ይህን ሱራ ማምበብ ይወደዳል
በውስጡ ስለ ጠንካራ አማኝ ወጣቶች ተወስቷል ፅናታቸውና አሏህ ያደረገላቸው ጥበቃ ተነግሯል የሙሳና የኸደርን ጨምሮ በነዙልቀርነይን ቂሷም ይደመማሉ።
ሙሳ ሦስት ጊዜ የኸደርን ትዕዛዝ ጣሱና በኸደር በቃ እንለያይ ተባሉ እኛስ በቀን ስንቴ የአሏህን ትዕዛዝ እየጣስን ነው? በል ተለያይተናል ጥፋ ከዚህ ይለናል ብለን ለምን አልፈራንም¡?
ሳምንታዊ በዓላችን ነው
በጊዜ ወደ መስጂድ ለመሄድ ሞክሩ።
መልካሙን ሁሉ ይግጠማቹህ
ጀሊሉ በራህመቱ ቁጣውንም ያንሳልን።