መንፈሳዊ ጉባኤ @menfesawi_gubae Channel on Telegram

መንፈሳዊ ጉባኤ

@menfesawi_gubae


ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ነውርም የለብሽም።
መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 4 : 7

@Menfesawi_Gubae

ጥያቄ ካላችሁ ከታች ባለው አድራሻ መጠየቅ ትችላላችሁ።

@HenokAsrat3

መንፈሳዊ ጉባኤ (Amharic)

ወዳጄ ሆይ፥ ሁለንተናሽ ውብ ነው፥ነውርም የለብሽም። መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 4 : 7nnመንፈሳዊ ጉባኤ ማንኛውም ሰው በአማርኛ የተጠቀሰ ሲሆን፣ እንዴት ተወዳጆኗል? የሚቀጠለው አስተማሪ እርስዎ ምንድን ነው? መንፈሳዊ ጉባኤ ማንኛውም የታሪፍ ድምፅ ቅንብሮ በወዳጅ መስመር ሲሆን፣ እንዴት ተወዳጆኗል? ይህ ፋብሪካም ሚስትት ወዳጅነትን ማንኛውም ልጅ በሚቀጥለው በአማርኛ የተፃፃው ነው።nnመንፈሳዊ ጉባኤ በየአመቱ በወዳጅ መስመር በሆኖ አንደኛውን መነሻ ይኖራል። የዚህ ፋብሪካም ሚስትት እይይታና ማህበረሰብ በሚፈጥረው ጊዜ ማንም አይወዳደርም።nnየመንፈሳዊ ጉባኤ ፋብሪካም መንፈሳዊ መንፈሳዊ ሃይማኖታዊ ወራትን መረጃና እርዳታ ሊፈጽማቸው እንደሆነ ለማቅረብ አሳልፌ ይህን ቦታን ይምረጡ።nnመንፈሳዊ ጉባኤ በመንፈሳዊ አማርኛ ፊደል በክሊንት አስተማሪዎችን እና መንፈሳዊ በቆሎ ሕጡእቶቹን የማይበኩት ነገር ነው።

መንፈሳዊ ጉባኤ

06 Jan, 16:47


ቀዳማዊ ልደቱ ጥንትና ፍጻሜ የሌለው የማይመረመር ስለሆነ ቀዳማዊ ልደቱን ለመግለፅ ቅድመ ዓለም ያለ እናት ከአብ እንደ ተወለደ ድኅረ ዓለምም ከእመቤታችን /እንበለ ዘርዓ ብዕሲ/ ያለ አባት ተወለደ፡፡ እሱም እመቤታችን ያለ አባት የወለደችው ፤ እግዚአብሔርም ያለ እናት የወለደው ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ሰባቱ መስተጻርራን /ተቃራኒ ነገሮች አንድ ሆነዋል ሕዝብና አሕዛብ ፤ በጠብና በክርክር ይፈላለጉ የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ በጌታችን ልደት ታርቀዋል
፡፡ ይኸውም ሊታወቅ ከዚህ አስቀድሞ ቤተ መቅደሱን ለማፍረስ ንዋየ ቅድሳቱን ለመዝረፍ ሕዝቡን ለመማረክ ምታ ነገሪት ብለው ይመጡ የነበሩ የሩቅ ምስራቅ /የፋርስ የባቢሎን ሰዎች በጌታችን ልደት ምክንያት ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤ "አይቴ ሃሎ ዘተወልደ ንጉሠ አይሁድ የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው" (ማቴ.2፥4) እያሉ መጥተው ወርቅ፣ እጣን፣ ከርቤ ገብረውለታል፡፡

  ነፍስና ሥጋ፡- በሲዖልና በመቃብር ተለያይተው የነበሩ ነፍስና ሥጋ ከእመቤታችን ከነፍሷ ነፍስ ከሥጋዋ ሥጋ ነሥቶ በተዋሕዶ ሰው በሆነ ጊዜ ነፍስና ሥጋን አስታርቋል፡፡
ሰውና እግዚአብሔር፡- አባታችን አዳም አትብላ የተባለውን ዕፀ በለስ በልቶ የሰውና የእግዚአብሔር የፍቅር ግንኙነት ለአምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ተቋርጦ ነበርና ጌታችን የሰውን ሥጋ ተዋሕዶ በተወለደ ጊዜ እርቀ ሰላም ተገኝቷል፡፡

ሰውና መላእክት፡- አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ጋር በተጣላ ጊዜ ቅዱሳን መላእክትም ስለተጣሉት በምትገለባበጥ ሰይፈ እሳት አስፈራርተው ከገነት ካስወጡት በኋላ ወደ ገነትም እንዳይገባ ገነትን ይጠብቁ ነበር፡፡ ጌታችን በተወለደ ጊዜ አንድ ሆነው ዝማሬ አቅርበዋል፡፡ ይኸውም ዮም አሐደ መርኤተ ኮኑ መላእክት ወሰብእ ከመ ይሰብህዎ ለክርስቶስ እንዲል፡፡ ሰውና መላእክት ክርስቶስን ለማመስገን አንድ ሆኑ እንዳለ ሊቁ፡፡

  ቤተ ክርስቲያን ፤ ጌታችን የተወለደባት እና ሰባቱ መስተጻርራን አንድ የሆኑባት፤ ሰውና መላእክት የዘመሩባት የብርሃን ጎርፍ የጎረፈባት እንስሳት እስትንፋሳቸውን የገበሩባት ቤተልሔም በቤተ ክርስቲያን ትመሰላለች፡፡

  ቤተልሔም፡- ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ ፤ ሰውና እግዚአብሔር ፤ ነፍስና ሥጋ ፤ ሰውና መላእክት አንድ ሆነው በቤተልሔም እንደዘመሩ ዛሬም የፍቅር ተምሳሌትና የአማኞች ሁሉ እናት በሆነችው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በዘር፣ በጎሣ፣ በጥቅም፣ በሥልጣን ሳንከፋፈል አንዲት ቤተ ክርስቲያንን በፍቅር እንድናገለግል በቤተልሔም የተደረገው የልደቱ ምሥጢር ይህን ያስተምረናል፡፡
ክርስቲያኖች የጌታን መወለድ የምናስበው በዚህ መንፈስ ነው፡፡
መልካም የልደት በዓል ይሁንልን አሜን !!!
      ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖❖ ❖ ❖
  💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫   
        ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖❖ ❖ ❖
❖ ❖ ❖ የልደት በዓል ማኅሌት  ❖ ❖ ❖
           ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
ርእይዎ ኖሎት አእኮትዎ መላእክት ፤
ለዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል፤
ዮም ሰማያዊ በጎል ሰከበ፡፡
ትርጉም፦ ቅድስት ድንግል ከሆነች ማርያም የተወለደውን እረኞች አዩት መላእክትም አመሰገኑት፤ እነሆ ዛሬ ሰማያዊው በበረት ተኛ፡፡
          ❖ ❖ ❖ ንግሥ ❖ ❖ ❖
ሰላም ለልደትከ ኦ አማኑኤል፤
ዘቀዳሚ ወዘደኃሪ ብሉየ መዋዕል፤
ኢየሱስ ክርስቶስ ዘአብ ቃል፤
እፎ እፎ አግመረተከ ድንግል፤
ወእፎ እንዘ አምላክ ሰከብከ በጎል፡፡
ትርጉም፦ በዘመናት የሸመገልክ መጀመርያና መጨረሻ የሆንክ አማኑኤል ሆይ ለልደት ሰላም እላለሁ የአብ ቃል የሆንክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ድንግል እንዴት ተሸከመችህ? አምላክስ ስትሆን እንዴት በበረት ተኛህ?
          ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ፤
ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኀደረ፤
እፎ ተሴሰየ ሐሊብ ከመ ሕፃናት፡፡
ትርጉም፦ በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ፤ በድንግል ማኅፀንም አደረ፤ እንደ ሕፃናት ወተትን እንዴት ተመገበ?
        ❖ ❖ ❖ መልክአ ኢየሱስ ❖ ❖ ❖
ሰላም ለአፅፋረ እዴከ ዘሕበሪሆን ጸዓዳ...
ትርጉም፦ቀለማቸው ነጭ ለሆኑት የእጆችህ ጥፍሮች ሰላም እላለሁ.....
         ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
አንፈርዓፁ ሰብአ ሰገል ፤
አምኃሆሙ አምፅኡ መድምመ ፤
ረኪቦሙ ሕፃነ ዘተወልደ ለነ፡፡
ትርጉም፦ሰብአ ሰገል የተወለደልንን ሕፃን አገኙ በደስታም ዘለሉ ስጦታቸውንም አመጡ፡፡
        ❖ ❖ ❖ ምስባክ ❖ ❖ ❖
ዲያቆኑ በቅኔ ማኅሌቱ  "መዝ 71:10" ይሰብካል።
“ነገሥተ ተርሴስ ወደሴያት አምኃ ያበውዑ ፤ ነገስተ ሳባ ወዓረብ ጋዳ ያመፅኡ ፤
ወይሰግዱ ሎቱ ኩሎሙ ነገሥተ ምድር ፡፡ ትርጉም፦ የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ! ነገሥታት ኹሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ኹሉ ይገዙለታል፡፡
        ❖ ❖ ❖ ምልጣን ❖ ❖ ❖
መዘምራን (መሪጌቶች) መሪና ተመሪ ኾነው የሚዘምሩት ሲኾን በመቀጠልም ኹሉም በኅብረት እየደጋገመ የሚዘምረው ነው! እንዲህ ይላል.....
ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደቱ ለክርስቶስ ፤
እም ቅድስት ድንግል ውእቱ ኢየሱስ ክርስቶስ፤
ዘሎቱ ሰብአ ሰገል ሰገዱ ሎቱ፤
አማን መንክር ስብሐተ ልደቱ፡፡
ትርጉም፦ እነሆ ዛሬ በክርስቶስ ልደት ምክንያት ደስታ ኾነ ከቅድስት ድንግል የተወለደው እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ለእርሱ ሰብአ ሰገል ሰገዱለት!
በእውነት የልደቱ ምስጋና ድንቅ ነው፡፡
          ❖ ❖ ❖ እስመ ለዓለም ❖ ❖ ❖
ተወልደ ኢየሱስ በቤተልሔም ዘይሁዳ፤
አዋልደ ጢሮስ አሜሃ ይሰግዳ፤
ሰብአ ሰገል አምፅኡ ሎቱ ጋዳ፤
ወይትኃሠያ አዋልደ ይሁዳ ፡፡
ትርጉም፦ኢየሱስ በይሁዳ ቤተልሔም ተወለደ፤ የጢሮስ ሴቶች ልጆችም በዚያ ይሰግዱለታል፤ ሰብአ ሰገል እጅ መንሻን አመጡለት፤ የይሁዳ ሴቶች ልጆችም ደስ ይላቸዋል፡፡
         ❖ ❖ ❖ ዑደት ❖ ❖ ❖
“ኹላችንም በልደቱን ብርሃን በማሰብና ጧፍ በማብራት "ሥዕለ አድኅኖ" ይዘው ከሚዞሩት ካህናት በስተኋላ ተሰልፈን እንዲኽ ይኼንን ዝማሬ እናቀርባለን!
“አማን በአማን አማን በአማን፤ መንክር ስብሐተ ልደቱ ፡፡
ትርጉም፦እውነት በእውነት እውነት በእውነት፤ የልደቱ ምስጋና ድንቅ ነው፡፡
         ❖ ❖ ❖ ዕዝል ❖ ❖ ❖
በጎል ሰከበ በአፅርቅት ተጠብለለ፤
ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኃደረ፤
ዮም ተወልደ እግዚእ ወመድኅን ቤዛ ኩሉ ዓለም፡፡
ትርጉም፦ በበረት ተኛ በጨርቅም ተጠቀለለ ፤ በድንግል ማኅፀን አደረ፤ የዓለም ኹሉ ቤዛ የኾነው ጌታና አዳኝ ዛሬ ተወለደ፡፡
        ❖ ❖ ❖ ሰላም ❖ ❖ ❖
ተስሃልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤
ንሰብክ ወልደ እም ዘርዓ ዳዊት ዘመፅአ ወተወልደ በስጋ፤
ሰብእ እንዘ ኢየአርቅ እመንበረ ስብሐቲሁ፤
ውስተ ማኅፀነ ድንግል ኃደረ ስጋ ኮነ ወተወልደ፡፡
ትርጉም፦ ጌታ ሆይ ምድርህን ይቅር አልክ ሃሌ ሉያ ከዳዊት ዘር የመጣውንና በሥጋ የተወለደውን ወልድን እንሰብካለን ከምስጋናው ዙፋን የማይራቆት ሰው ነው! በድንግል ማኅፀን አደረ ሥጋ ኾኖም ተወለደ፡፡
የሚቀደሰው ቅዳሴ   ☞    "ቅዳሴ ጎርጎርዮስ ካልእ"
የቅዳሴው ምስባክ   ☞ መዝ 71:15 ፤
የሚነበበው ወንጌል  ☞ ሉቃ2:1-21
    💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

መንፈሳዊ ጉባኤ

06 Jan, 16:47


ወንድም እህቶቼ እንኳን አደረሳችሁ

🙏🙏🙏🙏ይህንን ያውቃሉ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
❖ ❖ ❖እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት ተወልዶላችኋል ሉቃ.2፥11   ❖ ❖ ❖
     ❖ ❖ ❖ እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡  ❖ ❖ ❖
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

       ❖ ❖ ❖ " ጌና" ❖ ❖ ❖
ጌና እና ልደት {ዋዜማና ክብረ በዓል }
/የተለያዩ ቀናት/ ቢኾኑም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ጌና ልደትን እየተካ እንጠቀምበታለን ፤ ነገር ግን ይህ ሊስተካከል ይገባዋል፡፡ ልዩነት ስላለውም የኢትዮጵያ ብርሃን የተባለው አፈ ጳዝዮን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለጌናና ለልደት ለ2ቱም በዓላት ለየብቻቸው በመጽሐፈ ምሥጢር ድርሰት ደርሶላቸዋል፡፡
#ጌና ፤ የልደት በዓል ዋዜማ ቀን ሲኾን በዚህ ቀን ‹‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› የተባለለትን ‹‹የገና ጨዋታ›› እንጫወታለን፤ የምንጫወትበት የኳሱ ስያሜ ‹‹ሩር›› ሲባል ስያሜውን ያገኘው፤ ሰብዓ ሰገል እልፍ እልፍ ሠራዊት አስከትለው የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ ፍለጋ ወደ ንጉሡ ሔሮድስ ደርሰው ነበርና ፤ ሔሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ፈልጎና በውስጡ ሸሽጎ ለሰብዓ ሰገል ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ስታገኙትም ንገሩኝ ብሎ ሰድዷቸዋል ፤ ነገር ግን በዚያው ሳይነግሩኝ እንዳይሄዱ በማለት እነርሱ ሳያውቁ  ‹‹ሩር›› የተባለ ሰላይ በመሃላቸው አስገብቶ ነበርና ሰብዓ ሰገልን ይመራቸው የነበረው ኰከብ ተሠውሮባቸዋል ፤ ሰብዓ ሰገል ሠራዊታቸውን ቢያጣሩ ከመሃከላቸው የተቀላቀለ ሩር የተባለ የሔሮድስን ሰላይ አገኙ ይህንንም ሰላይ የሰብዓ ሰገል ሠራዊት አንገቱን በሰይፍ ቀልተውታልና ያን ለማስታወስ ዛሬ በገና ጨዋታ ላይ ሩር የተባለው ኳስ የሔሮድስ ሰላይን ‹‹ሩር›› እንዲያስታውስ አባቶች ሥርዐትን ሠሩ፡፡

     ❖ ❖ ❖ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ❖ ❖ ❖
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አይደለም፡፡ ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ በመላእክት ፤ በነቢያት ሲነገር ፤ ሲሰበክ የመጣ ነው እንጂ፡፡ ማቴ.1፥18፡፡ ሰው የመሆኑን ምሥጢር ለመጀመሪያ ጊዜ በማዕከለ ገነት የተናገረ እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡
አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወጥቶ ዕፀ በለስን በልቶ ከጸጋ እግዚአብሔር በተራቆተ ጊዜ /አዳም ኮነ ከመ አሐዱ እምኔነ/ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ዘፍ.3፥22 ብሎ ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው እንደሚሆን ተናግሯል፡፡ በዚህ ቃል መሠረት /መሪነት/ ቅዱሳን መላእክት ምሥጢረ ትንቢት ተገልጾላቸዋል፡፡ እነሱም የተገለጸላቸውን ምሥጢረ ትንቢት ኀላፍያትንና መጻእያትን ለሚናገሩ ነቢያት ነግረዋቸዋል፡፡ ቅዱሳን ነቢያትም ከእግዚአብሔር ያገኙትን ከመላእክት የሰሙትን መነሻ አድርገው በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ምሳሌያት በተለያዩ ዘመናት የወልደ እግዚአብሔርን ሥጋዌ ሰብከዋል /ገልጸዋል/ ዕብ.1፥1፡፡ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፡፡

    የጌታችን ልደት በትንቢተ ነቢያት ፦
👉 ከዓበይት ነቢያት መካከል አንዱ የሆነው ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ የሚከተለውን ትንቢት ተናግሯል፡፡
"እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች ( ኢሳ.7፥14፣ ሕዝ.44፥1) ፡፡ በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና የተወልደው አማኑኤል ጌታ ነው፡፡ ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ነቢዩ በጎላና በተረዳ ነገር “ሕፃን ተወልዶልናል ወልድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፡ ስሙም ድንቅ መካር ኀያል አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል“ በማለት የሚወለደው ሕፃን የባሕርይ አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ሥልጣን የባሕርይ ገንዘቡ እንደሆነ እና ለሥልጣኑም ወሰን ድንበር እንደሌለው ተናግሯል፡፡
👉 ከደቂቀ ነቢያት መካከል አንዱ ሚልክያስም በቤተልሔም ስለመወለዱ፡-
"የኤፍራታ ምድር አንቺ ቤተልሔም ከይሁዳ አለቆች ከቶ አታንሽም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና" (ሚክ.5፥2፣ ማቴ.2፥6) ብሏል፡፡
👉• ነቢየ እግዚብሔር ቅዱስ ዳዊትም "እነሆ በኤፍራታ ሰማነው ዛፍ በበዛበትም ቦታ አገኘነው እንግዲህስ ወደ እግዚአብሔር ማደሪዎች እንገባለን ብሎ የወመለዱን ምሥጢር ተናግሯል" (መዝ.131፥6)
👉• ነቢዩ ዕንባቆምም "አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ ሥራህንም ዐይቼ አደነቅሁ በሁለት እንስሶች መካከል አየሁህ ዘመኑ እንደደረሰ አድርጌ አውቅህአለሁ ዘመኑም በደረሰ ጊዜ ተገለጥክ" ብሎ በቤተልሔም በረት በተወለደ ጊዜ አድግና ላኅም እስትንፋሳቸውን እንደሚገብሩለት (ዕንባቆም 3፥1) ተናግሯል፡፡
ከዚህ በኋላ የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ እግዚአብሔር መልአኩን ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ድንግል ማርያም በመላክ አብሥሯታል፡፡ “ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል" በማለት፡፡ ሉቃ. 1፡32
እመቤታችንም በብዙ ኅብረ አምሳል ትንቢት ሲነገርለት፤ ምሳሌ ሲመሰልለት፤ ሱባኤ ሲቆጠርለት የነበረውን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በቤተልሔም ግርግም  ወለደችው፡፡
ይህንንም ብስራት በቤተልሔም ዋሻ መንጋቸውን ነቅተውና ተግተው ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች መጋቤ ሐዲስ አብሣሬ ትስብዕት ቅዱስ ገብርኤል ፤ እነሆ ዛሬ መድኀኒት በዳዊት ከተማ ተወልዶላችኋል ይኸውም ቡሩክ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሚያርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ የሚያድል ከዓለም በፊት ንጉሥ የነበረ ዛሬም ከዳዊት ባሕርይ /ዘር/ በቤተልሔም ዋሻ ዓለምን ለማዳን የተወለደ የዳዊት ልጅ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ተወለደ ሲል አበሰራቸው፡፡ (መዝ.73፥12)
💥 የጌታችንን ልደት ስናነሣ ሁለት ልደታት እንዳሉት እናምናለን፡፡ እኒሁም ልደታት /ልደት ቀደማዊና/ /ልደት ደኃራዊ/ ናቸው፡፡

ልደት ቀዳማዊ ፦ ቅድመ ዓለም ከአብ አካል ዘእም አካል ባሕርይ ዘእም ባሕርይ ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት የተወለደው ልደት ሲሆን /ነቢዩ ዳዊት እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ "ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽ ባህ መዝ.109፥3 ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ወለድኩህ ፤አንተ ልጄ ነህ እኔም ዛሬ ወለድኩህ" (መዝ.2፥7)
 
ልደት ደኃራዊ ፦ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈፀም በዕለት ሐሙስ ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ እንዲል ቃሉ፡፡ ቅድስት ድንግል ከምትሆን ከእመቤታችን እንበለ ዘርዓ ብዕሲ ያለ አባት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም የተወለደው ልደት ነው፡፡

መንፈሳዊ ጉባኤ

25 Dec, 03:47


👉🏾#ጋብቻ በፊት #መሳሳም ይቻላል ወይ?

👉 ጥያቄ፦ ሰላም አባቴ እንደምን ነዎት? እኔ እግዚአብሔር ይመስገን  ደህና ነኝ፣  ፍቅረኛሞች ቢሳሳሙ ነገር ግን ምንም ግንኙነት ባያደርጉ ሥርዓተ ተክሊል መፈፀም ይችላሉ? ፍቅረኛሞች ሆነው አንዱ ብቻ የመሳሳም ፍላጎት ኖሮት አንዱ ሳይፈልግ ቢስመው ሥርዓተ ተክሊል መፈፀም ይችላሉ? መሳሳምስ ከጋብቻ በፊት ይቻላል?

መልስ፡- ጠያቂያችንም ሆኑ ሌሎቻችሁ ይሄንን መሳሳም የሚባለውን ነገር በጣም አድርጋችሁ ልታስቡበትና ልትፀየፉት ይገባል፣ ይሄ ድርጊት ምን ዓይነት ፆር ነው? እኛም አባቶች ብንሆን ፈርዶብን ዘመኑን ለመዋጀት ሲባል የዘመኑም፣ የወጣቶቹም ቸግር ስለሆነ ይሄንን በጸጋ ተቀብለን፣ እንደ አጀንዳ አድርገን እያወራነው ነው፣ የመሳሳም እርካታው ምንድን ነው? በዓለሙም ቢሆን በባለሞያዎች ዘንድ ከጤናም አንፃር  መሳሳም የሚባለውን ነገር የሚስማሙበት አይመስለንም፡፡

አንድ ሰው አይምሮ ያለው ሰው፣ ማስተዋል የሚችል ይሄንን ድርጊት ማድረግ ከሥነ ምግባርማ ውጪ ነው፣ የሞራልም ችግር ነው፣ እንስሳ እንኳን ወደ እንስሳው ወንዱ ወይም ተባዕቱ ወደ እንስቷ ሲቀርብ እንኳን ወይም ደግሞ  ፍየሎቹ፣ ላሞቹ፣ በጎቹ ወልደው ልጆቻቸውን ይልሷቸዋል፣ የእነሱ እንኳን የተፈጥሮ ሕጋቸው፣ ሥርዓታቸው በጣም የሚገርም ነው፣ ከዚህ የወጣ ነገር የላቸውም፡፡

መሳሳም የሚባለው ነገር ሲጀመር እኮ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ሳይሆን ለሥጋዊ ማንነታችን፣ ለሥጋዊ ክብራችን የማይመጥንና፣ ዝቅ የሚያደርግ ነው፣ ይሄን ያህል በመንፈሳዊ ሕይወታችን ወይም ደግሞ በሥርዓተ ተክሊል ጋብቻ ዙሪያ፣ በቅዱስ ቁርባን ጋብቻ ባለው ነገር ከመናገራችን በፊት እንዲህ ዓይነት ፈተናና፣ ፆር ያለብን ሰዎች ይሄን መጥፎ የሆነ ድርጊት ብንተወው መልካም ነው፡፡

ሰይጣንም  ሁልጊዜ ለእኛ ቀዳዳ ነው የሚያበጅልን፣ ትንሽ ጭላንችል መግቢያ ቀዳዳ ካገኘ እሱን የበለጠ ያሰፋዋል፣ ከዚያ በኋላ በዚያ ገብቶ ሁላችንንም ተራ የሆነውን ኃጢአት እንደ መደበኛ ኃጢአት ያደርገዋል፣ ወደ ጥፋት ይወሰደናል፣ ጠያቂያችን በአነጋገር ለማቅለል ሞክረው ይሆናል እንጂ መሳሳም የሚለውን ነገር ሁለት ፍቅረኛሞች በዚህ ድርጊት ውስጥ ተፈተኑ ማለት ሌላውን ነገር ላለማድረግ ወይም አደረጉ ለማለት በፍጹም አያስችለንም፡፡

እነዚህ ሰዎች ለምን ይሳሳማሉ? በእርግጥ ብዙ ዘመድ ተነፋፍቀው ይሳሳማሉ፣ ይሄ ሃይማኖታዊም፣ መንፈሳዊም፣ ወይም ደግሞ ባህላዊም ሥርዓታችን ነው፣ ጠያቂችን የሚሉት ደግሞ የዚህ ዓይነት አሳሳም አይደለም፣ ለመንፈሳዊ ፍቅርም አይደለም፣ ከልቡ ስለወደዳት እግዚአብሔር አንቺን ስለሰጠኝ ብሎ በመንፈሳዊ ፍቅር አይደለም የሚሳሳሙት፣ ሥጋዊ ፍላጎታቸው፣ ፍትወታቸው ከአቅማቸው በላይ ሆኖ፣ በፍትወት እየነደዱ ነው የሚሳሳሙት፡፡

ስለዚህ ከዚያ ቀጥሎ የተደረገውን ነገር ስላልተገለፀልንም ሊሆን ይችላል እንጂ አንዳንዶቻችን ባናደርገው ሌሎቹ ያደርጉታል፣ ይሄ አያስፈልግም ነው የምንለው ፣ ይሄ ድርጊት ሥርዓተ ተክሊልና ሥርዓተ ቁርባን ያስከለክላል ወይ? ለሚለው ከዚህ ያለፈ ነገር ከሌለ እንዲህ ዓይነቶቹ  ነገሮች ምክር ነው የሚያስፈልጋቸው፣ ተግሣፅ  ነው የሚያስፈልጋቸው  ነውር ነው፣ እንዲህ ዓይነቱ አርአያነት ነገም ለሌላ ሰው ምሳሌ የምትሆኑበት ነገር  እናንተ እንዲህ ነበር፣ አንዳንዶቹ እየተጋደልን ነው፣ ዋጋ እየከፈልን ነው እያሉ መሳሳም ብቻ ሊሆን ይችላልና ከሥርዓተ ተክሊል ድንግልናቸውን፣ ንፅህናቸውን በሌላ ነገር ካላጎደፉ አይከለከሉም፡፡

ጠያቂያችን ሦስቱም ጥያቄዎች ተመሳሳይ ሰለሆኑ ነው፣ መሳሳም የሚለው ነገር ላይ  ይሄ ዘመነኛ ኃጢአት፣ ሰሞነኛ ኃጢአት፣ የወጣቱ ትልቅ የሆነ ፆር፣ ትልቅ የሆነ ውድቀት፣ ጉስቁልና ስለሆነ ሊተው ይገባል የሚል ነው፣ እርስዎም ምናልባት ከዚህ ያለፈ ስጋት ኖሮዎት ይሄንን ነገር ከዚህ በላይ በጥልቀት ሊያብራሩልንና፣ ሊገልፁልን የሚችሉት ሐሳብ ካለ ተጨማሪ ምክር እንድንሰጥበት ባለን የውስጥ መስመር ያግኙን፡፡

የመከረን የገሰፀን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ስሙ ይመስገን፣ አሜን።

መንፈሳዊ ጉባኤ

25 Dec, 03:38


ግሩም ምስጢር ያለው ወፍ
"ከራድዮን ወፍ ይባላል
ከራድዮን ነጭ ወፍ ሲሆን በሊቃውንት ዘንድ የታወቀ ነው። ጠቢባን በድካም ፈልገው አድነው ይይዙታል፣ የታመመ ሰው
ቢኖር ያቀርቡታል ፤ እሱም በሽተኛውን ትኩር ብሎ ያየዋል የማይድን ለሞት የቀረበ ከሆነ ፊቱን አዙሮ ይመለሳል፣ ቀኑ ገና
ከሆነ ግን አፉን ከፍቶ ከበሽተኛው አፍ እስትንፋሱን ይወስዳል፣ በልዑል እግዚአብሔር ኃይል የሰውየው ደዌ ሙሉ ለሙሉ
ወደ ወፉ በእስትንፋሱ ይተላለፋል። ሰውየው ይድናል ወፉ ይታመማል።
ፊት ነጭ የነበረው እንደ ከሰል ይጠቁራል፣ ህመም ሲሰማው ወደ አየር ይነጠቃል ሲብስበት ወደ ባህር ራሱን
ይወረውራል። በባህር 3 መዓልት 3 ሌሊት ቆይቶ ጽጉሩን መልጦ አዲስ ተክቶ፣ድኖ፣ታድሶ፣ኃያል ሆኖ ይወጣል።
ይህ ፍጥረት በዕለተ። ሃሙስ እግዚአብሔር ፈጥሮታል።
ስለምን ፈጠርው ቢሉ የወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስን ሞትና ትንሳዔ ለማያምኑ ትምህርት ምሳሌ አብነት ይሆን ዘንድ
ሥላሴ ይህን ወፍ የማዳን ኃይል ሰተው ፈጥረውታል።
ትንታኔ፦
ከራድዮን ወፍ ---- የክርስቶስ ምሳሌ
የታመመው ሰው --- የአዳም ዘር ምሳሌ ሲሆን
ወፉ በዐይኑ መመልከቱ --- በክርስቶስ ላመነ ሁሉ ድኅነት ምህረት ማግኘቱ ምሳሌ
ወፉ መታመሙ---- ክርስቶስ ስለ እኛ በደል መታመሙ ምሳሌ።
መጥቆሩ ---- ስለእኛ ቤዛ ከኀጢአተኛ የመቆጠሩ ምሳሌ
ወፉ ወደ ላይ መውጣቱ---- ክርስቶስ ከፍ ብሎ መሰቀሉ ምሳሌ
ወፉ በባህር 3ቀን 3ሌሊት መኖሩ ----ክርስቶስ በከርሰ መቃብር 3ቀን 3 ሌሊት መቆየቱ ምሳሌ
ከራድዮን ወፍ ታድሶ ኃያል ሆኖ ከባህር መውጣቱ ---ክርስቶስ በሲዖል የነበሩ ነፍሳትን አድሶ አንጽቶ ገነት አስገብቶ፤
እርሱም ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው በለበሰው ሥጋ ወደ ቀደሞ መለኮታዊ ሥልጣኑ ኃይሉ መቀመጡ ምሳሌ
ነው።
..........
እንግዲህ ምን እንላለን ሥላሴ አስቀድመው የአዳምን መበደል ሞትም እንዲመጣበት ያውቃሉና ገና ዓለም ሲፈጠር
እግዚአብሔር አንድያ ልጁን አሳልፎ ለመስጠት ዝግጁ እንደ ነበር የከራዲዮን ወፍ አፈጣጠር ምስክር ሆነን።
እግዚአብሔር ፍቅር ነው የምንለው ለዚህ ነው።
ይቆየን
ቸርነቱ ፍቅሩ ምህረቱ አይለየን
ምንጭ የሥነ ፍጥረት አንድምታ፣ መጽሐፈ አክሲማሮስ፤
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
ስመ ዖፍ ጥሩ ነጭ መልከ መልካም ወፍ የክርስቶስ አርኣያ የሰውነቱ አምሳል ፊላሎጎስ መጽሐፍ ተመልከት፡፡
ለዘተወልደ እምድንግል ምንተ ንብሎ ናስተማስሎ አርዌ ገዳምኑ አንበሳ ወሚመ ከራድዮን ዖፍ ጸዐዳ ንጉሠ ይሁዳ
እምዘርዐ ዳዊት ዘመጽአ (ድጓ)፡፡

መንፈሳዊ ጉባኤ

12 Dec, 03:07


ታህሳስ ፫ በታዕካ ነገስ በዓታ ማርያም ታላቋ ገዳም እንገና
          ።።።።   እንኳን አደረሳሽሁ።፡።።።።

✝️እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት (በዓታ ማርያም ውስተ ቤተ መቅደስ) ዓመታዊ መታሰቢያ ታላቅ የንግሥ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሰን፤ አደረሳችሁ።

✝️ታህሳስ ፫ በአታ ለእግዝእትነ ማርያም ውስተ ቤተመቅደስ

“እበውዕ ቤተከ ምስለ መባእየ” ፤ “ከመባዬ ጋራ ወደ ቤትህ እገባለሁ።” መዝ. ፷፭(፷፮)፥፲፫

እመቤታችን አባቷ ኢያቄም እናቷ ሐና ይባላሉ። በፈቃደ እግዚአብሔር በብስራተ መልአክ ወልደዋታል። የብፅዓት ልጅ ናትና ሶስት ዓመት ሲሆናት ይህች ልጅ አንድ ነገር ብትሆን ከእግዚአብሔርም ከልጃችንም ሳንሆን እንዳንቀር ሆዷ ዘመድ ሳይወድ አፏ እህል ሳይለምድ ወስደን እንስጥ ብለው መባዕ ጨምረው ወደ ቤተመቅደስ ይዘዋት ሄዱ።

ሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ መጥቅዕ መጥቶ ሕዝቡን ሰብስቦ የምግቧ ነገር ይያዝልኝ አለ። ወዲያው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ ይዞ ረቦ ታየ። ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ መስሎት ዛሬስ ክብሬን በሰው ፊት ሊገልጸው ነው ብሎ ሊቀበል ተነሣ። መልአኩ ወደ ላይ ራቀበት። የእርሱ ተወራጅ ስምዖንም እንኪያስ ለእኔ የመጣ ይሆናል ብሎ ቀረበ። ራቀበት። ካህናቱም ሕዝቡም በተራ ቢቀርቡ ራቀባቸው። ምናልባት ጥበበ እግዚአብሔር አይመረመርም ለዚህች ብላቴና የመጣ እንደሆነ እንይ ሐና ትተሻት እልፍ በይ አሏት። ትታት እልፍ አለች።

ድክ ድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ በሰው ቁመት ልክ ከመሬት ከፍ አድርጎ መግቧት ዐረገ። የምግቧ ነገር ከተያዘልንማ ትግባ እንጁ ብለው ከመካነ ደናግል አስገቧት። “ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ዐሠርተ ወክልዔተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት” ይላል። ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ሰማያዊ እየተመገበች መላእክት  እየጎበኟት ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ኖራለች።

የእናታችን ምልጃና ጸሎት አይለየን፤ ረድኤት በረከቷን ያሳድርብን፤ ከበዓሏ በረከትም ያሳትፈን። የዓመት ሰው ይበለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም

መንፈሳዊ ጉባኤ

10 Dec, 13:02


ወዳጄ ሆይ ከመብል ሽሽ፤ ከመጠጥም ራቅ፡፡ ጥጋብ ስንፍናን ትወልዳለችና፡፡ ጾምን ጠብቅ። በጾም ኃጢአት ይሠረያልና፡፡ እንዳይጠግብ፣ የሚጋልበውንም እንዳይጥለው ፈረስን እንደሚለጕሙት አንተም እንዲሁም ሥጋህ በፍትወት ነፍስህም በኃጢአት እንዳይወድቅ አፍህን ከመብልና ከመጠጥ ለጕም፡፡ ጌታችን እንበላና እንጠጣ ዘንድ አላዘዘንምና፡፡ ነገር ግን ወደ ፈተና እንዳትገቡ ጹሙ ጸልዩ አለን እንጂ፡፡

የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፡፡ ስለ መብል በወጥመድ ውስጥ ይወድቃሉና፡፡ አጥማጆችም በሚያጠምዱበት ጊዜ ወጥመዱን በመብል ይሠውሩታልና፡፡ እንዲሁም ሰይጣን ጣፋጩን ተስፋ አስደርጎ መራራውን ይሰጣል፡፡ ዳግመኛም ብዙውን ተስፋ አስደርጎ ትንሽን ይሰጣል፡፡ አዳምን አምላክ እንደሚሆን ተስፋ እንዲያደርግ አደረገው፡፡ ነገር ግን ከገነት ዕራቍቱን አስወጣው፡፡

በጌታውም ዘንድ የተናቀ አደረገው፡፡ በዚህም መርገምን ወረሰ፡፡ በእርሱ ምክንያትም ምድር ተረገመች፡፡ ሞትም በሰው ላይ ሁሉ ሠለጠነ። የሚበር ወፍ ወደ ምድር ካልተመለከተ ወደ ወጥመድ አይወርድም፡፡ እንዲሁም ለሚጾም ሰው ልቡ በሰማይ ያለውን ያስብ ዘንድ ሥጋው በኃጢአት እንዳይወድቅ ለሰውነቱ ምኞቷን ይከለክላት ዘንድ ይገባል፡፡

ጾም የጸናች ናት፡፡ ትሕትናም የንስሓ ራስ ናት፡፡ በጾም ኤልያስ ከመላእክት ጋር ተቆጥሯልና፡፡ ኤልሳዕም የመምህሩን የኤልያስን መንገድ ተከተለ፡፡ ዕጥፍ ድርብ በረከቱንም አገኘ፡፡

ወንድሞቼ ሆይ በአጋንንት ላይ በሥጋ ድል ማድረግን እናገኝ ዘንድ በጾምና በበጎ ሥራ ሁሉ የመምህሮቻችንን መንገድ እንከተል፡፡ ንጹሕና የተመረጠ ጾምን እግዚአብሔር ይወዳል፡፡ አመፃ ስንፍና ናት፡፡ እግዚአብሔር አማፅያንን ፈጽሞ ይጠላቸዋል፡፡ በአፉ እየጾመ ወንድሙን ለሚገድል ለእርሱ ወዮለት፡፡ በአፉ ጾምን ለሚያውጅ በአንደበቱ ደግሞ አመፃን ለሚናገር ለእርሱ ወዮለት፡፡

ወንድሜ ሆይ አፍህ ከጾመ ልብህም እንዲሁ ይጾም ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ እነሆ ዐይንኖችህ ክፉን ከመመልከት ይጹሙ፡፡ እጆችህና እግሮችህም ከክፉ ሁሉ ይጹሙ፡፡ የጠላት ወጥመዱ ብዙ ነውና፡፡ በንጉሥ ፊት ተጋዳይ ወታደርን ልትሆን ብትወድ የጦር ዕቃን ትይዝ ዘንድ ተገቢ ነው፡፡ እንዲሁም ከሰይጣን ወጥመድ መዳን የሚወድ ሰው የክርስቶስን ትዕዛዙን ይጠብቅ፡፡ ከገሃነም እሳት ትድን ዘንድ ከትዕቢት ራቅ፡፡ መንግሥተ ሰማያትንም ትወርስ ዘንድ ትሕትናን ፈልግ፡፡

ወዳጄ ሆይ እኔስ ከመብልና ከመጠጥ ትሸሽ ዘንድ ጾምንም በፍጹም ልብህ ትከተላት ዘንድ እፈልጋለሁ፡፡ ትሑታንን ውደዳቸው ከትዕቢተኞችም ራቅ፤ ከጥላቻ ፈቀቅ በል፤ ሰላምንም ፈልጋት፡፡ የክርስቶስን ትዕዛዝ ትፈጽምም ዘንድ በፍቅር ሩጥ፡፡ በአንተ ላይ የኃጢአት ፍሬ እንዳይታይም ከልብህ ቂምንና በቀልን አስወግድ፡፡ ክፉ ሕሊና በመጣብህ ጊዜ በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በምታስፈራ የፍርድ ዐደባባይ የምትቆምባትን የፍርድ ቀን አስባት፡፡

መንፈሳዊ ጉባኤ

08 Dec, 05:32


https://www.facebook.com/share/19tuiw5Qai/?mibextid=xfxF2i

መንፈሳዊ ጉባኤ

01 Dec, 04:33


ምክር ወ ተግሳጽ
ልጄ ሆይ ፤ ዋዘኛና ቀልደኛ አትሁን ፡፡ በመከራ ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታዝንና የምትራራ ሁን ፤ በድኃ ላይ አትጨክን ፤ ርስቱንና ቤቱንም በምክንያት አትውሰድበት ፤ ለመጨረስም የማትችለውን ነገር አትጀምር ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ በልተህ ስትጠግብ ረኃብን ፤ ስትበለጥግ ድኅነትን ፤i ስትሾም ሽረትን ፤ ሌላውንም ይህን የመሰለውን ሁሉ አትርሳ ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ ለሞተው ወዳጅህ ከማልቀስ ይልቅ በሕይወቱ ሳለ የክፋት ሥራ ለሚሠራ ወዳጅህ አልቅስለት ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ ባለ ጠጋ ሰው ሁሉ ይደግፈዋል ፤ ድኃ ሲወድቅ ግን ሰው ሁሉ ወዲያው ይገፋዋል ፡፡ ባለ ጠጋ ሲከሰስ በሸንጎ የተቀመጠው ሁሉ ይሟገትለታል ፤ ድሀ ሲከሰስ ግን በሸንጎ የተቀመጠው ሁሉ ይፈርድበታል ፡፡ መልካም ዳኛ በመካከላቸው የተቀመጠ እንደ ሆነ ግን ፍርዱ እንደ ፀሐይ ያበራለታል ፡፡ ስለዚህ በምትኖርበት ሀገር መልካም ዳኛ አያጥፋብህ ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ በማናቸውም ነገር ቢሆን ሞት አይቀርም ፡፡ ነገር ግን በሰው እጅ ከመውደቅ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻላል ፡፡

ለአፍህ መሐላ አታልምደው ፤ እግዚአብሔር ስሙን ከንቱ ያደረገውን ሳይቀስፈው አይቀርምና ስሙን በከንቱ አትጥራ ፡፡ ልጄ ሆይ ፤ የምትሠራውን ሥራ ሁሉ ሰው ቢያየው ቢሰማውም አይጎዳኝም ብለህ እንደ ሆነ ነው እንጂ አይታይብኝም ፤ አይሰማብኝም ብለህ አትሥራው ፡፡ አንተ ምንም ተሰውረህ ብትሠራው ከተሠራ በኋላ መታየቱና መሰማቱ አይቀርም ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ አንተ አስቀድመህ በሰው ላይ አትነሣ ፤ ሰው በአንተ ላይ ቢነሣብህ ግን እንዳትሸነፍ ጠንክረህ መክት ፡፡ እምነትህንም በእግዚአብሔር ላይ አድርግ ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር አትነጋገር ፡፡ ባሏ አለመኖሩን በደጅ ጠይቀህ ከደጅ ተመለስ እንጂ ወደ ቤት አትግባ ፡፡ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር የተነጋገርህ እንደ
ሆነ ግን ፤ ምንም ሌላ ምስጢር ባይኖራችሁ በመነጋገራችሁ ብቻ መጠርጠር አይቀርም ።

ልጄ ሆይ ፤ በጌታህም ቤት ቢሆን በሌላም ስፍራ ቢሆን ገንዘብ ወይም ሌላ እቃ ወድቆ ብታገኝ አታንሣ ፡፡ ብታነሣውም መልሰህ ለጌታህ ወይም ለዳኛ ስጥ እንጂ ሰውረህ አታስቀር ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ በፍፁም ልብህ ለማትወደው ሰው ቤትህንና የቤትህን ዕቃ አታሳይ ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ ንፁሕ አለመሆንህን እግዚአብሔር ያውቃልና በእርሱ ፊት ንፁሕ ነኝ አትበል ፡፡ በንጉሥ ፊትም ብልህ ነኝ አትበል ፤ የብልሃት ሥራ ሠርተህ አሳየኝ ያለህ እንደ ሆነ ታፍራለህና ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ ጠላት በዛብኝ ፤ ምቀኛ አሴረብኝ ብለህ እጅግ አትጨነቅ ፡፡ በዓለም የሚኖር ፍጥረት ሁሉ ጠላትና ምቀኛ አለበት እንጂ ባንተ ብቻ አይደለም ፡፡ ከዚሁም በጥቂቱ
እጽፍልሃለሁ ፡፡ በፍየል ነብር ፤ በበግ ተኩላ ፤ በአህያ ጅብ ፤ በላም አንበሳ ፤ በአይጥ ድመት ፤ በዶሮ ጭልፊት አለባቸው ፡፡

ይህንንም የመሰለ ብዙ አለ ፡፡ ሰውም እርስ በርሱ እንዲሁ ነው ፡፡ ስለዚህ የሚመጣብህን ነገር ሁሉ በትእግሥት ሆነህ ተቀበለው ፡፡ በመጨረሻው ግን ሁሉ አላፊ ነውና ጠላቶችህ ሁሉ ያልፋሉ ፡፡ ወይም አንተ አስቀድመህ ታልፍና ከዚህ ዓለም መከራና ጭንቀት ታርፋለህ ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ እስቲ ያለፉትን ሰዎች ሁሉ አስባቸው ፡፡ እነዚያ ሁሉ ጀግኖች ሁሉም መሬት ሆነዋል ፡፡ እነዚያ ሁሉ ዓለመኞች ፤ እነዚያ ሁሉ ቀልደኞችና ፌዘኞች ፤ እነዚያ ሁሉ ግፈኞች ፤ እነዚያ ሁሉ በድኃ ላይ የሚስቁና የሚሳለቁ ሁiሉም መሬት ሆነዋል ፡፡ እነዚያ ሁሉ ድሆች ሲበደሉ ፣ ሲያዝኑ ፣ ሲያለቅሱ ካንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲሰደዱ ፣ ሲራቡ ፣ ሲጠሙ ፣ ሲታረዙ የነበሩ መሬት ሆነዋል ፡፡

ስንት ሰዎች የነበሩ ይመስልሃል ? የድኃ እንባ ሲፈስ የወንዝ ውኃ የሚፈስ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡ ድኃ ሲጮህ ውሻ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡ ድኃ ታስሮ ወይም በሌላ ጭንቅ ነገር ተይዞ ሲሞት የወፍ ግልገል የሚሞት የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡ ጉልበት ካለን ብለው በደካሞች ላይ ያሰቡትን ሁሉ የሚሠሩ ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡

ሰውን ለማጥፋት እጅግ የሚጥሩ ሰውን ካላጠፉ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀድሞ የነበሩት ሁሉም መሬት ሆነዋል ፡፡ ከመሬት የተገኘ ሁሉ መሬት ስለ ሆነ ወደ መሬትም የማይመለስ ስለሌለ እኛም ነገ እንደዚያው እንሆናለን ፡፡ ስለዚህ በማናቸውም ምክንያት & የሰው ደስታውና አዘኑ እጅግ አጭር መሆኑን በጣም እወቅው ፡፡

ልጄ ሆይ ፤ ቀን በሥራህ ላይ ፤ ሌሊት በአልጋህ ላይ ፤ የሚጠብቅህ እግዚአብሔር ነውና ማታ ስትተኛ ፤ ጧት ስትነሣ እግዚአብሔርን አምላክህን መለመንና ማመስገን አትተው ፡፡

(ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ፤ ለልጃቸው ለፈቃደ ሥላሴ የፃፉት ምክር)

መንፈሳዊ ጉባኤ

30 Nov, 03:31


ህዳር 21 ታቦተ ጽዮን የምትከብርበት ዕለት

ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል መዝ 86+5
ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ  ይፈሩ መዝ 128+5
እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና ይላል መዝሙረኛው እግዚአብሔር የመረጣትን መጥላት ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት ነው

በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት፦

1 ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት ነው

2 ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት ነው

3 አበው  ነቢያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነቢዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ነቢዩ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተ መቅደስ፣ ነቢዩ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ያዩበትን ዕለትነው

4 ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት ነው

5  በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን ዕለት ነው

6 ለታቦተ ጽዮን ማደሪያ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ ነው

7 በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ ነው
መልካም በዓል

መንፈሳዊ ጉባኤ

29 Nov, 12:08


እግዚአብሔር ተስፋ አድርግ
                            
ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ በሙሉ ያለምንም ጥርጥር #በዝምታ_ይሠራል ። ይሁን እንጂ ሰዎች በመከራ ውስጥ ሆነው የእግዚአብሔር መልስ ከዘገየባቸው እንደማይሠራ  አድርገው ያስባሉ ። እነርሱ እግዚአብሔር አይሠራም ብለው በሚያስብበት  ሰዓት ሁሉ እርሱ ግን ለእነርሱ #በጥልቅ_እየሠራ ነው ። ሰዎች ይህንን ስለማይገነዘቡ የእግዚአብሔርን ሥራና የሥራውን ውጤት ፈጥነው ለማየት ይፈልጋሉ ። እነዚህ ሰዎች ግን በእምነታቸው ያመኑትን በዓይናቸው እስኪመለከቱ ድረስ ሊቆዩ ይገባቸዋል ። " እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ፤ በርታ ልብህም ይጽና ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ። " [መዝ 26*14 ] ።
እግዚአብሔርን እንዴት እንጠብቅ?

እግዚአብሔርን የሚጠብቅ ሰው እርሱን በተስፋ ፤ በእምነት ፤ በተሞላ ሙሉ ልብና ያለምንም ድካም ይጠብቀዋል ። ይህ በመሆኑም እንደዚህ ዓይነቱ ሰው እግዚአብሔር በመካከል ገብቶ እንደሚሰራና ሁሉም ነገር ለበጎ እንደሚሆን ያምናል ። " እግዚአብሔር ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ።" [ ሮሜ 8*28] ። " እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም ይሄዳሉ አይደክሙም " [ኢሳ 40*31] ። ኃይላቸው በመከራ የተናወጠባቸው ሁሉ እግዚአብሔርን በተስፋ በመጠባበቅ ኃይላቸውን ያድሳሉ ማለት ነው ። " ጎልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል " የሚል ቃል ተጽፋል [ መዝ 102*5] ። ስለሆነም ማንም ቢሆን እግዚአብሔር #እምነት በተሞላ ብርቱ ልብና በእርሱ ላይ በመተማመን ይጠብቀዋል ።
ነገር ግን አንድ ሰው እግዚአብሔር እርምጃ እንደሚወስድና እርምጃውም ግልጽና ኃያል እንደሆነ መተማመን አለበት ። ከዚሁ ጋር እርምጃው በተመቻቸ ሰዓት ፍሬያማ በሆነ መንገድ የሚከናወን ነው ። እግዚአብሔር አንድ የሆነ እርምጃ ለመውሰድ ከወደደ ምንም የሚጠባበቀው ሰዓት አይኖርም ። ኢየሱስ ክርስቶስ " ... አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም አላለምን ? /ሐዋ 1*7/ ። አንተ ችግርህን እግዚአብሔር እንደሚያቃልልህ በማመን መቼ ለችግርህ መፍትሔ እንደሚሰጥህ ሳታስብ በእርሱ እጅ ላይ ብቻ ጣለው ። ችግርህን እግዚአብሔር በጊዜው እንደሚያቃልለው መጠባበቅ የአንተ ሥራ አይደለም ።
        

መንፈሳዊ ጉባኤ

23 Nov, 00:16


በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ቸርነት፣ ደግነት፣ ምሕረትና ይቅር ባይነት የባሕርይ ገንዘቦቹ የሆኑት አምላካችን እግዚአብሔር በአምሳሉ የፈጠራቸው የሰው ልጆች ከመንገዱ በመውጣት በጠላት ወጥመድ ተይዘው እንዳይቀሩ “ወደ እኔ ተመለሱ” እያለ ዘወትር ይጠራቸዋል፡፡ ይህ ጥሪ የንስሓ ጥሪ ነው፡፡ ንስሓ መጸጸት፣ መቆጨት፣ በሠሩት ክፉ ተግባር ማዘን ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ንስሓ በሙሉ ልብ መመለስንና መለወጥን ያመለክታል፡፡ የሰው ልጅ ድካም የሚስማማውን ሥጋ እንደ መልበሱ ይደክማል፤ ይዝላልም፡፡ ከእውነት መንገድ፣ ከጽድቅ ሕይወት ወጥቶ ይስታል፡፡ ይሁን እንጂ የሚያስብ አእምሮና የሚያመዛዝን ሕሊና ያለው ፍጡር በመሆኑ የሠራውን ስሕተት አስተውሎ ይጸጸታል፡፡ ጸጸቱ የአሳብ ለውጥ መኖሩን ያመለክታል፡፡ ይህ የአሳብ ለውጥ ብቻ መፍትሔ አይሆንምና በተግባር መገለጥ አለበት፡፡ በአሳብም በተግባርም መለወጥ ማለት የንስሓ ጥሪን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ ጠቅለል አድርገን ስንመለከት ንስሓ እከብር ባይ ልቡና የሚያሳስበንን ሥጋዊ ፍላጎት ተከትለን፣ ስላጠፋነው ጥፋት፣ ስለበደልነውም በደል ምሕረትና ይቅርታ የምንጠይቅበት ለኃጢአትና ለጥፋት የጋበዘንን ሥጋችንን የምንገሥጽበት እና የምንቀጣበት፣ የእግዚአብሔርንም ቸርነት ደጅ የምንጠናበት ሥርዓት ነው፡፡ ስለዚህ ንስሓን ስናስብ ሦስት መሠረታዊ ነገሮችን መዘንጋት የለብንም። እነሱም፡- መናዘዝ፣ የሚሰጠንን ቀኖና መፈጸምና፣ ለኃጢአታችን ሥርየት የተሠዋልንን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም መቀበል የሚሉት ናቸው። ፩. ኃጢአትን መናዘዝ የራስን ጥፋት አውቆ ለእግዚአብሔርም ለሰውም መናዘዝ የንስሓ የመጀመሪያው ደረጃ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አስተምህሮ መናዘዝ ስንል ሰው በአሳብ፣ በንግግር እና በተግባር በፈጸመው ኃጢአት ተጸጽቶ “እባክህ ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቀኝ” ብሎ ጥፋቱን ለካህን ዘርዝሮ የሚናገርበት ሥርዓት ነው፡፡ አንድን ተነሳሒ እና ካህንን የንስሓ ልጅና አባት የሚያሰኘው ዋናው ጉዳይም ይህ ነው፡፡ የክርስቲያኖች የንስሓ አባት የመያዛቸው መሠረታዊ ዓላማም ይህ ነው፡፡ መናዘዝ የሚለውን ቃል ስናነሣ በሉቃስ ወንጌል የተጻፈውን የጠፋውን ልጅ ታሪክ ማስታወስ ይገባል፡፡ አንድ አባት ሁለት ልጆች ነበሩት፡፡ ከሁለቱ ልጆች መካከል ታናሹ ከአባቱ ንብረት የሚደርሰውን ተካፍሎ ለመውጣት ፈለገ፡፡ አባቱም ከሀብቱ ለልጁ ሊደርሰው ይገባል ያለውን ድርሻውን ከፍሎ ሰጠው፡፡ ልጁም ድርሻውን ተቀብሎ ወደ ሩቅ ሀገር በመሔድ ሀብቱን አባክኖ ጨረሰው፡፡ ኋላም በሚኖርበት ሀገር ጽኑ ራብ በሆነ ጊዜ ለአንድ ገበሬ የእሪያ ጠባቂ ሆኖ ተቀጠረ፡፡ ረሃብ ስለጸናበትም እሪያዎች ከሚበሉት አሰር ሊመገብ ቢፈልግም የሚሰጠውአልነበረም። ረሃብ ሲጸናበት “ወደ ልቡ ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በረሃብ እጠፋለሁ። ተነሥቼም ወደ አባቴ ልሔድ። አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም፤ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ አድርገኝ እለዋለሁ” አለ፡፡ ወደ አባቱ ሲሔድ አባቱ ገና ሩቅ ሳለ አይቶ አዘነለት። ሮጦም አንገቱን አቀፈና ሳመው። ጎረቤቶቹንም ጠርቶ ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም። ደስም ይበለን ብሎ ታላቅ ድግስ ደገሰ ይለናል (ሉቃ.፲፭፥ ፲፩-፴፪)፡፡ ይህን አምላካዊ ቃል በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ሊቃውንት በብዙ መንገድ ያመሠጥሩታል፡፡ እኛ ግን አንዱን ብቻ ብንመለከት የሁለት ልጆች አባት የተባለው የሁሉ ፈጣሪና አባት እግዚአብሔር ነው፡፡ ሁለቱ ልጆች ደግሞ ቅዱሳን መላእክትና አዳም /የሰው ልጆች/ ፣ የጠፋው ታናሹ ልጅ የተባለውም አዳም ፣ ወደ ልቡ መመለሱ ደግሞ ንስሓ ለመግባት መወሰኑን፣ ጥፋተኛ ነኝና ልጅህ ልሆን አይገባኝም አገልጋይህ አድርገኝ ማለቱም ጥፋተኛነቱን አምኖ፣ ተጸጽቶ መናዘዙን ያስረዳልናል፡፡ የሰው ልጅ የለበሰው ሥጋ ለኃጢአት የሚስማማ ከመሆኑ የተነሣ ዕለት ዕለት አውቆ በድፍረት፣ ሳያውቅ በስሕተት እንዲሁም በቸልተኝነት ሕገ እግዚአብሔርን ይተላለፋል፡፡ በዚህም ምክንያት ከቤተ እግዚአብሔርና ከመንፈሳዊ አገልግሎት ይርቃል፡፡ ይህም የሕሊና ዕረፍት፣ የአእምሮ ሰላም፣ የልብ ደስታ እንዲሁም ሰማያዊ ርስትን የሚያወርስ ተስፋንም ያሳጣዋል፡፡ ያን ጊዜም ያዝናል፤ ይከፋል፤ ወደ ልቡም ተመልሶ መፍትሔ ይፈልጋል፡፡ መፍትሔውም ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታርቅ ሽማግሌ መፈለግ ነው፡፡ ይህ ሽማግሌም ካህን ነው፡፡ ካህኑም እንደ ሽማግሌነቱ ከእግዚአብሔር ጋር አስታርቀኝ ብሎ የመጣበትን ሰው አስታርቅህ ዘንድ ጥፋትህ ምንድን ነው ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ እርቅ ፈላጊውም ጥፋቱን (ኃጢአቱን) ዘርዝሮ ይናገራል፡፡ መናዘዝ የሚባለውም ይህ ነው፡፡ ኃጢአትን ለካህን የመናዘዝ ሥርዓት በኦሪት የነበረ፣ በወንጌል የቀጠለ ነው፡፡ ለምሳሌ በኦሪት “ወንድ ወይም ሴት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይተላለፍ ዘንድ ሰው የሚሠራውን ኃጢአት ቢሠራ በዚያም ሰው ላይ በደል ቢሆንበት በሠራው ኃጢአቱ ላይ ይናዘዝ” (ዘፀ.፭፥፮) ተብሎ ተጽፏል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ኃጢአትን ለካህን መናዘዝ እንደሚገባ ለምጻሞች ቀርበው ኢየሱስ ሆይ ማረን እያሉ ወደ እርሱ ሲመጡ “ወደ ካህን ሒዱና ራሳችሁን አስመርምሩ” በማለት ወደ ካህናት ልኳቸዋል፡፡ ሔደውም ራሳቸውን ለካህን ሲያስመረምሩ (ኃጢአታቸውን ሲናዘዙ) ከበደላቸው ነጽተዋል(ሉቃ.፲፯፥፲፪-፲፭)። ራስህን ለካህን አሳይ ያለውም ለምጽ በኃጢአት ምክንያት የሚመጣ በሽታ ስለነበረ (ዘሌ.፲፫፥፵፭-፵፮) ከጊዜያዊውም፣ ለዳግም ሞት ከሚያበቃው ሞትም እንዲድን ነው። ለኃጢአት በሽታ መድኃኒቱ ንስሓ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ፪. ቀኖናን ተቀብሎ መፈጸም ቀኖና (canon) የሚለው ቃል ምንጩ ጽርዕ (የግሪክ) ነው። ትርጓሜውም መቃ፣ መስፈሪያ፣ መለኪያ፣ መለካት መቊጠር ማለት ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ፲፱፻፵፰፣ ገ.፯፻፺፱)። ከንስሓ ጋር በተያያዘ ያለው ትርጒም “አንድ ተነሳሒ በካህኑ ፊት ኃጢአቱን ከተናዘዘ በኋላ ካህኑ ለኃጢአት ማስተሥረያ የሚሰጠው የመንፈሳዊ ቅጣት መጠንና ዓይነት” ማለት ነው፡፡ ቀደም ብለን እንደተመለከትነው ሁሉ ካህኑ ኃጢአተኛውን ሰው ከእግዚአብሔር ጋር የሚያስታርቅ ሽማግሌ እንደ መሆኑ መጠን እርቁ እንዲፈጸም ጥፋተኛው ግለሰብ የሚጠበቅበትን መንፈሳዊ ግዴታ ለይቶ ማሳወቁ የማይቀር ነው፡፡ ምክንያቱም እርቅ ሲደረግ የበደለው አካል ይቅርታ ለማግኘት፣ የተበደለው አካል ደግሞ ይቅርታ ለማድረግ በየግላቸው ሊወጡት የሚገባቸው ድርሻ አለና፡፡ በዚህም መሠረት የተነሳሒ ድርሻ በፍጹም ልብ ከመመለስ በተጨማሪ የበደለውን መካስ፣ የቀማውን መመለስ እንዲሁም በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በዕንባና በዋይታ ወደ እግዚአብሔር ማልቀስ ነው፡፡ ይቅርታ ማድረግ ግን ምሕረትና ቸርነት የባሕርይ ገንዘቡ የሆነው የእግዚአብሔር ነው፡፡ ካህኑ ለኃጢአተኛው ሰው እግዚአብሔር ይቅር ይልህ ዘንድ መንፈሳዊ ተግባራትን ፈጽም ብሎ የሚያዝዘው ትእዛዝ ቀኖና ይባላል፡፡ ይኸውም በብሉይ ኪዳን የኃጢአት፣ የበደል፣ የደኅንነት ወዘተ.

መንፈሳዊ ጉባኤ

23 Nov, 00:16


መሥዋዕት ተብለው የፍየል፣ የበግ፣ የርግብ ወዘተ መሥዋዕት በማቅረብ ይፈጸም የነበረ ሲሆን በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጹም፣ ጸልይ፣ ስገድ፣ መጽውት የሚለው መጠን እንደካህኑ ሁኔታ የሚወሰን ይሆናል፡፡ ቀኖና በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ አስተምህሮ መሠረት ሰው ከስሕተቱ የሚታረምበት መንፈሳዊ ተግሣጽ ሲሆን ይህ ግን ምድራውያን ነገሥታት ለወንጀለኞች እንደሚሰጡት ቅጣት የሚታይ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ይቅር የሚለው ኃጢአተኛነቱን አምኖ በማዘኑ፣ በመቆጨቱና ከጥፋቱ በመመለሱ እንጂ ስለበደሉ በሚከፍለው ካሳ ብዛት አይደለምና፡፡ ለዚህም ቀደም ብለን ባየነው የጠፋው ልጅ ታሪክ ላይ ልጁ ለመናዘዝ ወደ አባቱ እየመጣ ሳለ “አባቱ ግን ገና ሩቅ ሳለ አየውና አዘነለት፥ ሮጦም አንገቱን አቀፈውና ሳመው” (ሉቃ.፲፭፥፳) የሚለው የሚያሳየው የአባቱን ርኅራኄ እንጂ ቀኖናው ከኃጢአቱ አቻ መሆኑን አይደለም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ “የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና” (፩ኛ ጴጥ.፬፥፫) ባለው መሠረት ነው።አባቶቻችንም ይህንን መሠረታዊ ትምህርት አብነት አድርገው ኃጢአተኛው በኃጢአት ባሳለፈበት ዘመን ፈንታ ቀሪ ዘመኑን በጽድቅ ጎዳና እንዲመላለስ የሚያበቃውን ቀኖና ይሰጡታል፡፡ ሐዋርያው “የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና” በማለት መናገሩ ከተመለሳችሁ ይበቃል ማለቱ አይደለም፡፡ በኃጢአት ፈንታ ፈቃደ እግዚአብሔርን ፈጽሙ ማለቱ እንጂ፡፡ አባቶች ካህናትም በዚሁ መሠረት ለኃጢአተኛ ሰው በቀማህበት ፈንታ መጽውት፣ ያለ ልክ በመብላትና በመጠጣት፣ በስካር፣ በኃጢአት ባሳለፍክበት ዘመን ፈንታ ጹም፣ ጸልይ፣ ስገድ በማለት ለኃጢአተኛው ቀኖና የሚሰጡት መንፈሳዊውን ጣዕም እንዲቀምስ ነው፡፡ እንዲያውም አባቶቻችን ለባለጸጋ ጾምን፣ ምንም ለሌለው ድሃ ምጽዋትን በማዘዝ ኃጢአተኞች ፈቃደ እግዚአብሔርን ለመፈጸም በሰውነታቸው ላይ ጨክነው መወሰንን እንዲለማመዱ ያዛሉ፡፡ ምክንያቱም ለባለጸጋ ምግብ በቤት ውስጥ ሞልቶ ተርፎ እያለ መጾም፣ ለድሃ ደግሞ ቆጥቦ ያስቀመጠውን ወይም ለምኖ ያገኘውን ገንዘብ መመጽወት ከባድ ነውና፡፡ ይሁንና ድሃ ጦሙን አድሮም ቢሆን ይመጸውታል፤ ባለጸጋም ለተወሰነ ቀን ነውና እንደምንም ራቡን ታግሦ ይጾማል፡፡ ከዚህም የተነሣ ሰውነታቸው ኃጢአትን ከመጸየፍ በተጨማሪ ለጽድቅ መታዘዝንም ይለማመዳል፡፡ ስለዚህ ተነሳሕያን የሚሰጣቸውን ቀኖና በዛ ብለው ሳያንጎራጉሩ፣ አነሰም ብለው ሳይጠራጠሩ በካህኑ ቀኖና ላይ የእግዚአብሔር ቸርነት እና የተነሳሒው ትሩፋት ተጨምሮበት ከታላቅ በደልና ኃጢአት እንደሚያነፃቸው አምነው ቀኖናቸውን ተቀብለው መፈጸም ይገባቸዋል፡፡ ፫. ሥጋውንና ደሙን መቀበል በክርስትና አስተምህሮ የአገልግሎቶች ሁሉ መደምደሚያው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን መቀበል ነው፡፡ የካህናትና የመምህራን መሾም ዋና ግቡ ምእመናንን አስተምረው ለሥጋውና ለደሙ ማብቃት ነው፡፡ ምክንያቱም የመንፈሳዊ አገልግሎት ሁሉ ግቡ ሰማያዊ ርስት መውረስ ነውና፡፡ ያለክርስቶስ ሥጋና ደም ደግሞ ሰማያዊ ርስት ማለትም የዘለዓለም ሕይወት የለም፡፡ ምክንያቱም “..እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ፤ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም” (ዮሐ.፮፣ ፶) ተብሎ ተጽፏልና፡፡ በጠፋው ልጅ ታሪክ አስቀድመን እንደተመለከትነው ልጁ ወደ አባቱ ቤት ሲመለስ አባቱ ፍሪዳ አርዶ፣ ድግስ ደግሶ ተቀብሎታል፡፡ የጠፋው ልጅ አዳም ነው፡፡ የጠፋውን አዳምን ፍለጋ የመጣው ደግሞ ክርስቶስ ነው፡፡ “የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቷልና” (ሉቃ.፲፱፥፲) እንዲል፡፡ ለአዳም ልጆች የሕይወት ምግብ ሊሆን የታረደው ፍሪዳም ራሱ ክርስቶስ ነው፡፡ በቀራንዮ ኮረብታ በዕለተ ዓርብ በመስቀል ተሰቅሎ ሥጋውን ቆርሶ፣ ደሙን አፍስሶ መሥዋዕት ሆኗልና፡፡ ጌታችን በዕለተ ዓርብ መሥዋዕት ከመሆኑ አስቀድሞ ሐሙስ ማታ “እንጀራን አንሥቶ ባርኮ ቈርሶ እንካችሁ ብሉ ይህ ሥጋዬ ነው፤ እንዲሁም ጽዋውን አንሥቶ አመስግኖ ሁላችሁ ከእርሱ ጠጡ፤ ስለብዙዎች ለኃጢአት ይቅርታ የሚፈስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው” (ማቴ.፳፮፥፳፮) በማለት ለደቀ መዛሙርቱ ሰጥቷቸዋል፡፡ ይህም የክርስቶስ ሥጋና ደም ለእኛ የሕይወት ምግብና መጠጥ ሆኖ መቅረቡን የሚናገር ነው፡፡ ስለዚህ እኛም የዘለዓለም ሕይወት ለማግኘትና ሰማያዊ ርስትን ለመውረስ የክርስቶስን ሥጋና ደም መቀበል ይኖርብናል፡፡ “ሥጋዬን የሚበላ፣ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ። ሕያው አብ እንደ ላከኝ እኔም ከአብ የተነሣ ሕያው እንደምሆን፥ እንዲሁ የሚበላኝ ደግሞ ከእኔ የተነሣ ሕያው ይሆናል” (ዮሐ.፮፥፶፮-፶፯) የሚለውም ይህንኑ የሚያስገነዝበንነው፡፡ በኦሪቱ በነበረው የመሥዋዕት ሕግ እስራኤላውያን የፋሲካውን በግ ሲመገቡ ጫማቸውን ተጫምተው፣ ወገባቸውን ታጥቀው፣ ኩፌታቸውን ደፍተው በትራቸውን ይዘው እየተቻኮሉ እንዲመገቡ ታዘው ነበር (ዘፀ.፲፪፥፲፩)፡፡ ይህም ዛሬ ላለነው ክርስቲያኖች ምሳሌ ሆኖን የአማናዊውን በግ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋውንና ደሙን ስንቀበል በጎ ምግባር ሠርተን፣ ወንጌሉን ተጫምተን፣ የንጽሕናን ዝናር ታጥቀን፣ አክሊለ ሦክን፣ ነገረ መስቀሉን እየዘከርን (መስቀሉን ተመርኩዘን)፣ ሞት እንዳለብን በማሰብ እንዳይቀድመን ፈጥነን ንስሓ በመግባት ሥጋውንና ደሙን መመገብ የሚገባን መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ ቀደም ብለን ባየነው የጠፋው ልጅ ታሪክም አባት ልጁ ከጠፋበት ሲመለስ ፊሪዳውን ከማረዱ በፊት “ባሪያዎቹን ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አምጡና አልብሱት፥ ለእጁ ቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ ስጡት” በማለት ልጁ ታጥቦ ንጹሕ የሆነውን ልብስ ለብሶና አዲስ ጫማ ተጫምቶ እንዲዘጋጅ ነበር ያደረገው፡፡ ልጁን ወደ ልቡ እንዲመለስና የአባቱን ቤት እንዲያስብ ያደረገው ረሃብ ነበር፡፡ “እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ አለ” በማለት መናገሩ ምስክር ነው፡፡ ከአባቱ ቤት ካለው ማዕድ ለመቀበል ግን አስቀድሞ ያንን ማዕድ አቋርጦ በመውጣት የበደለውን አባቱን ይቅርታ መጠየቅ ነበረበት፡፡ ስለሆነም አባቱን ማረኝ አለው፡፡ አባቱም ይቅር አለው፡፡ ከዚያ በኋላ ከፊሪዳው ተመገበ፡፡ እኛም ገና በአርባና በሰማንያ ቀናችን ጀምረን ስንመገብ የኖርነውን ሥጋውንና ደሙን መቀበል አቋርጠን ወደ ተለያየ የኃጢአት ሕይወት ብንገባም እንኳ ወደ ልባችን ተመልሰን ሥጋውንና ደሙን ለመቀበል ስንመጣ አስቀድመን ስለጥፋታችን ይቅርታ መጠየቅ እንደሚገባን ያስገነዝበናል፡፡ ይህም ሥጋውንና ደሙን ለመቀበል ንስሐ ገብተን መዘጋጀት የሚገባ መሆኑን ይገልጣል። አንድም የንስሓ ጉዞ መጨረሻው በክርስቶስ ሥጋና ደም መታተም የሚገባው መሆኑን እንድንገነዘብ ያደርገናል፡፡ በአጠቃላይ ሰው በኃጢአቱ ምክንያት ከእግዚአብሔር ከተለየ በንስሓ መመለስ ይኖርበታል፡፡ እግዚአብሔር አምላካችንም በነቢዩ ላይ አድሮ አምላካዊ ጥሪውን ያስተላለፈውና “ወደ እኔ ተመለሱ” እያለ የሚጠራን ለንስሓ ነው፡፡ ስለሆነም ሁላችንም በንስሓ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰን፣ ቅዱስ ሥጋውን በልተን፣ ክቡር ደሙን ጠጥተን ከቅዱሳን ማኅበር እንዲጨምረን የሚጠበቅብንን መወጣት አለብን፡፡ በንስሓ ተመልሰን በቤቱ እንድንኖር እግዚአብሔር በቸርነቱ፣ ቅዱሳን በአማላጅነታቸው አይለዩን። አሜን!!   

መንፈሳዊ ጉባኤ

06 Nov, 05:01


"በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

ጥቅምት ፳፯ (27) ቀን።

እንኳን ለመድኃኔዓለም ለስቅለቱ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ ለኢትዮጵያውያኑ ጻድቃን ማኅሌተ ጽጌን ከአባ ገብረ ማርያም ጋር በመሆን ለደረሱት ለታላቁ አባት ለአቡነ ጽጌ ድንግል፣ ጌታችን በዕለተ አርብ የጠጣው መራራ ሐሞት እያሰብ ሁል ጊዜ አርብ አርብ ኮሶ ይጠጡና የመድኃኔዓለም ዝክር ይዘክሩ ለነበሩት ለታላቁ አባት ለአቡነ መብዓ ጽዮንና በዋሻ ውስጥ አርባ ዓመት ለኖሩ መና ሲመገቡ ለነበሩት ለታላቁ አባት ለአቡነ ጊዮርጊስ ዘጣና ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ ለሀገረ ቃው ኤጲስ ቆጶስ ለአባ መቃርስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በዋሻ ከሚኖር ከጳውሎስና ከዮልያኖስ ከእነርሱም ጋር ላሉ ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

+ + +
የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ "እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን፤ መድኃኒቶሙ ለጻድቃን አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን፤ ስብሐት ዋህድ ዘምስለ ምሕረት፤ በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ። ትርጉም፦ እርሱ የቅዱሳን ክብራቸው፤ የጻድቃን መድኃኒታቸው ነው፤ ምድርን በሮማን አበባ አስጌጣት፤ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ከምሕረት ጋር ያለ የወልድ ምስጋና በመስቀሉና በቃሉ አባቶቻችንን ከፍ ከፍ አደረጋቸው።

+ + +
"ሰላም ለሕማሙ ወሰላም ለሞቱ። ሰላም ለገቦሁ ቅድስት ዘውኅዘ እምኔሃ ደመ ወማይ፡ፅሙር። አንቅዕተ ብዕል ወክብር። ሰላም ለግንዘቱ በዘጠብለልዎ ሰላም ለመቃብሩ ኀበ ቀበርዎ"። ትርጉም፦ ለሕማሙ ሰላምታ ይገባል፤ ለሞቱም ሰላምታ ይገባል። የሀብት (የብልጥግና) የክብር ምንጮች የኾነ ደምና ውሃ አንድነት (ተባብሮ) ከርሷ የፈሰሰ ለኾነች ለቅድስትጐኑ ሰላምታ ይገባል። በሚጠቀልሉት ገንዘብ ለኾነ ለግንዘቱ ሰላምታ ይገባል፤ በቀበሩት ዘንድ ላለ መቃብሩ ሰላምታ ይገባል። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።

+ + +
አቡነ ጊዮርጊስ ዘጣና፦ አገራቸው ጣና ዘጌ ነው። በዋሻ ውስጥ አርባ ዘመን ሙሉ ዘግተው ሲኖሩ መና ከሰማይ እየወረደላቸው ውሃም በዋሻ ውስጥ ፈልቆላቸው ይኖሩ ነበር። አንድ ቀን መልአክ መጥቶ ምን ቢጋደሉ የጌታችንን ስጋውን በልተው ደሙን ካልጠጡ እንደ ማይድኑ ነገራቸው። በመልአኩም ትዕዛዝ መሰረት ከዋሻው ወጥተው ሊቆርቡ ቤተ ክርስቲያን ገቡ በቅዳሴም ላይ ሳሉ አንድ ድንቅ ምስጢር ተመለከቱ ይህም በጸሎተ ሐሙስ ዕለት ካህኑ "ሀበነ" ሲል ጌታችን በዕለተ አርብ እንተ ተሰቀለ ሆኖ ደሙ ሲፈስ የካህኑ እጅ በደም ተነክሮ በመንበሩ ቆሞ ቢያዩት በድንጋጤ ሳይቀሳቀሱ አርባ ዓመት ተኝተዋል ይህም በሰው አቆጣጠር በጌታችን ዘንድ ግን ምን ያይህል ጊዜ እንደ ሆነ እራሱ ባለቤቱ ያውቀዋል። በመጨረሻም ጻድቁ በዐረፉ ጊዜ መቃብራቸውን አራዊት ቆፍረውላቸው መነኰሳቱ ገንዘው ቀብረዋቸዋል። ታቦታቸው በጣና ይገኝል። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት።



+ + +
አቡነ መብዓ ጽዮን፡- አባታቸው ንቡረ ዕድ እናታቸው ደግሞ ሀብተ ጽዮን ይባላሉ፡፡ በሌላኛው ስማቸው ተክለ ማርያም ይባላሉ፡፡ ይህንንም ስም ያወጣችላቸው እመቤታችን ናት፡፡ እመቤታችንን ከሕፃንነታቸው ጀምረው እጅግ ይወዷት ነበር፡፡ ትንሽ ልጅ ሳሉ አንድ ካህን ወደ ሀገራቸው በእግድነት መጣና አባታቸው ሀብተ ጽዮን አሳደሩት፡፡

እንግዳውም ካህን የእመቤታችንን ሥዕል ምስለ ፍቁር ወልዳን ይዞ ነበር፡፡ ሲተኛም በራስጌው ያኖራት ስለነበር በሀብተ ጽዮንም ቤት አድሮ ጠዋት ተነሥቶ ሲሄድ የእመቤታችንን ሥዕል በራስጌው እንዳኖራት እረስቶ ሄደ፡፡ ያንጊዜ ሕፃን የነበሩት አባ መብዓ ጽዮንም ሥዕሏን ወስደው ሳሟት፣ በእርሷም ደስ ተሰኙባት፡፡ ለሌላም ሰው አልሰጥም ብለው በአንገታቸው አሰሯት፡፡ ሀብተ ጽዮንም "ይህችን የእግዳው ካህን ንብረት የሆነች የእመቤታችንን ሥዕል ከቤት እንዳላስቀምጣት ኃጢአት ይሆንብኛል እንዳልሰጠውም ከየት አገኘዋለሁ" እያለ ሲቀጨነቅ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ያንን እንግዳ አገኘው፡፡ ባገኘውም ጊዜ ከቤት የተዋትን የእመቤታችንን ሥዕል እንዲወስድ ነገረው፡፡ መጀመሪያ ሕፃን መብዓ ጽዮን እንዳገኛትና በጣም እንደወደዳት ለሌላ ሰውም አልሰጥም ብሎ በግድ ቀምቶ እንዳስቀመጣት ነገረው፡፡ እንግዳውም ይህን ሲሰማ "የሥዕሊቱ ባለቤት እርሷ የሕፃኑ እንድትሆን ፈቅዳለታለች፤ ከእኔ ዘንድ መሆኗን ፈቅዳ ቢሆንማ ኖሮ ባልተረሳችኝ ነበር ለዚያ ላገኛት ልጅህ የተገባች ናት" ካለው በኋላ እርስ በእርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጥተው ተለያዩ፡፡

አቡነ መብዓ ጽዮን ዕድሜያቸው ከፍ ሲል ወላጆቻቸው ሚስት ሊድሩላቸው ሲሉ እርሳቸው ግን አላገባም ብለው የዚህን ዓለም ጣዕም ንቀው ነው የመነኑት፡፡ የምንኩስና ልብስ ከለበሱበት ጊዜ ጀምረው በበቅሎና በፈረስ ላይ ተቀምጠው አያውቁም፤ በአልጋም ሆነ በምንጣፍ ላይ አልተኙም ይልቁንም የአንድ ሰው ሸክም የሚያህል ትልቅ ድንጋይ በደረታቸው ተሸክመው ከአመድ ላይ ይተኙ ነበር እንጂ፡፡ ከሰንበት ቀናት ውጭ ሲቀመጡም ድንጋዩን በራሳቸው ላይ ይሸከሙታል፣ ሲሰግዱም በጀርባቸው ያዝሉት ነበር፡፡

አባታችን ለቅዱስ ሥጋ ወደሙ እጅግ ትልቅ ክብር ስለነበራቸው የቆረበ ሰው ከቤተክርስቲያን ወጥቶ ሲሄድ እንቅፋት እንኳን ሲመታው ስለሥጋ ወደሙ ክብር ብለው እግሩ የደማበትን ሰው ደሙን ይጠጡት ነበር፣ ደሙ የፈሰሰበትንም አፈር ይልሱታል፡፡ ይህም የመድኃኔዓለምን ሥጋና ደም ከማክበራቸው የተነሣ ነው፡፡ ጻድቁ ጌታችን በዕለተ ዓርብ መራራ ሐሞት መጠጣቱን አስታውሰው ሁልጊዜ ዐርብ ዐርብ ኮሶ ይጠጡ ነበር፡፡ መድኃኔዓለምም በየጊዜው በሕፃን አምሳል ይገለጥላቸዋል፡፡ በዕለተ ዓርብም እንደተሰቀለ ሆኖ ይገለጥላቸው ነበር፡፡ ዳግመኛም ጌታችን ለአቡነ መባዓ ጽዮን በመሠዊያው ላይ በነጭ በግ አምሳል ይገለጥላቸው ነበር፡፡

መከራ ሞቱን እያስታወሱ ሰውነታቸውን ይጎዱ እንደነበር በቅዱስ ገድላቸው ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡- "በተቀደሰች በዓርባ ጾምም የመድኃኔዓለምን ግርፋት እያሰበ ሰውነቱን በእጅጉ ገረፈ፡፡ ደሙ ከመሬት እስኪወርድ ድረስ ልቡንም አጥቶ ከምድር ላይ ወደቀ፡፡ የመድኃኔዓለምን መከራውን አስቦ እንደሞተም ሆነ፡፡ መድኃኔዓለምም ወደ እርሱ መጣና "ተነሥ እኔ ቁስልህን እፈውስሃለሁ" ብሎ የጀርባውን ቁስል ዳሰሰው፡፡ ምንም ሕማም እንዳላገኘውም ሆነ፡፡ መድኃኔዓለምም አባታችንን "በአንተው እጅ ትገደልን? እኔ እንኳ የተገደልኩት በአመፀኞች በአይሁድ እጅ ነው" አለው፡፡ በዚያችም ሰዓት ጌታ የመባዓ ጽዮንን ከንፈሮቹን ይዞ ሦስት ጊዜ እፍ አለበትና "የከበረ ትንፋሼም ከትንፋስህ ጋራ ይጨመር፣ ሥጋህም ከነፍስህ ጋራ የከበረ ይሁን› አለው፡፡ "አንተ በላዩ እፍ ያልህበትም የተቀደሰና የከበረ ይሁን" አለው"፡፡

መንፈሳዊ ጉባኤ

06 Nov, 05:01


ጌታችን ለአቡነ መብዓ ጽዮን የወርቅ በትር ሰጥቷቸው በእርሷ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጡባት ነበር፡፡ መቋሚያዋም እሳቸው ካረፉ በኋላ የሚሞተውን ሰው እየለየች ትናገር ነበር፡፡ አባታችን እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም በመልአክ ተጥቀው ተወስደው የሥላሴን መንበር ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር አጥነዋል፡፡ ጌታችን ከተረገመችና ከተወገዘች ዕፅ ጋር በተገናኘ ለአቡነ ዘርዐ ቡሩክና ለአቡነ መብዓ ጽዮን ልዩ ምሥጢር እንደነገራቸው በሁለቱም ቅዱሳን ገድላት ላይ በሰፊው ተጽፏል፡፡

አቡነ መብዓ ጽዮን በይበልጥ የሚታወቁት ሁልጊዜ ወር በገባ በሃያ ሰባት መድኃኔዓለምን አብልጠው በመዘከራቸው ነው፡፡ በዚህም ምክንያት "እንደ አንተም በየወሩ በሃያ ሰባት የሞቴ መታሰቢያ ለሚያደርግ ነፍሳትን ከሲኦል አወጣለታለሁ" የሚል ድንቅ ቃልኪዳን ከጌታችን ተቀብለውበታል፡፡ ይኸውም የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ሲነግራቸው ነው፡፡ ቅዱስ አባታችን "ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ! በዓልህን አደርግ ዘንድ አንተ የምትወደውን ግለጥልኝ" ብለው ጌታችንን ሲጠይቁት እርሱም "የሞቴን መታሰቢያ ያደረገ እንደ እኔ ነፍሳትን ከደይን ያወጣል፣ "በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ይሠራል፣ ከዚያም የበለጠ ይሠራል" ብዬ በወንጌሌ እንደተናገርሁ" አላቸው"፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን ለልጆቻቸው እንዲህ ብለው መከሯቸው፡- "ክርስቲያኖች ሁሉ የፈጣሪያችንን የመድኃኔዓለም ክርስቶስን የመታሰቢያ በዓሉን እናድርግ፡፡ የአባቶቻችን የሐዋርያት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የመላእክት መታሰቢያቸው ባረፉበት በተሾሙበት ቀን ይከበራል፡፡ እነርሱን የፈጠራቸው እርሱ መድኃኔዓለም ነው፣ ያከበራቸው፣ ከፍ ከፍ ያደረጋቸው፣ ስማቸውን ለጠራ መታሰቢያቸውን ያደረገ እንደሚድን ቃልኪዳን የሰጣቸው እርሱ ነው፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ ያደረገ ግን የተኮነኑ ነፍሳትን ከደይን ያወጣል፣ በሞቱም ጊዜ ሥቃይን አያያትም"፡፡

የአቡነ መብዓ ጽዮን በዓለ ዕረፍታቸውም እጅግ አብዝተው በሚዘክሩበትና ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ታስቦ በሚውለው በመድኃኔዓለም ቀን ጥቅምት ሃያ ሰባት ነው፡፡ ከአባታችን አቡነ መብዓ ጽዮን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!።

+ + +
አቡነ ጽጌ ድንግል፡- ደራሲና ማኅሌታዊ ሲሆኑ የላመ የጣፈጠ ከመብላት ተቆጥበው ጥሬ ቆርጥመው 9 ዓመት ከቆዩ በኋላ የእመቤታችንን ስደት በጣም በጥልቀት የሚተርከውን "ማኅሌተ ጽጌን" የደረሱ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ውኃም በሦስት ቀን አንድ ጊዜ ብቻ ነበር የሚጠጡት፡፡

አቡነ ጽጌ ድንግል ከደብረ ሐንታው ከአቡነ ገብረ ማርያም ጋር እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ድርሰቱን በመዝሙረ ዳዊት መጠን 150 አድገው ደርሰዋል፡፡ አቡነ ገብረ ማርያምና አቡነ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌን በጥምረት ሊደርሱት የቻሉት አቡነ ገብረ ማርያም በወሎ ክፍለ ሀገር በወረኢሉ አውራጃ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ በሚባለው ገዳም የሕግ መምሕር ሆነው በተሾሙበት ወቅት ነው፡፡ እነዚህም ሁለት ቅዱሳን የዘመነ ጽጌ የማኅሌት አገልግሎትን ሳይለያዩ በሰላምና በፍቅር በአንድነት አግልግለዋል፡፡ ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡-
አንድ ዓመት አቡነ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በሆነው መስከረም 25 ቀን ከደብረ ሐንታ መጥተው ደብረ ብሥራት አቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ገብተው ከመስከረም 25 ቀን እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ የ40 ቀን አገልግሎት ከአቡነ ጽጌ ድንግል ጋር ፈጽመው ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብራቸው ደብረ ሐንታ ይመለሳሉ፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ አቡነ ጽጌ ድንግል ከገዳማቸው ከደብረ ብሥራት ተነሥተው ወደ ደብረ ሐንታ ሄደው እንዲሁ እንደ አቡነ ገብረ ማርያም 40ውን ቀን አግልግለው ይመለሳሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ቅዱሳን እንደዚህ እያደረጉ በየተራ አንደኛው ወደ ሌላኛው ገዳም እየሄዱ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በፍጹም ፍቅርና በትሕትና አብረው እመቤታችንን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ ይኸውም በራሳቸው በአቡነ ገብረ ማርያም ገድል ላይ እና በአቡነ ዜና ማርቆስ ገድል ገጽ 72-73 ላይ በሰፊው ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ የሁለቱ ድርሰታቸው የሆነው "ማኅሌተ ጽጌ" ድርሰት የእመቤታችንንና የልጇን የጌታችንን ሥጋዊ ስደት የሚገልጽ ሲሆን በጨማሪም ስደት የማይገባው አምላካችን ወደ አህጉራችን አፍሪካ ተሰዶ የሠራቸውን ድንቅ ድንቅ ተአምራትና የእመቤታችንን ንጽሕናዋን ቅድስናዋን አማላጅነቷን የሚያስረዳ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡

አባ ጽጌ ድንግል ከማኅሌተ ጽጌ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ አስደናቂ ድርሰቶችን ደርሰዋል፡፡ የጻድቁ ቅዱስ ዐፅማቸው፣ ታቦታቸውና የደረሷቸው በርካታ ድርሰቶች በገዳማቸው ደብረ ጽጌ ውስጥ በክብር ተጠብቀው ይገኛሉ፡፡ አምሃራ ሳይንት ቦረና ከአቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም የ5 ሰዓት የእግር መንገድ ከተሄደ በኋላ የሚገኘው ገዳማቸው "ደብረ ጽጌ" ከአንድ ወጥ ዓለት ተፈልፍሎ የተሠራው ሲሆን አሠራሩም እጅግ ድንቅ ነው፡፡

የአቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ከአቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ጋር የሚያገናኘው "የእግዜር ድልድይ" የተባለ አስገራሚ ታሪክ ያለው ድልድይ አለው፡፡ ሁለቱ ቅዱሳን በመንፈስ ተጠራርተው ለመገናኘት ቢያስቡም የወለቃ ወንዝ ሞልቶ በአካል ሳይገናኙ ቀሩ፡፡ በዚህም በጣም አዝነው ከወንዙ ወዲያና ወዲህ ሆነው ተላቅሰው አፈር ተራጭተው ወደየገዳማቸው ቢመለሱም ያ ተላቅሰው የተራጩት አፈር በተአምር ትልቅ ድልድይ ሆነ፡፡ ድልድዩን ሁለቱም በበዓታቸው ሆነው በመንፈስ አዩት፡፡ የበጎ ነገር ጠላት ሰይጣንም ይህንን ሲመለከት ድልድዩን
በትልቅ ሹል ድንጋይ በስቶ ሊያፈርሰው ሲል አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመንፈስ አዩትና ከጋስጫ ተነሥተው በደመና ተጭነው በመሄድ ሰይጣኑን በግዘፈ ሥጋ ገዝተው ያንን ድልድዩን አፈርስበታለሁ ያለውን ትልቅ ሹል ድንጋይ አሸክመውት በዓታቸው ጋስጫ ድረስ ወስደውታል፡፡ ያ ድንጋይ ዛሬ በጋስጫ አቡነ ጊዮርጊስ ገዳም ለመነኮሳቱ ደወል ሆኖ እያገለገለ ይኛል፡፡ ድልድዩም እስከ አሁን ድረስ ለአካባቢው ኢስላም ማኅበረሰብ ብቸኛው የወለቃ ወንዝ መሻገሪያቸው ሆኖ እያገለገላቸው ነው፡፡
ከአባታች አቡነ ጽጌ ድንግል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ይሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን! ምንጭ፦ገድለ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ መዝገበ ቅዱሳን።

+ + +
አባ መቃርስ ዘሀገረ ቃው፡- ለዚህም ቅዱስ የዝንጉዎችን ምክር ተከትሎ ያልሔደ በኃጢአተኞችም ጎዳና ያልተጓዘ በዘባቾችም መቀመጫ ያልተቀመጠ የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ፈቃዱ የሆነ እንጂ ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያነብ የሚያስተምር ብፁዕ ነው የሚለው የነቢይ ዳዊት ቃል ተፈጽሞለታል።

ይህም አባ መቃርስ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅ በመክሊት ነግዶ ዕጥፍ አድርጎ አትርፎአልና እግዚአብሔርም በእጆቹ ያደረጋቸውን ታላላቆች ድንቆች ተአምራት ስንቱን እናገራለን። ስለርሱም እንዲህ ተባለ እርሱ በአገረ ቃው ተሾሞ በወንበር ተቀምጦ ሕዝቡን በሚያስተምራቸው ጊዜ ዘወትር ያለቅሳል ከደቀ መዛሙርቶቻቸውም አንዱ በእግዚአብሔር ስም ካማላቸው በኋላ ለምን ሁልጊዜ እንደሚያለቅሱ በመሐላው አምሎ ጠየቃቸው፡፡ እርሳቸውም ስለመሐላቸው ፈርተው ነገሩት "ዘይት በብርሌ ውስጥ ጎልቶ እንደሚታይ

መንፈሳዊ ጉባኤ

06 Nov, 05:01


የወገኖቼም ኃጢአት እንዲሁ በታየኝ ጊዜ አለቅሳለሁ" አሉት፡፡ በሌላም ጊዜ ጌታችን በመሠዊያው ላይ ሆኖ ተገልጦላቸው የእያንዳንዱን ሰው ኃጢአት መላእክት ሲያቀርቡለት አሳያቸው፡፡ ቀጥሎም "ሕዝቡን አስተምረህ ከክፋታቸው መልሳቸው" አላቸው፡፡ እሳቸውም "አይሰሙኝም" ቢሉት ጌታችንም "አስተምረሃቸው ከክፋታቸው ባይመለሱ ደማቸው በራሳቸው ላይ ይሆናል" አላቸው፡፡

መናፍቁ ንጉሥ መርቅያኖስና ተከታዮቹ ክብር ይግባውና ጌታችንን "ሁለት ባሕርይ" በማለታቸው ጉባዔ ሠርተው አባቶች ሲሰበሰቡ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ አባ መቃርስን አስከትሎ በጉባዔው ተገኘ፡፡ አባ ዲዮስቆሮስና አባ መቃርስም ሁለት ባሕርይ ባዮችን አስተምረዋቸው እምቢ ቢሏቸው አውግዘውና እረግመው ከቤተ ክርስቲያን ለዩአቸው፡፡ ለመከራም የተዘጋጁ ሆነው ራሳቸውን አሳልፈው ሰጧቸው፡፡ ከሃዲው ንጉሥም ወደ ጋግራ ደሴት አጋዛቸው፡፡ አባ ዲዮስቆሮስም ለአባ መቃርስ "አንተ በእስክንድርያ ሀገር ሰማዕትነት ትቀበላለህ" በማለት ትንቢት ነግረዋቸው ከአንድ ነጋዴ ጋር ወደ እስክንድርያ ላኳቸው፡፡ እዚያም ሲደርሱ መናፍቁ ንጉሥ መርቅያኖስ አባ መቃርስን ይዞ ብዙ ካሠቃያቸው በኋላ ኩላሊታቸውን ብሎ ገደላቸውና የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ጥቅምት 27 ቀን ሆነ፡፡ ክርስቲያኖችም ሥጋቸውን ወስደው ከነቢዩ ኤልሳዕና ከመጥምቁ ዮሐንስ ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት፡፡ ከሥጋቸውም ብዙ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ መቃርስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት27 ስንክሳርና መዝገበ ቅዱሳን።

+ + +
የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም። ወገብረ መድኃኒት በማእከለ ምድር። አንተ አጽናዕካ ለባሕር በኃይልከ"። መዝ73፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ27፥20-57።

+ + +
የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ተሣለኒ እግዝኦ እስመ ኬደኒ ሰብእ። ወኵሎ አሚረ አሥርሐኒ ቀትል። ወኬዱኒ ፀርየ ኵሎ ዓሚረ በኑኀ ዕለት"። መዝ55፥1-2። የሚነበቡት መልዕክታት 1 ኛቆሮ 12፥20-28፣ 1ኛ 2፥20-ፍ.ም፣ የሐዋ ሥራ 5፥12-17። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ3፥11-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ በዓል፣ የአባ ጽጌ ድንግልና የአቡነ መብዓ ጽዮን የዕረፍታቸው በዓልና የጽጌ ጾም ለሁላችንም ይሁንልን።
መልካም። ቀን

መንፈሳዊ ጉባኤ

26 Oct, 05:42


ወዳጄ ሆይ! ኃጢአተኛ ከኾንህ በደልህን ትናዘዝ ዘንድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፤ ጻድቅም ከኾንህ ከጽድቅ (ጎዳና) እንዳትወድቅ ወደ ቤተ ክርስቲያን ና፤ ቤተ ክርስቲያን የኃጥኡም የጻድቁም ወደብ ናትና፡፡

ኃጢአተኛ ነህን? ተስፋ አትቁረጥ፤ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህም ንስሐ ግባ፡፡ ኃጢአት ሠርተሃልን? እንግዲያውስ እግዚአብሔርን “በድያለሁ” በለው፡፡

እስኪ ንገረኝ! “በድያለሁ” ብለህ ለመናዘዝ ምን ውጣ ውረድ፣ ምን ዓይነት የሕይወት መርሕ፣ ምንስ መከራ አለው? “በድያለሁ” ብሎ አንዲት ቃል ለመናገር ክብደቱ ምኑ ላይ ነው? ምናልባት (ኃጢአት ሠርተህ ሳለ) በደለኛ አይደለሁም የምትል ከኾነ ዲያብሎስም አንተን አይወቅስህም፡፡ (በድያለሁ ብለህ ንስሐ የምትገባ ከኾነ ግን) ይህን (ዲያብሎስ ሊወቅስህ እንደሚችል) አስቀድመህ አስብ፡፡ …

ስለዚህ ክብርህን እንዳይወስድብህ ለምን አትከለክለውም? ለቅጽበት ያህልስ እንኳን የማይተኛ ከሳሽ እንዳለህ ዐውቀህ ለምን በደልህን ተናዝዘሃት አታስወግዳትም?

ኃጢአት ሠርተሃልን? እንግዲያውስ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ እግዚአብሔርን “በድያለሁ” ብለህ ንገረው፡፡ እኔ ከዚህ ውጪ ከአንተ የምፈልገው ሌላ ምንም ነገር የለኝም፡፡
መጽሐፍ ቅዱስም፡- “ንግር አንተ ኃጣውኢከ ቅድመ ከመ ትጽደቅ - ትከብር ዘንድ አንተ አስቀድመህ ኃጢአትህን ተናገር” ይላል (ኢሳ.43፡26)፡፡ ስለዚህ ኃጢአትህን ታስወግዳት ዘንድ ተናዘዛት፡፡

ይህን ለማድረግ ውጣ ውረድ የለውም፤ ዙሪያ ጥምጥም የቃላት ድርደራም አያሻህም፤ ገንዘብ መክፈል አያስፈልግህም፤ ወይም እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ነገሮች አያስፈልጉህም፡፡ አንዲት ቃል ተናገር፤ በደልህን በአንቃዕድዎ አስባት፤ “በድያለሁ” ብለህም ተናዘዛት፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

መንፈሳዊ ጉባኤ

22 Oct, 01:33


“ምን ፍሬ አፈራን?”  በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ልጆቼ! እስኪ ፍቀዱልኝና ዛሬ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡፡ ብዙውን ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ትመላለሳላችሁ፡፡ መልካም ነው፡፡ ግን ምን ለውጥ አመጣችሁ? ምን ፍሬ አፈራችሁ? ታገለግላላችሁን? ከአገልግሎታችሁ ምን ረብሕ አገኛችሁ?

ጥቅምን ካገኛችሁ በእውነት ምልልሳችሁ የጥበበኛ ምልልስ ነበር ማለት ነው፡፡ ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ወንጌላውያን እንዲህ እያስተማሩን ሳለ የማንለወጥ ከሆነ ግን የእስከ አሁን ምልልሳችን የአይሁድ ምልልስ ነበር ማለት ነው፡፡ አይሁዳውያን ሕገ ኦሪትን የተሰጠቻቸው ኃጢአታቸውን በእርሷ መስታወትነት አይተው ንስሐ እንዲገቡባት ነበር፡፡ እነርሱ ግን የንስሐ ፍሬ ሳያፈሩባት እንዲሁ ይመኩባት ነበር፡፡ ስለሆነም ለሕይወት የተሰጠቻቸው ሕግ ሞት ሆና አገኟት፡፡ እኛም እንዲህ ለኵነኔ ያይደለ ለጽድቅ የተሰጠችን ወንጌል ፍሬ የማናፈራበት ከሆነ ከአይሁዳውያን የባሰ ቅጣት ትፈርድብናለች፡፡

እስኪ ምሳሌ መስዬ ላስረዳችሁ፡፡ አንድ የሚታገል ሰው (wrestler) በየጊዜው ተጋጣሚውን እንደምን ማሸነፍ እንዳለበት ልምምድ የሚያደርግ ከሆነ ክህሎቱ ይዳብራል፡፡ ተጋጣሚውም በቀላሉ ማሸነፍ ይቻሏል፡፡ በየጊዜው ራሱን የሚያሻሽል (Update) የሚያደርግ ሐኪም ጐበዝ አዋቂና ሕመምተኞችን በአግባቡ የሚረዳ ይሆናል፡፡ በየቀኑ ቃሉ የሚነገረን እኛስ ምን ለውጥ አመጣን? ምን ፍሬ አፈራን?

እየተናገርኩ ያለሁት ለአንድ ዓመት ብቻ በቤተ ክርስቲያን የቆዩትን ምእመናን አይደለም፡፡ እየተናገርኩ ያለሁት ከልጅነታችን አንሥተን በቤቱ ለምንመላለስ እንጂ፡፡ ይህን ያህል ዘመን በቤቱ እየተመላለስን ፍሬ ካላፈራን ቤተ ክርስቲያን ደርሰን ብንመጣ ምን ጥቅም አለው? አባቶቻችን አብያተ ክርስቲያናት ያነጹልን ለምንድነው? ዝም ብለን እንድንሰባሰብ ነውን? እንደዚህማ በገበያ ቦታም መሰባሰብ አንችላለን፡፡ አበው አብያተ ክርስቲያናትን ያነጹለን ቃሉን እንድንማርበት፣ በተማርነው ቃልም የንስሐ ፍሬ እንድናፈራበት፣ ሥጋ ወደሙን እንድንቀበልበተ፣ እርስ በእርሳችን እንድንተራረምበት እንጂ ለሌላ ዓላማ አይደለም፡፡
ታዲያ ምን ፍሬ አፈራን?

መንፈሳዊ ጉባኤ

21 Sep, 16:57


https://vm.tiktok.com/ZMhFWjew7/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite

መንፈሳዊ ጉባኤ

20 Sep, 23:54


#ወንድሞቼ_ሆይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውድ ስጦታዎችን ይዛችሁ ስትመጡ አያለሁ፡፡ መልካም አድርጋችኋል፡፡ ነገር ግን ስትመለሱ ደግሞ መበለቶችን፣ ደሀ አደጎችንና ሕጻናትን ስትበድሉ አያችኋለሁ፡፡ ታድያ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ በወርቅ የተንቆጠቆጠ ምሥዋዕና ጽዋዕ ብታቅረቡ ምን ይጠቅማችኋል? ለምንስ መሥዋዕቱን ማክበር ስትፈልጉ አስቀድማችሁ ልባችሁን መባ አድርጋችሁ አታቀርቡም? ልባችሁ በጭቃ ተጨማልቆ ምሥዋዑ እንኳን ወርቅ ፕላቲንየምስ ቢሆን ምን ይረባችኋል? ምንስ ይጠቅማችኋል?

#ተወዳጆች_ሆይ!
አመጣጣችን በወርቅ የተለበጠ መሠዊያ ለማቅረብ ሳይሆን ይኸን ከልብ በመነጨ ለማቅረብ ይሁን፡፡ ከልባችን የምናቀርበው ነገር ሁሉ ከወርቅ የበለጠ መባ ነው፡፡

#ልብ_በሉ!
ቤተ ክርስቲያን የወርቅ ወይም የነሐስ ማቅለጫ ቦታ አይደለችም፤ ለቅድስና የተጠሩ ሁሉ እና የመላእክት ኅብረት እንጂ፡፡ስለዚህ ከስጦታችሁ በፊት ልባችሁን ይዛችሁ ኑ፡፡ እግዚአብሔር እኮ ሥጦታችንን የሚቀበለው ደሀ ሆኖ ሳይሆን ስለ ነፍሳችን ብሎ ነው፡፡

#ክርስቶስን_ማክበር_ትወዳላችሁን?
እንግዲያስ ዕራቆቱን ስታዩት ችላ አትበሉት፡፡ እናንተ ወደ ቤተ መቅደስ ስትመጡ እጅግ ውድ በሆኑ ልብሶች አጊጣችሁ ስትመጡ እርሱ በብርድና በመራቆት ሊሞት ነውና ብያንስ ትንሽ እንኳን እዘኑለት፡፡ ቤተ መቅደስ ረግጣችሁ ቤተ መቅደስ አትምጡ፡፡ በቃሉ “ይህ ሥጋዬ ነው” ያለው ጌታ በተመሳሳይ ቃሉ “ተርቤ ስታዩኝ አላበላችሁኝም፤ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም” ብሏልና።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

መንፈሳዊ ጉባኤ

20 Sep, 23:49


ፈረስ የሚጋልብ ሰው ልጓሙን በአግባቡ ካልያዘው በቀር ፈረሱም ጋላቢውም ይጎዳሉ፡፡ አንድ እባብ የነደፈው ሰው ባለመድኃኒቶችን አግኝቶ መርዙ ወደ ሰውነቱ ኹሉ እንዳይሰራጭ ካላደረገ በቀር ወደ ሞት ሊደርስ ይችላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ አንድ ትንሽ ቁስል በጊዜው ጊዜ ካልታከሙት በቀር ሰፍቶና ተስፋፍቶ ትልቅ ቁስል ወደ መኾን ያድጋል፡፡

በእኛ በክርስቲያኖች ዘንድም እንደዚህ ነው፡፡ የኃጢአት ቁስል የሚሰፋው ችላ ሲባል ነው፡፡ ገና ትንሽ ነው በሚባልበት ደረጃ ካላራቅነው በቀር ነገ ከነገ ወዲያ ትልቅ ቁስለ ነፍስ ይኾናል፡፡

ተመልከቱ! ዛሬ ላለመቈጣት የሚታገል ሰው ነገ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴን አይዘይድም፡፡ ሰዎችን የሚጎዳበት ዘዴ ካልዘየደም ብዙ ባልንጀሮች ይኖሩታል፡፡ ብዙ ባልንጀሮች ካሉት የሚጠላቸውም የሚጠሉትም ሰዎች አይኖሩም፡፡ ባልንጀራ እንጂ ጠላት የሌለው ሰውም የምግባር ኹሉ ፍጻሜ የኾነውን ፍቅር ገንዘብ ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ተወዳጅ ሆይ! ወደዚህ ምግባር ታድግ ዘንድ ወደዚህ እንዳታድግ የሚያደርጉህን ጥቃቅን ኃጢአቶችን ከአንተ አርቅ፡፡ ሰፍቶ ተስፋፍቶ ነገ እንዳይቸግርህ ዛሬ በእንጭጩ እያለ ችላ አትበለው፡፡

ይሁዳ ገና የገንዘብ ፍቅር ደረጃ ላይ እያለ ራሱን ቢመረምርና ይህን ለማራቅ ቢጥር ኖሮ በኋላ ከተሰበሰበው ገንዘብ ወደ መስረቅ ባላደገ ነበር፡፡ ገና ከመጀመሪያው ደረጃ እያለ ችላ ባይል ኖሮ የኃጢአት ኹሉ ራስ የኾነው ኃጢአት ወደ መፈጸም ባልደረሰ ነበር፡፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንደዚህ ልናደርግ እንደሚገባን ሲያስተምረን ከዝሙት ብቻ እንድርቅ ሳይኾን የእርሱ ሥር የኾነውንና አይቶ መመኘትን ችላ ልንለው እንደማይገባን ነገረን (ማቴ.5፡28)፡፡ ኃጢአት ሥር ሰዳና ሰፍታ ከመቸገራችን በፊት በችግኝ ደረጃ ላይ እያለች ነቅለን መጣል ቀላል ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

መንፈሳዊ ጉባኤ

10 Sep, 15:29


​​​​🌼 ልጄ ሆይ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ

ልጄ ሆይ....... ወጣትነት ፈትኖህ፤ለስጋህ አድልተህ፤ነፍስህን አቀጭጨኻት ከአለም የኖርክበትን ዓመትህን ጥለኸው በንሰሐ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ..... በአዲስ አመት ለአምላክህ የሚገባህን ግብር ትፈፅም ዘንድ በፍቅሩ አፀድ እንድትገኝ ካለመታዘዘ ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ....... በአፈር ከሚሸነፈው ስጋዊ ዘርህ ወጥተህ ሰማያዊነትን ከሚያለብስህ ከማይጠፋው ሰማያዊ ዘር ክብረት ታደርግ ዘንድ ሰውን ካለመውደድ ጥላቻ ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...... በምክንያቶች ተደልለህ አፅዋማትን ዘለህ፤ምስጋናን ነፍገህ፥አገልግሎትን ንቀህ ከአለም ጫጫታ ውስጥ የዘፈቀውን ማንነትህ እንዳያጠፋህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...... ዲያቢሎስ በቃል እንዳያስትህ፤በማማለል እንዳይጠልፍህ የመንጋውን ጠባቂ ቃልን ስማ፤ የመታዘዝን በረከት ታገኝ ዘንድ ከትምህክትህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ።

ልጄ ሆይ .....ቀናት ሳይሆን መንፈስህ ይለወጥ፤ፀሐይ ሳትሆን የህይወት ጀንበርህ ይለወጥ።

ልጄ ሆይ ......ዕለታት አይሰልጥኑብህ፤ ዘመናት  እስከ ሞትህ ጥግ ድረስ እስኪገፉህ ሳትጠብቅ አንተም እንደ ዘመንህ ተለወጥ

ልጄ ሆይ .....የእግዚአብሔር ፍቅር ለተከፈተ ልብ ቸር ነው ። ርህራሄው ጥልቅ ነው ። በአምሳሉ ፈጥሮሃል እና እንዳትጠፋ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት የደረስ ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል ። ስለዚህ ከዘመንህ ቀድመህ ተለወጥ።

ልጄ ሆይ ...አዛኝቷን ተለማመን፤መላአኩን ተማለደው ፤ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህን ጥራ፤ ፃድቃንን ዘክር እንጅ ላለመለወጥ ተማምለው ቀናት ብቻ ከሚለወጥባቸው ሰልፈኞች ተርታ አትገኝ ።

በንስሐ ወደ በረቱ የምንመለስበት ዘመን ይሁንልን! አሜን

🌻 መልካም አዲስ አመት ይሁንልን
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
━━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
       

መንፈሳዊ ጉባኤ

06 Sep, 02:15


የስሙንም ትርጉም ስንመለከት ‹‹ሩፋ›› ማለት ሐኪም ማለት ነው፡፡ ኤል ማለት እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ሩፋኤል ማለት የእግዚአብሔር ሐኪም ማለትነው፡፡ ሌላው መልአከ ሰላም ወጥዒና ወይም የሰላም እና የጤና መልአክ ይባላል፡፡

የሰው ልጆችን ከተያዙበት ከተለያዩ በሽታውች በጸሎቱ፣ በአማልጅነቱ እንዲፈውስ ስልጣን እና ጸጋ የተሰጠው ታላቅ መልአክ ነው፡፡
ሩፋኤል ማለት የእግዚአብሔር ሐኪም ማለት መሆኑን ነብየ

እግዚአብሔር ቅዱስ ሄኖክ በመጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 10 ቁጥር 13 ላይ ‹‹በበሽታ ሁሉ ላይ፣ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ፤ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው›› እንዲሁም እዛው መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ 6 ቁጥር 3 ላይ

‹‹በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መልእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው››  በማለት እግዚአብሔር ለቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የወጣውን፤ ቁስል እና ደዌ፤ ይፈውስ ዘንድ ስልጣን እንደሰጠው፣ ሐኪም እንዳደረገው ነግሮናል፡፡

እንዲሁም ፈታሄ ማሕፀን ይባላል፡፡ እንኳን በምጥ የተያዙትን ሴቶች፣ እናቶች፤ ቀርቶ እንስሳት እንኳን ምጥ ሲፀናባቸው፣ ስሙን ከጠሩት ይፈታቸዋል፡፡ ይህ መልአክ በተለይ ለሴቶች እጅጉን ረዳታቸው ነው፡፡ ከፀነሱበት ጊዜ አንስቶ እስኪወልዱ አይለያቸውም፡፡

በተለይ በእርግዝናቸው ጊዜ ስሙን እየጠሩ፣ መልኩን እየጸለዩ፣ ጸበሉን እየጠጡ እየተዳበሱ፣ ከተማጸኑት ጭንቀታቸውን ያቀላል፣ በሰላም ያዋልዳቸዋል፡፡

ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይሁንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችንን ስለ ቅዱስ ሩፋኤል እንዲያሳውቃቸው፣ ክብሩን እንዲገልጽላቸው ጠየቁት፡፡ ጌታም ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል እና ቅዱስ ሩፋኤልን እንደሚመጡ አዘዛቸው፡፡ እነሱም መጡ፡፡

ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ስለ ራሳቸው ከተናገሩ በኃላ ጌታም ቅዱስ ሩፋኤልን ‹‹ክብርህን ንገራው›› አለው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤልም ለጌታ ሰግዶ ለሐዋርያት ብዙ ምስጢር ነገራቸው፡፡

በተለይም ስሙን ለሚጠሩ፣ መታሰብያውን ለሚያደርጉ፣ በጸሎቱ ለሚማጸኑ፣ እንደማይለያቸው፣ እንደሚረዳቸው፣ ክብር እንደሚያሰጣቸው ለሐዋርያት ነግሯቸው ወደ ሰማያት አርጓል፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያትም በወቅቱ ወንጌልን ሲያስተምሩ፣ ስለ ቅዱስ ሩፋኤል ክብር እና በእሱ የሚገኘውን መልአካዊ እርዳታ፣ ለምዕመናኑ በደንብ አስተምረዋል፡፡

ቅዱስ ሩፋኤል ልቦናን ደስ የሚያሰኝ፤ ባለ መድኃኒት ፈዋሽ፤ የጸሎት መዝገብ መክፈቻ የተሰጠው፤ በዙፋን ላይ በክብር የሚቀመጡ መላእክት መሪ፤ የሰውንም ይሁን እንስሳን ማሕፀን የሚፈታ፤ አዋላጅ፣ ምጥን የሚያቀል፣ ታላቅ መልአክ ነውና እንጠቀምበት፡፡

ስለዚህ የቅዱስ ሩፋኤል ቀን የዘነበውን ዝናብ በዕቃ ቀድታችሁ አስቀምጡ፡፡ ያንንም ጸበል ቤታችሁን፣ ደጃችሁን፣ እንዲሁም የሥራ ቦታችሁን እርጩበት፣ እየቆጠባችሁ እህል ስታቦኩ አብኩበት ጠጡት ተጠመቁበት፡፡ ብዙ በረከት እና ፈውስ ታገኙበታላችሁ፡፡

እህል እና ገንዘብ የሚሰልብባችሁን የሰላቢ መንፈስ ያርቅላችኃል፡፡
ውጭ ሀገር ያላችው እህት ወንድሞቼ ጸበል መጠመቅ ስለማይመቻችሁ፤ ውኃ አቅርባችሁ፣ ያስለመዳችሁትን ጸሎት ውሃው ላይ ጸልያችሁ ‹‹አምላከ ቅዱስ ሩፋኤል›› ባርክልኝ ብላችሁ ቤት ውስጥ ተጠመቁ ጠጡት፡፡

ጳግሜን መጠመቅ ከጥንት አባቶቻችን ጀምሮ የነበረ እና በየአመቱ ጳግሜን መጠመቅ የሚናፈቅ ጊዜ ስለሆነ ተጠቀሙበት፡፡ በዚሁ አጋጣሚ እኛም እንጦጦ ማርያም ጳግሜን የጸበል አገልግሎት ስለምንሰጥ መጥታችሁ መጠመቅ ትችላላችሁ፡፡

#ጳግሜ_ሦስት_ርኅወተ_ሰማይ_ነው_ሰባቱ_ሰማያትይከፈታሉ_ጸሎታችን_በሙሉ_ያርጋል፡፡

ጳግሜ ሦስት ርህወተ ሰማይ ይባላል፡፡ ርኅወተ ሰማይ ማለት የሰማይ መከፈት ማለት ነው፡፡ ይህም የሰማይ መስኮቶች ወይም ደጆች የሚከፈቱበት እለት ነው፡፡ ርኅወተ ሰማይ ወይም የሰማይ መከፈት ሲባል፤ በሰማይ መከፈት እና መዘጋት ኖሮበት ሳይሆን፤

ቅዱሳን መላእክት የሰውን ልጆች ጸሎት፣ ልመና፣ ያለ ከልካይ፤ ወደ እግዚብሔር የሚያሳርጉበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ እንዲሁም ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገበ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ ነው ርኅወተ ሰማይ የተባለው፡፡

በእርግጥ በንስሐ ሆኖ ለሚጸልይ ሰው ለእርሱ ሁሌም የሰማይ ደጅ የተከፈተ ነው፡፡ ከዓመት ተለይታ ጳግሜ ሦስት የሰማይ መስኮቶች፤ ወይም ደጆች በሙሉ ተከፍተው፣ የምዕመናን ጸሎት በተለየ ሁኔታ የሚያርግበት ጊዜ እንደ ሆነ ሊቃውንተ ቤተ-ክርስትያንም ይነግሩናል፡፡

ስለዚህ በዚህም ቀን ማለትም ጳግሜ ሦስት ያስለመድናቸውን ጸሎቶች፤ አንዳንዶቻችንም ያቋረጥናቸውን ጸሎቶች፤ በርትተን ብንጸል ቅድመ እግዚብሔር ይደርሳል፡፡

በዚህችም ቀን የጸለይነውን ጸሎቶች፤ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል እና ቅዱሳን መላእክት ቅድመ እግዚብአብሔር ያሳርጉልናል፡፡ በዚህችም እለት የእግዚአብሔር ምህረት እና ቸርነት ለሰው ልጆች የሚወርድበት ታላቅ እለት ነው፡፡

አባቶቻችን እንደሚነግሩን ከሆነ፤ ጳግሜ ሦስት ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ፤ ያስለመዱትንና ሌሎችንም ጸሎቶች ሲጸልዩ ያድራሉ፡፡ ስለዚህ እኛም እንደ እነሱ ማድረግ ባንችል፤ የበረታን ሌሊት ስድስት ሰዓት፤ የቻልን ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት ተነስተን ጸሎት ልንጸልይ ይገባናል፡፡

#ጳግሜን_መጠመቅ_መተት_እና_ድግምትን_ይሽራል!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች እንደምታውቁት ያለንበት ጊዜ አጋንንት ተፈቶ የተለቀቀበት፣ ሰው በክፋት ከአጋንንት ያልተናነሰበት አንዳንዴም የሚበልጥበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው፡፡ በተለይ ብዙ ምዕመናን በመተት በድግምት እድላቸው ተወስዶ፣ ሕይወታቸው ባዶ እየተደረገ ነው፡፡

አጋንንት ጎታቾች እና መተት መታቶች ጳግሜን በሰው ላይ የሚመትቱትን መተት የሚያድሱበት ስለሆነ ጸበል በርትተን ብንጠመቅ እድሳታቸው ይሽራል፣ መተታቸውም ይከሽፋል፡፡ ስለዚህ በዚህ በወርኃ ጳግሜ በመተት እና በድግምት የምትሰቃዩ ወገኖቼ በርትታችሁ ጸበል ተጠመቁ ጠጡ፡፡

ምክንያቱም ዓመቱን ሙሉ በእድላችን ሲመተት ወደ እና ሕይወት ሲጎተት የነበረው አጋንንት ጳግሜን በርትተን ከተጠመቅን አጋንንቱ አዲሱን አመት አይሻገርም፡፡

በተመተተብን መተት እና በበላነው ድግምት ውስጣችን በተለይ ሆዳችን፣ እንዲሁም መላ አካላታችን ላይ ደዌ ሆኖ የተቀመጠው አጋንንት ይለቀናል፣ ውስጣችን ያለው የደዌ መተት ይሻራል፡፡
እንዲሁም በአውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን በቅዱስ ዮሐንስ ስም አስታከው ዛር አንጋሾች፤ ለዛር ደም የሚያፈሱበት፣ የሚገብሩበት ጊዜ ነው፡፡

አዲሱን አመት ደም በማፍሰስ፣ ለዛር በመገበር ስለሚቀበሉ ጸበል መጠመቁ ከእዚህ ችግር እናመልጣለን፡፡ በተለይ ቤተሰባችሁ በቅዱስ ዮሐንስ የሽፋን ስም ‹‹ለዓውደ ዓመት ነው፣ ለአድባር ነው፣ አዲስን ዓመት ለመቀበት ነው፣ የእናት አባታችን የአያቶቻችን አምላክ እንዳይጣላን ነው፣

በአዲሱ ዓመት ጠላታችን ደሙ እንዲፈስ ነው፣ ደም የምናፈሰው የእኛን ጦስ ይዞ እንዲሄድ ነው›› በማለት ገብስማ፣ ወሰራ፣ ባለ ነጠላ ዶሮ፤ ነጭ፣ ቀይ በግ እያሉ ያረዱትን እንዳትበሉ፡፡

አውቃችሁ በዮሐንስ ስም ለዛር የተገበረለትን ብትበሉ በደም የገባውን ዛር፤ በጸበል ለማስወጣት ትቸገራላችሁ፡፡ በቤታችሁ፣ በአከባቢያችሁ እንደዚህ አይነት ክፉ ልማድ ካለ ተቃወሙ፣ ለማስተው ሞክሩ፡፡ የእነሱ እዳ ነው ነገ ለእናንተ የሚተርፈው፡፡

በተረፈ ይህችን ወርኃ ጳግሜን እንደ አባቶቻችን እንድንጠቀምባት አምላከ ቅዱስ ሩፋኤል ይርዳን፡፡

መንፈሳዊ ጉባኤ

06 Sep, 02:15


መንፈሳዊ ጉባኤ:
#ጷግሜን_ለምን_እንጾማለን?

#ጷግሜን_ለምን_እንጠመቃለን?

#በመጠመቃችን_የምናገኘው_ጥቅም_ምንድን_ነው?

#ጷግሜን_መጠመቅ_መተት_እና_ድግምትን_ይሽራል፡፡

#ጷግሜ_ሦስት_ርኅወተ_ሰማይ_ነው_ሰባቱ_ሰማያት_ይከፈታሉ ጸሎታችን በሙሉ ያርጋል፡፡

/ዩ ትዩብ ላይ የለቀኩትን ትምህርት በጽሑፍ ቃል በቃል አቅርቤላችኃለሁ/

የወለላይቱ እመቤት ልጆች እንደሚታወቀው ወርኃ ጳግሜ፤ ኢትዮጲያን ብቸኛዋ ባለ አሥራ ሦስት ወራት ሀገር ያደርገች ልዩ ወር ናት፡፡ ታዲያ ይህችህ በሦስቱ ወንጌላውያን አምስት ፣ በዘመነ ዮሐንስ በአራት ዓመት ስድስት ቀን የምትሆነው ጳግሜ፣ ብዙ ምስጢር እና ልዩ ጥቅም የላት ወር ናት፡፡

#ጳግሜን_ለምን_እንጾማለን?

የጳግሜ ወር በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት የዓለም ፍጻሜ መታሰብያ ወር ተደርጋ ትታሰባለች፡፡ ጳግሜ የዓመታት መሸጋገሪያ፤ ጨለማው የክረምት ወቅት፤ ወደ ማብቂያው እና የሚያልፍበት፤ እንደ ሆነ ሁሉ፤

ዳግም ምጽዓትም ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ፤ ከጊዜያው ወደ ዘላለማዊ መሻጋገሪያ በመሆኑ ጳግሜ የእለተ ምጻት ምሳሌ የሆነችው፡፡ በዚህም ምክንያት የኦርቶዶክስ አማኞች የጳግሜን ወር በሱባኤ በጾም በጸሎት ያሳልፋሉ፡፡ በገዳም ያሉ አባቶች ጳግሜን በዝግ ሱባኤ ያሳልፋሉ፡፡

በእግርጥ ጳግሜ ከሰባቱ አጽዋማት ውስጥ ባትካተትም፤ ጳግሜን በግዴታ ሳይሆን በውዴታ ብንጾም የበረታን ሱባኤ ብንይዝባት፣ የቻልን በታቅቦ ብናሳልፋት ትልቅ ጥቅም አለው፡፡

አንደኛ በፈቃዳችን በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በሱባኤ ብናሳልፍ ጸጋና በረከት ያሰጠናል፡፡ ሁለተኛው ጳግሜ የአዲስ ዓመት መቀበያ የዋዜማ ቀናት በመሆኗ፤ አዲሱን ዓመት በጾም፣ በጸሎት በሱባኤ ብንቀበል አዲሱ ዓመት የበረከት፣ የረድኤት ይሆንልናል፡፡

አዲሱን ዓመት በተለይም በዋዜማው በመዝናናት፣ በመጨፈር፣ በመጠጣት እና በመዘሞት ከምንቀበል፤ በጸሎት ብንቀበል አዲሱ ዓመት የበረከት ዓመት፣ ያሰብነው ያቀድነው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚሳካበት ይሆናል፡፡

ቅድም እንዳልኩት የገዳም አባቶቻችን የጳግሜን ወር፤ መንፈሳዊ ጥቅም ስለሚያውቁ፤ በፈቃዳቸው በታላቅ ሱባኤ ሆነው ስለ ሀገር፣ ስለ መጪው አዲስ ዓመት መልካምነት ፈጣሪን ይማጸኑበታል፡፡ እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን እና፣ እነሱ የሄዱበትን መንገድ ተከትለን፤ እንደ እነሱ ልንጠቀም ያስፈልጋልና፤ ወርኃ ጳግሜን በጾም በጸሎት እና በሱባኤ ብናሳልፍ እንጠቀማለን፡፡

በተለይ በአሁኑ ጊዜ እኛም፣ ሀገራችንም ቅድስት ቤተ-ክርስትያናችንም የገጠመን ፈተና፣ እጅጉን ከባድ ነውና እግዚአብሔር እንዲታረቀን፣ ገጸ ምህረቱን እንዲመልስልን፣ ወረርሽኙን እንዲያጠፋልን፣ ለቅድስት ቤተ-ክርስትያናችንና ለሀገራችን ጽኑ ሰላም እና አንድነት እንዲሰጥልን ወርኃ ጳግሜን እንደ በፊቱ በመብላት በመጠጣት ሳይሆን በጾም በጸሎት ብናሳልፍ ጥቅሙ ለእኛው ነው፡፡

#ጳግሜን_ለምን_እንጠመቃለን?

#በመጠመቃችን_ምን_ጥቅም_እናገኛለን?

እንደሚታወቀው ብዙዎቻችን ወርኃ ጳግሜን እንጠመቃለን፡፡ ጳግሜን የምንጠመቅበት ዋናው ምክንያት ከሊቀ መልአኩ ከቅዱስ ሩፋኤል ጋር የተያያዘ ነው፡፡  

በዚህ በጳግሜ ወር በዓለም ላይ ያሉ ውቅያኖሶች፣ ባህሮች፣ ወንዞች፣ ኩሬዎች ጸበሎች በአጠቃላይ ውሃዎች ሰማይ ተከፍቶ፣ በመላክእት የሚባረኩበት ስለሆነ፤ ጳግሜን የቻልን ጸበል ቦታ ሄደን፣ ወይም በአከባቢያችን ጸበል ካለ እዛም ሄደን፤ መሄድ ባይመቸን፣ ቤታችን ውስጥ ባለው ውኃ ብንጠመቅ እንባረክበታለን፣ ከበሽታችንም እንድንበታለን፡፡

በጳግሜ ጸበል፣ እንኳን የሰው በሽታ፤ በሽታ ያለው እህል፣ በሽታው ይለቀዋል፡፡  ገበሬው ከጳግሜ ወዲያ ነው የሚጠፋውንና የማይጠፋውን እህል የሚለየው፤ በተለይ ዘንጋዳ ጳግሜ ላይ ነው በደንብ የሚያስታውቀው፡፡

በአባባልም ‹‹ዘንጋዳ እና ቡዳ ከመስከረም ወዲያ›› ነው የሚያስታውቀው ይባላል፡፡ የሚገርመው አባቶቻችን ጳግሜ ሦስት ሌሊት ስድስት ሰዓት በተለይ ፏፏቴ ያለው ወንዝ፤ ውሃው ሲቆም ያዩታል፡፡

ቀድሞ አባቶቻን ይህንን ተአምር ለማየት ጳግሜ ሦስት ሌሊት በተለይ ፏፏቴ ያለበት፣ ትልቅ ወንዝ ዳር ሄደው ያድሩ ነበር፡፡ ውሃው ቀጥ ብሎ ሲቆም ሰማይ ሲከፈት ያዩ ነበር፡፡ ጳግሜን በተለይም ጳግሜ ሦስት፣ የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በአሉ ስለሆነ፤

በዚህ ቀን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ውሆችን የሚባርክበት፤ እና ለሰው ልጆች በፈጣሪው ጸጋ፤ ድህነት እና ፈውስ የሚያሰጥበት ቀን ስለሆነ ብንጠመቅ ከበሽታችን እንድናለን፡፡

በመጸሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ወንጌል በምዕራ 5 ቁጥር 4 ላይ ‹‹አንዳንድ ጊዜ  የጌታ መልአክ ወደ መጠመቂያይቱ ወርዶ፣ ውኃውን ያናውጥ ነበርና፤ እንግዲህ ከውኃው መናወጥ በኃላ በመጀመሪያ የገባ ከማናቸውም ካለበት ደዌ ጤናማ ይሆን ነበር›› ይላል፡፡

የጌታ መልአክ ‹‹ውኃውን ያናውጥ ነበር›› የተባለው፤ ከሰማይ ወርዶ ውኃውን ይባርከው ነበር ለማለት ነው፡፡ ውኃውም የሚናወጠው የእግዚአብሔር መልአክ ውኃውን ሲባርከውና እና በመጠመቂያው፣ ለፈውስ ደጅ የሚጠኑት፣ ህሙማን ውሃው በመልአኩ መባረኩን የሚያውቁት ውኃው ሲናወጥ ነው፡፡

ዛሬም እንደ ቀድሞ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል፤ በዓለም ላይ ያሉትን ውሃዎች ሁሉ ስለሚባርካቸው፤ ብንጠመቅባቸው እንፈወሳለን፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቅዱሳን መላእክትም ውኃውን ይባርኩታል፡፡

ጳግሜ ሦስት ይህ ብቻ አይደለም ሊቀ መልአኩ ያስለመደን ነገር አለ፡፡ ይህም ሁል ጊዜ ጳግሜ ሦስት ሌሊት፣ ጠዋት፣ ከሰዓት አልያም ማምሻ ላይ ይዘንባል፡፡ ይህ ከሰማይ የሆነ የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል ጸበል ነው፡፡

በልጅነታችን ጳግሜ ሦስትን ‹‹ሩፋኤል አሳድገኝ›› እያልን እንጠመቃለን፡፡ ጳግሜ ሦስት በዘነበው ውኃ መጠመቅ ትልቅ መታደል እና ፈውስ ነው፡፡ በደዌ ይሰቃይ የነበረው ኢዮብም በዚህ ሳምንት ነው ተጠምቆ ነው የዳነው፡፡

የሚገርማችሁ በዚህ በከተማ ብዙም ስለማይታወቅ ነው እንጂ፤ በገጠር እና በክፍለ ሀገር የቅዱስ ሩፋኤል እለት የዘነው ዝናብ በእቃ ይቀዳና ይቀመጣል፡፡ በተቀዳው ጸበል ቦሃቃው ይረጭበታል፣ በውሃው እህሉ ይቦካበታል፣ ቤቱ ደጁ ይረጭበታል፡፡

ይህም የሚሆነው የቅዱስ ሩፋኤል እለት የዘነበው ውኃ የሰላቢ መንፈስን ስለሚያርቅ ነው፡፡ የሰላቢ መንፈስ ከቤታችን የእህል በረከት የሚያሳጣ፣ ለአንድ ወር ያሰብነውን ለሳምንት የማያዳርስ፣ ለዓመት ያልነው በሦስት ወር እንዲያልቅ የሚያደርግ፤ ክፉ መንፈስ ስላለ ይህን ያርቅልናል፣ በጸበሉ በረከት እህል አስቤዛውን ያበረክትልናል፡፡

እንደምታውቁት ቅዱስ ሩፋኤል ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሦስተኛው ነው፡፡ በመጀመሪያዋ እለተ ፍጥረት እግዚአብሔር መቶ ነገደ መላእክት ፈጥሮ በአሥር ከተማ ሲያኖራቸው

ቅዱስ ሩፋኤል ራማ ላይ ነው ከነ ሠራዊቱ ያረፈው ወይም የከተመው፡፡ በራማም መናብርት ተብለው ለሚጠሩት አሥሩ ነገድ አለቃ ወይም መሪ ሆኖ በእግዚአብሔር ተሹሟል፡፡ በኃላም መጋብያን በሚባሉ በሃያ ሦስቱ ነገድ ላይ ተሹሟል፡፡

ስለዚህ ጳግሜ ሦስት የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ሲመት ወይም የሹመት በዓሉ ነው፡፡

ይህንንም እራሱ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል በመጽሐፈ ጦቢት ምዕራፍ 12 ቁጥር 15 ላይ ‹‹ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ›› በማለት ተናግሯል፡፡

መንፈሳዊ ጉባኤ

21 Aug, 19:03


መንፈሳዊ ጉባኤ:
❖ ❖ ❖ ኪዳነ ምህረት (የካቲት 16) ❖ ❖ ❖
               ❖ ❖ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ❖
   ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡ ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችም እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄዘንድ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መትተህ ልምናዬን ትሰማኝ  እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡ እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጸውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡ ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበ አቡየ ሕያው ወበመንፈስ ቅዱስ ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል፡፡
   ሌላው በላዔ ሰብ በአማርኛ ሰው በላ ማለት ነው፤ ትክክለኛ ስሙ ግን ስምዖን ይባላል ቅምር በሚባል አገር የሚኖር እጅግ ባለጸጋ ነበር፤ እንደ አብርሃም እንግዶችን እየተቀበለ ድሆችን እየመገበ የሚኖር ጻድቅ ነበር፤ ሰይጣን በዚህ ስራው ቀናበት ሊፈትነውም በሦስት አረጋዊ ሽማግሌዎች ሥላሴ ነን ብሎ ተገለጠለት ልክ እንደ አብርሃም፤ ሐዋርያው ጳውሎስ ሰይጣን የብርሃን መልአክ መስሎ ይመጣል እንዳለ፤ እርሱም ሥላሴ መስለውት ተቀበላቸው ተንከባከባቸውም፤ ምግብ አቀረበላቸው ምግብ አንበላም የምንጠይቅህን ግን ትፈጽምልን ዘንድ ቃል ግባልን አሉት ቃል ገባላቸው እንግዲያውስ የምትወደን ከሆነ አንድያ ልጅህን ሰዋልን አሉት፤ መጀመሪያ ደነገጠ ኃላ አብርሃም ልጁን ሊሰዋ አልነበረምን እኔንም ሊፈትኑኝ ይሆናል ብሎ ለማረድ ተዘጋጀ፤ ተው የሚለው ድምጽ አልሰማም፤ አረደው አወራረደው ይዞላቸው ቀረበ፤ መጀመሪያ ቅመስልን አሉት ቀመሰው ወዲያው እነዚያ ሰዎች ተሰወሩበት እርሱም አህምሮውን ሳተ ተቅበዘበዘ ከዚያ በኃላ ምግብ አላሰኘውም የሰው ስጋ እንጂ መጀመሪያ ቤተሰቦቹን በላ ከዚያም ጓደኞቹን ጦርና የውኃ መንቀል ይዞ ከቤቱ ወጣ ያገኘውን ሰው እየገደለ ይበላል የበላቸው ሰው ቁጥር 78 ደረሰ፤ በመንገድ ተቀምጦ የሚለምን በደዌ የተመታ አንድ ደሃ አገኘ ሊበላው ወደ እርሱ ተጠጋ ግን ቁስሉን አይቶ ተጸየፈው፤ ደሃውም “ስለ እግዚአብሔር ከያዝከው ውኃ አጠጣኝ” አለው “ዝም በል ደሃ” ብሎት አለፈ፤ “አረ በውኃ ጥም ልሞት ነው ስለ ጻድቃን ስለ ቅዱሳን” አለው አሁንም ዝም ብሎት ሄደ ለሦስተኛ ጊዜ “ስለ አዛኝቷ ስለ ድንግል ማርያም” አለው፤ ሰውነቱን አንዳች ነገር ወረረው “አሁን የጠራከውን ስም እስኪ ድገመው ስለ ማን አልከኝ” አለው፤ ስለ አዛኝቷ ስለ እመቤቴ ማርያም አለው፤ ይህቺስ ደግ እንደሆነች በምልጃዋም ከሲኦል እንደምታወጣ ህጻን እያለው እናትና አባቴ ይነግሩኝ ነበር፤ በል እንካ አለው እጁን ዘረጋለት ጥርኝ ውኃ ጠብ አደረገለት ወደ ጉሮሮው አልወረደም የተሰነጠቀ እጁ ውስጥ ገባ እንጂ፤ በለዔ ሰብ ከዚያች ደቂቃ በኃላ አዕምሮው ተመለሰለት እንዲህም አለ “በአንድ ዋሻ ውስጥ ገብቼ ስለ ኃጢያቴ አለቅሳለሁ ስጋዬ ከአጥንቴ እስኪጣበቅ እጾማለሁ ወዮሊኝ ወዮታም አለብኝ አለ፤ ወደ ዋሻ ገባ ምግብ ሳይበላ ውኃም ሳይጠጣ 21 ቀን ኖሮ በርሃብ ሞተ ይላል ተአምረ ማርያም። ጨለማ የለበሱ ሰይጣናት እያስፈራሩ እያስደነገጡ ነፍሱን ወደ ሲኦል ሊወስዷት መጡ፤ እመቤታችን ፈጥና በመካከላቸው ተገኘች፤ ልጄ ወዳጄ ይህችን ነፍስ ማርሊኝ አለችው እናቴ ሆይ 78 ነፍሳትን የበላ እንዴት ይማራል አላት፤ የካቲት 16 ቀን በጎልጎታ የገባህልኝ ቃል ኪዳን አስብ ስምሽን የጠራ መታሰቢያሽን ያደረገን እምርልሻለው ብለኸኝ የለምን አለችው፤ እርሱም እስኪ ይህቺን ነፍስ በሚዛን አስቀምጧት አለ ቢያስቀምጧት ጥርኝ ውኃው መዝኖ ተገኘ፤ ስላንቺ ስል ምሬታለው ሰባት ቀን ሲኦልን አስጎብኝታችሁ ወደ ገነት አግቧት አላቸው። ቦታሽ እዚህ ነበር እያሉ ሲኦልን አስጎብኝተው ወደ ገነት አገቧት። ልመናዋ ክብሯ የልጇም ቸርነት ከሁላችን ጋር ይሁን።
❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖ ❖
በዕለቱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚቀርበውን የምስጋና ቃል እንደሚከተለው አቅርበናል መልካም በዓል፡፡
           ❖ ❖ ❖ ዋዜማ ❖ ❖ ❖
ሃሌ ሉያ (፬) ርግብየ ይቤላ በእንተ የዋሃታ፤
በሐኪ ማርያም ሐዳስዩ ጣዕዋ፤
እንዘ አመቱ እሞ ረሰያ ፤
ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤
          ❖ ❖ ❖ ምልጣን ❖ ❖ ❖
እንዘ ዓመቱ እሞ ረሰያ ፤
ታዕካ ሰማይ ኮነ ማኅደራ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤
ዳዊት ይሴብሕ ወይዜምር ዕዝራ ፤
        እግዚአብሔር ነግሠ
        እንተ ክርስቶስ በግዕት እንተ ታስተርኢ እምርኁቅ ብሔር፤
        በቤተልሔም አስተብረከት ዕጓለ አንበሳ ግሩመ ወለደት፡፡
           ❖ ❖ ❖ ይትባረክ ❖ ❖ ❖
እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤
ቃል ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ፡፡
           ❖ ❖ ❖ ሰላም ❖ ❖ ❖
ሃሌ ሉያ (3) ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋትሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤
የሐንፁ አሕዛብ አረፋተኪ በዕንቊ ክቡር፤
ወመሠረትኪ በወርቅ ንጹሕ ይሰግዱ ለኪ ውስተ ገጸ ምድር፤
በእንተ ዕበየ ክብርኪ አምላከ ፳ኤል ውእቱ ረዳኢኪ
ዘአድኀነኪ እምእደ ጸላዕትኪ፤
ወረሰየ ሰላመ ለበሐውርትኪ፡፡
         ❖ ❖ ❖ መልክአ ሥላሴ ❖ ❖ ❖
ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፡
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፡
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል ፡
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል
          ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ፤
እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፤
ከመ ትኩኒ ተንከተመ ለዉሉደ ሰብእ ለሕይወት ዘለዓለም፤
ለኪ ይደሉ ከመ ትኩኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤
ኦ መድኀኒተ ኵሉ ዓለም ፤
ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡
         ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት ❖ ❖ ❖
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ ;
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኀኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪየኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡
         ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኀኒት ለነፍስ ወሥጋ፤
እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ፤
ወኃጥአን ይስዕንዎን፤ ዘእንበለ ትብጻሕ ግብተ አሠንዩ ፍኖተ፤
ይፈኑ ለክሙ እመቅደሱ ረድኤተ መድኀኒተ መቤዛዊተ እሞ ቅድስተ፡፡

❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት ❖ ❖ ❖
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማልዎ በኮከብ፤
ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤
ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኀኒት ዘዐርብ፤
ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ሕሊና ቀዳማይ አብ፤
አመ እምገነቱ ተሰደ በኃዘን ዕፁብ፡፡
         ❖ ❖ ❖ ዚቅ ❖ ❖ ❖
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም ፤
አመ ይሰደድ እምገነት፡፡
          ❖ ❖ ❖ መልክአ ኪዳነ ምህረት በዓል ❖ ❖

መንፈሳዊ ጉባኤ

17 Aug, 20:06


✍️   ቅዱሱ ተራራ ✍️↲(፪ኛ ጴጥ፩÷፲፯-1፲፰ )

ደብረታቦር ማለት የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡
ከጌታችን ከመድኀኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ከ፱ኙ ዐበይት በዓላት መካከል የደብረታቦር በዓል አንዱ ነው፡፡
     በእስክንድርያ ግን ዐበይት በዓላቶቻቸው ፯ ናቸው፡: በዚህም ምክንያት ከዐበይት በዓላት ውስጥ አስገብተው ደብረታቦር አይቆጥሩትም ፡ይሁን እንጂ በበዓልነቱ አይከበርም ማለት ግን አይደለም።

      ደብረታቦር ወይም የታቦር ተራራ ጌታ በምድረ እስራኤል እየተዘዋወረ በማሰተማር ላይ በነበረበት ዘመን ነሐሴ ፲፫ ቀን ብርሃ መለኮቱንና ክብረ መንግስቱን የገለጠበት ታሪካዊ በዓል ነው፡፡ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ብዙውን ጊዜ የሚስተምረውና ተአምራት የሚያደርገው በተራራ ላይ ነበር፡(ማቴ ፲፯÷፬) ይህን በዓል ከቅዱስ ዮሐንስ በቀር ፫ቱም ወንጌላውያን በየወንጌሎቻቸው መዝግበውታል(ማር፬÷፪ ፲፫ ፤ ሉቃ ፱÷28-36)
     ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስም “ ከገናናው ክብር ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው የሚል ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ከምስጋናን ተቀብሎአልና እኛም በቅዱሱ ተራራ ከእርሱ ጋር ሳለን ይህ ድምጽ ከሰማይ ሲወርድ ሰማን” በማለት የተገለጸውን ምስጢር ታላቅነት መስክሮአል(፪ኛ ጴጥ፪÷፲፯-፲፰፣በዓላት በዲ.ን ብርሃኑ አድማስ)
     ቅዱሳን ሐዋርያት ብርሃነ መለኮቱን ካዩ በኋላ የቃላቸው ትምህርት የእጃቸውም ተአምራት ብቻ ሳይሆን የልብሳቸውም ቁራጭ ጥላቸው ጋኔን ያወጣ ድወይ ይፈውስ ነበር( ሥርዓተ አምልኮ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ)
      ይህ ተራራ ከገሊላ ባሕር በምስራቅ ደቡባዊ በኩል ፲ ኪ.ሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን 572 ኪ.ሜ ከፍታ አለው፡፡የታቦር ተራራ በሐዲስ ኪዳን በግልጽ ባይጠቀስም በብሉይ ኪዳን ግን ተጠቅሶ እናገኘዋለን(መሳ ፬÷፮-፲፬) ቅዱስ ዳዊትም “ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ ወይሰብሑ ለስምከ መዝራዕትከ ምስለ ኃይል፤ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል፡፡ ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው፡፡ እጅህ በረታች ቀኝህም ከፍ ከፍ አለች(መዝ 88÷12-13) ይላል፡፡ በደብረታቦር ዲቦራም ዘምራበታለች፡፡

      ጌታችን በቂሣርያ ሐዋርያትን “ሰዎች የሰው ልጅን ማን ብለው ይጠሩታል “ በማለት በጠቃቸው ቀን የቀሩት ደቀ መዛሙርት በተራራው ሥር ትቶ ሦስቱን ( ጴጥሮስን ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ወጣ፡፡ በተራራው ላይ ሳሉ የጌታችን መልክ ተለውጦ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፡ልብሱም እንደ በረዶ የነጻ ሆነ፡፡ በዚህ ጊዜ ብርሃነ መለኮቱንና ክብረ መንግስቱን ገለጠ(ሉቃ9÷29)
በደብረታቦር ተራራ ፭  ነገር ተከናውኗል፤
ሙሴና ኤልያስ ሲነጋገሩ ተሰምቷል፡፡
      -መልኩ ተለወጠ (ወተወለጠ አርአያሁ በቅድሜሆሙ) (ማቴ ፲፯÷፪) በዚህ ሰዓት በሐዋርያት ላይ ያደረ ሥጋዊ መንፈስ ራቀ፡ በውስጣቸው ያለው የጨለማ ፍርሃት አሰወገደላቸው( ጥርጥርን አለማመን እነዚህን ነገሮች ሀሉ ከልቡናቸው አስወገደላቸው፤ ፡የእግዚአብሔርን ክብር እንዲያስታውሉ አእምሮቸው ብሩህ ሆነ፡፡በደመና ውስጥ ሁኖ የምወልደው የምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን የሚል ቃል ተሰማ ( ዝንቱ ወእቱ ወልድየ ዘአፈቅር ወሎቱ ሰምዕዎ) ደመና የእግዚአብሔር የክብሩ ምሳሌ ነው፡፡

      ልብሱ እንደ በረዶ ነጻ ( ወአልባሲሁኒ ኮነ ከመ ፀዓዳ)
ጌታችን በደብረ ታቦር ተራራ የብሉይና የሐዲስ ኪዳ ሰዎችን ( ነቢያትና ሐዋርያትን ) አንድ አደረጋቸው፡፡ እሱ አምላካችን መጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ነውና ፡፡ሌላው ምስጢር ሙሴና ኤልያስ የተጠሩበት ሙሴ ነህ ይላሉ ኤልያስ ነህ ይላሉ ሲሉት እርሱ አምላከ ሙሴ አምላከ ኤልያስ መሆኑን ሊያሳይ ነው፡፡
       ከነቢያቱ ለሊቀ ነቢያት ሙሴ “ጀርባዬን ታያለህ ፊቴን ግን አታይም ( ዘዳ 33÷28) በተባለው መሠረት “እባክህ ክብርህን ( ፊትህን) አሳየኝ ይህ ካልሆነማ ባለሟል መባሌ ምኑ ላይ ነው (ዘጸ33÷18-23) የሚለውን የባለሟልነት ጥያቄውን ሙሴን ከሙታን አስነስቶ ስለክብሩ የቀናውን ኤልያስንም ከብሔረ ሕያዋን አምጥቶ ክብሩን አሳይቷቸዋል የሙሴን ጸሎት ሳይረሳ ልመናውን ፈጸመለት፡፡
በጀርባ የተመሰለው ከ5500 በኋላ የተፈጸመው ምስጢረ ሥጋዌ ነው፡፡
          ሙሴና ኤልያስ መሆናቸው በምን ይታወቃል?

   ሙሴ ብልቱትነቱ ኤልየስም በፀጉርነቱ አንድም በአነጋገራቸው ታውቋል፡፡ ሙሴም የእኔን የሙሴን ጌታ ማን ሙሴ ይልሃል እግዚአ ሙሴ ይበሉህ እንጂ ኤልየስም የእኔን የኤልያስን ጌታ ማን ኤልያስ ይልሃል እግዚአ  ኤልያስ ይበሉህ እንጂ ሲሉ ተሰምተዋል፡፡
       አንደድም ምውት ለሕያው ሕያው ለምውት ሲጸልዩ ተስምተዋል፡፡ አንድም ሙሴ እኔ ባሕር ብከፍል ጠላት ብገድል ደመና ብጋርድ መና ባወርድ እስራኤላውያንን ከክፋታቸው መመለስ አልተቻለኝም ላንተ ግን መልሶ ማደን ይቻልሃልና፡፡
    ኤልያስም እኔ ሰማይ ብለጉም እሳት ባዘንብ እስራኤላውያንን ከክፋታቸው መመለስ አልተቻለኝም ላንተ ግን መልሶ ማደን ይቻልሃልና ሲሉ ተስምተዋል ( አንድምታ ወንጌል ማቴ ምዕ.፲፯)
        ፍጻሜው ግን ደብረታቦር የመንግስተ ሰማያት ምሳሌ ናት፡፡ሕጋውያንም ደናግልም እንዲወርሷት ለማጠየቅ ከሕጋውያን ሙሴን ከደናግል ኤልያስን አመጣ፡፡
ይህ በዓል በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በተለይም በምእመናን ዘንድ የተለየ ስም አለው( ቡሄ ይባላል)፡፡
   ቡሄ ማለት መላጣ ( ገላጣ) ማለት ነው፡፡ በሀገራችን ክረምቱ አፈናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየው በደብረታቦር በዓል አካባበር ስለሆነ “ቡሄ “ ያሉት ለዚህ ሳይሆን አይቀርም፡፡
ሊቃውንት "ቤሄ ከዋለ የለም ክረምት ደሮ ከጮኸ የለም ሌሊት”እንዲሉ(የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ገጽ- 127-128)
- ሕፃናት የሚያጮሁት ጅራፍ ጩኸት ድምፅ የድምፀ መለኮት ጅራፍ ሲጮህ ማስደንገጡን የሦስቱ ሐዋርያት ምሳሌ ሲሆን  መደንገጣቸው በድምፀ መለኮቱ መደንገጣቸውን መውደቃቸውን ያስታውሳል፡፡
   - በአንዳንድ ቦታዎች የቡሄ ዕለት ማታ ችቦ ያበራሉ በደብረታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው፡፡
- ምእመናን በድበረታቦር ክብሩን አየን ዛሬም ያ ክበሩ ለገለጥን ያስፈልጋል፡፡ እገዚአብሔር ክብሩን የገለጠበት ያ ተራራ ዛሬ የእኛ አካል ሊሆን ያስፈልጋል፡፡ የእግዚአብሔር ክብሩና ጥበቡ የሚገለጥበት ማዳኑ የሚታይበት የተባረከ ሕይወት ሊኖረን ይገባል

- የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ስለእኛ ጸልዩ
    እንኳን አደረሰን

መንፈሳዊ ጉባኤ

17 Aug, 19:59


#እንኳን_አደረሳቹ_አደረሰን_የተዋህዶ_ልጆች_በሙሉ😘🙏
✝️🌿👉 #ቡሄ_ጅራፍ_ማስጮህ
✝️🌿👉 #ችቦ_ማብራት
✝️🌿👉 #ሙልሙል_ዳቦ - ሐይማኖታዊ ምስጢራቸው ምንድነው⁉️
#ደብረ_ታቦር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያዕቆብን ፣ ዮሐንስንና ጴጥሮስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ከወሰዳቸው በኋላ በዚያ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበትና ሙሴና ኤልያስን ጠርቶ የህያዋንና የሙታን አምላክነቱን ያሳየበት ከዘጠኙ የጌታ ዓበይት በዓለት ውስጥ አንዱ ነው።
✝️🌿💚💛
ቤተክርስቲያናችንም የተለያዩ ስርዓቶችን በመፈፀም አክብራው ታልፋለች፡፡ #በደብረ ታቦር በዓል የሚፈጸሙ ( #ቡሄ ፣ #ጅራፍ ማስጮህ ፣ #ችቦ ማብራትና #ሙልሙል_ዳቦ ) ትውፊታዊ የሃይማኖት ስርዓቶች ምሳሌዎች ምን እንደሆነ እናያለን፡፡
✝️🌿💚💛
#ቡሄ ቡሄ ማለት ብራ ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው
ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል ስለሆነ ብራ፣  ብርሃን ደማቅ የሚል ፍቺ ያለው ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡ አንድም ቡሄ ማለት ወቅቱ የክረምት ጨለማ አልፎ የብርሃን ወቅት ስለሚመጣ ሰማይም ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቀት ስለሆነ ብራ ተብሏል፡፡
✝️🌿💚💛
" ቡሄ ከዋለ የለም ክረም ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት እንዲሉ " አንድም ቡሄ…..ቡኮ "/ሊጥ" ማለት ነው፡፡ በዚህ በዓል ቡኮ ተቦክቶ ዳቦ/ ሙልሙል / ተጋርሮ የሚታደልበት በዓል ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡
✝️🌿💚💛
✝️🌿👉 #ሙልሙል_ዳቦ
ሙልሙል ዳቦ አመጣጡ ጌታችን ብርሃናዊ መለኮቱን በገለጠበት በዚህ ዕለት በደብረታቦር አካባቢ የነበሩ ህፃናት እረኞች ቀኑ የመሸ ስላልመሰላቸው / ጌታችን በብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ስለነበረ / በዛው ሆነው ከብትና በጎቻቸውን እየጠበቁ ሲቆዩባቸው የሰዓቱን መግፋት የተመለከቱ ወላጆች በችቦ ብርሃን ተጠቅመው ለልጆቻቸው የሚቀመስ ሙልሙል ዳቦ ይዘው
ወዳሉበት መምጣታቸውን ያሳያልና ታሪኩን እየዘከርን በዓሉን እናከብራለን፡፡
✝️🌿💚💛
#አንድም እንደ #ሐዋርያት_የምስራችሲነግሩን ወንጌል ሊሰብኩልን በየደጃፋችን መጥተው " ቢሄ በሉ " የሚሉትን ታዳጊዎችን ይበሉት ዘንድ ይሰጣቸዋል ይህም መጽሐፋዊ ነው ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን በደረሳችቡት ሁሉ ተመገቡ /ማቴ 10፥12/ ብሏልና ህፃናቱም የጌታን በዓል
ሊያበስሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ ሳይሆን ህፃናቱም የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡
✝️🌿💚💛
#መዝሙራቸው ደግሞ የምስራች ወንጌል ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋሪያት
በገቡበት ሀገር ሁሉ አስተምረው አጥምቀው የፀጋ ልጅነትን አሰጥተው እንደሚቆዩ ሁሉ ልጆችም ዘምረው አመስግነው መርቀው ውለዱ ክበዱ የመንግስተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ብለው አመስገነው ይሄዳሉና በሐዋሪያት ህፃናቱ ይመሰላሉ፡፡
✝️🌿💚💛
✝️🌿👉 #ችቦ_ማብራት
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥን የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን በደብረ ታቦር መለኮቱን ሲገልጥ ብርሃን አካባቢውን ሞልቶት ነበርና ያንን በዘመናችን ለመግለጥ የበዓሉ ዋዜማ ማታ ችቦ አብርተን አምላካችንን እናመሰግናለን፡፡ አንድም ደግሞ የችቦ ታሪክ ከላይ እንደገለፅነው የእረኞቹ ወላጆች ይዘውት የመጡት ብርሃን ነው፡፡
✝️🌿👉 #ጅራፍ
የጅራፍ ምሳሌነት በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ሚስጥር በእየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ሞቱ ምሳሌ ነው፡፡ በዚህ በዓል ጅራፍ መገመዱ እና ማጮሁ ሁለት አይነት ምሳሌ አለው፡፡
✝️🌿💚💛
✝️🌿 #የመጀመሪያው_ምሳሌ - ጌታችን በዕለተ አርብ የደረሰበትን ግርፋትና ህማም እናስብበታለን፣
✝️🌿 #ሁለተኛው_ምሳሌ -  ደግሞ ድምፁን ስንሰማ የባህሪ አባቱን የአብን የምስክርነት ቃልና
በግርማው ሲገለጥ የተሰማውን ነጎድጓድ ያስታውሰናል፡፡
✝️🌿💚💛
የጅራፍን ትውፊታዊ ውርስ መጽሐፋዊ ትምህርቱንና ምስጢሩን ከትውልድ ጠብቆ ማስተላለፉ ተገቢ ነው፡፡
✝️🌿💚💛
በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከነዚህ ሚስጢር ካላቸው ትምህርቶችና ትርጓሜያቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ በቅብብል እንደመጣልን እኛም ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ሳይለቅ ማስተላለፍ ይጠበቅብናል፡፡ የዚህ ነገር ባለ ድርሻ አካላት ደግሞ ወጣቶችና ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቡሄ ጨዋታ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ ፊዝና ሳቅ ይታይባቸዋል ተጫዋቾቹም ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን አይነት መልዕክት ያስተላልፋሉ። የሚብሰው አሳባቢ ነገሩ ደግሞ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛ መቀየሩ ነው፡፡
✝️🌿💚💛
ስለሆነም ይህን ነገር በተለይ የነገ የሀገር ተረካቢና የቤተክርስቲያን ተተኪ የሆንን ወጣቶች ማስተካከል ይኖርብል፡፡ ወላጆችም ሕፃናት በየደጃፋችን ላይ በዓሉን ሊያበስሩ ሲመጡ አስደንግጦ ከማባረር በሚገባው መልኩ አስተምረን መርቀን ማስተናገድ ይጠበቅብናል ባህሉም እንዳይተው የበኩላችንን አደረግን ማለት ነው። ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን

2,910

subscribers

1,633

photos

19

videos