Save Amhara Fano💪💪🌍 🛰🦅💚💛❤️

@saveamharafano


መረጃ እና አስተያየት
ለመስጠት በዚህ አድርሱን
👇👇 
@SaveAmharafanoam

የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥
ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ
ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ
እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም።

Save Amhara Fano💪💪🌍 🛰🦅💚💛❤️

23 Oct, 05:47


#አቶ ታዲዮስ ታንቱንም እንደ ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ?

የሐሰት ትርክት ፈጣሪዎችንና ቀባጣሪዎችን፤ ባወቁት፣ በተማሩበትና በኖሩበት ልክ ስለ ፖለቲካ ትክክለኛነት (Political correctness) ሳይጨነቁ፣ ‘ዶማ’ ን ፣ ‘ዶማ’ ብለው የሚገልጹት፤ አንጋፋው ጋዜጠኛና የታሪክ አዋቂ ታዲዮስ ታንቱ ከታሰሩ ዓመታት ተቆጥሯል። በዘጠና ዕድሜ መዳረሻቸው ላይ መስዋዕትነት እየከፈሉ ያሉ የታሪክና የዕውነት አባት ታዲዮስ ታንቱን አለማንሳት፣ አለመጥቀስ፣ አለማስታወስ ውለታ ቢስነት ብቻ ሳይሆን ወጪት ሰባሪነት ነው።

#በቀደመው ኢሕአዴግ (ወያኔ) ጊዜ ታዲዮስ ታንቱ በአገዛዙ ተይዘው ወደ ወሕኒ ቤት ተጋዙ። በመግቢያው በር ላይ ሁሉም ታሳሪዎች ብሔራቸውን እየተጠየቁና እየተናገሩ ነበር የሚገቡት። ታዲያ የታዲዮስ ታንቱ ተራ ደርሶ:-

” ብሔርዎት?!”

”ኢትዮጵያዊ”

ጠያቂውም:-

”አማራ ብለህ መዝግባቸውና አስገባቸው!” እንዳላቸው አብረዋቸው ታስረው ከነበሩ ሰዎች አድምጫለሁ። (ታዲዮስ ታንቱ የደቡብ ሰው መሆናቸውን ልብ ይሏል)

ታዲዮስ ታንቱ ለአማራው ከአማራው በላይ ተሰቃይተዋል። ተንገላተዋል። ተዘልፈዋል።የኢትዮጵያዊነት ውሉንና መሠረቱን ለቀጣፊዎች ለማስረዳት ብዙ ማስነዋል። የዘሩትም ዕውነት በብዙዎች ህሊና ውስጥ ተቀምጧል። መታደል ነው።

የታዲዮስ ታንቱ እስር፣ ምጸቱ፣ ፖለቲካው፣ ብልግናው፣ ጭካኔውን ላስተዋለው ዘግናኝ ነው።

ከምፀቱ እንኳን ብንጠቅስ አቃቢ ሕግ ”ምስክሬ” ብሎ ካቀረባቸው አንዱ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መሆኑ ነው። ቢያስገርመንም፤ አያስደነግጠንም። ብርሐኑ ነጋ የአድርባዮች ቁንጮ ነው። ታዲዮስ ታንቱም በነበራቸው የተለያዩ ቃለ – መጠይቆች ላይ የብርሐኑ ነጋን ”አድርባይነት፣ ፈታላነትና ጎባጣነት፤” ሳያለሰልሱ ይገልጹ ነበር። በዚያ ላይ እኚህን ቀጥተኛና ግልጽ፤ ቆራጥና አዋቂ የሆኑ ሰውን፤ የብርሐኑ ዓይነት ሰዎች ይጠየፏቸዋል። ለዚያም ይሆናል ለአቃቢ ህግ ብርሐኑ እራሱ ”ምሥክር ካልሆንኩኝ” ብሎ አቤቱታ ያቀረበው – የተባለው። አድርባይ ፕሮፌሰር ፤ ምስክር ብቻ ሳይሆን ”ሽጉጥ አውጥተህ ፤ ግደል!…” ቢባል ከመግደል አይመለስም።

”ለአመታት በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የእርስ በእርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡” ይሄ ሰሞኑን የተለቀቀ ዜና ሲሆን፤ ፍርድ ቤቱ ለሌላ ቀጠሮ ማለትም ለጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡”

ይሄ የጥላቻ ንግግር የሚባል ክስ ጋዜጠኞችን፣ አማራዎችን፣ የአማራ ጠበቃዎችን የኢትዮጵያ አርበኞችንና ለዕውነት የቆሙትን ሁሉ የሚያጠቃ መሆኑ ደግሞ አሳሳቢም፣ አናዳጅም ያደርገዋል።

የጥላቻ ንግግር ?…
1. ጭራቁ_አብይ አህመድ ፤ ”ኦሮሞ ጠል ማህበረሰብ አዲስ አበባ ውስጥ አለ። የቀን ጅቦች፣ በአንድ ሌሊት መቶ ሺ ሰው ታርዶ ሊያድር ይችላል፣….” ወዘተ…. ለነገሩ የአብይማ የጥላቻ ንግግር የዶሮ ወጥ አሠራር ድረስ ይሄዳል።

2. መጋጃው_ሽመልስ አብዲሣ፤ ”አማራን እንዳይነሳ አድርገን ሰባብረነዋል።”

3. ቀዌ_ጃዋር መሐመድ፤ ”እኛ ጋር ቀልድ የለም። አንድ ሰው ቀና ካለ በሜንጫ ነው አንገቱን የምንቆርጠው” ”Ethiopia out of Oromia”

4. ገራባው_በቀለ ገርባ፤ ”አንድም ኦሮሞ ከአማራዎች ጋር እንዳይገበያይ ኦሮምኛ ካላወራ አትግዛው፣ አትሽጥለት፣ ሴቶችም እንዳታገቡ”

ሌሎችም ብዙ መጥቀስ ይቻላል። ከላይ በመጠኑ የተናገሩትን ያስቀመጥኩት የፍቅር ስሜት ቀስቃሽ (Romantic) ወይም የሠላም ቋንቋ ሳይሆን የሚያጨራርስ፣ የሚያጋድል የሚያነታርክ የጥላቻ ንግግር መሆኑን ለማነጻጸር ነው። የተናገሩት ሰዎች ደግሞ በተለያየ የሥልጣን እርከን ላይ መገኘታቸውና ጠ/ሚ ሁሉ መሆኑን ሲያስቡ ታዲዮስ ታንቱን መክሰስ ውሃ አይቋጥርም። አያነሳም።አለያም የታሰሩት ከመጠንም፣ ከአቅምም በላይ ነው።

#በዕውነቱ ሐሳብን በነጻነት በመግለጽ መብታቸው የተጠቀሙትና መከራ እየወረደባቸው ያሉት አዛውንት ላይ፤ ፍትሕ በእጅጉ አላግጧል። ጨክኗል። ሃያ ሰባት ዓመት ሙሉ በሥልጣናቸውም በምግባራቸውም በአስተሳሰባቸውም ኢትዮጵያን ሲገድሉ ”አማራውንና ኦርቶዶክስ ኃይማኖትን አከርካሪውን ሰብረነዋል” ሲሉ የነበሩትን፣ ንጹሐኖችን ያለምንም ሐጢያታቸውና ወንጀላቸው በየ እስሩና ወሕኒው ሥልጣናቸውን መከታ በማድረግ ሲያግዙ፤ ንብረቱንም ሲዘርፉ የነበሩት ”አቦይ” ስብሐት ”ዕድሜያቸው በመጥናቱና በመግፋቱ” ነበር ፤ የመፈታታቸው ሰበብ እናም፣ ምክንያት።

ታዲያ፣ ታዲዮስ ታንቱ ዕድሜያቸው አልገፋምን?! ዕድሜ ማስተዛዘኛ የሚሆነው ለስብሐት ብቻ ነውን?… እንጠይቃለን። እናዝናለን። ያሳስበናልም።

ለተዛባውና ለተጣመመው፣ አድሎና ውስልትና ላለው የፍትሕ ስርዓታችሁ፤ የእኚህ አዛውንት መከራና እንግልት ትልቅ ማሣያ ነው። ። በእርግጥ ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስም ይህ ዕጣና መከራ ነበር ገጥሟቸው፣ ያለፉት። አሁንም እየጠበቃችሁት ያላችሁት የአቶ ታዲዮስ ታንቱን መታመማቸውን ወይም መድከማቸውን መሆኑን ድርጊታችሁ በእጅጉ ያሳብቃል።

ግን ስንት ጊዜ ነው የሰው ሕይወት ስታመነዥጉ የምትኖሩት?!..እናም አቶ ታዲዮስ ታንቱን ቢቻል ካሳ ከፍላችሁ፣ አለያም ተጸጽታችሁ፤ ልቀቋቸው። ”ፕሮፖጋንዳ” ዝም ተብሎ በጭካኔና በዋልጌነት ተሰርቶ አይውቅም። ለናንተም ”ፖለቲካ” የሚሆነው ሕፃናቶችን በድሮን ባለማሰቃየትና ባለመጨፍጨፍ፤ እንዲሁም እኒህን መሠል አዛውንቶችን ባለማንገላታትና በመፍታት እንጂ፤ አስሮ እስከወዲያኛው በመግደል አይደለም። እናም እጠይቃለሁ፣ እንጠይቃለንም። አቶ ታዲዮስ ታንቱንም እንደ ፕሮፌሰር አሥራት ወልደየስ?

Save Amhara Fano💪💪🌍 🛰🦅💚💛❤️

19 Oct, 12:15


የአሳምነው ልጆች!!

በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው ፋኖ በአማራ የሕልውና ትግል ውስጥ ቀዳሚ ተብለው ከሚጠቀሱ ድሎች መሀከል ግዙፉን ድል በእጁ አስገብቶታል። የማረከው ብቻ ቢቆጠር ከአንድ ክ/ጦር ሳይበልጥ አይቀርም😂

የምስራቅ አንበሶች!!

የዋርካው ተርቦች ....

እጅ ወደላይ !

Save Amhara Fano💪💪🌍 🛰🦅💚💛❤️

18 Oct, 17:35


#እምቢ በል!

#የአማራ ህዝብ ጥቃት የሚያንገበግብህ ከሆነ፣ የአማራ ህዝብ የሕልውና አደጋ እንዲቀለበስና ህዝባችን ነፃነቱን አረጋግጦ በሰላም እንዲኖር ቁርጠኛ እምነት ያለህ ከሆነ “እምቢ!” ማለት ያለበህ ጉዳዮች አሉ፡፡

1/ ቅርጫት ውስጥ እንድትገባ የሚፈልጉ ብዙ አካላት ስላሉ እምቢ በል፡፡ አንዱን ታጋይ ደግፈህ ሌላውን እንድትቃወም፣ አንዱን ቡድን ደግፈህ ሌላውን እንድትቃወም፣ የአንዱ ጎራ አባል እንድትሆን የሚፈልጉ አሉ፡፡ በዚህና በዚያ ሆነው ይወጉሃል፡፡ ያዋክቡሃል፡፡ እንዲህ ነህ፣ እንዲያ ነህ ይሉሃል፡፡ የእከሌ ደጋፊ ነህ፣ የእከሌ ተቃዋሚ ነህ ይሉሃል፡፡ ከአንተ የሚጠበቀው እምቢ ማለት ነው፡፡ ቅርጫት ውስጥ አለመግባት ነው፡፡ ሁልጊዜም ወገናዊነትክን ከአማራ ህዝብ ጋር ብቻ ማድረግ ነው፡፡ አማራ ክልል የሚገኘው ብቻ ሳይሆን በመላው ኢትዮጵያ የተሰራጨውና በውጭም የሚኖረው አማራ ሁሉ ወገንህ ነውና በእኩል መንፈስ እየው፡፡ ቀጭኗን መንገድ መራመድ ይገባሃል፡፡ በሂደት መንገዷ ትሰፋለች፡፡ ትግል ያሳፋታል፡፡ ብዙ ልባሞች መምጣታቸው አይቀርምና፡፡

2/ ብሄርተኝነትን ከዘረኝነት ጋር እያያዙ የሚያጣጥሉ ሰዎች ይገጥሙሃል፡፡ ብሄርተኝነትን ካለመዘመን ጋር እያያዙ የሚተነትኑ ያልገባቸው ሰዎች ይገጥሙሃል፡፡ “አማራ ብሄርተኛ ሊሆን አይችልም፣ የአካባቢ ማንነቶች ጠንካራ ናቸው፣ የአማራ ብሄርተኝነት አይነሳም” ወዘተ ወዘተ ይሉሃል፡፡ እንዲህ የሚሉህ ስለ ብሄርተኝነት አንድም መጽሃፍ አንብበው የማያውቁ ናቸው፡፡ አንተ ግን ብሄርተኝነት የከተማ/ዘመናዊት ክስተት መሆኑን እወቅ፡፡ በጎሳ ያልተደራጀ በመሆኑ እንደ አማራ ለብሄርተኝነት የተመቸ ህዝብ እንደሌለ ይግባህ፡፡ ዛሬ የሰልጣኔ ጣሪያ ላይ የደረሱት ከእንግሊዝ እስከ ጃፓን፣ ከአሜሪካ እስከ ጀርመን ሁሉም ብሄርተኞች መሆናቸውን እወቅ፡፡ ስለሆነም የአማራ አባቶች ስህተት ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ማለታቸው እንዳልሆነ፣ ስህተታቸው ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ የሚሉት አማራነታቸውን ጥለው እንደሆነና ስህተቱም እሱን እንደሆነ ይግባህ፡፡ ብሄርተኝነት መቼም የማይሸነፍ መሆኑንም በደንብ ማወቅ ይገባሃል፡፡ በአንደኛው ትውልድ ድክመት ድሉ ሊዘገይ ይችል ይሆናል እንጅ ብሄርተኝነት አይሸነፍም፡፡ ደካማው ትውልድ ለልጆቹ የቤት ስራ ሲያስቀምጥ ልባሙ ትውልድ ግን ነፃነትን ያወርሳቸዋል፡፡

3/ የአማራ ብሄርተኝነት ዣንጥላ መዋቅር መሆኑን አጥብቀህ ያዝ፡፡ ሌሎች የፖለቲካ፣ ወታደራዊ፣ የሲቪክ፣ የሚዲያ ወዘተ ድርጅቶች በብሄርተኝነቱ ስር ያሉ እንጅ ብሄርተኝነቱን የሚተኩ አለመሆናቸውን ጠንቅቀህ እወቅ፡፡ አንድ የአማራ ድርጅት ሊዳከም ይችላል፡፡ ሊፈርስም ይችላል፡፡ ያ ድርጅት ተዳከመ ወይም ፈረሰ ማለት ግን የአማራ ብሄርተኝነት አለቀለት ማለት እንዳልሆነ ይግባህ፡፡

4/ የአማራ ብሄርተኝነትን ከሃይማኖት ጋር አታቀላቅል፡፡ ሁሉም የየራሱ ቦታ አለው፡፡ የራስክን ሃይማኖት ያዝ፡፡ ነገር ግን መታገል ያለብህ ለሁሉም ሃይማኖቶች እኩልነት መሆን ይገባዋል፡፡

5/ በተሸነፈ ማህበረሰብ ውስጥ አሸናፊ ግለሰብ ሊኖር እንደማይችል ተረዳ፡፡ ችግር ውስጥ ካለ ማህበረሰብ ወጥተህ ተመችቶህና የሕሊና እረፍት አግኝተህ ልትኖር እንደማትችል ይግባህ። ስለሆነም ሁልጊዜም የህዝብህ ጉዳይ እንቅልፍ ይንሳህ፡፡ በሚገነባ እንጅ በአፍራሽ ተግባር ላይ አትገኝ፡፡ የተግባር ሰው ሁን! የስራ ሰው ሁኚ!!!

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!

አማራ ድብን አርጕ
ድባቅ መትቶ ያሸንፋል
ሳትጠፉ ነብሳችሁን አትርፉ።

Save Amhara Fano💪💪🌍 🛰🦅💚💛❤️

17 Oct, 16:27


የሚያኮራ እና መጠናከር ያለበት ጅምር!

የአማራ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ትዊተር (X) ላይ የጀመሩት እንቅስቃሴ በጣም የሚያኮራና ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው፡፡ ሁሉንም የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በሚገባ አሟጠን በመጠቀም ለህዝባችን ድምጽ መሆን መቻል አለብን፡፡ በተለይ ትዊተር ላይ የሚካሄዱት ዘመቻዎች የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶላቸው መልእክቶች በደንብ እየተቀረፁ ሳይቋረጡ መቀጠል ይገባቸዋል፡፡ ያለ ጥርጥር ተስፋ ሳንቆርጥ የምንሰራ ከሆነ ድምጻችን ሰሚ ያገኛል፡፡

ስለሆነም በተለይ ትዊተር ላይ የሚከሄዱት ዘመቻዎች በተቀናጀና በጥሩ ጥሩ ግራፊክሶችና መልእክቶች በታጀበ መልኩ እንዲቀጥሉ ዘመቻውን የጀመሩትን እህቶችና ወንድሞች ማበረታታት ይገባል፡፡
ውጤት እስክናመጣ እንታገል!

ያዝ ለቀቅ አያስፈልግም!
ፅናት!!!

የአማራ ብሄርተኝነት ይለምልም!!!

Save Amhara Fano💪💪🌍 🛰🦅💚💛❤️

13 Oct, 15:12


ሰበር ዜና!

የጎንደር ነዋሪዎችን የፋኖ ደጋፊ ናቸው በሚል ሲያሳስርና ሃብት ንብረታቸውን ሲያስወርስ ነበር የተባለው ሰንደቁ በወንዶች ጥይት ተደብድቦ መገደሉ ተሰማ!

ጠዳ ክ/ከተማ የፋኖ ደጋፊ ናቸው፣ ፋኖ የሆነ ቤተሰብ አላቸው በሚል ለወራሪው ዘራፊው_ሰራዊት ጥቆማ በመስጠት በርካታ ነዋሪዎችን ሲያሳስርና ሃብት ንብረታቸውን ሲያዘርፍ የነበሩ ባንዳ _ሚሊሻ ሰንደቁ ዛሬ ጥቅምት 03/2017 ዓ/ም ንጋት ላይበወንዶች ጥይት መገደሉ ይበል የሚሳኝ ነው።

Save Amhara Fano💪💪🌍 🛰🦅💚💛❤️

12 Oct, 15:11


ዘመነ በሠራቸው ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስራዎች ምክንያት የአማራ ወጣቶች ለሕልውናቸው እየተዋጉ ሕዝባቸውን ከጥቃት የሚከላከሉበትን የፋኖ መከላከያ ሠራዊት መሥርተዋል። ዘመነ ካሤ ከሌሎች ወንድሞቹ  ጋር ሆኖ የዐማራን ወጣት ከባድ መሳሪያ አስታጥቆታል። በጎንደር ፣ በሸዋ ፣ በወሎና በጎጃም ያሉ ወጣቶች በዘመነ ካሤ፣ በአሣምነው ጽጌ፣ በምሕረት ወዳጆ/ ምሬ/ ስም እየማሉ የሕዝባቸው የህልውና ጠባቂ ሆነዋል። መማርና መነገድ ፤ እየቻሉ ወደ ኅልውና ትግል የገቡት በሚሊዮን የሚቈጠሩ የዐማራ ወጣቶች አርአያ ያደረጉት እነ ዘመነ ካሤን ነው።

የዳንኤል ክስረት ከንቱ የ 104 ገጾች ስድብም ስድብ ሆኖ ይቀራል። ሰድቦ አሰዳቢ ወራዳ_ በወለጋና በመተከል በቡራዩና በአጣዬ፤ በሻሸመኔና አርሲ የተጨፈጨፈው ዐማራ ነፍጥ ለማንሣት ምክንያት እንደሌለው ተደርጎ የተቈጠረው በቤተ መንግሥቱ አሸርጓጅ ኮቸሮ ለቃቃሚ_ዳንኤል ክስረትና በእሱ አለቆች ብቻ ነው። ዐማራ በሰልፍ የጠየቀውን መብት ሲያጣ ሰይፍ አነሣ ብሎ ለማስረዳት ኅሊናን ማሠራት ይጠይቃል።

በራሪ ጀት እና ድሮን ያላስቆመውን ግዙፍ የሕዝብ ትግል በራሪ መጽሐፍ ይቀለብሰዋል ብሎ ማሰብ የተገባ አይደለም!!!

Save Amhara Fano💪💪🌍 🛰🦅💚💛❤️

12 Oct, 14:54


No comment!!!