Farankaa - ፈረንካ @farankaa Channel on Telegram

Farankaa - ፈረንካ

@farankaa


The primary goal of this page is to enhance the financial literacy of Ethiopians by offering valuable insights on investment, banking, insurance, capital markets, and taxation.

Farankaa - ፈረንካ (Amharic)

ፈረንካ - ፈረንካ በትምህርት በሰላም ተደምረናል። ኢትዮጵያዊያን በግንኙነት ለወገኑ የክፍል ቅናት እንዴት እንደሚንኩት ምንድን ነው? ይህ ፒዣግ ከኢስቶንመባሎች፣ ባንክሌም፣ ኢንሹራንስ፣ ባንክሌም ስታፊና ተቀናቃን ለእርስዎ የሚገነኘው በሰላም ተናገራለች።

Farankaa - ፈረንካ

07 Jan, 10:39


እንኳን አደረሳችሁ!

Farankaa - ፈረንካ

14 Dec, 06:49


ኑ አብረን እንሳቅ! (እያረርን ከመሳቅ ውጪስ ምን አማራጭ አለን?!)

የሐረሪ ክልል በክልሉ ሊያከናውን ላሰበው የኮሪደር ልማት እያንዳንዱ በከተማው ውስጥ ያለ የባንክ ቅርንጫፍ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 2,000,000 ብር እንዲያዋጣ ደብዳቤ ላከ።

ቅርንጫፎች እንዲህ አይነቱ ውሳኔ የሚወሰነው በየባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ስለሆነ ደብዳቤውን ወደዛ ልኮ ውሳኔ መጠባበቅ ያዘ።

ይሄንና ጥያቄዬ አልተከበረም ያለው ቆፍጣናው የሐረሪ ክልል በሐረር ከተማ እየዞረ የህዝብ ገንዘብ በአደራ ያስቀመጡ ቅርንጫፍ ባንኮች ላይ "ታሽጓል!" የሚል ማስጠንቀቂያ ለጥፎ ዘጋ!

በመሠረቱ ክልሉ ከቅርንጫፍ ባንኮቹ ላይ የሠራተኛ ደሞዝ ግብር ከመሰብሰብ የዘለለ መብት አልነበረውም። ያው ሀገሩ ኢትዮጵያ ነውና፣ ህግ አውጪው በዝቷልና የሆነው ሆነ።

Farankaa - ፈረንካ

11 Dec, 15:03


የፕላስቲክ ፌስታል መጠቀም የሚከለክለዉን ረቂቅ ህግ እንድምታ..
                       ***
ኢትዮጵያ የፕላስቲክ ፌስታል መጠቀም የሚከለክለዉን ህግ ለተወካዮች ምክር ቤት አቅርባለች።ረቂቅ ህጉ የፕላስቲክ ፌስታል ማምረትንና መጠቀም የሚከለክል ሲሆን...

የፕላስቲክ ከረጢት የተጠቀመ ወይም ለመጠቀም ይዞ የተገኘ ማንኛውም ሰው ከ5,000 ብር እስከ 10,000 ብር ይቀጣል።

የፕላስቲክ ከረጢት አምርቶ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ አስገብቶ ለገበያ ማቅረብ፣ ለንግድ ዓላማ ማከማቸት ከ50 ሺህ ብር እስከ መቶ ሺህ ብር ያስቀጣል። ከዚህ በተጨማሪም ከአምስት አመት የማይበልጥ ጽኑ እስራት ያስቀጣል።

የህጉ መጽደቅ ምን እንድምታ ይኖረዋል?

ረቂቅ ህጉ የአከባቢ አየር ብክለትን ለመቆጣጠር የወጣ እና አካባቢያዊ ቀጣይነትን/ Sustainability ለማረጋገጥ ያለመ ቢሆንም የህጉ መጽደቅ...

🧑‍🚀  በፕላስቲክ ፌስታል ፋብሪካ ዉስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ሥራ ያሳጣል።

ከእዚህ ቀደም ሚሊዮኖችን ኢንቨስት በማድረግ የተገዙ ማሽኖች ተለዋጭ የማምረት አቅም ከሌላቸው በቀር ከጥቅም ውጪ ይሆናሉ።

🏭 እኒህን ማሽኖች ከባንክ በመበደር የገዙ አምራቾች የባንክ እዳውን ለመክፈል ስለሚያቅታቸው ብድሮቻቸው ይበላሻሉ አሊያም nonperforming loan ይሆናሉ፣ ይሄ ደግሞ በተለይ እነዚህን ማሽኖች በብድር እንዲገዛ ፋይናንስ ያደረጉ እና በመያዣነት የያዙ ባንኮች ማሽኖቹን መሸጥ ስለማይችሉ ለኪሳራ ይዳረጋሉ።

Picture credit: OpenAI

Farankaa - ፈረንካ

03 Dec, 12:29


በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የFinancial stability Report ውስጥ የተገለጸው ከስርቆት ጋር በተገናኘ ባንኮች ስለገጠማቸው ኦፐሬሽናል ስጋት/Operational risk እና ሌሎች የኢኮኖሚና የቢዝነስ ጉዳዮ ላይ ከጋዜጠኛ አንዋር አብራር ጋር የተደረገ ውይይት።

https://youtu.be/Y1U8_ULGyRs?si=bbRA_oi8vzvGqSua

Farankaa - ፈረንካ

02 Dec, 04:17


ይሄንን ተቀበል...

ሁልጊዜ ፍጹም ልትሆን እንደማትችል፣ ህይወት ሁሌም በፈተና የተሞላች መሆኗን እንዲሁም አንዳንዴ ሰዎች ሊያበሳጩህ እንደሚችሉ አምነህ ተቀበል። መቀበል ሰላምን የማሸነፊያ የመጀመሪያው እርምጃ ነው።

መልካም ሳምንት!

Farankaa - ፈረንካ

01 Dec, 06:52


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ትላንት ይፋ ባደረገው፣ ሁለተኛው የፋይናንሺያል ስቴቢሊቲ ሪፖርት መሠረት የባንኮች operational risk ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩንና ከአመት በፊት በአጠቃላይ ከባንክ ዘርፉ ላይ የተሰረቀው የገንዘብ መጠን 1 ቢሊዮን ብር የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ይኸው ገንዘብ ወደ 1.3 ቢሊዮን ብር ከፍ ማለቱን፣ እንዲሁም በስርቆቱ 28 ባንኮች (ሁሉም ሊባል በሚችል መልኩ) መጎዳታቸውን ገልጿል።

በእነዚህ ስርቆቶች እና ማጭበርበሮች ውስጥ የባንኮች የውስጥ ሰራተኞች ጭምር የተሳተፋበት ሲሆን ስርቆቶቹ በዋናነት ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን፣ ሀሰተኛ ቼክ፣ ሀሰተኛ የባንክ ጋራንቲን፣ የተሰረቁ የኤቲኤም ካርዶችን፣ ሀሰተኛ የስልክ ጥሪዎችንና መልእክቶችን በመጠቀም የተከናወኑ መሆናቸውን ብሔራዊ ባንኩ የገለጸ ሲሆን ባንኮች ከጊዜ ወደ ጊዜ የፋይናንስ አካታችነትን ለማሳካት በሚተገብሯቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ምክንያት ስጋቱ እየጨመረ እንደሚሄድ የገለጸ ሲሆን ባንኮች እኒህን ስጋቶች ለመቀነስ ፖሊሲና ስትራቴጂ ቀይሰው እንዲሰሩ አሳስቧል።

Farankaa - ፈረንካ

30 Nov, 16:29


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሁለተኛ የፋይናንሺያል ስቴቢሊቲ ሪፖርት።👇

Farankaa - ፈረንካ

29 Nov, 10:01


የኡጋንዳ ማእከላዊ ባንክ በውጭ ሀገር ሀከሮች 17 ሚሊዮን ዶላር ገደማ መዘረፉን አመነ።

https://www.reuters.com/world/africa/hackers-steal-17-mln-uganda-central-bank-state-paper-2024-11-28/

Farankaa - ፈረንካ

26 Nov, 06:17


በኢትዮጵያ እየተቋቋመ ስላለው የተመሰከረላቸው የሒሳብ ባለሙያዎች /Charted Public Accountants/ ኢንስቲትዩት ምንነትና አስፈላጊነት፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እየተቋቋመ ስለሚገኘው ኢንቨስትመንት ባንኪንግ ምንነትና ፋይዳ እንዲሁም የሰው ኃይል ላይ ሊደረግ ስለሚገባው ኢንቨስትመንት/Human Capital Development/ መረጃ ከፈለጉ የሚከተለውን ያዳምጡ...

https://youtu.be/ZFxxY89vqf8?si=N4pJm9Y17tTwV2Qs

Farankaa - ፈረንካ

20 Nov, 04:29


ሌሎች ሰዎች እንዲወዱህ ብለህ እውነተኛ ማንነትህን አትቀይር፣ እራስህን ሆነህ ተገኝና ትክክለኛ ሰዎች ይወድዱሀል።

Farankaa - ፈረንካ

18 Nov, 16:29


https://www.linkedin.com/posts/feyselandassociates_tax-alert-new-directive-on-tax-invoice-management-activity-7263906198469459969-zR0j?utm_source=share&utm_medium=member_android

Farankaa - ፈረንካ

18 Nov, 05:30


የቁሳዊ ነገሮች ዋጋ የሚታወቀው በእጃችሁ ሳይገቡ በፊት ሲሆን፣ የሰው ልጆች ዋጋ ደግሞ የሚታወቀው ካጣችኋቸው በኋላ ነው!

መልካም ቀን፣ መልካም ሳምንት!

Farankaa - ፈረንካ

17 Nov, 05:11


"መልሶችህ እውቀትህን የሚያሳዩ ሲሆን፣ ጥያቄዎችህ ደግሞ እሳቤህን ያመላክታሉ።"

መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

Farankaa - ፈረንካ

16 Nov, 14:03


ከአስር ባሎች መካከል ዘጠኙ "ሚስቶች ሁልጊዜ ትክክል ናቸው" ማለታቸውን አንድ ጥናት አረጋገጠ።

አስረኛው ባል (ሚስቶች ሁልጊዜ ትክክል አይደሉም ያለው) ጥናቱ ከተደረገ በኋላ እምጥ ይግባ ስምጥ ይግባ አልታወቀም።

የት ሄዶ ይሆን ወገን?

መልካም የእረፍት ቀናት!

Farankaa - ፈረንካ

14 Nov, 16:23


Public offering and trading of securities Directive no. 1030/2024

Farankaa - ፈረንካ

14 Nov, 10:23


ሰነደ መዋእለ ንዋይን ለህዝብ የማቅረብ /Public offering/ እና የግብይት መመሪያ ይፋ ሆነ።

Farankaa - ፈረንካ

14 Nov, 06:36


ዘመን ባንክ የሠራተኞች ሙያዊ እድገት ተምሳሌት!

****

ላለፉት 3 ቀናት በ CaFEC SC አማካይነት በIFRS 9 Financial instruments ላይ የተዘጋጀ ስልጠና ለ Zemen Bank S.C.  ሠራተኞች ሰጥቼ አጠናቀቅሁ።

በስልጠናው ላይ በሰለጠነው ዓለም በእያንዳንዱ ሙያ ላይ ስለሚተገበረውና ቀጣይነት ስላለው የሙያዊ እድገት /Continuous Professional Development/ አስገዳጅነት ለሰልጣኞቹ ሳስረዳ...

"የእኛም ባንክ ለ LinkedIn ገንዘብ ከፍሎልን ስልጠና እንድንወስድ፣ ሙያችንን እንድናሳድግ እድል ሰጥቶናል፣ ስልጠና ከአመታዊ እና ከመንፈቃዊ የአፈጻጸም መለኪያ/performance evaluation ነጥቦች መካከል አንዱ ነው! ሰራተኞች በየመንፈቁ ሊማሩ ስለሚገባው ዝቅተኛ ሰዐት ተቀምጦ በእዛ እንመዘናለን"

ሲሉ ልቤን ያሞቀ ነገር ነገሩኝ።

ዘመን ባንክ የሠራተኞቹን ሙያዊ እድገት ለማረጋገጥ ያሳየው ቁርጠኝነት፣ በተለይ ደግሞ ስልጠናን ከአፈጻጸም መለኪያ ጋር ማያያዙ ለሌሎች ተቋማት ተምሳሌት ሊሆን የሚችልና ሊተገበር የሚገባው ነገር ሆኖ አግቼዋለሁ።

በሠራተኞች ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ለሠራተኞቹ ጥቅም ብቻ ሲባል የሚደረግ ሳይሆን ባንኩ በዘርፉ ላይ የሚኖረውን ተወዳዳሪነት የሚጨምርና በአጠቃላይ ለባንኪንግ ዘርፉ ስልጡንና ለለውጥ የተዘጋጀ የሰው ኃይልን የሚያበረክት መሆኑ ልብ ሊባል ይገባዋል ስል ጽሁፌን እደመድማለሁ።

Farankaa - ፈረንካ

13 Nov, 19:59


የታክስ ደረሰኝ አጠቃቀም እና አስተዳደር መመሪያ ማሻሻያ ቁጥር 188/2017

በደረሰኝ የሚደረግ ማጭበርበርን ለመግታት፣ በእያንዳንዱ የንግድ ሥራ ዘርፍ እና የንግድ አድራሻ የተለያየ ደረሰኝ እንዲታተም ማድረግ እንዲሁም በእያንዳንዱ ደረሰኝ ላይ ልዩ QR ኮድ (unique QR code) ማካተት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ገቢዎች ሚኒስቴር በፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 19(4) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን የማሻሻያ መመሪያ አውጥቷል።

Farankaa - ፈረንካ

11 Nov, 04:22


ከተማርክ፣ አስተምር
ካገኘህ፣ ስጥ።

ማያ አንጄሎ


መልካም የሥራ ሳምንት!

Farankaa - ፈረንካ

09 Nov, 13:48


https://www.linkedin.com/posts/kasrajh_innovation-sustainability-environmentalimpact-activity-7260531530349903872-eObE?utm_source=share&utm_medium=member_android

Farankaa - ፈረንካ

09 Nov, 13:48


ከላይ የተያያዘው ቪዲዮ "በሜክሲኮ ከባህር አረም ቤት መገንቢያ ጡብ ተመርቷል፣ አረም ወደ ገንዘብነት ተቀይሯል" ይለናል። በእኛም ሀገር አስፈላጊው ምርምር ቢደረግና እምቦጭን ወደ ፍራንክ መቀየር ቢቻል በጥቂት ወራት ሀይቆቻችንን ማጽዳት ይቻል ነበር። የአካባቢ ጥበቃ ከፍራንክ ጋር ሲያያዝ ፍሬ ያፈራል።

Farankaa - ፈረንካ

08 Nov, 10:53


ፍራንኮ ቫሉታ ተሰርዟል።

Farankaa - ፈረንካ

08 Nov, 06:45


አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ የትራምፕ መመረጥ ለአፍሪካ ምን ማለት እንደሆነ ለFirst Post tv የሰጡት ቃለመጠይቅ...

https://youtu.be/c9JkfbRnqmQ?si=2kr0QI2U_ry7st1b

Farankaa - ፈረንካ

08 Nov, 05:27


በገንዘብ ብዛት፣ በተከታይ ቁጥር፣ በዲግሪ ብዛት እና በማእረግ ጋጋታ አትደነቁ፣ ይልቅስ በደግነት፣ በታማኝነት፣ በትህትና እና በለጋስነት ተደነቁ።

መልካም ቀን!

Farankaa - ፈረንካ

07 Nov, 04:54


ህይወት "የሰው ዘር" በመሆን እና "ሰው" በመሆን መካከል ያለ ረጅም ጉዞ ነው። ቢያንስ በየቀኑ አንዳንድ እርምጃ በመራመድ ርቀቱን እናጥብብ።

መልካም ቀን!

Farankaa - ፈረንካ

06 Nov, 08:15


ሾርት ሚሞሪያሞች ትራምፕ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ላይ ያሉትን ረስተው የፕሬዚዳንቱን ዳግም መመረጥ celebrate እያደረጉ ይገኛሉ።

አስደማሚ የፖለቲካ ንቃት ነው።

ለማስታወስ ያህል ትራምፕ በቀድሞ የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው የህዳሴውን ግድብ በተመለከተ ይሄንን ብለው ነበር...

"It's a very dangerous situation because Egypt is not going to be able to live that way, They'll end up blowing up the dam. And I said it and I say it loud and clear -- they'll blow up that dam. And they have to do something"

"ሁኔታው እጅግ አደገኛ ነው ምክንያቱም ግብጽ በእዚያ መንገድ ለመኖር አትችልም። ግድቡን ያፈነዱታል (ግብጻውያን)። ይሄንን ተናግሬአለሁ፣ ድምጼን ከፍ አድርጌም በግልጽ እናገራለሁ፣ ያንን ግድብ ያፈነዱታል። የሆነ ነገር ማድረግ ይኖርባቸዋል።"

በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ሪፐብሊካን ይምጣ ዲሞክራት ቅድሚያ የሚሰጠው የአሜሪካውያንን እና የአይ*ሁዳውያንን ጥቅም ማስጠበቅ ነው። በምንም ታለበ በምን ያው በገሌ ብላለች ድመት። "ሰውዬው እብደታቸው ይብስባቸው ይሆን ወይስ ይሻላቸዋል?" የሚለውን በእንክሮ ከመከታተል በቀር ረገዳ የሚያስጨፍረንና እስክስታ የሚያስወርደን ነገር የለም።

Farankaa - ፈረንካ

06 Nov, 04:34


የህይወት ቀላሉ ፎርሙላ ...

ወደ ኋላህ ተመልከትና፣ አምላክህን አመስግን፤
ወደ ፊትህ ተመልከትና፣ በአምላክህ ተማመን።

መልካም ቀን!

Farankaa - ፈረንካ

05 Nov, 11:30


አይ ኤም ኤፍ ኢትዮጵያን በተመለከተ ሪፖርት አውጥቷል። የሪፖርቱን ሙሉ ነጥብ ማስፈንጠሪያውን በመንካት መመልከት ይቻላል።

https://www.imf.org/en/Publications/CR/Issues/2024/11/04/The-Federal-Democratic-Republic-of-Ethiopia-First-Review-Under-the-Extended-Credit-Facility-557019

Farankaa - ፈረንካ

05 Nov, 11:05


የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመጀመሪያውን ኤይርባስ A350 - 1000 አውሮፕላን በፈረንሳይ ቱሉዝ ተገኝቶ በመረከብ አውሮፕላኑን በመግዛት የእራሱ ያደረገ የመጀመሪያው አፍሪቃዊ አየር መንገድ ሆኗል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የአፍሪካ ኩራት!

Farankaa - ፈረንካ

04 Nov, 07:03


በምስል ላይ እንደሚታየው ግመሎቹ ከባህሩ ዳር የቆሙ እንስሳትን "ባህሩ ጥልቅ አይደለም ተቀላቀሉን ጎበዝ!" በማለት ግብዣ እያቀረቡላቸው ነው።

መካሪዎቻችንን እንምረጥ!

Farankaa - ፈረንካ

04 Nov, 05:36


የሒሳብ መግለጫዎች/Financial Statement የሆኑትን፡

- የሀብትና ዕዳ ሚዛን መግለጫ/Balance Sheet

-የገቢና ወጪ መግለጫ/Income statement

እንዲሁም

-የጥሬ ገንዘብ ፍሰት መግለጫ/Cash flow statement

ትንተናዎችን በቀላሉ ለመረዳት የተያያዘውን የፒዲኤፍ ፋይል በማውረድ ያንብቡ፣ የፋይናንስ ግንዛቤዎን ያሳድጉ።

መልካም የሥራ ሳምንት!

Farankaa - ፈረንካ

03 Nov, 07:59


እድገት ያለ ለውጥ የሚታሰብ አይደለም፤ ሐሳባቸውን መለወጥ የማይችሉ ሰዎች፣ ምንም ነገር ሊለውጡ አይችሉም።

በርናርድ ሾው

Farankaa - ፈረንካ

02 Nov, 19:02


ነገን የምትሞት ያህል ዛሬን ኑር፣ ለዘላለም የምትኖር ያህል ተማር።

ማሀተማ ጋንዲ

Farankaa - ፈረንካ

01 Nov, 15:55


ነጻ የፋይናንስ ስልጠናዎችን መውሰድ ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመዝገቡ።

https://bit.ly/3Uvyixf

Farankaa - ፈረንካ

31 Oct, 16:47


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች እርስ በእርስ የሚበዳደሩበትን የገንዘብ ገበያ/Interbank money Market ይፋ አደረገ።

Farankaa - ፈረንካ

29 Oct, 11:22


የፋይናንስ መግለጫዎችን/Financial Statements ምንነት እና እንዴት አንብቦ መረዳት እንደሚቻል የሚያሳይ ሰነድ ከሊንክድኢን ላይ አውርጄ አጋርቻችኋለሁ።


የፋይናንስ እንዲሁም ከሌሎች ሙያዎች ጋር የተገናኙ ነጻ ስልጠናዎችን እንዲሁም ሰነዶችን ለማግኘት የLinkedin አካውንት ከፍታችሁ ከባለሙያዎች ጋር ተዋወቁ።

Farankaa - ፈረንካ

27 Oct, 09:17


የቱንም ያህል ጎበዝ ብትሆን፣ የተሳሳተ ቦታ ላይ (ያለቦታህ) ከተገኘህ ዋጋ የለህም!

Farankaa - ፈረንካ

26 Oct, 11:16


77 ጠቃሚ የፋይናንስ ጥያቄዎችና መልሶች..

Farankaa - ፈረንካ

24 Oct, 07:18


አልለወጥ ያለው የኢትዮጵያ የሒሳብ እና ኦዲት የሥራ ባህል ነገር...

****

ከወርኃ መስከረም አንስቶ እስከ ጥቅምት 30 እና ከእዛ ቀጥሎ ባሉ ጥቂት ሳምንታት የኢትዮጵያ የሒሳብ ባለሙያዎችና ኦዲተሮች የምጥ ሰሞን ነው። የሥራው ጫና እንቅልፍ ይነሳል።

የንግዱ ማህበረሰብ ባለቀ ሰዐት ነው ፋይሉን ተከሽሞ ወደ ሒሳብ ባለሙያ አሊያም ወደ ኦዲተር የሚተምመው። ጉዳዩ ወደ ባህልነት የተቀየረ ሁሉ ይመስላል። ሁሌም "ነጋዴው ግብርን ዘግይቶ የሚከፍለው ገንዘቡን እስከመጨረሻው ቀን ሊጠቀምበት ስለሚፈልግ ነው" የሚል አመክንዮ ይቀርባል። ይሁንና አመክንዮው ውኃ አያነሳም። ለእዚህ ምክንያቱ ደግሞ ነጋዴው ሂሳቡን አሰርቶ፣ ኦዲት አስደርጎ ታክስ ዲክሌር አድርጎ ሁሉ እስከ ጥቅምት 30 ደረስ ክፍያውን ያለቅጣት መፈጸም ይችላል። ሒሳቡ ሳይሰራ፣ ኦዲት ሳይደረግ መዘግየቱን ምን አመጣው?

ይህ በየአመቱ ለኦዲተሮች እና ለአካውንታንቶች መጉበጥ ምክንያት የሆነው ባለቀ ሰዐት በሚደረግ ሩጫ የሚሰራውን የሒሳብ ሥራም ሆነ የኦዲት ሥራ ጥራት ያጓድላል፣ የሒሳብ ባለሙያውንም ላልተገባ ጫና ይዳርጋልና የሚመለከተው አካል ተገቢውን የግንዛቤ ማስጨበጫ የግብር ወራት ከመድረሳቸው አስቀድሞ ሊሰጥ ይገባል በማለት ጽሁፌን እደመድማለሁ።

Farankaa - ፈረንካ

22 Oct, 11:06


https://youtu.be/xNNMraqMuxk?si=dqYNsWyyPbUXcV37

Farankaa - ፈረንካ

18 Oct, 16:38


የድንገቴ የኢንቨስትመንት አማካሪዎች ነገር..

***

የኢትዮ ቴሌኮም አክሲዮን ለህዝብ ሽያጭ ይፋ ከሆነ ወዲህ ብዙዎች የኢንቨስትመንት አማካሪ ሆነው ብቅ ብለዋል። የእራስን ሐሳብ መግለጽ ችግር የለውም። ይሁንና ምክንያታዊ ባልሆነ መረጃ ላይ ተመስርቶ "በመሰለኝ እና በደሳለኝ ለሌሎች ምክር መስጠት ዘርፉን ጠንቅቆ ባለማወቅ የሚደረግ ድፍረት ነውና ሊቆም ይገባዋል።

አንዳንዶች የአምናውን የተጣራ ትርፍ ላይ ተመርኩዘው Earning per Share ወይም Dividend per share በማስላት ከወለድ ያልበለጠ ነው ብለው ሲያብራሩ ገጥሞኛል። ተቋሙ ለህዝብ ይፋ ያደረገውን comparative financial statement ስቃኝ፣ አምና ላይ ኢትዮ ቴሌኮም ገቢው በከፍተኛ ደረጃ ቢጨምርም (ከ71 ቢሊዮን ወደ 90 ቢሊዮን) የሰጣቸው ብድሮች/Financial assets በወቅቱ ባለማስከፈሉ ምክንያት IFRSን ተከትሎ በተዘጋጀው የሂሳብ መግለጫ ላይ በያዘው ወደ ስምንት ቢሊዮን የሚጠጋ impairment provision ምክንያት ትርፉ ከካቻናው ትርፍ ጋር ተቀራራቢ ሆኗል። ይሁን እንጂ ተቋሙ የብድር አሰባሰቡን ካሻሻለ፣ የብድር ጥራቱን ካሻሻለ ይሄ ወጪ ከprovision ወደ ገቢነት መቀየሩ አይቀሬ ነው።

ኢንቨስተሮች አክሲዮን የሚገዙት Dividend ለመሰብሰብ ብቻ አይደለም። Capital appreciation ሌላኛው ባለአክሲዮኖች የሚያገኙት ትርፍ ነው። በአመቱ ዋጋዬን እመልሳለሁ የሚል የዋህ ኢንቨስተር ሊኖር አይችልም። የኢትዮ ቴሌኮም አፈጻጸም ሲጨምር በአክሲዮን ገበያው ላይ ዛሬ ላይ የገዙትን አክሲዮን በተሻለ ዋጋ በመሸጥ ትርፍ ለማግኘት አክሲዮን የሚገዙ ብዙዎች ናቸው።

አገሬው "ሥራ ለሰሪው እሾህ ላጣሪው" የሚለው ያለምክንያት አይደለም። በሙያው ላይ authority ያላቸው ሰዎች በጉዳዩ ላይ አስተያየት ይስጡ፣ ሌላው ያዳምጥ። በሁሉም ጉዳይ ላይ ሁሉ ተንታኝ፣ ሁሉ አውሪ፣ ሁሉ ጸሀፊ ሊሆን አይችልም።

Farankaa - ፈረንካ

17 Oct, 12:32


Ethiotelecom የአክሲዮን ሽያጩን በይፋ ጀምሯል። ምዝገባውን ከመጀመራችሁ በፊት፣

1. የታደሰ መታወቂያ/ፓስፖርት
2. ጉርድ ፎቶ ግራፍ

አዘጋጁ።

ምዝገባውን ከፈጸማችሁ በኋላ ክፍያውን አሁኑኑ አልያም በ48 ሰዐት ጊዜ ውስጥ መፈጸም ትችላላችሁ።

Farankaa - ፈረንካ

17 Oct, 05:11


ባንክ ያልሆኑ የውጪ ምንዛሪ ቢሮዎች የኮምፕሊያንስ ነገር...

*
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አምስት ለሚደርሱ ባንክ ያልሆኑ የውጪ ምንዛሪ ቢሮዎች ፈቃድ መስጠቱን ከሰማን ብዙም አልቆየንም።

እኒህ የውጪ ምንዛሪ ቢሮዎች ገዢው ባንክ የሚያወጣውን መመሪያ እንዲሁም መመሪያውን መጣስ የሚያስከትለውን ቅጣት በተመለከተ ያላቸው ግንዛቤ እምብዛም ይመስላል። እኒህ ተቋማት ብሔራዊ ባንኩ የውጪ ምንዛሪ አስተዳደርን ለሚያወጣቸው ፖሊሲዎች ከባንኮች እኩል ተጠያቂ ናቸው።

በብሔራዊ ባንኩ ስር መተዳደር እና በጥቁር ገበያ ስር መስራት እጅግ የተለያዩ ነገሮች ናቸው። በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ማሊያ የጥቁር ገበያን አደራለሁ ብሎ ፈቃድ ያወጣም አይጠፋም። ናይጄሪያ ለብዙ ሺህ ባንክ ያልሆኑ የውጪ ምንዛሪ ቢሮዎች ፈቃድ ሰጥታ በኋላ ላይ ህገ-ወጥ ግብይት ላይ በመሳተፋቸው ፈቃዳቸውን ሰርዛለች። ብልጥ ከሌላው ይማራል።

National Bank of Ethiopia ፈቃዱን ባንክ ላልሆኑ የውጪ ምንዛሪ ተቋማት መስጠቱ ይበል የሚያስብል ቢሆንም ለእነዚህ ተቋማት በቂ የአቅም ግንባታ ከመስጠት አንስቶ ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ ይኖርበታል። ይህ ካልሆነ የአልማዝን ጠባሳ እያዩ በእሳት እንደመጫወት ይቆጠራል።

ከእዚህ ጽሁፍ ጋር የተያያዘው የውጪ ምንዛሪ መግዣ እና መሸጫ ዋጋ በትላንትናው እለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ከጎበኟቸው ባንክ ያልሆኑ የውጪ ምንዛሪ ቢሮዎች መካከል በአንዱ ውስጥ የተሰቀለ የዶላር መግዣና መሸጫ ዋጋ ገዢው ባንክ በቅርቡ ያወጣውን የ2% spread ህግ የጣሰ ሆኖ ተገኝቷል። ነገሩ ሳይቃጠል በቅጠል ነውና ገዢው ባንክ ተቋማቱ ልክ እንደባንኮቹ ሁሉ ለሚወጡ ህጎች ተገዢ እንዲሆኑ ማድረግ ይጠበቅበታል።

Farankaa - ፈረንካ

15 Oct, 13:53


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲስ ፖሊሲ እንምታ ምንድነው?

አዲሱ ፖሊሲ ባንኮች spreadን (በዶላር መግዣና መሸጫ መካከል ያለ ልዩነት) በተመለከተ የሚያስቀምጡት ልዩነት ከ2% እንዳይበልጥ ተገድቧል።

ለምሳሌ የዛሬውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመግዣ እና የመሸጫ ዋጋ ብናይ፣

መግዣ = 113.1308

መሸጫ = 113.1308 + (2%*113.1308)
= 115.3934

ይሆናል ማለት ነው።

ይሁን እንጂ መመሪያው ባንኮቹ ለሚሰጧቸው የተለያዩ ከውጪ ምንዛሬ ጋር የተያያዙ አገልግሎቶች (የመተማመኛ ሰነድ/LC, ዶክመንት ሲቀርብ ካሽ ይከፈል/CAD እና ቅድመ-ክፍያ/TT የመሳሰሉት) ላይ ተጨማሪ ክፍያዎችን፣ ማለትም እንደ...

📌LC opening commission

📌PO approval commission

📌 Service Charge

📌Confirmation Charge

📌SWIFT Charge

እና የመሳሰሉ ክፍያዎችን የማስከፈል መብት ተሰጥቷቸዋል።

ከእዚህ ቀደም በነበረው የኢብባ ፖሊሲ መሰረት ባንኮች የአገልግሎት ክፍያዎችን በሙሉ Spread ውስጥ እንዲያካትቱ ይጠይቅ የነበረ ሲሆን አዲሱ ፖሊሲ የተለያዩ የአገልግሎት ክፍያዎች ከSpread ተለይተው ለብቻ ከአስመጪዎች እንዲሰበሰቡ አዝዟል።

ብዙዎች ባንኮች የሚሸጡት ዶላር ላይ ቅናሽ እንደተደረገ አድርገው እየዘገቡ ያሉት ነገር ትክክል አይደለም።

ይሁንና አዲሱ ፖሊሲ አስመጪዎች ቀደም ሲል በተጋነነ የመሸጫ ዋጋ መሠረት ሲከፍሉ የነበረውን import duty ስለሚቀንስ የገበያ ዋጋው ተረጋግቶ ከቀጠለ የገቢ ንግድ እቃዎች ላይ የተወሰነ ቅናሽ ያመጣል።

Farankaa - ፈረንካ

15 Oct, 04:33


https://youtu.be/A06NXBP49r0?si=n2kH1ROXBvC3-a9p

Farankaa - ፈረንካ

12 Oct, 10:32


የእለቱ አባባል፣ በታዋቂው ቦክሰኛ መሐመድ አሊ!

Farankaa - ፈረንካ

12 Oct, 09:15


አዲስ ረቂቅ መመሪያ‼️

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን የDematerialization directive ረቂቅ ለህዝብ ውይይት ክፍት አድርጓል።

በአማርኛው ሰነደ መዋዕለ ነዋዮችን/አክሲዮኖችን/ ግዑዝ አልባ ማድረግ ተብሎ የተተረጎመው dematerialization በቀላሉ ከእዚህ ቀደም በወረቀት ሰርተፊኬት የሚሰጡ የአክሲዮን ባለቤትነት ማረጋገጫዎችን በአንድ ማዕከል/Central Depository/ በሚቀመጥ በSoftcopy certificate መተካትን የሚመለከት ነው።

Dematerialization አክሲዮኖችን በቀላሉ ከአንድ ባለአክሲዮን ወደሌላው በሽያጭ ለማስተላለፍ የሚረዳ ነው። ሂደቱ በዋናነት አክሲዮናቸውን በኢትዮጵያ የአክሲዮን ገበያ ላይ የማስመዝገብ ግዴታ የተጣለባቸው ተቋማትን (ባንኮች፣ የኢንሹራስ ኩባንያዎች እንዲሁም ሌሎች የህዝብ ጥቅም ያለባቸው ተቋማት) እና አክሲዮን ለህዝብ በመሸጥ የሚደራጁ ተቋማትን የሚመለከት ነው።

Farankaa - ፈረንካ

11 Oct, 14:16


ኢትዮ ቴሌኮም በሚቀጥለው ሳምንት 10% የባለቤትነት ድርሻ አዲስ በተቋቋመው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ/Ethiopia Securities Exchange-ESX/ አማካይነት አክሲዮን ለህዝብ በመሸጥ የመጀመሪያው ተቋም ለመሆን ዝግጅት መጨረሱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ብሩክ ታዬ ገልጸዋል።

ተጨማሪ ለማንበብ👇

https://www.reuters.com/business/media-telecom/ethio-telecom-kick-off-ethopian-stock-trading-with-10-flotation-next-week-2024-10-09/

Farankaa - ፈረንካ

11 Oct, 05:27


አዲሱ የሪል ስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታ ረቂቅ አዋጅ በዘርፉ ላይ ሲስተዋሉ የነበሩ ብዙ ችግሮችን ይፈታል ተብሎ ይገመታል።

ከእንግዲህ አማላይ ፎቶ መሸጥ አይቻልም፣ ቢሸጥ እንኳ ገንዘቡ በዝግ ሒሳብ ይቀመጣል፣ የተገነባው ሪልስቴት ስሙ ለባለቤቱ እስኪዘዋወር ድረስ በእግድ ውስጥ ይቆያል፣ እንደድሮው ከቤት ገዢ ገንዘብ ሰብስቦ ለባንክ ማስያዝ አይኖርም። ዘርፉ ስርዓት ሊይዝ ይገባል፣ እንደውም ዘግይቷል። ብዙዎች ጥሪታቸውን ተነጥቀዋል፣ አልቅሰዋል፣ ይበቃል መባሉ ትክክል ነው።

Farankaa - ፈረንካ

10 Oct, 11:45


አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የቀድሞ ተማሪዎቹ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ተሰባስበው ትዝታቸውን ያወጉ ዘንድ፣ ቤታቸውንና መነሻቸውን ይጎበኙ ዘንድ፣ ስኬታቸውን ያወጉ ዘንድ ጋብዟል።

እኔም እንደቀድሞ ተመራቂነቴ በኢሜል አድራሻዬ የጥሪ ካርድ ደርሶኛል። ከሁለቱ ቀን በአንዱ ተገኝቼ ትዝታዬን ከወዳጆቼ ጋር አወጋለሁ፣ ከሰዎች ጋር እተዋወቃለሁ።

መገኘት የምትችሉ የቀድሞ ተመራቂዎች ሁሉ ቤታችሁን፣ መነሻችሁን ትጎበኙ ዘንድ ተጋብዛችኋል።

Farankaa - ፈረንካ

09 Oct, 11:20


በፋይናንስ ገበያ ውስጥ Haircut ምንድነው?

የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ከአበዳሪዎቹ ጋር አዲስ የብድር ማራዘሚያ ድርድር የጀመረ ሲሆን በዩሮቦንድ የተበደረው 1 ቢሊዮን ዶላር ብድር ላይ 20% Haircut እንዲደረግለት ጠይቋል።

በፋይናንስ ገበያ ውስጥ ተበዳሪ ከአበዳሪው ጋር በሚያደርገው አዲስ የብድር ማራዘሚያና አከፋፈል ስምምነት መሠረት ከዋናው ገንዘብ ላይ ተበዳሪው የተወሰነ ቅናሽ እንዲደረግለት ሲጠይቅ Haircut ተብሎ የሚገለጽ ሲሆን ቅናሹ የሚገለጸው በፐርሰንት ነው።

ለምሳሌ፣

የኢትዮጵያ መንግስት 20% haircut እንዲደረግለት ጠየቀ ማለት ከዋናው የዩሮቦንድ ብድር ላይ 20% እንዲቀነስለት ጠይቋል ማለት ነው።

በእዚህ መሠረት አበዳሪዎቹ ከተስማሙ አዲሱ የዩሮቦንድ የብድር መጠን፣

= $1,000,000,000 - (20%*$1,000,000,000)
=$800,000,000/ስምንት መቶ ሚሊዮን ዶላር ይሆናል ማለት ነው።

Farankaa - ፈረንካ

08 Oct, 06:36


https://youtu.be/9zeSXD04Hk4?si=sQdC3uTT32uSuShU

Farankaa - ፈረንካ

07 Oct, 05:35


የመሬት ንዝረቱ ትዝብት፣

በትላንትናው የመሬት መንቀጥቀጥ በስድስተኛ ፎቅ ላይ ሆኜ ንዝረቱ እንደተሰማኝ ለክፉ ለደጉ በሚል ቆጣሪ አጥፍቼ፣ በር ቆላልፌ በደረጃ እግሬ አውጪኝ ብዬ ምድር ላይ ስወርድ ከእኔ እና አብሮኝ ከነበረ ጓደኛዬ በቀር አንድም የወረደ ሰው አልነበረም።

ይሄ ነገር ቅዥት ይሆን እንዴ ብዬ በመጠራጠር እዛው በምኖርበት ሰፈር ወዳለ ጓደኛዬ ስልክ መታሁ። "እኔ እኮ አዙሪት የያዘኝ መስሎኝ ነገ ሐኪም ቤት ስለ መሄድ እያሰብኩ ነበር?" አለኝ። በፍጥነት ከፎቅ እንዲወርድ መክሬው ተለያየን።

ታች ያሉ የህንጻው ጠባቂዎች ዘንድ በመሄድ ንዝረቱ ተሰምቷቸው እንደሁ ብጠይቅ ምንም እንዳልተሰማቸው ነገሩኝ። ምናልባትም 3ኛ ፎቅ ላይ የሆነ ዝግጅት ስለነበር የዝግጅቱ ሙዚቃ ሰዉን አዘናግቶት ሊሆን እንደሚችል ነገሩኝ። ወዲያው ወደ ማህበራዊ ድረ ገጽ አማተርኩ። ነገሩ እውነት መሆኑን አወቅኩ።

ስለጉዳዩ እርግጠኛ ከሆንኩ በኋላ ለጥበቃዎቹ ነዋሪውን እንዲያነቁ ነገርኳቸው። አንደኛው ሲከንፍ በየበሩ እያንኳኳ ያለውን ችግር ተናገረ። የሚደንቀው ነገር በጣት ከሚቆጠሩ ሰዎች ውጪ ሌላ ሰው የጥበቃውን መረጃ ከቁብ ቆጥሮ ከፎቁ የወረደ አልነበረም።

ይሄኔ ነበር እግዚአብሔር አይበለውና የከፋ ነገር ቢመጣ አንድም የተዘረጋ የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ስለሌለን አንድ ላይ ማለቃችን አይቀሬ የመሆኑ ነገር ውል ያለኝ።

አምላክ ሀገራችንን ይጠብቅ!

Farankaa - ፈረንካ

06 Oct, 17:52


ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት አዲስ አበባ ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር። በምኖርበት ኮንዶሚኒየም ላይ የተወሰንን ሰዎች ንዝረቱ ተሰምቶን ወደ ታች ወርደናል። ይሄንኑ ለማረጋገጥ Earthquake track የተሰኘ ገጽ ላይ ሳማትር እውነትነቱን አረጋግጦልኛል።

https://www.google.com/url?sa=t&source=web&rct=j&opi=89978449&url=https://earthquaketrack.com/et-44-addis-ababa/recent&ved=2ahUKEwi-7KqCqPqIAxWyBdsEHfsSKacQFnoECBIQAQ&usg=AOvVaw0n73D67_LsiJn1s8c3stEz

Farankaa - ፈረንካ

05 Oct, 08:54


Baga ayyaana irreechaaf geessan!

እንኳን ለኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ!

Farankaa - ፈረንካ

03 Oct, 15:43


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱ የውጪ ምንዛሪ ህግ ከመተግበሩ አስቀድሞ ከነዳጅ ጋር የተያያዘ የተጠራቀመ ክፍያ ላለባቸው ባንኮች 175 ሚሊዮን ዶላር ሊሸጥ መሆኑን አሳወቀ።

Farankaa - ፈረንካ

03 Oct, 10:04


ግልጽነት የጎደለው የባንኮች የተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ማስታወቂያ፣
*
ሰሞኑን ከሚደርሱኝ የስልክ ጥሪዎች መካከል "ባንክ ገንዘብ ዲፖዚት ሳደርግ ቫት ይቆረጥብኛል? በተመሳሳይ ባንክ ውስጥ ገንዘብ ባዘዋውር ቫት እከፍላለሁ? ብድር ስወስድ ቫት እከፍላለሁ?" እና የመሳሰሉት ይገኙበታል።

አብዛኞቹ ባንኮች በአጭር መልእክት የሚልኩት የተጨማሪ እሴት ታክስ እናስከፍላለን መልእክት ግልጽነት የጎደለውና ደንበኞች ላይ ውዥንብር የፈጠረ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

የአዋጅ ቁጥርን ጠቅሶ VAT ልናስከፍል ነው ተብሎ የሚላከውን መልእክት ስንቱ ደንበኛ ይረዳል? ቢያንስ በአዋጁ ላይ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የተደረጉትን የተቀማጭ ገንዘብና የብድር አገልግሎቶችን እንደማይመለከት መግለጽ እጅግ ከባድ ነገር ሆኖ ይሆን?

Farankaa - ፈረንካ

03 Oct, 05:42


የማይክሮፋይናንስ ተቋማት የውጭ ኦዲተር አሿሿም መመሪያ

Farankaa - ፈረንካ

03 Oct, 05:42


ብሔራዊ ባንክ ለአምስት የግል የውጪ ምንዛሪ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፈቃድ ሰጠ።