EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት @ethiopian_orthodox_tewahdo_books Channel on Telegram

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

@ethiopian_orthodox_tewahdo_books


ቅዱሳት መጻሕፍትን እንለዋወጥበት ዘንድ እንዲሁም አዳዲስ የሚወጡ መንፈሳዊ መጻሕፍትን እንድንተዋወቅበት ተከፈተ

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት (Amharic)

ኢትዮጵያ ኦርቶፒክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ እና ተስፋፋን መጻሕፍትን እና መባል እንዳሉ የቅዱሳት መጻሕፍት መጻሕፍትን እንዲለዋወጥ እና አዳዲስ የሚወጡ መንፈሳዊ መጻሕፍት እንዲበርህ እንጠቀማለን። ይህ እንግዳ ቤተሰቦ፣ ታሪክ እና ስምምነት ድርጅታዎች በእኛ ላይ የተጠቀሙትን መንፈሳዊ መጻሕፍት መጻሕፍት ለእያንዳንዳዎች እንዲሰማል። ከዚህ በታች በጊዜ ለማንኛውም ዓለም ዓለም ፈጣሪ የመጻሕፍት መንፈሳዊ ቀጥል ሶስተኛ አካልን መጻሕፍት ዘመቻ እንዲለዋወጥ ተዋናይ ማህበራዊ መንፈሳዊ መጻሕፍት ነው።

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

08 Dec, 11:27


Watch "ፍካሬ ሞት ወሕይወት | በዲያቆን በረከት ዓለምእሸት | #የመጻሕፍት_ዳሰሳ #ሐመረ_ብርሃን #Hamereberhan" on YouTube
https://youtu.be/PkYb5HEEsoA?si=D1iGjqvN53RMaAqX

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

30 Nov, 04:31


Watch "የክርስቶስ ስሞች // የመጽሐፍ ዳሰሳ በዲያቆን በረከት ዓለምእሸት #ከመደርደሪያችን @EMislene" on YouTube
https://youtu.be/NqsU4Hfavm0?si=_zhWcg-HVXbqQjdO

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

10 Nov, 18:57


በቅርብ ቀን

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

01 Nov, 16:56


-ቦታ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተክርስቲያን (መርካቶ ተክለ ሃይማኖት)
-ምክሀ ደናግል ሰንበት ትምህርት ቤት ቤተ መጻሕፍት

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

30 Oct, 19:47


https://youtu.be/sGvr9-HxdT8?si=vRgleR6nRP7PFGLt

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

21 Oct, 11:35


Deacon Henok Haile 's "Cana of Galilee" is now available in English. It's one of favorites, Congratulations Deacon Henok!

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

17 Oct, 17:10


©Ashagre Amte
የምንኵስናን ፈተና ከነክብሩ በሚገባ የሚገልጥ መጽሐፍ

መከራ በበዛበት በዚህ ዘመን ትውክልታችንን በእግዚአብሔር ላይ አድርገን ተስፋችን እንዲለመልም የሚያደርግ መጽሐፍ በርሓ ወድቀው በሚጋደሉ ሴት መነኰሳይት ተዘጋጅቶ ለንባብ መብቃቱን ያወቅሁት ሰሞኑን ነው። አንድ ዕለት በጠዋት ወደ ቢሮ ለመግባት ከመኪና ወርጄ በእገሬ ስጓዝ ጠፍቶኝ የነበረ መጽሐፍ ለመጠየቅ አንድ መጽሐፍ መሸጫ ስገባ ዓይኖቼ “ገድለ ምንኵስና” ከሚል መጽሐፍ ላይ ዐረፉ። ስመለከተው ያዘጋጁት “በአሰቦት ደብረ ወገግ ቅድስት ሥላሴ እና አባ ሳሙኤል ገዳም” የሚኖሩ ሴት መነኵሴ መሆናቸውን ተረዳሁ። መጽሐፉን ለማዘጋጀት የተጠቀሟቸውን ማጣቀሻ መጻሕፍት ዝርዝር ለማየት የመጨረሻውን ገጽ ብገልጥ ምንም አላገኘሁ። ፊት ለፊት ካለው ሥዕል ዝቅ ብዬ ስመለከት እውነተኛ ታሪክ የሚል አነበብኩ። መጽሐፉ እንደ ነገሩ የተጻፈ ቢሆን እንኳ ያሳተመው ገዳም ይጠቀም። እኛ ካልገዛነው ማን ገዝቶ ሊያነበው ነው ብዬ ገዝቼ ወደ ቤሮ ገባሁ።
መቅድሙን ሳነብ የምንኵስና ሕይወት እንዴት ዓይነት መንፈሳዊ ጥብዓት እንደሚጠይቅ፣ በስም የማውቃቸውን መነኰሳት ገድል በአጭር በአጭሩ ሲጠቃቅስ በጣም እየተሳብኩ በመምጣቴ ከገመትኩት በተቃራኒው በመሆኑ ተደሰትኩ። መጽሐፉን ሳነብ ትሕትና፣ መንኖ ጥሪት፣ ይቅር ባይነትና ተግባረ እድ ለምንኵስና ሕይወት ምሰሶዎች መሆናቸውን የሚገልጠው ጠጠር ባለ አማርኛ ነው። እውነተኛ ታሪክ መሆኑን የሚገልጠው ገድለ ምንኵስና የተባለው መጽሐፍ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ድርሰት ነው። ስምና ቦታው ከመለወጡ በቀር ሌላው በእውነት የሆነ፣ የተደረገ ምንም ማጋነንና ሐሰት ያልተጨመረበት ነው። እንዲያውም የአንባብያንን የዋህነት ለመጠበቅ ሲባል የሆነው ሁሉ አልተጻፈም” በማለት ለአንባብያን ማሳሰቢያ ይሰጣል።

ንብቤን ስቀጥል ቀስ በቀስ እየተሳብኩ ወደ ጥልቁ ባሕር ገባሁ። በጣም ብዙ አነበብኩ ብዬ ሳስብ የመጽሐፉን ገጾች መግፋት አለመቻሌን እረዳለሁ። በዚህም ምሥጢሩ ምንድን ነው? በማለት መመለስ የማልችለውን ጥያቄ ራሴን ጠይቄዋለሁ። በባለታሪኳ የደረሰውን ለማንበብ አሰቅቆኝ ለመተው ሳስብ መጨረሻውን የማወቅ ጉጉት ሰቅዞ ይይዘኛል። ፈተና ደፍቆ አስቀራቸው ስል በሚገርም ጥብዓት ድል አድርገውት በሩቅ እንደ ፋና ደምቀው ይታያሉ። የአገሬ እና የመነኰሳት ፈተና የሚመሳሰልብኝ እንዲህ ዓይነት መጻሕፍትን ሳነብ ነው። አንድ ምሽት እስከ ሌሊቱ ዐሥራ አንድ ሰዓት ሳነብ አድሬ ያነበብኩት ከመቶ ገጽ አይበልጥም ነበር። መጽሐፉ ሳያውቁት ከተጋድሎው ሜዳ ውስጥ ይጨምራል። በዚህ ምክንያት እኔ ራሴ ቀስ በቀስ የታሪኩ ተዋናይ የሆንኩ እስከሚመስለኝ ደርሸ ነበር። አጻጻፉ እንደ ልብ ወለድ ድርሰት ልብ አንጠልጣይ ስለሆነ ሰቅዞ ይዞ አልለቅህም ይላል። በዘመኑ የነበሩትን ፓትርያርክ ስም ባይጠቅስም ማን እንደ ሆኑ ለመገመት አያዳግትም። እርሳቸውም ቅዱሱ አባት ሦስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት መሆናቸውን እማሆይን በአካል ባገንሁዋቸው ጊዜ አጫውተውኛል። ለቦታቸው የተሰጠው ስያሜ ሌላ ቢሆንም ድርጊቱ የት ገዳም እንደተፈጸመ ማወቅ ይቻላል።
በዚህ ወቅት ሰው እንዳያነብ አእምሮውንም፣ ልቡናውንም ሰቅዞ የያዘ አገራዊ ጉዳይ መኖሩን ባልዘነጋውም መነኰሳትና አገራችን ኢትዮጵ የሚያሸንፉት አለቀላቸው ከተባለ በኋላ መሆኑን ስለማምን ለአንባብያን ለማጋራት ፈለግሁ። እንዲህ ያሉ መጻሕፍትን ስናነብ የጨለመው ይበራል፣ የጠመመው ይቀናል፣ የሄደው ተመልሶ፣ መጣሁ ያለው መጥፎ ነገር ተኖ ይጠፋል። እግዚአብሔር በኃጢአታችን ምክንያት እየቀጣን መሆን አለመሆኑን ራሳችንን እንድንመረምር ያግዘናል። አንድ ክርስቲያን ለሰማይ የከበደ መከራ ታግሎ ካሸነፈ ክርስቲያኖች ሁሉ ንስሓ ገብተን ወደ አምላካችን ብንጮህ የሰይጣንን ክንፍ ነቅለን በመጣል ሰላምን እናሰፍን ነበር።
መጽሐፉ የምንኵስና ሕይወት እንዴት ያለ መንፈሳዊ ተጋድሎ እንደሚጠይቅ ከገለጠ በኋላ ተጋድለው ሲያሸንፉ የሚገኘውን ጸጋ የሚያስነብበን “ሌሊት ላይ ሁሌም ግሑሶቹ ሊጎበኟቸው ሲመጡ እንደሚሆነው አባ ዘርዓ ብሩክ የተኙበት ቦታ በደማቅ ብርሃን ተሞላ። የዚያን ዕለቱን ከሌላው ጊዜ ለየት የሚያደርገው ብርሃኑ ደማቅ ቀይ መሆኑ ነበር። እማሆይ [ማየ ገነት] ደንግጣ እየተንቀጠቀጠች ወደ አባ ዘርዓ ብሩክ ስትመለከት ዓይናቸውን ወደ ሰማይ ሰቅለው ፈገግ ፈገግ ይላሉ። እማሆይ ከዚህ ቀደም በእንዲህ ያለ ሁኔታ ዓይታቸው ስለማታውቅ ለመሞት የሚያጣጥሩ መሰላት። ተርበተበተች፤ ለመጮህ ሰው ለመጥራት፣ በጠቅላላው ከቆመችበት ቦታ ለመንቀሳቀስ አቃታት። ባለችበት ቦታ እንደ እንጨት ደርቃ ዐይኗን አባ ዘርዓ ብሩክ ላይ ተክላ ቀረች። በዚህ ዓይነት ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ ያ ብርሃን፤ ያ ነፍስን ከሥጋ የሚለይ ጣፋጭ መዐዛ ቀስ በቀስ እያለ ወጥቶ ሁሉ ነገር እንደ በፊቱ ሆነ” (ገድለ ምንኵስና፣ ፳፻፲፪፣ ፫፻፲-፫፻፫፩) በማለት ነው።
አባ ዘርዓ ብሩክ ለዚህ ክብር የበቁት በጽኑ ተጋድሎ ነው። እማሆይ ማየ ገነት መንፈሳዊ አባታቸው የደረሱበትን ጸጋ ለማየት የቻሉት የመጣባቸውን መከራ ለበረከት መሆኑን አምነው በመቀበላቸው ነው። በመምህራቸው ላይ ያደረውን ጸጋ እንዲመለከቱ ያደረጋቸው ወደ ፊት የሚጠብቃቸው ጽኑ መከራ ስለነበር ፍጹማን የደረሱበትን የቅድስና ጣዕም ቀምሰው እንዲጸኑ ነው። ለዚህ አባባሌ አስረጅ አድርጌ የማቀርበው “እነዚያ ሁሉ መናንያን እዚያ በረሓ ላይ አንድ መጠለያ ቤት ሳይኖራቸው ግማሹ ቅጠልና ቅጠሉን አስሮ፣ ግማሹ እንደ ዋሻ ድንጋይ ክቦ፣ ግማሹ ትልቅ ዛፍ ሥር ይንን ቤት አድርጎ፣ ግማሹ ጋራው ሥር እንጨት ቆራርጦ፣ ጋራውን አስደግፎ፣ ግማሹ መሬትን ወደ ውስጥ ቆፍሮ ጉድጓድ አበጅቶ፣ ግማሹ ያለ ምንም መጠለያና ከለላ ባዶ ሜዳ ላይ እጆቹን ዘርግቶ ክረምት ከበጋ ጨለማ ሲፈራረቅበት፣ ግማሹ ከወገቡ በታች ጉድጓድ ቆፍሮ ከወገቡ በላይ እርቃኑን ለብርድና ለፀሐይ ለዝናብ ተጋልጦ ዐይኑን ወደ ሰማይ ሰቅሎ ለዓለም ሰላም ሲለምን፣ ግማሹ መላ ሰውነቱን በብረት ሰንሰለት አስሮና እራሱ ላይ ድንጋይ ተሸክሞ ኧረ ስንቱ ይዘርዘር። እነዚህ ሁሉ በእንዲህ ያለ ሁኔታ ሆነው ፊታቸው እንደ ፀሐይ እያበራና ወዛቸው ቅቤ፣ ማር፣ ጮማ ከሚመገቡት የበለጠ ወዝቶና አምሮ ሙሉ ደስታንና መንፈሳዊ ጸጋን ተጎናጽፈው ስታይ ነፍስ አልቀረላትም። ተመሰጠች የምትሆነውን አጣች። ሁሉም ፊት ላይ የሚታየው መንፈሳዊ ፈገግታና ፍጹም ሰላም የሰፈነበት ርጋታ ራሷን እንድትጠላ አደረጋት” (ገድለ ምንኵስና፣ ፳፻፲፪፣ ፬፻፶፫-፬፻፶፬) በማለት ነው። በመጨረሻም ይህ ሁሉ አልፎ ጸጋ እግዚአብሔር ተትረፍርፎ እንደ ፀሐይ ደምቆ ይታያል። ለመጣል የታገለው ሁሉ ክንፉ እንደተነቀለ አሞራ መምረር ቸግሮት አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን እንዳገኘው መልአክ መሬት ለመሬት ሲልወሰወስል ይታየናል። መንፈራገጥ ለመላላጥ ማለት እንዲህ ያለው ከንቱ ድካም መሆኑን መጽሐፉን አንብበን እንረዳለን። መልካም ንባብ።

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

12 Oct, 12:01


Watch "የ ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን መጽሐፍ ምርቃት ቀጥታ ከ ቦሌ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን #abagebrekidan #livestream #orthodox" on YouTube
https://www.youtube.com/live/FJCNmu9tGe0?si=N3INyWRcYOOZw3-d

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

09 Oct, 17:12


የአዲሱ መጽሐፌ መግቢያ

የታሪክ ማኅደር የኾነችው ጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ ብዙና ብዙ ፈተናዎችን ብታስተናግድም ዘወትር በማይለያት ጠባቂዋ በእግዚአብሔር ታዳጊነት፣ በልጆችዋ ብርታትና በከፈሉት መሥዋዕትነት ከነሙሉ ክብሯ ዘመናትን ተሻግራ ለዚህ ዘመን ደርሳለች። ባለፉት 50 ዓመታት እንደ ሀገሪቱ ኹሉ ታሪካዊቷ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ፈተናዎችን አስተናግዳለች፡፡ ይልቁንም አሁን ባለንበት ወቅት የገጠማት ተግዳሮት የቤተ ክርስቲያኒቱን ብቻ ሳይኾን የሀገሪቱ እና የሕዝቦችዋ የዘመናት አብሮነት የተገነባበትን መሠረት የሚንድ ፈተና እየ ኾነ መምጣቱ ብዙዎችን እያሳሰበ እያሳዘነም ነው፡፡

የፖለቲካው ሤራ በቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር (ቤተ ክህነት) ላይ ጥላውን ካጠላበት ውሎ አድሯል፡፡ በዘር፣ በአውራጃ፣ በወንዝና በጎጥ መደራጀትና መከፋፈል ሥር ከሰደደ ቆይቷል፡፡ ይህም በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይኾን በውጪ ሀገራትም እየ ታየ ያለ በጣም አሳዛኝ የዘመናችን ክሥተት ነው፡፡ ከኹሉም የከፋው ነገር ሀገሪቱን ሥጋት ውስጥ እየ ከተተ ያለው የዘውግ ፖለቲካ
ሥር ሰዶ የቤተ ክርስቲያኒቱን በር እያንኳኳ መኾኑ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያና ለሕዝቦቿ ያላትን ኹለንተናዊ የጥበብና የዕውቀት አበርክቶ ትውልዱ በቅጡ ስለ አልተገነዘበው እንደ አንድ የሃይማኖት ተቋም እንጂ እንደ ሀገር ባለውለታነቷ ጠጋ ብሎ አልተረዳትም፡፡ ይህን እና የመሳሰለውን ኹኔታ ሳይ ለምን የድርሻዬን አንድ ጠጠር አልወረውም በሚል የቤተ ክርስቲያኒቱን ኹለንተናዊ አበርክቶ፣ የገጠማትን ተግዳሮትና ለችግሩ የኾነ መፍትሔ ይጠቁማል ያልኩትን ይህን መጽሐፍ ለማዘጋጀት ተነሣሣሁ፡፡ እርግጥ በሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮች እየ ተጠመድኩ ትኩረት ሰጥቼ ስለ አልሠራሁት ነው እንጂ ዝግጅት ከጀመርኩ ከሦስት ዓመታት በላይ ተቈሯል፡፡

ይህን ታሪክ በዋናነት እንደ አጠቃላይ ካዘጋጀሁት የሀገሪቱ ታሪክ ጋር ላሳትመው ዐቅጄ ነበር የሠራሁት፡፡ ይኹን እንጂ ካለፈው ዓመት ጀምሮ የቤተ ክርስቲያኒቱ እና የአማኞቿ ፈተና ከቀን ቀን እየ ተባባሰ ሲመጣ፤ በዘውግ ፖለቲካ ላይ የተመሠረተ ‹‹ሲኖዶስና ቤተ ክህነት›› እውን ለማድረግ የፈለጉ ፖለቲከኞች ዐደባባይ ወጥተው ታሪካዊቷን አሐቲ ቤተ ክርስቲያን ሊከፋፍሏት ሰይፍ ይዘው ሲሰለፉ ሳይና የአባቶቻችን አቋምም ሞቅ ቀዝቀዝ፤ ወጣ ገባ፤ ያዝ ለቀቅ ሲል ስመለከት በጣም ደነገጥኩ፡፡ ምናልባትም መፍትሔ ከመጠቆም አንጻር የራሱ ሚና ይኖረው ይኾን? በሚል ተስፋ ይህ ሥራ ለትውልድ እንዲደርስ ራሱን አስችዬ ላሳትመው ወሰንኩ፡፡

‹‹ሐመር ዘዮናስ›› በሚል ርእስ ያዘጋጀሁት ይህ የታሪክ መጽሐፍ ከይዘት አንጻር ጠቅለል ብሎ ሲታይ ቤተ ክርስቲያኒቱ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን እምነቶችን ከተቀበለችባቸው ዘመናት ጀምሮ ለ3000 ዓመታት ያህል ‹‹የአብነት ትምህርት ቤት››ን ማእከል አድርጋ ለሥነ ጥበብ፣ ኪነ ጥበብና ለሀገር-በቀል ዕውቀቶች፥ እንዲሁም ለሀገር መንግሥት ግንባታ፣ ለሀገሪቱ አንድነትና ለሕዝቦችዋ አብሮነት ያበረከተችው ኹለንተናዊ አስተዋጽዖ የተቃኘ ሲኾን፤ አሁን የገባችበት ፈተናም እንዳለ ኾኖ ያሉዋትን መልካም ዕድሎችና ተስፋዎችን ለማሳየት ሞክሬአለሁ፡፡
በዚህ መጽሐፍ፣ ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማዳከም ሤራና መሠረቱ›› በሚለው ምዕራፍ ሥር ባለፉት 40 እና 50 ዓመታት ቤተ ክርስቲያኒቱ የገጠማት የውስጥና የውጪ ፈተና ከማጠየቂያ ጋር የቀረበ ሲኾን፤ እንዲሁም አሁን እየ ገጠማት ላለው ፈተና ምክንያት ናቸው ያልኳቸውን ችግሮች ከመጠቆም ባሻገር ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጀምሮ የሚመለከታቸውን አካላት ቢያካትት እና የቤተ ክህነቱ አስተዳደራዊ መዋቅር ቃለ ዐዋዲውን በጠበቀ መልኩ ማሻሻያ ቢደረግበት መፍትሔ ያመጣል ያልኩትን ሐሳቤን በግልጽ አቅርቤአለሁ፡፡

ከዚህም ሌላ ‹‹መጽሐፍ ቅዱስን የሚገዳደሩ አዳዲስ የታሪክ አስተሳሰቦች›› በሚል ርእስ ሥር እንደ ታሪክ ከሀገሪቱ ታሪክ ጋር ትስስር ያላቸው፤ አሻሚነት የሚታይባቸውና በተለያዩ ደራስያን የተጻፉ ጥቂት የማይባሉ መጻሕፍት አሉ፡፡ ከነዚህ መጻሕፍት በተወሰኑት ላይ የሚታየው አሻሚነት ከነባሩ የሃይማኖት ታሪክና አስተምህሮ በዋናነት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንዳይጣረስ በሚዛናዊ ሒስ ተቃኝቶ ትውልዱ እንዲረዳው ለማድረግ ተሞክሯል፡፡

እንዲሁም በተለያየ አጋጣሚ በጥናት መልክ የተሠሩ መጣጥፎችና ቢስተካከሉ የምላቸውን የተወሰኑ ነጥቦችን ከነሣሁ በኋላ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ በሃያ ሃያ (2020) ልታሳካ ቸው ትችላለች
ተብሎ ተገምቶ ስለ ነበረው ኹለንተናዊ ልማት በአንድ ጥናታዊ ጉባኤ ላይ እንደ መወያያ ኾኖ የቀረበ ጽሑፍና ከተሳታፊዎች የተነሡ አስተያየቶች ተካተውበታል፡፡ በመጨረሻም ‹‹በቤተ ክርስቲያኒቱ የሚታዩ አበረታች ኹኔታዎች›› በሚል ርእስ ሥር ባቀረብኩት አጭር ቅኝት መጽሐፉ ተጠናቋል፡፡

ታሪኩን ያየሁበት መነጽር እንደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ልጅነቴ እና እንደ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይነቴ ጥግ ይዤ አይደለም፡፡ በተቻለ መጠን ሐሳቤ ከሚዛን እንዳያጋድል ጥንቃቄ አድርጌና ትውልድ እንዲማርበት እየ ኾነ ያለውን እውነታ ከማሳየት ባሻገር የማንንም ክብር በማይነካ መልኩ ለቤተ ክርስቲያኒቱ መፍትሔ ይኾናል ያልኩትን ሐሳብ በግልጽነት ለማቅረብ ሞክሬአለሁ።

በመንግሥት መሥሪያ ቤት ለ28 ዓመታት አገልግሎት ከሰጠሁ በኋላ የጡረታ መብቴን እንዳስከበርኩ ከሕፃንነቴ ኮትኩታ ያሳደገችኝን፤ ተማሪ ኾኜ በንጹሕ አእምሮና በትጋት የተላላክኋትን ሳይጨምር በድጓ መምህርነትና በወረዳ ቤተ ክህነት ኀላፊነት ለ14 ዓመታት ያህል ያገለገልኳትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰከነ ዕድሜ፣ ባለኝ ዕውቀት፣ የንባብና የሥራ ልምድ ያወቅኩትን በማሳወቅና ትውልድን በማነጽ ልክሳት ዕቅድ ነበረኝ፡፡ ‹‹ከሌሎች እሻላለሁ›› ብዬ ባልመካም ከሌሎች የማይተናነስ ዐቅም እንዳለኝ በራሴ እተማመናለሁ፡፡ ያም ኾኖ ወደ ጨዋታ ሜዳው ለመግባት ኹኔታዎች ብዙ አይጋብዙም፡፡ በወጣትነት ዕድሜዬ ያላደረግኩትን መጎናበስና ማደግደግ ደግሞ ሕሊናዬ ሊፈቅድልኝ አልቻለም፡፡ ቀድሞውንስ የመንግሥት አገልጋይ ያደረገኝ ይኸው አይደል!!

ካልሰነፉ የድርሻን ለመወጣትና ጊዜን ለመጠቀም አማራጮች ብዙ ናቸው፡፡ ‹‹የዐማራ ደራስያን ማኅበር››ን በማጠናከር ጥቂት ከማይባሉ ገጣምያንና ጀማሪ ደራስያን ጋር የመገናኘት ዕድል ገጠመኝና፤ ‹‹አይዟችሁ፤ በርቱ!›› አልኳቸው፤ ተበረ ታቱ፡ ፡ እኔንም አበረታቱኝ፡፡ ያላቸውን መክሊት ተጠቅመው ድንቅ ሥራዎቻቸውን ሲያስነብቡን መንፈሴ ደስ አላት፡፡
በሌላም በኩል ባለፉት አርባ እና ኀምሳ ዓመታት ትኩረት ተነፍጎት የቆየውን ‹‹የዐማራ ሕዝብ የሽምግልና ሥርዓት›› ከትጉሆቹ ባልደረቦቼ ጋር ኾነን ከተኛበት ቀሰቀስነው፤ ሕጋዊ ማኅበር እንዲኾን አስቻልነው፤ ነባሩን የሽምግልና ሥርዓት ለማያውቀው አዲስ ትውልድ አስተዋወቅነው፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ኾኜም ብዕሬን አልረሳኋትም ነበርና ከ‹‹ኤሎሄ የግጥም መድበል›› (2012) ቀጥሎ ይህን መጽሐፍ ለትውልድ ለማበርከት የዐቅሜን ያህል ደከምኩ፡፡ ከድካማችን ጎን የእግዚአብሔር ብርታት አለና፤ የእርሱ ፈቃድ ታክሎበት መጽሐፉ ለኅትመት በቃ፡፡ ክብር እና ምስጋና ለእርሱ ይኹን፤ አሜን፡፡
በላይ መኰንን ሥዩም

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

08 Oct, 16:32


አዲስ መጽሐፍ በቅርብ ቀን

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

06 Oct, 19:18


©Tsegaw Mamo
ሊቅነት ፣ ትህትና እና ቅድስና በአንድ ላይ ሲተባበሩ አነበብን።
=====================================
እንደ መምህር ኤስድሮስ እና ወልደ አብ ያሉ ትጉህ አንባቢና የመንፈሳዊ አብርሆት መሪዎች ወዴት ሄዱ?
፤ እንደ አለቃ አካለ ወልድና አለቃ ምላት ሀብቴ ያሉ ጦርነትን ያስቆሙ አስታራቂ ሊቃዎንት ነበሩ።
-------------
"The world is a book and those who do not travel read only one page." ዓለም መጽሐፍ ነች ለማይጓዝባት ሰው ግን አንዷን ገጽ ብቻ ያነባል" ይላል Saint Augustine Hippo .ይኸ ጥቅስ በጥቂቱ የሚያገለግለው በችሮታ ያገኛትን ገጽ እንኳን በደንብ ማንበብ ለቻለ ሰው ነው ። ይኸ ዓለም ብዙ ድንቆችን አሳፍሮ እየተጓዘ ይገኛል።በዚህ ዘመን መገኘት ጥቅሙ ባለንበት ሆነን በጊዜና በቦታ ሳንወሰን ሁሉን እንድናነብ ዕድል ፊቷን ስላዞረችልን ነው ! ለዚህም ምሥጋና ይገባል። በጊዜ ሀዲድ ወደ ኋላም እየተጓዝን ደጋግ ሊቃዎንትን እንድንተዋወቃቸው ዕድል ተሰጥቶናል ።
-------------
ኢትዮጵያም እጅግ አንባቢ ፣ ተመራማሪ ፣ ትሁታን ፣ ፍትሀዊ፣ሀቀኛ እና ሀገር ወዳድ ቅዱሳን ሊቃዎንት እንደነበሯት ፍኖተ ሊቃዎንት ቅጽ ፩ በመረጃ እየነገረን ነው ። ይህ መጽሐፍ 503 ገጽ ያለው ሲሆን በሦስት ክፍሎች የተከፈለ ነው ። ክፍል ሁለት የመጽሐፉን 423 ገጾችን የሚሸፍን ሲሆን የ23 የኢትዮጵያ ሊቃዎንት የሕይዎት መንገድ በጥናታዊ መልኩ የሚተርክበት ግሩም ክፍል ነው ። መጽሐፉን ለየት የሚያደርገው በሊቃዎንቱ ዙሪያ እጥን ምጥን ያለ ጥናት ከማቅረቡ ባሻገር ከዚህ በፊት ያጠኑ ምሁራን የሰሩትን ስህተት በግልጽና በቅንነት እየሞገተ ለማረም መሞከሩ ነው ።
--------------
ከታወቁት ከታላላቆቹ ቅዱሳን ሊቃዎንት ከእነ ቅዱስ ያሬድና አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተጨማሪ ስለ ነበሩት እንደነ "ሕይዎት ብን ጽዮን " በ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሕጻንነቱ ትምህርቱን ጨርሶ ከትግራይ 220 የብራና መጽሐፍትን ጭኖ ወደ ሸዋ በመምጣት በርካታ ሊቃዎንትንና ቅዱሳንን በማፍራት እስከ ህንድ ውቂያኖስ ጠረፍ ድረስ ወንጌል ስላስፋፋው ፤ ስለ መምሕር ኤስድሮስ (የትርጓሜ መምሕር አባት) በጣና ገዳማት ከ300 በላይ መጽሐፍትን አስነብበው (ዓይነ ስውር ስለሆኑ) አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስን አንድምታ (የታች ቤት ትርጓሜ ) ስለፈጠሩት ታላቅ የመንፈሳዊ አብርሆት ሊቅ ፤ ከ600 በላይ መጻሕፍትን አንብበው በትርጓሜ ላይ ስለ ሚራቀቁት የፕሮቴስታንቱ ሚሺነሪ ሳሙኤል ጎባት ሳይቀር ስለ መሰከረላቸው ሊቅ "ወልደ አብ " ፤ ስለ እነ መምሕር አካለ ወልድ ፣ ስለ እነ አራት ዓይና ጎሹ ፣ ስለ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወዘተ ሊቅነትና ትህትና በመረጃ ይተነትናል ። ከሊቅነታቸውና ከሥነ ምግባራቸው የተነሳ ለሥልጣንና ለደረጃ እድገት በነገሥታት ሲታጩ ሥልጣንና ገንዘብ አንፈልግም ስላሉት ስለ እነ መምሕር ወልደ ሚካኤል ፣ አለቃ ውብሸት እንግዳ ፣ አለቃ ኅሩይ ፈንታ ምሁራዊ ተጋድሎ ይተርክልናል ። ዶ/ር እጓለ ገብረዮሐንስ" ከመጽሐፍ ጥሩዎቹ የሚደገሙት ናቸው" ይላሉ ። በእውነት ይኸም መጽሐፍ ከሚደገሙት አንዱ ነው ።
------------
አንድ ማኅበረሰብና ሀገር ሲገነባ የኖረው ስለ እውነት ፣ ፍትህ ፣ ሥነ ምግባር እና ሀገር የሚሰብኩና የሚኖሩ ሀቀኛ የሃይማኖት አባቶች በመኖራቸው ነው ። ይኸን መጽሐፍ በማንኛውም እምነት ውስጥ ያሉ ሰዎች እንዲሁም የታሪክና የማኅበረሰብ ጉዳይ ተመራማሪዎች ቢያነቡት እጅጉን ይጠቀማሉ። በስንት ችግርና መከራ ውስጥ ሆነው ዘመን ተሻጋሪ መጽሐፍትን ለሚጽፉልን እንደ እነ "አሻግሬ አምጤ " ያሉ ሁሉ ምሥጋና ይገባቸዋል

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

30 Sep, 18:20


ጥቅምት 2 2024 በቦሌ መድኃኔአለም ቤ/ክ የሚመረቀው የ አባ ገብረኪዳን መጽሐፍ

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

06 Sep, 16:13


የመጽሐፍ ዳሰሳ 
🗒   እሑድ  03/ ጷጉሜ /2016
   ከ9:00  - 11:30
📚    መድሎተ    አሚን
⛳️  በፍኖተ ጽድቅ  ሰንበት  ትምህርት ቤት   ቤተ መጽሐፍት



ፍኖት ሚዲያ

👉Facebook
https://www.facebook.com/FinoteTsidkeSundaySchool

👉Telegram
https://t.me/Finote1619

👉Instagram
https://www.instagram.com/finote16_19?utm_source=qr&igsh=MW90eHZvOGlnZndwOA=

👉Tik-Tok
https://www.tiktok.com/@finote1619_?_t=8oiZzAgbsXu&_r=1

👉you-tube
https://youtube.com/@finote1619?si=HDw0RDGj0I1kSAKI

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

06 Sep, 15:21


➽ በተጨማሪም ከዘላለማዊ ሕይወት ጋር በተገናኘ ከሚነሱ አስተምህሮዎች መካከል አንዱ የሆነውን እና ከዳግማዊ ምጽአቱ አስቀድሞ ክርስቶስ ከቅዱሳኑ ጋር ለአንድ ሺህ ዓመት በምድር ይነግሳል የሚለውን ‘የሺህ ዓመት-Millennialism’ አስተምህሮ ይዳስሳል።የአስተምህሮው መነሻ፣ ይህንን አስተምህሮ የሚቀበሉ አባቶች፣ ቅድመ ምጽአት ሺህ ዓመትና ድኅረ ምጽአት ሺህ ዓመት ምንድን ናቸው? እነ አባ ጊዮርጊስ ሳይቀር በድርሳኖቻቸው የሚያነሱት ምሳሐ ደብረ ጽዮንስ ምንድን ነው? የሚለውን ከገለጸ በሗላ በርግጥ በራእየ ዮሐንስ የተገለጸው ሺህ ዓመት የሚለው ትርጉም ምንድን ነው? የሚለውንና ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የሺህ ዓመት አስተምህሮን ለምን እንደማትቀበለው በዝርዝር ይመልስልናል።

➽ ይህ ምዕራፍ በኢትዮጵያውያን ኅሊና ዘንድ ያለውንና በእያንዳንዱ መጥፎ ገጠመኝ ሳይቀር ‘አይ ስምንተኛው ሺህ’ የሚባልለትን ስምንተኛው ሺህን በትቂቱ ካነሳ በሗላ apokatastasis የሚባለውን ሁሉም ሰውና የወደቁ መላእክት ሳይቀሩ ከመጨረሻው ፍርድ በሗላ ድኅነት ያገኛሉ_ፍጥረት ሁሉ ከውድቀት በፊት ወደነበረበት ደረጃ ይመለሳል የሚለውን አስተምህሮ ምንነት፣መነሻና ኢ_ኦርቶዶክሳዊነት ገልጾልን ምዕራፉን ያጠናቅቃል።
➽ የመጽሐፉ የአምስቱ ምዕራፍ ማጠቃለያ በአንዲት ገጽ በአንዲት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ተጠቃሏል።እንዲህ በሚል።
“...ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም::” (1ኛ ዮሐ 3፥2)

📋 በመጨረሻም መጽሐፉ “ነገረ ሞት በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት “ በሚል በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ ‘ጉባኤ ደቂቀ አበው’ መርሐ ግብር ላይ በአዘጋጁ የቀረበ ጥሩ ጥናታዊና ትምህርታዊ ጽሑፍ አካቶ አቅርቧል።
—---------------------------------------------------------------------------
“ ክርስቶስ ሆይ በጌትነትና በምስጋና በመጣህ ጊዜ አገልጋዮችህ እኛን ተድላ ደስታ ወዳለበት ዐደባባይ ጥራን፤በአዲስ ልብስ አጊጠን ከአንተ ጋር በዚያ እንመላለስ ዘንድ፡፡” መልክአ ኢየሱስ
—-------------------------------------------------------------------------
እስመ ኵሉ እምኔሁ ወኵሉ በእንቲአሁ ወኵሉ ቦቱ ወሎቱ ሰብሃት ለዓለመ ዓለም አሜን:-ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷

© ስምዐ ጽድቅ ኤልያስ
ጳጉሜን 1፡ 2016 ዓመተ ምሕረት

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

06 Sep, 15:21


🗒 ሳምንታዊ የመጽሐፍ ጥቆማ ዘዓርብ- ፰ 🗒 © ስምዐ ጽድቅ ኤልያስ
➾ የመጽሐፉ ርዕስ:- ኅልቀተ ዓለም: የኦርቶዶክሳዊ ነገረ ፍጻሜ ዘመን አስተምህሮ
➾ የመጽሐፉ አዘጋጅ፦ ቀሲስ አሉላ ለማ
➾ የመጽሐፉ ይዘት:-ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ሃይማኖት
➾ የመጽሐፉ የገጽ ብዛት:- 235
➾ የመጽሐፉ የምዕራፍ ብዛት:- አምስት
➾ የህትመትዓመት:-፩ኛ ዕትም 2009 ዓ.ም፥፪ኛ ዕትም 2016 ዓ.ም
➾ የተጠቀማቸው ዋቢ ድርሳናት ብዛት፦ 49
➾የመጽሐፉ የሽፋን ዋጋ፦ 400 ETB

📗 መግቢያ 📗

➽ በኢትዮጰያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዐቢይ ጾም እኩሌታ(ደብረ ዘይት)፣በመጋቢት 29 ፡ እና በወርኃ ጳጉሜጊዜያት በተለየ ሁኔታ በቤተክርስቲያን ጸሎታት ፣ ምንባባት ፣ ዝማሬ፣ ቅዳሴና ሥርዓተ አምልኮ ሚዘከር ፣የሚመሰጠር ፣የሚተረጎምና የሚዜም ርዕሰ ጉዳይ ነው ነገረ ኅልቀተ ዓለም (Eschatology)። የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ጥቆማየም ወቅቱ እርሱም ወርኃ ጳጉሜ በቤተክርስቲያናችን ሥርዓተ አምልኮና አገልግሎቶች አንዱ የዓለም ፍጻሜና የክርስቶስ ዳግም ምጽዓት የሚወሳበትና የሚዘከርበት ወቅት ስለሆነ ከወቅቱ ጋር የተስማማ መጽሐፍ ለመጠቆም ወደድሁ።

➽ የትምህርተ ሃይማኖታችን አንዱ ክፍል ነው። በነገረ መለኮት ትምህርት ነገረ ኅልፈተ ዓለምና ተያያዥ ጉዳዮችን የምንማርበት አንዱ የነገረ ሃይማኖት ዘርፍ ነው Eschatology:: በቤተክርስቲያናችን አእማደ ምሥጢራት ተብለው ከሚጠቀሱትም አንዱ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ይህንን ርዕሰ ጉዳይ ይዳስሳል።በርግጥም በሰው አእምሮ ከመረዳት በላይ የሆነ የነገረ ሃይማኖት ትምህርት ስለሆነ ምሥጢር መባል የተገባው ነው። አንድ ክርስቲያን ዘወትር በሚጸልየው ጸሎተ ሃይማኖት በተባለው የሃይማኖት መግለጫም <<....ዳግመ ይመጽዕ በስብሐት ይኵንን ሕያዋነ ወሙታነ ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግስቱ….ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን ሕይወተ ዘይመጽዕ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም >> ብለን የምናምነውን እንጸልያለን። የምንጸልየውንም እናምነዋለን።የሥርዓተ አምልኳችን ማዕከል የሆነው ቅዳሴያችን ደጋግሞ ያነሳሳዋል።

➽ በክርስቲያኖች ሕይወትና በአጠቃላይ በኦርቶዶክሳዊ ክርስትያኖች ሕይወት ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ፍጻሜ ዓለምንና ፍጻሜ ዓለምን የተመለከተው ጉዳይ። ገና ወደፊት የሚፈጸም ምሥጢር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለብዙ ግላዊ አስተያየት (Speculations) የተጋለጠም ይመስላል። ሐሳውያን ነቢያትና ባሕታውያን ለሚፈልጉት ነገር(ቢዝነስም ይሁን ለሌላ) ምዕመኑን ከሚያስፈራሩበትና ከሚስቡበት ርዕሰ ጉዳይ አንዱ ነው። በእኛ ማኅበረሰብ ዘንድ ደግሞ ነገሩ ትንሽ ለየት ባለ መልኩ እንደ ስምንተኛው ሺ የመሳሰሉ ሀቲቶች የማኅበረሰቡ ንግርቶች ተደጋግመው ይጠቀሳሉ። .በሌላ መልኩ እንደ ሺ ዓመት መንግስት ፣ መነጠቅ፣ ምሳሐ ደብረ ጽዮን፣ Universal Salvation የመሳሰሉ የሊቃውንት አተያዮችና ሀሳቦችም የሚነሱበትና ከኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አስተምህሮ አንጻር የሚታዩበት ክፍለ ትምህርትም ነው።

➽ ከዚህ ሁሉ አንጻር አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በቅዱሳት መጻሕፍት የተገለጠውንና በቅዱሳን አበው በመንፈስ ቅዱስ አብርኆት የተብራራውን እውነተኛውን ትርጓሜ መረዳትና ማወቅ የተገባና ራስንም ሌሎችንም ለመጠበቅና ለማዳን በእጅጉ ይጠቅማል። ይህ ኅልቀተ ዓለም የተሰኘው መጽሐፍም ነገረ ኅልቀተ ዓለምን በተመለከተ የሚነሱ ሀሳቦችን፣ አስተያየቶችን፣ ጥያቄዎችን ከኦርቶዶክሳዊ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ አንጻር ለማብራራት የሚሞክር መጽሐፍ ነውና ሊነበብ የሚገባው ነውና እንዲነበብ እንመክራለን። ጸሐፊውም ይህንን መጽሐፍ ስላበረከቱልን እናመሰግናቸዋለን::
➹ ማስታወሻ:- [ነገረ ኅልቀተ ዓለምንና ነገረ ምጽዓትን በተመለከተ ተጨማሪ ሰፊ ግንዛቤ ለማግኘት <ምጽዓተ ክርስቶስ> የተሰኘውን የመምህር ሣሙኤል ፈቃዱን መጽሐፍ መመልከት እጅግ ጠቃሚ ነው]።

📗 የመጽሐፉ ዓላማና አስፈላጊነት 📗
➽ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ሞትን በተመለከተ ኦርቶዶክሳዊ አረዳድ እንዲኖረን ያስችላል።
➽ ኅልቀተ ዓለምን በተመለከተ የኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ትምህርት ያስተዋውቃል።
➽ በአንዳንድ ርዕሰ ጉዳዮች ሊቃውንት የተለያየ አመለካከት ስላላቸው ቤተክርስቲያን የምትቀበላቸውን አስተምሮዎች ለማሳወቅና የብሔራዊ ሊቃውንትንም አመለካከት በተወሰነ መልኩ ለማየት ይጠቅማል።
➽ በዚህ ሩጫና መባከን በበዛበት ፣ ትኩረት በሚያሳጣ ዓለም ስለዘለዓለማዊ ሕይወት በማሰብ መንፈሳዊ ሕይወታችንን ለማስተካከል ይረዳል።
➽ ቤተክርስቲያን የምታስተምረውን ትክክለኛውን የነገረ ኅልቀተ ዓለም ትምህርት በመረዳት ሰውነትንና ሕይወትን ለወዲያው ዓለም ድልው አድርጎ ለመኖር ይጠቅማል።

📗 የምዕራፋቱ መሠረታዊ ጭብጥ 📗

🔸ምዕራፍ አንድ🔸
➽ ውሎ ውሎ ከቤት ኑሮ ኑሮ ከሞት እንላለን በብሒላችን። ዘወትር እንደጥላ ይከተለናል።ለሰው ልጅ የማይቀር እጣ ፋንታና ሰውን አንድ የሚያደርግ እውነታ ነው። ለሺዎች ዓመታት የሕይወት አንድ እውነታ ቢሆንም ሰው አሁንም መቀበል የሚከብደው እውነታ ቢኖር ሞት ይሉትን ኃይል ነው። “ሁሉም ሰው እንደሚሞት ያውቀዋል፣ ነገር ግን ይህን እውነት አይቀበለውም።” እንዲል ሞሬ ስካዋርትዝ። ለመሆኑ ሞት ምንድን ነው? ሞትን መቀበል ለምን ያቅተናል? በተለይ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች እንዴት ነው መረዳት ያለብን? ስንት ዓይነት ሞት አለ? ሞት ራሱን የቻለ ሕልውና ያለው አካል ነውን? ወይስ ሌላ? ሞትን ማን እና ምን አመጣው? ለሞት ተጠያቂው ማነው? ሞት የሕይወትን ትርጉም እንዴትና እስከምን ይወስናል? ሞትስ ለምን እንፈራለን? መጽሐፍ ቅዱስስ ስለሞት ምን ይላል? ሞትና ነጻ ፈቃድ ምን አይነት ግንኙነት አላቸው? ነፍስ ከሥጋ ከተለየች በሗላ ምን ትሆናለች? የራሷ ሕልውና ይኖራታል? ወይስ እንዴት ትኖራለች? ለሞቱ ክርስቲያኖች ጸሎተ ፍትሐት ለምን ይደረጋል? ከሞት በሗላ ያለው ሕይወትስ ምን ይመስላል? የዚህ መጽሐፍ የመጀመሪያው ምዕራፍ ይህንን በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ እጅግ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን ነገረ ሞትን በማነሳሳት እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎችን ይመልሳል።

➽ ብዙ ጊዜ በተግባር የምናየው የክርስቲያኖች የሞት አረዳድ የተንሸዋረረ እና ከሌሎች በክርስትና ተስፋ ከማይኖሩ እንኳ የከፋ ሆኖ ይታያል። ወዲህ የሕይወት መደምደሚያ፣መፈጸሚያ፣ማለቂያ አድርጎ ከሞት በሗላ ሕይወት የሌለ የሚያስመስል አረዳዳድ እናስተውላለን። ሰው ሲሞትብንም ሀዘናችን መራር ይሆንና እግዚአብሔር ጋር እስከ መጣላትና እሱ ላይ እስከማጉረምረም እንደርሳለን። አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ሞትን እንዴት ነው ሊረዳው የሚገባው? የሚለው ጉዳይ መሠረታዊ ነገር ነው።ሞትና ኃይሉ በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተሻረ እና በክርስቶስ ሞትም መቃብር ለዘለዓለም ሕይወት የምንወለድበት ማኅፀን ወደ መሆን ትርጉሙ ቢቀየርም አሁንም ሞት ላይ ያለን ተግባራዊ መረዳታችን ከዚህ ኦርቶዶክሳዊ እሳቤ የተዛነፈ መሆኑ ያሳስባል።ቅዱስ አትናቴዎስ በሐዲስ ኪዳን ሞት ጥፍሩና ጥርሱ እንደወላለቀና ኃይሉን እንዳጣ አንበሳ ነው የሚለንም ለዚህ ነው።ሰማዕታት ለሽልማት በቀይ ምንጣፍ የተጠሩ ይመስል ለሞት የተሽቀዳደሙትና የሚፋጠኑት የሞትን ኦርቶዶክሳዊ አረዳድ ገንዘብ ስላደረጉ ነው። ይህ ምዕራፍ የሞትን ምንነት በኦርቶዶክሳዊ ቅኝት ለመረዳት ከሞት ጋር ተያያዥ የሆነ ርዕሶችን ይዳስስልናል።

EOTC Books የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ. መጻሕፍት

06 Sep, 15:21


➽ በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንድ ጊዜ በዚህ ዓለም ስንኖር ስለሞት እያሰቡ መተከዝ፣ ማዘን፣ መጨነቅ በዚህ እንድንኖር የፈቀደልንን የደስታ ዓለም የፈጠረን አምላክ ማሳዘን አይሆንም ወይ? የሚል ሊኖር ይችል ይሆናል። ሞትን አላስብም ብሎ ሰው ራሱን ለማታለል ቢሞክር እንኳ ከሞትና ሞትን አስቦ አለመዘጋጀቱ ከሚያስከትለው ጥያቄና ፍርድ ነጻ መሆን አይችልም። በኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ተዘክሮተ ሞት ወይንም ሞትን ማሰብ መሠረታዊ ጉዳይ ነው።ለምን ያልን እንደሆነ ከኃጢአት እና ፈቃደ ሥጋው ከሚያመጣቸው ፍትወታት ጋር ለሚያደርገው ብርቱ ትግል የዘወትር ብርታቱ ስለሆነች ነው። ይወርሳት ዘንድ ያለችውን፣ተስፋም ለሚያደርጋት መንግስተ እግዚአብሔር ለመዘጋጀትና እሷንም ለማግኘት የሚሸጋገርባት ድልድዩ ስለሆነች ዘወትር ሞትን እናስበዋለን። ምዕራፍ አንድ ይህን እና የመሳሰሉ የነገረ ሞት ጉዳዮችን ካብራራልን በሗላ ሞት በአበው አስተምህሮ ምን እንደሚመስል በአጭሩ ዳስሶልን ምዕራፉን ይቋጫል።

➹ ማስታወሻ:-
[ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ስለሆኑት ስለሞትና ሕይወት በሰፊው ለመረዳት “ፍካሬ ሞት ወሕይወት” የሚለውን የመምህር ቃኘው ወልዴን መጽሐፍ መመልከቱ በእጅጉ ይጠቅማልና እንዲመለከቱት እንመክራለን ።]

🔸ምዕራፍ ሁለት🔸
➽ በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ትምህርትና ሥርዓተ አምልኮ በስፋት ከሚሰበኩ ርዕሰ ጉዳዮች አንዱ የጌታችን ዳግም ለፍርድ የመምጣቱ ነገር ነው። ቅዳሴያችንና ጸሎቶቻችን ደጋግመው ያነሱታል። ቀዳማዊ ምጽአቱ በትሕትና ለአድኅኖተ ዓለም ሲሆን ለደቀመዛሙርቱ እንደነገራቸው ዳግም ምጽአቱ ግን በግርማ መለኮት ለፍርድና ይህችን ዓለም እንደ ድንኳን ጠቅልሎ ለማሳለፍ የሚመጣበት ነው።የዚህ መጽሐፍ ሁለተኛው ምዕራፍ ስለዳግም ምጽአት ያብራራልናል።

➽ ምዕራፉ ዳግም ምጽአት በክርስትና ውስጥ ያለውን ቦታ በመግለጽ ይጀምርና በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ በብሉይም፣በሐዲስም የተገለጠበትን መንገድ በማተት የጌታ ዳግም መምጣት ምልክቶችን አንድ በአንድ ያብራራልናል።በዚህም ተደጋግሞ ስለሚነሳው ሐሳዊ መሲህ(ሐሰተኛው ክርስቶስ) ማንነትና ምንነት ይገልጽልናል።ቀጥሎም ስለመነጠቅ ምንነት እና በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን እንዴት እንደሚታይና መነጠቅን ለምን እንደማንቀበለው ያቀርብልናል። ከዚያም ጌታችን አምላካችን እንዴት ይመጣል? ለሚለው የሚመለሱ በግርማ መለኮትና በክበበ ትስብእት የሚሉ ነገሮች ምንነታቸውን ያቀርብና የአበውን ትምህርት ስለዳግም ምጽአተ ክርስቶስና ዳግም ምጽአቱ በሥርዓተ አምልኮ በምን ሁኔታ እንደሚገለጥ ያቀርብልንንና ምዕራፉን ያጠናቅቃል።

🔸ምዕራፍ ሦስት🔸
➽ ሦሥተኛው ምዕራፍ ነገረ ትንሣኤ ሙታንን ይዳስሳል።የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ የሆነው የቅዳሴ ትርጓሜ መጽሐፍ ሕይወትን በተመለከተ ሲገልጽ ሦሥት አይነት ሕይወት አለ ይላል።እነዚህም ሕይወት መልአካዊ፣ሕይወት እንስሳዊና ሕይወት ሰብአዊ ናቸው ። ይህንን ሲያብራሩም ሕይወት እንስሳዊ ደመ ነፍሳዊ ሲሆን በተፈጥሮ ወይንም በልደት ይሰጣቸውና በሚሞቱበት ጊዜ ተነስቶባቸው(ተወስዶባቸው) በዚያው እንደተነሳ የሚቀር ሕይወት ነው ይላሉ። ሕይወት መልአካዊ በተፈጥሮ የሚሰጥ፣እንደተሰጠ የሚቀርና የማይነሳ ሕይወት ነው።ሕይወት ሰብአዊ በተፈጥሮ ይሰጠናል በሞት ይነሳል(ይወሰዳል)፣በትንሣኤ ዘጉባኤ የሚመለስ ሕይወት ነው።በክርስትና እምነት ሰው ከሞተ ከፈረሰና ከበሰበሰ በሗላ አካሉ ከነፍሱ ጋር በመዋሐድ ይነሳል ብለን እናምናለን። ስለዚህም ምዕራፉ ትንሣኤ ዘጉባኤ ጊዜ የሚፈርስ የሚበሰብስ ሥጋችን በኃይለ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚነሳ ይገልጻል።

➽ ምዕራፉ ለሰው ልጆች ሁሉ ትንሣኤና የክርስትና ማዕከል የሆነውን የጌታችንን ትንሣኤ ልዩ መሆን፣በኩረ ትንሣኤ መሆን፣ጌታ ከሙታን ለመነሳቱ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎችን እንዲሁም ስለሙታን ትንሣኤ የጌታችን ትምህርት ምን እንደሚመስል ከገለጠልን በሗላ ትምህርተ ትንሣኤ ሙታን በሁለቱ ኪዳናት እግዚአብሔር እንዴት እንደገለጠልን ያብራራል።ከዚያም ነገረ ትንሣኤን ማለትም ትንሣኤ ልቡናን፣ ትንሣኤ ነፍስን፣፣ትንሣኤ ዘጉባኤን ፣ በትንሣኤ ዘጉባኤ አካላዊ ትንሣኤ እንዴት እንደሚነሳ፣ ሥጋ ወይም አካል የእግዚአብሔርን መንግስት አይወርስም ስለሚሉ ሰዎች፣የሰው አካል ከትንሣኤ በሗላ ምን ይመስላል? የሚለውን ካብራራልን በሗላ ነገረ ትንሣኤ ሙታን በቀደሙት የቤተክርስቲያን አበው እንዴት እንደተብራራ በመጠኑ ገልጾልን ምዕራፉን ይደመድማል።

🔸ምዕራፍ አራት🔸
➽ አራተኛው ምዕራፍ በጎቹና ፍየሎቹ፣ስንዴዎቹና እንክርዳዶቹ ስለሚለዩበት ስለመጨረሳው ፍርድ ያብራራል።የቤተክርስቲያን የነገረ ሃይማኖት ምንጭ እና እስትንፋሰ አምላካውያት በሆኑት በዐሥራው ቅዱሳት መጻሕፍት(ብሉይ ኪዳንና ሐዲስ ኪዳን) ስለዘላለማዊ ፍርድ እግዚአብሔር በአፈ ቅዱሳን በኩል ምን ብሎ ነገረን፣ ከመጨረሻው ፍርድ ጋር በተገናኘ የተነሳው የፎጢኖስ ክህደት፣ ጊዜያዊ ፍርድ(partial Judgment) ስለሚባለው ነገር፣ በመጨረሻው ፍርድ የሚፈረድባቸው እነማን ናቸው?እና የመጨረሻው ፍርድን ተገቢነት ፣ የሚፈርደው ማነው? ፍርድስ የሚተላለፈው በማን ላይ ነው? እነዚህንና የመሳሰሉትን ያብራራልናል።

➽ ምዕራፉ በተጨማሪም ከፍርድ በሗላ ስለሚኖሩ ሁኔታዎች ለምሳሌ ገነት፣ሲኦል፣ መንግስተ ሰማይ፣ገሃነም ስለመሳሰሉት እነዚህን በተመለከተ የቤተክርስቲያን ትምህርት፣ የሊቃውንት ልዩ ልዩ አመለካከቶች እና የሚነሱ ክርክሮችን ይዳስሳል።ለምሳሌ ገነትና ሲኦል የተለዩ መካናት ናቸው? ወይስ ሁኔታዎች ናቸው? መካነ ኃጥአን የሚባል አለ? የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን ይዳስስልናል። ሲኦልስ የተለየ የስቃይ ቦታ ነው ወይስ ሌላ ከእግዚአብሔርና ከፍቅሩ ውጭ መሆን? ነው ወይስ ሌላ? ገሃነምስ? የዘላለም የስቃይ ቦታ ወይስ ሌላ? እሳቱ የማይጠፋ ትሉ የማያንቀላፋ የሚለውስ ምንድን ነው? ወዘተ በእነዚህ ርዕሶች የተለያዩ ሊቃውንትን አተያይ ያቀርብልናል። በመጨረሻም መንጽሔ እሳት(Purgatory) የሚለው በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ያለውና ሙሉ በሙሉ ንጹሕ ሳይሆኑ ወይንም ለሰሩት ጥቃቅን ኃጢአቶች ሥርየት ሳያገኙ የሞቱ ሰዎች ከኃጢአታቸው ነጻ የሚሆኑበት ስፍራ አለ የሚለው አስተምህሯቸው ምንድን ነው? ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንስ ትምህርቱን የማትቀበልባቸው ምክንያቶች ምንድን ናቸው? የሚለውን አቅርቦልን የአበው አስተምህሮ ስለመጪረሻው ፍርድ ምን ብለው እንዳስተማሩ መጠነኛ ዳሰሳ አቅርቦልን ምዕራፉ ይጠናቀቃል።

🔸ምዕራፍ አምስት🔸
➽ የመጨረሻውና አምስተኛው ምዕራፍ ኅልፈተ ዓለምና ዘላለማዊ መንግስትን ይዳስሳል።የዓለም ኅልፈት የማያሳስበውና ሰው ያለ አይመስልም።ጉዳዩ ደቀመዛሙርቱንም አሳስቧቸው የዓለም ፍጻሜ መቼ ይሆናል? ሲሉ ክርስቶስን ጠይቀውታል። ለመሆኑ የዓለም ፍጻሜ መቼ ይሆናል? ዓለምስ እንዴት ነው የምታልፈው? ከዓለም ኅልፈት በሗላ የምንወርሰው ‘አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር’ የተባሉትስ ምንድን ናቸው? አዲስ ሰማይ ምንድን ነው? አዲስ ምድር ሲባልስ ምንድን ነው? አዲስ ያሰኘው ምኑ ነው? የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን በአጭሩ ያብራራልናል።

4,943

subscribers

274

photos

1

videos