አዲስ አበባ: ሕዳር 12/2017 ዓ.ም፡ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር 5ኛውን ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር በማስመልከት ባዘጋጀው የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ የአጭር ፊልም ውድድር ላይ አሸናፊ ለሆኑት ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡
በተካሄደው ውድድር ላይ 1ኛ በመውጣት የሁለት መቶ ሺ ብር (200,000 ብር) አሸናፊ የሆኑት እነ ቢንያም ሰለሞን “ሰማያዊ ሽብር’ በሚል አጭር ፊልም ሲሆን፤ 2ኛ የወጣው ኤልያስ ብርሃኑ “የንስር ዓይኖች” በተሰኘ አጭር ፊልም የመቶ ሺ ብር (100,000 ብር) አሸናፊ ሆኗል፤ በውድድሩ የ3ኛነት ደረጃን የያዘው ሰዒድ አወል “ክሊክ” በሚል አጭር ፊልም የ50,000 ብር ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በሽልማት መርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ለአሸናፊዎች ሽልማት የሰጡት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጉታ ባስተላለፉት መልዕክት የጥበብ ሥራ ሰውን ለማንቃት፣ለማስተማር ሁነኛ መንገድ በመሆኑ እኛን መሰል ተቋማት ይህንን መንገድ በመጠቀም የማሕበረሰቡን የሳይበር ደሕንነት ንቃተ ሕሊና ማጎልበት እና ባሕል መገንባት ላይ በትኩረት እንሰራለን ብለዋል፡፡ በ2016 ዓ.ም በተካሄደው 4ኛው የሳይበር ደህንነት ወር ላይ “ስውር ውጊያ” በሚል ርእስ አስተዳደሩ ባሰራው አስተማሪ ፊልም የተቋማትንና የማኅበረሰቡን የሳይበር ደህንነት ንቃተ ሕሊና ለማጎልበት የሚያስችል ውጤት መገኘቱን ያወሱት ም/ዋና ዳይሬክተሩ፤ አምና የነበረውን ተሞክሮ በማስፋት ዘንድሮም በርካታ ወጣቶችን ለማሳተፍ የሚያስችል የአጭር ፊልም ውድድር መዘጋጀቱና ጠቁመዋል፡፡
ተጨማሪውን ለማንበብ፡ • https://www.facebook.com/INSA.ETHIOPIA