በባሕርዳር ከተማ ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የስርዓቱ ሰራዊት መኖሩ ይታወቃል። በብርሃኑ ጁላ የሚመራው ወራሪ ሰራዊት ፣ በኮሚሸነር ደስየ ደጀን የሚመራው የክልሉ የፀጥታ ኃይል ተብዮ አድማ ብተና ፣ ሚኒሻ እና ፖሊስ እንዲሁም በደሳለኝ ጣሰው የሚመራው ሰላምና ደህንነት ቢሮ በአሁኑ ወቅት ከሞትና ኩብለላ የቀራቸውን ጥቂት ኃይል አሟጠው የፋኖን ትግል ለመግታትና ለመቋቋም ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ።
ጎን ለጎን ያወጡት እቅድ ግን በሁሉም አደረጃጀት ውስጥ ካላቸው ገዳይ ቡድኖች በተጨማሪ ከዚህ በፊት በኮሚሽነር ደስየ ደጀን ቡድን የተዘጋጁ የጥበቃ ኤጀንሲዎችን ባሕርዳር ከተማ ውስጥ ባሉ ትልልቅ የግድ ድርጅቶች ፣ ፋብሪካዎች ፣ የንግድ ተቋማት ፣ ሪልስቴቶች እና ትልልቅ የመኖሪያ መንደሮች ላይ በማሰማራት የ Community Intelligence በማጠናከር የፋኖን ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ሚስጥራዊ ግንኙነት መረጃ በመሰብሰብ የሥርዓቱ ድጋፍ ሲጨ ሃይል ለማድረግ ታቅዷል።
በዚህ እቅድ ውስጥ ሚኒሻውን እና አድማ ብተናው ወስጥ ልዩ ተልዕኮ የሚሰጣቸው ጥቂት ወታደሮች ወደ የጥበቃ ኤጀንሲዎች ሄደው የተቀላቀሉ ሲሆን ፤ወደ ሚመደቡበት ማንኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ተመሳስለው የፋኖን የከተማ እንቅስቃሴ መረጃ እየሰበሰቡ ፋኖ በከተማ ያለውን ሴል ሲያውቁ እና ሲያገኙ ከአድማ ብተናው እና ከብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ጋር በመሆን እርምጃ ለማስወሰድ የተዘጋጀ ነው።
በባሕርዳር ከተማ ማህበረሰብ ውስጥ የጥበቃ ኤጀኒሲዎች ተመራጭ እንዲሆኑ ለማድረግ ሆነ ተብሎ በሰላምና ደህንነት ቢሮ በአድማ ብተና ፈጻሚነት የተዘጋጀ የሰው ፣ የህጻናት ፣የሴቶች ፣ የንብረት እገታ አፈናዎች የተሰላቸው የነጋዴው እና መካከለኛ ኑሮ ነዋሪው የማህበረሰብ ክፍል እንዲማረር ከአደረጉ በኋላ የጥበቃ ኤጀንሲዎች እንዲመደቡላቸው ያደርጋሉ በመቀጠልም የራሳቸውን ገዳይ ቡድኖች እና መረጃዎችን ለማሰማራት መሆኑ ታውቋል።
በዚህ እንቅስቃሴ እና እቅድ ውስጥ ስርዓቱ ባህርዳር ከተማ ላይ ብቻ ለግዜው ያቅደው እንጂ በሌሎች ትልልቅ የአማራ ከተሞች ተሞክሮውን ለመተግበር የወደፊት እቅድ ተደርጓል ። አገዛዙ አካሄዱን የመረጡበት ምክንያትም ፋኖ የከተማ ሴሉን በማሳደጉ እና በከተሞች ሰርጎ ገብቶ የሚፈፅማቸው ኦፕሬሾኖችን ለመግታት በየቦታው የራሱን የመንግሥት ሴል ለማስቀመጥ እንደሆነ ታውቋል።
በባህርዳር ከተማ ዙሪያ የሚገኙት የባሕርዳር ብርጌድ ሻለቆች እንደ ደጉ በላይ ሻለቃ ፣ግዬን ሻለቃ ፣ አራራት ሻለቃ ፣አሳምነው ሻለቃ እና አራራት ሻለቃ ወደ ከተማው ሰርገው በመግባት የስርዓቱ ሎሌና ባንዳዎችን አንጠልጥለው በመውሰዳቸው አሁን በጥበቃ ኤጀንሲ ስም የመንግሥት ሃይል በማስቀመጥ ፋኖ ጥበቃ ናቸው ብሎ ተዘናግቶ ኦፕሬሽን በሚከውንበት ወቅት መረጃ በመስጠትና ከጀርባ ጭምር በመውጋት ከተማ ውስጥ የሚደረገው ኦፕሬሽን ስኬታማ እንዳይሆን የታቀደ አዲስ እቅድ ነው።
ለባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎች ማስተላለፍ የምንፈልገው መልዕት የፋኖኦፕሬሽኖች ባንዳ እና የስርዓቱ አዳሪዎች ላይ እርምጃ ሲወሰድና ታንቀው ሲወሰዱ ጥቂቶች ተመልክታችኋል። ይሁን እንጅ ከዚኽ በተቃራኒ እገታ ፣አፍኖ ገንዘብ ድርድር በከተማው የሚፈጽመው ሆነ ተብሎ የሥርዓቱ አፋኝና ዘራፊ ቡድን መሆኑን በጥቂቱም ቢሆን የምትረዱት ሃቅ ነው።
ስለሆነም አገዛዙ አሁን ተቋማትን በስውር ለማስጠበቅ የጥበቃ ሽፋን ኤጀንሲን አመጣለሁ እያለ በየአካባቢው የሚወተውተው ሁሉ ከጀርባው የተሸከመው የስርዓቱ ተልዕኮ መሆኑን ቀድማችሁ እንድታውቁና በአጠቃላይ የጥበቃ ኤጀንሲዎች በማን እንደሚዘወሩ ሴራቸውን ልትገነዘቡ ይገባል እንላለን ።
ይህንን የአገዛዙ ተንኮልና ሴራ እያዎቀ የአገዛዙን ሴራ በጥበቃ ኤጄንሲ ሥምና ሽፋን የተቋማት የጥበቃ ኤጀንሲ ይመደብልን ብሎ የሚያስተባብርና የሚንቀሳቀስ ግለሰብም ሆነ ድርጅት በየአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ኃይል ለማስጠቃት ከአገዛዙ ጋር ተናቦና ተባብሮ እየሰራ እንደሆነ በውስጥ አርበኞች መረጃ ደርሶናል ።
በዚህ መሰረት የአገዛዙ ተባባሪ በመሆንም ሆነ፤ ሴራውን ባለማወቅ የትኛውንም የጥበቃ ኤጀንሲ አዲስ ቅጥር የምትፈጽሙ ድርጅቶች ፣ ንግድ ተቋማት ፣ ፋብሪካዎች ፣ ሪልስቴቶች በአጽንዖት የምናስተላልፈው መልዕክት በአዲስ የቅጥር ውል የቀጠራችሁት የጥበቃ ኤጀንሲ አባል ከአገዛዙ ጋር በማበር ለሚፈጽመው ማንኛውም ፀረ-ፋኖ እንቅስቃሴ እና አገዛዙ ላቀደው አዲስ የፋኖ ጥቃት ሙሉ ሃላፊነት ትወስዳላችሁ። ይህንንም ተከትሎ የፋኖ ለሚወስደው ሴራውን የማክሸፍና የበቀል እርምጃ በጥበቃ ኤጀንሲ ድርጅቱ ብቻ ሳይሆን በቀጣሪ ድርጅቱ ጭምር ይሆናል።
የአማራ ፋኖ በጎጃም በባሕርዳር ከተማ የውስጥ ሸማቂ ኃይል የተላከ መልዕክት!!
#አማራ_ላይጨርስ_አልጀመረም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪
25/2/17 ዓ.ም