«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር @abdurhman_oumer Channel on Telegram

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

@abdurhman_oumer


وَالسَّلَامُ عَلَىٰ مَنِ اتَّبَعَ الْهُدَىٰ
« ሰላምም ቀጥተኛውን መንገድ በተከተለ ሰው ላይ ይኹን፡፡ »
[ ሱረቱ ጣሀ - 47 ]
በአላህ ፈቃድ የተለያዩ ዲናዊ ትምህርቶች ይተላለፉበታል!!
http://t.me/Abdurhman_oumer

Abdurhman Oumer አብዱረህማን ዑመር (Amharic)

አብዱረህማን ዑመር ከተለያዩ የትምህርት አስተማሪ ተናገሩ፣ ለእርስዎ ፍቅርና ሃሳብ እና ፍቅር አልቋልም ከሚል አቀባበል የጉዞ መስሪያ ቤት እና በፍቃዱ የተመረጡትን ሰዎች እናውቃለን። በተጨማሪ አስተማሪ ስለ መንግሥታችን እንስከም፣ እና በከለከለ ማህበረሰብ ማምጣት እንላለን። እናቅርብ ሲጨምሩ፣ የነገራችን እና በአላህ መንገድ ያድምጡ፣ እና የናታውያን ሰብሳቢ እናድርጉ። Join የተለያዩ የትምህርት አስተማሪ ሰው Abduhrman Oumer ከታች በቅንጅት እናቀርባለን።

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

24 Oct, 13:10


✏️ነሲሀ ቲቪዎች ወይም የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሴንተሮች ኢኽዋኖች መሆናቸው!!

https://t.me/Abdurhman_oumer/9231
👆
ይህ ኦድዮ ነሲሀ ቲቪዎች ወይም ኢብኑ መስዑድ ሴንተሮች እና እነ ጀይላን እነ ኢብሯሂም ቱፋ አንድ መሆናቸውን በአደባባይ ግልጽ ያደረጉበት ኦድዮ ነው። ኢብሯሂም ቱፋ አንድ ከሆኑ ቀደም እንዳሉ ይገልፃል።

አዩብ ደርባቸው የተባለው ግለሰብ ሱፍይ ነኝ ሰለፍያን ገድለን ቀብረናል አስከማለት የደረሱ የኢኽዋን ቁንጮዎችን እንደት እንደሚሰቃቅላቸው  ተመልከቱ

    የመርከዙ ሠዎች ዛሬ ኢኽዋን ሲሆኑ ወይም ኢኽዋን ጋር ሲተሻሹ ተከትለው ኢኽዋን የሆኑ ሙሪዶቻቸው፤ ገና በሽታው ሲጀምራቸው ይሄን አሁን ያሉበትን አቋማቸውን ግልፅ አድርገውላቸው ቢሆን ኖሮ፤ ተከትለዋቸው አይጠፉም ነበር።
    ግን ቀስ በቀስ በተለያዩ ሲስተሞችና በደራ በእልህ አሟሟቸው መንሀጅ ጋዝ ጋዝ እንዲላቸው አደረጓቸው። የሚጠሉትና የሚዋጉት የሱና ሠዎችን እንዲሆን አደረጓቸው።

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

24 Oct, 12:50


የሱና መሻይኾች በመረጃ የሚያቀርቡትን ምላሽ

በመረጃ መጋፋት አይችሉም።

ባይሆን “አፍንጫ ሲመቱት አይን ያለቅሳል!” እንደሚባለው ያልተባለ እያነሱ ሌላ ቦታ እየሄዱ ያጠለሻሉ። ሰውን ባልሆነ ነገር ቢዚ ያደርጋሉ።

በዚህ ድምፅ ላይ ሸይኽ አብዱል ሓሚድ

በመረጃ
🔺ኢልያስ አህመድ

🔺አዩብ ደርባቸው

🔺ዶክተር ጀይላን


ሙብተዲዕ ናቸው ብለዋል። ጠበቆቻቸው ሌላ ወራዳ ነገር ከመለቃቀም በመረጃ ሞግቱ።

ሸይኹ
ሙመይዓህ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሙመይዓህ የሚለው ቃል በሉጋም በል እንደውም በሐዲስም መረጃ እንዳለው ቁጭ አድርገዋል።

የሱና ሠዎች ያለ አግባብ ሙመይዓህ እንደተባሉም ከስር መሰረቱ ተብራርቷል።

  ➢ እዚህ ሀገር ላይ በዋናነት ሙመይዓዎች እነማን እንደሆኑ ተብራርቷል።

ሙሲር (በጥፋት አካሄዱ ላይ ሳይቶብት የሚዘወትር) ሙብተዲዕ እንደሚባል ብዙ ሠው የሚዘነጋው ጉዳይ ተወስቷል።

👇👇
https://t.me/Abdurhman_oumer/9230

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

24 Oct, 10:34


የመርካቶው እሳት አደጋ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ከጣላቸው ወንድሞቻችን መሀከል  በመልካም ስራው የምናውቀው ወንድማችን Hayder Negash  አንዱ ነው።

እስቲ በምንችለው እናግዘው

ንግድ ባንክ: 1000398663897 
                   ሀይደር ነጋሽ

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

23 Oct, 15:46


የሸርሑ ሱንና ሊልበርበሃሪይ ማብራሪያ

በኡስታዝ በሕሩ ተካ ተጀምሯል
👇👇
https://t.me/medresetulislah?livestream

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

23 Oct, 15:45


የዑምደቱል አህካም ደርስ

በኡስታዝ አቡል ቡኻሪ ተጀምሯል
👇👇
https://t.me/DarASSunnah1444?livestream=24a843ace97380b475

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

22 Oct, 12:07


ወደ ጥመት ባለቤቶች ፊትህን ባዞርክ ጊዜ የሆነ ቅጥፈት ወይም ጥመት ቀምሰህ ትመለሳለህ በዛ የተነሳ ወይ እንደነሱ ትበላሻለህ ወይም ልብህ ታሞ ትመለሳለህ ስለዚህ ተወቃሹ አንተም ጭምር ነህና ራስህን ጠብቅ!
قال ابن مسعود رضي الله عنه: «لا تمكن صاحب هوى من أذنيك فيقذف فيهما داء لا شفاء له».{ذم الكلام للهروي ٢٦٧
አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለት አብዱላህ ኢብኑ መሰዑድ እንዲህ ብሏል፦ {{ከስሜት ባለቤት ንግግር ሁለት ጆሮችህን ጠብቃቸው፣ በነርሱ ውስጥ መድኃኒት የሌለው በሽታ ያስገባባሀልና}} (📚 ዘሙል ከላም ሊል ሀረውይ)

· وقال ابن عباس رضي الله عنه: لا تُجالِس أهل الأهواء؛ فإنَّ مجالستهم ممرضة للقلوب؛ الشريعة للآجُرِّي"
አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለት አብዱላህ ኢብኑ አባስ እንዲህ ይላል፦ {{የስሜት ባለቤቶችን አትቀማምጥ እነሱን ማቀማመጥ ልብን ያሳምማል}} (📚 አሸሪዓ ሊል አጁሪ)

عن علي رضي الله عنه قال : قال رسول الله "من آوى محدثا؛ فعليه لعنة الله والملائكة والناس أجمعين" متفق عليه
አላህ መልካም ሥራቸው ይውደድለት ከዓልይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ በተወራ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ {{"የቢድዓ (የፈጠራ) ባለቤቶችን ያስጠጋን የአላህ ፣ የመላኢካዎችና የሰዎችም እርግማን በሱ ላይ ይሁን"።}} (📚 ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

t.me/Abdurhman_oumer

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

22 Oct, 11:10


አጠር ያለች መልስ የሙመይዐዎች አጨብጫቢ የሆነው የደሴው አቡ ሙዓዝ ሀሰን የኢብኑ ሙነወር ጅራት መሆኑንና ጅህልናውን ቁጭ ያደረገ ምላሽ

እንዲሁም የኢብኑ ሙነወር ፊትና ቀስቃሽነት

እነ ፉአድና መሰሎቻቸው ግልፅ ሙመይዓ ስለመሆናቸው የተቀመጠበት

🎙 በኡስታዝ አቡሂበቲላህ አብደረህማን ሰኢድ አልመርሲይ ሀፊዘሁሏህ

https://t.me/+tbfejxw0IQM3MzA0

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

22 Oct, 07:46


ሶሒሕ ሙስሊም

🎙በዱክቱር ሸይኽ ሑሰይን ሙሐመድ አስሲልጢ
ሀፊዘሁላህ
👇👇
https://t.me/medresetulislah

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

21 Oct, 20:01


ቁርአን ቃሪዕ!

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

21 Oct, 19:55


“ዓፊፍ” ማነው?
👇👇
t.me/Abdurhman_oumer/9219

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

21 Oct, 09:13


የጉራጌው ደዕዋ ሲነሳ ኡስታዝ ባህሩ ተካና አብረው ያሉ መሻይኮች እንዲሁም ወንድሞች ጉራጌ ላይ በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ከባድ የሆነ ስራ እየሰሩ መሆናቸውና ታላቅ የሆነ ለውጥ ማምጣታቸው የሚታወቅ ነው።
  ከብዙ ትግሎቻቸውና አበርክቶዎቻቸውም ውስጥ የሺርኩ ዋና መፍለቂያ ከሆነው ቦታ ቃጥባሬ ላይ ገብተው የተውሒድን ደዕዋ እየሰበኩ ሌሎችንም በርካታ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ አመርቂ ውጤት አምጥተዋል።
  እነኝህ የጉራጌ ተወላጅ ወድሞቻችን በጉራጌ ምድር ላይ በዚህ መልክ ሺርክና ቢድዓን ከመዋጋታቸውም በተጨማሪ በሒክማ በመስለሀ ስም ወደ ኢኽዋንና ወደ ሡፍያ በመዘንበል ከባድ የዲን ማጥፋት ዘመቻ በመክፈት የሚታወቁት “የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ስብስቦች”ን ወይም “የነሲሀ ሰዎች”ን ችግር እየተጋፈጡ ያሉ ጀግኖች ናቸው።
   በመሆኑም ይሄን ለምልሞ የነበረ ዳዕዋ ሽባ ለማድረግ (ለኢኽዋንና ለሱፍያ ለማስረከብ)  የሚጥሩትን እነኝህ “የመርከዝ ኢብኑ መስዑዶች ስብስቦችን" ወይም “የነሲሀ ቲቪ ሰዎችን” ሴራ ምንም ያህል አታላይ ቃላቶችን እየተጠቀሙ ለመሸወድ ቢጣጣሩም ሁሉም ሱና ወዳድ የሆነ ሁሉ ሊጠነቀቅና ከሱና ታጋዮች ጎን ሊቆም ይገባዋል።

አብዱረህማን ዑመር
https://t.me/Abdurhman_oumer/9216

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

20 Oct, 06:29


t.me/Abdurhman_oumer/9212
👆
ገጽ አንድን ለማገኘት

የአላህ ባሪያዎች ሆይ አላህን ፍሩ። ምላሶቻችሁ ባለ ሁለት አፍ ሰይፍ ናቸውና ተጠንቀቁ። ብዙ ሰዎች በተሰባሰቡበት ምላሳቸውን መልቀቅና የሰዎችን ነውር በመከታተል እንዲሁም ያችን (ነውር) በማሰራጨት ላይ ደንታ የላቸውም።
{{በምላሶቻችሁ በምትቅበባሉት ጊዜ ለእናንተም በእርሱ ዕውቀት በሌላችሁ ነገር በአፎቻችሁ በተናገራችሁና እርሱ አላህ ዘንድ ከባድ ኀጢአት ኾኖ ሳለ ቀላል አድርጋችሁ ባሰባችሁት ጊዜ (ከባድ ቅጣት በነካችሁ ነበር)።}} [ ሱረት አል-ኑር፣ 15-16 
ሙስሊም የሌሎቹን ነውር በመተው የራሱን ነውር በማስተካከል ላይ  ሊጠመድ (ሊያያተኩር) ነው የሚገባው። 
በሱና በነሱ መካከል ለመምከር ካልሆነ በስተቀር ማለት ነው። ወሬ እያወሩ  ተቀማምጠው ሳሉ ከሚያወሩት ወሬ ስህተታቸውን (እያወጣ ለማናፈስ) የሚይዝ ከሆነ ይሄ ከትልቁ ሀጢያት ነው። ያሉት ቢሆኑና በዛች (ስህተት) የወደቁ ቢሆኑምኳ ይሄ ከህሜት ነው።

የአላህ ባሮች ሆይ አላህን ፍሩ!! ምላስህ ወይ መልካምን ነገር ይሰበስብልሃል። አላህን በማውሳት፣ አላህን በመታዘዝ ብትጠቀምበት፣ ለበጎ ነገር ብትናገርበርት፣ ወይም መጥፎ ነገር ይሰበስብብሃል። ለመጥፎ ነገር ከተጠቅምክበት። ሐሜት፣ ነገር በማዋሰድ ሀራም የሆኑ ንግግሮችን ከተጠቀምክበት ማለት ነው።
ከብዙ ሰዎች ዘንድ ሀራም ንግግርን ህሜትንና ነገር ማዋሰድን ምን ቀላል አደረገው!?

ሰዎች ሆይ ታላቁን አምላክ አላህን ፍሩ ከምላስ ነውሮች አንዱ በንግግር ላይ መዋሸት መሆኑን እወቁ። ይህም የሙናፊቆች ባህሪ ነው። የአላህ ሶላትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁን እንዲህ አሉ፡- የሙናፊቆች ምልክት ሶስት ነው። ፦ ሲናገር ይዋሻል፣ ቃል ሲገባ ያፈርሳል፣ ተስፋ ሲጣልበት (ሲታመን) ይክዳዋል፣ ሲከራከር ይቀጥፋል፣ ቃል ኪዳን ሲገባም ይክዳል። ከእነዚህ አጸያፊ ባህሪያቶች ውስጥ የመጀመሪያው (መጀመሪያ የተጠቀሰው) በንግግር መዋሸት ነው። ብዙ ሰዎች ለዚህ ጉዳይ ደንታ የላቸውም። በንግግር ጊዜ መዋሸትን እንደ ቀልድ ወይም ሰዎችን እንደማሳቂያ አድርገው ይይዙታል።
በራሱ ላይ የወንጀል ሸክምን እንደሚሸከምና ነፍሱን ለአደጋ እንደሚያጋልጣት አያውቅም። እሱ  ተቀምጦ ሳለ ምንም በማይጠቅመው ንግግር ይዋኛል። ነብዩ (ዓለይሂሶላቱ ወሰላም)
{{የአንድ ሰው እስልምናው ከማማሩ ምልክቱ የማይመለከተውን ነገር መተው ነው።}} ብለዋል። አንድ ሙስሊም በዛ ውስጥ (ለዲኑ) የሚጠቅመውና ለራሱና፣ እንዲሁም ለሙስሊሞች መልካም ነገር ያለበት ነገር ላይ ካልሆነ በስተቀር ምላሱን ይጠብቃል። የላቀው አላህም {{ለሰዎችም መልካምን ተናገሩ፤}} ይላል። [ አል-በቀራህ - 83 ]

የመልካም ዝምታ መጽሐፍ ፒድኤፉን ለማግኘት
👇
t.me/Abdurhman_oumer/6728

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

20 Oct, 06:27


“ምላስን መጠበቅ!”

ከመልካም ዝምታ መጽሐፍ የተወሰደ የሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን የጁሙዓ ኹጥባ ትርጉም

 እናንተ ሰዎች ሆይ የላቀውን አላህ ተጠንቀቁት። ከምላሳችሁ ጠብቁ። ከንግግራችሁ መጨረሻ ተጠንቀቁ። አላህ እንዲህ ብሏል፦ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ፡፡ ሥራዎቻችሁን ለእናንተ ያበጅላችኋልና፡፡ ኀጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምርላችኋል፡፡ አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ፡፡}} [ ሱረቱ አል- አሕዛብ - 70 ]

በሌላ የቁርአን አንቀጽ የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፦
አላህ መልካምን ቃል ሥርዋ (በምድር ውስጥ) የተደላደለች ቅርንጫፍዋም ወደ ሰማይ (የረዘመች) እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ አላየኽምን? ምግቧን (ፍሬዋን) በጌታዋ ፈቃድ በየጊዜው ትሰጣለች። አላህም ለሰዎች ይገሰጹ ዘንድ ምሳሌዎችን ይገልጻል። የመጥፎም ቃል ምሳሌ ከምድር በላይ የተጎለሰሰች ለእርሷ ምንም መደላደል የሌላት እንደኾነች መጥፎ ዛፍ ነው። አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ላይ ያረጋቸዋል። ከሓዲዎችንም (በመካዳቸው ምክንያት ያቺን ቃል) አላህ ያሳስታቸዋል። አላህም የሚሻውን ይሠራል።}}
(ሱረቱ ኢብራሂም፣  24 -27)
ነብዩ (ዓይሰላቱ ወሰላም) {{በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካም ይናገር አሊያም ዝም ይበል። ብለዋል። (እሳቸው) ዓይሰላቱ ወሰላም
{{ሰዎች በፊቶቻቸው ወይም በአፍንጫዎቻቸው እሳት ውስጥ የሚወረወሩት ምላሳቸው ባጨደው (በምላሳቸው ውጤት) አይደለምን?}} ብለዋል።

የአላህ ባሮች ሆይ አላህን ፍሩ። ምላሳችሁን ጠብቁ። ንግግራችሁን መዝኑ። ንግግራችሁ በናንተ ላይ ይቆጠራል። መዝገባችሁ ላይ ይጻፋል።
{{ከቃል ምንም አይናገርም በአጠገቡ ተጠባባቂና ዝግጁ የኾኑ (መላእክት) ያሉበት ቢኾን እንጅ፡፡}}
[ ሱረቱ ቃፍ - 18 ]
ወይም እኛ ምስጢራቸውንና ውይይታቸውን የማንሰማ መኾናችንን ያስባሉን? አይደለም፤ መልክተኞቻችንም እነርሱ ዘንድ ይጽፋሉ፡፡ [ ሱረቱ አል-ዙኽሩፍ - 80 ]

የአላህ ባሮች ሆይ አላህን ፍሩ። እወቁ ንግግራችሁ በናንተ ላይ ይጠበቃል። በሱም ላይ ሒሳብ ትደረጋላችሁ።  (ትተሳሰባላችሁ) መልካም ከሆነ መልካም ፍሬ ያፈራላችኋል።
መልካም ንግግር ወደርሱ ይወጣል፡፡ በጎ ሥራም ከፍ ያደርገዋል፡፡
[ ሱረቱ አል-ፈጢር - 10 ]
መጥፎ ንግግር ከሆነ ነግሞ በማይጠቅምምበት (በትንሳኤ ቀን) ትነድማላችሁ። ከሁሉም በጣም አጸያፊና ከባድ ንግግር ማለት ደግሞ በላቀውና ከፍ ባለው አላህ ላይ ማጋራት (የሺርክ ንግግር) ነው። ከአላህ ውጭ ከሆነ አካል መለመን፣ ከአላህ ውጭ በሆነ አካል እርዳታ መጠየቅ፣ እነኝህ ከሺርክ ቃላቶች ናቸው። ተጠንቀቋቸው።

እንደዚሁም በጣም አስቀያሚ ከሆኑት ቃላት ውስጥ አንዱ ያለ እውቀት በአላህ ላይ መናገር ነው። ይህም ከሺርክ ጋር እኩል ነው። ከሺርክ ጋር እኩል ነው, ወይም ከሺርክ በላይ የሆነ ነው። ታላቁ አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል፡-
{{በርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን (ጣኦት) በአላህ ማጋራታችሁን፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ነው» (ጌታየ እርም ያደረገው) በላቸው።}}
[ ሱረቱ አል-አዕራፍ - 33 ]
ይህ ደግሞ(ያለ እውቀት) ምንም ቁርአናዊይና ሀዲሳዊይ ማስረጃ ሳይኖረው፣ አላህ ይሄን ሀላል (የተፈቀደ) አድርጎታል። ይሄን ደግሞ ሀራም (የተከለከለ) አድርጎታል ማለትን ይመስል ነው። ያለ እውቀት በአላህ ላይ መናገር አይቻልም። የሸሪዓን ህግጋት በመፍቀድና በመከልከል ረገድ በጥልቀት መመርመር ከሚችል እውቀት ካለውና ጉዳዩን መመልከት ከሚችል ሰው በስተቀር  መዋዠቅ አይፈቀድም።

በጣም አስቀያሚ ከሆኑ ቃላቶች መካከል የውሸት ምስክርነት ነው። የውሸት ምስክርነት በታላቁ አምላካችን በአላህ ላይ ከማጋራት (ከሺርክ) ጋር ይመሳሰላል። ( ይህ) ሰዎች የሚዘናጉበት የሆነው። (የውሸት) ምስክርነቱንም ጓደኞቹን፣ ወገኖቹንና ዘመዶቹን የሚያስደስትቱበት ነገር አድርገውታል። ምንም እንኳን ውሸቱን ቢሆንም፣ የሚናገረውን የማያውቅ ቢሆንምኳ በምስክርነት ይረዳቸዋል።  አላህም እንዲህ ብሏል፡-
{{«እነርሱ የሚያውቁ ኾነው በእውነት ከመሰከሩት በስተቀር ምልጃን አይችሉም»}}  [ ሱረቱ አል-ዙኽሩፍ - 86 ]
{{«ባወቅነውም ነገር እንጂ አልመሰከርንም፡፡ ሩቁንም ነገር (ምስጢሩን) ዐዋቂዎች አልነበርንም። አሉ»}} [ ሱረቱ ዩሱፍ - 81 ]

አንድ ሰው በምስክሩ እውነተኛ ካልሆነ (መመስከር) አይቻልለትም። በምስክሩ እውነቱን ሊገልጽ ፈልጎ መሆን አለበት። ስሜቱን ተከትሎ ለመሄድ መሆን የለበትም። እንዲሁም ከአንዱ ሰው ጋር ሆኖ በሌላኛው ላይ በማድላት ማዘንበልልን ፈልጎ መሆን የለበትም።

በሰዎች መካከል ካሉት አስቀያሚ ቃላቶች መካከል አንዱ ነገር ማዋሰድና ህሜት ነው። ህሜት ወንድምህን በሚጠላው መንገድ ማውሳትህ ነው። ወሬ ማዋሰድ ደግሞ በሰዎች መካከል ወሬን ማቀባበልና በመካከላቸው ማቆራረጥና ግንኙነታቸውን ማበላሸት ነው።
ታላቁ አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል {{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ከጥርጣሬ ብዙውን ራቁ፤ ከጥርጣሬ ከፊሉ ኃጢአት ነውና፡፡ ነውርንም አትከታተሉ፡፡ ከፊላችሁም ከፊሉን አይማ፡፡ አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? (መብላቱን) ጠላችሁትም፤ (ሐሜቱንም ጥሉት)፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ነውና።}} [ ሱረቱ አል-ሁጁራት - 12 ]
ታላቁ አምላካችን አሁንም አንዲህ ይላል፦ {{ወራዳንም ሁሉ አትታዘዝ፡፡ ሰውን አነዋሪንና በማሳበቅ ኼያጅን። ለበጎ ነገር በጣም ከልካይን፣ ወሰን አላፊን፣ ኃጢአተኛን። (ሁሉ አትታዘዝ)}} (ሱረቱ አል-ቀለም: 10 - 12)
ህሜትና ነገር ማዋሰድ በሰዎች መካከል ከሚያበላሹ ነገሮች በጣም አጸያፊዎቹ ናቸው። በመካከላቸውም ጠላትነትን ይፈጥራሉ።
እንደዚሁም በሰዎች ላይ መሳለቅም፣ ሰዎችን ማስተናነስም፣ እንዲሁም ስህተታቸውን መከታተልም፣ ሌሎች ሰዎች ዘንድ መጥፎ ስሜት የሚፈጥር ንግግሮቻቸውን ማስተላለፍም (እነዚሁ ሁሉ በጣም አስቀያሚና አጸያፊ ከሆኑ ነገሮች ናቸው።)

የላህ ባሮች ሆይ አላህን ፍሩ! የአላህ መልእክተኛ (ዓለይሂሰላቱ ወሰላም) እንዲህ ብለዋል፦ {{ አንድ ባሪያ ብዙም ግምት ባልሰጣ በሆነች የአላህን ቁጣ በምታስገኝ አንድት ንግግር ይናገራል። በዛች ንግግር ከምሥራቅና ከምዕራብ መካከል ካለው እርቀት በራቀ ወደ ጀሀነም ይወረወራል። አንድ ባሪያ ብዙም ግምት ባልሰጣት በሆነች የአላህን ውደታ በምታስገኝ አንድት ንግግር ይናገራል። አላህ በዛች ደረጃዎችን ከፍ ያደርግለታል።}}
ስለዚህ እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ አላህን ፍሩ! ከምላሳችሁም ተጠንቀቁ ምክንያቱም ምላስ ከአካል ክፍሎች ሁሉ በጣም አደገኛ ነውና በዚህ ምክንያት ሁሉም አካል ምላስን ያስጠነቅቃል።
በኛ ጉዳይ አላህን ፍራ! እኛ ባንተ ስር ነን። አንተ ከተስተካከልክ እኛም እንስተካከላል። አንተ ከተጣመምክ እኛም እንጣመማል ይላሉ}}
ነብያችን (ዓለይሂሰላቱ ወሰላም)  በብዛት ሰዎችን እሳት የሚያስገባ ነገር አፍና ብልት ነው ብለዋል። ይህ ማለትም (በብዛት ሰዎችን እሳት የሚያስገባ ነገር) ምላስ፣ ጸያፍ ንግግር፣ ቆሻሻ ስራ፣ ዝሙት ነው።
አሁንም የአላህ መልእክተኛ (ዓሊይሂሶላቱ ወሰላም)፦ {{በሁለቱ ከንፈሮቹ መካከል ያለውንና በሁሉቱ እግሮቹ መካከል ያለውን በመጠበቅ ቃል የገባልኝ ጀነትን ቃል እገባለታለሁ።}} ብለዋል።

ገጽ ሁለትን ለማግኘት
👇
t.me/Abdurhman_oumer/9212

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

20 Oct, 06:26


በወንድማችን ሙራድ አቡ አስማእ የተቀሩት ኪታቦች የሚገኙበት ሊንክ

https://t.me/+y7htmXLX6yFiYWI0
👆
አልቀዋዒድ ሙስላና ሌሎችም የሚለቀቅበት ሊንክ


https://t.me/+DqiKHDEaSksxMzZk
👆
ተንቢሀትና ሌሎችም የሚለቀቅበት ሊንክ

https://t.me/+qCJIYBZhq7gxZTBk
👆
ኪታቡ ተውሂድ ሊሸይኽ ሷሊህ አልፈውዛንና ሌሎችም የሚለቀቅበት ሊንክ

https://t.me/+oIhWmw0AGjg5MmE0
👆
ኪታቡ ተውሂድ ሊሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ዓብዱልወሀብና ሌሎችም የሚለቀቅበት ሊንክ

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

19 Oct, 19:11


በአላህ ፈቃድ ሌላ ይቀጥላል

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

19 Oct, 19:11


ተጠናቀቀ

«Abdurhman Oumer» አብዱረህማን ዑመር

19 Oct, 18:59


الدرس ٢

12,864

subscribers

1,475

photos

116

videos