4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች @amazing_fact_433 Channel on Telegram

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

@amazing_fact_433


እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች ቻናላችን በሰላም መጣቹ

እሄ ቻናል ያላወቀቹትን አስገራሚ ነገር በቪድዮ አልያም በፎቶ እና በፅሁፍ የምታገኙበት፣ የተለያዩ አስቂኝ የሆኑ አስገራሚ ነገሮች የምታገኙበትና እውቀትን የምትጨብጡበት ቻናል ነው።

ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc & @Kiya988

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች (Amharic)

እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች ቻናላችን በሰላም መጣቹ

በየቀኑ ቻናል ከቶም ምንም አላዉቁም? እናንተ በቪድዮ እና በፎቶ ወደቁን? ቻናል 4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች ነገሮች እውቀትን በመጨብጨብ ማህበረሰብ የሚያስተምሩበት ስራ ነው። በፎቶና በፅሁፉ በተነቀልሁበት ውስጥ ከሚደበዙ ታሪኮች እና አስተያየቶች ባይታገኙ የሚፈልጉ አስገራሚ ነገሮች እና ሴራዎች ላይ ተጨባጮ እውቀቶች የሚገኙባቸውን አስገራሚ ነገሮችን ይሰጣል። መሣሪያ ስልጠናዎች ከ @Abusheymc እና @Kiya988 ፣ አስገራሚ ነገሮች ንግዳቸውን ለማግኘት ይረዳሉ።

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

20 Nov, 19:02


እ.አ.አ በ1982 በአሜሪካ ቦስተን ከተማ የእግርኳስ ጨዋታ እየተካሄደ ባለበት ሰዓት ከሜዳ ውስጥ የተመታች ኳስ ጨዋታውን ከሜዳው በቅርብ እርቀት ሲመለከት የነበረን የአራት አመት ልጅን ጭንቅላቱን ክፋኛ ትመታውና ልጁ በጣም ይጎዳና ደም በደም ይሆናል።

ጂም ራይስ የሚባል ተጫዋች ከመጫወቻው ሜዳ ሆኖ የልጁን ክፉኛ መጎዳት ይመለከታል።

የድገተኛ ህክምና አባላት ብዙ ሰዋችን አቋርጠው የልጁን ህይወት ለማዳን እንደሚዘገዩ በማሰብ፤ጂም ጨዋታውን አቆርጦ በፍጥነት በመሮጥ ልጁን በማንሳት ወደ ድንገተኛ ህክምና አባላት በማድረስ ልጁ ወደ ሆስፒታል እንዲሄድ ይደረጋል።

ልጁ ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ ሆስፒታል ይደረሳል፤ዶክተሮቹም ጂም ለልጁ ቶሎ ባይደርስለት ኖሮ ልጁ እንደሚሞት ተናገሩ።

ጂም ራይስ በደም በተነከረ ማልያው ጨዋታውን ለመጫወት ወደ ሜዳ ገብቶ ተጫወተ።

የልጁ ቤተሰቦች ልጁን ለማሳከም አቅም ስላልነበራቸው፤ ጂም ልጁን ሆስፒታል ሄዶ በመጠየቅ ሙሉ የህክምና ወጪውን ሸፍ
ኖል።

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

20 Nov, 17:29


➡️ ዓለም አቀፍ ቋንቋ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ሳቅ ወይም ፈገግታ ነው፡፡ ሳቅ ድንበርና ባህል አይገድበውም፡፡ በተጨማሪም ከአንዱ ወደ ሌላው ሰው በቀላሉ ይተላለፋል፡፡

➡️ የሰው ልጅ ፈገግ ማለት የሚጀምረው በአራተኛው ወር የጨቅላነት እድሜው ነው፡፡

➡️ አንድ ሰው አዕምሮው እየበሰለ ሲሄድ ከረጅም ሳቅ ይልቅ ረቂቅ ፈገግታን በማሳየት ውስጣዊ ደስታውን ለሌሎች ይገልጻል፡፡

➡️ የሰው ልጅ የኢኮኖሚ፣ የስልጣንና የፖለቲካ መደብ ወደ ላይ እያደገ ሲሄድ የሳቅ ልምዱ እየቀነሰ ይመጣል፡፡

➡️ አብዛኛው ሰው በሃብት መሰላል ሽቅብ ወደ ላይ ሲወጣ መጀመሪያ ከሚቀይራቸው ባህርያቶች ውስጥ አንዱ የአሳሳቅ ስልቱን ነው፡፡

➡️የላይኛው መደብ ሰዎች ከገንዘብ እኩል የሚቆጥቡት ነገር ቢኖር ሳቅና ፈገግታን ነው፡፡

➡️ ሰው የሚስቀው ስለተደሰተ ወይም ቀልድ ስለሰማ ብቻ አይደለም፡፡ ሃዘንንና ድንጋጤን ጨምሮ በርካታ ሳቅ ቀስቃሽ ስሜቶች አሉ፡፡

➡️ ወፋፍራም ሰዎች ክብደታቸውን መቀነስ ከሚያስችሏቸው ዘዴዎች ውስጥ ምግብ መቀነስ እና ስፖርት መስራት ብቻ ሳይሆን ሳቅንም ማዘውተር ሌላው ብልሀት እንደሆነ ሳይኮሎጂስቶች ያስረዳሉ ፡፡

አንብበው ከወደዱት 👍👍👍

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

20 Nov, 16:25


በተለያዩ ክለቦች የተጫወተውና በቅርቡ ጫማ የሰቀለው ፈረንሳዊው bafetimbi gomis ይበልጥ የሚታወሰው : ግብ ካስቆጠረ በኋላ ሴሌብሬት ሲያደርግ በሚያሳየው የተለየ ትእይንት ነው ።

እና አንዴ ፡ ለሳውዲ አረቢያው አልሂላል በመጫወት ላይ እያለ ፡ በተጋጣሚያቸው አል ኢትሀድ ላይ አሪፍ ግብ አስቆጠረ ።

እና ወዲያው በሚታወቅበት መንገድ ሰለብሬት ሊያደርግ ወደ ሜዳው ጥግ በእግርና በእጁ ሄደና ፡ ነብር በአደን ወቅት እንደሚያደርገው ሁለት እጆቹን ዘርግቶ አይኑን አፍጥጦ አጠገቡ ወደነበረው ኳስ አቀባይ ተጠጋ ።

ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ነገር አይቶ የማያውቀው ታዳጊው ኳስ አቀባይ ፡ ይህንን እንደ ነብር እየጮኸ ወደሱ የሚመጣውን ሰው እንደመደንገጥ ብሎ አየው ።

ጎሚስ አሁንም በአራት እግር እየሄደ ወደሱ እየቀረበ ነው ።

በዚህ ጊዜ ፡ ታዳጊው ልጅ ነገሩ ከዚህ ብሶ ጉድ ከመሆኑ በፊት አንድ ነገር በማድረግ እንዳለበት ሲያስብ ውስጡ ሩጥ እንጂ ምን ትጠብቃለህ
RUN ...RUN አለው ። እና አላንገራገረም 🏃‍♂️
....
በሰወች ተይዞ እስኪቆም ድረስ ፡ የድረሱልኝ ጩኸት እያሰማ ሮጠ 😄
.....

በጨዋታው ማብቂያ ላይ ታዲያ gomis ፡ ከፍርሀቱ ሙሉ ለሙሉ ያልተላቀቀውን ታዳጊ ልጅ አስጠርቶ ማልያውን ሸልሞት አብረው ፎቶ ተነስተዋል

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

20 Nov, 04:30


*
#ልጅ ፡ አባቴ ባህሪዬ እንዴት ቢሆን ደስ ይልሃል ?

#አባት፡ እንደዚህ ሁን ልጄ

#ልጅ ፡ እንዴት ?

#አባት ፡ እንደ ውሃ ሁን ባስቸገረ ግዜ እሳትን ቢያጠፋም በተፈለገ ጊዜ ግን እንዲገኝ ዛፍ ማሳደጉን አይተውምና ፤ እንደጨውም ሁን ለሁሉም ምግብ ቢፈለግም በቀላሉ ይገዛ ዘንድ ግን-ዋጋው ውድ አይደለምና ፤

ከሁሉ ከሁሉ-ግን እንደ ወተት ሁን በተውት ግዜ በሌላ-መልክ ተመልሶ ይመጣል እንጅ አይበላሽምና-በተገፋም ግዜ ከፍ ከፍ ይላልና።

#ልጅ፡ እሽ አባቴ እንዳልሆንስ የምትፈልገው የለም ?

#አባት አለ ልጄ፤ እንደዚህ አትሁን

#ልጅ ፡ እንዴት ?

#አባት፡ልጄ ሆይ እንደ መርፌ አትሁን የሌሎች ብዙ ቀዳዳ እየደፈነ የራሱን አንዷን መድፈን አይችልምና፤ እንደ መቋሚያም አትሁን ለሌሎች መደገፊያ እየሆነ ለራሱ ግን መቆም አይችልምና ፤

ከሁሉ ግን እንደ ደወል አትሁን ! ከሁሉ ቀድሞ ነቅቶ ሌሎችን ለቅዳሴ ቢቀሰቅስም እርሱ ግን አያስቀድስምና።
...............
**** መልካም ቀን

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

19 Nov, 18:04


የአቀባበል ስነ-ስርአቱ ፡ ምን መምሰል እንዳለበት ፡ ጊዜ ወስዶ የመከረው የአሜሪካ መንግስት ዝግጅቱን አጠናቆ
በኦክቶበር 1 - 1963 የሀገረ ኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ፡ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ዋሽንግተን ሲደርሱ ፡ በወቅቱ የአሜሪካን ፕሬዝደንት JF ኬኔዲ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
.....
ከዛም ንጉሱ ከአሜሪካን ፕሬዝደንት ጋር በመሆን በግልፅ መኪና ሆነው ወደ ነጩ ቤተመንግስት ሲጓዙ ፡ በተጓዙበት ጎዳና ላይ ሁሉ ህዝቡ ግራና ቀኝ ግልብጥ ብሎ በመውጣት በዚህ መልኩ እያጨበጨበ ተቀበላቸው ።
....
እና ....
በወቅቱ በአሜሪካን ብቻ ሳይሆን በመላው አለም የነበረን ክብር ይህን ይመስል እንደነበር ሲታሰብ ያስቆጫል

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

19 Nov, 15:32


ይህን ያውቁ ኖሯል ?

አንድ ዝሆን በ24 ሰዓት ውስጥ 450 ኪሎግራም የሚመዝን ምግብ ይመገባል። ከሚመገበው ውስጥ በምግብ መፈጨት ሂደት የሚያልፈው 50 በመቶው ብቻ ነው። በ24 ሰዓት ውስጥ የሚፀዳዳው አንዴ ሲሆን 150 ኪሎግራም እበት ይጥላል

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

19 Nov, 14:48


ሌሎች በገዛ መሬታቸው በወራሪዎች እንደ እንሰሳ ሲገዙ በነበሩበት ሰዓት የጫካውን ንጉስ የቤት እንሰሳ ያደረግን ድንቅ ህዝብ ነን

ብዙ ችግሮችና የሚያማርሩ ጉዳዮች ቢኖሩም በእርግጥም የሚያኮራ ታሪክ እንዳለን አንዘንጋ✌️

@Amazing_fact_433

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

18 Nov, 18:55


ዶክተር መሐመድ ማሻሊ ግብፃዊ የህክምና ዶክተር ነው።

ደክተሩ ለህክምና አገልግሎት ለማግኘት ምንም ገንዘብ የሌላቸውን ለአገሩን ድሃ ዜጎችና ወገኖቹን ለ 50 አመት በነፃ አገልግሎት ሰጥቶ ነበረ።

ዶክተሩ በክሊኒክ ውስጥ በመገኘት በቀን ለ12 ሰዓት ከ30 እስከ 50 ለሆኑ ድሃ ወገኖቹ በነፃ ህክምና አገልግሎት ይሰጥ ነበረ።

ዶክተር ማሻሊ በአንቡላንስ የሚመጡ በሽተኞችን ብቻ አይደለም የሚያክመው፤መንገድ ላይ በእግሩ ወደ ቤቱ እየሄደ እያለ የህክምና ምክር አገልግሎት ይሰጥ ነበረ።

ይህ ዶክተር በህየውቱ መኪናና የእጅ ስልክ እንኳን ኖሮት አያቅም ነበረ ።

አንድ የግብፅ ባለሀብት ለመኪና መግዢያ 20,000 የአሜሪካ ዶላርና የመኖርያ ቤት ቢሰጠውም ዶክተሩ የተሰጠውን ገንዘብና ቤቱን በመሸጥ ምንም ለሌላቸው ድሃ ሰዋች የህክም ለመሰጠት የህክና እቃዋችንና መድሐኒቶችን በመግዛት የህክምና አገልግሎት ይሰጥ ነበረ።

በ1967 ከካይሮ የህክምና ት/ቤት ሲመረቅ ለምድን ነው እራስህን ለድሃ ሰዋች መሰዋእት የምትሆነው ተብሎ ሲጠየቅ እንዲህ በማለት ነበረ የመለሰው።

"አባቴ እኔ ዶክተር እንድሆን ከፍተኛ መሰዋእትነት ከፍሏል ። እኔም ሰዎችን በዘር በሀይማኖት ሳለይና በእኩል በማየት ለተቸገሩ ሁሉ አምስት ሳንቲም ሳላስከፍል በነፃ አገልግሎት እንደምሰጥ ለእራሴ ቃል ገብቻለሁ"

ዶክተር መሐመድ ማሻሊ በ2020 አ.ም በ76 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቶል


📱@Amazing_fact_433
📱@Amazing_fact_433

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

18 Nov, 17:34


ይህን አሳዛኝ የእናትነት መስዋዕትነት ምልክትና ተምሳሌት የሆነውን ፎቶ ያነሳው ደቡብ አፍሪካዊ ፎቶግራፈር ማርክ ደምብልተን ነው።

እናት አንበሳ ልጇን ከአዳኞች እንስሳት ለማዳን ስትል ሞት ቀረሽ ፍልሚያ አድርጋለች ።

ልጇን ለማዳን ባደረገችው ትግል አድና ለመብላት የምትጠቀምበትን አንዱን የፊት ጥርሷን አጥታለች፤ ቤተሰቦን በአደን ለምትመግብ አንበሳ የአንድ የፊት ጥርስን ማጣት ምን ያህል እንደሚጎዳ አስቡት።

እናት አንበሳ ልጇን ለማዳን ስትል ከሌሎች እንስሳት ጋር ከፍተኛ ፍልምያ አድርጋ ጥርሷን አጥታ ፊቷ ደም በደም ሆኖ በድል አድራጊነት ስሜት ልጇን በአፎ ይዛ ትታያለች።

ትንሹ አንበሳ ግን እናቱ እሱን ለማዳን ስትል የከፈለቸውን መስዋዕትነት ያወቀና የተረዳ አይመስልም።

ይህ ሁሉ መሰዋእትነት የተከፈለለት አንበሳ ነገ ሲያድግ መንጋውን በጀግንነት ከጠላት እንደሚመክትና እንደሚጠበቅ ተስፋ ይደረግበታል።

እናት

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

18 Nov, 17:21


"በ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ተነስቸ እሮጣለሁ ምክንያቱም ተፎካካሪዬ አሁንም እንደተኛ ስለማውቅ ጥሩ እድል ይሰጠኛል." ይህ ማይክ ታይሰን በየቀኑ ጎህ ሲቀድ ከእንቅልፋ ተነስቶ ይሮጥ እንደሆነ ሲጠየቅ የሰጠው ምላሽ ነበር።

ታይሰን አክሎም "ከተፎካከሪዎቼ አንዱ ከሌሊቱ 10 ላይ እንደሚሮጥ ካወቅኩኝ ፣ከሌሊቱ 8 ሰአት ላይ መሮጥ እጀምራለሁ እና አንዱ ተፎካካሪየ ከሌሊቱ 8 ሰአት ላይ ተነስቶ ልምምድ ስልጠናውን የሚያከናውን መሆኑን ካወኩ ልምምዴን ለመቀጠል ሙሉ በሙሉ መተኛትን አቆማለሁ."።

"ያለ ዲሲፒሊን፣ ምንም ያህል ተሰጥኦ ቢኖርህም ምንም አይጠቅምምህም" - ማይክ ታይሰን

በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የከባድ ሚዛን ሻምፒዮኑ ማይክ ታይሰን የእለት ተዕለት ከ5-8 ኪ.ሜ ሲሮጥ ከተቀረፀው ቪድዬ የተወሰደ ነው ፣ ጋዜጠኞች በ 1987(እ.አ) ስልጠናውን ለመዘገብ ካነሱት

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

18 Nov, 17:06


ይህን ያውቁ ኖሯል ?

በአለማችን ካሉ ፍጡራን እጅግ ከፍተኛ ድምፅ ያለው ፈስ በማንዛረጥ ዜብራ ቀዳሚው ነው። የፈሳቸው ድምፅ ከአንድ ኪሎሜትር በላይ ባለ ርቀት ይሰማል። ግማቱ ደግሞ አፍንጫ ይቆርጣል !

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

18 Nov, 12:39


የሆነ የክብር ሽልማት ቢኖር ለአንጋፋው ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ መሸለም ነበር 🫡

ለነገሩ እኛ ሃገር ሚሰራ ሰው አይበረታታም ተተኪ የሌለው ጋዜጠኛ ሸገር መቆያ ምንም አያምልጣችሁ Sheger FM Youtube ገፅ ላይ ጭንቅላት ሚያሰፋ ፕሮግራም ነው 🤔

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

18 Nov, 12:33


ክፍል 2

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

18 Nov, 12:31


ክፍል 1

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433

4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች

18 Nov, 12:31


Sheger Mekoya - አሳሪዋን ያፈቀረችው ሄለና ሲትሮኖቫ

መሳጭ ታሪክ

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433