The Jubair || The ጁበይር @thejubair00 Channel on Telegram

The Jubair || The ጁበይር

@thejubair00


ይህ የ The Jubair official የቴሌግራም ገፅ ነው

አላማችን ለኡማው ዲናዊም ሆነ ጠቃሚ ዱንያዊ ጉዳዮችን በአላህ ፍቃድ ከምናቀውም ይሁን በትክክል ከሚያቁት በመውሰድ ለእናንተ ለማስጨበጥ መሞከር ነው .

📛 ማሳሰቢያ ከላይ እንደጠቀስኩት እዚህ ቻናል ላይ ከዲናዊ ጉዳዮች ባሸገር ሌሎች የተለያዩ ዱንያዊ ሀሳቦችን እንዲሁም ደግሞ ሃላል ማስታወቂያዎችን ልታዩ ትችላላቹ !!

@Thejubair

The Jubair || The ጁበይር (Amharic)

ለአዲሱ አስተዳደር እና መረጃዎች ለኡማው ዲናዊም ከመጠቆማችሁ በፊት እንዲሰራልላችሁ ማገድ እናይሁንላችሁ። The Jubair ገፅ ከዚህ በኋላ ኮምፒዉተር ፣ ቆንጂ ፣ ጥምሮችን እና ሌሎች የሚቆጠሩ ዱንያዊ መረጃዎችን ለማስታወቂያ በተለያዩ ልዩ መረጃዎችን እና እንቅስቃሴ ለመቀጠል፣ እና ለመረጠ እንዲላቁት ይቀሳል። ከትክክል የኡማው ዲናዊም ጉዳዮች እና የቆንጂዎች መረጃዎች ከእናንተ ጋር እንዲፈጽሙ በመጀመር በኡማው እናንተም ለሚፈጽሙ ትክክል መረጃ እንዲያጋጥሙ ለተጠቁመው ቅጽበት ሀሳቦች፣ መስፈሪያዎች እና ተይዞ ያገኙ። በተጨማሪም በፈለጋችሁ ጠቃሚ ተመሳሳይ ዱንያዊ መረጃዎችን ለማሳካት እና የምንተኩልበትን ፈጣሪ ሊከባታችሁ የመቋቋም እናመሠጣችሁ። በጠቃሚ ጉዳዮች ላይ ለተገባዥነት የምንተኩልበትን ሐሳቦት እንዲሁም ተለያዩ ዱንያዊ መረጃዎችን እንዲለዩ የምንተኩልበትን እና የተባለውን መረጃዎች መምረጥ እና ላከበት መቀጠል ከፈቷችሁ በፊት በአላህ ፍቃድ ውስጥ ለመክፈል እና ከትልቅ ማህበረሰብ እና ትልቅ ልምድ እንዲሁም እንዲረዳ ወደ አዲስ አበባና በእንግሊዝ፣ እስካሁን ድረስ አቅራቢ ላይ እንዳለው በተለያዩ ጉዳዮ እና ሚኒስትሩ እንዲቀርብ የሙያ ማቅረብ በመጀመሪያ ከዙር እናንተን የምንገኘውን ለመወንጀል እንወዳለን። በተጨማሪም በሌላ ቤተሰብ መረጃም ላይ በጨዋታ እና ህመም ምክንያት እንዲሳልፈው ያውቃሉ። ለመምረጥ እና ለድረ-ገጽ እና እንዲያስተውሉ እንደምንችል በማረጋጋት ከኡማው ሀሳቦት ሸገራ ማስታወቂያዎችን ወደ ሁሉም የሚሰራበት መረጃዎችን በዚህ መልእክት እንሰጣለን። በምትክ ስለ The Jubair ገፅ አለበት ኡማው እናንተ ለመሆን እና ለመከታተል ለማቃለል በመዘጋጀት ከአንድ እስክትሆኑ እንደሆነ ፈቃድ እና መጠን ከሚደረግኩበት አገር እና በአካባቢዎች፣ የሚለውን አይነት ከፍተኛ ለመጠቀም በሂደት እና ከአንፃሩ የሚጠበቅቡበት ምክንያት ይቀላቀል ለማስችል እንደምንፈጽም በማስጨበጥ የሚፈልጉትን የኡማው ዲናዊም ገፅ በኡማው እናንተም ለሚከታተሉ መረጃዎች ለመወንጀል እና ለመሞክራት በጀምረው እንዲሰሙ በመጀመር እና በጽሁፉ በገጽ ይመሰክራል።

The Jubair || The ጁበይር

06 Jan, 11:59


"በመሬት መንቀጥቀጥ ጊዜ መባልና መደረግ ያለባቸው ነገሮች!"

በኡስታዝ አሕመድ ኣደም

             ሰኞ 6/7/1446 ዓ.ሂ

       

The Jubair || The ጁበይር

05 Jan, 17:58


ረቢ ረቢ ረቢ 🥺

The Jubair || The ጁበይር

03 Jan, 06:37


و يا سبحان الله ما أرحمك يا ارب 🤌🤍

The Jubair || The ጁበይር

29 Dec, 10:40


قُلْ مَنْ بِيَدِهِ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيْءٍ) يريد السموات وَمَا فَوْقَهَا وَمَا بَيْنَهُنَّ، وَالْأَرَضِينَ وَمَا تَحْتَهُنَّ وَمَا بَيْنَهُنَّ، وَمَا لَا يَعْلَمُهُ أَحَدٌ إِلَّا هُوَ. وَقَالَ مُجَاهِدٌ: "مَلَكُوتُ كُلِّ شَيْءٍ" خَزَائِنُ كل شي. الضحاك: ملك كل شي. وَالْمَلَكُوتُ مِنْ صِفَاتِ الْمُبَالَغَةِ كَالْجَبَرُوتِ وَالرَّهَبُوتِ، وَقَدْ مَضَى فِي" الْأَنْعَامِ ".
(وَهُوَ يُجِيرُ وَلا يُجارُ عَلَيْهِ) أَيْ يَمْنَعُ وَلَا يُمْنَعُ مِنْهُ. وَقِيلَ: "يُجِيرُ" يُؤَمِّنُ مَنْ شَاءَ. "وَلا يُجارُ عَلَيْهِ" أَيْ لَا يُؤَمَّنُ مَنْ أَخَافَهُ. ثُمَّ قِيلَ: هَذَا فِي الدُّنْيَا، أَيْ مَنْ أَرَادَ اللَّهُ إِهْلَاكَهُ وَخَوْفَهُ لَمْ يَمْنَعْهُ مِنْهُ مَانِعٌ، وَمَنْ أَرَادَ نَصْرَهُ وَأَمْنَهُ لَمْ يَدْفَعْهُ مِنْ نَصْرِهِ وَأَمْنِهِ دَافِعٌ. وَقِيلَ: هَذَا فِي الْآخِرَةِ، أَيْ لَا يَمْنَعُهُ مِنْ مُسْتَحِقِّ الثَّوَابِ مَانِعٌ وَلَا يَدْفَعُهُ عَنْ مُسْتَوْجِبِ الْعَذَابِ دَافِعٌ.

The Jubair || The ጁበይር

28 Dec, 06:47


«መልካም ሴት ስትሆኚ "እከሊትን'ማ ለእከሌ ነበር መዳር!" እስከመባል ኸይርሽ ይሰራጫል።»
منقول

The Jubair || The ጁበይር

27 Dec, 12:02


እንደው በቃ ወላሂ ዕድለኞች እኮ ነን ሀባይቢ
አላህን ከያዝን በየትም በኩል አሸናፊ ነን

አልሐምዱሊላህ


{ وَإِذۡ یَمۡكُرُ بِكَ ٱلَّذِینَ كَفَرُوا۟ لِیُثۡبِتُوكَ أَوۡ یَقۡتُلُوكَ أَوۡ
یُخۡرِجُوكَۚ وَیَمۡكُرُونَ وَیَمۡكُرُ ٱللَّهُۖ وَٱللَّهُ خَیۡرُ ٱلۡمَـٰكِرِینَ }
[Surah Al-Anfâl: 30]
እነዚያም የካዱት ሊያስሩህ ወይም ሊገድሉህ ወይም (ከመካ) ሊያወጡህ ባንተ ላይ በመከሩብህ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ ይመክራሉም አላህም ተንኮላቸውን ይመልስባቸዋል፡፡ አላህም ከመካሪዎቹ ሁሉ በላይ ነው፡፡
المختصر
واذكر - أيها الرسول - حين تَمالأ عليك المشركون ليكيدوا لك بحبسك أو بقتلك أو نفيك من بلدك إلى بلد غيره، ويكيدونك ويرد الله كيدهم عليهم، ويمكر الله، والله خير الماكرين.
تفسير السعدي
أي: [و] أذكر أيها الرسول، ما منَّ اللّه به عليك. ﴿إِذْ يَمْكُرُ بِكَ الَّذِينَ كَفَرُوا﴾ حين تشاور المشركون في دار الندوة فيما يصنعون بالنبي ـ صلى الله عليه وسلم ـ، إما أن يثبتوه عندهم بالحبس ويوثقوه. وإما أن يقتلوه فيستريحوا ـ بزعمهم ـ من شره. وإما أن يخرجوه ويجلوه من ديارهم. فكلُّ أبدى من هذه الآراء رأيا رآه، فاتفق رأيهم على رأي: رآه شريرهم أبو جهل لعنه اللّه،وهو أن يأخذوا من كل قبيلة من قبائل قريش فتى ويعطوه سيفا صارما، ويقتله الجميع قتلة رجل واحد، ليتفرق دمه في القبائل. فيرضى بنو هاشم [ثَمَّ] بديته، فلا يقدرون على مقاومة سائر قريش، فترصدوا للنبي ـ صلى الله عليه وسلم ـ في الليل ليوقعوا به إذا قام من فراشه. فجاءه الوحي من السماء، وخرج عليهم، فذرَّ على رءوسهم التراب وخرج، وأعمى اللّه أبصارهم عنه، حتى إذا استبطؤوه جاءهم آت وقال: خيبكم اللّه، قد خرج محمد وذَرَّ على رءوسكم التراب. فنفض كل منهم التراب عن رأسه، ومنع اللّه رسوله منهم، وأذن له في الهجرة إلى المدينة،فهاجر إليها، وأيده اللّه بأصحابه المهاجرين والأنصار،ولم يزل أمره يعلو حتى دخل مكة عنوة، وقهر أهلها،فأذعنوا له وصاروا تحت حكمه، بعد أن خرج مستخفيا منهم، خائفا على نفسه. فسبحان اللطيف بعبده الذي لا يغالبه مغالب.

The Jubair || The ጁበይር

24 Dec, 10:48


❄️ አዲስ የኪታብ ቂርኣት ደርስ ❄️

💠 أسباب شرح الصدور
(من كلام الإمام شمس الدين ابن القيم في كتابہ زاد المعاد في هدي خير العباد)

📚 የልብ መስፋትና መረጋጋትን ለማግኘት የሚረዱ ነገሮች

📝 ዝግጅት ፡- ኢማሙ ኢብኑል ቀይም ዛዱል መዓድ በተሰኘው ኪታባቸው

🔊 ማብራሪያ:-ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

                    ክ/1

      የዕለተ ሰኞ 22/6/1446 ዓ.ሂ
    
       የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ

       🔸🔹🔸🔹🔸🔹

🔗 https://tinyurl.com/2uee88kj

       🔸🔹🔸🔹🔸🔹

📚  የኪታቡን ፒ.ዲ.ኤፍ ለማግኘት

                

🔎 https://tinyurl.com/3pwj9zvk
🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸

🌐 https://zadalmead.com/

✔️ https://telegram.me/ahmedadem

✔️https://facebook.com/yenegew

✔️http://youtube.com/c/ZadulMaad

✔️ http://x.com/zad_al_mead

✔️https://instagram.com/zad_al_mead

📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

The Jubair || The ጁበይር

24 Dec, 10:48


❄️ የኪታብ ቂርኣት ደርስ ❄️

💠 أسباب شرح الصدور
(من كلام الإمام شمس الدين ابن القيم في كتابہ زاد المعاد في هدي خير العباد)

📚 የልብ መስፋትና መረጋጋትን ለማግኘት የሚረዱ ነገሮች

📝 ዝግጅት ፡- ኢማሙ ኢብኑል ቀይም ዛዱል መዓድ በተሰኘው ኪታባቸው

🔊 ማብራሪያ:-ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

                    ክ/2

      የዕለተ ማክሰኞ 23/6/1446 ዓ.ሂ
    
       የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ

       🔸🔹🔸🔹🔸🔹

🔗 https://tinyurl.com/2pzf5mya

       🔸🔹🔸🔹🔸🔹

📚  የኪታቡን ፒ.ዲ.ኤፍ ለማግኘት

                

🔎 https://tinyurl.com/3pwj9zvk
🔹 🔸 🔹 🔸 🔹 🔸

🌐 https://zadalmead.com/

✔️ https://telegram.me/ahmedadem

✔️https://facebook.com/yenegew

✔️http://youtube.com/c/ZadulMaad

✔️ http://x.com/zad_al_mead

✔️https://instagram.com/zad_al_mead

📚"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!"
አል-ኢማሙ ማሊክ

The Jubair || The ጁበይር

24 Dec, 10:43


ለሽልማቱ እንምረጠው⁉️
=================
(ባለፈ የመረጣችሁም ደጋግማችሁ መምረጥ ትችላላችሁ!)
||
እውነት ለመናገር ሁሉም ተወዳዳሪዎች የሚሸለሙትን ብር ወደ ኪሳቸው የሚያስገቡ ቢሆን ኖሮ፤ ወጣቱን ዒዘድንን ከመምረጥ ውጭ ሌላ አማራጭ የለኝም። ለእናንተ እርሱን ከመምረጥ የተሻለ ሌላ አማራጭ አላገኝላችሁም።

ነገር ግን ካሉት ተወዳዳሪዎች መካከል አንዱ የሆነው የአሚን ጠቅላላ ሆስፒታሉ ዶ/ር ሙሐመድ ሽኩር የ10 ሚሊዮን ሽልማቱን ወደ ኪሱ ሳይሆን የሚያስገባው በኪሱ ካለው ገንዘብ ጋር ጨምሮ እንደተለመደው በኸይር ሥራ ላይ እንደሚያውለው ቃል ገብቷል።

ዶ/ሩ ይህን የ10 ሚሊዮን ብር ምንም ሳይሸራርፍ ለእናቶችና ህፃናታ መታከሚያ እንደሚያውለው፣ በራሱ ገንዘብ የጀመራቸውን የኸይር ሥራዎች ማሳለጫ እንደሚያደርገው ተናግሯል። ስለሆነም ምንም እንኳ እስከዛሬ ከሠራቸው ዘርፈ ብዙ በጎ ሥራዎች አንፃር ሽልማቱ የሚገባውና እንዲያውም የሚያንስበት ቢሆንም፤ ለእናቶችና ህፃናት ከለገሰው ደግሞ ይበልጥ እንዲያሸንፍ ድምፅ ልንሰጠው ይገባል። በአጭሩ እርሱን ለመምረጥ የምንሰጠው ጊዜና መልዕክት ለመላክ በትንሹ የምናወጣት 3 ብር ለእናቶችና ህፃናት መረዳት ሰበብ ናት።



ለናሙና ያክል ዶ/ር ሙሐመድ በቅርቡ ከሠራቸው በጎ ሥራዎች መካከል፦



√ 250,000 ለመሬት መንሸራተት  አደጋ ለተጋረጠው  ለጎፋ ህዝብ፣

√ ከ3,000,000 በላይ ለቃዋቆቶ ኢብኑ ዐባስ መስጅድና መድረሳ፣

√ 300,000 ለሐላባ ወህደቱኒሳእ መድረሳ፣

√ ከ4.3 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁሶችን ከኢትዮ አግራ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር ለዳሎቻ ከተማ ጤና ጣቢያ፣

√ የ200, 000 ለቅበት ከተማ አስተዳዳር ማህበረሰብ አቀፍ ፋርማሲ፣

√ 2.5 ሚሊዮን ለኬራቴ ጤና ጣብያ፣


√ 250,000 ለጎፍለላ… ወዘተ ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው።




ዶ/ር ሙሐመድን በመምረጥ እናቶችንና ህፃናትን መርዳት እንደምንችል ስላወቅኩ፤ ወደ 9355 SMS ላይ BIW03 ብላችሁ በመላክ ትመርጡት ዘንድ ጋበዝኳችሁ።

ስትመርጡ በፓኬጅ ስለማይቻል ቢያንስ 3 ብር ባላንስ ይኑረው ስልካችሁ።
ከዛ ሚሴጅ ላይ ግቡና 9355 ላይ BIW03 ብላችሁ ጻፉና ላኩት።

ባይሆን BIW በሚለውና 03 በሚለው መካከል ስፔስ (ክፍት ቦታ) መኖር የለበትም። BIW የሚለው በsmall letter biw ሳይሆን ሁሉም ፊደላት በካፒታል ሌተር BIW ናቸው። በትክክል መላካችሁን የምታረጋግጡት፤ BIW03 የሚለውን ወደ 9355 ከላካችሁት በኋላ «You have voted for ( Dr Mohamed shikur ). Thank you for your participation. Abbay TV 'Ethiopia's Best'» የሚል መልዕክት ወዳውኑ ይደርሳችኋል። ከአንድ በላይ ሲም ካላችሁ፣ ወይም መደጋገም ከፈለጋችሁ፣ ወይም ባላችሁ ቤተሰብ ስልክ ሁሉ መላክ ከፈለጋችሁ፣ ካርድ ለሌላቸው እየሞላችሁ … ምረጡት። ድምፃችን እንዳይበታተንና አንድ ቦታ ላይ አድምተን ድምፅ እንድንሰጥ ወጥሩ ቅመሞች።

መልዕክቱን በተለያዩ ገፆችና ግሩፖች አሰራጩት።
መታከሚያ ያጡ ሚስኪን እናቶችና ህፃናት ያሸንፋሉ፤ ኢንሻ አላህ! ያው የኔ ገፅ ቅመሞች በንቃትና በእንዲህ አይነት የኸይር ተሳትፎ አትታሙም። እንኳን በዚህች በቀላሏ ከኪሳችሁም ሚሊዮኖችን አዋጥታችሁ በተደጋጋሚ ለሚስኪኖች ሰድቃችሁ አሳይታችኋል። ሰበብ ሲገኝ ደግሞ እድሉን መጠቀም ነው። አላህ ይቀበላችሁ!



||
t.me/MuradTadesse

The Jubair || The ጁበይር

22 Dec, 17:55


አቤቱ ስንፍናችን ...
ስንዘናጋ እንደርሳለን ጊዜ አለን እንላለን....
ስናጠፋ ደግሞ አላህ ምህረቱ ሰፊ ነው ይምረናል እንላለን
.
በዚሁ መሃል ከአምላካችን ስንትና ስንት ማይልስ ርቀን አለን!!
ረሕመትህን ያ ረብ


🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

22 Dec, 10:54


መከራ ያልፈታው ነቢያዊ ሕይወት
.
እኛና አላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም!

በምድር ላይ እያለን ጉዳት ደርሶብናል፤ ብዙ መከራ አይተናል የምንል ሰዎች እስቲ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ነጥቦች በማስተዋል የኛን እና ከአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ሁኔታ እናነፃፅር፡፡ ምን እንደረሰባቸውና ምን እንደደረሰብን እናመዛዝን …

~እናት አባትህ አሉ?
እርሣቸው እኮ ያለ እናትና አባት ነው ያደጉት፡፡ አባታቸው ሳይወለዱ፣ እናታቸው ደግሞ ገና የአምስት እና ስድስት ዓመት ልጅ እያሉ ነበር የሞቱባቸው፡፡
~ ልጆችህን አጥተሃል?
የአላህ መልዕክተኛ እኮ ሁሉም ስድስት ልጆቻቸው እርሣቸው በህይወት እያሉ ሞተዉባቸዋል፡፡ ከሴት ልጃቸው ፋጢማ በስተቀር፡፡
~ሥምህ ጠፍቷል አሊያም ተሰድበሃል፣ ተደብድበሃል?
እርሣቸው እኮ ተሰድበዋል፣ ተደብድበዋል፣ ገጣሚ፣ መተተኛ/ደጋሚ ተብለዋል፡፡ የመካና የጣኢፍ ምድሮችም የሚመሰክሩት ይህንኑ ነው፡፡
~ በቤተሰብህ የመጣብህ ችግር አለ? ባለቤታቸው በመናፍቃን በዝሙት ሥማቸው ጠፍቷል፡፡ በዚህም የእርሣቸውም የታላቁ ነቢይ ክብር ተነክቷል፡፡
~ዕዳ አለብህ?
የአላህ መልዕክተኛ እኮ ሲሞቱ ዕዳ ነበረባቸው፡፡ የጦር ልብሳቸው አንድ አይሁዲ ዘንድ በዕዳ ተይዞ ነበር፡፡
~ ተቸግረህ፣ ተርበህ ታውቃለህ?
ረሱሉ እኮ ከርሃብ የተነሳ ሁለት ሶስት ድንጋዮችን በሆዳቸው ላይ ያስሩ ነበር፡፡ ለምግብ ማብሰያ የሚሆን እሣት በቤታቸው ሳይቀጣጠል ተምርና ውሃ ብቻ እየተመገቡ ወራትን ያሳልፉ ነበር፡፡
~ ልጅህ ወይም የቅርብ ዘመድህ ተፈታ በሷ ሥነልቦና ተጎድተህ ታውቃለህ? የአላህ መልዕክተኛ እስልምናን በመስበካቸውና የአላህን የሐቅ መንገድ በማሳየታቸው ብቻ ተጠልተው ሁለት ሴት ልጆቻቸው በባሎቻቸው ተፈተዋል፡፡
~ሳትወድ በግድ ከምትወደው የትውልድ ሀገርህ ተሰደህ ታውቃለህ?
የአላህ መልዕክተኛ እኮ ተከታዮቻውን ይዘው እትብታቸው ከተቀበረበት ቀዬ ተሰደዋል፡፡ ለዓመታትም የስደት ሕይወት ገፍተዋል፡፡
~ የግድያ ሙከራ ተደርጎብህ ያውቃል? ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ከአንድና ሁለት ሶስት ጊዜ በላይ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል፡፡
~ በአደባባይ ቆሻሻ ተጥሎብህና ተስቆብህ ያውቃል?
ነቢዩ እኮ ሰላት በመስገድ ላይ እያሉ ሱጁድ ላይ ሆነው ቆሻሻ ተጥሎባቸዋል፡፡
~የእምነት ነፃነትህን ተነፍገሃል?
የአላህ መልዕክተኛ ለሶስት አመታት እምነታቸውን ደብቀው ኖረዋል፡፡
~ ማዕቀብ ተጥሎብህ ያውቃል?
ረሱሉ እኮ ለሦስት አመታት ያህል ማዕቀብ ተጥሎባቸው ከማህበረሰቡ እንዲገለሉ ተደርገዋል፡፡
~ አካልህ ላይ ጉዳት ደርሶ ያውቃል? ነቢያችን እኮ ተፈንክተዋል፣ ጥርሣቸው ተሰብሯል፡፡
.
ምናልባት አንተን እና እኔን አንድ ችግር አግኝቶን ያንኑ ችግር መቋቋም ተስኖን ይሆናል፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ግን ከነኚህና መሰል ብዙ ችግሮች ጋር ምንም እንዳልሆኑ ሆነው እያመሰገኑ ደስተኛ ሆነው ይኖሩ ነበር፡፡
ሶለዋቱ ረቢ ወሰላሙሁ ዐለይሂ

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

21 Dec, 17:54


ዛሬ ሒጃብ በሥርኣት አልለብስ ያለው ገላ ነገ ከፈንን በግድ ይለብሳል፡፡ ዛሬ መሬት ላይ ሥርኣት ያልያዘን ወጣት ነገ መሬት ሥር መቃብር ሥርኣት ያስይዘዋል፡፡
እንደ ዩሱፍ መሸሽ የሚችል ወጣት ጠፋ!
እንደ መርየም ለንጽህናዋ የምትጨነቅ ሴት ታጣች፡፡
አምላኬ ሆይ! ሀይለኛ ንፋስ ሊገልጠው በማይችል መሰተሪያ ሰትረን፡፡ ጉልበት አጣን አግዘን፡፡ መሆን አቃተን ደግፈን፡፡


🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

21 Dec, 10:53


በምትሠራው ነገር አለመፀፀት ከፈለግክ ያንን ነገር ለአላህ ብቻ ብለህ ሥራው። ለሰው ብለው የሠሩት ነገር ትችት አያጣውምና። ካሳነስክ ገብጋባ ይሉሃል። ካበዛህ ደግሞ ለጉራ ነው ብለው ያስወሩብሃል።

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

20 Dec, 17:53


ዓለም ላይ አምባገነኖች እና በዳዩች ከፍ ብለው እናይ ይሆናል። በኛ እይታ ስንገመግምም በርግጥ ከፍ ያሉ ይመስላሉ። አላህ በዳዩችን ከፍ ሲያደርጋቸው ወዷቸው አይደለም። ከዚያ ከፍታ ላይ ሊጥላቸው ብሎ እንጂ። ከትልቅ ከፍታ የወደቀ ምኑ ይተርፋል!።
አትጠራጠሩ.. .ጥሩ ፍፃሜ የአማኞች ነው።

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

20 Dec, 10:52


አትዘን! ቸግሮሃል? አላህ አለ! ይሰጥሀል
አትዘን! ጨንቆሃል? አላህ አለ! ይፈርጅሀል
አትዘን! አሞሃል? አላህ አለ! ይፈዉስሀል
አትዘን! ጉዳይ አጋጥሞሃል? ለአላህ ንገረው ሁሉንም ያሟላልሀል ብቻ አይኖችህን ወደ ሰማይ አዙራቸዉ እጆችህን ወደ ሰማይ ዘርጋቸዉ ቀልብህን ወደ ሰማይ ቀስደዉ።

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

19 Dec, 17:51


ከፊል አካልን ፀሀይ ላይ ከፊሉን ደግሞ ጥላ ላይ ማድረግ ክልክል ነው!!

ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡ አንድ ሰው በፀሀይ ብርሃንና በጥላ ላይ መቀመጥን ከልክለዋል፡፡ “የሸይጧን አቀማመጥ ነው!” ሲሉም ገልፀውታል፡፡ [ሶሒሑ አትተርጊብ ወትተርሂብ፡ 3081]
ታላቁ ዓሊም አሽሸይኽ ዐብዱልሙሕሲን አልዐባድ (አላህ ይጠብቃቸውና) እንዲህ ይላሉ፡-
“ይህም ማለት አንድ ሰው እንዲህ አይነቱን አቀማመጥ ከጅምሩም ይሁን አጋጥሞት ሊቀመጥ አይገባም፣ አይበጅምም፡፡ ከጅምሩም ስንል ሆን ብሎ በፀሀይና ጥላ ላይ መቀመጡን ለማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሊሆን የሚገባው ወይ ሙሉ ለሙሉ ፀሀይ ላይ ወይም ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ጥላ ላይ መሆን ነው፡፡ ምክንያቱም ሰውነት በአንድ ሁኔታ ላይ ማለትም ወይ ሙቀት ላይ ወይ ደግሞ ቅዝቃዜ ላይ ሲሆን ሚዛኑን የጠበቀ ይሆናል፡፡ ከፊሉ ጥላ ላይ ከፊሉ ፀሐይ ላይ ሲሆን ግን ከፊሉ ተፅእኖ ያርፍበትና ብርድ ያገኘዋል፡፡ ከፊሉ ደግሞ ሙቀት ያገኘዋል፡፡ ይሄ ደግሞ ጎጂ ነው፡፡ …” [ሸርሑ ሱነን አቢ ዳውድ፡ 27/478]

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

19 Dec, 10:51


ነብዩ ዐለይሂሠላም እንዲህ ይላሉ፡-
“የፈለግከውን ያክል ብትኖር ትሞታለህ!
የፈለግከውን ብትወድ ትለየዋለህ!
የፈለግከውን ስራ ዋጋውን ታገኛለህ!
እወቅ! የሙእሚን ክብሩ የሌሊት ሶላት መስገዱ፣ የበላይነቱም ከሰዎች መብቃቃቱ ነው፡፡”
(ሐኪም ዘግበውታል፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል)

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

18 Dec, 17:50


💵 ነጋዴው ሆይ ጠንቀቅ በል!💵

ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-

“ነጋዴዎች አመፀኞች ናቸው
ሶሐቦች፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ “አላህ ንግድን ፈቅዶ የለ እንዴ?" ሲሉ ጠየቁ።

ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ መለሱ፡-
“እንዴታ! ግን እነሱ
👉 ያወራሉ፡፡ ሲያወሩ ይዋሻሉ
👉 ይምላሉ፡፡ ሲምሉ ይወነጅላሉ"

🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴🌴
ሸይኹል አልባኒ “ሶሒሕ” ብለውታል፡፡ (አስሶሒሓህ፡ 1/366)

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

18 Dec, 12:42


ያ ሰላም ያ ሰላም ያ ሰላም 🤌

ሑረ-ል-ዓይን እንዳትቆጣብሽ ባልሽን አታናጂ!

🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

18 Dec, 10:50


“አላ ቢዚክሪላሂ ተጥመኢኑል ቁሉብ!!”
በቅርቡ በግምት የስምንት ሰዐት መንገድ ከአንድ ሾፌር ጋር ተጓዝኩ፡፡ ጉዞው ለኔ በህይወቴ ካሳለፍኳቸው ጉዞዎች እጅግ ልዩ ሆኖብኛል፡፡ ሾፌሩ ከኔ ጋር ከተለዋወጣቸው ጥቂት ቃላት ውጭ ይሄን ሁሉ ሰዐት ስንጓዝ ዚክር ላይ ነበር፡፡ ወላሂ እጅግ በጣም ነው የገረመኝ፡፡ እሱን አይቼ እኔም ዚክር እጀምርና ብዙም ሳልቆይ እራሴን ከሆነ የሀሳብ ባህር ውስጥ ስንቦጫረቅ አገኘዋለሁ፡፡ እመለሳለሁ፡፡ ዳግም እራሴን ከሌላ ቦታ አገኘዋለሁ፡፡ ሱብሃነላህ!!! እራሴን ታዘብኩት አልላችሁም፡፡ ነገሩ ከዚያም በላይ ነው የሆነብኝ፡፡ እራሴን ተጠየፍኩት፡፡ በወንድሜ በጣም ቀናሁኝ፡፡ አላህ በተውሂድና በሱና ላይ ያፅናው ብያለሁ፡፡
ግን ወንድሞችና እህቶች ስራችን ብለን ቁጭ ብለን ዚክር ላለማረጋችን አዋጣም አላዋጣም ምክኒያት ይኖረን ይሆናል፡፡ አሰልቺ ረጃጂም ጉዞዎችን ስናደርግ አሁንም አሁንም ከማዛጋት፣ አስቀያሚ ማስታወቂዎች ላይ ከማፍጠጥ፣ … ዚክር ብናረግ ምን ነበረበት? ሱብሃለህ!!! አንዴ ሱብሃለህ ሳንል ስንት መቶ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጠናል?! ስንት ረጃጅም ሰአቶችን በከንቱ አሳልፈናል? አራት መቶ አምስት መቶ ኪሎ ሜትሩ ይቅር:: የአራትና አምስት ሰዐት መንገዱም ይቅር:: ኧረ ሌላው ቀርቶ የፒያሳ መገናኛ፣ የመርካቶ አየር ጤና መንገድም ይቅር እሩቅ ነው እንበል:: በአንዲት አጭር ፌርማታ ስንትና ስንት ዚክር ማረግ ስንት አጅር ማፈስ አይቻልም? እውነት በዚክሩ የሚገኘው አጅር በገንዘብ ቢቀየር እንዲህ እንዘናጋ ነበር? አቤት የኛ ነገር!!!
እስኪ አንድ ደቂቃ በማይፈጁ ዚክሮች የሚገኘውን አጅር ያስቡ
- “ሱብሐነላሂ ወቢሐምዲሂ ሱብሐነላሂል ዐዚም” በሐዲስ እንደተነገረው እነኚህ ለምላስ የሚቀሉ፣ ሚዛን ላይ የሚከብዱ፣ አረሕማን ዘንድ የተወደዱ ቃላት ናቸው፡፡ በደቂቃ ስንቴ ማለት ይቻላል?
- “ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ” ከጀነት ድልብ ሀብቶች ውስጥ አንዷ ነች፡፡ በደቂቃ ስንቴ ማለት ይቻላል?
- የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባለቤት ጁወይሪያ ከፈጅር ሶላት እስከ ረፋድ ዚክር ስታደርግ ቆይታ “እኔ ካንቺ በኋላ አራት ከሊማዎችን ሶስት ጊዜ ደጋግሜ ብያለሁ፡፡ ብትመዘን እስካሁን አንቺ ካልሺው ትበልጣለች አሏት፡፡(ሱብሐነላሂ ወቢሐምዲሂ ዐደደ ኸልቂሂ፣ ወሪዷ ነፍሲሂ፣ ወዚነተ ዐርሺሂ፣ ወሚዳደ ከሊማቲሂ)
- አንዴ በነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ ሶላት ያወረደ አላህ በሱ ላይ 10 ሶለዋት ያወርድበታል፡፡ በደቂቃ ስንቴ ማድረግ ይቻላል? … እነኚህ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው፡፡
ውድ የኢስላም ወንድሞችና እህቶች ኢስላም እኮ ሂወት ነው፡፡ አይደል እንዴ? ጁሙዐ ወይም ረመዳን ብቻ ተጠብቆ ሽር ጉድ የሚባልበት ድግስ አይደለም፡፡ “የኢስላም ድንጋጌዎች በዙቡኝ” ያላቸውን ሰው “ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ” ብለው አይደል ያመላከቱት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም? ጌታችን እንዲህ ይላል፡ ((… እነዚያ ያመኑት ልቦቻቸውም አላህን በማስታወስ የሚረኩ ናቸው፡፡ አዋጅ! አላህን በማስታወስ (የአማኞች) ልቦች ይረካሉ)) (አረዕድ፡ 28) ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡ ((ጌታውን የሚያስታውስና እና የማያስታውስ ምሳሌ የህያው እና የሙት ምሳሌ ነው)) ቡኻሪና ሙስሊም፡፡ አሁን እኛ ህያዋን ነን ወይስ የቁም ሙት?
የአላህ ሰዎች ሀይላቸውም፣ ምግባቸውም፣ እስትንፋሳቸውም፣… ዚክር ነው፡፡ በአንድ ወቅት ያነበብኩት የኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ ንግግር ትዝ አለኝ፡፡ ካየሁት ቆየሁና ምናልባት በትክክል ላላሰፍረው እችላለሁ፡፡ በግርድፉ ይሄን ይመስላል፡፡ “እንደ ኢብኑ ተይሚያ ዚክር የሚያበዛ አላየሁም፡፡ በአንድ ወቅት ፈጅር ከሰገደ ጀምሮ ዚክር ያረጋል፡፡ ባለበት ሁኔታ ላይ እያለ ሰዐቱ በጣም ሄደ፣ ረፈደ፡፡ በሁኔታው ተገርሜ እያየሁት ነው፡፡ እንደተገረምኩ ገብቶታል፡፡ ዘወር ብሎ እንዲህ አለኝ፡- “ይሄ ምግቤ ነው፡፡ እሱን ካላገኘሁ ብርታት አይኖረኝም”
“ጌታችን ሆይ! አንተን ለማስታወስ፣ አንተን ለማመስገን እንዲሁም አንተን ባማረ መልኩ ለመገዛት አግዘን፡፡”


🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

18 Dec, 07:48


ከጨለመብን በኋላ ጸሐይ መውጣቷን እስካላቆመች ድረስ፤ ተስፋ የሚቆርጥ ሰው ተስፋ ካስቆረጠው ነገር በኋላ ወደፊት ያለው ነገር ደስታ መሆኑን ይወቅ።

مادامتِ الشمسُ تأتي بعدَ ظُلْمَتِنَا
         فليعلمِ اليأسُ أنَّ القادمَ الفرحُ


🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

17 Dec, 17:49


አላሁ አክበር!
~
እስከሚነጋ ወይም እስከሚመሽ ድረስ ዱዐ እንዲደረግልህ ትፈልጋለህ?
ያውም በመልአክ?!
ያውም በ 70 ሺህ መልአክ?
እንግዲያውስ ተከተለኝ።

ዐሊይ ብኑ አቢ ጧሊብ ረዲየላሁ ዐንሁ "የአላህ መልእክተኛን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ አሉ:–

( مَا مِنْ مُسْلِمٍ يَعُودُ مُسْلِمًا غُدْوَةً إلا صَلَّى عَلَيْهِ سَبْعُونَ أَلْفَ مَلَكٍ حَتَّى يُمْسِيَ , وَإِنْ عَادَهُ عَشِيَّةً إلا صَلَّى عَلَيْهِ سَبْعُونَ أَلْفَ مَلَكٍ حَتَّى يُصْبِحَ ، وَكَانَ لَهُ خَرِيفٌ فِي الْجَنَّةِ ).

"አንድ ሙስሊም ጧት ላይ የታመመን ሙስሊም አይጠይቅም በሱ ላይ እስከሚመሽ ድረስ ሰባ ሺ መልአክ ሶለዋት የሚያወርድበት ቢሆን እንጂ። በማታ ከጠየቀውም እስከሚነጋ ድረስ ሰባ ሺ መልአክ ሶላት ቢያወርድበት እንጂ።

አልባኒይ "ሶሒሕ" ብለውታል።

=
የቴሌግራም ቻናል :-


🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

17 Dec, 10:49


እስኪ አንዴ ወደ ውስጥ እንመልከት!

"ኢብሊስ ከሰው ልጅ ሶስት ነገሮችን ካገኘ ሌላ ነገር አይፈልግበትም።

① ሰውየው በራሱ ከተደነቀ፣
② መልካም ስራውን አብዝቶ ከተመለከተ እና
③ ወንጀሎቹን ከረሳ።"

በህጀቱል መጃሊስ ሊ’ብኒ ዐብዲል በር: 125
=



🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

16 Dec, 17:48


መጋገብን ማስተካከል። እራስን ከቦዘኔነት አርቆ በስራ መጥመድ።
(11) ስለዝሙት አደገኝነት፣ ከዝሙት መራቅ አላህ ዘንድ ስላለው ደረጃ ማንበብ፣ ማድመጥ፣ ማስታወስ።

(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 19/2010)


🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

05 Dec, 06:32


በጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ ያላቹ ወንድም እህቶቼ የአላህን ቃል አዳምጡ አስተንትኑ .
የአላህ እርዳታ ቅርብ ነው አላህም ከታጋሾች ጋር ነውና ታገሱ አላህ ያበርታቹ 🤎



https://youtu.be/qPx_txrO5g0?si=yOl3q3HzxWpkYo6R

The Jubair || The ጁበይር

03 Dec, 16:45


ለሴት እህቶቼ ከልቤ በልመናም ጭምር የምመክራችሁ ነገር፤ ፎቷችሁን አትፖስቱ። የፖሰታችሁትንም አጥፉ። በዚህ የፈሳድና የቴክኖሎጂ ዘመን አንድ ቀን በዚህ ድርጊታችሁ ታለቅሳላችሁ፣ ታፍራላችሁ፣ ትፀፀታላችሁ፣ የትዳር ህይዎታችሁና ማኅበራዊ ህይዎታችሁም ሊቃወስ ይችላል። ከዚህ በላይ በዝርዝር መናገር አይጠበቅብኝም። ሐራም ነው ሐላል ነው ብቻ እያልኩ እንዳይመስላችሁ። እንኳን ሐላል ያልሆነውን የተፈቀደ ቢሆን እንኳ ላላሰባችሁት የፈሳድ አላማ ስለሚውል ይቅርባችሁ። አልገባችሁም ምን እንደሚካሄድበት! የገባው በጥቅሻ ይገባዋል! የልጆቻችሁንም ፎቶ አትፖስቱ። ኋላ ምን እንደሚሆኑ አታውቁም። ዛሬ ላይ ለውሳኔ አልደረሱም። እናንተ ክፉ ነገር ባታስቡበትም ኋላ ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም። ኋላ ራሳቸው አድገው ጎልመሰው መፖሰት ይኑርባቸው አይኑርባቸው ይወስናሉ። ዛሬ ፖስታችሁባቸው እነርሱ ኋላ ካልፈለጉ ላንንተም ጸጸት ነው፣ ለነርሱም መሳቀቅ ነው።


||
t.me/MuradTadesse

The Jubair || The ጁበይር

02 Dec, 11:27


እኔ ብዙ ጊዜ ስለ ትዳር ሳወራ በቀልድ መልክ ስለሆነ ነገሮችን ሲሪየስ ስላልወሰዳችኋቸው እንጂ አሁን ላይ ትልቅና አሳሳቢ ከሚባሉ ነገሮች መካከል የሚገባ አጀንዳ ነው።

①ኛ) ፍች እየበዛ ነው።

②ኛ) የፍች ደረጃ ላይ ባይደርሱ እንኳ በብዙ ቤቶች ውስጥ በትዳዳር መጣጣምና ተፋቅሮ መኖር ተመናምኗል።

③ኛ) ከናካቴው ያላገቡና ትዳር የሚፈልጉ ብዙ ናቸው።

④ኛ) በበርካታ ዘመነኛ ፈሳድ ተጠምደው ከትዳር ራሳቸውን ያራቁና በዝሙትና ዘመዶቹ የተለከፉ ቀላል አይደሉም።

ስለዚህ: የተጋቡት ተስማምተው እንዲኖሩ፣ ያላገቡት ያላገቡበትን ምክንያት ፈትሾ እንዲያገቡ በማድረግ በርካታ ደስተኛ ቤተሰብ መመስረት ያስፈልጋል።

ያኔ ልጆቻቸው ለትዳር ሲጠየቁ፤ "እድሜዋ ገና ነው!"፣ "ትምህርቷን ትጨርስ!" ያሉ ወላጆች፣ ወላጅ እሺ ቢልም ልጅ "ትምህርቴን ልጨርስ!" በማለቷ፤ ትምህርት ከተጠናቀቀ በኋላ ቀስ በቀስ ጠያቂው ሲቀንስና ከሆነ ጊዜ በኋላ ከናካቴው ሲጠፋ… እውነት ለመናገር ለአራተኛም ቢሆን በተፈኘ የሚሉ ወላጆችና ልጆች አሉ።

ስለዚህ መስፈርቱን ለሚያሟሉ 2,3,4 ይተግበር። በተለይም የማይረባ ወንድ በሞቅታው ጊዜ አግብቷቸው ሞቅታው ሲበርድ ልጅ አስታቅፎ የተፈቱ እህቶች፣ ባላቸው የሞተባቸው የቲም አሳዳጊዎች  ይገቡ።

ጓደኞቻቸው ስላገቡና ገንዘብ ስላላቸው ብቻ ሌላውን መስፈርት ሳያሟላ 2,3,4 እያገቡ እህቶችን በዳይና በሴት ልጅ ተጫዋች የሆኑ ዋልጌ ወንዶች ይረፉ። በሐላል መሰተር ፈልገው ገንዘብም እያላቸው በፍርሃት ብቻ ከትዳር የታቀቡ የሚገጥማቸው የትዳር አጋር ይፈለግላቸው። በአቅም ማነስ ምክንያት ከትዳር የራቁ ወንዶች መነሻ ድጋፍና ቋሚ ገቢ የሚያገኙበት መንገድ ተመቻችቶ በሐላሉ ይሰተሩ።

በዚህ ዘመን አብዛሃኛው ወጣት ለዝሙት በሚያቀርቡ ነገሮች ዙሪያውን ተከቧል፣ ብዙሃኑ ተለክፏል። ፍቅር ገለመሌ እየተባለ ብዙ ሰው አላስፈላጊ ህይዎት እየመራ ነው። የት ይደርሳሉ ተብለው ተስፋ የተጣለባቸው ወጣቶች በዚህ ተሰናክለው ለራሳቸውም ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ምን ትላላችሁ⁉️

||
t.me/MuradTadesse

The Jubair || The ጁበይር

16 Nov, 10:48


🤌

The Jubair || The ጁበይር

14 Nov, 10:28


ለተረዳው ብዙ ስንቅ አለው በደምብ ይነበብ


«በ 1995 የመጀመርያ ድግሪ ልማር ጅማ ስመጣ የ10 ወር ልጅ ነበረኝ። የዛኔ የዛሬዋ ጅማ 50% ቷ ራሱ አልነበረም።ጅማ ቤተሰቤን ይዠ እንደገባሁ ከተማ ራሀ ሆቴል ከነቤተሰቤ አደርኩ። ጧት ተነስቼ ሚስቴንና ልጄን ሆቴል ትቼ ቆጪ JU አጠገብ ቤት ተከራየሁ። ወደ ሆቴሉ ተመልሼ የፈረስ ጋሪ ይዠ በአጂፕ በኩል ወደ ቆጪ ሻንጣየን እና ቤተሰቤን ጭኘ  ወደ ተከራየሁት መሄድ ጀመርኩ። 

እና ልጄ ሁለት ቀን ስለተጓዘ ደክሞት ነው መሰል ጸጥታ አብዝቶ ነበር። ጋሪው ላይ ወጣንና ነጂው ፈረሱን "ቼ.. ሂእ ሂኢ" ሲለው ልጄ ከት ብሎ ሳቀ። ባለቤቴ ጋር ተያይተን ሳቅ አልን። ጋሪው ነጅ  ደግሞ "ቼ ሲል ፈላው እናቱ እቅፍ ሆኖ ደግሞ ሳቁን ለቀቀው። ከዛ ልቤ ላይ አላህ የጣለውን ጣለና.. ለባለቤቴን "አብሽሪ ይሄ አገር ግጥማችን ነው (ይመቸናል)" አልኳት..ተፋኡሉ አምሮ። እና ዘንድሮ እኔም ፕሮፌሰር ነኝ። ያልጅም 4ኛ አመት ሜድስን ተማሪ ነው።

እና የነገር አለሙ ተፋኡልን እየተባሸርንበት መኖር እንጂ የምን ጨለማ ጨለማ ማየት። ይልቅ በጨለማው ውስጥ ብርሀኑን እየፈለግን በጭላንጭሉ ተስፋ መንቦግቦግ ነው። ብርሀን ባታይ ራሱ አይኔ ታሞ እንጂ ብርሀኑ አለ ብለህ በየቂን መጓዝ ነው። በመሀል ለሚከሰተው አታስብ። ያንተ ድርሻ አይደለም። ዩኒቨርሱ ባለቤት አለው። እንደከጀለ ይገለባብጠዋል።»

©: ፕሮፌሰር ቃልኪዳን ሐሰን




🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

08 Nov, 07:33


ሰሉ ዐለል ሀቢብ 🤍

The Jubair || The ጁበይር

01 Nov, 04:48


ሰሉ ዐለል ሀቢብ 🤍

The Jubair || The ጁበይር

04 Oct, 10:27


ኢሬቻ ኃይማኖታዊ በዓል አይደለም፣ ሺርክ አይደለም ለሚሉ፤ ይህን ምን እንበለው በሏቸው። ቪድዮውን አሰራጩት። ብዙዎች የሚያከብሩት ባለማወቅ ይሆናልና ይህን ሲያዩ የሚታረም አንድ ሰው እንኳ ሊኖር ይችላል።
||
https://t.me/MuradTadesse

The Jubair || The ጁበይር

29 Sep, 15:19


شرح دبرذيت

The Jubair || The ጁበይር

26 Sep, 08:44


«🔹በካፊሮች በዓል እንኳን አደረሳችሁ ማለት ይፈቀዳልን?

    በበአላት ሰሞን በተደጋጋሚ እገሌና እገሌ ላይክ አድርገውታል ከሚለን ፖስቶች መካከል ከፊሎቹ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክቶች ናቸው። ለጌታ መወለድ፣ ለጌታ መሰቀል፣ ለጌታ ሞቶ መነሳት (ትንሳኤና) መሰል ክስተቶች እንኳን አደረሳችሁ ሲባል ሼር ወይም ላይክ የሚያደርጉ ብዙ እህትና ወንድሞችን አስተውያለው። አንዳንዴ በስህተት ሌላ ግዜም ነገሩን እንደቀላል በመውሰድ የሚፈፀም ሊሆን ይችላል። ሆኖም እጅግ ከባድና በአኼራ ዋጋ የሚያስከፍል መዘናጋት ነው!!

    በካፊሮች በአል፤ እንኳን አደረሳችሁ... እንኳን ደስ አላችሁ... እንኳን አብሮ አደረሰን ማለት እነሱን ለማስደሰትም ይሁን ለመመሳሰል ከአላህ ዲን መንሸራተት እና የካፊሮችን ኩፍር የመናገር ስነልቦና መካብ ስለሆነ
ክልክል ነው። መከባበር እና አብሮነትን ለማሳየት ከእምነታችን መንሸራተት አይጠበቅብንም። ዲን ከምንም በላይ ነውና ሸሪዓን መተላለፍ ፍፁም ጥፋት ነው!!

   ፈጣሪ ወለደ ተወለደ የሚለው አስተምህሮ የጥፋትነቱ ክብደት ሰማያትንና ምድርን ሊሰነጥቅ እንደሚቀርብ ቁርአን ይነግረናል። አላህን የሚያስቆጣ ተግባር በመፈፀማቸው እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት ከሙስሊም አይጠበቅም!!

(وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحۡمَـٰنُ وَلَدࣰا * لَّقَدۡ جِئۡتُمۡ شَیۡـًٔا إِدࣰّا *  تَكَادُ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تُ یَتَفَطَّرۡنَ مِنۡهُ وَتَنشَقُّ ٱلۡأَرۡضُ وَتَخِرُّ ٱلۡجِبَالُ هَدًّا *  أَن دَعَوۡا۟ لِلرَّحۡمَـٰنِ وَلَدࣰا *  وَمَا یَنۢبَغِی لِلرَّحۡمَـٰنِ أَن یَتَّخِذَ وَلَدًا *  إِن كُلُّ مَن فِی ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِ إِلَّاۤ ءَاتِی ٱلرَّحۡمَـٰنِ عَبۡدࣰا *  لَّقَدۡ أَحۡصَىٰهُمۡ وَعَدَّهُمۡ عَدࣰّا *  وَكُلُّهُمۡ ءَاتِیهِ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ فَرۡدًا)

አልረሕማንም ልጅን ያዘ (ወለደ)» አሉ፡፡ ከባድ መጥፎን ነገር በእርግጥ አመጣችሁ፡፡ በእርሱ (በንግግራቸው ምክንያት) ሰማያት ሊቀደዱ፣ ምድርም ልትሰነጠቅ፣ ጋራዎችም ተንደው ሊወድቁ ይቃረባሉ፡፡ ለአልረሕማን ልጅ አለው ስለአሉ፡፡ ለአልረሕማን ልጅን መያዝ አይገባውም!! በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ (በትንሣኤ ቀን) ለአልራሕማን ባሪያ ኾነው የሚመጡ እንጂ ሌላ አይደሉም]
Surah Maryam 88 - 95

   ለመሆኑ አንድን ካፊር ለሀይማኖታዊ በአል እንኳን አደረሰህ ስትለው፤ ምን ማለት እንደሆነ ግልፅ አይደለምን?

እንኳን አደረሰህ...
ጌታ ተወልዶ ተሰቅሎ ሞቷል ብለህ ለማወጅ፣ ለመስቀል ለመስገድና  የፈጣሪን ክብር የሚነኩ ንግግሮችን ለመናገር እንኳን በቃህ!

እንኳን አደረሰህ...
ማርያም ፈጣሪዋን ወለደችው፤ በመጠቅለያም ጠቀለለችው እያልክ ለመዘመር እንኳን በቃህ!

የኩፍር ተግባርን ለመከወን ከሆነ የደረሰው ለምንስ እንኳን አብሮ አደረሰን እንላለን?

   እውቁ አሊም ኢብኑል ቀይም ረሂመሁላህ ይህ ተግባር የተከለከለ ስለመሆኑ የኡለማዎች የጋራ አቋም መሆኑን በመጠቆም እንዲህ ብለዋል፤ «ኩፍርን ብቻ በሚያንፀባርቁ የሀይማኖታቸው መገለጫዎች እንኳን አደረሳችሁ...እንኳን ደስ ያለችሁ ማለት ሀራም መሆኑ የሁሉም ሊቃውንት ስምምነት ያለበት ነው።
ለምሳሌ አንድ ሙስሊም በነሱ በዓላትና ፆም ጊዜ፤ «በአሉን የተባረከ ያድርግልህ» ወይም «መልካም የደስታ በአል ያድርግልህ» እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ቢያስተላልፍ፤ ተናጋሪው ከኩፍር ቢድን እንኳ ከባድ ወንጀል ነው የፈፀመው። ይህም፤ ልክ «እንኳን ለመስቀል ሰገድክ» ብሎ ደስታን እንደመግለፅ ነው!

ይህ እንደውም፤ አንድ ሰው ነብስ በማጥፋቱ፣ አልኮል በመጠጣቱ፣ ዝሙት በመፈፀሙና በመሰል ተግባራት እንኳን ደስ ያለህ ከማለት በወንጀልነት የከበደ እና አስቀያሚ ነው። ለኢስላማዊ ድንጋጌዎች ተገቢዉን ክብር የማይሰጡ ብዙ ሰዎች ይህንን ይፈፅማሉ።  ምን ያክል የሚያስጠላ የግባር እንደፈፀሙም አያስተውሉም። ቢድአ፣ ኩፍር እና ወንጀሎች በመፈፀማቸው እንኳን አደረሰህ፣ እንኳን ደስ ያለህ እና መሰል የደስታ መግለጫዎችን ያስተላለፈ፤ እራሱን ለአላህ ቁጣና ጥላቻ የተገባ እንዲሆን የሚያደርግ ምክኒያት ፈፅሟል»  አህካም አህሉዚማህ

   የዘመናችን ፈቂህ ሸይኽ ኡሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ አሉ «ካፊሮችን እንኳን አደረሳችሁ ማለት ኢብኑል ቀይም እንዳለው የዚህን ያክል ከባድ የሆነበት ምክኒያት እነርሱ የሚፈፅሟቸውን የኩፍር መገለጫዎች ማፅደቅ ስለሆነ ነው። ምንም እንኳን ለራሱ ይህንን ኩፍር መፈፀምን ባይወድም እነሱ መፈፀማቸውን ወዷልና። ሙስሊም ደግሞ የኩፍር መገለጫዎችን መውደድም ይሁን ሌሎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ማለት አይፈቀድለትም።»
መጅሙዑ ፈታዋ ወረሳኢል አሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን 3/44 

በተመሳሳይ መልኩ፤ ክሪስማስም ሆነ ሌሎች በአላት ላይ ስጦታ ወይም ፓስት ካርዶችን መለዋወጥ፤ እንዲሁም ማንኛውም ደስታን መግለጫ የሆኑ ነገሮችን መፈፀም በአሉን መካፈል ስለሆነ የተከለከለ ነው!!

   በዚህ ፅሁፍ መጠቆም የፈለኩት ምንም አይነት ማህበራዊ ግንኙነት ሀራም ነው የሚል መልእክት አይደለም። በተለይም ከክርስቲያን እና አይሁዶች ጋር ባለን ማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ የተፈቀዱ ብዙ በመልካም የመኗኗር እሴቶች አሉን።  ሆኖም ሀይማኖታዊ ወሰኖች የሉም ማለት አይደለም። የተፈቀደውን ስንተገብር እንደ ያልተፈቀደ ጋብቻ፣ በአላት ላይ መሳተፍ፣ ለሞቱት የአላህን ማርታ መለመንና ባጠቃላይ በዲን መመሳሰልን ግን በፍፁም አንፈፅምም። ይህንን የእምነትና የሀይማኖት ወሰን መናድ አይቻልም። ማንነታችንን ማክበር፣ ግንኙነታችንን በዲናዊ ገደቦች ማጠር ብሎም አለመሟሟት ለሌሎች ሞራል ዲንና ማንነት ከመጨነቅ ይቀድማል። ዲን ከምንም በላይ ነውና ከመሸማቀቅ እንውጣ። ይህ  የዲናችን መገለጫ እንጂ እንደ ማክረርና ፅንፈኝነት የሚታይ አይደለም። በነገራችን ላይ የአንድ እምነት ተከታይ ከሌሎች ለመቀራረብ ብሎ ከራሱ እምነት ጋር የሚጣላበት ሁኔታ ድሮ ቀርቷል። ሌሎቹም ቢሆኑ ይህ በኛ ሀይማኖት አልፈቀድም እና ይቅርታ ይሉሀል።
(فَلَا تُطِعِ ٱلۡمُكَذِّبِینَ * وَدُّوا۟ لَوۡ تُدۡهِنُ فَیُدۡهِنُونَ * وَلَا تُطِعۡ كُلَّ حَلَّافࣲ مَّهِینٍ)

አስተባባዮችንም አትታዝዙ፡፡ ብትመሳሰላቸውና ቢመሳሰሉህ ተመኙ፡፡
[Surah Al-Qalam 8 - 10]

ወላሁ አዕለም

አላህ ከጥፋት ሁሉ ይጠብቀን!»
         منقول

The Jubair || The ጁበይር

10 Sep, 12:06


መውሊድ በሸሪዓ ሚዛን

የጁሙዓህ ኹጥባህ

በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

©:NesihaTv

The Jubair || The ጁበይር

09 Sep, 12:08


📻 መውሊድ መቼ ተጀመረ?
🎙ሸይኽ ሙሐመድ ወሌ ረሒመሁ'ላህ

©: Hanif Multimedia

The Jubair || The ጁበይር

31 Aug, 09:17


3ቱም ደግሞ የሰውን ልጅ ቀዳሚውን ፍላጎት ከሚይዙ ናቸው።

The Jubair || The ጁበይር

30 Aug, 14:51


https://youtu.be/fi6eE_iWQf8?si=lS68uK0h37rW6mj8

The Jubair || The ጁበይር

17 Aug, 05:42


https://youtu.be/8GuCB49rLCo?si=8C9rEWPkUl_nnpSL

The Jubair || The ጁበይር

16 Aug, 04:33


🔴   ጁምዐችንን ሱረቱል ከህፍ በመቅራት
        እና ሰለዋት በማብዛት እናድምቀው🤍


إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا

አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡

[ሱረቱል-አሕዛብ - 56]

•●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ
      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ 😊

•●° መልካም ጁምዐ 🤍



🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

15 Aug, 16:09


ሚስት ሆይ...
የቤትሽን ምስጢሮች በወሬዎችሽ መሀል የወሬ ማጣፈጫ ላለማድረግ ፣ ሚስጥር እንዳያመልጥሽ ጥንቃቄ አድርጊ!  ጓደኛሽም ልብሸ መቋጠር ያልቻለውን ሚስጥርና ገመና የምትጠብቅልሽ እንዳይመስልሽ..!!
#የትዳር_ህይወት



🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

11 Aug, 10:26


ወዳጆቼ በእነዚህ 8 ጉዳዮች ምክንያት ዱዐችን ተቀባይነት አይኖርም እና  ይህን ቪድዮ አንድ አፍታ በመመልከት እነዚህን 8 ጉዳዮች ሳይረፍድ አሁኑኑ እናስተካክል !


አንድ አፍታ ቪድዮውን እዩትና ቪዲዮው ጠቃሚ ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ አንድን ኸይር ነገር ያመላከተ ሰው ልክ ያ ያመላከተውን ስራ እንደ ሰራው ሰው አይነት አጅር እንደሚያገኝ ነግረውናልና ይህን ቪድዮ አንድ አፍታ  SHARE በማድረግ መልዕክቱ ለብዙ ሰዎች እንዲዳረስ አድርጉ አላህ በዚህ ስራቹ ካሰባቹት በላይ ትልቅ አጅርን ይስጣቹ ! ባረከላሁፊኩም !


🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

03 Aug, 16:50


ወዳጆቼ ያለ አት-ተሒያቱ ወይም ያለ ተሸሁድ ሰላታችን ተቀባይነት የለውም እና ይህን ቪዲዮ አንድ አፍታ በመመልከት የአት-ተሒያቱ አባባላችንን እንፈትሽ !


ይህን ቪዲዮ በቲክቶክ ላይ ከ200ሺ ሰዎች በላይ አይተውታል እንዲሁም ደግሞ ከ21ሺ በላይ ለሆኑ ወዳጅ ዘመዶቻቸውም ሰዎች ሼር አድርገውላቸዋል !


እኛስ ሀባይቢ ለምን አሻራችንን አናሳርፍም አንድ አፍታ ቪድዮውን እዩትና ቪዲዮው ጠቃሚ ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ አንድን ኸይር ነገር ያመላከተ ሰው ልክ ያ ያመላከተውን ስራ እንደ ሰራው ሰው አይነት አጅር እንደሚያገኝ ነግረውናልና ይህን ቪድዮ አንድ አፍታ  SHARE በማድረግ መልዕክቱ ለብዙ ሰዎች እንዲዳረስ አድርጉ አላህ በዚህ ስራቹ ካሰባቹት በላይ ትልቅ አጅርን ይስጣቹ ! ባረከላሁፊኩም !




🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

03 Aug, 12:28


تفسير السعدي

﴿وَلَقَدْ كُذِّبَتْ رُسُلٌ مِنْ قَبْلِكَ فَصَبَرُوا عَلَى مَا كُذِّبُوا وَأُوذُوا حَتَّى أَتَاهُمْ نَصْرُنَا﴾ فاصبر كما صبروا، تظفر كما ظفروا. ﴿وَلَقَدْ جَاءَكَ مِنْ نَبَإِ الْمُرْسَلِينَ﴾ ما به يثبت فؤادك، ويطمئن به قلبك.



🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

28 Jul, 15:28


🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር
       አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍


خُذِ الْعَفْوَ وَأْمُرْ بِالْعُرْفِ وَأَعْرِضْ عَنِ الْجَاهِلِينَ

ገርን ጠባይ ያዝ፡፡ በመልካምም እዘዝ፡፡ ባለጌዎቹንም ተዋቸው፡:

وَإِمَّا يَنزَغَنَّكَ مِنَ الشَّيْطَانِ نَزْغٌ فَاسْتَعِذْ بِاللَّهِ ۚ إِنَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ

ከሰይጣንም (በኩል) ጉትጎታ ቢያገኝህ በአላህ ተጠበቅ፡፡ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነውና፡፡

إِنَّ الَّذِينَ اتَّقَوْا إِذَا مَسَّهُمْ طَائِفٌ مِّنَ الشَّيْطَانِ تَذَكَّرُوا فَإِذَا هُم مُّبْصِرُونَ

እነዚያ የተጠነቀቁት ከሰይጣን የኾነ ዘዋሪ በነካቸው ጊዜ (ጌታቸውን) ይገነዘባሉ፡፡ ወዲያውም እነሱ ተመልካቾች ይኾናሉ፡፡

وَإِخْوَانُهُمْ يَمُدُّونَهُمْ فِي الْغَيِّ ثُمَّ لَا يُقْصِرُونَ

ወንድሞቻቸውም ጥመትን ይጨምሩላቸዋል፤ ከዚያም (እነርሱ) አይገቱም፡፡

.
.
.

በተዓምርም ባልመጣሃቸው ጊዜ (በራስህ) «ለምን አትፈጥራትም» ይላሉ፡፡ ከጌታዬ ወደኔ የተወረደውን ብቻ እከተላለሁ፡፡ ይህ (ቁርኣን) ከጌታችሁ ሲኾን ለሚያምኑ ሕዝቦች መረጃዎችና መምሪያ እዝነትም ነው በላቸው፡፡


[ሱረቱል አዕራፍ : 199-203 ]



•●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ
     ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ 😊

•●° መልካም ምሽት 🤍



🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

28 Jul, 03:24


🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር
       አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍

وَلَوْ تَرَىٰ إِذْ وُقِفُوا عَلَى النَّارِ فَقَالُوا يَا لَيْتَنَا نُرَدُّ وَلَا نُكَذِّبَ بِآيَاتِ رَبِّنَا وَنَكُونَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ

በእሳትም ላይ በተቆሙ ጊዜ ምነው (ወደ ምድረ ዓለም) በተመለስን በጌታችንም አንቀጾች ባላስተባበልን ከምእምናንም በኾንን ዋ ምኞታችን! ባሉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (የሚያሰደነግጥን ነገር ባየህ ነበር)፡፡

بَلْ بَدَا لَهُم مَّا كَانُوا يُخْفُونَ مِن قَبْلُ ۖ وَلَوْ رُدُّوا لَعَادُوا لِمَا نُهُوا عَنْهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ

ይልቁንም ከዚህ በፊት ይደብቁት የነበሩት ሁሉ ለእነርሱ ተገለጸ፡፡ (ወደምድረ ዓለም) በተመለሱም ኖሮ ከእርሱ ወደ ተከለከሉት ነገር በተመለሱ ነበር፡፡ እነሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡

وَقَالُوا إِنْ هِيَ إِلَّا حَيَاتُنَا الدُّنْيَا وَمَا نَحْنُ بِمَبْعُوثِينَ

እርሷም (ሕይወት) «የቅርቢቱ ሕይወታችን እንጅ ሌላ አይደለችም እኛም ተቀስቀቃሾች አይደለንም» አሉ፡፡

.
.
.

[ሱረቱል አንዓም : 27-32]



•●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ
     ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ 😊

•●° መልካም ቀን 🤍

🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

27 Jul, 15:27


🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር
       አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍


كَلَّا إِذَا بَلَغَتِ التَّرَاقِيَ
ንቁ (ነፍስ) ብሪዎችን በደረሰች ጊዜ፤

وَقِيلَ مَنْ ۜ رَاقٍ
«አሻሪው ማነው?» በተባለም ጊዜ፡፡

وَظَنَّ أَنَّهُ الْفِرَاقُ
(ሕመምተኛው) እርሱ (የሰፈረበት ነገር ከዚህ ዓለም) መልለየት መኾኑን ባረጋገጠም ጊዜ፡፡

وَالْتَفَّتِ السَّاقُ بِالسَّاقِ
ባትም በባት በተጣበቀች ጊዜ፡፡

إِلَىٰ رَبِّكَ يَوْمَئِذٍ الْمَسَاقُ
በዚያ ቀን መነዳቱ ወደ ጌታህ (ፍርድ) ነው፡፡

فَلَا صَدَّقَ وَلَا صَلَّىٰ
አላመነምም አልሰገደምም፡፡

وَلَٰكِن كَذَّبَ وَتَوَلَّىٰ
ግን አስተባበለ፤ (ከእምነት) ዞረም፡፡

ثُمَّ ذَهَبَ إِلَىٰ أَهْلِهِ يَتَمَطَّىٰ
ከዚያም እየተንጎባለለ ወደ ቤተሰቡ ኼደ፡፡

أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰ
የምትጠላውን ነገር (አላህ) ያስከትልህ፡፡ ለአንተ ተገቢህም ነው፡፡

ثُمَّ أَوْلَىٰ لَكَ فَأَوْلَىٰ
ከዚያም ጥፋት ይጠጋህ ለአንተ የተገባህም ነው፡፡

أَيَحْسَبُ الْإِنسَانُ أَن يُتْرَكَ سُدًى
ሰው ስድ ኾኖ መትተውን ይጠረጥራልን?

أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِّن مَّنِيٍّ يُمْنَىٰ
የሚፈሰስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?
.
.
.

[ሱረቱል ቂያማህ : 26-40]




•●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ
     ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ 😊

•●° መልካም ምሽት 🤍

🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00

.

The Jubair || The ጁበይር

27 Jul, 03:24


🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር
       አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍

وَهَلْ أَتَاكَ حَدِيثُ مُوسَىٰ
የሙሳም ወሬ በእርግጥ መጥቶሃል፡፡

إِذْ رَأَىٰ نَارًا فَقَالَ لِأَهْلِهِ امْكُثُوا إِنِّي آنَسْتُ نَارًا لَّعَلِّي آتِيكُم مِّنْهَا بِقَبَسٍ أَوْ أَجِدُ عَلَى النَّارِ هُدًى
እሳትን ባየና ለቤተሰቦቹ፡- (እዚህ) «ቆዩ፤ እኔ እሳትን አየሁ፡፡ ከእርሷ ችቦን ላመጣላችሁ፤ ወይም እሳቲቱ ዘንድ መሪን ላገኝ እከጅላለሁ» ባለጊዜ (አስታውስ)፡፡

فَلَمَّا أَتَاهَا نُودِيَ يَا مُوسَىٰ
በመጣትም ጊዜ «ሙሳ ሆይ» በማለት ተጠራ፡፡

إِنِّي أَنَا رَبُّكَ فَاخْلَعْ نَعْلَيْكَ ۖ إِنَّكَ بِالْوَادِ الْمُقَدَّسِ طُوًى
«እኔ ጌታህ እኔ ነኝ መጫሚያዎችህንም አውልቅ፡፡ አንተ በተቀደሰው ሸለቆ በጡዋ ነህና፡፡

وَأَنَا اخْتَرْتُكَ فَاسْتَمِعْ لِمَا يُوحَىٰ
«እኔም መረጥኩህ፤ የሚወረድልህንም ነገር አዳምጥ፡፡

إِنَّنِي أَنَا اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدْنِي وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي
«እኔ አላህ እኔ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፡፡ ሶላትንም (በእርሷ) እኔን ለማውሳት ስገድ፡፡
.
.
.

[ሱረቱ ጣሃ : 9-16]



•●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ
     ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ 😊

•●° መልካም ቀን 🤍

🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00

.

2,403

subscribers

751

photos

288

videos