ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ @ortodoxtewahedo Channel on Telegram

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

@ortodoxtewahedo

ይህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዶግማንና ቀኖናን ትውፊትን እንዲሁም አስተምሮን የጠበቁ የተለያዩ የሚያስተምሩ ነገሮች ይለቀቁበታ፡፡ በተጨማሪ በ youtube #subscribe በማድረግ አገለግሎቱን ይደግፉ።

‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ››
ት.ኢሳ 58÷3
https://youtu.be/csxxAMGtC4I
ለመቀላቀል
http://t.me/ortodoxtewahedo

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (Amharic)

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ዮሐንስ ቀኖና ከአስተምሮን የጠበቁ ትውፊትን መምረጥና ወቅታ፣ እንዴት ከመረጋገጥ ጀምሮ አለበት። በቻናልው በ youtube ያለው ስራዎችን ለመቀላቀል እና በተጨማሪም ተጨማሪ አገለግሎቱን ብቻ ይመዝገቡ። በት.ኢሳ 58÷3 ማድረጉን ይበልጥ። ማለትም የትውፊቱን ከፈለፈበ የሆነ የተለያዩ አገልግሎት በዚህ መረጃ ያግኙ።

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

23 Nov, 19:50

💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

23 Nov, 19:10

በግምት ከሌሊቱ 8 ሰአት ገደማ ነው ሶስት ጓደኛማቾች እንደ ለመደባቸው ቅዳሜን ወጥተው ክለብ ለክለብ እየተዝናኑ ሰአታትን አስቆጥረዋል እንደ አጋጣሚ ሆኖ እጃቸው ላይ ያለውን ብር የትራንስፖርት እንኳን ሳያስከሩ መጨረሳቸውን ያስተዋሉት ከረፈደ ነበር ያው የሁልጊዜ ቤታችን ስለሆነ ዱቤ ይሠጡናል ብለው አስተናጋጁን ይጠሩትና የተፈጠረውን ያስረዱታል እንደ አጋጣሚ ሆኖ ሞባይል ባንኪንግ የማይጠቀሙበትን ተቀያሪ ስልካቸውን እንደያዙና እጃቸው ላይ በዚህ ሰአት ምንም ብር እንደሌላቸው ይነግሩታል እሱም ወደ ማናጀሩ መሄድ ሲጀምር.....see more

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

23 Nov, 18:25

ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡

በሌላ አገላለጽ ብነግራችኹ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡

እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

23 Nov, 18:01

📷 እርግጠኛ ነኝ ፕሮፍይሎን ለመቀየር ፈልገው ፕሮፍይል የሚያደርጉት ጠፍቶ  ተቸግረው ያውቃሉ።

የናንተን ችግር ለመፍታት በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ መንፈሳዊ ቻናል ይዘንላችሁ መተናል ከናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ join ማድረግ ብቻ ነው👇👇👇👇👇👇📷

https://t.me/addlist/gpX29GzfGs43MWE0

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

23 Nov, 17:03

🤔 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ⁉️

📌 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
📌 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
📌 ዘማሪ ዲ/ን ሮቤል ማቲያስ
📌 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ
📌 ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
📌 ዘማሪት ዶ/ር ሔለን ተስፋዬ

እና የሌሎችንም ...........

ዘማሪዎችን መዝሙሮች እና አዳዲስ
መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር OPEN
የሚለውን ይጫኑት። 👇

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
█ ▒ ░✞ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ❖ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ✞░ ▒ █
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

23 Nov, 16:36

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

23 Nov, 16:36

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስና ኢትዮጵያን በቅንነት ያገለገሉ ባለውለታዎች በግፍ የተገደሉበት ሃምሳኛ ዓመት የጸሎት ሥነ ሥርዓት ተካሄደ፡፡

የጸሎት ሥነ ሥርዓቱ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ኅዳር 14 ቀን 2017 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን ሃምሳኛ ዓመታቸው የተዘከረላቸው ሰማዕታት ኅዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም በደርግ የተገደሉ አባቶች እና ሐምሌ 7 ቀን 1971 ዓ.ም ከእስር ቤት በሰንሰለት እየታሰሩ ተወስደው የተገደሉ ናቸው፡፡

ከሰብአዊነት ውጭ በሆነ በግፍና በሚያሰቅቅ ሁኔታ በገመድ ታንቀው የተገደሉት ሁለተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስም በወቅት ከተገደሉት ሰማዕታት ውስጥ ናቸው፡፡

ኅዳር 14 ቀን 1967 ዓ.ም የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ሲቪል ባለሥልጣናት፣ ወታደራዊ መኮንኖችና ከዐምስት ዓመት በኋላ በ1971 ዓ.ም በሰንሰለት እየታሠሩ በግፍና በስቃይ በደርግ የተገደሉት አባቶች የመታሰቢያ ሐውልትና ዐጽማቸው ያረፈበት ቦታ በዘመናዊ አሠራር ለጉብኝት በሚያመች ሁኔታ በመንበረ ጸባዖት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተሠርቶላቸዋል፡፡

በ1971 ዓ.ም የተሰውት የሰማዕቱ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ዐጽም ሐምሌ 4 ቀን 1984 ዓ.ም አሟሟታቸውንና የት እንደተቀበሩ በዐይኑ ባየ በወቅቱ የደርግ ደኅንነት ክፍል ወታደር ጥቆማ ወጥቶ ሐምሌ 4 ቀን 1984 ዓ.ም በጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በክብር አርፏል፡፡

በጸሎት ሥነ ሥርዓቱ ላይ የእንግሊዝና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ፣ የምሥራቅ ጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ እና የቀድሞ የኢፌድሪ ፕሪዚዳንት ክብርት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ተገኝተዋል፡፡

ዘገባው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት ነው ።

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

23 Nov, 16:31

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

23 Nov, 16:31

ጾመ ነቢያት !

ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው።

ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው።

ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፤

፩.  ጾመ አዳም:- አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገት ከተባረረ በኋላ; በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ፤ አለቀሰ (እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ) ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ ‹‹ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በደጅህ ድኼ፣ በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡›› የሚል ነው፡፡ /ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ/ ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት ‹‹ጾመ አዳም›› ይባላል፡፡

፪. ጾመ ነቢያት:- ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው፣ ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች: ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም: ቅዱስ ሙሴ: ቅዱስ ኤልያስ፣ ቅዱስ ዳንኤል ና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: (ዘዳ 9:19, ነገ. 19:8, ዳን. 9:3፣ መዝ. 68:10, 108:24) ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል::

፫. ጾመ ሐዋርያት:- ሐዋርያት ‹‹ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን፣ ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?›› ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡

፬. ጾመ ማርያም:-  እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና ‹‹ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?›› ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና ‹‹ጾመ ማርያም›› ይባላል፡፡

፭. ጾመ ፊልጶስ:- ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት፤ አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ፤ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል፤ ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡

፮. ጾመ ስብከት:- የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡

፯. ጾመ ልደት:- የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት ስለሆነ ‹‹ጾመ ልደት›› ይባላል፡፡

ጾምን ትእዛዝ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን የፍቅርና የበረከት ምንጭ በመሆኑ ጭምር ደስ እያለን ብንጾመው የቅዱሳኑ በረከት ያድርብናል፡፡ ፆመ ነብያት ወይም የገና ፆም ሐሙስ ህዳር 15 ይጀምራል ታህሳስ 29 ይፈታል።

ሀገራችንም ሃገረ ሰላም እንድትሆን እና ለእኛ ለህዝቦቻ መተሳስብ ፍቅር አንድነቱን እንዲያድለን ወደ ፈጣሪያችን አብዝተን እንፀልይ !!!

@ortodoxtewahedo

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

23 Nov, 16:29

23 Nov, 16:28

ነቢያት ጌታ "ይወርዳል ይወለዳል" ብለው የተናገሩት ትንቢት እንዲፈጸም ተመኝተው ጾሙ ጸለዩ:: እኛ ስለምን እንጾማለን? ክርስቶስ ተወልዶ ፣ ተጠምቆ ፣ አስተምሮ ፣ ተሰቅሎ ፣ ሞቶ ፣ ተነሥቶ ፣ ዐርጎ ፣ በአባቱ ቀኝ አይደለምን? አሁን ለምን እንጾማለን? ብለን እናስባለን::

ጌታ በእኔና አንተ ልብ ውስጥ እውነት ተወልዶአልን? እውነት የእኛ ልብ እንደ ቤተልሔም ግርግም ለክርስቶስ ማደሪያ ሆኖአል? ማደሪያ አሳጥተን ከእናቱ ጋር አልመለስነውም?

የጥምቀቱ ትሕትና በእኛ ልብ መቼ ደረሰ? የስቅለቱ ሕማም መች በእኛ ሕሊና ተጻፈ? የትንሣኤው ተስፋ የዕርገቱ ልዕልና በእኛ ልቡና መቼ ዐረፈ?

ስለዚህ ነቢያት "ውረድ ተወለድ" ብለው የጾሙትን ጾም እንጾማለን:: ጌታ ሆይ በእኔ ሕይወትም ውስጥ ውረድ ተወለድ የእኔን ሰውነት ማደሪያህ አድርገው:: ሕዋሳቶቼ ከኃጢአት አርፈው እንደ ቤተልሔም ግርግም ማደሪያህ ይሁኑ:: 

የቤተልሔም እንስሳት ትንፋሽ ገበሩልህ ፣ የቢታንያ ድንጋዮች ዘማሪ ቢጠፋ ሊዘምሩ ዝግጁ ነበሩ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለክብርህ ተቀደደ ፣ ጨረቃ ላንተ ደም ለበሰች ፣ ፀሐይ ስላንተ ጨለመች ፣ ከዋክብት ለስምህ ረገፉ ፣ ዓለቶች ለፍቅርህ ተሰነጠቁ::

ከቤተልሔም እንስሳት ፣ ከቢታንያ ድንጋዮች ፣ ከቤተ መቅደስ መጋረጃ እኔ እንዴት አንሼ ልገኝ? የቢታንያ ድንጋይ ያወቀህን ያህል ሳላውቅህ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ የተረዳህን ያህል ሳልረዳህ እንዴት ልኑር? 

ዓለት ላንተ ሲሰነጠቅ የኔ ልብ ለምን ከዓለት ደነደነ? ጨረቃ ደም ስታለቅስ እኔ መከራህ ለምን አልተሰማኝም?
ሙታን በሞትህ ሲነሡ እኔ ምነው ከኃጢአት ሞት መነሣት ተሳነኝ?

ለዚህ ነው በእኔ ሕይወት ገና አልተወለድክም የምለው::

ስለዚህ ጌታ ሆይ የነቢያትህን ጾም ጸሎት ሰምተህ የወረድህ የተወለድህ ጌታ ሆይ በእኔም ሕይወት ውረድ ተወለድና እኔም ከመላእክት ጋር አብሬ ልዘምር ፣ ከሰብአ ሰገል ጋር ሥጦታህን ልቁጠር ፣ ከእረኞች ጋራ ልደነቅ:: ልደትህ ሳይገባኝ ምጽዓትህ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ::

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)

@ortodoxtewahedo

#ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
   ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል 👉 
@ortodoxtewahedo

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

23 Nov, 16:28

መሰረቷ ጉልላቷ እሱ ነው ሙሽራዋም መስቀል ላይ የሞተው ዛሬም ነገም ያውነው ለዘላለም አትንገሩን አዲስ ጌታ የለም

#ሊቀ መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ

ለመቀላቀል
👉 @ortodoxtewahedo

is the foundation, the dome, and the bridegroom died on the cross. Don't tell us today, tomorrow, forever. There is no new Lord.

#Choir Tedros Yosef

to join
👉 @ortodoxtewahedo

📔📒📕📗📘📙📙📚📔

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

23 Nov, 16:28

"እግዚአብሔር አምላክ ለአገልጋዮቹ የሚልቅ ጸጋን ከሰጠ፣ የሚነኩት ኹሉ ሰው ከበሽታው ከተፈወሰ፤ ጥላቸው ያረፈበት ተዓምር ከተፈጸመለት፤ ጴጥሮስ በጥላው ካደነ፤ የጳውሎስ የልብሱ ጨርቅ ዕራፊ መናፍስትን ካወጣ ከሁሉ ለምትልቅ እናቱማ ምን ዓይነት ሥልጣንና ኃይል ተሰጥቷት ይሆን?"

#ቅዱስ_ባስልዮስ

"If the Lord God gives great grace to His servants, if everyone they touch is healed of the disease, if a miracle is done for them to rest in their shadow, if Peter is hunted by the shadow, if the fabric of Paul's clothes casts out evil spirits, what kind of authority and power has been given to the greatest mother?"

#Saint_Basilios

ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ

23 Nov, 16:28

@ortodoxtewahedo