☪AHLEL MUSLIM☪ @ahlelmuslims Channel on Telegram

AHLEL MUSLIM

@ahlelmuslims


ኡማውን ማገዝ ለሚፈልግ 👇👇👇

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000598346748
Ahlel muslim social & charity organization.

https://t.me/ahlelmuslim1

አንድ ኡማ~አንድ ሰውነት

☪ AHLEL MUSLIM ☪ (Amharic)

ኡማውን ማገዝ ለሚፈልግ 👇👇👇nnከአማርኛ ወይም ከሌሎች ቋንቋዎች የተመረጠ በመንገዴ እና ያለፉትን በቀዝቃዛ ድምጽ በእንቅስቃሴ ገጽታችን ለመግባት ወደ ቡሌቭቅ ነፃነት ይመለሱ።nn'Ahlel Muslim' ከተማ እና ገንዘብ መረጃዎች አንድ ኡማ መንገድ ያሳያቸው የንግድ አባሎች፣ ለዘላቂ አገልግ ቋንቋ እና ልዩ ተነባባባባባዮች መሆን የታለው የኢትዮጵያ አገልግሎት እንዴት ለሚስክሩት እና ለሚተማመንበት የንግድ ሁለት አገልግሎትን ማስተባበር ይችላል።nnበትምህርት ለማደማር የተፈረመበት 'Ahlel Muslim' በTelegram እንዴት እንደሚስክሩ እንከላከል። በዚህ ኡማ በእንቅስቃሴ ስለመረጡ አገልግሎት ስለመዘጋጀት እና ስለመዝናኛችን ማከናወን ለምንወደው አልተሳሳተም። በዚህ ኡማ በመንገድ ከአማርኛ በላይ በተለያዩ የኢትዮጵያ ንግድ ላይ መረጃዎችን ይከታቱ።nnአካሉ ለመመልከት ለማስተወወር ወደ ቡጌቭኵ ሼት ለመላከከት ለሚስኩ ኡማም ይምረጡ።

AHLEL MUSLIM

21 Nov, 03:25


🗝
فَاصْبِرْ صَبْرًا جَمِيلًا

( አል-መዓሪጅ - 5)
መልካምንም ትዕግስት ታገሥ፡፡

🗝
🎧 Al-Ma'arij

🎙Moutasem Al-Hameedy

AHLEL MUSLIM

20 Nov, 16:18


ራስህን በጨለማ ተከበህ ባገኘህ ጊዜ ተስፋ አትቁረጥ ..ይህ መጨረሻው ነው በሚል እሳቤ በጨለማ ውስጥ ነፍስህን አትቅበር ። ከከረረ ጨለማ ኋላ ብርሀን እንደሚከተል ሁሌም አትዘንጋ...መተንፈስ እስከቻልክ ድረስ ተስፋ ማድረግንም ቻልበት .... ጀግናው ይህንንም ታልፈዋለህ !

(ባለዕዳው)

AHLEL MUSLIM

19 Nov, 13:59


ስለኒቃብ ለመጨረሻ ጊዜ አንድ ነገር ልበል አፉ በሉኝና🙌

"ኒቃብ ዝም ብሎ አይለበስም ...ኒቃብ ያለ እውቀት አይለበስም ...እንዴት ኒቃብ ለብሳ መጥፎ ስራ ትሰራለች ....ኒቃቢስት አይደለች እንዴት ..ለምን ...ኡኡኡ"

ወገኖቼ ኒቃብ መልበስ ማለት መመነን አይደለም ... ገዳም መግባትና አለምን መጣል አይደለም ኒቃብ የለበሰች ሴት ኖርማል ሂጃብ ከለበሰች ሴት የምትለየው ኒቃብ በመልበሷ ብቻ ነው ። ኒቃብ የሆነ የኢማን ደረጃ ስለተደረሰ የሚለበስ የተለየ ልብስ አይደለም ...ኒቃብ የለበሰች ሴት ትሳሳታለች...ትወድቃለች ! ስንወቅስ ከልብሱ ጋር ማያያዙን እናቁም ከሚሊየን ስህተተኞች አስሩ ኒቃቢስት ቢሆኑ በነሱ ላይ ኡኡ ማለት ሌላ ነገር ያስጠረጥራል 👐

እና ያለእውቀት አይለበስም የምትሉ ደሞ ራሳቹን ማታለል አቁማቹ ልበሱ...ከዛ ዲናቹን እወቁ ....እስከዚህ ድረስ ቀላል ነው🙂

ያለበሳቹም ሂጃባቹን አደራ ❤️
[ባለዕዳው]

AHLEL MUSLIM

19 Nov, 03:34


መሆን ያለበት ሁሉ እየሆነ ቀጥሏል ...ብዙ ጊዜ የኛ ፍላጎት በመሆን መስመር ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም ...ፍላጎቶቻችን ሁሉ የመሳካት እድላቸው ሰፊ ቢሆን ኖሮ ህይወታችን እጅግ የተጠላለፈ ይሆን ነበር ። ትላንት ፈልገን ማጣታችን ለዛሬው እድያ ትልቁ ሰበብ ይሆናል ...ትላንት ብናገኝ ዛሬ ልናገኝ የሚገባንን ነገር እናጣ ይሆን ነበር ።
እናም ተቀባይነት ላላገኘው ዱዓችን...ፈልገን ላጣነው.. ቀምረን ለወደቅነው ውደቀታችን ሁሉ ማመስገን ይገባናል ።


አልሃምዱሊላህ !

AHLEL MUSLIM

18 Nov, 17:00


🌃

AHLEL MUSLIM

18 Nov, 14:36


በማታደርጉት እና በማትሰጡት ነገር ለሰዎች ተስፋ አትስጡ ። ሁኔታችሁን እየቀያየራቹ በሰዎች ተስፋ ላይ አትጫወቱ ...የማትሰጡትን አታሳዩ ...የማታደርጉትን ቃል አትግቡ ።

መኖራቸው በተስፋ ላይ ብቻ የተንጠለጠለ ብዙ የደከሙ ነፍሶች አሉና ተጠንቀቁላቸው ።

AHLEL MUSLIM

18 Nov, 03:51


ያለፈውን እስከያዘው ነገር እርሳው ፤ ባለፉ ነገሮች ላይ መጠመድ እብደት ነው ።
ስለወደፊቱም አትጠበብ ፤ ምክንያቱም መጪው ከማይታየው ነው ። እስኪመጣ ድረስ አትጨነቅለት ።

" ጧት ላይ ሆነህ ማታን አትጠብቅ ፤ ማታ ላይ ሆነህ ጧትን አትጠብቅ " ረሱል ሰ.ዐ.ወ

የምን ሀዘን!

AHLEL MUSLIM

17 Nov, 17:58


ምናልባትም ላደረግነው ዱዓ ምላሽ አላገኘን ይሆናል ግን ደግሞ ለሰራነው ወንጀልም ቅጣት አልተቀበልንም!

AHLEL MUSLIM

17 Nov, 15:29


ብዙ የሚወዱህ ሰዎች አሉ...ስትደሰት አብረውህ ይደሰታሉ ..ስታገኝ ይፈነድቃሉ ...ስትታመም ያስታምሙሀል ስትቸገር ያቅማቸውን ለመርዳት ይሞክራሉ ። ግን ብዙዎች በዚህ ነገር ውስጥ የሚያልፉት ያልፋል በሚል እምነት ነው ...ህመምህ እንደማይድን ሲያውቁ ቀስ በቀስ ይሸሻሉ...መቸገርህ የጠና ጊዜና...አወዳደቅህ ክፉኛ ሆኖ መነሳትህን ሲጠራጠሩ ቀስ ብለው ያፈገፍጋሉ ።  እነሱ የሚያውቁት እንደሚወዷቹ ሁሌም አብረዋቹ እንደሚሆኑ ነበር .....ግን በቃ ይህ የሰው'ነት እጣ ነው።

ጋዛን ተመልከት በቢሊየን የሚቆጠር አፍቃሪ አላት ..በቢሊየን የሚቆጠር ወዳጅ አላት ስላለፈው እንቁ ታሪኳ እያነሳ የሚያነባ እልፍ ሰዉ አላት ...አሁን ግን ማን አላት ? የወደቀች ጊዜ....ችግሩ የጠናባት ጊዜ ከአጠገቧ ከጥቂት ጀግኖች ውጪ ማን አላት ? ማንም !
ባንተ ህይወት ውስጥም  የሚፈጠረው ይህ ነው ...በጥቂት አብሪዎች የአለምን ጨለማ ለመግፈፍ አትታገል አላህ ከመረጣቸው ጥቂቶች ውጪ አለም እንደዚያ ናት ! 

ላንተ ያለኸው አንተና አንተ ብቻ ነህና !
በል ወደአላህ ተጠጋ .....ላንቺም ነው 🙂


[ባለዕዳው]

AHLEL MUSLIM

17 Nov, 03:32


🌅

AHLEL MUSLIM

16 Nov, 16:54


ህመምህ እንዴት ጠንካራ መሆን እንዳለብህ እንዲያስተምርህ ፍቀድለት🙌

AHLEL MUSLIM

16 Nov, 15:54


ትላንትሽን ብዙ ሰዎች አበላሽተውት ይሆናል ጠንካራ ስለሆንሽ ግን ያ ትላንት አልፏል።

ዛሬ ግን የራስሽ ነው በዛሬሽ ላይ የማንንም ውሳኔ አትጠብቂ ወሳኟ አንቺ ነሽ የማንንም እርዳታ እንደማትሺ እና እንደሁሌው ለራስሽ እራስሽ እንደምትበቂ አሳዪ በፍፁም አንዲት ዘለላ እምባ ....እሱ ሽንፈት ነው ሃዘኑ በርትቶ መቋቋም ቢያቅትሽ እንኳን ተደብቀሽ እስኪወጣልሽ አልቅሺ ከዛ ግን ሰዎች ፊት ፈገግ በይ...

ደካማ ጎንሽን ካሳየሽ የሚሳለቅብሽ ብዙ ነው! ማንም ምንም ቢል ከመንገድሽ ላፍታ እንዳትቆሚ እየሄድሽ ስሚያቸው አደናቅፈው ቢጥሉሽ እን'ኳ ከነሱ ጋ ቆመሽ በመሟገት ጊዜሽን አታጥፊ አፈርሽን አራግፈሽ እርምጃሽን ቀጥይ ....
እንዲሰብሩሽ አትፍቀጂላቸው!!
.
.
      ©️

AHLEL MUSLIM

16 Nov, 03:41


ስህተት ላይ ያልወደቅን የነበረው፣ ሃራምን የራቅን ይመስለን የነበረው፣ ፀያፍን የተፀየፍን መስሎን የነበረው •••••ጌታችን ስላልፈተነን እንደነበር
እየቆየ_ነው_የሚገባን።

AMD k

AHLEL MUSLIM

15 Nov, 15:39


አንድን ሰው መጉዳት ልክ ድንጋይ ወደ ውቅያኖስ እንደመወርወር ቀላል ነው፣ነገር ግን ድንጋዩ ምን ያህል እንደጠለቀ መቼም አታውቅም

©️

AHLEL MUSLIM

15 Nov, 06:43


ወተት ከተበላሸ እርጎ ይሆናል!... እርጎ ከወተት የበለጠ ዋጋ ያለው ነው። በጣም የከፋ ከሆነ ወደ አይብ ይቀየራል...አይብ ከሁለቱም እርጎ እና ወተት የበለጠ ዋጋ ያለው ነው... እና የወይን ጭማቂ ወደ ጎምዛዛነት ከተለወጠ ወደ ወይን ጠጅ ይለወጣል...ይህም ከወይኑ ጭማቂ የበለጠ ውድ ነው። ስህተት ስለሰራህ መጥፎ አይደለህም!...

ክሪስቶፈር ኮሎምበስ አሜሪካን እንዲያገኝ ያደረገው የአሰሳ ስህተት ሰርቷል። የአሌክሳንደር ፍሌሚንግ ስህተት ፔኒሲሊን እንዲፈጥር አድርጎታል። ስህተቶችህ እንዲያሳዝኑህ አትፍቀድ። ፍጹም የሚያደርገው ልምምድ አይደለም። ፍፁም የሚያደርገው ከስህተታችን የተማርናቸው ስህተቶች ናቸው


©

AHLEL MUSLIM

15 Nov, 03:39


ጁምዓ ነው ....
📿📿📿📿📿📿📿📿📿📿
እከሌ የእከሌ ልጅ
ባንቱ ላይ ሰለዋት አውርዷል ተብሎ
ስምህ የዓለማቱ ነቢይ ﷺ ፊት
መነሳቱ ምነኛ ያማረ ነው….

اللهم صلِ و سلم  على سيدنا محمد ﷺ 💚
መልካም ጁማዓ 🥰
በዱአችሁ 🥰

AHLEL MUSLIM

14 Nov, 15:34


ጦርነት፣ ድካም፣ ርሐብ፣ መፈናቀል፣ ቤተሰብን በሞት ማጣት ተደራርበው አደከሙት። ከሰሜን ጋዛ ሰርጥ ረጅም ርቀት በእግሩ ተጉዞ ከወገቡ ተጎንብሶ ሻንጣውን ተደግፎ አረፍ አለ።
ወንድሞቼ አላህ ከእናንተ ጋር ይሁን


   Mahi mahiso

AHLEL MUSLIM

14 Nov, 12:46


ያረብ 🤲

AHLEL MUSLIM

14 Nov, 03:22


የተስፋ ገመድ….

• ግማሽ ተምር ከጀሀነም እሣት የሚጠብቀን ከሆነ፣

• ምጽዋት የጌታችንን ቁጣ የምታበርድልን ከሆነ፣

• ዉዱእ ባደረግን ቁጥር ወንጀላችንን የሚረግፍልን ከሆነ፣

• አላህን ስናወሳ አላህ የሚያወሳን ከሆነ፣

• ወንድሞችን ስንዘይር መላእክት ዱዓእ የሚያደርጉልን ከሆነ፣

• ሲዋክ አላህ (ሱ.ወ.) ዘንድ የሚያስወድደን ከሆነ፣

• አንድ መልካም ሥራ በአሥር የሚባዛልን ከሆነ፣

• መልካም ንግግር ምጽዋት ከሆነ ፣

• አላህን በጠረጠርነው ቦታ ላይ የምናገኘው ከሆነ፣
• …

ታዲያ ለምን  እንዘናጋለን !
… ከጀነት  በብዙ ርቀት ላይ ነው ለነው ብለን ለምን እንሰጋለን!
ወደ ጀነት ለመራመድስ ለምን እንፈራለን ….
በሉ በተስፋ እንጓዝ….

ሶባሐል ኸይር !
Abx

AHLEL MUSLIM

13 Nov, 16:35


በመስጠት ውስጥ ካለው በበለጠ እርካታ....ሌሎችን በማስደሰት ውስጥ ካለው በበለጠ ደስታ የትም የለም ። እኔነት ጠባብ መንገድ ነው ... ድብርት ...ወናነት እና ትርጉም የሌለው ህይወት ከዚህ ጠባብ መንገድ የተገኙ መጥፎ መሳፈሪያዎች ናቸው ። እመኑኝ የሌሎችን ቁስል በማከም ውስጥ፤ የሌሎችን ሸክም በማቅለል ውስጥ ..ሌሎችን በመርዳት ውስጥ የመኖር ጣዕም አለ ። ለሌሎች ፍቅር በመስጠት ውስጥ ተስፋ አለ ...ለሌሎች በመኖር ውስጥ መኖር አለ !

14,797

subscribers

1,576

photos

417

videos