የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

@loveis_one


አልቃሻን ማሳቅ ለኛ ቀላል ነው!!! 😁😂

እና ደሞ ሳያስፈቅዱ left ማለት አይቻልም 😠😠
#share ያርጉ ለጓደኞቻቹ 🙏
𝑓𝑜𝑟 𝑎𝑛𝑦 𝑝𝑟𝑜𝑚𝑜𝑡𝑖𝑜𝑛 & 𝑐𝑟𝑜𝑠𝑠 𝑐𝑜𝑛𝑡𝑎𝑐𝑡 @Amukii

ᴏᴛʜᴇʀ Group @yesaq_alem😂😂
የ ፍቅር አለም

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

04 Oct, 16:18


😁ፈገግ ያደርጋል!😁


አንድ አዲስ ሰለምቴ ጓደኛዬን መስጂድ እንዴት ነበር ? ሰገድክ ? አልኩት ።
አዎ ሰግጄ ፀለይኩኝ አለ ።
ከሰላት በኋላ ዐሪፍ ስብከት ሰማህ ?

"ምንም አይልም ። ሼኪው የሆነች ዱኒያ የምትባል ሴት ክዳቸዋለች መሰለኝ ። ዱኒያ ከሃዲ ናት ፣ ተጠንቀቋት ፣ አታባሯት ፣ አታላይ ናት ምናምን ሲሉ በማይገባህ አትግባ ስላልከኝ ቶሎ ወጣሁኝ ።"😂😂😂

ከአብዱረህማን አማን....

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

24 Sep, 18:57


ቡና እየጠጣው በጣም ጮክ ብዬ ፉት ስል ሰምቶ አንዱ

ማነው በNokia ስልክ Snake ጌም ሚጫወተው😂😁

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

24 Sep, 18:39


ካገባ ሁለት ወይም ሶስት አመት የሆነውን ጓደኛዬን አገኘሁት። ተጫወትን ተሳሳቅን። “ትዳር እንዴት ነው?” ስለው “አትስቅም አታለቅስምም” አለኝ😁

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

24 Sep, 18:02


Kal wave 🔥

WAVE መግባት የምትፈልጉ የቻናል ባለቤቶች በሙሉ አሪፍ ዜና ከ KAL WAVE 😍

ቻናላችሁ 1K + የሆናችሁ በሙሉ ፍጠኑ ተመዝገቡ

ለመመዝገብ @ETHIO_BEST_WAVER ላይ አናግሩኝ

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

03 Sep, 13:31


ውድ የሳቅ እና የፍቅር ዓለም ቤተሰቦች
በአዲስ መልኩ ቻናላችንን ሞቅ ደመቅ ሸብረቅ እናደርገዋለን

አላቹ ወይ🙌

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

03 Sep, 13:16


🌹ያችን ሴት ሁኚ🌹....
🍃

ማንም ስለፈለገ የማያገኛት🍃
በብልጭልጭ የማትታለለው
በቃ ለራሷ ክብር ያላትን🥀


@Loveis_one
@Loveis_one

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

03 Sep, 12:13


╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
          ....... የቁማር ፍቅር  ......
             ✎ ፀሐፊ፦ ሀፍሳ
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝

┎━─━─━─━─━─━─━─━─━┒
  በ @Loveis_one የተዘጋጀ
┖━─━─━─━─━─━─━─━─━┚

      ╔════•| ✿ |•════╗
             #ክፍል_አንድ [፩]
      ╚════•| ✿ |•════╝


   "እንዴ አባ 4 ሰአት ሞላኮ...."ከተኛችበት ዘላ ተነሳች።"መድረሳ እንደሚረፍድብኝ እያወቅክ በአላህ..."አጉረመረመች።አባቷ አደለም እሷን ለመቀስቀስ ቀርቶ ራሱ እንኳን አለመነሳቱን ስታይ ተገረመች።
"እንዴ አባ ያለመደብህን"ብርድ ልብሱን ገለበችው "አንተም ስራ መቅረትህ ነው እንግዲ ተነስ...ዛሬ ቤት መዋላችን ነው..."ፀጉሯ ላይ የጠቀለለችውን ሻሽ ፈታ አጠር ለስለስ ያለ ፀጉሯን ፈትታ በታተነችው።"እርቦኛል ደሞ ቁርስ እንብላ..."ብላ የፈታችውን ፀጉር መልሳ እያስያዘች ወደ ጠባቡ እቃ ክፍል ገባች።የሚሞቀውን አሟሙቃ ለራት የተረፈውን ዳቦ ይዛ ቁርስ አቀራረበች።አባቷ አልተነሳም።
"ኡፍ ደሞ ችግር አለብህ..."ጎኑ ቁጭ አለች።"ተነስ..."ነቀነቀችው።መልስ አልሰጣትም
"አባ ተነስ ለስሙስ እኔን ሬሳ መይት ትለኛለህ ከመቼ ወዲ ነው እንደዚ መተኛት የጀመርከው?"ትኮረኩረው ጀመር።
"ይኸው መድረሳ አስቀረኸኝ አንተም ስራ መቅረትህ ነው ቢያንስ ሌላው ቢቀር ቶሎ ቁርስ እንብላ...."የምትችለውን ያህል ነቀነቀችው።
መልስ የለም..... ደንገጥ አለች
"በማይቀለደው እየቀለድክ ባልሆነ...ኡፍ ርቦኛል ወላሂ ከፈለክ በልተን ስንጨርስ ትቀልዳለህ..."
ፀጥ...
"አባ..."በጀርባው ገልበጥ አረገችው።ልብ ምቱን ለማዳመጥ ፈልጋ ፈራች።ባይኖርስ??ቁሞ ቢሆንስ? እናት አባት እህት ወንድም ሆኖ ያሳደጋት ሚስኪኑ አባቷ ልቡ ደም መርጨት አቁሞ ቢሆንስ?? "ማይሆነውን"አለች በውስጧ።የአባቷ እዚ ሰአት ድረስ መተኛት ስጠራው አለመስማት ለጤና አለመሆኑ ገባት።ከሱብሂ ቡኋላ ቁርስ ሲሰራ ሲያዘገጃጅ ሲያብቃቃ እንጂ አንድ ቀን ተኝቶ ነግቶበት አያቅ።ምን ነካው??ማመን ግን አልፈለገችም።ቀስ ብላ ተነስታ ወደ ውጪ ወጣች።ወፍራሟ ጎረቤታቸው ደጅ እየጠረገች ነበር
"አሰሌ ተመድረሳቹ ዛሬም ቀረሽ ወይ?"
"አው እቴቴ አባ አልቀሰቀሰኝም ነበር እስካሁን ተኝቷል"አለች መሬት መሬቱን እያየች
"ምን ትያለሽ?እሱ የጧትም ሰው አደል እንዴ?ተንቅልፍ ጋር ይተዋወቃል ብለሽ ነው?"
"አላውቅም ስጠራውም አይሰማም ገብተሽ እይው"እምባዋ ወረደ
ወፍሯሟ ዝናሽ በአሰል ንግግር ደንግጣ መጥረጊያዋን ጥላው ወደ ውስጥ ገባች።አሰል በሩ ጋር ግድግዳውን ተደግፋ አቀርቅራ እጇን እያፍተለተለች መጠባበቅ ጀመረች
"ምን ትላለች እየተነፈሰም አደል?ሟርተኛ"ሚለውን ቃል ለመስማት የቋመጠች ቢሆንም ከጆሮዋ ሊጠፋ የማይችል የዘላለመም ጩኸት ተሰማት..
"ኡኡኡኡኡኡ አፈር ስሆን አፈር ስሆን...."የዝናሽ ጩኸት ሰፈሩን አመሰው።አሰል ሰማይ ምድሩ ቅብዥር አለባት።የተደገፈችውን ግድግዳ ታካ መሬቱ ላይ ቁጭ አለች አብሯት እምባዋ ተንሸራተተ።ከአይኖቿ የሀምሌ ዝናብ የሚያስንቅ እምባ ቡልቅ ቡልቅ ማለቱን ቀጠለ.... በየመሀሉ
"ለምን??"ትላለች።አባትም እናትም ሆኖ ያሳደጋት አባቷ አሁን ሞተ ብላ መቀበል ጭራሽ የማትችለው ነገር ሆነባት።የወደፊት ህይወት ያለሱ ጭራሽ የማይታሰብ ሲኦል ሆኖ ተገለጠላት።የዝናሽ አሰቃቂ ዋይታ መንደርተኛውን የሰበሰበ ቢሆንም ለአሰል ግን ቅስም ሰባሪ የህይወት ጣዕም መራራ መሆን እንደሚጀመር ሚያሳይ ማንቂያ ደውል ነበር።ደጋግሞ አስተጋባባት...."ለኔ ባረገው ለኔ ባረገው...."ዝናሽ ሰፈሩን ማደባለቅ ተያያዙት
"ያረብ ህልም አርገው"ተንሰቀሰቀች።መንደርተኛው ከየቤቱ እየተሯሯጠ መጣ።ለጊዜው የሷ እኩዬች መድረሳ ስላሉ እናቶች የሷን መኖር አላስተዋሉም ሁሉም ያለቅሳል ይጮሀል።የሰው መብዛት ሀዘኗን አባሰው።በህይወት ሳለ የሚገለምጡት ሚያጉረጠርጡበት ሁሉ ዛሬ ሲያለቅሱ ውስጧ ንዴት ተቀጣጠለበት።ያለችው ህልም ላይ እንጂ እውነት ሆኖ አልታይሽ አላት....

"አባትሽ እየጠራሽ ነው..."፣"አባትሽ ሽንኩርት ግዢ ብሎሻል..."እያሉ በሩቁ ትዕዛዝ ሚያስተላልፉላት ዛሬ ላይ ራሱን ከአደጋ እንደሚጠብቅ ትል ከተጠቀለለችበት ቦታ እየመጣ
"ጀናዛ ተሰናበቺ..."እያለ ናላዋን አዞረው።ከአባትነት ወደ ጀናዛነት።ሽንኩርት በውሀ በጥብጠው የበሉት ሽሮ ናፈቃት።ሶስት አራት ቀን ያደረውን ዳቦ ከአባቷ ጋር በፍቅር እንዳልበሉት ዛሬ ትኩስ ዳቦ ከጉሮሮዋ አልወርድ አለ።

ከሳምንት ቡኋላ.....

    ያላቸው ብቸኛ ቤተሰብ የአባቷ እህት ሂዳያ ብቻ ናት።እሷም ቢሆን ክረምት እነሱ ጋር ታሳልፍ ስለነበር ትወዳታለች።የወንድሟን ልጅ ለማሳደግ በአደራ ተቀብላ አሰልን ተወልዳ ካደገችበት ጎጃም ወደ አዲስ አበባ ወሰደቻት።ያለቀሰችው ማልቀስ... "ህልሜ ነው" ብላ በጉጉት "ከዛሬ ነገ ከእንቅልፌ ይቀሰቅሰኛል...ውሀ በሽሮ በጥብጠን አንድ ዳቦ ለሁለት ተካፍለን ሻይ በሳምንት አንዴ እያፈላን በፍቅር...በአሳማሚ ድህነት ማንም በማይሽረው ጥልቅ መዋደድ መኖር እንቀጥላለን..."ብላ የቃዠችው መቃዠት ሁሉ መና ሲሆን ታያት።

አክስቷ ወይዘሮ ሂዳያ ከባለቤቷ ከድር እና ከሁለት ልጆቿ ጋር ነው የምትኖረው።የመጀመሪያ ልጇ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ 3ተኛ አመት ፍልስፍና ተማሪ ነው።ሁለተኛ ልጇ ከአሰል በእድሜ አንድ አመት የምትበልጥ ጠይም ቆንጆ ናት።

ተወልዳ ከኖረችበት ጎጃም አዲስ አበባ መምጣቷ አባቷን በማጣት ሀ ብሎ የጀመረውን የጨለማ ህይወት ሁ ብሎ የሚያስቀጥለውን መንገድ መክፈት ጀመረ.....

        ...... ይቀጥላል ......

       ይቀጥል የምትሉ??👍

ቻናላችንን ለወዳጅ ዘመዶ ሼር በማድረግ ስራዎቻችንን ያበረታቱ። ስለምትከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን!
↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴↴
╬╬═════════════╬╬
       @Loveis_one
       @Loveis_one
╬╬═════════════╬╬

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

17 Nov, 15:53


ከቁስልህ ለመዳን ከፈለክ ቁስልህን መንካት ተዉ!! ደና ትሆናለዉ።

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

15 Nov, 19:40


በጣም የፍቅር ሰዉ ከመሆኔ የተነሳ 3 ሴቶች በአንዴ ማፍቀር እችላለሁ🤓🤓
ይላል አንዱ እዚጋ🤷‍♀
ማለት ነበር👊💪

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

15 Nov, 19:40


በደረቴ ልተኛ እልና… አንተ ልቤ ዉስጥ ስላለህ ያፍንሀል ብዬ እተዋለዉ😍😁

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

15 Nov, 19:40


ስስምሽ ስላየዉ🙈
ትላንትና በህልሜ
ዛሬ ቶሎ ተኛዉ
ልስምሽ ደግሜ😁
ታድያ ምን ያደርጋል
የህልሜ ደራሲ
አትታደል ቢለኝ
ህልሜን ገለባብጦ
ስስሙሽ አሳየኝ😂

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

15 Nov, 13:32


😍ጠብቄሽ ነበረ😁

የቆሸሸ ትሪ፡ ድስጥ እና መክተፊያ ሰብስቤ አስቀምጬ:በአንድ መዘፍዘፊያ ጠብቄሽ ነበረ መምጣትሽን አምኜ
በናፍቆት ዉስጥ ሆኜ
የቆሸሸ ልብሴን ደጅ ላይ ቆልዬ
ሳሙና ገዝቼ ተስፋን አንጠልጥዬ
እጄን ጎሮሮዬን በአልኮል ወልዉዬ
ጠብቄሽ ነበረ
ጥም እያቃጠለኝ ደርሶ እንደበረሀ
ወይ አልገዛሽ ነገር መሆኔን እያወቅሽ የናጠጠ ደሀ ጠብቄሽ ነበረ

ደረቅ ቧንቧ እያየሁ፡ አዘንኩብሽ ዉሀ😂😂

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

01 Nov, 05:18


አይዟቹ!!!!

ነገሮች ግራ የገባቹ……
በሰዉ የተጎዳቹ………💔
ያዘናቹ……
ተስፋ የቆረጣቹ……😔
ነገሮች የጨለመባቹ……
ያልተጠበቀ ነገር የደረሰባቹ……
አይዟችሁ

አላህ አለ🥹🥹

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

01 Nov, 05:15


በራሴ እያፈርኩ "ወንጀለኛ ነኝ" አልኩት እሱም መለሰልኝ እኔም በጣም መሀሪ ነኝ 🥹🥹

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

01 Nov, 05:14


ዛሬ እንደዚ መሆኑን ባዉቅ ኖሮ ትላንት የማልጀምረዉ ስንት ነገር ነበር!!💔🥀

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

29 Oct, 06:45


እና ዉዶቼ 😊 በጣም እንታመማለን ባላወቅነዉ ነገር ህመሙ እኛዉ ጋ ሆኖ ህመሙ አካላዊ አይደለም ዉስጣዊ ህመም ነዉ እሱም depression ነዉ ባለፈ ታሪክ ውስጣችንን ደግመን ደጋግመን እናደማዋለን why?? አለፈ እኮ ብዙዎቻችን በፍቅር፣በቤተሰብ፣ በቢዝነስ፣ በትምሮ ወዘተ ነገሮች ሳይሳኩልን ቀርቶ እናስባለን እንጨነቃለን ግን ቀደር ነው በቃ እንመን አላህ ለኛ አይሆናቹም ብሎ ነው እኮ!! Ya Ukiti Ya Ki Ena Balafa Tarek Wesetachun Atacananku በሌላ ነገር እዩ ብሎ እኮ እድል እየሰጠን ነዉ so the Past History Dosent Come in This Life 😇😇

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

29 Oct, 04:43


ምን ሆናቹ ነዉ ያዘናቹት??

ና ቁጭ በልና እንነግርሀለን

እሺ

ንገሩኛ

ባክህ ቀለሙ ያልደረቀ ወንበር ላይ የተቀመጥነዉ🙈🙈😂😂

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

28 Oct, 19:41


ብቸኝነትን ለምን መረጥክ ብለው ከጠየቁህ??የማታዩትን ቁስል እየሰፋው ነዉ በላቸዉ😔

የሳቅ እና የፍቅር ዓለም 🤣+🌍

18 Jul, 06:24


ጓደኛማቾች ስለ እድሜ እየተከራከሩ

ሚኪ፦ እኔ እኮ ኢህአዴግ ሲገባ ታዝዬ ነበር!!!
.
.
.
.
.
ሳሚ፦ሰክረህ ነው የታዘልከው😳😂