[ 🕊 ፍኖተ ቅዱሳን 🕊 ]
[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]
▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬
[ መታዘዝ ! ]
🕊
❝ ከአበው አንዱ አራት ሠራዊት በእግዚአብሔር ዘንድ አየሁ አለ።
የመጀመሪያው በደዌው ሆኖ እግዚአብሔርን የሚያመሰግን በሽተኛ [ ድውይ ዘበአኰቴት ] ነው:: ሁለተኛው ሰዎችን [ እንግዶችን ] ደስ እያለው በፍቅር የሚቀበልና የሚያሳርፋቸው ነው። ሦስተኛው በገዳም የሚኖር ከሰው ጋር የማይነጋገር [ ዝጉሐዊ ] ነው። አራተኛው ደግሞ ስለ እግዚአብሔር ብሎ ለመምህሩ የሚታዘዝና የሚላላክ ረድእ ነው።
በዚህ ረድእ በአንገቱ ላይ የወርቅ ባዝግና ተሸልሞ መንበሩም ከሁሉም በላይ ሆኖ አየሁት። ይህን ለሚያሳየኝ ይህ ታናሽ እንዴት ከሁሉ በለጠ ? ብዬ ጠየቅሁት።
እርሱም ፦ " እነዚህ መልካም የሠሩ በራሳቸው ፈቃድ ነው ፤ ይህ ግን የራሱን ፈቃድ ለእግዚአብሔርና ለመምህሩ የተወ ነው ፣ ስለዚህም ከፍ ያለ ክብርና መንበር ተሰጠው" አለኝ። ❞
🕊
የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡
† † †
💖 🕊 💖