ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta) @sigewe Channel on Telegram

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

@sigewe


በየቀኑ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በስንክሳር የሚታሰቡ የቅዱሳን ታሪክ፣ የኢትዮጵያኑ ቅዱሳን በየበዐላቸው ቀን አስደናቂ፣ አስገራሚ ገድላቸው፣ ቃል ኪዳናቸው፣ የቅዱሳን ሰላምታ፣ የየቀኑ የቅዳሴ መልዕክታ፣ የሐዋርያት ሥራ፣ የወንጌል ጥቅስ እና ምስባክ ይቀርብበታል።

የፌስቡክ አድራሻዬ ሊንክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta) (Amharic)

መላክና አስተያየትዎ ለምስጋና መዳሰልን ለጉዞው እና ስሙን ለመፍታት ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ እናት የገና ተመናሽ አንተበሽን ግጥነቴን አስነሰብናለሽ። አሁንም ለሁላችን ሊንክ ይግበርሽና ሌላዊና አገር ተመሳሳይ ትቅደትን እና አስተሳሰብሽን አግኝቼ መጣሽ። ቅዱሳን ታሪክ፣ ቃል ኪዳናቸው፣ ሰላምታ፣ መልዕክታ፣ ሥራ፣ ጥቅስ እና ምስባክ በየበዐላቸው ቀን በስንክሳር እንዲታሰቡ ስንጠቀም አስነሳለን። ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ ከታሪክ እንዲገባ እና በቅርብ ሥላሴ ልናሀል፡፡

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

03 Dec, 18:43


"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

                         ✝️ ✝️ ✝️
#የዕለቱ_አንገርጋሪ_ግእዝ_ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ፈጸመ ስምዓ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ፤ በመዋዕሊሁ ለዳኬዎስ ንጉሥ፤ ወኮነ መድኃኒተ ለኲሉ ዘነፍስ፤ #ወተፈሥሑ_ባስልዮስ_ወጎርጎሬዎስ"። ትርጉም፦ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ በንጉሥ ዳኬዎስ በዘመኑ ምስክርነቱን ፈጸመ፤ በዚህም ለነፍሳት ሁሉ መድኃኒት ሆናቸው፤ #ቅዱሳን_ባስልዮስና_ጎርጎርዮስ ተደሰቱ። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።
  

@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

03 Dec, 18:21


#የኅዳር ፳፭ (25) #የሰማዕቱ_የቅዱስ_መርቆሬዎስ የበዓለ ዕረፍት ሙሉ ቃለ እግዚአብሔር የማኅሌት ሥርዓት።

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

03 Dec, 14:32


ከዚያንም ጊዜ ንጉሥ መልክተኞችን ልኮ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወደርሱ አስመጣው በመዘግየቱም አድንቅ "ለአማልክት ዕጣን ለማድረግ ከእኔ ጋር ያልወጣህ የእኔን ፍቅር እንዴት ተውህ" አለው። በዚያንም ጊዜ ትጥቁንና ልብሱን ወረወረለትና ንጉሡን እንዲህ አለው "እኔ ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም ለረከሱ ጣዖታትም አልሰግድም"። ንጉሥ ዳኬዎስም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ እርጥብ በሆኑ የሽመል በትሮች እንዲደበድቡት አዘዘ። ሁለተኛም ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ ይገርፋት ዘንድ አዘዘ ንጉሡ እንዳዘዘ ይህን ሁሉ አደረጉበት።

በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ስለ ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳይነሡበት ፈርቶ የቀጰዶቅያና የእስያ ክፍል ወደ ሆነች ወደ ቂሣርያ በብረት ማሠርያ አሥሮ ላከው። በዚያም እንዲአሠቃዩት አዘዘ ከአሠቃዩትም በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ እንዳዘዘው ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና ተጋድሎውን ፈጽሞ በመግሥተ ሰማያት የሕይወት አክሊልን ተቀበለ። የማይጠፋ ሰማያዊ አክሊልንም ተቀዳጅቶ ወደ ዘላለም ሕይወት ከገባ በኋላ በዓለሙ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ታነፁለት እግዚአብሔርም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራትን በውስጣቸው ገለጠ።

ከተአምራቱም አንዲቱ ዑልያኖስ በነገሠ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ካደ በዚያንም ወራት ቅዱስ ባስልዮስ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ነበረ ተአምራቱ በተጻፈበት መጽሐፍ እንደተጻፈ ምእመናን በጽኑዕ ሥቃይ ዑልያኖስ ባሠቃየ ጊዜ መክሮ አስተምሮ ከስሕተቱ ይመልሰው ዘንድ ቅዱስ ባስልዮስ ወደርሱ መጣ።

ዑልያኖስም ቅዱስ ባስልዮስን በአየው ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችንን ሰደበ ቅዱስ ባስልዮስንም አሠረው በዚያ በእስር ቤትም የቅዱስ መርቆሬዎስን ሥዕል አይቶ በፊቱ ቅዱስ ባስልዮስ ጸለየ ሥዕሉም ከቦታው ታጣ። ያን ጊዜ ወደ ዑልያኖሰሰ ሒዷልና በጦርም ወግቶ ገደለውና ወዲያውኑ ወደቦታው ተመለሰ ከጦሩም አንደበት ደም ይንጠፈጠፍ ነበር። ቅዱስ ባስልዮስም ከሀዲ ዑልያኖስን እንደገደለው አውቆ እንዲህ ብሎ ተናገረ "የክርስቶስ ምስክር ሆይ የእውነት ፀር የሆነ ዑልያኖስን ገደልከውን?" ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ሥዕሉ ራሱን ዘንበለሰ አደረገ ቅዱስ ባስልዮስም ደስ ብሎት እግዚአብሔር አመሰገነ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ መርቆሬዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ ገድለ መርቆሬዎስና የኅዳር 25 ስንክሳር።

                           ✝️ ✝️ ✝️
#የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ልሳነ ከለባቲከ ላዕለ ጸላእቱ። አስተርአየ ፍናዊከ እግዚኦ። ፍናዊሁ ለአምላክነ ለንጉሥ ዘውስተ መቅደስ"። መዝ 67፥23-24 ወይም መዝ 88፥14-15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥17-32 ወይም ማቴ 20፥20-24።

                            ✝️ ✝️ ✝️
#የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "ቅረብ ኀቤሁ ወያበርህ ለክሙ። ወኢይትኀፈር ገጽክሙ። ዝንቱ ነዳይ ጸርሐ ወእግዚአብሔር ስምዖ"። መዝ 33፥5-6 የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥25-ፍ.ም፣ ያዕ 3፥4-13 እና የሐዋ ሥራ 21፥27-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 8፥22-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የሰማዕቱ የቅዱስ መርቆሬዎስ የዕረፍት በዓልና፣ ዕለተ ሰንበትና የነቢያት (የገና) የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
   

@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

03 Dec, 14:32


"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

            #ኅዳር ፳፭ (25) ቀን።

እንኳን #ለታላቁ_ሰማዕት_ለቅዱስ_መርቆሬዎስ (ፒሉፓዴር) በንጉሥ ዳኬዎስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል እግዚአብሔር አምላከ በሰላምና ጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእስላሞች ወገን ከነበረ #ቅዱስ-መርቆሬዎስ ተአምር አድርጎ ከመለሰው #ከቅዱስ_ዮሐንስ፣ #ከአቃርዎስና_ከሮማኖስ ከመታሰቢያቸወ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

                                
                           ✝️ ✝️ ✝️
#ቅዱስ_መርቆሬዎስ፦ መርቆሬዎስ ማለት የአብ ወዳጅ ማለት ነው። በሁለተኛ ትርጓሜ የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይ ማለት ነው። ይህም ቅዱስ አስሊጥ ከምትባል አገር ነው እርሷም የአባቱና የአያቱ አገር ናት እርሱ ግን ተወልዶ ያደገው በሮሜ ከተማ ነው።

የአባቱና የአያቱ ሥራቸው አውሬ ማደን ነበር በአንዲት ዕለትም እንደልማዳቸው ለማደን ወጡ ከገጸ ከለባት ወገንም ሁለት ወንዶች ተገናኙአቸውና የቅዱስ መርቆሬዎስን አያት ስዲሮስ በሉት። ሁለተኛም አባቱን አሮስን ሊበሉት ፈለጉ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክም ከለከላቸው "ከእርሱ የሚወጣ መልካም ፍሬ ስለ አለ አትንኩት" አላቸው።

ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ዙሪያቸውን በእሳት ከበባቸው በተቸገሩ ጊዜም ወደ ቅዱስ መርቆሬዎስ አባት አሮስ መጥተው ሰገዱለት በዚያንም ጊዜ እግዚአብሔር ፍጥረታቸውን ወደገራምነት ለወጠውና እንደ በጎች የዋሆች ሆኑ አብረውትም ወደ መንደር ገቡ።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ በተወለደ ጊዜ ስሙን ፒሉፓዴር ብለው ጠሩት የውሻ መልክ ያላቸው በእነርሱ ዘንድ ብዙ ዘመናት የሚኖሩ ሆኑ ከዚህም በኋላ ክርስቲያኖች ሆኑ የቅዱስ መርቆሬዎስ ወላጆች አስቀድሞ አረማውያን ነበሩና የክርስትና ጥምቀትንም ጸጋ በተቀበሩ ጊዜ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ኖኅ ብለው ሰየሙት እናቱንም ታቦት አሏት ፒሉፓዴርንም መርቆሬዎስ ብለው ሰየሙት። የውሻ መልክ ያላቸው ግን የእግዚአብሔር መልአክ በተገለጸላቸው ጊዜ እንደ ነገራቸው ለቅዱስ መርቆሬዎስ አባት የሚታዘዙና የሚያገለግሉ ሆኑ።

ንጉሡም የኖኅንና የውሻ መልክ ያላቸውን ዜና በሰማ ጊዜ ወደርሱ አስቀረባቸው በዚያንም ጊዜ እግዚአብሔር በንጉሡ ፊት የቀድሞ ፍጥረታቸውን መልሶላቸው የንጉሡ ያቀረባቸውን ሁሉንም አራዊት አጠፏቸው። ንጉሡም ይህን በአየ ጊዜ እጅግ ፈራ የአራዊትንም ተፈጥሮአቸውን ያርቅ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲማልድ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ለመነው። እርሱም በለመነ ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ተፈጥሮአቸውን መልሶላቸው ገራሞች ሆኑ።

ከዚህም በኋላ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት ንጉሡ ወስዶ ገዥና የሠራዊት አለቃ አድርጎ ሾመው የውሻ አርያ ያላቸውም ይታዘዙለት ነበር ከእርሳቸውም የተነሣ ሁሉም ይፈሩ ነበር። ከዚህም በኋላ የቅዱስ መርቆሬዎስን አባት የሾመውን ንጉሥ ይወጋ ዘንድ ከሀዲ ንጉሥ ተነሣ ንጉሡም ከጦር አባት ወደ ጦርነት ላከው። ከሀዲው ንጉሥ ግን እነዚያን የውሻ አርያ ያላቸውን አባብለውና ሸንግለው ወደርሱ የመጧቸው ዘንድ ወታደሮችን ላከ በአመጧቸውም ጊዜ ሃይማኖታቸውን ይለውጡ ዘንድ አብዝቶ ሸነገላቸው ባልሰሙትም ጊዜ ሊአሠቃያቸው ጀመረ አንዱ አምልጦ ሸሽቶ ወደ ጌታው ሔደ ሁለተኛውም በሰማዕትነት ሞተ።

ከጦር ሜዳ የቅዱስ መርቆሬዎስ አባት በመለሰ ጊዜ ሚስቱንና ልጁን ፈለጋቸው ግን አላገኛቸውም ንጉሡ የሱ ወገኖች ድል እንደሆኑ በሰማ ጊዜ የቅዱስ መርቆሬዎስ አባት መኰንኑ የሞተ መስሎት ነበርና የቅዱስ መርቆሬዎስን እናት ወስዶ ሊአገባት ፈለገ ከንጉሥ ወታደሮችም አንዱ ንጉሡ ያሰበውን በጽሞና ነገራት። እርሷም ይህንኑ ወታደር ከአገር ውስጥ በሥውር ያወጣት ዘንድ ለመነችውና ከልጇ ከብፁዕ መርቆሬዎስ ጋር ወጥታ ወደ ሌላ አገር ሔደች። ንጉሡም ከእርሱ የሆነውን የመኰንኑም የመርቆሬዎስን አባት ሚስቱን ለማግባት ማሰቡን እንዳይነግሩት አዘዘ የውሻ መልክኮች ያላቸው ከእርሱ ጋር እንዳሉ የተቆጣም እንደሆነ እንደሚአመጣቸውና አገሮችን ያጠፋሉ ብሎ ይጠራጠራልና ስለዚህ እጅግ ይፈራዋል።

ከዚህም በኋላ ደግሞ በንጉሡ ላይ ጦርነት ተነሣ የቅዱስ መርቆሬዎስም አባት ወደ ጦርነት ወጣ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ይዘው ማረኩት ወደ ሮሜውም ንጉሥ አቀረቡት ንጉሡም ክርስቲያን ነበርና የተማረከው መኰንን ክርስቲያን መሆኑን በአወቀ ጊዜ አልገደለውም በክብር አኖረው እንጂ እጅግም ወደደውና ከጥቂት ቀኖች በኋላ በመርዶሳውያን አገሮች ሁሉ ላይ ገዥ አድርጎ ሾመው።

ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ሚስቱና ልጁ መርቆሬዎስ ወዳሉበት አገር ደረሰ ሚስቱም በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ በአየችው ጊዜ ባሏ እንደሆነ አወቀችው እርሱ ግን አላወቃትም በአንዲትም ዕለት እርሱና ጭፍሮቹ ከእንግዳ ማረፊያ ቤት በወጡ ጊዜ ልጅዋን መርቆሬዎስን ወስዳ ያማሩ ልብሶችን አልብሳ ሒዶ ከመኰንኑ ፈረስ ላይ እንዲቀመጥ አዘዘችው እርሱም አባቱ ነው በተቀመጠም ጊዜም ጭፍሮች ይዘው ወደ መኰንኑ ፊት አቀረቡት መኰንኑም ልጁ እንደሆነ አላወቀምና በእርሱ ላይ ተቆጣ።

የመርቆሬዎስ እናት መጥታ "ጌታዬ ሆይ እኛ መጻተኞች ነን አንተም መጻተኛ እንደሆንክ በአወቅሁ ጊዜ ልጅህ ሁኖ ልጄ ከአንተ ጋር እንዲሆን አሰብኩ" አለችው። እርሱም ጠየቃት እንዴት እንደተሰደደችም መረመራት እርሷም ሚስቱ እንደሆች ነገረችው በዚያንም ጊዜ አወቃት ልጁን መርቆሬዎስንም አወቀው አጅግም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔር አመሰገኑት ያንንም የእንግዳ ማረፊያ ቤት ቤተ ክርስቲያን አደረጉት እግዚአብሔርም እያመሰገኑ በአንድነት ኖሩ።

ከዚህም በኋላ አባቱና እናቱ በሞቱ ጊዜ ንጉሡ ቅዱስ መርቆሬዎስን ወስዶ በአባቱ ፈንታ በመርዶሳውያን አገር ላይ ሾመው ቅዱስ መርቆሬዎስም መኰንንነትን በተሾመ ጊዜ ያ ገጸ ከልቡ ከርሱ ጋር ነበር ወደ ጦርነትም አብሮት የሚወጣ ሆነ። ለመዋጋትም በሚሻ ጊዜ የቀድሞ የአራዊት የሆነ ተፈጥሮውን እግዚአብሔር ይመልስለት ነበር ማንም ሊቋቋመው የሚችል የለም። ለቅዱስ መርቆሬዎስም ታላቅ የድል አድራጊነት ኃይል ተሰጠው ዜናውም በሁሉ ቦታ ተሰማ ከቤተ መንግሥት ሰዎችም ከፍ ከፍ አለ።

እንዲህም ሆነ ያን ጊዜ በዚያን ወራት በሮሜ አገር ጣዖትን የሚያመልክ ዳኬዎስ የሚባል ንጉሥ አለ። ጠላቶቹም የበርበር ሰዎች ተነሡበት እርሱም ከእርሳቸው ጋር ሊዋጋ ሠራዊቱን ሰብስቦ ወጣ እነርሱ ግን እንደ ባሕር አሸዋ ብዙ ነበሩ ብዛታቸውንም በአየ ጊዜ ደንግጦ እጅግ ፈራ ቅዱስ መርቆሬዎስም "እግዚአብሔር ያጠፋቸው ዘንድ በእጃችንም አሳልፎ ሊሰጣቸው አለውና አትፍራ" አለው።

ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዎስ የእግዚአብሔርን መልአክ በውጊያው ውስጥ አየው የተሳለ ሰይፍም በእጁ ውስጥ አለ ያቺንም ሰይፍ ሰጠውና እንዲህ አለው "ጠላቶችህን ድል በአደረግህ ጊዜ ፈጣሪህ እግዚአብሔር አስበው"። ጠላቶቹንም ድል አድርጎ በሰላም ተመለሰ መልአኩም ዳግመኛ ተገልጦለት "ለምን ፈጣሪህን የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ረሳህ" አለው።ጦርነቱም ከተፈጸመ በኋላ ንጉሥ ዳኬዎስ ለጣዖታቱ ዕጣን በማሳረግ በዓልን ሊያደርግ ወደደ ቅዱስ መርቆሬዎስም ለበዓል ማክበር አብሮት አልወጣም ወደ ቤቱ ሔደ እንጂ ሰዎችም ቅዱስ መርቆሬዎስ እንዳልመጣና ዕጣንን በማሳረግም እንዳልተባባረ አስረዱት።

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

03 Dec, 13:31


ገድለ ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ዘወርኃ ኅዳር።

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

03 Dec, 12:06


"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

                           
"#ሰላም_ለጽንሰትከ_በሥምረተ_አምላክ_ዘኮነ። #ወለልደትከ_ሰላም እንተ ከሠተ አሚነ። #ዜና_ማርቆስ_ጴጥሮስ ዘተወከፍከ ሥልጣነ። ዘተአስረ በቃልከ ይነሥእ ደይነ። ወዘፈታሕከ እምኩነኔ ይኩን ድኁነ"። ትርጉም፦ #በአምላክ_ፈቃድ ለሆነ #መጸነስህ_እና_በሃይማኖት_ለተገለጠ_መወለድህ_ሰላምታ_ይገባል፤ ሥልጣንን የተቀበልክ #ቅዱስ_ጴጥሮስ_አባ_ዜና_ማርቆስ_ሆይ! በቃልህ የታሰረ መከራን ይቀበላል፤ የፈታኸውም ከመከራ የዳነ ይሆናል። #መልክዐ_አቡነ_ዜና_ማርቆስ።
   

@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

03 Dec, 09:04


"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

                           
"#ሰላም_ለዝክረ_ስምክሙ ዘይሜንን ፀቃውዐ። እምዐቅምሃ ጽጌ ሠናይ ለሰብእ በዕቊረ አንህብት ረግዐ። ሐሊበ ፍቅርክሙ ይኩን ውስተ ልብየ ምሉዐ። #ካህናተ_ሰማይ_ውዳሴክሙ ከመ እሰንቁ ጥዕጡዐ። ለዐይን ኅሊናየ ጽላሌሁ ቅልዑ ቀሊዐ። ትርጉም፦ #ከተወደደ_የአበባ_ወለላ ተቀስሞ ለሰው በረጋ በንቦች ሰፈፍ ከተዘጋጀ የማር ወለላ ይልቅ ለሚበልጥ #ዝክረ_ስማችሁ_ሰላምታ_ይገባል፤ #ካህናተ_ሰማይ ሆይ! የፍቅራችሁ ወተት በልቤ መልቶ ምስጋናችሁን አከናውን ዘንድ ኅሊናየን ግለጡልኝ። #መልክዐ ፳ወ፬ቱ #ካህናተ_ሰማይ።
     

@sigewe

https://t.me/joinchat/AAAAAFGQ22bI0Ij80hYpFA

https://www.facebook.com/profile.php?id=61552828743736&mibextid=ZbWKwL

https://www.facebook.com/profile.php?id=100063896616886

ተአምኆ ቅዱሳን ወግጻዌ (የቅዱሳን ሰላምታ) Teamho Kidusan Wegtsawe (Yekidusa Selamta)

03 Dec, 08:19


የአቡነ ዜና ማርቆስ ገድል ልደታቸው በተመለከተ።

6,959

subscribers

11,587

photos

13

videos