የአላህ ባሪያዎች📿🕋

@markaz_islamm


cross @izzyqueen_zxz

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

22 Oct, 14:11


ለሁሉም ሁኔታ አይዞን፣ያልፋል የሚል ማፅናኛ አይወረወርም።ለአንዳንድ ገጠመኞች ቃላት ሁሉ ተሰብስበው ብርታት አይሆኑም።ዱዓ ብቻ ሚፈልጉ ክስተቶች አሉ።

''አላህ ልባችሁን ይጠግነው፣ብርታቱን ይለግሳችሁ''🤲

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

20 Oct, 14:05


ቀኑ ይለወጣል

የትላንቱ ችግር ነገ ላይ ተረት ነው
ያሳለፍነው ስቃይ ወደፊት ክብር ነው
በዛሬ ውስጥ ሆኖ ፈተናው ቢከብድም
ይለወጣል ቀኑ ዛሬ ነገ አይደለም !!

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

20 Oct, 13:55


ላንተ የተከለከልክ ቢመስልህም...እውነታው ግን

......ታዝኖልህ ነው

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

19 Oct, 17:33


إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

🦋አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡ ❣️

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

19 Oct, 16:14


🦋ለአንበሳው ሠግተውለት🦋

🦋በአንድ ወቅት ሰይዲ ኻሊድ ኢብኑ ወሊድ  አናታቸው ላይ አማኢማቸውን እንደለበሱ ከተፋፋመው ማዕረካ ላይ ይዘልቃሉ። ሞቅ ካለው የሰይፍ ፍጭት መሀል   የሰይድ ኻሊድ አማኢማ ከከሃዲያኖቹ እግር ሥር  ተንከባለለች።
ጥምጣሟን ፍለጋ ሰይድ ኻሊድ ብቻቸውን ሆነው  ወደ ከሃዲያኑ ተርታ ሲገሰግሱ ሶሃቦች በድፍረታቸው እየደነገጡ ኻሊድ ሆይ! በገዛ እጆቻችሁ  ወደ ጥፋት አታምሩ ተብሏል ምነው? እያሉ  ተጯጯሁ....ለአንበሳው ሰግተውለት።

ሰይዲ ኻሊድ ጦር ግድሙን አተራመሱት “ምነው ለአንዲት ጥምጣም ተብሎ ኸልቁን ማስጨነቁ” ያስብላል.... ጥምጣማቸውን ከወደቀችበት አንስተው ተመለሱና ለሷሂቦቻቸው እንዲህ ሲሉ አስረዱ
“ስሙኝማ ጓዶች ይህች አማኢማ ተራ ጨርቅ  አትምሰላችሁ...የአህመድ የጸጉር ዘለላ የተቋጠረባት ናት!

 የዐለሙ ራህመት በሓጅ ወቅት ላይ ፀጉራቸውን ተልጨው ነበር... ከጸጉራቸው ላይ እየዘገኑ  ለአስኋቡ ሁላ እንዲከፋፈልም አዘዙ....ሰይድ ጦልሃ ካከፋፈለው የጸጉር ዘለላ ላይ የአንድ ጉንጉን ባለዕጣ ሆንኩኝ...ግዜ ሳላጠፋ የአህመዱን ጉንጉን  ከጦር ፈረሴ ግንባር ላይ አንጠለጠልኳት....ከዚያማ       አንድንም ዘመቻ አልተሳተፍኩም በጸጉሩ በረካ  የጠላትን መንደር ድባቅ የመታሁ ብሆን እንጂ” አሉ
🦋🦋🦋🦋🦋

#khemis💚💚

🤍اللهم صل🤍 وسلم على🤍 سيدنا ونبينا 🤍وحبيبنا وشفيعنا🤍وقرة عيوننا 🤍محمد صلاةً🤍 تشرح🤍 بها صدورنا🤍

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

16 Oct, 17:33


💜 "ኩራት በተሰማችሁ ጊዜ ሞትን አስታውሱ"፡፡

ረሱል ﷺ

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

12 Oct, 17:07


🩸🩸

ተውበት ከወንጀል መዝገባችን
ሊያጠፋልን ይችላል
ከ ህሊናችን ላይ ሚያጠፋልንስ ምን ይሆን?

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

11 Oct, 11:20


♦️ሰይዲና ዐሊይ كرم الله وجهه ተጠየቁ ❞«ከሞት  የበለጠ ከባድ ነገር አለን?»

   🌹«አዎን የወደዱትን መለየት ከሞትም ይብሳል»
   
እንደርሳቸውስ ያጣ ማን አለ? የህይወት አባታቸውን የዐለሙን ራህመት እና የዘይነልዉጁድን ልጂት የሃሰነይኖቹን እናት ዛህራዬ ማጣት ይከብዳል!  
                               
ሶላት እና ሰላም  በአህመድ በኑር አበባው   በቤተሰቡም ላይ ይስፈን🌹

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

11 Oct, 11:19


ወደኔ
ከተመለሱ እኔ ወዳጃቸው ነኝ
እምቢ ካሉ እኔ ሀኪማቸው ነኝ

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

11 Oct, 11:18


🦋لو صلّى العبد على النّبي ﷺ بعددِ
‏أنفاسه، لم يكُن موفّيًا لحقّه.. ﷺ.

🩵አንድ ባርያ በተነፈሰ ቁጥር በሠይደልዉጁድﷺ ላይ ሶለዋት ቢያወርድ እንኳን ሐቃቸውን አላሟላም❞ይላሉ አንድ ዐሊም።🦋

اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد وآله صلاة تُقر بها عينه, وتدخلنا بها حصنه ,وتفيض بها علينا عطاءه ومنه, وتوردنا بها حوضه وكوثره وجواره في الجنة ,وتذهب عن القلب حزنه, وتهب بها للوطن نصره وأمنه .
وسلام على المرسلين والحمد لله رب العالميـــــــــن 🦋

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

08 Oct, 15:13


#ሊላሂ_ተዓላ..🎋
እህቴ ሆይ አላህን እንፍራው!
~
እስኪ ውስጥሽን አዳምጪው። ለማን ነው ይህን ያደረግሽው? አላህ ምን ይለኛል ብለሽስ አስበሻል? ተይው አላህ ዘንድ ሰው ዘንድ ራሱ ያስንቅሻል። ከጌታሽ ተጣልተሽ፣ ሰዎች ዘንድ ትዝብት ላይ ወድቀሽ ምን ትርፍ ታገኛለሽ?

ለማንኛውም ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" صِنْفَانِ مِنْ أَهْلِ النَّارِ لَمْ أَرَهُمَا ؛ قَوْمٌ مَعَهُمْ سِيَاطٌ كَأَذْنَابِ الْبَقَرِ يَضْرِبُونَ بِهَا النَّاسَ، وَنِسَاءٌ كَاسِيَاتٌ عَارِيَاتٌ، مُمِيلَاتٌ مَائِلَاتٌ، رُءُوسُهُنَّ كَأَسْنِمَةِ الْبُخْتِ الْمَائِلَةِ، لَا يَدْخُلْنَ الْجَنَّةَ، وَلَا يَجِدْنَ رِيحَهَا، وَإِنَّ رِيحَهَا لَيُوجَدُ مِنْ مَسِيرَةِ كَذَا وَكَذَا ".
"ሁለት አይነት ሰዎች ከእሳት ጓዶች ውስጥ ናቸው። እኔ አላየኋቸውም (ወደፊት ይመጣሉ።)
* እንደ ከብት ጅራት ያለ መግረፊያ ይዘው ሰዎችን በነሱ የሚደብድቡ ሰዎች እና
* ለብሰው የተራቆቱ፣ ለሌሎች ጥፋታቸውን የሚያስተምሩ፣ ከአላህ ትእዛዝ ያፈነገጡ፣ ፀጉሮቻቸው እንዳዘነበሉ የተከመሩ የግመል ሻኛዎች የሆኑ ሴቶናቸው። እነዚህ ጀነትን አይገቡም። ሽታዋንም አያገኙም። ሽታዋ ከብዙ ርቀት የሚገኝ ነው።"

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

06 Oct, 21:49


እያደግን ስንሄድ ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ)ለምን ይህች አለም ለአማኝ እስር ቤት ናት እንዳሉ እንገነዘባለን

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

06 Oct, 19:03


አብሽሩ!

የመሬት መንቀጥቀጡ የተከሰተው ከአዲስ አበባ 165 ኪሜ ርቀት ላይ አዋሽ አካባቢ ፈንታሌ በሚባል ተራራ ዙሪያ ነው።

የመሬት መንቀጥቀጡ ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ላይ የተከሰተ ሲሆን በአዲስ አበባ መውጫ አካባቢና በኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ተሰምቷል።

በመሆኑም በአዲስ አበባ ዙሪያ በመሬት መንቀጥቀጡ የተረበሻችሁ በመረጋጋት ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበው የመሬት መንቀጥቀጡ ከስምጥ ሸለቆ መከፈት ጋር ተያያዥነት ያለው ነው ተብሏል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በአዲስ አበባ የተከሰተ ሳይሆን ከ165 ኪሜ ርቀት ላይ ላለፉት አስራ አምስት ቀናት ሲሰማ የነበረ ነው።

የመሬት መንቀጥቀጥ ስሜቱ በድጋሚ ቢከሰት ፎቅ ላይ የሚኖሩ ሳይረበሹ ኮለን መጠጋት እና ጠረጴዛ ውስጥ በመግባት መከለል ይችላሉ። ምድር ላይ ያሉ ቤቱን ለቅቆ መውጣት የተሻለ አማራጭ ነው።

አላህ ሀገራችንን ይጠብቅልን።
.

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

06 Oct, 07:55


እንጃ ልኑር አልኑር አለሁም የለሁም
እኔ እኮ በደስታዬ ሳይቀር ደስተኛ አይደለሁም🥺

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

06 Oct, 07:54


ሀያትህን መቀየር ፈልገህ ግና ከየት መጀመር እንዳለብህ ካላወቅክ🦋
🩵በሠይደልውጁድ ﷺ ላይ ሶለዋት ማውረድ ጀምር🩵

✍️اللَّهُــــــــــــــمَّ صَلِّ عَلَى سيِّــــــــدِنَا محمدٍ الفاتِـــــــــحِ لِمَا أُغْلِــــــــــــــق َوالخَـاتِــــــــــــــــمِ لِمَا سَبَــــــــــق نَاصِـــــــــرِ الحَقِّ بالحـــــــــــــــــقِّ  والهـــــــــــــــــادِي إلى صِرَاطِـــــــــكَ الْمُسْتَقِيـــــــــــــــــــمِ، وَعَلَى آلِهِ حـــــــــقَّ قَدْرِهِ ومِقْــــــــــــدَارِهِ العَظِيــــــــــــــمِ‏🦋

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

05 Oct, 15:30


🦋እኔ የዐለሙ ራህመት ሙሀመድ ነኝ🦋

❝ወደ አሏህ ቤት ዚያራ ጉዞ ወጣሁ ይላሉ አንድ የአሏህ ባሪያ..።በመንገድ ላይ አንድን ሰው ተወዳጀሁ ታዲያ ይህ ሠው አይቀመጥም አይቆምም አይበላም  አይጠጣም አይሄድም አይመጣም በሠይደልዉጁድﷺ ላይ ሶለዋት ማውረድ ብቻ።
ብዛት ሶለዋት የሚያወርድበትን ምክንያት ጠየቅሁት እና እንዲህ አለኝ❞ ይላሉ

      ❝ከአባቴ ጋር ወደ መካ ጉዞ ጀመርን።በመሃል መንገድ አንድ ማረፊያ ቦታ ላይረፍት አረግን።ቦታው ላይ ተኝተን በነበርንበት በህልሜ አንድ ተጣሪ ጠርቶኝ ❝አንተ ሰው ንቃ!  አሏህ አባትህን ገድሎታል ፊቱንም ማጥቆርን አጥቁሮታል❞  ሲለኝ ሰማሁ በድንጋጤ ከእንቅልፌ  ነቃሁ።በፍጥነት ተሸፋፍኖ  የተኛውን አባቴን ፊት ስገልጥ  አባቴን እንደተባለው  ፊቱ ጠቁሮ ተኮራምቶ ሞቶ አገኘሁት። ልቤ ተሰበረች የበረታ ሐዘን ውስጥ ባለሁበት በድጋሚ እንቅልፍ አሸነፈኝ።
               አንድን ህልም በድጋሚ አየሁኝ። ከአባቴ ራስ እና እግር በኩል 4  4  ጥቋቁር አስፈሪ ፍጥረታት አባቴን ለመቅጣት እየተቻኮሉ  ነበልባልማ  ቁልምም ብረቶችን ይዘው አየኋቸው። በዚሁ አስፈሪ ሁኔታ ላይ  አንድ የፊቱ ወገግታ  ከጥጥ ፍልቃቂ የነጣ  ውብ ሰው አስፈሪዎቹን ፍጥረታቶች  ❝ከዚህ ሰው ራቁ❞ እያለ በብርሃኑ ሃይል አባረራቸው። የአባቴንም ፊት ገልጦ በኑር ፈገግታ ሞላው።

    ባለግርማው ሰው  ወደ እኔ ተጠግተው ❝አሏህ የአባትህን ፊት አብርቶለታል❞ አሉኝ።    ❝ማናችሁ ለአባቴስ ይህንን ለምን አደረጉለት❞ብዬ ስጠይቃቸው

          ❝እኔ የዐለሙ ራህመት ሙሀመድ ነኝ። አባትህ ነፍሱን በወንጀል ያጨማለቀ ድንበር አላፊ ነበር።ግና እኔ ላይ ሶለዋት ከማውረድ ቦዝኖ አያውቅም።  ❝🦋وأنا غياث لمن صلى علي🦋❞ በእኔ ላይ ሶለዋትን ለሚያበዛም የክፉ ቀን  ደራሽ እሆንለታልሁ!

የኔ ሠይደልዉጁድﷺ🩵

📜ከሠይድ ጀማሉዲን መውዒዛቸው ላይ የተገኘ

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

04 Oct, 17:18


🦋ሞኝ አወራ ብለህ አትመልስ አንተ ሰው,
ዝምታህ ይሻላል ምላሽ ከምትሰጠው...
ካናገርከውማ ደስታውን አገኘ ፍላጎቱም ሞላ,
ዝም ያልከው ጊዜ ግን,
በቁጭት ይሞታል ጥፍሩን እየበላ...🦋

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

27 Sep, 10:00


አንዳንዴ የሚያዳምጥህ ታጣለህ፤
ከጎንህ ሁኖ «ምን ሆንክብኝ» ብሎ
ውስጥህን የሚያበረታህ ወዳጅ ትፈልግና....
ሳታገኝ ስትቀር ታዝናለህ። ግን ምን እንደሆንክ
ሳታሳውቅ ደስተኛ መስለህ ትወጣለህ።

አንተ እኮ ጠንካራ ነህ! እንቺም እህቴ!

🫶🥀

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

27 Sep, 10:00


"
አላህ ካንተ ጋር መሆኑን ስትረሳ ብቸኝነት ይሰማሃል። 💛!

የአላህ ባሪያዎች📿🕋

27 Sep, 09:59


ጁምዓ.....

ሰይዲ ረሱሉላህ ﷺ እንዲህ ብለውናል :

" ጁምዐ ቀን እኔ ላይ ሰለዋት ማውረድን አብዙ ..
የኡመቴ ሰለዋት ሁሌ ጁምዐ ቀን ይቀርብልኛል..
እኔ ላይ ያወረደው ሰለዋቱ የበዛ የበለጠ ወደኔ ቅርብ ይሆናል "
" أَكْثِرُوا عليَّ مِنَ الصَّلاةِ في يومِ الجمعةِ ؛ فإنَّ صَلاةَ أُمَّتي تُعْرَضُ عليَّ في كلِّ يومِ جُمُعَةٍ ، فمَنْ كان أكثرَهُمْ عليَّ صَلاةً ؛ كان أَقْرَبَهُمْ مِنِّي مَنْزِلَةً ."
رواه البيهقي

ሰሉ አለ ነቢ
ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

1,828

subscribers

190

photos

116

videos