ሕዳር 14/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
ተገልጋዩች በሥራ ላይ ሰላሉ የግብር እና ቀረጥ ድንጋጌዎች፣ ተቋሙ ሰለሚሰጣቸው አገልግሎቶችና ቅድመ ሁኔታዎች ተገቢውን መረጃ እንደ አግባብነቱ በስልክ፣ በድረ ገጽ እና በአካል በመቅረብ መረጃዎችን የመጠየቅ፣ ምላሽ የማግኝት እና አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አላቸው፡፡
ማንኛውም የተቋሙ ተገልጋይ በጾታ፣ በዘር፣ በቋንቋ ፣በሃይማኖት ፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደረጃው እና መገለል አድልዎ ሳይደርስበት በተገቢው ሁኔታ አገልግሎት የማግኘት መብት አለው፡፡
ማንኛውም ተገልጋይ ክብሩና ስብዕናው ተጠብቆ የመስተናገድ እና ለሚያቀርባቸው አግባብነት ያላቸው የአገልግሎት ጥያቄዎች እንደሁኔታው አዎንታዊ ይሁን አሉታዊ ምላሽ የማግኘት መብት አለው፡፡
ተገልጋዩች ለሚያቀርቡት የአገልግሎት ጥያቄ ወዲያው ምላሽ ለመስጠት የማይቻልበት ሁኔታ ሲኖር እና ቀጠሮ የሚሰጥባቸው ከሆነ በሂደት ላይ የሚገኘው ጉዳያቸው ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ እና የት ክፍል እንደሚገኝ (ጉዳዩ እስኪጠናቀቅ በሚስጥር መያዝ የሚገባቸውን ጉዳዩች ካልሆነ በስተቀር) ጠይቀው የመረዳት መብት አላቸው፡፡
የተቋሙን ተገልጋዪች በተቋሙ አሠራር ፣ በሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሥነ ምግባር እና በአጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ካላቸው ቅሬታቸውን የማቅረብ ፣ ተገቢውን ወቅታዊ ምላሽ የማግኘት የመደመጥ መብት አላቸው፡፡
በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥና አሠራር ዙሪያ የታዘቡትንና ቢሆን ይሻላል የሚሉትን ተገቢ አስተያየት በማመስገንም ሆነ በመተቸት በነፃነት የመግለጽ መብት አላቸው፡፡
በታደሰ ኢብሳ