በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ። ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው " ሲል ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ጥናት ማድረጉን በጥናቱ ውጤት መነሻነትም የከፍትኛ ትምህርት ተቋማት / የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት በቀን ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል መደረጉን አሳውቋል።
በተደረገው የበጀት ማሻሻያ መሰረት በተቋማቱ የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ይሰራል ተብሏል። በአዲሱ የበጀት ተመን መሰረት ለዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው ተጠቁሟል። #MoE
@remedial_tricks
@remedial_tricks