የተከበራችሁ የሀይለማርያም ማሞ ብርጌድ አመራሮችና አባላት
የተከበራችሁ ከብዙ ጊዜ ድካም በኋላ ለዚህ አማራዊ ክብር የምርቃት ስነስርዓት የበቃችሁ የኮማንዶ አባላት ክቡራትና ክቡራን
ከምንም በላይ አስቀድሜ የአማራነት መዳኛ፣የማንነታችን ህልውና የደማቅ ታሪክ አርማ ለሆነው የአማራ ፋኖ ታላቁ የሀይለማርያም ማሞ ብርጌድ የተወርዋሪ የልዩ ኮማንዶ አባላት ልዩ የምርቃት ዕለት አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ !!
የአማራ ፋኖ ህዝብ ተበደለ ፍርድ ተጓደለ ብሎ የሞቀ ቤቱን ትቶ ምቾቱን ረስቶ ለበቀል ሳይሆን ለፍትህ ህዝቡን እና ፈጣሪውን ተማምኖ ከአምባ ገነኑ የብልፅግናው ስርዓት ጋር እየተፋለመ የሚገኝ እውነተኛ የህዝብ ልጅ ነው፡፡
የምንታገለው በትክክለኛና በተጠና የትግል መስመር፣መነሻችንን እና መድረሻችንን ለይተን የምናቅ በስንቅም በትጥቅም ፣በእውቀትም በክህሎትም የተደራጀን ከቲም እስከ ኮር ተቋም ገንብተን የምንታገል የምናታግል ጀግንነትን ከአባቶቻችን ፅናትን ከማንነታችን የወረስን እኛ አማራዊያን ነን፡፡
የአማራ ህዝብ ለኢትዮጵያዊነቱ ደሙን ያፈሰሰ አጥንቱን የከሰከሰ ፣ሀገር ገንብቶ ያስረከበ ባለውለታ ህዝብ ቢሆንም አሁን ላይ እንዲጠፋ የተፈረደበት፣በየቦታው የሚታረድ ፣ሰርቶ እንዳይበላ የተገደበ፣የሞት ድግስ የተደገሰለት እጁ አመድ አፋሽ የሆነ ህዝብ ስለሆነ ይህንን የሴራ ወጥመድ የምንሰብረው በልኩ ስንነቃ፣አንድ ሆነን ስንደራጅ፣ታጥቀን ስንታገል ብቻ ስለሆነ ሳንወድ በግድ ተገፍተን እየታገልን እንገኛለን።
አንድ ስንሆን እንጠነክራለን፣አንድነታችን መዳኛችን፣አብሮነታችን ድምቀታችን ስለሆነ ጊዜያዊ ልዩነታችንን ወደ ጎን በመተው የጠላቶቻችንን የሞት ሴራ በመበጣጠስ ሞት የተፈረደበትን ታላቁን የአማራ ህዝብ ልንታደገው ታላቅ ቃል ኪዳን አለብን።
እናንተ በብዙ መሰናክል ውስጥ አልፋችሁ በወታደራዊ ብቃት ፣በፖለቲካዊ ንቃት ተክናችሁ ለዚህ የምረቃ ዕለት የደረሳችሁ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር የሀይለማርያም ማሞ ብርጌድ ተወርዋሪ ልዩ የኮማንዶ አባላት:‐ዛሬ የገባችሁት ቃል ኪዳን በተሰው ጀግና ወንድሞቻችን ደም የተፃፈ እውነተኛ የማንነት ኪዳን ስለሆነ በፍፁም ወታደራዊ ዲስፕሊን ፣በአባቶቻችን ጀግንነት፣የጀመርነውን ትግል ለሀቅ በመቆም አንድ እርምጃ ወደ ፊት እንድታስፈነጥሩ አደራየን እያስተላለፍኩ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እናንተ በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር የሀይለማርያም ማሞ ብርጌድ ተወርዋሪ ልዩ የኮማንዶ አባላት ሆናችሁ የተመረቃችሁ መሆኑን በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከሰም ክፍለጦር ስም አበስራለሁ።
በድጋሜ እንኳን አደረሳችሁ!!