ታደሰ ደምሴ @ethiopia2123 Channel on Telegram

ታደሰ ደምሴ

@ethiopia2123


ሥነ_ግጥም




ግጥሞችን በዩቱብ ለመከታተል👇👇👇
https://youtube.com/@maryam2116

ታደሰ ደምሴ (Amharic)

የተቻለ አስተያየታችንን በተመለከተ መከታተል ለመከታተል ይሆናል። ሥነ_ግጥም በዩቱብ በሚከተለው ተጨማሪ አይነት ግጥሞች መምራት ጥሪ እና እንዲሁም ጥሩ መረጃዎች ለመከታተል የተለመኑ ብቻ ናቸው። ይህን ግጥም ከባለቤትም እውን አለኝ። ከፍተኛ እና ጥራሕ አዳዲስ መረጃዎችን ስለመረጃው፣ አስተያየት፣ እና ለመረጃው ለማቅረብ፣ እባኮትን በመዝጋታ ይሞክሩ። ወይም ለሌላ አይነት እና አስተዳዳሪዎችን በማንበብ ይሞክሩ። የቴሌግራም ቻነል፣ የዩቱብ፣ እርስዎ ሌላ ምንጭ፣ ትልቁ የስራ ጉዳዮችን ለመፈጸም፣ ላሎችን ለማድረግ፣ ለጥናትና ለሼጋው የሚያስተምሩ መረጃዎችን መረጃ ያስገኝ። ወደ ተጨማሪ ሊስተን በመጠቀም መረጃዎችን ለመፈለጊው ለክፍል እስከ ነገራችን እየተጠናቀቀ እንደሆነ ይምረጡ። ተጨማሪ ግጥም እና መረጃዎችን ያስገቡ።

ታደሰ ደምሴ

06 Jan, 21:19


በጎል ሰከበ በአጽርቅት ተጠብለለ ኃደረ ማኅጸነ ድንግል/፪/
እፎ 'ተሴሰየ'/፪/ ሀሊበ ከመ ሕፃናት ተሴሰየ/፪/

እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ🥰

መልካም በዓል

ታደሰ ደምሴ

06 Jan, 10:33


https://youtu.be/9TAprMH8mWU?si=BG2hQk_6UTHCdpXH

ታደሰ ደምሴ

30 Dec, 17:25


✍️ታሮስ አለሙ

ታደሰ ደምሴ

14 Dec, 09:09


እየበሰጨኝ💪👌✌️

ታደሰ ደምሴ

30 Nov, 07:16


"ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል..."

እንኳን አደረሳችሁ🥰

አብማ ማርያም

ታደሰ ደምሴ

27 Nov, 09:07


በመኖር  አጸድ ውስጥ
(በእውቀቱ ስዩም)

ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::

እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤

ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::

@ethiopia2123

ታደሰ ደምሴ

11 Oct, 21:13


@ethiopia2123

ታደሰ ደምሴ

28 Sep, 16:11


. ዕስኪ አምጡልኝ ፡ ዘዉግ አርማዬን ፡
ላጊጥበት ፡ ጥቁር ቀዩን ነጭ ሸማዬን ፡
ልድመቅ እና ፡ ደሞ እንደሰዉ ፡
ያን' አምላኬን ፡ በክህደት ጦስ ላሳንሰዉ ፡
በሱ አልፀናም ፡ ሐገር ምድሩ ፡
ስለት ልሙላ ፡አጎንብሼ ፡ ለአመት ግብሩ ፡
መጀን ልበል ፡ግኡዛንን፡ ወንዝ ዛፉን ፣ ዕሹሩሩ !🤭

ግ ጥ ም በ ዩ ሱ ፍ

ታደሰ ደምሴ

11 Sep, 06:11


የበረከት ዓመት ይሁንልን🥰

ታደሰ ደምሴ

29 Aug, 15:54


ታደሰ ደምሴ pinned «...ገና በልጅነቴ ያስኮረፈችኝ ስቃ የማታውቅ ሀገር አለችኝ!... -ይስሐቅ አብርሃም-»

ታደሰ ደምሴ

29 Aug, 15:53


...ገና በልጅነቴ ያስኮረፈችኝ
ስቃ የማታውቅ ሀገር አለችኝ!...
-ይስሐቅ አብርሃም-

ታደሰ ደምሴ

23 Aug, 12:28


"ልጄን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከምልከው የጎጃም አርሶ አደሮች ጋ ብልከው ይሻለኛል፤ምክንያቱም ሰው አድርገው ይልኩልኛል" ያሉት የአዲስ አበባ ኗሪ ማነበሩ?😎

እንደ ሕዝብ ይሕን ያክል ጅራፍ የወረደበት ምን እንደበደለ ስላልገባኝኮነው😌
በላይ በቀለ ግን ምነካህ😎 ያከበረህ ማሕበረሰብ ላይ😌

እድሜ ለመምህር ዘመድኩን በቀለ ይሁንና የሴራ መንፈስ የተወጋ ሆኗል!
እናስ እንደ ሞጣ ቀራንዬ ይሰቀል ትሉኝ ይሆን ይህን ምስል ባለማራገቤ?

አሁን ደግሞ ፍትህ ያለ ግብሩ በጅምላ ለተሰደበው ማሕበረሰብ!

ታደሰ ደምሴ

20 Aug, 16:12


ይኸው

በማይሞላ....ከረጢት ህልም
የህይወቴን....መንገድ ሳልም
ከዘመን ካብ....ስምዘገዘግ
የቆሰለው....ቁስሌ ሳይጠግ
ተሻገርኩት....ስንቱን ዓመት

ይኸው

በተፋቀ....ተስፋ ስሌት
በታመቀ....ብዙ ቅሌት
ባልተሰራ....የዓመት ዕቅድ
እየከመርኩ....ብዙ ሳቅድ
ሳቅድ ........ሳቅድ
የዘመን ካብ....በእጄ ስድጥ
ሰርክ ህይወቴን....ሳላሳልፍ
ከብሶቴ....ስስተቃቀፍ
ስንቴ አለፈኝ....የዘመን እልፍ

ይኸው

ልቤን እሳት....እንደፈጀው
ሽንቁር ጋኔን....ሳላበጀው
"ቀ.ጣ..ይ.ማ"....ብዬ ሳስብ
ድሪቶዬን....ሳልሰበስብ
ከተጉዋዥ ሰልፍ....ሳልሰለፍ
ከእምነቴ....ሳልሸከፍ
ታዘበችኝ....የመስቀል ወፍ

ይኸው

ልግም መርፌ....ቅቤ አልወጋ
በእብደት ሰርግ....ስል ሀይሎጋ
ከምወደው....ሳላወጋ
ስንቴ አለፈ....አይቶኝ በጋ?
ስንቴ አለፈ....አይቶኝ ክረምት?
በደስታ....ሳልጫወት
እንዴ ዝናብ....እንዴ መብረቅ
በመንገዴ....ሲፈራረቅ
ከራስ ሀሳብ....ስተናነቅ
ቁሜ ዓመቴን....ልሰርዘው
በዓደይ ቅጠል....ልገንዘው
ዛሬም ላቅድ....ልክ እንደሰው
ሰው መሆንን... እስክቀምሰው

Abrham F. Yekedas

ታደሰ ደምሴ

18 Aug, 09:56


ታደሰ ደምሴ pinned «የ7 አመት የተከራዩን ልጅ ደፍሮ ከዛም ባለፈ በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው አውሬው ጌትነት የተባለው ወንጀለኛ ግለሰብ 25 አመት የተፈረደበት ሲሆን አሁን ጠበቆቹ ቅጣቱን ለማቅለል ደፋ ቀና እያሉ ነው። እህቶቹ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች የሟች ህፃን ሄቨን እናትን በየሄደችበት እያስፈራሯት ይገኛል የኢትዮጵያ ህዝብ ፍርድ ይስጠኝ ያለችው እናት ፍትህ ትፈልጋለች። ቅጣቱ በቂ እንዳልሆነ ተጨማሪ ቅጣት ሊጣልበት እንደሚገባ…»

ታደሰ ደምሴ

18 Aug, 09:46


የ7 አመት የተከራዩን ልጅ ደፍሮ ከዛም ባለፈ በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው አውሬው ጌትነት የተባለው ወንጀለኛ ግለሰብ 25 አመት የተፈረደበት ሲሆን አሁን ጠበቆቹ ቅጣቱን ለማቅለል ደፋ ቀና እያሉ ነው።

እህቶቹ እንዲሁም ሌሎች ሰዎች የሟች ህፃን ሄቨን እናትን በየሄደችበት እያስፈራሯት ይገኛል የኢትዮጵያ ህዝብ ፍርድ ይስጠኝ ያለችው እናት ፍትህ ትፈልጋለች።

ቅጣቱ በቂ እንዳልሆነ ተጨማሪ ቅጣት ሊጣልበት እንደሚገባ ህዝብ ያንን እንደሚፈልግ ለማሳወቅ የፊርማ ማሰባሰብ እና ለእናቷ የገንዘብ ድጎማ ተጀምሯል።
https://www.change.org/p/justice-for-heaven-and-her-mother?recruited_by_id=94947080-5cca-11ef-af3a-c38f3884f55d&utm_source=share_petition&utm_campaign=psf_combo_share_initial&utm_term=signature_receipt&utm_medium=copylink

👆 በዚህ ሊንክ በመግባት ፊርማችንን መስጠት የቻልን ደግሞ የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ እንችላለን።

ቻናላችን በህጻኗ ላይ በተፈጠረው የግፍ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል።

ይህ ጉዳይ በጊዜ ካልተቋጨ ነገ እኔ እና እናንተም ቤት መግባቱ አይቀርም!

#ፍትህለሔቨን
#Justiceforheven

እናት 😭#በለቅሶ_ፍትህ_ፍትህ እያለች ትገኛለች
ለምታቁት ሰው ሁሉ ሼር ይደረግ በቲክቶክም ቪዲዮ ለሚሰሩ ሰዎች አድርሱልን ፍትህ ለቬበን 🙏

#Humanity is greater than situation

ታደሰ ደምሴ

12 Aug, 17:54


                   ስጀምር ❤️

ማፍቀር ምንማለት ነው እያልኩ የነበረ
በኔ ሲደርስብኝ ገባኝ እያደረ☹️

ለካ ማፍቀር ማለት ስለሰው መኖር ነው
ከራስ ላይ ቀንሶ ለሰው መጨነቅ ነው

አይመስለኝም ነበር ተችሎ የሚኖር
የራስን ፍላጎት የትም ሚወረወር

ሳፈቅር ግን ገባኝ ላንቺ ብቻ ሳስብ🥰
ማፍቀር እንደሚልቅ ከሰው አስተሳሰብ💖

አዎ ዛሬ አወኩኝ የፍቅርን ትርጉም
ለካ የተፈቃሪን ህመም ነው አብሮ መታመም

አሁን ግን ኮራሁኝ አፍቃሪ ስለሆንኩ😊
ለራሴ ብቻ ሳይሆን ለሰውም ስለኖርኩ፡፡
💗


   t.me/ethiopia2123
   t.me/ethiopia2123

ታደሰ ደምሴ

11 Aug, 21:43


የዜግነት ክብር
በኢትዮጵያችን ፀንቶ
የዜግነት ግብር
በኢትዮጵያችን ፀንቶ
ታየ ህዝባዊነት
አደባባይ ወቶ

ለሰላም ለፍትህ
ለህዝቦች ነፃነት
ድንበር እያጠርን
ቆዳ እየከለልን
ቆመናል በከንድነት

መሰረተ ፅኑ
ስብዕናን ያልሻርን
ህዞቦች ነን ሳንበላ
በጸጋው የኖርን

ድንቅ የባህል መድረክ
ያኩሪ ህዝብ ባለቤት
ሁልጊዜ ሰራጊ
በየቀኑ ደጋሽ
ዘላለም ለቅሶ ቤት

እንጠብቅሻለን
አለብን አደራ
ኢትዮጵያችን ኑሪ
እንደልማዳችን
መቃብር እንስራ

mikiyas_feyisa

ታደሰ ደምሴ

10 Aug, 15:11


ኖረሽ እይው በቃ
(በእውቀቱ ስዩም)
ጨለማ ነህ ብለሽ እኔን ስትተቺ
ዘለሽ አትጠግቢ፥ስቀሽ አትሰለቺ
ወርሃ ፅጌ ነው ፤አመት ሙሉ ላንቺ
ደሞ በየቀኑ
ፋሲካ ነው ኑሮሽ
ያለም ሰቀቀኑ
ሩቅ ነው ለጆሮሽ
(የፍጥረት ሰቆቃ)
ለጋ ነው ላ'እምሮሽ
ገላሽም ነው ጮርቃ
ሌላም አልልሽም፤ ኖረሽ እይው በቃ ፤
በየጎዳናሽ ላይ ፥አደይ የሚያነጥፍ
በየዛፉ ቅርፊት፥ ስምሽን የሚጥፍ
በዝቶልሽ፥ፈልቶልሽ ፥አንቺን ሚያሽሞነሙን
ቀምሰሺው አታቂም፥ የብቻነት ሸክሙን
አዎ!
መፈቀር ፥ መታጀብ ከኔክታር ይጥማል
ግን ደግሞ ይገጥማል
በተወደሱበት አንደበት መነቀፍ
ውብ ገላ ጠብቆ፣ ርጥብ ነፋስ ማቀፍ፥
አንዳንዴም ይገጥማል
የማይሰምር ምኞት ፥የማይልቅ ጥበቃ
ሌላም አልልሽም፤ ኖረሽ እይው በቃ፤
አንቺ ደስታ ወዳጅ
በለምለም አፀድ ውስጥ፥ ቢራቢሮ አሳዳጅ
ኑሮ ምትታይሽ፤ እንደ ጣኦስ ቀልማ
እንዳትሸወጂ ባዝማሪዎች ዜማ
በሸንጋዮች ቃላት
ህይወትም እንደ ጃርት፥የሾህ ቀሚስ አላት፤
ተድላም ከሃዘን ፣ጋር ያልፋል በፈረቃ
ከሳቅ በስተጀርባ፥ ይሰለፋል ሲቃ
ሌላ ምን ልበልሽ ፥
ኖረሽ እይው በቃ
(ከ-አዳምኤል)

ታደሰ ደምሴ

09 Aug, 13:52


አንድ ሰው ናፈቀኝ🥰

ገና ያላወቅሁት
ባይኔ ያላየሁት
ጭራሽ ያላሰብሁት
ግን ግን ግን
በፍቅር አንግሼ
በልቤ ላይ ሹሜ
በልቤ ዙፋን ላይ እሱን አስቀምጨ
እፎይ የምልበት ሁሌ 'ምኮራበት
ሁሌም አዲስ ፍቅር ወረት የሌለበት
እኔ እምገዛለት እሱም የሚወደኝ
.
.
.
አንድ ሰው ናፈቀኝ።

ከልዕልት ሰናይት ለኔ የተጻፈ(ከሞጣ ወደ ደብረ ማርቆስ)

🙏🙏🙏

@ethiopia2123

ታደሰ ደምሴ

08 Aug, 19:20


ወዴት ነህ ይለኛል፣
ሊያሳፍረኝ ታክሲ፣
ሊጭነኝ ወያላ፤

እኔና ሀገሬ፣
እኔድበት መንገድ፣
ግብ እንዳለን ሁላ!

/ይስማዕከ ወርቁ/

ታደሰ ደምሴ

08 Aug, 05:57


-
አንደኛውን ባሏን
ቀይባህር ስትሰደው፤
አንደኛውን ደግሞ
ዝምባብዌ  ስትሰደው፤
እኛ ልጆቿ ነን በመጣ በሄደው
ምንወናበደው!።

ኸረ ስንቱን ቻልነው፡
ኸረ ስንቱን ቻልነው፧
.
ያሁኑን አናውቅም
ያሁኑን አናውቅም
ቅዱስ ይሁን እርኩስ፤
እሳት የማያበርድ
እሳት የማይለኩስ።
ያሁኑን አናውቅም
መልአክ ይሁን ሰይጣን፥
አለም እያሳየ
ሰፈር እያሳጣን፤

ማማርን ከደም ጋር፡
ደስታሽን ከሀዘን እያጨማለቀው፤
እርሱን ብትፈቺ
ምን እንደሚመጣ
ፈጣሪ ነው ሚያውቀው።

አሁን ልመርቅሽ
.
አሜን በይ ...  አሜን
አሜን በይ ...  አሜን

እንባሽን በሳቅ ይተካው
ገላሽን እሳት  አይንካው
ችግርሽ ይምከን በሩቁ
ባሎችሽ  ይጨማለቁ።
ድንበር ላይ
እባብ ይጠምጠም
ያለፈሽ እግሩ ይቀልጠም
ቅሌትሽ ገሀድ አይውጣ
ጎዳናሽ አላፊ  አይጣ

ባሎችሽ ሜዳ ቢነሱኝ
እንደ ልጅ ምቦርቅበት፥
ከደጅሽ ገሸሽ አታርጊኝ
ስምሽን ልመርቅበት።
እምዬ የኔ አጎብዳጅ
እምዬ የኔ አሳቢ፡
ደህና ባል እስከምናገኝ
ሌላ ባል እንዳታገቢ!።

ስምሽን በአለም ስለጥፍ
መልክሽን በእጄ ሳቀልም፥
ወደድኩሽ ባልኩበት ቤቴ
ባይተዋር መጤ ብመስልም፤
ዝምታሽ የእርታሽ ወሰን
ልጅ ልቤን እያስደነቀው፥
ከልቤ ስለምወድሽ
አይጠፋም የምጠይቀው...

ባልሽ ግን ፀባዩ እንዴት ነው
ቀን በቀን ይለዋወጣል፥
አስመራ ሄደ ስትዪው
መቀሌ ደርሶ ይመጣል?
እንዴት ነው ሰሞኑን ውሎው
ህመሙ ሳሉ በዛበት
ከእንቅርቱ ድኖ ሳይገግም
ማንቁርቱ ተጨመረበት?
ሳስበው አንቺም መሮሻል
የምስኪን የደሃ ሮሮ፤
ሰቆቃው ይቀንስ ይሆን
ባልሽን ብትፈቺ ኖሮ?

ምከሰው ዳኛው ሆኖብኝ
እምባዬ የኔ ጠበቃ፤
ፍትህን ሽተው ለማግኘት
መበደል ብቻ ላይበቃ፤
ቁጭቴን እንዳልመሰክር
ሾተሏን እያቀመሱኝ፡
እንደ ልጅ መብቴን ሳልጠይቅ
ባሎችሽ ምላሴን ነሱኝ።

ባሎችሽ ሜዳ ቢነሱኝ
ባሎችሽ ሰፈር ቢነሱኝ
እንደ ልጅ ምቦርቅበት
ከደጅሽ ገሽሽ አታርጊኝ
ስምሽን ልመርቅበት ...

አሜን በይ  ..አሜን
አሜን በይ  ..አሜን!

የጠላሽ እቃው  ይንጠልጠል
የከዳሽ በሳት    ይቃጠል
ሚሰብክሽ ጥይት አይጠጣ
ሞቶልሽ ቀባሪ አይጣ
ጀግኖችሽ ህያው   ይሁኑ
ህልምሽም ይስመር በውኑ
ያልጠራሽ ይገፈፍ ልብሱ
ትል ይሁን አልጋው ትራሱ
ተስፋሽን በሩን የዘጋ
ባለበት ጎኑ   ይወጋ

ሰቆቃ ጩኸት ሲበዛ
መቸገር ቤትሽን ሲያምሰው፥
እምባሽንን ስላባባሰ
ባል ብለን የመረጥነው ሰው፤
እምዬ የኔ ገራገር
እምዬ የኔ አሳቢ፡
ደህና ባል እስኪላክልሽ
ሌላ ባል እንዳታገቢ!።

ያልደላሽ የምስኪን ቁንጮ
ልጆችሽ በልተው የረሱሽ
ከትቢያ ወስደው ለመጣል
ከዙፋን ስበው ያነሱሽ
ቢረግጡሽ የማትከፊ
ቢገፉሽ ክንድሽ የማይዝል
ባል ብለሽ ያገባሽው ሰው
ስጋሽን እስኪዘለዝል
ዝም ያልሽው ሆደ ሰፊዋ
እምዬ የኔ አሳቢ
ደህና ባል እስከምናገኝ
ሌላ ባል እንዳታገቢ!።

ባይከፋም እንዳምናው ባልሽ
ባይሰክር እፍኝ ባይጠጣም
በሰላም አፍሮ እንደገባ
በተአምር ሰላም አይወጣም
አንሻም ቃሉ ቢደልል
አንፈልግ ግርማው ቢበዛም፤
የርሱ አፍ ቅቤ ማቅለጡ
ለኛ ሆድ ቁራሽ አይገዛም።

እምዬ   የኔ ገራገር
እምዬ    የኔ አሳቢ
ደህና ባል እስከምናገኝ
ሌላ ባል እንዳታገቢ!።

by @mikiyas_feyisa

ታደሰ ደምሴ

07 Aug, 20:48


ቀስ በቀስ
እንደ ሳቅ ፈገግታ
እንደ ጧት ወገግታ
ቀስ በቀስ
እንደ ሕይወት ዳና
እንደ ትላንትና
ቀስ በቀስ
እንደ ራስ ቅል ጠጉር
እንደ ቆዳ ብጉር
ቀስ በቀስ
ተንሸራትቶ መምጣት
ሀገር ወደ ማጣት ።
----
HEnock Bekele

ታደሰ ደምሴ

06 Aug, 15:55


ታሪኩ እንዲህ ነው...

ክቡር ዳኛው የክስተቱን ዝርዝር ሁኔታ ከሰሙ በኋላ ልጁን እንዲህ ሲሉ ጠየቁ...

"በእርግጥ የሆነ ነገር ሰረቅክ? ዳቦና አይብ ሰርቀህ መደርደሪያ ሰባበርክ?"

ልጁም አንገቱን ደፍቶ በሃፍረት፡- "አዎ" ሲል መለሰ።

ዳኛ፡ "ለምን ሰረቅክ?"

ታዲጊው ልጅ:  "በጣም ፈልጌው ነው።"

ዳኛ፡ "ከመስረቅ ይልቅ መግዛት አልቻልክም ነበር?"

ልጅ፡ "ምንም ገንዘብ አልነበረኝም። "

ዳኛ፡ "ወላጆችህን ገንዘብ ልትጠይቅ ትችል ነበር። "

ልጅ፡ "እኔ ያለኝ፣ አልጋ ላይ የተኛች እና ስራ የሌላት የታመመች እናት ብቻ ነው... ለሷ ስል ዳቦና አይብ ሰርቄያለሁ"😪

ዳኛ፡ "እና አንተ... ምን እየሰራህ ነው? ሥራ የለህም?"

ልጅ፡- "የመኪና አጣቢ ሆኜ እሰራ ነበር። እናቴን ለመርዳት አንድ ቀን ዕረፍት ወሰድኩ፣ ለዚህም ነው ያባረሩኝ።"

ከልጁ ጋር የነበረው ውይይት ካለቀ በኋላ ዳኛው ፍርዱን አስታወቁ፡-

“ሌብነት በተለይም ዳቦ መስረቅ በጣም አሳፋሪ ወንጀል ነው። ለዚህ የስርቆት ወንጀል ሁላችንም ተጠያቂ ነን። ለዚህ የስርቆት ወንጀል ዛሬ እኔ ራሴን ጨምሮ እዚህ ክፍል ውስጥ የተገኘ ሁሉ ተጠያቂ ነው” አሉ።

በመቀጠልም "ሁሉም ተሰብሳቢዎች 10 ዶላር ይቀጣሉ እና ማንም ሰው 10 ዶላር ሳይከፍል ከአዳራሹ አይወጣም::"

ዳኛው ከኪሳቸው የ10 ዶላር ቢል አውጥተው እስክሪብቶ አነሱና እንዲህ ብለው መጻፍ ጀመሩ።

"በተጨማሪም የተራበውን ልጅ ለፖሊስ ያደረሰው ሱቅ ባለቤት 1000 ዶላር እንዲቀጣ አዝዣለሁ እናም ቅጣቱ በአንድ ሰዓት ውስጥ ካልተከፈለ ሱቁ ተዘግቶ ይቆያል።"

ዳኛው አክለውም “አንድ ሰው ዳቦ ሲሰርቅ ከተያዘ መላው የዚች ሀገር ህዝብና መሪ ሊያፍር ይገባል” አሉ።

በአዳራሹ ውስጥ የነበሩት ሁሉ ልጁን/ታዳጊውን/ ይቅርታ ጠይቀው ሙሉ ገንዘቡን ሰጡት።

ዳኛው እንባቸውን ለመደበቅ እየሞከሩ ከችሎቱ ወጡ። 

ተሰብሳቢዎቹ የዳኛውን ውሳኔ ከሰሙ በኋላ ዓይናቸው በእንባ ተሞላ።

ከማህበራዊ ሚዲያ አግኝተነው ስለወደድነው አጋራናችሁ።

እናንተስ ይህን ታሪክ በሚመለከት ምን ትላላችሁ?
ሃሳባችሁን አጋሩን።

ታሪኩን አስተማሪ ሆኖ ካገኛችሁት ሌሎችም ይማሩበት ዘንድ #like #share ማድረግን #አትርሱ

የላቁ እይታዎች እና እሳቤዎች