አንከር ሚዲያ Anchor Media @ankwar_media Channel on Telegram

አንከር ሚዲያ Anchor Media

@ankwar_media


አንከር ሚዲያ Anchor Media (Amharic)

አንከር ሚዲያ Anchor Media በአማርኛ ሊንክ የተማሪ የህዝብ መረጃ፣ ሕዝብ እና መረጃና ተግባራዊ መረጃን ሊመጣ የሚችል የተአምራቱ ነን። አንከር ሚዲያ Anchor Media ከዝርዝረኛ ቀናት ጋር በአንከር ሚዲያ መረጃ ፈቃዱን በማገኘት ሁኔታን ማስወስ ነው። የተማሪ የህዝብ መረጃዎችን ከፍተኛ እና እናምናለን። በተጨማሪም መረጃ በዚህ ቦታ ያሉትን የህዝብ መረጃዎችን ለመለየት ያስችለላል። ስለዚህ አንከር ሚዲያ Anchor Mediaን በተጨማሪም ቦታ ሊንድን በመመልከት ለመመልከት ሃሚንግ በዚህ ሊንክ ላይ በታላቅ ዘገባዎች ለመሄድ አንጋራት አሉን። አንከር ሚዲያ Anchor Media ወደ ከተማ ጊዜ ከአንተ ጋር ከተለያዩ ተማሪ የህዝብ መረጃዎች ይጠቀሙ። ይቅርታ!

አንከር ሚዲያ Anchor Media

02 Nov, 19:05


🔴🔴🔴የቀድሞው የወያኔው ጠ/ሚ ንግግር ባደረገ ቁጥር ደም የሚያፈላ ስለነበር ከ 2 ደቂቃ በላይ ማየት አልችልም ነበር ። በተለይም ከ ምርጫ 97 በኋላ ። የአሁኑ የአረመኔ የበሻሻው ደላላ እንዲሁ። የአሁኑ የምድር ጉድ እውቀትም ፣ እሴትም፣ መርህም አልባ እስመሳይ፣ አሳይ መሲህ ወራዳ ቆሻሻ ጭምር በመሆኑ ቋቅ የሚያደርግ ፣ የሚያቅለሸልሽ ነው። መሳይ መኮንን በፌቢ ገጹ የጻፈው የአብዛኛውን የኢትዮጵያ ህዝብ ስሜት የሚገልጽ ይመስለኛል ። ---ለጤንነቴና ለምቾቴ ስል ከዚህ ሰው ንግግር ራሴን ቆጥቤአለሁ። የትላንቱ ግን መዓት አይደል እንዴ ጎበዝ? ለፕሮግራም የምትሆን ቁርጥራጭ ቪድዮዎችን ነበር የተከታተልኳቸው። እየቆየ የሚላኩልኝ ክሊፖች የሰውዬውን የትላንት ውሎ አጃኢብ የሚያሰኙ ናቸው። ጭራሽ 'አበባይሆሽና ሆያሆዬ ለህጻናት መጥፎ መርዝ ነው' ሲል ሰማሁት። እብደቱን በሁለት ዲጂት ያሳደገበት ንግግሩ ነው። 'ኦሮሚያ የ100 ዓመት እድፍሽን አጥበን፥ ስልጣኑን ይዘናል' የሚል መዝሙር አዲስ አበባ ላይ ካልተዘመረ ብሎ አዲስ አበባ ላይ ጦርነት ያወጀ ግለሰብ ነው እንግዲህ 'አበባይሆሽ መርዝ ነው' ብሎ በብሄራዊ ቴሌቪዥን የሚናገረው?! በቃ - ፍሬኑን በደንብ በጥሶ እየገሰገሰ ነው። የሚያስቆመው አንዳች ሃይል ካልተገኘ ሰውዬው አይኑን ጨፍኖ ገደል ይዞን ሊገባ ነው። የፋኖ ትግል ያልገባህ ካለ እንግዲያውስ መልካም እንቅልፍ ብለናል። ምን ሀጢያት ብንሰራ ነው ግን እዚህ ሰው እጅ ላይ የጣለን?!

አንከር ሚዲያ Anchor Media

20 Jul, 06:38


🔴🔴ከአዳማ/ናዝሬት የተላኩልኝ ሁለት መረጃዎች

አንድ…

  በአዳማ/ናዝሬት ከዚህ ቀደም አንዲት የአማራ ተወላጅ ለዓመታት ለፍታ የሰራችውን ህንፃ ሸጣ ለመውጣት ወስና ለአንድ የኦሮሞ ተወላጅ በ150 ሚሊዮን ብር ለመሸጥ ትስማማለች። ይህን መረጃ የሰሙት የከተማው አመራሮችና የፖሊስ አዛዥ ሻጯን የአማራ ተወላጅ ወዲያው ይዘው እሥር ቤት ያስገቧታል። ለምን እንደታሰረች ምክንያት ስትጠይቅ የመንግስት ግብር አጭበርብረሻል የሚል ነበር። ነገር ግን ግብር አጭበርብራ አልነበረም። እነሱም የተለያዩ ሰበቦች እየደረደሩና ነገሩን እያከረሩት ሄዱ። እሷም በእስሯ ቀጠለች። እንገልሻለን ብለው የሚዝቱባት ፖሊሶችም ነበሩ። "ይህን ሁሉ ሀብት ያፈራሽው በኦሮሚያ ምድር ነው፣ጥለሽ ትሄጃለሽ።" የሚሉም ነበሩ።  በመሃል ሽማግሌ ገብቶ በ150 ሚሊዮን ብር ልትሸጥ የተስማማችውን ህንፃ በ90 ሚሊዮን ብር ሽጣ እንድትሄድ አስገድደዋታል።

ሁለት…

ሰሞኑን ደግሞ አንድ ባለሀብት ለተወለደበት የገጠር መንደር ንፁህ የመጠጥ ውሃ ጉድጓድ አስቆፍሮ የአካባቢው ማህበረሰብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንዲሆን በማድረጉ በሚዲያ ቀርቦ ንግግር ሲያደርግ የአዳማ /ናዝሬት አመራሮችና ፖሊሶች ይመለከቱታል። ወደ አዳማ ሲመጣ ይዘው እሥር ያስገቡታል። ባለሀብቱ የወሎ ተወላጅ ነው ኑር ሁሴን ይባላል። ምን ይሉታል "ኦሮሚያ ምድር ላይ ባገኘኸው ሀብት ሌላ ክልል ሄደህ ታለማለህ፣የ30 ሚሊዮን ብር መኪና ታሽከረክራለህ እና ሌላም…" በማለት በአሁኑ ሠዓት ድርጅቶቹን ሁሉ አሽገውበታል። ባለሀብቱ የስኳር ታማሚ ነው። እሱ እሥር ቤት ሆኖ የስኳር መጠኑ ጨምሮ በፖሊስ ጥበቃ አዳማ ጀነራል ሆስፒታል ተኝቷል። ባለሀብቱን ያሰሩት የመንግስት ኦነግ ሸኔዎች "እሺ ስንት ብር ነው የምትፈልጉ?" ሲባሉ 30 ሚሊዮን ብለው ቢሰጣቸውን እንደገና ጉዳዩን ለሌሎች ፖሊስና አመራሮች አስረክበው ሄደዋል። ይህ ባለሀብት በስኳር ህመም እየተሰቃየ በሆስፒታል ይገኛል። እንግዲህ ይህ ዓይነት የመንግስት አመራርና ፖሊስ ዓይን ያወጣ ዝርፊያ በኦሮሚያ በብዙ ከተሞች ላይ እየሆነ ያለ ነው።
Mesay Mekonen

አንከር ሚዲያ Anchor Media

18 Jun, 14:44


ሰበር ዜና
እናትዋ ጎንደር
ዛሬ ጠዋት ጎንደር ከተማ ዙሪያ ድንዛዝ በተባለ ቦታ በተፈፀመ
ጥቃታ ከ36 በላይ ወራሪ ሰራዊት ሲፈጭ ከ15 በላይ የሆነ
ደግሞ ቁስለኛ ተደርጓል

አንከር ሚዲያ Anchor Media

18 Jun, 14:03


በአማራ ክልል ያሉ የዛሬ የጦር ግንባር መረጃዎችን በቪዲዬ ይከታተሉ👇👇

https://youtu.be/VQR28oLqX-c?si=cpfNjqwhB7aalv7c

አንከር ሚዲያ Anchor Media

29 Apr, 12:41


የዩትዩብ ገፃችንን subscribe በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ👇👇
https://youtube.com/@Megenagnadaily?si=hYe79ngYPK8k3nbM

አንከር ሚዲያ Anchor Media

12 Mar, 17:09


ለሰአቱ መደመጥ ያለባቸው የግንባር ዉሎ መረጃዎች በቪዲዮ 👇👇👇
https://youtu.be/G3UrUUl-OEA?si=3QzslyrOTo1mzMiJ

አንከር ሚዲያ Anchor Media

12 Feb, 14:46


የብልጽግናው መንደር በአድዋ ሙዚየም ምርቃት አቅሉን ስቶ እየፈነጠዘ ነው። ታሪኩን የሰሩት የአድዋ ጀግኖች እንኳን ከድላቸው በኋላ እንዲህ ሰማይ ምድሩ አይበቃንም አላሉም። ጀግና ይሰራል እንጂ ብዙ አያወራም። ያዙኝ ልቀቁኝ አይልም። ጀግና ሁሉ በልቡ ነው። ሌሎች ይናገሩለታል፥ ይመሰክሩለታል እንጂ 'ከእኔ በቀር ጀግና የለም' ብሎ ጆሮ እስኪደነቁር አይጮህም። ብልጽግና በትልቁ አፍ ሰጥቶታል። ጆሮው ግን የዝሆን ነው። አማኑዔል ሆስፒታል ሲጠበቅ ቤተመንግስት የተገኘው የፓርቲው መሪ፥ ኢትዮጵያን በአውሮፕላን መስሎ 'ልትበር ሞተሯን እያሞቀች ነው' ሲል ይናገራል። 'እድልና ጥረት ከደጃፋችን ተገናኝቶ ታሪክ ሰራን' ሲልም ይመጻደቃል። በእርግጥ እድለኛ ነው። የደነዘዘና የነፈዘ ቲፎዞ ከጀርባው እንደጉድ ያጨበጭብለታል። አዶልፍ ሂትለር የጀርመንን ህዝብ አብዶ እንዳሳበደው ዓይነት ነገር።

ኢትዮጵያ ክንፏ ተሰብሯል። እግሯ ወልቋል። ሞተሯ ተበላሽቷል። በዘር ፖለቲካ ምሶሶዎቿ ወላልቀው ወደ አንድ አቅጣጫ ልትወድቅ እያዘመመች መሆኗ የማይደብቁት እውነት ነው። አብይ አህመድ በቅዥት ውስጥ ሆኖ ክንፍ አበጅቶላት በአየር ላይ ሊያከንፋት አካኪ ዘራፍ ይላል። አራቱም ሞተሮቿ በረሃብ እርዛት ጦርነትና ሙስና ተበላሽተው መጠገን እንዳይችሉ ሆነው ቀርተዋል። አብይ ዘንድ ወሬ በሽ ነው። እብደት ጤንነትን አስንቋል። ክህደት ነውርነቱ ተቀይሯል። ሀሰት ከእውነት በላይ ነግሷል። ምላስ ከአንጎል ልቆ ረዝሟል። አብይ አህመድ ጉም እያዘገነ፥ የተስፋ ዳቦ እያስገመጠ፥ አየሩን እያስመተረ፥ ስድስት ዓመታትን ዘለቀ። በቃህ ካልተባለ ይቀጥላል። በእርግጥም እድለኛ ነው።

በራሱ ቋንቋ መጠቀም ከተቻለ። ይሄ ግርግር አቧራ እንጂ አሻራ አይሆንም። ያንተ ዘመን የሚታወሰው በኢትዮጵያውያን ዕልቂት ነው። 1 ሚሊዮን በላይ የአድዋ ልጆችን ለእሳት የማገድክበት ጦርነት ዝንትዓለምህን ከስምህ ጋር ይነሳል። ያንተ ዘመን ኢትዮጵያውያን በዘር ፖለቲካ ተከፋፍለው በየአጥራቸው ሆነው የአድዋ ጀግኖች ያቆሙትን ምሶሶ እንዲገዘግዙ የተደረገበትን ቆሻሻና ክፉ አስተዳደርህን ያየንበት ነው። ሀገራችንን የምድር ሲዖል አድርገህ፥ ዜጋው በገዛ ሀገሩ በመቶ ሺዎች አፈናቅለህ፥ የአድዋ ልጆችን በሚሊዮን ቁጥር በረሃብ አለንጋ ጠብሰህ፥ ተስፋውን አድርቀህ፥ ጽልመትን አውርሰህ የቆየህበትን አስቀያሚ የስልጣን ዘመንህን ታሪክ በደማቁ ያስቀምጠዋል።

ይህቺ ግርግር አቧራ ናት። ከቀናት በኋላ በና ትጠፋለች። አድዋ በልባችን ውስጥ እንጂ ፒያሳ ባቆምከው ህንጻ የሚደምቅ አይሆንም። ሰው ገድለሃል። ኢትዮጵያውያንን ጨፍጭፈሃል። ሰራሁት ብለህ የምትመጻደቀው፥ ሰማይ ድረስ ቢቆለል ሃጢያትህን አያነጻውም። የክፋትና ሴጣናዊ ተግባርህን የሚደብቀው አይደለም። በፍጹም። ሳያላምጡ የሚውጡ፥ ሳይገባቸው የሚያጨበጩቡት ወፈ ሰማይ ደጋፊዎችህ የሚሰጡህ አድናቆት የልብህን ብርሃን እንዳጨለመው ይገባናል። ብዙም አይቆይም። አሻራ ስላልሆነ ይጠፋል። አቧራ ስለሆነ ይበናል። ታሪክ የሚያስታውስህ ባጨቀየኸውና ባቆሸሽከው እንጂ ባስጨበጥከው ጉም አይደለም።

አንከር ሚዲያ Anchor Media

30 Nov, 07:27


ከጎኑ ቀምለት የተባልከው የኦህዴድ መከላከያ እየፈፀመው የሚገኘው ዓለም አቀፍ ወንጀል !
----------

የአገሪቱ ሉዓላዊነት የመጨረሻ ጠባቂ እያሉ የሚያላግጡብን የኦህዴድ መከላከያ

በስነልቦና በአደረጃጀት በአመለካከት ሪፎርም ተደርጓል የተባለዉ የውንብድና መፈፀሚያ የኦህዴድመከላከያ

ያገኘኽዉን ያልተለወጠ ብር፣ ያገኘኽዉን ነዳጅ ዘርፈህ ብላ ተብሎ በአብይ አህመድ ፍቃድ የተሰጠው የኦህዴድ መከላከያ

አሁን ደግሞ በዓለም አቀፍ ወንጀል በሕገ ወጥ የሰዎች ዝዉዉር ከነ ሙሉ አቅሙ ከነሎጅስቲክሱ ተዘፍቆልሃል፡፡

ተከተለኝ….

* 53 ስደተኞች ጭኖ ሲያስኮበልል የተያዘው ንብረትነቱ "የፌዴራል መንግሥትይ" ነኝ የሚለው የአኦህዴድ የመከላከያ ኦራል መኪና ነው ፤ የኦራል መኪናው ኮድ መከ 2-2347 ነው።

ህገወጥ የሰው ዝውውር በመስራት አለም አቀፍ ወንጀል እየፈፀመ የሚገኘው የብርሃኑ ጁላ መከላከያ እሁድ ኅዳር 16/2016 ዓ.ም. ምሽት ከኧሌ ወደ ደቡብ ኦሞ
የኤርትራ ስደተኞችን ከፍተኛ ገንዘብ በመቀበል ወደ ኬንያ ሲያዘዋውር ተደርሶበት ተጋልጧል።

- የመኪናው አሽከርካሪ በምን ምክንያት ስደተኞቹን ሲያጓጉዝ እንደነበረ ለቀረበለት ጥያቄ " አለቃዬ ነው ያዘዘኝ " የሚል ምላሽ ነው የሰጠው።

ስደተኞቹ በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡ መሆናቸውን፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ የኧሌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
ስደተኞቹ ስለ እንቅስቃሴያቸው ተጠይቀው፣ <<ከሱዳን በመተማ በኩል አዲስ አበባ እንደመጡና አሁን ደግሞ ወደ ኬንያ እየሄዱ መሆኑን ተናግረዋል።>>

አንከር ሚዲያ Anchor Media

25 Nov, 15:48


በምዕራብ ጎጃም ዞን ደጋዳሞት ወረዳ ፈረስ ቤት ዛሬም ውጊያው ቀጥሎ መዋሉን ነዋሪዎቹ ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
ከጠዋቱ 2:00 አካባቢ ጀምሮ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ ማርፈዱን ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች በውጊያው ምክንያት ቀያቸውን ለቀው ሸሽተዋል ብለዋል። ትናንት ቀን ሙሉ በነበረው የተኩስ ልውውጥ በርካታ ሰብዓዊ ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

አንከር ሚዲያ Anchor Media

19 Nov, 19:52


ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ጀርመን በርሊን ሲገቡ በዚያው ጀርመን በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዉያን ብርቱ ተቃዉሞ እንደገጠማቸው የጀርመን ድምጽ ራድዮ ዘግቦ ተመልክተናል።

አንከር ሚዲያ Anchor Media

03 Nov, 04:37


አራት ኪሎ ተሸብሯል እንቅልፍ በአይናቸው አይዞርም ..‼️‼️
"16.5ሺ የመከላከያ ሰራዊት ከነመሳሪያቸው መጥፋታቸው ተነገረ "አንከር ሚዲያ

አንከር ሚዲያ Anchor Media

28 Oct, 12:09


ሀገሪቱን በጨበጣ የሚመራው ብልጽግና የተሰኘ የግዑዛን ስብስብ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ የተሰኘ አዲስ ክልል መመስረቱን አስመልክቶ ቸብርቻቻ ሲል ውሏል። የህወሀቷ ኢትዮጵያ በስንት ጣዕሟ?! የእነዚህ ብልጽግና የሚሏቸው ሰዎች የሞራል መርከስና የድንቁርና ጥልቀት የትኛውም ቃል አይገልጸውም። ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በሀዲያ ዞን መምህራን ስራ አቁመዋል። የህክምና ተቋማት ተዘግተው ባለሙያዎች ወደ ጉልበት ስራ ተሰማርተዋል። ደምወዝ ሳይከፈል አራት ወራት አልፏቸዋል። ለማዳበሪያ የተላከን ገንዘብ ባለስልጣናቱ ቅርጥፍ አድርገው በልተው ዛሬ አዲስ ክልል ለመመስረት ቁጭ ብለው ሲያጨበጭቡ ስታይ የሀገሪቱ መከራ እንዲሁ በቀላሉ የሚያልፍ እንዳልሆነ ትረዳለህ። የተበላው ገንዘብ የመምህራኑና የህክምና ባለሙያዎቹ ደምወዝ ነበር። የሚጠይቃቸው የለም። ሰውዬው ''ገንዘቡን እንደፈለጋችሁ ብሉት ግን ትንሽ ቆንጥራችሁ አንድ ደሳሳ ትምህርት ቤት ከሰራችሁ እኛ አንነካችሁም'' ስላለ፡ ምድረ ብልጽግና አይኑን ጨፍኖ ሀገሪቱን በጠራራ ጸሀይ እየጋጣት ነው።

ለዚህ ለኦሮሚያ ብልጽግና ስትራቴጂክ መስፋፋት ጥቅም ሲባል ተሸንሽኖ ለተመሰረተ አዲስ ክልል ሌሎች ነባርና አዳዲስ ክልሎች ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ስጦታ መስጠቻውን በድፍረት ሲናገሩ ስትሰማ እስከጥፍርህ በሚነዝር ድንጋጤ ውስጥ ልትገባ ትችላለህ። ትላንት ወደ 200 ሚሊየን ብር ለምስረታው የተቀበለው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከተሰጠው ላይ እየቆነጠረ በየክልሉ እየዞረ ይለግሳል። በበጀት እጥረት እስከአሁን ዞን መመስረት ያልቻለው ሲዳማ ክልል እንዲሁ በተጠራበት ክልል እየሄደ ሚሊዮኖችን ይሰጣል። ባለጊዜውና ባለጠጋው ክልል የሆነው ኦሮሚያ ወለጋን በረሃብ ጠብሶ፡ በድርቅ የሚሰቃየውን ቦረናን ወደ ጎን ትቶ፡ ከ1ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የተራበውን የክልሉን ነዋሪ ቁራሽ ዳቦ ከልክሎ ለተራ የፖለቲካ ግርግር 100 ሚሊዮን ብሮችን እየመዠረጠ እዚህም እዚያም ክልል ያቆማል። 500ቢሊየን ብር በጦርነቱ የወደመበት አማራ ክልል ጎንደር በረሃብ እየተገረፈ፡ ሰቆጣ ህጻናት በሞት እያለቁ 30ሚሊየን ብር ሆጭ አድርጎ የአብይ አህመድ የክልል ፖለቲካ ማጠናከሪያ እንዲሆን ይሰጣል። ከአንድ ኪስ ወደ ሌላ ኪስ። የአብይ አህመድ ቀሽም ድራማ።

እንዴት ያለ ፌክ ስብስብ ነው?! የኢትዮጵያ ትንሳዔ የዚህ የአቅመ ቢሶች፡ ደካሞችና ሌቦች ስብስብ የሆነው ብልጽግና የሚሉት ተውሳክ ፓርቲ ከምድረ ገጽ መወገድ ነው!!!!

Via:መሳይ መኮነን

አንከር ሚዲያ Anchor Media

27 Oct, 09:12


በመርሳ ከተማ ታስርው የነበሩ የ ፋኖ አባሎች እና የፖለቲከኛ እስረኞች በጀግናው የምስራቅ አማራ ፋኖ ከእስር ተፈተዋል።

አንከር ሚዲያ Anchor Media

25 Oct, 19:56


#መረጃ
ነገ ከጠዋቱ 3 ሰዓት አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ፊት ለፊት በሚገኘው አዲሱ ፍ/ቤት ህንፃ ላይ መሪጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ ይቀርባል።

የምትችሉ ይህ ወሮበላ ስረአት በግፍ ያሰረው ወንድማችንን በቦታው ተገኝታችሁ አጋርነት አሳዩ🙏🙏

አንከር ሚዲያ Anchor Media

24 Oct, 04:07


ኢትዮጵያ|ኤርትራ

በኤርትራው ደህንነት መስሪያ ቤት በሚዘውረው “Center for Research and Documentation” በተሰኘው ማህበራዊ ትስስር ገፅ “የኤርትራ ዜጎች በአፋጣኝ ኢትዮጵያን ለቀው እንዲወጡ” ትዕዛዝ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጉዳይ እየለየለት ይመስላል።

አንከር ሚዲያ Anchor Media

19 Oct, 17:43


ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድን ጨምሮ በርካታ ምሁራንን ያካተተ የአሜሪካ ኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳዮች ኮሚቴ በወቅታዊ የአማራ ክልል ሁኔታ ከአሜሪካ የኮንግረስ አባላት ጋር ተወያየ!

የአሜሪካ ኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳዮች ኮሚቴ The American-Ethiopian Public Affairs Committee ( AEPAC) በትላንትናው ዕለት በዋሽንግተን ዲሲ ለበርካታ የኮንግረስ አባላት በወቅታዊ የሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ሰፊ ገለፃ አድርጓል።

በተለይም የአይን ምስክሮችን በማቅረብ የብልጽግና መንግስት በንፁሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰውን የማንነት ተኮር ጥቃት በማስረዳት የኮንግረስ አባላት በአስቸኳይ የሰው ልጅ ዘር እልቂትን በአማራ ክልል ለማስቆም ምክርቤቱ ያለውን ሃይል በመጠቀም እርምጃ ይወስድ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል። 

በዉይይቱ ላይ ለኮንግረስ አባላቱ ገለፃ ያረገችዉ ጋዜጠኛ እና የሰብዐዊ መብት ተሟጋች መዐዛ መሃመድ በክልሉ መንግስት መር የሆነ የዘር ማጥፋት እየተካሄደ እንደሆነ አብራርታለች።

አንከር ሚዲያ Anchor Media

17 Oct, 10:51


እነዚህ መረጃዎች ከውስጥ የተላኩ ናቸው!

በቆቦ፣ አዩብ፣ ተኩለሽ፣ ደበረ ሰላም አቦ ድረስ ፣ላሊበላ፣ ብልብላ፣ ወገል ጤና ፣ ፀሀይ መውጫ እንዲሁም በሽዋ ደብረ ሲና፣ ሰላ ድንጋይ ድረስ በሚቀጥሉት ቀናት አገዛዙ በእግረኛ ወይንም በከባድ መሳሪያ ወይንም በድሮን እንደሚያጠቃ ከውስጥ መረጃ ደርሶናል። ስለዚህ በዚህ አካበቢ የምተገኙ ፋኖዎች እራሳችሁን ለመከላከል አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ እናሳስባለን።

በቅርቡ በላሊበላ እና አካባቢው በብልብላ እና አካባቢው በኮንቦልቻ እና አካባቢው ሰርባ እና አካባቢው ማማ ገዳም እና አካባቢው አብረሃ ጅራ ከተማው እና አካባቢው ደብተራ ጉጥ እና ከባቢው ኩራባስ ጣቁሳ እና አካበበቢው ወገል ጤና አካባቢው እናዋሪ እና ሊሙ አካባቢው በቅርቡ በከባድ መሳሪያ ወይንም በእግረኛ ወይንም በድሮን ስለሚጠቃ እራሳችሁን ለመከላከል አስፈላጊውን ሁሉ እንድታደረጉ እናሳስባለን።

ጎንደር ጭልጋ ከሰረባ ሻውራ ጣቁሳ ድርስ ላሊበላ ብልብላ ኤርፖርቱን ይዞ ጠላት መረጃ እንደሰበሰበ መረጃ ስለደረሰን በዚህ አካባቢ የምትንቀሳቀሱ ፋኖች በሚቀጥሉት ቀናት በእግረኛ ወይንም በከባድ መሳሪያ ወይንም በድሮን ጥቃት ሊኖር ስለሚችል አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ እናሳስበለን::

( ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን)

አንከር ሚዲያ Anchor Media

16 Oct, 16:44


የኤርትራ መንግስት የአብይ አህመድን የፖርላማ ንግግር ኦፊሻሊ ዛሬ ውድቅ አድርጎታል ። ከሀገር ጠባቂው ፋኖ ጋር ቁጭ ብለህ መነጋገር ያልቻልክ ከኤርትራ መንግስት ጋር በምን ቋንቋ ነው ነው ምትግባባው ?

አንከር ሚዲያ Anchor Media

16 Oct, 04:27


የዛሬው: የባህርዳር: ፋኖ: ድል: ልዩ: ነበር:: ከባህርዳር: ተነስቶ: በ6 ካሶኒ: በ2 ኦራልና: በ2 ፒካፕ: ወደ: አዴት: መስመር: ሲጏዝ: የነበረውን: ጨፍጫፊ: ሃይል: በሰባትአሚትና: በወንዳጣ: መካከል: በምትገኘው: ቦር: በተባለች: ስፍራ: 6 ሰአት: በፈጀ: ጦርነት: እንዳይሆን: አድርገው: ለብልበው: ወደ: ባህርዳር: ጎሬው: እንዲመለስ: አድርገውታል:: ከዚህ: የጁላ: ጦር: የማረኩት: መሳሪያ: ሌላ: የፋኖ: ቡድን: ሊመሰረት: እንደሚችል: ታውቋል:: የዛሬውን: ገድል: ይበልጥ: ልዩ: የሚያደርገው: ከፋኖ: ውጭ: ያለው: የአካባቢው: ገበሬ: ካህናትና: ወጣቶች: በጡሩንባ: ተጠራርተው: ይሄንን: ስግብግብ: ሃይል: ልቡ: እስኪጠፋ: ማስሮጣቸው: ነው:: እህትክን: ሚስትህን: ሴት: ልጅህን: ሊደፍር: ለሚመጣ:  የአራዊት: ሰራዊት: እንዳትራራ::

ፋኖ: ይችላል💪🏻💪🏻💪🏻

አንከር ሚዲያ Anchor Media

15 Oct, 19:25


መረጃ..!

በበርካታ የጎጃም አካባቢዎች የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች የእምዬ ምኒልክን የክተት አይነት አዋጅ እያወጁ ናቸው። “ሚስትህን የሚደፍር፤ ልጆችህን የሚገድል፤ ኃይማኖትህን የሚያስቀይር የጥላት ኃይል መጥቶብሃልና ወንድ ልጅ የሆንክ ሁሉ ጨርቄን ማቄን ሳትል ተነስ” የሚል አዋጅ እየተነገረ ነው።

ድል ለአማራ ህዝባዊ ፋኖ 💪💪💪

አንከር ሚዲያ Anchor Media

14 Oct, 19:33


አስተሳሰባችሁ አይፈቅድም!

"አማራ ወደ አዲስ አበባ አይገባም። ኢትዮጵያ ግን በቀይ ባሕር በኩል መውጫ ትፈልጋለች"

"6 ሚሊዮን የአዲስ አበባ ሕዝብ ከኦሮሞ መሬት  የገፈርሳና ለገዳዲን ውሃ  እንዳይጠቀም ማድረግ እንችላለን።  ነገር ግን እንደ ኢትዮጵያ ድንበርም ባይኖረን ባሕር በቅርብ ርቀት እያየን ቀይ ባህርን  አለመጠቀም አንችልም።"

"አዲስ አበባ ላይ ልዩ ጥቅም እንፈልጋለን። ቀይ ባሕር ግን የጋራችን ነው።"

"ህገ መንግስቱ አይሻሻልም የፈለገ መገንጠል ይችላል። ከኤርትራና ጅቡቲ ጋር ግን አንድ አገር እንሆናለን"

"አማራ ተስፋፊ፣ አሁን የተፈጠረውን ሁኔታ ሳይረዳ የአባቶቸ ግዛት የሚል ነፍጠኛ ነው። በምኒልክ ዘመን የነበረው ግዛት የኢትዮጵያ አካል ነው እያለ በብሔር ብሔረሰቦች ላይ መጫን ይፈልጋል። ነገር ግን በአክሱም ዘመን የነበሩ አባቶቻችን ቀይ ባሕርን ገዝተዋል። አሉላም ድንበራችን ነው ብሏል። አሁንም እኛ እናስመልሳለን።"

"የመድሃኒያለም ያለሽ" አለ ፋሲል ደሞዝ። በጣም ተጣረሳችሁ። ተጠራመሳችሁኮ።  የነፍጠኛ የምትሉትና የኦነግ ኃሳብ ተላተመባችሁ።  አልሆነላችሁም አንተ።

የባሕር በርም የአገር አንድነትም ስነ ልቦና ይጠይቃል። በበታችነት ስሜት ስትናጥ እየዋልክ አገራዊ እሳቤ መያዝ አትችልም። አስተሳሰብህ አይፈቅድም። የልዩ ጥቅም ነው አስተሳሰብም። ቀበሌያም። ደቡብን ወደ ቀበሌ ስትመትር ከርመህ ጅኦ ፖለቲክስ፣ እንደ ራሺያ መስፋት ያምርሃል? የት ታመጣዋለህ!(ጌታቸዉ)