Financial _ Ethiopia @financialethiopia Channel on Telegram

Financial _ Ethiopia

@financialethiopia


Finance is a term for the management, creation, and study of money and investments.
https://t.me/financialethiopia https://t.me/stockethiopia
https://t.me/sthare101
https://t.me/stargemstone
https://t.me/Saligebeya
https://t.me/madeinethiopia1

Financial _ Ethiopia (English)

Are you interested in finance, money management, and investments? Look no further than the 'Financial _ Ethiopia' Telegram channel! This channel provides a platform for individuals in Ethiopia to learn more about the world of finance, stay updated on the latest financial news, and engage in discussions with like-minded individuals.

Through this channel, members have access to valuable resources such as market analysis, investment tips, and discussions on various financial topics. Whether you are a seasoned investor or someone looking to learn more about financial literacy, 'Financial _ Ethiopia' has something for everyone.

In addition to financial insights, the channel also provides links to other related Telegram channels such as 'Stock Ethiopia,' 'STHARE101,' 'Star Gemstone,' 'Saligebeya,' and 'Made in Ethiopia 1.' These channels offer additional resources and information on specific areas of finance, allowing members to dive deeper into their areas of interest.

Join 'Financial _ Ethiopia' today and take the first step towards achieving your financial goals. Whether you are looking to grow your wealth, make smarter investment decisions, or simply increase your financial knowledge, this channel is the perfect place to start. Don't miss out on this opportunity to connect with a community of finance enthusiasts and experts in Ethiopia!

Financial _ Ethiopia

21 Nov, 07:19


ትችሉ ነበር አሁንም ትችላላችሁ!

አንዳንድ ሰዎች የእሳቤ ሂደት ይህንን ይመስላል፡-

“እንደምችል አውቀዋለሁ” በሚል ጠንካራ እሳቤ ይጀምራሉ፡፡

ትንሽ ተራምደው ያልጠበቁት ሁኔታ ሲገጥማቸው ቀስ በቀስ፣ “የምችል ይመስለኛል” ወደሚለው የጥርጣሬ ዘር ወዳለበት እሳቤ ወረድ ይላሉ፡፡

ብዙም ሳይቆዩ፣ “የምችል ይመስለኝ ነበር” ወደሚለው ደከም ወዳለ እሳቤ ይንሸራተታሉ፡፡

በመጨረሻ “አልችል” በማለት ጭራሹኑ ያቆሙታል፡፡

አንባቢዎቼ!!! ይህ ለብዙዎች ውድቀት ምክንያት የሆነ የእሳቤ ሂደት ለእናንተ አልተፈቀደላችሁም፡፡

እንደምንችል እናውቀው ነበር! እንችል ነበር! አሁንም እንችላለን!
በርቱና . . .

1. አንድን ነገር ከመጀመራችሁ በፊት ደካማ ጎናችሁ ላይ ሳይሆን ዝንባሌያችሁና ብርቱ ጎናችሁ ላይ አተኩሩ፡፡

2. የምትጀምሩት ነገር ውጤታማ የሚያደርጋችሁ እስከሆነ ድረስ እንቅፋት እንደሚያጋጥማችሁ አትዘንጉ፡፡

3. ካለማቋረጥ ራሳችሁን አሻሽሉ፡፡

4. ስትወድቁም ሆነ ስትሳሳቱ ከልምምዱ የምታገኙትን ትምህርታችሁን ያዙና ወደፊት ቀጥሉ፡፡

5. በፍጹም ተስፋ አትቁረጡ፡፡

Dreyob

Financial _ Ethiopia

20 Nov, 17:05


#Hibret Insurance SC#

▪️Job Position 1 - Digital Marketing Officer II
▪️Job Position 2 - Receptionist/ Front Desk Officer
▪️Job Position 3 - General Service Coordinator
▪️Job Position 3 - General Service Coordinator
▪️Job Position 4 - Human Capital Management Officer II
▪️Find More Details here
          💧💧💧💧💧

https://kebenajobs.com/job/hibret-insurance-sc-nov-20-24/

Deadline: November 22/ 2024

Financial _ Ethiopia

20 Nov, 14:03


Financial _ Ethiopia pinned «የኢንሹራንስ ዘርፍ በኢትዮጵያ የ30 ዓመታት ጉዞ!! የኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ እስከ ሰኔ 30/2017 ድረስ ሥጋት የመሸከም አቅም መጠን 12.5 ትሪሊዮን ብር መድረሱ ይነገራል፡፡ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ዕድገት በተሸከመው የስጋት መጠንም እንጂ ከዓረቦን ገቢ አንጻር ብቻ መመዘን ተገቢ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የኢንሹራንስ ዘርፍ ቁጥጥርና ክትትል ዳይሬክተር አቶ በላይ ቱሉ ይናገራሉ።…»

Financial _ Ethiopia

20 Nov, 13:16


የኢንሹራንስ ዘርፍ በኢትዮጵያ የ30 ዓመታት ጉዞ!!

የኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ እስከ ሰኔ 30/2017 ድረስ ሥጋት የመሸከም አቅም መጠን 12.5 ትሪሊዮን ብር መድረሱ ይነገራል፡፡

የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ዕድገት በተሸከመው የስጋት መጠንም እንጂ ከዓረቦን ገቢ አንጻር ብቻ መመዘን ተገቢ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የኢንሹራንስ ዘርፍ ቁጥጥርና ክትትል ዳይሬክተር አቶ በላይ ቱሉ ይናገራሉ።

ከዚህ ቀደም የኢንሹራንስ ዘርፉ ለኢኮኖሚው ያለው አስተዋጽኦ የሚለካው የዓረቦን ገቢውን በማስላት ብቻ ስለነበረ የተሳሳተ ምሥል መስጠቱን የኢንዱስትሪ ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡

በአብዛኛው የኢትዮጵያን የኢንሹራንስ ዘርፍ የ30 ዓመታት ጉዞ በዓረቦን ገቢ አንጻር መሻሻሎች እንዳሳየ ተገልጿል፡፡

ለመሻሻሉም ማሳያ በ2016 መጨረሻ 28.4 ቢሊዮን ብር የደረሰው ዓመታዊ ጥቅል የዓረቦን ገቢ መጠን  በ1985 ዓ.ም. 254 ሚሊዮን ብር እንደነበር ሪፖርተር ከሰሞኑ በዘገባው ጠቅሷል፡፡

በ30 ዓመታት ቆይታ የኩባንያዎቹ የካሳ ክፍያ መጠን ከ111.7 ሚሊዮን ብር ወደ 9.7 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሏል፡፡

በ2016 ዓመት መጨረሻ ላይ የኢንዱስትሪው አጠቃላይ የሀብት መጠን 65.8 ቢሊዮን ብር፣ የኢንቨስትመንት መጠኑም 36.6 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡

ባለፉት 30 ዓመታት የኢትዮጵያ መድን ሰጪዎች ቁጥር ከአንድ ወደ 18 ሲደርስ የቅርንጫፎች ቁጥር ደግሞ ወደ 812 ማደጉንም ማየት ይቻላል፡፡

በሥራ ዕድል የኢትዮጵያ መድን ኢንዱስትሪ 2,958 የሽያጭ ወኪሎች፣ 115 ንብረት ገማቾች፣ 62 ብሮከሮችን ጨምሮ 8,600 ለሚጠጉ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩ ተጠቅሷል፡፡

ኢንሹራንሶቹ በጋራ የመሰረቱት አገራዊ የጠለፋ መድን ሰጪ ኩባንያ የዘርፉን አጠቃላይ ሥጋት የመሸከም አቅም ከፍ የሚያደርግ እንደሆነም ይታመናል።

ኢትዮ ሪ ወደ ውጭ ይወጣ የነበረውን ካፒታል በተወሰነ መልኩ የሚቀንስ እና የኩባንያውን አድማስ ከኢትዮጵያ ውጭ በማስፋት ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በዚህ መጠን አድጎም የኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ዘርፍ ተመሳሳይ ኢኮኖሚ ካላቸው አገሮች ጋር ሲታይ በብዙ መሥፈርቶች ወደ ኋላ የቀረ ነው፡፡

በተለይም የህይወት ነክ ኢንሹራንስ ደካማ መሆን፣ የመድን ግንዛቤ አናሳነት፣ የሞተር (ተሽከርካሪ) ኢንሹራንስ ጥገኝነት፣ የተቋማቱ ደካማ ብራንዲንግና ፕሮሞሽን የሀገራችን መድን ዘርፍ ቀዳሚ ተግዳሮቶች ናቸው።

አሁን ላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ የመድን ኢንዱስትሪውን ለውጭ ኩባንያዎች ክፍት ማድረግ እንደ አማራጭ መቅረቡም ይታወቃል።


#ቅዳሜገበያ

Financial _ Ethiopia

20 Nov, 09:58


ክቡር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ በኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር በመሆን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ተሹመዋል።

https://t.me/financialethiopia https://t.me/stockethiopia
https://t.me/sthare101
https://t.me/stargemstone
https://t.me/Saligebeya
https://t.me/madeinethiopia1

Financial _ Ethiopia

20 Nov, 06:17


ዲጂታል ግብይት!!

በ2016 በጀት ዓመት 9 ነጥብ 7 ትሪሊዮን  ብር በዲጂታል መንገድ መዘዋወሩን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

ባንኩ ይህንን የገለጸው ዲጂታል የጤና አገልግሎት ክፍያ በሚል መሪ-ቃል የጤና ሚኒስቴር ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው።

በ2016 በጀት ዓመት 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ግብይት መፈፀሙን የባንኩ ፔይመንትና ሴትልመንት ዳይሬክተር ሰለሞን ዳምጤ ገልፀዋል።

ዳይሬክተሩ በማብራሪያቸው ሲቀጥሉም በቀን በአማካኝ የተደረገው የዲጂታል ገንዘብ ዝውውር 7 ነጥብ 6 ሚሊዮን መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን ይህንን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ወደ ጤናው ዘርፉም ለማምጣት በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም ነው ያስታወቁት።

የጤናውን ዘርፍ ከማዘመን አኳያ 70 በሚሆኑ የጤና ተቋማት የዲጂታል አገልግሎት ተግባራዊ መደረጉን የጤና ሚኒስቴር ያስታወቀ ሲሆን አስሩ ሙሉ ለሙሉ የወረቀት አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን ነው የገለፀው።

#ቅዳሜገበያhttps://t.me/stockethiopia
https://t.me/sthare101
https://t.me/stargemstone
https://t.me/Saligebeya
https://t.me/madeinethiopia1

Financial _ Ethiopia

20 Nov, 05:56


ብሔራዊ ባንክ " የባንክ ኢንዱስትሪውን" ነፃ ከማድረጉ በፊት አሰራሩን ወደ ላቀ ደረጃ ያሻግራሉ የተባሉ አደረጃጀቶች ሊያደረግ ነዉ
የፋይናንስ ዘርፉ ለውጭ ተዋንያን ቢከፈትም ቁጥጥር ማድረጌን እቀጥላለው ሲል ማእከላዊ ባንኩ ገልጿል።
የፋይናንስ ስርዓቱ ወደ ሊበራላይዜሽን እየተሸጋገረ ባለበት ወቅት መረጋጋትን ለማረጋገጥ በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ አዲሱን ማቋቋሚያ አዋጅ ይቀበላል ተብሎ የሚጠበቀው ብሔራዊ ባንክ አዳዲስ ክፍሎችን በማቋቋም ተቋማዊ ማሻሻያ እንደሚያደርግ አስታዉቋል።
የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ
በቅርቡ በፓርላማ ቀርበው የባንክ ኢንዱስትሪውን ነፃ ለማድረግና የብሔራዊ ባንክን አሠራር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በጉጉት የሚጠበቁትን ሁለት አዋጆችን ማንሳታቸው ታዉቋል።
ተቆጣጣሪ አካሉ ኢኮኖሚውን በዘመናዊ አሰራር ለመንዳት አካሄዱን በአዲስ መልክ እንደሚያደራጅና ይህም በብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅ ላይ በተደረጉ ለውጦች የተመቻቸ መሆኑን ገልጸዋል።
በሚቀጥሉት ሳምንታት ይፀድቃል ተብሎ በሚጠበቀው ረቂቅ አዋጅ መሰረት ማዕከላዊ ባንክ አዲስ ኮሚቴ ያቋቁማል። የህዝብ አስተያየትን ባካተተው የሁለት ቀናት ስብሰባ ላይ አቶ ማሞ አዲሱ አዋጅ ሰባት አባላት ያሉት የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ እንዴት እንደሚፈጥር አብራርተዋል። ይህ ኮሚቴ ለቦርዱ ይሁንታ የገንዘብ ፖሊሲን የማውጣት እና የመምከር ሃላፊነት አለበት።
በገዥው የውሳኔ ሃሳብ፣ የብሔራዊ ባንክ ቦርድ በገዥው እና በምክትል ገዥው የሚመራውን የገንዘብ ኮሚቴ እንዲቀላቀሉ በብሔራዊ ባንክ የተመረጡ ሁለት የውጭ ባለሙያዎችን ይሰይማል።
ኮሚቴው ቢያንስ በየሁለት ወሩ የሚሰበሰበው የብሄራዊ ባንክ ምጣኔን መወሰንን ጨምሮ የገንዘብ ፖሊሲዎችን ለሀገሪቷ እንደሚያቀርብ አቶ ማሞ አስረድተዋል። በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ምጣኔን 15 በመቶ አስቀምጧል።
ሌላው በአዲሱ አዋጅ የተቋቋመው አዲስ ክፍል የፋይናንስ መረጋጋት ኮሚቴ ነው። ይህ ኮሚቴ ለቦርዱ የውሳኔ አሰጣጥ ማክሮ እና ማይክሮ ፕራክቲካል ፖሊሲዎችን ያቀርባል እና በየወሩ በሚያደርጋቸው ስብሰባዎች የፋይናንስ ስርዓቱን በየጊዜው ይገመግማል፣ ይተነትናል እና የስርዓት ስጋቶችን ይለያል።
ቦርዱ የመጨረሻ አማራጭ አበዳሪን እና ሌሎች የችግር ጊዜ መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን በተመለከተ ከኮሚቴው በሚሰጠው ጥቆማ መሰረት ለብሔራዊ ባንክ የሚቀርቡ ፖሊሲዎችን በተመለከተ ውሳኔ ተብሏል።

Financial _ Ethiopia

19 Nov, 13:47


ሲጠበቁ የነበሩ ሁለት መመሪያዎች ፍትህ ሚኒስቴር ማጽደቁ ተሰምቷል።

መመሪያዎቹ "የሰነደ ሙዓለ ነዋይን ለህዝብ የማቅረብ ግብይት መመሪያ " እና "ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩ ድርጅቶች ቁጥጥር መመሪያ "  ናቸው።

ሁለቱን መመሪያዎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  በትላንትናው ዕለት መዝግቦ አጽድቋቸዋል።

የሰነደ ሙዓለ ነዋይን ለህዝብ የማቅረብ ግብይት መመሪያን በሚመለከት የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃና ተልህኩ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሰነደ ሙዓለ ነዋይን በሚመለከት ከዚህ ቀደም የተማከለ እና ሂደቱን የሚቆጣጠር ህግ እና ተቆጣጣሪ አካል ያልነበረ በመሆኑ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ማውጣት እና ግብይት በርካታ ችግሮች እንደነበሩበት ገልጸዋል።

በዚህ መሃል ለህዝብ የሚቀርቡ መረጃዎች ምንነት ፣ለሚቀርቡ መረጃዎች ሃላፊነት የሚወስዱ ሰዎች ማንነት፣ ሃላፊነት እና ግዴታቸው ምን ድረስ ነው፣ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ከወጣ በኋላ በዛ መንገድ የሚገኘው ገንዘብ ለምን ዓላማ እንደሚውል፣ አውጪዎች የሚኖርባቸው ተግባር እና ሃላፊነት ምንድነው የሚለውን ማወቅ ላይ ከዚህ ቀደም በነበሩ ህጎች ያለተዳሰሱ ስለነበር ገበያው በርካታ ችግሮች እንደነበሩበት ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።

ይህንን ችግር ለመቅረፍም የካፒታል ገበያ አዋጅን መሰረት በማድረግ አዲሱ መመሪያ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

መመሪያው በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ውስጥ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ለሽያጭ የሚቀርብበትን እና የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ግብይት የሚገዛበት ዝርዝር የያዘ የህግ ማዕቀፍ ነው።

በአዲሱ መመሪያ መሰረት ከአሁን በኋላ ሁሉም ሰነደ ሙዓለ ነዋዮች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ቀርበው መጽደቅ አለባቸው።

በዚህ ሂደት ላይ የሚሳተፉ አካላት የምዝገባ ሰነዳቸውን ለባለሥልጣኑ አቅርበው ማጸደቅ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የምዝገባ ሂደቱም ዝርዝር ሂደቶችን የያዘ ነው።

በአዲሱ መመሪያ መሰረት ከሰነደ ሙዓለ ነዋይ ጋር የተያያዙ ማስታወቂያዎች የሚተላለፉት ይዘታቸው እና ለህዝብ ይፋ የሚደረጉበት መንገድ ባለሥልጣኑ ተመልክቶ ሲያጸድቀው ብቻ ይሆናል።

መመሪያው ካካተታቸው እና ከዘረዘራቸው ጉዳዮች መካከል ዋና ዋናዎቹ :-

1 የሰነደ ሙዓለ ነዋይ ምዝገባ

2 ለ ኢንቨስተሮች መቅረብ ስላለበት የደንበኛ ሳቢ መግለጫ ይዘት እና የአቀራረብ መንገድ ሂደት እንዲሁም ተያይዞ ስለሚመጣ ሃላፊነት።

3 ስለ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ማስታወቂያ ይዘት እና አቀራረብ እንዲሁም ስለሚያስፈልገው ፍቃድ።

4 የሰነድ ሙዓለ ነዋይ ሽያጭ እና ድልድል
አጠቃቀሙ እና ስራ ላይ ስለሚውልበት አካሄድ እና ሁኔታ።

5 አንድ የሰነደ ሙዓለ ነዋይ አውጪ ሰነደ ሙዓለ ነዋይ ለህዝብ ሽጦ እንደ ህዝብ ኩባንያ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ በቀጣይነት ስለሚኖርበት ሃላፊነት እና የዚህ የህግ ጥሰቶች በቀጣይነት ስለሚያስከትሉት አስተዳደራዊ እርምጃዎች ይገኙበታል።

በዚህ መሰረት ከዚህ በኋላ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ካልተመዘገቡ ወይም በአዋጁ እና በመመሪያው ከዚህ ምዝገባ ነጻ ካልተደረጉ በቀር በኢትዮጵያ ውስጥ ለሽያጭ መቅረብ አይችሉም።

በተጨማሪም ማንኛውም ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን ለህዝብ ለማቅረብ የሚፈልግ ኩባንያ ሰነዶችን ለህዝብ ከማቅረቡ በፊት ዝርዝር መረጃዎችን ያካተተ የደንበኛ ሳቢ መግለጫ ለባለሥልጣኑ ማቅረብ እና ማጸደቅ የሚጠበቅበት ሲሆን ይህንን ከማድረጉ በፊት ማስታወቂያ ማሰራትም ሆነ ከኢንቨስተሮች ጋር ግንኙነት ማድረግ አይችልም።

መመሪያው በባለሥልጣኑ ገጽ ላይ ከተጫነበት ጊዜ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

በመመሪያው የመሸጋገሪያ ድንጋጌ መሰረትም አሁን ላይ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን እያቀረቡ ያሉ ኩባንያዎች እና አስቀድመው ተሽጠው በአክስዮን ባለድርሻዎች እጅ ላይ የሚገኙ ሰነደ ሙዓለ ነዋዮችን በሚመለከት በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ መመዝገብ እንዳለባቸው አስቀምጧል።

#Tikvahethiopia

Financial _ Ethiopia

19 Nov, 13:38


ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ 100 የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎችን ለማቋቋም ጥናት ጀመረ
ኤልያስ ተገኝ
October 23, 2024የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በ30 ሚሊዮን ዶላር መነሻ ካፒታል፣ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች 100 የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌት የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎች የማቋቋም ኢንቨስትመንት ጥናት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የመንግሥት ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት ተቋም ሆኖ እንዲያገለግል በ100 ቢሊዮን ብር የተፈቀደ ካፒታል የተቋቋመው ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ፣ የኢንቨስትመንት ስትራቴጂውን ዕውን ለማድረግ አጋር ይሆናል ከተባለው ዶዳይ የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌት አምራች ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. በሃያት ሬጀንሲ ሆቴል ተፈራርሟል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌት የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎች የማቋቋም ኢንቨስትመንት “ስትራክቸር” ሒደቱ እየተከናወነ ቢሆንም እስካሁን አልተጠናቀቀም፡፡

በመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ ላይ በተቀመጠው መሠረት ኢንቨስትመንቱ 30 ሚሊዮን ዶላር የመነሻ ካፒታል ሲኖረው፣ በ100 የተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎች እንደሚኖሩ ታሳቢ ያደርጋል ያሉት ብሩክ (ዶ/ር)፣ ሌሎች ቀሪ ጉዳዮችን መንግሥት ከኩባንያው ጋር የሽርክና ስምምነት (Shareholder Agreement) ሲፈራረም ይታያሉ ብለዋል፡፡

ለባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎች ኢንቨስትመንት ዶዳይ ኩባንያ የራሱን ኢንቨስትመንት ካፒታል ይዞ የሚቀርብ መሆኑን፣ ‹‹ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በበኩሉ የሚያደርገው አስተዋጽኦ የኢክዩቲ፣ የዓይነት አስተዋጽኦ (Kind Contribution) ወይስ ፍሪ ኮንትሪብዩሽን ነው የሚለው በቀጣይ በሚደረግ ድርድርና ስምምነት የሚታወቅ ነው፤›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

‹‹እኛ የተግባባነው ዋና ነገር ኢንቨስትመንቱን አብረን መሥራት እንፈልጋለን፣ ለመነሻ 30 ሚሊዮን ዶላር ስለሚያስፈልግ እሱን እናመነጫለን፣ 100 ያህል ቦታዎች ያስፈልጋሉ፣ እኛም ባሉን የመንግሥት ልማት ድርጅቶች መጠቀም እንችላለን፣ በእነዚህ ላይ ተመሥርተን ነው መስማማት ላይ የደረስነው፤›› በማለት ለሪፖርተር ያስረዱት ብሩክ (ዶ/ር)፣ በቀጣይ የሚፋጠነው ሥራ የኢክዩቲ አስተዋጽኦ ካለ ምን ያህል? በመቶኛስ የሚያስገኘው የኢንቨስትመንት ትርፍ መጠን ምን ይመስላል? የሚለውን መለየት ይሆናል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችና የሞተር ብስክሌቶች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ መከልከሉን እንደ መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም በኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረግ የጀመረው ዶዳይ ኩባንያ፣ እስካሁን 1,000 የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌቶችን መሸጡን፣ በተያዘው የበጀት ዓመት ይህንን አኃዝ ወደ 10,000 እንደሚያሳድገው ተገልጿል።

ዶዳይ ኩባንያና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ባደረጉት የኢንቨስትመንት መግባቢያ ስምምነት መሠረት በቀጣዮቹ 12 ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ 100 የባትሪ መለዋወጫ ጣቢያዎች ከመክፈት ባሻገር፣ በቀጣዮች ሦስት ዓመታት ሸገር ከተማን ጨምሮ 300 ጣቢያዎች በተለያዩ ቦታዎች ለመክፈት ዕቅድ መያዙ ታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ዘላቂና አመቺ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመዘርጋት ያለመ ነው የተባለው ይህ ኢንቨስትመንት የካርቦን ልቀት መጠንን በመቀነስና የከተማ እንቅስቃሴን በማሳደግ፣ ለአንድ መቶ ሺሕ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያለመ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ባለፈው የበጀት ዓመት በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ማገዱ የሚታወስ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የሞተር ብስክሌቶችም ሆኑ በአገር ውስጥ የሚገጣጠሙት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ መሆን ይጠበቅባቸዋል መባሉ አይዘነጋም፡፡

Financial _ Ethiopia

19 Nov, 13:33


አዲስ ግንባታ እቅድ።
የፋይናንስ ማእከል፣ አዲስ አበባ።

የ ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ከ ሮክስቶን ሪልስቴት አፍሪካ ጋር በአዲስ አበባ የሚገነባ የፋይናንስ ማዕከል ግንባታን በተመለከተ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

በሁለቱ ትብብር የሚሰራው ማዕከል ቢሮዎች፣ ንግድ ስፍራዎች እንዲሁም የመኖርያ ቦታዎች ይኖሩታል። ሰነዱን የተፈራረሙት  የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ብሩክ ታዬ እና ሚስተር ዲየትሪች ሮግ የሮክስቶን ስራአስፈጻሚ ናቸው።

ምንጭ። Ethiopian Investment Holdings. Finance is a term for the management, creation, and study of money and investments.
https://t.me/financialethiopia https://t.me/stockethiopia
https://t.me/sthare101
https://t.me/stargemstone
https://t.me/Saligebeya
https://t.me/madeinethiopia1

Financial _ Ethiopia

19 Nov, 10:54


የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ !!
 
የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ የወጣው ረቂቅ አዋጅ የነዳጅ አቅርቦት ፣ ስርጭት እና አጠቃቀም ላይ የሚስተዋለውን ብክነትና ህገ ወጥነት ችግር ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት ለመደንገግ በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከአስረጂዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ ኢሻ ያህያ ረቂቅ አዋጁ በነዳጅ ግብይትና ስርጭት ላይ ያለውን ቁጥጥር ለማጠናከርና ብክነትን ለመቀነስ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

ኮንትሮባንድና ህገወጥ የነዳጅ ስርጭትና ዝውውርን ለመቆጣጠር የሚያስችል መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የነዳጅ ሀብትን በቁጠባ ለታለመለት ዓላማ ለማዋል አዋጁ አስፈላጊ እንደሆነ ተጠቁሟል።

ነዳጅ አገሪቱ ባላት ውስን ሀብት በየአመቱ ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ የሚደረግበት ሸቀጥ መሆኑንም ተገልጿል።

#ቅዳሜገበያ

Financial _ Ethiopia

19 Nov, 06:58


የመኪና  ንግድ ኢንሹራንስ
በመኪና  ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችና የንግድ ድርጅቶች የሚያከናውኑትን ማንኛውንም እንቅስቃሴ የሚሸፍን  የኢንሹራንስ አይነት ነው ።   ሽፋኑ የሚከተሉት  ድርጅቶችን  አገልግሎት ይሠጣል ፡፡
1.   የመኪና  ሻጮችን
2.  የመኪና ጥግና  መአከላትን
3.  የመኪና ማጎጎዝ ድርጅቶችን
4.  ማንኛውም ከመኪና ንግድ ጋር የተሰማሩ  እንቅስቀሴወችን

https://t.me/financialethiopia https://t.me/stockethiopia
https://t.me/sthare101
https://t.me/stargemstone
https://t.me/Saligebeya
https://t.me/madeinethiopia1

Financial _ Ethiopia

19 Nov, 06:40


Motor trade insurance simply covers any activities undertaken by people and businesses working in the trade. These activities could include service and repair work, vehicle sales, restoration, or transportation. Any activity involving making a profit in the motor trade requires traders’ insurance.

https://t.me/financialethiopia https://t.me/stockethiopia
https://t.me/sthare101
https://t.me/stargemstone
https://t.me/Saligebeya
https://t.me/madeinethiopia1

Financial _ Ethiopia

19 Nov, 06:07


#Addis International Bank SC#

▪️Job Position 1 - HR ClerkJob Position 2 - Store Clerk
▪️Job Position 3 - Storekeeper
▪️Job Position 4 - Legal Aide
▪️Job Position 5 - Junior Construction and Design Officer
▪️Job Position 6 - Procurement Officer
▪️Job Position 7 - Programmer/System Analyst
▪️Job Position 8 - Hardware Engineer
▪️Job Position 9 - Digital Banking Technology Support Officer
▪️Job Position 10 - Attorney
▪️Job Position 11 - Senior MIS Officer
▪️Job Position 12 - Construction and Design Officer
▪️Job Position 13 - Senior Construction and Design Officer
▪️Job Position 14 - Branch Manager I
▪️Job Position 15 - Manager, Construction and Design Division
▪️Find More Details here
          💧💧💧💧💧

https://kebenajobs.com/job/addis-international-bank-sc-nov-18-24/

Deadline: November 22/ 2024

Financial _ Ethiopia

19 Nov, 05:08


የምናጭደው የዘራነውን ነው

2,132

subscribers

1,253

photos

9

videos