ጣና ሚዲያ Tana Media @tanamedia2 Channel on Telegram

ጣና ሚዲያ Tana Media

@tanamedia2


ጣናዊነት አዳማዊነት ኖኃዊነት!!!

ጣና ሚዲያ Tana Media (Amharic)

ጣና ሚዲያ Tana Media ማእከላዊ ተመሳሳይ ቦታ ነው እና ከዚያ ስለሚገኙ እና የሚከተለው መረጃውን ለመሰረተ ወደ ቶና ቻናሎድ ማለፊን ለመያዝ ይጠቀሙ። እንዴት ለእናቴ ሕንፃ ትምህርት እና ምንጭባት በአማርኛና በእንግሊዝኛ ለማነጋገር እና በዘማሪ ሚስጥሩን የሚደርስ ሕይወት ሲሳይ በዚህ ቻናሎድ እንደመግበር ዳታና ውስጥ ያላት ትምህርት ምንም ቀን እንኳን ለመግዛት እና እንደገና እና ስለሚመካ ህይወት ማሰባሰብ ወረርሽ እንደሚሰሙ ለማውረድ ሌሎች ተሳፋሪ ዝርዝር ጣና ሚዲያ Tana Media በተመሳሳይ ጊዜ እንዴት እንረዳለን ደግፎ ለማድረግ እና ለመረጃ ስብስብ ሚስጥሩን ይወስዳል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

03 Dec, 07:31


ኮለኔል አበራ አዛናው የ34 ዓመት መከላከያ ሠራዊትን ያገለገሉ የሥራ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው ጉምቱ የሥርዓቱ እና የአሁኑ ፋሽስት ሠራዊቱ አዛዥ የፈንጅ አምካኝ ባለሙያዎች ጠቅላይ ኃላፊ ሲሆኑ በዛሬው ዕለት በአማራ የህልውና ትግል መስመር ለመታገል የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝን ተቀላቅለዋል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

03 Dec, 05:54


መረጃ❗️
ከወልደያ ወደ ዶሮግብር  የጠላት ሀይሌ እሬሽን ጭኖ እየተጓዘ ሲሆን አናብስቶች ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ እንዲሁም ምቹ ሁኔታ ካለ አስታጥቄን እንዲረከቡት መረጃው ሸርርርርር በማድረግ ይዳረስ❗️

24/03/2017 ዓ.ም

ጣና ሚዲያ Tana Media

03 Dec, 05:54


ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም የድርጅታችን አማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ አመራሮች ከጤና ቡድን አመራር አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል ።

የአማራ ፋኖ በጎጃም አጥንት ስፔሻሊስት ሐኪሞችን፣  ጠቅላላ ሀኪም ነርሶችን፣ የድንገተኛ ቀዶ ህክምና፣ የጤና  መኮንኖችን፣ ላብራቶሪ ቴክኒሽያኖችን፣ፈርማሲስቶችን፣ የአንስቴዥያ ባለሙያወችን፣ የስነ-ምግብ ባለሙያወችን እና የጤና መረጃ ባለሙያወችን ጨምሮ 66 ፕሮፋሽናል የጤና ባለሙያወች አሉ።

ሐኪሞቻችን ለሰራዊታችን ከሚሰጡት ሕክምና ጎን ለጎን ለማህበረሰባችን የጤና ምክር እና አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ርብርብ ያደርጋሉ ።

የብልጽግና ሰራዊት ያወደማቸውን የጤና ተቋማት እና የተሰባበሩ የህክምና መሳሪያዎችን በመጠገን በጦርነት መሐል ህይወትን የማዳን ታሪካዊ ተልዕኳቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ።
እነዚህ ጀግኖች የመድሐኒት : የህክምና ቁሳቁስ እና ሌሎች የህክምና ግብዓቶች ድጋፍ በእጅጉ ይሻሉ ።

የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ደጋፊዎች ከጀግኖች ሐኪሞቻችን ጎን ትቆሙ ዘንድ ጥሪ እናስተላልፋለን።(ማርሸት ፀሐዩ)

ጣና ሚዲያ Tana Media

02 Dec, 19:28


የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) መግለጫ ..‼️‼️

ቀን ኀዳር 21 ቀን 2017

የድርጅቱ ዓለማቀፍ አስተባባሪ ኮሚቴ መቋቋሙን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ !

አገር ሰሪው ታላቁ የዐማራ ሕዝብ በደምና አጥንቱ የበዛ ዋጋ ከፍሎ በገነባት ኢትዮጵያ፣ ማንነቱ እንደወንጀል ተቆጥሮ የጥፋት ሰይፍ ተመዝዞበታል፡፡ ዐማራ፡- በትርክት፣ በሕግ፣ በፖሊሲና ይህን ተከትሎ በተፈጠሩ መዋቅራዊ ማጥቂያዎች ግልጽና ተጨባጭ የኀልውና አደጋዎች አጋጥሞታል፡፡

ላለፈው ግማሽ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ የፖለቲካ አየር ፀረ-ዐማራነትን የሚተነፍስ፤ የዐማራን እምባ የሚያፈስ፣ የዐማራን ደም የሚጠጣ፣ የዐማራን አጥንት የሚከሰክስ በጥቅሉ የዐማራ ሕዝብን ማጥቃት የፀረ-ኢትዮጵያ ኀይሎች "ፖለቲካ" ሆኖ ቆይቷል፡፡ ይህ ለግማሽ ክፍለ ዘመን የዘለቀ ፀረ-ዐማራ አስተሳሰብና የዚሁ አስተሳሰብ ውላጅ የሆኑት ተከታታይ አገዛዞች፣ የዐማራን ሕዝብ ርስት፣ ማንነት፣ ታሪክና መልካም ስም ጥላሸት ከመቀባት አልፈው ተፈጥሯዊ የመኖር መብቱን አደጋ ላይ ጥለውታል፡፡

ይህን ተከትሎ፣ ዐማራ እንደሕዝብ በሕይወት የመኖር ያለመኖር የኀልውና ትግል ውስጥ ገብቷል፡፡

ይህንንም የኀልውና አደጋ ለመቀልበስ እኛ የዐማራ ልጆች በአገር ቤት በነፍጥ ታላቅ ተጋድሎ እያደረገን መራር መስዋዕትነት እየተከፈልን ትግል ሜዳው ላይ እንገኛለን፡፡ በውጭ ዓለምም በማህበራዊ ንቅናቄና ዲፕሎማሲው ረገድ ከባድ ትንቅንቅ በመደረግ ላይ ነው፡፡

የኀልውና ትግሉ መነሻም የዐማራ ሕዝብ የመኖር መብት ጥያቄ ውስጥ መውደቁ በመሆኑ፣ ከዚህም የኀልውና አደጋ ለመውጣት በውስጥም በውጭም ከፍተኛ ትግል እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም፣ ትግሉ በወሳኝ ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡

ይህን በደም እየተጻፈ ያለ ደማቅ የትግል ታሪክ እየመራ፣ እያታገለና እየታገለ የሚገኘው ድርጅታችን የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) የውጭውን ማኀበረሰብ የተለመደ ሕዝባዊ ንቅናቄ አገር ቤት ለሚገኘው ትግል ግብዓት ሆኖ እንዲያገለግል በማሰብ በዛሬው ዕለት ማለትም፤ ኀዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ዓለማቀፍ አስተባባሪዎችን ሰይሟል፡፡

ድርጅታችን ላለፉት ሦስት ወራት ሌት ተቀን ሲሠራበት የቆየው ይህ የውጭ አደረጃጀት ጉዳይ ተጠናቆ ዛሬ ለፍጻሜ በቅቷል፡፡ ይህ የትግሉ የዕድገት ምዕራፍ አንዱ ስኬት ነው፡፡ ይህ ወሳኝ የታሪክ መታጠፊያ ምዕራፍ ድርጅታዊ አቅምን ማሳደግ የሚጠይቅ፣ ትግሉን ለዘላቂ ድል ለማብቃት በተቋማዊ ትግል አግባብ መመራቱን እንዲቀጥል የሚያደርግ የትግሉ ወሳኝ የአካል ክፍል ነው፡፡

በመሆኑም የሚከተለውን ጥሪ ለወገን ማስተላለፍ እንፈልጋለን!

የተከበራችሁ በውጭ አገራት ነዋሪ የሆናችሁ ዐማሮች፣ የዐማራ ወዳጆች የሆናችሁ ኢትዮጵያዊያን እና የዐማራና የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆናችሁ ወገኖቻችን ሆይ!

የዐማራ ሕዝብ የገባበት የኀልውና ትግል ተገዶ ስለመሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ የዐማራ ሕዝብ የገጠመው የኀልውና አደጋ ከዐማራ አልፎ የኢትዮጵያ ሀገረ-መንግሥት ኀልውናን አደጋ ውስጥ የሚከት ብሔራዊ የደህንነት አደጋ መሆኑ ታውቆ ያደረ ጉዳይ ነው፡፡

ፋሽስቱ የብልጽግና አገዛዝ በዐማራ ሕዝብ ላይ ዘርፈ ብዙ ጦርነቶችን ሲከፍት፡- ለዚህ ዘርፈ ብዙ የዘር ማጥፋት ዓላማ ያለው ጦርነት ሰፊ የሆነ የሰው ኃይል፣ የገንዘብ፣ የጦርና የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን፣ ፖሊሲና ሕጎችን አውጥቶ ተጠቅሟል፤ አሁንም በመጠቀም ላይ ነው፡፡ አገሪቱ ያላትን ሀብት በሙሉ ዐማራን ለማጥፋት እየዋለ ይገኛል፡፡

የጦር ወንጀለኛው የብልጽግና አገዛዝ የዐማራ ሕዝብን ለማጥፋት እግረኛ ሰራዊት፣ መካናይዝድ እና አየር ኀይል (ድሮንና የውጊያ ሂሊኮፕተር) በመጠቀም ህዝባችንን እንደ ቅጠል እያረገፈ ይገኛል፡፡ ጠላት ብልጽግና የአገሪቱን የካፒታል በጀት እስከማጠፍ ደርሷል፡፡ ታንኩንም ባንኩንም ለዚህ ጦርነት መድቦ በሙሉ ጉልበቱ ዐማራን ለማጥፋት እየሰራ ነው፡፡ በአንጻሩም አናብስት የዐማራ ልጆች በቀላልና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎች እየተናነቁ የጦር ወንጀለኛውን የብልጽግና ሰራዊት ሰብዓዊና ወታደራዊ አቅሞቹን እያሽመደመዱት ይገኛል፡፡

በዐማራ የቁርጥ ቀን ፋኖ ከባድ ምት በደረሰበት ቁጥር ንጹሃንን የበቀል ማወራረጃ ያደረገው የብልጽግናው አገዛዝ፣ በጦር ወንጀለኝነት ድርጊቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ አገዛዙ የመጨረሻ ያለውን ንጹሀንን በጅምላ የማጥቃት ተግባር እየፈጸመ ይገኛል፡፡

እኛም በአገር ቤት ትግሉን የምንመራ ውድ ልጆቻችሁ የዚህን አረመኔ አገዛዝ ግብዓተ መሬት ለማፋጠን የሞት ሽረት ትግል እያደረግን እንገኛለን፡፡ ለዚህ ዘመቻችን ቀኝ እጅ ሆኖ ሲያገለግለን የቆየው በውጭ አገራት የሚገኘው ወገናችንም የሚችለውን ሁሉ እንዲያግዝ ጥሪያችንን ስናስተላልፍ በትግሉ ተአማናኒነት እና በማስተባበር ብቃታቸው የተመሰከረላቸውን አስተባባሪዎች የትግል ግዴታ መስጠታችንን በማሳወቅ ነው፡፡

በውጭ አገራት የምትገኝ ውድ ወገናችን ሆይ!

ይህ የኀልውና ትግል የዐማራን ሕዝብ እንደሕዝብ ወደፊት የማሻገር አልያም እንደሕዝብ የመጥፋት ወሳኝ ታሪካዊ ዕጥፋት ጉዳይ ነው፡፡ ይህ የኀልውና ትግል ከፀረ-ዐማራ ኃይሎች ጋር የሚደረግ፣ የዐማራ ኀልውና ብቻ ሳይሆን፤ የኢትዮጵያም የኀልውና ትግል ነው፡፡ ይህ የኀልውና ትግል ፀረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ዐማራን ጨርሶ አገር አልባ እንዳያደርጉት የአገር ባለቤትነቱን መልሶ ለማረጋገጥ የሚያደርገው የሞት ሽረት ትግል ነው፡፡

እናም ሁሉም ዐማራ እና የዐማራ ወዳጆች በሙሉ የኀልውና ትግሉ አካል መሆን አለባቸው በሚለው ድርጅታዊ የትግላችን መርህ መሠረት፡- ትግሉ አካላዊ ብቻ ሳይሆን ሁሉን አቀፍ ንቅናቄና ድጋፍ በመሆኑ በውጭ አገራት የሚገኘው ወገናችን የ ኀልውና ትግል ሚናውን በማስፋት ለዘላቂ የጋራ ድላችን የጋራ ርብርብ እንድናደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በውጭ አገራት የሚገኘው ወገናችንን ሕዝባዊ ትግሉን በቀናኢነት፣ በፅናትና በቁርጠኝነት እንዲደግፍ ጥሪያችንን ስናቀርብ፣ ከዚህ ቀደም ም በኀልውና ትግሉ ላይ የተጫወተውን የትግል ታሪክ ቀያሪ ሚና በዚህ ወሳኝ የትግል ምዕራፍ ላይም እንደሚደግመው በመተማመን ነው፡፡

በመሆኑም የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትን የመሰረትነው አምስቱም እዞች ማለትም፥

• የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ
ግዛት እዝ፥
• ⁠የአማራ ፋኖ የጎንደር እዝ፥
• ⁠የአማራ ፋኖ የወሎ እዝ፥
• ⁠የአማራ ፋኖ በጎንደር፥
• ⁠የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት
የጎጃም እዝ የየእዙ ተወካዮች እና አዛዦች እንዲሁም በየእዞቹ ስራ አስፈጻሚዎች ተመርጠው የትወከሉ የውጭ አስተባባሪዎች ለረጅም ጊዜ ውይይት በማድረግ
ዶ/ር አምሳሉ አስናቀ የድርጅታችን ዓለማቀፍ አስተባባሪ ሰብሳቢ ሆነው እንዲመሩ የታመነባቸውና ሙሉ ዕውቅና የተሰጣቸው በመሆኑ ሁሉንም ዓይነት ድጋፍ እንድታደርጉላቸውና ጠቅላላ ስራ አስፈፃሚውን እንዲያዋቅሩ ሙሉ ውክልና የሰጠናቸው መሆኑን እናሳውቃለን::

ከ5ቱም ዕዝ የተውጣጡ የውጭ ኮሚቴውንም እንዲያስተባብሩ ሙሉ ውክልና ተሰቷቸዋል:: ለነዚህ አዲስ ለተወከሉ የውጭ አስተባባሪወች ከጎናቸው እንድትቆሙና እንድትደግፏቸው ስንል የትግል አደራ ጥሪያችንን በድጋሜ እናስተላልፍላችኋለን፡፡

እነዚህ ውክልና የተሰጣቸው የውጭ አመራሮች በየአገራቱ ቅርንጫፎቻቸውን ከአገር ቤቱ አመራር በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት የሚያደራጁ እና ከአማራ ማህበራትና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ጋር ተናብበውና ጤናማ ግንኙነት ፈጥረው የሚስሩ ይሆናል፡፡

ድል ፋኖ!

የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት
(አፋሕድ)

ህዳር 22 ቀን 2017
ከትግሉ ሜዳ

ጣና ሚዲያ Tana Media

02 Dec, 19:04


በአዲስአበባ ከተማ ስድስት ኪሎ ጃንሜዳ አካባቢ ምኒልክ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የእሳት አደጋ ተከስቷል። በአደጋው ስለደረሰው የጉዳት መጠን እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።

ጣና ሚዲያ Tana Media

02 Dec, 11:00


መርሃቤቴ | ሰኞ ገበያ

ሸዋ መርሓቤቴ አውራጃ ደራ ቱቲ ሰኞ ገበያ ከተማ በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለው የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ህዝባዊ ተቃውሞ አካሄደ!

ጣና ሚዲያ Tana Media

02 Dec, 10:36


የድል ዜና !!

በሸዋ ቀጠና ይፋት ደብረ ሲና ከተማ አማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ፂዮን ኮር የአርበኛ ፋኖ ራንቦ ክፍጦር ከንጋት ጀምሮ ታሪክ እየሰራ ይገኛል።ደብረሲና ከተማን የጨፍጫፊው አብይ አህመድ ብልግና ሠራዊት የመሸገባት ቢሆንም አይበገሬው  ፋኖ ወደ ከተማዋ ሰርገው  በመግባት በወሰኑ የቅኝት በድን በመብረቃዊ ጥቃት የአገዛዙን ተላላኪ ሚሊሻና ፖሊስን አይቀጡ ቅጣት መቅጣታቸው ተገልጿል።

በአውደ ውጊያው ምሽጉ ላይ እያለ የተመታው የአገዛዙ ሠራዊት መሳሪያውን እየጣለ መፈርጠጡም ታውቋል።

   በነበረው የግንባር ተጋድሎ ድል ማስመዝገቡን የገለፀው ክፍለ ጦሩ  የአብይ አህመድ ሠራዊት ስነ-ልቦናው የወደቀ ፣ ልምድ አልባ ፣መሳሪያና ትጥቅ በአግባቡ መሸከም የማይችል እንዲሁም ወኔው የተሰለበ መሆኑን ያረጋገጥንበት ነው ሲል የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ የአፄ አምደ ፂዮን ኮር የአርበኛ ራንቦ ክፍለ ጦር የህዝብ ግኑኙነት ኃላፊ ገልጿል

ጣና ሚዲያ Tana Media

30 Nov, 03:55


አራጁ የኦሮሞ መንግሥት አማራዎችን አርዶ በልቷል።ኦህዴድ ብልፅግና ድራማ ለሰራበት የደራው እርድ ክሊፕ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

ዛሬስ በአርሲ ለጨፈጨፋቸው ምን አለ?
ይሄው ነው…የተፈቀደ ሟች ነን እና ማን ከቁብ ይቆጥረናል?

ሞታችን የቁጥር ጨዋታ እንጅ፣ አስደንጋጭ ኢሰብዐዊነት ሆኖ እንዳይታይ… ፍርሃታችን እና አንድነት ማጣታችን ዋና ሰበብ ነው።
አብይ አህመድ ወንጀለኛ ነው!

ጣና ሚዲያ Tana Media

29 Nov, 20:53


በኦሮሚያ ክልል፣ አርሲ ዞን፣ ሽርካ ወረዳ፣ ሶሌ ፈረንቀሳና ሶሌ ጡጃ ቀበሌ ትላንት ኅዳር 19 ለኅዳር 20 አጥቢያ ከሌሊቱ 8፡00 ገደማ አንገታቸው እየተቀላ የተገደሉ አማራዎች!

ጣና ሚዲያ Tana Media

29 Nov, 19:52


የአለምአቀፉ ማህበረሰብ አይንና ጆሮውን ቀስ በቀስ ወደ ፋኖ ኃይሎች ማማተር ጀምሯል። እንግሊዛዊው ጋዜጠኛ ሳይመን ቬራም ከፋኖ ኃይሎችና ከተማረኩ የአገዛዙ ሰራዊቶች ጋር

ጣና ሚዲያ Tana Media

29 Nov, 19:14


በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች በቅርቡ ከስራ ሊቀነሱ እንደሆነ ታውቋል!

ከሰሞኑ የፀደቀው የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ "ተቋማት ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲፈፅሙ የሚያስችል ነው" ቢባልም ከአዋጁ ጋር ተያይዞ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች ከስራ ሊቀነሱ እንደሚችሉ ስማችን አይጠቀስ ያሉ ሁለት የመንግስት ምንጮች ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል። 

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚንስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ሂደቱ የግለሰቦችን መብት ያለአግባብ እንዳይጎዳ ሚዛኑን አስጠብቆ በመሄድ ረገድ ተገቢው ጥንቃቄ ይደረጋል ቢሉም በርካቶች ከስራቸው እንደሚቀነሱ እንደማይቀር ታውቋል።

አዋጁ እንደ ፍርድ ቤት፣ አቃቤ ህግ፣ ፖሊስ፣ መከላከያ፣ እና ደህንነትን የመሳሰሉ ተቋማት ውስጥ ተፈፃሚ ይሆናለሰ ተብሏል።

የዚህን የመንግስት ሰራተኞች ቅነሳ የሚጠቁም ነገር ግን ብዙ ሰው ልብ ያላለው አንድ መረጃ በአንድ የመንግስት ሚድያም ተለቆ ነበር።

"ሲቪል ሰርቪሱ ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ መሆኑ ተጠቆመ" የሚል መረጃ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ፕረስ ድርጅት ተሰራጭቶ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ያለው የሲቪል ሰርቪሱ ቁጥር ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ መሆኑን ዶ/ር ነገሪ መናገራቸውን ዘግቦ ነበር።

ዘገባው የጋዜጠኛ ኤሊያስ መሰረት ነው!

ጣና ሚዲያ Tana Media

29 Nov, 18:30


እሳትና ውሃ የሆነ ትግል ነው።
ይጥፉ ወይስ እንጥፋ ነው ጥያቄው?
መልሱ አንጠፋም ነው።
እምሽክ!!!

ጣና ሚዲያ Tana Media

28 Nov, 19:20


#ዘገባ:

የአማራ ማህበር በአሜሪካ ከመስከረም 15 እስከ ኅዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም. በአማራ ክልል በሚገኙ 38 ወረዳዎች 72 ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና የአየር ድብደባዎች 321 ሰዎች ሲሞቱ 113 ቆስለዋል በአጠቃላይ 434 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን መዝግቧል።

#REPORT:

AAA has documented 72 drone and airstrikes across 38 woreda administrations in Amhara Region for the period between September 25th and November 23rd, 2024 which have resulted in 434 casualties including 321 persons killed and 113 injured.

ጣና ሚዲያ Tana Media

28 Nov, 18:06


አዲስ አበባ ...

ጣና ሚዲያ Tana Media

28 Nov, 18:06


ድል እና 11ኛው ቀን
ደምበጫ በዓባይና(ወለጋ ድንበር) በተምጫ ሸለቆ ቆላማው አካባቢ መቃር ደጋ በዴስ ተራራ ላይ ተንጠልጥሎ ያደረው ጠላት ዛሬ ዋየምን ላይ ሲቆላ ውሎ ምሽት ላይ ብትንትኑ ወጥቷል💪

ጣና ሚዲያ Tana Media

28 Nov, 18:02


አማራ ክልል ከ4.7 ሚሊዮን ተማሪዎች አይማሩም!

አማራ ክልል በፌደራሉ መንግሥት ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚደረገዉ ዉጊያ 4.7 ሚልየን ህፃንት መማር አለመቻላቸዉን የአማራ ክልል የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት መድረክ ወይም ፎረም አስታወቀ።

በአማራ ክልል በሚደረገዉ ጦርነት 4.5 ሚሊየን ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው። የትምህርት ቤቶች ፈርሰዋል። መምህራን ተሰደዋል። ቀየው በጦርነት እና በ ድሮን ጥቃት ታርሷል። 969 የሚደርሱ የክልሉ የጤና ተቋማት ወድመዋል።  ይህ ቁጥር በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የውደሙትን  አይጨምርም።

የክልሉ የጤና ቢሮ እና ኢንስቲትዩት  ባደረጉት ጥናትና  ከአለም አቀፍ ተቋማት በሰበሰበው መረጃ  በክልሉ ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ካለፈው ዓመት ማብቂያ አንስቶ የመንግሥት ኃይሎች ቢያንስ 13 በሚደርሱ ከተሞች በጤና ተቋማት እና በሠራተኞች እንዲሁም በትራንስፖርት አገልግሎቶች ላይ ጥቃት ፈፅመዋል።

በአማራ ክልል ትምሕርት የሚሰጥባቸዉ ትምሕርት ቤቶች በከተሞች አካባቢዎች የሚገኙ ናቸዉ።

በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ሕግ ሀገራት  በጦርነት ውስጥ ቢሆን እንኳን የህክምና ተቋማት፣ ባለሙያዎች፣ ህሙማን እና አምቡላንሶች ልዩ ጥበቃ እንዲያገኙ የሚያዝ መሆኑን የጠቀሱት በአማራ ክልል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ፅሀፊ አቶ ታፈረ መላኩ ለዶቼቬሌ  እንደገለፁት

የጤና ተቋማትና  እና ትምህርት ቤቶች በመውደማቸው ሌሎች ደግሞ በሥጋት ምክንያት በመዘጋታቸው 4.7 ሚሊየን ህፃናት ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸው ተገልጿል በዚህም መስረት 4.870 ትምህርት ቤቶች ሲዘጉ 5379 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ወድመዋል

መንገድ የለም። መንቀሳቀስ አይቻልም። አገልግሎት መስጫ  ተቋማት ዝግ ናቸው። ሰዎች በየደቂቃው በሚለዋወጠው የአካባቢው  የፅጥታ ስጋት ምክንያት  በፍርሀት  ታስረው ነው ያሉት፣  የጤና ባለሙያዎች ህክምና እየሰጡ ሆስፒታሎች በጥይት ይደበደባሉ ።  ይህም  ሕዝብን የጤና አገልግሎት እንዳያገኝ አድርጎታል።እኛ እያልን ያለነው አለም አቀፍ የስባዊ መብት ህግ ይከበር ፣ ምንም የማያውቁ ሰላማዊ ሰዎች  እልቂት ይቁም ነው  ሲሉ ለ DW የገልፁት የክልሉ የ ጤና ባለሙያ ፕሮፊሰር ፈንቴ አንባው ናቸው ።

አለም አቀፉ ማህበረስብ እና ሚዳያዎችትኩረት ያላደረጉበት የአማራ ክልል ግጭት ከፖለትካ ነፃ የሆኑት ተቋማት ዋጋ እያሰከፈለ ሲሆን ባለሙያዎችም በመሳሪያ ታጅቦ ህክምና ለመስጠት ይገደዳሉ ፣ በየግዜው መሳሪያ ባነገቡ ሀይሎች  ባለሙያዎች፤  በሚደርስባቸው ጫና ምክንያት በሥራ ገበታቸው ላይ ወጣ ገባ እያሉ ለመሥራት መገደዳቸውን ተገልጿል ክልሉ በአሁኑ ወቅት የወደሙ የጤና ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ከ48 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልጋል ተብሏል።

 መረጃው የጀርመን ድምፅ ነው!

ጣና ሚዲያ Tana Media

14 Nov, 18:45


ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ዛሬ በኦህዴድ የግፍ ችሎት የተናገረው ነው !
------------------
“ወንጀል አልፈጸምኩም! ጥፋተኛም አይደለሁም! ነገር ግን የአማራ ሕዝብ የዘር ፍጅት ተፈጽሞበታል እየተፈጸመበትም ነው ብዬ አምናለሁ። ማመን ብቻ አይደለም ለአማራ ሕዝብ ጥቅም ስል እታገላለሁ! የአማራ ሕዝብ በወለጋ፣ በመተከል፣ በአጣዬ፣ በሻሸመኔ ፣ በማይካድራ... በመላው ኢትዮጵያ እና በግዛቱ እየታረደ- እኔ ፍራሽና ብርድ ልብስ ስላለኝ ብቻ ልተኛ ፈጽሞ አልችልም። የአማራን ሕዝብ የጨፈጨፉና ያስጨፈጨፉ እንዲሁም እኔን ጨምሮ ጓዶቼን በሐሰት የከሰሱትን ሹመኞች የናዚ (የሒትለር) ሹመኞች እንደተሰቀሉት፤ ለፍርድ አቀርባቸዋለሁ። ወንጀል አልፈጸምኩም ፣ ለሕዝብ ግን እታገላለሁ!"

ጣና ሚዲያ Tana Media

14 Nov, 18:43


🔥#የጠላት_እንቅስቃሴ_ወሎ‼️

ከምሽቱ 2:00 አካባቢ አገዛዙ ከደሴ ወደ ኩታበር አቅጣጫ 1ካሶኒ ሀይል አንቀሳቅሷል ጥንቃቄ ተገቢው አቀባበል ይደረግ ሲሉ የንስር አማራ ምንጮች ገልፀውል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

14 Nov, 17:45


ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ


ዛሬ በፍርድ ቤት ያደረገው ታሪካዊ ንግግር

ከዚህ በመቀጠል በተከሰስኩበት ክስ የእምነት ክህደት ቃሌን እሰጣለሁ።
በቀዳሚነት የተከሰስኩት ጉዳይ የአማራ ህዝብ እኩል ከሌሎች ብሄሮችና ህዝቦች ጋር የአገር ባለቤት ሆኖ እያለ አገር ተወስዶበታል ብሎ ተናግሯል የሚል ነዉ።ክሴ ይሄን የሚል በመሆኑ አሁን ለፍርድ የቀረበዉ የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ነዉ ማለት ነዉ።

የአማራ ህዝብ ላለፉት ሰላሳ አራት አመታት ፀረ አማራ ሀይሎች ተደራጅተው እና ተቀናጅተው ስልታዊ እና መንግስታዊ ጥቃት እያደረሱበት ያሉ ህዝብ ነዉ።
የአማራ ህዝብ የአገር ባለቤትነቱንበግልፅ በአደባባይ የተነጠቀዉ በ1983 ዓ.ም አማራ ጠል ሀይሎች የመንግስት ስልጣንን ተቆጣጥረዉ ባደረጉት የ ሰኔ 1983ቱ የቻርተሩ ጉባኤ ነበር።
ጉባኤው ያለምንም የአማራ ህዝብ ዉክልና የተካሄደ መሆኑን የስርአቱ ቁንጮ መለስ ዜናዊ በአደባባይ የመሰከረው ሀቅ ነዉ።በዚህ የቻርተር ጉባኤ የተመሰረተው የሽግግር መንግስት ባደረገው የክልል አከላለል ዉስጥ ምንም አይነት የአማራ ህዝብ ዉክልና ያልነበረው ሲሆን በዚህ የሽግግር መንግስት ዘመን የተዘጋጀው ህገመንግስትም የአማራን ህዝብ በማዉገዝ ተጀምሮ በማዉገዝ ያለቀ መሆኑን የቻርተሩ ጉባኤ ቃለጉባኤዎች ,የሽግግር ም/ቤቱ ቃለጉባኤዎች,የህገመንግስት ጉባኤ ቃለጉባኤዎች ዘላለማዊ ምስክር በመሆኑ ያስረዳሉ ።
በዘመኑ ትህነግ/ኢህአዴግ በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀሙት አድሏዊ ድርጊቶች ,መፈናቀሎች,የንብረት ዉድመት,የዘር ፍጅትእና አገር አልባነት ልለፈዉና የዛ ስርአት ቀጥተኛ ወራሽ የሆነውን የብልፅግና ፓርቲ እና መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ የፈፀመዉን እና እየፈጸመ ያለዉን በደል ልግለፅ።

የብልግና መንግስት በአማራ ህዝብ ተጋድሎ ወደ ስልጣን የመጣ ቢሆነም ህገመንግስታዊ ማሻሻያን ጨምሮ ፀረ አማራ የሆኑትን የመንግስት ፖሊሲዎች አስተካክላለሁ ብሎ ቃል ገብቶ የነበረ ቢሆንም በተግባር ግን አማራ ጠል መሆኑን ያስመሰከረዉ ጊዜ ሳይወስድ ነበር።
የብልፅግና መንግስት ከ ትህነግ ኢህአዴግ የወረሰውን የፌደራል እና የክልል ህገመንግስቶች ,ፖሊሲዎች እና መመሪያዎች ይዞ ቀጥሏል።ከ 50 በላይ በአማራ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት እንዲፈፀም ፀረ አማራነትን የሚቀሰቅሱ መፃህፍት አሳትሟል ።በምርምር መፅሄቶች ስም አማራ ጠልነትን ሰብኳል።በመንግስትነቱ በሚያስተዳድራቸው በኦሮምያ ቱሪዝም ቢሮ,በኦሮምያ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት,በኢትዮጽያ ፕሬስ ድርጅቱ ስር በሚታተሙ መፅሄትና ጋዜጦቹ በአማራ ህዝብ ላይ ለአመታት የቆየ የጥላቻ ዘመቻ አካሂዷል ።ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፀረ አማረ ንግግሮች እና ትንኮሳዎች ተደርገዋል።

በተጨማሪም የብልፅግና መንግስት የአማራ ህዝብ የፖለቲካ ዉክልና እንዳይኖረው በማድረግ ዛሬ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠረው ከአማራ ክልል ዉጭ የሚኖረው የአማራ ህዝብ ምንም አይነት የፖለቲካ ዉክልና የለዉም ።

ከመንግሥት የስራ ሀላፊነት ጠርጎ በማዉጣት አድሎአዊ አሰራርን በማስፈን በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በማፈናቀል ፣ በቢሊዮኖች የሚገመት የአማራን ህዝብ ሀብትና ንብረት በማውደም እንዲሁም ዘግናኝ የሆነ እንኳን ሊያዩት ሊሰሙት እንኳ የሚከብድ የዘር ፍጅት እንዲፈፀም አድርጓል ። ይህ የዘር ፍጅትበመላው ኢትዮጵያ በሶማሌ ፣ በኦሮሚያ ፣ በትግራይ ፣ በሲዳማ ፣ በቀድሞ የደቡብ ክልል ፣ በጋምቤላ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች የተፈፀመ ነው ።
ለዚህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የአይን ምስክሮች በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ፣ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ላይ የሚሰሩ ጥምረት እንዲሁም አለም አቀፍ የሆኑት የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና የሂውማን ራይትዎችን ዘገባዎች በማየት መረዳት ይቻላል ።
ጉዳዩን ሊከታተል ይችላል ተብሎ ይታሰብ የነበረው የብልፅግናው የአማራ ክልል መንግሥት ደግሞ እንኳን የአማራን ህዝብ ሊታደግ የገዛ ስልጣኑን የማያውቅ ፣ የፖለቲካ ነፃነቱን አሳልፎ የሰጠ እንዲሁም ከውሳኔ ሰጪነት ወደ ፈፃሚነት የወረደ ነው ። (ከክልሉ ውጪ ያሉ አማራዎች እንታገላቸዋለን እንጂ አንታገልላቸውም)ከማለት የደረሰ ሎሌ ነዉ።

በተደጋጋሚ ባጋጠሙ ጉዳዮችም ተፈትኖ የወደቀ ለምሳሌ በአማራ ልዩ ሃይል መፍረስ ፣ በፕሪቶሪያ ድርድር ፣ በሱዳን ወረራ ፣ በአጣዬ እና ሸዋሮቢት ፍጅት የአማራን ህዝብ መብት ማስከበር ያልቻለ ለተፈናቃይ ዱላ ለዘር ፈጂዎች ግን ካባ የሚሸልም ስብስብ ነው ።

የፌደራል መንግሥቱ ደግሞ ያለምንም እፍረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ፣ አቃቢ ህጉ ፣ መርማሪው ፣ ደህንነቱ ፣ የፍርድ ቤት አስተዳደር በአጠቃላይ የአንድ ብሔር/ሀይማኖት አባላት በመሆን ህግን የማጥቂያ መሣሪያ በማድረግ የአማርን ሕዝብ ልጆች ያጠቃል ።
የአማራ ሕዝብ ከላይ በጠቀስኳቸው ምክንያት የሀገር ባለቤትነቱ የተወሰደበት ፣ ሀገሩን የተቀማ በመሆኑ ፣ ድርጊቱም ሥርአታዊና መንግሥታዊ ለመሆኑ የሚመሠክሩ በርካታ ማስረጃዎች ያሉ በመሆኑ የአማራ ህዝብ ከዚህ የህልውና አደጋ ለመውጣት መንቃት ፣ መደራጀትና እራስን ከጥቃቶች መከላከል ይገባዋል የሚል የፀና አቋም ያለኝ በመሆኑ ይሄንን ዘረኛ እና ነውረኛ አንባገነን ሥርዓት ለመጣል ትግል እንደሚያስፈልግ እምነቴ ነው ።

በጭብጦቹም ላይ

* የሸዋ ፋኖን በማደራጀት በኩል የራሴን አስተዋፅኦ አድርጊያለሁ
*የአማራ ፋኖን ወደ አንድነት ለማምጣት ሲባል የተመሠረተው አመቻች ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆኜ ሠርቻለሁ
*የአማራ ፋኖ ምክርቤት እንዲመሠረት የራሴን አስተዋፅኦ አድርጊያለሁ

* አገሪቱ በተቀበለቻቸው ዓለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ድንጋጌዎችና የብልፅግና መንግሥት እመራበታለሁ በሚለው ህገመንግስት በሰፈሩት ሰብአዊና እና ዲሞክራሲያዊ መብቶቹን መሰረት በማድረግ የህዝቤን ግፍ እና በደል ለማስቆም በህቡዕ ሳይሆን በአደባባይ ታግያለሁ።

*የሰራሁት በሙሉ በግልጽ በአደባባይ የተፈፀመ እንጂ ምንም አይነት ህቡዕ ድርጅት አቋቁሜ አልሰራሁ።

*በህቡዕ አደረጃጀት ተፈፀሙ የሚሉትን ተግባራት አላዉቅም።አልፈፀምኩም

የኢትዮጵያ ህዝብ የአማራን ህዝብ በደል በደንብ ይገነዘባል ብዬ አምናለሁ የኢትዮጵያ ህዝብ "የአማራ ህዝብ እንባ በዋንጫ"ቢሰጣቸዉ የማይጎፈንናቸዉን የብልፅግና ስርአት ቁንጮዎች በቃችሁ ሊላቸዉ ይገባል።

በተጨማሪም የአማራ ህዝብ የህልዉና ትግል ለነፃነት ለእኩልነትና ለፍትህ የሚደረግ ትግል እንጅ ጠላቶቻችን እንደሚያወሩት ሌላዉን ለመጨፍለቅ የሚደረግ ባለመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ የአማራን ህዝብ የህልውና ትግል ደግፎ እንዲቆም እጠይቃለሁ።

አለማቀፉ ማህበረሰብም የአማራ ህዝብ እየተፈፀመበት ያለዉን የዘር ፍጅትና መፈናቀል ቸል በማለቱ በጣም እያዘንኩ ለአምባገነኑ መንግስት ጅምላ ጨራሽ ድሮዎኖች እና ተተኳሾችን የሚያቀብሉ አገራት ታሪክና እና እግዚአብሔር ፍርዱን ይሰጣችኋል እላለሁ።

አመሰግናለሁ ።
ኅዳር 5/2017 ዓ.ም

ዶ/ር ወንዶሰን አሰፋ
ፋኖ ሚዲያ -የአማራ ሕዝብ ድምፅ

ጣና ሚዲያ Tana Media

14 Nov, 11:51


አሳዛኝ ዜና‼️

የኦሮሚያ ተፈናቃይ አምሓሮች በድሮን ተጨፈጨፉ‼️

ዛሬ መንዝ ማማ ባሽ ንዑስ ወረዳ ላይ በፈፀመው የድሮን ጥቃት ከኦሮሚያ ክልል በሽመልስ አብዲሳ ኦነጋዊ አገዛዝ ተፈናቅለው በቀበሌ ሼድ ውስጥ የተጠለሉ አማራዎችን በድሮን ጨፋጭፏል!!!

ጣና ሚዲያ Tana Media

14 Nov, 07:42


በአዲስ አበባ፣ በናዝሬትና ወልቂጤ ከተሞች የዐማራ ተወላጆች አፈሳ!

የአማራ ወጣቶች በናዝሬት፣ ወልቂጤ፣ ሻሸመኔ አዋሳ እየታፈኑ ወደ ማጎሪያ እየተወሰዱ እንደሆነ ሰምቷል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

13 Nov, 19:31


የችሎት መረጃ..!

ጋዜጠኛና መምህርት መስከረም አበራ፣  ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፣  ጋዜጠኛ ገነት አስማማው፣ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸው፤ ዶ/ር መሠረት ቀለም ወርቅ፣ ረ/ፕ ማዕረጉ ቢያበይን፣ መንበር አለሙ፣ ሲሳይ መልካሙን ጨምሮ በርካታ የአማራ የህሊና እስረኞች ነገ ጠዋት በልደታ የገዛዙ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። የእምነት ክህደት ቃልም ይሰጣሉ።

በመሆኑም በአዲስ አበባ የምትገኙ ጋዜጠኞች በስፍራው እንድትገኙ ጥሪ ቀርቧል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

13 Nov, 07:18


የዙ-1M መሳሪያው በሙከራ ላይ!

ጣና ሚዲያ Tana Media

13 Nov, 07:18


እነኚህ ሁለት ምስሎች በአማራ ፋኖ በጎጃም “ዘሪሁን 13” የጦር መሳሪያዎች ማምረቻ ተቋም የተሰሩ መሳሪያዎች ናቸው።

❶አንደኛው ምስል ፀረ ተሽከርካሪ መሳሪያ ሲሆን

❷ሁለተኛው ምስል ዙ-1M መሳሪያ ነው!

ጣና ሚዲያ Tana Media

12 Nov, 19:52


የትራምፕ አስተዳደር ለአማራ ድምጽ ሆኗል። ይህ ትልቅ ዜና ነው!
ሴናተር ሩቢዮ በኢትዮጵያ # አማራ ክልል በሰላማዊ ዜጎች ላይ መፈጸሙ የተዘገበው እጅግ አሳስቦታል።

በዚህ ጦርነት ከየትኛውም ወገን በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈፀመው ግፍ ሙሉ በሙሉ ተጣርቶ አጥፊዎች በህግ መጠየቅ አለባቸው።

ጣና ሚዲያ Tana Media

12 Nov, 09:45


የአማራ ፋኖ በጎጃም የ6 ኛ ክፍለ ጦር የበላይ ዘለቀ ብርጌድ ያገኘነውን ድል በማስጠበቅ ለቀጣይ ድል እንዘጋጅ በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ቀበሌዎች ህዝባዊ ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡በውይይቱ ላይ የተገኙ ድሎችንና እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን በማስቀጠል መላ ህብረተሰቡ ትግሉን ጠለሸት ከሚቀቡ ተግባሮች መራቅ እዳለበት መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

የበለይ ዘለቀ ብርጌድ የህዝብ ግንኙነት ገረመው ታንቲገኝ

ጣና ሚዲያ Tana Media

12 Nov, 08:31


መረጃ ሸበል በረንታ ‼️

ትናንት ሕዳር (2) ምሽት 12ሰዓት ጀምሮ የሸበል በረንታው ሽፈራው ገርባው ብርጌድ የዕድውኃ ከተማን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ አድሯል ።

ጨለማን ተገን አድርጎ የገባው የወገን ኃይል የአብይ አህመድን ዙፋን ጠባቂ ኃይል በተፈፀመበት መብረቃዊ ጥቃት ሰፍሮበት የነበረውን ካምፕ ለፋኖ አስረክቦ አድሯል።

በምሽቱ ውጊያ ከ30 በላይ ሲሸኙ ከ43 በላይ የጠላት ኃይል ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። የወገንን ኃይል መቋቋም ያቃተው የጠላት ኃይል አሁን ረፋድ ላይ ከ3 ከተሞች የተውጣጣ ኃይል ብረት ለበስ ተሽከርካሪ እና ዙ-23 ይዞ ተጠግቷል።

ሽፈራው ገርባው የበላይ ቀኝ እጅ
ጨለማ ለብሶ ጠላት የሚፈጅ !

አርበኛ ጥላሁን አበጀ

ጣና ሚዲያ Tana Media

12 Nov, 07:34


አንድ ወዳጄ ከባህርዳር ተነስቶ ወደ ወልዲያ እየሄደ ነበር ይህንንም መልእክት አድርሶኛል!

ከደብረታቦር እንደወጡ ፋኖወች ፍተሻ ካደረጉ በኋላ እስከ ጋሳይ ቅኝት አድርገው በፍቅር ሸኝተው እንደላኳቸው ነገረኝ ነገር ግን ጋሳይን ካለፍን በኋላ እስከ ጋይንት ድረስ የተደራጁ ሽፍቶች መንገድ ላይ እያስቆሙ እንደዘረፏቸውና ብዙ መኪናወችም እንደተዘረፉ !

ከዚህ በፊት ሀሙሲት ላይም ሆነ ብዙ ቦታወች ላይ ፋኖ በወሰደው ድንገተኛ እርምጃ ከ10 በላይ የተደራጁ ሌቦቹን ማስወገዱን እናውቃለንና በዚህም ቀጠና የህዝብን ሰላም በሚያውኩ ሌባወች ላይ አስፈላጊ እርምጃ እንዲወሰድልን የሚል መልእክት አስላልፍ ብለውኛል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

11 Nov, 20:25


የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ  መሀመድ ቢሆነኝ ክ/ጦር  ለ13ኛ ዙር ያሠለጠናቸዉን የፋኖ ምልምል ሠራዊት ማስመረቁን አስታወቀ።

ተመራቂዎቹ በስነልቦና፣በወታደራዊ ባህልና ጨዋነት ተገንብተው ለግዳጅ ዝግጁ ከመሆን ባሻገር ማንኛውንም ስምሪት ለመውሰድ በተጠንቀቅ ላይ ከመሆን አልፈው የጠላት እንቅስቃሴን መግታት በሚያስችል በቂ ዝግጅት ስለጠናውን ማጠናቀቃቸው ተገልጿል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

11 Nov, 20:24


🔥#ሰበር_ዜና_ወሎ_ቤተ_አምሐራ‼️

የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጠለው የህልዉና ተጋድሎ

የአማራ ፋኖ በወሎ የምዕራብ ወሎ ኮር ቅርንጫፎች የአማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለጦር ክንፍ የሆነው አትሮንስ ብርጌድ እና የቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለጦር በጋራ በመሆን የአገዛዙን አራዊት ሰራዊት ሲያደባዩት መዋላቸው ተገልጿል!!

ዛሬ ማለትም በዕለተ ሰኞ በቀን 02/2017 ዓ/ም ከረፋዱ 4:30 እስከ እኩለ ቀን ድረስ በ036 ወዠድ ቀበሌ ላይ በተደረገ ውጊያ የፋሽስቱ አብይ አህመድ አራዊት ሰራዊት ከፍተኛ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት የደረሰበት ሲሆን አምስት (5) ሙት እና ሶስት (3) ቁስለኛ ተደርጓል።  በዚህም አውደ ውጊያ ላይ  የአትሮንስ ብርጌድ እና የቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለጦር የበላይነት ወስደው  ውለዋል። የአገዛዙ ጥምር ጦርም  እግሬ አውጭኝ በማለት ፈርጥጦ ወደ ከተማ ገብቷል።

የሰው በላው የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ ወንበደ ቡድን ሽንፈቱን ለማካካስ ደንሳ መሃል ከተማ ላይ ንፁሃንን እያንገላታና እየደበደበ መሆኑን  የአይን እማኞች ተናግረዋል።

ይህ በእንድህ እንዳለ በጥምር ጦሩ ላይ ከቀን ወደ ቀን እየደረሰበት ያለውን ጉዳት የተመለከቱ የሚሊሻ አባላት ከድተው ወደ ወንድሞቻቸው  እየተመለሱ መሆኑን የአትሮንስ ብርጌድ ዋና አዛዥ ፋኖ ጎሹ ሳይንቴው ገልጿል። አዛዡ አክሎም ከቀን 27/02/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ዛሬ ቀን 02/03/2017 ዓ/ም ድረስ ከስምንት በላይ ሚሊሾች ወደ ሰላማዊ ኑሯቸው እንደተመለሱ ተናግሯል።

የተቀሩትም በቅርቡ ወደኛ እንድመጡ እያልን ወንድማዊ ጥሪያችንን አስተላልፈናል ብሏል ፋኖ ጎሹ::

የህልዉና ተጋድሎው እስከ ድልና ነፃነት ተጠናክሮ ይቀጥላል!

©የአማራ ፋኖ በወሎ ቃል አቀባይ ፋኖ አበበ ፈንታው

#ላንጨርስ_አልጀመርነውም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

2/3/17 ዓ.ም

ጣና ሚዲያ Tana Media

11 Nov, 19:41


ጎጃም | ዲማ

አገዛዙ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዲማ ጊዮወርጊስ  ፍቅር እስከ መቃብር ሙዚየምን አቃጥሎታል። ከዚህ በተጨማሪ አራት ንጹሀንን እና አንድ ካህን ገድሏል። በወራሪው ሰራዊት ዲማ ጊዮወርጊስ   አብቁተ ተቋምም ዝርፊያ ተፈጽሞበታል። መረጃው የጋዜጠኚ ተስፋዬ ወ/ስላሴ ነው!

ጣና ሚዲያ Tana Media

10 Nov, 04:50


አገዛዙን በህዝባዊ ማዕበለ ሰራዊት መደምሰስ የሚቻልበት እድል እየመጣ ነው።

የክልሉን ሰራተኛ ደሞዝ ለድሮን ቦምብ መግዣ ያደረገው አገዛዝ ደሞዝ ያቋረጠባቸው ዞኖች ተበራክተዋል።

በአማራ ክልል ደሞዝ ሙሉ በሙሉ የተቋረጠባቸው ወረዳዎች

ታች ጋይንትም - ደቡብ ጎንደር

አንዳቤት ወረዳ - ደቡብ ጎንደር

እስቴ ወረዳ - ደቡብ ጎንደር

ስማዳ ወረዳ - ደቡብ ጎንደር

ሰዴሙጃ ወረዳ - ደቡብ ጎንደር

ፎገራ - ጎንደር

ወረባቦ - ደቡብ ወሎ

ራያ ቆቦ ወረዳ - ሰሜን ወሎ

ቡግና - ሰሜን ወሎ

ማቻክል ( አማኑኤል )= ምሥራቅ ጎጃም

ስናን ( ረቡገበያ)  = ምሥራቅ ጎጃም

እናርጅ እናውጋ = ምሥራቅ ጎጃም

ደጋ ዳሞት = ምዕራብ ጎጃም

ሰከላ = ምዕራብ ጎጃም

ደቡብ ሜጫ =  ሰሜን ጎጃም
ዳንግላ ከተማ አስተዳደር  = አዊ ዞን

ደሞዝ በከፊል የቆመባቸው ወረዳዎች

ሸበል በረንታ =ምሥራቅ ጎጃም

ባሶሊበን(የጁቤ) =ምሥራቅ ጎጃም በከፊል

ጎንቻ = ምሥራቅ ጎጃም

ጣና ሚዲያ Tana Media

09 Nov, 19:59


#ማይካድራ!
          
ዛሬ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በማይካድራ ከተማ ጥቅምት 30/ 2013 ዓ.ም በማይካድራ የህወሓት ኃይሎች በአንድ ቀን 1ሺህ 563 ንፁሀን አማራዎችን የጨፈጨፉበት ቀን ነው።

ጣና ሚዲያ Tana Media

08 Nov, 20:55


ጥንካሬን እና ብርታትን ፈጣሪ ይስጣችሁ!!

ጥፋታቸው ከአማራ ህዝብ መፈጠራቸው እና ከህዝባችን ጎን መቆማቸው ነው:: መንግስት ነኝ ባዩ አውሬ ወንጀለኛ ያለቸው የህዝባቸውን ጭፍጨፋ ስላጋለጡ ነው:: ጄኖሳይድ ይቁም ማለታቸው ነው:: አሁንም እንላለን በማሰር እና በመግደል ህዝብን ማጥፋት አትችሉም::
#StopAmharaGenocide

ጣና ሚዲያ Tana Media

08 Nov, 05:13


ትጥቅ ያወረዱ የአማራ ገበሬዎች ከነቤታቸው ተቃጠሉ‼️

በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ የሆነው ነገር በጣም ያሳዝናል። መጀመርያ ሙሉ በሙሉ አማራውን ገበሬ ትጥቅ አስወረዱ፣ አሁን ላይ እነሱ በሚፈልጉት ልክ እዋራጅ አገዳደል መግደል ጀመሩ። ከሁሉም ጀርባ ግን ኦህዴድ አለ።

ለመከላከልስ ጥረት አላደረጋቹህም? ብለን ለጠዬቅናቸው ጥያቄ የአካባቢው ኗሪዎች የሚከተለውን ምላሽ ሰተውናል።


ጠቡ የተነሳው ከትናንት ወዲያ ሁዳድ 5 ቀበሌ አንድ የ18 አመት  ወጣት በከንባታ ሚኒሻ ታግቶ ነበር ከዛ እዛ አከባቢ የነበሩ የአማራ አንዳንድ ሽማግሌዎች ለመኑ እንቢ አሉ ትናንት ደሞ ያ የታገተውን ልጅ ብር አልከፍል ሲሉ በምላጭ ፊቱን ተለተሉት እና ማታ 1:30 አከባቢ ደሞ ዳርጌ ላይ አንድ ከንባታ ማንነቱ ባልታወቀ ሰው ተገደለ። ይህን መነሻ በማድረግ ነው አማራን መግደል ቤት ማቃጠል የጀመሩት። ሁሉም በደንብ ታጥቀዋል፣ በኦህዴድ ሰልጥነዋል። አማራዎች ለመከላከል ማንም አልሞከሩም እንደሚታወቀው የአማራ ትጥቁን የኦህዴድ እና የዞኑ አመራሮች አሰቃይተው በግድ ተቀብለውታል። እንኳን ገበሬው የአማራ ሚኒሻው ትጥቅ የለውም። እነሱ ግን ሁሉንም ወጣቶች አደረጅተው በየ አዳራሻቸው እና ሰብስበውው "ፌስታል ይዛቹ ነው የመጣቹት ፌስቴል ይዛቹ ትሔዳላቹ" 1ከምባታ ቢሞት በጅምላ አማራ እንገድላለን" እያለ በስብሰባቸው ላይ ሊቀመንበሩ ይነግራቸው ነበር። ተብሏል።

መከላከያና ፌድራል ፖሊስ አካባቢው ላይ እያሉ ቤት ሲቃጠል ንብረት ሲወድም ህዝቡ ሲጨፈጨፍ አስቁሙሉን ብለን ብንማጸናቸውም ትዕዛዝ አልተሰጠንም በማለት ፊት ነሱን፣ ለመከላከልም አልፈለጉም ይላሉ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት የወረዳው ኗሪዎች።

ለወረዳው ኗሪዎች በጥቃቱ ምን ያህል ሰው ተጎዳ? አሁንስ ምንድነው ዋስትናቹህ ብሎ ቢዛሞ ሚዲያ ለጠዬቃቸው ጥያቄ ጥቃቱ አሁንም አልፎ አልፎ የቀጠለ በመሆኑ ምን ያህል ሰው እንደተጎዳ ማወቅ አልቻልንም ያሉት የቀበሌዋ ኗሪዎች ቤት ሲቃጠል አብረው የተቃጠሉትን አማራዎች እስከ አሁን አጽማቸውንም እንኳ ለመሰብሰብ እንደተቸገሩ ተናግረዋል።አክለውም እስከ አሁንም ብንጮህ ሊደርስልን የቻለ የህግ አካል የለም ያሉት አማራዎች አሁን ላይ በአንድ ቀን እንኳን ቢያልቁ ምንምአይነት የህግም የኃይልም ዋስትና እንደሌላቸው፣ በገዳዮቻችን ተከበን ነው ያለነው ሲሉ ገልጸውልናል።
ቢዛሞ

ጣና ሚዲያ Tana Media

07 Nov, 21:09


🔥#አንተ_ማን_ነህ
       #አንች_ማን_ነሽ

ጣና ሚዲያ Tana Media

07 Nov, 05:05


ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀዳሚ ስራቸው ዶክመንት የሌላቸውን / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ከሀገር ማስወጣት ነው ተብሏል።

የትራምፕ ዘመቻ ቃል አቀባይ ካሮሊን ሌቪት እንደገለፁት ትራምፕ በፕሬዚዳንትነት ስልጣናቸው ከሚወስዷቸው የመጀመሪያ እርምጃዎች መካከል አንዱ ዶክመንት የሌላቸው / ሰነድ አልባ ስደተኞችን በብዛት ለማስወጣት የገቡትን ቃል መፈጸም ነው።

ሌቪት ፥ ትራምፕ በአሜሪካ ህዝብ ዘንድ አስደናቂ የተባለ ድል ማስመዝገባቸውን ገልጸው “ ይህ ድል ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳቸው የገቡትን ቃል እንዲፈጽሙ ‘ ትዕዛዝ ‘ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል “ ብለዋል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

06 Nov, 17:57


በመስከረም ኩልል ካለ ምንጭ ጥርት ካለ ውኃ ጥምም አምሮትም ይከላል። በመስከረም የፀሐይ ስስ ሙቀቷን እንደ ቀጭን ኩታ እንለብሳለን። ምጥን ብርሃኗን ሳቂታ ገጿን በዐይን ሙሉ እናያለን። ከምድር ፍሬ በረከት ከእሸትም እሸት ጠብሰንም ፈልፍለንም አሽተንም እንመገባለን። በንቦች ዜማ ታጅበን የአበቦችን መዓዛ እንደ እናት ጣት በሚዳብስ በልስልስ ነፋስ እየታወድን እንመገምጋለን። ጥፋት ካለባት እንዲኽ መኾኗ ነው።

ስለዚህም መስከረምን እንወዳታለን። ትመጫለሽ መስከረም!!!

ጣና ሚዲያ Tana Media

06 Nov, 17:54


ሰበር ዜና!
የቀድሞው የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊና የዐማራ ሐኪሞች ፕሬዝዳንት ዶክተር ጋሹ ክንዴ የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክፍለ ጦር ተቀላቅለዋል፡፡

ጣና ሚዲያ Tana Media

06 Nov, 11:54


ሰውየው አድርጎታል!
_________

ከዘነበበት ማጠልሸት፣ ጥላቻ፣ መሳደድ፣ ወከባ፣ መገፋት፣ መጭበርበር ሁሉ አገግሞ፣ ለምንም ሳይበገር፣ በዚህ ዕድሜው እንደ ትኩስ ጉልበታም ወጣት ተገዳድሮ፣ ተፋልሞ፣ አንሠራርቶ ዳግመኛ አሸንፏል! አለማድነቅ አይቻልም በእውነቱ!

አሜሪካኖች የሚበጃቸውን መርጠዋል! የዚህ ሰው መመረጥ በአሜሪካ ላይ ብቻ ሣይሆን በዓለምም ላይ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ታሪካዊ ምርጫ ይመስለኛል!

ይሄንን ደረቱን ላገሩ፣ ላመነበት እውነት፣ ለሕዝቡ የሰጠ ጀግና መሪ ከልቤ አደንቀዋለሁ! በቢሊዮን ዶላሮች በተገነቡ የግሉ መዝናኛዎች እፎይ ብሎ የራሱን ኑሮ መኖር ሲችል፣ እሱ ግን ቀሪ ህይወቱን ለሀገሩ በመታገል ለማሳለፍ የወሰነ ሀገሩን አፍቃሪ አርበኛ ነው! ፓ! ያስቀናል የምር!!

በዓለም ላይ ከነመፈጠሬም ባያውቀኝም😂🤪፣ ትንጥዬ ድምፄን ባይሰሙኝም፣ ለራሴ አቋምና ህሊና ስል ግን... ይሄንን ብርቱ ሰው እና እርሱንም አምነው፣ ለብዙ እውነቶች ዘብ ቆመው፣ ምንም ዓይነት ፕሮፓጋንዳ ሳይበግራቸው መሪያቸው እንዲሆን የመረጡትን ከግራውም ከቀኙም ወገን ያሉ አሜሪካውያንን ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት እፈልጋለሁ!

Congratulations to Donald Trump, JD Vance, and to all Americans who are celebrating their winning moments at this time 🙏🙏🙏🥰🥰🥰❤️❤️

God bless the people of America (united under God, the land of the free and the home of the brave - as they say it)!! Cheers to USA!!🇺🇲🇺🇲 Make America Great Again (MAGA)!🇺🇸🇺🇸🇺🇲 And Make Our World Safe Again (MOWSA)!🌍🌍🌍🌍🙏🙏🙏🥰🥰🤩

ጣና ሚዲያ Tana Media

06 Nov, 10:19


Enjoy our content? Advertise on this channel and reach a highly engaged audience! 👉🏻

It's easy with Telega.io. As the leading platform for native ads and integrations on Telegram, it provides user-friendly and efficient tools for quick and automated ad launches.

⚡️ Place your ad here in three simple steps:

1 Sign up

2 Top up the balance in a convenient way

3 Create your advertising post

If your ad aligns with our content, we’ll gladly publish it.

Start your promotion journey now!

ጣና ሚዲያ Tana Media

06 Nov, 10:16


Enjoy our content? Advertise on this channel and reach a highly engaged audience! 👉🏻

It's easy with Telega.io. As the leading platform for native ads and integrations on Telegram, it provides user-friendly and efficient tools for quick and automated ad launches.

⚡️ Place your ad here in three simple steps:

1 Sign up

2 Top up the balance in a convenient way

3 Create your advertising post

If your ad aligns with our content, we’ll gladly publish it.

Start your promotion journey now!

ጣና ሚዲያ Tana Media

06 Nov, 07:29


Enjoy our content? Advertise on this channel and reach a highly engaged audience! 👉🏻

It's easy with Telega.io. As the leading platform for native ads and integrations on Telegram, it provides user-friendly and efficient tools for quick and automated ad launches.

⚡️ Place your ad here in three simple steps:

1 Sign up

2 Top up the balance in a convenient way

3 Create your advertising post

If your ad aligns with our content, we’ll gladly publish it.

Start your promotion journey now!

ጣና ሚዲያ Tana Media

06 Nov, 07:23


ራያ!

ወደ ራያ ገብቶ የነበረው ዘራፊው የህወሃት ታጣቂ ቡድን አካባቢውን ለቆ መውጣት መጀመሩን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ታጣቂ ኃይሉ አካባቢውን ለቆ እወጣ ያለው እንዴትና ለምን የሚለውን አጣርተን የምናደርሳችሁ ይሆናል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

06 Nov, 07:22


ሰበር ዜና!!

ዶናልድ ጆን ትራምፕ 47ተኛው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን ፎክስ ዘግቧል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

06 Nov, 07:18


የአውደ ውጊያ መረጃ

ዛሬ ውሎውን የአማራ ፋኖ በጎጃም ስድስት(6) ቦታዎች ላይ ውጊያ ሲያደርግ ውሏል። 5ኛ ክፍለ ጦር ጅጋ ፣ማንኩሳ ፣ቡሬ እና ፍኖተሰላም ከተማ ላይ ከባድ ውጊያ አድርጎ ጠላት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል።

ጠዋት 2ሰዓት የጀመረው ውጊያ አሁን አመሻሽ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ፍኖተ ሰላም ከተማን ሙሉ በሙሉ ከጠላት ነፃ አድርጓል ።በአሁኑ ሰዓት ጠላት ከተማውን ለቆ ከከተማው ውጭ ያሰራው የኮንክሪት ምሽግ ውስጥ ገብቷል። የ3ኛ ክ/ጦር ሙሉ ኃይል እና የሰከላው ጊዮን ብርጌድ በጋራ  የጠላትን ምሽግ በሞርተር እየደበደበ ይገኛል።

በሌላ በኩል የ3ኛ ክ/ጦሩ ዘንገና ብርጌድ እና ብይን ብርጌድ በጋራ ባደረጉት ውጊያ ቲሊሊ ከተማን ተቆጣጥሯል።በተመሳሳይ አዴት ዙሪያ አንሙት ያዛቸው ብርጌድም ውጊያ ላይ ውሏል።

መረጃው የጥላሁን አበጀ ነው

ጣና ሚዲያ Tana Media

05 Nov, 18:54


Enjoy our content? Advertise on this channel and reach a highly engaged audience! 👉🏻

It's easy with Telega.io. As the leading platform for native ads and integrations on Telegram, it provides user-friendly and efficient tools for quick and automated ad launches.

⚡️ Place your ad here in three simple steps:

1 Sign up

2 Top up the balance in a convenient way

3 Create your advertising post

If your ad aligns with our content, we’ll gladly publish it.

Start your promotion journey now!

ጣና ሚዲያ Tana Media

05 Nov, 18:35


#Gojjam መረጃ

ዛሬ ውሎውን የአማራ ፋኖ በጎጃም ስድስት(6) ቦታዎች ላይ ውጊያ ሲያደርግ ውሏል። በጅጋ ፣በማንኩሳ ፣በቡሬ፤ በአዴት እና በፍኖተሰላም ከተሞች ላይ ቀኑን ሙሉ የፈጀ ውጊያ ሲደረግ ውሏል።

የፋኖ ኃይሎች ወደ ፍኖተ ሰላም ከተማ ገብተዋል። በተመሳሳይ ወደ ቲሊሊ ከተማም የፋኖ ኃይሎች መግባታቸው ታውቋል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

01 Nov, 18:46


🔥#መረጃ_እብናት_ጎንደር‼️

  የአብይ ወምበር አስጠባቂ ሰራዊት በአለቆቹ ትዛዝ አማራንና ፋኖን አጠፋለሁ፣ ትጥቁንም አስፈታለሁ ብሎ በእብሪት መጦ ጦርነት ከከፈተብን 1 አመት ከ4 ወር አስቆጥሯል። ነገር ግን ከክላሽ እስከ ስናይፐር ፣ከብሬን እስከ ዲሽቃ ፣ከሞርታር እስከ ዘ23 አስረክበውን አስፈሪና እሳት የሆነ ግዙፍ ጦር መስርተናል።

ይሁን እንጂ አሁን ላይ ዘሎ ገብቶ መውጫ ያጣውና ተስፋ የቆረጠው የጁላ ጦር ዘመናዊ እና ከባድ መሳሪያዎች ለአናብስቱ የአማራ ፋኖ ጦር ቢያስረክቡም ቤት ከተቀመጠው ህዝባችን መሳሪያዎችን እየገፈፈ ህዝባቸንን ንብረቱን እየዘረፈና ከፋኖ የማረክሁት በሚል ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ይገኛል።

ለምሳሌ ያህል በደቡባዊ ጎንደር ዞን  እብናት ወረዳ ዝሀ ቀበሌ ላይ በዛሬው ዕለት መከላከያ ተብየው
#እየዘረፉ ፣የገበሬ መሳሪያ እየወሰዱ ይገኛሉ ፣የሚገርመው ደግሞ የኪስ ብር ራሱ አይቀርም ሲወስዱ ስለዚህ ወደሌሎች ቀበሌ ሊሄዱ ስለሚችሉ በፍጥነት ፋኖ የገበሬውን መሳሪያ ማውጣት አለበት ወይ ግለሰቡን ወደ እነሱ እዲገባ ማድረግ አለባቸው ሲሉ የአይን እማኞች ለንስር አማራ ገልፀዎል‼️

#መልዕክት

መሳሪያህን ለጁላ ሰራዊት አሳልፎ መስጠት ሞኝነትና ሊያጠፋን የመጣን ጠላት ማበረታታትና መደገፍ ነውና ከቻልን
#ከአማራ_ፋኖ ጎን እንሰለፍ አቅማችን የጤና ሁኔታችን የማይፈቅድ ከሆነ ደግሞ መሳሪያችንን ለወገን ሀይል አሳልፈን በመስጠት ትግሉን በማገዝ እንድናፋጥነው ጥሪ እናቀርባለን‼️

#አማራ_ታሪኩን_ይድሳል💪
#አማራ_ላይጨርስ_አልጀመረም💪
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

ጣና ሚዲያ Tana Media

01 Nov, 16:14


መተማ‼️

መተማ አከባቢ በነበረው ውግያ ጨፍጫፊው ሠራዊት ድጋሚ ፈርጥጦ ሱዳን ገብቷል! የአንድ ሀገር መከላከያ ነኝ የሚል ሀይል እንዲህ እየሮጠ ወደ ሱዳን ሲገባ የተመለከተ የሱዳን አርሶ አደር ሁኔታውን "Wallahi, lam ara fi hayati kullah jundun yaruddun hakadha...ፈጣሪ በሚያውቀው በህይወት ዘመኔ ወታደር እንዲህ ሲሮጥ አይቸ አላውቅም" ሲል መናገሩን የሱዳን ጋዜጦች ዘግበዋል!

#ድል ለመላው አማራ ፋኖ!

ጣና ሚዲያ Tana Media

31 Oct, 18:54


ተደጋጋሚ ጥቆማ!

ባህርዳር አባይ ማዶ ዲያስፖራ አካባቢ ተደጋጋሚ እገታዎችና ዝርፊያዎች እየተፈፀሙ እንደሆነ ተደጋጋሚ ጥቆማዎች ይደርሱኛል። ይሄን ወንጀል የሚፈፅሙ አካላት ደግሞ በፋኖ ስም የሚነግዱ ወንበዴዎች ናቸው። ህዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ ተማሯል። በተመሳሳይ በሌሎችም አካባቢዎች ተመሳሳይ ድርጊቶች እንደሚፈፀሙ ተደጋጋሚ ጥቆማዎች ይደርሱኛል። የፋኖ ኃይሎች በስማቸው የሚፈፀምን ይሄን ውንብድና እንዲያስቆሙ ጥሪያችንን ለማድረስ እንወዳለን!

ጣና ሚዲያ Tana Media

31 Oct, 17:58


I feel sorry.................................................................................................................................................................I'm gona to out from this u guys!!! 😢😢😢

ጣና ሚዲያ Tana Media

31 Oct, 10:29


#የአገዛዙ ጭካኔ‼️

ሃገሬ ዮሀንስ ትባላለች፣ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር ከፍተኛ አመራር የሆነው ፋኖ አቀናው በቀለ ባለቤት ስትሆን ሸንፈቱን እየተከናነበ የሚገኘው የብልፅግና አራዊት ሰራዊት ከጥቅምት 10/2017ዓ.ም ጀምሮ በፌጥራ ከተማ የሁለት አመቱን ህፃን ጨምሮ አግቷት ትገኛለች።

ከታገተችበት ቀን ጀምሮእስከ አሁን ድረስ ከነ ህፃኗ ያለችበት ሁኔታ የታወቀ ነገር እንደሌለ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ተጠሪ ክፍል ገልጿል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

31 Oct, 06:08


ታላቅ የተቃዉሞ ሰልፍ ጥሪ በሲያትል እና አካባቢዉ ለምትኖሩ አማራው ያን እና ኢትዮጵያዊያኖች በሙሉ !

ላለፉት 5 ዓመታት አማራው ባቀናውና በተወለደበት፣ በወለጋ ፣በአረሲ፣ በሐረር ወዘተ ቀን በቀን እየጨፈጨፍን የአማራን እልቂት አለማመዱን ::  ይባስ ብለው፣ ይህን የጅምላ ጭፍጨፋው  እዛው የአማራ ግዛት በተባለው ክልሉ ድረስ አምጥተው ለታል ።
 አማራዉ  በራሱ ክልል  በየእለቱ በዚህ አረመኔ ዘረኛ ቡድን በከባድ መሳሪያ፣በድሮን ይደበደባል ሰብሉ ይቃጠላል :: ይህ አልበቃ ብሎ ፣ ቤት ለቤት እየዞሩ ንፁሀንን  ይረሸናሉ ፣ ሴቶች ይደፈራሉ :: በአማራው ላይ የሚፈጸመዉ ግፍ ይበቃ ዘንድ የሁሉንም አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ እና የመላው አማራን ድጋፍ እንጠይቃለን ::

November 7/2024  ከጧቱ  10:00 am   Gerber Park 575 MLK Jr Way Seattle WA 98122 ተገናኝተን ለሚጨፈጨፈዉ ወገናችን ድምፅ እንድንሆን የሲያትል አማራ ማህበር ጠርቷል።

ሰዉ መሆን ብቻ በቂነዉ ግፍን ለመቃዉም

ገርበር ፖርክ የምንገናኘው ከጠዋቱ 9:00 am ሲሆን  ጉዟችን ልክ በ 10 am ጠዋት  ይሆናል እናም ቀደም ብለን እንገናኝ!!

መነሻችን Gerber park  Seattle  WA ሲሆን መድረሻችን state capital Olympia  Washington

ኑ...  ለወገኖቻችን አንድ ቀን ዋጋ እንክፈል!!

በእለቱ ሁላችንም ጥቁር ልብስ እንለብሳለን !!

ዝናብ እና ቅዝቃዜ ሊኖር ስለሚችል በቂ ዝግጅት አድርጉ !! መኪናችሁን ጋዝ መሙላት እንዳትረሱ !!

ጣና ሚዲያ Tana Media

30 Oct, 09:55


🔥#የድሮን_ቅኝት‼️

በፍኖተሰላም እና ጅጋ ቀጠና እንዲሁም ሁለቱ ቀጠና መሀከል ሆዳንሽ ላይ የድሮን አሰሳ እየተደረገ ነው በፍጥነት መረጃውን ይዛመት‼️

ጣና ሚዲያ Tana Media

30 Oct, 08:03


የጨነቀው አሸበርቲ መንግስት ትዕዛዝ
።።።።
ሁሉም የብልፅግና አባላት በየአካባቢያቸው ሄደው ጦርነቱን ከፊት ሆነው ከመከላከያ ሀላፊዎች ጋር እንዲመሩ ተወስኗል። በአጽንዖት የተነጋገሩት ወሬ በማስወራት እርስ በእርስ ማባላትና የፋኖ ቤተሰቦችን ማሰር ልጆቻቸውን ካላመጡ መቀጣጫ ማረግ የሚል ውሳኔ ወስነዋል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

30 Oct, 07:49


አዲስ ዘመን❗️

ትላንት  በቀን 19 ከጧቱ 4:00 አካባቢ በተደረገ የተኩስ ልውውጥ አዲስ ዘመን ከተማ ውስጥ አልሰማ ያሉ ባንዳዎች አንዱ ልዩ ሀይል  ሙት ሲሆን ሶስቱ ጓደኞቹ ከባድ ቁስለኛ ሆነው አዲስ ዘመን ሆስፒታል ገብተዋል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

29 Oct, 19:06


ትጥቅ እንዲያስረክቡ በመጠየቃቸው የደኅንነት ስጋት ላይ መኾናቸውን የአማራ ተወላጆች ገለጹ!

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በሚገኙ ስድስት ወረዳዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች “ራሳችንን ከታጣቂዎች ለመጠበቅ የገዛነውን መሳሪያ እንድናስረክብ ተጠየቅን፣ ይህ ደግሞ ለጥቃት ያጋልጠናል” ሲሉ ተናገሩ።

በዞኑ ባሉ የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩና ለአሜሪካ ድምጽ አስተያየት የሰጡ የአማራ ብሄር ተወላጆች፣ "ሸኔ" ብለው የጠሩት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ታጣቂዎች ያደርሱብናል ካሉት ጥቃት ራሳቸውን ለመከላከል እንዲችሉ በመንግሥት ዕውቅና መሳሪያ ገዝተውና ታጥቀው መቆየያቸውን ተናግረዋል። (መረጃው የአሜሪካ ድምፅ ነው)

#Amhara #Ethiopia

ጣና ሚዲያ Tana Media

28 Oct, 20:16


መረጃ‼️

በአዲስ አበባ በቀን ስራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች እየታፈሱ በግዳጅ ወደ ወታደራዊ ካምፕ እየተወሰዱ እንደሆነ ተነገረ

በአዲስአበባ በተለይ ኩዬፈቼ እና አዲሱገበያ በሚባሉ አካባቢዎች የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በቀን ስራ የሚተዳደሩ ወጣቶችን በማፈስ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ካምፖች እያስገቡ እንደሆነ ተገልፆል ፡፡

ወጣቶቹ ከአካባቢዎቹ ከታፈሱ በሆላ በፖሊስ ጣቢያ ከሁለት እስከ አራት ሳምንታት ታስረው  ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች እንደሚላኩ ታዉቋል ፡፡

በተለይ ከደቡብ ኢትዬጲያ የመጡ ወጣቶች የዚህ ተግባር ተጠቂዎች ናቸዉ ተብሏል፡፡

ጣና ሚዲያ Tana Media

28 Oct, 20:15


በዛሬው ዕለት በ 18/02/2017 ከምሽቱ 1 ሰአት ከአዲስ አበባ ጫንጮ እየተመላለሱ የሚሰሩ የፌደራል የመንግስት ሰራተኞችን በፐብሊክ ባስ እየሄዱ ባለበት ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ ከምትገኘው ከሱሉልታ እና ጫንጮ መካከል ካለች ቦታ ላይ በታጠቁ ሀይሎች ታፍነው መወሰዳቸውን የሚገልፅ መረጃ ከስፍራው ደርሶናል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

28 Oct, 12:01


እስኪ ምን እያሉ እንደሆነ ትርጉሙን የምትችሉ ንገሩን

ጣና ሚዲያ Tana Media

28 Oct, 11:58


በአዲስ አበባ ዙሪያ ሱሉልታ አካባቢ በሽመልስ አብዲሳ እና አዳነች አበቤ የተደራጁ የብልፅግና ካድሬዎች የኦሮሞን እና የሌላ ብሄር ህፃናት ሴቶችን በgroup በአሰቃቂ መልኩ እየደፈሩ ይገኛሉ፡ እነዚህ ሀይ ባይ የሌላቸዉ በአዲስ አበባ ዉስጥም ህፃናት ሴቶችን አፍኖ በመዉሰድ እየደፈሩ ይገኛሉ:: ሴት ህፃናቱ አባቶች ለመክሰስ ቢሞክሩም በፖሊስ ታፍነዉ ተወስደዋል። ይህም ብቻ ሳይሆን የብልፅግና መንግስት ባለስልጣናት ባለትዳር ሴቶችን ሳይቀር አፍነዉ በመዉሰድ በ group እንደሚጫወቱባቸዉ ታዉቋል፡ ቤተሰብም መክሰስ እንዳይችል ማስፈራራት ማገት የተለመደ ሆኗል።

የአዲስ አበባ ህዝብ ተዘጋጅ

ጣና ሚዲያ Tana Media

27 Oct, 19:53


#Amhara ጋይንት

ደቡባዊ ጎንደር ዞን ጋይንት ግንባር ለ2ኛ ቀን የቀጠለ ውጊያ እየተካሄደ ነው። ጀግናው የገብርዬ ክፍለ ጦርና የጋፋት ክፍለ ጦር ከታች ጋይንት ሰዴ ሙጃ እስከ ላይ ጋይንትና ጉና በጌምድር ወረዳዎች እጅግ ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ እንደሚገኝ ከገብርዬ ክፍለ ጦር ጠቅላይ መምሪያ ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

26 Oct, 16:55


ጣናውያን ኢትዮጵያውያን ሆይ አንድ ነገር ላስቸግራቹህ ነው!

ጣና ሚዲያ Tana Media

26 Oct, 10:44


የአርበኛ ዘመነ ካሴ የዕለቱ መልዕክት 👇
````````````

የክፍለ ዘመኑ ወንጀለኞች!!

በዚህ ጊዜ የአማራን ህዝብ በጅምላ ከሚጨፈጭፉት ጠላቶቻችን በላይ፥ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ብለው የሚያዩት ወገኖቻችን የህሌና ወንጀለኞች ፥የታሪክ ፍርደኞች ናቸው።ከተኮሰብን እና ካታኮሰው በላይ እጃቸውን አጣጥፈው የሚያዩን ወገኖቻችን ግዙፍ ወንጀለኞች ናቸው።
እነዚህ በሃዘን ድንኳን ውስጥ ነጭ ካባ ደርበው የተቀመጡ ወገኖች የመታረጃ ወረፋውን የሚጠብቅ  ባለሁለት እግር የቄራ ሰንጋዎች ናቸው።
ድል ሎተሪ አይደለም፥በደም፣በላብና በጥረት እንጅ በእድል አይገኝም።

"ጎመን በጤና" የጠፉ ህዝቦች የቅድመ-ልደተ-ክርስቶስ የጥንት "ወንጌል" ነው።የቆመና የደፈረ ብቻ ያሸንፋል።ህልውናው አደጋ ላይ የወደቀ ህዝብ ጎመንም ጤናም የለውም።ከፈፅሞ መጥፋት መዳን የመተንፈስ ያክል ከሁሉም ይቀድማል።
ክብርና ኩራት ከሌለው ህይወት ፥የአስከሬን ሳጥን የተሻለ ዋጋ አለው።
ነፃነት ካጣ ከተማ የመቃብር ከርስ ይሻላል።ምናልባት መቃብሩ ይሞቅ ይሆናል።

"አማራ" የሚለው ስማችን ብቻውን በሽህ አቅጣጫ የተሳለ የማይዶሎድም ሰይፍ ነው።ይህን የተፈጥሮ ሰይፍ ሁሉም አማራ ከልቡ ሰገባ በሙሉ ልብ ይምዘዘው።ውጤቱ ድል ነው።

አንድ አማራ!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!
{ክፋት ለማንም፥በጎነት ለሁሉም}
አድስ ትውልድ፥ አድስ አስተሳሰብ፥ አድስ ተስፋ።

[ቅዳሜ-ጥቅምት-16-2017 ዓ•ም]

ጣና ሚዲያ Tana Media

26 Oct, 05:09


"አምሓራን መውጋት እና መዋጋት ቅዱስ ጦርነት ነው ወጣቶች መዝመት አለባቹ"‼️
ዶክተር ገመችስ ደስታ

"ፖስተሮች ብሄረሰባት በአምሓራ ላይ እንዲዘምቱ፣ በየቸርቹ ቅስቀሳ ጀምረዋል" ተባለ።

•ፖ/ር እዩ ጩፋ
•ፖ/ር ዮናታን አክሊሉ
•ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም
•ዶ/ር ገመችስ ደስታ የቅስቀሳ ጅማሬን አድርገዋል ተብሏል።

በአዲስ አበባ ፣በኦሮምያ  እና በደቡብ
ክልል የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲና እና የብልፅግና ወንጌል አገልጋዮች ከዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም፣ዶክተር ገመችስ ደስታ፣እዩ ጩፉ፣ዮናታን አክሊሉ እና  በየደረጃው ከሚገኙ አገልጋዮች እና የተለያዩ የኦሮሞ ምሁራን ጋር በመተባበር በሀይማኖት ተቋማት ውስጥ ወጣቶችን ለውትድርና እንዲቀላቀሉ በመመልመል ስራ መሰማራታቸው ታውቋል።

በሰሜን የተነሳው ውጊያ ፀረ ፕሮቴስታንት እና ፀረ ብሔርብሔረሰብ በመሆኑ  በኦሮምያ፣በደቡብ እና በጋምቤላ ያላችሁ ወጣቶች መከላከያ ሠራዊትን በመቀላቀል የአምላካችሁን ቅዱስ ጦርነት ተዋጉ የሚል ስብከት እና ትንቢት ለምእመኑ እያሰሙ መሆኑ ምንጮቻችን ዘግበዋል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

25 Oct, 20:05


በአዲስ አበባ ፣በኦሮሚያ ክልል እና በደቡብ ክልል የሚገኙ የብልፅግና ፓርቲና እና የብልፅግና ወንጌል አገልጋዮች ከዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም፣ ዶክተር ገመችስ ደስታ፣ ኢዩ ጩፉ፣ ዮናታን አክሊሉ እና በየደረጃው ከሚገኙ አገልጋዮች እና የተለያዩ የኦሮሞ ምሁራን ጋር በመተባበር በሀይማኖት ተቋማት ውስጥ ወጣቶችን ለውትድርና እንዲቀላቀሉ በመመልመል ስራ መሰማራታቸው ታውቋል።

በሰሜን የተነሳው ውጊያ ፀረ ፕሮቴስታንት እና ፀረ ብሔር ብሔረሰብ በመሆኑ በኦሮምያ፣ በደቡብ እና በጋምቤላ ያላችሁ ወጣቶች መከላከያ ሠራዊትን በመቀላቀል የአምላካችሁን ቅዱስ ጦርነት ተዋጉ የሚል ስብከት እና ትንቢት ለምእመኑ እያሰሙ መሆኑ ምንጮቻችን ዘግበዋል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

25 Oct, 18:37


"የሠራሁት ወንጀል የለም። ህግን ባልተላለፍኩበት ኹኔታ የቅጣት ማቅለያ አስተያዬት በማቅረብ ለትውልዱ መልፈስፈስን አላስተምርም! የፈለጋችሁትን ፍረዱብኝ!!"

በስልክ በሚሰጣቸው ትዕዛዝ ለሚድፈርዱ አሻንጉሊት ፍርድ ቤቶች እና ዳኞች እውቅና አለመስጠት፤ የጋሽ ታዲዮስ ታንቱ "ሌጋሲ" ሆኖ ይቀጥላል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

25 Oct, 10:30


የ6 አመት እስር ፈረደባቸው!

በ84 አመቱ አዛውንት በአቶ ታዲዎስ ታንቱ ላይ ዛሬ ፍርደ ገምድሉ የፍትህ ስርዓት በእስር የቆዩበትን ጊዜ፣ እድሜያቸውን እና የጤናቸውን ሁናታቸውን ከግምት ውስጥ ሳያስገባ የ6 ዓመት ከ3 ወር ቅጣትና የ20ሺ ክፍያ በይኖባቸዋል፡፡

ህዝባችን ነጻ ሲወጣ አብረው ነጻ ይወጣሉ!

#Amhara #Ethiopia

ጣና ሚዲያ Tana Media

25 Oct, 10:29


የሰሜን ወሎ ዞን መቀመጫ ወልድያ ከተማ ከበባ ዉስጥ ፒያሳ ላል ሆቴልና ሌሎች ትላልቅ ሆቴሎች ለስብሰባ መጥተው የከተሙ ወታደራዊ አመራሮችና የፖለቲካ አመራሮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ተፈፅሞ አድሮዋል፡፡በተጨማሪም ማር ማቀነባበሪያ ከፍ ብሎ ከፍተኛ ውጊያ ሲደረግ አድሯል፡፡

ጣና ሚዲያ Tana Media

24 Oct, 11:02


https://rumble.com/v5jx90l-335794917.html

ጣና ሚዲያ Tana Media

23 Oct, 19:10


የአቶ አገኘሁ ተሻገር (ሽጉጤ) አጃቢ ፋኖን ተቀላቀለ‼️

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር አጃቢ የነበረው ሰለሞን ፈቃዴ ፋኖን ተቀላቀለ።
የአገኘሁ ተሻገር ቀድሞ አጃቢ የአማራ ፋኖ በጎንደር ጉና ክፍለ ጦርን መቀላቀሉ ተሰምቷል።

ጉናለማንኛውም የጉና ክ/ጦር አመራሮች ይህ ሰው በጥንቃቄ ተከታተሉት እንዳትበሉ‼️

ጣና ሚዲያ Tana Media

23 Oct, 12:19


ሰበር ዜና!

የአብይ አህመድ የአንድ ቡድን አገዛዝና ዙፋን ጠባቂ ሰራዊቱ ዛሬ ጥቅምት 13/2017 አ.ም ጠዋት ራያ ቆቦ ቀዩ ጋሪያ ከተማ ት/ቤት ላይ ከፈፀመው የድሮን ጥቃት በተጨማሪ መነሻዉን ቆቦ ከተማ ሆርማት ያደረገ መድፍ በዘፈቀደ ወደ ዞብልና ቀዩ ጋሪያ እያስወነጨፈ ይገኛል::

የዘፈቀደ የከባድ መሳሪያ ቅምቡላው አጠቃላይ እንደ ህዝብ የአማራ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ያለ ሲሆን ከሰው ህይወት በተጨማሪ በንብረት በት/ቤቶች ጤና ኬላዎችና ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም በደረሱ ሰብሎች ላይ ጭምር ከባድ ጉዳትና ዉድመት እያደረሰ ይገኛል::

ወቅቱ አዝመራ የሚሰበሰብበት ወቅት እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን የአብይ አህመድ ዙፋን ጠባቂ ሰራዊት ከጅምላ እስርና ማንገላታት በተጨማሪ ሆን ተብሎ ስምሪት ተሰጥቶት ገበሬው ምርቱን እንዳይሰበስብ እያደረገ ይገኛል::

ጣና ሚዲያ Tana Media

22 Oct, 17:56


የአማራ ክልል  ሕዝብ የናፈቀው ሰላምን እንጂ የጤፍ ሰብል ፎቶ አይደለም።

ጣና ሚዲያ Tana Media

22 Oct, 17:56


ድሮን በያይነቱ የምትገዛ ሀገር አንድ እንኳን ደህና የእሳት ማጥፊያ ሄሊኮፕተር የላትም!😢😭

ጣና ሚዲያ Tana Media

22 Oct, 17:49


በ 2017 አ/ም መስከረም እና ጥቅምት ላይ የድሮን ጥቃት ከተፈፀመባቸው ትምህርት ቤቶች በከፊል፦

ጎንደር ፡

- ሚካኤል ደብር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
/አዲስ ዘመን/

ጎጃም :

- ድማማ ትምህርት ቤት
/ፋግታ ለኮማ ወረዳ/

- አፈሳ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
/ዳንግላ ዙሪያ/

- ቅድስ ዮሐንስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት
/ሜጫ ወረዳ/

- ንዋዬ ማርያም አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
/እናርጅ እናውጋ ወረዳ ፈለገ ብርሃን ከተማ/

- ቀጋት ትምህርት ቤት
/ደብረ ኤልያስ/

እነዚህ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ተማሪዎችም በጥቃቱ ሞተዋል።
አብይ አህመድ የትምህርቱን ዘርፍ ርካሽ ፖለቲካ ከሰራበት በኋላ እንዲህ ነው የሚያደርገው።
ለዚህ ነው ትምህርት ነፃነታችንን እስክናረጋግጥ ይቆይ የምንለው።

ታድያ ወንድም እህቶቻችን በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ላይ እያሉ የእኛ የአማራ ፋኖን መመሪያ ተላልፎ በትምህርት ቤቶች መገኘት የድሮን እሳትን ያስገኝ እንደሆነ እንጂ እውቀትን መቅሰም በዚህ ሁኔታ የማይታሰብ ነው።

ቀጣይ ለሚኖረን ጥሪ ዝግጁ ሁኑ!

ጥቅምት ፲፪ ቀን ፪፻፲፯ ዓ.ም | ባ/ዳር
የግዮን አጠቃላይ ፪ኛ  ደረጃና ከፍተኛ ት/ም መሰናዶ ት/ቤ የተማሪዎች ንቅናቄ
"ትምህርት ከነፃነት በኋላ!!"

ጣና ሚዲያ Tana Media

22 Oct, 07:05


ለ12 ቀን ሲካሄድ የነበረውን ስብሰባ ሙሉ ለሙሉ ስከታተለው ነበር። እናም በተስፋ መቁረጥ ደምደውታል!

የመጨረሻ ውሏቸው፦
የስብሰባ አዳራሽ- አድዋ 00 ሙዚዬም

ውሎ ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን!

ጠ/ሚ እስካሁን የሰነበቱባቸውን የ10 ሰነዶችን ዋና ዋና የሚላቸውንና አዳማ ያቀረበውን ቪዲዮ ሙሉ ሳይሆን ሰሞኑን በሶሻል ሚዲያ ሲነሱ የነበሩትን ጉዳዮች ተቆርጦ እንዲቀርብ ተደርጓል። ከተቆረጡት ንግግሮች መካከል (ኤርትራን እንደጋዛ)  በዚሁ ውስጥ አጠቃላይ ሀገራዊና አለማቀፋዊ ሁኔታ አንስቷል። ከአንሳቸው ነጥቦች መካከል "አመራሩ የፅንፈኛ ምሽግ ናችሁ፣ እናንተ ሰርታችሁ ለውጥ አታምጡ፣ የሆነ ነገር ሲነገራችሁ አንገት መነቅነቅና ከንፈር መምጠጥ ሆኗል ስራችሁ" ብሏቸዋል።

ቀጥሎም "አጠቃላይ እኛ አሁን ባለው ሁኔታ ከንጉሱ ጀምሮ እስከ ኢህአዴግ ድርስ በምስለኔ እንጅ ሶማሌ በራሱ ተወላጅ ክልሉን መርቶ አያውቅም፣ አፋር በራሱ ተወላጅ ተመርቶ አያውቅም፣ ክልሎች አሁን ያላቸውን ያክል ነፃነት ኖሯቸው አያውቁም።" እያለም ቀባጥሯል። ታሪክ ስለማያውቅ ከዚህ የተለዬ ሊናገር አይችልም።

#ስለDiplomacy፦ ዙሪያችን ብዙ እድገታችንን የማይወዱ በክፉ አይን እየተመለከቱን ነው። የባህር በር ጥያቄ ጉዳይ ነገም የማንተወው ጉዳይ ነው ብሏል። በቪዲዮ ላይ ባለፈው ናዝሪት ላይ በተካሄደው ስብሰባ ኤርትራን እንደ ጋዛ እናደርጋታለን ያለውን ቆርጠውታል።

አብይ አህመድ ከፋኖ ጋር እየተካሄደ ስላለው ጦርነት ምንም ያለው ነገር የለም፤ ግን ንግግሮቹ ሁሉ የተስፋ መቁረጥ ይመስላል።

#####################

ከአብይ አህመድ ማጠቃለያ በመቀጠል ከንቲባ ተብዬዋ በአካል መጥታ የስራ መመሪያ ልሰጥ ነው በሚል ደስኩራለች።

በንግግሯም "እናንተ የምንሰራውን ስራ ጠላት ሲያራክሰው እያያችሁ ምንም አይመስላችሁም፣ እኛ ከተማዋ እየቀየርናት ነው፣ ማንም ቢጮህ እኛ ከጉዟችን የሚያግደን ነገር የለም።" የሚል እረጅም ሰዓት ወስዳ እጅና እግር የሌለው ማጠቃለያ ነበር።

በንግግሯ ተስፋ መቁረጧን መረዳት ችያለሁ። አዳነች ከተናገረቻቸው ነጥቦች "እስኪ የምር ብልፅግና ሁኑ፤ መጀመሪያ እናንተ የምር መሆን ብትችሉ የሚያቅተን ነገር የለም፣ ሌብነት ተንሰራፍቷል። አሁን ባለው ሁኔታ ተቋማዊ ሌብነት ባይኖርም ከወዲሁ ማስተካከል ካልቻልን ወደ ተቋማዊ ሌብነት መሄዱ አይቀርም። በየቡድኑ ስለ ሌብንት ብዙ አንስታችኃል ግን ማነው ሌባው? ማነው የእጅ መንሻ የሚቀበለው? ለምን መታገል አቃታችሁ ብላ ጥያቄውን ወደ ተሳታፊው መልሳዋለች።" ቀጥላ ግን ይሄኛውን ከላይ ያነሳችውን ነጥብ የሚያፈርስ ሀሳብ ሰንዝራለች። ይህ ሀሳብም እንዲህ ይላል:-  "ፊርማ አትፍሩ እኛ የኮሪደር ልማቱን ለማፋጠን ስንል አንዳንድ አሰራሮች ላንጠብቅ እንችላለን፤ የፋይናስ አሰራር እንጠብቅ ካልን በአሰብነው ጊዜ መጨረስ አንችልም፤ ስለዚህ የወረዳ አመራሮች በእኛ በኩል የመጣ ከሆነ 'ለለውጥ' ስለሆነ ያለምንም ፍርሃት የሚፈረም ነገር ካለ አትሸማቀቁ ፈርሙ እኛ ሀላፊነት እንወስዳለን" ብላለች።

ከፋኖ ጋር እየተደረገ ስላለው ጦርነት አለቃው አብይ አህመድ የፈራውን ሀሳብ እሷ አንስታዋለች።

"አማራ ክልል የተፈጠረውን ችግር ማስተካከል ያልቻልነው፤  ሕዝቡ በተግባርም በአመለካከትም የፋኖ ተባባሪ ስለሆነ ነው እንጅ ከመከላከያ አቅም በላይ ሆኖ አይደለም።" ብላለች።

አጠቃላይ የሁለቱም ማጠቃለያ በተስፋ የተሞላ ሳይሆን በተስፋ መቁረጥ የተደረግ ማጠቃለያ ነው ያደረጉት!

ስብሰባው ሲጠናቀቅ ተኝተው የነበሩት ተቀስቅሰው ወደ ቤታቸው ሂደዋል!

አንበርብር!

ጣና ሚዲያ Tana Media

21 Oct, 19:54


እስከ አሁን አልጠፋም።
#Update

መርካቶ ' ሸማ ተራ ' የተነሳው ከባድ የእሳት አደጋ እስካሁን አልቆመም።

እሳቱን መቆጣጠር አልተቻለም።

የፋሽስቱ አገዛዝ ሹም የሆነችው የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ " አደጋውን ቶሎ ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለዉን ጥረት  አዳጋች ያደረገዉ የአካባቢው መንገድ የእሳት አደጋ መኪና በተሟላ ሁኔታ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በመሆኑ ምክንያት ነው " ብለዋል።

አሁን ላይ " በሄሊኮፕተር ለመጠቀም እየጣርን  ነው " ሲሉ የሴራው ባለቤቶች በህዝብ ሀብት ውድመት አላግጠዋል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

21 Oct, 18:38


መርካቶን አንድደው ሞቋት! እየበለጠጋችሁ 🤔🤔

ጣና ሚዲያ Tana Media

21 Oct, 18:35


“የአዲስ አበባ የባለቤትነት ጉዳይ ቀዳሚው የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ነው፡፡ እኛ እንደ ኦነግ አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስር መሆን አለባት ነው የምንለው! የፌደራሉ መንግስት መሬት የለውም፤ ከፈለገ ባህርዳርን ዋና ከተማው ማድረግ ይችላል፡፡”
ቀጀላ መርዳሳ ከአዲስ ማለዳ ጋር ካደረጉት ቆይታ የተወሰደ

ጣና ሚዲያ Tana Media

21 Oct, 18:34


መርካቶ ሸማ ተራ

መርካቶ ሸማ ተራ ከጃቡላኒ የንግድ ማዕከል ጀርባ ወይም ሽንኩርት በረንዳ የሚባለው ሥፍራ ላይ ከበድ ያለ የእሳት አደጋ ተከስቷል ።

Via: ጌች ሐበሻ

ጣና ሚዲያ Tana Media

21 Oct, 07:48


የDK ነገር

እነዚያ በረሮ እንዳሉ እነዚህ ጊንጥ እያሉ ወገን ሊጨርሱ!

የዘር ፍጅት ጥሪ ነው

ውነቃ ዳንኤል "ጊዜ ተሰዓቱ ማን ተገኝ አለሽ?" በቅኔ መምህራን ቤት የሚነገረውን ተጠቅሞ ያስተላለፈው የዘር ፍጅት ጥሪ ነው።

ሲጀመር ስለ ጊንጥ ሳይኾን የተነገረው ስለ ትል ነው። ጊንጥ በአመዛኙ በአሸዋማ በረሃ አካባቢ የምትኖር ሲኾን በዛፍ ቅርንጫፍ ቅጠል ለቅጠል የሚሳበው ደግሞ ትል ነው። ጊንጥና ቅጠል የማይመስል ነገር። ጊንጥ የቱንም ያኽል ትንሽ ብትኾን ትጎረብጣለች። ትል ግን ከቅጠል ልስላሴ ወይም መሻከር የመመሳሰል ዕድሉ ሰፊ ነው።

ባሕታዊው ሠዓታቸው ሲደርስ አፋቸውን ለመሻር (ለማደፍ) የላመ የጣመ ስለሌላቸው የተገኘውን ቅጠል ይሸመጥጣሉ። በዚያ ሠዓት ከቅጠሎቹ መኻል ተወሽቃ ሳያዩአት ወደ አፋቸው የገባች ትል ድምፅ ታሰማለች። እርሳቸውም ጊዜ ተሰዓቱ ማን ተገኝ አለሽ? ብለው "አስተናግደዋታል"።

ይኽንን ጠቅሶ የብልጽግና ሠራዊት ፋኖን እዋጋለሁ በሚል ሰበብ ሕፃናትን፣ ንጹሐንን፣ ከብቶችን፣ ሰብሎችን፣ አብያተ እምነትን እና ተቋማትን በነጭ ፎስፈረስ ቦምብ መግደሉንና ማፈራረሱን ትክክለኛ ርምጃ ነው ሲል ተከላክሏል።

ባሕታዊው ትሊቱን የተመገቡት ዐውቀው ኾን ብለው ሳይኾን ስላላዩአት ነው። ውነቃ ዳንኤል ግን የተገኘ ሁሉ ይጨረገዳል፣ እዚያ አካባቢ የምንጨነቅለት ሕይወትም ተቋምም የለም በማለት የዘር ፍጅት ቀስቅሷል።

የባሕታዊው ድርጊት ያጣ የነጣ የሚያደርገው ፍትሐዊ ሲኾን የውነቃ ዳንኤል መልእክት ግን የዘር ፍጅት ዐቅዶ መሥራትን ቅቡል አድርጎ ለማንበር የተነገረ ነው።

አኹንም ያገኘነውን ከመጨፍጨፍ የሚያግደን የለም። ከተፈጃችሁ በኋላ ለሌላ ፍጅት ተዘጋጁ የሚል አደገኛ ቅስቀሳ ነው። እነዚያ በረሮ እነዚህ ጊንጥ እያሉ ወገን ሊጨርሱ ተነሥተዋል።

ዲ/ን አባይነህ ካሴ

ጣና ሚዲያ Tana Media

20 Oct, 18:24


#ሰበር_የድል_ዜና
ጊራና ከተማ በአማራ ፋኖ በወሎ እዝ ስር ገብታለች ..‼️‼️

በዛሬው እለት በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ አካባቢ በጀግናው ኮለኔል ፋንታሁን ሙሃባ በሚመራው አማራ ፋኖ በወሎ እዝና እና በብርሀኑ ጁላ አራዊት ሰራዊት መካከል ከፍተኛ የሆነ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ መዋሉን የገለፁት ምንጮቻችን የአማራ ፋኖ በወሎ እዝ ስር የሚገኙት ባለሽርጡ ክፍለጦር፣ልጅ እያሱ ክፍለጦርና መቅደላ ክፍለጦር አንድ ላይ በመሆን በሶስት አቅጣጫ ከመጣው የጠላት ሀይል ጋር እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሲያካሄዱ ውለዋል።
▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️▪️
በስተመጨረሻም ዛሬ ከመሸ የጊራናን ከተማን ጀግኖቹ  የኮለኔል ልጆች በቁጥጥር ስር ማስገባታቸውን ለማወቅ ተችሏል ። ጊራና ከተማ ሰርጎ ገብቶ የነበረው የጠላት ሀይልም ጀግኖቹ አፈር አብልተው አከርካሪውን በመምታት ሙትና ቁስለኛ የቀረውን ሃይል ደግሞ በፍርጠጣ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች እንዲፈረጥጥ አድርገውታል።

ጣና ሚዲያ Tana Media

20 Oct, 18:17


ዜና ጎንደር‼️
ጎንደር ከተማ ፈንጠር በሚባል ቦታ የአድማ ብተና ሀላፊ ከአጃቢዎቹ ጋር
እርምጃ ተወስዶበታል::
ጥቅምት 10/2017 ዓ.ም

ጣና ሚዲያ Tana Media

20 Oct, 18:16


የድል ዜና ጎንደር❗️

የአገዛዙ አራዊት ሠራዊት ተጨማሪ ኃይል ከባሕር ዳር ወደ ደብረ ታቦር ከተማ ለመግባት  በምድር ዙ- 23፣ BM-107፣ ዲሽቃና ሞርታርን እንዲሁም በሠማይ በሄሊኮፍተር የታገዘ ጉዞን ሢያደርግ ውሏል። በተመሣሣይ ከባሕር ዳር የተነሳውን ጦር ለመቀበል ከደብረ ታቦር ወደ አለም በር  የአገዛዙ ጦር በከባድ መሣሪያ ታግዞ ዘምቷል።

ድልን እሥትንፋሳቸው ያደረጉ የሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር እና የጉና ክፍለ ጦር አካል የሆነችው ጣይቱ ሻለቃ በጥምረት የአገዛዙን ጦር የተለያዬ ቦታ ላይ ደፈጣ ጥለውበታል። በደፈጣ የታጨደው የአገዛዙ ጦር ወደ ሁለቱም አቅጣጫ እግሬ አውጭኝ ካለ በኋላ ራሱን አደራጅቶ ተመልሷል።

ድንጋጤን መለያው ያደረገው የአቢይ ጦር በምድር ውጊያ እንደተሸነፈ ሢያረጋግጥ በሠማይ በሄሊኮፍተር ታግዞ ከእንደገና ውጊያን አድርጓል። ነገር ግን አሸናፊነት ከአባቶቻቸው የወረሱት፣ ሥነ ልቦናቸው በዕውነት የጸናው፣ ትግላቸው ሕልውናን ማሥቀጠል እንደሆነ ያመኑት የአሥቻለው ደሤ ቀኝ እጆች፣ የውባንተ አባተ ልጆችና የናሁሰናይ ወንድሞች በአገዛዙ የጦር ጋጋታ አልተረበሹም።

የአማራ ፋኖ በአለም በር ላይ የልብ ትጥቅን በደምብ ታጥቆ በውሥን ጦር አገዛዙን ሲለበልብ ውሏል። አለም በርና ዙሪያ ገባው ላይ በነበረው ውጊያ የአገዛዙ አመራሮችም ጭምር ሢደመሰሱ ደብረ ታቦር ሆሥፒታል በዚህ ሠዓት በአገዛዙ ቁሥለኞች ተሞልቷል። የአገዛዙ ከፍተኛ የጦር መሪም እንደቆሰለና ታቦር ሆሥፒታል እንደገባ አረጋግጠናል።

ሕልውናችን በተባበረ አማራዊ ክንዳችን
via:የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ