Mane Writer @mane121921 Channel on Telegram

Mane Writer

@mane121921


ምርትና አግልግሎቶን ለማስተዋወቅ ያናግሩኝ !!!

ለሀሳብ አስተያየታችሁ

ሀሳብ አስተያየት 👉 @Maneget
የtechnology ቻናላችን
@maf_digital

Mane Writer (Amharic)

በሰላም እንኳን መንፈሳዊ በርችት አንባቢዎች! በምርትና አግልግሎቶን የምንለዋድህ እንጂ ቈላውህ አይቆምልሽም። የመንፈሳዊ በርችትና አግልግሎቶች ለሚሰራበት ሰእሊ እንዴት እንደምንደርስ እንደሚወድ።

በትንሽ መንፈሳዊ መረጃዎችን ላይ ለሀሳብ አስተያየታችሁ ሽልማታ በወንድማማችን ለሚለውጥ ማሰባሰብ ይችላል። ከባቢሎን ለሀሳብም የበለጠ ምርትና አግልግሎቶችን በቀጥታ ይመስላል። ጥሩ ስርጭትን በወንድማማችን ለሚበቃ ማሰባሰብ እና ሚስትህን ለማስወገድ ይችላል።

ለቅሎን ካለ creator @Controllerof አንድ መንፈሳዊ እና እንስሳን የtechnology ቻናላችን @maf_digital ተነስተህ ለሀሳብን ለሚከተለው አግልግሎቶች ለመስጠት ቻውንት ያነሳንሃል። እና ትምህርትና ብቻ እንደሆነ ተታወቀንህ።

Mane Writer

20 Nov, 18:30


ኢላሪ(እውነተኛ ታሪክ)

እዮባ አጠገባችን መጣ።ደንግጬ እዮባ አልኩት።...ነይ ተነሽ እንሂድ አለኝ....እዮባ ግን እኮ ስለው ...ተነሺ አለኝ።አቤል ብድግ ብሎ ...ስማ እዮብ በመጀመሪያ አትጩህ ሁለተኛ ደግሞ ያለፍላጎቷ የትም አትሄድም አለው።እዮባም ወደ እሱ ዞሮ...በመጀመሪያ አንተ ምን አገባህ ፍቅረኛዬ ናት በዚህ በማታ ከወንድ ጋር  እንድትሆን አልፈልግም።...እረ እዮባ አቤል እኮ ጉአደኛዬ ነው።ተነሺ ብሎ እጄን ይዞ አስነሳኝ።ልክ ልንሄድ ስንል አቤል እዮብ የያዘኝን እጅ አስለለቀኝ እና....ያለ ፍላጎቷ የትም አትሄድም ፍቅረኛህ እንደሆነች አውቃለው ቢሆንም ግን እንዲ እንድታደርጋት አልፈቅድልህም አለው።እዮባም ...ጥሩ አንቺ ምረጪ እዚው ትሆኛለሽ ወይስ ከእኔ ጋር ትሄጃለሽ አለኝ።

ወደ አቤላ ዞር አልኩ።ፈገግ አለ።...አቤላ ሌላ ቀን እክስሀለው እሺ ይቅርታ አልኩት።አቤላም... እጠብቃለው በቃ ሂጂ አለኝ።ከእዮባ ጋር ተያይዘን ወጣን።እዮብም ምንም ሳይለኝ መኪና ውስጥ እንድገባ ብቻ ነገሮኝ ወደ መኪናው ገባ።

እየሄድንም ...የት ነው ምንሄደው እዮብ አልኩት።...ወደ ቤት ነው ምወስድሽ አሁን መሽቷል ምንም ማለት አልፈልግም ላስቀይምሽም አልፈልግም...አይ አይ ተናገር ምንም ዝም ማለት አይጠበቅብህም....ሲጀመር ጥፋትሽን እያወቅሽው ልነግርሽም አይገባም።

ቆይ ምንድ ነው ጥፋቴ ንገረኝ አቤል ጋር መምጣቴ ነው።አቤልም እኮ ጓደኛዬ ነው ደግሞ ምርቃቱ ነው።...እኔ ደግሞ ፍቅረኛሽ ነኝ አብረሽኝ እንድትሆኝ እኔም እፈልጋለው ...አብሬክማ ነበርኩ አንተ ነክ አብረህኝ ያልነበርከው።አንተን ብዬ መጥቼ ስላልተመቸክ አይደል አንዴ እንኳን ወደ እኔ ያልመጣከው....ኢላሪያ እያየሽ አልነበር እንዴ ሰውን...አዎ ጥፋተኛ ነክ አላልኩም ብቻ አንተም ቢዚ ነበርክ እኔም አቤል ቀጥሮኝ ስለነበር ሄድኩኝ።

ኢላሪያ አታናጅኝ ሲጀመር አቤል እንደሚወድሽ እያወቅሽ አሱ ጋር ስትሄጂ ዝም እንድል ነው ምትፈልጊው .....ወደደኝና ምን ይሁን እኔ እኮ አንተን ስለምወድህ መሰለኝ ከረድኤት ጋር ሆነክ አምኜክ የሄድኩት...ምንም የማይገናኝ ነገር አታውሪ...ምንም የማይገናኝ ነገር የለውም ረድኤት ትወድክ አይደል...ቢሆንም አንቺ ሴት ነሽ...ቆይ አንተ ቤት እያለው ከዳን ጋር ነበርኩ።ዳን ለእኔ የተለየ ስሜት አለው አይደል ታድያ ለምን እንደዚ አላልክም።

ከእሱ ጋር እኮ ጉአደኛ አይደላችሁ ....ከአቤል ጋርም ጓደኛ ነን።ዝም አለኝና መኪናው በፍጥነት መንዳት ጀመረ።...እዮባ ቀስ በል አልኩት።እያበረረው መኪናው በሬ ድረስ አደረሰኝ።ከወረድኩ በኃላ ግን ጥፋተኝነት ተሰምቶኝ ይቅርታ ልለው ዞር ስል ትቶኝ ሄደ።


ከተመቻችሁ like
https://t.me/mane121921

Mane Writer

20 Nov, 17:50


Selam ehit pharmacist nege sir fetichalew kelij gr tinishe nuro kebidonal sir felig atahun layisensm alen please ergin
(በተመረቀችበት ዘርፍ ስራ ልታገኙላት ምትችሉ ተባበሯት ቤተሰቦቼ)

Mane Writer

20 Nov, 17:46


ኢላሪ(እውነተኛ ታሪክ)

ክፍል 17


ከእዮባ ጋር በቃ በፍቅር ክንፍ አልን።በዛውም ልክ ረድኤት አላስቀምጥ ብላናለች።የነእዮባም ምርቃት እንደቀልድ ደረሰ።የእዮባ ምርቃት ዝግጅት እዚው አዲስ አበባ ነው የዳን እና የልዑል ግን ድሬ ነው።ሰሞኑንም እነ እዮባ ቢዚ ስለሆኑ አንገናኝም።በስልክ ብቻ አወራዋለው።

ዛሬ ግን ከአቤላ ተቀጣጣጥረን እያወራን።የምርቃት ዝግጅት እንደማያዘጋጅ ነገረኝ።...እንዴ ለምን አቤላ...ኢላሪ አስፈላጊ አይደለም ጋውን ለብሼ ከገባው በቂያቸው ነው...እንዴ እቤት ግን እሺ ይሉሀል አልኩ፦እሱም ደበስበስ አድርጎት...ተይው እሱን ብቻ አንቺ የዛን ቀን አብረሽኝ አትሆኝም አለኝ።...እእ አቤሎ ታውቅ የለ የእዮባም ምርቃት ነው እሱ ጋር እሄዳለው በነጋታው ደግሞ እነ ዳን ጋር ድሬ እንሄዳለን።....እኔስ ለሁሉም ጊዜ ሰተሽ ለኔ ትንሽዬ ሰዓት አጣሽ...እረ እንደዛ አይደለም።

ስቀልድሽ ነው ችግር የለውም እሺ የፍቅርሽን ጊዜማ አልሻማብሽም ግን ደግሞ ብታገኝኝ ደስ ይለኛል።...አመቻችቼ  እነግርሀለው በቃ።እንደቀልድም የነ እዮባ ምርቃት ደረሰ።ጠዋት ጊቢ አብረናቸው ለመሆን ልንቀበላቸው አስበን አልተመቸንም።የእዮባም ዝግጅት ከሰዓት ስለሆነ ተዘገጃጅተን ሄድን።

በቻልኩት አቅም ለመዘነጥ ሞክርያለው።ወደ ዝግጁትም ማለትም እዮባ ቤት ደረስን።ትልቅ ዝግጅት ነው የተደረገው።ወደ ውስጥም ገባን።የሚገርመው ግን ቀድማን ረድኤቴ መገኘቱዋ አጠገቡ ተቀምጣለች።ምንም ሳልል ሄጄ ሰላም አልኩት እነ ዳንም ነበሩ እነሱንም ሰላም ብለን ቁጭ አልን።

በጣም ደስ የሚል ዝግጅት ነበረ።ግን ከእዮባ ጋር የብቻችን ጊዜ ይኖረናል ብዬ አስቤ ነበር።ግን ጭራሽ የሆነ ሰዓት ግን ትንሽ ደቂቃ ለብቻው አገኘውት ስጦታዬን ሰጥቼው ትንሽ ብቻ አብረን እንደቆየን ረድኤት መታ ጠራችው።

ግን እሱ ለምን ጠራሽኝ እንደማለት ትቶኝ ሄደ።ተናደድኩኝ ግን ዝም አልኩ።ውስጥ ገብቼ ቁጭ አልኩ።ከዳን ጋር ቁጭ ብለን ብዙ ነገር አወራን ተጫወትን በዛ ሁሉ ሰዓት ግን ወደ እኔ አልመጣም።ወደ 11 ሰዓት ግን አቤላ ደወለ።ወጣ ብዬ አነሳውት።

ሄሎ አቤላ...ኢላሪ ..ወዬ ....የት ነሽ...እዮባ ጋር ነኝ....ውይ በቃ ችግር የለውም ተይው...ምኑን ነው ምተወው ...አይ እኔማ እራት ልጋብዝሽ ነበር ግን ሲል ቶሎ ብዬ...እና ጋብዘኛ አልኩት...አሁን ይመችሻል አለኝ በአግራሞት...አዎ...በቃ ያለሽበትን በቴክስት ላኪልኝ መጥቼ እወስድሻለው።እሺ ብዬ ዘጋውት።ለራሴም እዮባ እዚ ሆኜ ካላየኝ ብሄድ ይሻላል ብዬ ወደ ውስጥ ገባው

አቤልም እንደደረሰ እና እንድወጣ ነገረኝ።ሁሉንም ተሰናበትኳቸው የት እንደሆንኩ ሲጠይቁኝ ግብዧ አለብኝ ብዬ ወጣው።ዳንም ተከተለኝ።...ኢላሪ የት ነሽ...ዳን ቀጠሮ አለብኝ ይቅርታ እሺ...እዮብ ያውቃል እንደምትሄጂ ...ማለት...አቤል ጋር አይደል የምትሄጅው.....አዎ ነው...እና እዮብ ማወቅ አለበት...ለምን አቤልም ምርቃቱ ነው እናም ጉአደኛዬ ነው እና ምን ብዬ ነው ለእዮብ ማስፈቅደው...እሱን እንጃ ግን...ዝም በል ዳን ንገረው እሺ ቢዚ ስለሆነ ነው ያልነገርኩት ብቻ ነገ ድሬ እንገናኝ ብዬው ወጣው።

አቤላን አገኘዎት።ትልቅ ሬስቶራንት ሄደን ቁጭ አልን።አቤልም ትኩር ብሎ ካየኝ በኃላ ...በጣም አምሮብሻል ይሄ ሁሉ ለእዮብ ነው አይደል አለኝ።ፈገግ ብዬ አንገቴን ደፋው።...ታውቂያለሽ ኢላሪ አይንሽን ሳየው ሲለኝ አቋርጬ ...የመጀመሪያ ያፈቀርካት ሴት ትታይሀለች ብዬ ሳኩኝ...ነገር አትረሺም ብቻ ግን አዎ ሁሉ ነገርሽ የሷን ይመስለኛል።...እኔ ምልክ አሁን ያገባችውን ሰው ትታ ወዳንተ ብትመጣ ትቀበላታለህ....አይመስለኝም ኢላሪ ....አይመስለኝም ማለት አሁንም ስሜት አለክ ማለት ነው ለሷ አንገራገርክ እኮ.....እንደዛ ሳይሆን አሁን የማውቀው ካንቺ ፍቅር እንደያዘኝ ብቻ ነው።

ግን አቤላ ምን እንደማስብ ታውቃለህ አሁንም ትወዳታለህ እኔን እሷን መስዬ ስለታየውህ በእኔ ውስጥ እሷን ለማግኘት እየሞከርክ ነው።....በፍፁም ኢላሪ ታውቂያለሽ አሁንም ለራሴ ሚገርመኝ ነገር ከሷ በኃላ ማፍቀር እንደማልችል ነበር የማስበው ግን አሁን ላይ ላንቺ የሚሰማኝን ስሜት እኔ እራሱ ተቋቁሜው መቆሜ ይገርመኛል።

እሺ ግን አቤላ እኔ እና እሷ ትንሽ እንኳን የሚለይ ነገር የለንም።...እረ በደንብ አላችሁ እሷ በራሷ ሀሳብ ከደረቀች ደረቀች ነው።አንቺ ደግሞ የሰው ሀሳብ ላለመቃረን ትስማሚያለሽ አንቺማ ሀሳብም አታቀርቢ።እሷ እራጋታዋ እንዳለ ሆኖ ጨዋታ ላይ ጎበዝ ናት አንቺ ግን ሰው ባወራው ነው ምትዝናኝው ብቻ ሁለታችሁም እርጋታችሁ ይገርመኛል።

በል በል በቃክ ልጅቷ ስቅ አላት እኮ...አንቺ ግን ከእዮብ በፊት አፍቅረሽ አታውቂም ማለቴ ፍቅረኛ ኖሮሽ አያውቅም።...ውይ አያውቅም...ማለት እንዴት አላምንሽም...እህ ለምን የምሬን ነው ከትምህርት ወደ ቤት ነበር በቃ።...ማለት ቆይ ወንድ የለም እንዴ ስልሽ አያስቸግርሽም ቆንጆ ነሽ በዛ ላይ ጎበዝ እና ምርጥ ፀባይ ያለሽ ልጅ ነሽ ....እሱማ አይተፋም ግን እኔን ምን ይመለከተኛል...እረ እና ምንም ምንም አድርገሽ አታውቂም ብሎ በመገረም ይመለከተኝ ጀመር።

ሆ አንተ ምንድ ነዎ ምታወራው ተወኝ ...በለው እዮብ አፈሰ በይኛ አለኝ እየሳቀ።ድንገት ግን ስልኬ ጠራ እዮባ ነው።ወጣ ብዬ አነሳው።...ሄሎ እዮባ...የት ነሽ አላሪያ አለኝ።...ምነው በሰላም...ማለት የት እንደሆንሽ ማወቅ አልችልም ሳትነግሪኝ እኮ ነው የሄድሽው....ስላልተመቸክ እኮ ነው ቻው ሳልልክ የሄድኩት...አሁን የት ነሽ ...አቤል ጋር ነኝ።....የምርሽ ነው ....አዎ ምነው....እሺ የት ነሽ መጥቼ እወስድሻለው....እንዴ ለምንድ ነው ምትወስደኝ ....ምን ማለት ነው አንቺ ግን ቆይ ምንድ ነው ሀሳብሽ ...እንዴ እዮብ ምን አደረኩኝ አቤልም ምርቃቱ ነው እኮ ጉአደኛዬ አይደል እንዴ።....ጉአደኝነቱ ላንቺ ነው እሺ አሁን የት እንዳለሽ ንገሪኝ ስንገናኝ እናወራለን።

ሲጮህብኝ ደንግጬ ያለሁበትን ነገርኩት።ግን ደግሞ አሁን ወደ ቤት እገባለው ነገ እናወራን ብዬ ዘጋውት።ወደ አቤል ተመልሼ ቁጭ አልኩ። ...ችግር አለ እንዴ ኢላሪ ...እረ በጭራሽ ምንም ችግር የለም ብዬ ዝም አልኩ።ግን ብዙም ሳይቆይ እዮባ እኔ እና አቤል ያለንበት መቀመጫ ድረስ መጣ።

(ሙሉ ታሪኩን vip ቻናል ላይ ታገኙታላችሁ vip ለመቀላቀል👇👇👇
@Maneget

https://t.me/mane121921

Mane Writer

20 Nov, 08:18


ከዚህ በፊት በሪል እስቴት ዘርፍ በሴልስነት ስትሰሩ የነበራችሁ ሰዎች ቢያንስ የአንድ አመት ልምድ ካላችሁ በ15,000 ደሞዝ ተቀጥራችሁ መስራት ትችላላችሁ

@Maneget

Mane Writer

20 Nov, 06:41


ከምንም በላይ የብቸኝነትና ያለመፈለግ ስሜት በጣም ከባድ ነው ።
ሆድ ያስብሳል እራሳችንን እንድንጠላውና ያለንበትን ሁኔታ እንዳናመሰግን ያደርገናል ግን አይዞን ከዚህ ስሜት እራሳችንን እናርቅ አንዳንዴ በዙሪያችን የታሰርንበት ሰንሰለት መበጠስ መቻል አለብን።
የውሳኔ ሰው እንሁን አንዳንዴም እንቢ አይሆንም የሚለውን ነገር እንልመድ ነገሮችን ፊት ለፊት እንጋፈጣቸው።
ለልባችን ሰላም ሚሰጠን ቦታ ላይ ብቻ እንቆይ ።
እስቲ አንዳንዴ በራሳችን መወሰንን እንልመድ ልባችንን እንከተል እስከመቼ በሰዎች ላይ ተንተርሰን እስከመቼ ሰዎች በሚመሩን መንገድ ላይ ብቻ እየተጓዝን እንቆያለን።

Mane Writer

19 Nov, 19:21


ኢላሪ(እውነተኛ ታሪክ)


አቤልን ተሰናብዬ ወደ ዶርም ሄድኩኝ።ከአንድ ሳምንት በኃላ የተስማማንበት ለመዝናናት ለ 3 ቀን ሶደሬ ሄድን።እኔና ጉአደኞቼ 5 እዮባ ዳን ልዑል እና የእነሱ 3 ጉአደኞች እና ሚኪ ኦና ሁለት ጉአደኞቹ ሆነን ሄድን።እደደረስን room ያዝንን አንደኛዬን ለእራት እወጣለው ብዬ ተኛው።ወደ 12 ሰዓት ተነሳው ሁላችንም ተባብሰን ወጣን።ሁላችንም አብረን እራት በላን።በቃ ደስታዬ በቃላት አይገፅም።እራት በልተን እንደጨረስን አሸዋዋው ላይ ሁላችንም ቁጭ አልን።እዮባ አጠገቤ መቶ ተቀመጠ።ከምንም በላይ ደስተኛ የሆንኩትም እሱ ስላለ ነው።ድንገት ፊቴን ወደ ኃላ ዞር ሳደርግ ፕኑ እና ሚኪ ሌላ አለም ውስጥ ናቸው።ከእነዮባ ጉአደኛ ውስጥ አንዱ የቤቲ ፍቅረኛ ነው እሷም ከእሱ ጋር ናት።ዳኒ እና ሀኒን አቅፉት ከተቀሩት  ጋር በግሩፕ እያወሩ ነው።

እዮባ..ሀኒ ዳንን ታፈቅረዋለች አይደል አለኝ....ማለት አልኩት።...አይ እንደምታፈቅረው እኔ ከድርጊቷ በደንብ ተረድቻለው ...ዳኒስ የተረዳ ይመስልካል...አዎ በደንብ ግን ደግሞ እንዳትጎዳ ባላወቀ እየሆነ ይሆናል...እንዴ እዮባ ምን እያልክ ነው እንደውም ባላወቀ በሆነ ቁጥር የምትግዳው ጉዳት አይበልጥም ብለህ ነው።

አላውቅም ኢላሪ ዳን የሚያስበውን ማወቅ ከባድ ነው ግን ሀኒ እንድትጎዳ እንደማያደርግ እርግጠኛ ነኝ።...እንደዛ ቢሆን ደስ ይለኛል  ብዬ ዝም አልኩት።በትኩረት አየኝና...እሺ ቆይ አንቺ ለምንድ ነው ፍቅርን የምትሸሽው ....መቼ ሸሸው....ከዚህ በላይ እንደምታፈቅሪኝ አውቃለው ታድያ ለምን ትሸሽኛለሽ።

ተነስቼ ሄድኩኝ።ውይ እዮባ ምን አለ ቢረዳኝ ግን እኔ ከሱ ጋር መሆን ጠልቼ ነው እያልኩ ከራሴ ጋር እያወራው እዮባ ከኃላዬ መጣ።...ቆይ ለምን ትሸሻለሽ መሸሽ መፍትሄ ሆኖ አያውቅም አለኝ።ወደ እሱ ዞር ብዬ....እዮብ ምን አድርጊ ነው ምትለኝ አልኩት...ኢላሪ አትሽሺ ነገሮችን ተጋፈጪ እያልክሽ ነው አዎ አውቃለው ያንቺን ስሜት ለማወቅ ጊዜ ፈጅቶብኛል ግን ደግም አሁን እርግጠኛ ነኝ እንደምታፈቅሪኝ አልጠራጠርም...ስለዚህ ምን ይሁን አዎ እወድካለው ከመጀመሪያው ጀምሮ እወድካለው ካንተ ጋር ስሆን ምንም የምሆን አይመስለኝም።ከሌላ ሴት ጋር ነበር እየተባለ እንኳን እወድካለው።ስለው አቀፈኝ አቀፍኩት።...ስሚኝ ኢላሪ ሄዋኔ ናት ያልኩሽ ሴት ነሽ በጣም ነው የማፈቅርሽ በዚህ እንዳትጠራጠሪ።የዛን ምሽት የእኔና የእዮባ ፍቅር ተጀመረ።

https://t.me/mane121921

Mane Writer

19 Nov, 18:33


ዛሬ ከአንድ ፀሀፊጋ  የማውራት እድሉን አጊቼ ትልቅ እርእስ አንስተን እያወራን ነበር።
እና መቼስ ሰው ከሰው ነው ሚማረው አደል እሱ ከነገረኝ ብዙ ነገሮች አንፃር ቻናሌ ላይ እንደ research ነገር መስራት ፈልጌ ነበር አሁን ቻናሌ ላይ የሚከተሉኝ ሰዎች እነማን ናቸው ሚለውን አይቼ ነው ካሁን ቡሀላ ያሉትን ፅሁፎቼን ማዘጋጅላችሁ ስለዚህ የእናንተን ትክክለኛ እድሜና አሁን ምን ላይ እንዳላችሁ ሁላችሁ እንድታሳውቁኝ አደራ🙏

Mane Writer

19 Nov, 18:18


ኢላሪ እኔ ይሄን ሁሉ ነገር የነገርኩሽ ወደ ራሴ ላመጣሽ አይደለም አልዋሽም የኔ ብትሆኝ ደስ ይለኛል ግን ደግሞ አንቺም ስሜት አለሽ ስሜትሽን ደግሞ አልጋፋም።እጣፈንታሽ እኔ ከሆንኩ ግን የትም አትሄጂም ፈጣሪ ለእኔ ካለሽ ትመጫለሽ ካልሆነም ግን ሁሉንም እቀበላለው።ግን አሁንም ቢሆን ማንም ካንቺ እንድርቅ ሊያስገድደኝ አይችልም ተስማማን አይደል አለኝ።አዎ አልኩት።

በነገራችን ላይ vip ቻናላችን ላይ ኢላሪን ተለቋል በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃል።
vip ለመቀላቀል 100 ብር ያስከፍላል ከኢላሪ በተጨማሪ ሀና የተሰኘ ተወዳጅ ታሪክም እያስነበብን ነው🙏)
@Maneget
https://t.me/mane121921

Mane Writer

19 Nov, 18:18


ኢላሪ(እውነተኛ ታሪክ)

ክፍል 16


ካፌ ጨራርሰን ወደ ዶርም ገባን።እንደገባን ፕኑ አጠገቤ መታ እየተቅለሰለሰች...የኔ ቆንጆ የኔ ማዓረይ  በእናትሽ ሚኪንም ስንሄድ ጥሪው አለችኝ።በሳቅ ሞትኩኝ ብዙ ሰዓት ሳቄን ማቆም አቃተኝ።ትንሽ ረገብ ሲልልኝ ...ቆይ አንቺ ስልኩ አለሽ አይደል ለምን ደውለሽ ና አትይው ስላት...ውይ ኢላሪ እኔ ማለት ስላልፈለኩ ነው አይገባሽም እኔ ሴት ሆኜ እንዲ ብል ይጨንቃል ሀናም ከአፋ ነጥቃ ...ቆይ አንቺ ፕኑ ለአዳር የጠራሽው አስመሰልሽው እኮ ብላ ሳቀችባት።ፕኑም አኩርፉ ቁጭ ስትል ...በቃ እጠራልሻለው አልኳት።

ከተቀመጠችበት ፍንጥር ብላ ዘላ መጮህ ጀመረች።ሁላችን ሳቃችንን ለቀቅነው።እሷም አብራ መሳቅ ጀመረች።ሀኒም...አዲስ ፎንቃ እያየን ነው ብላ ሳቀች።ከምንም በላይ ዶርም የማሳልፈውን ጊዜ እወደዋለው።ቅዳሜ እና እሁድም ቤት ሄጄ ሰኞ ወደ ጊቢ ተመለስኩኝ።ክላስ ጨራርሰን ሁላችንም ገብተን ተኛኝ ወደ 11 ሰዓት ስልኬ ጠራ አቤል ነው። ሊያገኘኝ እንደሚፈልግ እና የተለመደው ቦታ እየጠበቀኝ መሆኑን ነግሮኝ ስልኩን ዘጋው።ተነስቼ ተጣጥቤ ወጣው።

ስደርስ ቁጭ ብሎ እየጠበቀኝ ነው።ሰላም ተባብለን። ትንሽ ነገር ካወራን በኃላ ለምን እንደፈለገኝ ጠየኩት።ከተቀመጠበት ዞር ብሎ አይኔን እያየኝ...ኢላሪ ፍቅር ያዘኝ አለኝ።እኔም በአግራሞት....እረረ ድሮም እንደማይቀርልክ አውቃለው እእ ቤዛ ናት አልኩት።...ኢላሪ አሁን የምንነግርሽ ነገር እንደሚደረደብርሽ አውቃለው ግን መናገር አለብኝ።ኢላሪ ካንቺ ፍቅር ይዞኛል አለኝ።ልክ ላወራ ስል አቋረጠኝ ...ኢላሪ እዮብን እንደምታፈቅሪው አውቃለው እናም በምርጫሽም አልገባም ስሜቴን መናገር ስላለብኝ ነው።እውነት ለመናገር የፍቅር ስሜት ሲሰማኝ የመጀመሪያዬ አይደለም።...አቤላ አፍቅረክ ታውቃለክ...አዎ...ማንን....መስማት ትፈልጊያለሽ ልንገርሽ..አዎ ንረገረኝ አልኩት እሺ ብሎ ይነግረኝ ጀመር።

የሀይስኩል ተማሪ እያለው ነበር 11 ክፍል እያለው አለ የተባለ የግል ትምህርት ቤት ነበር ምማረው።በጣም ሰቃይ ተማሪ ነበርኩ።ትምህርት ቤታችንም የሀብታም ነበር።እኔ ምን አስተሳሰብ ነበረኝ መሰለሽ እኔ ብቻ ሳልሆን አብዛኞቻችን ገንዘብ ካለን ምንም ፈልገን እንደማናጣ ነበር ምናስበው በተለይ ሴትን።እኛ ትምህርት ቤት ከሚማሩት ሴቶች አንዳቸው ቢሆን ስበውኝ አያውቁም ሁላ በጣም ነው ሚዘጉኝ ሁሉ ነገራቸው አርቴፍሻል ከአወራራቸው ጭምር ጊዜያዊ ሴቶች ናቸው።

በጣም ነው ሚቀፋኝ በዚህ ምክንያት ጢባራም ነው ይሉኛል።ግማሽ ሴሚስተር ላይ ግን አንዲት ልጅ ገባች።ሁሉም ተማሪዎች ስለ ቁንጅናዋ አወሩላት ግን እዚህ ግቢ ስለውበት መወራት የተለመደ ስለሆነ ግድ አልሰጠኝም ነበር።አንድ ቀን ግን ከአስተማሪ ጋር በውጤት ተጣልቼ ከአስተማሪዎች room ወጥቼ ወደ ክላስ መሄድ ጀመርኩ በጣም ተናድጄ ነበር።ድንገት ግን ከሆነች ልጅ ጋር ተጋጨን ገፍትሬ ጣልኩዋት።ከእኔም ብሶ እያየሽ አትሄጅም ብያት ጥያት ሄድኩ።

ምንም አላለችኝም።በቀጣይ ቀን ግን የጉአደኛዬ ፍቅረኛ የገፈትርኳትን ልጅ ተዋወቁዋት ጉአደኛዬ ናት ብላ ይዛት መጣች።ተዋወቅናት በጣም ረጋ ያለች ናት ከምነግርሽ በላይ ረጋ ያለች ናት።ከተዋወቅናትም በኃላ ቁጭ አለች።ጉአደኛዬም ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብሎ እሷ እኮ ናት አዲሶ ተማሪ አለኝ።ዝም አልኩት።ምሳ ሰዓት አንድ አንዴ የጉአደኛዬ ፍቅረኛ ይዛት ትመጣለች።አንድ ቀን ግን ከሆነ ልጅ ጋር በሀይለኛው መከራከር ጀመረች።እሱ ገንዘብ ሁሉንም ይገዛል እሷ ሁሉንም አይገዛም እያለች።በጣም ተናድጄ አጠገቡዋ ሄጄ ቆሜ ...እኔ በገንዘቤ አንቺን መግዛት እችላለው አልኩዋት።እስከዛሬ ፊቷ እንዲ ሲቀላ አይቼው አላውቅም በአንዴ ቲማቲም ሆነች እኔም ደገምኩላት....አሁን ገንዘብ ስላለሽ ሊሆን ይችላል ባይኖርሽ ግን እኔ እገዛሻለው እንዳልኳት በጥፊ ሞላችልኝ።ከቦርሳዋ ብዙ ብር አውጥታ ፊት ለፊቴ ለሁለት ቀዳደችው እና ፊቴ ላይ በተነችው።እንባ እየተናነቃት...ይሄ እኮ ወረቀት ነው እኔ ግን ሰው ነኝ እሺ ብላ ጥላኝ ወጣች።

ከዛ ቡሀላ ግን ይቅርታው ጠየኩዋት። ከዛም በላይ ግን ቀረብዋት።

በጣም ጉአደኛሞች ሆንን 12 ክፍል እኔም እሷም ጉአደኛዬም የጉአደኛዬ ፍቅረኛም አንድ ክላስ ደረሰን።በቃ ከልቧ ሰው ናት የላይ ውበት ብቻ ሳይሆን የውስጥ ውበቷም የተለየ ነው።እሷ እየበላች የተራበ ካየች አቁማ እየበላች ያለውን ሄዳ ትሰጣለች።በቃ ሴት ናት ከምንም በላይ ደግሞ በትምህርቷ በጣም ጎበዝ ናት።ሁላ እኔ እና እሷን ደሰጃ መለየት አቅቷቸው ሌላ ፈተና ተሰቶን በአንድ ነጥብ በልጣኝ አንደኛ ወጣች።

ምን አለፋሽ በቃ እሷን ላለመውደድ ምክንያት የለኝም አፈቀርኳት እሷም አፈቀረችኝ አብረን ሆንን።በፍቅር ክንፍ አልን።ግን ማትሪክ እየደረሰ ሲመጣ ተቀያየረችብኝ። ትነጫነጫለች ዝም ብላ ታለቅሳለች ትዘጋኛለች።በዛው ልክም ትታመም ጀመር እራሷን ትስታለች እኔ ደግሞ እንደዛ ሆና ሳያት መተንፈስ ሁላ ይሳነኛል።ብቻ እንደምንም ማትሪክ ተፈተንን።ትምህርት ቤት ዝግጅት አዘጋጁ አብረን ሄድን።መጠጥ አጠጪ ብላትም አልሰማም አለች።

ማታ ላይ ግን room ይዘን እዚህ ካላደርን አለችኝ።እምቢ ስትለኝ በቃ ይዜ እሷን አስተኛታለው ብዬ room ያዝኩኝ።ስንገባ ግን አብረህኝ ካልተኛን ከለችኝ።አይሆንም አልኳት ምክንያቱም እኔ እሷን ለአንድ ቀን ስሜት አልፈልጋትም።...እሷም እያለቀሰች ምን አለ አብረህኝ ብተኛ ሪሴን እንኳን ሰጥቼህ ብለይህ እባክህ አብረህኝ እደር ካንተ ጋር ለመጨረሻ ጊዜም ቢሆን ጥሩ ምሽት ማሳለፍ እፈልጋለው ትለኝ ጀመር።ግራ ተጋባው ስለምን መለያየት እንደምታወራ ጠየኩዋት...አቤላ ዝም ብለክ ና እቀፈኝ ልቀፍክ እኔነቴን ልስጥህ አባቴ እንደማፈቅርህ እያወቀ ካልተረዳኝ ከእኔ ደስታ ይልቅ የሱን ፍላጎት ከሰማ ምን ላድርግ አለችኝ የስካር መንፈስ ይሆናል ብዬ ላስተኛት ብሞክርም አልቻልኩም።

አሳሳተችኝ አብረን አደርን።ድንግል ነበረች አላውቅም ለምን እንደሆነ ግን አከበርኳት ደስ አለኝ።ጠዋት ተነስተን አብረን ሻወር ወስደን።ቁርስ እየበላን ማታ ያለችኝን ጠየኩዋት ደንገጥ ብላ...አቤላ ዛሬ ስላንተ እና ስለእኔ ብቻ እናውራ ዛሬን ስልካችንን አጥፍተን ስንዝናና እንዋል አለችኝ።እኔም እንዳለችኝ አደረኩኝ ከዛም በኃላ ግን ስልኬን አታነሳም ቴክስት አትመልስም።እንደምንም ብዬ ግን አገኘዋት ምክያቷንም ጠየኩዋት።አባትዋ እንደታመመ እና ከጉአደኛው ልጅ ጋር ሊድራት እንደሆነ እና በአባቷ ውሳኔ እንዳልተከፋች እና አባቷ ስለታመመ እሱን ማስደሰት እንደሞትፈልግ እና እንደሞትኩኝ አድርገህ እርሳኝ ብላ ሀሳቤን ሳትሰማ ጥላኝ ሄደች።

ውጤትም ለሁለታችንም መጣልን እሷ ጎንደር ደረሳት እኔ ደግሞ እዚ።እሷ ግን እንደማትሄድ ጉአደኛዋ ነገረችኝ።እኔ ግን ደህና መሆን አቃተኝ እንዳገባች እና ከተማ ቀይራ እንደሄደችም ተነገረኝ።እኔም እራሴን እያረጋጋው ወደ ጊቢ ገባው።እስካሁን የት እንዳለች አላውቅም ግን እንደወለደች ሰምቻለው ብቻ።ወደ አንቺ ስመጣ የመጀመሪያ ቀን ያየሁሽ ዳግምን የመታሽው ቀን ነው።እሱን ስትመችው እሷ ናት ቀጥታ ትዝ ያለችኝ።በቃ ኢላሪ ሙሉ ለሙሉ እሷን ነው ምታስታውሽኝ።በተለይ ፈገግታሽ እና ደግነትሽ ሳይ እሷ አጠገቤ ያለች ነው ሚመስለኝ።ሶስት አመት ምናምን የቀበርኩትን ፍቅር መተሽ በሴኮንዶች ቆፍረሽ አወጣሽው።

Mane Writer

19 Nov, 05:52


Mn mselshe 2015 matric tefetgne injebara nbr remedial yedersegn hije gn 1 week rasu alkoywm wedemnorbet hager askeyre eytmlalsku nw semar ynbrew coz gemashe Ken nbr emnemarew ena gebi locker ena bed nebregn gn altekembetm nbr because kebet weto mader ksew ga melamed kebedegn siwra kelal ymselal gn ke adis sw kemalakew  ksew ga abro menor betam kebdegn ena zendro gebi egebalew ena local negn gn ke family teleyche selmalak  even kebet weteche adre rasu alakm zemed ga mnamnm bihon eytmlalsku endalmar dmo be 2 taxi nw gebi medersew ya dmo ayawatam gebi mader dmo feraw ena mnm friend mibal neger yelegnm beka lene hulu negere family nw yemejemria lij negn kebet weteche selemalak betam feraw  ena endzi experience yalachew help me out eski ena local selhonku mn mn beyez temkrugnalachew help me out plss eski🙏🙏🙏

Mane Writer

18 Nov, 18:51


ኢላሪ(እውነተኛ ታሪክ)

ከፍታልኝ ወደ ውስጥ ስገባ እዮባ አልጋው ላይ በጀርባው ተኝቷል።አጠገቡ ሄጄ ቁጭ አልኩ ዝም ብዬ መመልከት ጀመርኩ።ድንገት ግን እዮባ ነቃ ኢላሪ አለኝ..እዮባ ደህና ነህ ....እዚ ምን ታደርጊያለሽ ኢላሪ ...ምነው ልሂድ ስለው ዝም አለኝ እሺ በቃ ብዬ ብድግ ስል እጄን ያዘኝ አትሂጂ አለኝ።እሺ ብዬ ቁጭ አልኩ።...ኢላሪ አንዴ ሻወር ልውሰድ እና እናወራለን ብሎ ወደ መታጠብያ ቤት ገባ።እኔም ተነስቼ ክፍሉን ማስተካከል ጀመርኩ።የመጠጥ ጠርሙስ ሰብስቤ ለሰራተኛዋ ሰጠሁዋት ለእዮባም የሚበላ ነገር ይዛለት እንድትመጣ ነግሪያት ቁጭ አልኩኝ።ታጥቦ ጨርሶ መጣ።ፎጣ ለብሶ ፊት ለፊቴ ቆመ ከላይ ግን ቲሸርት አልበሰም ነበር።የደረቱ ስፉት ደስ ሲል ብቻ የስፓርተኛ ሰውነት ነው ያለው።ከፈዘዝኩበት ደንገጥ ብዬ ፊቴን አዞርኩ እስኪለብስ ብዬ የተሰራለትን ላመጣ ወረድኩ።

ምግቡን ይዤ ወደ እዮባ ተመለስኩ።አጠገቡ ቁጭ አልኩኝ።ምግቡንም እንዲበላ ሰጠውት በልቶ ሲጨርስ የበላበትን አስቀምጦ በረንዳ ላይ እንሁን አለኝ።እሺ ብዬ በክፍሉ በኩል ያለው  በረንዳ ላይ ወተን ቁጭ አልን።ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን።አይን አይኑን እያየው...እዮባ ለምን እንዲ ትሆናለህ ባንተ እንዲ መሆን አጠገብክ ያሉትን የሚጨነቁልክ ሰዎችን እየጎዳክ ነው።ደግሞ ለመመረቅ አንድ አመት ነው የቀረክ እባክህ እዮባ እንዲ አትሁን።...ታውቂያለሽ ኢላሪ እኔ ማለት እኮ ከሴት እንዳልተፈጠርኩ የሴት እንባ እና ህመም ደንታ ማይሰጠኝ ለእኔ ስሜት እንጂ ለእነሱ ቅንጣት ታክል የማልጨነቅ እዮብ ነበርኩ።ለዛም አሁን ዋጋ እየከፈልኩ ነው።አንዳንድ ሴቶች እኮ አሉ ምንም ለራሳቸው ክብር የሌላቸው።አሉ ደግሞ የተመረጡ ግን ዞሮ ዞሮ ሴት ፍቅር ሲይዛት የማትፈልገውን ማንነት ትላበሳለች።ኢላሪ የእውነት እያፈቀረችኝ እኔ ግን ለስሜቴ ስል ብቻ እቀርባታለው ያቺም ሴት እኔን ላለማጣት የምፈልገውን ታደርጋለች።ብቻ ለእነዚህ ሴቶች እንባ መፍሰስ ፍቅር በደንብ አድርጎ እየቀጣኝ ነው።

የእነሱን ስሜት ስረዳው ራሴን ጠላውት።ኢላሪ አንቺ በደንብ አድርገሽ እያስከፈልሽኝ ነው።በአንድ ቀን እይታ ጭንቅላቴ ውስጥ የነበሩትን የሴቶች መአት በአንዴ ደረመሽው።ወንድ ልጅ አያፍቅር ነው ነገሩ ብሎ ፈገግ አለ።...እዮባ በቃ ልሂድ ብዬ ተነሳው...ምነው አትቆይም...አይ እዮባ ይመሻል ...እሺ በቃ ነይ ላድርስሽ ብሎ ከቤት የአባቱን መኪና ይዞ መሄድ ጀመርን።በመሀልም...እኔ ምልሽ ኢላሪ አለኝ..አቤት...ዳንን አግኝተሽው ወይም አውርተሽው ታውቂያለሽ አለኝ።...አው እዮባ ዛሬ አጊኝቼው ነበር አልኩት ምንም ሳይመልስልኝ ዝም አለ።ቤት አደረሰኝና ተሰናብቼው ተመለሰ።

አሁን ላይ ጊቢ ተመልሰናል ጊቢ ከተመለስን ቀን ጀምሮ ዳግም አላስቀምጥ ብሎኛል።አንዴ እራት ልጋብዝሽ አንዴ ተገናኝተን እናውራ የማይለው የለም።እኔ ደግሞ ዳግምን ፈጥሮብኝ እንዲው አላምነውም ቀልቤ አይወደውም።ዛሬ ካፌ ተሰብስበን እራት በላን።በትንሹም ቢሆን ጉአደኝነታችን ተመልሷል።እራት ጨርሰን ወክ ማድረግ ጀመርን።ድንገት ግን በመንገዳችን አንድ ልጅ ትጮሀለች።ሀኒም ... ይመስለኛል ከፍቅረኛዋ ጋር እየተጣላችነው አለችን።በዛው ስናልፍ ቀረብ ማለት ጀመርን።አንዲት ከአንድ ወንድ ጋር ቆማ እያወራች ነው ማለትም እየተጨቃጨቀች ነገር።እኛም ዳራችንን ይዘን እየሄድን ልጆቹ አጠገብ ደረስን።ቤዛ እና አቤል ናቸው።አኔ እንዳየዋቸው እነሱም አዩን።

እኔም ዝም ብዬ አለፍኩ።ድንገት ግን ቤዛ ...ቆይ ኢላሪያ አለችኝ።ሁላችንም ዞር ብለን ቆምን።አቤት አልኳት ቀጥታ አጠገቤ መታ በጥፊ ደረገመችኝ😒።ጉአደኞቼም አንቺ ብለው ሊደረግሙአት ሲሉ አስቆምኳቸው።አቤልም አጠገባችን መቶ...አንቺ ያምሻል እንዴ አላት።እሷም እምባ እየተናነቃት ...አዎ ያመኛል ምን አጠፋሽ ልትለኝ ነው ንገረኝ ምን አልባት እሷ ቤትኖር እኮ ታፈቅረኝ ነበር።በጣም አናዳኝ...ምንድ ነው ምታወሪው ምን እየሆንሽ ነው ስላት እየጮህች...ዝም በይ አንቺ የምትረጁኝ መስሎኝ ስሜቴን  ነገርኩሽ አቤልን የኔ እንድታደርጊልኝ ነበር።

አንቺ ግን በጣም ነው ምታስጠይው ወንዶችን እንዴት በፍቅርሽ መጣል እንዳለብሽ ታውቂያለሽ።በሁለት ጉአደኛሞች መሀል ስትገቢ ነበር መጠርጠር የነበረብኝ። በጭራሽ አቤልን አልሰጥሽም እሺ አለችኝ።ድንገት ግን ሀኒ መታ በጥፊ  ደረገመቻት።ደስ የሚል ስሜት ተሰማኝ።ሀኒም ትሰሚያለሽ አለቻት...ለመፈቀር እኮ ንፁህ ልብ ያስፈልጋል አንቺ ደግሞ እንደማየው እሱ የለሽም እንዴት እንዳፈቀርሽም ፈጣሪ ይወቀው አለቻት።አቤልም ነይ ብሎ ይዞት ሄደ።

ልክ አቤል እና ቤዛ እንደሄዱ ሁሉም ወደ እኔ አፈጠጡ።...ምን ሆናችሁ ነው እንዲ ምታዩኝ መቅዲ ቀደም ብላ...እንድታስረጅን ነዋ ...እህ ምኑን ላስረዳችሁ ቤቲም እየሳቀች...አሁን የተፈጠረው ነዋ ቆይ ከአቤል ጋር የማናውቀው ግንኙነት አላችሁ እንዴ አለችኝ...እረ ምን ሆናችሁ ነው እንደዚህ አይነት ነገር የለም።ግን እኔም ቤዛ እንዲህ የሆነችበት ምክንያት አልገባኝም አልኳቸው ወንዶቹ ቃል አልተነፈሱም ብቻ ሁሉም ሀሳቤ ባይዋጥላቸውም ዝም አሉ።

ሰሞኑን ደህና ነኝ አያቴ ትዝ ብትለኝም ጠንክርያለው።አሁን ላይ ፈተና ላይ ስለሆንን ውጥረት ላይ ነን።እንደምንም ብለን ፈተናችንንም ጨረስን።ማታ ካፌ እራት እየበላን።ስለ ሶስቱ ምርቃትም እያወራን ማለትም እዮብ ዳን ልዑሌ በአሁኑ ይመረቃሉ።ሁላችንም በጉጉት ልንሞት ነው።ግን ይሄ ጊቢ ያለነሱ ለእኛ ደባሪ ነው።አቤልም ይመረቃል ትተውን ሊወጡ ነው።በወሬ መሀልም ሰሞኑን ለምን የሆነ ቦታ ሄደን አንዝናናም ተባለ።ሁሉም ተስማሙ።ዳንም ....እርሶስ እማማ አለኝ...እስማማለው አባባ አልኩት።

በነገራችን ላይ vip ቻናላችን ላይ ኢላሪን እስከ ክፍል 23 ተለቋል በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃል።
vip ለመቀላቀል 100 ብር ያስከፍላል ከኢላሪ በተጨማሪ ሀና የተሰኘ ተወዳጅ ታሪክም እያስነበብን ነው🙏)
@Maneget
https://t.me/mane121921

Mane Writer

18 Nov, 17:46


ኢላሪ(እውነተኛ ታሪክ)

ክፍል 15

እዮባ ከተወኝ ቦታ እስከ ዶርም ድረስ እያለቀስኩ ሄድኩኝ።ልክ ስገባ ሁሉም ሁኔታዬን ሲያዪ ደንግጠው ምን እንደሆንኩ ጠየቁኝ።ማስረዳት ስላቃተኝ ምንም ሳልል ተኛው።ጊዜው እንደጉድ ይሮጣል እረፍት የምንወጣበት ጊዜም ደርሶ ልብሳችንን ማዘጋጀት ጀመርን ሁለት ሳምንት ሙሉ ጉአደኞቼን እንደልቤ አለማግኜቴ ቢከፋኝም ከዚህ ጊቢ ትንሽ መራቄ ደስብሎኛል።

አሁን ላይ ከእዮባም ሆነ ከዳን ጋር ካወራው ቆየው።ዳን ሰሞኑን ይደውላል ግን አንስቼው አላውቅም።ዛሬ ግን አነሳውት እንድንገናኝ ተነጋግረን ዘጋውት።ዳን የቀጠረኝ ቦታ ስደርስ ቀድሞኝ ደርሶ ነበር።ሰላም ተባብለን ቁጭ አልን።የምንፈልገውን አዘን መመገብ ጀመርን።አይኔ አይኔን እያየ...ለምንድ ነው ስልኬን የማታነሽው አለኝ...ይቅርታ ዳን ከሁሉም ነገር ትንሽ መራቅ ፈልጌ ነው።...ኢላሪ ነገሮችን ስለ ሸሸናቸው አይቀየሩም እኮ መጋፈጥ አለብሽ።

አንተ ግን ለምን ነበር የፈለከኝ...ኢላሪ አልዋሽሽም አንደኛ ስለ ናፈቅሽኝ ነው ሌላው ደግሞ ስለ እዮባ ላወራሽ ነው...ስለ እዮባ ምን...እዮባ ደህና አይደለም ምንም ቢሆን እዮባ ለኔ ከወንድም በላይ ነው ኢላሪ እባክሽ እዮባ ጋር ሂጂ ከእኔ በላይ የእዮባ ደስታ ያስደስተኛል።...ዳን ይቅርታ ግን እዮባን ብርቀው ነው ሚሻለኝ....አይ እንዲ አታድርጊ ኢላሪ እኔ እዮባን በደንብ ነው ማውቀው አንድን ሴት ከሁለት ጊዜ በላይ ስሞን ጠርቶ አውርቶ አያውቅም አንቺ ግን ከአፋ ጠፍተሽ አታውቂም።እባክሽ...እሺ ዳን እሞክራለው አወራዋለው አትጨነቅ ብዬው ትንሽ ተጨዋውተን ተለያየን።

ከዳን ጋር አንደጨረስኩ ወደ ቤት ሄድኩኝ።ስደርስ ግን እማዬ በረንዳ ላይ ቆማ ስልክ እያወራች ነው።ሰላም ብያት ልገባ ስል አስቆመችኝ። ስልኳን ስጨርስም...ኢላሪ ቤት እንግዳ አለሽ አለችኝ።...ማን ...ጊቢ እና እይ አለችኝ።ማን ሊሆን ይችላል እያልኩ ልክ ስገባ ግን ያልጠበኩት ሰው የእዮባ እናት ናት።

ደንግጬ እዮባ ምን ሆነ አልኳት...ውይ ልጄ ብላ ከመቀመጫዋ ብድግ አለች።አጠገቧ ሄጄ በድጋሚ .....እዮባ ምን ሆነ አልኳት ወጣት ስለሆነች ነው እርሶ ማልላት።እሷም ፈገግ ብላ...የኔ ልጅ ነይ እዚ ጋር ብላ አጠገቧ አስቀመጠችኝ።...መሲ ምንድ ነው ንገሪኝ እባክሽ አልኳት የእዮባ እናት ስም መሰረት ነው።መሲም እጄን አጥብቃ ይዛኝ ...የእኔ ልጅ እባክሽ እዮባን መልሽልኝ ልጄን እባክሽ ...መሲ እዮባ ምንድን ነው የሆነው ....የኔ ልጅ እዮባ ሙሉ ቀን ሲጠጣ ነው ሚውለው ለሊቱንም ቢሆን አይተኛም ዝም ብሎ ሲያወራ ሲጮህ ነው ሚያድረው።

እኔም አባቱን ለማናገር ሞከርን ግን አልቻልንም ልጄ ባንዴ ከሳብኝ ከሰውነት ጎዳና ወጣ የኔ ልጅ አንቺን እንደሚወድሽ አውቃለው እንዲ የሚሆንበት ምክንያት ግን አንቺን ስለሚወድ ብቻ እንዳልሆነ እርግጠኛ ነኝ ግን ምንም ይፈጠር ምንም እባክሽ ኢላሪ ቤቴ ሰላም አቷል ልጄን እርጅልኝ ሊመረቅ አንድ አመት ነው የቀረው እያለች ማልቀስ ጀመረች።

እናቴ አጠገቡዋ ተቀመጣ ማባበል ጀመረች።...መሲ እዮባ አሁን የት ነው ....ገብቶ ተኝቷል ቆልፌበት ነው የመጣውት ...እሺ የክፍሉን ቁልፉ ማን ጋር ነው.....አለ ማሪቱ ጋር ነው እንዳከፍቺ ብዬ ሰጥቻታለው አለችኝ።ወደ እዮባ ቤት ተሳፍሬ ሄድኩኝ ልክ ስደርስ መሲ ያለችኝ ልጅ ማሪቱ ከፈተችልኝ። የእዮባን ክፍል ከፍታልኝ ወደ ውስጥ ገባው።

(በነገራችን ላይ vip ቻናላችን ላይ ኢላሪን እስከ ክፍል 23 ተለቋል በዚህ ሳምንት ይጠናቀቃል።
vip ለመቀላቀል 100 ብር ያስከፍላል ከኢላሪ በተጨማሪ ሀና የተሰኘ ተወዳጅ ታሪክም እያስነበብን ነው🙏)
@Maneget
https://t.me/mane121921

Mane Writer

18 Nov, 16:57


ከልብ ሰው መውደድ እንዴት ነው ብትይኝ እኔ እሱን የወደድኩትን ያህል እልሻለሁ ።
ስለፍቅር አይኔን ስገልጥ የተመለከትኩት የመጀመሪያው ወንድ እሱ ነው።
ወንድ ልጅ እንዴት እንደሚታቀፍ እንዴት እንደሚሳም ያሳኝም ጭምር እሱ ነው።

ከቤተሰብ ከጓደኛ ከዘመድ ብቻ ምን ልበልሽ እራሴን ሆኜ ነፃ ሰው ምሆነው ከሱጋ ስሆን ነው።
ከሱጋ እስከጥግ ድረስ እቀብጣለሁ ስለምንም ነገር አልጨነቀም እንደፈልኩ እንድሆን ያደርገኛል ለራሴ እንኳን ደግሜ መናገር ሚያቅተኝን ነገር ለሱ ሲሆን ዝርግፍ አድርጌ ነው ምነግረው።

ሴትነቴን ስሰጠው የምድራችን እድለኛዋ ሴት የሆንኩ ያህል ተሰምቶኝ ነበር ለማፈቅረው ሰው ለወደፊት ባሌ በመስጠቴ እድለኛነት ተሰማኝ።
ፈጣሪ ሲወደኝ ነው እስከዛሬ በክብር ያቆየሁት እዛም እዛም ከመዝለል በአንዱ መፅናት መታደል ነው ብዬ ፈጣሪዬን አመሰገንኩት።

በጣም ብዙ ቀን ወደሰማይ ቀና ብዬ ተመልክቼ አይ ፈጣሪዬ ግን የትኛውን ጥሩ ስራዬን ቆጥረኽልኝ ነው ግን እሱን የሰጠኸኝ እያልኩ አመሰግነው ነበር።

አንድም ቀን ፊቴ ሳይጠቁር እሱን ካወኩባት ቀን አንስቶ ሁሌ ፈገግ እንዳልኩ(በነገራችን ላይ እኛ ለመሳቅ ትንሽ ምክንያት ነው ምንፈልገው አንዳንዴ ዝም ብለን ተያይተን ብቻ ድክም ብለን እንስቃለን) ብቻ ምናለፋሽ ፊቱን ብቻ አይቼ ምን እንደሚፈልግ አቃለሁ እሱም በድምፄ ብቻ ስሜቴን ይረዳኛል።
በፍቅር ሁለት አመት ከሰባት ወር ከቆየን ቡሀላ ግን እሱ ባለትዳርና የልጅ አባት እንደሆነ አወኩኝ .....

መጀመሪያ ቅዠት መስሎኝ ነበር ግን አደለም ምታምር የሶስት አመት ልጅ አለችው ብታይ በጣም ቆንጅዬ ናት ሚስቱም በጣም ነው ምታምረው።

አንዳንዴ ፍቅር እውር ነው ሲባል ምን እያሉ እንደነበር አይገባኝም አሁን በራሴ ደርሶ ሳየው ነው የተገለጠልኝ ብዙ ላስታውላቸው የሚገቡ ነገሮች እንደነበሩ አሁን ካለፈ ቡሀላ ነው የገባኝ ሁሌ ቤት ከገባ ቡሀላ አሁን ሰአቴን ለእናትና አባቴ ልስጣቸው ካንቺጋ ቀን ቀን ከስራ የተረፈኝን ሰአት አብረን ስለምናሳልፍ ሲለኝ እኔ ምን አይነት ትሁት ነው ብዬ እንደተገረምኩ ነበር።
ብቻ ምናለፋሽ ካለፈ ቡሀላ እንደ እግር እሳት ሚያንገበግበኝ ብዙ ማስተዋል የነበረብኝ ነገር እንዳለ ተረዳሁ ግን ከረፈደ ነው።

Mane Writer

17 Nov, 17:30


በነገራችን ላይ የታናሽ እህቴን ቻናል ለማታቁት ልጠቁማችሁ።

ፅሁፍ የማንበብ ፍቅር ካላችሁ ያለምንም ጥርጥር ሚወደድ ቻናል ነው ያላት።
ሁሌም በፅሁፎቿ ምታስገርመኝ ጎበዝ ልጅ ናት ገብታችሁ አበረታቱልኝ በዛውም በአጓጊ ታሪኮቿ ተዝናኑ

https://t.me/fidel_z28

Mane Writer

17 Nov, 17:27


ኢላሪ(እውነተኛ ታሪክ)

ክፍል 14



እዮባን እየሮጥኩ ተከተልኩት እዮባ ብዬ ጠራውት ...አቤት ምንድነው ምትፈልጊው ...እዮባ አዳምጠኝ ተረጋጋ እና ልንገርህ...ኢላሪ እስከዛሬ ስሰቃይ ዝምታሽ ሲገለኝ የት ነበርሽ እእ ንገሪኝ ዳን ነው ምወደው ብለሽ ብትነግሪኝ እኮ አላስቸግርሽም ዳን ወንድሜ ነው አንቺ ፈልገሽ ከሆነ ቢያሳምመኝም እችለው ነበር።ለምን ዝም አልሽ እ  አላሪ አንቺ እኮ ህልሜ ምኞቴ የወደፊት ሚስቴ እንድትሆኝ የምመኝሽ ሴት ነበርሽ።አዎ ከብዙ ሴት ጋር ብዙ ነገር አድርጌ ሊሆን ይችላል።

ለብዙ ሴት እንባ መፍሰስ ተጠያቂም ልሆን እችላለው።ግን አንቺን ኢላሪ አንቺን የእውነት አፈቀርኩሽ።ኢላሪ አንዳንዴ ቁጡነትሽን ሳይ እፈራለው ዙሪያሽን ሳይ እሰጋለው የኔ ላትሆን ብዬ አንቺን ለመርሳት ወይም በፍቅርሽ እንደተሸነፍኩ ላለማመን ከብዙ ሴት ጋር የፈለኩትን አደረኩኝ ግን ጭራሽ አልሆነልኝም።እያንዳንዱን ነገር እያደረኩ ትዝ ትይኛለሽ።


ማፍቀሬ ጥፋት ከሆነ የፈለግሽውን አድርጊ ግን ዝም አትበይኝ ብዬሽ ነበር። አሁን ምን አለ ብለሽ ነው ምታወሪው... እዮባ እባክህ አቋረጠኝና...አንቺ የምታውቂኝ እዚ ነዋ እዚ ግቢ እኔ ግን አይደለም።...ማለት እዮባ...ኢላሪ ትዝ ይላሻል መጀመሪያ አካባቢ በእኛ ምርጫ እራት ልንጋብዛቸው ብለን የወሰድኳቹ ቦታ እሱም ያንቺ ምርጫ  ነበር።እንደምትወጂውም የገባኝ የእናተ የማትሪክ  ውጤት የወጣ ቀን ይመስለኛል።ከቤተሰቦችሽ ጋር እዛው ቦታ ነበራችሁ እኔም ከአንዷ ጋር ነበርኩ።ድንገት ግን ተጋጨን አየውሽ።

ወደድኩሽ ላናግርሽ ብዬ ምን ብዬ እንደማወራ ግራ ገባኝ።እዮባ እየነገረኝ እኔ ሁሌ እዮባን የሆነ ቦታ እንዳየውት ይሰማኝ ለዚህ እንደነበሮ ገባኝ አለማስታወሰ እየገረመኝ ማዳመጤን ቀጠልኩ።ኢላሪ አናንተ እስክጨርሱ ጠብቄ ልጅቷን ትቼ ቤታችሁን ተከትዬ አየውት።አልዋሽሽም ቢያንስ በሳምንት ሶስቴ ድንገት ካየውሽ በሚል መጥቼ በራችሁ አካባቢ እቆማለው።እሚገርመው ግን እዚው አገኘውሽ።

መጀመሪያ የተዋወኩሽ ቀን ፈጣሪዬን እንዴት እንዳመሰገኩ።የልቤን አይተህ አመጣሀት ብዬ ደስ አለኝ ግን ሁሉም ከንቱ ነው የኔ ላትሆኝ ነገር መደሰቴ።ኢላሪ ተይ በቃ አታሰቃይኝ ብሎ ጥሎኝ ሄደ።

https://t.me/mane121921

Mane Writer

17 Nov, 16:33


ኢላሪ(እውነተኛ ታሪክ)

ክፍል 13

ደጃፉን ተምበርክኬ ብሶቴን አወጣሁት።ሳለቅስ የእዮባ ፍቅር በውስጤ እንዳለ ታወቀኝ።አምላኬ እባክህ እዮብን አትንሳኝ ከዚህ ፈተና አውጣኝ ፈጣሪዬ በፍቅር አትፈትነኝ እያልኩ አነባውት።የአያቴም ሀዘን አልወጣልኝም መሰል እሱዋንም እየጠራው እሲኪበቃኝ አለቀስኩ።

ካጎነበስኩበት ቀና ስል የሆነ ልጅ በትኩረት እያየኝ ነው።ምንም ሳልል አንድ ድንጋይ ላይ ቁጭ አልኩ።ማኪ ጋር ልቀመጥ ብዬ ያለቀስኩበት አይኔ ትንሽ ይልቀቅ ብዬ ለብቻዬ ቁጭ አልኩ።ትንሽ ቆይቼ ብድግ ብዬ ልሄድ ስል ልጁ እጄን ነካ አድርጎ እናት አለኝ።ዞር ብዬ አቤት አልኩት።...ይህውልሽ ምንም ሆንሽ ምንም በፈጣራ እና በፍቅር ተስፋ እንዳትቆርጪ እሺ...ማለት ፍቅር ስትል...ያው ባለሽበት እድሜ ዋናው መከራ ፍቅር ነው ብዬ ነው...እሺ አመሰግናለው ብዬ ማኪኝ ጠርቻት ወደ ጊቢ ተመለስኩ።

ቀጥታ ወደ ካፌ ሄድን።ምግብ አልበላ አለኝ ምግቡን ትቼ ማኪያቶ መጠጣት ጀመርኩ።ውስጤ ደህና አይደለም ህመም እየተሰማኝ ነው ግን ሄጄ ልተኛ ብል ይደብራቸዋል ብዬ ዝም አልኩ። የሆነ ሰዓት ግን ብዥ እያለብኝ መጣ እራሴን መቆጣጠር አቃተኝ እጄ መኝቀጥቀጥ ጀመረ።ድምፅ ይሰማኛል ግን ምን እንደሆነ መለየት አቃተኝ።አይኔን ስገልጥ ነጭ ኮርኒስ ይታየኛል ዞር ብዬ ስመለከት ክሊንክ መሆኑን ተረዳው።

አንድ ነርስጨ..ደህና ነሽ አለችኝ...ምንድ ነው ብዬ ጠየኳት...ራስ ስተሽ ወድቀሽ አምጥተውሽ ነው አይዞሽ ትንሽ እረፊበት ብላኝ ወጣች።ልክ እንደወጣች ጉአደኞቼ ተከታትለው ገቡ።እዮባ ዳኒና ልዑልም ነበሩ።ስትታመሙ ሚጨነቅላቹ ወይም አጠገባቹ ሰውን እንደማየት ደስ የሚል ነገር የለም።

ሁሉንም ደህና ነኝ ካልኩ በኃላ ልዑል አጠገቤ መቶ ..ደህና ነሽ አለኝ።...አዎ ልዑሌ ደህና ነኝ ግን ይበልጥ ደህና እንድሆን ግን ከእዮባ እና ከዳን ውጪ ውጡ ሁላችሁም አልኳቸው እሺ ብለው ወጡ።ልክ እንደወጡ ዳን ...ደህና ነሽ አለኝ እኔም ከተኛውበት ብድግ ብዬ...አይ አይደለውም አልኩት።እዮባም ቀበል አድርጎ...እና ዶክተር እንጥራ አለ...ይሄ ህክምና አያስፈልገውም እባካችሁ ደህንነቴን የምትፈልጉ ከሆነ ዝም ብላቹ አድምጡኝ።

እዮባ ዳን ላንተ ምንህ ነው አልኩት እዮባም...ዳን ለእኔ ወንድሜ ነው አለኝ።...እሺ እዮባ አንተስ ዳን...ለእኔም እዮብ ወንድሜ ነው።...እና አሁን ወንድምነታችሁ የት ሄደ ንገሩኝ ማናችሁም ምን አይነት ጥፋት አላጠፋችሁም እናም ለማንም መስዋት መሆን አይጠበቅባችሁም  እሺ ምክንያቱም ሁለታችሁም ከተሳሳተ ሰዎ ነው ፍቅር የያዛችሁ።ስለዚህ ይሄን አውቃችው ወደ ድሮ ወንድምነቻችሁ ትመለሳላችሁ ከኔጋርም እስከዛሬ ባላችሁ የጉአደኛ ቅርበት እንቀጥላለን ከዛ በጣም ደህና እሆናለው።

ይሄን እንዳልኩ ዳን ክፍሉን ለቆ ወጣ።እዮባም ወደ እኔ ጠጋ ብሎ...መቼም መቼም ኢላሪ አንቺኝ እንደጉአደኛ ተቀብዬሽ አላውቅም መቀበልም አልችልም ብሎኝ እሱም ጥሎኝ ወጣ።


ዛሬ ክላስ ጠዋት ነበረኝ ግን መግባት ስላስጠላኝ ለጓደኞቼ እንደማልገባ ነግሪያቸው ለሚኪ ደውዬ መቶ ከዚ ጊቢ እንዲወስደኝ ነገርኩት።ልክ እንደመጣ ሲነግረኝ ተነስቼ ወጣሁ።ከጊቢ እየወጣው ከቤዛ ጋር  ማለት ከአቤል አፍቃሪ ተገጣጠምን።ፈገግ ብዬ ሰላም ልላት ስል ግልምጥ አድርጋኝ ሄደች።ምን ሆና ይሁን ብዬ ዝም ብዬ ሄድኩኝ።በር ላይ ማይኮ መኪናውን ተደግፎ ቆሙአል።አቅፌ ሰላም አልኩት።ማይኮ ለእኔ ሁሉ ነገሬ ነው እሱን ሳገኘው ሰላም ይሰማኛል ወንድሜም አይደል😘 ሰላም ካለኝ በኃላ ምን ሆነሽ ነው ብሎ ጠየቀኝ....ምንም ብቻ ከዚህ ቦታ ውሰደኝ...እሺ በይ ግቢ አለኝ ወደ መኪናው ገብተን መንገድ ጀመርን። ..የት ልውሰድሽ ልዕልቴ አለኝ ማይኮ እና እናቴ ከድሮ ጀምሮ ልዕልቴ ነው ሚሉኝ እኔም የእውነት ልዕልት የሆንኩ ነው ሚመስለኝ።

የፈለክበት ውሰደኝ ደስ ያለክ ቦታ ...እሺ የእኔ አኩራፊ ብሎ ፈገግ አለ።ከትንሽ ጉዞ በኃላ የሆነ ቦታ ጋር ደረስን።አንድ የማያምር ጭር ያለ ቦታ ሆኖ ካፌ አለው።ብዙ ሰው እንዳየሁት ከሆነ ቁጭ ብሎ ለማንበብ ይጠቀምበታል።እኔና ሚኪም ገብተን ቁጭ አልን።ሁለታችንም ማኪያቶ አዘን ማውራት ጀመርን።

ሚኪም ትኩር ብሎ ካየኝ በኃላ...እሺ ምንድ ነው የተፈጠረው ንገሪኝ አለኝ።እኔም ሁሉንም ልዑል ያለኝን ነገርኩት።...ይኸውልሽ ኢላሪ ሲል አቋርጬው..ሚኪ እዮባን አፈቅረዋለው የእውነት እወደዋለው...ታድያ ለምን እንዲ አደረግሽ የምትወጂው ከሆነ ሁሉንም መጋፈጥ ነበረብሽ...አላውቅም በቃ ልዑሌ እንደዛ ሲለኝ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማኝ ምንም ማለት አቃተኝ እና ደግም ዳንንም ማጣት አልፈልግም።

ኢላሪ ጓደኝነት እና ፍቅርን አታወዳድሪ ኢላሪ እንዳይቆጭሽ...በቃ ሚኪ ስለዚህ አናውራ  እሺ ብሎ ወሬ ቀይረን ስንስቅ ስንዝናና ዋልን።ማታ ላይ ወደ 2 ሰዓት አካባቢ ጊቢ በር ላይ አድርሶኝ ሄደ።ወደ ውስጥ እየገባው እያለ ሀኒ ደወለች።ጊቢ ውስጥ እንዳለው ነግሪያት እነሱ ወዳሉበት ካፌ መሄድ ጀመርኩ።

ድንገት ከሩቅ እዮባን እና ረድኤትን አየዋቸው። ቀረብ እያልኩ ስመጣ እሷም አየችኝ።ወዲያው ተንጠራርታ እዮባን አይኔ እያየ ከንፈሩን  ሳመችው።ባለሁበት ፈዝዤ ቀረው ውስጤ እንደ እሳት ሲነድ ተሰማኝ።እዮባም ገፈተራት እኔ እንዳየውት ግን አላየኝም።እሱ ሳያየኝ ቶሎ ሄድኩኝ።የሆነ ሰው ከኃላዬ ጮክ ብሎ እዮባን ታፈቅሪዋለሽ አይደል አለኝ።እየወረደ የነበረውን እንባዬን ጠርጌ ዞር ስል ዳን ነው።

ደንግጬ ዳን አልኩት...ኢላሪ እዮባን ታፈቅሪዋለሽ አለኝ...ማለት ስለው አቋረጠኝ ንዴት እና ቁጣ በተቀላቀለበት ንግግር...ኢላሪ በእናትሽ ንገሪኝ እዮባን ታፈቅሪዋለሽ አለኝ አይኖቹ እንባ አቅረዋል ደነገጥኩኝ ምንም ሳልመልስለት አልፌው ሄድኩኝ።

ተከትሎኝ መጣ እና አስቆመኝ....እባክሽ ንገሪኝ አትሽሺ ሲለኝ እንባው ጠብ አለ።አቀፍኩት እሱም አጥብቆ አቀፈኝአንዳንዴ የምናፈቅረውን ላለማጣት እየጣርን የምናስብለት ሰውም እንዳይጎዳ መሞከር በጣም ከባድ ነው።ከኃላ ኢላሪ ተባልኩ ዞር ስል እዮባ ከረድኤት ጋር ቆመዋል።ዳንን ለቀቀኩት እዮባም ...ኢላሪ ለምን ንገሪኝ ለምን አልወድህም ዳንን ነው ምፈልገው ምርጫዬ አይደለክም ብትይ እኮ አልቃወምሽም አላስቸግርሽም ነበር ለምን በድብቅ ምንም ቢሆን ዳን ወንድሜ ነው በመሀላችሁ አልገባም ነበር ለሁሉም ነገር አመሰግናለው ብሎ ጥሎን ሄደ። ዳን ምንም ቃል አልተነፈሰም።እኔም እዮባን እየሮጥኩ ተከተልኩት።

share ማድረግ እንዳይረሳ

https://t.me/mane121921

Mane Writer

17 Nov, 05:44


እንዴት አደራችሁልኝ ቤተሰቦች።

ዛሬ እሁዳችሁ ለሁላችሁም ያማረና የደመቀ ይሁንላችሁ።
በህይወታችሁ መሰናክል ነው ብላችሁ ከምታስቡት ነገር አንዱን ወደጎን ጥላችሁ ለአዲሲቷ ሰኞ ተዘጋጁ።
ቀናችሁን ለህሊናችሁ ሰላም ለእናንተም እርካታን በሚሰጣችሁ ነገር ላይ አሳልፉት።

ለዛሬ መኝታ ይቅርብንና እስቲ የቤተክርስቲያን ደጁን እንርገጥ ,ከናፈቁን ጓደኞቻችንጋ ጊዜ እናሳልፍ ,እራሳችንን እናስውብ ,ቤታችንን ፅዱ እናድርገው።
የባከነ እሁድን እንዳታሳልፉ አደራ🙏

መልካም እሁድ።
መልካም እለተ ሰንበት።
mane

Mane Writer

16 Nov, 17:48


ኢላሪ(እውነተኛ ታሪክ)

ምን እንደሚለኝ እያሰብኩ ያለኝ ቦታ ደረስኩ። ልዑል ብቻውን ቁጭ ብሏል ወደ እርሱ ሄጄ ሰላም ተባብለን ቁጭ አልን።አንዳንድ ነገሮች ካወራን በኃላ ለምን እንደፈለገኝ ጠየኩት።ተስተካክሎ ተቀመጠ እና ...ይኸውልሽ ኢላራ ላወራሽ ካሰብኩ ትንሽ ቆየው ግን ነገሮች ተደራረቡ እና ደግሞ አንዳንድ ነገሮችኝ በደንብ ልይ ብዬ ነው።...ምንድ ነው እሱ ልዑል..ኢላሪ ያው ታውቂያለሽ ጓደኝነታችን እንደድሮ እንዳልሆነ መሀላችን ያልሆነ ነገር ተፈጥሯል አላውቅም ፈጣሪ በጓደኝነታችን ሊፈትነን ይሁን ትግስታችንን ሊያይ ፈልጎ ይሁን አላውቅም ለምን ይሄ እንደሆነ።

ኢላሪ ሁለት የምወዳቸው ወንድሞቼን እያጣው ነው።አንቺም አንዷ ጉአደኛሽን እያጣሽ ነው...ማለት ማንን ነው ማጣው..ሀኒን ነዋ...ሀኒ ስትል ..ኢላሪ ሀኒ ዳንን እንደምታፈቅረው አውቃለው..ማለት እንዴት...ኢላሪ እኔ ለሀና የብዙ ጊዜ ጉአደኛዋ ነኝ እና ስሜቱዋን እረዳለው እና አሁን ሀኒ ደህና ልትመስል ትችላለች ግን ደህና አይደለችም።

ቆይ ታዲያ ብዬ ላወራ ስል አቋረጠኝ...ኢላሪ ቆይ እኔን አዳምጭኝ አሁን የምጠይቅሽን ነገር ሳትደብቂ ንገሪኝ..እሺ ምንድ ነው...ከዳን ወይም ከእዮባ ፍቅር ይዞሻል ደንግጬ ዝም አልኩት።... እባክሽ ኢላሪ መልሽልኝ ከሁለት አንዳቸውን በተለየ አስተያየት የምታይው አለ።...ቆይ ልዑሌ ከአንዳቸው ፍቅር ከያዘኝ ችግር አለው።

ኢላሪ ይቅርታ ግን አለው አንዴ ከያዘሽ ተይ ማለት አልችልም ግን ባይሆን ደስ ይለኛል።ካልሆነ ግን ጉአደኞቻችንን ሲል አስቆምኩት..ከማናቸውም ፍቅር አልያዘኝም አትስጋ እሺ አልኩት...ኢላሪ የምርሽ ነው...አዎ ግን እዮባና ዳን አያወሩም እንዴ...ያወራሉ ግን እንደድሮ አደለም ፈልገውት አይደለም ታውቂያለሽ ሁለቱም ራሳቸውን ጥፋተኛ እያደረጉ ስለሆነ ነው።...እሺ ልዑሌ ወደ ድሮ እንዲመለሱ ምን ላድርግ።

ኢላሪ ዋና እሱን ላማክርሽ ነው የጠራሁሽ።ሁለቱንም በየተራ ታወሪያቸዋለሽ ምን ብለሽ እንደምታወሪ መናገር አይጠበቅብኝም አይደል...አዎ አውቃለው ግን መቼ እና የት...እሱ ለኔ ተይው ብቻ ስደውልልሽ መምጣት ነው አለኝ።

እሺ ብዬ ተሰናብቼው ወደ ዶርም ሄድኩኝ።ምንም ሳልል ገብቼ ነጠላ አውጥቼ ይዤ ልወጣ ስል ማኪ ..ወዴት ነው አለችኝ...ቤተክርስቲያን አልኳት ...አብረን እንሂድ እሺ ብዬ እኛ ቤተክርስቲያን ስንሄድ ሌሎቹ ካፌ ሄዱ።ልክ ቤተክርስቲያን ስደርስ ከማኪ ራቅ ብዬ እንባዬን እንደጉድ አዘራውት።

እንደተለመደዎ share አድርጉና ሰው ጋብዙ እንደጋበዛችሁት ሰው ብዛት ተጨማሪ ይለቀቃል

https://t.me/mane121921