ታህሳስ 25/2017፤ (ፕ.ል.ሚ. አዲስ አበባ)
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር በአዋጅ 1263/2014 በተሰጠው ሥልጣንና ሃላፊነት መሠረት የአየር ንብረት ለውጥን በተሰጠው የህግ አግባብና በሥርዓት ለመምራት ሰፋፊ ተግባራትን እያከናወነና ኃላፊነቱን በመወጣት ላይ መሆኑን ገልጿል ።
ከእነዚህም ወስጥ ሀገራችን ስትራቴጂያዊ ተጠቃሚ ሊያደርጋት የሚችለውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የካርቦን ግብይት ስትራቴጂ (National Carbkn Market Strategy for Ethiopia) ዝግጅት ዛሬ በተገኙበት በፕላንና ልማት ሚኒስቴር መሰብሰቢያ አዳራሽ ግብአት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ነው።
ይህም የተገለጸው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፋዊ ስምምነት (UNFCCC) አጋርነት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የካርቦን ገበያ ስትራቴጂ የማስጀመሪያ ሪፖርት (Inception Report) ሁሉም ባለድርሻ አካለት ማለትም የመንግስት ተወካዮች፥ የግሉ ዘርፍ አንቀሳቃሾችና የሚመለከታቸው የሲቪክ ማህበረሰብ አካላት በተገኙበት በተካሄደበት ወቅት ነው።
የእለቱን መርሃ ግብር በንግግር የከፈቱት የፕላንና ልማት ሚንስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ስዩም መኮንን እንደገለፁት ዛሬ የምናስጀምረው የኢትዮጽያ ብሔራዊ የካርቦን ግብይት ስትራቴጂ ከዚህ ቀደም በሀገራችን በተለምዶ ሲደረጉ የነበሩ የካርቦን ገበያ ተሳትፎዎች በሥርዓት እንዲካሄዱ የሚያደርግና የሀገራችንን ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ በሚያረጋግጥ መልኩ ለመምራት የሚያችል ነው ብለዋል።
ከዚህ ስትራቴጂ ዝግጅት ጎን ለጎን የካርቦን ገበያ በኢትዮጵያ የሚካሀረድበትን የህግ ማዕቀፍ ዝግጅትም ጎን ለጎን እየተሰራ መሆኑን የፕላንና ልማት ሚ/ር አስታውቋል።