Isaiah 48 Apologetics @thetriune Channel on Telegram

Isaiah 48 Apologetics

@thetriune


✟ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✟

"14 The grace of the Lord Jesus Christ, and the love of God, and the communion of the Holy Ghost, be with you all. Amen."
(2Corinthians 13:14)

📌 ሌላኛው ቻናላችን:- @ovadiah

Isaiah 48 Apologetics (Amharic)

ይህ ውስጥ በአማርኛ በመጻፍም እርስዎን አጋንንት እና ፍላጎት በራስን ለአገልግሎት ላይ ለውስጥ መረብ ሰጥቷል። ይህ ቡድን አምላክንና እንቅስቃሴዎችን እባክዎ ወደ አምላክ እና ወደ እናቴ ይዛችሁ። እንኳን ሊሞት እንጂ ሊወልድ አልሆነም። ይህ ቡድን ላይ የተመሠረተችው Isaiah 48 Apologetics በእኛና በከተማይቱ ምርጥ እና መናገርታው የሚታይ መሆኑ ነው።

Isaiah 48 Apologetics

13 Feb, 06:17


🚩 መንፈስ ቅዱስ

መንፈስ ቅዱስ:- ከአብ ጋር አንድ መለኮት የሆነው አምላካችን! https://t.me/TheTriune/908

መንፈስ ቅዱስ አምላክ አይደለምን? ለወሒድ ዑመር የተሰጠ መልስ (ክፍል 1) https://t.me/TheTriune/1080

መንፈስ ቅዱስ አምላክ አይደለምን? ለወሒድ ዑመር የተሰጠ መልስ (ክፍል 2) https://t.me/TheTriune/1084

መንፈስ ቅዱስ በነጠላዊያን ዘንድ ማነው? https://t.me/TheTriune/1062

መንፈስ ቅዱስ አካል እንደ ሆነ ብሉይ ኪዳን አያስተምርምን? https://t.me/TheTriune/586

♦️ መንፈስ ቅዱስ በFather Kappes https://answeringislamblog.wordpress.com/2021/10/03/holy-spirit-worshiped-as-god/

Isaiah 48 Apologetics

10 Feb, 04:46


🚩 የመሐመድ ኩረጃዎች

ዒዳ፦ https://t.me/TheTriune/1027

ዓሌይሂ ሰላም፦ https://t.me/TheTriune/1033

ረብል አለሚን፦ https://t.me/TheTriune/1038

አል-ራሕማን፦ https://t.me/TheTriune/1070

Isaiah 48 Apologetics

05 Feb, 18:46


https://vm.tiktok.com/ZMkgdYnw9/

Isaiah 48 Apologetics

05 Feb, 05:02


🚩 የሐዋርያት ስራና የእግዚአብሔር መልአክ

https://t.me/TheTriune/940 (ክፍል 1)

https://t.me/TheTriune/942 (ክፍል 2)

https://t.me/TheTriune/945 (ክፍል 3)

Isaiah 48 Apologetics

03 Feb, 04:58


🚩 የዕብራውያን ጸሐፊ

https://t.me/TheTriune/1184 (ክፍል 1)

https://t.me/TheTriune/1186 (ክፍል 2)

https://t.me/TheTriune/1192 (ክፍል 3)

https://t.me/TheTriune/1215 (ክፍል 4)

Isaiah 48 Apologetics

31 Jan, 12:58


🚩 የመሲሁ ዳግም ምጽአት በብሉይ ኪዳን

https://t.me/TheTriune/1001 (ክፍል 1)

https://t.me/TheTriune/1003 (ክፍል 2)

https://t.me/TheTriune/1008 (ክፍል 3)

https://t.me/TheTriune/1010 (ክፍል 4)

https://t.me/TheTriune/1012 (ክፍል 5)

https://t.me/TheTriune/1020 (ክፍል 6)

https://t.me/TheTriune/1023 (ክፍል 7)

Isaiah 48 Apologetics

31 Jan, 08:26


በግራኝ አሕመድ ወረራ ዘመን ለኢትዮጵያ ክርስትና መትረፍ ሰበብ የሆኑ በቀድሞ ሕይወታቸው ሙስሊም የነበሩና ክርስትናን የተቀበሉ ሁለት ሰዎች ነበሩ። አንደኛዋ የሐዲያዋ ተወላጅ ጥበበኛዋና ውቧ ንግሥት እሌኒ (በሌላ ስሟ የዘይላ ንግሥት) ስትሆን ሁለተኛው ደግሞ የመናዊው ባለ ብሩህ አእምሮ በቀድሞ ስሙ አቡ አል-ፈት በክርስትና ስሙ አባ ዕንባቆም ነበሩ። ንግሥት እሌኒ በፖለቲካና በወታደራዊው መስክ፣ አባ ዕንባቆም ደግሞ በመንፈሳዊ መስክ የሠሩት ሥራ የኢትዮጵያን ክርስትና ከጥፋት ታድጓል። በተለይም አባ ዕንባቆም የግራኝን ሠራዊት ያሸነፈውን ንጉሥ ገላውዴዎስን ከልጅነቱ ጀምሮ በማስተማር፣ ከዚያም በጦርነቱ ዘመን የእስልምናን ሐሰተኝነት የሚገልጡ ጽሑፎችን (ለግራኝ ለራሱ ደብዳቤዎችን መጻፍን ጨምሮ)፣ በኋላም በጦርነቱ የወደሙ ቅዱሳት መጻሕፍትን በመተካት እንዲሁም ከክርስትና የወጣውን ሕዝብ ወደ እምነቱ በመመለስ ረገድ ያበረከተው አስተዋፅዖ የሚረሳ አይደለም። የእነዚህ ሁለት ሰዎች በወቅቱና በቦታው መገኘት የእግዚአብሔር ተዓምራዊ ሥራ እንጂ ሌላ ሊባል አይችልም። የአባ ዕንባቆምን የሕይወት ታሪክና ጽሑፎች በተመለከተ አንድ ብዙ ዓመታትን የፈጀ ምሑራዊ ጽሑፍ በቅርቡ በሀገራችን ለሕትመት እንደሚበቃ መረጃው አለኝ።

Isaiah 48 Apologetics

26 Jan, 14:30


🚩 የዳንኤል 9 ማብራሪያ

https://t.me/TheTriune/980 (ክፍል 1)

https://t.me/TheTriune/982 (ክፍል 2)

https://t.me/TheTriune/985 (ክፍል 3)

Isaiah 48 Apologetics

18 Jan, 10:45


ኢትዮጵያዊው የታሪክ ምሑር ስርግው ሀብለ ሥላሴ በጻፉት ታሪክ መሠረት በኡሑድ ጦርነት ላይ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከመካ ተዋጊዎች ጎን ተሰልፈው ሙሐመድና ወታደሮቹን ተዋግተዋል። በዚህ ውጊያ ሙስሊሞች ክፉኛ የተሸነፉ ሲሆን ሙሐመድ ራሱ ቆስሎ ሁለት የፊት ጥርሶቹ ረግፈዋል (Sergew Hable Selassie, Ancient and Medieval Ethiopian History to 1270, p. 188.)። የእስልምና ውድቀትና የካዕባ መፍረስ በኢትዮጵያውያን እጅ እንደሚከናወን ሙሐመድ በትንቢት መልኩ ተናግሯል። ይህ በአረብ ሙስሊሞች ዘንድ ኢትዮጵያውያንን የመፍራትና በጥርጣሬ የመመልከት ስሜት መነሻው ከእስልምና ልደት እንደሚጀምር መረዳት ይቻላል። ከዚህ ጋር አያይዘን በየመን የኢትዮጵያ ጀነራል የነበረው አብርሃ ካዕባን ለማፍረስ ያደረገውን ዘመቻ ማንሳት እንችላለን። "መጥፊያችን በኢትዮጵያውያን እጅ ነው" የሚለው የአረብ ሙስሊሞች ስነ ልቦናዊ ስጋት ተጨባጭ ታሪካዊ መነሻ አለው። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያን እነርሱ እንደሚፈሩት በሰይፍ ሳይሆን በወንጌል እስልምናን ከምድረ ገጽ እናጠፋዋለን። መጥፊያው በኛ እጅ መሆኑን ራሱ አስቀድሞ አውቆታል።

Isaiah 48 Apologetics

09 Jan, 07:18


🚩 በዮሐንስ 1:1 የግሪክ አተረጓጎም ላይ ለዋሸው ኡስታዝ የተሰጠ መልስ (ክፍል 2)

https://vm.tiktok.com/ZMkfoTaCg/

Isaiah 48 Apologetics

08 Jan, 14:41


https://vm.tiktok.com/ZMkf9G81f/

Isaiah 48 Apologetics

07 Jan, 06:36


🚩 እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ! 2017 ዓ.ም

"ልጅም #ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን #ኢየሱስ ትለዋለህ"
(የማቴዎስ ወንጌል 1:21)

"ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት #የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን #ልጁን ላከ"
(ወደ ገላትያ ሰዎች 4:4)

Isaiah 48 Apologetics

04 Jan, 17:11


የዐዲስ ኪዳን ቀኖና ተኣማኒነት በሚል ርዕስ በወንድማችን ሚናስ የተጻፈ ጽሑፍ በዌብሳይታችን ላይ ተለቋል። ያንብቡት ለሌሎችም ያጋሩ https://ewnetlehulu.net/nt-canon-p-1/

Isaiah 48 Apologetics

03 Jan, 12:47


🚩 የአብርሃም እምነት

አባታችን አብርሃም በዘመናት ከተነሱት ታላላቅ የእግዚአብሔር ሰዎች መካከል አንዱ ነው። ይህ አባት በእግዚአብሔር ላይ ካለው ታላቅ እምነት የተነሳ፥ አባቶቹ ያላወቁት አምላክ መዳረሻውን ሳይነግረው "ከዘመዶችህ ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ" ሲለው፥ በእምነት ብቻ ተነስቶ ወጥቷል። በዚህም ምክንያት፥ ለአማኞች ሁሉ የእምነት አባት ተባለ (ገላ 3:7)

በአብርሃም ሕይወት ውስጥ፥ እምነቱ በእጅጉን የተፈተነበት ክስተት ቢኖር፥ እግዚአብሔር ልጁን ይስሐቅን እንዲሰዋለት የጠየቀው ሰዓት ነው። ይህ ክስተት በአይሁድ ዘንድ "አኬዳህ/" ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን፥ አብርሃም በእርግጥም እግዚአብሔርን እንደሚፈራ የተረጋገጠበት ክስተት ነው።

ይህ ታሪክ በብዙ መንፈሳዊ እውነቶች የተሞላ ሲሆን፥ ዛሬ ከብዙ በጥቂቱ ለመነጋገር እንሞክራለን

" አብርሃምም ሎሌዎቹን አላቸው። አህያውን ይዛችሁ ከዚህ ቆዩ፤ #እኔና #ልጄ ወደዚያ ሄደን እንሰግዳለን፥ ወደ እናንተም #እንመለሳለን።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 22:5)

በዚህ ስፍራ አብርሃም ልጁን ይስሐቅን ይዞ ሞሪያ ተራራ ጋር ከደረሰ በኋላ የተከሰተውን ታሪክ እናነባለን። በዚያም አብረዋቸው የመጡትን ሎሌዎች እንዲቆይዋቸው፥ እርሱና ልጁም ወደዚያ ሄደው ሰግደው እንደሚመለሱ ይነግራቸዋል

➣ አብርሃም ለምን "እንመለሳለን" አለ? ወደ ተራራው የሄደው ልጁን ሊሰዋው አልነበር? ታዲያ ለምን ልጁንም አካትቶ እንመለሳለን አለ?

እግዚአብሔር ጣልቃ ገብቶ ይስሐቅን እንዳይሰዋው እንደሚከለክለው ስላወቀ ነው ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ይህን የተናገረው የእግዚአብሔር መልአክ ጣልቃ ገብቶ እንደሚያስቆመው ከማወቁ በፊት ነውና። አብርሃም "እንመለሳለን" ሲል ይህ እንደሚፈጠር አላወቀም።

ሲቀጥል፥ እግዚአብሔር ጣልቃ እንደሚገባ ከመጀመሪያውኑ ቢያውቅ ኖሮ ፈተናው ፈተና ባልሆነ ነበር። ምክንያቱም ልጁን እንደማይሰዋው እያወቀ ነበር የሄደው ማለት ነው። ስለዚህ የምርም ልጁን ሊሰዋው አልነበረም ማለት ነው። ይህ ደግሞ ስህተት ነው። አብርሃም የምርም ይስሐቅን ሊሰዋው ነበር። ለዚያም ነው እግዚአብሔር "አንድ ልጅህን አልከለከልህምና" በማለት የመሰከረለት።

"እርሱም። እነሆኝ አለ። እርሱም። በብላቴናው ላይ እጅህን አትዘርጋ፥ አንዳችም አታድርግበት፤ #አንድ_ልጅህን #ለእኔ #አልከለከልህምና እግዚአብሔርን የምትፈራ እንደ ሆንህ አሁን አውቄአለሁ አለ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 22:12)

"እንዲህም አለው። እግዚአብሔር። በራሴ ማልሁ ይላል፤ ይህን ነገር አድርገሃልና፥ #አንድ_ልጅህንም #አልከለከልህምና"
(ኦሪት ዘፍጥረት 22:16)

✍️ ታዲያ ለምን "እንመለሳለን" አለ?

አብርሃም እንመለሳለን ያለበት ምክንያት፥ እግዚአብሔር ይስሐቅ ከመወለዱ በፊት በሰጠው ቃል ኪዳን መሰረት ነው። እግዚአብሔር ለአብርሃም፥ ይስሐቅ የሚባል ልጅ እንደሚሰጠውና፥ ቃል ኪዳኑንም ከእርሱና ከዘሩ ጋር እንደሚያደርግ ቃል ገብቶለት ነበር

"እግዚአብሔርም አለ። በእውነት ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅን ትወልድልሃለች፥ ስሙንም #ይስሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ #ከእርሱ በኋላ #ለዘሩ የዘላለም #ቃል_ኪዳን እንዲሆን #ቃል_ኪዳኔን #ከእርሱ ጋር አቆማለሁ።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 17:19)

"ቃል #ኪዳኔን ግን በሚመጣው ዓመት በዚሁ ጊዜ #ሣራ #ከምትወልድልህ #ከይስሐቅ ጋር አቆማለሁ። "
(ኦሪት ዘፍጥረት 17:21)

እግዚአብሔር ይህን ቃል ኪዳን የገባለት፥ ይስሐቅ ከመወለዱ ከአንድ ዓመት በፊት ነው። ይስሐቅ ይወለዳል፥ የእግዚአብሔርም ኪዳን ከእርሱና ከዘሩ ጋር ይሆናል። በዚህም ምክንያት ይስሐቅ ሞቶ ሊቀር አይችልም

♦️ አስተውሉ! የእግዚአብሔር ኪዳን ከይስሐቅ ጋር ብቻ ሳይሆን፥ ከዘሩም ጋር ነው። ስለዚህ ይስሐቅ ዘር ይኖረዋል ማለት ነው። የእግዚአብሔርን ኪዳን የሚያስቀጥሉ፥ ትውልዶች ከእርሱ በኋላ ይመጣሉ ማለት ነው

ለዚህም ነው አብርሃም በሙሉ ልብ "እንመለሳለን" ያለው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ቃል ገብቶለታልና። የእግዚአብሔርን ኪዳን የሚያስቀጥሉ ትውልዶች ከእርሱ ስለሚወጡ፥ ይስሐቅ ሞቶ ሊቀር አይችልም። አብርሃምም ያንን የተስፋ ቃል አምኗል።

➣ ለዚህም ነው የዕብራውያን ጸሐፊ፥ አብርሃም ልጁን ቢሰዋው እንኳ እግዚአብሔር ከሞት እንኳ ሊያስነሳው እንደሚችል አስቧል ያለው

"17-18፤ #አብርሃም በተፈተነበት ጊዜ #ይስሐቅን በእምነት አቀረበ፥ #የተስፋን_ቃል የተቀበለው። በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል የተባለለት እርሱም አንድ ልጁን አቀረበ፤ 19፤ እግዚአብሔር #ከሙታን_እንኳ_ሊያስነሣው_እንዲቻለው_አስቦአልና፥ ከዚያም ደግሞ በምሳሌ አገኘው።" (ወደ ዕብራውያን ምዕራፍ 11:18-19)

✍️ በቁ.18 ላይ እንዳስተዋላችሁት፥ አብርሃም በይስሐቅ ዘር ይጠራልሃል ተብሏል። ይህ ማለት የአብርሃም ዘር የሚቀጥለው፥ ስሙም የሚጠራው በይስሐቅ ነው ማለት ነው።

"እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው። ስለ ባሪያህና ስለ ብላቴናው አትዘን፤ ሣራም የምትነግርህን ቃል ሁሉ ስማ፤ #በይስሐቅ_ዘር_ይጠራልሃልና።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 21:12)

ይህ ማለት፥ ይስሐቅ ሞቶ አይቀርም ማለት ነው። የእግዚአብሔር ኪዳንን የሚያስቀጥል፥ የአባቱን የአብርሃምን ዘር የሚያስጠራ ሰው ነው ማለት ነው። ስለዚህ ይህን የሚያውቀው አብርሃም፥ ልጁን ቢሰዋው እንኳ እግዚአብሔር መልሶ ሕያው እንደሚያደርገው ቅንጣት ታህል አልተጠራጠረም።

ከሙታን እንኳ ሊያስነሳው እንዲቻለው እግዚአብሔርን ስላመነ፥ በሙሉ ልብ "እንመለሳለን" አለ። የእግዚአብሔርን ኪዳን የሚያስቀጥል፥ ዘሩን የሚያስጠራ ልጅ እንደሚሆን እግዚአብሔር ቃል ገብቶለታልና

♦️ አስተውሉ! በዘፍ 17 ሆነ በዘፍ 21 ላይ የምንመለከታቸው የተስፋ ቃላት፥ እግዚአብሔር ይስሐቅን ሰዋልኝ ከማለቱ በፊት ለአብርሃም የሰጣቸው ናቸው። ስለዚህም በሙሉ ልቡ ከልጁ ከይስሐቅ ጋር እንደሚመለስ ተናገረ። አምላኩን አምኖታልና

ከአብርሃም እምነት ምን እንማራለን?

ከአብርሃም እምነት ብዙ ነገሮችን እንማራለን። መታዘዝን፥ እጅግ ውድ ከምንለው ነገር በላይ እግዚአብሔርን መውደድ፥ ጽናትን ሁሉ እንማራለን። ከዚህም ባሻገር፥ የእምነትን ትርጉም እንማራለን

እውነተኛ እምነት እግዚአብሔር በገባው ቃል ላይ የተመሰረተ ነገር እንጂ፥ በኛ መሻት ላይ ወይንም በኛ ምኞት ላይ የተመሰረተ ነገር አይደለም። ወይንም ዘመነኞቹ እንደሚሉት "....የሆነ ነገርን ካለመኖር ወደ መኖር የምናመጣበት substance" አይደለም። እምነት ጌታ በተናገረው ነገር ላይ ተመስርተንና ተማምነን የምንወስደው እርምጃ ነው

አብርሃም፥ እግዚአብሔር ልጄን ከሞት እንኳ ያስነሳዋል ብሎ ያመነው የግል ምኞቱ ስለነበር አይደለም። ቀድሞ ከእግዚአብሔር በተቀበለው የተስፋ ቃል መሰረት ነው። ያ ቃል ኪዳን ስላለ ነው በልበ ሙሉነት እንዲህ ሊናገር የቻለው። ትክክለኛው የእምነት ትርጉም ይህ ነውና

✍️ እውነተኛን እምነት ጌታ በልባችን ያሳድር!

Isaiah 48 Apologetics

31 Dec, 20:38


https://vm.tiktok.com/ZMkAJU6X3/

Isaiah 48 Apologetics

22 Dec, 20:36


በኡስታዝ ወሂድ የተፃፈው የተደበቀው እውነት የተሰኘው መፅሀፍ ይተቻል, ይገመገማል!

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል🙏

Isaiah 48 Apologetics

21 Dec, 12:58


https://vm.tiktok.com/ZMkMNBUCu/

Isaiah 48 Apologetics

17 Dec, 12:57


https://vm.tiktok.com/ZMk2sQVLb/

Isaiah 48 Apologetics

04 Dec, 20:20


ኢትዮጵያን የአረብ ሊግ አባል የማድረግ እንቅስቃሴ ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ዕድገት ፋይዳ የሌለው በአንጻሩ ግን ጎጂ የሆነ እንቅስቃሴ ነው። ሊጉ ሃይማኖታዊ እንጂ ኢኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ዓላማ የሌለው ከንቱ ስብስብ ነው። የሊጉ አባል ሀገራት ምን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አገኙ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ምንም የሚል ነው። በፖለቲካውም ረገድ አባል ሀገራቱን ከመበታተን አልታደገም። ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ሶርያ፣ የመን፣ ሊብያ እና ኢራቅ አባላት በመሆናቸው ምን አተረፉ? በሊጉ ስር የተጠለሉት የእርዳታ ድርጅቶች በብዙ ሀገራት ይንቀሳቀሳሉ። መስጊዶችንና መድረሳዎችን ከማስገንባት የዘለለ ለሰው ልጆች የሚጠቅም ምን የረባ የልማት ሥራ ሠርተው ያውቃሉ? አባላቱን ለመቀላቀል በመንግሥት እየተሰጠ ያለው ሰበብ የግብፅን ተፅዕኖ ለመቋቋም ያስችላል የሚል ነው። ነገር ግን አዋጭነቱ ምን ያህል ነው? ጉዳቶቹስ ታስበውባቸዋል ወይ? ብሎ መጠየቅ አስተዋይነት ነው። ግብፅ ከምዕራባውያን የምትቀበላቸውን አጀንዳዎች በአረብ ሀገራት ላይ የምትጭነው በዚህ ሊግ አማካይነት መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። ሌሎቹ ሀገራት የሊጉ አባላት መሆናቸው የግብፅ ተገዢ ካደረጋቸው አባል መሆን ኢትዮጵያን ሰተት አድርጎ የግብፅ ብብት ስር የሚከት እርምጃ ላለመሆኑ ምን ዋስትና አለ? የግብፅን ጫና ለመቋቋም አዋጭ የሆነው መንገድ ሌሎች ሀገራትን ጠቅልሎ የግብፅ ተገዢ ያደረገ ማሕበር ውስጥ መግባት ሳይሆን የውስጥ አንድነት ማስጠበቅና በኢኮኖሚም ሆነ በፖለቲካ ረገድ የሀገራችንን ፍላጎት ከሚጋሩ ሀገራት ጋር የጋራ ሕብረት መፍጠር ነው። ግብፅ ሁል ጊዜ እኛን አጀንዳ አድርጋ በሊጉ ስብሰባዎች ላይ ማቅረቧ ሊጉን ለመቀላቀል በቂ ሰበብ አይሆንም። የግብፅን ክስና ሀሜት መስማት ካስፈለገ የግድ አባል መሆን አይጠበቅም። ሕንድን የመሳሰሉት ሀገራት በታዛቢነት እንደሚገኙት ሁሉ ታዛቢ ሆኖ መቅረብ ይቻላል። አረቦችና የአረብ ባሕል እንዳላቸው የሚያስቡ ሀገራት የፈጠሩት ማሕበር አባል መሆን አረባዊ ላልሆነችና አብዛኛው ሕዝብ ክርስቲያን ለሆነባት ሀገር ጠቃሚ አይደለም። ይሁን ከተባለም መዘዙ ከፍተኛ በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ውሳኔ እንጂ የጥቂት ፖለቲከኞችና የጥቂት ሙስሊም መሪዎች ውሳኔ ሊሆን አይገባውም።

Isaiah 48 Apologetics

03 Dec, 16:50


https://vm.tiktok.com/ZMkJJuYJ8/

Isaiah 48 Apologetics

01 Dec, 07:14


https://vm.tiktok.com/ZMhEVG8Gg/

Isaiah 48 Apologetics

29 Nov, 08:32


🚩 በዮሐንስ 1፥1 ግሪክ ዙሪያ ፍጹም ስህተት ለተናገረው ኡስታዝ ምላሽ

https://vm.tiktok.com/ZMhwfcywf/

Isaiah 48 Apologetics

27 Nov, 09:12


https://vm.tiktok.com/ZMhTSA2yh/

Isaiah 48 Apologetics

25 Nov, 11:22


🚩 ዘመኑ ቀርቧልና እንንቃ!

በዚህ ቪድዮ ላይ እንደምታዩት ይህ ሰው ያለ ምንም የወረቀት ገንዘብ፥ ያለ ምንም credit card, ያለ ምንም online transfer በቀኝ እጁ መዳፍ ብቻ ግብይት ሲፈጽም ይታያል። ያለ credit card እና ያለ online transfer በእጅ መዳፉ ብቻ እንደሚከፍል ቪድዮው ላይ ይናገራል

መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ስለ መጨረሻው ዘመን እንዲህ ይላል 👇

"16፤ ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ #በቀኝ_እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥ 17፤ የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም #ሊገዛ_ወይም_ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ" (የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 13:16-17)

አስተውላችሁ ካያችሁ ሰውየው የከፈለው በቀኝ እጁ ነው። ይህ ማለት ይህ ቴክኖሎጂ ሀሰተኛው ክርስቶስ የሚጠቀምበት ቴክኖሎጂ ነው ወይም ደግሞ እርሱ ለሚጠቀምበት ቴክኖሎጂ መሰረት የሚጥል ተመሳሳይ ቴክኖሎጂ ነው። ነገሩ ወዴት እያመራ እንደሆነ ግልፅ ነው። ዘመኑን እናስተውል። የእግዚአብሔር ቃል የሚናገረው ነገር step by step ሲፈጸም በአይናችን እያየነው ነው!

እንንቃ!

Isaiah 48 Apologetics

19 Nov, 18:07


https://vm.tiktok.com/ZMhnsYNoH/

Isaiah 48 Apologetics

18 Nov, 10:25


#the_maidens of paradise (if we ever did) and we will never do this"

✏️ Tafsir ibn abbas:- https://quranx.com/Tafsir/Abbas/21.17

የሙስሞች ነብይ የአጎት ልጅ የነበረውና፥ "ኻብራል ኡማ/የኡማው የብዕር ቀለም" ተብሎ የሚጠራው ኢብን አባስ እንደተረጎመው፥ አላህ ሚስትና ልጅ ብፈልግ ኖሮ እይዝ ነበር ሲል፥ ከፈለኩ በሰማይ ያሉ ሁሪዎችን ማግባት እችላለሁ ማለቱ ነው ብሏል። ይህ ማለት አላህ አንዲትን እንስት አግብቶ ልጅ መውለድ የሚችል ወንድ ነው ማለት ነው። ከሁሪዎቹ ጋር ተገናኝቶ ልጅ የሚያስወልድ ባህርይ አለው። ስለዚህ ጾታ ያለው የሙስሊሞች አምላክ ነው ማለት ነው።

➢ የሙስሊሞች አምላክ አላህ ጾታ ያለው ወንድ መሆኑን የሚያሳየውን ሌላኛውን የቁርአን አንቀጽ እንመልከት፦

"(እርሱ) ሰማያትንና ምድርን ያለ ብጤ ፈጣሪ ነው፡፡ ለእርሱ #ሚስት #የሌለችው ሲኾን እንዴት ለእርሱ #ልጅ #ይኖረዋል? ነገርንም ሁሉ ፈጠረ፡፡ እርሱም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡" (ሱራ 6:101)

በዚህ ስፍራ ላይ ቁርአን ለምን አላህ ልጅ እንደሌለው ሲናገር እንመለከታለን። አላህ ልጅ የሌለው ምክንያት ለባህርይው የማይስማማ ስለሆነ ሳይሆን፥ አላህ ልጅ የሌለው ሚስት ስለሌው ነው። ልጅ አልባ የሆነበት ምክንያት ሚስት ስለሌለው እንጂ ጾታ-የለሽ ስለሆነ አይደለም። ልክ አንድ ወንድ ሰው ሚስት ባትኖረው ልጅ እንደማይኖረው ሁሉ፥ አላህም ልጅ የሌለው ሚስት ስለሌለችው እንደሆነ ይህ አንቀጽ በግልጽ ይናገራል። ጾታ የሌለው ነገር ተቃራኒ ጾታን እንደ missing link ሊያቀርብ አይችልምና

ቅድም ልመመልከት እንደሞከርነው ሱራ 25:58 ላይ አላህ እንደማይሞት ተገልጿል። በቀጥታ እንደማይሞት ተገለጸ እንጂ ልክ እንደ ሱራ 6:101 ያልተሟላ ነገር ግን ቢሟላ የሚሞትበት መስፈርት እንዳለ አልተገለጸም። ሱራ 25:58 "...ገዳይ ሳይኖረው እንዴት ሊሞት ይችላል?.." አይልም። እንደዛ ቢል ኖሮ የማይሞተው መሞት ለባህርይው ስለማይስማማ ሳይሆን፥ የሚገድለው ስለሌለ ነው ይባል ነበር።

ሱራ 6:101 ግን "...ሚስት የሌለችው ሲኾን እንዴት ለእርሱ ልጅ ይኖረዋል.." ይላል። ይህ ማለት አላህ ያልወለደው ለባህርይው ስለማይስማማው ሳይሆን ሚስት ስለሌለው ነው። ስለዚህ አላህ ሚስት አግብቶ ልጅ ሊወልድ የሚችል ወንድ ነው ማለት ነው። ከሚስት/ሴት ተቃራኒ የሆነ የወንድ ጾታ አለው ማለት ነው። ልጅ የሌለው ሚስት አግብቶ መውለድ የሚችል ወንድ ሆኖ ሳለ ሚስት ስለሌለችው እንጂ ጾታ-አልባ በመሆኑ አይደለም።

✏️ አላህ በጾታው ወንድ መሆኑ በቁርአንና በሙፈሲሮች ብቻ ሳይሆን በሀዲሳትም ተረጋግጧል።

እንደ ሀዲሳቱ ዘገባ መሰረት አላህ ለመሐመድ በወንድ አምሳል የተገለጠ የወንድ ጾታ ያለው ገጸ-ባህርይ ነው 👉

👉 The Messenger of Allah (peace and blessings be upon him) said: "I saw my Lord in the form of a #young_man with no beard, with flowing hair that was curly and thick, in a green meadow."

Narrated by: Abdullah ibn Abbas
Graded as: Authentic (Sahih Marfu') by Ibn Taymiyyah
Source: Bayan Talbis al-Jahmiyyah, Volume 7, Page 290

👉 የአላህ መልእክተኛ አለ፦ "ጌታዬን ጺም እንደሌለው፥ ዥርግግ ያለ ወፍራምና ጥቅልል ጸጉር እንዳለው #የወጣት_ወንድ አምሳል ሆኖ በአረንጓዴ ሜዳ ላይ አየሁት"

ዘገባ፦ በአብደላህ ኢብን አባስ
ደረጃ፦ ትክክል (ሳሂህ መርፉዕ) በኢብን ተይሚያህ
ምንጭ፦ በያን ታልቢስ አል-ጃህሚያህ, ቅጽ 7, ገጽ 290

🔊 ታዲያ እንዴት ክርስቲያኖች ጾታ ያለው አምላክ አላቸው ይላሉ? ራሳቸው በመለኮት ጾታ ያለው አምላክ እያመለኩ???

Isaiah 48 Apologetics

18 Nov, 10:25


🚩 የማን አምላክ ነው ጾታ ያለው? (ክለሳ)

ሙስሊሞች "ክርስቶስ አምላክ ከሆነ እንዴት ጾታ ሊኖረው ይችላል?" የሚለውን ጥያቄ ሲያነሱት ማየት የተለመደ ነው። የጥያቀው አመክንዮ እጅግ ደካማ ሲሆን ከመሠረታዊ የክርስትና አስተምህሮዎች መካከል አንዱ የሆነውን የስጋዌን (incarnation) ትምህርት ችላ ያለ ነው።

ክርስቶስ በመለኮት ጾታ አለው ብለን አናምንም። ስጋን ከመንሳቱ በፊት ወይንም ደግሞ በስጋ ከመምጣቱ በፊት ሲኖርበት በነበረው ባህርይው መለኮት ነበር። መለኮት መንፈስ ነው (ዮሐ 4:24) በቦታ (ኤር 23:24) በጊዜ (ራዕ 22:13) እና በቁስ (ኢሳ 31:3) አይገደብም፥ አይወሰንም። ስለዚህ ጾታ የለውም። ክርስቶስም በስጋ ከመምጣቱ በፊት መለኮት ስለነበር (ዮሐ 1:1-3 ኤር 23:5-6) ጾታ አልነበረውም።

ጾታ የኖረው፥ ቀድሞ የእርሱ ያልነበረውን የሰውን ባህርይ የራሱ ሲያደርግ ነው (ፊሊ 2:6-7) ይህን ባህርይ የራሱ ሲያደርገው፥ ከኀጢአት በቀር ጠቅላላ ባህሪያቱ (attributes) የእርሱ ሆኑ። ከሰውነት ባህሪያት ደግሞ አንዱ ጾታ ነውና ክርስቶስ ሲሰገው፥ ጾታ ኖረው። ከስጋዌው በኋላ ክርስቶስ የመለኮትም የስጋም ባህሪያት ያሉት ሲሆን፥ ጾታ ሊኖረው የቻለበትም ምክንያት ይህ ነው። በስጋ በመገለጡ። እንጂ በስጋ የመጣው አምላክ ስላልሆነ አይደለም

♦️ አስተውሉ! በክርስትና አስተምህሮ መሰረት መለኮት ጾታ የለውም። እኛ ክርስቲያኖች መለኮት ጾታ አለው ብለን አናምንም። ክርስቶስ ጾታ ሊኖረው የቻለው፥ ሌላ ሁለተኛ ባህርይን የራሱ ስላደረገ እንጂ በአምላክነቱ ጾታ የለውም። ጾታ የመለኮት ባህርይ አይደለም።

✍️ እነርሱ ያነሱትን ጥያቄ በዚህ መልኩ ከመለስን ዘንድ፥ ወደ ተነሳንበት ርዕስ እንግባ። የማን አምላክ ነው ጾታ ያለው?

እጅግ በሚያስገርምና በሚያስደቅ መልኩ፥ ጾታ ያለው የሙስሊሞች አምላክ አላህ መሆኑን እንረዳለን! ለዚህ ማስረጃ የሆነውን የቁርአን አንቀፅ እንመልከት፦

"መጫወቻን (#ሚስትና #ልጅን) ልንይዝ #በሻን ኖሮ ከእኛ ዘንድ #በያዝነው ነበር፡፡ (ግን) ሠሪዎች አይደለንም" ሱራ 21:17

✏️ በዚህ ስፍራ የሙስሊሞች አምላክ አላህ ቢሻ ኖሮ ሚስትና ልጆችን ይይዝ እንደነበር ሲናገር እንመለከታለን። ብፈልግ ሚስትና ልጅን እይዛለሁ ማለት፥ ብፈልግ ሚስት አግብቼ ከዚያች ሚስት ልጅ መውለድ እችላለሁ ማለት ነው። ነገር ግን "ሰሪዎች አይደለንም" በማለት ይህን ነገር የማድረግ ፍላጎት እንደሌለው ይናገራል

ይህ ማለት የሙስሊሞች አምላክ አላህ ወንድ ነው ማለት ነው። ጾታ አለው። ሚስት አግብቶ ልጅ ያልወለደበት ምክንያት፥ ረቂቅ መለኮት ስለሆነ ሳይሆን ስላልፈለገ ነው። ጉዳዩ የፍላጎት እንጂ የባህርይ አይደለም። አላህ እንደ ወንድ ሚስት አግብቶ ልጅ የሚያስወልድ ባህርይ አለው። ነገር ግን ስላልፈለገ አያገባም። ልክ አንድ ሰው ከፈለገ ሚስት እንደማያገባው ልጅም እንደማይወልደው ማለት ነው። ስለዚህ የሙስሊሞች አምላክ አላህ በትክክል ጾታ አለው።

➢ ይህን ሀሳብ በይበልጥ ለመረዳት አንድ የቁርአን አንቀጽ እንደ ማነጻጸሪያ እናንሳ፦

"በዚያም #በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ" (ሱራ 25፥58)

በዚህ ስፍራ ላይ ቁርአን አላህ እንደማይሞት ሲናገር እንመለከታለን። ስለዚህ እንደ ቁርአን አስተምህሮ መሰረት ሞት ለአላህ ባህርይ የሚስማማ ነገር አይደለም። ከአላህ 99 ስሞች መካከል አንዱ "አል ሃይ" ወይንም "ሕያዉ" ሲሆን በሕይወት የሚኖረው ማለት ነው። ስለዚህ በዚህ መሰረት በእስልምና ውስጥ አላህ አይሞትም ተብሎ ይታመናል

በሱራ 25:58 ላይ "..አላህ ቢሻ ኖሮ በሞተ ነበር.." አይልም። ምክንያቱም ሞት ለባህርይው አይስማማውም። ሞት ለባህርይው ስለማይስማማ የሚሞትበት ዕድል የለም፥ እንዲሞት የሚያስችሉት ቅድመ-ሁኔታዎች አልተቀመጡም። ይህ ከባህርይው ውጪ የሆነ ነገር ነውና

✍️ በሱራ 21:17 ላይ ግን ከዚህ በተቃራኒ መልኩ "..ብንሻ.." በማለት ቢፈልግ ከሚስትና ልጆችን ሊይዝ እንደሚችል ገልጿል። ስለዚህ ይህን ተግባር የማድረግ ዕድል አለ ማለት ነው። ሚስት አግብቶ ልጅ እንዲወልድ የሚያስፈልገው ቅድመ ሁኔታ መሻቱ ነው። ነገር ግን ይህን የመስራት ፍላጎት ስለሌለው እንደማያደርገው ተናገረ። ይህ በእርግጥም አላህ ሚስት አግብቶ ልጅ ሊወልድ የሚችል የወንድ ጾታ ያለው ገጸ-ባህርይ መሆኑን ያረጋግጣል። ጉዳዩ የመሻት እንጂ የባህርይ አይደለምና።

♦️ ነገሩን በይበልጥ አስከፊ የሚያደርገው ደግሞ፥ ጾታ አለው ብለው ማመናቸው በመለኮት መሆኑ ነው። ሙስሊሞች እንደ ክርስቲያኖች መለኮት በስጋ ተገለጠ ብለው አያምኑም። ስለዚህ አላህ ጾታ አለው ሲሉ በስጋ አይደለም፥ ስጋ የለምና። ስለዚህ በትክክል አምላክ ጾታ አለው ብለው የሚያምኑት እነርሱ ናቸው ማለት ነው።

ይህ ደግሞ እስልምናን paganism ያደርገዋል። ምክንያቱም በመለኮት ጾታ አለው ብለው የሚያምኑት ፓጋኖች ናቸውና። ጣኦታዊ የነበሩት የጥንት ግሪካዊያን፥ ሮማዊያን፥ ከነዓናዊያን፥ ግብፃዊያን፥ ፋርሳዊያን፥ ባቢሎናዊያን፥ አሦራዊያን እና የሙስሊሞች ነብይ ሕዝቦች የነበሩት ጣኦታዊ አረባዊያን በሙሉ አማልክቶቻቸው በመለኮት ጾታ እንደነበራቸው ያምኑ ነበር። መለኮት ጾታ አለው በማለታቸው ወንድና ሴት አማልክት እንደነበሩ፥ እነዚህም አማልክት እንደሚጋቡና እንደሚወልዱ ያምኑ ነበር። እስልምናም አላህ ሚስት አግብቶ ልጅ መውለድ የሚችል ወንድ ነው በማለቱ፥ ሳይወድ በግድ ከፓጋኖቹ ምድብ ይመደባል።

▶️ የቁርአን ተንታኞች (ሙፈሲሮች) ይህን ጉዳይ በተመለከተ ምን አሉ?

ሙፈሲሮቹም ከቁርአኑ ጋር በመስማማት፥ አላህ ሚስት አግብቶ ልጅ መውለድ የሚችል ወንድ መሆኑን ይመሰክራሉ። ከዚያ በተጨማሪም፥ ቢፈልግ እነ ማንን እንደሚያገባም ይናገራሉ፦

"Had We desired to find some diversion, that which provided diversion, in the way of a partner or a child, we would have found it with ourselves, from among #the_beautiful_eyed_houris or #angels were we to do {so}. But We did not do so, thus We never desired it"

✍️ Tafsir Al Jalalayn:- https://quranx.com/Tafsir/Jalal/21.17

የቁርአን ተንታኞች ሁለቱ ጃላላዎች እንዳስቀመጡት፥ አላህ ብንሻ ሚስትና ልጅ ብንይዝ ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ አብራርተውታል። እርሱም፥ ከፈለገ ከመላእክትና ከሁሪዎች (በእስላማዊ ጀና ያሉ እንግዳ እንስት ፍጥረታት ናቸው) ሚስት አግብቶ መውለድ ይችላል ማለት ነው ብለዋል። ስለዚህ አላህ በሰማይ ከሁሪዎችና ከመላእክት ጋር ሊጋባ የሚችል ወንድ ነው ማለት ነው

"Then Allah revealed the following, when they said that the angels are Allah's daughters: (if we had wished to find a pastime) if we wished to #have #daughter; and it is said that it means: if we wished to #have a #wife; and it is also said that this means: if we wished to #have #children, (we could have found it in our presence) from us from among

Isaiah 48 Apologetics

14 Nov, 13:45


ሰላም ተወዳጆች። በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ስልጠናዎችን ለመስጠት በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን። እንደሚታወቀው ብዙ አገልጋዮችና ወጣቶች መጻሕፍትን የመግዛት አቅም የላቸውም። በዚህም ምክንያት የዚህች መጽሐፍ የመጀመርያና ሁለተኛ ዕትሞችን ከ80% በላይ በነጻ አድለናል። አሁንም ይህቺን መጽሐፍ ያሳተምነው በአንዳንድ ወገኖች መልካም ትብብር ቢሆንም ለሌላ ዙር ራሷን ችላ እንድትታተም እንፈልጋለን። ስለዚህ በስልጠና ወቅት ለአገልጋዮች በነፃ ማደል እንድንችል የተወሰኑ መጻሕፍትን ወጪ በመሸፈን እንድትተባበሩን እንለምናችኋለን። የተከፈለባቸውን መጻሕፍት ሁሉ በስልጠናዎች ወቅት በታማኝነት በነፃ ለአገልጋዮች እንሰጣለን። ፍቃደኛ የሆናችሁ ወገኖች @danit4all ብላችሁ በውስጥ ልታናግሩኝ ትችላላችሁ። እግረ መንገድ የመጽሐፏ ሙሉ ይዘት ዌብሳይታችን ላይ በነፃ ይገኛል። ዓላማችን የምድሩን ገንዘብ ማትረፍ ሳይሆን በነፃ የተሰጠንን በነፃ በመስጠት ክርስቶስ ጌታችንን ማክበር ነው።

Isaiah 48 Apologetics

11 Nov, 10:57


🚩 አብዱሉ "አንጌሎይ አውቱ/ἄγγελοι αὐτοῦ" ተብሎ መነበብ ያለበትን የግሪክ ሀረግ "አንጌሎኢ አውቶዩ" ብሎ አንብቦታል 😁

መቼ ይሆን pseudo-scholarship ከእስልምና ዕቅበተ-እምነት የሚወገደው?! 😁

Isaiah 48 Apologetics

09 Nov, 10:05


https://vm.tiktok.com/ZMhbLLLqd/

Isaiah 48 Apologetics

07 Nov, 17:04


አራት ዓይነት አፈጣጠር? በሚል ርዕስ የተጻፈውን ይህንን አዲስ ጽሑፍ ያንብቡ። የኢየሱስን ከድንግል መወለድ እንደ አራተኛ የሰው አፈጣጠር መንገድ ለሚቆጥሩት ሙስሊሞች የተሰጠ የማያዳግም ምላሽ ነው https://ewnetlehulu.net/four-creation/

Isaiah 48 Apologetics

01 Nov, 10:01


https://vm.tiktok.com/ZMhCRxtJ4/

Isaiah 48 Apologetics

27 Oct, 08:26


የድረ-ገጻችን አምደኛ የሆነው ወንድም ሚናስ ሌላ አዲስ ጽሑፍ ይዞልን መጥቷል። ይህንን ግሩም ጽሑፍ ለማንበብ አስፈንጣሪውን ይከተሉ https://ewnetlehulu.net/carmen-christi/

Isaiah 48 Apologetics

27 Oct, 05:54


« የምስራች ከወንድማችን የሺጥላ »

ተወዳጁ ወንድማችን  የሺጥላ ይገዙ(የሹ) ይህን አስደናቂ የአመክንዮ ስራ ነጮቹ ለዘመናት ሲጠቀሙበት እና ሲገለገሉበት የነበረውን የኅላውያን አመክንዮ ውብ ቅርጹ እንደያዘ በስርአቱ በተሰደረ እና የአገረኛውን የቋንቋ ብሂል ከነስዋሰው ዘውጉ ወደ ቋንቋችን  በመተርጎም ላደረገው ትልቅ አስተዋጻኦ እጂጉን ሊመሰገን ይገባዋል። የየሺጥላ ትርጉም ስራ ካልተሳሳትኩ በሀገራችን የስነ አመክንዮ አበርክቶት መጽሐፍ መካከል ሁለተኛው ስራ ይመስለኛል። ይህም ስራ አንድም የፕሮፌሰር ጋይዝለርን በአመክንዮው ርዕዮተ ሐሳብ ዘንድ ያበረከቱትን ጥበብ እና ታላላቅ ግንዛቤዎች የዚህን ጥልቅ ስራ ለመመልከት እድል ላላገኙ ወገኖች ጉልህ ሚናን እንደሚያሳርፍ ይሰማኛል። ሁለትም በአመክንዮው ዘንድ ያለውን እውቀት በማሳደግ የማመዛዘን ችሎታችንን በማጠናከር ሐገረኛ በሆነ ቋንቋ ስሙራዊ እና ርዕቱ ሙግቶችን ለማሰናዳት እጅጉን የሚጠቅም እና በተለይ በዕቅበተ እምነት ላይ ለሚሰሩ ወገኖች ትልቅ እውቀትን ከጥልቅ ምርምራዊ ሙግት ጋር ለሚደረግ ቅንጂታዊ የሙግት ትንተና ዝግጅት የሚጠቅም መጽሐፍ ነው።
እውቁ ክርስቲያናዊ ዐቃቤ እምነት፣ የደርዛዌ ነገረ መለኮት ምሁር እና ፈላስፋ ፕ/ር ኖርማን ጋይዝለር ለክርስቲያናዊ ዕቅበተ እምነት እና ሌሎች በስነ አመክንዮ፣ ስነ መለኮት እና ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ለማስተማር እና ለመማር የሚሆኑ መጽሐፍትን በመጻፍ ህይወቱን ሰጠ ታላቅ ሙህር ነበሩ። በምሁራዊ ብስለታቸው እና ጠጣርነታቸው የሚታወቁት ከ100 በላይ መጽሐፎችን እና ለቁጥር የሚያታክቱ መጣጥፎችን ፅፈዋል። እንዲሁም የክርስቲያን አለም እይታን በሚያጠናክሩ እና ዘውጋቸውን በጠበቁ የአመክንዮ መሰረታውያንን የሚያብራሩ ትምህርቶች ላይ ትልቅ ሚናን ያበረከቱ ክርስቲያናዊ ሙህር ናቸው። አመክንዮአዊ ስራ ለፍልስፍናዊ ሙግትን ብቻ ሳይሆን ለእምነት መጠበቂያ (ዕቅበተ እምነት ላይ) መሠረታዊነታቸውን በመናገር የሚታወቁ መምህርም ነበሩ።

ይህንን ስራ የሺጥላ በሐገረኛው ቋንቋ ሲተረጉም በዋጋ የማይተመን አስተዋፅኦ አድርጓል ብዬ አስባለሁ። በተጨማሪም የቋንቋ ክፍተቶችን በመሙላት ረገድ ትልቅ አበርክቶት እንዳለው መረዳቱ አዳጋች አይሆንም። ወንድሜ እግዚአብሔር ይባርክህ ተባረክልን🙏

ጸሐፊው ሌሎች እያዘጋጃቸው ያሉ መጻሕፍት አሉና እነሱም ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ እንዲታተሙ በገንዘብ ሕትመቱን መሸፈን የምትፈልጉ አናግሩት(👉@homme45)።

1) 📚የምክንያታውያን ታሪክ፣ ቅጽ ፩ በዝግጅት ላይ ነው (ስለ ሶፊስቶች፣ ፕሌቶ፣ አርስቶትልና ዶ/ር እጓለ ሰፊ ማብራሪያን የያዘ መጽሐፍና የጉድኝታዊ እውነትን ዐሳብና ሰው ከብሔሩና ከቆዳው ቀለም በላይ መሆኑን በማሳየት የሚሞግት ነው)፣
2) 📚የምክንያታውያን ታሪክ፣ ቅጽ ፪ (አመክንዮን በሰፊው የሚያብራራ፣ ዐዲሱን አመክንዮ (ሞዳል ሎጂክ) የሚተነትን፣ በታሪክ የታዩ አማኝ ዐሳብያንን ታሪክ የያዘ መጽሐፍ)፣
3) 📚የምክንያታውያን ታሪክ፣ ቅጽ ፫ (ከ 100 በላይ የሆኑ ተፋልሶዎችና ስለ ሃይማኖት፣ ፖለቲካ፣ ማኅበራዊ ዕሳቤ፣...ያለኝን አመለካከት የማንጸባርቅበት መጽሐፍ)፣
4) 📚ፈጣሪ አለ? ቅጽ ፬ (ሙግት ከሥነ ኑባሬን በሰፊው የሚዘረዝር ጽሑፍ)...እና ሌሎችም ተከታታይ ጽሑፎች በዝግጅት ላይ ናቸው።
5) 📚የፕላንቲንጋ የሕይወት ታሪክ

Isaiah 48 Apologetics

21 Oct, 14:32


እየሱስ እንዴት ከመጥምቁ ዮሐንስ ቀድሞ Exist አደረገ?

ዮሃ 1:30
አንድ ሰው ከእኔ በኋላ ይመጣል፥ #ከእኔም #በፊት #ነበርና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኖአል ብዬ ስለ እርሱ ያልሁት ይህ ነው።

#ነበር የሚለው የግሪክ ቃል፣ "ኤን" የሚልው imperfect verb ሲሆን፣ Aspectቱ ያልተገደበ Continuous past existence የሚገልፅ ነው።

አሁን፣ ከኢየሱስ በፊት ዮሃንስ ቀድሞ ተወልዶ ሳለ፣ እንዴት እየሱስ ከሱ ቀድሞ ነበር ተባለለት?

መልስህ፣ አይ፣ በአምላክ አእምሮ ውስጥ እንጂ በገሃድ አይደለም ካልክ፣ ጥያቄው የሚሆነው፣ በአምላክ አእምሮ ውስጥ አንዱ ከሌላው ቀድሞ ይታወቃል እንዴ? አምላክ ስለ እየሱስ አስቀድሞ አውቆ፣ ስለ ዮሃንስ ያላወቀበት ጊዜ ነበር እንዴ? ይህ ማለት፣ አምላክ ሁልጊዜም ሁሉን አዋቂ አልነበረም ብሎ የሚያምን ሰው የሚያመጣው ትርጉም ስለሆነ ደካማ ሙግት ነው።

Unless of course, the Son of God LITERALLY existed from eternity 🙂

Isaiah 48 Apologetics

09 Oct, 14:16


https://youtu.be/zn_hcOSDNOo?si=ixAs23mlW7iWGup-

Isaiah 48 Apologetics

06 Oct, 12:08


🚩 ሐዋርያው ጳውሎስ እንደ እስልምና አስተምህሮ ሀሰተኛ ሐዋርያና አሳች ሳይሆን ትክክለኛ የአላህ መልእክተኛ መሆኑ እንደሚታመን ለመዳሰስ ሞክረናል (ክፍል 3)

Share!

Isaiah 48 Apologetics

06 Oct, 12:06


https://vm.tiktok.com/ZMhBb3tPT/

Isaiah 48 Apologetics

03 Oct, 21:43


🚩 እሬቻ

"1 በመካከልህም ነቢይ ወይም ሕልም አላሚ ቢነሣ፥ ምልክትም ተአምራትም ቢሰጥህ፥ 2 እንደ ነገረህም ምልክቱ ተአምራቱም ቢፈጸም፥ እርሱም። ሄደን #የማታውቃቸውን ሌሎች #አማልክት እንከተል #እናምልካቸውም ቢልህ" (ዘዳ 13:1-2)

ሰሞኑን እሬቻ የተሰኘው በአል በአዲስ አበባ ሲከበር ነበር። ይህ በአል ሃይማኖታዊ በአል ሲሆን የኦሮሞ ሕዝብ ወንጌልን ሰሞቶ ወደ ክርስትና ከመምጣቱ በፊት የነበረበት ግልጽ ጣዖት አምልኮ ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ ወንጌል አማካኝነት የእስራኤልን አምላክ ከማወቁ በፊት የነበረበት ጣዖታዊ ባዕድ አምልኮ ነው

የእግዚአብሔር ቃል እንደሚናገረው ከግብፅ ምድር የወጡት እስራኤላውያን ካወቁት አምላክ ከእግዚአብሔር/ከያሕዌ በቀር ሌሎች አማልክትን ማምለክ እግዚአብሔር የሚጸየፈው ጣዖት አምልኮ ነው። በእሬቻ በአል የሚመለከው ዋቃና ሌሎቹ ጣዖታት (አቴቴ፥ ቦርንትቻ ወዘተ...) በሙሉ እስራኤል ያላወቃቸው እርኩሳን ጣዖታት ናቸው (ዘዳ 29:17 1ነገ 11:7) እነዚህን ጣዖታት ማምለክ በጣዖት አምላኪነት ያስጠይቃል፥ የእግዚአብሔርንም ቁጣ በምድር ላይ ያመጣል

✍️ መጽሐፍ ቅዱስ ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ውጪ የሆኑ አማልክት በሙሉ አጋንንት እንደሆኑ ይናገራል፦

"17 #እግዚአብሔር ላልሆኑ #አጋንንት፥ #ለማያውቋቸውም #አማልክት" (ዘዳ 32:17)

"አይደለም፤ ነገር ግን #አሕዛብ የሚሠዉት #ለአጋንንት እንዲሆን እንጂ #ለእግዚአብሔር እንዳይሠዉ እላለሁ፤ ከአጋንንትም ጋር #ማኅበረተኞች #እንድትሆኑ #አልወድም" (1ቆሮ 10:20)

ስለዚህ አንድ ሰው በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ወደዚህ በአል ከሄደና ተሳታፊ ከሆነ በአምልኮተ አጋንንት እየተሳተፈ ነው። አጋንንትን እያመለከ ነው። የእግዚአብሔር ቃል "..የአጋንንት ማህበርተኞች እንድትሆኑ አልወድም.." እያለ አንድ ሰው ወደዚህ ባዕድ አምልኮ ሄዶ ከተባበረ የእርኩሳን መናፍስት ማህበርተኛ እየሆነ ነው። እግዚአብሔርን ያልሆኑ ሰይጣናትን በቀጥታ እያመለከ ነው

በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑ ክርስቲያኖች ከጣዖታት ጋር #በምንም_አይነት መንገድ ሕብረት ሊኖራቸው አይችልም፦

" #ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም #ከጣዖት ጋር ምን #መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ #መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል። በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።" (2ቆሮ 6:16)

➢ ከላይ የተገለጸው አይነት ጣዖት አምልኮ ሁሉ ደግሞ የዘላለምን ሞት እንደሚያስከትል መጽሐፍ ቅዱስ አስረግጦ ይነግረናል፦

"ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም #ጣዖትንም_የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው #በዲንና_በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም #ሁለተኛው_ሞት_ነው" (ራዕ 21:8)

"ውሻዎችና አስማተኞች ሴሰኛዎችም ነፍሰ ገዳዮችም #ጣዖትንም_የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ #በውጭ_አሉ" (ራዕ 22:15)

"20 መዳራት፥ #ጣዖትን_ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት 21 መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ #የእግዚአብሔርን መንግሥት #አይወርሱም" (ገላ 5:20-21)

"9 ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም #ጣዖትን_የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ 10 ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን #መንግሥት #አይወርሱም" (1ቆሮ 6:9-10)

"ይህን እወቁ፤ አመንዝራም ቢሆን ወይም ርኵስ ወይም የሚመኝ እርሱም #ጣዖትን_የሚያመልክ በክርስቶስና በእግዚአብሔር #መንግሥት ርስት #የለውም" (ኤፌ 5:5)

▶️ የዚህ አስከፊ እርኩሰት ውጤት የዘላለም ሞት በመሆኑ፥ መጽሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ከጣዖት አምልኮ እንድንሸሽ አዝዞናል፦

"ልጆች ሆይ፥ #ከጣዖታት ራሳችሁን #ጠብቁ" (1ዮሐ 5:21)

"ስለዚህ፥ ወዳጆቼ ሆይ፥ #ጣዖትን ከማምለክ #ሽሹ" (1ቆሮ 10:14)

"ሕዝብም ሊበሉ ሊጠጡም ተቀመጡ ሊዘፍኑም ተነሡ ተብሎ እንደ ተጻፈ ከእነርሱ አንዳንዶቹ እንዳደረጉት #ጣዖትን #የምታመልኩ #አትሁኑ" (1ቆሮ 10:7)

"ነገር ግን #ከጣዖት ርኵሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም #ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ" (ሐዋ 15:20)

"አምነው ስለ ነበሩ አሕዛብ ግን #ለጣዖት ከተሠዋ ከደምም ከታነቀም ከዝሙትም #ነፍሳቸውን #እንዲጠብቁ ፈርደን እኛ ጽፈንላቸዋል" (ሐዋ 21:25)

" #ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም #ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ" (ሐዋ 15:28-29)

▶️ እሬቻ ባህል አይደለም። እሬቻ በባህል ስም የሚካሄድ ጣዖት አምልኮ ነው። በባህልና በሌሎች ሰበቦች ስም እግዚአብሔር በልጁ ወንጌል ብርሃን ካዳነንና ካላቀቀን ጣዖት አምልኮ ጋር ተመልሰን መቆራኘት፥ ተቆራኝተንም በዚህ እርኩሰት ረክሰን ነፍሶቻችንን ማጣት የለብንም!

ቃሉ እንደሚለው እግዚአብሔርን #ብቻ እናምልክ!

"ሳሙኤልም የእስራኤልን ቤት ሁሉ። በሙሉ ልባችሁ ወደ እግዚአብሔር ከተመለሳችሁ እንግዶችን አማልክትና አስታሮትን ከመካከላችሁ አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ #እግዚአብሔር አቅኑ፥ እርሱንም #ብቻ #አምልኩ፤ ከፍልስጥኤማውያንም እጅ ያድናችኋል ብሎ ተናገራቸው" (1ሳሙ 7:3)

"ያን ጊዜ ኢየሱስ። ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ #ለአምላክህ ስገድ እርሱንም #ብቻ #አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው" (ማቴ 4:10)

♦️ በክርስቶስ ስም የእሬቻን ጣዖት አምልኮ #እንቢ በሉት! Say #No to irecha Idol Worship in the name of Christ!

Isaiah 48 Apologetics

01 Oct, 18:48


🚩 እንደ እስልምና አስተምህሮ መሰረት ሐዋርያው ጳውሎስ የአላህ መልእክተኛ መሆኑን በማስረጃ ለመዳሰስ ሞክረናል (ክፍል 2)

Isaiah 48 Apologetics

01 Oct, 18:41


https://vm.tiktok.com/ZMhCRCmcr/

Isaiah 48 Apologetics

11 Sep, 17:00


መልስ ለሙስሊም https://vt.tiktok.com/ZS2BHsxbh/

Isaiah 48 Apologetics

10 Sep, 15:11


"በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል"
(መዝሙረ ዳዊት 65:11)

🚩 እንኳን ለ2017 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ! ጌታ ኢየሱስ በልባችን የሚነግስበት አመት ይሁንልን!

Isaiah 48 Apologetics

01 Sep, 15:43


🚩 በዚህ ቪድዮ ላይ እንደ እስልምና አስተምህሮ ሐዋርያው ጳውሎስ በአላህ የተላከ የአላህ መልእክተኛ እንጂ አሳችና ሀሰተኛ ሐዋርያ እንዳልሆነ ከእስልምና መተርጉማን (ሙፈሲሮች) ማስረጃዎችን በመጥቀስ ለመመልከት ሞክርናል

Share!

Isaiah 48 Apologetics

31 Aug, 18:36


የክርስቶስ አካል የተገነዘበት ጨርቅ እንደሆነ ሲነገር የኖረው የቱሪን ከፈን (Shroud of Turin) ዕድሜው 2000 ዓመታት እንደሆነ የሚያረጋግጥ ጥናት ይፋ ሆኗል። በዚህ ጨርቅ ላይ የሚታየው በዘመናዊ ካሜራ ቴክኖሎጂ ሊፈጠር የሚችለው ኔጌቲቭ ምስል የአንድ ከመስቀል የወረደ እጆቹና እግሮቹ የተቸነከሩ ሰው ትክክለኛ ምስል ሲሆን ምስሉ እንዴት እንደተፈጠረ ባይታወቅም ጨርቁ በመካከለኛው ዘመን የተዘጋጀ እንደሆነ በካርበን ዴቲንግ እንደተረጋገጠ ሲነገር ነበር የቆየው። አንዳንድ ምሑራን ለምርመራ የተወሰደው የጨርቁ ክፍል ከቃጠሎ በኋላ በመካከለኛው ዘመን በጨርቁ ላይ የተጣፈ እንጂ ዋናው ጨርቅ አለመሆኑን ቢናገሩም ሰሚ አላገኙም። አሁን በተደረገ አዲስና ልዩ ምርመራ ግን ትክክለኛ ዕድሜው እንደተረጋገጠ እየተነገረ ይገኛል። ይህንንም ዜና የዓለም ሚድያዎች እየተቀባበሉት ይገኛሉ። በርግጥ ቀደም ሲል የካርበን ምርመራው ዕድሜውን ቢያሳንስም በጨርቁ ላይ የተገኙት የዕፅዋት ቅሪቶች በመጀመርያው ክፍለ ዘመን በምድረ እስራኤል የሚበቅሉት እንደሆኑ ጥናቶች አሳይተዋል። በአሁኑ ወቅት በዚህ አዲሱ ግኝት የዓለም ተመራማሪዎች ግራ እየተጋቡ ይገኛሉ። ምርመራውን ካደረጉት ተመራማሪዎች መካከል አንዱ የሆነው እንግሊዛዊው ዴቪድ ሮልፍ ቀደም ሲል አምላክ የለሽ ቢሆንም ከግኝቱ በኋላ ክርስትናን ተቀብሏል። https://www.mirror.co.uk/news/world-news/athiest-who-set-out-prove-33507055
እነዚህን ሊንኮች ተመልከቱ፦
https://www.thesun.co.uk/tech/29974040/scientists-shroud-of-turin-evidence-imprint-jesus/
https://www.dailymail.co.uk/sciencetech/article-13758359/scientists-discovery-jesus-cloth-buried-shroud-turin.html
https://inews.co.uk/news/shroud-of-turin-real-jesus-evidence-3237452?ico=related_stories&srsltid=AfmBOorh55zRCT6hXE8xrWBdssAidQpho2uSCOKw265PtB5zF48vq_FP
ዋናው የጥናቱ ውጤት እዚህ ይገኛል፦
https://www.mdpi.com/2571-9408/5/2/47#

Isaiah 48 Apologetics

28 Aug, 14:42


https://vm.tiktok.com/ZMr37Umus/

Isaiah 48 Apologetics

25 Aug, 10:42


የምትጠብቁት የክፍል አንድ ትምህርተ ሥላሴ ትምህርት ተለቋል።

ከዕብራይስጥ ቅዱሳት መጽሐፍት እና ሊቃውንት አንጻር ድንቅ ዳሰሳ

https://youtu.be/GAxXQrEqWfU?si=zt1oBtDGIP79MWDx

ሼር ይደረግ።

Isaiah 48 Apologetics

22 Aug, 03:34


🚩 የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ (ክፍል 4)

ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ከራሱ ከዕብራውያን መልእክት ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃዎችን ማቅረብ ጀምረን ነበር። ሙስሊሞች ሆኑ ሌሎች ከክርስትና ውጪ ያሉ አካላት የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ስለማይታወቅ መጽሐፉ የመጽሐፍ ቅዱስ አካል መሆን የለበትም፥ የእግዚአብሔርም ቃል ሊሆን አይችልም ብለው ሊሟገቱ ይሞክራሉ።

ነገር ግን ባለፉት ክፍሎች ለማሳየት እንደሞከርነው ይህ ፍጹም ስህተት የሆነ አመለካከት ነው። የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ከምሁራንና ከቤተክርስቲያን ታሪክ ብዙ ማስረጃዎችን ማምጣት ይቻላል። በተጨማሪም ከራሱ ከዕብራውያን መልእክት ጸሐፊው ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችንም ማቅረብ ይቻላል

▶️ እግዚአብሔር ቢፈቅድ በዚህም ክፍል ላይ ካለፉት ክፍሎች በመቀጠል የዕብራውያኑ ጸሐፊ ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ መሆኑን የሚያረጋግጡ ተጨማሪ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃዎችን ማቅረብ እንቀጥላለን፦

8) በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀምጧል

"እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ #በሰማያት_በግርማው_ቀኝ_ተቀመጠ" (ዕብ 1:3)

በዕብ 1:3 ላይ የዕብራውያኑ ጸሐፊ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአባቱ የክብሩ ነጸብራቅና የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ መሆኑን፥ ሁሉንም በስልጣኑ ቃል እንደሚደግፍና ኃጢአታትንን በራሱ እንዳነጻ ከገለጸ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ መቀመጡን ይናገራል። ልጁ ጌታ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡ በብሉይ ኪዳን ስለ መሲሁ የተነገረ ትንቢት ሲሆን (መዝ 110:1) ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ዐርጎ በአባቱ ቀኝ መቀመጡ (ዕብ 10:12-13) የዚህ የብሉይ ኪዳን ትንቢት ፍጻሜ ነው። ይህ ትንቢት በተነገረበት በመዝሙረ ዳዊት አስተምህሮ መሰረት እግዚአብሔር በሰማይ ያለ ሲሆን (መዝ 102:19 መዝ 2:4) ዙፋኑም ያለው በዚያው በሰማይ ነው (መዝ 103:19 መዝ 11:4) ስለዚህ መሲሁ በእግዚአብሔር ቀኝ ይቀመጣል ማለት እግዚአብሔር ወዳለበት ወደ ሰማይ ዐርጎ በዙፋኑ ላይ በቀኙ ይቀመጣል ማለት ነው። መሲሁ ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ሰማያት አርጎ በአባቱ በእግዚአብሔር አብ ግርማ ቀኝ መቀመጡ ይህን ትንቢት ለመፈጸሙ የማይታበል ማረጋገጫ ነው።

በዕብ 1:3 ላይ ተገልጾ የምንመለከተው ይህ እውኑት ጌታ ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን የተነገረውን ትንቢት እንደፈጸመ ከማሳየት ባሻገር፥ የመልእክቱ ጸሐፊ ራሱ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ ሌላ ማሳያ ነው። ምክንያቱም ልጁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ቀኝ መቀመጡ በሐዋርያው ጳውሎስ መልእክቶች ላይ የተነገረ እውነት ነውና፦

"እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ #ክርስቶስ_በእግዚአብሔር_ቀኝ_ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ" (ቆላ 3:1)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ እንደተቀመጠ ሲናገር እንመለከታለን። በበፊተኛው ምዕራፍ ላይ እንደ ሰው ስርዓት ላሉት ምድራዊ ነገሮች እንዳይገዙ ከነገራቸው በኋላ (ቆላ 2:22) በምዕራፍ 3 ላይ ማሰብ ያለባቸው ክርስቶስ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት ያለውን ነገር እንዲሹ ይመክራቸዋል። ክርስቶስ ኢየሱስ ያለው በላይ በሰማይ ስለሆነ እርሱ ባለበት በላይ ያለውን እንጂ በምድር ያለውን እንዳይደለም ይነግራቸዋል (ቆላ 3:2) ቆላ 3:2 ላይ "በላይ" ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ሰማይን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል (ዮሐ 8:23) ስለዚህ ክርስቶስ የተቀመጠው በሰማያት በእግዚአብሔር ቀኝ ነው ማለት ነው።

በቆላ 3:1 ላይ ልክ እንደ ዕብ 1:3 ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ እንደተቀመጠ መገለጹ የሁለቱን ክፍሎች የሀሳብ አንድነት ከመጠቆም ባሻገር የሁለቱም መልእክታት ጸሐፊ አንድ ለመሆኑ ማሳያ ነው። በዕብ 1:3 ላይ በእግዚአብሔር አብ የግርማው ቀኝ የተቀመጠው አለማትን የፈጠረበት ልጁ መሆኑ እንደተገለጸ ሁሉ፥ በቆላ 3:1 ላይ በሰማያት በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠው ልጁ መሆኑ በዚያው በቆላሲስ መጽሐፍ ላይ ተገልጿል (ቆላ 1:13-14) ከዕብራውያን እና ከቆላሲስ መልእክታት እንደምንረዳው በሰማያት በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠው የአለማት ፈጣሪ የሆነው የእግዚአብሔር አብ ልጅ ነው። ይህ የሁለቱን ክፍሎች የትምህርት አንድነት ከማሳየት ባሻገር የሁለቱም መልእክቶች ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው።

በዕብራውያን መልእክት እና በቆላሲስ መልእክት መካከል እጅግ በጣም የሚያስገርም ሰፊ የሆነ የትምህርት አንድነት አለ። በሁለቱም መልእክቶች ልጁ ኢየሱስ የአባቱ የእግዚአብሔር አብ ትክክለኛ ምሳሌ መሆኑ ተገልጿል (ቆላ 1:15/ዕብ 1:3) የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ እንደሆነ ተገልጿል (ቆላ 1:15-16/ዕብ 1:2) ፍጥረት ሁሉ በእርሱ እንደተጋጠመ ተገልጿል (ቆላ 1:17/ዕብ 1:3) ከሃጢአት መንጻት/የሃጢአት ስርየት በልጁ እንደተከናወነ ተገልጿል (ቆላ 1:13-14/ዕብ 1:3) በአብ ቀኝ መቀመጡም ተገልጿል (ቆላ 3:1/ዕብ 1:3) በሁለቱ መልእክቶች መካከል ያለው የይዘትና የአስተምህሮ ቁርኝት የሁለቱም መልእክታት ጸሐፊ ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ጠንካራ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው።

"የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ #በእግዚአብሔር_ቀኝ_ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" (ሮሜ 8:34)

በዚህ ቦታ ላይም ሐዋርያው ጳውሎስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ እንዳለ ሲናገር እንመለከታለን። በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ በዕብ 1:3 ላይ ያለውን ራሱ ሀሳብ ከነ ቅደም ተከተሉ እየደገመው ነው። በዕብ 1:3 ላይ ልጁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ #በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ እንደተቀመጠ ይናገራል። ወደ ሰማያት አርጎ በአባቱ ግርማ ቀኝ የተቀመጠው ኃጠአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ ነው። በባለፈው ክፍል ለማየት እንደሞከርነው የክርስቶስ እኛን በራሱ ከኃጢአታችን ማንጻቱ በመስቀል ላይ ስለ እኛ በደል ተሰቅሎ መሞቱ ነው (ቲቶ 2:14 ኤፌ 1:7 ቆላ 1:13-14 ማቴ 20:28 1ዮሐ 4:10) ስለዚህ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ #በኋላ ማለት ስለ በደላችን ማስተሰርያ ሞቶ ከተነሳ በኋላ ማለት ነው። እንደ ዕብ 1:3 ቅደም-ተከተል መሰረት ከዚያ በኋላ ነው በሰማያት በግርማው ቀኝ የተቀመጠው

ይህን በዕብ 1:3 ላይ የምንመለከተውን ይህንን ቅደም-ተከተል በሮሜ 8:34 ላይ እንመለከተዋለን። በሮሜ 8:34 ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡን ሲገልጽ "..የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው.." በማለት በእግዚአብሔር ቀኝ ከመቀመጡ በፊት የሆኑትን ክስተቶች በዕብ 1:3 ላይ በምንመለከተው ቅደም-ተከተል መሰረት ያስቀምጠዋል። በሮሜ 8:34 ላይ የተጠቀሰው ሞትና ትንሳኤ በዕብ 1:3 ላይ በራሱ እኛን ከኃጢአታችን ማንጻቱ ነው። በሁለቱ ክፍሎች መካከል ያለው ይህ የሀሳብ፥ የአስተምህሮ እና የቅደም-ተከተል አንድነት የሁለቱም ክፍሎች ጸሐፊ ያው ራሱ ሐዋርያው ጳውሎስ መሆኑን የሚያሳይ ጠንካራ ውስጠ-ጽሑፋዊ (intertextual) ማስረጃ ነው።

Isaiah 48 Apologetics

22 Aug, 03:34


በዕብ 1:3 ላይ በእግዚአብሔር የግርማው ቀኝ የተቀመጠው አለማት የተፈጠሩበት ልጁ መሆኑ እንደተገለጸ ሁሉ፥ በሮሜ መልእክትም ሞቶ፥ ከሙታን ተነስቶ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ልጁ ኢየሱስ መሆኑ በዚያው በሮሜ መልእከት ላይ በተደጋጋሚ ተገልጿል፦

"ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር #ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" (ሮሜ 1:3-4)

" #በልጁ ወንጌል በመንፈሴ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና፤ ምናልባት ብዙ ቆይቼ ወደ እናንተ አሁን እንድመጣ በእግዚአብሔር ፈቃድ መንገዴን እንዲያቀናልኝ እየለመንሁ ሁልጊዜ ስጸልይ ስለ እናንተ ሳላቋርጥ አሳስባለሁ" (ሮሜ 1:9-10)

"ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር #በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን" (ሮሜ 5:10)

✍️ ጌታ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ እንደተቀመጠ በተናገረበት በዚያው አውድም ያ በቀኙ የተቀመጠው ልጁ መሆኑን ሐዋርያው ገልጿል፦

"ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን እግዚአብሔር የገዛ #ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና" (ሮሜ 8:3-4)

" #ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና" (ሮሜ 8:29)

"ለገዛ #ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?" (ሮሜ 8:32)

✍️ በሮሜ 8 እና በዕብ 1 መካከል ያለው ይህ ከፍተኛ የሆነ የአስተምህሮ ቁርኝት ሁለቱም መልእክቶች በአንድ ጸሐፊ ለመጻፋቸው ማስረጃ ከመሆኑ ባሻገር የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ራሱ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ ውሰጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው

9) እጅግ የሚበልጥ ስም አለው

"ከመላእክት ይልቅ እጅግ #የሚበልጥ_ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ ከእነርሱ አብዝቶ ይበልጣል" (ዕብ 1:4)

የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ በዕብ 1:3 ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአባቱ የክብሩ ነጸብራቅና የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ መሆኑን፥ ሁሉንም በስልጣኑ ቃል እንደሚደግፍና ኃጢአታትንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ እንደተቀመጠ ከገለጸ በኋላ በዕብ 1:4 ላይ ከመላእክት እጅግ የሚበልጥ ስምን እንደወረሰ ይናገራል። በዚህ ስፍራ ስም የሚለው "position, status" ማለት ሲሆን ከእርገቱ በኋላ ወደ ቀድሞ ክብሩ መመለሱን የሚገልጽ ቃል ነው። ከስጋዌው የተነሳ ከመላእክት ጥቂት አንሶ የነበረው ክርስቶስ (ዕብ 2:9) በምድር ላይ ሲመላለስ እንደ አባቱ ባርያ ነበር፥ አላማውም ለማገልገል ነበር (ማቴ 20:28 ማር 10:45 ኢሳ 42:1) ነገር ግን ከትንሳኤው በኋላ አለም ሳይፈጠር ወደነበረው ክብር ተመሰለ (ዮሐ 17:5)

ለዚህም ነው በዕብ 1:4 ላይ በሰማያት ዘግርማው ቀኝ ከተቀመጠ በኋላ ከመላእክት የበለጠን ስም ወረሰ የሚለው። ከስጋዌው በፊት ወደነበረው position, status አርጎ መመለሱን እያመለከተ ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ከስም/position ሁሉ በላይ የሆነው ስም የእግዚአብሔር ስም ሲሆን (መዝ 148:13) ክርስቶስ ኢየሱስ ከመላእክት እንኳን እጅግ የሚበልጥ ስም እንዳለው መነገሩ በስጋ የመጣው አምላክ ለመሆኑ የማይታበል ማስረጃ ነው። ምድር ላይ የነበረውን የባርያ አገልገሎት ከፈጸመ በኋላ ዐርጎ የተመለሰው ወደዚህ ክብር መሆኑ መገለጹ ክርስቶስ ከስጋዌው በፊት በመለኮታዊ ክብር የነበረው እግዚአብሔር ለመሆኑ ተጨባጭ ማስረጃ ነው።

➢ በዕብ 1:3 ላይ የተባለው ይህ ነገር የልጁ የክርስቶስ ኢየሱስን ስጋዌና አምላክነት ከማሳየት ባሻገር፥ የመልእክቱ ጸሐፊ ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ሌላ ማሳያ ነው። ምክንያቱም ልጁ ጌታችን ኢየሱስ ከስም ሁሉ በላይ ስም ያለው መሆኑ በሐዋርያው ጳውሎስ መልእክት ላይ የተነገረ እውነት ነውና፦

"በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው #ከስምም_ሁሉ_በላይ_ያለውን_ስም_ሰጠው" (ፊል 2:9)

በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቶስ ኢየሱስ ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም ከእግዚአብሔር አብ እንደተሰጠው እንመለከታለን። ይህ ማለት ክርስቶስ ኢየሱስ ምንም እንኳ በእግዚአብሔር መልክ/ባህርይ ሲኖር ሳለ የባርያን መልክ/ባህርይ ከያዘ በኋላ ለመስቀል ሞት እንኳ ሳይቀር ለአባቱ በመታዘዙ እግዚአብሔር ያለልክ ከፍ ከፍ አድርጎታል። ይህ ማለት ከስጋዌው በፊት ወደነበረው ክብሩ (ዮሐ 17:5) መልሶታል ማለት ነው። አለም ሳይፈጠር በፊት የነበረበት ክብር የመለኮት ክብር ሲሆን፥ ከትንሳኤው በኋላ በሰማያት በዙፋኑ በቀኙ በማስቀመጥ ወደዚያ ክብር መልሶታል። ያለ ልክ ከፍ አደረገው ማለት ይህ ነው።

በፊሊ 2:9 ላይ "ከፍ ከፍ" ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል "ὑψόω/ሂፕሲኦ" ሲሆን (Strong's G5312) ኢየሱስ በአብ ቀኝ ያለውን የመጨረሻውን ክቡርና ከፍተኛ የመንግስተ ሰማይ position ያመለክታል (ሐዋ 2:33 ሐዋ 5:31) ያም የእግዚአብሔር ዙፋን ነው (ራዕ 22:1) ስለዚህ ከስምም በላይ ስም ሰጠው ማለት ቀድሞ ወደነበረው የመጨረሻው ከፍተኛ position፥ አለም ሳይፈጠር ወደነበረው ክብሩ መለሰው ማለት ነው። ልዩነቱ አለም ሳይፈጠር የዚህ ክብር ባለቤት የሆነው በመለኮታዊው ባህርይው ብቻ ነበር። ከትንሳኤው በኋላ ግን የዚህ ክብር ባለቤት የሆነው ሰዋዊውም ባህርይ ኖሮት ነው። በዕብ 1:4 እና በፊሊ 2:9 መካከል ያለው የይዘት አንድነት የሁለቱም ክፍሎች ጸሐፊ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው።

♦️ በዕብራውያን 1 እና በፊልጵስዩስ 2 መካከል ሰፊ የሆነ የአስተምህሮ አንድነት ያለ ሲሆን ከሐዋርያው ጳውሎስ መልእክታት ውጪ በየትኛውም ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የምናገኘው አይነት አገላለጽ አይደለም። በሁለቱም ስፍራ ልጁ ክርስቶስ ኢየሱስ ከአብ ጋር በባህርይ አንድ እንደሆነ ተገልጿል (ፊሊ 2:6/ዕብ 1:3) ስለ ኃጢአታችን ተሰቅሎ መሞቱ ተገልጿል (ፊሊ 2:8/ዕብ 1:3) አርጎ ከስም ሁሉ በላይ ስም እንደተሰጠውም ተነግሯል (ፊሊ 2:9/ዕብ 1:4) ይህ በሁለቱ መካከል ያለው የማይታበል የሀሳብና የትምህርት አንድነት የሁለቱም ክፍሎች ጸሐፊ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው።

"ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ #ከሚጠራው_ስም_ሁሉ_በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ #ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል" (ኤፌ 1:20-21)

በዚሁ ስፍራም ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቶስ ከስም ሁሉ በላይ ስም እንዳለው ሲናገር እናነባለን። እግዚአብሔር አብ ልጁን ክርስቶስ ኢየሱስን ከሞት ካስነሳው በኋላ ከአለቅነት፥ ከሥልጣን፥ ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይ በዚህ አለም ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም አለም ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ እንዳስቀመጠው ይናገራል። ማለትም ክርስቶስ ከትንሳኤው በኋላ ያለው position የመጨረሻው ከፍተኛ position ነው። እርሱም በሰማያት ያለው የእግዚአብሔር ቀኝ የሆነው የግርማው ዙፋን ነው። ከሁሉ በላይ የሆነው ስም የሚያመለክተው ይህንን ነው

Isaiah 48 Apologetics

22 Aug, 03:34


በኤፌ 1:20-21 ክርስቶስ የበላያቸው እንደሆነ የተነገረላቸው ኃይላትና ጌትነት በሰማይ ያሉ መናፍስት ወይም መላእክት ሲሆኑ (ኤፌ 6:12 1ጴጥ 3:22 ይሁዳ 1:8-9) ከእነሱ የሚበልጥ እጅግ የሚበልጥ ስም እንዳለው ተገልጿል። በዕብ 1:4 ላይ የምንመለከተው ይህንን ነው። በሰማያት በግርማው ቀኝ ሲቀመጥ ከመላእክት እጅግ የሚበል ስምን መውረሱ ከአለቅነት፥ ከሥልጣን፥ ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይ በዚህ አለም ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም አለም ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያት በአብ ቀኝ መቀመጡ ነው። ይህ የዕብራውያን ጸሐፊ ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው።

♦️ በኤፌ 1 እና በዕብ 1 መካከል ጠንካራ የመልእክት አንድነት አለ። በሁለቱም ስፍራ አብ ሁሉን ወራሽ እንዳደረገው ተነግሯል (ኤፌ 1:22/ዕብ 1:2) ትንሳኤው ተነግሯል (ኤፌ 1:20/ዕብ 1:3) በአብ ቀኝ መቀመጡ ተነግሯል (ኤፌ 1:21/ዕብ 1:3) ከመላእክት እጅግ የሚበልጥ ስም እንዳለው ተነግሯል (ኤፌ 1:20-21/ዕብ 1:4) ይህን አይነቱን አገላለጽ ከሐዋርያው ጳውሎስ መልእክት ውጪ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የማይመለከተው ሲሆን፥ የሁለቱም መልእክታት ጸሐፊ ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጸሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው

▶️ ይቀጥላል

Isaiah 48 Apologetics

17 Aug, 14:02


🚩 አሳዛኝ ዜና 😭

ይህች በምስሉ ላይ የምትመለከቷት አንዲት ፍሬ የ7 አመት ሕጻን ልጅ እናቷ ስራ ላይ በነበረችበት ሰአት በአከራያቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ ተገድላለች! 😭

ወንጀለኛው ግለሰብ ይህችን ሕጻን ልጅ ወደ መጸዳጃ ቤት ስትሄድ ጠብቆ ካፈናት በኋላ እንዳትጮህ አፏ ውስጥ አሸዋ ከጨመረ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ በማህጸኗ እና በመቀመጫዋ ደፍሯታል 😭

ያደረሰባት ጉዳት እጅግ አስከፊ ከመሆኑ የተነሳ የጀርባ አጥንቷ እስኪታይ ድረስ ማህጸኗ ተጎድቷል። ወንጀለኛው ይህን ዘግናኝ ወንጀል ከፈጸመ በኋላ በሳፋ ውስጥ ያጠባት ሲሆን፥ ወድቃ የሞተች ለማስመሰል ገላዋን በምላጭ ተልትሎታል 😭

በስተ መጨረሻም የፈጸመው እርኩስ ወንጀል እንዳይጋለጥበት አንቆ ገድሏት እንደ ተጣለ እቃ የቤቱ ደጃፍ ላይ ጥሏታል። በሃይል ከማንቁ የተነሳ የልጅቱ አስክሬን ሲገኝ አንገቷ ውስጥ ጣቶቹ የሰረጎደበት ምልክት ተገኝቷል 😭

በአሁን ሰአት ላይ ወንጀለኛው ማረሚያ ቤት ውስጥ ቢገኝም የመንግስት አካላት በይግባኝ ሊያስፈቱት እንቅስቃሴ ጀምረዋል። የወንጀለኛውም ቤተሰቦች የልጅቱን እናት እያስፈራሯት በመሆኑ ሕዝብ ይፋረደኝ ብላ ሚድያ ላይ ወጥታለች 😭

▶️ እግዚአብሔር አምላክ የተጎጂዋን ቤተሰቦች እንባ እንዲያብስና ወንጀለኛውንና ተባባሪዎቹን እንዲፈርድባቸው እንማጸነዋለን! በየትኛውም ነገር ከተጎጂዎቹ ጋር መቆም የምንችል ሰዎች አብረናቸው እንቁም! 😭

♦️ እግዚአብሔር የሕጻን ሔቨንን ነፍስ በመንግሥተ-ሰማይ ያኑርልን!

Isaiah 48 Apologetics

12 Aug, 02:59


🚩 የዕንባቆም 1:12 ዕብራይስጥና አብዱሉ

በዕን 1:12 ላይ እግዚአብሔር ከዘላለም ጀምሮ እንደነበርና፥ ሰዎቹም እንደማይሞቱ ነብዩ ሲገልጽል እንመለከታለን። የክፍሉ ቀጥተኛና ተፈጥሯዊ ንባብ ይህ ነው። ነገር ግን አንድ ታዋቂ የሙስሊም ዓቃቢ-እምነት ነኝ ባይ ዕን 1:12 አንሞትም ሳይሆን አትሞትም ማለት ነው ብሎ ለመተርጎም ዳድቶታል፦

"አቤቱ፥ የተቀደስህ አምላኬ ሆይ፥ አንተ ከዘላለም ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ #አንሞትም፤ አቤቱ፥ ለፍርድ ሠርተኸዋል፥ ለተግሣጽም አድርገኸዋል" (ዕንባቆም 1:12)

הלוא אתה מקדם יהוה אלהי קדשי #לא_נמות יהוה למשפט שמתו וצור להוכיח (Hab 1:12)

ይህ አብዱል ዕን 1:12 የተረጎመበት መንገድ ፍጹም ብሉይ ኪዳን ለተጻፈበት የዕብራይስጥ ቋንቋ ባዕድና እንግዳ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ዕን 1:12 የአማርኛውና የኢንግሊዘኛው ትርጉሞች እንዳስቀመጡት "አንሞትም" ወይም "we shall not die" ተብሎ ሳይሆን "አትሞትም" ወይንም "you shall not die" ተብሎ ነው መተርጎም ያለበት ብሏል። ይህ እጅግ የአላዋቂዎች ስህተት ነው።

▶️ በመጀመሪያ ደረጃ በዕን 1:12 ላይ "לא נמות/ሎ ናሙት" ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ "እንዳንሞት" ተብሎ ተተርጉሟል፦

"እንዲህም አለ። እነሆ ስንዴ በግብፅ እንዲገኝ ሰምቼአለሁ፤ ወደዚያ ውረዱ፥ እንድንድንና #እንዳንሞትም ከዚያ ሸምቱልን" (ዘፍ 42:2)

ויאמר הנה שמעתי כי יש־שבר במצרים רדו־שמה ושברו־לנו משם ונחיה #ולא_נמות (Gen 42:2)

በዚህ ስፍራ የዮሴፍ አባት ያዕቆብ በግብፅ እህል እንዳለ በሰማ ጊዜ እንዳይሞቱ ምግብ እንዲገዙ ወደ ግብፅ ሲልካቸው እናነባለን። ሲልካቸው "እንዳንሞት" ሲል የተጠቀመው የዕብራይስጥ ሀረግ "לא נמות/ሎ ናሙት" የሚለው ሲሆን በዕን 1:12 ላይ ያለው ራሱ ሀረግ ነው። ትርጉሙም እንዳንሞት እንጂ እንዳትሞት ማለት አይደለም። የብዙ አካላትን አለመሞት የሚጠቁም ሀረግ እንጂ የነጠላ አካልን አለመሞት የሚያመለክት ሀረግ አይደለም። አብዱሉ ይህ ሀረግ የነጠላ አካልን አለመሞት ያሳያል ማለቱ የቋንቋውን አላዋቂነት ያሳያል

✏️ በዕብራይስጥ ቋንቋ "እንሞታለን" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "נמות/ናሙት" ሲሆን በድርብ ግስ ተናጋሪው ራሱን ከሌሎች አካላት ጋር በመጨመር እርሱም እነዚያም አካላት እንደሚሞቱ ለመግለጽ ወይንም ደግሞ ከአንድ በላይ አካላት ራሳቸውን አስመልክቶ እንደሚሞቱ ለመግለጽ ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው።

ለምሳሌ፦

"እነሆም፥ ሐሜትና ደስታ በሬውንና በጉንም ማረድ ሥጋንም መብላት የወይን ጠጅንም መጠጣት ሆነዋል፤ እናንተ። ነገ #እንሞታለንና እንብላ እንጠጣ ብላችኋል" (ኢሳ 22:13)

והנה ששון ושמחה הרג בקר ושחט צאן אכל בשר ושתות יין אכול ושתו כי מחר #נמות (Is 22:13)

በዚህ ስፍራ ላይ በኢየሩሳሌም ያሉ ሰዎች እንደሚሞቱ መናገራቸውን ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለው የዕብራይስጥ ቃል "נמות/ናሙት" የሚለው ቃል ነው። ስለዚህ ይህ ቃል ብዙ አካላት እንደሚሞቱ ለማመልከት ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ነው ማለት ነው።

ሌላ ምሳሌ፦

"አሁን እንግዲህ ይህች ታላቂቱ እሳት ታቃጥለናለችና ለምን #እንሞታለን? እኛ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ ደግሞ ብንሰማ እንሞታለን" (ዘዳ 5:25)

ועתה למה #נמות כי תאכלנו האש הגדלה הזאת אם־יספים אנחנו לשמע את־קול יהוה אלהינו עוד ומתנו (Deut 5:25)

በዚሁ ቦታም እንዲሁ በሲና ተራራ ላይ የእስራኤል ሕዝብ የእግዚአብሔር ድምፅ እየሰሙ ከቀጠሉ እንሞታለን ማለታቸውን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለው ቃል ይኸው "נמות/ናሙት" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል ነው። ስለዚህ ይህ ቃል ብዙ አካላት እንደሚሞቱ ለመግለጽ ጥቅም ላይ የሚውል ቃል ለመሆኑ ይህ ሌላኛው ማሳያ ነው።

♦️ ብዙ አካላት እንደሚሞቱ የሚገልጸው የዕብራይስጥ ቃል ይህ ሲሆን፥ ከዚህ በተቃራኒው አለመሞታቸውን ለመግለጽ ከዚህ "נמות/ናሙት" ከሚለው ቃል ፊት ለፊት "לא/ሎ" የሚለው ቃል ከፊቱ እንደ prefix ይገባል። "לא/ሎ" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል "not" የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን (Strong's H3808) ተቃራኒነትን፥ የአንድ ነገር አለመሆንን ለማመልከት ከግሶች በፊት ይገባል።

ለምሳሌ፦

"ይሁዳም አባቱን እስራኤልን አለው። እኛና አንተ ልጆቻችንም ደግሞ እንድንድን እንዳንሞትም ብላቴናውን ከእኔ ጋር ስደደው፥ እኛም ተነሥተን #እንሄዳለን" (ዘፍ 43:8)

ויאמר יהודה אל־ישראל אביו שלחה הנער אתי ונקומה #ונלכה ונחיה ולא נמות גם־אנחנו גם־אתה גם־טפנו (Gen 43:8)

በዚህ ስፍራ ላይ ይሁዳ ከቢንያም ጋር እንደሚሄዱ ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለው ቃል "נלכה/ንላኻ" የሚለው ቃል ነው። ከአንድ በላይ አካላት እንደሚሄዱ ከሚገልጹት የዕብራይስጥ ቃላት አንዱ ይህ ቃል ነው

✍️ ይኸው ራሱ የዕብራይስጥ ቃል አለመሄድን እንዲያመለክት ሲፈለግ ግን "לא/ሎ" የሚለው ቃል ከፊት ለፊቱ እንደ prefix ይገባል፦

"እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን። #አንሄድባትም አሉ" (ኤር 6:16)

כה אמר יהוה עמדו על־דרכים וראו ושאלו לנתבות עולם אי־זה דרך הטוב ולכו־בה ומצאו מרגוע לנפשכם ויאמרו #לא_נלך (Jer 6:16)

በዚህ ስፍራ ላይ በነቢዩ ኤርምያስ ዘመን የነበሩ አይሁድ በቅኑ መንገድ ላይ አንሄድም ማለታቸው ተገልጾ እንመለከታለን። በዚህ ስፍራ ላይ አለመሄዳቸው የተገለጸው በዘፍ 43:8 ላይ ያለው "נלכה/ንላኻ" የሚለው ቃል ተጠቅሶ ከፊት ለፊቱ "לא/ሎ" የሚለው ቃል እንደ prefix ገብቶ ነው። ስለዚህ እንደማይሄዱ ለማመልከት እንሄዳለን ከሚለው ቃል ፊት ለፊት ያ ቃል እንደ prefix ገብቷል። ይህ "לא/ሎ" የሚለው ቃል እንደ prefix ሲገባ ተቃራኒነትን፥ ያ ነገር አለመሆኑን እንደሚገልጽ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ነው።

ሌላ ምሳሌ፦

"ሕዝቡም። ምን #እንጠጣለን? ብለው በሙሴ ላይ አንጐራጐሩ" (ዘጽ 15:24)

וילנו העם על משה לאמר מה #נשתה (Ex 15:24)

በዚህ ቦታ ላይ የእስራኤል ሕዝብ ሙሴን ምን እንጠጣለን ብለው ሲያንጎራጉሩበት እንመለከታለን። መጠጣታቸውን የሚገልጸው የዕብራይስጥ ቃል "נשתה/ናሽታህ" የሚለው ቃል ነው። ከአንድ በላይ አካላት እንደሚጠጡ የሚገለጽ የዕብራይስጥ ቃል ነው

✍️ ይኸው ራሱ የዕብራይስጥ ቃል አለመጠጣትን እንዲያመለክት ሲፈለግ ግን "לא/ሎ" የሚለው ቃል ከፊት ለፊቱ እንደ prefix ይገባል፦

"21-22 እስራኤልም። በምድርህ ላይ እንለፍ፤ ወደ እርሻና ወደ ወይን ቦታ አንገባም፤ ከጕድጓድም ውኃን #አንጠጣም፤ ከምድርህ ዳርቻ እስክንወጣ ድረስ በንጉሥ ጐዳና እንሄዳለን ብለው ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልእክተኞችን ላኩ" (ዘኍ 21:21-22)

אעברה בארצך לא נטה בשדה ובכרם #לא_נשתה מי באר בדרך המלך נלך עד אשר נעבר גבלך (Num 21:21-22)

Isaiah 48 Apologetics

12 Aug, 02:59


በዚህ ስፍራ ላይ እስራኤላውያን ለሴዎን ንጉስ ከጉድጓድ ውሃ እንደማይጠጡ መልእክት እንደላኩለት እናነባለን። በዚህ ስፍራ ላይ አለመጠጣታቸው የተገለጸው በዘጽ 15:24 ላይ ያለው "נשתה/ናሽታህ" የሚለው ቃል ተጠቅሶ ከፊት ለፊቱ "לא/ሎ" የሚለውን ቃል እንደ prefix ገብቶ ነው። ስለዚህ እንደማይጠጡ ለማመልከት እንጠጣለን ከሚለው ቃል ፊት ለፊት ያ ቃል እንደ prefix ገብቷል። ይህ "לא/ሎ" የሚለው ቃል እንደ prefix ሲገባ ተቃራኒነትን፥ ያ ነገር አለመሆኑን እንደሚገልጽ የሚያረጋግጥ ሌላ ማስረጃ ነው።

♦️ በዕን 1:12 ላይ አለመሞታቸውን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለው ቃል "נמות/ናሙት" የሚለው ሲሆን ከፊት ለፊቱ "לא/ሎ" የሚለው ቃል እንደ prefix ገብቷል። ስለዚህ ቃሉ በትክክል "አንሞትም" ወይም "we will not die" ተብሎ ነው መተርጎም ያለበት። እንጂ በፍጹም "አትሞትም" ተብሎ አይተረጎምም።

ይህንንም ሀቅ ዕውቅ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አረጋግጠውታል፦

"12 Art thou not from everlasting, O LORD my God, mine Holy One? #we_shall_not_die. O LORD, thou hast ordained them for judgment; and, O mighty God, thou hast established them for correction." (Hab 1:12 KJV)

"Art not thou from everlasting, O Jehovah my God, my Holy One? #we_shall_not_die. O Jehovah, thou hast ordained him for judgment; and thou, O Rock, hast established him for correction" (Hab 1:12 ASV)

"Art thou not from everlasting, Jehovah my God, my Holy One? #We_shall_not_die. Jehovah, thou hast ordained him for judgment; and thou, O Rock, hast appointed him for correction" (Hab 1:12 DET)

"Wast thou not from the beginning, O Lord my God, my holy one, and #we_shall_not_die? Lord, thou hast appointed him for judgment: and made him strong for correction" (Hab 1:12 DRB)

"Art thou not from everlasting, O LORD my God, my Holy One? #We_shall_not_die. O LORD, thou hast ordained them for judgment; and O mighty God, thou hast established them for correction" (Hab 1:12 NWB)

"Aren`t you from everlasting, Yahweh my God, my Holy One? #We_will_not_die. Yahweh, you have appointed him for judgment. You, Rock, have established him to punish" (Hab 1:12 WEB)

"Art not Thou of old, O Jehovah, my God, my Holy One? #We_do_not_die, O Jehovah, For judgment Thou hast appointed it, And, O Rock, for reproof Thou hast founded it" (Hab 1:12 YLT)

▶️ ከኢንግሊዘኛ ትርጉሞች ባሻገር የአዲሱ መደበኛ ትርጉምም እንዲሁ "አንሞትም" በማለት ነው የተረጎመው፦

"እግዚአብሔር ሆይ፤ ከዘላለም ጀምሮ ያለህ አይደለህምን? የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ #እኛ_አንሞትም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲፈርዱ ሾመሃቸዋል፤ ዐለት ሆይ፤ ይቀጡ ዘንድ ሥልጣን ሰጠሃቸው" (ዕንባቆም 1:12 አ.መ.ት)

ስለዚህ የዕን 1:12 ትክክለኛ ትርጉም "አንሞትም" የሚለው እንጂ ለዕብራይስጥ እንግዳ የሆነው አብዱል የተረጎመበት መንገድና የሰጠው ትርጉም አይደለም።

♦️ አብዱሉ ዕን 1:12ን የተተረጎመበት መንገድ ትክክል የሚሆነው የዕብራይስጡ ቃል "תמות/ታሙት" የሚለው ቢሆን ኖሮ ነበር። "תמות/ታሙት" የሚለው አንድ ነጠላ አካልን የሚያመለክት ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ትሞታለህ" ማለት ነው። በዚሁ ቃል ተንተርሶ "አትሞትም" ማለት ካስፈለገ ደግሞ ከፊት ለፊቱ "לא/ሎ" የሚለው ቃል prefix ሆኖ ይገባል። ያኔ "አትሞትም" የሚል ትርጉም ይኖረዋል

ለምሳሌ፦

"እግዚአብሔርም። ሰላም ለአንተ ይሁን፤ አትፍራ፤ #አትሞትም አለው" (መሳ 6:23)

ויאמר לו יהוה שלום לך אל־תירא #לא_תמות (Jud 6:23)

በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔር ጌዴኦንን እንደማይሞት ነግሮት ሲያረጋጋው እንመለከታለን። ጌዴኦን አንድ ነጠላ አካል ሲሆን እሱ እንደማይሞት ለማመልከት "לא/ሎ" የሚለው ቃል ከፊት ለፊቱ እንደ prefix ገብቶ ጥቅም ላይ የዋለው ቃል "תמות/ታሙት" የሚለው ቃል ነው። አብዱሉ ዕን 1:12 የተረጎመበት መንገድ ትክክል የሚሆነው ዕን 1:12 ልክ እንደዚህ ክፍል ይህን ቃል ቢጠቀም ነበር። ቅሉ ግን አልተጠቀመውም።

ሌላ ምሳሌ፦

"ንጉሡም ሳሚን። #አትሞትም አለው። ንጉሡም ማለለት" (2ሳሙ 19:23)

ויאמר המלך אל־שמעי #לא_תמות וישבע לו המלך (2Sam 19:23)

በዚህ ቦታ ላይ ንጉስ ዳዊት ሳሚን እንደማይሞት ሲነግረው እንመለከታለን። ሳሚ አንድ ነጠላ አካል ሲሆን እሱ እንደማይሞት ለማመልከት "לא/ሎ" የሚለው ቃል ከፊት ለፊቱ እንደ prefix ገብቶ ጥቅም ላይ የዋለው ቃል "תמות/ታሙት" የሚለው ቃል ነው። አብዱሉ ዕን 1:12 የተረጎመበት አተረጓጎም ትክክል የሚሆነው ዕን 1:12 ይህን ቃል ይህ ክፍል እንደተጠቀመው ቢጠቀመው ነበር። ነገር ግን አልተጠቀመውም።

ዕን 1:12 ላይ "תמות/ታሙት" የሚለው ይህ ቃል ከፊቱ "לא/ሎ" የሚለው prefix ኖሮ ጥቅም ላይ ቢውል ኖሮ ክፍሉ ልክ ከላይ እንዳየናቸው ሌሎች ክፍሎች "አትሞትም" ተብሎ ይተረጎም ነበር። ዕን 1:12 ግን በ"תמות/ታሙት" ፋንታ "נמות/ናሙት" የሚለውን ቃል ስለሆነ የሚጠቀመው ትክክለኛው ሰዋሰዋዊ አተረጓጎም "አንሞትም" የሚለው ነው።

📮 በዕን 1:12 ላይ "נמות/ናሙት" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል በብሉይ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ የነጠላ አካልን ሞት ወይም አለመሞት አመልክቶ አያውቅም። ሁሌም ቢሆን ጥቅም ላይ የዋለው ከአንድ በላይ የሆኑ አካላትን መሞት ወይም አለመሞት ለማመልከት ነው። ለዚህም ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል

አብዱሉ ግን እሟገትበታለሁ ብሎ የተነሳውን ቋንቋ ስለማያውቅ እንዲህ አይነቱን የጀማሪ ስህተት ሰርቷል!

✍️ ተዋረድ ያለው አብዱል ዕብራይስጥ ይጠቅሳል!