አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ @alhidiyawoch Channel on Telegram

አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ

@alhidiyawoch


ኑ ተባብረን ባለን አቅም የቲሞችንና የተቸገሩ ሙስሊም ወገኖቻችንን እንርዳ
በልብስ👕👖 በገዘብ በአስዜዛ በጉልበት በሀሳብና
በተለያዩ በቤት ቁሳቁሶች መርዳት ትችላላቹ
ሰደቃ ወጀልን ታብሳለች ረሱል (ﷺ)

አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ (Amharic)

አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ የየቲሞ ተባብረን ባለን አቅም ላቀቁንና የተቸገሩ ሙስሊም ወገኖቻችንን እንርዳ፣ በአስዜዛዎችና ሀሳብን በቤት ቁሳቁሶች መርዳት ትችላላቹ። ማሽንም፣ ቈርጣ፣ ድመት ወመስርቶ ለባለዉ የሚቀርብ መልዕክት ሎኦ፣ ሀብታሙና በገዘብ በአላህ እናድርጋለን። ይህ መልኩ አልሂዳያ ትላንትን የድምፅ ማስተዋልና መስርዕዎችን ለማሳጣት በቁጥር መሐላት ይሆናል።

አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ

09 Jan, 19:25


ይህ የምታዩት የምግብ ዉጤት የዛሬ አመት ለተቸገሩ ወገኖቻችን ለረመዷን አስቤዛ ድጋፍ ያደረግነዉ ሲሆን።

ዘንድሮም እንደተለመደዉ ለረመዷን ለተቸገሩ መሳኢኖች የረመዷን አስቤዛ የማዘጋጀት ፕሮግራም ቅድመ ዝግጅታችንን እያደረግን እንገኛለን።

ይሄንን ድጋፍ በናተ እገዛ ሲሆን ያደረግነዉ ዘንድሮም የዚህ ኸይር ስራ ተሳታፊ እንደምትሆኑ እርግጠኞች ሆነን መተናል

አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ

07 Jan, 19:41


ለማንኛውም የእውነት ከልባችን ለሃይማኖታችን የምንቆረቆር ከሆነ ቅስም ሰባሪ ሰሞንኛ ስሜት ሲከሰት ብቻ ሳይሆን ሁሌም ለዲን አስተማሪዎች በቂ ትኩረትና እንክብካቤ እንስጥ። በዙሪያችን ወይም በአካባቢያችን ወይም የትም ቢሆኑ የምናውቃቸውን መሻይኾች፣ ዱዓቶች፣ ኢማሞች፣ ሙአዚኖች፣ የመስጂድ ጥበቃዎችና የፅዳት ሰራተኞች ጭምር በማገዝ ላይ እንረባረብ። ምናልባት በዚህ ሰዓት መታከሚያ ወይም ቤተሰብ ማሳከሚያ ያጡ ስንት ይኖሩ ይሆን? የእለት ጉርስ የተቸገሩስ? የቤት ኪራይ ያጨናነቃቸውስ? የመስጂድ ኮሚቴዎች፣ ባለ ሃብቶች፣ ሃላፊነት የሚሰማችሁ ወይም ማስተባበር የምትችሉ ሁሉ ክፍተት ያለበትን እያጤናችሁ የድርሻችሁን ተወጡ። አላህ ይሁነን።

Ibnu Munewor

https://t.me/AlAminOfficially

አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ

17 Dec, 16:29


በሌላ በኩል ደሞ ኡሙ አይመኖች ለሁለት ቤተሰብ ብርድ ልብስና ለ1ሰዉ መኝታ የምትሆን 2ፍራሽ ለየቲሞችና ለየቲም ቤተሰቦች 1ሻንጣ ልብስና 10ሺብር ድጋፍ ተደርጓል።

አል ሂዳያ የየቲሞች መርጃና በጎ አድራጎት ጀማአ

17 Dec, 13:55


በዛሬዉ እለት አል ሂዳያ ጀማአ በእዝነት የአካል ጉዳተኛ ህፃናት መርጃ ተቋም ያሳለፉት የጉብኝትና የዚያራ ፕሮግራም ይሄን ይመስል ነበረ


በዚያራችን ወቅት ለምግብነት የሚያገለግል ሩዝና ለአካል ጉዳተኛ ህፃናት የሚሆን ዳይፐርና ዋይብሶችን ይዘን ሄደናል።

በወቅቱም በርካታ አካል ጎዳተኛ ህፃናቶች የሚገኙበት ሲሆን አብዛሀኛወቹ መናገር የማይችሉና መስማት የተሳናቸዉ እንዲሁም መመገብ የማይችሉና ከነ ጭራሹ መራመድ የማይችሉ አንዳዶቹ ደሞ ከነ ጭራሹ መራመድም መናገርም መስማትም ማየትም የማይችሉ ህፃናቶች ናቸዉ።

እነዚ ህፃናቶች እጅግ በጣም እርዳታ የሚያስፈልጋቸዉና ህክምና በአግባቡ የማይደረግላቸዉ ከመሆኑ የተነሳ ብዙወቹ ለበሽታና መሰል ነገሮች እየተጋለጡ ይገኛሉ። ታዳ እነዚህን ህፃናት እየረዳች ያለቺዉ ዋና አሚሯ ብቻ ስትሆን እስካሁን ከጎኗ የቆመ ምንም አይነት ድርጅትም ሆነ የገቢ ምንጭ የላቸዉም እዝነት አካል ጊዳተኛ ህፃናት ተቋም በስሩ ከመቶ በላይ አካል ጉዳተኛ ህፃናት የሚገኚበት ተቋም ነዉ።

ይህንን ተቋም በቋሚነት አባል መሆን ለምትፈልጉ መገኛቸዉ አዲስ አበባ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል ዝቅ ብሎ ይገኛሉ።

7,311

subscribers

460

photos

10

videos