የሶማሊያ መንግስት የበረራ ክልከላውን ያሳለፈው ከጁባላንድ ክልል ያጋጠመውን ፖለቲካዊ ተቃውሞ ተከትሎ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ምንጮችን ጠቅሶ ኢስት አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ጁባላንድን በበላይነት ለመቆጣጠር መሞከሩን ተከትሎ የመንግስት ወታደሮች በደቡብ ምስራቅ ጁባላንድ እያሰፈረ ይገኛል፡፡
የሶማሊያ አየር መንገድ ወታደሮቹን ወደ ጁባላንድ ለማስፈር የተሰጠውን ትዕዛዝ እንደተቃወመ የተገለፀ ሲሆን፤ የሶማሊያ መንግስት በክልሉ በረራ እንደይደረጉ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
የጁባላንድ ተቀዋሚ ፓርቲ መሪ እና የቀድሞው የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አሊ ካየር÷ የፌዴራል መንግስት ወደ ጁባላንድ የሚደረጉ በረራዎችን መከልከሉ ተገቢ ያልሆነ የግዴለሽነት ውሳኔ እንደሆነ ገልጸዋል።
የፖለቲካ ተንታኞች የሶማሊያ መንግስት በጁባላንድ በረራ እንዳይደረግ ክልከላ መጣሉ ግዛቷን በመነጠል ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ መሰረቶችን ለማዳከም ያለመ እንደሆነ ተናግረዋል።
ውሳኔውን ተከትሎም ስትራቴጂክ ወደ ሆነችው የኪስማዮ ከተማ የሚደረጉ የትራንስፖርት አገልገሎቶች የደህንነት ስጋት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡
የጁባላንድ ክልል የፌዴራሉ መንግስት ከህገ-መንግስት ውጪ ጣልቃ በመግባቱ የተነሳ በመካከላቸው ከፍተኛ አለመግባባት መፈጠሩ ይታወቃል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L