በትኛውም ቦታ ለመስራት ዝግጁ ነኝ።
በትግል ውስጥ ከላይ ከታች የሚለው ስሜት አይሰጠኝም ።ዋናው ትግሉን ለማሸነፍ ጠጠር እየጣልሁ ነው ወይ የሚለው ነው።የየትኛውም ታጋይ ህልሙ ትጉሉን ማሸነፉ ብቻ ነው።
ወደላይም ወደታችም አይደለም የሄድሁት አሁንም እዚያው ትግል ላይ መሆኔ ብቻ ነው የሚሰማኝ።
በክርስትና እምነት ያለውን የሰጠ እንጅ ብዙ የሰጠ አይልም ። በናሳ ታሪክም አንድ የሚነገር ታሪክ አለ '' እኔ የማፀዳው እናንተ ህዋ ላይ ለመታደርጉት ጉዞ አእምሯችሁ እና ጤናችሁ እንዲጠበቅ ነው።'' በማለት ለህዋ ምርምሩ ድርሻ ያላት መሆኑን የፅዳት ሰራተኛይት ገልፃለች።
በፋኖ ትግልም የትም ላይ ያለን ታጋዮች ውሃ የሚቀዳም፣ የሚጋግርም ፣ጋንታ የሚመራም ፣ድርጅት የሚመራም እኩል ነው። ሁሉም አላማው ይህን መከረኛ ህዝብ ከሞትና ስቃይ ነፃ አውጥቶ የሀገር ባለቤት አድርጎ ማየት እንጅ የግል ጉዳዩን ለማሳካት አይደለም።
ስለዚህ በኔ ሹመት የተደሰታችሁም ይሁን የከፋችሁ እኔ አሁንም የተለየ ቦታ የለኝም ትናንት እንደታገልሁት ዛሬም እየታገልሁ ነው ምንም የተለየ ነገር የለውም። ድርጅቴ አምኖ ባስቀመጠኝ በየትኛውም ቦታ ለመስራት ዝግጁነኝ። መርህ አሰራር ማክበር ከዚህ ይጀምራል።
የአማራ ፋኖ በጎጃም አምኖ የሰጠኝን ይህን ከባድ ሃላፊነት ለመወጣት ያቅሜን ሁሉ የማደርግ መሆኑን እገልፃለሁ።
ፅናት ፣ ትዕግሥት ፣እምነት ፣ እውነት ።
ፅና!!!!!
እስቲበል አለሙ ዘሪሁን
https://t.me/Beteamharavoice