Doctor M nursing Home care @doctormhomecare Channel on Telegram

Doctor M nursing Home care

@doctormhomecare


በሙያቸዉ በተካኑ የጤና ባለሙያወች 24ሰአት ቤትወ ድረስ መጥተን የነርሲንግ አገልግሎት እንሰጣለን።
ይደውሉ
0920108524
0923284867

Doctor M nursing Home care (Amharic)

ዶክተር ኤም ቫርን አርቲስት በሙያቸዉ በተካኑ የጤና ባለሙያወች 24ሰአት ቤትወ ድረስ መጥተን የነርሲንግ አገልግሎት። የችሎት ሂደት እና ከቴክንክ መጠን ይገኛሉ። ለማጠናቀቅ አሳዛኝ ቁጥርዎን ላይ ይደወሉ።

Doctor M nursing Home care

31 Oct, 13:48


ጤናማ ያልሆነ የእርግዝና ምልክቶች

• የሚያስመልሰን ደም የቀላቀለ ከሆነ

• ከባድ የሆነ ማስመለስ ሁሌ ካለ ወይም በቀን ዉስጥ ብዙ ጊዜ ከተከሰተ

• ትኩሳት፣ የሆድ ህመም፣ ራስ ምታት ካለ

• ማስመለሱና ማቅለሽለሹ ከእርግዝና 20ኛ ሳምንት በኋላም ከቀጠለ

• ማስመለስና ማቅለሽለሹ ከእርግዝና ዘጠነኛ ሳምንት በኋላ ከሆነ የጀመረዉ

• ምግብ ተመግባችሁም ሆነ ዉሃ ጠጥታችሁ አልረጋ ብሎ የሚያስቸግራችሁ (በተለይም ክብደት መቀነስ ከጀመራችሁ)። ይሄ ሲፈጠር በሰዉነታችሁ ዉስጥ ያለዉ ፈሳሽ በጣም ቀንሶ የራሳችሁንም ሆነ የጽንሱን ጤና ሊያቃውስ ይችላል።

ማቅለሽለሽ ስሜቱ በጣም ከረበሻችሁ ሃኪማችሁን አማክራችሁ መድሃኒት መዉሰድ አማራጭ ሊሆን ይችላል።

ሌሎች እናንተ አድርጋችሁ የጠቀማችሁ መንገዶች ካሉ ከታች አስተያየታችሁን ስጡን። ሁሌም ጤንነታችሁን በሚመለከት ቀዳሚዉ እርግዝናችሁን የሚከታተለዉ ሃኪማችሁ ምክርና ህክምና መሆኑን አትዘንጉ!

ለተጨማሪ መረጃዎች
https://t.me/Doctormhomecare

Doctor M nursing Home care

25 Oct, 10:52


በአረጋውያን ላይ የሚከሠት የመገጣጠሚያ ህመም መቀነሻ 5 ፍቱን መፍትሄዎች

Osteoarthritis ( የመገጣጠሚያ ህመም) በአረጋውያን ላይ ከእድሜ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የአጥንት እና የመገጣጠሚያ በሽታ ነው። እድሜያችን እየገፋ ሲሄድ በመገጣጠሚያዎቻችን ላይ የሚገኘው cartilage መሣሣት ተከትሎ የመገጣጠሚያ ህመም, ጥንካሬ ማጣት እና የመንቀሳቀስ ችሎታ መቀነስ ይከሠታል ነገር ግን፣ መንስኤዎቹን በትክክል በመረዳት፣ ምልክቶችን ለይቶ ማወቅ እና ውጤታማ የህክምና ስልቶችን በመጠቀም፣ የአርትራይተስ በሽታ ያለባቸው አዛውንቶች የተሻለ የህይወት ጥራት ሊያገኙ ይችላሉ።
የ osteoarthritis መንስኤዎች:
1. እድሜ፡- ከእድሜ ጋር ተያይዞ በሚመጣ የ cartilage ጥንካሬ መቀነስ ምክንያት የመገጣጠሚያ ህመም የመጋለጥ እድል ይጨምራል።
2. ጀነቲክስ፡- አንዳንድ ግለሰቦች በተፈጥሮ ለአርትራይተስ በሽታ የመጋለጥ ከፍ ያለ እድል ሊኖራቸው ስለሚችል ለመገጣጠሚያዎች ህመም ይጋለጣሉ።
3. ጉዳት ወይም ከመጠን በላይ መጠቀም፡- ከዚህ ቀደም በመገጣጠሚያዎች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች፣ ተደጋጋሚ እንቅስቃሴዎች ወይም ከባድ እንቅስቃሴዎች
የ osteoarthritis ምልክቶች
1. የመገጣጠሚያ ህመም፡-ይህ በሽታ ያለባቸው አረጋውያን በተጎዳው መገጣጠሚያ (ዎች) ላይ ህመም ያጋጥማቸዋል ይህም በእንቅስቃሴ ወይም ክብደት በሚሰጡ እንቅስቃሴዎች ሊባባስ ይችላል።
2. ግትርነት( stiffness)፡ የመገጣጠሚያዎች እንደልብ አለመታዘዝ በተለይም ከስራ ውጪ ከሆኑ ጊዜያት በኋላ የ osteoarthritis የተለመደ ምልክት ነው።
3. የመንቀሳቀስ መቀነስ፡- በሽታው እየገፋ ሲሄድ አዛውንቶች በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸው ላይ ችግር ሊገጥማቸው ይችላል እና በተጎዳው መገጣጠሚያ (መገጣጠሚያዎች) ላይ የመንቀሳቀስ መጠን ይቀንሳል።
4. እብጠት፡- የመገጣጠሚያዎች እብጠት እና ህመም እና ምቾት ማጣት የተለመደ ነው።
የቤት ውስጥ የህመም መቀነሻ ስልቶች፡-
ለosteoarthritis በሽታ ሙሉ ፈውስ ገና ባይገኝም፣ የአረጋውያንን ምቾት እና እንቅስቃሴ በእጅጉ የሚያሻሽሉ በርካታ ውጤታማ የቤት ውስጥ ህመም አያያዝ ስልቶች አሉ። እነዚህም የሚከተሉትን ያካትታሉ:
1. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፡- እንደ መራመድ፣ መዋኘት እና ረጋ ያለ ሠውነትን የማፍታት እንቅሥቃሤ የመሳሰሉ ዝቅተኛ ተፅእኖ ያላቸውን ልምምዶች ላይ መሳተፍ የመገጣጠሚያዎችን እንቅሥቃሴ ለማሻሻል፣ ጡንቻዎችን ለማጠናከር እና ህመምን ለመቀነስ ይረዳል። አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ክብደትን በመቆጣጠርይረዳል ፣ በመገጣጠሚያዎች ላይ ያለውን ጫና ያስወግዳል።
2.የሙቀት እና የቀዝቃዛ ህክምና፡- ሙቀትን እንደ ሞቅ ያለ መጭመቂያ ወይም ማሞቂያ ፓድን መጠቀም ጡንቻዎችን ዘና ለማድረግ እና ጥንካሬን ለማስታገስ ይረዳል። የቀዝቃዛ ህክምና, በበረዶ የተሸፈነ ጨርቅ በመጠቀም, እብጠትን እና ህመምን መቀነስ ይቻላል.
3. ክብደትን መቆጣጠር፡- ጤናማ የሰውነት ክብደትን መጠበቅ በመገጣጠሚያዎች ላይ የሚደርሰውን ጫና ለመቀነስ ወሳኝ ነው። በፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ፕሮቲኖች እና ሙሉ እህሎች የበለፀገ አመጋገብ ክብደትን ለመቀነስ እና አጠቃላይ የጋራ ጤናን ያበረታታል።
4. አጋዥ መሳሪያዎች፡- እንደ መደገፊያ ከዘራ፣ መራመጃ ወይም ስፕሊንት ያሉ አጋዥ መሳሪያዎችን መጠቀም በተጎዱ መገጣጠሚያዎች ላይ ያለውን ጫና ለማቃለል ይረዳል
5. የህመም ማስታገሻ መድሀኒቶች፡- ፀረ-ብግነት መድሐኒቶች (NSAIDs)፣ እንደ ibuprofen፣ ህመምን ለመቆጣጠር ያገለግላሉ።

ለተጨማሪ መረጃዎች
https://t.me/Doctormhomecare

Doctor M nursing Home care

25 Oct, 07:59


ውድ የቻናላችን ተከታታዮች ለረጅም ጊዜ በስራ ምክንያት ጠፍተን የነበረ ቢሆንም አሁን በድጋሚ ተመልሰናል። ያላችሁን ማንኛውንም ጥያቄ ይጠይቁን ፤ እኛም ተከታታይ የጤና ትምህርቶችን ማቅረባችንን እንቀጥላለን።
🙏🙏🙏🙏

Doctor M nursing Home care

11 May, 18:05


ዘይትና የለውዝ ቅቤን ጨምሮ 91 የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስጠነቀቀ።
****
91 የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ይፋ መደረጋቸውን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን መረጃ መሰረት፣ በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ሳያሟሉ ተመርተው እየቀረቡ ያሉ ምርቶችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳስቧል።

የተከለከሉት በአጠቃላይ 91 የተለያዩ የምግብ ምርት ዓይነቶች መሆናቸውን ባለስልጣኑ አስታውቋል። 46 ዓይነት አይኦዳይዝድ ጨው፣ 27 ዓይነት የምግብ ዘይት፣ 10 ዓይነት ከረሜላ ፣5 ዓይነት አቼቶ 2 ዓይነት የለውዝ ቅቤ እና 1 የቫኔላ ፍሌቨር ምርቶችን እንደሚገኙበት ተገልጿል።

ባለስልጣን በገበያ ላይ ባደረገው ቁጥጥር የኢትዮጵያ አስገዳጅ ደረጃንና የገላጭ ጽሑፍ መስፈርቶች ስለማያሟሉ በተጨማሪም በቁጥጥር ወቅት የተገኙ ግኝቶች እንደሚያሳዩት ምርቶቹ በአብዛኛው በሚባል መልኩ የመጠቀሚያ ጊዜ፣ የአምራች ድርጅታቸው ስም፣ አስገዳጅ ደረጃ ምልክት፣ መለያ ቁጥርም ሆነ አድራሻቸው ምርቱ ላይ ያልተገለጸና የሌላቸው በመሆኑ የተነሳ ነዉ።

ምርቱ ሊይዛቸው የሚገቡ ንጥረ ነገሮች በውል ለማይታወቅ በተጨማሪም ከሚመለከታቸው የጤና ተቆጣጣሪ አካላት ፍቃድ የሌላቸው በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንዳያውላቸው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

ለጥንቃቄ የምርቱ ዓይነትና የተገኙትን ክፍተቶች ይፋ በማድረግ ህብረተሰቡ በትኩረት ተመልክቶ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጠይቋል።

የምርት ዓይነቶች እና ብራንድ ስማቸው

👉የምግብ ጨዉ
1. ሳባ የገበታ ጨው(Saba IODIZED Salt)
2. ንጋት የገበታ ጨው(Nigat IODIZED SALT)
3. አዲስ ብርሃን የገበታ ጨው ADDIS BERHAN IODIZED SALT
4. ሙና የገበታ ጨው(MUNA TABLE SALT)
5. ቤዝ የገበታ ጨው/BASE IODIZED SALT
6. ጉስቶ የገበታ ጨው/GUSTO IODIZED SALT
7. ማክ የገበታ ጨው/MAK IODIZED SALT
8. አባይ የገበታ ጨው/ABAY TABLE SALT
9. መስቱራ ባለ አዮዲን የተፈጨ ጨው MESTURA REFINED & IODIZED SALT
10. መነስ ጨው /MENES IODIZED SALT
11. ሙሉ የገበታ ጨው /Mulu Table Salt
12. ኢርኮ አዮዳይዝድ ጨው ERKO IODIZED SALT
13. አርዲ የገበታ ጨው/ARDI IODIZED SALT
14. ዘመን የገበታጨው/ZEMEN IODIZED SALT
15. ዘመን የገበታጨው/ZEMEN IODIZED SALT
16. ጨረቃ የገበታ ጨው/IODIZED SALT
17. ፋና የገበታጨው/Fana Table Salt
18. ዳናት የገበታጨው
19. ሶም የገበታጨው/som iodized salt
20. ጉግሳ በአዮዲን የበለፀገ የገበታጨው/GUGSA Iodised Salt
21. ሸጋ ጨው/SHEGA Iodized SALT
22. ፍዳክ የገበታ ጨው/FDAK IODIZED SALT
23. ኡሚ የገበታ ጨው/UMI IODIZED SALT
24. ጊዜ አዮዳይዝድ ጨው/GIZE IODIZED SALT
25. ባማክ የገበታ ጨው/bamak Iodized Salt
26. ማዚ የገበታ ጨዉ/MAZI IODIZED SALT
27. አዲስ የገበታ ጨዉ/ADDIS Iodized Salt
28. የገበታ ጨው/Iodized salt
29. TANA TABLE SALT/ጣና የገበታ ጨው
30. ጣና የገበታ ጨው
31. ማኢዳ የገበታ ጨው/MAEEDA IODIZED SALT
32. አሚን ጨው/Amin iodized salt
33. ሆም የገበታ ጨው/HOME IODIZED SALT
34. ጂኤም የገበታ ጨው/GM IODIZED SALT
35. ገዳ አዮዳይዝድ የታጠበ የገበታ ጨው/ GEDA IODIZED SALT
36. ዛማ አዮዳይዝድ የታጠበ ባለ አዮዲን ጨው /ZAMA SALT
37. ሶሲ የአዮዲን ጨው/Sosi Iodized Salt
38. ብቁ የገበታ ጨው/Biku iodized salt
39. H.T.F TABLE SALT /ኤች.ቲ.ኤፍ
40. AFRAN Iodized Salt
41. ኤምሬት ጨው/Emirate IODIZED SALT
42. ስፔሻል የገበታ ጨው/Special Iodized Salt
43. ሊያ የገበታ ጨው/ LIYA IODIZED SALT
44. አፊ ጨው/AFI IODIZED SALT
45. ዩስራ ጨው/ YUSERA SALT
46. ቡዜ የገበታጨው/BUZE IODIZED SALT

👉የምግብ ዘይት
1. ነጃ ንጹህ የምግብ ዘይት/ NEJA Pure Edible Oil
2. ረና ንጹህ የምግብ ዘይት/ Rina Edible Pure Food Oil
3. የኛ ንጹህ የምግብ ዘይት/Yegna Pure Edible Oil
4. ኑራ ንጹህ የምግብ ዘይት /Nura Pure Edible oil
5. ሕይወት ንጹህ የምግብ ዘይት /HIWOT Edible Cooking Oil
6. ሚድ ንጹህ የምግብ ዘይት /MID Pure Edible Oil
7. ጉና ንጹህ የኑግ የምግብ ዘይት/GUNA Pure Niger Edible Oil
8. አዲስ ንጹህ የምግብ ዘይት
9. ኑር ንጹህ የምግብ ዘይት/Nur Pure Edible Oil
10. ኑራ ንጹህ የምግብ ዘይት/NuraPure Edible Oil
11. ሶፊ ንጹህ የምግብ ዘይት/Sofi Pure Edible Oil
12. ደሴት ንጹህ የምግብ ዘይት/Deset Pure Food Oil
13. HADI COOKING OIL
14. Arif cooking oil
15. ሰነዓ ንፁህ የምግብ ዘይት /Senea pure food oil
16. ቃል ንፁህ የምግብ ዘይት/Kale Pure Food Oil
17. ናዲ የተጣራ ንጹህ የምግብ ዘይት/ Nadi pure food oil
18. ሰላም ንፁህ የምግብ ዘይት/Selam pure food oil
19. ኑኑ ንፁህ የምግብ ዘይት /Nunu pure food oil
20. MIFTAH pure food oil
21. ቤላ የተጣራ የኑግ ዘይት/BELLA Pure Niger Oil
22. ጣዝማ ንፁህ የምግብ ዘይት
23. ሚና ንፁህ የምግብ ዘይት
24. ብሌን ንፁህ የምግብ ዘይት/Blen Pure Edible Oil
25. ደስታ የተጣራ የኑግ ዘይት
26. ሐዲ የተጣራ የምግብ ዘይት
27. ሳራ የኑግ የምግብ ዘይት/Sara Niger Oil

👉የከረሜላ ምርቶች
1. ማሂ ከረሜላ/Mahi candy
2. ኢላላ ጣፋጭ ከረሜላ/Elaala sweet candy
3. ፋፊ ሎሊፖፕ/Fafi lolipop
4. ኢላላ ሎሊፖፕ ቢግ ጃር/Elaala lolypop big jar
5. ኮከብ ከረሚላ/KOKEB candy
6. ከረሜላ
7. ከረሜላ
8. ኤም ቲ ሎሊፖፕ/MT Loliipop
9. ኤ.ኤ ከረሚላ/A.A candy
10. ምንም ገለጭ ፁሑፍ የሌለው ከረሜላ

👉የአቼቶ ምርቶች
1. ሮያል አቼቶ/Royal VINEGAR
2. ዋልታ አቼቶ
3. ሮያል አቼቶ/ROYAL Vinegar
4. ሌመን አቼቶ/LEMEN ACETO
5. ሸገር አቼቶ/SHEGER ACETO

👉የለዉዝ ቅቤ
1. በእምነት ኦቾሎኒ ቅቤ/BEMNET PEANUT BUTTER
2. ናይስ/Nice peanut butter

👉የቫኔላ ፍሌቨር
1. ምንም ገላጭ ጽሑፍ የሌለው የቫኔላ ፍሌቨር መሆናቸውን ባለስልጣኑ አሳውቋል።

Doctor M nursing Home care

27 Apr, 11:08


Welcome everyone, you are free to ask any questions!!

Doctor M nursing Home care

18 Apr, 04:50


Share this channel to others,
ይህንን ቻናል ለሌሎች ያጋሩ፤ የሚፈልጉትን ይጠይቁ

https://t.me/Doctormhomecare

Doctor M nursing Home care

18 Apr, 04:49


አልማዝ ባለጭራ/ ስለ አልማዝ ባለጭራ ምን ያውቃሉ?
በግማሽ የሰውነት ክፍል ላይ በድንገት የሚወጣ ሽፍታ ሲሆን ብዙዉን ጊዜ ሽፍታው መስመር ይዞ ውኃ ቋጥሮ በጣም የሚያም ነው፡፡ በየትኛዉም የሰዉነት ክፍል ላይ ሊወጣ ይችላል አብዛኛውን ጊዜ ግን በጀርባ፣ በማጅራት፣ በደረት ወይም በፊት ላይ ይወጣል።
በአገራችን አባባሉ ሳይንሳዊ መሰረት ባይኖረውም አልማዝ ባለጭራ እየተባለ ይጠራል። የአልማዝ ባለጭራ በሽታ ዋና መንስኤ ጉድፍን የሚያስከትለው ቫሪሴላ ዞስተር ቫይረስ (Varicella Zoster Virus) ነው ፡፡ ህመሙ ምንም እንኳን ለህልፈተ ህይወት ባይዳርግም ከፍተኛ ስቃይ/ህመም ሊያመጣ ይችላል።
የህመሙ ምልክቶች
※ ብዙዉን ጊዜ በአንዱ የሰዉነት ክፍል በኩል/በቀኝ ወይም በግራ በኩል/የሚታይ ነው።
※ የማቃጠል፣ ማሳከክ
※ የመደንዘዝ ወይም መጠቅጠቅ ህመም
※ የጡንቻ ህመም (ድካም)
※ ህመሙ ከተከሰተ ከጢቂት ቀናት በኃላ ቀይ ሽፍታ መከሰት/ መጀመር
※ ትኩሳት
※ የራስ ምታት የመሳሰሉት ናቸው።
ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች
※ ከዚህ በፊት ጉድፍ የነበረባቸውን ሰዎች
※ የተወሰኑ የህመም አይነቶች እንደ ካንሰር፣ ኤች አይቪ፣ ስኳርና ሌሎች የሰዉነትን የበሽታ መከላከል አቅም የሚቀንሱ ህመሞች ካሉ
※ ዕድሜያቸው 50 ዓመትና ከዚያ በላይ ሲሆን
መወሰድ ያለባቸው መፍትሄዎች
ወደ ቆዳና አባለዘር ሐኪም መሄድ
ሕክምናው ከሐኪም ጋር በመነጋገር የሚካሄድ ሲሆን የተለያዩ አማራጮች ያሉት ነው፤ የአልማዝ ባለጭራ (ኸርፐስ) በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት እንደመሆኑ ጨርሶ ከሰዉነት ዉስጥ የሚያስወጣ መድሃኒት የለም ቢሆንም አንዳንድ ሁኔታውን ለማቅለል የሚታዘዙ የፀረ ቫይረስ መድኃኒቶች አሉ።
በአፍም እና በሚቀባ መልክ የሚወሰዱ መድኃኒቶች ቁስሉ ወዲያው እንደጀመረ ቶሎ መውሰድ አለባቸው፤ በፍጥነት ለማገገም ይረዳሉ።
በተጨማሪም፦ ህመምና ሽፍታ በአይን ዙሪያ ከወጣ ይህ አይነት ኢንፌክሽን ካልታከመ የማይመለስ ጉዳት በአይን ላይ ሊያመጣ ይችላል።
መልካም ጤንነት!!

ለተጨማሪ መረጃዎች
https://t.me/Doctormhomecare

Doctor M nursing Home care

17 Apr, 05:05


ሰላም የቻናላችን ተከታታዮች ይሄንን ቻናል ሼር በማድረግ ብዙ ሰዎች እንዲቀላቀሉና ጤናቸውን በተመለከተ ብዙ እንዲያውቊ ያድርጉ !

https://t.me/Doctormhomecare

Doctor M nursing Home care

16 Apr, 16:48


መሃንነት(ልጅ መውለድ አለመቻል)

መሃንነት ምንድነው?

ባልና ሚስት በወር ውስጥ ለተወሰኑ ቀናት ግንኙነት እያደረጉ ለአንድ አመት ከቆዩና በዚህ ግዜ ውስጥ እርግዝና ካልተፈጠረ መሃንነት ይባላል። ይህ ግን በአመቱ ውስጥ ምንም አይነት የወሊድ መቆጣጠሪያ ሳይጠቀሙ መሆን ይኖርበታል። የሴቷ እድሜ ከ35 ዓመት በላይ ከሆነና በስድስት ወር ውስጥ እርግዝና ካልተፈጠረ የሐኪም እርደዳታ ማግኘት አስፈላጊ ነው።

መሃንነት የሚለው ቃል ጭራሽኑ ማርገዝ አለመቻል ወይም አንዴ ካረገዙ በኋላ መድገም አለመቻልን(secondary infertility) የሚያመለክት ይሆናል።

ብዙውን ጊዜ ባለመውለዳቸው የሚኮነኑት ሴቶች ቢሆኑም ምክንያቱ ግን በወንዱ ፣ በሴቷ፣ ወይም በሁለቱም በኩል ባለ የመሃንነት ችግር ሊሆን ይችላል። አልፎ አልፎም አስፈላጊ ምርመራ ተደርጎ የመሃንነቱን መንስኤ ማግኘት የማይቻልበት ሁኔታ (unexplained infertility) ይኖራል።

ለሴቶች መሃንነት መንስኤዎች ምንድናቸው?

ዋና ዋና መንስኤዎች የሚከተሉት ናቸዉ ።

1. እንቁላሎችን ወደ ማህጸን የሚያስተላልፉ ትቦዎች ወይም ማህጸኑ በጠባሳነት መጎዳት

የቱቦወቹ መጎዳት የወንዱ ስፐርም ወደ እንቁላል እንዳይደርስ እክል ይፈጥራል። ጠባሳዎቹ ምንም አይነት የህመም ምልክት ሳይሰጡ መሃንነትን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ጠባሳዎቹ የሚፈጠሩበት ምክኒያቶች

. በአግባቡ ሕክምና ያልተደረገለት የአባለዘር በሽታ በማህጸን ትቦዎች ጠባሳን ሲያስከትል፣

. በውርጃ ወይም በወሊድ ጊዜ የሚከሰቱ የኢንፌክሽን በሽታዎች በማህጸኑ/ በማህጸን ቱቦዎች ላይ ጠባሳ ስያስከትሉ፣

2. እንቁላል የማዘጋጀት ችግር

ለዚህ ምክንያቱ የሚፈለጉት ሆርመኖች በበቂ ሁኔታ ስለማይኖሩ ሊሆን ይችላል። የወር አበባ ከ21 ቀናት ወዲህ ወይም ከ35 ቀናት ወዲያ የሚመጣ ከሆነ ይህ ችግር ሊኖር ይችላል ። አልፎ አልፎም በጣም መወፈር ወይም በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ኪሎ መቀነስ የእንቁላል ማዘጋጀት ሊያስተጓጉል ይችላል

3. የማህጸን እጢ

4. እንደ ስኳር በሽታ ፣ ሳንባ ነቀርሳ ያሉ በሽታዎችም መሃንነት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ለወንዶች መሃንነት መንስኤዎች ምንድን ናቸዉ?

ዋና ዋና መንስኤዎች እነዚህ ናቸው

1. ሰውነታቸው የሚያመርተው ስፐርም ቁጥር በቂ አለመሆን፣ ወይም የተሰሩት ስፐርሞች ቀልጣፋነት ማነስ።

2. በተለያዩ ምክንያቶች(ኢንፈክሽ ፣ ጨረር፣ወዘተ) ስፐርም የሚያፈልቁ ፍሬዎች ሲጎዱ። በዚህም ምክኒያት ምንም እንኳን በወሲብ ጊዜ ማፍሰስ ቢችሉም ፣ የወንዴ ፈሳሽ ውስጥ ስፐርም አይኖርም ። በመሆኑም ማስረገዝ አይችሉም ።

3. ስፐርም ከብልታቸው መፍሰስ አይችልም። የዚህ ምክኒያት በአባላዘር በሽታዎች የፈሳሹን መተላለፊያ ቱቦዎች በመጎዳት ሊሆን ይችላል።

4. ቫሪኮሰል

5. ስንፈተ ወሲብ

6. የተለያዩ የውስጥ ደዌዎች

የመሃንነት ምርመራ ምን ምን ያጠቃልላል?

ከአንድ አመት በቂ የወሲብ ግንኙነት በኋላ እርግዝና ካልተፈጠረ የጤና ባለሙያ ያማክሩ።

የሚከተሉት ምርመራዎች የመሃንነት ችግር ባላቸው ላይ ሊካሄዱ ይችላሉ።

. የሴቷም ሆነ የወንዱ የተሟላ የጤና መረጃ እንዲሁም አካላዊ ምርመራ

. የወንዴ ፈሳሽ(ሲመን) ምርመራ

. የማህጸን ንፋጭ ምርመራ

. ከወንዱ ቆለጦች ፈሳሽ ናሙና (ኤፍ.ኣን.ኤ ሳይቶሎጂ) ምርመራ

. በደም ውስጥ ያሉ የሆርሞኖች ምርመራ

. የማህጸን ራጂ(ሂስተሮሳልፒንጎግራፊ)

. ላፓራስኮፒ(የሆድ እቃ በካሜራ ምርመራ)

እንዱሁም እንደሁኔታው ሌሎች ምርመራዎች ሊደረጉ ይችላሉ።

የመሃንነት ህክምናው ምንድን ነው?

ህክምናው እንደ ምሃንነቱ መንስኤ የሚለያይ ሲሆን

. ምክር አዘል ትምህርት

. የዘር ፍሬ አመራረት እጋዥ መድሃኒቶች

. ኢንትራ ዩተራይን ኢንሰሚነሽን(የወንዴዘር ፈሳሽ ወስዶ በቀጥታ በሴቷ ማህጸን ውስጥ ማስቀመጥ )

. እንዲሁም እጅግ የተራቀቀውን ከማህጽን ውጪ ጽንሰትን(ኢንቪትሮ ፈርትላይዘሽን) እስከ መጠቀም ይደርሳል።

ከህክምናው በኋላ የማርገዝ እድሉ ምን ይመስላል?

ከ80-90% የሚሆኑ የታካሚዎች ላይ የመሃንነታቸው መንስኤ ሊታወቅ ይችላል። ተገቢውን ህክምና ከሚያደርጉ መሃኖች ውስጥ ከ50-60% ማርግዝ እንደሚችሉ ጥናቶች ያሳያሉ። ከ15-20% ያህል ደግሞ ያለምንም የህክምና በጊዜ ሂደት ማርገዝ የሚችሉበት አጋጣሚ አለ።

ጉዳቶቹስ?

መሃንነት የሚያስከትለው እፕካላዊ ጉዳት ባይኖርም የስነልቦናዊ ጉዳቱ ግን ከፍተኛ ሊሆን ይችላል። በጥንዶቹ ትዳር ላይ ችግር ሊያጋጥም ፣ ግለሰቦቹም ለጭንቀትና ውጥረት ሊዳረጉ ይችላሉ።

መሃንነት እንዴት መከላከል ይችላል?

መሃንነት እብዛኛውን ጊዜ በአባላዘር በሽታዎች(ጨብጥና ክላሚድያ ተጠቃሽ ናቸዉ ) ጥቃት የሚመጣ በመሆኑ ከልቅ ወሲብ መቆጠብ አንዱ የመከላከያ ዘዴ ነው።

ለተጨማሪ መረጃዎች
https://t.me/Doctormhomecare

Doctor M nursing Home care

15 Apr, 18:58


✍️ የሆድ መነፋት
አየር ሰውነት ምግብን አድቅቆ ወደኃይልነት ሲለውጠው በጨጓራና በትንሹ አንጅት ውስጥ የሚፈጠር ነው። የሆድ መነፋት የሚፈጠረው አየር (gas) በሆድ ክፍላችን ውስጥ ከመጠን በላይ ሲሆን እና ሆዳችንን ሲወጥረው ነው ። ማጋሳት ወይም አየር በአፍ ማስወጣት እና ፈስ (ጋዝ) ዋነኛ የአየር ማስወጫ መንገዶች ናቸው ።

መንስኤዎቹ

🔹አየር መዋናነት ከምግብ በኋላ ለሚፈጠር የሆድ መነፋት ምክንያት ነው ። ሁሉም ሰው በሚመገብበት ወቅት ወይም በሚጠጣበት ጊዜ አየርን ያስገባልነገር ግን አንዳንድ ሰው ደግሞ ከሚጠበቀው በላይ ያስገባል ። ለምሳሌ ምግብና መጠጥጥ በፍጥነት መመገብ እና መጠጣት ፣ ማስቲካ ማኘክ ፣ሲጋራ ማጤስ ..
🔹 የሆድ ድርቀት
🔹 ሌላው ምክንያት ደግሞ የሆድ ክፍላችን ውስጥ የአየር ዝውውር አነስተኛ ሲሆን ነው ።
🔹 በተጨማሪም የአንጀት አካባቢ በሽታዎች
🔹 የጨጓራ በሽታ
🔹 የምግብ አለመስማማት
🔹 ከመጠን በላይ ውፍረት
🔹 የሆድ ውስጥ ትላትሎች ሲኖሩ
🔹 አእምሮአዊ ችግሮች( ጭንቀት ፣ ስጋት ፣ መደበት . . . )

ምልክቶቹ

🔹 የሆድ መነፋት አብረውት እንደ ሆድ ህመም
🔹 ተደጋጋሚ ማስፈሳት (ጋዝ ማስወጣት)
🔹 ምቾት የማይሰጥ ጥጋብ፥
🔹 ግሳት
🔹 ሆድ መጮህ የመሳሰሉት ….

መከላከያው

🔹 በቂ ውሃ መጠጣት (በይበልጥ ጠዋት በባዶ ሆድ )
🔹 ጨው የበዛባቸውን ምግቦች መቀነስ
🔹 ጋዝ ያላቸውን መጠጦች መቀነስ( እንደለስላሳ መጠጦች )
🔹 የሰውነት ክብደትን የተመጣጠነ ማድረግ
🔹 በፍጥነት አለመመገብ
🔹 አብዝቶ ማስቲካን አለማኘክ ( ጋዝ ከመጠን በላይ ወደ ሆድ ስለሚያስገባ)
🔹 አብዝቶ በእስትሮ አለመጠጣት
🔹 ሆድን ማሳስጅ ማድረግ በቂ የደም ዝውውር እንዲኖር


➷ የሆድ መነፋት ምቾትን በመንሳት የእለት ተዕለት ውሏችንን እንዳይረብሽ በቶሎ ባለሙያ ማማከር እና መፍትሄ ላይ መድረስ ይመከራል።

ለተጨማሪ መረጃዎች
https://t.me/Doctormhomecare

Doctor M nursing Home care

15 Apr, 09:57


#የማህፀን_እባጭ
(Uterine Myoma) እና
#እርግዝና

#የማህፀን_እባጭ(#Myoma/fibrinoids) ከማህፀን ጡንቻ የሚነሱ ከፍተኛ ችግር የማያስከትሉ የማህፀን ላይ እባጮች ወይም እጢዎች ናቸው።
ባብዛኛው ምልክት የለሽ ሲሆን በድንገት ለሌላ ጉዳይ አልትራሳውንድ ወይም ሲቲ ስካን ሲነሳ ሊታይ ይችላሉ።

የማህፀን እባጭ ከእርግዝና በፊት መጠኑ የበዛ ከሆነና ቱቦች ከዘጋ እርግዝና ይከለክላል። ይህም ሲባል ከመቶ እባጭ ካላቸው እናቶች ከ1-2 በመቶ ብቻ የሚሆኑት እንደምክንያት ሊነሳ ይችላል።

የማህፀን የውስጥ ግርግዳ ላይ የወጣ እባጭ ደግሞ ተደጋጋሚ ውርጃን (#RPL) በማምጣት ይታወቃል። ይህም የሚሆነው የማህፀን ግረግዳ እንዲኮማተር እና የፅንሰት መጣበቅ(#implantation) እንዳይኖር ያደርጋል።

መጠኑ ትላልቅ እና ብዛት ያለው የማህፀን እባጭ በእርግዝና ወቅት የሚከተሉት ውስብስብ ችግሮች ሊያስከትል ይችላል።
1. የእባጭ ጠባይ መቀየር(#red degeneration):
እርግዝናው እያደገ ሲመጣ ማህፀን እና እባጩ እያደጉ ይሄዳሉ። በዚህም ወደ እባጩ የሚሄደው የደም ዝውውር በቂ ካለመሆን የተነሳ ዕጢው ላይ ከፍተኛ ጫና በመፍጠር ህመምን ያስከትላል።
2. የፅንስ ያቀማመጥ ችግር ያስከትላል፡ ፅንሱ እንደልቡ እንዳይንቀሳቀስ በማገድ ትክክለኛ ያልሆነ አቀማመጥ(#malpresentation) እና አመጣጥ(#malposition) እንዲኖረው ያደርጋል።
3. የፅንስ እድገት መስተጓጎል(#IuGR)ያስከትላል
3.የማህፀን በር መዝጋት ያመጣል(#Tumor previa)፡ እባጩ የታችኛው የማህጨፀን ክፍል የያዘ ከሆነ የማህፀን በር በመዝጋት ለኦፕራሲዮን(#cs) ያጋልጣል።
4.የምጥ መርዘም(# prolonged labor)ያስከትላል: የማህፀን ጡንቻዎች በሚፈለገው መጠነ ቁርጠት የማምጣት አቅም በመቀነስ ለረዘመ ምጥ ምክነያት ሊሆን ይችላል።
5. ከወሊድ በኋላ ለከፍተኛ ደም መፍሰስ(#PPH) ያጋልጣል።

ለተጨማሪ መረጃዎች

https://t.me/Doctormhomecare

Doctor M nursing Home care

14 Apr, 18:27


#ሄፓታይተስ_ቢ (#HEPATITIS_B)

ተላላፊ የሆነ በ ሄፓታይተስ ቢ ቫይረስ አማካይነት የሚከሰት በሽታ ነው። በጊዜ ሂደት ውስጥ ከባድ የሆነ የጤና ችግር ሊያስከትል ይችላል። ቫይረሱ አንዳንድ ሰዎችን በጣም ሊያሳምማቸው ይችላል። ይህ በሽታ በአብዛኛው የአለማችን ክፍሎች ኢትዮጵያንም ጨምሮ ይገኛል።

🏥 #እንዴት_ይተላለፋል?
ሰዎች ቫይረሱ ከተሸከመ ሰው ደም ጋር ሲነካኩ ሄፓይተስ ቢ ይይዛቸዋል። ሄፓታይተስ ቢ ከተያዘች እናት ወደ ልጇ በወሊድ ወቅት ሊተላለፍ ይችላል። ቫይረሱ ካለበት ሰው ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት በማድረግም ሊተላለፍ ይችላል።

🏥 ብዙ ሰዎች ሄፓታይተስ ቢ እያለባቸው ለብዙ አመታት ህመም ሳይሰማቸው ሊኖሩ ይችላሉ። በጊዜ ሂደት ውስጥ ለጉበት መበላሸት፧ ለጉበት ስራ ማቆም እና ለጉበት ካንሰር ሊዳርግ ይችላል።

    💊 ሰዎች ሄፓታይተስ ቢ እንዳለባቸው እንዴት ያውቃሉ?
  
      ብቸኛ መንገድ የደም ምርመራ ሲያደርጉ ነው።   ይህ ከእጅ ላይ ደም በመውሰድ የሚደረገ ቀላል ምርመራ ነው። አንድ ነብሰጡር አናት በእርግዝና ወቅት ምርመራ ማድረገ ግድ ይላታል።

      💊 ሰዎች ሄፓታይተስ ቢ እንዳለባቸው ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።  ሄፓታይተስ ቢ እንዳለባቸው የሚያውቁ ሰዎች ቫይረሱ ወደ ሌላ ሰው አንዳይተላለፍ እርምጃዎችን መውሰድ ይችላሉ፣ ማለትም ኮንዶምን መጠቀም። ዋንኛው የመከላከል መንገድ ክትባት መውሰድ ነው። ሄፓታይተስ ቢ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ እናቶች በእርግዝና ወቅት ወደ ጤና ተቋማት በማቅናት የእርግዝና ክትትል እንዲያደርጉ ማድረግ እና ስለ በሽታው ግንዛቤ መፍጠር ያስፈልጋል። ሆፓታይተስ ቢ ቫይረስ ካለባት የተወለደ ህፃን በተወለደ በ12 ሰዓት ውስጥ መከተብ እለበት።

ለተጨማሪ መረጃዎች

https://t.me/Doctormhomecare

Doctor M nursing Home care

13 Apr, 10:25


#ሾተላይ (RH-Incompatablitiy) ምንድን ነው?

ሾተላይ በመባል የሚታወቀው ክስተት ብዙ ጊዜ አንዲት እናት ከመጀመሪያ እርግዝናዋ በኃላ በተደጋጋሚ የሚከሰት የጽንሱ መጥፋት ነው።

👉 ይህ ለምን ይሆናል?

የሰዎች ደም በአራት መደብ ይከፈላል(A, B, AB, O) እነዚህ ደግሞ እያንዳንዳቸው በሁለት አበይት መደብ ይከፈላሉ፡ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) እና አር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-)። ለምሳሌ፦ የአንድ ሰው የደም ዓይነት A+ ወይም A- ሊሆን ይችላል። የሰው ማንነቱ ከእናቱና ከአባቱ በሚወስደው የዘር-መል ይወሰናል። የደም ዓይነትም በዚሁ መልክ እንወስዳለን። ከአር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) አባት እና ከአር ኤች ኔጋቲቭ(Rh-) እናት የሚፈጠር ጽንስ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የመሆን እድሉ የሰፋ ነው።

ሾተላይ የሚከሰተው አንዲት ሴት የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ሆኖ ከዚህ በፊት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) የሆነ ደም ወደ ሰውነቷ ሲገባ ደሟ ውስጥ አር ኤች ፖዘቲቭ(Rh +) የሆኑ የደም ህዋሶችን የሚያጠፋ ንጥረ-ነገር በደሟ ውስጥ ይመረታል። ይህ ንጥረ-ነገር አንዴ ከተመረተ በደሟ ውስጥ እስከ ህይወቷ ፍጻሜ ድረስ ይኖራል።

በመሆኑም በማህጸንዋ ውስጥ የያዘችው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ የተመረተው ንጥረ-ነገር ጽንሱን እንደ ባእድ አካል ስለሚቆጥረው ያጠቃዋል። በዚህም ምክንያት በተደጋጋሚ የምትይዘው ጽንስ የደም ዓይነቱ አር ኤች ፖዘቲቭ ከሆነ አስፈላጊውን ህክምና ካልተደረገላት ይሞትባታል። የደም ዓይነቱ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) ከሆነ ግን በጤና ይወለዳል። ይህ እንዲሆን ግን
የአባትየው የደም ዓይንት አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) መሆን አለበት?

👉 ሕክምናው

የደም ዓይነቷ አር ኤች ኔጋቲቭ (Rh-) የሆነች እናት ሕክምናዋ በሆስፒታል ውስጥ መሆን አለበት።

በደሟ ውስት ያለውን የንጥረ-ነገር መጠን መለካትና የጽነሷን የጉዳት መጠን በማየት ብዙ ሳይጎዳ እንዲወለድ ማድረግ።

በሀገራችን በቅርቡ የተጀመረው ጽንሱ በማህጸን ውስጥ እያለ ደም በመለገስ እንዲያድግና እንዲወለድ ማስቻል።

👉 እንዴት እንከላከለው?

ማንኛዋም ሴት ከማርገዟ ወይም ማንኛውንም ደም ከመውሰዷ በፊት የደም ዓይነቷን ማወቅ አለባት።

የወንድ አጋሯን የደም ዓይነት ማወቅ አለባት።

እርግዝና አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ አጋሯ ከተፈጠረ መጀመሪያ በሚደረግላት ምርመራ (indirect coomb’s test) ንጥረ-ነገሩ አለመመረቱን ያረጋግጣል። እዳይመረት የሚከላከል መድኃኒት (Anti-D) 7ተኛ ወሯ ላይ ይሰጣታል። ከወለደች በኃላ የልጇ የደም ዓይነት አር ኤች ፖዘቲቭ( Rh +) ከሆነ በድጋሚ መድኃኒቱ ይሰጣታል።

እርግዝናው ከማህጸን ውጭ ወይም በውርጃ ቢያበቃም መከላከያውን መድኃኒት መውሰድ አለባት።


ለተጨማሪ መረጃዎች

https://t.me/Doctormhomecare

Doctor M nursing Home care

12 Apr, 05:07


ቂጥኝ  (syphilis) ምንድነው ?

ቂጥኝ እንደ ጨብጥ በጾታዊ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ ሲሆን በሽታው ካለበት ሰው ጋር በቀጥታ ንክኪ እንዲሁም ከእናት ወደ ጽንስም ይተላለፋል።

የበሽታው የመጀመሪያው ምልክት በብልትና በብልት አካባቢ አነስ ያለና የማያም ቁስል ሲሆን በአብዛኛው ይህ ምልክት የህመም ስሜት ስለሌለው በቸልታ ሊታለፍ ይችላል። ይህ ምልክት በራሱ ጊዜ ከጠፋ ከጥቂት ሳምንት በኋላ በተዋልዶ አካላት ላይ የንፊፊት ማበጥ፣ የሚያሳክክ የሰውነት መንደብደብ በተለይ በእጅ፣ መዳፍ እና በውስጥ እግር ላይ፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታት፣ የአጥንትና የጡንቻ ህመም ያስከትላል።

ከዚህ በኋላ በሽታው ለረዥም ጊዜ በሰውነት ውስጥ በመሰወር ዋና ዋና የሰውነት አካላትን ለምሳሌ እንደ ልብ፣ አንጎል፣…. ያሉትን በማጥቃት ለሞት ይዳርጋል።

ምክንያቱ

📌 የቂጥኝ አምጪ ሕዋስ ትሬፖኔማ ፓሊደም (Treponema Pallidum) የተባለው ባክቴሪያ ነው፡፡ ባክቴሪያው በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በሚደረግ የብልት፣ የፊንጢጣ ወይም የአፍ በጾታዊ ግኑኝነት ወቅት በንክኪ ወደ ሰውነት ይገባል፡፡ ከበሽታው ታማሚ ጋር መርፌ መጋራትም ለቂጥኝ ሊያጋልጥ ይችላል፡፡
📌 በተጨማሪም በሽታው ካለባት እናት ወደ ፅንሱ በእርግዝና ወቅት ይተላለፋል፡፡ በመሆኑም ፅንሱን ማህፀኑ ውስጥ እንዳለ ወይም ከተወለደ ከደቂቃት በኋላ ሊሞት ይችላል፡፡
📌 ቂጥኝ ደም በመለገስ የሚተላለፍበት አጋጣሚ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ምክንያቱም፣ በአብዛኛው አገራት የተለገሰው ደም በጥንቃቄ የቂጥኝ ምርመራ ይካሄድበታል፡፡

ምልክቶቹ

📌 የቂጥኝ ምልክቶች በሶስት የበሽታው ደረጃዎች ላይ ተለያይተው ይቀመጣሉ፡፡ በበሽታው ከተያዘ በኋላ ከ 9 - 90 ቀናት (በአማካይ 21 ቀናት) የሚሆን የመራቢያ ጊዜ ይኖራል፡፡ በዚህን ጊዜ ምንም አይነት ምልክት አይታይም፡፡ በእያንዳንዱ የበሽታው ደረጃ ላይ ልዩ ልዩ ምልክቶች ሊታዩ ወይም ይህ ነው የተባለ ምልክት ላይታይ ይችላል፡፡

ደረጃ 1 - መጀመሪያው (Primary Syphilis)

📌 የመጀመሪያው የቂጥኝ ደረጃ የሚመጣው ከመራቢያው ጊዜ በኋላ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ህመም የሌለው ነገር ግን በጣም የተበከለ Chancre (ሻንከር) የተባለ ቁስል በብልት አካባቢ አልፎ አልፎ ደግሞ በአፍ አካባቢ ይመሰረታል፡፡
📌 ይህ የበሽታው ደረጃ ከሌሎቹ በጣም ተላላፊ ነው፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ሰው ንክኪ በሚፈጥርበት ወቅት በበሽታው ሊበከል ይችላል፡፡ ቁስሎቹ ያለ ምንም ሕክምና ከሶስት እስከ ስድስት ሳምንት ውስጥ ሊጠፉ ይችላሉ፡፡ 25% በሚሆኑት ጉዳዮች ላይ ወደ ሁለተኛው ደረጃ ይሸጋገራሉ፡፡

ደረጃ 2 - ሁለተኛው (Secondary Syphilis)

📌 ሁለተኛው የቂጥኝ ደረጃ ከአንድ እስከ ሶስት ወራት ድረስ ሊቆይ ይችላል፡፡ ይህ ደረጃ በአብዛኛው ከቆዳ የተያያዘ ነው፡፡ ሮዝ ቀለም ያላቸው ሽፍታዎች በመዳፍ፣ በውስጥ እግር እና በተለያዩ የቆዳ ክፍሎች ላይ ይወጣሉ፡፡ እነዚህም በከፍተኛ ሁኔታ ተላላፊ ናቸው፡፡
📌 በተጨማሪም የፀጉር መሳሳት፣ የጉሮሮ ቁስለት፣ በአፍና በአፍንጫ የሚወጡ ነጭ ልጣፊዎች፣ ትኩሳት፣ ራስ ምታት እና የክብደት መቀነስ ያሉትን ምልክቶች ሊያጠቃልል ይችላል፡፡
📌 ልክ እንደ መጀመሪያው ደረጃ ሁሉ ሁለተኛውም ያለ ሕክምና ሊሰወር ይችላል፡፡ከዚህ ቀጥሎ የበሽታው የድብቅ ደረጃ (Latent Stage) ላይ ይገባል፡፡ ከሁለተኛው ወደ ሶስተኛው ደረጃ እንደ መሸጋገሪያነት የሚያገለግል ነው፡፡ ይህ ደረጃ ያለ ምንም ምልክት ለአመታት ይቆያል፡፡ ከዚህ በኋላ ቂጥኝ ወደ ሶስተኛውና አደገኛው ደረጃ ይሸጋገራል፡፡

ደረጃ 3 - ሶስተኛው (Teritiary Syphilis)

📌 ያለ ሕክምና ከቆዩ አንድ ሶስተኛ የሚሆኑት ተጠቂዎች ወደ ሶስተኛው ደረጃ ያመራሉ፡፡ ሶስተኛው እና የመጨረሻው ደረጃ ከመጀመሪያው ኢንፌክሽን ከ 3 እስከ 15 ዓመታት በኋላ ነው፡፡
📌 በዚህ ደረጃ ላይ በሽታው ተላላፊ አይሆንም፡፡ ነገር ግን ባክቴሪያው ደም ውስጥ ዘልቆ ስለገባ በልብ፣ በአንጎል፣ እና በነርቮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል፡፡ ይህ ሲሆን ዝም ብሎ መከታተል ለአይነ-ስውርነት፣ ለመስማት አለመቻል ለፓራላይሲስ (Paralysis) አልፎ ተርፎም ለሞት ሊዳርግ ይችላል፡፡

ምርመራው

📌 በደም ምርመራ በሽታውን መለየት ይቻላል፡፡

ለተጨማሪ መረጃዎች

https://t.me/Doctormhomecare

Doctor M nursing Home care

11 Apr, 17:35


✍️ የሆድ ድርቀት ለምን እንደሚከሰት ያውቃሉ?
የሆድ ድርቀት፦ አንድ ሰዉ ለተከታታይ ሳምንታትና ከዚያ በላይ በቂ ጊዜ ሰገራ መዉጣት የሚያስቸግረዉ ከሆነ ወይም በሳምንት ከሶስት ጊዜ በታች ሰገራ የሚወጣ ከሆነ የሆድ ድርቀት አለዉ ተብሎ ይገለፃል፡፡

👉ጊዜያዊ የሆነ የሆድ ድርቀት ብዙ ጊዜ የሚከሰት ነገር ነዉ፡፡ ነገር ግን ለረጅም ጊዜ የቆየ የሆድ ድርቀት በሚከሰትበት ወቅት የታማሚዉን የዕለት ተዕለት የስራ እንቅስቃሴ ከማወኩም በላይ ታማሚዉ ሰገራ በሚወጣበት ወቅት ረዘም ላለ ጊዜ የማስማጥና ሌሎች ምልክቶችም አሉት፡፡
🛑የሆድ ድርቀት ምልክቶች ምንድናቸው?
➡️በሳምንት ከሶስት ጊዜ በታች ሰገራ መዉጣት
➡️ የደረቀ ሰገራ መዉጣት
➡️ ሰገራ በሚቀመጡበት ወቅት ማስማጥ
➡️ ሰገራ በሚቀመጡበት ወቅት አንዳች ነገር ደንዳኔዎትን የዘጋዉ ነገር ያለ ስሜት መሰማት
➡️ሰገራ ለመዉጣት እርዳታ መፈለግ(በእጅዎ ሆድዎትን መግፋት)
🛑ለሆድ ድርቀት የሚጋልጡ ነገሮች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?
📜 በእድሜ መግፋት
📜ሴት መሆን
📜 በቂ ፈሳሽ ያለመዉሰድ
📜በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን ያለመጠቀም (አነስተኛ የፋይበር መጠን ያላቸዉን ምግቦች ማዘዉተር)
📜 አነስተኛ ወይም ምንም አይነት የአካል እንቅስቃሴ ያለማድረግ
📜ለድርቀት ሊያጋልጡ የሚችሉ መድሃኒቶችን መጠቀም፡-ለምሳሌ የደም ግፊት ለመቀነስ የሚረዱ፣ለስነዓዕምሮ ችግሮች የሚሰጡ ናቸዉ፡፡
🛑የሆድ ድርቀት መንስዔዎችስ ምን ሊሆኑ ይችላሉ?
የሆድ ድርቀት አብዛኛዉን ጊዜ የሚከሰተዉ ከምግብ መፈጨት በኃላ የሚቀረዉ ቆሻሻ ወይም ሰገራ በአንጀት ዉስጥ የሚያደርገዉ እንቅስቃሴ(ጉዞ) በጣም ዘገምተኛ በሚሆንበት ወቅት ሲሆን የሚከተሉት መንስዔዎች አሉት፡-
📜 የአንጀት መታጠፍ
📜 የትልቁ አንጀት ካንሰር
📜 የትልቁ አንጀት ጥበት
📜አንጀት ላይ ጭነት ሊፈጥሩ የሚችሉ ሌሎች የሆድ ዉስጥ ካንሰሮች
📜የህብለ ሰረሰር ጉዳት መኖር
📜ስትሮክ
📜የፓርኪንሰንስ ህመም
📜 ሰገራን ለማስወገድ የዳሌ ጡንቻዎች መለጠጥ ያለመቻል
📜 የዳሌ ጡንቻዎች መልፈስፈስ
📜የስኳር ህመም
📜 የፓራታይሮይድ ዕጢ ችግር
📜እርግዝና
📜 የታይሮይድ ዕጢ ሆርሞኖች ማነስ
🛑የሆድ ድርቀት ህክምና ምንድነው?
➽ለረጅም ጊዜ የቆየ የሆድ ድርቀት በሚኖርበት ወቅት ከሚመከሩ ነገሮች ዉስጥ የአመጋገብና የአኗኗር ዘይቤ ለዉጥ ማድረግ ሲሆን ይህም ሰገራ በአንጀት ዉስጥ የሚቆይበትን ጊዜ ይቀንሳል፡፡ይህን ማድረግዎ ለዉጥ ካላመጣ የህክምና ባለሙያ ማማከር ይጠበቅብዎታል፡፡
💧የፋይበር አወሳሰዶትን መጨመር እና በቂ ፈሳሽ መዉሰድ፡- ቀስ በቀስ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የጥራጥሬ ዘሮች በብዛት መመገብ
💧 የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘዉተር፡- ይህ የአንጀትን የጡንቻዎችን እንቅስቃሴ ስለሚጨምር ድርቀትን ይከላከላል
💧የሰገራ መምጣት ስሜት ባለዎት ጊዜ ሳያሳልፉ መዉጣት
💧 የሰገራ ማለስለሻ መጠቀም
💧የዳሌ ጡናቻዎች ስልጠና፡- በዚህ ረገድ በሰለጠኑ ባለሙያዎች በመታገዝ ሰገራን ከሰዉነት ለማስወገድ የሚረዱትን ጡንቻዎችን በማላላትና በማጠንከር ማሰልጠን ሰገራን በቀላሉ ለመዉጣት ይረዳል፡፡
💧 የቀዶ ጥገና፡-በቀዶ ጥገና ሊስተካከሉ የሚችሉ የጤና ችግሮችን ለምሳሌ የፊንጢጣ መቀደድ፣ሬክቶሴሌና የአንጀት ጥበት የመሳሰሉት ሲሆኑ እነዚህ ሁኔታዎች ሲኖሩ የቀዶ ጥገና ባለሙያን ማማከር ይመከራል፡፡
ማሳሰቢያ፦የሆድ ድርቀት ካልታከመ ለብዙ ስር የሰደዱ ችግሮች ማጋለጡ አይቀሬ ነው፣ በተለይ ለስንፈተ-ወሲብ ና ለፊንጢጣ መሰንጠቅ፤በመሆኑም ችግሩ እንደተከሰተ በ አቅራቢዎ በሚገኝ የጤና ተቋም መታየት ይኖርብዎታል!!

ለተከታታይ የጤና ነክ መረጃዎች
https://t.me/Doctormhomecare

Doctor M nursing Home care

10 Apr, 05:38


ኩላሊታችን ጉዳት ላይ መሆኑን የሚያመለክቱ 5 ምልክቶች

የኩላሊት ህመም በአለማችን ለበርካቶች ሞት ምክንያት የሆነ በሽታና ነው፡፡

ተመርምረው በሽታው እንዳለብዎ ካወቁ በኋላ ጥንቃቄ የሚሻም ነው፡፡
እስኪ ምልክቶቹን እንመልከታቸው

1. መጠነኛ የጀርባ ህመም ስሜት
ጀርባችን አካባቢ ህመም በተደጋጋሚ ከተሰማን እና ምቾት ከነሳን ፤ኩላሊታችንን መታየት እንዳለብን አመላካች ነውና ጥንቃቄ እናድርግ ፡፡
ይህ የኩላሊት ሕመም ምልክት በሁለቱም ጎኖቻችን ሊከሰት ይችላል፡፡
ነገር ግን ቀድሞ የግራ ጎናችን ሕመም ስሜት ካሳየ ፤ ወዲያው በአጭር ጊዜ ውስጥ የቀኝ ጎናችንም ሳለባ ይሆናል፡፡
ችግሩን ግን ወዲያው ወዲያው በመሽናት ማስቀረት ያስችላል፡፡

2. የሽንት ሁኔታ

ሌላው ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ጉዳይ ፤ ሽንታችን ሲመጣ የምንወስደው ጊዜ ነው ፡፡አንድ ሰው ሽንቱ እንደመጣ ቢሻና ይመከራል፡፡
ሳንሸና ረጅም ጊዜ የምንቆይ ከሆነ ደግሞ ፤ ለኩላሊት ህመም የመጋለት እድሉ ይሰፋል፡፡
ስንሸና የማቃጠል ስሜት ፤ ያልተለመደ የሽንት ጠረን ፤ አንዱ ምልክት ነው ፡፡

3. እብጠት

ኩላሊት ስራውን በአግባቡ መከወን ካልቻለ፤ ከሰውነታችን ውስጥ አላስፈላጊ ቆሻሻ ማስወገድ የማይችልበት ደረጃ ላይ ከደረሰ እብጠት ይከሰታል፡፡
እብጠቱ እግር; ቁርጭምጭሚት፤ እና ፊት ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ ሲዉል ሲያድር ደግሞ ወደ ልብ እና ሳንባ ይዛመታል፡፡

4. የቆዳ ችግር

ኩላሊት ስራዉን በአግባቡ ካልሰራ በሰውነታችን የተለያዩ ቦታዎች ላይ ድርቀት, ሽፍታ, እና ከባድ የማሳከክ ሁኔታ ሊከሰት ይችላል፡፡

5. ኦክሲጅን

ኩላሊት ኢሪትሮፖይት ሆርሞን የማምረት ስራ ያከናውናል፡፡
ኢሪትሮፓይት ሆርሞን በበኩሉ ኦስሲጅን ተሸካሚ የቀይ ደም ሀዋስ ያመርታል፡፡
የቀይ ደም ሴል ወይም ህዋስ እጥረት በሰውነታችን ውስጥ ሲከሰት ፤አኔሚያ (iron deficiency) ወይም የብረት እጥረት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡
በአንድ ግለሰብ ላይ የአይረን መጠን መቀነስ ፤ሰውየው ሞቃታማ ስፍራም ሆኖ ብርድ ብርድ የሚል ስሜት እንዲሰማው፤ ብሎም ስር ለሰደደ ድካም እንዲጋለጥ ያደርገዋል፡፡
የኩላሊት ጤና ለማሻሻል ምን ማድረግ አለብን ?
-ሲጋራ አለማጨስ
-ፈሳሽ አብዝቶ መውሰድ
-በአካላዊ እንቅስቃሴዎች ተሳትፎ ማድረግ ጥቂቶቹ መከላከያ ዘዴዎች ናቸው፡፡

ሰናይ ቀን ይሁንላችሁ‼️

ለተከታታይ የጤና ነክ መረጃዎች
https://t.me/Doctormhomecare