✞ርቱዓ ሃይማኖት✞ @retua_haymanot Channel on Telegram

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

@retua_haymanot


በክርስቶስ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ፣ እና በቤተ ክርስቲያን አባቶች እምነት ላይ የተመሠረትን ክርስቲያኖች ነን፤ እርሱንም የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን።


የዩትዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያርጉ👇 youtube.com/@retua_haymanot

አንብበን እንለወጥ፡፡
ይህን ቻናል ጆይን በማድረግ የማናውቃቸውን ነገሮች እንወቅ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ ሃሳብ አስታየት ካላችሁ በ @Ahadu_kal ያካፍሉን

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞ (Amharic)

በዚህ ገጽ አንድ ቻናልን ይዟል፡፡ የህዝብ ቻናላችንን የሚገዛ መፅሀፍትን እና መንፈሰኞችን እንዲሁም ተከብሏል፡፡ በምሳሌ አንብበን ለመድሃኔት ፣ ለመረጃና ለሊንክ እና ሌሎችም ትምህርቶችን በቻናል መዝገብ መከታተል ማለትም እንደሆነ ነው፡፡ ጠቃሚ በሆነው ነገር በመሳሪያም አብሮ እንወቅ፡፡ የቻናል ጆይን ለሌላ ሰራዊትና ህዝብ አሳቦ ተጠቅመን ከዛሬ ወዲህ ያስተውማል፡፡ በ@Ahadu_kal ላይ ያካፍሉን፡፡

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

08 Jan, 11:31


🛐 ጸሎት 📖
"""""""'''''''''""""""""''


☑️ ዘር ነውና መከር አለው
☑️ እንባ ነውና ሳቅ አለው
☑️ ትግል ነውና ድል አለው
☑️ ጩከት ነውና መልስ አለው
☑️ መተንፈስ ነውና ሕይወት አለው
☑️ መራቆት ነውና ፀጋ አለው
☑️ ንግግር ነውና ማስተዋል አለው
☑️ መንበርከአ ነውና ማሸነፍ አለው



                👇👇
         ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
        █   𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲      █ 
        ◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

08 Jan, 09:04


▶️ Open የሚለውን ንኩ የፈለጋቹትን 📕ኦርቶዶክስሳዊ 📕ቁም ነገር ታገኙበታላችሁ።

1.ጉዞ ወደ እግዚአብሔር.....Open

2.ሕማማት......................Open

3.ቅዱስ አትናቲዎስ...........Open

4.አባቶችህን እወቅ...........Open

5.ሃይማኖተ አበው............Open

7.ትንሿ ቤተክርስቲያን.......Open

8.የብርሃን እናት...............Open

9.ማህሌተ ፅጌ................Open

10.የኤፍራጥስ ወንዝ.........Open

11.ተግባራዊ ክርስትና........Open

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

07 Jan, 15:34


🌿🌿🌿መንፈሳዊ ጥያቄዎች 🍀🍀




1, ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው ?
2, ሰንበት በብሉይ ቅዳሜ, በሐዲስ እሁድ ለምን ሆነ?
3, አእማደ ሚሥጢራት ለምን ሚሥጢር ተባለ?
4, 10ሩን የቅድስና ማዕረጋት ዘርዝሩ?
5, ሚሥጢር ማለት ምን ማለት ነው ?
6, ሚሥጢረ ሥጋዌ ማለት ምን ማለት ነው?


መልስ ለማግኘት👇👇👇

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

07 Jan, 05:50


#ቅዱስ_ኤፍሬም_ስለ_ልደተ_ክርስቶስ_እንዲህ_አለ፦

ጌታ ሆይ ቅድስት እናትህ ድንግል ሳለች አንተን ፀንሳ በመውለድ እናትነትን ገንዘቧ አደረገች፤ ድንግል ሆና ሳለች ከጡቶቿ ወተት ፈሰሰ፤ ድንግል ከሆነች መሬት ንጹሕ ምንጭ እንዲፈልቅ፤ እንዲሁ ድንግል ከሆነችው እናትህ ጡቶች ወተት ፈለቀ፡፡ እርሱዋ አንተን ብትሸከምህ አንተ ጽንዕ ሰጥተሃት ነው፤ በተራብክ ጊዜ አንተን ከጡቶቹዋ ትመግብህ ዘንድ፣ ነቢዩ ዳንኤል በታላቅ ተራራ የመሰለህ አንተን አንደ ሕፃናት ታቀፈችህ፤ በፈቃድህ የተጠማህ አንተን በእጆቹዋ በፍቅር ትዳብስህ ዘንድ፤ የምህረት እሳት የሆንኽ አንተ ክንዶቿን መለኮታዊው እሳት እንዳይቃጥላቸው ጠበቅኻቸው፡፡

ጌታ ሆይ እናትህ ግሩም የሆኑ ተአምራት የተፈጸሙባት መካን ናት። ወደ እርሱዋ የሁሉ ጌታ የሆነው ገባ፤ የአገልጋዩን አርአያ ነስቶ ተወለደ። የእግዚአብሔር ቃሉ የሆነ እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ ዝምተኛ ሆኖ ተወለደ። ነጎድጓድ የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ ጭምት ሆኖ ተወለደ። እረኛ የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ በግ ሆኖ በመወለድ በአባግዕ ቋንቋ ተናገረ፡፡

ጌታ ሆይ የእናትህ ማኅፀን ከተፈጥሯዊው ሥርዓት በተቃራኒው ፈጸመ፤ ሁሉን ያከናወነ በባለጸግነቱ ወደ እርሷ ገባ፤ ደሃ ሆኖ ተወለደ። ከሁሉ በክብር የሚልቀው እርሱ ወደ እርሷ ገባ፤ ትሑት ሆኖ ተወለደ። በክብሩ ገናና የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ የባሪያውን መልክ ይዞ ተወለደ። ብርቱ የሆነው እርሱ ወደ እርሱዋ ገባ፤ ጥበቃ እንደሚያስፈልገው ሕፃን ሆኖ በማኅፀን ተገኘ። ፍጥረትን ሁሉ የሚመግበው መራብንና መጠማትን ገንዘቡ አደረገ፤ (አጣጣመ) ሁሉን በበረከቱ የሚያለብሰውና የሚያስጌጠው እርሱ ራቁቱን ተወለደ።

እኛን ለማዳን ሲል የእኛን ተፈጥሮ ገንዘቡ ላደረገ ለእርሱ ክብር ምስጋና ይሁን።

መልካም በዓለ ልደት......

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

03 Jan, 17:06


«ወንድምህን አትናቀው»

ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው። እህትህን አትናቃት። ምንም ይሁን ምን ሰው አትናቅ። ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከሆነ ክርስቶስን እየሰደብከዉ እንደሆን አስተውል።

"እንዴት?" ያልከኝ እንደሆንም ይህ የምትንቀው ወንድምህ የከደርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል። የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እሱን ናቅኸው ማለት ክርቶስን ናቅኸው ማለት ነው።

ወንድምህን የምትንቅ ከሆነም በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ እራቁቱን ከሰቀሉት፣ ሐሞትንና ከርቤን ቀላቅለው ከሰጡት፣ በፊቱ ላይም ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም። ስለዘህ ወንድምህን ከመናቅ ተጠንቀቅ።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@retua_haymanot
@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

02 Jan, 05:45


🔔 ከመምህራን የማንን ትምህርት ማግኘት ይፈልጋሉ?👇

┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ምሕረተአብ አሰፋ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዘበነ ለማ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ሄኖክ ኃይሌ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ዮርዳኖስ አበበ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር ያረጋል አበጋዝ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መጋቢ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 መምህር እዮብ ይመኑ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር ገብረ እግዚአብሔር
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔መምህር አባ ገብረ ኪዳን
┗━━━━━━━━━━━━━━┛

🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

02 Jan, 04:15


✞ጥያቄ✞✞

➥ ቤተክርስቲያን የማትቀበለው ጉባኤ ከተዘረዘሩት ውስጥ የቱ ነው?

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

01 Jan, 20:02


የአእላፋት ዝማሬ የሚደረግበት ቀን እና ሰአት መቼ እንደሆነ በ ጃን ያሬድ የቴለግራም ቻናል ላይ ተለቋል!
መግለጫ ለማየት join በሉ

@yeaelafat_zmare

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

01 Jan, 19:23


🌿🌿🌿መንፈሳዊ ጥያቄዎች 🍀🍀




1, ሰንበት ማለት ምን ማለት ነው ?
2, ሰንበት በብሉይ ቅዳሜ, በሐዲስ እሁድ ለምን ሆነ?
3, አእማደ ሚሥጢራት ለምን ሚሥጢር ተባለ?
4, 10ሩን የቅድስና ማዕረጋት ዘርዝሩ?
5, ሚሥጢር ማለት ምን ማለት ነው ?
6, ሚሥጢረ ሥጋዌ ማለት ምን ማለት ነው?


መልስ ለማግኘት👇👇👇

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

31 Dec, 20:07


እስኪ ንገረኝ! በባልንጀራህ ላይ የምትቀናው ለምንድን ነው? ሥልጣንንና በጎ ስምን ሲቀበል ስላየኸው ነውን? ክብርና ዝና ራሳቸውን ባልጠበቁ ሰዎች ላይ ምን ጉዳት እንደሚያመጣ አታስተውልምን? ወደ ትዕቢት፤ ወደ ውዳሴ ከንቱ፤ ወደ ዕብሪት፣ ወደ እንዝህላልነት፣ ይበልጥ ወደ ግድየለሽነት እንደሚወስዳቸው አታውቅምን? ይህ የምትቀናበት ሰው በእነዚህ ክፋቶች ከመያዙም በላይ ሥልጣኑና ዝናው ገና ከመታየታቸው የሚጠወልጉ ናቸው፡፡ እጅግ የሚከፋው ይህ ነውና፡- ከዚህ የሚመነጩ ክፋቶች የማያልፉ ሲኾኑ ከዚህ የሚገኘው ደስታ ግን እንደ ተባለው ገና ከመታየቱ የሚጠፋ ነው፡፡ ታዲያ ንገረኝ እስኪ፥ በዚህ ሰው ነው የምትቀናው?

“ባለ ሥልጣን ሲኾን'ኮ ብዙ ተዕዕኖ ያደርጋል፡፡ ኹሉንም ነገር እርሱ እንደ ወደደው ማድረግ ይችላል፡፡ የተቃወሙትን ይቀጣል፤ ያወደሱትን ደግሞ ይሾማል ይሸልማል፡፡ ማድረግ የሚፈልገውን የማድረግ ኃይልም አለው" ልትል ትችላለህ፡፡ እነዚህ ንግግሮች የዚህ ዓለምና ከምድር ጋር የተጣበቁ ሰዎች ንግግሮች ናቸው፡፡ መንፈሳዊውን ሰው ምንም ማንም ሊጎዳው አይችልምና፡፡

በምን መንገድ አብዝቶ ሊጎዳው ይችላል? ከሥልጣኑ ሊሽረው ይችላልን? ታዲያ ይኼ ምንድን ነው? ይህ በርትዕ ከተደረገ ጠቀመው እንጂ አልጎዳውምና፡፡ ሥልጣነ ክህነትን ሳይገባው የተቀበለን ሰው ያህል እግዚአብሔርን የሚያሳዝነው የለምና፡፡ ያለ ርትዕ ካደረገበት ግን ተጎጂው ካህኑ ሳይኾን ሌላው ነው። ያለ ርትዕ መከራን የሚቀበልና ይህንን በአኰቴት የሚታገሥ ሰው በእግዚአብሔር ፊት የበለጠ ባለሟልነትን (ሞገስን) ያገኛልና፡፡

ስለዚህ እንዴት ምግባርን ተላብሰን ራሳችንንም ክደን መኖር እንደ አለብን እንጂ እንዴት ሥልጣን፣ ክብርና ጌትነት ማግኘት እንዳለብን ዓላማ አድርገን አንያዝ፡፡ እግዚአብሔር የማይወዳቸውን ብዙ ነገሮች እንዲያደርጉ የሥልጣን ቦታዎች ሰዎችን ያባብላሉና፡፡ ሥልጣንን እንደሚገባ ለመጠቀምም ጽኑዕ የነፍስ (መንፈሳዊ) ብርታት ያስፈልጋልና፡፡ ሥልጣን የሌለው ሰው በፈቃዱም ይኹን ያለ ፈቃዱ ራሱን እንደሚገዛ ኹሉ፥ ጽንዓ ነፍስ ኖሮት ሥልጣን የሚይዝ ሰውም እንደዚሁ ፈቅዶም ይኹን ሳይፈቅድ ራሱን ይገዛል፡፡

(የማቴዎስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተረጎመመው ድርሳን 40 ገጽ 332-333
ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

29 Dec, 06:48




ራስን ዝቅ ስለማድረግ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

እግዚአብሔርን የምትወዱት አንድም እግዚአብሔር የሚወዳችኁ ልጆቼ! ትሕትናን ገንዘብ ማድረግ ምን ያኽል ጥቅም እንዳለው፥ በአንጻሩ ደግሞ ትዕቢትን ገንዘብ ማድረግ ምን ያኽል ጕዳት እንዳለው ታውቁ ዘንድ እወዳለኁ፡፡ ምንም ያኽል ምግባር ትሩፋት ቢኖረን፣ ብንጾም፣ አሥራት በኵራት ብናወጣ፣ ሌላም ብዙ የብዙ ብዙ ምግባራትን ብናደርግ ትሕትና ግን ከሌለን ከንቱ ነን ብዬ እነግራችኋለኁ፡፡

ምንም ያኽል ኃጥአን ሳለን ነገር ግን የተሰበረ ልቡና ካለን፥ በምግባር በትሩፋት አሸብርቀው ሳለ ትዕቢተኞች ከኾኑት ሰዎች ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጆች ነን ብዬ እነግራችኋለኁ፡፡

ከቀራጩ በላይ ማን ኃጢአተኛ ነበር? /ሉቃ.18፡9-14/፡፡ ነገር ግን ይኽ ኃጢአተኛ ሰው ዓይኑን ወደ ሰማይ ቀና አድርጐ ሊያይ ባለመውደዱ፣ በምትመሰገንበት በቤተ መቅደስህ መቆም የማይቻለኝ ኀጥእ ነኝ በማለቱ ከማይቀማው፣ ከማይበድለው፣ ከማያመነዝረው፣ በሳምንት ኹለት ጊዜ ከሚጾመው፣ ከገንዘቡ ኹሉ ዓሥራት ከሚያወጣው ፈሪሳዊው ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነትን አገኘ፡፡ ይኽስ እንዴት ሊኾን ቻለ?

ይኽን ያኽል ምግባር ትሩፋትን ገንዘብ አድርጐ የነበረው ፈሪሳዊው የክፋት ኹሉ ስር የኾነውን ትዕቢት በልቡናው አኑሮ ስለነበር ነው ብዬ በእውነት እነግራችኋለኁ፡፡ ብፁዕ ጳውሎስም ይኽን በማስመልከት ሲናገር፡- “ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን፤ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልኾነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል” አለ /ገላ.6፥4/፡፡ ፈሪሳዊው ግን ይኽን አላደረገም፡፡ ይልቁንም ሌላውን ሰው ኹሉ እየኮነነ፥ በሕይወት ካለ ሰው ይልቅም እጅግ ጻድቁ ርሱ ብቻ እንደኾነ እያሰበ ወደ ቤተ መቅደሱ መጣ እንጂ፡፡ ይኽ ፈሪሳዊ ራሱን ያነጻጸረው ከዐሥር፣ ወይም ከአምስት ወይም ከኹለት ወይም ከአንድ ሰው ብቻ አይደለም፤ በዚኽ ዓለም ከሚኖሩ ሰዎች ርሱን የሚተካከለው ማንም እንደሌለ በአደባባይም ጭምር ተናገረ እንጂ፡፡ የሚተካከለው እንደሌለ ብቻም አይደለም፤ ዳግመኛም በሰው ኹሉ ላይ ፈረደ እንጂ፡፡ ይኽን በማድረጉም በሽቅድድሙ መም ላይ ወደቀ፡፡

ብዙ ዕቃዎችን የጫነች መርከብ ብዙ አስቸጋሪ የሚባሉ ማዕበላትን ተሻግራ ከወደቡ ጫፍ ልትደርስ ጥቂት ብቻ ሲቀራት ከዐለት ጋር ተላትማ እንደምትሰጥምና ጭናው የነበረው ኹሉ እንዳልነበረ እንደሚኾን ኹሉ ይኽ ፈሪሳዊም ብዙ ከጾመ፣ ሌላም ብዙ በጐ ምግባራትን ከያዘ በኋላ አንደበቱን ባለመግዛቱ ምክንያት የነበረውን ሀብተ ሥጋ ሀብተ ነፍስ ኹሉ አጣ፡፡ ምንም እንኳን ወደ ቤተ መቅደሱ ለጸሎት መምጣቱ በጐ ምግባር ቢኾንም ባደረገው ነገር ስለተመጻደቀበት፣ ራሱን ከፍ ከፍ ስላደረገበት ባዶውን ወደ ቤቱ ሔደ ብዬ በእውነት እነግራችኋለኁ፡፡

ይቀጥላል....

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

27 Dec, 17:47


“ባትመለሱ እግዚአብሔር ሰይፉን ይስላል” (መዝ. 7፥12)፡፡

እግዚአብሔር እንደዚህ ዓይነት አነጋገርን የሚናገረው ለምን ይኾን? ሰማዕያኑ ከቁሳዊነት ጋር ካላቸው ቁርኝት የተነሣና በእነዚህ ጥንቱንም በሚያውቋቸው መንገዶች ሊያስፈራቸው ሊያስደነግጣቸው ብሎ ነው፡፡ ልብ በሉ! ወታደሮች የጦር ዕቃ መሣሪያን የሚታጠቁት ጠላታቸውን ለመቅጣት ነው፡፡ እግዚአብሔር የጦር ዕቃ መሣሪያ እንደ ያዘ ኾኖ መታየቱ ግን ሰዎችን ለመቅጣት ሳይኾን ፈርተን ወደ ቀልባችን እንድንመለስና ከመከራ [ሥጋ ከመከራ ነፍስ] እንድንድን ብሎ ነው፡፡ ስለዚህ “ሰይፍ” ብሎ መናገሩ የጥልቅ ፍቅሩ ምልክት ነውና የምንደነግጥ አንኹን፡፡

ቃላቱ ለመስማት እንኳን ጭንቅ የኾኑት ከፍጹም ቸርነቱ የተነሣ ነው፡፡ እንደምታውቁት፥ አባቶች ልጆቻቸውን እንዳይቀጧቸው ሲፈልጉ አምርረው ይቈጧቸዋል፡፡ እግዚአብሔርም እንደዚሁ በኃይላተ ቃላቱ ፍርሐታችንን ከፍ የሚያደርገው እንዳይቀጣን ስለሚፈልግ ነው፡፡  እሳተ ገሃነም እንዳዘጋጀ የሚነግረን በእሳተ ገሃነም እንዳይቀጣን ብሎ ነው፡፡ ስለ መንግሥተ ሰማያት ከተነገረው በላይ በወንጌላት ውስጥ ስለ ምረረ ገሃነም ተጽፎ የምናገኝበት ዋናው ምክንያትም ይህ ነው፡፡ ልል ዘሊላን የኾኑ ሰዎች ዘንድ የምረረ ገሃነም ፍርሐት ያህል ወደ ምግባር ስለማይመራቸውና ከክፋት እንዲርቁ ስለማያደርጋቸው፥ ስለዚሁ ምክንያት እግዚአብሔርም ከጣዕመ መንግሥተ ሰማያት ይልቅ አብዝቶ ስለ ምረረ ገሃነም ይናገራል፡፡ ስለዚህ የሚያስፈሩ የሚያስነግጡ ቃላትን ባደመጥን ጊዜ የሚሰጡን በቁዔት ብዙ የብዙ ብዙ ነውና የምንታወክ አንኹን፡፡

ይልቅ የእግዚአብሔር በአንድ መልኩ ታጋሽ፥ በሌላ መልኩ ደግሞ ፈታሒ በጽድቅ ኰናኒ በርትዕ መኾኑን እናስብ፡፡ አስታውሱ! እግዚአብሔር ታጋሽ ነው፡፡ ስለዚህም ተስፋ ድኅነት የለንም አንበል፡፡ ግን ደግሞ እግዚአብሔር እውነተኛ ፈራጅም ነው፡፡ ስለዚህም ልል ዘሊላን አንኹን፡፡ በዚህ ዓለም ብዙ የብዙ ብዙ ይታገሣል፤ በወዲያኛው ዓለም ግን እዚህ ካሳያቸው ትዕግሥቱ ረብ ጥቅም ያላገኙት ሰዎች ለምረረ ገሃነም አሳልፎ ይሰጣቸዋል፡፡ እንግዲያውስ ዕጣ ፈንታችን ፅዋ ተርታችን ይህ እንዳይኾን በዚህ ዓለም ሳለን ከትዕግሥቱ የምንጠቀም እንኹን ብዬ እነግራችኋለሁ፡፡

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ውርስ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ)

@retua_haymanot
@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

23 Dec, 04:05


ይህን ያህል ቀን ጾምኩ አትበሉኝ፡፡ ይህን አልበላሁም ወይም ያንን አልበላሁም፣ የወይን ጠጅ አልጠጣሁም አትበሉኝ።

ይልቁንስ ከግልፍተኝነት ወደ ገርነት፣ ከጭካኔ ወደ ደግነት የተሸጋገርኽ እንደሆነ አሳየኝ፡፡ በአንተ ውስጥ ጥላቻና ቂም ቢኖሩ፣ በወይን ፋንታ ውኃ ብትጠጣ ምን ይጠቅማል? ጾም ብቻውን ስማያዊ ምንዳ አያስገኝምና፤ ትርጉም በሌለው በባዶ የፆም ሥርአት ራስህን አታስገዛ።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

20 Dec, 17:01


የተሳሳተ እምነት ያለበት መናፍቅ ሰው ከመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦችን እና ጥቅሶችን በማቅረብ አያታልልህ፤ እውቀት ያለው መስሎ እንዳይታልልህ ተጠንቀቅ። ዲያብሎስም እንደዚሁ ያደርጋል (ሉቃስ 4:10-11)፤ ዓላማው ማስተማር ሳይሆን ማታለል እና አንተን ከትከክለኛው መንገድ ማስወጣት ነው።

#ቅዱስ_አምብሮስ

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

20 Dec, 10:41


ኢሰማዕነ ወኢርኢነ ወኢነገሩነ አበዊነ ከመቦ ባዕድ አምላክ ዘእንበሌከ

| ከአንተ ሌላ (ከአንተ በቀር ሌላ) አምላክ እንደ አለ አልሰማንም አላየንም አባቶቻችንም አልነገሩንም ።
መፅሐፈ ሰዓታት

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

14 Dec, 17:12


"ስለ እንቅልፍ ፈንታ ሌሊቱን ሁሉ በትጋህ ማደር፥ እግዚአብሔርን በማገልገል ሁኖ ጾምና ትጋህ፥ መጽሐፍ መመልከት በልዑል እግዚአብሔር ዘንድ ለሥራ ሁሉ የከበረች መሠረት ናት።"

#ማር_ይስሐቅ

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

14 Dec, 12:17


ደብረ ዘይት

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ነገረ ምጽአትን (ደብረ ዘይትን) በልዩ ሁኔታ በዓመት ሦስት ጊዜ ታስባለች።
- የመጀመሪያው ከታኅሣሥ 4-6 ካሉት ቀናት እሑድ ላይ ሲውል ሲሆን መዝሙሩም "ሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ - ለሰው ዕረፍት ሰንበትን ሠራ" የሚለው ነው።
- ሁለተኛው በዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት በእኩለ ጾም (በዕለተ ደብረ ዘይት) ሲሆን መዝሙሩም "እንዘ ይነብር እግዚእነ - ጌታችን በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ" የሚለው ነው።
- ሦስተኛው በዘመነ ክረምት በጳጒሜን ካሉት ዕለታት እሑድ ላይ ሲውል ሲሆን መዝሙሩም "ከመ እንተ መብረቅ ዘይወጽእ እምጽባሕ" የሚለው ነው።

በዚህም መሠረት የዘመነ አስተምሕሮ አምስተኛ እሑድ ወይም የጾመ ነቢያት አራተኛ እሑድ ደብረ ዘይት ትባላለች።

በዚች ዕለት "ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁ የበራ ይሁን” የሚለው የጌታችን ትምህርት ይነገርባታል፡፡ ሉቃ ፲፪፥ ፴፩-፵። መዝሙሩም ሰንበት ለሰው ልጆች ዕረፍት ትሆን ዘንድ የተሠራች መሆኗን የሚገልጥ ነው። መልካም ሥራ ሠርተው ስለ ተገኙ ሐሤት የተመላበት ዕረፍትን ያገኙ አባቶች ዜና ይነገርባታል፤ የእነርሱን አሠረ ፍኖት በመከተል በመልካም ግብር ጸንተን እነርሱ ያገኙትን ዕረፍት ለማግኘት እንድንነቃቃ ትምህርት ይሰጣል፡፡

የዕለቱ ምንባባት፦
፩ ቆሮ. ፲፭፥፲፪ - ፴፫ (15፥12-33)፤
፪ ጴጥ. ፫፥፲ - ፍጻሜው (3፥10-ፍጻሜው)፤
ሐዋ. ፳፥፳፰ - ፍጻሜው (20፥28-ፍጻሜው)፤

የዕለቱ ምስባክ (መዝ. ፻፴፩፥፲፭)፦
ለነዳያኒሃኒ አጸግቦሙ እክለ፤
ወለካህናቲሃኒ አለብሶሙ ሕይወተ፤
ወጻድቃኒሃኒ ትፍሥሕተ ይትፌሥሑ፡፡

ትርጕም፦
ድኆችዋን እህልን አጠግባቸዋለሁ፤
ለካህናቶቿም ሕይወትን አለብሳቸዋለሁ፤
ጻድቃኖቿም እጅግ ደስ ይላቸዋል፡፡

ወንጌል፦ ሉቃ ፲፪፥፴፪ - ፵፩ (12፥32-41)፤
ቅዳሴ፦ ዘአትናቴዎስ

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

13 Dec, 05:17


"አጠገብህ ስለሌለው ሰው ድክመት በተናገርክ ቁጥር፤ ሰይጣን ይዘፍንበት ዘንድ ምላስህን በገና አድርገህ እንደሰጠህ ይቆጠራል።"

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

12 Dec, 18:06


ዝምታን መርጠዋል፤መናገርን ስለ ጠሉ አይደለም እግዚአብሔርን በዝምታ ለማዳመጥ ስለፈለጉ ነው፤ ለምድራዊ ምግብ ጊዜ አልነበራቸውም መብላትን ስላልወደዱ አይደለም፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስለተመገቡ ነው፤ ከሰዎች ጋር መሆንን ጠልተው አይደለም፤ እግዚአብሔርን ማገልገል ስለሚፈልጉ ነው እንጂ። እንቅልፍን ስለጠሉ አይደለም፤ነገር ግን የክርስቶስን መምጣት በጉጉት ስለሚጠብቁ ነው።

አንደኛው አባት እንዳለው፣ “ከእናንተና ከእግዚአብሔር ጋር አብሬ መሆን አልችልም።”

የገዳማውያን አባቶቻችን በረከት ይደርብን

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

08 Dec, 13:58


ሕይወቴ ሁሉ በእኔና በእኔ መካከል ያለ ትግል ነው፤ እኔ መሆን እንደምፈልገው እና እግዚአብሔር እኔ እንድሆን እንደሚፈልገው መካከል ያለ ትግል ።

ቅዱስ ኒቆላዎስ

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

08 Dec, 12:29


የሰው ልጅ እውቀት ለበጎ ወይም ለክፉ ይውላል። እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያበረከተው እውቀት ሁሉ ለበጎ ነው፤ ለጥፋት ግን አይደለም። ነገር ግን የሰው ነፃ ፍቃድ መበላሸቱና የእግዚአብሔርን ፍርሃት ማጣቱ ለሰው ልጅ በጎ ተብሎ የተሰጠውን እውቀት ወደ ክፉ ለውጦታል፤ ስለዚህም በዚህ ዓለም እንዲህ ብዙ እንሰቃያለን።

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

08 Dec, 12:21


የእግዚአብሔር ፍቅር ምስጢር በጣም ጥልቅ ነው፤ ማንም ሊገልፀው አይችልም። ውበቱ እጅግ ድንቅ ነው፤ ከፍታውም ሊለካ አይችልም። … በዚህ ፍቅር፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ፈቃዱ ደሙንና ሥጋውን ለእኛ ሰጥቶናል። ሕይወቱንም ለሕይወታችን አሳልፏል።

#ቅዱስ_ቀለሜንጦስ

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

06 Dec, 19:11


💁‍♂ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል።  ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
               ክፈት        ክፈት               
               ክፈት        ክፈት               
                                                   
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
                                                    
                                                   
                                                    
                                                    
                                                     
               ክፈት         ክፈት              
               ክፈት         ክፈት

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

06 Dec, 18:16


ክርስቲያን ሆይ ይህን ልብ በል!!

ወገኔ ሆይ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የእግዚአብሔር ወዳጆች ለተባሉት ወንድም/እኅት/፣ ከሐዋርያትና ከሰማዕታት ጋር ከበዛው ጸጋቸው ተካፋይ፣ ከእርሱም ምስክሮች ጋር አንድ ማዕድ የምትካፈል፣ የቅዱሳን ርስት ወራሽና ቅን በሆነው ፍርዱ ደስ ይልህ ዘንድ ከነቢያት የፍርድ ወንበር ላይ የተቀመጥክ፣ ከቅዱሳን መላእክት ጋር በምስጋና የምትሳተፍ፣ ከሱራፌልም ጋር የምትነጋገር፣ ከኪሩቤል ጋር በሰማያዊ ዙፋን ላይ የተቀመጥክ፣ ከክርስቶስ የጸጋ ስጦታ ተካፋይ የሆንክ፣ የብቸኛ ልጁ ሰርግ ታዳሚ ትሆን ዘንድ የተጠራህ የሰማያውያን ሠራዊተ መላእክት ወዳጅ፣ የሰማያዊቱ ኢየሩሳሌም ዜግነት ያለህ ነህ፡፡ አእምሮህ ውስጥ እነዚህ በክርስቶስ ለአንተ የተሰጡት የእግዚአብሔር ቸርነቶች ከተቀመጡ የጨለማው ዓለም ገዢ አገልጋዮች የሆኑ አንተን ሊያሰነካክሉህ አይችሉም፡፡ በንስሐ ጽና፡፡ ሕሊናን ከሚያቆሽሹ ከንቱ አስተሳሰቦች ራስህን ንጹሕ አድርግ፡፡ ከእነዚህ ፈጽመህ ራቅ ከንቱ በሆኑ አስተሳሰቦችም አትሸበር፡፡”

(አብርሃም ሶርያዊ)

@retua_haymanot
@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

06 Dec, 18:04


💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️

💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️

👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️

⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️

🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️

በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
                👇👇👇
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel



        
                     🔔
          🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
          ♦️ፊላታዎስ ሚዲያ♦️
                    👇🏽👇🏽
🧏መናፍቃን ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች⁉️
የጌታችን እናት የአዳም የውርስ ኃጢአት/ጥንተ አብሶ/አለባት⁉️
የጌታችን እናት አልተነሳችም⁉️
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
         👆👆👆
👉ለነዚህ ጥያቄዎች እና ለመሳሰሉት በቂምልሽ ተሰቶበታ ይቱብላይ ታገኙታላቹ።

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

06 Dec, 17:42


❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
🔅ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር🔅

📜 የሀገራችን የኢትዮጵያ ቀዳማዊና ጥንታዊ ስለሆነው የግእዝ ቋንቋ መሠረታዊ ትምህርት እንሰጣለን። እርስዎም አባቶቻችን ያቆዩልንን ቋንቋ በመማርና ለትውልድ በማስተላለፍ ኃላፊነትዎን ይወጡ!
📜

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

06 Dec, 16:59


💍ከጋብቻ በፊት ሩካቤ (sex) መፈጸም ምን ችግር አለው⁉️

💁‍♂ከትዳር በፊት መሳም (ከንፈር ወዳጅ /kiss) ይቻላልን⁉️

👨‍🦱🧑‍🦳ፍቅረኛሞቹ እጅግ በጣም ስለሚውዋደዱ (ሩካቤ/sex) ቢፈጽሙ ምን ችግር አለው⁉️

⛪️በቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ከተዋደዱ በኋላ ስሜታቸው ይገደባል⁉️

🤵‍♂የስሜት መግለጫዎች መፈጸም ይቻላል⁉️

በነዚህ ትምህርቶች ዙሪያ እየተማርን እንገኛለን
እርሶም እውቀቱ እዲኖርዎ ከፈለጉ ይህን ማስፈንጠሪያ Link ጠቅ ያድርጉት
                👇👇👇
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel
     @EOTC_-OPEN_channel



        
                     🔔
          🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌
          ♦️ፊላታዎስ ሚዲያ♦️
                    👇🏽👇🏽
🧏መናፍቃን ከሚያነሷቸው ጥያቄዎች⁉️
የጌታችን እናት የአዳም የውርስ ኃጢአት/ጥንተ አብሶ/አለባት⁉️
የጌታችን እናት አልተነሳችም⁉️
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
https://youtu.be/8tUjf9miCtQ?si=K22Xvwmx3Xo89L8k
         👆👆👆
👉ለነዚህ ጥያቄዎች እና ለመሳሰሉት በቂምልሽ ተሰቶበታ ይቱብላይ ታገኙታላቹ።

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

06 Dec, 16:38


💁‍♂ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል።  ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን
መጫን በቂ ነው።
               ክፈት        ክፈት               
               ክፈት        ክፈት               
                                                   
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት
                                                    
                                                   
                                                    
                                                    
                                                     
               ክፈት         ክፈት              
               ክፈት         ክፈት

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

06 Dec, 16:16


መስቀሉን  ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቻናል ለህይወታችሁ ጠቃሚ ስለሆነ መስቀሉን  ይጫኑ Join ይበሉት
/Start      

                  🔳🔳
                  🔳🔳
         🔳🔳🔳🔳🔳🔳
         🔳🔳🔳🔳🔳🔳
                  🔳🔳
                  🔳🔳
                  🔳🔳
                  🔳🔳

         መስቀሉ አርማችን ነው።

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

05 Dec, 12:38


እጅግ መሳጭ ከሆነው የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መልዕክት ወደ ኦሎምፒያስ ከተላከ የተቀነጨበ ነው:-

"የአንድ ፈረስ ፈረስነቱ ምኑ ላይ ነው? በወርቅ ልጓም ማሸብረቁ፣ እጅግ ቅንጡ በኾነ ኮርቻው፣ ከሐር በተሠሩና በባለ ብዙ ኅብረ ቀለማት ባጌጠ ልብሱ፣ እጅግ በጣም በተጋጌጠ ቆቡ እንዲሁም በወርቅ ገመድ በተገመዱ ፀጉሮቹ ላይ ነውን? ወይስ እጅግ ፈጣንና ብርቱ በኾኑት እግሮቹ፣ ለመሮጥ በሚያመቸው በሰኮናው፣ ረጅም ጉዞና ውጊያም ለማድረግ ባለው ተነሣሽነቱ፣ በጦር ሜዳ ላይ በማይደነብር ባሕርይው፣ ሸሽቶ ማምለጥ ካለበትም ጋላቢውን ለማሸሽና ለማዳን ባለው ጉብዝናው ላይ ነው? አንድን ፈረስ መልካም ፈረስ የሚያስብሉት መጀመሪያ ላይ የጠቀስናቸው ነገሮች ሳይኾኑ በኹለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀመጥናቸው ነገሮች አይደሉምን? አህያና በቅሎስ አህያና በቅሎ የሚያስብላቸው ምናቸው ነው? ደስ እያላቸው ሽክምን የመሸከም ኃይላቸው፣ ይህን ተሸክመው በቀላሉ ጉዞዎችን ማድረጋቸው፣ ለዚህም እንደ ዓለት የጠነከረ ሰኮና ስላላቸው አይደለምን? እነዚህ እንስሳት ይህን ተግባር ለማከናወን ከአፍአ የሚያደርጉት ጌጣጌጥ አስተዋጽኦ ያደርጋልን? በጭራሽ!

የምናደንቀው ወይንስ የትኛዉን ወይን ነው? ብዙ ቅጠልና ቅርንጫፍ ያለውን ወይስ ፍሬ አፍርቶ ጎንበስ ያለውን? ከአንድ የወይራ ዛፍ የምንጠብቀውስ ምንድን ነው? ትልልቅ ቅርንጫፎችና ለማየት ደስ የሚያስኝ ቅጠል እንዲኖረው ነው ወይስ በቅርንጫፉ ኹሉ ላይ ፍሬ እንዲያፈራ?

መልካም! በሰው ልጆች ዘንድም እንዲህ እያደረግን እንመልከተው፡- አንድን ሰው ሰው የሚያስበለው ምን እንደ ኾነና ይህንንም ምን እንደሚጎዳውና እንደሚያጠፋው እንየው፡፡ እናስ ሰውን ሰው የሚያስብለው ምኑ ነው? ድኽነት የሚያስፈራው ሀብቱ አይደለም፤ በሽታ የሚጎዳው ጤንነቱ አይደለም፤ ተቃውሞ ሊነሣበት የሚችለው የሕዝብ ውዳሴ አይደለም፤ ከፊት ለፊቱ ሞት በሚጠብቀው ሕይወተ ሥጋው አይደለም፤ ባርነትን ሊያስቀሩበት በማይቻለው ነጻነቱም አይደለም፤ እውነተኛ ዶክትሪንና የቅድስና ሕይወትን በጥንቃቄ ይዞ መገኘቱ ነው እንጂ።

ተመልከቱ! አንድ ሰው ራሱ እውነተኛ ዶክትሪንና የቅድስና ሕይወትን አስፈላጊ በኾነ ጥንቃቄ እስከያዘው ድረስ (ሌላ ሰውስ ይቅርና) ዲያብሎስም ቢኾን ሊወስድበት አይችልም። እጅግ ተንኰሎኛውና ጨካኝ የኾነው ጋኔንም ይህን ጠንቅቆ ያውቃል። የኢዮብን ሀብትና ንብረቱን ያጠፋበት ስለዚሁ ዋና ዓላማ ነበር።

ዲያብሎስ ይህን ያደረገው ኢዮብን ድኻ ለማድረግ አስቦ አልነበረም፤ ኢዮብ በእዚአብሔር ላይ ነቀፋን እንዲናገር እንጂ። ሰውነቱን በቁስል የመታው ሥጋው እንዲደክም ፈልጎ አልነበረም፤ የነፍሱን በጎነት ሊያሳጣው ወድዶ እንጂ፡፡ ኾኖም በአንድ ቅጽበት ያለውን ኹሉ ቢያሳጣውም፣ በእኛ እይታ እጅግ ክፉ መስሎ የሚታየን ከባለጸግነቱ አውርዶ እጅግ ድኻ ቢያደርገውም፣ በብዙ ልጆች ተከብቦ ይኖር የነበረውን ልጅ አልባ ቢያደርገውም፣ በአደባባይ ላይ ሰውን ከሚገርፉ ጨካኞች በላይ ከፍቶ መላ ሰውነቱን ቢገርፈውም (ምክንያቱም የቆስለ ሰውነትን በትላትል መበላት የሚገርፉትን ሰው በጥፍር ከመቧጠጥ በላይ ይፀናልና)፣ እጅግ ክፉ ተግሣጽን በገዛ ጓደኞቹ ቢያመጣበትም (ምክንያቱም ኢዮብን ለመጠየቅ መጥተው ከነበሩ ጓደኞቹ አንዱ፡- “እንደ ኃጢአቶችህ መጠን አልተቀጣህም" የሚሉና ሌሎች የነቀፋ ቃላትን ተናግሮታልና)፣ ከከተማውና ከገዛ ቤቱ አውጥቶ ወደ ሌላ ከተማ እንዲወጣ ብቻ ሳይኾን እዚያ ከሔደ በኋላም እጅግ በቆሸሽ ስፍራ እንዲኖር ቢያደርገውም ግን ከዚህ ኹሉ በኋላ እርሱ (ዲያብሎስ) ራሱ ባዘጋጀው መንገድ የበዛ ክብርን አመጣለት እንጂ ምንም ጉዳትን አላደረሰበትም። እጅግ ብዙ ነገሮችን ቢወስድበትም የምግባር ሀብቱን ይበልጥ ጨመረለት እንጂ ካለው ነገር አንዳችስ እንኳን አልወሰደበትም፡ ምክንያቱም ከእነዚህ ነገሮች በኋላ አስቀድሞ ከነበረው ነገር በላይ አግኝቷል፡፡

እንግዲህ ኢዮብ እነዚህን የሚያኽሉ መከራዎችን ከሰው ሳይኾን ከሰዎች ኹሉ እጅግ ከሚከፋው ከዲያብሎስ እንኳን ምንም ጉዳት ካልደረሰበት፣ እነ እገሌ ይህንና ያንን የመሰለ ጉዳት አደረሱብኝ የሚሉት ሰዎች ምን ዓይነት ምክንያትን ነው የሚያቀርቡት? እጅግ ታላላቅ ተንኰሎችን የተሞላ ዲያብሎስ አለ የሚለውን መንገድ በመጠቀም ከተንቀሳቀሰና ጦሩን ኹሉ ካራገፈ፣ ለዚህ አንድ ሰው ብቻ ይህን ኹሉ ክፉ ነገር በላዩ ላይ ከጨመረበት፣ hዚህ በላይ እጅግ ከፍቶም የዚህን ጻድቅ ሰው ቤተሰብ ኹሉ ቢገድልበትም አንዲት ጉዳትስ እንኳን ማድረስ ካልተቻለው፣ ይልቁንም አስቀድሜ እንደተናገርኩት ከጠቀመው፣ ሰዎች'ማ እነርሱ ራሳቸው ራሳቸውን ካልጎዱ በስተቀር እነ እገሌ እንዲህና እንዲህ አድርገው ጎዱን ብለው እንዴት ወቀሳን ማቅረብ ይቻላቸዋል?"

(ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ወደ ኦሎምፒያስ የተላኩ መልዕክቶች ገጽ 54-57 በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ)

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

03 Dec, 12:20


"አንደበትህን 'ይቅር በለኝ (ይቅር በሉኝ)' ማለትን አስለምድ፤ እውነተኛ የኾነ ትሕትና ይሰጥሃልና።"

ባሕታዊው አባ ኢሳይያስ

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

02 Dec, 18:01


"የቤተ ክርስቲያን ካህን ለአንተ እንደ መንፈሳዊ አባት ይኹንልህ፡፡ አንድ ሕመምተኛ ስውር በሽታዎቹን በግልፅ ለሐኪም እንደሚያሳይና ከዚያም እንደሚድን ኹሉ፥ አንተም ምሥጢሮችህን ለካህን በግልፅ ንገር፤ [ትድንማለህ]፡፡”

(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ)

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

29 Nov, 02:21


"ጾም ከምግብ መከልከል ብቻ እንደሆነ የሚያስብ ሰው ተሳስቷል። እውነተኛ ጾም ከክፉ መራቅ ነው።"

ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

28 Nov, 06:10


"ትሑት ሰው ምንጊዜም ቢሆን የእርሱን ድካም ስለሚያውቅና የእግዚአብሔርን እርዳታ ስለሚሻ የእግዚአብሔር ኃይል በእርሱ ላይ ያድራል። በክንዱ ሳይመካ በእግዚአብሔር እርዳታ ስለተመካም ያሸንፋል።"

(ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ)

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

24 Nov, 08:33


እንኳን ለጾመ ነቢያት አደረሳችሁ፡፡
ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ ነው፡፡ ይህን ጾም ነቢያት ለአዳም የተሰጠውን “አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚለውን የተስፋ ቃል በማሰብ ከሰማየ ሰማያት ይወርዳል፤ ከድንግል ማርያም ይወለዳል፤ በሞቱም ሞት የተፈረደበትን የሰው ልጅ ነጻ ያወጣዋል ብለው የጾሙት ጾም ነው፡፡ ሊቀ ነቢያት ሙሴ (ዘፀ. ፴፬፥፳፰)፣ ነቢዩ ኤልያስ (፩ነገ. ፲፱፥፰)፣ ነቢዩ ዕዝራ፣ ነቢዩ ዳንኤል፣ ነቢዩ ነህምያ፣ ቅዱስ ዳዊት፣ ሌሎችም በየዘመኑ የተነሡ ነቢያት ጾመውታል፡፡

እኛ በሐዲስ ኪዳን ያለን ክርስቲያኖች ደግሞ የቀደሙት ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል እያሉ የጾሙትን በማሰብ በመጾማችን ድኅነተ ሥጋ፣ ድኅነተ ነፍስ፣ በረከተ ሥጋ፣ በረከተ ነፍስ እንድናገኝበት እንጾመዋለን፡፡

ጾመ ነቢያት ከልደት አስቀድሞ የሚጾም ሲሆን ፋሲካው ደግሞ የጌችን የልደት በዓል ነው (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፭ ቊጥር ፭፻፷፰)፡፡ ጾመ ነቢያት ከኅዳር ፲፭ (15) ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ ፳፰ (28) ቀን (በዘመነ ዮሐንስ እስከ ታኅሣሥ ፳፯ (27) ቀን) ድረስ ለ፵፬ (44) ቀናት (በዘመነ ዮሐንስ ለ፵፫ ቀናት) ይጾማል፡፡ ከእዚህም መካከል ፵ (40) ቀናት ጾመ ነቢያት፣ ሦስቱ ቀናት ጸመ አብርሃም ሶርያዊ ሲሆኑ የቀረው አንድ ቀን ደግሞ የገሃድ ጾም ነው፡፡ ጾመ ነቢያትን ከኅዳር ፲፭ ጀምሮ ሳይጸሙ የልደትን ዋዜማ ወይም ገሃድን ብቻ መጾም የቤተ ክርስቲያን ሥርዐት አይደለም፡፡
ይቀጥላል. . .

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

24 Nov, 08:33


በጾመ ነቢያት ያሉ ሰንበታት ስያሜ
በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ከመስከረም ፳፮ እስከ ታኅሣሥ ፳፭ ያለው ጊዜ መጸው ሲባል በውስጡ ጽጌ፣ አስተምሕሮ እና ስብከት የሚባሉ ሦስት ክፍሎች አሉት፡፡

አስተምሕሮ፦ ከኅዳር ፮ እስከ ታኅሣሥ ፯ ወይም ፲፫ ያለው ጊዜ ሲሆን ምልጃን ይቅርታ መጠየቅንና መለመንን ያመለክታል፡፡

በቅዱስ ያሬድ የዜማ መጻሕፍት እንደተቀመጠው በዘመነ አስተምሕሮ ውስጥ የሚገኙ ሰንበታት አስተምሕሮ (ኢተዘኪሮ)፣ ቅድስት (ሎቱ ስብሐት)፣ ምኵራብ (አምላክ ፍጹም በሕላዌሁ)፣ መጻጉዕ (ይቤሉ እስራኤል) እና ደብረ ዘይት (ሠርዐ ሰንበተ ለሰብእ ዕረፍተ) ተብለው ይጠራሉ፡፡ ሳምንታቱን በዚህ መልክ የከፋፈለው ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ነው፤ ከመጀመሪያው ሳምንት (ከአስተምሕሮ) በቀር የአራቱ እሑዶች ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ጋር አንድ ዐይነት ነው፡፡ የዘመነ አስተምሕሮ ሰንበታት ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ስያሜ ጋር ተመሳሳይ ይሁን እንጂ በእነዚህ ሳምንታት ሌሊት የሚዘመሩ መዝሙራት፣ በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ ምንባባትና የሚቀርቡ ትምህርቶች ግን በይዘትና በምሥጢር ይለያያሉ፡፡ ትምህርቶቹ በምሥጢር ይለያያሉ ስንልም በዚህ ወቅት የሚነገረው ምሥጢርና ይዘት በወቅቱ ላይ የሚያተኩር መሆኑን ለመግለጽ ነው እንጂ በየትኛውም ጊዜ በቤተ ክርስቲያናችን የሚቀርበው ትምህርት የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው።

በዚህም መሠረት የዛሬዋ እሑድ ቅድስት ትባላለች።
ቅድስት መባሏም የሰንበት ቅድስና የሚዘከርባት ለቀደሳት ለእግዚአብሔርም ምስጋና እንዲገባ የሚነገርባት በመሆኗ ነው፡፡ "ኵሎ ዘፈቀደ ገብረ እግዚአብሔረ በሰማይኒ ወበምድርኒ በባሕርኒ ወበኵሉ ቀላያት”፣ "እግዚአብሔር የወደደውን ኹሉ አደረገ (ፈጠረ)፣ በሰማይም በምድርም በባሕርም በቀላያትም (በጥልቆችም) ሁሉ" የሚለው የዳዊት መዝሙር ይሰበካል፡፡ መዝ. 134፥6። የሚዘመረው መዝሙርም “ሎቱ ስብሐት ወሎቱ አኮቴት ለዘቀደሳ ለሰንበት...”፤ “ሰንበትን ላከበራት (ለቀደሳት ለለያት) ለእርሱ ክብርና ምስጋና ይገባዋል..." የሚለው ነው፡፡

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

24 Nov, 07:57


#ቅዱስ_ሚናስ (#ማር_ሚና)

ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) በምድረ ግብጽ ተወዳጅ ከሆኑ ሰማዕታት ዋነኛው ነው። በግብጻውያን ልዩ ቦታ አለው ማር ሚናስን ጠርተው አይጠግቡትም። ምክንያቱም ከታላላቅ ሰማዕታት አንዱ በመሆኑና ዛሬም ድረስ ለጆሮና ለዐይን ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ስለሚሠራ ነው። በተለይ ለታመመ ለደከመና ለተጨነቀ ፈጥኖ ደራሽ ባለ በጎ መድኃኒት ፈዋሽና አማላጅ ነው።

ቅዱስ ሚናስ ትርጉሙ ታማኝና ቡሩክ ማለት ነው። በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የደጋግ ክርስቲያኖች ልጅ፣ በልጅነቱ የቅድስና ሕይወትን ያጣጣመ፣ በዘመኑ ሰው እጅግ ተወዳጅ የነበረ፣ ሃብትን ክብርን ሥልጣንን ንቆ በጾምና በጸሎት የተወሰነ፣ በመጨረሻም በክርስቶስ ስላመነ በአላውያን ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ህዳር 15 በሰማዕትነት ያረፈበት ሲሆን ሰኔ 15 ደግሞ ቤተ ክርስቲያኑ መርዩጥ በተባለ አገር የከበረችበት ነው።

#በአንድ_ወቅት፦
ዐሥራ ስምንት ቀሳውስት በሥራ ጉዳይ አቡነ ቄርሎስ ፮ኛን ለማነጋገር መርዩጥ ወደ ሚገኘው የቅዱስ ሚናስ ገዳም ጉዞ ጀመሩ። ቀሳውስቱ በጉዞአቸው መንገድ ስተው ሲባዝኑ ከአንድ የበረሓ ሰው ጋር ተገናኙ።

የበረሓው ሰው መርዩጥ የሚገኘው የቅዱስ ሚናስ ገዳም ለመሄድ መንገድ እንደሳቱ ቀድሞ ተረድቶ ነበርና "የማር ሚናስን ገዳም ነው የምትፈልጉት? በማለት ይጠይቃቸዋል። እነርሱም ችግራቸውን እንዴት እንዳወቀ በልባቸው እያደነቁ "አዎን" አሉት። የበረሓው ሰውም እየመራ ከገዳሙ አደረሳቸው አቡነ ቄርሎስ ፮ኛም ወደ በር ወጥተው ተቀበሏቸው።

ከዚያም "ምነው ዘገያችሁ? መንገድ ሳታችሁ እንዴ?" ብለው እንደ ቀልድ ጠየቋቸው። እነርሱም "አዎን! በጣም ተቸግረን ሳለን ይህ የበረሓ ሰው ደርሶልን መንገዱን አሳየን" ብለው ወደ ሰውየው ለማመልከት ዘወር ሲሉ እርሱ በአካባቢው የለም። አቡነ ቄርሎስም "መንገድ እንደጠፋችሁ ስለተረዳሁ ሚናስን ልኬላችሁ ይዟችሁ የመጣው እርሱ ነው" አሏቸው።

አምላካችን ከቅዱሱ ሰማዕት በረከትን ይክፈለን!!

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

23 Nov, 17:21


"አንድ ሰውስ እንኳ ድኻ ነኝ ወይም ድኻ አደግ ነኝ ብሎ ተስፋ አይቁረጥ፤ ከድኻ ማኅበረሰብ የተገኘሁ ነኝ ብሎ ማንም አይዘን፤ ከአንካሳ ልብና ከሰነፍ ሕሊና በቀር የሚያሳዝን ምንም ምን የለምና። በጎ ምግባርን እንዳንይዝ የሚከለክለን አንዱና ብቸኛው ዕንቅፋት መንፋሳዊ ድካም እና የሕሊና ዓቅመ ቢስነት እንጂ ሌላ ምንም አይደለምና።

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ውዳሴ ጳውሎስ መጽሐፍ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተረጎመው)

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

22 Nov, 19:27


አብ ተስፋዬ ነው፣ ወልድ መጠጊያዬ ነው፣ መንፈስ ቅዱስም መሸሸጊያዬ ነው።

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

21 Nov, 09:27


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ዐሥራ ሁለት በዚች ቀን ለሰው ወገን የሚያዝንና የሚራራ፤ በእግዚአብሔር ጌትነት ዙፋን ፊት ሁልጊዜ በመቆም ለፍጥረቱ ሁሉ የሚማልድ፤ የመላእክት አለቃ በሰማያትም ለሚኖሩ ኃይሎች ሁሉ አለቃቸው ለሆነ ለቅዱስ ሚካኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ እኛንም በዚህ በከበረ መልአክ ጸሎትና አማላጅነት ይማረን ለዘላለሙ አሜን።

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

20 Nov, 17:21


ቅዱስ ያሬድ “ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ አስተምሕር ለነ ሰአልናከ፤ በዐሥርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ፤ ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ ዓይኑ ዘርግብ፤ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ፤ ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ ይሰግድ በብረኪሁ እስከ ይመጽእ ሥርየት ለኃጥአን፤ ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ መኑ ከማከ ክቡር -
ሚካኤል ሆይ ከመላእክት እንዳንተ የከበረ ማን ነው? በ14ቱ ልመናህ ለእኛ ታማልድልን ዘንድ ለመንንህ፡፡
” በማለት ስለ ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ዘምሯል፡፡

“በዐሥርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ = በ14ቱ ልመናህ” የተባለበት ምክንያት፡-

እስራኤላውያን በባቢሎን ሰባ ዘመን በምርኮ በነበሩበት ወቅት፥ ቅዱስ ሚካኤል በየአምስት ዓመቱ በእግዚአብሔር ፊት እየቆመ ለእስራኤላውያን ምልጃን ያቀርብ ስለነበረ (በሰባ ዓመት ውስጥ በየአምስት ዓመቱ ምልጃን ሲያቀርብ፥ በእግዚአብሔር ፊት ለምልጃ የቆመው 14 ጊዜ ይሆናል። 70/5=14) እኛም ያንን እያሰብን እንማጸነዋለን፡፡ “የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፡- አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?” ዘካ. ፩፥፲፪ እንዲል፡፡

ሌላው ቅዱስ ሚካኤል በዓመት ውስጥ 14 በዓላት አሉት፡፡ በእነዚህ በ14ቱ በዓላት በእግዚአብሔር ፊት እየሰገደ ለሰው ልጆች ምሕረትን፥ ይቅርታን ይለምናል፡፡ በዚህም የተነሣ ቅዱስ ያሬድ “በዐሥርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ” ያለው በ14ቱ በዓላቱ የሚያቀርባቸውን ልመናዎች በማንሣት ነው፡፡

የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓላት በዓመት 14 ናቸው፡፡

፩ኛ. ኅዳር ፲፪ የተሾመበት፣ ዲያብሎስን ድል የነሣበት፣ ሕዝበ እስራኤል የመራበት ዕለት ነው፡፡
፪ኛ. ኅዳር ፲፫ በዓለመ መላእክት ያሉ አእላፍ መላእክት በዓለ ሢመቱን ተሰብስበው ያከበሩበት ቀን ነው፤ ዕለቱም አእላፍ መላእክት ይባላል፡፡
፫ኛ. ታኅሣሥ ፲፪ ዱራታኦስና ሚስቱ ቴዎብስታን የረዳበት፤ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነበት መታሰቢያ ዕለት ነው፡፡
፬ኛ. ጥር ፲፪ የድሃዋን ልጅ ተላፊኖስን የረዳበት፤ ያዕቆብን ከወንድሙ ከኤሳው እጅ የጠበቀበት ዕለት ነው፡፡
፭ኛ. የካቲት ፲፪ የሚበላው የሚጠጣው የሚለብሰው ላጣ አንድ ሰው፥ በሰው አምሳል ተገልጦ ከሀብታም ሲበደር ዋስ የሆነበት፤ ሶምሶንን ረድቶ አሕዛብን ያጠፋበት ዕለት ነው፡፡
፮ኛ. መጋቢት ፲፪ ማቴዎስ የተባለውን ሰው፥ ሚስቱን እና ልጆቹን የረዳበት፤ የበለዓምን አህያ ያናገረበት ዕለት ነው፡፡
፯ኛ. ሚያዝያ ፲፪ ኤርምያስን ከእስር ቤት ያወጣበት ዕለት ነው፡፡
፰ኛ. ግንቦት ፲፪ ዳንኤል በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ሳለ ዕንባቆምን ምግብ አስይዞ በአንዲት የራስ ጠጕሩ አንጠልጥሎ ከኢየሩሳሌም ዳንኤል ወዳለበት ወደ ባቢሎን ወስዶ ዳንኤልን በጉድጓዱ ውስጥ የመገበበት ዕለት ነው፡፡
፱ኛ. ሰኔ ፲፪ ባሕራንን የረዳበ፤ አፎምያን ከሰይጣን ያዳነበት ዕለት ነው፡፡
፲ኛ. ሐምሌ ፲፪ የድሃይቱን ልጅ ተላሶንን ከባሕር አውጥቶ የጠበቀበት፤ ንጉሥ ሰናክሬምን ከነሠራዊቱ ደምስሶ ንጉሥ ሕዝቅያስን ያዳነበት ዕለት ነው፡፡
፲፩ኛ. ነሐሴ ፲፪ ሶስናን ከእደ ረበናት ያዳነበት፤ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስን ረድቶ መክስምያኖስን ድል ያደረገበት ዕለት ነው፡፡
፲፪ኛ. ጳጕሜን ፫ ቅዱስ ሩፋኤል ያሳረገው የዓመቱን ጸሎት ዕጣን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብበት ዕለት ነው፡፡
፲፫ኛ. መስከረም ፲፪ ሰማዕቱ ፋሲለደስን የረዳበት፤ እግዚአብሔር ከተጣላው በኋላ ይቅር እንዳለውና ምሕረትም እንዳደረገለት ወደ አሞፅ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ የተላከበት ዕለት ነው፡፡
፲፬ኛ. ጥቅምት ፲፪ ነቢዩ ሳሙኤል ዳዊትን ቀብቶ እንዲያነግሠው የላከበት እና ዳዊትን የረዳበት ዕለት ነው፡፡

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

20 Nov, 17:21


ቅዱስ ያሬድ “ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ አስተምሕር ለነ ሰአልናከ፤ በዐሥርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ፤ ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ ዓይኑ ዘርግብ፤ ልብሱ ዘመብረቅ ሐመልማለ ወርቅ፤ ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ ይሰግድ በብረኪሁ እስከ ይመጽእ ሥርየት ለኃጥአን፤ ሚካኤል እመላእክት መኑ ከማከ ልዑል፤ መኑ ከማከ ክቡር -
ሚካኤል ሆይ ከመላእክት እንዳንተ የከበረ ማን ነው? በ14ቱ ልመናህ ለእኛ ታማልድልን ዘንድ ለመንንህ፡፡
” በማለት ስለ ቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ዘምሯል፡፡

“በዐሥርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ = በ14ቱ ልመናህ” የተባለበት ምክንያት፡-

እስራኤላውያን በባቢሎን ሰባ ዘመን በምርኮ በነበሩበት ወቅት፥ ቅዱስ ሚካኤል በየአምስት ዓመቱ በእግዚአብሔር ፊት እየቆመ ለእስራኤላውያን ምልጃን ያቀርብ ስለነበረ (በሰባ ዓመት ውስጥ በየአምስት ዓመቱ ምልጃን ሲያቀርብ፥ በእግዚአብሔር ፊት ለምልጃ የቆመው 14 ጊዜ ይሆናል። 70/5=14) እኛም ያንን እያሰብን እንማጸነዋለን፡፡ “የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፡- አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው?” ዘካ. ፩፥፲፪ እንዲል፡፡

ሌላው ቅዱስ ሚካኤል በዓመት ውስጥ 14 በዓላት አሉት፡፡ በእነዚህ በ14ቱ በዓላት በእግዚአብሔር ፊት እየሰገደ ለሰው ልጆች ምሕረትን፥ ይቅርታን ይለምናል፡፡ በዚህም የተነሣ ቅዱስ ያሬድ “በዐሥርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ” ያለው በ14ቱ በዓላቱ የሚያቀርባቸውን ልመናዎች በማንሣት ነው፡፡

የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓላት በዓመት 14 ናቸው፡፡

፩ኛ. ኅዳር ፲፪ የተሾመበት፣ ዲያብሎስን ድል የነሣበት፣ ሕዝበ እስራኤል የመራበት ዕለት ነው፡፡
፪ኛ. ኅዳር ፲፫ በዓለመ መላእክት ያሉ አእላፍ መላእክት በዓለ ሢመቱን ተሰብስበው ያከበሩበት ቀን ነው፤ ዕለቱም አእላፍ መላእክት ይባላል፡፡
፫ኛ. ታኅሣሥ ፲፪ ዱራታኦስና ሚስቱ ቴዎብስታን የረዳበት፤ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነበት መታሰቢያ ዕለት ነው፡፡
፬ኛ. ጥር ፲፪ የድሃዋን ልጅ ተላፊኖስን የረዳበት፤ ያዕቆብን ከወንድሙ ከኤሳው እጅ የጠበቀበት ዕለት ነው፡፡
፭ኛ. የካቲት ፲፪ የሚበላው የሚጠጣው የሚለብሰው ላጣ አንድ ሰው፥ በሰው አምሳል ተገልጦ ከሀብታም ሲበደር ዋስ የሆነበት፤ ሶምሶንን ረድቶ አሕዛብን ያጠፋበት ዕለት ነው፡፡
፮ኛ. መጋቢት ፲፪ ማቴዎስ የተባለውን ሰው፥ ሚስቱን እና ልጆቹን የረዳበት፤ የበለዓምን አህያ ያናገረበት ዕለት ነው፡፡
፯ኛ. ሚያዝያ ፲፪ ኤርምያስን ከእስር ቤት ያወጣበት ዕለት ነው፡፡
፰ኛ. ግንቦት ፲፪ ዳንኤል በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ ሳለ ዕንባቆምን ምግብ አስይዞ በአንዲት የራስ ጠጕሩ አንጠልጥሎ ከኢየሩሳሌም ዳንኤል ወዳለበት ወደ ባቢሎን ወስዶ ዳንኤልን በጉድጓዱ ውስጥ የመገበበት ዕለት ነው፡፡
፱ኛ. ሰኔ ፲፪ ባሕራንን የረዳበ፤ አፎምያን ከሰይጣን ያዳነበት ዕለት ነው፡፡
፲ኛ. ሐምሌ ፲፪ የድሃይቱን ልጅ ተላሶንን ከባሕር አውጥቶ የጠበቀበት፤ ንጉሥ ሰናክሬምን ከነሠራዊቱ ደምስሶ ንጉሥ ሕዝቅያስን ያዳነበት ዕለት ነው፡፡
፲፩ኛ. ነሐሴ ፲፪ ሶስናን ከእደ ረበናት ያዳነበት፤ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስን ረድቶ መክስምያኖስን ድል ያደረገበት ዕለት ነው፡፡
፲፪ኛ. ጳጕሜን ፫ ቅዱስ ሩፋኤል ያሳረገው የዓመቱን ጸሎት ዕጣን ወደ እግዚአብሔር የሚያቀርብበት ዕለት ነው፡፡
፲፫ኛ. መስከረም ፲፪ ሰማዕቱ ፋሲለደስን የረዳበት፤ እግዚአብሔር ከተጣላው በኋላ ይቅር እንዳለውና ምሕረትም እንዳደረገለት ወደ አሞፅ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ የተላከበት ዕለት ነው፡፡
፲፬ኛ. ጥቅምት ፲፪ ነቢዩ ሳሙኤል ዳዊትን ቀብቶ እንዲያነግሠው የላከበት እና ዳዊትን የረዳበት ዕለት ነው፡፡

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

16 Nov, 10:22


"ዲያብሎስ በእናንተ ላይ እጅግ ክፉ ነገርን በማምጣት አሳዝኖአችኋልን? እናንተም ኢዮብን አብነት አድርጋችሁ እግዚአብሔር ይመስገን በማለት አሳዝኑት፡፡ ዲያብሎስን ድል ማድረግ ስትሹ ይህን መሣርያ ዘወትር ያዙ፤ ምስጋና፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

@retua_haymanot
@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

16 Nov, 07:26


አዲስ የአእላፋት መርሙር ተለቀዋል!

መዝሙሮቹን በቴለግራም ለማጥናት JOIN በሉ!

@janyared

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

16 Nov, 06:05


https://www.youtube.com/live/HYiTwAUj328?si=6ZLcyl8bM5_4EZEP

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

15 Nov, 17:44


ለክብርሽ ተደርሶ፥ ለፍቅር የተቆመ፤
ሥሙር ማኅሌትሽ፥ በቸር ተፈጸመ፤
ድንግል እመቤቴ፦
የኛ መከራ ግን፥ አለቅጥ ረዘመ!

እንኳን አደረሰን!

(ዲያቆን ዮርዳኖስ አበበ )

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

10 Nov, 10:56


"እኔ እለምናለሁ አንቺ ጸሎቴን ታሳርጊያለሽ ልጅሽም ኃጢአቴን ያስተሠርያል። የልቤን ግዳጅ ይሰጠኛል። እኔ ቁስለኛ ነኝ አቺ የመድኃኒት ሙዳይ ነሽ። ልጅሽም ባለ መድኃኒት ነው፡፡"
አርጋኖ፣ ዘሐሙስ

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

09 Nov, 16:06


ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

(የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም)

@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

08 Nov, 16:18


ከቅምሻ የቀጠለ
(ከኤፌሶን ወንዝ ከዲያቆን ሄኖክ መጽሐፍ)
በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ

ወዳጄ ሆይ ሰውነትህ በአምላክ ደም የተገዛ ክቡር ሰውነት ነው። አካልህ "አንተ" እንጂ "ያንተ" አይደለም። "በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ" ይላል። ስለዚህ በከበረ የእግዚአብሔር ልጅ ደም የተገዛ ሰውነትህን ለሰይጣን በርካሽ አትሽጠው:: አትግደል የሚለው ሕግ ራስህንም ይጨምራል::

ቤተ መቅደስ የሆነ ሰውነትህን ለማፍረስ አታስብ። "ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ" ፩ኛ ቆሮ. ፫፥፲፯ ሰዎች አስቀይመውህ ይሆን? "አሳያቸዋለሁ፤ ስሞት የእኔን ነገር ይገባቸዋል" ብለህ በሰዎች ተቀይመህ ራስህን አትጉዳ። እመነኝ ብትሞት ሰዎች ከሳምንት በላይ አያስታውሱህም። ለሕይወትህ ዋጋ ያልሠጡ ሰዎች ለሞትህ ዋጋ አይሠጡም። ፈጥነውም ይረሱሃል። ለሚረሱህ ሰዎች ብለህ የማይረሳህን አምላክ አታሳዝን። ሰው ስለ አንተ ግድ የለውም እግዚአብሔር ግን የራስህን ጸጉር ሳይቀር በቁጥር ያውቀዋል። እንኳንስ ራስህን ልትጎዳ አንዲት ጸጉር እንኳን ከአንተ እንድትወድቅ አይፈልግም። እግዚአብሔርን በኃጢአት ብታሳዝነው እንኳን ኖረህ ንስሓ እንድትገባ እንጂ እንድትሞት አይፈልግም። አባትህ ነውና ከእርሱ ጋር ባትሆንም እንድትኖር ይፈልጋል።

በምሳሌ ልንገርህ፦ ሁለት ሴቶች አንድን ሕፃን "የኔ ልጄ ነው" ብለው እየተከራከሩ ጠቢቡ ሰሎሞን ፊት ቀረቡ። ጠቢቡ ሰሎሞን ሰይፍ አመጣና "ልጁን ቆርጬ ለሁለት ላካፍላችሁ" አላቸው። አንደኛዋ ሴት "እሺ እንካፈል" ስትል እውነተኛዋ እናት ግን "ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" አለች። እናት መሆንዋም በዚህ ታወቀ። (፩ኛ ቆሮ. ፫፥፩፮-፳፰)

ወዳጄ ያንተም ኑሮህ ከእግዚአብሔር ጋር ላይሆን ይችላል። ዓለም የራስዋ አድርጋህም ይሆናል። በሱስ ውስጥ ትዘፍቀህ፣ እንደ ሶምሶን በደሊላ እቅፍጀ፣ እንደ ዴማስ በተሰሎንቄ ውበት ተማርከህ ይሆናል። እግዚአብሔር ግን አባትህ ነውና ሞትህን አይፈልግም። "ልጄ ከሚሞት እርስዋ ትውሰደው" እንዳለችው እናት ፈጣሪህ ከነኃጢአትህም ቢሆን እንድትሞት አይፈልግም። ከእርሱ ጋር ባትኖርም መኖርህን ይፈልጋል። "የሟቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ" ሕዝ. ፲፰፥፴፪

የይሁዳ ኃጢአቱ ጌታውን መሸጡ አልነበረም። ራሱን መግደሉ ነው። እግዚአብሔር የሚያዝነው ከበደልህ በላይ በእርሱ ተስፋ ቆርጠህ ራስህን ስትጎዳ ነው።

ወዳጄ የአንተን መኖር የሚፈልጉ ብዙ ናቸው። ፈጣሪ ወደዚህች ዓለም ያለ ምክንያት አላመጣህም። በአንተ አለመኖርም የሚጎድል ነገር አለ። አንተን የሚመስል ሌላ ሰው አልፈጠረምና ለዚህ ዓለም አንተን የሚተካ የለም፣ በክብር ወደዚህ ዓለም ያመጣህ አምላክ በክብር ወደራሱ እስኪወስድህ ድረስ "በራስህ ላይ ክፉ ነገር አታድርግ"

"የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ፦ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ፡ ብሎ ጮኸ" ሐዋ. ፲፮፥፳፯-፳፰ ይህ ሰው እስረኛ ያመለጠ መስሎት ራሱን ሊያጠፋ ሲል ጳውሎስ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ" አለው።

ወዳጄ አንተስ ተስፋ የቆረጥኸው ምን ያመለጠ መስሎህ ነው? የትምህርት ዕድል ያመለጠህ መስሎህ ነው? ገና ሺህ የትምህርት ዕድሎች አሉህ። ዕድሜህ ያመለጠህ መስሎህ ነው? ነገ የሚጠብቁህ ብሩሕ ዘመናት እኮ ቁጭ ብለው አሉ? የሚረዳኝ ሰው የሚያስብልኝ ሰው አጥቼያለሁ? ብለህ ከሆነም ካልሰሙህ ጥቂቶች በላይ ልንሰማህ የምንሻ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ"

መከራ ጸናብኝ ኑሮ ጨለመብኝ የሀገሪቱ ሁኔታ ተስፋ አሳጣኝ ብለህ ይሆን? እኛስ አብረንህ አይደልንም? አብረን ከገባንበት ችግር አብረን ብንወጣ አይሻልም? ከአንተ በባሰ ሁኔታ የታሰርንና የተገረፍን ጳውሎሶችና ሲላሶች "ሁላችን በዚህ አለንና በራስህ ክፉ አታድርግ" ስንልህ ስማን። ይልቅ አንተም እንደ ወኅኒው ጠባቂ "እድን ዘንድ ምን ላድርግ ብለህ?" ነፍስህን የምታድንበትን መንገድ ወደ መቅደሱ ቀርበህ ጠይቅ።

ወዳጄ ይህንን ጽሑፍ ያነበብኸውም በሕይወት ስላለህ ነው። የአንተን ዓይን የሚጠብቁ ብዙ ጽሑፎች፣ የአንተን ጆሮ የሚፈልጉ ብዙ ድምፆች፣ የአንተን መሐረብ የሚፈልጉ ብዙ ዕንባዎች፣ የአንተን ሳቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀልዶች ... ገና ብዙ ብዙ አሉ። ስለዚህ ሰይጣንን አሳፍረው። እንዲህ በለው "ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልህ" ሚክ. ፯፥፰

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ - የኤፌሶን ወንዝ ገጽ 9-14)

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

06 Nov, 04:20


📚 ውዳሴ ማርያምን የደረሰው ሊቅ ስም ማን ይባላል



✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

03 Nov, 17:10


1⃣7⃣ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

03 Nov, 17:01


💁‍♂⛪️እርሶ በቴሌግራም የቱን ቢያገኙ ደስ ይሎታል⁉️

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

01 Nov, 12:50


እግዚአብሔር የሚጠላቸው ሰባት ነገሮች።

1 ትዕቢተኛ ዓይን
2 ሐሰተኛ ምላስ
3 ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ
4 ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ
5 ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር
6 በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር
7 በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።

መጽሐፈ ምሳሌ 6፡16-19

@retua_haymanot
@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

31 Oct, 05:48


አንድ ምድራዊ ንጉሥ "ጠላቱን ያልወደደ ሰው በሞት ይቀጣል" ብሎ አዋጅ ቢያውጅ ሁሉም ሰው በአካለ ሥጋ ላለመሞት ሲል ሕጉን ለመጠበቅ የሚፋጠን አይደለምን? ወዮ! ምድራውያን ነገሥታት በሥጋዊ ሞት እንዳይቀጡን ብለን ፈርተን የሚያወጡትን ሕግ ለመፈፀም የምንፋጠን ሆነን ሳለ፥ ለነገሥታት ንጉሥ ለእግዚአብሔር ሕግ አለመታዘዛችን እንደ ምን ያለ ወቀሳ ያመጣብን ይሆን?

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
@retua_haymanot
@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

26 Oct, 12:10


ራስህን ኃጥእ አድርግ!

‹‹በብዙ ሲጋደሉ እንደኖሩ የቅዱሳንን ታሪካቸውን ሰምተናል፡፡ ነቢይ ዕዝራ የዱር ዛፍ ፍሬ እየተመገበ ውሃም እየጠጣ በምድረ በዳ እየጾመ ኖረ፡፡ ነቢይ ኢሳይያስም የሜዳ ጎመን እየቆረጠ ከእርሱም እየተመገበ ውሃም እየጠጣ በተራራ እየጾመ ኖረ፡፡ እግዚአብሔር ስሙን ‹የበረሃ ኮከብ› ብሎ የጠራው የመነኰሳት በኩር የሆነ አባ እንጦንስና አባ መቃርስም በደረቅ ኅብስትና በውሃ ብቻ ሲጋደሉ ኖሩ፡፡ እኚህ ምድራዊያን ሲሆኑ ሰማያውያን ሆኑ፡፡ ነቢይ ኤልያስም በኅብስትና በውሃ ብቻ በምድረ በዳ ሲጋደል ኖረ፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ ግን ሰባት ዓመት ሙሉ ውሃ ሳይቀምስ ኖረ፡፡ ከመነነ በኋላ እስከሞተበት ዕለት ድረስ እህል የሚባል አልቀመሰም፡፡ እርሱ ግን ራሱን በእግዚአብሔር ፊት ዝቅ ያደርግና በትሕትናም ሆኖ ስለ ኃጢአቱ ሁልጊዜ ያለቅስ ነበር፡፡ ይህም የእግዚአብሔር ሰው አባ በግዑ ይህን ሁሉ የተጋደለ በራሱ ኃይል አይደለም፤ በእግዚአብሔር ኃይል ነው እንጂ፡፡ አንተም ወንድሜ ሆይ! ራስህን ዕወቅ፡፡ ምንም ተጋድሎን ብታደርግ ጾምኩ፣ ተራብኩ፣ ስለ እግዚአብሔርም ብዬ ራሴን አደከምኩ፣ እግዚአብሔርንም ስላገለገልኩ በሥራዬም እድናለሁ አትበል-መጨረሻህን አታውቅምና፡፡ አንተ ግን ስለ እግዚአብሔር ብለህ ራስህን ኃጥእ አድርግ ያን ጊዜ እግዚአብሔር ያጸድቅሃልና፡፡››

#ገድለ_አባ_በግዑ

@retua_haymanot
@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

25 Oct, 18:47


ኢየሱስ ክርስቶስ፡-

“ጨለማን ያሳደደው ብርሃን ዓለምን ሁሉ ያበራው ፋና የማይነዋወጥ መሰረትና የማይፈርስ ግንብ የማይሰበር መርከብና የማይሰረቅ ማህደር የለዘበ ቀንበርና የቀለለ ሽክም እርሱ ለአባቱ ኃይል ጥበቡም የሚሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

“ለሁሉ ያስባል፤ ሁሉንም ያጠግባል ለዕውራን ያዩ ዘንድ ብርሃንን ይሰጣቸዋል፡፡ የተዘጉ መስኮቶችን ይከፍታል ህሙማንን ይሰማቸዋል፡፡ የተደፈነችውን ጆሮ እንድትሰማ ያደርጋል፡፡ ከሰውነት የለምፅን ልብሶች ገፍፎ የስጋን መጎናፀፊያ ያለብሳል፡፡ የደረቀውን የእጅ ክንድ ያቀናል፣ የአንካሳውን እግር እንዲሄድ ያደርጋል ነፍስን ወደ ሕዋስዋ ይመልሳታል መንፈስንም በማደሪያዋ ያኖራታል፡፡ አለቆች ባሏቸው አጋንንት የእርያን መንጋ ያሰጥማል ከደከመችውም ሰውነት ደዌን ያርቃል፡፡

“ከክንፍህ የጽድቅ ፀሐይና የጥቅም ምንጭ የሚወጣ የጽድቅ ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንተ ጌትነትና ክብር ምስጋናም ይገባሃል ለዘላለሙ አሜን፡፡”

(ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ)

@retua_haymanot
@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

24 Oct, 06:46


"መጥፎ ቀን እና ጥሩ ቀን የሚባል ነገር የለም። ያለው ጸሎት አድርገህ የወጣህበት ቀን እና ጸሎት ሳታደርግ የወጣህበት ቀን ነው። ያልጸለይክባቸው ቀናት በክፉ ምኞትና የሥጋ ፍላጎት የተሞሉ ስለሆኑ ክፉ ቀናት ናቸው።"


#ቅዱስ_ቄርሎስ_ሣድሳዊ

@retua_haymanot
@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

17 Oct, 07:58


https://t.me/Orthodoxyy1

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

16 Oct, 17:10


በዚህ ምድር ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር ካልተዛመድን በሰማያት ልንዛመደው አንችልም፤ የመንግሥቱ ጣዕም ያለው በዚህ ነውና። ከእግዚአብሔር ጋር  ያለው ዝምድና እዚህ ምድር ላይ ይጀምራል። ይህም እንደ እግዚአብሔር እንደ ራሱ "ልጄ ሆይ ልብህን ስጠኝ።" ምሳ 23፥26 በሚለው ጥያቄ ይጀምራል። በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ልብን አንጽቶ በፍቅር ከሞላው በኋላ በዚያ ራሱን ያሳድራል። ወንጌል "የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናትና።"ሉቃ 17፥21 ብሎ እንደሚናገር ይህ የእግዚአብሔር መንግሥት ማረጋገጫ ይሆናል።

ስለዚህ የሰማያትን መንግሥት ከማግኝት በፊት ሰው በውስጡ ያለውን የእግዚአብሔርን መንግሥት ማግኝት መቻል አለበት። ይህ ይሁን እንጂ አንድ ሰው የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያገኝ የሚችለው እንዴት ነው? ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ኅብረት ሊያገኝ የሚችለውስ እንዴት ነው? ሁል ጊዜ ከእርሱ ጋር የሚሆነውስ እንዴት ነው? በዚህ ዙሪያ የምሰጣችሁ ምክር ምንጊዜም ቢሆን በእርሱ እንድትጠመዱ ሲሆን ይህም በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላለው ስለ እርሱ ሥራና ስለ ራሱ በማንበብ የሚከናወን ይሆናል።

ከቅዱሳኑ ጋር ስላለው ዝምድና ስለ ድንቅ ባሕርያቱና በማንኛዎቹም አጋጣሚዎች ውስጥ ስላለው ስለ እርሱ እጅ አንብቡ። በዚህ ጊዜ ልባችሁ በእርሱ ፍቅር ይንቀሳቀሳል። በማንኛውም ጊዜ ውስጥም ከእርሱ ጋር ይገናኝ ዘንድ ዝግጁ ነው ።

አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

@retua_haymanot
@retua_haymanot

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

09 Oct, 17:30


ገላትያ ፮ ፥ ፪ - ፲ ።

² ከናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ ።
³ አንዱ ምንም ሳይሆን ምንም የሆነ ቢመስለው ራሱን ያታልላልና።
⁴ ነገር ግን እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሥራ ይፈትን ፥ ከዚያም በኋላ ስለ ሌላው ሰው ያልሆነ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል ፤
⁵ እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና ።
⁶ ነገር ግን ቃሉን የሚማር ከሚያስተምረው ጋር መልካምን ነገር ሁሉ ይከፋፈል ።
⁷ አትሳቱ ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም ። ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳልና ፤
⁸ በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና ፥ በመንፈስ ግን የሚዘራው ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል ።
⁹ ባንዝልም በጊዜው እናጭዳለንና መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት ።
¹⁰ እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ ።

ሉቃስ ፰ ፥ ፳፪ - ፳፭ ።

²² ከዕለታቱም ባንዱ ርሱ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳ ገብቶ፦ ወደ ባሕር ማዶ እንሻገር አላቸው ፤ ተነሡም ።
²³ ሲሄዱም አንቀላፋ ። ዐውሎ ነፋስም በባሕር ላይ ወረደ ፥ ውኃውም ታንኳይቱን ይሞላ ነበርና ይጨነቁ ነበር ።
²⁴ ቀርበውም፦ አቤቱ ፥ አቤቱ ጠፋን እያሉ አስነሡት ። ርሱም ነቅቶ ነፋሱንና የውኃውን ማዕበል ገሠጻቸው ፤ ተዉም ፥ ጸጥታም ሆነ ።
²⁵ ርሱም፦ እምነታችሁ የት ነው? አላቸው ። ፈርተውም ተደነቁ ፥ ርስ በርሳቸውም፦ እንዲህ ነፋሳትንና ውኃን እንኳ የሚያዝ ለርሱም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው? አሉ ።

✞ርቱዓ ሃይማኖት✞

09 Oct, 13:05


ሰማዕት ቅድስት አርሴማ

መስከረም ሃያ ዘጠኝ በዚህች ቀን ከቅድስት አርሴማ ከእመምኔቷ ከአጋታ ጋር ደናግል በሰማዕትነት አረፉ። ይህም እንዲህ ነው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን እርሱ መልኳ ውብ የሆነ ብላቴና ድንግል ሊአገባ ሽቶ በየሀገሩ ሁሉ ሒደው መርጠው ያመጡለት ዘንድ አሽከሮቹን አዘዘ።

ይችንም የሚመስላት የሌለ ቅድስት አርሴማን በሮሜ አገር በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ አገኙዋት። ሥዕሏንም ሥለው ለንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ላኩለት ንጉሡም ሥዕሏን በአየ ጊዜ እጅግ ደስ አለውና ለሠርግ እንዲመጡ ወደ መኳንንቱ ላከ።

እሊያ ደናግልም ይህን ነገር በአወቁ ጊዜ ይረዳቸው ዘንድ ድንግልናቸውንም ይጠብቅ ዘንድ አልቅሰው ወደ እግዚአብሔር ለመኑ። ከዚህም በኋላ ተነሥተው በሥውር ሸሹ የንጉሥ ድርጣድስ ግዛት ወደ ሆነ ወደ አርማንያ ሀገርም ደርሰው በአንድ ቦታ ተቀመጡ ከእርሳቸውም ጋር የተሰደዱ ቁጥራቸው ሰባ አምስት የሆነ ወንዶች፣ ሴቶችም ሠላሳ ዘጠኝ የሆኑ ከእርሳቸው ጋራ አሉ። ምግባቸውን አያገኙም ነበርና በታላቅ ችግር ውስጥ ኖሩ ከእነርሱም መብራት የምትሠራ አንዲት ሴት ነበረች ከእርሷም የእጅ ሥራ ከሚገኘው በየጥቂቱ ይመገባሉ።

ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስም የከበረች አርሴማን በፈለጋት ጊዜ አላገኛትም ግን በአርማንያ አገር እንዳለች ስለርሷ ሰማ። ደግሞ ለአርማንያ ንጉሥ ለድርጣድስ ስለርሷ ከዲዮቅልጥያኖስ ሸሽታ እንደ መጣች የአርሴማን ሥራ ነገሩት እርሱም አንዱን የአርማንያ መኰንን ለእኔ ጠብቃት ወደ እኔም ላካት ብሎ አዘዘው።

ደናግሉም ይህን በሰሙ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ተሠወሩ ወደ ንጉሥም ወነጀሉአቸው ንጉሡም ቅዱስት አርሴማን በክብር አድርገው ያመጧት ዘንድ አዘዘ እርሷም ወደ እርሱ መምጣትን እምቢ በአለች ጊዜ እየጎተቱ ወስደው ወደርሱ አደረሷት።

የቅድስት አርሴማንም ላህይና ደም ግባቷን በአየ ጊዜ ድንግልናዋን ሊያረክስ ሽቶ እናቷ አጋታን አባብላ እሺ ታሰኝለት ዘንድ አዘዛት አጋታም ወደርሷ ሒዳ ልቧን አስጨከነች እንዲህም አለቻት። ዕወቂ ይህ ርኲስ አረሚ እንዳያረክስሽና ሰማያዊ ሙሽራሽን እንዳትተዪ እርሱም ክብር ይግባውና የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው ክርስቶስ ነው።

ንጉሡም ይዞ ወደ እልፍኙ ሊአስገባት ከአደባባይ መካከል ተነሥቶ ድንግል አርሴማን ያዛት። በዚያንም ጊዜ በቅድስት አርሴማ ላይ የእግዚአብሔር ኃይል አደረባትና በምድር ላይ ጣለችው እርሱ ግን በጦርነት እጅግ የጸና አርበኛ ስለ ነበር በታናሽ ሴት ብላቴና ስለተሸነፈ ያን ጊዜ አፈረ። ራሷንም በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘና ቆረጧት ከዚህም በኋላ ደናግሉን ሁሉ ከእናታቸው አጋታ ጋር ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ።

አንዲት የታመመች ድንግል ነበረች በዐልጋዋ ላይም እንደተኛች ወደ ወታደሮች ጮኸች መጥተውም እንደ እኅቶቿ ራሷን ቆረጡ ሁሉም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እነዚያንም ከሮሜ አገር አብረው የመጡ ወንዶችን ገደሏቸው ቁጥራቸውም ሰባ አምስት ናቸው ሥጋቸውም በተራራ ላይ የተጣለ ሁኖ ቀረ።

ሰማዕታትም ከተገደሉ በኋላ በንጉሡ ላይ ጋኔን ተጫነበት መልኩም ተለውጦ እንደ እርያ ሆነ። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ወደርሱ መጥቶ በላዩ ጸልዮ እስከ አዳነው ድረስ ስለዚህም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመነ። የቅዱሳን ሰማዕታትንም ሥጋቸውን ከተጣለበት ሰብስበው በአማረ ቦታ አኖሩአቸው ያማረች ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያንም ተሠራችላቸው። ከእነርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕት ቅድስት አርሴማ ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኅ_መስከረም)

@retua_haymanot
@retua_haymanot
@retua_haymanot