ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ @orthodoxamero Channel on Telegram

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

@orthodoxamero


ዲያቆን ፍፁም ከበደ

ሀሳብ ካሎዎት @Fisumkeb

+ ግሩፕ ለመቀላቀል +

https://t.me/NablisNablis

+ facebook Link...

https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede

TikTok
https://www.tiktok.com/@zdfitsumkebede1?_t=8pguEgtdsVq&_r=1

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ (Amharic)

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ በአስተያየ ድምፅ ለማስተዋወቅ ወደ orthodoxamero በተጨማመኑት አንዳንድን ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነት የመረጃችንን የቴሌግራም አባላቶች ለመቆጣጠር እና በአእምሮ የገንዘብ ነፃ ላይ የሚቀጥል ይሆናል. እስከ ሊንክ አሳካሪ እና ለመጠቀም በነሐሴቁርና የእናቴጌር በረራ ተገኝቶ አእምሮን ለመጠቀም ይሽጡ. ከዚህም የጂማል እና ፋሽን ፔጅሮችን ለመምረጥ ያለ መብት ያቀረባል. የቴሌግራሙን ምላሽ ለመጠቀም ካለበት እናቴጌር በስልክ ላይ ወደ @Fisumkeb ላይ ብሽጡ። አሁን ለመመልከት የውይይት መሳሪዎችን በፋሽን ለመጠቀም በደረሱት፣ ስለ ታላቅ ውጤት እና የሂደት መሳሪያዎች ሊንክ ከሆነ ልዩነት እንደሚያደርግ አእምሮን ይሽጡ።

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

21 Nov, 06:57


https://www.youtube.com/live/ohCsTilZipU?si=oRJwRBmFtAch_-xO

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

20 Nov, 19:33


✞ ይለይብኛል ሚካኤል ✞


ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል(2)
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል (2)

አያምርብኝ ብዘነጋው ታሪኬን
ሚካኤል ነው ያስጌጠልኝ ህይወቴን
አረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን
ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን

ሚካኤል ያን ሁሉ ዘመን የታገሰኝ
ሚካኤል===ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ
ሚካኤል===የከፍታዬ መሰላል
ሚካኤል===መነሻዬ ሆነሀል

አዝ====
እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን

አዝ====
ውድቅ አረገው የጠላቴ ክፉ እቅድ
አራመደኝ በከፍታዬ መንገድ
ሊያስቀረኝ አልቻለም ሊጎትተኝ ባላጋራ
ተጥሎ ስላለ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ

ሚካኤል===እሳታዊ ነው ነበልባል
ሚካኤል===ጠላቴ ፊትህ ይቀልጣል
ሚካኤል===ለኔ አይኔ ነው መከታዬ
ሚካኤል===የዘለዓለም ጠባቂዬ

አዝ===
እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ 
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን

መዝሙር
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

20 Nov, 19:14


https://youtu.be/k0PovZY5Z7U?si=eJ8ixG2d7Bg07wo_

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

20 Nov, 15:04


ኅዳር 12

~ ለውጦ ማክበር ~

ንግሥት ክሌዎፓትራ "ሳተርን" ለሚባል ጣዖት ያሠራችው ቤት በእስክንድርያ ነበር። ይህ ቤተ ጣዖት እስከ እለ እስክንድሮስ ፓትርያርክ ዘመን 212-326 ድረስ ነበር። እለእስክንድሮስም ሊያጠፋ ሲነሣ በሕዝቡ ልቡና ገና አምልኮ ጣዖት ስላልጠፋላቸው 18 ፓትርያሪኮች ያልነኩትን አንተ ለምን ታፈርስብናለህ ብለው ተቃወሙት። እለእስክንድሮስም ሕዝቡን መክሮና አስተምሮ የሳተርን በዓል ይውልበት የነበረበትን ዕለት ወደ ቅዱስ ሚካኤል የበዓል ዕለት አደረገው። (ስንክ ሳር ኅዳር 12፣ Coptic Encyclopedia, Vi S.p 1617)።

ከእምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የእስክንድርያ ሰዎች በእለ እስክንድሮስ በኩል እየበረሩ ገቡ። የጣዖት መክበሪያ የነበረው በእለ እስክንድሮስ ጸሎት የቅዱስ ሚካኤል መክበሪያ የእግዚአብሔር መመስገኛ ኾነ። ይህን ቤተ ጣዖት ሳስብ ምናልባት በኃጢአታችን ምክንያት የእኛን ሰውነት የሚወክል ይኾን እላለሁ። ብዙዎቻችን የእግዚአብሔር መቅደስ የኾነውን ሰውነታችንን የአጋንንት መርኪያ ቤተ ዘፈን አድርገነዋልና።

የሰው ልቡና የእግዚአብሔር ቤተ መንግሥት ነው። ኾኖም ሰዎች ሰውነታቸውን እያረከሱና ከእግዚአብሔር ፍቅር እየራቁ ሲሄዱ የአጋንንት መኖሪያ ሊያደርጉት ይችላሉ። በመኾኑም የሕይወታችን ዋና ጉዳይ መኾን ያለበት መቅደስ ሰውነታችንን መጠበቅ ነው። በእለእስክንድሮስ አምሳል በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለአገልግሎት የሚፋጠኑ ካህናትን በቅዱስ መስቀል ባርከው እንዲያነጹን መቅረብ ነው። ዝሙት የተባለ ጣዖት በልቡናችን ውስጥ የያዘውን ቦታ በካህናት ፊት ተናዘን እንድንነጻ የሚያደርገውን የንስሐን ቀኖና መቀበል ነው። ሕይወታችንን እያዛጉ ያሉትን ማናቸውንም ባዕድ የኾኑ ነገሮች በልቡናችን ውስጥ ሥር እንዳይዙ መጠንቀቅ ነው።

በእርጥም እኛ ፈቃዳችንን ለእለእስክንድሮሳዊ ፈቃድ ካስገዛን ሰውነታችን የቅዱሳን መላእክት በዓል መክበሪያ ወደ መኾን ይታደሳል። ቅዳሴ፣ ማኅሌትና ልዩ አገልግሎት ያለማቋረጥ የሚቀርብበት ንጹሕ መቅደስ ይኾናል። እንግዲያውስ ኹላችንም በሰውነታችን ውስጥ ቅዱስ ሚካኤልን እንፈልገው፤ በበዓልነት በእኛ ውስጥ እንዲከብር እንፍቀድ። ሰዎች የቅዱስ ሚካኤልን ያማረ የምልጃ ሽታ በእኛ ሰውነት ውስጥ እንዲያሸቱት እናድርግ! ወደ ቅዱስ ሚካኤላዊ የአገልግሎት ሕይወት ለመግባት እንመኝ፤ ደጋግመንም እንሻ!

( "ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው" fb የተወሰደ ።)

እንኳን አደረሳችሁ!!


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

20 Nov, 14:52


https://www.youtube.com/live/cmU6yLCPvvk?si=uyd4iLUGnaXKbbPf

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

16 Nov, 20:51


ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ

አዘጋጅ ማኅበረ ኤዶምያስ ጠቅላላ መንፈሳዊ ማኅበር

የኔታ መምህር ኅይለ ማርያም ዘውዱ ( ዘቦሩ ሜዳ )

እሁድ  ህዳር  8 / 2016

ጉባኤ ነገረ ድህነት

ሰአት ማታ 3:00 ጀምሮ

ትምህርቱ የሚሰጥበት የቴሌግራም ገፅ ሊንክ
👇👇👇
https://t.me/edomiyass21
https://t.me/edomiyass21
https://t.me/edomiyass21
https://t.me/edomiyass21

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

16 Nov, 15:01


+ ምጽዋት +

ምጽዋትን ለተቸገረ ወገኑ የሚሰጥ ሰው ለእግዚአብሔር መስጠቱ ነው ።

፦ ምጽዋት ለአምላክ የሚሰጥ ብድር ነው ።
፦ ምጽዋትን የሚመጸውት ለችግረኛ የሚራራ ሰው ለእግዚአብሔር ያበድራል በስጦታውም መጠን እግዚአብሔር ይከፍለዋል( ምሳ19፥17 ሲራ 29፥1)


ምጽዋት ብልህ ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስቀምጡት አደራ ነው ። ገንዘብ /ንብረትን/ በታመነ ሰው ዘንድ ማስቀመጥ /አደራ ማስጠበቅ / የተለመደ ነው። በፈለጉት ጊዜ የሚገኝ ስለሆነ ።

"ያላችሁን ሽጡ ሽጣችሁ ምጽዋት ስጡ የማያረጅ ከረጢት ለእናንተ አድርጉ የማያልቅ ድልብም በሰማይ ሌባ ከማይደርስበት ነቀዝ ፣ ብል ከማያበላሹበት ገንዘባችሁ ካለበት ልባችሁ በዚያ ይኖራል ። ሉቃ 12-32 ማቴ 6-19-21 እንዲል ማለት ነው ።

ምጽዋት ሰው ለሰው ያለው በጎ ፈቃድ የሚገለጥበት ክርስቲያናዊ የሥነ ምግባር ዘርፍ ነው ። በዚህ ዓለም ጥረት ከራሳቸው ተርፈው ለሌሎች ማካፈል ችግረኞችን መርዳት የሚቻላቸውን ብቻ ሳይሆን በመጠነኛ ኑሮ የሚተዳደሩ ደጋግ ሰዎች ያለንን ተመግበው ለሀብታችን ለዕውቀታችንና ጉልበታችን ሳስተን የምንኖር ከሆነ መንግሥተ ሰማያትን በምን እንወርሳለን ? ብለው ከሚበሉት ከሚጠጡት ከፍለው ይረዳሉ ይመጸውታሉ ። በኑሮአቸው በዝቅተኛነት የመስጠት ፈቃዳቸውን የልግስና ብልፅግናቸውን አያግደውም ። ከአቅማቸው የሚያልፍ እንኳ ቢሆን ጨክነው ያደርጉታል ። ፪ኛ ቆሮ ፰-፪ ።( ኪዳነ ጽድቅ ገጽ 96-97 )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

11 Nov, 11:22


ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደሆነ ወደ አለመገረዝ አይመለስ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ (1ኛ ቆሮንቶስ 7፥19-20) (ቁ.18) ፦ ሳይገረዝ አምኖ የተጠመቀ ክርስቲያን ሳይገረዝ መኖር ይችላል ። የአንድምታው ተርጓምያን ሐዋርያው ይህን አሳብ ያነሣበትን ምክንያት ሲገልጹ"ግዙር ቆላፍ አምነዋል ግዙር ቆላፍነትን ተመኝቶ ነበር ቆላፍም ግዙርነትን ተመኝቶ ነበር " ይላሉ ። ሐዋርያው ያለገረዘም ባለመገዘሩ ፣ የተገረዘም በመገዘሩ እንዲጸኑ ጽፎላቸዋል ።

መገረዝም ቢሆን አለመገዘርም ቢሆን ከንቱ ነው ። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ነው እንጂ(ቁ.19) ፦ ገላ 5፥6፣6፥15 ያነጻጽሩ ። ሰውን የሚያጸድቀው የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ነው እንጂ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አያጸድቅም ።

እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር(ቁ.20) ፦ ተገርዞ የተጠራ ተገርዞ ይኑር ። ሳይገረዝ የተጠራ ሳይገረዝ ይኑር ። ("የሐዋርያው የቅዱሰሰ ጻውሎስ መልእክታት ከሮሜ እስከ ገላትያ" መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ ዳምጤ ገጽ-237)

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

08 Nov, 18:39


ቮይስ ቻት ኑ ግቡ

በጋራ አብረን እንዘምር🥰🙏

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

08 Nov, 18:28


https://t.me/edomiyass21?videochat=d0408ab5128ac840b9

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

08 Nov, 10:42


አህያና ግርዛት

አሁን ሐዲስ ኪዳን ነው:: መገረዝ ግዴታ አይደለም:: ዋናው ጥምቀት ነው:: ባንገረዝ ምንም አይጎድልብንም:: በዚህ ጉዳይ በመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ውዝግብ ተነሣ:: አሕዛብ ሳይገረዙ ኖረዋልና ጸረ ግዝረት ሆኑ:: አይሁድ ደግሞ እንዴት ግዝረት እንተዋለን አሉ::

ወደ ክርስትና የተጠሩት እነዚህ ሁለት ወገኖች ሁለቱም ከራሳቸው አመጣጥ አንጻር እውነት አላቸው:: አሕዛብ የማያውቁትን ነገር መቀበል ሊገደዱ አይችሉም:: ክርስትናም አላስገደዳቸውም:: አይሁድ ደግሞ የኖሩበትን መተው አይችሉም:: ክርስትናም ግዝረትን ባይጠይቅም አልከለከለም::

በመጨረሻ በብዙ ምክር የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን አሕዛብንም ያላገለለ እስራኤልንም ያላቃለለ ውሳኔ ወሰነች:: ውሳኔውን በጥሩ ቃል በመልእክቱ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ገልጾታል::

"ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ። ... እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር" 1 ቆሮንቶስ 7:18፣ 20

በዚህ መሠረት ኦሪትን ተቀብለው ተገርዘው ወደ ክርስትና የተጠሩት እስራኤል በመገረዛቸው ይቀጥሉ እንጂ ወደ አለመገረዝ አይመለሱ ተባለላቸው:: ሳይገረዙ የተጠሩት አሕዛብ ግን መገረዝ የእነርሱ ልማድ አልነበረምና አይገረዙ ተባለ:: ይህ ለእስራኤል የተወሰነ ውሳኔም እንደ ኢትዮጵያ ኦሪትን ተቀብላ ለኖረችና ተገርዛ ሳለ የተጠራች (ሐውልቶችዋ ሳይቀር የተገረዘ ወንድን የሚያሳዩባት) ሀገርም ላይ ይጸናል::

ይህ ውሳኔ ለሁሉም እንደ ግዝረት ያሉ ሕግጋት ይሠራል::

"ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደ ሆነ፥ ወደ አለመገረዝ አይመለስ፤ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ"

"ማንም አህያ እየበላ ተጠርቶ እንደ ሆነ አህያ ወዳለመብላት አይመለስ ፤ ማንም አህያ ሳይበላ ተጠርቶ እንደሆነም አህያ አይብላ"
(የአህያን ስም በአሳማ በአይጥ በውሻ ወዘተ እየቀየሩ ዐረፍተ ነገር ይሥሩ:: ሃሳቡ ያው ነው) ግዝረትም የማይበሉ ምግቦችም ከ613 የአይሁድ ሕግጋት (The 613 Mitzvot) ውስጥ ናቸው::

እስራኤል በግዝረት ቀጥሉ ሲባሉ ደስ አላቸው አሕዛብም አትገረዙ ሲባል ደስ አላቸው:: ለእስራኤል ሔደህ የአሕዛብን ዜና ብትነግራቸው ምንም እንኩዋን ግዝረት ግድ ባይሆንም ቅር ይላቸዋል:: የአህያ መበላት ዜናም የሚያስደስተው አህያን እንዴት ልንተው እንችላለን ብለው ለተጨነቁ አሕዛብ ብቻ እንጂ ለእኛ ሆድ የሚበጠብጥ ዜና ነው::

ከዚያ ውጪ እንደ ክርስቲያን ብሉ ብለን ልንሰብከው የሚገባን የሕይወት እንጀራ ሥጋ ወደሙ ብቻ ነው::

እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት ይኑር!

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ
2017 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ቄራ (የበሬ)

"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" ኤፌሶን 4:29

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

07 Nov, 05:37


የተሻለ ነገር

የተሻለ ነገር አስበህልኝ ነው
ፈተናው የበዛው
ነገ መልካሙን ቀን አያለሁ
በዚህም አምናለሁ


  ሰው ነኝ መቼም እቸኩላለሁ
  የሀሳቤን ቶሎ እሻለሁ
   አዳዴማ በቃ እረስቶኛል
   እላለሁኝ እኔን ትቶኛል
        አተ ግን ስጦታህ ብዙ ነው
        ታደርግልኛለህ በጊዜው
        አንተኮ አትፈልግም ውድቀቴን
        ሁል ጊዜ በጭንቀት ማንባቴን


አንዱን ቺግር ሳልሻገረው
ይደረባል ገዝፎ ሌላኛው
የሕይወትን ውጣ ውረድ
አይቻለሁ ስንቱን መንገድ
        ጨለማው ቢረዝም ሌሊቱ
        አይኔ አይቀርም ብርሃን ማየቱ
        እሩቅ የመሰለው ይቀርባል
        ሰላም ወደ ቤቴ ይገባል


ፈተናዬ ቢበዛብኝም
የሀዘኔ ማብቂያው ቢርቅ
አምላክ ባንተ ታሪክ ይሆናል
የደስታ ቀን ለኔም ይመጣል
      አንተ አትሳሳትም በስራህ
      ፍፁምና መልካም አባት ነህ
      እስከሚሆን ድረስ ተራዬ
      እጠብቅሃለሁ ጌታዬ


አለፈኮ ዘመኔ እያልኩኝ
በማጉረምረም ይሄው አለሁኝ
ፅናት ጎሎት ልቤ ቢያማርም
ያሰብክልኝ ያልከው አይቀርም
       አንተ ግን ስጦታህ ብዙ ነው
       ታደርግልኛለህ በጊዜው
       አንተኮ አትፈልግም ውድቀቴን
       ሁል ጊዜ በጭንቀት ማንባቴን

https://t.me/Yemezmur_gitimoche

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

06 Nov, 11:27


ኦርቶዶክሳዊ ኑሮ

"ሁል ጊዜም በተወሰነ ሰዓት የመንቃት ልምድ ይኑርህ። ምክንያተኝነትን ከአንተ አስወግድ። ከሰባት ሰዓት በላይ የእንቅልፍ ጊዜ አይኑርህ። ከእንቅልፍህም በነቃህ ጊዜ የተሰቀለውን ጌታችንን በመስቀል ላይ እንዳለ አድርገህ አስብ። ራስህን በብርድልስ ሙቀት አታታል። ከመኝታህ አፈፍ ብለህ ተነሣ። ለጸሎት ስትዘጋጅ ወገብህ የታጠቀ መብራትህ የበራ ይኹን። የጸሎት ልብስህን ልበስ። ይህ ጊዜ የዝግጅት ጊዜ ነው። በሠራዊት ጌታ በልዑል እግዚአብሔር ፊት ልትቆም መኾንህን አስብ። ሁል ጊዜም አእምሮህ የአባትህን የአዳምን የእናትህን የሔዋንን ውድቀት ያስታውስ። አምላክህን የሚያስብ በጎ ሕሊና እንዲኖርህ አባትህ አዳም ተጠልፎ በወደቀበት የሥጋ ሐሳብ፣ የሥጋ ኃጢአት ተጠልፈህ እንዳትወድቅ ፈጣሪህን ለምነው። በፊቱ የምትቆምበትን ጸጋ ብርታት እንዲሰጥህ ለምነው።

... በሕመምህ ጊዜ መጀመሪያ በእግዚአብሔር ታመን፥ አዘውትረህ የጌታ ሥቃይ ይታሰብህ። ሥቃይህንና ሕመምህን ያሥታግስልህ ዘንድ የምታውቀውን ጸሎት ያለማቋረጥ ጸልይ። በሕይወት ዘመንህ ሰላማዊና የተረጋጋ ሕይወት እንዲኖርህ ከፈለግህ ሕይወትህን ሊታመን ለሚችለውና አደራውን ለመጠበቅ ለሚቻለው ለእግዚአብሔር አስረክብ። ራስህን ለእግዚአብሔር አሳልፈህ መስጠት ካልቻልክ ፍጹም የኾነ መረጋጋትን አገኛለሁ ብለህ እንዳታስብ። ፍቅር የሚገባውን አምላክህን ውደደውና በፍቅር ኑር። (ታደለ ፈንታው (ዲ/ን)፣ መክሊት፣ 2004 ዓ.ም፣ ገጽ 90-99)።

#ኦርቶዶክሳዊ_ኑሮ😍😍
#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

05 Nov, 10:35


++++++ጠባቧ_መንገድ++++++

"በተጨባጭ እውነታ ሰፊውንና ልቅ የኾነውን መንገድ ይዘን ሳለ ጠባቡንና የቀጠነውን መንገድ እየተከተልን እንደ ኾነ በማሰብ እንዳንታለል በራሳችን ላይ ቅርብ ትኲረት እናድርግ። ቀጥሎ የሰፈረው ነገር ጠባብ መንገድ ማለት ምን እንደ ኾነ ያሳይሃል፦ ሆድን ማጎስቆል (ስስትን መግደል)፣ ትጋሃ ሌሊት (ሌሊቱን ሙሉ መቆም)፣ ጥቂት ውኃ መጠጣት፣ ቍራሽ ዳብ መብላት (ከፊለ ኅብስት)፣ በተዋርዶ ድርቅ መንጻት፣ መናቅ፣ ፌዝን መቀበል፣ መሰደብ፣ የገዛ ፈቃድን ቆርጦ መጣል፣ በሚያስቆጣ ነገር መታገሥ፣ ባለ ማጉረምረም ንቀትን መታገሥ፣ ስድቦችን ቸል ማለት፣ ያልተገባ ጠባይን ጸንቶ መታገሥ፤ ሲታሙ አለመቆጣት፣ ሲዋረዱ አለመቆጣት፣ ሲነቀፉ ትሑት መኾን ነው። የገለጽናቸውን ጎዳናዎች የሚከተሉ ብፁዓን ናቸው፣ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና። ማቴ 5፡3-13።" እንዲል ዮሐንስ ዘሰዋስው። (ሳሙኤል ፍቃዱ (ተርጓሚ)፣ ምዕራግና ድርሳን፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 102)።

በዚህ አባት ጽሑፍ ውስጥ አንደኛ ራሳችንን መመርመር እንዳለብን ተገልጿል። ልቅ በኾነው ሰፊ መንገድ በተባለው የዓለማዊነት መንገድ ላይ መኾን አለመኾናችንን በትኩረት እንድናስተውል ምክረ ሐሳብ ቀርቧል። ኹል ጊዜም ቢኾን ትክክለኛ ወደ ኾነው መንገድ ለመግባት አስቀድሞ የቆምንበትን መንገድ እና በዚያ መንገድ እንድንጓዝ ያደረገንን ውስጣዊ ፍላጎት መረዳት ያስፈልጋል። ምን ያህልስ ጊዜ ልቅ በኾነው የኃጢአት መንገድ ተጉዘን ይኾን? ምን ያህልስ የዚያ መንገድ ጣዕም በውስጣችን ቀርቶ ይኾን? እንዴትስ ከዚያ መንገድ መውጣት እንችላለን። እያልን በእርጋታ ለራሳችን ጥያቄ እያቀረብን ራሳችንን እንመርምር።

ኹለተኛው መሠረታዊ ነገር ጠባብ መንገድ ማለት ምን ማለት እንደ ኾነ የተገለጸበት ነው። ጥቂት መመገብን ከመለማመድ ጀምሮ ማንኛውንም ክፉ የተባሉ ነገሮችን የሚያደርጉብንን መታገሥ ተገቢ መኾኑን ያስረዳል። መንገዱን ጠባብ ያሰኘውም፥ የተገለጹትን ነገሮች ለመተግበር እጅግ የሚከብዱ ስለ ኾነ ነው። ጽድቁንና መንግሥቱን እያሰብን የምንኖር ከኾነ ግን ከባድ ሊኾኑ አይችሉም። ጠባቡ መንገድ ጣዕመ መንግሥተ እግዚአብሔርን እያሰቡ ኃጢአትን መጥላትን ማዕከል ያደረገ ነውና። የሚንቁንን፣ የሚሰድቡንን፣ የሚያሙንን መታገሥ ለብዙዎቻችን አስቸጋሪ ነው። በእውነትም የሚጠሉንን ላለመጥላት እየታገልንን ኹሌ ራሳችንን ትዕግሥትን ብናለማምድ እግዚአብሔር ይረዳናል። ትዕግሥት በእኛ ጥረት ብቻ ሳይኾን ከእግዚአብሔርም ጸጋ ኾኖ የሚሰጥም ነገር ነውና። እኛ ከልባችን ክፉን በትዕግሥት ስንቀበል እግዚአብሔር ጽናቱን ይሰጠናል። የጠባቡ መንገድ መድረሻው መንግሥተ እግዚአብሔር መኾኑን በሕሊናችን ውስጥ አስቀምጠን፥ መንግሥቱን እያሰብን እንኑር። አንድ ሯጭ ትኲረቱን በሙሉ የሚያደርገው ቀድመውት ያሉ ተወዳዳሪዎች ላይ እንደ ኾነ ኹሉ እኛም ትኲረታችንን ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር አቅጣጫ ካደረግን በእኛ ላይ የሚደረጉ ክፉ ነገሮችን ኹሉ ሳናያቸው ማለፍ እንችላለን።
ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው

https://t.me/OrthodoxAmero

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

31 Oct, 04:33


"ቤተክርስቲያንን የሚያስቀጥሉ ሦስት ሰንሰለቶች አሉ እነርሱም:---
ትዳር ፣ ምንኩስና እና ክህነት ናቸው።

እነዚህ እክል ስለገጠማቸው ነው ቤተክርስቲያን እየተቸገረች ያለቸው እንጂ ሌሎች ሰዎች ወይም አህዛብ ክፉ ስለሆኑ አይደለም። እነሱ ደግ የሚሆኑበት ዘመን ነገም እኔ አልጠብቅም ሰይጣን ባለበት መልካም ነገር አይመጣም።

እኛ ግን የጎደለን ይህ ነው፣ በተከበረ ትዳር ፣በተከበረ ምንኩስና እና በተከበረ ክህነት ቤተክርስቲያን ትቀጥላለች።

ምሳሌ እንዴት ካልን፦
የተከበረ ትዳር:- የተከበረ መነኩሴ ይወልዳል።
የተከበረ መነኩሴ:- የተከበረን ጵጵስናን ያመጣል።
የተከበረ ጳጳስ:- የተከበረን ክህነትን ይሾምና
የተከበረው ክህነት:- የተከበረ ትዳርን ባርኮ ያጋባል። የተከበረው ትዳር መልሶ እንደገና የተከበረ ካህንን ይወልዳል።

በዚህ ዑደት ነው ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖረው። አሁን ግን ምንጩ ደፍርሷል። ለዚህም ሁላችንም መስተካከል አለብን። አሁን እኔ ሁሉም ሥርዓት እየፈረሰ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ! ተምረን ማግባትና፣ተምረን መመንኮስም ሆነ ክህነት መያዝን ማስቀጠል አለብን።"

(ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ)

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

28 Oct, 10:31


በኢትዮጵያ ያለችው የጌታ ቤተ ክርስቲያን ብትሰራባቸው ብዬ በጣም ከማስበው:

ክፍል 2

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚነበቡ መጽሐፍት ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ አገላለጾች ከጊዜው አንጻር ታይተው ቢሻሻሉ.. ሃይማኖት ያልሆኑ ጉዳዮች ስለሆኑ ቀላል ይመስለኛል.. በተለይ እንደው ቢያንስ ዋና ዋናዎቹን

ለምሳሌ “ትውልድ ሁሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ” የሚል ዓይነት አገላለጽ እኛ ኦርቶዶክሳዊ በሆነ መልኩ ለመረዳት ብንሞክርም ቃሉ ግን የሰዎችን የመፈጠር ምክንያት የሳተ ይመስላል..

በእመቤታችን በኩል መድኃኒት እርሱ ኢየሱስ ቢመጣና ትውልድ ሁሉም ስለዚህ ቢያመሰግናትም.. ግን ደግሞ የመፈጠራችን ምክንያቱ ራሱ እንደው እመቤታችንን ለማመስገን ነው የሚለው አወዛጋቢ ስለሆነ ሃይማኖት ደግሞ ስላልሆነ(ይሰመርበት) አገላለጹ ቢቀየርና ለማለት በታሰበው መልኩ ቢገለጽ.. ያው ሰውን የሚያስትም እንዳይሆን ማለት ነው..

ሌሎችም እንዲህ ዓይነቶችን ይመለከታል ።

(#ሐዋርያዊ_መልሶች "አክሊል" )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

27 Oct, 11:12


+ የማይነገር መቃተት +


ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል ። 8፥26

የማይነገር መቃተት ምንድ ነው ? ከተባለ ፦ መቃተት አስጨናቂ በሆነ ነገር መድከም ማለት ።

የመቃተት ትርጉም መልፍት ፣ መድከም ከሆነ መንፈስ ቅዱስ ይለፍል ፣ ይደክማል ማለት ነው ወይ ተብሎ ከተጠየቀ፦ መንፈስ ቅዱስ ምን ያህል እንደሚረዳን ወይም እንደሚያግዘን ይገባን ዘንድ (ይረዳን ዘንድ ) ለሰው ልጆች በሚነገረው አነጋገር ስለ ተነገረ ነው እንጂ መንፈስ ቅዱስ አይደክምም ተብሎ ይመለሳል ። የማነገር መቃተት የሚለው መንፈስ ቅዱስ ይደክማል ተብሎ ስለማይነገር  ነው ። መንፈስ ቅዱስ ጉልበቴ ተንቀጠቀጠ ጭንቅላቴ ዞረ አይልምና ። በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ይህን የመሰሉ አነጋገሮች ይገኛሉ ።

በሰባተኛው ቀን ከሠራው ሥራ ሁሉ አረፈ (ዘፍ 2፥2 ) እግዚአብሔር ሥራ ሰርቶ ድካም አይሰማውም ። ዕረፍትም አያስፈልገውም ። ለሰው ልጆች በሚገባቸው አነጋገር ለመግለጽ ነው እንጂ ። አንድም የሰንበትን ዕረፍ ለሰው ልጆች ለመሥራት ነው ። "ጌታችን ያረፈበት ቀን ሰንበተ (ዕረፍት) ተብሎአልና ። እስራኤል በኃጢአት ላይ ኃጢአት ሲጨምሩ እግዚአብሔር በኢሳይያስ አንደበት "ሸክም ሆነብኛል ልታገሣቸውም  ደክሜያለሁ " ብሎአል (ኢሳ.1፥14 ) ። እግዚአብሔር እንደ ሰው በትግዕሥቱ አይደክምም ። ወይም እንደ ሰው ትዕግሥቴን ጨርሻለሁ አይልም። "ልታገሣቸው ደክሜያለሁ " ማለቱ ፦ ብዙ ቢተገሣቸውም ከኃጢአታቸው የማይመለሱ መሆናቸውን ለመግለጽ ነው እንጂ ። ( የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ከሮሜ እስከ ገላትያ ትርጓሜ/ማብራርያ መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ ዳምጤ ገጽ -106)

#ዓምደ_ሃይማኖት

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

25 Oct, 14:29


"ስስታም ሰው... ኹሉንም እንደ እሳት የሚበላ፣ ኹሉንም ስልቅጥ አድርጎ የሚውጥ፣ የሰው ዘርን ኹሉ የሚጠላ ነው። ኹሉም ነገር የራሱ ይኾን ዘንድ ሽቶ አንድ ሰውስ እንኳን በሕይወት እንዲኖር አይወድም። በዚህ ላይም አያበቃም::

"ገንዘባቸውን ይወስድ ዘንድ ባለጸጎች እንዲኖሩ አይወድም፤ ይሰጣቸው ዘንድ ስለማይሻም ጦም አዳሪዎችን ይጸየፋቸዋል። ኹሉም የእርሱ ይኾን ዘንድ ሰዎች ኹሉ እንዲጠፉ ይፈልጋል፡፡ ምድርም ኹለመናዋ ወርቅ እንድትኾንለት ይወዳል እንጂ እንዲሁ ምድር ብቻ እንድትኾን አይፈልግም። ምድር ብቻ ሳትኾን ኮረብቶችም፤ ዕንጨቶችም፣ ምንጮችም፤ በአጭሩ ኹሉም ነገር ወርቅ ይኾን ዘንድ ይፈልጋል። [ሰማይም ወርቅ ብታዘንብለት አይጠላም።]"

~ የማቴዎስ ወንጌል፥ ቅጽ 2፣ ድርሳን 28፥5


#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

25 Oct, 08:04


የትግራይን ቤተክርሲቲያን ገነጠልን "ሲኖዶስ" አቋቋምን እያሉን ነው!!


የእግዚአብሔር መንግሥት በእልህ እና ዘረኝነት አይወረስም ። ድርጊቱ ኢ ቀኖናዊ በመሆኑ ክህነት የሌለው ሲኖዶስ የሽማግሌዎች ስብስብ እንጅ ሲኖዶስ ሊሆን አይችልም ። ብድግ ተብሎ ሲኖዶስ መመሥረት ቢቻል ኖሮ ኢትዮጵያ ከ1600 ዓመት በላይ ደጅ ባልጠናች ነበር።

የትግራይ አካባቢ በክርስትናው ወርቃማ ታሪክ ያለው ነበር። ምን ያደርጋል አባት ነን ብለው ሕዝቡን ሸወዱት ክርስቶስን እና የክርስቶስ መንጋ በዘር ከፍለው በስልጣን እና ቂም የተያዙ ጳጳሳት ነን የሚሉ ሽማግሌዎች ጥቁር ታሪክ እየሠሩ ኑው። ፖለቲካን እና ሃይማኖትን እየለየን !!

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

99,939

subscribers

1,339

photos

29

videos