ ነገሮችን ቢያስረዶት ይገባታል…ብስልና አስተዋይ የ22 ዓመት ወጣት ነች….ይልቅ እናንተ  በመሀከላችሁ ያለውን ችግር ፈታችሁ ሰላም ከሆናችሁና ስትወጣ ስትገባ የሚከታተላት ሰው መመደብ ካቆማችሁ የልጃችሁን ደስታና ሳቅ መመለስ ብቻ ሳይሆን መቼም መልሳችሁ አታጦትም››
ወ.ሮ ስንዱ መለሱ ‹‹እሺ እንዳልክ እናደርጋለን….ኃይሌ እንዲህ ማድረግ ያቅተናል እንዴ?››
‹‹አረ አያቅተንም..ችግር የለውም ሁሉን ነገር እኔ አስተካክለዋልው..አሁን ከፈቀድክልኝ ወደካማፓኒው አንድ አጭር ስልክ መደወል አለብኝ..ከባድ የስራ ጉዳይ ነበረ ..ምን እንዳደረሱት ልጠይቃቸው፡፡››

‹‹ችግር  የለም..በቃ  ጨርሰናል..አሁን  ለጥዋት  ጉዙ  እቃችንን  መሸካከፍ  መጀመር እንችላለን፡፡››
‹‹ጥሩ…››ብለው ቀድመው ከመቀመጫቸው ተነሱና  ወደክፍላቸው በመሄድ ስልካቸውን ካስቀመጡበት አንስትው በጀርባ በኩል ባለው በር ከቤት ወጡ….  ስልክ ደወሉ…
‹‹ስማ አቃቂ ለልጄ ልብ የሰጠቻት ልጅ ቤተሰቦችን ታውቃቸወላህ አይደል..?››
‹‹አዎ አውቀዋለው››
‹‹አሁኑኑ እዛ ሂድና ቀስ ብለህ ማንም ሳያይህ ወደቤታቸው የሚገባውንና የሚወጣውን ሰው ተከታተል…ከተቻለህ ሁሉንም ፎቶ አንሳ››
‹‹እሺ….ግን በቀጥታ ምን ለማጣራት ነው የምንፈልገው…?ነገሩን ማወቄ ስራዬን ያቀልልኛል››
‹‹አዎ….ምን መሰለህ..ለማንም እንዳትናገር..ልጄ ምን አልባት እዛ ቤት ተደብቃ ይሆናል የሚል ጥርጣሬ አድሮብኛል…እና ከአሁኑ ጀምረህ በቃ እስክልህ ደረስ እንዳልኩህ ተከታተለልኝ…እሷን በተመለከተ የሆነ ትንሽም ቢሆን ፍንጭ ካገኘህ ወዲያው አሳውቀኝ፡፡››
‹‹ስልኩን ዘጉና ኪሳቸው ውስጥ ከተው ወደውስጥ ተመለሱ …ወ.ሮ ስንዱ አልጋቸው ላይ አረፍ ብለው አገኞቸው ፡፡በራፉን ዘጉን የራሳቸውን አልጋ ትተው ወደባለቤታቸው ሄዱና ከጎናቸው ተቀመጡ፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

16 Nov, 02:01


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሀያ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

‹‹አግብተሀል እንዴ?››
ድንገት ከርዕሳቸው ውጭ የሆነ ጥያቄ ስለጠየቁት ድንግርግር አለው፡፡
‹‹ለምን መሰለህ የጠየቅኩህ..?እንዲሁ ሳስበው አንተን ያገባች ሴት በጣም እድለኛ ትመስለኛለች….፡፡››
‹‹ምን አልባት ልትሆን ትችላለች ..እስከአሁን ግን አለገባሁምም አረ እንደውም ፍቅረኛም የለኝም››
ፈገግ አሉ….‹‹ሸክላ ሰሪ በገል ይበላልል›› አሉ…ብዙ ማወቅም እኮ መጥፎ ነው››
‹‹እንዴት?››
‹‹የምትፈልገውን ሁሉ የምታሟላ ሴት ለማግኘት በጣም ይከብድሀላ…ሁሉን ነገር አሟልታ ጥንቅቅ ያለች ሴት አታገኝም..በዛ እርግጠኛ ሆኜ ልነግርህ እችላለው…ግን ምትወድህና ምትወዳት ልጅ ሆና እራሷን ለመለወጥና ለማሻሻል የምትጥር ከሆነ በቂ ነው…አንተ ጎበዝ አንደበተ ርትኡ ባለሞያ ስለሆንክ መስመር ታስይዛታለህ››
እንዴት ብሎ መምከሩን ትቶ ተመካሪ እንደሆነ አልገባውም፡፡‹‹እሺ…የእናንተን ጉዳይ ከዳር ካደረስኩ በኃላ አስብበታለው….ምን አልባት እናንተ ትሆናላችሁ የምትድሩኝ…››
‹‹ለዛውም ድል ባለ ድግስ ነዋ››

‹‹እሺ..አሁን ይበቃናል…የምሳ ሰዓት ስለደረሰ ወደሳሎን እንሂድ››
‹‹አዎ ..ይበቃናል..ይሄኔ ኃይሌ ብቻውን ደብሮታል››
ፈገግ እለ ….. ከመቀመጫው ተነሳና ወደውጭ መራመድ ጀመረ…ወ.ሮ ስንዱም ተከተሉት፡፡


ከሳምንት በኃላ……..
በቢሾፍቱ ቆይታቸው በባልና ሚስቶቹ መካከል አስገራሚ የሚባል ለውጥ ነው የታየው፡፡ቢያንስ እረስ በርስ በመሀከላቸው ያለ ንግግር የጥሩ ጓደኛሞች መምሰል ከጀመረ ሰነባብቷል…ይሄ ለውጥ ሰለሞንን ይበልጥ እንዲበረታታ እና ሙሉ ኃይሉን ስራው ላይ እንዲያውል አግዞታል፡፡
‹‹እንግዲህ ዛሬ የመጨረሻ ቀናችን ነው ነገ ወደአዲስአባ እንመለሳለን…ሶስት ቀን እረፍት እንወስድና ምን አልባትም ለመጨረሻ ጊዜ ለሌላ 15 ቀን ወደሌላ መዝናኛ ቦታ እንሄዳለን፡፡በቀጣይ የምንሄድበት ከዚህ የተለየ ነው…ሌሎች ሰዎች ማለቴ ጎብኚዎች የሚኖሩበት ቦታ ነው…እዛ ምንሄደው ነፃ ሆናችሁ እንድትዝናኑ ነው..እኔም አብሬያችሁ ኖራለው ግን ነፃ ናችሁ…እዚህ እንዳለው ብዙ ማዕቀብና እገዳ የለም…ስልካችሁን እንደፈለጋችሁ መጠቀም ትችላላችሁ.ሰሻል ሚዲያ ቴሌቪዝን ማየት ትችላላችሁ …ከሰው መተዋወቅና መገባበዝ ትችላላችሁ..አንድ ማትችሉት ነገር መለያየት ብቻ ነው….ለ15 ቀን የምታደርጉትን ሁሉ አብራችሁ ታደርጋላችሁ..››
‹‹ገባን ..ያልከው 15 ቀን የመጨረሻችን ይመስለኛል››
አዎ እኔም እንደዛ ነው የማስበው..በእውነት እዚህ ባሳለፍነው 15 ቀን ሁለታችሁም ካሰብኩት በላይ ከፍተኛ ጥረት አድርጋችኃል …እናም ትልቅ ለውጥ እንዳመጣችሁም ይሰማኛል…እናንሰትስ ምን ይሰማችኃል…?አቶ ኃይለልኡል እስኪ ከእርሶ ልጀምር፡፡

‹‹እኔ በጣም ደስተኛ ነኝ…እስከዛሬ ሚሲቴን ብቻ የምበድል መስሎ ነበር የሚሰማኝ ለካ ልጄንም ራሴንም ጭምር ነበር እያሰቃየው የነበረው….እውነት አንተና ልጄ የእድሜ ልክ ባለውለታዎቼ ናችሁ››
ፊቱን ወደወ.ሮ ስንዱ ዞረና ተመሳሳዩን ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡
‹‹አዎ…ኃይሌ እንዳለው ደስተኛ ነን…በፊት ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ ገዳም ገብቼ መመልኮስ ነበር ምኞቴ ..ምክንያቱም ህይወት አስጠልታኝ ነበር…ቤቴም ኑሮዬም ይቀፈኝ ነበር…ጨለማ የሆነ ሀዘን ውስጥ ገብቼ ነበር..አንድ ያለችኝ አስደሳች ነገር ልጄ ብቼ ነበረች
..እሷም ከጠፋች በኃላ ደግሞ ነገሮች ለእኔ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሚሆኑ መገመት ቀላል ነው…አሁን ግን እንደዛ አይደለም የሚሰማኝ….ደግመኛ እንደመወለድ አይነት የመታደስ ስሜት እየተሰማኝ ነው…የመከራና የሀዘን ቆዳዬን ከላዬ ገፍፌ ጥዬ በአዲስ ተስፋና ፍቅር ተወልጄለሁ..አሁን ቤቴም ባሌም ይናፍቁኛል….ሃይሌን ከዚህ በፊት ለሆነው ሁሉ ይቅር ባዬዋለሁ.. እሱም ይቅር እንደለኝ ገምታለው፡፡››
ኃይለልኡል ተፈናጥረው ከመቀመጫቸው ተነሱና ሚስታቸው ላይ ተጠመጠሙ…ሁለቱም ተቃቅፈው መላቀስ ሲጀምሩ….ሰለሞንንም ስሜታዊ አደረጉት፡፡ተላቀው ወደቦታቸው ለመመለስ..ከ10 ደቂቃ በላይ ፈጅቶባቸዋል፡፡
ሰለሞን ንግግሩን ቀጠለ‹‹ጥሩ እንግዲህ… እዚህ ደረጃ ላይ ከደረስን አንዳንድ አጠቃላይ ስለሆኑ ነገሮች እናውራ፡፡ያው እናንተ በጋብቻ ውስጥ ረጅም እድሜ ስለአሰለፋችሁ ከእኔ የበለጠ ልምድ እንዳላችሁ አውቃለሁ....አሁን የማወራው የምታውቁትን ነገር ነው…ላሳውቃችሁ ሳይሆን ላስታውሳችሁ ፈልጌ ነው››
‹‹ጥሩ እየሰማንህ ነው ….ቀጥል››
‹‹እንግዲህ እቤት የባል ብቻ አይደለም፣የሚስትም ብቻ አይደለም፣ እቤት የልጆችም ጭምር ነው።በዚህ ምክንያት ለሁሉም ኑዎሪዎች እኩል ምቹ መሆን አለበት።እናንተ ከአሁን ወዲያ በቤታችሁ የሚዘረጋው ስርአት ህግና የአኗኗር ዘየ..ሶስታችሁን በእኩል ከግምት ያስገባ መሆን አለበት፡፡ሌላው ንብረታችሁን በተመለከተ የእኔ የሚለውን ቃል ከመጠቀም የእኛ የሚለውን የጋራ ቃል መጠቀም የተሻለ ነው።የእኛ ቲቪ..የእኛ ቤት...የእኛ ጊቢ የእኛ ፋብሪካ፣ብሎ የመናገር ልምድ ሊኖራችሁ ይገባል።እያንዳንድ የቤተሰብ አባል የእዛ ቤተሠብ

የአክሰዬን ባለድርሻ ናቸው።ያንን ደግሞ በተግባርም በስነ-ልቦናም መረጋገጥ አለበት።በቤተሰብ ቢዝነስ ውስጥ ስለሚፈጠር ዋና ዋና ክስተት ስለትርፍም ሆነ ኪሳራ ሁሉም ሰው በተገቢው መጠን መረጃ ሊኖረው ይገባል….ሁሉንም ኃላፊነት አንዱ አካል ብቻ ጠቅልሎ መውሰድ የለበትም…እዚህ ላይ በተለይ አቶ ኃይለልኡል ብዙ ነገር ማስተካከል የሚጠበቅቦት ይመስለኛል››
‹‹ገብቶኛል..እሺ…አስተካክላለው፡፡››

‹‹ሌላውና ወሳኙ … የተለየ ችግር ከሌለ በስተቀር ባልና ሚስት መኝታ ክፍላቸውንም ሆነ አልጋቸውን መለየት የለበቸውም…በተጨማሪም ባልና ሚስት በምንም አይነት ሁኔታ ወደመኝታቸው ሲሄድ አኩርፈውና በውስጣቸው ተበሳጭተው ወይ ቂም ይዘው መሆን የለበትም።መኝታ ክፍል ለባለትዳሮች እንደቤተመቅደስ ነው መሆን ያለበት ። የሚሳሳሙበት... የሚተቃቀፉበት.... የሚዋደድበትና የሚፋቀሩበት ….ስለጋብቻቸው እና ስለልጆቻቸው ደህንነትና ሰላም የሚማከሩበትና የሚፀልዩበት የገመና መክተቻ ቦታቸው ነው መሆን ያለበት ። ስለዚህ ... ቅያሜያቸውን ሆነ ቅሬታቸውን ሳሎን ጨርሰው ለጭቅጭቃቸው መፍትሄ አበጅተውለት እና ይቅር ተባብለው ነው በሳቅና በፈገግታ ወደመኝታቸው መሄድ ያለባቸው። አዎ ወደመኝታ ክፍላቸው ሲያመሩ በፍፁም ሰላምና ፍቅርና መሆን አለበት...የበለጠ ለመፍቀር...የበለጠ ለማረፍና ..የበለጠ ለመታደስ ።ይሄ ሁለታችሁንም በእኩል ደረጃ የሚመለከት ጉዳይ ነው፡፡››
ሁቱም አንገታቸውን እላይ እታች በማነቃነቅ መስማማታቸውን ገለፁ

‹‹ሌላው በቤት ውስጥ አንደኛው ሌለኛውን ማገልገል አለበት...ማገልገል ማለት በፍፅም ፍቃደኝነትና ፍላጎት አንደኛው ሌላኛውን መርዳት ማለት ነው።ባል የቤቱ ንጉስ ከሆነ ሚስት ደግሞ ንግስት ነች ማለት ነው ልጆች ደግሞ ልኡላን ናቸው።ማንም ከማንም የበለጠ አስፈላጊ አይደለም...ማንም ከሌላኛው ያነሰ አይደለም።ለቤቱ ሙሉነትና ፍፁምነት ሁሉም የየራሱ ኃላፊነትና ድርሻ አለው።በፍቅርና በጋብቻ ህይወት ውስጥ እርስ በርስ ያለ መከባበር በጣም ወሳኝ ነው።አንድ ለሌላዎ ጥያቄዎችን አስተያየቶችን ሲኖሩት በትህትና እና ክብር በተሞላ ሁኔታ ጥያቄውን ማቅረብ አለብት።እርስ በርስ ያለ ግንኙነት የማስመስል መሆን የለበትም...እንግዳ ሲኖር የሚደረግ አርቴፊሻል የማስመሰል እንክብክቤ እና አክብሮት

አትሮኖስ

14 Nov, 18:11


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
:
:
#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰሎሞን ሁለቱን ባለትዳሮች ፊት ለፊት አስቀምጦ እያወራ ነው፡፡‹‹የፈለገ ጥረት ብናደርግ ለእያንዳንዱ ብሎን የራሱን ትክክለኛ መፍቻ ካልተጠቀምን ልንፈታው አንችልም!! በህይወታችንም ውስጥ ችግሮች ሲያጋጥሙን ተረጋግተን ለችግሩ ትክክለኛ የመፍትሄ ሀሳብ ማስቀመጥና ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ካልቻልን እንዲሁ ስንባክን እና በችግሩ ውስጥ ስንዳክር ነው የምንኖረው፡፡ይሄንን በስራ አለም በትክክል እየተገበራችሁ ውጤታማ እንደሆናችሁ አውቃለው…በትዳር ህይወታችሁስ?ዋናው ጥያቄ እሱ ነው፡፡››
አቶ ኃይለልኡል ተቀበሉት‹‹ገብቶናል…እንደምንም ብለን በመሀከላችንን የተፈጠረውን ክፍተት በማስወገድ እና ፍቅራችንን መመለስ እንዳለብን በደንብ ተረድተናል…አዎ እንደምታየውም ጥሩ መሻሻል እያሳየን ይመስለኛል፡፡››
ሰለሞን ቀጠለ‹‹ጥሩ ግን ፍቅር ብቻውን በሰላም ለመኖር በቂ አይደለም፡፡በመሀከላችው ምንም አይነት ጥል የሌለ ጥንዶች በመሀከላቸው ፍቅር እንዳለ እርግጠኛ መሆን አይቻልም…እንደዛውም ዘወትር በነጋ በጣባ የሚጣሉና የሚጨቃጨቁ ጥንዶችም በመሀከላቸው ያለው ፍቅር አልቋል ወይም ቀዝቅዞል ማለት አይደለም….ከዛ ይልቅ እንዴት እርስ በርስ እንደሚግባቡ እና አንዱ የአንዱን ፍላጎት እንዴት እንደሚረዳ አልገባቸውም ማለት ነው፡፡ስለዚህ አሁን መልሳችሁ ማደስ የሚገባችሁ ፍቅራችሁን ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ የመግባባት ችሎታችሁንም ጭምር ነው፡፡አንዳችሁ ሌላችሁን በጥልቀት ለመረዳት እስከምን ድረስ ለመጓዝ ትፈቅዳላችሁ?ይሄ ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡››

ወ.ሮ ስንዱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገሩ‹‹ትክክል ነህ ልጄ… ለፍቀራችን መበላሸት ዋናው ምክንያት እንደውም እርስ በርስ የመግባባት ችሎታችን ስለተበላሸ ነው….እሱም እኔን እኔም እሱን ለመረዳት ምንም የምናደርገው ጥረት አልነበረም…ሁለታችንም እርስ በርስ እንከን ነበር የምፈላለገው….ያንን በደንብ ተረድቼለው፡፡››
‹‹አዎ ይሄ ችግር የእናንተ ብቻ ሳይሆን የአብዛኛው ባለትዳር ችግር ነው…አንድ ሰው በፍቅር ሲወድቅ በመጀመሪያ ስለራሱ ምቾና ደስታ እንጂ ስላፈቀረው ሰው ደህንነት አይደለም የሚጨነቀው…ሁለቱም ተጣማሪዎች በጋብቻ ጥምረት ውስጥ ለእነሱ የሚመች ሰፋ ያለ ግዛት ቶሎ ብሎ ለመያዝ ይጣጣራሉ…ሁለቱም ተመሳሳይ ፍላጎት ስላላቸው ፍትጊያ ይፈጠራል…አንዱ የሌለኛውን ድምበር ማለፍ…ይሄኛው የዛኛውን ቀይ መስመር መደፍጠጥ ይጀምራል……ከሁለት አንዱ በፍጥነት ነቅቶ ወደኃላ በመመለስ መረጋጋት ውስጥ ካልገባ ችግሩ መስመር ይስታል፡፡
እኔ 25፡50፡25 የሚል ፕሪንስፕል አለኝ፡፡በትዳር ውስጥ እሷ(ሚስትዬው) እሱ(ባልዬው) እና እነሱ (ባልና ሚስቶቹ)አሉ፡፡እና ስሜታቸው፤ፍላጎታቸው፤የህይወት አላማቸው ወ.ዘ.ተ ተጠቅልሎ መቶ ፐርሰን ቢሰጠው፡፡እሷ የግሏ ፍላጎት በግሏ የሚያስደስታት ነገር፤ መዝናኛ ቦታ፤ጓደኞች፤ 25 ፐርሰንት ትይዛለች….እሱም ለብቻው 25 ፐርሰንት ይይዛል፡፡50 ፐርሰንቱ ግን የጋራቸው ነው፡፡በጋራ የሚያቅዱበት፤በጋራ የሚሰሩበትና የሚለፉበት ቤት መስራት፤ልጆች መውለድና ማሳደግ…ወዘተ፡፡ሁል ግዜ ተሰፍሮ 25፤50፤25 ላይሆን ይችላል፡፡በተለይ ሴቶች ከእነሱ 25ፐርሰንት 10ሩን ወይም 15 ቱን ቆርሰው ለጋራቸው ያውሉታል…ወንዶች ደግሞ ከሞላ ጎደል አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ከጋራቸው ላይ ቆረስ አደርገው የእነሱን 25 ፐርሰንት 30 እና 40 አንዳንዴም ከ50 በላይ ያደርሱታል..የዛን ጊዜ የጋብቻው ባላንስ ይናጋል፡፡ምሰሶው መነቃነቅ ይጀምራል..እርማት ካልተደረገለት ጋብቸውን እያከሳ ይሄድና መጨረሻ ያከትምለታል፡፡…የምናገረው ግልፅ ነው አይደል››
‹‹አዎ..በጣም ግልፅ ነው፡፡››
‹‹በምሳሌ ይበልጥ ለማስረዳት አንድ ገጠር የምትኖር አክስቴ ከአስር በላይ ባሎች አግብታለች፡፡ግማሹን እነሱ ናቸው የፈቷት ግማሾቹን እራሷ ነች ያደረገችው፡፡ከሁሉም ግን የሳበኝን አንደኛውን ልንገራችሁ፡፡አገባሁት አለች..በጣም ሰላማዊ ..ምንም አይነት ክፉ ነገር ማይናገር…የጠየቅኩትን ሁሉ የሚያሞላልኝ ሰላማዊ ሰው ነበር አለች፡፡በፊት ከለመደቻቸው ተደባባዳቢ እና ተጨቃጫቂ ባሎች ጋር የትኛውም ፀባዩ የሚገጥም

አልነበረም፡፡ግን ብዙም ሳይቆይ ሰለቻት….ሁሉ ነገር ዝም እና ጭጭ ያለ ሆነባት…በቃ ግንኙነታቸው ውስጥ ነፍስ አጣችበት ፡፡አንድ ቀን በለሊት ተነሳና በሬዎቹንና ሞፈር ቀንበሩን ይዞ ወደማሳ ወጣ …ሲሄድ ቁርስም አልሰጠችውም..ምሳም ይዛ መሄድ ቢገባትም አልወሰደችለትም..ጭራሽም አልሰራችም…በጣም የባሰው ነገር ደግሞ የቤቱን እቃ ብረትድስት ፤ሰሀን ፤ብርጭቆ አንድም ሳታስቀር ከቤት ጀምራ የቤቱን መግቢያ ደጃፍ…ወለሉን ጠቅላላ አዝረክርካ እና ሞልታ ኩርሲ ላይ ቀጭ ብላ ትጠብቀው ጀመር ፡፡.
ከዛ መጣ…ከውጭ ጀምሮ ያዝረከረከችውን እቃ አንድ በአንድ ጎንበስ ብሎ እየለቀመ…‹‹እታዋቡ …ሰላም ነሽ….?ምንም አልሆንሺብኝም አይደል….?››እያለ ሁሉንም እቃ ወደመደርደሪያ መልሶ ስሯ ቁጭ ብሎ በልምምጥ ጭንቅላቷን መዳበስ ጀመረ..
ከዛ ይህቺ አክስቴ ምን ብታደርግ ጥሩ ነው‹‹ ብድግ አለችና ሻንጣዋን ይዛ‹‹እንዴት ቁርስ አላበላሁህ ..ምሳ አለመጣሁልህ….ቤቱን እዲህ አዝረክርኬ ነው የጠበቅኩህ..ምን እስካደርግህ ነው የምትጠብቀው…?ምንም አይነት የወንድነት ወኔ የለህም እንዴ…?ሁለት ሴት አንድ ቤት አይኖርም… ነውር ነው››ብላ ጥላው ወጣች..በዛው ፈታችው ፡፡አያችሁ ትዳር በጣም ውስብስብ ግንኙነት ነው፡፡የበዛ ጭቅጭና ጥል ብቻ ሳይሆን የበዛ ሰላምና ፀጥታም ሊያፈርሰው ይችላል፡፡፡ዋናው በሁሉም ነገር ሚዛን ጠብቆ መጓዝን መልመድ ነው፡፡››
የተወሰነ ትንፋሽ ወሰደና ፊትለፊቱ ካለ የታሸገ ውሀ በማንሳት አንዴ ተጎንጭቶለት ከንፈሩን አረጣጠበና ንግግሩን ቀጠለ፣እነሱም ልክ በቅርብ ፈተና እንደደረሰበት ቸካይ ታማሪ በጥሞናና በትኩረት እየተከታተሉት ነው‹‹አሁን ልብ በሉ፣ ጥረታችን በመካለላችሁ ያላውን ግጭትና ጭቅጭቅ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይደለም..አይ እንደዛማ አይሆንም እናንተ ሰው ናቸው፣ሁለት ሰዎች ደግሞ በአንድ ጣሪያ ስር አብረው እስከኖሩ ድረስ በሆነ ነገር መነጋገራቸውና በነገሩ ላይ የተለያየ ተቃራኒ ሃሳብ ማንፀባረቃቸው አይቀርም…ስለዚህ መነጋገርና መጨቃጨቅ ኖርማል ነው…አሁን ምንድነው ምናደርገው.. በማንኛውም ጉዳይ ላይ አለመግባባት ተከስቶ ስትነጋገሩ በምን መልኩ ነው ኮምንኬት የምታደርጉት..?ነገሩን ማስረዳትና ማሳመን ላይ ነው ትኩረታችሁ ወይስ ያንን ምክንያት አድርጎ በስድብና በዘለፋ ማጥቃትና ልብ መስበር…አያችሁ ትልቁ ችግር መጋጨታችን ሳይሆን በያንዳንዱ ግጭታችን አንዳችን ለሌላቸውን የልብ ቁስለትና የነፍስ ህመም መስጠታችን ነው፡፡ማጥፋት ያለብን እርስ በርስ መወጋጋቱን ነው…አንዳችን ሌላችን ላይ በምንም አይነት ሰበብ የሚያቆስል ነገር ጦር አስበን አይደለም አምልጦን እንኳን መወርወር ለብንም፡፡እርስ በርስ ከፍ ባለ ቃላት

በተነጋገራችሁ ቁጥር ደግሞ እየተጣላችሁ መሆኑን አታስቡት..መጣላት ቃሉ እራሱ አሉታዊ ነው፡፡እየተጣላችሁ ሳይሆን በጋለ ስሜት እየተነጋገራችሁ ነው፡፡በቃ እንዲህ ነው ማሰብ ያለባችሁ፡፡እንደዛ ካሰባችሁ ቀጥታ ችግሩ በጋለ ስሜት መነጋገራችን ብቻ ስለሆነ ስሜታችሁን በማረጋጋት ነገሩን ትፈታላችሁ፡፡እየተጣላን ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ግን ጋና ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው ወይም ሽማግሌ ልትፈልጉ ነው፡፡ልብ በሉ ጮክ ብሎ መናጋገር ሁል ጊዜ መጣላት አይደለም አብዛኛውን ጊዜ በጋለ ስሜት

አትሮኖስ

14 Nov, 18:11


​​መነጋገር ነው፡፡ለዘሬው ይበቃናል…አሁን ወደመናፈሻው እንሂድና ትንሽ ዘና እያልን ብና እንጠጣ››
‹‹ጥሩ….እንሄድ››ብለው ሶስቱም ከተቀመጡበት ተነሱና እቤቱን ለቀው ወጡ
////
በማግስቱ…….
ሰሎሞን ባለትዳሮችን ቢሾፍቱ ይዞ ከከተመ አራተኛ ቀኑ ነው፡፡የዛሬው ፕሮግራም ሁለቱን በተናጠል ማነጋገር ስለሆነ አሁን ከወ.ሮ ስንዱ ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ለብቻ ፊት ለፊት ቁጭ ብለው እያወሩ ናቸው፡፡
‹‹ወ.ሮ ስንዱ አሁን ነገሮች እንዴት እየሄዱ ነው?››
‹‹እድሜ ላንተ …ጥሩ ስሜት እየተሰማኝ ነው…ከስንት ዓመት በኃላ ከኃይሌ አንደበት መልካም ነገር መውጣት ጀምሯል››
‹‹ጥሩ እንግዲህ ሰው ምን ጊዜም ከስህተት ጋር ሚኖር ፍጡር ነው፡፡ከሰው ጋር ስንኖር ስህተት ፈላጊ ከሆን በማንኛውም ሰው ላይ ከመጠን ያለፈ ስህተቶችን በቀላሉ ማግኘት እንችላለን…..ያ ደግሞ ከሰው ጋር አያኖኑረንም…አንዳችን የሌላችንን ክፍተት ለመድፈን መፈጠራችንን እስካላሰብን ድረስ ምንም ነገር ሰላም ሊሆን አይችልም፡፡››

‹‹ትክክል ነህ..በህይወት ዘመናችን አውቀንም ሆነ ሳናውቅ…እርስ በርስ በጣም ተጎዳድተናል…በእልህም በጥፋት ላይ ጥፋት እየደረብን የሁለታችንንም ጣር ስናበዛው ነበር››
‹‹ያለፈው አፏል..አሁን ማሰብ ለነገው ነው፡፡የትናንቱን ጥፋት እያነሳን የምንመረምረው ከልባችን ይቅር እንድትባባሉ እንዲያግዛችሁ እና ዳግመኛው ተመሳሳይ አይነት ስህተት በህይወታችሁ እንዳትሰሩ ነው፡፡››
‹‹ገብቶኛል ልጄ በጣም ገብተኛል..ግን ምን መሰለህ ሀይሌ አንዳንዴ እንዲህ እንደምታየው አይምሰልህ… ህፃን ሆኖ የህፃን ስራ ሲሰራ ታገኘዋለህ ››
‹‹ውቃለው ይሄ የእሷቸው ብቻ ሳይሆን የብዙ ሰዎች ባህሪ ነው….ሰባ አመት ቢሞላን እንኳን ሁላችንም ውስጥ ሳያድግ ህፃን እንደሆነ የሚቀር ማንነት አለ…ሁሌ ውስጣችን ሆኖ ስነልቦናችንን የሚያናውፀው…እናታችን ጉያ ውስጥ እንድንወሻቅ የሚያስመኘን …አባታችን ጭንቅላታችንን እንዲዳብሰንና አይዞህ እንዲለን የሚያስናፍቀን…..አያጂቦ የሚያስፈራን ጭራቅ በህልማችን የሚመጣብን… አዎ ሳያድግ በጮርቃነት የቀረ ማንነት አለን….ለዛ ነው ልጅነት ላይ በሆነ ጎኑ የተሰበረ ሰው አድጎም በቀላሉ ጤነኛ መሆን የማይችለው….ለዛ ነው ጉዳቱ የሚያሳድደው..ለዛነው አንዳንድ ጉድለተችና የህይወት ሽንቁሮች የእድሜ ልክ ህመም ሆነው የሚቀሩት..ልጅነታችን ላይ ተጠጣብቀን እንድንቀር የሚያስገድደን፡፡››
እንግዲህ እኔ አሁን ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጌ ትቼ ከእሱ ለመስማማት ነው የምፈልገው…ግን ሰላማችን ምን ያሕል ይቆያል ?የሚለውን በእርግጠኛ ሆኜ ለማንም ማስተማመኛ መስጠት አልችልም››
‹‹ይገባኛል…የእርሶ ግምት ወደፊት በግንኙነታችሁ እንቅፋት ሊሆነ ይችላል ብለው የሚያስብት ወይም የሚያሰጋዎት ነገር ምንድነው?››
‹‹ይሄማ ግልፅ ነው…እንደምታየኝ እኔ እድሜዬ አምሳ ሞልቷል….ልክ እንደሀያ አመት ወጣት ላስደስተውና ፍላጎቱን ሁሉ በሚፈልገው መልክ ላሟላለት አልችልም..እሱ ደግሞ ከእንቡጦች ጋር መቅበጥና መዳራት ለምዶል፡፡››
‹‹ይሄውሎት ወ.ሮ ስንዱ ..ወሲብ ብቻውን ለወንድ ልጅ በቂ አይደለም፣አንድ ሚስት ለባለቤቷ ሌላ ማንኛውም ሴት ልትሰጠው የምትችለውን ነገር ሊኖራት ያስፈልጋል።ወንድ

በወሲብ ስለተመቸችው ብቻ ከአንድ ሴት ጋር ለዘላለም አብሯት አይኖርም። ወንድ ልጅ ሚስቱ ክብር እንድትሰጠው ይፈልጋል።››
‹‹አዎ ..እሱስ ትክክል ነህ …በዚህ በዚህ ብዙ ጥፋት አለብኝ..ሁልጊዜ እሱን መከራከርና ንግግሩን ሁሉ በመቃረን ማሸማቀቅ ሆነ ብዬ የማደረገው የዘወትር ድርጊቴ ነው፡፡››
‹‹አዎ…ወንድ ልጅ አንድ ገበያ ህዝብ ቢንቀው መታገስ ይችል ይሆናል ..የምታፈቅረውን ሴት ወይም የባለቤቱ ንቀት እና ችላ ባይነት የሚቋቋምበት ምንም አይነት ፅናት የለውም።‹ሴት የላከው ሞት አይፈራም› የሚባለው ለምን ይመስሎታል…አንድ ሴት የምታፈቅረውን ወንድ አክብራ አበረታታ በትህትና ምንም ነገር እዲያደርግላት ብትጠይቀው አይኑን ሳያሽ
ያደርገዋል ለማለት ተፈልጎ ነው››
‹‹ገባኝ ልጄ ይሄ የእኔ ትልቁ ስህተት ነው..እንደማርመው ቃል ገባልሀለው››
‹‹ጥሩ…እንግዲህ ቅድም እንዳሉት ወሲብ ላይ ያሎትን ነገር ብዙም አይጨናነቁበት …በመሀከል ያለ ጥልና ጭቅጭቅ ሲወገድ..ፍቅርና መተሳሰብ በቦታው ሲተካ የወሲብ ችሎታውም ሆነ አምሮቱ አብሮ ይመጣል…ደግሞ ያው ሁላችንም እንደምናውቀው ወሲብ እርካሽና ገንዘብ ያለው ሁሉ ሊገዛው የሚችል ነገር ነው።አንድ ሚስት  ስብዕናዋን ከወሲብ በላይ በሆኑ ነገሮች መገንባትና ማነፅ አለባት። ወንድ ልጅ እራሷን በሜካፕ ዲኮር ከምታደርግ ሴት ይልቅ ለችግሮች መፍትሄ የማመንጨት ብልሀት ባላት ሴት ይሳባል።አንድ ሴት ወንዶች የሚፈልጉትን ነገር ሳይሆን ሁል ጊዜ ባሏ የሚፈልገውን ነገር ማድረግ አለባት፡፡" በፍቅር የተሠራ ኃጢአት ፍቅር ከሌለበት አምልኮ ይበልጣል›ይባላል፡፡››
‹‹አልገባኝም ይህ ደግሞ ምን ማለት ነው?››
‹‹ይህ ማለት ወንዶች ሁሉ ወንድ በመሆናቸው ብቻ አንድ አይነት አይደሉም ለማለት ነው…አንድ ሚስት የባለቤቷን ልዩ ባህሪዎች ጥንቅቅ አድርጋ ማወቅ አለባት…ምን ይወዳል..?ምን ይጠላል…?ምን አይነት ምግቦች ይመቹታል…?ምንአይነት መጠጥ ያስደስተዋል…?ሚስቱ ምን አይነት ልብስ ስትለብስ ፊቱ ይፈካል…?የመሳሰሉትን ዝርዝር ባህሪዎችኑ ማወቅና ያንን ታሳቢ አድርጎ መንቀሳቀስ ይጠበቅባታል…ይሄ ለወንዱም ይሰራል፡፡ አንድ ሚስት እሷ ሴት ስለሆንች ባለቤቷም ሌላ ሴት እንደሆነ ማሰብ የለባትም።በሁለቱ መሀከል የማይካድ የጻታ ልዩነት አለ፡፡የፃታ ልዩነት ማለት ደግሞ የባህሪ እና የፍላጎትም ልዩነትም ጭምር ማለት ነው።

‹‹አዎ ..እሱስ እውነትህን ነው››
‹‹አዎ..ለምሳሌ ባሎች ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን ሚስታቸው በቀጥታ በእጆቾ ያበሰለችውን ምግብ መመገብ በጣም ያስደስታቸዋል… ሌላው ሁል ጊዜ ችግር እያወራች
ከምታማርር እና ሁሉን የውጭ ስራዎች ባሏ እንዲሰራቸው ከምትጠብቅ ሴት ይልቅ ጀግና እና ችግርን ፊት ለፊት ለምትጋፈጥ ሴት ክብር አለው። ››
‹‹አሁን  ምን  እንደተረዳሁ  ታውቃለህ..አንዳንድ  ጥቃቅን  ናቸው  ብለን  ትኩረት የማንሳጣቸው ነገሮች በህይወታችን ትልቅ ዋጋ እንደሚያስከፍሉን ነው፡፡››
‹‹አዎ ትክክል ብለዋል››
‹‹አግብተሀል እንዴ?››
ድንገት ከርዕሳቸው ውጭ የሆነ ጥያቄ ስለጠየቁት ድንግርግር አለው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

13 Nov, 17:16


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_ስምንት


#ዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰለሞንና በፀሎት በስልክ እያወሩ ነው፡፡

‹‹ለመሆኑ የት ነው ያለሽው?››ሲል ጠየቃት

‹‹ምነው ጠየቅከኝ?››

‹‹አይ ..እንዲሁ ደህንነትሽ አሳስቦኝ ነው….ምን አልባት የማይመች ቦታ ካለሽ ልረዳሽ እችላለው፡፡››

‹‹ምነው ወደቤትህ ወስደህ ደብቀህ ልታኖረኝ አሰብክ››

‹‹ምነው ..ችግር አለው.?.የእውነት የማይመች ቦታ ካለሽ ንገሪኝ››

‹‹አሁን ካለሁበት ቦታ የተሻለ ሊመቸኝ የሚችለው ምን አልባት ገነት ነው….እሱንም ደግሞ ስላላየሁት እርግጠኛ አይደለሁም››

‹‹እንዴ…ከእናትና  አባትሽም  ቤት  የተሻለ  ቦታ  ነኝ  ነው  የምትይኝ…ይሄንን  ማመን አልችልም፡ ››

‹‹ነገርኩህ እኮ…››

‹‹‹እ ..ገባኝ››

‹‹ምኑ ነው የገባህ?››

‹‹ከእናትና አባት ቤት በበለጠ የሚመች ቦታ የፍቅረኛ ቤት ነው››
‹‹በጣም ተሳስተሀል..አዲስ ቤተሰብ አግኝቼለሁ…አራት ናቸው..ሽማግሌ አባትና እናት፣አንድ ዋንድ ሴትና ወንድ ልጅ አላቸው..ሁለት ክፍል ሰርቢስ ውስጥ ነው የሚኖሩት፣ኑሮቸው ከእጅ ወደአፍ ነው… ፍቅራቸው ግን ሞልቶ የፈሰሰ ነው….ለዘላለም ልጃቸው አድርገው ተቀብለውኛል…ከአሁን ወዲህ ባለው ህይወቴ ሙሉ አነሱ ወላጆቼ እና ቤተሰቦቼ እንደሆኑ እንዲቀጥሉ ምንም ነገር አደርጋለው››

‹‹የሚገርም ነው….እናትና አባትሽ ይሄንን ንግግርሽን ቢሰሙ ልባቸው የሚሰበር ይመስለኛል፡፡››
‹‹እንግዲህ ምንም ማድረግ አልችልም…በእነሱ ስህተት ነው ከቤት የወጣሁትና እነሱን ያገኘሁት…አሁን አግኝቼ በደንብ አጣጥሜቸዋለው…እና ወደቤት ብመለስ እንኳን ወላጆቼን ከእነሱ ጋር ነው ማነፃፅራቸው…እና ለእነሱ ቀላል የሚሆንላቸው አይመስለኝም››
‹‹….ለመሆኑ ማንነትሽን ያውቃሉ?›
‹‹አይ አያውቁም.. እኔ ለእነሱ እናቷ የሞተችባት እና የእንጀራ አባቷ ሰክሮ በለሊት ሊደፍራት ሲል አምልጣ የወጣች ሚስኪን ሴት ነኝ››
‹‹ይሄንን ታሪክ አንቺ ነሽ የፈጠርሽው?››

‹‹አዎ…..››
‹‹የምትገርሚ ልጅ ነሽ ..እኔጋም መጥተሸ ተመሳሳይ ታሪክ ብትነግሪኝ አምኜ ልረዳሽ መሞከሬ አይቀርም ነበር››
‹‹የእነሱ እኮ መርዳት አይደለም….እናትና አባት መሆን ነው…..እንደልጃቸው መቀበል››
‹‹ የእውነት አዲሶቹን ቤተሰቦችሽን እኔ እራሱ ለመተዋወቅ ጓጓሁ› ›
‹‹መጓጓትህ ትክክል ነህ››
‹‹ነገሮች ከተስተካከሉ በኃላ ታስዋውቂኛለሽ ብዬ ገምታለው››
‹‹መጀመሪያ እስኪ እኛ ለመተዋወቅ ያብቃን››
‹‹እንዴ እኛኮ በደንብ ተዋወቅን፣ለአመታት የማውቅሽ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው..ያው አካል ለአካል አልተገናኘንም ብዬ ነው፡፡››
‹‹ባክሽ የስልኬ ጋላሪ ባንቺ  ፎቶዎ ተጨናንቆል  ››ብሎ ያልጠበቀችውን አስደንጋጭ ነገር ነገራት፡፡
‹‹እንዴ በምን ምክንያት?››
‹‹እንዴ ..ደንበኛዬ አይደለሽ?››
‹‹እና የሁሉንም ደንበኞችህን ፎቶ ትሰበስባለህ ማለት ነው?››
‹‹ቆንጆ እና የተለየ የሆኑትን ..አዎ››
‹‹በቻይንኛ ቆንጆ ነሽ እያልከኝ ነው፡፡››
‹‹እ..ምነው አይደለሽም እንዴ?››
‹‹እኔ እንጃ ….ለማንኛውም ደስ የሚል ስሜት እንዲሰማኝ አድርገሀል…እና እኔስ የአንተን ፎቶ የማግኘት መብት ያለኝ አይመስልህም?››

‹‹አይ..አዲሶቹን ቤተሰቦችሽን እንድምታስተዋውቂኝ ቃል ካልገባሽ የምታገኚ አይመስለኝም››
‹‹አዲሶቹን ቤተሰቦቼን….እኔ እንጃ ..ስለምሰስታቸው የማደርገው አይመስለኝም››
‹‹‹ትገርሚያለሽ…፣ዋናዎቹን ቤተሰቦችሽን እኮ ተቆጣጥሬቸዋለው…..ለማንኛውም ይህን የመሰለ ቤተሰብ ስላገኘሽ ደስ ብሎኛል….ይሄውልሽ በህይወት ውስጥ ሶስት አይነት ሰዎች አሉ፡፡ቅጠል የሆኑ ሰዎች… ቅርንጫፍ የሆኑ ሰዎችእና… ስር የሆኑ ሰዎች።ቅጠል የሆኑ ሰዎች ወቅትንና ሁኔታዎችን ጠብቀው ወደ ህይወትሽ የሚገብ ናቸው።ደካሞች ስለሆኑ በእነሱ ተፅዕኖ ስር ፈፅሞ እንዳትወድቂ። ከአንቺ የሚፈልጉትን የሆነ ነገር ስላለ ነው ወደህይወትሽ የሚመጡት... የመከራ ንፍስ በህይወት ዙሪያ ሲነፍስ መርገፍ ይጀምራሉ።እነዚህ ሰዎች አንቺን ማፍቀር የሚቀጥሉት በዙሪያሽ ያሉ ነገሮች ጥሩ እስከሆኑ ጊዜ ብቻ ነው።ንፋስ እንደመታው የወየበ ቅጠል ከላይሽ ላይ ተዘንጥለው ይረግፋሉ። ቅርንጫፍ ሰዎች ደግሞ በአንፃራዊነት ጠንካሮች ናቸው ግን ልትጠነቀቂያቸው ይገባል።ህይወት ጨከን ስትል መገንጠላቸው አይቀርም። ምክንያቱም ጠንከር ያለ የህይወት ጫና የመሸከም አቅም የላቸውም።ነገሮች ጨለምለም ሲሉ እና ተስፋም የሌላቸው ሲመስሉ ጥለውሽ ዞር ለማለት አያመነቱም። ሌሎቹ ልክ እንደአንቺ አዲሶቹ ቤተሰቦች ስር የሆኑ ሰዎች ናቸው። እነዚህ በህይወትሽ በጣም አስፈላጊ ሰዎች ናቸው።ለመታየት ብለው የሚሰሩት ስራ የለም።በመከራሽም በደስታሽም ጊዜ አብረውሽ ናቸው።አስከሞት የታመኑሽ ናቸው።ሲያፈቅሩሽ በነፃ ምንም መልስ ካንቺ ሳይጠብቁ ነው፣እንደዚህ አይነት አንድ ወይም ሁለት ሰው ከጎንሽ ማግኘት የህይወት ዘመን ሽልማት ነው፡፡
‹‹ጥሩ አድርገህ ገልጸኸዋል፡፡እነሱ ብቻ ሳይሆኑ፣አንተም ለእኔ ስር ነህ…በቃ ቸው…ነገ እንደዋወላለን፡፡››
‹‹ቸው …..ደህና ሆኚ››ብሎ ስልኩን ከዘጋ በኃላ …ባለበት ቆሞ ትካዜ ውስጥ ገባ..ይህቺን ልጅ በተመለከተ የተለየ አይነት ኬሚስትሪ በሰውነቱ እየተረጨ ነው….ነገሮች ወዴት እያመሩ ነው?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡

በማግስቱ……
በፀሎት ከሞላ ጎደል ጤንነቷ እየተመለሰ ነው…አረ እንደውም ድናለች ማለት ይቻላል..የእግሯ ስብራት ሙሉ በሙሉ ተጠግኖ በደንብ መራመድ ችላለች..የፊቷ ቁስለትም ሙሉ በሙሉ ጠጓል..አሁን ብቸኛ ችግሯ ፊቷ ላይ ተሸነታትሮ የሚገኘው ጠባሳ ብቻ ነው….እንግዲህ ግማሽ ፊቷን ባደረሰው በተበታተነው ጠባሳ ውስጥ ምን ያህሉ እንድሚጠፋና ከበፊት ቆዳዋ በቦታው እንደሚመለስ ምን ያህሉ ደግሞ እንዳዛው እንደሚቀር ምንም የምታውቀው ነገር የለም…ያንን ለማወቅ በርከት ያሉ ተጨማሪ የማገገሚያ ቀኖች ያስፈልጋታል…ከዛ በኃላ የቆዳ ስፔሻሊስቶች ጋር ሔዳ ሰርጀሪ መሰራትም የግድ ያስፈልጋት ይሆናል….ለጊዜው ያ እያሳሰባት አይደለም…‹‹እሱን ጊዜው ሲደርስና ሁሉ ነገር ተስተካክሎ ወደቤት ከተመለስኩ በኃላ አስብበታለው››ብላ ወስናለች….አሁን ከጎኗ አቶ ለሜቻ ቁጭ ብለው እያጫወቷት ነው፡፡
‹‹ለልጆቾህ ያለህ ፍቅር ያስገርመኛል››
‹‹አይ ልጄ ሁሉም ወላጆች እኮ ልጆቻቸውን አብዝተው ይወዳሉ…››በትህትና መለሱላት፡፡
‹‹እሱን ማለቴ አይደለም..የእናንተ የተለየ ነው…አይኖችህ ከልጆቾህ ላይ አይነቀሉም….ሙሉ ትኩረትህ ልጆቾህ ላይ ነው..ስለእለት ውሏቸው ታውቃለህ….ጥዋትና ማታ አብረሀቸው ባንድ መሶብ ቀርበህ ሁለቱንም እያጎረስክ ነው የምትበላው፣ብዙ ብዙ ነገር…››
‹‹ልጄ ወድጄ አይደለም እኮ…. እንደምትይው እኔ አባትሽ በብዛት ተትረፍርፎ ያለኝ ፍቅር ነው…ገንዘብ ኖሮኝ ይሄን ስሩ ብዬ መቋቋሚያ..ወይም መነገጃ ጥሪት አልሰጣቸው….ሁል ጊዜ ታዲያ ይሄንን ነገር በምንድነው የማካክሰው ብዬ ሳስብ አንድ የማገኘው መልስ…ጊዜዬንና ፍቅሬን ሳልሰስት መስጠት ነው..አዎ ቢያንስ በዛ ነው ልክሳቸው የምችለው፡››
‹‹ግን እንሱ ምን ያህል እድለኞች መሆናቸውን ያውቃሉ?››

‹‹አይ እነሱ ሳይሆኑ እኔ ነኝ እድለኛ….ምንም ባላደርግላቸው እንኳን ማንም ፊት በኩራት አባዬ ብለው ይጠሩኛል፡፡በቀደም ለሊሴ ይሄ ፌስቡክ ነው ምን በምትሉት ነገር ላይ በተንዠረገገ ፂሜንና በጎፈረ ፀጉሬ የተነሳሁትን የተጎሳቆለ ፎቶ ለጥፋ አባዬ መልካም

አትሮኖስ

13 Nov, 17:16


​​የአባቶች ቀን ..እወድሀለው… ዘላለም ኑርልኝ› ብላ የለጠፈችውን ሰው አሳየኝ…አየሽ እኔ ጎስቆላ አባቷን አለም ፊት በአደባባይ ይዛ ለመውጣት አልተሳቀቀችም..እንደውም በኩራት ነበር ያደረገችው…..ከአራት አመት በፊት ምን ሆነ መሰለሽ..እኔ አባትሽ የተቀደደና ያደፈ ቱታ ለብሼ አንድቤት ጣሪያላይ ወጥቼ ቆርቆር እየጠገንኩ ነበር…ስራዬን ጨርሼ ከጣሪያው በመሰላል በመውረድ ላይ እያለሁ እታች ትላልቅ ሱፍ ለባሽ ሰዎች ቤቱን እየተመለከቱት ነው…ከመሀከላቸው ልጄ በሬዱ ነበረችበት…ለካ ያ ቤት የባንክ እዳ ኖሮበት ጫረታ ላይ ሊያወጡት ከባንክ የመጡ የስራ ኃላፊዎች ነበሩ ..የልጄ ሀለቃዎች…ልክ ልጄን እንዳየኋት ተመልሼ ወደላይ መውጣት ጀመርኩ..ለካ ልጄም በዛው ቅፅበት አይታኝ ኖሮ‹‹…አባዬ
..አባዬ ና አንዴ ውረድ››ስትል የት ልግባ….ምርጫ ስላልነበረኝ ወደታች ወረድኩ…ቆሻሻዬን ሳትጠየፍ ጉስቁልናዬን ከቁም ነገር ሳጥቆጥር አገላብጣ እየሳመች ወደሀለቆቾ ይዛኝ ሄደችና…‹‹አባቴ ነው ..ተዋወቁት ብላ አስተዋወቀችኝ…አክብራ አስከበረችኝ››እነሱን ከሸኘሁ በኃላ ለብቻዬ ገለል ብዬ እንደህፃን ልጅ አለቀስኩ…እና ምን ልልሽ ነው እኔ ነኝ እድለኛው፡፡››
‹‹አይ ጋሼ…እኔ አንተ አባቴ ብትሆን በጀርባዬ አዝዬ ድፍን አዲስአበባን እዞር ነበር….››
‹‹አይ አንቺ…አሁንም አባትሽ ነኝ ..አይደል እንዴ?››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው ..አንተ ያደረክልኝ…ግማሹን አባቴ አድርጎልኝ አያውቅም፡፡ማለቴ አሁን እየተነፈስኩ ያለሁት ባንተ ደግነት ነው››
‹‹አይ አንቺ ልጅ….››
‹‹ጋሼ››
‹‹አቤት ልጄ››
‹‹አንድ ነገር ልጠይቅህ ነበረ.. ግን ፈራሁ››
‹‹እንዴ ..እኔ እኮ አባትሽ ነኝ ምን ያስፈራሻል?››
‹‹እንተን.ማለቴ ያው በህመሜ ምክንያት ረጅም ጊዜ ስተኛና ከቤት ሳልወጣ ስለቆየሁ ተጨናንቄያለው…ለተወሰነ ቀን ከለሊሴ ጋር ላንጋኖ ወይም የሆነ ቦታ ሄደን ትንሽ ተዝናንተን ብንመጣ ብዬ ነበር››
‹‹ከለሊሴ ጋር ስራዋስ ልጄ?››

‹‹አልሰማህም እንዴ….ሀለቃዋ እኮ ለስራ ሌላ ሀገር ለአንድ ወር ስለሄደ ፍቃድ ሰጥቶታል፡፡››
‹‹እንደዛ ነው››፣አሉና መልስ ሳይሰጡ ወደትካዜ ውስጥ ገቡ…ምን ብለው ሁለት የደረሱ ሴቶችን እንደሚፈቅዱላቸው ምን ብለውስ እንደሚከለክሎቸው ግራ ገባቸው››
‹‹በፀሎትም መልሱን ለመስማት አፏን ከፍታ በጉጉት መጠበቋን ቀጠለች››
‹‹የእኔ ልጅ ያልሽው ትክክል ነሽ..አየር መቀየርና ትንሽም ዘና ማለት አለብሽ…ግን ሁለታችሁም ሴቶች ናችሁ …ለምን ወንጪ አትሄዱም››
‹‹እንዴ ጋሼ..ደስ ይለኛል….ቦታው አሪፍ ይመስለኛል››
‹‹አዎ ቦታውማ ገነት በይው..ግን ከቦታውም በላይ ትውልድ አካባቢዬ ነው..አሁንም ዘመዶቼ እዛ አሉ..ወንድሞቼ እህቶቼ ብዙ ናቸው..ለሊሴም ቦታውን በደንብ ታውቀዋለች..እዛ ከሄዳችሁ እኔ አባታችሁ ምንም አላስብም….የፈለጋችሁትን ያህል ቀን መቆየት ትችላላችሁ..ግን የእናትሽ የጽዋ ማህበር የዛሬ ሳምንት ነው..ከዛ በፊት እንድትሄዱ አትፈቅድላችሁም››
‹‹አመሰግናለው ጋሼ..››ከመቀመጫዋ ተነሳችና አቅፋቸው ግንባራቸውን ሳመቻቸው፡፡››
‹‹ልጄ አመሰግናለው››
‹‹እኔ ነኝ እንጂ ማመሰግነው››
‹‹አይ አመሰግናለው ያልኩሽ ሁል ጊዜ በድርጊቶችሽ ልጄ በሬዱን ስለምታስታዊሺን ነው..አፈሩን ገለባ ያድርግላትና እሷም እንደእዚህ አንደአንቺ የሆነ ነገር ጠይቃኝ እሺ ካልኳት አቅፋ ትስመኝ ነበር….››
‹‹ይቅርታ ጋሼ እሷን እንድታስታውስ ስላደረኩ››
‹‹አይ…እንዳስታውሳት ስለምታደርጊኝ ሚከፋኝ መሰለሽ….?ልጄን መቼም መርሳት አልፈልግም…ደግሞ የምትረሳም ልጅ አይደለችም…የእኔ በሬዱ ቶሎ ተወልዳ በፍጥነት አድጋ…በጮርቃነቷ በስላ..በችኮላ ጥሩጥሩ ነገሮችን ሰርታ እኔ አባቷን አስደስታ የሞተች ድንቅ ልጅ ነች.…በይ የሆነች ለቅሶ ቢጤ አለችብኝ፣ደረስ ብዬ ልምጣ..እስከዛ ከእናትሽ ጋር

ተጫወቺ…››አሉና የሚተናነቃቸውን እንባ እንደምንም ተቆጣጥረው ወደውስጣቸው በመመለስ ከመቀመጫቸው ተነሱ፡፡
‹‹እሺ ጋሼ…እንዳትቆይ››
‹‹አልቆይም ልጄ..››አሉና ኮፍያቸውን ከጠረጴዛ ላይ አንስተው ጭንቅላተቸው ላይ አስተካከለው እያደረጉ ቤቱን ለቀው ወጡ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

12 Nov, 20:58


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሰባት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ይዘውት የሄዱት ቦታ ከቢሾፍቱ ከተማ በባቦጋያ ሀይቅ አካባቢ ከከተማው ወጣ ብሎ የሚገኝ ቪላ ነው፡፡ይህ ቪላ ቤተሰቡ ከውጥረት ረገብ ለማለት ሲፈልግ የሚገለገልበት ስፋራ ነው፡፡ለአለፉት አንድ አመት ከግማሽ ማንም ዝር ብሎበት አያውቅም ነበር፡፡ሰለሞን ስፍራውን…»

አትሮኖስ

12 Nov, 17:21


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ይዘውት የሄዱት ቦታ ከቢሾፍቱ ከተማ በባቦጋያ ሀይቅ አካባቢ ከከተማው ወጣ ብሎ የሚገኝ ቪላ ነው፡፡ይህ ቪላ ቤተሰቡ ከውጥረት ረገብ ለማለት ሲፈልግ የሚገለገልበት ስፋራ ነው፡፡ለአለፉት አንድ አመት ከግማሽ ማንም ዝር ብሎበት አያውቅም ነበር፡፡ሰለሞን ስፍራውን ሲያይ ከውበትም ሆነ ከፀጥታ አንፃር ሲታይ ሙሉ በሙሉ እሱ እንደሚፈልገው አይነት ሆኖ ነው ያገኘው፡፡አንድ ሺ ካሬ ሜትር በላይ የሚሆን ቅፅር ግቢ ነው፡፡መሀከል ላይ ግዙፍና ባለግርማ ሞገስ ጥንታዊ ግን ደግሞ ጥሩ ይዞታ ላይ ያለ ግዙፍ ቪላ ቤት አለበት…ግቢው ውስጥ እድሜ ጠገብ ግዙፍ ባለግርማ ሞገስ የባህር ዛፍና የጥድ ዛፎች ስብስባ ላይ እንደተቀመጠ ታዳሚ እዚህም አዛም ዙሪያውን ተሰራጭተው ይታያሉ…ገና ግቢውስጥ ገብተው እንዳቆሙ የቤት ጠባቂዎች በልና ሚስቶች በፍጥነት መጥታው መኪናዋ አጠገቡ ቆሙ፡፡መኪናዋን ሲነዳ የነበረው እራሱ ሰሎሞን ስለነበረ….ሞተሩን

አጠፋና ቀድሞ ወረደ…አቶ ኃይለመለኮትን ወ.ሮ ስንዱም ወረዱና ከጠባቂዎቹ ጋር ሰላምታ መለዋወጥ ጀመሩ…ከዛ ቀጥታ ወደ ቤት ነው የገቡት….ቀድመው ደውለው ስለነበር..እቤቱ ምሉ በሙሉ ፀድቶና የእነሱም መኝታ ክፍል ተዘጋጅቶ ነበር የጠበቃቸው….
ታፈሰ ‹‹ጋሼ ባዘዙኝ መሰረት ሶስት ክፍል ለመኝታ አዘጋጅቼያለው…ይሄው እርሶ እዚህ ግቡ….እትዬ ደግሞ ቀጥሎ ያለው …ወንድም አንተ ደግሞ የፊት ለፊተኛው ክፍል…..ድንገት ስለሆነብን ሁሉንም ነገር ማዘጋጀት አልቻልንም….የጎደለውን ንገሩኝና ከተማ ወጣ ብዬ ገዝቼ አሟላላሁ››
አቶ ሃይለመለኮት ወደሰለሞን እያመለከቱ‹‹ተፈሰ…ይሄውልህ እዚህ 15 ቀን ነው የምንቆየው….በዚህ 15 ቀናት ውስጥ የእኛም ሆነ የአንተ ሀለቃ እሱ ነው….ምንም ነገር ቢያዝህ እሱ ያለውን ነው የምታደርገው…እኛም እንደዛው››ሲሉ መመሪያ አስተላለፉ፡፡
ታፈሰ…የአቶ ኃይለልዕልን ንግግር ከበፊት ቆፍጣና ባህሪያቸው ጋር አልሄድ ስላለው ..ግራ በመጋባት አፍጥጦ ያያቸው ጀመር…እሱ እንደሚየውቀው እኚ ግዙፍ አዛውንት ለሰው ምንም ሊሰጡ ይችላሉ የአዛዥነት ቦታቸውን ግን ፈፅሞ ሸርፈው እንኳን ለሌላ ሰው ይሰጣሉ ብሎ ማመን ይከብደዋል፡፡
‹‹ታፈሰ ..ሰምተኸኛል…የሁሉ ነገር አዛዣችን እሱ ነው››ደገሙለት፡፡
‹‹አዎ ..ገባኝ ጌታዬ…እንዳሉት ይደረጋል››
‹‹አሁን ሁላችንም ወደክፍላችን እንግባና ትንሽ አረፍ እንበል ..አይደል?››ወ.ሮ ስንዱ የሰለሞንን አይኖች በልምምጥ እያዩ ጠየቁ፡፡
ቆይ አንዴ ክፍላችሁን ልይ ብሎ..ለአቶ ኃይለልኡል የተመደበውን ከፍቶ አየው፡፡ቀጥሎ የወ.ሮ ስዱን ከፈተና አየው፡፡‹‹ጥሩ በቃ ግቡና እረፉ››
ሁለቱም ገቡና የየራሳቸውን ክፍል ዘጉ
‹‹አንተም ወደክፍልህ ግባ ጌታዬ..እኔ ደግሞ እቃችሁን ከመኪና ላውርድ››
‹‹ቆይ አብሬህ ልምጣ››ብሎ ተከተለው፡፡የታፈሰ ባለቤት ለእንግዶቹ ምግብ እያበሰለች ስለነበር ታፈሰ እቃዎቹን ማለት ይዘው የመጡትን አስቤዛ እና ሻንጣዎች ሲያወርድና ወደቤት ሲያስገባ ሰሎሞን አገዘው፡፡እንደጨረሱ፡፡‹‹ተለቅ ያለ ክፍል የለም?››ሲል ጠየቀው፡፡

‹‹ምን አይነት ክፍል…ማለቴ ለምን የሚሆን?››
‹‹ለመኝታ ቤት የሚሆን ..ሁለት አልጋ የሚያዘረጋ››
‹‹ቆይ ..ኮሪደሩ መጨረሻ ላይ ያለው ክፍል ሰፋ ይላል››
‹‹ማየት እችላለሁ?››
‹‹አዎ ይቻላል….››ብሎ ይዞት ሄደና ከፈተለት…ሰለሞን ወደውስጥ ዘልቆ ሳይገባ በራፉ ላይ በመቆም አንገቱን ወደውስጥ አስግጎ ተመለከተው….አቦራ የጠጣና ለብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ያልዋለ ቢሆንም የሚፈልገው አይነት ክፍል ነው፡፡››
‹‹ታፈሰ ይሄንን ክፍል በአስቸኳይ ልታስፀዳልኝ ትችላለህ….?››
‹‹እችላለሁ..አፀዳዋለው››
‹‹አይ ብቻህን ይከብድሀል..ሰው ቅጠርና በፍጥነት ወለሉም ግድግዳውም ይፅዳ….ውስጥ ያሉት እቃዎችም ወደሌላ ክፍል ይዘዋወሩ››
‹‹እሺ››
ተሰናብቶት ንፁህ አየር ሊቀበልና እግረመመንገዱን አካባቢውን ለመቃኘት ወጥቶ ሄደ፡፡
///
በማግስቱ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ ሁለቱንም የማይጣጣሙ ባለትዳሮችን አንድ ክፍል ጎን ለጎን እንዲቀመጡ አደረገና እሱ ከፊት ለፊታቸው ተቀመጠ..ጉሮሮውን አፀዳዳና የመግቢያ ንግግሩን ጀመረ
‹‹በሰዎች መካከል ለተለያየ አለማ ተብለው የሚደረጉ የእርስ በርስ ጉድኝቶችና ቁርኝቶች አሉ፡፡ከነዛ መካከል ግን በጣም ውስብስቡ የጠበቀውና የጠለቀው ግንኙነት በአንድ ወንድ እና ሴት መካከል የሚፈጠር የጋብቻ ጉድኝት ነው፡፡በጋብቻ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ሁሉ ጊዜ ቀላል የተባለ መንገድ አይገኝም….አንዱ ጋብቻ ውስጥ የሚፈጠረው ችግር ከሌላው ጋብቻ ችግር በአይነትም በይዘትም ፍፁም የተለየ በመሆን ችግሩን ለማስተካከል የሚወሰደውም እርምጃ የዛኑ ያህል የተለያ ነው፡፡በዛ ላይ ሁሉም ችግሮች እዲፈቱ  በጥንዶቹ  መካከል  ስክነት፣  ትዕግስትን፣ጥረትን  እና   እራስ  መግዛትን

ይጠይቃል፡፡አሁን ልብ በሉ ፣ጥረታችን በመካለላችሁ ያላውን ግጭትና ጭቅጭቅ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይደልም..አይ እንደዛማ አይሆንም እናንተ ሰው ናቸው፣ሁለት ሰዎች ደግሞ በአንድ ጣሪያ ስር አብረው እስከኖሩ ድረስ በሆነ ነገር መነጋገራቸውና በነገሩ ላይ የተለያየ ተቃራኒ ሃሳብ ማንፀባረቃቸው አይቀርም…ስለዚህ መነጋገርና መጨቃጨቃችሁ ኖርማል ነው…አሁን ምንድነው ምናደርገው በማንኛውም ጉዳይ ላይ አለመግባባት ተከስቶ ስትነጋገሩ በምን መልኩ ነው ኮምንኬት የምታደርጉት..?ነገሩን ማስረዳትና ማሳመን ላይ ነው ትኩረታችሁ ወይስ ያንን ምክንያት አድርጎ በስድብና በዘለፋ ማጥቃትና ልብ መስበር…አያችሁ ትልቁ ችግር መጋጨታችን ሳይሆን በያንዳንዱ ግጭታችን አንዳችን ለሌላቸውን የልብ ቁስለትና የነፍስ ህመም መስጠታችን ነው፡፡ማጥፋት ያለብን እርስ በርስ መወጋጋቱን ነው…አንዳችን ሌላችን ላይ በምንም አይነት ሰበብ የሚያቆስል ጦር አስበን አይደለም አምልጦን እንኳን መወርወር የለብንም፡፡
እርስ በርስ ከፍ ባለ ቃላት በተነጋገራችሁ ቁጥር ደግሞ እየተጣላችሁ መሆኑን አታስቡት..መጣላት ቃሉ እራሱ አሉታዊ ነው፡፡እየተጣላችሁ ሳይሆን በጋለ ስሜት እየተነጋገራችሁ ነው፡፡በቃ እንዲህ ነው ማሰብ ያለባችሁ፡፡እንደዛ ካሰባችሁ ቀጥታ ችግሩ በጋለ ስሜት መነጋገራች ብቻ ስለሆነ ስሜታችሁን በማረጋጋት ነገሩን ትፈታላችሁ፡፡እየተጣላን ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ግን ገና ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው ወይም ሽማግሌ ልትፈልጉ ነው፡፡ልብ በሉ ጮክ ብሎ መናጋገር ሁል ጊዜ መጣላት አይደለም ..አዎ አብዛኛውን ጊዜ በጋለ ስሜት መነጋገር ነው፡፡ሌላው በምንም አይነት ሁኔታ ንግግራችሁ ሰው ፊት አይሁን፡፡የምንወደው ሰው ላይ ያለንን ቅሬታ ብቻውን በሆነበት ጊዜ ነው መናገር ያለብን…እንደዛ ሲሆን ነው ውጤታማና ጥፈቱን ለማረም ፍቃደኛ የሚሆነው…ወቀሳው..ሰው ፊት ሲሆን ግን ሰውዬው የበለጠ በእኛ ቅሬታ እንዲያድርበት መንገድ ያመቻቻል፡፡
‹‹እንግዲ ሁላተችሁም እንደምታውቁት አሁን ለእኛ እዚህ መገኘት ዋናዋ ምክንያት በፀሎት ነች፡፡እኔ በስራ በተለይ ከሀገር ውጭ በነበርኩበት ጊዜ በጣም ብዙ ባለትዳሮችን አማክሬያለሁ ትዳራችውም መካከል ያለውን ችግር በመተጋገዝ ለመፍታት ችያለሁ....በብዙዎችም ረክቼለው..ከብዙ ቤተሰቦች ጋርም እቤተሰብ ለመሆን ችያለው….ግን እመኑኝ እንዲህ እንደእናነተ የተለየ ጉዳይ ገጥሞኝ አያውቅም››
‹‹የተለየ ስትል?››

አትሮኖስ

12 Nov, 17:21


‹‹እስከአሁን ወደእኔ መጥተው የሚያናግሩኝ ከሁለት አንዱ ማለቴ ባልዬው ወይም ሚስትዬው ናቸው….የእናንተ ግን ልጃችሁ ነች ያናገረችኝም የቀጠረችኝም፡፡››
‹‹አዎ እሱስ ትክክል ነህ››
‹‹ስለዚህ አሁን ስራችንን ስንጀምር እሷን እያሰብን መሆን አለበት ፡፡በፍቅር የታነፀ ትዳር ውስጥ ያላደጉ ልጆች በመጨረሻ በስነ-ልቦናም ሆነ አካላዊ በሽታ እንደማያጣቸው የተረጋገጠ ነው። ልጅ ስናሳድግ ጥሩ ልብስ ፣ጥሩምግብና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት እንዲያገኙ መጣር ብቻ ሳይሆን የተሞላ ፍቅርም እየመገብን ማሳደግ እንዳለበት እንደወላጅ ግንዛቤው ሊኖረን ይገባል።የመፈቀር እና የመፈለግ ስሜት ማጣት በከፍተኛ ሁኔታ የልጆችን በራስ የመተማመን ችሎታን ከመሸርሸሩም በላይ ለአእምሮ ውጥረትና ድብርትም እንዲዳረጉ ያደርጋቸዋል።ለልጆች በፍቅርና በእንክብካቤ ማደረግ ደስተኛ ሆኖ ለመኖር ብቻ ሳይሆን ጤነኛም ሆኖ ለመኖር በጣም አስፈላጊ ነገር ነው።በወላጆቹ የሚወደድ እና ወላጆቹም የሚወድት ልጆች በጣም ደስተኛ ናቸው።በፍቅር ውስጥ መኖር ጤነኛ ሆኖ ለመኖር እና የበሽታ የመከላከል አቅማችንን ለመጨመር እንደሚያግዝ በሳይንስ የተረጋገጠ ነው።ስለዚህ ልጆቻችን በፍቅር ታንፀው የመፈለግና የመወደድ ስነልቦና ኖሮቸው ማደግ አለባቸው፡፡ለዚህም ወላጆች ሁሉ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው፡፡፡ እንደውም እናንተ እድለኛ ናችሁ፡
‹‹እድለኛ ናችሁ ስትል?››
‹‹እንዴ በፀሎት እኮ በጣም የምትገርም ብስልና በቀላሉ የማትሰበር ልጅ ነች፣አብዛኞቹ በእሷ እድሜ ያሉ ልጆች በእንደዚህ አይነት ችግሮች ውስጥ ሲያልፉ ከፍተኛ ድብርት ውስጥ ይገቡና ለተለያዩ ሱሶች ይጋለጣሉ ..ከዛም አልፈው በህይወት ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ይገቡና እራሳቸውን ወደማጥፋት ይሄዳሉ….በፀሎት ግን ያደረገችው ከውጥረቱ ራሷን ዞር አድርጋ እናንተን ለመርዳትና ወደመስመር ለመመለስ መጣር ላይ ነው ያተኮረችው››
‹‹አዎ እውነትህን ነው …በልጄ ታላቅ ኩራት ተሰምቶኛል….ምንም ጭረት ሳይነካት ወደቤቷ እንድትመለስ ማድረግ ያለብኝን አደርጋለሁ..ማለት ሁለታችንም ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን አይደል ስንዱ?››
‹‹አዎ ትክክል ነህ…ለዛም አይደል እዚህ የተገኘነው››

‹‹እንግዲያው ጀመርን …ከአሁን በኃላ የምናወራውና የምንናገረው ሁሉ እየተቀዳ ነው.››.ብሎ አይፓዱን አስተካክሎ ተጫነውና ቦታውን ይዞ ተቀመጠ…››
ለሶስት ሰዓት ቀጠለ…..በመጀመሪያ ወ.ሮ ስንዱ አቶ ኃይለመለኮት ላይ ያላቸውን ቅሬታ እስከአሁን በደሉኝ የሚሉትን ነገር እንዲያወሩና አቶ ኃይለመለኮት ደግሞ ለደቂቃ እንኳን ሳያቆርጡ እንዲሰሙ አደረገ…በቀጣዩ ሰዓት ደግሞ አቶ ኃይለልኡል በተራቸው ሚስታቸው ላይ ያላቸውን ቅሬታ በዝርዝር እንዲናገሩ አደረገ……..ቀጣዩን አንድ ሰዓት ደግሞ እራሱ ሰሎሞን ጥያቄ እየጠየቃቸው ሁለቱም ተራ በተራ እዲመልሱ ተደረገና የጥዋቱ ክፍለጊዜ አለቀና ሶስቱም ተያይዘው ወደሳሎን ሄዱ ..ምሳው በስርአት ተዘጋጅቶ ስለጠበቃችው ሶስቱንም ጠረጴዛውን ከበው ፀጥታ በተጫነው ና እርስ በርስ በተፈራራ በሚመስል ሁኔታ ምሳቸው ተበልጦቶ አለቀ..ብና ተፈልቶ ስለነበረ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ንፋስ እየተቀበሉ ጠጡ
‹‹አሁን ለአንድ ሰዓት ያህል መኝታ ክፍላችሁ ገብታችሁ አረፍ በሉ….ሰዓት ሲደርስ እኔ መጥቼ ቀሰቅሳችኃላው››
እሺ ብለው ሁለቱም ከመቀመጫቸው ተነሱ..ሰለሞን ከኃላ ተከተላቸው….››መኝታ ቤታቸው እንደደረሱ ሊከፍቱ ሲታገሉ‹‹ይቅርታ ሳልነግራችሁ መኝታ ቤታችሁ ተቀይሮል..ተከተሉኝ››ብሎ ቀደማቸው፡፡
‹‹የማ…? የእኔም ነው የተቀየረው?››
‹‹አዎ ወ.ሮ ስንዱ….ሁለታችሁም ተከተሉኝ..››
ግራ በማገባት ሁለቱም በዝምታ ከኃላው ተከተሉት …የኮሪደሩ መጨረሻ ላይ ካለው በራፍ ሲደርስ ቆመና ከፈተው….‹‹ግቡ ››
‹‹ማ እኔ ነኝ እሷ?››
‹‹ሁለታችሁም››
እርስ በርስ ተያዩ…ቀጥሎ በጋራ እሱ ላይ አፈጠጡበት…አንድ ክፍል ውስጥ አብረው ከተኙ አስር አመት አልፏቸዋል..አሁን በአንዴ እንዴት….?ጉዳዩ ሁለቱንም እኩል ነው ያስበረጋጋቸው፡፡

ጫን ባለ የአዛዥነት ቃና‹‹እባካችሁ ግቡ››አላቸው
ምርጫ ስላልነበራቸው አቶ ኃይለልኡል ቀድመው ገቡ…ወ.ሮ ስንዱ ተከተሏቸው….ሁለቱም ጎን ለጎን ቆመው ክፍሉን ዙሪያ ጋባ ቃኙት …ሻንጣቸው ሆነ ጠቅላላ እቃቸው በየቦታው ተቀምጦል…ሁለት አልጋ ማዶ ለማዶ ግድግዳ ተጠግቶ ይታያል…፡፡
ያው ..ሁለት አልጋ አለ …ተነጋገሩና አንዳንደ አንድ ተካፈሉ …በቃ መልካም እረፍት..ሰዓቱ ሲደርስ መጥቼ ቀሰቅሳችኃላው››አለና ከክፍሉ ወጥቶ በራፉን መልሶ ዘግቶላቸው ወደገዛ ክፍሉ ሄደ፡፡
///
የሁለት ሰዓት የረፍት ጊዜ ከሰጣቸው በኃላ በጥዋቱ ጊዜ ባለው ፕሮግራም የቀረጸውን ወደኮምፒተሩ ገለበጠና ይዞ ወደእነሱ ክፍል አመራ…በስሱ ቆረቆረ…ወዲያውን ነበር የተከፈተለት፡፡
‹‹መጣህ ..?እየጠበቅንህ ነበር››
‹‹አዎ መጥቻለው››
‹‹ስንዱ ተነሽ..እንሂድ››አቶ ኃይለልኡል ተናገሩ፡፡
‹‹አይ ቆይ መሄድ አያስፈልግም ….እዚሁ እናድረግው››
‹‹ይሻላል ..እሺ ግባ..››ብለው በራፉን ለቀቁለትና ወደውስጥ በመመለስ አልጋቸው ጠርዝ ላይ ተቀመጡ ፡፡ወ.ሮ ስንዱም የራሳቸው አልጋ ላይ እንደተቀመጡ ነው፡፡
ወንበር ሳባና ከሁለቱ መካከል ተቀመጠና ኮምፒተሩን ጠረጳዛ ላይ አስቀመጠው፡፡
‹‹ይሄውላችሁ በትዳር ውስጥ ችግር መፈጠርና አለመስማማት የእናንተ ብቻ ሳይሆን የሚሊዬን ጥንዶች ችግር ነው..እመኑኝ ያልተስማማንበት ነገር ይህ ነው ያ ነው ብላችሁ ቀኑን ሙሉ ስትዘረዘሩ ብትውሉ የእናንተ ከሌላው ትዳር ውስጥ ከተፈጠረው ችግር የተለየ ሊሆን ይችላል እንጂ የባሰ ግን አይደለም፡፡ስሙኝ አብዛኛውን ጊዜ በትዳር ውስጥ ችግር ሲከሰት በትዳር ውስጥ ችግር የፈጠረውን ነገር ከማየት ይልቅ እራሱ ትዳርን እንደችግር የመውሰድ  አዝማሚያ  ይታያል።ያ  ደግሞ  ከትዳራቸው  ውስጥ  ሾልኮ  ስለመውጣት

ስለመፋታት እንዲያስብ ያደርጋቸዋል።እንደሀሳባቸው ትዳራቸውን ፈተው የተሻለ ወዳሉት ወደሌላ ትዳር መሸጋገር ቢችሉም ችግሩም አብሯቸው ነው ወደአዲሱ ትዳራቸው የሚሸጋገረው።
መፍትሄው ትዳሩን እንደችግር ወስዶ ያልሆነ ድምዳሜ ላይ ከመድረስ ይልቅ ትዳሩ ውስጥ የተከሰቱ ችግሮች ምን ምን ናቸው ብለው በመለየት እነሱን ለማስወገድ መጣር እና በዛ ሂደት የጋብቻውን ህልውና ማስቀጠል ይበጃል።ምክንያቱም የመኪናህ ጓማ ቢያልቅ ጎማውን ትቀይራለህ እንጂ መኪናዋን ሙሉ በሙሉ አታስወግድም።አይደለም ጎማ ሞተሩ ቢነክስ እንኳን ሞተር አስወርደህ ከእንደገና ተፈቶና ተበታትኖ ችግሩ ተለይቶ ከተወገደ በኃላ መልሶ ይገጣጠምና መኪናው እንደነበረ ይቀጥላል... ጋብቻም እንደዛ ነው የሚደረገው።እና አሁን እያደረግን ያለነው በመሀከላችሁ ያለውን ችግር የመቃቃራችሁን መንሴ መለየት ነው፡፡አሁን በጥዋቱ ክፍለ ጊዜ ሁለታችሁም የተናገራችሁትን እዚህ ኮምፒተር ላይ ከፍትላችኃላው በጋራ አብራችሁ ታዩታላችሁ…ይሄ መልሳችሁ የተናገራችሁትን እንድታዳምጡና የትኛው ትክክል ነው..የትኛው ንግግራችሁ ተጋኗል የሚለውን መልሳችሁ እንድታስበቡበት ይረዳችኃላ…በቃ አሁን ቀጥታ ወደማዳመጡ እንግባ ››አለና ኮምፒተሩን ከፈተና ለ.ወሮ ስንዱ አቀበላት…አቶ ኃይለልኡል ያለምንም ንግግር ከተቀመጠበት የራሱ አልጋ ተነሳና ሄዶ ወ.ሮ ስንዱ አልጋ ላይ ከጎኗቸው ተቀመጠና በኮምፒተር የሚታየውን የራሳቸውን ንግግር ለማደመጥ ዝግጁ ሆነ…ሰለሞን በፀጥታ ከተቀመጠበት ተነሳና ክፍልን ለቆ በራፍን ዘጋላቸውና ወጥቶ ሄደ…

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

አትሮኖስ

12 Nov, 17:21


​​YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

12 Nov, 16:33


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #አስራ_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ በፀሎት ግቢው ውስጥ ባለ የዛፍ ጥላ ስር ወንበር አውጥታ ቁጭ ብላለች…ፊራኦል ግንዱን ተደግፎ እሷን በትኩረት እያያት እያወሩ ነው፡፡ ወሬው ስለሟች እህቱ ስለበሬዱ ነው፡፡በእሷ ሞት ምክንያት ምን ያህል እንደተጎዳና የእሱ ብቻ ሳይሆን የቤተሱም ኑሮ እንደተመሰቃቀለ…»

አትሮኖስ

11 Nov, 17:00


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#አስራ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

በፀሎት ግቢው ውስጥ ባለ የዛፍ ጥላ ስር ወንበር አውጥታ ቁጭ ብላለች…ፊራኦል ግንዱን ተደግፎ እሷን በትኩረት እያያት እያወሩ ነው፡፡ ወሬው ስለሟች እህቱ ስለበሬዱ ነው፡፡በእሷ ሞት ምክንያት ምን ያህል እንደተጎዳና የእሱ ብቻ ሳይሆን የቤተሱም ኑሮ እንደተመሰቃቀለ እየነገራት ነው፡፡
‹‹ሀዘንንም ጨመሮ ሁሉም ነገር ጊዜያዊ መሆኑን አውቀህ ከክስተቶች ጋር እራስን አታጣብቅ…ከነገሮች ጋር እራስህን አስማምተህ ፍሰስ..እናም እራስህን ደስተኛ ለማድረግ ሞክር..ጊዜ የማይፈውሰው ህመም የለም››ብላ ልታፅናናው ሞከረች፡፡

‹‹ጊዜ ሁሉንም ህመሞች እኩል አይፈውስም….አንዳንድ ህመሞች በዕድሜያችን ልክ ተሰፍረው የተሰጡን ናቸው..አንዳንድ ስብራቷች የዘላለም ናቸው፡፡እህቴ ከሞተች ሁለት አመቷ አልፎ ሶስተኛውን ልናገባድድ ነው…ግን አሁንም ድረስ አባዬ እህህ እንዳለ ነው….እማዬን እደምታያት አይኗን እንዲህ የደከመው ከእድሜ የመጣ ህመም ወይም ጭስ አይደለም…የዘወትር ለቅሶ ነው….አየሽ አንዳንድ ስንጥቆች እንዲህ በቀላሉ ጊዜ ስላለፈ ብቻ አይደፈኑም…››

‹‹ትክክል ልትሆን ትችላለህ …ግን መሞከሩ አይከፋም…››

‹‹.በይ አሁን ወጣ ብዬ ልምጣ፡፡››

‹‹ሩቅ ካልሆነ ለምን እኔንም ይዘኸኝ አትወጣም?››

‹‹አይ ይሄንን ሻርፕሽን ከላይሽ ላይ ካልጣልሽ ከእኔ ጋር ከእዚህ ጊቢ መውጣት አትችይም..ጓደኞቼ እኮ ያቺ ሊንጃ ዘመድህ እያሉ ፉገራቸውን አልቻልኩትም››

‹‹እንዲሁ …ከአንቺ ጋር መታየቱ ይደብረኛል አትልም››

‹‹አይ… ያ እውነት እንዳልሆነ አንቺም ታውቂያለሽ…ለማንኛውም ቀላል ነገር ነው የጠየቅኩሽ…ሻርፕሽን ከላይሽ ላይ አንሺና አብረን እንሂድ››

‹‹አንተ ባለጣባሳዋ ዘመድህ ከሚሉህ ሊንጃዋ ቢሉህ አይሻልህም?፡፡››

‹‹አይ ግድ የለም..ባለ ጠባሳዋ ቢሉኝ ይሸለኛል…››

‹‹እንግዲያው ቀረብህ ሂድ በቃ››

‹‹አንቺም ቀረብሽ…ቻው››ብሏት ወጣ……ፊራኦል ሆነ ብሎ በአላማ ነው እንደዚህ የሚያደርጋት፡፡በፀሎትን መጠራጠር ከጀመረ ቀናቶች አልፈዋል…የምትለውን አይነት ልጅ እንዳልሆነች ውስጡ እየነገረው ነው….ምን አልባት የተጠራጠረው እውነት ከሆነ ምን እንደሚያደረግ ግራ ገብቷታል….አጋልጦና አሳልፎ ይሰጣታል? ለአባቱ ይናገራል…?ለወላጆቾ አሳውቆ ለሽልማት ያቀረቡትን 5 ሚሊዬን ይቀበላል…?እንደዛ ካደረገ በእርግጠኝነት አባቱን ለዘላለም እንደሚያጣ እርግጠኛ ነው…ማጣት ምን እንደሆነ ደግሞ በእህቱ ሞት በደንብ ስለተማረ አባቱን ደግሞ ካጣ ከዛ በኃላ ሰው እንደማይሆን እርግጠኛ ነው…ብቻ የተወሳሰብ ነገር ውስጥ እንደገባ እርግጠኛ ነው….አንዳንዴ ነገሮችን በጥልቀት ከመቆፈር እራሱን ማገድ ቢችል ይመኛል…ምንም ትሁን ማንም ችላ ብሎ ሊተዋት ይወስንና ውሳኔውን ለረጅም ጊዜ አፅንቶ ማቆየት አይችልም….

‹‹ውይ በፀሎት….ምን አይነት ልጅ ነሽ?››እንደጀማሪ እብድ ብቻውን መንገድ ላይ እየለፈለፈ እየሄደ ነው፡፡

ከሄደ በኋላ ግን እሷ ከፍተኛ ትካዜ ውስጥ ነው የገባችው፡፡ይሄ ልጅ ሙሉ ፊቷን እንድታሳየው ወጥሮ ይዞታል…አውጥተው አይናገሩ እንጂ የቤቱ ሰው ሁሉ ቀንና ለሊታ ፊቷን ጠቅላላ አልብሶ በአንገቷ ዙሪያ ተጠፍሮ ታስሮ የሚውለውን ሻርፖን ከዛሬ ነገ ለምን አይነሳም? የሚሉ ጥያቄ በውስጣቸው እየተጉላላ እንዳለ እርግጠኛ ነች….ይሄንን ማድረግ አትችልም…ቀኑ ከመድረሱ በፊት እራሷን ማጋለጥና ማንናቷን ማሳወቅ ሁሉን ነገር ነው ትርምስምስ የሚያደርግባት፡፡ከመቀመጫዋ ተነሳችና ከሻንጣዋ ውስጥ ስልኳን በማውጣት ወደጓሮ ሄደች …ወደእሷ ሰው ከመጣ በግልጽ ለማየት የሚቻላትን ቦታ መርጣ ተቀመጠችና የጠፋውን ስልክ አበራችው…..ሰሎሞን ጋር ደወለች፡፡

‹‹እሺ እንዴት ነህ?››

‹‹ሰላም ነኝ..አንቺ ደህና ነሽ….ከአሁን አሁን በደወለች እያልኩ በማስብበት ጊዜ ነው የደወለሽው››

‹‹ምነው አዲስ ነገር አለ?››

‹‹አዎ …ዛሬ አባትሽ ቤት አስጠርተውኝ ነበር››

‹‹አትለኝም!! ታዲያ እንዴት ሆነልህ?››

‹‹ሁሉ ነገር አንቺ እዳልሽው ነው የሆነው…ስለእኔ በድንብ ሲያጠኑ ነበር የከረሙት..የስልክ ልውውጣችንንም አግኝተው አዳምጠውታል…..በአጠቃላይ እውነቱን እንደተናገርኩ ተረድተዋል››

‹‹እና መጨረሻው ምን ሆነ?››በጉጉት ጠየቀች
‹‹ምን ይሆናል..?ያው አሁን ቁጭ ብዬ ዝርዝር እቅድ እያወጣሁ ነው….ሁለቱም ነገሮችን መስመር ለማስዝ ያልኳቸውን እንደሚያደርጉ ውሳኔያቸውን አሳውቀውኛል፡፡››

‹‹በጣም ደስ ይላል….በዚህ ፍጥነት ይስማማሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር››

‹‹እኔም ከአንቺ በላይ ፈርቼ ነበር…ግን አንቺን በጣም ስለሚወዱሽ ምንም ምርጫ የላቸውም…እንደተረዳሁት ከሆነ ሁለቱም ጋብቻቸውን ስለማዳንና ፍቅራቸውን ስለማደስ ደንታም የላቸውም…ግን ደግሞ በምንም ብለው በምንም አንቺን መልሰው እጃቸው ለማሰገባት ከልብ ይፈልጋሉ..ለዛ ነው በፍጥነት የተስማሙት፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነህ…እሷን ለማግኘት እርስ በርስ ተገዳደሉ ብተላቸው በተሻለ ቀሏቸው አሁን ከፈጠኑት በላይ ፈጥነው ያደርጉት ነበር፡፡››

‹‹እንዴ ..አንቺ ደግሞ አጋነንሺው…እርስ በርስ ከተገዳደሉ እንዴት ብለው ነው አንቺን የሚያገኙሽ…ለማንኛውም ስራው ስለተጀመረ ስልክሽን ባትዘጊው ጥሩ ነው…ምክንያቱም ስለእነሱ አነሱን ጠይቄ ማወቅ የማልችለውን መረጃ አንቺ ነሽ ልትነግሪኝ የምትችይው…ለዛ ደግሞ የግድ በፈለኩሽ ግዜ ማግኘት አለብኝ፡፡››

‹‹በስልኬ ተከታትለው ከደረሱብኝስ?››

‹‹ስልኩን አዲስ ቁጥር ነው…ማንም አያውቀውም ያልሺኝ መስሎኝ?››

‹‹አዎ ትክክል ነህ አዲስ ነው…አሁን ግን አንተ ታውቀዋለህ››

‹‹እኔ ለእነሱም ሆነ ለሌላ ለማንም ሰው አልሰጥም…ለአንቺ ስል ሳይሆን ለራሴ ስል….ሁለተኛ አሁን አንቺን መፈለጉን እርግፍ አድርገው ትተው ጋብቻቸውን ላይ ሙሉ ትኩረት እንዲያደርጉ አጥብቄ ነግሬያቸዋለሁ እነሱም ሙሉ በሙሉ ተስማምተዋል››

‹‹እና መቼ ልትጀምሩ ነው?፡፡››

‹‹እንደነገርሺኝ በፍጥነት ወደቤትሽ መመለስ ትፈልጊያለሽ..ስለዚህ ምንም ጊዜ ማባከን አያስፈልግም…ነገ ስራ እንጀምራለን…ለሚቀጥሉት 15 ቀን ቢሾፍቱ ወዳለው ቤታችሁ እንሄዳለን ፡፡ከዛ በኋላ ደግሞ ውጤቱን እናይና ወደአንዱ ጋር እንሄዳለን፡፡;;

‹‹እንዴ ሁለቱም ለመሄድ ተስማሙ››

‹‹አዎ…በደንብ ተስማምተዋል..ነገ ሶስት ሰዓት አዲስአበባን ለቀን እንወጣለን››

‹‹ይገርማል….በዚህ ፍጥነት ከከተማው ይዘኸቸው ትወጣለህ ብዬ አላሰብኩም ነበር››

‹‹አየሽ ነገሩ ለአመታት የተከማቸና ስር የሰደደ ስለሆነ …..ሙሉ ትኩረት ይፈልጋል….አዲስአባባ ተቀምጦ ደግሞ በሙሉ ትኩረት እንዲህ አይነት ነገር ለመከወን ምቹ አይደለም….ለዛ ነው ከከተማው ላርቃቸው የፈለኩት››

‹‹በጣም እያስደስትከኝ ነው…››
‹‹ተይ እንጂ….ገና ምኑም ሳይያዝ ምስጋና ከጀመርሽ በኋላ ጥሩ አይመጣም››

‹‹አያያዝህን አየሁት …እንደምታሳከው በጣም ነው ምተማመንብህ››

‹‹አመሰግናለሁ›››

‹‹እሺ.. በቃ ቻው››

‹‹ቆይ…የስልኩን ነገር ምን አልሺኝ?››

‹‹እሺ…አልዘጋውም…ግን ቀጥታ አትደውልልኝ….ለማውራት ስትፈልግ መልእክት ላክልኝ..ከዛ ሁኔታዎችን አመቻችቼ በተቻለኝ ፍጥነት ደውልልሀለው››

‹‹ተስማምተናል..በይ ቻው››
‹‹ስልኩ ተዘጋ….በጣም ደስ አላት…ነገሮች ሁሉ ባሰበቻው መንገድ እንዲህ መስመር ስለያዙላት ወደላይ አንጋጣ ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡

አትሮኖስ

11 Nov, 17:00


​​….ከሶስት ቀን በኃላ
አቶ ለሜቻ ነገሮችን ተቀብለው….ቱታቸውን ለብሰውና ሌሎች ሁለት ሰዎችን ቀጥረው ቀጥታ ቤቱን ወደመገንባት ስራ ገቡ..ይሔ ሁኔታ የቤቱን ሰው ሁሉ በጣም ሲያስደስት በፀሎትን ደግሞ በይበልጥ አስፈነጠዛት፡፡ቢያንስ አንድ ነገር ልታደርግላቸው በመቻሏ የውስጥ እርካታ ተሰማት….ማንነቷን በሚያቁበት ቀን መልሰው ብስጭት እና ቁጭት ውስጥ እንደሚገቡ እርግጠኛ ነች..ቢሆንም ግን ምርጫ ያላትም…በዚህ ጉዳይ ላይ እሷቸው ትክክል ናቸው ብላ አታስብም…ሰው እርስ  በርሱ  መረዳዳትና  አንዱ  የሌላውን  ኑሮ  ማቃናት  ያለና  የነበረ  ተግባር ነው….እሷቸው ይሄንን ጉዳይ ከክብር አንፃር ማየታቸው የእሷቸውን ኑሮ ብቻ ሳይሆን የጠቅላላ የቤተሰቡ ኑሮ እየጎዳ ያለው፡፡
ስራውን ከጀመሩት በኋላ እንደፊቱ አልከበዳቸውም..እንደውም ይበልጥ ጉጉት አሳደረባቸውና ከወር በኃላ ለሚከበረው ከልጃቸው የ3ተኛ አመት የሙት አመት መታሰቢያ ቀን በፊት ጥንቅቅ አድርገው መጨረስ አቅደው ቀን ከሌት መስራት ጀምረዋል፡፡አዎ ልጃቸው በህይወት ብትኖር ኖሮ እሰከዛሬ ይሄንን ቤት ሰርታ እንደምትጨርስ ያምኑ ነበር…አሁንም የሙት አመት መታሰቢያዋን ሲደግሱ የሙት መንፈሷ ሊያያቸው እንደሚመጣ እርግጠኛ ናቸው… ታዲያ ያንን ጊዜ ለእነሱ ቤት መስራት ህልሞ ስለነበረ ተሰርቶ ስታየው በጣም ደስ ብሏት እንደምትመለስ እርግጠኛ ናቸው…፡፡

እንደ ወትሮ መሽቶ ቤተሰቡ ሁሉ ተሰብስበው በሳቅና በጫወታ እራታቸውን በልተው ቡና ተፈልቶ ተጠጥቶ ከተጠናቀቀ በኃላ አምስት ሰዓት አካባቢ ሁሉም ሰው ወደመኝታው ሄደ…ፊራኦልም የውስጡን በውስጡ ይዞ ልክ እንደወትሮ እንደተኛ ሰው ሆኖ አደፈጠ…..በጨለማ ውስጥ አፍጥጦ እስከሰባት ሰዓት ድረስ በሀሳብ ሲባትት ነበር…ልክ ሰባት ሰዓት ሲሆን ቀስ ብሎ ከተኛበት ሶፋ ላይ ተነሳና መብራቱን አበራ ..የቤቱን ዙሪያ ገባ ቃኘ….በፀሎትና ለሊሴ ተዘረጋግተው እንደተኙ ነው፡፡ከወላጆቹ ክፍልም ምንም የሚሰማ እንቅስቃሴ የለም…..ቀስ ብሎ ወደሴቶቹ መኝታ ተጠጋ… ሁለቱም አይናቸውን ጨፍነው ጥልቅ የሚባል እንቅልፍ ውስጥ ናቸው፡፡ይሄኔ ህልም እያለሙ እንደሚሆን ገመተ…ቀስ አለና በፀሎት በተኛችበት በኩል ዞሮ ከራስጌዋ ጎን ካለ መቀመጫ ላይ ተቀመጠ…ቁልቁል አዘቅቆ አያት…ቀስ ብሎ እጁን ዘረጋና ፊቷ ላይ የተጠቀለለውን ሻርፕ ጫፍ ይዞ ጎተተው…ቀስ በቀስ ከፊል ፊቷ እየታየው መጣ …ሻርፑን ሙሉ በሙሉ ከፊቷ አስወገደእና በትኩረት ይመለከታት ጀመር…..ድንገት ተገላበጠችን በጀርባዋ ተንጋለለች ..በዛን ጊዜ ሙሉ በሙሉ ለእይታው ተጋለጠች….አሁን እርግጠኛ ሆነ…ምንም እንኳን የተወሰነ መጓሳቆል ቢታይባትም …ምንም እንኳን ቀኝ የፊቷ ክፈል ላይ ብዛት ያላቸው ጭረቶችና ጠባሳዎች ቢኖሩም እራሷ ነች…ለአመታት በድብቅ ከሩቅ ሲያያት የነበረችው..የእህቱን ውድ ልብ በውስጧ የተሸከመችው ልጅ….
‹‹እሺ አሁን ምንድነው የማደርው?››እራሱን ጠየቀ…ቀስ ብሎ ሻርፑን መልሶ ፊቷን ሸፈነና ከተቀመጠበት ተነስቶ መብራቱን አጠፋና ወደ መኝታው ተመለሰ….ሙሉ ለሊቱን እንቅልፍ ሊወስደው አልቻለም…..
አሁን ያወቀውን ነገር ባያውቅ ምኞቱ ነበር….አንዳንድ ማወቆች ሸክማቸው ያጎብጣል..አውቆ የሆነ ነገር ማድረግም አለማድረግም እዲህ አስቸጋሪ ሲሆን ምነው ምንም ነገር ባላወቅኩ ኖሮ ያስብላል፡፡ይህቺን ልጅ አፍቅሯት ነበር…የሞች እህቱን ልብ የተሸከመችው ልጅ መሆኗን ሳያውቅ በፊት ከእሷ ፍቅር ይዞት ነበር..ለእሷም ሆነ ለማንም ይሄንን ስሜቱን ተናግሮ አያውቅም….ግን እሱ በፍቅር እንደተነደፈ እርግጠኛ ነበር‹‹እሺ አሁን ምንድነው የማደርገው….?››እራሱን ጠየቀ…ብዙ ጊዜ ስለፍቅር ና ውበት ሲያወራ እርዕስ የምትቀይረውና ወሬውን የምትገፋው ለምን እንደሆነ አሁን ገባው…‹‹ይህቺ ልጅ ተአምረኛ ነች››ሲል አሰበ‹‹እራሷን በበሬዱ ቦታ ለመተካት እየጣረች ነው…አዎ ወደቤታችን የመጣችው ድንገት በአጋጣሚ ሳይሆን ሆነ ብላ አስባና አቅዳበት ነው… አንተ ወንድሜ ነህ ስትለኝ እንዲሁ ለአባባል ብቻ የምትጠቀምበት ይመስለኝ ነበር..ለካ እሷ ከአንጀቷ ነው፡፡››ሲል አሰበና በድቅድቅ ጨለማው ፈገግ አለ….‹‹ይሄን ጉድ ወላጆቹ ሲሰሙ ምን አይነት ምላሽ እንደሚሰጡ አሰበ…..ለመገመት አንኳን አልቻለም፡፡በተለይ አባቱ በበሬድ ጉዳይ ስሜተ ስስ እንደሆነ ያውቃል….ፈራ …በጣም ፈራ…. ‹‹ግን እሷስ እስአመቼ እንዲህ ከወላጆቾም ተሰውራ እውነቱን ከእኛም ደብቃ ትዘልቃዋለች..?እቅዷ ምንድነው?››ሊገባው አልቻለም፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

10 Nov, 17:56


​​‹‹በጣም ጥሩ…በቃ ሁለታችሁም ጋብቻችሁን ለማዳንና በመሀከላችሁ ያለውን መቃቃር ለማስወገድ ከእኔ ጋር አብሮ ለመስራት ፍቃደኛ ከሆናችሁ ሌላው ነገር እኮ ቀላል ነው…ቃል እገባላችኃላው እንወጣዋለን……በፀሎት በደስታ ወደቤቷ እንድትመለስ እናደርጋለን፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነህ…ግን የእኔ ሀሳብ ምን መሰለህ….አሁን ስትደውልልህ ወደ ቤቷ እድትመለስ አሳምናት ..በቃ እኛ ተስማማን አይደል…ከነገ ጀምሮ ከፈለክ ከአሁን ጀምሮ ማድረግ ያለብንን ነገሮች ንገረን እና ማድረግ እንጀምራለን..እሷ ግን ዛሬ ነገ ሳትል ወደቤቷ ትመለስ..እሷ እዚሁ እቤቷ እያለች እኛ ችግራችንን መፍታት እንችላለን››
‹‹ይቅርታ ይሄ መንገድ የሚሰራ አይመስለኝም››አለ ሰለሞን
‹‹ብሩን እኮ እንከፍልኃለን..ማለቴ አምስት ሚሊዬኑን እንከፍልሀለን..አይደል ኃይሌ..?››.ወ.ሮ ስንዱ ለዘመናት አድርገው በማያውቁት መንገድ ባልዬውን በአይናቸውም በቃላቸውም እየተለማመጡ ጠየቁ፡፡
‹‹አዎ..ትክክል ነች…ከፈለክ አሁኑኑ የ5 ሚሊዬኑን ቼክ ልፅፍልህ እችላለው…አዎ››
‹‹ይቅርታ እኔ ያልሰራሁበትን ገንዘብ የምቀበል አይነት ሰው አይደለሁም…በዛ ላይ 5 ሚሊዬኑን ከፍልሀለው አለች እንጂ እኔ ስራዬን እሷ ባለችው መንገድ እንኳን በውጤት ባጠናቅቅ…ይሄንን ብር እቀበላለሁ አላልኩም..እኔ ለሰራሁት ስረ የሚገባኝን ብር ብቻ ነው እንዲከፈለኝ ምፈለገው..እኔ እናንተን ብሆን ግን ሁሉን ነገር ልጃችሁ ባለችው መንገድ እንዲከናወን ጊዜ ሳላባክን እንቀሳቀስ ነበር….ቢያንስ እኮ እነዚህን እናንተ የምትሉትን ነገር ለልጃችሁ አቅርቤ የምትለውን ለመስማት የተወሰነ ቀናቶች ሞክረን እናንተ ግንኙነታችሁን ለማሻሻል የምታደርጉትን ጥረት አይተን ጥረቱ ፍሬ እያፈራ መሆንኑ መመዘን አለብን…እኔ ባለሞያ ነኝ..በፀሎት ደግሞ ዋና ቀጣሪዬ ነች..ታማኝነቴ ለእሷ ነው….እሷ ባለችው መንገድ ለመጓዝ ስትወስኑ ደውሉልኝ..አሁን ልሂድ..ብሎ ከመቀመጫው ሲነሳ ሁሉቱም በድንጋጤ ከተቀመጡበት ተስፈንጥረው ተነሱና ግራና ቀኝ ትከሸውን ይዘው መልሰው አስቀመጡት..
‹‹እሺ በቃ እንዳልክ ይሁን..አሁን ማድረግ ያለብንን ንገረን..ምንም ጊዜ ሳናባክን ወደተግባር መግባት አለብን፡፡ለመሆኑ ምን ያህል ጊዜ የሚፈጅ ይመስልሀል?፡፡››
‹‹ወር ..ሁለት ወር..ወይም ሶስት ወር..ወይም አመት››
‹‹አልገባኝም?››አቶ ኃይለልኡል ኮስተር ብለው ጠየቁ
‹‹ጊዜውን ምታረዝሙትም ምታሳጥሩትም እናንተው ናችሁ፡፡የጋብቻ አማካሪ ውጤታማ የሚሆነው ሁለቱ የጋብቻ ተጣማሪዎች በመሀከላቸው ያለውን ችግር ለመፍታት ቁርጠኛ በሆኑበት መጠን ነው…እኔ እገዛ ነው የማደርግላችሁ..ትልቁን ስራ የምትሰሩት እናንተው

ናቸሁ…ምን ያህል ፍቃዳኛ ናችሁ ?ቁርጠኝነታችሁስ…?ችግሩን ለመፍታት ምን ያህል ርቀት ድረስ ትጓዛላችሁ?››
‹‹ነገርንህ እኮ …ልጄ እንድትመለስ እንኳን ከባሌ ጋር ሰላም ማውረድ ይቅርና ከዳቢሎስ ጋርም ተስማሚ ብባል አደርገዋለው…››
‹‹የእኔም አቋም ከእሷ የተለየ አይደለም››
‹‹እንደዛ ከሆነ እንጀምር…ከዚህ ከተማ ለቀንናት እንወጣለን…የፈለጋችሁበት ቦታ መምረጥ ትችላላችሁ ..ላንጋኖ ሰዳሬ ወይም ሌላ ቦታ ከተማና …ግርግር ያለበት ቦታ ግን አይሆንም››
‹‹እሺ..ሌላስ?››
‹‹ስልክ ሁለታችሁም በቀን ለአንድ ሰዓት ያህል ብቻ ነው የምትጠቀሙት…ከምትፈልጉትሰ ሰው ጋር የምትደዋወሉት  በዛ በተፈቀደላችሁ ሰዓት ብቻ ነው….››
‹‹ይሁን እሺ…››
‹‹በቃ ከአሁን ጀምሮ ተዘጋጁ ..ነገ ሶስት ሰዓት አንንቀሳቀሳለን..ቀድሜ ደውልላችኃላው፡፡››
‹‹እሺ..ተስማምተናል፡፡››
‹‹በቃ ደህና ዋሉ…››መቀመጫውን ለቆ ተነሳ…ደስ እያለው እቤቱንም ሰፈሩንም ለቆ ሄደ…

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

10 Nov, 11:10


ቼልሲ ከ አርሰናል የሚያደርጉትን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ በ ነፃ በስልኮዎ ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ(JOIN) የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉ አሁኑኑ እንዳያመልጥዎ 👇

አትሮኖስ

10 Nov, 10:55


የ ስንተኛ ክፍል ተማሪ ናችሁ?

አትሮኖስ

10 Nov, 10:44


ምን አይነት ፊልም መመልከት ይፈልጋሉ?😱😱😱😱😱😱😱😱😱👇👇👇

▶️የቱርክ ፊልም    JOIN 👈 ይንኩ

▶️የአሜሪካ ፊልም   JOIN 👈 ይንኩ

▶️ የህንድ ፊልም     JOIN 👈 ይንኩ

▶️የቻይና ፊልም      JOIN 👈 ይንኩ

▶️የአማርኛ ፊልም      JOIN 👈 ይንኩ

▶️ተከታታይ ፊልሞች    JOIN 👈 ይንኩ

▶️ አኒሜሽን ፊልሞች    JOIN 👈 ይንኩ

▶️አክሽን ፊልሞች     JOIN 👈 ይንኩ

▶️የጫካ ፊልሞች     JOIN 👈 ይንኩ

▶️የፍቅር ፊልሞች    JOIN 👈 ይንኩ

▶️የsex ፊልሞች    JOIN  👈  ይንኩ

እንደ ምርጫው መርጦ ይቀላቀሉ

                    JOIN

ይቀላቀሉ                        ይቀላቀሉ

አትሮኖስ

09 Nov, 17:23


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አራት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ሰላሞን የሆነ ሰው እየተጫወተበት እንደሆነ ነው የተረዳው‹‹ግን ማን ነው እንዲህ ያለ ጫወታ ከእኔ ጋር ለመጫወት የሚደፍረው?››በዙሪያው ያሉ ሰዎችን እያሰበ እራሱን እስኪያመው ቢያስጨንቅ በዙሪያው ካሉ ሰዎች እንዲህ መላ ቅጡ የጠፋበት ቀልድ ከእሱ ጋር ለመቃለድ…»

አትሮኖስ

09 Nov, 17:22


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰላሞን የሆነ ሰው እየተጫወተበት እንደሆነ ነው የተረዳው‹‹ግን ማን ነው እንዲህ ያለ ጫወታ ከእኔ ጋር ለመጫወት የሚደፍረው?››በዙሪያው ያሉ ሰዎችን እያሰበ እራሱን እስኪያመው ቢያስጨንቅ በዙሪያው ካሉ ሰዎች እንዲህ መላ ቅጡ የጠፋበት ቀልድ ከእሱ ጋር ለመቃለድ የሚሞከር ሰው ሊመጣለት አልቻለም፡፡

ነገሩ ቀልድ እንዳልሆነ የተረዳው ልክ በተነገረው መሰረት ከሶስት ቀን በኃላ ተመሳሳይ ስልክ ሲደወልለት ነው፡፡በጉጉት አነሳው፡፡

‹‹ሄሎ..አወቅከኝ?››

‹‹መሰለኝ… አደናጋሪዋ ልጅ ነሽ አይደል?››

‹‹መሰለኝ….የባንክ ቁጥርህን ላክልኝ?››

‹‹ምን ለማድረግ?››

‹‹በተነጋገርነው መሰረት ስራ ማስጀመሪያ መቶ ሺ ብሩን እንድልክልህ ነዋ››

‹‹እንዴ? ስራው ምን እንደሆነ ሳላውቅ…ልስራው አልስራው መወሰን የምችለው እኮ ስራውን ሳውቅ ነው…መጀመሪያ በአካል ተገናኝነተን ስለስራው ማውራት አለብን››

‹‹ለጊዜው በአካል ላገኝህ አልችልም…ስራው በአባትና እናቴ መካከል ያለውን ችግር መቅረፍ ነው…እናትና አባቴ ያለፉትን 28 አመታት በጋብቻ አሳልፈዋል….እኔ ሀያ አንድ አመቴን ጨርሼ 22 ዓመት ውስጥ ነኝ…በእድሜዬ አንድም ቀን ሰላም ሆነው አይቻቸው አላውቅም…መኝታ  ለይተው  በየራሳቸው  መኝታ  ቤት  ነው  የሚያድሩት….ሁል  ጊዜ
እንደተጣሉና እንደተጨቃጨቁ ነው.ከዛም አልፎ አንዱ ሌለኛውን ለማስወገድም እስከመፈለግ የሚያደርስ ጥላቻ በመካከላቸው አለ..ወይ አይፋቱ ወይ እንደሰው የእውነት አብረው አይኖሩ፣….እና የፈለኩህ ይሄንን የሻገተና የበሰበሰ ጋብቻ የበሰበሰውን ቅጠል ከላዩ አራግፈህ የደረቀውን የጋብቻ ግንድ ቆርጠህ ከስር አዲስ የፍቅር ቅርንጫፍ እንዲያቆጠቁጥ እንድታደርግ ነው…ቢያንስ እንደባለትዳር መልሰው መተቃቀፍ ባይችሉ እራሱ እንደጓደኛሞች እንዲጨባበጡ ማድረግ እንድትችል ነው፡፡ይሄ ጉዳይ የእኔ የህይወቴ ትልቁ አላማ ነው…እባክህ ይሄንን ጉዳይ እንደጉዳይህ ልትይዘው ትችላለህ….?›››

‹‹በእውነቱ ከጠበቅኩት በተቃራኒ የሆነ መሳጭ ነገር እየነገርሺን ስለሆነ ቀልቤን ገዝተሸዋል…የምትይውን በደንብ እየተከታተልኩሽ ነው፡፡፡ለመሆኑ እኔን የምታናግሪው አባትሽ ወክለሽ ነው ወይስ እናትሽን…..?ማለት እኔን ለስራው እንድታናግሪኝ የጠየቀሽ ማን ነው?፡፡››

‹‹በእውነቱ ሁለቱም ስለዚህ ጉዳይ የሚያውቁት ነገር የለም….›

‹‹ይሄ ደግሞ ነገሩን ይበልጥ ውስብስብ ያደርገዋል..እሺ ቆይ ለመሆኑ እኔን ለምን…?እንዴት እኔን መረጥሽ?››

‹‹ለጊዜው ማንነቱን ልነግርህ የማልችለው አንድ አንተን የሚያውቅ ሰው ነው ሰለአንተ በሆነ ጉዳይ አንስተን ስንጨዋወት በጋብቻ ጉዳይ ላይ እንደምትሰራና በጉብዝናህም እንደሚተማመንብህ የነገረኝ..እንዳአጋጣ ሚ ሆኖ ደግሞ ያንን ሰው እኔ አምነዋለው…እሱ ጎበዝ ነህ ካለህ ጎበዝ ነህ ማለት ነው…

ተመለሰልህ?፡››

‹‹በከፊል አዎ…ግን እንደነገርሺኝ በወላጆችሽ መካከል ያለው ችግር ለረጅም አመት የተከማቸ የተወሳሰበና ዘርፈ ብዙም ነው፡፡››

‹‹በትክክል ገልፀኸዋል››

‹‹ችግሩ ምን መሰለሽ..በቀደም እንደነገርኩሽ አንድ የጋብቻ አማካሪ በጋብቻ መካከል የተፈጠረ ችግርን ለመፍታት የሚችለው ሁለቱም ተጋቢዎች በመሀከላቸው ችግር እንዳለ አምነው ያንን ለማስተካከል ከአማካሪው ጋር ለመተባበር ሙሉ ፍቃደኛ ሲሆኑ ብቻ ነው…አሁን ያንቺን ጉዳይ ስንመለከት ወላጆችሽ ጉዳዩን እንኳን አያውቁትም..ቢያውቁትም ፈፅሞ ከእኔ ጋር ለመስራት ላይቀበሉት ይችላሉ.››.

‹‹እሱን ለእኔ ተወውና አሁን የባንክ ቁጥርህን ላክልኝ… ገንዘቡን ትራንስፈር ላድርግልህ››

‹‹ይሄውልሽ ፣እኔ በነገርሺን ታሪክ በጣም ተስቤያለሁ…አንድ ወጣት ሴት በወላጆቾ ግንኙነት ተረብሻ እንዲህ ነገሮችን ለማስተካከል ስትጥር እኔም የበኩሌን እገዛ ለማድረግ ፍጽም ፍቃደኛ ነኝ..እዚህ ላይ ዋናው ገንዘብ አይደለም.. እሱ በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣ ነው…አሁን መጀመሪያ አንቺ ራስሽ ወላጆችሽን ከቻልሽ አንድ ላይ አስቀምጠሸ ካልሆነም ለየብቻ ያሰብሽውን ንገሪያቸውና ለማሳመን ሞክሪ..እነሱ ፍቃደኛ ከሆኑ በኃላ ደውይልኝ..ከዛ ፕሮግራም እናወጣና ያለውን ችግር እያየን ለማስተካከል እንሞክራለን፡፡››

‹‹እነሱን በቀጥታ ማናገር አልችልም››

‹‹ለምን?››

‹‹ስሜ በፀሎት ኃይለልኡል ይባላል››

‹‹እሺ በፀሎት…ለምንድነው ወላጆችሽን ማናገር የማትችይው..?እነሱን ማናገር የማትቺይ ከሆነ እንዴት አድርጌ ነው ወላጆችሽን መርዳት የምችለው?››

‹‹ማለት ስሜን የነገርኩህ ስለእኔ የተወሰነ መረጃ እንዲኖርህ ነው..በፀሎት ኃይለልኡል በልና ድህረገፆች ላይ ወይም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ፈልግ ..ከ30 ደቂቃ በኃላ መልሼ ደውልልሀለው፡፡››አለችና ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጋችበት፡፡

ስልኩ ቢዘጋም እሱ ግን ስልኩ ላይ እንዳፈጠጠ ነው…የገባው የመሰለው የልጅቷ ሁኔታ መልሶ እየተበታተነበት ነው‹‹…ድህረ-ገፅ ላይ ስለእሷ ምን…?ታዋቂ ሰው ነች ማለት ነው…?››

ጎግል ከፍቶ ››በፀሎት ኃይለመለኮት››ብሎ ሰርች መድረግ ጀመረ..በርካታ መረጃዎች ተዘረገፉ….እውነትም ይህቺ ልጅ ታዋቂ ነች መሰለኝ..ብሎ የመጀመሪያውን ሲያነብ

‹‹የታዋቂ ቢሊዬነሩ የኃይለመለኮት ብቸኛ ወራሽ በውድቅት ለሊት ከቤት ወጥታ ከጠፋች 14 ቀን አልፏታል፡፡››

‹‹ታዋቂው ቢሊዬነር ብቸኛ ልጅ በፀሎት ለምን ከቤቷ ጠፋች?››
‹‹በጸሎት ኃይለመለኮትን ያለችበትን የጠቆመ የ5 ሚሊዬን ብር  ሽልማት እንደሚሸልሙ አባቷ ለፋና ቴልቨዥን በሰጡት መግለጫ አሳወቁ››

በሚያነበው ዜና ሁሉ ደነዘዘ…..ማንበቡን አቆመና..ደወለላት

‹‹ሄሎ ..››

‹‹አሁን በመጠኑ ገባህ?››

‹‹ማለት አሁንም እንደጠፋሽ አይደለሽም አይደል…..?ማለቴ ወደቤት ተመልሰሻል?››

‹‹አይ  አልተመለስኩም…ወደቤት  እንድመለስም  እንደወጣው  በዛው  እንድቀርም የምታደርገኝ አንተ ነህ፡፡››

‹‹አልገባኝም››

‹‹ከእቤት የጠፋሁት የወላጆቼ ጭቅጭቅና የእርስ በርስ ጥላቻ ምርር ብሎኝ ነው….እኔ የእነሱን ሀብታቸውንም ሆነ ውርሳቸውን አልፈልግም፡፡ እኔ የምፈልገው ፍቅራቸውን ነው..ቢያንስ የሁለት ጓደኛሞችን አይነት እርስ በርስ የመግባባት እና የመረዳዳት ደረጃ ላይ እስኪደርሱ ወደዛ ቤት አልመለስም…እና እቅዴ ምን መሰለህ..ለእነሱ ደብዳቤ ፅፌ ልክልሀለው….በዛ ደብዳቤ ላይ ግልፅ የሆነ ፍላጎቴን አሰፍራለሁ…ማለቴ በግልፅ ከአንተ ጋር ሰርተው በማሀከላቸው ያለውን ግንኙነት ካስተካከሉ…እናም ያንን አንተ ካረጋገጥክልኝ ወደቤት እመለሳለው..ካለበለዚያ በቃ እኔም እነሱን እረሳለው አነሱም እኔን ይረሱኛል ማለት ነው፡፡›

‹‹በተሰቀለው..ነገሩ ካሰብኩት በላይ የተወሳሰበና ..አደገኛም ጭምር ነው፡፡››

‹‹ለዚህ እኮ ነው አምስት ሚሊዬን ብር እንድታገኝ የማደርግህ..ገብቷሀል አይደል አባቴ እኔን ላገኘ ወይም ያለሁበትን ለጠቆመ ሰው የ5 ሚሊዬን ብር ሽልማት አዘጋጅቷል ..ያ ማለት ነገሮች እንደተሳኩ እርግጠኛ በሆንኩ ጊዜ አንተ እንድታገኘኝና ለቤተሰቦቼ እንድታስረክበኝ አደርጋለሁ…እናም ለሽልማት የተዘጋጀውን ብር ከአባቴ ተቀብዬ ለአንተ አስረክብሀለው፡፡››

አትሮኖስ

09 Nov, 17:22


‹‹ገባኝ..አሁን እኔን ያሳሰበኝ የብር ጉዳይ አይደለም..አስበሽዋል ግን በጠቅላላ በሀገሪቱ ጉራንጉር እየተፈለግሽ ነው…በጥቂቱ እንደተረዳሁት አባትሽ እጅግ ተፅዕኖ ፈጣሪና የፈለገውን ማድረግ የሚችል ሰው ነው…እንዳልሽው ለእነሱ የፃፍሺውን ደብዳቤ ይዤ እቤት
ድረስ ስሄድ አሜን ብሎ የሚቀበልለኝ ይመስልሻል?ያለሽበትን ቦታ በትክክል የማውቅ ነው የሚመስለው…ሊያሳስረኝም ሆነ ሌላ ነገር ሊያደርገኝ ይችላል….ያንን አስበሽዋል?፡፡››

‹‹አይ አባቴን አውቀዋለው..እንደዛ አያደርግም…መጀመሪያ እርግጠኛ ለመሆን ያሰልልሀል..ስትገባ ስትወጣ ከማን ጋር እንደምትገናኝ ምን አይነት ሰው እንደሆንክ ያጣራል
፣ስልክህን ያስጠልፋል…ይሄንን የተነጋገርነውን ሁሉ ከቴሌ አስወጥቶ ያዳምጣል…ከዛ እኔ ልጅ በዚህ ነገር እንዴት እንደቆረጥኩ እርግጠኛ ይሆንና ከአንተ ጋር ይተባበራል..ወይም እኔን ልጁን እስከወደያኛው ይሰናበታኛል፡፡››

‹‹ገባኝ…በእውነቱ ሁኔታዎች በጣም ቢያስፈሩኝም …ግን እምቢ ልልሽ አልችልም….ተስማምቼለው፡፡››

‹‹ጥሩ በቃ ያልኩህን አድርግ..የባንክ ቁጥርህን ላክልኝ…ደብዳቤውን ነገ እንዲደርስህ አደርጋለው…ከዛ ሁኔታዎችን አመቻችና እናትንና አባቴን አግኛቸው……….ከዛ በኃላ ያሉትን ነገሮች እንነጋገራለን፡፡››

‹ጥሩ እንዳልሽ…ስፈልግሽ በዚህ ቁጥር ነው የማገኝሽ?››

‹‹አይ አንተ ልታገኘን አትችልም..እኔ ነኝ የማገኝህ…ቻው››ስልኩ ተዘጋ፡፡

አሁንም እንደደነዘዘ ነው፡፡የባንክ ሂሳብ ቁጥሩን ላከላት…ከአንድ ሰዓት በኃላ እንዳለችው 100 ሺ ብር እንደተላከለት በስልክ ቁጥሩ ሚሴጅ መጣለት…አሁን የበለጠ ብርድ ብርድ አለው…

‹‹ሠሎሞን ምን አይነት ነገር ውስጥ እራስህን እያስገባህ ነው?፡፡››ጠየቀ…መልሶ ድህረ ገፅ ላይ ገባና የበፀሎትን የተለያ ፎቶዎችን ዳውንሎድ አደረገ ፣እንዲህ አይነት የተሰወሳሰበ ነገሮችን አስባ ለመከወን የምትንቀሳቀስ ሳይሆን ቢነግሯት እንኳን የማዳመጥ ትግስት ያላት አትመስልም፡፡እያንዳንዱን ፎቶ በየተራ እየገለጠ ተመለከት...ወርቃማ ፀጎሯን..ጥቋቁር አይኖቾን ..አፍንጫዋንና የሚያጎጉ ብስል እንጆሪ መሳይ ከንፈሮቹን አንድ በአንድ ነጥሎ ለየብቻ አጠናቸው…ይሄንን ጉዳይ ብቻውን አመንዥጎ ሊወጣው ስለማይችል አስቴር ጋር ደወለ….ቤት ነኝ ስትለው….ጃኬቱን ከተሰቀለበት አንስቶ በእጁ እንዳንጠለጠለ ሄደ፡፡

///
በማግስቱ
በፍራቻ እንደተሸበብ የሆንኩትን ልሁን በሚል ስሜት የውስጥ ፍራቻውን እና ስጋቱን በላይ ገፅታው መኮሳተር ሸፍኖት የአቶ ኃየለ መለኮትን ቤተመንግስት መሰል ግዙፍ ህንፃ መጥሪያ ተጫነ….ብዙም ሳይቆይ የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጋርድ የሚመስል ሙሉ ጥቁር ሱፍ የለበሰ ጠብደል ወጣት በራፍን ከፈተና‹‹አቤት ጌታዬ ምንድነበር?››አለው፡፡

ከስር እስከ ላይ አየውና ሁኔታውን ገመገመ..ይሄን የመሰለ ዘናጭ መለሎ የዚህ ቤት ዘበኛ እንዳይሆን ብቻ ሲል አሰላሰለ…ከላይ ወደታች አፍጥጦ እያየው እንደሆነ ሲገባው ወደቀልቡ ተመለሰና ‹‹አቶ ኃይለመለኮትን ወይም ባለቤታቸውን ፈልጌ ነበር››

‹‹ቀጠሮ አላህ?››

‹‹አይ የለኝም››

‹‹ይቅርታ ጌታዬ …እንደዛ ከሆነ ልታገኛቸው አትችልም…አሁን ባሉበት ሁኔታ ምንም አይነት እንግዳ አያስተናግዱም››

‹‹ይገባኛል..የእኔ ጉዳይ ግን የተለየ ነው፡››

‹‹ጌታዬ የተግባባን አይመስለኝም….መልዕክት ካለህ ስጠኝና ላድርስልህ..አስፈላጊ ከሆነ እራሳቸው ደውለው ያገኙሀል..ከዛ ውጭ አዝናለሁ ልረዳህ አልችልም››ብሎ ከእሱ መልስ ሳይጠብቅ የከፈተውን በራፍ መልሶ ሊጠረቅምበት ሲል እጁን በፍጥነት ዘረጋና አስቆመው…

ዘበኛው‹‹ይበልጥ በንዴት አፈጠጠበት››

‹‹አልተረዳሀኝም..ጉዳዬ ከበፀሎት ጋር የተገናኘ ነው..ምን መሰለህ..››
ንግግሩን ሳይጨርስ እጁን ጨመደደና ወደውስጥ ጎትቶ በማስገባት በራፉን ቀረቀረው፡፡

‹‹በጸሎት ምን..?ያለችበትን ታውቃለህ..?የት ነች..?››

‹‹ቀጥታ አባቷን ወይ እናቷን ነው ማናገር የምፈልገው››

‹‹እሺ ና ግባ›› እየተሸቆጠቆጠ ፊት ለፊት እየመራ ወደግዙፉ ሳሎን ይዞት ገባ…እቤቱ ግዝፈትና ሰው አልባ ስለሆነ ያስፈራል…‹‹እባክህ እዚህ ሶፋ ላይ አረፍ በል …ጋሼን አናግሬያቸው መጣሁ…፡፡››ብሎ መልስ ሳይጠብቅ የፎቁን መወጣጫ የሩጫ ያህል እየተራመደ ወደላይ ወጣ….እዛው በቆመበት የቤቱን ዙሪያ ገባ እየጎበኘ በመደነቅ ላይ ሳለ ነበር ልጁ ተመልሶ የመጣው

‹‹ተከተለኝ ጋሼ ቢሯቸው ናቸው..አስገባው ብለዋል..እየጠበቁህ ነው››
በፍጥነት ደራጃውን ወጣና ደረሰበት፡፡ የመጀመሪያውን ፎቅ እንደወጡ ወደግራ ታጠፈና በኮሪደሩ የተወሰነ ከተራመዱ በኋላ በግራ በኩላ ካለው ገርበብ ያለ ክፍል እንዲገባ በእጁ ጠቆመውና እሱ ወደኃላ ዞሩ የመልስ ጉዞ ማድረግ ጀመረ..ሰለሞን ወደ ክፍሉ ተጠጋና በእጁ ቆረቆረ…አሁንም ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ እንደሆነ ይሰማዋል..ወዲያው በራፉ ተከፈተና አንድ ባለግርማ ሞገሳም ግዙፍ አዛውንት ፊት ለፊቱ ቆመው እጃቸውን ለሰላምታ ሲዘረጉለት አገኘ…በደመነፍስ እጁን ዘረጋና ጨበጣቸው …

‹‹ግባ ›› አሉን እጁን እንደያዙ ወደውስጥ ይዘውት ዘለቁ…ከጠረጴዛቸው ፊት ለፊት ካለው ሶፋ ቅድመው ተቀመጡና ፊትለፊታቸው እንዲቀመጥ በእጃቸው ጠቆሙት...

ቦርሳውን ከትከሻው ላይ አወርዶ ፊት ለፊቱ ጠረጴዛ ላይ አስቀመጠና… ተቀመጠ፡፡

‹‹እሺ፣ስለ በፀሎት የምታውቀው
ነገር እንዳለ ነበር የተነገረኝ ..?››

‹‹ትክክል››

በመርማሪ  አይናቸው  ከስር  እስከላይ  እየገመገሙት‹‹ለመሆኑ  ልጄን  የት  ነው ምታውቃት?››ሲሉ ጠየቁት

‹‹አላውቃትም››

‹‹አልገባኝም..እሺ ያለችበትን ታውቃለህ?››

‹‹አይ አላውቅም፡፡››

‹‹ሰውዬ እኔ አሁን ቀልድ ላይ ያለው ይመስልሀል?››እንደቆሰለ ነብር ተቆጡ፡፡

‹‹ይረጋጉ፣እሷን ለማግኘት የሚጠቅሞትን ነገር ነው ይዤሎት የመጣሁት››አለና ጠረጴዛ ላይ ያለውን ቦርሳውን ወደራሱ ስቦ በመክፈት ከውስጡ ሁለት የታሸገ ፖስታ አወጣና አቀበላቸው..አገላብጠው አዩት ፣ለአባዬ እና ለእማዬ
ይላል..የልጃቸው የእጅ ፅሁፍ ነው፡፡ከመቀመጫቸው በደስታ ብድግ አሉ ፣ ወዲያው ፖስታውን ሸርክተው ቀደዱትና ውስጡ ያለውን ደብዳቤ አውጥታው እዛ ክፍል ውስጥ ከውዲህ አዲያ እየተሸከረከሩ አነበቡት

‹‹ወይኔ ፈጣሪ…ልጄ በህይወት አለች….ልጄ በህይወት አለች..ወደሰሎሞን ተንደረሩን ከተቀመጠበት ጎትተው አቆመትና እያገላበጡ ጉንጩን ሳሙት፤ ጨምቀው አቀፉትና ከግራ ወደቀኝ ወዘወዙት፣‹‹ቆይ አንዴት ናት? ››እጁን ያዙትና የጎተቱ ከክፍሉ ወጡ… ግራ ገባው፡፡ ብዙ ክፍሎችን አልፈው የሆነ ክፍል ከፈቱን ይዘውት ገቡ…ግዙፍ መኝታ ቤት ነው..ፊት ለፊት ያለው ግዙፍ አልጋ ላይ ተዘርረው የተኙ ግዙፍ ሴትዬ አሉ፡፡

‹‹ስንዱ ልጃችን በህይወት አለች..ልጃችን ደብደቤ ላከችልን…እይ .. ተመልከቺ፡፡‹‹በእጃቸውን ያንከረፈፉትን ደብዳቤ አቀበሏቸው….ሴትዬዋ የበፀሎት እናት እንደሆነች ገባው…ይሄን ቤተሰብ ከገባበት እንዲህ አይነት የተረማመሰ ህይወት እንዴት አድርጎ ሊታደግ እንደሚችል ሲያስብ ገና ካሁኑ ደከመው…ሴትዬዋ በተዳከመ አይናቸው በተጋደሙበት የልጃቸውን ደብዳቤ በእንባ ታጅበው አንብበው ጨረሱ፡፡

‹‹ወይኔ …አየህ ልጃችንን ለዚህ ያበቃናት እኛው ነን..እኔና አንተ ነን ጥፋተኞቹ…እኔና አንተ ለአንድ ልጃችን እንኳን መሆን የማንችል ከንቱዋች ነን››

‹‹እንግዲህ ጀመረሽ…አይገባሽም እንዴ ..?ልጃችን ምንም አይነት አደጋ አልደረሰባትም…አልታገተችም..ሆስፒታልም አልገባችም….ይሄ በቂ አይደለም፡፡››

አትሮኖስ

09 Nov, 17:22


​​‹‹አይደለም…ይህ በፍፁም በቂ አይደለም….ልጄን አምጣልኝ…ልጄን በአካል እፈልጋለው››

‹‹ለማንኛውም ተመልሼ መጣለሁ..ና ወደቢሮ እንመለስ …››ብለው ሰለሞንን አስከትለው ወደቢሯቸው ተመለሱ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

09 Nov, 16:54


🟡• BETTING መበላት ላማረራችሁ ምርጥ ቻናል እንሆ

ተቀላቀሉን 👇👇

https://t.me/+OeCLHsoVmaYxYmNk

አትሮኖስ

09 Nov, 16:43


የፍቅረኛችሁን   ሰው   ስም   የመጀመርያ ፊደል   በመጫን  ስለ ፍቅረኛዎ ይወቁ

😍😍😍
ዳይ ለሁላችሁም ነው እንዳያመልጥዎ!!!!👇👇👇👇👇

አትሮኖስ

08 Nov, 17:38


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሶስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ እለቱ እሁድ ነው፡፡ከፊራኦል ጋር ለመውጣት ስለተነጋገሩ እየተዘጋጀች ነው፡፡ለሊሴ እየረዳቻት ነው፡፡ ሰው ከለገመ ከሻማ በላይ በቀላሉ ቀልጦ የሚጠፋ ከጠነከረ ደግሞ ከአልማዝም በላይ ማይቆረጥና ማይሸረፋ ተአምራዊ ፍጡር መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡በፀሎትም የማያልፍ የመሰላት…»

አትሮኖስ

08 Nov, 17:00


‹‹ትክክል ነሽ እህቴ… ቢሆንም ግን.. አልፏ አልፏም ቢሆን ባለሞያ መጠቀም ብንለምድ ደግሞ ተጨማሪ ማህረሰባዊ ጥቅም እናገኝበታለን…አንዳንድ ችግሮች ከሽማግሌ አቅም በላይ ይሆናሉ..ዕውቀት የሚጣይቁ.. የባለሞያ ክትትልና መመሪያ የሚፈልጉ በጋብቻ ውስጥ ሚፈጠሩ ችግሮች አሉ፡፡››

‹‹በዛ እስማማለው….ግን የእውነት ሀለቃሽ ጎበዝ ነው?››

‹‹በጣም…. በጉብዝናውና በእውቀቱ ምንም ጥርጣሬ የለኝም፡፡››

‹‹እሺ ጥሩ››

‹‹በቃ ተጫወቺ ኩሽና ሄጄ እማዬን ላግዛት፡፡››ብላ ከመቀመጫዋ ተነሳች፡፡

‹‹እሺ ሂጂ …ግን ስልክሽን መጠቀም እችላለሁ?››
‹‹አረ ችግር የለውም…..››አለችና ከጃኬት ኪሷ አውጥታ እጇ ላይ አስይዛት ሄደች….በፀሎት ስልኩን ከፈተችና መፈለግ ጀመረች …..ሪሰንት ኮል ውስት ገብታ ስትፈልግ ሰሎሞን ቦስ የሚል አገኘችና ቁጥሩን በቃሏ ሸመደደች፡፡

በማግስቱ ፊራኦልን ለመደወል የምትገለገልበት ቀላል ስልክና በማይታወቅ ሰው ስም የወጣ ሲም ካርድ እንዲፈልግላት ጠየቀችው…..ያለችውን በግማሽ ቀን ውስጥ አሰረከባት፡፡እና ለብቻዋ የምትሆንበትን ሰዓት አመቻቸችና ከቤቱ ራቅ ብላ ወደጓሮ በመሄድ ደወችለት፡፡
‹‹ሄሎ ኪያ የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ፡፡››

‹‹አዎ ትክክል ነው፡፡››

‹‹እባክህ እገዛህን ፈልጌ ነበር ››
‹‹ችግር የለውም …ቁጥር ልክልሻለሁ… ፀሀፊዬ ጋር ደውይና ቀጠሮ ያዢ››የሚል ምክረሀሳብ አቀረበላት፡፡

ቆፍጠን ብላ‹‹እንደዛ ማድረግ አልችልም››አለችው፡፡

‹‹ማለት?››በንግግሯ ግራ እንደተጋባ ያስታውቃል፡፡

‹‹በጣም ሚስጥራዊ ስራ ነው እንድትሰራልኝ የምፈልገው…››

‹‹የእኔ እህት ንግግርሽ ምንም አልገባኝም..ምን አይነት ሚስጥራዊ ስራ…ለማንኛውም ቢሮ ብቅ በይና በአካል ተገኛኝተን እናውራ››

‹‹አይ እንደዛ ማድረግ አልችልም..ቢያንስ ለጊዜው እንደዛ ማድረግ አልችልም….››

‹‹ታዲያ እንዴት ማድረግ ነው የምትችይው….?፡፡›››ከመገረም ውስጥ ሣይወጣ ጠየቃት፡፡

‹‹ስራው የአምስት ሚሊዬን ብር ስራ ነው…ቅድሚያ ክፍያ መቶ ሺብር እከፍልሀለው…ብሩ እንደደረሰህ ስራውን ትጀምራለህ…..ስራው በስኬት ማጠናቀቅ ከቻልክ እንዳልኩህ 5 ሚሊዬን ብር ታገኛልህ …ይመችሀል፡?››

‹‹ማነሽ…የተሳሳተ ቦታ የደወልሽ መሰለኝ…አምስት ሚሊዬን ብር የምትከፍይኝ ምን እንዳደርግልሽ ብትፈልጊ ነው…?አውቀሻል..እኔ ፍቅርና ጋብቻን በተመለከተ የምክር አገልግሎት የምሰጥ ባለሞያ ነኝ፡፡››ምን አልባት የተሳሳተ ቦታ ደውላ የእሱንም ሆነ የራሷን ጊዜ እያቃጠለች ነው ብሎ ስለገመተ ሊያብራራላት ሞከረ…
‹‹በጣም የተወሳሰበና በነገሮች የተቆሳሰሉ የጋብቻ ተጣማሪዎችን ማገዝ ትችላለህ..?እንደምንም ችግራቸውን ቀርፈውና ይቅር ተባብለው ወደሰላማዊ ህይወት እንዲመለሱ ማድረግ ትችላለህ?፡፡››

‹‹እንደማስበው …ማለቴ ከድምፅሽ እንደምረዳው ገና ወጣት ነሽ….ይሄውልሽ አንድ የጋብቻ አማካሪ በስራው ውጤታማ መሆን የሚችለው ሁለቱ ተጣማሪዎች በመጀመሪያ በመካከላቸው ችግር እንዳለ አምነው ..ከዛም ሁለቱም ለችግሩ በጋራ ኃላፊነቱን ወስደው ለመለወጥ ፍፅም ፍቃደኛ ሲሆኑና ባለሞያው የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ምክር ከቁም ነገር ወስደው ተግባራዊ ሲያደርጉ ነው….አዎ አንቺና የትዳር አጋርሽ ለመለወጥና ትዳራችሁን ለመታደግ ፍላጎቱ ኖሮችሁ ፍጽም ተባባሪ የምትሆኑ ከሆነ አዎ እኔ ጋብቻችሁን ወደቦታው ልመልሰው እችላለው፡፡በዛ ቃል ልገባልሽ እችላለው›

‹‹ጥሩ ..መቶ ሺ ብሩን አዘጋጅቼ ከሶስት ቀን በኃላ ደውልልሀለው››

‹‹ይሄውልሽ….እኔ የማስከፍለው ክፍያ አንቺ ከጠራሽው ብር ጋር ፈጽሞ አይቀራረብም…ቀብድ ያልሽው ብር እራሱ በጣም ይበዛል፡፡››

‹‹አይ ክፍያውን አንተ ሳትሆን እኔ ነኝ የምወስነው….ይሄውልህ እደግመዋለው..ቅድሚያ ክፍያ 100 ሺ ብር ከፍልሀለው…ስኬታማ ሆነህ ጋብቻውን ማከም ከቻልክ የ 5 ሚሊዬን ብር ቼክ ከታላቅ ምስጋና ጋር እጅህ ይገባል…ካልተሳካልህ ደግሞ ከ100 ሺ ብሩ ውጭ ምንም ተጨማሪ ክፍያ አይኖርም፣ገባህ…..?ይሄ ማለት ሌሎች ስራዎችህን በሙሉ ሰርዘህ ወይም ወደሌላ ጊዜ አዘዋውረህ ሙሉ ትኩረትህን የእኔ ጉዳይ ላይ እንድታደርግ ስለምፈልግ ነው..አንድ ወርም ፈጀብህ ስድስት ወር አላውቅም…እስኪሳካልህ ወይም ተስፋ እስክትቆርጥ ሙሉ ትኩረትህን እፈልጋለው…በል ቻው፡፡››ሰልኩን ዘጋችው።

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

08 Nov, 17:00


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

እለቱ እሁድ ነው፡፡ከፊራኦል ጋር ለመውጣት ስለተነጋገሩ እየተዘጋጀች ነው፡፡ለሊሴ እየረዳቻት ነው፡፡
ሰው ከለገመ ከሻማ በላይ በቀላሉ ቀልጦ የሚጠፋ ከጠነከረ ደግሞ ከአልማዝም በላይ ማይቆረጥና ማይሸረፋ ተአምራዊ ፍጡር መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡በፀሎትም የማያልፍ የመሰላት አሰቃይ ህመም በጥቂት ቀናት ውስጥ ጥሏት ሄዶ ንፅህና ጤነኛ ልጅ ሆናለች፡፡የእግሯን ስብራት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ድኗል…የፊቷ ቁስል ግን ምንም እንኳን ቢድንም ጣባሳውና ቁስለቱ አሁንም በግልጽ ፊቷ ላይ ይታያል… በዚህ ምክንያት አሳባ ከፊል ፊቷን ሁሌ በሻርፕ እንደሸፈነችው ነው፡፡ዋና ምክንያቷ ግን ማንነቷ በቀላሉ እንዳይለይ በማሰብ ነው፡፡አሁንም ተመሳሳይ አለባበስ አድርጋ በዛ ላይ ጥቁር መነፅር አይኗ ላይ ሰክታ ዝግጁ ሆነች፡፡

‹‹ግን እህቴ ለምንድነው እኔን የማታስከትሉት?››ለሊሴ ተነጫነጨች፡፡

‹‹አይ …መጀመሪያ ከወንድሜ ጋር የምንሄድበት ቦታ አለ…ባይሆን ከዛ ቶሎ ከጨረስን እንደውልልሽና ትቀላቀይናለሽ››

‹‹ይሁንላች ግን ታበሳጭቼባችኋለሁ››

በታክሲ ከሰፈር ሁለት ፌርማታ ያህል ርቀው ከሄዱ በኃላ ‹‹ደርሰናል እንውረድ›› አላት፡፡ያን ያህል ቅርብ ይሆናል ብላ አላሰበችም ነበር፡፡እንደወረዱ ቀጥታ ፊት ለፊት የሚገኝ በፅድና በባህርዛፍ አፅድ የደመቀ ሰፊ መናፈሻ ውስጥ ነው ይዞት የገባው…ቀጥታ ከሰው ነጠል ያለ ቦታ ይዞት ሄደና ቁጭ እንድትል መቀመጫ አመቻችቶላት ከፊት ለፊቷ ተቀመጠ‹‹እሺ ምን ትጠቀሚያለሽ?››

‹‹ቆይ እስኪ… ምን አስቸኮለህ…መጀመሪያ ትምጣ››

‹‹ማን?››

‹‹ምን ….ማንን ልናገኝ ነው የመጣነው…?ፍቅረኛህ ነቻ…በል ደውልላት፡፡››

‹‹ስልክ የላትም››

‹‹ታዲያ እንዴት ነው የምታገኘን››
‹‹የልቤን ምት አዳምጣ ትመጣለች››

‹‹ጥሩ ትቀልዳለህ….ይሄ የተለመደ መገናኛ ቦታችሁ ነው ማለት ነው…ገባኝ›› አስተናጋጁ መጣችና‹‹ምን ልታዘዝ ?››ብላ ጠየቀች፡፡

በፀሎት ቀደም ብላ‹‹ሰው እየጠበቅን ነው….››ብላ ለአስተናጋጆ መለሰችላት

‹‹አይ አሷን አንጠብቅም..ቆንጆ ፒዛ አሰሪልን…ፒዛው እስኪደርስ እሷም ትደርሳለች››

አስተናጋጆ ትዕዛዙን ተቀብላ ሄደች፡፡

ፊራኦል ወደእሷ አትኩሮ እያያት…..‹‹እስኪ ሻርፑን አንሺው››በማለት ያልጠበቀችውን ጥያቄ ጠየቃት

‹‹እንዴ ለምን?››

‹‹ሙሉ ፊትሽን ለማየት ፈልጌ››

‹‹ኖ ዌይ…..›

‹‹ምን ችግር አለው?››

‹‹እኔ  እራሴ  ሙሉ  በሙሉ  ፊቴ  እንደዳነ  እና  እንደማያስጠላ  እርግጠኛ  ስሆን እገልጠዋለው፡፡››

‹አንቺ እንዴት ልታስጠይ ትችያለሽ…ውብ እኮ ነሽ››

‹‹ሙሉ ፊቴን ሳታይ ውብ መሆኔን በምን አወቅክ…?››ኮስተር ብላ በመገረም ጠየቀችው፡፡

‹‹እኔ እንጃ ውብ እንደሆንሽ ግን እርግጠኛ ነኝ፡፡››

መልስ ልትሰጠው አፏን ስትከፍት አስተናጋጇ የታዘዘውን ፒዛ ይዛ ፊታቸው ስታስቀምጥ አፏን ያለምንም ንግግር ከደነች፡፡

‹‹‹ለእኔ እስፕራይት አምጪልኝ…..ላንቺስ ?›

‹‹እንዴ ልጅቷ ሳትመጣ….?››
‹‹ባክሽ የሆነ ነገር እዘዢ እሷ ስትመጣ የራሷን ነገር ታዛለች››

ግራ እየገባት አዘዘች …ፒዛውን ቆርሶ መብላት ሲጀምር ፣ በገረሜታ ተከተለችው… በልተው ጨርሰው እንኳን ልጅቷ አልመጣችም››

‹‹እንደዛ  ቅኔ  ምትቀኝላት  ልጅ  እስከአሁን  ካልመጣች  ከአሁን  ወዲያም  የምትመጣ አይመስለኝም፡፡››

‹‹መጣችእኮ››

‹‹የታለች?››

‹‹ይህቹት ፊት ለፊቴ ቁጭ ብላ እያወራቺኝ ነው፡፡››

‹‹እየቀለድክብኝ ነው እንዴ?››

‹‹እሺ አትበሳጪ..እኔ ምንም አይነት ፍቅረኛ የለኝም….አንቺን ወጣ አድርጌ ማዝናናት ስለፈለኩ ነው እንደዛ ያልኩሽ››

‹‹አንተ ውሸታም……..ቆይ ምንም ፍቅረኛ ሳይኖርህ ነው እንደዛ ፈዘህ በውድቅት ለሊት ቅኔ ስትዘርፍ የነበረው››

‹‹በተጨባጭ ፍቅረኛ የለኝም አልኩሽ እንጂ በምናቤ ስዬ የማስባት ሴት የለችም አላልኩሽም…..እንደዛ አወራ የነበረው በልቤ ውስጥ ተንሰራፍታ የተቀመጠችውን ልክ እንደአንቺ ውብ የሆነችውን ልጅ እያሰብኩ ነበር››

‹‹ምን አይነት አዝግ ልጅ ነህ….?እኔ ደግሞ እንዴት አይነት ቆንጆ ልጅ ትሆን እያልኩ ለሊቱን ሙሉ ሳስብና ስጓጓ ማደሬ››

‹‹ምን ያጓጓሻል…የፈለገ ውብ ብትሆን ካንቺ አትበልጥ…አንቺ እኮ ሁለመናሽ ውብ ነው…ማለት ስብዕናሽ ፖስቸርሽ..እርግጠኛ ነኝ መልክሽም ውብ ነው..ፍቅረኛዬ ልክ አንቺን ካልመሰለች ልቤን ማሸነፍ አትችልም››ፊራኦል ቀጥታ መንገር ፈርቶ ነው እንጂ ከበፀሎት ፍቅር ከያዘው ሰነባብቷል…ስሩ ሆና እራሱ ትናፍቀው ከጀመረች ቆይታለች..ለዛ ነው ሙሉ ፊቷን ማየት በጣም የናፈቀው…ቆንጆና ውብ ፊት ነው በምናቡ የሳለው…
‹‹ጥሩ ..ግን ስለውበትና ቁንጅና እኮ በእህትና በወንድም መካከል የሚወራ ኮንሰፕት አይደለም…..ባምርም ባስጠላም እንደእህትህ ነኝ…ለውጥ አያመጣም፡፡››

‹‹እንደእህት እና እህት ግን ይለያያል››

ለዚህ ንግግሩ ምን ብላ መልስ ልትሰጠው እንደምትችል ሊመጣላት አልቻለም…‹‹.እኔ የእህትህን ልብ በውስጤ የተሸከምኩ ሴት መሆኔን ብታውቅ ይሄን ሁሉ ርቀት ለመጓዝ አይዳዳህም ነበር››ስትል በውስጧ አብሰለሰለች

//////

በማግስቱ-----
እቤት ውስጥ ማንም የለም..ሌንሳ ብቻ ከበፀሎት ጎን ቁጭ ብላ እያወራቻት ነው፡፡
እህቴ ስራ በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ሆኜያለው….ይገርምሻል ፀሀፊ ሆናለው ብዬ አንድም ቀን ኣስቤ አላውቅም ነበር…››

‹‹ላንቺ እኔ በጣም ደስ ብሎኛል… ስራውን ግን እንዴት ነው..እየለመድሽው ነው? ››

‹‹አሪፍ ነው ..ተመችቶኛል፡፡››
‹‹የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ ነው ያልሽው?››

‹‹አዎ እህቴ …ብታይ ሰውዬው ማለቴ አለቃዬ በጣም ነው የሚያሳዝነው፡፡››

‹‹ለምንድነው የሚያሰዝነው? እሱም ፍቅር ይዞታል እንዴ?፡፡››

‹‹አይ እሱን አላውቅም … ያሳዝናል ያልኩሽ…ምንም ደንበኛ የለውም….ዝም ብለን እኔና እሱ ቢሮ ውስጥ ተፋጠን ነው የምንውለው…››ለምን ያሳዝናል እንዳለች ታስረዳት ጀመር፡፡

‹‹ምነው በስራው ጎበዝ አይደለም እንዴ?››

‹‹አረ በቅርብ ነው ከውጭ የመጣው..በሞያው ኤክስፐርት ነው…እንደነገረኝ ከሆነ አሜሪካ እያለ በሞያው ከሶስት አመት በላይ ሰርቶ በጣም ብዙ ሰዎችን ረዳቷል …እዚህ መጥቶ የራሱን ድርጅት ቢከፍትም እንዳሰበው አልሆነለትም….እንደምታውቂው የእኛ ሰው ድብቅ ነው …ባለትዳሮችም ቢሆኑ እዛው ቤታቸው ውስጥ ሲቋሰሉ ይኖራታል እንጂ ገበናቸውን ወደአደባባይ ማውጣት አያስብትም ..ባስ ቢልባቸው እንኳን እዛው የሰፈር ሽማጊሌ ጠርተው በምስክር ፊት ይጨቃጨቃሉ እንጂ ወደባለሞያ አይሄዱም፡፡ለዚህ ጉዳይ ባለሞያም እንዳለው የሚያውቅ የማህበረሰብ ክፍል አንድ ፐርሰንት የሚሞላ አይመስለኝም፡
‹‹ታዲያ እኮ የሰፈር ሽምግልናው ቀላል ነገር አይምሰለሽ…ሁለቱም ለእኛ ጥሩ ያስባል እና ያስማማናል የሚሉትን ሰው በማሀከላቸው አስቀምጠው ችግራቸውን በግልፅ በመነጋገር
ለመፍታት መሞከር ትልቅ ዋጋ ያለው ማህበራዊ እሴታችን ነው፡፡በዚህም መንገድ በጣም በርካታ ሺ ትዳሮች በየአመቱ ስንጥቃቸው ይደፈናል ስብራታቸው ይጠገናል፡፡››

አትሮኖስ

08 Nov, 16:56


Betty እባላለሁ እድሜ  23 ነው በጣም ቆንጆ  እና ለ kiss የሚገፋፋ ከንፈር አለኝ ስራዬ የ ሆቴል  አስተናጋጅ ነኝ
በምሰራበት ሆቴል በጣም ብዙ ደምበኞች ነበሩኝ  ቀኑን ባላስታውስም ወደ 2:30 አካባቢ ይሆናል ከደንበኞቼ አንዱ መኝታ ቤቱ ድረስ ቢራ እንዳመጣለት ይጠይቀኛል እኔም ቢራዉን ወሰድኩለት ክፍሉ ስገባ ግን ያልጠበኩት
see more....

አትሮኖስ

08 Nov, 05:04


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሁለት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ አቶ ለሜቻ ተንሰቅስቀው እያለቀሱ ነው..፡፡የቤቱ ሰው ሁሉ በድንጋጤ ተሸብሯል…፡፡በፀሎት የምትገባበት ጠፍቷት አብራቸው እንባዋን እያረገፈች ነው፡፡፡ልጃቸው ፊራኦል ላጠፋው ጥፋት አባትዬው ይቅር እንዲሉት በጉልበቱ ተንበርክኮ እየለመናቸው ነው፡፡ ‹‹ልጄ…»

አትሮኖስ

07 Nov, 17:35


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

አቶ ለሜቻ ተንሰቅስቀው እያለቀሱ ነው..፡፡የቤቱ ሰው ሁሉ በድንጋጤ ተሸብሯል…፡፡በፀሎት የምትገባበት ጠፍቷት አብራቸው እንባዋን እያረገፈች ነው፡፡፡ልጃቸው ፊራኦል ላጠፋው ጥፋት አባትዬው ይቅር እንዲሉት በጉልበቱ ተንበርክኮ እየለመናቸው ነው፡፡

‹‹ልጄ ይቅር የምልህ..እያንዳንዱን የገዘኸውን ዕቃ ወይ በየገዛበት መልሰህ ካልሆነም ለሌላ በመሸጥ ገንዘቡን አንድም ሳታጎድል ለልጅቷ ስትመልስ ነው፡፡››

‹‹እሺ አባዬ እንዳልክ አደርጋለው፡፡››

‹‹እኮ ተነስና አድርግ››

‹‹አሁን እኮ መሽቷል….ነገ በጥዋት ተነስቼ እንዳልከው አደርጋለው››

‹‹እስከዛው ላይህ አልፈልግም፣ወይ ቤቱን ለቀህ ውጣ ወይ እኔ ልልቀቅልህ››

‹‹አረ አባዬ… አንተ ምን በወጣህ እኔ ወጣለሁ….››ብሎ ከተቀመጠበት ሲነሳ በፀሎት ከተቀመጠችበት ሆና ጣልቃ ገባች…ጋሼ የሆነው ነገር ሁሉ የእኔ ሀሳብ ነው….ቆርቆሮውም..ሲሚንቶውም ሁሉም የተገዛው በእኔ ሀሳብ ነው፡፡በወቅቱ እሱ እንደማይሆን ነገሮኝ ተቃውሞኝ ነበር..እኔ ነኝ ያስገደድኩት…ስለዚህ ወቀሳውም ቅጣቱም የሚገባው ለእኔ ነው…ለሊሴ ታክሲ ልትጠሪልኝ ትችያለሽ?››

ጥያቄዋ ሁሉንም ሰው አስደነገጠ፡፡

‹‹እንዴ ታክሲ ምን ሊያደርግልሽ?››ለሊሴ ጠየቀች፡፡

‹‹የጋሼን ቅጣት ተግባራዊ ለማድረግ ነዋ…ሆቴል ድረስ የሚወስደኝ ታክሲ ጥሪልኝ…ከቤት መባረር ያለብኝ እኔ ነኝ››

‹‹ተይ እንጂ ልጄ..ለምን ጡር ውስጥ ታስገቢኛለሽ?››አቶ ለሜቻ ለዘብ ብለው ተናገሩ

‹‹ጋሼ ..ይሄ ምንም ጡር አይደለም…ይሄንን እቃ ያስገዛሁት ለራሴ ስል ነው….ያው እንደምታዩት በዚህ አያያዜ ለመዳን ሁለትና ሶስት ወር ይፈጅብኛል ..ከዳንኩ በኋላም ቶሎ የምሄድበት ቦታ ስለሌለኝ ከእናንተ ጋር ቢያንስ ስድስት ወር ኖራለው..ስድስት ወር ሙሉ ደግሞ እንዲህ የለሊሴን መኝታ አስለቅቄ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ መኖር ከባድ ስለሆነ ነው

ሀሳብን ያመጣሁት..እኔ እንደውም ቤቱን ተረባርበን በአንድ ወር ውስጥ አልቆ እኔ ከእነለሊሴ ጋር እኖርበታለው ብዬ ነው››ስትል አብራራች፡፡

‹‹ልጄ ቢሆንም አግባብ አይለም..በእኛ ላይ ይሄን ሁሉ ብር መከስከስ እኛም አሜን ብለን መቀበል ነውር ነው…ሰውን ተይው …እግዚያብሄሩስ ምን ይለናል?››
‹‹አሁን ልጅህ ለሊሴ ብር አግኝታ እንዲህ ብታደርግ ይሄን ያህል ትበሳጭባታለህ?›› ዝም አሉ
‹‹ገባኝ አትበሳጭባትም….እኔንም እንደልጅህ አድርገህ ከምር ብትቀበለኝ ኖሮ ይሄን ያህል ቅር አትሰኝም ነበር..በቃ ለሊሴ ደውለሽ ታክሲውን ጥሪልኝ››
ለሊሴ  ፈራ  ተባ  እለች…  ስልኳን  ከተቀመጠበት  አነሳችና  ለመደወል  ስትዘጋጅ  ጋሽ ለሜቻ‹‹ልጄ ስልኩን አስቀምጪው..እስኪ ሁላችሁም ተቀመጡና እንረጋጋ…››

‹‹አዎ  ልጆች  ሁላችሁም  ተቀምጡ….ለሊሴ  እስኪ  ሲኒውን  አቀራርቢና  ቢና እናፍላ››እናትዬው ውጥረቱ ረገብ ስላለ ተደስተው የተናገሩት ነበር፡፡
////
በማግስቱ

‹‹…አየሩ በጥላቻ ጥላሸት ጠቁሯል፡፡ከፍቅር ዕጦት በሚመጣ የፍራቻ ግንብ ተከልያለው….በንዴቴ አጥር ስር ተሸሽጌ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፡፡ይበርደኛል..አዎ በጠራራ ፀሀይ ይበርደኛል…ይርበኛል..እየበላው ሁሉ ይረበኛል….፡፡ጉሮሮዬ በጥማት ተሰነጣጥቆል….ግን ከዛ ከጥማቴ የሚፈውሰኝ ውሀም ሆነ ምድራዊ ወይን የለም፡፡››በፀሎት ነች የምታወራው…ፊራኦል ግን ምንም አልገባውም

‹‹አንዳንዴ እንደፈላስፋ ነው የምታወሪው?››

‹‹እንደእኔ ህይወትህን ሙሉ በብቸኝነት በራፍ ዘግተህ ለብዙ ሰዓታት በትካዜና በቁዘማ የምታሳልፍ ከሆነ ወደፈላስፋነት መቀየርህ የግድ ነው፡፡ከሞት ደጃፍ ደርሶ..በቃ አበቃልኝ ብሎ ተስፋ ከቆረጠ በኃላ ወደህይወት ተመልሶ ሁለተኛ እድል የተሰጠው እደእኔ አይነት ሰው ነገሮችን በተለየ መልክ ባያይ ነው የሚገርመው፡፡›››

‹‹አልገባኝም የሞት አፋፍ ላይ መድረስ ስትይ?››

ደነገጠች..አንደበቷን አንሸራቷት ሚስጥር ልታወጣ በመድረሶ እራሷን ወቀሰችና‹‹ማለቴ በዛ ለሊት በሞተሬ ከእዚህ በራፍ ጋር ስለ መጋጨቴ እያወራው ነው…የሞትኩ ማስሎኝ ነበር እኮ››

‹‹እ..እሱ እንኳን እውነትሽን ነው….ግን አሁን ፊትሽ ቁስሉ ደርቆል እኮ …ለምን ቀንና ለሊት በሻርፕ ትሸፍኚዋለሽ…››

‹‹እርግጥ እንዳልከው ድኗል ግን ጠባሳው ያስጠላል..እንዲህ ሆኜ ሰው እንዲያየኝ አልፈልግም ..በተለይ ወንዶች ››
ፈገግ አለ….‹‹ዝም ብለሽ እያካበድሽው ነው እንጂ እርግጠኛ ነኝ ከነጠባሳሽ በጣም ቆንጆ ልጅ ነሽ…እንደውም እንዲሁ አቋምሽን ሳየው የት እንደሆነ የማውቃት አርቲስት ወይም ሞዴል ነገር እየመሰልሽኝ ደነግጣለው፡፡››

‹‹አየህ አንደውም ለዚህ ነው ፊቴን ዘወትር በሻርፕ ምጆብነው››

‹‹አልገባኝም››

‹‹ሙሉ በሙሉ ገልጬልህ ፊቴን በደንብ ካየኸው የትኛዋ ሞዴል ወይ አርቲስት እንደሆንኩ ወዲያው ስለምትለየኝ፣እንደዛ እንዳይሆን ስለፈለኩ ነው››

‹‹ትቀልጂያለሽ አይደል?››

‹‹ምን ላድርግ ብለህ ነው….በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያለ እንደእኔ አይነት ሰው ባይቀልድ ነው የሚገርመው››

‹‹እስኪ እርእሱን እንቀይር ፣ሌላው ስለአንቺ የሚገርመኝ  እስከአሁን ሞባይል ይዘሽ አለማየቴ ነው››

‹‹የለኝም…..ማለቴ ከቤቴ ስወጣ ይዤ መውጣት አልቻልኩም፡፡››

‹‹ታዲያ  ልግዛልሽ…ማለቴ  በራስሽው  ብር  የምትፈልጊውን  አይነት  ስልክ  ልገዛልሽ እችላለሁ፡፡››

ፈገግ አለችና‹‹በራስህ ብር ብትገዛልኝ አይሻልም?››

‹‹ደስ ይለኝ ነበር..ግን አቅሜ ላንቺ የሚመጥን ስልክ ለመግዛት በቂ አይመስለኝም…››

‹‹የእኔ አቅም ምን ያህል ነው..?በምንስ ሚዛን ለካሀው…?ለማንኛውም ለጊዜው አያስፈልገኝም…ስፈልግ ግን ነግርሀለው፡፡››

‹‹ይገርማል… በአንቺ እድሜ ያለች ሴት ስልክ አያስፈልገኝም ስትል አጃኢብ ነው፡፡››

‹‹ምኑ ይገርማል..?ለጊዜው ማንም ጋር ለመደወል እቅድ የለኝም..››

‹‹ሶሻል ሚዲያስ….እንዴት ያስችልሻል፡፡››

‹‹ዕድሜዬን ሙሉ ስልክና ላፕቶፕ ላይ አረ አንቺ ልጅ አይንሽ ይጠፋል እየተባልኩ እስክሪን ላይ አፍጥቼ ነው የኖርኩት…ሶሻል ሚዲያ ከጨለማ ሀሳቦቼ እና ከድብርቶቼ መሸሺጊያ እና መደበቂያ ዋሻዬ  ነበር…አሁን  ግን ችግሮቼን ፊት ለፊት መጋፈጥ  ነው የምፈልገው

….እስከአሁን ከኖሩኩት ህይወት በተቃራኒ ነው መኖር የምፈልገው፡፡ይልቅ ከቻልክ ነገ መፅሀፎች ገዝተህልኝ ትመጣለህ፡፡››

‹‹እሺ ምን ምን መፅሀፍ እንደምትፈልጊ ትንግሪኝና ገዝቼልሽ መጣለው፡፡››

‹‹ጥሩ አሁን ደግሞ ምርጥ አንድ ሙዚቃ ብትጋብዘኝ በጣም ደስተኛ እሆናለው…››
‹‹ጥሩ …አለና ከአጠገቡ ያለውን ክራር አንስቶ ክሮቹን በእጁ እያጠበቀ እና እያላላ ቅኝቱን አስተካከለና‹‹ምን አይነት ዘፈን ይሁንልሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹መቼስ በዚህ ውድቅት ለሊት ስለሀገር ዝፈንልኝ አልልህም…የፍቅር ዘፈን ይሁንልኝ፡፡›› እንደማሰብ አለና ክራሩን መገዝገዝ ጀመረ ..አፏን ከፍታ ነበር የምታዳምጠው…
የነገን ማወቅ ፈለኩኝ … መጪውን አሁን ናፈቅኩኝ.. የፍቅር ምርጫዬ አንቺ ነሽ…ልቤንም መንፈሴን የገዛሽ ወሰንኩኝ ልረታ አስቤ፣አካሌን መንፈሴን ሰብስቤ

በፍቅር ህይወቴን ላኖረው..ላልመኝ ፍፁም ሌላ ሰው የፍቅርን ትርጉም ገልፀሸ አስተማርሺኝ
ካንቺ ደስታ ፣እኔን እያስቀደምሺልኝ ፍቅር ለካ ለራስ …ማለት እንዳልሆነ ስታደርጊው አይቶ… ልቤ በቃ አመነ ከነገርሽ…. ባህሪሽ ማርኮኛል…

አትሮኖስ

07 Nov, 17:35


ካንቺ ልኖር ..በፍቅር አስሮኛል ዛሬ ባንቺ ….በጣም ረክቼያለሁ ነገም አብረን ….ሰላም አገኛለው፡፡
በህይወቷ ብዙ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን ተካፍላ ታውቃለች…በአባቷ ቤት ሳለች በተለያዩ ጊዜ ትላልቅ የተባሉ የሀገሪቱ ዘፋኞች እቤታቸው ድረስ መጥተው ሲዘፍኑ ምቹ ሶፋ ላይ ቁጭ ብላ አድምጣ ታውቃላች…በተለያየ ጊዜ ከሀገር ውጭ ለመዝናናት በሄደችበት ጊዜ አለም አቀፍ አርቲስቶች ባዘጋጁት ውድ ኮንሰርት ላይ ታድማ ታውቃለች..እንዲህ እንደአሁኑ ግን ምቹ ባልሆነ ደረቅ ወንበር ላይ በውድቅት ለሊት ብርድ እያንዘፈዘፋት እየሠማችው እንዳለ ሙዚቃ በተመስጦ እያንዳንዱን ቃላት በደስታ አድምጣና አጣጥማ አታውቅም…
‹‹ፍቅረኛህ በጣም የታደለች መሆኗን ታውቃለች?፡፡››
‹‹ታውቃለች..የእኔ ፍቅር እኔን ከእነድምፄ ከመላ እኔነቴ ጋር በጣም ታፈቅረኛለች..በጣም በጣም..››
‹‹አንተስ?››
‹‹እኔማ አፈቅራታለሁ ብል..ቃላቱ የውስጤን ስሜት አይገልፅልኝም….ፍቅር ማለት ምን ማለት ነው…እሷ ስትናፍቀኝ እኮ መተንፈስ እራሱ ከባድ ይሆንብኛል…ምስሏ እናቴ ደግነት ላይ አየዋለሁ…የአዲስ አበባ ከንቲባ ብሆን የከተማዋን ዋና ዋና መንገድ ሁሉ ለስሟ መጠሪያ እንዲሆን አደርግ ነበር….አረ አንጦጦ ታራራ ጫፍ ላይ ቤተመቅደስ ባንፅላት ሁሉ

ደስ ይለኛል…..እና ለእሷ ያለኝ ፍቅር እንዲህ አይነት እብደትና ጅልነት በአንድ ላይ የተቀየጠበት ስሜት ነው፡፡ አንዳንዴ ልብሴን አወላልቄ እርቃኔን ሰው በሚርመሰመስበት መርካቶና ፒያሳ እየተሸከረከርኩ….እኔ እሷን አፈቅራታለው..በጣም አፈቅራታለው..እያልኩ ስጮህ ብውል ደስ ይለኛል..አዎ እንደዛ አድርግ የሚል ስሜት ይተናነቀኛል…ግን ከጃኬቴ ውጭ የተቀረውን ለማውለቅ ወኔ አላገኝም፡፡
‹‹እንዴ..አንተ ለካ ድምፃዊ ብቻ ሳትሆን እብድ የሆንክ አፍቃሪ ነህ….በል በል ነገ እሁድ አይደል..ይህቺን እንደእብድ የምታፈቅራትን ልጅ ታስተዋውቀኛለህ፡፡
‹‹ማንን ፍቅረኛዬን?፡፡››
‹‹አዎ››
‹‹ባስተዋውቅሽ ደስ ይለኝ ነበር…ግን እሷ እዚህ መምጣት አትችለም?››
‹‹ለምን..እ ..ገባኝ..አማቾቻን ትፈራለች ማለት ነው?››
አልመለሰላትም….ዝምታውን ‹‹ትክክል ነሽ ››የሚል መልስ እንደሰጣት አድርጋ ወሰደች፡፡
‹‹በቃ እንደዛ ከሆነ እኔም ውጩ ናፍቆኛል …በኮንትራት ታክሲ ያለችበት ድረስ ትወስደኛለህ፡፡
‹‹እርግጠኛ ነሽ?››
‹‹አዎ እርግጠኛ ነኝ››አለችው..ግን ውስጧ የእርግጠኝነት እና የደስታ ስሜት አይደለም እየተሰማት  ያለው….ፊራኦል  እንዲህ  የሚያሳብድ  አይነት  ፍቅር  ውስጥ  መሆኑንና
…እንደዛም ያሳበደችውን ሴት ፊት ለፊት አግኝታ ልትተዋወቃት መሆኑን ስታስብ ደስታ ሳይሆን ፍራቻ ነው የተሰማት…‹‹ግን ለምንድነው የፈራሁት….?በምን ምክንያት ነው ቅር ያለኝ?››ስትል እራሷን ጠየቀችና አማተበች፡፡
ሁኔታዋን በትኩረት ሲከታተል የነበረው ፊራኦል ‹‹ ….ምነው አማተብሽ ሰይጣን አየሽ እንዴ?››ሲል ጠየቃት
‹‹አይ ውስጤ ሲገላበጥ ስለተሰማኝ ነው?››
‹‹ማ ሰይጣን?››

‹‹አዎ ሰይጣን እኮ ሌላ ምንም ሳይሆን የልባችን ክፋት ነው፡፡ሰይጣን ቅናታችንና ተንኮላችን ነው፡፡››
‹‹እና እንደዛ ከሆነ እኮ በአንቺ ልብ ውስጥ መቼም ሊገባ አይችልም…››
‹‹እንዴት? እኔ ጥሩ ሰው ነኝ አንዴ?››
‹‹እኔ በዚህ እድሜዬ ሶስት በጣም ደግና ቅን ሰዎችና አውቃለሁ››
‹‹እሺ እነማን ናቸው?››
‹‹አንቺንና አባቴን እና …
‹‹ማን…ፍቅረኛህን?››
‹‹አይ አይደለም….ሞች እህቴ በሬዱ…ብታይ የአባቷ ልጅ ነበረች…በጣም ቅን ደግና ሁሌ ለሰው የምትኖር ነበረች…እዚህ መንደር አይደለም በቀበሌው ውስጥ ጦሪ የሌላቸው አቅመ ደካሞችን በየቤታቸው እየሄደች ልብሳቸውን ታጥባለች ..ታበስልላቸዋለች…..የታመሙትን ታስታምማለች…የሆነ ነገረ ሰርታ ብር ካገኘች በማግስቱ እጇላይ የለም…ቸገረኝ ላላት ሁሉ አድላ ባዶዋን ስትቀር ትንሽ እንኳን ቅር አይላትም፡፡ትንሽ ትልቁ እንደመረቃት ነበር፣ዳሩ ምን ዋጋ አለው?››
‹‹ማለት….?››
‹‹ምርቃት እህቴን ከመኪና አደጋ ከለላት…?ምርቃት በወጣትነቷ እንዳትቀሰፍ እረዳት
?አረዳትም…በመዝረፋና ማጅራት በመምታት ሰውን ሲያስለቅሱ የሚውሉ ድርዬና ወሮበሎች እንቅፋት እንኳን ሳይነካቸው በሳለም ህይታቸውን ያጣጥማሉ ፃድቋ የእኔ እህት ግን ገና ምኑንም ሳትይዘው ተቀጠፈች….››
‹‹አይ እንዲህማ አታስብ…እግዚያብሄር እሷን በጊዜ የጠራበት የራሱ የሆነ ምክንያት ይኖረዋል….ምን ይታወቃል የረዘመ ህይወት ብትኖር እንዲህ ንፁህና ቅዱስ እንደሆነች እንደማትቀጥል ስለሚያውቅ ይሆናል በጊዜ የሰበሰባት..ወይንም ህይወቷ በመከራ የተሞላ ሊሆን ይችል ይሆናል…ወይንም ደግሞ በማይድን በሽታ ተይዛ የአልጋ ቁራኛ ሆና ለዘመናት የምትማቅቅ ሊሆን ይችላል….እግዚያብሄር ከደግነቷ አንፃር አይቶ ከክፉ ነገሮች ሊከልላት አስቦ ይሆናል በጊዜ የወሰዳት፣ደግሞ ልብ በል እግዚያብሄር አይሳሳትም…በዛ ላይ እደነገርከኝ እህትህ ሙሉ በሙሉ ሞታ አልሞተችም….አሁንም በሌላ ሰው አካል ውስጥ ከፊል አካሎ ህያው ሆኖ እየኖረ ነው…ሞታ እንኳን ደግነቷን ማስቀጠል ችላለች፡፡››
‹‹ጥሩ አፅናኚ ነሽ…ግን በአቋሜ አንደፀናሁ ነው….ደግነት ይከፍላል በሚሉት ብሂል አላምንም..እንደውም ደግነት ሲከፍል ሳይሆን ሲያስከፍል ነው ያየሁት..እናም አንቺንም ምመክርሽ ደግነትሽን በልክ አድርጊው ብዬ ነው፡፡››
ክትከት ብላ ሳቀች …ሳቋ በገደል ማሚቱ እስተጋብቶ ጆሮ እየተመሰገ ነው   ‹‹..ምን
አይነት መመሳሰል ነው››
‹‹ምን አልከኝ?››
‹‹‹አይ ምንም››
‹‹ይሄውልህ አባትህ ማለት የሰው መልአክ ናቸው፡፡ሙሉ ስብዕና የተላበሱ ቅዱስ ሰው፡፡አንዳንድ ሰው እኮ አንደበቱ ጣፋጭና መልካም ሆኖ ምግባሩ የተበላሸ ይሆናል…ወይም ደግም በምግባሩ አስደናቂና መልካም ሆኖ በአንደመበቱ ያቆስልሀል፡፡አባትህ ግን አንደበታቸው ከምግባራቸው በፍፁም ስምም የሆነላቸው ድንቅ ሰው ናቸው..እንደነገርከኝ እህትህም የአባትህ ቢጤ ነች….እኔ ግን ..አረ ተወኝ በዚህ ሰዓት በእኔ ምክንያት ስንት ሰው እያለቀሰ እና እየተሰቃየ መሆኑን ብታውቅ ከአባት እና እህትህ ጋር ልታነፃፅረኝ አይዳዳህም ነበር፡፡
‹‹ኸረ ተይ አንቺ ሰውን ልታስቀይሚና ልታስጭንቂ ..የማይሆነውን››

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

06 Nov, 06:37


5+5×5-5 = ?

አትሮኖስ

06 Nov, 05:57


የ1000 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 9 ደቂቃ ብቻ ነው የቀራው። ቶሎ ከስር JOIN ሚለውን ነክታቹ JOIN REQUEST ላኩ 🏃‍♀️🏃‍♂️

አትሮኖስ

06 Nov, 05:53


የተወለዱበትን ወር በመምረጥ ኮከቦን ይመልከቱ

አትሮኖስ

05 Nov, 17:42


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ይህቺን ፀሀፊ ልጅ ወዶታል…እሷ እራሷ የመጀመሪያ ደንበኛው ከመሆኗም በላይ ሌላ ደንበኛ አገኝታለታለች፡፡ስልኩን አወጣና ደወለ……አስቴር ጋር… ‹‹እሺ ወንድሜ ደህና ነህ?›› ‹‹አለሁልሽ…የላክሻት ልጅ መታለች ልልሽ ነው፡፡›› ‹‹እንዴት ነው …ተስማማችሁ?››…»

አትሮኖስ

05 Nov, 17:21


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ይህቺን ፀሀፊ ልጅ ወዶታል…እሷ እራሷ የመጀመሪያ ደንበኛው ከመሆኗም በላይ ሌላ ደንበኛ አገኝታለታለች፡፡ስልኩን አወጣና ደወለ……አስቴር ጋር…

‹‹እሺ ወንድሜ ደህና ነህ?››

‹‹አለሁልሽ…የላክሻት ልጅ መታለች ልልሽ ነው፡፡››

‹‹እንዴት ነው …ተስማማችሁ?››

‹‹አዎ ጎበዝ ልጅ ትመስላለች››

‹‹ጎበዝ?››

‹‹አዎ ምነው?››

‹‹አይ በአንድ ቀን እንዴት ጎበዝ መሆኗን አወቅክ ?ብዬ ገርሞኝ ነዋ››

‹‹ማለቴ እንዲሁ  ሳያት ተግባቢና ቀልጣፍ ነገር ነች ልልሽ ነው››

‹‹ወንድሜ ፍቅር እንዳይዝህና እንዳትጎዳብኝ…ልጅቷ ፍቀረኛ አላት››

‹‹አይዞሽ አታስቢ አውቃለው፣በዛ ላይ እኔ ማፈቀሪያ ጭንቅላቴ የተበላሸብኝ ሰው ነኝ….››

‹‹ምኑ ነው ምታውቀው?››

‹‹እንዳላት ነዋ››

‹‹ከምኔው?››

‹‹ውይ ኪያ ደግሞ ….በቃ ቻው ማታ ቤት እንገናኝ››

‹‹እሺ ቻው ወንድሜ››በተንከትካች ሳቅ አጅባ ስልኩን ዘጋችው፡፡

////
ወላጇቾ ብቻ ሳይሆኑ ያደገችበትና የእድሜዋን ግማሽ የኖረችበት እቤቷም ጭምር ናፈቃት‹‹ ቤት ማለት..ግን ምን ማለት ነው?ስትል እራሷን ጠየቀችና መልሱን ከአእምሮዋ ውስጥ በርብራ ለማግኘት አይኖቾን ጨፍና ማሰላሰል ጀመረች

‹‹አዎ እቤት ከድንጋይ ወይም ከእንጨት የሚታነፅ የሰው ልጅ መጠለያ ነው።ያንን ህንፃ ከመጠለያነት ወደ ቤትነት የሚቀይረው ግን የታነፀበት ማቴሪያል ጥራትና ውበት አይደለም...ውስጡ ያሉት  ዘመናዊ የቤት እቃዎች እና ውድነትም አይደለም። ህንፃው ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች እርስ በርስ ያላቸው ግንኙነትና የፍቅር ትስስር መጠን ነው ህንፃውን እቤት የሚያደርገው።ለዚህ ነው ከኖርኩበት የተንጣለለ ቪላ ይልቅ አሁን እየኖርኩበት ያለሁት ባለ ሁለት ክፍል ጎስቋላ ቤት የተሻለ የሚሞቀውና የሚደምቀው
››መልሱን ለራሷ ሰጠች፡፡ ቀኑን እንዲሁ በሀሳብና በትካዜ ጊዜውን ብታሳልፍም ሲመሽ ግን ሁሉ ነገር የተለየ ሆነ፡፡

ማታ የቤተሰቡ አባል ጠቅላላ ተሰብስበው በሞቅ ደስታ ከወትሮ በተለየ ድግስ መሰል እራት ቀርቦ በመጎራረስ ከበሉና ቡናም ተጠጥቶ ከተነሳ በኃላ በፀሎት ሽንት ቤት ለመሄድ እንድምትፈልግ ለለሊሴ ነገረቻት…ያሰበችው እሷ ደግፋ እንድትወስዳት ነበር…በተቀራራቢ እድሜ ስለሚገኙ እቤት ውስጥ ካሉ ሰዎች ሁሉ እሷን ማዘዝ ወይም ትብብር መጠየቅ ቀላል ይላታል፡ ….ለሊሴ ግን እንዳሰበችው አላደረገችም….
‹‹ወንድሜ በፀሎትን ሽንት ቤት ትወስዳታላህ?››ብላ ስትጠይቀው ክው ነበር ያለችው….እሱ አንደበት አውጥቶ ፍቃደኝነቱን ሳይናገር በቀጥታ ከተቀመጠበት ተፈናጥሮ ተነሳና ወደእሷ በመሄድ ልክ ትናንት ለሊት እንዳደረገው ከስር ሰቅስቆ ልክ እንደህፃን ልጅ አቀፋት….እንዲህ አይነት ሁኔታ በህይወቷ ገጥሞት ስለማያውቅ መደንገጥ ብቻ ሳይሆን እፍረትም ተሰማት…‹‹.ወላጆቹ እንዲህ ሲያቅፈኝ ምን ይላሉ ?››የሚለው ሀሳብ አእምሮዋ ተሰነቀረና ያንን ለማጣራት እይታዋን በቤቱ ዙሪያ ስትሽከረከር ሁሉም በራሳቸው ጫወታ ተመስጠው እርስ በርስ እያወሩ እየተሳሳቁ ነው……አንከብክቦ እንዳቀፋት ይዟት ወጣ
..ቀጥታ ሽንት ቤት ወሰዳና ወደውስጥ አስገብቶ አቆማት…ልክ እንደሌሊቱ ውሀ በሀይላንድ ከቧንቧው ቀድቶ አመጣላትና የሽንት ቤቱን መጋረጃ ወደታች መልሶ ‹‹ስትጨርሺ ጥሪኝ
››ብሎ ከአካባቢው ዞር አለ፡፡

የሽንት ቤት ጣጣዋን ከጨረሰች በኋላ ቀጥታ ወደቤት አይደለም ይዞት የገባው፡፡ልክ እንደለሊቱ ወንበር አመቻችቶ ስለነበር ተሸክሞ ወስዶ አስቀመጣት….‹‹ቀኑን ሙሉ ተኝተሸ ስለዋልሽ አሁን ትንሽ ንፍስ ይንካሽ››

‹‹አዎ ትክክል ነህ፣በዛ ላይ ጨረቃዋም ናፍቃኝ ነበር፡፡››
እሱም ለራሱ መቀመጫ አምቻችቶ ከፊት ለፊቷ እየተቀመጠ‹‹ከጨራቃዋ ጋር ወዳጅ ናችሁ እንዴ?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹አዎ ለዛውም የእድሜ ልክ››

‹‹ያን ያህል ብቸኛ ነሽ ማለት ነው?››

‹‹እንዴት ከጨረቃ ጋር ለመወዳጀጀት ብቸኛ መሆን የግድ ነው እንዴ?››

‹‹አይ የግድ ባይሆንም ከልምዴ ስነሳ ብዙውን ጊዜ ከጨረቃዋ ጋር ለረጅም ጊዜ የማውጋት ልምድ ያላችው እንቅልፍ አልባ ብቸኛ ሰዎች ናቸው……በተለይ በፍቅር የተሰበሩ››

‹‹እንዴ በፍቅር የተሰበሩ ነው ያልከው..አይ እንደዛ እንኳን አይደለም…..ባይሆን እንዳልከው ከቤተሰብ ጋር በተያያዘ በሚፈጠር ብቸኝነት ብንለው የተሻለ ነው..የፍቅር ጉዳይማ ቢሆን በምን እድሌ..ፍቅር እኮ በጣም ምርጥ ነገር ነው፡፡››

‹‹ትክክል ነሽ… ፍቅር በጣም ወሳኝ ስሜት ነው….አንድ ሰው ሩሚን ‹‹ፍቅር ምንድነው?››ብሎ ጠየቀ።ሩሚም ..‹‹ፍቅር ምን እንደሆነ ትክክለኛ ትርጉሙን ልታውቅ የምትችለው ውስጡ መጥፋት ስትችል ነው።›› ብሎ መለሰለት…..፡፡

‹‹አዎ ትክክለኛ አባባል ይመስለኛል….ፍቅር የምትተነትነውና የምታወራው ነገር አይደለም፣ፍቅር ኖረህ የምታጣጥመው የተቀደሰ ስሜት ነው….በፍቅር መጥፋት ጥሩ አባባል ነው››

‹‹አይ ጥሩ…ለማንኛውም ለደቂቃም ቢሆን እስቲ ከጨረቃዋ ጋር ብቻችሁን ልተዋችሁ…. መጣሁ›› ብሎ ተነስቶ ወደቤት ገባ..እሷ አይኖቾን ወደላይ አንጋጠጠች…ሰማዩ ጥርት ብሎ ይታያል ፡፡ጨረቃዋ ሙሉ ክብ ሆና ደፍናለች..ዙሪያዋን የተበተኑና ከዋክብቶች ብልጭ ድርግም እያሉ ይታያሉ…አናትና አባቷ ትዝ አሏት..ይሄኔ የእሷን መጥፋት ምክንያት በማድረግ የመጨረሻውን ጥል እየተጣሉና የመጨረሻ የተባለውን አንጀት በጣሽ ስድብ
እየተደሰዳደብ እንደሆነ በምናቧ አሰበችና ሙሉ ሰውነቷ ሽምቅቅ አለባት..ሰውነቷ ሲሸማቀቅ ደግሞ የእግሯ ሆነ የፊቷ ጥዝጣዜ ህመም ተቀሰቀሰባት….
ድንገት የሰማችው ድምፅ ነው ከሀሳቧ ያባነናት…..ያልገመተችውን ነገር ነው እያየች ያለችው..ፊራኦል ፊት ለፊቷ ቅድም የነበረበት ቦታ ቁጭ ብሎ ክራር እየከረከረ የሙሀመድ አህመድን የትዝታ ሙዚቃ ያንቆረቁራል….ፍዝዝ ብላ በፍፁም ተመስጦ ታዳምጠው ጀመር፡፡
ስንቱን አስታወስኩት…ስንቱን አስብኩት ልቤን በትዝታ ወዲያ እየላኩት
አንዴ በመከራ …አንዴ በደስታዬ ስንቱን ያሳየኛል ..ይሄ ትዝታዬ

በድምፁ ድንዝዝ ብላ ጠፋች………… የትናንቱ ፍቅር ….ጣሙ ቁም ነገሩ ምነው ያስተዋሉት ያዩት በነገሩ
ሁሉም እንደገና ኑሮን ቢያሰላስል አይገኝም ጊዜ ያኔን የሚመስል፡፡

ዘፈኑን ሲጨርስ‹‹አንተ..አንድ ሺ አመት በዚህ ምድር ላይ ኖረህ ከዛሬ 500 ዓመት በፊት ያለውን ጊዜ ናፍቀህ የምትተክዝ እድሜ ጠገብ አዛውንት ነው የምትመስለው፡፡››የሚል አስተያየት ሰጠችው፡፡

‹‹ያን ያህል?››

‹‹አዎ …ድምፅህ በጣም ግሩም ነው….ሙዚቃ ትሰራለህ እንዴ?››

‹‹አይ ያን ያህል እንኳን ሰራለሁ ማለት አልችልም …በፊት በፊት ቀበሌ ኪነት ከጓደኞቼ ጋር እሞክር ነበር አሁን ከህይወት ሩጫ ጋር አብሮ አልሄድ አለኝና ተውኩት፣እንዲህ አንደዛሬው ጨረቃዋ ሙሉ ስትሆን እንዲህ እቀመጥና ለእሷ አዜምለታለው፡፡››

‹‹እንዴ..ለእኔ የዘፈንክልኝ መስሎኝ ውስጤ በደስታ ተፍነክንኮ ነበር ..ለካ ለጨረቃዋ የተዘፈነውን ዘፈን ነው ሳይፈቀድልኝ የሰማሁት…..››

‹‹አይ እንደዛ አንኳን ለማለት አልችልም…የዛሬው ዘፈን ቀጥታ ላንቺ ነው..ምስጋናና ይቅርታ ለመጠየቅ፡ ብዬ ነው የዘፈንኩት፡፡››

‹‹አልገባኝም..ይቅርታውስ ለምን ?ምስጋናውስ?፡፡››

‹‹ይቅርታው ገና ስትመጪ ጀምሮ በሙሉ ልቤ ስላልተቀበልኩሽና ለእኔም ሆነ ለቤተሰቦቼ እንደሸክም ስለቆጠርኩሽ…ምስጋናው ዛሬ እናቴንም ሆና መላ ቤተሰብን አንበሽብሸሽ በማስደሰትሽ…..››

አትሮኖስ

05 Nov, 17:21


​​‹‹ተው ተው..አሁን ከዚህ ውብ እና አስደሳች ሙዚቃ በኃላ እንዲህ አይነት ንግግር አስፈላጊ ነው…?ይሄውልህ ምን አልባት አንተ ፍቅር በሚፈስበት ቤት ውስጥ በስስት በሚተያዩ ወላጆች እቅፍ ውስጥ ያደክና እስካሁንም እየኖርክ ያለህ ሰው ስለሆንክ ስለመገፋትና ጥላቻ ያለህ እውቀት አናሳ ይመስለኛል….አዎ እንዳልከው ከልብህ በደስታ አልተቀበልከኝም ይሆናል…ግን ደሜን ሲጠርጉ አብረህ ጠርገሀል….በህመም ስጮህ አዝነህ ስትሸማቀቅ ነበር…በእኩለ ለሊት እንደህፃን ተሸክመህ ሀኪም ቤት ወስደሀኛል…. ሽንት ቤትም ስታመላልሰኝ ነበር፡፡ …አእምሮህ የተወሰኑ ክፉ ነገሮችን አሰቦ ቢፈታተንህም ልብህ ግን መልካምና በፍቅር የተሞላ ስለሆነ ድርጊቶች በአጣቃላይ መልካምና ውብ ነበረ….በዚህም ምስጋናዬ ለዘላለም ነው…፡፡ደግሞ አደረግሽ ላልከኝ ..ምንም ያደረኩት ነገር የለም..እኔ እራሴ የምጠቀምበትን ዕቃዎችና የምበላቸውን ምግቦች ነው የተገዛበት፣ይልቅ አንድ ነገር ላስቸግርህ አስቤያለው፡፡››

‹‹ምንድነው..ምችለው ከሆነ ችግር የለውም… ጠይቂኝ››

‹‹በእኔ እና አንተ መካከል በሚስጥር የሚያዝ ነው››

‹‹እኮ ልስማው››
‹‹ትናንት ለሊት የነገርከኝ ትዝ ይልሀል አባትህ ዕቁብ የገባበትን ምክንያት››

‹‹አዎ ትዝ ይለኛል፡፡››

‹‹እንደነገርከኝ ከሆነ ከእዚህ ቤት ቀጥሎ አንድ ሰርቢስ ሊሰራ ነው….››

‹‹አዎ  ይሄ  የተቆለለው  ብሎኬት  ለዛ  የተገዛ  ነው፡፡ነፍሷን  ይማርና  እህቴ  ነበር የገዛችው…ይሄም አሻዋ እንደዛው፡፡››

‹‹ጥሩ ….ስለዚህ ቀሪ የሚያስፈልገው ነገር ምን ምን ይመስልሀል?››

‹‹ያው  ሀያ  ቆርቆሮ  ..ሚስማር  ሲሚንቶ….በራፍ  መስኮት..በዋናነት  እነዚህ  ናቸው የሚያስፈልጉት..ከዛ አባዬ እራሱ ግንበኛም ሀናጢም ስለሆነ የባለሞያ ወጪ የለበትም››

‹‹ስንት ብር የሚፈጅ ይመስልሀል?››

የጥያቄው መአት ውሉ ስላልገባው‹‹ምን አስበሽ ነው?››ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹ንገረኝ ስንት ይፈጃል?››
‹‹ለማሰቢያ የሚሆኑትን 5 ደቂቃ ካባከነ በኃላ  ብዙ ነው እስከ50 ሺብር የሚፈጅ ይመስለኛል…››

‹‹ጥሩ አንድ ሀሰብ አለኝ..ሁለት ክፍል ቢሆን ግን ጥሩ ነው››
በጭለማ ውስጥ አፍጥጦ አያት..ይህቺ ልጅ ጭንቅላቷን የተመቻችው ከቆይታ በኃላ ተናግቶ አሁን እያቃዣት ይሆን እንዴ ?››ሳል አሰበ፡፡

‹‹አልገባኝም፡፡››

‹‹አንዱ ክፍል የሚቀጥለው እናንተ ጎረምሶቹ እንድታድሩበት አይደል.?››

‹አዎ ትክክል ነሽ…››

አንዱ አነስ ያለ ክፍል ደግሞ እንዲህ ወደ ዋናው መንገድ ጠጋ ብሎ ቢሰራና በውጭ በኩል በራፍ ቢወጣለት ጥሩ አይደል…?››

‹‹ለምኑ ነው ጥሩ የሚሆነው?››

‹‹አንተ ደግሞ አይገባህም እንዴ ?ለለሊሴ ፀጉር ቤት እንድትከፍትበት  ነዋ…ሞያ አላት
….የራሷን አነስተኛ ፀጉር ቤት ብትከፍት እኮ በጣም ድንቅ ነው፡፡››

‹‹በጣም ድንቅ ነው..ግን አንቺ ሰላም ነሽ?››

‹‹አዎ ሰላም ነኝ…..ምነው ጠየቅከኝ?››

‹‹ይሄ ሁሉ የምታወሪው የሟች እህቴ እቅድ ነበር..አሁን አንቺ በማይጨበጥ ሀሳብ እንድቃዥ እያደረግሺኝ ነዋ፡፡››

‹‹አይ እንደዛ አይደለም…ነገ ስራ መቅረት ወይም ማስፈቀድ ትችላለህ? ››

‹‹እችላለው…ግን ለምን?››
‹‹100 ሺ ብር እሰጥሀለው..ያልኩህን ሁለት ክፍል ቤት ለመስራት የሚያስፈልግጉትን እቃዎችን በሙሉ ትገዛና አምጥተህ ግቢውስጥ ትዘረግፈዋለህ…ከዛ ጋሼ ትንሽ ይቆጣል ግን ምንም ማድረግ ስለማይችል ቤቱን ወደመስራት ይገባል፡፡››

‹‹እየቀለድሽ አይደለም አይደል፡?››

‹‹እኔ በቤተሰብ ጉዳይ አልቀልድም?››

‹‹መቶ ሺ ብር ብዙ ነው እኮ..?ከየት ታመጫለሽ..?››

‹‹ከዛ የበለጠ ብር አለኝ…እና ደግሞ ካልበቃም…ጌጣ ገጦቼን ብዙ ብር እንደሚያወጡ የነገርከኝ አንተው ነህ…..ቤቱ እንዳለቀ እሱን እንሸጥና የፀጉር ቤት ዕቃዎችንና ማሽኖችን እንገዛበታለን ለሊሴን ሰርፕራይዝ እናደርጋታለን፡፡
በዛውም እግረመንገዳችንን የሞች እህትህን ምኞት እውን እናደርግና ነፍሷ ባለችበት አፀደገነት እንድትደሰት እናደርጋለን….ግን እስከዛው ጉዳዩ በእኔ እና በአንተ መካከል ሚስጥር ነው….በል አሁን እግሬን እየጠዘጠዘኝ ነው ወደውስጥ መልሰኝ፡፡››አለችው፡፡

‹‹እሺ..ግን እወቂ በቁሚ እንድቃዥ እያደረግሺኝ ነው…እህቴ በሬዱ ከሞት ተነስታ እያወራች ያለ እየመሰለኝ ነው፡፡››አለና እንዳመጣት አንከብክቦ አቅፎ ወደውስጥ ይዞት ገባ፡፡እሷም ‹‹አዎ ..አሁን እያወራች ያለች እህትህ ነች ..የእሷ ልብ ባይቀይረኝ እኔ እንዲህ አይነት ለሰው አሳቢና ተጨናቂ ሰው አልነበርኩም››ስትል በውስጦ አብሰለሰለች፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

05 Nov, 17:07


የ ስንተኛ ክፍል ተማሪ ናችሁ?

አትሮኖስ

05 Nov, 16:54


🥰ለፕሮፋይል የሚሆኑ ገራሚ ገራሚ ፎቶዎችን ለማግኘት ከስር ጆይን ያድርጉ የፈለጉትን አይነት ያገኛሉ ይ🀄️🀄️ሉን!👇

https://t.me/+UqU8zCoHqyw2NzQ0

አትሮኖስ

04 Nov, 17:22


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አስር


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሀሳቧን ሳትጨርስ ፊራኦል ከውጭ ስልኩን እየጎረጎረ መጥቶ ፊት ለፊቷ ቁጭ አለ…ለረጅም ደቂቃዎች አላናገራትም …

‹‹ይሄን ያህል ምን ቢመስጥህ ነው?››

‹‹ባክሽ የድሮ መስሪያ ቤቴ..ማለቴ ቆርቆሮ ፋብሪካ ምናምን ብዬ አውርቼሽ ነበር አይደል?››

‹‹እ..ስለምትናፍቅህ ልጅ እያወራኸኝ ነው?››

‹‹አዎ ..ትክክክል?››
‹‹እና እሷ ምን ሆነች?››

‹‹እባክሽ ጠፋች…አንድ ብቸኛ ልጃቸው ጠፋችባቸው…ከዛሬ ነገ አገኛታለሁ ብዬ ስቃትት የእህቴንም ልብ ይዛ ጠፋች››

‹‹ጠፋች ማለት?››

‹‹እኔ እንጃ ..ዛሬ ሶስተኛ ቀኗ ነው…ማህበራዊ ሚዲያው ሁሉ ስለእሷ ነው የሚያወራው››

‹‹ስለጠፋች ብቻ?››

‹‹አዎ አባትዬው ያለችበትን ለጠቆመ 5 ሚሊዬን ብር በሽልማት መልክ እክፍላለሁ ብሎ ስላሳወጀ ምድረ ዱርዬ ጠቅላላ መንገድ ላይ ያገኞትን ወጣት ሴት ሁሉ እያስቆሙ ከእሷ ፎቶ ጋር ማስተያያት ጀመረዋል፡፡››

‹‹እየቀለድክ መሆን አለበት?››
‹‹እውነቴን ነው…አታይውም እንዴ..?››ብሎ ስልኩን አቀበላት… ማህበራዊ ሚዲያውን የተቆጣጠረውን ሁለት ሶስት ፎቶዋን አየች…ውስጧን በረዳት…ግማሽ ፊቷ በፋሻ የተሸፈነ ቢሆንም አስተውሎ ያያት ሰው ሊለያት ይችላል…ፊቷ የተቀመጠው ፊራኦል እስከአሁን እንዴት እንዳለያት ተደንቃለች፡፡
ስልኩን መለሰችለት‹‹ምን ሆና ይሆን …..?የሀብታም ልጅ ነገር ይሄኔ ቀብጣ ሊሆን ይችላል?››ስትል አፏ ላይ እንደመጠላት ተናገረች፡፡

‹‹አይ እንደዛ እንኳን ብሎ ድምዳሜ ላይ መድረስ አይቻልም…እሷ የሀብታም ልጅ ስለሆነች ነገሩ ጮኸ እንጂ በየቀኑ እኳ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች እዚህም እዛም ከያሉበት ተወስደው የሚጠለፉበት…በሰው ሚሊዬን ብር የሚጠየቅበት ሀገር ነው እኮ ያለነው….ስንቶች የተጠለፈባቸውን ልጃቸውን ወይም ባላቸውን ለማስመለስ ቤታቸውን ሸጠዋል…?ስንቶች የመኪናቸውን ሊቭሬ አስይዘው አራጣ ተበድረዋል….?.ንብረቱን አሟጦ ሸጦ ከከፈለስ በኋላ ስንቱ ሬሳ ተልኮለታለል…….እዚህ አገር በዚህ ጊዜ እየሆኑ ያሉትን ነገሮች እንኳን ለማውራት ለማሰብም ይከብዳ…እና ይህቺ ልጅ ምን እንደገጠማት ማንም የሚያውቅ የለም….፡፡››

‹‹እንዲህ አይነት ነገር መኖሩን አላውቅም››

‹‹እንዴ!! ሀገር ውስጥ እየኖርሽ አልነበረም እንዴ…..?ክፍለሀገር ያለች የእናቱን ሞት ሰምቶ ሄዶ መቅበር ያልቻለ ስንት አለ….?ዘመድ ከዘመድ ከተቆራረጠ እኮ ቆየ፣ስንቱ የትውልድ አካባቢውን ሄዶ ለማየት ልክ እንደአውሮፓና አሜሪካ እንደመሄድ ከባድና የማይቻል ሆኖበታል…እና የዚህች ልጅ ቤተሰብ ጭንቀታቸውን ተመልከቺ…ስንቱን ያስባሉ… እህቴ ብትሆንስ ብዬ ሳስብ ዝግንን ይለኛል…እንደውም በቀደም የሰማሁትን ታሪክ ላጫውትሽ…››
በጉጉት ትኩረቷን ወደእሱ አቅንታ‹‹እሺ እየሰማሁህ ነው..››አለች ፡፡

ከአስር ወራት በፊት አዳማ አካባቢ ካለ አንድ የጠበል ቦታ ታጣቂዎቹ ድንገት ይመጡና የተወሰኑ ሰዎች አፍነው ይወስዳሉ፡፡ከተወሰዱት ውስጥ አንዱ ከአርሲ አካባቢ ነው የመጣው…የተጠየቀውን ብር ወላጆቹ በቀላሉ ማሟላት አይችሉም ቢሆንም ተለምኖና ከየሰው ተለቃቅሞ ከተጠየቀው ሩቡን ያህል ብር ለታጣቂዎች ይላክና የልጁ መለቀቅ ይጠበቃል..ግን ከዛሬ ነገ ይመጣል ሲባል ወራቶች ያልፋሉ፣..እናት እንቅልፍ ታጣለች…ቀንና ለሊት ማልቀስ ይሆናል ስራዋ…ልጇ ይኑር ይሙት የምትጠይቀው ሰውና የምታጣራበት መንገድ አልነበራትም…በመጨረሻ ሰው መፍትሔ ያለውን ይነግሯታል…የሞተ ሰው ነፍስ ጠርተው የሚያናግሩ ሰዎች ጋር ይዘዋት ይሄዳሉ…እንደተባለውም የልጇ ነፍስ ሲጠራ ይመጣል..‹‹አዎ እማዬ እኔ ልጅሽ ከሞትኩ 6 ወር አልፎኛል….እርምሽን አውጪ ይላታል››እናትም ወደቤቷ ተመልሳ ድንኳን ጥላ የልጇን እርም ታወጣለች…ዘመድ አዝማድ ሁሉ ለቅሶ ደርሶ እርማቸውን ያወጣሉ..በጣም የሚገርመው ምፀት ደግሞ ምን መሰለሽ እሷን ለቅሶ ለመድረስ ከሚመጡት የቅርብ ዘመዶቾ ውስጥ ሶስቱ ዳግመኛ በታጣቂዎች ተጠልፈው አረፉት፡፡››

ንግግሩ ይበልጥ ሆድ እንዲብሳት አደረጋት..እንባዋን ሊዘረገፍ ሲተናነቃት ተሰማት..
እሱ ንግግሩን ቀጠለ…‹‹አባዬ ይሄንን ባይሰማ ደስ ይለኛል…ከሰማ በጣም ነው የሚያዝነው….እሷን ሰፈራቸው ድረስ እየሄደ ከመኪና ስትወርድና ከቤት ስትወጣ እንደሚያያት አውቃለው…ልጄን በውስጧ ይዛለች..እሷን ሳያት ልጄ በከፊልም ቢሆን በህይወት እንዳለች ይሰማኝና እፅናናለው ይላል…ይገርምሻል እኔ እራሱ እንዲዚህ እንዳስብ ተፃዕኖ ያደረገብኝ እሱ ነው››

‹‹ይገርማል ….ግን ጋሼ ምን በሩቅ አሳያቸው ማለቴ እቤት ገብተው ቢያዮት እኮ ሰዎቹ የሚቃወሙ አይመስለኝም፡››

አዎ እንዳልሽው አይቃሙም ይሆናል..ግን አባዬ እኛን ፊት ለፊታቸው ካዩ ይሳቀቃሉ…ልጅቷ ፊት ከቀረብን ማልቀሳችን አይቀርም.. እሷ ፊት ማልቀስ ማለት ደግሞ ልጅቷ ልክ በሌላ ሰው ህይወት እንደምትኖር እንድታስብ ማድረግና ልጅቷን መጉዳት ነው….ሁላችንም ከእሷም ሆነ ከቤተሰቡ በስህተት እንኳን መገናኘት የለብንም ብሎ ቁርጥ ያለ ትዕዛዝ ለሁሉም አስተላልፏል…እኔንም ከዛ ፋብሪካ ስራዬን ጥዬ እንድወጣ ያስገደደኝ በዛ ምክንያት ነው፡፡አሁን አሁን ግን ያንን የእሱን ትዕዛዝ ለመጠበቅ እየተቸገርኩ ባለሁበት ሰዓት ነው…ይሄው አንደምታይው ልጅቷ የጠፋችው…››

‹‹‹በቃ ደከመኝ መሰለኝ ትንሽ ልተኛ ››ብላ አልጋ ልብሱን ወደላይ ሳበችና ሙሉ በሙሉ ተሸፈነችና ..በፀጥታ እንባዋን ዘረገፈች…አባትና እናቷ አሳዘኗት….ቢሆንም ለአመታ ያበሳጮትን ብስጭት ልትረሳላቸው አልቻለችም….በውሳኔዋ ፀንታ እስከመጨረሻው መቆየት እንዳለባት ዳግመኛ ወሰነች፡፡‹‹አዎ አሁን እያዩት ያሉት ስቃይ ይገባቸዋል››በማለት በረጅሙ ተነፈሰች፡፡

////
ሰለሞን በሶስተኛው ቀን አርፍዶ ሶስት ሰዓት አካባቢ ወደቢሮ እየሄደ ሳለ ስልኩ ጠራ…የማያውቀው አዲስ ቁጥር ነው…አነሳው፡፡

‹‹ኪያ የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ ነው፡፡››ድርጅቱን ኪያ ብሎ የሰየመው አስቴርን ለማስደሰት ስለፈለገ ነበር…አስቴር እናቷ ከመሞታቸው በፊት ‹‹ኪያ ›› እያሉ ነበር የሚጠሯት እሱም አልፎ አልፎ ይሄንን ስም ይጠቀማል…ድርጅት ለመመስረት ሲያስብ ግን ወዲያው በምናብ የመጣለት ስም ይህ ኪያ የሚለው ስም ነው፡፡እንደምንም ብሎ አግብቶ ከእሷ ጋር አንድ ቤት መኖር ሲጀምሩ ደግሞ ሙሉ በሙሉ በወጥነት ኪያ የሚለውን ስም ይጠቃማል..ሚስቱም ሆነ ድርጅቱ በአንድ ስም ይጠራሉ…ይህ ነው እቅዱ፡፡

ሴሎቹ ሁሉ ተነቃቁ…‹‹በስተመጨረሻ ተሳካ…በስተመጨረሻ የመጀመሪያ ደንበኛዬን አገኘሁ….‹‹ሰሎሞን ጀግና ነህ፣›››ብሎ ተደሰተና ድምፁን ጎርነንና ሻከር አድርጎ፡፡‹‹አዎ ትክክል ኖት..ምን ልታዘዝ?፡፡››ሲል መለሰ፡፡
‹‹እባኮት የቢሮዎትን ትክክለኛ አድርሻ ላስቸግሮት…?››

‹‹ሜክሲኮ ኬኬር ህንጻ 3ተኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 102 ፡››

‹‹አመሰግናለው ..ከ15 ደቂቃ በኃላ ደርሳለሁ›› ስልኩ ተዘጋ፡፡
እሱ ደግሞ ቢሮ ለመደርረስ 5 ደቂቃ ብቻ ነው የሚቀረው..

አትሮኖስ

04 Nov, 17:22


​​‹‹ቢያንስ የመዘጋጃ 10 ደቂቃ ይኖረኛል›› ሲል አሰበ…‹‹ ደንበኛዬ መጀመሪያ የምትፈልገውን ምክር ሆነ ማንኛውንም አገልግሎት በነፃ ነው የምሰጣት ..ክፍያ አልቀበልም….››ሲል ወሰነ ፡፡መልሶ ደግሞ ሀሳቡን ቀየረ‹‹አይ እንደዛማ አይሆንም….የእኛ ሰው ላልከፈለበት ነገር የሚሰጠው ዋጋ ትንሽ ነው….ምክሬን ከልቧ ሰምታ ተግባራዊ ለማድረግ የምትሞክረው ገንዘብ ካወጣችበት ብቻ ነው….ስለዚህ ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያማ ላስከፍላት የግድ ነው…አዎ የተወሰነ አስከፍላታለው.፡፡››ሲል ውሳኔውን አሻሻለ፡፡.ቢሮው ደረስና ከፍቶ ገባ….፡፡የተዝረከረኩ ነገሮችና የተቀዳደቁ ወረቀቶችን አነሳሳና አስተካከለ…ቢሮው ሁለት ክፍል ሲሆን የመጀመሪያውን የፊት ለፊቱን በመተው ወደ ውስጠኛው አለፈና ወንበሩ ላይ ተመቻችቶ ተቀመጠ፣ሌላ ነገር ለማሰብ ከመጀመሩ በፊት በራፉ ተቆረቆረ…..ድምፁን ከፍ አድርጎ ከመቀመጫው እየተነሳ ወደፊት ለፊቱ በራፍ እየተራመደ

‹‹ይግቡ ››አለ..

በራፉ በስሱ ተከፈተና አንድ አንገተ መቃ ጠይም ወጣት ታየችው….ሙሉ በሙሉ ከፍታ ወደውስጥ ገባች….፡፡ስሯ ደረስና እጁን ለሰላምታ ዘረጋ፡፡

‹‹ሰለሞን ገብረየስ›› እባላሁ፡፡

‹‹ለሊሴ ለሜቻ ›› ስሟን አስተዋወቀችው፡፡

‹‹ግቢ ››አለና ወደ ውስጠተኛው ክፍል እየመራ.. ዞሮ ወንበሩ ላይ ተቀመጠና ከፊት ለፊቱ እንድትቀመጠ ጋበዛት..ተቀመጠች፡፡

‹‹እሺ ምን ልታዘዘዝ…?እዚህ ቤት ውስጥ ያለነው እኔና አንቺ ብቻ ነን..እዚህ የምንነጋገርነው ነገር እስከመጨረሻው በእኔና አንቺ መካከል ሚስጥር ሆኖ ተቀብሮ የሚቀር ስለሆነ ሁሉንም ነገር ያለምንም መሳቀቅና ይሉኝታ ንገሪኝ …ከዛ መፍትሄ እንፈልጋለን….››

የልጅቷ አይኖች ፈጠጡ….ግራ በመጋባት

..‹‹‹ይቅርታ….እህትህ ነች የላከችኝ፡፡››አለችው

‹‹እህትህ የእኔ ?ለምን፡፡››ግራ መጋባቱ የእሱ ተራ ሆነ.፡፡

‹‹ፀሀፊ ይፈልጋል ብላኝ ነው››

‹‹ኦ……ገባኝ››የንዴት ሳቅ ሳቀ፡፡
ባልጠበቀችው ሁኔታ ቀጥታ ወደገደለው ገባላት‹‹እሺ እንደዛ ከሆነ ጥሩ፣ስራ መች መጀመር ትችያለሽ?››

‹‹ነገ››

‹‹ጥሩ በቃ››

‹‹በቃ…ማለቴ ሌላ የምትጠይቀኝ ነገር የለም?››

‹‹እኔ እንጃ ምን እጠይቅሻለው…..?አንቺ የምትጠይቂኝ ጥያቄ አለሽ?››

‹‹አዎ… ስንት ትከፍለኛለህ?››

‹‹ስንት እንድከፍልሽ ትፈልጊያለሽ?››

‹‹አራት ወይም አምስት ሺ ብትከፍለኝ ደስ ይለኛል፡፡››

‹‹ለመጀመሪያ የሶስት ወር የሙከራ ጊዜ አራት ሺ ብር ከፍልሻለው…ከዛ በኃላ ደግሞ አብረን እናየለን….ሌላ ይያቄ አለሽ …?››

‹‹የለኝም፡፡››

ኪሱ ገባና ቁልፍ መያዣውን አውጥቶ ከውስጡ የቢሮውን ትርፍ ቁልፍ አወጣ‹‹.ይሄው የቢሮ ቁልፍ..የስራ መግቢያ ሰዓት 2.30 ነው….ነገ ስመጣ ቢሮ ከፍቶ መግባት አይጠበቅብኝም ማለት ነው?፡፡››አላት፡፡

‹‹አዎ ትክክል ››አለችና ቁልፉን ይዛ ለመሄድ ተነሳች፡፡

‹‹ይቅርታ ነገ ሰራተኛ ሆኜ ስራ ከመጀመሬ በፊት ዛሬ እንደ ደምበኛ አገልግሎት ማግኘት እችላለሁ…?.››

ጥያቄዎ አስደምሞት በትኩረት አያት፡፡‹‹ቁጭ በይ›› አላት፡፡

ተመልሳ ቁጭ አለች፡፡

‹‹እሺ እየሰማሁሽ ነው፡፡››

‹‹የጋብቻ ጉዳይ ሳይሆን የፍቅር ጉዳይ ነበር››

‹‹ገባኝ››

‹‹ሁለት አፈቀርንሽ ብለው እንዳገባቸው እየጨቀጨቁኝ ያሉ ወንዶች አሉ…ከሁለቱም ጋር ከሁለት አመት በላይ እውቂያ አለኝ፡፡አንዱ የተማረ እስማርት የሚባል የመንግስት ሰራተኛ ነው…የመንግስት ሰራተኛ ነው ስልህ ያው ይገባሀል አይደል…ከወር እስከ ወር ያለውን ወጪ ለመሸፈን የሚቸገር አይነት ሰው ነው..ሁለተኛው ነጋዴ ነው…ደህና ድርጅት አለው
….ሁለቱም እንዳገባቸው ጠይቀውኛል ..የትኛውን እሺ ማለት እንዳለብኝ ግራ ተጋብቻለው…..እንዴትና በምን አይነት መስፈርት ነው መምረጥ የምችለው?››

‹‹የትኛውን ይበልጥ የምትወጂው ይመስለኛል…?››

‹‹እኔ እንጃ ከመንግስት ሰራተኛው ገር ስሆን በጣም ዘና እላለሁ..ቀልዶቹ ያስቁኛል

….ነጋዴው ደግሞ የፈለኩት ቦታ ወስዶ ያዝናናኛል..ጥሩ ጥሩ ስጦታ በመስጠት ያስደስተኛል….ግን ንግግሩ ደረቅና የጠነዛ ነገር ነው…ግራ ተጋብቻለው…አንዳንዴ ሁለቱ ተጨፍለቀው አንድ ሰው ቢሆኑና እሺ ብያቸው በተገላገልኩ እላለው፡፡››

ለተወሰነ ደቂቃ አሰበና መናገር ጀመረ‹‹እንግዲህ ይህንን ችግርሽን ለመፍታት ሶስት ወር የተከፋፈለ የቤት ስራ እስጠሸለሁ፡፡

‹‹ሶስት ወር ሙሉ አልበዛም?››
አይ አልበዛም…ለእድሜ ልክሽ አብሮች የሚኖረውን ሰው እኮ ነው የምትመርጪው

….ፍቅረኛ ብቻ ሳይሆን የዕድሜ ልክ ባልሽን ነው የምትመርጪው…   ጓደኞችሽ እና
ወዳጆችሽ ፊት ይዘሽው ምትሄጂውን ሳይሆን ከቤተሰቦችሽ ወስደሽ ምትቀላቀይውን ሰው ነው የምትመርጪው….እና ደግሞ ያንቺን ባል ብቻ ሳይሆን ነገ ለምትወልጃቸው ልጆችም አባት የሚሆነውን ሰው ነው እየመረጥሽ ያለሽው፣እና እዚህ ጉዳይ ላይ ሶስት ወር አይደለም ሶስት አመትም ብታሳልፊ እንደብክነት የሚቆጠር አይደለም…..ግን እንዲህ ስልሽ ይሄን ሁሉ አድርገንም ይንን ሁሉ ጊዜ አባክነንም ፍፅም ትክክለኛውን ሰው መምረጥ እንችላለን ለማለት አይደለም….የፍቅር  ጓደኛ በመምረጥ ሂደት ውሥጥ ፍጽም ትክክል የሚባል ምርጫ የለም…ግን በብዙ መስፈርት ሲለካ የተሻለውን መምረጥ እንችላለን..እና ለዛ ሶስት ወር አይበዛም፡፡

‹‹አሳምነሀኛል…የማደርገውን ንገረኝ፡፡››አለችው፡፡

በመጀመሪያ ወር አንደኛውን ምረጪና ከእሱ ጋር ብቻ ተገናኚ…ሌላውን የሆነ ምክንያት ስጪውና ሙሉ በሙሉ ግንኙነት አቋርጪ….

በስልክም ቢሆን አታግኚው፣ፎቶውንም ቢሆን እንዳትመለከቺ ….ሙሉ ትኩረትሽን አንደኛው ላይ ብቻ አድርጊ….ልክ ወሩ ሲያልቅ ይሄኛውን በተመሳሳይ ከግንኙነት ውጭ አድርጊውና ከሌለኛው ጋር ተገናኚ…በሶስተኛው ወር ደግሞ ሁለቱንም ሳታገኚ ለብቻሽ አሳልፊ፣ስለሁለቱም በጽሞና አስቢ …ከዛ አብረን እናወራበታለን፡፡››

‹‹ጥሩ ይመስላል ..አዎ እንዳልከኝ አደርጋለሁ…..አዎ እንደዛ ባደርግ ጥሩ ይመስለኛል….ግን በጣም የተቸገረች ጓደኛዬ ነበረች..ምን የመሰለ ትዳሯ ሊፈርስባት ነው…እባክህ እርዳት ቆይ እንደውም ልደውልላለት..››አለችን ስልኳን አንስታ እየደወለች መቀመጫዋን ለቃ ወደውጭ ወጣች፡፡
ሰሎሞን‹‹ዋው የመጀመሪያ ኢትዬጵያዊት ደንበኛዬን ኢንፕረስ አደረኳት ማለት ነው…››ሲል አሰበና .ደስ አለው ..፡፡

ስልክን አናግራ ተመልሳ መጣች…‹‹ጓደኛዬ ነገ መምጣት ትችላለች..?እባክ ችግሯ በጣም አጣዳፊ ስለሆነ እንደምንም ጊዜህን አሸጋሽገህ አግኛት፡፡››ተለማመጠችው፡፡

‹‹ነገ ምንም ደንበኛ የለኝም በፈለግሽው ሰዓት ቅጠሪያት››

‹‹አመሰግናለው…አራት ሰዓት ትመጣለች..በቃ ቻው..ጥዋት እንገኛን ››ብላ ለመሄድ መንገድ ከጀመረች በኃላ ወደኃላ ዞራ..‹‹ይቅርታ ክፍያውን ዛሬ ስላላያዝኩ ነው…..ነገ ይዤ እመጣለው››

‹‹ችግር የለውም…ሲሳካ ምሳ ትጋብዢኛለሽ ››አላት

‹‹አመሰግናለው››ብላ በደስታ እየሳቀች ወጥታ ሄደች፡፡

​​ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

03 Nov, 17:52


​​‹‹ጋሼ እኔ አስገድጄያት ነው…..ያው ለእኔው እኮ ነው… ደህና ደህና ምግብ ካልተመገብኩ ከስብራቴ ቶሎ አልድንም..ውጌሻዋ ያለችውን አልሰማህም፡፡››

‹‹ቢሆንም ..ይሄው እኔ እኮ ለአስቤዛ የሚሆን ብር ይዤ መጥቼለው ››አሉና እጃቸውን በወደኪሳቸው ሰዳው የተወሰኑ ድፍን ብሮችን አውጥተው ዘረጉ
በፀሎት እንባዋ ካለፍቃዶ ዘረገፈች…ይገርማል ወላጆቾ ቤት እያለች ዘወትር የምታለቅሰው በእነሱ ጥል እና ጭቅጭቅ በመበሳጨት ነበር..እዚህ ቤት እግሯ ከረገጠ ጀምሮ ግን እንባዋ የሚረግፈው በመሀከላቸው በምታየው ፍቅርና ለእሷ በሚያደርጉላት እንክብካቤ ስሜቷ እየተነካ ነው…ሰው ለሀዘንም ለደስታም እንዴት ተመሳሳይ ምላሽ ይሰጣል..?‹‹ጋሼ እኔ በጣም ብዙ ብር አለኝ …ችግሬ ብር አይደለም..ከእናንተ የምፈልገው ፍቅር ብቻ ነው……››

‹‹ይሁን እስኪ ..ግን እንዲህ መሆን አልነበረበትም.››.እያሉ ከቆሙበት ተንቀሳቀሱና ወደውስጥ ዘልቀው ፊት ለፊት ያለው ደረቅ ወንበር ላይ ተቀመጡ፡፡ወ.ሮ እልፍነሽና ለሊሴ አስቤዛውን ተጋግዘው ወደ ጓዲያ ወሰዱት፡፡

አቶ ለሜቻ ማውራት ጀመሩ…‹‹ምንም ነገር ከፈለግሽ ለእኔ ለአባትሽ ንገሪኝ..በስልክ እድንጠራልሽ የምትፍጊው ሰው ካለም…..ችግር የለው››

‹‹ጋሼ ሙሉ በሙሉ እስከምድን ድረስ ከማንም ሰው ጋር መገናኘት አልፈልግም..ደግሞ እመነኝ እኔ በመጥፋቴ ማንም የሚያስብ ሆነ የሚጨነቅ ሰው አይኖርም….እንደውም ጠፍታለች ሳይሆን ለሆነ ስራ የሆነ ሀገር እንደሄድኩ ነው የሚያስቡት..ከዚህ በፊትም ሁለት ሶስቴ አድርጌዋለው››
ከመቼ ወዲህ እንዲህ ውሸታም እንደሆነች ለራሷም ግራ ገባት ፡፡አሁን የት ሄደሽ ነበር ቢሏት የት ልትል ነው?፡፡ለመዝናናት ካልሆነ ለመኖር ወይም ለተወሰነ ጊዜ ቆይት ከአዲስአባባ ውጭ እግሯን አንስታ አታውቅም…ስለየትኛውም ሌላ ከተማ የጠለቀ እውቂያ የላትም..ብቻ ከቤሰተቦችሽ ተገናኚ እያሉ እንዳያጨናንቋት ማድረግ ያለባት እንደዚህ እንደሆነ በውስጧ አምናለች፡፡

‹‹ይሁን..እንግዲያው …እኛ አለንልሽ..አይዞሽ…ግን እንዲህ ብርሽን አታባክኚ… ስትድኚ በጣም ያስፈልግሻል ››
‹‹አይ ጋሼ..ስለእኔ አታስብ..እናቴ ብዙ ብር ጥላልኝ ነው የሞተችው…ባንክ በቂ ብር አለኝ፡፡››
‹‹ይሁን ልጄ..ብር ግን አያያዙን ካላወቁበት ስር የለውም..ሲታይ ብዙ የመሰለ ብር ከእጅ በኖ ሲጠፋ ቀናት አይፈጅበትም ››

‹‹ገባኝ….፡፡››

‹‹እሺ በቃ… አሁን አረፍ በይ..ሰፈር አንዲት ለቅሶ አለች… ደረስ ብዬ መጣሁ››

‹‹እሺ ጋሼ››

ወጥተው…ሄዱ…እሷም ወደትካዜዋ ገባች፡፡

ድንገት በቀኝ በኩል ወደአለው ግድግዳ ቀና ብላ አይኗን ስትተክል ግዙፍ ፎቶ ላይ ፈዛ ቀረች…የበሬዱ እንደሆነ እርግጠኛ ነች….
ከንፈሯቾ በፀደይ ወራት ለመበላት እንደደረሰ የጎመራ ብርቱካን ይመስላሉ…ስስ ነው በጣም ስስ..የሚገመጥ ሳይሆን የሚመጠጥ አይነት እና ደግሞ ጠባብ ነው ጠባብ የሚስጥር በር መሳይ  ጠባብ፡፡አይኖቾ ብርሀናቸውን ከከዋከብት የተዋሱት ይመስላል
…አፍንጫዋ ዝንፈት በሌለው የሂሳብ ስሌትና ትንግርት በሚያበስር የስነ.ከዋክብት ትንቢታዊ ጥበብ እንደተሰራ የግብፃችን ፕራሚድ አይነት ነው፡፡ፀጉሯ ምድረ አራዊት ሁሉ ተሰብስበው የሚኖሩበትና አማዞን ደን መሰል ነው፡፡እንዲህ ፎቶዋ ሲታይ ይሄ ቢሰተከካከል ብሎ ምንም እንከን ወይም ጉድለት ሊገኝበት የማይችል አይነት ነው፡፡
‹‹ሞት ግን ምንድነው?›› እራሷን ጠየቀች….ሞት በቀላሉ ጭሩሱኑ ባይኖር ብለን የምናማርረው ነገር አይደለም…ሞት ባይኖር ምድር የበለጠ የምትሰለች አስቸጋሪና አስጨናቂ ስፍራ ትሆን ነበር…ስለዚህ ሞት የህይወትን ያህል እጅግ አስፈላጊ የአምላክ ስጦታ እንደሆነ ታምናለች ይሁን እንጂ ሰው ደግሞ የህይወትን ጫፍ እንኳን ሳያይ እንዲህ በጨቅላ እና በለጋ ህይወቱ ሲቀጠፍ ያሳዝናል..‹‹በተለይ ለወላጆቾ እና ለሚያፈቅሯት ሰዎች ይሄንን እውነት መቀበል በጣም ከባድ ነው፡፡››ስትል አሰበች
‹‹አንቺ ሞተሸ አልሞትሽም ዋናው አንቺነትሽ ለእኔ ህይወት ሰጥቶኛል….የአንቺ ልብ ከእኔ ማንነት ጋር ከተዋሀደ በኃላ ቀይሮኛል፡፡››ስትል በውስጧ አጉረመረመች፡፡ሀሳቧን ሳትጨርስ ፊራኦል ከውጭ ስልኩን እየጎረጎረ መጥቶ ፊት ለፊቷ ቁጭ አለ…ለረጅም ደቂቃዎች አላናገራትም

​​ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

03 Nov, 17:52


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ዘጠኝ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

አቶ ኃይለ መለኮት እቤታቸው ባለ የገዛ ቢሯቸው ውስጥ ተሸከርካሪ ወንበራቸው ላይ ተቀምጠዋል…በቀኝ እጃቸው የሚያብረቀርቅ ማካሮብ ሽጉጣቸውን ይዘው ፊታለፊታቸው ያሉት ሶስት ግለሰቦች ላይ በየተራ እያነጣጠሩ ምላጩን በስሱ እየዳበሱ ይናገራሉ

‹‹በመጀመሪያ ማንን ልግደል?››

‹‹ጌታዬ ይቅር ይበሉን…አጥፍተናል….››

‹‹አጥፍተናል….ጥፋት እኮ በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል ስህተት የሆነ ድርጊት ስታደርግ ነው፡፡ለምሳሌ እዚህ መኖሪያ ቤቴ ላይ ጋዝ አርከፍክፈህ ክብሪት በመለኮስ ግማሹን ህንፃ ብታወድመው ጥፋት አጥፍተሀል ብዬ የጠየቅከውን ይቅርታ ልቀበልህ እችላለው፡፡ ምክንያቱም እቤቱን አሁን ካለበት ይዘት ይበልጥ አስውቤ ከእንደገና ላስገነባው እችላለሁ…ወይም ከፋብሪካዎቼ ትልቁን መርጠህ ሙሉ በሙሉ ብታወድመው እንደጥፋት ቆጥሬ ይቅርታህን ልቀበል እችላለው…ወይንም ሽጉጥህ ባርቆብህ ቀኝ እጄን ብትመታኝና በዛ የተነሳ እጄ ቢቆረጥ አዎ ይቅርታህን ልቀበል እችላለው፡፡ግን አሁን ምንም አላስቀረህልኝም፡፡ልጄ ሁለ ነገሬ ነች…ምንም መተኪያ ምንም ማካካሻ የላትም…ያ ማለት ይቅርታ ላደርግላችሁ ፈፅሞ አልችልም.››

‹‹ጌታዬ ይገባናል፣ አንተ ትክክል ነህ..ግን ቢያንስ በፍለጋው ላይ ጠንክረን እየሰራን ነው….የሆነ ትንሽ ቀን ጨምርልንና አቅማችንን አሟጠን እንፈልጋት… የሆነ ያህል ጊዜ ስጠን… ካልተሳካልን ያሰብከኸውን ታደርጋለህ፡፡››

‹‹አዎ እሱማ አደርጋለው….ዋጋማ ትከፍላላችሁ….አሁን የምናደርገው…..››ንግግራቸውን ሳያጠናቅቁ ስልካቸው ጠራ…የደቀኑትን ሽጉጥ ሳያወርድ ስልኩን አንስተው ማውራት ጀመሩ፡፡

‹‹እሺ…ጥሩ …ሶስቱም ነው እይደል… በጥንቃቄ ጠብቋቸው››
ስልኩን ከዘጉ በኃላ ንግግራቸውን ቀጠሉ‹‹ስልኩ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ…?የእናንተ የሁለታችሁን አንዳንድ ልጃችሁን ያንተን ደግሞ ምትወዳትን ሚስትህን አሳግቼቸዋለው…ልጄ በሚቀጥሉት ሶስት ቀን ውስጥ ተገኝታ ወደቤቷ ካልተመለሰች ያው የምወዳትን ልጄን ስላሳጣችሁኝ ለዛ ክፍያ የምትወዱትን ሰው ታጣላችሁ ማለት ነው፡፡››ሲል ሰቅጣጭ መርዶ አረዷቸው፡፡

ሶስቱም ሰዎች ላይ የታየው ድንጋጤ ሲእላዊ ነበር፡፡፡አቶ ኃይለልኡል ሰዎቹን ከቢሮቸው አሰናብተው ሽጉጡን ወደመሳቢያው ውስጥ መልሰው በማስቀመጥ ቆለፉበትና ወጥታው ወደ ባለቤታቸው ወ.ሮ ስንዱ መኝታ ቤት ሄዱ
….ሚስታቸው አልጋው ላይ ተሰትረው ጉልኮስ ክንዳቸው ላይ ተሰክቶ እህህ እያሉ ነው..ለዘመናት ወደዋቸው የማያውቁት ባላቸውን ድምፅ ሲሰሙ የከደኑትን አይን ገለጡ እና በመከራም ቢሆን ከንፈራቸውን አነቃነቀው ማውራት ጀመሩ

‹‹ኃይሌ…ልጃችን አልተገኘችም?››

‹‹አይዞሽ አታስቢ ..ትገኛለች….አንቺ ምንም አትጨነቂ››ሊያፅናኗቸው ሞከሩ፡፡

‹‹እንዴት አልጨነቅ…?በዚህ አለም ላይ ያለቺኝ እሷ ብቻ ነች..በህይወቴ ሙሉ የበደልከኝን በደል እንድረሳልህ…የሰራህብኝን ስራ ይቅር እንድልህ ከፈለክ ልጄን አግኝልኝ….ልጄን ካገኘህልኝ ያልከኸውን ሁሉ አደርግልሀለው….እንደውም ምንም ሀብት ሳልካፈልህ እፈታሀለው…እፈታህና ገዳም እገባለው..አዎ ልጄ ሰላም መሆኗን ካረጋገጥኩ ከህይወትህ ዞር እልልሀለው›

‹‹አረ ተይ …ለእኔም ልጄ እኮ ነች…እሷን ለማግኘትና ወደቤቷ ለመመለስ ከአንቺ ጋር ይሄንን አድርጊልኝ እያልኩ የምደራደር ጭራቅ ነገር እመስልሻለው….?ተይ እንጂ..አሁን ወጣ ብዬ ፖሊሶቹ ምን ላይ እንደደረሱ መጠየቅ አለብኝ..ሀኪሞቹ ሚሉሽን ስሚና ጤናሽን ተነክባከቢ..ልጃችን ስትመጣ እንደዚህ ሆነሽ እንደታገኚሽ አልፈልግም…እናቴ በእኔ ምክንያት ሽባ ሆነች ብለ መፀፀት የለባትም››ብሎ ወጥቶ ሄደ…..
///
በፀሎት ከእንቅልፏ የባነነችው በቤቱ ውስጥ ግርግር እና የብዙ ሰው ድምፅ ስትሰማ ነበር..አይኖቾን ስትገልጥ ግን ያሰበችውን ያህል ብዙ ሰው አልነበረም ነበር…ወ.ሮ እልፌ
፤አቶ ለሜቻና አንድ ሙሉ ሱፍ የለበሰ ጎልማሳ ሰው ነበር በቤቱ ያሉት….ግን ያ ጎልማሳ ሰው ሲያወራ ድምጹ መመጠኛው እንደተበላሸበት ማይክራፎን ከጣሪያ በላይ ይጮኸ ስለነበረ የብዙ ሰው ድምጽ ይመስላል….
አይኗን ስትገልጥ አየና ወደእሷ ተጠጋ.‹‹ልጄ ተነሳሽ..?ጥሩ …ይሄ ዶክተር ታፈሰ ይባላል..የጓደኛዬ ልጅ ነው….አንቺን እንዲያይልኝ አስቸግሬው ነው፡፡›››አቶ ለሜቻ ናቸው ተናጋሪው፡፡

‹‹አባቴ ዝም ብለህ ነው እኮ የተቸገርከው..ደህና ነኝ እኮ››
ከወ.ሮ እልፍነሽ ጋር በተስማማችው መሰረት ቢሻክራትም አንቱታውን በአንተ ቀይራ ማውራት ጀመረች…

‹‹ደህና መሆንሽና አለመሆንሽን እኔ ሀኪሙ አይቼ ብወስን አይሻልም›› ዝም አለችው….
ወደእሷ ተጠጋና  አያት…ግንባሯና ከፊል ፊቷ በስነስርአት መታሸጉን አረጋገጠና  ..አንድ መርፌ በክንዷ ወግቷት መድሀኒት አዘዘላት…
‹‹በቃ ጋሼ..የወንድሞት ልጅ በጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች..ቁስሉ ጊዜውን ጠብቆ ፋሻው ተነስቶ በደንብ ፀድቶ ከእንደገና መታሸግ አለበት…›››

‹‹ምንም የሚያሰጋ ነገር የለም እያልከኝ ነው?››

‹‹አይ የለም ሰላም ትሆናለች..ግን ምን አልባት ፊቷ ላይ ጠባሳ ሊሆንባት ይችላል፡፡››

‹‹ያንን ማስቀረት አይቻልም?››አቶ ለሜቻ ጠየቁ፡፡

‹‹ያው የቆዳ ስፔሻሊስቶች ያስተካከሉታል..በአሁኑ ጊዜ ብር ካለ የማይስተካከል ነገር የለም..ዋናው በህይወት መትረፏና አካለ ጎዶሎ አለመሆኗ ነው…የጠባሳው ነገር የገንዘብ ጉዳይ ነው… ይስተካከላል፡፡››

‹‹ይሁን እንግዲህ…….አንተንም አስቸገርኩህ››

‹‹አረ ጋሼ…ለርሶ ባልታዘዝ አባቴ አያናግረኝም….በማንኛውም ሰዓት ካመማት ደውሉልኝ..አሁን ልሂድ….፡፡እግዜር ይማርሽ እህቴ››

‹‹አመሰግናለው ዶ/ር፡፡››

‹‹ዶ/ር አቶ ለሜቻን አስከትሎ ቤቱን ለቆ ወጣ ..ክፍል ውስጥ ወ.ሮ.እልፍነሽና በፀሎት ብቻ ቀሩ፡፡

‹‹ጋሼ ዝም ብሎ እኮ ነው የሚጨነቀው?››

‹‹እሱ..እንዲሁ ነው….ታያለሽ ነገ ደግሞ ሌላ ዶክተር ለምኖ ይዞ ይመጣል..እስክትድኚ እረፍት አይኖረውም››

አቶ ለሜቻ ተመልሰው ከመምጣታቸው በፊት ለሊሴ ከሄደችበት ተመልሳ መጣች፡፡ ይዛ የመጣችው ዕቃ ግን የሳሎኑን ግማሽ የሸፈነ ነበር….ከአምስት በላይ ፔስታል ከባለታክሲው
ጋር እየተጋገዙ ወደውስጥ አስገቡ….ከገዛችው ዕቃዎች ውስጥ ለበፀሎት አዲስ አንሶላዎች
…ምቾት ያለው ብርድልብስ ፣ቢጃማ ..ሸበጥ ጫማ..ቅባት…ፓንቶች..ብቻ ያስፈልጋታል ያለችውን እና በእይታዋ የገባላትን ዕቃ ሁሉ ገዝታ ነበር..ከዛ የቤት አስቤዛ አትክልቱን..ፍራፍሬውን..ፓስታ ..መኮሮኒ..ስጋና የመሳሰሉትን እልክ የታጋባች ይመስል ቤቱን ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በቁሳቁስ ሞላችው…፡፡
አቶ  ለሜቻ  ዶክተሩን  ሸኝተው  ሲመለሱ  ትተው  የሄዱት  ሳሎን  ሌላ  መልክ  ይዞ ሲጠብቃቸው ከመደንገጣችው ብዛት ባሉበት ደርቀው ቆሙ….

‹‹ሊሊሴ ምንድነው ይሄ ሁሉ?››
‹‹አየህ አባዬ አንሶላው አያምርም…

ብርድ.ልብሱስ….?.እሄው ቢጃማም ገዛሁላት…››

‹‹ጥሩ አደረግሽ…ብሩን ከየት አመጣሽው?››

‹‹እኔማ ከየት አመጣለው….እራሶ ሰጥታኝ ነው፡››አለች ወደበፀሎት እየጠቆመች፡፡

‹‹ይሄንን ካሮት፤ ቆስጣ ፤ስጋ ፤መኮሮን ይሄን ሁሉ በእሷብር ነው የጋዛሽው ››

‹‹አዎ አባዬ››

‹‹እንዴት እንዲህ ታደርጊያለሽ ለሊሴ…?ችግር ላይ ካለች ልጅ እንዴት? ››

አትሮኖስ

02 Nov, 21:22


ቤቲንግ ይጫወታሉ መበላትስ ሰልችቶታል እንግዲህያዉንሱ በነፃ ያለምንም ክፍያ በቀን ከ 10-15 odd የሚለቀቅበት ቻናል ልጠቁማቹ ይጠቀሙበታል ይቀላቀሉ

አትሮኖስ

02 Nov, 21:07


ከ17 ደቂቃ በኃላ ይጠፋል


የ200 ብር ካርድ የሚያሸንፍ  ጥያቄ !!

በኢትዮጽያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ ረሀብ መቼ አመተ ምህረት ነዉ

አትሮኖስ

02 Nov, 17:00


​​ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

02 Nov, 17:00


‹‹ያው የተገኘውን ነዋ….ከሁለት አመት በፊት ነው ከተግባረእድ በፀጉር ስራ የተመረቀችው…..አፈሩን ገለባ ያድርግላትና ሁለት አመት ከፍላ ያስተማረቻት ሟች እህቷ ነበረች…የሆነ ቤት ተቀጥራ ለአንድ አመት ሰርታ ነበር ፡፡አልተስማማችም መሰለኝ ሰሞኑን ለቀቀች ….አሁን ሌላ ቦታ እየፈለገች ነው፡፡ አንድ ወዳጇ ፀሀፊነት አግኝቼልሻለው ብላት ያንን ለማረጋገጥ ነው የሄደችው፡፡››

የሟቿ ስም ሲጠራ እንደተለመደው የበፀሎት ሰውነት ሽምቅቅ አለ‹‹ግን እቤታችሁ ፊት ለፊት ነው….የሆነች ትንሽ ክፍል ቢኖር እኮ የራሷን ስራ ብትሰራ ጥሩ ነበር››

‹‹እሱማ እንዳልሽው ጥሩ ነበር …ልጄ ግን ቀላል ይመስልሻል…?ለእኛ ያንን ማድረግ ከባድ ነው፡፡እህቷ ልክ አሁን አንቺ እንዳልሺው አይነት እቅድ ነበራት…ተምረሽ ስትጨርሺ ከምሰራበት ባንክ ተበድሬም ቢሆን የራስሽን ፀጉር ቤት ከፍትልሸለሁ ብላ ቃል ገብታላት ነበር…ልጄ ቃሏን የምታጥፍ ሰው አልነበረችም……››እንባቸው በአይናቸው ግጥም ብሎ ረገፈ….አብራ አለቀሰች…እንደምንም ለመረጋጋት እየሞከሩ ንግግራቸውን ካቆሙበት ቀጠሉ‹‹እንዳልሺው…እንደምንም እቤቱን ብንሰራላት እንኳን ማሽኑን ከየት መጥቶ ይገዛል…..እንዳልሽው ግን አንድ ቀን እንደዛ ማድረጋችን አይቀርም…››በትካዜ መለሱላት፡፡

‹‹እማዬ››

‹‹አቤት ልጄ››

‹‹የሆነ ቦርሳ ነበረኝ አይደል..?››

‹‹አዎ አለሽ ..ላምጣልሽ?››

‹‹አዎ ካላስቸገርኮት››

‹‹የምን መቸገር አመጣሽብኝ..አመጣልሻለሁ››አሉና የበላችበትን እቃ ከተቀመጠበት አንስተው ወደውስጥ በመግባት ከደቂቃዎች በኃላ ቦርሳውን አንጠልጥለው አመጡና ስሯ አስጠግተው አስቀመጡላት፡፡

ዚፑን ከፈተችና ከላይ ያሉትን ሁለት ጅንስ ሱሪ…ሁለት ቲሸርቶች አወጣችና አልጋ ላይ አስቀመጠች….ከዛ በኋላ ያለውን እስር እስር ባለሁለት መቶ ኖት ብር ነው…ስንት ብር እንደሆነ አታውቅም …በተለያየ ጊዜ ዝም ብላ ቁም ሳጥኗ ውስጥ እየወረወረች ያጠራቀመችው ገንዘብ ነው..ምን አልባ ሶስት ወይም አራት መቶ ሺ ብር ይሆናል፡፡አንዱን እስር አወጣችና ልብሱን መልሳ ከታ.. ዚ..ፑን ዘጋችና ከራስጌዋ አስቀመጠችው…

‹‹እማዬ..››

አቀርቅረው ሲኒ እያጠቡ ነበረ ..ስትጠራቸው ቀና አሉና‹‹አቤት ልጄ.. ጠራሺኝ?››አሉ

‹‹እንኩ ይሄንን ብር››
ለደቂቃዎች ያህል ክው ብለው አዮት…‹‹ምን እያልሽ ነው ልጄ?››

‹‹ለቤት አንዳንድነገር ይግዙበት….››

‹‹እንዴ ይሄን ሁሉ ብር?››

‹‹ትንሽ እኮ ነው…ሀያ ሺ ብር ነች››
ፈገግ ብለው ‹‹አይ ልጄ… ሀያ ሺ ብር እኮ በአንድ ጊዜ እንዲህ ከነክብሩ እዚህ ቤት ገብቶ አያውቅም..በይ መልሺው…..ከህመምሽ ስታገግሚ ያስፈልግሻል፡፡››

‹‹አይ አያስፈልገኝም…››

‹‹አይ ልቀበልሽ አልችልም….ለሜቻስ ዝም ሚለኝ ይመስለሻል?››

ከጎኗ ያስቀመጠችውን ሻንጣ መልሳ ሳበችና ዚፕን እስከመጨረሻው በመክፈት.. ከነልብሱ ዘቅዛቃ ፍራሹ ላይ ዘረገፈችው….
ወ.ሮ እልፍነሽ በህልማቸው እንኳን አይተው የማያውቁት አይነት የብር ቁልል እየተመከቱ ነው..ያለፍቃዳቸው የተከፈተውን አፋቸውን መልሰው መክደን አቃታቸው፡፡

‹‹አዩ አይደለ….ይሄ ሁሉ ብር አለኝ….ደግሞ አዩት ይሄንን ሀብልና የጆሮ ጌጥ ብዙ መቶ ሺ ብር የሚያወጣ ነው..ከቸገረኝ እሸጠዋለው….እና ይሄንን ብር ይቀበሉኝና እቤት ውስጥ የጎደለውን ነገር ያሟሉበት….ደግሞ እናንተ ማለት እግዚያብሄር ለእኔ የሰጣችሁ ስጦታዎቼ ናችሁ …እንኳን ብሬን ህይወቴን እሰጣችኃላው፡፡

የተገለበጥኩት መንገድ ላይ ወይም ሌላ ሰው ጊቢ ቢሆን አኮ…እንኳን ብሬን ህይወቴን እንኳን ማትረፍ አልችልም ነበር…እዛው ሳጣጥር ገድለው ቀብረውኝ ..ገንዘቡን በሙሉ ይወስዱት ነበር፡፡››

‹‹በስመአብ በይ ልጄ ….ተይ ተይ…››

‹‹እውነቴን ነው….እናንተ ሻንጣውን እንኳን ምን እንዳለበት ከፍታችሁ አላያችሁትም››

‹‹የሰው ዕቃ ያለፍቃድ እንዴት ይታያል …?.ነውር አይደለ እንዴ?››
‹‹እኮ እኔም ለማለት የፈለኩት ያንን ነው..በዚህ ዘመን ነውር የሚባል ነገር ጠፍቷል…ሰው ቁስአምላኪ ሆኗል….እምነት ..ሀቀኝነት ..ክብር  …እውነት ….የሚባሉ ቦዶ ቃላት ሆነዋል››
‹‹ካልሽ እሺ ልጄ……ለሜቻ ግን ምን ብዬ እንደማስረዳው አላውቅም››

‹‹ግድ የሎትም ጋሼን እኔ አሳምናቸዋለሁ፡፡››

ብሩን ተቀበሏትና..‹‹ልጄ እቤቴን እንዲህ እንደሞላሽው ላንቺም የሞላ ህይወት ይስጥሽ..››አይናቸውን ግድግዳው ላይ ወደተሰቀለው የሟች ልጃቸው ፎቶ ላኩና ፍዝዝ ብለው‹‹ልጄ  እንዲህ ድንገት መጥታ መአት ብር እጄ ላይ በማስቀመጥ ..እማዬ የሚያስፈልግሽን ነገር ግዢበት ..እቤት የጎደለ ነገር ካለ አሟይ…ትለኝ ነበር….አንድ ቀን የራሷን ኑሮ ሳትኖር እንደጓደኞቾ ጌጣጌጥና መዘነጥ ሳያምራት ቤተሰቦቾን እንዳገለገለች ሞተች….አሁን ሳስበው ልጅ ከጊዜዋ ቀድማ እንደዛ በስላ ትልቅ ሰው የሆነችውና በደግነትና ቤተሰቦቾን በማገልገል ብኩን የሆነችው ምን አልባት ቶሎ እንደምትሄድ አውቃ ይሆን እንዴ
?እላለሁ..ብቻ ተይው…..አንቺን እግዜር ይባርክሽ››

‹‹አሜን እማዬ››

‹‹ልጄ››

‹‹ወይ እማዬ››

‹‹እማዬ  ማለትሽ  ካልቀረ  …አንቱታውን  ተይው…ልጆቼ  አንቺ  ነው  የሚሉኝ
…..አባታቸውንም አንተ ነው የሚሉት…እንግዲህ አንቺም ልጃችን ሆነሽ የለ….ከአነሱ ለምን ትለያለሽ..አንቱታውን ተይው››

‹‹አመሰግናለው እማዬ…..በጣም ነው ማመሰግነው..አሁን ትንሽ ልተኛ፡፡››

‹‹ተኚ ልጄ.. ተኚ››አሉና ወደጓዲያቸው ገብተው…አሮጌ ሞባይላቸውን ፈለጉና ለልጃቸው ለለሊሴ ደወሉና ስራ ፍለጋውን ጥላ ወደቤት እንድትመጣ ነገሯት….

እንደመጣች ወደጓዲያ ወስደው ብሩን እያሳዩ የሆነውን ሲነግሯት ከመደንገጧ የተነሳ አፏ እንደኩበት ደረቀና ምላሶን ምታረጥብበት ምራቅ አጣች…ይህቺ ልጅ ለ በቤቱ መከራ ወይ መዘዝ አስከትላ ትመጣለች የሚል ከፍተኛ ፍራቻ በውስጦ ሲገላበጥ ነበር..ተቃውሞዋን እንደወንድሟ አውጥታ አታንጸባርቀው እንጂ በውስጧ ለመቶኛ ጊዜ ደጋግማ አስባበታለች…አሁን ግን እናቷ እየነገሯት ያሉት ተቃራኒውን ነው…መአት ሳይሆን በረከት ነው እጃቸው ላይ ያለው…በዛ ላይ ጥሩ ገድ አላት…ለወር ስራ ፍለጋ ስትኳትን ነበር..አሁን  ግን  የተሻለ  የተባለ  ስራ  ባልጠበቀችው  መንገድ  ለዛውም  በቀላሉ አግኝታለች፡፡ፀሀፊነት፡፡ስራውን ያገኘችላት..በፊት ትሰራበት የነበረ ፀጉር ቤት በደንብኝነት ታውቃት በነበረች አስቴር በምትባል ሴትዬ አማካይነት ነው፡፡

‹‹እማዬ በቃ እሷንም ሆስፒታል ወስደን ማሳከም እንችላለን ..ብዙ ብር ነው፡፡››

‹አዎ እንደዛ ብያት ነበር..ግን ቦርሳዋ ውስጥ ብዙ ብር አለ ….ይሄንን ለቤት የጎደለ ነገር ግዙበት መታከም ከፈለኩ በዚህ እታከማለው አለችኝ…››አብራሩላት

‹‹ውይ እማዬ እንደዛ ከሆነ ደስ ይላል..አሁን ምን እናድርገው››
‹‹እኔ እንጃ የጠራሁሽ ለዛ ነው…አንቺ ያስፈልጋል የምትይውን ነገር ለቤቱም ለእሷም ገዝተሸ ነይ፡፡››
‹‹አዎ ትክክል ነሽ እማዬ ››አለችና ብሩን ከእጃቸው ላይ ተቀብላ ግማሹን ገመሰችና‹‹..ይሄንን አስቀምጪው..በዚህ የሚያስፈልገንን ነገር ገዝቼ መጣለሁ...ዝም ብለን ብሩን ታቅፈን ከጠበቅነው አባዬ ሁንም ተቀብሎን ነው የሚመልስላት››ስትል ስጋቷን ነገረቻቸው፡፡

‹‹አዎ ልጄ… እሱ እንደዛ ነው የሚያደርገው››

‹‹በይ አታስቢ…ብላ ብሩን ቦርሰዋ ውስጥ ከታ እንዳመጣጡ ጓዲያውን ለቃ ወጣችን ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ላይ ያለችውን በፀሎትን እስከአሁ አይታት በማታውቀው መንገድ በስስት አይን እያየቻት እቤቱን ለቃ ወጣች፡፡

አትሮኖስ

02 Nov, 17:00


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ስምንት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ሰለሞን ለዚህ ነው ከውጭ ከተመለሰ በኃላ ለመደላደል ስራ መጀመር እንዳለበት የወሰነው
‹‹ምንድነው መስራት ያለብኝ?ምን አይነት ዕውቀት ነው ያለኝ?ምን አይነት ጥሪትስ አለኝ?ህብረተሠብስ ምን አይነት ሸቀጥ ወይም አገልግሎት ነው መግዛት የሚፈልገው?። መልሶቹ ቀላል አልነበሩም...ወደ አእምሮው የሚመጣው መልስ ወደግል ስራ የሚያስገባው ሳይሆን እንደውም በተቃራኒው የሚያርቀ ነው የሆነበት።

1/ይሄ የምኖርበት ህብረተሠብ በዚህ ሰአት ግዙፍ ችግሩ ምንድነው...?ወረቀትና እስኪሪብቶ ያዘና ዘርዝሮ መፅፍ ጀመረ

1/ኑሮ ውድነት
2/የሠላም እጦት
3/የፍቅር እጦት
4/ቴክኖሎጂ ቅኝ ግዛት
5/...!!የአየር ፀባይ መዛባት
የፃፈውን መለስ ብሎ አየው ...ለደቂቃዎች ብቻውን ተንከትክቶ ሳቅ ። ዝርዝሩን አንድ አነስተኛ የግል ቢዝነስ ለመክፈት ሳይሆን አዲስ ጠቅላይ ሚንስቴር ሆኖ ተሹሞ በሀገሪቱ ስር ነቀል ለውጥ የሚያመጡ የፓሊሲ አማራጮችን ለማርቀቅ መነሻ ሀሳቧችን እያሰላ ያለ ፓለቲከኛ ነው  የሚመስለው።

‹‹እስቲ የህብረተሠብም የኑሮ ውድነትን የሚቀርፍ ምን አይነት ቢዝነስ ነው የሚኖረው...?ኑሮ ውድነቱ እንኳን ግለሠብ መንግስትስ ለማስተካከል አቅም አለው...?የመለኮት ጣልቃ ገብነት ከሌለስ  መፍትሄ ይኖረዋል?።››ሲል አሰበና በራሱ ድርጊት ዳግመኛ ሳቀ፡፡ ከዘረዘራቸው ሀሳቦች የ3 ተኛው ሀሳቡን ገዛው።‹‹ፍቅር እጦት የእኔም የማህበረሰብም የጋራ ችግር ነው።የፍቅር እጦት ደግሞ የሌሎች ችግሮች ሁሉ መነሻ ምክንያት ነው።ደግሞ በሙሉ አቅሜ መስራት የምችለው ስራ እሱን ነው …ሞያዬም ችሎታዬም እሱ ላይ ነው››ሲል አሰበና ወሰነ፡፡

አሜሪካ እያለ ተቀጥሮ የሚሰረባትን የፍቅርና የጋብቻ አማካሪ ድርጅት እዚህ ሀገሩ መሀል አዲስ አበባ ላይ በራሱ ለመክፍት ወሰነ…‹‹የራስህን ቢዝነስ ጀምር›› ብላ ስትጨቀጭቀው ለነበረችው አስቴር ነገራት፡፡፡አንገቱ ላይ ተጠምጥማ ጉንጩን እየሳመች በሀሳብ በጣም መደሰቷንና በማንኛውም ነገር ከጓኑ እንደሆነች አበሰረችው…እሷ የተደሰተችበት ነገር ደግሞ በእሱ ህይወት ትልቅ ቦታ ስላለው ወዲያውኑ በደስታ ወደእንቅስቃሴ ገባ……ፍቃድ ለማውጣት ቢሮ ለመከራየትና አስፈላጊ የቢሮ እቃዎችን አሞልቶ ለመክፈት 40 ቀን ብቻ ነበር የፈጀበት፡፡

ይሁን እንጂ ለአንድ ወር ያህል በሰአት ቢሮ እየገባ በሰዓት ቢወጣም አንድም ደንበኛ ማግኘት አልቻለም…ሁሉ ነገር ተስፋ አስቆራጭ የሆነበት፡፡ግራ ገባው ፣በመጀመሪያውም ዝግና ድብቅ ባህል ባለበት ሀገር የጋብቻና የፍቅር አማካሪ ድርጅት ከፍቶ ውጤታማ ሆናለው ብሎ በማሰብ በራሱ ጅልነት ተበሳጨ…የስድስት ወር የቢሮ ኪራይ ባይከፍልና ለፈርኒቸር እና የቢሮ እቃዎችን ለማሟላት ከመቶ ሺ ብሮች በላይ ባያወጣ ኖሮ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ ዘጋግቶ ሌላ የቅጥር ስራ ይፈልግ ነበር..ግን ለጊዜው እንደዛ ማድረግ አይችልም…‹‹አዎ ለአስቴር ምን እላታለሁ….?እንድታፍርብኝማ አላደርግም…እሷ ከምታፍርብኝ አለም ጠቅላላ ብትገለባበጥ እመርጣለሁ….ስለዚህ የሆነ ነገር ማድረግ አለብኝ››በማለት ወሰነና ቀኑን ሙሉ ሲያሰላስል ዋለ… የሆነ ነገር ብልጭ አለለት፡ስልኩን አነሳና ደወለ፡፡
ከአራት ጥሪ በኃላ ተነሳ፡፡

‹‹ሄሎ ወንድሜ….›››የሚል ድምፅ በስልኩ እስፒከር አቆርጦ ጆሮው ውስጥ ተሰነቀረ…

‹‹አለሁልሽ››

‹‹ምነው ድምፅህ?››

‹‹ደህና ነኝ….የሆነ ነገር ላማክርሽ ነበር?››

‹‹ይቻላል..ግን ስራ አሪፍ ነው እንዴ?….››

‹‹አሪፍ ነው …አሁን አንድ ደምበኛዬን ወደትዳር ከመግባቷ በፊት ማድረግ ስለሚገባት ቅድመ ዝግጅት ማወቅ ፈልጋ ነበር.. እሷን እንደሸኘሁ ነው የደወልኩልሽ››ዋሻት፡፡

‹‹ደስ ይላል ወንድሜ …ህልምህን መኖር ጀምረሀል ማለት ነው….››

‹‹አንቺ ከጎኔ ሆነሽ እስከደገፍሺኝ ድረስ ምንም ማላሳከው ነገር የለም…..አሁን ለምን መሰለሽ የደወልኩልሽ…ፀሀፊ ብቀጥር ብዬ አሰብኩ…››ያሰበውን ነገራት፡፡

‹‹አዎ አንተ ….እስከዛሬ እንዴት አላሰብንበትም…?ለፕሮቶኮሉ እራሱ አስፈጊ ነው…ባለጉዳዬች እንደመጡ አንተን ማግኘት የለባቸውም በፀሀፊህ በኩል ቀጠሮ ይዘውና ተገቢውን ቅድመ ማሟላት ያለባቸውን ነገር አሟልተው መሆን አለነበት…አሪፍ ነው…››

‹‹እና እንዴት ላደርርግ ?ማስታወቂያ ላውጣ….?››

‹‹አይ እኔ በሶስት ቀን ውስጥ ምርጥ ፀሀፊህ ቀጥርልሀለው….አንተ በዚህ ጉዳይ ምንም አትጨነቅ…..ሶስት ቀን ብቻ ስጠኝ››

‹‹እሺ ማታ እቤት እንገናኝ››

‹‹እሺ ቻው ..ወንድሜ››

‹‹ቻው..››

ወንድሜ የሚለው ቃል ከአንደበቷ በወጣ ቁጥር በአንገቱ የተንጠለጠለ የብረት ሰንሰለት ነው የሚታየው….ሆነ ብላ እሱን ለማጥቃት አስባ ከአንደበቷ የምታወጣው ነው የሚመስለው….‹‹አደራ እኔ እህትህ ባልሆንም ልክ እንደእህትህ ነኝና ሌላ ነገር በአእምሮህ እንዳይበቅል››የሚል ማስጠንቀቂያ ነው የሚመስለው፡፡
የእናትና አባቱ ልጆች የሆኑት እህቱ ወንድሜ የሚለውን ስም በአመት አንዴ እንኳን ሲጠቀሙ አልሰማም….ትዝም የሚላቸው አይመስለውም…እሷ ግን ልክ እንደዘወትር ፀሎት እንደውዳሴ ማርዬም ነው በየእለቱ የምትደግመው፡፡
///.....////...../////

በፀሎት ጥዋት ከእንቅልፏ ስትባንን እቤት ውስጥ ከወ.ሮ እልፍነሽ በስተቀር ሌላ ማንም ሰው አልነበረም፡፡

‹‹እማዬ ሰው ሁሉ የት ሄደ?››እማዬ ብላ መጣራቷን ለራሷም እየገረማት ነው…ደግሞ አፏ ላይ አልከበዳትም…ወላጅ እናቷ…ሌላ ሴት እናቴ እያለች መጥራት መጀመሯን ብትሰማ ልብ ድካም ይዟት ፀጥ እንደምትል እርግጠኛ ነች፡፡

‹‹ወይ ልጄ… ነቃሽ…ልቀስቅሳት ወይስ ትንሽ ትተኛ እያልኩ ከራሴ ጋር ስሟገት ነበር፡፡ በረሀብ ሞትሽ እኮ››ብለው  ወደ ጓዲያ ገብና የእጅ  ማስታጠቢያ  ይዘው መጥተው,ሊያስታጥቧት ጎንበስ አሉ…እንደምንም ከአንገቷ ቀና ብላ ተነሳችና ‹‹ያስቀምጡት እኔ እታጠባለው››

‹‹አረ ችግር የለውም ልጄ ..ችግር የለውም››

‹‹ግድ የሎትም….››.

‹‹እንግዲያው ታጠቢ …ቁርስሽን ላቅርብ ›› ብለው ማስታጠቢያው ስሯ አስጠግተው አስቀመጡላትና ተመልሰው ወደ ጓዲያ ሔድ

…….እግሯ በተንቀሳቀሰች ቁጥር ጥዝጣዜው ነፍሶ ድረስ ይሰማታል…..ፊቷ ላይ አሁንም ተራራ የሚያህል ቁስል የተሸከመች እየመሰላት ነው…እንደምንም ተንፏቀቀችና እጇን ታጥባ የሚመጣላትን ቁርስ መጠበቅ ጀመረች…ጩኮ ከእርጎ ጋር ነበር የመጣላት…ጩኮ መች በልታ እንደምታውቅ አታስታውስም….ቤቷ ቁርስ ሲቀርብ አስር …አስራአምስት አይነት ምግብ ጠረጴዛ ሞልቶ ነው….ከዛ ውስጥ ሶስት ወይም አራት አይነቱን አፕታይቷ የፈቀደላትን መርጣ በልታ ሌላውን ትተዋለች..አሁን የቀረበላት ምግብ ይህን ያህል ግን አስደሳች አልነበረም…….እርቧት ስለነበረ እየተስገበገበች በላች…
ያጋባችውን ሰሀንና ብርጭቆ መልሳ…እጇን ታጠበችና…..‹‹እማዬ ማንም የለም እንዴ?››ስትል ደግማ ጠየቀች፡፡

‹‹ልጄ ለሊሴ ስራ ፍለጋ ብላ ወጥታለች…ፊራኦል ስራ ነው ..አባትሽም እንደዛው››መለሱላት፡፡

‹‹ለሊሴ ምን አይነት ስራ ነው የምትፈልገው?››

አትሮኖስ

02 Nov, 06:26


#የቃል_ቅሌት

ከሚሊዮናት ውስጥ
የቅርብ ዘመድ ጠፍቶ
አንድ ረዳት አጥቶ
ጠባብ ኩሽና ውስጥ
ቢገኝ አንድ አዛውንት
ደርቆ ተኮራምቶ
ከዚህ ዓለም ጣጣ
በሞት ተለያይቶ
በስላም “አረፈ”
“ተገላገለ” እንጂ
እንዴት “ሞተ” ይባላል?!?

ቃል”ም እንደሰው ልጅ
ለካ እንዲህ ይቀላል!!

🔘ፋሲል ተካልኝ🔘



#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

01 Nov, 18:07


#የሀገሬ_ሰው

“እንደምን አድርጎ እንዴት ነው 'ሚኖረው?
የጽልመቱን ዘመን
በብሩህ ብርሐን ማነው 'ሚቀይረው?

ለምንድን ነው?” አለ “ማነው “ሚመልሰው?”
እልፍ አዕላፍ ጥያቄ ጠየቀ የሀገሬ ሰው::
በገዛ ሀገሩ ላይ
በሐሳብ መግባባት መስማማት ሲጠፋ
ቂም በቀል ጥላቻ
ሥቃይና በደል ግድያው ሲከፋ
እሥራት እንግልት ስደቱ ሲስፋፋ
ሰላም ተናግቶበት
ፍቅርም መክኖበት ሲቀር ያለ ተስፋ
ጣዕሟ ቢጠፋበት ሕይወት ብትመረው
ዘመኑን በአግባቡ በቅጡ ያልኖረው
ምስኪኑ የሀገሬ ሰው መኖር ቢቸግረው
ለፈጣሪው አለው

አኗኗሬን ሳይሆን..ሞቴን አሳምረው!!!”

🔘ፋሲል ሃይሉ🔘

አትሮኖስ

01 Nov, 17:24


​​እናትና አባቱም እሷን በዳሩ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ነው ተከታትለው የሞቱባቸው……‹‹አሁን ምክንያት አይኖራትም››ብሎ ወስኗል፡፡
ለዚህ ነው ከውጭ ከተመለሰ በኃላ ለመደላደል ስራ መጀመር እንዳለበት የወሰነው፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

01 Nov, 17:24


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሰባት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ስራው "የፍቅርና የጋብቻ አማካሪነት ነው።የተማረው ፍልስፍና ነው።ሁለተኛ ዲግሪውን ግን አሜሪካ ሄዶ በስነልቦና መስራት ችሏል፡፡በፍቅርና ጋብቻ አማካሪነት የሰራውም እዛው አሜሪካ ነው….ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ ሶስት አመት ተቀጥሮ ሰርቶል፡፡አሜሪካዊያኑ በፍቅርና በጋብቻ ጉዳይ ችግር ሲያጋጥማቸው ባለሞያ ጋር መሄድና ድጋፍ ማግኘት ባህላቸው ነው፡፡በመጀመሪያ ወደትዳር ከመግባታቸው በፊት ማድረግ ስለሚገባቸው ስነልቦናዊ ቅድመ ዝግጅት ለማወቅ ባለሞያው ጋር ይሄዳሉ..ትዳር ውስጥ ገብተው ችግር ሲያጋጥማቸው…እርስ በርስ ያለው ተግባቦታቸው አመርቂ ካልሆነ…የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት የሚያጨቃጭቃቸው ከሆነ…የወሲብ አለመጣጣም በመሀከላቸው ካለ ብቻ ማንኛውንም ችግር በመሀከላቸው ከተፈጠረ ወደ ጋብቻ አማካሪ ሄዶ ሞያዊ ምክር መጠየቅና ከዛም የሚሰጣቸውን ምክርና ትዕዛዝ ለየብቻም ሆነ አንድላይ በመተግበር ችግሩን ለመቅረፍ የሚያደርጉት ጥረት ያስቀናል፤ሌላው ይቅር ጋብቻቸው እንደማይሰራ እርግጠኛ ከሆኑ እንኳን ጤናማና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዴት መለያየትና ጓደኛሞች ሆኖ መቀጠል እንደሚችሉ ምክር ለማግኘት ተያይዘው ወደ ጋብቻ አማካሪ ቢሮ ይሄዳሉ..ይህ ጉዳይ በጣም ነበር የሚያስገርመው፡፡በተለይ በመሀከላቸው ልጆች ካሉ ለየብቻ ሆነው እራሱ
የልጆቻቸውን ስነልቦና ጠብቀው እንዴት ተግባባተው ማሳደግ እንዳለባቸው ዝርዝር መመሪያ ከአማካሪዎች በመስማት ያንን ሳያዛንፉ በመተግበር የልጆቻቸውን ደስታ ሆነ የእነሱን ሰላም ይጠብቃሉ፡፡ያም ሆኖ ግን ምንም እንኳን በስራው በጣም ደስተኛና ጥሩ ገቢ የሚያገኝበት ቢሆንም ከአምስት አመት በኃላ ጠቅልሎ ወደሀገሩ ተመለሰ….ሲሄድ መቼም ላይመለስ ነበር…..ሀገር ቤት ባሉ ነገሮች ጠቅላላ ተስፋ ቆርጦ ነበር…ግን እንዲመለስ የሚያስገድደው ቁራጭ ምክንያት አገኘ……እና ተመለሰ፡፡

ሰለሞን ወደ ሀገር ቤት እንደተመለሰ መጀመሪያ ተቀጥሮ ለመስራት  ስራ ለማፈላለግ ሞክሮ ነበር….።አስቴር ግን የራሱን ስራ መጀመር እንዳለበት በተደጋጋሚ ጊዜ ግፊት ስታደርግበት እራሱን ከተበታተንበት ሰበሰበና እና መኝታ ቤቱ ውስጥ ገብቶ በላዩ ላይ ዘጋና ስብሰባ ተቀመጠ።አስቴር የልጅነት ጓደኛው እናም ደግሞ ፍቅሩ ነች…ወጣት ሲሆኑ ደግሞ እህቱ ሆነች…እስከአሁንም እህቱ ሆና ቀረች..እሱ በልቡ ተመልሳ ፍቅሩ እንድትሆን ነው የሚመኘው….አላማውም እቅዱም ያ ነው..እሷ ግን ያንንን መስመር ጠርቅማ ዘግታበት አባቱን አባቷ እናቱን እናቷ አድርጋ ለእሱ ደግሞ እህቱ ሆናለች፡፡

ከልጅነቱ ጀምሮ ነው የሚያውቃት፡፡ ገና ሰባት ወይ ስምንት አመቱ ላይ…የእናቷን ጠርዙ የነተበ የቀሚስ ጫፍ በትናንሽና ለስላሳ እጆቾ ጨምድዳ ይዛ ስርስሯ ኩስ ኩስ እያለች ስትመጣ ነበር የሚያውቃት…የዛን ጊዜውን የልጅነት መልኳን አሁንም በአእምሮው ሰሌዳ ላይ በጉልህ ተስሎ ይገኛል..በአጭሩ ተቆርጦ እርስ በርሱ ተጠቅልሎ የተንጨፈረረ ወርቃማ ፀጉር…ጎላ ጎላ ብላው በፍርሀት የሚንካባለሉ አይኖች…በእንባና በአቧራ ብራብሬ የሆነ አሳዛኝ ፊት….ልክ የግቢው አጥር ተከፍቶላቸው የፊትለፊቱን ትልቁን የሳሎን በራፍ አልፈው ወደጓሮ ሲዞሩ ከኃላ ተከትሎቸው ይሄዳል…እናትዬውን ተከትላ ማድቤት ስትገባ ተከትሏቸው ይገባል…
‹‹የእኔ ልጅ፣ እስኪ እኔ ስራዬን ልስራበት አንቺ ከሰሎሞን ጋር አብራችሁ ተጫወቱ››እያለች እናትዬው ታባብላታለች…እሷም የእናትዬውን ልመና ተቀብላ ከእሱ ጋር ለመጫወት ፍቃደኛ እንድትሆን በአይኖቹ ጭምር ይለማመጣታል….የተቋጠረ ግንባሯን ሳትፈታ በቀሰስተኛ እርምጃ ወደእሱ ትጠጋለች…በደስታ አጇን አፈፍ አድርጎ ይይዛትና እየጎተተ ወደትልቁ ቤት ይዞት ይሄዳል…ከታላቅ እህቱ ጋር በጋራ ወደሚኖርበት መኝታ ክፍላችው ይዞት ይገባል፣..ያሉትን መጫወቻዎች ሁሉ ከየመደርደሪያዎቹን ከየአልጋ ስሩ እየጎተተ ያወጣና  ፊት ለፊቷ  ወለሉ  ላይ  ይቆልላል፣ለእሱ  የሰለቹትን  መጫወቻዎች  ለእሷ  ብርቅ  ነበሩ….እናትዬው እነሱ ቤት በተመላላሽነት በሳምንት ሶስት ቀን ትሰራለች፡፡እና እነዛን ሶስት ቀናት በናፍቆትና በፍቅር ነበር የሚወዳቸው… ሳምንቱን ሙሉ ለምን እንዳማይመጡ ይገርመው ነበር..ከዛ አባቱ እሱን አንደኛ ክፍል አስመዝግቦ ትምህርት ሲያስጀምረው ለእሷም እንደዛው ደብተርና ዩኒፎርም ገዝቶ እሱ የሚማርበት ትምህርት ቤት እናቷ እንድታስመዘግባት አደረገ…አንድ ትምህርት ቤት አንድ ክፍል መማር ጀመሩ…ይሄ ደግሞ የሚገናኙበትን የቀን ብዛትና አጋጣሚ አሰፋው…..ጓደኝነታቸው አብሮ ዕቃ ዕቃ ከመጫወት የተጀመረ ….ከዛ ኤለመንተሪ ጀምረው እስከ ሀይ እስኩል በተመሳሳይ ጊዜ በተመሳሳይ ክፍል ውስጥ ነው የተማሩት።

የተወሰኑ ክፍሎችን አንድ ክፍል ጥቂት ክፍሎችን ደግሞ አንድ መቀመጫ ላይም አብረው ተቀምጠው የመማር አጋጣሚዋች ነበሯቸው።ስለዚህ እሷ ልክ አብረውት እንደተወለድ ወንድሞቹ እና እህቱ እድሜ ልኩን ነው የሚያውቃት፡፡
ፍቅር የጀመሩት 8ተኛ ክፍል ሲማሩ ነው።በወቅቱ እሱ 8ተኛ ቢ ሲማር እሷ ደግሞ 8ተኛ ኤፍ ክፍል ነበረች።ግን ቢሆንም ብዙውን ጊዜ ወደት/ቤት ሲሄድና ወደሰፈር ሲመለሱ ተጠራርተውና ተጠባብቀው ነበር።እና አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ሲወጡ እየጠበቀችው ነበር።አብረው ወደቤት መመለስ ቢጀምሩም ግን አንደበቷ እንደተቆለፈና እንደተበሳጨች ነበር...ምን እንደሆነች ቢጠይቃትም በቀላሉ ልትነግረው አልቻለችም..በኋላ በስንት ጭቅጭቅ ከቦርሳዋ አንድ ወረቀት አውጥታ ሰጠችው።ምንድነው? ብሎ በጉጉት ተቀብሎ አነበበው።
አስቴርዬ የእኔ ቆንጆ..የፍቅርሽ ፍላፃ ልቤ ላይ ነው የተሰካው….እስካሁን ሰንኮፉን
አልነቀልኩትም…ያልነቀልኩት ሲሰካብኝ ከነበረው ጊዜ በላይ ስነቅለው ያመኝ ይሁን በሚል ስጋት ነው…….ምን አልባት አንቺው በትንፋሽሽ አዘናግተሸ በልስልስ እጆችሽ ቀስ ብለሽ ብትነቅይልኝ መልካም ይሆን ይመስለኛል፡፡፡አንቺ እኮ ከአለም ሴቶች ጭምር ተወዳዳሪ
የሌለሽ ውብ ነሽ።እኔ አፍቃሪሽ በአንቺ ፍቅር መንገላታት ከጀመርኩ አመታት አልፈዋል።ግን እስከዛሬ ስቃዬን በውስጤ አፍኜ ህመሜን የቻልኩት ከጓደኛዬ ከሰለሞን ጋር ግንኙነት ያላችሁ ስለሚመስለኝ ነበር።ግን በቀደም ወኔዬን አሰባስቤ ስጠይቀው ጓደኛሞች ብቻ እንደሆናችሁ ነገረኝና ነፍሴን በሀሴት አስጨፈራት።እና ውዴ አንቺስ ምን ትያለሽ...
?መልስሽን በጉጉት እጠብቃለሁ... የአንቺው አፍቃሪ መስፍን ጋዲሳ›› ይል ነበር።

አነበበውና ግራ የመጋባትና የመደነጋገር ስሜት ተሠማው..በደብዳቤው ላይ እንደተጠቀሰው በቀደም በብዙ ጓደኞቻቸው መካከል ስለፍቅር አንስተው ሲያወሩ መስፍን እንደቀልድ ‹‹አስቴርና ሰለሞን ፍቅረኛሞች ናቸው›› አለ ወዲያው ሰለሞን ከአፉ ተቀበለና
‹‹እውነት አይደለም እኔና አስቴር ፍቅረኛሞች ሳንሆን ጓደኛሞች ነን ››ብሎ መልስ ሰጠ ።ነገሩ በዚህ ተደመደመ።ደብዳቤውን ባነበበበት ወቅት ግን መሠፍን ሆነ ብሎ ለገዛ የግል ጥቅሙ ጥያቄውን ጠይቆት እንደነበረና እሱንም ማኖ እንዳስነካው ገባውና በጅልነቱ ተበሳጨ።

ግን ደግሞ የአስቴር ወቅታዊ ኩርፊያ አልገባውም ነበር።‹‹መስፍን ደብዳቤ ለፃፈላት እኔን ለምን ልታኮርፈኝ ቻለች?››እራሱን ጠየቀ
"እና እኔ ምን አጠፋው..የምታኮርፊኝ?"ፈራ ተባ እያለ ጠየቃት፡፡

አትሮኖስ

01 Nov, 17:24


"አይ አንተማ ምንም አላጠፋህ …እኔ ነኝ እንጂ ዘላለም በብላሽ ከአንተጋር የምንዘላዘለው..ነው ወይስ እናቴ የቤታችሁ አገልጋይ ስለሆነች አትመጥነኝም ብለህ አስበህ ነው?"አለቸው።እና እየተመናጨቀች ተለይታው ወደቤቷ አመራች።

ሰለሞንም ደንዝዞ ወደቤቱ ገባና በመጨረሻ ስትለየው የተናገረችውን ዓ.ነገር ሲያሰላስል አደረ።"....እኔ ነኝ እንጂ ዘላለም በብላሽ ከአንተጋር የምንዘላዘለው...

‹‹ምን ለማለት ፈልጋ ነው?ታፈቅረኛለች ማለት ነው?እኔስ አፈቅራታለሁ እንዴ? መስፋን የፃፈላትን ደብዳቤ ሳነብ ለምን ቅር አለኝ,,,?ቀንቼ ነው እንዴ?ፍቅር ሲይዝ እንዴት ነው የሚያደርገው?ስምንተኛ ክፍል ሆኖ ፍቅረኛ መያዝ ይቻላል እንዴ?››እነዚህንና መሰል ጥያቄዎች ባልጠና እና ለጋ ጭንቅላቱ ሲያወርድና ሲያወጣ እንዲሁ እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ነጋ...፡፡ከዛን በኋላ በማግስቱ አናገራት

….እንደሚያፈቅራትና እሷ ፍቃደኛ ከሆነች ፍቅረኛው እንድትሆን እንደሚፈልግ ነገራት..እሷም በደስታ ፈንጥዛ እላዩ ላይ ተጠመጠመችበት….ከዛ የታዳጊነት ፍቅራቸው እስከ አስረኛ ክፍል ቀጠሉ…የበለጠ ጊዜ በሄደ መጠን በእነሱም መካከል ያለ ፍቅር እየደረጀና ስር እየሰደደ መጣ፡፡አስረኛ ክፍል በጀመሩ በሶስተኛው ወር አንድ ቀን ጥዋት የትምህርት ቤት ሰዓት ደርሶ ቀድሞ ወጥቶ ቢጠብቃት ልትመጣ አልቻለችም...ተማሪ ሁሉ ሄዶ ማለቁንና ሰዓቱ መርፈድንም ከግንዛቤ በማስገባት በለሊት ቀድማ መሄዶን ጠረጠረና በሩጫ ወደትምህርት ቤት...በረፍት ሰዓት ክፍሏ ሄዶ ቢያያት እንዳልመጣች ጓደኞቾ ነገሩት።ግራ ተገባ።
አስቴር ከትምህርት ቤት በቀላሉ የምትቀር አይነት ልጅ አይደለችም። ለትምህርቷ የምትሰጠው ትኩረት ቀላል የሚባል አንዳልሆነ ያውቃል…ታዲያ እንዴት?።እናም ያለ መምጣቷ ዜና አልተዋጠለትምና እሱም እንዳመመው በመናገር አስፈቅዶ ወደቤት ሄደ…ወደቤት የሄደበት ዋና ምክንያት የአስቴር እናት እንጀራ ልትጋግር ወይም ሌላ ስራ
ለመስራት ወደእነሱ ቤት የምትመጣበት ቀን ስለሆነ አስቴር ለምን እንደቀረች ሊጠይቃት ነበር እቅዱ፡፡እቤት ሲደርስ ግን ማንም አልነበረም..የአስቴር እናትም እንዳልመጣች በኩሽናው መቆለፍ አረጋገጠና ደብተሩን አስቀምጦ ወጣና ወደ እነአስቴር ቤት አመራ… ሰፈራቸው ሲደርስ እቤታቸው ፊት ለፊት ድንኳን ተተክሎ ነጠላ ያዘቀዘቁ ሴቶችና ጋቢ የደረብ ወንዶች ሲተረማመሱ ከሩቅ አየ...ሰውነቱ እስኪንቀጠቀጥ ድረስ ነው የደነገጠው፡፡

‹‹አስቱካ ምን ሆነች?››በሩጫ ነበር ተንደርድሮ ድንኳኑ መሀከል የተገኘው...አስቴር በአራት በሚበልጡ ሴቶች ግራና ቀኝ ተደግፋ ‹‹ወይኔ እናቴ እያለች›› ስትንፈራፈር ተመለከታት"ተመስገን"አለና ትንፋሹን ወደውስጥ እየሳበ ለመረጋጋት ሞከረ።‹‹ተመስገን
››ያለው እናቷ ስለሞቱ አይደለም...በፍፁም ።ይልቅ እሷ በህይወት ስላለችልለት ተደስቶ ነው።እንጂማ እናቷ ከህፃንነቱ ጀመሮ ከገዛ እናቱ በመቀጠል ያሳደጉት ያዘሉትና የመገቡት ሴት ናቸው…….የእሳቸውም ሞት በጣም አስደንግጦታልም አሳዝኖታልም…
ከዛ ከሀዘን ቤት እስክትወጣም ሆነ ከዛ በኋላ ከስሯ አልተለየም።ግን እሷን ማፅናናት እና ወደ ህይወቷ እንድትመለስ ለማድረግ ቀላል አልሆነለትም።ምክንያቱም ለአስቴር እናቷን ማጣት እናትን ብቻ ሳይሆን መላ ዘር ማንዘሯን ማጣት ማለት ነበር።ምክንያቱም አባቷን ጭራሹኑ እሷ እንደተፀነሰች የሞተ እና ዘመዶቹንም የማታውቅ ሲሆን በተመሳሳይ እናቷም የረባ የቅርብ ዘመድ ያልነበራት ብቻዋን ወልዳ ብቻዋን ያሳደገቻት ነበረች እና እሷም ስትሞትባት ሌላ አይዞሽ የሚላትና የሚያፅናናት አንድም የቅርብ ዘመድ አልነበራትም።በኋላ የእናትና አባቱ ተማከሩና አስቴርን እንደልጃቸው አድረገው ወደቤታቸው አመጧት፡፡

ትዝ ይለዋል የአስራ አምስት አመት ልጅ እና የአስረኛ ክፍል ተማሪ እያለ ነበር…አስቴር የቤተሰቡ አባል ሆና የተቀላቀለች፡፡አዎ እሷ ስትመጣ እሱ ከእህቱ ጋር ከሚጋራው ክፍል ተፈናቀለና ሌላ ትልቁ ወንድሙ ለቆ ዩኒቨርሲቲ በገባበት ክፍል ከአመፀኛው ወንድሙ ጋር ደባል ሆኖ ገባ…
እድሜውን ሙሉ የኖረበትን ክፍልና የተኛበትን አልጋ እንዳለ ለአስቴር አስረከበ….እንደዛ በመሆኑ አልከፋውም….፡፡ለሌላ ሰው ልቀቅ የተባለ ቢሆን ኖሮ ከፍተኛ አብዬት ያስነሳ እንደነበር እርግጠኛ ነው….ለአስቴር ስለሆነ ግን እንደውም ደስ ያለው ይመስላል…እርግጥ እሱ ከመኝታው ሳይፈናቀል በእሱ ምትክ እህቱ እንድትለቅላት ቢደረግ ወይንም ሌላ ሶስተኛ አልጋ ወደክፍሉ እንዲገባ ተደርጎ እሷ እንድትተኛ ቢደረግ በጣም ደስተኛ ይሆን እንደነበር እርግጠኛ ነው..ግን ለምን ተብሎ ሊጠየቅ የማይችለው አባቱ ኮስተር ብሎ የወሰነው ውሳኔ ስለሆነ ያለምንም ማቅማማት ነው ተግባራዊ የሆነው፡፡

አስቴር ከእሱ በአንድ አመት ስትበልጥ ከእህቱ ስህን ደግሞ በሁለት አመት ታንሳለች…..ስለዚህ የሁለቱንም ጓደኛ ነች፡፡
ይሄ ውሳኔ በደስታ እንዲፈነጥዝ እና በወላጆቹም እንዲኮራ አደረገው።እና እህቱም ጓደኛውም ሆነች...።የነካኩት የፍቅር ጉዳይ ግን እንደተዳፈነ ቀረ...።
አስቴር ‹‹ እቤታቸውንም ልባቸውንም ከፍተው እንደገዛ ልጃቸው የተቀበሉኝን ሰዎች ልጃቸው ጋር ባልጌ አላሳዝናቸውም…እኔ እና አንተ ከአሁን በኋላ እህትና ወንድም እንጂ ፍቅረኛሞች መሆን አንችልም›› ብላ ቁርጥ ያለ ውሳኔዋን ነገረችው፡፡እሱ በቀላሉ ውሳኔውን ሊቀበል አልቻለም፡፡

ይበልጥ ሊያጣት እንደሆነ ባወቀ ቁጥር ውስጡ የንዴት እሳት እየነደደ ይለበልበው ጀመር፡፡
እና ውሳኔዋን እንድትቀይርና እንድታስተካክል በወጣች በገባች ቁጥር ሲያስቸግራት እሷም እሱን ተስፋ ለማስቆረጥ እርምጃ ወሰደች…ስምንተኛ ክፍል ሆነው ደብዳቤ የፀፈላትን መስፍንን 11 ክፍል ፍቅረኛ አድርጋ ተቀበለችው፡፡

ከዛሬ ነገ እሱን ትታ ወደእኔ ትመለሳለች ብሎ በትእግስ ሲጠብቅ ሁለቱም 12ተኛ ክፍል ማትሪክ ተቀበሉና ዩኒቨርሲቲ ገቡ…ልክ በተመረቁ በ3ተኛ ወሯ መስፍን እነ ሰለሞን ቤተሰቦች ጋር አስቴርን ለማግባት ሽማጊሌ ላከ…ወዲያው ቀለበት አሰሩና ከሶስት ወር በኃላ ተጋቡ፡፡

በዚህን ጊዜ ሰለሞን ሁሉ ነገር አስጠላው…ሁሉን ነገር ጣጥሎ በትምህርት አሳቦ ወደውጭ የተሰደደበት ዋና ምክንያት የእሷ ማግባት ነበር…ለአመስት አመት እዛው ኖረና ድንገት ለመመለስ ወሰነ…ይሄንን ወደሀገር የመመለሱን ውሳኔ የወሰነበት ዋናው ምክንያትም  አስቴር ከ5 አመት የጋብቻ ቆይታ እና አንድ ልጅ ከወለዱ በኃላ ተፋተው እሱም ልክ እንደእሱ አገር ጥሎ እንደተሰደዱ ስለሰማ ምን አልባት ከአመት በፊት የተነጠቅኩትን ፍቅሬን መልሼ የማግኘት እድል ይኖራኛል በሚል ተስፋ ነበር የተመለሰው፡፡ከልጅነት እስከጎልማሳነት የዘለቀ እንቅፋት የበዛበት ውስብስብ ፍቅር…እና ሁሉ ጊዜ ስለራሱና ስለፍቅሩ ሲያስብ ‹‹ጠንቆይ ለራሱ አያውቅም እያለ ››ይተርታል..፡፡
እሱ ለላፉት ሶስትና አራት አመታት ለብዙ ሺ ጥንዶች እንዴት ያፈቀሩትን ሰው ማሳመንና የራሳቸው ማድረግ እንዳለባቸው..ፍቅራቸውን እንዴት መንከባከብ እንደሚገባቸው ውጤታማ ምክር እየሰጠ ተግባራዊ እንዲያደርጉት ሲጫናቸውና ደከም ያሉትንም ሲበሳጭባቸው ከርሞል..ግን የራሱን ከልጅነቱ ጀምሮ ሲያበቅለውና እየተንከባከበ ሲያሳድገው የነበረውን ፍቅር የሆነ ዘዴ ፈጥሮ ፍሬውን ለመብላት ፈፅሞ አልቻለም፣አሁን ግን ቆርጦ ነው የመጣው አዎ
…አስቴርን ከአነልጇ ያገባታል ..የልቡም የቤቱም ንገስት ያደርጋታል››ሰው ምን ያላል እቤተሰብ ምን ይላሉ አሁን አይሰራም ..እስከዛሬ እሷ እንደምክንያት የምታቀርባቸው

አትሮኖስ

31 Oct, 17:52


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_ስድስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ አንድ ሰዓት የቤቱ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ጠባቧን ሳሎን ሞሏት…መጨረሻ ላይ የመጣው ፊራኦል ነበር…በእጁ አንድ ኪሎ ሙዝ ይዞ ነበር፡፡ ለሊሴ ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ ተነስታ ከእጁ መንጭቃ ተቀበለችው እና‹‹..ወንድሜ ሙዝ ገዛኸልኝ….!!! ደሞዝ ደረሰ እንዴ?››ስትል በፈገግታ…»

አትሮኖስ

31 Oct, 17:00


እንባዋ ከአይኖቾ ያለፍቃዷ ረገፈ…
‹‹አመሰግናለው ጋሼ..በእውነት በጣም አመሰግናለው፡፡››

‹‹ልጅ አባት አያመሰግንም..ዝም ብሎ ብቻ ይወደዳል….በቃ በእኛ መካከል ፍቅር ብቻ ነው ያለው..በሉ ብርዱን ብዙም አትዳፈሩት….››አሉና እንደአመጣጣቸው ወደውስጥ ተመልሰው ገቡ፡፡

ስሯ የተቀመጠውን ፊራኦልን በጭለማ ውስጥ አፍጥጣ እያየችው ‹‹ታድለህ››አለችው

‹‹ማለት?››

‹‹እኚን የመሰለ ..የተባረከ እና ፍቅር የሆነ አባት ስላለህ ››

‹‹አዎ አባዬ የእኔ ብቻ ሳይሆን የሀገር ምድሩ አባት ነው…ለሰው ሁሉ ያለው ፍቅር የሚገርም ነው..አንዳንዴ እንደውም ስለሚያበዛው እበሳጭበታለው››

‹‹ጥላቻ እንጂ ፍቅር ሲበዛ እኮ አያበሳጭም››

‹‹አይ ያበሳጫል..ልጅ ሆነን ለእኛ ገዝቶ የመጣውን ሙዝ መንገድ ላይ ላገኛቸው ልጆች ሁሉ አንድ አንድ እየመዘዘ ሲያድል እቤት ሲደርስ ባዶ ፔስታል ብቻ ይቀራል…አባዬ እንደዛ ነው….ቢሆንም ግን በጣም ደሀ ግን በጣም ተወዳጅ አባት ስላለኝ አመስጋኝ ነኝ ››

‹‹አይ አባትህማ ደሀ ተብለው የሚገለፁ አይደሉም…ግርማቸውና ርህራሄያቸው ቢሊዬን ብር ያወጣል….እመነኝ ምነው የእኔም አባት በሆኑ ብዬ ቅናት እያንገበገበኝ ነው፡፡››

‹‹ምንም መቅናት አያስፈልግሽም…በቃ አሁን ልጄ ነሽ ብሎሻል አይደል……ለእሱ ከእኔ የተለየሽ አትሆኚም ፣ላጋንን አይደለም…ታይዋለሽ…..ቅድም ካንድ ጓደኛው ጋር በስልክ ሲከራከር ነበር››

‹‹ለምን?››ለማወቅ ጓጉታ ጠየቀችው፡፡

‹‹የፊታችን እሁድ ማለት ከሶስት ቀን በኃላ የሚወጣል እቁብ አለው…ስምንት ሺ ብር አካባቢ መሰለኝ፡፡እና የወንድሜ ልጅ ታማብኝ ማሳከሚያ ቸግሮኛል …ወይ እቁብን ሰጡኝ ወይ ደግሞ ከወጣለት ሰው እንድገዛ አመቻቹልኝ እያለ ሲለምናቸው ነበር…እኔ ደግሞ ለራሱ ጉዳይ ቸግሮት አንቺን እንደሰበብ እየተጠቀመ መስሎኝ‹‹‹አባ ብሩን ለምን ፍልገህ ነው?››ብለው፡፡
‹‹ይህቺን ልጅ ደህና ሆስፒታል ወስጄ ማሳከም አለብኝ..ከዚህ ሁሉ ሺ ቤቶች የእኔን ቤት ጋር መታ የተላተመችው ያለምክንያት አይደለም..እግዜር እኔን ሊፈትን ይሆናል የላካት…ደግሞስ እንዲህ ተጎድታ የተኛችው ለሊሴ ብትሆን ወይም አንተ ብትሆን እንዲህ ዝም እል ነበር?ልጄ በሬዱ አደጋ ባጋጠማት ጊዜ ቶሎ በፍጥነት አንስቶ ሆስፒታል ሚወስዳት ሰው ብታገኝ ኖሮ በለጋነቷ አትቀጠፍብኝም ነበር…..ከሁለት ሰዓት በላይ መኪና ውስጥ ተቀርቅራ ደሟ ሲንዠቀዠቅ……›› አለኝ…አባዬ የልጁ የበሬዱ ሞት ብቻ ሳይሆን አሟሟቷም ሁል ጊዜ እንደረበሻቸው ነው፡፡
በፀሎት የምትሰማው ነገር ከአእምሮዋ በላይ እየሆነባት ነው፡፡

‹‹ታዲያ አባትህ እንደዛ ሲሉህ አንተ ምን አልካቸው?››

‹‹እውነቱን መስማት ነው የምትፈልጊው?››

‹‹አዎ እውነቱን››

‹‹እንግዲያው እኔ አባቴ ያንን እቁብ እንዴት አድርጎ እንዴት ተቸግሮ በየሳምንቱ በመጣል ያጠራቀመው ብር እንደሆነ ስለማውቅ ተቃውሞ ነው ያሰማሁት..ታያለሽ አይደል ያን የተከመረውን ብሎኬት እንዲህ ከተደረደረ ሶስት አመት አለፈው…እህቴ በሬዱ ነበረች ከመሟተዋ በፊት የገዛችው….ቤተሰብ አሁን ባለው አኗኗር እየተጨናነቀ ስለሆነ አባቴ አንድ ክፍል ቤት ቀጥሎ እንዲሰራ አቅዳ ነበር፣ግን ያው ሞት ቀደማት ….እና አባቴ ከእቁቡ የሚገኘው ብር ለዚህ አዲስ ተቀጥሎ ለሚሰራው ክፍል ቆርቆሮና ምስማር መግዣ ነበር ያሰበው…አላማው ቤቱን መስራት ብቻ ሳይሆን የእህቴንም እቅድ ተግባራዊ ማድረግ
የአእምሮ ሰላም ማግኘት ነበር…በዚህ ምክንያት በቀላሉ ልስማማ አልቻልኩም…በእኔ አመለካከት እስከአሁን ላንቺ ያደረግነው ትብብር በቂ ነው የሚል እምነት ነው ያለኝ፡፡እና የቤተሰቦችሽን ስልክ ፈልገን ደውለንላቸው እንዲወስዱሽ ነበር ሀሳብ ያቀረብኩለት፡፡››

‹‹እና ታዲያ አባትህ ምን አሉ?››

‹‹የከፋት ልጅ ነች…በራሷ ውሳኔ እንደዛ ካላደረገች እኔ እንደዛ እንድታደርግ አልገፋትም…የእኛ ሀላፊነት የቻልነውን ማድረግ ነው..ሌላው የእሷ ውሳኔ ነው..ልጄ በየቤቱ ወጣቱ እራሱን የሚያጠፋውና ህይወቱን የሚያበላሸው እንዲህ የሚያዳምጠው አጥቶ ያም ያም ሲገፋውና ሲያሳድደው ነው…የቻልነውን እናደርጋለን.››አለኝ፡፡

‹‹አሁን እንግባ በቃኝ››አለችው፡፡
ከተቀመጠበት ተነሳና ሰቅስቆ አቀፋት..ወደውስጥ ይዞት ገባና ቀስ ብሎ ቦታዋን አስተካክሎ አስተኛትና….በራፉን በትክክል ዘግቶ ወደሶፋው በመሄድ ተኛ…እሱ ወዲያው እንቅልፍ ቢወስደውም እሷ ግን እስኪነጋጋ ድረስ እንቅልፍ በአይኗ አልዞረም ነበር….ጥዋት ግን ሁሉም ሲነሱ እሷ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወስዷት ነበር፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

31 Oct, 17:00


‹‹ስምህ ፊራኦል ነው አይደል ምን ማለት ነው?፡፡››

‹‹በትክል የስሙ ትርጉምን ለማወቅ ፈልጋ ሳይሆን እንዲሁ ወደጫወታ እንዴት እንደምትገባ ግራ ስለገባት የሰነዘረችው ጥያቄ ነበር ‹‹ከዘመድ ሁሉ በላይ ነህ..ወይም ከዘመድ ሁሉ በላይ ሁን ማለት መሰለኝ....እኔ ግን ከዘመድ ሁሉ እኩል እንጂ በላይ መሆን አልፈልግም፡፡››

‹‹ሶሻሊስት ነገር ነህ ማለት ነው?››

‹‹በይው..እንዳንቺ አይነት ካፒታሊስት በበዛበት አለም ሶሻሊስት መሆን ከባድ ቢሆንም አዎ ሳሻሊስታዊ ነኝ፡፡››

‹‹እኔ ካፒታሊስታዊ መሆኔን በምን አወቅክ?››

‹‹በወዝሽ››
ከቀናት በኃላ ከት ብላ ሳቀች‹‹እንዴ እንዲህ ቆሳስዬ እና ግማሽ ፊት በባንዴጅ ታሽጎ ወዜን እንዴት ማወቅ ቻልክ?፡፡››

‹‹ወዝሽ  እኮ  ፊትሽ  ላይ  ብቻ  አይደለም  ያለው…የቆዳሽ  ልስላሴ  እኮ  የሰው አይመስልም…ጌጣጌጦችሽም አንዱ ምስክር ናቸው…››

‹‹እንዴ አርቴ እኮ ነው፡››

‹‹አይ ቤተሰቦቼ..ማለቴ እህቴ አርቴ ነው ብላ ስታወራ ሰምቼለሁ....እኔ ግን ስለጌጣጌጥ የተወሰነ እውቀቱ አለኝ …አርቴ እዳልሆኑ እርግጠኛ ነኝ››

‹‹ጎበዝ ነህ!!››

የተወሰነ ደቂቃ በመካከላቸው ፀጥታ ሰፈነ ‹‹ምንድነው የምትሰራው?››ስትል ድንገት ጠየቀችው..ጥያቄዋ እንዲሁ በመሀከላቸው የተጀመረውን ጫወታ ለማራዘም ብላ እንጂ ምንም ይስራ ምንም የሚያስጨንቃት አይነት ሆኖ አይደለም፡፡

‹‹ገንዘብ ያስገኝ እንጂ ያገኘሁትን ሁሉ ሰራለሁ››

‹‹ማለት…?››

‹‹ማለትማ ማርኬቲንግ ነው የተመረቅኩት…ሱፐር ማርኬት ውስጥ ሰርቼ አውቃለሁ…የጅውስ ማከፋፈያ ፋብሪካም ተቀጥሬ ሰርቼ አውቃለው…..ቆርቆሮ ፋብሪካም ሰርቼ ነበር..አሁን ግን አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ውስጥ ነው እየሰራሁ ያለሁት፡፡››ሲል አብራራላት
‹‹አኸ…ስለጌጣጌጤ የተናገርከው ከዛ ልምድ በመነሳት ነዋ››

‹‹ይሆናል››

‹‹ግን ቆርቆሮ ፋብሪካ የትኛው ቆርቆሮ ፋብሪካ ነው የሰራኸው?››

‹‹በፀሎት ቆርቆሮ ፋብሪካ…እዛ ሁለት አመት ሰርቼው›› ከድንጋጤዋ የተነሳ ..ትን አላት…

ደንግጦ ተነሳና ጀርባዋን ደገፋት

‹‹ደህና ነኝ ደህና ነኝ››

‹‹ምነው ..ያልሆነ ነገር ተናግሬ አስደነገጥኩሽ እንዴ?››

‹‹አይ በፀሎት የሚባል ቆርቆሮ ፋብሪካ መኖሩን አላውቅም ነበር…››

‹‹እንግዲህ ቆርቆሮን በተመለከተ ምንም እውቀት የለሽም ማለት ነው…..በፀሎት እኮ አገሪቱ ውስጥ ካሉ ትላልቆቹ ቆርቆሮ አማራቾች መካከል አንዱ ነው…ባለቤትነቱ የቢሊዬነሩ ባለሀብት የአቶ ኃይለመለኮት ነው…..በፀሎት የልጃቸው ስም ነው፡፡›

‹‹አይገርምም..የእኔም ስም በፀሎት በመሆኑ እኮ በእኔ ስም የሚጠራ ቆርቆሮ ፋብሪካ ባለማወቄ ተደንቄ ነው...ሰውዬውን ማለቴ ባለቤቱን ታውቃቸዋለህ?››

‹‹አዎ …አውቃቸዋለው…ማለቴ በመጠኑ .. ሁለት ወይም ሶስት ቀን እሷቸውን የማናገር እድል ነበረኝ››

‹‹ልጃቸውንስ?››

‹‹እሷን የፋብሪካው በራፍ ላይ በትልቁ ቢልቦርድ ላይ የተለጠፈው ምስሏ ለአመታት ሳየው ነበር ….ይሄኔ እሷ በስሟ ወላጆቼ ፋብሪካ እንዳላቸው ሁሉ አታውቅም ይሆናል..ግን ይገርምሻል አሁን በጣም ትናፍቀኛለች…ብዙ ቀን ላገኛት ሞክሬ ነበር ግን አውሬ መሳይ ጋርዶቾ ሊያስጠጉኝ አልቻሉም….ግን በቅርብ እንደማገኛትና እንዲህ እንደእኔና እንዳንቺ ፊትለፊት ተቀምጠን ብዙ ብዙ ነገር እንደምናወራ እርግጠኛ ነኝ…በሆነ መንገድ የግድ ማግኘት አለብኝ››

ንግግሩን ስትሰማ በተቀመጠችበት ሰውነቷ ሲንቀጠቀጥና የልብ ምቷ ሲጨምር ታወቃት…

‹‹ትናፍቀኛለች ነው ያልከው…..ግራ አጋቢ ነገር ነው››ይብልጥ እንዲያወራ የሚያበረታታ ዓ.ነገር ጣል አደረገች፡፡

‹‹ግራ አትጋቢ…አብራራልሻለሁ …ቆይ እንደውም…››አለና ኪሱ ገባና የገንዘብ ቦርሳውን አወጣ ….ምን ሊያደርግ ነው ብላ ስትጠብቅ….ከፈተውን አንድ ጉርድ ፎቶ አወጣና አቀበላት…‹‹አየሻት…በፀሎት ማለት ይህቺ ነች…››ብሎ መች እንደተነሳች የማታውቀውን የገዛ ፎቶዋን እጇ ላይ አስቀመጠላት…ለተወሰነ ጊዜ ድንዝዝ አለች፡፡

‹‹ፎቶዬን እንዴት…..?››

‹‹ምን አልሺኝ?››

በመዘባረቋ ደንግጣ‹‹ማለቴ ..የልጅቷን ፎቶ አንተ ጋር ምን ይሰራል….?››

‹‹…ስለምትናፍቀኝ አልኩሽ እኮ…እርግጥ ቀጥታ እሷ አይደለም የምትናፍቀኝ ….እህቴ በሬዱ ነች…አወሳሰብኩብሽ አይደል፡፡ታላቅ እህቴ በሬድ ከሁለት አመት በፊት ነው በአደጋ ምክንያት የሞተችው…ታላቄ ነበረች..የሁለት አመት ታላቄ..የቤቱ እጅግ ተወዳጅ ልጅ ነበረች….ባንክ   ነበር   የምትሰራው…የቤታችንን   ወጪ   ግማሹን   እሷ   ነበረች
የምትሸፍነው…ግን ድንገተኛ የመኪና አደጋ ደረሰባትና ሆስፒታል ገባች፣የዛን ጊዜ እኔ የነበፀሎት ቆርቆሮ ፋብሪካ ነበር የምሰራው….እና እህቴ ክሪትካል ኬዝ ላይ ደረሰችና ጭንቅላቷ በጣም ተጎድቷ ስለነበረ ወደውጭ ሄዳ ብትታከም ጥሩ እንደሆነ ሀኪሞቹ ምክር ሰጡ ..እኛ አቅማችን አይችልም ነበር…በአጋጣሚ በዛን ጊዜ በፀሎት የልብ በሽታዋ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ወደውጭ ለህክምና ለመሄድ ዝግጅት ላይ ነበረች…እኔ እህቴን ለማሳከሚያ የእርዳታ ብር ለመሰብሰብ እላይ እታች በመሯሯጥ ላይ ነበርኩ ….ከመስሪያ ቤት ሰራተኞች እየተሰበሰበ ሳለ አቶ ኃይለመለኮት ድንገት ፋብሪካውን ለመጎብኘት ይመጣሉ..እና እያለቀስኩ እርዳታ ከሰራተኞች ስሰበስብ አይተውኝ ወደመኪናቸው ይዘውኝ ገቡና ምን እንደሆንኩ ጠየቁኝ…እያለቀስኩ በቤተሰባችን የደረሰውን መከራ ነገርኮቸው………

‹‹በቃ እርዳታ መሰብሰቡን አቁም እኔ እህትህን አሳክምልሀለው››አሉኝ በፍፅም እውነት አልመሰለኝም ነበር…ግን ከምራቸው ነበር..‹‹ከአስር ቀን በኋላ ልጄን ለልብ ህክምና ወደታይላንድ ይዤት ስለምሄድ እህትህንም እዛ ሔዳ መታከም ትችላለች..የህክምና ማስረጃውን ጨርሱ የጉዞ ሰነድችን የእኔ ሰዎች ያመቻቻሉ››ብለው አስፈነጠዙኝ፡፡
ቃላቸውን ጠብቀው እህቴን ከአባቴ እና ከገዛ ልጃቸው ጋር ይዘው ታይላንድ ሄዱ…እህቴ ታይላንድ በገባች በአስራ ሶስተኛው ቀን ህይወቷ አረፈ….….በዛን ጊዜ ደግሞ በተመሳሳይ ቀን የፀሎት ልቧ ፌል አድርጎ በህይትና በሞት መካከል ስታጣጥር ነበረ…ብቻ ፕሮሰሱ ብዙ ነው…በስተመጨረሻ አባቴ ልጄ ሙሉ በሙሉ እንዳትሞት ልቧን መለገስ እፈልጋለው አለና ፍቃደኛ ሆኖ እዛው የእህቴ የበሬድ ልብ ለበፀሎት ተገጠመላትና..አባቴ የእህቴን ሬሳ ጭኖ መጣ እልሻለው፡፡፡››
‹‹በጣም የሚገርም ልብ ሰባሪ ታሪክ ነው የነገርከኝ››

‹‹አዎ በጣም ልብ ሰባሪ ነው…አይገርምም የአንዱ ቤት ደስታ በሌላው ቤት ሀዘን ላይ መብቀሉ…አንዱ እንዲስቅ ሌላው ማልቀስ አለበት…ህይወት እንዲህ ኢፍትሀዊ መሆኗን ከዛ በፊት አላውቅም ነበር››

‹‹በቃ አትበሳጭ ..እናውራ ብዬ ..አስደበርኩህ አይደል?››

‹‹አረ በፍጽም..››ብሎ ሊያብራራት ሲል የሰርቢሱ በራፍ ተከፈተ… ሁለቱ ፊታቸውን ሲያዞር አቶ ለሜቻ ነበሩ፡፡

‹‹እንዴ ልጄ አመመሽ እንዴ… ?ፊራኦል ለምን ሳትቀሰቀኝ?››ልጃቸውን ተቆጡት

‹‹አይ አባዬ …አላመማትም..እንቅልፍ እምቢ ሳላላትና እቤቱ ስለሞቃት ነው ውጭ የወጣነው፡፡››

‹‹አዎ አበባ ..ደህና ነኝ…እንቅልፍ እምቢ ስላለኝ ነው፡፡››እንዳላመማት አረጋገጠችላቸው፡፡

ስሯ ቀረቡና ከጀርባዋ ቆመው ግንባሯን እያሻሹ..‹‹ልጄ …ሀሳብ ስታበዢ እኮ ነው እንቅልፍ የሚነሳሽ…..ከህመምሽ በፍጥነት ለማገገም ደግሞ የምግብን ያህል እንቅልፍም ወሳኝ ነገር ነው….አይዞሽ አልኩሽ እኮ..እኔ አባትሽ እያለሁልሽ ምንም አትሆኚ… በዛ ላይ እሱም ወንድምሽ..ለሊሴም እህትሽ ነች..፡፡.››

አትሮኖስ

31 Oct, 17:00


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

አንድ ሰዓት የቤቱ ሰው ሁሉ ተሰብስቦ ጠባቧን ሳሎን ሞሏት…መጨረሻ ላይ የመጣው ፊራኦል ነበር…በእጁ አንድ ኪሎ ሙዝ ይዞ ነበር፡፡
ለሊሴ ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ ተነስታ ከእጁ መንጭቃ ተቀበለችው እና‹‹..ወንድሜ ሙዝ ገዛኸልኝ….!!! ደሞዝ ደረሰ እንዴ?››ስትል በፈገግታ ተሞልታ ጠየቀችው፡፡

‹‹አይ እንደምታውቂው ቀኑ ገና 18 ነው….በ18 ደግሞ ደሞዝ የለም…ስለዚህ ሙዙ ላንቺ አይደለም››ሲል መለሰላት፡፡

ለሊሴ ግራ ገብቷት‹‹ እና››ስትል አይኖቾን በማፍጠጥ ጠየቀችው፡፡
‹‹ለበሽተኛዋ ማለቴ… ለእንግዳዋ ነው››ሲል ያልጠበቀችውን መልስ ሰጣት፡፡

‹‹እ ነው…እሺ…››አለችና ፔስታሉን ወደበፀሎት ወስዳ ስሯ አስቀመጠችላት…፡፡

በሳቅና በጫወታ በደመቀ ምሽታ እራት ተበላ… ቡና ተፈልቶ ተጠጣ….ከጓዲያ የተጠቀለለ የጥጥ ፍራሽ ወጣና ወንበሮቹ ተሰብስበው ከእሷ ጎን ተነጠፈ…ለሊሴ ከጎኗ በተነጠፈው የጥጥ ፍራሽ ላይ ስትተኛ ፊራኦል ደግሞ ከእነሱ ራቅ ብሎ ግድግዳውን ተደግፎ ካለ አሮጌ ሶፋ ላይ አንድ አልጋ ልብስ ተከናንቦ ተኛ…
‹‹ለሊሴ ታዲያ ስትበራገጂ እግሯን እንድትነኪባት››

‹‹አረ አታስቢ እማዬ …እጠነቀቃለሁ፡፡››

ለሊሴ በፀሎትን ‹‹ለሊት የሆነ ነገር ከፈለግሽ ቀስቅሺኝ››አለችትና የለበሰችውን አልጋ ልብስ ተከናነበች፡፡

‹‹እሺ ቀሰቅስሻለሁ..ደህና እደሩ ››ስትል መለሰች፡፡
‹‹ደህና እደሪ….ወንድሜ ደህና እደር››

‹‹ምኑን ደህና አደርኩት ….ዛሬ ደግሞ ምን አልባት ሴኖ ትራክ ይሆናል ቤታችን ላይ የሚወጣው…. ››

‹‹ወንድሜ ደግሞ.. አሽሙራም ነገር ነህ››
‹‹እሺ መብራቱን ላጥፋው?››ፊራኦል ጠየቀ፡፡

‹‹አጥፋው››በፀሎት መለሰች፡፡

መብራቱ ጠፋ፡፡ ፀጥታ ሰፈነ፡፡ ሁሉም ፀጥ ያለና በእንቅልፍ የተዋጠ ይመስል ነበር..በፀሎት ግን ፈፅሞ እንቅልፍ ሊወስዳት አልቻለም...ጨለማው ውስጥ አይኗን አፍጥጣ በጭንቀት እያሰላሰለች ነበር..ይሄኔ የአባቷ ቅጥረኞች ድፍን አዲስ አበባን እየገለባበጦት እንደሚሆን እርግጠኛ ነች..

‹‹የፈለገ ቢገለባብጡ የፈለገ ያህል ቢሞክሩ አያገኙኝም….››ስትል እርግጠኛ ሆነች፡፡ስልኳን ከቤት ይዛ አለመውጣቷ አሁን ነው ያስደሰታት….እንደዛ ባታደርግ ኖሮ ያንን ተከትለው ያለችበትን ለማግኘት ይሞክሩ ነበር አሁን ግ ምንም እድል የላቸውም…አዎ አሁን ባልና ሚስቶቹ እየተናቆሩም ቢሆን እሷን በመፈለጉ አንድ ላይ ለማውራትና ለመተባበር ይገደዳሉ…ምን  አልባትም  ወደቀልባቸው  እንዲመለሱ  ምክንያት  ሊሆናቸው  ይችል
ይሆናል… ይሄ የእሷ ምኞት ነው፡፡ካለበለዚያም ይለይላቸውና እርስ በርስ ይገዳደሉ ይሆናል፡፡ ‹‹እንደዛ ከሆነ እስከወዲያኛው እገላገላቸዋለው››አለችና በረጅሙ ተነፈሰች፡፡ እንዲሁ ስትገላበጥና ስትተክዝ እኩለ ለሊት ሆነ፡፡ በአእምሮዋ የሚጉላላው ሀሳብ ብቻ አይደለም እቅልፍ የነሳት… የእግሯም ጥዝጣዜ ጭምር ነው ፡፡በዛ ላይ ሽንቷን ወጥሯታል….‹‹እንዴት ነው የማደርገው.?››ስትል እራሷን ጠየቀች፡፡.እንደምንም ተቆጣጥራው እስከንጊት ለማቆየት ብትጥርም አልቻለችም..አምልጧት ከመዋረዷ በፊት ከጎኗ ድብን ያለ እንቅል የተኛችውን ሊሊሴን መጣራት ጀመረች‹፡፡

‹‹ሌሊሴ….ሌሊሴ››
ያልጠበቀችው ሻካራ ድምጽ መልስ ሰጣት..‹‹አትልፊ እህቴን እንኳን በጥሪ በመድፍም ልትቀሰቅሻት አትችይም››
ግራ ተጋብታ ምን እንደምትመልስ እያሰላሰለች ሳለ መብርቱ በራ…በቁምጣና በጃፖኒ ቲሸርት ውጥርጥር ያለ ሰውነቱን በከፊል አጋልጦ ካለችበት በሶስት እርምጃ ርቀት ቆሟል…

‹‹ምን ልስጥሽ?››ሲል ጠየቃት

‹‹አይ..ሽንት ቤት መሄድ ፈልጌ ነበር››ፈራ ተባ እያለች መለሰችለት፡፡

‹‹ምን ፖፖ ላምጣልሽ?››
ፖፖ ቢያመጣላት እዚህ እፍንፍን ያለ ቤት ይሄ ሁሉ ሰው ባለበት እንዴት አድርጋ እንደምትሸና አሰበችና‹‹ አይ ሽንት ቤት ነው መሄድ የፈለኩት›› በማለት መለሰችለት፡፡

‹‹እንግዲያው እሺ›› አለና ወደበራፍ በመሄድ የተቀረቀረውን በራፍ ወለል አድርጎ ከፈተና ተመልሶ ወደእሷ መጣ …ምን ሊያደርግ ነው ብላ አፍጥጣ እያየችው ሳለ በርከክ ብሎ ስሯ ተቀመጠና የለበሰችውን ብርድ ልብስ ከላዮ ላይ ገፈፈ፡፡ እጆችን በትከሻዋና በእጆቾ መካከል አሰቅስቆ አስገባ..

‹‹ምን እያደረክ ነው?››ግራ በተጋባ ድምፅ ጠየቀችው፡፡

‹‹መቼስ እንዲህ ተሰባብረሽ ልራመድ አትይም….እንደፈረደብኝ አቅፌ ሽንት ቤት እየወሰድኩሽ ነው››

‹‹አረ ተው ..እነጋሼ ብያዩን ምን ይሉናል?››
‹‹አይዞሽ እነጋሼ ልጃቸው ምን አይነት ልጅ እንደሆነና እንዴት አድርገው እንዳሳደጉት ስለሚያውቁ ምንም አይሉም…..ምን አልባት ግን ይመርቁኝ ይሆናል››አለና አንከብክቦ አቅፎ ከቤት ይዟት ወጣ፡፡የልጁ ድርጊት ፍጽም ያልጠበቀችው ስለሆን በጣም ነው የተደመመችው፡፡

እንደተሸከማት ከሰርቢስ ቤቱ ጫፍ በኩል ክፍቱን ካለ አንድ ክፍል ወስዶ ወደውስጥ ደፉን አሳለፈና ደግፎ አቆማት…ከዛ ቀኝ እጁን ዘረጋና በቀይ የኤሌክትርክ ገመድ ጫፍ ላይ የተንጠለጠለውን ማብሪያ ማጥፊያ ሲጫናው የሽንት ቤቱ መብራት ቦግ ብሎ በራና በክፍሉና በአካባቢው ያለው እይታ ወለል ብሎ አንዲታየ አደረገ …
ደረቱ ላይ ተደግፋ እንደቆመች ሽንት ቤቱን ቃኘችው..ስፋቱ ሁለት ካሬ እንኳን አይሞላም
…በዛ ላይ ከለመደችው አይነት መፀዳጃ ቤት ፍፅም የተለየና የማይነፃፀር አይነት ነው….ይህን መሰል አይነት ሽንት ቤት በምስል አንኳን አይታው የማታውቀው አይነት ነው፡፡እርግጥ ፅዳቱ የተጠበቀ በመሆን ዝግንን የሚል የመቅፈፍ አይነት ስሜት እንዲሰማት የሚያደርግ አይነት አይደለም…ቢሆንም በምቾት ዘና ብላ የምትቀመጥበት አይነት አይደለም…‹‹በቃ እንደምንም ግድግዳውን ተደግፈሽ ቁሚ..››ትዕዛዙን ስትሰማ እንደምንም የተበታተነ ሀሳቧን ሰበሰበች፡፡

እስከአሁን ደረቱን ተደግፋ መቆሟን ትዝ ሲላት እንደመደንገጥ አለችና ግራና ቀኝ እጇን የሽንት ቤቱን በራፍ ግራና ቀኝ ጉበን ይዛ ቆመች…ትቷት ወደኃላ ሸሸና መራመድ ሲጀምር
በመደንገጥና በመገረም ስሜት‹‹እንዴ? ጥለኸኝ ልትሄድ እንዳይሆን?››ስትል ጠየቀችው፡፡
እርምጃውን ሳያቋርጥ ‹‹መጣሁ..››አለና ከበራፉ አካባቢ አንድ ባዶ ሀይላንድ ላስቲክ ይዞ ወደ ቧንቧው በመሄድ ውሀ ቀድቶ ከሞላበት በኃላ ..ወደእሷ ተመለሰና እጁን አንጠራርቶ ከሽንት ቤቱ ቀዳዳ አጠገብ አስቀመጠላትና …‹‹..ግቢና እንደምንም ተቀመጪ››አላት፡፡
ወደውስጥ ዘልቃ ገባች‹‹በራፍ የለውም እንዴ?››ሌላ ያስጨነቃትን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹አይዞሽ….ምንም አትሆኚም››አለና ወደላይ ተሰብስቦ የተጠቀለለ ጨርቅ ነገር አላቀቀና እንደመጋራጃ ወደታች ለቆ ጋረደላት…..የእግሯን ጥዝጣዞ እንደምንም ችላ በአንድ አይኗ አጨንቁራ በማየትና ነገሮችን በመቆጣጠር እደምንም ተቀምጣ ለመተንፈስ ቻለች..ጨርሳ ስትወጣ ተንደርድሮ ከበራፍ ተቀበላትን ሰቅስቆ አቀፋት፡፡

‹‹ካላስቸገርኩህ ጨረቃዋ ደስ ትላለች ..ትንሽ ውጭ መቀመጥ እንችላለን?››ስትል በልመና ቃና ጠየቀችው፡፡
‹‹እንደፈለግሽ.. ››አለና ግድግዳውን አስደግፎ አቆማትና ትቷት ወደውስጥ ሊገባ መራመድ ጀመረ…
‹‹እንዴ ብቻዬን ልቆይ እኮ አይደለም ያልኩህ ..አንተ ምትገባ ከሆነማ እኔ ብቻዬን ፈራለሁ››

‹‹በለሊት ሞተር ስትጋልቢ እንዴት ሳትፈሪ…?ለማንኛውም ወንበር ላመጣልሽ ነው››አለና ወደቤት ገባና አንድ ባለመደገፊያ ወንበር በማምጣት አደላድሎ ወስዶ አስቀመጣትና ከጎኗ ጠፍጣፋ ድንጋይ አስቀምጦ ተቀመጠ፡፡

አትሮኖስ

31 Oct, 06:26


ከሰማይ ጋር እኩል ሳቅን
ያቺን ምድር አሳቀቅን
ልምዷ ሆኖ ከንባ ማውጋት
ባትችልበት ፈገግ ማለት
ቀንታ ብትስቅ እንዴው ድንገት ...
ፈገግ አልን እንደ ዘበት
እቴ እሷ ....
እንኳን ልትስቅ
አለች ስቅቅ
ምን ተሻለት
ሰላም ጠፍቷት
አይዞሽ በቃ
የፈጠረን እስኪል በቃ

🔘🖋ሄለን ፋንታሁን🔘

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

31 Oct, 06:15


#አሁንስ_አበደናል


ያኔ ድሮ ድሮ እያለን ጤነኛ
ከመታመማችን በፊት ሆነን ለኛው ለኛ
አንዱ ላንዱ ያለምንም ክፋት ነበረ ዘበኛ
ማቀፍ መሳም እንጂ አልነበር ምቀኛ ዘረኛ
ከውጪ ለመጣ ወራሪ ቀማኛ
በዘር በሀይማኖ ሳይለዩ በጉሳ
ለእናት ሀገራቸው ነበሩ ዘበኛ ያቆዩለን ለኛ
፧፧፧
ካለው ላይ አካፈሎ የራበውን አጉራሽ
    ለበረደው አልባሽ
        ችግርንም ታጋሽ
            ሌላውን አስታዋሽ
                ነበረ ለሌላው ሂወቱንም ለጋሽ
         ፧፧፧፧፧፧               
     አሁን ግን ቀረና
      ያሁሉ ጠፋና
      ሆነናል ደመኛ

አሁንስ አበደናል
   ፧፧፧፧፧
ለሰው ደግ ማሰብ ቅንነት ረስተናል
ከአፈር ተፈጠረን አፈር ለሚበላን ማሰብ አቅቶናል
ልክ እንድ እንስሳ ማስብ ጀምረናል
አውሬም ሆነናል

ጭካኔ ለመደናል
ከመልመድም አለፈን አስተማሪ ሆነናል
ሴጣን እንኮዋን ሳይቀር በኛላይ ቀንቶዋል

      አብደናል

          ደምን የሚጠጣ
          ሰላም አንድነትን ፍቅር የሚጠላ
          ያኔ ሴጣን ነበር
          ያኔ ጀዳል ነበር ለዚ የሚጓጓ
                   .
                   .
ቁራን ይቀራልን
ጸበሉ ይመጣልን
የፈጣሪ ቁጣ ከላይ ሳይወርድብን
ቆረጠን እንጣለው ልክ እንደድሮዋችን
፧፧
👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

30 Oct, 19:03


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፡ ፡ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ለመጀመሪያ ጊዜ የቀኝ እጇ የመሀል ጣት ተነቃነቀ…እቤቱ ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ በደስታ ፈገገ ..ከአስር ደቂቃ በኋላ አይኖቾ ተከፈቱ፣አራቱም የቤቱ አባላት የተኛችበትን ፍራሽ በሁሉም አቅጣጫ ከበው በፈገግታ ያዩት ጀመር….ግራ ገባት፡፡መልሳ አይኖቾን…»

አትሮኖስ

30 Oct, 17:37


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ለመጀመሪያ ጊዜ የቀኝ እጇ የመሀል ጣት ተነቃነቀ…እቤቱ ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ በደስታ ፈገገ ..ከአስር ደቂቃ በኋላ አይኖቾ ተከፈቱ፣አራቱም የቤቱ አባላት የተኛችበትን ፍራሽ በሁሉም አቅጣጫ ከበው በፈገግታ ያዩት ጀመር….ግራ ገባት፡፡መልሳ አይኖቾን ጨፈነች…፡፡መንቃቷ እራሱ የእውነት ሳይሆን በህልም አለም ውስጥ የተፈጠረ መንቃት ነው የመሰላት ፡፡ለዛ ነው ዳግመኛ እይኖቾን የጨፈነችው..፡፡መልሳ ስትገልጥ ያየችው ተመሳሳይ ነገር ነው….አራት ወዛቸው የተመጠጠ የለበሱት ልብስ የነታተበ ..በአባቷ ግቢ ውስጥ አትክልቶችን ከሚንከባከቡ ሰራተኞች በላይ ኑሮ የጠበሳቸው ጠና ያሉ ሰውዬ…ቆዳቸው የተሸበሸበ እናት… የ ሀያ አመት ልጅ እግር የምታምር ግን ደግሞ ያልተመቻት ልጃገረዶች..ባለጡንቻ ፈርጣማ እና ባለኮስታራ ፊት ሀያ አምስት ወይም ስድስት የሚሆነው ወጣት ..ጭስ የጠጣና ያረጀ የማዳበሩያ ኮርኒስ ያለው ጠባብ ክፍል…መሬት ላይ የተነጠፈ ፍራሽና ያረጀ በህይወቷ እንኳን ለብሳው አይታው የማታውቀው አይነት ብርድ ልብስ ለብሳ ነበር እራሷን ያገኘችው፡፡ግን እንደዛም ሆኖ የተለየ እና የማታውቀው ቦታ ያለች መስሎ አልተሰማትም….የሆነ ከዘመናት በፊት ታውቀው የነበረ እና ስትናፍቀው የቆየችው ቦታ ተመልሳ እንደመጣች አይነት ስሜት ነው እየተሰማት ያለው

‹‹…የት ነኝ?››

‹‹ልጄ…አሁን ሰላም ነሽ …ትንሽ አደጋ ደርሶብሽ ነው?››

‹‹የምን አደጋ?››

‹‹አሁን ሰላም ነሽ..በውድቅት ለሊት ሞተር ስትነጂ ነበር…ተገልብጠሸ ነው፡፡››

‹‹ሞተር››

‹‹አዎ..ሞተር..ከማን ስትሸሺ ነበር….?እስከአሁን ለፖሊስ አላሳወቅንም…..ይሄውሽ እኔና ቤተሰቦቼ በህይወት ፈተና ጋር ግብግብ ገጥመን በትግል የምንኖር ሰዎች ነን…ከሆነ ወንጀል ጋር የተያያዘ ታሪክ ካለሽ እባክሽ.እኛንም ጣጣ ውስጥ እንዳንገባ ከአሁኑ ንገሪን››ሲል ፊራኦል ተናገረ፡፡

‹‹ምነካህ ልጄ? ልጅቷ ገና አሁን መንቃቷ ነው…ተው እንጂ ነውር ነው›እናትዬው ገሰፁት..አባትዬውም ለባለቤታቸው ድጋፍ በመስጠት‹‹ልጄ አዎ..አሁን ዋናው ያንቺ መትረፍ ነው ፡፡ሌላውን ቀላል ነው…የሰው ልጅ በህይወት ካለ የማያልፈው መከራ የማያሸነፍው የህይወት ትግል የለም..አሁን አንቺ ምንም አታስቢ..እኔነኝ የተባለ ውጌሻ ጠርቼያለሁ፡፡ ወለምታ ወይም ስብራት ነገር ካለሽ ያዩልሻል…ከዛ ካገገምሽ በኋላ ለቤተሰቦችሽ እንደውልላቸውና መጥተው ይወስዱሻል››
በፀሎት ለሊት በውድቅት ለሊት ከቤቷ አምልጣ እንዴት እንደወጣችና ምን እንዳደረገችና አሁን ያለችበት ቤትም የእነማን እንደሆነ ትዝ እያላት ሲመጣ ….የመረጋገትና የደስታ ስሜት ተሰማት

‹‹አመሰግናለሁ…ምንም ወንጀል አልሰራሁም….ፖሊስም እየፈለገኝ አይደለም…አሁን ደክሞኛል ልተኛ..››አለችና መልሳ አይኖቾን ጨፈነች፡፡

‹‹ሰማችሁ አይደል..ምንም ወንጀል አልሰራሁም ብላለች..አሁን ዞር በሉላት …ትንፋሻችሁ እራሱ በሽታ ነው የሚሆናባት››አባትዬው ተቆጡ፡፡

‹‹አባዬ ደግሞ ፣አንተ ሁል ጊዜ ሰው እንዳመንክ ነው.. ሚገርመው ደግሞ ሰዎች ቃላቸውን እያጠፉ አንተን ማሳዘናቸውን አያቆሙም… አንተም ደግሞ ደግመህ ደጋግመህ እነሱን ማመንህን አታቆምም››ፊራኦል ተነጫነጨ፡፡

‹‹ልጄ ገለባ ቢዘሩት አይበቅልም ተጠራጣሪ ሰው አይፀድቅም ይባላል..ያገኘሁትን ሰው ሁሉ በመጠራጠር ህይወቴን ሳሰቃይ ከመኖር እያመንኩ ብከዳ ይሻለኛል…ቢያንስ በማመኔ ምክንያት የሚደርስብኝ ችግር ምክንያቱ እኔ አይደለሁም..››
ፊራኦል በወላጆቹ ውሳኔ ባለመስማማት ‹‹በሉ እሺ እኔ ወደ ስራ ሄጃለሁ፡፡››በማለት ቤተሰቡን ተሰናብቶ ግቢውን ለቆ ሲወጣ በራፍ ላይ ውጌሻዋ ወደውስጥ ስትገባ ተላለፉ፡፡

‹‹ቤቶች አቶ ለሜቻ››ሁሉም ግር ብለው ወጥተው ውጌሻዋን ተቀበሉና ወደውስጥ አስገቧት፡፡

‹‹የትኛው ልጅህ ነች… ለሜቻ?››
‹‹የወንድሜ ልጅ ነች ከድሬደዋ ልትጠይቀኝ መጥታ ነው››

‹‹እና ምን ገጥሟት ነው?››

‹‹ባኮት ከሆነ የሰፈር ልጅ ጋር ሞተር ተፈናጣ ስትሄድ ሞተሩ ተገለበጠባቸውና ትንሽ ተጎዳች..ምን አልባት ስብራት ወይም ወለምታ ይኖራት እንደሆነ ብለን ስለተጠራጠርን ነው ያስቸገርኖት፡፡››

በፀሎት የሚነጋገሩትን ሁሉ አይኖቾን ጨፍና እየሰማች ነው…

‹‹ታዲያ ተኝታለች?››
‹‹አሁን ነቅታ ነበር…እንዴት ነው እንቀስቅሳት?››ወ.ሮ እልፍነሽ ጠየቁ፡፡

‹‹አይ ቆይ ተዋት ..ህመሙ እራሱ ይቀሰቅሳታል፡፡››አሉና ስሯ ፍራሽ ላይ ተቀመጡ…

‹‹ እስቲ እሱን የከሰል ፍም አቅርቡልኝ››ትዕዛዝ ሰጡ፡፡
ማንደጃው ቀረበላቸው…‹‹ እስኪ አንዳችሁ ኑና የለበሰችውን ልብሷን አውልቁላት…..››ለሊሴ ፈጠን ብላ መጣችና ከላይ የለበሳቸውን ጃኬት… ቦዲ ተራ በተራ አወለቀችላት… በጡት ማስያዣ ብቻ አስቀረቻት ፡፡አንገቷ ላይ ያለው የእጅ መዳፍ የሚያህል አብረቅራቂ እንቁ ፈርጥ ያለበት ጌጥ የሁሉንም አይን በቅፅበት ተቆጣጠረ
….ጆሮዋ ላይም ያንጠለጠለችው የጆሮ ጌጥ ከአንገት ሀብሏ ጋር እንዲናበብ ተደርጎ የተሰራ ለልደት በዓሏ ከአባቷ የተበረከተላት ልዩ አይነት ጌጥ ስለሆን በተለይ የሌሊሳን ትኩረት በደንብ ነው የተቆጣጠረው…ሁሉም ግን አርቴ እንጂ ትክክለኛ ነው ብለው አላሰቡም ነበር፡፡
ውጌሻዋ ቦርሳቸው ውስጥ እጃቸውን ሰደዱና በብልቃጥ ከለጋ ቅቤ ጋር ተለውሶ የተዘጋጀ መዳህኒታቸውን አወጡና ፊት ለፊታቸው አስቀምጠው በሌባ ጣታቸው ዛቅ እያደረጉና በመሀል አጣታቸው ላይ አድርገው በመላ መዳፋቸው ላይ ለቀለቁና ስራቸው በቀረበላቸው የከስል ፍም ላይ ጠጋ አድርገው ሙቀት እንዲያገኝ ካደረጉ በኃላ ከአንገቷ ጀምሮ ትከሻዋን እያሹ መፈተሽ ጀመሩ‹‹ ..ምንም አልሆነችም እስኪ ሱሪዋን አውልቁልኝ››ሌላ ትዕዛዝ ሰጡ..በዚህ ጊዜ አቶ ለሜቻ ከተቀመጡበት ተነሱና ወደውጭ ወጡ..ሴቶቹ እንደምንም

ታጋግዘው የለበሰችውን ጅንስ ሱሪ ከላዮ ላይ አወለቁና በፓንት ብቻ ለውጌሻዋ አስረከቧት
…ውጌሻዋ ተመሳሳዩን እሽት ከጭኖቾ ጀመረው ወደታች መውረድ ጀመሩ…ቀኝ እግሯ ቁርጭምጭሚቷ ጋር ደርሰው ጨበጥ..ጨበጥ ሲያደርጓት ግን ከተኛችበት እንደመብረቅ አጓርታ ተነስታ ቁጭ አለች…ሁሉም በድንጋጤ የሚያደርጉት ጠፋቸው..‹‹አዎ እዚህ ጋር ችግር አለ‹‹አሁን በደንብ አድርጋችሁ ግራና ቀኝ ትከሻዋን ያዟት፡፡››የውጌሻዋን ትዕዛዝ ስትሰማ አይኖቾ በፍራቻ ተጉረጠረጠ፡፡በእድሜዋ መርፌ ለመወጋት እሩሱ በስንት እዝጊዎታና ማባበያ ነው...ታዲያ አሁን እንዲህ ላይቨ በስቃይ ስትፈተን እንባዋ ረገፈ
፡፡እናትና ልጅ ግራና ቀኛ ትከሻዋን አጥብቀው እንዳትነቃነቅ ያዙዋት..ሴትዬዋ እየጨመቁና እያሽከረከሩ ያሾት ጀመር…በህይወቷ ተስምቷት የማያውቀው አይነት ህመም…..ተሰማት..የሆነ መጋዝ ጥርስ ያለው አዞ በሁለት መንጋጋዎች መሀከል እግሮቾን አስገብቶ እያኘካት ነው የመሰላት..እንባዋ ብቻ ሳይሆን ንፍጦም በአፍንጫ ላይ እየተዝረከረከ እንደሆነ ይታወቃታል…ለዛ ግን የምትጨነቅበት ሁኔታ ላይ አይደለችም…..ውጌሻዋ ከ10 ደቂቃ በኃላ የተሰበረውን አጥንት ወደቦታው ከመለሱ በኃላ እንዳይነቃነቅ በቀርከሃ በደንብ አድርገው ካሰሩት በኋላ በፋሻ ጠቅልለው አጠናቀቁ…ከዛ እቃቸውን ሰብስባው ተነሱ…ለሊሴ የራሷን ቢጃማ አለበሰችትና መልሰው አስተኞት፡፡

‹‹እልፍነሽ››

‹‹አቤት እማማ››
‹‹ለሜቻ ድሬደዋ ሀብታም ወንድም አለው እንዴ?››

ወ.ሮ እልፍነሽ ጥያቄው መደናገር ውስጥ አስገባቸው‹‹ለምን ጠየቁኝ?››

አትሮኖስ

30 Oct, 17:37


‹‹አይ እንዲሁ ነው..ይህቺ የወንድሙ ልጅ እጅግ የሀብታም ልጅ እንደሆነች ያስታውቃል››

‹‹እንዴት ነው
ሚያስታውቀው…?

ያደረገችውን ልብስና የደረገችውን አርቴፊሻል ጌጥ ተመልክተው ነው?››
‹‹አይ ፍፅም እነሱን አይቼ አይደለም…ሰውነቷን አይቼ ነው…ልስላሴው እኮ ከሀር ጨርቅ በላይ ነው…..እጅግ ቅንጡ አስተዳደግ ያደገች የንጉስ ልጅ ነው የምትመስለው…አዎ በደንብ ያስታውቃል፡፡››አሉ እርግጠኛ በመሆን፡፡
ወ.ሮ እልፍነሽ‹‹ይሆናል››ብለው በድፍኑ መልስ ሰጡ፡፡

‹‹እንግዲ..ከሶስት ቀን በኃላ መጥቼ አያታለው…ሾርባ ነገር እያደረጋችሁ በደንብ ተንከባከቧት …ትድናለች……በሉ›› ብለው ሲወጡ አቶ ለሜቻ ወደውስጥ ገቡና ወደባለቤታቸው በመቅረብ….‹‹የእኔ አለም….ለውጌሻዋ የሚከፈል ብር አለሽ አንዴ?››ሲሉ ልብን በሚሰረስር ትህትና ጠየቁ፡፡

‹‹ስንት ይሆን….?››

‹‹ሁለት መቶ ብር ነው..እኔ ጋር መቶ ብር አለ፡፡››

በፀሎት በወገባቸው ዙሪያ የተጠመጠመ መቀነታቸውን ሲፈቱ አጨንቁራ እያየቻቸው ነው..ከቋጠሮ ውስጥ ድፍን ሁለት መቶ ብር አወጡና ለባለቤታቸው ሰጦቸው….

‹‹መቶ ብሩን አትሰጪኝም…?››

‹‹ኪስህማ ባዶ መሆን የለበትም…ግድ የለህም ሂድ ውጌሻዋን ሸኛት ››
አቶ ለሜቻ የተሰጣቸውን ብር በእጃቸው እያሻሹ ወደ ውጭ ወጡ…ወ/ሮ እልፍነሽ ወደጓዲያ ገብና በጓድጓዳ ሰሀን ምግብ እና በብርጭቆ ውሀ ይዘው በመምጣት ስሯ ቁጭ አሉ ፡፡

የተኛች መስሎቸው ቀስ ብለው ትከሻዋን ያዙና ‹‹የእኔ ልጅ ..የእኔ ልጅ››ሲሉ ሊቀሰቅሷት ሞከሩ… ቀስ ብላ አይኗን ስትገልጥ እንጀራ የጠቀለለ እጃቸው አፏ አካባቢ ደርሶል….‹‹በ…ቃኝ…እማ….ማ››
‹‹አይ….በቃኝ አይሰራም…ካልበለሽ አትድኚም…እንደምንም ባይጣፍጥሽም ታግለሽ መብላት አለብሽ››ኮስተር አሉባት፡፡

አሳዘኗት…‹‹ቆይ ማንነቴን አያውቁ ለምንድነው እንዲህ እየረዱኝ ያሉት….?ነው ወይስ የልጃቸውን ልብ የተሸከምኩ መሆኔን ደመነፍሳቸው ነግሯቸው ይሆን?››መልስ በቀላሉ ልታገኝለት ያልቻለችው ጥያቄ እራሷን ጠየቀች፡፡
ለእሳቸው ስትል እንደምንም አፏ ከፈተች…አፏ ውስጥ ከተቱት…በመከራ አላመጠችና ዋጠች..እንቁላል ፍርፍር ነው…በመከራ አምስት ጉርሻ ያህል አጎረሶትና ወደላይ ደግፈው ውሀ እንድትጠጣ ካደረጉ በኃላ አስተኟት…፡፡ከዛ አቶ ለሜቻም ውጌሻዋን ሸኝተው ስለተመለሱ ለቤተሰቡ ጠቅላላ ቁርስ ቀረበና ተሰብስበው እየተጎራረሱ  ሲበሉ አየች….ያ ደግሞ ይበልጥ ስለወላጆቾ ቤት እንድታስብና ልቧ እንዲሰበር አደረገ ..ለእሷ እንቁልል ጠብሰው ያባሏት ሴትዬ ለቤተሰቡ ደረቅ ዳቦ በሻይ ነው ማቅረብ የቻሉት፡፡የገረማት ደግሞ እሱንም በፍቅር እየተሳሳቁ ይጎራረሳሉ፡፡

እሷ ቤት በየቀኑ ጠረጴዛ ሙሉ ለአይን እራሱ የሚያታክት ምግብ ይቀርባል፡፡ የሚበላው ግን አስር ፐርሰንትም አይሞላም…ከዛ የተረፈው ምን እንደሚደረግ አታውቅም..ምን አልባት እዛ ጊቢ ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች ይታደል ይሆናል… ወይም ደግሞ ተበላሽቶ ገንዳ ውስጥ ሊደፋም ይችል ይሆናል…..እዚህ ግን እቤቱ ያፈራውን ምርጥ ምግብ ለማያውቁት እንግዳ ሰው አብልተው እነሱ ደረቅ ዳቦ ይቆረጥማሉ..ለዛውም በጫወታ የደመቀ በደስታ የታጀበ ቁርስ ነው እየበሉ ያሉት…እነሱ ቤት ግን በኩርፊያ የታጀበ ቁርስ ነው የሚሆነው..ወሬ ካለውም በአሽሙርና በነቆራ የታጀበ በሚያስጠላ ጥል የሚገባደድ ነው የሚሆነው፡፡
ይበልጥ ሆድ ባሳት….‹‹በምንም አይነት ወደእዛ ቤት በቀላሉ አልመለስም››ለራሷ ዳግመኛ ቃል ገባችና አይኗን ጨፈነች..ደክሞት ስለነበረ ወዲያው ነበር ጭልጥ ያለ እንቅልፍ የወሰዳት፡፡

‹‹የእኔ ልጅ ተነሽ….›› የሚል ድምጽ ነበር ከእንቅልፏ ያባነናት..ምን ያህል እንደተኛች አታውቅም፡፡ ብቻ አይኖቾን ስትገልጥ ልክ እንደቅዱሙ ያች ደግ እናት ምግብ በሰሀን ይዛ ልክ እንደህፃን ልጅ ልታጎርሳት ስሯ ቁጭ ብላለች፡፡

‹‹እማማ…አራበኝም እኮ ..አሁን አይደል እንዴ የበላሁት?››
‹‹አይ አሁን እኮ ሰባት ሰዓት ሆኗል…አባትሽ ላንቺ ሲል ነው ስጋ ገዝቶ የመጣው… እኔ እናትሽ ደግሞ ቆንጆ አድርጌ ሰርቼሻለሁ››

‹‹በሰማችው ነገር አንባዋ በአይኗ ግጥም አለ….››
‹‹ነይ እስኪ ለሊሴ ትንሽ ቀና ትበል ትራስ ደርቢላት›ለሊሴ መጣችና ደግፋ ቀና አድርጋ ትራስ ደረበችላትና ወደቦታዋ ተመለሰች …ቡና እያፈላች ነው..አቶ ለሜቻ ከለሊሴ ፊት ለፊት ባለ ደረቅ ወንበር ላይ ቁጭ ብለው በፀጥታ እየተመለከቷት ነው፡፡

‹‹እንጀራውን ጠቅልለው ወደ አፏ ዘረጉት…አፏን ከፍታ ተቀበለቻቸው…አላምጣ ከወጣች በኃላ…

‹‹እናንተስ አትበሉም?››ስትል ጠየቀች፡፡

‹‹አዬ ልጄ …አኛማ በልተን ጨርሰን ቡና ስንጠብቅ አታይንም..አንቺ ብይ››አቶ ለሜቻ መለሱላት፡፡ወይዘሮ እልፍነሽ አብልተዋት ከጨረሱ በኃላ አቶ ለሜቻ ከተቀመጡበት ተነስተው ወደእሷ ተጠጉና ፍራሹ ጫፍ ላይ ተቀመጡ…የሆነ ነገር ሊጠይቋት እንደሆነ ገብቷት ዝግጁ ሆነች፡፡

‹‹ስምሽ ማነው ልጄ?››እስከአሁን ስሟን እና ማንናቷን እንኳን ሳያውቁ ይሄን ሁሉ እገዛና እንክብካቤ ሲያደርጉላት እንደቆዩ ስታስተውል ግርም አላት፡፡‹‹በፀሎት እባላለሁ››

‹‹እኔ አባትሽ..ለሜቻ እባላለሁ..እናትሽ ደግሞ እልፍነሽ ነው ስሟ….የመጀመሪያ ወንዱ ልጄ ፍራኦል..እሷ ደግሞ የእሱ ተከታይ ለሊሴ ትባላለች..፡፡››የቤተሰቡን አባላት ሁሉ በስማቸው እየጠሩ አንድ በአንድ አስተዋወቋት…በፅሞና እያዳመጠቻቸው መሆኑን ከተገነዘቡ በኃላ ንግግራቸውን አራዘሙ‹‹በእውነት በዛ ውድቅት ለሊት በዛ ሞተር ሆነሽ ከቤታችን ጋር ተጋጭተሸ ስትወድቂ በህይወት የምትተርፊ መስሎ አልተሰማኝም ነበር… ሁላችንም በጣም ፈርተን ነበር..ግን አምላክ ደግ ነው እና አጋልጦ አልሰጠንም…ተርፈሻል….ይመስገነው››
አሁን እሷቸው ሲናገሩ ሞተሩና ቦርሳዋ ትዝ አላት….ሞተሩ ምንም ቢሆን ግድ የላትም ቦርሳዋ ግን ያስፈልጋታል…
‹‹ወይኔ አባባ የሆነ ቦርሳ ይዤ ነበር …ጣልኩት እንዴ?››እሰከዛን ሰዓት ድረስ እንዴት ትዝ እንዳላላት ለራሷም ገረማት.፡፡፡

‹‹…አይ ልጄ አልጣልሺውም… ቦርሳውም ሞተሩም ጓዲያ ተቀምጦልሻል…ሞተሩን ወደውስጥ ያስገባነው ምን አልባት ችግር ላይ ሆነሽ ከፖሊስ እየሸሸሽ ወይም ከሆነ ሰው እየተደበቅሽ ከሆነ እንዳትጋለጪ ብለን ነው…››

‹‹አይ አባባ…እምልሎታለው የነገርኳችሁ እውነቴን ነው..ከፖሊስ ጋር የሚያገኛኘኝ ምን ነገር የለም…ከእንጀራ አባቴ ጋር ተጣልቼ ነበር …በለሊት ከቤት ወጥቼ በንዴት ስነዳ የነበረው››

‹‹አዎ እኔም ጠርጥሬለው…የቤተሰብ ችግር እንደሆነ ታውቆኝ ነበር››

‹‹ውይ ልጄ ይሄኔ እናትሽ በጭንቀት ልትፈነዳ ደርሳለች››ወ.ዘሮ እልፍነሽ በእናትነት አንጀታቸው የተሰማቸውን ተናገሩ ….ስለራሳቸው ልጆች እያሰቡ ስለነበር ነው ስሜቱ የተጋባባቸው፡፡
በፀሎት‹‹አይ እናቴ አትጨነቅም››ፍርጥም ብላ መለሰች፡፡

‹‹ምን ማለትሽ ነው ልጄ …?በጣም ነው እንጂ የምትጨነቀው..እናንተ ልጆች የእናትን አንጀት እስክትወልዱ ድረስ አይገባችሁም…ይሄኔ በየፖሊስ ጣቢያው እና በየሆስፒታሉ አንቺን ፍለጋ እየተንከራተተች ነው፡፡››ወ.ሮ እልፍነሽ ጠንካራ እምነታቸውን በድጋሜ ገለፁ፡፡

‹‹እይ እደዛ ማለቴ አይደለም ..እናቴ ከሁለት ወር በፊት ነው የሞተችው›››

‹‹ውይ ታዲያ እንጀራ አባትሽ እናት የሞተባትን ልጅ ምን አድርጊ ነው የሚልሽ….?ሌሎች እህትና ወንድም የለሽም›?›

‹‹የለኝም እኔ ብቻ ነኝ››
‹‹ታዲያ በውድቅት ለሊት ምን አጣላችሁ?››

አትሮኖስ

30 Oct, 17:37


​​ምትመልሰውን መልስ ማሰላሰል ጀመረች….በአእምሮዋ አስልታ ከመወሰኗ በፊት ከአንደበቷ ሾልኮ ወጣ…..‹‹ሰክሮ መጥቶ ሊደፍረኝ ሞከረ፡፡››ስትል አፈረጠችው፡፡፡
እቤቱ ሁሉ በድንጋጤ ፀጥ አለ….ሁለቱ አዛውንት ወላጆች ስቅጥጥ አላቸው፡፡እሷ እራሷ በተናገረችው ውሸት እራሷ ደነገጠች…በመደንገጧ ደግሞ የማተቆጣጠረው እንባ በጉንጮቾ ላይ እንዲረግፍ አደረገ…አቶ ለሜቻ በቀኝ ወይዘሮ እልፍነሽ በግራ አቅፈዋት እያሻት ያባብሏት ጀመር‹‹ልጄ አይዞሽ..ከዛሬ ጀምሮ እኔ እናትሽ ነኝ….እሷቸውም አባት ይሆንሻል፡፡››ቃል ኪዳን ገቡላት፡፡
‹‹በቃ ልጄ ምንም አታስቢ… እኛ ቤተሰቦች ነን…አሁን ሁሉን ነገር እርግፍ አድርገሽ እርሺና እራስሽን አስታሚ …በደንብ ከዳንሽ በኃላ ..የሚሆነውን እናደርጋለን.፡፡.ልትከሺውም ከፈለግሽ..ወይም ሌላ ነገር ካሰብሽ በማንኛውም ነገር ከጎንሽ ነን..አሁን ግን ስለምንም ነገር አትጨነቂ በሽታሽን ላይ ብቻ አተኩሪ …እንደምታይው ኑሮችን ደከም ያለ ነው …ትልቅ ሆስፒታል  ወስደን  ልናሳክምሽ  አንችልም….ግን  ደግሞ  ውጌሻው  የማያሽልሽ  ከሆነ የመንግስት ሆስፒታልም ቢሆን አመላልሰን እናሳክምሻለን..ምንም አታስቢ፡፡››የአቶ ለሜቻ ማበረታቻ ቃል ነበር፡፡
‹‹በጣም አመሰግናለው…..በእውነት በህይወቴ እንደእናንተ የወደደኝ ሰው የለም……ሰው ሰውን እንዲሁ በነፃ በዚህ መጠን መውደድ እንደሚችል አላውቅም ነበር…በጣም አመሰግናለው..››አለችና ሸርተት ብላ ተኛች…አይኗን ጨፈነች፡፡
ወ.ሮ እልፍነሽም‹‹ልጄ..ሲያዩሽ እኮ መልዐክ ነው የምትመስይው፡፡ አንቺን ምን አይነት ሰው ነው ላይወድሽ የሚችለው?››ብለው አልጋ ልብሱን ወደላይ ስበው አለበሶትና ከስሯ ዞር አሉ….

ስለዋሸቻቸው ፀፀታት..ግን ምርጫ የላትም..እንዲህ ካላደረገች ከቤተሰቦችሽ እናገናኝሽ ብለው ያስቸግሯታል..እሷ ደግሞ ወደእዛ ምድራዊ ሶኦል ወደሆነ ና ፍቅር ወደነጠፈበት ቤት እንዲ በቅርብና በቀላሉ የመመለስ ምንም አይነት እቅድ ያላትም….፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

28 Oct, 17:55


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አራት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


በፀሎት ከጠፋች ከአንድ ሰዓት በኃላ ነበር አባትዬው ዜናውን የሰሙት፡፡በመጀመሪያ የቤቱ ሰው ሁሉ ያሰበው የተለመደው የልብ በሽተዋ ተነስቷባት ተዝለፍልፋ የሆነ ቦታ ወድቃ ይሆናል ተብሎ ነበር ፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል ጋርዶቹ ፤ ዘበኞቹና አስተናጋጆቹ ሳይቀር የቤቱ ጥጋጥግ ከ50 በላይ ክፍሎች አንድ በአንድ እየከፈቱ አንድም ቦታ ሳይቀር ፈልገው ጅባት ካሉ በኃላ ነበር የጋርዶቹ ሀላቃ ፈራ ተባ እያለ የአቶ ኃይለመለኮትን መኝታ ቤት ያንኳኳው….በለሊት ልብሳቸው ሆነው የልጃቸውን የልደት በዓል ምክንያት በድካም የዛለ ሰውነታቸውን አልጋ ላይ አሳርፈው ገና እንቅልፍ እንዳሸለባቸው ነበር በራፋቸው የተንኳኳው…በመጀመሪያ በህልማቸው መስሏቸው ነበር፡፡ በኋላ ግን የምርም ክፍላቸው እየተንኳኳ መኆኑን ገባቸውና እየተነጫነጩ አልጋቸውን ለቀው በንዴት ውስጥ ሆነው በራፉ ሊከፍቱ እየሄዱ ባሉበት ቅፅበት ከመኝታ ቤታቸው ቀጥሎ ካለው ከፍል ውስጥ ያሉት ወ.ሮ ስንዱ ድምፅ ሰምተውና ደንግጠው ክፍላቸውን ከፍተው እየወጡ ነበር፡፡ ሁለቱም በአንድ ጊዜ እያንኳኳ ያለው ጋርድ ላይ አፈጠጡበት፡፡
‹‹ምን ተፈጥሮ ነው?››

‹‹ጋሼ..እንዴት እንደሆነ አናውቅም…..ልጆቹ እየተከታተሏት ነበር….››ለማስረዳት አስቦ መንተባተብ ጀመረ..፡፡

‹‹ምን እያወራህ ነው?››

‹‹በፀሎት..››

‹‹በፀሎት ..ልጄ ምን ሆነች..?አመማት እንዴ…?የልብ ህመሟ ተቀሰቀሰባት?››እናትዬው በመርበትበት በጥያቄ አጣደፉት፡፡

‹‹አይ አላመማትም…ላለፉት አንድ ሰዓት ውስጥ ስንፈልጋት ነበር…የለችም…››

‹‹የለችም ማለት…….?››

‹‹ጓደኞቾ ደብቀው ይዘዋት ሄደው መሰለኝ…. ግቢው ውስጥ የለችም፡፡››

‹‹እንዴ ..ይሄ ምን ማለት ነው..?ያን ሁሉ ጠብደል ጎረምሳ በጠባቂነት የቀጠርኩት እንዲህ አይነት ነገር እንዲከሰት ነው እንዴ…?ሰውዬ የእያንዳንዳችሁን ግንባር በሽጉጥ ሳልነድልላችሁ ልጄን ካለችበት ፈልጉና አስረክቡኝ…፡፡››በመራር ንግግር ቀድሞም የደነገጠውን ሰውዬ ይበልጥ ፍርሀት ለቀቁበት፡፡

‹‹እሺ ጌታዬ… ሁሉም ሰው እየፈለጋት ነው፣ይሄንን ነገር እርሶም በሰዓቱ መስማት አለቦት ብዬ ነው ቀድሜ ያሳወቅኳት…››

‹‹ወይኔ ልጄን..ይሄ የእነሱ ሳይሆን ያንተ ጥፋት ነው…››እናትዬው ቁጣቸውን ወደባላቸው አዞሩት፡፡

‹‹ይሄ ደግሞ ምን ማለት ነው?››ባልና ሚስቶች የተለመደውን ጭቅጭቃቸውን ቀጠሉ፡፡

‹‹ልጄን እንደከብት እረኛ ቀጥረህባት ስታጨናንቃት ነው ለዚህ ያበቃችው፡፡››

‹‹ሴትዬ እስኪ አሁን ተይኝ….እኔ ለራሴ ግራ ገብቶኛል ይበልጥ ግራ አታጋቢኝ.››አሉን ፊት ለፊት እየሄደ ያለውን ጋርድ ተከትለው ኮሪደሩን አቆርጠው መሄድ ጀመሩ..፡፡ወ.ሮ ስንዱም ማጉረምረማቸውን በለቅሶ አጅበው የለበሱትን ቢጃማ እንኳን ሳይቀይሩ ከኋላ መከተል ጀመሩ…፡፡በፀሎት ግን ለሊቱን ሙሉ ብትፈለግ ..በየወዳጅ ዘመድ ቤት ቢደወል…በከተማ አውራ ጎዳናዎች ከሰላሳ በላይ መኪኖችን ተሰማርቶ ብትፈለግ ድኩዋን ለማግኘት አልተቻለም…

በስተመጨረሻ የግቢው ካሜራ ቅጂ ለሁለተኛ ጊዜ በዝግታ ሲታይ ነው እራሷን በአለባበሶ ቀይራ ብቻዋን በሞተር ሳይክል ግቢውን ለቃ እንደወጣች የታወቀው፡፡ይሄ ደግሞ በቤተሰቡ ላይ የነበረውን ድንጋጤና ፍራቻ ይበልጥ አናረው..ምክንቱም አወጣጧ አስባባት መሆኑን ስለተረዱ….፡፡ከዛ አባትዬው አቶ ኃይለመለኮት ያላቸውን ተሰሚነትና ከመንግስት ሰዎች ጋር ያላቸውን ትስስር በመጠቀም ለእያንዳንዱ ፖሊስና ትራፊክ ፖሊስ ፎቶዋና የሞተር አይነትና ታርጋ ቁጥሩ ተበትኖ እንድትፈለግ መመሪያ እንዲተላለፍ ተደረገ ፡፡

በማግስቱም ምንም ፍንጭ ሳይገኝ በመንጋቱ እቤቱ ሁሉ በወዳጅ ዘመድ ተጨናነቀ፡፡..ወላጆቹ በስጋትና ፍራቻ ብቻ ሳይሆን በሰው ትንፋሽም መፈናፈኛ አጣ…አቶ ኃይለመለኮት ሲጨንቃቸው ከአጀቡ ተነጥለው ቀጥታ ወደልጃቸው መኝታ ቤት ገቡና ከውስጥ ዘግታው አልጋዋ ጠርዝ ላይ ቁጭ ብለው ግድግዳው ላይ የተለጠፈውን ግዙፍ የልጃቸውን ፎቶ እየተመለከቱ በትካዜ መንሳፈፍ ጀመሩ....እንባቸው መቆጣጠር አልተቻላቸውም…እንደህፃን ልጅ ነው ተንሰቅስቀው ያለቀሱት….በህይወታቸው እንዲህ አይነት ለቅሶ መቼ እንዳለቀሱ ፍጹም ትዝ አይላቸውም….አዎ ልጃቸው የልብ ንቅለተከላ በተደረገላት ጊዜ በህይወታቸው በጣም ያዘኑበትና የተጨናነቁበት ጊዜ ነበር…በቀሪ ህይወታቸውም መቼም ተመሳሳይ ሀዘን ውስጥ እገባለሁ የሚል ግምት አልነበራቸውም….ግን ተሳስተው ነበረ..አሁን ያሉበት ጭንቀትና ስጋት ከዛን ጊዜም ከፍ ያለ ነው…. ፡፡ልጃቸው አንድ ነገር ብትሆን ምን እንደሚሆኑ ምንም የሚያውቁት ነገር የለም..፡፡ግን በእርግጠኝነት ሌላ ኃይለመለኮት እንደሚሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው..ምን አልባት አብደው ጨርቃቸውን ሊጥሉ ይችሉ ይሆናል...ወይንም ንዴታምና አውሬ አይነት ሰው ሊሆኑ ይችላሉ ….ልባቸው ፍስስ እያለባቸው ነው….አይናቸውን ከወዲህ ወዲያ እያሽከረከሩ የልጃቸውን እቃዎች በስስት ሲቃኙ አይናቸው አንድ ፖስታ ላይ አረፈ..በድንጋጤ ተነሱና ወደእዛው ተራመድ፡፡ አነሱት… ሁለት ነው…፡፡ከላዩ ላይ የተፀፈውን አነበቡት..፣አንደኛው ለአባዬ ይላል…ሁለተኛውን አዩት ለእማዬ ይላል…እሱን ጠረጴዛው ላይ መልሰው አስቀመጡና ለእሷቸው የተጻፈውን ይዘው ወደአልጋ ጠርዝ ተመላሱና ፖስታውን ቀደው ወረቀቱን በማውጣት ማንበብ ጀመሩ፡፡

አባዬ….እንዴት እንደምወድህ ታውቃለህ አይደል? በጣም ነው የምወድህ..ግን ሁሌ ትናፍቀኛለህ…፡፡ሁሌ እሩቅ ውጭ ሀገር ያለህ ነው የሚመስለኝ….እቤት እያለህ እራሱ የሌለህ መስሎ ነው የሚሰማኝ…እርግጥ አንተ ሁሉ ነገር ተሟልቶልኝ በቅምጥል የምኖር ደስተኛ
ልጅ ነው የምመስልህ…እየቀያየርኩ ምነዳችወ ከሶስት በላይ ዘማናዊ መኪናዎች አሉኝ፣በወር ከመቶ ሺ ብር በላይ በእጄ ይሰጠኛል….በየሄድኩበት እየሄዱ የሚጠብቁኝ ቁጥራቸውን የማላውቃቸው ጋርዶች አሉኝ……በአመት ሁለትና ሶስት ጊዜ የፈለኩትን ውጭ ሀገር ሄጂ እዝናናለሁ…በአጠቃላይ ኑሮዬ ለአብዛኛው ኢትዬጵያዊ በተረት አለም እንኳን ሰምቶት የማያውቀው የህልም አለም አይነት ነው…ግን እኔ በእድሜዬ እናትና አባቴ ሲሳሳሙ አይቼ የማላውቅ ልጅ እንደሆኑክ ማንም አያውቅም..አረ መሳሳሙ ይቅር አንድ መኝታ ቤት ውስጥ አብረው ሲያድሩ አይቼ አላውቅም… አይገርምም…..፡፡

አባዬ ልጅ ሆኜ እርግቤ እያልክ ነበር የምትጠራኝ..እርግቤ ስትልኝ እንዴት እንደምደሰት አታውቅም ፡፡የእውነትም ያንተ ነጭ እርግብ ሆኜ አድማሱን ሰንጥቄ በሰማይ መብረር የምችልና ጨረቃ ጋር ደርሼ ከዋክብቶችን ጨብጬ ምጫወትባቸው ይመስለኝ ነበር…በቃ ትንሽ መልአክ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ነበር የምታደርገው..ግን አባዬ አንተ ያልተረዳኸውነ ነገር እኔ ከ19 ዓመቴ በኋላ ማለቴ የሌላ ሴት ከሰውነቴ ካወሀድኩ ጀምሮ እኔ እኔን አይደለሁም…..ትዝ ይልሀል እርግቤ አትበለኝ በስሜ ጥራኝ ብዬ ያስተውኩህ እራሴው ነኝ..ለምን ብለህ ጠይቀኸኝ ግን አታውቅም..ምን አልባት ዝም ብዬ እርግቤ የሚለው ሰም ደስ ስለማይለኝ መስሎህ ሊሆን ይችላል እንደዛ ግን አይደለም….ከልብ ነቅለ-ተከላ ከተደረገልኝ በኃላ ክንፏ የተሰበረባት መብረር የማትችል እና በየጓሮ የምትንፏቀቅ እርግብ እንደሆንኩ እየተሰማኝ ስለመጣ ነው ያስቆምኩህ..ለአንድ ልጅ እኮ በሰማይ እንዳሻት እንድትበር የሚያደርጋት የአባቷ ፍቅር ቀኝ ክንፍ እና የእናቷ ፍቅር ግራ ክንፍ ሲሆናት ነው….የወላጆቾ ፍቅር ነው እንድትበር የሚያደርጋት….ያ እንደሌለኝ ስረዳ ነው ስሙ ያስጠላኝ፡፡ለምን

አትሮኖስ

28 Oct, 17:55


​​እንደሆነ አላውቅም ከድሮዬ በተለየ ፍቅር ይርበኛል፡፡
አባዬ እንደነፍስህ የምትወዳቸው ሁለት የአንተ አንደኛ ሰዎች አንድ ቤት እየኖሩ እንደጠላት ሲታያዩ ከማየት የበለጠ የሚያስጣላና ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር የለም….አሁን አሁን ሳድግ ተስፋ ቆርጬ ተውኩ እንጂ በፊት እናትና አባቴ ግራና ቀኝ እጄን ይዘው እርስ በርስ እያወሩና እየተሳሳቁ ወደ መዝናኛ ቦታ ወይም ዘመድ ቤት ይዘውኝ ሲሄዱ አልም ነበር..ሁሌ የማየው ህልም እንደዚህ አይነት ነበር…ያን ህልም ግን አንድም ቀን እውን ሆኖልኝ አያውቅም….ከቤት ውጭ ከሁለታችሁም ጋር በተመሳሳይ ጊዜ የትም ሄጄ ሆና የትም ቦታ ተገኝቼ አላውቅም……ወይ አንተ ትጎድላለህ ወይ ደግሞ እማዬ ትጎድላለች…ይሄ ምን ያህል ልቤን እንዳቆሰለው አታውቅም….ደግሞ ታውቃለህ በውስጤ

የተሸከምኩት የሌላ ሰው ልብ ነው…ያንን ልብ በአደራ ነው የተረከብኩት ….ላሰቃየውና ላጨናንቀው መብት የለኝም…. እንደአለመታደል ሆኖ ግን በፍቅር የተሰጠኝን ልብ በስርአቱ ተንከባክቤ እንድይዘው እናንተ እየፈቀዳችሁልኝ አይደለም፡፡

አባዬ ይገርምሀል ..ሁል ጊዜ ስለአንተእና ስለእማዬ ሳስብ ‹‹ ቆይ ሁል ጊዜ እንዲህ እየተጠላሉ..ለምን ባልና ሚስት ተብለው አንድ ላይ መኖራቸውን ቀጠሉ? ብዬ በተደጋጋሚ እራሴን ጠይቅ ነበር…፡፡አሁን ግን ለምን እንደሆነ መገመት እችላለው…አንድም እኔ እንቅፋት ሆኜባችሁ ነው…እንደውም ብዙ ጊዜ አንቺን በስለት ነው የወለድንሽ ብላችሁ በየአመቱ መደገሳችሁ ለበጣ ይመስለኛል..ተፈልጋ ለዛውም በስለትና በፀሎት ተወለዳ በጸሎት የሚል ስም የወጣላት አንድ ብቸኛ ልጅ ያላቸው ጥንዶች እንዴት እንዲህ ሊጠላሉ ይችላሉ..?እንዴት ልጃቸውን በፍቅር እጦት ሊያሳቃዩና ሊያሰቅቁ ይችላሉ…? ይሄ የሚያመለክተው ለእኔ ያላችሁ ፍቅር የውሸት እንደሆነ ነው፡፡ፈፅሞ ሁለታችሁም ትወዱኛላችሁ ብዬ አላስብም ፡፡ምን አልባት ከእኔ በላይ ሀብታችሁን አምርራችሁ ትወዱ ይሆናል፣ሁለታችሁም ላለመለያየትና በዛአይነት ጥላቻ ውስጥ ሆናችሁም ቢሆን በአንድ ጣሪያ ስር መኖር መቀጠሉን የመረጣችሁት ሀብታችሁን ላለመበታተን ሰስታችሁ ይመስለኛል፡፡እና ለዚህ ስል ሄጄያለው…ከእናንተ በጣም እርቄ ሔጄያለው፡፡አንድ ቀን ግን ተመልሼ መጣለሁ፡፡ መች እንደምመጣ አላውቅም፡፡ እሱ የእናንተ ውሳኔ ነው…እንድመለስ ከፈለጋችሁ በዚህም ብላችሁ በዛ ህይወታችሁን አስተካክሉ…፡፡ወይ በቃን ብላችሁ ተለያዩና የየራሳችሁን ህይወት መኖር ቀጥሉ፣ቢያንስ በዚህ ውሳኔ ከሁለት አንዳችሁ በቀሪ ህይወታችሁ ደስተኛ የመሆን እድል ይኖራችኋል…ካለበለዘያም ቁጭ ብላችሁ ተነጋገሩና ይቅር ተባብላችሁ ያለፈ ህይወታችሁን ጨለማ ታሪከ ዘግታችሁ ለራሳችሁ እንደባልና ሚስት ለእኔም ደግሞ እንደወላጅ ለመሆን ተዘጋጁ…..እስከዛው ልትፈልጉኝ እንዳትሞክሩ ልታገኙን አትችሉም…ብታገኙኝም ወደቤት ለመመለስ ፍቃደኛ አልሆንም….ግን ባለሁበት ሆኜ በራሴ መንገድ እከታተላችኃላው….በእናንተ ዙሪያ መኖር ለእኔ ምቹ ነው ብዬ ባመንኩበት ሰዓት እመጣለሁ..ካልሆነም ከእናንተ እንደራቅኩ የራሴን ህይወት እኖራለሁ..፡፡አባዬ አይዞህ ስለበሽታዬ አትጨነቅ…አትጨነቅ የምልህ በእኔ ጥንካሬ ስለምተማመን አይደለም..በውስጤ ያለው የልጅቷ ልብ እጅግ ጠንካራ ስለሆነ ነው፡፡ ያንን ደግሞ ያወቅኩት የእኛን ቤት ያንን ሁሉ ጥላቻና ጥል ተቋቁሜ እስከአሁን በህይወት የኖርኩት እና ኮላፕስ ያላደረኩበት ብቸኛ ምክንያት የተሸከምኩት ልብ ጥንካሬ ነው፡፡በል ቸው አባዬ… ለማንኛውም እራስህን ጠብቅ …በጣም እወድሀለው፡፡
ይላል ደብዳቤው፡፡አቶ ሃይለመለኮት ደነዘዙ፡፡ምን ማድረግና ምን አይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው እየገባቸው አይደለም፡፡ልጃቸው በእሷቸውም ሆነ በሚስታቸው ይሄን ያህል መጎዳቷ እና መማረሯን ፈፅሞ ልብ ብለውት አያውቁም ነበር፣በዚህም በራሳቸው አፈሩ…. ደብዳቤውን ደረት ኪሳቸው ውስጥ ከተቱና ክፍሉን ለቀው ወጡ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

27 Oct, 21:34


ለፕሮፋይል የሚሆኑ ገራሚ ገራሚ ፎቶዎችን ለማግኘት ከስር ጆይን ያድርጉ የፈለጉትን አይነት ያገኛሉ ይ🀄️🀄️ሉን!👇

አትሮኖስ

26 Oct, 18:06


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_ሶስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ በፀሎት የልብ ንቅለ ተከላ ካደረገች በኋላ ልክ እንደዛሬው አይነት በህይወቷ ወሳኝ የሆኑ ትላልቅ ውሳኔዎችን አሳልፋለች….አንዳንዴ‹‹ በእውነት እንዲህ እያሰብኩና እያደረኩ ያለሁት እኔው ነኝ?››ብላ በራሷ እስክትደመም ድረስ ነበር ለውጦ፡፡ ‹‹አሁን የሌላ ሰው ለዛውም…»

አትሮኖስ

26 Oct, 17:58


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

በፀሎት የልብ ንቅለ ተከላ ካደረገች በኋላ ልክ እንደዛሬው አይነት በህይወቷ ወሳኝ የሆኑ ትላልቅ ውሳኔዎችን አሳልፋለች….አንዳንዴ‹‹ በእውነት እንዲህ እያሰብኩና እያደረኩ ያለሁት እኔው ነኝ?››ብላ በራሷ እስክትደመም ድረስ ነበር ለውጦ፡፡

‹‹አሁን የሌላ ሰው ለዛውም የሟች ንፁህ ልብን በሰውነቴ ተሸክሜ ርካሽ የሆነ ስራ ፈፅሞ አልሰራም››የሚል አቋም ላይ ደርሳ በዛ መሰረት ነው የምትንቀሳቀሰው…ትንሽ ለስሜቷ የማይመችና የሚቆረቁር ነገር ሲያጋጥማት እንደድሮው ‹‹ቆይ እስኪ ልሞክረው›› ብላ ዘላ አትገባበትም….ጊዜ ወስዳና ተረጋግታ ታስብበታለች..ነገሩን ትመዝንና እሷንም ሆነ ሌላውን ሰው የሚያሳዝንና የሚያስከፋ መስሎ ከተሰማት ወዲያው መንገዷን ታስተካክላለች….ይሄ በብዙ ነገሮች ጠቅሟታል…ግን ደግሞ ቤተሰቦቾን በተመለከተ እንደበፊቱ ነገሮችን አይታ እንዳላየች እንድታልፍ አላደረጋትም…እያንዳንዱ በመሀከላቸው ያለው ጥላቻና ጥል በጣም ያስጨንቃትና እረፍት ይነሳት ጀመር…ለምን ብላ እንድትጠይቅ..ጥፋቱ የማንኛቸው ይሆን እያለች እንድትመረምርና ፣እንዴት ሊስማሙና ትክክለኛ ባልና ሚስት ሆነው ለእሷም መቼ እንደ ትክክለኛ ወላጅ የምትፈልገውን ፍቅር ሊለግሷት እንደሚችሉ ማለምና መተከዝ የጀመረችው ከበርካታ ወራቶች በፊት ነው፡፡

በፀሎት  ጨረቃ በነገሰችበትና ከዋክብቷች ሰማዩ ላይ ተበትነው በሚንሸራሸሩበት በዛ ውድቅት ለሊት እቤቷን ጥላ ..ከእናትና አባቷ ርቃ …ከጋደርዶቾ አምልጣ መሄዷን እንጂ ወዴት እንደምትሄድ ለምን ያህል ሰዓት መንዳት እንዳለባትና የመንገዷ ማዳረሻ የት እንደሆነ ምንም የምታውቀው ነገር የለም፡፡ዝም ብላ ብቻ በዛ ውድቅት ለሊት የአስፓልቱን መሀከል ይዛ በመድሀንያለም ቤተክርስቲያንን አጠር ታኮ በሚገኘው መንገድ ወደፊት በመውጣት ዋናውን አስፓልት ገባችና ቀጥታ ወደ ስቴዲዬም ሚወስደውን መንገድ ያዘች….መስቀል አደባባዩን እንደጨረሰች ወደግራ ታጠፈችና ወደላንቻ የሚወስደውን የአስፓልት መንገድ ያዘች..
ከትራፊክ መጨናነቅ ነፃ የሆነውን መንገድ በፍጥነት መጋለብን ተያያዘችው…ምንም ሳታውቀው ለአንድ ሰዓት ያህል ከነዳች በኃላ አቃቂ ድልድይ ጋር ስትደርስ ወደቀኝ ተጠማዘዘችና ወደአቃቂ የሚወስደውን መንገድ ገባች ፣…መንዳቷን ቀጠለች…ድንገት ተረጋጋችና ሞተሩን አቀዝቅዛ አቆመችና አካባቢውን ስታስተውል የምታውቀው ሰፈር ሆኖ በማግኘቷ ደነገጠችም.. ተገረመችም….እዚህ ሰፈርና እዚህ ቦታ ለመምጣት ባለፈው ሁለት አመት ስትመኝ ነበር….ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን በህልሟ እዚህ አካባቢ መጥታ ስትዳክር ነው የምታየው..ግን መጥታ የምትፈልገውን ነገር ለማድረግ አባቷ ሊፈቅድላት አልቻለም..ለጠባቂዎችም በጥብቅ ስለተነገራቸው እንኳን አሁን ያለችበት ሰፈር ይቅርና ክፍለከተማው ውስጥም ዝር እንድትል እንዳይፈቅዱላትም ፤ከዚህ ቀደም ምንአልባትም ከአመት በፊት ሰፈሩንና እቤቱን ለአንድ ጊዜ በስንት ጭቅጭቅ ያሳያት እራሱ አባቷ ነበር፡፡

በጊዜው መኪናዋን አሁን ሞተሯን ያቆመችበትን ቦታ አቁሞ…የቤቱን በራፍ በጥቁሩ የመኪና መስታወት ወደውጭ እየጠቆመ…‹‹አየሽ የልጅቷ ቤተሰቦች የሚኖሩት እዚህ ነው..እኛ አሁን የሚገቡት አባቷ ናቸው…አብሯቸው ያለው ደግሞ ልጃቸው ነው….እናትና እህቷም አሉ››እያለ ነበር ያብራራላት፡፡

‹‹አባዬ እንዲት እንዲህ ጭንቁርቁስ ያለ ቤት እንዲኖሩ ትፈቅዳለህ..?እየው እስኪ አጥሩን..እቤታቸውን ተመልከተው››በምሬት አባቷን መጠየቋን ታስታውሳለች፡፡

‹‹ልጄ ምን ላድርግ ?በግድ በወታደር አስገድጄ ሌላ ቤት ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ አልችል››

‹‹ማለት…?››

‹‹ነግሬሻለሁ እኮ …ቤተሰቡ ከእኛ አምስት ሳንቲምእንደማይቀበሉ ምለው ነው የነገሩን››

‹‹አባዬ ይሄ ምንም ሊገባኝ አልቻለም…የተሸከምኩት እኮ የልጃቸውን ልብ ነው….በልጃቸው ሞት እኮ ነው አሁን እኔ በህይወት መኖር የቻልኩት…አልገባህም አባዬ …ለምን እሷ ሞታ እኔ ኖርኩ..?እግዚያብሄር ይሄን እንዴት ፈቀደ…?.አባዬ በየቀኑ የጥፋተኝነት ስሜት እየተሰማኝ ነው…እየተሰቃየሁልህ ነው…››

‹‹አውቃለው  ልጄ…እነሱ  ፍቃደኛ  ቢሆኑ  እኔ  የሀብቴን  ግማሽ  እንኳን  ብሰጣቸውና
..ላደረጉልኝ ነገር ምስጋና ባቀርብ ደስ ይለኝ ነበር…ግን ተቀባይ ከሌላ መስጠት ስለፈለግሽ ብቻ አይሳካልሽም፡፡››

‹‹ቢሆንም አባ ..እኔ ልቧን ሰጥታኝ ህይወቴን እንዲራዘም ያደረገቺኝን ልጅ ቤተሰቦች እንዲህ በጉስቁልና እንዲኖሩ አልፈልግም…..ልጃቸው በህይወት ኖራ ቢሆን ትጦራቸው ነበር…የሆነ የሆነ ነገር ታደርግላቸው ነበር….ብቻ አላውቅም የሆነ ዘዴ ፍጠርና እርዳቸው፡፡››

‹‹አይ ልጄ አልገባሽም እንዴ…ልጃቸው ላንቺ ልብ ከመስጠቷ ከአመታት በፊት በእኛ ፋብሪካ የሚሰራውን ወንድ ልጃቸውን እራሱ ስራ እንዲለቅ አድርገውታል…..ለማንኛውም የተቻለኝን እሞክራለው..አሁን ይሄን ያህል ካየሻቸው ይበቃሻል… አንሂዱ ››ብሎ ነበር ከአካባቢው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የለቀቁት፡፡

ከዛ ወዲህ ግን ፍፅም ወደአካባቢው እንድትጠጋና ከቤተሰቡ ጋርም በምንም አይነት መንገድ ተገኛኝታ እንዳትተዋወቅ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ተሳክቶላቸዋል…አሁን ግን ይሄው በደመ ነፍሷ ከቤቱ ፊት ለፊት አስፓልቱ ጠርዝ ላይ ሞተሯን አቁማ ቁልቁል አዘቅዝቃ እያየችው ነው፡፡

‹‹ወደእዚህ መምጣት በአእምሮዬ ስሌት ውስጥ አልነበረም….ሳስበው ግን የልጃችሁ ልብ ነው እየመራ እዚህ ድረስ ያመጣኝ››ስትል አጉረመረመች፡፡ድንገት ስሜታዊ ሆነችና ነዳጁን ረገጠችና ጨምቃ የያዘዘችውን ፍሬን ለቀቀች…አስፓልቱ ን ለቃ ቀጥታ ወደቤቱ አቅጣጫ መንዳት ጀመረች

…የሞተሩ ፍሬን ድንገት እምቢ አላት… ያ ደግሞ ጠቅላላ ሰውነቷ በፍራቻ እንዲቀዘቅዝ ነው ያደረጋት…ሞተሩ ከቁጥጥሯ ውጭ እየወጣ ነው.. መንገድን ሰታ ወደቀኝ እየተጓዘች ነው…›የተውሸለሸለ የእንጨት አጥር ቤት ጥሳ ገባች…. የቆርቆሮ በር ካለው ሰርቢስ ቤት በራፍ ጋር ተላትማ በአየር ላይ ተንሳፈፈችና መሬት ላይ ጧ…ጧጧ ብላ ወደቀች....ሞተሩ አጥሩን ጥሶ ሲገባና ከቆርቆሮ በራፉ ሲጋጭ የፈጠረው ድምፅ የፍንዳታ አይነት ነው….እሷ ወዲያው ነው ጭልም እያለባት የሄደው…እንዲህ ባለ ሁኔታ እራሷን አደጋ ላይ የመጣል እቅድ አልነበራትም…….ከቤት ውስጥ ግን ቡዙ ጫጫታና ትርምስ ተሰማ…

‹‹አማዬ ምንድነው……?››

‹‹.ልጆቼን ..››

‹‹ልጆቼን ››

‹‹አባዬ ሰላም ነህ?››

የሶስት ወይም የአምስት ሰዎች ድምጽ እየተሰማት ነው….እያንዳንዱ ድምፃ ልቧ ላይ እየተንጠባጠ እያቀለጣት ያለ ነው የመሰላት፡፡‹‹ምን ሆኜ ነው …?ምን ተፈጠረ…?ይሄን እያሰበች ሳለ ጭልም እያለባት ሄደ ፣እንደምንም ላለመጥፋት ብትሞክርም አልቻለችም
…እራሷን ሙሉ በሙሉ ሳተች….፡፡እቤቱ ውስጥ ያለ አንድ ጎረምሳ እና አንድ ወጣት ሴት… እናት አባት በዛ ውድቅት ለሊት ፈጣሪ ምን አይነት መብረቅ እንደላከባቸው ለማወቅ በሀይለኛ ድንጋጤ እንደተመቱ የተተራማመሱ የቤታቸውን በራፍ እንደምንም ተራ በተራ እየተጋፉ ወደውጭ ወጡ….የውጭ መብራት አብርተው ሲመለከቱ ..ከበራፉ በሶስት ሜትር ርቀት መሬት ላይ የተዘረጋ ጥቁር እና ነጭ ቀለም የተቀባ ዘመናዊ ሞተር ሳይክል
ይታያል...ከሳይክሉ ሁለት ሜትር ርቀት አንድ ሄሌሜት ያደረገ ባለመካከለኛ ቁመት ሰው እጥፍጥፍ ብሎ ወድቆ ይታያል....ሁሉም በቃል ሰይነጋገሩ እየሮጡ ሰውዬውን ከበቡት…

አትሮኖስ

26 Oct, 17:58


​​‹‹አባዬ…ይሄ ነገር በእኛ እንዳይሳበብ…ከመነካካታችን በፊት ለፖሊስ ደውለን እናሳውቅ፡፡››ወንዱ ልጅ ስጋቱን ለአባቱ ተናገረ፡፡
‹‹ልጄ ገና ለገና እንጠየቃለን ብለን በሰው ህይወት ላይ እንፈርዳለን….?አይ እንደዛ ማድረግ አልችልም›› በማለት…ሰውዬው ተጠጋና ቀስ ብሎ ሄልሜቱን ፈቶ አወለቀው….ረጅምና ዞማ ፀጉሯ ዝንፍል ብሎ መሬቱን ሞላው፡፡ፊቷ በደም ተሸፍኗል፡፡

‹‹በጌታ ሴት ነች››እናትዬው ተናገሩ፡፡
አባትዬው እጁን ወደ ልጅቷ አንገት ላከና በህይወት መኖሯን አለመኖሯን ለማረጋገጥ ሞከረ፡፡‹‹ተመስገን አለች፣ትተነፋሳለች….ቀስ ብለን ወደቤት እናስገባት…››

‹‹እንዴ አባዬ ለፖሊስ እንደውልና እነሱ ሀኪም ቤት ይውሰዷት››ወንዱ ልጅ ስጋቱን መለሶ አስተጋባ፡፡

‹‹አይ…አይሆንም ፡፡በዚህን ሰዓት እንደዚህ አይነት አለባበስ ለብሳ እንዲህ አይነት ሞተር የምትነዳ ሴት የሆነ ችግር ላይ እንደሆነች እርግጠኛ ነኝ፣…ምን ላይ እንዳለች ሳናውቅ ለፖሊስ በመደወል አሳልፈን አንሰጣትም…አይሆንም..ይልቅ ና ከታች ቀስ ብለህ ያዛት
…ወደቤት እናሳገባት….››አባትዬው ጠንከር ባለ ንግግር ውሳኔያቸውን አሳወቁ፡፡
ወጣቱ ሳይመስለው አባትዬው እንዳለው አደረገ ….ወስደው ጠባቧ ሳሎን ከተዘረጋው ልጆቹ ተኝተውበት ከነበረ ባለሜትር ከ20 ፍራሽ ላይ አስተኟት፡፡እናትዬው ቦርሳውን አንጠልጥላ በማስጋበት ወደ ጓዲያ ወስደው አስቀመጡት፡፡ ….ከላይ የለበሰችው ልብስ አወለቁላትና የቆሰለ ወይም የደማ ቦታ እንዳለ መፈለግ ጀመሩ ግንባሯ ላይ ከጀርባ በኩል የሚፈስ ደም አለ ግማሽ ፊቷ ቆዳዋ ተገሽልጦ በደም ተሸፍኗል፡፡ ሌላ ቦታ ሰላም ትመስላለች፣ቢያንስ ለጊዜ የሚታይ ቦታ የለም፡፡

‹‹ምን እናርግ..ፊቷ እኮ በጣም ተጎድቷል…ደሟም እየፈሰሰ ነው..የግድ ህክምና ማግኘት አለባት፡፡››

ሴቷ ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናገረች‹‹እዚህ ከጀርባችን ያለው ኪሊኒክ ለምን አንወስዳትም?››

‹‹በሊሊት ይሰራሉ እንዴ?››

‹‹አዎ ተረኞች አሉ…፡፡››

ወደኪሊኒክ በመውሰዱ ሁሉም ተስማሙ…ወጣቱ ልጅ እና አባትዬው ተራ በተራ እያዘሉ ከቤታቸው ግማሽ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ኪሊኒክ ወሰዷት…ሀኪሞቹ ቁስሏን አፅድተው ግንባሯ ላይ የለውን ስንጥቅ ሰፍተውና ግማሽ ፊቷን በፋሻ ሸፍነው ህክምናቸውን ጨረሱ…ለማንኛውም ሆስፒታል ወስደው ሙሉ ምርመራ እንድታደርግ እንዲያደርጉ አዛው… ሸኞቸው፡፡

እነሱ ግን ቀጥታ ወደቤት ነበር የመለሶት፡፡….እሷ ያ ሁሉ ሲሆን ከገባችበት ከፊል ሰመመን አልነቃችም ነበር፡፡….ከዛ አቶ ለሜቻ ከልጃቸው ከፊራኦል ጋር እየተረዳዱ በማዘል ወደበት ከመለሷት እና መልሰው ካስተኞት በኃላ በዛ ውድቅት ለሊት በሞተሩ የተጣሰውን የውጭ አጥር ወደነበረበት መለሱና ሞተሩን ተጋግዘው ወደውስጥ በማስገባት ጎዲያ ውስጥ አስገብት፡፡
ፊራኦል‹‹አባዬ ምን እያደረክ እንዳለ ምንም አልገባኝም?››ሲል አባትዬውን የጠየቀው
‹‹ልጄ እንደምታያት ልጅቷ ሴት ነች..ወጣት ሴት…..እንዴትም አድርጌ ባስበው በዚህ እድሜ ያለች ሴት ልጅ በሰላም ሆና በዚህ ውድቅት ለሊት ሞተር አትነዳም…ልጅቷ የሆነ ችግር ላይ ነች….››

‹‹እኮ እኔም እኮ ምለው እንደዛ ነው..ችግር ላይ ነች..እኛንም አብራ ችግር ውስጥ ትከተናለች እያልኩህ ነው፡፡››

‹‹ልጄ ስጋትህ ይገባኛል …ትክክልም ነህ፡፡እኔ ግን አባት ነኝ…እንደእሷ ልጆች አሉኝ..ነገ እንሱም የሆነ ችግር ውስጥ ሊገቡ እና እንዲህ የማያውቁት ቦታ በማያውቁት ሰው እጅ ሊወድቁ ይችላሉ ..ለልጆቼ ጡር አላቆይም…ይህቺ ልጅ ከገባችበት ሰመመን ነቅታና ከህመሟ አገግማ የሆነችውን ከነገረችን በኃላ ምን ማድረግ እንዳለብን እንወስናለን..እስከዛ ግን አይሆንም››

‹‹ከረፈደብንስ?›››

‹‹ከረፈደብን ስትል….?››

‹‹ምን አልባት ባትነቃስ?››

‹‹ተው ልጄ ..እንደዛ አይሆንም….አምላክማ እንዳዛ አሳልፎ አይሰጠኝም፣በል አሁን ተነስ ከብርድ ላይ እንግባ፡፡››

አካባቢው ትኩረት የሚስብ ነገር አለመኖሩን ካረጋገጡ በኃላ ከለሊቱ 10 አካባቢ ለመተኛት ወደውስጥ ተያይዘው ገቡ…እናትዬው እና ለሊሴ የለሌት እንግዳዋን በግራና በየቀኝ አጅበው በድንጋጤ እንዳፈጠጡ ቁጭ ብለዋል….፡፡
እናትዬው ወ.ሮ እልፍነሽ አንዴ ጓዳ ፤ሌላ ጊዜ ሳሎን ይመላለሳሉ…መልሰው ደግሞ ከጎኗ ቁጭ ይላሉ… በፍራቻና ግራ በመጋባት እህህ እያሉ ያጉረመርማሉ‹‹ይሄኔ እናቷ አላየቻት፣ወይ የሰው ልጅ፣አሁን እሺ ባትነቃስ?››ብቻቸውን ይለፈልፋሉ፡፡

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

25 Oct, 21:50


በ ONLINE ገንዘብ መስራት ይፈልጋሉ ?

አትሮኖስ

25 Oct, 21:41


ሴት ልጅ አንተን እንዳፈቀረችክ የምታቅበት 10 ምልክቶች ከታች #JOIN ብለክ ተተቀምበት እና ህዝቤ ሆይ ምን ትተብቂያለሽ ገብተህ አንበዋ😋😋😋😋
👇👇👇👇👇👇👇

አትሮኖስ

25 Oct, 18:50


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_ሁለት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ በፀሎት በእንባዋ እና ሜካፕ ቅልቅል የተበላሸውን ፊቷን በሳሙና ታጠበችና አፀዳችው….መልሶ ሜካፕ መጠቀም ሳያስፈልጋት ቀጥታ ወደሳሎን ሄደች፡፡ከላይ ከአንደኛ ፎቅ እስቴሩን ተጠቅማ ወደታች ስትወርድ በመጀመሪያ አይኗ የገቡት እናትና አባቷ ነበሩ… ጎን ለጎን ተጣብቀውና እጅ ለእጅ ተቆላልፈው…በየመቀመጫው እየተዞዞሩ እንግዶቹን…»

አትሮኖስ

25 Oct, 18:50


አትሮኖስ pinned «#ጉዞ_በፀሎት (አቃቂ እና ቦሌ) ፡ ፡ #ክፍል_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ 22 አመቷ ነው፡፡እንዲሁ ከውጭ ለሚመለከታት ሰው ሁሉ የተሟላላት እንከን አልባ ውበት ይዛ እንከን አልባ ኑሮ እየኖረች በእንከን አልባ ደስታ የምትሰቃይ ቅምጥልጥል እድለኛ ነው የምትመስለው፡፡ ግን ቀርቦ ህይወቷን በጥልቀት ላጠና እህ ብሎ የውስጧን ላደማጠ ምን ያህል…»

አትሮኖስ

25 Oct, 18:35


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


በፀሎት በእንባዋ እና ሜካፕ ቅልቅል የተበላሸውን ፊቷን በሳሙና ታጠበችና አፀዳችው….መልሶ ሜካፕ መጠቀም ሳያስፈልጋት ቀጥታ ወደሳሎን ሄደች፡፡ከላይ ከአንደኛ ፎቅ እስቴሩን ተጠቅማ ወደታች ስትወርድ በመጀመሪያ አይኗ የገቡት እናትና አባቷ ነበሩ… ጎን ለጎን ተጣብቀውና እጅ ለእጅ ተቆላልፈው…በየመቀመጫው እየተዞዞሩ እንግዶቹን ያዋራሉ፡፡‹‹እንኳን ሰላም መጣችሁ›› እያሉ የውሸት የተጠና ሳቅ ይስቃሉ፡፡ከአስር ደቂቃ በፊት እንደዛ በፀያፍ ቃላት ሲጠዛጠዙ ላያቸው ሰው አሁን በእንደዚህ አይነት ቅርበት መጣበቅ ይችላል ብሎ ማንም ሊያስብ አይችልም፡፡

‹‹ሰላም ተስፋዬ እና ሰላሞን ቦጋለ እንኳን የእናንተን ገፀ ባህሪ ቢሰጣቸው በዚህ ልክ አስመስለው መጫወት መቻላቸውን በጣም እጠራጠራለሁ፡፡››እያለች ወደታች ወርዳ መድረኩ ላይ ወደተዘጋጀላት የክብር ቦታ ሄዳ ተቀመጠች፡፡ወዲያው እሷን ብለው የመጡ የሰፈርና የዩኒቨርሲቲ ጓደኞቾ ዙሪያዋን ከበቧት..እሷም ወላጆቾን እንደአርአያ ወስዳ የውስጧን ብስጭትና ንዴት በሆዷ ቀብራ አንድ ልደቷ እየተከበራላት እንዳለ ደስተኛ ቀበጥ የሞጃ ልጅ በፈንጠዝያና በፌሽታ ልደቷን ማክበሩ ላይ ትኩረቷን አደረገች….፡፡

ከመቀመጫዋ ተነሳችና ከእናቷ ጋር ደነሰች…ከዛ ከአባቷም ጋር ደነሰች…እናም በሁለቱ መሀከል ሆና ለሶስት ሆነው እንዲደነስ አደረገች….ይሄ እንቅስቃሴያቸው እያንዳንዱ ዳንሳቸውና የእርስ በርስ መተቃቀፋቸው በፕሮፌሽናል ቪዲዬ ማን እየተቀረፀና ፎቶም እየተነሳ መሆኑን ታውቃለች….ለዛም ነው እንደዛ እያደረገች ያለችው‹‹ልጄ እስከዛሬ ከነበረው ልደትሽ ሁሉ ይሄ ልዩ ነው…ይሄው ሀያ አንድ አመት ሙሉ ያንቺን ልደት ሳከብር አንድ ቀን አብሬሽ እንድደንስ ጋብዘሺን አታውቂም ነበር….ዛሬ ግን…››ለሶስት ሆነው እጅ ለእጅ ተያይዘው በመደነስ ላይ ሳሉ ነበር አባቷ ስሜታዊ ሆኖ የተናገረው፡፡

እናትዬውም ወዲያው ነበር የራሷን ሀሳብ ያስቀመጠችው‹‹አባትሽ እውነቱን ነው….እኔም ብሆን ከልጄ ጋር የመደነሱን እድል ሳገኝ ይሄ የመጀመሪያ ቀኔ ነው…በጣም ደስ ብሎኛል፡፡››

‹‹እርስ በርሳችሁስ?››ስትል ሁለቱንም ያስደነገጠ ጥያቄ ጠየቀቻችው፡፡

‹‹ማለ…ት?››እናትዬው በተለጠጠ ንግግር ጠየቀቻት፡፡

‹‹አንቺና አባዬ እንዲህ እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ ከደነሳችሁ ምን ያህል አመት ሆናችሁ?››ጥያቄውን አፍታታ ደገመችው፡፡

‹‹እኔ እንጃ ልጄ እኔ አላስታውሰውም…..ምን አልባት አንቺ ከመወለድሽ በፊት ይመስለኛል››አባትዬው መለሰ፡፡

‹‹አያችሁ..ልጅ ወላጆቹ የሚያወሩትን ሳይሆን የሚያደርጉትን ነው ኮርጆ ደግሞ የሚያደርገው..እናንተ በዚህ መልክ ስትደንሱ አይቼ ስለማላውቅ ነው እኔም ላደርገው ያልቻልኩት…ፍቅርን በተመለከተ ጥሩ አርአያዎቼ አልነበራችሁም ማለት ነው..አዎ እውነቱ እንደዛ መሰለኝ፡፡››

‹‹አይ ያ እውነት አይደለም፡፡ልጄ እኛ በጣም እኮ ነው የምንወድሽ፡፡››

‹‹እሱ አይደለም ጥያቄው..እናንተስ እርስ በርስ እንዴት ናችሁ…..?ከመሀከላችሁ ማንኛችሁ ናችሁ የታመማችሁት….?ምናችሁን ነው የሚያማችሁ….?እንዴት ነው ይሄን ሁሉ አመታት እርስ በርስ መጠላላት የማይደክማችሁ…..?እንዴት አንዳችሁ እንኳን አትሸነፉም….?ለማንኛውም እኔ ማውራቱ ደከመኝ …ይብቃን…..ከአሁን ወዲህ ልደት ብዬ ስለማልደግስ የዛሬው የመጨረሻችን ነው፡፡››

‹‹የመጨረሻ ማለት?››አሁንም ልጃቸሁን እንደአምስት አመት ህጻን የሚያዩት አባቷ ኮስተር ብለው ጠየቁ፡፡

‹‹አባዬ አትኮሳተር ፡፡አሁን ሀያ አንድ አመት ሞላኝ…እራሴን ችዬ ከቤት መውጪያ ጊዜዬ ከመድረሱም በላይ እያለፈብኝ ነው…በእናነተ ላይ መንጠልጠልና መደገፍ ይበቃኛል…ከነገ ጀምሮ ጋርዶችህ እንዲከተሉኝ አልፈልግም….በሹፌርም አልንቀሳቀስም…..በአጠቃላይ እንደምርኮኛ ወፍ ለዘመናት ካስቀመጥከኝ ጎጆ በሩን ሰብሬ ወጣላሁ ..ክንፌን በሰፊው ዘርግቼ በሰፊው ሰማይ ላይ ባሻኝ አቅጣጫ በራለሁ..አንተም ልታስቆመኝ ያለህ ኃይል በሙሉ በቂ አይሆንም፡፡››.

ይሄ ንግግር በሁለቱም ወላጆች ላይ መብረቃዊ ድንጋጤ ነው ያስከተለው‹‹ልጄ እንዲህ አይነት ቀልድ ከመቼ ወዲህ ነው መቃላለድ የጀመርነው..?ይሄ እቤት ዘመንሽን ሁሉ የምትኖሪበት ያንቺ የእድሜ ልክ ቤተመንግስት ነው…እዚሁ አግብተሸ እዚሁ ወልደሽ እዚሁ ነው የምታረጂው..ይሄን ምን ጊዜም ከአእምሮሽ እንዳታወጪው፡፡››

‹‹አባዬ… እናንተም መቼም ቢሆን ይህቺን ቀን ከአእምሮችሁ አታውጧት….››

‹‹እሺ ልጄ አሁን ለእንዲህ አይነት ጭቅጭቅ ጊዜው አይደለም… በድጋሚ መልካም ልደት..››

‹‹አመሰግናለው ..››ብላ

ሁለቱንም በየተራ ጉንጫቸውን ሳመችና ልርገፍ እያለ የሚታናነቃትን እንባዋን እንደምንም ከትራ ወደመቀመጫዋ ተመሰችና ከጓደኞቾ ጋር ተቀላቀለች፡፡፡

የልደት ዝግጅቱ ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ የጀመረ ሲሆን እሰከአራት ሰዓት ያለው ዝግጅት ለሁሉም የሚሆን ሰከን ያለ ሙዚቃ ያለበት የምግብና የመጠት መስተንግዶ ጨምሮ… የተረጋጋ የእርስ በርስ ጫወታ… የኬክ ቆረሳና.. የሻማ ማጥፋት ስርአት …የስጦታ ዝግጅት የተደረገበትና የተለመደ አይነት ነበር…ከአራት ሰዓት በኃላ ግን ጠና ጠና ያሉት ሰዎች አባትና እናቷንም ጨምሮ ግዙፍንና የተንጣለለውን ሳሎን ለወጣቶቹ ለቀው በመሰናበት ሄዱ፡፡የዝግጅቱ አጠቃላይ ሁኔታ ተቀየረ..ሙዚቃዎቹ የፈጠኑና የሚያስጨፍሩ ሆኑ፤ መጠጡ የጠነከረና አስካሪ እየሆነ ሄደ….ይሄም ሆኖ ግን በፀሎትን የሚጠብቁ ሁለት ጋርዶች የሳሎንን የግራና ቀኝ በራፍ ይዘው በተጠንቀቅ እንደቆሙ ነው፡፡እሷም በአይነ ቁራኛ እያየቻቸው ነው…በየሆነ ደቂቃ ልዩነት መጠጥ እንዲወስዱላቸው ለአስተናጋጆቹ መልዕክት ማስተላፏን ፈፅሞ አትረሳም…..መጀመሪያ ስራ ላይ ስለሆኑ መጠጥ እንደማይጠጡ በመናገር መልሰው ነበር..በኃላ ግን እራሷ ሄዳ ‹‹በልደቴ ቀንማ ቢያንስ አንድ ጠርሙስ መጠጣት አለባችሁ ››ብላ እንዲቀበል አስገደደቻቸውና  ተቀበሏት…በአንድ ብቻ ግን አላቆሙም፤ አራትና አምስት መደጋገም ቻሉ..፡፡ሰዓቱ እኩለ ለሊት አልፎ ሰባት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ሰክሮ ሚለፋደደው በዛ….በፀሎት ግን ከመጀመሪያም ጀምሮ እየጠጣች አልነበረም ….ዛሬ የምትጠጣበት ቀን እንዳልሆነ ከመጀመሪያውኑ ነው የወሰነችው…እንደምንም ጋርዶቹን በጥንቃቄ እያየች…እየተሹለከለከች የፎቁን ደረጃ ተያያዘችውና ወደላይ ወደመኝታ ቤቷ አመራች…ከፍታ ገባች እና መልሳ ከውስጥ ቆለፈችው፡፡

የለበሰችውን ቀሚስ በፍጥነት አወለቀችና ቅድም አዘጋጅታ የነበረውን ጅንስ ሱሪ ለበሰች…፡፡ወርቃማ አርቴፊሻል ፀጉሯን አወለቀችና ጥቁር ሆኖ ከኃላ ረጅም ከፊት አጭር ሆኖ ከፊል ግንባሯን ሚሸፍን ሌላ ፀጉር አጠለቀችና ከላይ ኮፍያ ያለው ጥቁር ጃኬት ደረበችበት፡፡ አይኗ ላይ ጥቁር መነፅር ሰካችና መስኮቱን ከፈተች…፡፡

…መለስተኛ የቆዳ ሻንጣዋን ከአልጋዋ ላይ አነሳችና በጀርባዋ አንጠለጠለችው… አዎ በጀርባ የሚገኘውን የአደጋ ጊዜ መውጫ ተጠቅማ ወደ ምድር መውረድ ጀመረች፡፡ይሄንን መወጣጫ ልጅ እያለች ጀምሮ በጣም ትፈራዋለች፡፡ መጀመሪያ ቀኝ እግሯን አስቀደመች

አትሮኖስ

25 Oct, 18:35


​​…….ሰውነቷ ተንቀጠቀጠባት..የሆነ ስህተት ፈጥራ እግሯ አዳልጦት ከመወጣጫው ላይ ተንሸራታ ብትፈጠፈጥ ሁሉ ነገር እንደሚያበቃለትና የአሰበችውን አንዱንም ሳታሳካ እግረ ሰባራና አካለ ጎዶሎ ሆና ለሌላ ስቃይ እደምትዳረግ አሰበችና ዝግንን አላት…በአእምሮዋ የተፈጠረው ክፉ ሀሳብ እዳይፈጠር እየጸለየች..በጥንቃቄ ወደታች መውረዷን ተያያዘችው…ምንም እንኳን ያን የአደጋ ጊዜ ጠባብ መወጣጫ ተጠቅሞ ወደታች መውረድ ሊወስድ ከሚገባው የጊዜ ስሌት በላይ የወሰደባት ቢሆንም ግን ደግሞ ምንም ክፉ ነገር ሳይከሰትባት ሻንጣዋን እንዳዘለች መውረድ ቻለች…ከዛ በግቢው ውስጥ ባሉ የጽድ ዛፎች እየተከለለች፣ከጀርባ ወደሚገኘው ገራዥ አመራች..የአባቷ ታናሽ ወንድም አልፎ አልፎ የሚጠቀምባት ሞተር ሳይክል ወደ ቆመበት ስፍራ አመራችና ቀድማ ሄልሜቱን አንስታ ጭንቅላቷ ላይ ከሰካች በኃላ መተሩን አስነስታ ቀጥታ ወደመውጫው በራፍ አስፈነጠረች፡፡…ወጪ ገቢ ስላለ የውጪ በራፍ አንደኛው ተካፋች ወለል ብሎ እንደተከፈተ ነው፡፡
ዘበኛው ሞተሩን ቢያውቃትም ማን እየነዳት እንደሆነ መለየት አቅቶት ላስቁም ወይስ ልፍቀድ…? በሚል ግራ መጋባት ውስጥ ሳለ ምንም እንዲል እድል ሳትሰጠው አስፈንጥራ የግቢውን ድንበር ጥሳ ዋናው አስፓልት ላይ ወጣች፡፡ ዘበኛው የፈለገ ቢገምት የቤቱ ቅምጥል ልጅ ትሆናለች ብሎ ሊገምት እንደማይችል እርግጠኛ ነች…ዘበኛው ሞተርም እንደምትነዳ እንኳን አያውቅም…

ይቀጥላል

#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

24 Oct, 17:08


​​‹‹ወዳጆችሽን ወይስ ውሽሞችሽን…?ለማንኛውም..ያለመረጃ ሰውን አትወንጅይ››

‹‹እኔ እኮ ነኝ ..ምን ያህል ጨካኝና ነፍሰ ገዳይ እንደሆንክ በደንብ አውቃለሁ….እርግጥ ቀጥታ ቃታ ስበህ ሰውን አትገድልም…ውሾችህ ግን የጠላሀውን ሰው ሁሉ ሄደው ቦጫጭቀው እንዲገድሉት በአንድ ቃል ታዛቸዋለህ..እነሱም በየጊዜው ለምትጥልላቸው አጥንት ሲሉ አድርጉ ያልካቸውን ያለማቅማማት ይደርጉታል…››

‹‹እሺ አሁን ቢበቃሽ አይሻልም..?ሳሎን ሙሉ እንግዶችን ሞልተን እኔና አንቺ እዚህ በማይረባ ነገር አንጨቃጨቅ..ግድ የለም..ስድብና ዘለፋሽን ነገ ካቆምሺበት ትቀጥይዋለሽ…የት እሄድብሻለው?››

‹‹አሹፍብኝ…..አንድ ቀን ትክክለኛው ቀን መጥቶ እኔም በተራዬ አሾፍብህ ይሆናል!››
በፀሎት ከዚህ በላይ የወላጆቾን ጆሮ የሚበጥስ ሰቅጣጭ ጭቅጭቅ ማዳመጥ አልፈለገችም…እንባዋን እያንጠባጠበች በሩጫ ወደክፍሏ ተመለሰች፡፡

‹‹በቃኝ…..ለእነዚህ ሰዎች እኔ አልገባቸውም….በቃኝ…..››ቀኝ እጆን አነሳችና ልቧ ላይ አስቀመጠች…የሆነ ሸክም ነገር ልቧ ላይ እንደተጫነባት እየተሰማት ነው፡፡‹‹አልችልም…በእናንተ ምክንያት ባደራ የተቀበልኩትን የሰው ልብ ማበላሸት አልፈልግም…..››ከቁም ሳጥኗ በላይ የተሰቀለውን ሻንጣ ወንበር ላይ ቆማ አወረደች..ኮመዲኖዋን ከፈተችና በተለያየ ጊዜ ለተለያዩ ወጪዎች ከወላጆቾ የሚሰጣትን ስፍር ቁጥር ከሌለው ገንዘብ ውስጥ እየተረፋት እንደቀልድ ወርወር እያደረገች ያከማቸችውን ብር እየዛቀች ሙሉ በሙሉ ወደሻንጣው ከተተች…ከዛ ሁለት ሱሪ ፤ ሁለት ቲሸርት የተወሰኑ ፓንቶችን ጨመረችና ፣ዚፑን ዘጋች..፡፡ከዛ ሌላ ጅንስ ሱሪ ቲሸርትና ባለኮፍያ ጠቆር ያለ ጃኬት መረጠችና አልጋው ላይ ዝግጁ አድርጋ በማስቀመጥ ወደ መታጠቢያ ቤት ገባች…፡፡

ይቀጥላል


#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

24 Oct, 17:08


#ጉዞ_በፀሎት
(አቃቂ እና ቦሌ)


#ክፍል_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

22 አመቷ ነው፡፡እንዲሁ ከውጭ ለሚመለከታት ሰው ሁሉ የተሟላላት እንከን አልባ ውበት ይዛ እንከን አልባ ኑሮ እየኖረች በእንከን አልባ ደስታ የምትሰቃይ ቅምጥልጥል እድለኛ ነው የምትመስለው፡፡ ግን ቀርቦ ህይወቷን በጥልቀት ላጠና እህ ብሎ የውስጧን ላደማጠ ምን ያህል የማይደረስበት ሽንቁር በህይወቷ እንዳለ በቀላሉ ይረዳል…ግን ያንን እሷን የመቅረብን እድል የሚያገኝ ሰው ጥቂት ነው ..ወይም ጭሩሱኑ የለም……እንዴት ተደርጎ..፡፡

አባቷ በሀገሪቱ ከሚገኙ ጥቂት ቢሊዬነሮች አንድ ናቸው፡፡ቢሊዬን ብር ያላቸው ሰውዬ የወለዱት አንድ ልጅ ብቻ ነው…አንድ ብቸኛ ሴት ልጅ፡፡በዛ የተነሳ የበዛ እንክብካቤ፤ ለከቱን ያለፈ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገባት ያለች ልጅ ነች፡፡እርግጥ ቁጥጥሩ ከጊዜ በኋላ የመጣ ነው፡፡እስከ15 ዓመቷ ድረስ በነፃነት ነፃ ሆና ያደገች ልጅ ነበረች…ከ15 ዓመቷ በኋላ ግን ከጤንነቷ ጋር በተያያዘ ነገሮች የተለየ መልክ ያዙ….፡፡

በፀሎት የልብ ህመምተኛ መሆኗ የታወቀው ከ15 ዓመቷ በኋላ ነበር ፡፡ 17 ዓመት ከሞላት በኋላ ግን ነገሮች ፈር ለቀቁና ህመሟ ከፍተኛ ደረጃ ደረሰ…በየሄደችበት ቦታ የተለየ ነገር ገጥሟት ትንሽ ስትጨናነቅ መውደቅና እራሷን መሳት ስትጀምር…24 ሰዓት በክትትል ስር እንድትሆንና ጠባቂዎች ከአጠገቧ እንዳይለዩና በመንገዷ ሆነ በማንኛውም እንቅስቃሴዋ ምንም አይነት እንከን እንዳያጋጥማትና ካጋጠማትም በፍጥነት አፋፍሰው ሆስፒታል እንዲወስዷት የታቀደ የጥንቃቄ እርምጃ በአባቷ ተወሰደ ..በዚህ ውሳኔ መሰረት ሳትወድ በግዷ ነፃነቷም ተነጠቀ፡፡

በፀሎት በአስተዳደጓ ምክንያት ገና የታዳጊነት ህይወቷን ሳታገባድድ ነው  ህይወት ስልችት ያለቻት፡፡ አቶ ኃይለ መለኮት ስጦታው ሀብታቸውን ተከትሎ ባለዝና እና ታዋቂ ከመሆናቸውም በላይ የተናገሩት የሚደመጥላቸው፤ ያዘዙት የሚፈፀምላቸው ተፈሪ ሰው ናቸው፡ወይዘሮ ስንዱ መሸሻ የአቶ ኃይለ መለኮት የትዳር አጋር ናቸው..አብረው በጋብቻ 28 ዓመት አሳልፈዋል፡፡

ከዚህ ውስጥ በዚህ ትዳር ውስጥ ፍቅር አብሯቸው የነበረው ለስምንት ዓመት ያህል ብቻ ነበር፡፡ከዛ በኋላ አንድ ቤት በጋራ ተጋርተው ከሚኖሩ ዳባሎች የተለየ ትርጉም ያለው ትዳር አልነበረም..አንደውም እርስ በርስ በእየእለቱ እያደገ የሚሄድ ጥላቻ…አንዱ ሌለኛውን ለማበሳጨትና ደስታ ለመንጠቅ የሚደረግ ተንኳልና አሻጥር እናም ደግሞ ከዛም አልፎ አንዱ ሌለኛውን ለማስወገድ እስከመመኘት የሚደረስ የበቀል ስሜት …..በቃ በጋብቻቸው ውስጥ ያለው ነገር ይሄ ነው፡፡አዎ ሁለቱም ወላጆቾ በመረረ የእርስ በርስ ጥላቻ ነፍሳቸው የበከተ..አንደኛው የሌለኛውን ጉዳት ብቻ ሳይሆን ሞትም ጭምር አምርሮ የሚመኝ.. አንድ ህንፃ ውስጥ በሚገኝ ሁለት ክፍል ውስጥ ተነጣጥለው የሚተኙ….የጋራ ጣሪያና የጋራ ሳሎን ስለሚጠቀሙ የሚቀፋቸው…..የሁለት አለም ሰዎች ናቸው..ወላጆቾ፡፡ግን ይህ ሁሉ ሆኖ ሁለቱም በእኩል ደረጃ ከልባቸው የሚያፈቅሩት አንድ ነገር አለ..ልጃቸውን፡፡ብቸኛ ልጃቸው በፀሎት…፡፡ ከተጋቡ ከስድስት አመት በኃላ በስንት ስለትና የህክምና እርዳታ ነው የወለዷት..ስሟንም በፀሎት ያሏት በፀሎት አገኘንሽ ለማለት ፈልገው ነው፡፡ከእሷ በፊትም ሆነ ከእሷ በኋላ ሁለቱም ሌላ ልጅ አልወለዱም….ሳይፈልጉ ቀርቶ አይደለም…እንዴትስ ላይፈልጉ ይችላሉ?፡፡ የዚህን ሁሉ ሀብት ወራሽ ሚሆን ስድስት ሰባት ልጆች ቢኖራቸው ምን አልባት በመሀከላቸው ያለው መራራቅና ጥላቻ የዚህን ያህል ሊንቦረቀቅ አይችልም ነበር ብላው ብዙዎች ያወራሉ….…ያም ሆነ ይህ አሁን በዚህ ወቅት ከ28 ዓመት የጋብቻ ቆይታ በኃኋላ ሆድ ከጀርባ በሆነ ግንኙነት የ22 ዓመት ልጃቸው የልደት በዓል በጋራ በአማረ እና በሸበረቀ ሁኔታ ለማክበር ሽርጉድ እያሉ ነው፡፡

አዎ በፀሎት ዛሬ የልደቷ ቀኗ ነው ፡፡ የ22 ዓመት የልደት በዓሏ፡፡በዚህም ምክንያት ቦሌ ከመድኃንያለም ቤተክርስቴያን ጀርባ ሁለተኛ መንገድ ላይ በሚገኘው ቤታቸው ድል ያለ የልደት ዝግጅት አዘጋጅተው ከ100 በላይ ሰዎች ተጠርተዋል፡፡እርግጥ ይሄን የልደት ዝግጅት ቀደም ብላ አልፈለገችውም ነበር፡፡አቧቷ ነው ችክ ብሎ ካልተደገሰ ያለው፡፡በኋላ እሷም በዝግጅቱ ደስተኛ ሆነች፡፡በዝግጅቱ ላይ ከታደሙት መካከል ግማሽ ያህሉ የእሷ የዩኒቨርሲት ጎደኞቾ እና መሰል እኩዬቾ ናቸው፡፡ቀሪዎቹ ደግሞ የሁለት ተፃራሪ ፓርቲ የጋራ ስብሰባ ላይ የታደሙ የሚመስለው የእናቷ እና የአባቷ የቅርብ ሰዎችና የስራ ባለደረቦች ናቸው፡፡
የድግሱን መስተንግዶ ሆነ የመጠጥና የምግብን ዝግጅት በሀላፊነት ወስዶ እያዘጋጀ ያለው በከተማው አሉ ከተባሉት ሆቴሎች ውስጥ አንዱ ነው፡፡ዲጄ ከመቀጠሩም በላይ የራሱ ባንድ ያለው አንድ ታዋቂ ድምፃዊ በዝግጅቱ ላይ ተገኝቶ ዘፈኑን እንዲያቀርብ ተደርጎል፡፡ለአንድ የ21 አመት ቀንበጥ ወጣት ልደት 3 ሚሊዬን ብር ወጪ ሆኗል ቢባል ማን ያምናል…?ግን የሆነው እንደዛ ነው፡፡

በጸሎት ለልደት በዓሏ በልዩ ትዕዛዝ በሀገሪቱ አለች በተባለች ዲዛይነር የተዘጋጀላትን ውብ ቀሚስ ለብሳ ብዙም ያልደመቀ የተወሰነ ሚካፕ ነካ ነካ አድርጋ የምትወደውን ከፈረንሳይ የተላከለላትን ሽቶ ነስነስ አድርጋ አጠር ባለ ፀጉሯ ላይ 50 ሺ ብር የተገዛ ዘንፋላ ባለ ወርቃማ ቀለም የኢጣልያን ፀጉር ደርባበት በከፊል የተለወጠና የተቀየረ መልኳን ይዛ ከክፍሏ ወጣች..አንደኛ ፎቅ ላይ ካለ መኝታ ቤቷ ቀጥታ የልደት ዝግጅቱ ወደሚካሄድበት ምድር ቤት ወደሚገኘው ግዙፉ ሳሎን ከመሄዷ በፊት ወላጆቾ ወደታች መውረድ አለመውረዳቸውን ለማረጋገጥ ከእሷ መኝታ ቤት በተቃራኒው ኮርነር ጎን ለጎን ወደሚገኘው የወላጆቾ መኝታ ቤት አመራች፡፡መጀመሪያ የሚገኘው የእናቷ መኝታ ቤት ስለሆነ በቀስታ ቆረቆረች..ከውስጥ መልስ እየጠበቀች ሳለች ቀጥሎ ካለው የአባቷ መኝታ ቤት የእናቷን ድምፅ ሰማች…፡፡…ግራ ገባት››

‹‹ውይ..ዛሬ ሰላም ሰፍኗል ማለት ነው… እንደዛ ባይሆን እማዬ አባዬ መኝታ ቤት አትገባም ነበር››ብላ አሰበችና በደስታ ፈገግ ብላ ወላጆቾን ላለመረበሽ ፊቷን አዙራ ልትመለስ ስታስብ በጆሮዋ ሾልኮ የገባው ጠንከር ያለ የእናትዬው ንግግር ከእርምጃዋ ገታት፡፡

ቆም አለች ….ጥርት ብሎ እየተሰማት አይደለም..ፊቷን መለሰችና ወደአባቷ መኝታ ቤት ቀረበች..ጆሮዋን በራፉ ላይ ለጠፈች….ሰቅጣጭ ንግግር እየተመላለሱ ነው፡፡

‹‹እስኪ ከውሽሞችህ መካከል አንዷን እንኳን መርጠህ ብትጠራ ምን አለበት…? ሶስት ውሽሞችህን በአንድ ቤት፣እኔን እሺ ግድ የለም ለእነሱ ስሜት አትጨነቅም…ነው እርስ በርስ አይተዋወቁም..?››

‹‹አሁን ለምንድነው የምትነዘንዢኝ…….?ከፈለግሽ አንቺም ውሽሞችሽን መጥራት ትቺያለሽ››

‹‹በእውነት እንዴት ደግ ነህ እባክህ…..እንኳን ውሽማዬን ወንድ ጓደኞቼን መጥራት እንደማልችል አንተም እኔም እናውቀዋለን››

‹‹ለምን ?ምን ችግር አለው..?ድግሱ እንደሆነ የተትረፈረፈ ነው!!››በሹፈት ቃና የታሸውን የአባትዬውን መልስ ሰማች፡፡

‹‹አዎ የተትረፈረፈ ነው…ግን ውሽማ የለኝም እንጂ ቢኖረኝም ላንተ ስለማስብ አልጠራውም››

‹‹ለምን ?››

‹‹ሌላ የሰው ነፍስ በእጅ እንዲጠፋ አልፈልግም....ምን አይነት ቀናተኛና በሽተኛ እንደሆንክ እኔም አንተም እናውቃለን…እስከዛሬ ገና ለገና ከአንቺ ጋር አወሩ ብለህ ስንት ወዳጆቼን አስገደልክ?፡፡››

አትሮኖስ

21 Sep, 17:00


‹‹የእኔ ፍቅር መጣህ..ይሄ ጉድጓድ እንዴት ነው የሚከፈተው? የምታውቀው ነገር አለ..?ወንድሜን ይዘውት ሳይሄዱ አይቀርም››ቃተተች፡፡
‹‹ተረጋጊ ውዴ..ወንድምሽን ወደውጭ ነው ይዘውት የሄዱት….ምስራቅ ልታስጥለው ተከትላዋለች ፡፡ሚረዷትን ሁለት የእኔን  ሰዎች ሰጥቻታለው፡፡ስለአንቺ ስትነግረኝ አንቺን ለማስመለስ ነው ወደእዚህ የመጣሁት››
‹‹እንዴት ?ማለቴ ምስራቅን እንዴት አወቅካት?››ግራ ያጋባትን ነገር ጠየቀችው፡፡
‹‹የእሷንም የወንድምሽንም ፎቶ እኮ አሳይተሸኛል….እሷም ካርሎስ ነኝ ስላት አወቀችኝ…በይ አሁን ቶሎ ብለን  ከዚህ ስፍራ እንውጣ…….››
ተያይዘው ወደግራውንድ ፍሎር መውጫውን ደረጃ ተያያዙት ፡፡መሳሪያ ከወዲህ ወዲያ ይተኮሳል፤ ራቅ ብሎ ቦንብ ይፈናዳል..የሰው ጩኸትና ለቅሶ ከየቦታው ይሰማል..አየሩ የተጠበሰ እና ያረረ የሰው ስጋ በክሎታል፡፡የግራውንድ ፍሎሩ ላይ በሰላም ደረሱ፡፡ ወደውጭ ወደሚያስወጣቸው በራፍ እየተቃረቡ ሳለ….የአውሮፕላን ድምፅ ሰሙ ካርሎስ እሷን ከስር አደረገና ከላዬ ላይ ተኛባት..ወዲያው የሚያደበላለቅ የፍንዳታ ድምፅ ተሰማ፡፡
…../////….
ምስራቅ ከህንፃው እንደምንም ተሹለክልካ መውጣት ከቻለች በኃላ በቋጥኞች መካከል እራሷን ሸሽጋ ናኦልን ፍለጋ አካባቢውን መቃኘት ጀመረች….ከውስጡ ይልቅ ውጩ በጨረቃ ብርሀን የፈካ ስለሆነ ለእይታ ምቹ ነው፡፡ ብዙም ሳትደክም ሶስት ጋንግስተሮች ናኦልን መሀከላቸው አድርገው በቅርብ እርቀት ወደሚገኝ የጥበቃ ማማ ይዘውት ሲሄዱ ተመለከተች፡፡ከዛ ወደእዛው ለመሄድ ወደግራዋ ዞር ስትል ከእሷ አንድሜትር ርቀት ከፊት ለፊቷ ካለው ቁጥቋጦ ውስጥ የተወሸቀ አንድ ሰው በግንባሯ ትክክል መሳሪያውን ደቅኖ  ተመለከተች…ፊቷ ላይ ባትሪውን ለቀቀባት..
በእጇ ላይ ያለው የቦንብ  ቀለበት ውስጥ እጣቶን ሰንቅራ…አሳየችው….፡›
‹‹ተረጋጊ ..ካርሎስ ነኝ››ሲላት እፎይታ ተሰማት‹‹ኑሀሚስ?››አስከትሎ ያቀረበላት ጥያቄ ነበር፡፡
ከዛ ከኃላው የነበሩ ሁለት ሰዎችን ጠርቶ  እንዲረዷት ነገራቸውና እሱ ኑሀሚን ፍለጋ ወደውስጥ ገባ…..
…////..
ምስራቅ ካርሎስ የሰጣትን ሁለቱን ሰዎች ከኃላዋ አስከትላ ናኦል ወዳለበት ተጠጋች….ሰዎቹን ለማደናገር ናኦል ካለበት ሀያ ሜትር ርቀት አካባቢ ባለች ጎጆ ቤት ላይ ቦንቡን ወረወረች፡፡ አካባቢው በፍንዳታ ተናጋ ፡፡በናኦል ዙሪያ የነበሩ ጋንግስተሮች ሀሳብ ተበታተነ ፡፡በዚህ ጊዜ ምስራቅ አጠገቧ ያሉ አጋዞቾን ናኦልን እንዳይመቱ እየተጠነቀቁ ተኩስ እንዲከፍቱ አዘዘቻቸውና እሷ በጀርባ በኩል ዞራ በደረቷ መሳብ ጀመረች…፡፡አሁን በሶስት ሜትር ርቀት ናኦል እየታያት ነው፡፡በዙሪያው ያሉት ጋንግስተሮች ተበታትነው ሁለት ብቻ ናቸው የቀሩት …ከጀርባቸው ተስፈነጠረችና በአንደኛው ላይ እጆቾን በጉሮሮው ዙሪያ  ሰቅስቃ አንገቱን ቀነጠሰችው፡፡በግራ ያለው ጓደኛው መሳረያውን ወደእሷ ሲያዞር  ከጎኑ ያለው  ናኦም ተጠመጠመበት….መሳሪያው ያለ ኢላማ መንጣጣት ጀመረ……፡፡ምስራቅ በፍጥነት ደረሰችለትና የሰውዬውን ፊኛ በእርግጫ ነረተችው…፡፡.አጓራና መሳሪያውን ለቀቀው..፡፡ናኦል ወዲው መሳሪያውን በማንሳት በልቡ አካባቢ ለቀቀበት..፡፡ሰውዬው ፀጥ አለ….፡፡ምስራቅ ናኦል ላይ ተጠመጠመችበት‹‹…ተርፈሀል..ኦዎ አገኘሁህ›› ብላ ግንባሩን ጉንጩን ትልሰው ጀመር…..፡፡‹‹እወድሀለው እሺ …በጣም ነው ምወድህ…ደግሞ አልፈታህም..እሺ…ደግሞ…..››ንግግሯን ሳትጨርስ መሳሪያ ሲንጣጣ ሰሙ ..ግን አርፍደው ነበር…የተተኮሱት ጥይቶች  ሁሉ በምስራቅ  ጀርባ ውስጥ ነበር የተቀረቀሩት…ላካ ከጀርባ ከለላ ይዞ የጎደኞቹን ሞት ሲመለከት የነበረ ሌላ ጋንግስተር ነበር….የካርሎስ ጓደኞች ተኩሱን ተከትለው ወደተኳሹ ደራርበው በመተኮስ ገደሉት..ግን ያመጣው ውጤት አልነበረም፡፡ ምስራቅ በናኦል እቅፍ ውስጥ እንዳለች ዝልፍልፍ ብላ ወደታች መንሸራተት ጀመረች፡፡
….///..
የአውሮፕላኑን ጆሮ ሰንጣቂ ድምፅ ተከትሎ ህንፃ ውስጥ የነበሩረው ካርሎስ ኑሀሚን ከስር አድርጎ እሱ ካላዬ ተኛ…ወዲያው ከአውሮፕላኑ በተለቀቀ ከባድ ቦንብ አካባቢው በፍንዳታና በእሷት ጉማጅ  ተናጋ…የሰው ጆሮ ጭው ከሚያደርግ  ቀፋፊ ድምፅ ውጭ ሌላ ነገር መስማት አቆመ…ማንም በህይወት ያለ ሰው አይኑን መከፈት አቃተው….ምፅአት የታወጀ መሰለ፡፡ከምን ያህል ደቂቃ በኃላ እንደሆነ አታውቅም….ኑሀሚ ወደቀልቦ ቀስ በቀስ ተመለሰች..ገሮሮዋን ክፉኛ እየከረከራት ነው..መተንፈስም ከባድ ሆኖባታል…እንደምንም አይኗን ስትከፍት ከላዮ ካርሎስ ተኝቶል..‹‹የእኔ ፍቅር…ታፈንኩ እኮ..‹››ምንም እየመለሰላት አይደለም…እንደምንም ከላዬ አንከባለለችውና ከስሩ ሾልካ ወጣች..የሆነ የተደፋ ውሀ አካባቢውን ያጥለቀለቀው መሰላት… ተነከረችበት…ካርሎስን ወዘወዘችው……በእጁ ይዞት  የነበረውን ባትሪ ተቀበለችውና አባራችበት፡፡ውሀ የመሰላት ደም ነበር..ካርሎስ  ጭንቅላቱ ከኃላ በኩል ፈርሶል ….ጀርባው በቦንብ ፍንጥርጣሪ ወንፊት ሆኖል፡፡.ህልም ውስጥ ያለች ነው የመሰላት፡፡

‹‹እንዴት እንዲህ ይሆናል..?ይሄ እኳ የእኔ ሞት ነበር›…በምን እዳህ ሞቴን ትሞትልኛለህ..?››ተንበርክካ አቅፋው ትወዘውዘው ጀመር….፡፡ሁሉ ነገር አስጠላት….፡፡‹‹በቃ እኔም አብሬህ መሞት ነው የምፈልገው…››ይሄንን ስትወስን ስለመንትያ ወንድሟ እንኳን ማሰብ አልፈለገችም፡፡.ከካርሎስ  ጋር ተስተካክላ ተኛች፡፡መሳሪያውን በጉሮሮዋ ትክክል አስተካከለች..እጆን ዘርግታ ምላጩን ለመሳብ ሞከረች…ግን አልተመቻትም…..፡፡የመሳሪያውን አቅጣጫ  ቀየረች..በዛ ቅፅበት ግን ጭለማ የዋጠው አዳራሽ በብርሀን ተጥለቀለቀ…የብርሀኑ መጠን ከአይኗ ማየት  አቅም በላይ ስለሆነ ጨፈነች…ብዛት ያላቸው የእግር ኮቴ እና የመሳሪያ ቅጭልጭልታ ሰማች…ደስ አላትና መሳሪያውን ለቀቀች፡፡ የካርሎስን በድን አቅፋ ተኛች..የእሷ ሀሳብ እየመጡ ያሉት የዳግላስ ሰዎች ስለሆኑ እዛው በተኛችበት ተኩሰው በመግደል ከካርሎስ ጋር እንድትሞት ያደርጉኛል ብላ ነበር….ስሯ ደርሰው አንጠልጥለው ሲሸከሞትና በብስጭት አይኖቾን ገልጣ ሰታያቸው ግን ያሰበቻቸው እንዳልሆኑ ገባት፡፡የአካባቢው መንግስት ወታደሮች እንደሆኑ ተረዳች..ወዲያው አንከብክበው ወስደው ወደውጭ አወጧት…በአካባቢው ክንፏን ጥላ የተኮፈሰች ዳኮታ አውሮፕላን ውስጥ   ይዘዋት ሲገቡ ወንድሞ ናኦል የሆነ አረንጓዴ ፎጣ ተከናንቦ በድንጋጤ እየተንቀጠቀጠ አየችው፣ከጎኑ ስትቀመጥ…ከወለሉ ላይ የተዘረረውን የምስራቅን አስከሬን ተመለከተች፡፡ወንድሟ ላይ ተጠመጠመችበት…..አውሮፕላኗ  በአየሩን እየሰነጠቀች ጥቅጥቁን የአማዞን ደን አናት ላይ እየተምዘገዘገች ብራዚሊያ ስታርፍ ሁሉ ሁለቱ መንትዬች እንደተቀቀቀፉ  ነበር፡፡
….
እንግዲህ ዛሬ ያ ክስተት ከተከሰተ ከአራት ቀን በኃላ እዛ አማዞን ስምጥ ውስጥ የሆነውን እና ያዩትን በጠቅላላ ለሚመለከተው አካል መረጃ ሰጥተው…የካርሎስም እሬሳ ከሌሎች ተለይቶ ከቦታው ተነስቶ ወደቤተሰቦቹ እንዲላክ አድርገው…የምስረቅን ሬሳ  በሚያምር ውብ ሳጥን አሳሽገው ወደሀገራቸው ለመብርር  ዝግጁ ሆነው እየጠበቁ ነው፡፡
ግን መንትዬቹ ከዚህኛው እጦታቸው እና የልብ ስብራታቸው ያገግሙ ይሆን….?ደግመኛ ለማፍቀርስ መች ይሆን ዝግጁ የሚሆኑት…?ለዚህ ሁሉ ጥያቄ ለጊዜው መልስ ባይኖርም አንዳቸው ለአንዳቸው ሲሉ በህይወት መኖራቸውን  እንደሚቀጥሉ ግን በእርግጠኝነት ማወቅ ይቻላል፡፡

ተፈፀመ

አትሮኖስ

21 Sep, 17:00


ስለቆይታችን አመሰግናለው ዘግየትም እያልኩ ያበሳጭኋችሁ እንዳላቹ ይሰማኛል እናንተንም ይቅርታችሁን እጠይቃለሁ ካሁን በኋላ ለሚለቀቁት ታሪኮች ቢያንስ አንድ ቀን ቢዘል ነው እንደበፊቱ ሁለት ሶስት ቀን እያቆየሁ አላበሳጫችሁም ቃል እየገባሁ ነው።

በቅርብ አሪፍ ታሪክ እጀምራለሁ

ቤተሰቦች እስገዛ #YouTube ቻናሌን #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

21 Sep, 17:00


#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)

#የመጨረሻ_ክፍል


#ክፍል_ሀያ_ስድስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


‹‹በል አስወጣቸው››ዳግላስ አንቦረቀ፡፡
‹‹ምን እየሆነ ነው ምን አጠፋን?››ኑሀሚ በተመሳሳይ የድምፅ ቃና  ጠየቀችው፡፡
‹‹ጠላቶቼ ይሄንን ቦታ እንዴት ሊያውቁት ቻሉ?››
‹‹እኛ ታዲያ ምን እናውቃለን? የራስህን ሰዎች አትመረምርም››
‹‹መሳሪያውን ወደ ግንባሯ ደቀነና‹‹እንደንዴቴ ሶስታችሁንም እዚህ ግንባር ግንባረችሁን ደፍቼያችሁ እሄድ ነበር፡፡ግን እንዳደረሳችሁብኝ ኪሳራ በሰላም እና በቀላሉ መሞት አይገባችሁም…ሶስታችሁም እባክህ ግደለን እያላችው በየቀኑ እንድትለምኑኝ ነው የማደርገው…በተለይ አንቺን…በሉ ያዟቸው..››

እሱን ከበው የነበሩ ጋንግስተሮች ወደቤት ውስጥ ገቡን ሶስቱንም እየገፈተሩ ወደውጭ አስወጣቸው…..በኮሪደሩ አልፈው ሳሎን ገቡ …ከዛ በደረጃው ወደግራውንድ ይዘዋቸው ሄዱ…ሰው ሁሉ ይተረማመሳል….መሳሪያዎች ከመጋዘን እየወጡ ይታደላሉ..ሀገር ወራሪ መጥቶ ለፊልሚያ እየተሰናዱ ነው የሚመስለው….ወደምድር ቤት ይዘዋቸው ወረዱ….ምድር ቤት ያለው  ትርምስ ከግራውንዱም ይብሳል….የተመረቱትን ኮኬይን አሰተካክለው ካርቶን ውስጥ በማስገባት ያሽጋሉ… ሌሎች ደግሞ የታሸገውን ወደጥግ እየወሰዱ ይደረድራሉ….ዳግላስ  እነኑሀሚን ለጠባቂዎቹ ተዋቸውና እያንቧረቀ ትእዛዝ በመስጠት ወደሰራተኞቹ ሄደ፡፡
‹‹እንዴ ይሄን ሁሉ ኮኬይን የሚደረድሩት እንዴት ሊየደርጉት ነው?››ምስራቅ ነች በሹክሹክታ የጠየቀችው፡፡
ኑሀሚን‹‹አልገባኝም ….ምን አልባት…..››ብላ ግምቷን መናገር ስትጀምር ያልጠበቁት ነገር ከፊት ለፊታቸው ተመለከቱ፡፡ የምድር ቤቱ ጥግ ላይ ያለ ወለል እንዴት አድርገውት እንደሆነ አይታወቅም ሲከፈት አዩ…
‹‹እንዴ!! ከዚህ በታች እቤት አለ እንዴ?››ናኦል ነው በገረሜታ የተናገረው፡፡
‹‹አይ እቤት አይመስለኝም….ከዚህ አካባቢ                                   ማምለጫ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ነው፡፡
‹‹አንቺ እውነትሽን ሳይሆን አይቀርም…››
ስትል ሰዎች በካርቶን የታሸገውን ካርቶን እየተሸከሙ በተከፈተው ወለል በመሄድ እንደመሰላል  ባለ ብረት እየተንጠለጠሉ ወደታች መውረድ ጀመሩ፡፡፡
‹‹ሰዎች ትክክል ነኝ…ይሄ ከዚህ ስፍራ ማምለጫ የምድር ውስጥ መንገድ ነው….እናም እኛንም በዛ ውስጥ ይዘውን ሊሄዱ ነው››ኑሀሚ ነች ተናጋሪዋ፡፡
ምስራቅ‹‹የሆነ ነገር ማድረግ አለብን ..እዛ ውስጥ ይዘውን ገብተው ከዚህ ካስመለጡን እንዳለው ለወራት አስቃይቶ ነው የሚገድለን..መሞታችን ካልቀረ ደግሞ እዚሁ ለማምለጥ እየሞከርን ብንሞት ይሻላል››
‹‹ትክክል ነሽ ለማምለጥ መሞከሪያ ጊዜው አሁን ነው››ናኦልም በምስራቅ ሀሳብ ተስማማች፡፡
ምስራቅ ‹‹ናኦል››ስትል ተጣራች፡፡
‹‹በጣም ነው የምወድህ እሺ፣ማለቴ አፈቅርሀለው››አለችው፡፡
‹‹አውቃለው እኔም አፈቅርሻለው…ግን እያስፈራሺኝ ነው››
‹‹አትፍራ….ኑሀሚ አንቺንም ወድሻለው››
አቦ አንቺ ደግሞ አትረብሺኝ …ኑዛዜ አስመሰልሺው….ትኩረቴን እየበታተንሺው ነው…..ተመልከቱ እነዛ ሁለት ሰዎች ለእያንዳንዱ ሰው የእጅ ቦንብ እያደሉ ነው….ሲቀርብን በፍጥነት የተወሰነ ቦንብ በእጃችን ማስገባት አለብን…ከዛ…..››ኑሀሚ ንግግሯን ሳታገባድድ ምስራቅ ወደጎን ተስፈንጥራ  ጠረጴዛ ስር ሾልካ በመግባት ስትሰወር እነሱን ሲጠብቁ የነበሩ ጠባቂዎች የሚወስዱት እርምጃ ግራ ገብቷቸው ወዲህ ወዲያ ሲራወጡ ኑሀሚ የናኦልን ክን ድ ይዛ በግራ በኩል ስትሮጥ ከጠባቂዎቹ አንዱ ተወርውሮ የናኦል እግር ላይ ተጠምጥሞ አስቀረው….ኑሀሚ ወንድሟን ለቃ ሩጫዋን ቀጠለችና ከኮኬይኑ ካርቶን ጀርባ ተሰወረች….አንዱ መሳሪየውን ደቅኖ ተከተላት…በአየር ላይ ተንሳፈፈችን ጉሮሮውን ዘጋችለት…እጥፍጥፍ ብሎ ስሯ ወደቀ..መሳሪያውን ተቀበለችና ምላጩን ተጭና ዝም ብላ አንደቀደቀችው…እቅዷ ትርምስ መፍጠር ነው…ያሰበችው ተሳካላት፡፡ ሰው በፊትም ስጋትና ድንጋጤ ላይ የነበሩ ሰራተኞች የመሳሪያ መንደቅደቅ ሲሰሙ ሚይዙት የሚጨብጡት ጠፍቷቸው ከወዲህ ወዲያ መተረማመስ ጀመሩ ፡፡ይህ ደግሞ ለነኑሀሚ ጥሩ ሁኔታ ፈጠረላቸው፡፡
///
ወደቀኝ ታጥፋ ጠረጴዛ ተከልላ የተሰወረችው ምስራቅ ተንሸራታ ቦንብ የምታድለው እንስት ላይ ነው የተከመረችባት …ልጅቷ በድንጋጤ ቦንብ ያለበትን ካርቶን ለቀቀችው፡፡ መሬት ወድቆ ተዘረገፈ….ምስራቅ ልጅቷን በአንድ እጇ ይዛ በሌላ እጆሶስት ሚሆኑ ቦንቦችን ያዘች….ከግራ በኩል ይተኮስባት ጀመር..ምርጫ ስላልነበራት ልጅቶን ከፊት ለፊቷ  አቆመቻት…የሚተኮሰው ጥይት ሁሉ ልጅቷ ሰውነት ውስጥ ተሰገሰገ….ምስራቅ ወደኃላ አፈገፈገችና ቦታዋን ለቀቀች….ተኳሹ መሬት ላይ ከተዘረገፍት ቦንቦች አንድን አገኘው….አካባቢው ባልተጠበቀ ፍንዳታ ተናጋ…ዋና ዋና መብራቶቹ ጠፉና ጭላንጭል ድንግዝግዝ ብርሀን ብቻ ቀረ… ምድር ቤቱ በጥቁር ጭስ ተዋጠ…ምስራቅም ኑሀሚም በየፊናቸው  ናኦልን ሲፈልጉ ድንገት ተገናኙ….

‹‹ናኦልን አይተሸዋል…?››ኑሀሚ ነች ጠያቂዋ፡፡
‹‹አላየሁትም እየፈለኩት ነው፡፡ወደውጭ ይዘውት ወጥተው ሊሆን ይችላል›››ምስራቅ መለሰች፡
‹‹አይ በምድር ውስጥ ይዘውት ገብተው ከሆነስ..?እኔ ወደእዛ ልሂድ አንቺ ወደውጭ ውጪና ፈልጊው፡፡››
‹‹እርግጠኛ ነሽ….?››
‹‹አዎ ጊዜ አናጥፋ…››ተስማሙ……
ምስራቅ ወደውጭ መውጫው ከሚራኮቱት ሰዎች ጋር እየተጋፋች ስትሄድ ኑሀሚ ደግሞ ወደውስጠኛው የምድር ውስጥ መሹለኩያ ሮጠች…..፡፡
ኑሀሚ አስር ሜትር ርቀት ሲቀራት ወደእሷ ተተኮሰባት… ወደግራዋ ተስፈነጠረችና የሆነ የብረት ካዝና ስር ከለላ ይዛ እራሷን ለመከላከከል መተኮስ ጀመረች…

‹‹አንቺ ሸርሙጣ..ነይ ውጪ››የዳግላስ ድምፅ መሆኑን ለየች….እልክ ተናነቃት፡

‹‹እየተኮሰች ተሸለክልካ በመሀከላቸው ያለውን ርቀት ወደሳባት ሜትር አጠበበች…፡፡አሁን በግልፅ እየታያት ነው….አልማ ተኮሰች…ሆዱን ቦተረፈችው…አጎራና መሬት ተዘረረ…..፡፡ከግራና ከቀኝ ጠባቂዎች ወጡና ግማሹ ወደእሷ እየተኮሱ ለጓደኞቻቸው ሽፋን መስጠት ጀመሩ፡፡ ሁለቱ ደግሞ በደም የጨቀየውን ዳግላስን  እየጎተቱ ወደተከፈተው ጉድጎድ አስገቡት…ወደታች ይዘውት ወረዱ.፡፡ከዛ  እነሱ ተከተሉ…አንዱን ግንባሩን ብላ አስቀረችው፡፡ወደጉድጓዱ ተስፈነጠረች…ወንድሟን ይዘውት ሄደው ከሆነ መከተል አለባት…አንድ እርምጃ ሲቀራት እንዴት እንደሆነ በማታውቀው ዘዴ ወለሉ ተመልሶ ተዘጋ ፡፡ወደውስጥ የሚያሾልክ ምንም አይነት ቀዳዳ ሆነ ክፍተት በአካባቢው የለም፡፡መሳረያውን በወለሉ ላይ አርከፈከፈች…በንዴትና ተስፋ መቁረጥ በጉልበቷ ተናበረከከች…በዚህ ጊዜ ከኃላዋ አንድ በጣም ደስ የሚል ከገነት የመሰላ የጥሪ ድምፅ ሰማች‹‹…ኑሀም ኑሀሚ››
‹‹ዞር አለች››
‹‹ኑሀሚ ካርሎስ ነኝ››
ተንደርድራ ድምፅ ወደሰማችበት አካባቢ ተስፈነጠረች…..ኦ እራሱ ነው….በወገቡ ዙሪያ ቦንብ ደርድሮ  እንደዘንዶ የተጠመዘዘ ዝናር በጀርባው አንጠልጥሎ ዘመናዊ አውቶማቲክ መሳሪውን ደቅኖ አገኘችው…ተጠመጠመችበትና ከንፈሩ ላይ ተጣበቀች….

አትሮኖስ

19 Sep, 18:37


አትሮኖስ pinned «#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ ( በአመዞን ደን ውስጥ) ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አምስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ናኦልና ኑሀሚ ብራዚል ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ  ይገኛሉ.. ከኢትዬጵያ ደህንነት መስራቤት ተልእኮ ተሰጥቶችው የመጡ ሁለት የደህንነት ሰዎች አብረዋቸው አሉ…ሁለቱ መንትዬች በኮንክሪት ግግር እንደቆመ ሀውልት ጎን ለጎን ተጣብቀው  ቆመዋል…ከፊት ለፊታቸው በአንድ ሜትር ርቀት አንድ የታሸገ የሬሳ ሳጥን…»

አትሮኖስ

19 Sep, 18:35


#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ_አምስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ናኦልና ኑሀሚ ብራዚል ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ  ይገኛሉ.. ከኢትዬጵያ ደህንነት መስራቤት ተልእኮ ተሰጥቶችው የመጡ ሁለት የደህንነት ሰዎች አብረዋቸው አሉ…ሁለቱ መንትዬች በኮንክሪት ግግር እንደቆመ ሀውልት ጎን ለጎን ተጣብቀው  ቆመዋል…ከፊት ለፊታቸው በአንድ ሜትር ርቀት አንድ የታሸገ የሬሳ ሳጥን ወለል ላይ ተቀምጦ ይታያል…እሬሳውን ጭኖ ወደኢትዬጵያ የሚበረው አውሮፕላን በሰላሳ ሜትር ርቀት ላይ ይታያል…እዛ ሬሳ ሳጥን ውስጥ ለዘላለም አሸልባ  የተኛችው ምስራቅ ነች፡፡

ናኦል እና ኑሀሚ ከዳግላስ ወጥመድ አምልጠው የሲኦል ወጥመድ ከሆነው ከእዛ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ወጥተው እንሆ አስተማማኝን ቦታ ላይ ቆመዋል…ከአንድ ሰዓት በኃላ በአገራቸው አየር መንገድ ወደሀገራቸው ለመብረር ዝግጅታቸውን ሁሉ አጠናቀዋል…ግን እዚህ ለመድረስ የከፈሉት መሰዋዕትነት ሁለቱንም እስከወዲያኛው ያፈራረሳቸው ነው፡፡አሁን በድናቸው ነው የሚንገዋለለው፡፡እግዚያብሄር በእድሜያቸው መጀመሪያ በዛ በህፃንነታቸው ጊዜ  ሚወዱዋቸውን ወላጆቻቸውን በመንጠቅ አሸማቆቸው ነበር  በእድሜያቸው አጋማሽ ደግሞ በእድሜ ልካቸው አብራቸው የነበረችውን፤ ከጎዳና አንስታ ህይወት የሰጠቻቸውን፤የተዘረፈውን  የወላጆቻቸውን ንብረት ያስለመለሰልችላቸውን.. እናም ከዛም አልፍ እሷን ለማትረፍ አህጉር አቆርጣ እዚህ ሁሉ ጣጣ ውስጥ የገባችላቸውን የዚህችን  ሴት ህይወት ማጣት ለሁለቱም ቅስም ሰባሪ ነው፡፡ለናኦል ደግሞ ነገሩ የተለየ ነው….ይህቺን ሴት ገና የ12 ዓመት ልጅ እያለ እዛ በረንዳ ፤ላይ ካያት ቀን ጀምሮ በልዩ ሁኔታ ይወዳት ነበር…እዚህ ነገር ውስጥ ያስገባት እራሱ ነው፡፡እህቴ ጠፋችብኝ አፋልጊኝ ብሎ ደወላላት..እሱን ለመርዳ ከጎሬዋ ወጣች..ለብቻው ልትተወው ስላልፈለገች አህጉር አቋርጣ ተከትላው መጣች ..አንድ ወር ሊደፍን ትንሽ ቀን ለቀረው ቀናት በመከራና በስጋት ውስጥ ቢሆኑም እንኳን እጅግ ጣፋጭ የሆነ የፍቅር ህይወት አሳልፈዋል….የህይወትን ጣእም እና የፍቅርን ትርጉም አሳይታዋለች ..አስተምራዋለች፡፡….ከእሷ ጋር የመሰረቱት የውሸት ትዳር ለእሱ በህይወቱ ካጋጠመው ተጨባጭ እውነቶች መካከል ምን እልባትም ዋነኛው  ነው…በሰላም ወደሀገራቸው ሲመለሱ ለምኖና እግሯ ላይ ወድቆ ጋብቻቸው ባለበት እንዲቀጥልና በእሷ እቅፍ ውስጥ ለዘላለም መቅለጥ ነበር የሚፈልገው፡፡እቅዱ እንደዛ ነበር….ብቸኛ ምኞቱም ያ ነበር..፡፡ግን አሁን ሁሉ ነገር እንዳልነበረ ሆኗል….፡፡በሰልም እየሰቀችና እተፍለቀለቀች አብራው የመጣችው ሴት ይሄው ህይወት አልባ በድን እሬሳ ሆነ  በሳጥን ውስጥ ታሽጋ  ወደሀገሯ እየተመለሰች ነው፡፡እና ደግሞ በጣም እያበሳጨው ያለው ነገር  ምንም እንዳልተፈጠረ በህይወት ቆሞ አየር እየሳበ መሆኑን ሲያስብ ነው….ደግሞ እኮ የእሱን ሞት ነው ሞተችው፡፡
ነገሩ እጌት ነው  የተከሰተው  ብለን ወደኃላ ዞረን ስናስታውስ……
..
ከአራት ቀን በፊት  ነው፡፡ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ  የታገቱበት ክፍል ተከፈተ….የመጣው  የተለመደው የዳግላስ ተላላኪ ነው፡፡
ወደኑሀሚ አትኩሮ እየተመለከተ ‹‹ጌታዬ እየጠበቀሽ ነው››አላት፡፡

ኑሀሚ ከ30 ደቂቃ በፊት አምጥቶ የሰጣትን ውብ የራት ቀሚስ ለብሳና ተዘጋጅታ  የጠበቀችው ነበር፡፡ምስራቅንና ወንድሟ ናኦልን ተራ በተራ ጉንጫቸውን ሳመችና በዝግታ እርምጃ ልጁን ተከትላ ወጣች፡፡ቀደም ብሎ የተላከላትን ቀሚስ ለብሳ ወደታባለችው የእራት ግብዣ መሄድ የምርጫ ጉዳይ አይደለም…ግዴታ ነው..፡፡በሰዓቱ እያስጨነቃት የነበረው  ከእራት ቡኃላስ ሚለው ነበር?….ወደአልጋ እንሂድ ቢለኝስ?እንደዛ ስታስብ ዝግንን የሚያደርግ ቀፋፊ ስሜት ነበር የተሰማት፡፡እሷ ግን እኮ እንደዛ አልነበረችም፡፡ለአላማዋ ጥቂትም ጥቅም ይኑረው እንጂ ከማንም ወንድ ጋር ተጋድሞ ወሲብ መፈፀም ልክ እንደካርታ ጫወታ  ዘና ብላ ምትፈፅመው ቀላልና ትርጉም የማይሰጣት ጉዳይ ነበር…ደግሞም በሰላይነት ሕይወቷ እንዲጠቅማት በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ላይ በቂ ስልጠና ወስዳለች…አሁን ግን አንድ ነገር ገብቷታል..ለካ በዛን ጊዜ ነገሩ ቀላልና የማያስጨንቅ ሆኖ የሚታያት  ስለሰለጠነችበት ብቻ አልነበረም…ልቧ ኦናና ባዶ ስለነበረ ነበር እንጂ፡፤አሁን ግን አንድ ሰው ገብቶበታል…ያ ሰው ደግሞ እሷን ለማዳን በቅርብ ርቀት ባለ ጫካ ውስጥ ሆኖ እቅዱን ስለሚያሳካበት ዘዴ እየተጨነቀና እያሰበ ነው…እና  እሷ ካለፍላጎቷም ቢሆን ከሌላ ሰው ጋር ወደአልጋ የመሄድን ጉዳይ በቀላሉ ምታየው አይደለም….ይሄ ነው ያስጨነቃት…የተንጣለለው ሳሎን ውስጥ ስትገባ ግዙፉ ጠረጴዛ በምግብና በመጠጥ ተሞልቶ ተመለከተች፣አንድ ሴትና ሁለት ወንድ አስተናጋጆች ፈንጠር ብለው ግድግዳውን ተደግፈው ትእዛዝ በመጠባበቅ ላይ ናቸው…እንደገባች ዳግላስ ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ተራመደ…ቀለል ያለ አለባበስ ነው የለበሰው…ከላይ ሰማያዊ ሸሚዝ ከዳለቻ ጅንስ ሱሪ ጋር አድርጎል…በፈገግታ ተጠጋትና እጁን ለሰላምታ ዘረጋላት…ፈራ ተባ እያለች እጇን ሰነዘረችና ጨበጠችው፡፡

እጇን ሳይለቅ እየጎተተ ወደ ጠረጴዛው ወሰዳትና  ወንበር ስቦ አስቀመጣት..ከዛ ራመድ አለና  ከፊት ለፊቷ ሄዶ ተቀመጠ፡፡ወዲያው ለአስተናጋጆች በእጁ ምልክት ሲያሳይ ተንደርድረው መጡና ብርጭቆቸውን በመጠጥ ሞልተውላቸው ወደቦታቸው ተመለሱ፡፡
ከተቀዳለት መጠጥ አንዴ ጠቀም አድርጎ ከተጎነጨለት በኃላ‹‹እንዴት ነው ቆይታ ?››ሲል ጠየቃት፡፡
ያለምንም ማስተባበል‹‹በጣም አሰልቺ ነው››ስትል ፍርጥም ብላ መለሰችለት፡፡
‹‹እንግዲህ የአጋጣሚ ጉዳይ ሆነና ለስራ ጉዳይ ወጣ ማለት ነበረብኝ…አሁን ግን ተመልሼለው…ከዚህች ደቂቃ ጀምሮ ፍፅም ደስተኛ እንድትሆኚ የተቻለኝን አደርጋለሁ…ከነገ ጀምሮ የአማዛንን ድንቅ ውበት ጎዲያ ጎድጓዳዋን እያዞርኩ አሳይሻለው..እንስሳቱን ፤ወፎችን ፤ፏፏቴዎችንና ወንዙን ሁሉንም አንድ በአንድ አሳይሻለው..እናም ከቦታው ጋር በፍቅር እድትተሳሰሪ የተቻለኝን እጥራለው..ከቦታው ብቻ ሳይሆን ከእኔም ጋር ፍቅር እንዲይዝሽ እፈልጋለው››ሲል ተናዘዘላት፡፡
‹‹እርግጠኛ ነህ ከአንተ ፍቅር እንዲይዘኝ ማድረግ ትችላለህ?››
‹‹እንግዲህ እቅዴ እንደዛ ነው››
‹‹ጥሩ ነው››ብላ በአጭሩ መለሰችለት
‹‹ምኑ ነው ጥሩ?››በጫወታው እንዲገፉበት ስለፈለገ ጥያቄውን ቀጠለበት፡፡
‹‹እስከማውቅህ ድረስ ሁሉንም ነገር    በጉልበትና በማስግደድ ነው የምታደርገው…..ቡኃላ እንዳፈቅርህ ማድረግ ሲያቅትህ እንዳትተኩስብኝ ነው የምፈራው…፡፡››ስትለው ከጣሪያ በላይ ተንከትክቶ ሳቀ..‹‹በይ በባዶ ሆዴ ከዚህ በላይ መሳቅ አልችልም ..እራት እንብላና ወደበረንዳ ወጣ ብለን መጠጣችንን እየተጎነጨን የጀመርነውን ጫወታ እንጨርሰዋለን…››አለና ሰሀን አነሳ …እሷም እንደእሱ አደረገኝ..እራት በልተው አስኪያጠናቅቁ ሀያ ደቂቃ አካባቢ የፈጀባቸው ሲሆን በዛን ጊዜ ውስጥ ብዙም የረባ  ነገር እልተነጋገሩም…፡፡.እራቱ እንደተጠናቀቀ ዳጋላስ እጁን ሊታጠብ ቀድሞ ወደመታጠቢያ ክፍል ገባ …ወዲያው ከአስተናጋጆቹ አንዱ እቃ የሚያነሳሳ መስሎ ተጠጋት እና ጎንበስ ብሎ‹‹ነገ በዚህን ሰዓት››አላት፡፡፡አልገባትም‹‹ዋት››አለችው፡፡ደገመላት‹‹ነገ በዚህን ሰዓት..ተዘጋጁ››ብሎ የተበላበትን  ሰሀን ሰበሰበና እንዳቀረቀረ ከሳሎን ወጥቶ ሄደ፡፡

አትሮኖስ

19 Sep, 18:35


ከእሷ ፍቅር  ከካርሎስ የተላከ መልእክት እንደሆነ ገባት፡፡‹‹እኛን ለማስመለጥ ነገ ልክ በዚህን ሰዓት ጥቃት ይፈፅማሉ ማለት ነው›› ስትል አሰበችና ..ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደመታጠቢያ ቤት ስትሄድ ዳግላስ ደግሞ ታጥቦ ሲወጣ መንገድ ላይ ተላለፉ ፡፡
ታጥባ እንደመጣች ከመቀመጧ በፊት ከመንገድ ላይ ተቀብሎ‹‹ወደበረንዳ እንሂድ›› አላት፡፡   ፊለፊት ወደሚታየው የሳሎኑ በረንዳ ይዞኝ ይሄዳል ብላ  ጠብቃ ነበር ..እሱ ግን በተቃራኒው ወደውስጥ ነበር እየጎተተ የወሰዳት፡፡ ግራ ገባት…፡፡መኝታ ቤቱን ከፈተና ወደውስጥ አስገባት…፡፡ወለሉ መሀል ላይ ያለው አስር ሰው የማስተኛት ብቃት  ያለው  የነገስታት የሚመስለው ግዙፍ አልጋ ነጭ እና ውብ አልጋልብስ ለብሶ ይታያል፡፡ ሙሉ አልጋውና ወለሉ  በአጠቃላይ በአበባ ተበትኖበት ለሙሽራ የተዘጋጀ ክፍል ይመስላል..ይሄንን አይነት ክፍል ይዟት የገባው ካርሎስ ቢሆን ኖሮ በደስታ ብዛት እራሷን ሁሉ ልትስት ትችል ነበር..አሁን ግን ድንጋጤና ፍርሀት ነው የተሰማት፡፡ ቀጥታ መኝታ ቤቱን ሰንጥቆ አለፈና የኃላውን በራፍ በመክፈት ወደባልኮኒው ወጣ…በፍዘትና በተንቀረፈፈ እርምጃ ተከተለችው፡፡ባልኮኒው ላይ ሁለት ምቹ ወንበሮች እና አንድ በመጠጥ የተሞላ  ውብ አነስተኛ ጠረጴዛ  አለ…አንድን እንድትቀመጥበት ጎተተላትና ከተቀመጠች በኃላ ሌለኝ ላይ ተቀመጠ…በእውነት  ባልኮሊው ላይ ተቀምጦ  ጥቅጥቁን የአማዛን ደን በዛ ጭለማ ስትመለከት ልዩ አይነት የድንዛዜ አይነት ስሜት ነው የተሰማት….በአለም ላይ የሚገኝ አንድ ውስን ቦታ ሳይሆን በቤርሙዳ ቀለበት ውስጥ ሾልካ ሌላ ፕላኔት ላይ የተጣለች አይነት ስሜት እንዲሰማት ነው ያደረጋት..መጠጡን እየተጎነጩ ብዙም ያልደመቀ የፈራችውን ያህልም በውጥረት ያልተጨናነቀ ገዜ እያሳለፉ ቀጠሉ…የዚህ የእራት እና የመጠጥ ግብዣው መጨረሻ የቱ ላይ እንደሚያከትም እንዳስጨነቃት ነው..ግን ደግሞ እንዲህ አይነት ፈተና የሚገጥማት ለዚህች ቀን ብቻ ነው‹‹ ልክ ነገ  በዚህን ሰዓት የእኔ ጀግና ከሌሎች ዳግላስን ማጥፋት ከሚፈልጉ  ጠላቶቹ ጋር በመተባበሩ ያስመልጠኛል…ከዛ ምን አልባትም…ሁሉነገር እንደታሰበው በድል ተጠናቆ ከምወደው ካርሎስ ጋር በደስታ ተቃቅፌ ምሳሳምበት ሰዓት ይሆናል››በማለት በውስጦ አሰበችና ሳይታወቃት   ፈገግ አለች፡፡
ሁኔታዋን በትኩረት ሲከታተል የነበረው ዳግላስ ‹‹ፈገግታው ከምን የመነጨ ነው?››ሲል ጠየቃት
‹‹እየሰከርኩ መሰለኝ ይሄ መጠጥ ይብቃኝ….››አለችውና ከጥያቄው ጋር የማይገባኝ መልስ ሰጠችው፡፡
‹‹ገና መች ጀመርነውና….ዘና ብለሽ ጠጪ..እንደምታይው አልጋውም ዝግጁ ነው››አላት..፣፣ለእሱ እስኪታወቀው ድረስ ደነገጠች፡፡
‹‹አይዞሽ አትደንግጪ…መተኛት ብቻ ነው….ሳትፈልጊ የሚሆን ነገር የለም››አላት
‹‹ይሄ ያንተ ባህሪ አይደለም››አለችው
‹‹እና የማን ባህሪ ነው?››  በፈገግታ ጠየቃት፡፡
‹‹እዛ ሊማ አውሮፕላን  ውስጥ አግኝቼው የነበረው  የሚስኪኑ ዳግላስ  ባህሪ ነው››
‹‹ያው እሱን ነው የምወደው ስላልሽ፣ካንቺ ጋር ባለኝ ግንኙነት በተቻለኝ መጠን እሱን ለመሆን እየጣርኩ ነው››
‹‹ይሳካልህ ይመስልሀል?››
‹‹አዎ የአንቺን ልብ ለማሸነፍ …..የግድ ሊሳካልኝ ይገባል››አላትና የጎደለውን ብርጭቆዋን ሞላላትና የእሱን እየቀዳ እያለ ኪሱ ውስጥ ያለው ሞባይል ድምፅ አሰማ ..ጠርሙሱን አስቀመጠና ስልኩን ከኪሱ አውጥቶ ከፈተና አየው..ደነገጠ፡፡
‹‹ምንነው ?ምን ተፈጠረ?››
የኮሎምቢያው ምክትል ጠ/ሚንስቴር ነው የደወለልኝ..በጣም ወሳኝ ጉዳይ መሆን አለበት …አለና አነሳው፡፡ይሄ ሰው የአካባቢው መንግስታትን ጉምቱ ባለስልጣኖች በጉቦ አጨማልቆ እየተጠቀመባቸው እንደሆነ አሰበች በጣም ተገረመች፡፡ እያወሩ ያሉት በስፓኒሽኛ ስለሆነ ምን እየተነጋገሩ እንደሆነ መረዳት አልቻለችም..ግን ከዳግላስ ንዴትና የፊት መቀያየር ነገሩ ከበድ ያለ እንደሆነ ገብቷታል…ስልኩን ዘጋና ከተቀመጠበት ተነሳ….ወደመኝታ ቤቱ ሄደ..በተቀመጠችበት ሆና እየተከታተለችው ነው፡፡ጎንበስ አለና ቁም ሳጥኑ ስር ያለውን ካዝና ከፈተ ፡፡የሆኑ ሰነዶችን አወጣና በአነስተኛ ቦርሳ ከተተና ትከሻው ላይ አንጠለጠለው፡፡ሽጉጡን አወጣና አቀባበለ…ከዛ በግራ በኩል ወዳለው ግድግዳ ሄደና የሆነ የብሬከር ሳጥን የሚመስል የፕላስቲክ ክዳን ያለውን ነገር ከፈተና ተጫነው..ጆሮ ሰቅጣጭ ሳይረን ግቢውን አናጋው…..ግቢውን ለሚጠብቁ ጋንግስተሮችና ለመላው የግቢው ኑዋሪዎች አደጋ ላይ መሆናቸውን እንዲያውቁ ያደረገው ነገር እንደሆነ ገባት፡፡ ኑሀሚ ከመደንገጧ የተነሳ ከተቀመጠችበት መነቃነቅ አልቻለችም..ቀጥታ ወደእሷ ሄደና የያዘውን ሽጉጥ ግንባሯ ላይ ደቅኖ በአንድ እጁ ክንዷን በመያዝ እየጎተተ  ከመኝታ ቤት ይዞት ወጣ.፡፡ሳሎኑ ባዶ ነው፡፡ቀጥታ ወንድሟና ምስራቅ ወዳሉበት ክፍል ነው ይዞት የሄደው …በራፉ ጋር ሲደርሱ ሽጉጡን ከግንባሯ አነሳና የበራፍ ቁልፍ ላይ አነጣጥሮ ተኮሰው ፡፡ የበራፉ ቁልፍ ብረቶች ተበታትነው ወለሉ ላይ ወደቁ ..በእርግጫ ሲለው በራፉ ወለል ብሎ ተከፈተ…፡፡
ምስራቅና ናኦል እርቃን ሰውነታቸው ከአልጋ ላይ ተንከባለው ወርደው እራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል ከለላ ለመያዝ ሲሞክሩ  ነበር…ዳግላስ ኑሀሚን ወደውስጥ ወረወራትና በራፉን  መልሶ ዘጋው…..፡፡
ሁለቱም ከያሉበት ወደኑሀሚ ተንደረደሩና ከግራና ከቀኝ አቀፏት‹‹ምንድነው የሆነው…?.ሳይረኑ ምንድነው…?ለምንድነው የተበሳጨብሽ…?ልትገይው ሞክረሽ ነው?››በጥያቄ ብዛት አጣደፋት፡፡
‹‹አይደለም…ከኮለምቢያ ም/ጠቅላይ ሚንስቴር የሆነ ስልክ ከተደወለለት በኃላ ነው ነገሮች ሁሉ የተቀያየሩት..››
‹‹ወይኔ  የእኛ ሰዎች ሊያስመልጡን እየሞከሩ መሆናቸው ነግረውት ነው፡፡››
‹‹አዎ እንደዛ መሰለኝ….የእነካርሎስ እቅድም ይሰናከላል..በቃ አሁን እራሳችንን ለማዳን መንቀሳቀስ አለብን››
‹‹ምን እናድርግ››
ኑሀሚ የለበሰችውን የእራት ቀሚስ ከላዬ ላይ ሞሽልቃ አወጣችና  የራሷን ሱሪ ለበሰች..ሁሉም ልብሳቸውን እና ጫማቸውን አድርገው ዝግጁ ሆኑ፡፡
‹‹እናንተ እዚህ ጠብቁኝ እኔ  ይሄንን  የመስኮት ግሪል የምናፈርስበትን ነገር ይዤ እመጣለው፡፡››አለች ኑሀሚ፡፡
‹‹እንዴ ግሪሉ በምን ይፈርሳል…?››ግራ የገባው ናኦል ጥያቄ አቀረበ፡፡

‹‹እኔ እንጃ አላውቅም…፡፡ብቻ መሳሪያም ቢሆን ይዤ መጣለሁ፡፡ከዛ ከእዚህ ዘለን ገንዳ ውስጥ ለማረፍ እንሞክራለን… ››
‹‹ብንሰበርስ?››

‹‹እንሰበራ …ዋናው ማምለጣችን ነው››

ምስራቅ‹‹እንደዛ ከሆነ እኔ እሻላለሁ….እኔ ልሂድ›› ብላ ወደውጭ መራመድ ስትጀምር ኑሀሚ ፊቷ ተጋረጠች….፡፡
ኑሀሚ ለመስማማት አልፈቀደችም‹‹እኔ እሄዳለው አልኩሽ…››.ብላ እሷን ወደውስጥ ገፍትራ ልትወጣ በራፍን ስትከፍት ዳግላስ አስፈሪ ሆነው  አስፈሪ መሳሪያ በታጠቁ አራት ሰዎች ታጅቦ በራፍ ላይ ገጭ አለባት…..ከዛ በድንዛዜ ወደኃላዋ አፈገፈገች፡፡

አንድ ክፍል ቀረው...........

ይቀጥላል


ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

17 Sep, 17:00


‹‹እንተኛ…?.በዚህ ሰዓት ?ገና አንድ ሰእት እኮ ነው››ናኦል ተቃውሞውን አሰማ፡፡

‹‹አውቃለሁ ግን እንተኛ በቃ….ከውስጥ ግቡ ››አለችና ብርድልብሱን ሰቅስቃ ከውስጥ ገባችና እነሱም እንዲገቡ አደረገች….ምስራቅ ኑሀሚ ለምን ባልተለመደ መልኩ በዚህ ሰዓት መተኛት እንደፈለገች ለማወቅ ሰልጓጓች እናድርግ ያለቻትን ያለተቃውሞ አደረገች …ናኦል ግን ምንም የጠረጠረው ነገር ስለሌለ አሁንም በንጭንጩ እንደገፋበት ነው፡፡

መተኛታችን ካልቀረ እኔ ብቸኛ ወንድ ስለሆንኩ ከመሀከላችሁ ልተኛ?››አዲስ ጥያቄ አቀረበ፡፡

‹‹አይቻልም ይልቅ ብርድልብሱን ተከናነቡ››ኑሀሚ ፍርጥም ብላ ሀሳቧን ሰነዘረች፡፡

ሙሉ በሙሉ በብርድልብሱ ተሸፋፈኑ፡፡ ሁለቱንም እጇቾን  በሁለቱም አንገት  ሰቅስቃ አስገባችና ወደደረቷ አስጠግታ አቀፈቻቸው››ከዘ ሁለቱንም ጆሮ ወደአፎ እንዲጠጋ ካደረገች በኃላ በሰለለ ሹክሹክታ‹‹እንድንሸፋፈን የፈለኩት ከሰዎቹ ካሜራ ለመሰወር ነው፡፡የምነግራችሁ ነገር አለኝ…ካርሎስ የዳግላስን ጠላቶች አሳምኖ ይዞቸው መጥቷል…እዚሁ አጠገባችን ቅርብ ቦታ ነው ያሉት..እዚህ መሀከላችንም ሰው አላቸው…ቅድም ሲፈትሸኝ ነበረው ሰውዬ ከእነሱ ጋር ነው የሚሰራው…እንደዛ ያደረገው ለአኔ መልእክት ለማሳተላለፍ ብሎ ነው…ከነገ ጀምሮ በማንኛውም አመቺ በሆነ ሰዓት ጥቃት ይፈጽማሉ..ምንኛውንም አይነት ተኩስ ወይም ፍንዳታ ስንሰማ ከእዚህ ህንጻ በአፋጣኝ ለመውጣት መሞከር እንዳለብንና ከወጣን በኃላ በጓሮ በኩል ባለው የማዋኛ ገንዳ ባሻገር ወደአለ ጫካ እንድንጓዝ ነግሮናል፡፡››ስትል ወረቀቱ ላይ ያነበበችውን በአጠቃላይ ምንም ሳታስቀር ነገረቻቸው፡፡

‹‹ከዚህ ህንፃ ታዲያ እንዴት ነው የምናመልጠው፡፡››ናኦል በተመሳሳይ ሹክሹክታ ጠየቀ፡፡

‹‹እኔ እንጃ…ግን በደንብ በማሰብ  የሆነ ዘዴ ማግኘት አለብን……ከተቻለ እነሱ ከውጭ ማጥቃት ሲጀምሩ እኛም ከውስጥ የተቻለንን እንድናደርግ የሚረዳን መሳሪያ ብናገኝ ጥሩ ››ምስራቅ ነች ሀሳብ ያቀረበችው፡፡

‹‹መሳሪያው እንኳን ብዙም አይቸግረንም…እንደሚታወቀው እዚህ እኛ የምንኖርበት ፍሎር ላይ የሚኖሩ ጠባቂዎች ከአራት አይበልጡም… እነሱን በእጅ ለእጅ ፊልሚያ አሸንፍን መሳሪያቸውን መንጠቅ ከባድ አይደለም..ችግሩ እስቴሩን ተጠቅመን ወደታችኛው ወልል ስንሄድ ነው፣፣እዛ ያሉት  ከሀምሳ በላይ ነፍሰበላ አውሬዎች ናቸው ..በእነሱ መሀለ ሰንጥቀን ማምለጥ የማይታሰብ ነው፡፡››ስትል ስጋቷን ተናገረች

‹‹ታዲያ ምን ይሻለናል››ናኦል በጭንቀት ጥያቄ አቀረበ፡፡

‹‹በመስኮት በኃላ በኩል ቀጥታ ወደምድር የምንወርድበትን ዘዴ ማሰብ አለብን፡፡ገመድ ማግኘት አለብን ማለት ነው…..በዛ ላይ ደግሞ መስኮቶቹበብረት ፍርግርግ የተከለሉ ናቸው››

ምስራቅ ትክክል ነሽ…ብቸኛና አስተማማኙ የማምለጫ መንገዳችን በመስኮት በኩል ነው.. ፍርግርጎቹን በሆነ ዘዴ ማስወገድ አለብን ማለት ነው…እንደገመድ የምንተቀምበትን መንጠላጠያም ማግኘት ይጠበቅብናል….ለማንኛውም ዛሬ ለሊት ይሄንን ስናስብ እና ስናሰላስል ማደር አለብን..እስከ ነገ ጥዋት ድረስ ጥርት ያለ እቅድ ነድፈን ዝግጅት እናደርጋለን…ሌላው ደግሞ…››ብላ ልትቀጥል ስትል የበራፍ መከፈት ድምጽ ሰሙና ከተቃቀፉበት ተላቀው የለበሱትን ብርድ ልብስ ከፊታቸው ላይ ገለጡ፡፡የዘወትር አገልጋያቸው…አንድ ሰማያዊ ፔስታል በእጁ ይዞ  በራፉ ላይ ቆሟል

‹‹እ ምን ፈለክ?››አለችው ኑሀሚ

‹‹እንቺ …ይሄ ላንቺ ነው…..ይሄንን ልበሺና ተዘጋጂ..ከ30 ደቂቃ በኃላ መጥቼ ወስድሻለው፡፡››

ግራ ተጋብታ‹‹ወዴት ነው የምትወስደኝ?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹ሀለቃ ዳግላስ እራት አብረሽው እንድትበይ ይፈልጋል››በማለት ያልጠበቀችውን ድብ እዳ ነገራት

‹‹ዳግላስ !!አለ እንዴ?››

‹‹አዎ ከአንድ ሰዓት በፊት ነው የደረሰው››

‹‹እና ከ30 ደቂቃ በኃላ መጥተህ ለእራት ከእሱ ጋር እንድንበላ ትወስደናለህ ማለት ነው?››

አይ አነሱ እዚሁ ነው ሚበሉት….አንቺን ብቻ ነው የምወስድሽ››አለና ፔስታሉን በቅርቡ ባለ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጦ ወጣና በራፉን መልሶ ከውጭ ቆልፎ ሄደ….እነ ኑሀሚ እርስ በርስ ተፋጠው በገረሜታ ተያዩ፡፡
ከዚህ እስርና ወጥመድ የማምለጥ ተስፋቸው  ከፍ ባለበት ቅፅበት የዳግላስ ከሳምንት መጥፋት በኃላ ድንገት መከሰት መርዶ ይሁን  የምስራች መለየት አልቻሉም፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose

አትሮኖስ

17 Sep, 17:00


ሚያስበው፡፡፡
ኑሀሚ ምስራቅ ላይ ተለጥፋ ቆመችና ከንፈሯን በእጇቾ ከልላ‹‹ምን አቅደሽ ነው››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ምን አቀድኩ››

‹‹ጫማሽን ምታወልቂ አስመስለሽ… ስለት ነገር ከወለሉ ላይ አንስተሸ ፓንትሽ ጠርዝ ላይ ስትወትፊ አይቼሻለው››
‹‹አይዞኝ አታስቢ የሰውዬውን ጉሮሮ አልበጥስብሽም››

‹አትቀልጂ…ሙከራችን በደንብ የታሰበበትና እና የሚያዋጣ መሆን አለበት…አትቸኩይ..››

ምስራቅ‹‹አታስቢ …አልኩሽ እኮ›› ብላ ተንቀሳቀሰችና ዘላ ገንዳ ውስጥ ገባች….ኑሀሚም ተከተለቻትና ገባች…ምስራቅ ወደግራ በኩል መዋኘቷን ስትቀጥል… ኑሀሚ ቀጥታ ወደ ዳግላስ መዋኘት ጀመረች….የምስራቅ እቅድ ዳግላስን መግደል ከሆነ ልታስቆማት ይገባል..አሁን ባሉበት ሁኔታ እሱን መግደል….የሚያመጣው ምንም ጥሩ ነገረ የለም..፡አነዛ አወሬ ታጣቂዎች በደቂቃዎች ውስጥ ቦጫጭቀው ይጥሏቸዋል…ከፋም ለማም ከሱ ጋር መደራደርና እሱኑ እለስልሰው ይዞው ትክክለኛው ጊዜ እስኪመጣ መጠበቁ የታሻለ እንደሆነ ታስባለች፡፡እና ወደእሱ የሄደችው ልትከላከልለት ነው፡፡
ስሩ ስትደርስ ‹‹እሺ ደግላስ ማለት የትኛው ነህ፡፡ስትል ጠየቀችው ፡፡

‹‹ማለት››

‹‹ዳግላስ ማለት አሁን አጠገቤ እዚህ አማዞን ደን መሀከል በነፀው ህንፃ ልዩ በሆነ ገንዳ ውስጥ እየዋኘ ያለው ነው ወይስ ከዛ ፔሩ ሊማ አግኝቼው ኤኪዬቶስ አንድ አልጋ ክፍል ውስጥ አብሬው ያደርኩት ሰው ነው››
‹‹ላንቺ ..የትኛው ቢሆንልሽ ትምርጫሽ››

‹‹ትቀልዳለህ እንዴ…ከዛኛው ዳግላስ ፍቅር ሊይዘኝ እኮ ትንሽ ነበር የቀረኝ …ተጨማሪ አንድ ቀን አብረን ማሳለፍ ብንችል አልቆልኝ ነበር››
‹‹ይሄኛውንም ዳግላስ እኮ ገና እየተዋወቅሽው ነው…ከዛኛው የተሻለ ተወዳጅና ተመራጭ ሊሆን ይችላል››
‹‹አይ በፍፅም …ይሄኛውም ትገደል ብሎ የሞት ፍርድ የፈረደብኝ ነው…ይሄኛው ዳግላስ በአውሬ ሊያስበላኝ የነበረ ነው….ይሄኛው በመርዝ ተመርዤ እንድሞት አድርጎኝ የነበረ ነው፡፡››
‹‹አዝናለው…..ያኛውን ዳግላስ ባመጣልሽ ደስ ይለኝ ነበር..ግን እንደምታይው አሁን ፊትሽ ያለው ይሄኛው ደግላስ ነው፡፡ግን የጊዜ ጉዳይ ነው ይሄኛውንም ዳግላስ ላደረገብሽ ነገር ይቅር ትይዋለሽ…እንደዛኛውም ልትወጂው ትችያለሽ….››
‹‹እኔ እንጃ… አይመስለኝም›› አለችና ሌላ ነገር ልትመልስላት ስትል ምስራቅ ቅፅበታዊ ጆሮ ሰንጣቂ ጩኸት አሰማች… ሁለቱም ተሯርጠው ወደእሷ ሄዱ….አካባቢዋ ያለው የገንዳ ውሀ በደም ቀልሟል… ኑሀሚ አውሬ የነደፋት ነው የመሰላት፡፡
ጎትተው ከገንዳው አወጧት..ናኦል የሚሆነው ግራ ተጋብቶ ወዲህ ወዲያ በድንጋጤ እየተወራጨ ነው፡፡
‹‹አታስቡ ትንሽ ነገር ነው …ወደታች ወደወለሉ ሰምጬ ስዋኛ የገንዳው ወለል ላይ አረፍኩና የሆነ ስለት ነገር ነው እግሬን የቆረጠኝ…..››ስትል ሁኔታውን አብራራችላቸው፡፡
ውስጥ እግሯን አንስተው ሲያዮት መሀከሉ ላይ ሽርክት ብሎ ተቆርሷል … በውስጡ የተቀረቀረበትም ጠጠር ተፈንቅሎ የወጣ ነው የሚመስለው፡፡ዳግላስ አበደ ፡፡ ሰረተኞቹን ጠርቶ ጮኀባቸው….እንዴት ስለት ነገር ገንዳ ውስጥ እንዳስገቡ ጠየቃቸው…መልስ መስጠጥ የቻለ  አልነበረም….የሚደርባቸው ቅጣት እየሳቡ በመንቀጥቀጥ ሰሙት፡፡
ወዲያወ የግቢው ሀኪም መጣና ቁስሉን አፀድቶላት በተገቢው መንገድ አሸገለት…ከዛ ሁሉ ነገር ተረጋጋና ሁሉም ልብሳቸውን ለባብሰው ዝግጅቱን ለማተዳም ጠረጴዛ ከበው ተቀመጡ፡፡በግዙፍ ጠራጴዛ ምግቡ ተደረደረ፡፡ መጠጡ ተኮለኮለ፡፡ ጉብታ የሚያህል ባለደረጃ ኬክ እየተገፈ መጣ…አከባቢው ሁሉ በባለ ቀለም የሻማ ብርሀን ተንቦገቦገ…በህይወታቸው በጣም የሚገርም …የሚያምረውንና ውዱን የልደት በዓለቸውን ማክበር ጀመሩ….በሀከል ኑሀሚ ወደምስራቅ ጆሮ ጠጋ ብላ…‹‹እግርሽን ለምንድነው የቆረጥሽው››ስትል ጠየቃቻ..ሆነ ብላ እንደዛ እንዳደረች ያወቀችው እሷ ብቻ ነች፡፡
ዛሬም እንደድሮው የምትገርሚ ሴት ነሽ..አንቺን ደብቆ የሆነ ነገር ማድረግ መቼስ አይተሰብም…ከኢትዬጵያ ስነሳ እንዳይገኝ ተደርጎ እግሬ መሀል የተቀበረ ችብስ ነበር..አሁን ሶስታችንም አንድ ቦታ በመገኘታችን ለሰዎቻችን  መልዕክት ማስተላለፊያ ጊዜው ስለሆነ ነው ያደረኩት..አንቺን እስክናገኝ ነበር የምጠብቀው… አሁን ምልክቱን ሰጥቻቸዋለው….እንግዲ ከቻሉ ያድኑናል››አለቻት፡፡
ኑሀሚ ለይ የተስፋ ብርሀን በውስጧ ሲፈነጥቅ ታወቃት…የካርሎስ ሙከራ ባይሳካ እንኳን ሌላ ትስፋ አላቸው ማለት ነው…በህይወት ተደረራቢ ተስፋ አለ ማለት ደግሞ ለመኖርም ተደረራቢ የኃይል ክምችት አለ ማለት ነው፡፡ዛና ባላ ሁኔታ ልደቷን ማክበር ጀመረች…ዳግላስን እንደጠላቷ እና ለቀናቶች ሊገድላት ሲያሳድዳት እንደነበረ ሰው ሳይሆን ልክ እንደ ረጅም ጊዜ ጓደኛዋ እየተንጠለለችበትና እየተላፋቸው አብራው መደነስ ጀመረች፡፡
///

‹‹ሰውዬው ነካ ያደርገዋል እንዴ?››በማለት እያጉረመረሙ ሶስቱም በንዴት ወደክፍላቸው ገቡ ፡፡

‹‹ሰውዬው ግን እንዴት አንቺን ነጥሎ ጠረጠረ..ነው ወይስ ወዶሽ ይሆን….?››ምስራቅ ነች በቀልድ መልክ አስተያቷን የሰነዘረችው፡፡


   ‹‹ ባክሽ እርሺው ብሽወቅ ነገር ነው…የሚናገረውን ነገርም አያውቅም እኮ!! እስኪ እዚህ ኪሴ ውስጥ ምን ይኖራል?›› ብላ እጇን ወደኪሷ ስትከት የሆነ ነገር አገኘች፡፡ወዲያው መዛ አላወጣችውም…‹‹ወደሽንት ቤት ግቢ››የሚለው የሰውዬው ትዕዛዝ ትዝ አላት…ሁሉም ነገር ትርጉም ሰጣት፡፡‹‹ቆይ ሽንቴ መጣ ብላ ወደሽንት ቤት ሮጠችና ገብታ በራፉን ከውስጥ ቀረቀረች፡፡እጇን ወደኪሷ ከተተች፡፡ አወጣች፡፡ ወረቀት ነው፡፡እርግጠኛ ነች፡፡ይሄንን ወረቀት ያስቀመጠላት የፈተሸት ወታደር እንደሆነ እርግጠኛ ነች፡፡‹‹ግን ማን ነው የላከላት?መልዕክቱ ምንድነው ?….በመስገብገብ ገለጠችው፡፡ማንበብ ቀጠለች፡፡

የእኔ ፍቅር ከአንቺ አጠገብ ነው ያለሁት፡፡ትንፋሽሽ ሁሉ ይሰማኛል..የልብ ምትሽ ድውድውታም ልክ እንደ ጃዝ ሙዚቃ እያዳመጥኩት ነው….ከነገ በኃላ በማንኛውም ሰዓት የሆነ ነገር ሊፈጠር ስለሚችል ሶስታችሁም ዝግጁ ለመሆንና ላለመነጣጠል ሞክሩ….ፍንዳታ ስትሰሙና ግርግር ሲፈጠር እንደምንም ከህንጻው እንዴት መውጣት እንደምትችሉ ከአሁኑ አስቡበት፡፡በተቻለ መጠን ከውስጥ የሚረዳችሁ ሰው እናመቻቻለን፡፡ ከዛ በጀርባ ባለው በመዋኛ ገንዳው በኩል ወዳለው ጫካ ነው የምትመጡት….በዛ በኩል ያለውን ጥበቃ ቀድመን ስለምናፀዳው ሁሉ ነገር ቀላል ይሆናል….በይ ይሄንን ወረቀት እንዳነበብሽ አስወግጂው…ይሄ ቅዠት አብቅቶ አብሬሽ ወደኢትዬጵያ እስክጓዝ ቸኩያለሁ››ይላል…..

ውስጧን የሚያነዝር አይነት ደስታ ነው የተሰማት…ከዚህ በፊት ከወደደችው በላይ ወደደችው…እናም ደግሞ ናፈቃት…አሁን በዚህችው ደቂቃ አግኝታ ልትጠመጠምበትና ልትስመው ተመኘች..ወረቀቱን አፎ ውስጥ ከተተችና አኘከችው….ከራሰና ከተበጣጠቀ በኃላ ገንዳ ውስጥ ተፋችውና ውሀውን ለቀቀችበት ፤እየተበታተነ በቱቦ ውስጥ ገብቶ ተሰወረ….አፏን ተጉመጠመጠችና የተቀረቀረውን ክፍል ከፍታ ወጣች…ወንድሟና ምስራቅ አልጋው  ላይ ጎን ለጎን ተኝተው ሲጎነታተሉ ነበር የደረሰችው፡፡የእሷን መምጣት ሲመለከቱ አደብ ገዝተው በተኙበት እሷን መመልከት ጀመሩ፡፡ወደእነሱ ሄዳ መሀከላቸው ሰቅስቃ ገባችና እንደእነሱ ተጋደመች፡፡
‹‹እህቴ ደግሞ ››ናኦል ተነጫነጨ

‹‹እህቴ ምን?››

‹‹ይሄ ሁሉ ክፍት ቦታ እያለልሽ በመሀከላችን ምን አስገባሽ?››

‹‹እንደውም እነዚህ ሰዎች እራት እስኪያመጡልን ትንሽ እንተኛ…››የሚል ያልጠበቁትን ሀሳብ አቀረበች፡፡

አትሮኖስ

17 Sep, 17:00


#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ_አራት
፡፡
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


የተወሰነ አርፈው ናፈቆታቸውን ካቀዘቀዙ በኃላ ናኦል‹‹እህቴ ዛሬ ቀኑን ታውቂያለሽ….››ሲል ግራ ያጋባትን ጥያቄ ጠያቃት፡፡
ወንድሜ ደግሞ መንጋትና መምሸቱን ካልሆነ በስተቀር እለቱና ቀኑኑ መለየት ካቀምኩ ቆየሁ…ለካ በህይወታችን ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ ነገሮች በመከራ ቀኖቻችን ውስጥ ስንሆን ትርጉም አይኖራቸውም፡፡››
‹‹እንግዲያው ልንገርሽ ዛሬ ጥር 11 ነው …ልደታችን ነው፡፡››

ያልጠበቀችውን ዜና ነው የነገራት….መላ ሰውነቷን ነው የወረራት‹‹ኦ …ደሰስ ይላል…››መልሰው ተንጫጩ …..
ምስራቅ‹‹እናንተ ለምን እነዚህ አስተናጋጆቻችንን ጥቂት ውለታ አንጠይቃቸውም…››የሚል ድንገቴ ሀሰብ አቀረበች፡፡
‹‹ምን ››

ልደታችሁን  ለማክበር  የሚሆን  ጥቂት  ሻማ  …የተወሰነ  ከረሜላ  ካለ…ኬክም  ቢገኝ አንጠላም…ኮኬይንም  ቢያቀርቡልን ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው…››አላች…ተሳሳቁ፡፡
‹‹ሌላውን አላውቅም.. ኮከይኑ ግን አይጨክኑብንም…..›› ምስራቅ ወደ መጥሪያው ሄደችና ተጫነችው…
‹‹እንዴት ፍቅር ምን ፈልገሽ ነው››ናኦል ምስራቅን ጠየቃት..ኑሀሚ ሁለቱንም አፈራረቀች ና       በገረሜታ ታያቸው ጀመር..ምስራቅ የእሷን ምልከታ ሳታስተውል ‹‹ትቀልዳላችሁ እንዴ.. ከመጠየቅ ደጅ አዝማችነት ይቃራል፡፡ሲባል አልሰማችሁም፡፡››በማለት በራፉ በድጋሚ ለማንኳኳት እጇን ስትሰነዝር  ….በድንገት በራፉ ተከፈተ…፡፡
ኑሀሚን ያመጣት ወጣቱ ልጅ ነው በራፉን የከፈተው…. የሚፈልጉትን ጠየቀችው፡፡ ‹‹ሀለቃዬን ጠይቄ ከፈቀደ የሚሆነውን አደርጋለው››ብሎ መልሶ በራፉን ዘግቶ ሄደ….፡፡ኑሀሚ ግን  በነበረችበት እንደፈዘዘች ነው፡፡
‹‹ምንድነው ያፈዘዘሽ››

‹‹የእኔ ፍቅር አለሽ እኮ…አንቺም ወዬ አልሺው ››

‹‹እና ›

‹‹እኔ እዚህ በአማዞን ጫካ ከአውሬውም ከሰው አውሬውም ለማምለጥ በመጣር ፍዳዬን በማይበት ሰዓት እናንተ ፍቅሬ ማሬ መባባል ጀመረችሁ››
‹‹ታዲያ በመሀከላችን ያለውን ለዘመናት የታፈነ ፍቅር ጭረን ካላቀጣጠልነው አንቺን ለመፈለግና ለማግኘት የሚያስችለንን ብልሀትና ጥንካሬ ከየት እናመጣን…. በነገራችን ላይ ያው አንቺ ወደ እዚህ እንደመጣሽ ሰሞን ነው የተጋባነው…››
‹‹የተጋባነው››

አዎ …ወዳሻንጣዋ ሄደችና የጋብቻ ሰርተ ፍኬታቸውን አውጥታ አሳየቻት…..ማመን አልቻለችም…ምስራቅ የሚያደርጉትን ሆነ የሚያወሩትን ሁሉ ሰዎቻቸው እየተመለከቷቸው እንደሆነ ታውቃለች….የጀመሩትን ማስመሰል አስከወዲያኛው መቀጠል አለባቸው….አዎ ከዚህ እስኪወጡ ከናኦል ጋር ባልና ሚስቶች ናቸው….ከወጡስ በኃላ አንዴት ይሆናል የሚለውን እርግጠኛ አይደለችም…..ልጁን በፊት ከምትወደው በተለየ መንገድ ወዳወለች…..ጠረኑ ክፉኛ ለምዳዋለች…..ፍቅሩ ልቧ ውስጥ እየተንጠባንጠበ ነው…..ይሄንን የጋብቻ ሰርተፍኬት እንደቀልደ በቃ አሁን ጉዛችን አበቅቶለታል ብላ ቀዳዳ የወረቀት ቅርጫት ውስጥ ለመክተት ጥንካሬው መቼም ቢሆን የሚኖራት አይመስላትም፡፡
ከተረጋጉ በኃላ ኑሀሚ ሰውቷን ለመታጠብ ፈለገች እና ወደሻወር ቤት ገባች፡፡ታጥባና ነፅታ ስትወጣ ክፍላቸው ውስጥ የተለየ ነገር ነበር የጠበቃት….በርከት ያሉ የሴት ቀሚሶች እና ሙሉ የወንድ ሱፍ ሱሪ የያዘ ተሸከርካሪ የልብስ መደርደሪያ ወለሉ መሀከል ላይ ተቀምጦ ናአልና ምስራቅ ፊት ለፊቱ  ቆመው በአድናቆት እየተመለከቱት ደረሰች፡፡
ያገለደመችውን ፎጣ በደንብ አጥብቃ አሰረችና ‹‹ምንድነው ይሄ››ስትል ጠየቀች፡፡

‹‹ይህን ያመጣው ልጅ..በጠየቃችሁት ጥያቄ መሰረት ልዳታችሁን ለማክበር ተፈቅዷል…..ከዚህ የሚሆናችሁን ልብስ መርጣችሁ ልበሱና ልደቱ ወደሚከበርበት ቦታ ከ30 ደቂቃ በኃላ መጥቼ ወስዳችኃላው›› ብሎል፤ብለው አስረዷት፡፡
‹‹አንቺ ሰዎቻችን ደግ ናቸው…….መጀመሪያ በደንብ አስደስተውን የምንፈልገውን ነገር እንድናደርግ ከፈቀዱልን በኃላ ከዛ አመስግነናቸው እንድንሞት ነው የፈለጉት፡፡››አለች ምስራቅ፡፡
‹‹እሱስ ቢሆን ማን አየበት  ይመስገን ነው››….ብላ ካመጣጡላቸው ቀሚሶች መካከል ለእሷ
የሚሆናትን መምረጥ ጀመረች….በሀያ ደቂቃ ውስጥ ሶስቱም ልክ እቤተ-መንግስት ከንግሱ ጋር የእራት ግብዣ እንዳላባቸው መኮንንቶች ሽክ ብለው ዘንጠውና አምረው በቀጣይ
የሚሆነው መጠበቅ ጀመሩ፡፡

እንደተባሉት ያው ልጅ ቤቱን ከፍቶ ይዞቸው ወጣ፡፡ቀጥታ ከህንፃው በጎሮ በኩል ካለ እስካአሁን ካላዩት በአበቦች ያሸበረቀ የቅርጫት ኳስ ሜዳ ስፋት ያለው የተንጣለለ  የመዋኛ ገንዳ ያለበት ቦታ ነው የወሰዳቸው፡፡ ገንዳው ዳር ባለ በሰራሚክ ንጣፍ ባማረ ጎጆ የምግብ አይነትና፤ የመጠጥ አይነቶች ሞልተውበታል….ዙሪያውን መቀመጫዎች ሲኖሩ አስተናጋጅ መሰል ሁለት ሴትና አንድ ወንድ ዝግጅቱን ለማሳመር ከላይ ወደታች ይሯሯጣሉ፡፡ይዞቸው የመጣው ሰው ለገንዳው እይታ ምቹ የሆነ መቀመጫ ሰጣችውና ሶስቱም በተርታ ተቀመጡ፡፡
..በትካሻቸው ከባድ መሳሪያ የተሸከሙ ሰዎች በአከባቢ ራቅ ካለ ስፍራ በየተወሰነ ርቀት ፈንጠር ፈንጠር ብለው ሁኔታውን በጥንቃቄ ሲቃኙ ይታያል ፡፡ጥርት ካለው ከአማዞን ደን ሚነፍሰው ልስልና እርጥብ አየር ጋር አብሮ የሚነፍስ ጥኡም የላቲን ሙዚቃ እየተሰማ ነው፡፡በአካባቢው ሌላ ሰው የለም፡፡ድንገት ከገንዳው ብልቅ ብሎ ወደ ዳር የሚወጣ ሰው ተመለከቱ… ከእነሱ በ5 ሜትር  ርቀት ላይ ስለሆነ ማንነቱ ጥርት ብሎ ይታያቸዋል፡፡
ወደ ኑሀሚ በፈገግታ እየተመለከተ‹‹በሰላም ተመልሰሽ ወደቤትሽ በመምጣትሽ ደስ ብሎኛ››አላት፡፡
‹‹እንዴት አልመጣ ….ብጨክን ብጨክን ባንተ ጨክኜ መቅረት እችላላሁ››ብላ ምፀቱን በምፀት መለሰችለት…መልሷ በጣም አሳቀው፡፡
‹‹በጣም ናፍቀሺኝ ነበር….በህይወቴ እንደአንቺ ለማግኘት ያስቸገረኝ ሰው የለም….ድሮም ውድ ነገር ለማግኘት በጣም ከባድ መስዋዕትነት ይጠይቃል…ለማንኛውም መልካም ልደት ለሁለታችሁም…..ሰዎቹ  መሰናዶቸውን እስኪያጠናቅቁ ትንሽ ልዋኝ.. ከመሀከላችሁ መዋኘት    …የሚፈለግ ሰው ካለ ግን መጥቶ መወኘት ይችለል፡፡››ብሎ ወደገንደው መሀል እየዋኘ ሄደ፡፡
ምስራቅ ብድግ ብላ ልብሷን ማወላለቅ ጀመረች….ሁለቱም መንትያዎች ‹‹ሴትዬዋ አበደች እንዴ›› የሚል እይታ አፍጥጠው ያዮት ጀመር…፡፡
‹‹ፍቅር..ምን እየሰራሽ ነው››ናኦል ነው የጠየቃት…በእነዚ ሰው በላ አውሬ በሆኑ ሽፍቶች ፊት እርቃን ሰውነቷን ማሳየቱን ጥሩ ሆኖ አላገኘውም፡፡፡
‹‹ምን ነካችሁ ዛሬ እኮ የአናንተ ልደት ብቻ አይደለም..ጥምቀትም ጭምር ነው..ታዲያ ባገኘነው አጋጣሚ ብንጠመቅ ምን ይላችኃል?፡፡›› ብላ ጎንበስ በማለት ጫማዋን አወለቀችና ወለሉን እየነካካች ወደ ገንደው ተንቀሳቀሰች….ኑሀሚ ተነሳችና እሷ አንዳደረገችው ልብሷን በፍጥነት አወላለቀች.‹‹ሴቶቹ ጤናም የላቸው እንዴ››በማለት አልጎምጉሞ ባለበት መንቋራጠጡን ቀጠለ…ኑሀሚ ልብሷን አውልቃ እንዳጠናቀቀች ሄደችና ምስራቅ ጎን ቆመች…ዳግላስ ገንዳው መሀከል ባለ ከመነደሪ ላይ ተኝቶ ጭንቅላቱን በክንዱ ደገፍ በማድረግ አይኖቹን ሁለቱ እንሰት ላይ ተክሎ በገረሜታ ከሩቅ ይመለከታቸው…እንዲሁ ለማለት ያህል ጋበዛቸው እንጂ ያደርጉታል ብሎ አልጠበቀም ነበር…የኑሀሚን ሙሉ ተክለ ቁመና ሲያይ በሰውነቱ ሁሉ ሙቀት ተረጨና ውጥርጥር አለ…ለሳምንታት ሲያልመውና ሲመኘው የነበረው ገላ ይሄው በእሱ ቁጥጥር ስር ሆኖ ከፊት ለፊቱ እየታየው ነው….እሱ የእዚህ አካባቢ ገዢና አስተዳዳሪ ብቻ ሳይሆን የዚህ አካባቢ አምላክ ..ሁሉን አድራጊ..ሁሉን ፈጣሪ እንደሆነ ነው

አትሮኖስ

16 Sep, 00:28


አትሮኖስ pinned «#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ ( በአመዞን ደን ውስጥ)፡ ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_ሶስት ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ሁለቱም እርቃናቸውን ተኝተው ፊት ለፊት እየተያዩ ማውራት ቀጠሉ? "የሆነ ነገር ትጠይቀኛለህ ብዬ ስጠብቅ ነበር  ግን ማድረግ አልቻልክም"አለችው እንደመደንገጥ ብሎ ፀጉሯን በእጆቹ እየላገ"ምንድነው የእኔ ፍቅር?ምን ልጠይቅሽ?" "ከዚህ በፊት የዛሬ ሳምንት አካባቢ ከዚህ ደን በሰላም ከወጣን ደግመህ…»

አትሮኖስ

15 Sep, 17:50


ሞት አብራ ለመሞት ነው ፅኑ ፍላጎቷ፡፡
እርግጥ ካርሎስ እንዳላት ከዳግላስ ጠላች ጋር በማበር ስለእሱም ሆነ ስለድርጅቱ… ስለሚኖርበት አከባቢና ..ስለግዛቱ የሚያውቀውን መረጃ ሁሉ በመስጠት እሱን እንዲያወድሙትና በዛ ግረግር መካከል እሷን ከወንድሟ እና ከምስራቅ ጋር ሊያስመልጣቸው የተቻለውን ሁሉ እንደሚጥር ቃል ገብቶላታል….ደግሞ የገባውን ቃል ለማክበር የተቻለውን ያህል እንደሚጥር እርግጠኛ ነች…ምን አልባትም በእነዚህ አራት ቀኖች የሚፈልጋቸው ሰዎች ጋር ተገናኝቶ እቅድ እየነደፈ ይሆናል፡፡
አሁን እሷን የጨነቃት እስከመቼ እዚህ አፍነው እንደሚስቀምጧት ነው..የመጨረሻ ተሰላቸች፡፡ እና የሆነ ነገር አድርጋ ትኩረታቸውን ማግኘት እንዳለባት እና ትኩረታቸውን ለማግኘት ደግሞ እንሱን ማበሰጨት አንድ ዘዴ እንደሆነ አመነች፡፡ውጭ እሷ እንድታመልጥ ሳይሆን ከውጭ ሌላ ሰው መጥቶ እሷ ላይ ጥቃት እንዳያደርስ ጥበቃ እያካሄደ የሚመስለውን ወጣት ልታጠቃው እቅድ ነደፈች፡፡ከልተፈታተናት ላትጎዳው ወስናለች…..አፀፋዊ ምላሹ ጠንካራ ከሆነ ግን ቢሞትም ግድ የላትም…፡፡
ዝም ብላ ካለወትሮዋ ወደእሱ ተንቀሳቀሰች፡፡መሳሪውን አዘቅዝቆ እንደያዘ ባልተለመደ እንቅስቃሴዎ ግራ ተጋብቶ አፍጦ እያያት ነው፡፡ቀረበችው፡፡ በመሀከላቸው ያለው ርቀት ሁለት ሜትር ብቻ ሆነ፡፡ወስና እግሯን ልታወናጭፍ ስትል ከወደ በራፉ ብዛት ያለው የእግር ኮቴና ድምፅ ሰማችና ባለችበት ተረጋግታ ቆመች፡፡ፊቷን አዙራ ስታይ እውነትም ሶስት የሚሆኑ የታጠቁ ግሰበች ናቸው ..ወደ እነሱ እየመጡ ነው፡፡ ፊት ለፊቷ በቆመው ልጅ እድለኝነት ተገረመችና ፈገግ አለች፡፡
ወዲያው ነበር አፋፍሰው ይዘዋት የወጡት፡፡የ 20 ደቂቃ የእግር መንገድ ካስኬዷት በኃላ ወንዝ ዳር አካባቢ ደረሱ፡፡ወዲያው ጀልባ ላይ ነው ይዘዋት የወጡት…ከዘ በኃላ ለአንድ ሰአት ተኩል ያህል ከጀልባ  አልወረዱም..አሰልቺ የሆነ ጉዞ ነበር የተጓዙት፣ከዛ ባልጠበቀችው ሁኔታ እዛ ጥቅጥቅ ደን ውስጥ ሚኪና ነው የጠበቃት፡፡አንከውክወው መኪናው ውስጥ አስገቧትና ጥቁር ጨርቅ በጭንቅላቷ አጥልቀው አንገቷ ድረስ በማልበስ ሙሉ በሙሉ እይታዋን ከለሉት፡፡ በጥቅጥቅ ደን ውስጥ የእግር መንገድ በምትመስል ቀጭን መንገድ ጫካውን እየሰነጠቁ፤አውሬዎችን እያስደነበሩ፤ለሁለት ሰዓት ያህል ይዘዋት ተጓዙና  ድንገት የመንገዳቸው መጨረሻ ደረሱ፡፡መኪናዋ እንደቆመች የተሸፈነችበት ፅልመታዊ ጥቅር ልብስ ከጭንቅላቷ ላይ ገፈው አነሱላት፡፡ወዲያው ከአካባቢው ብርሀን ጋር እራሷን ማሳማማት አልቻለችም…ብዥ አለባት፡፡ቀስ እያለች ዙሪያ ገባዋን ማየት ስትችል እዛ ደን ውስጥ ይገኛል ብላ ያልጠበቀችው  አንድ ግዙፍ ግቢ ከፊተ ፊቷ ገጨ ብሎ አየች፡፡እንድትወርድ በምልክት ነገሯት፡፡ ወረደች፡፡ውስጧን በደስታ ተጥለቀለቀ…አዎ ቦታው እራሱ ነው፡፡ወንድሟና ምስራቅ ጎን ለጎን ሆነው እዚህ ስፍራ የተነሱትን ፎቶ ነው የላከላት…ወንድሟን ልታገኝ በመሆኑ ተደስታ እግሮቾን በአየር ላይ አድርጋ ዘለለች ፡፡
ይዘዋት ከመጡት መካከል አንዱ በተሰባበረ እንግሊዘኛ እንድትከተለው ነግሯት ወደዋናው ቤት ይዞት ሄደ.፡፡አንደኛ ፎቅ ላይ እንደወጡ አንድ ልጅ እግር ወጣት ተቀበላትና ታጣቂውን አሰናብቶ እሷን ይዞት ወደውስጥ ገባ፡፡ግዙፉን ሳሎን እየሰነጠቁ አለፉ… የተወሰኑ ኮሪደሮችን ከለፉ በኃለ የሆነ ክፍል ጋር ሲደርሱ ቆመና ከኪሱ ቁልፍ አውጥቶ መክፈት ጀመረ፡፡
‹‹እናንተ ሰዎች ያማችኃል እንዴ..አሁንም ክፍል ውስጥ አስገብታችሁ ለተጨማሪ ቀን ለትቆልፉብኝ ነው…ወንድሜን እንድታገናኙኝ አፈልገለሁ…ለሀለቃህ ለዳግላስ ንገረው… ወንድሜን አገናኘኝ ብላለች በለው….አሁኑኑ ንገረው››

ልጅ የእሷን ንግግር ከቁም ነገር ሳይቆጥር ቁልፉን ከፈተና በራፉን ወደውስጥ ገፋው….
ወለል ብሎ ሲከፈት ገፍትሮ ወደ ውስጥ ይከተኛል ብላ ስትጠብቅ ከውስጥ ያልጠበቀችው ፀጋ ነበር የጠበቃት..ወንድሟና ምስራቅ ቢጃማቸውን እንደለበሱ በሚያምር እና ምቾቱ በተጠበቀ መኝታ ክፍል ውስጥ ጎን ለጎን ቆመው በራፉ ላይ አፍጥጠው ስታይ ማመን አልቻለችም፡፡ ተንደርድራ ሄዳ ተጠመጠመችባቸው.. ሁለቱም ወደላይ ተሸክመው በአየር ላይ እያሸከረከሯት መጨፈር ጀመሩ…ልጁ ለደቂቀ ያህል ፈንጠዝያቸውን ከታዘበ በኃላ መልሶ በራፉን ዘግቶና ከውጭ ቆልፎ ወደስራው ሄደ….፡፡
ከናፍቆተቸው ለመውጣት አንድ ሰዓት በላይ በመተቃቀፍ እና መሳሳም አስፈልጎቸው ነበር…፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


በዛውም list ሊሆን 15 ቀን ብቻ የቀረውን Airdrop ላይ ተሳተፉ  ብዙ ሰው እየተሳተፈ ነው👇👇👇👇


1  t.me/empirebot/game?startapp=hero405867113
🔥Play with me, grow your startup.

💸 +5k coins as your first gift
💵 +25k coins if you have Telegram Premium

አትሮኖስ

15 Sep, 17:50


#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)፡


#ክፍል_ሀያ_ሶስት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ሁለቱም እርቃናቸውን ተኝተው ፊት ለፊት እየተያዩ ማውራት ቀጠሉ?

"የሆነ ነገር ትጠይቀኛለህ ብዬ ስጠብቅ ነበር  ግን ማድረግ አልቻልክም"አለችው

እንደመደንገጥ ብሎ ፀጉሯን በእጆቹ እየላገ"ምንድነው የእኔ ፍቅር?ምን ልጠይቅሽ?"

"ከዚህ በፊት የዛሬ ሳምንት አካባቢ ከዚህ ደን በሰላም ከወጣን ደግመህ ጠይቀኝ ብዬህ ነበር...አሁን ሳስበው ግን ጥያቄውን ሙሉ በሙሉ ረስተኸዋል…በፊትም ከልብህ አልነበረም የጠየቅከኝ ማለት ነው "አለች እንደማኩረፍ ብላ።
"አንቺ በጣም ተሳስተሻል...ያንን ጥያቄ ለደቂቃም ረስቼው አላውቅም..አሁን ደግሜ ብጠይቃትና እምቢ ብትለኝ እንዴት ነው የምቋቋመው?"ብዬ ሰግቼ ነበር ...
"እና "

"እናማ...አንቺ ቆንጆ ጠይም ወጣት ወደሀገርሽ ይዘሽኝ ብትበሪ ምን ይመስልሻል?"

"ይዞ መሄድን ይዤህ ሄዳለው።ግን ልመለስ ብትል ማንም አይሰማህም"

"ይሁን ተስማምቼያለው...አልፎ..አልፎ ሀገሬ ሲናፍቀኝ ይዘሽኝ መጥተሽ እንደምታሳይኝ እተማመናለው።››
"እሱን ፀባይህ እየታየ የሚወሰን ነው።"ብላ ከመኝታዋ ተነሳችና እርቃን ገላዋን ለእሱ እይታ አጋልጣ ወረደች..ቀጥታ ወደሰካችው ስልኳ ሄደችና ነቀለችው።ተመልሳ መጣችና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ ብላ ወደሀገር ቤት ወንድሟ ጋር ደወለች.፡፡ከሰከንዶች በኃላ የወንሟን ተወዳጅ ድምፅ በጆሮዋ ሲንቆረቆር ልትሰማ እንደሆነ ስታስብ ሰውነቷን ሌላ ዙር ሙቀት ወረራት...ግን እንዳሰበችው የወንድሟ ሞባይል ሊጠራ አልቻለም...ደግማ ሞከረች።በሁለተኛ ቁጥሩም ሞከረች ተመሳሳይ ነው።
"ብሽቅ...በዚህ ቀን ሞባይሉን ያጠፍል"ተበሳጨች።ሌላ ተለዋጭ ሀሳብ መጣላት።የምስራቅ ቁጥርን ከሞባይሏ ፈለገችና ደወለች።ልክ እንደወንድሟ ስልክ የእሷም አይሰራም።
‹‹የሰዎቹ ስልክ ሁሉ አይሰራም"በተኛበት አይኖቹን እያቁለጨለጨ እየተመለከታት ለነበረው ካርሎስ ነገረችው። ከተኛበት ተነሳና ከአልጋው ወርዶ አልጋ ልብሱን ከአልጋው ላይ ገፎ እርቃን ሰውነቷን በማልበስ"አይዞሽ ተረጋጊ...አህጉር አቋራጭ ጥሪ እኮ ነው እያደረግሽ ያለሽው፡፡ ኔትወርኩ ችግር ሊኖርበት ይችላል...አሁን ባይሆን ጥዋት ሲነጋ ሊሰራ ይችላል...ካልሆነም ሌላ ዘዴ እንፈልጋለን።››ሲል ሊያፅናናት ሞከረ፡፡
ሌላ ዘዴ ሲላት በአእምሮዋ ተለዋጭ ዘዴ ብልጭ አለባት፡፡ ለወንድሞ...ነፃ እንደወጣችና ከቀናት በኃላ ወደሀገሯ እንደምትመለስ ልትፅፍለት ወሰነችና ኢሜሏን ከፈተች። ከአለም እይታ በተሰወረችባቸው 20 በሚሆኑ ቀናቶች በርካታ ኢሜሎች ተልከውላታል።አብዛኛዎቹ ከወንድሟ.. ከዛም ከመስሪያ ቤቷ ሲሆን ለመጨረሻ ጊዜ ግን የተላከላት ከማትጠብቀው ሰው ነበር… በድንጋጤ ከተቀመጠችበት ተነስታ ስትቆም ካርሎስ አልብሷት የነበረው አልጋ ልብስ ከላዩ ላይ ወደቀና እርቃኗን ቀረች...
‹‹ምንድነው ፍቅር...?››

‹‹ሰውዬው ተደጋጋሚ መልዕክት ልኮልኛል?››
ግራ ገባው"የትኛው ሰውዬ?"
"ሀለቃህ...ዳግላስ?"

ከመደንገጡ የተነሳ ተንደርድሮ ወደእሷ ቀረበና ሞባይሉን ከእጇ ተቀበላትና ኢሜሉን ተራ በተራ እየከፈተ አየ...ከዛ በድንጋጤ እግሮቹ ዝሎ ወለሉ ላይ ተዘረፈጠ..ኑሀሚም ድንጋጤው ክፍኛ አዝሏት ስሩ ተንበረከከች፡፡
ስልኩን ተቀብላው ኢሜሉን በማንበብ የሆነውን ለመረዳት የሚያስችል ጥንካሬ ከውስጧ ማግኘት አልቻለችም።ሽው እያለ መጥቶ እርቃን ሰውነቷን የሚገርፋት እርጥብ አየር ነፍሷን ጭምር እያቀዘቀዘው ነው።
"ምንድነው የሆነው?"ጥንካሬዋን አሰባስባ የሆነውን ሁሉ ከእሱ አንደበት ለመስማት ጠየቀችው።ስልኩን መልሶ ከፈተና በኢሜሏ የተላከለትን ፎቶዎች አወጣና"ወንድምሽ...እዚህ መጥቷል"አላት
"ወንድሜ ?እዚህ እንዴት?››ካርሎስ የሚያወራው ነገር ምንም እየገባት አይደለም፡፡

"አላውቅም ግን..እይ ተመልከቺ ዳግላስ እጅ ነው ያለው...ፎቶውን ወደእሷ አቅርቦ እያሳያት"ይሄውልሽ...ይሄንን ቦታ በደንብ አውቀዋለው፡፡ ማንም ሊደርሶበት የማይችለው የዳግላስ ምሽግ የሆነው ሳንቹዋሪ ነው።››
ፎቶውን ተቀበለችና በፍዘት ትመለከተው ጀመር...ዥውውውው አለባትና ቀድሞ ስልኩ ከእጇ ላይ ተንሸራቶ ወደቀባት...ፈጠን ብሎ ሊደግፍት ሲንቀሳቀስ ቀድማ ወደኃላዋ እራሷን ስታ ተዘረረች...በፋጥነት ተነሳና አፋፍሶ አቅፎ አልጋ ላይ አስተኛት።ልብስ ደራርቦ አለበሳትና ከድንጋጤ እስክትወጣ መጠበቅ ጀመረ።
###
ኮሎምቢያ/አማዞ ደን ማህፀን ውስጥ
ካርሎስ በተሰበረ ልብ ምርጫ አልባ ሆኖ በህይወቱ የመጨረሻውን ፍቅር ያፈቀራትን ይቺን ጠይም ኢትዬጵያዊ ሴት ሳይወድ በግድ ከማናአስ ወደ ቲጎና በፕሌን… ከዛ ደግሞ በጀልበ ከብራዚል ድንበር ወደኮሎምቢያ አሻግሯትና ላቲሲያ ከተማ ጫፍ ድረስ ሸኛት፡ከዛ እሱ ከዳግላስ የንፍስ ጠላቶች ጋር ለመደራደር ደቡብ ምእራብ ኮሎምቢያ ድንበር ተጠግታ ወደምትገኘው የቪንዚዎላዋ ሳና-ካርሎስ ከተማ ጉዞ ጀመረ …፡፡
ይህቺን ያፈቀራትን አፍሪካዊ ሴት ማዳን ማለት እራሱን ማዳን ማለት ነው፡፡ሰው እራሱን ለማዳን ደግሞ ምንም ያደርጋል፡፡ዳግላስን ያገኙትን ማንኛውንም አጋጣሚ ተጠቅመው ሊያጠፉት የሚፈልጉ የቢዝነስ ተፎካካሪዎች እንዳሉት ያውቃል..እሱ ደግሞ ስለ ዳግላስ የቢዝነስ ሚስጥሮች ፤ መግቢያ መውጫውን ፤ድክመትና ጥንካሬውን በደንብ ያውቃል…አሁን የሚያገኛቸው ሰዎቹ ደግሞ ሃይልና ብር አላቸው….እነሱ እሱን አምነውት ከተቀበሉትና አብረውት ለመስራት ከወሰኑ ዳግላስን እስከወዲያኛው አስወግዶ ኑሀሚንና ወንድሟን ነፃ ለማውጣት የሰለለችው ቢሆን ተስፋ አለው፡፡ያ ተስፋ ካልተሳካ ነፍሱን እንደሚያስከፍለው ያውቃል…ቢሆንም ግድ የለውም…ያቺ የሰለለች ተስፋ ከመቶ አንድ ፐርሰንት ብትሆንም እንኳን  ከመሞከር ወደኃላ አይልም..ለዛ ነው እሷን ወደዳግላስ ልኮ እሱ የዳግላስን ጠላቶች አግኝቶ ለመደራደር ጊዜ ሳያባክን ጉዞ የጀመረው፡፡
ኑሀሚ ካርሎስ እንደነገራት ላቲሲያ ከተማ በተቀመጠችበት ሆቴል ነው አንድ ሰዓት እንኳን ሰትቆይ የዳግላስ ሰዎች በቁጥጥር ስር ያዋሏት፡፡በመጀመሪያ እዛ ላቴሲያ ከከተማው ወጣ ብሎ አማዞን ወንዝ ደር ካለ ወደ አንድ  ሰዋራ ቤት ነበር የወሰዷት፡፡ለአራት ቃናት ያህል እዛው አስቀመጧት፡፡በየቀኑ የሚያስፈልጋትን ያህል ምግብ ፤ልብስ እና መጠጥ ያቀርቡላታል፡፡ግን ማንም ሊናግራት የሚደፍር ፤ብታናገራቸውም የሚመልስላት አልነበረም፡፡በየቀኑ ምግብ እና መጠጥ እንዲሁም የሚያስፈልጋትን ነገር የሚያመጡ ሁለት ሰዎች አሉ….መጥተው እቤቱ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠውላት ይሄዳሉ….ብታናግራቸው አይመልስላትም፡፡ጠባቂዎቾ እርስ በርስም ቁጥብ ቃላትን ሲለዋወጡ ብትሰማ እንኳን በማይገባት ቋንቋ ስለሆነ ምንም መረዳት የምትችለው ነገር አልነበረም ፡፡ይበልጥ ልትቆጣጠረው የሚከብዳት ጥልቅ ድባቴ ውስጥ እየገባች መጣች፡፡እሷ ካለችበት ቤት አስር ሜትር እርቃ ባለች ጎጆ አንድ ዘመናዊ መሳሪያ የታጠቀ ጎረምሳ ሁሌ ንቁ ሆኖ ሲጠብቃት  ታየዋለች…ወደእሷ መጥቶ ለማውራት   አይሞክርም…እሷም ወደእሱ ለመቀረብ ምንም ጥረት ኣላደረገችም፡፡ይህን ጠበቂ ወይ ጥላው ወይ ገድላው በቀላሉ ማምለጥ እንደምትች ታውቃለች…..ግን ያ አይደለም እቅዷ፡፡ አሁን ሂጂ አምልጪ የሚላት አዛኝ ሰው ቢኖር እራሱ እሺ ምትልበት ሁኔታ ላይ አይደለም ያለችው፡፡አሁን የእሷ ጥረት ወደፊት ስምጥ ወደሆነው የአማዞን ደን ማህፀን ውስጥ ገብቶ ወንድሟን ማግኘት ነው…ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍላት ግድ የላትም፡፡እንደው ወንድሟንና ምስራቅን የማትረፍ እድሉ ባይኖራት እንኳን የዩትን መከራ አብራ አይታ የሚጎነጩትን

አትሮኖስ

12 Sep, 18:04


#ኢትዬጵያዊ_ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ_ሁለት


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ካርሎስና እና ኑሀሚ በአምስተኛ ቀናቸው ነበር ከአከባቢው የተንቀሳቀሱት፡፡በዛን ወቅት ኑሀሚ የተመረዘችው መርዝ ሙሉ በሙሉ ከሰውነቷ ተወግዶ… የሟሸሸ የነበረም ሰውነቷ ተነቃቅቶ….ጥንካሬዋም በተወሰነ ፐርሰንት ተመልሶ ነበረ፡፡ ባለውለታቸውን የሆነችውን ጎጆ በፍቅር ተሰናብተው አካባቢውን ለቀው የአማዞንን ወንዝ ደርቻ ተከትለው በምስራቅ አቅጣጫ ለአንድ ሰዓት ተኩል በእግር ከተጓዙ በኃላ አንድ እሮጌ ጀልባ የያዘ ግለሰብ አጋጠማቸው፡፡ከእሱ ጋር በገንዘብ ተደራደሩና ታብቲንጋ ከተማ ድረስ እንዲያደርሳቸው ተስማምተው ጉዞ ጀመሩ፡፡የዛኑ ቀን አመሻሽ ላይ ያሰቡበት ቦታ ደረሱ፡፡
‹‹ይህቺ ከተማ የአየር ትርንስፓርት አገልግሎት አላት ነው ያልከኝ..?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ አላት..ማኑሳ ድረስ መሄድ ይቻላል፡፡››
‹‹ታድለን…በቃ ነገሮች ወደመጨረሻው ምዕራፍ እየተቃረበ ነው ማለት ነው…ተዲያ ወደከተማው እንግባና የአየር ትኬት ካገኘን እንሞክራ››
‹‹አይ ወደከታማ መግባት አንችልም..፡፡እንደምታያት ይህቺ አንስተኛ የጠረፍ ከተማ ብራዚል ውስጥ ትገኝ እንጂ ለኮሎምቢያ ቅርብ መሆኗን እንዳትረሺ..ያ ማለት ደግሞ የዳግላስ ተፅእኖ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ይኖራል ማለት ነው፡፡ በተለይ ወደ ብራዚል ከገባን ቀጥታ የአየር ትራንስፖርት የሚገኝባት ከተማ ይህቺ ስለሆነች ቀጥታ ወደእዚህ እንደምንመጣና ወደአየር መረፊያ ጎራ እንደምንል በቀላሉ ይገምታል..ስለሆነም ከተማው ውስጥ ዋና ዋና ቦታዎች እና በተለይ ደግሞ አየር ማረፊያ ላይ ሰዎቹን እንደሚያስቀምጥ እርግጠኛ ነኝ፡፡
‹‹እና ምን ይሻለናል?፡፡››በስጋት ጠየቀችው፡፡
‹‹ረጅሙን መንገድ ነው የምንመረጠው..ማለት አሁንም ወደ ምስራቅ ጉዞችንን እንቀጥልና ወደ ቤንጃሚን ኮንስተንት ከተማ ነው የምንሄደው፡፡››
‹‹ቤንጃሚን ኮንስተንት ደግሞ ማን ነች?››
ቤንጃሚን ኮንስተንት አማዞን ደን ውስጥ ከበቀሉ የብራዚል የጠረፍ ከተሞች ውስጥ አንዷ ስትሆን ከተማዋ ጃዋሪ በተባለ ወንዝና በአማዞን ወንዝ ተከባ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ነች፡፡ከዚህ አሁን ካለንበት ከተማ በጀልባ የሁለት ሰዓት ቢፈጅብን ነው፡፡ማንም ወደ ዛች ከተማ ይሄዳሉ ብሎ እይገምተንም…እዛ ከደረስን በኃላ የተሻለ የተባለ ዘመናዊ ጀልባ እንከራይና ቀጥታ ወደ ማናአስ እንጓዛለን፡፡
‹እንዳልክ …ግን የሆነ ቻርጅ ያለበት ቦታ ፈልግን ስልኬን ቻርጅ ማድረግ አለብኝ፡››የምታስበውን ነገረችው፡፡
‹‹ምን ሊያደርግልሽ?››
‹‹ትቅዳለህ..ለወንድሜ ደውዬ ቢያንስ እስከሁን በጤና መሆኔን ላሳውቀው ነዋ፡፡››
‹‹አይ አይሆንም…ስልክሽን አብርተሸ ለወንድምሽ ደወልሽለት ማለት ያለሽበትን አካባቢ ቀጥታ ለሀገርሽ መንግስት እናም ጉደዩን ለሚከታተሉ ለአካባቢው መንግስታት አሰወቅሽ ማለት ነው..ያ ሆነ ማለት ደግሞ ዳግላስም በቀላሉ ዜናውን አገኘ ማለት ነው፡፡እና ሁሉም እኛን ለማግኘት በአካባቢው አሰሳ ይጀምራሉ…ከዚህ በፊት እንዳለኝ ልምድ ደግሞ ከየትኛውም መንግስት ቀድሞ ደጋላስ አፈፍ እንደሚያደርገን እርግጠኛ ነኝ››
‹‹እና ምን ይሻላል?››
‹‹የሚሻለውማ..ማናስ እስክንገባ መቻል….ነው…ወንድምሽም ዘላለም ከሚያጣሽ…ስድስት ሰባት ቀን በናፍቆት እና በትካዜ ቢሰቃይ ይሻላል፡፡አሁን አንቺ እዚሁ አካባቢ እራስሽን ከሰው እይታ ከልለሽ ትጠብቂኛለሽ… እኔ እራሴን ለውጬ ከታማ ገብቼ እመለሳለሁ››
‹‹እንዴ… እኔን እዚህ ብቻዬን ጥለኸኝ ምን ትሰረለህ?››
እጁን ወደኪሱ ሰደደና የሆነ መሀረብ አውጥቶ ቋጠሮውን ፈታና ሁለት የጨው አንኳር የሚመስል አብረቅራቀ መአድን አነሳና በእጇ መዳፍ ላይ አስቀመጠ፡
‹‹ምንድነው?››በመገረም እያየች ጠየቀችው፡፡
‹‹እንቁ ነው..በደኑ ውስጥ በአጋጣሚ በስራ ላይ እያለው በእጄ የገባ ነው..እንደዚህ አይነት ንብረት በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆንም በእጅ ከገባ ለገዛ ጥቅም ደብቆ መስቀመጥ በሞት የሚያስቀጣ አደገኛ ወንጀል ነው..በወቅቱ ለዳግላስ ማሰረከብ ነበረብኝ…እኔ ግን ደመነፍሴ አንድ ቀን አጣብቂኝ ውስጥ ስገባ  ይጠቅምሀል ብሎ ሹክ ስላለኝ..የመጣው ይምጣ ብዬ ደብቄ አስቀምጬው ነበር፣.እና አሁን ወደከተማ ሄጄ ወደገንዘብ ልቀይረው...እረጅም የጀልባ ጉዘ ስለሚጠብቅ ብዙ ገንዘብ ያሰፈልገናል…››
መጀመሪያ እንቁውን መለሰችለት..መልሶ በመሀረቡ ቋጠረውና ወደኪሱ ከተተው..፡፡
ከሷ የእጅ ቦርሳዋን አነሰችና ዚፕን ከፈተች፣ከላይ ያሉትን እቃዎች አወጣች ፡፡ፊቱን አዙሮ ሊሄድ ሲል ከስር እንደታሸገ የተቀመጠውን ዶለር መዥርጣ አወጣችና እጁ ላይ አስቀመጠችለት፡፡
‹‹ይሄ አይበቃም?››
አይኖቹ በመገረም ደመቁ‹‹አንቺ ይሄን ሁሉ ብር ከየት አመጣሽ?››
የዛሬን አያድርገውና ሀለቃህ ዳግስ ነበር የሰጠኝ..እና አይበቃም›››….ብላ እንዴት እንዳገኘች ታሪኩን አስረዳችው
‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ..ይሄ እኮ በጣም ብዙ ብር ነው….በይ አሁን ጀልበ እንፈልግ››አለና ብሩን መልሶላት ቦርሳ ውስጥ ከከተተ በኃላ ተያይዘው ወደፊት ለፊት መራመድ ጀመሩ፡፡
እንደተነጋገሩት እዛው አድረው ንጊት ላይ ወደ ቤንጃሚን ኮንስተንት ከተማ በጅልባ ተጓዙ፡፡ እዛ አንድ ሰዓት ብቻ በማሳለፍ ሌላ ዘመናዊ የተባለ ጀልባ ተከራዩና ወደአማዞኒያ ግዛት ዋና ከተማ ማናአስ ጉዞ ጀመሩ፡.ያው ጉዞ ቀላል አልነበረም….6 ቀን ነው የፈጀባቸው ፡፡ግን ደግሞ በህይወት ረጅም ዘመን ለመኖር ስድስትና ሰባት ቀን መስዋት ማድረግ ያን ያህል ክፉ የሚባል ስላልሆነ አላማረረችም ፡፡
…ታብቲንጋ….ሳኦ ፍረንሲስኮ…ኮረንቲዛ….ዲ አማተራ…ሳኦ ዶሚንጎ….ሳንታ አንቶኒኦ….ሳኦ ፍሊክስ… ሳንታ ሉዚያ… የመሳሰሉን አያሌ ታዋቂ ቦታዎችንና የኣማዞን ወንዝ ዳር ከተሞችን አቋርጠው ማናአስ ከተማ ደረሱ ፡፡
ማናአስ(Manaus) በሀገረ ብራዚል የኣማዞኑያ ግዛት ዋና ከተማ ነች፡፡በብራዚል 2.2 ሚሊዬን ኑዋሪዎች የሚኖሩበት 7ተኛው ትልቋ ከተማ ስትሆን ከተማዋ በአማዞን ደን ውስጥ ከተቆረቆሩ ከ1 ሚሊዬን በላይ ኑዋሪዎች ካሏቸው ሁለት ትልልቅ ከተሞች መካከል አንዶ እና ዋነኛዋ ነች.››
በዛ ላይ የአማዞን ደንን እና የአማዞን ወንዝን ሚስጥር ለመበርበር እና ጥናት ለማጥናት ከመላው አለም የሚሰባበሰቡ ሳይንተስቶችና ተመራማሪዎች በዋናነት የሚከትሙባት ከተማ ነች፡፡በዚህ የተነሳ የአማዞን ልብ የሚል ቅፅል ስም ይሰጧታል፡፡በተጨማሪ አንዳንዶችም የትርፒካሎ ፓሪስም እያሉ ያሞካሻታል፡፡
ማናአስ  ከተማና አካባቢው በኬሚካል ፕሮጀክት..በለውዝ ምርት ….በሳሙና ምርት….በመርከብ ግንባታ እና በጎማ ተክል ምርት በጣም የታወቀች ነች፡፡፡በተለይ በጎማ ምርት ከ1800 አመት በፈት ጀምሮ የታወቀች በመሆኗ ከሀገሪቱ ሀብታም ከተሞች ግንባር ቀደሞ እንድትሆን አስችሏታል፡፡ማናአስ ከተማ በ2014 እ.ኤ.አ የአለምን ዋንጫ ካስተናገዱ 12 የብራዚል ከተሞች አንዷ እንደሆነች ይታወቃል፡፡በከተማዋ ምስራቅ አቅጣጫ ድፍርሱ የኒግሮ ወንዝ እና ሰማያዊው የሶሊመስ ወንዝ አንድ ላይ ተቀላለቅሎ ወደአማዞን በገባርነት የሚፈስባት ልዩና አስደማሚ ስፍራንም በመደመም ማየት ይቻላል፡፡

አትሮኖስ

12 Sep, 18:04


ማናአስ ሲገብ ፍርሀታቸው ከላያቸው ላይ ረግፎ ...የድል ብስራት ፈንጠዝያ ልባቸውን ሲያሞቀውና ...በሀሴት ነፍሳቸው ስትደንስ እየታያቸው ነበር፡፡ በእኩለ ለሊት ለስድስት ቀን ተኩል ከተጓዙበት ጀልባ ወርደው የከሳ አካላቸውንና የወፈረ ተስፍቸውን ይዘው የወረዱት፡፡ቀጥታ ወደከተማዋ መካከል ተጓዙ።ከተማዋም ልክ እንደእነሱ ደምቃና በቀለማት አሸብርቃ ነበር።ልክ እነሱን በፈንጠዝያ ለመቀበል እንዲህ ጠብ እርግፍ ብላ ተዘጋጅታ ያማረች ሙሽራ ነው የምትመስለው ።
እንደምንም የሚያረፍበት ቤርጎ ፈልገው ያዙና ተከራይተው ወደውስጥ ገቡ፡፡ እቃቸውን አራግፈው አስቀመጡ፡፡እሷ ፈጥና ስልኳን እና ቻርጀሯን አወጣችና ሰከችው፡፡ነፃ መውጣቷን ለወንድሞ ደውላ እስክትግረው እና ድምፁንም አስክትሰማ ቸኩላለች፡፡ስልኩን ከሰካች በኃላ ወደአልጋው ሄዳ ቁጭ አለች..ከርሎስም ከጎኗ ተቀመጠ፡፡
‹‹ምንድነው አንተ ከተማዋ እንዲህ ያሸበረቀችው?"ስትል በመንገዷ ያየችውን ነገር ካርሎስን ጠየቀችው።
"ገና በዓልን ለማክበር ነው እንዲህ ሽር ብትን የምትለው...በየአመቱ በዚህ ጊዜ የተለመደ ነው።››
"ውይ ገና ደረሰ ማለት ነው?"
"ታከብሪ ነበር እንዴ?"
"ገናን እንኳን በተለየ ሁኔታ አላከብርም..ግን በሀገሬ ኢትዬጰያ ከ10 ቀን በኃላ የሚከበረውን የጥምቀት በአል ነው በተለየ ሁኔታ የማከብረው።ታውቃለህ አሁን እግዚያብሄር ፈቅዶ እዚህ ከደረስኩ ተጨማሪ ቀናቶችን ማባከን አልፈልግም ....ቀጥታ ወደሀገሬ ሄጄ ከእንዳልኩህ መጪውን የጥምቀት በዓል በሀገሬ ምድር ላይ ከወንድሜ ጋር ማክበር አለብኝ።››
‹‹እና በሳምንት ውስጥ ትሄጂያለሽ ማለት ነው?"ሲል በቅሬታ ጠየቃት።

"አይ ነገ ወደብራዚሊያ ብበር...ከተሳካልኝና ትኬት ማገኝ ከሆነ ከነገወዲያ ወደሀገሬ እበራለሁ..."
"ቆይ ክብረ በዓሉ ሀይማኖታዊ ነው?ማለቴ እንዲህ በትኩረት ልታከብሪው የጓጓሽበት ምክንያት አልባኝም።"
""ሀይማኖተዊነቱ እንዳለ ሆኖ አንድም እኔና ወንድሜ የተወለድንበት የልደት ቀናችን ነው...ሁለተኛው ደግሞ እናትና አባታችንን በሞት የተነጠቅንበት ቀን ነው። በዚህም ምክንያት ግማሽ ደስታ ግማሽ ሀዘን...ከፊል ሳቅ ከፊል ለቅሶ የምናለቅስበት ቀን ነው።በእንደዛ አይነት ቀን ወንድሜን ብቻውን እንዲሆን ማድረግ አልችልም።ለቅሶውንም አብሬው ማልቀስ ሳቁንም ከእሱ ጋር መሳቅ ነው የምፈልገው።››
ካርሎስ ለረጅም ደቂቃ በትካዜ ዝም አለና"አሁን ደስታዬ ሁሉ ጥሎኝ በነነ"አላት፡፡

ደንግጣ በመሀከላቸው ያለውን ክፍተት አስወግዳ ወደእሱ ተጠጋችና "ምነው? ምን ተከሰተ?"ስትል ጠየቀችው።
"እኔ እንጃ አንዳንድ ነፃነት አዙሮ አዙሮ እጦትና ቦዶነት ላይ ነው ሚጥለን… አሁን ነው ያወቅኩት።እንደዚህ ጥልቅ ብቸኝነትና የሚሸረካክት የእጦት ስሜት እንደሚሰማኝ ባውቅ ኖሮ ምን አልባት እዛው የአማዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ እየዟዟርን ዘላለማችንን እንድንኖር አደርግ ነበር"

አንተ ምን አይነት ክፉ ነህ..ትከሻውን በፍቅር ነቀነቀችውና ወደራሷ ጎትታ ጉንጩን ሳመችው፡፡ ወደኃላዋ ስትመለሰ መልሶ ጎተተና ከንፈሯ ላይ ተለጠፈባት፡፡ ...በቀላሉ ሊላቀቁ አልቻሉም፡፡ ተያይዘው አልጋው ላይ ወደኃላቸው ተዘረሩ   ፡፡ከዛ ለመጀመሪያ ጊዜ በምቾት በሚያነጥረው አልጋና በሚለሠልሰው ፍራሽ ላይ ለስላሳ ፍቅር ሰሩ...በሁለቱም ምናብ በተሻለ ምቹ ቦታ ፍቅር መስራት የተሻለ እርካታ ያስገኛል የሚል ስሌት ነበራቸው።ግን እንደዛ አይደለም ...እንደውም ከስቃይ የተለወሰ ተራክቦ ልዩ እና ቸኮሌት አይነት ጣዕም አለው።

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


በዛውም list ሊሆን 22 ቀን ብቻ የቀረውን Airdrop ላይ ተሳተፉ  ብዙ ሰው እየተሳተፈ ነው👇👇👇👇


1  t.me/empirebot/game?startapp=hero405867113
🔥Play with me, grow your startup.

💸 +5k coins as your first gift
💵 +25k coins if you have Telegram Premium

አትሮኖስ

11 Sep, 06:45


🌼ውድ የቻናሉ ተከታዎችእንኳን ለ 2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሠላም  በጤና አደረሳችሁ

❤️በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የደስታ እና የፍቅር አመት እንዲሆን  ለሁላችሁም ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እንመኛለን !

   🌼መልካም አዲስ ዓመት ለሁላችን🌼
@atronosee
         

አትሮኖስ

10 Sep, 19:13


አትሮኖስ pinned «ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ ( በአመዞን ደን ውስጥ) ፡ ፡ #ክፍል_ሀያ_አንድ ፡ ፡ #በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ ፡ ፡ ልጅም ቶሎ ያንጠለጠለውን የእጅ ቦርሳ ጠረጴዛ ላይ አደረገና ከብር የተሠራ የሚመስል ሁለት የእጅ ብራስሌት መጀመሪያ ምስራቅ እጅ ላይ ቀጥሎ ናኦል እጅ ላይ አጠለቀና ከኪሱ ስልኩን አውጥቶ በማብራት ሲነካካ እጃቸው ላይ ያጠለቀላቸው ብራስሌት ቀለሙን ከብራማነት ወደ ደማቅ ሰማያዊነት ቀየረ።ዝም ብሎ ሁኔታውን…»

አትሮኖስ

10 Sep, 19:10


ሀሳቧ ለወንድሞ ደብዳቤ ለመፅሀፍ ነው፡፡ለሊት እንዛ በአየሩ ነጎድጓድ ሲረጭ… ከሰማይ ዶፍ ዝናብ ሲወርድ… በውስጧ በተፈጠረባት ፍራቻ ድንገት ብሞትስ? ወንድሜ የሆነ ነገር ሳልለው እንዴት ይሆናል? ብላ አሰበችና በሰላም ለሊቱ ነግቶ ለጥዋት ፀሀይ ከበቃች ለወንድሟ ደብዳቤ ጻፋ እንደምታስቀምጥ ለራሷ ቃል ገባች፡፡ድንገት ብትሞት ካርሎስ ደብዳቤውን ለወንድሞ አንደሚያደርስላት እርግጠኛ ነች፡፡ ደብዳውን መፃፍ ጀመረች፡፡
ወንድሜ-
…የእኔ ትዝታ
ደህና ሁን
….. ቀንና ማታ
ትዝ ይልሀል ይሄን ዘፈን እየደጋገምኩ ስዘፍንልህ? በጣም እኮ ነው የምወድህ...ገና እናታችን ማህፀን ውስጥ ሆነን እንኳን ምርጥ ጎደኛዬ ነበርክ..እና እዛም ሆነን በጣም ነበር የምወድህ...ከተወለድን በኃላም የእናታችንን ግራና ቀኝ ጡት ተካፍለን አይን ለአይን እየተያየን በፍቅር ስንጠባ ሁሉ እወድህ ነበር...ወላጆቻችን ሞተው ቤታችን ሁሉ በለቀስተኞች ተሞልቶ ዋይ ዋይ በሚባልበት በዛን ወቅት እናትና አባቱን አጥቶ ወንድሜ እንዴት ይቋቋመዋል?ብዬ አጨነቅ ነበር...ግን እኮ የሞቱት የእኔም ወላጆች ነበሩ፤የተጎዳሁት እኔም ነኝ...ግን ደግሞ ከእኔ በላይ አንተ ታሳዝነኝ ነበር።ጎዳና ተጥለን ስንኖርም የእኔ ረሀብ ሳይሆን ያንተ ሆድ መንጓጓት ነበር የሚያሳምመኝ።ብቻ ገና ከፅንሰታችን ጀምሮ እስከዚህች ሰዓት ድረስ አንተ ብቸኛ ወንድሜ ነህ...አንተ ብቸኛ የልብ ጓደኛዬ ነህ...አንተ ብቸኛ ዘመዴና የልቤም የነፍሴም ሰው ነህ።

ወንድምአለም ለስራ በመጣሁበት የሠው ሀገር አንድ ትዝታውን ተነጥቆ አእምሮው የተናጋበትን ሰው በሰባአዊነት ረዳለሁ ብዬ የማልወጣበት ቅርቃር ውስጥ ገብቻለሁ።ሠውን ለመርዳት ሲሉ ችግር ውስጥ መግባት እኮ የአንተ እንጂ የእኔ ባህሪ አልነበረም።ግን ያው ሰው ነኝና አንዳንዴ ስህተት እሰራለሁ… እናም … በቀላሉ የማይታረም ስህተት ሰራሁ።ልረዳው ያልኩት ሰው ኮኬይን አምራች አለምአቀፍ ሽብርተኛ ሆኖ ተገኘ።እኔንም አፍነው አማዞን ማህፀን ውስጥ ጣሉኝ፡፡ ላንተ ለወንድሜ ለመትረፍ ስል ብዙ ታገልኩ፤ሊቀብሩኝ ከቆፈሩት ጉድጓድ ሌላ ሰው ገድዬ በመቅበር ለማምለጥ ሞክሬ ነበር።ከዛ እንደውቅያኖስ ዝርግ እንደሸረሪት ድር የተጠማዘዘና የተወሳሰበ ከሆነው ደን በቀላሉ ወጥቶ የአንተ የወንድሜን አይን ለማየት መቻል ቀላል ሆኖ አላገኘሁትም።ካርሎስ በሚባል አንድ ቀና ሰው ድጋፍ ለማምለጥ ባደረኩት ጥረት ከአጋቾቼ እገታ የራቅኩ ቢሆንም በአጋጣሚ በአንድ መርፌ መሠል እሾህ እጣቴን ተወግቼ ተመርዤለሁ...እርግጥ ይሄ ካርሎስ የተባለው መልካምና ተወዳጅ ሰው ከጫካው ባህላዊ መድሀኒት ፈልጎ አክሞኛል … ፍፅሞ እስከወዲያኛው በመዳኔ እርግጠኛ ባልሆንም የተወሰነ ለውጥ ግን እያየሁ ነው፡፡
አንድ ሩሲያ የስለላ ስልጣና ስወስድ መምህሬ የነበረ ሰው ‹‹በጉዞህ ተስፋ አትቁረጥ...ይሄ የሚሆነው ግን ነገሮች በትንሹም ቢሆን እያደጉና እየተሻሻሉ ከሄድ ብቻ ነው።ነገሮች ባሉበት የቆሙ ከሆነ ወይም እድገታቸው የኃሊት ከሆነ በጊዜ ተስፋ መቁረጥ እና አቅጣጫን ማስተካከል የብልህ ውሳኔ ነው።››ይል ነበር፡፡
ምን አልባት መርዙ ቀድሞ ሰውነቴን የመረዘው መሠለኝ።እና ምን አልባት ወደነእማዬ የመሄጂያ ቀኔ የደረሠ ይመስለኛል።እና እንደዛ ከሆነ መጠንከር አለብህ።አታየኝም ብለህ ብትዝረከረክና እራስህን ብትጥል በጣም ነው ሚደብረኝ።
ይበልጥ ጠንካራና ትልቅ ሰው መሆን አለብህ።ቸኮሌት ፍብሪካው ሲያልቅ ሁሌ በየአመቱ በልደት ቀኔ አንድ ሶስት ካርቶን ለህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ላሉ ህፃናት በእኔ ስም ትሰጥልኛለህ።እነሱ ደስ ሲላቸው እያየሁ እኔም ደስ ይለኛል።
ምስራቅን ቸው በልልኝ።ወንድሜን አደራ ብሎሻል በልልኝ።በጣም ነው የምወድህ የእኔ ወንድም።፡፡
ፅፋ ስትጨርስ ወረቀቱን አጣጠፈችና ከጀርባው የወንድሟን ሙሉ አድራሻ ከነስልክ ቁጥሩ ፅፍበት አጣጥፍ አስቀመጠች።

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


በዛውም list ሊሆን 19 ቀን ብቻ የቀረውን Airdrop ላይ ተሳተፉ  ብዙ ሰው እየተሳተፈ ነው👇👇👇👇


t.me/empirebot/game?startapp=hero405867113
🔥Play with me, grow your startup.

💸 +5k coins as your first gift
💵 +25k coins if you have Telegram Premium

አትሮኖስ

10 Sep, 19:10


ኢትዬጵያዊቷ ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ_አንድ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ልጅም ቶሎ ያንጠለጠለውን የእጅ ቦርሳ ጠረጴዛ ላይ አደረገና ከብር የተሠራ የሚመስል ሁለት የእጅ ብራስሌት መጀመሪያ ምስራቅ እጅ ላይ ቀጥሎ ናኦል እጅ ላይ አጠለቀና ከኪሱ ስልኩን አውጥቶ በማብራት ሲነካካ እጃቸው ላይ ያጠለቀላቸው ብራስሌት ቀለሙን ከብራማነት ወደ ደማቅ ሰማያዊነት ቀየረ።ዝም ብሎ ሁኔታውን ሲከታተል የነበረው ዳግላስ መናገር ጀመረ
"አሁን እንግደህ እህታችሁን እኔ ሳልሆን ለእናንተ ማመጣላችሁ ..እናንተ ናችሁ ለእኔ የምታመጡልኝ..." ብሎ ኑሀሚ የእሱን ሰው ገድላ ከሌላ ከእሱ ሰው ጋር እንደኮበለለች...እስከአሁንም በመላው አማዞን ደን ውስጥ ቢያስፈልጋት ሊያገኛት እንዳልቻለ...እሷን መሞቷን ካላረጋገጠ ወይም በህይወት እጅ ካላስገባት የሰላም እንቅልፍ እንደማይወስደው..ወንድሟን ያስመጣበት ምክንያት ተሳክቶላት እንኳን ማምለጥ ብትችል ለወንድሟ ደህንነት ስትል በፍቃዷ መልሳ እጅ እንድትሰጥ አቅዶ ያደረገው እንደሆነ አብራርቶ ከአሁን ሰዓት በኃላ እዛው እሱ የሚኖርበት ወለል ላይ የራሳቸው ክፍል እንደሚሰጣቸው እና እጃቸው ላይ በተጠለቀላቸው አንባር ሙሉ የ24 ሰዓት ክትትል እንደሚደረግላቸው ነገራቸው። እሷ መጥታ በፍቃዷ እጇን እስክትሰጥ ወይንም መሞቷ እስኪረጋገጥ ድረስ ከክፍላቸው መውጣት እንደማይችሉ...ፀባያቸውን እስካሳመሩና ችግር ለመፍጠር እስካልሞከሩ ድረስ የሚፈልጉት ነገር እንደሚያሟላላቸው አብራርቶላቸው.. ወደክፍላቸው እንዲወስዳቸው አዘዘ...።የታዘዘውም ታጣቂ እየጎተ ወሰዶ አንድ ለቀቅ ያለ ሻወርና ማንበቢያ ክፍል ያለው ባለአንድ ክፍል ቤት ውስጥ አስገብቶ ከውጭ ዘጋባቸው..
እቤት ውስጥ ከገብ በኃላ እንኳን ናኦል እና ምስራቅ  ለረጅም ደቂቃ ደንዝዘውና ፈዘው ማህል ወለል ላይ በዝምታ ተገትረው ነበር።

ናኦል እንባ እየተናነቀው"ምስራቅ ምን ውስጥ ነው የገባነው..?ይሄ ሰውዬ ተጫወተብን"አላት ።
ምስራቅም ወደእሱ ተንደረደረችና  አቀፈችው ።አንገቱ ስር ሽጉጥ ብላ በጆሮው "አትደንግጥ...እቅድ አለኝ"አለችው።

ዝም አለ...ከዚህ ለመውጣት ምን አይነት ተአምራዊ ዕቅድ ሊኖራት እንደሚችል ምንም ሊገለፅለት አልቻለም።ቢሆንም ከሞስራቅ ጋር ባሳለፋቸው በርካታ አመታት ብዙ ተአምር መሳይ ነገሮችን ስትከውንና ደጋግሞም ሲሳካላት ታዝቦልና የተናገረችው ነገር ንቆ ሊያልፈው አልደፈረም።...
ብራዚል/አማዞን ደን ውስጥ
አካባቢው ድቅድቅ ጨለማ ነው፡፡ጨረቃዋም በሰማይ ላይ ብርሀን አልፈነጠቀችም፡፡ከዋክብቱም የከሰሙ መስለዋል ፡፡ኑሀሚ ካርሎስ የሰራላት የአንጨት ርብራብ አልጋ ላይ ተኝታ የእጇ ጥዝጣዜ ታዳምጣለች፡፡እርግጥ ከትናንቱ የተሻ ጤንነት ላይ ብትገኝም ሰውነቷ ግን ሙሉ በሙሉ እደዛለ ነው፡፡በህይወቷ በእንዲህ አይነት ደካማንትና አቅመ ቢስነት ተሰምቷት አያውቅም፡፡ ካርሎስ በሶስት ቀን ውስጥ ሙሉ በሙሉ እደምታገግም ነግሯት ነበር ፡፡ አሁን አሁን ያለችበት ሁኔታ ስታስበው በሶስት ወር ተሽሏት ከዚህ አካባቢ የምትንቀሳቀስ እየመሰላት አይደለም፡፡ያም ሆኖ ግን ትናንትና ጉሮሮዋን ፈጥርቆ ነፍሷን ሊነጥቃት የነበረው ሲኦላዊ ህመም ዛሬ በሙሉ አቅሙ የለም፡፡ያ የሆነው ደግሞ ካርሎስ እጇ ላይ ባሰረለት የባህል መድሀኒት ምክንያት ነው፡፡
እንደምንም አንገቷን ወደ ዳር ሸርተት አድርጋ አየችው፡፡ እዛው ርብራብ አልጋ ጎን ባለ ጠፍጣፍ ድንጋይ ላይ ተቀምጦ አንገቱን በካኔቴራው ሙሉ በሙሉ ሸፍኖ የእንጨት አልጋውን ቋሚ ተደግፎ ጨልጥ ያለ እንቅልፍ ተኝቷል፡፡ አሳዘናት፡፡ቢቻላት ኩርምት ብሎ በተቀመጠበት እንቅልፍ የወሰደውን ይሄን መልካም ሰው ጎትታ ወደራሷ ስባ እሷ የተኛችበት የእንጨት ርብራብ ላይ ከጎኗ ሽጉጥ አድርጋው ብትተኛ ደስ ይላት ነበር ፡፡
ወዲያው ሀሳቧን ሳትጨርስ ነጎድጓድ በሰማዩ አንፀባራቂ ብርሀን እየረጨ ያንቧርቅ ጀመር፡፡የሚያስፈራ ደራጎናዊ ድምፅ አካባቢውን ያናጋው ጀመር፡፡ ኑሀሚ እንኳን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ እንደዚህ አይነት ቦታ ሆና ይቅርና በሀገሯ ሰማይ ስር በገዛ ቤቷ እያለች ሳይቀር እንዲህ አይነት ነጎድጎድ በጣም ነው የሚያስፈራት፡፡፡እንደምንም ደካማ እጃን አንቀሳቀሰችና ትከሻው ላይ አኑራ በመወዝወዝ..‹‹ካርሎስ ካርሎስ›› ስትል ጠራችው፡፡

በርግጎ ተነሳ‹‹..ምን …አመመሽ እንዴ?››
‹‹አይ ነጎድጎድ ፈራለሁ››
ከተቀመጠበት ተነሳና ወደእሷ ተንቀሳቀሰ….ርብራቡ ጠርዝ ላይ ከጎኗ ተቀመጠና እጆቿን በእጆቹ ውስጥ አስገብቶ ያሻሽላት ጀመር፡፡ከእሱ ሰውነት ወደእሷ እየተላለፈ ያለው ሙቀት ብቻ ሳይሆን ብርታትና ጥንካሬ ጭምር ነው፡፡
በድጋሚ‹‹በጣም እኮ ነው የፈረሁት››አለችው፡፡
‹‹አይዞሽ…ስጋታችን፤ፍረሀቶችንና እና ጥርጣሬዎቻችን ሰው በመሆናችን የተሰጡን ፀጋዎች ናቸው፡፡ካለበለዚያማ እህያና በቅሎ መሰል አይነት ስሜቶች ስለሌላቸው ከእኛ የተሻሉ እደለኞች ናቸው ልንል መሆኑ ነው?፡፡››
‹‹እሱስ እውትህን ነው››አለችና ይበልጥ ተለጠፈችበት

ወዲያው ሰማዩን አግቶ ይዞ የነበረውን ዝናብ ዘረገፈው፡፡የተሰራችው ጊዜያዊ ጎጆ ሙሉ በሙሉ በዛ ድቅድቅ ጨለማ የሚወርደውን የዝናብ ውሀ አግዳ ለማስቀረት ጥንካሬው አልነበራትም፡፡ሁለቱም በ5 ደቂቃ ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በዝናብ ራሱ፡፡እሷ ከህመሙና የሰውነት ጥንካሬዋ በመዳከሙ የተነሳ ዝናቡንና ቅዝቃዜውን መቋቋም ስላልቻለች ትዘፈዘፈች፣ካርሎስ የሚያደርገው ጠፋበት፡፡ ሙሉ በሙሉ ወደእንጨት አልጋው ወጣና ከእሷ ተስተካክሎ ተኛ…አቀፋትና ወደራሱ አስጠግቶ ከሰውነቱ ለጠፋት፡፡የናፈቀውን የእናቱን ጡት እንዳገኘ ህፃን ልጥፍ አለችበት፡፡የተሻለ ምቾት ተሰማት፡፡ከዝናብ ውርጅብኝ የምትሸሸግበት መጠለያ ዋሻ ያገኘች አይነት ስሜት ተሰማት፡፡ እጆቹን በረጠበ ልብሷ ስር ሰቅስቆ በማስገባት ሰውነቷን ላይ አሳረፈና ይዳብሳት ጀመር..፡፡ከዛ ቀስ እያለ ከንፈሩን ከንፋሯ ላይ አሳረፈና በቀስታ ይመጣት ጀመር፡፡አሁን ከውስጧ እየተቀጣጠለ ያለው ሙቀት ወደላይኛው የሰውነት ቆዳ በመድረስ ከላይ የሚያርፋባትን ዝናብ የሚያስከትልባትን ቅዝቃዜ እያተነ የሚያስወግድላት እየመሰላት ነው፡፡ጭልጥ ያለ ምናባዊ ህልም ውስጥ ነው የገባችው፡፡ከንፈራቸው ሳይላቀቅ ዝናቡም ከመቆሙ በፊት እሷ ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ወሰዳት፡፡

ስትነቃ ጎጆዋ በጥዋት የደመቀ የፀሀይ ፈንጣቂ አድምቋታል፡፡ሁሉ ነገር ብሩህ ፣ ሁሉ ነገር ዳማቅ ሆኖ ነው እየታየ ያለው፡፡እራሷን ለማንቀሳቀስ ሞከረች፡፡ አሁንም ሰውነቷ እንደተሳሰረ ነው፡፡ወደ ጎን አንገቷን መልሳ ተመለከተች፡፡ ለሊት ጎኗ ተኝቶ የነበረው ጉብል አሁን የለም፡፡አይኖቾን ብታንከራትትም ጎጆው ባዶ ነው፡፡ አንደምንም እራሷን አበረታታ ከተኛችበት ተነሳች፡፡ ዱላ መሰል እንጨት ተደግፋ እንደምንም እግሮቾን እየጎተተች ወደጎጆዋ በራፍ ሄደች፡፡ፊት ለፊቷ ያለው አማዞን ወንዝ እየተገማሸረ ጥሩ አቋም ላይ አንዳለ የማራቶን ራጭ ወደፊት እየገሰገሰ ነው፡፡አካባቢውን የሞሉት ውብና ማራኪ ወፎች ወዲህና ወዲያ አክሮባት እየሰሩ ይዝናናሉ.. አይኖቾን አሩቅ ስታማትር ካርሎስ በ500 ሜትር ርቀት በፓንት ብቻ አማዞን ወንዝ ውስጥ ጠልቆ ገብቶ ዓሳ ላመስገረ ሲዳክር ተመከተችው፡፡ፈገግ አለችና ወደ ውስጥ ተመለሰች፡፡ወደ ሻንጣቸው ተጠጋች ፡፡ውሀ የማያሳገባውን የሻንጣ ዚፕ ከፍታ ውስጥ ያለውን የካርሎስን ማስታወሻ ደብተር ከእነእስኪሪብቶው አወጣች፡፡እዛው መሬት ይዛ ተቀመጠችና ለመፅሀፍ ተዘጋጀች፡፡

አትሮኖስ

09 Sep, 11:46


ውስጧ ተንቦጫቦጨ እና ዝም አለች፡፡እሱ ወደስራው ተመለሰና እየጠበሰ ያለውና ዓሳ አገላበጠ ፡፡ ቀድሞ ጠብሶ ያስቀመጠውን ዓሳ ይዞ ወደ እሷ ተጠጋ የሰራው የእንጨት አልጋ ርብርብ ጠርዝ ላይ ቁጨ አለና ከዓሳው እየቆረሰ እሾኩን በጥንቃቄ ከስጋው እየለየ ያጎርሳት ጀመር፡፡በዝግታና በዝምታ ትጎርስ ጀመር፡፡ይሄ በክፉ ቀኗ በክፉ ሁኔታ ላይ ያገኘችው የበአድ ሀገር ሰው እያደረገላት ያለው እንክብካቤ እና እያሳያት ያለው ፍቅር በህይወቷ ከወንድሟ ውጭ ካለ ሌላ ሰው አግኝታው የማታውቀው ነበርና እጅግ ስሜታዊ አደረጋትና ሳታስበው እንባዋ በጉንጮቾ እየተንከባለለ መርገፍ ጀመር፡፡
‹‹ምን ሆንሽ ..?አመመሽ እንዴ?››ደነገጠ፡፡

‹‹አይ..ደስ ብሎኝ ነው…ህይወቴን ብዙ ጊዜ ደጋግመህ አድነሀታል…እድሜ ልኬን ከፍዬ የማልጨርሰው ውላታ አለብኝ …..እንዴት አድርጌ እንደምከፍልህ አላውቅም…››አለችው፡፡
‹‹ካሰብሽበት ቀላል ነው››አላት

‹‹ምን ንገረኝ….?አደረገዋለው››

‹‹አገርሽ ይዘሺኝ ትሄጂና ታገቢኛለሽ፡፡››
ድንግጥ..አለች…አይኖቾ.ፈጠጡ፡፡
‹‹አረ ተረጋጊ ..ስቀልድ ነው..አትደንግጪ››

‹‹አይ አልደነገጥኩም››

‹‹እሱማ በደንብ ደንግጠሸል..ግን የትኛው ነው ያስደነገጠሸ?››

‹‹ከምንና ከምኑ?››

‹‹ማለቴ ወደሀገር ውሰጂኝ ያልኩሽ ነው ወይስ አግቢኝ ያልኩሽ?››

‹‹ሁለቱም አላስደነገጡኝም..ያው ቀልድህን እንደሆነ አውቃለው…ይሄንን ከመሰለ የምድር ገነት የሆነ ሀገር ለቀህ ውቅያኖስ ሰንጥቀህ አህጉር አቋርጠህ ኢትዬጵያ ድረስ ትሄዳለህ?››
‹‹ካንቺ ጋር ከሆነ አትጠራጠሪ…ይህቺ ኢትዬጵያ የምትባለው ሀገር አንቺን የመሰለች ጠይም መልአክ ማብቀል ከቻለች ምድሯም ለምለም አየሯም ማራኪ እንደሚሆን ጥርጥር የለኝም፡፡››
‹‹እርሱስ ትክክል ነህ …እናንት የአለም ጉዙፍ ወንዝ ቢኖራችሁም እኛ ደግሞ የአለም ረጅሞ ወንዝ  የአባይ ባለቤት  ነን፡፡በተፈጥሮ ሀብት በኩልም ደኑ ብትል፤ ተራራው፤ ሀይቁ ብትል፤ወንዙ፤ በረሀው ብትል፤ እሳተ ጎመራው…የባዬ ደይቨርሲቲ ሀብታም ሀገር ነች፡፡እንደ እናንተ ቡና የኢኮኖሚ ምንጫችን ነው፡፡እንደእናንተ በኳስ ተጫዋቾች ባንታደልም..በኳስ ደጋፊነት እና ተንታኝነት ከእናንተ አንተናነስም፡፡››
‹‹በገለፃሽ እኮ ይበልጥ እያበረታታሺኝና እያስጎመዠሽኝ ነው፡፡››

‹‹እስኪ መጀመሪያ ከእዚህ ደን በህይወት እንውጣና የዛን ጊዜ ሀሳብህን  የማትቀይር  ከሆነ እና ይህንን ጥያቄ ደግመህ የምታቀርብልኝ ከሆነ በሁኔታው ላይ  ደግመን እናየዋለን፡፡

ይቀጥላል

ቤተሰቦች እባካችሁ #Subscribe እያደረጋቹ።
#Share #like and #subscribe my #YouTube 

👇Sebscribe

YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose


በዛውም list ሊሆን 22 ቀን ብቻ የቀረውን Airdrop ላይ ተሳተፉ  ብዙ ሰው እየተሳተፈ ነው👇👇👇👇


1  t.me/empirebot/game?startapp=hero405867113
🔥Play with me, grow your startup.

💸 +5k coins as your first gift
💵 +25k coins if you have Telegram Premium

አትሮኖስ

09 Sep, 11:46


#ኢትዬጵያዊቷ_ሰላይ
( በአመዞን ደን ውስጥ)


#ክፍል_ሀያ


#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ብራዚል/አማዞን ወንዝ አቅራቢያ

ኑሀሚ በሶስተኛው ቀን የሽሽት ጉዞ በህይወትና በሞት መካከል ሆና የመጨረሻዋን ትንፋሿን ለመሳብ ከፍተኛ ጥረት የምታደርግበት ሁኔታ ላይ ወደቀች፡፡ይሄ የሆነው ድንገት ነው፡፡በብራዚል አማዞኑያ ክልል እየጠለቁ ገብተው የአማዞን ደን እየተሸለከለኩ ሰው ያለበት ቦታ ለመድረስ ጥረት ላይ እያሉ ድንገት የሚያምር ቀይና ውብ አበባ አይታ እሱን ለመቀንጠስ እጇን ስትዘረጋ አበባውን ከያዘው የግንድ ቅርንጫፍ ተለጥፎ ያለ እሾክ ነገር ጠቅ አደረጋት፡፡ትንሽ ነው የደም ጠብታ የታየው፡፡ግን ልብላቤው የተለየ የንብ መነደፍ አይነት ነበር፡፡ግን ደግሞ ብዙም ልታካብድ ስላልፈለገች ለጓደኛዋ እንኳን አልነገረችውም ነበር፡፡ከ10 ደቂቃ በኃላ ግን እግሯ መደናቀፍ ስውነቷ መዛል እና በሙቀት መንደድ ጀመረ…ከዛ በግንባሯ ላብ መንቆርቆር ጀመር…
ካርሎስ ድንገት ወደኃላ እየቀረች ስታስቸግረው ዞር ብሎ ሲያያት በጣም ነው የደነገጠው፡፡

‹‹እንዴ ምን ሆነሻል?››

ለመተንፈስ እንኳን እየተቸገረች..‹‹እኔ እንጃ አራሴን ማንቀሳቀስ እያቃተኝ ነው›››

‹‹ታዲያ አትነግሪኝም እንዴ?››አለና ወደእሷ በመጠጋት ደግፎ ለማረፍ ምቹ ወደሆነ ቦታ ወሰዳት እና ምቹ ቅጠል ጎዝጉዞ አስቀመጣት፡፡
ግንባሯን በእጆቸ እየደበሰ ሙቀቷን መለካት ጀመረ…. ‹‹የወባ መከላከያ አልወሰድሽም እንዴ?››
‹‹አረ ወስ..ጄ..ለሁ››በተቆራረጠ ትንፋሽ መለሰችለት፡፡

ግራ ገባው…‹‹.እስቲ ግንዱን ደገፍ በይ…››አላት፡፡
ደገፍ እንድትል ሲረዳት የቀኝ እጇን የመሀል እጣት ተመለከተ ….ለብቻው ተነርቶ አብጧል፡፡‹‹እንዴ እጣትሽን ምን ሆነሽ ነው?››
እይኗን ወደእጣቷ ወረወረችና አየችው…ደነገጠች‹‹ወይኔ ከደቂቃዎች በፊት እሾክ ወግቶኝ ነበር፤ቀላል አድርጌ ነበር የወሰድኩት፡፡››
አስከአሁን ከደነገጠው በላይ ደነገጠ፡፡ትከሻው ላይ ያለውን ጠመንጃ አወረደና አቀባብሎ ስሯ አስቀምጦ በእጇ አስያዛትና ‹‹የሆነ ነገር ካየሽ ተኩሺ… ስለምሰማ በአስቸኮይ እመጣለሁ…መድሀኒት መፈለግ አለብኝ …. ከዚህ እንዳትንቀሻቀሺ ››አለና፡፡ ጓዙን ጠቅላላ ከጎኗ አስቀምጦ ሽጉጡንና እና ጩቤውን ይዞ ሄደ….ከ15 ደቂቃ አታካች እና አድካሚ ፍለጋ በኃላ ነው የሚፈልገውን ቅጠል ያገኘው፡፡በጥንቃቄ ቆረጠውና ተመልሶ ሲመጣ እሷ ሙሉ በሙሉ እራሷን ስታ ተዘርራ ነበር፡፡
ቶሎ አለና ትንፋሿን አዳመጠ፤በትንሹ ቲር ቲር እያለች በውስጦ ትንፈራገጣለች፡፡ እጇን አነሳና ጉልበቱ ላይ አስተካከሎ አስቀመጣት፡፡ወገቡ ላይ የሻጠውን ጩቤ ከጎኑ አወጣና የተመረዘውን የመሀል እጣቷን ሸረከተው፤ጥቁር ደም ከውስጡ መንፎልፎል ጀመረ፡፡ይበቃል በሚለው መጠን ካፈሰሰ በኃላ የጨቀጨቀውን ቅጠል እየጨመቀ ፈሳሹን ወደውስጥ ያንጠባጥብ ጀመረ፡፡ከዛ ሙሉ የእጇን መዳፍ ውጩንም ውስጥንም በቅጠሉ ጠቀለለውና ከስር የለበሰውን ካኔቴራ አውልቆ በመቀዳደድ ልክ እንደፋሻ ጠቀለለውና በቀስታ አስተካክሎ ሰውነቷ ላይ አስቀመጠው፡፡ እሷን ፎጣ ነገር አልብሶት ወደቦታዋ መልሶ አስተኛትና ውጤቱን መጠበቅ ጀመረ…በጣም ተጨንቋል፡፡ይህቺን ልጅ በዚህ ደን ውስጥ ካጣት ከዛ በኃላ ያለው ህይወት እንዴት ሊቀጥል እንደሚችልም ምንም አያውቅም…ከሳምንት በፊት ያወቃት ሳይሆን እድሜ ልክ በልቡም በነፍስም የነበረች ሴት እንደሆነች ነው እያሰበ ያለው፡፡አሁን እጁ ላይ ከሞተችበት ልቡም ሆነች ነፍሱ ከዚህ በፊት ቦዳ ከሆነችው በላይ በጥልቀት ባዶ ትሆናለች፡፡ለመኖር ወኔም ፍላጎትም አይኖረውም፡፡በዚህ እርግጠኛ ስለሆነ ውስጡን በረደው፡፡
ስለእሷ እያሰበ የእሷን መንቃት እየተጠባበቀ ሳለ የሆነ ጆሮው ላይ ሿሿሿ የሚል ድምጽ ሰማ…ይሄ ድምፅ የወንዝ መስገምገም ድምፅ እንደሆነ ያውቃል፡፡ጆሮውን በደንብ ቀስሮና ስሜቱን ሰብስቦ እርግጠኛ ለመሆን አዳመጠ፤ትክክል ነው….ተነሳ ቆመ፡፡ የእሷን ቦርሳም ሆነ እሱ ይዞ የነበረውን ሻንጣ ውስጥ ከተተ፡፡ ሽጉጡንም ከተተና በተከሻው አዘለው…ከዛ ጎንበስ አለና እሷን ልክ እንደተወዳጅ ልጁ በጥንቃቄ ከስር ሰቅስቆ ያዛትና አቅፎ ወደላይ አነሳት፡፡የገመተውን ያህል አልከበደችውም….‹‹ድሮስ በፍቅር የተሸከሙት ሸክም የክብደቱን ያህል መች ይፈተናል?››አለና በውስጡ አሰበ ፡፡እሷን ተሸክሞ ከሀረጋ ሀረጎች እና ከጥሻዎች ጋር  እየታገለ  ለ15  ደቂቃ  ወንዙ  ሿሿሿታ  ወደሚሰማበት  አቅጣጫ  ይዞት  ተጎዛ፡፡ የሚንፎለፎለው ወንዝ የአይኖቹ እይታ ውስጥ ሲገብ ውስጡ በእርካታ ሀሴት አደረጋች፡፡ወደወንዙ ዳርቻ ተጠጋና ምቹ ያለውን ቦታ መርጦ ቀስ ብሎ ተንበረከከና አስቀመጣት ››ወዲያው ደህና ደህና ችካል መሰል እንጨቶችን መርጦ ጉድጎድ በመቆፈር አስተካክሎ ተከላቸው፡፡በአግዳሚ ማገር አራቱንም ኮርነር አገናኛና አርብራብ ሰራላቸው…እዛ እርብራብ ላይ ምቹና ለስላሳ ቅጠል ለምልሞ ጎዘጎዘበት፡፡በመቀጠል ረጃጅም ቋሚዎቹን ቆራረጠና አራት ቦታ ተክሎ ልክ እንደጎጆ ቤት ከላይ ጫፋቸውን አንድ ላይ ሰበሰባና በሀረግ አሰራቸው፡፡ከዛ እንደክብ ዙሪያውን እያሽከረከረ አሰረና አጠናካረው.፡፡ከዛ ኮባ መሳይ ሰፊ ቅጠሎችን በመመልመል አለበሰውና በግማሽ ቀን ውስጥ የሚያምር ጊዜያው ጎጆ ሰራ፡፡ከዛ ኑሀሚን ከመሬት ላይ አንስቶ በጥንቃቄ ወደጎጆው አስገባትና ያዘጋጀላት ርብራብ ላይ አስተኛት፡፡ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን ኑሀሚ ከገባችበት ሰመመን አልነቃችም..ጥሩ ነገር ግን ሙቀቷ በመጠኑ ቀንሶ  አተነፋፋሶም እየተስተካከለ መጥቶ የሰላም እንቅልፍ የተኛች መስላለች፡፡ስለዚህ ሰውነቷ ለመድሀኒቱ ለመልስ እየሰጠና በሰውነቷ የገባው መርዝ እየተዳከመ እና እየተወገደ እንደሆነ ስላመነ ተረጋግቷል፡፡
ልብሱን አወላልቆ ወደወንዙ ውስጥ ገባና እየዋኘ በዛውም አራት የሚሆኑ አሳዎችን አሰገረና ከወንዙ ወጥቶ ልብሱን በመለባበስ ወደሰራት ጎጆ ተመልሶ እንጨት እርስ በርስ በማፋተግ እሳት አቀጣጥሎ ዓሳውን መጥበስ ጀመረ፡፡ልክ የመጀመሪያውን ዓሳ አብስሎ ጨርሶ ሁለተኛውን እያዘጋጀ ሳለ ኑሀሚ አይኖቾን ገለጠች፡፡ብዣ እንዳለባት ነው፡፡ሞት ጫፍ ላይ ደርሶ መመለስ አይነት ስሜት እየተሰማት ነው፡፡ዙሪያውን ስትቃኝ ጥቅጥቅ የአማዞን ድን ሳይሆን አዲስ የተሰራ የገጠር ጎጆ ቤት ነው የሚታያት፡፡አይኖቾን ስታሽከከረክር በጎጆዋ በራፍ አሻግራ ስታይ ሰማያዊ የጠራ መልክ ያለው ወራጅ ወንዝ ይታያታል..ከወንዙ ማዶ ግን መልሶ በግዙፍ ዕድሜ ጠገብ ዛፎች የተዋቀረ ጥቅጥቅ ደን ነው የምታያት…እይታዋን ወዳለችበት ስታጠብ ጭስ ነገር አየች…ቀስቀስ ስትል ድምፅ ስለሰማ የያዘውን ነገር ጣጣለና ተፈናጥሮ ተነስቶ ስሯ ቆመ….‹‹ነቃሽ…?እንዴት ነሽ ..?አሁን ምን ይሰማሻል?››በጥያቄ አጣደፋት፡፡
‹‹በጣም ደህና ነኝ..ፍፁም ሰላም ነው እየተሰማኝ ያለው…እንዴት እዚህ መጣን …?የሆነ ዛፍ ስራ አልነበርኩ..?ወንዙ ከየት መጣ?፡፡››
‹‹ትክክል ነሽ…በአካባቢው ወንዝ እንዳለ ሳውቅ ወደእዚህ ይዤሽ መጣሁና ይህቺን ጎጆ ሰራሁ..አሁን ቆንጆ የዓሳ ጥብስ ሰራቼለው፡፡እሱን ስትበይ ደግሞ ጠንካራ ትሆኚያለሽ››
‹‹ይዤሽ መጣሁ ስትል..እንዴት አድርገህ…?መቼስ በእግሬ መንቀሳቀስ አልችልም ነበር..አይደል እንዴ?››
‹‹ያው አቀፍኩሽና አመጣሁሽ..እሩቅ እኮ አይደለም..አንድ ሶስት ኪሎ ሜትር ቢርቅ ነው፡፡››