ኢማን መልቲሚዲያ @sineislam Channel on Telegram

ኢማን መልቲሚዲያ

@sineislam

<< `በጊዜያቱ እምላለሁ ፤ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው ፤ እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩት ፥ በእውነትም አደራ የተባባሉት ፥ በመታገስም አደራ የተባባሉት ብቻ ሲቀሩ።` >>
ሱረቱል ዐስር፦(1፥3)

https://telega.io/c/sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ (Amharic)

ኢማን መልቲሚዲያ ብለን ኢማንን መልቲሚዲያውን ሊተረጋገን ሲይዝ ጥሪ በልዩነት ለማግኘት ያስችላል። በአሁኑ ሰዓት፣ ሰው ሁሉ በእርግጥ በከሳራ ውስጥ ነው እና እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሠሩትን በእውነት አደራ የተባባሉትን ለአገልግሎት፣ እና በመታገስ አደራ የተባባሉትን ለማቀረን እንዲረዳ አያቆምም። ማንኛውም እሴት ወይም እስከ ሥር ሊኖር ይችላል፣ ድረስ ኢማን መልቲሚዲያ መሲብም ለሚሆኑ ሁሉ እና ለጠበቃኞቹ ስሞች እንዲሆን በስለት ነው። በአገልግሎት፣ በየስራ እና በመሥዋዕት ያለው መሲብ መንስኤዎችን እንዲያሳውቅ እንችላለን።

ኢማን መልቲሚዲያ

20 Nov, 06:03

1. በጣም ብዙ የምትናገር ከሆነ ፤ ትዋሻለህ።

2. በጣም ብዙ የምታስብ ከሆነ ፤ ድብርት ውስጥ ትገባለህ።

3. በጣም ብዙ የምታለቅስ ከሆነ ፤ የአይን እይታህን ታጣዋለህ።

4. በጣም ብዙ የምታፈቅር ከሆነ ፤ ማንነትህ ይጠፋል።

5. በጣም ብዙ ስለሰዎች የምታስብ ከሆነ ፤ ዋጋህን ሰዎች እያጡት ይመጣሉ።

6. በጣም ብዙ የምትጫወት ከሆነ ፤ አብዛኛውን ጊዜ ማንም ከቁምነገር አይቆጥርህም።

7. በጣም ብዙ የምታምን ከሆነ ፤ በሰዎች ትካዳለህ።

8. በጣም ብዙ የምትሰራ ከሆነ ፤ በውጥረት ትሞታለህ።

9. በጣም ብዙ የምትመገብ ከሆነ ፤ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ውስጥ ትገባለህ።

10. በጣም ብዙ እንቅልፍ የምትተኛ ከሆነ ፤ ስራ ፈት ትሆናለህ።

11. በጣም ብዙ ገንዘብ የምታባክን ከሆነ ፤ የወደፊት ነገር ምንም አይኖርህም።

12. በጣም ብዙ ሜክፕ የምትጠቀም ከሆነ ፤ የአንተን ውበት እያጣኋው ትመጣለህ።

13. በጣም ብዙ ነገር የምትመለከት ከሆነ ፤ ትኩረትህን እያጣኸው ትመጣለህ ።

14. በጣም ብዙ ስለ ህይወት የምታስብና የምታሳድድ ከሆነ ፣ ሁሉንም ነገርህን ታጣለህ።

15. በጣም ብዙ ነገር የምትጠብቅ ከሆነ ፤ በጣም ትከፋለህ። በጣም ብዙ አትሁን ምክንያቱም ያ በጣም ብዙ ነገር ብዙ ይጎዳሀልና።

@sineislam
@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

19 Nov, 07:35

20 ምርጥ መልዕክቶች

1. ነገሮች ሲጠኑባችሁ ወደ ሱጁድና ዱዓእ ፍጠኑ እንጂ ብሶትና ለቅሶ አታብዙ፡፡

2. ሁሉም ነገር ይሄዳል፤ ሲሄድ ግን አይመለስም፡፡ ዱዓእ ሲቀር፡፡ ዱዓእ ተስፋን፣ በረከትን፣ ሲሳይን፣ ድልን፣ ስጦታን ይዞ ይመለሳል፡፡

3. በምድር ላይ አንድም ስኬታማ ሰው የለም፡፡ ለወላጆቹ መልካም የመዋል ታሪክ ያለው ቢሆን እንጂ፡፡

4. የሰው ልጅ ሆኖ ከሀሳብ ነፃ የሆነ የለም፡፡ ሆኖም ግን ያለበት ሀገር ዱንያ መሆኗን እያስታወሰ ፈገግ የሚል ብዙ ሰው አለ፡፡

5. ምርጦቹ ጓደኞችህ ዱንያ የሳቀችልህ ቀን አይደናገጡም፡፡ በዞረችብህ ጊዜም አይደሰቱብህም፡፡

6. ግርማ ሞገስን ከሚያጎናጽፉ ነገሮች መካከል ብዙ አለማውራት፤ የፊትን ዉበት ከሚጨምሩ ነገሮች መካከል ፈገግታን ማብዛት ይገኙበታል፡፡

7. የሰው ልጅ ባያምንበትም እንኳ የሚናገርን ሰው ሀሳብ ቢያዳምጥ የሚማረው ነገር ይኖራል፡፡

8. ልጅህን ቁርኣንን አስተምረው፤ ቁርኣን ሁሉንም ነገር ያስተምረዋል፡፡

9. ትላልቅ ሰዎችን አክብሩ፤ ዘመናቸው ባልሆነ ዘመን ውስጥ እየኖሩ ነውና፡፡

10. ሁሉንም ሰው ለማስወደድና ለማርካት አትፍጨርጨር፡፡ በዚህ ጉዳይ ነቢያትም እንኳን አልተሳካላቸውምና፡፡

11. ዉስጥህን ህመም እየተሰማህ ፈገግ የምትል ከሆነ የጥንካሬህ ማሳያ ነው፡፡

12. የሰው ልጅ የሚመዘነው ባለው ነገር ሳይሆን በሚሰጠው ነው፡፡ ፀሐይ እሳት ጭምር አላት ነገርግን ብርሃን ትሠጣለች፤ ፍጥረተ ዓለሙን በብርሃን ትሞላለች፡፡

13. በእናቱ እግር ሥር አገልጋይ ሆኖ የኖረ በሰዎች አናት ላይ ንጉስ ሆኖ ይኖራል፡፡

14. ብዙ በመናገር የማይታወቅ ሰው መናገር ሲጀምር ትኩረት ይስባል፡፡

15. ባመለጠችህ አንዲት ኮከብ አትከፋ፡፡ ሰማይ በከዋክብት የተሞላች ናት፡፡ እሷን ከረሳህ ምናልባት ጨረቃ ትወጣልህ ይሆናል ማን ያውቃል፡፡

16. ከአላህ (ሱ.ወ.) መልካም ነገር እንጂ አላየንም፣ አልሰማንም፡፡ ወደ ቀናው መንገድ መራን፣ ጤና ሰጠን፣ ዕድሜ ሰጠን፣ ቤተሰብ ሰጠን፣ ብዙ ብዙ ነገር ሰጠን፡፡

17. ልንረሳቸው ብንፈልግ እንኳን ዉስጣችን የማይረሳቸው ብዙ ኃጢአቶችን ይዘን እየዞርን ነው፡፡

18. የሐዘን ባቡር ፉርጎው ቢበዛም ቢረዝምም የመጨረሻ ፌርማታው ደስታ ስለመሆኑ  አንጠራጠር፡፡

19. ዕድሜ ዕድል ነው፡፡ አንዳንድ  ደግሞ ዕድሜ ነው፡፡ ዕድሜህ ሊሆን የሚችልን ዕድል በቀላሉ አታሳልፍ፡፡

20. የተጃጃለ ሰው ሁኔታው እንደ በራሪ አዕዋፍ ነው፡፡ ከፍ ባለ ቁጥር ሰውን አሳንሶ ይመለከታል፡፡

@sineislam
@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

17 Nov, 08:41

ሁለት ወጣቶች ከበረሃው አቅጣጫ አንድን ሰው አንጠልጥለው ለዳኝነት ዑመር ሸንጎ ፊት አቆሙት።

"ምንድን ነው?" አለ ዑመር ግራ ተጋብቶ
"የሙእሚኖች መሪ ሆይ ይህ ሰው አባታችንን ገሎብናል ተገቢው ቅጣት ይፈፀምልን" አሉ
ዑመር ወደ ሰውየው ዞሮ "እውነት አባታቸውን ገድለሀልን?" ሲል ጠየቀው።

"አዎ" አለ።
"ለምን ገደልከው?!"

"ግመሉን እየነዳ አጥሬን ዘልቆ ገባ ከግቢዬ ውጣ ብለው አልሰማም አልወጣም አለኝ። ለማባረር ትንሽዬ ድንጋይ አንስቼ ብወረውር አናቱ መሐል ላይ አርፎ በዛው ምክንያት ሞተ" አለ። በዚህ ጊዜ ዑመር ውሳኔ አስተላለፈ። ቂሳስ ነውና እንዲገደል ወሰነ።

ሰውዬው ፈቃድ ጠይቆ መናገር ጀመረ
"የሙእሚን መሪ ሆይ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረው ጌታ እለምንሀለው ሚስቴና ልጆቼን በምድረ በዳው በረሀ ብቻቸውን ትቻቸዋለሁ ተሰናብቻቸው እንድመለስ ፍቀድልኝ። ከአላህ በታች እኔ እንጂ ማንም ዘመድ የላቸውም" አለ
"ወደ ቤተሰብህ ሄደህ እስክትመለስ ተያዥ ዋስህ ማነው?"

"የማውቀውም የሚያውቀኝም ማንም የለም" አለ ዓይኖቹን እያስለመለመ

ስሙንም፣ ቤቱንም፣ ጎሣውንም የሚያውቅ የለምና ሁሉም ሰው ዝም ጭጭ አለ። ሰውየው ቢቀር የሞት ውሳኔው ተያዡ ላይ ተፈፃሚ ስለሚሆን አንገትን በሰይፍ ለሚያስቀነጥስ ዋስትና ማን ይድፈር?!

ልጆቹ በረሃብ እየሞቱ ይግደለው ወይስ ያለ ተያዥ ይልቀቀው የሚያደርገው ጠፍቶት ግራ በመጋባት አንገቱን አቀረቀረ። አባታቸው ወደተገደለባቸው ልጆች ዞሮ አውፍ ይሉት ዘንድ ቢጠይቅ በፍፁም አባታችንን የገደለ መገደል አለበት ብለውት ይባስ ተጨነቀ።

"እናንተ ሰዎች ሆይ!" በማለት የተሰበሰበውን ህዝብ ተጣራ "ለዚህ ሰው ዋስ የሚሆነው ማነው?" አለ ከፍ ባለ ድምፁ።  አቡ ዘር አል-ጊፋሪ ተነሳና "የሙእሚን መሪ ሆይ! እኔ ተያዥ ዋስ እሆነዋለሁ" አለ

"ገዳይ ነው ባይመለስ የሞት ፍርድ ውሳኔው ተፈፃሚነቱ ባንተ ላይ እንደሚረጋገጥ ታውቃለህ አይደል?!" አለ ዑመር
"አዎ አውቃለሁ"

"እንዴት ለማታውቀው ሰው ዋስ ለመሆን ደፈርክ"

"የአማኝነት ገፅታዊ ምልክቶችን ከፊቱ ላይ አነበብኩ በአላህም ፈቃድ ተመልሶ ይመጣል ኢንሻ አላህ"

ዑመርም "አቡ ዘር ሆይ ከሦስት ቀን በላይ ከዘገየ እንደማልተውህ እወቅ" እያለ ሰውየውን ወደቤተሰቡ እንዲሄድ ፈቀደ። ልጆቹንና ቤተሰቡን እንዲሰናበት ከዛም የቅጣቱ ውሳኔ ተግባራዊ ይደረግበት ዘንድ የሶስት ቀን ጊዜ ገደብ ተሰጠው።

  ወደ ቤተሰቦቹ ዘንድ አቅንቶ ባለቤቱን አተኩሮ አያያት ቁም ነገር ያለው ወሬ እያወራችው ቢሆንም እሱ ግን ቀልቡ ተሰርቋል። ንፋሱ ሐዘኑን ሊያባብስ በስሱ የሚነፍስ አቀጣጣይ ማራገቢያ ይመስላል ሽው ሽው ይላል።
"የት ሄድክ" አለችው  ሽምጥ የጋለበውን ቀልቡን አይታ። ከሐሳቡ ሳይንደረደር ወርዶ በእንባ እየታጀበ የገጠመውን ሁሉ በዝርዝር ነገራት።

ዕንባዋ ኩልል ብሎ እየፈሰሰ  "ፀሐይ ንዳዷን ስትለቅ ውላ መጥለቂያዋ ሲቃረብ ውበትን፣ መስከንንና ደብዘዝ ብሎ መጉላትን ታሳያለች ጠዋት ልንሞቃት ወጥተን እናንጋጣለን ቀትር ሲቃረብ እናማራለን አብሽር አላህ የተሻለ አለው" ብላ አፅናንታ በእቅፏ አስተኛችው።

ከሦስት ቀናት በኋላ ዑመር ቀጠሮውን አልዘነጋም። የአስር ሰላት እንደተሰገደ ከመዲና መስጂድ ሚንበር ላይ ሆኖ  አስሰላቱል ጃሚዓ ሲል ተጣሪው ተጣራ። ሰው ሁሉ ወደሜዳው ወጥቶ ተሰበሰበ። አባታቸው የተገደለባቸው ሁለቱ ልጆች በቦታቸው ተሰየሙ። አቡ ዘርም ከፊት ለፊት ተቀመጠ።

"ሰውየው የታል?!" አለ ዑመር ወደ አቡዘር ፊቱን አቅጣጭቶ ዓይን ዓይኑን እየተመለከተ።
  "አላውቅም" አለ አቡዘር።

ሰሐቦች በተፈጠረው ነገር ደንግጠዋል።  ክስተቱን የሚያይ ሁሉ ከንፈሩን ይመጣል። አንዳንዱ አንገቱን በሃዘን ይነቀንቃል። እውነት ነው አቡ ዘር ዑመር ዘንድ ተወዳጅ ቢሆንም የአላህ ህግ ግን ከሁሉም ነገር በላይ ነው።

ፀሐይ ያለወትሮዋ እንደምትጠልቅ ነገር ወደ መግቢያዋ በፍጥነት ቁልቁል በመንደርደር ላይ ሳለች አንድ ሰው እየጋለበ ወደስብስቡ ገሰገሰ "አላሁ አክበር" የሚሉ ድምፆች ከወዲህ ወዲያ እየተሰሙ አካባቢው በተክቢራ ተናጠ።
"መኖርያህንም አድራሻህንም አናውቅም ነበር እንዴት መጣህ?!" አሉት ዑመር።

"በአላህ እምላለሁ የፈጠረኝን ጌታ በእጅጉ እፈራለሁ ሙስሊሞች የገቡትን ቃል መሙላት አቆሙ ታማኝነታቸው ተረሳ እንዳይባል ሰዓቴን ሳላዛንፍ ሚስትና ልጆቼን ለአላህ ትቼ ይኸው ልገድል መጥቻለሁ" አለ ሳግ እየተናነቀው።
"አንተስ እንዴት ዋስ ሆንከው" አሉ ዑመር ወደ አቡ ዘር ዞረው ከዓይናቸው ላይ ዕንባቸውን እየጠረጉ።  "መልካም ሰዎች ከሙስሊሞች ጠፍተዋል እንዳይባል ሰግቼ" አለ አቡዘር።
ወደ ሁለቱ ወጣቶች "እናንተስ ምን ትላላችሁ?" ብሎ ጥያቄውን ሲሰነዝር

ተንሰቅስቀው እያለቀሱ ያ አሚሩል ሙዕሚኒን "ይቅር ብለነዋል እኛስ ብንሆን አውፍና ይቅርታ ከሙስሊሞች ዘንድ ጠፋ መባልን እንዴት አንስጋ?!" አሉ። ዑመር ፂሙ እስኪርስ እያነባ አካባቢውን ለቆ ወደ ቤቱ አቀና።

ታማኝነት የሙስሊሞች መገለጫ መሆኑን እናስታውስ ላመኑት ይጠቅማልና ማስታወስ

@sineislam
@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

07 Nov, 10:33

New arrivals
Available on hand
Dm @sayby
Call 0938146260
Price 3000-3500

ኢማን መልቲሚዲያ

07 Nov, 08:00

Kurulus osman ክፍል 279/280 👇

https://t.me/+aRuL1lLIwLFlNmE0

ኢማን መልቲሚዲያ

03 Nov, 16:14

Khimar+abaya

3500 birr

በፈለጉት size እና ከለር አማራጭ አሉት

ከ6 ፍሬ በላይ ለሚገዙ ደንበኞቻችን ቅናሽ አለን
እንዲሁም ክፍለሀገር ላሉ ደንበኞች እንልካለን

ይደውሉ

0954872000

And for more information
Contact us on telegram below
@elhud1

https://t.me/Eluscollection
Dm @elhud1

ኢማን መልቲሚዲያ

02 Nov, 04:42

ሁለት ወጣቶች ከበረሃው አቅጣጫ አንድን ሰው አንጠልጥለው ለዳኝነት ዑመር ሸንጎ ፊት አቆሙት።

"ምንድን ነው?" አለ ዑመር ግራ ተጋብቶ
"የሙእሚኖች መሪ ሆይ ይህ ሰው አባታችንን ገሎብናል ተገቢው ቅጣት ይፈፀምልን" አሉ
ዑመር ወደ ሰውየው ዞሮ "እውነት አባታቸውን ገድለሀልን?" ሲል ጠየቀው።

"አዎ" አለ።
"ለምን ገደልከው?!"

"ግመሉን እየነዳ አጥሬን ዘልቆ ገባ ከግቢዬ ውጣ ብለው አልሰማም አልወጣም አለኝ። ለማባረር ትንሽዬ ድንጋይ አንስቼ ብወረውር አናቱ መሐል ላይ አርፎ በዛው ምክንያት ሞተ" አለ። በዚህ ጊዜ ዑመር ውሳኔ አስተላለፈ። ቂሳስ ነውና እንዲገደል ወሰነ።

ሰውዬው ፈቃድ ጠይቆ መናገር ጀመረ
"የሙእሚን መሪ ሆይ ሰማያትንና ምድርን በፈጠረው ጌታ እለምንሀለው ሚስቴና ልጆቼን በምድረ በዳው በረሀ ብቻቸውን ትቻቸዋለሁ ተሰናብቻቸው እንድመለስ ፍቀድልኝ። ከአላህ በታች እኔ እንጂ ማንም ዘመድ የላቸውም" አለ
"ወደ ቤተሰብህ ሄደህ እስክትመለስ ተያዥ ዋስህ ማነው?"

"የማውቀውም የሚያውቀኝም ማንም የለም" አለ ዓይኖቹን እያስለመለመ

ስሙንም፣ ቤቱንም፣ ጎሣውንም የሚያውቅ የለምና ሁሉም ሰው ዝም ጭጭ አለ። ሰውየው ቢቀር የሞት ውሳኔው ተያዡ ላይ ተፈፃሚ ስለሚሆን አንገትን በሰይፍ ለሚያስቀነጥስ ዋስትና ማን ይድፈር?!

ልጆቹ በረሃብ እየሞቱ ይግደለው ወይስ ያለ ተያዥ ይልቀቀው የሚያደርገው ጠፍቶት ግራ በመጋባት አንገቱን አቀረቀረ። አባታቸው ወደተገደለባቸው ልጆች ዞሮ አውፍ ይሉት ዘንድ ቢጠይቅ በፍፁም አባታችንን የገደለ መገደል አለበት ብለውት ይባስ ተጨነቀ።

"እናንተ ሰዎች ሆይ!" በማለት የተሰበሰበውን ህዝብ ተጣራ "ለዚህ ሰው ዋስ የሚሆነው ማነው?" አለ ከፍ ባለ ድምፁ።  አቡ ዘር አል-ጊፋሪ ተነሳና "የሙእሚን መሪ ሆይ! እኔ ተያዥ ዋስ እሆነዋለሁ" አለ

"ገዳይ ነው ባይመለስ የሞት ፍርድ ውሳኔው ተፈፃሚነቱ ባንተ ላይ እንደሚረጋገጥ ታውቃለህ አይደል?!" አለ ዑመር
"አዎ አውቃለሁ"

"እንዴት ለማታውቀው ሰው ዋስ ለመሆን ደፈርክ"

"የአማኝነት ገፅታዊ ምልክቶችን ከፊቱ ላይ አነበብኩ በአላህም ፈቃድ ተመልሶ ይመጣል ኢንሻ አላህ"

ዑመርም "አቡ ዘር ሆይ ከሦስት ቀን በላይ ከዘገየ እንደማልተውህ እወቅ" እያለ ሰውየውን ወደቤተሰቡ እንዲሄድ ፈቀደ። ልጆቹንና ቤተሰቡን እንዲሰናበት ከዛም የቅጣቱ ውሳኔ ተግባራዊ ይደረግበት ዘንድ የሶስት ቀን ጊዜ ገደብ ተሰጠው።

  ወደ ቤተሰቦቹ ዘንድ አቅንቶ ባለቤቱን አተኩሮ አያያት ቁም ነገር ያለው ወሬ እያወራችው ቢሆንም እሱ ግን ቀልቡ ተሰርቋል። ንፋሱ ሐዘኑን ሊያባብስ በስሱ የሚነፍስ አቀጣጣይ ማራገቢያ ይመስላል ሽው ሽው ይላል።
"የት ሄድክ" አለችው  ሽምጥ የጋለበውን ቀልቡን አይታ። ከሐሳቡ ሳይንደረደር ወርዶ በእንባ እየታጀበ የገጠመውን ሁሉ በዝርዝር ነገራት።

ዕንባዋ ኩልል ብሎ እየፈሰሰ  "ፀሐይ ንዳዷን ስትለቅ ውላ መጥለቂያዋ ሲቃረብ ውበትን፣ መስከንንና ደብዘዝ ብሎ መጉላትን ታሳያለች ጠዋት ልንሞቃት ወጥተን እናንጋጣለን ቀትር ሲቃረብ እናማራለን አብሽር አላህ የተሻለ አለው" ብላ አፅናንታ በእቅፏ አስተኛችው።

ከሦስት ቀናት በኋላ ዑመር ቀጠሮውን አልዘነጋም። የአስር ሰላት እንደተሰገደ ከመዲና መስጂድ ሚንበር ላይ ሆኖ  አስሰላቱል ጃሚዓ ሲል ተጣሪው ተጣራ። ሰው ሁሉ ወደሜዳው ወጥቶ ተሰበሰበ። አባታቸው የተገደለባቸው ሁለቱ ልጆች በቦታቸው ተሰየሙ። አቡ ዘርም ከፊት ለፊት ተቀመጠ።

"ሰውየው የታል?!" አለ ዑመር ወደ አቡዘር ፊቱን አቅጣጭቶ ዓይን ዓይኑን እየተመለከተ።
  "አላውቅም" አለ አቡዘር።

ሰሐቦች በተፈጠረው ነገር ደንግጠዋል።  ክስተቱን የሚያይ ሁሉ ከንፈሩን ይመጣል። አንዳንዱ አንገቱን በሃዘን ይነቀንቃል። እውነት ነው አቡ ዘር ዑመር ዘንድ ተወዳጅ ቢሆንም የአላህ ህግ ግን ከሁሉም ነገር በላይ ነው።

ፀሐይ ያለወትሮዋ እንደምትጠልቅ ነገር ወደ መግቢያዋ በፍጥነት ቁልቁል በመንደርደር ላይ ሳለች አንድ ሰው እየጋለበ ወደስብስቡ ገሰገሰ "አላሁ አክበር" የሚሉ ድምፆች ከወዲህ ወዲያ እየተሰሙ አካባቢው በተክቢራ ተናጠ።
"መኖርያህንም አድራሻህንም አናውቅም ነበር እንዴት መጣህ?!" አሉት ዑመር።

"በአላህ እምላለሁ የፈጠረኝን ጌታ በእጅጉ እፈራለሁ ሙስሊሞች የገቡትን ቃል መሙላት አቆሙ ታማኝነታቸው ተረሳ እንዳይባል ሰዓቴን ሳላዛንፍ ሚስትና ልጆቼን ለአላህ ትቼ ይኸው ልገድል መጥቻለሁ" አለ ሳግ እየተናነቀው።
"አንተስ እንዴት ዋስ ሆንከው" አሉ ዑመር ወደ አቡ ዘር ዞረው ከዓይናቸው ላይ ዕንባቸውን እየጠረጉ።  "መልካም ሰዎች ከሙስሊሞች ጠፍተዋል እንዳይባል ሰግቼ" አለ አቡዘር።
ወደ ሁለቱ ወጣቶች "እናንተስ ምን ትላላችሁ?" ብሎ ጥያቄውን ሲሰነዝር

ተንሰቅስቀው እያለቀሱ ያ አሚሩል ሙዕሚኒን "ይቅር ብለነዋል እኛስ ብንሆን አውፍና ይቅርታ ከሙስሊሞች ዘንድ ጠፋ መባልን እንዴት አንስጋ?!" አሉ። ዑመር ፂሙ እስኪርስ እያነባ አካባቢውን ለቆ ወደ ቤቱ አቀና።

ታማኝነት የሙስሊሞች መገለጫ መሆኑን እናስታውስ ላመኑት ይጠቅማልና ማስታወስ

@sineislam
@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

29 Oct, 10:48

online ቂርአት መቅራት የምትፈልጉ እህት ወንድሞቼ ሳይሞላባቹ ቶሎ ተመዝገቡ የምንቀበለዉ ጥቂት ተማሪ ነዉ ይፍጠኑ ለመመዝገብ👇👇👇
              @AbdurehimK55

ኢማን መልቲሚዲያ

29 Oct, 10:47

   ቁርዐንን በቀላሉ በኦላይን  ተምረዉ ዉጤታማ መሆን ከፈለጉ አሁኑኑ ይመዝገቡ።

ለመመዝገብ እባክዎን በዚ bot ይመዝገቡ👇👇

https://t.me/Wahdatul_Bot

ትምህርቶቻችን በነዚህ ቀናቶች ይሰጣሉ፦

ሰኞ፣
ማክሰኞ፣
እሮብ፣
አርብ እና
ቅዳሜ (ከምሽቱ 2:30 ይጀምራል እና ከጥዋቱ 12:30 ይጀምራል)።

  የእኛ የቁርአን ትምህርት ፕሮግራማችን እነዚህን     ያካትታል፣
ነዘር
ተጅዊድ
ሒፍዝ እና
ቃዒደቱ-ን-ኑራኒያ

(የእኛ የቁርዓን ትምህርት ፕሮግራማችን የክፍያ መጠን በወር 400 ብር ነው)።

ለበለጠ መረጃ በቴሌግራም  Abdurahim: (https://t.me/AbdurehimK55) (https://t.me/Wahdatul_Bot )ሊያገኙን ይችላሉ።

ኢማን መልቲሚዲያ

20 Oct, 19:06

ሙስሊም ከሆንክ/ሽ ይሄ ጥያቄ 👆🏾ራሳችሁን ጠይቁ 👆🏾

@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

06 Oct, 18:07

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ

✍️.......🦋روحي🦋ነኝ

ውድና የተከበራቹ የላቀው አላህ ሱብሀነሁ ወተአላህ ፍጥረት ውድ ባሪያዎች እንዴት ናቹልኝ??

እኔ አልሀምዱሊላህ ደናናኝ ምስጋና ለአለማቱ ፈጣሪ ለሆነው አላህ ጥራት ልቅና ንግስና ክብር ለሱ የተገባ ይሁን 🤲

አንድ ነገር ላስቸግራቹ ነበር ?
አፍ በሉኝ እኔ እስካሁን እዚህ ግሩፕ ለይ ስቆይ በቃላት አጠቃቀምም  በንግግርም ምናልባት አስቀይሜያቹ ቀልባቹን ሰብሬም ከሆነ .
የሰው ልጅ ነኝና እንዳንዴ ሰው ስንሆን ሳናውቅም ይሁን አውቀን እናጠፋለን (እንሳሳታለን )  ከሰው ልጅ ስህተት ከብረት ዝገት አይታጣምና እኔም ካጠፋው አላህ አፍ እንዲለን እናንተም እኔንለአላህ ብላቹ  አፍ በሉኝ እኔ አፍ ብያቹሀለው ..!!

እናም ለምትወዱንኝ አላህ ይውደዳቹ ያክብራቹ እፍ ላላቹኝም አላህ ወንጀላቹን ሁሉ ይማርላቹ አላህ ይጠብቃቹ ከይራቹን ያብዛላቹ 🤲

እና አላህ በከይር ያገናኘን ምናልባት ካልተመለስኩም እዚ ማለትም ከኦን ከጠፋው ሀጃ አጋጥሞኝ ይሆናል ምናልባትም ሩሄ ከኔ ተለይታ ይሆናልና ለአላህ ስትሉ ዱአ አድርጌልኝ አደራ በዱአቹ አትርሱኝ አልረሳቹም ኢንሻ አላህ
ለአላህ ብዬ ነው የምወዳቹ ሙስሊም እህት ወንድሞቼ አላህ ያቆይልኝ በከይር ሀያታቹን በአፍያ ያርዝምልኝ

ጀዛኩሙላሁ ከይር ለሁላቹም

ፊ አማኒላህ
ወሰላሙ አለኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ

ኢማን መልቲሚዲያ

06 Oct, 11:12

🍁በመስኮት ለገባች
አንዲት ትንሽ ጨረር..

🍁የሰው ልጅ ዘንግቷል
የእውነቱን ሀገር!!
 
✍️.......🦋روحي🦋

@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

05 Oct, 18:30

🫵ሰው ሆይ በደንብ አድርገህ ስማኝ ልብህን ሰተህ አድምጠኝ 👂

👉በጎዳህ ሰው አትዘን
👉ጥሎህ በሄደም ሰው አትከፋ
👉በሰበረህም ቂም አትያዝ
👉ባሳዘነህም አትዘንበት
👉ባሳመመህ ሰውም አትበሳጭ

🫳ምክኛቱም እንደነሱ የወደደህ ፣ ያሰበልህ፣ ያስደሰተህ ፣ያጠነከረህ የለም !!

🤌ለምን መሰለህ እነሱ ባያስከፉህ፣ ባይሰብሩህ ፣ባያስደብሩህ ፣ባያሳምሙህ፣ ባያሳዝኑህ መች ትጠነክር ነበር ⁉️

🫳መች ይቆርጥልህ ነበር እእ?
🫴 ስለ ራስህ መኖር ማሰብ እራስህን ማዳመጥ መት ትጀምር ነበርነፃነህን መች ይፋ ታወጣ ነበር ??

🫴ስለዚ የጎዱህን ለመጉዳት ከማሰብ አስበህላቸው እንዳጠነከሩህ ሰብረውህ ሊሄዱ አስበው እንደ ተጠገንክ አንዳስከፉክ ሲያስቡ ደስተኛ እንድትሆን እንዳደረጉ አሳያቸው ❗️

✍️.......🦋روحي🦋
@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

04 Oct, 18:06

🍁"አምስት ነገሮችን ከአምስት ነገሮች በፊት ተጠቀምባቸው።

☝️የአላህ መልእክተኛ
.اللهم  صل وسلم علي نبينا محمد وعلى
آله وصحبه أجمعين .
እንድህ ብለዋል
⓵ ወጣትነትህን ከማርጀትክ በፊት
⓶ ጤንነትህን ከመታምህ በፊት
⓷ ሀብትህን ከመደህየትህ በፊት
⓸ ትርፍ ጌዜህን ከመጨናነቅህ በፊት
⓹ ህይወትህን ከመሞትህ በፊት

✍️.......🦋روحي🦋
@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

03 Oct, 18:46

ከመናገርህ በፊት አስብ ቃላት ከመሰንዘርህ በፊት መዝን ምክኛቱም የተናገርከው ነገር የሰውን ልብ ሊጎዳ ይችላል !!
ምናልባት ይቅርታ ብለን የነሱን ይቅርታ ልናገኝ እንችላለን ግን ይቅርታ ነገሩ እንድንተወው እንጂ ወደነበረበት አይመልስም !!
የፈሰሰ አይታፈስ ትላንት አይመለስ ከመናገርቻን በፊ እናስብ ብለን መለስ !

                       🦋Ruhi🦋......✍️

@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

01 Oct, 12:45

🍁ከብዙ ጥሩ ፊቶች 1 መልካም ልብ ይበልጣል🫀

🍁ስለዚ ከመልክም ይልቅ መልካምነት ውበት አለው 🥀

                       🦋Ruhi🦋......✍️

@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

01 Oct, 03:35

2:07
ጣፋጭ ቲላዋ🎧

                       🦋Ruhi🦋......✍️

@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

01 Oct, 03:31

🥀የትም መሄጃ በሌለህ በሱ ምድር ላይ እየኖርክ ወንጀል ስትሰራ ያይሃል። ወደሱ እስክትመለስ ጊዜ ሰጥቶህ ኃጢኣትህን ይደብቅልሃል። ከዚያም ለተውበት ይወፍቅህና ይቅር ይልሃል። በተውበትህም ይደሰታል። ኢስቲግፋር ስታደርግ ላንተ ያለው ውዴታ ይጨምራል። ክፉ ስራህን ወደበጎ ሀሰናት ይቅይርልሃል።

🥀☝️እሱ የላቀ የሆነው «አዛኙ ጌታህ አላህ ነውና!»
...

🥀🥀ሰባሀል ከይር ??

                       🦋Ruhi🦋......✍️

@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

30 Sep, 17:43

💜 ሞት መስተካከልህን አይጠብቅም
ተስተካከልና ሞትን ጠብቀው ።

🦋Ruhi🦋......✍️

@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

29 Sep, 18:13

🥀አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላህ

ውድ @sineislam ቤተሰብ እንዴት ዋላቹልኝ

ኢማን መልቲሚዲያ

29 Sep, 16:00

🍁በአላህ ከሚተማመኑት ያድርገን 🤲

🌗መሽቶ መንጋቱአይቀርምና በአላህ ለይ ተስፋ አትቁረጥ እርግጠኛ ሁን 🥀

🦋Ruhi🦋......✍️

@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

29 Sep, 13:01

🍁ከብረት ምርኩዝ የሰው ምርኩዝ ይበልጣ❤️‍🩹

🦋Ruhi🦋......✍️

@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

29 Sep, 11:50

🍁 🦋ለውዲቷ እህቴ 🦋ምክር ከኔ አንደበት  🥀

🍁ወንዶችን ወደማይሆን መንገድ ወደማይሆን ፍቅር 🫶 እትወስውሻቸው ።

🫸ማለት አንቺ አለባበስሽ ስርአት ከሌለው የወንድምሽን ቀልብ ምትሰርቂ ከሆነ  አላህ እንድትሸፍኚው ያዘዘሽን ውበት በገሀድ አደባባይ ለይ ለምን ታወጫለሽ

⭕️ማንም አያግባውም ስለኔ አለባበስ  እኔ ለመፈተን ብዬ አለበስኩም ማን እየኝ  ውደደኝ አለው  ......ወዘተረፈ  ብለሽ የምትይው ❗️

ላ ኡክቲ ወሏሂ ተሳስተሻል አንቺ አስበሽ የለበስሽውን አላህ ያውቃል

🫸ግን እንዲ እንድትለብሺ እንድትገላለጪ ማን ፈቀደልሽ

👀አልታይም ብትይም የሚስብ አለባበስ ለብሰሽ ወተሽ ማንም አያየኝም ማለት አትችይም

👉 ምክኛቱም አለባበስሽም ሆነ ነገረ ስራሽ ያስታውቃል ለመታየት ወንምሽን ለመፈተን እንደሆነ ስለዚ አድቢ 🫷👇

🫴ዘመን አመጣሽ ፋሽን ተከትለሽ የለበስሽው ልብስሽ ወላሂ ነገ አሱ ነው ወደ አሳት የሚሰድሽ‼️ አጉል ጓደኝነት🫂 በማይሆ በተራ ተግባር ላይ ትቀየመኛለች ሼም ነው ይህን ባለብስ ብለሽ አታሳ
🗣
🤏ያቺ የማይሆነውን ልብስ ያምርብሻል ደሞ ኖርማል ነው ልበሽ ብላ ያለችሽ❗️

አስገድዳሽ አላለበሰችሽም ሀሳብ ሰጠችሽ እንጂ.. በሷ አታማክኚ ተረዳሽ ሀቢብቲ ⁉️

🫲🫱 ነገ አላህ ፊት ስትቆሚ እሷም በስራዋ አንቺም በስራሽ ነው ምትጠየቁት።
🫳 ስለዚ ለዱንያ ስራሽ አታጥፊ ስትባይ ሰበብ ጓደኛሽንም ማንንም ምክኛት አደርድሪ ነገ አላህ ፊት እኔ ነኝ አው እንደዛ ያልኳት ብላ ከእሳት አታድንሽም ነቃ በይ ውቢቷ🫵‼️

🚷የተላጠ ሙዝ መሆኑ ቀርቶብሽ የሱፐር ማርኬቱን ያን የታሸገው ሲያዩትም ሚያምረውን ውብ ተፈላጊ ሁኚ እንጂማ ፈላጊ አቱኚ የኔ ውድ ሀቢበቲ ስለምወድሽ❤️‍🩹 ነው ይህን የምመክርሽ 🤌

🥀ለውቢቷ ለልበ ብርቱዋ ለቆንጆዋ ሁሉም ሚቀናባት በስብእናዋ በዛ ሀያእ ባለው አለባበስ በአደቧ ና በስነ ምግባሯ የሁሉን ቀልብ ለምትገዛዋ ለተከበረችው ለምወዳት ለሆነችው እህቴ ነው ይሄን የምመክረው ላንቺ 🫵አው አሁን የምታነቢዋ 👀ልዩኮ ነሽ እኔም በጣም ነው ምወድሽ 🥀

                           🦋Ruhi🦋......✍️

@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

29 Sep, 10:12

🍁💦በጣም ብዙ በሴት ፍቅር የምርም ያበዱ ወንዶችን ተመልክቻለሁ።
ሴት ግን በጭራሽ አጋጥሞኝም አያውቅ።ለምን እንዳንተ ሞኝ ስላልሆነች!

🫵አንተ ግን ምስኪን አፍቃሪ ነህ አበድክላት ...<ወደድኳት ወደደችኝ በስተመጨረሻም የሚሻላትን አገባች ...ብቻዬን ተወችኝ> በሚል ሰበብ የሚያብዱ ብዙ ናቸው።

🍁ወንድዬ የኔ የዋህ እባክህ ለእናትህ ለቤተሠብህ በዙሪያህ ላሉ ሁሉ ተስፋ ነህ። በማይረባ ነገር አትክሸፍ።እርሷ ካገኘችውና ከምታስበው በላይ ምርጥ ወንድ እስክትሆን በፀጥታ ስራ ።አሁን ግዜው ይዞ የመገኘት ነው ወዳጄ ልቤ በርታ 👌

🍁كن قوي لي اجلك  
🍁ብለዋል አረቦቹም።
🥂🥂ቺርስ በየዋህነት ለገበርካቸው ንፁህ ፍቅርና ለተከዳው ውብ ታማኝነትህ።

      🍁ምክሩ ለወንድሞቸነው🫵 👳
🫵🧕ሴቶች ባላየ እለፉ🖐

🍁ደግሞ አላህንም ፍሩ ወንድሞቻችንን አታሰቃዩ

   👂👂👂ይሰማል አ⁉️

🦋روحي🦋......✍️

@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

29 Sep, 06:52

🍁ወደ አላህ ልቡን ስብር አድርጎ
ከተጠጋ...

☝️አላህ ይጠግንለታል
🥀🥀

🦋روحي🦋......✍️
@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

29 Sep, 06:05

🍁ምስጋና ለፈጠረን ☝️

🍁የጭንቅ ምሽቱን አሳልፎን የዛሬን  ብርሀ ላሳየን ☝️

🍁ቀናችንን ቃሉን አዳምጠን እንጀምር ከይር ሰምተን ከይር ለናገር እንሞክር 🗣

🫵ሰባሀል ከይር🖐

🦋روحي🦋......✍️
@sineislam

ኢማን መልቲሚዲያ

28 Sep, 18:03

🥀ሁሉም ለከይር ነው 🫀

@sineislam
🦋روحي🦋......✍️

31,680

subscribers

455

photos

96

videos